ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ረ : ፳ኛ ፊደል (በግእዝ እልፍ ቤት፣ በአበገደ ተራ ቍጥር)። "በፊደልነት ስሙ 'ርእስ'፡ በአኃዝነት 'ረ፪፻' ይባላል። "
ረ: ንኡስ አገባብ።
"በመንገድኸ ላይ ብዙ ወንበዴ አለ፡ 'ረ' በል እንዴት መጣኸ።
" "'ረ' ጕድ፡ 'ረ' ተው ይቅርብኸ። " "የረን ጠባይ ያልተረዱ ሰዎች ግን 'እረ' እያሉ ይጽፋሉ። " "ረጋ ብለኸ 'ረግ' ን እይ። "
ረ: የመና፣ የነ ተወራራሽ።
አጠራቀመ፣ አጠናቀረ፡ ምንድን፣ ምንድር።
ረመመ): ረሚም፡ ረመ)።
ረመሰ (ረምሰ): ከውሃ ከጭቃ አገባ፣ ወሸቀ፣ ነከረ፣ ዘፈቀ፣ ዘፈዘፈ፣ አራሰ፣ አቀዘቀዘ። "ተባ ብለኸ ኣተባን ተመልከት።" (ትግ): ጐዳ፣ እሰነፈ፣ አደከመ፣ ኣኰሰሰ። (ዕብ፡ ራማስ፡ ረገጠ። ራማሽ፡ ኼደ)፣ ቀሰቀሰ፣ ነቀነቀ፣ ወዘወዘ። ዐሸ፣ ለወሰ፣ አቦካ።
ረመረመ: በእግር ጠቀጠቀ፣ ረገጠ፣ አበራየ፣ አኼደ። "(ያይጥ ተረት): እኔን እኔን ይጠሉ፣ ዐሬን ወሬን ይረመርሙ።"
ረመሽት: በመራቤቴ ክፍል ያለ እገር።
ረመደ: እግሩ ምድር ነካ፣ ረገጠ ለመኼድ።
ረመደደ: ረመጠጠ።
ረመዳን (ዐረ): ኅፅበተ ንስሓ።
ረመጠ (ረመፀ): ከረመጥ አገባ፣ ሸጐጠ፣ ቀበረ፣ ደፈነ፣ ጠበሰ።
ረመጠጠ (ትግ፡ ረምጠጠ፡ ቈነጠጠ): ረገጠ፣ ተነ፣ ደፈጠጠ። "ረመደደን እይ።"
ረማሽ: የረመሰ፣ የሚረምስ፣ ወሻቂ፣ ዘፍዛፊ፣ አቡኪ፣ ለዋሽ።
ረማጭ (ረማፂ): የረመጠ፣ የሚረምጥ። "(ተረት): አማጭ ረማጭ።"
ረምራሚ: የረመረመ፣ የሚረመርም።
ረምታ (ረዐመ): የብዙ ሰልፈኛ እግር ድምፅ። "ረምታ ከረመረመ ሲወጣ ይችላል።"
ረምድ: የሕፃን ዐይን በሽታ፣ ዐይንን የሚጨፍን፣ የሚጫን፣ ከእባት ከናት ወደ ልጅ የሚራመድ።
ረሰረሰ (ትግ፡ ረስረሰ፡ አርከፈከፈ፡ ረበረበ፡ ረጩ): ወረዛ፣ ፈጽሞ ራሰ፣ ሾቀ፣ ጨቀየ።
ረሣ: ዘነጋ፣ ረሳ።
ረስራሳ: የረሰረሰ፣ የራሰ።
ረሸተ: የእኸልን ዘር አበዛ።
ረሸነ (ረስነ፡ ጋለ። ዐረ፡ ረሸ፡ አርከፈከፈ፡ ውሃን): በረሽ መታ፣ ገደለ።
ረሺ (ረሳዒ): የረሳ፣ የሚረሳ፣ ገዳፊ።
ረሽ ጠመንዣ: ረሸነ።
ረሽ: ግንጥል ጠመንዣ፣ ጥይቱ የሚበተን የወፍ ማደኛ።
ረቀረቀ (ረከረከ። ትግ፡ ራዕርዐ): መላልሶ መታ፣ ደበደበ፣ በክርን ደቀደቀ። "ዛሬ ሌሊት ዝናቡ ሲረቀርቀው ዐደረ፣መሬቱን ሲደበድበው ማለት ነው።"
ረቀረቀ: አብዝቶ ፎከረ።
ረቀቀ (ረቀ): ቀጠነ፣ ሣሣ፣ አነሰ፣ ደቀቀ፣ ከግዘፍ ራቀ። "(ነገሩ ረቀቀ): ጥልቅ ኾነ።"
ረቀየ: ፈነጠቀ፣ ነዛ፣ በተነ፣ ወረወረ ውሃን፣ ሽቶን፣ መድኀኒትን፣ ደምን፣ ወፈርን። "ወረራን አስተውል የዚህ ዘር ነው።"
ረቂቅ: (ቆች): የረቀቀ፣ ቀጪን፣
ሥሥ፣ ላይን የማይታይ፣ ቢታይም የማይጨበጥ፣ ነፍስ፣ መልአክ፣ ነፋስ፣ ውሃ፣ እሳት፣ ብርሃን፣ ጨለማ፣ ጪስ፣ ጉም የመሰለው
ኹሉ። "(የረቂቅ ረቂቅ): እግዜር።" መዠመሪያ የተጻፈ ማንኛውም ጽፈት፣ ከርሱ ለሚቀዳ ምስክር የሚኾን፣ ቀሪ ደብዳቤ ወይም ሌላ። በጣም ያነሰ፣ ጥቃቅን ጽፈት፣ የድጓ ምልክት። የደቀቀ፣ የላመ፣ የለዘበ፣ ልም፣ ልዝብ፣ የመገበሪያ ዱቄት።
ረቂቅነት: ረቂቅ መኾን።
ረቃቂ: የሚረቅ።
ረቅራቂ: የረቀረቀ፣ የሚረቀርቅ፣ መቺ፣ ደብዳቢ።
ረበረበ (ረበበ): (ዘጸአት ፵፡ ፬) በተራ አስቀመጠ፣ ሰደረ፣ ደረደረ፣ ደረበ፣ አነባበረ (ፅንፊትን በፍም፣ በእድሞ ጋድም ላይ)።
ረበረበ: አርከፈከፈ፣ ረጨ (ውሃን)።
ረበበ (ረቢብ፡ ረበበ): ዘረጋ፣ ጋረደ፡ በላይ አደረገ (የክንፍ፣ የባለክንፍ) (አድራጊ)። "(ዠበበ) ብለኸ አንዣበበን፣ ጠለለን ተመልከት። " ረበበ: ተዘረጋ፣ ተጋረደ፣ ሰፈረ፣ ዐደረ፣ መላ (ተደራጊ)። "ደጉን ሰው መንፈስ ቅዱስ ረቦበታል" እንዲል ባላገር (ኢሳይያስ ፷፩፡ ፩፡ ሉቃስ፡ ፫፡ ፳፪፡ ፬፡ ፩)።
ረበተ፡ ፈራ፡ ታወከ። "ረበደን፡ አስተውል። "
ረበከ: ወዘፈ፣ ረፈጠ፣ ረፈቀ።
ረበየ)፡ አረባየ፣ ረገጠ፣ ረመረመ፣ ጠቀጠቀ (በጤፍ ርሻ ላይ ከብትን ነዳ)።
ረበደ: የአረበደ ከፊል ነው።
ረበጠ (ዐረ): አሰረ፣ ቀፈደደ።
ረቢ (ረባሒ): የሚወልድ፣ የሚበዛ፣ የሚረባ፣ የሚጠቅም፣ ጠቃሚ።
ረቢ (ዐረ): የኔ ጌታ፣ እግዜር። "ዘሩ 'ረበበ' ነው። "
ረባ (ረብሐ): ወለደ፣ በዛ።
ረባ (ረብዐ): አራት አደረገ።
ረባ (ትግ፡ ረባዕ): ያራት ዓመት በቅሎ፣ ፪ ሸረፍ ድርስ።
ረባ: (ረብሐ)።
ረባ: ጠቀመ (ኢሳይያስ ፴፡ ፭፡ ፊልጵስዩስ ፫፡ ፰)። "(አይረባ)፡ የማይረባ፣ የማይጠቅም። "
ረባዳ: ዘጣ፣ ዘብጥ፣ ጐድጓዳ (ዋዲያት)፡ በገደልና በአረኸ መካከል ያለ ስፍራ። "ረባዳ መሬት" እንዲሉ።
ረብ አለ: ተዘረጋ፣ ተኛ፣ ተጋደመ።
ረብ: መተኛት፣ መጋደም።
ረብራቢ: የረበረበ፣ የሚረበርብ፡ ደርዳሪ፣ አርከፍካፊ።
ረብጣ: ጥቅል (ያቡጀዲ ጣቃ)፡ ባንድነት የታሰረ የንግድ ዕቃ።
ረተረተ)፡ አረተረተ፣ አረጠረጠ፣ አሶመሶመ። "ዘበዘበ፡ ነገር፡ ኦዋሸከ፣ እዚያም፡ እዚያም፡ ኣለ።"
ረታ (ረትዐ): ኣሸነፈ፣ ድል አደረገ፣ በሙግት፣ በክርክር፣ በሰንጠረዥ። "የማታ ማታ እውነት ይረታ (ገቢር)።"
ረታ ተባ: በቀጥታ ተናገረ። "ኣንደበቱ ረታ።"
ረታ: ቀና፣ ቀጥ አለ፣ ሰላ (ተገብሮ)።
ረታ: የሰው ስም።
ረታኝ: ስለቴን አደረሰልኝ፣ ታቦቱ። አሸነፈኝ።
ረትመት: የወንዝ ስም፣ በሞላሌ አጠገብ ያለ ዠማ። "ረት፡ የረታ፣ መት፡ የመታ ማለት ይመስላል።"
ረቺ (ረታዒ): የረታ፣ የሚረታ፣ አሸናፊ።
ረዐይት (ረዐየ): ረዣዥሞች ሰዎች፣ ከጥፋት ውሃ በፊት የነበሩ፣ በራሳቸው ደመና የሚገፉ፣ ቁመታቸው ፫ሺህ ክንድ።
ረከሰ: በረሰ፣ ተሻረ፣ ጠፋ፣ ተበላሸ፣ አስማቱ፣ ክታቡ። ወረደ፣ ተዋረደ፣ ወደቀ ከመወደድ፣ ከመክበር ተለየ ሰው በነውር፣ የሚገዛው ዐጣ እኸሉ፣ ዕቃው በገበያ። (ረኵሰ): አደፈ፣ ርኩስ ኾነ፣ ከቅድስና ራቀ (ዘፍጥረት ፯፡ ፲፪። ሐጌ ፪፡ ፲፫)። "(ታቦት ረከሰ): ዲያቆን ወይም ቄስ ስላመነዘረ በስሕተት ታቦት ረከሰ ይባላል።"
ረከረከ: (ረኰተ): (ትግ፡ ሐባ፡ ረክረከ): አጐበጠ፣ ወለደ፣ አወላግዶ ጻፈ፣ የበራ ሽንት እስመሰለ። "ረገረገን ተመልከት።"
ረከበ: ወጣ፣ በላይ ኾነ፣ ተቀመጠ። (ረኪብ፡ ረከበ): አገኘ፣ ደረሰ። "የረከሰው ቀሊል እንዲሉ።"
ረከቦት: የፈላ ቡና ወይም የስኒ ማስቀመጫ ማቅረቢያ፣ ከእንት ከብረት የተዘጋጀ ዕቃ።
ረኪ: የሚረካ።
ረኪስ: ለሸያጭ ጕዳት፣ ለገዢ ጥቅም የሚኾን ለውጥ። መርከስ፣ አለመወደድ።
ረካ (ዕብ፡ ራኸ፡ ላላ። ረወየ): ጠጣ፣ ጠጥቶ ጠገበ፣ ራሰ (ሐጌ ፩፡ ፯)።
ረካሽ: የከብት ትራፊ ሣር፣ ሽንት ስለ ተሸነበትና ስለ ተረገጠ ርካሽ ተባለ። የሚረክስ።
ረካቢ: የረከበ፣ ያገኘ፣ የወጣ።
ረክራኪ: የረከረከ፣ የሚረከርክ፣ አገባቦ፣ ወልጋጅ።
ረኸጥ (ርሕፀ): ኤርጣጣ፣ ሰነፍ፣ ውዝፍ ሴት፣ ወፍራም የፈሰሰ ውሃ የማታቀና፣ ምጣድ የለሽ።
ረዋጺ: የሮጠ፣ የሚሮጥ፣ በራሪ፣ ፈጣን፣ ኦሮቢ፣ ፈርጣ። "ሯጭ አበበ ቢቂላ።"
ረዘመ (ረዚም፡ ረዘመ): በለጠ፣ ላቀ፣ በዛ፣ ተረፈ ከሌላው ልክና መጠን ዐለፈ የቁመት፣ የመጠን (፩ኛ ሳሙኤል ፲፪፡ ፳፫)።
ረዘረዘ (ረዘዘ): ፌዴፈዴ ተረፈ።
ረዘዝ (ትግ፡ ረዘዘ፣ ደከመ፡ ደነዘዘ። ሐረር፡ ረዘ): ዘጋ፣ ሸጐረ፣ ቈለፈ፣ ቀረቀረ፣ በቤት፣ በግጥን ውስጥ አደረገ፣ አኖረ ዕቃን፣ ገንዘብን።
ረዛሚ: የሚረዝም፣ በላጭ።
ረዣዥም: ውስጥ ብዙ ረዥም (ሉቃስ ፲፪፡ ፰)።
ረዣዥሞች: የብዙ ብዙ ማለት ነው። "ቁመታቸው ፫ሺህ ክንድ የኾነ የደቂቀ ሴት ልጆች ሰማይ ዳሶች (ሔኖክ ፪፡ ፪)።"
ረዥሜ: የረዥም ወገን፣ የዶሮ ቅልጥም።
ረዥም (ሞች): የረዘመ፣ የበለጠ፣ የበዛ፣ የተረፈ፣ መለሎ፣ ትልቅ፣ ቀውላላ። "(ተረት) የሞተ ልጅ ዐንቱ ረዥም ነው (ትልቅ)።" "በረዥም ፈንታ እረጅም ማለት የስሕተት ስሕተት ነው።"
ረዥምነት: ረዥም መኾን።
ረደፈ (ዐረ): ደረበ።
ረደፈ: ሰደረ፣ ደረደረ፣ ተራ ሰጠ።
ረዳ (ረድአ): ሸክምን፣ ሥራን ተቀበለ፣ ዐዝ፣ ደገፈ፣ አሳረፈ፣ አገለገለ።
ረዳ (ጽጌ፣ ረዳ): የዕንጨት ስም፣ ያበባው መልክ ነጭ፣ መዐዛ ጣፋጭ የኾኑ፣ ከሥር እስከ ፍ እሾኸ አለሙ።
ረዳ መንገሻ: የልብስ ስም። ጥለትና ቍቲት ያለው፣ ከባሕር የመጣ ሸማ፣ በነጠላና በኩታ በቡልኮ ዐይነት የተሠራ። "ረዳ መንገሻ የተባለው በነጋዴ ውስጥም ነው።" (ግጥም): "ድሩም ማጉም መጣ ቍርጥ ረዳ መንገሻ፣ የንቅፍል ዐጀቡ ልጅ-ተንበሩን ያዢና እንኺድ ወደ ርሻ።"
ረዳ: የሰው ስም።
ረዳት (ቶች): ረጂ፣ ረድ (ዘፍጥረት ፪፡ ፳)።
ረዳትነት: ረዳት መኾን፣ ዐጋዥነት።
ረዴ (ረዳኢ፡ ረድኤት): ረጂ። "የምሽት ረያ እንዲሉ።"
ረዴ (ረድእየ): የሰው ስም፣ የኔ ረዳት ማለት ነው።
ረዴት (ረድኤት): ዕገዛ፣ ጥበቃ፣ በረከት፣ ጸጋ።
ረድ (ረድእ): መነኮሳትን፣ አስተማሪን የሚረዳ፣ ጥቍር ራስ አናኮ፣ ደቀ መዝሙር፣ ተማሪ። "ረድ ለሴትም ይነገራል (የሐዋርያት ሥራ ፱፡ ፴፸)።"
ረድፍ: ተረረ።
ረድፍ: ተራ። "በረድፍ በረድፉ፣ በየረድፉ፣ በተራ በተራው፣ በየተራው።"
ረዶች (አርድእት): አናኮዎች፣ ተማሪዎች።
ረጀ (ረወጠ): ።
ረጀ (ዐረ፡ ረጀወ፣ ተመለስ): ኹለተኛ ተመልሶ የፈላ ቡና።
ረጀት (ቶች): አነስተኛ ምጣድ ከመኩብሽ የምትበልጥ። "ዘሩ ረጋ ነው።"
ረጂ (ረዳኢ): የረዳ፣ የሚረዳ፣ ዐጋዥ (ኢሳይያስ ፴፩፡ ፫)።
ረጃሌ: ተረከዝ የማይሸፍን መጫሚያ ነጠላ። "ዳግመኛም ረጃሌ እግርን ጕብዝናን ያስተረጕማል።"
ረጃት: ከእባትና ከናት የወረደ ውርስ፣ ለልጅ ያለፈ ገንዘብ፣ ቅርስ፣ ርዝራዥ። "(ተረት): ያባትን ሞቱን አይወዱ፣ ረጃቱን ኣይሰዱ።" "(የረጃት ባሪያ): ከእባት የተወረሰ አገልጋይ።" ከወላጅ ወደ ልጅ የሚተላለፍ ደዌ።
ረገመ፡ (ረጊም፡ ረገመ)፡ ስደበ፡ አዋረደ፡ (፪ኛ ሳሙኤል፡ ፲፯፡ ፭፡ ፯፡ ፲፩፡ ፲፫)።
ረገረገ (ረከረከ): ነቀነቀ፣ ወዘወዘ።
ረገረገ: ዐጨቀ፣ ጠቀጠቀ፣ ከተተ፣ መላ፣ ጐደጐደ፣ አከማቸ።
ረገረገ: ከጭቃ አገባ፣ ደባለቀ።
ረገረገ: ጠፈጠፈ፣ ረገጠ፣ ደመደመ።
ረገበ፣ (ረጊብ፡ ረግበ)፡ ላላ፡ ጐረበ።
ረገቢ፣ የሚረግብ፡ የሚላላ።
ረገብ ፣ (ረጊብ)፡ መርገብ።
ረገብ፡ አለ፡ ላላ፡ ጐረብ፡ አለ። "ሳበ፡ ብለኸ፡ (ጥብ) ሳብን፡ እይ። "
ረገዘ: (ረጊዝ፡ ረገዘ)፡ በጦር፣ በሾተል፡ ወጋ፡ (ግእዝ)።
ረገደ፡ (ረገፀ)፡ ምድርን፡ በእግሩ፡ ደቃ።
ረገደ፣ ራደ፡ ተንቀጠቀጠ፡ ፈራ፡ አከበረ። "አቶ፡ እከሌ፡ ከተሾመ፡ ዠምሮ፡ ሰው፡ ኹሉ፡
ይረግድለታል።
"
ረገደ፡ አመካን ፣ ከፈለ።
ረገጠ ፣ (ረገፀ)፣ በሰኰና፣ መታ፡ ከብት፣ ሰውን ፣ ወይም፡ ሰው፡ ሰውን፡ በእግር፣ ደበደበ፡ ኣረባየ፡ (፪ኛ ነገሥት፡ ፯፡ ፲፯፡ ፳)። "ምድርን፡ በሣማው፡ ተጠቀ፡ ረመረመ። "
"(ወሰንን፡ ረገጠ)፡ ከለለ። "
"(ዐውድማን፡
ረገጠ)፡ አስተካከለ፡ ደመደመ። "
"(ስበትን፡ ረገ) ተነ፡ አሰረ። "
"(ወይንን፡ ረገጠ)፣ መቀጠመቀ። "
"(በርኖስን፡
ሸማን፡ ረገጠ)፡ ዐጠ። "
ረገጠ፡ መ፡ ፈረሱ፡ ፈረሲቱን፡ የመምህራን፡ ዐማርኛ፡
ነው።
ረገጠ፡ ጣሰ፡ ዐለፈ፡ ዳኛን።
ረገጠ፡ ፈረ፡ አሸበሸበ፡ ዘለለ።
ረገጣ፡ ርግጫ፣ የመርገጥ፡ ሥራ፡ ርምርማ፡ ጥቅጠቃ።
ረገጥ፡ መርገጥ። "(ፀጥ፡ ረገጥ)፡ ጫማ፡ ያረፈባት፡ ምድር። "
"እከሌ፡ ከባልንጀራው፡
ጋራ፡ ስለ፡ ተጣላ፡ ወጥ፡ ረገጡ፡ እንዳይደርስ፡ ተከልክሏል። " "ወጥረ፡ ጉጥ፡ በል፡ የሀጥር፡ አንጻር፡ ማለት፡ ይኾናል። "
ረገፈ ፣ ፈረሰ፡ ዐፈር፡ መሬት፡ ኾነ።
ረገፈ፡ (ረጊፍ፡ ረግፈ፡ አስጌጠ፡ ሸለመ)፡ ወደቀ፡ ተጣለ፡ ተንጠባጠበ፡ (ኢዮብ ፲፫ ' ፳፭)። "አበባው፡ ፍሬው፡ አዝመራው፡ እንባው፡ ረገፈ፡
እንዲሉ።
" "ከዋክብት፡
የስቅለት፡ ለት፡ እንደ፡ ቅጠል፡ ረገፉ። " "(ፈንጣጣው፡ ከፍኙ፡ ዕከኩ፡ ቂጥኙ፡ ረገፈ)፣ ጠፋ። "
ረገፈ፡ ቀረ፡ ተለየ።
ረገፍ፡ የቀረ፡ የተለየ። "ሠም፡ ረግፍ፡ እንዲሉ። "
ረጊ፣ (ረጋዒ)፡ የሚረጋ፡ ሰው፡ ከብት።
ረጋ፡ (ረግዐ)፡ ቆመ፣ ዐረፈ ተሰበሰበ፡ ተጋገረ፡ ወፈረ፡ ይደግ፡ ደረቀ፡
ጸና፡ ተፀንስ።
"(ተረት)፡ የረጋ፡ ወተት፡ ቅቤ፡ ያወጣዋል። "
"(አገር ረጋ)፡ ሰላም፡ ኾነ፡ ጸጥ፡ አለ። "
"ረጃን፡ እይ፡
የዚህ፡ ዘር፡ ነው። "
ረጋ፡ ሠራሽ፡ ረጋ፡ የሠራው፡ መሣሪያ፡ ዕቃ፡
ማማር፡ ጥናት፡ ጥንካሬ፡ የሌለው፡ ድዝድዝ።
ረጋጭ (ጮች)፡ የረገጠ፡ የሚረግጥ፡ ሓሪ፡ (ኢሳይያስ ፲፮፡ ፲)። "ጭቃ ረጋጭ፡ እንዲሉ። "
ረጋጭነት፡ ረጋጭ፡ መኾን፡ ጨፋሪነት።
ረጋፊ ፣ የሚረግፍ፡ የሚወድቅ፡ ወዳቂ፡ ጠፊ። "ዓለም፡ ዐላፊ፣ መልክ፡ ረጋፊ፡ እንዲሉ። "
ረጋፊ: ያስረገፈ፣ የሚያስረግፍ፣ አስጣይ።
ረግ ፣ ንኡስ፡ ኣገባብ፡ የአንክሮና፡ የሐዘን፡ ተጨማሪ፡
ቃል።
"ረግ፡ ወየው፡
ረግ ፣ ሞዬ ፣ እንድትል፡ አልቃሽ። "
"ኝ፡ ና፡ ምእላድ፡
እየኾኑ፡ ሲያጋንኑት፡ ረገኝ፡ ረግኝ፡ ረግናደር፡ የነገር፡ ዘዬ፡ ይኾናል። " "እያለ፡ በጐን። "
ረግረጊያ: መወዝወዣ፣ መታወቂያ፣ ወገብ ጕድጓድ።
ረግረጋም: ረግረግ ያለበት፣ የበዛበት ቀበሌ፣ ባለረግረግ።
ረግረጌ: የረግረግ ወን፣ ወይም ዐይነት። "(ረግረግ ጌ): የረግረግ ምድር።"
ረግረግ (ጎች): በውስጡ ውሃ፣ በላዩ ጭቃና ቀጤማ ሙሽ ያለበት ስፍራ፣ ሲረግጡት የሚያረገርግ፣ የሚንቀጠቀጥ መሬት (ኢዮብ ፵፡ ፳፩። መዝሙር ፵፡ ፪። ኢሳይያስ ፳፪፡ ፲፩)።
ረግረግ: መነቅነቅ፣ መወዝወዝ፣ መንቀጥቀጥ፣ መታጠቅ፣ መምላት፣ መኩራት፣ ደጋግ።
ረጠረጠ: ተወ መቆምን፣ መርጋትን። "ረተረተን እይ።"
ረጠረጠ: የረጠጠ ደግሞ ነው።
ረጠበ (ረጥበ): ተነከረ፣ ራሰ፣ ረሰረሰ፣ ቀየ፣ ወዛ፣ ለመለመ (ተገብሮ)።
ረጠበ: ሰጠ፣ ቀለተ፣ በጠፋ ተካ፣ ረዳ፣ ዐገዘ (ገቢር)። "(እጁ ረጠበ): ገንዘብ ኣገኘ።"
ረጠጠ (ዐረ፡ ረጸጸ፣ አነጣጠረ። ዕብ፡ ራጼጽ፡ አሸበሸበ): ዐመቀ፣ ተጫነ፣ ጨቈነ፣ ወዘፈ። "ረጸጸ የቀስትን፣ ራጼጽ የሰውነትን ጭቈና ያሳያል።"
ረጠጠ: ርጥብነት ያለበት እንጀራ፣ ረጠጠ።
ረጣቢ: የሚረጥብ፣ ሰጪ።
ረጣጭ: የረጠጠ፣ የሚረጥጥ፣ ዐማቂ፣ ተጫኝ።
ረጥል: ኪሎ። በግእዝ ልጥር፣ በአማርኛ ነጥር፣ በፈረንጅኛም ሊትር ይባላል።
ረጥረጥ አለ: አረጠረጠ።
ረጥረጥ አለ: ወፈረ ወጡ።
ረጨ (ረቀየ): ፈነጠቀ፣ ነዛ፣ በተነ፣ ወረወረ ውሃን፣ ሽቶን፣ መድኀኒትን፣ ደምን፣ ወፈርን። "ወረራን አስተውል የዚህ ዘር ነው።"
ረጨ: ፈነጣጠቀ፣ በታተነ፣ ወራወረ።
ረጨረጩ (ርሕፀ): በፍርሀት ተንቀጠቀጠ።
ረጪ (ረቃዪ): የረጨ፣ የሚረጭ፣ በታኝ።
ረፈረፈ (ትግ፡ ረፍረፈ፡ ፈረፈረ): ጣለ፣ ለሸለሸ፣ አስተኛ፣ አጋደመ በሽታ ሰውን።
ረፈረፈ: ረበረበ፣ ጐዘጐዘ።
ረፈቀ (ረፊቅ፡ ረፈቀ፡ ተቀመጠ): አስቀመጠ፣ ቍጭ አደረገ፣ ወዘፈ፣ ተነ፣ ጨቈነ።
ረፈተ (ዐረ፡ ረፈፀ): ወታደርን አሰናበተ፣ አሳረፈ። "ረፈጠን እይ።"
ረፈደ (ረፍደ): የጧት ጊዜ ዐልፎ ከሦስት ሰዓት በላይ ኾነ።
ረፈጠ (ዐረ፡ ረፈዐ፣ እንቢ አለ): ረፈቀ፣ አስቀመጠ።
ረፈጥ: ከቀፎ በአፍኣ የትም ወድቆ የሚታይ የንብ ኵስ፣ ብጫ መሳይ።
ረፋቂ: የረፈቀ፣ የሚረፍቅ፣ ወዛፊ፣ ተኝ፣ ጨቋኝ።
ረፋድ: የረፈደ ፀሓይ፣ ሙቀት የዠመረበት ጊዜ።
ረፍረፎ: ያልተሠራ፣ ያልተመሸጠ የሲት ጠጕር፣ ቈንዳላ።
ረፍራፊ: የረፈረፈ፣ የሚረፈርፍ፣ ረብራበ፣ ጐዝጓዥ።
ሩ (ሩጸት): ግልቢያ፣ ፍርጠጣ፣ ሽምጠጣ (፩ኛ ቆሮንቶስ ፲ ፱፡ ፳፬)። "(የልም ሩጫ): ሳይሮጡ መሮጥ።"
ሩሕ (ዐረ): ትንፋሽ።
ሩሕ: ከናንህ የአስማት መጻፍ፣ ወይም ክታብ። "ሩሕ፣ እፍ ማለትን፣ ከናንህ ጥንተ ጸሓፊውን፣ ከነዓንን ያሳያል።"
ሩቅ (ቆች) (ርሑቅ): የራቀ፣ ባይን የሚታይና የማይታይ ነገር፣ ሰማይ፣ ሩቅ ዐደራ፣ ጥብቅ እንዲሉ።
ሩቅ ውዱቅ: ከፈጣሪ የራቀ፣ በአንጦርጦስ የወደቀ ሰይጣን። "ዕሩቅ ቢል ከክብር ብርሃን የተራቈተ ያሠኛል።"
ሩቅነት: ሩቅ መኾን፣ አለመቅረብ።
ሩቅና ቅርብ: ርሱ፣ አንተ፣ ርሷ፣ አንቺ፣ እነርሱ፣ እናንተ የሚባሉ የስም ምትኮች። "የቦታ እዚያ፣ እዚህ።" "(የቅርብ ሩቅ): ባይን ሲያዩት ቅርብ የሚመስል፣ ወደ ርሱ ሲኼዱ ግን ዳገትና ቍልቍለት፣ ዘወርዋራ መንገድ ያለበት ስፍራ፣ ጊዜ ፈጅ።"
ሩብ (ቦች): የብር አራተኛ ክፍል ገንዘብ።
"ከጣሊያን ወዲህ ግን 'ስሙኒ' ይሏታል። "
ሩት: የሴት ስም፣ በቅዱስ መጽሐፍ የታወቀች የሞአብ አገር ሴት።
ሩካቤ: የወንድና የሴት መገናኘት።
ሩዝ (ዞች): የእኽል ስም፣ በእስያ ክፍል በሸንና፣ በህንድ አገር በዝቶ የሚበቅል ነጭ እኸል፣ እንደ ምስር እየተቀቀለ ከወጥ ጋራ ይበላል።
ሩጋ፡ ስማርድ።
ሩፋኤላዊት: ወይም ወልደ ሩፋኤል፣ ወለተ ሩፋኤል በማለት ፈንታ ሩፌ ይባላል። "አቶ ሩፌ፣ እመት ናፌ እንዲሉ።"
ሩፋኤል: የመልአክ ስም፣ ከሰባቱ የመላእክት አለቆች አንዱ፣ ፫ኛ አለቃ። "ትርጓሜው፣ የአምላክ ፈውስ ማለት ነው።"
ሩፌ: የወንድና የሴት መጠሪያ ስም፣ ይኸውም ከፊለ ስም ነው።
ሪሓን (ርሔ): ነጭ ሽቶ። "ርያንን እይ፣ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።"
ሪሕ (ዐረ፡ ነፋስ): ከቀዝቃዛ ነፋስ፣ ከብርድ የሚመጣ የእግር ቍርጥማት፣ የደም ሥር በሽታ፣ ነዘራ፣ ቃንዛ።
ሪሕ: ቍርጥማት።
ሪም: ጥቂት መሬት፣ ዐረመ፣ ዕሪም።
ሪቅ (ቆች): ቁመተ ረዥም፣ ጐነ ሰፊ ጐታ። "ዘንችን እይ።" "ዕሪቅ ተብሎ ቢጻፍ ግን ዕንጨቱ ታርቆ የተሠራ ማለት ነው።" "መቶ ዳውላ እኸል ይይዛል።"
ሪቅ: ረዥም ጐታ፣ ራቀ።
ሪቦ ጋድሚያ። ርብ: በጐንደር አውራጃ ያለ ያገርና የወንዝ ስም። "ከርብ እስከ መተማ" እንዲሉ።
ሪቦ ጋድሚያ: ረበበ።
ሪወጠ): ሮጠ (ሮጸ)፣ በረረ፣ ፈጠነ፣ ጋለበ፣ ፈረጠጠ፣ ሸመጠጠ። "(ተረት)፣ ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል።" "ገጠጠ ብለኸ አንጋጠጠን ተመልከት።"
ሪዛም: ሪዝ ያለው፣ ባለሪዝ፣ ሪዘ ብዙ ሪዙ ያደጋ፣ የረዘመ ሰው።
ሪዝ (ዞች): ዕድሜው ከአንድ ዓመት የማይበልጥ የበግ ጥቦት፣ ጠጕሩ በውድ የሚሸጥ፣ በርኖሱ እስከ ሠላሳ ጥሬ ብር የሚያወጣ፣ ተባቱም እንስቱም ሪዝ ይባላል።
ሪዝ: ገና ያቀነቀነ፣ የበቀለ ጢም፣ ሸንጎበት።
ሪዝን፡ ተመልከት፡ የዚህ ዘር ነው።
ሪያ: አውሬ፣ ኡሪያ።
ራሔል: የሴት ስም፣ የያዕቆብ ሚስት።
ራሔሎ: የልጆች በሽታ፣ ወረርሽኝ፣ ክረምት ሲወጣ የሚመጣ ጕንፋን፣ ትክትክ፣ ባንዳንድ ዘመን እየበረታ ልጆችን ይገድላል። "ባላገሮችም ራሔሎ ኺጂ ቶሎ ቶሎ እያሉ ንፍሮ ይበትናሉ።" "ይህ ስም የማቴዎስ ወንጌል (ም፡ ፪፡ ቍ፡ ፲፰)፡ ራሔል ስለ ልጆቿ፣ አለቀሰች፣ መጸናናትም አልቻለችም፣ የሉምና ካለው ንባብ የተያያዘ ነው።"
ራማ: የሰማይ ስም፣ ከ፯ቱ ሰማያት አንዱ፣ የጠፈር ሦስተኛ። "ትርጓሜው፡ ልዕልና፣ ርዝመት፣ ደርብ፣ ሰገነት ማለት ነው።"
ራሰ (ርሕሰ። ዕብ፡ ራስ አራሰ፡ ለወሰ): ተነከረ፣ ተዘፈቀ፣ ተዘፈዘፈ፣ ረጠበ። "ረሰን፣ ተመልከት።"
ራሰ (ርእሰ): ራስ ተባለ፣ ራስ ኾነ፣ ላቀ፣ ሠለጠነ፣ ከሌሎች በለጠ በክብር፣ በማዕርግ።
ራሰ (ርእስ): ካንገት በላይ ያለ ጭንቅላት፣ ዐናት የሕዋሳት ኹሉ ጠቅላይ፣ የአካል የጎላ የማንኛውም ነገር ፵ፍ መጨረሻ። "ከራስ በላይ ነፋስ እንዲሉ።" "(የንዝርት ራስ): ቀንድ ቅል።" "ራሱ፡ ራስኸ፡ ራሳቸው፡ ራሳችኹ፡ ራስዎ፡ ራሷ፡ ራስ፡ ራስሽ፡ ራሳችን፡ ራሴ፡ እሱ፡ ራሱ፡ እኔ፡ ራሴ፡ እያለ በ፱ ሰራዊት ይዘረዝራል።"
ራሰ መላጣ: በራ፣ ጠጕር አልባ።
ራሰ ሠሪ: ጠጕር የምትሠራ ሴት፣ ዐሻሚ፣ ጐንጓኝ፣ ቈናኝ።
ራሰ በራ: በስተፊቱ ጠጕር የሌለው፣ መላጣ።
ራሰ ቡሓ: በራሱ ላይ ነጭ ዕከክ ቈረቈር ያለበት ስው።
ራሰ ቢስ: መጥፎ፣ ምናምንቴ ሰው።
ራሰ ክፍት: ያየውን፣ የሰማውን በቶሎ የሚያዝ፣ ዕውቀት የሚገባው፣ ብልህ ሰው።
ራሰ ዘናና: ራሰ ትልቅ፣ ጭንቅሎ፣ ጭንቅላታም፣ ገመሞ ራስ።
ራሰ: ርሳስ።
ራሱ ዞረ: ናላው ተናወጠ፣ ተበበ፣ አበደ።
ራሱን መለስ ቀለስ አደረገ።
ራሱን ሰወረ: ባለመታወቅ ኖረ።
ራሱን ተደገፈ: ራሰ። (የተጨማሪ ትርጉም ዝርዝር አልቀረበም)
ራሱን ቻለ: ሰው ሳይዘውና ሳይደግፈው ተቀመጠ፣ ቆመ (ሕፃኑ፣ በሽተኛው)። ገዢ ወጣ፣ ትዳር ያዘ፣ መታገዝን ተወ፣ አባት እናቱን አላስቸገረም።
ራሱን አራቀ: "እኔ በማለት ፈንታ እሱ አለ (ዮሐንስ ፲፯፡ ፩፫)።"
ራሱን ዐወቀ: አእምሮው ተመለሰ።
ራሱን አወጣ: አዳነ፣ እተረፈ።
ራሱን አዋረደ: ትሕትናን ገንዘብ አደረገ።
ራሱን ጣለ)፡ አዋረደ፣ መናኛ ልብስ ለበሰ። (ጋኔን ጣለው): አንከባለለው፣ አንደባለለው። (ምን እግር ጣለው): አመጣው፣ አደረሰው። (ጣለበት): ፍቅር አሳደረበት።
ራሱን ጣለ: አዳፋ ልብስ ለበሰ።
ራሳ: በይፋት ክፍል ያለ አገር ወይም ተራራ።
ራሳም ሆነ (ከራሱ ከበደ)። (ደነደነን እይ)
ራሳም ዱላ: ከንተሮ፣ ቋራም በትር።
ራሳም: ጭንቅላታም።
ራስ (ርሒስ): መራስ።
ራስ ላይ ወጣ: አሰከረ፣ አዞረ (ጠጅ ሰውን)።
ራስ መሸፈኛ: ሠርመዲ።
ራስ መጠበቂያ: ሰይፍ፣ ዱላ፣ ሽጕጥ፣ ጠመንዣ።
ራስ ማሰሪያ: ሻሽ፣ ደበላ።
ራስ ምታት: የራስ በሽታ፣ ከፀሐይ ቀት የሚመጣ ምች። "መታን እይ።"
ራስ፡ ሳመ)፡ አጥብቆ ለመነ፣ ዐደራ አለ (ስላንድ ሥራ ምክንያት)።
ራስ ሳይጠና ጕተና ሳይተርፍ: መቸር፣ አላቅም መሥራት።
ራስ ስሞሽ: ጥብቅ ልመና፣ ጅጊ።
ራስ ቍር: (ጌራ ኀጺን): የብረት ቆብ፣ የጥንት ጦረኛ በራሱ ላይ የሚደፋው፣ ቦርቦርቲ (፩ኛ ተሰሎንቄ፡ ፭፡ ፰)።
ራስ ቅል: የራስ ቅል፣ የራስ ዐጥንት። "ቅል የሚመስል (ዮሐንስ ፲፱፡ ፲፯)።"
ራስ በራስ: በላይ በላዩ፣ ቶሎ ቶሎ። "ላምን ትውለድ በታኅሣሥ፣ ሚስትህ ትውለድ ራስ በራስ።"
ራስ ቢትወደድ: ድርብ የማዕርግ ስም፣ ባለሙሉ ሥልጣን። "ራስ ቢትወደድ ተሰማ የልጅ ኢያሱ ሞግዚት ነበሩ።" "ባተን አስተውል።"
ራስ ብቻ ሰው: "እከሌ እንድራሱን (ብቻውን)፣ ኹለት ራሱን መጣ፣ ኹለት ሰው ኹኖ ሌላ ሰው ጨምሮ አስከትሎ ማለት ነው።"
ራስ አለ: ራሰ።
ራስ አእምሮ: ዕውቀት፣ ማስተዋል። "ይህ ሰው ራስ የለውም።"
ራስ ከብዶ: ራሰ ትልቅ ዓሣ። "የሐዲስ መምህራን ሥጋው አይበላም ይላሉ።"
ራስ ከብዶ: የቅኔ አገባብ ስም። "መጽሐፈ ሰዋስው ፫፻፲፩ኛ ገጽ ተመልከት።"
ራስ ክምር: ራሱ (ፍሬው)፣ ክብ እንክብል፣ ኳስ የሚያኸል ዕንት። "ዳግመኛም ስሙ የፈረስ ዘንግ ይባላል።" ራሱ ክምር የሚመስል ራሰ፣ ክምር ታናሽ ቅጠል ጐጐት።
ራስ ወርቅ (ጌራ ወርቅ): ራስ የተባለ መኰንን በራሱ ላይ የሚያደርገው የራስ ወርቅ (ወርቀ ርእስ ሽልማት፣ በራስ ቍር ዐይነት የተሠራ)።
ራስ ዳሸን (ራስ ዘዐሸን): የስሜን ተራራ። "ዐሸን ራስ ማለት ነው።" "ዳሸንንና ሏሒትን እይ።"
ራስ ጠባቂ: በሕፃን ራስ ላይ የበቀለ አንድ ሽበት።
ራስ ጠባቂ: ታማኝ አሽከር።
ራስ ፍልጠት፡ ሆድ ቍርጠት እንዲሉ።
ራስ ፍልጠት: እኩሌታ የራስ ዕመም።
ራስ: ከአንገት በላይ ያለ የሰውነት ክፍል (ቁንጮንና ቆንዳላንም ያስተረጉማል)። ምሳሌ: "ዳዊት የጎልያድን ቸብቸቦ በቈረጠ ጊዜ የፍልስጥኤም ሰዎች ድል ሆነው ሸሹ።"
ራስ: የማዕርግ ስም፣ ከንጉሥነት በታች፣ ከደጃዝማችነት በላይ ያለ ማዕርግ። "ራስ ጐበና፣ ራስ ዳርጌ፣ ልዑል ራስ መኰንን እንዲሉ።" "ሀምባ ራስ ቢል የተራራ የመንደር ሹም ማለት ነው።" "ዐምባን እይ።"
ራስጌ ቤት: የንጉሥ ዕልፍኝ። "ያንጣፊ አለቃም ራስጌ ቤት ይባላል።"
ራስጌ: በስተራስ በኩል ያለ ስፍራ፣ የግርጌ አንጻር። "ጌን ተመልከት።"
ራሶች (አርእስት): ብዙዎች ወናቶች፣ ጭንቅላቶች።
ራሶች: የራስነት ማዕርግ ያላቸው ጌቶች፣ መኳንንት።
ራሪ: የሚራራ።
ራራ (ራኅርኀ): ዐዘነ፣ ምሕረት አደረገ (ሮሜ ፱፡ ፲፭)።
ራሮት: ዐዘን፣ ሀዘኔታ።
ራሽ: የሚርስ፣ ልጥ፣ ዓመድ ያበባ፣ እኸል።
ራቀ (ርሕቀ): ተገለለ፣ ተወገደ፣ ተነጠለ፣ ተለየ፣ ፈቀቅ አለ (፪ኛ ነገሥት፡ ፭፡ ፲፱። ሉቃስ ፳፪፡ ፵፩)። "ካይን የራቀ ከልብ ይርቃል።" "ይህች ልጅ በውበቷ ዛፍ የራቀው ዐረግ ትመስላለች።"
ራቂ (ረሓቂ): የሚርቅ፣ የሚወገድ።
ራቂ (ረሓቂ): የቅርብ ሴት ትእዛዝ አንቀጽ። "ሴትዮ ከመጥረቢያ አጠገብ ራቂ።"
ራቂያ: ርቀት።
ራቅ (ረሐቅ): ለቅርብ ወንድ የሚነገር ትእዛዝ አንቀጽ፣ ገለል በል፣ ወግድ።
ራቅ (ርሒቅ): መራቅ፣ ገለል።
ራቅ ማሰሬ: የማዕርግ ስም፣ የቀድሞ ሊጋባ ራቅ ማሰሬ ይባል ነበር። "ትርጓሜውም ማሰሬን (ጅራፍን፣ ጨንገርን) ራቅ ማለት ነው።" "በጐንደርና በጐዣምም የገዳም መጋቢ ራቅ ማሰሬ እየተባለ ይሾም ነበር።" "አሰረን፣ ጽራግን፣ ጃንን ተመልከት።"
ራቅ ራቅ አለ: ገለል ገለል አለ።
ራበ (ርኅበ): ሆድን ሞረሞረ፣ ውስጥ ውስጡን በገበገ።
"(ሽለላ) እንደ ራበኝ እንደ ሞረሞረኝ ከበላ ሰው ጋራ ልሞት ነው መሰለኝ። "
ራብ (ረኃብ): ችጋር፣ ቀጠና፣ ጠኔ።
"(ተረት) ባቄላ የራብ ዱላ።
" "(በራብ ዐለንጋ ተገረፈ) ይልሰው ይቀምሰው ዐጣ።
"
ራብተኛ (ርኁብ): የተራበ፣ ችጋረኛ፣ ራብ ያለበት፣ የበዛበት። "ሲበዛ ራብተኞች ያሠኛል። "
ራብዕ (ረብዐ): አራተኛ ፊደል።
"ኣ፡ ራብዕ፡ ባ፡
ራብዕ" እንዲል ፊደል ቈጣሪ።
ራብዕነት: ራብዕ መኾን፣ አራተኛነት።
ራት: የማታ ምግብ፣ እራት።
ራቻ: በበትር የተወቃ እኸል፣ አረተ፣ እራቻ።
ራእየ ማርያም: የመጽሐፍ ስም፡ በሲኦል የኃጥኣንን ነፍሳት ቅጣት ያየችው ማየት።
"ልጇ እያዞረ አሳይቷታል ይላሉ።
"
ራእየ ዮሐንስ: የዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ራእይ።
"የመጽሐፍ ስም፡ ኀላፍያትንና መጻእያትን የሚናገር መጽሐፍ።
"
ራእይ (ርእየ): በሕልምና በተመሥጦ ጊዜ በዐይነ ኅሊና የሚታይ ረቂቅ ነገር።
ራዎት (ረወየ): ርኰት፣ ኰዳ፣ የእጅ ዋንጫ። "በግእዝ መርወይ ይባላል (ኢዮብ፡ ፴፯)።" "ዳግመኛም የጋሻ ዋንጫ ይሉታል፣ ከጋሻ ጋራ የሚያዝ ማለት ነው።" "ሲበዛ ራዎቶች ይላል።" "ራዎት ኩፋርን እይ።"
ራዎት: የካባ ቆብ፣ አንካቦ መሳይ።
ራዛ (ዞች): ነጭ እሞራ፣ እንደ ሩዝ ንጣት ያለው አንበጣ በል።
ራዠ (ረዘየ): ተሣቀየ፣ ተጨነቀ፣ ዛበረ። "ረዘየ ጥንታዊ ዐማርኛ ነው።"
ራያ (ዮች): የአገር ስም፣ በትግሬ አውራጃ ያለ ቈላ በረሓ። ሕዝቡም ራያ ይባላል። "እነዚሁም ጋሎች ናቸው።" "ራያና አዘቦ እንዲሉ።"
ራደ (ርዕደ): ፈራ፣ ተንቀጠቀጠ፣ ተብረከረከ።
ራዲዮ: ነፋስ ስልክ፣ ኣለሽቦ፣ በነፋስ ኀይል ድምፅ መስጫና መቀበያ መኪና። "እንደ ፈረንጅ አቈጣጠር በ፲፰፻፺፱ ዓ.ም ማርኮኔ የሚባል ጣሊያን ያወጣው።" "ስልክን እይ።"
ራድ (ረዓድ): ፍራት፣ ብርክ፣ እንቅጥቅጥ፣ ከቅምጥ የሚፈነቅል።
ራፎን: የጠንቋይ ጽፈት፣ ፲፯ ጊዜ የሚጻፍ አስማት።
ሬ (ትግ ጽሒራ): መቃብር አፍራሽ፡ ሬሳ አውጭ፡ በግእዝ፡ "ጽዕብ"
ይባላል።
ሬ: አይጨስ ነደድ፡ ወረረ።
ሬማ: የዛፍ ስም፣ ቅጠሉ ቡና የሚመስል ዕንጨት፣ ለቤተ ክርስቲያን ደወል ይኾናል።
ሬሳ (ሶች): ነፍስ የተለየችው ሥጋ፣ የወደቀ፣ የተጋደመ በድን። "(ተረት): ርጥብ ሬሳ ደረቁን አስነሣ።" "እቤተ ክርስቲያን ሲደርስ የጠላቴ ሬሳ የኔ ከቤት ይነሣ።" "ከበደን እይ።" "(የባሪያ ሬሳ): ዘመድ ስለሌለው ለባዕድ ተሻካሚ የሚከብድ።" "ሀረግን አስተውል።"
ሬሳ ሸሽ: በጣረ ሞት ጊዜ ከሰው ከእንስሳ የሚወጣ ዘር፣ ቅዘን፣ ተቅማጥ፣ የበድን ዕጣቢ። "ሬሳ ከረሳ ሊወጣ ይችላል።"
ሬስ: የፊደል ስም ረ። "ትርጓሜው ራስ ማለት ነው።"
ሬባም: የባለጌ ስድብ።
ሬብ: ሥጋዊ የፈጋራ መዝጊያ (ማጡኔው ወይም ሸምቀቆው እንደ መረብ የሚከፈትና የሚዘጋ)። "ጐንደሮች ግን ሬብን 'ቂጥ' ይሉታል። " "ሙርጥን እይ።
"
ሬቦ: ቃለ አኅስሮ (የማዋረድ ቃል)።
ሬት (የሚመር ዕፅ): ከሚመር ዕፅ ሁሉ ይልቅ የሚመር፡ እንደ ማጭድ ዝርዝር ጥርስ ያለው ዕንጨት። "ወንዴ ሬት"፣ "ሴቴ ሬት" እንዲሉ።
ሬቶች: "አባታችን ሰው እናታችን ሬት ናት" የሚሉ ሰዎች፣ ነገዶች፣ ወገኖች (ተረት)።
ሬንዥ: የምድር ዘይት፣ ድፍድፍ ወይም ጭቃ፣ ቅጥራን፣ አስፋልት። "የመፍቻውና የቅጥራኑም ምስጢር አጣብቆ መያዝ ነው።"
ሬንጅ (ዐረ): በያይነቱ ቀለም።
ሬንጅ (ዥ): እንግሊዝ መፍቻ።
ሬዋ: የዋስማ ዐይነት።
ር: የዜማ ምልክት (አንብር)።
ርኁብ (ርኅበ): የተራበ፣ ጥራዝ፣ ጥቂት መጣፍ፣ የጽጉብ ተቃራኒ።
ርኅሩኅ (ራኅርኀ): የራራ፣ የሚራራ፣ ወዛኝ። "ራራን ተመልከት።"
ርኅሩኅነት: ርኅሩኅ መኾን፣ ዐዛኝነት።
ርኅሩኆች (ርኅሩኃን): የሚራሩ፣ ሀዛኞች።
ርኅራኄ: መራራት፣ ዐኔታ፣ ቸርነት፣ ደግነት።
ርመጃቸው: ርገጫቸው።
ርመጅ: የሴት ልጅ ስም፣ ርገጭ።
ርሚጦ (ረምፅ): በረመጥ ተጠብሶ የበሰለ የውሻ መኖ።
ርሚጦሽ: ዝኒ ከማሁ። "እንቍልልጦሽ የውሻ ርሚጦሽ እንዲሉ ልጆች።"
ርምስ: የተረመሰ፣ ወሽቅ፣ ንክርዝፍዝፍ።
ርምስምስ አለ: ተርመሰመሰ።
ርምስምስ: የተርመሰመሰ፣ አኚትጕ ንዳን፣ ዘመሚት፣ ሀሸን።
ርምረማ: ረገጣ፣ ጥቅጠቃ።
ርምርም: የተረመረመ፣ የተረገጠ፣ ጥቅጥቅ ርግጥ የጤፍ ዕርሻ።
ርምርሞሽ: የመረምረም ሥራ።
ርምቡቅ: ልልነት ያለው መሬት፣ ሲረግጡት የሚሠረጐድ።
ርምድ: የቂጥኝ ቍስል፣ ካንዱ ወዳንዱ በሩካቤ የሚተላለፍ። የተረመደ፣ የተላከከ።
ርምጃ: ርግጫ፣ አካኼድ (ዘፍጥረት ፴፫፡ ፲፬። ፩ኛ ሳሙኤል፡ ፳፡ ፫። መዝሙረ ዳዊት ፲፯፡ ፲፩። ፵፬፡ ፲፰)።
ርሞ: በፀሓይ ሙቀት የጋለ አሸዋ፣ ሲረግጡት እንደ ረመጥ የሚያቃጥል።
ርሰት (ርሕሰት): ርጥበት፣ ርጥብነት።
ርሱ (ርእሱ፣ ለሊሁ): እሱ ራሱ፣ ቅሉ፣ ባለቤቱ። "እንቶ ያ።" "እሱን እይ።" "ደቂቅ አገባቦች፡ በ፣ የ፣ ከ፣ ለ ሲሰማሙት፡ በርሱ፣ የርሱ፣ ከርሱ፣ ለርሱ ይላል፣ ትርጓሜውንም በዚያ፣ የዚያ፣ ከዚያ፣ ለዚያ በል።"
ርሱ ቅሉ: ርሱ ራሱ። "ርሱ የቅሉ ቅጽል ነው።" "ዳግመኛም ቅሉ ግን ተብሎ ይፈታል።"
ርሳስ (ዐረ፡ ርጻጽ): የጥይት ዐረርና ሌላም መሣሪያ የሚኾን ማዕድን፣ እንደ ብረት ከመሬት የሚወጣ። "ዐረር የግእዝ ስሙ ነው።"
ርሳስ (ዐረ፡ ቢልስን): ቀለም በተጌጠኛ ዕንጨት የተሸፈነ ከሰል፣ ጽፈት መጻፊያ፣ ቢጋር መበገሪያ።
ርሳስ: አድማስ፣ ቱንቢ (ዘካርያስ ፮፡ ፲)።
ርሳታ (ርስዐት): ዝንጋታ።
ርሳቸው: እሳቸው፣ ራሳቸው፣ ቅላቸው፣ ባለቤታቸው፣ እነዚያ፣ እኒያ፣ እሊያ።
ርሳችን: እሳችን፣ ራሳችን፣ ቅላችን፣ ባለቤታችን፣ እኛ።
ርሳችኹ: እሳችኹ፣ ራሳችኹ፣ ቅላችኹ፣ ባለቤታችኹ፣ እናንተ።
ርሴ: እሴ፣ ራሴ፣ ቅሌ፣ ባለቤቴ፣ እኔ፣ እኔው።
ርስ (ርእስ): እስ፣ ራስ፣ ባለቤት፣ የስም ምትክ እየኾነ በ፱ ሰራዊት ይዘረዝራል። "እስን ተመልከት።"
ርስ በርስ: ክስ በክሱ፣ እዚያው በዚያው።
ርስ በርስ: ወገን ከወገን፣ ዘመድ ከዘመድ። "ዕውቀትና ትምርት የሌለው ሕዝብ ርስ በርስ ይዋጋል።"
ርስ: ወገን፣ ቤተ ዘመድ።
ርስሽ: እስሽ፣ ራስሽ፣ ቅልሽ፣ ባለቤትሽ፣ አንቺ።
ርስተ፡ (ኞች)፡ የርስት ጌታ፡ ባለርስት፡ ትክለኛ።
ርስተ ምድር፡ ኀላፊ፡ የሚያልፍ።
ርስተ ሰማይ፡ የማያልፍ።
ርስተ ጕልት፡ ንጉሥ ለባለማሉና ላገልጋዩ ርስት አድርጎ የሰጠው ጕልት፡ ርስትነት ከጕልትነት ያለው መሬት። ጐለተ ብለኸ ጕልትን ተመልከት።
ርስት ተከለ፡ ርስትን ሰጠ፡ አስረከበ።
ርስት አደረገ: ፈጽሞ ረሳ።
ርስት፡ ካባት ወደ ልጅ ሲወርድ፡ ሲያያዝ፡ ሲተላለፍ የሚኖር መሬት፡ ምድር፡ ቦታ፡ ስፍራ። ልጅም ባይኖር በዘር ይወርዳል እንጂ፡ ወደ ባዕድ አይኼድም።
ርስት: መሬት፣ ወረሰ።
ርስት: ዝንግት፣ ተወት።
ርስት: የርስት ስም፣ የገባር፣ የግንደ በል።
ርስኸ: እስኸ፣ ራስኸ፣ ቅልኸ፣ ባለቤትኸ፣ አንተ።
ርስዎ: እስዎ፣ ራስዎ፣ ቅልዎ፣ ባለቤትዎ፣ እንቱ።
ርስዎታ: ርስዎ ማለት፣ አንቱታ፣ ክብር፣ ሬታ።
ርሷ: እሷ፣ ራሷ፣ ቅሏ፣ ባለቤቷ፣ ያች።
ርሩ (ርኅሩኅ): የራራ፣ ያዘነ (ምሳሌ ፳፪፡ ፬)።
ርሾ (ዕብ፡ ሽኦር): የቡሖ የወተት ቅሬታ፣ ሌላውን የሚያቦካ፣ የሚያሖመጥጥ (ማቴዎስ ፲፫፡ ፴፫። ፲፮፡ ፮)። "ሲበዛ ርሾዎች ይላል።"
ርሾ: ተቀማጭ የኾነ ጥቂት ገንዘብ።
ርቀት (ርሕቀት): ራቂያ፣ ሩቅነት (መክብብ ፯፡ ፳፬)።
ርቀት: ረቂቅነት፣ ቅጥነት፣ ሥሥነት (ላቀ)።
ርቀት: ራቂያ፣ ራቀ።
ርቄ (ርሒቅየ): እኔ ለሚል ቦዝ አንቀጽ፣ ተገልዬ ተለይቼ ማለት ነው።
ርቄ: በመንዝ ክፍል ያለ አገር። "ዝናቡ መጣ ከወደ ርቄ፣ ሊሞት ነው አሉ መላጣው ብርቄ እንዲል እረኛ።"
ርቆሽ: ዝኒ ከማሁ።
ርቢ (ዎች): ባለቤቱ ባልኾነ ሰው ዘንድ የከብት መርባት። "የርቢ ከብት፣ የከብት ርቢ" እንዲሉ። "ከ፲፱፻፴፫ ዓ.ም ወዲህ ግን የፈረንጅ ተማሮች ርቢን 'ርባታ' ይሉታል፡ የስሕተት ስሕተት ነው።
"
ርቢት (ርብዒት): ካራት አንድ ውጤት።
ርባ (ርባሕ): የግስ አንቀጽ፣ ወለድ፣ ርባ (የርባታ ከፊል ነው)።
ርባ ሥባ: ለቤት እንስሳ የሚነገር ምርቃት።
"ለሰውም ይኾናል፡ 'ውለድ፣ ብዛ፣ ይድላኸ' ማለት ነው።
"
ርባ ቅምር: ቅምር የተባለ ላለቅነትና ለጭፍርነት ለርባታ ተወስኖ የተመደበ ግስ ነው፡ ሌሎችም የሰዋስው ክፍሎች ይነገሩበታል።
ርባ ዘርዛሪ: ዘጠኙ ሰራዊት (ከውእቱ እስከ ንሕነ ያሉ የስም ምትኮች) (መራሕያን)።
ርባ ግስ: የግስ ርባታ ከነጓዙ።
ርባታ: በሩቅ ወንድ የተነገረ ያንድ ግስ ብዛት፣ ብዙነት። "ተመልሰሽ ርባን እይ፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። " (የዋህ ርባታ): ከዐወቀ እስከ ዐወቅና መዠመሪያ በ፱ መደብ የሚረባ። (ዐቢይ ርባታ): በ፹ መደብ የሚረባ አንቀጽ (ይህ በግእዝ ነው)። "በአማርኛ ግን ፷፩ ይኾናል። " (ንኡስ ርባታ): አርእስት፣ ቅጽል፣ ሳቢ፣ ዘር (ደቂቅ ርባታ)፡ ባ፲ መደብ የሚረባ ነባር አንቀጽ፣ ጥሬ ዘር። "መጽሐፍ ግን በረብና በርባና ፈንታ 'ርባታ' ይላል (፩ኛ ዜና መዋዕል ፲፬፡ ፲፬፡ ኢሳይያስ ፳፫፡ ፲፰)። " አረባብ: አወላለድ፣ አጠቃቀም፡ መርባት።
ርባና ቢስ: ጥቅመ መጥፎ።
ርባን (ርባና): ረብ፣ ጥቅም።
ርባን ሥራ: በላዩ ቀጪን ሽቦ የተጠመጠመበትና ረቂቅ ንቅስ ያለበት የወርቅ፣ የብር መስቀል፣ ቀለበት፣ ኵክ ማውጫ፣ ድኰት፣ ግርጃ። "ላንጥረኛውና ለሸያጩ ጥቅም የሚሰጥ ስለ ኾነ 'ርባን ሥራ' ተባለ። "
ርባን የለሽ: ጥቅም አልባ።
ርባን ጌጠኛ: ቀለበት።
ርብ: ያገር ስም። ረበበ።
ርብረባ: ስደራ፣ ድርደራ።
ርብራብ፡ መረባርብ።
ርብርብ፡ የተረባረበ፡ የተርከፈከፈ፡ ንብብር፡ ድርብርብ፡
ርክፍክፍ።
ርብርቦሽ፡ ንብብሮሽ።
ርብትብት፡ (ቶች)፡ የተርበተበተ፡ ፈጥኖ፡ መናገር፡ መሥራት፡
የማይችል።
ርብትብት፡ አለ፡ ተርበተበተ።
ርብክ: የተረበከ፣ ውዝፍ፣ ጭቃ፣ ዐዛባ (ከተቀመጠበት የማይነሣ ሰው) ርፍቅ።
ርብድብድ (ዶች): የተርበደበደ፡ ፈሪ።
ርብድብድ አለ: ተርበደበደ።
ርቦ (ዎች): የቍና አራተኛ ታናሽ ስፌት።
ርቦ በቁሙ: ረባ (ረብዐ)።
ርቦ አፍሳሽ: ካራት አንድ ለባለመሬት የሚሰጥ ተጋዥ።
ርተኛ (ኞች): የርት ባለርት፣ ርት ያለው፡ ማርት አድራጊ። በግእዝ "ማሪ" ይባላል።
ርተኛነት: ማርተኛ መሆን።
ርቱ: የርሱ ርት። "ርቱም ርቴ፣ ምቱም ምቴ እንዲሉ።"
ርታታ (ርትዐት): የሙግት ፍጻሜ፣ ዕድል፣ ቀጥታ።
ርት (ማረየ): ጦስ፣ ደንቃራ፡ ሰውን ለመጕዳት የተቀበረ መድኀኒት። በአውሬና በወፍ ጩኸት፣ በውሻ ዕንጥስታ፣ በአሳት ማናፋት ማመን፡ ከዚህ የተነሣ "እንዲህ ይኾናል፣ ይደረጋል" ማለት፡ መላ መምታት፡ ጥንቈላ።
ርት (ርቱዕ): የረታ፣ የቀና። "ፍት ርት እንዲሉ።"
ርት ዐደር: ተረቶ ያደረ፣ የቈየ።
ርት: የተረታ፣ የተሸነፈ።
ርትረታ: ሶምሶማ፣ ዝብዘባ።
ርችት (ረጪ): የሚበተን የመድፍ ጥይት።
ርኝት: ዐዉርና ወፍራም ሰው። "ዘሩ ወረን ነው።"
ርኤም (ሞች): የበረዶ እንስሳ፡ ፪ ቀንዶቹ ባለብዙ ተቀጥላ የኾኑ።
"መጽሐፍ ግን 'ሪም' ይላል (ዘኍልቍ ፳፫፡ ፳፪፡ ዘዳግም ፴፫፡ ፲፯)። " ርኤም ከረከንድ: ርኤም የዋሊያ፡ ከረከንድ የፈረስ ወገን ነው፡ አንድ ስም አይዶለም። "አውራሪሥን እይ። "
ርእሰ ሀገር: ዋና ከተማ፣ መናገሻ፣ መዲና።
ርእሰ መድጐስ: ሦስት ዐይነት የድጕስ መሣሪያ።
ርእሰ ደብር: ማዕርጉ ከሊቀ ጠበብት በታች የኾነ የደብተሮች ሹም።
"ደብር የተባለ መቅደሱ ነው።
"
ርእሰ ደብር: የተራራ ራስ፣ ፵ፍ።
ርእስ (ርእሰ): ራስ፣ አለቃ (ግእዝ)። ርእስ: የፊደል ስም (ረ)።
ርኩም (ሞች): የአሞራ ስም፣ እረኸላረኽ ተራራ ለተራራ እየዞረ እባብ ፈልጎ የሚበላ ኣሞራ፣ ተባቱም እንስቱም ርኩም ይባላል፣ ድምፁ እንደ ነጋሪት ይተማል። "(ተረት): ያፌን እስክውጥ ዕድሜ ይስጠኝ ይላል ርኩም።"
ርኩሰ: ርኩስ፣ የርኩስ ርኩስ (ዘሌዋውያን ፲፫፡ ፭)።
ርኩስ: የረከሰ፣ ንጹሕና ቅዱስ ያይደለ፣ ነውረኛ፣ በዝሙት በኀጢአት ያደፈ፣ የተጨማለቀ።
ርኩስነት: ርኩስ መኾን።
ርኩሶች: የረከሱ፣ ነውረኞች፣ ኀጢአተኞች (፪ኛ ጴጥሮስ ፪፡ ፲፫)።
ርኵት: የውሃ መያዣ፣ ረካ።
ርካሽ: የተናቀ፣ የተዋረደ ሽያጭ። "በርካሽ ተሸጠ ተገዛ እንዲሉ።"
ርካብ (ቦች): ወደ ኮርቻ መውጫ፣ ባለማፈኛ ኹለት ጠፍር፣ በጫፉ ሰፋፊ የብረት ቀለበት ያለው፣ ቀለበቱም ርካብ ይባላል። "ርካቡ ተበጠሰ፣ ርካብ ቈነጠጠ እንዲሉ።"
ርካብ: መገናኛ ቀን፣ ሐዋርያት ከትንሣኤ በኋላ ጌታን ያገኙበት ዕለት፣ የትንሣኤ ፳፭ኛ፣ የበዓለ ኀምሳ እኩሌታ በዓል፣ ሮብ የሚውል። "ከዚህ የተነሣ ካህናት ቢያመቱ ስለ ቤተ ክርስቲያን ጕዳይ በኢየሩሳሌም ይሰበሰባሉ።"
ርካብ: የጨረቃና የፀሓይ መገናኘት፣ መነጻጸር፣ በመርሐ ዕውር፣ ዐውደ አበቅቴ ይባላል፣ ፲፱ ዓመት ነው።
ርካብሽ: ወርቅ የምራት ስም።
ርካታ: የውሃ የመጠጥ ጥጋብ።
ርክሰት (ርኵሰት): ርክስና።
ርክስ (ረኪስ): መርከስ።
ርክስ አለ: ረከሰ፣ ጠያቂ ዐርክስና፣ ርኩስነት፣ ርካሽ መኾን።
ርክርክ: የተረከረከ፣ ውልግድግድ ጽፈት፣ የድጓ ምልክት።
ርክክብ: ቅብብል።
ርክፍካፍ: የተርከፈከፈ፣ የተረበረበ።
ርክፍካፎ: ትርፍ ቃል። "የነገር ርክፍካፎ እንዲሉ።"
ርክፍካፎ: ካፊያ፣ ነጠብጣብ። "(ተረት): በሐምሌ ወጨፎ በኔ ርክፍካሮ።"
ርኰት: ራዎት፣ የውሃ መያዣ ከጕማሬ ቈዳ የተበጀ። "በግእዝ ጸፈን ይባላል።"
ርዝመት (ኑዏ): ዝኒ ከማሁ፣ የቁመት ብዛት፣ ሞላልነት (ዘፍጥረት ፯፡ ፲፭። ዘዳግም ፴፡ ፳። ሕዝቅኤል ፲፱፡ ፲፩። ፩ኛ ሳሙኤል ፯። ማቴዎስ ፳፫፡ ፲፬)።
ርዝማን: ረዥምነት፣ ብልጫ።
ርዝራዥ: ረጃት።
ርዝራዥ: ፍድፋጅ፣ ትርፍራፊ ዱቄት።
ርያን (ርሔ): ነጭ የሽቱ ቅጠል፣ ጣፋጭ፣ ሪሓን።
ርዳ (ርዳእ፡ ተራድእ): ወግዝ፣ ተጋገዝ፣ የሳንሳ ያዝ።
ርዳታ: ወዜታ፣ በገንዘብ በጕልበት መርዳት።
ርድና: ረድነት።
ርገጤ፡ የሰው፡ ስም፡ ርገጥ፡ ማለት፡ ነው።
ርጉ፡ (ርጉዕ) ፣ የረጋ፡ የጸና፡ ግግር።
ርጉም፡ (ሞች)፣ የተረገመ፡ አባት፡ እናት፡ አውራሾች፡ አሳዳጎች፡
የካዱት።
ርጉም፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ አባቱን፡ ያስገደለ፡
የጐንደር፡ ንጉሥ።
ርጉም፡ ኾነ ፣ ምርቃት፡ ዐጣ።
ርጉኖ፡ ነውር፡ አልዛ፡ ጥብቅ፡ የጠበቀ።
ርጋ፡ ዕረፍ፡ ጸጥ፡ በል፡ (ግጥም)፡ ርጋ፣ ይወጣሉ፡ ደጋ። "ወክፈሌን፡ አስተውል። "
ርጋታ ፣ (ርግዐት)፡ ዕረፍት፡ ጸጥታ፡ ዝምታ፡ ሰላም።
ርጋጭ ርጋጭ፡ አለ፡ ያፈር፡ ጣዕም፡ ሰጠ፡ ውሃው።
ርጋጭ፡ የተረገጠ፡ ውሃ፡ መሬት፡ (ሕዝቅኤል ፵፡ ፯)።
ርጋፊ ፣ ርጋፎ፡ የረገፈ፡ የወደቀ፡ ድቃቂ፣ ፍርፋሪ።
ርግ ፣ ዱካ፣ ፈለግ፣ (ኢዮብ ፱፡ ፯)።
ርግመት፣ (መርገም)፣ አደፍ፡ (ትክቶ)፡ ግዳጅ፡ በኦሪት፡ ሕግ፡ ሴትን፡ ከሰው፡
አንድነት፡ የሚለይ፡ ለብቻ፡ የሚያስቀምጥ።
ርግማን ፣ መርገም፡ መረገም። "በግእዝ፡ ርግመት ' ይባላል፡ (ዘዳግም ፳፫፡ ፭)። "
ርግረጋ፣ ንቅነቃ፡ ውዝወዛ።
ርግቡ፡ ያ፡ ርግብ፡ የርሱ፡ ርግብ።
ርግብ ፣ (ረጊፍ)፡ መርገፍ።
ርግብ ፣ ገር፡ ደግ፡ ህዛኝ፡ ርኅሩኅ፡ ሰው፡ ርግብ፡
ሆዷ፡ ዐዛኚቷ፡ ማሪያም።
ርግብ፡ (ቦች)፡ የከፍተኛ፡ ወፍ፡ ስም፡ በቤትና፡ በዱር፡
የሚኖር፡ የዋህ፡ ወፍ፡ የመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ምሳሌ። "ተባቱንና፡ እንስቲቱን፡ ለመለየት፡ ርግብ፡ ነው። "
ርግብ፡ ርግብ፡ አለ፡ ክድን፡ ግልጥ፡ አለ፡ ቅንድቡ።
ርግብ፡ ርግብ፡ አለ፡ ጠብ፡ ጠብ፡ እለ።
ርግብ፡ አለ፡ ረገበ።
ርግብ፡ አለ፡ ረገፈ።
ርግብ፡ አደረገ፡ ፈጽሞ፡ ተወ።
ርግብ፡ የረገበ፣ ጕርብ፡ ልል፡ (ቅጽል)።
ርግብማ፡ ወርቸ፡ ነጭ፡ ፍየል።
ርግብግቢት፡ የተርገበገበች፡ ከግንባር፡ በላይ፡ ከቍንጮ፡
ያ፡ በታች፡ በመካከል ያለች፡
ሥሥ፡ የራስ፡ ዐጥንት ፣ የሆድና፡ የደረት፡ መገናኛም፡ ርግብግቢት፡
ትባላለች።
ርግብግብ፡ (ቦች)፣ የተርገበገበ፣ ልምጥምጥ። "ርግብግብ፡ የላም፡ ጋሻ፡ ለናትኸ፡ ግባላት፡
እንዳሉ፡ ዐጤ፡ ቴዎድሮስን ፣ አባ፡ ውርጂ፡ አንተን፡ ይስጠኝ። "
ርግብግብታ፡ የፀሓይ፡ ሰሌዳ፡ ንቅናቄ፡ ወራውራን።
ርግቧ፡ ርግቢቱ፡ ያች፡ ርግብ፡ (ዘፍጥረት ፰፡ ፲፩)።
ርግቧ፡ የርሷ፡ ርግብ።
ርግት፡ አለ፡ ጸጥ፡ አለ።
ርግት፡ ጸጥ፡ ዕርፍ።
ርግዱ፡ የወንድና፡ የሴት፡ ስም፡ ሰዎች፡ ይራዱ፡
ይፍሩ፡ ማለት፡ ነው፡ ዳግመኛም፡ ይርገዱልኸ፡ ይርገዱልሽ፡ ይባላሉ።
ርግድግድ፡ አለ፡ ተገደገደ።
ርግድግድ፣ የተገደገደ፡ እንግድግድ፣ ፍግምግም።
ርግድግድታ፡ ፍግምግምታ።
ርግጠኛ፡ (ኞች)፡ እውነተኛ፡ የታመነ፡ ሐቀኛ።
ርግጡን፡ እውነቱን።
ርግጥ፡ (ርጉዕ)፡ የተረገጠ፡ የተጠቀጠቀ።
ርግጥ፡ (ጥዩቅ)፡ ድርስ፡ እውነት፡ ነገር፡ ሐቅ፡ (ማቴዎስ ፲፪፥ ፳፰)።
ርግጥ፡ ኾነ፡ ተረገጠ፡ ታመነ። "(ጥጥ) ርግጥ፡ አደረገ፡ ረገጠ። "
ርግጫ፣ የመርገጥ፡ ሥራ፡ ርምርማ፡ ጥቅጠቃ።
ርጎ፡ የረጋ፡ ወተት፡ ወፍራም፡ ዝቡጥቡጥ፡ (ዘፍጥረት ፲፰፡ ፰)።
ርጐፍት፣ ጣፋጭ፡ ሽታ፡ ያለው፡ ቅጠል።
ርጓ፡ ቀን፡ ሽመል፡ ወይም፡ ቀርክሓ፡ በግራና፡
በቀኝ፡ እጅ፡ ከሸማ፡ ጠርዝ ፣ ውጭ ፣ የምትቆም፡ የምትረጋ፡ በመወርወሪያ፡ ውስጥ፡
ተጋድማ፡ ከቀሠም፡ ጋራ፡ ድውርን፡ የምታር፡ የምታሽከረክር፡ የሸማኔ፡ ዕቃ። "ዳግመኛም፡ ርጓ፡ (ርግዑኦ)፡ ለቅርቦች፡ ወንዶችና፡ ሴቶች፡ ትእዛዝ፡
አንቀጽ፡ ይኾናል፡ ይኸውም ፣ በፈትልና፡ በጥለት፡ መወርወሪያዎች፡ መካከል ያሉትን፡ ኹለቱን፡ ያሳያል፡ ትርጓሜውም፡ ቂረፋ፡
ማለት፡ ነው።
"
ርጓ ቀጪን፡ ሽመል ፣ ረጋ።
ርጣጭ፡ ርጥጥ፡ ወዛፋ።
ርጥ፡ የጨፍ፡ እንጀራ፡ አነባበሮ፡ ድልኽ፡ ሰሊጥ፡
ኑግ፡ ተልባ፡ ያለበት። "(ተረት)፣ እንግዴህ፡ ለርጥ፡ አምሮቴ፡ ቍርጥ። "
"ዕርፍ፡ መጣያን፡
አስተውል።
"
ርጥረጣ፡ ርትረታ፡ ሩጫ፡
ርጥበት፡ ርሰት፡ ልምላሜ፡ ጠል።
ርጥባርጥብ፡ የርጥብ፡ ርጥብ፡ ብዙ፡ ዐይነት፡ ርጥብ ፣ ሥጋና፡ ቅቢ፡ ያለበት፡ ምግብ።
ርጥባን፡ ርዳታ፡ የጠፋ፡ ምትክ።
ርጥብ፡ (ቦች)፡ የረጠበ፣ የራሰ፡ የለመለመ፡ (ኢዮብ ፰ - ፲፮)። "(ተረት)፣ ሳይርቅ፡ በቅርቡ፡ ሳይደርቅ - በርጥቡ። "
"እጅን፡ እያ። "
ርጥብ፡ ልጅ፡ ያልጠና፡ ያልጠነካረ፡ ዐራስ፡ ጨቅላ።
ርጥብ፡ ሬሳ፡ ሙቶ፡ ያልዋለ፡ ያላደረ፡ ትኵስ፡
ሬሳ።
"ርጥብ፡ ሬሳ፡
ደረቁን፡ አስነሣ፡ እንዲሉ። "
ርጥብ፡ ቈርበት፡ ተገፎ፡ ያልሰነበተ፡ ቄዳ።
ርጥብ፡ አስተኔ፡ የርጥብ፡ ዐይነት፡ ወይንም፡ ወገን።
ርጥብ፡ እማኝ፡ በሸንጎ፡ የሚነሣ፡ ዐዲስ፡ ምስክር።
ርጥብ፡ ዕንጨት፡ ያልተቈረጠ፡ ወይም፡ ተቈርጦ፡
ያልደረቀ፡ ዕንጨት።
ርጥብ፡ ጋን፡ ሰረረ)፡ አለልክ ቀበጠ፣ አበደ።
ርጥብነት፡ ርጥብ፡ መኾን።
ርጥጥ፡ የተረጠጠ፡ ዕምቅ፡ ጭቍን፡ ተቀማጭ፡ ውዝፍ፡
የሰንበት፡ እበት።
ርጨት ፣ ርቺት።
ርጭ፡ አለ፡ ዝም፡ ጭጭ፡ አለ፡ በውሃ፡ እንደ፡
ተመታ፡ ልጅ።
ርጭ፣ ጭር፡ ዝም፡ ጸጥታ፡ ዝምታ።
ርጭ፡ ጸጥ።
ርፍራፊ፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ ንስናሽ።
ርፍርፍ፡ የተረፈረፈ፡ የተኛ፡ ንስንስ፡ ጕዝጕዝ።
ርፍቅ፣፡ የተረፈቀ፡ ውዝፍ።
ርፍቆች ፣ ውዝፎች፡ ወንዶችና፡ ሴቶች፡ ።
ርፍጥ፡ ፍቅ፡ ቅምጥ።
ሮሐ፡ የላሊበላ፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ የተሠራችበት፡
አገር።
"የሮሐ፡ ትርጓሜ፡
በግእዝ፡ እራገበ፡ አታጨለ፡ ነው። "
ሮማ ፣ ሮሜ ፣ ሮም፡ የከተማ፡ ስም፡ በአውሮጳ፡ ውስጥ፡ የሚገኝ፡
የጣሊያን፡ ዋና፡ ከተማ። "ይኸውም፡ ሮምሎስ፡ ከሚባል፡ ካቅኒው፡ ስም፡ የመጣ፡ ነው። " "ጊዮርጊስ፡ ወልደ፡ ሐሚድ፡ ሮምሎስና፡ ወንድሙ፡
ኢታሎ፡ ከዳዊት፡ ሸሽተው፡ ከፍልስጥኤም፡ የኼዱ፡ የዔሳው፡ ዘሮች፡ ናቸው፡ ይላል። "
ሮማነ፡ ወርቅ፣ ከወርቅ፡ የተበጀ፡ የሮማን፡ ቅርጽ።
ሮማን፡ የተክል፡ ስም፡ ፍሬው፡ የሚበላ፡ ተክል፡
ቅርፊተ፡ ቀይ፡ ሲበዛ፡ ሮማኖች፡ ይላል፡ (ዘጸአት ፳፰፡ ፴፫)።
ሮማዊ፡ የሮም፡ አገር፡ ሰው፡ የሮማ፡ ተወላጅ።
ሮማዊት፡ የሮም፡ ሴት።
ሮማውያት፡ የሮማ፡ ሴቶች።
ሮማውያን፡ የሮም፡ ሰዎች፡ የሮማ፡ ተወላጆች።
ሮማይስጥ፡ የሮምሎስ፡ ቋንቋ፡ ላቲን።
ሮም፡ በላዩ፡ የሴት፡ ሻንቅላ፡ ሥዕል ያለበት፡ የፈረንጅ፡ ዐረቄ።
ሮምታ፡ ባለማቋረጥ፡ ግባት፡ ተኵስ።
ሮሞች፡ ሮማውያን፡ የግእዝ፡ ሮሞች' ያማርኛ፡ ነው።
ሮሮ፡ (ኦሮ)፡ ጥቃት። "እከሌ፡ ሮሮ፡ አይመረውም፡ እንዲሉ። "
ሮቃ፣ (ኦሮ)፣ ሖመር።
ሮቄ፡ ማጥ።
ሮቢት ፣ የኦሮ፡ ነገድ፡ በይፋት፡ ክፍል፡ ያለ፡ ቀበሌ።
ሮቤል: የሰው ስም፡ የያዕቆብ የበክር ልጅ።
ሮብ (ረቡዕ): የቀን ስም፡ አራተኛ ቀን።
"ሮብና ዐርብ ከበዓላ ኀምሳና ከልደት ከጥምቀት በቀር በክርስቲያን ሕግ ሥጋና ቅቤ፣ ዕንቍላል አይበላም። "
ሮብ ለት (ዕለተ ረቡዕ): የሮብ ቀን፣ ሮብ የሚባል ቀን።
ሮብ የቀን ስም: ረባ (ረብዐ)።
ሮብ: የወንዝ ስም (በበጌምድር የሚገኝ ዠማ)።
ሮንዜ፡ ባንድ፡ ቀበሎ፡ የገባ፡ ብዙ፡ ድር፡ በነጠላ፡
በቡልኮ፡ ጠርዝና፡ ጠርዝ፡ የሚታይ፡ ሮንዛዊ፡ የሮንዝ፡ ማለት፡ ነው።
ሮንዜ፡ የማግ፡ ጥሙር፡ በኩታ፡ በነጠላ፡ መፃፍ፡
በጥለት፡ ፈንታ፡ የተሠራ።
ሮንዝ፡ ዕጥፍ፡ ደርብ፡ ሽርብ፡ ፈትል።
ሮጠ: በረረ።
ሮጥ፡ (ረዊጽ)፣ መሮጥ።
ሮጥ፡ ሮጥ፡ አለ፡ ሩጫ፡ ዠመረ።
ሮጸ፣ ጋለበ ፣ ሮጠ።
ሯ አለ: ፍስስ አለ፡ ነደደ ውሃው፡ ነበልባሉ።
ሯጭ (ረዋጺ)፣ የሮጠ፡ የሚሮጥ፡ በራሪ፡ ፈጣን፡ ኦሮቢ፡ ፈርጣ።
ሯጭነት፡ ሯጭ፡ መኾን፡ ኦሮቢነት፡ በራሪነት።
ሯጮች ፣ (ረዋጽያን)፣ የሮጡ፡ የሚሮጡ ፣ ፈጣኖች።
No comments:
Post a Comment