Tuesday, June 10, 2025

 

: የሐ ዲቃላ ፫ኛ ኀ። በግእዝና በዐረብ ድምፁ እንደ የሚነገር። በተራ ቍጥር ዘጠነኛ ሲኾን ስሙ ኀርም ፡ በአኃዝነት ኀ፣ ፭፻ ይባላል። ጻፎችም ግእዙን ለራብዕ ለውጠው ስሙን ብዙኃን ይሉታል። (ነገር ግን በፊደልነት መደበኛው ዘጠነኛ ነው።)

በረዶነጭ በረዶ፣ ኆጻ መሰል ጥቃቅን።

: የኀ ዲቃላ በመኾኑ ስለ ቀለበቱ ኈ፱፻ ይባላል።

ኀለየ: ዐሰበ (ግእዝ)

ኀለፈ)ዐለፈ (ግእዝ)

ኀላፊዋቢ፡ ሰጪ፡ መድን፡ ዘበኛ፡ በሰጠው፣ በሸጠው፣ በጥበቃው የሚያልፍ፡ ተጠያቂ፡ ተያዥ።

ኀላፊዋና ባለቤት፡ አዛዥ። "የሥራ ኀላፊ" እንዲሉ።

ኀላፊያለፈ፡ የሚያልፍ ዘመን፡ ትውልድ።

ኀላፊነትኀላፊ መሆን፡ ተያዥነት።

ኀላፊዎች(ኀላፍያን፣ ያት)ያለፉ፡ የሚያልፉ ነገሮች።

ኀልዮማሰብ።

ኀሙስ(ኀመሰ)የቀን ስም፡ ዐምስተኛ ቀን፡ በሮብና በአርብ መካከል ያለ። በሕዝብ አነጋገር ዐሙስ ይባላል፡ "ጸለየን" እይ።

ኀሚዐምስተኛ፡ የቀባርዋ ምት።

ኀምሳ()የቁጥር ስም፡ ፭ ጊዜ ወይም ጊዜ ፭። "ዐመሰን" ተመልከት።

ኃምስ፭ኛ ፊደል። " ኃምስ ኃምስ" እንዲል የፊደል ተማሪ። የአገር ስም መጨረሻ ፊደል በኃምስነት ሲነገር በቂ ይሆናል። "ሺዌ" "ጐንደሬ" "ጐዣሜ"የሺዋ፣ የጐንደር፣ የጐዣም ሰው ማለት ነው። ፮ኛውን "" እይ።

ኃምስነት፭ኛነት።

ኀምራዊየቀይ ዐይነት፡ የቀይ ወገን። "ኀምራዊ ሐር" እንዲሉ።

ኀምርወይን ጠጅ፡ የጥቁር ቀይ ደማባ።

ኀሠሠ: የወር ስም፡ ፬ኛ ወር ከመስከረም። "ምስጢሩ፡ ጌታን፡ ለመፈለግና፡ ያለበትን፡ ለመመራመር፣ ወደቤተልሔም፡ የሰብአ፡ ሰገልን፡ መምጣት ያሳያል። ባላገርም፡ ትሣሥ፡ ይለዋል።"

ኀሳርውርደት፡ ዐሳር።

ኀረመ: ለየ፣ ከለከለ።

ኀረገ (ግእዝ): ወጣ (ዐረገ)

ኀራም: የተለየ፣ የተከለከለ፣ የተገዘተ። (ለምሳሌ: "ኀራም ነው" እንዲሉ)

ኀራጅ(ዐረ፡ ኸረጀ፡ ወጣ)ዋጋን በማሳረር የሚሸጥ ዕቃ።

ኀራጅ አለዕቃን፣ ከብትን፣ ንብረትን አደባባይ አውጥቶ እያጫረተ ዋጋ ላበለጠ ሸጠ።

ኀርም(ኀረመ)የፊደል ስም፡ ፫ኛ " ኀርም " እንዲሉ። ትርጓሜው ልዩ፣ ብቸኛ ማለት ነው።

ኀርም: የኀ ፊደል ስም፣ ዘጠኝ። (ኀርምን እይ)

ኀበረ (ግእዝ): ዐበረ።

ኀተመ: በማኅተም ረገጠ፡ ዐተመ።

ኀቲምመርገጥ፡ ማተም።

ኀቲም ቀለበትየማኅተም ቀለበት፡ ስም የተጻፈበት።

ኀዋት (አኀው። ትግርኛ: አኅዋት): ወንድሞች፣ ወንድማማቾች፡ ባንድ ስፍራ ተሰብስበው ውርርድ፣ ጋሬዳ የሚያደርጉ ጓደኞች፣ ባልንጀሮች። (ለምሳሌ: "የኀዋት ዳኛ" እንዲሉ) (ጅልንና ቂልን ተመልከት)

ኀው (እኅው): በትግሪኛ ወንድም ማለት ነው።

ኃዘና፡ የመሶብ ዐይነት ዕቃ ወይም ቅርጫት፣ የጥራር እንጀራ ማስቀመጫ። ዐረብኛ "ኸዝና" ከሚለው ጋር አንድ ነው፤ "ኸዝና" የገንዘብ ሣጥን ይባላል።

ኀያል(ኀየለ)ኀይለኛ (ግእዝ)

ኀይለ መለኮትየመለኮት ኀይል።

ኀይለ ሚካኤልየሚካኤል ኀይል።

ኀይለ ማርያምየማሪያም ኀይል።

ኀይለ ሥላሴየሥላሴ ኀይል።

ኀይለ ሩፋኤልየሩፋኤል ኀይል።

ኀይለ ቃልየኀይል ንግግር።

ኀይለ ቃልየቃል(ወልድ)፡ ኀይል።

ኀይለ አንበሳየአንበሳ ኀይል።

ኀይለ እግዚአብሔርየእግዜር ኅይል።

ኀይለ ገብርኤልየገብርኤል ኀይል።

ኀይለ ጊዮርጊስየጊዮርጊስ ኀይል።

ኀይለኛ (ኞች)ሐርበኛ፡ ጐበዝ፡ ብርቱ (ኢሳ፴፩፡ )

ኀይለኛ()ነትኀይለኛ መሆን።

ኀይሉኀይሌየወንድ ከፊለ ስም፡ ዳግመኛም "የርሱ ኀይል" "የኔ ኀይል" ተብሎ ይተረጐማል። ኀይል እንደ ግእዝ ሥርዐት ዘርፍና ቅጽል ይዞ ሲነገር፡

ኀይል መንፈሳዊየመልአክ ኀይል።

ኀይል ሥጋዊየሰው ኀይል።

ኀይልብርታት፡ ጕልበት፡ ጕብዝና፡ ጥናት፡ ጥንካሬ፡ ችሎታ። (ዐየለን ተመልከት)

ኀይልገንዘብ፡ ሰራዊት (ግእዝ) (የጦር ኀይል እንዲሉ)

ኀደረ (ግእዝ): ዐደረ።

ኀጢአተኛ (ኞች)(ኃጥእ፣ ኃጥኣን)ባለኀጢአት፡ ኀጢአታም፡ ሕግ አፍራሽ፡ ክፉ አድራጊ፡ ግፈኛ፡ በደለኛ፡ አመንዝራ (መዝ፴፮፡ ፩። ፩፡ ፳)

ኀጢአተኛነትኀጢአተኛ መሆን፡ አመንዝራነት።

ኀጢአቱን አመነበድያለሁ አጥፍቻለሁ አለ፡ ንስሓ ገባ፡ ስሕተቱንና ድፍረቱን ለቄስ ነገረ፡ ተናዘዘ።

ኀጢአት ሠራሕግን ተላለፈ፡ የማይገባ ሥራ ሠራ፡ ክፉ አደረገ፡ አመነዘረ።

ኀጢአትከሕግ የወጣ ክፉ ሥራ፡ በደል፡ ዐመፅ፡ ምንዝር፡ በኀልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር የሚደረግ።

ኀጢአትያመንዝራ ዘር ርክሰት።

ኀጢኣት ሠራ: ሕግን ተላለፈ፡ ሰረቀ፡ አመነዘረ።

ኃጥእ(ኀጥአ)ኀጢአተኛ ሰውጽድቅንና እውነትን ያጣ ወይም ያላገኘ።

ኀጫ(ኆጻ)ነጭ ጸዐዳ የእብነበረድ፣ አፈር አሸዋ የሚመስል።

ኀፍረት(ኀፍረ)ዕፍረትየወንድና የሴት ብልት (ኢሳ፫፡ ፲፯) "ዐፈረን" አስተውል።

ኂጣን(ኄጠ፡ ኀየጠ)ሽንገላ፡ ድለላ (ፖለቲክ)

ኅሊና ቢስክፉ ዐሳቢ፡ ዐሳበ መጥፎ።

ኅሊናዐሳብ፡ ልባዊ ረቂቅ ሥራ።

ኅሊናውን ሳተልበ ቢስ ሆነ፡ አእምሮውን ዐጣ።

ኅላፍ (ፎች)እኩሌታ የብራና ቅጠል፡ ታጥፎ ተላልፎ ከሙሉው ጋራ የሚጠረዝ።

ኅልፈተ ዓለምየሰማይና የምድር መደምሰስ፡ መጥፋት።

ኅልፈትማለፍ፡ መታጣት።

ኅምርእንሶስላ፡ ሒና።

ኅሩይ(ኀረየ)የሰው ስም፡ የተመረጠ፡ ምርጥ።

ኅርመት በነጥብ የተወሰነ አንድ ቃል።

ኅርመትየፊደል ቅንጣት፡ አንዱ ቅርጽ፣ ንቅስ አጣጣል፡ የማተሚያ ቃል፡ (ግእዝ) የንስሳ፣ የአሞራ፣ የጦር መሣሪያ፣ የፀሐይ፣ የጨረቃ፣ የኮከብ ሥዕል የተቀረጸበት ማተሚያ፡ መርገጫ።

ኅብስተ ሕይወት : ድንጋይ ዳቦ።

ኅብስተ ሕይወት: የሕይወት እንጀራ (ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ)

ኅብስተ መና: ከሰማይ ከወረደ መና የተጋገረ ኅብስት። እስራኤል ዘመን በገዳም የተመገቡት። (መና ቅንጣቱ፡ ኅብስት ዳቦው) (ለምሳሌ: "እመት እከሊት የጋገረችው ዳቦ ኅብስተ መና ይመስላል")

ኅብስት (ኀበዘ፣ ኅብዝት): ክብ እንክብል ጭብጦ የሚያካክል ዳቦ። ለቡሔ፣ ላራስ ጥሪ የሚጋገር። (ሲበዛ ኅብስቶች ይላል። በግእዝ ግን እንጀራም ኅብስት ይባላል። ዕብስትን አስተውል)

ኅብረት: አንድነት፣ ስምምነት።

ኅብር : ባንድ ቃል ኹለት ትርጓሜ የሚያሳይ ቅኔ ወይም ግጥም። (ለምሳሌ: "ሀብኒ ማየ፡ ለእመ አልብኪ ማይ" - ውሃ ስጪኝ፡ ውሃ ባይኖርሽ ማይ - ይህን የመሰለ። ጉባኤ ቃና - "መላእክተ ላዕል ወትረ እምገጸ ዓለም ተኀብኡ፡ አዕዋፈ ሰማይ ኵሎሙ አኮኑ ሥጋ መላእክት በልዑ" (ራእይ ፲፱፡ ፲፰) አዝማሪ ስለ ንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ - "ቡዳ ነው ተብዬ እኔ ታምቻለኹ፡ ርስዎ አደባባይ ነግ ሰው (ነግሠው) እበላለኹ። " ከረመ ብለኸ ከርሞን እይ። "ራበኝም ስላት ትልክልኛለች፡ በረደኝም ስላት ትልክልኛለች፡ ሌባዬ ተይዛ ባልጋ ተጨንቃለች። " ይተጌ ተዋበች በሞቱ ጊዜ (ራስ ዐሊ) መጽሐፈ ቅኔና የለቅሶ ዜማ ግጥም ተመልከት። ግጥም - "ሥጋውና ጠጁ ሞልቶ በቤታቸው፡ ፈጣሪ ጠላና እንጀራ ነሣቸው")

ኅብር: አንድ ስምም፡ የጠባይ፣ የግብር፣ የነገር። (ለምሳሌ: "እከሌና እከሌ ኅብር ናቸው")

ኅብሮች: ስምሞች፣ ግጥሞች።

ኅዋ: ከምድር በላይ ያለ ክፍት ባዶ። (በግእዝ መሠረቱ ኀወወ ነው።)

ኅይለ ድንግልየድንግል ማሪያም ኀይል።

ኅዱግ: ያቡን ምክትል (ዱግ)

ኅዳር ሚካኤል (የኅዳር ሚካኤል): በኅዳር ፲፪ኛ ቀን የሚውል፣ የሚከብር የቅዱስ ሚካኤል በዓል።

ኅዳር ታጠነ: የኅዳር ሚካኤል ለት በሰማይ በጽርሐ አርያም ስለ ዓለም ደኅንነት ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ የፈጣሪን መንበር ዐጠኑ፡ ጸሎትን አሳረጉ። በምድር በቤተ ክሲያን ጸሎተ ዕጣን ተደረገ። ስለ ወባና ስለ ወረርሽን ቈለኛ ሁሉ በየመሬቱ እሳት አንዶ ጪስ አጨሰ። (ከዚህ በኋላ የደጋው ቈላ ወረደ፡ የቈላው ደጋ ወጣ)

ኅዳር ጽዮን (የኅዳር ጽዮን): በኅዳር ፳፩ ቀን የሚነግሥ የመቤታችን ታቦት።

ኅዳር: የወር ስም (፲፫ኛ ወር) ሰዎች ሁሉ ሰብላቸውን ለመጠበቅ ጐዦ እየሠሩ በዱር የሚያድሩበት።

ኅዳግ (ኀደገ): በመጽሐፍ አርእስት አንጻር በጽፈት ሥር ያለ ባዶ ብራና ወረቀት ሳይጻፍበት የተተወ፣ የቀረ (የእጅ ማረፊያ፣ መጨበ፵)

ኅድረት : የንስጥሮስ ሃይማኖት፡ "ቃል ከማርያም በተወለደ ሰው ዐደረ እንጂ፡ ከድንግል ማርያም ሥጋ ነሥቶ አልተወለደም" ማለት (የተዋሕዶ ተቃራኒ)

ኅድረት: ማደር።

ኅጥር(ዐረ፡ ዐጥር)የሽቶ ስም፡ በያይነቱ ሽቶ። ኅጥር ስንቡል እንዲሉ (፫ኛውን ዐጠረ እይ)

ኅጭጭ አለእንደ ኆጻ ጮኸ፡ ስጥጥ አለ።

ኅፅቦ(ኀፀበ)ታጥቦ የተወቀጠ የስንዴ ፍትግ። "ጐረደ" "ላጠ" "ብላኸ" "ጕርዶንና""ልጦን" እይ።

ኆረጠፈጀ፡ ሖረጠ።

ኆጻኀጫከገደል ከተራራ የሚገኝ ነጭ የእብነበረድ አሸዋ፡ የብራና ማጠቢያ፡ ማጽጃ። በግእዝ ግን የባሕር አሸዋ፡ ጠጠር ማለት ነው።

ኋለኛ (ው፣ ኞች)የኋላ፡ በኋላ ያለ። ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ።

ኋለኛይቱያች ኋለኛ። "" ቦታን ያመለክታል።

ኋሊት(ድኅሪት፣ ድኅሪተ)ፊጥኝ፡ ግርንግሪት።

ኋሊትኋለኝት።

ኋላ(ከዋላ)ደቂቅ አገባብ። የቦታ ስምዠርባ። በስተኋላ ቆመ፡ ወደ ኋላ ኼደ። ዃላ ተብሎ ሊጻፍም ይችላል።

ኋላ ቀር (ኋላ ቀሮች): የማይራመድ፣ ከስልጣኔ ወደ ኋላ የቀረ።

ኋላየጊዜ ስምየሚመጣ ጊዜ ከዚህ በኋላአሁን ተመለስና ኋላ

ኋልዮ: የኋላ ሽንቁር፣ ከኋላ ያለው።

ኋልዮተ ጥርስ: ከጥርሱ ኋላ።

ኋት(ክዋ)ለሩቅ ሴት የአንቀጽ ዝርዝር። "እኔ እሷን ገደልኋት"

ኋቸው(ክዎሙ፡ )ለሩቆች ወንዶችና ሴቶች የአንቀጽ ዝርዝር። "እኔ እነሱን ወደድኋቸው"

ኋችኹ(ኩክሙ፡ )ለቅርቦች ወንዶችና ሴቶች የአንቀጽ ዝርዝር። "እኔ እናንተን አመንኋችኹ" ከዚህ የቀረውን "ኀን" ግስና ነባር "" ተራ ተመልከት።

ኋደሬ: ከጀንገደር የተበጀ ጣብ (ጐዣም)

No comments:

Post a Comment

ሽፋን

  ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ