Friday, June 6, 2025

፲፱ኛ፡ ፊደል፡ በግእዝ፡ አልፍ፡ ቤት፡ በአበገደ። በፊደልነት፡

ቀሓ፡ የአገር፡ የወንዝ፡ ስም፡ በበጌምድር፡ ውስጥ፡ ያለ፡ ዠማ። ምሳሌ: "የውሃ፡ የውሃ፡ ምን፡ አለኝ፡ ቀሓ"፡ እንዲሉ።

ቀሃ፡ የወንዝ፡ ስም፡ ቀሓ።

ቀህረማን (ዐረ)፡ ቈርበት፡ ካሪም።

ቀለ: ተለጠፈ፣ ታዘለ።

ቀለሔ፡ የቀለሕ፡ ዐይነት፡ ባዶ፡ ፍሬ፡ የሌለው፡ እኸል። ቀለኸን፡ እይ።

ቀለሔ፡ የኔ፡ ቀለሕ።

ቀለሕ(ሖች)፡ በቂጡ፡ ከምሱር፡ በውስጡ፡ ባሩድ፡ በፉ፡ ዐረር፡ የሌለበት፡ ውስጠ፡ ክፍት፡ ንሓስ።

ቀለሕ፡ ምላሽ፡ የርሳስ፡ መምታት፡ የቀለሕ፡ መመለስ፡ (መቅረት)

ቀለለ(ቀሊል፡ ቀለ)(ዘፍጥረት ፰፡ ፫)፡ ከክብደት፡ ከክብር፡ ከብዛት፡ ከብርታት ራቀ፡ አነሰ፡ ጐደለ። (ግጥም)"እንዴት፡ አደርጋለኹ፡ ብዬ፡ ስጨነቅ፡ እያደር፡ ይቀላል፡ ዐባይና፡ ሥንቅ። "

ቀለል፡ መቅለል።

ቀለል፡ አለ፡ አነስ፡ ጐደል፡ አለ።

ቀለል፡ የራቀ።

ቀለልተኛ፡ ቀላልነት፡ ያለው፡ ከመክበድ፡ የራቀ።

ቀለመ(ቀሊም፡ ቀለመ)፡ ቀለም፡ እዘጋጀ፡ ኣቦካ፡ ዐሸ።

ቀለመ፡ ምድር፡ ሳያስነካ፡ ያዘ፡ ቀለበ።

ቀለመ፡ ነካ፡ ነበዘ፡ አሳደፈ።

ቀለመ፡ ዐረደ፡ ቈረጠ፡ ከረከመ፡ ዐንገትን፡ ሥጋን፡ ቀሠምን።

ቀለመ፡ አጠቀሰ፡ ጻፈ፡ ጣፈ፡ ቀለምን፡ (ቃልን)፡ በብራና፡ በወረቀት፡ ላይ፡ አሳረፈ።

ቀለመ፡ ወርቅ፡ የወርቅ፡ ቀለም፡ የወንድና፡ የሴት፡ ስም።

ቀለመ፡ ጠጥ፡ ዐይነ፡ ባርማምጠ።

ቀለመው፡ ቀለሙ፡ ልብሱን፡ ነበዘው፡ አሳደፈው፡ ልብሱ፡ ቀለሙን፡ ሠረበው፡ ጠጣው፡ ተዋሐደው።

ቀለመጠ) (ቀመጠ፡ ለመጠ) አቀላመጠ፣ በምላስ ሙሬነት ወይም አማካይነት አፉን ጠረገ፣ አጮኸ፣ ምራቁን ዋጠ፣ አጣጣመ።

ቀለማት፡ ቀለሞች፡ ሕብሮች። "፯ቱ፡ ቀለማት"፡ እንዲሉ።

ቀለም(ሞች)፡ ከስንዴ፡ ዐራራና፡ ከአሜራ፡ ሥር፡ ከአውጥ፡ ፍሬ፡ የተበጀ፡ ጥቍርና፡ ቀይ፡ ልጥልጥ፡ ወይም፡ ፈሳሽ፡ (ኤርምያስ ፴፮፡ ፲፰) "በጥቍሩ፡ ሙጫ፡ በቀዩ፡ ከርቤ፡ ይገባበታል። " "ነጭ፡ ብጫ፡ ሰማያዊ፡ አረንጓዴ፡ ወይን፡ ጠጅ፡ ቀለም፡ የመሰለው፡ ኹሉ። " "እፍራንን፡ ዶልንና፡ ነድን፡ እይ፡ ዶለ፡ ነደደ። "

ቀለም(ዐረ)፡ ከጐሽ፡ መቃ፡ የተቀረጸ፡ ብር፡ መጻፊያ፡ ።

ቀለም፡ ቀሠም፡ ቀጪን፡ መቃ።

ቀለም፡ ቀባ፡ ላከከ፡ በቀለም፡ ሸፈነ፡ አለበሰ።

ቀለም ቀንድ፡ ቀለም፡ ያለበት፡ የቀለም፡ ቀንድ። (ግጥም፡ ተማሪ፡ በሞተ፡ ጊዜ)"ዐፈር፡ መልሱ፡ እንጂ፡ ደንጊያ፡ ለምናችኹ፡ የቀለም፡ ቀንድ፡ ነው፡ ትሰብሩታላችኹ። "

ቀለም፡ ትምርት፡ ቃለ፡ እግዚአብሔር። (ግጥም)"ይማርልኝ፡ ብዬ፡ በጌምድር፡ ሰድጄ፡ ቀለም፡ ገባው፡ አሉ፡ እሳት፡ ኾነ፡ ልጄ። " "ዐጤ፡ ቴዎድሮስ፡ ልጇን፡ ያቃጠሉባት፡ ሴት። "

ቀለም፡ አገባ፡ ነከረ፡ ዐለለ።

ቀለም፡ አግቢ፡ ዐላይ፡ (ኢሳይያስ ፴፮፡ ፪)

ቀለም፡ ደም፡ ግባት፡ ውበት፡ ላሕይ። (ግጥም)"ሥራ፡ ፈቶ፡ ዋለ፡ ትላንት፡ ሸማኔው፡ ያ፡ ቀለምሽ፡ ነወይ፡ የተበላሸው። "

ቀለም፡ ገባው፡ ምሁር፡ ኾነ፡ ትምርት፡ ዐወቀ።

ቀለም፡ ጐሽ መቃ፡ ከቅጥነቱና፡ ከውስጠ፡ ድፍንነቱ፡ በቀር፡ መቃ፡ የሚመስል።

ቀለምሽሽ(ምሸሽ)፡ ርቦ፡ ከቀለም፡ (ጐሽ፡ መቃ)፡ የተሠራ።

ቀለምጺጽ፡ የሠማ፡ የጋለ፡ ምጣድ፡ ድስት፡ ማሰሮ፡ ጀበና፡ ቂጥ፡ ብልጭልጭታ።

ቀለምጺጽ፡ የእሳት፡ ፍንጣሪ፡ ብራሪ፡ (ግእዝ)

ቀለሰ(ቀሊስ፡ ቀለሰ)፡ መለሰ፡ አጐበጠ፡ አደገነ፡ ቈለፈ።

ቀለሰ፡ አለቍንጮ፡ ቅስትኛ፡ ሠራ። "ጐዦ፡ ቀለሰ፡ እንዲሉ። "

ቀለሰ፡ አቀረቀረ። "ዐንገቱን፡ ቀለሰ፡ እንዲሉ። "

ቀለሰ፡ ኣረ፡ ከቀኝ፡ ወደ፡ ግራ፡ አዞረ።

ቀለሰ: አጐበጠ

ቀለሳቅለሳ፡ የመቀለስ፡ የማጕበጥ፡ ሥራ።

ቀለስ፡ መለስ።

ቀለስ፡ አለ፡ መለስ፡ አለ።

ቀለሸ)(ቀለበሸ)አቅለሸለሸ፡ አጥወለወለ፡ ልውጣ፡ ልውጣ፡ አለ።

ቀለቀለ) (ቀልቀለ) አንቀለቀለ (አንቀልቀለ) ባለማቋረጥ አነደደ፣ አንበለበለ። "በተገብሮነትም፡ ይፈታል።"

ቀለቀልቀልቃላ(ሎች)፡ የተንቀለቀለ፡ የሚንቀለቀል፡ ዘዋሪ፡ ቀዥቃዣ፡ ቀውቃዋ።

ቀለቀንዳ፡ አፈኛ፡ ተናጋሪ፡ ለፍላፊ፡ ወንድ፡ ወይም፡ ሴት። "ቀለ፡ ቃለ፡ ቀንዳ፡ ቀንድ፡ ቃለ፡ ደረቅ፡ ማለት፡ ነው። "

ቀለበ(ቀሊብ፡ ቀለበ፡ ቀለጰ) ረዳ፡ መገበ፡ ኣበላ፡ አጠጣ፡ (፪ኛ ሳሙኤል፡ ፲፱፡ ፴፪፡ ፴፫)

ቀለበ(ገለወ)፡ ሸፈነ፡ በውስጥ፡ አደረገ።

ቀለበ፡ ቀለጠፈ፡ ሰበቀለ።

ቀለበ፡ የተወረወረ፡ ነገርን፡ ምድር፡ ሳያስነካ፡ ያዘ፡ ተቀበለ፡ ጨበጠ፡ እጅ፡ አደረገ። ቀለመን፡ እይ።

ቀለበሰ፡ ከጫፍ፡ ወደ፡ ውስጥ፡ ወይም፡ ወደ፡ ውጭ፡ ዐጠፈ፡ ሸነቀረ፡ ቀነፈ።

ቀለበሸ፡ መለሰ፡ ገለበጠ፡ የውስጡን፡ በላይ፡ አደረገ፡ አቅለሸለሸ።

ቀለበተ፡ ቀለበት፡ ሠራ፡ አከበበ።

ቀለበታም፡ ቀለበት፡ ያለው፡ ባለቀለበት፡ ሰው፡ ዕቃ።

ቀለበት(ቀለበ)፡ ከብርና፡ ከወርቅ፡ ከንሓስ፡ ከመዳብ፡ የተሠራ፡ የጣትና፡ ያንገት፡ ክብ፡ ጌጥ፡ (ዘፍጥረት ፴፰፡ ፲፰) (ተረት)"በዋስ፡ ያለ፡ ከብት፡ በጣት፡ ያለ፡ ቀለበት። " "ሲበዛ፡ ቀለበቶች፡ ያሰኛል። " "ቀለበት፡ በጣት፡ የሚያዝ፡ ጣት፡ ቀለቡ፡ ማለትን፡ ያሳያል። "

ቀለባ፡ ቅልቢያ፡ ቅልቦሽ፣ (ቍላቤ)፡ መቅለብ።

ቀለብ፡ ሠራተኛ፡ በየወሩ፡ የሚቀበለው፡ ጥሬ፡ እኸል፡ ጥሩ፡ ታደፍ፡ (፩ኛ ነገሥት፡ ፩፡ ፯) "ባመት፡ ሲኾን፡ ምንዳ፡ ይባላል። "

ቀለብላባ፡ ቅልብልብ፡ (ቦች)፡ የተቅለበለበ፡ ክልብልብ፡ ስግብግብ፡ ችኩል። (ተረት)"ለቅልብልብ፡ ዐማት፡ ሢሶ፡ በትር፡ አላት። "

ቀለብተኛ(ኞች)፡ ቀለብ፡ ተቀባይ፡ ባለቀለብ፡ ቀለብ፡ ተሰፋሪ፡ በቀለብ፡ ዐዳሪ፡ ሎሌ፡ ገረድ፡ አሽከር፡ ወታደር።

ቀለተ(ትግ)፡ ረጠበ፡ ዐገዘ፡ ረዳ፡ በጠፋ፡ ተካ፡ ሰጠ።

ቀለተኛ፡ የቀለት፡ ወገን፡ ባለቀለት።

ቀለተኞች፡ ቀለት፡ ፈላጎች፡ ተቀባዮች።

ቀለታ፡ ዕገዛ፡ ርዳታ፡ ስጦታ፡

ቀለት፡ ርጥባን።

ቀለኸ(ቀለሕ)፡ ዝነበበ፡ ፍሬ፡ አልባ፡ ቀረ፡ የብር፡ ያበባ፡ ያገዳ፡ እኸል።

ቀለወ፡ ከለበ።

ቀለዋ፡ የዛፍ፡ ስም፡ ፍሬው፡ ለዕከክና፡ ለኮሶ፡ መድኀኒት፡ የሚኾን፡ አነስተኛ፡ የወይናደጋ፡ ዕንጨት።

ቀለው፡ ቀለው፡ አለ፡ ክልብ፡ ክልብ፡ አለ። (ግጥም)"ካንዱ፡ ቤት፡ አንዱ፡ ቤት፡ ስትይ፡ ቀለው፡ ቀለው፡ አንዱ፡ የነደደው ማዥራትሽን፡ ባለው። "

ቀለዘ፡ ኣለልክ፡ ደረቀ፡ ከቸለ፡ ጨለኸ።

ቀለደ(ቀሊድ፡ ቀለደ)፡ አሾፈ፡ ተረበ፡ አቧለተ፡ ዋዛ፡ ፈዛዛ፡ ተናገረ፡ አላገጠ፡ አፌዘ፡ አፌጠ፡ አሌጠ።

ቀለደ: አላገጠ አፌዘ

ቀለጠ፡ ተመታ። "በጥፊ፡ ቀለጠ። "

ቀለጠ፡ ወፈረ፡ ደነደነ፡ በጣም፡ ሠባ።

ቀለጠ፡ ደመቀ፡ አማረ። "ዘፈኑ፡ ቀለጠ፡ እልልታው፡ ቀለጠ። "

ቀለጠ፡ ጝ፡ ፈሰሰ፡ ተናደ፡ ወደቀ፡ ፈረስ፡ (መዝሙር ፳፪፡ ፲፬። ኢሳይያስ ፲፫፡ ፯) (ተረት)"እንደ፡ ፈንታሌ፡ ትቀልጣለኸ። "

ቀለጠ፡ ጠፋ። "ገንዘቤን፡ ለማንም፡ አበደርኹና፡ የትም፡ ቀልጦ፡ ቀረ። "

ቀለጠመ(ትግ፡ ቀልጸመ)፡ ቅልጥም፡ አወጣ፡ ቅልጥማም፡ ኾነ።

ቀለጠመ(አንጕዐ)፡ ቅልጥም፡ መታ፡ ሰበረ፡ ቅልጥም፡ አሳክሎ፡ ቈረጠ። "ገለጠመን፡ እይ፡ የዚህ፡ ሞክሼ፡ ነው። "

ቀለጠመ፡ ቅልጥም፡ በሚያኸል፡ ሽክና፡ ጠጣ፡ ዥው፡ አደረገ፡ ጨለጠ። "ገበሬው፡ ቀን፡ ከዱር፡ እቤት፡ በገባ፡ ጊዜ፡ ጠላውን፡ ባንኮላ፡ ቀለጠመው። "

ቀለጠጠ)(ገለጠጠ)፡ አንቀለጠጠ፡ ከፈተ፡ ፈጽሞ፡ ገለጠ፡ አንገለጠጠ። "በተገብሮነትም፡ ይፈታል። "

ቀለጠጥ፡ ቀልጣጣ፡ ቅልጥጥ፡ የሚንቀለጠጥ፡ እንቅልጥ፡ ከለላ፡ አልባ።

ቀለጠፈ(ቀለጠ፡ ለጠፈ)፡ ፈጠነ፡ ተከወነ፡ ቶሎ፡ ኾነ፡ ተደረገ፡ ሥራው፡ ነገሩ።

ቀለጣጠመ፡ ሰባበረ፡ ኰረታተመ፡ (፪ኛ ነገሥት፡ ፲፰፡ ፬። ሆሴዕ ፲፡ ፪) ጊዜ።

ቀለጤ፡ በዋል፡ ፈሰስ፡ ወፍራም፡ ሰው።

ቀለጦ፡ እንኵሮ፡ በተነኰረ፡ ጊዜ፡ ከገበር፡ ምጣድ፡ ላይ፡ ተለጥጦ፡ የሚወጣ፡ ሥሥና፡ ደረቅ፡ የንኵሮ፡ ቅሬታ።

ቀለፈፈ፡ ገለፈፈ፡ ቀፈፈ፡ ቈረጠ።

ቀለፋ)(ቈለፈ ቀፈለ)አንቀላፋ፡ ተኛ፡ ተጋደመ፡ ዐይኖቹን፡ ጨፈነ፡ ከንፈሩን፡ ገጠመ፡ ሰውየው፡ (ዘፍጥረት ፪፡ ፳፩። ኢሳይያስ ፵፫፡ ፲፯። ሉቃስ ፰፡ ፳፫)

ቀሊል፡ የቀለለ፡ ላባ፡ ገለባ፡ ላንፋ፡ የመሰለው፡ ኹሉ። ረከበን፡ እይ።

ቀሊል፡ የግእዝቀላል፡ የአማርኛ፡ ነው፡ ።

ቀሊል፡ ድበላ አደፍ፡ ያበባ፡ እኸል። "ብሥል፡ ተቀሊል"፡ እንዲሉ።

ቀላ(ቀልዐ። ዕብ፡ ቃላዕ)፡ መታ፡ ለጋ።

ቀላ(ቀዪሕ)፡ መቅላት።

ቀላ(ቄሐ)፡ ደም፡ መሰለ፡ (ምሳሌ ፳፫፡ ፴፩) (ሰማዩ፡ ቀላ)፡ ደመነ። (ዐይኑ፡ ቀላ)፡ በርበሬ፡ መሰለ።

ቀላ፡ ቈረጠ።

ቀላ፡ አለ፡ ቀላ።

ቀላል(ሎች)፡ የቀለለ፡ የቀለለች፡ የተሙን፡ ተቤሳ፡ ዶሮ። አገረ፡ ብለኸ፡ እግርን፡ ወገብን፡ ተመልከት።

ቀላል፡ መሬት፡ አሸዋማ፡ ስፍራ፡

ቀላል፡ ሴት፡ ቁም፡ ነገር፡ የሌላት።

ቀላል: ወሬኛ ሰው አባንፋው

ቀላመደ(ቃለ፡ ዐመፀ)፡ ዋሸ፡ ዘላበደ፡ ቀሣፈተ፡ በቃል፡ በደለ፡ ቃሉን፡ ከዳ።

ቀላሚ፡ የሚቀልም፡ ነባዥ፡ አሳዳፊ።

ቀላማ(ሞች)፡ ወላድ፡ ፈረስ፡ እንስት።

ቀላማጅ(ጆች)፡ የቀላመደ፡ የሚቀላምድ፡ ዘላባጅ፡ ቀሣፋች።

ቀላሳ፡ ጐባጣ፡ መላሳ።

ቀላሽ፡ አሪ፡ በሬ፡ (ጐዣምና፡ ጐንደር)

ቀላሽ፡ የቀለሰ፡ የሚቀልስ፡ መላሽ፡ አጕባጭ።

ቀላቀለ፣ አላቆጠ፣ አሸ፣ አዋዋደ፣ አቦካ። (ዘፍ. ፲፰፡ ፮፣ ፩ሳሙ. ፳፰፡ ፳፬)

ቀላቀለ፡ ደባለቀ፡ ቀየጠ፡ ዘነቀ።

ቀላቃይ፡ የቀላቀለ፡ የሚቀላቅል፡ ደባላቂ፡ ቀያጭ።

ቀላቢ(ላል) የሚቀልብ፡ ከላይ፡ ከሰማይ፡ ተቀባይ፡ ያዥ፡ ጨባጭ። "ኳስ፡ ቀላቢ"፡ እንዲሉ።

ቀላቢ(ዎች)፡ የቀለበ፡ የሚቀልብ፡ አብሊ፡ አጠጪ፡ ረድ፡ መጋቢ፡ ገረድ፡ ።

ቀላች(ቾች)፡ የቀለተ፡ የሚቀልት፡ ረጣቢ።

ቀላወጠ፡ ከጀለ፡ አፈጠጠ። (ተረት)"የወደዱትን፡ ሲያጡ፡ የጠሉትን፡ ይቀላውጡ። "

ቀላዋ(ከላዋ)፡ ከላባ።

ቀላዋጭ(ጮች)፡ የቀላወጠ፡ የሚቀላውጥ፡ አፍጣጭ። (ተረት)"ወጥን፡ ማን፡ ያውቃል፡ ቢሉ፡ ቀላዋጭ። "

ቀላዋጭነት፡ ቀላዋጭ፡ መኾን፡ አፍጣጭነት።

ቀላያት፡ ጥልቆች፡ ውቅያኖሶች።

ቀላይ(ቀለየ፡ ጠለቀ)፡ ጥልቅና፡ ሰፊ፡ ባሕር፡ ውቅያኖስ፡ (ዘፍጥረት ፩፡ ፪)

ቀላይ፡ የሚቀል፡ የማይከብድ።

ቀላድ(ዶች)፡ ከቃጫ፡ ከንሰት፡ ጭረት፡ የተገመደ፡ ገመድ።

ቀላድ፡ በቀላድ፡ የተለካ፡ አንድ፡ ጋሻ፡ መሬት። በግእዝ፡ ሐብለ፡ ርስት፡ ይባላል፡ (መዝሙር ፻፭፡ ፲፩)

ቀላድ፡ ጣለ፡ መሬትን፡ ለመለካት፡ ቀላድን፡ በምድር፡ ላይ፡ ዘረጋ፡ የረዘመውን፡ በገመድ፡ ያጠረውን፡ በክንድ፡ ለካ፡ መጠነ።

ቀላድ፡ ጣይ(ዮች)፡ ቀላድ፡ የሚጥል፡ (የሚዘረጋ)፡ ምድርን፡ የሚለካ።

ቀላድ: መቀርቀብ፡ ማሰር፣ መወደን፣ መጠመር።

ቀላጅ(ጆች)፡ የቀለደ፡ የሚቀልድ፡ አላጋጭ።

ቀላጤ(ቃለ፡ ሐፄ)፡ የንጉሥ፡ ቃል።

ቀላጤ(ዎች)፡ የንጉሥ፡ የዳኛ፡ ቃል፡ ነጋሪ፡ መልክተኛ። "ዐጤን፡ ይበልጡ፡ ቀላጤ፡ ሙክትን፡ ይሻል፡ ወጠጤ፡ እንዲሉ። "

ቀላጤ፡ ዋሻ፡ ቀላጤ፡ ካዲስ፡ አበባ፡ ወደ፡ ደብረ፡ ብርሃን፡ ሲኼድ፡ የሚያድርበት፡ ዋሻ፡ ስፍራ።

ቀላጥም (ሞች)፡ በቅልጥም፡ ልክ፡ የተሰበረ፡ (የተቈረጠ)፡ የቃሬዛና፡ የመሰላል፡ አግዳሚ፡ ዕንጨት።

ቀላጥቤ፡ ተናጋሪ፡ ለፍላፊ፡ ወሬ፡ አማቂ።

ቀላጭ፡ የሚቀልጥ፡ የሚማ፡ ፈሳሽ፡ ፈራሽ፡ ሠም፡ ሞራ፡ ተራራ።

ቀላጭ፡ ጌታ፡ ባለጠጋ፡ ሀብታም፡ ሰውነቱ፡ የሚያምር፡ ጭፍጭፍ፡ የሚል።

ቀላጭቱ፡ እመቤቲቱ፡ ወይዘሮዪቱ፡ (ኢሳይያስ ፵፯ ' )

ቀላጮች፡ ጌቶች፡ መኳንንት፡ ባለጠጎች፡ (፩ኛ ቆሮንቶስ፡ ፮፡ ፱)

ቀሌን፡ ቀርን፡ ዥ፥ዝኆን።

ቀሌንጅ()፡ ታናሽ፡ የዝኆን፡ ጥርስ።

ቀልማዳ፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ ዋሾ።

ቀልቀል(ትግ)፡ ኵስ፡ ዐይነ፡ ምድር፡ በዐዘቅተ፡ ኵስሕ፡ አፋፍ፡ ኹኖ፡ የሚጣል።

ቀልቀል፡ አፋፍ፡ ገደል፡ (ግእዝ)

ቀልቀልቱ፡ ዝኒ፡ ከማሁ።

ቀልቀሎ(ዎች)፡ የወጠጤ፡ ስልቻ። "ኦሮ፡ ግን፡ ትንሿን፡ ኰረጆ፡ ትልቁን፡ ቀልቀሎ፡ ይለዋል። "

ቀልበ፡ ቢስ(ሶች)፡ ልበ፡ ቢስ፡ ቀልበ፡ መጥፎ።

ቀልበ፡ ደረቅ፡ የጋኔን፡ ስም፡ ለዛ፡ ሙጥጤ።

ቀልበ፡ ጮሬ፡ ሾላካ፡ የማይጠመድ። ጮሬን፡ እይ።

ቀልባ፡ ቅልብጭ፡ የቀለበጪ፡ ቀልጣፋ፡ ቅልጥፍ፡ ስብቅል።

ቀልባሳ፡ የታጠፈ፡ ቀናፋ።

ቀልባሽ፡ የቀለበሰ፡ የሚቀለብስ፡ ቀናፊ።

ቀልባጣ(ቀልብ፡ ዐጣ)፡ ቀባጣሪ፬ አፉ፡ እንዳመጣ፡ የሚናገር።

ቀልባጣ፡ ቀባጣሪ ቀልብ።

ቀልቤ፡ ጫፉ፡ ደረቅ፡ አከቻማ።

ቀልብ ቀለበሰ፡

ቀልብ(ኦሮ)፡ ልብ፡ የልብ፡ ዕውቀት፡

ቀልዝ፡ ፍልማ፡ መሬት፡ (ጐዣም)

ቀልደኛ(ኞች)፡ ቀልድ፡ ወዳድ፡ ቧልተኛ፡ ፌዘኛ፡ ዋዘኛ።

ቀልድ፡ ከውነት፡ የራቀ፡ ጨዋታ፡ ተረብ፡ ቧልት፡ ፌዝ፡ ወዘበሬታ።

ቀልጠፍ፡ አለ፡ ፈጠን፡ አለ፡ ቀለጠፈ።

ቀልጠፍ፡ ፈጠን።

ቀልጣሚ፡ የቀለጠመ፡ የሚቀለጥም፡ ቅልጥም፡ መቺ፡ ሰባሪ።

ቀልጣማ፡ ሰባራ፡ ቶሎ፡ የሚሰበር።

ቀልጣፊ ቀልጣፋ(ፎች)፡ የሚቀለጥፍ፡ ከዝብዝብ፡ የራቀ፡ ፈጣን፡ (፩ኛ ሳሙኤል፡ ፲፰፡ ፲፯)

ቀልጣፋነት፡ ቀልጣፋ፡ መኾን።

ቀልጥፍ፡ የቅርብ፡ ወንድ፡ ትእዛዝ፡ አንቀጽ፡ ፍጠን፡ መር፡ በል፡ (ማሕርቆስ ፰፡ ፲፬)

ቀመ፡ አመለጠ፡ ጠፋ፡ ታጣ፡ (ተገብሮ)

ቀመለ(ቀሚል፡ ቀመለ)፡ ቅማል፡ አበጀ፡ ያዘ፡ ኣፈራ፡ ወለደ።

ቀመለ፡ ለቀሙ፡ በጥፍር፡ ዳጠ፡ ገደለ።

ቀመመ፡ ቅመምን፡ መድኀኒትን፡ ሰበሰበ፡ ፈጨ፡ አላመ፡ አዘጋጀ፡ ደባለቀ፡ ቀላቀለ፡ አንድነት፡ አደረገ፡ መጠነ።

ቀመሰ(ቀሠመ)፡ ጣመ፡ ለከፈ፡ በጥቂቱ፡ በላ፡ ጠጣ፡ ዋጠ፡ (ኢዮብ ፲፪፡ ፲፩) "አቶ፡ እከሌ፡ መድኀኒት፡ ስለ፡ ቀመሰ፡ እቤት፡ ዋለ። " "አብነትን፡ እይ። "

ቀመሰ፡ ተመታ፡ ተደበደበ። (በግብር)

ቀመሰ፡ ተቀበረ። "ዐፈርን፡ ተመልከት። "

ቀመሳቅምሻ፡ የመቅመስ፡ ድርጊት።

ቀመስ፡ መቅመስ። (ኹኔታ)

ቀመስ፡ አደረገ፡ ቀመሰ።

ቀመስ፡ የበላ። "ፈረንጅን፡ እይ። "

ቀመረ(ቀምሮ፡ ቀመረ)፡ ቈጠረ፡ መደበ፡ ለየ፡ ከፈለ።

ቀመር(ዐረ)፡ ጨረቃ።

ቀመር(ገመር)፡ የዥብ፡ ንጉሥ፡ ወቸገል፡ መልኩና፡ ጨፈረር፡ ጠጕሩ፡ ከዥብ፡ ኹሉ፡ የተለየ፡ ዥቦች፡ ፈርተው፡ ይሸሹታል፡ ትራፊውንም፡ ይበላሉ።

ቀመር፡ ቍጥር፡ የቍጥር፡ መደብ፡ ወይም፡ ክፍል፡ ዐውድ፡ ሰንጠረዥ።

ቀመር፡ ዋልታ፡ በዙሪያው፡ ከላይ፡ እስከ፡ ታች፡ ባለክፍል፡ ብስ፡ ያለው፡ (ግእዝ)

ቀመር፡ ፍሬው፡ ትንንሽ፡ የኾነ፡ አደን፡ ጓሬ።

ቀመቀመ(ከመከመ)፡ ጫፍ፡ ጫፉን፡ ሰፋ፡ ዘመዘመ።

ቀመቀመ፡ ብዙ፡ ጊዜ፡ ጠጣ።

ቀመቀመ፡ ወጣ፡ በቀለ፡ ቀነቀነ።

ቀመት፡ የሚዛን፡ ልክ፡ ፪፡ ተረን፡ ፩ ' ቀመት፡ ነው።

ቀመኛ(ቀበኛ)፡ ልብስ፡ የሚበላ፡ ከብት፡ የልብስ፡ ቀማኛ።

ቀመደ)(ገመደ)አቅመደመደ፡ እባብኛ፡ አስኬደ፡ እንደ፡ ገመድ፡ ጐተተ፡ ዐቅሙ፡ ቢስ፡ አደረገ፡ አሽመደመደ።

ቀመድማዳቅምድምድቅምድማጅ፡ የተቅመደመደ፡ ጕትት፡ ሽምድምድ።

ቀመጠ)(ቀምጦ፡ ቀመጠ)አስቀመጠ፡ ቍጭ፡ አደረገ፡ አሳረፈ፡ ጐለተ፡ እነበረ፡ ኣኖረ፡ አቈየ፡ አሰነበተ፡ (ዘፍጥረት ፪፡ ፲፭። ፩ኛ ነገሥት፡ ፭፡ ፭። ሉቃስ ፱፡ ፲፬፡ ፲፭) "ረፈቀን፡ አስተውል። " "አስቀመጠ፡ አስደራጊ፡ ሲኾን፡ ባድራጊነት፡ መተርጐሙ፡ (ቀመጠ)፡ በዘመን፡ ብዛት፡ ስለ፡ ተረሳ፡ ነው። " "(ዐወሰ)፡ ብለሽ፡ አስታወሰን፡ ተመልከት። "

ቀመጠለ(ገመደለ)፡ ፈጽሞ፡ አጐደለ፡ አሳነሰ። ጕዳይ

ቀመጠለ፡ ዐረደ፡ ጐመደ፡ ቀነጠሰ።

ቀሚ(ቀማሒ ቀማዒ)፡ የቀማ፡ የሚቀማ። "ሲበዛ፡ ቀሚዎች፡ ይላል። "

ቀሚሳዊ፡ እንደ፡ ቀሚስ፡ የሰውን፡ ገላ፡ የሚያጠልቅ።

ቀሚሴ(ቀሚስየ)፡ የኔ፡ ቀሚስ።

ቀሚሴ፡ የቂጥኝ፡ ስም፡

ቀሚስ(ሶች)፡ በ፫፡ ወገን፡ የተሰፋ፡ የሴት፡ ልብስ፡ ልኩ፡ ፮፡ ዘንግ፡ ፳፬፡ ክንድ፡ ነው። (ጥልፍ፡ ቀሚስ)፡ በሐር፡ የተጠለፈ፡ የተዘመዘመ። (ጥበብ፡ ቀሚስ)፡ ጥበብ፡ ያለበት፡ የጥበብ፡ ቀሚስ፡ (ዘጸአት ፵፡ ፲፬)

ቀሚስ፡ ለበሰ፡ ረዥም፡ የግምጃ፡ እጀ፡ ጠባብ፡ ዐብደላ፡ ካኒ፡ ተሸለመ፡ አጠለቀ።

ቀሚስ፡ እጀ፡ ሰፊ፡ የቄስ፡ የመነኵሴ፡ ልብስ፡ ረዥም፡ ጥብቆ፡ የሸማ፡ የሐር፡ የዳባ፡ (ዘፍጥረት ፴፯፡ ፳፫፡ ፴፪)

ቀሚስ፡ ዋና፡ ዲያቆን፡ የሱቲ፡ ቀሚስ፡ ለብሶ፡ ተንሥኡ፡ ጸልዩ፡ የሚል፡

ቀሚስ፡ የመሶብ፡ ልብስ።

ቀሚስ፡ የበቅሎ፡ የፈረስ፡ ኮርቻ፡ ልብስ።

ቀማ(ቀምሐ። ትግ፡ ቀምዐ)፡ ነጠቀ፡ ወሰደ፡ (ሚክያስ ፪፡ ፪)፡ ሸክሙን፡ ካናቱ፡ ሱሪውን፡ ከባቱ። (ተረት)"ዥብ፡ የኔ፡ ስለው፡ ወናፌን፡ ቀማኝ። " "ዘረፈን፡ እይ። "

ቀማ፡ መጥፋት፡ መታጣት።

ቀማመሰ፡ ለካከፈ።

ቀማሚ(ዎች)፡ የቀመመ፡ የሚቀምም፡ ሰብሳቢ፡ አዘጋጂ። "መድኀኒት፡ ቀማሚ፡ እንዲሉ። "

ቀማማ፡ ነጣጠቀ።

ቀማሪ፡ የቀመረ፡ የሚቀምር፡ ቈጣሪ፡ መዳቢ።

ቀማሽ(ሾች)፡ የቀመሰ፡ የሚቀምስ፡ ቀን፡ ከሕዝብ፡ አስቀድሞ፡ በቤተ፡ መንግሥት፡ የሚበላ፡ የሚጋበዝ፡ መኰንን፡ ባለማዕርግ። "እንወራረድ፡ አህያ፡ እንረድ፡ እኔ፡ ጠባሽ፡ አንተ፡ ቀማሽ፡ እንዲሉ፡ እረኞች። "

ቀማሽነት፡ ቀማሽ፡ መኾን።

ቀማኛ(ኞች)፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ ነጣቂ፡ ዳንዴ፡ ወንበዴ፡ ሽፍታ፡ ነጥቆ፡ በረር።

ቀማኛነት፡ ቀማኛ፡ መኾን፡ ነጣቂነት።

ቀማይ(ዮች)፡ የቀመለ፡ የሚቀምል፡ ቅማል፡ ገዳይ።

ቀምሶ፡ ጥሞ። "ቀምሶ፡ ሰጠ፡ እንዲሉ። "

ቀምቀሞ፡ እጅግ፡ በጣም፡ ዐጪር፡ ጠጕር፡ በራስና፡ ባገጭ፡ ላይ፡ በቅሎ፡ የሚታይ።

ቀምቃሚ(ዎች)፡ የቀመቀመ፡ የሚቀመቅም፡ ሰፊ፡ ዘምዛሚ።

ቀምበር፡ የበሬ፡ ዕቃ ቀነበረ።

ቀምቶ፡ በላ፡ እየነጠቀ፡ የሚበላ።

ቀምቶ፡ ነጥቆ።

ቀምጣላቅምጥል፡ የተቀመጠለ፡ ጐደሎ።

ቀምጣይ፡ የቀመጠለ፡ የሚቀመጥል፡ አጕዳይ።

ቀሠመ (ቀሢም ቀሠመ): አበባን፣ ደምን፣ ርጥበት ያለውን ነገር ኹሉ ለቀመ፣ ሰበሰበ፣ መጠጠ።

ቀሰመ: ለቀመ፣ ቀሠመ።

ቀሰመ: ቀመመ፣ እጣፈጠ (ግእዝ)

ቀሠማ: ለቀማ፣ ስብሰባ፣ መጠጣ።

ቀሠም (ሞች) (ቀሠብ): የቀጪን መቃ ቍራጭ፡ የማግ መደወሪያ። "ቀለምን እይ፡ ቀለመ። "

ቀሰም (ቀጪን፣ መቃ): ቀሠመ።

ቀሠም: የወርቅ፣ የብር ጥብጣብ።

ቀሰሰ (ቀሲስ፡ ቀሰ): ቅስና ተቀበለ። "(ተረት) ያልተሾመ እያዝ፡ ያልቀሰሰ አይናዘዝ። "

ቀሰሰ: ቀዘዘ፡ ፈዘዘ።

ቀሰስ: የፈዘዘ።

ቀሰስተኛ (ኞች): ፈዛዛ።

ቀሰረ (ቀተረ): ገተረ፣ አቆመ። "ቀና '' 'ሰና' ተወራራሽ መኾናቸውን አትዘንጋ። "

ቀሠረ: ገተረ፣ ቀሰረ።

ቀሰቀሰ (ትግ፡ ቀስቀሰ፣ አወከ): ነቀነቀ፣ አነቃ፣ አስነሣ።

ቀሰቀሰ: በረበረ፣ ፈተሸ። "ሌባ በተያዘ ጊዜ ዘበኞች ኪሱን ይቀሰቅሱታል። "

ቀሠብ (ዐረ: ቀጸብ): መቃ ውስጠ ክፍት ዕንጨት፡ ወይም ብረት።

ቀሰብ: ባሕረ ጃን ቀሠብ።

ቀሠብ: ባሕረ ጃን የበቅሎ ዕቃ ጌጥ፡ ዐልፎ ዐልፎ ብስ ነዳላ የሚታይበት፡ በያይነቱ ቀለም ያለው ወረቀት።

ቀሠብ: ውድ የሬት ሽቱ (መሓልየ መሓልይ ፬፡ ፸) "በግእዝ ዐልው ይባላል። "

ቀሰተ (ቀስተወ): ደገነ፣ አጐበጠ። ቀሳች: የቀሰተ፣ የሚቀስት፡ ደጋኝ፣ አጕባጭ። ቀስት (ቶች): የወስፈንጠር፣ የፍላጻ መወርወሪያ ደጋን፡ የጦር መሣሪያ (፩ኛ ሳሙኤል ፲፰፡ ፬) አቀሳሰት: አደጋገን፡ መቀሰት።

ቀሠተ: ደገነ፣ ቀሰተ።

ቀሠጠ (ቀሢጥ ቀሠጠ): በስውር ከፍሎ ሰረቀ፣ ወሰደ፡ ዐበለ።

ቀሰጠ: ሰረቀ፣ ቀሠጠ።

ቀሠፈ (ቀሢፍ ቀሠፈ): መዓት አመጣ፡ ዕድሜ አሳጠረ፡ ቀጪ፣ ቀጠፈ፡ በድንገት ገደለ፣ አጠፋ፣ ባጪር አስቀረ (ዐፍለኛን) (ዘዳግም ፭፡ ፲፩፡ ፪ኛ ሳሙኤል ፮፡ ፯)

ቀሠፈ: ሰቀዘ፣ ወጠረ፣ አስጨነቀ፡ ጐን በስ፣ ቀና አላሠኝ አለ።

ቀሠፈ: ደገነ፣ አጐበጠ።

ቀሲስ: ቄስ። "አቡነ ቀሲስ" እንዲሉ።

ቀሳ (ዕብ፡ ቃጻህ፡ ለየ): ብቻ፣ ብቻነት፣ ልዩነት። "ፈረንጆች 'ካራንቴን' ከሚሉት ጋራ ይሰማማል። "

ቀሳ ወጣ: ከቤት ወደ ዱር ኼደ፡ በደን ተቀመጠ፣ ተኛ፣ ታመመ፡ ከቤተሰቡ ተለየ (የሚጋባ በሽታ ተስቦ ስለ ያዘው)

ቀሣሚ: የቀሠመ፣ የሚቀሥም፡ ለቃሚ፣ ሰብሳቢ (ንብ፣ ጥንዝዛ፣ ጣዝማ፣ ዝንብ፣ ብራብሮ፣ ወፍ)

ቀሳሪ: የቀሰረ፣ የሚቀስር፡ ገታሪ።

ቀሳራ (ቅስር): የተቀሰረ፡ ገታራ፣ ግትር።

ቀሳሽ (ሾች): የሚቀስ፣ ቄስ የሚኾን።

ቀሳቀሰ: በራበረ።

ቀሳቀሰ: አነቃቃ።

ቀሣጢ: የቀሠጠ፣ የሚቀሥጥ፡ ዐባይ፣ ሌባ። "ቀሣጢ ሌባ" እንዲሉ።

ቀሣጢነት: ቀሣጢ መኾን፡ ሌብነት፣ ዐባይነት።

ቀሣፈተ: ቀላመደ፣ ዐበለ፣ ዋሸ፣ ወላ ወለ፣ ዘላበደ፣ ቀባጠረ፣ ቀባዠረ፡ ቅሥፈት የሚያመጣ ነገር ተናገረ።

ቀሣፊ: የቀሠፈ፣ የሚቀሥፍ፡ ገዳይ፣ አጥፊ፣ መልአከ ሞት።

ቀሣፋች: የቀሣፈተ፣ የሚቀሣፍት፡ ዐባይ፣ ወላዋይ፣ ቀባዣሪዞ ዠር።

ቀሣፋችነት: ወላዋይነት፣ ቀባዣሪነት።

ቀስ አለ: ዝግ አለ።

ቀስ አለ: ዝግ አለ ቀሰሰ።

ቀስ: ዝግ ቀሰሰ።

ቀስ: ዝግ። "ቀስ በል!" "ቀስ ብሎ" እንዲሉ። "(ተረት) ሴትና ቄስ ቀስ። "

ቀስመን: የልብ ቃታ፡ ዘሩ ቀሰመ ነው።

ቀስመን: ግድ፣ ግዴታ።

ቀሥም: አዝመራ (ግእዝ)

ቀስር: ዝኒ ከማሁ። "(ተረት) ምስር ሙርጠ ቀስር። "

ቀስቃሽ (ሾች): የቀሰቀሰ፣ የሚቀሰቅስ፡ ነቅናቂ፣ አስነሽ፡ በርባሪ፣ ፈታሽ።

ቀስቅስ: የልዑል ራስ ካሳና የልዑል ራስ እምሩ ፈረስ ስም፡ 'ነቅንቅ፣ አንቃ፣ አስነሣ' ማለት ነው።

ቀስተ ደመና: የደመና ደጋን (ባላ፬ ሕብር)፡ የማርያም መቀነት። "በበልግ ዝናም ጊዜ ጫፍና በሰሜንና በደቡብ፣ መካከሉ ወደ ላይ ወደ ሰማይ ኹኖ ይታያል። " "ከላይ ወደ ታች አረንጓዴ፣ ቀይ፣ ብጫ፣ ሰማያዊ ቀለም አለው። "

ቀስተኒቻ: የዕንጨት ስም፡ ለቀስት፣ ለወስፈንጠር የሚኾን (ጕብጠት የሚስማማው ዕንጨት)፡ ኹለተኛ ስሙ ሰሪቴ ይባላል። "መቃን ተመልከት። "

ቀስተኛ (ኞች): በቀስት የሚዋጋ፣ ባለ ቀስት፡ አውሬ የሚያድን፣ ነዳፊ (ዘፍጥረት ፳፩፡ ፳)

ቀስቱን ለጠጠ: ሳበ፣ ወጠረ፣ ገተረ፣ አዘገበ።

ቀስታ: ዝግታ። "በግእዝ ድቡት ጽሚት ይባላል፡ ንኡስ አገባብ ነው። " "ታቦት የተሸከመ ቄስ በቀስታ ይኼዳል። "

ቀሥፋታ: ዝኒ ከማሁ ለቀሣፋች።

ቀረ (ቀረየ): ተረፈ፣ ዳነ፣ ተተወ። "ሳይያዝ ሳይገደል ቀረ። "

ቀረ: ቈየ፣ ዘገየ፡ ተቀመጠ። "ሳይኼድ ሳይመጣ ቀረ፡ እቤት ቀረ። "

ቀረ: ቆመ፣ ተከለከለ። "በኤልያስ ዘመን ዝናም ቀረ። " "ለእስራኤል የሚወርድ መና በፊንቆን ቀረ። "

ቀረ: ተለወጠ፣ ዐለፈ። "(ሲቀር ይቀራል): የሞተ ሰው ከቀባሪዎች ተለይቶ በመቃብር ሲቀር ሀብቱ እንዳልነበረ ይኾናል፡ በቤት ይቀራል (መዝሙር ፵፱፡ ፲፯) " "ቀረ : መነሻ እየኾኑት ሲነገር፡ ከቀረ ሊቀር ሲቀር፡ ባሉታም ካልቀረ ላይቀር ሳይቀር ይላል። " " : ራብዕ የኾኑት አን ጐርደው ነው። " "(ባጪር ቀረ): ቶሎ ሞተ። "

ቀረ: አነሰ፣ ጐደለ። "ሳይመላ ቀረ። "

ቀረ: ዐጣ፣ ነጣ፣ ባዶ እጅ ኾነ። "መና ቀረ። "

ቀረመተ (ቀሪም፡ ቀረመ): ከፈለ፣ ተነተነ (ሥጋን፣ ዐጥንትን)

ቀረመት: ቅርምት፡ ቅርጫን የሙዳ ክፍል።

ቀረሰሰ) (ቀሰሰ): አንቀረሰሰ (ጥልቁ ) አዘገመ፣ በቀስታ አስኬደ፣ ወሰደ። "ትግሬ 'ሐባብም ቀርሰሰ' ብሎ 'ከሳ' ይላል።"

ቀረሰስ (ቀርሳሳ): የተንቀረሰሰ፣ ዝግተኛ፣ ዘገምተኛ።

ቀረረ (ቈሪር፡ ቈረ): ጠለለ፣ ጠራ (ጥራት አገኘ) (ቅራሪው፣ አተላው በታች፣ ጥሩው በላይ ኾነ)

ቀረረ: የጦር ግጥም ገጠመ፣ አጕራራ።

ቀረራ: የርሾ ጥላይ።

ቀረርቱ: ሽለላ፣ የጦር ዘፈን።

ቀረሮ: የዛፍ ስም።

ቀረሸ: ምግብን ከሆዱ ጥቂት ፍልቅ አደረገ፣ አወጣ፡ አስታወከ፣ አፈሰሰ (ሕፃኑ)

ቀረሸ: አወጣ አስታወከ አስመለሰ

ቀረሸመ: ገጨ፣ ሰበረ።

ቀረሻሸመ: ሰባበረ።

ቀረሻሽምቦ: ቅጠል ቀረሸመ፡ ቅራት ያሞራ ቤት ቀራ።

ቀረሻሽምቦ: በቀላል የሚሰበር ዕንጨት፡ አገዳው ውስጠ ክፍት የኾነ የጨቆ የረግረግ ቅጠል፡ መሽረብ፣ ውሃ መምጠጫ፣ መጠጫ ዕፅ።

ቀረሽ: የቀረው፣ የጐደለው። "ዱላ ቀረሽ፣ ላባ ቀረሽ" እንዲሉ።

ቀረቀረ (ቀቀረ): አገባ፣ ሸጐረ፣ ለገደ፣ ወረወረ።

ቀረቀረ (ትግ፡ ቀርቀረ): ከረከረ፡ አሳጥሮ ቈረጠ።

ቀረቀረ: ጐረሠ፣ በላ። "(ተረት) ጦም ከማደር ዳቦ ቀርቅር። "

ቀረቀረ: ጥይትን ለጠመንዣ አጐረሠ።

ቀረቀበ (ቀረበ): ኹለት ሸክምን፣ ጭነትን ባንድነት አሰረ፣ ወደነ፣ ጠመረ፣ ቈረኘ፣ አረተ።

ቀረቀፈ: ከረከረ።

ቀረበ (ቀርበ): ቅርብ ኾነ፡ ለጠቀ፣ ተጠጋ (ዘፍጥረት ፳፱፡ ፲)

ቀረበ: ነዳ፣ ወሰደ (ከብትን)

ቀረበ: እሰው ፊት ተቀመጠ (ገበታው)

ቀረበበ (ገረበበ): አንቀረበበ፡ እንገረበበ፣ አንቀረደደ፣ አንከረፈፈ። "በተገብሮነትም ይፈታል። "

ቀረበጠ): አንቀራበጠ፣ ካንዱ ስፍራ ወደ ሌላው አዛውሮ አስቀመጠ።

ቀረባ (ኦሮ): ወረንጦ (ጫፍና ጫፉ በመቃረብ እሾኸን፣ ሥንጥርን ቈንጥጦ ከእግር፣ ከገላ የሚነቅል መሣሪያ)፡ መቈንጠግና መዘንጠያ።

ቀረባ: የመንዳት ሥራ፡ መቅረብ።

ቀረብ (ቀሪብ): ጠጋ፣ ለጠበቅ።

ቀረብ አለ: ጠጋ አለ፡ ቀረበ።

ቀረት አለ: ቅዝዝ አለ፡ ጥቂት ጐደለ (ስፍሩ)

ቀረት: አነስ፣ ጐደለ።

ቀረነ (ቀሪን፡ ቀረነ): ቀንድ አወጣ፡ ጠላ፣ ወጋ።

ቀረነተ: በቅራና አጥብቆ አሰረ፣ ቀረቀበ።

ቀረና (ትግ፡ ቀርንዐ): ቀንድ ቀንድ አለ፡ ሸተተ፣ ገማ። "ጐረናን እይ። "

ቀረንደላ: የተቃጠለ እኸል።

ቀረንጠሎ: ባሪያ (የባሪያ ወገን) ወይም ልብሱ።

ቀረዋ: ከወደ ጫፉ ቀና ያለ ጐራዴ።

ቀረዋ: የብረት ቍና (በሐረርጌ የሚገኝ) "አንዳንድ ሰዎች ቀረዋ የሚባል ፈረንጅ ስላመጣው በርሱ ስም ቀረዋ ተባለ ይላሉ፡ እውነት መኾኑን እንጂ። "

ቀረዘ (ቀረጸ): ያዘ፣ እነሣ፣ ተሸከመ።

ቀረደደ (ቀረፀ): ቈረጠ፣ ቈረሰ፣ ገመሰ (ጐመንን፣ እንጀራን፣ ምድርን)

ቀረደድ: ቀርዳዳ፡ የተንቀረደደ፣ የሚንቀረደድ፡ ከረፈፍ፣ ከርፋፋ።

ቀረጠ (ቀረፀ፡ ጸ): ቈረጠ፡ አሾለ።

ቀረጠ: ዕዳሪ አወጣ።

ቀረጠ: ወደ ገበያ መጥቶ ከሚሸጥ ነገር ላይ አነሣ፣ ወሰደ (ማርቆስ ፪፡ ፲፬)፡ ወይም በዚህ ፈንታ አሞሌ፣ ብር፣ አላድ፣ ሩብ መሐለቅ ተቀበለ። "፫ኛውን ዐጠረ በ፭ኛ ተራ ተመልከት፡ ቀረጸን እይ። "

ቀረጠፈ (ቀረጠ፡ ቀጠፈ): የጌሾን ቀንበጥና ቅጠል በቅርብ በቅርብ እየመታ ቈረጠ፣ አጠቀነ፣ አደቀቀ። "የጐመንና የሥጋ ሲኾን ቀረደደ ከተፈ ያሠኛል። "

ቀረጠፈ: ሰውነትን ዐመመ።

ቀረጣ: መቅረጥ።

ቀረጣጠፈ: ቈራረጠ፣ አጠቃቀነ፣ አደቃቀቀ።

ቀረጣጠፈ: ዐማመመ።

ቀረጥ (ቀረፅ): ካሥር አንድ (ዐሹራ)

ቀረጥ (ጦች): ያነስተኛ ዛፍ ስም፡ ሰዎች እየቀረጹ የጭራ፣ የጅራፍ፣ የማማሰያ፣ የማንካ፣ የወስፌ ዕንወት ያደርጉታል።

ቀረጥ: ቀርጣ፡ ዕዳሪ በማረሻ መስቀልኛ የሚቈረጠ።

ቀረጨመ): ተቀራጨመ፣ ተሰበሰበ፣ ተጠራቀመ፣ ተቀናበረ።

ቀረጪ): አንቀራጩ፣ ቈረጠመ፣ አንቀጫቀጨ (ቈሎን) አፋጩ (ጥርስን)

ቀረጪጪ: አጥብቆና አጥልቆ ነከሰ፣ ጐዳ፣ አሳመመ (እስካጥንት ድረስ)

ቀረጸ (ቀሪጽ፡ ቀረጸ): ቀረጠ፡ ዐነጠጠ፣ ፈለፈለ፣ ጐበጐበ፣ አሰመጠ፣ አሰነበረ፣ ነቀሰ።

ቀረፀ: ቈረጠ (ጠጕርን)

ቀረፈ (ቀሪፍ፡ ቀረፈ): ላጠ፡ መለጠ፣ ለጠጠ (ቅርፊትን አስወገደ)፡ ሰበረ፣ ፈለጠ፣ ነጠለ፣ አነሣ።

ቀረፈ: ተወ፣ አጠፋ። "ቂሙን ቀረፈ" እንዲሉ።

ቀረፈፈ) (ከረፈፈ): አንቀረፈፈ፣ አረዘመ፣ አንከረፈፈ፣ አንቀረበበ። "በተገብሮነትም ይፈታል።" "ቀረደደ ብለኸ ኣንቀረደደን እይ።"

ቀረፈፍ: ቀርፋፋ፡ ከረፈፍ፣ ከርፋፋ።

ቀረፋ: መቅረፍ።

ቀረፋ: ሽቱነትና ቅመምነት ያለው ቅርፊት (ከባሕር የመጣ) (ዘፀአት ፴፡ ፳፫፡ ኢሳይያስ ፵፡ ፳፬፡ ራዕይ ፲፰፡ ፲፫) "በግእዝ ቀንሞን ይባላል። "

ቀሪ (ዎች): የቀረ፣ የሚቀር፡ ተለዋጭ፣ ዐላፊ፡ የማይፈለግ ነገር (ቀሪ)፡ አባትና እናቱን ቀብሮ ሳይሞት የሚቈይ፡ ቋሚ።

ቀሪቦ: ሞኝ ሰው፡ ብርታት የሌለው።

ቀሪቦ: ወዲያው ተበጥብጦ የሚጠጣ የዳር አገር ጕሽ።

ቀሪነት: ቀሪ መኾን፡ ዐላፊነት።

ቀራ: ሌሊት ከብትን ጠበቀ (ጐዣም) "ዘሩ በግእዝ ቀርዐ ነው። "

ቀራረመ: ለቃቀመ፣ ሰባሰበ።

ቀራረፈ: መቀራረፍ፡ መመላለጥ፣ መላላጥ፣ መፈላለጥ።

ቀራቅር: በጠገዴ ወረዳ የሚገኝ ከተማ።

ቀራቢ (ዎች): የሚቀርብ፣ የሚነዳ፣ የሚጠጋ፡ ነጂ።

ቀራንዮ: በኢየሩሳሌም ውስጥ ያለ ቦታ፡ የራስ ስፍራ ማለት ነው።

ቀራውሎ: ሞኝ፣ ቂል።

ቀራጭ (ጮች): የቀረጠ፣ የሚቀርጥ፡ እሿይ፣ ዐጣሪ፡ የገበያ ግብር ተቀባይ (ማቴዎስ ፱፡ ፲-፲፩፡ ሉቃስ ፫፡ ፲፪)

ቀራጭነት: ቀራጭ መኾን።

ቀራፊ (ዎች): የቀረፈ፣ የሚቀርፍ፡ የሚልጥ፣ የሚመልጥ፣ ሰባሪ፣ ፈላጭ፡ የሙጋድ ዕንጨት አቅራቢ።

ቀራፎ (ዎች): የቅል ስባሪ፣ ፋጋ፡ ቂል ሰው።

ቀርም: የፍሬ ለቀም (ግእዝ) "ሰው እንዳቅሙ፡ እኸል እንደ ቀርሙ" እንዲሉ።

ቀርቀም: በውሃ ዳር የሚበቅል ታናሽ ቅጠል።

ቀርቀሬ (ቀልቀላዊ): የቀርቀር፡ ቈላ፣ ጐድጓዳ (የታች ታች) "(ተረት) ቀርቀሬ ወርጄ ማር ስልስ ማር ልክፈል። "

ቀርቀር (ቀልቀል): ገደል፣ ተራራ።

ቀርቀቦ: ማንቀርቀቢያ ሰፌድ።

ቀርቃሪ: የቀረቀረ፣ የሚቀረቅር፡ አግቢ፣ ሸጓሪ።

ቀርቃሬ: ቀባ፣ መሪ ወፍ (ጐንደር)

ቀርቃቢ: የቀረቀበ፣ የሚቀረቅብ፡ ኣሳሪ፣ ወዳኝ።

ቀርቃባ (ቦች): በኹለት ወገን የታሰረ መንታ ጭነት።

ቀርቃባ ጠፍር: ካንዳንድ በኩል ጫፉ እየታጠፈ የተሰፋ ቅራና፣ የቀርቃባ ጠፍር።

ቀርበቦ (ዎች): በጋን ቂጥ የተበጀ የበሬ ግንባር (ቈዳ)፡ ሚዛን ቍና። "እስላም በመንደሯ በቀርበቦ ትማታለች" እንዲሉ።

ቀርበታ ሆድ: ሆደ ትልቅ።

ቀርበታ: የውሃ ኣቍማዳ።

ቀርቦታል: ተጠግቶታል። "ደጉን ሰው መንፈስ ቅዱስ ቀርቦታል፡ ክፉውን ሰው ሰይጣን ቀርቦታል" እንዲሉ።

ቀርነ በግዕ: የበግ ቀንድ፡ እሱን የሚመስል የድጕስ መሣሪያ።

ቀርን: ቀንድ (ግእዝ)

ቀርካሓ (ቀርክሓ፡ ከርካዕ): የዛፍ ስም፡ ውስጥ ክፍት ዕንጨት። "እንዝርት፣ ተራዳ፣ ሣጠራ ይኾናል፡ ለቤት ሥራ ያገለግላል። "

ቀርዱ: የአራራት ተራራ።

ቀርዳጅ: የቀረደደ፣ የሚቀረድድ፡ ቈራጭ፣ ገማሽ።

ቀርጠሙሽ: የቀድሞ ዘመን የጋሻ ጌጥ። "የሙሽ ቅርጥ ማለት ይመስላል። "

ቀርጣፊ: የቀረጠፈ፣ የሚቀረጥፍ።

ቀርጥ: የርሻ ክፍል (መዛሮ)

ቀሸ: አኰራ፣ ለጠጠ (ባነጋገር)

ቀሸመደ: በፍጥነት ሰበረ፣ አነከተ።

ቀሸመድ (ቀሽማዳ፣ ቅሽምድ): የተቀሸመደ (ሰባራ፣ ስብር)፡ ደካማ።

ቀሸማመደ: ሰባበረ፣ አነካከተ።

ቀሸረ (ቀተረ): ከሸነ፣ አሳመረ።

ቀሸረ: ነፋ፣ ቀበተተ (ሆድን) "ገሸረን እይ። "

ቀሸረረ: ከሳ፣ ደረቀ። "ከሸለለን ተመልከት። "

ቀሸረር (ቀሽራራ): የከሳ፣ የደረቀ፡ ደረቅ።

ቀሸቀሸ) (ከተከተ): ተንቀሻቀሸ፣ ተሰባበረ፣ ተንከታከተ።

ቀሻሪ: የቀሸረ፣ የሚቀሽር፡ ከሻኝ፣ አሳማሪ።

ቀሽመሪ: ሠቅጌጠኛ፣ መታጠቂያ። "መሪ ቄስ ማለት ይመስላል። "

ቀቀለ: አሞቀ፣ አፈላ፣ አበሰለ፣ አነፈረ (እኸልን፣ ሥጋን)፡ ወጥ ሠራ (ዘጸአት ፴፬፡ ፳፮፡ ፪ኛ ነገሥት ፮፡ ፳፱፡ ሰቆቃው ፬፡ ፲፡ ዘካርያስ ፲፬፡ ፳፩)

ቀቀለ: አራሰ አረሰረሰ

ቀቀረ (ጸለወ): ዦሮውን መለሰ፣ ጣለ (ለመስማት፣ ለማድመጥ)

ቀቀበ: ነፈገ፣ ሠሠተ፣ ሰገበ።

ቀቀበታም: ሥሥታም፣ ንፉግ፣ ስግብግብ፣ ስገባ በል (ዮሴፍ)

ቀቀበት: ቀቀባ (ሰገባ)፡ ንፍገት፣ ሥሥት።

ቀቀተ (ቄቀየ): ነፈገ፣ ጮቀ፣ ቤሰ፣ ሠሠተ።

ቀቀት: ቅቅት፡ ንፍገት፣ ሥሥት።

ቀቃ (ከካ): መታ፣ አቈሰለ፡ ነደለ፣ ፈነቀለ። "ቃቃንን እይ፡ የዚህ ዘር ነው። "

ቀቃሪ: የቀቀረ፣ የሚቀቅር።

ቀቃይ (ዮች): የቀቀለ፣ የሚቀቅል፡ አፍሊ፣ አንፋሪ፣ ወጥ ሠሪ። "ንፍሮ ቀቃይ፣ ዶዮ ቀቃይ" እንዲሉ።

ቀቅ: ትንሽ ካሳ ለቈሰለ የሚሰጥ። "የቀቅ ከፈለ" እንዲሉ።

ቀቅ: ዋግ፣ ብትን (ድልኸ የሚመስል የእኸል በሽታ)፡ ስንዴን የሚመታ ቀጭ ብርድ።

ቀበለ) አቀበለ፡ እጅ፡ በጅ፡ ሰጠ፡ አስረከበ፡ እስያዘ፡ (ነህምያ ፲፫፴፩)

ቀበሌ (ዎች)፡ ገደማ፡ ዘንድ ()፡ ጋ።

ቀበሎ፡ ድር፡ ሲቋጠር፡ በስተጥርስ፡ በኩል፡ ተቀምጦ፡ መቀበል።

ቀበረ (ቀቢር፡ ቀበረ)፡ ራስን፡ ወደ፡ ምዕራብ፡ እግርን፡ ወደ፡ ምሥራቅ፡ አድርጎ፡ ሬሳን፡ አንጋለለ፡ በዠርባ፡ አስተኛ፡ በድንን፡ ማንኛውንም፡ ነገር፡ ዐፈር፡ አለበሰ፡ ሸፈነ፡ በጕድጓድ፡ ውስጥ፡ ደፈነ፡ ደበቀ፡ ሸሸገ።

ቀበረ፡ ሰውን፡ ጐዳ፡ ጨቈነ፡ እንዳይታወቅ፡ እንዳይከብር፡ እንዳይጠቀም፡ አደረገ። (አዝማሪ)"የወዲያ፡ ሰዎች፡ ክፋታቸው፡ ሬሳ፡ አስቀምጠው፡ መብላታቸው። ...... ሰው፡ መልካም፡ ወንድሙን፡ ሳይቀብር፡ አይበላም"(ጦቢት ፲፯) (በቁም፡ ቀበረ)፡ ወንጀለኛን፡ ከራሱ፡ በታች፡ እመሬት፡ አገባ፡ እንደ፡ ራስ፡ ዐምዶ።

ቀበረረ) አንቀባረረ፣ አቀማጠለ፣ አንደላቀቀ፣ አሞላቀቀ፣ የልጅን ጠባይ አበላሸ። በተገብሮነትም ይፈታል።

ቀበረር፡ ቀብራራ፡ የተንቀባረረ፡ እንቅብር፡ ቅምጥል፡ አያት፡ ያሳደገው፡ ልጅ።

ቀበራ፡ ደፈና፡ የመቅበር፡ ሥራ፡ ዐፈር፡ ምለሳ።

ቀበራርት፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ የካህናት፡ ዐማርኛ።

ቀበር፡ የቀበረ። (ተረት)"ማን፡ ይንገር፡ የነበር፡ ማን፡ ያርዳ፡ የቀበር። "

ቀበርቾ፡ መድኀኒትነት፡ ያለው፡ ዕንጨት፡ ሥሩ፡ ወፍራምና፡ ሞላላ፡ ነው። ሰው፡ ትኵሳት፡ በያዘው፡ ጊዜ፡ ይታጠነዋል፡ ትኵሳትንም፡ በላብ፡ የሚያጠፋና፡ የሚቀብር፡ ስለ፡ ኾነ፡ ቀበርቾ፡ ተባለ።

ቀበርቾ፡ የዕፅ፡ ስም፡ ቀበረ።

ቀበሮ (ዎች)፡ ያውሬ፡ ስም፡ የተኵላ፡ ወገን፡ የዱር፡ ውሻ፡ የበግ፡ ጠላት። (ተረት)"ቀበሮ፡ የበሬ፡ ቍላ፡ ይወድቅልኛል፡ ብላ፡ ስትከተል፡ ትውላለች። " ቀበሮ፡ ማለት፡ በቈፈረው፡ ጕድጓድ፡ ውስጥ፡ ተቀብሮ፡ ገላውን፡ መደበቁን፡ ያሳያል። ተባቱም፡ እንስቱም፡ ቀበሮ፡ ይባላል። ኹለቱን፡ ለመለየት፡ ቀበሮዎችቀበሮውቀበሮዋቀበሮዪቱ፡ ያች፡ ቀበሮ፡ ነው።

ቀበሮ፡ ቀበረው፡ (ግእዝ)

ቀበሮችቀበሮዎች(ሕዝቅኤል ፲፫)

ቀበቀበ (ገበገበ)፡ ኹለተኛ፡ በርጥብ፡ ዐረሰ፡ ዐየመ፡ ኣለሰለሰ።

ቀበቀበ፡ ተከለ፡ ቸከለ።

ቀበቀበ፡ እንደ፡ ገና፡ ብረትን፡ ቀጠቀጠ፡ ዐደሰ፡ አሾለ፡ አሰላ።

ቀበቀበ፡ ደጅ፡ መታ፡ ቍር፡ ቍር፡ አደረገ።

ቀበቀብቀብቃባ፡ ገበገብ፡ ገብጋባ፡ ንፉግ፡ ሥሥታም።

ቀበተተ፡ አሳበጠ፡ ነፋ፡ ወጠረ፡ ነረተ። ምሳሌ: "የነፋሽ፡ የቀበተተሽ"፡ እንዲል፡ ኵስኵስት፡ ተጫዋች። ቀበጠጠን፡ እይ፡ የዚህ፡ ለውጥ፡ ነው።

ቀበታ፡ የባጥ፡ ገበታ፡ ዋልታ። ቀና፡ መወራረሳቸውን፡ አስተውል።

ቀበቶ (ዎች)፡ በአንድ፡ ወገን፡ በጫፉ፡ ላይ፡ ዘለበት፡ ያለበት፡ ሰፊ፡ ወይም፡ ጠባብ፡ ከነት፡ ከተንቤን፡ የተበጀ፡ መታጠቂያ፡ የሱሪ፡ የቀሚስ፡ የጐራዴ፡ የሽጕጥ፡ መያዣ። (የወርቅ፡ ቀበቶ)፡ ውስጡ፡ ጠፍር፡ ላዩ፡ ወርቀ፡ ዘቦ፡ ያለበት፡ ቀበቶ። ሠቅንን፡ ተመልከት።

ቀበነነ (ትግ፡ ሐባ፡ ቀበነ፡ በሰና)፡ ነፋ፡ ወጠረ፡ ቀበተተ።

ቀበና (ኦሮ)፡ ቀዝቃዛ፡ ውሃ፡ ወይም፡ ሌላ፡ ነገር።

ቀበና፡ በአዲስ፡ አበባ፡ ውስጥ፡ በስተምሥራቅ፡ ያለ፡ ወንዝ፡ ቀበሌውም፡ በወንዙ፡ ስም፡ ቀበና፡ ይባላል።

ቀበኛ (ቀማ)፡ ልብስ፡ የሚበላ፡ ከብት፡ በሬ፡ ላም፡ አህያ፡ በቅሎ፡ የልብስ፡ ቀማኛ፡ ማለት፡ ነው። ሲበዛ፡ ቀበኞች፡ ያሠኛል።

ቀበዘቃበዘ፡ ወዲያና፡ ወዲህ፡ ዐይኑን፡ ወረወረ፡ ዦሮውን፡ ጣለ፡ የጠፋውን፡ ለመሻት፡ ወሬ፡ ለመስማት፡ ዞረ፡ ዛበረ፡ ባዘነ።

ቀበዝባዛቅብዝብዝ፡ የተቅበዘበዘ፡ ቅንዝንዝ፡ ባካና።

ቀበዞ፡ የቀበዘ፡ ፊትና፡ ኋላ፡ የሚሮጥ፡ የሚያይ፡ የሚመለከት፡ እግረ፡ ቀላል።

ቀበያበጠ፡ ቀላወጠ። የቅኔ፡ ቤት፡ ዐማርኛ፡ ነው።

ቀበደደ (ቀበተተ)፡ መታ፡ ደበደበ፡ ሰረረ። ቀበጠጠን፡ አስተውል።

ቀበደድቀብዳዳእንቅብድእንቅብ፡ ሆድ

ቀበጠ (ቀብጸ)፡ ጨዋነትን፡ ጭምትነትን፡ ዐጣ፡ ተወዘወዘ፡ ተነቃነቀ፡ ዘለለ፡ ፈነደቀ፡ ተጫወተ። (ተረት)"የቀበጡ፡ ለት፡ ሞት፡ አይገኝም። " ወበራን፡ እይ።

ቀበጠጠ፡ ቀበተተ።

ቀበጢና፡ የቀበጠች፡ ዕረፍት፡ አልባ፡ ፫ኛውን፡ ቅብጢ፡ ተመልከት፡ ከዚህ፡ ጋራ፡ አንድ፡ ነው።

ቀበጣጠረ፡ ለፋለፈ፡ መላልሶ፡ ተናገረ።

ቀበጥ (ጦች)፡ እብድ፡ ዐይነት፡ ልጅ፡ አይሉት፡ ዐዋቂ፡ ከፈሱ፡ የተጣላ፡ ሰው፡ አፍ፡ ቂጡ፡ የሣቀ።

ቀበጥባጣቅብጥብጥ፡ የተቅበጠበጠ፡ ቍንጥንጥ፡ ብስጩ።

ቀቢ (ዎች) (ቀባዒ)፡ የቀባ፡ የሚቀባ፡ ለቅላቂ፡ ደላሽ። ምሳሌ: ቀለም፡ ቀቢ፡ እንዲሉ።

ቀባ (ስም)፡ ማጓ፡ በዋሻ፡ በፍርኵታ፡ በገደል፡ ንቃቃት፡ በውስጠ፡ ክፍት፡ ዛፍ፡ መካከል፡ ያለ፡ ንብ፡ ከነማሩ።

ቀባ (ቀብዐ)፡ ላከከ፡ ለቀለቀ፡ ደለሰ፡ ቅቤን። የሕፃንን፡ ሕዋሳት፡ ሜሮን፡ አስነካ፡ በራስ፡ ላይ፡ ዘይት፡ አፈሰሰ፡ አከበረ፡ ሾመ፡ ሥልጣን፡ ሀብት፡ መብት፡ ችሎት፡ አሳደረ፡ ዐደለ፡ ሰጠ፡ ካህን፡ ነቢይ፡ ንጉሥ፡ አደረገ። (ተረት)"አልቀባም፡ ብትል፡ ትመስክር። "

ቀባ፡ ኀጢአተኛ፡ በደለኛ፡ አስመሰለ፡ ስም፡ አሳደፈ።

ቀባ፡ መሪ፡ ሰውን፡ ወደ፡ ቀባ፡ የምትመራ፡ ወፍ። በቡልጋ፡ ቡሊ፡ በመራቤቴ፡ ባቲ፡ በጐንደር፡ ቀርቃሬ፡ ትባላለች።

ቀባ፡ መቀቢያ፡ አደስ፡ ሽነት፡ ርጐፍት፡ ሌላም፡ ይህን፡ የመሰለ፡ ኹሉ።

ቀባ፡ ቈራጭ፡ እዱር፡ ኼዶ፡ ቀባ፡ የሚቈርጥ፡ ሰው።

ቀባ ብለሽ ቅቤን ኣስተውል።

ቀባ፡ ኰላ፡ ዐደሰ፡ ጌጥን፡ በወርቅ፡ ቤትን፡ በቀለም፡ በበረቅ።

ቀባሪ (ዎች)፡ የቀበረ፡ የሚቀብር፡ ዐፈር፡ መላሽ፡ ደፋኝ። (ተረት)"ቀባሪ፡ በፈጣሪ " ደኸየ፡ ብለኸ፡ ድኻን፡ እይ።

ቀባሪ፡ የጐዳ፡ የሚጨቍን። ምሳሌ: "ድኻ፡ ቀባሪ፡ እንዲሉ። "

ቀባሪነት፡ ቀባሪ፡ መኾን።

ቀባርዋ፡ በወልቃይት፡ የሚደረግ፡ የዱላ፡ ምክት። በመርሐ፡ ቤቴና፡ በዜጋመል፡ ቈላ፡ አባት፡ ልጁን፡ አጋም፡ ሥር፡ አቁሞ፡ የዱላ፡ ምክት፡ ያስተምረዋል። በመቺና፡ በመካች፡ መካከል፡ ወደ፡ ላይ፡ አሳይቶ፡ እግርን፡ ወደ፡ ታች፡ አመልክቶ፡ ትከሻን፡ በማለት፡ ታላቅ፡ ቅልጥፍና፡ ይታያል። ይኸንንም፡ ትምህርት፡ ያወቀ፡ አንድ፡ ሰው፡ ዐሥር፡ ሰው፡ ሊመታ፡ ይችላል። ቀባርዋ፡ ምስጢር፡ ሸማን፡ በግራ፡ እጅ፡ ላይ፡ ጠቅሎ፡ ራስን፡ መከለል፡ መጋረድ፡ ነው። በመቺና፡ በተመቺ፡ (በመካች)፡ መካከል፡ ያለውንም፡ ያመታት፡ ስም፡ አንቷን፡ ዳባዲ፡ እስከ፡ ዐሥር፡ ይቈጥረዋል።

ቀባሮች፡ የቀበሩ፡ ቀባሪዎች፡ (ሕዝቅኤል ፴፱፡ ፲፬፡ ፲፭)

ቀባበረ፡ መላልሶ፡ ቀበረ፡ ደፋፈነ።

ቀባባ፡ መላልሶ፡ ቀባ፡ ደላለሰ፡ አባበሰ።

ቀባዠረ፡ ቃዠ፡ ወዣበረ፡ ዘባረቀ፡ የኾነ፡ ያልኾነውን፡ ተናገረ።

ቀባዣሪ (ዎች)፡ የቀባዠረ፡ የሚቀባዥር፡ ወዣባሪ፡ ዘባራቂ።

ቀባጠረ፡ አገኝ፡ ዐጣውን፡ የባጥ፡ የቈውን፡ ተናገረ፡ ለፈለፈ፡ ዘበዘበ። ቀባዠረን፡ ተመልከት።

ቀባጣሪ (ሮች)፡ የቀባጠረ፡ የሚቀባጥር፡ ተናጋሪ፡ ለፍላፊ።

ቀባጣሪ፡ አማጭ፡ የጋብቻ፡ መካከለኛ። ገለገለ፡ ብለኸ፡ ግልገልን፡ እይ።

ቀባጣሪነት፡ ቀባጣሪ፡ መኾን፡ ለፍላፊነት።

ቀባጭ (ጮች)፡ የቀበጠ፡ የሚቀብጥ።

ቀብር፡ መቃብር፡ የሬሳ፡ ማጋደሚያ። (ግጥም)"ቀብር፡ ቀብር፡ አሉ፡ ቀብር፡ ምናለበት፡ ደግ፡ ሥራ፡ ሠርቶ፡ ገብቶ፡ ቢተኙበት። "

ቀብር፡ ሥርዐተ፡ መቃብር፡ ለቅሶ። ምሳሌ: "እቀብር፡ ውዬ፡ መጣኹ"፡ እንዲሉ።

ቀብቀብ፡ አለ፡ ተንቀበቀበ።

ቀብቃቢ፡ የቀበቀበ፡ የሚቀበቅብ፡ ዐራሽ፡ ቀጥቃጭ፡ ቸካይ።

ቀብቃባነት፡ ቀብቃባ፡ መኾን፡ ገብጋባነት።

ቀብታች፡ የቀበተተ፡ የሚቀበትት፡ ነፊ፡ አሳባች።

ቀብዣራ፡ ዝኒ፡ ከማሁ።

ቀብዥር፡ የነጋሪት፡ ድምጥ። አብጅርን፡ አስተውል።

ቀብድቃብዱ (ኦሮ)፡ መያዣ፡ ዕቃን፡ ከመግዛት፡ በፊት፡ ለሸያጩ፡ የሚሰጥ፡ ገንዘብ። በግእዝ፡ ዐረቦን፡ ይባላል።

ቀተለ (ቀቲል፡ ቀተለ): ገደለ፡ ነፍስ አሳለፈ። "ጕራጌ እግዜር ይማርኸ ቢሉት፡ ይቀትለኝ ማን ኹኖ እንዳለ። " ተቃተለ: ታገለ፣ ተጋደለ።

ቀተረ (ቀቲር፡ ቀተረ): ሰዓት ሆነ፡ ፀሐይ ወይም ጮራው በሰማይ መካከል በራስ አንጻር ታየ፡ ከዚህ የተነሣ ጥላ ታጣ። ቀተረ: ቀረቀረ፣ ሸጐረ። "ገተረንና ቀሰረን ተመልከት።" "ገና ሰና ይወራረሳሉና፡ ፫ቱ ኹሉ በሚስጢር አንድ ናቸው።" ቀተረ: ነፋ፣ አሳበጠ፣ ወጠረ፣ ቀበተተ። "የቂል በትር ሆድ ይቀትር" እንዲሉ። "ቀሸረን አስተውል።"

ቀተረ (ቀቲር፡ ቀተረ): ሰዓት ሆነ ፀሐይ ወይም ጮራው በሰማይ መካከል በራስ አንጻር ታየ፡ ከዚህ የተነሣ ጥላ ታጣ።

ቀተረ: ቀረቀረ ሸጐረ "ገተረንና ቀሰረን ተመልከት።" "ገና ሰና ይወራረሳሉና፡ ፫ቱ ኹሉ በሚስጢር አንድ ናቸው።"

ቀተረ: ነፋ አሳበጠ ወጠረ ቀበተተ "የቂል በትር ሆድ ይቀትር" እንዲሉ። "ቀሸረን አስተውል።"

ቀታሪ: የቀተረ፣ የሚቀትር፡ ቀርቃሪ፣ ሸጓሪ፣ ነፊ፣ ወጣሪ።

ቀታሪ: የቀተረ፣ የሚቀትር፡ ቀርቃሪ ሸጓሪ ነፊ ወጣሪ

ቀትረ ቀላል: ቅርጠ ቀላል፡ ወፍራም ያይደለ ሰው።

ቀትረ ቀላል: ቅርጠ ቀላል ወፍራም ያይደለ ሰው።

ቀትር: ቁመና የሰውነት ቅርጥ ቀጥ ያለ

ቀትር: እኩለ ቀን አውራ ተሲያት (ሙቀት የሚጸናበት ጊዜ) ጌታችን በቀትር ተሰቀለ።

ቀትር: እኩለ ቀን፣ አውራ ተሲያት (ሙቀት የሚጸናበት ጊዜ) ጌታችን በቀትር ተሰቀለ። "(የቀትር) በቀትር የሚጸለይ ጸሎት፣ አቍጣሮ።" "የቀትር እባብ፣ የቀትር ጋኔን" እንዲሉ። ቀትር: ቁመና፣ የሰውነት ቅርጥ፣ ቀጥ ያለ።

ቀነዘፈ: (ቀዘፈ) ዐረደ፣ ቀነጠሰ፣ ባንድ ጊዜ ከወገብ ቈረጠ፣ መለመለ።

ቀነዘፈ: እንባ አወረደ፣ ዱብ ዱብ አደረገ፣ አንጠባጠበ።

ቀነዝናዛ: ቅንዝንዝ፣ የተቅነዘነዘ፣ የሚቅነዘንዝ፡ ፍንዝንዝ፣ ክልፍልፍ።

ቀነደለ: ቀነደበ፣ በጣ፣ ቈረጠ፡ ቅንድብን፣ መጥፎ ጠጕርን ከሥሩ ለመንቀል፣ ለማጥፋት።

ቀነደረ: (ቀነጠረ) ቄደረ፣ ኰራ።

ቀነደሸ: ሰበረ፣ አነከተ፡ ቀንድን፣ ሌላውንም። "ገነደሰን እይ።"

ቀነደሸ: አረጀ፣ ጐበጠ። "የቀነደሸ ሽማግሌ እንዲሉ።"

ቀነደበ: ቀንድን፣ ዐናትን መታ፡ በቀንድ ወይም በሌላ።

ቀነደበ: ቅንድብን ቀነደለ።

ቀነደበ: በዋንጫ ጠጣ፣ አጐደለ።

ቀነዳ: እንደ ቀንድ ደረቀ፣ ከረረ። "እከሌ ወገቡ ቀንድቶ ጐንበስ ቀና ማለት አቅቶታል።"

ቀነጀ: ተነጠለ፣ ነጠላ፣ አንድ ብቻ ሆነ፡ እንዳውራሪሥ ቀንድ፣ እንደ ከረከንድ።

ቀነጠበ: (ቀንጠበ) ከፍ ቈረጠ፣ በጠሰ፣ ቀነጠሰ።

ቀነጣ: (ቀንጠወ፡ ቀነጸ። ትግ፡ ቀንጥአ) ታበየ፣ ራሱን ከፍ አደረገ፡ ርስዎ ያለውን አንተ አለ፡ ነቀፈ፣ አዋረደ፣ አላገጠ።

ቀነጣ: አንደዬ ወደ ላይ አንደዬ ወደ ታች አለ።

ቀነጣጠበ: ቈራረጠ፣ በጣጠሰ፣ ቀነጣጠሰ።

ቀነጨበ (ትግ፡ ቀንጨበ፡ አነቀረ): በጥቂቱ ተማረ፣ ቈነጠረ፣ ቈንጥሮ ወሰደ።

ቀነጨበ: የገበጣ ጨዋታ ዠመረ።

ቀነፈ: ዐጠፈ፣ መለሰ፣ ቀለበሰ፣ ሸበለለ (የልብስን ጫፍ)

ቀነፌ (ቀነፋዊ): የሰው ስም፡ ጠላትን ዕጠፍ መልስ ማለት ነው።

ቀነፌ: የኔ ቀነፍ።

ቀነፍ: ዝኒ ከማሁ፡ ሸብላይ።

ቀና (ቀኒእ): መቅናት።

ቀና (ቀንአ፡ ሐመመ): ተመቀኘ፣ ምቀኛ ሆነ። "መቀኘን እይ፡ ከዚህ ወጥቷል።" "መዠመሪያው የደግ ይህ የክፉ ነው።" (ግጥም) "አጐንብሼ መኼድ አላውቅ ብዬ እንደ ሰው እቀና ብዬ ነው ቤቴ የፈረሰው።"

ቀና (ቀንአ፡ ረትዐ): ቀጥ አለ፣ ቀጥታ ሆነ።

ቀና (ተቀንየ): ተገዛ፣ ዕርሻ ተማረ፣ ለመደ፣ ሰላ ወይፈኑ።

ቀና: ለማ፣ ሰመረ፣ በጀ፣ ደኑ በረሓው።

ቀና: ቀጥታ፣ እውነት። "ቀናውን ተናገረ።"

ቀና: ታዘዘ፣ ዕሺ፣ በጎ አለ፣ ቅን ሆነ አሽከሩ።

ቀና: ታጠቀ፣ ገበረ አገሩ።

ቀና: አለ፣ ወደ ላይ አየ።

ቀና: አላቀረቀረም (ዮሐንስ ፰፡ ፯፡ )

ቀና: አደረገ፣ ራስን ደገፈ፣ አንተራሰ።

ቀና: ገባ፣ ሠረጸ። "ትምህርት ቀንቶታል።"

ቀና: ገደለ፣ አስወጣ፣ አሻረ ኮሶን።

ቀናሽ (ሾች): የቀነሰ፣ የሚቀንስ፡ አጕዳይ።

ቀናተኛ (ኞች): (ቀናኢ) (ናሆም ፩፡ ) በገንዘቡ፣ በሰው የቀና፣ የሚቀና፡ ምቀኛ።

ቀናት (ቀናእት): የቀኑ፣ የሚቀኑ ምቀኞች።

ቀናት: ቀናተኛ

ቀናት: ቀኖች፡ ኹለትና ከኹለት በላይ ያሉ ብዙዎች።

ቀናነሰ: ነሣሣ፣ አጐዳደለ።

ቀናው ቀንቶታል: ኾነለት፣ ኾኖለታል፣ ገባው፣ ታወቀው፡ ጕዳዩ ተፈጸመለት። "ግዳይ ቀናው እንዲሉ።"

ቀናፊ: የቀነፈ፣ የሚቀንፍ፡ ዐጣፊ፣ ቀልባሽ።

ቀናፋ: ቅንፍ፡ የተቀነፈ፣ የተመለሰ፣ የተቀለበሰ፡ ምልስ፣ ቅልብስ፣ ክፈፍ።

ቀኔ: ዘገር፣ አበታ ጦር (ዘኍልቍ ፳፭፡ ፯፡ )

ቀን (መዓልት): የብርሃን ስም፡ ከጧት እስከ ማታ ያለው ጊዜ፡ ፲፪ የብርሃን ሰዓት (ዘፍጥረት ፩፡ ) "ቀን ለሰራዊት ሌሊት ለአራዊት፡ ቀንና ሌሊት እንዲሉ።" (ግጥም) "መሸ መሰለኝ ሲጨልም እንደ ቀን ጣይ የለም።" "ደቂቅ አገባቦች፡ በ፡ የ፡ ከ፡ ለ፡ ወደ፡ በመነሻ እየተጨመሩበት ሲነገር፡ በቀን፡ የቀን፡ ከቀን፡ ወደ ቀን፡ ቀን ለቀን ይላል።"

ቀን (ቀነየ): ፳፬ ሰዓት፡ ሌሊትና መዓልት፡ በግእዝ ዕለት ይባላል። "አንድ ቀን ኹለት ቀን።" "ቀንና ጨርቅ እንደ ምንም ያልቅ እንዲሉ።" "ዕለትን ቀን ማለት በፀሓይ ነው፡ በጨረቃ ግን ሌሊት ይባላል።" "ዳዊት (ይውዕል ወይትቀነይ እስከ ይመሲ) ይላልና (መዝሙር ፻፬፡ ፳፫)" "የቀን ምስጢር፡ ሥራ መሥሪያነትን ያሳያል።"

ቀን፡ መቍጠሪያ፡ ያ፲፪ቱን ወር ዝር ዝር ከ፩ እስከ የሚቈጥር ሰሌዳ ወይም ሰንጠረዥ። "በግእዝ ዐውደ ዕለት ይባላል።"

ቀን፡ አያውቁ፡ ዓለማውያን ሰዎች የሚሞቱበትን ቀን አያውቅም።

ቀን፡ ኾነ፡ በጣም ረፈደ።

ቀን፡ ወጣ፡ ክረምት ዐለቀ። "ቀን ወጣ፡ ብር ነጣ እንዲሉ።"

ቀን፡ ወጣ፡ ክፉ ጊዜ ዐልፎ ደግ ዘመን መጣ።

ቀን፡ ወጣለት፡ ሀብታም ኾነ፡ ከበረ።

ቀን፡ ጐደለበት፡ አደጋ ወደቀበት፡ ሙከራ አገኘው።

ቀን፡ ጣለው፡ ተዋረደ፡ ተቸገረ፡ ዐጣ፡ ነጣ።

ቀን: (የቀን ክፍል፣ ጊዜ)

ቀንቃኝ (ኞች): የቀነቀነ፣ የሚቀንቅን፡ መርማሪ፣ ፈታሽ፡ ዘፈን ዠማሪ (ዕዝራ ፪፡ ፷፭) (የሃይማኖት ቀንቃኞች): በወዲያ ግብጾች፡ ባገራችን ደብረ ሊባኖሶች።

ቀንቃኝነት: ቀንቃኝ መኾን፡ መርማሪነት፣ ዠማሪነት።

ቀንበር፡ (ሮች): ሳይቈረጥ በቁሙ ተልጦ፡ ላይ ላዩ የደረቀ፡ በርሻ ጊዜ በበሬ ትከሻ የሚውል፡ ጥኑ ጠንካራ ዕንጨት፡ ባላ፬ ብስ የበሬ ዕቃ። "ዳግመኛም፡ ርን፡ አጥብቆ።"

ቀንበር፡ መንቈር።

ቀንበር፡ ሰበር፡ ዳንዴ፡ ወንበዴ፡ ሕግ አፍራሽ።

ቀንበር፡ ቀምበር፡ (በረ፡ ቀን፡ በረ፡ ቀምሕ) የቀን፡ የፍሬ፡ በር፡ እየተባለ፡ ይተረጐማል።

ቀንበር: (ግብረ፡ ሐዋርያት ፲፭፡ )

ቀንበጥ፡ (ቀነጠበ): ለጋ እንቦቀቅላ፡ ለምለም ጫፍ፡ ያልጠና ቅጠል ከነዕንጨቱ።

ቀንበጦች: ለጎች፡ ለምለሞች።

ቀንባራ፡ ቅንብር፡ የቀነበረ፡ ደረቅ እንጀራ።

ቀንቧ፡ አለ፡ እንደ ቅንቦ በፍጥነት ተሰበረ፡ ተቀለጠመ።

ቀንዛሪ፡ (ዐረ፡ ኸንዚር): በልቶ የማይጠግብ፡ ዐሣማ።

ቀንዛሪ: የቀነዘረ፡ የሚቀነዝር፡ እንዳሣማ፡ በቃኝ የማይል።

ቀንዛፊ: የቀነዘፈ፡ የሚቀነዝፍ፡ ዐራጅ፡ መልማይ፡ አፍሳሽ።

ቀንዛፋ: ቅንዛፊ፡ የተቀነዘፈ፡ ምልማይ።

ቀንደ፡ መለከት፡ ከቀንድ የተበጀ፡ የቀንድ መለከት፡ ቀንዳ መለከትም ይባላል።

ቀንደ፡ ገላላ፡ ቀንዱ ወደ ጐን የኼደ።

ቀንደ፡ ጐዳ፡ ቀንዱ ወደ ዦሮው የወረደ፡ የተጠመዘዘ፡ በሬ።

ቀንደኛ፡ (ኞች): የሕዝብ መሪ፡ ዋና፡ አል፡ ጉባኤ፡ ተጠሪ፡ ተናጋሪ።

ቀንዱ፡ ሰማይ፡ ጠቀስ፡ ምድር፡ አበስ፡ ዐይቦ፡ የሚባል፡ በሬ፡ ጌታችን፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ፍጹም፡ አምላክና፡ ሰው።

ቀንዲል: የማብሪያ ስም፡ የፈትል፡ የዘይት፡ የቅባኑግ፡ የሻማ፡(የሞራ) መደብ፡ ከሸክላ ወይም ከብረት የተሠራ፡ ጌጠኛ፡ መቅረዙ ከጠንካራ ዕንጨት የተቀረጸ (ኤርምያስ ፶፪፡ ፲፱) "ይህ ቀንዲል የቤተ መቅደስ ነው፡ የመንደሩ ግን እግራም ስለ ኾነ መቅረዝ የለውም።"

ቀንዲሎች: ማብሪያዎች (ዘጸአት ፲፡ ፬፡ ፳፭)

ቀንዲት: የእንስት በግ ስም።

ቀንዳ፡ ቀንዳ፡ አለ፡ እፊት፡ እፊት፡ እበልጥ፡ እበልጥ፡ አለ፡ ባነጋገር፡ ባካኼድ።

ቀንዳ: ቀንድ፡ ቀንዳ መለከት እንዲሉ።

ቀንዳላ፡ ቅንድል፡ የተቀነደለ፡ ተቈርጦ የወደቀ።

ቀንዳማ: ዝኒ ከማሁ፡ ባለቀንድ።

ቀንዳም (ሞች): ቀንድ ረዥም፡ በሬ፡ ዶባ፡ አጋዘን፡ ሳላ።

ቀንዳሻ: የተቀነደሸ፡ ሰባራ።

ቀንዳሽ: የቀነደሸ፡ የሚቀነድሽ፡ ቀንደ ሰባሪ።

ቀንዳቢ: የቀነደበ፡ የሚቀነድብ፡ መቺ።

ቀንዳውጣ፡ (ቀንድ፡ አውጣ): የተንቀሳቃሽ ስም፡ በበጋ ደርቆ፣ ይሞትና በክረምት ታድሶ ቀንድ የሚያወጣ፡ ዛጐል፡ ልብሱ ተሳቦ። "ቀለመ ብለኸ ቀለምን እይ።" "ቀንድ ዘርፍ ኹኖ ሳለ ከባለቤት ቀድሞ ሲነገር ቀንዳውጣ።"

ቀንዳይ: የቀነደለ፡ የሚቀንድል፡ በጪ፡ ቈራጭ።

ቀንድ፡ ከብት፡ ቀንድ ያለው፡ የቀንድ ከብት፡ በሬ፡ ላም፡ የቤት እንስሳ።

ቀንድ: (ቈንደየ፡ ቀርን) በአንስሳትና በአራዊት ራስ ላይ የበቀለ ሥጋዊ ጦር፡ ጸብት፡ ዋንጫና ዋጋምት፡ መለኪያ፡ የንዝርት ራስ የሚሆን። "አራዊት የተባሉ የዱር እንስሳት ናቸው።" "አውሬን አስተውል።" (የጠጅ ቀንድ): ጠጅ መያዣ፡ ማኖሪያ። (የጨረቃ ቀንድ): ለጋ የጨረቃ ቅርጽ፡ ቀንድ መሳይ። (በቀንዱ' ዐፈር ያዘ): ጠብ ፈለገ፡ አረ። "ያውራሪሥ ቀንድ ባፍንጫው ላይ እንዲታይ፡ እንደ ዝኆንና ዕሪያ ጥርስ፡ ቀንዱ የኾነ ሞርስ ፍንጭት የሚባል፡ የባሕር አውሬ አለ።" "የዝኆንም ጥርስ በግእዝ (ቀርን) ቀንድ ይባላል።"

ቀንዶ: ያጋዘን ዐይነት የዱር እንስሳ። "በ፪ቱ ቀንዶቹ ላይ ብዙ የቀንድ ዐጽቅ አለው፡ ዕድሜው በቀንዱ ብዛት ይቈጠራል።" "ዐይነቱ ብዙ ስለ ኾነ፡ በግእዝ ድስክን፡ ርኤም፡ ሀየል ይባላል።" "ልጆችም በተረታቸው ሰባት ቀንዶ ይሉታል። ይኸውም ምሳሌ ከራእየ ዮሐንስ የመጣ ነው።" "እንደዚሁም ብዙ ቀንድ ያለው ዋሊያ፣ የፌቆ ዐይነት በስሜን ተራራ ይገኛል።"

ቀንዶች: የንስሳና ያውሬ ጦሮች፡ የበዳ ጸብቶች።

ቀንጃ: አጣማጅ የሌለው በሬ።

ቀንጝቢ: የቀነጨበ፡ የሚቀነጭብ፡ ቈንጣሪ።

ቀንጣ፡ ቀንጣ፡ አለ፡ ፈጠን ፈጠን አለ።

ቀንጣቢ: የቀነጠበ፡ የሚቀነጥብ፡ ቈራጭ፡ በጣሽ፡ ቀንጣሽ።

ቀንጣባ፡ ቅንጣቢ፡ ቅንጥብ፡ የተቀነጠበ፡ ብጥስ፡ ቅንጥስ።

ቀኖት: ችንካር፡ ምስማር (ግእዝ)

ቀኖና ያዘ: ንስሓ ገባ፡ በሱባዔ ተቀመጠ።

ቀኖና: ሕግ፡ ሥርዐት፡ ደንብ።

ቀኖና: ንስሓ፡ የኀጢአት ቅጣት።

ቀኘ (ቀነየ): አስቀኘ፡ ቅኔ እሳ ወቀ፡ አሰጠ።

ቀኛዝማች፡ (ቾች) (ቀኝ፡ አዝማች): የቀኝ አዝማች፡ ከሻለቃው በስተቀኝ ስፍራ ጭፍራውን የሚያዘምት፡ የጦር መሪ። "ግራዝማችን ተመልከት።"

ቀኛዝማች፡ አሻግሬ) የደጃች ባልቻ በዥሮንድ ባዲስ አበባ ወይም በሲዳሞ ወንድና ሴት ልጅ በወለዱ ጊዜ ሕፃናቱን ወደ ወግዳ ይልካሉ፣ ወንዱንም ኾነ ሴት ልጃቸውን ለባላገር ይድራሉ።

ቀኛዝማችነት: ተሾመ፡ ቀኛዝማች ተባለ፡ ማዕርግ አገኘ። (በቀኝ አውለኝ): ቀኑን ሙሉ ጠብቀኝ፡ ክፉውን አርቅልኝ።

ቀኝ(ኞች)፡ ቀናዪ፡ መቅንዪ፡ የማን)፡ በግራ፡ አንጻር፡ ያለ፡ ስፍራ፡ ወይም፡ እጅ። "ጌታ፡ በፍርድ፡ ቀን፡ ጻድቃንን፡ በቀኝ፡ ኃጥኣንን፡ በግራ፡ ያቆማቸዋል። " "ቀኝ፡ ከስም፡ አስቀድሞ፡ እየገባ፡ በዘርፍነት፡ ይነገራል፡ ቅጽልም፡ ይኾናል። "

ቀኝ፡ እጅ፡ የቀኝ፡ እጅ፡ በቀኝ፡ በኩል፡ ያለ፡ ኀይለኛ፡ ፈጣን።

ቀኝ፡ ጌታ፡ የቀኝ፡ ጌታ፡ በደብር፡ አለቃ፡ ቀኝ፡ የሚቆም፡ ባለማዕርግ፡ ካህን።

ቀኝ: ድር፡ ዝሓ፡ ጥንካሬውን ያሳያል። "እውነተኛው የቀኝ ትርጓሜ ቅን ማለት ነው።"

ቀኝም ሰረሩ ግራም ሰረሩ: መገናኛው ኰሩ ወጣ

ቀወለለ)፡ ገወለለ)፡ ተንቀዋለለ፡ (ተንገዋለለ)፡ ዞረ፡ ተንከዋረረ፡ ተንሰዋለለ፡ አደገ፡ ረዘመ። ምሳሌ: "ዱር፡ ለዱር፡ ስንቀዋለል፡ ውዬ፡ የጠፋብኝን፡ በግ፡ አገኘኹት " "ወስፋቴ፡ ስለ፡ ሞተ፡ የጐረ ሥኩት፡ እንጀራ፡ ባፌ፡ ተንቀዋለለ " "ይህች፡ ልጃገረድ፡ ባል፡ ሳታገባ፡ ቁመቷ፡ ተንቀዋለለ "

ቀወለል፡ ቀውላላ (ሎች)፡ የተንቀዋለለ፡ ዘዋሪ።

ቀወመ) ቆመ ብለሽ ቁምን እይ።

ቀወመ)፡ ቆመ፡ ተነሣ፡ ቀጥ፡ አለ፡ ተገተረ፡ ታገደ፡ ተገታ፡ ቀረ፡ ታጐለ፡ ተግ፡ አለ። (ገበያ፡ ቆመ)፡ መሸጥ፡ መለወጥ፡ መግዛት፡ ተዠመረ። (ዋዜማ፡ ቆመ)፡ በ፱፡ ሰዓት፡ ለእግዚአብሔር፡ ምድር፡ በምልዓ፡ አለ፡ ሌላውንም፡ አደራረስ፡ አደረሰ። (ማሕሌት፡ ቆመ)፡ ጧት፡ ስቡሕ፡ አለ፡ በከበሮና፡ በጸናጽል፡ እስከ፡ ፯፡ ሰዓት፡ አመሰገነ። (ሳታት፡ ቆመ)፡ ከመንፈቀ፡ ሌሊት፡ እስከ፡ ጧት፡ በዜማ፡ ፈጣሪን፡ ሲያመሰግን፡ እመቤታችንን፡ መላእክትን፡ ጻድቃንን፡ ሲለምን፡ ዐደረ።

ቀወሰ፡ አጐበጠ፡ ደገነ፡ ቀውስ፡ አበጀ።

ቀወቀወ)፡ ቃዠ።

ቀወቀወ)፡ ከወከወ(ጎገወ)አንቀወቀወ(አንጎገወ)፡ አንከወከወ፡ አንቀዠቀዠ።

ቀወቀው፡ ቀውቃዋ(ሎች)፡ የተንቀወቀወ፡ የሚንቀወቀው፡ ከወከው፡ ከውካዋ፡ ገውጋዋ፡ ዕርፊተ፡ ቢስ፡ ቂጡ፡ ምድር፡ የማይነካ፡ ቀዥቃዣ።

ቀዊ፡ የቀዋ፡ የሚቀዋ፡ ቍራ።

ቀዋ (ቀዊዕ፡ ቆዐ)፡ ፍሬ፡ ለቀመ፡ ቀሠመ፡ አወለበ፡ ጠረጠረ።

ቀዋሚ (ዎች)፡ የቆመ፡ የሚቆም፡ ጸንቶ፡ የሚኖር፡ ዐምድ፡ ሐውልት።

ቀዋሚ፡ ነገር፡ ደንበኛ፡ ውለኛ፡ ሥራ፡ ተራካሪ።

ቀውሰኛ (ኞች)፡ በነገር፡ ተቃራኒ፡ ከሕዝብ፡ ከማኅበር፡ የማይስማማ።

ቀውስ (ዐረ)፡ ቀስት።

ቀውስ፡ እሳት፡ የእሳት፡ ቀስት፡ ጠንቋይ፡ የናትና፡ የልጅን፡ ስም፡ ገጥሞ፡ በአ፲፪፡ እየገደፈ፡ ይቈጥርና፡ ላንዳንድ፡ ሰው፡ "ኮከብኸ፡ ቀውስ፡ እሳት፡ ነው"፡ ይለዋል።

ቀውስ፡ የነገር፡ መሳሳት፡ አለመግጠም።

ቀውስ፡ የኮከብ፡ ስም፡ ቀስት፡ ይዞ፡ የሚታይ፡ የኅዳር፡ ኮከብ፡ ቀስተኛ።

ቀውቀውቱ፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ ከውከውቱ።

ቀውጢ (ዐረ፡ ቀውሲ)፡ ቀስተኛ።

ቀውጢ፡ ቀን፡ ሽብረኛ፡ ሁከተኛ፡ ጦረኛ፡ ብላ፡ ተባላ፡ ቀን። ምሳሌ: "ቀውጢ፡ ቀን፡ በመጣ፡ ጊዜ፡ ጌቶቹ፡ አንድ፡ ጋን፡ ጠጅና፡ ዐምስት፡ እብድ፡ አያጡም" (ፊታውራሪ፡ ሀብተ፡ ጊዮርጊስ)

ቀዎት፡ በይፋት፡ ውስጥ፡ ያለ፡ አገር።

ቀዎቶች፡ የቀዎት፡ ሰዎች፡ የቀዎት፡ ተወላጆች።

ቀዘመ)፡ ገዘመ)፡ አቅዘመዘመ፡ ወረወረ፡ እምዘገዘገ፡ አውዘገዘገ።

ቀዘቀዘ(ቀዘዘ)፡ በረደ፡ ከሙቀት፡ ራቀ፡ ሰንሰለት፡ ኾነ።

ቀዘባ፡ ርጥብ፡ ለጋ፡ ለምለም፡ ስንዴና፡ ገብስ። (የዘፈን፡ አዝማች)"የማነሽ፡ ቀዘባ፡ አንች፡ ዐይነ፡ ሌባ። " ቀዘባ፡ ማለት፡ በጥር፡ መታጨድ፡ ይገባው፡ የነበረ፡ እየካቲት፡ ላይ፡ ሲያልፍ፡ ነው።

ቀዘነ፡ ቶሎ፡ ቶሎ፡ ዕዳሪ፡ ወጣ፡ ተቀመጠ፡ ብጥብጥ፡ ዐይነ፡ ምድር፡ በፍጥነት፡ ለቀቀ፡ ሿ፡ አደረገ። (ግጥም)"ፍየል፡ ከቀዘነ፡ ዲያቆን፡ ከዘፈነ፡ አይድንም፡ ይሞታል፡ እየመነመነ "

ቀዘነ፡ ፈራ፡ ተንበደበደ።

ቀዘዘ (ገዘዘ)፡ ፈዘዘ፡ አልመላም። ቀፈፈንቀረንቀሰሰን፡ ተመልከት።

ቀዘዝ፡ አለ፡ ቀረት፡ አለ፡ የስፍር። ጨከከን፡ እይ።

ቀዘዝተኛ፡ ቀሰስተኛ፡ ደካማ።

ቀዘፈ (ቀዲፍ፡ ቀደፈ)፡ ግራና፡ ቀኝ፡ ባሕርን፡ ገፋ፡ ገለጠ፡ ከፈለ፡ የመርከብ፡ መንገድ፡ አበጀ፡ መራ።

ቀዘፈ: ወደ ወደብ መርከብን መራ

ቀዘፋ፡ ገለጣ፡ ከፈላ፡ የመቅዘፍ፡ ሥራ።

ቀዛኝ፡ የቀዘነ፡ የሚቀዝን፡ ኮሶኛ፡ ሆደ፡ በሽተኛ።

ቀዛዛ፡ የቀዘዘ፡ ፈዛዛ።

ቀዛፊ፡ የቀዘፈ፡ የሚቀዝፍ፡ መርከብ፡ መሪ፡ ቋትለኛ። በግእዝ፡ ኖትያ፡ ኀዳፍ፡ ይባላል።

ቀዛፎች፡ የቀዘፉ፡ የሚቀዝፉ፡ (ሕዝቅኤል ፳፯፳፮)

ቀዝቃዛ፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ የቀዘቀዘ፡ በራድ።

ቀዝቃዛነት፡ ቀዝቃዛ፡ መኾን።

ቀዝቃዛዋ፡ ቀዝቃዛዪቱ፡ ያች፡ ቀዝቃዛ (ለሴት) (ኤርምያስ ፲፰፲፬)

ቀዝቃዛው፡ ያ፡ ቀዝቃዛ (ለወንድ)

ቀዝቃዥ፡ የሚቀዘቅዝ፡ በራጅ፡ ውርጭ፡ ውሃ፡ አየር።

ቀዠቀዠ)፡ አንቀዠቀዠ፡ አክለፈለፈ፡ አክለበለበ።

ቀዠቀዥ፡ ቀዥቃዣ (ዦች) የተንቀዠቀዠ፡ የሚንቀዠቀዥ፡ ክልፍልፍ።

ቀዣበረ፡ ዘባረቀ፡ ቀባዠረ።

ቀየመ፡ ቄመ

ቀየሰ፡ (ዐረ) ለካ፡ መጠነ፡ ነደፈ፡ በገረ።

ቀየረ፡ (ዐረ) ለወጠ፡ ሌላ፡ አደረገ፡ አዛወረ።

ቀየረና፡ ቀየሰ፡ በከተማ እንጂ በባላገር አይነገርም።

ቀየደ፡ መናገር ከለከለ፣ ለንባዳ አደረገ።

ቀየደ፡ ሰከለ፡ አሰረ፡ ጋዳ። (ተረት) "እንዳትበላ ለጐት፡ እንዳትኼድ ቀየዷት።"

ቀየደ፡ ከፈለ፡ መከተ፡ ጋረደ፡ ከለለ።

ቀየጠ፡ (ትግ፡ ቀየጸ፡ ፎከረ) ዘነቀ፡ ቀላቀለ፡ ደባለቀ።

ቀዩት፡ ቀይ ብራብሮ እንስት።

ቀዪእ): ማስታወክ፣ ማውጣት።

ቀያ፡ በመንዝ ክፍል ያለ አገር።

ቀያሪ፡ የቀየረ፡ የሚቀይር፡ ለዋጭ፡ አዛዋሪ።

ቀያሽ፡ (ሾች) የቀየሰ፡ የሚቀይስ፡ ነዳፊ፡ በጋሪ።

ቀያቀይ፡ የቀይ ቀይ።

ቀያቴቀይ፡ አበባ።

ቀያየረ፡ ለዋወጠ።

ቀያየጠ፡ መላልሶ ቀየጠ።

ቀያይ፡ የውስጠ ብዙ ቀይ ቅጽል።

ቀያዮች፡ ቀዮች። "ዐረቦች ቀያዮች ናቸው።" (ጥያ) ቀያቴ፡ ቀይ ጠመኔና ቀይነት ያለው አበባ።

ቀያጅ፡ (ጆች) የቀየደ፡ የሚቀይድ፡ መካች፡ ጋራጅ፡ አሳሪ።

ቀያጭ፡ (ጮች) የቀየጠ፡ የሚቀይጥ፡ ዘናቂ፡ ቀላቃይ፡ ደባላቂ።

ቀያፋ፡ የሰው ስም፡ ጌታችንን ያስቀለ፡ ሊቀ ካህናት።

ቀዬ፡ (ኦሮ) ደጅ፡ ካጥር ውጭ የሚገኝ ስፍራ።

ቀይ፡ (ቀይሕ) የቀላ፡ ደም፡ ጁኅ፡ ጃዊ' እንድኪ፡ ፍሕሶ፡ ነት፡ ዐረብ፡ አንቀልባ፡ የሱፍ፡ አበባ። (ድምቅ ቀይ): ደምማ።

ቀይ፡ መልክ፡ አይገፋም፡ እጅግ አያምርም፡ ደመ ግቡ አይኾንም።

ቀይ፡ መስቀል፡ በዓለም ኹሉ የተወደደ፡ የበጎ አድራጎት ማኅበር። ሥራውም በጦርነት ጊዜ ጠላትና ወዳጅ ሳይለዩ ቍስለኛን ማንሣትና ማከም፡ ማስታመም ነው፡ እንደ አውሮጳ አቈጣጠር ነሐሴ ፳፪ ቀን ፲፰፻፷፱ . . በዠኔብ ተዠመረ።

ቀይ፡ ሥር፡ የተክል ስም።

ቀይ፡ በሬ፡ ሶረን።

ቀይ፡ በቁሙ ቀላ።

ቀይ፡ በግ፡ ዳንግሌ።

ቀይ፡ አርእስቱ፡ በቀይ ቀለም የሚጻፍ፡ ከዳዊት መዝሙሮች አንዱ።

ቀይ፡ ዐፈር፡ ቦረቦር፡ ሸክላ።

ቀይ ዐፈር: (መዝሙር ፪፡ )

ቀይ፡ ከስም አስቀድሞ እየገባ በቅጽልነት ይነገራል።

ቀይ፡ ዳማ፡ በጠይምነትና በቀይነት መካከል ያለ ሰው፡ ጠይምነቱ ወደ ቅላት የሚያደላ።

ቀይ፡ ዶሮ፡ ሶረኔ መልክ።

ቀይ፡ ግምጃ፡ ሶራ።

ቀይ ግምጃ:  አይሁድ የስቅለት ለት ለጌታ ያለበሱት።

ቀይ፡ ጣላ፡ ቀይ ያለበት፡ (የጣለበት) ጥጥ።

ቀይ፡ ፈረስ፡ ሐመር፡ ዳማ (ራዕይ ፮፡ )

ቀይ: በሬና ላም።

ቀይድ፡ (ትግ፡ ቀይዲ) ስካላ፡ ጋዲ።

ቀዮች፡ የቀሉ፡ ቀያይ የኾኑ ስዎች፡ ሌሎችም ሥነ ፍጥረቶች።

ቀደል፡ ጥላት፡ የጭላት ዐይነት።

ቀደመ (ቀዲም፡ ቀደመ) በሩጫ በለጠ፡ ዐለፈ፡ ዐልፎ ኼደ፡ ወደ ኋላ ተወ። ምሳሌ: "አሳሄል በሩጫ ከፈረስ ቀደመ።" "የቀደመን ሞት ይወስደዋል።"

ቀደመ፡ በቀዳማ፡ ላይ፡ ሰቀለ፡ አንጠለጠለ። (ግጥም)"እንግዴህ፡ አላምንም፡ ፈረሰኛውን፡ ቀደሙት፡ ይሉኛል፡ መርቆሬዎስን። "

ቀደመ፡ ዠመረ፡ ፈለመ፡ ጨፈለቀ፡ ፊተኛ።

ቀደማ፡ መቅደም፡ ቅድሚያ።

ቀደማ፡ ጭፍለቃ፡ ዕዳሪ፡ ማውጣት።

ቀደም (ቀዳሚ)፡ በኵር፡ ፊተኛ። ምሳሌ: "ግንባር፡ ቀደም"፡ እንዲሉ።

ቀደም፡ ቀደመ። (የባለጌ፡ ተረት)"ሳትጋደም፡ ፈሷ፡ ቀደም። " ነበረን፡ እይ።

ቀደም፡ አለ፡ ቀደሙ።

ቀደም፡ ያለፈ፡ ጊዜ፡ (ኤፌሶን ፳፪) ምሳሌ: "ከዚህ፡ ቀደም"፡ እንዲሉ። (በቀደም፡ ለት)፡ ካለፈው፡ ሳምንት፡ በአንዱ፡ ቀን። (እየቀደም)፡ እያደር።

ቀደሰ (ቀድሶ፡ ቀደሰ)፡ ለየ፡ ባረከ፡ እነጻ፡ አከበረ፡ አመሰገነ፡ ቅዱስ፡ አደረገ፡ ከርኵሰት፡ አራቀ። ምሳሌ: "እራት፡ የሌለው፡ ቄስ፡ እንደ፡ ልቡ፡ አይቀድስ። " (ግጥም)"አብ፡ እሳት፡ ወልድ፡ እሳት፡ መንፈስ፡ ቅዱስ፡ እሳት፡ ቄስ፡ እንዴት፡ ይሞታል፡ ጐሥዐን፡ ሲቀድሳት። "

ቀደሰ፡ ቈረበ።

ቀደደ፡ ሸረከተ፡ ሠጠጠ፡ ሠነጠቀ፡ ተለተለ፡ በሸረከ፡ በጨቀ፡ ( ነገሥት )

ቀደደ፡ በሳ፡ ሸነቈረ፡ ነደለ። ምሳሌ: "ውሻ፡ በቀደደው፡ ዥብ፡ ይገባል"፡ እንዲሉ። (መንገድ፡ ቀደደ)፡ አወጣ፡ ኣበጀ። (ፈሱን፡ ቀደደ)፡ ፈሳ፡ ላጥ፡ አደረገ።

ቀደደ: ዘረከተ

ቀደዳ፡ ሽርከታ፡ ሥንጠቃ፡ ሽንቈራ።

ቀደጀ) ቀደወ) አቀዳጀ (አስተቀጸለ)፡ ዘውድን፡ አክሊልን፡ ራስ፡ ቍርን፡ ራስ፡ ወርቅን፡ ጐፈርን፡ አቍዳማን፡ በራስ፡ ላይ፡ ጫነ፡ አጠለቀ፡ ሸለመ፡ አስጌጠ።

ቀደጀ) ኦሮ፡ "ከደነ" ሲል ቀዳዴ ከሚለው ጋራ በምስጢር ይገጥማል።

ቀዳ (ቀድሐ)፡ ውሃን፡ ጠላን፡ ጠጅን፡ ማንኛውንም፡ ፈሳሽ፡ ነገር፡ ካለበት፡ ስፍራ፡ ዕቃ፡ ጠለቀ፡ ወደ፡ ሌላ፡ አወረደ፡ ጨመረ፡ አንቈረቈረ፡ ሞላ፡ በአንኮላ፡ በጭልፋ፡ ደነበቀ፡ ወለፈ፡ ገለበጠ።

ቀዳ፡ አለልክ፡ አለቀሰ፡ እንባውን፡ አፈሰሰ።

ቀዳ፡ አስቀመጠ፡ አስቀዘነ፡ ነዳ።

ቀዳ፡ ጪር፡ ጻፈ።

ቀዳሚ (ዎች)፡ የቀደመ፡ የሚቀድም።

ቀዳማ (ቀዳማይ)፡ በስተደረት፡ ያለ፡ የኮርቻ፡ ከፍተኛ፡ ድጋፍ፡ የደኃራ፡ አንጸር።

ቀዳማዊ፡ የቀዳሚ፡ ወገን፡ ወይም፡ ዐይነት፡ አንደኛ፡ መዠመሪያ፡ ሰው፡ ማንኛውም፡ ፍጥረት።

ቀዳማይ፡ ከትንቢት፡ አንቀጽ፡ በፊት፡ የሚነገር፡ ተቀዳሚ፡ አንቀጽ፡ ኀላፊ።

ቀዳሽ (ሾች)፡ የቀደሰ፡ የሚቀድስ፡ ባራኪ፡ አመስጋኝ፡ ቈራቢ፡ ሰሞነኛ፡ ዲያቆን፡ ቄስ፡ ቆሞስ፡ ጳጳስ።

ቀዳው፡ ዝናቡን፡ ለመጠን፡ አዘነበው።

ቀዳደደ፡ ሸረካከተ፡ ሠነጣጠቀ።

ቀዳዳ፡ ብስሽ፡ ንቍር፡ ሥንጥቅ፡ (ኢሳይያስ ፲፰) (ተረት)"ከቀዳዳ፡ ይሻላል፡ ጨምዳዳ። "

ቀዳዳ፡ ነገር፡ የማይችል፡ የማይቋጥር፡ ሰው።

ቀዳጅ (ጆች)፡ የቀደደ፡ የሚቀድ፡ ሸርካች፡ ሠንጣቂ፡ ሸንቋሪ።

ቀድሞ (ቀዲሙ)፡ ጥንት፡ ዱሮ፡ ፊት።

ቀድሞቅድም፡ የጊዜ፡ ንኡስ፡ አገባብ።

ቀድሞ፡ ቦዝ፡ እፊት፡ ኹኖ።

ቀድሞ፡ ዘመን፡ ያለፈ፡ የጥንት፡ ጊዜ፡ ቀድሞ፡ የዘመን፡ ዘርፍ፡ ነው።

ቀድሞውን፡ ቀድሞውኑ፡ ዱሮውን፡ ዱሮውኑ።

ቀጂ (ጆች)፡ የቀዳ፡ የሚቀዳ፡ ጨማሪ፡ አንቈርቋሪ።

ቀጂነት፡ ቀጂ፡ መኾን።

ቀጋ (ጎች)፡ ከሥር፡ እስከ፡ ጫፍ፡ ኹለንተናው፡ እሾኸ፡ ያለው፡ ዕንጨት። አበባው፡ ነጭ፡ ሽታው፡ ጣፋጭ። (ተረት)"የውጭ፡ ዐልጋ፡ የቤት፡ ቀጋ። "

ቀጠለ (ቀጸለ)፡ በቁመት፡ ላይ፡ ቁመት፡ በሥራ፡ ላይ፡ ሥራ፡ አከለ፡ ጨመረ፡ ቋጠረ፡ ገጠመ፡ ሰፋ፡ አረዘመ። ቀጸለን፡ እይ፡ ቀጠለ፡ ዐማርኛ፡ ቀጸለ፡ ግእዝኛ፡ ነው።

ቀጠለ (ቈጸለ)፡ ሣሣ፡ ረቀቀ።

ቀጠለ፡ ለመለመ፡ ጨበጨበ።

ቀጠለ፡ ተራ፡ መታ፡ ተከተለ፡ ለጠቀ።

ቀጠላ፡ ሻሽ፡ ቀጸለ።

ቀጠላ፡ ዐሰላ።

ቀጠላ፡ ጥሩ፡ የማር፡ እንጀራ፡ ከወለላ፡ በቀር፡ ከዳና፡ ቀለሕ፡ የሌለበት።

ቀጠረ(ቀጸረ)፡ ገነባ፡ ካበ፡ አዞረ፡ ከበበ፡ ከተማን፡ አገርን፡ የውጭ፡ ዐጥር፡ ዐጠረ፡ ጀጐለ። "ከተማ፡ እንደ፡ ሐረር፡ አገር፡ እንደ፡ ሺን፡ ነው። "

ቀጠረ(ዐደመ፡ ዐሠረ)፡ ቀን፡ ወሰነ፡ በዚያ፡ ለት፡ መጥተሽ፡ እንድትቀርብ፡ አለ። "ኹሉም፡ የቅጥርን፡ ምስጢር፡ አይለቅም። " (ተረት)"ቀን፡ ቢቀጥሩ፡ ውሻ፡ ቢጠሩ፡ ይደርሳል፡ በግሩ። "

ቀጠረ፡ አሽከር፡ ሎሌ፡ ገረድ፡ ኣሳደረ፡ ቀለብ፡ ደመ፡ ወዝ፡ ምንዳ፡ ሊሰጥ።

ቀጠሮ፡ ታፌ፡ ያለ፡ በ፰፡ ከጠበቃዬ፡ ያለ፡ ባ፲፭፡ ቀን፡ የሚቀርብበት።

ቀጠሮ፡ አፍራሽ፡ ቀጠሮ፡ የማያከብር፡ ተቃጥሮ፡ የሚቀር።

ቀጠሮ፡ የሰዓት፡ ልክ፡ የጊዜ፡ ውሳኔ፡ ሰው፡ ተገናኝቶ፡ ጕዳዩን፡ የሚፈጽምበት፡ እዳኛ፡ ፊት፡ ቀርቦ፡ የሚነጋገርበት።

ቀጠቀጠ (ቀጥቀጠ፡ ቀጽቀጸ)፡ መታ፡ ደበደበ፡ ሰበረ፡ አደቀቀ።

ቀጠቀጠ፡ ብረት፡ ሠራ፡ አሾለ፡ አጠፈፈ።

ቀጠቀጠ፡ ወቀጠ፡ ገብስን፡ የወይፈንንና፡ የወጠጤን፡ ቍላ።

ቀጠቀጥ ቀጥቃጣ፡ የተንቀጠቀጠ፡ የሚንቀጠቀጥ፡ ሥጋ፡ ፈሪ፡ ንፉግ። ፈንዛን፡ እይ።

ቀጠበ (ቀጸበ፡ ዕብ፡ ቃጻብ)፡ ጨረሰ፡ ቈረጠ፡ ጠቀሰ፡ ከነዳ፡ ለካ፡ መጠነ፡ አመለከተ፡ ምልክት፡ አደረገ፡ ከሰለ፡ ድርን። ለዕድሜም፡ ይነገራል።

ቀጠባ፡ ማሪያም፡ የቀጠባ፡ ማሪያም (የማርያም ቤተክርስቲያን ቀጠባ አካባቢ)

ቀጠባ፡ የቀበሌ፡ ስም፡ በደብረ፡ ሊባኖስ፡ ውስጥ፡ ያለ፡ የማሪያም፡ አጥቢያ። "አቡነ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ ከይፋት፡ አገር፡ በትምርት፡ በታምራት፡ ማርከው፡ ከነልጆቿ፡ ደብረ፡ ሊባኖስ፡ አምጥተው፡ ስን፡ (ክርስቶስ፡ ቀጸባ)፡ ያሏት፡ አንዲት፡ ቅድስት፡ ሴት፡ ነበረች፡ የመቤታችንን፡ ታቦት፡ በዚህ፡ ስፍራ፡ ስለ፡ ተከለች፡ ከውሻ፡ ገደል፡ በታች፡ ያለው፡ ቀበሌ፡ በስ፡ ቀጠባ፡ ተባለ፡ ይላሉ። ቀጠባ፡ ትርጓሜ፡ ጠቀሳት፡ ጠራት፡ አቀረባት፡ ማለት፡ ነው። "

ቀጠነ (ቀጢን፡ ቀጠነ)ነነ፡ ከሳ፡ ከውፍረት፡ ከድንዳኔ፡ ራቀ፡ ሣሣ፡ ረቀቀ። (ሊጡ፡ ጠላው፡ ቀጠነ)፡ ውሃ፡ ኾነ። (ፍርድ፡ ቀጠነ)፡ ጐደለ። (ተረት): "ከውሃ፡ የቀጠነ፡ ከዐይን፡ የፈጠነ። "

ቀጠና፡ ትንሽ፡ ረኃብ፡ ሼጥ፡ ያለ፡ ዘመን፡ (ዘዳግም ፳፰፳፪፡ ፪ኛ ነገሥት ፲፱፡ ዓሞጽ ) (ተረት): "ምንም፡ ቢታረስ፡ በዘጠና፡ ቤቱን፡ አይስትም፡ ቀጠና። "

ቀጠናማ፡ ቀጠናም፡ ባለቀጠና።

ቀጠን (ቀጢን)፡ መቅጠን።

ቀጠን፡ አለ፡ ቀጠነ።

ቀጠን፡ ያለ፡ የቀጠነ።

ቀጠጠ (ረትዐ፡ ትግ፡ ቀጸጸ፡ መላ፡ ዕብ፡ ቃጻጽ፡ ቀረፀ)፡ ቈረጠ፡ ዐወደ፡ ሸለተ።

ቀጠጠ፡ ነፋ፡ አሳበጠ፡ ቀሰጠጠ።

ቀጠጠ፡ ገብጠትን፡ ጠማማነትን፡ አራቀ።

ቀጠጣ፡ ቈረጣ፡ ሽለታ።

ቀጠጥና፡ ቀጥታነት፡ ያለው፡ ቀጪን፡ ዕንጨት፡ መጠነ፡ ታናሽ፡ የቅጠሉ፡ ስም፡ ያህያ፡ ዦሮ፡ ነው። ደባክድን፡ ተመልከት።

ቀጠጥና፡ ዕንጨት፡ ቀጠጠ።

ቀጠጦ፡ ፍሬው፡ ቀጫጫ፡ የኾነ፡ ማሽላ።

ቀጠፈ (ቀጢፍ፡ ቀጠፈ)፡ ቈረጠ፡ ሰበረ፡ ቀነጠበ፡ ርጥብ፡ ቅጠልን።

ቀጠፈ፡ በልጅነት፡ ገደለ። ቀሠፈን፡ እይ።

ቀጠፈ፡ ዐበለ፡ ዋሸ።

ቀጠፋ፡ ቈረጣ፡ ቅንጠባ።

ቀጠፋ፡ የቅኔ፡ ጫፍ፡ መነሻ፡ የሌለው፡ ኹለት፡ ቤት፡ ቅኔ።

ቀጣ (ቀጽዐ)፡ አሰረ፡ መታ፡ ገረፈ።

ቀጣ፡ ከላይ፡ ዐንገትን፡ ከታች፡ ባትን፡ ጐመደ፡ ቈረጠ። ምሳሌ: "አይቀጡ፡ ቅጣት፡ ቀጣ"፡ ከራስ፡ በታች፡ በቁም፡ ቀበረ።

ቀጣ፡ ገንዘብ፡ አስከፈለ።

ቀጣሪ(ሮች)፡ ዐጥር፡ ያጠረ፡ የሚያጥር፡ አሽከር፡ የቀጠረ፡ የሚቀጥር።

ቀጣቀጠ፡ ደባደበ፡ ወቃቀጠ።

ቀጣቢ፡ የቀጠበ፡ የሚቀጥብ፡ ከንጂ፡ አመልካች፡ ሸማኔ።

ቀጣኒት፡ የቀጠነች፡ ምድር፡ ሴት።

ቀጣኒት፡ የተንቀሳቃሽ፡ ስም፡ መልኳ፡ ላይ፡ ላዩ፡ አረንጓዴ፡ ታች፡ ታቹ፡ ብጫ፡ የኾነ፡ ያንበጣ፡ ወገን፡ ዳግመኛም፡ ያቦ፡ ፈረስ፡ ትባላለች።

ቀጣና (ኖች)፡ በገደልና፡ በገደል፡ መካከል፡ ያለ፡ ዕርከን፡ የቃጥላ፡ አረፍት፡ ሰው፡ የሚያልፍበት፡ ከብት፡ የሚሰማራበት።

ቀጣይ (ዮች)፡ የቀጠለ፡ የሚቀጥል፡ አካይ፡ ተከታይ፡ ቋጣሪ።

ቀጣጠለ፡ ጨማመረ፡ ቈጣጠረ፡ ገጣጠመ። ፬ኛውን፡ ና፡ እይ።

ቀጣጠፈ፡ ቈራረጠ፡ ቀነጣጠበ።

ቀጣጣይ (ዮች)፡ የቀጣጠለ፡ የሚቀጣጥል፡ ነገረሠሪ።

ቀጣጣፊ፡ የቀጣጠፈ፡ የሚቀጣጥፍ።

ቀጣፊ (ፎች)፡ የቀጠፈ፡ የሚቀጥፍ፡ ቈራጭ።

ቀጣፊ፡ ሌባ፡ ዐባይ፡ ዋሾ፡ ቈርጦ፡ ቀጥል፡ (ሚክያስ )

ቀጣፊነት፡ ቀጣፊ፡ መኾን።

ቀጤማ፡ ቄጠማ፡ በረግረግ፡ ላይ፡ የሚበቅል፡ ለምለም፡ ሣር፡ (ኢዮብ ፲፩) የፀሓይ፡ ጥላ፡ ለእረኛ፡ የዝናም፡ ልብስ፡ ገሣ፡ ምንጣፍ፡ ኬሻ፡ ይኾናል። በግእዝ፡ ሰት፡ ይባላል። "ለመለመ፡ ብለኸ፡ አለመለመን"፡ እይ። "ሮቹ፡ ረዣዥሞች፡ የኋላ፡ እግሮቹ፡ ዐጫጪሮች፡ የኾኑ። "

ቀጥ፡ መቅናት።

ቀጥ፡ አለ፡ ቀና።

ቀጥ፡ አደረገ፡ አቀና።

ቀጥሎ፡ ቦዝ፡ አንቀጽና፡ ንኡስ፡ አገባብ፡ አክሎ፡ ቋጥሮ፡ ጨምሮ፡ ተከትሎ። በደጊመ፡ ቃል፡ ሲነገር፡ "ቀጥሎ፡ ቀጥሎ"፡ ይላል።

ቀጥቃጭ(ጮች)፡ የቀጠቀጠ፡ የሚቀጠቅጥ፡ ብረተ፡ ሠሪ፡ ጠይብ፡ ባለጅ።

ቀጥቃጭነት፡ ቀጥቃጭ፡ መኾን፡ ባለጅነት፡ ሠራተኛነት።

ቀጥታ፡ ቀጥ፡ ማለት፡ ወይም፡ ቀጥ፡ ያለ፡ ዙሪያ፡ ጥምጥም፡ ያይዶለ። ምሳሌ: "ቀጥታ፡ መንገድ"፡ እንዲሉ። "በቀጥታ፡ መጣ፡ በቀጥታ፡ ኼደ"፡ ቢል፡ ግራ፡ ቀኝ፡ ሳይል፡ ያሠኛል።

ቀጨ (ትግ፡ ቈጸየ፡ ወለም፡ አለ)፡ ትከሻን፡ አሳመመ፡ ሥርን፡ አዞረ። ገን፡ እይ፡ በግእዝ፡ መሠረቱ፡ ቀጽዐ፡ ነው።

ቀጨ (ትግቀጸየ)፡ ስንደዶን፡ አክርማን፡ እሸትን፡ ከላይ፡ ከመካከል፡ ቈረጠ፡ ነጨ፡ ገነጠለ፡ አጠፋ፡ አበላሸ፡ ሰብልን።

ቀጨ፡ ቀሠፈ፡ አለዕድሜ፡ በልጅነት፡ ገደለ።

ቀጨለ፡ ቃጨለ፡ ጮኸ፡ ከለለ፡ ተሰማ። "በቀለ፡ አቅጨለጨለን፡ በቃጨለ፡ አቃወለን"፡ ይመለከቷል።

ቀጨመ፡ ቅም፡ ያዘ፡ አፈራ፡ (ገቢር)

ቀጨሞ (ዎች)፡ የንጨት፡ ስም፡ ፍሬው፡ ሲቀምሱት፡ የሚጐመዝዝ፡ የሚያስቀምጥ፡ ቀጪን፡ ዕንጨት።

ቀጨቀጨ፡ በጥርሱ፡ ስበረ፡ ቀጠቀጠ፡ ዐኝ፡ ዐኝ፡ አለ፡ አደቀቀ።

ቀጨቀጭ፡ በጤፍ፡ ውስጥ፡ የሚበቅል፡ ዐረግማ፡ ቅጠል፡ ጤፍ፡ እንጀራ፡ ሲበሉ፡ ቀጥ፡ ቀጭ፡ የሚል፡

ቀጨኔ፡ ባዲስ፡ አበባ፡ ውስጥ፡ ያለ፡ ቀበሌ። ምሳሌ: "ቀጨኔ፡ መድኀኔ፡ ዓለም"፡ እንዲሉ።

ቀጨኔ፡ ነጭ፡ አደንጓሬ።

ቀጨጨ (ቈጢጥ፡ ቈጠጠ)፡ ቀጠነ፡ ኰሰመነ፡ ሰለተ።

ቀጪ (ቀጻዒ)፡ የቀጣ፡ የሚቀጣ፡ መቺ፡ ገራፊ። ምሳሌ: "አንጥያኮስ፡ በእስራኤል፡ ላይ፡ ግፍ፡ ስለ፡ ሠራ፡ ቀጪ፡ አዘዘበት። "

ቀጪነት፡ ቀጪ፡ መኾን።

ቀጪኔ (ዎች)፡ የግመል፡ ዐይነት፡ የዱር፡ እንስሳ፡ ነብርማ፡ ዐንገቱና፡ የፊት፡ እግሮቹ፡ ረዣዥሞች፡ የኋላ፡ እግሮቹ፡ ዐጫጪሮች፡ የኾኑ።

ቀጪኔ፡ የስንዴ፡ ስም፡ በጣም፡ ቀጪን፡ ስንዴ።

ቀጪኔ፡ ጐራዴ። ሾተልን፡ ተመልከት።

ቀጪን (ኖች፡ ቀጢን)፡ የቀጠነ፡ የማነነ፡ ሞናና፡ ሰው፡ ፈትል፡ ሸማ፡ ፉጨት። ቍጥኔን፡ እይ፡ የዚህ፡ ዘር፡ ነው።

ቀጪን፡ ሊጥ፡ ውሃ፡ የበዛበት፡ ቡሖ።

ቀጪን፡ ሠጥር፡ ከጐድን፡ ኹሉ፡ የምትቀጥን፡ ታናሽ፡ የጐን፡ ዐጥንት።

ቀጪን፡ እመቤት፡ ከድኸነት፡ የወጣች፡ ራሷን፡ የቻለች።

ቀጪን፡ ፈታይ፡ ኩታው፡ በቀለበት፡ የሚሾልክ፡ ድርና፡ ማግ፡ የምትፈትል፡ ሴት።

ቀጪንነት፡ ቀጪን፡ መኾን።

ቀጪኖ፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ ለቀጪኔ።

ቀጪዎች፡ ቀጮች፡ ጕዲት፡ ግራኝ፡ ዐጤ፡ ቴዎድሮስ፡ ሐበሻን፡ እንደ፡ እስራኤል፡ ፫፡ ዘመን፡ የቀጡ፡ በዚህ፡ ላይ፡ የፋሺስት፡ ሲመር፡ ፸፭፡ ይኾናል።

ቀጫጫ (ጮች)፡ የቀጨጨ፡ ቀጪን፡ ኰስማና።

ቀጫጯን (ኖች)፡ ብዛቱና፡ ቅጥነቱ፡ ባንድነት፡ የሚታይ፡ ውዥኝን፡ ዐደይ፡ አበባን፡ ፍየለ፡ ፈጅን፡ ቀጨሞን፡ የመሰለ።

ቀጭ፡ ማጋጫ፣ ደበሎ፣ ደላጎ፣ ምገጭ፣ ቀቀ።

ቀጭጭ።

ቀጭ፡ አደረገ፡ ጨ፡ መታ።

ቀጭ፡ ከንፈርን፡ የሚያቈስል፡ አግርን፡ የሚሠነጥቅ፡ ብርድ፡ ውርጭ። ምሳሌ: "(እኸሉን፡ ቀጭ፡ መታው)"፡ አለፍሬ፡ አስቀረው።

ቀጭ፡ የቀጨ፡ የሚቀጭ፡ ቈራጭ፡ ገንጣይ። ምሳሌ: "ዝርዝረ፡ ቀጭ"፡ እንዲሉ።

ቀጭቀጨ፡ በውጋዴ፡ በረሓ፡ የሚገኝ፡ ቅጠል፡ የግርሽጥ፡ ዐይነት፡ ሰው፡ ኹሉ፡ እያኘከ፡ ውሃውን፡ ይመጠዋል።

ቀጭታ፡ የቀጨች፡ የምትቀጭ።

ቀጸለ: ትምርትን አጠና፣ ጨመረ።

ቀጸለ: ዐማ፣ ነቀፈ፡ ስም አጠፋ።

ቀጸለ: ደረበ፣ በላይ አደረገ (ግእዝ) "ከተለን፣ ቀጠለን ተመልከት። "

ቀጸላ: ኅባኔ፡ ሻሽ (የራስ፣ የፊት መሸፈኛ)፡ ዐይነ ርግብ፣ ወገሮ፣ ሠርመዲ (በዙሪያው የወርቅ መርገፍ ያለበትና የሌለበት) የሐር፣ የፈትል፣ የግምጃ አጣፊኝ፡ ሥሥ፣ ቀጪን መደረቢያ (፩ኛ ነገሥት ፳፡ ፴፰)

ቀጸላ: ዐሰላ፣ ቀጠለ።

ቀጸላ: የማር እንጀራ፣ ቀጠለ።

ቀጸላ: የወንድና የሴት የክርስትና ከፊለ' ስም፡ በሕዝብ አነጋገር ቀጠላ ይባላል።

ቀጸበ (ቀጺብ ቀጸበ): ጠቀሰ፡ ባይን፣ በጣት ጠራ፣ አመለከተ፣ አዘዘ፡ አፈጠነ።

ቀጻ (ቀጽዐ): ባንድ ልክ ብራናን፣ ወረቀትን ቈረጠ፣ አፈፈ፣ ቀፈፈ።

ቀፈረ: አቆመ፣ ዘረጋ (ዦሮን)፡ ፊት ለፊት ቀቀረ (የከብት)

ቀፈረረ (ከፈረረ): አንቀፈረረ፡ አረዘመ (ረዘመ)

ቀፈረር: ቀፍራራ፡ የተንቀፈረረ፡ እንቅፍር፡ ርዝማኔው የሚያስቀይም።

ቀፈቀፈ: በሳ፣ ሰበረ (ዕንቍላልን)፡ ፈለፈለ፣ ብዙ ወለደ (ጫጩትን፣ ዶሮው፣ ሰዉ)

ቀፈቀፈ: ግራና ቀኝ እየመታ ከመካከለ ከረከረ። "የቀፈፈንና የቀፈቀፈን ልዩነት አስተውል፡ ቀረቀፈን እይ። "

ቀፈታም: ሆደ ዘርጣጣ፣ ቦርጫም።

ቀፈት (ቀፈፈ): ቀፈድ የቈርበት ቀለበት። "በግእዝ ግን ፵ንቃ፣ ደንደስ ማለት ነው። "

ቀፈት መራ: ቈርበትን ጠለፈ፣ አያያዘ፡ ወይም ቈዳን ወጠረ፣ ገደገደ። "ቀፈደን እይ። "

ቀፈት: ትልቅ ሆድ፡ ቦርጭ፣ ደንደስ መሳይ (ጐንደር) "ቈለፈ ብለኸ ቈለፈትን ተመልከት። "

ቀፈት: የጠፋ ከብት ጭገሬታ ምልክት።

ቀፈደ: ቅፍንድን በሳ፣ ቀፈድ አበጀ፡ እሱንም እየጠለፈ አሰረ (ሸክምን፣ ሣርን፣ ነዶን፣ ገለባን፣ ዕቃን)

ቀፈደደ: ማሰሪያን በመጠምጠም አጥብቆ አሰረ (ሰውን) (ገቢር)

ቀፈደደ: ደነዘዘ፣ ፍጥነት፣ ቅልጥፍና አልባ ኾነ (ተገብሮ)

ቀፈደድ: ቀፍዳዳ፡ ደነዝ፣ ደንዛዛ።

ቀፈዲያም: ዝኒ ከማሁ።

ቀፈዳም: ቀፈታም፡ ሰውነተ ሻካራ፣ ቈርፋዳ።

ቀፈድ: ቀፈት፡ በቈርበት ዙሪያ በቅፍንድ ግፍ ያለ ቀዳዳ ጠፍርና ገመድ የሚያስገባ። "ቀፈድና ቀፈት አንድ ስም ነው። "

ቀፈፈ: ለመነ፡ መንደር ለመንደር እየዞረ "በአንተ ስማ፣ ለማርያም፣ ስለ ቸሩ እግዚአብሔር" አለ።

ቀፈፈ: ሰቀጠጠ፣ ጨመደደ፣ ጨፈገገ፣ ከበደ፣ አሳመመ። "ዛሬ ሰውነቴን ይቀፈኛል። "

ቀፈፈ: ቈረጠ፣ ከረከመ፣ አስተካከለ (የቈዳን፣ የብራናን፣ የቅልን ጫፍ) "አፈፈን አስተውል። "

ቀፈፋ: ክርከማ፣ ልመና።

ቀፋሪ: የቀፈረ፣ የሚቀፍር፡ ቀቃሪ።

ቀፋራ: ቅፍር፡ የተቀፈረ፡ ቅቅር።

ቀፋፊ (ዎች): የቀፈፈ፣ የሚቀፍ፡ ከርካሚ፣ ለማኝ።

ቀፋፋ: ከርፋፋ።

ቀፋፎ: ቀራፎ፣ ሞኝ።

ቀፍቃፊ: የቀፈቀፈ፣ የሚቀፍቅፍ፡ ፈልፋይ፣ ከርካሪ።

ቀፍዳጅ: የቀፈደደ፣ የሚቀፈድድ፡ አሳሪ።

ቀፎ (ዎች): ከሐረግ፣ ከመቃ፣ ከቀጯን ዕንጨት የተታታ፣ የተሠባጠረ የንብ ቤት፡ በኹለት ወገን አፍ በመካከል ፍንጭ ያለው።

ቀፎ ለቀፎ: ውስጥ ለውስጥ። "አቶ እከሌን የመታው ጥይት ቀፎ ለቀፎ ኼዶ ስለ ወጣ ሳይገድለው ቀረ። "

ቀፎ ቈራጭ: ከቀፎ ውስጥ ማርን የሚቈርጥ። "መኪና ሰፊ" እንደ ማለት ያለ ነው።

ቀፎ: ሆድ፣ ውስጠ ክፍት ነገር።

ቀፎ: የዓሣ መያዣ።

ቍለላ፡ ክመራ።

ቍለፋ፡ ቅርቀራ፡ ሽጐራ።

ቍላ(ቍልሕ)፡ በሰውና፡ በንስሳ፡ በእራዊት፡ ብልት፡ ሥር፡ ተንጠልጥሎ፡ የሚታይ፡ ሥጋዊ፡ ጓሚያ፡ ፍሬ፡ ቈለጥ፡ ኹለትነት፡ ያለው። (የጦጣ፡ ቍላ)፡ ፍሬው፡ የሚንጣጣ፡ ዕንጨት።

ቍላ፡ ሙርጥ፡ ዘንጉ፡ ወንዳወንዴ።

ቍላ፡ ቀረሽ፡ ወንዲላ፡ ኀይለኛዪቱ፡ ሴት፡ (መሳፍንት ፬፡ ፳፩)

ቍላ፡ በንቅብ፡ በላይ፡ ወግዳና፡ በቡልጋ፡ ክፍል፡ የሚገኝ፡ ቀበሌ፡ መዋጊያ፡ ስፍራ።

ቍላ፡ ባለሽ፡ ዘመቻ፡ ባንድ፡ አይቅር።

ቍላዎች፡ ቈለጦች።

ቍሌት፡ ጥብስ፡ የሥጋ፡ ወጥ፡ ጥቂት፡ እንጂ፡ ብዙ፡ ያይዶለ፡ ውሃ፡ ያነሰው።

ቍልላት(ጕልላት)፡ የክምር፡ የጕቾ፡ ሥራ፡ ኹኔታ።

ቍልል(ጕልል)፡ የተቈለለ፡ ክምር፡ የሣር፡ የገለባ፡ ጕቾ።

ቍልልታ፡ የደንጊያ፡ የመሬት፡ ክምር፡ በዕለተ፡ ፍጥረት፡ የተቈለለ፡ ከጕባ፡ የቀጠነ።

ቍልመማ፡ ቅለሳ፡ ጥምዘዛ።

ቍልምማት፡ ቅልሳት፡ ጕብጠት።

ቍልምም፡ የተቈለመመ፡ ዝልስ፡ ዝቅዝቅ፡ ቅልስ፡ ጥምዝ።

ቍልምጫ፡ የማይረባ፡ ምስጋና፡ ልምምጥ፡ (ኢዮብ ፴፪፡ ፳፪)

ቍልቍለት፡ ከደጋ፡ ወደ፡ ቈላ፡ ከተራራ' ወደ፡ ጥግ፡ መውረጃ፡ መንገድ፣ "በግእዝ፡ ቍልቍሊት፡ ይባላል። "

ቍልቍለቶች፡ ዘቅዛቆች፡ ተዳፋቶች (ሕዝቅኤል ፴፰፡ ፳)

ቍልቍል፡ የተቈለቈለ፡ ዝቅዝቅ፡ ታች።

ቍልቍሎሽ፡ ዝኒከማሁ ለቍልቍለት፡ ዝቅዝቆሽ።

ቍልቋል(ሎች)፡ በቈላና፡ በወይናደጋ፡ የሚበቅል፡ ወተታም፡ ዛፍ፡ ከሥር፡ እስከ፡ ጫፍ፡ ትንንሽ፡ እሾኸ፡ አለው፡ ውስጠ፡ ክፍት፡ የኾነ፡ ዕንጨቱ፡ እየተፈለጠ፡ ለጣራ፡ ይኾናል። (ተረት) "ካጋም፡ የተጠጋ፡ ቍልቋል፡ ሲያለቅስ፡ ይኖራል። "

ቁልቢ(ኦሮ)፡ ነጭ፡ ሽንኵርት።

ቁልቢ፡ በሐረርጌ፡ አውራጃ፡ ያለ፡ አገር።

ቍልቢጥ(ጦች)፡ ቃጤ፡ ዕፍኝ፡ የምትይዝ፡ መስፈሪያ።

ቍልዕ(ቀልዐ፡ ከላ፡ አስወገደ)፡ ቅምጥ፡ ዐይናር፡ መክላት፡ ማስወገድ፡ የሚገባው።

ቍልዕ፡ ለግእዝም፡ ይኾናል።

ቍልጭ፡ አለ፡ ቈለ፡ ጥርት፡ አለ።

ቍልጭ፡ የቈለ፡ የጠራ፡ የበራ።

ቍልጭልጭ፡ አለ፡ ተቍለጨለጨ።

ቍልጭልጭ፡ የተቊለጨለጨ፡ የሚቍለጨለጭ፡ የሰው፡ የዥብሪ፡ የተከበበ፡ አውሬ፡ ዐይን።

ቍልጭልጭታ፡ የዐይን፡ ጥራት፡ ጥሩነት፡ ቍልጭልጭ፡ ማለት።

ቍልፋት፡ ቅልሳት፡ ጕብጠት።

ቍልፍ፡ አለ፡ ቅልስ፡ ዕጥፍ፡ ዝግት፡ አለ። "እምግቡ፡ ውስጥ፡ ጕድፍ፡ ቢገባበት፡ አንዠቴ፡ ቍልፍ፡ አለ፡ እንዲል፡ ባላገር። "

ቍልፍ፡ የመዝጊያ፡ የሣጥን፡ የልብስ፡ ማገናኛ፡ በመክፈቻ፡ በጣት የሚቈለፍና፡ የሚከፈት፡ ጓጕንቸር፡ አዝራር፡ አግራፍ፡ ባልና፡ ሚስት፡ (ጥሬ) (መርፌ፡ ቍልፍ) መካከሉ፡ ታጥፎ፡ ዳርና፡ ዳሩ፡ የሚገናኝ፡ የቀሚስ፡ የጥብቆ፡ መግጠሚያ። (ዐለንጋ፡ ቍልፍ)፡ ፵ፍና፡ ፉ፡ ብስ፡ ኾኖ፡ በጠፍር፡ (ዐለንጋ)፡ የሚዘጋ፡ ቅርቃር። (ሸርሙጣ፡ ቍልፍ)፡ በወስፌ፡ በምስማር፡ የሚከፈት፡ መናኛ። "ሠረገላን፡ ተመልከት። "

ቍልፍ፡ የተቈለፈ፡ የተዘጋ፡ የታጠፈ፡ ምላስ፡ ዥራት ምልስ፡ ቅልስ፡ ዝግ፡ (ቅጽል)

ቍልፍ፡ የድንኳን፡ ጣራና፡ ግድግዳ፡ ማያያዣ፡ የንሓስና፡ የጥብጣብ፡ ቀለበት፡ (ዘጸአት ፳፮፡ ፮)

ቍልፍልፍ፡ አለ፡ ተቈላለፈ።

ቍልፍልፍ፡ የተቈላለፈ።

ቍልፍነት፡ ዝግነት፡ ቅልስነት።

ቍልፎች፡ ጓጕንቸሮች፡ ቀለበቶች፡ አዝራሮች፡ (ዘጸአት ፴፭፡ ፲፯)

ቁመተ፡ ሥጋ፡ የሥጋ፡ መቆም፡ አቋቋም። ምሳሌ: "አቡነ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ ለቁመተ፡ ሥጋ፡ በሑዳዴ፡ ቅጠል፡ ይበሉ፡ ነበር። "

ቁመተ፡ ዶሮ፡ ዐጪር፡ ሰው።

ቁመታም፡ ቁመቱ፡ የረዘመ፡ ሰማይ፡ ዳሱ።

ቁመት፡ በቁሙ፡ ቆመ።

ቁመት፡ የአካል፡ ልክ፡ መጠን፡ ከራስ፡ እስከ፡ እግር፡ ከግራ፡ እጅ፡ ጣት፡ እስከ፡ ቀኝ፡ ጣት (የሰው) ከእግር፡ እስከ፡ ዠርባ፡ ከራስ፡ እስከ፡ ዥራት (የእንስሳ) ከሥር፡ እስከ፡ ጫፍ፡ ያለ (የዛፍ) (ሕዝቅኤል ፲፱፲፩) ምሳሌ: "ቁመተ፡ ዐጪርቁመተ፡ ረዥም"፡ እንዲሉ። በግእዝ፡ ቆም፡ ይባላል።

ቁመና፡ የቁመት፡ ኹኔታ። ምሳሌ: "ይህ፡ ሰው፡ ቁመናው፡ ያምራል። "

ቁመኛ (ኞች)፡ አስማተኛ፡ ቡዳ፡ ዐይነ፡ ወግ።

ቁመኛቡዳ (ቀወመ)

ቍመዳ፡ ድረታ፡ ደፈና።

ቁማር(ዐረ)፡ የንጉሥና፡ የንግሥት፡ ሥዕል፡ ሌላም፡ ምልክት፡ ከቍጥርና፡ ከፊደል፡ ጋራ፡ በላዩ፡ ያለበት፡ የጨዋታ፡ ወረቀት፡ ወይም፡ ዕንጨት። "ሰውን፡ ባንድ፡ ጊዜ፡ ያከብራል፡ ያደኸያል። " "ቁማርን፡ መዠመሪያ፡ ያወጡ፡ የጢሮስና፡ የሶርያ፡ ሰዎች፡ ናቸው፡ ይባላል። "

ቁማርተኛ(ኞች)፡ ቁማር፡ ወዳድ፡ ተጫዋች፡ ዐዋቂ።

ቁማሽ(ዐረ)፡ ጣቃ።

ቍማጭ፡ ቍራጭ፡ ጕማጅ።

ቁም (ቅዉም)፡ የቆመ፡ የተገተረ፡ ደማዊት፡ ነፍስ፡ ያለችው፡ የቤት፡ እንስሳ፡ ለዕቃም፡ ይነገራል። ምሳሌ: "ቁም፡ ሣጥን"፡ እንዲሉ።

ቁም፡ ለቁም፡ ቀውላላ፡ ሰውነቱን፡ ሰውነቷን፡ የማይሰበስብ፡ የማትሰበስብ።

ቁም ሣጥን: ቁሞ የሚከፈት፡ የቆመ ያልተጋደመ፡ በውስጡ ከታች እስከ ላይ ዐልፎ ዐልፎ የዕቃ መሰደሪያ ዕርከን ያለውና የሌለው።

ቁም፡ ሥቃይ፡ የሥጋ፡ መከራ።

ቁም፡ ስቅል፡ የተሰቀለ፡ ሰውነት፡ ጭንቅ፡ ሥቃይ። ምሳሌ: "ፋሺስቶች፡ አንዱን፡ ሐርበኛ፡ ይዘው፡ ቁም፡ ስቅሉን፡ አሳዩት "

ቁም፡ ቁመት፡ ቁመና። ምሳሌ: "ፍራት፡ ከቁም፡ ይጥላል"፡ እንዲሉ።

ቁም፡ ትእዛዝ፡ አንቀጽ፡ "አትኺድ፡ ርጋ፡ ቀጥ፡ በል"

ቁም፡ ነገራም (ሞች)፡ ሐቀኛ፡ እውነተኛ፡ ልጨኛ፡ የሰው፡ ውለታ፡ የማይቀርበት፡ በቃሉ፡ የጸና።

ቁም፡ ነገር፡ ሐቅ፡ ርግጥ፡ ጠቃሚ፡ ጕዳይ።

ቁም፡ እስር፡ ሳይታሰር፡ የተጋዘ፡ "ከዚህ፡ ኣትለፍ"፡ የተባለ፡ ሰው፡ (፩ኛ ነገሥት ፴፮ ፴፯)

ቁም፡ ከብት፡ ብርና፡ ወርቅ፡ ያልኾነ፡ በግ፡ ፍየል፡ ፈረስ፡ በቅሎ፡ አህያ፡ ግመል፡ በሬ።

ቁም፡ ዜማ፡ ዝማሜ፡ ጽፋት፡ መረግድ፡ ጸናጽል፡ ከበሮ፡ የሌለበት፡ ዋና፡ ዜማ።

ቁም፡ ደንጊያ፡ የቆመ፡ የተገተረ፡ ያልተጋደመ።

ቁም፡ ጥፈት፡ ጕልሕና፡ ማለፊያ፡ ጥፈት፡ ረቂቅ፡ ያይዶለ፡ በሩቅ፡ የሚታይ፡ ሳይጋደም፡ በቀጥታ፡ የተጣፈ፡ ሰው፡ ቁሞ፡ በዘንግ፡ መጠን፡ የሚያነበው።

ቁምስናቆሞስነት፡ ቆሞስ፡ መኾን። "ቁምስና፡ የግእዝቆሞስነት፡ ያማርኛ፡ ነው። "

ቁምሶ፡ ከስንዴ፡ ጋራ፡ የተጋገረ፡ እንሰት። "ዘሩ፡ ቀመሰ፡ ነው፡ "

ቁምሩ፡ ታናሽ፡ ርግብ፡ ቡያ፡ የወፍ፡ ዐይነት። "ባረብኛ፡ ቁምሪ፡ ትባላለች። "

ቁምባ፡ ያገር፡ ስም።

ቍምድ፡ የተቈመደ፡ ድርት፡ ግብረ፡ መርፌ፡ ውስብስብ።

ቍምጣ፡ ቁመቱ፡ ከጕልበት፡ በላይ፡ የኾነ፡ ዐጪር፡ ሱሪ፡ ወንበር፡ የለሽ።

ቍምጤ፡ ብጣሽ፡ ቍራጭ፡ ነገር።

ቍምጤ፡ የሣር፡ ስም።

ቍምጥ፡ ቍርጥ፡ ጕምድ፡ መቈመጥ። (ተረት)"ቈማጣ፡ ቢለው፡ ያው፡ ቍምጥ፡ ነው፡ ሌላ፡ ምን፡ ይመጣል፡ አለ። "

ቍምጥ፡ አለ፡ ጕምድ፡ ብጥስ፡ አለ።

ቍምጥ፡ የተቈመጠ፡ ቍርጥ፡ ጕምድ።

ቍምጥምጥ፡ አለ፡ ቍርጥርጥ፡ አለ።

ቍምጥና፡ ቈማጣነት፡ ቢስ፡ ገላ፡ ደዌ፡ ሥጋ። (ተረት)"ከሹመት፡ ክፉ፡ ግብዝና፡ ከበሽታ፡ ክፉ፡ ቍምጥና "

ቁሞች፡ ከብቶች፡ እንስሶች።

ቍስለ ሥጋ: የሥጋ ቍስል፣ ቍምጥና፣ ወይም ሌላ።

ቍስለ ነፍስ: የነፍስ ቍስል፣ ኀጢአት (ነፍስን የሚጐዳ)

ቍስለት: ንዝንዝ፣ ጭቅጭቅ።

ቍስለኛ (ኞች): ተመቶ፣ ተወግቶ፣ ተገርፎ፣ ተቈርጦ፣ ተፈንክቶ፣ ተቃጥሎ የቈሰለ ሰው፣ ባለቍስል።

ቍስሉ ሰፋ: አፋገ፣ በዙሪያ ጨመረ።

ቍስላም: ቍስል ያለበት፣ የበዛበት።

ቍስል (ሎች): ደምና መግል፣ እዥ የሚፈሰው ዕከክ ዐይነት፣ ብጕንጅ፣ ችፌ፣ ቂጥኝ፣ ሸሐኝ፣ ነቀርሳ፣ ኪንታሮት የመሰለው ኹሉ (ስም)

ቍስል (ቍሱል): የቈሰለ (ቅጽል) (፪ኛ ነገሥት ፰፡ ፳፱፡ ፱፡ ፲፭)

ቍስቈሳ: ጠቀሳ፣ ጭመራ።

ቍስቋም ማሪያም: የቍስቋም ማርያም።

ቍስቋም: እመቤታችን ተሰዳ የተቀመጠችበት የግብጽ ተራራ።

ቍስቋም: የታቦት ስም፡ በኅዳር ቀን የሚነግሥ የእመቤታችን ጽላት።

ቍስቋሞች: የቍስቋም ካህናት፣ እወዳጆች።

ቍስጥንጥንያ: የቈስጠንጢኖስ መናገሻ ከተማ። "እንደ ፈረንጅ አቈጣጠር ከ፲፬፻፷፯ . ወዲህ ግን የቱርክ መዲና ኾናለች። "

ቍረማ: ኵርኵማ።

ቍረንጮ: ያለቀ፣ የደቀቀ አሮጌ ዝተት፡ ቍርጩ የሚለብሰው። ቍረንጮ ያለቀ የደቀቀ አሮጌ ዝተት (ቍርጩ የሚለብሰው ")

(ተረት) "የለማኝ ለማኝ ቍረንጮዬን ቀማኝ"

ቍረንጯም: ቍረንጮ ለባሽ።

ቍሪት: የግል ገንዘብ፣ ቅርስ። "ባረብኛ 'ሰና' ተወራራሽ ስለ ኾኑ ቍሪትና ቅርስ አንድ ወገን ናቸው። " "ጥሪት ቍሪት" እንዲሉ።

ቍራ (ሮች): ጥቍር አሞራ፡ ሲጮኸ ቍር ዋዋ የሚል (ዘፍጥረት ፰፡ ፮፡ ፩ኛ ነገሥት ፲፯፡ ፬፣፯) (ተረት): "ጩኸት ለቍራ፡ መብል ላሞራ። " "ቍራ አራት ዐይነት ነው፡ ኹለቱ ፍጹም ጥቍሮች (በደጋ፣ በቈላ የሚኖሩ)፡ ሦስተኛው በራሱ ላይ ነጭ አለበት፡ በምሳሌ እንደ ቄስ ይታሰባል፡ እንስሳ፣ አውሬ በሞተ ጊዜ ኹለት ዐይን ያወጣል፡ (ለሌሎች ይባርካል) " "ቧሔ ቍራ" እንዲሉ። "አራተኛው ደረቱና ዐንገቱ ነጭ ነው፣ መጠኑም ከሦስቱ ያንሳል። " "ቍራ በዕብራይስጥ ቆሬእ፣ በግእዝ ቋዕ ይባላል፡ ፈላስፎች ፪፻ ዓመት ይኖራል ይላሉ። "

ቍራ ይጮኸበታል: ከነዋሪዎቹ ክፋት የተነሣ አገሩ፣ ከተማው ይፈታል፡ ጠፍ ይኾናል (ኢሳይያስ ፴፬፡ ፲፩)

ቍራሽ (ሾች): የዳቤ፣ የንጀራ ክፍል (ትልቁም፣ ትንሹም) (ዘፍጥረት ፲፰፡ ፭፡ ማቴዎስ ፲፬፡ ፳) "የዳቦ ሲኾን ጕርማጅ ይባላል። "

ቍራን (ዐረ፡ ቀረአ፡ አነበበ): የመጽሐፍ ስም፡ እስላሞች ለነቢያችን መሐመድ ከሰማይ ወረደ የሚሉት መጽሐፍ (ብሉይንና ሐዲስን የሚያስተባብል) "ትርጓሜው ንባብ (ምንባብ) ማለት ነው። " "ባረብኛ ቁርኣን ይባላል። "

ቍራኛ (ኞች): ከጠላት ጋራ የታሰረ እስረኛ፡ በሰው ያደረ መንፈስ ርኩስ።

ቍራኛነት: ቍራኛ መኾን።

ቍራጭ (ጮች): ጕራጅ፣ ጕማጅ፣ ሙዳ፣ ዕራፊ (፪ኛ ሳሙኤል ፭፡ ፩፡ ማቴዎስ ፱፡ ፲፮፡ ማርቆስ ፪፡ ፳፩) "(የሰይጣን ቍራጭ): ጭራሽ ክፉ ሰው። "

ቍሬማ: እኸል የማያበቅል መሬት።

ቍሬማ: ዝኒ ከማሁ፡ ራሱ በትር ኵርኵም ያረፈበት።

ቍር (ቍርዕ): የብረት ቆብ፣ ቦርቦርቲ፣ ራሰ ከል። "በግእዝ ጌራ ኀጺን ይባላል።" "ራስን ተመልከት።"

ቍር (ቅሩሕ፡ ቅሩዕ፡ ኵሩዕ): የተቈራ፣ የተበጣ፡ ብጥ፣ ቍርም፡ ቡቅር፣ ልጩ፡ የራሱን ጠጕርና ጥፍሩን በገዳም ቀብሮ የኼደ ጠበለተኛ።

ቍር: ቅዝቃዜ፥ቈረረ።

ቍር: ብርድ፣ ቅዝቃዜ። "ባላገር ግን ቍር በማለት ፈንታ ቈራ ይላል። " "ቍርዬን እይ። "

ቍር: ዝኒ ከማሁ፡ ክርከማ። "ጥፍር-ቍርጫ" እንዲሉ።

ቍር: የብረት ቆብ፡ ቈራ።

ቍርማሚ: የዳቤ፣ የዳቦ ሾለቅ፡ ኵርማን ቀንድ መስሎ የሚታይ።

ቍርም: የተቈረመ።

ቍርምቢ: ወጠጤ፡ ቍርንቢ።

ቍርስ አለ: ተቈረሰ።

ቍርስ አደረገ: ቍርስ በላ፣ ተመገበ፡ አፉን አጝሸ። "(ጥርስ) ቍርስ መቍረስ መቈረስ። "

ቍርስ አደረገ: ቈረሰ።

ቍርስ: የተቈረሰ፣ የተፈተተ (ቅጽል)

ቍርስ: ጥቂት ምግብ፡ ጧት የሚበላ (ሙሽት) (ስም)

ቍርስርስ: ቍርስራሽ፡ የተቈራረሰ፡ ክፍልፍል፣ ክፍልፋይ።

ቍርር: የተቈረረ፡ ድርብርብ፣ ንብብር (ድንጋይ) "በቍርር ላይ ቍርር" እንዲሉ።

ቍርሾ: ትንሽ ቂም (የቈየ)

ቍርቍምባ: ዓሣ መያዣ (የሻታ ዐይነት)፡ ባለገመድ ጠርሙስ መሳይ።

ቍርቍሩ: ኵኵሉ።

ቍርቍሩ: ቍርቍር፡ የርሱ ቍርቍር።

ቍርቍራ: የዛፍ ስም፡ ፍሬው የሚበላ፣ የበረሓ ዕንጨት፣ እሾኸ፣ ቈላፋ። "በዜጋመል ገባ ይባላል። "

ቍርቍር አደረገ: መዝጊያ መታ።

ቍርቍር: በተጕለት ውስጥ ያለ ቀበሌ።

ቍርቍር: የተቈረቈረ፣ የተበሳ ግንድ፡ የተደፈነ፣ ድፍን፣ ጥቅጥቅ፣ ምሥርት።

ቍርቍዝ: ዝኒ ከማሁ።

ቍርቊስት: የዓሣ ስም፡ መናኛ ዓሣ።

ቍርቊሻ: የጨዋታ፣ የውጊት ፈተና።

ቍርቈራ: ምሰት፣ ቍፈራ፣ ሽንቈራ፣ ምሥረታ፣ ጕርበጣ፣ ደፈና።

ቍርቈራ: የጥሪ ምልክት።

ቍርባ: ድንገተኛ በሽታ የሚያስታውክና የሚያስቀምጥ፣ ሰውነትን የሚያደርቅ።

ቁርባብቻ: ከቈዳና ከጨርቅ የተሰፋ ከረጢት።

ቍርባን ውጭ ክርስትና: (አይገባም የቀረው ነው) አስቀድሞ ሊደረግ የሚገባው በኋላ እንዳይደረግ ለማስጠንቀቅ፡ ቍርባን ውጭ ክርስትና እየተባለ ይተረታል። "፫ኛውን ጠባ እይ። "

ቍርባን: ለግዜር፣ ለጣዖት የሚቀርብ መሥዋዕት፣ ዕርድ፡ ስንዴን፣ ወይንን፣ ዕጣንን የመሰለ የተቀደሰና ማለፊያ ስጦታ ኹሉ።

ቍርባን: የክርስቶስ ሥጋና ደም በስንዴ ኅብስትና በወይን ጠጅ መልክ የሚሰጥ። "በሚገባ የተቀበለውን ወደ ፈጣሪ የሚያቀርብ ስለ ኾነ፡ ዳግመኛም ቄሱ ከጸሎትና ከቅዳሴ ጋራ በቅዱስ መንበር ላይ ላምላክ የሚያቀርበው በመኾኑ ቍርባን ተባለ። "

ቍርብ ጭታ: ዕትራት።

ቍርብጭ አለ: ዕትር አለ።

ቍርብጭ: የቈረበ፡ ጕርብ።

ቍርታት (ቍርሐት): ብጥታት፣ ፍቅታት፣ ቡቅራት፣ ልጭታት። "ቍርሐት ባጤ ዘርዐ ያዕቆብ ታሪክ ይገኛል። "

ቍርንቢ: ተባት ፍየል፡ ታናሽ ወጠጤ፡ ላውራ በግም ይነገራል (ሕዝቅኤል ፬፡ ፪) "ቍርን ቀርን፡ ቢ ቢጽ፡ ቀንዳም ቢጤ ማለት ይመስላል። " "ኵርንቢን እይ። "

ቍርንባጥ: ዐጪር።

ቍርንቦች: ተባቶች፡ ወጠጦች (ዘፍጥረት ፴፡ ፴፭)

ቍርንድይ: የትንባኾ ልጥልጥ።

ቍርንጭ: መጥፎ ጠባይ ያለው ሰው፣ ቈጭባራ። "በመለ ቍርንጭ" እንዲሉ።

ቍርንጭ: ዐጨርና ቍጥርጥር የሻንቅላ ጠጕር።

ቍርኙ: የተቈረኘ፣ የተጠመደ፣ የታሰረ።

ቍርኝት: የተቈረኘተ፡ ንፍ፣ ሆደ ጒስር።

ቍርዛም (ሞች): ያልተገዘረ፡ ባለቍርዝ።

ቍርዝ (ዞች): የወይፈን፣ የበሬ ብልት።

ቍርዝ: ልንቡጥ፣ ሽፍን፣ ወሸላ።

ቍርዝ: የተቈረዘ፣ ዛብ የሚመስል ጅራፍ ሽርብ። "ቍርዝ ያሠኘው ጥብቅነቱ ነው።"

ቍርዬ (ቍራዊ): ያሞራ ስም፡ በመከር ጊዜ ከውጭ አገር እየመጣ እኽል የሚበላ፣ በውሃ ዳር የሚያድር፡ ሲኼድ ቍር (ኵር) የሚል የባሕር አሞራ፡ ሲመጣም ኾነ ሲመለስ በኣየር መጥቆ ተራ ይመታና እየተከታተለ በመሪ ይኼዳል፡ አገሩም ኣውስትራልያ ነው ይላሉ። "በግእዝ ኰራኪ ይባላል፡ ዳግመኛም ስለ እግሩ ረዥምነት ሽመላ ይሉታል። " "እሱም ከ፲፭፻ ዓ፡ ም፡ በፊት አሜሪካን ያውቃል። " "ሽመላን እይ። "

ቍርጠማ: የመቈርጠም ሥራ፡ ጕርደማ።

ቍርጠት: የሆድ በሽታ (አንዠትን እየቈረጠ የሚያም)፡ ትርጓሜው መቍረጥ፣ መቈረጥ። "ለሆድ ቍርጠት ብላበት፡ ለራስ ምታት ጩኸበት" እንዲሉ።

ቍርጠኛ (ኞች): ርግጠኛ፣ የማይወላውል፣ የማያመነታ።

ቍርጡ ታወቀ: ርግጡ፣ እውነቱ፣ ድርሱ፣ መጨረሻው ተገኘ፣ ተረዳ።

ቍርጣ: ጭፍልቅ፡ የገላ ተኵስ በቁመት።

ቍርጣሚ: ዕኛኪ።

ቍርጣና ብርባሮ: መስቀልኛ የዠርባ ተኵስ (አግድምና ሽቅብ የተተኰሰ) "ከዚህ የተነሣ ቍስሉ፣ ጠባሳው የሰንጠረዥ መደብ ይመስላል። "

ቍርጣና ብርባሮ: የዕዳሪ ዕርሻ።

ቍርጥ ነገር: ያለቀ፣ የደቀቀ ጕዳይ።

ቍርጥ አለ: ብጥስ አለ።

ቍርጥ ኾነ: ተረገጠ፣ ተፈጸመ።

ቍርጥ ፍርድ: ስቀለው፡ ግደለው የሚል [ፍርድ]

ቍርጥ: ርግጥ ያለቀ፣ የተፈጸመ (ኢሳይያስ ፳፰፡ ፪)

ቍርጥ: የሰራዊት ክፍል (ልዩ ልዩ ጭፍራ) (፩ኛ ሳሙኤል ፲፫፡ ፲፯)

ቍርጥ: የተቈረጠ፡ ጕምድ፣ ሙዳ ሥጋ። "እጀ ቍርጥ" እንዲሉ። "ቈረፀን እይ። "

ቍርጥማታም: ቍርጥማት የሚያጠቃው ሰው፡ ባለቍርጥማት።

ቍርጥማት (ቍርጥ፡ ማት): ቍርጠኛ ቍጣ፡ ሥቃይ።

ቍርጥማት: ያጥንት፣ የጥርስ፣ የዥማት በሽታ (፩ኛ ነገሥት ፲፭፡ ፳፫)

ቍርጥም አደረገ: ቈረጠመ።

ቍርጥም: የተቈረጠመ፣ የታኘከ፡ ዕኝክ።

ቍርጥራጭ: ዝኒ ከማሁ፡ የበገና ጠፈር፣ ጠፍር።

ቍርጥርጥ አለ: ብጥስጥስ አለ። "እከሌና እከሌ ቍርጥርጥ ያለ ጥል ተጣሉ። "

ቍርጥርጥ: የተቈራረጠ፡ ብጥስጥስ።

ቍርጩ ድኻ: አገኛለኹ ከማለት ተስፋው የተቈረጠ፡ ወርቀ ለባሽ፣ ይልሰው ይቀምሰው የሌለው፡ ለምኖ ዐዳሪ፣ መናጢ፡ ችግረኛ።

ቍርጩ: አንዳች ኣልባ።

ቍርጭምጭሚት (ቶች): በኹለት ወገን ያለ የእግር ጕጥ፡ የጫማና የቅልጥም መገናኛ (፪ኛ ሳሙኤል ፳፪፡ ፴፯፡ ሕዝቅኤል ፵፯፡ ፫)

ቍርጭኝ: ዐጪር ድጓ፣ ሰንበት አምኜ። "ቍርንጭን፣ ቍረንጮን፣ ቍርንጫጭን እይ፡ የቈረጪ ዘሮች ናቸው። "

ቍርጭኝ: ዐጪር ድጓ፣ ቈረጨ።

ቍርፅ: የተቈረፀ፡ ቍርጥ (ዐጪር)፡ የዜማ ምልክት።

ቍርፌ: አሮጌ ጋሻ።

ቍርፍድ: ዝኒ ከማሁ።

ቍሻሻ: ጥራጊ፣ እድፍ፣ ጕድፍ፣ ግባስ።

ቍሽሽ አለ: ቈሸሸ።

ቍሽሽ: መቈሸሽ።

ቍሽቢያም: የቍሽብ ወገን፡ ወስፋቱ እኸል የማይቀበል።

ቍቁ (ቈቀወ): ኡኡ።

ቍቁ አለ: ጮኸ፡ "ኑልኝ፣ ድረሱልኝ፣ የሰው ያለኸ!" አለ።

ቍቁታ: ቍቁ ማለት፡ የተገፋ፣ የተበደለ ሰው የሚያደርገው ጩኸት። "ቍቁታውን ለቀቀ፡ ጩኸቱን አበዛ (አደጋ ስለ ደረሰበት) "

ቍቅ አለ: ተፈሳ።

ቍቅ: ታናሽ የፈስ ድምዕ። "ቍቅም ከፈስ ተቈጠረችና። " (ተረት): "ቍቂያም፡ ፈሱን ቍቅ ያደረገ ሰው፡ ባለቍቅ። "

ቍቅታ: ቀጪን ፈስ፡ ቍቅ ማለት።

ቍባ፡ ጕባ፡ ዕንቍላል፡ ቤት፡ ቍባ፡ ግእዝኛ፡ ነው።

ቁባት (ዕቅብት): የተጠበቀች፡ ካስቀመጣት መኰንን በቀር ሌላ ወንድ እንዳይደርስባት፡ በጃን ደረባ ተጠብቃ የምትኖር ሴት፡ ምልምል፡ ሥራ ቤት ገረድ (የተጠበቀች ሴት)

ቁባት፡ የተጠበቀች፡ ዐቀበ።

ቁባቶች (ዕቁባት): ጥብቆች ሴቶች፡ ነገሥታት፡ መኳንንት በተራ የሚደርሱባቸው፡ የሚገናኟቸው፡ የንግሥታት ተወራጆች (የንጉሶች ተተኪዎች)

ቍቤላ፡ የዝኆን፡ ጊደር፡ ዘር፡ ለመቀበል፡ የምትችል።

ቁብ (ዐቀበ፡ ዕቁብ)፡ ዐሳብ፡ ግድ። በጋልኛ፡ ግን፡ ጣት፡ ማለት፡ ነው።

ቍብ፡ መቀመጥ፡ ቈበበ

ቍብ፡ ቍብ፡ አለ፡ ጕብ፡ ጕብ፡ አለ፡ ቈረበ።

ቍብ፡ አለ፡ ጕብ፡ አለ፡ ቍጭ፡ አለ።

ቁብ፡ የለሽ፡ ዐሳብ፡ የለሽ፡ ግድ፡ የለሽ።

ቍብ፡ ጕብ፡ ቍጭ፡ መቀመጥ።

ቍብላ፡ ትልቅ፡ ወይፈን፡ በትከሻው፡ ቀንበር፡ ለመቀበል፡ ዘሩን፡ ለማቀበል፡ የሚችል።

ቍብታ፡ ጕብታ፡ ጕብ፡ ማለት።

ቍተማ: ስለፋ።

ቍቲት (ቶች): የነጠላ፣ የኩታ፣ የጋቢ፣ የቡልኮ ዘርፍ (የሚቋጭ፣ የሚከረር፣ የሚሸረብ) ቍቲት በጣሽ: ሸማኔ ቍቲትን እየበጠሰ ድርን የሚቋጥር።

ቍትቻ (ቀቶት): አስከፋዩ የኅዋት ዳኛ (ተከፋዩ ጋሬዳ የኾነ ገንዘብ)

ቍቻ: እየተጠበሰ የሚበላ እንጕዳይ (እሆድ ቋት የሚገባ)

ቍነና: ጕንጐና፣ ሽረባ።

ቍና (ዎች): መስፈሪያ፣ የስፌት ዕቃ፡ ትንሽና ትልቅ መሸመቻ፡ አጋማሽ መገበሪያ፡ "ቍና" እንዲሉ። (ተረት): "ለስማ መጥሪያ ቍና ሰፋች። " (አዝማሪ): "እንዳይቀደድ ይህ ቍና፡ ብድር አለበትና" (ማቴዎስ ፯፡ ፪ ማርቆስ ፬፡ ፳፬ ሉቃስ ፮፡ ፴፰) (የንጉሥ ቍና): ሌባሻይ።

ቍና፡ መስፈሪያ፡ ቈነነ።

ቍና፡ ቍና፡ ተነፈሰ፡ ከሩጫ፡ ብዛት፡ የተነሣ፡ እጅግ፡ በጣም፡ ተነፈሰ።

ቍና፡ ተኩል፡ የስፍር፡ ስም፡ አንድ፡ ተግማሽ።

ቍና ፈጅ: አንድ ቍና እኸል የሚይዝ ሸክላ።

ቍናሳም: ግማታም፣ ጥንባታም።

ቍናስ: ግማት፣ ጥንባት፣ የማይሽር ቍስል፣ መጥፎ ሽታ።

ቍን(ቍንጽ፡ ቀነጸ)፡ የተባይ፡ ስም፡ ቀን፡ ተደብቆ፡ ይውልና፡ ሌሊት፡ የሰውን፡ ገላ፡ የሚመጠምጥ፡ የሚልስ፡ የሚበላ፡ ጥቍር፡ ተባይ፡ ተፈናጣሪ፡ ዘላይ። "ሲበዛ፡ ቍንጮች፡ ያሠኛል። " "ሞያሌን፡ ተመልከት። "

ቍን፡ ቤት፡ ውሻ።

ቍንቍኔ: ጥንጣን፣ ነቀዝ፣ ብል፣ ትል (ግእዝ) "ቅንቅንን እይ፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። "

ቍንቍን አለ: ቈጥቋጣ ኾነ።

ቍንቍን: ቍንቍኔ።

ቍንቍን: የተቈነቈነ፡ ትንትን።

ቍንናት: የጭራ፣ የሽሩባ ሥራ፡ ጕንጕናት፣ ሽርባት።

ቍንናና: የፈጠነ፣ የከበደ።

ቍንን (ኖች): የተቈነነ፡ ትት፣ ጕንጕን፣ ሽርብ፡ ጕኒና (ቆብ፣ ጭራ)፡ ጅንን፣ ኵሩ።

ቍንን በላይ ነኸ: የመንዝ ባላባት፣ የኰሩ፣ የተጀነኑ፣ የተቋፉ (ከዐጤ ምኒልክ እስከ ዐጤ ኀይለ ሥላሴ የነበሩ ደጃዝማች) "በርኖስና ካባ በለበሱ ጊዜ ቆቡንና ኳሱን ወደ ደረታቸው፣ መላሰሻውን ወደ ዠርባቸው ያደርጋሉ፡ ዘወትር በበቅሎ ተቀምጠው ፈረስ ያስባሉ፡ በድርብ ወይም በጃኖ አፍንጫቸውን ይዘው ይታያሉ። " "ጐንደር ራስ ወልዴ ዘንድ ኼደው ሳሉ ዳዊት ገዙና አርእስቱን ወደ ታች፣ ኅዳጉን ወደ ላይ አድርገው በዘረጉት ጊዜ አንዱ ጐንደሬ፡ 'ጌታው ዳዊቱ ተዘቅዝቋል' አላቸው፡ እሳቸውም አለመማራቸውን ለመሰወር 'ጠላቴን እንዲዘቀዝቅልኝ ብዬ ነው እንጂ፡ ዐጥቼው መሰለኸን' አሉት ይባላል። "

ቍንን: የቈነነ፣ የፈጠነ፣ የከበደ፣ የደቀቀ።

ቍንዥና፡ ቈንዦ፡ መኾን፡ ውበት።

ቍንድድ፡ የተቈነደደ፡ የተገረፈ፡ ግርፍ።

ቍንድዶ፡ ከሐረር፡ ከተማ፡ ወደ፡ ጅጅጋ፡ ሲኼዱ፡ በስተግራ፡ የሚታይ፡ ተራራ፡ ነፋሳም፡ ብርዳም።

ቍንዶ(ጕንዶ)፡ ባለያ፡ ሴት፡ ሥራ።

ቍንዶ፡ በርበሬ(ጕንደ፡ በርበሬ)፡ የቅመም፡ ስም፡ ወጥ፡ ተሠርቶ ሊወጣ፡ አቅራቢያ፡ የሚጨመር፡ የሚነሰነስ፡ መከለሻ፡ ከባሕር፡ የመጣ፡ የንጨት፡ ፍሬ።

ቍንጠጣ፡ ቍንጥር፡ ረገጣ።

ቍንጢብራ፡ ኀፍረተ፡ ብእሲት።

ቍንጥ፡ ቍንጥ፡ አለ፡ ተቍነጠነጠ።

ቍንጥንጥ፡ አለ፡ ቅብጥብጥ፡ አለ።

ቍንጥንጥ፡ የተቍነጠነጠ፡ ቅብጥብጥ።

ቍንጥጥ አደረገ፡ ልምዝግ ንክስ  ደረገ፡ ቈነጠጠ 

ቍንጥጥ፡ የተቈነጠጠ የተለመዘገ የተ ቀጣ ልጅ 

ቍንጪት፡ ከቍጫጭ የምታንስ  ንቀሳቃሽ፡ ዳግመኛም ባላገሮች ነፍሳት ይሏታል ።

ቍንጫቶ፡ ጕልጓሎ።

ቍንጮ"ያጤ፡ ምኒልክ፡ እናት፡ የወይዘሮ እጅጋየኹ፡ አጫዋች፡ ባናቱ፡ አንድ፡ ቀጪን፡ ቍንጮ፡ የነበረው፡ ታቦት፡ ዘፋኝ፡ ገና፡ ተሳዳቢ። " "አሽከሩም፡ የልብ፡ ዐውቃ፡ ይባላል። " "ጀጀበን፡ እይ። "

ቍንጮ(ዎች)(ቍንጾ)፡ የሕፃን፡ ዐናት፡ ጠጕር። "ዳግመኛም፡ በግእዝ፡ ቍንዝዕ፡ ይባላል። "

ቍንጮ፡ የጣራ፡ የክዳን፡ ጫፍ፡ ጕልላት፡ የሚቀመጥበት። "የቤት፡ ቍንጮ፡ እንዲሉ። " (የሴት፡ ቍንጮ)፡ ልባም፡ ባለያ፡ ሴት።

ቍንጮ፡ ያ፡ መኻል፡ ራስ።

ቍንጯም፡ ቍንጮው፡ ያደገ፡ የረዘመ፡ ልጅ።

ቍንጯም፡ አሞራ፡ ጕትዬ።

ቍንጸላ: ኵስተራ፣ ሰበራ፣ ግንጠላ።

ቍንጻይ: የቍንጽል ዐይነት።

ቍንጽል (ሎች) (ሡዕ): የተቈነጻለ፡ ኵስታሪ፣ ቍራጭ፣ ግንጣይ (የጧፍ፣ የጥራዝ) "በግእዝ ግን ቀበሮ፣ ተኵላ ማለት ነው። "

ቍዘማ፡ ዐዘን፡ ለቅሶ፡ ሙሾ፡ የሐዘን፡ እንጕርጕሮ፡ (ሮሜ ፳፮)

ቍዝራት፡ የሆድ፡ መነፋት።

ቍዝር (ሮች)፡ የተቈዘረ፡ ጕኝር፡ ጕስር።

ቍዝር፡ አለ፡ ጕስር፡ አለ፡ ተቈዘረ።

ቍዳማ፡ አቍዳማ፡ የብር፡ ጌጥ፡ በባሕር፡ ዐረብ፡ ተሰፍቶ፡ በግንባር፡ ላይ፡ የሚታሰር፡ ያዳል፡ ገዳይ፡ ምልክት።

ቍድ፡ መብራት፡ የሚኾን፡ ቋድ

ቍድስ፡ የተቈረሰ፡ ቍርስ፡ የምግብ፡ ክፍል። በአረብኛ፡ ግን፡ የቤተ፡ መቅደስ፡ ክልል፡ ገረገራ፡ ማለት፡ ነው፡ በአማርኛም፡ የኅብስተ፡ ቍርባንን፡ ፍታቴ፡ ያሳያል።

ቍግ (ጎች)፡ የገመድ፡ ጅራፍ፡ ጫፍ፡ ውልብልቢት፡ ጕተና፡ መሳይ። ቍግ፡ የሚኾኑ፡ ና፡ ስንደዶ፡ ጥፍር፡ አንዶ፡ እንሰት፡ ቃጫ፡ ጭራ፡ ዶቢ፡ የበሬ፡ ኋላ፡ እግር፡ ዥማት፡ ናቸው።

ቍጠባ፡ ቅነሳ፡ የመቈጠብ፡ ሥራ፡ ፈረንጆች፡ ኤኮኖሚ፡ ይሉታል።

ቍጠኛ፡ ቍጡ፡ ቍጣ፡ ወዳድ፡ ባለቍጣ፡ ተቈጪ።

ቍጠጣ፡ የመቈጠጥ፡ ኹኔታ።

ቍጡ (ቍጡዕ)፡ የተቈጣ፡ የሚቈጣ፡ ብስጩ፡ ገሣጭ፡ ገላማጭ።

ቍጡነት፡ ቍጡ፡ መኾን።

ቍጢሶ፡ ባላንጣ፡ ምንዝር፡ ባለጢንጦ።

ቍጢሶ፡ አለ፡ ተለየ፡ ተገለለ፡ ዕልፍ፡ ብሎ፡ ተቀመጠ።

ቍጢጥ፡ በቋፍ፡ መቀመጥ።

ቍጢጥ፡ አለ፡ በእግሮቹ፡ ጣቶች፡ ተቀመጠ፡ ቍጣጥ፡ የሚጥል፡ መስሎ።

ቍጣ (ቍጥዓ)፡ ተግሣጽ፡ ዘለፋ፡ ግልምጫ፡ መዓት። (የሰማይ፡ ቍጣ)፡ መብረቅ።

ቍጣሮ፡ አቍጣሮ፡ የመቍጠሪያ፡ ጸሎት።

ቍጣጣም፡ ቍጣጠ፡ ብዙ፡ ባለቍጣጥ።

ቍጣጥ (ጦች)፡ የንቦሳ፡ የግልገል፡ የሕፃን፡ ወፈር፡ ያለ፡ ቅዘን። ግእዝም፡ (ቍጥ)፡ የጦር፡ ውልብልቢት፡ (ቍጠጥ)፡ ቅጥነት፡ ቀጪንነት፡ ይላል።

ቍጥራት(ቶች)፡ የቊጥር፡ ኹናቴ እስራት፡ (፩ኛ ሳሙኤል ፴፡ ፲፪)

ቍጥር(ሮች)፡ የተቈጠረ፡ (ሕዝቅኤል ፭፡ ፫) "የባቄላ፡ ቍጥር"፡ እንዲሉ። ሒሳብ፡ ስሌት፡ ልክ፡ መጠን፡ መደመር፡ መቀነስ፡ ማብዛት፡ ማካፈል።

ቍጥር(ሮች)፡ የተቋጠረ፡ የታሰረ፡ እስር።

ቍጥር፡ አኃዝና፡ ፊደል፡ ጥቅልና፡ ዝርዝር።

ቍጥር፡ አለ፡ ተቋጠረ።

ቍጥር ዠመረ: አንድ አለ።

ቍጥር፡ የተቈጠረ ቈጠረ።

ቍጥር፡ የተቋጠረ፡

ቍጥርጥራም፡ ባለብዙ፡ ቍጥር።

ቍጥርጥር፡ አለ፡ ተቈጣጠረ።

ቍጥርጥር፡ የተቈጣጠረ፡ እስርስር፡ ሣር፡

ቍጥቍጥ፡ መቈንጠር፡ ቍጠባ፡ ቍንጠራ።

ቍጥቍጥ፡ አደረገ፡ በጥቂት፡ በጥቂት፡ አወጣ፡ ሰጠ።

ቍጥቍጥ፡ የተቈጠቈጠ፡ ምልምል፡ ቍርጥ።

ቍጥቈጣ፡ ቈረጣ፡ ልብለባ።

ቍጥቋጦ(ዎች)፡ ከምድር፡ ከፍ፡ ያለ፡ በጣም፡ ያላደገ፡ ወጣት፡ ግራር፡ ሌላውም፡ እሾኸ፡ ያለው፡ ዕንወት፡ ኹሉ። "ቴዎድሮስ፡ መጣ፡ ዐይኑን፡ አፍጦ፡ ወይ፡ መሸሸጊያ፡ ታናሽ፡ ቍጥቋጦ"(እረኛ)

ቍጥቋጭ፡ የቍጥቋጦ፡ ጭፍጫፊ።

ቍጥባት፡ ቍጠባ።

ቍጥብ፡ የተቈጠሰ፡ በሣጥን፡ በከረጢት፡ ያለ፡ የተቀመጠ፡ ለወጪውም፡ ይነገራል።

ቍጥን (ቁጥን)፡ ጥጥ። "ቁጥን፡ ዐረብኛ፡ ቍጥን፡ ግእዝኛ፡ ነው፡ ከቀጠነ፡ ጋራ፡ ይሰማማል። ፈረንጆች፡ ኩቶን፡ ይሉታል። "

ቍጥጥ፡ አደረገ፡ ቈጠጠ።

ቍጥጥ፡ የተቈጠጠ፡ በልብስ፡ በመሬት፡ ላይ፡ ያለ።

ቍጥጥር፡ ምርምር።

ቍጩት፡ የማክረር፡ ሥራ።

ቍጫ፡ በ፡ ቡልኮ፡ አምሳል፡ ከፈረንጅ፡ አገር፡ ተሠርቶ፡ የመጣ፡ ልብስ፡ ቍቲቱ፡ የሚቋጭ።

ቍጫም፡ ቍጭ፡ ያለበት፡ የበዛበት፡ ስፍራ፡ የድንጋይ፡ ሥር።

ቍጫጭ (ጮች)፡ ታናሽ፡ ፍጥረት፡ ከጕንዳን፡ ከዘመሚት፡ ከምሥጥ፡ እጅግ፡ የምታንስ፡ ተንቀሳቃሽ፡ የጤፍ፡ ቅንጣት፡ የምታኸል፡ ከነፍሳት፡ የምትበልጥ።

ቍጫጮ፡ ጕጫጮ፡ ዐጪር፡ ሣር።

ቍጭ፡ መቀመጥ።

ቍጭ፡ ብዬ፡ የማሽላ፡ ስም፡ ዐጪር፡ ማሽላ።

ቍጭ፡ አለ፡ ተቀመጠ።

ቍጭ፡ ወረረው፡ ከበበው፡ ወረሰው፡ አለበሰው።

ቍጭር፡ ሸሐኝ፡ የለገመ፡ ቍስል፡ ባለመጅ። "ቍጭር፡ ይቀመጥብኸ"፡ እንዲሉ። "ጭንቍርና፡ ጭንኰር፡ ከዚህ፡ ጋራ፡ አንድ፡ ነው። "

ቍጭቋጮ፡ የጣት፡ ትግል፡ ወይም፡ ትንቅንቅ።

ቍጭብርብር፡ ጠባዩ፡ ዐይጥ፡ የበጣጠሰ፡ ሰው፡ ፈትል፡ የኾነ።

ቍጭት፡ አለው፡ ጸጸተው።

ቍጭት፡ ጸጸት፡ ያልተገለጠ፡ ቂም፡ ቍርሾ። ምሳሌ: "በጠላ፡ ቤት፡ ጠብ፡ ቢነሣ፡ እከሌ፡ እከሌን፡ በቍጭት፡ መታው። "

ቍፂያም፡ ቍጋም፡ የከሳ፡ ሰው፡ ከሲታ፡ ሴት፡ ዥማታም።

ቍፈራ: ቍፋሮ፡ ምንቀራ፣ ጕድፈራ፣ ምሰት።

ቁፋ (ዐረ): ታናሽ ቅርጫት።

ቁፋሂ: ዋዌ ነው፡ ቅርጫትም ያሠኛል። ባለቅኔዎች ግን ቅኔ ማሕሌት ይሉታል።

ቁፋዳ: አቁፋዳ (አኩፋዳ)፡ የተማሪ ኰረጆ፡ በዙሪያው የቈዳ የገመድ ቀፈድ ያለው የምግብ መያዣ (ከሰሌን፣ ከሌጦ የተበጀ)

ቍፍር: የተቈፈረ፣ የተማሰ። (ተረት): "ካባ ቍፍር እሸት ተበልቶለት። "

ቂላቂል፡ የቂል፡ ቂል፡ ሞኛሞኝ።

ቂላዋት(ቂል፡ ኀዋት)፡ የቂል፡ ወንድም፡ (ወንድሞች)፡ ጅላዋት።

ቂላዋት የቂል፡ ወንድም: ቄለ።

ቂል(ሎች)፡ ጅል፡ ግጅል፡ ሞኝ፡ ከርፋፋ፡ መነፍ፡ ተላላ፡ ነኹላላ፡ እንከፍ፡ ነጕላ፡ ነፈዝ። (ተረት)"ቂል፡ አይሙት፡ እንዳያጫውት"(እንዲያጫውት) "አሉታ፡ በጽድቅ፡ መፈታቱን፡ አስተውል"

ቂል፡ አስተኔ፡ የቂል፡ ዐይነት።

ቂል ጅል ቄለ

ቂል: ተንቀርፋፊ፡ የሚንቀረፈፍ፡ ተንከርፋፊ።

ቂሎ፡ የዘንጋዳ፡ ስም፡ ቀጪን፡ ረዥም፡ አገዳ።

ቂመኛ(ኞች)፡ ባለቂም፡ ቂምን፡ በልቡ፡ የሚያኖር፡ የሚይዝ (መዝሙር ፵፬፡ ፲፮)

ቂሙን፡ ቀረፈ፡ ብድሩን፡ መለሰ፡ እንደ፡ መቱት፡ መታ እንዳዋረዱት፡ አዋረደ፡ ቂሙን፡ ተወ።

ቂም (ቀመደ)

ቂም፡ ቍርሾ (ቀየመ፡ ቄመ)

ቂም፡ ቍርሾ፡ ብሶት፡ ቍጭት፡ ክፉ፡ ዐሳብ፡ (ሮሜ ፲፪፡ ፲፬) (ተረት)"ቂም፡ ይዞ፡ ጸሎት፡ ሳል፡ ይዞ፡ ስርቆት። " (የካህን፡ ቂም)፡ ጭጐጐት፡ ፍቅሩ፡ ጥኑ።

ቂም፡ በቀል፡ የበቀል፡ ቂም።

ቂም፡ አተረፈ) አቈየ።

ቂም፡ ያዘ፡ ቂምን፡ በልቡ፡ አሳደረ።

ቂስ: የሰው ስም፣ የሳኦል አባት።

ቂራጥ: ግብዝ ወርቅ፡ "በግእዝ ተምያን ይባላል። " "ፈረንጆች ካራት ይሉታል። "

ቂርቆስ: የሰው ስም፡ ጨርቆስ።

ቂሮስ ዳርዮስ: ከቂሮስ ልጅ ከካምቢስ ቀጥሎ የነገሠ ዳርዮስ ሦስተኛ የፋርስ ንጉሥ፡ ቂሮስ የዳርዮስ ቅጽል ነው።

ቂሮስ: የሰው ስም፡ መዠመሪያው የፋርስ ንጉሥ።

ቂብ፡ ሴትኛ፡ መቀመጥ፡ መምላት። ዘሩ፡ ቈበበ፡ ነው።

ቂብ፡ አለ፡ መላ፡ የሆድ።

ቂብ፡ አለች፡ ተቀመጠች።

ቂንር አለ: ዕብጥ አለ። "ሆዱ ቂንር ብሏል እንዲል ባላገር። ጐኘረን እይ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። "

ቂንር: ቅንር፡ የተነፋ፣ ንፍ።

ቂንቂን አለች: እታይ እታይ አለኹ አለኹ አለች፡ ተሽኰነተረች።

ቂንቂን: መውጣት፣ መታየት።

ቂንዳም፡ ቂንድ፡ ያለበት፡ ባለቂንድ፡ ያገዳ፡ እኸል።

ቂንድ (ዶች)፡ ያገዳ፡ ገለባ፡ ፍሬ፡ ዐቃፊ፣ ምስጢሩ፡ የቀንድ፡ ነው።

ቂንጥ(ቂጥ)፡ ቂብ፡ መቀመጥ። "በረረን፡ እይ። "

ቂው፡ አለች፡ ጭው፡ አለች፡ ተባት፡ ፈለገች፡ እንስት፡ ዶሮ።

ቂው፡ ጭው።

ቂድር፡ አለ፡ ህርት፡ አለ።

ቂድር፡ የቄደረ፡ የሚቄድር፡ ኵሩ፡ ትቢተኛ።

ቂጡ፡ ቀጤማ፡ ቈረጠ፡ ፈጽሞ፡ ደስ፡ ተሠኘ፡ ተደሰተ።

ቂጡን፡ ጣለ፡ ያለቀ፡ ሱሪ፡ ታጠቀ።

ቂጣ (ቀጣ)፡ የምግብ፡ ስም፡ ዱቄቱ፡ በውሃ፡ ተለውሶ፡ ታሽቶ፡ ሳይቦካ፡ ወዲያውኑ፡ በፍጥነት፡ የሚጋገር፡ የመንገደኛ፡ የችግረኛ፡ መብል፡ (ዘጸአት ፳፱) ምሳሌ: "የገብስ፡ የስንዴ፡ ያጃ፡ የጤፍ፡ የሽንብራ፡ የምስር፡ ቂጣ፡ የጠላ፡ ቂጣ"፡ እንዲሉ። ሲበዛ፡ ቂጣዎች፡ ይላል።

ቂጣ፡ ቈሎ፡ ከግንቦት፡ ልደታ፡ ዠምሮ፡ ባ፲፪ቱ፡ ወር፡ መባቻ፡ የሚደረግ፡ ልማዳዊ፡ አምልኮ፡ ባዕድ፡ የበዓለ፡ ናእት፡ ምሳሌ፡ (ዘሌዋውያን ፳፫) "ቂጣና፡ ቈሎ"፡ ወይም፡ "ቂጣ፡ ከቈሎ፡ ጋራ"፡ ማለት፡ ነው። ቈሎው፡ የስንዴ፡ ቂጣው፡ የጤፍ፡ ኹኖ፡ በተልባ፡ ብጥብጥ፡ ይበላል። "ልደታ፡ ከወር፡ እወርሽ፡ አድርሽኝ"፡ እየተባለ፡ አስቀድሞ፡ ተልባው፡ በቂጣው፡ ይረጫል፡ ቈሎውም፡ ይበተናል። የመቤታችን፡ ልደት፡ ርግጠኛው፡ በመስከረም፡ ፲፡ ቀን፡ ሲኾን፡ ከሣቴ፡ ብርሃን፡ ሰላማ፡ በግንቦት፡ ፩፡ ቀን፡ ያደረገው፡ ይህን፡ አምልኮ፡ ለማጥፋት፡ ነው፡ ይባላል።

ቂጣ፡ ቈረጥ፡ ዘወትር፡ ቂጣ፡ የሚበላ፡ ቂጣ፡ ወዳድ፡ ቂጣ፡ የሚቈርጥ፡ የሚገምጥ።

ቂጣ፡ በል፡ የጭፍራ፡ ስም፡ ማደሪያ፡ ያልተሰጠው፡ ወታደር፡ ቂጣ፡ በል፡ ይባላል፡ እሱ፡ የሚያርሰውንም፡ መሬት፡ የቂጣ፡ በል፡ ምድር፡ ይሉታል።

ቂጣ፡ ያልሠለጠነ፡ ባላገር፡ አእምሮው፡ ያልተገራ።

ቂጣ፡ ጥረሾ፡ ከገብስ፡ የተጋገረ። (የዝንጀሮ፡ ቂጣ)፡ የቅጠል፡ ስም፡ በገደል፡ ቀጣና፡ የሚበቅል፡ ሰማያዊ፡ ቅጠል፡ ኹናቴው፡ ከማነሱ፡ በቀር፡ ቂጣ፡ የሚመስል። ዳግመኛም፡ እረኞች፡ በአየር፡ ላይ፡ ስለሚያሽከረክሩት፡ ሽክርክሪት፡ ይባላል።

ቂጣለኝ (ቂጣ፡ አለኝ)፡ የቀበሌ፡ ስም፡ በላይኛው፡ ወግዳ፡ ካጤ፡ ዋሻ፡ በስተቀኝ፡ ያለ፡ ቀበሌ።

ቂጣም፡ ቂጠ፡ ትልቅ፡ ሰው።

ቂጥ (ቀጣ)፡ መቀመጫ፡ የስ፡ የእበት፡ መውጫ፡ መፍሻ፡ መተንፈሻ። "ቂጥ፡ ምስጢር፡ ግራና፡ ቀኙ፡ እንደ፡ ብራና፡ ቅጽ፡ ትክክል፡ መኾኑንና፡ የመካከሉን፡ ክፍልነት፡ ያሳያል። "

ቂጥ፡ ለቂጥ፡ ገጠመ፡ ዐበረ፡ ዐደመ፡ አሤረ።

ቂጥ፡ መቀመጥ።

ቂጥ፡ አለ፡ ከፍ፡ ባለ፡ ስፍራ፡ በጫፍ፡ ተቀመጠ፡ ቂብ፡ አለ።

ቂጥኛም (ሞች)፡ ቂጥኝ፡ የያዘው፡ ባለቂጥኝ። "መነኵሴና፡ ቂጥኛም፡ ሰው፡ ኹሉ፡ እንደሱ፡ እንዲኾን፡ ይፈልጋል። " ወረደ፡ ብለኸ፡ ውርዴን፡ አስተውል።

ቂጥኝ (ቀጣ፡ ቂጥ)፡ የቍስል፡ በሽታ፡ ብዙ፡ ስምና፡ ዐይነት፡ ያለው፡ ያመንዝሮች፡ ቅጣት። (ግጥም): "ምን፡ ይይዛት፡ ብዬ፡ ዝንጀሮን፡ ቂጥኝ፡ አለመጠርጠሬ፡ ጕድ፡ አረገችኝ። "

ቂፉንቂ: ጨፋና አሞራ፡ የቅኔ ቤት ዐማርኛ ነው።

(መድረቅ)

፡ መድረቅ፡ ቃቃ

አለ (ትግ፡ ቀዐነ፡ ደረቀ): (ጥቅጥ) ደረቅ መጠጥ ቀንበር አለ።

ቃ፡ አለ፡ ደረቀ፡ ቃቃ

አደረገ: ቀንበር አደረገ።

፡ ጭረቱ፡ ቀላድ፡ ወይም፡ ገመድ፡ የሚኾን፡ የሬት፡ ዐይነት፡ ዕንጨት። ወንድ፡ ብለኸ፡ ወንዴንዘመደ፡ ብለሽ፡ ዘመድን፡ እይ።

: መድረቅ።

ቃለ(ዐረ)፡ አለ፡ ተናገረ።

ቃለ፡ ሕይወት፡ የሕይወት፡ ቃል፡ ጌታችን፡ ያስተማረው፡ ወንጌል፡ "ቃሌን፡ የጠበቀ፡ ሞትን፡ አይቀምሰውም"፡ የሚል፡ (ዮሐንስ ፮፡ ፷፰። ፰፡ ፶፩) "ቃለ፡ ሕይወት፡ ያሰማዎ"፡ እንዲሉ፡ ተማ ሮች፡ ከትምርት፡ በኋላ።

ቃለ ምልልስ) ፈረስን ለመከልከል፣ ለመንዳትና ለመጋለብ የሚነገር ቃል ነው።

ቃለ፡ ሰላላ) ቃለ ቀን ሴት ድምጥ።

ቃለ፡ አኅስሮ፡ የማዋረድ፡ ቃል፡

ቃለ፡ አራኅርኆ፡ የማራራት፡ ቃል። ሆይን፡ ተመልከት። "ይህ፡ ኹሉ፡ በግእዝ፡ ሰዋሰው፡ ንኡስ፡ አገባብ፡ ይባላል፡ መሠረቱም፡ ኦ፡ ነው። "

ቃለ፡ አክብሮ፡ የማክበር፡ ቃል፡

ቃለ፡ አጋኖ(ሆይ)፡ የማጋነን፡ ቃል፡ ከዚህ፡ ዠምሮ፡ ቃለ፡ አራኅርኆ፡ አለው፡ ድረስ፡ የሆይ፡ ትርጓሜ፡ ነው።

ቃለ አጋኖ: ወይም አራኅርኆ አንክሮና አክብሮም ከዚሁ ይገባሉ። "ሴት ሆይ ማለት ነው።"

ቃለ፡ አፍርሆ፡ የማስፈራት፡ ቃል።

ቃለ፡ እግዚአብሔር፡ የግዜር፡ ቃል፡ የሃይማኖት፡ ትምርት፡ ወይም፡ ርሱ፡ ራሱ፡ ጌታችን።

ቃሉ፡ ያ፡ ቃል፡ የርሱ፡ ቃል።

ቃሉን፡ አከበረ፡ በቃሉ፡ ጠና፡ የተናገረውን፡ አደረገ።

ቃሊም(ሞች)፡ ዐረ፡ ቃሊብ፡ (ኵየት)፡ የመጠጫ፡ ትንባኾና፡ እሳት፡ ማስቀመጫ፡ የት፡ የሚመስል፡ የሚያኸል።

ቃሊም፡ የወንዝ፡ ዳር፡ ደገፍ፡ ዐቃባ።

ቃሊቱ፡ ያች፡ ቃል።

ቃላተኛ(ኞች)፡ ቃልቻ፡ ትንቢት፡ ተናጋሪ፡ ባለቆሌ፡ ካህነ፡ ጣዖት፡ (ዘሌዋውያን ፲፱፡ ፳፮፡ ፳፡ ፮) ቆሌንና፡ ቃልቻን፡ እይ።

ቃላት(ቃሎች)፡ ድምፆች፡ ነገሮች።

ቃሌ፡ ነው፡ ብያለኹ፡ ተናግሪያለኹ።

ቃል(ሎች)፡ ብትን፡ (ዝርው)፡ ቃል፡ ድምፅ፡ ነገር፡ አፍ።

ቃል፡ ለምድር፡ ለሰማይ፡ አለ፡ ፈጽሞ፡ ማለ፡ ማላውን፡ አጸና።

ቃል፡ ለቃል፡ አፍ፡ ላፍ።

ቃል፡ ማሰሪያ፡ የጋብቻ፡ ውል፡ ፈጠም።

ቃል፡ ሰጠ፡ ዕሺ፡ እሰጣለኹ፡ አደርጋለኹ፡ አለ፡ ማለ።

ቃል ትምርት: በቃል የሚማሩት የንባብ፣ የዜማ ጸሎት።

ቃል፡ ዐባይ፡ የዋሾ፡ የቀጣፊ፡ የሐሰተኛ፡ ቃል።

ቃል፡ ኪዳን፡ ተጋባ፡ ተዋዋለ፡ ተማማለ፡ (፬ኛ ነገሥት፡ ፭፡ ፲፪። ኢሳይያስ ፶፯፡ ፰። ሕዝቅኤል ፴፬፡ ፳፭)

ቃል፡ ኪዳን፡ የማይቀር፡ የማይታበል፡ እንደ፡ መሐላ፡ ያለ፡ የውል፡ ውለኛ፡ ቃል። በግእዝ፡ ኪዳነ፡ ቃል፡ ይባላል።

ቃል፡ ወልድ፡ ከቅድስት፡ ሥላሴ፡ ኹለተኛው፡ አካላዊ፡ ቃል፡ (ማሕርቆስ ፪፡ ፰። ዮሐንስ ፩፡፡ ፩። ፩ኛ ዮሐንስ፡ ፭፡ ፯)

ቃል፡ ገቢ፡ ዋና፡ ሚዜ።

ቃል፡ ገባ፡ የማይፈርስ፡ ውል፡ አደረገ፡ ።

ቃልቻ(ቾች)፡ ቃላተኛ፡ ባለዛር፡ ሌሊት፡ ድቤ፡ ሲመታ፡ የሚያድር፡ ቡሓ፡ በግ፡ ወሰራ፡ ዶሮ፡ ነጭ፡ ኰርማ፡ ጥቍር፡ ፍየል፡ ዕረዱ፡ ሠዉ፡ የሚል።

ቃልዎ፡ ይድረሰኝ፡ አለ፡ ተገዘተ፡

ቃሏ፡ የርሷ፡ ቃል።

ቃመ(ቀሐመ)፡ እሸትን፡ ንፍሮን፡ ቈሎን፡ ከውስጥ፡ እጁ፡ ወዳፉ፡ ወረወረ፡ ቻመ፡ ገተመ፡ ቸቸረ፡ ባፉ፡ ምርትን፡ ስጥን፡ ገለባን፡ ዐመድን፡ ገፈረ፡ ተረፈሰ፡ ቸፈረ፡ ሰመሰመ፡ ዐፈሠ።

ቃሚ(ቀሓሚ)፡ የቃመ፡ የሚቅም፡ ቻሚ፡ ሰምሳሚ።

ቃሚያ (ቃሕም)፡ አንድ፡ ጊዜ፡ ተቅሞ፡ የሚታኘክ፡ የሚዋጥ፡ በውስጥ፡ እጅ፡ የተለካ፡ የተመጠነ፡ የዳቦ፡ የንጀራ፡ ፍርፋሪ፡ ድቃቂ። "በግእዝ፡ ፍተ፡ ቃሕም፡ ይባላል። "

ቃም(ቅሒም) መቃም።

ቃም፡ አደረገ፡ ቃመ።

ቃም፡ ዝኒ፡ ከማሁ። "ዐፈር' ቃም፡ እንዲሉ። "

ቃም፡ የቅርብ፡ ወንድ፡ ትእዛዝ፡ አንቀጽ፡ ገትም።

ቃሞቅሞ፡ የመምህራን፡ ዐማርኛ፡ ነው።

ቃሰተ: ኣኣ አለ፡ ቃተተ፣ ቃዘነ፣ ጣረ፣ ተጨነቀ (ከውጋት የተነሣ፣ በቀስት እንደ ተነደፈ ሰው) አቃሰተ: ኣቃተተ፣ ኣቃዘነ፣ ኣጣረ፣ አስጨነቀ። አቃሳች: ያቃሰተ፣ የሚያቃስት፡ አቃታች። ማቃሰት: ማቃተት፣ ማቃዘን፣ ማስጨነቅ። ማቃሰቻ: ማቃተቻ፣ ማቃዘኛ (ብርቱ ሕማም)

ቃሰነ (ቃዘነ): ጐመዠ፣ ቃቃ።

ቃሰነኛ: ባለቃሰን፡ ቃሳኝ ጕምዡ።

ቃሰን: ጕምዠታ።

ቃሳኝ: የቃሰነ፣ የሚቃስን፡ ጐምዢ።

ቃረ (ትግ፡ ቀሐረ): ተኰሰ፣ ፈጀ፣ አቃጠለ። "ሥሩ በግእዝ ቀርሐ ነው። "

ቃረ: ሳለ፣ አፋጩ፣ ፈገፈገ።

ቃረመ (ቀሪም፡ ቀረመ): ካጨዳ በኋላ የወደቀውን የእኸል ዛላ ለቀመ፣ ሰበሰበ።

ቃሩራ: ጠርሙስ።

ቃሪያ በርበሬ: ያልቀላ፣ ያልበሰለ፣ እሳት ያልመሰለ፣ ጨርቋ በርበሬ፡ ሲበሉት አፍን የሚያቃጥል።

ቃሪያ ጥፊ: አይበሉብሽ የውስጥ እጅ ዠርባ። "ቃሪያ ለጥፊ ቅጽል መኾኑን አስተውል፡ በላን እይ። "

ቃሪያ: እንጭጭ፣ ጓሚያ ፍሬ።

ቃሪያ: ያልበሰለ ፍሬ፡ ቃረ።

ቃሪያ: ያልተማረ፣ ያልሠለጠነ ሰው።

ቃራሚ: የቃረመ፣ የሚቃርም፡ ለቃሚ፣ ሰብሳቢ።

ቃራም: ቃር የማይለየው።

ቃሬዛ: የሬሳ፣ የቍስለኛ፣ የበሽተኛ፣ የወደቀ ከብት ማንሻ፣ መሸከሚያ (ኹለት ኣጣና ባለቀላጥም) (ግብረ ሐዋርያት ፭፡ ፲፭) "ወስካን አስተውል። "

ቃሬዛ: የድግስ ስም፡ ስለ ሙታን ፍታትና ቍርባን ምክንያት ካህናት በደጀ ሰላም የሚመገቡት ምግብ፣ የሚጠጡት መጠጥ።

ቃር (ቀሐር): የልብ ትኵሳት (በምግብ ምክንያት የሚመጣ)

ቃር አያውቅሽ: ታሞ የማያውቅ ሰው፡ ጤናማ።

ቃርሚያ: ቃርሞሽ፡ ዝኒ ከማሁ (ዘሌዋውያን ፲፱፡ ፲)

ቃሮዳ: በበጌምድር ከደንቀዝ በታች ከይፋግ በላይ ያለ አገር።

ቃቂ: የቃቃ፣ የሚቃቃ፡ ጐምዢ።

ቃቂል: ቃጭል (ግእዝ)

ቃቃ (ትግ፡ ቃዕቅዐ፡ ግእዝ፡ ቃሕቅሐ፡ ቈቍዐ፡ ሰቈቈ): ጐመዠ፣ ሠየ፡ ተቃረ፣ ፈለገ። "ከብቶቹ ቃቅተዋል" እንዲል ባላገር።

ቃቃታ: ጕምዠታ፣ ሥየታ።

ቃቃታ: ፈጥኖ ኣለመናገር፣ አፈ ጸያፍነት።

ቃቃን: የአለት መንደያ (ንጥር ብረት፣ ካክራ) "በትረ ቃቃን" እንዲሉ። "ቀቃን ተመልከት። "

ቃቄር (ሮች): ቍራ (ግእዝ)

ቃቄዳ: ግትቻ፣ ዕላቂ፣ ሰፌድ።

ቃበበ (ትግ፡ ቀበበ)፡ አፌዘ፡ አላገጠ።

ቃበበ (ዕብ፡ ቃባብ)፡ ናቀ፡ ሰደበ፡ ረገመ።

ቃብትያ፡ እንደ፡ ባልያ፡ ያለ፡ ተራራ።

ቃተ) (ቀአተ): አቃተ፣ ተሳነ፣ ቸገረ፣ አልቻልም አለ። "ቀአተ ጥንታዊ ዐማርኛ ነው።" አቃች: ያቃተ፣ የሚያቅት፣ ተሳኝ። ማቃት: መሳን፣ መቸገር።

ቃተተ: ዞረ፣ ለፋ፣ ደከመ፡ የጭንቅ ትንፋሽ ተነፈሰ።

ቃተኛ: በያይነቱ ወጥ ያለበት ያነባበሮ ዐይነት፣ ዐምዛ።

ቃታ (ቃቃ): የጠመንዣ፣ የሽጕጥ፣ የመድፍ ጥይት ማስነሻ፣ መተኰሻ ብረት።

ቃታ (ቃተተ): የማያቋርጥ ትንፋሽ። "ሕፃኑ እጅግ ስለ ሮጠ ቃታ ይዞታል። "

ቃታች: የቃተተ፣ የሚቃትት፡ ደካሚ።

ቃት (ቃቃ): ያለ የስንዴ እንጀራ።

ቃነጠ)አሽቃነጠ፡ ዘፈነ፡ አረገደ፡ እስክስታ፡ ወረደ።

ቃና(ቃነየ)፡ የዜማ፡ የመጠጥ፡ ጣዕም። "በግእዝ፡ ግን፡ ዜማ፡ ማለት፡ ነው። " "ንስርንና፡ ምስርን፡ እይ። "

ቃና፡ የቀበሌ፡ ስም፡ በቡልጋ፡ ውስጥ፡ ያለ፡ ስፍራ፡ ጉባኤ፡ ቃና፡ የተዠመረበት።

ቃና፡ ጌታችን፡ ውሃን፡ ወይን፡ ጠጅ፡ ያደረገበት፡ አገር፡ በገሊላ፡ አውራጃ፡ ያለ።

ቃናው፡ ተለወጠ፡ ጣዕሙ፡ ሌላ፡ ኾነ።

ቃንዛ፡ መንዘር፡ የደም፡ ሥር፡ በሽታ።

ቃንዲላ፡ ጅራፍ።

ቃንጤ፡ ፈሊጥ፡ ዐመል። "እከሌ፡ ቃንጤው፡ አይታወቅም፡ እንዲሉ። "

ቃኘ(ቃነየ)፡ ቀነቀነ፡ ዜማ፡ ዠመረ፡ አስቀድሞ፡ አዜመ።

ቃኘ(ትግ፡ ቀነየ)፡ ሰነበተ፡ ቈየ።

ቃኘ፡ ዐሠሠ፡ ጐበኘ፡ ሰለለ።

ቃኘ፡ የበገናን፡ የክራርን፡ ዥማት፡ (ኦውታር)፡ አጠበቀ፡ አላላ፡ አቃና፡ አሰማማ።

ቃኘ፡ ፈቀደ፡ ማተረ፡ ከብትን።

ቃኘው፡ የልዑል፡ ራስ፡ መኰንን፡ ፈረስ፡ ስም።

ቃኚ(ዎች)፡ የቃኘ፡ የሚቃኝ፡ ቀንቃኝ፡ ጐብኚ፡ ሰንባች፡ ዐሣሽ።

ቃውት፡ የዛፍ፡ ስም፡ ርዝማኔና፡ ቀጥታ፡ ያለው፡ ዕንጨት፡ ለደመራ፡ ይፈለጋል።

ቃዘነ፡ ተንከራተተ፡ ባዘነ። ቃበዘን፡ እይ፡ ከዚህ፡ ጋራ፡ አንድ፡ ነው።

ቃዛኝ፡ የቃዘነ፡ የሚቃዝን፡ ተንከራታች፡ ባዛኝ።

ቃዠ (ጋዠ)፡ መጥፎ፡ ሕልም፡ አይቶ፡ በንቅልፍ፡ ልቡ፡ ጮኸ፡ አንቋረረ፡ አላዘነ።

ቃየል፡ የሰው፡ ስም፡ የአዳም፡ መዠመሪያ፡ ልጅ።

ቃዳ፡ ዝም፡ እመም፡ ተለላ፡ ወረራ።

ቃጠለ)፡ ተቃጠለ፡ ነደደ፡ ዐረረ፡ ገመነ፡ ተኰማተረ፡ ተጋጠመ።

ቃጠሎ፡ የእሳት፡ አደጋ።

ቃጠረ፡ ቀጠረ፡ ቀጠሮ፡ ሰጠ፡

ቃጠነ)፡ አቃጠነ፡ ወዲያና፡ ወዲህ፡ አለ፡ ነገር፡ አሳካ፡ አዋሸከ።

ቃጣ (ቀጣ)፡ እጁን፡ አነሣ፡ ዘረጋ፡ ደከረ፡ ደቀነ፡ አቀረበ፡ ለመምታት፡ ለመያዝ፡ ለማግኘት። (ተረት): "በሰው፡ ቂጣ፡ እጇን፡ ትቃጣ(ትዘረጋ) "

ቃጣሪ፡ የቃጠረ፡ የሚቃጥር፡ ዳኛ፡

ቃጤ፡ ታናሽ፡ መስፈሪያ፡ ቍልቢጥ።

ቃጥላ፡ በመካከሉ፡ ዝንጀሮና፡ ጦጣ፡ የሚኼዱበት፡ ከአረኸ፡ በላይ፡ የቆመ፡ ገደል፡ ምስጢሩ፡ እንደ፡ ተቀጠለ፡ መኾንና፡ ሣር፡ አለማብቀል፡ ነው።

ቃጥላ፡ ያኽላል፡ እጅግ፡ ረዥም፡ ነው።

ቃጫ፡ ቦራ፡ የፈረስ፡ መልክ፡ ብጫነት፡ ያለው።

ቃጭ፡ ሰይፍ፡ የመታው፡ የቈረጠው፡ ገላ።

ቃጭል (ሎች፡ ቃቂል)፡ በሕፃን፡ በጥጃ፡ በበቅሎ፡ በተዋጊ፡ በግና፡ በተናካሽ፡ ውሻ፡ ዐንገት፡ የሚንጠለጠል፡ ድምፅ፡ ሰዉ፡ ጌጥ፡ ለቅዳሴ፥ ለሰው፡ መጥሪያ፡ የሚኾን፡ ታናሽ፡ መርዋ፡ (ዘጸአት ፳፰፴፫፴፬) (ተረት): "በደንባሪ፡ በቅሎ፡ ቃጭል፡ ተጨምሮ። " ብልብላን፡ እይ።

ቃጭማ፡ የዛፍ፡ ስም።

ቃፍር: ከጥቦት የሚበልጥ በግ።

ቄለ፡ ጀለ፡ ተሞኘ፡ የማይረባ፡ ቃል፡ ተናገረ።

ቄሎ፡ ከቅል፡ የተበጀ፡ መስፈሪያ።

ቄሰ ገበዝ: ቅስናን ከግብዝና ያሰተባበረ፡ የቤተ ክርስቲያን ንዋየ ቅድሳትና ገንዘብ ጠባቂ፣ ሹም።

ቄሳር: የሮማውያን ንጉሥ ስም፡ 'ሆድ ቀዳጅ' ማለት ነው (ሉቃስ ፪፡ ፩፡ ፳፡ ፳፭)

ቄስ (ቀሲስ): ካህን፣ ጳጳስ (እጁን በራሱ ላይ ጭኖ መንፈሳዊ ሥልጣን የሰጠው) የቤተ መቅደስ አገልጋይ፡ ባራኪ፣ ቀዳሽ፣ ናዛዥ፣ የነፍስ አባት፡ ሲበዛ 'ቄሶች' ያሠኛል። (ተረት) "እራት የሌለው ቄስ እንደ ልቡ አይቀድስ" "ቄስ ያማርኛ፡ ቀሲስ የግእዝ ነው። "

ቄስ በደጅ: ከቤት በስተውጭ የሚገኝ ቅጠል (መድኀኒትነት ያለው)

ቄስ አሞራ: ቍራ፣ ጥንብ ባራኪ፡ ራሰ መላጣ፣ ጥንበ በላ።

ቄስ ዐጤ (ቄሰ ሐፄ): የንጉሥ ነፍስ አባት፣ ዘውድ ዐጣኝ፣ ማእድ ባራኪ።

ቄስ ዐጤ ዘወልድ: በዘፋኝ ዳዊት ባጤ በካፋ ዘመን የነበሩ ቄስ፡ ፍጹም ሊቅ፣ ቅባቶችን ከሞት ያዳኑ።

ቄስ: በቁሙ ቀሰሰ።

ቄራ (ቀረየ): በግና ፍየል፣ በሬ (የርድ ከብት ኹሉ) እየገባ የሚታረድበት ስፍራ፡ ሉካንዳ፣ ሥጉያ።

ቄራ: ማማ (የሰብል መጠበቂያ)፡ ረዥም ቈጥ ያዝመራ ዐልጋ። "ምስጢሩ ሰብሉ ከተነሣ በኋላ መንደድ መቃጠልን ያሳያል። "

ቄርሎስ: የሰው ስም፡ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት። "በጽርእ ፈለገ እግዚእ ማለት ነው ይላሉ። "

ቄብ (ዕብ፡ ንቄባ፡ ቀዳዳ)፡ ያልተጠቃች፡ እንስት፡ በግ፡ ፍየል፡ አህያ፡ ዶሮ።

ቄብ፡ ሻለቃ፡ ዝቅተኛ፡ ጦር፡ አዛዥ።

ቄቦች፡ ያልተጠቁ፡ እንስቶች፡ እንስሶች።

ቄንጠኛ(ኞች)፡ ነቃፊ፡ አላጋጭ፡ ባለቄንጥ።

ቄንጠኛ፡ ጌጠኛ፡ ተሽኰንታሪ፡ ተሽሞንኝ፡ አለባበስ፡ አሳማሪ።

ቄንጥ፡ ልዩ፡ ኹኔታ፡ ጌጥ።

ቄንጥ፡ ጡር፡ ነቀፋ፡ ነውር፡ መስቃ።

ቄንጦ፡ የንጨት፡ ስም፣ ትንንሽ፡ ቈላፋ፡ እሾኸ፡ ያለው፡ ዛፍ።

ቄደረ (ዐረ፡ ቀደረ፡ ቻለ)፡ ኰራ፡ ተበውቀት፡ በችሎታ።

ቄደር (ቄድር)፡ የመጽሐፍ፡ ስም፡ ክርስቲያን፡ ሃይማኖቱን፡ ክዶ፡ ማተቡን፡ በጥሶ፡ ቂጥኝ፡ አውጥቶ፡ ቢረክስ፡ ንስሓ፡ ከገባ፡ በኋላ፡ ቄሶች፡ ይህን፡ መጽሐፍ፡ እየደገሙ፡ ያጠምቁታል።

ቄጆ (ቀዳ)፡ ማለቢያ፡ ቋጮጮ፡ አኮሌ፡ ግሬራ።

ቄጥ፡ የበሬ፡ ዕከክ።

(ትግ፡ ቈጸየ)፡ ጸጸተ፡ አተከዘ። ምሳሌ: "ያለፈው፡ አይቍጭኸ፡ ለሚመጣው፡ ተጠንቀቅ። " (አዝማሪ): "ተይ፡ መጭ፡ በቅሎ፡ ተይ፡ መጭ፡ ነገር፡ ካልሰሙት፡ አይቈጭ "

፡ የቀ፡ ዲቃላ፡ በመኾኑ፡ ስለ፡ ቀለበቱ፡ ቈ፲፻፡ ይባላል።

ቈለ፡ ተገለጠ፡ ጠራ፡ በራ፡ ጐላ።

ቈለለ(ጐለለ)፡ ደረደረ፡ ደረበ፡ አነባበረ፡ ከመረ፡ ጐቸ፡ አበዛ። "ዋጋ፡ ቈለለ"፡ እንዲሉ።

ቈለል፡ ቈለል፡ አደረገ፡ ከብለል፡ ከብለል፡ አደረገ፡ አንገዋለለ፡ ዐይኑን።

ቈለመመ ቀለሰ፡ ዘለስ፡ ዘቀዘቀ፡ አጐበጠ፡ ጠመዘዘ። ቸለሰን፡ እይ።

ቈለመምቈልማማ፡ የተቀለሰ፡ የተዘለሰ፡ ቀላሳ፡ ጐባጣ፡ ጠምዛዛ፡ ቀንድ።

ቈለመጠ) አቈላመጠ፣ ውዳሴ ከንቱ ሰጠ፣ ፊት ለፊት አመሰገነ፣ ተለማመጠ (ኢዮብ ፲፱፡ ፲፯። ፴፪፡ ፳፩። ምሳሌ ፲፱፡ )

ቈለቈለ)(ቈልቈለ)አቈለቈለ (አቈልቈለ)፡ ዘቀዘቀ፡ ቍልቍለት፡ አደረገ፡ ቍልቍል፡ ነዳ፡ ወሰደ፡ አወረደ፡ አጐነበሰ፡ (ዘዳግም ፳፮፡ ፲፭)

ቈለቈል(ሎች)፡ ባረኸ፡ በቈላ፡ በበረሓ፡ ስፍራ፡ የሚበቅል፡ የቍልቋል፡ ወገን፡ ዕንጨት። "ደሙ፡ መርዝነት፡ ስላለው፡ ዐይጥ፡ ከሰሶ፡ ጋራ፡ በበላው፡ ጊዜ፡ ያብዳል፡ ርስ፡ በርሱ፡ እየተናከሰ፡ ያልቃል። "

ቈለቈልዳ ዝኒ፡ ከማሁ፡ ዳ፡ ከዕዳ፡ መጥቶ፡ ተጨምሯል።

ቈለበጠ፡ አነሰ። ቈለጠበን፡ እይ።

ቈለኛ(ኞች)፡ በቈላ፡ የተወለደ፡ በቈላ፡ የሚኖር፡ ሰው፡ እንስሳ።

ቈለዘ፡ ቈጠቈጠ፡ እሾኸ፡ ቈረጠ፡ (ግእዝ)

ቈለዘመ)፡ ተቈላዘመ፡ ተጐናዘለ፡ ተዘናፈለ፡ ተጠላለፈ፡ የሣር፡ የጠጕር።

ቈለጠ(ፈተወ)፡ ቋመጠ፡ ተወነገ፡ ተወሰጠ፡ ተወዘወዘ።

ቈለጠበ፡ ብልጥ፡ ኾነ፡ በሰው፡ ነገር፡ ገባ።

ቈለጠብኸ፡ ብልጠት፡ አበዛኸ።

ቈለጣም፡ ቈለጠ፡ ትልቅ፡ ሰው።

ቈለጥ(ጦች)፡ ቍላ፡ የወንድ፡ (ተባት)፡ ብልት፡ ፍሬ።

ቈለጭ(ጕራጌ)፡ እንቍራሪት፡ ጕርጥ።

ቈለጭ፡ ዐይናማ፡ ዐይነ፡ ጥሩ፡ ዐይነ፡ ትልልቅ።

ቈለጭ፡ የሰው፡ ስም።

ቈለጭ፡ የዓሣ፡ ስም።

ቈለጰለጠሰ) (ቀለጰ ለጠሰ) አንቈላጰላጠሰ፣ የቧልት፣ የጨዋታ ግስ። "ራሴን በራሴ ካላንቈላጰላጠስኹት ማን ያንቈላጰላጥስልኛል" እንዲል የቅኔ ተማሪ። "ትርጓሜውም ኰፈሰ፣ አከበረ ማለት ነው።" "ዳግመኛም በግእዛዊው ቀለጰና በለጠሰ ዘይቤ ሲፈቱት መብላትንና መተኛትን ያሳያል።" "ቀለበን፡ ተመልከት።"

ቈለፈ(ቈሊፍ፡ ቈለፈ)፡ ውስጥ፡ ለውስጥ፡ ዘጋ፡ ቀረቀረ፡ ሸጐረ።

ቈለፈ፡ ሸፈነ፡ ወሸለ።

ቈለፈ፡ አጐበጠ፡ ቀለሰ፡ ዐጠፈ።

ቈለፈ፡ ያዘ፡ ዐነቀ፡ አለቅ፡ አለ።

ቈለፈታም፡ ልንቡጣም፣ቦርጫም፡ ዘርጣጣ። "ቀፈትን፡ እይ። "

ቈለፈት፡ ሸለፈት፡ ልንቡጥ፡ ሸንኰፍ፡ ሽፍን፡ ሽፍናት፡ ወሸላ። "በግእዝ፡ ቍልፈት፡ ይባላል። "

ቈለፈት፡ ቦርጭ፡ ትልቅ፡ ሆድ።

ቈላ(ቀለወ)፡ በሠማ፡ ምጣድ፡ ጥሬ፡ እኸልን፡ አንጣጣ፡ አበሰለ፡ በጐባጣ፡ ዕንጨት፡ ዐመሰ፡ አማሰለ፡ ወጥን፡ ዐመፀኛን፡ ጠበሰ፡ (ኤርምያስ ፳፱፡ ፳፪)

ቈላ(አንሳሕስሐ)፡ አንቀሳቀሰ፡ ወዘወዘ፡ ነሰነሰ። "ውሻ፡ ጌታውን፡ ባየ፡ ጊዜ፡ ዥራቱን፡ ይቈላል። "

ቈላ፡ ሰውን፡ በጅራፍ፡ ገረፈ፡ በጥይት፡ መታ።

ቈላ ቍስል): የቈላ ቍስል፣ ጐርምጥ፣ ጫዌ።

ቈላ፡ አቃረ፡ አቃጠለ፡ ልብን።

ቈላ፡ ከደጋ፡ በታች፡ ያለ፡ አገር፡ ወይም፡ በረሓ፡ ምድረ፡ በዳ፡ ፀሓይ፡ እንደ፡ እሳት፡ የሚፋጅበት፡ የሚያቃጥልበት፡ እንጭርጭር፡ ስፍራ፡ የገሃነመ፡ እሳት፡ ምሳሌ።

ቈላ፡ ደጋ፡ ረገጠ፡ አንደዬ፡ ወደ፡ ታች፡ አንደዬ፡ ወደ፡ ላይ፡ አለ፡ አመነ፡ ካደ።

ቈላ: ቈለኛ

ቈላይ(ዮች)፡ የቈለለ፡ የሚቈልል፡ ከማሪ።

ቈላፊ(ዎች)፡ የቈለፈ፡ የሚቈልፍ፡ ዘጊ።

ቈላፋ፡ ጫፈ፡ ቀላሳ፡ ዕንጨት፡ ከዘራ፡ ብረት። ወንቃፍን፡ እይ።

ቈላፍ፡ ወሸላ፡ ሽፍን፡ ያልተገረዘ፡ አረመኔ፡ (ግእዝ) "በሱማልኛም፡ ቈለፍ፡ ይባላል። "

ቈላፍነት ወሸላነት፡ (ኤርምያስ ፬፡ ፬። ሮሜ ፬፡ ፲፡ ፲፪)

ቈልማ፡ ቀንደ፡ ዘላሳ፣ ቈለመመ።

ቈልማ፡ ቀንዱ፡ ዘላሳ፡ ዘቅዛቃ፡ ቀላሳ፡ የኾነ፡ በሬ። ጐዳንና፡ ጕመላን፡ አስተውል።

ቈልማሚ፡ የቈለመመ፡ የሚቈለምም፡ ቀላሽ፡ አጕባጭ፡ ጠምዛዥ።

ቈልማሜ፡ ዳቦ፡ ቈሎ፡ የቈልማማ ዐይነት፡ ወገን።

ቈልጣባ፡ ጮሌ፡ ጥልቅ፡ ብዬ።

ቈሎ(ቅልው)፡ የተቈላ፡ በሠማ = ምጣድ፡ ላይ፡ የበሰለ፡ (ቅጽል) ዳቦን፡ እይ። (የወፍ፡ ቈሎ)፡ ወፍ፡ የሚመገበው፡ የምድር፡ ፍሬ። (የጦም፡ ቈሎ)፡ በፍልሰታ፡ ለካህናት፡ የሚሰጥ፡ ቈሎ፡ ገባር፡ በሑዳዴ፡ ለሹም፡ የሚሰጠው፡ ዱቄት፡ ዕንጨት፡ ጭምር፡ (ስም)

ቈመለለ ቀመቀመ።

ቈመለለ፡ ዘለሰ፣ ቈለመመ።

ቈመቈመ)(ኰመኰመ)አሽቈመቈመ፡ ጠራ፡ ኑ፡ ኑ፡ አለ፡ አውራ፡ ዶሮ፡ ጫጩቶችን ' ምግብ፡ ሊሰጣቸው።

ቈመደ(ጐመደ)፡ ክርን፡ አዋሰበ፡ ድርና፡ ማግን፡ መጣፊያ፡ አደረገ፡ የልብስን፡ ቀዳዳ፡ ደረተ፡ ደበደበ፡ ደፈነ። "ቈመደ፡ በባላገር፡ አይ ነገርም። "

ቈመጠ(ቀመጠ)፡ የእጅንና፡ የእግርን፡ ጣት፡ አቈሰለ፡ ቈረጠ፡ ጐመደ፡ በጠሰ፡ አሳጠረ።

ቈመጠ፡ መታ፡ ጠዘለ፡ ደበደበ፡ ነረተ።

ቈመጥ፡ ባ፩፡ ወይም፡ ባ፬፡ ወገን፡ ስለት፡ ያላት፡ በሎታ፡ በትከሻ፡ የምትንጠለጠል፡ ዐጪር፡ ዱላ፡ ራስ፡ መጠበቂያ።

ቈመጥማጣቍምጥምጥ፡ የተቈማመጠ፡ ጕምድምድ።

ቈሚጥ፡ ድንክ፡ ዐጪር፡ ሰው፡

ቈማመጠ፡ ቈራረጠ፡ ጐማመደ።

ቈማጅ፡ የቈመደ፡ የሚቈምድ፡ አዋሳቢ፡ ደራች።

ቈማጣ(ጦች)፡ የተቈመጠ፡ ጣት፡ አልባ፡ ዱሽ፡ ሽንድፍድፍ፡ ገላውን፡ ቍስል፡ ድል፡ ያደረገው፡ አባ፡ ጐንዳ።

ቈማጣ፡ ቈመጥማጣ፡ የቈመጥማጣ፡ ቈማጣ፡ ድርብ፡ ስድብ።

ቈማጣነት፡ ቈማጣ፡ መኾን።

ቈማጤ፡ የተክል፡ ስም፡ ቈማጣ፡ የሚመስል፡ ጣፋጭ፡ ፍሬ፡ ሻካራ፡ ፍርክርክ።

ቈማጭ፡ የቈመጠ፡ የሚቈምጥ፡ ቈራጭ፡ ጐማጅ።

ቈሰለ (ቈሲል፡ ቈስለ): ተነካ፣ ተላጠ፣ ተገጠበ፣ ደማ።

ቈሰለ: በጦር ተወጋ፣ በቀስት ተነደፈ፣ በሰይፍ፣ በጥይት ተመታ፡ (ልቡ ቈሰለ)፡ ዐዘነ፣ ተናደደ።

ቈሰሰ): ቈረሰሰ። (ጐሰሰ): ተንቋሰሰ፣ ተንቈረሰሰ፣ ተጐተተ። መንቋሰስ: መንቈርሰስ፣ መጐተት። መንቋሰሻ: መንገድ፣ እግር። አንቋሰሰ: አንቈረሰሰ፣ ጐተተ። ማንቋሰስ: ማንቈርሰስ፣ መጐተት። ማንቋሰሻ: ማንቈርሰሻ።

ቈሰቈሰ (ኰሰኰሰ): ጠቀሰ፣ ገፋ፣ አገባ፣ ጨመረ (ማገዶን ወደ እሳት)

ቈሰቈሰ: ነካ፣ አወከ። "ጐተጐተን እይ። "

ቈሳሰለ: በብዙ ወገን ቈሰለ።

ቈሳቍስ: የቤት ዕቃ፣ ሰባራ ሥንጥር። "ቈሳቊስ በግእዝ ዕቆች ማለት ነው፡ አንዱ ቈሰቈስ ይባላል። "

ቈሳቈሰ: ፋፋ፣ ጨማመረ።

ቈስቋሽ (ሾች): የቈሰቈሰ፣ የሚቈሰቍስ፡ ጠቃሽ፣ ገፊ፣ ጨማሪ።

ቈስቋሽነት: ቈስቋሽ መኾን።

ቈስጠንጢኖስ: በ፪፻፺፱ . በግሪክ አገር የነገሠ መዠመሪያ የክርስቲያን ንጉሥ።

ቈሥፌ: መልካም ሽታ ያለው ዛፍ።

ቈረ: ፈጽሞ ደኸየ፡ የለት ጕርሥ፣ ያመት ልብስ ዐጣ፡ ነጣ፣ መነጠ።

ቈረመ: በቀላል መታ፣ ኰረኰመ (ራስን) "ቈራን ለኰፈን አስተውል። "

ቈረመመ: አሾለቀ፣ አሾጠጠ።

ቈረመደ): ተቈራመደ፣ ተጨበጠ፣ ተኰራመተ (ከችግር፣ ከብርድ የተነሣ)

ቈረመድ: ቈርማዳ፡ የተቈራመደ፡ ጨባጣ፣ ኰርማታ።

ቈረሰ: ፈተተ፣ ገመሰ፣ ገመደለ፣ ቀረደደ፣ ከፈለ፣ ጐረመደ (ማቴዎስ ፲፬፡ ፲፱፡ ሉቃስ ፱፡ ፲፮)

ቈረሰሰ) (ቈሰሰ): አንቈረሰሰ፣ ዝኒ ከማሁ፣ እንቀረደደ።

ቈረሰንና ሸረፈን እይ።

ቈረሳ: ፍተታ።

ቈረረ (ቈለለ): ጫነ፣ ደረበ፣ አነባበረ። "ቈረነን አስተውል። "

ቈረረ (ቈሪር፡ ቈረ): በረደ፣ ቀዘቀዘ።

ቈረር: ድርብ (የደንጊያ ምልክት) "አንድ ቊራ በታየ ጊዜ መንገደኞች ኹለት ደንጊያ ያነባብራሉ። "

ቈረቈሰ: አጫረ (ጠብን፣ ጦርነትን) ዠመረ፣ ፈተነ።

ቈረቈሰ: የገና ጨዋታን ባረከ፡ ዕሩርን መታ፣ በትርን ገዉ።

ቈረቈረ (ዕብ፡ ቃር): ማሰ፣ ቈፈረ፣ ሰረሰረ፣ በሳ፣ ነደለ፣ ሸነቈረ፡ ከተማን መሠረተ፣ ዠመረ። "ዘሩ ቈረረ ነው። "

ቈረቈረ: መታ (ጠረጴዛን፣ ገበታን)

ቈረቈረ: አቈሰለ (ራስን)

ቈረቈረ: ወጋ፣ ጐረበጠ፣ ነካ፣ አሳመመ (ገላን፣ ሆድን፣ ዐይንን)

ቈረቈረ: ደፈነ፣ መረገ፣ ጠቀጠቀ (የሸክላን ቀዳዳ) በዶሮ ማርና በብረት ዐር፣ በጨርቅ፣ በሾኸ። "ደበደበን እይ። "

ቈረቈራም: ቈረቈር ያለበት፣ የበዛበት ልጅ።

ቈረቈር: የራስ ቍስል (ከመጥፎ ምላጭ፣ ከፀሓይ ሙቀት የተነሣ የሚመጣ) "(ተረት) በቡሓ ላይ ቈረቈር። "

ቈረቈንዳ: ፍሬው የወጣ ያገዳ ራስ።

ቈረቈዘ: ጐኑ ጠበበ፡ ቁመቱ ዐጠረ።

ቈረበ (ቀርበ): ቀደሰ፣ ሠለሰ፡ ቍርባን ሥጋ አምላክ ተቀበለ። "ከቈረበች ባሰች፣ ከመነኮሰች አፈረሰች" እንዲሉ።

ቈረበ ብለኸ ቍርባንን እይ

ቈረበ: ጐረበ፣ ተቋጠረ፣ ውሃ ያዘ፣ ዐዘለ፣ ዐተረ።

ቈረበበ: ቀረደደ፡ ቀረበብ፣ ቀርባባ፡ የተንቀረበበ፣ የሚንቀረበብ፡ ቀረደድ፣ ቀርዳዳ፡ ከረፈፍ፣ ከርፋፋ፡ ዦሮ ትልቅ ሰው።

ቈረበበ: አንቈረበበ፡ አቈረበጨ፣ አጐረበ። "በተገብሮነትም ይፈታል። "

ቈረበብ: ቈርባባ፡ የተንቈረበበ፣ የሚንቈረበብ፡ ቍርብጭ።

ቈረበተ: ቈርበት ኣለበሰ፣ ጐለበ፣ ለጐመ።

ቈረባ (ትግ፡ ቈርብዐ): ደረቀ።

ቈረነ: ዐወደ፣ ቦጨቀ።

ቈረነ: ዶንጊያ ተከለ፡ ምልክት አደረገ (ሕዝቅኤል ፴፱፡ ፲፭) ትርጓሜ። "ቈረረን እይ፡ ነና፣ ይወራረሳሉ። "

ቈረን: የጤፍ አገዳ ቅሬታ፡ እንደ ቀርን (ቀንድ) ሽቅብ የቆመ፣ ያሾተለ። "የጤፍ ቈረን" እንዲሉ።

ቈረኘ (ትግ፡ ቁረነ): አሰረ፣ ጠመደ። "ገረኘን አስተውል። "

ቈረኘተ (ቈረኘ): ነፋ፣ ጐሰረ።

ቈረዘ: ሸረበ፡ ቍርዝ አወጣ፡ ሸፈነ።

ቈረዘዘ): ኣንቈረዘዘ፣ አንጠለጠለ (ተንጠለጠለ)

ቈረጠ (ቀረፀ): ጐረደ፣ ጐመደ፣ መደመደ፣ ሸለተ፣ በጠሰ (እንዳገዳ ከፍ፣ እንደ ባቄላ ከሥር)፡ አጠፋ (ኤርምያስ ፪፡ ፳) "አፈፈን፣ ዋጋን፣ ካሳን፣ መቅንን፣ ሤራን፣ ቀጻን፣ ተስፋን እይ። "

ቈረጠ: ሐሳቡን አንድ ወገን አደረገ፡ ጨረሰ፣ ፈጸመ። (ግጥም): "ያውና እዚያ ማዶ ፍሪዳ ተጥሏል፡ ቢላዋው ደንዞ ልብ አልቈርጥ ብሏል። " "(ባሕርን በዋና ቈረጠ):** ተሻገረ። "

ቈረጠ: ሆድን ዐመመ።

ቈረጠ: ለየ፣ ወሰነ (ቀንን)

ቈረጠ: ቀነሰ፣ አጐደለ።

ቈረጠ: ፍርድን ሻረ፣ ደመሰሰ፣ ለወጠ፡ ወይም ኣጸና፣ አጸደቀ (ጥፋተኛን በመቅጣት፣ በመግደል)

ቈረጠመ: ገላን፣ ዐጥንትን ዐመመ።

ቈረጠመ: ጐረደመ፣ በጥርስ ሰበረ፣ ከረተሰ፣ ዐኘከ፣ በላ (ዕንጨትን፣ ጥሬን፣ ቈሎን፣ ምላስን) (ራዕይ ፲፮፡ ፲) "ቈረጠመ እንደ መከርተፍ፣ ዐንከ እንደ መሰለቅ ነው። "

ቈረጠጠ): አንቈራጠጠ፣ አላሳርፍ አለ፣ አንጐራደደ።

ቈረጠጥ: ቈርጣጣ፣ የተንቈራጠጠ፡ ጐረደድ፡ ጐርዳዳ።

ቈረጣ: የመቍረጥ ሥራ፡ "አገዳ ቈረጣ፣ ዕንጨት ቈረጣ፣ ጠጕር ቈረጣ፣ ወይን ቈረጣ" እንዲሉ (ሚክያስ ፯፡ ፩)

ቈረጣጠመ: ዐኛኘከ፣ በላላ፡ ዐማመመ።

ቈረጪ: ዐጠረ፣ ዐጢር ኾነ።

ቈረፀ (ቈሪፅ፡ ቈረፀ): ቈረጠ፣ ሸለተ፣ አሳጠረ።

ቈረፈ: ቈፈረ፣ ማሰ፡ ከፈለ፣ ተነተነ።

ቈረፈ: ጨረፈ፣ ለኰፈ፡ መለሰ፣ ቀለበሰ።

ቈረፈደ: ደረቀ፣ ሻከረ (ልስላሴ ዐጣ) (ዳባው፣ ቍርበቱ)

ቈረፈድ: ቈርፋዳ፡ የቈረፈደ፣ የሚቈረፍድ፡ ደረቅ፣ ሻካራ ቈዳ።

ቈረፈፈ): ቈረቈዘ፣ ተንቀረፈፈ፣ ረዘመ፣ ተንከረፈፈ፣ ተንቀረበበ፣ ግመልኛ ኼደ።

ቈረፈፈ): አንቈረፈፈ፣ ቈፈነነ፣ የእጅን ጣት ቈለፈ፣ ወበጠ።

ቈሪ (ቈራሒ፡ ቀራዒ): የቈራ፣ የሚቈራ፡ በጪ፣ ተኳሽ፣ ቀቢ፣ ነቃሽ፣ ቈራሚ።

ቈሪት: የእንስት በግ ስም።

ቈሪፍ: ዝኒ ከማሁ፡ ዦሮ ትልቅ።

ቈራ (ቀርሐ): ቦቀረ፣ ላጩ፣ ነጩ።

ቈራ (ቈርሐ፡ ቀርዐ፡ ኰርዐ): በጣ፣ ፈቃ፣ ጋረጠ፡ ተኰሰ፣ ነቀሰ፡ ቀባ፣ ምልክት አደረገ፡ መታ፣ ቈረመ። "ስም ጠርቶ"

ቈራ: ራስ ቈርቶ እንዲሉ። "ቈርሐ ትግሪኛ ነው። "

ቈራ: ቍር፥ቈረረ።

ቈራሚ: የቈረመ፣ የሚቈርም፡ መቺ፣ ኰርኳሚ።

ቈራሳ: ገማሳ።

ቈራረሰ: ፈታተተ፣ ገማመሰ፣ ከፋፈለ።

ቈራረጠ: ጐራረደ፣ ጐማመደ (፪ኛ ዜና መዋዕል ፴፬፡ ፯)

ቈራሪ: የቈረረ፣ የሚቈርር፡ ደራቢ፣ አነባባሪ።

ቈራሽ (ሾች): የቈረሰ፣ የሚቈርስ፡ ፈታች።

ቈራቢ (ዎች): የቈረበ፣ የሚቈርብ፡ ቀዳሽ፣ ሠላሽ፡ በቍርባን የተወሰነ ምእመን።

ቈራብት: ቈርበቶች፣ ማሶች። (ግእዛዊ ተረት): "ኣነ አእምር ግብሮሙ ለቈራብት። " "የቈራብትን ሥራ እኔ ዐውቃለኹ አለ ዥብ። " "ቈራብት ቈራቢዎች ተብሎ ቢተረጐም ግን ሰሞነኞች ለሳታት ለተልእኮ ሌሊት መኼዳቸውን ያስረዳል። "

ቈራጣ (ጦች): አካለ ጐደሎ። "እግረ ቈራጣ፣ ዥራተ ቈራጣ" እንዲሉ።

ቈራጣ: የደሴት ስም (በጣና ውስጥ ያለ ደሴታዊ ሀገር)፡ ባጠገቡ ካለው የብስ ባሕር የቈረጠው፣ የለየው ማለት ነው።

ቈራጤ: የቈራጣ፣ ቈራጣዊ፡ የኔ ቈራጣ፡ ሥሥ ልብስ፣ በቀላል የሚቀደድ። (ላራ)

ቈራጥ (ጦች): ሐሳቡን ባንድ ነገር ላይ ያደረገ፣ የማያወላውል፡ በሞቱ የቈረጠ ጐበዝ (ምሳሌ ፭፡ ፱) "ድኻ ቈራጥ ነው" እንዲሉ።

ቈራጥ ወለቴ: በቈራጣ ውስጥ የነበረች ቅድስት፡ የቈራጣ ወለቴ።

ቈራጥ: የተቈረጠ።

ቈራጥነት: ቈራጥ መኾን።

ቈራጭ (ጮች): የቈረጠ፣ የሚቈርጥ፡ ጐራጅ፣ ጐማጅ፣ ጨራሽ። "እንጥል፣ ምንጭር ነገር፣ ዕንጨት ቀፎ፣ ቀባ ቈራጭ" እንዲሉ።

ቈራጭ ፈላጭ ቢል፡ የሚቈርጥ፡ የሚፈልጥ፡ ንጉሥ፡ ባለወግ ማለት ነው።

ቈራጭ ፈላጭ: የወንጀለኛን እጅ እግር የሚቈርጥ ንጉሥ፡ ከራስ እስከ ፈጋራ መኻል ለመኻል ሰውን የሚፈልጥ፡ አረመኔ።

ቈራጭ: ባለወግ፣ ሰያፊ፣ ገራፊ፣ ሰቃይ፣ ገዳይ። "በግእዝ መስተራትዕ ይባላል። "

ቈራጭ: እጅና እግርን፡ ወይም ዐንገትን።

ቈራጭ: ዋና፣ የበላይ፣ ጠቅላይ ሹም፡ ራስ ደጃዝማች፡ ከበታቹ ያሉ ብዙዎች አገረ ገዢዎች የፈረዱትን ፍርድ የሚልጥ፣ የሚሽር፣ የሚለውጥ፣ የሚገለብጥ፣ የሚያጸድቅ።

ቈራጭነት: ቈራጭ መኾን፡ የበላይነት።

ቈራፋ: ዦሮው የረዘመና የተቀለበሰ ሰው።

ቈሬ: የሰው ስም፥ቆሬ።

ቈሬ: የቤት ዕቃ ስም፡ በጣባ፣ በወጭት፣ በሳሕን አምሳል የታነጸ ዕቃ፡ ዘሩ ቈረቈረ ይመስላል። "ገበቴን እይ። "

ቈርሪቋ: የቈረቈረ፣ የሚቈረቍር፡ መሥራች፣ ጐርባጭ፣ ወገን፣ ደፋኝ።

ቈርቍር: በሺ ሸንቋሪ። "ግንደ ቈርቍር" እንዲሉ። "ቈርቍር የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ ሲኾን በቅጽልነት መፈታቱን አስተውል። "

ቈርቈሮ: ፈረንጆች ብረትነት ያለውን ደንጊያ አቅልጠው የሠሩት ብረትማ የቤት ክዳን (ቦይና ሸንተረር ያለው) "በምስማር እየተቈረቈረ ስለሚከደን ቈርቈሮ ተባለ (ዘኍልቍ ፴፩፡ ፳፪፡ ኢሳይያስ ፩፡ ፳፭) " "በግእዝ ናእክ ይባላል። "

ቈርቋዛ: የቈረቈዘ፣ የማያድግ፡ ዐጪር ልጅ፣ ጥጃ።

ቈርበተ ሐሊብ: የወተት ስልባቦት፡ ለጋ ቅቤ (የንቍላል አስኳል የሚመስል)፡ ብጫ የሰደፍ ዶቃ፡ ወይም መቍጠሪያ ባለመዐዛ። "በግእዝ አርማስቆስ ይባላል። " "ቀሀረማንን እይ። "

ቈርበተ ሞኝ: ሲያዩት አላዋቂ የሚመስል ሰው።

ቈርበተ ዐሊም: ቈርበት (ርበት) የጸሎት ዕቃ (መቍጠሪያ)፡ ዐሊም የተማረ ማለት ነው።

ቈርበት ነክ: ሥር የሌለው ነገር።

ቈርበት ካሪም: ዝኒ ከማሁ።

ቈርበት: የሰው ገላ ቈዳ (ዘሌዋውያን ፲፫፡ ፪-)

ቈርባ ቈርባ አለ: ዝኒ ከማሁ።

ቈርነናታም: እንቍራሪትኛ የሚጮኸ።

ቈርነናት (ቈርነናዓት): ጓጕንቸር፣ እንቍራሪት፡ ጯኺ፣ ነወሬ።

ቈርኬ (ኦሮ): ቀጪኔ።

ቈርኬ: የቢራ መክደኛ።

ቈርዛዛ: የተንቈረዘዘ፡ እንቍርዝ።

ቈርጠጥ ቈርጠጥ አለ: ጐርደድ ጐርደድ አለ።

ቈርጣሚ: የቈረጠመ፣ የሚቈረጥም፡ ጐርዳሚ።

ቈርጦ ቀጥል: ዐባይ ጐመድ፣ ቀጣፊ፣ ኹለት ምላስ።

ቈርጦ ኼደ: ሐሳቡን ከዓለም ለይቶ ወደ መንፈሳዊ ሥራ ዐለፈ፣ ነጐደ። "ደበረ ብለኸ ተድበረበረን አስተውል። "

ቈርጦ: በጥሶ፣ ጐምዶ።

ቈሸሸ: አደፈ፣ ተበከለ፣ ተኵለፈለፈ፡ ትቢያ ለበሰ። "በየቀኑ የማይጠረግ ቤት ይቈሽሻል። "

ቈሸበ (ትግ፡ ሐባ፡ ቈሽበ፡ ዝግተኛ ኾነ): ጀጀበ፣ ጀጀረ፡ መብል ከለከለ።

ቈሸበለ): አንቈሻበለ፣ ለመነ፣ ተለማመጠ፣ አባበለ፣ አቀማጠለ።

ቈሸንዳ: የከሳ ሰው፡ ወይም ከብት።

ቈሸዳም: ቈሸድ ያለው፣ ባለቈሸድ።

ቈሸድ: የደረቀ እንጀራ፡ ዘኬ።

ቈሻ: ርጥብ፡ የማሽላ እንቀት፡ የሐረርጌ ሴቶች አስቀድሞ በሙቀጫ ይወቅጡታል፡ ዳግመኛም ያልሙታል፣ ይለነቅጡታል።

ቈሻሻ: የቈሸሸ፣ እድፋም፡ ጽዳት የሌለው፣ ዐሣማ።

ቈሻባ (ቍሽብ): የተቈሸበ (መብል የማይገፋ)

ቈሽት (ቶች): ሆድ ዕቃ፡ ከጨጓራ ጋራ ያለ ሥጋዊ ከረጢት (የብጥብጥ ምግብ መታቈሪያ) "በግእዝ ቈሥጢ ይባላል። "

ቈሽት አንድድ: ሀኬተኛ፣ ልግመኛ፣ እከየኛ ሰው።

ቈቀረ: አነሰ፣ ጠቀነ፣ ዐጪር ኾነ።

ቈቀር (ሮች): ታናሽ የዕጣን ቅንጣት፡ ልዝብ፣ ጣፋጭ። "አንኳርን እይ። "

ቈበሩን፡ ደፈቀ፡ ካፉ፡ አወጣ፡ አፈሰሰ።

ቈበራም፡ ቈበር፡ ያለው፡ ባለቈበር፡ ብዙ።

ቈበር፡ ቆበር፡ ካፍ፡ የሚወጣ፡ ብዙም፡ ራቅ፡ ዐረፋ።

ቈበቈበ (ጐበጐበ፡ ኰበኰበ)፡ ዐተረ፡ ጐረበ፡ ቈረበ፡ ቍብ፡ ቍብ፡ አለ።

ቈበበ (ጐበበ)፡ ገላውን፡ ሰብስቦ፡ እንደ፡

ቈባ፡ ተናጋሪ፡ ሴት፡ ተናጣቢ፡ አፈኛ፡ ምላሰኛ።

ቈባባ፡ የቈበበ፡ ጐባባ።

ቈብቋባ፡ የቈበቈሰ፡ የሚቈበቍብ፡ ጕርብ፡ ቍርብጭ።

ቈቦ፡ ባንኮበር፡ በኩል፡ ያለ፡ አገር። ምሳሌ: "ሐር፡ ዐምባና፡ ቈቦ"፡ እንዲሉ። ቈባና፡ የቈቦ፡ ዘር፡ ቈበበ፡ ነው።

ቈቦ፡ እንደ፡ ጕብ፡ በቀላል፡ ተቀመጠ። ሸረቈጠን፡ ተመልከት።

ቈቦ፡ የዛፍ፡ ስም፡ አነስተኛ፡ ወተታም፡ ዕንጨት። ቅል፡ በሚያካክል፡ የፍሬው፡ መሸፈኛ፡ ውስጥ፡ ነጭ፡ ሐር፡ የሚመስል፡ ባዘቶ፡ አለው፡ ወተቱም፡ ለመጋኛ፡ መድኀኒት፡ ይኾናል። ዳግመኛም፡ ጦቢያ፡ ሦስተኛም፡ ቅንቦ፡ ይባላል። ጋሳም፡ ጕሎን፡ ቈቦ፡ ይለዋል።

ቈተመ: ነቃ፣ ተጋ።

ቈተመ: ጓጓ፣ ሰለፈ (አንድ ነገር ለማግኘትና ለማድረግ)

ቈተቸ (ቀተወ): ውርርድ አደረገ።

ቈታሚ: የቈተመ፣ የሚቈትም፡ ሰላፍ።

ቈቻ: ብርታት፣ ጥንካሬ። "ዘሩ ቈተቸ ነው። " ቈቻ ዋለ: ከቀትር በፊት ካንድ በሬ፣ ከቀትር በኋላ ከሌላ በሬ ጋራ ተጠመደ፣ ዐረሰ፡ ከኹለት ተወዳደረ።

ቈነ፡ ለቀመ፡ አጥመዘመዘ፡ ገደለ፡ ሰውየው።

ቈነሰ: በሰበሰ፣ ገማ፣ ጠነባ።

ቈነነ (አርጐነነ): አጐነነ፣ ደቀቀ።

ቈነነ: ለካ፣ መጠነ፣ ሰፈረ (ድርጎን)

ቈነነ: ቀስ አደረገ፣ በቀስታ አስኬደ፡ ጀነነ፣ አኰራ፣ አጓደደ፣ አቋፈ።

ቈነነ: ታታ፣ ጐነጐነ፣ ሸረበ፣ ሠራ (ጭራን፣ የራስ ጠጕርን)፡ ቋድ አስመሰለ። "ጐነነን" ተመልከት።

ቈነነ: ከባድ ኾነ።

ቈነነ: ፈጠነ፣ በርትቶ ኼደ፣ ሮጠ።

ቈነን ቈነን: ቶሎ ቶሎ አለመኼድ።

ቈነዠ(ቍንዝዕ፡ ቈንዳላ)፡ ኦሞላ፡ አማረ፡ ተዋበ፡ የሴት፡ ልጅ፡ ገላ። "በቈነዠ ፈንታ፣ ቈነጀ፡ እየተባለ፡ ይጻፋልና፡ ስሕተት፡ ነው። "

ቈነዠች፡ ዐቅመ፡ ሔዋን፡ አደረሰች፡ ጠጕሯ፡ እትከሻዋ፡ ላይ፡ ወረደ።

ቈነዣዥት፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ የሚያማምሩ፡ ልጃገረዶች፡ (ዓሞጽ ፰፡ ፲፫። ፩ኛ ጢሞቴዎስ፡ ፭፡ ፪) "በግእዝ፡ ደናግል፡ ይባላሉ። "

ቈነደለ፡ ሽሩባ፡ ሠራ፡ ጐነጐነ፡ ቈነነ ዐሸመ።

ቈነደደ(ነደደ)፡ በቋንዶ፡ ገረፈ፡ ለቈጠጠ።

ቈነደደ፡ አደረቀ፡ አሻከረ፡ አሳጠረ፡ ቁመትን።

ቈነዳ(ቈንደየ)፡ ዘለለ፡ ረገደ።

ቈነጠ(ቀንጠወ)፡ ሆዱ ተነፋ፡ ቍንጣናም፡ ኾነ።

ቈነጠ፡ ጐነጠ፡ ነካ፡ በንክሻ።

ቈነጠጠ፡ ለመዘገ፡ ቀጣ፡ ልጅን።

ቈነጠጠ፡ ረገጠ፡ ርካብን፡ በእግር፡ አውራ፡ ጣት።

ቈነጠጠ፡ ሸፈነ፡ ጠቀለለ፡ ማገረ፡ ጣራን፡ በግምጃ፡ በሐር።

ቈነጠጠ፡ ነከሰ፡ በላ፡ ትንኝ፡ ጕንዳን፡ ገላን።

ቈነጠጠ፡ አጣበቀ፡ አጣብቆ፡ ያዘ፡ እሾኸን፡ ምስማርን፡ በወረንጦ፡ በጕጠት፡ ትንባኾን፡ በጣት።

ቈነጤ፡ የቈነጥ፡ ዐይነት፡ የሐሜት፡ ስም።

ቈነጥ፡ ትንኝ፡ ዝንብ፡ ባፉ፡ የሚጐንጥ።

ቈነጩ፡ ቍንጫ፡ ኾነ፡ ቍንጫ፡ አፈራ፡ ቤቱ።

ቈነጩ፡ ነቀሰ፡ አሳደገ፡ ቍንጮን።

ቈነጯ፡ ዐረምን፡ ውራን፡ ጐለጐለ፡ ነቀለ።

ቈነጸለ: ቈረጠ፣ ገነጠለ (ጥራዝን)

ቈነጸለ: ኰሰተረ፣ ሰበረ፣ አለማ (መብራትን) "ተረከሰን እይ። "

ቈነጻጸለ: ሰባበረ (ከሰልን)

ቈነጻጸለ: ቈራረጠ፣ ገነጣጠለ።

ቈናኒ: የቈነነ፣ የሚቈንን፡ ፈጣና፣ ከባድ።

ቈናኝ (ኞች): የቈነነ፣ የሚቈንን፡ ጐንጓኝ፣ ሸራቢ፣ ጠጕር ሠሪ።

ቈንቋና (ትግ፡ ቈንቋን): ዝኒ ከማሁ፡ ቈጣቢ፣ ሥሥታም።

ቈንቋኔ: የቈንቋና ወገን፡ እንደ ነቀዝ በቀስታ ሰውነትን የሚጐዳ (ቅኔ ቈንቋኔ እንዲሉ)

ቈንቋኝ: የቈነቈነ፣ የሚቈነቍን፡ ተንታኝ።

ቈንዢት፡ የሴት፡ ስም።

ቈንዦ፡ የቈነዠች፡ ያማረች፡ የተዋበች፡ ውብ፡ ደማም፡ መልከ፡ መልካም፡ ያ፲፭፡ ዓመት፡ ልጃገረድ፡ ደረተ፡ ሳንቃ፡ ዐንገተ፡ መቃ፡ አፍንጫ፡ ስንደዶ፡ ጥርሰ፡ በረዶ። (ተረት)"የስንዴ፡ ዐራራ፡ የቈንዦ፡ መራራ " "በልማድም፡ ወንድ፡ ቈንዦ፡ ይባላል። " "ቈንዦ፡ የሚነገረው፡ ለልጃገረድና፡ ለምታምር፡ ሴት፡ ሲኾን፡ ጣሊያን፡ ገዝቶ፡ ከኼደ፡ ቈንዦ፡ ቤት፡ ቈንዦ፡ መብል፡ ቈንዦ፡ ልብስ፡ እየተባለ፡ ባዲስ፡ አበባ፡ ይነገራል። " "ሴትን፡ ከወንድ፡ ለመለየት፡ ቈንዦዋ፡ ቈንዦዪቱ፡ ያች፡ ቈንዦ፡ (ኤርምያስ ፲፬፡ ፲፯) "

ቈንዦነት፡ ዝኒ ከማሁ፡ (ኤርምያስ ፫፡ ፬)

ቈንዦዎች፡ የቈነዠ፡ የሚያምሩ፡ ሴቶች።

ቈንደል፡ የማሽላ፡ ስም፡ መልኩ፡ ብጫ፡ ዋሜራው ' ረዥም፡ የኾነ፡ ማሽላ፡ ኮልኝ። (ግጥም)"ከማሽላው፡ ቈንደል፡ ከጤፉ፡ ጐራዴ፡ ረ፡ ለማን ኛው፡ ታደላለኸ፡ ሆዴ "

ቈንዳ፡ ቈንዳ፡ አለ፡ መር፡ መር፡ አለ።

ቈንዳላ፡ ጕተና፡ ጐፈሬ፡ ረፍረፎ፡ ጠጕር' (መኃልየ መኃልይ ፭፡ ፪ ፲፩። ኢሳይያስ ፵፯፡ ፪) "በጋልኛ፡ ግን፡ ወጣት፡ ልጅ፡ ማለት፡ ነው። "

ቈንዳዳ፡ ደረቅ፡ ሻካራ፡ ያጠረ፡ ጠጕር።

ቈንዳጅ፡ የቈነደደ፡ የሚቈነድድ፡ ገራፊ።

ቈንጣጭ፡ የቈነጠጠ፡ የሚቈንጥጥ፡ የሚ ነክስ፡ ነካሽ፡ ረጋጭ፡ (ዘዳግም ፯፡ ፳)

ቈንጪ፡ የቈነጨ፡ የሚቈነጭ፡ ለቃሚ፡ ጐልጓይ።

ቈንጻይ: የቈነጸለ፣ የሚቈንጽል፡ ኰስታሪ።

ቈኘተ: ታታ፣ አሠባጠረ፣ አዋሰበ።

ቈወጪ፡ ቍጫጭ፡ አፈራ።

ቈዘመ፡ ዐዘነ፡ ተከዘ፡ አለቀሰ፡ አሞሸ፡ ዋይ፡ አለ፡ (ሕዝቅኤል ፳፩ ፡ ማርቆስ ፴፬ ቆሮንቶስ )

ቈዘረ፡ ጐኘረ፡ ነፋ፡ ጐሰረ። ቈረዘን፡ እይ።

ቈዛሚ (ሞች)፡ የቈዘመ፡ የሚቈዝም፡ ዐዛኝ፡ አልቃሽ።

ቈዝሞ፡ ዐዝኖ፡ ተክዞ፡ (ማርቆስ ፲፪)

ቈየ(ዕብ፡ ቃዌህ)፡ ባንድ፡ ስፍራ፡ ጥቂት፡ ወይም፡ ብዙ፡ ጊዜ፡ ተቀመጠ፡ ኖረ፡ ነበረ፡ ዘገየ፡ (ዘፍጥረት ፰፡ ፲፪) "የቈየ፡ ሰው፡ የዘገየ፡ መጨረሻውን፡ ያየ"(አዝማሪ)

ቈየ፡ ቆመ፡ ጠበቀ፡ ሰውን።

ቈየት፡ አለ፡ ዘግየት፡ አለ።

ቈየት፡ ዘግየት።

ቈዪ(ቀላዊ)፡ የቈላ፡ የሚቈላ። ያለፈው፡ አንቀጽ፡ የሚመጣው፡ ስም፡ መኾኑን፡ አስተውል።

ቈይ፡ አትኺድ፡ እዚሁ፡ ተቀመጥ፡ ሥራን፡ ነገርን፡ ተው። (ተረት)"ኣላቻ፡ ጋብቻ፡ ቈይ፡ ብቻ፡ ቈይ፡ ብቻ። " (ባጣ፡ ቈዪኝ)"ካንቺ፡ የተሻለች፡ ሴት፡ ባላገኝ፡ ባል፡ ሳታገቢ፡ ጠብቂኝ"

ቈይታ፡ የባለሥልጣኖች፡ ብቻ፡ ምክር፡ የምስጢር፡ ንግግር። በፈረንጅኛ፡ ሲያንስ፡ ይባላል።

ቈይታ፡ ያዘ፡ ንጉሡከባለሎቹ፡ ጋራ፡ መከረ።

ቈደሰ (ቀደሰ)፡ ቈረሰ፡ ከፈለ፡ ጥቂት፡ ጥቂት፡ በላ፡ ዛቲን፡ መክፈልትን፡ ከቅዳሴ፡ በኋላ።

ቈዳ፡ የሥጋ፡ ኹሉ፡ ልብስ፡ መሸፈኛ፡ ርጥቡም፡ ደረቁም፡ ቈዳ፡ ይባላል። ምሳሌ: "የበሬ፡ የበግ፡ የፍየል፡ ያጋዘን፡ የሡሥ፡ የምዳቋ፡ ቈዳ"፡ እንዲሉ። (ግጥም)"ባህያ፡ ቈዳ፡ የተሠራ፡ ቤት፡ ብትንትን፡ ይላል፡ ዥብ፡ የጮኸ፡ ለት። " አንጋሬንና፡ ሌጦን፡ እይ።

ቈዳ፡ ፍሬ፡ የማይሰጥ፡ መሬት።

ቈጊ፡ የቈጋ፡ የሚቈጋ፡ ገራፊ።

ቈጋ፡ ገረፈ፡ በጅራፍ፡ መታ፡ ቈነደደ። ጋጋን፡ ተመልከት።

ቈጠሰ፡ ከፈለ፡ ለየ፡ ርስትን።

ቈጠረ(ቈጸረ)፡ አንድ፡ ኹለት፡ ሦስት፡ አለ፡ ዐሰበ፡ አሰላ፡ ፊደል፡ ተማረ። (ድር፡ ቈጠረ)፡ ፫፡ በቅል፡ ፬፡ በቅል፡ አደረገ።

ቈጠረ፡ ርስቱን፡ ከብቱን፡ በወንድ፡ ዐማቱና፡ በጨዋ፡ ፊት፡ ዘረዘረ፡ ነገረ፡ አስረዳ፡ አስታወቀ።

ቈጠረ፡ ቅኔ፡ አዘጋጀ፡ ቤት፡ መታ። (ግጥም)"ሰዋስው፡ ጨዋታ፡ ዐማርኛ፡ ቅኔ፡ ቈጥረኸ፡ ስደድልኝ፡ እፈታለኹ፡ እኔ። "

ቈጠራ(ቈጸራ)፡ የመቍጠር፡ ሥራ።

ቈጠቈጠ(ቈጠጠ፡ ቀጠጠ)፡ እሾኽ፡ ቍጥቋጦ፡ ቈረጠ፡ መለመለ፡ (ዳንኤል ፬፡ ፲፬፡ ፳፫) ኰተኰተን፡ ተመልከት።

ቈጠቈጠ፡ ለበለበ፡ ፈጀ፡ አቃጠለ፡ አንገበገበ።

ቈጠቈጠ፡ ቈጠበ፡ ቈነቈነ፡ ቈነጠረ።

ቈጠቈጥ፡ ቈጥቋጣ፡ የተንቈጣቈጠ፡ የሚንቈጣቈጥ፡ ቈንቋና፡ ቈጣቢ።

ቈጠቈጭ፡ ቈጭቋ፡ የተንቈጨቈ፡ ስብርብር፡ እንክትክት።

ቈጠበ፡ በልክ፡ በመጠን፡ በስሌት፡ በሒሳብ፡ በቍጥቍጥ፡ ገንዘብ፡ አወጣ፡ ወጪን፡ ቀነሰ፡ አሳነሰ፡ ተቀማጭን፡ አበዛ፡ አበረከተ፡ በየጊዜው፡ ገንዘብ፡ አስቀመጠ፡ ያዘ፡ ጨበጠ፡ አተረፈ፡ አካበተ።

ቈጠጠ (ቈጢጥ፡ ቈጠጠ)፡ የወተት፡ ኵስ፡ ኰሳ፡ ዐራ። ቈጠቈጠን፡ እይ።

ቈጠጯ፡ ቍጭ፡ አለ። ጐቸን፡ እይ።

ቈጣ፡ አለ፡ ጥቂት፡ ሖምጠጥ፡ አለ።

ቈጣ)፡ ቈጥዐ)፡ አስቈጣ፡ አስገሠጸ፡ አዘለፈ፡ አስገላመጠ።

ቈጣስር (ቈጥ፡ አስር፡ አሰር)፡ የጋብቻ፡ ስም፡ ውሉ፡ በቈጥ፡ የታሰረ፡ የተፈጸመ፡ ጋብቻ። "እሚስቱ፡ አባት፡ እናት፡ ቤት፡ ኼዶ፡ የሚኖር፡ ወንድ፡ በታዛይ፡ ከሚስቱ፡ ጋራ፡ በቈጥ፡ ስለሚተኛ፡ ጋብቻቸው፡ ቈጣስር፡ ተባለ፡ ይኸውም፡ ማተብንና፡ ቀለበትን፡ ቃልን፡ ያስተረጕማል። "

ቈጣሪ(ሮች)፡ የቈጠረ፡ የሚቈጥር፡ ተማሪ፡ "ዘኬ፡ ቈጣሪ"፡ እንዲሉ። ኮከብን፡ እይ።

ቈጣሪ፡ የተበራውን፡ ኤሌትሪክ፡ ልክ፡ የተቀዳውን፡ ውሃ፡ መጠን፡ የሚነግር፡ መኪና፡ በውስጡ፡ የሚዞር፡ ቍጥር፡ ያለበት።

ቈጣቈጠ፡ ቈራረጠ፡ መላመለ።

ቈጣቢ (ዎች)፡ የቈጠበ፡ የሚቈጥብ፡ አስቀማጭ፡ ጨባጭ፡ አካባች።

ቈጣጠረ መላልሶ፡ ቈጠረ።

ቈጣጭ፡ የቈጠጠ፡ የሚቈጥጥ፡ ጥጃ፡ ግልገል፡ ሕፃን።

ቈጥ (ቀጣ)፡ አራት፡ እግሩ፡ እመሬት፡ የተተከለ፡ የንጨት፡ ዐልጋ፡ ሲበዛ፡ ቈጦች፡ ይላል። ቈጥ፡ የንጨቱን፡ ትክክል፡ ኹኖ፡ መቈረጥ፡ ያሳያል። (ተረት): "ቈጡን፡ ኣወርድ፡ ብላ፡ የብብቷን፡ ጣለች። "

ቈጥቋጭ፡ የቈጠቈጠ፡ የሚቈጠቈጥ፡ ለብላቢ፡ ቈራጭ፡ መልማይ።

ቈጨቈጪ፡ ጣትን፡ ከጣት፡ ኣዋሰበ፡ አስታገለ፡ አስተናነቀ።

ቈጨበረ፡ ብስጩ፡ ኾነ።

ቈጨበር፡ ቈጭባራ (ሮች)፡ ቍጡ፡ ብስጩ፡ ዐመለ፡ ቢስ።

ቈጨጨ፡ አነሰ፡ ቍርንጫጭ፡ ኾነ። ጐጨጨን፡ አስተውል።

ቈጫ (ኦሮ)፡ ዔሌ፡ ድንጋይ፡ ልብሱ።

ቈጫ፡ ያገር፡ ስም፡ በወላሞ፡ ክፍል፡ ያለ፡ ወረዳ፡ ማለፊያ - ቡልኮ፡ የሚሠራበት።

ቈጮ (ወላሞ)፡ እንሰት።

ቈፈረ (ቀፈረ): ማሰ፣ ጫረ፣ መነቀረ፣ ኳተ፣ ኰተኰተ፣ ጐደፈረ፣ አጐደጐደ (ዘፍጥረት ፳፯፡ ፲፱፡ መዝሙር ፯፡ ፲፭) (ተረት): "ሲቀላውጡ ዐይን አፍጦ፡ ሲቈፍሩ አንፈራጦ። "

ቈፈር: ማስ፣ ማር፡ ቈፈር ቈፈር አደረገ፡ ማስ ማስ ሣር ጫር አደረገ።

ቈፈቈፈ (አንቈፈቈፈ): አስጮኸ፣ አስጠራ።

ቈፈቈፍ: ቈፍቋፋ፡ የተንቈፈቈፈ፣ የሚንቈፈቈፍ፡ ጯኺ፣ ጠሪ (ዶሮ)፡ ንፉግ፣ ሥሥታም፣ ቈጥቋጣ (ሰው)

ቈፈነ: በረደ፣ ቀዘቀዘ።

ቈፈነነ: ዐጠፈ፣ ጨበጠ፣ አደረቀ (ጣትን) "ጐፈነነን ተመልከት። "

ቈፈነን: ቈፍናና፡ የተቈፈነነ፣ የታጠፈ፣ የተጨበጠ።

ቈፈናም: ቈፈን የያዘው፣ ባለቈፈን፡ ጣቱ ሊይዝና ሊጨብጥ የማይችል።

ቈፈን: ብርድ፣ ቅዝቃዜ።

ቈፈጠነ: ጕድለት አልባ ኾነ።

ቈፋሪ (ሮች): የቈፈረ፣ የሚቈፍር፡ ማሽ፣ ዶመኛ።

ቈፋፈረ: ጫጫረ፣ መነቃቀረ።

ቈፍና: በመርሐ ቤቴ ክፍል ያለ አገር፡ ብርድ ያለበት። "ቈፍና የሩቅ ሴት ቦዝ አንቀጽ ነው። "

ቈፍጣና (ኖች): ዝግጁ፣ ድርጁ፣ ስንዱ (በሞያ፣ በሀብት፣ በኑሮ፣ በጌጥ)

ቅለዳ፡ ትረባ።

ቅሉ፡ ንኡስ፡ አገባብ፡ ስንኳ፡ (ማቴዎስ ፳፭፡ ፳፱)

ቅሉ፡ ያ፡ ቅል፡ የርሱ፡ ቅል።

ቅሉ፡ ግን። "እሱ፡ እሷ፡ አንተ፡ እኔ፡ ቅሉ"(፪ኛ ሳሙኤል፡ ፲፰፡ ፲፫)

ቅላት(ቂሐት)፡ ቀይነት፡ ደም፡ መምሰል፡ (ምሳሌ ፳፫፡ ፳፱)

ቅላጤ፡ ተጨማሪ፡ ዜማ፡ ከዋናው፡ የተለየ።

ቅሌ(ኦሮ)፡ ጥንግ፡ ዕሩር።

ቅሌታም(ሞች)፡ ቀላል፡ ሰው፡ ባለቅሌት፡ መንፈሰ፡ ቀላል።

ቅሌት መቅለል ቀለለ።

ቅሌት፡ ያመል፡ የጠባይ፡ መቅለል፡ (፪ኛ ቆሮንቶስ ፩፡ ፲፯) "በግእዝ፡ ቅለት፡ ይባላል። " "ነደደ፡ ብለኸ፡ ንዴትን፡ አስተውል። "

ቅሌን፡ ጨርቄን፡ አለ፡ ምክንያት፡ ሰበብ፡ ኣበዛ፡ ተፍተለተለ።

ቅል(ሎች)፡ ሐረግማ፡ ቅጠል፡ በቅጥር፡ ውስጥና፡ በዱር፡ የሚበቅል፡ (ዮናስ = ፮፡ ፱) በትግሪኛ፡ ቅልዕ፡ ይባላል። (የጕድፍ፡ ቅል)፡ ሞኝ፡ ሰው፡ ዐሞተ፡ ቢስ፡ ደካማ። ባርን፡ ተመልከት።

ቅል፡ ሞላላ፡ የውሃ፡ መቅጃ፡ አንኮላ፡ ሸክና፡ ዐቦሬ።

ቅል፡ ባገኝ፡ ቅልን፡ ተስፋ፡ አድርጎ፡ የሚዘምት፡ ሰው።

ቅል፡ ብቻ፡ ራስ። (እየቅል፡ እየቅሉ)፡ እየብቻ፡ እየብቻው፡ እየራስ፡ እየራሱ። "ዱባና፡ ቅል፡ አበቃቀሉ፡ እየቅል። " "ቅሉ፡ ቅልኸ፡ እያለ፡ ይዘረዝራል። ራሱ፡ ራስኸ፡ ማለት፡ ነው። ራስን፡ እይ። "

ቅል፡ ዐንገት፡ ቀጪን፡ የቅል፡ ዐንገት፡ የደጋን፡ መንዘሪያ፡ የምትኾን።

ቅል፡ ክብ፡ እንክብል፡ ቋንጅል፡ መንቀል። (ተረት)"አሞራውም፡ በረረ፡ ቅሉም፡ ተሰበረ። "

ቅልምጫ፡ ያፍ፡ ድምፅ፡ በምግብ፡ ጊዜ።

ቅልሞሽ፣፣ ቅልቦሽ፣፣ ቀለበ።

ቅልሳት፡ ጕብጠት።

ቅልስ፡ የተቀለሰ፡ ምልስ፡ ቍልፍ፡ ዐንገት፡ ጐዦ፡ ከዘራ፡ ገና፡ ጥንቅሽ፡ ሙጭ።

ቅልስልስ፡ አለ፡ ተቅለሰለሰ።

ቅልስልስ፡ የተቅለሰለሰ፡ ደካማ።

ቅልሽልሽ፡ አለው፡ ሽቅብ፡ ሽቅብ፡ አለው፡ በሽ፡ አለው።

ቅልሽልሽ፡ የተቅለሸለሸ፡ ጥውልውል።

ቅልሽልሽታ፡ የሆድ፡ እውክታ።

ቅልቀላ፡ ድብሊቃ፡ ቅየጣ፡ ዝነቃ።

ቅልቅል(ሎች)፡ የተቀላቀለ፡ ድብልቅ፡ ቅይጥ፡ ዝንቅ፡ እኸል፡ ማዕድን። (ደም፡ ቅልቅል), እውክታ፡ ብልዝ።

ቅልቅል፡ አለ፡ ቅዥቅዥ፡ አለ፡ ተንቀለቀለ።

ቅልቅል፡ አለ፡ ድብልቅ፡ አለ፡ ውጥንቅጥ፡ ኾነ።

ቅልቅልነት፡ ቅልቅል፡ መኾን፡ ድብልቅነት።

ቅልበሳ፡ ዐጠፋ፡ ሽንቀራ፡ ቅነፋ።

ቅልብ(ቦች)፡ የተቀለበ፡ የተመገበ፡ የበላ፡ ሙክት፡ ገች፡ ድልብ።

ቅልብ፡ የተያዘ፡ የተጨበጠ።

ቅልብልብነት፡ ስግብግብነት።

ቅልብሳት፡ ዕጥፋት፡ ቅንፋት፡ የሱሪ፡ የጥብቆ፡ የበርኖስ፡ የለምድ፡ የዳባ፡ ፍና፡ ጫፍ፡ የዝናር፡ ዳርና፡ ዳር፡ እየተቀለበሰ፡ የተሰፋ።

ቅልብስ፡ የተቀለበሰ፡ ቅንፍ፡ ሽንቅር፡ ከንፈር፡ ልብስ።

ቅልብሽ፡ አለው፡ ቅልሽልሽ፡ አለው፡

ቅልብሽ፡ የተመለሰ፡ የተገለበጠ፡ ወደ፡ ላይ፡ የወጣ፡ የሆድ፡ ውስጥ፡ ምግብ።

ቅልብጭ፡ አለ፡ ቅልጥፍ፡ አለ።

ቅልውጥ፡ የማድ፡ ክጀላ።

ቅልዝ፡ አለ፡ ክችል፡ አለ።

ቅልዝ፡ የቀለዘ፡ ዕንጨት፡ በጋ፡ ተክረምት፡ ያለፈበት።

ቅልጠፋ፡ ፍጥነት፡ ክር፡ ባጪር።

ቅልጣቅልጥ(ቅልጥ፡ አቅልጥ)፡ የቅልጥ፡ ቅልጥ፡ የምት፡ ምት፡ በሰንበር፡ ላይ፡ ሰንበር፡ ያረፈበት። "የዝንጀሮ፡ ቅልጣቅልጥ"፡ እንዲሉ።

ቅልጣን ምቾት ቀለጠ።

ቅልጣን፡ ምቾት፡ ድሎት፡ ከልክ፡ ያለፈ፡ ሀብት። "መሬት፡ ውሃ፡ ሲያይልበት፡ ሠም፡ ቅባት፡ ሙቀት፡ ሲበዛበት፡ እንዲቀልጥ፡ ቅልጣንም፡ ከባለቤቱ፡ ዐልፎ፡ ለሌላ፡ መትረፉን፡ ያሳያል"(ዘዳግም ፳፰፡ ፶፬፡ ፶፮። ኤርምያስ ፲፫፡ ፳፯)

ቅልጥ፡ አለ፡ ፍስስ፡ አለ፡ ፈጽሞ፡ ሠባ፡ ደመቀ።

ቅልጥ፡ የቀለጠ፡ የ፡ የፈሰሰ፡ የፈረሰ፡ የተመታ።

ቅልጥልጥ፡ አለ፡ ተቅለጠለጠ።

ቅልጥልጥ፡ የተቅለጠለጠ፣ ወዛም።

ቅልጥማም(ሞች)፡ ቅልጥም፡ ረዥም፡ ቋቲሮ፡ ሰው፡ አሞራ።

ቅልጥም(ሞች)፡ ከቋንዣ፡ እስከ፡ ቍርጭምጭሚት፡ ያለ፡ የእግር፡ ክፍል፡ መለልታ፡ አገዳ።

ቅልጥም፡ ሰባሪ፡ ቅልጥምን፡ ወደ፡ ሰማይ፡ አውጥቶ፡ እየለቀቀ፡ አለት፡ ላይ፡ የሚሰብርና፡ ቅባቱን፡ የሚጠጣ፡ አሞራ። ዠርባው፡ ጥቍር፡ ኾኖ፡ ቅላትና፡ ንጣት፡ ያለው፡ ባና፡ መሳይ፡ ነው። በስተጕያውና፡ በስተጭኑ፡ ነጭ፡ ሱሪ፡ የታጠቀ፡ ይመስላል።

ቅልጥም፡ አለ፡ ስብር፡ አለ፡ ተቀለጠመ።

ቅልጥም፡ አደረገ፡ ስብር፡ አደረገ፡ ቀለጠመ።

ቅልጥም፡ ከብብት፡ እስከ፡ ኵርማ፡ ከክርን፡ እስከ፡ አንባር፡ ያ፡ ያለው፡ ጡንቻ፡ ክንድ፡ ለከብትም፡ የፊት፡ እግር፡ እንደዚሁ፡ ይነገራል።

ቅልጥም፡ የቅልጥም፡ ቅባት፡ (ሥሥ፡ ቅልጥም)፡ የኋላ፡ እግር፡ ከጕልበት፡ በታች፡ ከነቅባቱ። መቅንን፡ ተመልከት። "ወዶ፡ የዋጡት፡ ቅልጥም፡ ከብርንዶ፡ ይጥም"፡ እንዲሉ።

ቅልጥም፡ የተቀለጠመ፡ የተሰበረ፡ ስብር።

ቅልጥምጥም፡ አለ፡ ስብርብር አለ፡ ተቀለጣጠመ።

ቅልጥምጥም፡ የተቀለጣጠመ ስብርብር።

ቅልጥጥ፡ ቅልጥጥ፡ አለ፡ ሽቅብ፡ ሽቅብ፡ ግራና፡ ቀኝ፡ ዝንጀርኛ፡ አየ።

ቅልጥጥ፡ አለ፡ ግልጥ፡ አለ፡ ተንቀለጠጠ።

ቅልጥፍ፡ የቀለጠፈ፡ ፈጥኖ፡ የኾነ፡ የተደረገ።

ቅልጥፍና፡ ቀልጣፋነት።

ቅልጥፍጥፍ፡ አለ፡ ክውንውን፡ አለ፡ ተቀለጣጠፈ።

ቅልጥፍጥፍ፡ የተቀለጣጠፈ፡ ክውንውን።

ቅልጥፍጥፍታ፡ ቅልጥፍጥፍ፡ ማለት።

ቅሏ፡ ቅሊቱ፡ ያች፡ ቅል፡ (ዮናስ ፬፡ ፮፡ ፯፡ ፲)

ቅሏ፡ የርሷ፡ ቅል።

ቅመመን፡ የቅመም፡ ዱቄት፡ ን፡ ምእላድ፡ ነው።

ቅመመን፡ ድብልቅ፡ ውጥንቅጥ። "ፈረንጆች፡ ኮክቴል፡ ከሚሉት፡ ጋራ፡ ይሰማማል። "

ቅመማ፡ ስብሰባ፡ ቅልቀላ፡ ድብለቃ፡ ምጥና።

ቅመማም፡ ቅመም፡ ያለው፡ ባለቅመም።

ቅመማቅመም፡ የቅመም፡ ቅመም፡ ብዙ፡ ዐይነት፡ ቅመም።

ቅመም(ሞች)፡ አብሽ፡ ድንብላል፡ ኰረሪማ፡ ዝንጅብል፡ ነጭ፡ አዝሙድ፡ ጥቍር፡ አዝሙድ፡ ሰናፍጭ፡ ፌጦ፡ ነጭ፡ ሽንኵርት፡ ቀይ፡ ሽንኵርት፡ በሶብላ፡ ጐመን፡ ዘር፡ (የዘይት፡ ቅመም)፡ ተልባ፡ ኑግ፡ ሰሊጥ፡ ሱፍ፡ "የዚህ፡ ኹሉ፡ ማጣፈጫ፡ ጨው፡ ነው። "

ቅመራ፡ ቈጠራ፡ ምደባ፡ ከፈላ።

ቅሚያ፡ ንጥቂያ፡ (ኤርምያስ ፶፩፡ ፲፫። ናሆም ፪፡ ፲፪። ማቴዎስ ፳፫፡ ፳፭)

ቅማላም፡ ኾነ፡ ቀመለ።

ቅማል(ሎች)፡ ከሰው፡ እንፋሎትና፡ ላብ፡ በልብስና፡ በራስ፡ ጠጕር፡ ውስጥ፡ የሚፈጠር፡ ተባይ፡ ነጭና፡ ጥቍር።

ቅማል፡ ቅማላም(ሞች)፡ ቅማል፡ ያለበት፡ የበዛበት፡ የሚንፋሰስበት፡ ሰው።

ቅማል፡ ጅራም(ቅማንጅራም), ቅማንጅር፡ የሚታይበት፡ ሰው፡ ባለቅማንጅር።

ቅማል፡ ጅር(ቅማንጅር)፡ የቅማልጓዝ፡ የቅንድብና፡ የሽፋል፡ የጢም፡ ቅጫም።

ቅማሽ፡ ቢጀ፡ ጕርሻ፡ (ዮሐንስ ፲፫፡ ፳፮)

ቅማት ፬ኛ፡ አያት ቀደመ።

ቅማት፡ ቅማያት፡ የቅድም፡ አያት፡ አባትና፡ እናት፡ የሽማት፡ ልጆች።

ቅማንት(ከመ፡ አንተ)፡ የነገድ፡ ስም፡ በበጌምድር፡ አውራጃ፡ በከርከር፡ በጭልጋ፡ ያለ፡ ሕዝብ። "አንድ፡ ቅማንት፡ ዐደን፡ ዐድኖ፡ ከደን፡ ሲወጣ፡ አንድ፡ . . . . አገኘውና፡ መኑ፡ አንተ፡ አለና፡ ቢጠይቀው፡ ከመ፡ አንተ፡ ብሎ፡ ስለ፡ መለሰለት፡ በዘመን፡ ብዛት፡ ከመ፡ አንተ፡ በማለት፡ ፈንታ፡ ነገዱ፡ ቅማንት፡ ተባለ፡ ይላሉ። " "ዐዋጅ፡ የተሻለውን፡ መንገድ፡ ለመያዝ፡ የሚል፡ መጣፍ፡ ተመልከት፡ ዳግመኛም፡ አለቃ፡ ታየ፡ የጻፉትን፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ታሪክ፡ እይ። "

ቅማንቶች፡ የቅማንት፡ ነገዶች፡ ወገኖች።

ቅማንጅር፡ የቅማል፡ ጓዝ፡ "መለ። "

ቅማያት ፬ኛ፡ አያት፡ ቀደመ።

ቅማጫም፡ ተቅማጣም።

ቅማጭ፡ ተቅማጥ።

ቅም: (ይህ ቃል ትርጉም አልተሰጠውም፣ ምናልባት የሌላ ቃል አካል ሊሆን ይችላል)

ቅምሖ(ቀምሕ፡ ፍሬ)፡ ዕጢ፡ የሥጋ፡ ቅንጣት።

ቅምሖ፡ ለግዳ፡ ለቅዳ፡ በስተውስጥ፡ በጕረሮ፡ ጫፍ፡ ግራና፡ ቀኝ፡ የሚወጣ፡ ዕብጠት። "ዐዋቂ፡ በጊዜው፡ ካልቧጠጠው፡ ምግብና፡ ምራቅ፡ መዋጥ፡ ይከለክላል፡ ዦሮ፡ ግንድን፡ እንደ፡ ጦር፡ ይወጋል፡ እጅግ፡ ባበጠ፡ ጊዜ፡ የገባና፡ የንኰይ፡ ፍሬ፡ ስለሚያካክል፡ ቅምሖ፡ ተባለ። " "ፈረንጆች፡ ቶንሲል፡ ይሉታል። "

ቅምም፡ የተቀመመ፡ ቅልቅል፡ ድብልቅ፡ ምጥን፡ ቅመም፡ የገባበት፡ ድልኸ።

ቅምምጦሽ፡ የትከሻ፡ ሸክም፡ ፈረቃ።

ቅምስ፡ አደረገ፡ ልክፍ፡ አደረገ።

ቅምስ፡ የተቀመሰ።

ቅምር፡ የተቀመረ፡ የተቈጠረ፡ ክፍል፡ ምድብ። "ርባ፡ ቅምር፡ እንዲሉ። "

ቅምቀማ፡ ስፌት፡ ዝምዘማ።

ቅምቅማት(ቶች)፡ ዝምዝማት፡ (ዘጸአት ፳፰፡ ፴፪)

ቅምቅም፡ አለ፡ ጥቂት፡ ጥቂት፡ ጣፈጠ።

ቅምቅም፡ የተቀመቀመ፡ ዝምዝም።

ቅምቡርስ ትል ቅንቡርስ።

ቅምና ቅል (ቀመጠ)

ቅምድምድ፡ አለ፡ ተቅመደመደ።

ቅምጠላ፡ የማጕደል፡ ሥራ፡ ቅንጠሳ።

ቅምጥ፡ ቂጥ፡ መቀመጫ። "ራድ፡ ከቅምጥ፡ ይፈነቅላል፡ እንዲሉ። "

ቅምጥ፡ ዐይናር፡ ሌሊት፡ በንቅልፍ፡ ጊዜ፡ ካይን፡ የሚወጣ፡ እድፍ።

ቅምጥ፡ ዕጦት፡ ችግር፡ ሥራን፡ ትቶ፡ ከመቀመጥ፡ የሚመጣ።

ቅምጥ፡ የተቀመጠ። "ያተር፡ ቅምጥ፡ እንዲሉ። "

ቅምጥላ፡ የዕውቀት፡ ቅሬታ፡ (ተረፈ፡ አእምሮ)

ቅምጥላው፡ ጠፋ፡ አእምሮው፡ ታጣ፡ በስካር፡ ምክንያት፡ (ኅሊናውን፡ ሳተ)

ቅምጥል(ሎች)፡ የተቀማጠለ፡ ()፡ ድልድል፡ ዘንፋላ፡ ብዙ፡ ምግብና፡ ልብስ፡ አማራጭ፡ ጌታ፡ ወይዘሮ፡ (ኢሳይያስ ፵፯፡ ፩ - ) "ሴትን፡ ከወንድ፡ ለመለየት፡ ቅምጥሉ፡ ያ፡ ቅምጥል። "

ቅምጥል፡ አለ፡ ጕድል፡ እንስ፡ አለ።

ቅምጥልነት፡ ቅምጥል፡ መኾን፡ ድልድልነት።

ቅምጥልጥል፡ አለ፡ ተዘናፍሎ፡ ተኛ።

ቅምጥልጥል፡ የተቀመጣጠለ።

ቅምጥሏቅምጥሊቱ፡ ያችቅምጥል፡ (፩ኛ ጢሞቴዎስ፡ ፭፡ ፮)

ቅምጦሽ፡ የጨዋታ፡ ስም፡ ልጆች፡ አንዱ፡ ባንዱ፡ ትከሻ፡ ላይ፡ እየተቀመጡ፡ የሚያደርጉት፡ የኳስ፡ ጨዋታ።

ቅምጫና(ኖች)፡ ቅል፡ ቋንጅል። "መንቀልን፡ እይ። "

ቅሞ፡ ሖምጣጣ፡ የቅሞ፡ ፍሬ፡ ተረር።

ቅሞ፡ የዛፍ፡ ስም፡ ፍሬው፡ የሚቃም፡ አነስተኛ ዕንጨት።

ቅሰራ: ግተራ።

ቅሳር: ሠረዝ፣ ጭረት። "ኹለቱን ነጥብ ዐቢይ ሠረዝ፣ ንኡስ ሠረዝ የሚያሠኘው ቅሳር ነው። "

ቅሣር: ጭረት፣ ቀሰረ።

ቅስሙ ተሰበረ: ሥውነቱ ተጐዳ።

ቅሥም: ሰውነት፣ ቀሰመ።

ቅስም: ካ፬ቱ ባሕርያት የተቀመመ ሰውነት ኹናቴ። "በግእዝ ቅሳሜ ይባላል። "

ቅሥም: የተቀሠመ፡ ልቅም፣ ስብስብ፣ አውላ።

ቅስስ አለ: ፍዝዝ አለ።

ቅስስ: ቅዝዝ፣ ፍዝዝ።

ቅስር ቅስር አለ: ግትር ግትር አለ።

ቅስር አለ: ግትር አለ።

ቅስቀሳ: ንቅነቃ፣ ብርበራ፣ ፍተሻ።

ቅስቃሴ (ነሰሕሳሕ): መቀስቀስ፡ ቅስቃሴ።

ቅስቅስ አለ: ንቅንቅ አለ።

ቅስቅስ: የተቀሰቀሰ፣ የተበረበረ፡ ንቅንቅ፣ ብርብር፣ ፍትሽ።

ቅስት: የተቀሰተ፡ በበር፣ በድልድይ ውስጥ የተበጀ የግንብ፣ የሳንቃ ደጋን፣ ቅሥፍ። "(ጥቀ) መቀሰት፡ መደገን፣ መጕበጥ። " "መቀሰቻ፡ መጕበጫ። "

ቅስና: ቄስነት።

ቅሥፈታም: ባለቅሥፈት።

ቅሥፈት: መቅሠፍት፡ መቀሠፍ (ባፍላ፣ በልጅነት መሞት) "በግእዝ ግን ግርፋት ማለት ነው። "

ቅሥፍ: የተቀሠፈ፡ የጐበጠ፣ ቅስት።

ቅረብ: ለጥቅ፣ ተጠጋ።

ቅረብ: ንዳ፣ ውሰድ።

ቅሪላ (ሎች): ከርጥብ የበሬ ቈዳ ጐኑ በስንዝር ልክ ተቀዶ የለፋ፡ ጠፍር በያይነቱ ቅራና መጫኛ ይኾናል።

ቅሪት: የፀነሰች ሴት ደሟ በማሕ (ጥር) የቀረ፡ እርጉዝ።

ቅራሚ: የተቃረመ፡ ያጫጅ ቅሬታ።

ቅራሞ: ዝኒ ከማሁ።

ቅራሪ: የመጠጥ ስም፡ ጠላ ባለቀ ጊዜ የሚጠጣ መናኛ መጠጥ። "አንደኛ፣ ኹለተኛ ቅራሪ" እንዲሉ።

ቅራቅንቦ: እንቶ ፈንቶ፣ ምናምን ዕቃ፡ ኵሳንኵስ፣ ሰባራ ሥንጥር። "ቅላቅንቦ ቢል፡ የቅንቦ ቅል ማለት ይመስላል። "

ቅራተኛ: ባለቅራት፣ ጠባቂ።

ቅራት: ሌሊታዊ ጥበቃ።

ቅራት: ያሞራ ቤት።

ቅራና (ኖች): የቀርቃባ ጠፍር። "በትግሪኛ ግን አንድ ፈርጅ ሸማ ማለት ነው። " "የቅራና ምስጢር እንደ ቀርን (ቀንድ) ኹለት መኾኑን ያሳያል። " "ከቈረኘና ከገረኘም ይሰማማል። " "ቅሪላን፣ ቀረነተን ተመልከት። "

ቅራፊ: የተቀረፈ፡ ንጣይ፣ ልጣጭ።

ቅሬ (ቃረ): ዐጣሪ፣ ዘፋኝ፣ አረኾ (የሴት ወሮ በላ፣ ባለጌ)፡ ማን ዘራሽ፣ መሸተኛ፣ አቅራሪ፣ ጋለሞታ፣ ሴትኛ፣ ዐዳሪ (ሸርሙጣ)፡ ነውር ጌጧ። "የቅሬ ምስጢር የተቃረች ማለት ነው። " "ወለደ ብለኸ ልጅን እይ። " "ቅሬ ለወንድምም ይነገራል። "

ቅሬታ: ተረፍ፣ ትራፊ (ዐብድዩ ፩፡ ፲፰፡ ሶፎንያስ ፪፡ ፲፱)

ቅሬነት: ቅሬ መኾን፡ ዐጣሪነት፣ ጋለሞታነት።

ቅሬዎች: ዐጣሮች፣ አረኾዎች፣ ጋለሞቶች።

ቅር (ቍር): የሽንብራ በሽታ የሚያደርቀው፣ ዐልፎ ዐልፎ ጭብርር የሚያደርገው (አለፍሬ የሚያስቀረው)

ቅር ቅር አለው: ውል ውል አለው።

ቅር አለ: ትዝ አለ፡ ታሰበ፡ በልብ ተጕላላ።

ቅር አለው: ግር አለው፡ ቸገረው።

ቅር: ትዝ፣ ውል። "ቅር ሲላላ አንተ ለሚባል ትእዛዝ ይኾናል። "

ቅር: የቀረረ።

ቅርሚያ: ለቀማ፣ ስብሰባ።

ቅርምቻ: ትንተና፣ ክፍያ።

ቅርምዝ (ዐረ): ቀይ ግምጃ፣ ድኪ፡ ጃዊ (ኢሳይያስ ፩፡ ፲፰)

ቅርምዝ: ቈረኘ።

ቅርሥ: ተቀማጭ ገንዘብ።

ቅርስ: ተቀማጭ ገንዘብ፡ ወይም ከአባት የወረደ፣ ተካባች ብር። "ባረብኛ 'ቅርሽ' ይባላል፡ የብር ክፍልፋይ፣ ታናሽ ገንዘብ፣ 'መሐልቅ' እንደ ማለት ነው። " "ቍሪትን ተመልከት። " "ግርሽና ቅርሽ አንድ ስም ነው። " "ዳግመኛም ብር በትግሪኛ 'ቀርሽ' በጋልኛ 'ቀርሺ' ይባላል። "

ቅርር አለ: ቀረረ።

ቅርርት: ዝኒ ከማሁ።

ቅርሻታም: ቅርሻት ያለበት፣ የሚታይበት፣ የሚበዛበት፡ ኹል ጊዜ የሚቀረሽ ልጅ፣ ትፋታም።

ቅርሻት: እውከት፣ ትፋት።

ቅርሽምሽም አለ: ስብር አለ፡ ተቀረሻሸመ።

ቅርሽምሽም: ስብርብር።

ቅርቀራ: ሽጐራ፣ ውርወራ።

ቅርቃር (ሮች): መዝጊያ እንዳይከፈት በስተውስጥ ኹኖ የሚከለክል ዕንጨት።

ቅርቃር: ሳንቃን ከሳንቃ የሚያገናኝ መስቀልኛ ውሻል፣ ርስ በርሱ የተሳካ።

ቅርቅምቢጥ: ሰቡልጋ ውስጥ ያለ ቀበሌ።

ቅርቅምቢጥ: ቅምምጦሽ፡ ቅልጥፍናን ያሳያል።

ቅርቅር: የተቀረቀረ (ሽጕር)

ቅርቅብ: የተቀረቀበ (ውድን፣ እርት)

ቅርቅፍ: የተቀረቀፈ፡ የግንድ ድቃቂ።

ቅርቅፍት: ደንጊያ የበዛበት ሻካራ መንገድ።

ቅርቢያ: ቀረቤታ፡ ቅርብነት፣ ጎረቤትነት፣ ልነት።

ቅርብ (ቦች): ቅሩብ፡ የቀረበ፣ ሩቅ ያይደለ፡ የተጠጋ፣ በጐን፣ ባጠገብ ያለ። (ተረት): "ሳይርቅ በቅርቡ፣ ሳይደርቅ በርጥቡ። " "ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት። " "(ቀመጠ) ተቀመጠ ብለኸ ተቀማጭን አስተውል። " "በ፣ የ፣ ከ፣ ለ፡ መነሻ እየኾኑት ሲነገር፡ በቅርብ፣ የቅርብ፣ ከቅርብ፣ ለቅርብ ይላል። "

ቅርብ ለቅርብ: ጐን ለጐን፣ አጠገብ ላጠገብ።

ቅርብ ዘመድ: ኹለት ቤት፡ ሦስት ቤት።

ቅርታ: ትዝታ፣ ችግር፣ ዐሳብ፣ አለመደሰት፡ ዐዘን። "አቶ እከሌ በኔ ነገር ቅርታ ገብቶታል። "

ቅርት አለ: ድንገት ትንፋሹ ተቈረጠ፡ ድብን አለ።

ቅርት: ሙትት፣ ዝርግት፣ ዟ፣ ሰተት።

ቅርናታም: ባለቅርናት፣ ግማታም፡ አውራ ፍየል።

ቅርናት: የብብት የተቃጠለ ቈዳና ቍረንጮ፡ ክፉ ሽታ፣ ግማት።

ቅርን: ቀረመት (የሥጋ ክፍያ)፡ በብዙ ወገን ቈርጠው መድበው የሚካፈሉት።

ቅርንት አለ: ግምት አለ።

ቅርንት: መቀርናት።

ቅርንጥሳም: ቅርንጥስ ያለው፣ ባለቅርንጥስ።

ቅርንጥስ: ጨርቅ፣ ጭርንቍስ (የተጠቃቀመ)፡ ዛተሎ፣ ዘባተሎ፣ ንጥስ።

ቅርንጫፍ (ቀርነ፡ ጫፍ፡ ጫፈ፡ ቀርን): እሾኸ፡ የዛፍ ጫፍ (ውልብልቢት) "ቅርን ከቀርን፡ ጫፍ ከጨፈጨፈ መጥቶ አንድ ስም ኹኗል። "

ቅርንፉድ (ዶች): የቅመም ስም፡ ከባሕር የሚመጣ ቅመም። "ባረብኛ ቅርንፉል ይባላል። "

ቅርንፉድ: ታናሽ የጠመንዣ መዘውር።

ቅርደት: ያገር ስም።

ቅርደዳ: ቈረጣ፣ ገመሳ።

ቅርድ (ዐረ፡ ቀርድ): ዝንጀሮ፣ እንዳሞድ።

ቅርድ: የማዥራት ግድ አግዳሚ፡ ሸለቆ፣ ሠርጓዳው፣ ጐድጓዳው።

ቅርድድ: የተቀረደደ፣ የተቈረጠ።

ቅርጠ ቀላል: ቀጪን ሰው፡ ቀትረ ቀላል።

ቅርጠ ቢስ: ቁመናው የማያምር ሰው፡ ቅጠ መጥፎ።

ቅርጠፋ: ቈረጣ።

ቅርጣሽ: ኵስታሪ፡ ቀረጠ።

ቅርጣሽ: የመብራት ቍራጭ (ኵስታሪ)

ቅርጣፊ: የጌሾ፣ የሰንበሌጥ ድቃቂ።

ቅርጥ የለሽ: ቅጥ የለሽ፣ መልከ ቢስ።

ቅርጥ: ቅጥ (አካላዊ ሥራ)፡ መልክ፣ ቁመና፣ ኹኔታ።

ቅርጥ: የተቀረጠ፣ የሾለ፡ "ካህናት ግን ቅርጽ ይላሉ። "

ቅርጥፋት: ቅርጠፋ፣ መቀርጠፍ፡ ክርክራት።

ቅርጥፍ አለ: ተቀረጠፈ።

ቅርጥፍ: የተቀረጠፈ።

ቅርጫሚ: ጥርቃሚ።

ቅርጫት (ቶች): ከመቃ፣ ከቀርክሓ፣ ከክትክታ፣ ከቀጨሞ፣ ከሐረግ የተበጀ ዕቃ፡ ማንኛውንም ነገር መያዣና ማስቀመጫ፡ ሰብል መሰብሰቢያ፡ እኸል መስፈሪያ። "የንጨቱን መቀረጽና ሹለት ያሳያል። "

ቅርጫት: ከንጨት የተበጀ ዕቃ፥ ቀረጠ።

ቅርጫንቀረመት: ቀረጠ።

ቅርጭም: የተቀራጨመ፣ ጥርቅም።

ቅርጭጭ አደረገ: ንክስ ውግት አደረገ፡ ቀረጪው።

ቅርጭጭ: የተቀረጪ፡ ንክስ።

ቅርጭፍት: ዕሩር የቋር ቍራጭ።

ቅርጽ (ጾች): የተቀረጸ፡ ቅርጥ፣ ንጥ፣ ፍልፍል፣ ንቅስ (ደንጊያ፣ ዕንጨት፣ ብረት፣ መዳብ፣ ንሓስ፣ ወርቅ፣ ብር፣ ማንኛውም ማዕድን)

ቅርጽ: የሰው መልክ፣ ምስል፡ ጣዖት።

ቅርፊት (ቅርፍት): ልጥ ያለበትና የሌለበት የንጨት ልብስ፡ ተቀርፎ የወደቀ አለት፣ ምርጊት። "የዳቦ፣ የሮማን ቅርፊት፡ የቍስል ቅርፊት" እንዲሉ።

ቅርፋ: (ቀረፈፈ)

ቅርፋ: ድንብላል።

ቅርፍርፍ ቂጥኝ: ዝኆን ማለት ነው። ተረት: "ዝኆንም ለሆዱ፣ ድምቢጥም ለሆዱ ወደ ወንዝ ወረዱ።"

ቅርፍርፍ አለ: ተቅረፈረፈ።

ቅርፍርፍ: የተቅረፈረፈ፡ ሥንጥቅጥቅ፣ ፍርክርክ።

ቅርፍርፍታ: ቅርፍርፍ ማለት።

ቅርፍርፍነት: ፍርክርክነት።

ቅርፎ: ያንኮላ፣ የቅምጫና ጫፍ ቍራጭ።

ቅሽምድ አለ: ስብር አለ።

ቅሽር: የተቀሸረ (አለባበስ፣ አሳማሪ፣ ክሽን፣ ንፍ)

ቅቀላ: የመቀቀል ሥራ።

ቅቀራ: የመቀቀር ሥራ።

ቅቅላት: የቅቅል ኹኔታ።

ቅቅል ዋጭ: ቅቅልን የሚወድ፣ የሚውጥ።

ቅቅል: የተቀቀለ፣ የበሰለ ሥጋ።

ቅቅታም (ሞች): ሥሥታም፣ ንፉግ፣ ጩቅ ቢስ፣ እጁን ቢሉት የማይወድቀው።

ቅበ፡ ቢስ፡ ክቾ፡ ነገረ፡ ደረቅ፡ ለዛ፡ ቢስ፡ ዕድለ፡ ቢስ።

ቅበላ (ቀበላ)፡ የአርባ፡ ሑዳዴ፡ ዋዜማ፡ እሑድ፡ ቀን፡ የጦም፡ መቀበያ። የሐምሌ፡ ሠላሳኛ፡ ቀንም፡ የፍልሰታ፡ ጦም፡ ቅበላ፡ ይባላል።

ቅቡጭ (ቅቡጽ)፡ ያነሰ፡ የጐደለ።

ቅቡጭ፡ አለ፡ እንስ፡ ጕድል፡ አለ፡ ይበቃል፡ ሲሉት፡ በድንገት፡ ዐለቀ፡ ጠፋ፡ ታጣ።

ቅባቅዱስ (ቅብዕ፡ ቅዱስ)፡ ሜሮን፡ የተቀደሰ፡ ሽቱ፡ ሕፃን፡ የክርስትናው፡ ለት፡ ታቦት፡ በመባረኪያው፡ ቀን፡ የሚቀባው፡ ባገራችን፡ የወይራ፡ ፍልጥ፡ ዘይት፡ ነው።

ቅባታም፡ ቅባት፡ የሚወጣው፡ ባለቅባት፡ ተልባ፡ ኑግ፡ ሰሊጥ፡ ሱፍ፡ ጕሎ፡ ባር፡ ቅል፡ የመሰለው፡ ኹሉ።

ቅባት (ቅብዐት)፡ ቅቤ፡ ዘይት፡ ሞራ፡ ቅልጥም፡ ላት፡ የዶሮ፡ ሥብ፡ ጋዝ፡ የመሰለው፡ ኹሉ።

ቅባት፡ ዕድል፡ ተሰጦ፡ ሀብት፡ ጸጋ።

ቅባት፡ የሃይማኖት፡ ስም፡ ባጤ፡ ሲፋል፡ ዘመን፡ ዕውር፡ ዘኢየሱስ፡ የሚባል፡ ሰው፡ ያወጣው፡ ሃይማኖት። ቤተ፡ ኤዎስጣቴዎስ፡ የቤተ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ ተቃራኒ። የቅባት፡ ባህል፡ በአጭር፡ ቃል፡ ይህ፡ ነው፡ "ቃል፡ ሥጋ፡ ለብሶ፡ ሰው፡ በኾነ፡ ጊዜ፡ (ዜገ)፡ የባሕርይ፡ ክብሩን፡ ዐጣ፡ ለቀቀ፡ ሲቀባ፡ (መንፈስ፡ ቅዱስን፡ ሲቀበል)፡ ግን፡ ተገብሮ፡ ተፈጥሮ፡ ጠፍቶለት፡ በሰውነቱም፡ ባምላክነቱም፡ አንድ፡ ወገን፡ የባሕርይ፡ አምላክ፡ ኾነ"፡ ይላሉ፡ (ኪዳነ፡ ወልድ፡ ክፍሌ)

ቅባቶች፡ በቅባት፡ ሃይማኖት፡ የሚያምኑ፡ "ለዘሐመ፡ ልብ፡ ቃለ፡ ሃይማኖት፡ መድኀኒቱ፡ አኮኑ፡ ቅባት"፡ የሚሉ።

ቅባኑግ፡ ከኑግ፡ የሚወጣ፡ ቅባት፡ ዘይት፡ የጦም፡ ወጥ፡ የሚሠራበት። አወጣጡም፡ ለጥልጦ፡ በማፍላትና፡ በማሸት፡ በፀሓይ፡ ሙቀት፡ ነው። በግእዝ፡ ቅብዐ፡ ንሒጕ፡ ይባላል።

ቅባጥርሴ፡ ትርክም፡ ምናምን፡ ነገር።

ቅቤ፡ ዐንጓች፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ ለቅቤ፡ ጠባሽ

ቅቤ፡ አድርቅ፡ ውርጭ፡ ብርድ።

ቅቤ፡ ከተናጠ፡ ወተት፡ የሚገኝ፡ ውጤት። የረጋ፡ ወተት፡ ቅቤ፡ ይወጣዋል።

ቅቤ፡ ጠባሽ፡ እወደድ፡ ባይ፡ አከንፋሽ፡ ቅቤ፡ መዛኝ፡ "ቅቤ፡ መዛኝ፡ ድርቅ፡ ያወራል"፡ እንዲሉ።

ቅቤው፡ ወጣ (ትግ፡ ጸዐየ)፡ ሽፍታ፡ ኾነ፡ ሰፈፈ።

ቅቤያም፡ ባለቅቤ፡ ብዙ፡ ቅቤ፡ የሚወጣት፡ ላም።

ቅብ (ቅቡዕ)፡ የተቀባ፡ የተለቀለቀ፡ የታደለ፡ የተኰላ። ምሳሌ: "ወርቅ፡ ቅብ"፡ እንዲሉ። ተመልሰኸ፡ ቅብን፡ ተመልከት።

ቅብ (ቅብዕ)፡ ቅቤ፡ የዘይት፡ ዐይነት፡ ኹሉ።

ቅብ፡ የተቀባ፡ ተቀባ።

ቅብል፡ የተቀበሉት።

ቅብር (ቅቡር)፡ የተቀበረ፡ የተደፈነ።

ቅብር፡ አለ፡ ድፍን፡ አለ፡ ተቀበረ።

ቅብር፡ አደረገ፡ ድፍን፡ አደረገ፡ ቀበረ።

ቅብርር፡ ቀብራራ።

ቅብርር፡ አለ፡ ተንቀባረረ።

ቅብቀባ፡ ዕየማ፡ ቅጥቀጣ፡ ችከላ።

ቅብቃብ (ቦች)፡ ደረቅ፡ ዕንጨት፡ ችካል፡ ካስማ፡ የከብት፡ የመሠረት፡ ገመድ፡ ጠፍር፡ ማሰሪያ፡ የድንኳን፡ አውታር፡ መሳቢያ፡ መወጠሪያ፡ (ዘኍልቍ ፲፮፴፪)

ቅብቅብ (ቦች)፡ የተቀበቀበ፡ የታረሰ፡ ለስላሳ፡ ዕርሻ። (ተረት)"አፍና፡ ቅብቅብ፡ ኹል፡ ጊዜ፡ እያበላም። "

ቅብቅብ፡ የተተከለ፡ የተቸከለ፡ እመሬት፡ የገባ፡ ቅብቃብ፡ ችክል።

ቅብቅቦ፡ በጨው፡ የታጀለ፡ የማሽላ፡ እሸት፡ በድብዳብ፡ የተሸፈነ።

ቅብትት፡ አለ፡ ንፍት፡ ውጥር፡ አለ።

ቅብትት፡ አደረገ፡ እጅግ፡ በጣም፡ ቀበተተ።

ቅብትት፡ የተቀበተተ፡ የተነፋ፡ የተወጠረ፡ ንፍ፡ ውጥር፡ ንርት።

ቅብንን፡ አለ፡ ንፍት፡ ውጥር፡ አለ፡ ተቀበነነ።

ቅብንን፡ የተቀበነነ፡ ንፍ፡ ውጥር፡ ሆድ፡ ዳቦ።

ቅብዐ፡ መንግሥት፡ የመንግሥት፡ ቅባት፡ ንጉሥና፡ ንግሥት፡ ተቀብተው፡ የሚነግሡበት።

ቅብዐ፡ ክህነት፡ የክህነት፡ ቅባት፡ ካህንና፡ ጳጳስ፡ ተቀብተው፡ የሚሾሙበት፡ ዘይት።

ቅብዝብዝ፡ አለ፡ ተቅበዘበዘ፡ (ኢዮብ ፲፭፳፭)

ቅብዝብዝታ፡ ቅብዝብዝ፡ ማለት፡ ብክነት።

ቅብዥርዥር፡ ውዥብርብር።

ቅብጠት (ቅብጸት)፡ ዝላይ፡ ጨዋታ፡ ልፊያ፡ ድሪያ፡ ከጨዋ፡ ደንብ፡ የተለየ፡ ሥራ፡ ያለቀ።

ቅብጢ (ቅብጣዊ)፡ የቅብጥ፡ ቋንቋ፡ ጥንታዊ፡ የምስር፡ ልሳን፡ ፊደሉ፡ ከጽርእ፡ ፊደል፡ አንድነት፡ ያለው። ቅብጥ፡ ከጽርእ፡ የሚለየው፡ ፡ ፊደል፡ ሲጨምር፡ ነው። ሌላም፡ ሄሮግሊፍ፡ የሚባል፡ የተቀደሰ፡ ሥዕላዊ፡ ፊደል፡ በግብጽ፡ ነበረ።

ቅብጢ፡ ቀበጥ፡ ቀበጢና፡ ሴት። ዘሩ፡ ቀበጠ፡ ነው።

ቅብጢ፡ ቅብጣዊ፡ የቅብጥ፡ ግብጻዊ፡ የግብጽ፡ ሰው።

ቅብጥ (ቀቢጽ)፡ መቅበጥ።

ቅብጥ፡ አለ፡ ፍንድቅ፡ አለ፡ ፈጽሞ፡ ቀበጠ።

ቅብጥ፡ ግብጽ፡ ምስር። ፡ ለ፡ ለ፡ መለወጡን፡ አስተውል። ኹለቱም፡ በግእዝ፡ መጽሐፍ፡ ይገኛል። ግብጥን፡ እይ።

ቅብጥርጥሬ፡ የቅብጥርጥር፡ ዐይነት።

ቅብጥርጥር፡ ልፍለፋ፡ ዝብዝብ፡ ሰበብ።

ቅብጥና፡ ቀበጥነት፡ ፍንደቃ።

ቅብጥጥ፡ አለ፡ ቅብትት፡ አለ።

ቅብጥጥ፡ የተቀበጠጠ።

ቅትር አለ: ውጥር አለ።

ቅትር አለ: ውጥር አለ

ቅትርት (ቶች): በሞፈርና በድግር ውስጥ የተቀረቀረች ቅርቃር። "የመንኰራኵር ብረት፡ ወይም ዕንጨት መወጠሪያ መሳይ (፩ኛ ነገሥት ፯፡ ፴፫)"

ቅትርት (ቶች): በሞፈርና በድግር ውስጥ የተቀረቀረች ቅርቃር "የመንኰራኵር ብረት፡ ወይም ዕንጨት መወጠሪያ መሳይ (፩ኛ ነገሥት ፯፡ ፴፫)"

ቅትት: መቃተት። ቅትት ቅትት አለ: ትንፍስ ትንፍስ አለ። "ቃታን እይ። "

ቅነሳ: የመቀነስ ሥራ።

ቅነፋ: ዐጠፋ፣ ምለሳ፣ ሽብለላ።

ቅናሽ: ከጠላ የተቀነሰ ዐሠር ውሃ ሰለልታ።

ቅናተ ኤልያስ: የኤልያስ መታጠቂያ።

ቅናተ ዮሐንስ: የዮሐንስ መጥምቅ መታጠቂያ።

ቅናተኛ፡ ቀናተኛ፡ ቅናት፡ ያደረበት።

ቅናት(ቅንአት)፡ ክፉ፡ ምኞት፡ ምቀኝነት፡ ሌላው፡ ሠርቶ፡ እንዳይጠቀምና፡ እንዳይመሰገን፡ የመቃወም፡ ሐሳብ፡ (ሮሜ ፲፫፡ ፲፫) "ጌታችን፡ አልዓዛርን፡ ከመቃብር፡ ባስነሣው'ጊዜ፡ ፈሪሳውያን፡ ቅናት፡ ዐደረባቸው። "

ቅናት፡ መታጠቂያ።

ቅናት አደረገ: አበከረ።

ቅናት፡ የዜማ፡ ምልክት።

ቅናት: መነኵሴ፣ ባሕታዊ ወገቡን የሚጠልፍበት፣ ዐንገቱን የሚያገባበት፣ በደረት በኩል መስቀልኛነት ያለው ሰንሰለት ጠፍር፡ ጌታችን የታሰረበት ገመድ ምሳሌ።

ቅናት: ምቀኝት፣ ቀና።

ቅናት: በኮርቻ መካከል በቀኝ በኩል የተሰፋ ጠፍር ነት ወይም ባሕር ዐረብ የለበሰ፣ በጫፉ ዘለበት ያለበት፡ በፈረስ፣ በበቅሎ፣ በግመል፣ በአህያ ሆድ ላይ ከቀኝ ወደ ግራ በመለብለቢያ ከመቀነቻ ጋራ የሚገጥም።

ቅናት: ትጥቅ (ኢዮብ ፲፪፡ ፲፰፡ ፳፩)

ቅናት: የመነኵሴ መታጠቂያ፡ ከተንቤን፣ ከባሕር ዐረብ የተበጀ። "(ቅናትና ቅንአት በግእዝ ልዩዎች ሲኾኑ ባማርኛ ይተባበራሉ። "

ቅናዋት፡ ችንካሮች፡ ምስማሮች።

ቅናዋት፡ የዜማ፡ መዝሙር፡ መስቀል፡ ነክ፡ ሰው፡ ሲሞትና፡ ቅዳሜ፡ ቀን፡ የሚባል።

ቅናጅ፡ የባሪያ፡ ስም፡ የፍናጅ፡ ልጅ፡ ፫ኛ፡

ቅናጥ፡ ጐሣ፡ ደሳ፡ የዘላን፡ ጐዦ፡ ልብስ።

ቅኔ(ዎች)፡ የድርሰት፡ ስም፡ ክፍሉና፡ ስሙ፡ ፲፫፡ የኾነ፡ የግእዝ፡ ግጥም፡ ሲሰሙት፡ ደስ፡ የሚያሠኝ፡ እጅግ፡ የሚጥም፡ ኹል፡ ጊዜ፡ ዐዲስ፡ (መዝሙር ፺፮፡ ፳) "መጽሐፈ፡ ቅኔ፡ ተመልከት። " "ዘርፍና፡ ተሳቢ፡ ኹኖ፡ ሲነገር። "

ቅኔ፡ ማሕሌት(ማሕሌተ፡ ቅኔ)፡ በቤተ፡ ክሲያን፡ ውስጥ፡ ያለ፡ ምዕራባዊ፡ ክፍል፡ ደብተሮች፡ ማሕሌት፡ የሚቆሙበት፡ ቅኔ፡ የሚቀኙበት፡ የቅኔ፡ ወረብ፡ ግጥም፡ ዘፈን፡ (ምስጋና)፡ የሚያሰሙበት፡ ስፍራ። "ቅኔ፡ የማሕሌት፡ ዘርፍ፡ መኾኑን፡ አስተውል። " "ቅኔ፡ እንደ፡ ግእዙ፡ መገዛት፡ ተብሎ፡ ቢተረጐም፡ ካህናት፡ ለፈጣሪ፡ በማሕሌት፡ የሚገዙበት፡ ያሠኛል። "

ቅኔ፡ ሰጠ፡ ተቀኘ፡ አበረከተ።

ቅኔ፡ ቈንቋኔ፡ የተማሪን፡ ሰውነት፡ እንደ፡ ቅንቅን፡ እንደ፡ ነቀዝ፡ የሚጐዳ፡ ማለት፡ ነው "ቅኔ፡ ቈንቋኔን፡ ድጓ፡ ዶግዷጌን፡ አያምጣብን፡ እያሉ፡ ይጸልዩና፡ ያሳርጉ፡ ነበር፡ ይባላል፡ የጥንት፡ የጕራጌ፡ ወይም፡ የአገው፡ ቄሶች። "

ቅኔ፡ ቈጠረ፡ ዐሰበ፡ አዘጋጀ።

ቅኔ፡ ቤት(ቤተ፡ ቅኔ)፡ የቅኔ፡ ትምርት፡ ቤት።

ቅኔ፡ ነጋሪ፡ ቅኔ፡ አስተማሪ።

ቅኔ፡ ዐዋቂ፡ ሲቀኝ፡ ይበል፡ ወሰው፡ መልካም፡ የሚያሠኝ፡ ሊቅ፡ ቅኔ፡ የሚያውቅ።

ቅኔ፡ ዘረፈ፡ ሳይቈጥር፡ ተቀኘ።

ቅኔ: "መንፈቆ ከደነ ሣዕረ ገርጀሞ፡ ወመንፈቆ ኀደግነ ለከርሞ። "

ቅን(ኖች)፡ ቅኑእ፡ ቅኑይ፡ ርቱዕ)፡ የቀና፡ የተገዛ፡ ታዛዥ፡ ፈቃደኛ፡ ገር፡ ትሑት፡ ደግ፡ ሰው፡ (ዘዳግም ፳፭፡ ፩። ምሳሌ ፪፡ ፰፡ ፯)

ቅን: ገር ታዛዥ ተዋራጅ

ቅንሳት: ጕድለት፣ ሕጸጽ።

ቅንስ: ዝኒ ከማሁ፡ ከላዩ ተነሥቶለት የጐደለ፣ ጐደሎ።

ቅንቀና: ምርመራ፣ ፍተሻ፣ ቅኚት፣ ሙሾ።

ቅንቅናም (ሞች): ሥሥታም፣ ንፉግ።

ቅንቅን (ኖች) (ቍንቍኔ): የተንቀሳቃሽ ስም፡ ከጤፍ የሚያንስ የዶሮና ያልጋ ተባይ።

ቅንቅን: ሥሥት፣ ንፍገት።

ቅንቅን: በገላ ላይ የሚፈስ ረቂቅ ዕከክ። "ክሽክሽትን እይ። "

ቅንቅን: ነቀዝ (ምሳሌ ፲፪፡ ፬)

ቅንቡርስ(ሶች) የትል፡ ስም፡ ርጥበት፡ ባለው፡ ጕድፍ፡ ውስጥ፡ የሚገኝ፡ ነጭ፡ ትል። "ንን፡ ጣልቃ፡ ስን፡ ምእላድ፡ አድርጎ፡ (ቅቡር)፡ የተቀበረ፡ ተብሎ፡ ይተረጐማል። "

ቅንባ፡ ቍንጠራ።

ቅንብር፡ አለ፡ ቀነበረ።

ቅንብርብር፡ አለ፡ ተቀነባበረ።

ቅንብርብር፡ የተቀነባበረ፡ ክውንውን።

ቅንብቢት፡ ክብ፡ ተራራ፡ ያለበት፡ አገር፡ ስም፡ በቡልጋ፡ አጠገብ፡ ይገኛል። "ቅንብቢት፡ የተቀነበበች፡ ማለት፡ ነው። "

ቅንብብ፡ የተቀነበበ፡ የተከበበ፡ የሕፃን፡ ርግብግቢት፡ ጠጕር።

ቅንብቻ(ቾች)፡ የተረሳና፡ ትርፍ፡ ዕቃ፡ ማስቀመጫ፡ ማኖሪያ፡ ከቈዳ፡ የተሰፋ፡ መናኛ፡ ኰረጆ፡ አፈ፡ ክፍት፡ ስፌት።

ቅንብቻ፡ ሆድ፡ ሆደ፡ ጕስር፡ ሰው።

ቅንቦ(ዎች)፡ ወተታም፡ የቈላ፡ የ በረሓ፡ ዕንጨት። "የፍሬው፡ እንቡጥ፡ ቅል፡ ያካክላል፡ በውስጡም፡ ነጭ፡ ሐር፡ የሚመስል፡ ባዘቶ፡ ይገኝበታል ኹለተኛ፡ ስሙ፡ ጦቢያ፡ ይባላል። " "ወተቱም፡ እውሃ፡ ውስጥ፡ ጠብ፡ አድርጎ፡ ሲቀምሱት፡ ለመጋኛ፡ መድኀኒት፡ ይኾናል፡ ቅንቦ፡ ማለት፡ ቀልጣማነቱን፡ ያሳያል። "

ቅንት (ቅኑት): የቀነተ፣ የታጠቀ። "ቅንት እንደ ገበሬ፣ ጥምድ እንደ በሬ" እንዲሉ።

ቅንነት(ርትዐት)፡ ቅን፡ መኾን፡ ፈቃደኛነት ' ታዛዥነት፡ ትሕትና፡ (፩ኛ ዜና መዋዕል ፳፱፡ ፲፯)

ቅንዘፋ፡ ምልመላ።

ቅንዝረኛ(ኞች)፡ ሴሰኛ፡ አመንዝራ፡ ወንድ፡ ወይም፡ ሴት።

ቅንዝር፡ ምንዝር፡ ሴሰን፡ ከልክ ያለፈ፡ ዝሙት።

ቅንዝርና፡ ሽርሙጥና፡ ምንዝርና።

ቅንዝፍ፡ ቅንዝፍ፡ አለ፡ ፍስስ፡ ፍስስ፡ አለ፡ እንባው።

ቅንዝፍ፡ አለ፡ ፍስስ፡ አለ።

ቅንዝፍ፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ የታረደ፡ የፈሰሰ።

ቅንደላ፡ ብጥታት፡ ቈረጣ።

ቅንደባ፡ ምት።

ቅንድብ(ቦች)፡ ነፋስና፡ ውሃ፡ ጪስ፡ የማያስገባ፡ ያይን፡ መክደኛ፡ መሸፈኛ፡ ቈርበቱ፡ ቈዳው፡ በላይ፡ በታች፡ ያለው፡ በግእዝ፡ ቅርንብ፡ ይባላል፡ (መዝሙር ፲፩፡ ፬። ፻፴፪፡ ፬) "ቅንድቤ'ርግብ፡ ርግብ፡ ይላል፡ እንዲል፡ ባላገር። "

ቅንድብ፡ መሸለል፡ ማጋጠም፡ ማገናኘት፡ ኵልን፡ ሲኳሉ፡ ወይም፡ ትክክል፡ ያልኾነ ውን፡ ያይን፡ ቅንድብ፡ በስፌት፡ ማስተካከል።

ቅንድብ፡ ሸፋሽፍት፡ በቅንድብ፡ ጠርዝ፡ ያለ፡ ጠጕር፡ ጭፋር፡ ያይን፡ ዐጥር፡ ጨፈቃ። "ቅንድቤ፡ ተሰብሮ፡ ዐይኔ፡ ውስጥ፡ ገባ። "

ቅንድብ፡ የሽፋል፡ ጠጕር፡ (ዘሌዋውያን ፲፬፡ ፱)

ቅንድብ፡ የተቀነደበ፡ የተመታ።

ቅንጁ፡ የተቀናጀ፡ ሌላ፡ ኹለተኛ፡ በሬ፡ ቀንጃ፡ ከቀንጃ፡ ጋራ፡

ቅንጠባ፡ ቈረጣ፡ ብጠሳ፡ ቅንጠሳ።

ቅንጡ(ዎች)፡ የተቀናጣ፡ የጠገበ፡ ቅምጥል።

ቅንጣት(ቶች)፡ አንድ፡ ፍሬ፡ (ማቴዎስ ፲፫፡ ፴፩)

ቅንጣት: አንድ ፍሬ። ቀነጣ።

ቅንጥ፡ ድሪያ፡ ልፊያ።

ቅንጦተኛ፡ ጥጋበኛ፡ እብሪተኛ።

ቅንጦት፡ ጥጋብ፡ እብሪት፡ ቅምጥልነት።

ቅንጦት: ጥጋብ፣ ቀነጣ።

ቅንጫቢቅንጭብ፡ የተቀነጨበ፡ ቍንጥር፡ ጥቂት፡ ነገር።

ቅንጭብ(ቦች)፡ የንጨት፡ ስም፡ በቈላ፡ በበረሓ፡ አገር፡ የሚበቅል፡ አነስተኛ፡ ዛፍ፡ ወተታም።

ቅንጭብ፡ አደረገ፡ ቀነጨበ፡ ቅንጭብን፡ ወይም፡ ሌላ፡ ነገርን።

ቅንፋት: ዕጥፋት፣ ቅልብሳት።

ቅንፍ: የፊደል፣ የቃል ማጠሪያ፣ መክበቢያ ()

ቅኝት፡ የበገና፡ ዥማት፡ መጥበቅ፡ መላላት፡ መቃናት፡ መሰማማት።

ቅዘናም (ሞች)፡ ኹል፡ ጊዜ፡ የሚቀዝን፡ ፈሪ፡ ጡርቂ። (የልጅ፡ ቅዘን)፡ ዐይን፡ አበባ፡ ብጫ፡ ጥለት። (የልጅ፡ ቅዘን፡ ይንካልኸ)፡ ሰው፡ ዐዲስ፡ ልብስ፡ በለበሰ፡ ጊዜ፡ የሚቀበለው፡ ምርቃት።

ቅዘን፡ ተቅማጥ፡ ሻታ።

ቅዘን፡ የቅርብ፡ ወንድ፡ ትእዛዝ፡ አንቀጽ።

ቅዛዛ፡ ቅዛዝ፡ መስተዋት።

ቅዝምዝም፡ የተቅዘመዘመ፡ ምዝግዝግ፡ እንዝግዝግ፡ ውዝግዝግ። ባላገር፡ ግን፡ ቅዝምዝም፡ በማለት፡ ፈንታ፡ ቅምዝምዝ፡ ይላል።

ቅዝቃዜ፡ ብርድ።

ቅዝታ፡ ቅርታ፡ ታናሽ፡ ሕጸጽ።

ቅዝዝ፡ አለው፡ ቅፍፍ፡ አለው።

ቅዝፊያ፡ ዝኒ፡ ከማሁ።

ቅዠታም (ሞች)፡ የቃዠ፡ የሚቃዥ፡ ባለቅዠት፡ ራሰ፡ ቢስ።

ቅዠት፡ የሕልም፡ ጩኸት፡ ከንቱ፡ እይታ።

ቅየማ፡ ቅያሜ፡ ኵርፊያ።

ቅየሳ፡ ቅይሳት፡ የመቀየስ፡ ሥራ፡ ብገራ፡ ምጠና።

ቅየራ፡ ቅያሬ፡ ቅይራት፡ ልወጣ፡ ውላጤ።

ቅየዳ፡ ምከታ፡ እሰራ፡ ስከላ፡

ቅየጣ፡ ቅልቀላ፡ ድብለቃ፡ ዝነቃ።

ቅያስ፡ ልክ፡ መጠን፡ ንድፍ፡ ቢጋር፡ ካርታ።

ቅይም፡ አለ፡ ተቀየመ።

ቅይም፡ የተቀየመ።

ቅይስ፡ የተቀየሰ፡ ቦታ፡ መንገድ፡ መሬት።

ቅይር፡ የተቀየረ፡ የተዛወረ፡ ልውጥ።

ቅይዳት፡ መከታ፡ ግርዶ፡ ሰካላ፡ እስራት፡

ቅይድ፡ የተቀየደ፡ የተከፈለ፡ የተመከተ፡ ስክል፡ አፈ፡ እስር፡ ድዳ።

ቅይጥ(ጦች)፡ የተቀየጠ፡ ዝንቅ፡ ቅልቅል፡ ድብልቅ፡ ውጥንቅጥ፡ የወፍጮ፡ የልመና፡ እኸል፡ ዲቃላ።

ቅደም፡ ተከተል፡ ፊትና፡ ኋላ፡ ኹን።

ቅደም፡ የቅርብ፡ ወንድ፡ ትእዛዝ፡ አንቀጽ፡ "ኺድ፡ ዕለፍ"

ቅደሳ፡ የመባረክ፡ የማመስገን፡ ሥራ።

ቅዱሰ፡ ቅዱሳን፡ የቅዱሳን፡ ቅዱስ፡ የካህናት፡ አበል፡ (ዘሌዋውያን፡ ) ከዚህም፡ በቀር፡ ቅዱስ፡ ከስም፡ አስቀድሞ፡ እየገባ፡ በቅጽልነት፡ ሲነገር፡ ቅዱስ፡ ገብርኤልቅዱስ፡ ጊዮርጊስቅዱስ፡ ዮሐንስቅዱስ፡ ሚካኤልቅዱስ፡ ጳውሎስቅዱስ፡ ጴጥሮስ፡ ይላል።

ቅዱሳት፡ ንጹሓት፡ ቡሩካት፡ ሴቶች።

ቅዱሳት፡ አንስት፡ ጌታችን፡ በዚህ፡ ዓለም፡ ሳለ፡ እሱን፡ የተከተሉና፡ በገንዘባቸው፡ ያገለገሉት፡ ፴፡ ሴቶች።

ቅዱሳን፡ አማልክት፡ ሥላሴ፡ (ዳንኤል ፲፩)

ቅዱሳን፡ የተቀደሱ፡ ንጹሓን፡ ቡሩካን፡ መላእክት፡ ጻድቃን።

ቅዱስ፡ መጽሐፍ፡ ብሉይና፡ ሐዲስ፡ ኪዳን። "መጽሐፍ፡ ቅዱስ"፡ ቢል፡ ስሕተት፡ ነው።

ቅዱስ፡ በቁሙ፡ ልዩ፡ የተቀደሰ፡ የተባረከ፡ የነጻ፡ የበቃ፡ ቡሩክ፡ ንጹሕ፡ ምስጉን።

ቅዱስ፡ ባለጌ፡ የተለየ፡ ልዩ፡ ባለጌ።

ቅዱስ፡ ከላይ፡ ጥርስ፡ የሌለው፡ የሚያመሰኳ፡ ጥፍረ፡ ሥንጥቅ፡ የቤትና፡ የዱር፡ እንስሳ፡ ሥጋው፡ የሚበላ።

ቅዱስ፡ የርኩስ፡ ተቃራኒ።

ቅዱስ፡ የኪዳን፡ መዠመሪያ፡ "ሳይደወል፡ ቅዱስ"፡ እንዲሉ።

ቅዱስጌ፡ በቡልጋ፡ አውራጃ፡ ያለ፡ አገር፡ የተቀደሰ፡ ምድር፡ ወይም፡ (ጌቅዱስ)፡ አንድ፡ ቅዱስ፡ የኖረበት፡ የጸለየበት፡ የሰበከበት፡ የቅዱስ፡ አገር፡ ምድር፡ ማለት፡ ነው፡ ነገር፡ ግን፡ ምድር፡ የምትነገረው፡ በሴት፡ አንቀጽ፡ መኾኑን፡ አስተውል።

ቅዳሜ (ቀዳም)፡ የሰባተኛ፡ ቀን፡ ስም፡ ሰባተኛው፡ ቀን፡ በእረፍትነት፡ ከእሑድ፡ ስለ፡ ቀደመ፡ ቅዳሜ፡ ተባለ፡ እንጂ፡ ቅዳሜ፡ መባል፡ የሚገባው፡ ለእሑድ፡ ነበር።

ቅዳሜ፡ ሹር፡ የስቅለት፡ ማግስት፡ የሚውለው፡ ቅዳሜ፡ ወፍጮ፡ ስለሚፈጭበትና፡ ሌላም፡ ለፋሲካ፡ የሚኾን፡ ሥራ፡ ስለሚሠራበት፡ ቅዳሜ፡ ሹር(የተሻረ፡ ቅዳሜ)፡ ተባለ። ውስጠ፡ ምስጢሩ፡ ግን፡ ክርስቲያኖች፡ በዘመነ፡ ሐዲስ፡ በቅዳሜ፡ ፈንታ፡ እሑድን፡ ማክበራቸውን፡ ያሳያል። ይኸውም፡ የተዠመረው፡ በታላቁ፡ ቈስጠንጢኖስ፡ ዘመን፡ ነው።

ቅዳሴ (ጥደ) መቀደስ(ጥቀ) መቀደስ፡ ቅደሳ፡ ምስጋና።

ቅዳሴ፡ ሰማ፡ አደመጠ፡ (አስቀደሰ)

ቅዳሴ፡ ቤት፡ የቤት፡ ቅደሳ፡ ምረቃ፡ ኅዳር፡ ፯፡ ቀን፡ የጊዮርጊስ፡ ቅዳሴ፡ ቤቱ፡ ነው። መስከረም፡ ፲፯፡ ቀን፡ የመስቀል፡ ቅዳሴ፡ ቤቱ፡ ይከበራል።

ቅዳሴ፡ ታጐለ፡ ሳይቀደስ፡ ቀረ፡ ተዳፈነ።

ቅዳሴ፡ የመጽሐፍ፡ ስም፡ በንባብና፡ በዜማ፡ የሚጸለይ፡ የቍርባን፡ ጸሎት፡ የቂሳርያው፡ ባስልዮስና፡ ሌሎችም፡ ጳጳሳት፡ ያዘጋጁት፡ ድርሰት። (ፈራ) ፈረየ)፡ ብለኸ፡ ፍሬን፡ እይ።

ቅዳሴ፡ ገባ፡ ዠመረ፡ ወጠነ፡ ቅዳሴን።

ቅዳሴ፡ ጠበል፡ ማየ፡ መቍረርት፡ ቅዳሴ፡ ውጭ፡ የሚጠጣ፡ የቅዳሴ፡ ጠበል።

ቅዳዴ፡ የብጫ፡ ጣቃ፡ ቅዳጅ፡ ወታደሮች፡ በራሳቸው፡ ላይ፡ የሚያስሩት፡ የሚቀዳጁት። አቡቅዳዴ፡ እንዲሉ።

ቅዳዶቴ፡ የኔ፡ ሸማ፡ ቅዳጅ።

ቅዳዶት፡ ዝኒ፡ ከማሁ።

ቅዳጅ (ጆች)፡ የሸማ፡ የበርኖስ፡ የደበሎ፡ ሥንጣቂ፡ ትልታይ። ምሳሌ: "ዐዋጅ፡ ዐዋጅ፡ የደበሎ፡ ቅዳጅ"፡ እንዲሉ።

ቅዴታ፡ ያዢር፡ ዕዳ፡ ባላገር፡ እያዋጣ፡ ለሹም፡ የሚከፍለው፡ ፈሰሴ።

ቅድ፡ ሸፋሽፍት። ምሳሌ: "ያይን፡ ቅድ"፡ እንዲሉ። (ዮሐንስ፡ ቅድ)፡ ዐጤ፡ ዮሐንስ፡ ይታጠቁት፡ የነበረ፡ ሱሪ።

ቅድ፡ በከፊል፡ የተጻፈ። ምሳሌ: "ቅድ፡ ድጓ፡ ቅድ፡ ወንጌል፡ እንዲሉ። "

ቅድ፡ አፍ፡ ወሬኛ፡ እንዳገኘ፡ የሚናገር።

ቅድ፡ የተቀደደ፡ ቀደደ።

ቅድ፡ የተቀደደ፡ የተሸረከተ፡ ሽርክት።

ቅድሙንቅድሙኑ፡ ፊቱን፡ ፊቱኑ።

ቅድሚያ (ቅድመት፡ ቅድምና)፡ ዥመራ፡ ፍለማ።

ቅድም፡ አያት፡ የወንድና፡ የሴት፡ አያት፡ አባትና፡ እናት፡ (እሚታ)

ቅድም፡ ከጥቂት፡ ሰዓት፡ ከአኹን፡ በፊት። ምሳሌ: "አቶ፡ እከሌ፡ ቅድም፡ መጥቶ፡ ኼደ። "

ቅድሳት፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ ጸጋ፡ ክብር፡ ቍርባን። ንዋይን፡ ተመልከት።

ቅድስተ፡ ቅዱሳን፡ ከቅዱሳን፡ ይልቅ፡ የተቀደሰች፡ ከከበሩ፡ የከበረች፡ መቅደሰ፡ ኦሪት። ቅድስት፡ ፳ው፡ ክንድ፡ ቅዱሳን፡ የተባሉት፡ እንደ፡ ቅድስት፡ ያሉት፡ ፵ው፡ ክንድና፡ እንደ፡ ቅኔ፡ ማሕሌት፡ ናቸው። በግእዛዊት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ግንቡ፡ (ግድግዳው)፡ የ፫ነት፡ ጣራው፡ የ፩ነት፡ ምሳሌ፡ ነው።

ቅድስት፡ ሥላሴ፡ የተቀደሰች፡ ሦስትነት።

ቅድስት፡ የቤተ፡ ክርስቲያን፡ ኹለተኛ፡ ክፍል።

ቅድስት፡ የተቀደሰች፡ የተባረከች፡ ንጽሕት። ምሳሌ: "ቅድስት፡ ሐናቅድስት፡ ማርያምቅድስት፡ አርሲማ"፡ እንዲሉ።

ቅድስት፡ የአርባ፡ ሑዳዴ፡ ኹለተኛ፡ እሑድ፡ ወይም፡ ሳምንት።

ቅድስና፡ ቅዱስነት፡ ንጽሕና።

ቅድድ፡ አለ፡ ሽርክት፡ አለ።

ቅድጁ (ቅድው)፡ የተቀዳጀ፡ ካህን፡ ንጉሥ፡ የተቀዳጀች፡ ንግሥት፡ ልጃገረድ።

ቅድጅት፡ ያክሊል፡ ያበባ፡ አደራረግ።

ቅጅ (ቅዱሕ)፡ የተቀዳ፡ የተገለበጠ፡ የተጨመረ። ምሳሌ: "አንድ፡ ጋን፡ ቅጅ"፡ እንዲሉ።

ቅጅ (ቅድሕ)፡ የጠላ፡ የጠጅ፡ የማንኛውም፡ መጠጥና፡ ዘይት፡ ቅቤ፡ ውጤት። የፊተኛው፡ ቅጽል፡ የኋለኛው፡ ስም፡ ጥሬ፡ መኾኑን፡ አስተው።

ቅጅ፡ ጽፈት፡ ግልባጭ፡ (ዕዝራ ፲፩፡ አስቴር )

ቅጠ፡ መልካም፡ ቅጡ፡ (ኹኔታው)፡ ያማረ፡ የሰመረ።

ቅጠ፡ ቢስ፡ ቅጠ፡ መጥፎ፡ የማያምር፡ ሰው።

ቅጠለ፡ ወርቅ (ቈጽለ፡ ወርቅ)፡ ከወርቅ፡ የተሠራ፡ የወርቅ፡ ቅጠል።

ቅጠለ፡ ወርቅ፡ በወረቀት፡ ተጠቅሎ፡ የሚጠጣ፡ ትንባኾ፡ ወርቅ፡ የሚያወጣ፡ ቅጠል፡ ማለት፡ ነው።

ቅጠላ፡ ጭመራ፡ እከላ።

ቅጠላም፡ ቅጠለ፡ ብዙ፡ ባለቅጠል

ቅጠላቅጠል፡ የቅጠልቅጠል፡ ብዙ፡ ዐይነት፡ ቅጠል

ቅጠላዊ፡ የቅጠል፡ መልክ፡ ቀለመ፡ ቅጠል

ቅጠል (ሎች፡ ቈጽል)፡ በእኸልና፡ በተክል፡ በዛፍ፡ ዐጽቅ፡ ላይ፡ የሚወጣ፡ ልምላሜ፡ ብዙ፡ ዐይነት፡ መልክና፡ ሕብር፡ ያለው። (ተረት): "ፍየል፡ ከመድረሷ፡ ቅጠል፡ መበጠሷ። "

ቅጠል፡ ዦሮ፡ በቅጠል፡ አምሳል፡ የተሠራ፡ ዕቃና፡ ጌጥ፡ የጦር፡ ብረት።

ቅጠል፡ የለሽ፡ ለዛ፡ ቢስ፡ ንግግሩ፡ ጣም፡ የሌለው፡ ሰው።

ቅጠል፡ የታጠፈ፡ ብራና፡ ወረቀት።

ቅጠልማ፡ ዝኒ፡ ዓዲ፡ ከማሁ።

ቅጠልያ፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ ቅጠል፡ የሚመስል።

ቅጠባ፡ ክንዳታ፡ ምጠና፡ ምልከታ፡ ክሰላ።

ቅጣተኛ፡ ቅጣት፡ የተቀበለ።

ቅጣት (ቅጽዐት)፡ መቅጣት፡ መቀጣት፡ ግርፋት፡ እስራት።

ቅጣት (ቅጽዓ)፡ ትእዛዝ፡ አንቀጽ። ምሳሌ: "አንተ፡ ሰው፡ ይህች፡ ሴት፡ አጥፍታለችና፡ ቅጣት "

ቅጣት: መከራ ሥቃይ መቅሰፍት አደጋ (ሔኖ ፲፭፡ ፴፱)

ቅጣጥይ፡ በመጨረሻ፡ የሚወጣ፡ መንጋጋ።

ቅጣፊ፡ የቅጠል፡ ቍራጭ፡ ቅንጣቢ።

ቅጤ፡ የቅጥ፡ (የሰይጣን)፡ ዐይነት፡ ወገን፡ የተቀጣ፡ እባብ። ምሳሌ: "አንድስ፡ ቅጤ"፡ እንዲሉ። እባብ፡ ቅጤ፡ መባሉ፡ በርገማን፡ እግሩን፡ ዐጥቶ፡ በደረቱ፡ ስለ፡ መኼዱ፡ ነው፡ (ዘፍጥረት ፲፬)

ቅጥ (ቅጹዕ)፡ የተቀጣ፡ የተቈረጠ።

ቅጥ፡ ሥርዐት፡ ደንብ፡ አገባብ፡ ትክክል፡ ልክ፡ (ምሳሌ ፲፩፳፬) ምሳሌ: "በቅጥ፡ አለቅጥ፡ ሠራ"፡ እንዲሉ።

ቅጥ፡ ሽልት፡ ቀጠጠ።

ቅጥ፡ ዐይነት፡ ኹኔታ፡ ምሳሌ። ምሳሌ: "ሀዘንሽ፡ ቅጥ፡ ዐጣ፡ ከቤትሽም፡ አልወጣ፡ የገደለው፡ ባልሽ፡ የሞተው፡ ወንድምሽ " "ቅጡም፡ የምንኵስና፡ ነው"፡ እንዲሉ።

ቅጥ ዐጣሽ: የወፍ ጩኸት።

ቅጥ፡ የለሽ፡ ያልተቀጣ፡ ቅጡ፡ (ጠባዩ፡ ሥራው)፡ የማይታወቅ፡ ምሳሌ፡ አልባ።

ቅጥ፡ የተቀጠጠ፡ ቍርጥ፡ ዕጭድ፡ ሽልት።

ቅጥለት፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ ንዴት፡ ብግነት።

ቅጥላት፡ የቅጥል፡ አሠራር፡ ኹኔታ።

ቅጥል (ሎች)፡ በቅርቃር፡ በምስማር፡ በስፌት፡ በቍጥር፡ የተቀጠለ፡ የሞፈር፡ የልብስ፡ የገመድ፡ ተጨማሪ፡ ነገር፡ የጐደለ፡ መሙሊያ። ቅጽልን፡ እይ።

ቅጥልጣል፡ ቅጠላዊ፡ ቅጠልያ፡ የወርቅ፡ የብጫ፡ የወይባ፡ ዐይነት። በግእዝ፡ ሐመልሚል፡ ይባላል።

ቅጥልጣይ፡ ዝኒ፡ ከማሁ።

ቅጥልጥላም፡ ቅጥልጥል፡ ለባሽ፡ ባለቅጥልጥል።

ቅጥልጥል፡ የተቀጣጠለ፡ ደበሎ፡ ዝተት።

ቅጥራት፡ ያጥር፡ የቅጥር፡ ሥራ።

ቅጥራን፡ የሙጫ፡ ቅመም፡ መጣብቅ፡ የሚኾን፡ ሙጫ፡ ያለበት፡ የስንዴ፡ ዐራራ፡ ቀለም። "የወይን፡ የበለስ፡ ቅጥራን፡ ቢል፡ ዐዞ፡ ከል፡ ሖም ጣጣ፡ ማለት፡ ነው። " ማንኛውም፡ ነገር፡ ሲቦካ፡ መጣብቅ፡ ይኾናል። "ፈረንጆች፡ ቅጥራንን፡ ካትራም፡ ይሉታል። " ዝፍትን፡ አስተውል።

ቅጥር (ቅጹር)፡ የተቀጠረ፡ የታጠረ፡ ቤት፡ ከተማ፡ (ቅጽል)

ቅጥር(ሮች)፡ አሽከር፡ ሎሌ፡ ምንደኛ፡ ጌታችን፡ አንድ፡ አገልጋይ፡ ለኹለት፡ ጌታ፡ መገዛት፡ አይችልም፡ እንዳለ፡ ገረድን፡ ቅጥር፡ ማለት፡ ባንድ፡ ሰው፡ ፈቃድ፡ መታጠሯን፡ በቅጥር፡ (ዐጥር)፡ ውስጥ፡ ማደሯን፡ ያስረዳል።

ቅጥር(ቅጽር)፡ መካበቢያ፡ የግንብ፡ የካብ፡ ዐጥር፡ (ስም)

ቅጥቀጣ፡ ድብደባ፡ ብረት፡ ሥራ፡ ወቀጣ።

ቅጥቃጤ፡ ቅጥቀጣ፡ ቅጥቅጣት፡ (ግእዝ)

ቅጥቅጣት፡ መቀጥቀጥ፡ (ጥቀ)

ቅጥቅጥ(ጦች)፡ የተቀጠቀጠ፡ ብረት፡ ወርቅ፡ (፪ኛ ዜና፡ ፱፡ ፲፭) የክትክታና፡ የፍየለ፡ ፈጅ፡ ግጥግጥ።

ቅጥቅጥ፡ ውቅጥ፡ ተባት፡ ፍየል፡ ወይንም፡ በግ።

ቅጥበት፡ ጥቅሻ። በግእዝ፡ ቅጽበት፡ ይባላል። ቀጸበን፡ ተመልከት።

ቅጥቡ፡ ሞላ፡ ዕድሜው፡ ዐለቀ፡ ተፈጸመ።

ቅጥባት፡ ቅጠባ፡ የድር፡ ልክ፡ ምልክት፡ ክስል።

ቅጥብ (ቦች)፡ የተቀጠበ፡ የተከነዳ፡ የተለካ፡ ምልክት፡ መቍረ።

ቅጥብ፡ የዕድሜ፡ መጨረሻ፡ ዕለተ፡ ሞት።

ቅጥነት፡ መክሳት፡ ቀጪንነት።

ቅጥን፡ አለ፡ ክስት፡ አለ፡ ቀጠን።

ቅጥን፡ የቀጠነ፡ ቀጪን። በግእዝም፡ "ታናሽ፡ ጣት፡ ቅጥን"፡ ይባላል።

ቅጥንብር (ቅጥና፡ ሕብር)፡ ቁመትና፡ ቀለም፡ (መልክ)

ቅጥይ (ዮች)፡ ዐጽቅ፡ ክንፍ፡ ቅርንጫፍ፡ ፮ኛ፡ ጣት።

ቅጥጥ፡ አለ፡ ዐበጠ፡ ተነፋ፡ ተቀበጠጠ።

ቅጥጥ፡ አደረገ፡ ንፍት፡ ቅብትት፡ አደረገ።

ቅጥጥብ፡ ያይን፡ ጥቅሻ፡ ለግጥ፡ ዘበት፡ ፌዝ። በግእዝ፡ ትዕይርት፡ ይባላል።

ቅጥፊያ፡ ቅጥፈት፡ ዕብለት፡ ውሸት፡ ሐሰት።

ቅጥፋት፡ የኻያጅና፡ የቀሪ፡ ቀንበጥ፡ መለያ።

ቅጥፍ፡ አለ፡ ቍርጥ፡ አለ፡ ተቀጠፈ።

ቅጥፍ፡ የተቀጠፈ፡ የተቈረጠ።

ቅጥፍና፡ ቀጣፊነት።

ቅጫማም፡ ቅጫም፡ ያለበት፡ የበዛበት፡ ባለቅጫም።

ቅጫም (ሞች)፡ የቅማል፡ ቅንጣት፡ ከጤፍ፡ የሚያንስ፡ ረቂቅ፡ የዕከክ፡ ትል። ቅማንጅርን፡ እይ።

ቅጭል፡ መቃጨል።

ቅጭል፡ አለ፡ ቃጨለ።

ቅጭልጭል፡ አለ፡ ቃጨለ።

ቅጭልጭል፡ የተቅጨለጨለ፡ የቤተ፡ ንጉሥ፡ የቤተ፡ ክሲያን፡ አጫዋች።

ቅጭቅጭ፡ አደረገ፡ አንቀጫቀጨ።

ቅጭት፡ ቅጭታት፡ የትከሻ፡ መውረድ።

ቅጭት፡ አደረገ፡ ቍርጥ፡ ግንጥል፡ አደረገ።

ቅጭጭላት፡ ለገድ፡ ነፈላ።

ቅጭጭላት፡ የፈረስ፡ ጕንጭ፡ ትርፍ፡ ሥጋ፡ ተበጥቶ፡ የሚወጣ።

ቅጸላ: ጭመራ፡ ትምርት፣ ሐሜት።

ቅጽ (ቅጹዕ): የተቀጸ፡ ያልታጠፈ ብራና፡ ወይም ወረቀት።

ቅጽ: የጥራዝ፡ የመጣፍ ልክ መጠን፡ ቁመትና ጐን። "ቀጻ ቅጽ የካህናት፡ ቀጣ ቅጥ የሕዝብ ነው። "

ቅጽላዊ ግስ: "ገራ" "ገር" "ገራም" "ገረመ""ልብ" "ልባም" "ለበመ"፡ የመሰለው ኹሉ።

ቅጽል (ሎች): ግብርን፣ ዐይነትን፣ መጠንን ለመግለጥ ከስም አስቀድሞ የሚነገር ቃል። "ደግ፣ ክፉ፣ ቀይ፣ ጥቍር፣ ረዥም፣ ዐጪር፡ የመሰለው ኹሉ። " "ሌላውም ካ፭ቱ አዕማድ የሚወጣ ቅጽል የሠራተኛ ስም፡ ገዳይ፣ አስገዳይ፣ ተገዳይ፣ ተጋዳይ፣ ተገዳዳይ፣ ኣጋዳይ፡ አገዳዳይ ይላል። " "ዳግመኛም አበድ፣ አሰስ፣ ነበር፣ ቀበር፣ ሰበር፣ ነደድ፣ ሰደድ የሚል ቅጽል አለ። " "ወንዛወንዝ፣ ጨርቃጨርቅ፣ ቅጠላቅጠል፣ ርጥባ ርጥብ፡ ይህ ደጊመ ቃል ወይም ተናባቢ፡ ቅጽል ይባላል። "

ቅጽል ለቅጽል ሲቀጸል: ድፍን ጥቍር ይላል። "ከዚህ የቀረውን ባገባብ ተመልከት። "

ቅጽል ሲኾን: ሴት ልጅ ይላል።

ቅጽል ሲኾን: ዕጡብ ብልኅት፡ ዕጡብ ነገር ያሠኛል።

ቅጽል ተምሳሌ: ቅጽል ከምሳሌ ጋራ ባንድነት ሲነገር፡ እሱም የቅኔ ትምርት ነው።

ቅጽበተ ዐይን: የአይን ጥቅሻ፡ ወይም ፍጥነት፡ ዐይን ተጨፍኖ እስኪገለጥ ያለ እጅግ በጣም ዐጪር ጊዜ (ኤርምያስ ፲፰፡ ፯) "ቀጠበን አስተውል። "

ቅጽበት: ከስሳ ካልኢት (ሰጎንድ) አንዲቱ ጭረት።

ቅጽበት: ጥቅሻ፣ ፍጥነት።

ቅፈፍ: ቀፈፋ።

ቅፈፍ: ቍራጭ ብራና።

ቅፈፍ: የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ (ከርክም፣ ለምን)

ቅፋፊ: የተቀፈፈ፣ ተቀፎ የወደቀ።

ቅፍ: ዝኒ ከማሁ።

ቅፍለት (ዐረ፡ ቃፍላ): ተከታትሎ፣ አተርትሮ ባንድነት የሚኼድ፣ የሚጓዝ ባለጭነት የነጋዴ ግመል (ዘፍጥረት ፴፯፡ ፳፭)

ቅፍለቶች: ሲራራ የጫኑ ግመሎች (ኢዮብ ፮፡ ፲፰-፲፱)

ቅፍርናሖም: በምድረ እስራኤል ክፍል ያለ ቀበሌ።

ቅፍቀፋ: ሰበራ፣ ፍልፈላ፣ ክርከራ።

ቅፍቅፋት: የንቍላል፣ የግንድ ስብርባሪ፣ ድቃቂ።

ቅፍቅፍ: የተቀፈቀፈ፣ የተፈለፈለ (ፍልፍል)፡ የተከረከረ።

ቅፍንድ: የቈርበት ዘርፍ። "ቀፈደን እይ። "

ቅፍድ: የተቀፈደ፣ በቀፈድ የታሰረ።

ቅፍድድ አደረገ: ቀፈደደ።

ቅፍድድ: የተቀፈደደ።

ቅፍጣን: የላይ ልብስ ዐጽፍ፡ ጌጠኛ መደረቢያ (ከነጭ ሐር የተሰፋ)

ቅፍፍ አለው: ጨፈገገው፣ ከበደው፣ ጨደደው።

ቆለ፡ ቢስ፡ ውቃበ፡ ቢስ።

ቆሊያም፡ ባለቆሌ፡ ዛራም።

ቆሌ(ቃላዊ)፡ ዛር፡ ለፍላፊ፡ የቃልቻ፡ መንፈስ፡ ውቃቢ፡ ለዛ።

ቆል(ዕብ)፡ ቃል።

ቆመ፡ ረጋ፡ ጸና፡ ነገሩ።

ቆመ፡ ብእሲ፡ ዐምደ፡ ወርቅ። "መኻል፡ ለመኻል፡ አንድ፡ ሊቅ፡ ተደግፎት፡ ስለሚቆም፡ ዐምደ፡ ወርቅ፡ በካህናት፡ ቋንቋ፡ ቆመ፡ ብእሲ፡ ተባለ። ትርጓሜው፡ "ሰው፡ ቆመ"፡ ወይም፡ "የሰው፡ ቁመት"፡ ማለት፡ ነው። ይህ፡ አነጋገር፡ ስምዖን፡ ዘዐምድን፡ ያሳያል። "

ቆመ፡ ተገተረ፣ (ቀወመ)

ቆመልኝ፡ ባለጋራዬን፡ ሞገተልኝ።

ቆመብኝ፡ ጠበቃ፡ ኾነብኝ።

ቆማ፡ በበጌምድር፡ ክፍል፡ ያለ፡ አገር። ምሳሌ: "ቆማ፡ ፋሲለደስ"፡ እንዲሉ።

ቆማ፡ የሩቅ፡ ሴት፡ ቦዝ፡ አንቀጽ፡ ንኡስ፡ አገባብ፡ "ተገትራ" ምሳሌ: "ልጃገረዲቱ፡ ባል፡ ሳታገባ፡ እንዲሁ፡ ቆማ፡ ቀረች "

ቆሜ፡ የዜማ፡ ስም፡ ረዥም፡ ዜማ፡ የቆማ፡ ቆማዊ፡ ማለት፡ ነው።

ቆም (ቀዊም) መቆም።

ቆም፡ ቁመት።

ቆም፡ አለ፡ ፈጥኖ፡ ቆመ።

ቆሞስ(ሶች)፡ ማዕርጉ፡ በኤጲስቆጶስና፡ በቄስ፡ መካከል፡ የኾነ፡ መነኵሴ፡ ምንኵስና፡ ሰጪ፡ ታቦት፡ ባራኪ።

ቆሬ (ዕብ፡ ቆራህ): የሰው ስም፡ ከሌዊ የተወለደ የሌዊ ዘር።

ቆሮ (ዎች): የኦሮ፣ የሻንቅላ ዋና ባላባት፡ አምሳለ ንጉሥ። "አባ ቆሮ ቢል የቆሮ ኣባት ማለት ነው። "

ቆቁ: ቆቅ።

ቆቅ (ቆቃሕ): በዱር የሚኖር የዶሮ ዐይነት ፍጥረት። "ተባቱም እንስቱም ቆቅ ይባላል። " (ተረት): "እኔ ዐውቃለኹ የቆቅ መላ፡ ወይ በራለች፡ ወይ ደፍጣለች። " "ሲበዛ ቆቆች ያሠኛል። "

ቆቅ ማሪ አቦዬ: የንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ አባት አቶ አቦዬ አንድ ሰው ቆቅ ቢያመጣላቸው በርኅራኄ ስለ ለቀቋት ቆቅ ማሪ የስማቸው ቅጽል ኹኖ ሲነገር ይኖራል።

ቆቅ: ንቁህ፣ ጠንቃቃ ሰው።

ቆቅሐ፡ ቃሕቅሐ): ቍር ቍር አደረገ፣ ሰበረ፣ ቀፈቀፈ፣ ፈለፈለ፣ አወጣ፣ መለሰ።

ቆቅማ: ቆቅ የሚመስል ዶሮ።

ቆቋ: ያች ቆቅ።

ቆበ፡ ጣል፡ ቆቡን፡ ከራሱ፡ አውልቆ፡ የጣለ፡ የወረወረ፡ ያሽቀነጠረ።

ቆበ፡ ጥላቆብ፡ ጥላው፡ ቆቡን፡ እንደ፡ ጥላ፡ የሚቈጥር፡ ዓለማዊ፡ መነኵሴ።

ቆበተ፡ ጠበቀ፡ ዐቀበ።

ቆበተ: ቁባት አደረገ፡ ጠበቀ።

ቆባስጥል (ቆብ፡ አስጥል)፡ በይፋት፡ ክፍል፡ ያለ፡ ቀበሌ፡ ታቹ፡ ገደል፡ ላዩ፡ ቆብ፡ የሚያስጥል፡ ኀይለኛ፡ ነፋስ፡ የሚነፍስበት፡ ሜዳ።

ቆብ (ቦች) (ቆብዕ)፡ ከሰሌን፡ ከሸማ፡ ከክር፡ ከጠጕር፡ ከሣር፡ ገመድ፡ ከበርኖስ፡ የተበጀ፡ የራስ፡ ማግቢያ፡ መክደኛ፡ የተባረከ፡ መንፈሳዊ፡ ምሳሌ፡ ምሳሌነቱም፡ የንጽሐ፡ መላእክት፡ ነው። ሌላም፡ የአይሁድ፡ የእስልም፡ የባኒያን፡ የፈረንጅ፡ ቆብ፡ አለ። ባርሜጣን፡ እይ። (የፀሓይ፡ ቆብ)፡ ለጽድቅ፡ ያይደለ፡ ለፀሓይ፡ የሚደረግ፡ ማታለያ፡ ቆብ

ቆብ፡ ፡ መነኰሰ።

ቆቱ: የሐረርጌ ኦሮ ስም፡ ወራሽ፣ ቈፋሪ ማለት ነው።

ቆንስል (ሎች): የፈረንጅ ንጉሥ መልክተኛ፡ በኼደበት አገር ለወገኖቹ ዳኛ፣ ጠባቂ፡ ለላከው መንግሥት ወኪል ኹኖ በባዕድ አገር የሚቀመጥ። "የንግሊዝ፣ የፈረንሳይ፣ የጀርመን፣ የመስኮብ፣ የጣሊያን ቆንስል" እንዲሉ። "በፈረንጅኛ ኮንሱል ይባላል። "

ቆግላ (ኦሮ፡ ጎግላ፡ ክንፍ)፡ ርግብግብ፡ ለማጣ፡ ሰው።

ቆፍ (ዕብ): ዝንጀሮ፡ በብዙ ወገን ሰውን የሚመስል አውሬ።

ቆፍ፡ በአኃዝነት፡

ቆፍ: የፊደል ስም

(): መሰበር፣ መጮኸ።

፡ መጮኸ፡ ቋቋ

ሣር: አንጓ ያለው ወፍራም ሣር፡ ሲሰብሩት የሚቀለጠም (ቋያ)

፡ ቄጆ፡ ማለቢያ፡ አኮሌ፡ ግሬራ፡ ሰበዙ፡ እየተጠመዘዘ፡ የተሰፋ።

እቋ አለ: ተሰበረ፣ ተሰማ። "የሙክቱ እግር እቀጭ እቋ ይላል። "

ቋሊማ፡ አንዠት፡ ውስጥ፡ የተከተተ፡ ደቃቅ፡ የሥጋ፡ ክትፎ። "ቋሊማ፡ ማለት፡ አንዠቱ፡ እንደ፡ ቀለም፡ (ቀሠም)፡ ውስጠ፡ ክፍት፡ መኾኑን፡ ያሳያል። " "ፈረንጆች፡ ሶሲሶ፡ ይሉታል። "

ቋመጠ፡ ጐመዠ፡ ሠየ፡ አኹን፡ አኹን፡ አለ።

ቋሚ (ዎች፡ ሞች)፡ ቀን፡ ዕንጨት፡ እየሰበረ፡ ማታ፡ በጌታው፡ ፊት፡ የሚቆም፡ አሽከር፡ ሎሌ። ምሳሌ: "ቋሚ፡ ለጓሚ"፡ እንዲሉ።

ቋሚ፡ ለቤት፡ ሥራ፡ በምድር፡ የሚተከል፡ አራት፡ ማእዘን፡ ዕንጨት፡ ወይም፡ ብረት።

ቋሚ፡ በሕይወት፡ ያለ። (ሳታት፡ ቋሚ)፡ አወዳሽ፡ ደብተራ።

ቋሚ፡ ድግስ፡ ሲበላ፡ ሲጠጣ፡ ዐዳይ፡ አሳላፊ፡ አስተናባሪ።

ቋሚነት፡ ቋሚ፡ መኾን፡ ፈላጭነት።

ቋማጭ፡ የቋመጠ፡ የሚቋምጥ፡ ጕምዡ።

ቋም ሜዴ ቆመ።

ቋም፡ የውሃ፡ መጠን፡ ዘንግ፡ አቁሞ፡ ወይም፡ በቁመት፡ የሚለካ፡ መልካ፡ ሜዴ፡ ቆመው፡ የሚሻገሩት። ወደ፡ ፊት፡ አቋምን፡ እይ።

ቋሳ (ቈስያ): የተክል ስም፡ ዱባ።

ቋረኛ (ኞች): የቋራ ሰው፣ የቋራ ተወላጅ። "ቋረኛ ኢያሱ" እንዲሉ።

ቋሪት: በጐዣም ውስጥ ያለች ቀበሌ።

ቋሪት: የቀበሌ ስም ቋር።

ቋራ: በበጌ ምድር አውራጃ ያለ አገር ስም።

ቋራም (ሞች): ቋር ያለው፣ ባለቋር፡ ራሳም፣ ጕጣም።

ቋሬ: ቋራዊ፡ የቋራ አገር ልብስ (ሸማ)፡ በቋራ ተፈትሎ የተሠራ ዝቅዝቅ ገበርባሬ፡ "በትግሪኛ ግን ጃኖ ማለት ነው። "

ቋር: የንጨት፣ የፈትል ቋጣራ (ዐይን) ጕጥ።

ቋር: የዱላ ራስ። "ቋራም ዱላ" እንዲሉ።

ቋርፍ: የዱር ፍሬና ሥራሥር፡ እንቅርብጭን፣ የወፍ ቈሎን የመሰለ፡ የመናኝ፣ የዝንጀሮ ምግብ።

ቋሮ: ራሳም ዓሣ።

ቋሸ): አቋሸ፣ ሥጋን በንጀራ አጣበቀ፣ ያዘ፣ ዐንከ፣ በላ፣ በጥርሱ እንደ ቈሻ አደቀቀ፣ አለነቀጠ።

ቋቍቻ (ቈቍዐ): የገላ በሽታ (የዕከክ ዐይነት)፡ ዐንገትን፣ ጕንጭና ጕንጭን፣ ደረትን የሚያሳክክ፣ የሚያፍረከርክ (ሴቴ) "ዳግመኛም አጓጐት ይባላል (ዘሌዋውያን ፲፬፡ ፶፮) "

ቋቅ አለ (ቄአ): አስታወከ፣ አስመለሰ።

ቋቅ አለው: ጐጓው አስታወከው።

ቋቋ አደረገ: ኳኳ፣ መታ መታ አደረገ።

ቋቋቴ: ኳኳቴ፡ የንጨት (የጦጣ ቍላ) እንቡጥ፡ እረኞች እያፈነዱ የሚያንቋቁት፣ የሚያስጮኹት።

ቋቋቴ: የጣት አንጓ።

ቋቋቴ: ያሮጌና ያሮጊት ወገብ ሲጫኑት፡ የሚንቋቋ።

ቋተ) (ኰዐተ): አቋተ፣ ቋት አበጀ፣ እቋት ጨመረ፣ ደቀነ (ጥሬ እኸልን) አቋች: ያቋተ፣ የሚያቍት፣ ደቃኝ። ማቋት: መጨመር፣ መደቀን። ማቋቻ: መጨመሪያ፣ መደቀኛ (በጭቃ ተበጅቶ እበት የተለቀለቀ) አንድ ዕፍኝ እኸል የሚይዝ ሞላላ ሥራ፣ ከወፍጮ በስተላይ በኩል ያለ። "ዐገሸ ብለኸ ዕግሽን እይ።" አስቋተ: አስደቀነ። ማስቋት: ማስደቀን። ተቋተ: ተጨመረ፣ ተደቀነ።

ቋቱ ጠብ አለ: ጥቂት ጥቅም ተገኘ።

ቋቱ ጠብ አላለለትም: አላገኘም፡ እንጀራ አልጠገበም (ሆዱ)

ቋታ: ቋቅታ፡ ቋቅ ማለት! ጓታ፣ እውከት፣ ምላሽ።

ቋት (ምእላደ ሐሪጽ): የዱቄት መፍሰሻ፣ መግቢያ፣ ማረፊያ፣ መጠራቀሚያ፣ መከማቻ፡ በማቋቻ አንጻር በስተታች ያለ ጕድጓድ (ከጭቃ፣ ከሸክላ የተሠራ) (የፈስ ቋት): ምትሀት ያለው የአስማት ድጋም (ባለማቋረጥ ፈስ የሚያስፈሳ)

ቋት: ሆድ።

ቋትለኛ (ኞች): የቋትል ወገን፣ ዋነተኛ፣ መርከብ መሪ። "በግእዝ ኖትያዊ ኅዳፍ ይባላል።"

ቋትለኛ (ኞች): የቋትል ወገን፣ ዋነተኛ መርከብ መሪ "በግእዝ ኖትያዊ ኅዳፍ ይባላል።"

ቋትል: ከባሕር፣ ከማዕበል፣ ከጐርፍ፣ ከውሃ ምላት ጋራ የሚታገል፣ የሚጋደል፡ ዋና፣ ዐዋቂ።

ቋትል: ከባሕር፣ ከማዕበል፣ ከጐርፍ፣ ከውሃ ምላት ጋራ የሚታገል፣ የሚጋደል፡ ዋና ዐዋቂ

ቋና፡ በበጌ፡ ምድር፡ ክፍል፡ ያለ፡ አገር።

ቋንቍራ: ቅራቅንቦ ዕቃ፣ ግሴት ሰባራ ሥንጥር፡ መንገደኛ የሚይዘው ቅል፣ ወረንጦ።

ቋንቍሬ: የስም ቅጽል፡ የቋንቍራ፣ ቋንቍራዊ። "ቋንቍሬ ባቡ" እንዲሉ።

ቋንቍሬ: የኔ ቋንቍራ።

ቋንቋ ለወጠ: ሌላ ልሳን ተናገረ።

ቋንቋ: ልዩ ልዩ ሕዝብ (ራእይ ፲፬፡ ፯፡ ፲፯፡ ፲፭)

ቋንቋ: አፍ፣ ልሳን፣ ነገር፣ የምላስ ፍሬ (ባንደበት ሲነገር የሚሰማ) (ግብረ ሐዋርያት ፪፡ ፮፣ ፮፣ ፲፩፡ ፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፪፡ ፲) "እከሌና እከሌ ቋንቋ ለቋንቋ ይተዋወቃሉ። " "ሲበዛ ቋንቆች ያሠኛል። " "በጋልኛ ጕረሮ ቆንቆ ይባላል፡ በምስጢር ከዚህ ጋራ ይሰማማል። " "ሰው በየጊዜው እንዲወለድ ቋንቋም በየዘመኑ ይፈጠራል። " "ዘነጠንና ጦለበን ተመልከት። " "መደበኛው የኢትዮጵያ ቋንቋ ግእዝ፣ ዐማርኛ፡ ሌሎችም ትግሬ፣ ትግሪኛ፣ አገውኛ፣ አዳልኛ፣ ወላምኛ፣ ጋልኛ፣ ሱማልኛ፣ የከፋ፣ የሲዳሞ፣ የሻንቅላ፡ ከነዚህም በቀር ብዙዎች ዘርፎች አሉ። "

ቋንዣ፡ ቈረጠ፡ እግርን፡ ሰነከለ።

ቋንዣ፡ ቈራጭ፡ ዐመፀኛ፡ ወንጀለኛ፡ ሽፍታ፡ ምሕረት፡ የማይገባው።

ቋንዣ አባላ: ዐባላ።

ቋንዣ፡ ከጕልበት፡ በስተኋላ፡ ከባት፡ በላይ፡ ያለ፡ የእግር፡ ማጠፊያ፡ ዋና፡ የደም፡ ሥር። "ሲበዛ፡ ቋንዦች፡ ይላል። "

ቋንዶ(ዎች)፡ ያረግ፡ ስም፡ ጥኑ፡ ጠንካራ፡ ዐረግ።

ቋንዶ፡ ዐረግ(ቀንደ፡ ሐረግ)፡ ያረግ፡ ቀንድ፡ ዋና፡ ዐረግ፡ ዐዋቂ።

ቋንጃ፡ የእግር፡ ማጠፊያ፡ ቋንዣ።

ቋንጅል(ሎች)፡ ቅል ' ቅምጫና።

ቋንጢት፡ ከሲታ፡ ሴት፡ "ንሺ፡ ቋንጢት፡ እንዲሉ። "

ቋንጣ(ነቅጸ)፡ ተዘልዝሎ፡ የደረቀ ሥጋ።

ቋንጣ፡ ቀጪን፡ ሰው፡ ኰስማና፡ አካለ ደረቅ።

ቋንጣ፡ በንዝርት፡ ራስ፡ ላይ፡ ያለች፡ ቈላፋ፡ የሽቦ፡ ብረት።

ቋንጣ፡ ደረቅ፡ የበለስና፡ የወርካ፡ ፍሬ።

ቋንጣዊ፡ የቋንጣ፡ ማለት፡ ነው፡ የጠፍሩን፡ ድርቀት፡ ያሳያል።

ቋንጤ፡ በቈዳ፡ የተታታ፡ ወንበር።

ቋንጦች፡ የደረቁ፡ ዝልዝሎች፡ በለሶች፡ ሽቦዎች፡ ኰስማኞች፡ ሰዎች።

ቋኛት (ቶች): ካረግ፣ ከመቃ የተበጀ ሞላላ ቅርጫት (ዓሣ መያዣ)

ቋኛት ሆድ: ሆዱ እንደ ቋኛት የኾነ ሰው።

ቋዝመን፡ እንደ፡ ጩቤ፡ ያለ፡ ታናሽ፡ ካራ፡ ጋፋቶች፡ የሚታጠቁት።

ቋያ፡ ቋ፡ የበረሓ፡ ሣር፡ ሳይታጨድ፡ ቈይቶ፡ የደረቀ። "የቋያ፡ እሳት"፡ እንዲሉ። ሰደደ፡ ብለኸ፡ ሰደደን፡ ተመልከት።

ቋድ (ዶች)፡ የጠፍር፡ የክር፡ የገመድ፡ የሐር፡ የጥለት፡ የሽቦ፡ አራት፡ ማእዘን፡ ጕንጕን። ፈረንጆች፡ ቋድን፡ ኮርዶን፡ ይሉታል።

ቋድ፡ አበጀ (ትግ፡ ቀወደ፡ ቆደ)፡ ወዘበ፡ ዕዛብ፡ ሠራ፡ ጐነጐነ፡ አጠላለፈ፡ ከቈዳ።

ቋድ፡ ዛብ፡ ሥራ፡ ማተብ።

ቋድ፡ የዱሮ፡ ጠመንዣ፡ ስቦ፡ መተኰሻ።

ቋጠረ(ቈጸረ)፡ በሆድ፡ በልብስ፡ ያዘ፡ አረገዘ፡ ዐቈረ፡ (ምሳሌ ፴፡ ፬። ኢዮብ ፴፡ ፰፡ ፴፯)

ቋጠረ፡ ነገር፡ ፀነሰ፡ ዠመረ፡ ወጠነ፡ ሤራ፡ ዐድማ፡ አደረገ። "አቶ፡ እከሌ፡ የቋጠረው፡ አይፈታም"፡ እንዲሉ።

ቋጠረ፡ አሰረ፡ ቀጠለ።

ቋጠረ፡ እሰጥ፡ አለ፡ ውርርድ፡ ተከለ፡ (ጐንደር)

ቋጠረ፡ ጣቱን፡ ከጣቱ፡ ጋራ፡ አዋሰበ፡ ጋንን፡ ከነአተላውና፡ ከነጠላው፡ ለማንሣት።

ቋጠረ፡ ፊቱን፡ ኰፈተረ፡ ሰገጠ፡ ጨመደደ።

ቋጠራ፡ አሰራ፡ እርግዝና።

ቋጣሪ(ዎች)፡ የቋጠረ፡ የሚቋጥር፡ አሳሪ፡ ቀጣይ፡ ሸማኔ፡ ሢረኛ። "ነገር፡ ቋጣሪ"፡ እንዲሉ።

ቋጣራ፡ ዕጢ፡ የንጨት፡ ዐይን፡ ቋር፡ ጕጥ።

ቋጣራነት፡ ቋጣራ፡ መኾን፡ ጕጕለት።

ቋጣሮ፡ ቈቀር፡ ቡጢ፡ የተሳሰረ፡ ሣር፡ የቅጠል፡ ችቦ፡ (ሚልክያስ ፩፡ ፲፫)

ቋጥኝ (ኞች፡ ቀጣ)፡ ገለብ፡ ገዎቻ፡ ከገደል፡ ተቀርፎ፡ ወይም፡ ተቈርጦ፡ የወረደ፡ ደንጊያ፡ ቤት፡ የሚያኸል።

ቋጨ (ትግ፡ ቈጸየ)፡ ጠመዘዘ፡ አከረረ፡ ጠመረ፡ ገመደ፡ ፪ቱን፡ ወይም፡ ፫ቱን፡ ፈትል፡ ደበለ፡ አንድ፡ አደረገ።

ቋጨራ፡ የታሰረ፡ ጓሳ፡ ነዶ፡ አንድ፡ ጭብጥ።

ቋጪ፡ የቋጨ፡ የሚቋጭ፡ አክራሪ፡ ጠማሪ።

ቋፈ (አቋፈ): ቈነነ፣ ቀስ አደረገ (በመንገድና በምግብ ላይ)

ቋፍ: በገደል ላይ የዝንጀሮ አቀማመጥ።

ቋፍ: ጫፍ፣ አፋፍ፡ ዐጕል ኑሮ። "በቋፍ አትቀመጥ፡ ትወድቃለኸ። "

: (የሩቅ ወንድ ዝርዝር) በብዙዎች ስም ጫፍ የሚነዝር።

No comments:

Post a Comment

ሽፋን

  ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ