ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ተ ፡ ፳፪ኛ ፊደል (በግእዝ
እልፍ ቤት በአበገደ) ። በፊደልነት ስሙ "ታው" አኃዝ ሲኾን "ተ = ፲፻" ይባላል ።
ተ ፡ የመደረግና የመደራረግ ልማድ። "ጣፈ፡ ተጣፈ፡ ተፈ፡ ላከ፡ ተላከ፡ ተላላከ። በኣዐ በሚነሣ ግስ በመደረግ ብቻ ራብዕ ይኾናል። አመነ፡ ታመነ፡ ዐወቀ፡ ታወቀ።"
ተ ፡ የከና የጠ ተወራራሽ። "እስኪ፡ እስቲ፡ እስክ፡ እስት፡ ከየት፡ ተየት፡ ወጠረ፡ ወተረ፡ ቀበጠጠ፡ ቀበተተ።"
ተሐዋሲ: ተንቀሳቃሽ።
ተሐዋስያን: ተንቀሳቃሾች ነፍሳት።
ተሓደደ: ታረሰ፣ ተዘራ፣ ታረመ፣ ታጨደ፣ ተወቃ።
ተሖደደ: ተጦመቀረ፣ ተተወ ምሳው። (ሐና፣ ከ ተወራራሽ ስለሆኑ ኰደደ፣ ኾደደ እያለ ተጽፎ ይገኛል)።
ተለለ (ጸሊል፡ ጸለለ፡ ተንካፈፈ): ጠለለ ጠራ ጥሩ ኾነ ።
ተለለ (ጸልሎ፡ ጸለለ፡ አጨለመ): አላዋቂ ኾነ ።
ተለለ: ሞላላ ተኳኳነ፡ ተራዘመ፡ ተንዛዛ (ለምሳሌ ነገሩ፣ ሰዉ)።
ተለለ: አመመ፣ በገረ፣ አሠመረ።
ተለለ: ፈሰሰ፣ ወረደ። "እንባው ተለል አለ እንዲሉ።"
ተለላ: እመም፣ ገዝም፣ ቃዳ።
ተለል ተለል አለ: ተላላ፣ ሞኛሞኝ ኾነ።
ተለል አለ: መጥለል ዠመረ፣ ፈሰስ አለ።
ተለል: መትለል።
ተለመ (ተሊም፡ ተለመ): ዕርሻ ዠመረ ወረሰ (አንድ ፈር እወጣ ቦደነ ገመሰ) ።
ተለመ: ያዘ፣ ለከፈ (በሽታ ሰውን)።
ተለመሰሰ: ተኛ፣ ተለሸለሸ።
ተለመነ: ተማለደ፡ ልመናን ተቀበለ፡ በጎ አለ። (ዘፍ. ፲፬፡ ፳፩፣ ፪ሳሙ. ፳፩፡ ፲፰) "እባክኸ ስጠኝ፣ መጽውተኝ" ተባለ። "እለምን ትለኹ፣ ተለመነኝ" እንዲሉ ባልቴቶች።
ተለመነ: ተቀፈፈ፣ ተቧገተ፡ "በእንተ ስማ ለማርያም" ተባለ።
ተለመከከ: ተቀባ፣ ተላከከ።
ተለመዘገ: ተቈነጠጠ።
ተለመደ: ተጠና፣ ተያዘ፣ ታወቀ፣ ገባ ትምርቱ።
ተለመጠ: ለማጣ ኾነ፣ ዘባ፣ ደራ።
ተለመጠ: በጠፍር ተሳለ፣ ለዘበ።
ተለመጠ: ተለጠጠ፣ ተቈነነ።
ተለመጠጠ: ተቃጠለ፣ ተገረፈ፣ ሰፊ ኾነ።
ተለመጨጨ: ተለጠሰ፣ ተኛ።
ተለማ: ትልሚያ፣ ዥሠራ።
ተለማመነ: ተጋነየ፡ ተለማመጠ፡ ልመናን ተቀባበለ።
ተለማመጠ: ተጋነየ፡ ለመነ፡ ተለማመነ፣ ተማለለ፡ "ይስበረኝ፣ ይሠንጥረኝ"
አለ፡ በትሕትና፣ በለዘብታ ቃል ተናገረ።
ተለማማኝ: የተለማመነ፣ የሚለማመን፡ ተለማማጭ።
ተለማማኝነት: ተለማማጭነት።
ተለማማጭ: ተለማማጮች፡ የሚለማመጥ።
ተለማማጭ: አልማጭ እንዲሉ።
ተለማማጭነት: ተለማማኝነት።
ተለማኝ: ተለማኞች፡ ተማላጅ፡ የሚለመን፡ ለማኝን የማያሳፍር።
"አብ አይበልጥሞይ አባትኸ ተለማኝ፣ እናትኸ"
(አዝማሪ)።
ተለማዘገ: ተቈናጠጠ።
ተለማገገ: ተሳሳበ፣ ተጣባ።
ተለማጠጠ: ተለቋጠጠ፣ ተረፈ።
ተለማጭ: ተለጣጭ፣ ተቈናኝ።
ተለማጭ: የሚለመጥ፡ ክትክታ፣ ቀጨሞ፣ ቀስተኒቻ የመሰለው ኹሉ።
ተለምዶ: ተጠንቶ፣ ተይዞ፣ ታውቆ፣
"ሥራዬ"
ተብሎ።
"በኃይለ ሥላሴ ተለምዶ ተለምዶ መጣ ሙሶሊኒ የባሕር ላይ ዘንዶ" (ክራር መቺ)።
ተለሰቀ: ተጣበቀ፣ ተያያዘ፡ ብዙው አንድነት ኾነ።
ተለሰነ: ተቀባ፣ ተለቀለቀ፣ ታሸ፡ ታሠሠ፣ ተተካከለ። (ማቴ. ፳፫፡ ፳፯፣ ግብ. ሐዋ. ፳፫፡ ፫)
ተለሳለሰ: ልስልስ ተኳዃነ፡ ተለዛዘበ።
ተለሳቂ: የሚለሰቅ፣ ለጥ የሚል።
ተለሳኝ: የሚለሰን ግብ፣ ግድግዳ።
ተለስ: የሰሌን ምንጣፍ።
ተለሽለሽ: ተጣለ፣ ወደቀ፣ ተጋደመ፣ ተኛ፣ ተረፈረፈ፡ ምድር አላበሰ።
ተለቀ: ላቀ፡ ትልቅ ኾነ።
ተለቀለቀ: ተቀባ። (ኢሳ. ፱፡ ፭)
ተለቀለቀ: ታጠበ፡ ጠራ፣ ጥሩ፣ ንጹሕ ኾነ።
ተለቀለቀ: ዐበጠ፣ ተገጠመ፡ ልክ አለ፣ በዛ።
ተለቀሰ: ታዘነ፣ ተቈዘመ፡ "ውይ!" ተባለ፡ ውሎ ተዋለ፣ ተነባ፣ መነጩ ፈሰሰ፣ ወረደ፣ ተንቧቧ።
ተለቀተ: ተለቃ፡ ተበደረ።
ተለቂ: ተለቃሒ፡ የተለቃ፣ የሚለቃ፡ ተበዳሪ።
ተለቃ: ተለቅሐ፡ ተሰደረ ሰው፣ ተሰጠ ገንዘቡ።
ተለቃለቀ: ተቀባባ።
ተለቃለቀ: ተጣጠበ፣ ተናጻ። (ተረት)
"ታርቄ ተመርቄ ታጥቤ ተለቃልቄ"።
ተለቃላቂ: የሚለቃለቅ፣ ተጣጣቢ።
ተለቃሽ: የማች ቤተ ዘመድ።
ተለቈደ: ለንባዳ ኾነ።
ተለቅላቂ: የሚለቀለቅ፣ የሚቀባ፣ የሚታጠብ።
ተለበለበ: ተተኰሰ፡ ተቃጠለ (ቅርፊት ቅርፊቱ፣ ቈዳ ቈዳው)።
ተለበመ (ተለበወ): ታወቀ፡ ተረዳ።
ተለበመ: ተሰፈረ፡ ተመላ፡ ተሠየመ።
ተለበሰ (ተለብሰ): ተጠለቀ፡ ተደገደገ፡ ታሰረ፡ ተቦደነ።
ተለበቀ: ተጐሰመ፡ ተመታ።
ተለበበ: ገባ፡ ተከተተ (ገጹ)፡ ተጠለቀ (ልባቡ)።
ተለበደ (ተለበጠ): ተለጐመ፡ ተጐለሰ፡ ተሰፋ።
ተለበጠ: ተለጠፈ፡ ተሸፈነ፡ ለበሰ፡ ተጌጠ (ለምሳሌ በኢሳይያስ ፴:፳፪ ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተለበጠ: ተሠነበጠ፡ ተለጠጠ።
ተለባለበ: ተታኰሰ፡ ተፋጀ።
ተለባላቢ: የሚለባለብ ወይም የሚፋጅ።
ተለባሽ: የሚለበስ ወይም የሚጠለቅ።
ተለባቂ: የሚለበቅ፡ የሚመታ።
ተለባበሰ: ተሰዋወረ፡ ተደባበቀ፡ እንዳይሰማ፡ እንዳላወቀ ተኳዃነ።
ተለባበጠ: ተሸላለፈ።
ተለባብሶ: የውሻ ስም፡ "ተቻችሎ ልበ ሰፊ ነገር ዐላፊ ተኳኹኖ" ማለት ነው።
ተለባጅ: የሚለበድ፡ ተለጓሚ።
ተለባጭ: የሚለበጥ ታቦት ወይም ወርቅ።
ተለብላቢ: የሚለበለብ (ዕርፍ፣ ሞፈር፣ ቀንበር፣ ሽመልመሌ)።
ተለተለ (ትግ፡ ተልተለ፡ ሸደሸደ): ፈታ ተረተረ መዘዘ (ያዲስ ልብስን ማግ ከድር ለየ አወጣ - ሥሩ "ተለለ" ነው) ።
ተለተለ: ቀደደ፣ ሠነጠቀ፣ በጣ (ቅሪላን፣ ዦሮን፣ ፊትን)። "ዘለዘለንና ተነተነን እይ።"
ተለተመ: ተመታ፣ ተገጨ፣ ተተመተመ፣ ተወጋ።
ተለነቀጠ: ተፈጨ፣ ላመ፣ ለዘበ።
ተለከፈ: ቀረበ፣ ተደቀነ፡ ለቅልውጥ።
ተለከፈ: ተቀመሰ፣ ተነካ፣ ተነከሰ።
ተለከፈ: ተዠመረ፣ ተያዘ።
ተለኪ: የሚለካ።
ተለካ: ተለክአ፡ ተመጠነ፣ ተሰፈረ፣ ተሸለገ፣ ተረተመ፣ ተከነዳ፣ ተመዘነ። (ተረት)
"በሞኝ ቁመት መቃብር ይለካበት"። የሙሴን ዜና ሞት ተመልከት።
ተለካከፈ: ተቀማመሰ፣ ተነካካ፡ ተነከሰ።
ተለካከፈ: ተዠማመረ፣ ተያያዘ።
ተለካኪ: የሚለካካ፡ ተመጣጣኝ።
ተለካካ: ተመጣጠነ፣ ተሸላለገ፣ ተከነዳዳ።
ተለኰሰ: ተተኰሰ፣ ተቃጠለ፣ ተያያዘ።
ተለኰፈ: ላመል ተመታ፣ ተተነኰሰ።
ተለኳኰሰ: ተተኳኰሰ፣ ተቀጣጠለ።
ተለወሰ: ላቆጠ፣ ታሸ፣ ተዋዋደ፣ ተቦካ።
ተለወጠ: (ተወለጠ) ሌላ ሆነ፡ ለምሳሌ፣ እንደ ሎጥ ሚስት እንደ ማየ ቃና። ከፋ፣ ወይም ደግ ሆነ። ተሸጠ፣ ለባለቤቱ ተሰጠ። ታደሰ፣ ረቀቀ። (፩ቆሮ. ፲፭፡ ፶፩፣ ፶፪)
ተለዋሽ: የሚለወስ፣ የሚታሽ ዶቄት፣ ብትን፣ ድልህ።
ተለዋወጠ: አሁን ሰው አሁን ሌላ ሆነ፡ ለምሳሌ፣ በትረ ሙሴን ዕሥሥትን መሰለ፡ ተቀያየረ፣ ተዘዋወረ፣ ተወራረሰ። ተሻሻጠ፣ ተገዛዛ። ተጎሳቆለ፣ ተጣቆረ፡ የሰውንነት።
ተለዋዋጭ: (ብዙ ቁጥር: ተለዋዋጮች) የሚለዋወጥ፡ ተሻሻጭ። ጠባዩ ወይም ሁናቴው አንድነት የሌለው።
ተለዋዋጭ: ተወራራሽ ፊደል።
ተለዋዋጭ: የሚለዋወጥ፡ ተሻሻጭ። ጠባዩ ወይም ሁናቴው አንድነት የሌለው። ተወራራሽ ፊደል።
ተለዋዋጭነት: ተለዋዋጭ መሆን።
ተለዋዋጭነት: ተለዋዋጭ መሆን።
ተለዋዘዘ: ተላዘዘ።
ተለዋዘዝ: ርጥብ አስተኔ።
ተለዋጭ: የሚለወጥ፡ ዕሥሥት አይነት ሰው።
ተለዋጭነት: ተለዋጭ መሆን።
ተለዘ (ትግ፡ በጣ): ደከመ (ጠለሰን" አስተውል) ።
ተለዘበ: (ለዘበ) ዘነጋ፣ ተዘለነ፣ አመነ። (ተረት)
"ባንዱ ታዘብ፣ ባንዱ ተለዘብ"
እንዲሉ።
ተለየ: ተለመደ፣ ታወቀ።
ተለየ: ተሌለየ፡ ተነጠለ፣ ተሠነጠቀ፣ ተከፈለ አንድነትን፡ ዐጣ።
ተለየ: ዐረፈ፣ ሞተ።
ተለያየ: ተፈራቀቀ፣ ተነጣጠለ፡ በአሳብ፣ በሞት፡ ወዲያና ወዲህ ተኳዃነ። (መዝ. ፳፪፡ ፲፬)
ተለያዪ: የሚለያይ፡ ተፈራቃቂ።
ተለይ:
"ብቻሽን ሁን"። "ተለይ ባዳ" እንዲል እረኛ።
ተለደፈ: ተለጠፈ።
ተለገለገ: ተሳበ፡ ተጠባ፡ ተመገገ።
ተለገመ: ለገመ ኾነ፡ ተደረገ (ልግመ)።
ተለገደ: ተወተፈ፡ ተቀረቀረ፡ ተመረገ።
ተለጊ: የሚለጋ ዕሩር።
ተለጋ: ተቀላ፡ ተመታ።
ተለጋ: ተጠጣ፡ ተሠረገበ።
ተለጋሚ: ለጋሚ።
ተለጋጅ: የሚለገድ፡ ተቀርቃሪ።
ተለጐመ: ልጓም፣ ጥይት፣ ኳስ ጐረሠ።
ተለጐመ: ተሰፋ፡ ተለበደ፡ ዐረብ ለበሰ።
ተለጐመ: ዝም አለ፡ አልተናገረም።
ተለጐመ: ገባ፡ ተቀረቀረ።
ተለጐደ: ተለደፈ፡ ተለጠፈ።
ተለጐጠ: ተወተፈ፡ ገባ።
ተለጓሚ: የሚለጐም (ከብት፣ ስፌት)።
ተለጠመ: ተጠጋ፡ ተከደነ፣ ተገጠመ።
ተለጠሰ: ተኛ፣ ተጋደመ፣ አልነሣ አለ።
"ዛሬ እከሌ ምን ሁኗል፡ ቀኑን ኹሉ ዐልጋ ላይ ተለጥሶ ዋለ"።
ተለጠቀ: ሌሎች ተከተሉት።
ተለጠቀ: ተጨፈቀ፣ ተለሰቀ።
ተለጠፈ: ተመረገ፣ ተጨመረ፣ ተደረበ፣ ተጣበቀ፣ ተገናኘ፣ ተያያዘ።
ተለጣሚ: የሚለጠም፡ ተሿሚን፣ ባለጊዜን የሚጠጋ ሠከቴ።
ተለጣቂ: የሚለጠቅ፡ ተከታይ ያለው።
ተለጣፊ: የሚለጠፍ፡ ተጣባቂ።
ተለፈለፈ: ብዙ ሰዓት ተነገረ።
ተለፈጠ: ተለፍጸ፡ ተለወሰ፣ ታሸ፣ ታበቀ።
ተለፈፈ: ተነገረ፣ ታወጀ፣ ተሰበከ።
ተለፈፈ: ታጠፈ፣ ተጠቀለለ።
ተለፊ: የሚለፋ፣ የሚዠለጥ፡ ለፊ።
ተለፋ: ለፋ፡ ተጣረ፣ ተደከመ።
ተለፋለፈ: ቀጥሎ ቀጥሎ ተነጋገረ፣ ተንሣ፣ ተኸ።
ተለፋቀ: ተነዛነዘ፣ ተጨቃጨቀ፡ አንዱን ነገር መልሶ መላልሶ ተናገረ።
ተለፋደደ: ተለፋጨቀ፣ ተጨማለቀ በአነጋገር።
ተላ (ዕብ፡ ቱሎዕ): ኾነ ተገኘ ተፈጠረ ተፍለከለከ ተርመሰመሰ ወጣ (የትል - ዘፀ፡ ፲፯፡ ፳፡ ዘኍ፡ ፭፡ ፳፪) ።
ተላ: ውሃ ተራጨ፡ ተሳካ፣ ተሳላ። (አልተላም) ፡ አልበጀም፡ አልተሳላም ።
ተላለመ: ዠማመረ፣ ዐራረሰ።
ተላለቀ: ተቀራደደ፡ ተጋደለ፡ ተጝተ።
ተላለከ: ተዳፈረ፣ ተጋፋ፣ ተወዳደረ።
ተላለፈ: ተለዋወጠ (የሕብር፡ የመልክ) (ዘፍ፴፩፡ ፰፡ ፲) (ተደራራጊ)።
ተላለፈ: ተዳፈረ፡ ሕግ አፈረሰ (ዳን፫፡ ፳፰) (አድራጊ)።
ተላለፈ: ካንዱ ወደ ሌላው ተረማመደ፡ ተጋባ፡ ተዛመተ (ተደራራጊ)።
ተላለፈ: ወደ ፊትና ወደ ኋላ ኼደ (ተገብሮ)።
ተላላ (ጽሉል): ድልል፣ ሞኝ፣ ደንቈሮ፣ ዝንጉ። "(ተረት)፣ የዝንብ ተላላ ካንድ በሬ ደም ይቀርባታል።"
ተላላሰ: ተላሀሰ፡ ተነካካ።
ተላላሰ: ተላሐሰ፡ የመላላስን ብድር ተከፋፈለ፡ የፍቅር መሳሳም ተሳሳመ።
ተላላቀ: ተበላለጠ።
ተላላቂ: ተበላላጭ።
ተላላቂ: የሚተላለቅ፡ ተጋዳይ። "ላቀ" ብለኸ "ተላላቀን" እይ ።
ተላላቂ: የሚተላለቅ፡ ዐለቀ።
ተላላበ: ተቀጣጠለ።
ተላላከ: ተላአከ፡ ተጻጻፈ፡ ደብዳቤን በደብዳቤ፣ ቃልን በቃል ብዙ ጊዜ ተመላለሰ።
ተላላኪ: ተላላኪዎች፡ ተላኣኪ፡ የሚላላክ አሽከር፡ መልክተኛ፣ መላክትን አድርሶ መላሽ፣ ተመላሽ።
ተላላጠ: ተጋፈፈ፣ ተገፋፈል፣ በኹሉ ወገን ተላጠ፣ ተመላለጠ።
ተላላፈ: ተጋፈፈ፣ ተላላጠ።
ተላላፊ (ፎች): የተላለፈ፡ የሚተላለፍ፡ መንገደኛ፡ በሽታ፡
ሕግ አፍራሽ (ምሳ፱፡ ፯፡ ፳፮፡ ፲፱፡ ኢሳ፵፰፡ ፰፡ ሆሴ፲፬፡
፱)።
ተላላፊነት: ተላላፊ መኾን።
ተላሌ: የተላላ ወገን፣ የተደበቀን ዕቃ ማግኘት ያልቻለውን ሰው። "ተሳሌ ሆይ እንድል የማሲንቆ ምት።"
ተላመ: ላመ፡ ተለነቀጠ።
ተላመደ: ተለማመደ፡ ተቃረበ፣ ተቀራረበ፣ ተዋወቀ፣ ተሰማማ።
"ተላመደ"
የግእዝና ያማርኛ፣
"ተለማመደ"
ያማርኛ ብቻ ነው።
ተላመጠ: ተዛባ፣ ተጓበጠ ርስ በርሱ።
ተላመጠ: ታኘከ፣ ተመሰኳ፡ ለዘበ፣ ተለነቀጠ።
ተላሚ (ዎች): የተለመ፣ የሚተልም፣ ዠማሪ፣ ሀራሽ።
ተላማ: ተያያዘ፣ ተጋጠመ (ተጠገነ)።
ተላሰ: ተልሕሰ፡ ተጠረገ፣ ጠዳ፣ በላ።
ተላሰ: ተቃጠለ፣ ተመለጠ።
ተላሰሰ: ተነቀለ፣ ተሰሰ።
ተላቀ: ተልህቀ፡ ተበለጠ፡ እነሰ።
ተላቀሰ: ተዛዘነ፣ ዋይታ ተቀባበለ፡ ተናባ፣ እንባ በንባ ተራ።
ተላቀቀ: ተደራራጊ፡ ተለያየ፣ ተፋታ።
ተላቀቀ: ተደራጊ፡ ተፈቀደ፣ ተፈቀደለት፣ መብት ተቀበለ፡ ተሰናበተ ለማገት።
ተላቃቂ: የሚላቀቅ፣ የሚፋታ፣ የሚለያይ።
ተላቈጠ: ላቈጠ።
ተላበሰ: ተደራረበ (አመሳቅሎ ለበሰ፡ አደገደገ፡ የካህን)።
ተላተለ: ፈታታ፣ ቀዳደደ፣ ለያየ።
ተላተመ: ተዋጋ፣ ተጋጨ፣ ተተማተመ።
ተላትም: ተላተም፡ የሰው ስም፡ ፀ፰፻ ዓ.ም. የነገሠ የኢትዮጵያ ንጉሥ። "ተዋጋ"፣ "ተተማተም" ማለት ነው። አባቱ "ለትም" ይባላል።
ተላከ: በቤተ ልሔም ሐሪጽ ዐሸ፣ ቍርባን ሠራ፣ ዐበዘ፣ ጋገረ፣ አገለገለ።
ተላከ: ተልእከ፡ መልክት ይዞ ሄደ፣ መጣ።
ተላከከ: ተቀባ፣ ተዶለሰ፣ ተለጠፈ፡ ተጣበቀ፣ ተገጠመ፡ ተመካኘ።
ተላከፈ: ተቃመሰ፣ ተናካ፣ ተናከሰ።
ተላከፈ: ተዣመረ።
ተላኪ: ተለኣኪ፡ የተላከ፣ የሚላክ ብላቴና፣ ዲያቆን።
ተላካ: ተከናዳ።
ተላካኪ: የሚላከክ፡ ተጣባቂ።
ተላኰሰ: ተታኰሰ።
ተላኰፈ: ተናካ፣ ተተናኰሰ።
ተላወሰ: ተንቀሳቀሰ፣ ተነቃነቀ። ለምሳሌ፣ ሽል በማህፀን ይላወሳል። (ተደራራጊ) ጥቂት ጥቂት ሄደ፣ ተራመደ። ተልኰሰኰሰ፣ ተረገጠ። (ተደራጊ)
ተላወጠ: (ተዋለጠ) ገንዘብን በገንዘብ፣ ከብትን በከብት፣ ዕቃን በዕቃ ተሰጣጠ፣ ተቀባበለ፣ ተገዛዛ፡ በባለቤትነት ተዛወረ። (ሕዝ. ፳፯፡ ፲፭)
ተላዋሽ: የሚላወስ፣ ተንቀሳቃሽ።
ተላዘበ: ተለዛዘበ፣ ተዳቀቀ፣ ተላላመ።
ተላዘዘ: ተራራሰ።
ተላገ (ተልሕገ): ተፋቀ፡ ታነጠ፡ ተነጠጠ፡ ለዘበ፡ ለሰለሰ፡
ተተካከለ፡ በምላስ የተላሰ መሰለ።
ተላገ: ተማሰለ (አብሲቱ)።
ተላገደ: ተዛበት፡ ተናናቀ። ልማዱ ግን "ተላገደ" ማለት "አላገጠ፡ ተሣለቀ፡ ዘበተ፡ ናቀ፡ አቀለለ፡ ጡር መስቃ፡ ተግዳሮት ተናገረ"
ነው (ለምሳሌ በ፩ኛ ሳሙኤል ፲፯:፲፣ ዕንባቆም ፩:፲፣ ሶፎንያስ ፪:፰ ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተላገጠ: ተፊያፊያዘ፡ ተቃለደ። መምህራን ግን "ተላገደ" ይላሉ።
ተላጊ: የሚላግ፡ ተፋቂ።
ተላጋ: ተማታ፡ ተጋጨ። (እንቆቅልሽ)
"ትንሽ ዐለንጋ ወንዝ ለወንዝ ትላጋ።
"
ተላጐደ: ተላጠፈ።
ተላጠ: ሸሸ፣ በረረ። "እኛ ሲመጡ እኛ ሲላጡ" እንዲል ፈካሪ።
ተላጠ: ተሻረ፣ ተለወጠ፣ ቀረ። "ፍርድ ተላጠ" እንዲሉ።
ተላጠ: ተገፈፈ፣ ተለየ። (ዘፍ. ፴፡ ፴፰)
ተላጠ: ተፈሳ፣ ተለቀቀ።
ተላጠቀ: ተጣጋ፣ ተቃረበ።
ተላጨ: ተፈገፈገ፣ ተገፈፈ፣ ተጠረገ፣ ተወገደ፣ ተጣለ፣ ወደቀ። (ኢሳ. ፲፭፡ ፪)
ተላጪ: የሚላጭ።
ተላጭ: የሚላጥ፣ የሚሻር ዛፍ፣ ብይን።
ተላፈ: ተለየ፣ ተገፈፈ።
ተላፈ: ተቃጠለ፣ ተላጠ።
ተላፈ: ተበላ፣ ተጠጣ።
ተላፈፈ: ለፈፋን ተቀባበለ፡ ተነጋገረ።
ተላፈፈ: ተላፈ፣ ተነጠለ።
ተላፊ: የሚላፋ፣ ለፋ።
ተላፊ: የሚላፋ፣ ተጫዋች።
ተላፊ: የሚላፍ፣ የሚለይ።
ተላፋ: ተላፍዐ፡ ተፋተገ፣ ተሻሸ፣ ተጫወተ፣ ተዳለቀ፣ ተቈላመጠ።
ተላፋፊ: የተላፈፈ፣ የሚላፈፍ።
ተልባ (ተላቤ): የቅመም ስም (ቅባትነትና ማላጋነት ያለው ቅመም ከማር ጋራ) ።
ተልባ መጠጥ: የተልባ መጠጥ፣ ያቶ በዛብኸ ጦር።
ተልባ ማሻ: "በውስጡ ብር ያለበት ግምጃ የለበሰ ገበቴ አለቃ ገብረ ሐና ቀማኞችን ስለ ፈሩ የሚካኤል ታቦት ነው ብለውታል።"
ተልባ ተልቢቱ: ተረታዊ የሴት ስም።
ተልባ ተልባ: ውለ ቢስ፣ የማይታመን ሰው፣ ተንሸራታች። "እከሌ ተልባ ነው እንዲሉ።"
ተልባ እግር (የተልባ እግር): "ከተልባ ልጥ፣ የተሠራ ክታን፣ ጥሩ ልብስ። በግእዝ ዐጌ ይባላል (ኢሳይያስ ፫፡ ፳፫)። ፈረንጆችም ሊኖ ይሉታል።"
ተልባ ውሃ: ሰጐዣም ክፍል የሚገኝ ታላቅ ተራራ።
ተልባ ድርጥ (የተልባ ድርጥ): "በውሃ የታሸ የተልባ ልቍጥ። ደረጠ ብለኸ ድርጥን እይ።"
ተልብማ: ተልባ መሳይ፣ ቀለመ ተልባ፣ መልከ ተልባ፣ እባብ፣ ቦረቦጭ፣ ሌላውም ነገር ኹሉ።
ተልታይ (ዮች): የተለተለ፣ የሚተለትል፣ ተርታሪ፣ ሠንጣቂ።
ተልከሰከሰ: ረከሰ፣ ለከሰ።
ተልከሰከሰ: ቅጥ ዐጣ፡ ተበተነ፣ ተረገጠ፣ ረከሰ።
ተልከሰከሰ: ባንድ ስፍራ መለስ ቀለስ አለ። (ግጥም)
"እከደከድዬ ነገር ተበላሸ፡ እሥጋ ገበያ ስልከሰከስ መሸ"።
ተልከሰከሰ: አመነዘረ፣ ሸረሞጠ።
ተልከስካሽ: የማይለቅ፣ የማይሄድ በሽታ።
ተልከፈከፈ: በምላሱ ነካ ነካ አደረገ፡ ተልከሰከሰ።
ተልከፍካፊ: የሚልከፈከፍ።
ተልካሳ: ሰነፍ፣ ለከሰ።
ተልካሳ: ደካማ፣ ዐቅመ ቢስ፣ ሰነፍ፣ ታካታ፣ ሥራ ጠብ የማይልለት።
ተልካሻ: ተልካሾች፡ ዝኒ ከማሁ። (ሽለላ)
"ከወታደርም አለ ተልካሻ፡ ጠመንዣ ይዞ ድንጋይ የሚሻ"።
ተልኰሰኰሰ: ተላወሰ፣ ለኰሰ።
ተልኰሰኰሰ: ተላወሰ፣ ተረገጠ። ተልኰሰኰሰ፣ ተረገጠ። (ተደራጊ)
ተልኰፈኰፈ: ተኵለፈለፈ።
ተልፈሰፈሰ: ተዝለፈለፈለ፣ ተጥመለመለ፡ ደከመ፣ ዛለ።
ተመለለ: ረዘመ፣ ወጣ።
ተመለመለ: ተለየ፣ ተመረጠ፣ ከበረ።
ተመለመለ: ተኰተኰተ፣ ተቀነጠበ፣ ተቈረጠ።
ተመለሰ: ተተረጐመ።
ተመለሰ: ተደገመ፣ ተከለሰ።
ተመለሰ: ንስሓ ገባ።
ተመለሰ: ወጣ (ለምሳሌ መብል፣ መጠጡ) (በገባበት)።
ተመለሰ: ገባ፣ ተከተተ።
ተመለስ: በአርእስትና በኅዳግ የተጻፈ ቃል ምልክት ፲።
ተመለከ: ተሸነፈ፣ ተገዛ።
ተመለከ: አምላክ ሆነ፡ ተጸለየበት፣ ተሰገደበት።
ተመለከተ (ተመልከተ): አየ፡ አስተዋለ፣ ጠበቀ (ነገርን፣ መጻፍን፣ ፊትን) (ያዕቆብ ፩:፳፬)።
ተመለከተ: ምልክት ሆነበት፣ ተደረገበት፣ ተጻፈበት (ለምሳሌ የዜማው መጻፍ)።
ተመለካከተ: ምልክት ተቀባበለ፣ ተጠቋቈመ። "ያ የተነጋገርነው ምልክት ይሁንህ" ተባባለ።
ተመለጠ: መላጣ ሆነ፡ ተላጠ፣ ተቀረፈ፡ ጠጕርና ቅርፊት ዐጣ።
ተመለጠነ: ታወቀ ድጓው፡ ተዜመ፣ ተመራ አንገርጋሪው።
ተመላ/ተሞላ (ተመልአ): የቢሩ ተገብሮ ፍችው እንደ ተገብሮው ነው፡ ጢም፣ ቲፍ አለ።
ተመላለሰ: ብዙ ጊዜ ወዲህ መጣ ወዲያ ሄደ (፩ኛ ሳሙኤል ፴:፴፩፡ ዮሐንስ ፲፪:፴፭፡ ገላትያ ፭:፲፮)። ወጣ ገባ አለ።
ተመላለሰ: ተለዋወጠ።
ተመላለሰ: ተከፋፈለ (ብድርን)።
ተመላለሰ: ተገላመጠ፣ ግራና ቀኝ አየ (ዘጸአት ፪:፲፪)።
ተመላለጠ: ተላላጠ፣ ተቀራረፈ።
ተመላላሽ: የተመላለሰ፣ የሚመላለስ፡ ደጀጠኒ።
ተመላሽ: የሚመለስ ሰው፡ የተውሶ ከብት፣ እቃ፡ የወጣበት የሚገባ ገንዘብ።
ተመላታ (ተመላትሐ): ጕንጭን ተማታ፣ ተጻፋ።
ተመላከተ: ተያየ (ተመለከተ)።
ተመላጎደ: ተማታ፣ ተናጎደ፡ ተነባጀለ፡ የሞኝ አነጋገር ተናገረ።
ተመላጭ: የሚመለጥ፣ የሚቀረፍ።
ተመልማይ: የሚመለመል፡ ተኰትኳች።
ተመልከት:
"ደራን"።
ተመልካች (ቾች): የተመለከተ፣ የሚመለከት፡ አስተዋይ፣ ጠባቂ፣ እረኛ፣ ነቢይ፣ ዳኛ (፩ኛ ሳሙኤል ፱:፱፣ ፲፩፣ ፲፰፣ ፲፱፡ ፪ኛ ዜና መዋዕል ፴፫:፲፱፡ ኢሳይያስ ፶፪:፲፰)። "የበዪ ተመልካች" እንዲሉ።
ተመልካችነት: ተመልካች መሆን፡ አስተዋይነት፣ ጠባቂነት፣ እረኝነት።
ተመልክቶ: አስተውሎ። በግእዝ ግን "መመልከት" ይባላል።
ተመመ (ደመመ): ድም ድም አለጮኸ ናረ ተሰማ (በሩቅ ነጋሪቱ ጐርፉ - ኤር፡ ፴፩፡ ፴፭፡ ሕዝ፡ ፵፫፡
፪)።
ተመመ: ተጨረሰ፣ ተቈላቈለ።
ተመማ: ጩኸት፣ ንረት (ኢዮብ ፴፯፡ ፪)።
ተመሰ: ደበሰ ደመሰ።
ተመሰለ: መሰል፣ አምሳያ ሆነ። "ይሥሐቅ በዔሳው ተመሰለ። " "ሰይጣን በብርሃን መልአክ ተመሰለ። "
ተመሰለ: በጦርነት ጊዜ የንጉሥን የጦር ልብስ ለበሰ።
ተመሰለ: ተሣለ፣ ተቀረጸ፣ ተበጀ (ምስሉ)።
ተመሰለ: ተተረተ፣ ተነገረ (ምሳሌው)።
ተመሠረተ (ተመሥረተ): ተጣለ፣ ተዠመረ፣ ተወጠነ፣ ተሠራ፣ ተበጀ፣ ተገነባ (መሠረቱ)።
ተመሰቃቀለ፡ ተዘበራረቀ፣ ተጠላላ፣ ተደበላለቀ፣ ተገለባበጠ።
ተመሰተረ: ተነቀለ፣ ተለቀመ።
ተመሰተረ: ተነቀለ፣ ተለቀመ።
ተመሰከረ: ተነገረ፣ ታወቀ፣ ተረዳ።
ተመሰገነ (ተመዝገነ): ምስጋና አገኘ፡ ወሰው ተባለ፣ ተወደሰ፣ ተሞገሰ። "ተመስገን ጌታዬ ከሞላ ጐታዬ" እንዳለ ገበሬ።
ተመሰገነ: የሚመሰገኝ፡ ጻድቅ።
ተመሰጋገነ: ተወዳደሰ፣ ተሞጋገሰ፡ ምስጋና ተቀባበለ።
ተመሠጠ: ልቡ፣ ሰውነቱ ወደ ሰማይ ተነጠቀ፡ ተወሰደ፣ ወጣ።
ተመሰጠረ (ተመስጠረ): መሰጠረ።
ተመሳ (ተመስሐ): ተጐረሠ፣ ተበላ (ምሳው)።
ተመሳሰለ: ተነጻጸረ፣ ተባበረ (በመልክ፣ በሥራ)።
ተመሳሳይ (ዮች): የተመሳሰለ፣ የሚመሳሰል፡ ተነጻጻሪ፣ ተባባሪ።
ተመሳሳይነት: ተመሳሳይ መሆን፡ ተባባሪነት።
ተመሳቀለ፡ አራት ገጽ መስቀልኛ ኾነ። "ራስጌና፣ ግርጌው ሳይለይ ቀረ፣ ተዘባረቀ፣ ተጣላ።"
ተመሳቃ: ተፈካከረ፡ "እኔን አንተ አታኽለኝም" አለ።
ተመሳቃይ፡ የሚመሳቀል፣ የሚጣላ።
ተመሳካሪ: የሚመሳከር።
ተመሳይ (ዮች): የሚመሰል።
ተመሳጠረ: ተራቀቀ፡ በምስጢር፣ በስውር፣ በድብቅ ተነጋገረ፣ ተጨዋወተ። ለደግም ለክፉም ይነገራል።
ተመሳጣሪ: የተመሳጠረ፣ የሚመሳጠር፡ ምስጢረኛ።
ተመሳጣሪነት: ተመሳጣሪ መሆን።
ተመስማሳ: ትምስምስ፣ የተትመሰመሰ፣ የሚትመሰመስ፣ ርብትብት።
ተመሥራች: የሚመሠረት፣ የሚወጠን።
ተመስካሪ: የሚመሰከር፣ የሚነገር።
ተመስገ: ተሰበሰበ፣ ተከማቸ፣ ተኛ።
ተመስገ: ገባ፣ ተሰካ፣ ተጨመረ።
ተመስገን: የሰው ስም፡ "ክብርኸ ይስፋ፣ መንግሥትኸ ይባረክ"።
ተመሥጦ: መነጠቅ (ወደ ላይ ማረግ) (የልብ፣ የኅሊና)።
ተመረመረ: ተጠየቀ፣ ተፈተነ፣ ተፈተሸ፡ ጭምጭምታው ተሰማ፣ ያለበት ታወቀ፡ ተቈፈረ፣ ጐደጐደ።
ተመረረ: ተጠቃ፡ ዐዘነ፣ ተበሳጨ።
ተመረቀ: ተቀቀለ፣ በሰለ፡ መረቅ ኾነ።
ተመረቀ: ተባረከ፡ ንባብን፣ ዜማን፣ ቅኔን፣ ትርጓሜን የማስተማር መብት አገኘ።
ተመረነ: ተያዘ፣ ተወሰነ፣ ታሰረ፣ ተጠመጠመ፣ ተቈራኘ።
ተመረኰዘ (ተመርጐዘ): ምርኵዝ ያዘ፣ ጨበጠ፣ ተደገፈ።
ተመረኰዘ: ተደገፈ (ምርኵዝ በቁሙ)፣ (ማረ)።
ተመረዘ: ክፉ ፈሳሽ መርዝ ገባበት፡ በመርዝ ተወጋ፡ ተጠላ፡ ተተኰረ።
ተመረገ (ተመርገ): ተለጠፈ፣ ተደፈነ (ግድግዳው፣ ግንቡ በጭቃ)።
ተመረገደ: ተዜመ፣ ተባለ (መረግዱ)።
ተመረጠ: ተወደደ፣ ተለየ፣ ተመለመለ።
ተመሪ (ተመራሒ): የሚመራ (ዕውር፣ መሬትን፣ ቅኔን፣ ዜማን)፣ ተቀባይ።
ተመሪነት: ተመሪ መሆን።
ተመሪዎች: የሚመሩ ደብተሮች፣ ሕዝቦች።
ተመራ: ቅኔን፣ ዜማን፣ ቀላድን ተቀበለ።
ተመራ: በመሪ ሄደ (ዕውሩ፣ ውሃው)።
ተመራ: በሰው ቤት ዐደረ (እንግዳው፣ ወታደሩ)።
ተመራመረ (መረመረ): ተጠያየቀ፣ ተፈላለገ፣ ተሳለለ።
ተመራማሪ: የተመራመረ፣ የሚመራመር፡ ተሳላይ።
ተመራማሪነት: ተመራማሪ መሆን።
ተመራረቀ: ተበራረከ፡ የምርቃት ብድር ተመላለሰ።
ተመራረዘ: ተጠላላ።
ተመራሪ: የሚመረር፡ ተቈጪ።
ተመራራ: ማደሪያን፣ መሬትን ተቀባበለ።
ተመራቂ: የሚመረቅ፡ ምርቃት ተቀባይ።
ተመራዥ: የሚመረዝ፣ የሚጠላ።
ተመራጊ: የሚመረግ (ቤት)።
ተመራጭ (ጮች): የሚመረጥ፣ የሚመለመል።
ተመርማሪ: የሚመረመር፡ ተጠያቂ።
ተመርጋጅ: የሚመረገድ።
ተመሸገ: ታጠረ፣ ተከበበ፣ ተቀጠረ፣ ተካበ፡ ተማሰ፣ ታረደ፣ ተጐደበ።
ተመሸጠ: ተለጠሰ፣ ተኛ።
ተመቀሰ: ተቈረጠ፣ ተቀደደ (በመቀስ)።
ተመቀኘ (ሐመመ): ቀና፡ ምቀኛ ሆነ (ሰውን ለመጕዳት፣ ለማጥፋት)።
ተመቀኛኘ: ተቀናና፡ ምቀኛ ተኳዃነ።
ተመቃኘ: ተቃና።
ተመተ: ተጋደለ፣ ተገዳደለ፣ ተላለቀ፣ ተጣፋ።
ተመተመ (ተመመ): መታ ለተመገጫ ወጋ ።
ተመተመ: "ዝም በል ኣትናገር አለ አንዱ የሥጋ ቤት ባልደረባ ባቡጀዲ የተሸፈነ ሥጋ ሰርቆ ሲኼድ ዐጢ ምኒልክን እሰገነት ላይ ቆመው ቢያያቸው" አፉን በእጁ ተመተመ እሳቸውም ሣቁና ኺድ አሉት።"
ተመተመ: በእጅ አባበለ (ሕፃንን፣ በቅሎን፣ ፈረስን)።
ተመተመ: አበሰለ፣ አመጠጠ (እሳትንፍሮን)።
ተመተመ: እረመደ።
ተመተመ: ደመደመ፣ አስተካከለ (ልጥፍን በጭድ)።
ተመታ: ተቀጠቀጠ።
ተመታ: ተበጠበጠ፣ ተለቀ።
ተመታ: ተባለ፡ ተጠዘለ፣ ተወገረ፣ ተደበደበ፣ ተመደወተ፣ ተገረፈ።
ተመታ: ተወጋ፣ ተገደለ፣ ተሸነፈ።
ተመታች: ተሰረረች (ፈረሲቱ)።
ተመቸ: ደላ፣ ተስማማ፣ ሆነ (አገሩ፣ ኑሮው፣ ፍራሹ)። "ተመቸና ተመታ" በአማርኛ ይገጥማሉ። "ጣይቱ ብጡልን ሰው ሁሉ ጠልቷታል፡ 'ትመቻለሽ' ብሎ ምኒልክ ይዟታል" (አለቃ በዛብህ)። "መታን" እይ።
ተመቸው: ደላው፣ ተስማማው።
ተመቺ ች (ቾች): የሚመታ፡ የተወጋ፣ ድል የሆነ።
ተመቻቸ: ተደላደለ፣ ተሸራሸ፣ ተተካከለ፣ ተሰማማ።
ተመች: "ተረታሁ፣ አነሣሁ" በል።
ተመችቶታል: ደልቶታል፣ ሆነውታል፣ ተቀብሎታል።
ተመነሸ (ተመሸነ): "መንሽ" ተባለ።
ተመነሸ: ተወጋ፣ ተወረወረ።
ተመነቀ: ተነቀነቀ፣ ተወዘወዘ።
ተመነቀረ: ተማሰ፣ ተቈፈረ፣ ተጐደፈረ።
ተመነቃቀረ: ተጠላላ።
ተመነተገ: ተቀማ፣ ተነጠቀ።
ተመነተፈ: ተቀማ፣ ተነጠቀ።
ተመነቸከ: ተጨቀጨቀ፣ ተነዘነዘ።
ተመነነ: ተናቀ፣ ተተወ።
ተመነዘረ: ተሴሰነ፣ ተቀነዘረ፣ ተሸረሞጠ።
ተመነዘረ: ተዘረዘረ፣ ተበተነ፣ ተሸረፈ፣ ተከፈለ።
ተመነዛዘረ: ተበታተነ፣ ተለዋወጠ።
ተመነዠኸ: ተመነዠኸ፣ ተለነቀጠ፣ ላመ።
ተመነደለ: ታጠበ፣ ጠራ።
ተመነደረ: ታነጠ፣ ተገነባ፣ ተሠራ (መንደሩ፣ ዐምባው)።
ተመነደበ (ተመንደበ): ተመታ፣ ተነረተ፣ ተደበደበ።
ተመነደበ: ተቈረጠ፣ ተመደመደ።
ተመነደበ: ተቸገረ፣ ተጨነቀ፣ መከራ ተቀበለ።
ተመነደገ: ተነጠቀ፣ ተቀማ።
ተመነደገ: አደገ፣ ረዘመ።
ተመነገለ: ነገለ።
ተመነገገ: ተያዘ፣ ታሰረ (ከብቱ፣ መንጋጋው)።
ተመነጠረ: ተጠረገ፣ ታጨደ፣ ታጠበ፣ ተገረፈ። (ተረት): "ያልጠረጠረ ተመነጠረ። "
ተመነጠቀ: ተነጠቀ፣ ተቀማ።
ተመነጠቀ: ወጣ፣ ቶሎ ሄደ።
ተመነጨረ: ተጫረ፣ ተበተነ።
ተመነጨቀ: ተጨቀጨቀ፣ ተነዘነዘ፡ ተመነጠቀ።
ተመነጫጨረ: ተበታተነ።
ተመናሸ: ተዋጋ (መንሽ)።
ተመናሸ: ተዋጋ፣ ተወራወረ።
ተመናቀረ: ተጣላ፣ ተለያየ፣ ተራራቀ፡ ማዶና ማዶ እየረገጠ ሄደ።
ተመናተገ: ተቀማ፣ ተናጠቀ።
ተመናተፈ: ተቀማ፣ ተናጠቀ።
ተመናቸከ: ተጨቃጨቀ፣ ተነዛነዘ።
ተመናቸፈ: ተቧጨቀ፡ ተመናቸከ።
ተመናኘ: - ያላሳብ፣ ተዳደለ፣ ናኘ።
ተመናኘ: በገፍ ተሰጣጠ፣ እንደ ልብ ተዳደለ፣ ተቀባበለ።
ተመናዘረ: ገንዘብ ለገንዘብ ተላወጠ።
ተመናደበ: ተማታ፡ ተቋረጠ።
ተመናደበ: ተማታ፡ ተቋረጠ።
ተመናጐለ: አስቀያሚ ነገር ተናገረ፡ ተነኋረጠ።
ተመናጠረ: ተጣረገ፣ ተወደ፣ ተጋረፈ።
ተመናጠቀ: ተናጠቀ፣ ተቀማ።
ተመናጨረ: ተባተነ።
ተመናጨቀ: ተመነተከ፣ ተጨቃጨቀ።
ተመን: ዘንዶ (ግእዝ)።
ተመንዛሪ: የሚመነዘር ብር።
ተመንጣሪ: የሚመነጠር፡ ታጫጅ።
ተመኘ (ተመነየ): ዐሰበ፣ ከጀለ፡ በልቡ ፈለገ፡ "ባገኘሁት" አለ (፩ኛ ዜና መዋዕል ፲፩:፲፯)።
ተመኛኘ: ተከጃጀለ።
ተመኝ: የሚመኝ፡ ከጃይ።
ተመከ: ላይ ተሰደ፣ ተሠረጐደ፣ ሥዕል ተቀበለ፣ ታተመ።
ተመከመከ: ላላ፣ ለሰለሰ።
ተመከረ (ተመክረ): ሆነ፣ ተደረገ (ተዶለተ፣ ተሴረ፣ ታደመ) ምክሩ፡ ምክር ተቀበለ ሰውየው።
ተመከረበት: ጉዳዩ እንዲፈጸም፣ ጥፋተኛው እንዲቀጣ ተደረገበት።
ተመከተ: ተቀየደ፣ ተጋረደ፣ ተከለለ (የቤቱ ውስጥ፣ ሰውየው፣ ጋሻው)።
ተመከኛኘ:
"የሠራኸው አንተ ነህ፣ አንተ ነህ" ተባባለ።
ተመኪ (ተመካሒ): የሚመካ፣ ተከባሪ።
ተመኪዎች/ተመኮች: የሚመኩ (ለምሳሌ በ2ኛ ጢሞቴዎስ 3:2 ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተመካ (ተመክሐ): "ካለ እከሌ እኔን ማን ያኸለኛል" አለ፤ በገዛ አፉ ተወደሰ፤ ራሱን አከበረ (ለምሳሌ በኢሳይያስ 10:15 ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተመካ: ባንድነገር ታመነ (መካ)።
ተመካሪ: የሚመከር።
ተመካች: የሚመክት፡ ተቀያጅ።
ተመካኘ (ተመክነየ): ተፈጠረ፣ ሆነ፣ ተደረገ ምክኛቱ፡ ተሰበበ፣ ተላከከ።
ተመካኘ: ተደረገ (ምክንያቱ) (መከን)።
ተመካከረ: ምክር ተለዋወጠ (መዝ፡ ፻፴፫፥፪፡ ዕብ፡ ፫፥፲፫) ።
ተመካከተ: ተገራረደ።
ተመክሮ: መመከር (ግእዝ)። ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውም ።
ተመዘመዘ: ራስ ረሰረሰ።
ተመዘመዘ: ቀጠነ፣ ረዘመ።
"ይህ መኰንን ጠጅ ስላበዛ ጥርሱ ተመዝምዟል። "
ተመዘመዘ: ተተለተለ፣ ተተረተረ፡ ተሳበ፣ ተመዘዘ።
ተመዘቀ: ተነቀለ።
ተመዘቀ: አንድ ነገር ተነቀለ።
ተመዘበረ: ተመዝበረ፡ ፈረሰ፣ ተናደ፡ ባድማ ኾነ፣ ጠፋ፣ ተፈታ።
ተመዘነ: ተለካ፣ ተሰፈረ፣ ተመጠነ ዕቃው፡ ተገመተ ጠባዩ። (፩ሳሙ. ፪፡ ፫)
ተመዘዘ: ተሳበ፣ ተጐተተ፣ ተነቀለ፣ ወጣ።
ተመዘዘ: ተፈተለ፣ ቀጠነ።
ተመዘዘ: አደገ፣ ረዘመ፣ ተመነደገ።
ተመዘገበ: ተጻፈ፣ እመዝገብ ገባ።
ተመዛኝ: የሚመዘን፡ ተለኪ።
ተመዛዘነ: በሚዛን ተተካከለ፣ ተመጣጠነ ከመበላለጥ ራቀ፡ ተለዋወጠ።
ተመዛዘዘ: ተነቃቀለ።
ተመዛዛኝ: የሚመዛዘን።
ተመዛዥ: የሚመዘዝ፡ ተነቃይ።
ተመዝማዥ: የሚመዘመዝ።
ተመዠረጠ: ተነቀለ፣ ተመዘዘ፣ ወጣ።
ተመየደ: ተበጠረ፣ ተነቀሰ።
ተመይ: የሚመላ።
ተመደመደ: ተቈረጠ፣ ተጠረገ፡ ተናደ፣ ፈረሰ፡ ተደለደለ፣ ተተካከለ።
ተመደበ: ተደለደለ፣ ተስጣጣ፣ ተካከለ መደቡ።
ተመደበ: ታዘዘ፣ ተቈረጠ፣ ተወሰነ፣ ተደነገገ ነገሩ፣ ጊዜው። (፩ሳሙ. ፱፡ ፳፬፣ ፪ዜና. ፲፡ ፲፭፣ መዝ. ፸፱፡ ፲፩፣ ፻፪፡ ፲፫)
ተመደነ: ተማረ፣ ሠለጠነ።
ተመደወተ: ተመታ፣ ተጠዘለ፣ ተደወለ።
ተመዳቢ: የሚመደብ፡ ተወሳኝ።
ተመዳወተ: ተማታ፣ ተጣዘለ፣ ተዳወለ።
ተመድቦ: ተወስኖ፣ ተቈርጦ፣ ታዞ።
ተመገ: ልል ኾነ፣ ተመከ።
ተመገመገ: ተሳበ፣ ተጐተተ፣ ተጠባ፣ ተመጠመጠ፣ ተለገለገ።
ተመገበ: ተሾመ፣ መጋቢ ኾነ።
ተመገበ: ተቀለበ፣ በላ፣ ጠጣ፡ ተጠበቀ። (፪ነገ. ፬፡ ፯፣ ፩ቆሮ. ፱፡ ፲፬፣ ራእ. ፲፪፡ ፲፬)
ተመገዘ: ተገዝዐ፣ ተወሠረ፡ ተገዘገዘ፣ ተከረከረ፣ ተከረከመ፣ ተቈረጠ፣ ተሠነጠቀ።
ተመጋቢ: የሚመገብ፡ ተቀላቢ፣ ተሿሚ።
ተመጋዥ: የሚመገዝ፡ ተከርካሪ።
ተመጋገበ: ተጐራረሠ፣ ተቀባበለ ምግብን።
ተመጠመጠ: ተሳበ፡ ተጠባ።
ተመጠመጠ: ተሳበ፣ ተጠባ (መጠማጥ)።
ተመጠቀ: መጠቀ።
ተመጠነ: ተለካ፣ ተመዘነ (ለምሳሌ በ፩ኛ ነገሥት ፫:፰ ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተመጠወተ፣ ተመጸወተ: ተሰጠ፣ ታደለ፡ ምጧቱ። ተሰጠው፣ ተቀበለ ሰው።
ተመጠወተ፡ ተመጸወተ: ተሰጠ ወይም ታደለ (ምጧቱ)። ተሰጠው፣ ተቀበለ ሰው።
ተመጠጠ: ተሳበ፣ ተጐተተ፡ ተጠጣ፣ ተመለጠ።
ተመጣኝ: የሚመጠን፣ የሚለካ።
ተመጣዳቂ፡ ተመጻዳቂ።
ተመጣዳቂነት፡ ተመጻዳቂነት።
ተመጣጠነ: ተለካካ፣ ተመዛዘነ።
ተመጣጣኝ: የሚመጣጠን፣ ተመዛዛኝ።
ተመጣጭ: የሚመጠጥ።
ተመጥዋች፣ ተመጽዋች: የሚመጠወት ገንዘብ፡ የሚቀበል ሰው።
ተመጨለሰ: ሣሣ፣ ብራ ሆነ (ቅባት በነካው ጊዜ)፡ ተለጠሰ፡ ተኛ፡ ተለጠፈ።
ተመጻደቀ፡ እኔ፡ እከሌ፡ አለ፡ ተገበዘ፡ በገዛ፡ አፉ፡
ተመሰገነ፡ ወይም፡ ተመሰጋገነ። በመ፡
ምክንያት፡ ተደራጊ፡ በጻ፡ ምክንያት፡ ተደራራጊ፡ መኾኑን፡ አስተውል።
ተመጻደቀ: በገዛ አፉ ተመሰገነ፣ ጸደቀ።
ተመጻዳቂ (ቆች)፡ የተመጻደቀ፡ የሚመጻደቅ፡ ግብዝ፡ ኣፈ፡
ጻድቅ፡ ሰዱቃዊ፡ ፈሪሳዊ።
ተመጻዳቂነት፡ ግብዝነት።
ተሙለጨለጨ: አልያዝ፣ አልረገጥ አለ።
ተሙን (ዐረ፡ ሱሙን): "የገንዘብ ስም፣ የዱሮ መሐልቅ አላድ ሳይመጣ የነበረ፣ ባንድ ብር ኹለት ይመነዘራል። የብር ስምንተኛ ማለት ነው። መሐልቅም በተሙን ፈንታ ስለ ተተካ ተሙን ይባላል። (ማስረጃ)፡ ተሙን ተቤሳ ፩፡ መሐልቅ ካ፩፡ ቤሳ።"
ተማለ: ሆነ፣ ተደረገ፡ "ማለው እንዲህ ያድርገኝ፣ እንዲህ ይጨምርብኝ" ተባለ (ለምሳሌ በ፩ኛ ሳሙኤል ፳፭:፳፪፣ ፩ኛ ነገሥት ፲፱:፪ ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተማለለ (ተማሕለለ): ተረሳ፣ ተዘነጋ።
ተማለለ: ለመነ፣ ልመና ያዘ፣ ጸለየ (ሮሜ ፩:፲)። "አህያ ተማሎ ዥብ አወረደ" እንዲሉ።
ተማለደ: ተለመነ፣ ይቅር አለ፣ ተባለ፡ ምሕረት አገኘ፣ ዳነ (ለምሳሌ በኢዮብ ፳፪:፳፱ ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተማላ (ተማላዒ): ሲሄድ ይዞ ኻያጅ። "እንደ ተማላ ወሰደው" እንዲሉ።
ተማላ: ተተካከለ።
ተማላ: ተያያዘ፡ አንድነት ሆነ (ተኳኳነ)።
ተማላይ: የተማለለ፣ የሚማለል።
ተማላጅ: የተማለደ፣ የሚማለድ፡ ተለማኝ፣ እግዜር።
ተማመሰ (ተሓመሰ): ተተረማመሰ (በተደጋጋሚ መታመስ)።
ተማመቸ (ተሓመወ): ተጋባ፡ ዐማችና ዐማት ተኳዃነ፡ ተዛመደ (ዕዝ፱፡ ፲፬)።
ተማመነ (ተኣመነ): ተዋደደ፣ ተሰማማ፡ ተማማለ፡ አዎን ተባባለ። "ማለ" ብለህ "ተማማለን" እይ።
ተማመፀ: ተበዳደለ።
ተማሚ (ተሓማዪ): የሚተማማ፡ ተነቃቃፊ።
ተማሚ: የሚተም። "ዐማ ብለኸ ተማማን አስተውል።"
ተማማለ (ተማሐለ): የማላ ብድር ተከፋፈለ፡ (ዛሬ አንዱ ነጻ፣ ሌላው ማለ)፡ ሳንቃ ተዛጋ፡ በመማማል ተፈራረቀ፣ ተገዛዘተ (ለምሳሌ በመዝሙረ ዳዊት ፻፪:፰ ላይ እንደተጠቀሰው)። "የማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ ይማማላል። "
ተማማለ: ተስያሲያረ፣ ተደማደመ (ለምሳሌ በ፩ኛ ነገሥት ፲፭:፳፯፣ ፲፯:፱፣ ፪ኛ ነገሥት ፱:፲፬ ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተማማለ: ክፉ እንዳይሰራ ተዋዋለ፣ ተማመነ (ለምሳሌ በዘፍጥረት ፳፮:፴፩፣ ፩ኛ ሳሙኤል ፲፰:፫፣ ኢሳይያስ ፳፰:፲፭:፲፰ ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተማማረ (ተማሀረ): ትምርትን ተቀባበለ፡ ተማሪው ካስተማሪው፣ አስተማሪው ከተማሪው ተማረ ማለት ነው።
ተማማረ (ተማሐረ): ይቅር ይቅር ተባባለ።
ተማማኝ: የሚተማመን፣ የሚዋደድ።
ተማም (ዐረ): ልክ፣ ትክክል፣ ፍጹም።
ተማም: ተመተመ።
ተማሰ: ተኳተ፣ ተቈፈረ፣ ታረሰ፣ ተጐደፈረ፣ ጐደጐደ።
ተማሰለ: ተገላበጠ፣ ተቀላቀለ፣ ተደባለቀ፡ ተዋሐደ (አንድ ሆነ)።
ተማረ (ተምህረ): ፊደል ቈጠረ፣ አጋዘ፡ አነበበ፣ አዜመ፡ ጽፈት፣ ድጕሰት፣ ዕርሻ፣ ዐናጢነት፣ ገንቢነት፣ ቀጥቃጭነት፣ ሸማኔነት፣ በገና፣ መሰንቆ፣ ፈረስ ግልቢያ፣ ውሃ ዋና፣ ስፌት፣ ንግድ፣ ማንኛውንም የእጅ ጥበብ አጠና፣ ለመደ።
ተማረ: ሲያውቅ አበደ፣ ዞረ።
ተማረ: ጦርነት ተዣመረ፡ ተፋተነ፡ ተቈራቈሰ፡ ነገር ተፈላለገ።
ተማረረ: ተጣላ፣ ተቋጣተነፋፈረ፣ ተባባሰ።
ተማረረ: ነሸረ።
ተማረተ: ተጣላ፣ ተፋጀ፣ ተከራከረ፣ ተሳደበ፡ ፍሬ ከገለባ እንዲለይ በአሳብ፣ በነገር ተለያየ።
ተማረከ (ተማህረከ): እጠላት እጅ ገባ፣ ተያዘ፡ ተዘረፈ፣ ተበዘበዘ፣ ተወሰደ።
ተማረክ: "እጅኸን ስጥ"፡ ተያዝ።
ተማረዘ: በመርዝ ተናደፈ፡ መርዝ ተቃመሰ፡ ተጣላ።
ተማሪ (ዎች)/ተመሃሪ: የተማረ፣ የሚማር፣ የሚያጠና፡ ደቀ መዝሙር። "ተማሪ ዘኬ ቈጣሪ" እንዲሉ።
ተማሪ ቤት: ተማሪ ያለበት፣ የሚማርበት፣ የሚያድርበት የተማሪ ቤት።
ተማራ: ተያይዞ ሄደ፡ "መንገዱ ይህ ነው" ተባባለ፡ ተጓተተ። "ዕውር ለዕውር ቢማራ ኹለቱም ገደል ይገባሉ። "
ተማራኪ: የሚማረክ።
ተማሮች: የተማሩ፣ የሚማሩ ተማሪዎች።
ተማሸ: ጊዜው ተላለፈ።
ተማሽ: የሚማስ፡ ቦረቦር።
ተማተመ: ለታተመ።
ተማተበ (ተማዕተበ): ተመሳቀለ፡ ተባረከ (መባረክ)።
ተማታ: መታ (አድራጊ)።
ተማታ: ተሸናቈጠ፣ ተጋፈ (ተደራራጊ)።
ተማታ: ተባባለ፣ ተደባደበ፣ ተጋጨ።
ተማቹ: የሰው ስም።
ተማች: መቺ፣ የሚማታ፣ ዱለኛ።
ተማችነት: ተማች መሆን፣ ዱለኛነት።
ተማከረ: ከወዳጁ፣ ከሚስቱ ምክር ተከፈለ።
ተማከተ: ተካለለ።
ተማካሪ: የሚማከር።
ተማወቀ: ተሞቀ።
ተማዘነ: ተላካ፣ ትክክል ተኳዃነ፣ ተናሣ።
ተማዘዘ: ተናቀለ፣ ተዋጣ።
"እከሌና እከሌ ተጣሉና ሰይፍ ተማዘዙ።
"
ተማዘዘ: ዘር ተቋጠረ።
ተማዛኝ: የሚማዘን።
ተማገረ: ተጠለፈ፣ ታሰረ፣ ተተበተበ።
ተማገዘ: ተገዛገዘ።
ተማገደ: ተጨመረ፣ ገባ፣ ተዶለ፣ ተጋፈጠ።
ተማጋሪ: የሚማገር፡ ታሳሪ።
ተማጋች: ተማጋቾች፡ የተገተ፣ የሚገት፡ ተነጋጋሪ፣ ተከራካሪ፡ ጠበቃ፣ ነገረ ፈጅ፡ የነገር አባት፡ የዋስ ተጋች፡ የቈማጣ ፈትፋች እንዲሉ።
ተማጋችነት: ተጋች መኾን፡ ጥብቅና።
ተማጋጅ: የሚማገድ።
ተማጠ: "እህ" መባል፣ ወደ ታች መገፋት።
ተማጠ: እህ ተባለ፣ ወደ ታች ተገፋ።
ተማጠነ (ተማሕፀነ): ሸሸ፡ ገዳም ገባ፡ ተጠጋ፡ ደወለ። (ካህናት ግን "ተማፀነ" ይላሉ (፩ነገ፡ ፪፡ ፳፰))።
ተማጠነ: ተላካ፣ ተማዘነ።
ተማጠነ: ተጠጋ፣ ዐጠነ።
ተማጠነ: ተጠጋ፣ ከሰሰ (ከዐጠነ (ሐፀነ) ግስ የመጣ)።
ተማጠነ: ከሠሠ።
ተማጠነ: ከሰሰ። "ሰው ይማጠንኻል" እንዲሉ።
ተማጠነ: ይግባኝ "ይሰማልኝ" አለ። (ካህናት ግን "ተማፀነ" ይላሉ (ግብ ሐዋ፳፭፡ ፳፩))።
ተማጠጠ: ከጭቃ ላይ ውሃን ተሻማ።
ተማጣኝ: የተማጠነ፡ የሚማጠን፡ ተጠጊ፡ የሙጥኝ ባይ፡ ደዋይ፡ ከሳሽ።
ተማጣጭ: የተማጠጠ፣ የሚማጠጥ፡ ጥም የያዘው ከብት።
ተማጯ: መፋቅ፣ መፈግፈግ፣ መጠርገግ፣ ወይም መጽዳት።
ተማጯ: ተፋቀ፣ ተፈገፈገ፣ ተጠረገ፣ ጸዳ።
ተማጯ: ተፋቀ፣ ተፈገፈገ፣ ተጠረገ፣ ጸዳ።
ተሜ: የቍልምጫ አጠራር።
ተምለገለገ: ተሙለጨለጨ።
ተምለግላጊ: የሚምለገለግ።
ተምሳሊት (ተመሳሊት): የምትመስል ሴት።
ተምሳሊት ብዙ: አትኮኝ የለሽ።
ተምሳሊት: ምሳሌ፣ አምሳል፣ አምሳያ።
ተምር (ሮች): የዘንባባ ዐይነት ዛፍ (ጣፋጭ ፍሬ ያለው ቤቴ ዘንባባ - ዕንጨቱም ፍሬውም "ተምር" ይባላል)።
ተምር: ታምር፣ ድንቅ፣ አመረ።
ተምሸከሸከ: ተበጣጠሰ (መሸከ)።
ተምሸከሸከ: ተበጣጠሰ፣ ተቈራረጠ፣ ተሰባበረ። "እንጀራው ከምጣድ ሲወጣ ተምሸከሸከ (ተሰባበረ)"።
ተምተም አለ: ቸኰለ፣ ፈጠነ፣ በብዙ ስፍራ ፈለገ፣ ተፈተፈ።
ተምተም: ችኰላ፣ ፍጥነት፣ ተፈተፍ።
ተምታሚ (ዎች): የተመተመ፣ የሚተምትም፣ ለታሚ፣ ደምዳሚ።
ተምታታ: ተፋጀ፣ ተሸበረ፣ ተጯጯኸ።
ተምትሜ: የሰው ስም።
ተምትም: ለትም፣ ግጭ።
ተምች (ቾች): ጥቍር ትል (በርኖሴ የጤፍ ፀር)።
ተምች: መታ፣ ብዙውን ሰው እንደ "ተምች በአንድ ጊዜ ደበደበ፣ ገደለ።"
ተምነሸነሸ: ተሸለመ፣ አጌጠ፣ ተጌጠ፡ ተሽሞነሞነ።
ተምዘገዘገ: ተውዘገዘገ።
ተሞለሞለ: ክብ ሆነ፡ ተጋገረ (ለምሳሌ ሙልሙል)።
ተሞለሰሰ: ተነቀለ፣ ተነጨ።
ተሞለቀቀ: ተዛቀ፣ ተነቀለ።
ተሞላቀቀ: ተናቀለ፣ ተጋፈፈ።
ተሞላቀቀ: ተንደላቀቀ፣ ተቀማጠለ፣ ተንቀባረረ (ባለገ)።
ተሞላቃቂ: የሚሞላቀቅ፡ ተንቀባራሪ።
ተሞላጀጀ: ተንሰዋለለ።
ተሞላፈጠ: ተሞዣለጠ።
ተሞረሞረ: ሾለ፣ ሞጠሞጠ።
ተሞረሞረ: ተቦረቦረ (ሆዱ ባዶ ኾነ)።
ተሞረደ: ተፈገፈገ፣ ተዘረዘረ፣ ተሳለ፣ ለዘበ።
ተሞራረተ: የርት ብድር ተከፋፈለ።
ተሞራረደ: ተፈጋፈገ፣ ተዘራዘረ።
ተሞራጅ: የሚሞረድ፡ ተዘርዛሪ።
ተሞሸ: ተዠመረ፣ ተቀነቀነ (ለቅሶው)፡ ተረገደ፣ ተጨበጨበ፡ ተመታ (ነጋሪቱ)።
ተሞሸለቀ: ታጨደ፣ ተላጨ፣ ተላጠ፣ ተገፈፈ፣ ተቃጠለ፡ ተሰረቀ።
ተሞሸረ: ሙሽራ ሆነ፣ አጌጠ፣ ተሸለመ፣ ማዕርግ አየ፡ እጕላ ቤት ገባ፣ ተከተተ።
ተሞሸረ: ተጠቀለለ፣ ተሸበለለ፡ ውሳጣዊ፣ ውስጠኛ ሆነ።
ተሞሻሪ: የሚሞሸር፣ የሚሸበለል።
ተሞቀ: ሞቀ፡ ታጠነ፡ ሙቀቱ ለቂ ተሰጠ። (ተረት) "ሥራ ጠፍቶ ጪስ ይሞቃል"።
ተሞናደለ (ሞነደለ): አማረ (በአካሄድ፣ በአረማመድ)።
ተሞኘ: ተደለለ፣ ተታለለ፡ ጀለ፣ ቄለ፣ ተሸነገለ።
ተሞኛኘ: ተዳለለ፣ ተሸናገለ።
ተሞከረ (ተመከረ): ተፈተነ፣ ተዠመረ፣ ተበገረ።
"ተመከረ"
ግእዝኛ ነው።
ተሞከተ: ተወቀጠ፣ ተቀጠቀጠ፡ ተቀለበ፣ በላ፣ ሠባ፡ ሙክት ሆነ።
ተሞካሪ: የሚሞከር፡ ተበጋሪ።
ተሞካሸ (ተመኵሰየ): ሞክሼ ሆነ (ተኳኳነ)፡ በአንድ ስም ተጠራ።
ተሞካች: የሚሞከት፣ የሚሠባ።
ተሞካከረ: ተፈታተነ።
ተሞዘቀ: ተመታ፣ ተከረከረ።
ተሞዘቀ: ተመታ ወይም ተከረከረ።
ተሞዠቀ: ተወረ፣ ተጠረገ፣ ተበጠረ፣ ተፈገፈገ።
ተሞዠቀ: ተወረ፣ ተጠረገ፣ ተበጠረ፣ ወይም ተፈገፈገ።
ተሞዣለጠ: ተላፋ፣ ተሞላፈጠ፡ ሥራ ፈታ።
ተሞዳሞደ: ተደማደመ፡ ውስጥ ለስጥ ተመካከረ። መሰጠረን እይ።
ተሞጀረ: ተጨመረ፡ በዝቶ ገባ፣ ተዶለ።
ተሞገሰ: ልጅነት አገኘ፡ ተወደደ።
ተሞገሰ: ተመሰገነ፡ ግጥም ተገጠመለት፡ ዘፈን ተዘፈነለት።
ተሞገተ: ተነዘነዘ፣ ተጨቀወቀ፣ ተነተረከ፡ ተጠየቅ ተባለ።
ተሞገደ: በዝቶ ተማገደ፣ ተዠገደ።
ተሞገደ: ተወገጠ፣ ታወከ።
ተሞጋች: የሚሞገት፣ የሚጠየቅ።
ተሞጋገሰ: ተመሰጋገነ፡ ግጥም ተቀባበለ።
ተሞጨለፈ: ተሰረቀ፡ ተነጠቀ፡ ተቀማ፡ ተወሰደ።
ተሞጫጨረ: ተጫጫረ፣ ተቦጫጨረ፡ ተበለሻሸ ጽፈቱ።
ተሰለለ: ታየ፣ ተገመተ፣ ተመረመረ፣ ተጐበኘ።
ተሰለመጠ: ተዋጠ፣ ተሰለቀጠ።
ተሠለሰ: ፫ ጊዜ ታረሰ፡ ተቀበቀበ፡ ታየመ፡ ለሰለሰ።
ተሠለሰ: ሦስት ሆነ፡ ተባለ።
ተሠለሰ: ተመሰገነ፡ ምስጋና ተቀበለ።
ተሰለሰለ፡ ተሸነሸነ፣ ተነጣጠለ።
ተሰለቀ: ቀስ ብሎ ኼደ፣ ተቈነነ።
ተሰለቀ: ኹለተኛ ተፈጨ፣ ደቀቀ፣ ተደቈሰ፣ ላመ፣ ለዘበ።
ተሰለቀጠ፡ ተዋጠ፣ ወደ ሆድ ወረደ፣ አደረገ።
ተሰለቃቀጠ፡ ተዋዋጠ።
ተሰለበ፡ በርቀት ተወሰደ፣ ዐለቀ። "ዥብ ምንም አንድ እግሩ ዐጪር ቢኾን መንገድ ይሰለብለታል።"
ተሰለበ፡ ተቈረጠ፣ ተጐመደ፣ ተጝደደ (ዘዳግም ፳፫፡ ፩)።
ተሰለበ፡ ተገፈፈ፣ ተነሣ።
ተሰለተ፡ ተከፈለ፣ ተለየ።
ተሰለተ፡ ተዘቅዝቆ፡ ተከደነ፣ ሣሣ ክዳኑ።
ተሰለቸ፡ ተጠገበ፣ ተጠላ፣ ተፈላጊ ሳይኾን ቀረ፣ ተነቀፈ። "ማር ሲበዛ ይመራል እንዲሉ።"
ተሰለፈ: ሰይፍ ታጥቆ፣ ወንጭፍ፣ ቀስት፣ ጠመንዣ ጨብጦ፣ ጋሻ አንግቦ፣ ጦር ይዞ፣ ተራ መታ፣ ተሰደረ፣ ተደረደረ፣ ቆመ።
ተሰለፈ: ተደቀነ፣ ተደከረ።
ተሰላ፡ ታሰበ፣ ተቈጠረ።
ተሰላለመ: ሰላምታ ተሰጣጠ፣ ተቀባበለ፣ እንዴት ዐደርኸ፣ ዋልኸ፣ ሰነበትኸ ተባባለ፣ ተሳሳመ።
ተሰላለበ፡ ተጐማመደ።
ተሰላለፈ: ተቀራረበ፣ አንጸር ለአንጻር፣ ፊት ለፊት ተቋቋመ።
ተሰላላፊ: የሚሰላለፍ፣ የሚቀራረብ።
ተሠላሽ: የሚሠለስ፡ የሚታየም።
ተሰላቂ: የሚሰለቅ፣ ለዛቢ።
ተሰላች፡ የሚሰለት ጣራ።
ተሰላይ: የሚሰለል፣ ተጐብኚ።
ተሰላፊ (ፎች): የሚሰለፍ፣ ተደርድሮ የሚቆም ሐርበኛ፣ ቀስተኛ፣ ጦረኛ፣ ነፍጠኛ፣ ዘማች።
ተሰመለ፡ ተዠለጠ፣ ለፋ፣ ለሰለሰ፣ ተላገ፣ ተፋቀ፣ ለዘበ።
ተሰመረ (ተፀመረ)፡ ተቸነከረ፣ በምስማር ተመታ።
ተሠመረ: ተበገረ፡ ተጣለ፡ ተነደፈ (መሥመሩ)።
ተሰመራ፡ ተሰማራ (ተረዐየ፡ ወፈረ)፡ "ወደ ሥራ ኼደ፣ ወደ ዱር ገባ፣ ተሠራጨ (ሕዝቅኤል ፴፬፡ ፲፬)።"
ተሰመነ፡ ስምንት ኾነ፣ ተባለ።
ተሰመነመነ፡ ተድቀሰቀሰ፣ እንቅልፍ ተጫነው።
ተሰመጠ፡ ተሳጠመ።
ተሰሚ: የሚሰማ፣ የሚደመጥ፣ ጨዋ፣ ሽማግሌ፣ ሊቅ።
ተሰማ (ተሰምዐ)፡ ተደመጠ፣ እሰው ዦሮ ገባ (ግብረ ሐዋርያት ፲፡ ፴፩)።
ተሰማ፡ ታደመጠ፣ ነገሩ ታወቀ (ትንቢቱ)።
ተሰማ፡ የወንድ መጠሪያ ስም።
ተሰማመረ፡ ተጊያጊያጠ፣ ተሸላለመ።
ተሰማሚ፡ የሚሰማማ፣ ተደማማጭ።
ተሰማማ፡ ተወያየ፣ ተናገረ፣ ተዋሐደ፣ በኣንድነት ተባበረ፣ እታረቀ፣ ተፋቀረ።
ተሰማማ፡ ተደማመጠ፣ ተፈቃቀረ፣ ተዋደደ፣ ተዋዋለ (ምሳሌ ፲፱፡ ፲። ማቴዎስ ፳ ' ፩፡ ፪፡ ፲፫። ግብረ ሐዋርያት ፳፰ ' ፴)።
ተሰምሪ፡ ተሰማሪ፡ የተሰመራ፣ የሚሰመር፣ የተሰማራ፣ የሚሰማራ (ሰው፣ ከብት)።
ተሰሰ: ተላሰሰ፣ ተነቀለ፣ ተጠረገ።
ተሠሠት: ተነፈገ፡ ተቀቀተ።
ተሰረሰረ: ተሰነፈጠ፣ ተበሳ፣ ተነደለ።
ተሰረረ: ተወጣ፣ ተጠቃ፣ ተመታ (በታች ኾነ ተወጣበት) ። (ተረት) ፡ "ዥብ እሰር ብሎ ተሰሮ ገባ"።
ተሰረረ: ተጣደ፣ ሰፋ፣ ተጋገረ።
ተሰረረች: ተጠቃች፣ ተመታች፣ ቄብነቷ ቀረ።
ተሰረቀ (ተሰርቀ): ተነሣ፣ ተወሰደ (በሌባ እጅ)፣ ተሞጨለፈ።
ተሰረነቀ: ታፈነ፣ ተሰነፈጠ።
ተሠረዘ: ተጻፈ (ሠረዙ)።
ተሠረዘ: ጠፋ፡ ቀረ (ጽፈቱ)።
ተሰረየ (ተሰርየ): ቀለለ፣ ተተወ፣ ይቅር ተባለ (ኢሳይያስ ፯፡ ፯። ሮሜ ፬፡ ፯)።
ተሰረጀ: ተጠለፈ፣ ተሰናከለ፣ ተጣለ፣ ወደቀ።
ተሰረገ: ተደራጀ፣ ተደገሰ።
ተሰረገ: ተጌጠ፣ ተሸለመ፣ ተኳለ፣ ተዳረ፣ ሚስት አገባ።
ተሠረገበ: ተጠጣ፡ ተጨለጠ።
ተሠረጐዶ: ተሰበረ፡ ጐደጐደ፡ ጐደለ።
ተሠረጓጐደ: ተሰባበረ፡ ተጓደለ።
ተሠሪ (ዎች): በየመንደሩ የሚሠራ፡ በገባር ቤት የሚቀመጥ ወታደር (ምሪተኛ)።
ተሠሪነት: ተሠሪ መኾን።
ተሰራ (ተሰርሐ)፡ ታረሰ፣ ተቈፈረ፣ ተገበረ፣ ተዘመረ፣ ታጨደ፣ ተከመረ፣ ተወቃ።
ተሠራ (ተሠርዐ): ታግን፡ ተወሰነ፡ ተደነገገ፡ ተደነባ።
ተሠራ: ሥራት ለበሰ፡ ለመደ፡ ተዳኘ። (ግጥም):
"ፈረንጅ ወርዶ ወርዶ ማረፊያው ጅቡቴ፡ ተሠራኹ ተቀጣኹ፡ ማረኝ አካላቴ።
" (ኹለተኛ ተሠራ): በጠና ታሞ ሙቶ ተነሣ (ዮሐ፲፩፡ ፵፬)።
ተሠራ: ተመራ፡ ስፍራ ያዘ።
ተሠራ: ታነጠ፡ ተገነባ፡ ተነገደ፡ ተሰፋ፡ ተጻፈ፡
ተጐነጐነ። "አይዞኸ ወንድሜ፡ ተሠራውጋሜ" እንዲል፡ ሐርበኛ።
ተሠራ: ኾነ፡ ተደረገ፡ ተበጀ፡ ተዘጋጀ፡ ተፈጠረ፡ ተገኘ (ፊልጵ፩ ፳፯)።
ተሰራረቀ: ተሞጨላለፈ።
ተሰራረገ: ተዳዳረ።
ተሠራራ: ተኳዃነ፡ ተደራረገ።
ተሠራዥ: የሚሠረዝ፡ ቀሪ።
ተሰራጀ: ተጣለፈ፣ ተጣጣለ፣ ተዋደቀ።
ተሰራጊ: የሚሰረግ፣ የሚዳር፣ የምትዳር።
ተሠራጪ: የሚሠራጭ (ከብት፣ መርዝ)።
ተሰርሳሪ: የሚሰረሰር፣ የሚበሳ።
ተሰርቆ ኼደ: ከጌታው ሳይሰናበት ተደብቆ ነጐደ፣ ኰበለለ።
ተሠርጓጅ: የሚሠረጐድ።
ተሰቀለ (ተሰቅለ)፡ ተንጠለጠለ፣ ታበተ፣ ከምድር ራቀ፣ ሰፈረ (ዕቃው፣ ዶሮው፣ ሰዉ) (የሐዋርያት ሥራ ፪፡ ፳፫)። "(የባልቴት፡ ግጥም)፡ ዐርብ ሊሰቀል ማታውን ተሰናበታት እናቱን። እናትዬ፡ ቈይ ታዪኛለሽ ተሰቅዬ። እኔን ይስቀለኝ ይስቀለኝ ሐሰት ባንተ ዘንድ አይገኝ።"
ተሰቀለ፡ ሰራ።
ተሠቀሠቀ: ተወጋጋ፡ ተበሳሳ፡ ተለየ፡ ተነጠለ።
ተሠቀቀ: ተጠላ፡ ተሰለቸ፡ ተሰቀጠጠ። ልማዱ ግን "ጠላ ሰለቸ" ነው (ኢዮ፴፮፡ ፴፫፣ ዘካ፲፩፡ ፰)።
ተሠቃቂ: የሚሠቀቅ፡ የሚሰለች።
ተሰቃይ፡ የሚሰቀል፣ የሚንጠለጠል፣ ተንጠልጣይ።
ተሰቈረ፡ ተበሳ፣ ተሸነቈረ።
ተሠቅሣቂ: የሚሠቀሠቅ፡ የሚበሳሳ።
ተሰበሰበ: ቀለጠፈ (ባለባበስ፣ ባቀማመጥ)። "ሸነቀጠን እይ።"
ተሰበረ (ተሰብረ): ነከተ፣ ተቀለጠመ፣ ደቀቀ፣ ተሠነጠቀ፣ ተለበጠ (ሕዝቅኤል ፳፯፡ ፴፬)። "ሲሰበር ይሰንጠር እንዲሉ።" (ልቡ ተሰበረ): ፈጽሞ ዐዘነ። (ቢሰበር ዕዳ): ሰበበኛ ሰው። (ይሰበር ደጋኔ): ከባሕር የመጣ ቀጪን ድር።
ተሰበረ: ተነደለ፣ ተጣሰ፣ ፈረሰ።
ተሰበረ: ተደፋ፣ ዘነበለ።
ተሰበረ: ታጨደ፣ ተቈረጠ።
ተሰበቀ: ተበጠበጠ፣ ተማስለ፣ ተምታታ፣ ታሸ።
ተሰበቀ: ተነገረ፣ ኾነ፣ ተደረገ (ሰብቁ)።
ተሰበቀ: ተወዘወዘ፣ ተነቀነቀ።
ተሰበቃቀለ: ተቀለጣጠፈ፣ ተመሰቃቀለ።
ተሰበበ: ተመካኘ።
ተሰበተ: ሰባት ኾነ።
ተሰበተ: ታረሰ፣ ተገለገለ።
ተሰበከ: ተነገረ፣ ተወራ፣ ተባለ፣ ተሰማ (ማቴዎስ ፳፬፡፡ ፲፬። ሉቃስ ፳፬፡ ፵፯)።
ተሰበከተ: ተገረፈ፣ ተጠጣ።
ተሰበዘ: ተሻጠ፣ ተሸጐጠ፣ ተጨመረ፣ ገባ።
ተሰባ (ተሰብሐ): ተገለጠ፣ ተረዳ።
ተሰባሰበ: ተጠራራ፣ ተለቃቀመ፣ ተጠረቃቀመ፣ ተከመቻቸ።
ተሰባሪ: የሚሰበር። "ሰውና ዕንጨት ተሰባሪ ነው።"
ተሰባቀለ: ተቀላጠፈ።
ተሰባቀለ: ተዘናፈለ፣ ተመሳቀለ (ኤርምያስ ፮፡ ፪)።
ተሰባበረ: ተቀለጣጠመ (፪ኛ ዜና መዋዕል ፲፬፡ ፲፫)።
ተሰባኝ: ተገለጠልኝ፣ ገባኝ። "(አልተሰባኝም)፡ አልተገለጠልኝም፡ አልገባኝም።"
ተሰባው: ተገለጠለት፣ ተረዳው፣ ገባው።
ተሠባጠረ: ተሠበጣጠረ: ተዋሰበ፡ ተዛነቀ፡ ጣልቃ ገባ፡ አንድ ዐለፍ ሆነ፡ ቆመ።
ተሠባጣሪ: የሚሠባጠር፡ የተጠቀጠቀና ያልተጠቀጠቀ፡ ባለጽፈት ወረቀት፡ ቀሪና ኻያጅ።
ተሰብሳቢ: የሚሰበሰብ።
ተሰተረ (ተሰትረ): ተዘረጋ፣ ተሰጣ።
ተሰታተረ: ተዘረጋጋ።
ተሰነሰነ፡ ተለበለበ፣ ተሸነሸነ፣ ተነተነ፣ ነጠለ፣ በዛ።
ተሠነቀ: ተቈላ፡ ተፈጨ፡ ተጋገረ፡ ተዘጋጀ።
ተሰነቀረ፡ ተሻጠ፣ ተጋረጠ፣ ገባ።
ተሰነቃ (ተሰንቀወ)፡ ተጠረበ፣ ታነጠ፣ ተላገ።
ተሰነቃ፡ ተመታ፣ ተከረከረ፣ ተገረፈ።
ተሠነበጠ: ተሠነጠረ፡ ተለበጠ፡ ተሠነተረ፡ ተከረከረ፡ ተከፈለ።
ተሠነተረ: ተበጣ፡ ተቀደደ፡ ተሠነጠቀ።
ተሠነታተረ: ተበጣጣ፡ ተቀዳደደ።
ተሰነከለ፡ ተመታ፣ ተጐዳ።
ተሰነካከለ፡ ተጓጐለ፣ ተወለካከፈ።
ተሰነካካይ፡ የሚሰነካከል።
ተሰነኰረ፡ ተዘነኰረ።
ተሰነዘረ፡ ተለካ፣ ተመጠነ።
ተሰነዘረ፡ ተሠነተረ፣ ተበጣ፣ ተሠነጠቀ።
ተሰነዘረ፡ ተቃጣ።
ተሰነደቀ፡ ቀስ ብሎ ታቦትኛ ኼደ።
ተሰነደቀ፡ ተቀረጸ፣ ክብ ሆነ።
ተሰነደቀ፡ ታሰረ።
ተሰነደደ፡ ተሠራ፣ ተበጀ፣ ስንድዱ ተሰካ፣ ተደረደረ፣ ቀጥተኛ ሆነ።
ተሰነገ፡ ስናግ ገባበት።
ተሰነገ፡ ተበሳ፣ ተሸነቈረ፣ ገባ፣ ተቀረቀረ።
ተሰነገ፡ ተነቀነቀ፣ ተደናቀፈ፣ ዘክዘክ አለ። "በቅሎ።"
ተሰነገ፡ ተጠመጠመ፣ ታሰረ።
ተሰነገ፣ ተጨነቀ፣ ተጠበበ።
ተሰነገለ፡ ተወለወለ፣ ጠራ፣ ተብለጨለፈ፣ ተሳለ፣ ሰላ (ሕዝቅኤል ፳፩፡ ፲፡ ፲፩፡ ፲፭)።
ተሰነገጩ፡ ነቀነቀ፣ ዘክዘከ፣ አደናቀፈ።
ተሰነጋ፡ ተኰላሸ፣ ወጣ፣ ተጐነደለ፣ ተቀጠቀጠ፣ ተወቀጠ፣ ታሸ፣ ታሰረ፣ ተሠነጠቀ፣ ፈሰሰ።
ተሰነጠ፡ አማረ፣ ጌጠኛ ሆነ።
ተሠነጠረ: ተለበጠ፣ ተሠነበጠ (መክ፲፡ ፱)። (ተረት):
"ሲሰበር ይሠንጥር።
"
ተሠነጠቀ: ተሰበረ፡ ነበበ፡ ተተረተረ፡ ተተረረ፡ ኹለት ሆነ (ኤር፲፫፡ ፬)።
ተሠነጣጠረ: በብዙ ወገን ማለት ነው።
ተሠነጣጠቀ: ተሰባበረ፣ ተቃደደ (በብዙ ወገን ተሠነጠቀ)። "እግሬ ተሠነጣጠቀና አላስኬድ አለኝ። "
ተሰነፈጠ፡ ተሰረነቀ፣ ተሰረሰረ።
ተሠናተረ: ተባጣ፡ ተቃደደ።
ተሰናነፈ፡ ተናነሰ፣ ተበላለጠ። "እከሌና እከሌ በሙያ አየሰናነፉም።"
ተሰናናፊ፡ የሚሰናነፍ፣ ተበላላጭ።
ተሰናኘ፡ ተሰማማ፣ ተጋጠመ፣ ተባበረ፣ ተላለፈ (ከትውልድ ወደ ትውልድ)።
ተሰናከለ፡ ተጠለፈ፣ ተሰረጀ፣ ተጨናጐለ፣ ተወላከፈ፣ ተደናቀፈ፣ ዕንቅፋት መታው፣ ጕዳት አዠኘው፣ ታወከ። "ኀጢአት ሠራ፣ በኀጢአት ወደቀ፣ መንፈሳዊ ሙቀቱ በረዶ ቀዘቀዘ (ምሳሌ ፬፡ ፲፪። ኤርምያስ ፵፮፡ ፮። ሮሜ ፱፡ ፴፪። ፲፩፡ ፲፩)።"
ተሰናካይ፡ የሚሰናከል።
ተሰናዳ፡ ተዘጋጀ፣ ተደራጀ (፩ኛ ሳሙኤል ፲፯፡ ፪)።
ተሰናዳ፣ ገባ፣ ተጨመረ፣ ተከተተ (የሥንቅ፣ የዕቃ፣ የማንኛውም ነገር) (ተደራዝ)።
ተሰናጂ፡ የሚሰናዳ፣ የሚዘጋጅ፣ ግቢ፣ ተጨማሪ።
ተሰናጊ፡ የሚሰነግ፣ የሚገባ።
ተሠናጠቀ: ተቃደደ፡ ተካፈለ፡ ተራከበ፡ ግማሽ ግማሹን ወሰደ።
ተሠናጣቂ: የሚሠናጠቅ (ተካፋይ)።
ተሠንታሪ: የሚሠነተር (ተበጪ)።
ተሰንዛሪ፡ የሚሰነዘር፣ ተሠንታሪ።
ተሰንዳቂ፡ የሚሰነደቅ፣ በቀስታ የሚኼድ፣ የሚታሰር፣ ታሳሪ።
ተሰንጊ፡ የሚሰነጋ፣ የሚኰላሽ።
ተሠንጣቂ: የሚሠነጠቅ (ተቀዳጅ)።
ተሠኘ: ተባለ፡ ተነገረ።
ተሠኛኘ: ተባባለ፡ ተነጋገረ።
ተሰከለ፡ ታሰረ፣ ተቈረኝ።
ተሰኪ፡ የሚሰካ፣ የሚሻጥ።
ተሰካ (ተሰክዐ)፡ ተሻጠ፣ ተሳገ፣ ገባ፣ ተደረደረ፣ ቆመ፣ ተገተረ። "እከሌ፡ ዐጥር ላይ፡ ተሰካ፡ እንዲሉ።"
ተሰካይ፡ የሚሰከል፣ ዐመለኛ (የጋማ ከብት)።
ተሰወረ፡ ተሸፈነ፣ ተከለለ፣ ታባ፣ ተደበቀ፣ ተሸሸገ፣ የማይታይ ሆነ (፪ኛ ሳሙኤል ፲፯፡ ዮሐንስ ፰፡ ፶፱)።
ተሰወረ: ታወረ።
ተሠዊ (ተሠዋዒ): የሚሠዋ (ያመት ጥቦት፣ ክርስቶስ)።
ተሠዋ (ተሦዐ): ታረደ፡ ጭዳ ተባለ።
ተሰዋሪ፡ የሚሰወር፣ ተደባቂ፣ ተሸሻጊ።
ተሰዋወረ፡ ተደባበቀ።
ተሰየመ (ተሰምየ)፡ ስም ተሰጠው፣ ወጣለት።
ተሠየመ: ተሰፈረ፡ ተመላ፡ ተለበመ።
ተሠየመ: ተሾመ፡ ከበረ።
ተሰየፈ፡ ሾጠጠ፣ ሾጣጣ ሆነ።
ተሰየፈ፡ በሰይፍ ተመታ፣ ተቈረጠ፣ ተከለለ፣ ተገደለ።
ተሰያሚ፡ የሚሰየም፣ ስም ተቀባይ።
ተሰያፊ፡ የሚሰየፍ፣ ተገዳይ።
ተሰደሰ፡ ስድስት ሆነ፣ ተባለ።
ተሰደረ፡ ተወለደ፣ ረባ፣ ተደረደረ፣ ተመዴዴ፣ ተኵሎኰለ፣ ተራ መታ።
ተሰደረገ: ፈጠነ፣ አለፈ፣ ሄደ።
ተሰደቀ (ተሰድቀ)፡ ተዘረጋ።
ተሰደቀ፣ ተቀባ፣ ተደለሰ።
ተሰደበ፡ ተወረፈ፣ ተነቀፈ፣ ተዘለፈ፣ ተዋረደ፣ አነሰ፣ ቀለለ፣ ኰሰሰ፣ ረከሰ (ሉቃስ ፲፰ - ፴፪)። "ሰጠን፡ እይ።"
ተሰደደ (ተሰደ)፡ ግብር መሮት፣ አገዛዝ ጸንቶበት፣ ችግር በዝቶበት ካገር ወጣ፣ አገር ጥሎ ቈርበት ጠቅሎ ኼደ። "(ተረት)፡ ካብሮ፡ አደግኸ፡ አትሰደድ።"
ተሰዳሪ፡ የሚሰደር፣ ተደርዳሪ።
ተሰዳቢ፡ የሚሰደብ፣ ተነቃፊ።
ተሰዳጅ (ጆች)፡ የሚሰደድ፣ የሚኼድ።
ተሰዳጅነት፡ ተሰዳጅ መኾን።
ተሰገሰገ: ተቀራረበ፣ ተጠቀጠቀ፣ ጠበበ።
ተሰገሰገ: ገባ፣ ታጨቀ።
ተሰገደ: ኾነ፣ ተደረገ (ቀረበ ስግደቱ ለፈጣሪ)።
ተሰገደደ: ተመለሰ፣ ተሰበሰበ፣ ተደበቀ፣ ተከለለ፣ ተሰወረ።
ተሰገጠ: ተሰፋ፣ ተቀመቀመ፣ ተዘመዘመ (ቅሉ፣ ካባው)።
ተሰጋለበ: ተቻኰለ፣ ተጣደፈ ለመብላት።
ተሰጋጭ: የሚሰገጥ፣ የሚሰፋ።
ተሰግሳጊ: የሚሰገስግ (በሸማ ጫፍ የተጣለ ሰፊ ጥለት)።
ተሰጐደ: ተመታ፣ ተገጨ።
ተሰጐደ: ታጠፈ፣ ተቀነፈ፣ ጐደጐደ፣ ተደጐሰ፣ ተጐበጐበ፣ ተሸለመ፣ ተጌጠ።
ተሰጓጅ: የሚሰጐድ፣ ተደጓሽ።
ተሰጠ (ተሰጥወ)፡ ተቸረ፣ ተለገሰ፣ ታደለ፣ ተረከበ፣ ከተቀባይ እጅ ገባ። "(ለሞት ተሰጠ)፡ ይሞት፣ በቃ ተባለ፣ ዐለፈ።"
"(የዝኆን ዦሮ ተሰጠው)፡ ሰምቶ እንዳልሰማ ሆነ፣ ነገርን ሁሉ ናቀ፣ ቸል አለ።"
ተሰጠ፡ ተነገረ፣ ተመለሰ፣ ተወሣ (ቃሉ፣ ነገሩ)።
ተሰጠሰጠ፡ ተደባደበ፣ ተጋረፈ፣ ተማታ።
ተሠጠጠ: ተቀደደ።
ተሰጠጣ፡ ተዳደለ፣ ተቀባበለ፣ ተረካከበ።
ተሰጣ (ተሰጥሐ)፡ ተዘረጋ፣ ተዘረረ፣ ተሰተረ፣ ተበተነ።
ተሰጣጠ፡ ተዳደለ፣ ተቀባበለ፣ ተረካከበ።
ተሰጥዎ፡ መዘምራን የሚያዜሙት የቅዳሴ ጓዝ። "እግዚኦ፡ ተሣሀለነን፡ ምስለ፡ መንፈስከን፡ የመሰለ፡ ትርጓሜው፡ መመለስ።"
ተሰጦ (ተሰጥዎ)፡ ዕድል።
ተሰጪ፡ ጭ፡ የሚሰጥ፣ የሚታደል።
ተሰጪነት፡ ተሰጪ መኾን።
ተሰፈረ፡ ቀለብ ተቀበለ (ወታደሩ)።
ተሰፈረ፡ ተለካ፣ ተመጠነ (እኽሉ)።
ተሰፈረ፡ ያበደረውን እኽል ተከፈለ። "በሰፈሩበት ቍና መሰፈር አይቀርም።"
ተሰፊ፡ የሚሰፋ (ሸማ፣ ዐጥፍ፣ በርኖስ)።
ተሰፋ (ተሰፍየ)፡ ተጠቀመ፣ ተደረዘ፣ ተዘመዘመ።
ተሰፋሪ፡ ቀለብ ተቀባይ፣ ቀለብተኛ።
ተሰፋሪ፡ የሚሰፈር፣ የሚለካ (እኽል)።
ተሢያሢያረ: ተማማለ፡ ተደማደመ።
ተሲያት (ተስዐ) (ሰዓት): ከሠለስት በላይ ያለ ጊዜ፣ ረፋድ። (አውራን አስተውል)
ተሲያት ሆነ: ረፈደ። ዘጠኝ ሰዓት። (ተሱዓት ሰዓት) ምሳሌ: "መንገደኛው በተሲያት መጣ" እንዲሉ። (ሰዓትን እይ)
ተሳለ (ተሳአለ)፡ ታቦትን፣ ጣዖትን ተጠያየቀ፣ ተለማመነ፣ ተለማመጠ፣ ተማኰተ። "ልማዱ ግን እንደ መጀመሪያው አድራጊነት ነው (መዝሙር ፻፴፪፡ ፪። ዮናስ ፩፡ ፲፮)።" "ከበሽታ ብታድነኝ፣ ከጭንቅ ብታወጣኝ፣ መከራዬን ብታቀልልኝ ጧፍ፣ ዕጣን፣ ዘይብ እሰጣለኹ፣ ግምጃ እጋርዳለኹ አለ።"
ተሳለ (ተስሕለ)፡ ተሞረደ፣ ተፈገፈገ፣ ተሰነገለ፣ እስኪሰላ ድረስ ተለመጠ (ሕዝቅኤል ፳፩፡ ፲)። "(ተረት)፡ በተሳለ፡ ያርዷል፡ በታየ፡ ይፈርዷል።"
ተሳለ (ተስዕለ)፡ ሆነ፣ ተደረገ (ሳሉ ተጐበሰተ)።
ተሳለ (ተስእለ)፡ ተለመነ፣ ተጠየቀ። "ሳለን፡ ለመነ፡ ተሳለን፡ ተለመነ፡ ማለት፡ አልተለመድም።"
ተሣለ (ተሥዕለ): ተነደፈ፡ ተበገረ፡ ተመሰለ።
ተሳለ፡ ተዘረዘረ (መጋዙ፣ ማጭዱ) (ራእይ ፲፬፡ ፲፬)።
ተሳለ፡ የስለት ልጅ ሆነ፣ ለግዜር ተሰጠ (መሳፍንት ፲፫፡ ፯)።
ተሳለለ: ተጐበኛኘ፣ ተላላከ፣ ተጠያየቀ፣ ተነጋገረ፣ ተመራመረ፣ ተመሳጠረ።
ተሳለመ: ቤተ ክርስቲያን፣ መስቀል፣ የቄስ እጅ ሳመ፣ ተባረከ፣ እጅ ነሣ፣ ሰላምታ ሰጠ፣ ተሰናበተ (ግብረ ሐዋርያት ፳ ፥ ፩። ፩ኛ ጴጥሮስ ፭፡ ፲፬)። "ተሳለመ፡ ተደራራጊ ሲኾን፡ በአድራጊነትና በተደራጊነት መፈታቱን ልብ አድርግ።"
ተሣለቀ: አላገጠ (ሠለቀ) ።
ተሳለበ፡ ተጓመደ።
ተሳለፈ: ተቃረበ፣ ተፋጠጠ ለመዋጋት፣ ለመጋደል።
ተሳላ፡ ተሳሰበ፣ ተፋሰሰ፣ ተቈጣጠረ።
ተሳላ፡ ተከናወነ፣ ተቃና፣ ተቀናበረ፣ ተሳካ (ማርቆስ ፱፡ ፵፱)።
ተሳላሚ: የሚሳለም፣ ተባራኪ።
ተሣላቂ: የተሣለቀ፡ የሚሣለቅ፡ የሚዘብት፡ አላጋጭ (ምሳ፳፩፡ ፲፩)።
ተሳላይ: የተሳለለ፣ የሚሳለል፣ ተጠያቂ፣ ተመራማሪ።
ተሣልቆ: መሣለቅ (ግእዝ)።
ተሳማ (ተሳምዐ): ተዳመጠ።
ተሳሰረ (ተአስረ): ተያያዘ፣ ተቈራኘ።
ተሳሰረ (ንግግር): ተንተባተበ፡ ከስካር ወይም ከበሽታ የተነሳ መናገር አቃተው። “አፉ ተሳሰረ” እንዲሉ።
ተሳሰበ (ተሓሰበ): ተፈቃቀደ፡ ተቈጣጠረ፡ ተሳላ፡ ተረዳዳ (መመካከር ወይም መረዳዳት)።
ተሣሠተ: ተናፈገ።
ተሳሳመ (ተሳዐመ): ተጨማጨመ፣ አፍ ላፍ፣ ጕንጭ ለጕንጭ፣ ትከሻ ለትከሻ ተገናኘ። "አህያና አህያ ሲገናኝ ይሳሳማል።"
ተሳሳሚ (ተሳዓሚ): የተሳሳመ፣ የሚሳሳም።
ተሣሣቀ: በሣቅ ተፈራረቀ፡ ተጨዋወተ። (ተረት):
"እንሣሣቅስ ታልሽ ነዶዬን ጥለሽ (ባላገር ዝንጀሮዋን)። "
ተሳሳበ (ተሳሐበ): ተጓተተ። "ምድርን ተለካካ በገመድ።"
ተሳሳቢ (ተሓሳቢ): የተሳሰበ፡ የሚተሳሰብ፡ ተቈጣጣሪ (የሚመካከር)።
ተሳሳቢ (ተሳሓቢ): የተሳሳበ፣ የሚሳሳብ፣ ተጓታች።
ተሳሳቢ: የሚሳሳብ፡ ሳበ (የሚመካከር)።
ተሳሳቢ: የሚተሳሰብ፣ ዐሰበ።
ተሳሳቢነት: ተጓታችነት።
ተሳረረ: ተዛዘለ፣ ተነባበረ፣ ተገናኘ።
ተሳረቀ: ተሞጫለፈ።
ተሣራ: ተዋጋ፡ ተማታ፡ ተቀራደደ።
ተሣራ: ተዳረገ።
"እከሌና እከሌ ክፉ ተሣርተዋል!" እንዲሉ።
ተሣቀ: ሆነ፡ ተደረገ (ሣቁ) (ሕዝ፴፮፡ ፬)። "በትና ለት ሲሰማሙት፡ ተሣቀበት፣ ተሣቀለት"
ይላል።
ተሳቀለ፡ ተነሣ፣ ተንጠላጠለ፣ ተማዘነ።
ተሣቀቀ: አይቶ አግኝቶ ዐጣ፡ ዐፈረ፡ ኩም አለ።
ተሣቀየ: ጭንቅ ተቀበለ፡ ተጨነቀ።
ተሣቃቂ: የተሣቀቀ፡ የሚሣቀቅ።
ተሳበ (ተስሕበ): ተጐተተ፣ ተመዘዘ፣ ረዘመ።
ተሳበ: ተወጠረ፣ ተለጠጠ፣ ተገተረ።
ተሳበ: ተጠራ፣ መጣ፣ ቀረበ።
ተሳበ: ዐረገ፣ ወጣ (ግብረ ሐዋርያት ፲፩፡ ፲)።
ተሳበረ: ተማታ፣ ተቀላጠመ። "አህያ ላህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሳበር።"
ተሳበረ: ተሸናነፈ፣ ተረታታ፣ ድል ተኳዃኑ። "ዐይን ላይን ተሳበረ እንዲሉ።"
ተሳበቀ: ተወዛወዘ፣ ተነቃነቀ።
ተሳበቀ: ተጠላለፈ፣ ተያያዘ።
ተሳቢ (ተሰሓቢ): የሚሳብ፣ ተጐታች (ሞፈር፣ ፈረስ፣ በቅሎ፣ ሠረገላ፣ እባብ፣ ዘንዶ፣ ዐረግ፣ ላስቲክ፣ ቀስት)።
ተሳቢ፡ ቃል፡ ነገር: "ሳቢና ተሳቢ እንዲሉ።"
ተሳቢነት: ተሳቢ መኾን፣ ጐታችነት።
ተሳቦ: እየተሳበ የሚኼድ (ትል፣ ቀንዳውጣ፣ ዛጐል፣ ልብሱ)።
ተሳተረ: ተዘረጋ።
ተሳተፈ: ተገናኘ፣ አንድ ኾነ፣ ተቋረሰ፣ ዐብሮ በላ፣ ተፋተተ፣ ተካፈለ።
ተሳታፊ: የሚሳተፍ።
ተሳነ: አቃተ (ከግስ ሳነ የመጣ)።
ተሳነፈ፡ ተዳከመ (ሰነፍ፣ ተኳዃነ ልብና ሰውነት)።
ተሳከረ፡ ተሳሳተ፣ ተዛነቀ፣ ተዘባረቀ፣ ተቃወመ (ሰዉ፣ አእምሮው፣ ነገሩ፣ ሥራው)።
ተሳካ (ተሳክዐ)፡ ተዋደደ፣ ተቀናበረ፣ ተሳላ።
ተሳይ፡ ብፅዐት የሚያደርግ (ሳለ)።
ተሳይ፡ የሚሳላ፣ የሚቈጣጠር፣ ተሳሳቢ።
ተሳይ፡ የሚሳል፣ ባለብፅዐት።
ተሳይ፣ የሚሳል፣ የሚሰነገል።
ተሳደረ፡ ተደራደረ።
ተሳደበ (አድራጊና፡ ተደራራጊ): ሰደበ፣ ተዋረፈ፣ ተናቀፈ፣ ተኳሰሰ፣ ተራገመ (ሕዝቅኤል ፴፭፡ ፲፪። ነህምያ ፱፡ ፳፯)። "ተሳደበን፡ ሰደበ፡ ማለት፡ የልማድ፡ ስሕተት፡ ነው።"
ተሳደበ፡ ተባለ፣ ተለያየ (ልክክ፡ ሳይል ቀረ) (ግድግዳው፣ ግንቡ)።
ተሳደደ፡ ተባረረ (፪ኛ ቆሮንቶስ ፩፡ ፮)።
ተሳዳቢ፡ የተሳደበ፣ የሚሳደብ፣ ሰዳቢ፣ ተራጋሚ (ዘሌዋውያን ፳፬፡ ፲፬። ፩ኛ ቆሮንቶስ ፩፡ ፲፩)።
ተሳዳቢነት፡ ተሳዳቢ መኾን።
ተሳዳቢዎች፡ ተሳዳቦች፣ የሚሳደቡ፣ ሰዳቢዎች (፩ኛ ቆሮንቶስ ፮፥ ፲)።
ተሳዳጅ፡ የሚሳደድ፣ የሚባረር፣ ተባራሪ።
ተሳገ፡ ተሳጋ፡ ተሻጠ፡ ተሰካ፡ ተጨመረ፡ ገባ።
ተሳገደ: ስግደትን ተቀባበለ።
ተሳፈረ፡ ተሰፋፈረ (ተዓየነ)፣ አቅጣጫ ላቅጣጫ ተቀመጠ፣ ተቀማመጠ (ሰራዊቱ)።
ተሳፈረ፡ ተሰፋፈረ፣ ተላካ፣ ተለካካ።
ተሳፈረ፡ እመርከብ፣ እባቡር፣ አይሮፕላን ላይ ወጣ ለመኼድ።
ተሳፋሪ (ሮች)፡ የሚሳፈር፣ በሠረገላ፣ በካሚዎን የሚቀመጥ።
ተሴሰየ: ጐረሠ፣ በላ፣ ተመገበ፣ ተቀለበ። (ጥሴ)
ተሤረ: ታደረ፡ ታደመ፡ ተመከረ፡ ተዶለተ፡ ተቈረጠ (ውሳኔ አገኘ ሤራው)።
ተስ (tes): (ቅድመ ቅጥያ) የተደራጊና የተደራራጊ ግስ ባዕድ መነሻ። ምሳሌ: ከረከረ፡ - ተስከረከረ፣ ነጎደ፡ - ተስተናገደ።
ተስለመለመ: ተጭለመለመ፣ ተዝለፈለፈ።
ተስማሚ: የሚስማማ፣ ተፋቃሪ።
ተስማማ: ተፋቀረ፣ ተዋዋደ፣ ጤና ኾነ፣ ጠቀመ፣ ረባ።
ተስረቀረቀ: ተንሠቀሠቀ፣ መላልሶ ሥቅቅ ብሎ ክፉኛ ካንዠት አለቀሰ።
ተስረቀረቀ: አለቀሰ፣ ረቀረቀ።
ተሥረገረገ (ሐዘዘ): ተዋጠ፡ ሰጠመ።
ተስቦ (ተስሒቦ): የበሽታ ስም፣ ሰውን የሚያሳብድ፣ ዐይንን የሚያፈርጥ፣ የራስ፣ የተቅማጥ፣ የትኵሳት ሕመም። "በአየር እየተሳበ ካንዱ ወደ ሌላው ስለሚጋባ ተስቦ ተባለ።" "(ግጥም)፡ የዚህ ዓለም ፍጥረት ኹሉ በሽተኛ፣ ተስቦ መጣና እንዲህ አረገኛ።"
ተስቦ: ክፉ በሽታ። እንዲሁም ሳበ።
ተስተስ (ተስታሳ): የተንተሰተሰ፣ የሚንተሰተስ፣ ፈሪ።
ተስተስ አለ: የፍራት ነገር ተናገረ።
ተስከረከረ: አደፈ፣ ከረከረ። (ከረከረን እይ)
ተስከረከረ: አደፈ፣ ደፈረሰ ወይም ዘቀጠ።
ተስገበገበ: ቸኰለ፣ ተጣደፈ። "ኹሉን ውጨው አለ።"
ተስገብጋቢ: የሚስገበገብ።
ተስጣጣ፡ ተገላበጠ፣ ተገላለጠ።
ተስፋ (ሰፈወ): አለኝታ ወደ ፊት አገኛለኹ የማለት ጽኑ እምነት ።
ተስፋ ማርያም: (የሰውና የቀበሌ ስም) በተጕለት ውስጥ ያለ አጥቢያ።
ተስፋ ሰጠ: ይሰኻል፣ ታገኛለኽ አለ።
ተስፋ ቆረጠ: ተበሳጨ፣ አላገኝም አለ።
ተስፋ አደረገ: ማግኘትን አመነ።
ተስፋ: (ከሰፈወ) አለኝታ፣ ወደፊት አገኛለኹ የማለት ጽኑ እምነት። (በቤተ ክርስቲያን) ስለ ሞቱ ሰዎች ለካህናት የሚዘጋጅ ባቡቴ።
ተስፋዬ: (የወንድና የሴት ስም) "የኔ ተስፋ" ማለት ነው። (በተስፋ) ባለኝታ፣ በተስፋ እየኖረ ደጅ የሚጠና። (ባል ብለኽ ባለን ተመልከት)
ተስፋፋ፡ ተመቻቸ፣ ተደላደለ፣ ተሸራሸ። "ተስፋፍቶ፡ ተቀምጧል፡ እንዲሉ።"
ተረ: ለፋ፡ ደከመ በሥራ።
"ዛሬ ስማትር ውዬ መጣኹ"።
ተረመመ (ተረመ): ዝም ጭጭ ተባለ።
ተረመሰ)፡ ተተራመሰ፣ ተሸበረ፣ ታወከ፣ ታመሰ፣ ተፋጀ፣ ተበጠበጠ፣ ተመሳቀለ።
ተረመሰ: ተወሸቀ፡ ረመሰ።
ተረመሰ: ተወሸቀ፣ ተነከረ፣ ተዘፈቀ፣ ተዘፈዘፈ፣ ራሰ፣ ቀዘቀዘ።
ተረመሰ: ታሸ፣ ተለወሰ፣ ተቦካ።
ተረመረመ: ተጠቀጠቀ፣ ተረገጠ፣ ተበራየ።
ተረመደ: ተነካ፣ ተረገጠ፣ ተጨቈነ፣ ተተመተመ፣ ተደመደመ (ከእንጀራ፣ ከውስጥ እግር ጋራ ተላከከ፣ ተጣበቀ፣ ዐብሮ ተነሣ መበያው እሾኹ)።
ተረመደደ: ተረመጠጠ።
ተረመጠ: ገባ፣ ተሸጐጠ፣ ተቀበረ፣ ተደፈነ፣ ተጠበሰ።
ተረመጠጠ: ተረገጠ፣ ተደፈጠጠ።
ተረማመደ: ተላለፈ፣ ተጋባ፣ ተሸጋገረ (በሽታው)።
ተረማማጅ: የሚረማመድ፣ ተላላፊ።
ተረማማጅነት: ተላላፊነት።
ተረማሽ: የሚረመስ።
ተረሰና: ኰሰተረ (አንድ ዘር ናቸው ከመዛወር በቀር ልዩነት የላቸውም)።
ተረሳ (ተሰብሐ): ተገለጠ፣ ተረዳ።
ተረሳ (ተረስዐ): ተዘነጋ፣ ተገደፈ፣ ታጣ፣ ጠፋ፣ ተተወ፣ ቀረ። "(ተረት)፡ በቃል ያለ ይረሳል በመጣፍ ያለ ይወረሳል።"
ተረሳ: ራሰ።
ተረሳሳ (ተራሐሰ): ተራጠበ።
ተረሳሳ (ተራስዐ): ተዘነጋጋ፣ ተጣ።
ተረሳረሰ: ተራራሰ።
ተረሳሺ: የሚረሳሳ።
ተረሳኝ: ተገለጠልኝ፣ ገባኝ። "(አልተሰባኝም)፡ አልተገለጠልኝም፡ አልገባኝም።"
ተረሳው: ተገለጠለት፣ ተረዳው፣ ገባው።
ተረረ፡ ቀጥታ ኾነ ።
ተረረ (ትግ) ፡ ጠና ጠነከረ በረታ ።
ተረረ: ሠነጠቀ ከፈለ ረደፈ ደረደረ ። (ጠረረ" ብለኸ "ጥራርን" አስተውል)።
ተረረ: ብለኸ ተሬን እይ።
ተረር አለ: ሥንጥቅ አለ።
ተረር: የቅሞ ፍሬ፣ ዘለላው በየረድፉ የሚንጠለጠል።
ተረሸተ: በዛ፣ ተጠጋጋ (ብቋያው)።
ተረሸነ: ተመታ፣ ተገደለ፣ ሞተ (ባረር)።
ተረሺ: የሚረሳ።
ተረቀረቀ: ተመታ፣ ተደበደበ (ዠርባው)።
ተረበ (ሰረበ): ፈሰስ፣ ወረደ።
ተረበ፡ ነደፈ ጠቅ አደረገ ወጋ ።
ተረበ: ቀለደ አላገጠ አፌዘ ።
ተረበረበ ፣ ተርከፈከፈ፡ ተረጫ።
ተረበረበ፣ ተሰደረ፡ ተደረደረ፡ ተደረበ፡ ተነባበረ፡ ተጣለ፡
ወደቀ፡ ተጋደመ። "የሰናክሬም፡ ሰራዊት፡ እንደ፡ ግንድ፡ ተረበረበ። "
ተረበኛ (ኞች): ተረብ ወዳድ፣ ባለ ተረብ።
ተረበከ: ተወዘፈ፣ ተረፈ፣ ተረፈቀ።
ተረበደ: ተቸኰለ።
ተረበደ: ተቸኰለ፣ ተለፈለፈ። ማስታወሻ: "ዐነጠሰ" እና "ዐነከሰን" እይ፡ አካኼዳቸው ከአረበደ ጋር አንድ ነው። በአስደራጊውና በተደራጊው “አ” መታጣቱን አስተውል።
ተረባ: ተባለ፣ ተነገረ (ርባታው)። ተረባ: ተጠቀመ፣ ጥቅም አገኘ (ሰውየው) (ኢሳይያስ ፴፡ ፭፡ ዮሐንስ ፲፪፡ ፲፱)። ተረቢ: የሚረባ፡ ተጠቃሚ። መረባት: መባል፣ መነገር፣ መጠቀም። መረቢያ: መጠቀሚያ።
ተረባረበ፡ ተራዳ፡ ተደራረበ፡ ተነባበረ።
ተረባረበ፡ ተራጨ።
ተረባራቢ፡ የሚረባረብ፡ ተነባባሪ።
ተረባባ: ተጠቃቀመ።
ተረባየ: ተረገጠ፣ ተረመረመ። "(ረበየ) ' ከዐረየ የወጣ ነውና፣ በረየን እይ። "
ተረብ: ቀልድ፣ ለግጥ፣ ፌዝ።
ተረተ: ኾነ፣ ተደረገ፣ ተቀበረ።
ተረተረ፡ ሠነጠቀ ፈነከተ (ዕንወትን ራስ ቅልን) ።
ተረተረ፡ አቀና ቀጥ አደረገ (ጐባጣን) ።
ተረተረ፡ ዕዳሪ አወጣ ጠጋ ፈለቀ ።
ተረተረ፡ ዘረዘረ ነጠለ” ። አራት ያለውን ይተረትራል" (ትርጓሜ ሕዝቅ፡ ፲፬፡ ፳፩) ።
ተረተረ (ተረረ) ፡ ስፌትን ጥምጥምንፈታ ለየ ክርን ሢርን መዘዘ በጠሰ (ተለተለን" እይ) ።
ተረተር (ሮች): የምድር ዠርባ፣ የኰረብታ፣ የተራራ መንገድ፣ መንደርደሪያ።
ተረተርማ: የተረተር፣ ባለተረተር፣ ተረተራም ስፍራ።
ተረተኛ: ዝኒ ከማሁ፣ የተረት ሰው።
ተረታ: ተሸነፈ፣ ድል ኾነ።
ተረታም: ባለተረት፣ የተረት ጌታ፣ ተረት ዐዋቂ፣ ተረተ ብዙ።
ተረታታ: ተበያየነ፣ ተሸናነፈ፣ ረቺና ተረቺ ተኳዃነ፣ የመርታትን ብድር ተመላለሰ።
ተረት (ቶች): ልብ ወለድ፣ ፈጠራ ነገር (ሉቃስ ፳፬፡ ፲፩)።
ተረት፡ በምሳሌ፡ ዜማ፡ በሃሌ፡ እንዲሉ።
ተረት፡ ተረት፡ የላም፡ በረት፡ የተረት መቅድም፣ ከተረት በፊት የሚባል፣ የሚነገር።
ተረት (ቶች) ፡ ልብ ወለድ ፈጠራ ነገር (ሉቃ፡ ፳፬፡ ፲፩) ። (ተረት በምሳሌ ዜማ በሃሌ" እንዲሉ)።
ተረት: "ምንም ቢጠም መንገድ፣ ምንም ቢከፋ ዘመድ። "
ተረት: ስለ ያለፈ ወይም ስለ ጊዜ ነገር እውነት አስመስሎ ማውጋት።
ተረቺ: የሚረታ፣ የሚሸነፍ።
ተረነቀ: አነሰ፡ ዐጠረ፡ ተቈነ።
ተረንተራ (ተረን ተሪ) ፡ ማፉዳቦርሳ ኩፋዳ የገንዘብ መያዣ ። በግእዝ "ቍናምት" ይባላል ።
ተረኛ (ኞች): ዘቡ፣ ሥራው የርሱ የኾነ፣ ባለተራ።
ተረከ: አወጋ አወራ ያለፈ ነገርን ኣሳሰበ (እንዲህ ነበር" አለ) ።
ተረከመ - ጠረቀመ) ፡ ተተራከመ፡ ተሰበሰበ ተጠራቀመ ።
ተረከመ: ትርንጎ ።
ተረከሰ: ቀለሰ አጐበጠ ።
ተረከረከ: ዕጥፍ ዘርጋ፣ እለተወላገደ።
ተረከበ: ተቀበለ፡ እጅ አደረገ ።
ተረከበ: ካንዱ ወደ ሌላው ዐለፈ፣ ተሰጠ። "(እንደ ተረከበው)፡ እንደ ተቻለው፡ እንዳቅሙ፡ እንደ መጠኑ።"
ተረከከ: ጠረቀቀ ሠነጠቀ ፈነከተ ።
ተረከዘ (ዐረ፡ ረከዘ፡ አቆመ፡ የብስ፡ ረገጠ): ቀዘፈ ወደ ወደብ መርከብንመራ ።
ተረከዘ፡ ሎሚ: ተረከዙ ሎሚ የሚመስል ጫማው ንትብ ፈለግ ሥንጥቅ የሌለበት ሰው ።
ተረከዘ፡ ክት፡ እግሯ፡ የሚያምር፡ ሴት፡ ተረከዘ፡ ዐጪር።
ተረከዙ፡ ሎሚ፡ የሚመስል፡ ጫማው፡ ንትብ፡ ፈለግ፡ ሥንጥቅ፡ የሌለበት፡ ሰው:
ተረከዝ (ዞች): የእግር ኋለኛ ጫፍ፣ መርገጫ፣ መቆሚያ፣ ሰኰና (ግብረ ሐዋርያት ፫፡ ፯)።
ተረካበ: ተቀበለ፣ እጅ አደረገ።
ተረካቢ: የተረከበ፣ የሚረካብ፣ ተቀባይ።
ተረካቢነት: ተረካቢ መኾን፣ ተቀባይነት።
ተረካከሰ: ተሰጣጠ፣ ተቀባበለ።
ተረካካቢ: የተረካከበ፣ የሚረካከብ፣ ተቀባይ።
ተረኰሰ: ሰበረ ኰሰተረ ኣለማ መብራትን "።
ተረወ: ደረሰ መጣ ።
ተረዘዘ: ተዘጋ፣ ተቈለፈ፣ በቤት ተቀመጠ። "የተያዘ የተረዘ እንዲሉ።"
ተረደፈ: ተሰደረ፣ ተደረደረ፣ ተራ መታ።
ተረዳ: ተጠና፣ ታወቀ።
ተረዳ: ታግዞ ተደገፈ።
ተረዳ: የዘመዱን ሞት ሰማ። "አጥብቆ ጠያቂ የናቱን ሞት ይረዳል።"
ተረዳ: ፈጽሞ ዐወቀ፣ ገባው (ትምርቱ፣ ነገሩ)። "አልተረዳውም፡ አልገባኝም።"
ተረዳጂ: የተረዳዳ፣ የሚረዳዳ፣ ተደጋጋፊ።
ተረጂ: የሚረዳ (ሽማግሌ)፣ መርዶ ሰሚ (ጠላት የመጣበት ሕዝብ)።
ተረገ: ሠረግ ተንቀጠቀጠ ።
ተረገመ ፣ (ተረግመ)፣ ተለየ፡ ተካደ፡ ርጉም፡ ተባለ፡ በሌላ፡ ወይም፡
በገዛ፡ እፉ፡ (ዘዳግም ፳፩፡ ፳፫። ፩ኛ ሳሙኤል፡ ፳፭፡ ፳፪። ማርቆስ ፲፬፡ ፸፩)።
ተረገረገ: ተንቀጠቀጠ፣ ተነቀነቀ፣ ተወዘወዘ (ግፍና ጫፉ)።
ተረገረገ: ታጨቀ፣ መላ ተጠቀጠቀ፣ ተጐደጐደ፣ ግጥም እለ፣ በዛ።
ተረገረገ: ኰራ፣ ተጓደደ፣ ተደገ።
ተረገዘ ፣ ተፀነሰ፡ በሆድ፡ ቀረ፡ ተቋጠረ፡ ዘሩ፡ ደሙ፡
ልጁ።
"(ተረት) የተረቱ፡ በሆድ፡ የዘለ ፣በለምድ። "
ተረገደ፡ ተጨፈረ፡ ተዘለለ፡ ተረገጠ፡ ተሸበሸበ።
ተረገጠ፡ (ተረግፀ)፣ በርግ፵፡ ተመታ፡ ተደበደበ፡ (ነገሥት፡ ፱፡ ፵፫። ኢዮብ ፭፡ ፬። ኢሳይያስ ፲፬፡ ፲፱። ሉቃስ ፰፡ ፳)። "ረገጠ፡ በማለት፡ ፈንታ፡ ተረገጠ፡ ይላል፡
ስሕተት ነው። "
"መዓርገ፡ መላእክትን፡
እንደ፡ ግማ፡ ተረግጦ፡ እንዲሉ፡ መተርጕማን። "
ተረገጠ፡ ተፈረ፡ ተዘለለ፡ ተሸበሸበ።
ተረገጠ፡ እውነት፡ ኾነ።
ተረገጠች፡፡ ተመታች፡ ተሰረረች፡ ፈረሷ፡ አህያዋ።
ተረጋሚ ፣ የሚረገም፡ የሚካድ።
ተረጋገመ፡ ተካካደ፡ ተለያየ፡ እቀብርኸ፡ አልደርስም፡
እቀብሬ፡ አትድረስ፡ ተባባለ።
ተረጋገጠ፡ ርግጥ፡ (ኾነ)፡ ተኳዃኑ፡ ተደላደለ።
ተረጋገጠ፡ በእግር፡ ተቃጠቀ፡ ተረማረመ፡ (ሉቃስ ፲፪ ፣ ፩)።
ተረጋጋ ፣ ተጽናና፡ በረታ፡ ታገሠ፡ ቻለ፡ (ተደራጊ)።
ተረጋጋ፡ ተጸናና፡ ተበረታታ፡ (ተደራጊ)።
ተረጋጭ፡ የሚረገጥ፡ ጭቃ።
ተረግራጊ፡ የሚረገረግ፣ የሚወዘወዝ (ኵሩ ተደጋጊ" - "ኩሩ ወይም ተደጋጋሚ) ።
ተረጐመ: ከቋንቋ ወደቋንቋ ገለበጠ መለሰ ፈታ ገለጠ አስረዳ (መጽሐፍ አሰማ ስለ ምን ነገረ አንድም ኣለ ዘረዘረ)።
ተረጠበ: ርጥባን ተቀበለ፣ ተረዳ፣ ታገዘ፣ ተተለተ (ሰው)።
ተረጠበ: ተሰጠ (ገንዘቡ)።
ተረጠጠ: ታመቀ፣ ተጨቈነ፣ ተቀመጠ፣ ተወዘፈ።
ተረጨ (ተረቅየ): ተፈነጠቀ፣ ተበተነ፣ ተነዛ፣ ተወረወረ (ጠበሉ፣ ጠለሸቱ) (ኢዮብ ፵፩፡ ፲፩)። "የበሽተኛው ፊት በጠበል ተመታ፣ የኀጢፊተኛው ሰውነት የጸሎት ውሃ ዐረፈበት (ዕዝራ ፲፡ ፳፪)።"
ተረጪ (ተረቃዪ): የሚረጭ (ውሃ፣ ሽቱ፣ ራስ፣ ዕቃ)።
ተረፈ፡ በዛ ከልክ ወለፈ ከመጠን በለ ። (ከሀብታም ይተርፈዋል" እንዲሉ - "ተረት" - ላሳር የጣፈው ቢነግድ አይተርፈው) ።
ተረፈ፡ ብንያም: የብንያም ነገድ ቅሬታ፣ የሞት ትራፊ።
ተረፈ፡ ኤርምያስ: የኤርምያስ መጽሐፍ፣ ደረቅ ትንቢት የሚናገር (ማቴዎስ ፳፯ ፥፱)።
ተረፈ (ተርፈ) ፡ ዳነ ቀረ ተፈታተፈወሰ ተተወ ።
ተረፈ: መሧዕት አኰቴት።
ተረፈሰ: አብዝቶ ዘግነ ዐፈሠ ተርፎ እስኪፈስ ቃመ (ትፈረን" እይ) ።
ተረፈስ፡ ተርፋሳ፡ ዝኒ፡ ከማሁ።
ተረፈረፈ: ተነሰነሰ፣ ተረበረበ፣ ተጐዘጐዘ።
ተረፈረፈ: ተጣለ፣ ወደቀ፣ ተለሸለሸ፣ ተኛ፣ ተጋደመ (የቍስለኛ፣ የበሽተኛ)።
ተረፈቀ: ተቀመጠ፣ ተወዘፈ፣ ተዘፈዘፈ፣ ተጨቈነ፣ ወደ ታች ተባለ።
ተረፈጠ: ተረፈቀ፣ ተቀመጠ።
ተረፈፈ - ደረበበ) ፡ አንተረፈፈ፡ መላ ቅዝ አደረገ፡ አንደረበበ ። አንተረፈፈ፡ የፈሳሽ ። አንደረበበ፡ የደረቅ ነው ።
ተረፋ) ተንተራፋ፡ ተሰበረ ተፈለቀ ተጨማለቀ (ፈሰሰ ውሃው ደሙ) ።
ተረፋቂ፡ ሥራ ፈት።
ተረፋቂ: የሚረፈቅ፣ ተወዛፊ።
ተረፍ፡ ትራፍ፡ ትሩፍ፡ ትሩፋን፡ ትሩፋት: የግእዝ ናቸው።
ተረፍራፊ: የሚረፈረፍ (ሣር፣ ቅጠል፣ ሽቶ)።
ተራ (ተራቀየ): ተፈናጠቀ፣ ተባተነ።
ተራ፡ መታ: አተረተረ፣ ተሰደረ፣ ተደረደረ።
ተራ፡ ሰው፡ አልባሌ:
ተራ፡ ረድፍ፡ ፊና፡ ወረፋ: (ዘፀአት ፳፰፡ ፲፱፡ ፳)።
ተራ፡ ቍጥር: ፩ኛ፡ ፪ኛ፡ እየተባለ የሚጻፍ።
ተራ፡ የሸቀጥ፡ መደብ፡ መደብር፡ ስፍራ: (እኸል ተራ በግ ተራ ጌሾ ተራ አጣና ተራ ማእዘን ተራ ሰንጋ ተራ" እንዲሉ) ።
ተራ: ረድፍ (ከግስ ተረረ የተገኘ)።
ተራመመ: ተጠረገ፣ ተፈገፈገ፣ ታጠበ (ጠዳ)።
ተራመደ: ዐለፈ፣ ኼደ፣ ሠገረ፣ ተሻገረ፣ ገሰገሠ፣ ፈጠነ። (ተደራራጊ ሲመስል በተደራጊነት መፈታቱን አስተውል)።
ተራማሚ: የሚራመም፣ ተፈግፋጊ።
ተራማጅ (ጆች): የተራመደ፣ የሚራመድ፣ ኻያጅ፣ ግሥጋሽ፣ ሠጋር፣ ፈጣን።
ተራማጅነት: ተራማጅ መኾን፣ ፈጣንነት።
ተራረመ (ተሓረመ): ዕርም ተባባለ፡ ተለያየ፡ ተራራቀ (ተራረቀ)።
ተራረቀ (ተዓረቀ): ተጐናበሰ፡ ተሰማማ፡ ተወዳጀ፡ ተፈቃቀረ፡ ተሳሳመ (መሰማማት ወይም መፈቃቀር)።
ተራረፈ (ተዓረፈ): ሸክምን ተቀባበለ፡ ተረዳዳ፡ ተጋገዘ (ሸክም መረዳዳት)።
ተራረፈ: በበቅሎ የተቀመጠው በእግሩ ሲኼድ፡ እግረኛው ተቀመጠ (መጋራት)።
ተራሪ: የተረረ፣ የሚተርር፣ ሠንጣቂ፣ ደርዳሪ።
ተራራ: ረዥምና ከፍተኛ ዐምባ፣ ብርቱ ስፍራ፣ የምድር ራስ።
ተራራማ: ተራራ ያለበት፣ የበዛበት አገር፣ ባለተራራ።
ተራራም፡ ዝኒ፡ ከማሁ።
ተራራቀ (ተራሐቀ): ተነጣጠለ፣ ተለያየ።
ተራራቂ (ተራሓቂ): የሚራራቅ፣ የሚለያይ።
ተራሮች፡ ዐምቦች: (ዘፍጥረት ፬፡ ፭)።
ተራቀቀ: ተጠበበ፣ ፈለሰፈ፣ ብልኅ ኾነ፣ ጥልቅ ነገር ተናገረ (ረቂቅ)፣ ተኳዃነ።
ተራቃቂ: የተራቀቀ፣ የሚራቀቅ።
ተራቃቂነት: ተጠባቢነት።
ተራቈተ (ተዐርቀ): ተገፈፈ፡ ታረዘ፡ ባዶ ኾነ (ተጋፈፈ) (ራቁቱን መሆን)።
ተራቈተ እና አራቈተ ተደራራጊና አደራራጊ ሲመስል፣ በተደራጊነትና በአድራጊነት መፈታቱን አስተውል (የቃላት አጠቃቀም ማብራሪያ)።
ተራቈተ: ታረዘ፡ ዐረቀ ።
ተራቋች: የሚራቈት፡ የሚታረዝ (ራቁቱን የሚሆን)።
ተራበ: ባዶ ኾነ፣ ችጋር ያዘው፣ ምግብ ሻ፣ ፈለገ (ማቴዎስ ፬፡ ፪፡ ፳፩፡ ፲፰)።
ተራቢ: የሚራብ።
ተራቢ: የተረበ፣ የሚተርብ፣ ቀልደኛ፣ አላጋጭ፣ ፌዘኛ።
ተራባ (ተራብሐ): ተዋለደ፣ ተባዛ (የረባ፣ የራበ)፡ ተደራራጊና ተደራጊ ኀላፊ ትንቢት በጽፈት ሲገጥሙ፡ 'ይራባሉ' (ይትራብሑ ሐለዉ)፡ 'ይራባሉ' (ይርኅቡ ሐለዉ) ይላል። "ባንደኛው 'ራ' ን ባን፣ በኹለተኛው 'ራ' ን ብቻ አጥብቅ። " መራባት: መዋለድ፣ መባዛት።
ተራተረ: ፈታታ፣ ለያየ፣ ሠነጣጠቀ፣ ፈነካከሉ።
ተራታ (ተራትዐ): ተቃና (ነገሩ)።
ተራች (ቾች): የተረተ፣ የሚተርት (ጥሳ መሳይ)።
ተራከሰ (ረከሰ): ተነካካ፣ ተዳደፈ፣ ርኩስ ተኳዃነ፣ ተናናቀ።
ተራከበ (ተከተበ): ተጋባ፣ ተመሳቀለ።
ተራከበ: ተቀራመተ፣ ተናቀ፣ ተሠናጠቀ፣ ተካፈለ፣ ተተናተነ፣ ተሻማ፣ ተቃማ። "ዥቦች ሌሊት በዱር አንድ እህያ አገኙና ተራከቡት።"
ተራከበ: ተናኘ፣ ተጋጠመ፣ ተዳረሰ።
ተራኪ (ዎች): የተረከ፣ የሚተርክ፣ ወግ ዐዋቂ።
ተራኰተ: ተጣላ፣ ተከራከረ፣ ተሟገተ። "እከሌና እከሌ በዳኛ ላይ ሲራኰቱ ዋሉ።"
ተራኰተ: ተፋተ፣ ተናነቀ፣ ተጋፋ፣ ታገለ። "ዥቦች ጥንብ ስላገኙ ዛሬ ሌሊት ሲራኮቱ፣ ሀደሩ።"
ተራኳች: የተራኰተ፣ የሚራኰት፣ ተከራካሪ፣ ታጋይ።
ተራወጠ: ተሯሯጠ፣ ተባረረ፣ ተሽቀዳደመ።
ተራዋጭ: ተሯሯጭ፣ የሚራወጥ፣ የሚሯሯጥ፣ ተባራሪ፣ ተሽቀዳዳሚ። "ድፍርስ ቅራሪ።"
ተራዘመ: ተባለጠ፣ ተበላለጠ፣ ተራራቀ፣ ተባዛ፣ ተበራከተ።
ተራዛሚ: የተራዘመ፣ የሚራዘም፣ የሩቁን የሚያቀርብ መነጽር፣ በሩቅ የሚመታ መድፍ፣ አሸጋጋሪ።
ተራደፈ: ተከታተለ፣ ተቀጣጠለ፣ ቅደም ተከተል ተኳዃነ፣ ተደራረበ።
ተራዳ (ሠርዌ): ተርክሓ (የድንኳን ምሰሶ፣ ዋልታ፣ ደጋፊ፣ ተሸካሚ)።
ተራዳ፡
የድንኳን ምሰሶ፡ ረዳ ።
ተራዳ: ተረዳዳ፣ ተቀባበለ፣ ተፈራረቀ፣ ተራረፈ፣ ተጋዘ፣ ተደጋገፈ።
ተራድኦ: መራዳት (ግእዝ)።
ተራዶች: ፫ ወይም ፫ የድንኳን ምሰሶዎች።
ተራገመ ፣ ረገሙ፡ (ምሳሌ ፳፯፡ ፲፬)። "ተራገመ፡ ተደራራጊ፡ ሲኾን፡ አድራጊ፡ መኾኑ፡
በልማድ፡ ነው፡ እንጂ፡ በቋንቋው፡ ሕግ፡ አይዶለም። "
ተራገመ ፣ ተሳደበ።
ተራገበ፡ ተጓረበ፡ ነፋስ፡ ተሰጣጠ፡ ተቀባበለ፡ ተናፈሰ።
ተራገጠ፣ (ተራገፀ)፡ በርግ ፣ ተማታ፡ ተላፋ፡ ተጫወተ፡ ተዛለለ። "(ተረት)፣ አህያ፡ ላህያ፡ ቢራቱጥ፡ ጥርስ፡ አይሳበር። "
ተራገጠ፡ ረገጠ፡ (አድራጊ)።
ተራገጠ፡ ተዳካ፡ ተዋሰነ፡ ተካለለ፡ (ተደራራቢ)።
ተራገፈ (ረገፈ): ተፈታ፣ ወለቀ፣ ወረደ (ኮርቻው፣ ልጓሙ፣ ጭነቱ)።
ተራገፈ: በነነ (ዐቧራው፣ ዱቄቱ)።
ተራጋ ፣ ተጻና፡ ተበራታ።
ተራጋሚ፡ ረጋሚ፡ የሚራገም፡ ጥቍር፡ ምላስ።
ተራጋጭ (ጮች)፡ የሚራገጥ፡ ከብት።
ተራጋጭ፡ ረጋጭ።
ተራጋጭነት፡ ተራጋጭ፡ መኾን።
ተራጋፊ: የሚራገፍ (ልብስ፣ የጋማ ከብት መጫሚያ)።
ተራጠበ: ተረጣጠበ፣ ተራራሰ፣ ተሰጣጠ፣ ተቀባበለ።
ተራፊ: የሚተርፍ፣ የሚቀር፣ ዳኝ፣ ቀሪ፣ ተረፍ፣ ቅሬታ።
ተሬ: ተራማ፣ ተረረ።
ተሬ: ተራዊ፣ ተራማ፣ የተራ (አንድ የወንድ ልጅ ሽሩባ በራስ አማካይ ከግንባር እስከ ማዥራት ያለ ዕሽም ተረተር መስሎ የሚታይ)።
ተሬ: ታናሽ ጕባ፣ ቍልልታ።
ተር አለ: ቀጥ አለ።
ተር አደረገ: ቀጥ አደረገ።
ተር: ቀጥ።
ተር: ቀጥ ተረረ።
ተርመሰመሰ: ተንቀሳቀሰ፣ ተነቃነቀ፣ ተላወሰ።
ተርመስማሽ: የሚርመሰመስ፣ ተንቀሳቃሽ፣ ተላዋሽ።
ተርመጠመጠ፡
ረመጥ ላይ ተንደባለለ፡ ተኵለፈለፈ፡ ተልከሰከሰ ሥጋው ።
ተርመጥማጭ: የሚርመጠመጥ፣ ተልከሰካሽ።
ተርሞጠሞጠ: ዝኒ ከማሁ።
ተርሴስ: በእስያ ክፍል ያለ አገር (መዝ፡ ፸፪፡ ፲)።
ተርበተበተ፡ ተንተባተበ፡ ተንቀጠቀጠ።
ተርበትባች፡ የሚርበተበት።
ተርበደበደ: ፈራ፣ ተንበደበደ፣ ተንቀጠቀጠ።
ተርበድባጅ: የሚርበደበድ።
ተርብ (ቦች):የተንቀሳቃሽ ስም፣ በመርዙ የሚነድፍ፣ በክንፉ የሚበር (የውሻ ሳንጃን እይ)።
ተርብ: ንብ።
ተርቦ: ጦሙን ውሎ ዐድሮ ሰንብቶ። "አቶ እከሌ ተርቦ ተጠምቶ ቤት ሠራ። "
ተርታ ሰው: ሹመት ማዕርግ የሌለው ተራ ሰው።
ተርታ ነገር: ቁም ነገር ያልኾነ ጕዳይ።
ተርታ: መናኛ፣ ተረረ።
ተርታ: መናኛ፣ ትሑት፣ ተራ፣ መደዳ (፩ኛ ነገሥት ▪ ፮፡ ፴፯። ፯፡ ፲፪። ዕብራውያን ፱፡ ፭)።
ተርታሪ: የተረተረ፣ የሚተረትር፣ ሠንጣቂ፣ ፈንካች፣ ጨፍላቂ።
ተርከፈከፈ: ተረጨ፣ ተረበረበ፣ ተንጠባጠበ።
ተርከፍካፊ: የሚርከፈከፍ (ውሃ፣ ሽቱ፣ መድኀኒት)።
ተርካሳ: ቀላሳ፣ ጐባጣ፣ ጕብር።
ተርካኪ: የተረከከ፣ የሚተረክክ፣ ጠርቃቂ፣ ሠንጣቂ፣ ፈንካች።
ተርገረጊ: የሚረገረግ፣ የሚወዘወዝ፣ ኵሩ፣ ተደጋጊ።
ተርገበገበ፡ ተንዘፈዘፈ፡ ተወዘወዘ፡ ተነቀነቀ፡ ተለማመጠ ልምጥልምጥ፡ ዕጥፍ፡ ዘርጋ፡ ክፍት፡ ክድን፡
አለ።
ተርገብጋቢ፡ የሚርገበገብ፡ ተለማማጭ።
ተርገደገደ፡ ተንደገደ፡ ተፍገመገመ።
ተርገድጋጅ፡ የሚርገደገድ።
ተርገፈገፈ: ተወዘወዘ (ሥጋው)።
ተርጓሚ (ሞች):የተረጐመ፣ የሚተረጕም፣ ሊቅ (የብሉይ፣ የሐዲስ፣ የሊቃውንት (ያቡ ጕም ሻህር)፣ የመጽሐፈ መነኮሳት መምር)።
ተርጓሚ: ደርጋሚ (ንባብን በትርጓሜ የሚያስተባብል) (፪ኛ ጴጥሮስ፡ ፫፡ ፲፯)።
ተርፋ አለ: ደነገጠ፣ ተከፈለ፣ ዘለለ፣ ፈሰሰ።
ተርፋሽ: የተረፈሰ፣ የሚተረፍስ፣ ዘጋኝ፣ ቃሚ።
ተሸ: ተተኰሰ፣ ተቀቀለበት፣ ተጋገረበት፡ ሥራ ለመደ (ሸክላው)።
ተሸለለ: ተሸለተ፣ ተሸነገለ።
ተሸለለ: ተሸደሸደ፣ ተወሰወሰ፣ ተቶረበ፣ ተያያዘ፣ ተጋጠመ፣ ተሰፋ።
ተሸለለ: ኾነ፣ ተደረገ፣ ተባለ (ስለላው)።
ተሸለመ: ሽልማት ተቀበለ፣ ለበስ።
ተሸለመ: ተሣለ፣ ተነቀሰ፣ ተመሰለ፣ ተጌጠ፣ ተዥጐረጐረ።
ተሸለቀቀ: ተቀደደ፣ ተላጠ፣ ተገፈፈ፣ ከቈዳ ከቅርፊት ውስጥ ወጣ፣ ተለየ።
ተሸለቀቀ: ጠበበ፣ ቀጠነ።
ተሸለተ (ተቀርፀ): ተቀረፀ፣ ተቈረጠ (በጉ) (ዘዳግም ፲፰፡ ፬። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ፬፡ ፪)።
ተሸለተ: ተጠረበ፣ ተላገ፣ ሾለ።
ተሸለገ: ታሰበ፣ ተለካ፣ ተሰላ፣ ተገመተ፣ ተገመገመ።
ተሸለፈ: ሣሣ፣ ቀለለ።
ተሸለፈ: ተታለለ፣ ተሸነገለ።
ተሸለፈፈ: ተለፈፈ፣ ተላከ።
ተሸላለመ: ተጊያጊያጠ፣ ጌጥ ተቀባበለ፣ የመሸለም ብድር ተከፋፈለ።
ተሸላለገ: ተጎማመተ፣ ተገማገመ።
ተሸላላሚ: የሚሸላለም፣ የሚጊያጊያጥ።
ተሸላሚ: የሚሸለም።
ተሸላች: የሚሸለት፣ የሚቀረፅ፣ ተቈራጭ።
ተሸላጊ: የሚሸለግ፣ ተገምጋሚ።
ተሸመሸመ: ተከረተፈ፣ ተፈ፣ ተሸረከተ።
ተሸመቀ: ተደፈጠ።
ተሸመቀቀ: ተሳበ፣ ዐጠረ፣ ተጨመደደ፣ ተጠጋ፣ ጠበበ።
ተሸመተ: ተገዛ፣ ተሸጠ፣ ተለወጠ፣ ለገዢ ተሰጠ።
ተሸመተረ: ተሸነቈጠ፣ ተገረፈ።
ተሸመጠጠ: ተሮጠ፣ ተጋለበ።
ተሸመጠጠ: ተዠመዥ፣ ተፈተለ፣ ተሠራ (እሸቱ፣ ፈትሉ፣ ሽሩባው)።
ተሸመጠጠ: ተጌጠ፣ ተሸለመ፣ ተደጐሰ።
ተሸመጠጠ: ተጠጣ፣ ተለጠ።
ተሸመጠጠ: ታሰለ፣ ተዋሸ።
ተሸመጠጠ: ታጠረ፣ ተዋሰበ።
ተሸማመቀ: ተደፋፈጠ።
ተሸማመተ: ተገዛዛ፣ ተሻሻ፣ ተለዋወጠ።
ተሸማቀቀ: ተሳስበ፣ ተጣበበ፣ ተጨማደደ።
ተሸማች: የሚሸመት፣ የሚገዛ፣ የሚሼጥ።
ተሸረሞጠ: ተሠረጓጐደ።
ተሸረሸረ: ተበረበረ፣ ፈረሰ፣ ተነደለ።
ተሸረበ: ተደበለ፣ ተጠሞረ፣ ተደረበ፣ ተታታ።
ተሸረከተ: ተቀደደ፣ ተዘረከተ።
ተሸረከተ: እንዳገኘ ተናገረ።
ተሸረካከተ: ተቀዳደደ፣ ተዘረካከተ።
ተሸረደደ: ታማ፣ ተነቀፈ፣ ተለገጠ፣ ተሾፈ።
ተሸረጠ: ተገለደመ።
ተሸረፈ: ተመነዘረ፣ ተዘረዘረ፣ በዛ።
ተሸረፈ: ተሰበረ፣ ተቈረሰ።
ተሸረፈ: ተነቀለ፣ ተመዘዘ።
ተሸራሞጠ: ፈሳ፣ ተጓደለ፣ ሸሸ፣ ተሠረጐደ፣ ወጣ፣ ገባ፣ ኾነ።
ተሸራረፈ: ተሰባበረ፣ ተቈራረሰ።
ተሸራሸረ: ተጓደለ፣ ተቃለለ፣ ተፈጋፈገ (የምግብ፣ የሰው)።
ተሸራሽቶ: ተደላድሎ፣ ተመቻችቶ። "ተሸራሽቶ ተቀመጠ፣ ቆመ እንዲሉ።"
ተሸራከተ: ተቃደደ፣ ተዘራከተ።
ተሸራጭ: የሚሸራሞጥ።
ተሸራፊ: የሚሸረፍ፣ የሚመነዘር (ሸክላ፣ ሸራፋ፣ ሰባራ)። "ጥርሰ ሸራፋ፣ አፈ ሸራፋ እንዲሉ።"
ተሸርሻሪ: የሚሸረሸር፣ ቦረቦር።
ተሸርጦለታል: ገለል ብሎለታል።
ተሸሸ: ኾነ፣ ተደረገ (ሽሽቱ)።
ተሸሸገ: ተደፈነ፣ ታባ፣ ተሰወረ፣ ተደበቀ (ዘፍጥረት ፫፡ ፰፡ ፲። ፩ኛ ሳሙኤል፡ ፲፡ ፳፪። ምሳሌ ፳፪፡ ፫)።
ተሸሻጊ: የሚሸሸግ፣ ተደባቂ።
ተሸቀጠ: ተሸጠ፣ ተለወጠ፣ ተገዛ።
ተሸቈረረ: ተጠየፈ፣ ተሠቀቀ።
ተሸበለለ: ተጠቀለለ።
ተሸበለቀ: ሾለ፣ ገባ፣ ተቀረቀረ፣ በሽብልቅ ተወጋ።
ተሸበሸበ: ተሸነሸነ፣ ተጠጋጋ፣ ተቀራረበ።
ተሸበበ: ተጠለፈ፣ ታሰረ (በቅሎው ፈረሱ አህያው ግመሉ ታበተ ሽቢያው ለኮው) ።
ተሸባ: ተበጀ፣ ተለጠፈ፣ ታሰረ።
ተሸባለለ: ተጠቃለለ።
ተሸባቢ: የሚሸበብ፣ የሚታበት (ከብት)።
ተሸብሻቢ: የሚሸበሸብ (ልብስ)።
ተሸተረ: ተሸለመ፣ ተጌጠ፣ ተንቈጠቈጠ።
ተሸተተ: ካፍንጫ ገባ፣ ተሳበ፣ ተማገ።
ተሸታሪ: የሚሸተር።
ተሸነ: ጭርቅ አለ፣ ተለቀቀ፣ ተንፎከፎክ፣ ወረደ፣ ፈሰሰ፣ ተንዣረረ።
ተሸነሸነ: ተሸበሸበ፣ ተጠጋጋ (በመቀነት፣ በክር)፣ ተሠነጠቀ (በጥልቆ)።
ተሸነቀረ: ተሰበሰበ፣ ታጠፈ፣ ተቀነፈ፣ ተሸጐጠ።
ተሸነቈረ: ተበሳ፣ ተነደለ፣ ተቀደደ።
ተሸነቈጠ: ተገረፈ፣ ተሸመተረ፣ ሾጥ ተደረገ፣ ተመታ።
ተሸነቋቈረ: ተበሳሳ፣ ተቀዳደደ።
ተሸነተረ: ተበጣ፣ ተቀደደ።
ተሸነታተረ: ተበጣጣ።
ተሸነከፈ: ታጠፈ፣ ተኰረተመ፣ ታሰሪ።
ተሸነጠ: ተበለተ፣ ተነጠለ፣ ተለየ፣ ወጣ።
ተሸነፈ: ድል ኾነ፣ ተረታ፣ ተመታ፣ ተሻረ፣ ታከተ፣ ደከመ።
ተሸነፈጠ: ታጠፈ፣ ተዘቀዘቀ።
ተሸናቈጠ: ተጋረፈ፣ ተማታ።
ተሸናነፈ: ድል ተነሣሣ፣ ተረታታ።
ተሸናፊ: የሚሸነፍ፣ ድል ዃኝ።
ተሸንቋሪ: የሚሸነቈር፣ የሚበሳ፣ ተበሺ።
ተሸንቶ ዐደረ: ጥቂት መንገድ ኼዶ ሌሊቱን በውጭ አሳለፈ።
ተሸንካፊ: የሚሸነከፍ (ዐመለኛ ከብት)።
ተሸኘ: ከሰው ጋራ ዐብሮ ኼደ።
ተሸኚ: የሚሸኝ (መንገደኛ)።
ተሸኛኘ: ተሰነባበተ።
ተሸከመ: ሸክም ኾነ፣ ተያዘ፣ ታዘለ። "ልማዱ ግን አድራጊነት ነው።"
ተሸከመ: ያዘ። "(ዘለ፡ ተነ፡ ተደበለለ፡ ቻለ) (፬ኛ ነገሥት፡ ፰፡ ፬። ማቴዎስ ፲፩፡ ፳፱። ሉቃስ ፪ - ፳፰)።"
ተሸከሸከ: ተሸደደ፣ ተዘረዘረ ተዘከዘከ።
ተሸከሸከ: ተወቀጠ።
ተሸከፈ: ተተፈተፈ፣ ጠቀነ።
ተሸካሚ: የተሸከመ የሚሸከም (፩ኛ ሳሙኤል፡ ፴፩፡ ፬፡ ፭። ነህምያ ፬፡ ፲፯)። "አላህ፡ ተሸካሚ፡ ብለምነው፡ ሸክም፡ አዘዘብኝ፡(ቃልቻ)።"
ተሸካሚነት: ተሸካሚ መኾን።
ተሸካከመ: ሸክምን ለማንሣት ተጋዝ፣ ተረዳዳ፣ የማሸከም ብድር ተከፋፈለ፣ እንኮኮ ተባባለ፣ ተዛዘለ።
ተሸካከረ: ተቀያየመ።
ተሸክሻኪ: የሚሸከሸክ (የገብስ ቈሎ)።
ተሸያየተ: ዕጣ ተጣጣለ።
ተሸያጭ: የሚሼጥ፣ የሚለወጥ፣ ተለዋጭ።
ተሸደሸደ: ተወሰወሰ፣ ተሸከሸከ፣ ተሸለለ።
ተሸዳሸደ: ተወሳወሰ።
ተሸጋሸገ: ተፈጋፈገ፣ ተራራቀ ወይም ተጠጋጋ፣ ተቀራረበ።
ተሸጋሻጊ: የሚሸጋሸግ፣ ተራራቂ፣ ተቀራራቢ።
ተሸጋገረ: ካንዱ ግንብ ጫፍ ወደ ሌላው መደምደሚያ ተላለፈ፣ ተዳረሰ (ዐለፈ፣ ደረሰ)። "ካመት ዓመት።"
ተሸጋገነ: ተዋዋበ፣ ተቈነዣዠ።
ተሸጋጋሪ: የሚሸጋገር (ጋድም ሠረገላ)፣ ተላላፊ (በሽታ)።
ተሸጋጋሪነት: ተላላፊነት።
ተሸጐረ: ተወረወረ፣ ተቀረቀረ።
ተሸጐበ: ታጠፈ፣ ተቀለሰ።
ተሸጐጠ: ገባ፣ ተወተፈ፣ ተደበቀ፣ ተሸሸገ (ኢያሱ ፰፡ ፬)።
ተሸጓሪ: የሚሸጐር (መወርወሪያ)።
ተሸጓጭ: ሰንበሌጥ።
ተሸጓጭ: የሚሸጐጥ፣ ተደባቂ።
ተሸፈሸፈ: ታደ፣ ተቈረጠ።
ተሸፈነ: ለበሰ፣ ተከለለ፣ ተጋረደ፣ ተጨፈነ፣ ዘውስጥ ኾነ፣ ተከደነ።
ተሸፈጠ: ተከዳ፣ ተካደ፣ ዐሎ ተባለ፣ ተሞኘ፣ ተሸነገለ።
ተሸፋኝ: የሚሸፈን።
ተሸፋፈነ: ተከናነበ።
ተሸፋፈጠ: ተከዳዳ፣ ተካካደ።
ተሸፋፋኝ: የሚሸፋፈን፣ ተከናናቢ።
ተሸፋፍኖ: ተከናንቦ። "ተሸፋፍኖ በተኙ ገልጦ የሚወጋ ጌታ አለ።"
ተሹለከለከ: በደን፣ በጥሻ ውስጥ ለውስጥ ዐለፈ።
ተሻ: ተፈለገ፣ ተፈቀደ።
ተሻለ: በለጠ። (ሻለን እይ)
ተሻለ: በለጠ፣ ተመረጠ፣ ረባ፣ ጠቀመ። "ከመሞት መሰንበት ይሻላል።"
ተሻለ: በሽታው ቀለለ፣ ቍስለ ጠገገ፣ ዳነ።
ተሻለው: በጎ ኾነ።
ተሻለገ: ተጋመተ፣ ተሳሰበ፣ ተሳላ።
ተሻመቀ: ተዳፈጠ፣ ተዳባ (ሉቃስ ፲፩፡ ፺፮)።
ተሻመተ: ተላወጠ።
ተሻሚ: የሚሻማ፣ ተናጣቂ፣ ተቃሚ።
ተሻማ: ተናቀ፣ ተቃማ።
ተሻማ: ተናጠቀ። (ጥማሻማን እይ)
ተሻማ: ተጋራ፣ ተፋለመ።
ተሻረ: ተዋረደ፣ ሹመት ዐጣ፣ ከማዕርግ ተሰናበተ። "(አዝማሪ)፡ አገራችን ደጋ እርሻው በደጃችን ያ ቢሾም ያ ቢሻር እኛ ምን ተዳችን።"
ተሻረ: ዐለፈ፣ ቀረ።
ተሻረ: ጠፋ፣ ተፈታ፣ ድል ኾነ፣ ፈረሰ።
ተሻረከ: ተወዳጀ፣ ተባበረ፣ ተጋጠመ።
ተሻሪ: የሚሻር።
ተሻራኪ: የሚሻረክ፣ ተባባሪ።
ተሻሸ (ተሐሰየ): የማሸትን ብድር ተከፋፈለ፡ ተመላለሰ (እርስ በእርስ መሻሻት)።
ተሻሸ: ዳተኛ፡ ዝግተኛ ኾነ፡ ፍጥነት ዐጣ (ዘገምተኛ መሆን)።
ተሻሻለ: ታደሰ፣ ተጠገነ፣ ተለዋወጠ፣ አማረ። "ተሻሻለ፡ የተሻለ፡ ድርብና፡ ተደራራጊ፡ መኾኑን፡ ልብ፡ አድርግ።"
ተሻሻጠ: ተለዋወጠ፣ ሸየጠ።
ተሻሻጠ: ተታከለ፣ ተሳካ።
ተሻሻጠ: ተገበያየ፣ ተገዛዛ፣ ተለዋወጠ፣ ተቀባበለ።
ተሻሻጭ: የሚሻሻጥ፣ ተለዋዋጭ።
ተሻበ: ተመዘዘ፣ ቀጠነ፣ ተጠመጠመ።
ተሻተተ: ተጣጠነ፣ ሽታ ተቀባበለ፣ ተጫሰ፣ ተነፋነፈ።
ተሻታች: የሚሻተት።
ተሻኰተ: ተወዳደረ፣ ተፈካከረ። "እገና ተማታ ተጣፋ (ተጻፋ) ዕቃን ለመግዛትና ለመሼጥ ለመርታትና ለመረታት።"
ተሻኳች: የተሻኰተ፣ የሚሻኰት፣ ተወዳዳሪ።
ተሻወተ: ተሻኰተ፣ ተቈታቸ።
ተሻገረ: በወንዝ፣ በዥረት፣ በዠማ፣ በባሕር፣ በጐድጓዳ ስፍራ ላይ ዐለፈ፣ ወዲያ ማዶ ኼደ (ዘፍጥረት ፴፪፡ ፳፪። ዮሐንስ ፸፭ ፥ ፳፬)። ሥሩ ሠገረ ነው።
ተሻጋሪ: የሚሻገር፣ የሚያልፍ።
ተሻጠ: ተተከለ፣ ተሰካ፣ ተሳና፣ ቆመ።
ተሻጭ: የሚሻጥ፣ የሚሰካ።
ተሻፈነ: ተካለለ።
ተሼጠ: ተለወጠ። "ለገዢ ተሰጠ (መዝሙር ፻፭፡ ፲፯)።"
ተሽ: (ቅድመ ቅጥያ) የደጋግሞ ቃል፣ ተደራጊ ግስና ቅጽል ባዕድ መነሻ።
ተሽ: (ቅድመ ቅጥያ) የደጋግሞ ቃል፣ ተደራጊ ግስና ቅጽል ባዕድ መነሻ። ምሳሌ: ከረከረ፡ - ተሽከረከረ፣ ተሽከርካሪ፡ ቈጠቈጠ፡ - ተሽቈጠቈጠ፣ ተሽቈጥቋጭ፡ ቀረቀረ፡ - ተሽቀረቀረ፣ ተሽቀርቃሪ።
ተሽላል: ግብዝ ነገር፣ ሸፍጥ፣ ሽንገላ።
ተሽሎታል: ጤና አግኝቷል።
ተሽመለመለ: መሄድ አቃተው፡ ዕጥፍ ዕጥፍ አለ እግሩ።
ተሽመለመለ: ተሸበለለ።
ተሽመለመለ: ተሸበለለ። (መለለን እይ)
ተሽመደመደ: ተቅመደመደ (ወገቡ)፣ ተገመደ (እግሩ)።
ተሽሞነሞነ: ተሸፈነ፣ ተከናነበ፣ ተኵነሰነሰ፣ ተሽኰነተረ፣ ተሸተረ።
ተሽሞንጝኝ: የሚሽሞነሞን፣ ተሽኰንታሪ።
ተሽረከረከ: ተፍረከረከ፣ ፈረሰ (ሽርክናው፣ ምክሩ፣ ዐድማው፣ ሤራው)።
ተሽቀረቀረ: ተሸለመ፣ አጌጠ፣ ተጌጠ።
ተሽቀርቃሪ: የሚሽቀረቀር፡ ጌጥ ወዳድ።
ተሽቀነደረ፡ ተደሰተ፡ የኵራት፡ አካኼድ፡ ኼደ፡ ተቀናጣ፡
ዘለለ።
ተሽቀነጠረ: ተቀናጣ። (ቀነደረን እይ)
ተሽቀንዳሪ፡ የሚሽቀነደር፡ ዘላይ።
ተሽቀዳደመ፡ ተቀዳደመ፡ ተሯሯጠ፡ በሩጫ፡ ተበላለጠ።
ተሽቀዳዳሚ፡ ተቀዳዳሚ፡ የተሽቀዳደመ፡ የሚሽቀዳደም።
ተሽቈለቈለ፡ ተቈለቈለ።
ተሽቈመቈመ፡ ተጠራ፡ ተሽኰመኰመ።
ተሽቈመቈመ፡ ፊትን፡ መለሰ፡ ጠመዘዘ፡ ከማእድ።
ተሽቈመቈመ: ተጠራ፣ ተሽኰረመመ፣ ተጫወተ፣ ወይም ተዳራ።
ተሽቈጠቈጠ፡ ፈራ፡ ተንቀጠቀጠ፡ ተለማመጠ፡ ተርገበገበ።
ተሽቈጥቋጭ፡ የሚሽቈጠቈጥ፡ ፈሪ፡ ርግብግብ፡ ተለማማጭ።
ተሽበለበለ: ተባበለ፣ ተለመነ፣ ተገለገለ፣ ተቈላመጠ።
ተሽከረከረ: ዞረ፣ ሾረ፣ ሄደ፣ ተንደረደረ ወይም ተንከባለለ። "እግዜር ዐሙስ ከባሕር፣ ዐርብ ከየብስ በእግር የሚሽከረከሩ፣ በክንፍ የሚበሩ ፍጥረቶች ፈጠረ፡ እነዚሁም እንስሶችና አሞሮች (ወፎች) አውሬዎች ናቸው። "
ተሽከርካሪ (ሮች): የሚዞር ወይም የሚሽከረከር፡ እንስሳ፣ አውሬ፣ መኪና በያይነቱ።
ተሽኰመኰመ: ተሽቈመቈመ፡ ተጠራ፡ ተሽኰረመመ፡ ተጫወተ፡ ተዳራ።
ተሽኰረመመ: ተዳራ ወይም ተግደረደረ።
ተሽኰረኰረ: ተቋጠረ፡ ታየ (ደመናው)።
ተሽኰረኰረ: ጨረቋ ጓሚያ ሆነ፡ ተድበለበለ።
ተሽኰርማሚ: የተሽኰረመመ ወይም የሚሽኰረመም፡ ተግደርዳሪ (ወንድና ሴት እንስት ዶሮ)።
ተሽኰነተረ: አጌጠ፣ ተጌጠ ወይም አማረ፡ "ባልታጠበ እጅ አትንኩኝ" አለ።
ተሽኰንታሪ: የተሽኰነተረ ወይም የሚሽኰንተር።
ተሽጐደጐደ፡ ተዥጐደጐደ (ዠጐደ)።
ተሽጠጠ: ተባለ፣ ተነገረ፣ ሆነ፣ ተደረገ ሽሙጡ፡ ተሸረደደ፣ ተቀለደበት ሰውየው።
ተሾለከ: ሳይታይ ተሰርቆ ኼደ።
ተሾለከ: ታለፈ፣ ተወጣ (ሳንው)።
ተሾመ: ተመላ፣ ምሉ ኾነ።
ተሾመ: ተበጀ፣ ተዘጋጀ።
ተሾመ: ታከበ፣ ተሰበሰበ።
ተሾመ: ከበረ፣ ሥልጣን አገኘ፣ ስም አወጣ፣ አገር ገዛ።
ተሾመ: ዝም፣ ጥርቅም አለ።
ተሾካሾከ: በሹክታ ተነጋገረ።
ተሾካሿኪ: የተሾካሾከ፣ የሚሾካሾክ።
ተሾፈ: ተቀለደ፣ ተዘበተ።
ተሿለከ: በጠባብ በር ተላለፈ።
ተሿሚ: የሚሾም፣ የሚሸለም።
ተሿሿመ: ማዕርግ ተቀባበለ፣ ሹም ተኳዃኑ። "ተሸላለመ፡ እንደ፡ አትናቴዎስና፡ እንደ፡ እንጦንስ።"
ተሿሿሚ: የሚሿሿም።
ተቀ: ተጋጋለ፣ ተላላበ፡ ተበራታ።
ተቀለመ: ተያዘ፡ ቀለበ።
ተቀለሰ፡ ተመለሰ፡ ጐበጠ፡ ተቈለፈ።
ተቀለሰ: ዞረ፣ ሁለተኛ መጣ (፪ኛ ሳሙኤል ፲፱:፲፭)።
ተቀለበ፡ ተመገበ፡ በላ፡ ጠጣ፡ (ኤርምያስ ፭፡ ፰)።
ተቀለበ፡ ተያዘ፡ ተጨበጠ።
ተቀለበሰ፡ ከጫፍ፡ ታጠፈ፡ ተሸነቀረ፡ ተቀነፈ።
ተቀለበሸ፡ ተመለሰ፡ ተገለበጠ።
ተቀለተ፡ ተረጠበ፡ ተረዳ፡ ታገዘ።
ተቀለደ፡ ተሾፈ፡ ተቧለተ፡ ተተረበ፡ ተፌዘ።
ተቀለጠመ፡ ተመታ፡ ተሰበረ።
ተቀለጣጠመ፡ ተሰባበረ።
ተቀለጣጠፈ፡ ተከነዋወነ፡ ተጣጣመ።
ተቀለፈፈ፡ ተቀፈፈ፡ ተቈረጠ።
ተቀላ፡ (ተቀልዐ)፡ ተመታ፡ ተለጋ፡ ዕሩሩ።
ተቀላ፡ ተቈረጠ፡ ዐንገቱ፡ ራሱ።
ተቀላለበ፡ ተመጋገበ።
ተቀላለበ፡ ተቀባበለ።
ተቀላለተ፡ ተረጣጠበ።
ተቀላቀለ፡ ተደባለቀ፡ ተቀየጠ፡ ተዘነቀ፡ (ዕብራውያን ፬፡ ፪)።
ተቀላቃይ፡ የሚቀላቀል፡ ተደባላቂ።
ተቀላቢ፡ (ዎች)፡ የሚቀለብ፡ ተመጋቢ፡ ገበታ፡ ዐቃፊ። (ተረት)፡ "አብዝቶ፡ ከማረስ፡ ከተቀላቢው፡ ማሳነስ። "
ተቀላቢነት፡ ተቀላቢ፡ መኾን።
ተቀላች፡ የሚቀለት፡ ተረጣቢ።
ተቀላወጠ፡ ተከጀለ፡ ምግቡ።
ተቀላጠመ፡ ቅልጥምን፡ ተማታ፡ ተሳበረ።
ተቀላጠፈ፡ ተፋጠነ፡ ተከናወነ፡ ተጨረሰ።
ተቀልባሽ፡ የሚቀለበስ፡ ተቀናፊ።
ተቀልጣሚ፡ የሚቀለጠም፡ ተሰባሪ።
ተቀመለ፡ ተለቀመ፡ ተያዘ፡ ተዳጠ፡ ተገደለ።
ተቀመመ፡ ተዘጋጀ፡ ተቀላቀለ፡ ተዋዋደ፡ አንድነት፡
ኾነ።
ተቀመሰ፡ ተጣመ፡ ተለከፈ፡ ተበላ፡ ተጠጣ፡ በጥቂቱ።
ተቀመረ፡ ተቈጠረ፡ ተመደበ፡ ተለየ፡ ተከፈለ።
ተቀመቀመ፡ ተሰፋ፡ ተዘመዘመ።
ተቀመጠ፡ ቍጭ፡ አለ፡ ተጐለተ፡ ነበረ፡ ኖረ፡ ቈየ፡
ሰነበተ፡ (ዘፍጥረት ፰፡ ፲፬። መክብብ ፭ - ፲፯። ዳንኤል ፩፡ ፳፩። ፪፡ ፴፰)። "ተቀመጥ፡ በወንበሬ፡ ተናገር፡ በከንፈሬ፡ እንዲሉ። " (ተረት)፡ "የተቀመጠ፡ ተቈመጠ። "
ተቀመጠ፡ በፈረስ፡ በበቅሎ፡ ባህያ፡ በግመል፡ በዝኆን፡
ተነ።
ተቀመጠ፡ ዐረፈ፡ ሰፈረ፡ (ዘኍልቍ ፱፡ ፲፰)፡
ተቀመጠ፡ ኰሳ፡ ቀዘነ።
ተቀመጠለ፡ ታረደ፡ ተጐመደ፡ ተቀነጠሰ።
ተቀመጠለ፡ ጐደለ፡ አነሰ።
ተቀማ፡ (ተቀምሐ)፡ ተነጠቀ፡ አለውድ፡ በግድ፡ ተወሰደ፡ ገንዘቡ፡
ተወሰደበት፡ ሰዉ። (ተረት)፡ "ባባቱ፡ ከተማ፡ ልጁ፡ ተቀማ። " "በቢርነት፡ ሲፈታ፡ ገንዘቡን፡ ተቀማ፡ ይላል። "
ተቀማመጠ፡ ተሸካከመ፡ የመሸከም፡ ብድር፡ ተከፋፈለ፡
ሸክምና፡ ተሸካሚ፡ ተኳዃነ።
ተቀማሚ፡ የሚቀመም።
ተቀማቀመ፡ እንጀራ፡ መብላት፡ ዠመረ፡ ተላመደ፡ ሕፃኑ።
ተቀማጠለ፡ ተቀመጣጠለ፡ (ሐንቀቀ)፡ ደኅና፡ ጠባዩ፡ ዐመሉ፡ ተጓደለ፡ ተንደላቀቀ፡
ተንቀባረረ፡ ተዘናፈለ፡ ተደላደለ፡ "ዶሮ፡ ዕለሱ፡ ጣይ፡ በንቅብ፡ አግቡ"፡ አለ።
ተቀማጣይ፡ የሚቀማጠል፡ ተንቀባራሪ።
ተቀማጭ፡ (ጮች)፡ የሚቀመጥ፡ ነባሪ፡ ኗሪ፡ (ኤርምያስ ፮፡ ፯፡ ፰። ፩ኛ ዜና - ፱ - ፪። ሕዝቅኤል ፴፱፡ ፱። ማቴዎስ ፳፪፡ ፲)። (ተረት)፡ "ለተቀማጭ፡ ሰማይ፡ ቅርቡ። "
ተቀማጭ፡ ገንዘብ፡ ለብዙ፡ ጊዜ፡ የማይነካ፡ የማይጐድል፡ ወርቅና፡
እኸል፡ የክፉ፡ ቀን፡ መጠባበቂያ፡ (ዘፍጥረት ፵፩፡ ፴፫ - ፴፬፡ ፴፭፡ ፴፮፡ ፵፰፡ ፵፱)። "ይኸንንም፡ ፈረንጆች፡ ሪዘርብ፡
ይሉታል።
"
ተቀማጭነት፡ ተቀማጭ፡ መኾን፡ ነባሪነት።
ተቀምቃሚ፡ የሚቀመቀም፡ ተዘምዛሚ፡ ቀሚስ፡ በርኖስ።
ተቀምጨ፡ ያገዳ፡ እኸል፡ ጕረንጆ።
ተቀሠመ: ተለቀመ፣ ተሰበሰበ፣ ተመጠጠ።
ተቀሰረ: ተገተረ፣ ቆመ።
ተቀሰቀሰ: ተበረበረ፣ ተፈተሸ።
ተቀሰቀሰ: ተነቀነቀ፣ ነቃ፣ ተነሣ።
ተቀሰተ: ተደገነ፣ ጐበጠ።
ተቀሠፈ: በዝርዝር ተቀጪ፣ ተቀጠፈ፣ ተገደለ፣ ሞተ (ኤርምያስ ፶፡ ፳፩)።
ተቀሠፈ: ተደገነ፣ ጐበጠ።
ተቀስቃሽ: የሚቀሰቀስ፡ እንቅልፋም ሰው፣ አውሬ።
ተቀረረ: ተጠለለ፣ ተቀዳ፣ ተመለጠ።
ተቀረሸመ: ተገጨ፣ ተሰበረ።
ተቀረሻሸመ: ተሰባበረ።
ተቀረቀረ: ገባ፣ ተሸጐረ፣ ተወረወረ።
ተቀረቀበ: ታሰረ፣ ተወደነ፣ ተጠመረ፣ ታረተ፣ ተቈረኘ።
ተቀረቀፈ: ተከረከረ።
ተቀረበ: ሰውየውን ሌሎች ተጠጉት።
ተቀረበ: ተነዳ፣ ተወሰደ።
ተቀረነተ: ታሰረ፣ ተቀረቀበ።
ተቀረደደ: ተቈረጠ፣ ተቈረሰ፣ ተገመሰ።
ተቀረጠ: ሾለ፣ ተበጀ (ብርዑ)።
ተቀረጠ: ተሰጠ፣ ተከፈለ (ግብሩ) (ዕዝራ ፬፡ ፲፫)።
ተቀረጠፈ: ተቈረጠ፣ ጠቀነ፣ ደቀቀ።
ተቀረጣጠፈ: ተቈራረጠ።
ተቀረጪ: ተነከሰ።
ተቀረጸ: ተቀረጠ፣ ተነጠጠ፣ ተፈለፈለ፣ ተጐበጐበ፣ ሰመጠ፣ ተነቀሰ። (ታቦት ተቀረጸለት) ;በቃ ጻድቅ ቅዱስ ኾነ ፤ ስሙ በጽላት ላይ ተጻፈ ፤ ቤተ ክሲያን ታነጸለት ።
ተቀረፈ: ተላጠ፣ ተመለጠ፣ ተለጠጠ፣ ተነጠለ፣ ተነሣ፡ ተሰበረ፣ ተፈለጠ። "ገደል ተቀረፈና ወደቀ። "
ተቀራመተ: ተቃረጠ፣ ተተናተነ፣ ተራከበ፣ ተካፈለ።
ተቀራማች: የተቀራመተ፣ የሚቀራመት፡ ተተናታኝ፣ ተካፋይ።
ተቀራረበ: ተጠጋጋ፣ ተገነኛኘ።
ተቀራረጠ: ቀረጥ ተሰጣጠ፣ ተቀባበለ፣ ተግባበረ።
ተቀራረፈ: ተሰባበረ፣ ተሠነጣጠቀ፡ ተላላጠ፣ ተመላለጠ።
ተቀራራቢ: የሚቀራረብ።
ተቀራሸመ: በቀንድ ተማታ፣ ተጋጨ፣ ተሳበረ።
ተቀራቀበ: ተገተ፣ ተከራከረ፣ ተማረተ።
ተቀራደደ: በሰይፍ ተማታ፣ ተወፋጨፈ፣ ተቈራረጠ፣ ተራረደ።
ተቀራዳጅ: የሚቀራደድ።
ተቀራጨጨ: ተናከሰ።
ተቀራጭ: የሚቀረጥ፡ ቀረጡ ያልወጣለት (ሸቀጥ)።
ተቀራፊ: የሚቀረፍ።
ተቀርቃሪ: የሚቀረቀር፡ ተሸጓሪ።
ተቀርቃቢ: የሚቀረቀብ፡ ተጠማሪ።
ተቀርዳጅ: የሚቀረደድ።
ተቀርጣፊ: የሚቀረጠፍ።
ተቀሸ: ኰራ፣ ተለጠጠ።
ተቀሸመደ: ተሰበረ፣ ነከተ።
ተቀሸረ: ተነፋ፣ ተቀበተተ።
ተቀሸረ: ተከሸነ፣ አማረ፣ ሰመረ።
ተቀቀለ: ሞቀ፣ ፈላ፣ በሰለ፣ ነፈረ፡ ተሠራ (ወጡ)።
ተቀቀለ: ራስ ረሰረሰ (የባቄላ፣ ያተር፣ የሽንብራ ቈሎ) በፈላ ውሃ።
ተቀቃይ: የሚቀቀል (እኸል፣ ጐመን፣ ዓሣ፣ ሌላም ምግብ)።
ተቀበለ፡ ቅብል፡ ኾነ፡ እፈጣሪ፡ ፊት፡ ደረሰ፡ ከበረ፡
ተወደደ፡ (ሉቃስ ፬፡ ፲፱ ፣ ፪ ፣ ፳፬)።
ተቀበለ፡ ተሰጠው፡ አገኘ፡ እጅ፡ አደረገ፡ ተረከበ፡
(ሉቃስ ፳፬፡ ፵፫)።
ተቀበለ፡ አማረ፡ ደመቀ፡ ተስማማ። ምሳሌ: "አቶ፡ እከሌ፡ የለበሰው፡ ልብስ፡ ተቀብሎታል። " (እንግዳ፡ ተቀበለ)፡ በቤቱ፡ አሳደረ፡ አስተናገደ፡ (ማቴዎስ ፲፡ ፵)። (መከራ፡ ተቀበለ)፡ ተሣቀየ።
ተቀበለ፡ ጐረሠ፡ ዋጠ፡ ጠጣ፡ ቍርባንን። ቈረበን፡ ተመልከት።
ተቀበለ: ረከበ።
ተቀበለ: ተረከበ።
ተቀበረ (ተቀብረ)፡ በመቃብር፡ ተኛ፡ ተጋደመ፡ ዐፈር፡ ቀመሰ፡
ለበሰ፡ ተደፈነ።
ተቀበረ፡ ተጐዳ፡ ተጨቈነ።
ተቀበቀበ፡ ተቀጠቀጠ፡ ታደሰ።
ተቀበቀበ፡ ተተከለ፡ ተቸከለ።
ተቀበቀበ፡ ታረሰ፡ ታየመ፡ ለሰለሰ።
ተቀበተተ፡ ዐበጠ፡ ተነፋ፡ ተወጠረ፡ ተነረተ፡ ቍንጣን፡
ያዘው።
ተቀበነነ፡ ተነፋ፡ ተወጠረ፡ ተቀበተተ።
ተቀበጠጠ፡ ተቀበተተ።
ተቀቢ (ተቀባዒ)፡ የሚቀባ፡ ጳጳስ፡ ንጉሥ፡ ዝኆን፡ ገዳይ።
ተቀባ (ተቀብዐ)፡ ተላከከ፡ ተለቀለቀ፡ ተደለሰ፡ ቅቤው፡ ራሱ። ታደለ፡ ጸጋ፡ መንፈስ፡ ቅዱስን፡ ተቀበለ፡
ካህኑ፡ ንጉሡ። ዳግመኛም፡ በገቢርነት፡ ሲፈታ፡ "ቅቤን፡ ተቀባ"፡ ይላል።
ተቀባ፡ የሰው፡ ስም።
ተቀባሪ፡ የሚቀበር፡ የሚደፈን።
ተቀባበለ፡ ተሰጣጠ፡ ተረካከሰ፡ ዕቃን፡ ገንዘብን፡
(ራእይ ፲፩፡ ፲)። በእንግድነት፡ ተፈራረቀ፡ (ሮሜ ፲፭፡ ፯)።
ተቀባበረ፡ ተደፋፈነ፡ የመቅበር፡ ብድር፡ ተመላለሰ፡
የችና፡ የቋሚ፡ ወገን።
ተቀባባ፡ ተለቃለቀ፡ ተደላለሰ፡ ተባበሰ፡ ተወዛዛ።
ተቀባባሪ፡ የሚቀባበር።
ተቀባባይ፡ የተቀባበለ፡ የሚቀባበል፡ ተረካካቢ።
ተቀባይ፡ የተቀበለ፡ የሚቀበል፡ ተረካቢ፡ ያዥ። ምሳሌ: "ገንዘብ፡ ተቀባይ፡ እንግዳ፡ ተቀባይ፡ ተስጥዎ፡
ተቀባይ"፡ እንዲሉ።
ተቀባይነት፡ ተቀባይ፡ መኾን፡ ተረካቢነት።
ተቀባዮች፡ ዘፈን፡ መዝሙር፡ መላሾች፡ (ዕዝራ ፪፡ ፷፭)።
ተቀብዖ፡ መቀባት።
ተቀተረ: ተቀረቀረ፣ ተሸጐረ።
ተቀተረ: ተቀረቀረ፣ ተሸጐረ። ተቀተረ: ተነፋ፣ ዐሰጠ፣ ተወጠረ፣ ተቀበተተ። "(ጥት) ቅትር፡ (ቅቱር)፣ የተቀተረ፣ የተቀረቀረ፡ ንፍ፣ ውጥር።"
ተቀተረ: ተነፋ፣ ዐሰጠ፣ ተወጠረ፣ ተቀበተተ። "(ጥት) ቅትር፡ (ቅቱር)፣ የተቀተረ፣ የተቀረቀረ፡ ንፍ፣ ውጥር።"
ተቀታተረ: ተወዳደረ፣ ተገዳደረ፣ ተከራከረ፣ ተፈካከረ፣ ተቋቋመ። "(ተረት)፡ ከባለቀትር አትቀታተር (ከባለጊዜ አትፈካከር)።" "ዳግመኛም ባለቀትር ደሙ የፈላ ማለትን ያሳያል።"
ተቀነሰ: ተነሣ፣ ጐደለ፡ ከብዛት ከመምላት ኣነሰ። "ከበስመ አብ ተቀንሶለት። " "እነሰ ሲሉት ተቀነሰ። "
ተቀነረ: ተነፋ፣ ዐበጠ።
ተቀነቀነ: ተመረመረ፣ ተፈተሸ።
ተቀነቀነ: ተቃኘ፣ ተዠመረ።
ተቀነበበ፡ ተከበበ፡ ክብ፡ ኾነ፡ የሥራ፡ የጠላት፡
ጦር፡ ሰራዊት።
ተቀነባበረ፡ ተዘገጃጀ፡ ተደረጃጀ፡ ተከነዋወነ፡ ተቋቋመ።
ተቀነተ: በወገብ ላይ ታሰረ (መቀነቱ፣ ቅናቱ፣ ሠቁ፣ ቀበቶው)።
ተቀነዘፈ፡ ታረደ፡ ተቀነጠሰ፡ ተመለመለ።
ተቀነዘፈ፡ ወረደ፡ ፈሰሰ፡ ተንጠባጠበ።
ተቀነደለ፡ ተበጣ፡ ተቈረጠ።
ተቀነደሸ፡ ተሰበረ፡ ነከተ።
ተቀነደበ፡ ተመታ።
ተቀነደበ፡ ተቀነደለ።
ተቀነደበ፡ ተጠጣ፡ ጐደለ።
ተቀነጠበ፡ ከላይ፡ ተቈረጠ፡ ተበጠሰ፡ ተቀነጠሰ።
ተቀነጣጠበ፡ ተቀነጣጠሰ።
ተቀነጨበ፡ ተቈነጠረ፡ ተወሰደ፡ ከጫፍ።
ተቀነፈ: ታጠፈ፣ ተመለሰ፣ ተሸበለለ፣ ተቀለበሰ።
ተቀና፡ ተገዛ፡ ተሼጠ፡ ተለወጠ።
ተቀናሽ: የሚቀነስ፣ የሚጐድል።
ተቀናቀነ: ተመራመረ።
ተቀናቃኝ (ኞች): የተቀናቀነ፣ የሚቀናቀን፡ ተመራማሪ።
ተቀናቃኝነት: ተመራማሪነት።
ተቀናበረ፡ ተዘጋጀ፡ ተደራጀ፡ ተከናወነ።
ተቀናባሪ፡ የሚቀናበር፡ ተከናዋኝ።
ተቀናና፡ ተመቀኛኘ።
ተቀናዘረ፡ ተዋሸሙ፡ ከመጠን፡ ተላለፈ።
ተቀናደበ፡ ተማታ፡ ተዋጋ፡ ተጋጩ፡ በቀንድ፡ በበትር።
ተቀናጀ፡ ከሌላ፡ ሰው፡ በሬ፡ ጋራ፡ ተጠመደ።
ተቀናጠበ፡ ተቀናጠሰ።
ተቀናጣ፡ ጠገበ፣ ወበራ ይይዘውን፡ ዐጣ፡ ዘለለ፡ ተላፋ።
ተቀናፊ: የሚቀነፍ፡ ተቀልባሽ (እጅጌ፣ ሱሪ)።
ተቀንዳይ፡ የሚቀነደል፡ ተበጪ።
ተቀንጣቢ፡ የሚቀነጠብ።
ተቀኘ፡ (ተቀንየ)፡ ዐወቀ፡ ተናገረ፡ ገለጸ፡ ቅኔን።
ተቀኘ፡ ተባለ፡ ተነገረ፡ ተሰጠ፡ ቅኔው፡ (ኢሳይያስ ፳፮፡ ፩)።
ተቀዘነ፡ ፈጥኖ፡ ወጣ፡ ወረደ፡ ፈሰሰ።
ተቀዘፈ፡ ተገፋ፡ ግራ፡ ቀኝ፡ ተባለ፡ ተገለጠ፡ ተከፈለ።
ተቀየመ፡ ተጸየፈ፡ ተከፋ፡ ዐዘነ፣ አኰረፈ።
ተቀየሰ፡ ተለካ፡ ተመጠነ፡ ተነደፈ፡ ተበገረ።
ተቀየረ፡ ተለወጠ፡ ተዛወረ።
ተቀየደ፡ ተሰከለ፡ ታሰረ፡ ተጋዳ።
ተቀየደ፡ ተከፈለ፡ ተመከተ፡ ተጋረደ።
ተቀየጠ፡ ተዘነቀ፡ ተቀላቀለ፡ ተደባለቀ፡
ተቀያሚ፡ የሚቀየም፡ ተጸያፊ፡ አኵራፊ።
ተቀያሪ፡ የሚቀየር፡ ተዛዋሪ፡ ወታደር፣ ዘበኛ።
ተቀያየመ፡ ቂም፡ ተያያዘ፡ ተኰራረፈ፡ ሆድና፡ ዠርባ፡
ተኳዃነ።
ተቀያየረ፡ ተለዋወጠ፡ ተዘዋወረ።
ተቀያያሪ፡ የሚቀያየር፡ ተለዋዋጭ፡ ተዘዋዋሪ።
ተቀያጅ፡ የሚቀየድ፡ ተጋራጅ፡ የቤት ውስጥ።
ተቀያጭ፡ የሚቀየጥ፡ አደፍ፡ ወይም፡ ጥሩ።
ተቀደመ፡ ሳይመታ፡ ተመታ።
ተቀደመ፡ ቀደመ፡ ቀዳሚ፡ ኾነ። "ተቀደመን፡ ቀደመ፡ ማለት፡ የተለመደ፡ ስሕተት፡
ነው። ረገጠ፡ ብለኸ፡ ተረገጠን፡ አስተውል። "
ተቀደመ፡ በቀዳማ፡ ላይ፡ ተሰቀለ።
ተቀደመ፡ ወደ፡ ኋላ፡ ኾነ፡ ታለፈ።
ተቀደሰ (፪ዜና፡ ፴፡ ፳፯)፡ ተለየ፡ ተባረከ፡ ነጻ፡ ከበረ፡ ተመሰገነ፡
ምስጋና፡ ተቀበለ። (ተረት)፡ "ዥብ፡ ሲበላኸ፡ በልተኸው፡ ተቀደስ። "
ተቀደሰ፡ ተቈረበ።
ተቀደደ፡ ተሸረከተ፡ ተሠነጠቀ፡ ተሠጠጠ፡ ተበሳ፡
ተሸነቈረ፡ (ዮሐንስ ፳፩፡ ፲፩)። (ተረት)፡ "ካያያዝ፡ ይቀደዳል፡ ካነጋገር፡ ይፈረዳል። "
ተቀደደ፡ ወሬ፡ ነዛ።
ተቀዳ (ተቀድሐ)፡ ወረደ፡ ተጨመረ፡ ተንቈረቈረ፡ ተደነበቀ፡
ተጠለቀ፡ ተጨለፈ፡ ተገለበጠ።
ተቀዳ፡ ተጻፈ፡ ተከተበ።
ተቀዳሚ፡ የሚቀደም፡ የሚታለፍ፡ በሩጫ፡ ሌላ፡ የሚበልጠው።
ተቀዳሚ፡ የሚቀድም፡ ቀዳሚ፡ በኵር፡ ግንባር፡ ቀደም፡
አንጋፋ። ምሳሌ: "ጌታችን፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ በወዲያኛው፡
ዓለም፡ ከአብ፡ አለናት፡ በዚህ፡ ዓለም፡ ከድንግል፡ ማርያም፡ አላባት፡ በመወለዱ፡ ተቀዳሚ፡ ተከታይ፡ የለውም፡ ላባቱም፡
ለናቱም፡ አንድ፡ ልጅ፡ ነው። "
ተቀዳሽ፡ የሚቀደስ፡ የሚባረክ፡ ተመስጋኝ።
ተቀዳሽነት፡ ተቀዳሽ፡ መኾን።
ተቀዳው፡ ብዙ፡ እንባ፡ ወረደው፡ ፈሰሰው።
ተቀዳው፡ ጋኑ፡ ይህን፡ ያኸል፡ ጠጅ፡ ወይም፡ ጠላ፡
ወጣው።
ተቀዳደመ፡ ተላለፈ፡ ፊትና፡ ኋላ፡ ተኳዃነ፡ (፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፬፡ ፩፡ የሐዋርያት ሥራ ፲፪፡ ፲፬)።
ተቀዳደሰ፡ ተበራረከ፡ ተመሰጋገነ።
ተቀዳደደ፡ ተሠነጣጠቀ፡ ተሸረካከተ፡ ተበጫጨቀ።
ተቀዳዳሚ፡ የሚቀዳደም።
ተቀዳጀ (ተቀጸለ)፡ በራሱ፡ ላይ፡ የሐር፡ የግምጃ፡ ቅዳጅ፡
ጠመጠመ፡ አክሊል፡ አደረገ፡ ዘውድ፡ ደፋ፡ በአበባ፡ ተሸለመ፡ አጌጠ። የተቀዳጀ፡ ምስጢር፡ አክሊሉና፡ አበባው፡ ከወደ፡ ላይ፡ ባዶ፡ ዘውዱም፡ ዐልፎ፡
ዐልፎ፡ ክፍት፡ መኾኑን፡ ያሳያል።
ተቀዳጀ: ቀጸለ።
ተቀዳጅ፡ የሚቀደድ፡ ጥንካሬ፡ የሌለው፡ ልብስና፡
የቈዳ፡ ዐይነት።
ተቀጠለ፡ በላይ፡ በጫፍ፡ በቀለ።
ተቀጠለ፡ ተጨመረ፡ ታከለ፡ ተቋጠረ፡ ተሰፋ፡ ረዘመ።
ተቀጠረ፡ (ተቀጽረ)፡ ታጠረ፡ ተከበበ።
ተቀጠረ፡ ለጌታ፡ ለመቤት፡ ዐደረ፡ ለሰው፡ ታዛዥ፡
ኾነ።
ተቀጠቀጠ፡ (ተቀጥቀጠ)፡ ተመታ፡ ተደበደበ፡ ተሰበረ፡ ደቀቀ፡ (ኢሳይያስ ፵፪፡ ፫። ኤርምያስ ፴፰፡ ፬)። በሐዘን፡ ተቀጠቀጠ፡ እንዲሉ።
ተቀጠቀጠ፡ ተሠራ፡ ሾለ፡ ጠፍጣፋ፡ ኾነ።
ተቀጠቀጠ፡ ተወቀጠ፡ (ዘዳግም ፳፫፡ ፩)
ተቀጠበ፡ ተከነዳ፡ ተለካ፡ ተመጠነ፡ ተመለከተ፡ ምልክት፡
ኾነበት፡ ተደረገበት፡ ተከሰለ።
ተቀጠጠ፡ ተቈረጠ፡ ታጨደ፡ ተሸለተ፡ (መሳፍንት ፮፡ ፴፯)።
ተቀጠፈ፡ በልጅነት፡ ሞተ፡ ተገደለ፡ ተቀሠፈ፡ ተቀጨ።
ተቀጠፈ፡ ተቈረጠ፡ ተቀነጠሰ፡ ተሰበረ፡ ጐመኑ፡ ቅጠሉ።
ተቀጣ (ተቀጽዐ)፡ ተመታ፡ ተገረፈ፡ እወህኒ፡ ቤት፡ ገባ፡
ታሰረ።
ተቀጣ፡ መቀጮ፡ ከፈለ።
ተቀጣ፡ ተሠራ፡ ተመከረ፡ ተገሠጸ፡ ተጠበቀ፡ በአሳብ፡
በሰውነት። ምሳሌ: "እኔን፡ ያየኸ፡ ተቀጣ"፡ እንዲል፡ ሌባ፡ ሲገረፍ።
ተቀጣ፡ እጁ፡ ምላሱ፡ ተቈረጠ።
ተቀጣሪ፡ (ሮች)፡ የሚቀጠር፡ የሚታጠር፡ እሥራ፡ የሚገባ።
ተቀጣቀጠ፡ ተማታ፡ ተደባደበ፡ ተዳቀቀ።
ተቀጣቢ፡ የሚቀጠብ፡ ተመጣኝ።
ተቀጣይ፡ የሚቀጠል፡ የሚጨመር፡ የሚታከል።
ተቀጣጠለ፡ ተቈጣጠረ፡ ተያያዘ፡ ተናደደ።
ተቀጣጠለ፡ ተከታተለ፡ ተለጣጠቀ፡ ተገጣጠመ።
ተቀጣጠረ፡ "እዚህ፡ ድረስ፡ እመጣለኹ"፡ በማለት፡ ተነጋገረ።
ተቀጣጠበ (ተቃጸበ)፡ ተጠቃቀሰ፡ በምልክት፡ ተያየ፡ ተላገደ፡
አላገጠ፡ ተመሳቀ።
ተቀጣጣ (ተቃጽዐ)፡ የቅጣት፡ ብድር፡ ተመላለሰ።
ተቀጣጣይ፡ የሚቀጣጠል፡ ተያያዥ።
ተቀጣጥሎ፡ ተያይዞ፡ ተከታትሎ፡ (፪ኛ ሳሙኤል ፳፩፡ ፩)።
ተቀጣፊ፡ የሚቀጠፍ፡ ብስል፡ የተክል፡ ፍሬ፡ ጐመን።
ተቀጥላ፡ በ፫፡ ፊደል፡ ግስ፡ መነሻና፡ መድረሻ፡
የተጨመረ፡ ባዕድና፡ ምእላድ፡ ፊደል፡ ቍጥር፡ ፯፡ ተመልከት።
ተቀጥላ፡ ተቀጽላ፡ በወርካ፡ በቍልቋል፡ በማንኛውም፡ ዛፍ፡
ኹሉ፡ ራስ፡ በስንደዶ፡ ዐናት፡ ላይ፡ የሚበቅል፡ ቅጠል፡ የጫት፡ አምሳያ። "ባለመድኀኒቶች፡ አብነት፡ ያደርጉታል፡ መናኛው፡
ተገድራ፡ ይባላል። " ገደረን፡
እይ። (የማሰሮ፡ ተቀጥላ)፡ ገንፎ።
ተቀጥቃጭ፡ የሚቀጠቀጥ፡ ተወቃጭ
ተቀጨ፡ ተቀሠፈ፡ ተገደለ።
ተቀጨ፡ ተቈረጠ፡ ተነጨ፡ ተገነጠለ።
ተቀጨ፡ ዐንገቱ፡ ታመመ፡ ዘወር፡ ብሎ፡ ማየት፡
አቃተው።
ተቀጨቀጨ: ነዘነዘ።
ተቀጪ፡ የሚቀጣ፡ ዐመፀኛ፡ ወንጀለኛ።
ተቀጸለ: ተቀዳጀ።
ተቀጸለ: ተቀዳጀ፣ ተሸለመ፣ ተጌጠ።
ተቀጸለ: ተጠና (ትምርቱ)።
ተቀጸለ: ታማ፣ ተነቀፈ፡ ስሙ ከፋ።
ተቀጸል ጽጌ: ሐፄጌ፡ ንጉሥ ሆይ አበባን ተቀዳጅ፣ በራስኸ ላይ አድርግ፣ ልበስ፣ ባበባ አጊጥ ማለት ነው፡ ቃሉም ከድጓ የመጣ ነው። "ይኸውም የደመራ ለት እንደ አክሊል የሚጐነጐነውን የመስቀል አበባ ያሳያል፡ የመስከረምንም ያበባ ወር መኾን ያስረዳል። "
ተቀጸል ጽጌ: የበዓል ስም፡ በመስከረም ፲ኛ ቀን በያመቱ የሚከብር የመስቀል በዓል፡ ይኸውም የጌታችን ግማደ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ የመምጣቱ መታሰቢያ ነው። "እሱንም ያስመጡት ባ፲፬፻ ዓመተ ምሕረት የነበሩ ዐጤ ዳዊት ስለ ኾኑ በዓሉ ባማርኛ ዐጤ መስቀል ይባላል። " "ዐጪ ብለኸ ዐጤን እይ። "
ተቀጸል: ለቅርብ ወንድ የሚነገር ትእዛዝ አንቀጽ።
ተቀጻ (ተቀጽዐ): ተቈረጠ፣ ታፈፈ፣ ተቀፈፈ።
ተቀጽላ: ተቀጥላ፣ ቀጠለ።
ተቀጽላ: ገደረ።
ተቀፈረ: ቆመ፣ ተዘረጋ፣ ተቀቀረ።
ተቀፈቀፈ: ተበሳ፣ ተሰበረ፣ ተፈለፈለ፣ ተወለደ።
ተቀፈቀፈ: ተከረከረ።
ተቀፈደ: ተበሳ፣ ታሰረ።
ተቀፈደደ: በጥብቅ ታሰረ።
ተቀፈፈ: ተለመነ፡ "ራበኝ፣ ጠማኝ"
ተባለ።
ተቀፈፈ: ተቈረጠ፣ ተከረከመ፣ ተተካከለ።
ተቍለጨለጨ፡ ከብለል፡ ከብለል፡ አለ።
ተቍነጠነጠ፡ ተቅበጠበጠ፡ ተወዘወዘ።
ተቍነጥናጭ፡ የሚቍነጠነጥ፡ ተወዝዋዥ፡ ተቅበጥባጭ።
ተቃ፡ ተጋጨ፡ ጠጠሩ፡ ብይው።
ተቃለለ፡ (ቀለለ)፡ ተናቀ፡ ተዋረደ፡ (ተደራጊ)።
ተቃለለ፡ ተዋገደ፡ ተገባደደ፡ (ተደራራጊ)።
ተቃለበ፡ ተራዳ፡ ተማገበ።
ተቃለተ፡ ተራጠበ።
ተቃለደ፡ ተዋዛ፡ በቀልድ፡ ተነጋገረ።
ተቃለጠ፡ ተማታ፡ ተደባደበ፡ ደም፡ ተፋሰሰ።
ተቃላይ፡ የተቃለለ፡ የሚቃለል፡ ተዋራጅ። "ኑ፡ ባይ፡ አክባሪ፡ እንቢ፡ ባይ፡ ተቃላይ"፡ እንዲሉ። "በልማድ፡ ግን፡ ተቀላይ፡ ይሉታል፡ አያሠኝም። "
ተቃላጅ፡ የተቃለደ፡ የሚቃለድ፡ የሚዋዛ።
ተቃመ፡ (ተቅሕመ)፡ ተቓመ፡ ተገተመ፡ ተገፈረ፡ ተሰመሰመ።
ተቃመለ፡ ተቀማመለ፡ የመቅመል፡ ብድር፡ ተመላለሰ፡
ቅማልን፡ በመግደል፡ ተፈራረቀ፡ (አንዱ፡
የሌላውን፡ ቅማል፡ ገደለ)።
ተቃመሰ፡ ተላከፈ፡ ተዳረሰ።
ተቃመሰ፡ ተማታ።
ተቃሚ፡ (ተቃማሒ)፣ የሚቃማ፡ የሚሻማ፡ ተናጣቂ፡ ተሻሚ።
ተቃሚ፡ የሚቃማ፡ ቀማ።
ተቃሚ፡ የሚቃም።
ተቃማ፡ (ተቃምሐ)፡ ተናጠቀ፡ ተሻማ።
ተቃረ: ተሳለ፣ ተፋጩ፣ ተፈገፈገ።
ተቃረ: ጐመዠ፣ ሠየ፡ ተመኘ፣ ፈለገ (ከብት ዐምቦን፣ ወጥን)።
ተቃረመ: ተለቀመ፣ ተሰበሰበ።
ተቃረረ: ተቃዳ፣ ተለጠ።
ተቃረበ: ተናዳ፣ ተዋሰደ።
ተቃረበ: ተዳረሰ፣ ተዋጎደ።
ተቃረበ: ተጣጋ፣ ተገናኘ፡ እዳኛ ፊት ጐን ለጐን ተቋቋመ።
ተቃረነ: ተጣላ፣ ተዋጋ።
ተቃረጠ: ተቀራመተ፣ ተካፈለ።
ተቃራሚ: የሚቃርም፡
ተለቃሚ፣ ተሰብሰቢ።
ተቃራቢ: የሚቃረብ፡
ተገናኝ።
ተቃራኒ (ዎች): የተቃረነ፣ የሚቃረን፡ ተሰማሚነት የሌለው፣ ተጣይ፡ ክፉና ደግ፣ ሞትና ሕይወት፣ እውነትና ሐሰት፣ ጨለማና ብርሃን፣ ንፍገትና ቸርነት፣ ፍራትና ጕብዝና የመሰለው ኹሉ።
ተቃራኒነት: ተቃራኒ መኾን።
ተቃቀፈ (ተሓቀፈ): ተቋቈረ፡ ተደጋገፈ (እርስ በእርስ ማቀፍ)።
ተቃቃረ: ተሳሳለ፣ ተፋጩ፣ ተፈጋፈገ፡ ተመኛን፣ ተፈላለገ።
ተቃቃረ: ተሸካከረ፣ ተቀያየመ።
ተቃቃሪ: ተፈላላጊ፣ ተቀያያሚ።
ተቃቃፊ (ተሓቃፊ): የሚተቃቀፍ (የሚተቃቀፍ ሰው)።
ተቃበረ፡ ተዳፈነ፡ ዐፈር፡ ተማለሰ። መቃበር፡ መዳፈን።
ተቃበጠ፡ ተላፋ፡ ተቈናጠጠ፡ ተዳራ፡ ተቈላመመ።
ተቃበጥ፡ የቂጥኝ፡ ስም፡ በፈጋራ፡ ውስጥ፡ የሚወጣ፡
የቂጥኝ፡ ምላሽ፡ ወይም፡ ዕግል። ከሴት፡
ሴት፡ በመኼድ፡ ባለማረፍ፡ በቅብጠት፡ ስለሚመጣ፡ ተቃበጥ፡ ተባለ።
ተቃባ (ተቃብዐ)፡ ተዳለሰ።
ተቃባ፡ ደም፡ ተፋሰሰ፡ አበ፡ ደም፡ ተኳዃነ፡ ተጋደለ። ምሳሌ: "እከሌና፡ እከሌ፡ ደም፡ ተቃብተዋል"፡ እንዲሉ።
ተቃባጭ፡ የተቃበጠ፡ የሚቃበጥ፡ ልፊያ፡ ወዳድ።
ተቃና፡ (ተራትዐ)፡ ተሳላ፡ ተሳካ፡ ተስተካከለ።
ተቃና፡ (ተቃንአ)፡ ተመቃኘ።
ተቃኘ፡ ተሰለለ፡ ተጐበኘ፡ ታሠሠ።
ተቃኘ፡ ተቀነቀነ፡ ተዠመረ፡ ተባለ።
ተቃኘ፡ ጠበቀ፡ ላላ፡ ተሰማማ፡ ተቃና።
ተቃወመ፡ ተጣላ፡ ተከራከረ፡ ተገተረ።
ተቃወሰ፡ ተለያየ፡ ተሳሳተ፡ ተጣመመ፡ ተሳከረ፡ ተዋሰበ፡
ተዘባረቀ፡ ነገሩ።
ተቃዋሚ፡ የተቃወመ፡ የሚቃወም፡ ተከራካሪ።
ተቃዋሞች፡ የሚቃወሙ፡ ተማጋቾች።
ተቃዋሽ፡ የሚቃወስ፡ ተሳሳች።
ተቃደሰ፡ ተመሳገነ።
ተቃደደ፡ ተሠናጠቀ፡ ቅዳጅ፡ ተካፈለ፡ ተተናተነ።
ተቃዳጅ፡ የሚቃደድ፡ ተተናታኝ።
ተቃጠረ፡ ተቀጠረ፣ ቀጠሮ፡ አደረገ፡ ከሴት፡ ተነጋገረ።
ተቃጣ፡ ተደከረ፡ ተደቀነ፡ ተዘረጋ፡ ተዘጋጀ። ምሳሌ: "ከተቃጣ፡ መቅሠፍቱ፡ ከወረደ፡ ማቱ፡ ያ፡ ድናችኹ"፡ እንዲል፡ መራቂ፡ ሽማግሌ።
ተቃጣሪ፡ የተቃጠረ፡ የሚቃጠር።
ተቃጣይ፡ የሚቃጠል፡ ነዳጅ፡ ሞራ፡ ቅባኑግ፡ ጋዝ፡
ቤንዚን፡ ነፍት።
ተቃጨለ፡ ተመታ።
ተቃጨለ፡ ተማታ፡ ተጋጨ።
ተቃጪ፡ ተቋረጠ፡ ተጋደለ።
ተቈ፡ ተጸጸተ፡ ዐዘነ፡ ተቈረቈረ፡ ተቀየመ (መዝሙረ ዳዊት ፻፲፪፡ ፲)።
ተቈለለ፡ (ተጐለለ)፡ ተደረበ፡ ተነባበረ፡ ተከመረ፡ ተጐቸ።
ተቈለመመ፡ ተቀለሰ፡ ተዘለሰ፡ ተዘቀዘቀ፡ ጐበጠ፡ ተጠመዘዘ፡
ማዥራቱ፡ ወደ፡ ምድር፡ ማንቍርቱ፡ ወደ፡ ላይ፡ ኾነ።
ተቈለቈለ፡ ተዘቀዘቀ፡ ቍልቍል፡ ኼደ፡ ወረደ።
ተቈለፈ፡ ተሸፈነ፡ ተወሸለ።
ተቈለፈ፡ ተዘጋ፡ ተቀረቀረ፡ ተሸጐረ።
ተቈለፈ፡ ተያዘ፡ ታነቀ።
ተቈለፈ፡ ጐበጠ፡ ተቀለሰ፡ ታጠፈ።
ተቈላ፡ ተወዘወዘ፡ ተንቀሳቀሰ።
ተቈላ፡ ተገረፈ፡ ተመታ፡
ተቈላ፡ ታመሰ፡ ተንጣጣ፡ ተጠበሰ፡ በሰለ።
ተቈላለፈ፡ ተገነኛኘ፡ ተጣላ።
ተቈላላፊ፡ የሚቈላለፍ።
ተቈላመመ፡ ተቃለሰ፡ ተጠማዘዘ፡ ተዳራ።
ተቈላመጠ፡ ቍልምጫ፡ ተቀበለ።
ተቈላፊ፡ የሚቈለፍ፡ ተሸጓሪ።
ተቈልማሚ፡ የሚቈለመም፡ ፍሪዳ፡ ሙክት።
ተቈልቋይ፡ የሚቈለቈል፡ ወደ፡ አረኸ፡ የሚወርድ።
ተቈመደ፡ ተደረተ፡ ተደበደበ፡ ተዋሰበ፡ ተደፈነ።
ተቈመጠ፡ ቈሰለ፡ ተቈረጠ፡ ተጐመደ፡ ተጐረደ፡ ተበጠሰ፡
የእጁና፡ የእግሩ፡ ጣት፡ ታጣ፡ ዐጠረ፡ ዐጪር፡ ኾነ።
ተቈማመጠ፡ ተቈራረጠ፡ ተጐማመደ፡ ተበጣጠሰ።
ተቈሰቈሰ: ተነካ፣ ታወከ።
ተቈሰቈሰ: ተጠቀሰ፣ ተገፋ፣ ገባ፣ ተጨመረ።
ተቈሳቈሰ: ተዋጋ፣ ተጋደለ።
ተቈረመ: ተመታ፣ ተኰረኰመ።
ተቈረማመደ: ተጨባበጠ፣ ተኰረማመተ።
ተቈረሰ: ተፈተተ፣ ተገመሰ፣ ተገመደለ፣ ተቀረደደ፣ ተከፈለ፣ ተጐረመደ።
ተቈረረ: ተጫነ፣ ተደረበ፣ ተነባበረ።
ተቈረቈረ: ተማሰ፣ ተቈፈረ፣ ተበላ፣ ተነደለ፣ ተሸነቈረ።
ተቈረቈረ: ተዠመረ፣ ተመሠረተ።
ተቈረቈረ: ተደፈነ፣ ተመረገ፣ ተጠቀጠቀ።
ተቈረቈረ: ተጐረበጠ፣ ተነካ፣ ተወጋ፡ ቈሰለ።
ተቈረቈረ: ዐሰበ፣ ተጸጸተ፣ ዐዘነ፣ ተከዘ።
ተቈረበ: ተቀደሰ፡
መሥዋዕቱ ቀረበ።
ተቈረበለት: ተቀደሰለት፡
ስሙ ተጠራ።
ተቈረበተ: ተጐለበ፣ ተለጐመ።
ተቈረኘ: ታሰረ፣ ተጠመደ።
ተቈረኘተ: ተነፋ፣ ተጐሰረ።
ተቈረዘ: ተሸረበ፣ ተሸፈነ።
ተቈረጠ: ተለየ፣ ተወሰነ (ቀኑ)፡ "ዳግመኛም በገቢርነት ሲፈታ ጠጕሩን ተቈረጠ ይላል። "
ተቈረጠ: ተሰየፈ።
ተቈረጠ: ተጐረደ፣ ተጐመደ፣ ተመደመደ፣ ተሸለተ፣ ተበጠሰ፡ ጠፋ፣ ታጣ (ዘጸአት ፴፡
፴፫-፴፰፡ ፪ኛ ዜና መዋዕል ፯፡ ፲፰)።
ተቈረጠ: ዐለቀ፣ ተጨረሰ፣ ጐደለ፣ ተቀነሰ፣ ቆመ (ዘፍጥረት ፰፡
፪)። (ደመ ወዙ ተቈረጠበት - ተቈረጠለት) ;ተቀነሰበት ተወሰነለት ።
ተቈረጠመ: ተጐረደመ፣ ተሰበረ (በመንጋጋ ወፍጮነት ተከካ፣ ተፈጩ)፡ ተከረተሰ፣ ታኘከ፣ ተበላ።
ተቈረፀ: ተቈረጠ፡
ዐጪር ኾነ።
ተቈረፈ: ተጨረፈ፡
ተቀለበሰ፡ ተማሰ፡ ተከፈለ።
ተቈራ (ተቄርሐ፡ ተቀርዐ፡
ተኰርዐ): ተበጣ፣ ተፈቃ፣ ተጋረጠ፡ ተተኰሰ፣ ተነቀሰ፣ ታተመ፣ ተቀባ፣ ተመታ፣ ተቈረመ።
ተቈራረሰ: ተጎማመሰ፣ ተከፋፈለ።
ተቈራረጠ: ተበጣጠሰ፣ ተጐማመደ (ዳንኤል ፪፡
፭)።
ተቈራረጠ: ተጠላላ፣ ተለያየ።
ተቈራራጭ: የሚቈራረጥ።
ተቈራሽ: የሚቈረስ፡
ተፈታች።
ተቈራቈሰ: ተፋተነ፣ ተከራከረ፣ ተማከረ፣ ተዣመረ፣ ተማታ፣ ተዋጋ (፪ኛ ሳሙኤል ፪፡ ፲፬)።
ተቈራቋሽ (ሾች): የተቈራቈስ፣ የሚቈራቈስ፡ ተፋታኝ፣ ተማች፣ ተዋጊ (እስክندرን፣ ፉዝን የመሰለ)።
ተቈራኘ (ተደራጊና፡ ተደራራጊ): ከባለ ደም ጋራ በሰንሰለት ታሰረ፣ ተሳሰረ፣ ተጣመደ፣ ተያያዘ።
ተቈራኘ: ተጠጋ፣ ዐደረ፣ ተዋሐደ (ጋኔን ሰውን)።
ተቈራኚ: የሚቈራኝ።
ተቈራጭ: የሚቈረጥ፣ የሚበጠስ፣ የሚያልቅ፣ የሚቀነስ።
ተቈርቋሪ: የሚቈረቈር፡
ዐሳቢ፣ ዐዛኝ።
ተቈርቋሪነት: ተቈርቋሪ መኾን፡ ዐዛኝነት።
ተቈርጣሚ: የሚቈረጠም፣ የሚበላ።
ተቈሸበ: ተጀጀረ፡
መብላት ኣቃተው።
ተቈበረ፡ ተበሳጨ፡ ተበጣበጠ።
ተቈታቸ: በመብል፣ በመጠጥ ተወራረደ፡ እሰጥ አገባ ተባባለ።
ተቈታቺ: የተቈታቸ፣ የሚቈታች፡ ተወራራጅ።
ተቈነ፡ ተነቀለ፡ ተጐለጐለ፡ ዐረሙ።
ተቈነቈነ: ተከተፈ፣ ተተነተነ።
ተቈነነ: ተለካ፣ ተመጠነ፣ ተሰፈረ (ድርጎው)።
ተቈነነ: ተታታ፣ ተጐነጐነ፣ ተሠራ።
ተቈነነ: ተጀነነ፣ ኰራ፣ ተቋፈ።
ተቈነነ: ተፈጠነ፣ ተከበደ፣ ተደቀቀ።
ተቈነነ: ድርጎ ተቀበለ (መነኵሴው)።
ተቈነነ: ጐመለለ።
ተቈነዣዠ፡ ቍንዥናን፡ ተሰጣጠ፡ ጠጕርን፡ በመመሸጥና፡
ባለባበስ።
ተቈነደለ፡ ተጐነጐነ፡ ተቈነነ።
ተቈነደደ፡ ተገረፈ፡ ተለቈጠጠ።
ተቈነደደ፡ ደረቀ፡ ሻከረ፡ ዐጪር፡ ኾነ።
ተቈነጩ፡ ተለቀመ፡ ተገደለ፡ ቍንጫው።
ተቈነጸለ: ተቈረጠ፣ ተገነጠለ።
ተቈነጸለ: ተኰሰተረ፣ ተሰበረ።
ተቈናቈነ: ተሣሠተ፣ ተተናተነ፣ ተንቈጣቈጠ።
ተቈናቋኝ: የተቈናቈነ፣ የሚቈናቈን።
ተቈናኒ: የሚቈነን፣ ተፈጣና፣ የከበደ።
ተቈናኝ: የሚቈነን፡
ተጓዳጅ፣ ተቋፊ።
ተቈናደደ፡ ተጋረፈ።
ተቈናዳ፡ ተዛለለ፡ ተቃበጠ።
ተቈኘተ: ተታታ፣ ተሠባጠረ፣ ተዋሰበ።
ተቈዘረ፡ ተጐኘረ፡ ተነፋ፡ ተጐሰረ።
ተቈደሰ፡ ተቈረሰ፡ ተከፈለ።
ተቈጋ፡ ተገረፈ፡ ተቈነደደ፡ በቍግ።
ተቈጠረ፡ (ተቈጽረ)፡ ታሰበ፡ ተሰላ፡ ቍጥሩ፡ ታወቀ፡ ተነገረ፡
ከቍጥር፡ ገባ፡ (ግብረ፡
ሐዋርያት ፩፡ ፳፮። ሮሜ ፬፡ ፲፫፡ ፱)።
ተቈጠቈጠ፡ ተቈረጠ፡ ተመለመለ።
ተቈጠቈጠ፡ ተቈጠበ፡ ተቈነጠረ።
ተቈጠበ፡ ወጪው፡ አነሰ፡ ተቀመጠ፡ በዛ፡ በረከተ፡
ተረፈ፡ ተካበተ፡ ገንዘቡ።
ተቈጠጠ፡ ተኰሳ፡ ታራ።
ተቈጢታ፡ የምትቈጣ። ምሳሌ: "የፈሲታ፡ ተቈጢታ"፡ እንዲሉ።
ተቈጣ (ተቈጥዐ)፡ ገሠጸ፡ ዘለፈ፡ ወቀሠ፡ ገላመጠ። ምሳሌ: "የማይመቱት፡ ልጅ፡ ቢቈጡት፡ ያለቅሳል። "
ተቈጣ፡ ሖመጠጠ፡ ሸመጠረ።
ተቈጣ፡ ተናደደ፡ ጮኸ፡ ተበሳጨ፡ (ዘዳግም ፱፡ ፰)። (ተረት): "በባዳ፡ ቢቈጡ፡ በጨለማ፡ ቢያፈጡ። "
"ፌንጣ፡ ብትቈጣ፡
እግሯን፡ ጥላ፡ ኼደች። " (ሥሩ፡ ተቈጣ)፡ ዐበጠ፡ ተነፋ። (ፈጣሪ፡ ተቈጣ)፡ ዐባር፡ ቸነፈር፡ ሰይፍ፡ ማራኪ፡ አመጣ። ምሳሌ: "እግዜር፡ ሲቈጣ፡ በዝናም፡ ዐር፡ ያመጣ። "
ተቈጣ: ገሠጸ።
ተቈጣሪ፡ የሚቈጠር፡ የሚታሰብ፡ የሚሰላ።
ተቈጣቢ፡ የሚቈጠብ።
ተቈጣጠረ፡ ተያያዘ፡ ተሳሰረ።
ተቈጣጣ፡ መላልሶ፡ ተቈጣ፡ ገሣሠጸ።
ተቈጣጣሪነት፡ ተቈጣጣሪ፡ መኾን።
ተቈጥቋጭ፡ የሚቈጠቈጥ፡ የሚመለመል፡ ተመልማይ፡
ተቈጪ፡ የሚቈጣ፡ የሚገሥጽ።
ተቈጪነት፡ ተቈጪ፡ መኾን።
ተቈፈረ: ተማሰ፣ ተማረ፣ ተመነቀረ፣ ተኳተ፣ ጐደጐደ።
ተቈፈነነ: ታጠፈ፣ ተጨበጠ፣ ደረቀ።
ተቈፋሪ: የሚቈፈር።
ተቈፋጠነ: ተዘጋጀ፣ ተደራጀ፣ ፍጹም ኾነ፣ አማረ፣ ተጌጠ።
ተቅለሰለሰ፡ ደከመ፡ ሰለተ።
ተቅለሸለሸ፡ ሳይስማማ፡ ቀረ፡ መብል፡ መጠጡ፡ ታወከ፡
ሆዱ።
ተቅለበለበ፡ ተክለበለበ፡ ተስገበገበ፡ ቸኰለ፡ ቀለብ፡
ለመፈለግ።
ተቅለብላቢ፡ የሚቅለበለብ፡ ተስገብጋቢ።
ተቅለጠለጠ፡ ወዛ፡ ቅቤ፡ የተቀባ፡ መሰለ፡ ጭፍጭፍ፡
አለ።
(ግጥም)፡ "ምንም፡ ተቀባብተሽ፡ ብትቅለጠለዉ፡ ተማሪ፡
ውድ፡ ነው፡ የሱሪ፡ ጨው፡ አምጪ። "
ተቅላላ፡ ብዙ፡ ጊዜ፡ ቀላ፡ ቀያቀይ፡ ኾነ።
ተቅመደመደ፡ ተጐተተ፡ ዐቅም፡ ዐጣ፡ ተሽመደመደ።
ተቅመድማጅ፡ የሚቅመደመድ፡ ተጐታች።
ተቅማጣም፡ ቅዘናም፡ ተቅማጥ፡ የሚበዛበት፡ ሰው።
ተቅማጥ፡ ቅዘን፡ ሻታ፡ ብጥብጥ፡ ዐይነ፡ ምድር።
ተቅረፈረፈ: በብዙ ወገን ተቀረፈ፣ ተፍረከረከ።
ተቅረፈረፈ: ከመለዘብ ራቀ፣ ልስላሴ ዐጣ፣ ሞዠቀ።
ተቅበዘበዘ፡ ተቅነዘነዘ፡ ናወዘ፡ ባከነ፡ ዛበረ፡ ባዘነ፡
(ኤርምያስ ፲፬፡ ፱፡ ሆሴዕ ፱፡ ፲፯፡ ዓሞጽ ፰፡ ፲፪)።
ተቅበዝባዥ (ዦች)፡ የሚቅበዘበዝ፡ የሚናውዝ፡ ዘዋሪ፡ (ዘፍጥረት ፬፡ ፲፪)።
ተቅበጠበጠ፡ ተቍነጠነጠ፡ ተወራጨ፡ ተወዘወዘ፡ ተነቀነቀ፡
ተበሳጨ፡ ዐመለ፡ ቢስ፡ ኾነ። ምሳሌ: ዐመለኛ፡ በቅሎ፡ ሲቀመጡበት፡ ይቅበጠበጣል። ሀብታም፡ ሰው፡ በማእድ፡ ጊዜ፡ ይቅበጠበጣል።
ተቅበጥባጭ፡ የሚቅበጠበጥ፡ የሚወራጭ።
ተቅነዘነዘ፡ ተፍነዘነዘ፡ ተክለፈለፈ፡ ተንቀዠቀዠ።
ተቅዘመዘመ፡ ተወረወረ፡ ተምዘገዘገ፡ ተውዘገዘገ።
ተቅዘምዛሚ፡ የሚቅዘመዘም፡ በትር።
ተቅጠለጠለ፡ ተከታተለ፡ ተገናኘ።
ተቅጠልጣይ፡ የሚቅጠለጠል፡ ተከታታይ።
ተቅጨለጨለ፡ ብረትና፡ ብረት፡ ብርና፡ ብር፡ ተጋጨ።
ተቅጨልይ፡ የሚቅጨለጨል።
ተቆመ፡ መኼድ፡ መራመድ፡ ቀረ፡ ተተወ፡ ቀጥ፡ ተባለ።
ተቆመ፡ ተባለ፡ ደረሰ፡ ተዜመ። ምሳሌ: "ሳታቱ፡ ዋዜማው፡ ማሕሌቱ፡ ተቆመ"፡ እንዲሉ።
ተቋለፈ፡ ተገናኘ፡ ተያያዘ፡ አልላቀቅ፡ አለ።
ተቋላ፡ ተጋረፈ፡ ተታኰሰ፡ በጥይት፡ ተማታ።
ተቋላፊ፡ የሚቋለፍ ፣ ተያያዥ።
ተቋመጠ፡ በቈመጥ፡ ተማታ፡ ተጓመደ።
ተቋሰለ: ተማታ፣ ተዋጋ፣ ተፈናከተ፣ ተዳማ።
ተቋሰለ: ተቀያየመ፣ ተጣላ፣ ተባባሰ።
ተቋረሰ: ተፋተተ፣ ተካፈለ፣ ተሳተፈ።
ተቋረበ: አንድ መጐናጸፊያ ለብሶ (ባንድነት ቈረበ)፡ በቅዱስ ቍርባን ተማመነ።
ተቋረጠ: ሥራ ሊሠራ ተዋዋለ፡ ሥራውን ጨርሶ የሚያስረክብበትን ቀን ተነጋገረ (ተደራራጊ)።
ተቋረጠ: ቀረ (መምጣቱ፣ መሰጠቱ፣ መሠራቱ) (ተደራጊ)።
ተቋረጠ: ተባጠሰ።
ተቋረፈ: ተካፈለ፣ በላ፣ ተመገበ (ቋርፍን)።
ተቋረፈ: አጠለቀ፣ ተላበሰ (ዳባን)።
ተቋራጭ (ጮች): የተቋረጠ፣ የሚቋረጥ፡ ተዋዋይ፣ መሐንድስ። "ሥራ ተቋራጭ" እንዲሉ።
ተቋራጭነት: ተዋዋይነት።
ተቋቈረ (ተዓቈረ): ተቃቀፈ (ተቋቁሞ መቆም)።
ተቋቋ: ተቀፈቀፈ፣ ተፈለፈለ።
ተቋቋመ፡ ተነሣሣ፡ ተቀታተረ፡ ተከራከረ፡ ተወዳደረ፡
(መከተ)። ምሳሌ: "ምን፡ ታደርጋለኸ፡ ምን፡ ታመጣለኸ"፡ ተባባለ፡ (ኢያሱ ፲፡ ፰፡ የሐዋርያት ሥራ ፲፰፡ ፮)።
ተቋቋመ፡ ኾነ፡ በጀ፡ ተሳካ፡ ተቀናበረ።
ተቋቋሚ፡ የሚቋቋም፡ ባለጋራ፡ ሥራ፡ ትዳር።
ተቋቋሞች፡ ተከራካሮች፡ ተቃዋሞች፡ (ሮሜ ፲፫፡ ፪)።
ተቋደሰ፡ በገዛ፡ አፉ፡ ተመሰገነ። ተቃደሰን፡ አስተውል።
ተቋደሰ፡ ተቋረሰ፡ ተካፈለ፡ ተሳተፈ።
ተቋጠረ፡ (ተቈጽረ)፡ ተቀጠለ፡ ታሰረ፡ ገመዱ፡ ጠፍሩ፡ ድሩ።
ተቋጠረ፡ ተቈጣጠረ፡ ተሳሰበ፡ ተሳላ። "ኀጢአታቸውን፡ ይቋጠራቸዋል። ከዚያ፡ እቋጠራቸዋለኹ"፡ (ሆሴዕ ፱፡ ፱። ዮኤል ፫፡ ፪)።
ተቋጠረ፡ ተፀነሰ፡ ተረገዘ።
ተቋጠረ፡ ዐረግ፡ ተማዘዘ፡ "እከሌ፡ ቢወልድ፡ እከሌን"፡ ተባባለ።
ተቋጠረ፡ ዐተረ፡ ታቈረ፡ ጓጐለ።
ተቋጣ (ተቋጥዐ)፡ የቍጣ፡ ብድር፡ ተመላለሰ፡ ተጋሠጸ።
ተቋጣሪ፡ ተቈጣጣሪ፡ (ሮች)፡ የሚቈጣጠር፡ ተሳሳቢ፡ ስሌተኛ፡ (ኤርምያስ ፴፫፡ ፲፫)። "ቋንቋቸውን፡ የማያከብሩ፡ ሰዎች፡ ግን፡ ኮንትሮል፡
ይሉታል"። "ወደ፡ ፊት፡ ቋጠረ፡ ተቋጠረ፡ ብለኸ፡ ተቋጣሪን፡
አስተውል"።
ተቋጣሪ፡ የሚቋጠር፡ ተቀጣይ። "ጐንደሮች፡ ግን፡ ተቈጣጣሪን፡ ተቋጣሪ፡ ይሉታል። ቈጠረ፡ ተቋጠረ፡ ብለኸ፡ ተቋጣሪን፡ እይ። "
ተቋጥሮ፡ መቋጠር። "የተቋጥሮ፡ ዝምድና"፡ እንዲሉ።
ተቋጨ፡ ተጠመዘዘ፡ ከረረ፡ ተገመደ፡ ተጠመረ፡ ተደበለ፡
እንደ፡ ቈጫ፡ (ዔሊ)፡ ኾነ።
ተቋፈ: ተቈነነ፣ ዝንጀርኛ ኼደ፣ ተዋበ።
ተቋፊ: የሚቋፍ፡
ተቈናኝ።
ተበለሰሰ: ተለጠጠ (ተገለጠጠ)፡ ተነጠለ።
ተበለሻሸ: ተጣፋ፣ ተጠፋፋ።
ተበለቀጠ: ተገለጠ፣ ተከፈተ።
ተበለቃቀጠ: ተገላለጠ፣ ተከፋፈተ።
ተበለተ: ተለየ፣ ተነጠለ፡ ተቈረጠ፡ ድኻ (ብቸኛ) ሆነ፡ ብቻውን ቀረ።
ተበለጠ: አነሰ፡ ዐጪር ሆነ፡ ጐደለ፡ ተሞኘ፣ ተታለለ።
ተበለጠጠ: ተገለጠ (ተከፈተ)።
ተበላ (ተበልዐ): ተነከሰ፣ ተጐረሰ፣ ተገመጠ፣ ተመሳ፣ ታረበ፣ ተዋጠ፡ ተቃጠለ፣ ተቈረጠ። ግጥም: “እበላ ብዬ ተበላሁ፡ ምነው ሳልበላ በቀረሁ። ” ማስታወሻ: "ነብርን" እይ።
ተበላለጠ: ተራራቀ፡ ተላላቀ፡ ተራዘመ።
ተበላላ: ተነካከሰ፣ ተጋጋጠ፣ ተገማመጠ።
ተበላላጭ: የተበላለጠ፣ የሚበላለጥ (የሚራዘም)።
ተበላቀጠ: ተጋለጠ፣ ተከፈተ፡ ሴትኛ ኼደ (ተራመደ)።
ተበላጨ (ተፋለጸ): ተጋጨ፡ ተሠነጠቀ (ተተረተረ)፡ ተለያየ፡ ተሰበረ፡ ሱፋጭ ሆነ።
ተበሰ: ተጣላ፣ ተጠላላ (ተቋጣ፣ ተበጣበጠ)።
ተበሠረ (ተበሥረ): ተባለ፣ ተነገረ (ተወራ) የምሥራቹ።
ተበሰበሰ (በሰበሰ): ራሰ፣ ታሸ (ተገላበጠ)።
ተበሰከ (ተበትከ): ተበተከ (ተበጠሰ)።
ተበሳ: ተሰረሰረ፣ ተፈለፈለ (ተሸነቈረ፣ ተነደለ) (ኢዮብ ፴፥፲፯)።
ተበሳሰከ: ተበታተከ (ተበጣጠሰ)።
ተበሳሳ: ተሸንቋቈረ (ተነዳደለ)።
ተበሳበሰ: ተራራሰ፣ ተጋማ (ተበላሸሸ፣ ተበሻቀጠ፣ ተለዋወጠ)።
ተበሳጨ: ዐዘነ፣ ተቈጣ (ተናደደ)።
ተበረቀሰ: ተነደለ፣ ተበሳ (ተጣሰ)፡ ወደቀ (ፈረሰ)።
ተበረቃቀሰ: ተበታተነ፣ ተሰባበረ (ፈራረሰ)።
ተበረበረ (ተበርበረ): ተበዘበዘ፣ ተወረረ (ተዘረፈ)፡ ወሪሳ ተመታ (አገሩ)፡ ተገለበጠ (አኺዶው)።
ተበረታታ: ተጠነካከረ፣ ተደጋገፈ (ተዛዘነ፣ ተጋገዘ)።
ተበረኰተ: ተደፈነ (ተረመጠ)።
ተበረገደ: ተከፈተ፣ ተከፈለ፣ ተተረተረ (ተፈለጠ)።
ተበረገገ: ተፈነከተ፣ ተወለለ።
ተበራ: በራ። ማስታወሻ: ለተገብሮ ግስ ተደራጊ አንቀጽ የለውም።
ተበራረከ: ተመሰጋገነ፣ ተመራረቀ (ተቀዳደሰ)፡ ምርቃት ተሰጣጠ (ተቀባበለ)።
ተበራበረ: ተበዛበዘ፣ ተዛረፈ።
ተበራታ: ተጠናና (ተጠነካከረ)፡ “አይዞህ፣ አይዞህ” ተባባለ።
ተበራከተ: ተባዛ፣ ተራባ (ተዋለደ)።
ተበራየ: ተኼደ፣ ተረገጠ (ታሸ)።
ተበራገደ: ተከፋፈተ፣ ተለያየ (ተበላቀጠ)።
ተበራገገ (መሰባበር): ተፈናከተ፣ ተሳበረ።
ተበራገገ (መደንበር): ተደናገጠ፣ ተደናበረ።
ተበርባሪ: የሚበረበር (ተበዝባዥ)።
ተበሸረከ: ተበጠረቀ (ተቀደደ፣ ተሸረከተ)።
ተበሸራረከ: ተቀዳደደ (ተሸረካከተ)።
ተበሸተ: ታመመ (ተደወየ)።
ተበሺ: የሚበሳ (ሞፈር፣ ቀንበር)፡ የመሰለው ሁሉ።
ተበሻቀጠ: ተራራሰ (ተበሳበሰ)፡ ተነወረ (ተነቀፈ፣ ተሰደበ)፡ ረከሰ።
ተበቀለ: ዕዳ (ብድራት) ከፈለ፡ ቂምን (ደምን) አወጣ (መለሰ) (መሳፍንት ፮፥፴፩፣ ራእይ ፲፰፥፮፣ ፲፱፥፪)።
ተበቀበቀ: በጣም ታረሰ።
ተበቀተ: ተነዘነዘ፣ ተነተረከ (ተጨቀጨቀ)።
ተበቃች: የሚበቅት።
ተበቃይ (ዮች): ቂመኛ፣ ደም መላሽ (ዘዳግም ፲፱፥፮፣ ናሆም ፩፥፪)።
ተበበት: በብብት ተያዘ፡ ከብብት ገባ፣ ተከተተ።
ተበተበ: ዐመ፣ ደገመ። "አሰረ፡ ብለኸ፡ አሰርኩሽን፡ እይ።"
ተበተበ: ወረረ፣ ያዘ፣ ከበበ።
ተበተበተ: ተቦረቦረ (ተቦጠቦጠ፣ ተፈለፈለ)፡ ተበላ (ተቃጠለ፣ ተበገበገ)።
ተበተብ: ተብታባ። "ኰልታፋ፡ ለንባዳ፡ አፈ፡ እስር፡ ወንዱን፡ አንቺ፡ ሴቷን፡ አንተ፡ የሚል፡ መሣቂያ።"
ተበተብኩሽ: አሰርኩሽ፣ ተበተብኩሽ። "አሰረን፡ እይ።"
ተበተነ: ተዘራ (ተዘረዘረ፣ ተለየ፣ ተፈታ፣ ተነሰነሰ) (ኢሳይያስ ፲፩፥፲፪፣ ፴፫፥፫፣ ያዕቆብ ፩፥፲፪፣ ፲፫)።
ተበተከ (ተበትከ): ተበሰከ (ተቈረጠ)።
ተበታተነ: ተለያየ (ተሠራጨ፣ ተወራኘ)።
ተበታተከ: ተበሳሰከ (ተበጣጠሰ፣ ተቈራረጠ)።
ተበታኝ: የሚበተን (ጉም፣ ደመና፣ ጭስ፣ ዐመድ፣ ትቢያ፣ ዐቧራ፣ ሰራዊት)።
ተበከለ: አደፈ፣ ተበላሸ፣ ተኰለፈ፣ ጠፋ፣ ቈሸሸ።
ተበከረ (በከረ፣ ተበኵረ): በካር ሆነ፡ ወለደ። ምርቃት: “ጨምሪ፣ ጨምሪ፡ በወንድ ልጅ ተበከሪ። ”
ተበከረች (ተበኵረት): መዠመሪያ ወለደች።
ተበዘበዘ: ተዘረፈ፣ ተቀማ፣ ተበረበረ፡ ተበተነ፣ ባከነ (ኤርምያስ ፱፥፲፱፡ ኢዩኤል ፩፥፲)። ተረት: “ላም ሲበዘበዝ ጭራውን ያዝ”።
ተበዛበዘ: ተዛረፈ፣ ተቃማ፣ ተሻማ።
ተበዣገደ: ተሳሳተ፣ ተበላሸ (አእምሮው)።
ተበየነ: ተተቸ፣ ተፈረደ፣ ተለየ (ነገሩ፣ ሰው)። ተበየነበት: ተፈረደበት። ተበየነለት: ተፈረደለት።
ተበየደ: ተደፈነ፣ ተመረገ፣ ተቀባ።
ተበያየነ: ተፈራረደ፣ ተነጣጠረ፣ ተበጣጠረ።
ተበያጅ: የሚበየድ (ተደፋኝ፣ ቈርቈሮ፣ ታኒካ)።
ተበደለ: ታመፀ፣ ተገፋ። ተረት: “ድኻ ተበድሎ ማሩኝ ይላል ቶሎ”። ትርጉም: ተለወጠ፣ ተቀየረ።
ተበደረ (ተበድረ): ታረጠ፣ ተለቃ፣ ተሰጠ (ገንዘቡ)፡ ወይም ሰው ገንዘብ ወሰደ (ዘዳግም ፳፰፥፲፪)። ምሳሌ: “አትበደር፡ ባለህ እደር”።
ተበደገ: ተሠነጠቀ፣ ተለየ፣ ተከፈለ።
ተበዳሪ (ሮች): የተበደረ፣ የሚበደር (የተለቃ፣ የተዋሰ)፡ ልቆኛ (ምሳሌ ፳፱፥፲፫፡ ኢሳይያስ ፳፬፥፪፡ ሉቃስ ፯፥፵፩)።
ተበዳይ: የሚበደል (፪ኛ ቆሮንቶስ ፯፥፲፪)።
ተበዳደለ: ተማመፀ፣ ክፉ ተሣራ፡ ተጐዳዳ፣ ተጨቋቈነ።
ተበዳደረ (ተባደረ): ተሰጣጠ፣ ተቀባበለ (ብድርን)።
ተበጀ (በጀ): ተሠራ፣ ተዘጋጀ፡ ማለፊያ ሆነ፣ ተሻለ።
ተበጃጀ: ተሰማመረ፣ ተጊያጊያጠ።
ተበገረ (ደፋር): ተደፈረ።
ተበገረ: ተሞከረ፣ ተፈተነ፡ ተነደፈ፣ ተመጠነ፣ ተሣለ፣ ተመለከተ።
ተበገበገ: ተተኰሰ፣ ተቃጠለ፡ ተገረፈ፡ በብዙ ቈሰለ። ማስታወሻ: "ገበገበን" ተመልከት፡ የበገበገ ግልባጭ ነው።
ተበጋሪ: የሚበገር፣ የሚሞከር፣ የሚደፈር፣ የሚነድፍ።
ተበጠሰ: ተበተከ፣ ተበሰከ፡ ተቀነጠሰ።
ተበጠረ: ተነፈሰ፣ ተንገዋለለ፣ ተንቀረቀበ፡ ጥሩ ሆነ፡ ቆመ።
ተበጠረቀ: ተነደለ፣ ተበሳ፣ ተሸነቈረ።
ተበጠበጠ: ተጠመቀ፣ ተበረዘ፡ ተደረተ፣ ታመሰ፣ ደፈረሰ፡ ታወከ።
ተበጣ (ተበጥሐ): ተፈቃ፣ ተቈራ፣ ተተፈተፈ፣ ተሠነተረ (እንደ ሻንቅላ ቈዳ)።
ተበጣሪ: የሚበጠር (ጤፍ፣ ጐፈሬ)።
ተበጣሽ: የሚበጠስ፡ ተቈራጭ።
ተበጣበጠ: ተበሳጨ፣ ተናደደ፡ ተወዛወዘ።
ተበጣባጭ: የሚበጣበጥ፡ ተበሳጪ።
ተበጣጠሰ (ተቀማጠለ): ተንደላቀቀ፣ ተሞላቀቀ፣ ተቀማጠለ።
ተበጣጠሰ (ተቆረጠ): ተጐማመደ፣ ተቈራረጠ። ተረት: “ለጥምቀት ያኾልነ ቀሚስ ይበጣጠስ። ”
ተበጣጠሰ (ተበላሸ): ተበላሸ (የወተት)።
ተበጣጠሰ (ተጣላ): ተጣላ፣ ተለያየ።
ተበጣጠረ: ተገተ፣ ተከራከረ፣ ተነጣጠረ፣ ተነጋገረ፣ ተለያየ።
ተበጥባጭ: የሚበጠበጥ (ማር፣ ተልባ፣ ኑግ፣ ሰሊጥ፣ ሱፍ፣ መድኃኒት)።
ተበጨቀ (ተበትከ): ተበጠሰ፣ ተቈረጠ፣ ተበተከ፣ ተበሰከ።
ተበጫጨቀ: ተቈራረጠ፣ ተበጣጠሰ፣ ተቀዳደደ።
ተበጯ: የሚበጣ (ተሠንታሪ)፡ ዕብጠት።
ተባ (ተብዐ፣ ጠብዐ)፡ ጨከነ ጠነከረ (ወንድ ወጣው) ።
ተባ: ተሞረደ፣ ሰላ፣ ፈጠነ።
ተባለ (ተመታ): ተመታ፣ ተመደወተ።
ተባለ (ተብህለ): ተተነባ፣ ተወራ፣ ተነገረ፡ ተጠራ፣ ተሰየመ። ምሳሌ: “እሱ ማን ይባላል?”፣ “አንተ ማን ትባላለህ?” (ስሙ፣ ስምህ ማነው?)። ማስታወሻ: “ይባላል” (ይወራል)፡ “አይባልም” (አይወራም፣ አይነገርም)።
ተባለጠ: ተዛነፈ። ማስታወሻ: መጽሐፍ ግን "በበለጠ" ፈንታ "ተባለጠ" ይላል (፪ኛ ቆሮንቶስ ፪፥፲፩)።
ተባለጥ: ተዛነፍ።
ተባላ (ተባልዐ): ተናከሰ፣ ተጋመጠ፣ ተቧወቀ፣ ተዘባተረ (ነከሰ፣ በላ)። ማስታወሻ: መጽሐፍ ቅዱስ ግን “ተፋጀ” በማለት ፈንታ “ተባላ” ይላል (፩ኛ ሳሙኤል ፬፥፲፫)።
ተባሰለ: ተጣላ፣ ተማረረ (ተናሸረ)።
ተባረረ: ተሳደደ፣ ተሯሯጠ (ተቻኰለ) (፩ኛ ሳሙኤል ፬፥፲፪፣ ኢሳይያስ ፲፫፥፲፬)።
ተባረከ (መታረድ): ተከረከረ፣ ታረደ።
ተባረከ (ምስጋና): ተመሰገነ፣ ተመረቀ (ምርቃት ተቀበለ)።
ተባረከ (በረከት): ተቀደሰ፡ በዛ (በረከተ) ዘሩ።
ተባረከ (አምልኮ): መስቀል፣ የቄስ እጅ ሳመ (ተሳለመ)።
ተባረክ: “ዘር ይውጣልህ” (ምርቃት)።
ተባረደ/ተባረዘ/ተበራረዘ: ተዳከመ (የኃይል፣ የጕልበት፣ የመንፈሳዊ ሙቀት)።
ተባራሪ: የሚባረር፡ ጥይት፣ ኮሶ።
ተባራኪ: የሚባረክ (ተቀዳሽ፣ ተመራቂ)።
ተባቀ: ተባጠሰ።
ተባቀተ: ተነታረከ፣ ተጨቃጨቀ።
ተባቃ: ተዳከመ፡ ተሰላቸ፡ ተጣገበ፡ ልክ ተኳዃነ (ተካከለ)።
ተባበለ (ተሓበለ): ተካካደ፡ ተሸፋፈጠ፡ አልተማመነም።
ተባበለ: ተሽበለበለ፣ ተለመነ፣ ተቈላመጠ።
ተባበለች: በወርቅ እንክብል፣ በሸማ ጥቅል ተለመነች።
ተባበሰ: ተጠራረገ፣ ተወዛወዘ።
ተባበረ (ተኃበረ): ተመሳሰለ፡ ተዋሐደ፡ ተሰማማ፡ ተጋጠመ፡ ተሻረከ፡
አንድ ተኳዃነ (ማቴ፳፫፡ ፴፡ ግብ፡ ሐዋ፲፰፡ ፲፪)።
ተባባለ (ተማታ): ተማታ፣ ተደባደበ፣ ተዋጋ።
ተባባለ (ተባሀለ): ተነጋገረ፣ ተማገተ፣ ተከራከረ፣ ተማከረ (፩ኛ ሳሙኤል ፲፥፲፩፣ ኢዮብ ፪፥፲፩)። አገላለጽ: “ውረድ እንውረድ ተባባሉና፡ አስደበደቡት አፋፍ ቆሙና። ”
ተባባሰ (ተባአሰ): ተከፋፋ፣ ተጣላ (ተጠላላ፣ ተናሸረ፣ ተማረረ)። ተረት: “ቀን ለተባባሰው ማጭድ አታውሰው። ” “ያጨሽ ላያገባሽ፣ ከባልሽ ሆድ አትባባሽ። ”
ተባባሪ (ዎች): የተባበረ፡ የሚተባበር፡ ተሻራኪ።
ተባባሪነት: ተባባሪ መኾን።
ተባባተ (ተባሐተ): ተሳለፈ (ተዋጋ፣ ታገለ፣ ተጋደለ)፡ ተሸናነፈ።
ተባተበ: ደጋገመ።
ተባተበ: ጠማጠመ፣ መላልሶ አሰረ።
ተባቱ ዳንግሌ: ይባላል።
ተባት: ቍልፍ። "ወንዴ ቍልፍ ከሴቴው ጋራ የሚገጥም። ሴቴው የሐር ቋድ ነው።"
ተባት: ወንድ፣ ሴትን የሚያሶልድ።
ተባትና እንስት: ወንዴና ሴቴ (ደንጊያ፣ ዐፈር፣ ውሃ፣ ዕንጨት፣ እንስሳ፣ አውሬ፣ ወፍ፣ ሰው፣ ወይም ሌላ ፍጥረት) (ዘፍጥረት ፯፡ ፪። ማርቆስ ፲፡ ፮)።
ተባነነ (በነነ): ተበታተነ፡ ተጫጫሰ።
ተባነነ: ባከነ፡ ዶቄቱ።
ተባከለ: ተዳደፈ።
ተባዘተ (ባዘተ): ተነቀሰ፣ ባዘቶ ሆነ።
ተባዛ (ተባዝኀ): ተዋለደ፣ ተራባ፣ ተበራከተ (ዘፍጥረት ፩፥፳፰)።
ተባየነ: ተፋረደ።
ተባይ (ዮች): የሚበላ፣ የሚባላ (ትኋን፣ ቍን፣ ቅማል፣ ጕንዳን፣ ዘመሚት፣ ዝንጀሮ፣ ጦጣ፣ ዕሪያ፣ ዐሣማ)።
ተባደለ: ተለዋወጠ፣ ተቀያየረ፡ ተለያየ፣ ተጓዳ።
ተባደላ ሆነ: የተለዋወጠ፣ የተለያየ፣ የተራራቀ፣ የተፈራቀቀ ሆነ።
ተባደገ: ተለያየ፣ ተከፋፈለ፣ ተሠነጠቀ።
ተባጠሰ: ተቋረጠ።
ተባጣ (ተባጥሐ): ተሠናተረ።
ተቤተ: ታበየ፡ ኰራ።
ተቤዠ (ተቤዘወ): ተዋጀ፣ ተገዛ፡ ቤዛ አገኘ፣ ዳነ፡ ነጻ ወጣ፣ ተለቀቀ። ማስታወሻ: ልማዱ ግን "አዳነ" ነው። መጽሐፍም በጸሓፊ ምክንያት “በተቤዠ” ፈንታ "ተበጀ" ይላል፡ የስህተት ስህተት ነው (መዝሙር ፳፭፥፳፪፣ ፻፮፥፲፡ ኤርምያስ ፲፭፥፳፩፡ ሚክያስ ፬፥፲)።
ተብለጠለጠ: የበለጠ ድርብ፡ ላቅ ላቅ፣ ከበር ከበር አለ፡ ተትኰረኰረ።
ተብለጥላጭ: የተብለጠለጠ፣ የሚብለጠለጥ፡ ተትኰርኳሪ።
ተብለጨለጨ: የበለጨ ድርብ፡ ብልጭ ብልጭ፣ ቦግ ቦግ (ተግ ተግ) አለ።
ተብላላ: ተሳሳበ፣ ተዋዋደ። ምሳሌ: “ድፍድፉ ተብላልቷል። ”
ተብሰለሰለ: ተንገበገበ (ተትከነከነ)፡ በልብ ወጣ (ወረደ)።
ተብሰከሰከ: ተንበሸበሸ (ተቀማጠለ)።
ተብሰክሳኪ: የሚብሰከሰክ (የሚቀማጠል)።
ተብረቀረቀ: ተብለጨለጨ (ተፍለቀለቀ)፡ ብልጭ ብልጭ፣ ፍልቅ ፍልቅ አለ።
ተብረከረከ: ፈጽሞ ጕልበት ዐጣ (ተንቀጠቀጠ)።
ተብቃቃ (በቃ): ፈጽሞ በቃ፡ ልክ ሆነ (ተዳረሰ)።
ተብተብ አለ: ቸኰለ ።
ተብተከተከ: ተብሰከሰከ (ተቈራረጠ፣ ተበጣጠሰ)፡ አማረ (ሰመረ)፡ ዐይን ብቻ ሆነ።
ተብታቢ: የተበተበ፣ የሚተበትብ (አሳሪ፣ አስማተኛ፣ ጕንዳን፣ ዕከክ)።
ተብከነከነ: ግራ ቀኝ አየ፣ ተቅበዘበዘ።
ተብጠለጠለ (ተበጽለ): ፈጽሞ ተቀደደ፣ ተበተነ፡ እንደ ቀይ ሽንኵርት ተላጠ፣ ተመለጠ።
ተብጠሰጠሰ: ተንቀባረረ፡ ፈጽሞ ተበላሸ። ምሳሌ: “ወተት ሲሉት ማር፡ ማር ሲሉት ወተት ስጡኝ አለ፡ ባለጌ። ”
ተቦረቀ: ተዘለለ (ጮቤ ተመታ)። ሌላ ትርጉም: ተወረበ።
ተቦረቦረ (ተበረበረ): ተጐረጐረ (ባዶ ሆነ)።
ተቦቀረ: ተላጨ፣ ሳዱላ ሆነ።
ተቦተረፈ: ተነከሰ (ተቦጨቀ)፡ ሥጋው ተወሰደ።
ተቦካ (ቦካ): ተለወሰ፣ ታሸ፡ ተበጠበጠ፣ ረጥ ረጥ አለ (የሽሮ፣ የዶየ፣ የገንፎ)።
ተቦደሰ: ተገመሰ፣ ተጐመደ።
ተቦደነ (ልብስ): ተጠመረ፣ ተደረበ፣ ገጠመ።
ተቦደነ (እርሻ): በመቅን ታረሰ፣ ተተለመ።
ተቦደነ (ግንባታ): በድርብ ግቢት ላይ ሸብ ተደረገ፣ ተደገደገ።
ተቦጠለቀ: ወጣ። ምሳሌ: “ሕፃኑ ነገር ተቦጠለቀው” (ይቦጠለቀዋል) እንዲሉ።
ተቦጠቦጠ: ተበተበተ፣ ተጐረጐረ፡ ውስጥ ውስጡን ተበላ።
ተቦጨቀ (ተበጨቀ): ተባዘተ፡ ታወደ፣ ተቈረጠ፡ ታማ።
ተቦጫቂ: የሚቦጨቅ፡ ታጅ።
ተቦጫጨቀ: ተቀዳደደ፣ ተበጣጠሰ።
ተቧደነ: ተጣመረ፣ ተያያዘ፣ ተቀናጀ፣ ተጋጠመ፡ አንዳንድ ወገን ሆነ።
ተቧዳኝ: የሚቧደን።
ተቧጠጠ: ተጠጠ፣ ተጨረ።
ተቧጣጭ: የሚቧጠጥ (ጕረሮ፣ ለግዳ፣ ቅምሖ)።
ተቧጨረ: ተወረ፣ ተጫረ፡ ተሰነዘረ፡ ታከከ።
ተቧጨቀ: ተናከሰ፣ ተባላ፣ ተናጠቀ።
ተተለመ: በበሽታ ተያዘ፣ ተለከፈ።
ተተለመ: ተዠመረ፣ ታረሰ፣ ተቦደነ፣ ተገመሰ።
ተተለተለ: ተቀደደ፣ ተሠነጠቀ፣ ተበጣ።
ተተለተለ: ተፈታ፣ ተተረተረ፣ ተመዘዘ፣ ተለየ፣ ወጣ።
ተተላሚ: የሚተለም፣ ተዠማሪ።
ተተመተመ: ተመታ፣ ተለተመ፣ ተገጨ፣ ተወጛ።
ተተመተመ: ተረመደ።
ተተመተመ: ተደመደመ።
ተተማተመ: ተላተመ፣ ተጋጨ፣ ተዋጋ።
ተተማታሚ: የሚተማተም፣ ተላታሚ (አውራ በግ)።
ተተረማመሰ: ተበጣበጠ፣ ተመሰቃቀለ።
ተተረረ: ተሠነጠቀ፣ ተከፈለ።
ተተረበ: ተቀለደ፣ ተፌዘ።
ተተረበ: ተነደፈ፣ ተወጋ።
ተተረተ: ተመሰለ፣ ተነገረ፣ ተወጋ።
ተተረተረ)፡ ተንተረተረ፣ ተረጠረጠ፣ ተሶመሶመ። "ነገር፡ ኦወሸከ፡ እዚያም፡ እዚያም፡ አለ፡ ማለት፡ ነው።"
ተተረተረ: ተነጠቀ፣ ተፈነከተ (፩ኛ ነገሥት፡ ፲፫፡ ፭)።
ተተረተረ: ተፈታ፣ ተለየ።
ተተረተረ: ዕቃ ወዘተ ከቦታው ወጥቶ ተበታተነ፣ ተጨፈለቀ። ምሳሌ: ዕዳሪው ተተረተረ። የሰውነት ክፍል ቀጥ አለ፣ ቀና አለ። ነገር ተዘረዘረ፣ ተነጠለ።
ተተረከ: ተወጋ፣ ተነገረ፣ ተወራ።
ተተረከሰ: ተቀለሰ፣ ጐበጠ።
ተተረከከ: ተጠረቀቀ፣ ተሠነጠቀ፣ ተፈነከተ።
ተተረኰሰ: ተሰበረ፣ ተኰሰተረ፣ ለማ።
ተተረጐመ: ተገለበጠ፣ ተመለሰ፣ ተፈታ፣ ተገለጠ።
ተተራተረ: ተፈናከተ፣ ተበታተነ።
ተተራከከ: ተፈናከተ።
ተተራጐመ: ተፋታ ርስ በርስ።
ተተራጐመ: ተፋታ ርስ በርስ።
ተተርታሪ: የሚተረትር፣ ተሠንጣቂ።
ተተበተበ: ተወረረ፣ ተያዘ፣ ተከበበ (ሥጋው፣ ሰውነቱ)።
ተተበተበ: ተጠመጠመ፣ ታሰረ (ማሰሪያው፣ ሰውየው)።
ተተበተበ: ታዘመ፣ ተደገመ (አስማቱ)።
ተተባተበ: ተጠላለፈ፣ ተጠማጠመ፣ ተሳሰረ፣ ተያያዘ፣ ተወሳሰበ (ዕብራውያን ፲፪፡ ፩)።
ተተብታቢ: የሚተበተብ።
ተተቸ: ታተተ፣ ተባለ፣ ተነገረ። (ትቹ)
ተተነባ: ተነገረ፣ ተባለ፣ ተወራ (አስቀድሞ)።
ተተነተነ: ተለየ፣ ተከፈለ፣ ተመደበ፣ ተደለደለ፣ ተቈነነ፣ ታደለ።
ተተነኰለ: ኾነ፣ ተደረገ (ተንኰል)። ልማዱ ግን እንደ መዠመሪያው አድራጊነት ነው (ዘፍጥረት ፴፩፡ ፯። ዘዳግም ፲፱፡ ፲፩)።
ተተነኰሰ: ጥቂት ተመታ፣ ላመል ተለኰፈ፣ ተነካ።
ተተነኳኰለ: ተንኰል ተሠራራ፣ ተጐዳዳ።
ተተነኳኳይ: የተተነኳኰለ፣ የሚተነኳኰል።
ተተነፈሰ: ጥቂት ተባለ፡ ተነገረ (ቃሉ)፡ ወጣ (ትንፋሹ) (ኢዮ፲፭፡ ፪)።
ተተናተነ: ተጋራ፣ ተካፈለ፣ ተከፋፈለ፣ ተዳረሰ፣ ተዳደለ።
ተተናታኝ: የሚተናተን፣ ተካፋይ።
ተተናኰለ: ተጣላ፣ ጐዳ፣ ተጠናወተ።
ተተናኰሰ: ተላኰፈ፣ ተናካ።
ተተናኳይ: የተተናኰለ፣ የሚተናኰል፣ ተናዋች።
ተተናኳይነት: ተተናኳይ መኾን።
ተተናፈሰ: ትንፋሽ ተቀባበለ፡ እፍ ተባባለ (ተደራራጊ) ።
ተተናፈሰ: ወዳፍንጫው ነፋስን አግብቶ አወጣ (አድራጊ)።
ተተኛኛ: ተዋደቀ፣ በግብረ ሥጋ ተገነኛኘ፣ ተዋወቀ።
ተተከለ: ቤስት ተቀበለ።
ተተከለ: ተመሠረተ፣ ጸና (ለማ)።
ተተከለ: ተቸከለ፣ ተቀሰቀሰ፣ ተከሰመ፣ ተሻጠ፣ ገባ፣ ተሸጐጠ፣ ቆመ (፩ኛ ሳሙኤል፡ ፲፯፡ ፵፱። ሕዝቅኤል ፲፱፡ ፲፫። ሉቃስ ፲፯፡ ፯። ሮሜ ፯፡ ፭)።
ተተከተከ: ተጠቀጠቀ፣ ተወጋ፣ ተበላ።
ተተኪ: የሚተካ፣ የሚወከል፣ ተወካይ።
ተተኪነት: ተወካይነት።
ተተካ: ተወከለ፣ ተሰጠ፣ ተከፈለ፣ ተረጠበ (ስጦታው ለሰው፣ ሰውየው ስጦታን)።
ተተካከለ: ተደላደለ፣ ተበጃጀ፣ ተዘጋጀ፡ ተወዳደረ።
ተተካይ: የሚተከል፣ ቀዋሚ።
ተተኰሰ: መላ ተፈጸመ፣ ተጨረሰ።
ተተኰሰ: ተለኰሰ፣ ተለበለበ፣ ተቃጠለ (ኢሳይያስ ፵፫፡ ፪)።
ተተኰሰ: ተላከከ፣ ተገጠመ፣ ተቀባ።
ተተኰሰ: ተካሰ፣ ተቀበለ።
ተተኰሰ: ተዳመጠ፣ ቀጥ አለ።
ተተኰሰ: ጮኸ፣ ተሰማ (ጥይቱ)።
ተተኰረ: ታየ፣ ዐይን ተጣለበት።
ተተኳኰሰ: ተለኳኰሰ፣ ተለባለበ።
ተተኳኰረ: ተፋጠጠ፣ በትኰራ ተያየ።
ተተወ: ተለቀቀ፣ ተፈታ፣ ተገደፈ፣ ተጣለ፣ ቀረ፣ ተማረ (ነህምያ ፮፡ ፱። ኢሳይያስ ፳፯፡ ፲)።
ተተገ: በክፋይ መታ፣ ወጋ፣ አቃጠለ። (ተገተገን እይ)
ተተገተገ: ተገረፈ፣ ተተኰሰ።
ተተገነ: ተጠጋ፣ ተጠለለ (የሰው)።
ተተገነ: ታጠረ፣ ተቀጠረ፣ ተጀጐለ፣ ተከለለ፣ ታቀበ (የተክል ቦታ በካብና በንጨት)።
ተተፈተፈ: ተበጣ፣ ተፈቃ፣ ተቈራ፣ ተቈረጠ፣ ተሠነተረ።
ተተፋ: ተቀረሸ፣ ወጣ፣ ተመለሰ።
ተታለለ: ተደለለ፣ ተሸነገለ፣ ተሞኘ፣ ቄለ ደነቈረ፣ ዘነጋ (ኤርምያስ ፳፡ ፯። ፩ኛ ጢሞቴዎስ፡ ፪፡ ፲፬)።
ተታለመ: ተዣመረ።
ተታላይ: የሚታለል፣ የሚደለል፣ ተደላይ።
ተታላይነት: ተታላይ መኾን፣ ሞኝነት፣ ንዝህላልነት።
ተታታ: ተጠፈረ፣ ተጠለፈ፣ ተዋሰበ፣ ተያያዘ።
ተታከለ: ርስት ተሰጣጠ፣ ተቀባበለ።
ተታከለ: ተቻከለ።
ተታኰሰ: በጥይት፣ በእሳት ተማታ፣ ተዋጋ፣ ተቋላ፣ ተጣበሰ።
ተታኰሰ: ተላኰሰ።
ተታጊ: የተተገ፣ የሚተትግ፣ ወጊ፣ አቃጣይ።
ተታጋ: ትጋትን ተሰጣጠ።
ተትመሰመሰ: ተድበሰበሰ፣ ተድመሰመሰ፣ ተርበተበተ፣ መለስ ቀለስ አለ።
ተትመከመከ: ተድበሰበሰ። "ነገሩ እሳት ጨሶ ሳይነድ እንደ መቅረት።"
ተትረፈረፈ: የትርፍ ትርፍ ኾነ።
ተትከነከነ: ተብሰለሰለ፣ ተናደደ።
ተትጐለጐለ፡ እንደ ጉም በዝቶ ተጣቦ ወጣ (የጪስ፣ የላበት)።
ተቶረበ: ተሰፋ፣ ተወሰወሰ፣ ተሸደሸደ፣ ተሸለለ፣ ተሸከሸከ።
ተቸ: ዐተተ፣ የነገር ማስረጃ አመጣ። "ብዙ ቢተቹ ይሰለቹ" (ተረት)።
ተቸለሰ: ተከነበለ፣ ተገለበጠ፣ ተደፋ፣ ተፈሰሰ። በማዥራት ተኛ፣ ተዝለሰለሰ።
ተቸመቸመ: ተቸረቸመ፣ ጠረሰ፣ ተደመደመ። ተሠራ፣ ተዘራ፣ ቆመ፣ በዛ።
ተቸሰረ: ተረፈቀ፣ ተደነሰረ።
ተቸረቸመ: ተሰበረ፣ ተሸረፈ፣ ጠረሰ፣ ታጠፈ።
ተቸረቸረ: ተበተነ፣ ተተነተነ፣ ተዘረዘረ፣ ተሸጠ።
ተቸረቸፈ: የሙ ለውጥ ነው።
ተቸበቸበ: ተጣለ፣ ተመታ፣ ተደበደበ፣ ተወቃ። ተሸጠ፣ ተለወጠ። ታረደ፣ ተቈረጠ። ተጨበጨበ።
ተቸቸረ: ተገፈረ፣ ተቃመ።
ተቸነነ: ተጀነነ፣ ኰራ፣ ተቈነነ፣ ተዓደደ። ተወነገ፣ ተወሰጠ።
ተቸነከረ: ተሰመረ፣ ተወጋ፣ ተመታ፣ ተጣበቀ (መክ ፲፪፡ ፲፩)።
ተቸናኝ: የሚቸነን፣ ተጀናኝ፣ ተጓዳጅ።
ተቸከለ: ተተከለ፣ ተቀበቀበ፣ እመሬት ገባ።
ተቸኰለ: "መንገደኛው ተ(ከ)ቸኰለ ቶሎ ይኺድ" ማለት ነው። ('ተ' በ 'ከ' ሞክሼነት የተነገረ ዐቢይ እገባብ ነው እንጂ የመደረግ ልማድ አለመኾኑን አስተውል)።
ተቸገረ: ተጨነቀ፣ ተራበ፣ ተጠማ፣ ታረዘ፣ ዐጣ፣ ነጣ፣ ደኸየ፣ ግራ ገባው (ግብ ሐዋ ፲፡ ፲፯፡ ያዕ ፬፡ ፱)።
ተቸጋሪ: የሚቸገር፣ ተጨናቂ።
ተቸፈነነ: ተጀነነ፣ ኰራ፣ ቀለለ (ትእዛዝን)።
ተቸፈገ: ተፈተ፣ ተጠቀጠቀ።
ተቸፋቸፈ: ተጨቃጨቀ፣ ተነዛነዘ።
ተቺ: የተቸ፣ የሚተች፣ ሐተተኛ።
ተቺነት: ተቺ መሆን።
ተቻለ: ተወሰነ፣ ተጨረሰ። ተመቸ፣ ኾነ፣ ደላ፣ ተደረገ። ምሳሌ: "ዛሬ አይቻለኝም"፣ "በተቻለኝ ጊዜ እመጣለኹ"።
ተቻቻለ: ተሸካከመ፣ ተወሳሰነ፣ ተጣወረ፣ ተጋገሠ (ኤፌ ፬፡ ፪)።
ተቻቻረ: ችሮታን ተቀባበለ።
ተቻቻይ: የሚቻቻል፣ ተጣዋሪ። (የቅኔ) አገባብ።
ተቻቻይነት: ተቻቻይ መኾን።
ተቻኰለ: ተጣደፈ፣ ተፋጠነ፣ ተጐተጐተ።
ተቻኳይ: የሚቻኰል፣ ተጣዳፊ፣ ተፋጣኝ።
ተቻይ: የሚቻል።
ተነ: (ከነ) መነሻነትንና አንድነትን የሚያሳይ ደቂቅ አገባብ ኹኖ ከነ በገባበት ይገባል ።
ተነኋረጠ: ተነፋነፈ።
ተነሰነሰ: ተበተነ፡ ተዘራ፡ ተጐዘጐዘ።
ተነሰነሰ: ተወዘወዘ፡ ተንቀሳቀሰ።
ተነሣ (ተነሥአ): ተከለከለ፣ ራቀ፣ ተወሰደ፣ ተገለለ። "ዳዊት ኦርዮን ባስገደለ ጊዜ ረድኤት ተነሣው"።
ተነሣ (ተንሥአ): አፈፍ፣ ብድግ፣ ኩፍ አለ፡ ቆመ፣ ነወር አለ፣ ስፍራውን ተወ። "የሰውን ልጅ ተነሣ አይሉም፣ እስኪነሣ ይጠብቃሉ"።
ተነሣ: ብድግ አለ፡ ነሣ ።
ተነሣ: ተቀነሰ፣ ጐደለ።
ተነሣ: ተንሳፈፈ፣ ተንካፈፈ።
ተነሣ: ተወሣ፣ ተነገረ። (እሳት ተነሣ): ቃጠሎ ሆነ። (ነፋስ ተነሣ): በኀይል ነፈሰ፣ ዐቧራው ቀጥ አለ። (ጾር ተነሣበት): ፍትወት ያዘው፣ አስጨነቀው። "ድልን" አስተውል፣ "ደላ (ድሕለ)"።
ተነሣ: ተዠመረ፣ ተወጠነ።
ተነሣ: ከበረ፣ ገነነ።
ተነሣ: ወጣ፣ ለቀቀ።
ተነሣ: ዳነ፣ ተፈወሰ። "ታሞ የተነሣ፡ እግዜርን ረሳ"።
ተነሣለት: ብድግ አለለት።
ተነሣለት: ተቀነሰለት።
ተነሣሣ (በክፉ፡ ተነሣ፣ ተገሰለ): ተቋቋመ።
ተነሣሣ: ተከላከለ።
ተነሣሣ: ተያያዘ፣ ተጨባበጠ።
"እጅ"፣ "ተነሣሣ" እንዲሉ።
ተነሣሽ: የሚነሣሣ፡ ተቋቋሚ።
ተነረተ: ተመታ፡ ተጠዘለ።
ተነረተ: ተነፋ፡ ተቀበተተ።
ተነሸጠ: ታሰበ፡ ተነሣሣ።
ተነሽ (ሺ): ብድግ በይ።
ተነሽ: የሚነሣ፣ ብድግ የሚል (ሰው፣ ዕቃ፣ ከብት)፡ በኀይለ ቃል የሚነገር ንባብ።
ተነሽ: ጐዳይ፣ ተቀናሽ (ነገር፣ ገንዘብ፣ ቍጥር)።
ተነሽናሽ: የሚነሰነስ፡ ተበታኝ (ያን እንገባን ዐጡንባር)።
ተነቀለ: ተመዘዘ፡ ነገለ፡ ተመነገለ፡ ወጣ፡ ወለቀ (ሕዝ፲፱፡ ፲፪፣ ሉቃ፲፯፡ ፮)።
ተነቀለ: ከርስቱ ተወገደ።
ተነቀሰ: ተመሰከረ።
ተነቀሰ: ተሸለመ፡ አማረ።
ተነቀሰ: ተቀነሰ፡ ጐደለ።
ተነቀሰ: ተበጠረ፡ ተለየ፡ ጠራ።
ተነቀሰ: ተነቀለ፡ ወጣ። "ነገር በነገር ይጠቀሳል፡ እሾኸ በሾኸ ይነቀሳል"።
ተነቀሰ: ተጠቀጠቀ፡ ተወጋ፡ ተወቀረ፡ ጠቈረ። (ተረት) "አላንድ የላት ጥርስ፣ በዘነዘና ትነቀስ"።
ተነቀረ: ተጠጠ፡ ተጨለጠ።
ተነቀበ: ተበሳ፡ ተነደለ፡ ተሰፋ።
ተነቀተ: ተከረተፈ፡ ተቀቀለ (እንቀት ኾነ)።
ተነቀነቀ: ተቀሰቀሰ፡ ተወዘወዘ (ኢሳ፳፬፡ ፳፣ ሉቃ፮፡ ፴፰)።
ተነቀፈ: ተሰደበ፡ ተናቀ፡ ተጸየፈ፡ ተነወረ፡ ተወቀሠ፡
ተዘለፈ።
ተነቃቀለ: ተመዛዘዘ፡ ተመነጋገለ፡ ወለላቀ።
ተነቃቀሰ: ተመሰካከረ።
ተነቃቀሰ: ተነቃቀለ።
ተነቃቀሰ: ተጠቃጠቀ (የመናቀስ ብድር)፡ ተመላለሰ፡ ተጠቋቈረ።
ተነቃቀፈ: ተሰዳደበ፡ ተናናቀ።
ተነቃቃፊ: የሚነቃቀፍ፡ የሚናናቅ።
ተነቃነቀ: ተንጠለጠለ (አዘበዘበ፣ አረገዘ)፣ ግንቡ፣ ካቡ። "ርግጠኛው ትርጓሜ ግን ነቀነቀ፣ አንጠለጠለ ነው።"
ተነቃናቂ: የተነቃነቀ፡ የሚነቃነቅ፡ ተንቀሳቃሽ።
ተነቃይ: የሚነቀል፡ ተመዛዥ።
ተነቃፊ: የሚነቀፍ፡ ተሰዳቢ።
ተነቈረ: ተነከሰ፡ ተወጋ፡ ተበሳ፡ ወጣ።
ተነቅናቂ: የሚነቀነቅ፡ ተቀስቃሽ።
ተነበበ: ተነገረ (ንባቡ፣ መጻፉ፣ ሕጉ)።
ተነበዘ: ልብ አጣ፣ ተለወጠ።
ተነበዘ: መነቸከ፣ ተመረዘ።
ተነበዘ: ተሰለበ፣ ተቈረጠ።
ተነበዘ: ተቀማ፣ ተገፈፈ።
ተነበየ: ተነባ፡ ትንቢት ተናገረ። "እርሳቸውም ይነበያሉ"። "ነፈሰ" ብለኸ "ተነፈሰን" እይ፡ አካኼዱ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
ተነበየ: ትንቢት ተናገረ (ነበየ፣ ነባ)።
ተነባ (ነባ): ተለቀሰ፣ እንባው ፈሰሰ።
ተነባ: ተነበየ፡ ትንቢት ተናገረ፡ (ነበየ፣ ነባ) ።
ተነባረረ: ባጕል ድምፅ ጮኸ፣ አለቀሰ፣ ተንዠባረረ።
ተነባበረ: ተደራረበ፣ ተረዳዳ፣ ተገጣጠመ።
ተነባባሪ: የሚነባበር፣ የሚደራረብ። "ዐባሪ ተነባባሪ" እንዲሉ።
ተነባባሪነት: ተነባባሪ መሆን።
ተነባነበ: ተነዛነዘ፣ ተለፋለፈ።
ተነባጀለ: ተነኋረጠ።
ተነተረከ: ተነዘነዘ፡ ተጨቀጨቀ፡ ተበቀተ።
ተነተነ: ለኰፈ።
ተነታረከ: ተነዛነዘ፡ ተጨቃጨቀ፡ ተባቀተ።
ተነትራኪ፡ የተነተረከ፣ የሚነተርክ ።
ተነነ (ተኒን፣ ተነ) ፡ በነነ ጨሰተበተነ ።
ተነነፍሱ: "ሳይሞት በሕይወት ሳለ የሰከረው ዓሣ ተነነፍሱ ተያዘ።"
ተነከሌ: ርሱ ተነከሌ አያንስም።
ተነከሰ: ተዘነተረ፣ ተቦጨቀ፣ ተበላ፣ ተዘከዘከ።
ተነከረ (ተነክረ፣ ተጠምዐ): ተዘፈቀ፣ ተደፈቀ፣ ተዘፈዘፈ፡ አከል ገባ፣ ታለለ፣ ራሰ።
ተነከረ: ተደነቀ።
ተነከረ: ተጠመቀ (ሰውየው በጠበል፣ በመድኀኒት)።
ተነከረ: እውሃ ገባ፣ ነከረ።
ተነከረ: ጠነከረ።
ተነከረ: ጠነከረ።
ተነከታቴው: ተነመጨረሻው።
ተነከነከ: ተበላ።
ተነካ: ተዳበሰ፣ ተዳሰሰ፣ ድል ተባለ፣ ተገጠበ፣ ቈሰለ፣ ተበደለ። (ተረት): "ያልተነካ ግልግል ያውቃል። "
ተነካሪ: የሚነከር (ልጥ፣ ገመድ፡ ዐተር፣ ባቄላ፣ ሽንብራ)።
ተነካከሰ: ተዘነታተረ፣ ተቦጫጨቀ።
ተነካኪ: የሚነካካ።
ተነካካ: ተላላሰ (ዶቄቱ)፡ ተጠላላ።
ተነኰለ: እጠፋ።
ተነኰሰ: በቀላል መታ፣ ነካ፣ ለኰፈ።
ተነኰረ: ተገለበጠ፣ በሰለ፣ እንኩሮ ሆነ።
ተነኰተ (ነኰተ): ተቃጠለ፣ ከነእንቡጡ ተቈላ፣ በሰለ።
ተነኳኰሰ: ለኳኰፈ።
ተነዃለለ: ተደናቈረ፡ የሞኝ አነጋገር ተናገረ።
ተነወረ: ተደፈረ፣ ነውረኛ ሆነ፣ ተባለ፣ ስሙ ጠፋ (ኢሳ ፲፫፡ ፲፮፣ ሚክ ፫፡ ፯)።
ተነዋሪ: የሚነወር።
ተነዋወረ: ነውርን ተዘካዘከ።
ተነዘረ: ተመታ፣ ጮኸ።
ተነዘረ: ተወረወረ፣ ተነደፈ።
ተነዘረ: ተጸፋ፣ ሾረ፣ ተፈተለ።
ተነዘነዘ: ተጨቀጨቀ፣ ተነተረከ።
ተነዛ: ተሠራጩ (መርዙ)።
ተነዛ: ተረጨ፣ ተፈነጠቀ፣ ተበተነ። (ተረት):
"ጌታ ያዛል ውሃ ይነዛል (ይረጫል)"።
ተነዛነዘ: ተጨቃጨቀ፣ ተነታረከ።
ተነዛናዥ: የሚነዛነዝ፡ ተጨቃጫቂ።
ተነደለ (ተነድለ): ተፈለፈለ፣ ተሸረሸረ፣ ተበሳ፣ ተሸነቈረ፣ ተቀደደ፣ ፈረሰ።
ተነደቀ: ተገነባ፣ ተናሰ።
ተነደፈ: ተለካ፣ ተበገረ።
ተነደፈ: ተበተነ፡ ተጠዘጠዘ፣ ተወጋ (፩ነገ ፲፩፡ ፩)። "ዳዊት ቤርሳቤሕን ባየ ጊዜ በሐጸ ዝሙት ተነደፈ። "
ተነዳ: ተቀረበ፣ ተወሰደ፣ ኼደ (፪ዜና ፮፡ ፴፰፣ ምሳ ፯፡ ፳፪፣ ኢሳ ፰፡ ፲፩፣ ሉቃ ፰፡ ፳፱፣ ግብ ሐዋ ፰፡ ፴፪፣ ያዕ ፫፡ ፬)። (ያቶ እከሌ፡ መንጋ በወንጭፍ ይነዳል): እጅግ በጣም ብዙ ነው።
ተነዳደለ: ተበሳሳ።
ተነዳፊ: የሚነደፍ፡ ተወጊ።
ተነገረ: ተባለ፣ ተወራ፣ ተሰበከ፣ ተተረከ፣ ታወጀ፣ ተተነባ።
ተነገተ: ተያዘ፡ ተንጠለጠለ (በአንገት)።
ተነጋሪ: የሚነገር (ትምርት፣ ዐዋጅ፣ ትእዛዝ)።
ተነጋገሠ: ተመሰጋገነ፡ ንጉሥነትን ተቀባበለ።
ተነጋገረ: ተባባለ፣ ተገተ፣ ተከራከረ።
ተነጋገረ: ተጫወተ፣ ተጨዋወተ።
ተነጋጋሪ: የተነጋገረ፣ የሚነጋገር፣ ተማጋች።
ተነጋጋሪነት: ተማጋችነት፣ ጠበቃነት።
ተነጐረ: ነጐረ (ተመሳሳይ ትርጉም)።
ተነጐተ: ተጋገረ፡ ዕንጐቻ ሆነ።
ተነጓለለ: ተደናቈረ፡ እንደ ነጕላ ተናገረ፣ ተነፋለለ።
ተነጠለ: ተለጠጠ፣ ተለየ፡ ነጠላ ሆነ፣ ተዘረጋ።
ተነጠሰ: ሆነ፡ ተደረገ (ንጥሻው)።
ተነጠረ: ነጠረ።
ተነጠቀ (ተመሥጠ): አፈፍ አለ፣ ምድር ለቀቀ፡ ወደ ላይ፣ ወደ ሰማይ ኼደ፣ ዐረገ፣ ወጣ (፪ቆሮ ፲፪፡ ፪፡ ፬፣ ፩ተሰ ፬፡ ፲፯)።
ተነጠቀ: ተቀማ፣ ተሳበ፡ ድንገት ተወሰደ (ሰው፣ ገንዘቡ፣ ገላው) (ምሳ ፪፡ ፳፪፣ ኤር ፭፡ ፯፣ ሕዝ ፴፫፡ ፲፭)።
ተነጠጠ: ተፋቀ፡ ተሰነጠ፡ በሥርና በጫፍ ሰንበር ተደረገበት (፬ነገ ፮፡ ፲፰፡ ማሕ፯፡ ፫፡ ኤር፲፡ ፭) (ለስላሳ ሆነ፡ ተከፋፈለ)።
ተነጠፈ (ተነጽፈ): ተጣለ፡ ተዘረጋ፣ ተሰተረ፣ ተጸፈጸፈ።
"መላእክት የስቅለት ለት በመስቀል ዙሪያ እንደ ሻሽ ተነጠፉ። "
ተነጣቂ: የሚነጠቅ፣ ዐቅመ ቢስ።
ተነጣይ: የሚነጠል፣ የሚለይ።
ተነጣጠረ (ተናጸረ): በአንጻር ቁሞ ከዳኛ ተያየ፣ ከባለጋራው ጋራ ተነጋገረ፣ ተከራከረ፣ ተገተ።
ተነጣጠረ: ተመሳሰለ (ነገሩ)።
ተነጣጠቀ: ተቀማማ።
ተነጣጠፈ: ተጣጣለ፣ ተዘረጋጋ።
ተነጣጣሪ (ሮች): የተነጣጠረ፣ የሚነጣጠር፡ ተከራካሪ፣ ተማጋች።
ተነጣጣይ: የሚነጣጠል፣ ተለያዪ።
ተነጣፊ: የሚነጠፍ (መሬት፣ ምንጣፍ)።
ተነጩ: ተፈገፈገ፣ ተሞዠቀ፣ ተላጠ፣ ተመለጠ፡ ቈሰለ (ኢሳ ፲፭፡ ፪)።
ተነጫነጨ: ተበሳጨ፣ ተጨቃጨቀ፡ ዐመል ናጫ ሆነ።
ተነጫጨ: ተነቃቀለ፡ ተላላጠ።
ተነጻጸረ: ተያየ፡ ተመሳሰለ።
ተነጻጻሪ: የተነጻጸረ፡ የሚነጻጸር፡ ተመሳሳይ።
ተነፈሰ: ለነፋስ፣ ለትንፋሽ ተሰጠ፡ በሰፌድ መሣሪያነት ተበጠረ፡ ወጣ፡ ተለየ (እብቁ፣ ገለባው) (ተደራጊ).
ተነፈሰ: አለ፡ ተናገረ። "ውሃ ከፈሰሰ ንጉሥ ከተነፈሰ (አይመለስም)"።
ተነፈሰ: እፎይ አለ፡ ነፈሰ ።
ተነፈሰ: ካፉ ትንፋሽ አወጣ፡ እፎይ አለ፡ ዐረፈ (አድራጊና ተደራጊ) (ዘፀ፴፩፡ ፲፯)።
ተነፈራረቀ: ተሠነጣጠቀ።
ተነፈነፈ: ተሸተተ።
ተነፈነፈ: ተበላ፡ ተጋጠ፡ ተነጯ።
ተነፈገ (ጼአ): ክፉኛ ሸተተ፣ ገማ፣ ከረፋ፣ ራቀ፣ ተገለለ (ጥሩው መዐዛ)። "ነፈሰ" ብለኸ "ተነፈሰን" እይ፣ አካኼዱ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
ተነፈገ: ተሠሠተ፣ ተከለከለ (ምግቡ፣ ገንዘቡ)።
ተነፈገ: ተሠሠተ፣ ነፈገ።
ተነፋ (ተነፍየ): ተንዘረዘረ፣ ወረደ።
ተነፋ (ተነፍጎ): እፍ ተባለ፡ ነፋስ ተቀበለ።
ተነፋ: ታበየ፣ ተቈጣ፣ አኰረፈ።
ተነፋ: ዐበጠ፣ ተቀበተተ (ዘኍ፭፡ ፳፩)።
ተነፋለለ: ተደናቈረ፡ ቂልኛ ተናገረ።
ተነፋረቀ (ነፈረቀ): ተላቀሰ።
ተነፋረቀ: ተነኋረጠ። "ከፊቴ ወዲያ ኺድ፡ አትነፋረቅብኝ"።
ተነፋነፈ (ትግ፡ አነፈ): በአፍንጫው ተናገረ፡ ተነኋረጠ።
ተነፋነፈ: ተሻተተ፡ ጠረን ተቀባበለ።
ተነፋነፍ: የዱሮ ዘመን ሰፊ ሱሪ፡ ከስፋቱ የተነሣ ነፋስ እየጠለፈ ድምፅ የሚሰጥ ስለ ሆነ ተነፋነፍ ተባለ። እሱን የሚታጠቁ ጥብጣባቸውን ሳይፈቱ ወደ ላይ ገልበው ይኰሳሉ።
ተነፋናፊ: ተሻታች።
ተነፋናፊ: የተነፋነፈ፡ የሚነፋነፍ።
ተነፋፈረ: ፈጽሞ ተጣላ፣ ተማረረ፣ ተባሰለ፣ ተባባሰ፣ ተዛዛተ።
ተነፋፈቀ: ተፈላለገ፡ "ባየኹት ባገኘኹት"
ተባባለ።
ተነፋፋ: ዐባበጠ።
ተነፋፋቂ: የሚነፋፈቅ፡ ተፈላላጊ።
ተና: ጠ፣ ተወራራሽ መኾናቸውን አትርሳ።
ተናሰ: ተሠራ፡ ተገነባ (ናሱ፣ ግንቡ)።
ተናሣ (ተናሥአ): ተማዘነ፣ ተሳቀለ።
ተናረተ: ተማታ፡ ተጣዘለ።
ተናሸረ: ተማረረ፡ ነሸረ ።
ተናሸረ: ንስርኛ ፈጽሞ ተጣላ፡ ተባባሰ፡ ተማረረ፡ ተነፋፈረ፡ ተባባለ፡
ተናጩ፡ ተማለጠ (ንስር በማጕርጥ፣ በመንቈር ጦርነት እንደሚያደርግ)።
ተናቀ: ተዋረደ፡ ቀለለ፡ ተጠላ (ማር፰፡ ፴፩)።
ተናቀለ: ተላቀቀ፡ ተለያየ፡ ተማዘዘ።
ተናቀሰ: ተመሳከረ።
ተናቀሰ: ተቃነሰ፡ ተጓደለ።
ተናቀሰ: ተጣቈረ።
ተናቃላ: ከሥራው፣ ከደንቡ፣ ከይዘቱ የተለያየ። "እከሌ እኮ ሳይቸግረው ተናቃላ ኹኖ ቀረ"።
ተናቃነቀ: ተንቀሳቀሰ፡ ተወዛወዘ፡ ዋዠቀ፡ ተናወጠ (የንቅልፋም፣ የጥርስ፣ የምድር)።
ተናቈረ: ተጣላ፡ ተናከሰ፡ ተዋጋ (የዶሮ፣ ያሞራ፣ የወፍ)።
ተናበ (ተንህበ): ተቀጠቀጠ፣ ተሠራ።
ተናበ: ረባ፣ ተፈለፈለ።
ተናበበ: ተዛረፈ፣ ተያያዘ፡ ዘርፍና ባለቤት ተኳዃነ።
ተናበበ: አንዱ መጻፍ ከሌላው ጋራ ቃሉ ትክክል መሆኑ ተመረመረ።
ተናባ (ተናብዐ): ተላቀሰ።
ተናባቢ ቀለም: "እጀ ሰብ"፣ "ዐይነ ወግ"፣ "ጥርሰ ገጣጣ"፣ "ዐይነ ፈጣጣ"፣ "መልከ ቀና" እየተባለ የሚነገር ቃል፡ ይህ በግእዝ ሲናበብ ነው። ዘርፍና ባለቤት አንድ ቃል ሲሆን፡ "ገደላገደል"፣ "ወንዛወንዝ"፣ "ውርውር"፣ "ወርቃወርቅ"፣ "ጨርቃጨርቅ"፣ "ሥራሥር"፣ "ቅጠላቅጠል"፣ "ርጥባርጥብ"፣ "ብረታብረት"፣ "ጥጋጥግ"፣ "ሴታሴት" እያለ በራብዕ ይናበባል። በሳድስም ሲናበብ፡ "ስም አጥፊ"፣ "ነገር ዐላፊ" ይላል። ይኸውም በግእዝ (አጥፋኤ ስም፣ ኀላፌ ነገር) ያሰኛል።
ተናባቢ: የተናበበ፣ የሚናበብ፡ ተያያዥ።
ተናተነ: ለያየ፣ ከፋፈለ።
ተናነሰ: ተጓደለ፣ ተቀናነሰ፣ ተከፋፈለ።
ተናነቀ: ዐገለ።
ተናነቀ: ወገብ ለወገብ ተያያዘ፡ ሠመር ገባ፡ ገጠመ፡ ታገለ። (ተረት): "ስንተዋወቅ አንተናነቅ" (ለመተዋወቅ ሲባል መጋደል የለብንም)።
ተናናረ: ተዛለለ፡ አንተስ አንተስ ተባባለ።
ተናናቀ: ተጠላላ፡ ተኳሰሰ።
ተናናዶ: ፈራረሰ፣ ወዳደቀ።
ተናኘ፣ ተናኜ: የወንድና የሴት መጠሪያ ስም። "አቶ ተናኘ"፣ "እመት ተናኜ" እንዲሉ።
ተናኘ: ተሰጠ፣ ታደለ፣ ገባ፣ ተሠራጨ፣ ተነዛ፣ ተወራኘ፣ ተበተነ፣ ተዘራ።
ተናኝ: የሚተን፣ በናኝ።
ተናከሰ: ተዘናተረ፣ ተባላ (ተደራራጊ)።
ተናከሰ: ነከሰ (አድራጊ)።
ተናከረ: ተለያየ (ከመንገድ ወጣ፣ ዐረፈ፣ ሰፈረ)።
ተናከረ: ተዛፈቀ፣ ተዳፈቀ።
ተናከተ: ተሳበረ፣ ተዳቀቀ። "ነካ ብለኸ ተናካን" አስተውል።
ተናካ: ነካ። የላይኛው ተደራራጊ፡ ይህ አትዘንጋ አድራጊ መሆኑን።
ተናካ: ድል ተባባለ፣ ተጣላ። "ነካና ነከተ" በአማርኛ ይተባበራሉ። (ግጥም): "ንጉሥ ይባረኩ አቡን አስመጥተው፣ ካረመኔ ጋራ ተናክተው ተናክተው። "
ተናካሽ: ተናዳፊ (ነዘር፣ እባብ) (ዘኍ ፳፩፡ ፫)።
ተናካሽ: ነካሽ።
ተናካሽ: የተናከሰ፣ የሚናከስ። (ዐዋጅ): "ተዋጊ በሬኸን፣ ተናካሽ ውሻኸን ያዝ። " (ተረት): "ተናካሽ ውሻ የዥብ መቋደሻ። "
ተናኰረ: ተናቈረ፣ ተዋጋ።
ተናወረ: ተዋጣ (ጕድንን)።
ተናወጠ: ተነዋወጠ፡ ተናጋ፣ ተነቃነቀ፣ ተናጠ (ኢሳ ፳፬፡ ፲፱፣ ኤር ፶፡ ፵፮)።
ተናዋጭ: ተነዋዋጭ፡ የሚናወጥ፣ የሚነዋወጥ፣ የሚነቃነቅ፡ ተነቃናቂ።
ተናዘዘ:
"የጄን ለልጄ"
አለ፡ ርስቱን፣ ገንዘቡን አወረሰ፡ ኃጢአቱን ለቄስ ነገረ፡ "ይህን ሠርቻለኹ፡ ይፍቱኝ"
አለ (በሕይወት ሳለ፡ ወይም በሞት ጊዜ) (ማር ፩፡ ፭)።
ተናዛዥ: የሚናዘዝ። (ጥና) መናዘዝ: ይዘታን ማውረስ፣ ኃጢአትን መግለጥ፣ መንገር።
ተናደ (ተንዕደ): ተጐተተ፣ ተዘረጠጠ፡ ፈረሰ፣ ወደቀ (ክምሩ)፡ ሸሸ (የጦር ሰራዊቱ)፡ ተንከባለለ (ናዳው)።
ተናደ: ተተረተረ፣ ተፈታ (ጥንጥኑ)።
ተናደደ: ተበሳጨ፣ ተቈጣ፡ በቍጣ ነደደ፣ ጨሰ፣ ተቃጠለ፣ በገነ፣ ዐረረ።
ተናደደ: ተያያዘ፣ ተቀጣጠለ።
ተናደፈ (ነደፈ): በመርዝ ተዋጋ፣ ተጠዛጠዘ፡ ልማዱ ግን ነደፈ፣ ወጋ ነው። "ንቦ ንቦ ኣትናዶፊ፡ የነከሌ ነኝ ብለሽ ዕለፊ" (ሴቶች የሰርግ ለት)።
ተናዳ (ተናድአ): ተቃረበ፣ ተዋሰደ።
ተናዳጅ: የተናደደ፣ የሚናደድ።
ተናዳጅነት: ተናዳጅ መሆን።
ተናዳፊ (ነዳፊ): የተናደፈ፣ የሚናደፍ፡ ንብ፣ ተርብ፣ ጥንዝዛ፣ እባብ፣ ጊንጥ፣ ናዜራ፣ ቀስተኛ፣ ወባ።
ተናዳፊነት: ተናዳፊ መሆን።
ተናገሠ: ንጉሥ ተኳዃነ፣ ባንድ ዘመን ነገሠ።
ተናገረ: (በግእዝ፡ ተደራራጊ፡ በአማርኛ፡ አድራጊ) ቃል ሰጠ፣ ነገረ። "ተቀመጥ በወንበሬ፡ ተናገር በከንፈሬ። "
ተናገረ: ለፈለፈ፣ ቀባጠረ።
ተናጋሪ (ሮች): የተናገረ፣ የሚናገር፣ ለፍላፊ፣ አፈኛ (ኢዮ፲፩፡ ፪፣ ምሳ ፪፡ ፲፪፣ ግብ ሐዋ፲፰፡ ፳፬)።
ተናጋሪነት: ተናጋሪ መሆን፡ አፈኛነት።
ተናጠ: ተገፋ፣ ተወዘወዘ፣ ተነቀነቀ (ወደፊትና ወደኋላ ተባለ፡ ወይም አለ)።
ተናጠለ፣ ተነጣጠለ: ተለያየ፣ እየብቻ ተኳዃነ። ተነጣጠለ ብዙ ጊዜ ፈጽሞ ለማለት ይነገራል።
ተናጠቀ (ተማሠጠ): ተቃማ፣ ተሻማ (ሕዝ ፴፱፡ ፬፣ ማቴ ፲፩፡ ፲፫፣ ግብ፡ ሐዋ ፳፡ ፳፱)። "ጌታችን በሕፃንነት ሳለ ሰው ኹሉ ይናጠቀው ነበር" ይላል አረጋዊ መንፈሳዊ።
ተናጠበ: ተራገጠ፣ ተቅበጠበጠ።
ተናጠበ: ተዳፈረ፣ ተሳደበ።
ተናጠፈ: ተዘራጋ።
ተናጠፈ: ተዘራጋ።
ተናጣ: ተናጻ።
ተናጣላ ሆነ: ከሥራ ተወገደ፣ ራቀ።
ተናጣላ: የተናጠለ፣ የተለያየ።
ተናጣቂ (ቆች): የተናጠቀ፣ የሚናጠቅ፡ ተቃሚ፣ ተሻሚ (፩ቆሮ ፲፭፡ ፲፩)።
ተናጣቢ: ዐመለኛ፣ ክፉ፣ ተራጋጭ፣ ቅብጥብጥ ላም (ሆሴ ፬፡ ፲፮)።
ተናጣቢ: የተናጠበ፣ የሚናጠብ፡ ተሳዳቢ።
ተናጣቢነት: ተናጣቢ መሆን።
ተናጪ: ተበሳጨ፣ ተጨቃጨቀ፡ ዐመለኛ ናጫ ሆነ።
ተናጯ: ተናቀለ።
ተናጻ: ታጠበ፡ ተጣጠበ፡ ተለቃለቀ።
ተናፈሰ: ተዛወረ፡ ሽር ሽር አለ፡ ነፋስ ተቀበለ፡ ስፍራ ለወጠ፡ ከአዲስ አየር ተገናኘ።
ተናፈቀ: ተሻ፡ ተፈለገ።
ተናፈገ: ተነፋፈገ፣ ተሣሠተ፣ ተሻማ።
ተናፈጠ: እንፍ አለ፡ ንፍጥን አወጣ፣ አፍንጫውን አጠራ፡ (ተናጻ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ)።
ተናፈጠና አናፈጠ: ተደራራጊና አደራራጊ ሲመስሉ በአድራጊነትና በአስደራጊነት መፈታታቸውን አስተውል።
ተናፋሽ: የሚናፈስ፡ የክት ልብስ።
ተናፋቂ: የሚናፈቅ፡ የሚፈለግ፡ ተፈላጊ።
ተኔ፡ ዝኒ ከማሁ።
ተን: "በገባበት በደጊመ ቃል ግስ መነሻ እየተነገረ የመደረግ ልማድ ይኾናል። (ማስረጃ)፡ በዝበዝ፡ ተንበዝበዝ፡ በለበለ፡ ተንበለበለ፣ ገደደ፡ ተንገደገደ፣ ነጠበ፣ ተንጠባጠበ፡ ደፈደፈ፡ ተንደፋደፈ፡ ቀጠቀጠ፡ ተንቀጠቀጠ (ቀለቀለ)፡ ተንቀለቀለ፡ ሰረሰረ፡ ተንሰረሰረ።"
ተን: የጉም፣ የጪስ ብናኝ (ግእዝ)።
ተንሰለጀጀ (ሰለጀጀ)፡ ደከመ፣ ፈዘዘ፣ ተንሰዋለለ።
ተንሰለጀጀ: ደከመ፣ ፈዘዘ፣ ተንሰዋለለ።
ተንሰረሰረ: ተቀቀለ፣ በሰለ፣ ነፈረ። (ጥር)
ተንሰረተተ: ረዘመ፣ ተጐተተ።
ተንሰራፋ: ሰፋ፣ ሰፊ ኾነ፣ ተንጋለለ፣ ተዘረጋ፣ ብዙ ስፍራ ያዘ፣ ተንዘራፈጠ (መዝሙር ፻፬፡ ፳፭)።
ተንሠቀሠቀ: ዕርር ምርር አለ፡ ተስረቀረቀ፡ ባለማቋረጥ አለቀሰ፡ ተንፈቀፈቀ፡ በሹል ነገር በመሠቅሠቂያ እንደ ተወጋ (ፊልክ ፭)።
ተንሰዋለለ፡ እንቀዋለለ፣ እንከዋረረ፣ አንሰለጀጀ።
ተንሰገሰገ: ተስገበገበ፣ ቸኰለ (ሳያኝክ)።
ተንሢያጠጠ: ተፋጨ፡ በቀጪን ድምፅ ጮኸ (ብረቱ፣ እባቡ፣ ዐይጡ)።
ተንሳቀቀ (በቀቀ): ተላቀቀ፣ ተከፋፈተ። ማስታወሻ: ልማዱ ግን ተደራጊ ነው።
ተንሣይ (ትንሣኤ): መነሣት። የታላቅ በዓል ስም፡ በያመቱ እሑድ ለት የሚከብር በዓል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጋቢት ፳፯ ቀን ዐርብ ሙቶ በ፫ኛ ቀን የመነሣቱ መታሰቢያ። ተንሣይ የአማርኛ፣ ትንሣኤ የግእዝ ነው።
ተንሣይ: ትንሣኤ፣ ነሣ።
ተንሳፈፈ፡ ሰፈፈ።
ተንሳፋፊ፡ የሚንሳፈፍ (ቀላል ነገር፣ ጾም፣ ባሕር)።
ተንሶለሶለ፡ ዞረ፣ ተንቀዥቀዠ፣ ተንቀለቀለ።
ተንሶከሶከ፡ አሶከሶከ።
ተንሸረሸረ: ሠሣረ፣ ተራመደ።
ተንሸረሸረ: ሾረ።
ተንሸረሸረ: ወደ ውጭ ኼደ፣ ዞረ፣ አየር ለወጠ፣ ተናፈሰ፣ ነፋስ ተቀበለ፣ ጥሩ ልብስ ለብሶ፣ አምሮ፣ ተሸትሮ።
ተንሸርሻሪ: የሚንሸረሸር፣ የሚሾር።
ተንሸቀሸቀ: ፈራ፣ ራደ፣ ተንቀጠቀጠ።
ተንሸቅሻቂ: የሚንሸቀሸቅ፣ ተንቀጥቃጥ።
ተንሸቅሽቋል: ርዷል፣ ተንቀጥቅጧል።
ተንሸዋረረ: ተጣመመ፣ ተንጋደደ (ወደ ጐን እየ)።
ተንሸዋራሪ: የሚንሸዋረር፣ የሚንጋደድ።
ተንሻለለ: ተንፋቀቀ፣ ተሳበ (በምሰሶ ላይ)። "እንሽላሊትኛ ወጣ ወረደ።"
ተንሻረረ: ወደ ላይና ወደ ታች ተወረወረ (በገደል በግንብ በምሰሶ ላይ ፈጥኖ ዐለፈ ተንሻለለ - ገበሎው እባቡ እንሽላሊቱ) ።
ተንሻተተ: ተንሸራተተ።
ተንሻታች: የሚንሻተት፣ ተንሸራታች።
ተንሻፈፈ: ሸፋፋ ኾነ፣ ወነከሰ። "ነፋስ እንደ ነካው አንበጣ ባንድ ወገን ረገጠ ኼደ።"
ተንሾካሾከ: ሹክታን ተመላለሰ፣ ተሾካከ።
ተንሾካሿኪ: የተንሾካሾከ፣ የሚንሾካሾክ፣ ተሾካሿኪ።
ተንሿሿ: ፈላ፣ ገነፈለ፣ ፈሰሰ፣ ወረደ፣ ተሰማ።
ተንቀለቀለ፡ በኀይል፡ ነደደ፡ ተንበለበለ።
ተንቀለቀለ፡ አለልክ፡ ረዘመ።
ተንቀለቀለ፡ ዞረ፡ ተንቀዠቀዠ፡ ተንቀወቀወ፡ ናወዘ።
ተንቀለጠጠ፡ ተከፈተ፡ ተገለጠ፡ ተንገለጠጠ።
ተንቀላበሰ፡ ኣልብሱኝ፡ አንተርሱኝ፡ አለ፡ ተደገፈ።
ተንቀላባሽ፡ የተንቀላበሰ፡ የሚንቀላበስ፣ ተደጋፊ።
ተንቀልቃይ፡ የሚንቀለቀል፡ የሚነድ፡ ነዳጅ፡ ናዋዥ።
ተንቀሳቀሰ (አንሳሕስሐ፡ ተሐውሰ): ተነቃነቀ፣ ተላወሰ (ኢዮብ ፴፯፡
፳)።
ተንቀሳቀሰ፣ ተነቃነቀ። ለምሳሌ፣ ሽል በማህፀን ይላወሳል። (ተደራራጊ)
ተንቀሳቃሽ (ተሐዋሲ): የሚንቀሳቀስ፡ ተነቃናቂ፣ ተላዋሽ፡ በእግር የሚሽከረከር፣ በክንፍ የሚበር እንስሳ፣ አውሬ፣ ወፍ፡ ኀሙስ ከባሕር፣ ዐርብ ከየብስ የተፈጠረ ፍጥረት ኹሉ፡ ደመ ነፍስ ያለው (ዘፍጥረት ፩፡
፳)።
ተንቀሳቃሽ: በያይነቱ ፈረንጆች የሠሩት መኪና።
ተንቀሳቃሽነት: ተነቃናቂነት፣ ተላዋሽነት።
ተንቀሳቃሾች (ተሐዋስያን): ተሽከርካሮች፣ በራሪዎች፣ እንስሶች፣ አውሬዎች፣ ወፎች፣ መኪኖች።
ተንቀረሰሰ (ተንቈረሰሰ): ቀስ ብሎ ኼደ፣ ዘገመ (ላዘ)፣ አዘገመ።
ተንቀረቀበ: ተንቀጠቀጠ፣ ተናወጠ፡ ተወዘወዘ፣ ተንገዋለለ፣ ተለየ።
ተንቀረበበ: ተንገረበበ፣ ተንቀረደደ፣ ተንከረፈፈ፡ ረዘመ።
ተንቀረደደ: ዝንጀርኛ ኼደ፡ ተንቀረበበ፣ ተንቀረፈፈ፣ ተንከረፈፈ (እግሩን ሱፋጭ እንደ ቈረጠው ሰው)።
ተንቀራጨ: ተቈረጠመ፣ ተንቀጫቀጨ፡ ተፋ።
ተንቀርቃቢ: የሚንቀረቀብ፡
እንቀቱና ዶቄቱ የሚለይ።
ተንቀሸረረ: ቀሸረረ።
ተንቀበቀበ፡ ተንገበገበ፡ ነፈገ፡ ሠሠተ።
ተንቀበደደ፡ አረገዘ፡ ተነፋ፡ ዐበጠ።
ተንቀባረረ፡ ተቀማጠለ፡ ተንደላቀቀ፡ ተሞላቀቀ።
ተንቀባራሪ፡ የሚንቀባረር።
ተንቀብቃቢ፡ የሚንቀበቀብ፡ የሚነፍግ።
ተንቀወቀወ፡ ተንከወከወ፡ ተንቀዠቀዠ።
ተንቀዋላይ፡ የሚንቀዋለል።
ተንቀዠቀዠ፡ ተክለፈለፈ፡ ተክለበለበ።
ተንቀጠቀጠ፡ ተንጠበጠበ፡ ተነቀነቀ፡ ራደ፡ ተንዘፈዘፈ፡
ተወዘወዘ፡ (ኢዮብ ፳፮፡ ፲፩። ፴። ፯፡ ፩)።
ተንቀጠቀጠ፡ ነፈገ፡ ሠሠተ።
ተንቀጥቃጭ፡ የሚንቀጠቀጥ፡ ተንዘፍዛፊ፡ (ዘዳግም ፳፰፡ ፷፭)።
ተንቀጫቀጨ፡ ተጋጩ፡ ተፋጩ፡ የጥርስ።
ተንቀፈረረ: ረዘመ፣ ግመል መሰለ።
ተንቀፈደደ: ተንቀረደደ።
ተንቀፍዳጅ: የሚንቀፈደድ፡
መንቀፍደድ፣ መንቀርደድ።
ተንቃቂ: የሚንቃቃ።
ተንቃቃ: ሞቀ፣ መጠጠ፣ ደረቀ፣ ቀነበረ፡ ተጕላላ። "ቃታን፣ ቃትን እይ፡ የዚህ ዘር ነው። "
ተንቃቃ: ድምፅ ሰጠ፡ ተንገጫገጨ።
ተንቃፈፈ: ተንጋፈፈ፣ ተንከረፈፈ።
ተንቈማቈጪ፡ ተነነጩ፡ ቡችልኛ፡ ጮኸ።
ተንቈረቈረ: ተቈለቈለ፣ ወረደ (ወደ ታች) ኼደ (ከብቱ)።
ተንቈረቈረ: ፈሰሰ፣ ተቀዳ፣ ተመላ (መጠጡ)።
ተንቈረበበ: ቈረበ፣ ጐረበ።
ተንቈረዘዘ: ተንጠለጠለ፡
ሊወርድ፣ ሲፈስ፣ ሲንጠባጠብ ቀረበ (እንባው፣ ደሙ፣ ወተቱ)።
ተንቈረፈፈ: ተቈፈነነ፣ ተወበጠ። "ይህ ዶሮ ሊሞት ነው፡ ተንቈርፋል። "
ተንቈራባ: ተንኳኳ፣ ተንኰራፋ።
ተንቈራጠጠ: ተንጐራደደ፡
ከቤት ወደ ውጭ ወጣ፡ ከውጭ ወደ ቤት ገባ፡ ወዲያና ወዲህ አለ። "ሰንጋ ፈረስ በተቀመጡበት ጊዜ ይንቈራጠጣል፡ ሴት ምጥ ሲይዛት ትንቈራጠጣለች። "
ተንቈራጣጭ: የሚንቈራጠጥ፡
ተንጐራዳጅ።
ተንቈራፋ: ተንኰራፋ፣ ተንቈራባ።
ተንቈርቋሪ: በማንቈርቈሪያ፣ በመንቈርቈሪት የሚንቈረቈር፣ የሚመር (ጠጅ፣ ጠላ፣ ማንኛውም ፈሳሽ ነገር)።
ተንቈጠቈጠ፡ በላይ፡ በታች፡ ተሸለመ፡ አጌጠ፡ ባላበባ፡
ቍጥቋጦ፡ መሰለ።
ተንቈጠቈጠ፡ ደቀቀ፡ ተንከታከተ፡ ከሰማይ፡ የወረደ፡
ጭንቍላ፡ ኾነ።
ተንቈጣቈጠ፡ ተቈናቈነ፡ ሠሠተ፡ ቈጠበ።
ተንቈፈቈፈ: ነፈገ፣ ሠሠተ።
ተንቈፈቈፈ: ጮኸ፣ ጠራ (ጩቱን)። "ርግጠኛው ግን ተጮኸ፣ ተጠራ ነው። "
ተንቋቋ: ጮኸ (ጣቱ፣ ወገቡ)።
ተንቋጠጠ፡ ተኰሰተረ፡ ኰራ። ምሳሌ: "እከሌ፡ የተንቋጠጠ፡ ቤት፡ ሠራ"፡ እንዲሉ።
ተንበለበለ: ነደደ፡ ተንቦገቦገ፣ ተንቀለቀለ።
ተንበላጠጠ: ተገላመጠ፡ ፈራ፡ ወዲያና ወዲህ አየ።
ተንበላጣጭ: የሚንበላጠጥ፡ ጭላዳ፣ ሌባ፣ ነፍሰ ገዳይ።
ተንበረበረ: ተበረበረ።
ተንበረከከ: በረከ፣ በረከከ፡ ሰገደ (ኢዮብ ፴፱፥፫፣ ኢሳያስ ፵፬፥፲፭)፡ ተኛ።
ተንበረክ (ቦታ): ሥር፣ ታች፡ መንበርከኪያ ቦታ (ወንበር)።
ተንበረክ (ግንባታ): የአዲስ ግንብ ልባስ፡ ሰንበሌጥ መካከሉ በገመድና በእንጨት የተማገረ።
ተንበርካኪ: የሚንበረከክ፡ ግመል (ሰጋጅ)።
ተንበሸበሸ: ተቀማጠለ (ተንቀባረረ)።
ተንበሸበሸ: ተንቀባረረ፣ በሸበሸ።
ተንበሸከከ: ተንቀባረረ (ተንበጠረረ)።
ተንበቀበቀ: እንደ ቅል ውሃ ጮኸ።
ተንበከበከ (በከበከ): ተንደከደከ።
ተንበደበደ (በደበደ): ፈራ፣ ተንቀጠቀጠ፣ ራደ (ኢያሱ ፪፥፳፬፡ ኢሳይያስ ፳፩፥፬)።
ተንበጠረረ (በጠረረ): ተጓደደ፣ ዳ አለ፡ ዳተኛ ሆነ።
ተንበጥራሪ: የሚንበጠረር፡ ተጓዳጅ።
ተንበጨበጨ (በጨበጨ): ብግምስሎ ወረደ። ማስታወሻ: "በጪን" እይ።
ተንቤኔ: የተንቤን ሰው፣ የተንቤን ተወላጅ፣ ትግሬ።
ተንቤን: በተንቤን ውስጥ የሚሠራ ቀይ ቈርበት ነት።
ተንቤን: በትግሬ ክፍል ያለ አገር።
ተንቦለቦለ: ቡልቅ ቡልቅ አለ፡ ተትጐለጐለ፡ ፈለቀ፣ ወጣ፡ ወረደ፣ ፈሰሰ፣ ተንዶለዶለ (የጪስ፣ የውሃ)። ማስታወሻ: "ቦለለን" እይ፡ የ"ቦለቦለ" ሥር እርሱ ነው።
ተንቦረቀቀ (ቦረቀቀ): ሰፋ፣ ሰፊ ሆነ (ተንቧለለ)።
ተንቦቀቦቀ: በዝቶ ወረደ (ፈሰሰ)፡ ተንዶለዶለ፡ ፈራ።
ተንቦዠቦዠ: ሞቅ አለው፣ ተደሰተ፣ ተብረዠረዠ።
ተንቦገቦገ: ትግ ትግ አለ፡ ዘለለ፡ በኃይል ነደደ (ናሆም ፫፥፫)።
ተንቦጫረቀ: በባሕር፣ በኩሬ (በጮረቃ) ውስጥ ተንደፋደፈ፣ ተንቧጨ፣ ተንፈራገጠ።
ተንቦጫራቂ: የሚንቦጫረቅ (ወፍ፣ ሕፃን)። ማስታወሻ: "ወንዘረጭን" እይ።
ተንቦጫቦጨ: ተበጣበጠ፣ ተማታ፣ ተፋሰሰ።
ተንቧለለ: ቦላሌ ለብሶ ኼደ፡ ተጫሰ (በዝቶ ወጣ)።
ተንቧቧ: ተንፋፋ፣ ተንሿሿ፣ ወረደ፣ ፈሰሰ።
ተንቧቸ: ተንቦጫረቀ (ተንቻቻ፣ ተንጫጫ፣ ተጫወተ)፡ እንደ ልቡ ሆነ።
ተንተሰተሰ: ነቃ፣ ተሠነጠቀ፣ ፈራ።
ተንተረከከ: ሠባ፣ ወፈረ።
ተንተረከከ: በሰለ።
ተንተረፈፈ: ተመላ፣ ተንደረበበ፣ ቲፍ አለ።
ተንተራሰ: ራሱን በትራስ ላይ አደረገ፣ ተደገፈ፣ ቀና አለ (ዘፍጥረት ፳፰፡ ፲፰። ማርቆስ ፬፡ ፴፰)። "መናኝ ጤዛ ልሶ ደንጊያ ተንተርሶ ይኖራል።"
ተንተራፋ: ተሰበረ፣ ተፈለቀ፣ ተጨማለቀ (ውሃው፣ ደሙ)።
ተንተበተበ: ተሳሰረ።
ተንተበተበ: ተቈላ።
ተንተበተበ: ድዳ፣ ለንባዳ ኾነ (አንደበቱ)፣ ተርበተበተ።
ተንተባታቢ: የሚንተባተብ።
ተንተከተከ: ሞቀ በጣም፣ ፈላ፣ ነፈረ፣ ተንጠቀጠቀ።
ተንተወለበለበ: ተወዘወዘ፣ ተነቀነቀ፡ ለፈለፈ።
ተንታ: በወሎ ክፍል ያለ አገር ።
ተንታኝ: የተነተነ፣ የሚተንትን (ከፋይ፣ ዐዳይ)።
ተንቷቷ: ተበጣጠሰ።
ተንቸሰቸሰ: ሐረሰ፣ ተነሣ (ላብ ወጣ፣ አረፋ ወጣ)።
ተንቸረፈፈ: ኰረፈ፣ "አልናገር" አለ።
ተንቸበቸበ: ተጠበሰ፣ በሰለ፣ ተቃጠለ።
ተንቸከቸከ: ተሸነ፣ ተንፎከፎከ፣ ተጠበሰ።
ተንቻረረ: ተንሻረረ፣ ተንሻለለ፣ ዘለለ።
ተንቻቻ: ተነሣ፣ ተንጐርጐረ።
ተንኦሮይ፡ የሚንጋለል፣ በዠርባው የሚተኛ።
ተንከላወሰ: ተላወሰ፡ ተንጠራወዘ፡ ኣዘገመ።
ተንከረተተ/ተንከራተተ: ዞረ፡ ተንከዋተተ፡ ተንከዋረረ፡ ተንቀዋለለ፡ መንገድ መታው።
ተንከረደደ: ራሱ ዞረ፡ ተንቀጠቀጠ።
ተንከረጠጠ: ተነፋ ወይም ተንቀበደደ።
ተንከረፈፈ: ቄላ ወይም ተሞኘ።
ተንከረፈፈ: ተዘረጋ፣ ተንቀረፈፈ ወይም ተንቀረበበ።
ተንከረፈፈ: ዳር ዳር አለ።
ተንከራ: ጠንካራ ዕንቍ (ግእዝ) ።
ተንከራበተ: ተንገላታ ወይም ተጕላላ።
ተንከራተተ: ግራ ቀኝ አየ (ለማግኘት፣ ለመቀበል)። "ይህ ልጅ ዐይኑ ይንከራተታል። "
ተንከርታች/ተንከራታች: የሚንከረተት ወይም የሚንከራተት።
ተንከሸለለ: ከሸለለ።
ተንከባለለ (ጸድፈ): ገደል ገባ፡ ተገላበጠ፡ ተንደባለለ (፪ሳሙ፡ ፳፡ ፲፪)። ገላውን በአመድ ዐከከ፡ ዐጠበ። ተቍለጨለጩ፡ ተዥገረገረ።
ተንከባላይ (ዮች): የሚንከባለል፡ ተገላባጭ፡ ተንደባላይ።
"ሀ ባይ ዐመድ ላይ ተንከባላይ እንዳለ ተማሪ"።
ተንከተከተ: ባለማቋረጥ ሣቀ።
ተንከታከተ: ተሰባበረ፡ ተቀለጣጠመ።
ተንከታከተ: ገደል ገባ፡ ተንከባለለ።
ተንከወከወ: ባከነ፡ ተንቀዠቀዠ፡ ተንቀወቀወ፡ ዞረ።
ተንከዋረረ: ተንቀዋለለ፡ ዞረ።
ተንከዋተተ: ተንከዋረረ፡ ተንከራተተ።
"የትም ሲንከዋተት ውሎ መጣ"።
ተንከዋታች: ተንከራታች።
ተንከፈረረ: ሞተ፣ ደረቀ ወይም ተንቀፈረረ።
ተንከፈከፈ: መርገጥ አቃተው፣ ተሳነው፣ ተሠቀቀ (ውስጥ እግሩ)።
ተንካረረ: ተንጋለለ።
ተንካካ: ገደል ገባ፡ ተንከባለለ።
ተንካፈፈ (ጸለለ): ቀለለ፣ ሰፈፈ ወይም ተንሳፈፈ፡ በውሃ ላይ ሆነ፣ ተቀመጠ ወይም ሄደ።
ተንካፋፊ: የሚንካፈፍ፡ ቀላል ነገር።
ተንኰለ ቢስ: ተንኰሉ አጥፊ፣ ጐጂ የኾነ።
ተንኰለኛ: ጥበበኛ፣ መሠሪ ሰው፣ መኼጃው የማይታወቅ (እባብ)።
ተንኰለኛነት: ተንኰለኛ መኾን።
ተንኰሉ: የሰው ስም።
ተንኰላኰለ: መኼድ ዠመረ (የሕፃን)።
ተንኰላኰለ: መኼድ ዠመረ፡ የሕፃን።
ተንኰል: ክፉ ጥበብ፣ ምክር፣ ደባ (ማርቆስ ፯: ፳፪)።
ተንኰረፈፈ: አኰረፈ፡ ኩፍ አለ።
ተንኰራኰረ: ደቀቀ፣ ተሰባበረ ወይም ተፈረፈረ።
ተንኰራኳ: ተንከባለለ ወይም ተጋጩ።
ተንኰሻኰሸ: ተንቀሳቀሰ፡ በደረቅ ሣርና ቅጠል መካከል መላወሱ ተሰማ።
"ቃየል በደን ውስጥ ሲንኰሻኰሽ ዕውሩ ላሜኅ ደንጊያ ወርውሮ ገደለው"
(ዘፍጥረት ፬:፳፫-፳፬)።
ተንኰታኰተ: እንኵቶ ሆነ፡ ተንከታከተ።
ተንኰፈኰፈ: ተቈጣ፣ አኰረፈ ወይም ሮጠ (ሽማግሌው)።
ተንኳለለ: ኮለል አለ፡ ፈጥኖ ፈሰሰ።
ተንኳላይ: የሚንኳለል (ባዜቃ)።
ተንኳላይ: የሚንኳለል፡ ባዜቃ።
ተንኳሽ: የተነሳ፣ የሚተነኵስ (ለኳፊ)።
ተንኳሽነት: ተንኳሽ መኾን።
ተንኳኳ: ተንቋቋ፡ ደረቀ።
ተንኳፈፈ: ተንካፈፈ። "ሰፈፈ ብሎ ተንኳፈፈ" እንዲል ባለቅኔ።
ተንዘለዘለ: ተንጠለጠለ፡ ዞረ፡ አለል ዘለል አለ፡ አመንዝራ ሆነ፡ ባለገ፡ ከልክ አለፈ።
ተንዘረበበ: ተንጠለጠለ።
ተንዘረዘረ: ተነፋ፣ ተነቀነቀ፣ ተወዘወዘ፣ ተንቀጠቀጠ፣ ዞረ፣ ተዘራ፣ ለነፋስ ተሰጠ።
ተንዘረገገ: ተጎተተ፣ ቀስ ብሎ ሄደ። (ለምሳሌ: ቶሎ ቶሎ ና፣ አትንዘርገግ)።
ተንዘረጠጠ: ተንጠረዘዘ፣ ተንቀበደደ፣ ተንገፈጠጠ፣ አረገዘ፣ ተነፋ።
ተንዘረፈፈ: ዘርፍ ሆነ፣ መሰለ፡ ረዘመ፣ ተሳበ፣ ተጎተተ፡ ተንቀረፈፈ።
ተንዘራጋ: ወደቀ፣ ተጣለ፣ ዟ አለ፣ ተንፈራገጠ።
ተንዘራፈጠ (ዘረፈጠ): እንደ ልቡ ተቀመጠ፡ ተሸራሸ፣ ሰፋ (ሰፍሐ)፣ ተንሰራፋ፡ ተፈረነሰ።
ተንዘገዘገ: ተምዘገዘገ፣ ተቅዘመዘመ።
ተንዘፈዘፈ: ተርገበገበ፣ ተንቀጠቀጠ።
ተንዘፈዘፈ: ተንቀጠቀጠ ወይም ተንቀጠቀጠ።
ተንዘፈጠጠ: ተንዘረጠጠ፣ ተንገፈጠጠ፣ አረገዘ፣ ሆዱ ተነፋ። (ዘበጠጠን እይ)
ተንዘፈጠጠ: ተዛባ፡ ከቅርጽ ወጣ፡ አረገዘ፡ ታበየ። (ዘበጠጠ ተመልከት)።
ተንዘፍዛፊ: የሚንቀጠቀጥ ወይም የሚንቀጠቀጥ ሰው።
ተንዘፍዛፊ: የሚንዘፈዘፍ፣ ተርገብጋቢ።
ተንዛረጠ: ዘረጥ አለ።
ተንዛዛ በዛ፣ ረዘመ፣ ከልክ ዐለፈ፣ ተረፈ፣ ተትረፈረፈ።
ተንዛዛ ደግሞ ተንከዋረረ፣ ዞረ ማለት ነው።
ተንዛዛ: በዛ፣ ረዘመ፣ ከልክ ዐለፈ፣ ተረፈ፣ ተትረፈረፈ።
ተንዛዛ: ደግሞ ተንከዋረረ፣ ዞረ ማለት ነው።
ተንዛፈፈ: ሰፋ፣ ተንሰራፋ፣ ተዘረጋ፣ በዛ፣ አደገ፣ ረዘመ፣ አጠላ፣ ጥላ ሆነ።
ተንዠረገገ: ተንጨረገገ፣ ወረደ፣ ተንጠለጠለ።
ተንዠረገገ: ተንጨረገገ፣ ወረደ፣ ተንጠለጠለ።
ተንዠቀዠቀ: በዝቶ ወረደ፣ ፈሰሰ፣ ውረድ በሌ ሆነ።
ተንዠባረረ : ለገሰ፣ ቸረ፣ ተንቀባረረ።
ተንዠባረረ: በጣም ሰከረ፣ ዘነጋ፣ አረጀ፣ ዦዠ፣ ከልክ ዐለፈ።
ተንዠዋለለ: ረዘመ፣ ተጐተተ። (ገዥለን እይ)።
ተንዣለለ: ሾለቀ፣ ሞለለ፣ ሠላጤ መሰለ።
ተንዣረረ: ተሸነ፣ ፈሰሰ፣ ወረደ፡ ቀጠነ።
ተንዣበበ: ተዘረጋ፡ በክንፍ፣ በነፋስ ዞረ፡ ሰፈፈ።
ተንዣዣ: በዛ፣ ተለገሰ፣ ተንቻቻ።
ተንደላቀቀ: ተቀማጠለ፣ ተንቀባረረ፣ ተሞላቀቀ፡ አግድሞ አደገ።
ተንደረሰሰ፡ ቀስ፡ ብሎ፡ ተራመደ፡ እ ንደ፡ ዔሊ፡ ኼደ፡ ተንቀረሰሰ።
ተንደረበበ፡ ረጋ፡ ጨመተ፡ ጭምት፡ ኾነ።
ተንደረከከ፡ በሰለ፡ መረተ፡ ተንገለጠጠ፡ ፍሬው፡ ፍሙ።
ተንደረከከ፡ ዐጠረ፡ ዐጪር፡ ኾነ፡ ሰዉ።
ተንደረደረ፡ ከላይ፡ ወደ፡ ታች፡ ሮጠ፡ ፈጠነ፡ መጣ፡
ኼደ።
ተንደርዳሪ፡ የተንደረደረ፡ የሚንደረደር፡ ቍልቍል፡ ሯጭ።
ተንደቀደቀ፡ ጮኸ፡ ተቈጣ፡ ፎከረ።
ተንደበሰሰ: ተንደበዘዘ።
ተንደበዘዘ: የስንፍና ኣካኼድ (ቀስ ብሎ ኼደ)፡ አዘገመ፣ ተንቀረደደ፣ ተንቀፈደደ።
ተንደበደበ: ተጕረበረበ፡ ፈረሳቤት ኾነ።
ተንደባለለ: ተንከባለለ፡ ገላውን፣ አካሉን ባማድ ባቧራ ዐከከ (ዐጠበ)፣ ፈገፈገ።
ተንደባላይ: የሚንደባለል፣ ተንከባላይ (አህያ፣ ፈረስ፣ ሰቅሎ፣ ዐሣማ፣ ደም የጠገበ ውሻ፣ ዣርት)።
ተንደከደከ: ደቅደቅ አለ፡ ፈላ።
ተንደገደገ: ተቈላ፡ ተንደቀደቀ፣ ተንዶሸዶሸ።
ተንደፋራ ፣ ተንደፋደፈ፡ ተንፈራፈረ፡ ተንከባለለ፡ ተንደባለለ።
ተንደፋደፈ፡ ተንፈራፈረ፡ ተንፈራገጠ፡ ተንዘፈዘፈ፡ ተንደፋራ።
ተንደፋዳፊ፡ የሚንደፋደፍ፡ ተንፈራፋሪ።
ተንዳሰሰ ፣ አዘገመ፡ ትዃንኛ፡ ኼደ።
ተንዳሰሰ ፣ ደሳሳ፡ ኾነ፡ ተለመጠ።
ተንዳከከ: ፍጥነት ዐጣ።
ተንዶለዶለ: በዝቶ ወረደ፣ ፈሰሰ (፪ዜና ፴፪:፬)።
ተንዶሸዶሸ፡ ተቈላ፡ ተንጦሸጦሸ።
ተንዷዷ: ፈነዳ፣ ጮኸ፣ ተተኰሰ።
ተንጃጃ፡ ተንጋጋ፡ ተነዳ። እንጃ፡ ባፍኸ፡ ሙሉ፡ ዥብ፡ ይንጃጃ፡ እንዲል፡
እረኛ፡ (ጃጃ)ና፡ ጋጋ፡ አንድ፡ ናቸው።
ተንገለጀጀ፡ ተንሰለጀጀ፣ ተንሰዋለለ፣ ተንቀዋለለ፡ የሞኝ፣ የቂል አካሄድ ሄደ፡ ተሞኘ፣ ቄለ።
ተንገለጠጠ፡ ተንቀለጠጠ፣ መረተ፡ ተገለጠ።
ተንገላታ፡ ተጕላላ፣ ተጐዳ፡ ተበደለ፣ ተጠቃ፣ ተራበ፣ ተጠማ፣ ተራቈተ።
ተንገላታ: ጐላ።
ተንገላቺ፡ የሚንገላታ፣ የሚጐዳ፣ የሚጕላላ።
ተንገላወደ፡ ሥራ አልባ ሆነ፡ ተንቀዋለለ።
ተንገረበበ: አልጠጋ አለ።
ተንገረገበ: ተጐዳ፣ ተጠቃ።
ተንገረገበ: ፈላ፣ ተቀቀለ።
ተንገረገፈ: ተንቀጠቀጠ፣ ተመታ።
ተንገራጠጠ: እንቢ አለ።
ተንገራጣጭ: ፈቃደኛ ያይዶለ፡ የማይታዘዝ፣ እንቢተኛ።
ተንገርባቢ: የሚንገረበብ፡ ተንከርፋፊ።
ተንገርጋቢ: የሚንገረገብ።
ተንገሸገሸ: ተነቀነቀ፣ ተወዘወዘ፣ ተንገፈገፈ (ከመመረር፣ ከመጥላት፣ ከመሰልቸት የተነሣ)።
ተንገበገበ: ተቃጠለ (ተሰበለበ፣ ተስገበገበ)። ተረት: “ለገቢህ ተንገብገብ። ”
ተንገብጋቢ: የሚንገበገብ (ተስገብጋባ)።
ተንገታገተ: ነገር መላለሰ፡ ተንገዛገዘ።
ተንገቸገቸ: አጋሰስኛ፣ አህይኛ ኼደ፡ ዘክዘክ፣ ዘጥዘጥ አለ።
ተንገቸገቸ: ዘክዘክ አለ፡ (ገቸ) ።
ተንገዋለለ፡ ዞረ፣ ተንጓለለ፣ ጓለበ፣ ለየ።
ተንገዋላይ፡ የሚንገዋለል።
ተንገዛገዘ፡ ተንገታገተ፣ ለንባዳ ሆነ፡ ሲናገር ተርበተበተ።
ተንገደገደ፡ ተግተረተረ፣ ተርገደገደ፣ ተፍገመገመ።
ተንገዳገደ፡ ተወዛወዘ፣ ተነቃነቀ።
ተንገድጋጅ፡ የሚንገደገድ፣ ተግተርታሪ፣ ገደገድ፣ ገድጋዳ፣ ወዝዋዛ፣ ነቅናቃ፣ ቀጥቃጣ።
ተንገጫገጨ፡ ተጋጩ፣ ተንቀጫቀጨ።
ተንገፈለለ፡ ሳያፈራ ቀረ፡ ላንፋ ብቻ ኾነ (አገዳው)።
ተንገፈለለች፡ ልጃገረዲቱ ባል ሳታገባና ሳትወልድ ቀረች።
ተንገፈገፈ፡ ተሠቀቀ፣ ተንገሸገሸ።
ተንገፈጠጠ፡ ሰፋ፣ ተነፋ (ከበሮ መሰለ)፡ ተንዘረጠጠ፣ ተንቀበደደ።
ተንጋለለ፡ በዠርባ ተኛ፣ ተንካረረ (ለመታከም፣ ለማመንዘር፣ ለማጥባት)። (ተረት)፡ "ከጸደቁ አይቀር ይንጋለሉ"። "የመንታ እናት ተንኦሮ ትሞት"።
ተንጋተተ: ተንጋፈፈ፣ ተንከረፈፈ፡ አባ አይረባ ኾነ።
ተንጋደደ፡ ተጣመመ፣ ተወላገደ፣ ተወላገመ፣ ተወላቀመ።
ተንጋዳጅ፡ የሚንጋደድ፣ የሚጠም፣ ተጣማሚ።
ተንጋጋ፡ ተቃጠለ፣ ነደደ።
ተንጋጋ፡ ተንጃጃ፡ ረባ፣ በዛ፡ በብዛት ኼደ፣ ተነዳ።
ተንጋጠጠ፡ ቀና (ሰማይ)፣ ሰማይ አየ (ዐይኑ)፡ ሰገገ (ዐንገቱ)።
ተንጋጣጭ፡ የተንጋጠጠ፣ የሚንጋጠጥ፡ ሰማይ፣ ዳሱ።
ተንጋፈፈ፡ ተንቀረፈፈ፣ ተንቃፈፈ።
ተንጐራዳጅ: የሚንጐራደድ፡ ተንቈራጣጥ።
ተንጐበደደ: ጐበደደ።
ተንጐደጐደ (አንጐድጐደ)፡ ጮኸ፣ ተሰማ።
ተንጐዳጐደ፡ በቤት ውስጥ ሮጠ፣ ወዲያና ወዲህ አለ፣ አተፈተፈ።
ተንጐፈለለ፡ ረዘመ (ጐፍላው)።
ተንጐፈጐፈ፡ "ሩጭ ሩጭ" አለ (ያሮጌ ያሮጊት)።
ተንጐፈጠጠ፡ ጐፈጠጠ።
ተንጓለለ፡ ተንገዋለለ።
ተንጓሰሰ: ተንቋሰሰ፣ ተንቈረሰሰ፣ ተጐተተ፡ ቀስ ብሎ ኼደ።
ተንጓበበ: ጐበበ። የሞፈር ጫፉ ወደ ታች፣ መካከለኛው ወደ ላይ ሆነ።
ተንጓጓ፡ ጮኸ፣ ተሰማ (የሆድ፣ የደንጊያ፣ የደመና)።
ተንጓፈፈ፡ ደከመ፣ ታከተ፡ በቀስታ ኼደ፣ ተንቈረሰሰ (ከርጅና የተነሣ)።
ተንጠለጠለ፡ ተሰቀለ፡ ተሰቀጠጠ፡ ተንዘለዘለ (ዘዳ፳፰፡ ፷፮። ፪ሳሙ፡ ፳፩፡ ፲፫። ሰቈ፭፡ ፲፪)።
ተንጠለጠለ፡ ከበደ፡ ደመናው ፊቱ፡ አረገዘ፡ ግንቡ።
ተንጠላጠለ፡ ዛፍን፡ ገደልን፡ ምሰሶን፡ ትከሻን ወጣ፡ ተወጣጣ፡ ተዛዘለ።
ተንጠላጣይ፡ የተንጠላጠለ፡ የሚንጠላጠል፡ ተዛዛይ።
ተንጠልጣይ፡ (ዮች)፡ የሚንጠለጠል፡ የሌት ወፍ፡ ተሰቅጣጭ።
ተንጠረበበ፡ ጠቈረ፡ ከበደ፡ ተንጠለጠለ።
ተንጠረገገ፡ ተንጠረበበ።
ተንጠረጠረ፡ ተንቀረቀበ፡ ተለየ።
ተንጠረጠረ፣ ተንቀጠቀጠ፡ ተንጠበጠበ።
ተንጠራራ፡ እደርስ እደርስ፡ አገኝ አገኝ፡ እይዝ እይዝ አለ፡ አላቅሙ ተመኘ።
ተንጠቀጠቀ፡ ተንተከተከ፡ ተፈናጠረ።
ተንጠቀጠቀ፡ ተንተገተጉ፡ ተብረቀረቀ፡ ተሸለመ፡ ተንቈጠቈጠ።
ተንጠቀጠቀ፡ ፈላ፡ በሰለ።
ተንጠበጠበ: ተንቀጠቀጠ።
ተንጠባጠበ: መዝነብ ዠመረ፣ ጠብ ጠብ አለ፡ ተንጠፈጠፈ፡ የትም ወድቆ ቀረ። መጽሐፍ ግን በተንጠባጠበ ፈንታ "ተንጠበጠበ" ይላል (ሚክ ፭፡ ፯)።
ተንጠባጣቢ: የሚንጠባጠብ (የተክል፣ የእኸል ፍሬ)።
ተንጠፈጠፈ፡ ፈሰሰ፡ ጠብ ጠብ አለ፡ ተንጠባጠበ።
ተንጣለለ፡ ፈሰሰ፡ ሰፋ፡ ሰፊ ሆነ፡ ተዘረጋ፡ ተኛ፡ በዛ፡ በረከተ፡ የውሃ፡
የቤት፡ የድንኳን። "የተንጣለለ ቅቤ" "የተንጣለለ መሬት" "የተንጣለለ ምርት" እንዲሉ።
ተንጣላይ፡ የሚፈስ፡ የሚንጣለል።
ተንጣረረ፡ ተፈሳ፡ ጮኸ።
ተንጣጣ፡ ቀባጠረ፡ ለፈለፈ።
ተንጣጣ፡ ተቈላ። (ተረት)፡ "የምጣዱ ሳለ የንቅቡ ተንጣጣ። "
ተንጣጣ፡ ተፈሳ፡ ጮኸ።
ተንጦለጦለ፡ ተንቀዠቀዠ። "ካንዱ ቤት አንዱ ቤት ኣለ"።
ተንጦሸጦሸ፡ ጦሽ ጦሽ አለ፡ ተንጣጣ።
ተንጦዘጦዘ፡ ተንከወከወ፡ ተዚያ እዚያ አለ።
ተንጨረገገ: ተንዠረገገ፡ ተንጠለጠለ።
ተንጨረገገ: ጠቈረ።
ተንጨረጨረ: መልሶ መላልሶ እንደ እንጭራር ጮኸ።
ተንጨረጨረ: እጅግ ተቈላ፡ ተጠበሰ።
ተንጨረፈፈ: አደገ፡ ረዘመ፡ ቆመ፡ ደረቀ፡ ተንጨፈረረ።
ተንጨበረረ፡ (ጨበረረ)፡ ተቃጠለ፡ ተንጨፈረረ።
ተንጨፈረረ: ተንጨረፈፈ።
ተንጨፈጨፈ: በማጠቢያ ላይ ተመታ፡ ታጠበ።
ተንጨፈጨፈ: አዠ፡ ወዛ፡ የፊት።
ተንጫረረ: ተቃጠለ፡ ተንጨበረረ፡ ዐረረ፡ ገመነ፡ ተኰማተረ፡
ጮኸ።
ተንጫጫ፡ ተንቻቻ፡ ጮኸ፡ ተፋጀ። (ተረት)፣ "ተልባ ቢንጫጫ በሙቀጫ። "
ተንፈላሰሰ: ባልጋ፡ በፍራሽ፡ በመከዳ ላይ ተደገፈ፡ አንደዬ በቀኝ፡ አንደዬ በግራ ተኛ፡ ተጋደመ፡ በዠርባው ተንከባለለ፡ ተገላበጠ፡ ከድሎት፡ ከምቾት የተነሣ።
ተንፈላሳሽ: የሚንፈላሰስ (ደም የጠገበ ውሻ)።
ተንፈሳለቀ: ተንፈላሰሰ፡ አላገጠ።
ተንፈረከከ: እግሩ ተለያየ።
ተንፈረዘዘ (ተፈርዘዘ): ጠገበ፡ ተቀበነነ፡ በጥጋብ ተነፋ፡ ዐበጠ ሆዱ፡ ተደሰተ፡ ተቀማጠለ፡ ጸጥ አለ፡ ረጋ ሰውየው።
ተንፈረፈረ: ተሠራ፡ ፈላ፡ ተግፈለፈለ እንፍርፍሩ።
ተንፈራገጠ: እግሩ ተንቀሳቀሰ፡ ታጠፈ፡ ተዘረጋ ከጣር፡ ከመከራ የተነሣ።
ተንፈራጠጠ: በስፋት ቆመ፡ ተቀመጠ፡ ተንዘራፈጠ።
ተንፈራጣጭ: የተንፈራጠጠ፡ የሚንፈራጠጥ።
ተንፈራፈረ: ተንደፋደፈ፡ ተንዘፈዘፈ፡ ተንቀጠቀጠ (፩ሳሙ፡ ፳፩፡ ፲፫)።
ተንፈራፋሪ: የተንፈራፈረ፡ የሚንፈራፈር።
ተንፈጯፈጨ: ፈላ እንደ ላብ፡ መነ፡ ወረዛ፡ አዠ፡ መረቁ፡ ምራቁ፡
ውሃው።
ተንፋለለ: ረዘመ፡ ወረደ፡ ወደቀ።
ተንፋሰሰ: ውህኛ ኼደ በቅሎው።
ተንፋሳሽ: የተንፋሰሰ፡ የሚንፋሰስ።
ተንፋቀቀ: በቂጡ ኼደ።
ተንፋቃቂ: የሚንፋቀቅ፡ በቂጡ መሬትን የሚፈትግ፡ መሬት ቂጡን የሚፈትገው በሽተኛ ሰው።
ተንፋከከ: ተራራቀ እግሩ፡ ወይም ሰውየው ባካኼዱ።
ተንፋፋ: ወረደ፡ ፈሰሰ፡ ብዙ ድምፅ ሰጠ።
ተንፎሸፎሸ: ወሬ ነዛ፡ ነፋ፡ ቀለለ።
ተንፎከፎከ: ተሸነ፡ ተንዠቀዠቀ።
ተንፎደፎደ: ተንበደበደ፡ ፈራ (መፍራት)።
ተኖ: ሰኞ፣ ጨሶ ተበትኖ።
ተኖረ: ተቈየ፣ ተዘገየ፣ ተከረመ።
ተኗኗረ: በኑሮ ተባበረ።
ተኛ: (ዊ) "በስም ጫፍ እየታከለ 'ወገን' ቅጽልነትን ያሳያል። (ማስረጃ) ገበያ፡ ገበያተኛ፡ ዋና፡ ዋነተኛ: ያ፡ ያተኛ፡ ነገር፡ ነገረተኛ፡ ቀለብ፡ ቀለብተኛ፡ ምስጢሩም ሲሠራ የዋለ የኖረ ማታ መጋደሙን መጨረሻ ዕረፍቱን (ሞቱን) ያሳያል። ብዙ ጊዜም ኛ ከቶ እየተለየ ብቻውን ይነገራል፡ ኛን ተመልከት።"
ተኛ: በግብር ዐወቀ፣ ተናኘ (ሴትን)። (ግጥም)፡ "ካንተ ተኝታ ሌላ ታማራት በል ተነሣና በዱላ በላት።"
ተኛ: ዐረፈ፣ ሞተ (፩ኛ ቆሮንቶስ፡ ፲፭፡ ፯፡ ፲፰)።
ተኛ: የቅርብ ወንድ ትእዛዝ፣ አንቀጽ። "ተጋደም እንቅልፍ ይውሰድኸ (፩ኛ ሳሙኤል፡ ፫፡ ፮፡ ፮፡ ፱)።"
ተዐቃቢ: ተጠባቂ (የሚጠበቅ)።
ተዐቅቦ: መጠበቅ፡ ተጠብቆ መኖር። "አንቀጽን" እይ (መጠበቅ)።
ተዓቃቢ: ተጠባባቂ። "ዮሐንስ ተዓቃቢ" እንዲሉ።
ተዓቅቦ: መጠባበቅ። (ጥቅ) ዕቅብ: የታቀበ፡ የተሸፈነ፡ ግድግዳ፡ ድግፍ (የተጠበቀ)።
ተኦሮጭ፡ የሚጋለጥ፡ ተራቋች።
ተከለ: ሰካ፣ ሳገ፣ አቆመ።
ተከለ: ቀላድ (ምድር) ሰጠ (ውርርድ ተከለ)፡ ማር እሰጥ አለ።
ተከለ: ትኋን ያልጋ ተባይ።
ተከለ: አጸና፣ መሠረተ (አለማ)። "ግብር ተከለበት፡ ሳል ተከለበት እንዲሉ።"
ተከለለ: ለበሰ፣ ተጋረደ፣ ተመከተ፣ ተቀየደ፣ ታጠረ፣ ተቀጠረ።
ተከለለ: ለበሰ፡ ተጋረደ፡ ተመከተ፡ ተቀየደ፡ ታጠረ፡
ተቀጠረ። ተሰወረ፡ ታወረ። ተወሰነ፡ ተገደመ፡ መማጠኛ፡ መደወያ ኾነ። ተቈረጠ፡ ተሰየፈ። አክሊል ደፋ፡ ተቀዳጀ።
ተከለሰ: ተመልሶ ተሠራ፣ ተጠና።
ተከለሰ: ተመልሶ ተሠራ፡ ተጠና። ተፈተነ፡ ቀለጠ፡ ነጠረ (ዘካ፲፫፡ ፱)። ተጨመረ፡ ተቀላቀለ። ተጨረሰ፡ ተፈጸመ፡ መላ። ተደቀለ።
ተከለበሰ: ተከነበለ፡ ተቸለሰ፡ ፈሰሰ።
ተከለከለ (ተከልከለ): ተከላ፡ ታገደ፡ ቆመ፡ ታገረ፡ ቀረ፡ ተጠበቀ፡ ሐይ ተባለ፡ ተተወ (ዘፀ፴፮፡ ፮፡ ዘኍ፲፮፡ ፵፰-፶፡ ኢዮ፳፱፡ ፱፡ ፵፪፡ ፪፡ ሮሜ፩፡ ፲፲፪)። "መነኵሴ ሥጋ እንዳይበላና ጠጅ እንዳይጠጣ በገዳም ሥራት ተከለከለ"። "፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ማዚያ ፳፯ ቀን ሥራ እንዳይሠራ በአዋጅ ተከለከለ"።
ተከለፈ: ተሰረቀ፣ ተቀማ፣ ተነጠቀ።
ተከላ: ትክሎሽ (ትክለት)፣ የመትክል ሥራ።
ተከላሽ: የሚከለስ፣ የሚጨመር።
ተከላከለ: ተጠባበቀ፡ እየሸሸ እያፈገፈገ ጥቂት ጥቂት ተዋጋ፡ አልሞት ባይ ተጋዳይ፡ ተኳዃነ። ተነሣሣ።
ተከላካይ (ዮች): የተከላከለ፡ የሚከላከል።
ተከላይ: የሚከለል፣ ተጋራጅ።
ተከልካይ: የሚከለከል፡ የሚጠበቅ።
ተከመረ: ተደረደረ፡ ተደረበ፡ ተዘመመ፡ ተጐቸ፡ ተቈለለ። ወደቀ፡ በላይ ኾነ፡ ተጫነ ለመያዝ። ለምሳሌ
"እከሌ በደን ውስጥ ሲኼድ ድንገት ነብር ተከመረበት።
"
ተከመረ: ተደረደረ (ተደረበ ተዘመመ ተጐቸ ተቈለለ) ።
ተከመቻቸ: ተሰባሰበ ወይም ተጠረቃቀመ ማለት ነው።
ተከመከመ: ተከፈከፈ፡ ተተካከለ (ጠጕር)።
ተከማሪ (ሮች): የሚከመር ነዶ ወይም ድርቆሽ ማለት ነው። ይሁን እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ (፩ ነገሥት ፯:፲፮-፲፯) ላይ 'ጉልላት' ከሚለው ቃል ይልቅ 'ተከማሪ' የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል።
ተከሰለ: በከሰል፣ በርሳስ ተመለከተ፡ ተጻፈ፡ ታረመ፡ ተሠረዘ።
ተከሰመ: ተተከለ፡ ተቸከለ፡ ተቀበቀበ፡ ተገደገደ፡ ተወጠረ።
ተከሰሙ: ገባ፡ ሰፈረ፡ ሀደረ።
"እከሌ ዛር ተከስሞበታል" (ማለትም ዛር አድሮበታል)።
ተከሰሰ: ባለጋራ ወጣበት፡ በክስ ተያዘ፡ ከነገር ገባ፡ እዳኛ ፊት እንዲቀርብ ቀላጤ መጣበት፡ "ሰው ይማጠንኻልና በዚህ ቀን እንድትመጣ" ተባለ፡ ደብዳቤ ወይም ማዘዣ ተጻፈለት። (ተረት)
"የትም ተከሰስ፡ አለቃሽ ድረስ።
"
ተከሰረ (ከሰረ): ብዙ ገንዘብ ወጪ ሆነ (ለአንድ ሥራ)።
ተከሠተ (ተከሥተ): ተገለጠ፣ ግልጥ ሆነ፣ ታየ ወይም በራ።
ተከሰከሰ: ተጠጋጋ፡ በዛ።
ተከሰከሰ: ተፈነከተ፡ ደቀቀ ወይም ተሰበረ። "ማታ ስሄድ ወደቅሁና እሾህ ተከሰከሰብኝ። "
ተከሳሽ (ሾች): የሚከሰስ፡ የከሳሽ ወደረኛ፡ መልስ ሰጪ።
ተከሳሽነት: ተከሳሽ መሆን።
ተከሳከሰ: ተባባለ፡ ተፈናከተ፡ ተሳበረ፡ ተዳቀቀ።
ተከረ (ተከነ) ፡ ተቀጨቀጠ ነዘነዘ ።
ተከረ: ተፋተነ፡ ተዣመረ፣ ተባባለ።
ተከረመ: ተወጣ፣ ተዘለቀ ወይም ታለፈ (ክረምቱ፣ ዓመቱ)።
ተከረረ (ከረረ): በጥብቅ ተፈተለ፡ ወይም እንደ ገና ፪ኛ ጦዘ፣ ተጠመዘዘ በንዝርት፡ በ፪ ውስጥ እጅ (ለምሳሌ በዘጸአት ፳፮:፩ ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተከረበ: ተነፋ፣ ዐበጠ ወይም ተወጠረ።
ተከረበተ: ተገለገለ፣ ተገለበጠ ወይም ተጋደመ።
ተከረተ: ተከረተፈ፡ ተዘረጋ ወይም ተሰጣ።
ተከረተሰ: ተቈረጠመ፣ ተሰበረ፣ ታኘከ ወይም ደቀቀ።
ተከረተፈ: ተገረደፈ ወይም ተፈጨ።
ተከረቸመ: ተቸነከረ፡ ተጠቀጠቀ፡ እግር ብረት ገባበት፡ በጥብቅ ታሰረ።
ተከረነተ: በጥብቅ ታሰረ ወይም ተጠፈረ።
ተከረና: በኵርማ ተደሰቀ ወይም ተወጋ።
ተከረከመ: ተቈረጠ፣ ተቀረጠፈ ወይም ታፈፈ።
ተከረከረ: ተመገዘ፣ ተገዘገዘ ወይም ተቈረጠ።
ተከረፈተ: ፈጽሞ ተከፈተ።
ተከራረመ: ተዘላለቀ።
ተከራከረ: ተገተ፣ ተፈካከረ፡ በነገር ተመላለስ፡ ነው አይዶለም ተባባለ፡ ተፈታጨቀ፡ እምነት ክደትን ተነጋገረ (ለምሳሌ በዘፍጥረት ፳፮:፳፣ ኢሳይያስ ፵፩:፲፩ እና ሉቃስ ፪:፴፬ ላይ እንደተጠቀሰው)። "መከርከር ለመቀረጥ እንደ ሆነ፡ ይህም አንዱ ሌላውን ለማሸነፍ ነው። "
ተከራካሪ (ዎች): የተከራከረ ወይም የሚከራከር፡ ተጋች ወይም ተጨቃጫቂ።
ተከራካሮች: ተከራካሪዎች።
ተከራየ: ለተከራይ ተሰጠ (ቤቱ)።
ተከራየ: ውሉ ሲያልቅ ሊለቅ ወይም ሊመልስ (ሰው ቤት) በክራይ ገባ፡ የሰው ከብት ወሰደ።
ተከራዩ: ያ ተከራይ።
ተከራይ (ዮች): ማንኛውንም ነገር የተከራየ ወይም የሚከራይ፡ ተዋዋይ።
ተከራይቷል: በክራይ ተይዟል።
ተከራይዋ: ያች ተከራይ።
ተከርካሪ: የሚከረከር፡ ተመጋዥ።
ተከሸነ: ተቀረደደ፡ ተከተፈ፡ ትክክል ሆነ።
ተከሸነ: አማረ፡ ሰመረ።
ተከሸከሸ: ታኘከ፡ ተበላ።
ተከበሰ: ተጠመጠመ፡ ተደመረ፡ ተከመረ፡ ተደረበ። ተጠመዘዘ፡ ተጠቀለለ፡ ታሰረ። ዐበጠ፡ ተድበለበለ።
ተከበረ (ከበረ): በሰው ዘንድ ወይም በገዛ አፉ ተመሰገነ፡ ተጓደደ። ታረፈ፡ በዓል ኾነ። በሹም ሥልጣን ተያዘ፡ ተጠበቀ ርስቱ፡ ገንዘቡ።
ተከበበ: ታጀበ። ክብ ኾነ፡ ተደረገ።
ተከበበ: ዙሪያው ተያዘበት።
ተከበከበ: ተደገሰ፡ ተሰረገ፡ በመብል ተጠበቀ።
ተከበደ: ተጨቈነ፡ ተጨነቀ።
ተከባሪ (ከባሪ): የሚከበር፡ ራሱን አኵሪ፡ "እኔ እከሌ የእከሌ ልጅ" ባይ፡ ተጓዳጅ።
ተከባሪነት: ተከባሪ መኾን።
ተከባበር: ክብር ተቀባበለ፡ "አንተ ትብስ አንተ ትብስ"
ተባባለ።
ተከባቢ: የሚከበብ፡ ክብ የሚኾን።
ተከባባሪ: የሚከባበር፡ ወዳጅ፡ ባልንጀራ።
ተከባከበ: ተሰራረገ፡ ተመጋገበ፡ ተከናከነ (በየጊዜው በየሰዓቱ መገበ፡ አይንፈስ ብኸ አለ፡ ተጠንቅቆ ጠበቀ)።
ተከባካቢ: የሚከባበር፡ ወዳጅ፡ ባልንጀራ።
ተከባካቢ: የተከባከበ፡ የሚከባከብ።
ተከተለ (ከተለ): ለጠቀ፡ ቀጠለ፡ ዐጀበ፡ በነገር፣ በሥራ፣ በሥልጣን፣ በንብረት ተተካ (ለምሳሌ በዘፀአት ፲፬:፰ ላይ እንደተጠቀሰው)። "ተለጠቀ፣ ታጀበ" ቢል በቀና ነበር።
ተከተል: የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ፡ "በስተዠርባ ኺድ፡ ለጥቅ።
" "ቅደም ተከተል"። "ተመልከት ዐላማኸን፡ ተከተል አለቃኸን"
እንዲሉ።
ተከተመ: ተቈረቈረ፡ ተሠራ፡ ተበጀ።
ተከተረ: በልብ ተያዘ፡ ዐደረ።
ተከተረ: ተደለደለ፡ ተከበበ፡ ተገደበ፡ ታገደ፡ በዛ።
"ባጤ ይሙቱ የተከተረ፡ በስለት የተመተረ።
"
ተከተበ (ተከትበ፣ ተከስበ): ተጻፈ፡ ተጣፈ፡ ተሠነተረ፡ ተሠነጠቀ (ክንዱ)፡ ተቈረጠ (ዐጽቁ፣ ጫፉ)፡ ተጋባ፡ ተገናኘ፡ ተራከባ፡ ተቀላቀለ፡ ተዛመደ፡ አንድ ሆነ (ከትብት)።
ተከተተ: ተሰበሰበ፡ ተጠራቀመ፡ ተወመረ፡ ተዶለ፡ ገባ፡
ተሰናዳ፡ በውስጥ ሆነ። "ሰው ከተከተተ ዥብ ካኰተኰተ" እንዲሉ።
ተከተተ: ተጨረሰ፡ ተፈጸመ።
"ነገር ዐለቀ ተከተተ"፡ "አባቴ እሸቴ ሞተ" (ነጋድራስ ተሰማ)።
ተከተከ: ክፉኛ አሳለ።
ተከተከተ: ተቀጠቀጠ፡ ተጨፈጨፈ፡ ተቈረጠ።
ተከተፈ: ተመተረ፡ ተቈረጠ፡ ጠቀነ፡ ሸከፈ፡ ደቀቀ።
ተከታለበ: ተካለበ።
ተከታሚ: የሚከተም፡ ከተማ የሚሠራበት።
ተከታሪ: የሚከተር፡ ተከባቢ።
ተከታቢ: የሚከተብ (ልጅ፣ ተክል፣ ከብት)።
ተከታቢዎች: የሚከተቡ (ልጆች፣ ከብቶች)።
ተከታተለ: ተቀጣጠለ፡ ተለጣጠቀ፡ ነገር ተጠባበቀ።
ተከታተመ (ተዓየነ): ፊት ለፊት፡ አንጻር ለአንጻር፡ ጐን ለጐን ተሳፈረ፡ ተሰፋፈረ (ድንኳን ተከለ፡ ሰፈር አደረገ) (የዘማች፣ የጦር ሰራዊት)። "ይዩ"።
ተከታታይ (ዮች): የተከታተለ ወይም የሚከታተል፡ ተጠባባቂ።
ተከታች: የሚከተት።
ተከታይ (ዮች): የተከተለ ወይም የሚከተል፡ ለጣቂ፡ አሽከር፡ ገረድ፡ ልጅ፡ ወራሽ፡
ደቀ መዝሙር፡ ጥጃ፡
ግልገል፡ ተተኪ (ለምሳሌ በ፩ኛ ጴጥሮስ ፫:፲፫ ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተከታይ: ታናሽ ወንድም፡ ጡት ኣስጣይ።
ተከታይነት: ተከታይ መሆን።
ተከታፊ: የሚከተፍ (ብርንዶ፣ ቅቅል)።
ተከነ: በገነ ነደደ ገመነ ፈላ በሰለተቈጣ ።
ተከነበለ: ተበጀ (አክንባሎው)፡ ተሰፋ (ወስከንባዩ)።
ተከነበለ: ተከደነ ወይም ተገጠመ።
ተከነበለ: ወደቀ፣ ተደፋ፣ ተቸለሰ፣ ተገለበጠ ወይም ፈሰሰ።
ተከነተረ: ተመታ፣ ተገደለ ወይም ቶሎ ሞተ።
ተከነተሸ: ተበጠሰ፣ ተቈረጠ ወይም ዐጪር ሆነ።
ተከነቸረ: ተከነተረ፣ ደበነ ወይም ተፈነቸረ።
ተከነዋወነ: ተቀለጣጠፈ።
ተከነዳ: ተለካ፣ ተመጠነ ወይም ተሰፈረ። እንዲሁም ተከፈለ ወይም ተሰጠ።
ተከነዳዳ: ተለካካ።
ተከናነበ: ተጐናነበ ወይም ተሸፋፈነ (ለምሳሌ በኤርሚያስ ፲፬:፫-፬ እና ፩ቆሮንቶስ ፲፩:፬-፭ ላይ እንደተጠቀሰው)። ምሳሌ: "እከሌ ንብ በከበበው ጊዜ ተከናነበ። " (ተረት) "ትለብሰው የላት፣ ትከናነበው አማራት። "
ተከናናቢ: የሚከናነብ ወይም ተሸፋፋኝ።
ተከናከነ: ተቀናቀነ።
ተከናከነ: ተከባከበ (ጠበቀ)።
ተከናወነ (ከነወነ/ከወነ): (ጣዕጣ፣ ተሰልጠ) ተቃና፣ ተሳካ፣ ቀለጠፈ፣ ዐለቀ ወይም ተጣጣመ ማለት ሲሆን ፍጹም ሆነ ማለትም ነው (ለምሳሌ በዘዳግም ፳፱:፱ እና መዝሙር ፩:፫ ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተከናዋኝ: የሚከናወን።
ተከናዳ: በክንድ ተላካ።
ተከንባይ: የሚከነበል ወይም የሚደፋ።
ተከኪ: የሚከካ።
ተከካ: ተሰበረ፡ ተፈነከተ፡ ተከፈለ።
ተከወሰ: ተነቀነቀ፡ ተበጠበጠ።
ተከወነ: ተበጀ፡ ተዘጋጀ፡ ተደረገ፡ ተቀናበረ፡ አጌጠ፡
አማረ፡ ሰመረ።
ተከዘ: አዘገመ፣ ቈየ። "ዐለንጋ እስቲዝ በክርን ይተክዙ። እራት እስቲቀርብ በጥሬ ተከዘ።"
ተከዘ: ፈሰሰ፣ ወረደ (ግእዝ)።
ተከዚ: ተከዜ። "የዠማ ስም ከላስታ የሚነሣ ወንዝ በአትባራ ከ፪ቱ አባዮች ጋራ የሚገጥም ታላቅ ፈሳሽ የትግሬንና የበጌምድርን ጠቅላይ ግዛቶች የሚለይ ዥረት በግእዝ ሲናበብ ተከዜ ይባላል።"
ተከየ (ተሀከየ): ሰነፈ፡ ለገመ፡ ሀኬተኛ፡ ልግመኛ፡ እከየኛ ኾነ፡ ቸል አለ።
ተከየ: ለገመ፡ ሰነፈ፡ ቸል አለ፡ ዋሾ፣ ቀጣፊ፣ አታላይ ኾነ ።
ተከደነ: ተጨፈነ (ዐይኑ)፣ ተዠመረ (እንቅልፉ)።
ተከዳ (ተከድዐ): ታዛዥ ዐጣ፡ ብቻውን ቀረ።
ተከዳተኛ (ኞች): የከዳት ወገን፡ ሽፍታ፡ ወንጀለኛ፡ እያዘነጋ ሰው የሚገድል (ሚክ፮፡ ፲፩)።
ተከዳተኛነት: ከዳተኛ መኾን፡ ሽፍትነት።
ተከዳት (ከዳዕት): የከዱ፡ የሚከዱ።
ተከዳኝ: የሚከደን፡ ጣራ፡ ሰንበሌጥ።
ተከዳዳ: ተካካደ።
ተከጀለ: ታሰበ፡ ተሻ፡ ተፈለገ፡ ተላወጠ፡ የምግብ፡
የባለምግብ።
ተከጃይ: የሚከጀል።
ተከጃጀለ: ተፈላለገ፡ ተፈቃቀደ፡ "ባገኘኹት ባገኘኹት"
ተባባለ፡ በልብ፡
ባሳብ።
ተከጃጃይ: የሚከጃጀል፡ ተፈላላጊ።
ተከፈለ (ተከፍለ): ተለየ፡ ሁለት ሆነ። ለሙሴ ኤርትራ፣ ለኢያሱና ለኤልያስ፣ ለኤልሳዕ ዮርዳኖስ ተከፈለ (ለምሳሌ በዘፀአት ፲፬:፳፩፣ ኢያሱ ፫:፲፮፣ ፪ ነገሥት ፪:፰-፲፬ ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተከፈለ: ተመለሰ ወይም ተሰጠ (ገንዘቡ)፡ ተቀበለ (አበዳሪው)።
ተከፈተ: ተወለለ፣ ተገለጠ፣ በራ፣ ተፈታ ወይም ተለቀቀ፡ መናገር ተቻለው (ለምሳሌ በ፩ ነገሥት ፲፮:፴፬፣ ሉቃስ ፩:፷፬ እና ሕዝቅኤል ፴፫:፳፪ ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተከፈነ: ለበሰ፣ ተሸፈነ፣ ተጠቀለለ ወይም ተገነዘ።
ተከፈከፈ: ለበሰ።
ተከፈከፈ: ተበጠረ ወይም ተከመከመ።
ተከፈከፈ: ተከደነ፣ ተመታ ወይም ተተካከለ።
ተከፈፈ: በክፈፍ ተሠራ፣ ተበጀ ወይም ተሰፋ፡ ክፈፍ ሆነበት ወይም ተደረገበት።
ተከፊ: የሚከፋ፡ ተቀያሚ።
ተከፋ: ተቀየመ፣ ዐዘነ፣ ተከዘ ወይም ተቈቈረ (ለምሳሌ በኢሳይያስ ፲፭:፬ ላይ እንደተጠቀሰው)። "የተከፋ ተደፋ" እንዲሉ።
ተከፋች: የሚከፈት።
ተከፋይ: ተቀባይ።
ተከፋይ: የሚከፈል፡ ለባለዳ የሚሰጥ።
ተከፋፈለ: ብድርን ተቀባበለ።
ተከፋፈለ: ተለያየ (እየብቻው፣ እየራሱ)፡ ተኳዃነ ወይም ተፈራቀቀ።
ተከፋፈት: ተዘረጋጋ ወይም ተገላለጠ።
ተከፋፊ: የሚከፈፍ።
ተከፋፋ: ክፉ ተኳዃነ፡ ተቀያየመ፣ ሆድ ተባባሰ ወይም ተጨካከነ።
ተከፋፋይ: የሚከፋፈል ወይም የሚለያይ።
ተከፍካፊ: የሚከፈከፍ (ቤተ ክርስቲያን፣ የሀብታም ቤት)።
ተኵለፈለፈ: ጥርክርክ ኾነ፡ እንዳሣማ፡ ኵልፍልፍ።
ተኵላ (ሎች) ፡ ያውሬ ስም
(የበረሓ ውሻ የበግ ያንበሳ ጠላት ነጣቂ - "ዐይንን" ተመልከት) ።
ተኵስ: ከቀኝ ወደ ግራ የተሰፋ የነጠላ ጠርዝ ስፌት። "ተኵስ ስፌት እንዲሉ።"
ተኵስ: የዐይን፣ የከብት፣ የገላ ጠባሳ፣ የሌባ ምልክት፣ የነፍጥ ድምጥ።
ተኵነሰነሰ: ካህንኛ ታቦትኛ ለባበሰ፣ ተሸላለመ ወይም ተሽቀረቀረ።
ተኪ: የተካ፣ የሚተካ፣ ከፋይ፣ ወካይ።
ተካ፣ ተካልኝ: የሰው ስም።
ተካ: (ትግ፡ ተክአ)።
ተካለለ: ተገራረደ፣ ተዋሰነ፣ ተዳካ።
ተካለሰ: ተጫረሰ፣ ተማላ።
ተካለሰ: ተጫረሰ፡ ተማላ። ተዳቀለ።
ተካለበ: ተሯሯጠ፡ ተቻኰለ፡ ተጣደፈ።
ተካላይ (ዮች): የሚካለል፡ ተዋሳኝ።
ተካላይ: የሚካለል፣ ተዋሳኝ።
ተካሰ: ካሳ ተቈረጠለት፡ ተቀበለ፡ ተረከበ። (ተረት)
"እካስ ያለ ታግሦ፡ እጸድቅ ያለ መንኵሶ። "
ተካሠሠ (ተኃሠሠ/ተፈላለገ): ፈለገ፣ ጠየቀ፣ ማለደ፣ ለመነ፡ ተቀናቀነ። "ሹመት ተካሠሠ" እንዲሉ መተርጕማን።
ተካሰሰ:
"ዳኘኝ ዳኘኝ"
ተባባለ፡ የክስ ብድር ተከፋፈለ፡ እዳኛ ፊት ተቃረበ፡ ተቋቋመ (ዘፀአት ፳፪:፬)።
ተካሰሰ: ሹመት ተቀናቀነ።
ተካሳሽ: የተካሰሰ ወይም የሚካሰስ።
ተካረመ: ተቻቻለ፣ ተዛለቀ ወይም ተኗኗረ።
ተካረረ: ተጋመደ፡ ተማረረ ወይም ተባባሰ።
ተካሪስ፣ አተካሪስ: በቀሚስ ላይ የተሰፋ ድንድን፣ መታጠቂያ። "አባ፡ ብለኸ፡ አባ ወራን፡ እይ።"
ተካራ፣ ተኻራ: አተካራ።
ተካሽ: የሚካስ፡ ካሳ ተቀባይ።
ተካበ (ተክዕበ): ተደረበ፡ ተነባበረ፡ ደንጊያ በደንጊያ ላይ ኾነ። የሰው ስም።
ተካበበ: የከባቢ ተከባቢ፡ ተኳዃነ፡ ተዟዟረ።
ተካበች: የሴት ስም።
ተካበደ: ከበደ፡ (ተመናዘለ)። "ሸኽ አለልክ ይካበዳል። "
ተካባጅ: የሚከብድ፡ (የሚካበድ)።
ተካተተ: ተከናወነ (ዐለቀ፣ ደረሰ፣ ተፈጸመ)።
ተካቶ: ተፈጽሞ፡ ዐልቆ፡ ተወርሶ።
ተካነ (ተክህነ): ዳቆነ፣ ድቍና ተቀበለ ወይም ካህን ሆነ ማለት ነው (ለምሳሌ በዘፀአት ፳፱:፴፬ ላይ እንደተጠቀሰው)። በተጨማሪም የክህነት ሥራ ሠራ፣ አገለገለ፣ ቀደሰ ወይም ሠለሰ ማለት ነው።
ተካነ: ቅቤና ቅመም ገባበት ማለት ነው፡ ጣመ፣ ጣፈጠ። ወጥ ሲሆንም ይጠቀሳል።
ተካነ: ዲያቆን ኾነ፣ ካነ።
ተካኝ (ኞች): የሚካን፣ ክህነት የተቀባይ።
ተካኝ: ተናዳጅ ተከነ።
ተካኝ: የሚተክን፣ ተናዳጅ።
ተካኝ: የሚካን፣ ካነ።
ተካከለ (ልክ ሆነ): ልክ ሆነ፡ ሳይበላለጥ ቀረ (ኢዮብ ፳፰፥፲፱፡ ሕዝቅኤል ፴፩፥፰)። “ድግርና ገባር ሲተካከል ያምር” እንዲሉ።
ተካከለ (ተመሳሰለ): ተመሳሰለ፣ ተነጻጸረ፣ ተመጣጠነ። "ተከለን" ተመልከት።
ተካከለ (ተመደመደ): ተመደመደ፣ ተደለደለ።
ተካከለ: መላልሶ ተከለ።
ተካከለ: ትክክል፣ ተኳዃነ።
ተካከከ: የማከክ ብድር ተመላለሰ። (ለምሳሌ) "አህያ በጥርስ ይተካከካል"።
ተካካሰ: ተቀባበለ፡ ተከፋፈለ፡ ተረካከበ (ካሳን)።
ተካዥ: የሚተክዝ፣ የሚያዝን፣ ዐዛኝ፣ ተቈርቋሪ።
ተካይ፣ ነቃይ: "ሰውን በ(ከ)ርስት በ(ከ)ማዕርግ የሚተክል የሚነቅል ባለሥልጣን።"
ተካይ: የተከለ፣ የሚተክል (ቸካይ፣ ከሳሚ፣ አቋሚ) (ዮሐንስ ፲፭፡ ፩)።
ተካይነት: ተካይ መኾን።
ተካደ (ተክሕዶ):
"ልጄም አይዶል"
ተባለ፡ ተለየ፡
ተረገመ (ሉቃ፲፪፡ ፱)። ተሸፈጠ።
ተካደነ: ተሻፈነ፡ ተላበሰ።
ተካደደ: ተካካደ።
ተካዳ (ተካድዐ):
"አላውቅኸም"
ተባባለ። ተናከሰ፡ ተባላ።
ተካፈለ: ተጋራ፣ ተፋለመ፡ ግማሽ ግማሹን፣ ድርሻ ድርሻውን ወሰደ፣ ተራከባ ወይም ተናተነ (ለምሳሌ በማቴዎስ ፳፯:፴፸፭ ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተካፈተ: አፍ ለአፍ ተጋለጠ፡ ክፉ በጎ ተነጋገረ ወይም ተመላለሰ።
ተካፋይ (ዮች): የሚካፈል፡ ምንዝር፣ ባላንጣ ወይም ዝሞት (ለምሳሌ በ፩ ቆሮንቶስ ፲:፳ ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተካፋይነት: ተካፋይ መሆን፡ ባላንጣነት።
ተክለ ሃይማኖት: ፲፻ ዓ.ም. የነገሠ የላስታ ንጉሥ።
ተክለ ሃይማኖት: በ፯፻ ዓ.ም. የነበሩ የኢትዮጵያ ሐዋርያ፣ ጻድቅ።
ተክለ ሃይማኖት: በ፱፻ ዓ.ም. የነበሩ ዕጨጌ።
ተክለ አልፋ: በ፲፰፻ ዓ.ም. ከደብረ ሊባኖስ ተይዘው ስለ ሃይማኖት በፍየል ዐምባ ተገርፈው ምላሳቸው ተቈርጦ በውሃ ጥም የሞቱ መናኝ ሊት መምር።
ተክለፈለፈ: ተክለበለበ፣ እዚያም እዚያም ተገኘ፣ "ከኹሉ ኣለኹ" አለ።
ተክሊል አደረገ: ሞላ፡ ሥርዐቱን ፈጸመ፡ በተክሊል አገባ።
ተክሊል: የሕግ ጋብቻ ሥርዐት፡ ከለለ ።
ተክሊል: የክርስቲያን ጋብቻ ሥነ ሥርዐት። (ሙሽራውና ሙሽራዪቱ አክሊል ተቀዳጅተው አበባ ይዘው አንድ መጐናጸፊያ ለብሰው የተባረከ ቀለበት አድርገው ቃል ኪዳን የሚገቡበት ሥጋውንና ደሙን የሚቀ በሉበት መንፈሳዊ ሕግ እስከ ሞት ድረስ አለመፋታትንና አለመለያየትን የሚሰብክ የሚያስተምር ለሥጋም ለነፍስም ጥቅም የሚኾን ጸሐፈ ብለኸ መጽሐፍን እይ) ።
ተክሌ: ከፊለ ስም፣ "የኔ ተክል ተብሎም ይተረጐማል።"
ተክል: ቡቃያ፣ ችግኝ፣ ፍሬው የሚበላና የማይበላ፣ ዕንወት፣ የሽቱ ቅጠል፣ ትንሽም ትልቁም ዛፍ።
ተክል: ዘርፍ፣ ይዞ፣ ተክለ ጊዮርጊስ፣ ተክለ ሚካኤል፣ ተክለ ማርያም፣ ተክለ ሥላሴ፣ ተክለ ጻድቅ እያለ የክርስትና ስም ይኾናል።
ተክልዬ: የኔ ተክለ ሃይማኖት። "ሰነቃ፡ ብለኸ፡ ሳንቃን፡ እይ።"
ተክረጠረጠ: ዐተረ፣ ተድበለበለ፣ ጓጐለ ወይም ተቋጠረ።
ተክበሰበሰ: ተጐተተ፡ ተግበሰበሰ፡ ታቦትኛ ኼደ።
ተክተፈተፈ: ተጣደፈ፡ ተቻኰለ።
ተክታኪ: የተከተከ፣ የሚተከትክ፣ ጠቅጣቂ።
ተክነዘነዘ: ተቅነዘነዘ።
ተክነፈነፈ: ተወዘወዘ፣ ተርገበገበ፡ ተቅነዘነዘ።
ተኰለሰመ: ተከረከረ፣ ቈሰለ።
ተኰለኰለ: ተደረደረ፡ ጐን ለጐን ተተከለ፡ ተቀመጠ። ዐበጠ፡ ጠጠረ።
ተኰለፈ: ተበከለ፣ ተበላሸ፣ ጠፋ።
ተኰላ: ታጠበ፡ ጠራ፡ ተፈገፈገ፡ ተወለወለ፡ ታደሰ፡ እኮመር ገባ።
"የተኰላ ወርቅ"
እንዲሉ።
ተኰላ: የሰው ስም።
ተኰላሸ: ተቀደደ፡ ተሠነተረ፡ ተሰነጋ፡ ተጐነደለ፡ የከብቱ ቍላው።
ተኰላሸ: የከብቱ ቍላ ተቀደደ፣ ተሠነተረ፣ ተሰነጋ ወይም ተጐነደለ።
ተኰላተፈ፡ ተኰለታተፈ: ተንተባተበ፡ ተሳሰረ።
ተኰላተፈ/ተኰለታተፈ: ተንተባተበ ወይም ተሳሰረ (በአነጋገር)።
ተኰልኰሎ (ዎች): ታናናሽ ልጆች፡ በማዘንት ዙሪያ ተኰልኵለው የሚታዩ።
"ተልኰሎ ውሰጠ ብዙ ነው"።
ተኰልኰሎ: ሕፃናት ኰለኰለ ።
ተኰልኰሎዎች: ኰልኰሌ፡ ቅራቅንቦ።
ተኰልኳይ: የሚኰለኰል፡ ተደርዳሪ።
ተኰመሸሸ: ይህ ማለት ዐፈረ ወይም ተሰቀጠጠ፡ ዕፍረት ማለት ነው።
ተኰመተረ: ተቋጠረ፣ ቋጠራ ሆነ ወይም ተጨመተረ ማለት ነው።
ተኰመታተረ: ተጨመታተረ ወይም ተጨመዳደደ።
ተኰመኰመ: ታኘከ፣ ተበላ፣ ተጠጣ፣ ወይም ተሰማ ማለት ነው።
ተኰማተረ: ዐረረ፣ ተጨማደደ፣ ተጨማተረ ወይም ተጨባበጠ ማለት ሲሆን ይህም ያንጀት፣ የዥማት ወይም የፈትል ባህሪን ያመለክታል።
ተኰማታሪ: የሚኰማተር ሰው፡ የግርሽጥ እንቡጥ።
ተኮማጠጠ: ተሸማጠረ፡ ተበሳጨ፡ አሳዛኝ ነገር ተናገረ።
ተኮማጠጠ: ተሸማጠረ፣ ተበሳጨ፣ ወይም አሳዛኝ ነገር ተናገረ ማለት ነው።
ተኰሰ: መላ ፈጸመ (ጕዳይን)።
ተኰሰ: ሞቀ፣ ወበቀ (ፀሓዩ) (ዘፍጥረት ፲፰፡ ፩። ፩ኛ ሳሙኤል፡ ፲፩፡ ፱፡ ፲፩)።
ተኰሰ: ሰፋ (ነጠላን፣ ቅጥልጥል፣ ደበሎን)።
ተኰሰ: ነደደ፣ ተቃጠለ (እሳቱ፣ ቍጣው) (ኢዮብ ፵፪፡ ፯)።
ተኰሰ: ኣሰማ - ድምጽ አደረገ (ጠመንዣን፣ መድፍን፣ ሽጕጥን)።
ተኰሰ: ካሰቀቅ፣ ከፈለ (ላቈሰለው ሰው)።
ተኰሰ: የግንብን ደንጊያ መጋጠሚያ በኖራ በስሚንቶ ላከከ፣ ቀባ፣ ገጠመ።
ተኰሰ: ዳመጠ፣ ቀጥ ለጥ አደረገ፣ አስተካከለ (የታጠበ ልብስን)።
ተኰሰተረ: ተሰበሰበ፣ ቀለጠፈ።
ተኰሰተረ: ተጠነቀቀ፡ ተሰበሰበ፡ ቀለጠፈ።
ተኰሳ (ተኰስሐ): ታራ፡ ተጣለ ወይም ተንጠባጠበ።
ተኰስታሪ: የሚኰሰተር።
ተኰረ: ለበመ አስተዋለ ዐይኑን ጣለ (ትክ ብሎ እየተመለከተ ዐወቀ አነጣጠረ) ።
ተኰረመተ: ታጠፈ፣ ተጨበጠ፡ ዐዘነ።
ተኰረተ: ተሰበሰበ፡ ተቀመጠ፡ ፍሬ ሆነ።
ተኰረተመ: ተሰበረ፡ ዐጪር ሆነ።
ተኰረኰመ: ተጨበጠ፣ ተመታ፣ ተገጨ፡ ተሰበረ፣ ተሸረፈ ወይም ታጠፈ።
ተኰረኰረ: ተጐረጐረ ወይም ታከከ።
ተኰረኰረ: ተጐጠጐጠ ወይም ተጐተጐተ።
ተኰራ (ተኰርዐ): ራሱን በበትር ተመታ ወይም ተቈረመ።
ተኰራ (እምከመ ኰርዐ): ከኰራ፣ ከተጓደደ ሰው ተኰራ (መዋረዱ አይቀርም)። "ወልድ በራስህ ተኰራህ (ከተመታህ፣ ከተጓደድህ)፡ አብ አይዶለሞይ አባትሽ፡ ተለማኝ እናትህ" (አዝማሪ)።
ተኰራመተ/ተኰረማመተ: ተጣጠፈ ወይም ተጨባበጠ።
ተኰራኰመ: በኵርም ተማታ ወይም ተጋጨ።
ተኰራኰረ: ተዋጋ፣ ተጐጣጐጠ (በጣት)።
ተኰራኰረ: ተጐራጐረ ወይም ተካከከ።
ተኰራኰረ: ተጐታጐተ ወይም ተታጋ።
ተኰርኳሚ: የሚኰረኰም፡ ተሰባሪ።
ተኰርኳሪ: የሚኰረኰር።
ተኰተኰተ: ተቈጠቈጠ፡ ተመለመለ፡ ተቈረጠ።
ተኰተኰተ: ተጫረ፡ ተቈፈረ፡ ታገለ፡ ታረመ።
ተኰትኳች: የሚኰተኰት፡ ተመልማይ።
ተኰቸመ: ተኰሰተረ።
ተኰነ: ኾነ ተገኘ ተፈጠረ (የትዃን) ።
ተኰነተሸ፡ ተበጠሰ (ተቈረጠ ዐጪር ኾነ) ።
ተኰነነ: ከጽድቅ ራቀ፡ ተፈረደበት፣ ተቀጣ ወይም ተጐዳ፡ ዘብጥያ ወህኒ ቤት ገባ፡ ሲኦል ገሃነመ እሳት ወረደ፡ ሥቃይ ተቀበለ፡ መከራውን አየ (ለምሳሌ በዮሐንስ ፫:፲፰ ላይ እንደተጠቀሰው)። "እከሌ በቁሙ ተኰነነ"፡ "የተኰነነች ነፍስ" እንዲሉ።
ተኰናኝ (ኞች): የሚኰነን፡ ኃጢአተኛ።
ተኰኳ: ተጣለ፡ ወደቀ። ተመታ፡ ተፈነከተ። ተሼጠ፡ ተለወጠ።
ተኰየሰ: ተከመረ፡ ተቈለለ።
ተኰደኰደ: ተገረኘ፡ ታሰረ። በደዌ ተያዘ፡ ሆዱ እስኪያብጥ፡ እስኪነፋ (ሉቃ፲፬፡ ፪)።
ተኰፈሰ: ተመየደ፣ ተበጠረ ወይም ጐፈረ።
ተኰፈሰ: ከንቱ ውዳሴ ተቀበለ ወይም ተመሰገነ።
ተኰፋነነ (ኰፈነነ/ኰነነ): ጨርቁን አፍንጫው ላይ አደረገ፡ ኰራ (መኰንን መሰለ)። ተደራራጊ ሲመስል በተደራጊነት መፈታቱን ይመልከቱ።
ተኰፋነነ: ኰራ፡ (ኰፈነነ) ።
ተኳለ (ተኵሕለ): ኵልና መድኀኒት ተቀባ፡ ተጌጠ (ራእ፫፡ ፲፰፡ ፪ነገ፡ ፱፡ ፴)። የተኳለ፡ የተዳረ፡ ተኵሎ የተዳረ፡ ወግ ማረግ የደረሰው ልጅ።
ተኳለፈ: ተባከለ።
ተኳሰ (ኳሰ): ኳስ ሆነ፡ ተቋጠረ፡ ተድበለበለ።
"ዛሬ የበላሁት መብል እልቤ ላይ ተኳሰና ሳይስማማኝ ቀረ። "
ተኳሰሰ: ተናናቀ።
ተኳሳ: ሙቀታም፣ ወበቃም ስፍራ። "የሚፋጅ፣ የሚያቃጥል፣ በርበሬ፣ ሰናፍጭ፣ ፌጦ የመሰለው ኹሉ።"
ተኳረፈ/ተኰራረፈ: ተቀያየሙ፡ ቂም ተያያዘ፡ መልስ ተከላከለ።
ተኳር: የተኰረ፣ የሚተኵር (ልበኛ፣ ለባሚ፣ ኦስተዋይ፣ አነጣጣሪ)።
ተኳርነት: ተኳር መኾን።
ተኳሽ: የተኰሰ፣ የሚተኩስ (የማይስት አነጣጣሪ፣ ለኳሽ፣ አቃጣይ)። "ፍጥም አፍራሽ ቤተ ክሲያን ተኳሽ እንዲሉ።"
ተኳሽነት: ለኳሽነት።
ተኳኰሰ: ለባለበ።
ተኳኳለ (ተኳሐለ): ኵል ተቃባ፡ ተቀባባ።
ተኳዃነ: ተጠማመረ፣ ተደራረገ፣ ተፋቀረ፣ ተዋደደ ወይም ተሰማማ ማለት ነው። ለምሳሌ: "አቶ እከሌና እመት እከሊት አልተኳዃኑም"።
ተኳይ: የሚኳል፡ የሚቀባ።
ተኸሬ: በመረሬ የሚዘራ ስንዴ ስም ።
ተኹለደሬ: በወሎ ክፍል ያለ አገር።
ተኼደ: ተተረጐመ፡ ተገለጠ፡ ተረዳ።
ተኼደ: ታለፈ፡ ታለፈበት፡ ተረገጠ፡ ተወቃ፡ ተፈለፈለ።
ተኾለተ: ኹለት ኾነ፡ ኹለት ተባለ።
ተኾነ (ከኾነ): ከተደረገ፡ ከበጀ።
"ገብለኸ"
"መጋዞን"
እይ።
ተኾነ: የሰው ስም።
ተወ: ለቀቀ ባለ ፈታ ገደፈ ርግፍ አደረገ ማረ (ሉቃ፡ ፭፡ ፳፰)” ። ተውኸ ተዉ ተዋችኹ
ተወች ተውሽ ተውኹ ተውን" እያለ ይዘረዝራል ። (ተረት - ያምራል ብሎ ከተናገሩት ይከፋል ብሎ የተዉት) ።
ተወሓሐደ: ተዋዋደ፡ ተለወሰ፣ ተገነኛኘ፣ ተዛመደ፣ ተሰማማ፣ ተኳኳነ።
ተወለለ: ተከፈለ፣ ተሠነጠቀ፣ ተከፈተ።
ተወለማመጠ: የተወላመጠ ድርብ።
ተወለቀ፡ ታሸ፡ ተበጠበጠ፡ ተመታ።
ተወለቃቀመ: ተወለጋገመ።
ተወለከፈ: ታጐለ፣ ተሰነከለ፣ ታወከ።
ተወለካከፈ: ተሰነካከለ፣ ተደነቃቀፈ።
ተወለወለ: ተመታ፣ ተጠፈጠፈ፣ ቀለጠ።
ተወለወለ: ተጠረገ፣ ታሠሠ፣ ታበሰ፣ ታደፈ፣ ተሰነገለ፣ ጠራ።
ተወለደ: ተዘመደ።
ተወለደ: ከማሕፀን (ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከጠባብ ወደ ሰፊ) ወጣ፣ መጣ፣ ወረደ፣ ተገኘ። "ክርስቶስ ከአብ ያለናት ከማርያም ያላባት ተወለደ። " ጨረቃን እይ።
ተወለደ: ጠበቃ ኾነ፣ ተወከለ።
ተወለጋገመ: ተወለቃቀመ።
ተወለጋገደ: ተወለጋገመ።
ተወላለደ: ተዘማመደ። (እንደ "ተወላ ለደ")
"ቤተ ዘመድ እንደ መኳዃኑ። "
ተወላመመ: ተጣመመ፣ ተዛወረ።
ተወላመጠ: ተዘዋወረ።
ተወላቀመ: ተወላገመ።
ተወላከፈ: ተሰናከለ፣ ተደናቀፈ።
ተወላወለ: በጥፊ ተማታ፣ ተቃለጠ፣ ተጠፋጠፈ።
ተወላወለ: ተወዛወዘ።
ተወላዲ: የወልድ አካል የግብር ስም፡ ትርጓሜው ተወላጅ።
ተወላዳ: የዠግንነት ሥራ ሠራ፡ ወንድ ወጣው። በሥራ ታወቀ፡ ተወናወነ፣ ተዛመረ፣ ተፈናፈነ፡ ተዋጋ፣ ተጋደለ። (ግጥም) "ሰመጎ ዥረት ያልተወላዳ ሚስት አይጩለት፡ አህያ ይንዳ። "
ተወላጅ: የተወለደ፣ የሚወልድ፡ የ፫፣ ያ፬ ቤት ዘመድ።
ተወላገመ: ተጣመመ፣ ተወላቀመ።
ተወላገደ: ተወላገመ።
ተወሰነ፡ ተደነገገ፡ ተደነባ፡ ታገገ፡ ተገደበ፡ ተጠበቀ፡
ተከለከለ፡ ተከለለ።
ተወሰነ: ተገደመ (መማጠኛ፣ መደወያ ኾነ)።
ተወሰከ፡ ተጨመረ፡ ተነ።
ተወሰወሰ፡ ተሰፋ፡ ተሸደሸደ፡ ተሸከሸከ፡ ተሸለለ።
ተወሰወሰ፡ ተዋኘ፡ ውስጥ ለውስጥ ታለፈ።
ተወሰደ፡ ተይዞ ኼደ፡ ተጋዘ፡ ተነዳ፡ ተቀማ፡ ተነጠቀ፡ ጠፋ (ገላ ፪: ፲፡ ፲፫)።
ተወሰጠ፡ ተወነገ፡ ገባ።
ተወሣ፡ (ተወሥአ)፡ ታሰበ፡ ተመለሰ፡ ተባለ፡ ተነገረ፡ ተሰጠ መልሱ።
ተወሳሰበ፡ ተጠላለፈ፡ ተጠማመረ፡ ተወታተበ፡ ተተባተበ።
ተወሳሰነ፡ ተደነጋገገ፡ ተደነባባ።
ተወሳሰደ፡ ተቀማማ፡ ተነዳዳ፡ ተጋጋዘ።
ተወሳሳኝ፡ የሚወሳሰን።
ተወሳኝ፡ የሚወሰን፡ የሚከለል።
ተወሳወሰ፡ ተሸዳሸደ።
ተወሳወሰ፡ ተወዛወዘ፡ ተነቃነቀ፡ ተዛመረ፡ ተወላዳ፡
ተፈናፈነ።
ተወሳዋሽ፡ የተወሳወሰ፡ የሚወሳወስ፡ ተነቃናቂ።
ተወሳጅ፡ የሚወሰድ፡ የሚኼድ።
ተወረ: ተጫረ፣ ተቧጨረ።
ተወረሰ፡ ተገኘ፡ ተያዘ፡ ተወሰደ። በቃል ያለ ይረሳል፡ በመጣፍ ያለ ይወረሳል። (ስው የው ተወረሰ)፡ ርስቱ፡ ትዳሩ ተወሰደበት።
ተወረስ፡ ንብረቱ የተወረሰበት ሰው። ዘምቶ ተወረስ እንዲሉ።
ተወረረ፡ ተከበበ፡ ተዘረፈ፡ ተበዘበዘ፡ ተበረበረ፡
ተማረከ። የተናቀ ከተማ ባህያ፡ ይወረራል እንዲሉ።
ተወረበ፡ ተባለ፡ ተዜመ፡ ወረቡ።
ተወረበ፡ ታጨደ፡ ተላጨ፡ ሣሩ፡ ጠጕሩ።
ተወረወረ፡ ተለቀቀ፡ ተነደፈ። (ምርቃት)፡ የተቃጣ አይምታኸ፡ የተወረወረ አይውጋኸ።
ተወረወረ፡ ተሸጐረ፡ ተቀረቀረ፡ ተቈለፈ።
ተወረወረ፡ ተጓነ፡ ተጣለ።
ተወረወረ፡ ገባ፡ ጠለቀ፡ ዐረበ።
ተወረደ፡ (ወረደ)፡ ፈጸመ፡ ጨረሰ። እከሌ ዕዳውን ተወረደ እንዲሉ። ዕዳው ከቍጥር እየጐደለ ማለቁን ያሳያል።
ተወረደ፡ አነሰ፡ ተቀነሰ፡ ዐጸጸ፡ ጐደለ።
ተወረደ፡ ዝቅ ተባለ፡ ቍልቍል ተኼደበት፡ ዛፉ፡ ገደሉ።
ተወረፈ፡ ተሰደበ፡ ተፀረፈ፡ አንተ እንዲህ ተባለ።
ተወረፈ፡ ተወረበ፡ ተዘለለ፡ ታለፈ።
ተወራ፡ ተነገረ፡ ተባለ።
ተወራረሰ፡ ተገነዛዘበ፡ ተቈላለፈ፡ ውርስ ተቀባበለ።
ተወራረደ፡ ተበለተ፡ ተጠባ፡ ተቈረጠ፡ ሥጋው።
ተወራረደ፡ ተገተ፡ ተከራከረ፡ ተቈታቸ፡ ተወዳደረ፡ እምነት፡
ክደት፡ ተነጋገረ፡ እሰጥ አገባ ተባባለ። እንወራረድ፡ አህያ እንረድ፡ እንዲል እረኛ፡ ሰጠን ተመልከት።
ተወራረፈ፡ ተሰዳደበ።
ተወራራሽ፡ (ሾች)፡ የተወራረሰ፡ የሚወራረስ፡ ተያያዥ፡ ተገነዛዛቢ።
ተወራራሽ፡ ገ፡ ከ፡ ቀ፡ ተለዋዋጭ ማለት ነው፡ ቍጥር ፲፱ እይ።
ተወራራጅ፡ የሚወራረድ፡ ተማጋች፡ ጠበቃ፡ ነገረ ፈጅ።
ተወራሽ፡ የሚወረስ፡ ርስት፡ ሥራ፡ ጥበብ፡ መንግሥተ ሰማይ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ባምላክነቱ ተወራሽ፡ በሰውነቱ ወራሽ ነው።
ተወራሽነት፡ ተወራሽ መኾን።
ተወራቢ፡ የሚወረብ፡ የሚታጨድ፡ የሚላጭ፡ የሚዜም።
ተወራወረ፡ ተጓጓነ፡ ተጣጣለ፡ ውርወራን ተመላለሰ።
ተወራጅ (ጆች)፡ አነስተኛ ሰው፣ ዝቅተኛ ምክትል ሹም ወይም ሌላ ነገር።
ተወራጨ፡ ተቅበጠበጠ፡ ተባጣበጠ፡ ጸጥታ ዐጣ፡ ተበሳጨ፡ የጣርና የጋር፡ የጭንቅ እንቅስቃሴ ተንቀሳቀሰ።
ተወርዋሪ፡ የሚወረወር፡ ዋነተኛ፡ ኮከብ፡ ዐይን፡ እባብ (ኢሳ ፴፬: ፲፭)።
ተወሸለ፡ ተሸፈነ፡ በውስጥ ኾነ።
ተወሸለ፡ ተወከለ፡ ተወተፈ፡ ገባ።
ተወሸመ፡ ውሽማ ኾነ።
ተወሸቀ፡ ተጨመረ፡ ገባ፡ ተሸጐጠ፡ ተረፈቀ፡ ተወዘፈ፡
ተቀመጠ። እከሌ ዛሬ እቤት ተወሽቆ ዋለ።
ተወሸቀ: ረመሰ።
ተወሸጋገረ፡ ተወነጋገረ፡ ተወነካከረ።
ተወሻሸመ፡ ውሽማ ተኳዃነ፡ ተገነኛኘ።
ተወሻገረ፡ ተወናገረ፡ ተወናከረ።
ተወቀሠ፡ ተገሠጸ፡ ተዘለፈ፡ ተመከረ፡ ተነቀፈ።
ተወቀረ፡ (ተወቅረ)፡ ተነቀሰ፡ ተጠቈረ፡ ተጠረበ፡ ሰላ፡ ሻከረ፡ በጀ፡ ተሰመረ፡
ተጠረቀ (ዘዳ ፬: ፲፮፡ ፪ነገ ፲፪: ፲፪፡ ፪ዜና ፴፫: ፯)።
ተወቀጠ፡ ተመታ፡ ተቀጠቀጠ።
ተወቀጠ፡ ተወጋ፡ ተፈተገ፡ ተሸከሸከ፡ ተደለዘ።
ተወቂ፡ የሚወቃ እኽል።
ተወቃ፡ ተጣለ፡ ተመታ፡ ተደበደበ፡ ተኼደ፡ ተፈለፈለ።
ተወቃሪ፡ የሚወቀር፡ የሚነቀስ፡ ወፍጮ፡ ጥርስ።
ተወቃሽ፡ የሚወቀሥ፡ ወቀሣ፡ ተግሣጽ፡ ቍጣ፡ ተቀባይ።
ተወቃቀሠ፡ ወቀሣን ተነጋገረ፡ ተመላለሰ።
ተወቃጭ፡ የሚወቀጥ፡ ከብት፡ እኽል።
ተወበረ: ተሳሳተ፣ ተደናገረ።
ተወተረ: ተሳበ፣ ተገተረ፣ ተወጠረ፣ ተለጠጠ።
ተወተበ፡ ተወሸለ፡ ተጠመጠመ።
ተወተወተ: ተነዘነዘ፣ ተጐተጐተ።
ተወተፈ: ተሸጐጠ፣ ተከደነ።
ተወት አደረገ: ለቀቅ አደረገ።
ተወት: ለቀቅ።
ተወነባበረ፡ ተደነጋገረ።
ተወነነ፡ ተወነገ፡ ተወሰጠ፡ ያውሬ።
ተወነነ፡ ኰራ፡ ተጀነነ፡ የሰው።
ተወነካከረ፡ ተወነጋገረ።
ተወነዘፈ፡ ተለበሰ።
ተወነጀለ፡ ወንጀለኛ ተባለ፡ ተከሰሰ፡ ተያዘ።
ተወነጃጀረ፡ ተወነጋገረ፡ ተፈነጃጀረ፡ ተራራቀ።
ተወነገ፡ ተሻጠ፡ ተወነጠ፡ ተወሰጠ፡ ተወነነ፡ ተወዘወዘ። (ዘፈን)፡ አንደዬ፡ አድጌ፡ ተወንጌ አለ።
ተወነገረ፡ ተደነቀረ።
ተወነጋገረ፡ ተወነካከረ።
ተወነጠ፡ ተወነገ፡ ተወዘወዘ። (ጥወ) መወነጥ፡ መወነግ፡ መወዝወዝ።
ተወነጨፈ፡ (ተወፅፈ)፡ ተወረወረ፡ ተለቀቀ፡ ተሰደደ።
ተወነጨፈ፡ ፈጥኖ ኼደ፡ ዐለፈ፡ ተረመደ፡ ቀለጠፈ።
ተወናቀፈ፡ ተወላከፈ፡ ተደናቀፈ።
ተወናበደ፡ ተሳሳተ፡ ተናጠቀ፡ ተቃማ።
ተወናበደ፡ ተደናበረ፡ ተሯሯጠ፡ ዞረ።
ተወናከረ፡ ተለያየ፡ ተራራቀ፡ የግድግዳ፡ የጣራ።
ተወናከረ፡ ወዲያና ወዲህ ረገጠ፡ ተውተረተረ።
ተወናወነ፡ ተወዛወዘ፡ ተወላወለ፡ ተወሳወሰ፡ ተወላዳ።
ተወናደመ፡ (ተኣኀወ)፡ ወንድም ተኳዃነ፡ ወንድሜ ወንድሜ ተባባለ፡ ካንድ ኹለት ኾነ፡ ተቀናጀ፡ ተጓደነ።
ተወናጀለ፡ በወንጀል ተካሰስ፡ ተከራከረ፡ ተገተ፡ ተነጋገረ፡ ወንጀለኛ ተባባለ፡ ጕድ ለጕድ ተዋጣ፡ ተጐላጐለ።
ተወናጀረ፡ ተወናገረ፡ ተፈናጀረ።
ተወናጀበ፡ ተወላከፈ፡ ተደናቀፈ፡ ሰክሮ (ኤር ፳፭: ፲፮)።
ተወናገረ፡ ተወናከረ።
ተወናጨፈ፡ በወንጭፍ ተወራወረ፡ ጦርነት አደረገ፡ ተማታ።
ተወናጨፈ፡ ተላለፈ፡ ተረማመዶ በፍጥነት።
ተወናፈለ፡ ጕልበት ተበዳደረ፡ ተራዳ፡ ተጋዘ፡ በሥራ ተፈራረቀ።
ተወናፋይ፡ የሚወናፈል፡ ተጋጋዥ።
ተወንጫፊ፡ የሚወነጨፍ።
ተወከለ: ታመነ፣ ተተካ፡ ምትክ ኾነ፡ በሰው ፈንታ ሠራ።
ተወከወከ: ተጐተጐተ።
ተወካይ: የሚወከል፣ የሚታመን፣ የሚተካ፡ ተተኪ።
ተወዘመ: ተባለ፣ ተቆመ (ዜማው)፡ ዘነበለ (ራሱ)።
ተወዘረ: ተጌጠ፣ ተሸለመ። ወይዘሮ ማለት ከዚህ የወጣ ነው፡ ወየዘረንን ይመልከቱ።
ተወዘተ: ተጫነ፣ ተቀመጠ፣ ተረፈቀ።
ተወዘወዘ: ተናጠ፣ ተሰበቀ፣ ተነቀነቀ (ተነዘነዘ)፡ ተንገሸገሸ፡ ባንገት ወረደ፣ ናቃ።
ተወዘገ: ተፈተለ፣ ተመዘዘ፣ ተሳበ፣ ተጐተተ፡ ቀጠነ፣ ረዘመ፣ ከረረ።
ተወዘፈ: ተወዘተ፣ ተረበከ፣ ተረፈቀ፣ ተጐለተ፣ ተቀመጠ፣ ተጋደመ፡ ታጐለ።
ተወዛች: የሚወዘት፡ በረመጥ ላይ ተቀማጭ።
ተወዛወዘ: ተነቃነቀ፣ ተናጋ፣ ተወላወለ፡ ተንቦጫቦጨ፣ ተነዋወጠ። (የቧልት ዘፈን) "ያ ውና እዚያ ማዶ ዛፍ ይወዛወዛል፡ እነአጎቴ ናቸው፡ ዐረግ ይመዛሉ። "
ተወዛዋዥ: የሚወዛወዝ፡ ተነቃናቂ።
ተወዛዛ: ተባበሰ፡ በቀላል ተቀባባ (እጁና ፊቱ)።
ተወዛፊ: የሚወዘፍ፡ ተረፋቂ።
ተወዝዋዥ: የሚወዘወዝ፡ እስክስተኛ።
ተወዣበረ: ተሳሳተ፣ ተደናገረ።
ተወያየ: ተዛዘነ፡ ዐዘንን፣ ትካዜን ተነጋገረ፡ ተካፈለ።
ተወደለ: በወዴላ ላይ ተጫነ፣ ተጨመረ።
ተወደሰ: ቀረበ፣ ተባለ (ምስጋናው)።
ተወደሰ: ተመሰገነ (እግዜሩ፣ ሰዉ)።
ተወደሰ: ተቆመ፣ ተደገመ፣ ተዜመ (መወድሱ፣ ሳታቱ፣ ዳዊቱ)።
ተወደስ: ዝኒ ከማሁ። ደንደስን ይመልከቱ።
ተወደረ: ተገመደ፣ ተጠመረ።
ተወደረ: ታሰረ፣ ተጋዳ።
ተወደረ: እሰጥ ተባለ።
ተወደበ: ተበጀ፣ ወደብ ሆነ።
ተወደነ: ተቦደነ፣ ተደገደገ።
ተወደነ: ታሰረ፣ ተቈረኘ፣ ተቀረቀበ።
ተወደወደ: ተደበደበ፣ ተማሰለ፣ ተወከወከ።
ተወደደ፡ ተከበበ፡ ታገደ፡ ተከለከለ፡ ተመለሰ።
ተወደደ፡ ተከፈለ፡ ተሠነጠቀ፡ ተቈረጠ።
ተወደደ: ተፈቀረ፣ ተፈቀደ፣ ታመነ (የሰው)።
ተወደደ: እሳት ሆነ፣ ተጨበጠ (የገበያ)።
ተወዳሪ: የሚወደር።
ተወዳሽ: የሚወደስ፡ ተመስጋኝ።
ተወዳደሰ: ተመሰጋገነ።
ተወዳደረ: ተሳሰረ፣ ተቈረኛኘ።
ተወዳደረ: ተተካከለ፡ ሳይበላለጥ ቀረ።
ተወዳደረ: ተፈካከረ፣ ተላለከ፣ ተገተ፣ ተከራከረ፣ ተወራረደ።
ተወዳዳሪ (ዎች): የሚወዳደር፡ ተፈካካሪ።
ተወዳዳሪነት: ተፈካካሪነት።
ተወዳጀ: ተዋደደ፣ ወዳጅ ተኳኳነ።
ተወዳጅ: የሚወደድ፣ የሚፈቀር።
ተወጃወጀ: ተወጋወገ።
ተወጃጀ: ተገዛዛ፣ ተለዋወጠ፣ ተሻሻጠ።
ተወገረ: በድንጋይ ተመታ፣ ተደበደበ። (ዘፀ፳፩፡ ፳፰። ፩ነገ፡ ፳፩፡
፲፬) ምሳሌ: "የነበረ ገብሬል ተወገረ። " "ክርስቶስ ሲወገር ድንጋይ ያቀበለ" እንዲሉ።
ተወገነ: ወገን ተባለ፣ ተዘመደ።
ተወገዘ፡ ተገዘተ፣ ውጉዝ ተባለ፣ ተለየ፣ ተወገደ።
ተወገዘ: ተረገመ።
ተወገደ፡ ተለየ፣ ተገለለ፣ ራቀ።
ተወገደ: ራቀ።
ተወገጠ፡ ተቸገረ፣ ተጨነቀ፣ ተወጠረ።
ተወገጠ፡ ተወቀጠ።
ተወጊ፡ የሚወጋ አገር ጠላት።
ተወጋ (ተወግአ)፡ ተለተመ፣ ተሸቀሸቀ፣ ተዘረከተ፣ ተጠቆመ።
ተወጋ (ተወግዐ)፡ ተነገረ፣ ተባለ (ወጉ)።
ተወጋ፡ ተጠላ፣ ተመረዘ፣ ተነቀፈ።
ተወጋ፡ ተጻፈ፣ ተመለከተ፣ ምልክት ተደረገበት።
ተወጋሪ: የሚወገር፣ ተደብዳቢ።
ተወጋወገ፡ ዋጋ ተነጋገረ፣ ውጣ ውረድ ተባባለ።
ተወጋዥ፡ የሚወገዝ፣ የሚለይ።
ተወጋጅ፡ የሚወገድ፣ የሚርቅ።
ተወጋገዘ፡ ተገዛዘተ፣ ተለያየ።
ተወጠረ: ተነፋ፣ ተቀበተተ፡ ተዘረጋ፣ ተሳበ፣ ተለጠጠ፣ ተገተረ።
ተወጠረ: ተጠየቀ፣ ተወገጠ።
ተወጠረ: ኰራ፣ ተቈነነ፣ ተቋፈ። "አትወጠርብኝ" እንዲል ባላገር።
ተወጠነ (ተወጥነ): ተዠመረ፣ ተፈለመ፣ ተቀደመ፣ ተሠራ። (መዝ፻፴፱፡ ፲፭)
ተወጠወጠ: ተሠራ፣ ተቈላ፣ ተጠበሰ፣ ተቀቀለ፣ ተማሰለ። (ተረት) "ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከንባዩ ቂጥ። "
ተወጠጠ: ተወጠረ፣ ተገተረ።
ተወጠጠ: ኰራ፣ ታጀረ።
ተወጣ/ተወጣበት: ተኼደ፣ ታለፈ (ዳገቱ፣ ዐቀበቱ)፡ ታረገ (ሰማዩ)።
ተወጣ: ሠራ፣ አደረገ፣ ወረሰ፣ ፈጸመ። "አሩቴን ተወጣሁ" እንዲል ባላገር።
ተወጣ: ተጠቃ፣ ተመታ፣ በታች ኾነ፣ ተወጣበት።
ተወጣሪ: የሚወጠር፣ የሚለጠጥ፣ ተለጣጭ፡ የሚኰራ፣ ኵሩ፡ ቀስ ብሎ ኻያጅ።
ተወጣኝ: የሚወጠን፡ ተዠማሪ።
ተወጣጠረ: ተሳሳበ፣ ተዘረጋጋ (ርስ በርሱ)።
ተወጣጠነ: ተዠማመረ፣ ተፈላለመ።
ተወጣጣ: አንዱ ባንዱ ላይ ወጣ፡ ተቀማመጠ፡ መቀማጭነትን ወይም መቀመጫነትን ተፈራረቀ።
ተወጣጣ: ከዚያም ከዚያም ተሰባሰበ፣ ተጠራቀመ (የሰው፣ የገንዘብ)።
ተወጫመደ: ዕጥፍ ዕጥፍ፣ ውትር ውትር አለ፡ ግራና ቀኝ ረገጠ፣ ተውተረተረ።
ተዋሐደ: አንድ ሆነ፡ ከመንታነት፣ ከኹለትነት ራቀ፡ (ሥጋ ለበሰ)።
ተዋሓጅ: የሚዋሐድ፡ አንድ ዃኝ።
ተዋሕዶ: የሃይማኖት ስም፡ የቃልን ሥጋ መልበስና አንድ አካል፣ አንድ ልጅ፣ አንድ ሠሪ መሆን፣ ፍጹም አምላክነትና ፍጹም ሰውነት፡ ፪ (2) ልደት፣ ፪ (2) ባሕርይ፣ ፪ (2) ግብር እንዳለው የሚያስረዳ የሐዋርያትና የ፫፻፲፰ (318) ሊቃውንት እምነት። በጽርእ "ኦርቶዶክስ" ይባላል።
ተዋሕዶዎች: በተዋሕዶ ሃይማኖት የሚያምኑ (ደብረ ሊባኖሶች፣ አንኮበሮች፣ አዘዞዎች፣ ዲሞች፣ ዋልድቦች፣ አኩስሞች፣ ማኅበረ ሥላሴዎች)፡ እነዚሁም ቤተ ተክለ ሃይማኖት ናቸው።
ተዋለ: ቀኑ ታለፈ፡ ተፈጸመ፣ መሸ።
ተዋለ: ውል ተደረገ፣ ታሰረ፣ ተቋጠረ።
ተዋለቀ: ተሳደበ፣ ተዋጋ፣ ተጋደለ።
ተዋለቀ: ተናቀለ፣ ተፋለሰ።
ተዋለደ: ተራባ፣ ተዛመደ፡ የወንድ ወገን ከሴት፣ የሴት ወገን ከወንድ በዘር ተቀላቀለ፡ አባትና ልጅ ተኳዃነ። (ሕዝ፴፩፡ ፮)
ተዋሰ፡ (ተውሕሰ)፡ ዕቃ ወሰደ፡ ተበደረ (፪ነገ ፬: ፫)።
ተዋሰ፡ ለሰው ተሰጠ፡ ከብቱ፡ ዕቃው በዋስ አለዋስ።
ተዋሰ፡ ዋስ ኾነ፡ ተያዘ፡ እዋሳለኹ አለ።
ተዋሰበ፡ ተዋተበ፡ ተጣለፈ፡ ተጣመረ፡ ተሳሰረ፡ የድር፡
የገመድ፡ የመጫኛ፡ የሹራብ።
ተዋሰነ፡ ወሰን ተራገጠ፡ ተዳካ፡ ተካለለ፡ ተላካ፡ ተደናገገ፡
ተደናባ።
ተዋሰደ፡ ተቃማ፡ ተናዳ፡ ተቃረበ።
ተዋሣ፡ (ተዋሥአ)፡ ተመላለሰ፡ መልስ ተሰጣጠ።
ተዋሳቢ፡ የሚዋሰብ፡ ተጣማሪ።
ተዋሳኝ፡ (ኞች)፡ የተዋስነ፡ የሚዋሰን፡ ተካላይ።
ተዋረሰ፡ ተያያዘ፡ ተገናዘበ፡ ተገናኘ፡ ተቋለፈ።
ተዋረደ፡ ተሻረ፡ ከሰረ፡ ዐጣ፡ ነጣ፡ ባልንጀራው በለጠው፡ ደኸየ፡ ከክብር፡ ከማዕርግ ወደቀ፡ ከጌትነት ራቀ፡ ጐሰቈለ።
ተዋረደ፡ ትሑት ኾነ፡ ታዘዘ።
ተዋረድ፡ ትሕትናን ገንዘብ አድርግ።
ተዋረድ፡ ዝቅታ፡ ደረጃ።
ተዋረፈ፡ ተሳደበ፡ ተፃረፈ። (ተረት)፡ ቢዋደዱ ጦም ገደፉ፡ ቢጣሉ ተዋረፉ።
ተዋራሽ፡ የሚዋረስ፡ ተገናዛቢ።
ተዋራጅ፡ የሚዋረድ፡ ታዛዥ፡ ዕሺ ባይ።
ተዋርዶ፡ መዋረድ፡ ርን ተጭነኸ አንብብ (ግእዝ)። “ተዋርዶ ከማግኘት ኰርቶ ማጣት፡ እንዲሉ።”
ተዋርዶ፡ ዝቅ ብሎ (ዐማርኛ)።
ተዋሸመ፡ በውሽምነት ተገናኘ፡ ልብስ ተጋፈፈ፡ ተዋደቀ።
ተዋሽ፡ ዕቃ የሚወስድ።
ተዋሽ፡ የሚዋስ፡ ዋስ የሚኾን።
ተዋቀሠ፡ ተቋጣ፡ ተከራከረ፡ በደል ለበደል ተገላለጠ።
ተዋቀረ፡ ተቋጠረ፡ ተጠረቀ፡ ተዠመረ፡ ጣራው። (ተረት)፡ ሲገደገድ ያልበጀው፡ ሲዋቀር እሳት ፈጀው።
ተዋቀረ፡ ተናቀሰ፡ ተጠቃጠቀ፡ ተጣረበ።
ተዋቀጠ፡ ተፋተግ፡ ተቀጣቀጠ፡ ተማታ፡ ተደባደበ።
ተዋቃ፡ ተነቃነቀ፡ ተሳደበ።
ተዋቃሽ፡ የሚዋቀሥ፡ ተከራካሪ።
ተዋበ (ተውህበ): ተሰጠ፣ ተሰጭ ሆነ።
ተዋበ (አደመ ሠነየ): አማረ፣ ቆነዠ።
ተዋበች (አደመት ሠነየት ቀደወት): የሴት ስም፣ አማረች፣ ቆነዠች። ዋና ምስጢሩ ለባል ተሰጠች ማለት ነው።
ተዋኔ፣ ፈላስፋ፡ ዋኘ ።
ተዋኔ (ተዋናዪ) ፡ የፈላስፋ ስም (በጐዣም አውራጃ የነበረ ታላቅ ሊቅ ቅኔን የፈጠረ ባሕረ ምስጢሩን ዋኝቶ የመረመረ ቁም ነገር ባለው ፍልስፍና ከደቀ መዛሙርቱ ' ጋራ ሲጫወት የኖረ) ።
ተዋኘ፡ በዋና ተሞከረ፡ ተደፈረ፡ ተወሰወሰ፡ የውሃ ምላት።
ተዋከበ: ተቻኰለ፣ ተጣደፈ፣ ተዳፋ።
ተዋካ (ተዋክሐ): ተቘከረ፣ ተደናፋ፣ ተፋጀ፣ ተጯጯኸ።
ተዋወቀ (ተዓወቀ): ተላመዱ፡ ተለማመደ።
ተዋወከ (ተሃወከ): ተበጣበጠ፣ ተተራመሰ።
ተዋዋለ (ተዋዐለ): በግብር፣ በነገር ተሰማማ፡ "ይህን ብታደርግ ይህን አደርጋለኹ" ተባባለ። ተጻጻፈ፣ ተፈራረመ፡ ቃል ኪዳን ተጋባ።
ተዋዋሰ፡ ተበዳደረ፡ ዕቃ ተሰጣጠ፡ ተቀባበለ።
ተዋዋሰ፡ ዋስ ተጠራራ፡ ሥራት ገባ (ተጋባ)።
ተዋዋሽ፡ የሚዋዋስ።
ተዋዋቂ: የተዋወቀ፡ የሚተዋወቅ።
ተዋዋበ (ተዋሀበ): ውበትን ተሰጣጣ፣ ተሸጋገነ።
ተዋዋይ (ዮች): የተዋዋለ፣ የሚዋዋል፡ ተሰማሚ።
ተዋዋጠ: ተባላ፣ ተበላላ፣ ተሰለቃቀጠ።
ተዋዛ: ዋዛ ተናገረ፣ ተነጋገረ፣ ተቃለደ፡ ቈሎ ተጓረሠ።
ተዋየ: ተጮኸ፣ ታዘነ፣ ተቈዘመ፣ ተለቀሰ፡ ዋይ ተባለ።
ተዋደረ: ተጋመደ፣ ተጣመረ።
ተዋደቀ: ተጣጣለ፡ ከድኸነት ጋር ተዋደቀ፡ ተገዳደመ፣ ተተኛኛ፡ ተነባበረ፣ ተደራረበ፣ ሬሳ በሬሳ ላይ ተኳኳነ። (ዘሌ፳፮፡ ፴፯)
ተዋደደ: ተሰማማ፣ ተፋቀረ፣ ተማመነ። (ዮሐ፲፫፡ ፴፬። ሮሜ፲፪፡ ፲)
ተዋደደ: ተሳካ፣ ተጋጠመ።
ተዋዳጅ: የሚዋደድ፣ ተፋቃሪ።
ተዋጀ: ተገዛ፣ ተለወጠ።
ተዋገረ: ተማታ፣ ተደባደበ።
ተዋገነ: ተዛመደ፣ ወገን ተኳኳነ።
ተዋገዘ፡ ተጋዘተ።
ተዋገደ፡ ተገባደደ፣ ተቃለለ፣ ተቃረበ (ሥራው)።
ተዋጊ (ወጊ)፡ ከብትን/ሰውን የሚዋጋ ክፉ በሬ። ጦረኛ፣ ሐርበኛ፣ ጎበዝ ሰው።
ተዋጊዎች/ተዋጎች፡ ጦረኞች፣ ሐርበኞች።
ተዋጋ (ተዋግአ)፡ ተላተመ፣ ተተማተመ፣ ተዳሰመ (በቀንድ፣ በጦር፣ በሰይፍ፣ በጠመንዣ)፣ ተማታ፣ ተጋጩ፣ ተሸቃሸቀ።
ተዋጋ (ተዋግዐ)፡ ወግን ተነጋገረ፣ ዋጋን ተሳሰበ።
ተዋጠ: ተበላ፣ ተሰለቀጠ፡ እሆድ ገባ። (ኤር፴፡ ፲፯። ፩ቆሮ፡ ፲፭፡ ፶፬) "ሲዋጥ በመረቅ" እንዲሉ።
ተዋጠ: እባሕር ጠለቀ፣ በረግረግ ሠረገ፣ ሰጠመ።
ተዋጠ: ጠብቆ ተነገረ፣ ተጐረደ፣ ቀረ (የፊደል፣ የቀለም)።
ተዋጠረ: ተዘራጋ።
ተዋጠነ: ተዣመረ፣ ተፋለመ።
ተዋጣ: ተከረ፣ ተፋተነ፣ ተባባለ፡ የጕልበትን ልክ ተዋወቀ።
ተዋጣ: አማረ፣ ሰመረ (ሥራው)።
ተዋፅኦ: መዋጮ፡ ወጣ ።
ተው: "ዕንክ በሬን ካንድ ነገር ላይ ለመከልከል የሚነገር ቃል ነው። ዕንካን ተመልከት።"
ተው: ልቀቅ፣ ጣል።
ተው: እባክሽ በል። "ተው ኺድ፡ ተው ተነሥ፡ ተው ብላ።"
ተውለቀለቀ: የወላለቀ ድርብ፡ ተነቃቀለ።
ተውለብላቢ: የሚውለበለብ፡ ሰንደቅ ዓላማ።
ተውሳከኛ፡ ዝኒ ከማሁ።
ተውሳካም፡ በሽተኛ፡ የበሽታ ጐሬ፡ ጤና ቢስ።
ተውሳክ፡ ብዙ ዐይነት በሸታ፡ ወረርሽኝ።
ተውሳክ፡ ተጨማሪ ቍጥር፡ ለቀንና ለጦም፡ ለበዓል የሚነገር።
ተውሶ፡ ዝኒ ከማሁ፡ መዋስ። ገንዘብ የተውሶ ጠፋ፡ ተጨርሶ። ለሩቅ ወንድ ቦዝ አንቀጽ፡ ሲኾን እከሌ መሣሪያ ተውሶ አመጣ ይላል።
ተውረከረከ፡ ተብረከረከ።
ተውረገረገ፡ ተረገረገ።
ተውሸለሸለ፡ ተውተፈተፈ፡ ጥብቅነት ዐጣ።
ተውበኻ(ሻ)ል አሉ ደኅኔ: የዘፈን አዝማች ("አምረኻል፣ ቆንዥተኻል፣ ለማማር ተሰጥተኻል")።
ተውተረተረ: ተግተረተረ፡ ዐልፎ ዐልፎ ተተከለ፣ ተገረገረ፡ ተወናከረ። (ግጥም): ስውተረተር ደረሰልኝ ዐተር።
ተውተበተበ፡ ተውሸለሸለ፡ ተውተፈተፈ።
ተውተፈተፈ: ተውሸለሸለ፣ ተውተበተበ።
ተውዘገዘገ: ተምዘገዘገ፣ ተቅዘመዘመ።
ተውዠለዠለ: ተጐተተ፣ ተሳበ፡ ተውዠመዠመ።
ተውዠመዠመ: ረዘመ፣ ተሳበ፣ ተጐተተ።
ተውጠነጠነ: ታሰበ፣ ተጕላላ።
ተዉ: የቅርብ ወንዶችና ሴቶች፣ በርስዎታም የቅርብ ወንድና ሴት ትእዛዝ አንቀጽ። "ተዪ፡ ተይ፡ ልቀቂ፡ ጣዪ። ትቶት፡ ጥሎት። ትቶት ኺዷል ጣም የለውም።"
ተዘለለ: ተበለጠ፡ ተተወ፡ ታለፈ።
ተዘለለ: ተዘረረ፡ ዐረፈ፡ ዐሳቡን ጣለ፡ "ምን አለብኝ" አለ።
ተዘለለ: ተጠመቀ፡ ተበጠበጠ፡ ተቦካ።
ተዘለለ: ተጨፈረ፡ ተረገደ።
ተዘለሰ: ተቈረጠ፡ ተመነጠረ፡ ተኛ፡ ተጋደመ።
ተዘለቀ: ተነበበ፡ ተወጣ፡ ታለፈ፡ ከንጨት እንጨቱ ተጨረሰ መጻፉ።
ተዘለነ: ጐጆ ነቀለ፡ ደሳ ጠቀለለ፡ ስፍራ ለቀቀ፡ ተጐዳኘ፡ ተዛወረ።
ተዘለዘለ: ተሠነጠቀ፣ ተሸነሸነ፣ ቀጠነ፣ ረዘመ።
ተዘለዘለ: ተነከሰ፣ ተዘነተረ።
ተዘለጐሰ: ተዘለለ፣ ተገደፈ፣ ተበላሸ።
ተዘለፈ: ተዘለሰ፡ ዘነበለ።
ተዘለፈ: ተገሠጸ፡ ተወቀሠ፡ ተመከረ፡ ተነቀፈ፡ ተሰደበ (ዘፍ 20:16)።
ተዘላለቀ: ተከራረመ፡ ተኗኗረ።
ተዘላሽ: የሚዘለስ።
ተዘላኝ: የሚዘለን፡ ተዛዋሪ።
ተዘላዘለ: ተሠናጠቀ፡ ተሸናሸነ።
ተዘላዘለ: ተናከሰ፡ ተዘናተረ።
ተዘላይ: የሚዘለል፡ የሚታለፍ፡ ጕድባ፡ ፈረፈር።
ተዘልዛይ: የሚዘለዘል፡ ሙዳ።
ተዘመመ: ተሠራ፡ ገባ ዝማሙ።
ተዘመመ: ተዘነበለ፡ ተዜመ፡ ተባለ፡ ተደረገ ዝማሜው።
ተዘመመ: ተደረደረ፡ ተጐቹ፡ ተከመረ በሞላላው።
ተዘመረ: ተሠራ፡ ታረሰ፡ ታጨደ።
ተዘመረ: ተዜመ፡ ተመሰገነ፡ ተዘፈነ፡ ተደረደረ፡ ተመታ (በገናው)።
ተዘመተ: ተኼደ፡ ተገሠገሠ፡ ተዘረፈ፡ ተቀማ።
ተዘመዘመ: ተሰፋ፡ ተጠቀመ፡ ተቀመቀመ፡ ተጠለፈ፡ ተጌጠ።
ተዘመደ: ተወለደ፡ ዘመድ ሆነ፡ ተወገነ።
ተዘማመደ: ተገነኛኘ፡ ተያያዘ፡ ተገናኘ።
ተዘምዛሚ: የሚዘመዘም፡ ተቀምቃሚ።
ተዘምዶ: ዝምድና (የግእዝ ቃል)።
ተዘረረ: ተዘለለ፣ ተዘረጋ፣ ተሰጣ፣ ተሰተረ፡ ተኛ፣ ተጋደመ።
ተዘረነቀ: ተበላሸ፣ ተዘባረቀ።
ተዘረነቀ: አያገባው ገባ፣ ተጨመረ፣ ተዶለ፣ ተነከረ።
ተዘረከተ: ተቀደደ፣ ተዘረገፈ።
ተዘረከተ: ተነፋ (ተነፍን)።
ተዘረካከተ: ተቀዳደደ፣ ተሸረካከተ።
ተዘረኰተ: ተዘለጎሰ፣ ተገደፈ፣ ተጣለ፣ ወደቀ፣ ተዘለለ።
ተዘረዘረ : ተመነዘረ፣ ተሸረፈ።
ተዘረዘረ : ተሞረደ፣ ተፈገፈገ፣ ተሳለ።
ተዘረዘረ : ተሸከሸከ፣ ተዘከዘከ፣ ሳሳ፣ ተራራቀ።
ተዘረዘረ : ገባ፣ ተመለሰ (ፊደሉ)።
ተዘረዘረ: ተመነዘረ፣ ተሸረፈ።
ተዘረዘረ: ተሞረደ፣ ተፈገፈገ፣ ተሳለ።
ተዘረዘረ: ተሸከሸከ፣ ተዘከዘከ፣ ሣሣ፣ ተራራቀ።
ተዘረዘረ: ተበተነ፣ ተለየ።
ተዘረዘረ: ገባ፣ ተመለሰ (ፊደሉ)።
ተዘረገፈ: ወጣ፣ ፈሰሰ፣ ስፍራውን ለቀቀ (ሰቆቃወ ኤርሚያስ ፪፡ ፲፩)።
ተዘረጋ: ተሰተረ፣ ተሰጣ፣ ተዘረረ፣ ተጠፈጠፈ፣ ሣሣ፣ ተጋደመ፣ ተገለጠ፣ ተወጠረ፣ ተነጠፈ።
ተዘረጋጋ: ተሰታተረ።
ተዘረጠጠ: ተሳበ፣ ተጎተተ።
ተዘረጠጠ: ተናደ፣ ፈረሰ።
ተዘረጠፈ: ተሰደበ፣ ተፀረፈ።
ተዘረፈ: ተወረረ፣ ተበዘበዘ፣ ተቀማ፣ ተነጠቀ፣ ተወሰደ።
ተዘረፈረፈ: ወጣ ወይም ፈሰሰ።
ተዘራ (ተዘርዐ): ተበተነ፣ ተነሰነሰ፣ ተሸነ፣ ጠብ ጠብ አለ (ሕዝቅኤል ፴፮፡ ፱፣ ማቴዎስ ፲፫፡ ፲፱፣ ፳፣ ፳፪፣ ፳፫)።
ተዘራ (ተዘርወ): ተንቀረቀበ፣ ተነቀነቀ፣ ለነፋስ ተሰጠ፣ ተለየ።
ተዘራ ወርቅ: ዝኒ ከማሁ። ወርቅ ተፀነሰ፣ ተረገዘ ማለት ነው።
ተዘራ፡ የሰው ስም።
ተዘራረፈ: ተቀማማ፣ ተነጣጠቀ።
ተዘራከተ: ተቃደደ፣ ተዘራገፈ።
ተዘራዘረ : ተረደ፣ ተፈጋፈገ፣ ተሳሳለ።
ተዘራዘረ: ተለያየ፣ እየብቻ ተኳኳነ።
ተዘራዘረ: ተረደ፣ ተፈጋፈገ፣ ተሳሳለ።
ተዘራገፈ: ተቃደደ፣ ተሸራከተ፣ ተዘራከተ።
ተዘራጋ: ተሳተረ (ኢዮብ ፫፡ ፲፫)።
ተዘራጠጠ: ተናናደ፡ ተሳሳበ፣ ተጓተተ።
ተዘራፊ: የሚዘረፍ፡ ተነጣቂ።
ተዘርዛሪ: የሚዘረዘር፣ አጋዥ፣ ማጭድ።
ተዘርጊ: የሚዘረጋ፣ ተወጣሪ።
ተዘርጋፊ: የሚዘረገፍ፣ የሚወጣ።
ተዘርጣጭ: የሚዘረጠጥ፣ የሚናድ፣ ጕቾ፣ ዘመመን።
ተዘቀዘቀ: ተቈለቈለ፣ ፈሰሰ፣ ተደፋ፣ ቍልቍል አመራ፣ ወረደ። (ለምሳሌ: የሌት ወፍ እንደ ጃን ጥላ ተዘቅዝቃ ትሰቀላለች፣ ትሰፍራለች፣ ትተኛለች)።
ተዘቃዘቀ: ቍልቍል ተሳቀለ።
ተዘቅዛቂ: የሚዘቀዝቅ ኮከብ፣ ዋነተኛ።
ተዘበለለ: ታራ፣ ተኰሳ፣ ተዘፈዘፈ።
ተዘበራረቀ: ተደበላለቀ፣ ተዘናነቀ፣ ተቀያየጠ።
ተዘበተ: ተቈለለ፣ ተከመረ።
ተዘበተ: ተዛተ፣ ተፎከረ።
ተዘበተ: ኾነ፣ ተደረገ፡ ለግጡ።
ተዘበተረ: ተዘነተረ።
ተዘበዘበ: ተነዘነዘ፣ ተነተረከ፣ ተጨቀጨቀ፡ በዛ፣ ተጐተተ ነገሩ።
ተዘበጠረ: ተሠባጠረ።
ተዘባረቀ: ተቃወሰ፣ ተሳሳተ፣ ተዛወረ፡ አለስፍራው ገባ፡ የግራው በቀኝ፣ የቀኙ በግራ፣ የዳሩ በመኻል፣ የመኻሉ በዳር፣ የኋላው በፊት፣ የፊቱ በኋላ ኾነ።
ተዘባረቀ: ተደባለቀ፣ ተቀላቀለ።
ተዘባበተ: ተዛዛተ፣ ተፎካከረ።
ተዘባዘበ: ተነዛነዘ፣ ተነታረከ፣ ተጨቃጨቀ።
ተዘተበ: ተመሳ፣ ምሉ ሆነ።
ተዘተዘተ: ተነከሰ፣ ተበጣጠሰ፣ ተገተገተ።
ተዘነቀ: ተቀላቀለ፣ ተዋሀደ ወይም ተጣመረ።
ተዘነቀ: ተቀየጠ፣ ተቀላቀለ፣ ተደባለቀ።
ተዘነበለ (ዘነበለ): ተጐነበሰ።
ተዘነተረ: ተነከሰ፡ ተቀደደ ወይም ታኘከ፡ በሚንጨባረቅ ሁኔታ ተበላ።
ተዘነተረ: ተነከሰ፣ ተዘበተረ፣ ተቦጨቀ፣ ተቦተረፈ።
ተዘነኰረ/ተዘነከረ: ተበላሸ፡ ፍሬ ፈርስኪ ሆነ።
ተዘነኰረ/ተዘነከረ: ተበላሸ; ፍሬ የለሽ/ፈርስኪ ሆነ።
ተዘነኰረ/ተዘነከረ: ጠፋ፣ አለቀ፣ ፍሬ አልባ ሆነ።
ተዘነኳኰረ: ሙሉ በሙሉ ጠፋ ወይም አለቀ (ብዙ ቁጥር/አጽንኦት)።
ተዘነኳኰረ: ተበላሸሸ።
ተዘነደበ: ረዘመ፡ ወጣ።
ተዘነጀረ: ታሰረ፡ ሁለት ፍንጅና ጠገግ ባለው እግረ ሙቅ ተገጠመበት (2ሳሙ 3:34)።
ተዘነጋ: ተረሳ፡ ታጣ፡ ጠፋ።
ተዘነጋጋ: ተረሳሳ፡ ተጣጣ።
ተዘነጓጐለ: ተለያየ፡ ተበለሻሸ።
ተዘነጠለ: ተነፋ፡ ወፈረ፡ ቦርጭ አወጣ።
ተዘነጠለ: ተፈነቀለ፡ ተነደለ።
ተዘነጠለ: አላገባብ ተነበበ።
ተዘነጠፈ: ረዘመ፡ ረዥም ሆነ።
ተዘነጠፈ: ረገፈ፡ ወረደ (ሐ 62:22)።
ተዘነጣጠለ: ተበሳሳ፡ ተቀዳደደ፡ ተሸረካከተ።
ተዘናበለ: ተጐናበሰ፡ ተደናቀፈ፡ ተጣመመ (ሰቆ 4:14)።
ተዘናተረ: ተናከሰ፣ ተዘባተረ፣ ተባላ።
ተዘናተረ: እርስ በእርስ ተነካከሱ፡ በጥርስ ተጣሉ።
ተዘናነፈ: በርዝመት ወይም በትብት እርስ በእርስ ተወዳደሩ።
ተዘናነፈ: ተበላለጠ።
ተዘናጐለ (መዝጐለ፣ ተመዝጐለ): ተቃወመ፡ ተከራከረ፡ ስምምነት አጣ፡ ተለየ፡ ተበላሸ።
ተዘናጠለ: ተፈናቀለ፡ ተቃደደ፡ ተዋጋ፡ ተሸራከተ።
ተዘናፈለ: ተንፈላሰሰ፣ ተፈረነሰ፣ ተጋደመ፣ ተቈላዘመ፣ ተጐናዘለ (ለምሳሌ: ሣሩ፣ ጤፉ፣ መኰንኑ)።
ተዘናፈለ: ተዘረጋጋ፡ ተኛ፡ ተዝናና፡ ተዘረጋ (ለምሳሌ ሣር፣ ጤፍ፣ የሹም ልብስ)።
ተዘንባይ: የሚዘነበል።
ተዘንጣይ: የሚዘነጠል፡ ተቀዳጅ።
ተዘከረ: (ዘከረ) አሰበ፣ ፈረደ። ለምሳሌ: "አምላኬ ሆይ፣ ኃጢአቴን አትዘከርብኝ። " (እዚህ ላይ ተደራጊና አድራጊነቱን መለየት አስፈላጊ ነው።)
ተዘከረ: ለድሀና ለለማኝ ሰጠ (ትክክለኛው ግን "ተሰጠ" ነው።)
ተዘከረ: ለድሀና ለለማኝ ተሰጠ። (ምንም እንኳን 'ሰጠ' የሚለው ግስ በትክክል 'ተሰጠ' መሆን አለበት)።
ተዘከረ: ተጸለየ፣ ተባረከ፣ ተቆረሰ።
ተዘከረ: አሰበ፣ ፈረደ። "አምላኬ ሆይ፣ ኃጢአቴን አትዘከርብኝ። " (እዚህ ላይ ተደራጊና አድራጊ መሆኑን አስተውል)።
ተዘከረኝ: "ዳኛ ማርያም ሆይ፣ አስበኝ፣ ፍረድልኝ" ሲባል ጥቅም ላይ ይውላል።
ተዘከዘከ: ተነቀነቀ፣ ተሰነገ (ተናወጠ)።
ተዘከዘከ: ተነከሰ፣ ተበላ፣ ተቦተረፈ።
ተዘከዘከ: ተዘረዘረ፣ ተሸከሸከ፣ ተቀደደ።
ተዘከዘከ: ተዘቀዘቀ፣ ተዘረገፈ፣ ወጣ፣ ፈሰሰ።
ተዘካሪ: የሚዘከር፣ ሰጪ።
ተዘካዘከ: ተዘራረበ፣ ተሸካሸከ፣ ተቃደደ።
ተዘካዘከ: ተዘራገፈ፣ ተዋጣ።
ተዘክሮ: ማሰብ። "ተዘክሮ ሞት" እንዲሉ።
ተዘክሮ: ማሰብ። ለምሳሌ: "ተዘክሮ ሞት" እንዲሉ። (የግእዝ ቃል ነው)።
ተዘክሮ: አስቦ ሰጥቶ።
ተዘክሮ: አስቦ ሰጥቶ። (በአማርኛ)
ተዘወረ: መዘውር ኾነ፣ ዞረ፣ ተጠመዘዘ።
ተዘወተረ ዘወትር ተሠራ፣ ሆነ፣ ተደረገ።
ተዘዋተረ ወይም ተዘወታተረ ነገሩ ወይም ጕዳዩ ተመላለሰ ማለት ነው።
ተዘዋወረ: ተዟዟረ፣ ተጠማዘዘ፡ መዘውር፣ ተኳዃነ፡ ተለዋወጠ፣ ተቀያየረ።
ተዘዋዋሪ: የሚዘዋወር፡ ተጠማዛዥ፡ ተላላፊ፣ መኪና፣ በሽታ።
ተዘውታሪ የሚዘወተር ነው።
ተዘዘ: ተመናቸከ።
ተዘየረ ተጐበኘ፣ ተደረሰ፣ ሰላም ተባለ፡ ምስጋና ተቀበለ።
ተዘየረ: ተጐበኘ፣ ተደረሰ፣ ሰላም ተባለ፤ ወይም ምስጋና ተቀበለ።
ተዘየነ ተሸለመ፣ ተጌጠ።
ተዘየነ: ተሸለመ ወይም ተጌጠ።
ተዘገበ: ተሰበሰበ፣ ተጠራቀመ፣ ተከማቸ።
ተዘገነ: ተጠረኘ፣ ጥርኝ ኾነ፡ ተቃመ።
ተዘገጃጀ: ተደረጃጀ፣ ተሰነዳዳ፣ ተቀነባበረ።
ተዘጊ: የሚዘጋ፣ የሚገጠም።
ተዘጋ: በተዘጋ ቤት ተቀመጠ፡ በውስጥ ኾነ (ሕዝ፫፡ ፳፬)።
ተዘጋ: ተገጠመ፣ ተከደነ፣ ተደፈነ፡ ልክክ አለ፡ ወለነ (፬ነገ ፮፡ ፴፬፡ ኢሳ፳፬፡
፪፡ ፲)።
ተዘጋቢ: የሚዘገብ፡ ደላቢ።
ተዘጋጀ (ተዘጋደየ): ተደራጀ፣ ተሰናዳ፣ ተበጃጀ፣ ተቀናበረ (ተደራጊ)።
ተዘጋጋ: ተገጣጠመ፣ ተደፋፈነ።
ተዘጠረ ምሉ ሆነ፡ ተነፋ፣ ተወጠረ፣ ዐበጠ።
ተዘጠረ: ምሉዕ ሆነ፡ ተነፋ፣ ተወጠረ፣ ዐበጠ።
ተዘጠነ ዘጠኝ ሆነ፣ ተባለ።
ተዘጠነ: ዘጠኝ ሆነ ወይም ተባለ።
ተዘፈቀ: ተደፈቀ፣ ተነከረ፣ ጠለቀ፣ ሰጠመ።
ተዘፈነ: ተዜመ፣ ተገጠመ፣ ተዘለለ፣ ተጨፈረ፣ ተጨበጨበ (አንዳንድ ጊዜ በዋልድባ ይዘፈናል)። አዳኞች፣ ዝኆንና አንበሳ ገዳዮች ባጠገቡ ይዘፍኑበታል።
ተዘፈዘፈ : ታራ፣ ተወዘፈ።
ተዘፈዘፈ: ተነከረ፣ ራሰ።
ተዘፈዘፈ: ታነከረ ወይም ታጠበ። ተዘረጋ ወይም ፈሰሰ።
ተዚያ (ከዚያ) ተዚያ ወዲያ በቂ።
ተዚያ (ከዚያ): ከዚያ ወዲያ በቂ።
ተዚያዚያመ ተጯጯኸ፣ ተቀባበለ።
ተዚያዚያመ: ተጯጯኸ ወይም ተቀባበለ።
ተዛለለ: ተላለፈ፡ ተረማመደ።
ተዛለለ: ተላለፈ፡ ተረማመደ።
ተዛለለ: ተናናረ፡ ተፈረ፡ ተጨፋፈረ። (መጽሐፍ ግን በዘለለ ፈንታ ተዛለለ ይላል - ሉቃ 1:44)።
ተዛለለ: ተገተ፡ ተከራከረ፡ እሰጥ አገባ ተባባለ፡ ተሯከረ፡ ተወዳደረ።
ተዛለቀ: ተካረመ፡ ተቻቻለ፡ ዐብሮ ኖረ፡ አረጀ።
ተዛለፈ: ተናቀፈ፡ ተሳደበ።
ተዛመተ: ተላለፈ፡ ተዋራ።
ተዛመደ: ተቀላቀለ፡ ተዋሐደ፡ ተዋለደ፡ ተዋገነ፡ ዘመድ ተኳዃነ፡ ጡት ተጣባ (ነሐ 13:4)።
ተዛረፈ: ቅኔ ተነጋገረ፣ ተመላለሰ (እንደ ዕቡይ ካሳና እንደ አለቃ ዶሪ)።
ተዛረፈ: ተበዛበዘ፣ ተቃማ፣ ተናጠቀ።
ተዛረፈ: ዘርፍ ተኳኳነ፣ ተያያዘ፣ ተናበበ።
ተዛራ: ተፋሰሰ፣ ተለያየ።
ተዛቀ: ተጠረገ፣ ተጋፈ፣ ተሰበሰበ፣ ተወሰደ።
ተዛቂ: የሚዛቅ፣ የሚጠረግ ቦይ።
ተዛበተ: ተቃለደ፣ ተዋዛ።
ተዛበተ: ተፋከረ።
ተዛባ: ተላመጠ፡ ተቃወሰ፣ ተሳሳተ የነገር።
ተዛተ: ሆነ፣ ተደረገ፣ ተነገረ (ዛቻው)፡ ተፎከረ።
ተዛነቀ: ተቃየጠ፣ ተሠባጠረ፣ ተደባለቀ።
ተዛነቀ: እርስ በእርስ ተቀላቀለ፡ ተዋሀደ።
ተዛነበ: ተፋሰሰ፡ ተራጩ።
ተዛነብ: ተፋሰስ።
ተዛነፈ: በርዝመት ወይም በትብት መወዳደር፡ መርዘም።
ተዛነፈ: ተባለጠ፣ ተራዘመ።
ተዛነፍ: (የቅርብ ወንድ ትዕዛዝ አንቀጽ) ተባለጥ።
ተዛነፍ: ልዩ፡ በልጧል፡ ትርፍ። ለቅርብ ወንድ "በርታ!" ለማለት እንደ ትእዛዝም ያገለግላል።
ተዛነፍ: የተዛነፈ፣ የተባለጠ። (ይህን ቃል እንደ ስም ሲጠቀም ዝንፋት ይሆናል)።
ተዛና (ተዝያነወ): ተዳራ፡ ተጫወተ፡ ተቃበጠ።
ተዛና: ተሸራሸ፡ ተደላደለ፡ ተመቻቸ።
ተዛናፊ: የሚወዳደር ወይም የሚበልጥ ሰው።
ተዛናፊ: የሚዛነፍ፣ የሚባለጥ።
ተዛወረ: ተላለፈ፣ ተላወጠ፣ ተቃየረ ሥራን፣ ስፍራን።
ተዛወረ: ተገለበጠ፣ ተጋባ በሽታው፣ ዕቃው።
ተዛወቀ: ተዛነቀ፣ ተዘባረቀ፣ ተሳሳተ።
ተዛዋሪ: የሚዛወር።
ተዛዘለ (ተሐዘለ): ተሸካከመ፡ ተደራረበ፡ ተነባበረ፡ የሸክም ሸክም ተኳዃነ።
ተዛዘለ: ግራና ቀኝ ተባለ፡ ተነገረ፡ ተፈራረቀ፡ ተመላለሰ (ዳዊቱ) (ዜማው)።
ተዛዘበ (ተሓዘበ): ተገናዘበ፡ ተገነዛዘበ፡ ተጠላለፈ።
ተዛዘበ: በትዝብት ተያየ፡ ተጠራጠረ፡ ተናናቀ፡ ተነቃቀፈ።
ተዛዘነ (ተሐዘነ): ተላቀሰ፡ ተወያየ፡ ተራረፈ፡ ተረዳዳ፡ ተካፈለ፡ ተዳረሰ። "አባት ልጆቹን ተዛዝናችኹ ብሉ" እንዲል።
ተዛዘነ: ተከፋፋ (ያዕ፭፡ ፱)።
ተዛዘዘ (ተኣዘዘ): የማዘዝ ብድር፡ ተመላለሰ እርስ በርስ።
ተዛዛተ: ተፋከረ፣ ተዘባበተ፣ ተወዳደረ፣ በጠብ ተነጋገረ፡ አንተ አንተ ተባባለ።
ተዛዛኝ: የተዛዘነ፡ የሚተዛዘን፡ የሚረዳዳ፡ ያገኘውን ተካፍሎ የሚበላ።
ተዛዛይ: የሚተዛዘል አንበጣ፡ ፌንጣ፡ የመሰለው ኹሉ።
ተዛገመ: ተዘጋገመ፡ ተጓጓዘ።
ተዛጋ: ተወራኘ፣ ተቃረበ፣ ተጣበበ፣ ተጋጠመ፡ (ተማማለ)።
ተዛፈቀ: ተዳፈቀ፣ ተሳጠመ።
ተዜመ በዜማ ተባለ፣ ተነገረ፣ ተቃኘ፣ ተዘመረ፣ ተቀደሰ፣ ተወደሰ።
ተዜመ: በዜማ ተባለ፣ ተነገረ፣ ተቃኘ፣ ተዘመረ፣ ተቀደሰ፣ ተወደሰ ማለት ነው።
ተዝለሰለሰ: ተዝለፈለፈ፡ ተቅለሰለሰ፡ ተለሸለሸ።
ተዝለገለገ: ተምለገለገ፣ ተሳበ፣ ተጎተተ (እንደ ለሐጭ)፡ ተንሸራተተ (እንደ እባብ)።
ተዝለፈለፈ: ተጥመለመለ፡ ደከመ፡ ባለ፡ አልነሣ አለ፡ ተስለመለመ።
ተዝረበረበ: ተንጠባጠበ፣ ተዝረከረከ።
ተዝረከረከ: ልብሱንና ሰውነቱን አልሰበስብ አለ (ከርጅና፣ ከሞኝነት የተነሣ)።
ተዝረከረከ: በብዙ ስፍራ ተወራ።
ተዝረከረከ: ተዝረፈረፈ፣ ተጣለ፣ ወደቀ፣ ተገደፈ።
ተዝረጠረጠ: ተዝረከረከ፣ ወደ ኋላ ቀረ።
ተዝረፈረፈ: ተዝረከረከ፣ ወደቀ፡ ተቈናዘለ (የሣር፣ የጠጕር) (ማሕ፭ - ፲፩)።
ተዝበደበደ: ፈራ፣ ተርበደበደ።
ተዝቦቀቦቀ: ዝኒ ከማሁ።
ተዝቦጠቦጠ: ተበጠበጠ፣ ተደባለቀ፣ ተቀላቀለ፡ ወፈረ።
ተዝናና: ብዙ ተናገረ፡ ተቅበጠበጠ።
ተዝካረ በቀል: የበቀል መታሰቢያ፡ በጦርነት ለሞቱ ሰዎች የተሰራ ሐውልት። (ወጋ ብለህ ተወጋን የሚለውን አስተውል።)
ተዝካር (ሮች): ለሟች መታሰቢያ በየዓመቱ የሚደረግ ድግስ ሲሆን ምግብና መጠጥ የሚቀርብበት።
ተዝካር አወጣ: ለሟች መታሰቢያ ስም አስጠራ፡ አስቆረበ፡ ለካህናት አበላ አጠጣ፡ ለድሆችም ምጽዋት ሰጠ።
ተዝካር አወጣ: ለሟች ስም አስጠራ፡ አስቆረበ፡ ለካህናት አበላ አጠጣ፡ ለድኾችም ምጽዋት ሰጠ።
ተዞረ ማለት ተከበበ፣ በዙሪያ ኼደ፣ ታወጠ፣ ዑደት ተደረገበት (ቤተ ክርስቲያኑን፣ ድምሩን)።
ተዟዟረ ማለት ዙረትን ተመላለሰ፣ ተላለፈ ማለት ነው።
ተዠለጠ: ተረገጠ፣ ለፋ፣ ተዘቀዘቀ።
ተዠመረ: ተወጠነ፣ ተፈለመ፣ ተቀደመ።
ተዠመገገ: ተሸመጠጠ፣ ተዠረገገ፣ ተሳበ፣ ተጐተተ።
ተዠማመረ: ተወጣጠነ፣ ተፈላለመ።
ተዠማሪ: የሚዠመር፣ ተፈላሚ።
ተዠረገደ : ረዘሙ፣ ቁመታም ኾነ።
ተዠረገደ : ተወለደ፣ ተፈለፈለ።
ተዠረገደ: ተመታ፣ ተደበደበ።
ተዠረገገ: ተዠመገገ፣ ተበጠሰ።
ተዠነቀ: ተጨመረ፣ ገባ።
ተዠነጠፈ: ተቈረጠ፣ ተዠመገገ።
ተዠገደ: ተማገደ፣ ተሞጀረ።
ተዣመረ: ተዋጠነ፣ ተፋለመ።
ተዣረ (ተዝኅረ): ራሱን ኰፈሰ፣ ሌላውን ናቀ፣ አኰሰሰ፣ ኰራ፣ ታበየ፣ ዐዲስ ልብስ ለብሶ ተሽኰንትሮ። (ዐጀረን እይ)።
ተዥበረበረ: ተንጸባረቀ፣ ተጥበረበረ፣ ቅር ግር አለው።
ተዥገረገረ: ዥግራ መሰለ፣ ጠቃጠቆ ሆነ፣ ተንከባለለ፣ ነጩና ጥቍሩ ታየ።
ተዥጐረጐረ: ነብር መሰለ፣ ነጣ፣ ጠቍረ (የዝናም፣ የደመና)።
ተዥጐደጐደ: በዝቶ መጣ፣ ገባ።
ተየከ)፡ መምላት፣ መንተርፈፍ። "ቲክ፡ አለ፡ ጢም፡ እለ፡ መላ።"
ተየከሰ: ተጠየቀ። ልማዱ ግን ጠየቀ ነው።
ተየካሽ (የተየከሰ): ጠያቂ; ተጠያቂ።
"ለጉባኤውም ለተየካሹ ምነው ቢገቡ ኾነ ምላሹ" (ኪ፡ ወ፡ ክ)።
ተያዘ (ተእኅዘ)፡ ተጨበጠ፡ ተገታ።
"ሠለጠ"
ብለኸ
"ሥልጣንን"
እይ። እወጥመድ ገባ። ተዋሰ፡ "በጐደለ እመላለኹ፡ በጠፋ እተካለኹ"
አለ። (ቤቱ ተያዘ): በዳኛ እጅ ኾነ።
ተያዡ: የሚያዘው፡ የርሱ ተያዥ፡ ያ ተያዥ።
ተያዢ (ዥ፡ ዦች)፡ የሚያዝ፡ የሚጨበጥ፡
ዋስ፡ መድን፡ ኀላፊ፡ ተጠያቂ።
ተያዥ ኾነ: መድን ኾነ፡ ተዳነ።
ተያዥነት: ተያዥ መኾን፡ ዋስትና።
ተያዧ: የርሷ ተያዥ፡ ያች ተያዥ።
ተያየ (ተራአየ): ተነጻጸረ፡ አኳያ ለአኳያ ተኳዃነ፡ ተፋዘዘ (ዘጸአት ፳፭፥፳)። "እባብን" ተመልከት።
ተያያዘ (ተኣኀዘ)፡ ተጣመረ፡
ተቈላለፈ፡ ተጣበቀ፡ ተቀጣጠለ፡ ነደደ፡ ተጣላ፡ ግብ ግብ አለ፡ ታገለ፡
ተናነቀ (ማቴ፲፭፡ ፲፬)።
ተያያዥ: የሚያያዝ፡ የሚታገል።
ተይዟል: ለሰው ተረክቧል ዕቃው፡ ገንዘቡ፡ ቤቱ፡ ተያዥ ኹኗል ዋሱ።
ተይዟል: በጠና ታል (ይዞታል)።
ተደለለ: ተሞኘ፣ ተታለለ፣ ተሸነገለ፡ ከቍጣ ተመለሰ።
ተደለሰ: ተላከከ፣ ተመረገ፣ ተቀባ።
ተደለቀ: ተመታ፣ ተደሰቀ፣ ተጐሰመ።
ተደለቀ: ተቈነነ፣ በቀስታ ኼደ።
ተደለኸ: ተወቀጠ፣ ተደለዘ፣ ተፈጨ፡ ላመ፣ ላቈጠ፣ ተለወሰ፣ ተዘጋጀ።
ተደለዘ: ተመረገ፣ ተበየደ፣ ተደፈነ።
ተደለዘ: ተወቀጠ፣ ተወገጠ።
ተደለደለ: ተመላ፣ ተጨመረ፣ ትክክል ኾነ።
ተደለደለ: ተከፈለ፣ ተመደበ። "ምድር ሲደለደል ለማሳ ሲታል" እንዲሉ።
ተደለደለ: ተገደበ፣ ታገደ፣ ተከተረ።
ተደለደለ: ዐበጠ፣ ተቀበጠጠ።
ተደለፈሰ: ተዛቀ፣ ተሰረረ።
ተደላ (ደላ): ጠመመ፣ ጐደለ (ብይኑ)።
ተደላለስ: ተቀባባ።
ተደላቂ: የሚደለቅ (ተቈናኝ)።
ተደላይ: የሚደለል፡ ተሸንጋይ፣ ተታላይ።
ተደላደለ: ተተካከለ፣ ቆመ፣ ተመቻቸ፣ ጌተየ፣ ተሰማማ፡ ተካፈለ።
ተደላዳይ: የሚደላደል፣ የሚመቻች።
ተደልዳይ: የሚደለድል (ተከታሪ)።
ተደመመ፡ ተቀበረ፡ ተደፈነ፡ ተስጣጣ።
ተደመመ፡ ተደነቀ፡ ተገረመ፡ ዝም፡ አለ።
ተደመመን፡ አደነቀ፡ ማለት፡ ልማዳዊ፡ ስሕተት፡ ነው።
ተደመሙ፡ አደነቀ፡ አነከረ።
ተደመሰሰ፡ ተፋቀ፡ ተፈገፈገ፡ ጠፋ፡ ተበላሸ፡ እንዳልነበረ፡
ሆነ።
ተደመረ፡ ተሰበሰበ፡ ታከበ፡ ተከማቸ፡ አንድነት፡
ኾነ፡ ተደረገ፡ ቆመ፡ ተጠመጠመ።
ተደመደመ፡ ተረገጠ፡ ተተካከለ።
ተደመደመ፡ ተጨረሰ፡ ተፈጸመ፡ ተቈረጠ።
ተደመደመ፡ ደነዘ፡ ዶለዶመ።
ተደመጠ፡ (ደምፀ)፡ ተሰማ፡ እዦሮ፡ ገባ።
ተደማመጠ፡ ተሰማማ፡ ድምጥ፡ ተቀባበለ።
ተደማሚ፡ የሚደመም፡ ተደፋኝ
ተደማሪ፡ የሚደመር፡ ዝርዝር፡ አኃዝ።
ተደማደመ፡ ውስጥ፡ ለውስጥ፡ አሤረ፡ ዐድማ፡ አደረገ፡
በሰውር፡ መከረ፡ ተመሳጠረ፡ ተሞዳሞደ፡ ሰው፡ አይስማ፡ ተባባለ።
ተደማጭ፡ የሚደመጥ፡ ተሰሚ፡
ተደምሳሽ፡ የሚደመሰስ፡ ጠፊ።
ተደምዳሚ፡ የሚደመደም።
ተደሞ፡ መደነቅ፡ ማድነቅ "
ተደሰመ፡ ተገጨ ተለተመ፡ ተተመተመ።
ተደሰመ፡ ታጠረ፡ ተዘጋ፡ ተደፈነ።
ተደሰቀ፡ ተመታ፡ ተደቃ።
ተደሰተ ፣ ተድላ፡ ደስታ፡ አደረገ፡ ፈነ ደቀ።
ተደሳች፡ የሚደሰት።
ተደረመሰ፡ ተደረባ፡ ፈረሰ፡ ተናደ፡ ወደቀ፡ ሠረገ።
ተደረሰ፡ ተቀረበ፡ ተነካ።
ተደረሰ፡ ተነገረ፡ ተባለ፡ ስብከቱ፡ ድርሰቱ "
ተደረሰበት፡ ተለጠቀ።
ተደረበ፡ ተካበ፡ ተጨመረ፡ ተጫነ፡ አበረ፡ ገጠሙ፡
አንድ፡ ሆነ፡ (፬ነገ፡ ፩፡ ፩)።
ተደረበ፡ ተዳበለ፡ የታቦት።
ተደረባ፡ ተናደ፡ ተንሸራተተ፡ ወረደ፡ ወደቀ፡ ተወረወረ፡
ድራሩ፡ አፈሩ፡ አውጭ፡ ሬሳውን፡ ስለ፡ በላው። መቃብሩ፡
ተደረባ፡ እንዲሉ።
ተደረተ፡ ተደበደበ፡ ተጠቃቀመ፡ እንደ፡ ደረት፡ ኾነ።
ተደረነቀ፡ ታመቀ፡ ተረጠጠ።
ተደረዘ፡ ደርዝ፡ ኹኖ፡ ተሰፋ፡ ተለጐመ።
ተደረደረ፡ ተመታ፡ በገናው፡ (ሆሴ፲፪፡ ፲፩)።
ተደረደረ፡ ተሰደረ፡ ተኰለኰለ፡ ተደከነ፡ ደንጊያው፡ ነዶው።
ተደረደረ፡ ተራ፡ መታ፡ ተሰለፈ፡ ሰዉ።
ተደረደረ: ተደረበ፣ ተዘመመ፣ ተጐቸ ወይም ተቈለለ።
ተደረጃጀ ፣ ተዘገጃጀ፡ ተቀነባበረ፡ ተሰነዳዳ።
ተደረገ፡ (ተገብረ)፡ ተሠራ፡ ተበጀ፡ ኾነ፡ ተከወነ፡ ተፈጸመ፡ (ሉቃ፭ ' ፲፪)።
ተደረገመ ፣ ጠፋ፡ ወደመ፡ ዓይኑ፡ መብራቱ።
ተደረገመ፡ ገባ፡ ተጠረቀመ፡ እሾኹ።
ተደረጠ፡ ተበጠበጠ፡ ታወከ፡ ተነቀ።
ተደረጠ፡ ታሸ፡ ተመታ።
ተደራ፡ ተሰበቀ፡ ተነቀነቀ።
ተደራ፡ ተተረተረ፡ ተዘረጋ፡ ድር፡ ሆነ። ከዚህ፡ እስከ፡ ደራ፡ አንጀትህ፡ ይደራ፡ እንዲሉ፡
ልጆች።
ተደራሰመ፡ ተገራሰመ፡ ተደናበረ፡ ተ ደናቀፈ።
ተደራረሰ፡ ተቀራረበ፡ ተነካካ።
ተደራረበ፡ ተነባበረ፡ ተለባበስ፡ ተጣጠፈ።
ተደራረገ፡ ተሠራራ፡ ተበጃጀ፡ ተኳዃነ።
ተደራረገ፡ ድርጎ፡ ተሰጣጠ፡ ተቀባበለ፡ ተለዋወጠ፡ አንተ፡ ይኸን፡ ውሰድ፡ እኔ፡ ያንን፡ እወስዳለኹ፡ ተባባለ።
ተደራራቢ፡ የሚደራረብ፡ ተነባባሪ።
ተደራራጊ፡ ፩ኛ፡ ዐምድ፡ ተሳሳቢ፡ አንቀጽ፡ ተጋደለ፡ ተገዳደለ። የሚደራረግ፡ ፪፡ አካል፡ ተጋዳይ፡ ተገዳዳይ።
ተደራራጊ፡ የሚደራረግ፡ የሚሠራራ።
ተደራቢ፡ (ዎች)፡ የሚደረብ፡ አባሪ፡ ተጨማሪ።
ተደራች፡ የሚደረት፡ ዐዲስ፡ ወይም፡ አ ሮጌ፡ ሸማ።
ተደራደረ፡ ተሰማማ፡ ተዋዋለ፡ ለመታ።
ተደራደረ፡ ተሳደረ፡ ተኰላኰለ።
ተደራጀ፡ ተዘጋጀ፡ ተቀናበረ፡ ተደገሰ፡ ተሰናዳ፡ (ተደራጊ)።
ተደራገመ፡ ጕንጭን፡ ተማታ፡ ተጣፋ።
ተደራጊ፡ ፫ኛ፡ ዐምድ፡ ተሳቢ፡ አንቀጽ፡ ተገደለ። ተሠሪ፡ አካል፡ ተገዳይ።
ተደራጊ፡ የሚደረግ፡ የሚሠራ።
ተደራጊነት፡ ተሠሪነት፡ ብጁነት።
ተደርዳሪ፡ የሚደረደር፡ ተሰዳሪ፡ ተኰልኳይ።
ተደርዳሪ፡ የተንቤን፡ ሽብሽቦ፡ በዝናር፡ ላይ፡ የተሰፋ፡ የጥይት፡ ቤት።
ተደርጎ፡ ተሠርቶ፡ ኹኖ።
ተደቀለ፡ ተዴቀለ፡ ተወለደ፡ ዲቃላ፡ ሆነ።
ተደቀቀ፡ (ደቀቀ)፡ ኢሳይያስ፡ ም፶፫፡ ቍ፭፡ ደቀቀ፡ በማለት፡
ፈንታ፡ ስለ፡ ኀጢአታችን፡ ተደቀቀ፡ ይላልና፡ ስሕተት፡ ነው። ደቀቀ፡
አጕል፡ ግስ፡ ስለ፡ ሆነ፡ ተደቀቀን፡ አይሻም።
ተደቀነ፡ ቀረበ፡ ተጠጋ፡ ተቋተ፡ ተደከረ።
ተደቀደቀ፡ ተወቀጠ፡ ተወጋ፡ ተጠቀጠቀ፡ ተጠረገ፡ ተወለወለ፡
ተከረና።
ተደቂ፡ የሚደቃ፡ መሬት፡ ዠርባ።
ተደቃ፡ ተመታ፡ ተወጋ።
ተደቃኝ፡ የሚደቀን፡ ተደካሪ።
ተደቈሰ፡ ተመታ፡ ተዳመጠ።
ተደቈሰ፡ ተፈጨ፡ ደቀቀ፡ ላመ፡ ለዘበ።
ተደቅዳቂ፡ የሚደቀደቅ፡ ጠመንዣ።
ተደቋሽ፡ የሚደቈስ፡ ላሚ፡ ለዛቢ።
ተደበለ: ተጨመረ፣ ተደረበ፡ ተሸረበ፣ ተጠሞረ።
ተደበለለ: ተሸከመ፣ ተጠገረረ።
ተደበለለ: ተጣለ፣ ወደቀ።
ተደበላለቀ: ተቀያየጠ፡ ተሸበረ፣ ተተረማመሰ፣ ተመሰቃቀለ።
ተደበሰ: ተጐበጐሰ፣ ተቀላቀለ።
ተደበረ: ደብር ኾነ፡ ተገደመ፣ ከበረ፣ በለጠ፡ ሳታትና መወድስ ተቆመበት፡ ካመት እስካመት ተቀደሰበት።
ተደበቀ: ተከተተ፣ ተሸጐጠ፣ ታባ፣ ተሰወረ፣ ተሸሸገ።
ተደበበ: ተሠራ፣ ተበጀ፡ ተዘረጋ፣ ተወጠረ፣ ተገተረ፡ ጠየመ።
ተደበተ: ተጨቈነ (እንቅልፍ ተጫነው)።
ተደበተረ: ተዘረጋ፣ ተጻፈ፡ እደብተር ገባ፡ ደብተራ ኾነ።
ተደበደበ: ተመታ፣ ተወገረ፣ ተገደለ፣ ሞተ (ዘዳ፳፩:፩፣ ኢሳ፲፫:፲፮)።
ተደበደበ: ተደፈነ፣ ተመረገ (የተሠነጠቀው ሸክላ)።
ተደበደበ: ተጣፈ፣ ተደረተ፣ ተለበደ።
ተደባለቀ: ተቀላቀለ፣ ተቀየጠ፣ ተዘነቀ።
ተደባላቂ: የሚደባለቅ፡ ተቀላቃይ።
ተደባሪ: የሚደበር፣ ደብር የሚኾን።
ተደባቂ: የሚደበቅ፡ ተሸሻጊ።
ተደባበቀ: ተሰዋወረ።
ተደባቢ: የሚደገብ፡ ተወጣሪ።
ተደባየ: ተረገጠ፡ በደባያት ሞተ።
ተደባደበ: ተማታ፣ ተዋገረ፣ ተጋደለ።
ተደባደበ: ተከራከፈ፣ ተጣጣረ፣ ተጫነቀ (ዳን፮:፲፬፣ ፪ሳሙ:፳:፲፭፣ ኢዮ፵:፳)።
ተደባዳቢ: የተደባደበ፣ የሚደባደብ፡ ተማች።
ተደብዳቢ: የሚደበደብ፡ ተገዳይ።
ተደነሰ፡ ተዘለለ፡ ተጨፈረ፡ ሆነ፡ ተደረገ፡ ዳንሱ።
ተደነሰረ፡ ተሸራሸ፡ ተመቻችቶ፡ ቍጭ፡ አለ።
ተደነቀ፡ (አደነቀ)፡ አነከረ።
ተደነቀ፡ (ደነቀ)፡ ድንቅ፡ ሆነ፡ እጹብ፡ ተባለ፡ ተገረመ፡
ተደመመ፡ ነገሩ፡ ሰው።
ተደነቀረ፡ ቆመ፡ ተሸጐረ፡ ተቀረቀረ፡ ተደገፈ፡ ተለገደ፡
ተጋረጠ፡ ተተከለ፡ ተሰካ ገባ። አንድ፡ ሰው፡ በጨለማ፡ ሲሄድ፡ በውስጥ፡ እግሩ፡
እሾኸ፡ ተደነቀረበት።
ተደነቀፈ፡ ተወለከፈ፡ ሰንካላ፡ ሆነ።
ተደነቃቀፈ፡ ተሰነካከለ፡ ተወለካከፈ።
ተደነቈለ፡ ተጠነቈለ፡ ተወጋ፡ ተዛቀ፡ ተነቈረ።
ተደነበቀ፡ ተቀዳ፡ ተጠለቀ።
ተደነባ፡ ታነጸ፡ ተጠረበ።
ተደነባ፡ ታገገ፡ ተወሰነ፡ ታወጀ።
ተደነባበረ፡ ተለካካ፡ ተወሳሰነ።
ተደነባበረ፡ ተወነባበረ፡ ተወነባበደ።
ተደነከረ፡ ተዘለለ፡ ተረገደ።
ተደነጀ፡ ተደነገገ፡ ተወሰነ።
ተደነገለ፡ ተጠበቀ፡ ድንግል፡ ሆነ።
ተደነገገ፡ ተሰራ፡ ተወሰነ፡ ተደነባ፡ ታገገ፡ ተጠነቀቀ።
ተደነጋገረ፡ ተሳሳተ፡ ተረሳሳ።
ተደነጋገገ፡ ተወሳሰነ።
ተደነጐረ፡ ተደደቀ፡ ተቈፈረ፡ ተፈነቀለ፡ ተገለበጠ።
ተደነፋ፡ ተዘለለ፡ ተጨፈረ፡ ተፎከረ፡ ዘራፍ፡ ያንተ፡
አሽከር፡ ተባለ።
ተደነፋፋ፡ ተፎካከረ።
ተደናቀፈ፡ ተወላከፈ፡ ተሰናከለ።
ተደናቂ፡ የሚደነቅ።
ተደናቈለ፡ ተዘናቈለ፡ ተናቈረ።
ተደናቈረ፡ ነገር፡ ለነገር፡ ሳይዳመጥ፡ ቀረ፡ ተጯጯኸ፡
ተለፋለፈ።
ተደናበረ፡ ተዋሰነ፡ ተዳካ።
ተደናበረ፡ ተጠናበረ፡ ቀኝና፡ ግራ፡ ረገጠ፡ ተሳሳተ።
ተደናከረ፡ (ተደናገረ)፡ ተወላገደ፡ ተደናቀፈ።
ተደናገረ፡ ተሳተ፡ ታጣ፡ ተረሳ።
ተደናገገ፡ ተዋሰነ።
ተደናገጠ፡ ተፋራ፡ ተዛዘነ።
ተደናፋ፡ ተፋከረ።
ተደንጋጊ፡ የሚደነገግ፡ ተወሳኝ።
ተደንጓሪ፡ የሚደነጐር፡ ተደዳቂ።
ተደከመ: ተጣረ፣ ተለፋ፡ ተሠራ (ሥራው)፡ ኾነ፣ ተደረገ (ድካሙ)። "ይህ ሥራ እጅግ ተደክሞበታል"።
ተደከረ: ተደቀነ፣ ተገተረ፣ ቆመ፣ ቀረበ፡ ተሰለፈ።
ተደከነ: ተሰደረ፣ ተደረደረ፡ ተነባበረ፣ ተደራረበ።
ተደካ: ተለካ፣ ተረገጠ፣ ተወሰነ።
ተደካሪ: የሚደከር፡ ተደቃኝ።
ተደወለ: ተቃጨለ፣ ተመታ፣ ተጠዘለ፣ ተመደወተ።
ተደወረ: ዞረ፣ ተዘወረ፣ ተጠነጠነ፣ ተጠቀለለ።
ተደዋሪ: የሚደወር (ግራ)።
ተደዋይ: የሚደወል፡ ተመቺ።
ተደዘደዘ: ተመታ፣ ተጠዘለ።
ተደደ: ተሰረቀ፣ ተወሰደ።
ተደደቀ: ተወጋ፣ ተፈነቀለ፣ ተደነጉረ፣ ተገለበጠ።
ተደዳቂ: የሚደደቅ፡ ዕዳሪ፣ ተደንጓሪ።
ተደገለ: ተቀየመ።
ተደገለለ: ተጠቀለለ፡ ተጠመጠመ፣ ታሰረ።
ተደገመ: ተነበበ፣ ተጸለየ፡ ተመለሰ።
ተደገመ: ታከለ፣ ተጨመረ። (ግጥም): "የመሸሻ ሴፉ ተሰቅሏል ዳዊቱ፡ ኣውርዱና ስጧት ተደገመች እቱ"።
ተደገሰ: ተቈላ፣ ተፈጨ፣ ተዘጋጀ፣ ተደራጀ፣ ተሰናዳ፣ ተቀናበረ፣ ተጠመቀ፣ ተጋገረ።
ተደገነ: ጐበጠ፡ ታሰረ፣ ተዘጋጀ፡ ተቀሰተ፣ ተቀሠፈ፣ ተደከረ፡ ጐረሠ፣ ታለበ።
ተደገደገ: ታሰረ፣ ተሸነፈጠ፣ ዞረ፣ ተጠመጠመ፣ ተቦደነ።
ተደገገ: ባነጋገር ታበየ፣ ኰራ፣ ታጀረ፣ ተገደረ፡ "አንተ እኔን ኣታኸለኝም" ኣለ፡ ጡር መስቃ ተናገረ።
ተደገገ: ዐበየ።
ተደገፈ: ታቀበ፣ ተያዘ፡ ተጠጋ፣ ተመረኰዘ፣ ተንተራሰ (ኢሳ ፲፪)። "መጽሐፍ ግን በተደገፈ ፈንታ 'ተገደፈ' ይላል፡ ስሕተት ነው" (ዮሐ ፲፫:፳፭)።
ተደጋሽ: የሚደገስ፣ የሚዘጋጅ።
ተደጋደገ: ተበሳቈለ፣ ተለዋወጠ፣ ተጣቈረ።
ተደጋገመ: ተናበበ፡ ተመላለሰ።
ተደጋገፈ: ተያያዘ፣ ተጠጋጋ፣ ተጋጠመ፣ ተቃረበ፣ ተቀራረበ።
ተደጋጊ: የሚደገግ፡ ኵሩ ሰው፣ ናቂ።
ተደጋጋፊ(ፎች): የሚደጋገፍ፡ ተከታትሎ።
ተደጋፊ: የሚደገፍ፡ ተመርኳዥ።
ተደጐመ: ታገዘ፣ ተረዳ፣ ተደገፈ፡ ኣገኘ፣ ተቀበለ።
ተደጐሰ: ነት ለበሰ፡ ተጌጠ፣ ተሸለመ።
ተደጓሽ: የሚደጐስ፣ የሚሸለም።
ተደፈረ፡ በዛ፡ ተቈለለ። ምርቱ፡ ተደፍሯል፡ እንዲሉ።
ተደፈረ፡ ተሰደበ፡ ተነጠበ፡ ተናቀ፡ ተዋረደ።
ተደፈረ፡ ተነካ፡ ተደረሰበት።
ተደፈቀ፡ ተዘፈቀ፡ ተነከረ፡ ገባ።
ተደፈቀ፡ ተዳጠ፡ ተፈጪ፡ ላመ።
ተደፈነ፡ ተቀበረ፡ ተመረገ፡ ተጠቀጠቀ፡ ተሸፈነ፡
ተዘጋ፡ ተጨፈነ፡ በውስጥ፡ ሆነ፡ መላ፡ ተመላ።
ተደፈደፈ፡ ተለጠፈ፡ ተቀባ፡ ተመረገ።
ተደፈደፈ፡ ታሸ፡ ተለወሰ፡ ድፍድፍ፡ ሆነ።
ተደፈጠ፡ ተሰካ፡ ተዋደደ፡ መደፈጫው።
ተደፈጠ፡ ተሸመቀ፡ ሆነ፡ ተደረገ፡ ደፋጣው።
ተደፈጠጠ፡ ተረገጠ፡ ተዳመጠ፡ ተወቈነ፡ አዳ፡ ሆነ።
ተደፊ፡ የሚደፋ፡ ተከንባይ።
ተደፋ፡ ባፍ፡ ጢሙ፡ በግንባሩ፡ ወደቀ። (ተረት)፡ የተከፋ፡ ተደፋ።
ተደፋ፡ ፈሰሰ፡ ተገለበጠ፡ ተዘቀዘቀ፡ ተዘረገፈ፡
ተጋገረ።
ተደፋሪ፡ የሚደፈር።
ተደፋቂ፡ የሚደፈቅ።
ተደፋኝ፡ የሚደፈን፡ ተመራጊ።
ተደፋፈረ፡ ተሰዳደበ፡ ተነጣጠበ።
ተደፋፈጠ፡ ተሸማመቀ።
ተደፍ፡ የሸማኔ፡ መምቻ፡ በጥርስ፡ ላይ፡ የሚዋደድ።
ተደፍዳፊ፡ የሚደፈደፍ፡ ተለዋሽ።
ተዳለለ: ተሸናገለ፡ "ሰምቶ እንዳልሰማ፡ ሲያውቅ እንደማያውቅ ተኳዃነ"።
ተዳለሰ: ተቃባ።
ተዳለቀ: ተዳሰቀ፣ ተጓሰመ፡ ተጫወተ።
ተዳላ: ተመቻቸ፣ ተሰማማ።
ተዳሎ: የውሻ ስም። "ተሞኛኝቶ፣ ተሸናግሎ" ማለት ነው።
ተዳመጠ፡ (ተደራራጊ)፡ ተሳማ።
ተዳመጠ፡ (ተደራጊ)፡ ተረገጠ፡ ተዳጠ፡ ተደፈጠጠ፡ ተለሰቀ፡ ትክክል፡
ኾነ።
ተዳማ፡ ተዋለደ፡ በዘር፡ ተቀላቀለ።
ተዳማ፡ ደም፡ ተፋሰሰ።
ተዳማጭ፡ የሚዳመጥ፡ የሚሳማ።
ተዳማጭ፡ የሚዳመጥ፡ ፍልቅቅ ' መንገድ።
ተዳሰ፡ ተፈጨ፡ ደቀቀ።
ተዳሰመ፡ ተጋጩ፡ ተላተመ፡ ተተማተመ።
ተዳሰሰ፡ ተነካ፡ ተዳበሰ።
ተዳሳሽ፡ የሚዳሰስ፡ ተዳባሽ።
ተዳረ፡ ተሰረገ፡ ሚስት፡ አገባ፡ ተሞሸረ።
ተዳረሰ ፣ ተካፈለ፡ ተዳደለ፡ ትክክል፡ ተሰጠ፡ (ተሰጣጠ)።
ተዳረሰ፡ ተቃረበ፡ ዝር፡ ተባባለ።
ተዳረሰ፡ ተዋገደ፡ ተገባደደ፡ ሊያልቅ፡ ቀረበ።
ተዳረቀ፡ ተነዛነዘ፡ ተጨቃጨቀ።
ተዳረቀ፡ ደረቅ፡ ተኳዃነ።
ተዳረች፡ ካባት፡ ከናቷ፡ ቤት፡ ወጣች፡ ለባል፡ ተሰጠች፡
(፩ሳሙ፡ ፲፰፡ ፲፱)።
ተዳረገ፡ ተለካ፡ ተሰፈረ፡ ተመጠነ፡ ተቈነነ፡ ተሰጠ፡ ድርነው፡ ተቀበለ፡ ሰውየው።
ተዳረገ፡ ተሣራ።
ተዳረገ፡ ተፈቀደ፡ ታዘዘ።
ተዳሪ፡ የሚዳር፡ የምትዳር፡ ተሰራጊ።
ተዳራ፡ (ተማሐዘ)፡ ተዛና፡ ተቃበጠ፡ ተዋዛ፡ ተጫወተ፡ ተላፋ፡
ተዳለቀ፡ ተዳሰቀ፡ ኀፍረት፡ ለኀፍረት፡ ተገላለጠ፡ ተቈላመመ፡ (ዘፍ ፳፮ ' ፰)።
ተዳራ፡ ድር፡ ተቀባበለ።
ተዳራጊ፡ የሚሣራ።
ተዳራጊ፡ የተዳረገ፡ የሚዳረግ፡ ሰው፡ ወ ይም፡ ድርጎ።
ተዳቀለ፡ ተራከበ፡ ተገናኘ፡ የተክልና፡ የተክል።
ተዳቀለ፡ ተዋለደ፡ ተዛመደ፡ የሰውና፡ የሰው።
ተዳቀቀ፡ ተሳበረ፡ ተሳለቀ፡ ተዳከመ፡ አቅም፡ አጣ።
ተዳቃ፡ በኰቴ፡ ተማታ።
ተዳበለ (ተደበለ): ደባል ኾነ፡ በሰው ቤት ተቀመጠ፣ ኖረ።
ተዳበሰ: ተዳሰሰ፣ ተነካ፡ ተፈለገ።
ተዳባ: ተሻመቀ፣ ተዳፈጠ።
ተዳባሽ: የሚዳበስ፡ ተዳሳሽ።
ተዳባይ: የሚዳበል።
ተዳነ፡ (ተድኅነ)፡ ተዋሰ፡ መድን፡ ተያዥ፡ ሆነ።
ተዳኘ፡ ለዳኛ፡ ታዘዘ፡ ተከሰሰ፡ ስርአት፡ ለበሰ፡
በግራ፡ ቆመ፡ ተፈረደበት፡ ተሰራ፡ ተቀጣ።
ተዳከመ: ተሰላቸ፣ ተሳነፈ (ወደ መሸነፍና ወደ ሞት ተቃረበ)።
ተዳካ (ተዳወለ): ምድርን ተራገጠ፣ ተላካ፣ ተዋሰነ፣ ተካለለ።
ተዳኸ: በጕንብስ ተኼደ።
ተዳኺ: የሚዳኸ (መታደያ)። "ባለቅኔዎች ግን ቤተ ልሔም ይሉታል"።
ተዳወለ: ተማታ፣ ተጣዘለ፣ ተመዳወተ። "ደካን እይ"።
ተዳወረ: ተደወረ።
ተዳደለ (ተዓደለ): ተሰጣጠ፡ ተቀባበለ (ድርሻን፡ ፈንታን)።
ተዳደሰ (ተሐደሰ): ዐዲስ ተኳዃነ፡
ተጠጋገነ።
ተዳደረ (ተኃደረ): ተኳዃነ፡ ተሰማማ፡ ተኗኗረ።
ተዳደነ: ተፈላለገ፡ ተገዳደለ።
ተዳደፈ: ተጓደፈ፣ ተራከሰ፣ ተረካከሰ፣ ተባከለ፣ ተጨማለቀ።
ተዳዳረ፡ ተሰራረገ።
ተዳጠ: ተረገጠ፣ ተደፈጠጠ።
ተዳጠ: ተፈጪ፣ ላመ።
ተዳጭ: የሚዳጥ (ፌጦ፣ ተልባ)።
ተዳፈረ፡ ተሳደበ፡ ተናጠሰ፡ ተጋፋ።
ተዳፈቀ፡ ተዛፈቀ፡ ተናከረ፡ ተሳጠመ፡ ተሳመጠ።
ተዳፈነ፡ (ተደራራጊ)፡ ተቃበረ፡ ሰው፡ ለሰው።
ተዳፈነ፡ (ተደራጊ)፡ ተደፈነ፡ ተቀበረ፡ ተሸሸገ፡ (ተረት)፡ እሳት፡ ሲዳፈን፡ የጠፋ፡ ይመስላል።
ተዳፈነ፡ ቀረ፡ ታጐለ፡ ግብሩ፡ ቅዳሴው።
ተዳፈጠ፡ ተሻመቀ፡ ተዳበቀ።
ተዳፋ፡ ተፋሰሰ፡ ተዋደቀ፡ ተቻኰሰ፡ ተጋፋ፡ ተጋደለ።
ተዳፋሪ፡ የተዳፈረ፡ የሚዳፈር፡ ተሳዳቢ፡ ተናጣሲ።
ተዳፋት፡ ዘቅዛቃ፡ ስፍራ።
ተድላ ሥጋ: የሥጋ ተድላ (ኀላፊ)።
ተድላ ነፍስ: የነፍስ ተድላ (የማያልፍ)።
ተድላ ደስታ: የደስታ ምቾት።
ተድላ ገነት: የገነት ተድላ፡ አዳምና ሔዋን ከስሕተት በፊት የነበሩበት። "በግእዝ ገነተ ተድላ ይባላል፡ የተድላ ገነት ማለት ነው"።
ተድላ: ምቾት፡ ለሰውነት የሚሰማማ (መብል፣ መጠጥ)፡ ማለፊያ ኑሮ (ሐዘን፣ ቅጣት፣ ችግር፣ ጕድለት የሌለበት)።
ተድመነመነ፡ ጠቋቈረ፡ ጨላለመ።
ተድረመረመ፡ ተጕረመረመ።
ተድረምራሚ ፣ የሚድረመረም፡ ተጕረ ምራሚ።
ተድረቀረቀ፡ መብረቅኛ፡ ጮኸ።
ተድቀሰቀሰ፡ በንቅልፍ፡ ዛለ፡ ደከመ፡ ሰለተ፡ ሰውነቱ፡
ደቀቀ፡ አቅም፡ አጣ፡ መነሣት፡ አቃታው።
ተድበለበለ፣ ተድቦለቦለ: ተንከበከበ፡ ክብ ኾነ። ዐበጠ፣ ተነፋ።
ተድበለበለ: ተርበተበተ።
ተድበልባይ: የሚድበለበል፡ ተንከብካቢ።
ተድበሰበሰ: ተደናገረ፣ ተሳሳተ (ዐረም ለበሰ)።
ተድበስባሽ: የሚድበሰበስ፡ ተደናጋሪ።
ተድበረበረ (ተድበለበለ): ተድፈነፈነ፡ ደንበር ደንበር እለ።
ተድበከበከ: ወፈረ።
ተድጐለጐለ: ወፈረ፡ መልክ ዐጣ፡ ቅንቡርስኛ ኼደ፣ ተላወሰ።
ተድፈነፈነ፡ ተጭፈነፈነ፡ ዳፍንታም፡ ሆነ።
ተድፈጠፈጠ፡ ተፍረጠረጠ።
ተዶለ: ተጨመረ፣ ተከተተ፡ ገባ፣ ተሰናዳ።
ተዶለተ: ተሰበሰበ፣ አንድነት ኾነ፡ ታደመ፣ ተመከረ፣ ተሤረ፣ ተቋጠረ።
ተዶለተ: ተዶለ፣ ተጨመረ፣ ተቀላቀለ።
ተዶረረ፡ ኰራ፡ ተመካ፡ ተቈጣ፡ አኰረፈ።
ተዶራሪ፡ የሚዶረር፡ ትምክተኛ። ሰራ ንን፡ እይ።
ተዶገዶገ: ተጨረ፣ ተሞጫጨረ፡ ቀጠነ፣ አነሰ፣ ደቀቀ።
ተጀለ: ተሸፈነ፡ ለበሰ፡ ተጠቀለለ፡ ለሰለሰ።
ተጀቦነ፡ ለበሰ፡ ታጀለ፡ ተሸፈነ።
ተጀነነ፡ (ዐረ፡ አበደ)፡ ኰራ፡ ታበየ። በዕለተ፡ ፍጥረት፡ የዲያብሎስን፡ አለማመስገን፡
ያሳያል።
ተጀነጀነ፡ ገባ፡ ተጨመረ፡ መላ፡ ተረገ ረፃ፡ ተጐዘጐዘ። (የቧልት፡ ዘፈን)፡ ያውና፡ እዚያ፡ ማዶ፡ ያገዳ፡ ጐዦ፡ ፍቅር፡
ገባና፡ ተጀነጀነ።
ተጀናኝ፡ የሚጀነን፡ የሚኰራ፡
ተጀጀረ፡ ከምግብ፡ ተከለከለ፡ ቍሽቢ ያም፡ ኾነ።
ተጀጐለ፡ (ተጨጐለ)፡ ተካበ፡ ታጠረ፡ ተቀጠረ፡ ተማገረ፡ ተሸመጠጠ።
ተጅመለመለ ፣ እንደ፡ ግመል፡ ተቀጣ ጥሎ፡ ኼደ።
ተገለለ፡ ተለየ፣ ተወገደ፡ ፈቀቅ አለ፡ ብቻውን ኾነ (ለዕርቅ፣ ለጸሎት)።
ተገለለ፡ ታጨደ፣ ተቈረጠ፣ ተነቀለ፡ ተጠራቀመ።
ተገለማመጠ፡ ተገራመመ።
ተገለሰሰ፡ ተለፈፈ፣ ተገለጠ።
ተገለበ፡ ተቃጠለ፣ ዐረረ።
ተገለበ፡ ተገለጠ፣ ተገለበጠ።
ተገለበጠ፡ ተቀዳ፣ ተጨመረ፣ ተጋባ (ማር፪፡ ፳፪)፡ ፈሰሰ፣ ተከነበለ።
ተገለበጠ፡ ተተረጐመ፣ ተመለሰ (ቋንቋው፣ ብራናው)።
ተገለበጠ፡ ተኛ፣ ተፈነደሰ። "ያንን ለከት ውጨ ውጨ፣ እንድክ ዐልጋ ተገልብጨ" እንዲሉ ልጆች።
ተገለበጠ፡ ከዳ፡ ወደ ጠላት ኼደ።
ተገለበጠ፡ ውስጠኛው ላይኛ ሆነ፡ ተዛወረ (ምሳ፲፩፡ ፲፩፣ ፳፮፡ ፳፳፯)።
ተገለባበጠ፡ ተዘዋወረ፣ ተቀያየረ፣ ተለዋወጠ።
ተገለባባጭ፡ የሚገለባበጥ (ድንጋይ፣ ሌላም ነገር)።
ተገለደመ፡ ታሰረ፣ ተሸረጠ።
ተገለገለ፡ ተለመነ፣ ዕሺ አለ፡ በላ።
ተገለገለ፡ ተነቀለ፣ ተወሰደ።
ተገለገለ፡ ተገመሰ፣ ታረሰ።
ተገለገለ፡ ታገዘ፣ ተረዳ፡ አገልግሎትን ተቀበለ።
ተገለጠ፡ ተገለበ፣ ተገፈፈ፣ ተከፈተ፣ ተራቆተ፡ ታየ፣ ተረዳ፣ ተከሰተ (ዘፀ፫:፲፯፣ ኢሳ:፵፱:፱)። "አምላክ በሥጋ ተገለጠ"።
ተገለጠጠ፡ ተዛቀ፡ ተሣቀ።
ተገለጸ፡ ተገለጠ፣ ተከሠተ።
ተገለፈጠ፡ ተሣቀ፣ ተገለፈፈ።
ተገለፈፈ፡ ተላጠ፣ ተላፈ፣ ተገፈፈ፣ ተፋቀ።
ተገለፈፈ፡ ተሣቀ፡ ተገለጠ (የከንፈር)።
ተገላለበ፡ ተገላለጠ።
ተገላለጠ፡ ተከፋፈተ፣ ተገላለበ፣ ተጋፈፈ፡ ነገር ለነገር ተዋጣ።
ተገላላጭ፡ የሚገላለጥ።
ተገላመጠ፡ ቀኝና ግራ፣ ፊትና ኋላ ዝንጀርኛ እየ (አድራጊ)።
ተገላመጠ፡ ተተኰረ፣ ተገሠጸ (ተደራጊ)።
ተገላማጭ፡ የሚገላመጥ።
ተገላበጠ፡ ተንከባለለ፣ ተዛወረ፡ ስፍራ ለወጠ (ዘፍ፫፡ ፳፬፣ ሉቃ፩፡ ፵፩)። (ተረት)፡ "ያልተገላበጠ ያራላል"።
ተገላቢ፡ የሚገለብ፡ ተገላጭ።
ተገላባጭ፡ የሚገላበጥ፡ ተንከባላይ።
ተገላተመ፡ ተቻኰለ፣ ተጣደፈ፡ ተጋጨ፣ ተላተመ።
ተገላገለ፡ ተላቀቀ፣ ተለያየ፡ ታረቀ፣ ተሰማማ።
ተገላገለች፡ ወለደች፡ ከምጥ ተለያየች። "እርጉዚቱ በደኅና ተገላገለች"።
ተገላጋይ፡ የሚገላገል፡ ታራቂ።
ተገላጭ፡ የሚገለጥ (መጋረጃ)፡ ወይም ሌላ።
ተገልባጭ፡ የሚገለበጥ፡ ተለዋጭ፣ ወረተኛ።
ተገልጋይ፡ የሚገለገል፣ የሚታረስ (መሬት)፡ የሚታገዝ፣ የሚረዳ (ሰው)።
ተገመለ፡ ተለበለበ፡ ግመል መሰለ።
ተገመሰ፡ ተተለመ፣ ታረሰ፡ ተቈረሰ፣ ተከፈለ፣ ተፈነከተ።
ተገመተ፡ ተሰላ፣ ታሰበ፣ ተገመገመ።
ተገመደ፡ ከረረ፣ ተሸረበ፣ ተደበለ።
ተገመደለ፡ ተቈረሰ፣ ተገመሰ።
ተገመደለ፡ ጐደለ፣ ተቀመጠለ።
ተገመገመ፡ ተያያዘ፡ ገመገም መስሎ ቆመ (፩ሳሙ:፲፬:፭፣ ነሐ፫:፳፮)።
ተገመገመ፡ ተገመተ፣ ተሸለገ፣ ታሰበ፣ ተሰላ (ዘሌ፭:፲፭)።
ተገመጠ፡ ተነከሰ፡ ተቈረሰ፣ ተሰበረ፣ ተሸረፈ፣ ተበላ።
ተገመጠጠ፡ ተነቀፈ፣ ተናቀ።
ተገማመሰ፡ ተፈነካከተ።
ተገማመተ፡ ተሳላ፣ ተዋጋ (ተዋግዐ)፡ ተሳሰበ፣ ተገማገመ፣ ተሸላለገ።
ተገማመጠ፡ ተነካከሰ፡ ተቈራረሰ፣ ተሰባበረ፣ ተሸራረፈ።
ተገማሽ፡ የሚገመስ፡ ተተላሚ።
ተገማች፡ የሚገመት ሀብት፡ ግምት ተቀባይ፣ ወሳጅ።
ተገማጅ፡ የሚገመድ፡ ሣር፣ ልጥ፣ ጭረት።
ተገማገመ፡ ተገማመተ፣ ተሳላ፣ ተሻለገ፣ ተሸላለገ፣ ተሳሰበ።
ተገማጋሚ፡ የሚገማገም፡ ተሳይ።
ተገማጠጠ፡ ተነቃቀፈ፡ ተንገራጠጠ፡ እንቢ አለ።
ተገማጣጭ፡ እንቢተኛ፣ ተንገራጣ።
ተገማጭ፡ የሚገመጥ፡ ተሸራፊ።
ተገምዳይ፡ የሚገመደል፡ ተቈራሽ።
ተገምጋሚ፡ የሚገመገም፡ ተሸላጊ።
ተገሰለ (ተአርወየ): ተነሣሣ፣ ተቈጣ፣ ተናደደ፣ ጮኸ።
ተገሰሰ (ተገሰ): ጠፋ፣ ተደመሰሰ፡ ተዳበሰ፣ ተዳሰሰ።
ተገሰሰ: ረባ፣ በዛ።
ተገሰሰ: ተሻረ፣ ተለወጠ፣ ተገለበጠ።
ተገሠጠ፡ ተሳለ፣ ተነጠሰ።
ተገሠጠ፡ ተገሠጸ።
ተገሠጸ፡ ተዘለፈ፡ ቍጣ መጣበት (ወረደበት)፡ ተሠራ፣ ተቀጣ፣ ተመከረ።
ተገሳሽ: የሚገሰስ፡ ተለዋጭ።
ተገረ: ተቈጣ፣ ግልፍተኛ ኾነ፣ ገፈ።
ተገረ: ነገደ፣ ወጥቶ ወርዶ። "ቸገረን ተመልከት።"
ተገረመ: ተደነቀ፡ ዕጹብ ድንቅ ተባለ። ልማዱ ግን "አደነቀ" "አነከረ" ነው።
ተገረመመ: ተገላመጠ።
ተገረሰሰ: ተነቀለ፣ ፈለሰ፣ ወደቀ፣ ተጋደመ።
ተገረበደ: ፈጽሞ ተከፈተ፣ ተወለለ።
ተገረኘ: ታሰረ፣ ተኰደኰደ።
ተገረዘ: ተቈረጠ፣ ተቀነጠበ።
ተገረደ: ተጦለ፣ ተለየ፡ ተቀጠረ፡ ግርድ፣ ገረድ ኾነ።
ተገረደመ: ተገመጠ፣ ተሰበረ፣ ነከተ፣ ደቀቀ፣ ተበላ።
ተገረደደ: ጠረሰ፣ ተቸረቸመ።
ተገረደፈ: ተፈጨ፣ ተከረተፈ፡ ጕርሃ ኾነ።
ተገረገመ: ተሠራ፣ ተበጀ (ግርግሙ)።
ተገረገመ: ተሸረፈ፣ ተሰበረ (ጥርሱ)።
ተገረገረ: ተቀረቀረ፣ ተተከለ።
ተገረገረ: ታወከ፣ ታገረ፣ ታገደ።
ተገረፈ: ቀና፣ ዕርሻ ለመደ።
ተገረፈ: ተሸለመ፡ ተተኰሰ።
ተገረፈ: ተቈነደደ፣ ተሸመተረ፣ ተሸነቈጠ፣ ተቀጣ፣ ተጠበጠበ (፪ቆሮ:፲፩:፳፬)።
ተገሪ: የሚግራ፣ የሚፈተን።
ተገራ (ተረየፀ፣ ገርሀ): ሥግሪያን ተማረ፣ ለመደ፡ ሰውን ተሸክሞ ኼደ፡ ተሠራ፣ ተቀጣ፣ ተፈተነ።
ተገራመመ: ተገለማመጠ፡ በክፉ ዐይን ተያየ።
ተገራሰመ: ተጋጨ፣ ተገላተመ፣ ተደናቀፈ፣ ተወላከፈ።
ተገራረመ: ተደናነቀ (እንደ እንጦንስና እንደ አቢብ)።
ተገራረደ: ተካለለ፣ ተመካከተ።
ተገራዥ: የሚገረዝ ወንድ ልጅ፡ ተቀንጣቢ ሸለፈት።
ተገራደመ: ተጋመጠ፣ ተሳበረ።
ተገራፊ: የሚገረፍ፡ ጥፋተኛ ሰው።
ተገርማሚ: የተገረመመ፣ የሚገረመም።
ተገርዳፊ: የሚገረደፍ፡ ተከርታፊ።
ተገሸለጠ: ተላጠ፣ ተመለጠ፣ ተገፈፈ።
ተገሸለጠ: ተሣቀ፣ ተገለፈጠ፣ ተገለፈፈ።
ተገሸረ: ተቀመጠ፣ ተረፈቀ።
ተገሸረ: ተተወ፣ ቈየ።
ተገሻሪ: የሚገሸር፡ ተቀማጭ።
ተገበ: (ጠገበ) - እንደጠገበ።
ተገበረ (ተጸብሐ)፡ ተሠራ፣ ታረሰ፣ ተዘመረ፣ ታረመ፣ ታጨደ። መምህራን ግን "ተገበረን" እንደ "ገበረ" ሠራ ብለው ይተረጉሙታል።
ተገበረ፡ ተቀረጠ፣ ተከፈለ፣ ተሰጠ ግብር።
ተገበረ፡ ተቀበለ፣ እጅ አደረገ፣ ወሰደ ሹሙ።
ተገበዘ: ግብዝና ተሾመ (ዝበዝ ሆነ)። ሌላ ትርጉም: ተደለዘ (ተመረገ፣ ተቀባ)፡ ሰነ (ተለቀለቀ፣ ተቀላቀለ)። ሌላ ትርጉም: ተከየ (ለገመ፣ ሰነፈ፣ ቸል አለ)፡ ዋሾ (ቀጣፊ፣ አታላይ) ሆነ።
ተገበየ፡ ተገዛ፡ ተለወጠ፡ ተሺጠ፡ ተሰዶ።
ተገበያየ፡ ተገዛዛ፡ ተለዋወጠ፡ ተሻሻጠ፡ ተቀባበለ፡
ተሰጣጠ።
ተገበደ: ተፈለጠ (ተተረተረ፣ ተሠነጠቀ)።
ተገበጠ: ተመታ፣ ተለየ፣ ተከመረ፣ ተከማቸ።
ተገቢ: የሚገባ። ምሳሌ: “ተገቢ ነገር”፣ “ተገቢ ሥራ” እንዲሉ።
ተገባ: መግባት ተቻለ። ሌላ ትርጉም (ደለወ): ሆነ (በጀ፣ ተመቸ፣ ተወደደ፣ ቀና)። ሌላ ትርጉም: በቃ (ተዘጋጀ)። ምሳሌ: “እከሌ ነፍስ መግደሉ ስለተመሰከረበት ለሞት ተገባ”። ሌላ ትርጉም: ተተካ (ተወከለ)።
ተገባበዘ: ተጠራራ፣ "ብላ፣ ጠጣ" ተባባለ፣ የግብዣ ብድር ተከፋፈለ፣ ተጐራረሰ።
ተገባባ: ተዳዳረ (ተዘማመደ፣ ተሰጣጠ)፡ ተደማመጠ (ተሰማማ)። ተረት: “ባይገባቡ በደጃፍ ይገቡ”።
ተገባዥ: የሚገበዝ (ግብዝ የሚሆን)።
ተገባደደ: ተዋገደ (ተቃረበ፣ ተዳረሰ)።
ተገብሮ፡ መሠራት፡ ሥራ አመል። "ተፈጥሮን ተገብሮ አይመልሰውም" እንዲሉ።
ተገብሮ፡ 'ን' የሌለበት ቃል፡ መደረግ። (ማስረጃ)፡ "አሞራውም በረረ፡ ቅሉም ተሰበረ"።
ተገብሮ)፡ ቦካ፣ ሖመጠጠ፣ ሸመጠረ፣ ወይም ተቈጣ (ለምሳሌ በማቴዎስ 13:33 ላይ እንደተጠቀሰው)።
ተገብቶ (ጥብ): ተተክቶ።
ተገተ: በፍርድ ቤት ተነጋገረ፣ ተከራከረ። (ተረት) "በኹለት በትትር አይማቱ፡ በኹለት ዳኛ አይገቱ"።
ተገተመ: ተቃመ፣ ተቻመ።
ተገተረ: ተሳበ፣ ተለጠጠ፣ ተወጠረ፣ ተወተረ (ሕዝ፵፩:፲፮:፳፮)። ቆመ፣ ተቀሰረ፣ ተደከረ። (ግጥም): "ብነግርሽ ብነግርሽ አታጠናቅሪ፣ እንደ ተርኪስ ባቡር ተገትረሽ ቅሪ"።
ተገተነ: ተነጨ፣ ተቦጨቀ፣ ተዘነተረ፡ ተበላ፣ ተዋጠ።
ተገተገ: (ተተገ) - እንደተተገ።
ተገተገ: ተጕለት፣ የአገር ስም፣ ጐለተ።
ተገተገተ: ተነከሰ፣ ታኘክ።
ተገታ (ተገትዐ): ተያዘ፣ ተወሰነ፣ ታገደ፣ ቆመ።
ተገታሪ: የሚገተር፡ ተለጣጭ፣ ተወጣሪ።
ተገታተረ: ተላሳበ፣ ተወጣጠረ።
ተገቺ: የሚገታ፡ አጥባቂ ያይደለ።
ተገነ: (ጸቈነ) - እንደጸቈነ።
ተገነበለ (ተገንጰለ)፡ ተገለበጠ፣ ተጋደመ።
ተገነኛኘ፡ ተቀራረበ፣ ተገጣጠመ፣ ተወሳሰበ፣ ተገናዘበ።
ተገነዘ (ተገንዘ)፡ ተከፈነ፣ ተሸፈነ፣ ተጠቀለለ፣ ለበሰ፣ ታሰረ፣ ተቋጠረ።
ተገነዘበ፡ ታሰበ፣ ታወሰ፣ ተጤነ፣ ልብ ተባለ፡ ልማዱ ግን ዐሰበ፣ አስታወሰ ነው።
ተገነደሰ፡ ተሰበረ፣ ወደቀ፣ ተጣለ፣ ተጋደመ (ግንዱ)፡ "እንደ ግንድ ተኛ" (ሰዉ)።
ተገነጠለ፡ ተሳበ፣ ተቈረጠ፣ ተበተነ፣ ተለየ፣ ተበላሸ።
ተገነጣጠለ፡ ተለያየ፣ ተበጣጠሰ፣ ተበታተነ፣ ተበለሻሸ።
ተገነፈለ፡ ገነፈለ።
ተገነፋ፡ "ነፋን" እይ።
ተገናኘ (ተራከበ)፡ ተቃረበ፣ ተያየ፣ ተዋወቀ፣ ተሳሳመ (ዘፍ፳፱:፲፩፣ ፴፩:፵፭)።
ተገናኘ፡ ተጋጠመ፣ ተጣመረ፣ ተያያዘ፣ ተዋሰበ፣ ተደረበ፣ አንድ ኾነ። (ግጥም)፡ "አንቺ ወዲያ ማዶ እኔ ወዲህ ማዶ፡ ኣንገናኝም ወይ ገደሉ ተንዶ"።
ተገናኘች፡ ላም ጥጃዋን አጠባች፡ ታለባች።
ተገናኝ፡ የሚገናኝ፣ ግጥሚያ (መግጠም) (አንድነት)፡ (በተገናኝ)፡ በመግጠም።
ተገናዘበ፡ ገንዘብ ለገንዘብ ተሰጣጠ፡ ተዋረሰ፣ ተወራረሰ፣ ተገናኘ፣ ተጣመረ፣ ተያያዘ፣ ተቋለፈ።
ተገናዛቢ፡ የሚገናዘብ፡ ተያያዥ፣ ሜንጦ አዝራር።
ተገናዥ፡ የሚገንዝ የሰው በድን (ሬሳ)።
ተገናጠለ፡ አንዱም አንዱም ገንጥሎ ሰብሮ ወሰደ፡ ተባጠሰ።
ተገኔ: የሰው ስም፣ "የኔ ተገን ማለት ነው።"
ተገን: (ጸቈን) - ጀጐል፣ ዐጥር፣ ቅጥር፣ ከለላ፣ በተን ውስጥ ያለ ሞቃት ስፍራ። "ዓለም ጥበብ ጨለማ ተገን እንዲሉ።"
ተገን: ግንብ፣ ከፍተኛ ምድር።
ተገንዛቢ፡ የሚገነዘብ፡ ታሳቢ፣ ዐሳቢ።
ተገንጣይ፡ የሚገነጠል (ዕንወት) (ሽጕጥ)።
ተገኘ (ተረክበ)፡ ተፈጠረ፣ ተወለደ፣ መነጨ፡ ተገለጠ፣ ታየ።
ተገኘ (ገኘ)ን ተገናኘ (ገነኘ)ን ይከተላል።
ተገኘ፡ መጣ፣ ቀረበ፡ ገባ፣ ታወቀ፣ ተረዳ (ኤር፲፩:፱፣ ፊልጵ፪:፰)። (ንጉሥ ባዳራሽ ተገኘ)፡ ግብር ለማብላት፣ ፍርድ ለመስጠት ባዳራሽ ተቀመጠ። (የት ተገኘኸ፣ ተገኘሽ)፡ የወንድና የሴት ስም።
ተገኘ ወርቅ፡ የሰው ስም።
ተገኛ: መጠጊያ፣ መከለያ፣ ተገን።
ተገኝ፡ የመጠሪያ ስም፡ "ልጅ ተገኘ" ማለት ነው።
ተገዘመ፡ ተናቀ፣ ተነቀፈ፡ ተሸነፈ፣ ተዋረደ፣ ተገዛ፣ ተገረዘዘ።
ተገዘረ (ተገዝረ)፡ ተገረዘ፣ ተቆረጠ፣ ተቀነጠበ።
ተገዘተ (ተወግዘ)፡ በቄስ ሥልጣን ተያዘ፣ ታሰረ፡ ተከለከለ፣ ተለየ። "ቃልዎ ይድረሰኝ፣ አላደረግሁም፣ ባደርግም አይለምደኝም" አለ፣ ማለ። "ተወገዘ፣ ራቀ"። (ተረት)፡ "የተገዘተች ነፍስ፡ የተለጐመች ፈረስ"።
ተገዘዘ (ተገዘ)፡ ተጀጐለ፣ ታጠረ፣ ተቀጠረ፣ ተጋረደ፣ ተከለለ። ትግሬም "ዘዘ" ብሎ በንጉሥ አለ አማጠነ፣ አዳኘ ይላልና፣ ከለለ ካለው ይገባል።
ተገዘገዘ (ተገዘ፣ ተገዝዐ፣ ተወሠረ)፡ ተከረከረ፣ ተመገዘ፣ ተከረከመ።
ተገዘገዘ፡ ደከመ፣ ሰለተ።
ተገዛ (ተገዝአ)፡ ተገበየ፣ ተሸመተ፡ ለገዢ ተሰጠ።
ተገዛ፡ ገበረ፣ ዜገ፡ ታዘዘ፣ ታዛዥ ሆነ (ሕዝ፳፱፡ ፳፣ ኤፌ፮፡ ፭፡ ፯)። "ሲገዙ ይገዙ" እንዲሉ።
ተገዛሪ፡ የሚገዘር።
ተገዛች፡ የሚገዝት፡ በክሕደት፣ በነውር የተጠረጠረ መናፍቅ፡ ወይም ሌላ ሰው።
ተገዛዘተ፡ ተዋገዘ፣ ተወጋገዘ፡ ተለያየ።
ተገዛዛ (ተጋዝአ)፡ ተገበያየ፣ ተሻሻጠ፣ ተለዋወጠ።
ተገዛገዘ፡ ተማገዘ።
ተገዥ (ዦች)፡ ገባር፣ ዜጋ፣ ቅኝ።
ተገዥነት፡ ገባርነት፣ ዜግነት፣ ቅኝነት።
ተገደለ (ተገድለ፣ ተቀትለ)፡ ተመታ፣ ተደበደበ፣ ተወጋ፣ ታረደ፣ ሞተ፣ ጠፋ፣ ወይም ዐለፈ (ማር፲፡ ፴፩)።
ተገደመ፡ ገዳም ሆነ፣ ለገዳም ተሰጠ፣ ወይም መስቀል ዞረበት።
ተገደረ (ገደረ)፡ ጡር፣ መስቃ ተናገረ፡ ሰደበ፣ ነቀፈ፣ ናቀ፣ አቀለለ፣ ተላገደ (አድራጊ)።
ተገደረ፡ መጻተኛ ሆነ፡ ተለገጠበት።
ተገደረ፡ ምስጋና ቢስ ሆነ፡ ተሰደበ፣ ተነቀፈ።
ተገደረ፡ ተቀጠለ፡ በላይ ወጣ፡ በቀለ።
ተገደረ፡ ዐጣ፣ ተቸገረ። (ተረት)፡ "ደግ አድራጊ አበደረ፡ ክፉ አድራጊ ተገደረ"።
ተገደበ፡ ኃደረ፣ ዕድሩ።
ተገደበ፡ ተከተረ፣ ተወሰነ፣ ተደለደለ፣ ታገደ (፪ነገ ፲፱:፳፬)።
ተገደደ፡ ግድ ተባለ፡ በግድ ታዘዘ።
ተገደገደ፡ ተተከለ፣ ቆመ፣ ተወጠረ። (ተረት)፡ "ሲገደገድ ያልበጀው፣ ሲዋቀር እሳት ፈጀው"።
ተገደፈ (ተገድፈ)፡ ተተወ፣ ተሻረ፣ ተፈሰከ፣ ተበላ፣ ተጣለ፣ ተዘለለ፣ ተረሳ፣ ጐደለ፣ ወደቀ፣ ቀረ፣ ወይም ጠፋ።
ተገዳሚ፡ የሚገደም ወይም ገዳም የሚሆን።
ተገዳቢ፡ የሚገደብ፡ ተከታሪ፣ ታጋጅ።
ተገዳይ፡ የሚገደል ወይም ተደብዳቢ።
ተገዳደለ፡ መላልሶ ተጋደለ ወይም ተላለቀ።
ተገዳደመ፡ ተገናኘ ወይም ተዋወቀ።
ተገዳደረ፡ ተጠቃቀሰ፣ ተነቃቀፈ።
ተገዳደረ፡ ተፈካከረ፣ ተወዳደረ፣ ተከራከረ፣ ተገተ፡ "እኔ እበልጥ፣ እኔ እበልጥ" ተባባለ፣ ተቀታተረ፣ ተቋቋመ።
ተገዳዳሪ (ሮች)፡ የሚገዳደር፣ ተቻቻይ፡ ተወዳዳሪ፣ ተፈካካሪ፣ ተቃዋሚ።
ተገዳጅ፡ የሚገደድ፣ ባሪያ፣ ገባር።
ተገድራ፡ በዛፍ ላይ የበቀለ፣ ብዙ ተቀጽላ፣ ጀፍጀፎ።
ተገድራ: በዛፍ ላይ የበቀለ ብዙ ተቀጽላ፣ ጀፍጀፎ” ። ቀ ለገ ጸ ለደ ለ ለረ እንደ ተለወጠ አስተውል” ።
ተገጠመ፡ ተዘጋ፣ ታተመ፣ ልክክ አለ፡ ታሸገ።
ተገጠመ፡ ተዘፈነ፡ ሆነ፣ ተደረገ (ግጥሙ)።
ተገጠበ፡ ተነካ፣ ቆሰለ፣ ተመለጠ፣ ተላጠ፣ ተላፈ፣ ተጋጠ።
ተገጠገጠ፡ በዝቶ ተሠራ ቤቱ፡ ተተከለ ድንኳኑ።
ተገጠገጠ፡ ተቀጠቀጠ፡ ተላጠ፣ ተለጠ፡ ተመነጠረ።
ተገጠጠ፡ በመጥሌ ገጽ ታየ፡ ክፉ ተባለ፡ ፊት ዐጣ።
ተገጣሚ፡ የሚገጠም፡ ተዘጊ።
ተገጣበረ፡ ተናቀ፣ ተነቀፈ፣ ተሰደበ፡ ተዋረደ፣ ተገጠጠ።
ተገጣጠመ፡ ተቀናበረ፣ ተቀነባበረ፡ ተከናወነ፣ ተከነዋወነ፡ ተገናዘበ፣ ተገነዛዘበ።
ተገጣጠበ፡ ተቋሰለ፣ ተላላጠ፣ ተመላለጠ።
ተገጣጣሚ፡ የሚገጣጠም፡ ተቀናባሪ፣ ተከናዋኝ፣ ተገናዛቢ።
ተገጨ፡ ተመታ፣ ተለተመ፡ ተኰረኰመ።
ተገጨረ፡ ተቋፈ፡ ቀስ ብሎ ኼደ።
ተገጨረ፡ ተደነሰረ፣ ተጐበለ። "በመካከል ተገጭሮ" ትርጓሜ ሕዝቅኤል (ገጽ፡ ፫)።
ተገፈተ፡ ተገፈፈ፣ ተቀመሰ፣ ተጠጣ፣ ተዠመረ።
ተገፈተረ፡ ተገፋ።
ተገፈፈ፡ ተሠነተረ፣ ተሰነዘረ፣ ተለየ፣ ተገለለ፣ ተነሣ፣ ተላጨ፡ ልብሱን ተቀማ፣ ተራቈተ (ኤር፲፫:፳፪)።
ተገፊ፡ የሚገፋ ሰው (ወተት)።
ተገፋ (ተገፍዐ)፡ ዕልፍ አለ፡ ቦታውን ለቀቀ።
ተገፋ፡ ተበደለ፡ ግፍ ተቀበለ።
ተገፋ፡ ተናጠ፣ ተወዘወዘ። "ለቀቀ" ብለኸ "ለቃቃን" እይ።
ተገፋተረ፡ ተጋፋ።
ተገፋፊ፡ የሚገፈፍ።
ተገፋፋ (ተጋፍዐ)፡ ግፍ ተቀባበለ።
ተጕለቴ (ቶች)፡ የተጕለት ሰው።
ተጕለቴ፡ የተጕለት ዜማ።
ተጕለት፡ ያገር ስም፡ ለመልከኛ፣ ለባለል የተሰጠ አገር (በወግዳ ሰሜን ያለ)።
ተጕለት: ያገር ስም፡ ጐለተ ።
ተጕላላ፡ ተራበ፣ ተጠማ፡ ተጐዳ፣ ተቸገረ፡ ጕልሕ መከራ ተቀበለ፡ ተንቃቃ፣ ተበደለ።
ተጕላላ፡ ወጣ፣ ወረደ። "ሳር እሥቃለኹ እንደ ማሽላ፣ ነገር በሆዴ እየተጕላላ" (ክራር መቺ)።
ተጕላላ: ተንገላታ፡ ጐላ ።
ተጕመተመተ፡ ተድረመረመ።
ተጕመጠመጠ፡ ታጠበ፣ ጠዳ (ልማዱ ግን "ዐጠበ" ነው)።
ተጕመጥማጭ፡ የሚጕመጠመጥ፡ በሽተኛ፣ ኮሶኛ።
ተጕማማ፡ በስውር፣ በድብቅ ተወራ፣ ተነገረ።
ተጕማማ: ውስጥ ለውስጥ ተወራ (ጐማ)።
ተጕረመረመ: ተድረመረመ፣ ተቈጣ፣ ወፈረ።
ተጕረምራሚ: የሚጕረመረም፡ ቍጡ።
ተጕረፈረፈ: ተዝረከረከ፣ ተዝረፍረፈ፡ ተጣለ፣ ወደቀ።
ተጕደፈደፈ፡ የጐደፈ ድርብ፡ ተኵለፈለፈ።
ተጊ: የሚተጋ፣ የሚያስብ፣ ተጣጣሪ።
ተጊያጊያጠ፡ ተላበሰ፣ ተሸላለመ፣ ተሰማመረ።
ተጋ: (ተግሀ) - እንደተጋ።
ተጋለለ፡ ተለያየ፣ ተራራቀ።
ተጋለበ፡ ሆነ፣ ተደረገ (ግልቢያው)፡ በፈረስ ተሮጠ (ሜዳው)።
ተጋለበ፡ ተጋለጠ፣ ተራቆተ።
ተጋለጠ፡ ኀፍረቱ ታየ፡ ተዋረደ፡ ብቻውን ኾነ፡ ተጋለበ፣ ተራቈተ፡ አባት፣ እናት፣ ሚስት ሞቱበት፡ አደባባይ ዋለ፡ ደረቱን ጣለ።
ተጋመሰ፡ ተካፈለ፣ ተጋራ፡ ተፈናከተ፡ እኩሌታ ኾነ።
ተጋመጠ፡ ተናከሰ፣ ተዘናተረ፣ ተባላ (ገመጠ)።
ተጋማ፡ ተበሳበሰ፣ ተበለሻሸ።
ተጋማጭ፡ የተጋመጠ፣ የሚጋመጥ፡ ተናካሽ (ነካሽ) ጋማ ከብት።
ተጋሰሰ: ተዳፈረ።
ተጋረደ (ተንጦልዐ): ተጣለ፣ ተዘረጋ፣ ተለቀቀ (መጋረጃው)።
ተጋረደ: ተከለለ፣ ተጠለለ፣ ተሰወረ፡ ተመከተ (ሰዉ ቤቱ)።
ተጋረጠ: ተሰካ፣ ተተከለ (ጋሬጣው)፡ ተፈቃ፣ ተበጣ (ግንባሩ)።
ተጋረፈ: ተማታ፣ ተቈናደደ፣ ተለቋጠ፣ ተሸማተረ (ገረፈ)።
ተጋረፈው: ምች መታው፡ አሳከከ፣ ኣሳበጠው፣ አቈሰለው።
ተጋሪ: የሚጋራ፣ ተፋላሚ።
ተጋራ: ተካፈለ፣ ተካፍሎ ወሰደ፡ ተፋለመ። "ይህን ዕንጨት ባትጋራኝ" እንዲል።
ተጋራ: ተዳረሰ።
ተጋራጅ: የሚጋረድ (መንበር፣ ዕልፍኝ፣ ግምጃ)።
ተጋራጭ: የሚጋረጥ፡ ተፈቂ።
ተጋበሰ፡ ተሰበሰበ፣ ተከማቸ።
ተጋበዘ: ተጠራ (በላ፣ ጠጣ፣ ተመገበ)። ሌላ ትርጉም: "ሰውን ልምታ፣ ልደብድብ" አለ፡ ተከለከለ።
ተጋቢ: የሚጋባ፡ ተላላፊ (ዕመም)።
ተጋባ (ተጋብአ): ተዛመደ፡ ተዳረ (ለሚስት ተሰጠ)፡ ባል ሆነ (ሉቃስ ፲፯፥፳፯)። ሌላ ትርጉም: ተገለበጠ (ተዛወረ፣ ተላለፈ)፡ ባዶ ሆነ።
ተጋባች: ተዳረች (ሚስት ሆነች) (ኢሳይያስ ፷፪፥፬)።
ተጋባዥ (ዦች): የሚጋበዝ፡ በዪ (በላተኛ)።
ተጋቦት (ተጋብኦት): መዛወር (ማለፍ)፡ የበሽታና የሌላውም።
ተጋተ (ተግዕተ): በጥርኝ ጠጣ፣ ተጐነጨ።
ተጋች: የሚጋት (ሕፃን፣ በሽተኛ)።
ተጋነነ፡ ተከባበረ፣ ተመሰጋገነ፣ ተባዛ።
ተጋኘ፡ የፀሓይ ሙቀት፣ የነፋስ ግጭት፣ ኀይል፣ ቅዝቃዜ እሰው አካል ተጋባ፣ ተናኘ።
ተጋኝ: የተገነ፣ የሚተግን፣ ጀጓይ።
ተጋዘ (ተግዕዘ)፡ ተወሰደ፣ መጣ።
ተጋዘ (ተግእዘ)፡ ተጠላ፣ ተነቀፈ፣ ተሻረ፣ ተዋረደ፣ ታሰረ፣ ተቀጣ።
ተጋዛ፡ ተጠመነ፡ የሰውን መሬት በርቦ አፍሳሽነት ወይም በጕልበት በእኩል ዐራሽነት ተዋዋለ።
ተጋዢ (ዦች)፡ ተጠማኝ፣ የሰው ምድር ዐራሽ።
ተጋዢነት፡ ተጠማኝነት፡ ርቦ አፍሳሽነት።
ተጋዥ፡ የሚጋዝ፣ የሚወሰድ፣ የሚታሰር።
ተጋደለ (ተጋደለ፣ ተቃተለ)፡ ተሳለፈ፣ ተጋጠመ፣ ታገለ፣ ተናነቀ፣ ተዋጋ፣ ወይም ተተረተረ (ሉቃ፲፫፡ ፳፬)።
ተጋደመ፡ አግድም ተኛ፣ ተዘረረ፣ ወይም ወደቀ (፩ሳሙ ፲፱፡ ፳፬)።
ተጋደመ: ተዘረጋ፣ ተዘረረ፣ ጐኑ ምድር ነካ (፩ኛ ሳሙኤል፡ ፫፡ ፱። ፩ኛ ነገሥት፡ ፲፱፡ ፭፡ ፮)።
ተጋደረ (ገደረ)፡ አላገጠ፣ አፈዘዘ (ማር ፲፬፡ ፴፫)።
ተጋደደ፡ ለጊዜው ተበደረ፣ ተዋሰ።
ተጋደደ፡ ተጣመመ፣ ተጠማዘዘ። "በሮቹ ሊዋጉ ተጋደዋል"።
ተጋደደ፡ ታየ፣ ተጣባ። "ኮሶ ተጋደደው" እንዲሉ።
ተጋደደ: ተደባበቀ፣ ተካለለ።
ተጋዳ፡ ታሰረ፣ ተወደረ፡ ታገደ፣ ተከለከለ።
ተጋዳሚ፡ የሚጋደም ወይም የሚተኛ።
ተጋዳይ (ተጋዳሊ፣ ተቃታሊ)፡ የተጋደለ፣ የሚጋደል፣ ጦረኛ፣ ሐርበኛ፣ ሰልፈኛ፣ ተዋጊ፣ የጦር ገበሬ፣ ሰማዕት፣ ወይም ጻድቅ። (ተረት)፡ "አልሞት ባይ ተጋዳይ"።
ተጋዳዮች፡ የተጋደሉ ወይም የሚጋደሉ (ኢሳ፴፬፡ ፫)።
ተጋገሠ (ተዓገሠ): ተቻቻለ፡ ዝም ተባባለ፡ እንዳላየ፣ እንዳልሰማ ተኳዃነ።
ተጋገረ፡ በሰለ (እንጀራው፣ ዳቦው)፣ ረጋ፣ ጠና (በረዶው፣ ውርጩ፣ ዐመዳዩ)።
ተጋገረ፡ ዝም አለ፡ ሳይናገር ቀረ።
ተጋገተ (ተዓገተ): ተካሰበ፡ ተያያዘ (ዕግትን)።
ተጋገዘ (ተሓገዘ): ተቀባበለ፡ ተረዳዳ፡ ተፈራረቀ፡ ተራረፈ።
ተጋጋለ፡ ብርቱ ጥል ተጣላ፣ ተፋጀ፡ ተነሣሣ።
ተጋጋለ፡ ተጋጋመ፣ ተቃጠለ።
ተጋጋመ፡ ተፋፋመ፣ ተጋጋለ፣ ተቀጣጠለ፣ ተላላበ (እሳቱ፣ ጠቡ፣ ጦርነቱ)።
ተጋጋሪ፡ የሚጋገር፣ የሚረጋ ሊጥ።
ተጋጋዥ (ተሓጋዚ): የተጋገዘ፡ የሚተጋገዝ፡ የሚረዳዳ፡ ተቀባባይ።
ተጋጠ (ተግሕጸ)፡ ተላጠ፣ ተመለጠ፣ ተነጨ፣ ተገጠበ፣ ተበላ፣ ታማ።
ተጋጠመ፡ ተቃረበ፣ ተገናኘ፣ ተሳካ፣ ተዋደደ፣ ተሰማማ፣ ተያያዘ (የጠባይ፣ የግብር፣ የክፉና የበጎ)።
ተጋጠመ፡ ተጣላ፣ ተዋጋ (የበሬ፣ የጦረኛ) (ዘዳ፩፡ ፵፬)።
ተጋጠጠ፡ ተቆረጠ፣ ተገፈፈ፣ ተጠረገ፣ ተደደ፣ ተማጠጠ።
ተጋጣሚ፡ የተጋጠመ፣ የተገናኘ፡ የሚጋጠም፣ የሚገናኝ፡ ተቃራቢ፣ ተገናኝ።
ተጋጨ፡ ተጣላ፣ ተላተመ፣ ተተማተመ፡ ጥቂት ጦርነት አደረገ (ኢሳ፶፱፡ ፲፣ ሕዝ፫፡ ፲፫)።
ተጋጪ፡ የሚጋጭ (ድንጋይ፣ ብረት)።
ተጋጭ፡ የሚጋጥ ዐጥንት።
ተጋፈ (ተግሕፈ)፡ ታፈሠ፣ ተጠረገ፣ ተጠጣ።
ተጋፈጠ፡ ቀረበ፣ ገባ (ሰዉ ከጦርነት)።
ተጋፈጠና አጋፈጠ፡ ተደራራጊና አደራራጊ ሲመስሉ (ሲኾኑ) ስለ ልማድ በተደራጊነትና ባድራጊነት መፈታታቸውን አስተውል፡ ይኸውም "ገፈጠና (ጋፈጠ)" ስላልተለመዱ ነው።
ተጋፈፈ፡ (ልብስን ተቃማ፡ ገፈፈ)።
ተጋፈፈ (ተደራራጊ)፡ ልብስን ተቃማ፣ ተዋሸመ።
ተጋፈፈ (ተደራጊ)፡ ታጨደ፣ ተጠረገ፣ ተሰባሰበ፣ ተያዘ (ገርሣው፣ ልሻው፣ ዘኬው፣ ዓሣው)።
ተጋፊ (ዎች)፡ የሚጋፋ፡ ኀይለኛ። በልማድም፡ "ገፊ" ተብሎ ይተረጐማል።
ተጋፋ (ተጋፍዐ)፡ ግፍ ተሣራ፣ ተባደለ፡ ተዳፈረ (ሚል፫:፰)።
ተጋፋ፡ ተጣበበ፣ ተነቀ።
ተጋፋ፡ ገፋ (ዘሌ፲፱:፴፫)።
ተጋፋጭ፡ የሚጋፈጥ፡ ተማች፣ ተዋጊ፣ አይፈር፣ ለፊቱ ጐበዝ።
ተጋፍቼ፡ የጋን ማቶት ጠላ ሲቀዱ ጋኑን የሚገፉበት (ዐሸት የሚያደርጉበት)።
ተጌጠ፡ ተሸለመ፣ ተሽኰነተረ፣ አማረ (ሰውየው)። "ጌጠኛ ሆነ፣ ተለበሰ" (ልብሱ)።
ተግ ቦግ ብል: ቆም።
ተግ ተግ አለ: ቦግ ቦግ አለ።
ተግ፣ ቱግቦግ: ተገተገ።
ተግ አለ: ቦግ አለ፣ በራ ቆመ።
ተግለበለበ፡ ፈጥኖ ቶሎ ቶሎ ነደደ፡ ተወዘወዘ፡ ዕጥፍ ዘርጋ አለ።
ተግመነመነ፡ የገመነ ድርብ፡ ተትከነከነ፣ ተናደደ።
ተግማማ፡ የገማ ድርብ፡ መላልሶ ገማ።
ተግሣጽ፡ ዘለፋ፣ ቍጣ፡ የምክር ኀይለ ቃል (ቅጣት)።
ተግበሰበሰ፡ ተጐተተ፡ ተክበሰበሰ፡ ታቦትኛ ኼደ።
ተግበሰበሰ፡ የተጋበሰ ድርብ፡ በጅጉ ተሰበሰበ።
ተግባረ ሥጋ፡ ሥጋዊ ሥራ፡ እርሻ፣ ቍፋሮ፣ ጸናጽል፣ ከበሮ፣ ውሃ ዋና፣ ሰንጠረዥ፣ በገና፣ ፈረስ ግልቢያ፣ ጥፈት፣ ድጕሰት፣ ንግድ፣ የመሰለው ሁሉ.
ተግባረ ነፍስ፡ የነፍስ ሥራ፡ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ ፍቅር፣ ትሕትና፣ ትዕግሥት፣ ምጽዋት፣ የመሰለው ሁሉ.
ተግባረ እድ፡ የእጅ ሥራ።
ተግባረ ፈት፡ ሥራ ፈት፣ ሰነፍ፣ ማጋጣ፣ ምናውዬ፣ በዋል ፈሰስ (ምሳ፳፮:፲፮)።
ተግባር፡ ሥጋዊና መንፈሳዊ ሥራ።
ተግባባ: ተስማማ፡ ነገርን ተቀባበለ።
ተግብ ኾነ: ቀዘቀዘ፣ በረደ፣ ተጫነ፣ ከበደ (ክረምቱ)።
ተግብ: ነፋስና ብርድ፣ ውሽንፍር ያለው ወሊስ ዐፈና።
ተግተለተለ: ተያያዘ፣ ተቅጠለጠለ፣ ተሳሳበ።
ተግተመተመ: ተምታታ፣ ተገላተመ፣ ተጋጨ (ሰው ከዕቃ ጋራ)።
ተግተረተረ: የተገተረ ድርብ፡ ተውተረተረ፣ ተንገደገደ። "እንቅፋት መታኝና ልወድቅ ተግተርትሬ ዳንኹ"።
ተግተርታሪ: የሚግተረተር፡ ተንገድጋጅ።
ተግታ: ቦግታ፣ መቆም።
ተግታ: ተገተገ።
ተግታጊ: የተተ፣ የሢተትግ፣ ገራፊ።
ተግዠለዠለ፡ ረዘመ፣ ተሳበ፣ ተጐተተ።
ተግደረደረ፡ ኰራ፣ ታበየ፣ ተግበዘዘ፡ ሳይኖረው ያለው መሰለ፡ ባፍ፣ በልብስ ከበረ። ሲፈልግ "አልፈልግም" አለ፣ ወላወለ። (ተረት)፡ "ስትግደረደሪ፡ እምሽን እንዳታድሪ"።
ተግደርዳሪ (ሮች)፡ የሚግደረደር፣ ያለው መስሎ የሚታይ፣ "ከማን አንሼ"። (ተረት)፡ "ቀን በበቅሎ፡ ማታ ቈሎ (ይቀመጣል ይቈረጥማል)" ማለት ነው። "ተግደርዳሪ ጦም ዐዳሪ" እንዲሉ።
ተግደርዳሪነት፡ ኵራት፣ ኵሩነት፣ ግብዝነት።
ተግዳሮት፡ በዋሉት ውለታ ሰው መውቀስ።
ተግዳሮት፡ ትቢት፣ ኵራት፣ ጡር፣ ሽሙጥ፣ ቅጥጥብ፡ ለግጥ ለግድ ስድብ፣ ውርደት።
ተግጀለጀለ፡ ተጐተተ።
ተግፈለፈለ፡ ጨዋታ አበዛ።
ተግፈለፈለ፡ ፈላ፣ በሰለ፣ ተሠራ።
ተግፈጠፈጠ፡ ጨሰ፣ ተጫሰ፣ ነደደ።
ተጐለለ፡ ተሠራ፣ ተጫነ (በላይ ኾነ ጕልላቱ)፡ ዐለቀ፣ ተፈጸመ (ክዳኑ)።
ተጐለመ፡ ተከፈለ፣ ተቈረጠ፣ ተሰጠ።
ተጐለሰሰ፡ ተሸነፈ፣ ደከመ፣ ተጨቈነ፡ ዐውቆ በቀላል ወደቀ (ከድካም የተነሣ)።
ተጐለበ፡ ተለበደ፣ ተጠፈረ፣ ተሸፈነ፣ ተለጐመ።
ተጐለበ፡ ተጠረጠረ (አሹቁ፣ ሽንብራው)።
ተጐለተ፡ ቆመ፣ ተጠመዘዘ፣ ተተከለ፡ ተከለለ፡ ተሰጠ፡ ተቀመጠ፣ ተረፈቀ።
ተጐለደመ፡ ተናጋ፣ ተለየ፣ ታጠፈ፡ ፈነገጠ፣ ወጣ።
ተጐለጐለ፡ ተቈነጫ፣ ተለቀመ።
ተጐለጐለ፡ ተናደ፣ ተፈታ፣ ተተረተረ፣ ተበላሸ።
ተጐለጐለ፡ ወጣ፣ ተዘረገፈ። "አርዮስ አንዠቱ፣ ንስጥሮስ ምላሱ ተጐልጕሎ ሞተ"።
ተጐለጐለ፡ ፈጠጠ፣ ጐረጠ።
ተጐለጐለ)፡ የተጣመመ፣ የተጣበበ፣ የተመታተረ፣ የጣጣለፈ።
ተጐለፈጠ፡ ተጐለፈፈ።
ተጐለፈፈ፡ ተጐለሰሰ።
ተጐላመሰ፡ ተዳራ፣ ተበራታ፣ ተቃበጠ።
ተጐላቢ፡ የሚጐለብ፡ ተለባጅ።
ተጐላች፡ የሚጐለት (መሬት)።
ተጐላይ፡ የሚጐለል (የቤት ቍንጮ)።
ተጐላጐለ፡ ተዋጣ፣ ተዘካዘከ። "እከሌና እከሌ ጕድ ለጕድ ተጐላጐሉ"።
ተጐላጐለ፡ ተፋጠጠ፣ ተጓረጠ።
ተጐመረ፡ ተነፋ፣ ዐበጠ፣ ክምር መሰለ፡ ኰራ።
ተጐመተ፡ ተጐመደ፣ ተቈረጠ፣ ተከፈለ።
ተጐመደ፡ ተቈረጠ፣ ተበጠሰ፣ ተሰለበ።
ተጐማለለ፡ ተቈነነ፣ ተኰፋነነ፡ የኵራት ርምጃ ተራመደ።
ተጐማለለ: ተቈነነ ጐመለለ ።
ተጐማመደ፡ ተቈራረጠ፣ ተበጣጠሰ።
ተጐማሪ፡ የሚጐመር፣ የሚነፋ፣ የሚያብጥ፣ የሚኰራ።
ተጐማጅ፡ የሚጐመድ፡ ተቈራጭ።
ተጐሰመ: ተመታ፡ ታወከ፣ እህ አለ (ዐዘነ)።
ተጐሰረ: መላ፣ ተጠቀጠቀ፣ ታመቀ፣ ተነፋ፣ ተወጠረ፣ ተከረበ።
ተጐሰጐሰ: ተጐረሠ፣ ተበላ፣ ተጠቀጠቀ፣ ገባ፣ ተከተተ።
ተጐሳቈለ (ጐሰቈለ): ተዋረደ፡ የቀይ ጥቍር፣ የረዥም ዐጪር፣ የወፍራም ቀጪን ኾነ፡ ከቈሉበት፡ የጋፉበት መሰለ፡ ተጣቈረ።
ተጐረመመ: ተቈረጠ፣ ተፎነነ።
ተጐረመደ: ተገመሰ፣ ተቈረሰ፣ ተቈረጠ፣ ተፈተተ።
ተጐረሠ: ተበላ፣ ምግብ ኾነ፡ ተከረተፈ፣ ተሸመሸመ፣ ተፈጨ።
ተጐረበጠ: ተነካ፣ ተቈረቈረ።
ተጐረተ: ተጐራ፣ ተከመረ።
ተጐረደ: ቀረ፣ ታጣ፣ ተዋጠ፡ አልተነገረም (ፊደሉ)።
ተጐረደ: ተጐመደ፣ ተቈረጠ፣ ተሰበረ፣ ተጐነደበ፣ ዐጠረ፡ ተቀየደ፣ ተከፈለ፡ ተፈተገ። "በውስጥ እግሬ እሾኽ ተጐረደብኝ (ተሰበረብኝ)"።
ተጐረደመ: ተቈረጠመ፣ ተሸረደመ።
ተጐረጐመ: ወለቀ፣ ተነቀለ።
ተጐረጐረ: ተኰረኰረ፣ ተበረበረ፣ ተጓጐጠ፣ ተሻ፣ ተፈለገ።
ተጐረፈ: ጐረፈ።
ተጐራ: ተሰበሰበ፣ ተከማቸ፣ ተከመረ፣ ተነባበረ፣ ተደራረበ፣ ተቈለለ።
ተጐራረሠ: ተመጋገበ፡ ጕርሻ ተመላለሰ።
ተጐራረደ: ተቈራረጠ፣ ተበጣጠሰ።
ተጎራበተ: ተደራጊና ተደራራጊ፡ አጎራበተ አድራጊና አደራራጊ መኾኑ ሥርወ ቀለሙን ሳይለውጥ መካከሉ "ራብዕ" ስለ ኾነ ነው።
ተጎራባች: የሚጎራበት።
ተጐራጅ: የሚጐረድ፡ ተቈራጭ።
ተጐራጐረ: ተፋተሸ፣ ተበራበረ።
ተጐርጓሪ: የሚጐረጐር፡ ተፈታሽ።
ተጐሸመ: ተደሰቀ፣ ተደሰመ፣ ተጐጐመ።
ተጐሸመጠ: ተነካ፣ ተጐነጠ።
ተጐሻመጠ: ተናካ፣ ተጓነጠ፣ ተናጠበ።
ተጐበለ፡ ቍጭ፡ አለ፡ ተቀመጠ።
ተጐበኘ፡ ታወቀ፣ ታየ፣ ተፈቀደ፣ ተሰለለ።
ተጐበኛኘ፡ ተጠያየቀ፣ ተፈቃቀደ።
ተጐበጐበ: ተጌጠ፣ ተሸለመ፣ ተደጐሰ። ሌላ ትርጉም: በቡጢ ወይም በጕሽም ተመታ። ሌላ ትርጉም: በቡሖው አብሲት ተመረበት።
ተጐባ: ተደገፈ (ተገፋ፣ ተነሣ)። ሌላ ትርጉም: ጕቦ ተቀበለ (ተበሰተ፣ በላ)።
ተጐባ: ተደገፈ፣ ተገፋ፣ ተነሣ። ሌላ ትርጉም: ጕቦ ተቀበለ፣ ተበሰተ፣ በላ።
ተጐባባ: ተሰጣጠ፣ ተቀባበለ (ጕቦን)፣ በጕቦ ተረዳዳ፣ ተደጋጋፈ።
ተጐባኘ፡ ተፋቀደ፣ ተሳለለ።
ተጐባጐበ: በቡጢ ተማታ፣ ተጓሸመ።
ተጐብኚ፡ የሚጐበኝ፣ ተሰላይ።
ተጐተተ: ተሳበ፣ በደረት፣ በልብ ኼደ፡ ምድር አበሰ፣ አዘገመ (ምሳ፯:፳፪)። ረዘመ፡ ተጠራ፣ ቀረበ።
ተጐተጐተ: ተነቀነቀ፣ ተጣደፈ፣ ተወተወተ።
ተጐታች: የሚጐተት፡ ተሳቢ።
ተጐታጐተ: ተቻኰለ፣ ተነዛነዘ፣ ተዘበዘበ።
ተጐቸ: ተከመረ፣ ተዘመመ፣ ተቈለለ።
ተጐነበሰ፡ ጐነበሰ፣ ሰገደ (ዘፍ፵፫:፳፰፣ ዳን፰:፲፰፣ ማር፩:፯፣ ፊልጵ፪:፲)።
ተጐነደለ፡ ተነደለ፣ ተቀደደ፣ ተሰነጋ፣ ተኰላሸ፣ ተበጠሰ።
ተጐነደበ፡ ተጐረደ፣ ተጐመደ፣ ተቈረጠ።
ተጐነዳደበ፡ ተጐራረደ፣ ተቈራረጠ።
ተጐነጐነ፡ ተታታ፣ ተቈነነ፣ ተጠመረ፡ ዕጥፍ ድርብ ኾነ (ዘፀ፳፯:፬)።
ተጐነጐነ፡ ተደፈደፈ፡ ተለወሰ፣ ተዋዋደ።
ተጐነጠ፡ ተደፈረ፣ ተነካ፣ ተገፋ፣ ተነቀነቀ።
ተጐነጨ፡ በጕንጭ ተያዘ፣ ተጠጣ። ልማዱ ግን "ያዘ"፣ "ጠጣ" ነው፡ "በተ" የሚነሣ ያ፬ ፊደል ግስ ተደራጊነት እንጂ አድራጊነት እንደሌለው አልተመረመረም። "ገረመንና ደመመን"፣ "ደነቀን" እይ።
ተጐነጨፈ፡ ተዠመገገ።
ተጐነፈ፡ ታጠበ፣ ታጀለ፡ ተቀረጸ፣ ተደጐሰ።
ተጐናበሰ፡ ታረቀ፣ ተራረቀ፡ ይቅር ተባባለ፣ ተሰማማ።
ተጐናባሽ፡ የሚጐናበስ፡ ታራቂ።
ተጐናተረ፡ ተቈናጠረ፣ ተበሳጨ፣ ተቈጣ።
ተጐናነበ፡ ተከናነበ፣ ተጐናጸፈ፣ ተጀቦነ (በላይ፣ በታች ለበሰ)።
ተጐናዘለ፡ ተቈላዘመ፣ ተዘናፈለ፣ ተመሳቀለ፡ ተጠጋጋ (ሰብል በነፋስ)።
ተጐናጣፊ፡ የሚጐናጠፍ (ቄስ) (ታቦት)።
ተጐናጸፈ፡ የካህናት፡ ተጐናጠፈ የሕዝብ ነው።
ተጐናፊ፡ የሚጐነፍ፣ የሚታጀል፣ የሚደጐስ።
ተጐንጓኝ፡ የሚጐነጐን (ልጥ፣ ሐር) (የመሰለው ኹሉ)።
ተጐኘረ፡ ተመላ፣ ታጨቀ፣ ተጐሰረ።
ተጎዘመ፡ ተቆረጠ፣ ተከፈለ፡ ታመመ (ሥራው፣ ዐጨዳው)።
ተጐዘጐዘ፡ ተበተነ፣ ተመነዘረ፣ ተነሰነሰ፣ ተመቻቸ፣ ተነጠፈ (ሣሩ፣ ቅጠሉ)። ተቀመጠ (ሰው)።
ተጐዛጐዘ፡ ተደላደለ፣ ተሸራሸ።
ተጐዝጓዥ፡ የሚጐዘጕዝ፣ ተበታኝ፣ ቀጤማ።
ተጐደበ፡ ተማሰ፣ ተቈፈረ፣ ተቈረጠ፣ ታረደ፣ ጐያጐደ።
ተጐደጐደ፡ ገባ፣ ተከተተ፣ ተረገረገ፣ ተቀበረ።
ተጐደፈረ (ተጐጽፈረ)፡ ተጫረ፣ ተመነቀረ፣ ተማሰ፣ ተቈፈረ፡ ተዛቀ፣ ተበተነ።
ተጐዳ (ተጐድዐ)፡ ተመታ፣ ተሰበረ።
ተጐዳ፡ በዋጋ ተበለጠ።
ተጐዳ፡ ዐጣ። "እከሌ ልጁን ተጐዳ" እንዲሉ።
ተጐዳ፡ ከሳ፣ ተጠነ፣ መነመነ፡ ወፍራም ቀጭን ኾነ (ምሳ፳፪:፫)።
ተጎዳሪ፡ አላጋጭ፣ ነቃፊ።
ተጐዳቢ፡ የሚጐደብ፣ ተቈፋሪ።
ተጐዳኘ (ጐደኘ)፡ ተጓዘ፣ አገለለ፣ ከመንገድ ወጣ፣ ተለየ፣ ስፍራ ለወጠ፣ ተዛወረ፣ ራቀ፣ ወይም ተወገደ። በተጨማሪም ወደ ቤት ገባ ወይም ጐራ አለ።
ተጐዳዳ፡ ተሰዳደለ።
ተጐጂ፡ የሚጐዳ፣ የሚርበው፣ የሚጠማው፣ የሚቸግረው።
ተጐጂነት፡ ራብተኛነት፣ ችጋረኛነት።
ተጐጐመ፡ ተለተመ፣ ተወጋ።
ተጐጠረ፡ ተጐሰረ፣ ተወጠረ።
ተጐጠጐጠ፡ ተመዘዘ፣ ተነቀለ።
ተጐጠጐጠ፡ ተወጋ፣ ወጣ፣ ተቦጠቦጠ።
ተጐፈጨረ፡ ተጨቈነ፡ ተጫረ፣ ተወረ።
ተጓመተ፡ ተቋረጠ፣ ተካፈለ።
ተጓመደ፡ በዱላ ተማታ፣ ተደባደበ።
ተጓመደ፡ ተጓረደ፣ ተሳለበ።
ተጓረሠ: መብል ተሰጣጠ፡ ባፍ ተቀባበለ። (ቈሎ አንጓረሥ): አንቃለድ፣ አንዳለል።
ተጓረበ: ተራገበ፣ ተጨማደደ።
ተጓረደ: ተቋረጠ፡ በዱላ ተማታ።
ተጓረጠ: ተፋጠጠ፣ ተሞጫጨረ።
ተጓሸመ: ተዳሰቀ፣ ተዳሰመ።
ተጓበጠ: ተቃለሰ፣ ተዛባ።
ተጓተተ: ተሳሳበ፣ ተዋሰደ።
ተጓታች: የተጓተተ፣ የሚጓተት፡ ተሳሳቢ።
ተጓዘ (ግዕዘ)፡ ዘገመ፣ ዝግ ብሎ ኼደ።
ተጓዥ፡ የሚጓዝ፡ ዘምተኛ፣ መንገደኛ፣ ቤተሰብ።
ተጓደለ፡ ተናነሰ፣ ተቀናነሰ፣ ቆመ፣ ወይም ተቋረጠ።
ተጓደነ (ጓደነ)፡ ተጓዪነ ወይም ዘላን ሆነ። ሥሩ ጐደነ ነው።
ተጓደደ፡ "ካለ ጓዴ" አለ፡ በጓደኛው ተመካ።
ተጓደደ (ጓደደ)፡ ኰራ፣ ተደገገ፣ ታበየ፣ ታጀረ (ዘኍ፲፭:፴፣ ዘዳ፰:፲፬፣ ኢሳ፲:፲፭፣ ሮሜ፪:፳፫)።
ተጓደፈ፡ ተዳደፈ፣ ተቋሸሸ፡ ተራከሰ፡ ጕድፋም ተኳዃነ። "መሬቱና ፍጉ ተባላ"።
ተጓዳ (ተጓድዐ)፡ ተባደለ።
ተጓዳኝ፡ የሚጓደን ወይም ተዘላኝ።
ተጓዳጅ፡ የሚጓደድ፣ ኵሩ፣ ተደጋጊ (ምሳ፳፩:፳፬)።
ተጓዳጆች፡ የሚጓደዱ፡ ተደጋጎች (ሮሜ፩:፴)።
ተጓጐለ (ተሃጐለ): ተጣፋ፣ ተጠፋፋ፣ ተሰናከለ፣ ተሰነካከለ (፪ኛ ዜና ፲፮፥፭)።
ተጓጐጠ፡ ተወጋ፣ ተሸቀሸቀ፣ ተቈሰቈሰ።
ተጓጓዘ (ተጋዐዘ)፡ ተዛገመ፣ ተዘጋገመ።
ተጝደደ: ፈጽሞ አካቶ ተቈረጠ፣ ተጠረገ።
ተጠለለ፡ (ተጸለለ)፡ ከዝናም በቤት፡ በዋሻ፡ ከፀሓይ በጥላ፡ በዛፍ ሥር ተጠጋ፡ ዐረፈ፡ ተከለለ፡ ተጋረደ፡ ተሸፈነ። "ሚካኤል ሚካኤል ባንተ ጥላ ልጠለል" እንዲል ታቦት ዘፋኝ።
ተጠለለ፡ (ጠለለ)፡ ላይ ላዩ ተቀዳ፡ ተጨለፈ።
ተጠለቀ፡ ተለበሰ።
ተጠለቀ፡ ተመረመረ።
ተጠለቀ፡ ተገባ፡ ተገባበት።
ተጠለቀ፡ ተጠቀሰ፡ ተጨለፈ፡ ተቀዳ።
ተጠለቅ፡ ተመርመር። ጠየቀ ብለኸ ተጠየቅን እይ።
ተጠለፈ ፣ ተሰረጀ፡ ተሰናከለ፡ ተያዘ፡ ታሰረ።
ተጠለፈ፡ ተሣለ፡ ተመሰለ፡ ተጌጠ፡ ተሸለመ፡ ተዘመዘመ።
ተጠለፈ፡ ተነጠቀ፡ ተወሰደ።
ተጠለፈ: ታሰረ። "በቅሎው ፈረሱ አህያው ግመሉ ታበተ፣ ሽቢያው ለኮው።"
ተጠላ፡ (ተጸለለ)፡ ተወጠረ፡ ተዘረጋ ጥላው፡ ተከለለ፡ ተጋረደ ፀሓዩ፡ ሰዉ በጥላ።
ተጠላ፡ (ተጸልአ)፡ ተነቀፈ፡ ተጸየፈ፡ ተሰለቸ፡ ረከሰ።
ተጠላለፈ፡ ተወሳሰበ፡ ተያያዘ፡ ተቈላለፈ።
ተጠላላ፡ ተነቃቀፈ፡ ተቈራረጠ፡ ተበጣጠሰ።
ተጠላላፊ፡ የሚጠላለፍ፡ ተወሳሳቢ።
ተጠላፊ፡ የሚጠለፍ፡ ተዘምዛሚ።
ተጠመለለ፡ (ተጠብለለ)፡ ታጠፈ፡ ተቈለመመ።
ተጠመሰሰ፡ ተጣሰ፡ ተለጠሰ፡ ተኛ።
ተጠመረ፡ (ተፀመረ)፡ ተደረበ፡ ተደመረ፡ ተቀረቀበ።
ተጠመቀ፡ ተነከረ፡ ታጠበ፡ ጠበለተኛው።
ተጠመቀ፡ ተጠመዘዘ፡ ሸማው።
ተጠመቀ፡ ተጨመቀ፡ ጥሩ ሆነ፡ ማሩ፡ ዘይቱ፡ ወይኑ (ዘሌ፳፬፡ ፪)።
ተጠመቀ፡ ክርስትና ተነሣ፡ ሕፃኑ፡ አረመኔው (ማር፩፡ ፱)።
ተጠመቀ፡ ውሃ ተመላበት፡ ተበጠበጠ፡ ተዘለለ፡ ተሾመ፡ ጠላው።
ተጠመነ፡ ተጋዛ፡ የርሻ ውል ተዋዋለ።
ተጠመዘዘ፡ ዞረ፡ ተመለሰ፡ ተገመደ፡ ከረረ።
ተጠመደ፡ ተበጀ፡ ተዘጋጀ፡ ተሸሸገ፡ ወጥመዱ።
ተጠመደ፡ ተጠላ፡ ተመረዘ።
ተጠመደ፡ እቀንበር ገባ፡ ዐንገቱ ታሰረ፡ ተገዛ፡ አገለገለ።
ተጠመደ፡ ጥይት ጐረሠ፡ ተለጐመ።
ተጠመጠመ፡ ተሸበለለ፡ ተጠቀለለ፡ ተደመረ፡ ተከበሰ፡
ገመዱ፡ ጠፍሩ፡ ጠጕሩ (፪ሳሙ፡
፲፰፡ ፱። ኢዮ፸፰፡ ፲፯)።
ተጠሚ፡ የሚጠማ።
ተጠማ፡ (ተጠምዐ)፡ ተነከረ፡ ራሰ።
ተጠማ፡ (ጠማ)፡ በጥም ተያዘ፡ አፉ ደረቀ፡ ኵበት ሆነ። (ተረት)፡ "የተጠማ ከፈሳሽ፡ የተበደለ ከነጋሽ። "
ተጠማለለ፡ ተጣጠፈ፡ ተቈላመመ።
ተጠማመረ፡ ተገነኛኘ፡ ተጠማመደ።
ተጠማመደ፡ ተቈረኛኘ፡ ተጠላላ።
ተጠማሪ፡ የሚጠመር፡ ተቀርቃቢ።
ተጠማቂ፡ የሚጠመቅ፡ ጠላ፡ ሰው፡ ተጠምዛዥ ልብስ።
ተጠማኝ፡ ተጋዢ፡ የሰው መሬት ዐራሽ። (ተረት)፡ "ተጠማኝ ቢሰነብት ባለርስት ይኾናል። "
ተጠማዘዘ፡ ተዘዋወረ፡ ተጣመመ፡ ተጋመደ።
ተጠማጅ፡ የሚጠመድ፡ በሬ፡ አሽክላ።
ተጠማጠመ፡ በ፪፡ እጁ የሰውን ወገብ ዐንቆ ያዘ (ማሕ፫፡ ፬)።
ተጠማጠመ፡ ተሸባለለ፡ ተጠቃለለ፡ የመጠምጠም ብድር ተከፋፈለ።
ተጠምዛዥ፡ የሚጠመዘዝ።
ተጠምጣሚ፡ የሚጠመጠም፡ እባብ፡ ዘንዶ።
ተጠሞረ፡ ተደረበ፡ ተሸረበ፡ ተሸርቦ፡ ተከረረ፡ ተደወረ።
ተጠሰቀ፡ ተመታ፡ ተደሰቀ።
ተጠሰቀ፡ ተወጠቀ፡ ተጠቀጠቀ።
ተጠረመሰ፡ ተሰበረ፡ ተፈጩ።
ተጠረረ፡ ተጠለቀ፡ ተለበሰ፡ ጥሩሩ (ተገብሮ)።
ተጠረረ፡ ጥሩር አጠለቀ፡ ለበሰ፡ ጦር እንዳይወጋው፡ ቀስት እንዳይነድፈው (ገቢር)።
ተጠረቀ፡ ተወጋ፡ ተሰመረ፡ ተቸነከረ፡ ብረት ለበሰ (ኣስቴ፰፡ ፲፬)።
ተጠረቀመ፡ ገባ፡ ጥብቅ ኾነ፡ ታሰረ፡ ተዘጋ።
ተጠረቃቀመ፡ ተሰባሰበ፡ ተከመቻቸ።
ተጠረበ (ተጸርበ)፡ ታነጠ፡ ተሸለተ፡ ሾለ፡ ሣሣ፡ ቀጠነ፡ ጠፈጠፈ።
ተጠረነቀ፡ ታሰረ፡ ጥብቅ ኾነ፡ ድርጭት መሰለ።
ተጠረኘ፡ ተከፈለ፡ ተዘገነ፡ ተያዘ፡ ጥርኙ፡ እኸሉ፡
ውሃው፡ በጥርኝ።
ተጠረኘ፡ ጥርኝ ኾነ።
ተጠረገ፡ ተዛቀ፡ ተማጠጠ።
ተጠረገ፡ ታደፈ፡ ታበሰ፡ ተወለወለ፡ ጠዳ፡ ጠራ።
ተጠረገ፡ ታጨደ፡ ተቈረጠ፡ ተመነጠረ።
ተጠሪ፡ (ዎች)፡ የሚጠራ፡ ወኪል፡ ቶፋ፡ ምትክ፡ የሌላ ሰው ንብረት ጠባቂ።
ተጠሪነት፡ ወኪልነት፡ ቶፍነት።
ተጠራ፡ ተወከለ፡ ተተካ።
ተጠራ፡ ተጮኸ፣ ና ተባለ፡ ለግብዣ፡ ለሰርግ፡ ለዕድር፡ ለሌላም ጕዳይ፡ ቃል ዐለፈለት።
ተጠራረገ፡ ተባበሰ፡ ተወዛዛ።
ተጠራራ፡ ተጯጯኸ፡ ና ተባባለ።
ተጠራቀመ፡ ተጠናቀረ፡ ተሰበሰበ፡ ተዘገበ፡ ተከማቸ፡
ገንዘቡ፡ ሰዉ፡ ውሃው።
ተጠራቂ ፣ የሚጠረቅ።
ተጠራቃሚ፡ የሚጠራቀም።
ተጠራቢ፡ የሚጠረብ፡ የሚታነጥ።
ተጠራጊ፡ የሚጠረግ።
ተጠቀለለ፡ ተሰበሰበ፡ ተኰሰተረ፡ ተሸበለለ፡ ተጠመጠመ፡
ክብ ሆነ፡ ዐረጉ፡ ልጡ፡ ገመዱ፡ ድንኳኑ፡ ወረቀቱ፡
ብራናው፡ ቍርበቱ (ሕዝ፪፡
፱)።
ተጠቀለለ፡ ተፈጸመ፡ ተጨረሰ።
ተጠቀመ (ተጠቅበ)፡ ተሰፋ፡ ተጣፈ፡ ተደረተ፡ ተለገበ (ኢያ፱፡ ፭)።
ተጠቀመ፡ ጠኀበ፡ ረካ፡ ጥቅም፡ አገኘ፡ ተረባ (ኢሳ፵፯፡ ፲፪)።
ተጠቀሰ፡ በምልክት ተጠራ።
ተጠቀሰ፡ ተባለ፡ ተነገረ፡ ጥቅሱ።
ተጠቀሰ፣ ተነካ፡ ተሳበ፡ ተጐተተ፡ ቀረበ፡ ተማረ።
ተጠቀሰ፡ ተኰሰተረ፡ ተተረኰሰ።
ተጠቀሰ፡ ገባ፡ ተነከረ፡ እንጀራው፡ ተጠለቀ፡ ወጡ።
ተጠቀጠቀ፡ ባ፭ ጣት ተወጋ፡ ታተመ፡ ድፎው፡ ጥፍጥፉ፡ ተነቀሰ፡
ጥርሱ።
ተጠቀጠቀ፡ ተረገጠ፡ ተረመረመ።
ተጠቀጠቀ፡ ተበላ፡ ተወጠቀ።
ተጠቀጠቀ፡ ተደፈነ፡ ተዘጋ፡ ጨለመ።
ተጠቀጠቀ፡ ተጠጋጋ፡ ተቃረበ።
ተጠቂ፡ የሚጠቃ፡ ጥቃተኛ።
ተጠቃ፡ (ች)፡ ተወጋ፡ ተሰረረ። የሚነገረው ለጊደር ነው።
ተጠቃ፡ ተገፋ፡ ተበደለ፡ ተሸነፈ፡ ተዋረደ፡ ተጐዳ፡
ተጨቈነ
(ምሳ፲፪፡ ፱። ኢሳ፪፡ ፲፩። ሰቈ፩፡ ፲፩ - ፪ቆሮ፡ ፲፫፡ ፯)።
ተጠቃለለ፡ (ተጠቀለለ)፡ ተፈጸመ፡ ተከናወነ፡ ጣጣው ዐለቀ።
ተጠቃለለ፡ ተሸባለለ፡ ተጠማመተ።
ተጠቃለለ፡ ዐረፈ፡ ሞተ፡ አንድ ወገን ሆነ፡ ተከፈነ፡ ተገነዘ።
ተጠቃሚ፡ የሚጠቀም፡ የሚረባ፡ ተረቢ።
ተጠቃሚነት፡ ተጠቃሚ መኾን።
ተጠቃሽ፡ የሚጠቀስ፡ የሚባል፡ የሚነገር፡ የሚጠራ።
ተጠቃቀመ፡ ተሰፋፋ፡ ተጣጣፈ።
ተጠቃቀመ፡ ተረባባ፡ ጥቅም ተሰጣጠ፡ ተቀባበለ።
ተጠቃቀሰ፡ ተነካካ፡ በምልክት ተነገረ፡ ዐይን ላይን ተገናኘ፡ ተቀጣጠበ።
ተጠቃቃሚ፡ የሚጠቃቀም።
ተጠቃጠቀ፡ ተረጋገጠ፡ ተረማረመ።
ተጠቃጠቀ፡ ተበሳሳ፡ ተነቃቀሰ።
ተጠቃጠቀ፡ ተደፋፈነ፡ ተደባበቀ።
ተጠቈመ ፣ ተሳበ፡ ታረቀ፡ ተተካከለ፡ ባይ።
ተጠቈመ፡ ላመል፡ ተወጋ፡ ተጫረ፡ ታከከ።
ተጠቈመ፡ ምልክት ተቀበለ።
ተጠቈረ፡ (ጠቈረ)፣ ተነቀስ፡ ተወቀረ፡ ጥርሱ።
ተጠቈረ፡ በመርፌ፡ በሾኸ፡ ተሣለ፡ ታተመ፡ ገላው።
ተጠቈረ፡ ተጐነፈ፡ ዘንጋዳው።
ተጠቅላይ፡ የሚጠቀለል፡ ተሸብላይ።
ተጠቅጣቂ፡ የሚጠቀጠቅ፡ ተደፋኝ፡ ተረምራሚ።
ተጠቋሚ፡ የሚጠቈም፡ ምልክት ተቀባይ።
ተጠቋቈረ፡ ተነቃቀሰ።
ተጠበሰ፡ በጥይት ተመታ።
ተጠበሰ፡ ተተኰሰ፡ ተቃጠለ።
ተጠበሰ፡ ፈላ፡ በሰለ፡ ተቈላ፡ ተንቃቃ፡ ደረቀ።
ተጠበረ፣ ተሠራ፡ ተጌጠ፡ ተሸለሙ፡ አማረ።
ተጠበቀ ፣ ቈየ፡ ዘገየ፡ ተመደበ፡ ተወሰነ። "ኀጢአተኛ ለክፉ ቀን ይጠበቃል" (ኢዮ፡ ፳፩፡ ፴)።
ተጠበቀ፡ (ተዐቅበ)፡ ተከለከለ፡ ታገደ፡ ተወሰነ፡ ከክፉ ነገር ራቀ፡ ተጠነቀቀ (ዘዳ፬፡ ፳፫። ሕዝ፴፫ ' ፭)።
ተጠበቃዬ፡ የሳምንት ቀጠሮ፣ ከጠበቃዬ ጋራ ማለት ነው።
ተጠበቅ፡ (ተዐቀብ)፡ ተጠንቀቅ፡ ከኀጢአት ተወገድ፡ ራቅ (ዘዳ፰፡ ፲፩)።
ተጠበበ፡ (ጠበበ)፡ ተተነኰለ፡ ተንኰል አደረገ (ዘፀ፩፡ ፲። አስቴ፰፡ ፫)።
ተጠበበ፡ ተለቀመ፡ ተዋሰበ፡ ተሠባጠረ፡ ተጣለ፡ ተሠራ ጥበቡ፡ ተፈለሰፈ።
ተጠበበ፡ ተጨነቀ፡ ተቸገረ።
ተጠበበ፡ ዐወቀ፡ ተራቀቀ፡ ፈላስፋ፡ ብልኀተኛ ሆነ።
ተጠበጠበ፡ (ተጠብጠበ)፡ ተገረፈ፡ ተሸነቈጠ፡ ተመታ።
ተጠበጠበ፡ ተበለጠ፡ ተጠባ።
ተጠበጠበ፡ ተቸኮለ፡ ተገሠገሠ።
ተጠቢ፡ (ተጠባሒ)፡ የሚጠባ፡ የሚበለት።
ተጠባ፡ (ተጠብሐ)፡ ተበለጠ፡ ተቈረጠ።
ተጠባ፡ (ተጠብወ)፡ ተሳበ፡ ተጐተተ፡ ተመጠጠ፡ ተመጠመጠ፡ ተመገመገ፡ ተጠጣ።
ተጠባሪ፡ የሚጠበር፡ ተሸላሚ።
ተጠባሽ፡ የሚጠበስ፡ የሚቈላ።
ተጠባቂ፡ የሚጠበቅ ዕቃ፡ ሰው።
ተጠባበቀ፡ (ተዓቀበ)፣ ተከላከለ፡ ተከታተለ፡ የሚያደርገውን፡ የሚናገረውን አየ፡ ሰማ (ማቴ፱፡ ፲፯። ሉቃ፭፡ ፴፰)።
ተጠባበቀ፡ ተዋሰነ፡ ተወሳሰነ።
ተጠባባቂ፡ ተከታታይ፡ ሰላይ፡ ነገር አቀባይ።
ተጠባባቂነት፡ ሰላይነት፡ የክፉ፡ የበጎ።
ተጠብጣቢ፡ የሚጠበጠብ፡ ተገራፊ።
ተጠቦ፡ ተጨንቆ፡ ተቸግሮ። "እከሌ ቤቱን ተጨንቆ ተጠቦ ሠራ" እንዲሉ።
ተጠነሰሰ፡ (ተፀንሰ)፡ ተበጠበጠ፡ ጥንስስ ሆነ።
ተጠነሰሰ፡ ተፀነሰ፡ ተረገዘ፡ በሆድ ቀረ፡ ተቋጠረ።
ተጠነቀቀ፡ ተዘጋጀ፡ ተኰሰተረ፡ ተከወነ፡ ተፈጸመ፡
ተጨረሰ።
ተጠነቀቀ፡ ተጋ፡ ተጠበቀ።
ተጠነቈለ፡ ተረተ፡ ተደረገ፡ ጥንቈላው።
ተጠነቈለ፡ ተወጋ፡ ተደነቈለ፡ ተነቈረ።
ተጠነቋቈለ፡ ተነቋቈረ።
ተጠነበፈ፡ ተገደለ፡ ወደቀ፡ ተጣለ፡ ጥንብ መሰለ።
ተጠነባበረ፡ ተደነባበረ።
ተጠነካከረ፡ ተጠናና፡ ተበረታታ (ሕዝ፳፩፡ ፲፮)።
ተጠነገደ፡ ሞተ፡ ተጨረሰ፡ ዐለቀ፡ ሺቅ አለ፡ እንደ ሰናክሬም ሰራዊት።
ተጠነጠነ፡ (ተጸንጸነ)፡ ተጠቀለለ፡ ኮበ፡ ተደወረ፡ ተዳወረ።
ተጠነፈፈ፡ ውሃው ከንፍሮ ውስጥ ፈሰሰ፡ ተንጠፈጠፈ፡ ንፍሮው ከውሃ ተለየ።
ተጠና፡ ታወቀ፡ ልብ ተደረገ፡ በቃል ተያዘ፡ ትምርቱ።
ተጠናቀቀ፡ ተከናወነ።
ተጠናቈለ፡ ተናቈረ፣ ተተናኰለ፡ ተጋፋ፡ ተጠነቋቈለ፡ የጥንቈላ ብድር ተከፋፈለ።
ተጠናበረ፡ ተደናበረ።
ተጠናና፡ ተበረታታ።
ተጠናከረ፡ ተጣና፡ ተበራታ፡ ጠንካራ ተኳዃነ።
ተጠናወተ፡ ዘወትር፡ ዐመመ፡ ጨነገፈ፡ ወረደ፡ በምች፡
በክፉ ሽታ።
ተጠናወተ: ወረደ (ጠነወተ) ።
ተጠናወታት፡ ወረዳት፡ ፅንሱ፡ ሽሉ።
ተጠናገረ፡ ተጠናበረ።
ተጠንቀቅ፡ ዕወቅ፡ ተጠበቅ፡ ትጋ፡ ንቃ፡ ኰስተር በል። "ላለፈው ቤት አይሠራም፡ ለሚመጣው ተጠንቀቅ። "
ተጠንቃቂ፡ የሚጠነቀቅ።
ተጠኸነነ፡ ተጀነነ፡ ኰራ።
ተጠወረ፡ (ተጸውረ)፡ ሸክም ሆነ፡ ተያዘ፡ ተወሰነ፡ ተቻለ፡ ተለመደ።
ተጠዋለገ፡ ተለዋወጠ፡ ተጣቈረ።
ተጠዋሪ፡ (ዎች)፡ የሚጦር፡ በሰው ትከሻ የሚኖር፡ ጡረተኛ።
ተጠዋሪነት፡ ተጠዋሪ መኾን፡ ጡረተኛነት።
ተጠዘለ፡ ተመታ፡ ተመደወተ።
ተጠዘለ፡ ደነደነ፡ ወፈረ።
ተጠዘጠዘ፡ ተነዘነዘ፡ ተነዘረ።
ተጠዘጠዘ፡ ተነደፈ፡ ተወጋ።
ተጠዛጠዘ፡ ተናደፈ፡ ተዋጋ።
ተጠየረ፡ ሠገረ፡ በረረ፡ ከነፈ።
ተጠየረ፡ ተዘጋጀ፡ ተደራጀ።
ተጠየረ፡ አለመጠን ኰራ፡ ምድርን ለመርገጥ ተጸየፈ።
ተጠየቀ፡ ተመረመረ፡ "የሚኾነውን ንገረኝ" ተባለ ነቢዩ፡ ጠንቋዩ (ሕዝ፳፡ ፫፡ ፴፩)።
ተጠየቀ፡ ተሞገተ፡ "ተጠየቅ" ተባለ።
ተጠየቀ፡ ተጐበኘ፡ ተፈቀደ።
ተጠየቅ፡ የጠያቂ ሙግት አዝማች ወይም መነሻ። (ግጥም)፡ "ተጠየቅ ጠይቀኝ ማር እሰጥ አገባ፡ እንዴት ይዘለቃል የጎረቤት ሌባ። "
"ተጠየቅ ተጠለቅ" እንዲሉ።
ተጠየቅታ፡ ተጠየቅ ማለት፡ ጥያቄ፡ ጥይቅ።
ተጠየተ፡ በጥይት ተመታ፡ ተገደለ፡ እንደ አቡነ ጴጥሮስ።
ተጠየተ፡ ተሠራ፡ ተበጀ፡ ጥይቱ።
ተጠየተ፡ ተሰበሰበ፡ ታሰረ ዛላው እሸቱ።
ተጠየፈ፡ ተጠላ፡ ተነቀፈ። ልማዱ ግን እንደ ኹለተኛው አጠየፈ፡ ጠላ፡ ነቀፈ ነው።
ተጠያሪ፡ የሚጠየር፡ ሠጋሪ፡ በራሪ።
ተጠያቂ፡ ተሞጋች፡ ተየካሽ።
ተጠያቂ፡ የሚጠየቅ፡ ሊቅ፡ መምር፡ ሽማግሌ።
ተጠያየቀ፡ ተመራመረ፡ ተሳለለ፡ ተነጋገረ (ሉቃ፳፪፡ ፳፫)።
ተጠያየቀ፡ ተጐበኛኘ፡ ተፈቃቀደ።
ተጠያያቂ፡ የተጠያየቀ፡ የሚጠያየቅ፡ ተሳላይ።
ተጠያፊ፡ የሚጠየፍ፡ ነቃፊ።
ተጠጀ፡ ተጣለ፡ ተበጠበጠ።
ተጠገረ፡ ለጠገራ ተለወጠ፡ ተሼጠ።
ተጠገረረ፡ በሸክም ተያዘ።
ተጠገረረ፡ ተደበለለ፡ ተሸከመ።
ተጠገበ፡ በቃ፡ ተሰለቸ፡ ተተወ። "የሰው ገንዘብ አይጠገብም" እንዲሉ።
ተጠገተ፡ ታለበ፡ ላሙ፡ ጡቱ፡ ወተቱ።
ተጠገነ፡ ታሰረ፡ ተጠቀለለ፡ ታከመ፡ ተፈወሰ፡ ዳነ፡
ታደሰ።
ተጠገነ፡ ታገዘ፡ ተረዳ።
ተጠጊ፡ የሚጠጋ፡ ቀራቢ።
ተጠጋ፡ ቀረበ፡ በጥግ ቆመ፡ ተቀመጠ፡ ተደገፈ፡ ተማጠነ (፪ሳሙ፡ ፬፡ ፫)። (ተረት)፡ "ዥብን ሊወጉ ካህያ ይጠጉ። "
ተጠጋኝ፡ የሚጠገን፡ ታዳሽ።
ተጠጋገነ፡ ተሳሰረ፡ ተጠቃለለ፡ ተዳደ።
ተጠጋገነ፡ ተረዳዳ፡ ተጋገዘ።
ተጠጋጊ፡ የሚጠጋጋ፡ ተደጋጋፊ።
ተጠጋጋ ፣ ተቀራረበ፡ ተደጋገፈ።
ተጠግቶታል፡ ቀርቦታል፡ ዐድሮበታል። "ሰይጣን ተጠግቶታል" እንዲሉ።
ተጠጠ: ተጠረገ፣ ተጨረሰ፣ ዐለቀ።
ተጠጠተ፡ (ተጸጸተ)፡ ተቈጨ፡ ዐዘነ፡ ተቈረቈረ (፩ሳሙ፡ ፲፭፡ ፴፭። ማቴ፳፩፡ ፳፱)።
ተጠጣ፡ ፉት ተባለ፡ ተማገ፡ ተጨለጠ፡ ወደ አንዠት ወረደ፡ ገባ።
ተጠጣች፡ የሚጠጠት፡ ዐዛኝ።
ተጠፈረ፡ (ተጸፍረ)፡ ተቈረጠ፡ ተከረከመ ጥፍሩ።
ተጠፈረ፡ በጠፍር ታሰረ፡ ተተበተበ፡ ተገረፈ፡ ተታታ፡ ተማገረ፣ ተጐለበ።
ተጠፈነ፡ (ተጸፍነ)፡ ተጠለፈ፡ ታሰረ፡ ተዘጋ።
ተጠፈነነ፡ ተጀነነ፡ ኰራ።
ተጠፈጠፈ፡ (ተጸፍጸፈ)፡ ተዘረጋ፡ ሣሣ፡ ተነጠፈ፡ ተለበጠ።
ተጠፈጠፈ፡ በጥፊ ተመታ፡ ተወለወለ።
ተጠፋ፡ (ተጠፍሐ)፡ በጭን ላይ ተነዘረ።
ተጠፋ፡ ተጨበጨበ።
ተጠፋጠፈ፡ በጥፊ ተማታ፡ ተወላወለ።
ተጠፋፈጠ፡ ተጣጣመ።
ተጠፋፋ፡ ተገዳደለ፡ ተተማተ።
ተጠፍጣፊ፡ የሚጠፈጠፍ፡ የሚሣሣ።
ተጣለ፡ (ተጽዕለ፡ ተጥሕለ)፡ ተወረወረ፡ ተገደፈ፡ ወደቀ፡ ተተወ (፪ዜና፡ ፲፰፡ ፲፬። ኢሳ፡ ፲፩፡ ፲፪። ፴፬፡ ፫። ዳን፫፡ ፮። ራእ፲፪፡ ፱፡ ፲፫)።
ተጣለ፡ ተበጠበጠ፡ ታሸ ማሩ።
ተጣለ፡ ተናደ፡ ተዘረጠጠ።
ተጣለ፣ ተኛ፡ ተጋደመ።
ተጣለ፡ ተጨመረ፡ ገባ፡ ተዶለ።
ተጣለፈ፡ ተሰራጀ፡ ተዋሰበ፡ ተቋለፈ።
ተጣላ፡ (ተጻልአ)፡ ተፃረረ፡ ተቃረነ፡ ተቃወመ፡ ሰላም ዐጣ፡ ሳይስማማ ቀረ። (ተረት)፡ "ሳይጣሉት የተጣላ ሲርብ ያበላ፡ አይረሳም የቀረው ነው። "
"አህያ የለኝም፡ ከዥብ አልጣላም። " (ውሻ፡ አይበላሽ፡ ጥል፡ ተጣላ)፡ በምድር ድንበር በሴት ከንፈር ስለ ተገናኘ ዕርቅ አልባ ሆነ። (ከፈሱ የተጣላ)፡ እብድ።
ተጣመ፡ (ተጥዕመ)፡ ተቀመሰ።
ተጣመመ፡ ተጠማዘዘ፡ ተንጋደደ፡ ተወላገደ።
ተጣመረ፡ (ተፃመረ)፡ ተገናኘ፡ ተጣመደ፡ ተዋደደ፡ ተያያዘ፡ ድርና ማግ ሆነ፡ የተባትና የእንስት።
ተጣመደ፡ ተቈራኘ፡ ተጣላ።
ተጣማ፡ ተቀላቀለ፡ ተደባለቀ፡ ተያያዘ። "በግብጽ እሳትና በረድ ተጣምቶ ዘነመ። "
ተጣማሚ፡ የሚጣመም፡ ተንጋዳጅ።
ተጣማሪ፡ የሚጣመር፡ ተያያዥ።
ተጣማጅ፡ የሚጣላ።
ተጣማጅ፡ የሚጣመድ፡ ትክክል የሚያርስ፡ የሚስብ በሬ።
ተጣሰ፡ ተወደደ፡ ተሰበረ፡ ተረገጠ፡ ተኛ፡ ተነደለ፡
ተቀደደ፡ ፈረሰ።
ተጣሰ፡ ተፈጨ።
ተጣረ፡ ተተጋ፡ ተለፋ፡ ተደከመ።
ተጣረሰ፡ ተሳሳተ፡ ተበላሸ፡ ተቃወሰ፡ የሙግት፡ የክርክር፡
የነገር።
ተጣረሰ፡ ተጋጨ፡ ጥርሱ።
ተጣረረ፡ (ተፃረረ)፡ ተጣላ፡ ጥል እበቀለ።
ተጣረገ፡ ተጫጨደ፡ ተመናጠረ።
ተጣሪ፡ የሚጣራ፡ ጠሪ።
ተጣራ ፣ (ተጻረየ፡ ተናጽሐ)፡ ተናጻጥሩ ኾነ (ተኳዃነ)።
ተጣራ፡ (ተጣርአ፡ ተጻርሐ)፡ ጠራ።
ተጣራ፡ ፈጽሞ ተሼጠ።
ተጣራሪ፡ (ተፃራሪ)፡ የሚጣረር፡ ተጣይ፡ የማይሰማማ፡ "እሳትና ውሃ"፡ "ዐይንና ፈር"፡ የመሰለው ኹሉ።
ተጣቀመ፡ ተያያዘ፡ ተማላ።
ተጣቀሰ፡ በቅንድብ፡ በከንፈር፡ ተጣራ።
ተጣቀሰ፡ ተናካ፡ ተሳሳበ።
ተጣቈሰ፡ ተደገመ፡ ዘሩ።
ተጣቈሰ፡ ተጐሸመጠ፡ ተደፈረ።
ተጣቈረ፡ ተናቀሰ።
ተጣቈረ፡ ተጐሳቈለ፡ ተዳደፈ።
ተጣበሰ፡ በጥይት ተቋላ፡ ተማታ።
ተጣበሰ፡ ተጋረፈ፡ ተሸናቈጠ።
ተጣበቀ፡ ተላከከ፡ ገጠመ፡ ተሰማማ፡ ተያያዘ፡ አልላቀቅ አለ፡ ደገደገ (፪ነገ፡ ፭፡ ፳፯። ፲፰፡ ፮)።
ተጣበበ፡ ተጠጋጋ፡ ተጨናነቀ፡ እንደ ሮማን ሆነ።
ተጣባ፡ (ተጣበወ)፡ ተመጋመገ፡ ተማጠጠ።
ተጣባ፡ (ተጻብሐ)፡ የጧት ሰላምታ ተሰጣጠ፡ "እንዴት ዐደርክ" ተባባለ (፪ነገ፡ ፬፡ ፳፱)።
ተጣባ፡ (ተጻብአ)፡ ተጣላ፡ ተዋጋ።
ተጣባ፡ መስከረም ተቃረበ (ደረሰ)።
ተጣባቂ፡ የሚጣበቅ፡ ተላካኪ።
ተጣና፡ ተበራታ፡ ተጠናከረ።
ተጣወረ (ተጻወረ ፣ ተካሀለ)፡ ተቻቻለ፡ ተላመደ። "እከሌ ይህን ሥራ ተጣውሮታል። "
ተጣዘለ፡ ተማታ፡ ተመዳወተ፡ ተጣረዘ።
ተጣይ ፣ የሚጣላ፣ ጠላ።
ተጣይ፡ (ተጸዓሊ፡ ተጠሓሊ)፡ የሚጣል፡ ወዳቂ።
ተጣይ (ተጻላኢ)፡ የሚጣላ፡ ተፃራሪ፡ ተቃራኒ።
ተጣይ የሚጣል ፣ ጣለ።
ተጣደ፡ ተሰረረ፡ በላይ ሆነ፡ ተነ።
ተጣደ፡ ዐለፈ፡ ተሰጠ፡ ቀረበ፡ ተደቀነ።
ተጣደፈ፡ ተቻኰለ፡ ተዋከበ።
ተጣዳፊ፡ የተጣደፈ፡ የሚጣደፍ፡ ጥዱፍ።
ተጣዳፊነት፡ ችኩልነት።
ተጣገበ፡ ተባቃ፡ ተሰላቸ።
ተጣጋ፡ (ተጣግዐ፡ ተፃግዐ)፣ ደረቀ፡ ተቃረበ፡ ልጥቅ አለ፡ የሆድ፡ የምላስ (ኢዮ፳ नाइन፡ ፲። መዝ፳፪፡
፲፭። ፵፬፡ ፳፭)።
ተጣጠረ (ተሓጸረ): ተካበበ፡ ተካለለ።
ተጣጠቀ (ተዓጠቀ): የትጥቅን ብድር ተመላለሰ፡ ተጠማጠመ (ለባበሰ፡ ጠማጠመ)።
ተጣጠበ (ተኃፀበ): ተሻሸ፡ ተለቃለቀ፡ ተናጻ።
ተጣጠነ (ተዓጠነ): የዕጣንን ጪስ ተሰጣጠ፡ ተቀባበለ ("እንዳጠነ ታጠነ")፡ ተጫሰ።
ተጣጠፈ (ተዓጸፈ): ተኰራመተ።
ተጣጣ (ተኃጥአ): ሳይገናኝ፡ ሳይተያይ ቀረ፡
ተረሳሳ፡ ተራራቀ። "አፍና እጅ አይተጣጣም" እንዲሉ። "ጠጣን" ተመልከት።
ተጣጣ፡ (ጣእጥአ)፡ ተከናወነ፡ ተቻለ።
ተጣጣ ተረሳሳ፣ ዐጣ።
ተጣጣ፡ ጥዋ ተቀባበለ፡ ማኅበር ተከፋፈለ።
ተጣጣለ፡ "ዕጣ ዕጣ ለዚህ ጌታ ይውጣ" ተባባለ።
ተጣጣለ፡ ተዋደቀ፡ ተወዳደቀ፡ ተገዳደመ፡ የመጣልን ብድር ተከፋፈለ።
ተጣጣለ፡ ካንዱ አገር ወደ ሌላው ተላለፈ።
ተጣጣመ፡ (ተጣዐመ)፡ ተጠፋፈጠ፡ ተፋቀረ፡ ተሰማማ።
ተጣጣመ፡ ዐለቀ፡ ተጨረሰ፡ ተከናወነ፡ ሥራው።
ተጣጣረ፡ (ተጻዐረ)፡ ተጨናነቀ። (ተጋ፡ ታተረ) (ሮሜ፰፡ ፳፪፡ ፳፫። ፪ቆሮ፡ ፭፡ ፱)።
ተጣጣሪ፡ የተጣጣረ፡ የሚጣጣር፡ ትጉህ፡ ታታሪ።
ተጣጣቢ: ርስ በርሱ የሚተጣጠብ፡ የሚናጻ።
ተጣጣፈ፡ ተጋጠመ፡ ተገናኘ፡ ተሰማማ፡ ተኳዃነ፡ የባልና የሚስት።
ተጣጣፈ፡ ተጻጻፈ፡ ጥፈትን ተረዳዳ፡ በደብዳቤ ተዋዋለ፡ ተነጋገረ፡ ተላላከ።
ተጣጣፊ የሚጣጣፍ፡ ተጻጻፊ፡ ተዋዋይ።
ተጣፈ፡ ተጠቀመ፡ ተሰፋ፡ ተለጠፈ።
ተጣፈ፡ ተጻፈ፡ ተከተበ።
ተጣፈረ፡ (ተጻፈረ)፡ ጥፍር ተቋረጠ።
ተጣፈረ፡ በቃሪያ ጥፊ ተማታ።
ተጣፈጠ፡ (ጣፈጠ)፡ ጣፋጭ ሆነ፡ በሰው ዘዴ።
ተጣፊ፡ (ተጣፋኢ)፡ የሚጣፋ፡ ተጋዳይ።
ተጣፋ፡ (ተጣፍሐ፡ ተጻፍዐ፡ ተመላትሐ)፡ በጥፊ ተጠፋጠፈ።
ተጣፋ፡ (ተጣፍአ)፡ ተጋደለ፡ ተተማተ።
ተጣፋ፡ ሽው አለ፡ ዐይንን አሳበጠ።
ተጣፋ፡ ተሻኰተ፡ አገና፡ ተማታ፡ ኣጥፋኝ፡ አላጥፋኸ ተባባለ፡ የገዢና የሸያጭ።
ተጤነ፡ ታሰበ፡ ልብ ተባለ፡ ተመረመረ።
ተጥለቀለቀ፡ ተንጣለለ፡ ውሃ ለበሰ፡ ተሸፈነ።
ተጥመለመለ፡ ተዝለፈለፈ፡ ተሽመደመደ፡ እንደ ጠፍር ሆነ።
ተጥመዘመዘ፡ ተፍተለተለ፡ ታመመ።
ተጥረበረበ፡ ተሽቈጠቈጠ፡ ተለማመጠ፡ ተርገበገበ፡ ሰውን ለመጋበዝ።
ተጥረከረከ፡ ተጕደፈደፈ፡ ተኵለፈለፈ።
ተጥበረበረ ፣ ተብረቀረቀ፡ አልታይ አለ።
ተጥባበ ነገር፡ የነገር መልስ ዘዴ።
ተጥባብ፡ ክፉ ምክር።
ተጥናና፡ ተረጋጋ።
ተጥወለወለ፡ ተናወጠ፡ ዞረ፡ የነፋስ፡ የልብ፡ የራስ።
ተጦለ፡ ተጠረገ፡ ተገፈፈ፡ ተለየ፡ ተወገደ።
ተጦመ፡ ሳይበላ፡ ሳይጠጣ ቀረ (ዋለ)፡ ጦም ሆነ ጊዜው።
ተጦረ፡ (ተጸውረ)፡ ታዘለ፡ ተጠዋሪ ሆነ፡ ተቻለ፡ ታገዘ፡ ተረዳ።
ተጧሪ፡ (ዎች)፡ የሚጦር፡ የሚታገዝ፡ የሚረዳ ሽማግሌ።
ተጧጧረ፡ (ተጻወረ)፡ ተዛዘለ፡ ተሸካከመ፡ ተረዳዳ፡ ተጋገዘ፡
ያሮጌና ያሮጊት።
ተጨለጠ፡ ተጨረሰ፡ ተነቀረ።
ተጨለፈ ፣ ተጠለቀ፡ ተቀዳ፡ ከሰታቴ፡ ከአፍላል ወጣ።
ተጨላፊ፡ የሚጨለፍ፡ የሚቀዳ።
ተጨመላለቀ፡ የተጨማለቀ፡ ድርብ፡ በብዙ ወገን፡ በፊት፡ በኋላ፡ በቀኝ፡ በግራ፡ ተዳደፈ።
ተጨመረ፡ (ተፀመረ)፡ ገባ፡ ተላ፡ ተከተተ፡ ተሰናዳ (ማቴ፭፡ ፳፭)።
ተጨመረ፡ ታከለ፡ አንድ ኾነ፡ ወረደ።
ተጨመረ: ተቀላቀለ።
ተጨመቀ፡ ተጨቈነ፡ ተጠመዘዘ፡ ተንጠፈጠፈ፡ ውሃው፡
ጥሩው፡ ወለላው፡ ወረደ።
ተጨመተረ፡ ተኰመተረ፡ ተጨመደደ።
ተጨመታተረ ፣ ተኰመታተረ፡ ተመዳደደ።
ተጨማለቀ፡ ነገር አበዛ፡ ችክ ምንችክ አለ። ለፈደደን ተመልከት።
ተጨማመረ ፣ ተባበረ፡ ተነባበረ፡ ተደራረበ።
ተጨማማሪ፡ የሚጨማመር፡ ተነባባሪ።
ተጨማሪ፡ የሚጨመር፡ የሚታከል፡ ኹለተኛ። "ተጨማሪ ዲያቆን" እንዲሉ።
ተጨማሪነት፡ ተጨማሪ መኾን፡ ዐባሪነት።
ተጨማተረ፡ ተኰማተረ፡ ተጨማደደ።
ተጨምሮ፡ ታክሎ። (ተረት)፡ "በደንባሪ በቅሎ ቃጭል ተምሮ። "
ተጨረ: ተጫረ፣ ተቧጨረ።
ተጨረመደ: ተበላ።
ተጨረማመተ: ተጨመዳደደ።
ተጨረሰ: ተፈጀ፡ ተገደለ፡ ተፈጸመ፡ ዐለቀ፡ ተከወነ፡
ተደመደመ (ኢዮ፴፪፡ ፲፭)።
ተጨረሰ: ተፈጸመ፣ መላ።
ተጨረገደ: ተቈረሰ፡ ተገመጠ፡ ተበላ።
ተጨረገደ: ታጨደ፡ ተቈረጠ።
ተጨረፈ: በቀላል፡ በጥቂት ዥል ተመታ፡ ተቈረጠ።
ተጨሪመተ: ተጨማተረ፡ ተጨማደደ።
ተጨራመመ: ተጣመመ።
ተጨራመደ: ተወጫመደ።
ተጨራረሰ: ተገዳደለ።
ተጨራገደ: ተማታ፡ ተደባደበ በበሎታ።
ተጨራገደ: ተጫጨደ፡ ተቋረጠ።
ተጨቀጨቀ: ተነዘነዘ፡ ተነተረከ።
ተጨቀጨቀ: ተወቀጠ።
ተጨቀጨቀ: ተጠቀጠቀ፡ ተደፈነ።
ተጨቃጨቀ: ተነዛነዘ፡ ተነታረከ።
ተጨቃጫቂ (ቆች): የተጨቃጨቀ፡ የሚጨቃጨቅ፡ ተነዛናዥ።
ተጨቃጫቂነት: ተጨቃጫቂ መኾን።
ተጨቈነ: ተረጠጠ፡ ታመቀ፡ በታች ኾነ፡ ተቸገረ፡ ተጨነቀ (ሉቃ፮፡ ፴፰። ዓሞ፪፡ ፲፫)።
ተጨቈነ: ተጨፈቀ፡ ተለሰቀ።
ተጨቋቈነ: ተጠጋጋ፡ ተወፋፈቀ።
ተጨቋኝ: የሚጨቈን፡ ተጨፋቂ፡ ተለሳቂ።
ተጨበጨበ፡ ኾነ፡ ተደረገ፡ ጭብጨባው። "እከሌ ስብቅል ነገር ስለ ተናገረ ጨበጨበለት። "
ተጨነቀ፡ (ተጽዕቀ)፡ ተጠበበ፡ ተቸገረ፡ ታወከ፡ ግራ ገባው (ዘፍ፮፡ ፮)። (ግጥም)፡ "እግዜር ያውቃል፡ ሰው በከንቱ ይጨነቃል። ፲፪፡ ኾነን አንዲት ሴት ወደን፣ እሷ ትሥቃለች እኛ ተጨንቀን። "
ተጨነቈረ: ደከመ፡ አነሰ። ሊከደን ሊገጠም ጥቂት ቀረው ሸፋሽፍቱ።
ተጨነባበሰ፡ ተጫጫሰ።
ተጨነገፈ፡ ተመለመለ፡ ረገፈ።
ተጨነጓጐለ፡ ተጓጐለ፡ ተሰነካከለ።
ተጨናቂ፡ (ቆች)፡ የተጨነቀ፡ የሚጨነቅ (መክ፬፡ ፩)።
ተጨናቈረ: ባንድ ዐይን ተያየ፡ በ፪ኛው አልተያየም።
ተጨናበሰ፡ ታወከ፡ አልድን፡ ትክክል አላይ፡ አልነድ፡ አልበራ አለ፡ ጨሰ፡ ሊጠፋ ቀረበ፡ ያይን፡ የእሳት፡ የመብራት።
ተጨናበረ፡ ተሳሳተ፡ ተደናገረ።
ተጨናነቀ፡ ተጠጋጋ፡ ተቀራረበ፡ ተንታበረ፡ ተደራረበ።
ተጨናጐለ፡ ታጐለ፡ ተሰናከለ፡ ሳይዋጣ ባጓጕል ቀረ።
ተጨከነ፡ ኾነ፡ ተደረገ፡ ጭካኔው።
ተጨካከነ፡ ሳይተዛዘን ቀረ።
ተጨወየ ፣ ጨው፡ ጨዋ ኾነ፡ ከተነሰነሰበት።
ተጨዋወተ፡ ተነጋገረ፡ ጨዋታ ተመላለሰ፡ ተለዋወጠ።
ተጨጐለ፡ ተጀጐለ፡ ተከበበ፡ ተጋረደ፡ ተሸፈነ፡ ተጌጠ፡
ተሸለሙ፡ አማረ፡ ሰመረ፡ ተንቈጠቈጠ።
ተጨፈለቀ: ተሠራ፡ ተቀጠቀጠ፡ ጠገራው።
ተጨፈለቀ: ተረገጠ፡ ተዳጠ፡ ተደፈጠጠ።
ተጨፈለቀ: ታረሰ፡ ተተረተረ፡ ተሠነጠቀ ዕዳሪው።
ተጨፈላለቀ: ተዳዳጠ፡ ተደፋጠጠ፡ ተጨመላለቀ።
ተጨፈረ: ተዘለለ፡ ተረገደ።
ተጨፈቀ: ተጠጋጋ፡ ተጠቀጠቀ፡ ተቸፈገ፡ በዛ።
ተጨፈቀ: እንክብል ኾነ፡ ተድበለበለ።
ተጨፈቀ: ደንጊያ ተጫነበት፡ ተለሰቀ፡ ቀጥ አለ።
ተጨፈነ: ተከደነ፡ ተደፈነ፡ ተሸፈነ (ኢሳ፳፱፡ ፱። ፴፪፡ ፫)። "ድመት፡ ውሻ፡ ዐይጥ፡ አንበሳ፡ ነብር፡ ዥብ፡ ተኵላ፡ ቀበሮ፡
ዋልጋ፡ እነዚህን የመሰሉ ሁሉ ዐይናቸው ተጨፍኖ ይወለዳሉ፡ ምክንያቱም የጨለማ ጭፍሮች ስለ ኾኑ ነው"
ተጨፈገ: ተፈቀ፡ ተቸፈገ።
ተጨፈገገ: ተቋጠረ፡ ጠቈረ።
ተጨፈጨፈ: ተቈራረጠ፡ ተተፈተፈ።
ተጨፈጨፈ: ታለፈ፡ ተሻረ ነገሩ።
ተጨፋለቀ: ተጨማለቀ፡ ተቀጣቀጠ።
ተጨፋቂ: የሚጨፈቅ።
ተጨፋኝ: የሚጨፈን።
ተጨፋጨፈ: በሰይፍ ተማታ፡ ተቈረጠ።
ተጨፋፈቀ: ተጠጋጋ፡ ተጨቋቈነ።
ተጨፋፈነ: ዐይንን ተከዳደነ፡ ተሸፋፈነ።
ተጨፍላቂ: የሚጨፈለቅ፡ ዕዳሪ ብረት።
ተጨፍጫፊ: የሚጨፈጨፍ ቅጠል።
ተጫለጠ፡ ተጫረሰ፡ ተቃዳ፡ ተረረ።
ተጫሚ፡ የሚጫማ።
ተጫማ፡ (ተሥእነ)፡ ጫማ ለበሰ፡ አጠለቀ፡ ኹለት እግሩን ከጫማ አገባ (ኤፌ ፮፡ ፲፭)።
ተጫረ (ተጽሕረ): ተወረ፡ ተቈፈረ፡ ተኳተ፡ ተፋረ፡ ተጐደፈረ፡
ተበተነ።
ተጫረ: ተዛቀ፡ ተወሰደ ፍሙ።
ተጫረ: እሳትን ተበዳደረ።
ተጫረሰ: ተጋደለ፡ ተላለቀ።
ተጫረተ: ተፈካከረ፡ ተበላለጠ፡ በ፲፡ በ፭፡ በ፻፡ በ፶ እሰጥ አክል እምር፡ ተባባለ፡ በግዥ ዋጋ ተለያየ።
ተጫራች (ቾች): የተጫረተ፡ የሚጫረት፡ ተበላላጭ፡ ተፈካካሪ።
ተጫቈነ: ተጫጫነ፡ ተፈቀ።
ተጫነ፡ (ተጽዕነ)፡ ጭነትን፡ ኮርን ተሸከመ።
ተጫነ፡ በሸክምነት በላይ በተሸካሚነት፣ በታች ኾነ፡ ተከመረ፡ ጨቈነ፡ ከበደ። "እከን፡ እርጅና፡ እንቅልፍ ተጭኖታል" እንዲሉ። (ተረት) "ሰው ይውደድኸ፡ ድንጋይ ይጫንኸ። "
ተጫነ፡ በከብት፡ በማንኛውም ነገር ተቀመጠ። (ሽለላ)፡ "ግፉ በዛ ግፉ በዛ፡ በመርኩ ተጭኖ ሐበሻ ሊገዛ። "
ተጫነ፡ ባጋሰስ ዠርባ መጣ፡ ኼደ፡ እኸሉ፡ ዕቃው። (ተረት) "ነገር ቢበዛ፡ ባህያ አይጫንም። "
ተጫነቀ፡ (ተጻዐቀ)፡ ተጣጋ፡ ተጣ፡ ተፋተገ፡ ተጋፋ።
ተጫናቂ፡ (ተጻዓቂ)፡ የሚጫነቅ፡ ተጣባቢ፡ ተጋፊ።
ተጫን፡ የሰው ስም፡ "ጠላትን ቍን፡ ክበድ" ማለት ነው።
ተጫኝ፡ የተጫነ፡ የሚጫን፡ ኀይለኛ።
ተጫወተ (ተጻወተ)፡ ሥጋዊና መንፈሳዊ ነገር ተናገረ፡ ተላፋ፡ ዘፈነ፡ አዘመረ፡ አላገጠ። "እከሌ በእከሌ ተጫወተበት" እንዲሉ። "የሀብታም ልጅ ሲጫወት የድኻ ልጅ ይሞት። "
ተጫዋች፡ (ቾች)፡ የተጫወተ፡ የሚጫወት፡ ዘፋኝ፡ አዝማሪ፡
አማሪት፡ ገንቦኛ፡ አረኾ።
ተጫዋች: ኰመኰመ።
ተጫጨ (ተሓፀየ): ተፈላለገ፡ ተፈቃቀደ፡ የጋብቻ ውል ተዋዋለ።
ተጫጨደ: ተቋረጠ፡ ተጣረገ።
ተጫጫሰ: ተፋፋመ፡ ተያያዘ፡ በዛ፡ በረታ ጠቡ።
ተጫጫነ፡ ተሸካከመ፡ ተካበደ። "ክረምቱ ተጭኗል፡ እከሌን እንቅልፍ ተጭኖታል" እንዲሉ።
ተጫፈረ: ተዛለለ፡ ተቃረበ፡ ተያያዘ፡ ተቀናጀ።
ተጫፈቀ: ተጣጋ፡ ተጫቈነ።
ተጫፋሪ: የሚጫፈር፡ ተያያዥ ንግግር።
ተጭቈነቈነ: እንደ ጭቍኝ ቅጠል ኾነ፡ ተጣበበ።
ተጭበሰበሰ፡ አላይ አልነድ አለ፡ በሽተኛ ዐይን፡ ርጥብ ዕንጨት።
ተጭበረበረ፡ እንደ ጕጕትና እንደ ሌት ወፍ ኾነ፡ ብርሃን ማየት አቃተው፡ ተሳነው።
ተጭበረበረ፡ እውነት እያለው የሌለው መሰለ፡ ተሳሳተ፡ ተደናገረ።
ተጭፈነፈነ: ተጭበሰበሰ።
ተጮኸ፡ ቍቁ ውይ ተባለ፡ ድረሱልኝ ለማለት፡ ለማልቀስ፡ እንባ ለማፍሰስ። (ጥጮ) "ቢጮኸ ኦሮ" እንዲሉ።
ተጯጯኸ፡ ጩኸትን ተቀባበለ፡ ተፋጀ።
ተጰጰሰ: ጳጳስ ሆነ፣ ተሾመ።
ተጸለለ: ጨለመ፣ አላዋቂ ኾነ።
ተፀረረ፡ ተሠራ፡ ተለበሰ፡ ፅሩሩ።
ተፀረረ፡ ተጠረረ፡ ፅሩር፡ ለበሰ፡ ሰዉ።
ተፀነሰ (ተፀንሰ)፡ ተጠነሰ፡ ተጠነሰሰ፡ በሆድ፡ ቀረ፡ ታቈረ፡
ተቋጠረ፡ ተረገዘ።
ተጸናና (ተጻንዐ)፡ ተበረታታ።
ተጸጸተ፡ ተጠጠተ፡ ተቈጪ፡ ዐዘነ፡ ምነው፡ ባልሠራኹት፡
አለ።
(ተረት)፡ አንድ፡ ቀን፡ ቢስቱ፡ ዓመት፡ ይጸጸቱ።
ተጸፋ (ተጸፍዐ፡ ተጠፍሐ)፡ በጥፊ፡ ተመታ፡ ፊቱ፡ ተዜመ፡ ተባለ፡ ጽፋቱ።
ተፃረረ፡ ተጣላ።
ተፃራሪ፡ የተፃረረ፡ የሚፃረር፡ ተጣይ።
ተጻብኦ፡ ሕልመ ዝሙት፡ የፍትወት ጦርነት፡ ሶፍያ።
ተጻብኦ: (ጸብአ፡ ተጻብአ) - መጣላት፣ መዋጋት፣ ወይም ሩካቤ ሕልም ነው።
ተጻጻፈ (ተጻሐፈ)፡ ደብዳቤ፡ ተመላለሰ፡ ተላላከ፡ ተቀባበለ፡
በወረቀት፡ ተነጋገረ።
ተጻፈ (ተጽሕፈ)፡ ተጣፈ፡ ተከተበ፡ ታተመ።
ተጽናና፡ ሐዘኑን፡ ተወ፡ ተረጋጋ፡ ተጥናና።
ተፈለመ: ተቀደመ፡ ተዠመረ፡ አስቀድሞ ተወጋ፡ ቈሰለ።
ተፈለሰ: ፈለሰ፡ ተመነቀረ፡ ፈረሰ።
ተፈለሰፈ: ተጠባበ፡ ተራቀቀ፡ ተፈተነ፡ ተመረመረ፡ ተዘጋጀ፡
ተከወነ፡ ተደረገ፡ ጐላ፡ ተረዳ፡ ወጣ፡ ጥበቡ፡ ብልኀቱ።
ተፈለቀ: ተቀደደ፡ ተሠነጠቀ።
ተፈለቀቀ: ላላ፡ ተከፈተ።
ተፈለቀቀ: ተፍታታ፡ ተበተነ።
ተፈለገ: ተሻ፡ ተፈቀደ (ኢሳ፷፭፡ ፩)።
ተፈለገ: ተከፈለ፡ ተሠነጠቀ።
ተፈለጠ (ተፈልጠ፡ ተፈልጸ): ተሠነጠቀ፡ ተሠነጠረ፡ ተሰበረ፡ ተፈነከተ፡
ተሸነሸነ።
ተፈለፈለ: ተማሰ፡ ተፈረፈረ።
ተፈለፈለ: ተቀረጸ፡ ተሰረሰረ፡ ተበሳ፡ ተነደለ።
ተፈለፈለ: አማረ፡ ሸበረቀ፡ የመልክ ያያል።
ተፈለፈለ: ከአንቍርባ፡ ከቂንድ ተለየ፡ ተቀፈቀፈ፡ ወጣ፡ ተወለደ።
ተፈላለመ: ተቀዳደመ፡ ተዠማመረ።
ተፈላለገ: ተፈቃቀደ።
ተፈላለጠ: ተሠነጣጠቀ፡ ተፈነካከተ።
ተፈላላጊ: የሚፈላለግ፡ ተፈቃቃጅ።
ተፈላሚ: የሚፈለም፡ ተዠማሪ።
ተፈላቀቀ: ተለያየ፡ ተፈራቀቀ፡ ተላቀቀ።
ተፈላጊ (ዎች): የሚፈለግ ልብስ፡ ጕርሥ፡ ሌላም ነገር። ፈረስ ለጦርነት፡ በቅሎ ለጌትነት፡ በሬ ለስበት፡ ጥገት ለወተት። ያደን ለት ውሻ፡ የሽብር ለት ጋሻ ተፈላጊ ነው። በዘመናችን ግን ተፈለገ፡ ተፈላጊ በማለት ፈንታ አስፈለገ፡ አስፈላጊ፡ ይህ ነገር ለኔ አስፈላጊዬ ነው፡ አስፈላጊ መስሎ ስለ ታየኝ እየተባለ በስሕተት ይነገራል፡ ይጻፋል።
ተፈላጊነት: ተፈላጊ መኾን።
ተፈላጭ: የሚፈለጥ ግንድ፡ ደንጊያ፡ ነገር።
ተፈልቃቂ: የሚፈለቀቅ።
ተፈልፋይ: የሚፈለፈል።
ተፈሰከ: ፋሲካ ኾነ፡ ተተወ ጦሙ፡ ተበላ ሥጋው (፪ነገ፡ ፳፫፡ ፳፪)።
ተፈሰፈሰ: ተመታ፡ ተደበደበ።
ተፈሳ: ቱስ አለ፡ ተንጣጣ፡ ተንጣረረ፡ ተንዛረጠ።
ተፈረመ: ተጻፈ፡ ተደረገ ፊርማው፡ ምልክቱ።
ተፈረቀ: ተለየ፡ ተከፈለ።
ተፈረቀቀ: ተፈነቀለ፡ ተፈለቀቀ፡ ተሠነጠቀ፡ ተለየ፡ ራቀ።
ተፈረነሰ: እንደ ልብ ተኛ፡ ተጋደመ፡ ተዘረረ፡ ተፈነደሰ።
ተፈረከሰ: ተሰበረ፡ ደቀቀ።
ተፈረካከሰ: ተሰባበረ።
ተፈረደ: ተበየነ፡ ታደለ ፍርዱ፡ እውነቱ ከሐሰት ተለየ።
ተፈረደ: ፍርድ ተቀበለ (፩ቆሮ፡ ፪፡ ፲፭)።
ተፈረደለት: ተበየነለት።
ተፈረደበት: ተበየነበት።
ተፈረደኝ: ተበየነልኝ።
ተፈረደኝ: የሰው ስም።
ተፈረጀ: ከሴቱ ወጣ፡ አገር ለወጠ፡ ያላየውን አየ፡ የደጋ ወይም የቈላ አየር ተቀበለ።
ተፈረፈረ: ተፈለፈለ፡ ተማሰ፡ ተቈፈረ።
ተፈረፈረ: ደቀቀ፡ ጠቀነ።
ተፈሪ መኰንን: የቀዳማዊ ዐጤ ኀይለ ሥላሴ ባማርኛ መጠሪያ ስም። ዐሰበ ብለኸ ዐስብን ተመልከት።
ተፈሪ በር: የተፈሪ በር፡ በውጋዴ ክፍል ያለ ቀበሌ።
ተፈሪ: የሰው ስም።
ተፈሪ: የተፈራ፡ የሚፈራ፡ የሚታፈር፡ ኀይለኛ ጐበዝ።
ተፈሪነት: ተፈሪ መኾን።
ተፈሪዎች: የሚፈሩ፡ የሚከበሩ ሰዎች።
ተፈራ (ተፈርሀ): ተጠረጠረ፡ ታፈረ፡ ከበረ፡ አልተደፈረም (ኤር፪፡ ፮)።
ተፈራ (ተፈርየ): ተፈጠረ፡ ተፀነሰ፡ ተገኘ፡ ተወለደ ፍሬው፡ ልጁ።
ተፈራ ወርቅ: ዝኒ ከማሁ።
ተፈራ: የሰው ስም።
ተፈራሚ: የሚፈረም ምልክት።
ተፈራረቀ (ተባረየ): ተረዳዳ፡ ተጋገዘ፡ ተራረፈ፡ ተለዋወጠ፡ ተዘዋወረ።
ተፈራረደ: ተበያየነ (ግብ ሐዋ፳፭፡ ፱-፲፡ ፳)።
ተፈራሪ: የተፈራራ፡ የሚፈራራ፡ ጕልበት እኩል (ትክክል)።
ተፈራራ: ተፋፈረ።
ተፈራራሚ: የሚፈራረም፡ የሚጻጻፍ።
ተፈራራቂ (ዎች): የተፈራረቀ፡ የሚፈራረቅ፡ ተለዋዋጭ፡ ተዘዋዋሪ ሌሊትና መዓልት፡ በጋና ክረምት፡ መናዝል፡ ሐዘንና ደስታ፡ ሹመትና ሽረት፡ ማጣትና ማግኘት፡ የመሰለው ኹሉ።
ተፈራቀቀ: ተላቀቀ፡ ተለያየ፡ ተራራቀ።
ተፈራቃቂ: የሚፈራቀቅ፡ ተለያዪ።
ተፈራከሰ: ተሳበረ፡ ተዳቀቀ።
ተፈርፋሪ: የሚፈረፈር።
ተፈቀረ (ተፈቅረ): ተወደደ፡ ወዳጅ ሆነ።
ተፈቂ: የሚፈቃ፡ ተበጪ።
ተፈቃ (ተፈቅዐ): ተቈራ፡ ተበጣ፡ ተሠነጠቀ፡ ተጋረጠ።
ተፈቃሪ: የሚፈቀር፡ የሚወደድ።
ተፈቃቀረ: ተሰማማ፡ ተኳዃነ።
ተፈቃቃሪ (ዎች): የተፈቃቀረ፡ የሚፈቃቀር፡ ተሰማሚ።
ተፈቃቃሪነት: ተሰማሚነት።
ተፈተለ፡ ተጠፋ፡ ተወዘገ፡ ተመዘዘ፡ ተሳበ፡ ተጠመረ፡
ተገመደ፣ ተጠመዘዘ።
ተፈተለከ፡ ተፈታ፡ ሾለከ፡ ወጣ፡ አመለጠ።
ተፈተረ፡ ታነቀ፡ ተጨነቀ፡ ተወጠረ።
ተፈተሸ፡ ተቀነቀነ፡ ተመረመረ፡ ተበረበረ።
ተፈተተ፡ ተቈረሰ፡ ተገመሰ፡ ተከፈለ፡ ተተነተነ።
ተፈተነ (ተፈትነ)፡ ተሞከረ፡ ተፈተሸ፡ ተመረመረ፡ ተጠየቀ፡
ተጠበሰ፡ ቀለጠ፡ ፈሰሰ፡ መከራ፡ ተቀበለ። ምሳሌ: ኢዮብ፡ ፯፡ ዓመት፡ ተፈተነ።
ተፈተነ: ቀለጠ፣ ነጠረ (ዘካ ፲፫፡ ፱)።
ተፈተገ: ተላጠ፡ ተመለጠ።
ተፈተገ: ተወቀጠ፡ ተሸከሸከ፡ ታሸ፡ ታጨደ።
ተፈተፈ: (ፈተፈተ) - እንደፈተፈ።
ተፈተፈተ፡ ራሰ፡ በጣት፡ ደቀቀ። ጠለቀ ብለኸ፡ ተጠለቀን፡ አስተውል።
ተፈታ: ቀረ፡ ተወገደ ግዝቱ።
ተፈታ: ተለቀቀ፡ ተተወ።
ተፈታ: ተሸነፈ፡ ድል ኾነ ጦሩ።
ተፈታ: ተባረታ አንደበቱ (ሉቃ፩፡ ፷፬)።
ተፈታ: ተተረተረ፡ ተከፈተ።
ተፈታ: ተገለጠ፡ ተተረጐመ።
ተፈታ: ተጸለየለት። (ግጥም): "በዳሞት ተልኳል፡ ጥናው ሲመጣ ነው፡ ተድላ ጓሉ ሙቶ ጐዣም ሊፈታ ነው። "
ተፈታ: ተፈቀደ (ዘሌ፲፩፡ ፳፩)።
ተፈታ: ጠፋ፡ ፈረሰ፡ ተሻረ፡ ተበተነ፡ ተበላሸ (ዮሐ፲፡ ፴፭)። (ተረት): "የሚፈታ ከተማ ነጋሪት ቢመታ አይሰማ። "
ተፈታሪ፡ የሚፈተር፡ የሚጨነቅ፡ የሚወጠር።
ተፈታሽ፡ የሚፈተሽ፡ ተመርማሪ።
ተፈታተነ፡ ተመራመረ፡ ፈተና፡ ተቀባበለ፡ በተንኰል፡
ተከታተለ፡ ተገዳደረ፡ ተወዳደረ፡ ይቻላል፡ አይቻልም፡ ተባባለ፡ (ዘፀ፲፯፡
፯፡ ሚል፫፡ ፲፭)።
ተፈታተገ: ተመላለጠ።
ተፈታታ: ደሙ ተበታተነ።
ተፈታታኝ፡ የተፈታተነ፡ የሚፈታተን፡ ተመራማሪ፡ ተከታታይ።
ተፈታች፡ የሚፈተት፡ ተቈራሽ።
ተፈታኝ፡ የሚፈተን፡ ተመርማሪ።
ተፈታይ፡ የሚፈተል ንድፍ፡ አምልማሎ።
ተፈታጊ: የሚፈተግ፡ የሚወቀጥ።
ተፈትሖ: መፈታት፡ መጽነን። "እመቤታችን በዚህ ዓለም ያለተፈትሖ ኖረች። "
ተፈች: የሚፈታ፡ የሚሸነፍ፡ ድል ዃኝ።
ተፈነ: ተካደነ፡ ተሻፈነ።
ተፈነቀለ: ተገለበጠ፡ ተለየ፡ ተቀረፈ (ናሖ፩፡ ፳)።
ተፈነቃቀለ: ተገለባበጠ፡ ተለያየ።
ተፈነተወ: ተጠረገ፡ ተገለጠ፡ ጠራ።
ተፈነቸረ: ተጣለ፡ ወደቀ፡ ተገደለ፡ ሞተ።
ተፈነከረ: ፈጽሞ ተገለጠ፡ ተከፈተ፡ ተዘረጋ መጻፉ።
ተፈነከተ: ተፈለጠ፣ ተከፈለ፣ ተገመሰ፣ ተሰበረ፣ ተተረረ።
ተፈነካከረ: ተገላለጠ፡ ተከፋፈተ።
ተፈነካከተ: ተፈላለጠ፡ ተገማመሰ፡ ተሰባበረ።
ተፈነደሰ: ተሠነጠቀ፡ ነቃ፡ ተፈነከተ።
ተፈነደሰ: ተኛ፡ ተጋደመ።
ተፈነዳደሰ: ተሠነጣጠቀ፡ ተፈነካከተ።
ተፈነጃጀረ: ተወለጋገደ፡ ተወነጋገረ።
ተፈነገለ: ተጣለ፡ ወደቀ፡ ተገለበጠ።
ተፈነጋገለ: ተጣጣለ፡ ተገለባበጠ (በቀኝ፡ በግራ፡ በፊት፡ በኋላ ተፈነገለ)፡ ሥሩ ተቃረበ፡ ጫፉ ተራራቀ።
ተፈነጠረ: ተለየ፣ ወጣ፣ ዘለለ (ዓሞ፫፡ ፭)።
ተፈነጠቀ: ተረጨ፣ ተነዛ፣ ተበተነ፡ ዐልፎ ዐልፎ ወደቀ፣ ተዘራ።
ተፈነጠዘ: ተለበሰ፡ ተጌጠ፡ ኾነ፡ ተደረገ ደስታው፡ ፈንጠዝያው።
ተፈነጣጠረ: ተበታተነ።
ተፈነጣጠቀ: ተረጫጩ፡ ተበታተነ።
ተፈና: ተዛለለ።
ተፈናቀለ: ተገላበጠ፡ ተለያየ። "አቶ እከሌ ሰካር ስለ ኾነ ከሥራው ተፈናቀለ። "
ተፈናቃይ: የሚፈናቀል፡ ተገላባጭ።
ተፈናከተ: ተፋለጠ፡ ተጋመሰ፡ ተሳበረ።
ተፈናጀረ: ተለያየ፡ ተራራቀ፡ ተጣመመ።
ተፈናገለ: ተዋደቀ።
ተፈናጠረ: ተሳቀለ፡ ተንጠላጠለ።
ተፈናጠረ: ተዛለለ፡ ተወራወረ።
ተፈናጠረ: ተዛራ፡ ተባተነ።
ተፈናጠቀ: ተረጩ (ተፈነጠቀ)።
ተፈናጠጠ: ከዳራ በስተኋላ በወዴላ ላይ ተቀመጠ።
ተፈናጣሪ: የሚፈናጠር፡ ተዛላይ፡ ፌንጣ።
ተፈናጣቂ: የሚፈናጠቅ (ተፈንጣቂ)።
ተፈናጣጭ: የተፈናጠጠ፣ የሚፈናጠጥ።
ተፈናፈነ: ተነፋነፈ፡ ተወላዳ፡ ተዛመረ።
ተፈንቃይ: የሚፈነቀል፡ ተገልባጭ።
ተፈንካች: የሚፈነከት፡ ተፈላጭ።
ተፈንጋይ: የሚፈነገል፡ የሚወድቅ፡ በተቀመጠበት የማይረጋ።
ተፈንጣቂ: የሚፈነጠቅ፣ ተረጪ።
ተፈከረ፡ ተፎከረ: ተገለጠ፡ ተነገረ፡ ተቈጠረ ሞያው፡ ግዳዩ፡ ተደነፋ።
ተፈካከረ፡ ተፎካከረ (ተቃሐወ): ተወዳደረ፡ ተከራከረ፡ ተቀታተረ፡ ማን ከማን አንሶ ተባባለ።
ተፈካካሪ፡ ተፎካካሪ (ዎች): የተፈካከረ፡ የተፎካከረ፡ የሚፈካከር፡ የሚፎካከር፡
ተወዳዳሪ፡ ተከራከሪ።
ተፈወሰ: ታከመ፡ ዳነ፡ ፈውስ አገኘ (ሉቃ፲፫፡ ፲፬) (የዳነ)።
ተፈዋሽ: የሚፈወስ፡ ድኅነት ፈላጊ (የሚፈወስ)።
ተፈየደ: ተረባ፡ ተጠቀመ።
ተፈደነ: ታሰረ፡ ተወደነ፡ ተቀፈደደ (የታሰረ)።
ተፈዳፈደ: ተባዛ፡ ተባለጠ (የተባዛ)።
ተፈጀ: ተጨረሰ፡ ዐለቀ፡ ተጠነገደ፡ ተገደለ (ዘዳ፴፪፡ ፳፬) (መጨረስ ወይም መጥፋት)።
ተፈጃጀ: ተወራረሰ፡ ተላለቀ (መተላለቅ)።
ተፈገመ: በግንባሩ ወደቀ፡ ተደፋ (መደፋት)።
ተፈገፈገ: ተፋቀ፡ ተጠረገ (የተፋቀ)።
ተፈጋፈገ: ተሸጋሸገ፡ ተራራቀ (መራራቅ)።
ተፈጋፈገ: ተፋፋቀ፡ ተጣረገ (መፋፋቅ)።
ተፈጋፋጊ: የሚፈጋፈግ፡ ተሸጋሻጊ (የሚሸጋሸግ)።
ተፈጠመ (ተፈጸመ፣ ተፈፅመ): በዚህ ቀን እቀርባለኹ፡ ወይም ኹለተኛ አልደርስም፡ ንጉሥ ይሙት በማለት ነገሩ ተጨረሰ፡ ዐለቀ፡ ተዘጋ (የተጠናቀቀ)።
ተፈጠረ: ተገኘ፡ ተሠራ፡ ተደረገ፡ ተወለደ።
ተፈጠረቀ: ፈነዳ፡ ወጣ።
ተፈጠፈጠ: ተፈነከተ፣ ቈሰለ (፪ዜና ፳፭፡ ፲፪፡ ሆሴ፲፡ ፲፬፡ ፲፫፡ ፲፮)።
ተፈጣሚ: የሚፈጠም፡ የሚዘጋ (የሚዘጋ)።
ተፈጣጠመ: ተቃጠረ፡ ልጄ እከሊትን ለእከሌ ልጅ ሰጠኹ፡ እኔም ተቀበልኹ፡ ንጉሥ ይሙት ተባባለ፡ ተዋዋለ (መዋዋል ወይም መቃጠር)።
ተፈጣጠረ: ተሠራራ፡ ተደራረገ።
ተፈጣጣሚ: የሚፈጣጠም፡ ተዋዋይ (የሚዋዋል)።
ተፈጥሮ: መፈጠር፡ ባሕርያዊ ግብር።
ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውም።
ተፈጨ (ተፈጽሐ): ተከካ፡ ተከረተፈ፡ ተሸመሸመ፡ ደቀቀ፡ ተሰለቀ፡
ተዳሰ
(የተፈጨ ወይም የተደቀቀ)።
ተፈጸመ: በቃ፡ ብቃት አገኘ።
ተፈጸመ: ዐለቀ፡ ተጨረሰ፡ መላ ሞላ፡ ደረሰ።
ተፈጻሚ: የሚፈጸም፡ የሚጨረስ።
ተፊ: (ተፋኢ) - የተፋ፣ የሚተፋ፣ አስታዋኪ።
ተፊታ: የምትተፋ ሴት።
ተፊያፊያዘ: ተዋዛ፡ ተላገጠ።
ተፊያፊያጠ: ተቃለደ።
ተፋ: (ተፍኦ) - እንደተፋ።
ተፋለመ: ተጋራ፡ ተካፈለ።
ተፋለሰ: ተሳሳተ፡ ተቃወሰ፡ ተዛወረ፡ ተዛነቀ፡ ተዘባረቀ፡
ተለዋወጠ።
ተፋለሰ: ተጣላ፡ ተገተ፡ ተከራከረ፡ ተማታ፡ ተዋለቀ።
ተፋለቀ: ተፋሰሰ፡ ተገናኘ፡ ተዘዋወረ፡ ተላለፈ።
ተፋለገ: ተፋቀደ።
ተፋለጠ: ተፈናከተ። በግእዝ ግን ተለያየ ማለት ነው።
ተፋላሚ: የተፋለመ፡ የሚፋለም፡ ተጋሪ፡ ተካፋይ።
ተፋሰሰ: ተሳሰበ፡ ተሳላ በባቄላ።
ተፋሰሰ: ተንጠባጠበ።
ተፋሰሰ: ተከናበለ፡ የደም ብድር ተከፋፈለ። "እከሌና እከሌ ደም ተፋሰሱ። "
ተፋሳሽ: የተፋሰሰ፡ የሚፋሰስ፡ የሚተሳስብ፡ የሚሳላ።
ተፋረ (ተፍሕረ): ተጫረ፡ ተቈፈረ፡ ተማሰ፡ ተጐደፈረ።
ተፋረመ፡ ተፈራረመ: ፊርማ ተጻጻፈ፡ ተቀባበለ፡ በፊርማ ተዋዋለ።
ተፋረሰ: የሽያጭን ንግግር ተከዳዳ።
ተፋረደ: ተባየነ (ኢሳ፵፫፡ ፳፮፡ መክ፮፡ ፲፡ ሕዝ፳፡ ፴፮፡
ማቴ፲፪፡ ፵፩፡ ፵፪)።
ተፋራ (ተፋርሀ): ተጠራጠረ።
ተፋራጅ: የተፋረደ፡ የሚፋረድ፡ ባለ ደም፡ የች ወገን።
ተፋቀ (ተፍሕቀ): ተወ፡ ተጠረገ፡ ተፈገፈገ፡ ተለየ፡ ተወገደ፡
ተላገ፡ ለዘበ፡ ከሳ (ዘሌ፡
፲፬፡ ፵፫)።
ተፋቀረ: ተዋደደ፡ ተስማማ።
ተፋቂ: የሚፋቅ፡ ተላጊ።
ተፋቃሪ: የተፋቀረ፡ የሚፋቀር፡ ተዋዳጅ።
ተፋተለ፡ ተቃጠረ፡ ተገናኘ።
ተፋተለ፡ ተጣመረ፡ ተጋመደ።
ተፋተረ፡ ተናነቀ፡ ተጫነቀ።
ተፋተተ፡ ተቋረሰ፡ ተካፈለ፡ ተተናተነ፡ ተሳተፈ።
ተፋተነ፡ ተከረ፡ ተፋተግ፡ ታገለ፡ ጕልበት፡ ለጕልበት፡
ተያየ።
ተፋተገ: ተላፋ፡ ተሻሸ፡ ተላላጠ።
ተፋታ (ተፋትሐ): ተለያየ፡ ተላቀቀ።
ተፋታ: ተተራጐመ።
ተፋታች: ተለያየች፡ ተላቀቀች (ከባሏ ቤት ወጣች)።
ተፋታጊ: የተፋተገ፡ የሚፋተግ፡ ልፊያ፡ ወዳድ።
ተፋቺ: የሚፋታ፡ የሚለያይ፡ ዐብሮ የማይኖር ባል።
ተፋከረ፡ ተፋከረ: ተደናፋ፡ ተቋጠረ፡ ተመላለሰ ግዳይን።
ተፋዘዘ: ፊት ለፊት ተኳዃነ፡ ተያየ፡ ተነጻጸረ፡ ዐይንን ከዐይን ለማሳበር (ፊት ለፊት መተያየት)። (ተረት): "እንቅልፍ ታበዢ፡ ከነብር ትፋዘዢ" (በንቁ መሆን አስፈላጊነት ላይ ያለ አባባል)።
ተፋዛዥ: የተፋዘዘ፡ የሚፋዘዝ (የሚፋዘዝ)።
ተፋጀ: ፈጀ፡ ተጨቃጨቀ፡ ተጯጯኸ፡ ተዋካ (መጨቃጨቅ ወይም መጣላት)።
ተፋጂ: የሚፈጅ፡ የሚፋጅ፡ አቃጣይ (የሚጨቃጨቅ ወይም የሚያነሳሳ)።
ተፋጠረ: ተሣራ።
ተፋጠነ: ተቻኰለ፣ ተጣደፈ።
ተፋጠጠ: ተጓረጠ፡ ተሳለፈ፡ ተፋዘዘ፡ ተቻኰለ፡ ተጣደፈ (መጣደፍ ወይም መቸኮል)።
ተፋጣኝ: የሚፋጠን፡ ሠራተኛና ሥራ።
ተፋጣጭ: የተፋጠጠ፡ የሚፋጠጥ (የሚፋጠጥ)።
ተፋጨ (ተፋጽሐ): ተፈጋፈገ፡ ተሳሳለ፡ ተንቀጫቀጨ (መጋጨት ወይም መጣላት)።
ተፋጯ (ተፋጸየ): ኾነ፡ ተደረገ፡ ፉጨቱ (የተደረገ ፉጨት)።
ተፋፈረ (ተኃፈረ): ተፈራራ፡ ተከባበረ።
ተፋፈገ: ተከማቸ፣ ተነባበረ፣ ተጠጋጋ፣ ተደራረበ፣ ተጨናነቀ።
ተፋፋመ (ተፋሐመ): ተበራታ፡ ተቃረበ።
ተፌ: ፈጣን፣ ቀልጣፋ ሰው።
ተፌ: ፈጣን፣ ተፈተፈ።
ተፌዘ: ኾነ፡ ተደረገ፡ ፌዙ፡ ተቧለተ።
ተፌጠ: ተቀለደ፡ ተቈጠ፡ ተለገጠ፡ ተፌዘ።
ተፍለቀለቀ: ሠገረ፡ ተንሸረሸረ፡ በሠጋር ኼደ።
ተፍለቀለቀ: ተብለጨለጨ፡ ተብረቀረቀ።
ተፍለቀለቀ: ፈላ፡ ተንተከተከ፡ ዘለለ፡ ጨፈረ።
ተፍለከለከ: ተንቀሳቀሰ፡ ተስለከለከ፡ ልውጣ ልውጣ አለ ዐልቅቱ፡ ዓሣው፡ የመሰለው ኹሉ።
ተፍሳሳ: መላልሶ ተፈሳ፡ ልማዱ ግን ፈሳ ነው።
ተፍረመረመ: ተወዘወዘ፡ ተነከሰ፡ ተበላ፡ ተጋጠ፡ ተነፈነፈ።
ተፍረመረመ: ተጋ፡ ተጣጣረ፡ ተፍጨረጨረ።
ተፍረመረመ: ተፍጨረጨረ፣ ፈረመ።
ተፍረምራሚ: የሚፍረመረም፡ ተጣጣሪ፡ ተፍጨርማሪ።
ተፍረቀረቀ: ተሰባበረ በብዙ ወገን።
ተፍረቀረቀ: ነፈረቀ፡ መገለ፡ ተፍረጠረጠ።
ተፍረከረከ: ተፈረፈረ፡ ተሸራረፈ፡ ፈራረሰ፡ ተቅረፈረፈ።
ተፍረገረገ: ተቅዘመዘመ፡ ተረገረገ፡ ተወዘወዘ።
ተፍረጠረጠ: ተድፈጠፈጠ።
ተፍተለተለ፡ ቅሌን፡ ጨርቄን፡ አለ፡ ሰበብ፡ አበዛ፡
በቀስታ፡ ኼደ፡ ፍጥነት፡ ዐጣ፡ ተጐተተ።
ተፍተለተለ፡ ታሸ፡ ወጣ፡ ተጥመለመለ።
ተፍተልታይ፡ የሚፍተለተል፡ ተጐታች።
ተፍተፍ አለ: ፈጠን ፈጠን አለ።
ተፍተፍ: ፍጥነት ችኰላ ።
ተፍታታ: ተበተነ፡ ተዘረዘረ የደም፡ የነገር።
ተፍታፊ: የተፈተፈ፣ የሚተፈትፍ (በጪ፣ ቈራጭ)።
ተፍነከነከ: ተደሰተ፡ በደስታ ተወዘወዘ።
ተፍነዘነዘ: ተቅነዘነዘ፡ ተክነፈነፈ፡ ተክለፈለፈ፡ ተወዘወዘ፡
ታወከ፡ ሮጠ።
ተፍጃጀ: በብዙ ወገን ወጪ ኾነ፡ እጅ በዛበት (ብዙ ወጪ መደረጉ)።
ተፍገመገመ (ተንተነ): ተንገደገደ፡ ተርገደገደ (መወዛወዝ ወይም መንገዳገድ)።
ተፍገመገመ: ተንገደገደ፡ ፈገመ ።
ተፍገምጋሚ: የሚፍገመገም፡ ተንገድጋጅ (የሚወዛወዝ)።
ተፍገረገረ: ተጠንቅቆ ሠራ፡ ተጣጣረ፡ ተትኰረኰረ፡ ጫተረ፡ ከችግር ለመውጣት ለመዳን ተፍጨረጨረ (መታተር ወይም መጣጣር)።
ተፍገረገረ: ተጣመረ፡ ተዋሰበ (የተጣመረ)።
ተፍገርጋሪ: የሚፍገረገር፡ ተዋሳቢ (የሚታተር)።
ተፍጨረጨረ: ፈጽሞ ተጋ፡ ታተረ፡ ተትኰረኰረ።
ተፍጨርጫሪ: የሚፍጨረጨር፡ የሚተጋ።
ተፎነነ: ተሠነጠቀ፡ ተቈረጠ፡ ተጐረደ፡ ዐጪር ኾነ።
ተፎናኝ: የሚፎነን፡ ተቈራጭ፡ ተጐራጅ።
ተፎጠረ: ታሰረ፡ ተሸበበ።
ተፎፌጥ: በፉጨት ተጣራ፡ ተጠራራ (በፉጨት መጥራት)።
ቱ: "እንስትን ከተባት ለመለየት የሚነገር ዝርዝር። ፈረስ፡ ፈረሲቱ፡ በግ፡ በጊቱ፡ ፍየል፡ ፍየሊቱ። በራብዕና በኃምስ በሳብዕ በሚጨርስ ስም ግን ዪቱ ይላል። ቷን ቀን ተመልከት።"
ቱሊ: ተረፈ ኵስሕ። "ቱኒን እይ።"
ቱሊያም: ቱሲ ያለበት፣ ባለቱሊ።
ቱልቱላ: ታሞ፣ ተራራ፣ ተመመ።
ቱልቱላ: ከተንድ ከንሓስ የተበጀ ናሽ የድምፅ መሣሪያ (ውስጠ ክፍት ሰው መጥሪያ መሰብሰቢያ) ።
ቱልት (ቶች) ፡ የቅጠል ስም (ሥሩዐለንጋ የሚመስል ማላጋ ቅጠል - ጠንቋዮች "የምድር ዐለንጋ" ይሉታል) ።
ቱማታ: የብዙ ሰው ጩኸት፣ ፍጅት፣ ውካታ፣ መጫጝ።
ቱማታ: የጨበጣ ውግ፣ ወግቶ ማሽቀንጠር።
ቱማታ: ገዳይ። "በቱማታ የሚገድል ሐርበኛ እንዳቶ በዛብኸ ያለ ጨካኝ ጐበዝ።"
ቱምቢ: የግንብ ጠርዝና ማእዘን (ያዲስ ሕንጻ ማስተካከያ ብረት ወይም ርሳስ ፉበቀጪን ገመድ የተያዘ) ።
ቱስ አለ: ሳይሰማ ተፈሳ፣ ቶሰቶሰ።
ቱስ አለ: ተፈሳ፣ በታች ተተነፈሰ።
ቱስ ያለ: "ዘረጥ ሳይል አይቀርም" እንዲሉ።
ቱስኪያም: ፈሳም (የሚያስመልስ ሰው)።
ቱስክ አለ: ቶሰከ።
ቱስክ: ድምጽ የለሽ ፈስ።
ቱረባ: ውስወሳ፣ ሽድሽዳ።
ቱሪናፋ: (ተረፋ) የማይረባ ወታደር፣ ሰነፍ።
ቱር አለ: (ሰረረ) ተነሣ፣ በረረ።
ቱር አለ: እጅግ ነጣ፣ ጸዐዳ ኾነ፣ ራዛ መሰለ።
ቱር: (ሰሪር፡ ነጺሕ) - መብረር ወይም መንሣት።
ቱርብ: የተቶረበ፣ ውስውስ፣ ሽድሽድ፣ ሽልል፣ ሽክሽክ፣ መናኛ ስፌት፣ ከጥብቅ ስፌት ቀዳሚ።
ቱርክ ባሻ: ማዕርጋቸው፣ ታምሬ ስማቸው (የዐፄ ምኒልክ ጋሻ ዣግሬ ነበሩ)።
ቱርክ: (ኮች) - የቱርክ ሰው ወይም ህዝብ።
ቱርክ: ባሻ (የቱርክ ባሻ) በምጥዋ የነበረ የቱርክ ጦር ሰራዊት አዛዥ ሻለቃ ባጤ ሠርጸ ድንግል ዘመን ዮናኤል የሚባል ሐርበኛ በሾተል ወግቶ የገደለው። ከዚህ በኋኋላ ይህ ስም ወደ ቤተ መንግሥት የገባ ይመስላል። ፓሻንና ባሻን ተመልከት።
ቱርክኛ: የቱርክ ቋንቋ።
ቱቢት (ዐረ፡ ቱቤት)፡ ጥቍር የሐሀን ልብስ ሥራ ካባ (ከባሕር የመጣ) ።
ቱባ: ሙሉ የባሕር ድር ማግ ጥለት ሐር፣ ጉድለት የሌለበት።
ቱቦ: ከሰሚንቶና ከአሸዋ የተበጀ አሸንዳ፣ ሰፊና ጠባብ፣ ቦምባ፣ የውሃ መውረጃ ፉካ። ቱቦ ጣሊያንኛ ነው።
ቱኒ፡ ፈሪ በከን ።
ቱኒ: ፈስ (ዘሩ "ተነነ" ነው) ።
ቱኒያም: የቱኒ ባለቱኒ ፈሳም።
ቱንቢ: አድማስ ቱምቢ ።
ቱኪ: (ኳደሬ) የጭቃ ሹም፣ ተወራጅ፣ ተከታይ፣ ዕግት ተሸካሚ።
ቱኪ: የጭቃ ሹም ተወራጅ።
ቱግ አለ: በፍጥነት ነደደ፣ ተቈጣ።
ቱግታ: የችቦ አበራር።
ቱፌ: የወተት መና ቀዳዳ ውታፍ (በነቀሉት ጊዜ በነፋስ ኃይል ወተት ወይም ቅቤ የሚተፋ) ።
ቲ: ምእላድ። "ፀጕል፡ ፀጕለቲ፡ ፉን፡ ፉነቲ።"
ቲሃ: (ተዪህ፡ ቴሀ)።
ቲርማ: ጅር የዝንጀሮ ጓዝ ።
ቲቲቲ አለ: በጎችን ለውጊያ አዘዘ፣ አተማተመ።
ቲቲቲ: አውራ በግን ለማዋጋት እረኛ የሚያሰማው ድምፅ።
ቲክ (ተየከ) ፡ መምላት መንተርፈፍ (ቲክ አለ" - ጢም እለ መላ) ።
ቲውሽ: (ተው፡ ወሽ) አህያን ለማገድና ለመከልከል የሚባል ቃል። እንቱሽን አስተውል።
ቲፍ አለ: መላ፣ ጢም አለ፣ ተርፎ እስኪፈስ።
ቲፍ አለ: በትንፋሽ ድምፅ አሰማ፣ ተጠነቀቀ (ፍየሉ)።
ቲፍ: መተንፈስ መምላት (ሲተነፍሱ ባፍንጫ ርጥበት ማውጣት) ።
ታ: "በሣልስ ቅጽል መጨረሻ እየገባ አንዳንድ ጊዜ ለሴት መለዮ ቅጽል በቂ ይኾናል። የፈሲታ፡ ተቈታ፡ ጠፍር፡ በሊታ፡ ብትኼድ፡ ልጓም፡ በሊታ፡ መጣች። ሣቂታ፡ ሰፊታ፡ እንዲሉ። የሳቢ ዘርም ምእላድ ሲኾን ረሳ፡ ርሳታ፡ ረዳ፡ ርዳታ፡ ዘነጋ፡ ዝንጋታ፡ ቸለለ፡ ቸልታ፡ ቀረ፡ ቅርታ፡ ዋለ፡ ውለታ፡ ቀደደ፡ ቅዴታ፡ ሰማ፡ ስሞታ፡ እያለ ይነገራል።"
ታ: "በራብዕ በሚጨርስ የ፪ና የ፫ ፊደል፣ ግስ ለሩቅ ሴት የቦዝ ዝርዝር። በላ፡ በልታ፡ ቀና፡ ቀንታ፡ ሠራ፡ ሠርታ፡ ዘነጋ፡ ዘንግታ፡ ዘረጋ፡ ዘርግታ። መጨረሻው ራብዕ ባልኾነ ግስ ሲገባ ሰጠ፡ ሰጥታ፡ ቀረ፡ ቀርታ፡ ይላል።"
ታ: (ትግ፡ ሐባ) የሩቅ ሴት ነባር አንቀጽ ናት፡ ነች። "ተኣምራትስ ይህታ፡ ሰንበትን መሻር ይህታ፡ እንዲሉ የሐዲስ ተርጓሞች። ዳግመኛም ይህች ናት ተብሎ ይተረጐማል።"
ታ: ምእላድ። ፍችው ማለት። "እግዚኦ፡ እግዚኦታ፡ ሃሌ፡ ሃሌታ፡ አወን፡ አወንታ፡ አል፡ ኣሉታ፡ ይሉኝ፡ ይሉኝታ።"
ታኅሣሥ: (ወር)።
ታለ: አይሰጥ (የሀብታም ንፉግ)፣ የሰረሰር ዐጥንት።
ታለለ: (ዕብ፡ ታላል)።
ታለለ: ቀለም ገባ፡ ተነከረ። (በደም ታለለ): ተዘፈቀ፡ ተለወሰ።
ታለለ: በደም ተነከረ፣ ሀለለ።
ታለመ: ታየ፡ ተገለጠ (ዕልሙ)።
ታለመ: ጠፋ፡ ወደመ፡ ታባ፡ ተሰወረ።
ታለበ (ተዐለመ): ኾነ፣ ተደረገ፣ ተጨመረ (ምልክቱ)።
ታለበ: ተሳበ፣ ተጐተተ (ጡቱ)፡ ወጣ፣ ፈሰሰ (ወተቱ)።
ታለበች (ተሐልበት): ተገናኘች፡ ወተቷ ላላቢ ተሰጠ።
ታለፈ: ተኼደ፡ ተዘለለ (መንገዱ፡ ሰዉ፡ ነገሩ)።
ታላላቆች: ዓሦች፣ ዓሣ ነባሪዎች። (ዘፍ. ፩፡ ፳፩)
ታላቄ: የታላቅ ወንድምና እት መጥሪያ፡ "የኔ ታላቅ" ማለት ነው።
ታላቅ: ትልቅ፣ የበለጠ፣ ላቀ።
ታላቅ: የሥጋ ስም፡ የኋላ እግር።
ታላቅነት: ታላቅ መኾን፡ ከፍተኛነት።
ታላቢ: የሚታለብ፣ የምትታለብ ጡቷ።
ታልማ: ታናሽ አንዠት፣ ለማ።
ታልማ: የወተት አንዠትና የጨጓራ መገናኛ ታናሽ አንዠት ጥቅል።
"ታልማው ፈሰሰ"
እንዲሉ። የታልማ ትርጓሜ
"ታለምልም፣ ታብራ"
ማለት ነው።
ታመመ (ተበሸተ): ታመመ (ዐመመ)።
ታመመ (ተአመመ): ተጀመረ፣ ተሠራ (ዐረሙ፣ ዕዳው፣ ቍፋሮው)።
ታመመ: በደዌ ዳኛ፡ ባልጋ ቁራኛ ተያዘ፡ ታማሚ ሆነ፡ ተበሸተ (፩ነገ፲፭፡ ፳፫፡ ፊልጵ፪፡ ፳፯)። "በ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. በግንቦት ወር የሰው ሁሉ ቀኝ ዦሮ ታመመ" (የታሪክ ማጣቀሻ)።
ታመመ: ዐዘነ፡ ተቈረቈረ።
ታመሰ (ተኀመሰ): አምስት ሆነ፡ ተከፋፈለ።
ታመሰ: ሞቀ፡ ተንቃቃ።
ታመሰ: ጪስ እንደ ገባው ንብ ታወከ፡ ተተራመሰ።
ታመረ (ተአመረ፣ ተአምረ): ምልክት ሆነ፣ ታየ፣ ታወቀ።
ታመቀ: ታበቀ፡ ተረጠጠ።
ታመተ (ተሐመተ): ነደደ፡ ተቃጠለ፡ ከሰለ፡ ዐመድ ሆነ።
ታመተ: ተመተረ፡ ተከተፈ።
ታመተ: ተጠበሰ።
ታመተ: ዐማት ሆነ ተባለ፡ ሆነች ተባለች።
ታመቸ: ዐማች ሆነ ተባለ።
ታመነ (ተአመነ): አመነ፣ ወደደ። “ጌታ አሽከሩን ታመነ” (ዘዳግም ፳፰፥፷፮፡ ኢሳይያስ ፳፮፥፲፬፡ ፊልጵስዩስ ፫፥፫)። "ታመነን" "አመነ" ብሎ መተርጎም ልማዳዊ ስሕተት ነው።
ታመነ (ተአምነ): ተወደደ፣ ከበረ፡ ተወከለ (አሽከሩ፣ ሎሌው)።
ታመነ (ተዘለነ): ተዘለነ፣ ተዘለለ፡ ሐሳቡን ጣለ፡ “ምን አለብኝ” አለ።
ታመደ: ታመተ፡ ዐመድ ሆነ፡ ተቈረጠ።
ታመገ: ተሰበሰበ፡ ተከማቸ፡ ተመሰገ (ጅብ አለ)።
ታመፀ: ተከዳ፡ ተገፋ፡ ተበደለ።
ታሚ: የሚታማ፡ ስሙ በክፉ የሚነሣ።
ታማ፡ ገማ፣ ሸተተ። ለምሳሌ፣
"ቃናው ተለወጠ"
እንዲሉ።
ታማ: ሻገተ፡ በሰበሰ፡ ሸተተ፡ ገማ። "ደነበሸን" እይ።
ታማ: በሰበሰ፣ ተለወጠ፣ ተበላሸ። "ጥጥ ለበሰ (ኢያሱ ፱፡ ፲፪)።"
ታማ: ተነቀፈ፡ ተሰደበ። (ተረት): "ባልንጀራኸ ሲታማ የኔ ብለኸ ስማ" (የራስ ጉዳይ እንደሆነ ያህል በትኩረት አዳምጥ)።
ታማለች: አርግዛለች፡ ፀንሳለች (ዘፍ፫፡ ፲፮)። "ያማታል": ምግብ አይስማማትም፡ ያስታውካታል፡ ቅሪት ስለ ሆነች (ስለፀነሰች)።
ታማሚ (ሐማሚ): የታመመ፡ የሚታመም፡ ዕመምተኛ፡ ጤና ቢስ (፩ሳሙ፡ ፴፡ ፲፫፡ ማቴ፮፡ ፳፫)።
ታማቂ: የሚታመቅ፡ ተረጣጭ።
ታማኝ (ኞች): የታመነ፣ የሚታመን፣ የተወከለ፣ እውነተኛ፣ ጻድቅ፡ የማይጠረጠር። የማይታመን: ወስላታ ሰው።
ታማኝነት: እውነተኛነት፣ ርግጠኛነት።
ታምረ ማርያም: የማርያም ታምር ወይም መጽሐፍ።
ታምረኛ: ባለታምር፡ ጕደኛ፣ ድንቀኛ።
ታምረየስ (ተአምረ ኢየሱስ): የጌታችን የኢየሱስ ታምር፡ የመጽሐፍ ስም።
ታምር (ራት): ጕድ፣ ድንቅ፣ ምልክት፡ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ነገር፡ ሙት ማንሳት፣ ዕውር ማብራት። በግእዝ "ተአምር (ተአምራት)" ይባላል።
ታምሮች: ታምራት፡ ጕዶች፣ ድንቆች።
ታሞ አይድኔ: (ምሳሌያዊ አነጋገር፡ በሽታው የማይተው ወይም የማይድን)።
ታሞ: በመርሐ ቤቴ ውስጥ ያለ ተራራ።
ታሞ: ተበሽቶ፡ ዐዝኖ።
ታሠሠ (ተኀሠ): ተዞረ፡ ተሻ፡ ተፈለገ።
ታሠሠ: ተጠረገ፡ ተወለወለ፡ ታበሰ (ምጣዱ)። "በጭት ታሠሠ"፡ ታላቅ ጭንቅ ሆነ፡ ተደረገ (ታላቅ ችግር ደረሰ)።
ታሠረ (ተዐሠረ): ዐሥር ሆነ፡ ተባለ (ዐሥር ሆኖ ተቆጠረ)።
ታሰረ (ተአስረ): ተያዘ፣ ተጋዘ፣ ተቈረኘ፣ ተተበተበ፡ በፍቅር አንድ ሆነ፣ ጸና (፩ኛ ሳሙኤል ፲፰፥፩)። እግር ተወርች ታሰረ: እግሩ ከእጁ ጋር በአንድነት ተቀፈደደ። የፊጥኝ ታሰረ: ሁለት እጁ የኋሊት ተገረኘ።
ታሰቀ: ተጠለፈ፡ ተጌጠ፡ ተዥጐረጐረ (የተጌጠ)።
ታሰበ (ተሐሰበ): ተጤነ፡ ታወሰ፡ ትዝ አለ (ኢሳ፷፭፡ ፲፯፡ ግብ ሐዋ፲፡ ፴፩) (የታሰበ)።
ታሰበ: ታወሰ። "በትግሪኛ ግን ዘነበለ ማለት ነው።"
ታሳሪ: የተያዘ፣ የሚታሰር።
ታሳቢ (ተሐሳቢ): የሚታሰብ፡ የሚታወስ (የሚታሰብ)።
ታረመ (ተሐርመ): ተተወ፡ ተከለከለ፡ ተለየ፡ ተቀደሰ (ዘሌ፳፯፡ ፳፩) (የታረመ)።
ታረመ: ተቈረጠ፡ ተሰጠ መሬቱ (የተቆረጠ መሬት)።
ታረመ: ተነቀለ፡ ተኰተኰተ፡ ተወገደ ጸያፉ፡ ስሕተቱ፡ ግድፈቱ (የተነቀለ)።
ታረሰ (ተሐርሰ): ተተለመ፡ ተገመሰ፡ ተገለገለ፡ ተሰበተ፡ ታየመ፡
ለሰለሰ
(ሕዝ፴፮፡ ፱) (የታረሰ)። (ተረት): "በዱሮ በሬ አይታረስም" (ምሳሌያዊ አነጋገር)።
ታረሰች (ተኀረሰት): ተመገበች፡ ተቀለበች፡ በሚገባ በላች፡ ጠጣች (የተመገበች)።
ታረረ (ተአረ): ታጨደ፣ ተሰበሰበ፣ ተለቀመ፣ ተጠቀለለ።
ታረቀ (ተዐርቀ): ቀና፡ ቀጥ አለ (ቀጥ ማለት)።
ታረቀ: ጐበጠ፡ ተቀለሰ፡ ተለመጠ (ጐባጣ መሆን)።
ታረቀ: ጥልን ተወ፡ ተስማማ (መታረቅ ወይም መስማማት)። "፱ኛውን ወይ" እይ።
ታረበ: በላ፡ ተመገበ፡ ተጋበዘ (አድራጊ) (በላ)።
ታረበ: ተበላ፡ ወደ ሆድ ገባ፡ ወረደ እራቱ (ተደራጊ) (የተበላ)።
ታረተ: ታከበ፡ ተከበበ፣ ተጐረሰ፣ ተበላ፡ ተቀረቀበ፣ ታሰረ፣ ተወደነ፣ ተወቃ።
ታረተ: አራት ሆነ፣ ተባለ።
ታረዘ (ተዐረዘ፡ ለበሰ): ልብስ ዐረረበት፡ ተራቈተ (ኢዮ፳፬፡ ፲፡ ማቴ፳፭፡ ፴፰) (ልብስ ማጣት ወይም መራቆት)።
ታረዘ: ዐረቀ።
ታረደ (ተሐርደ): ተገዘገዘ፡ ተከረከረ፡ ተቈረጠ፡ ተቀረደደ ማንቍርቱ (የታረደ)። (ተረት): "ያባያ እናት አትታረድም" (ምሳሌያዊ አነጋገር)።
ታረደ: ተማሰ፡ ተጐደበ፡ ጐደጐደ (የተቆፈረ)።
ታረገ: ተወጣ፡ ወደ ላይ ተኼደ፡ ተኼደበት (ወደ ላይ የተወሰደ)።
ታረገ: ኣቡነ ዘበሰማያት ተባለ፡ ተጸለየ (ጸሎት መጸለይ)።
ታረፈ: ተቈረጠ፡ ዕራፊ ኾነ (የተቆረጠ)።
ታረፈ: ኾነ፡ ተደረገ ዕረፍቱ፡ ቍጭ ተባለ (ዕረፍት መሆን)።
ታሪከ ሙሴ: የሙሴ ታሪክ፣ ሙሴ ያደረገው ታምር፣ የጻፈው መጽሐፍ።
ታሪከ ታየ፡ እይ።
ታሪከ ነገሥት: የንጉሦች ታሪክ፣ የነገሥታትን ትውልድና ዘመን፣ አገዛዛቸውን፣ ሥራቸውን፣ ዕድሜያቸውን፣ በጊዜያቸው የኾነውን የተደረገውን የሚናገር መጽሐፍ (ክብረ ነገሥት)።
ታሪከ ዓለም: የዓለም ታሪክ፣ ጊዮርጊስ ወልደ ሐሚድ በግእዝ ቋንቋ የጻፈው።
ታሪከኛ: ታሪክ ያለው፣ ባለዝና፣ ስመ ጥር።
ታሪካም: ባለታሪክ፣ ታሪክ የሠራ፣ የሚያወራ።
ታሪክ: (ኮች) ዜና፣ ያለፈ ነገር፣ በቃል በመጽሐፍ ሲያያዝ የመጣ።
ታሪክ: ባላገሮች "ከጥንት ፍጥረት ስላልነበረ፡ አህያና ፈረስን በማራከብ በሰው ዘዴ ስለተገኘ፡ በምድራችን እንዲህ ያለ በቅሎ አያውቅም" ተብሎ ይላሉ። የስሙም ምክንያት ይህ እንደሆነ ይተርካሉ።
ታራ: ተኰሳ፡ ተዘበለለ፡ ወደቀ (የተደበደበ)።
ታራ: የሰው ስም፣ የአብርሃም አባት።
ታራሚ: የሚታረም፡ የሚነቀል (የሚታረም)።
ታራቂ (ተዐራቂ): ቀጥ የሚል፡ ተቀላሽ (የሚታረቅ)።
ታራቂ: የሚታረቅ፡ ተፋቃሪ (ያዕ፫፡ ፲፯) (የሚታረቅ ሰው)። (ተረት): "ካጣቢ አድራቋ፡ ከተጋች ታራቂ" (ምሳሌያዊ አነጋገር)።
ታራጅ: የሚታረድ፡ ሙክት፡ ፍሪዳ (የሚታረድ እንስሳ)።
ታራጅ: የአየር (የትንፋሽ) ወደ ሳንባ መመላለሻ ሥጋዊ ውዥሞ፡ ቀጪን ጕረሮ፡ ፈረንጆች ፋረንክስ ይሏታል (የጉሮሮ ክፍል)። (ሽለላ): "ነፋኝ ቀበተተኝ እታራጄ ድረስ፡ አምላኬ አትግደለኝ የልቤን ሳላደርስ" (የሽለላ ምሳሌ)።
ታሸ (ተሐስየ): ተለወሰ፡ ለፋ፡ ተዳመጠ፡ ዞረ፡ ተጠመዘዘ፡
ተደረጠ
(የታሸ)።
ታሸለ: ተጨመረ፣ ታከለ፡ ቀላ፣ ነጣ፡ ተለካ፣ ተከነዳ፣ ተቀጠበ።
ታሸመ: ተሠራ፡ ተጐነጐነ፡ ተደበለ (የተሠራ ሽሩባ)።
ታሸገ: በጥብቅ ተዘጋ፣ ተመረገ፣ ተደፈነ፡ ተፈረመበት (ታተመ)።
ታሻሚ: የሚታሸም ጠጕር፡ ራስ (የሚታሸም ጸጉር)።
ታቀበ (ተዐቅበ): ተጠበቀ፡ ተመላ፡ ተሠየመ (መጠበቅ)።
ታቀበ: ተጠጋ፡ ተደገፈ፡ ተሸፈነ፡ ተከለለ።
ታቀደ (ተዐቅደ): ተለካ፡ ተወሰነ (የታቀደ)።
ታቀፈ (ሐቀፈ): ዐቀፈ፡ ያዘ (፪ነገ ፬፡ ፲፮)። "ታቀፈን ዐቀፈ ማለት የስሕተት ልማድ ነው"። "ዐደገ (ኀደገ) ብለኸ ፪ኛውን ታደገ ተመልከት"።
ታቀፈ (ተሐቅፈ): ተያዘ፡ ታቈረ (በክንድ፡ በክንፍ) (የታቀፈ)።
ታቃፊ: የታቀፈ፡ የሚታቀፍ፡ ዐቃፊ፡ ሕፃን ያዥ (የሚታቀፍ)።
ታቈረ (ተዐቍረ): ተቋጠረ፡ ታቀፈ (የታቆረ)።
ታበለ (ተሐብለ): ተዋሸ፡ ውሸት ኾነ፡ ተቀጠፈ። (የማይታበል): ከውነት በቀር ሐሰት የማይኾን፡ ተነግሮ ሳይፈጸም የማይቀር፡ አይደርስም ተብሎ የማይጠረጠር (ያምላክ ቃል)።
ታበሰ: ተጠረገ፣ ተወለወለ።
ታበቀ (ተወጋ): ተወጋ።
ታበቀ: ደቀቀ፣ ታመቀ፣ ተመረጠ።
ታበበ: ተሰደበ፣ ተነቀፈ።
"በገበታ ላይ ትዝብትን፣ ነቀፋን ፈራ፡ ዳር ዳር አለ" (ምሳሌ ፳፫፥፲፫)።
ታበበ: ትዝብትን ፈራ (አበበ) ።
ታበተ: ተጠለፈ፣ ታሰረ፣ ተንጠለጠለ።
ታበዘ (ተኀብዘ): ተጋገረ።
ታበየ (ተዐበየ): ተቢተ፡ ከፋ፡ ተመካ፡ ተደገገ፡ ተጓደደ፡ ልቡ ዐበጠ፡ ተነፋ (በኵራት)፡ "እኔን ማን ያኸለኛል" አለ፡ ራሱን ከፍ አደረገ፡ ኰፈሰ (ኤር፵፰፡ ፳፱)።
ታበየ: ተደገገ ዐበየ ።
ታባ (ተኀብአ): ተሸሸገ፡ ተሰወረ፡ ተደበቀ።
ታባቢ: የታበበ፣ የሚታበብ፣ ባለይሉኝታ።
ታቦር: ጌታችን የአምላክነቱን ክብር ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ተራራ (በምድረ እስራኤል ያለ)።
ታቦተ ሕግ: በውስጧ ሕግ ያለባት ታቦት።
ታቦተ ሙሴ: የሙሴ ታቦት።
ታቦተ ጽዮን: በዳዊት ዐምባ የነበረች ታቦት። "ነብሪድ ይሥሓቅ ግን አኵስም መጥታለች ይላል።"
ታቦቲቱ: ታቦቷ፣ ያች ታቦት (፪ኛ ዜና መዋዕል፡ ፭ ' ፬፡ ፭)።
ታቦት ተሸካሚ: በራሱ ላይ ታቦት የሚይዝ ቄስ፣ መነኵሴ።
ታቦት፡ ተከለ)፡ ቤተ ክርስቲያን ሠራ።
ታቦት አነገሠ: "በወረብ፣ በዘፈንና በልልታ፣ በከበሮ፣ በጸናጽል፣ በጭብጨባ አከበረ፣ በቤተ ክሲያን ዙሪያ ሦስት ጊዜ አዞረ።"
ታቦት ወጣ: ነገሠ፣ ዑደት ተደረገ።
ታቦት ዘፋኝ: ለታቦት ስለ ታቦት የሚዘፍን።
ታቦት ዘፋኝ: ለታቦት የሚዘምር።
ታቦት ዘፋኝ: ስለ ታቦት የሚዘፍን የታቦት ዘፋኝ።
ታቦት: "ቁመቱ አንድ ክንድ ተስንዝር፣ ጐኑ አንድ ክንድ፣ ውፍረቱ ሦስት ጣት የኾነ የክርስቲያን ጽላት። ታቦት መባልን ከሣጥኑ ወስዷል። ስመ አምላክ አልፋ ወዖ፣ የመልአክ፣ የነቢይ፣ የቅድስት ማርያም፣ የሐዋርያ፣ የጻድቅ፣ የሰማዕት ስም ታቦተ እገሌ እየ ተባለ በላዩ ይጻፍበታል። በየማእዝኑ ጫፍ የአርባዕቱ እንስሳ ሥዕል ይቀረጽበታል። ከግብጽ መጥተው በአኵስም የነበሩት መዠመሪያዎቹ ታቦቶችም ታቦተ ማርያምና ታቦተ ሚካኤል ናቸው።" ታቦት: (ቶች)።
ታቦት: በራስ ላይ የተሣነ እጅ በሸኩቻ ጊዜ መዶሻን የሚረታ ትርፍ ተምሳሊት።
ታቦት: ጌታ፣ መኰንን፣ ባለቤት። "ታቦተ መልካም ዐጸደ ክፉ እንዲሉ። ዐጸድ የተባለ ቤተ ሰብ ነው።"
ታቦትኛ: የታቦት አካኼድ።
ታተመ (ተኀትመ): ማኅተም ተደረገበት፡ በመኪና ተጻፈ (የታተመ)።
ታተረ: ተጋ፣ ጣረ፣ ለፋ (በጥረትን አከናወነ)።
ታተበ (ተዐትበ): ተቈረጠ (የተቆረጠ)።
ታተተ (ተሐተ): ተመረመረ፡ ተተቸ (የተመረመረ)።
ታተተ (ተአተተ): ተወገደ፣ ራቀ፣ ተገለለ፣ ተለየ።
ታቱ (ታሕቱ): ታች፣ ሥር (የ'ቱ' ዝርዝርነት አባትን ያመለክታል)።
ታቱ ሥግራ አለ (ትግ ታተ): የልጅን እጅ ይዞ መንገድን መራ፣ መሄድን አስተማረ። (ተእቱ) "ትገባለህ" ተብሎ ይተረጎማል። (አቱን አስተውል)።
ታታ (ከተወተ፣ ትግ ተትዐ): ወንፊትን መረብን ሠራ፣ አልጋን ጠፈረ፣ ጠለፈ፣ አዋሰበ፣ አያያዘ፣ ሦስቱን ክር ወይም ገመድ ጐነጐነ። "የተፈተለ ከሁለት፣ የተታታ ከሦስት" እንዲሉ።
ታታሚ: የሚታተም መልክት፡ ማንኛውም ጽሑፍ (የሚታተም ጽሑፍ)።
ታታሪ (ታታሪዎች): የታተረ፣ የሚታትር፣ ጣሪ፣ ትጉህ።
ታታሪነት: ትጉህነት።
ታቹን: ጥግ ጥጉን፣ ሥር ሥሩን፣ ቈላ ቈላውን።
ታቼ: (የሰው ስም) "ታች" የሚል መጠሪያ ነው።
ታች (ታሕት፣ ተሐተ): ንኡስ አገብአብ፡ ጥግ፣ ሥር፣ ዝቅታ፣ ግርጌ። (በና ከ ሲሰማሙት) "በታች" "ከታች" ይላል።
ታች በላቸው: "ከብቶቹን ካፋፍ ወዳረኸ አውርዳቸው" ማለት ሲሆን፣ "ጠላቶቻችንን አዋርዳቸው፡ አንተ የበላይ፣ እነሱ የበታች ይሁኑ" የሚለውንም ያመለክታል።
ታች በሌ: (የሰው ስም) "ታች በል" የሚለውን የሚወክል ስም። (ታቼ የዚህ ከፊል ነው።)
ታች ቤት: በታች ያለ ቤት። (በጐንደር የበኣታ አጥቢያ፡ የሐዲስ መምህራን የነበሩበት)።
ታች አለ: ወደ ታች ነዳ፣ ቍልቍል ወሰደ።
ታችኛ (ታችኞች): የታች፣ የቈላ፣ በታች የሚኖር። "ታችኛው"፣ "ታችኛዋ"፣ "ታኛዪቱ"፣ "ታችኞቹ" እያለ ይዘረዝራል።
ታችኞች: ቈለኞች፣ አጋንንት፣ ኀጢአተኞች።
ታቾች: ጥጎች፣ ሥሮች፣ ግርጌዎች።
ታነቀ: በምግብ ተዘጋ ጕረሮው። (ተረት): "ሥሡ ሲበላ ይታነቃል፡ ሐሰተኛ ሲናገር ይታወቃል" (እውነት መደበቅ እንደማይቻል)።
ታነቀ: በገመድ፡ በጠፍር ዐንገቱ ታሰረ፡ ተፈተረ፡ ተሰቀለ፡ ተንጠለጠለ፡ ሲል አለ በገዛ እጁ ወይም በሌላ ሰው እጅ (መታነቅ)።
ታነደ: አንድ ሆነ፣ አንድ ተባለ።
ታነጠ: ተሠራ (ቤቱ)።
ታነጠ: ታነጸ (ተሐንጸ)፡ ተጠረበ፡ ተላገ፡ ተፈለፈለ፡ ተቀረጸ፡ ተበሳ።
ታኒካ (ዎች): ጋዝ ዘይት ፍት ቤንዚን ሌላም ቅባት በያይነቱ ከውጭ እገየሚመጣበት ሥሥ ቈርቈሮ (ትንሹ ጣሳ" ይባላል) ።
ታኒካ፡
የወርቅ ሰሌዳ (ዘፀ፡ ፳፰፡ ፴፮፣ ፴፰) ።
ታናሹ: የርሱ ታናሽ፡ ያ ታናሽ።
ታናሼ: የኔ ታናሽ፡ የበታቼ።
ታናሽ (ሥጋ): የሥጋ ስም፡ ከታወቁት ብልቶች አንዱ ዋነኛው። ግጥም: “ታናሽ ታላቅ በላን ከርካ አደባባይ፡ ክርስቲያን ሆይ አለልብ ሥጋ ይጣፍጣል ወይ?” ማስታወሻ: ይህ ግጥም አፄ ዮሐንስ “በግድ ቁረብ” ያሉት እስላም የገጠመው ነው ይባላል።
ታናሽ (ሾች): በቁሙ፣ በዕድሜ፣ በመጠን፣ በማንኛውም ነገር ከሌላው ያነሰና ዝቅ ያለ። ምሳሌ: “ታናሽ ወንድም”፡ “አባተ ታናሽ” እንዲሉ።
ታናሽ: በሚባለው የሥጋ ብልት ውስጥ የሚገኝ ቀይ ሥጋ፣ "በግእዝ ጸክ' ይባላል። እሱንም የእስራኤልና የአማራ ዘር አይበላውም። ዳግመኛም ስለ መንቀጥቀጡ ሥጋ ፈሪ ይሉታል።
ታናሽ: ትንሽ፡ በቁሙ፡ አነሰ ።
ታናሽነት: ታናሽ መሆን፡ ሕፃንነት፣ ልጅነት (መዝሙር ፻፳፱፥፩-፪)።
ታናሿ ታናሽቱ: ያች ታናሽ፡ የታላቅ እህት ተከታይ ሴት ልጅ (ዘፍጥረት ፲፱፥፴፩)።
ታናሿ: የርሷ ታናሽ።
ታናቂ: የሚታነቅ።
ታናናሽ (ሾች): ውስጠ ብዙ፡ ጥቃቅን። “ታናናሾች ልጆች”።
ታንቆ ሞተ: ዐንገቱን አስሮ ተንጠልጥሎ በገዛ እጁ ማለት ነው (፪ሳሙ ፲፯፡ ፳፫፡ ማቴ፳፯፡ ፭) (ራሱን ማጥፋት)።
ታንከኛ (ኞች): ታንክ ነጂ፣ ባለታንክ፣ ተኳሽ።
ታንክ (ኮች): የጦር መሣሪያ፣ ኪና፣ በጦርነት ሰዓት ብዙ ጥይት የሚተስ የሀረር ጋን። በ፲፱ኛው ሴክል በትልቁ ጦርነት ጊዜ ያወጡት እንግሊዝና ፈረንሳይ ናቸው ይባላል።
ታንኳ (ዎች): ከቀርክሓና ከሸንበቆ ከደንገል የተበጀ የባሕር መንገደኛበላዩ ተቀምጦ የሚሻገርበት (ማቴ፡ ፬፡ ፳፩፣ ፳፪)” ።
ታንጕት: የሴት ስም።
ታኘከ (ተሐንከ): ተቈረጠመ፡ ተመሰኳ፡ ተበላ (ቈሎው፡ ንፍሮው፡ ዐጥንቱ፡ ሣሩ፡ ቅጠሉ) (የታኘከ ወይም የተበላ)።
ታኘከ: ተበላ፣ ተጠጣ፣ ወይም ተሰማ።
ታኝ: (የተለየ ትርጉም አይገኝም፡ ምናልባት የቀደመ ቃል ወይም ቅጥያ ሊሆን ይችላል)።
ታከለ፣ ታከለች: የወንድና የሴት ስም።
ታከለ: ተጨመረ፣ ተደገመ፡ ልክ ሆነ። አልቃሽ: “እታከል ከግመል ከግዜር ጋራ ሞተኸ፡ ትቀረው የለሞይ እሑድ ተለይተኸ። ”
ታከመ: ታገመ፡ ሰውነቱ ታሸ፡ ተጠገነ።
ታከረ: ተለወጠ፡ ቈየ፣ ዘገየ፡ ታደሰ።
ታከበ: ተሰበሰበ፣ ተከማቸ።
ታከተ (ተሰበሰበ): ተሰበሰበ፣ ተከማቸ፣ ታረተ።
ታከተ (ተከተ): እንደታከተ።
ታከተ (ደከመ): ደከመ (ተ)።
ታከተ: ታረተ፣ አከተ።
ታከከ: ቀረበ፣ ተጠጋ።
ታከከ: ተላገ፣ ተፋቀ።
ታከከ: ተፈገፈገ፣ ተጠቈመ፣ ተጫረ።
ታካሚ: የሚታከም፡ ሕመምተኛ፡ በሽተኛ።
ታካታ: ለታካች ደካማ።
ታካች (ቾች): የታከተ፣ የሚታክት፣ ሰነፍ (ምሳሌ ፮፡ ፮፡ ፴)።
ታካችነት: ታካች መኾን፣ ስንፍና፣ ደካማነት።
ታካኪ: የሚታከክ፡ ተጠጊ።
ታኰተ (ተአኵተ): ተመሰገነ፣ ተባረከ፡ ተጸለየ፡ ጸሎቱ ሆነ፣ ተደረገ።
ታወሰ (ተሐውሰ): ታሰበ፡ ትዝ አለ።
ታወረ (ፆረ): ዐይኑ ጠፋ፡ ፈሰሰ፡ ዕውር ኾነ (ኢሳ፳፱፡ ፱፡ ሮሜ፡ ፲፩፡ ፯)።
ታወረ: ጥፍሩ ረገፈ፡ ጐለደፈ (የጣት)።
ታወቀ (ተዐውቀ): ተለመደ፡ ተለየ። (ተረት):
"የወፍ ወንዱ የሰው ሆዱ አይታወቅም። "
ታወከ (ተሀውከ): ፈራ፣ ደነገጠ፡ ተናወጠ፣ ተነቃነቀ፣ ተበጠበጠ፡ ተነሣሣ፡ ተሸበረ፣ ተተራመሰ (፪ኛ ነገሥት ፮፥፲፩፡ መዝሙር ፮፥፪-፫፡ ዮሐንስ ፮፥፲፰)።
ታወደ: ተዞረ (ቤተ ክሲያኑ)፡ ኾነ፡ ተደረገ (ዑደቱ)።
ታወጀ: ተነገረ፡ ተለፈፈ (ዐዋጁ)።
ታወገ (ተዐወገ): አላገጠ፡ አለመጠ።
ታዊ: ዝኒ ከማሁ ።
ታዋቂ: የሚታወቅ፡ የሚለመድ።
ታዋኪ: የሚታወክ፣ የሚሸበር።
ታዋጊ (ጎች): አላጋጭ፡ አልማጭ (፩ጢሞ፡ ፭፡ ፲፫)።
ታው: ስመ ፊደል ተ። "ትርጓሜው መጨረሻ ማለት ነው።"
ታዘለ (ተሐዝለ): በዠርባ ተለጠፈ፡ ተደረበ፡ ተያዘ፡ ሸክም ኾነ፡ ተፈናጠጠ።
"የታዘለ በለምድ፡ የተረገዘ በሆድ"
እንዲሉ።
ታዘበ (ተሐዘበ): አየ፡ ተመለከተ፡ መሰከረ፡ ዐሰበ፡ ጠረጠረ፡ ናቀ፡
ነቀፈ። "የማታደርገውን አደርጋለኹ ብትል ሰው ይታዘብኻል"
[ይባላል]።
ታዘበ: ተጐነጐነ፡ ተበጀ፡ ተሠራ።
ታዘበ: ተጠለፈ፡ ተቈለፈ (ኹሽ)።
ታዘበ: ጠረጠረ፡ ዐዘበ ።
ታዘብኩሽ ቂጤ: ናቅኹሽ፡ ነቀፍኩሽ።
ታዘነ (ተሐዝነ): ተተከዘ፡ ተለቀሰ፡ ኾነ፡ ተደረገ (ሐዘኑ)።
ታዘዘ (ተነገረ): ሥራው ወይም ግብሩ ተነገረ። የክራር መቺ ግጥም: “አዙረህ አዙረህ አገሬ መልሰኝ፡ በሹም የታዘዘ ዐፈር አታልብሰኝ። ”
ታዘዘ (ተአዘዘ): ሰማ፣ ተቀበለ፡ "በጄ"፣ "ይሁን"፣ "እሺ"፣ "በጎ" አለ፡ ተገዛ፣ አገለገለ (ዘፍጥረት ፳፱፥፲፰-፳)።
ታዛ: ከምድራኸ ቀጥሎ ግራና ቀኝ በሰበሰብ ያለ ቅይድ።
ታዛ: የምድራኸ ቅይድ፡ ዘለ ።
ታዛቢ (ቦች): የታዘበ፡ የሚታዘብ፡ የማኅበረተኛ፡ ተመልካች፡
ምስክር። "ታዛቢ ነሽ"
[የሴት ስም]።
ታዛቢነት: ታዛቢ መኾን፡ ተመልካችነት፡ ምስክርነት።
ታዛዥ (ዦች፣ ተአዛዚ): የሚታዘዝ፡ ተላላኪ፣ አሽከር፣ አገልጋይ፣ ሎሌ፡ እሺ ባይ፣ ፈቃደኛ፣ ገር፣ ትሑት።
ታዛዥነት: ትሑትነት፣ ፈቃደኛነት፡ ታዛዥ መሆን።
ታዛይ ከል: ተፈናጣጭን ከልካይ፡ የወዴላ ዘለበት።
ታዛይ: ከቤት ግንብና ግድግዳ በስተውጭ ተለጥፎ የተሠራ ጓዳ።
ታዛይ: የሚታዘል ሕፃን፡ ሙጫሊ፡ ተፈናጣ።
ታየ (ስም): የሰው ስም።
ታየ (ተርእየ): ተገለጠ፣ ታወቀ፣ ተረዳ (፩ኛ ጢሞቴዎስ ፫፥፲፯)። "ለልጅ ይታየዋል" እንደሚባለው።
ታየመ: ታረሰ፡ ተቀበቀበ፡ ለሰለሰ።
ታየረ: ተቀላቀለ፡ ተደባለቀ፡ ተዋዋደ።
ታየበት: ተፈረደበት፣ ተበየነበት፣ ተረታ።
ታየች: የሴት ስም።
ታደለ (ተዐድለ): ተፈረደ።
ታደለ: በተራ ተሰጠ (መብሉ፡ መጠጡ፡ ልብሱ፡ ገንዘቡ) (አስ፩፡ ፯)። "ዕድል ተቀበለ" (ሰዉ)። (ተረት):
"ያልታደለ ከንፈር ሳይሳም ያረጃል።
" "አማረን" እይ።
ታደመ: ተሤረ፡ ተመከረ (ክፉው)።
ታደመ: ተጠራ፡ ተቀጠረ፡ ተሰበሰበ።
ታደመ: ታደመች (የወንድና የሴት ስም)።
ታደሰ (ተሐደሰ): ተጠገነ፡ ተለወጠ፡ ዐዲስ ኾነ፡ ተመለሰ።
ታደሰ ች: የወንድና የሴት መጠሪያ ስም።
ታደሰ: ተሠራ፣ ተደነገገ፣ ተቀጣ።
ታደረ: ሌሊቱ ተፈጸመ፡ ነጋ።
ታደረ: ተኖረ።
ታደረ: ታገገ፡ ተደነባ፡ ጸና።
ታደነ: ተፈለገ፡ ተሻ፡ ተያዘ (እወጥመድ ገባ)፡ ተወጋ፡ ተገደለ።
ታደገ (ስም): የሰው ስም።
ታደገ (ተኀድገ): ተተወ፡ ከመከራ ወጣ፡ ዳነ።
ታደገ (አኅደገ): አስተወ፡ አስጣለ፡ አስለቀቀ፡ አዳነ፡ ተቤዠ፡ ራሱን ለውጦ በታሰረ ፈንታ ታስሮ፡ ተይዞ ወባት ገብቶ (ዘዳ፳፪፡ ፳፯ - ፪ሳሙ፡ ፲፱፡ ፱)። "ታደገን አዳነ" ማለት የልማድ ስሕተት አፈታት ነው።
ታደገ (አደገ): አደገ።
ታደገ (አዳነ): አዳነ (ዐደገ)።
ታደገ (ጎለመሰ): አካለ መጠን ካደረሰ፣ ከጐለመሰ።
ታደገ: ተቈረጠ፡ ተመለሰ፡ ቀና ቀጥ አለ፡ ተገዛ።
ታደፈ (ተኀደፈ): ታሠሠ፡ ተጠረገ፡ ተወለወለ።
ታዲያ፥ ታዲያስ: ንኡስ አገባብ፣ ኀይለ ቃል። "ተዚያ ወዲያ ማለት ነው። ታዲያ ምን ትለኛለኽ፣ ታዲያስ ምን ታደርገኛለኽ።"
ታዲያን አስተውል። 2ኛውን እስቲ እይ።
ታዲያን: "አስተውል" ማለት ነው። "2ኛውን እስቲ እይ" ተብሎ ሲነገር ይገኛል።
ታዳሚ: የሚታደም፡ ወደ ሰርግ ቤት ተጠሪ።
ታዳሽ: የሚታደስ፡ ተጠጋኝ።
ታዳኝ: የሚታደን፡ ተገዳይ (እውሬ)።
ታዳይ (ዮች): የሚታደል፡ ተሰጪ ገንዘብ፡ ተቀባይ ሰው።
ታዳጊ (አኅዳጊ): የታደገ፡ የሚታደግ፡ የተቤዠ አዳኝ (፪ነገ፡ ፲፫፡ ፭፡ ምሳ፳፫፡ ፲፩)። "ስለ ታዳጊው ጌታ" እንዲሉ።
ታዳጊ (አዳኝ): አዳኝ (ዐደገ)።
ታዳጊ (አዳጊ): የሚያድግ፡ ለግላጋ፣ ወጣት።
ታዳጊ አልባ: አዳኝ የሌለው (መዝ፯፡ ፪)።
ታዳጊ: የሚቈረጥ፡ የሚመለስ፡ የሚገዛ (ጐባባ ዕንጨት)።
ታዳጊ: የሚያድግ (አደገ)።
ታዳጊነት: አዳኝነት።
ታዳጎች: የታደጉ፡ የሚታደጉ፡ አዳኞች (ሕዝ፴፪፡ ፳፩)።
ታጀረ (ተዝኅረ): ተዣረ፡ ተጓደደ፡ ኰራ፡ ተጐላመመ።
ታጀበ: በፊት፣ በኋላ፣ በቀኝ፣ በግራ ተከበበ።
ታጀበ: ተሰበሰበ፡ ታከበ፡ ተከማቸ፡ ተመሰ፡ ታወቀ።
ታጃቢ: የሚታጀብ፡ ባለጭፍራ።
ታጅ: የሚታጨድ ሣር፡ እኸል።
ታገለ (ተዐገለ): ተጫረ፡ ተኰተኰተ።
ታገለ (ተጋገለ) (ተዓገለ፡ ተቃለሰ): ተናነቀ፡ ለመጣል፡ ለመቀማት (ዘፍ፴፪፡ ፳፬)።
ታገለ: ተመለሰ፡ ታደሰ።
ታገለ: ተናነቀ፡ ዐገለ ።
ታገመ (ተሐግመ): ተሳበ፡ ተጠባ፡ ተመጠጠ፡ ተመጠመጠ።
"ድምቢጥን"
እይ።
ታገሠ (ተዐገሠ): ቻለ፡ ጸና፡ ዝም አለ (ሮሜ፱፡ ፳፪)። ነገር ግን (ዐገሠ) ቻለ፡ ታገሠ ተቻለ ተብሎ ቢተረጐም በቀና ነበር።
ታገሠ: ቻለ (ዐገሠ) ።
ታገሥ (ተዐገሥ): ቻል፡ ጽና፡ ዝም በል!
ታገረ: ታወከ፣ ተመከተ፣ ተረዳ፣ ታገዘ።
ታገሻ: ተቋተ፡ ተደቀነ (ጥሬው፣ ቅይጡ)።
ታገተ (ተዐግተ): ተያዘ፡ ተወሰደ (ዋሱ፡ ገንዘቡ)።
ታገዘ (ተሐግዘ): ተረዳ፡ ዐረፈ።
ታገደ: ተገታ፣ ተከለከለ፣ ተከተረ፣ ተወሰነ፣ ቆመ፣ ቀጥ አለ፡ ተጠበቀ።
ታገገ (ተሐገገ): ተወሰነ፡ ተደነገገ፡ ተሠራ (ሕጉ)።
ታጋመደ፡ ተጣመረ፣ ተጠማጠመ፣ ተጠማዘዘ፣ ተዋሰበ።
ታጋሚ (ተሐጋሚ): የሚታገም፡ በሽተኛ፡ ሕመምተኛ።
ታጋሽ (ሾች): የታገሠ፡ የሚታገሥ፡ ቻይ (መክ፯፡ ፰፡ ናሖ፩፡ ፫)።
ታጋሽነት: ታጋሽ መኾን፡ ቻይነት።
ታጋች: የሚታገት ሰው።
ታጋዥ (ተሐጋዚ): የሚታገዝ፡ የሚረዳ። (ግጥ) ዕግዝ (ሕጉዝ): የታገዘ፡ የተረዳ፡ ያረፈ።
ታጋይ (ተዓጋሊ): የታገለ፡ የሚታገል (ትግል)።
ታጋጅ: የሚታገድ፣ ተከታሪ።
ታግዳ: የሴት ስም፡ ቶሎ ያልተወለደች ልጅ።
ታጐለ (ተሀጕለ): ጠፋ፣ ቀረ፣ ተዳፈነ፣ ተቋረጠ፡ ግብሩ፣ ቅዳሴው (ነህምያ ፮፥፫)።
ታጐረ: ተሰበሰበ፣ ተከማቸ፣ ታጀበ፣ ተዘጋ።
ታጠረ (ተሐጽረ): ተከበበ፡ ተከለለ፡ ተቀጠረ፡ ተጀጐለ፡ ተገረገረ፡
ተማገረ፡ ተሸመጠጠ፡ ተገነባ፡ ተካበ።
ታጠረ (ተዐጽረ): ተጠመቀ፣ ተጨመቀ።
ታጠረ: ተሸጠ፣ ተለወጠ፣ ተሸቀጠ።
ታጠረ: ተገበረ፣ ተከፈለ፣ ተቀረጠ።
ታጠቀ: በወገቡ አሰረ (ዐጠቀ) ።
ታጠቅ: ያጤ ቴዎድሮስ የፈረስ ስም (ግጥም)፡ "ታጠቅ ብሎ ፈረስ፡ ካሳ ብሎ ስም፡ ዐርባርብ ይሸበራል ኢየሩሳሌም"።
ታጠበ (ተኀፅበ): ተረገጠ፡ ተንጨፈጨፈ፡ ታሸ፡ ጐረፈ፡ ተለቀለቀ፡
ጠራ፡ ጸዳ፡ ነጣ።
ታጠነ (ተዐጥነ): የዕጣንን፡ የሎሚን ቅርፊት፡ የማንኛውንም የጣፋጭ ዕንጨትና የመድኅኒት ጪስ ተቀበለ፡ ዘገበ (ልብሱ፡ ሰዉ፡ ቀፎው)። "ኅዳርን" ተመልከት።
ታጠፈ (ተዐጽፈ): ዕጥፍ ኾነ፡ ተመለሰ፡ ተቀለበሰ፡ ተኰረመተ (ቈርበቱ፡ እንጀራው፡ ልብሱ፡ ምንጣፉ፡ እግሩ) (ኢሳ፴፬፡ ፬)።
ታጠፈ: አቅጣጫውን ትቶ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ተመልሶ ኼደ።
ታጣ (ተኀጥአ): ተገደፈ፡ ተረሳ፡ ጠፋ (ሕዝ፴፫፡ ፳፰)።
ታጣሪ: የሚታጠር ስፍራ፡ ጊዜ።
ታጣቂ (ዐጣቂ): የታጠቀ፡ የሚታጠቅ፡ አደግዳጊ። (ግጥም):
"መይሳው ካሳ ባጪር ታጣቂ፡ ዘመድ ከዘመድ አደባላቂ። "
ታጣቢ: የሚታጠብ ልብስ፡ ዕቃ፡ ሰው።
ታጣኝ: የሚታጠን ታቦት፡ ሥዕል፡ መቅደስ፡ የወተት፡ የጠጅ፡ የጠላ ዕቃ።
ታጣፊ (ዎች): የሚታጠፍ ጣት፡ ባለማጠፊያ ዕቃ፡ ጌጥ።
ታጥቦ ጭቃ: የሪያ ዕጥበት።
ታጨቀ (ተዐጽቀ): ገባ፡ ተጨመረ፡ ተከተተ፡ ታጀበ።
ታጨች: ባል መጣላት፡ ሀብቷ ቀና።
ታጨደ (ተዐጽደ): ተቈረጠ፡ ተቦጨቀ (ራእ፲፬፡ ፲፮)።
ታጪ: ለሹመት፡ ለማዕርግ ታሰበ፡ ተፈለገ።
ታጸፈ: ታጠፈ፡ ተመለሰ።
ታፈረ ደጁ: የውሻ ስም፡ ደጁ ተፈራ ማለት ነው (ውሻው ደጃፉን እንዲጠብቅ)።
ታፈረ: ተፈራ፡ ተከበረ።
ታፈገ: ታጀበ፣ ተከማቸ፡ ተመሰገ።
ታፈፈ: ተከረከመ፣ ተቀፈፈ፣ ተከመመ፣ ተቈረጠ።
ታፋ: ከጭን በላይ፣ ከቂጥ አጠገብ በስተጐን ያለ ጥላ ሠርጓዳው የሙሓይት ካከል። አንቀጹ ተፈተፈ ነው።
ታፋሪ: የሚታፈር፡ የሚከበር።
ታፋፊ: የሚታፈፍ።
ታፌ: የአሥር ቀን ቀጠሮ። "ኦፌን ይዤ" ማለት ነው።
ታፍ ታፉ: ሳይጠራቀም፣ ሳይበዛ መሥራት።
ቴ: ምእላድ። "ምናምን፡ ምናምንቴ።"
ቴምብር: ማኀተም የማኀተም ሥዕል (የዓለም ነገሥታት በደብዳቢ ማኅደር ላይ የሚለጥፉት - "ቴምብር" ፈረንሳይኛ ነው) ።
ቴምብሮች: ኹሉትና ከኹለት በላይ ያሉ ብዙዎች።
ቴዎድሮስ: "ዐምስቱን ጠቅላይ ግዛቶች አንድ ያደረጉ የሐበሻ ንጉሥ።"
ቴዎድሮስ: የሰው ስም (ምሥራቃዊ ስማዕት - ስንክ፡ ጥር ፲፪) ። በጽርእ "ቴዎዶሮስ" "የግዜር ስጦታ" ማለት ነው ይላሉ።
ቴፈ (ተየፈ): መላተነሣ ተንሳፈፈ ተንካፈፈ” ። ቴፈና ተፋ" በምስጢር ይገጥማሉ ። የቴፈ ሥር በግእዝ "ተፈየ" ነው።
ቴፈና: ተፋ፣ በሚስጢር ይገጥማሉ።
ት: "ለቅርብ ወንድ፣ ለቅርብ ሴትና ለሩቅ ሴት፣ ለቅርቦች ወንዶችና ሴቶች የኀላፊ ትንቢት መነሻ ይኾናል። (ማስረጃ)፡ ትጥፋለኽ፡ ትጥፊያለሽ፡ ትጥፋለች፡ ትጥፋላችኹ፡ በትእዛዝም ለሩቂቱ ሴት ብቻ ትጣፍ፡ እያለ ይገባል። በአዐ በሚነሣ ግስ ግን ኹሉም ራብዕ (ታ) ይኾናል። በር ስዎታም ለቅርብ ሴት የአንቀጽ ዝርዝር ሲኾን እንኳዕ ከህ መን እዘመን አደረሰዎት ይላል።"
ት: "በራብዕ ለሚጨርስ ግስ የዘር ምእላድ። ገባ፡ መግባት፡ ዘጋ፡ መዝጋት፡ ዘረጋ፡ መዘርጋት፡ ቀባ፡ መቀባት፡ ዘራ፡ መዝራት። አንዳንዶዬም በግእዝ በሚወርስ ግስ ምእላድ ሲኾን እየ፡ ማየት፡ ደረጀ፡ መደርጀት፡ ሰጠ፡ መስጠት፡ ይላል።"
ት: "በትንቢት መነሻ እየገባ በቂ ይኾናል። ትለብሰው የላት፡ ትከናነበው አማራት። ይኸውም በየም ፈንታ የተነገረ ነው።"
ት: "ጥሬነት ባለው ስም 'ት' እየተጨመረ ለሴት ዝርዝር ይኾናል። ማሞ፡ ማሚት፡ ልጅ፡ ልጅት፡ ወንድ፡ ወንዲት፡ ዐጅሬ፡ ሀጅሪት፡ ዝንጀሮ፡ ዝንጀሪት።"
ት: ለሩቅ ሴት የአንቀጽ ዝርዝር። "እሱ እሷን ዐወቃት።"
ትሑት: (ተሐተ) - እንደተዋረደ።
ትሕትና/ትሑትነት: ዝቅታ፣ የፈቃድ ውርደት።
ትሕትናም: ባለትሕትና፣ ኵራት አልባ።
ትኋን: ያልጋ ተባይ፡ ተኰነ ።
ትለም: ሚት፣ ዕርፍና ጭ፣ የሚኾን ዕንጨት፣ ወንዴና ሴቴ።
ትለም: የቅርብ ወንድ፣ ትእዛዝ አንቀጽ።
ትሉ (ትብሉ): ትናገሩ። "እናንተ እንዲህ ትሉ የለምን።"
ትሉ: የማያንቀላፋ፣ እሳቱ የማይጠፋ ገሃነመ እሳት።
ትሉ: ያ ትል፣ የርሱ ትል።
ትሊ: መዠመሪያ የመጣ ሥሥ አቡጀዲ።
ትላበራ (ትግ፡ ሚሕ): "ትል እበራ፡ ሌሊት የሚያበራ ትል፡ ኤሌትሪክ ያለው ሀፍም ያበራል።"
ትላትል: የትል ትል፣ ብዙ ዐይነት ትል።
ትላንት/ትናንት: ትማልም።
ትላንትና/ትናንትና: ዝኒ ከማሁና፣ ምእላድ ነው። (ግጥም)፡ ትላንትና ማታ፡ ዛሬ፣ ሌሊት፡ በልሜ፡ ምሰሶው ተሰብሮ እባሕር ላይ ቆሜ። 'ከ' መነሻ ኹኖት በዘርፍነት ሲነገር፡ ከትላንት በስቲያ፡ ከትላንት ወዲያ ይላል። እስተን ተመልከት።
ትል (ሎች): ብል፣ ነቀዝ፣ ተምች፣ ግንደ ቈርቀር፣ ቅንቡርስ፣ መሰክ፣ ሸሽ፣ ኮሶ፣ እኝት የመሰለው ኹሉ። የሥጋ ትል፣ የሀመድ ጥል። "እበት ትል ይወልዳል እንዲሉ።"
ትል: ትላም፣ ትል ያለበት፣ የበዛበት፣ ባለትል፣ አመንዝራ።
ትልልቅ: ታላላቅ፡ ረዣዥም፣ ውስጠ ብዙ፡ ከፍ ከፍ ያለ።
ትልልቆች: ታላላቆች፡ ረዣዥሞች፣ ዐዛውንቶች፣ ሽማግሎች፣ ከበርቴዎች፣ ጌቶች።
ትልልፍ: ድፍረት (፪ዜና፡ ፴፮፡ ፲፬)።
ትልም: የተተለመ፣ ዥምር፣ ፈር፣ ቡደን።
ትልሞች: ፈሮች፣ የርሻ ውጥኖች (ኢዮብ ፴፰)።
ትልቁ: ትልቂቱ፡ ታላቋ፣ ታላቂቱ ቷ። "በል" (ዘፍ. ፲፱፡ ፴፩፣ ዳን. ፬፡ ፴)።
ትልቅ ኾነ: ላቀ።
ትልቅ: ታላቅ፡ ከፍ ያለ፣ በመጠን የረዘመ፣ በማዕርግ የበለጠ፣ ዕዛውንት። ወንድና ሴትን ለመለየት፡
ትልተላ: ትርተራ፣ ልየታ፣ ሥንጠቃ።
ትልታይ: ከድር የወጣ ማግ፣ ከማግ የተለየ ድሮ።
ትልት አለ: ተላ።
ትልት: መትላት።
ትልትላት: ብጥታት፣ ሥንጥቃት።
ትልትል: የተተለተለ፣ ትርትር ሸማ፣ ብጥ፣ ቅድ፣ ሥንጥቅ።
ትልዝ አለ: ድክም አለ (ነዲዱ፣ መብራቱ)።
ትልዝ: የተለዘ፣ የደከመ።
ትሎማ: የላ ስምና ነገድ።
ትሎት: (ተለወ፡ ትልወት) - እንደተለወ።
ትማትም (ሞች): "የተክል ስም፡ ክብ እንክብል፡ ቀይ ፍሬ፡ ወጥ የሚኾን ዐረግማ ተክል፡ ኹለተኛ ስሙ ያቡን ወጥ ነው።"
ትም አለ: ቍልቍል ሮጠ፣ ተመመ።
ትም አለ: ቍልቍል ኼደ፣ ወረደ፣ ሮጠ።
ትም አደረገ: በፍጥነት ፈጸመ፣ ጨረሰ (እኸልን፣ ገንዘብን)።
ትምህርተ ኅቡኣት: የመጻፍ ስም፡ እንደ ክታብ በደረት የምትያዝ፣ በቅዳሴ ጊዜ የምትነበብ፣ ከመጽሐፈ ኪዳን የተከፈለች ታናሽ መጻፍ። "የመንፈሳውያት ምስጢሮች ትምርት" ማለት ነው።
ትምርት (ትምህርት): ንባብ፣ ዜማ፣ ቅኔ፣ ትርጓሜ፣ ቃለ እግዚሐር። በአማርኛ መጻፍ ውስጥ "ትምርት" እንጂ "ትምህርት" ማለት አይገባም።
ትምርት ቤት: ትምርት የሚነገርበት የትምርት ቤት።
ትምርት ዠመረ: ፊደል ቈጠረ።
ትምቡሼ: ልዝብ፡ ትንቡሼ ።
ትምተማ: ልተማ፣ ድምደማ።
ትምትም አደረገ: ድም ድም አደረገ።
ትምክ አለ: ሥርጕድ አለ፣ ወደ ውስጥ ገባ፣ ትክክልትን ወጣ።
ትምክ: የተመከ፣ ልል፣ ስጕድ፣ ሥርጕድ።
ትምክምክ አለ: ተትመከመከ።
ትምክምክ: የተመከመከ።
ትምክምክ: የተትመከመከ፣ ድብስብስ።
ትምክተኛ (ምኩሕ): የተመካ ወይም የሚመካ፤ ኩሩ።
ትምክት (ትምክሕት): መመካት።
ትሰሚ፡ ትሰሜ፡ ትሰሚያለሽ፡ የሴት ስም (ትደመጪያለሽ ማለት ነው)።
ትሰሚ/ትሰሜ/ትሰሚያለሽ: የሴት ስም፣ ትደመጪያለሽ ማለት ነው።
ትሣሥ: ፬ኛ ወር ከመስከረም፡ የጥያቄ፡ የመመራመር ወር ማለት ነው (ማቴ፪፡ ፪)። በግእዝ ታኅሣሥ ይባላል።
ትስብእት (ከሰብእ): ሰውነት፣ ሰው መሆን። ጌታችን ያለ ዘር የተፀነሰበት፣ ሥጋ የለበሰበት (የመጋቢት 29 ቀን በዓል)።
ትረባ: መተረብ።
ትረካ: መተረክ።
ትሩፋት: የሴቶች ሳድስ ቅጽል።
ትሩፋት: የበዙ፣ የተረፉ የነፍስ ሥራዎች (በቂ)።
ትሩፋን: ቅሬቶች።
ትሩፋን: ዕዝራ ሱቱኤል ያያቸው መ፣ ፍጹማን፣ በፍጻሜ ዘመን የሚገለጹ።
ትሩፋን: የተረፉ፣ የቀሩ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ያልተመለሱ፣ ከእስራኤል ተለይተው በፋርስ የኖሩ።
ትሩፍ: ሃይማኖቱ የጸና፣ ምግባሩ የቀና፣ ትርፍ የጽድቅ ሥራ የሠራ ሰው። በግእዝ ትሩፍ ይባላል፣ ፍጹም ማለት ነው።
ትሩፍ: በፋርስና በባቢሎን ከሰባ ዘመን መከራና ሞት የቀረ የእስራኤል ወገን።
ትሩፍ: የይሁዳ ነገድና የብንያም ትሬታ ካሥሩ ነገድ ጋራ ያልተማረከ (ነህምያ ፩፡ ፪፡ ፫)።
ትራስ: በቃል መጨረሻ የሚገባ ፊደል (ሽ፣ ኒ)። "ውጦሽ፣ ጢሎሽ፣ ግመኒ፣ ጥንበኒ።"
ትራስ: የራስ ድጋፍ፣ መከዳ፣ ብርኳኔ።
ትራፊ (ትራፍ): የተረፈ፣ የቀረ (ኢሳይያስ ፲፩፡ ፲፩)።
ትር ማን/ትርጁማን: ተርጓሚ፣ አስተርጓሚ።
ትርምስ: ሽብር፣ ፍጅት፣ ሁከት፣ ብጥብጥ።
ትርምስ: ብጥብጥ (ተረመሰ)።
ትርምስምስ አለ: ምስቅልቅል አለ።
ትርምስምስ: ብጥብጥ፣ ምስቅልቅል።
ትርር: የተተረረ፣ ሥንጥቅ።
ትርሽማ: የወታደር ድንኳን፣ አነስተኛ የሆነች ዐሯ። ጉይዲ ግን ባለመደረቢያ የንጉሥ ድንኳን ጌጠኛ ይለዋል።
ትርተራ: ልየታ፣ ፍንክታ፣ ጭፍለቃ።
ትርታሪ: ከስፌት የተፈታ ክር።
ትርታሮ: ጭፍልቅ።
ትርትር አለ (የርግብ እንቅስቃሴ): ተንቀጠቀጠ፣ ርግብ ርግብ አለ።
ትርትር አለ: ሥንጥቅ አለ፣ ተፈታ።
ትርትር: የተተረተረ፣ የተፈታ፣ ሥንጥቅ፣ ፍንክት፣ ጭፍልቅ።
ትርንጎ (ዎች) ፡ የተክልስም (ጣዕም ከመዐዛ ያለው ተክል - ዛፉም ፍሬውም "ትርንጎ" ይባላል) ።
ትርከካ: ሥንጠቃ፣ ፍንከታ።
ትርኪ ምርኪ: ቅባጥርሴ፣ ቅራቅንቦ፣ የማይረባ፣ ውጥንቅጥ ምናምን ነገር።
ትርኪ: ከተረከ፣ ምርኪ፡ ከማረከ ይወጣል።
ትርክም: የተሰበሰበ ጥርቅም።
ትርክምክም: ብዙ ትርክም።
ትርክክ አለ: ሥንጥቅ አለ፣ ተተረከከ።
ትርክክ: የተተረከከ፣ ጥርቅቅ፣ ሥንጥቅ፣ ፍንክት።
ትርክዛ (ኀዳፍ): መቅዘፊያ፣ የውሃ መግፊያ፣ የባሕር ላይዳ።
ትርኰሳ: ሰበራ፣ ስተራ (የጠለስ)።
ትርኳሽ ሾ: የተተረኰሰ፣ ኵስታሪ (ዘካርያስ ፫ - ፪)።
ትርው አለ: ዝር አለ።
ትርው አትበል: አትድረስ።
ትርው ዝር: መድረስ።
ትርጁማን (ዐረ፡ ተርጁማን): አስተርጓሚ።
ትርጉም:
"እጅግ ብዙ" ማለትም ነው። "እከሌ ቸር ነው፡ አንድ አገር እንጀራ ሰጠኝ"። ዳግመኛም "ያንድ አገር እንጀራ" ተብሎ ይተረጎማል።
ትርጉም: ሕዝብ ማለትም ነው።
"ማገረ"
ብለህ
"ማገርን"
ተመልከት።
ትርጕም: የተተረጐመ፣ የተፈታ፣ የተገለበጠ፣ የተገለጸ፣ ግልጥ ንግግር።
ትርግ ትርግ አለ: ሥርግ ሥርግ አለ (የልብ፣ የርግብግቢት)።
ትርጐማ: የመተርጐም ሥራ፣ ግልበጣ፣ ምለሳ።
ትርጓሜ: ዝኒ ከማሁ፣ ፍች፣ ስለ ምን።
ትርጓሜው: አካላዊ ትንፋሽ ማለት ነው።
ትርፈሳ: ዘዝና፣ ዐፈሣ።
ትርፌ: የወንድና የሴት ስም፣ "የኔ ትርፍ" ማለት ነው።
ትርፍ (ፎች): ዝኒ ከማሁ፣ ከስፍር ከቍጥር ውጭ የኾነ እኸል፣ ገንዘብ፣ ፋይዳ፣ ጥቅም፣ ሰው በድካሙ የሚያገኘው (ዘዳግም ፰፡ ፲፫። መክብብ ፩፡ ፫)።
ትርፍ የጋራ: "ነጋዴው ገንዘብ ተበድሮ ትርፍ የጋራ ይነግዳል"።
ትርፍ: የጋራ ትርፍ፣ ያበዳሪና የተበዳሪ ነው፣ ከኹለት ይከፈላል።
ትርፍራፊ: ፍድፋጅ።
ትርፍርፍ አለ: ተትረፈረፈ።
ትርፍርፍ: ዝኒ ከማሁ።
ትርፍነት/ትርፍቻ: ትርፍ መኾን (ሮሜ ፫፡ ፪)።
ትቢተኛ (ኞች): ኵራተኛ፡ ጨርቁን አፍንጫው ላይ አድርጎ ሰውን የሚንቅ፡ ባለትቢት፡ ትቢታም፡ የማይታዘዝ (ዘዳ፳፩፡ ፲፰፡ ፪ጢሞ፡ ፫፡ ፬)።
ትቢተኛነት: ኵራተኛነት።
ትቢት (ትዕቢት): ኵራት።
ትቢያ: ወቧራ ብናኝ ደቃቅ ዐፈር አሸዋ (ኢዮ፡ ፴፰፡ ፴፰፡ መዝ፡ ፩፡
፬) ። በግእዝ "ተቤሳ ጸበል" ይባላል ።
ትባት (ትብዕ): ስለት፣ ሹለት፣ ጥንካሬ፣ ፍጥነት።
ትቤ፡ ያዢ (ስም)።
ትቤት: በሺን አገር በሂማልያ አጠገብ ያለ ረዥም ተራራ (የመነኮሳት መኖሪያ ደብር - ቅዱስን
የመሰለ)” ። ጌታችንም በ፲፪ ዓመቱ በዚህ ስፍራ እንዳስተማረ የሚያስረዳ በሺን ቋንቋ የተጻፈ የብራና ጽፈት በገዳሙይገኛል"
ይባላል ።
ትብ (ትቡዕ): የተባ፣ ስል፣ ፈጣን፣ ጠንካራ። "ቢላዋ፣ መጥረቢያ፣ ማንኛውም መሪያ አንደበት።"
ትብተባ: ጥምማ፣ እሰራ።
ትብትባት/ትብትቦሽ: ጥምጥማት፣ እስራት።
ትብትብ: ዝዝዝብ ነገር። "፪ኛው፡ ት፡ ይጠብቃል።"
ትብትብ: የተተበተበ፣ ጥምጥም፣ ውስብስብ፣ እስርስር፣ እርት-እክት (ግብረ ሐዋርያት ፰ ፳፫)።
ትብትብ: የአረቄ አሸንዳ።
ትተጋ: የእሳት በጣ ውግ።
ትት (ቶታን): የተታታ፣ ጥፍር፣ ውስብስብ፣ ጥልፍልፍ፣ ቍልፍልፍ (የስንደዶ፣ የክር፣ የገመድ ጠፍር)።
ትት: የወፍ ቤት።
ትትጊ (ትግ): ፋደት፣ ዐራጅ (ኢሳ ፴፬፡ ፲፩፡ ሶፎ ፪፡ ፲፬)።
ትቻ: ዘጠነኛ የቀባርዋ ምት።
ትች: የተተቸ፣ ከፈራጅ ሽማግሌ፣ ከዳኛ አንደበት የሚወጣ የፍርድ ወይም የነገር ማስረጃ። "ሰው ፊት አይቶ ይፈርዳል፣ እግዜር ግን ልብን ይመረምራል"፡ "ሰው አየ፣ እግዜር እየ"፡ "እግዜር መንግሥትን ይጠብቅ፣ ዐመፀኛን ያውድቅ፣ ሐሰተኛን ያርቅ፣ ፍትሕ ርትዕ ይጠንቅቅ፣ ማማለጃ ተቀብለው ፍርድ አድልተው በልተው ጠጥተው ከብረው ብታያቸው አትቅናባቸው" እንደ ማለት።
ትችት: (ዝኒ ከማሁ) መጨረሻው 'ት' ምእላድ ነው። (ትች ቅጽልና ጥሬ ነው። ትችት ግን ጥሬ ብቻ ይሆናል)።
ትናንት: ትናንትና፣ ትላንት፣ ትላንትና።
ትናጋ: ላንቃ (የአፍ ውስጥ ላይኛው ክፍል - ኢዮ፡ ፳፡ ፲፫፡ መዝ፡ ፻፴፯፡ ፯፡ ሰቈ፡ ፬፡ ፬፡ ሕዝ፡ ፫፡ ፳፮) ።
ትናግ (ስናግ፣ ስናቅ፣ ትግ ት ንሐግ): ኵጕረሮ፣ ወደ ሰርን የትንፋሽ መውጫ ኹለት ቀዳዳ።
ትን ብን: ባፍን መውጣት።
ትን አለ: ብን አለ፣ ወደ ስናቅ ወጣ፣ ሰረነቀ፣ ዐነዘዘ (ትንፋሹ፣ መጠጡ)።
ትን: ባፍንጫ መውጣት፣ ተነነ።
ትንሣኤ ሙታን: የሞቱ ሰዎች መንቃት፣ ከመቃብር መውጣት።
ትንሣኤ ዘጉባኤ: የጉባኤ ሰዎች ኹሉ መነሣት፡ ጉባኤ የተባለ ይህ ዓለም ነው።
ትንሽ (ኅዳጥ): የቁጥር ንኡስ፡ ብዙ ያይደለ፣ ጥቂት። “እከሌ ትንሽ ገንዘብ ሰጠኝ”።
ትንሽ (ንኡስ): ያነሰ፣ ሕፃን፣ ብላቴና። “ትንሽ ልጅ” እንዲሉ። ለመለየት: "ትንሹ" (ያ ትንሽ)፣ "ትንሿ"፣ "ትንሽቱ" (ያች ትንሽ) ያሰኛል።
ትንሽ: በቁሙ፣ አነሰ።
ትንሽ: ያነሰ፣ አነሰ።
ትንሽነት: ሕፃንነት፣ ለጋነት፣ ጥቂትነት።
ትንቅንቅ: መነቃነቅንም ያሳያል።
ትንቡሼ: የትንቡሽ ወገን፡ ድንቡጭ (ድንቡሎ)። ምሳሌ: “ትንቡሼ ገላ ነይ” እንዳለ ዘፋኝ።
ትንቡሼ: ድንቡሎ፣ በሸበሸ።
ትንቡሽ: ወፍራም (ድልድል፣ ለስላሳ)።
ትንቡሽቡሽ: ቅምጥል (እንቅብር)፡ የደላው (የተመቸው) ሰውነት።
ትንቢ: የተነባ፣ የሚተነባ፡ ትንቢተኛ።
ትንቢተኛ (ትንቢታዊ): ትንቢት ተናጋሪ፣ ባለትንቢት፣ ንግረኛ፣ አገኛለሁ እሾማለሁ ባይ።
ትንቢተኞች: ባለንግሮች፣ ንግርተኞች።
ትንቢት ተናገረ: ወደፊት እንዲህ ይሆናል አለ።
ትንቢት አንቀጽ: የዐሁንና የቅርብ የቈየ፣ የዘገየ፣ ኀላፊ ግስ፡ "ይገድል"፣ "ይገድላል"፡ "ይገድል ነበር" እየተባለ የሚነገር።
ትንቢት: ሳይሆን፣ ሳይደረግ፣ ሳይመጣ፡ ይሆናል፣ ይደረጋል፣ ይመጣል ተብሎ በምሳሌና በምሳሌ፣ በነቢይ አፍ የተነገረ ንግግር። "ደረቀ" ብለኸ "ደረቅን" እይ።
ትንቢት: ንግርት (ነበየ)፣ ተነበየ።
ትንቢት: ከኢሳይያስ እስከ ሚልክያስ ያለ የነቢያት መጻፍ።
ትንቢት: የረኛ ዘፈን።
ትንባኾ: "የተክል ስም፡ ሰው ኹሉ ልጥልጡን ባፉ የሚገርመው፡ ሥንተኑን ባፍንጫው የሚምናው፡ ጨሱን የሚጠጣው ቅጠል። ባረብኛ ትንባክ ይባላል።"
ትንባዃም: ትንባኾ ጠጪ፣ ባለትንባኾ፣ ሱረም።
ትንቧለል: የሴት ስም፡ “እንዳሳባ፣ በሰፊው ትኑር” ማለት ነው።
ትንቧለል: የሴት ስም (ቦለለ) ።
ትንተና: ልየታ፣ ከፈላ፣ ምደባ።
ትንታ: ብንታ፣ ንዛዥ።
ትንታግ (ጎች): ክፋይ ቍጡ ኀይለኛ ተናጋሪ ሰው (ምሳ፡ ፳፮፡ ፲፰) ።
ትንታግ: ክፋይ፡ ተገተገ ።
ትንትናት: የመተንተን ኹኔታ።
ትንትን: የተተነተነ፣ የተከፈለ ክፍል2።
ትንትግ ትንትግ አለ: ቶሎ ሎቶ ተቈጣ።
ትንንሽ (ሾች): ውስጠ ብዙ፡ ታናናሽ፣ ጥቃቅን። “የኛማ ልጆች ትንንሾቹ፡ ይናደፋሉ እንደ ንቦቹ”። ማስታወሻ: "ታናሽ" እና "ትንሽ"፣ "ታናናሽ" እና "ትንንሽ" አንዳንድ ወገን ናቸው።
ትንንቅ: ትንቅንቅ፡ ግብግብ፡ ትግል (ፍልሚያ)።
ትንንን አለ: እንደ ትንኝ ሮጠ (ሕፃኑ)።
ትንኝ (ኞች፣ ትንንያ): የተንቀሳቃሽ ስም።
ትንኝም: ለሆዱ ዝኆንም ለሆዱ ወደ ወንዝ ወረዱ እንዲሉ።
ትንኵስ አደረገ: ተነኰሰ።
ትንኵስ: የተተነኰሰ፣ የተለኰፈ፣ ልኵፍ።
ትንኰላ: የተንኰል ሥራ፣ ክፋት።
ትንኰሳ: ልኰፋ፣ ንክሻ።
ትንኳሽ (ሾች): የቈላ ቍጭ፣ በነከሰ ጊዜ እንደ እሳት የሚያንበገብግ።
ትንግርተኛ (ኞች): ታሪከኛ፣ ድንቅ አድራጊ።
ትንግርት: ጕድ፣ ድንቅ፣ ታሪክ። በግእዝ "ንክርት" ይባላል።
ትንፋሽ: ከሰው፣ ከእንስሳ፣ ከወፍ፣ ከአውሬ አፍ የሚወጣ ሕይወታዊ ነፋስ። ላብም ትንፋሽ ይባላል።
ትንፋገን: ወረዘት፣ ነፈገ።
ትንፋገን: ወረዘት፣ የርጥበት ሽታ።
ትንፋጋም: ባለትንፋግ፣ ግማታም።
ትንፋግ: መጥፎ ሽታ (የፍግ፣ የሽንት፣ የአይነ ምድር)።
ትንፋግ: መጥፎ ሽታ፣ ነፈገ።
ትንፍስ ትንፍስ አለ: ቶሎ ቶሎ ተነፈሰ።
ትንፍስ: የተነፈሰ፡ የተተነፈሰ።
ትንፍሽ አለ: ጥቂት ተናገረ።
ትንፍሽ: መተንፈስ፡ ካፍ ነገርን ማውጣት።
ትኝት አለ: ውድቅ አለ፣ ተኝቶ ተጋድሞ ተዘርሮ።
ትኝት: ረብ፣ ጋደም።
ትእዛዝ አንቀጽ: ከ"ዘንድ" ቀጥሎ ለቅርብ ወንድ የሚነገር ግስ። "ዕወቅ"፡ "ተጠንቀቅ"።
ትእዛዝ: የጌታና የፈጣሪ ቃል፡ "አታድርግ" የሚል፡ ከሥራ አስቀድሞ የሚሰጥ፣ የሚጻፍ፣ የሚነገር። "አትስረቅ"፣ "አታመንዝር"፣ "በሐሰት አትመስክር"።
ትከሻ (ተኬሳ): ንቃ ዕድል” ። ትከሻ ወረደው" ተቀታመው ።
ትከሻ ወረደው: ተቀመጠ፣ ታመመ።
ትከሻም: ዕድላም፣ ክቡር፣ ክባድ ሰው።
ትከዛ: ዐዘና፣ መሬት፣ ቍርቈራ።
ትኩ (ትግ፡ ትኩእ): የሰው ስም፣ ምትክ ማለት ነው።
ትኩሳታም: ወባም፣ ንዳዳም፣ ትኩሳተ ብዙ።
ትኩሳት: ወበቅ፣ ሙቀት፣ ሐሩር፣ ንዳድ፣ የወባ-የምች በሽታ (ዘፍጥረት ፰፡ ፳፪። መዝሙር ፪፡ ፭። ኤርምያስ ፲፯፡ ፰)።
ትኵስ ቅቤ: ዐዲስ፣ ለስታ፣ ለጋ ቅቤ።
ትኵስ/ትኩስ: የተተኰሰ፣ ሙቅ፣ ላበት፣ እንፋሎት ያልተለየው (፩ኛ ሳሙኤል ፳፩፡ ፮)። "ትኵስ፡ እንጀራ፡ ትኵስ፡ በድቍስ፡ ትኵስ፡ ዳቦ፡ ትኵስ፡ ዶም፡ እንዲሉ።"
ትኵር ብሎ አየ: ተኰረ።
ትኵር: የተተኰረ፣ ባለማቋረጥ የታየ።
ትካር: ዝኒ ከማሁ፣ አሳዛኝ ነገር።
ትካት: ፊት ቀድሞ ዱሮ ጥንት (ሰብአ ትካት" እንዲሉ) ።
ትካትና ትክቶ: የግእዝ ቃል ነው። ሓቂ።
ትካዜ: ዐዘን፣ ዐሳብ፣ እህህታ፣ ቍዘማ፣ የለቅሶ ዜማ (ሕዝቅኤል ፬፡ ፲፮። ፩ኛ ጴጥሮስ፡ ፭፡ ፯)።
ትክ (ሰኪው): መተኰር (ዐይንን አለመንቀል) ።
ትክ ብሎ አየ (ሰከወ): ተኰረ፣ ባለማቋረጥ አስተዋለ።
ትክለኛ (ኞች): ባለመሬት፣ ቀላድ ያል።
ትክል (ትኩል): የተተከለ፣ የቆመ፣ የጸና። "ትክል ድንጋይ እንዲሉ።"
ትክል አለ: መሬት ቆመ፣ ባፍጢሙ ወደቀ፣ ተደፋ።
ትክትክ (ቅጽል): የተተከተክ፣ ጥቅጥቅ።
ትክትክ አለ: ሳለ፣ ኡሁ ኡሁ አለ።
ትክቶ: ግዳጅ፣ በየወሩ ከሴቶች የሚፈስ ደም።
ትክን: የተከነ፣ የፈላ፣ የበሰለ። "ትክን አለ፡ እፍታ አልባ ኾነ። ትክን ያለ ወጥ እንዲሉ።"
ትክክለኛ: የተካከለ፣ የተመሳሰለ፡ አንድ ዓይነት፣ ልከኛ፡ እውነተኛ፣ ሐቀኛ።
ትክክለኛነት: ተመሳሳይነት፣ ርግጠኛነት፣ እውነተኛነት።
ትክክለኞች: የተካከሉ፣ ድልድሎች ሰዎች፡ እውነተኞች፣ ሐቀኞች።
ትክክል ሆነ: አልተበላለጠም፡ አልተናነሰም።
ትክክል መናገር አቃተው: (የአንደበት ችግር)።
ትክክል አደረገ: አላጐደለም፡ አላበለጠም።
ትክክል: ልክ፣ እኩያ፣ አምሳል፣ ወደር፣ አቻ፣ ድልድል።
ትክክልነት: እኩያነት።
ትክክሎች: እኩዮች፣ አቻዎች።
ትክክሏ: የሴት ስም።
ትክዝ (ትኩዝ): የተከዘ፣ ያዘነ።
ትክዝ አለ: ዕዝን አለ፣ ዐዘን ገባው።
ትኰሳ: ልብለባ፣ ዳመጣ።
ትኰራ: ምልከታ።
ትኳን/ትዃን (ኖች): "የተባይ ስም፡ በቤት ውስጥ በጣራ በግድግዳ ባልጋ በማንኛውም መኝታ ላይ ኹኖ የሰውን ገላ የሚቀነቅን፡ የሚበላ፡ የሚልጥ፡ የሚያቃጥል፡ የሚያንገበግብ፡ ግማታም ፍጥረት። (ተረት)፡ እኔን ቢወዱኝ ወዳፍንጫቸው ወሰዱኝ፣ አንቺን ቢጠሉሽ አጥመዝምዘው ጣሉሽ፡ አለቻት ትዃን ቍንጫን። የቤቴ መቃጠል ለትዃኑ በጀው።"
ትዃን፡ ትዃናም፡ ትዃን ያለበት፡ የበዛበት፡ ቈጥ፣ ምንጣፍ።
ትዋብ: ታምር፣ ትመር፣ ትኩራ።
ትውልድ: የሰው ወገን፣ ነገድ፣ ጐሣ። (መክ፩፡ ፬)
ትውልድ: የተወለዱበት የዘር አገር።
ትውስ (ተሐውሶ): መታወስ።
ትውስ አለው: ታሰበው።
ትውስታ: ትዝታ፡ ዕስብታ፡ ዐሳብ።
ትውስት፡ ሊመልሱ መውሰድ።
ትዛዝ: በቁሙ፣ አዘዘ።
ትዝ አለው: ታሰበው፣ ታወሰው።
ትዝ: መታሰብ።
ትዝቢ (ዎች): ሌባ፡ ቀጣፊ፡ ሰው የሚታዘበው።
ትዝብተኛ (ኞች): ባለትዝብት፡ ጠርጣሪ፡ ናቂ።
ትዝብት (ትሕዝብት): ጥርጥር፡ የፍራት ዐሳብ፡ ንቀት፡ ነቀፋ።
ትዝብትን ፈራ: (አተበበ)።
ትዝታ: ዕስብታ፣ ትውስታ።
ትያትር (ትያጥሮን): የተምሳሊትዋታ ።
ትይዩ: የተያየ፣ የተነጻጸረ፡ አንጻር፣ አፍዛዣ፣ አቅጣጫ፣ ስፍራ፣ ፊት ለፊት (፩ኛ ነገሥት ፰፥፵፬-፵፰፡ ዳንኤል ፰፥፬)።
ትደነቂያለሽ፡ የሴት፡ ስም።
ትዳሩን፡ አሸነፈ)፡ ራሱን ቻለ።
ትዳር ፣ ዐዳር ፣ ዐደረ።
ትዳር: ኑሮ፡ ንብረት፡ ጐዦና ጕልቻ።
ትድግ: ለውጥ፡ የመከራ ምትክ።
ትድግና: ለውጥነት፡ ምትክነት፡ ማዳን።
ትድግና: ማዳን፣ ዐደገ።
ትጉ (ጎች፣ ዎች፣ ትጉህ): የተጋ፣ የሠጋ፣ ሥግ፣ ንቅ፣ ሀሳቢ (ምሳሌ ፲፫፡ ፬)።
ትጕልጕል አለ፡ ተትጐለጐለ፡ ተጫነቀ፣ ተጣበበ።
ትጕልጕል፡ የተትጐለጐለ፣ የተጣበበ (ማሕ፫:፮) (ትርጓሜ)።
ትጕልጕል: የተጣበበ (ጐለጐለ) ።
ትጕልጕልታ፡ የጥበት አወጣጥ።
ትጉነት: ትጉህነት፣ ትጉ መኾን።
ትጋት (ትግሀት): ንቃት፣ እንቅልፍ ማጣት (ኢሳይያስ ፳፩ ' ፯። ሉቃስ ፪፡ ፰)። "ሲበዛ ትጋቶች ይላል (መዝሙር ፷፫፡ ፮)።"
ትግ ብልጭ: ትግ ትግ አለ፣ ተንተገተገ።
ትግ: ብልጭ ተገተገ።
ትግል (ትግያ) (ትግልት) (ትዕግልት): ግብግብ፡ ትንንቅ።
ትግሥተኛ (ኞች): ታጋሽ፡ ልበ ሰፊ፡ ነገር ዐላፊ ሰው።
ትግሥተኛነት: ትግሥተኛ መኾን።
ትግሥት (ትዕግሥት): የሥቃይ፣ የመከራ ችሎታ፡ ዝምታ፡ ርጋታ፡ ጸጥታ።
ትግሪተኛ: ዝኒ ከማሁ፣ ቍጡ፣ ወፈፍተኛ።
ትግሪታም (ቲግራዊ): ቍጣም፣ ወፈፍታም።
ትግሪት: ቍጣ፣ ወፈፍታ።
ትግሪት: ዛር፣ ክፉ መንፈስ፣ ወዶ።
ትግሪት: የበረሓ ሠሥ፣ ዲግዲግ፣ እንሸ።
ትግሪኛ (ትግራይ): የቋንቋ ስም፣ "የትግሬ ወን ልሳን ከግእዝና ካማርኛ የሚገጥም።"
ትግሬ (ቲግራ): "በጤግሮስ ወንዝ ዳር የሚኖር ታላቅ ነብር፡ ቍጡ፡ ኀይለኛ። ባላገርም በበረሓ ትግራ የምትባል አውሬ ኣለች እያለ ያወራል።"
ትግሬ ሐባብም ፍላጻን መንፈጽ ይለዋል፡ ቀስቱ ከነፍጥ፡ ፍላጻው ከጥይት ጋራ አንድ ነውና።
ትግሬ፡ ትግሪዳ (ታ): መንገድገድ፣ መፍገምገም፣ ፍግምግምታ (ከቢር)።
ትግሬ ግን
"ነፍነፈ" ብሎ
"ጣለ፣ አወደቀ"
ይላል።
ትግሬ: "ከሐማሴን ቀጥሎ ያለ ያገርና፣ የነገድ ስም፡ ቈላ ምድር፡ ሐባብ በመረብ ግራና ቀኝ ከምጥዋ እስከ ተከዚ የሚ፹ኝ ወረዳ ኹሉ። የነገድ ስም ሲኾን ነጋዴ ማለት ነው ይላሉ። ባላገሮቹም ታችኛውን ትግረ ላይኛውን ትግራይ ይሉታል። በግእዝ ግን ደጋውም ቈላውም ባንድነት ትግሬ ይባላል። ትግሬ የትግራና የትግራይ ሰው (ዐማርኛ)።"
ትግሬ: ትግሪኛ
ትግሬ: የቋንቋ ስም፣ "ግእዝን መደብ ኣድርጎ ከወረብና ከዕብራይስጥ ከሱርስት የሚስጥም የሐባብ ልሳን።"
ትግሬም ጋቢን ፈርጊ ይለዋል።
ትግሮች: የትግራ አገር ሰዎች፣ "የትግሬ ተወላጆች ትግሪኛ የሚናገሩ ነገዶች ደገኞችና ቈለኞች።"
ትግተጋ: ገረፋ፣ ትኰሳ።
ትግትግ: የተተገገ፣ የተገረፈ፣ ግርፍ።
ትግን: የተተነ፣ የተጀጐለ።
ትጥቅ (ዕጠቅ): የወገብ ጌጥ፡ የሆድ ድጋፍ፡ ድግ እስራት፡ ጥምጥማት።
ትፋሕ: ፍሬው ክብ እንክብል የኾነ ጣፋጭ ተክል (ምሳ፡ ፳፭፡ ፲፩፡ ማሕ፡ ፪፡
፳) ። በግእዝ "ኮል" ይባላል ።
ትፋታም: ባለትፋት፣ ቅርሻታም።
ትፋት (ትፋእ): ቅርሻት፣ ምላሽ (ምሳሌ ፳፮ ፥፲፩። ኢሳይያስ ፲፱፡ ፲፬። ኤርምያስ ፵፰፡ ፳፮)።
ትፍ (ትፉእ): የተተፋ።
ትፍተፋ: የመብጣት፣ የመቈራት ሥራ።
ትፍታ: አክታ፣ ምራቅ።
ትፍትፋት: ብጥታት፣ ፍቅታት፣ ቍርጣት።
ትፍትፍ: በኩታና በቀሚስ ዳር የተጣለ ጥቍርና ብ፵ ጥለት።
ትፍትፍ: የተተፈተፈ፣ ብጥ፣ ፍቅ፣ የሰው ፊት ብርንዶ።
ቶ: "መጨረሻው ራብዕ በኾነና ባልኾነ የ፪ና፣ የ፫ ፊደል ግስ ለሩቅ ወንድ የቦዝ ዝርዝር። ገባ፡ ገብቶ፡ ወጣ፡ ወጥቶ፡ በላ፡ በልቶ፡ ጠጣ፡ ጠጥቶ፡ ሸኘ፡ ሸኝቶ፡ ስጠ፡ ስጥቶ፡ ዘነጋ፡ ዘንግቶ፡ ዘረጋ፡ ዘርግቶ።"
ቶሎ (ተለወ): ንኡስ አገባብ፣ ፈጥኖ፣ ቸኵሎ። "ቶሎ መጣ፡ ቶሎ ኼደ። በደለ ብለኸ ተበደለን እይ።"
ቶሎ ቶሎ: ፈጥኖ ፈጥኖ፣ ወዲያው ወዲያው።
ቶመቶመ)፡ ትምትም፡ የተተመተመ ልትም። "ትምትም በልጥፍና በልስን መካከል ያለ የምርግ ሥራ። ጕርዖን፡ እይ።"
ቶመቶመ)፡ አቶመቶመ፣ እጕረመረመ፣ አጕተመተመ።
ቶማስ: የሰው ስም፣ ካሥራ ኹለቱ ሐዋርያት አንዱ።
ቶሜ: ጐረጐማ።
ቶሰቶሰ: በድብቅ ሳያሰማ ፈሳ (ከግስ ቶሰከ የመጣ)።
ቶሰቶስ (ቶስቷሳ): ፈሳም፣ ፈሪ፣ ነገር የማይችል (ፈሳም የሚመለስ)።
ቶሰከ: ሳይሰማ ተፈሳ።
ቶረበ: አራርቆ ወጋ (ተርታ ስፌት ሰፋ ወሰወሰ ሸደሸደ ሸለለ ሸክሸክ) ።
ቶራ (ሶር): የበረሓ እንስሳ፣ የዱር ላም፣ ያጋዘን ወገን። ተባቱም እንስቱም ቶራ ይባላል።
ቶራ (ግእዝ): ኹለቱ ቀንዶቿ ባለብዙ ባላ ባልቾ የኾኑ የበረዶ እንስሳ ወተታም የወሊያ ወገን (ዘዳ፡ ፲፬፡ ፭) ።
ቶራ መስክ: ቀድሞ ዘመን ቶራ ይሰማራበት የነበረ መስክ። በ፲፱፻፱ ዓ.ም የርስ በርስ ትልቅ ጦርነት ተደርጎ ራስ ሉል ሰገድና ፊታውራሪ ዘውዴ ጐበና ሌሎችም የጦር አለቆች ከነሰራዊታቸው የሞቱበት ሜዳ።
ቶራ ፈረስ (ሶር ወፈረስ): እንደ ቶራ ኹለት ቀንድ፣ እንደ ፈረስ ጋማና ጭራ ያለው የዱር እንስሳ። ፈረንጆች ግኑ ይሉታል።
ቶራ: ተንገደገደ፣ ፈገመ።
ቶራቢ: የቶረበ፣ የሚቶርብ (ሸድሻጅ፣ ሸክላኪ)።
ቶሮች: ኹለትና ከኹለት በላይ ያሉ ብዙዎች።
ቶፋ (ፎች): ሸክላ ባሬታ (ሴቶች ትና ማታ ግብር ውሃ ይዘው የሚወጡበት - አንቀጹ "ወተፈ" ነው - "ቻለ" ብለኸ "አይቻልን" አስተውል) ።
ቶፋ: ወኪል፣ ምትክ፣ ተጠሪ፣ ገባሪ።
ቷ አለ: ተበጠሰ (ቷቷ)።
ቷ አለ: ዉ አለ፣ ተበጠሰ። ፈጥኖ ወጣ፣ ፈሰሰ (የሴት ደም)። ቦግ ቧ አለ፣ ቶሎ በራ።
ቷ: የሩቅ ሴት ዝርዝር። "ላሚቷ በገቷ።"
No comments:
Post a Comment