Friday, June 6, 2025

: '' ፈንታ እየተነገረ ገቢር ተሳቢ ይኾናል። "ጨለማው ላይን ያዘ። "

: ተቀባይ እየኾነ በብትን ሁሉ ይገባል። "ላምላክ ምስጋና ይግባው""ለሰው ሞት አነሰው""ለሥራ ተጋ""ለእውነት አደላ""ለወሬ አቈተመ" ፍችው "በቁም ቀሪ" ነው። በመራሕያንም ሲነገር "ለርሱ" "ላንተ" "ለኛ" ይላል።

: ከተናባቢ ሳድስ ቅጽል ይወጣል። "ታቦትን" እይ።

: ከጋራ። "እባብ ለባብ ይተያያል በካብ። " ይኸውም '' 'ምስለ' የመጣ ነው። በአጫፋሪነትም "እባብና እባብ" ተብሎ ይፈታል።

: '' ተለዋጭ። "ማረ ግላ" (መዓረ ግራ)

: የቦታ ደቂቅ አገባብ፡ ፍችው "ወደ" "እከሌ አገር ላገር፡ መንደር ለመንደር ዞረ። " '' የቀረው ነው፡ "ከመንደር ለመንደር" ያሠኛል።

: '' ተወራራሽ። "ይን" ተመልከት።

ለሐም: ለሐጪ ብዙ ሰው፡ ባለለሐጭ ላንቁሶ አውሬ እንስሳ።

ለኈሳስ: ሹክታ።

ለሐቀ: አጥብቆ ያዘ፣ ምድርን። (ግእዝ)

ለሐጭ: (ልሕጸ) ቀጪን ምራቅ፡ ከአፍ እየወጣ የሚፈስ። (ልጋግን እይ።)

ለሐፍ: (ዐረ.) ጥሩ የላይ ልብስ መደረቢያ፡ ባለዘርፍ ምንጣፍ። (ምሳ. ፯፡ ፲፮)

ለሌ: ለየ፡ እየለሌ፡ እየለየ፣ እያራቀ።

ለመለመ: ለምለመ፡ ጠደቀ፣ አቀጠለ፣ ለጋ ኾነ፣ ጀፈጀፈ። (ዘኁ. ፲፡ ፯፡ ፰፣ ማር. ፲፫፡ ፳፰) መለመለን እይ። ፈጠፈጠንና ቈጠቈጠን ተመልከት።

ለመመ: ደገደገ፣ እደፈ።

ለመሰሰ: መሰሰ፡ አስተኛ፣ ለሽ አደረገ ሣርን፣ ሰብልን።

ለመሸ: ፀወሰ፡ ተጥመለመለ፣ ሽባ ኾነ፣ ሰለለ።

ለመሸቀ: ረሰረሰ።

ለመነ: ማለደ፣ ስጦታ ጠየቀ፡ "ስጡኝ፣ አድርጉልኝ፣ ሥሩልኝ፣ አብሉኝ፣ አጠጡኝ፣ አብሱኝ፣ ችሩኝ" እለ፡ አባበለ፣ እሽበለበለ፣ ቀፈፈ፣ ቧገተ። (ተረት) "የለመነ መነመነ" (ሹም፣ መነ)፡ አዘዘ። ጸለየን እይ።

ለመከከ: መረገ፣ ቀባ፣ ላከከ።

ለመዘ: ጠመዘዘ፣ ፈተለ።

ለመዘገ: አጥብቆ ቈነጠጠ።

ለመደ፡ ብለኸ፡ ልማድን ተመልከት።

ለመደ: ለሚድ፣ ለመደ፡ ተማረ፣ ደገመ፣ አጠና፣ ያዘ፣ ተስማማ፣ ዐወቀ (ጎባው)፡ ባንድ ሥራ ላይ ሠለጠነ። "ጽፈት ለመደ፣ ኣገር ለመደ" እንዲሉ።

ለመደ: ለምድ አበጀ፣ ሰፋ።

ለመደች: ከባሏ ተስማማች። (ግጥም) "እከሊት ለምዳለች፡ እንዝርቴን ደጋኔን አምጡልኝ ብላለች"

ለመገገ: ሳበ፣ ጐተተ፣ ጠባ።

ለመጠ: ለመጠጠ።

ለመጠ: ለመጸ፡ ለማጣ አደረገ፣ ኦጐበጠ፣ አሀባ፣ ኦዘበጠ፡ አደራ ጣራን፣ ወገብን፣ ዕንጨትን፣ ብረትን፣ ማንኛውንም ነገር።

ለመጠ: ለጠጠ፣ ቈነነ። "ምን ይለምናኻል፡ ቶሎ ቶሎ "

ለመጠ: እነጣ፣ ለምጥ እወጣ፡ የተላ ዕንጨት አስመሰለ።

ለመጠ: ፈገፈገ፣ ሳለ፣ አሰላ፡ ምላጭን በጠፍር፣ አለዘበ፣ አለሰለሰ።

ለመጠጠ: ፈጀ፣ አቃጠለ፣ ለቈጠጠ፣ ገረፈ፡ አሰፋ።

ለመጥ ለመጥ: ቈነን ቈነን።

ለመጥ አለ: ተለመጠ።

ለመጥ: መለመጥ።

ለመጮ: ለጠሰ፡ አስተኛ።

ለመጮጮ: አሞቀሞቀ።

ለሚ: የሚለማ፣ የሚለመልም።

ለማ: ለምዐ፡ ለመለመ፣ በጀ፣ ሰመረ፣ በዛ አዝመራው። (ኢሳ. ፲፫፡ ፳) (ተረት) "ከለማበት የተጋባበት" "የጠፋ ዐዳር ከለማ አንድ ነው" "ለሰው ብትል ትጠፋለህ፡ ለግዜር ብትል ትለማለህ"

ለማ: በራ፣ ገነነ መብራቱ።

ለማ: የሰው ስም።

ለማልሞ: ከበጌምድር ወደ ስሜን መውረድ ረዥም ገደል።

ለማልሞ: ወጣት ጐበዝ።

ለማመጠ: አጐባበጠ፣ ሳሳለ።

ለማን ዐዝና: የኮከብ ስም።

ለማኝ ሳያራ: ማለዳ ጧት። "እከሌ ለማኝ ሳያራ መጣ"

ለማኝ: ለማኞች፡ የለመነ፣ የሚለምን፡ ድኻ፣ ቀፋፊ፣ ቧጋች። (ተረት) "የለማኝ ለማ ቍረንጮዬን ቀማኝ"

ለማኝነት: ለማኝ መኾን።

ለማዳ: ለማዳዎች፡ የለመደ፣ የሚለምድ፡ የቤት አውሬ፡ ሰዎች ከዱር ይዘው ወደ ቤት ያመጡት።

ለማጥ: አልምጥ፡ የተለመጠ፣ የደራ፡ ድርዝብ።

ለማጭ: የለመጠ፣ የሚለምጥ፡ አዝቢ፡ አዝባጭ።

ለም አገር: የወይኑ ዘለላ ጋን የሚመላ፣ የስንዴው ዛላ ዕፍኝ የሚመላ።

ለም: ለምዕ፡ ለምለም፡ የቀና፣ የለማ መሬት፡ እኸልና ተክል የሚሆን፣ ባለመስኖ (የካህናትና የመኳንንት ርስት አብዛኛው) "ለም መሬት፣ ለም ከጠፍ" እንዲሉ። ለምጨቅን ተመልከት።

ለምለም ምላስ: ደረቅ ያይዶለ፣ ዐጥንት፣ ጕልጥምት የለሽ። "በለምለም ምላሱ፣ በሠላሳ ጥርሱ" እንዲሉ።

ለምለም አደረገ: "እንደ ቀጤማ ያለምልምም" እንዲል ተማሪ።

ለምለም: ለምለሞች፡ የለመለመ፣ ለጋ ቅጠል፣ ርጥብ ሣር፣ እንግዴ፣ ቀጤማ፣ ቀንበጥ፣ እንቦቀቅላ የመሰለው ኹሉ።

ለምለም: ፍጥ፡ እንጀራ፣ ወዛም፣ ለስላሳ ማለት ነው።

ለምለምነት: ለምለም መኾን።

ለምላሚ: የሚለመልም፣ ጠዳቂ።

ለምዛጊ: የለመዘግ፣ የሚለመዝግ፡ ቈንጣጭ።

ለምደኛ: ለምዳም፣ ባለለምድ፣ ለምደ ለባሽ።

ለምደኛ: የለምድ ዐይነት፡ ከወደ መላበሻው በክር የተጋጠመ ዐንገት ልብስ።

ለምድ አወጣ: ገፈፈ።

ለምድ: ለምዶች፡ ከግምጃ፣ ከሐር፣ ከተለፋ ያንበሳ፣ የነብር፣ የግስላ ቈዳ በደበሎ ዐይነት ተበጅቶ የተሰፋ የጦር ሰራዊት መደረቢያ ልብስ ከጥንት ዠምሮ የተለመደ።

ለምድ: የፍየል ቈዳ። (ዘፍ. ፳፯፡ ፲፮)

ለምድ: ያንቀልባ አይነት፡ አንቀልባ። "የታዘለ በለምድ፡ የተረገዘ በሆድ" እንዲሉ።

ለምድ: ደበሎ። (ማቴ. ፯፡ ፲፭) (ተረት) "መናጆ የሌለው በሬ፡ ለምድ የሌለው ገበሬ"

ለምዶ ዝላይ: ከቅጠል ላይ ልጃገረዶች ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየዘለሉ የፋሲካና የገና ለት የሚጫወቱት የባላገር ጨዋታ፣ ከጥንት ካባት የቈየ የተለመደ። አንደርዶን ተመልከት።

ለምዶ: ተምሮ፣ ዐውቆ።

ለምጣም: ለምጣሞች፡ ለምጥ የወጣበት፣ ያለበት፡ ባለለምጥ።

ለምጣጭ: የለመጠጠ፣ የሚለመጥጥ፡ አቃጣይ፣ ገራፊ።

ለምጥ: ለምጽ፡ የበሽታ ስም፣ ገላን ነጭ የሚያደርግ ርኩስ በሽታ።

ለምጦ: ኣፉና አፍንጫው ለምጥ የሚመስል ፈረስ።

ለምጨቅ: ለም ጭቃ፡ ሣርና ጭቃ።

ለሰለሰ: ሥራ ተወ፣ ተቀምጦ ዋለ።

ለሰለሰ: ተላ፣ ተፋቀ፣ ከሻካራነት ራቀ፣ ለሀበ። "ሀሩ ለሰሰ" ነው።

ለሰሰ: ላበ፣ ሞቀ በጥቂቱ።

ለሰስ አለ: ዝኒ ከማሁ።

ለሠቀ: ለጥ አደረገ። ለሰቀ።

ለሰቀ: ለጸቀ፡ ለጠቀ፣ ለጥ፣ ቀጥ አደረገ፡ ጨፈቀ፣ አጣበቀ እየያዘ ርጥብ፣ ጨፈቃን።

ለሰነ: ለስኖ ለሰነ፡ ነገረ፣ ተናገረ። (ግእዝ)

ለሰነ: ምርግን ወይም ልጥፍን፣ ትምትምን፣ ጕርዖን በብዙ ጭድና በቀጪን ጭቃ ለቀለቀ፡ በንፊት ሉሕ ዐሸ፣ ዐሠሠ፣ አስተካከለ። ለሰነ በግእዝ "ብሰሰ" ይባላል።

ለሰው ይምሰል ሠራ: ግብዝ ሆነ። "ሸመነን" ተመልከት።

ለሳቂ: የለሰቀ፣ የሚለስቅ፡ ፋቂ።

ለሳኝ: ለሳኞች፡ የለሰነ፣ የሚለስን፡ ልስን ዐዋቂ።

ለሳኝነት: ለሳኝ መኾን።

ለሴ: ሙቀት ያለው ጢብኛ፡ ለከት ሙልሙል። (ተረት) "ለመነኵሴ መልካም ለሴ"

ለሴ: ጢብኛ፡ ለሰሰ።

ለስ አለ: ለብ አለ።

ለስ አለ: ለብ አለ፡ ለሰሰ።

ለስላሳ: ልስልስ፡ የለሰለሰ፣ የለዘበ፣ ልዝብ። (ዘፍ. ፳፯፡ ፲፩፡ ፲፯) ባዘቶ የድመት ጕር። ዐመልን እይ።

ለስላሳነት: ለስላሳ መኾን።

ለስላሽ: የሚለሰልስ፡ ለዛቢ።

ለስታ ቅቤ: ለጋና ትኩስ ቅቤ።

ለስታ: ለስድ፡ ለብታ፣ ሙቀት።

ለስታ: ትኵስ፡ ለሰሰ።

ለስታ: ጥስ፡ ለስ ማለት።

ለስድ: ለስታ ቅቤ። (ግእዝ)

ለሸለሸ: ለሰነ።

ለሸለሸ: ጣለ፣ አወደቀ፣ አጋደመ፡ ፈጽሞ ኣስተኛ፣ ረፈረፈ። "የኅዳር በሽታ ሰዉን ኹሉ ለሸለሸው"

ለሽ አለ: ትኝት አለ በደረቱ።

ለቀለቀ: ለቅለቀ፡ በዘይት፣ በቅቤ፣ በቀለም፣ በበረቅ፣ በኖራ፣ በበት ቀባ። "እከሊት እበት ይዛ የሰው ቤት ትለቀልቃለች" እንዲሉ።

ለቀለቀ: ቀላልና መጨረሻ ዕጥበት ዐጠበ፣ አጠራ፣ አጸዳ። (ተረት) "ጋን ቢለቀልቁት ምንቸት ይመላል"

ለቀለቀ: አሳበጠ፣ ገጠመ ጕረሮን፡ አበዛ ድንኳንን።

ለቀለቀ: ወዘወዘ፣ አስጨፈረ።

ለቀመ: (ዘፀ. ፲፯፡ ፬፣ ዘኍ. ፲፭፡ ፴፪፡ ፴፫) ቅንጣትን በ፪ ጣት አነሣ፡ ዕንጨትን ሰበሰበ፣ አጠራቀመ፡ ጕድፍን ከፍሬ ለየ፡ የፊደልን ቅርጽ ከሣጥን ውስጥ እያወጣ በአቃፋ ብረት ላይ ደረደረ።

ለቀመ: ሣርን ነጨ፣ ጋጠ፣ በላ።

ለቀመ: ወሰደ። (ግጥም) "እንግዴህ ነገሬን ተከንፈሬ አለቅም የሰው ዶሮ አለና ካፌ የሚለቅም"

ለቀመ: ጠበበ፣ ጥበብ ሠራ፡ አዋሰበ፣ አሠባጠረ።

ለቀማ: ስብሰባ። (ተረት) "ላም ባልዋለበት ኵበት ለቀማ"

ለቀም አደረገ: አፈፍ አደረገ፡ ያዘ በአፍ ወይም በእጅ።

ለቀም: ግጦሽ፡ የከብት መብል። (ጥም) "ለቀም"፡ ያዝ።

ለቀሰ: ለቂስ ለቀሰ። ትግ፡ ሐባ፣ ለቅስ፡ አለቀሰ፣ ዐዘነ፣ ተከዘ፣ ቈዘመ፣ ኣሞሸ፣ ቀነቀነ፣ ኣነሳ፣ እንባ ኣፈሰሰ፡ ተንሠቀሠቀ፣ "ዋይ! ውይ! ወየው!" አለ። (ተረት) "ልጅና ቄስ በሰው ገንዘብ ያለቅስ" "እንኳን እናቴ ሙታ እንዲያውም አልቅስ አልቅስ ይለኛል"

ለቀቀ፡ ባለ፡ ፈታ፡ ገደፈ፡ ርግፍ፡ አደረገ፡ ማረ (ሉቃስ ፭፡ ፳፰)"ተውኸ፡ ተዉ፡ ተዋችኹ፡ ተወች፡ ተውሽ፡ ተውኹ፡ ተውን፡ እያለ፡ ይዘረዝራል።" (ተረት): "ያምራል ብሎ ከተናገሩት፡ ይከፋል ብሎ የተዉት።"

ለቀተ: አለቀተ፡ አለቃ፣ አበደረ።

ለቀጠ: የለነቀጠ ሥር። "ቀለጠ" ተውሮ "ለቀጠ" ተብሏል።

ለቃ: ለቅሐ፡ አለቃ፣ አበደረ፣ ሰጠ። ለቀተንን አስተውል፡ የዚህ ዘር ነው።

ለቃለቀ: ቀባባ፡ ዐጣጠበ።

ለቃሚ: ለቃሚዎች፡ የለቀመ፣ የሚለቅም። (ኤር. ፮፡ ፱) ሰብሳቢ፣ አዋሳቢ። "ዓለቃሚ" "ዕንጨት ለቃሚ" "ፊደል ለቃሚ" "ጥበብ ለቃሚ" እንዲሉ።

ለቃቀመ: አነ፣ ብድግ ብድግ አደረገ፣ ሰባሰበ፣ ነሣ።

ለቃቃሚ: የለቃቀመ፣ የሚለቃቅም፡ ልክስክስ።

ለቄታ: ለሰለሰ።

ለቈታ: ሕግ፡ ስልቻ፣ አቍማዳ።

ለቈደ: ለቀደ፣ ያዘ፡ ድዳ፣ ለንባዳ አደረገ፡ ትክክል መናገር ከለከለ፡ ኣፍ ያዘ።

ለቈጠጠ: ባረፈ፣ ቈነደደ፣ ፈጀ፣ እቃጠለ።

ለቅ ሕፅን: ሠላጤ ሾጣጣ ዳቤ "ከስምንት አንድ የኵርማን እኩሌታ።"

ለቅላቂ: ለቅላቂዎች፡ የለቀለቀ፣ የሚለቀልቅ፡ ቀቢ፣ ዐጣቢ።

ለቅሶ: ሐዘን፣ ትካዜ፣ ቍዘማ፣ ሙሾ፡ የንባ መመንጨት፣ መፍሰስ፣ መውረድ። (ተረት) "እንደ ነደደች ተነሥታ የሰው ለቅሶ አጠፋች"

ለቅሶኛ: ለቅሶኞች፡ ባለለቅሶ፣ እለቅሶ ቤት ኻያጅ፣ የሬሳ ዐጀብ።

ለቆ ዐዘል: ለቆ ያዘለ ደረቅ የበልግ ሣር።

ለቆ: ለቆዎች፡ ለቀወ፡ የሣር ልምላሜ።

ለቆ: ላቀ።

ለቋዳ: ልቍድ፡ የተለቈደ አፈ እስር።

ለበለበ (ለበበ): በቀላል ተኰሰ፡ አቃጠለ፡ ገረፈ፡ ጠበሰ፡ ፈጀ፡ አንገበገበ። "ገመለን" ተመልከት።

ለበለበ: ለፈለፈ።

ለበለበ: ጠለፈ፡ አሰረ፡ እገናኘ፡ አያያዘ።

ለበመ (ለቢብ፣ ለበ፣ ለበወ): ልብ አደረገ፡ ዐወቀ፡ ዐዋቂ ኾነ፡ መተ፡ አስተዋለ። "ልብን" እይ።

ለበመ፡ አስተዋለ፡ ዐይኑን፡ ጣለ፡ ትክ፡ ብሎ፡ እየ፡ ተመለከተ፡ ዐወቀ፡ አነጣጠረ።

ለበመ: ሰፈረ፡ አዘጋጀ፡ አሰናዳ፡ ሠየመ፡ መላ።

ለበሰ (ለብሰ): (ዘዳግም ፲፭:፳፯) አጣፋ፡ አጠለቀ፡ ታጠቀ፡ አደገደገ፡ ሶደነ፡ አሰረ፡ ኣሸነፈጠ፡ አሸረጠ፡ ተሸለመ፡ አጌጠ፡ ተጐናጸፈ። (ተረት) "የበላን ያብላላዋል፡ የለበሰን ይበርደዋል። " "የለበሰ የማንንም ጐረሠ። "

ለበሰ (ረወየ): አብዝቶ ጠጣ፡ ከለበሰ፡ ረካ።

ለበሰ: ተሸፈነ፡ ተደበቀ።

ለበሰ: ከለለ፡ መከተ (ደንን፣ ጨለማን፣ ጋሻን)

ለበሰ: ወዶ ተቀበለ። "እከሌ ስድቡን ለብሶት ዐደረ" እንዲሉ። "ሠራ" ብለኸ "ሥራትን""ፈረደ" ብለኸ "ፍርድን" እይ።

ለበሳ: መልበስ።

ለበስ አለ: ወፈር አለ (ሸማው)

ለበስ: የለበሰ። "ጉም ለበስ" "ብረት ለበስ" እንዲሉ።

ለበቀ: በለበቅ መታ።

ለበቀ: ጐሰመ፡ ጐን። "እከሌ ሐሞት በዝቶበት ልቡን ሲለብቀው ዋለ። "

ለበቅ (ቆች): ወፍራም ልምጭ፡ የከብት መምቻና መንጃ።

ለበበ (ለቢብ፣ ለበ፣ ሐሰለ): ከፈረስና ከበቅሎ፣ ካህያ፣ ከግመል ግንባር ልባብን አገባ፡ አጠለቀ።

ለበናም: ለንቦጫም።

ለበን: ለንቦጭ። በአረብኛ ግን "ወተት" ማለት ነው።

ለበን: የጠመንዣ ስም። "ዐጪር ለበን" "ረዥም ለበን" እንዲሉ፡ ይኸውም ጐራሽ ነው።

ለበደ (ለበጠ): ለጐመ፡ ጐለበ፡ በኮርቻ ዕንጨት ላይ ቈዳን ሰፋ።

ለበደ (ትግርኛ): መነጠረ፡ ጣደ፡ አስረረ፡ መረገ።

ለበዳ: ምንጠራ፡ መረጋ።

ለበጠ (ለቢጥ፣ ለበጠ): ለጠፈ፡ ሸፈነ፡ አለበሰ፡ አስጌጠ (በወርቅና በብር) (ለምሳሌ በዘኍልቍ ፲፮:፴፰ ላይ እንደተጠቀሰው)

ለበጠ: ሐሰትን እውነት አስመሰለ፡ ሸለፈ፡ ሸረደደ።

ለበጠ: ሠነበጠ፡ ለጠጠ።

ለበጣ ነገር: ካንገት በላይ እንጂ ከልብ ያልኾነ፡ ግብዝ፡ የለበጣ ነገር።

ለበጣ: ለበጥ፡ ሽለፋ፡ ሽንገላ፡ ሽርደዳ፡ ምፀት።

ለባለበ: ተኳኰሰ።

ለባልብ: ለምለም ወጣት። "ለባልብ" ዕብራይስጥ "ላብሌብ" ካለው የወጣ ነው።

ለባሚ (መላኢ): የለበመ ወይም የሚለብም፡ ዐዋቂ፡ ጭምት፡ አስተዋይ፡ የሚመላ፡ ሠያሚ፡ ዐቃቢ።

ለባሽ (ሾች): የሚለብስ፡ ቀዳሽ። በግእዝ "ለባሲ" ይባላል፡ "ሥጋን" ተመልከቱ።

ለባቂ: የለበቀ ወይም የሚለብቅ፡ መጥፎ ጠጥ (ኮሶ፣ እንቆቆ)

ለባበሰ: አጠላለቀ፡ ተጣጠቀ።

ለባቢ: የለበበ ወይም የሚለብብ፡ ልባብ ኣግቢ።

ለባጅ: የለበደ ወይም የሚለብድ።

ለባጣ: የተለጠጠ።

ለባጭ (ጮች): የለበጠ ወይም የሚለብጥ፡ አስጊያጭ፡ ሸላፊ፡ ሠንባጭ።

ለቤ: ለሴ፡ ጢብኛ።

ለብ አለ: ለስ አለ።

ለብ አለ: ለስ አለ።

ለብ አደረገ: ጥቂት አሞቀ፡ ቅዝቃዜን ኣራቀ።

ለብ ያለ: ለስ ያለ (ለምሳሌ በራእይ :፲፮ ላይ እንደተጠቀሰው) "ሸገገን" ተመልከት።

ለብላቢ: የለበለበ ወይም የሚለበልብ (የሚያቃጥል እሳት፣ በርበሬ፣ ሳማ፣ ፌጦ፣ ዝንጅብል)

ለብላቢት/አለብላቢት (ቶች): ሲነኳት የምትለበልብ ዐረግ። በግእዝ "አብላሊት" ትባላለች።

ለብላባ: ለፍላፊ።

ለብሰኸ ፍጀው: ዐዲስ ልብ የለበሰውን ሰው እንዲህ ይሉታል። "ፍጀው" ማለት "ጨርሰው" ማለት ነው።

ለብቃ ኢየሱስ: በለብቃ ያለ የኢየሱስ ታቦት።

ለብቃ: በመርሐ ቤቴ ክፍል የሚገኝ አገር፡ ፍል ውሃ ያለበት፡ ወባም፡ ሙቀታም።

ለብታ: ለስታ፡ ቀላል ሙቀት።

ለብታ: ለብ ማለት።

ለተለተ: ለጽለጸ፡ ወዲያና ወዲህ አለ፡ እንደ ሚዛን ልሳን እንደ ላት ተወዘወዘ፣ ተወዛወዘ።

ለተለት: ለትላታ፡ የተወዘወዘ፣ የሚወዛወዝ።

ለተመ: ለቲም ለተመ፡ ፈተገ፡ በጭንቅላት መታ፣ ወጋ፣ ደሰሙ፣ ገጨ፣ ተመተመ። "በድንገት ሳላስበው አውራ በግ ለተመኝ" "ሌሊት ከቤት ስወጣ መዝጊያ ግንባሬን ለተመኝ" "ጥጃ ሲጠባ በአፉ እናቱን ይለትማል" ጐሰመን እይ።

ለተተ: ለትቶ ለተተ፡ ኰለተፈ፡ ለፋ፡ ለሰለሰ፡ ደከመ፡ መኼድ መሥራት አቃተው፡ ሰነፈ። ለተለተን እይ፡ የዚህ ደጊም ነው።

ለታ: የሰው ስም፡ በመንዝ የግድም ባላባት።

ለታሚ: የለተመ፣ የሚለትም፡ ወጊ፣ ተባት በግ፣ ጕመላ።

ለታተመ: ተማተመ።

ለታታ: ለታት ኰልታፋ፡ የለተተ፣ የለፋ።

ለቴራውያን: የሎቴር ወገኖች፣ ደቀ መዝሙሮች፣ ባህሉን ተከታዮች።

ለት ለታ: ዕለት። "ያን ለት"፡ አሁን "ለታ"

ለት: ሎቱ፡ በዘማች አንቀጽ መፊረሻ በሩቅ ወንድ ዝርዝርነት እየገባ በቁም ቀሪ ኹኖ ይነገራል። (ማስረጃ) "መባለት" "ወረደለት" "ዐለፈለት" ይኸውም የበጎ ነው። በትንቢትና በትእዛዝ አንቀጽም ሲገባ "ይመጣለት" "ይምጣለት" ይላል።

ለት: ቀን፣ ዕለት።

ለትም: የሰው ስም፡ በ፰፻ .. የኢትዮጵያ ንጉሥ።

ለነቀጠ: ትግለንቀጠ፡ በሙቀጫ ተወቅጦ በውሃ የተዘፈዘፈውን የማሽላ እንቀት ፈጫ፡ አላመ፣ አለዘበ። ለቀጠን እይ፡ ሥሩ ርሱ ነው።

ለነበር: ለወግ፣ ለታሪክ፣ ለዝና። "ለነበር ነው" ይላል።

ለነበደ: ለበደ፡ ኰለተፈ፣ ረን አለ።

ለንቃጭ: የለነቀጠ፣ የሚለነቅጥ፡ አላሚ።

ለንቋጣ: ለንቋጦች፡ የንጨት ስም። በወይናደጋ ቈላ የሚበቅል አነስተኛ ዛፍ፣ ልጠ ማላጋ።

ለንባዳ ኾነ: ላዕልዐ፡ አፈ እስር ኾነ፡ መናገር አቃተው።

ለንባዳ: ለንባዶች፡ ለፍዳዳ፣ ኰልታፋ።

ለንቦም: ባለለንቦጭ።

ለንቦጭ: ለበጠ፡ ረዥምና ወፍራም ታችኛ ከንፈር።

ለንጨጭ: ለጠጠ፡ ታችኛ የጋማ ከብት ከንፈር፡ በትግሪኛ "ምንጭር" ይባላል።

ለንጭ: ያለው፡ ባለ ትልቅ ከንፈር ሰው።

ለከለከ: በምላሱ እየጨለፈ ውሃ ጠጣ፡ ሊጥን ዋጠ፡ የውሻ።

ለከመ: ለኰመ፡ ወሬ ለቀመ፣ አወራ፣ ተናገረ፣ ለፈለፈ፣ አሳበቀ። ትግሬ ግን "ለከመን ይዞ ኼደ፣ ወሰደ" ይለዋል።

ለከሰ: ልህሰ፡ ደከመ፣ ዐቅም ዐጣ፣ ሰነፈ፣ ታከተ።

ለከስካሳ: የተልከሰከሰ፣ የሚልከሰከስ።

ለከርሞ: ለአመት።

ለከተ: ለካ፡ ገጠመ፡ ዝም አሠኘ።

ለከት: ለከቶች፡ ታናሽና ሞላላ፣ ጢብኛ የሊጥ መፈተኛ። "አክሥቴ ቤት አለኝ ለከት" እንዲል እረኛ።

ለከት: ልክ መግጠሚያ፡ ዝምታ። "እከሌ ላፉ ለከት የለውም" እንዲሉ። ለካን አስተውል።

ለከንበል: የሬሳ በደረት መደፋት፡ ለሬሳ የቀረው ነው።

ለከፈ: ለኪፍ፣ ለከፈ፡ ቀመስ፣ ነካ፣ ነከሰ። "ውሻ ለከፈው"

ለከፈ: አቀረበ፡ ደቀነ። "ከምድራህ ላይ ዘወር በል፡ እዚህ ምን ለክፎሃል"

ለከፈ: ዠመረ፣ ያዘ። "በሽታ ለከፈው"

ለከፋ: ልክፊያ፡ ቅምሻ።

ለኪ: ለካኢ፡ የለካ፣ የሚለካ፡ ሸላጊ።

ለካ: ለክአ፡ መጠነ፣ ሰፈረ፣ ቀጠበ፣ ሸለገ፣ ረተመ፣ ከነዳ፣ መዘነ። (ራእ. ፳፩፡ ፲፯) "ውሃ በዘንግ ይለካል" እንዲሉ።

ለካ: ትእዘዝ አንቀጽ፡ መጥን፣ ስፈር፣ ከንዳ፣ መትር።

ለካ: ንኡስ አገባብ፡ "እኔ ነገሩ አልገባኝም ነበር፡ ለካ እንዲህ ኑሯልን" እኮንና ብያን እይ። ተደጋግሞ ሲነገር "እውነት እውነት፣ ርግጥ ርግጥ" እንደ ማለት "ለካ ለካ" ይላል፡ ምስጢሩ ልክን አይለቅም። ያው የነገር አጐላማሽ ነው።

ለካሚ: ለካሚዎች፡ የለከመ፣ የሚለክም፡ ወሬኛ፣ ወሬ ማዱ፣ ለፍላፊ።

ለካከፈ: ቀማመሰ፣ ነካካ።

ለካፊ: ላካ፡ ለካፊዎች፡ የለከፈ፣ የሚለክፍ፡ ቀማሽ።

ለካፊ: ጥካ፡ አቅራቢ፣ ደቃኝ።

ለካፋ: የተለከፈ፣ የሚለከፍ፡ የተደቀነ፣ የሚደቀን።

ለክ ለክ አደረገ: ዋጥ ዋጥ፣ ጠጣ ጠጣ አደረገ።

ለክ አደረገ: በፍጥነት ዋጠ።

ለክ: ዋጥ፣ ሰልቀጥ።

ለክላኪ: የለከለከ፣ የሚለከልክ፡ ዋጭ።

ለኮ መሬት: በለኮ የተለካ መሬት፡ በዘመቻ ግልቢያ የተገኘ መሆኑንም ያሳያል።

ለኮ: ኦሮ፡ የፈረስ፣ የበቅሎ መሳሲያ ጠፍር ወይም ገመድ ከልባብ ጋራ የተቋጠረ፡ ፫ ክንድ የሚሆን።

ለኰሰ፡ ለበለበ፡ አቃጠለ፡ ፈጀ፡ "ቤትን፡ ደንን፡ ድምርን፡ አፍን፡ የዐይን፡ ሥርን፡ ክንድን፡ የሌባን፡ ግንባር፡ ዐዲስ፡ ቍስልን፡ ዕባጭን፡ ሸሐኝን።"

ለኰሰ: ለኈሰ፡ ተኰሰ፣ አቃጠለ፣ አያያዘ፣ አነደደ።

ለኰሰ: ሰነቀረ፣ አጋባ ነገርን፣ በሽታን።

ለኰሠ: እሳት አያያዘ፡ ለኰሰ።

ለኮቴ: ለኾቴ፡ መሳል፡ የመሳል፣ ደንጊያ።

ለኰፈ: ኰለፈ፡ ጥቂት መታ፣ ተነኰሰ።

ለኰፍ አደረገ: ለኰፈ።

ለኰፍ: መለከፍ።

ለኳሳ: ዐቅለ ቢስ፣ ለዋሳ።

ለኳሽ: ለኳሾች፡ የለኰሰ፣ የሚለኵስ፡ ተኳሽ፣ አቃጣይ።

ለኳኰፈ: በቀላል መታታ፣ ተነኳኰሰ።

ለኳፊ: የለኰፈ፣ የሚለፍ፡ ተንኳሽ።

ለኳፋ: ዝኒ ከማሁ።

ለኸ: ሀሎከ፡ "አንተ" ለሚባል ለቅርብ ወንድ የአንቀጽ ዝርዝር ሲሆን (ትማር አለኸ፣ ትጽፍ አለኸ) በማለት ፈንታ "ትማራለኸ፣ ትጽፋለኸ" ተብሎ ይነገራል።

ለኹ: ሀሎኩ፡ "እኔ" ለሚል በግስ መጨረሻ እየገባ የሚነገር የአንቀጽ ዝርዝር። (በልቼ አለኹ፣ ጠጥቼ አለኹ) በማለት ፈንታ "በልቻለሁ፣ ጠጥቻለሁ" ይባላል። "" ተቀዳሚውን ፊደል ራብዕ አድርጎ ስለ ተጐረደ "ለኹ" ተባለ።

ለወሰ (ሎሰ): በጭቃ ከለ፡ ረገጠ።

ለወዘ: (ሎሰ) ቀላቀለ፣ አላቆጠ፣ አሸ፣ አዋዋደ፣ አቦካ። (ዘፍ. ፲፰፡ ፮፣ ፩ሳሙ. ፳፰፡ ፳፬)

ለወዘዘ: ስር "ሯጽ" ነው። ለዘዘ እንደ ለውዝ ሆነ።

ለወዘዝ/ለውዛዛ: የለወዘዘ፡ ለዛዝ፣ ለዛዛ፡ ደረቅነትና ርጥብነት ያለው።

ለወገ: የሎገ ዘር ነው። "ሎማን" ተመልከት።

ለወጉ፡ ለደንቡ ("ለወጉ ለማረጉ")

ለወጉ/ለወጓ፡ የወንድና የሴት ስም።

ለወጠ፡ ሸየጠ።

ለወጠ: ሌላ አደረገ፡ ቀየረ። ለምሳሌ፣ የሀገሪቱን አስተዳደር ለወጠ። (፪ዜና ፴፮፡ ፬) የራሱን ገንዘብ ሰጥቶ የሌላውን ገንዘብ ገዛ፡ ተቀበለ፡ እጅ አደረገ፡ ወሰደ። ዶላር ብሩን ለወጠ ቀድሞ ያምንበት የነበረውን ሃይማኖት ትቶ ሌላ ሃይማኖት ተቀበለ፡ ሃይማኖቱን ለወጠ ሲባል በኦሪት ያምን የነበረ ሰው ወደ ወንጌል እንደመቀየር ወይም እስልምናን ትቶ ክርስትናን እንደመቀበል ነው። የለበሰውን ልብስ አውልቆ ሌላ ልብስ ለበሰ፡ አሮጌውን በአዲስ ተካ፡ የሥራ ልብሱን አስቀምጦ የክት ልብሱን ለወጠ ጠባዩን ወይም መልክን ቀየረ፡ ሰውነቱን ለወጠ ሲባል ፊቱን አጠቆረ ማለት ነው። (፩ነገ ፳፪፡ ፬፡ ኤር ፶፪፡ ፴፫)

ለወጠ: አደሰ፣ አረቀቀ። አሸተተ፣ አገማ፣ ጠረኑን፣ መዓዛውን፣ ቃናውን ቀየረ።

ለወጥ አለ: ተለወጠ።

ለወጥ: (ተወልጦ) መለወጥ።

ለዋ (ለወየ): አብዝቶ ጠጣ፡ ሰበከተ፡ ለገሸ።

ለዋሳ (ለዋሶች): (ቅጽል) የተለወሰ፡ ደካማ።

ለዋሳነት: (ልውሰት) ለዋሳ መሆን፣ ደካማነት።

ለዋሽ (ለዋሾች): የለወሰ፣ የሚለውስ፡ አላቋጭ።

ለዋወጠ: ቀያየረ፣ መላልሶ ለወጠ።

ለዋጭ (ለዋጮች): (ወላጢ፣ መወልጥ) የለወጠ፣ የሚለውጥ፡ አጣሪ፣ ቸርቻሪ። (ዮሐ. ፪፡ ፲፬)

ለውለው አለ: ዘው ዘው አለ፡ እዚያም እዚያም ሄደ፣ ተገኘ።

ለውለው: (ቅጽል) ዝኒ ከማሁ።

ለውላዋ: (ቅጽል) (ለውለወ) ውልብልብ፣ ቀውቃዋ።

ለውንድዝ: የሚያስፈራ ደሴት።

ለውዜ: "የኔ ለውዝ"፡ ዜማህ የለውዝ ጣዕም ያለው ማለት ነው።

ለውዝ (ዞች): የተክል ስም፡ ፍሬው የሚጣፍጥ እንጨት። "ለውዝ ገውዝ" እንዲሉ (ለምሳሌ በኤርምያስ :፲፩ ላይ እንደተጠቀሰው)

ለውጤ: የሰው ስም፡ ምትኬ ማለት ነው።

ለውጥ: ልዋጭ፣ ልው፣ ምትክ፣ ፈንታ። (ዘሌ. ፳፯፡ ፲፣ መዝ. ፵፬፡ ፲፪፣ ኢሳ. ፫፡ ፳፬፣ ኤር. ፳፪፡ ፲፩)

ለውጥነት: ለውጥ መሆን።

ለውጦች: ምትኮች፣ ፈንቶች።

ለዘለቃ: ለፍጻሜ፡ ለመጨረሻ።

ለዘለዘ: (ለዘዘ፣ ነዘነዘ) ጠባ፣ መጥመጠ፡ አረሰረሰ፣ መዘመዘ።

ለዘለዝ (ቅጽል): ለዝላዛ፡ የለዘለዘ፣ የሚለዘልዝ።

ለዘላለም: ለብዙ ዘመን።

ለዘር በቃ: ደረሰ፣ አደገ፣ ጐለመሰ፡ ረባ (ጠቀመ)

ለዘበ: ተባለ፣ ተወረበ ዜማው።

ለዘበ: ደቀቀ፣ ላመ፣ ለሰለሰ፡ ምላሱ፣ ነገሩ፣ ጠባዩ፣ ዶቄቱ፣ እጅ ሥራው። (ምሳ. ፳፱፡ ፸፭)

ለዘብ: ወረብ፡ በበዓል ቀን በቅኔ ማህሌትና በዑደት ጊዜ ታቦት ሲነግሥ በጸናጽልና በከበሮ እየተመላለሰ የሚባል ረዥም ዜማ።

ለዘብታ: ቀስታ፣ ትሕትና።

ለዘዘ: ርጥብ፣ አስተኔ ሆነ፡ ከመክረር፣ ከመጠጠር ራቀ። ለምሳሌ፣ "ዐተሩንና ባቄላውን የንጀራ ጕዝጓዝ ብታደርገው ይለዝዛል" እንዲሉ። (ለወሀዘንን እይ።)

ለዚያ (ሎቱ): ለእርሱ ማለት ነው።

ለዚያ: (ተውላጠ ስም) ለርሱ።

ለዚያኛው፣ ለዚያች በቂ።

ለዚያኛው: ለዚያች: በቂ።

ለዛ ሙጥጤ: (ቅጽል) ክቾ፣ ደመ ቢስ።

ለዛ ቢስ: (ቅጽል) ውበት ወይም ማማር የሌለው፡ ለዛው መጥፎ።

ለዛ: (ትግርኛ: ለዘየ፡ አለገገ) ወዝ፣ ውበት፣ የነገር ጣዕም።

ለዛቢ: የሚለዝብ።

ለዛባ: (ቅጽል) ለስላሳ፣ ሻካራ ያይደለ።

ለዛዛ (ቅጽል): ለዛዝ፡ የለዘዘ፣ የሚለዝ።

ለዛዛነት: ለዛዝነት፡ ለዛዛ፣ ለዛዝ መሆን።

ለዝና: የወንድና የሴት ስም።

ለየ፡ ከፈለ፡ መደበ፡ ደለደለ፡ ቈነነ፡ ዐደለ። ተለተለንና፡ ሰነሰነን፡ ሸነሸነን፡ ተመልከት።

ለየ: ለእየ፡ (ለእየ)፡ እያንዳንዱ፣ እየራሱ፣ እየፊናው፣ እየብቻው የሚባለው ቃል፡ "" ተቀባይና በቁም ቀሪ ሁኖ በመነሻው ሲመራበት ለያንዳንዱ፣ ለየራሱ፣ ለየፊናው፣ ለየብቻው ተብሎ ይነገራል። እየን እይ።

ለየ: ሌለየ፡ (ዘዳ. ፬፡ ፵፩) ነጠለ፣ ሠነጠቀ፣ ከፈለ፣ ገመሰ፣ ተነተነ፣ መደበ፡ አራቀ፣ አገለለ፣ እየብቻ አደረገ። "የግዜር መቅሠፍት ግብጾችን ሲገድል እስራኤልን ለይቶ ተዋቸው" (ተረት) "ከልጅ ልጅ ቢለዩ ዓመትም አይቈዩ" (ለሌ) እይ፡ ከለየ ጋራ አንድ ነው።

ለየ: ዐወቀ፣ ተረዳ፣ ለመደ። "ተማሪው ፊደል ለይቷል" በለተን አስተውል።

ለዪ: ሌላዪ፡ የለየ፣ የሚለይ።

ለያየ: ነጣጠለ፣ ከፋፈለ።

ለይኩን: ፍቱን መድኃኒት ወይም አብነት።

ለይኩን: ፍቱን መድኃኒት ወይም አብነት።

ለደለደ (ለጠለጠ): ለሰለሰ ተሰማማ ተዋዋደ ወፈረ (ለምሳሌ የወጥ፣ የመረቅ፣ የምራቅ፣ የሳሙና፣ የንዶድ አረፋ)

ለደለድ: ለድላዳ የለደለደ፣ የተዋዋደ።

ለደመ

ለደመ: ለጠመ ለተመ

ለደፈ

ለደፈ (ትግርኛ: ሐባ ለፅፈ): ለጠፈ (ለምሳሌ ምራቅን) ባላገር "ለጠፈ" ከማለት ይልቅ "ለደፈ" ይላል፡ ይህም '' እና '' ተወራራሽ መሆናቸውን ያሳያል።

ለዳፊ: የለደፈ ወይም የሚለድፍ፡ ለጣፊ

ለገለገ (ለገገ): ሳበ ()፡ መዝመዝ።

ለገለገ (ትግርኛ: ሐባ፡ ለግለገ): የወተት።

ለገለገ: አደገ፡ ወጣ።

ለገለግ/ለግላጋ: ወጣት፡ አዳጊ።

ለገመ (ለጐመ): ተከየ፡ ከፋ፡ ቸል አለ፡ ጠመመ።

ለገመ፡ ከየ።

ለገመ: አቄመ፡ አቀበረ (የቍስል)

ለገሰ: ባለመቈጠብ ሰጠ፡ ናኘ፡ ቸረ።

ለገሰ: ብዙ ዝናብ ጣለ፡ ወለሰ።

ለገሠ: ቸረ፡ ለገሰ።

ለገሸ: አለልክ ጠጣ።

ለገበ (ትግርኛ): ልብስን ጣፈ፡ ሥሩ ለጐመ ነው።

ለገተ (ለጐተ): ለገደ።

ለገቸ: አስጠጋ፡ አሳዘነ፡ አማለ።

ለገቻ: ማስጠጋት፡ ዐዘን፡ ውል ማሳ።

ለገን (ልጕን): የሸክላ ዕቃ፡ የደቅ ዐይነት፡ ደቅ ዋዲያት። ሲበዛ "ለገኖች" ይላል።

ለገዘ) (ለከሰ): አልገዘገዘ፡ አንገታገተ፡ አንገዛገዘ።

ለገደ (ትግርኛ: ለገጸ): ቀለደ፡ ተረበ። በአረብኛ '' እና '' ተወራራሽ ስለ ኾኑ ትግርኛ "ለገጸ" በአማርኛ "ለገደ" ተባለ። "ለገጠ" እይ።

ለገደ: ኣገባ፡ ወተፈ፡ ቀረቀረ፡ ደነቀረ፡ መረገ።

ለገዳ: ቅርቀራ፡ ውተፋ።

ለገድ: ነፈል፡ ቅጭጭላት።

ለገገ (ሠወነ): ተለቀቀ፡ ወጣ፡ ተመለለ።

ለገጠ) (ትግርኛ: ለገጸ): ተለገጠ፡ ተፌዘ፡ ተቀለደ፡ ኾነ፡ ተደረገ (ለግጡ፣ ሽሙጡ)

ለገጭ ገባ: መነገገ፡ ለገጭን ያዘ።

ለገጭ: የከብት ታችኛ መንጋጋ። "አገጭን" እይ፡ '' '' ፈንታ የገባ ነው።

ለጊ: የለጋ ወይም የሚለጋ፡ የሚመታ፡ አጠንጊ።

ለጋ (ረጋ): (ዎች) የሠራተኛ፡ የባለጅ፡ ተወላጅ ያልሆነ ሰው፡ ከጠይቦች ተምሮ ሸክላን ብረትን የሚሠራ። "(ተረት) ላይሉኝ፡ ወሶ፡ ደርሼ፡ ነበር፡ እረጋ፡ ለቅሶ፡ ረጋ፡ በጋልኛም፡ ምስክር፡ ማለት፡ ነው።"

ለጋ (ትግርኛ: ለግዐ፡ እንገርን ዐለበ): ዕሩርን፣ ጥንግን ከእጁ ለቆ እመሬት ሳታርፍ በዱላ ቀልቦ መዠመሪያ ቀላ መታ፡ አጠነጋ። "ለግዐ" ጥንታዊ ዐማርኛም ሲባል ይቻላል።

ለጋ ልጅ: ካ፲፭ ዓመት በታች ያለ ልጅ።

ለጋ፡ ቅቤ፡ ለስታ፡ ቅቤ፡ እንዲሉ።

ለጋ ቅቤ: ትኵስ፡ ለስታ ቅቤ።

ለጋ ደመና: ጥቍረት፣ ጥቍርነት የሌለው ደመና።

ለጋ ጐበዝ: ወጣት፡ ልጅ እግር ሦታ።

ለጋ ጨረቃ: ብርሃኗ ያልሞላ፡ ያልደመቀ።

ለጋ: ቀንበጥ፡ ሙሽራ፡ ያልጠና፡ ያልጠነከረ ቅጠል፡ ልጅ፡ ለምለም፡ እንቦቀቅላ (ለምሳሌ በ፩ኛ ዜና መዋዕል ፳፱:፩፣ ኢሳይያስ ፲፭: ላይ እንደተጠቀሰው) "ለጋ ጐመን" እንዲሉ። (ግጥም) "እኔ እንቢ አሻፈረኝ እወጣለሁ ደጋ፡ ዐንገቷ ይመስላል የጠንበለል ለጋ። "

ለጋ: ባለማቋረጥ ቶሎ ቶሎ ጠጣ። "ሸመጠጠን" እይ።

ለጋሚ (ዎች): የለገመ ወይም የሚለግም።

ለጋስ (ሶች): የለገሰ ወይም የሚለግስ፡ ቸር፡ ሰጪ (አባ መስጠት) (ለምሳሌ በኢሳይያስ ፴፪: ላይ እንደተጠቀሰው)

ለጋስነት: ለጋስ መኾን።

ለጋዎች/ለጎች: ቀንበጦች፡ ለምለሞች።

ለጋጅ: የለገደ ወይም የሚለግድ፡ ቀርቃሪ።

ለግ መስፈሪያ: ሎን።

ለግላጊ: የለገለገ ወይም የሚለገልግ፡ የሚስብ፡ የሚጠባ፡ መግማጊ፡ ግልገል፡ ቡችላ።

ለግዳ: ቅምሖ፡ የጕረሮ ዕብጠት (በኹለት ወገን የሚበቅል በማንቍርት ጫፍ የሚለገድ) "ለቅዳ" ተብሎ ሊጻፍም ይቻላል።

ለግድ: ለግጥ።

ለግጠኛ (ኞች): ፌዘኛ፡ ቀልደኛ።

ለግጥ (ፈየጠ): (መጣበቅ)

ለግጥ: ፌዝ፡ ቀልድ፡ ሽሙጥ። (ተረት) "ቀብረው ሲመለሱ እግዜር ይማርዎ። " መምህራን ግን "ለግድ" ይሉታል። "ለገደን" ተመልከት።

ለግጦ: ለግጥ።

ለጐመ (ለገበ): አገልግልን፣ ማንኛውንም ስፌት በቈዳ፣ በተንቤን ሰፋ፡ ለበደ፡ አለበሰ (መላውን ወይም ከንፈሩንና እግሩን) "ከፈፈን" እይ።

ለጐመ (ለጕም፣ ለጐመ): ልጓምን፣ ጥይትን፣ ኳስን ለበቅሎ፣ ለፈረስ፣ ለጠመንዣ፣ ለባሪያ አጐረሠ፡ ቀረቀረ።

ለጐመ: ዝም አሠኘ፡ አሰረ (አፍን) (ለምሳሌ በዘዳግም ፳፭: ላይ እንደተጠቀሰው)

ለጐደ: ለደፈ፡ ለጠፈ (የምራቅ፣ የንፍጥ፣ የጭቃ)

ለጐጠ: በቀላል ወተፈ፡ አገባ።

ለጓሚ (ሞች): የለጐመ ወይም የሚለጕም (ፈረስ፣ በቅሎ ጫኝ)

ለጓጅ: የለጐደ ወይም የሚለጕድ፡ ለዳፊ።

ለጓጣ: የተለጐጠ፡ ወታፋ።

ለጓጭ: የለጐጠ ወይም የሚለጕጥ፡ ወታፊ።

ለጠ: ዳለጠ ለዘበ፡ ከመሻከር ራቀ፡ ሥራ ፈታማገጠ

ለጠመ: ትግ፣ ሐበሻ: ለጽመ፣ ሰካ፣ ዶቃን፡ አስጠጋ፣ ከደነ፣ ገጠመ። ለጠበን እይ፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።

ለጠም: መክደኛ፣ መግጠሚያ፡ ለጠብ።

ለጠሰ: ብዙ ሰዓት አስተኛ፣ አጋደመ፡ ድቄቱ፣ ዝናሙ፣ ሰውን፣ ሰብልን።

ለጠሰ: አስተኛ፣ ለጠሰ።

ለጠቀ፡ (ከተለ)

ለጠቀ: ለሰቀ፡ ወጋ፣ ሰፋ፣ አጣበቀ። "እከሌ ጠላቱን በጦር ከመሬት ለጠቀው"

ለጠቀ: ለጸቀ፡ ተከተለ፣ ደረሰ፣ ተጠጋ፣ ቀረበ።

ለጠቅ: ለጺቅ፡ ጠጋ፣ ቀረብ። (ተረት) "ሲኖሩ ለጠቅ፣ ሲሄዱ መንጠቅ"

ለጠፈ: ትግ፣ ሐበሻ: ለዕፈ፡ በግድግዳ ወይም በግንብ ላይ ጭቃን፣ ኖራን ጨመረ፣ መረገ፣ ደረበ፣ አጣበቀ፣ አገናኘ፣ አያያዘ። ለደፈን እይ።

ለጠፈ: ጥፋትን በሰው ላይ አደረገ፣ ላከከ።

ለጠፈበት: "ይህን ያደረገ እከሌ ነው" አለ።

ለጣሚ: የለጠመ፣ የሚለጥም፡ ከዳኝ፣ ገጣሚ።

ለጣሽ: የለጠሰ፣ የሚለጥስ ከባድ እንቅልፍ፣ በሽታ።

ለጣቂ: የለጠቀ፣ የሚለጥቅ፡ ተከታይ፣ ለሳቂ።

ለጣቃ: ጠባቃ።

ለጣጠፈ: አንድ ጊዜ፣ ሁለት ጊዜ ለጠፈ፡ መራረገ፡ ደራረበ።

ለጣፊ: ለጣፎች፡ የለጠፈ፣ የሚለጥፍ፡ መራጊ፣ አጣባቂ። "ጣፊ ለጣፊ" እንዲሉ።

ለጣፋ: ነገር ለቃሚ።

ለጥ አለ: ትክክል ሆነ። ለጠጠ።

ለጥቄ: የሰው ስም፡ ለጥቅ፣ ተከተል ማለት ነው።

ለጥኣን፡ የወረደ፡ ለጻድቃን፡ ይተርፋል።

ለጨ: ድጥ ሆነ

ለፈለፈ: ለቃ።

ለፈለፈ: ለፈፈ፡ ቀባጠረ፣ ነገር አበዛ፣ ባለማቋረጥ ቶሎ ቶሎ ተናገረ። (ተረት) "ይጠፉ በለፈለፉ"

ለፈሰ: አልፈሰፈሰ፡ አዝለፈለፈ፣ ኦጥመለመለ፣ አደከመ፣ አዛለ።

ለፈስፋሳ: የሚልፈሰፈስ፡ ዘለፍላፋ።

ለፈረስ ደረሰ (የልቡ፡ ደረሰ)፡ እንዳሰበው፡ ተደረገ፡ ተከናወነ።

ለፈተተ: በርጥበትና በድርቀት መከል ኾነ።

ለፈወቀ: በምግብ ጊዜ አፉን አጮኸ፡ "እንጯ እንጯ" አደረገ።

ለፈደ: ዘበዘበ፣ ነገር አልቈርጥ አለ።

ለፈደደ: ጨምላቃ ኾነ።

ለፈደድ: ለፍዳዳ፡ የተለፋደደ፣ የሚለፋደድ፡ ጨመለቅ፣ ጨምላቃ፣ ነገረ በክ።

ለፈዲያም: ዝብዝባም፣ ነገረ ጐትት። ለፈደደን እይ።

ለፈድ: ዝብዝብ፣ ጣመ ቢስ ነገር።

ለፈጠ: ለፈጸ፡ ዐሸ፣ ለወሰ፡ አበቀ፣ አበሰበሰ።

ለፈጨቀ: ነዘነዘ፣ ጨቀጨቀ። ለፈደደን ተመልከት።

ለፈጫ: ልፋጭ አደረገ፡ ልፋጭ አወጣ።

ለፈፈ: ለፊፍ፣ ለፈ፡ እየዞረ ኾኖ ነገረ፣ ዐወጀ፣ አሰማ፣ ሰበከ። (፩ነገ. ፳፪፡ ፴፮)

ለፈፈ: ዐጠፈ፣ ጠቀለለ።

ለፈፋ: የመልፈፍ ኹናቴ፡ ዕወጃ።

ለፊ: ለፋዒ፡ የለፋ፣ የሚለፋ፣ የሚደክም፡ ውርደት ተቀባይ። (ግጥም) "ሰዉ ሰው ላይ ገቢ ነው የተያዘ እንደኹ ለፊ ነው"

ለፋ፡ ደከመ፡ ሰነፈ፡ ሰለቸ፡ (፩ኛ ሳሙኤል፡ ፯፡ )

ለፋ: ትግ፡ ለፍዐ፡ ታሸ፣ ተፈተን፡ ተረገጠ፣ ተገለጠ፣ ለሰለሰ፣ ለተተ፣ ደቀቀ።

ለፋ: ጣረ፣ ጋረ፣ ደከመ።

ለፋለፈ: ቀበጣጠረ፣ ነገር መላለሰ።

ለፋፊ: ለፋፊዎች፡ የለፈፈ፣ የሚለፍ። (፩ነገ. ፳፪፡ ፴፯)

ለፋፊነት: ለፋፊ መኾን።

ለፍላፊ: ለፍላፊዎች፡ የለፈለፈ፣ የሚለፈልፍ፡ ቀባጣሪ፡ የዝምታ ጠላት።

ለፍላፊነት: ለፍላፊ መኾን፡ ቀባጣሪነት።

ለፍላፋ: አፈኛ፣ ተናጋሪ።

ለፍቃ: ለፍዳዳ፣ የሚለፋጨቅ፡ ነዝናዛ፣ ጨቅጫቃ።

ለፍታታ: ርጥብ አይሉት ደረቅ፡ ርሻ የቈዳ ተለዋወዝ።

ለፍቶ መና: ዐርሶ ነግዶ የማያልፍለት፡ ትርፍ የለሽ።

ለፍቶ: ጥሮ፣ ደክሞ። "ለፍቶ ዐደር" እንዲሉ።

ለፎ: ለፈየ፡ አገዳ፣ መቃ፣ የግዳይ መቍጠሪያ።

ለፎ: ጀሌ፣ መደዴ፣ ወያኔ።

ሉሕ: (ለውሕ) ልዝብ ሳንቃ ጠርብ፡ ሰሌዳ፣ ብራና፣ ወረቀት።

ሉህ: ሰሌዳ።

ሉሖች: ሳንቆች፣ ወረቀቶች።

ሉል ሰገድ: የሰው ስም፡ "ሉል የሰገደለት" ማለት ነው። አስቀድሞ የንጉሥ ብቻ ነበረ፡ ዛሬ ግን የኹሉ መጠሪያ ኹኗል። ነገሠ ብለህ ንጉሥን እይ።

ሉል ዐደይ: ዐደይ አበባ የሚመስል ሉል ብጫቴ።

ሉል: ዐረ፡ ሉእሉእ፡ በቁሙ፣ ከባሕር የሚገኝ ዕንቍ፡ ንጉሥ ሲነግሥ በእጁ የሚጨብጠው፡ ይኸውም አገር በጄ ማለትን ያሳያል፡ በግእዝ ባሕርይ ዕንቈ ባሕርይ ይባላል። "ሉልና ዘውድ" እንዲሉ።

ሉሎች: ዕንቆች።

ሉሜ: በአዳ ወረዳ ያለ ቀበሌ።

ሉቃሳም: ሉቃሳሞች፡ የሉቃስ፣ ባለሉታስ፡ ችጋራም፣ ራብተኛ፣ በልቶ የማይጠግብ፣ ሥሡ፣ ገብጋባ። ባላገር ግን "ልቋስ" "ልቋሳም" ይላል።

ሉቃስ: ከብት ያለቀበትና ረኃብ የጸናበት ጊዜ፡ ክፉ ቀን። ይኸውም በ፲፰፻፹፩ .. ዠምሮ ነው።

ሉቃስ: የሰው ስም፡ ካራቱ ወንጌላውያን አንዱ። ግብረ ሐዋርያትንም የጻፈ ርሱ ነው። ቍጥሩና ማዕርጉ ከ፸፪ቱ አርድእት።

ሉቃስ: የዘመን ክፍል፡ አራተኛ ዓመት ጳጕሜ የምትኾንበት ፬ኛነቱ ለዮሐንስ ነው።

ሉባ (ኦሮ): በ፰ ዓመት የሚሻር ጠቅላይ ባለሥልጣን (የዱሮ)

ሉባ: ማለፊያ፡ ብርቱ ልጅ፡ ፈጣንና ቀልጣፋ ማለትንም ያሳያል።

ሉካንዳ: ሉካንዳዎች፡ የምግብ ቤት፣ የመብል መደብር፡ ሥጉያ። "ሉካንዳ" በጣሊያንኛ "ሎካንዳ" ይባላል።

ሉክ: ኰፊር።

ሉክ: ወረቀት፣ ሉሕ።

ሉድ: የሴት ስም።

ሉግ: ፲፪ ዕንቍላል የሚይዝ መስፈሪያ (ለምሳሌ በዘሌዋውያን ፲፬: ላይ እንደተጠቀሰው)

: እሱ፣ እነሱ በተባሉት ሰራዊት እየገባ 'ከእንዲ' በኋላ የዘንድ አንቀጽ ሁሉ መነሻ ይኾናል። "ሊማር ይወዳል""ሲማሩ ይወዳሉ""ሊበሉት ያሰቡትን አሞራ ስሙን ይሉታል ዥግራ"

ሊል ዘሊል: ሰነፍ፣ ሞኝ፣ ንዝህላል፣ አውታታ። "ሊል የዘሊል ከፊል ቢሆን ፍጹም ጋድሚያ ተብሎ ይተረጎማል" ፪ኛውን "ዘለለ" ተመልከት። ዳግመኛም "ዘሊል" የሊል አይነትና ወገን ያሠኛል። "" የግእዝ "" ነውና።

ሊል: ለየ፡ ከሥራ፣ ከትጋት የተለየ።

ሊል: ልይል፡ የሩቅ ወንድ ፫ኛ ዘንድ አንቀጽ።

ሊሎ: ለየ፡ ሌሊታዊ አሞራ፣ ጕጕት ወይም የሴት ወፍ። ትግሬ ሐባብ ግን ንስርን "ሊሎ" ይለዋል፡ ይኸውም ግልገልን ከናቱ ለይቶ መውሰዱን ያሳያል።

ሊሙ: በጅማ አውራጃ የሚገኝ አገር። "ሊሙ ያቅኒው" ስም ነው።

ሊቀ ሐመር: የመርከብ አዛዥ። ፈረንጆች "አሚራል" ይሉታል።

ሊቀ ሀገር: አገረ ገዢ።

ሊቀ ሊቃውንት: ከሊቃውንት የበለጠ፣ የሊቃውንት ሊቅ።

ሊቀ መላእክት: የመላእክት አለቃ፡ ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ሩፋኤል።

ሊቀ መንበር: የጉባኤ አለቃ።

ሊቀ መኳስ: ሊቀ ሞገስ፡ የመወደድ አለቃ፣ ጭራና መነሳንስ ይዞ በንጉሥ አጠገብ የሚቆም ባለል፣ የንጉሥ አሳሳች፣ የባለል አለቃ።

ሊቀ መዘምራን: የመዘምራን አለቃ።

ሊቀ መጣኞች: የይግባኝ ሰሚዎች አለቃ፡ ይኸውም በጐንደር መንግሥት ነው።

ሊቀ ምርፋቅ: የምርፋቅ አሳራጊ፣ መነኵሴ።

ሊቀ ምርፋቅ: የዳስ ሹም፣ አሳዳሪ።

ሊቀ ሰማዕታት: የሰማዕታት አለቃ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ።

ሊቀ ረድ: የረድ አለቃ፡ እንደ ደብረ ሊባኖስ ባለው ገዳም የመጋቢ ምክትል አዛዥ።

ሊቀ ካህናት: የካህናት አለቃ፡ ጳጳስ፣ ኤጲስቆጶስ፣ ንቡረ እድ፣ ዕጨጊ። ዳግመኛም በግእዝ "ሊቀ ኖሎት" (የረኞች አለቃ) ይባላል።

ሊቀ ደብተራ: የደብተራ አለቃ፣ መሪ፣ ጌታ ወይም ሌላ።

ሊቀ ዲያቆን: የዲያቆን አለቃ፣ አስተዳዳሪ። ይህ ማዕርግ መዠመሪያ ከሐዋርያት ለቅዱስ እስጢፋኖስ ተሰጥቷል።

ሊቀ ጠበብት: ያዋቆች፣ የደብተራዎች አለቃ፡ የቤተ ክርስቲያን ሹም ከዋናው አለቃ በስተግራ በወንበር የሚቀመጥ።

ሊቀ ጳጳሳት: የጳጳሳት አለቃ፡ ጳጳሳትን የሚሾም፣ የሚሽር፣ በሮም፣ በእስክንድርያ፣ በቍስጥንጥንያ፣ በአንጾኪያ ወንበር የሚቀመጥ፡ ሌላውም ከበታቹ ጳጳሳት የሚሾም ኹሉ ሊቀ ጳጳሳት ይባላል።

ሊቃውንት: ሊቆች፡ ባላገር ግን "ሊቃውንት" በማለት ፈንታ "ሊቃውንቶች" ይላል። ሊቃውንት የበገና ዥማት (እውታር)

ሊቄ: ሊቅየ፡ በቤተ ክርስቲያን የማዕርግ ስም፡ ከሊቃውንት በትምርት ብልጥ ያለውን ንጉሡ "ሊቄ" ይለዋል። "ሊቄ በጸሎቱ" እንዲሉ።

ሊቅ: ልሂቅ፡ ካምሳ ዓመት በላይ ያለ ሽማግሌ ዐዋቂ፣ ጨዋ ዐዛውንት፣ አሮጌ (አረጋዊ) "ከሊቅ እስከ ደቂቅ" እንዲሉ። "ሊቅ" "አሊቃ" (ግእዝ)

ሊቅ: ምሁር፣ የተማረ፣ ትምርት የጠዘበ፣ በትምርትና በዕድሜ የበሰለ፡ አለቃ፣ መምህር፣ ጌታ፣ ብለይና ሐዲስ ዐዋቂ። ፈረንጆች "ዶክተር" ይሉታል። አፍን እይ።

ሊቅ: የሊቃውንት መጻፍ፡ ሃይማኖተ አበው፣ አፈ ወርቅ፣ ቄርሎስ፣ ኤጲፋንዮስ፣ ቅዳሴ አቡ ሻህር።

ሊቅ: የተማረ፡ ላቀ።

ሊቅነት: ሊቅ መኾን፡ ምሁርነት፣ ዐዋቂነት፣ ፍጹም ትምርት።

ሊቆች: ሊቃውንት፣ ሊቃናት፡ እጅግ የተማሩ ዐዋቆች፣ መምህሮች።

ሊበን (ኦሮ): ያገርና የነገድ ስም።

ሊባ: የታናሽ ማእዘን ስም፡ ፭ኛ የዓለም ማእዘን (በምሥራቅና በደቡብ መካከል በባሕር አንጻር ያለ)

ሊባኖስ: በሊባኖስ የተወለደ፡ የሊባኖስ ሰው፡ ጻድቅ መነኵሴ፡ ከተስዐቱ ቅዱሳን በፊት ወዳገራችን በ፫ኛው .. መጥቶ ወንጌልን እየሰበከ ብዙ ጊዜ የኖረ፡ ካባ ተክሌ አስቀድሞ ደብረ ሊባኖስን ያቀና። ፪ኛ ስሙ 'መጣዕ'፡ ፫ኛ ስሙ 'ይስሪን' ይባላል። "አባ ሊባኖስ" እንዲሉ።

ሊባኖስ: በሶርያና በእስራኤል ምድር መካከል ያለ ደጋ፡ ከፍተኛ ስፍራ፡ ዛፋም፡ ደናም ተራራ፡ አርዝ የሚበቅልበት።

ሊባኖስ: የዛፍ ስም፡ አስታ የሚመስል ዕንጨት ዐዲሳበቦች የሚተክሉት።

ሊትር: (This seems to be a heading for the following terms).

ሊትር: ሊትሮች፡ ቃሩራ፣ ጠርሙስ፡ የውሃና የመጠጥ፣ የመድኀኒት ማስቀመጫ። የሊትር ልክ ወይም ሚዛን በግእዝ "ልጥር" በአማርኛ "ነጥር" ይባላል። "ሊትር" ፈረንጅኛ ነው።

ሊጋባ (ቦች): ሰውን ወደ ቤተ መንግሥት ሊያገባ (ሊያስገባ) የተሾመ፣ የአጋፋሮችና የከልካዮች የበላይ ባለሥልጣን። ማስታወሻ: ቀድሞ ዘመን "ራቅ ማሰሬ" ይባል ነበር።

ሊጋባ: የማዕርግ ስም። ገባ።

ሊጥ: በቁሙ፣ ለጠጠ።

ሊጦን: የጸሎት ስም፡ በቤተ ክርስቲያን ቄሶች የሚያዜሙትና የሚደግሙት ምስጋና፡ ዘጠኝ ክፍል ያለው፡ ፈረንጆች ሊታንያ ይሉታል። የደረሰው ባስልዮስ ዘቂሳርያ ነው፡ ከሰኞ እስከ እሑድ ይባላል።

ሊፍ: ንጣጭ።

ሊፍ: የሳንቃ ንጣጭ፣ የባሕር ዕቃ መጠቅለያ።

(አልአ): የሐዘንና የማድነቅ ቃል ወይም የመልከት። "አንተንም መሬት ይበላኻላ እንደ ሞኝ ሰው እንደ ተላላ። "

: ለሩቅ ሴት የአንቀጽ ዝርዝር፡ ፍቺው "ላት" (ማስረጃ) "ይስሙ" -> "ይስሙላ" መዠመሪያውን "ላት" እይ።

: በስም መጨረሻ እየተጨመረ ቅጽልና አንቀጽ ይኾናል። (ማስረጃ) "አበባ" -> "አበቢላ""ወንድ" -> "ወንዲላ""ኩቲ" - "ኵቲላ""ዐር" - "ዐሪላ" በቅጽልነትም፣ በአንቀጽነትም "አላት" ተብሎ ይተረጐማል።

ላሑ: ሥሥ ጠጕር፡ ከመተኛት በቀር መቆም የማይችል፡ በጋልኛ "ሉጫ" ይባላል።

ላሕማ: (ዐረ. ለሐመ) መረገ፡ መጣብቅ ሙላጭ፡ የደብዳቤ፣ የቀዳዳ ቆርቆሮ ወይም ታኒካ መምረጊያ፣ መድፈኛ፡ በአረብኛ "ልሐማ" ይባላል። (ሸብን ተመልከት።)

ላሊበላ: ላሊ በላ፡ የንጉሥ ስም፡ በላስታ የነገሠ የኢትዮጵያ ንጉሥ ፲፪ መቅደስ ባንድ ዋሻ ውስጥ ያነጸ። "ላስታ ላሊበላ" እንዲሉ። አንዳንድ ሰዎች "ዐጤ ላሊበላ የተወለደ ለት በንብ ስለ ተከበበ ማር ይበላ እንደ ማለት በአገው ቋንቋ ላሊበላ ተባለ" ይላሉ።

ላሊበላ: ላሊበላዎች፡ የነገድ ስም። "ሌሊት ወየው ዓለም" እያለ ለምኖ የሚበላ ስለ ኾነ "ላሊበላ" ተባለ። ሐባብ "ሌሊት" ሲል "ላሊ" እንዲል። (መዝ. ፩፡ ፪) "የላሊበላ ጋብቻ በየተዝካሩ ቤት ነው" (ተረት) "ላሊበላ ዐደራውን አይበላ" ደብራሆምንና ሐሚናን እይ። "ዐጤ ላሊበላም ሲጦም እየዋለ ማታ (ሌሊት) በመብላቱ ላሊበላ (ሌሊተ በላ) የተባለ ይመስላል" ብንል የተመቸ ነው። "ሌሊት"–በቁሙ፣–"ለየ"

ላላ አለ: ራስ ረገብ አለ፡ ላላ።

ላላ አደረገ: በጥቂቱ አላላ።

ላላ: ላሕልሐ፣ ላኅልኀ፡ ራስ ለሰለሰ፣ ረገበ፡ ከመድረቅ፣ ከመጥበቅ፣ ከመክረር ራቀ፡ የማሰሪያ፣ የያንደበት፡ የእጅ፣ የሌላውም ነገር። (፪ሳሙ. ፳፪፡ ፵፮፣ ምሳ. ፳፬፡ ፲)

ላላ: ላሕልሖ፡ መላላት።

ላላቴ: ታናሽ ዕብስት፣ ለስላሳ፣ ተስፋ።

ላላገ: ፋፋቀ፡ አለዛዘበ።

ላሎ ምድር: የላሎ ምድር፡ ወይም ርስት።

ላሎ: የሰው ስም፡ የግማሽ መንዝ ባላባት።

ላመ ፈጅ: ታላቅ የብረት ድስት፡ መካከለኛ ጐላ።

ላመ: ልሕመ፡ ደቀቀ፣ ተሰለቀ፣ ለዘበ፣ ለሰለሰ፡ ደከመ፣ ለፋ፡ የዶቄት፣ የሰውነት።

ላመል (ለዐመል): ለልማድ፡ ጥቂት፡ ትንሽ።

ላመል: ጥቂት ዐመልን።

ላመት: የሚመጣው ዓመት። "ለላመት" (ለዓመት)፡ ዝኒ ከማሁ፡ ለከርሞ።

ላሙ: ላም። "ላሙ ሲገኝ ዐላቢው አይገኝ"

ላሚ: የሚልም፡ ለዛቢ።

ላሜዳ: ላይዳ፣ ላይ።

ላሜድ: የፊደል ስም ""፡ ትምርት ወይም የተማረ ማለት ነው።

ላም ላጊ: ላምን የሚጠባ ሸሌ፣ መጠማጥ።

ላም አለ: ልዝብ አለ፡ ላመ።

ላም ዐንገት: ፈሪ፣ ርግብግብ።

ላም: ላሕም፡ የቤት እንስሳ፣ እንስት የቀንድ ከብት፡ የበሬ ጣምራ፣ የጥጃ እናት፡ የዋህ ዐመለ ደንሴ። "እከሌ ላም ነው" እንዲሉ። (ተረት) "ላም የዋለችበትን ትመስላለች። ለላም ቀንዷ አይከብዳትም" "ላም አለኝ (አለችኝ) በሰማይ፡ ወተትም አልጠጣ፡ ዐሲቡንም አላይ" "የሥጋ መድኀኒት ላም፡ የነፍስ መድኀኒት ማርያም" እንዲሉ። ሲበዛ "ላሞች" ይላል (. ፱፡ ፫) "ላም" በግእዝ የወል ስም ስለ ኾነ ለተባቱም ይነገራል (ምሳ. ፲፬፡ ፬) "ላም ባልዋለበት ኵበት ለቀማ"

ላም: ላሙ: የላም መንጋ።

ላም: ላሚቱ፡ ያች ላም። (ዘኁ. ፲፱፡ ፭፣ ፰፣ ፱፣ )

ላም: ጥም፡ ልሒም፡ መላም።

ላምባ: ላምፓ (ሮማይ፡ ላምፖስ)፡ ችቦ፣ ቲሃ።

ላምባ: ልንጳስ፡ መብራት የሚኾን የምድር ዘይት ጋዝ። "ላምባ" ጋዝ ማለት በአረብኛ ነው።

ላምዛን: አነባበሮ፡ ለመዘ።

ላምዛን: አነባበሮ፡ ሊጡ ታሽቶ የተቦካ።

ላሰ: ለሐሰ፡ ምላስ ጠረገ፣ አጠዳ፣ በላ፣ ተመገበ። "እከሌ በጣም ጠግቧል ማርም ኣይልስ" "እሳት የላሰ"፡ ተንጠልባ የማያናግር።

ላሰ: አቃጠለ፣ መለጠ።

ላሰሰ: ትግ፡ ላሕሰሰ፡ ኣብዝቶ ነቀለ፡ ሰሰ እሸትን፣ ጤፍን።

ላሰሰ: አብዝቶ ነጨ፣ ነቀለ። "ሞለቀቀን" እይ።

ላሣ): ንሣ፡ ተቀበል፣ ውሰድ።

ላሳሽ: የላሰሰ፣ የሚላስስ፡ ነቃቂ።

ላስ አደረገ: ጥርግ አደረገ።

ላስ አደረገ: ፈጀ፣ ጨረሰ እሳት።

ላስ: ልሒስ፡ መላስ።

ላስቲክ: ላስቲኮች፡ ፈረንጆች ከእንጨት ደም የሚሠሩት፡ ሲስቡት የሚረዝም፣ ሲለቁት የሚያጥር ነገር፡ ነትና፣ ተንቤን መሳይ ሥሥና፡ ወፍራም። እንደ ርጥብ ስልቻ ይነፋና ለተንቀሳቃሽ መኪና እግር ይኾናል፣ ለሌላም ጕዳይ ይገባል፡ ጠንካራው "ጎማ" ይባላል። ላዘገን ተመልከት።

ላስታ ላሊበላ: ያጤ ላሊበላ እግር ላስታ፡ ወይም የላስታው ላሊበላ። ላሊበላን እይ።

ላስታ: ያገር ስም፡ በየጁ አጠገብ ያለ አገር።

ላስቶች: የላስታ ሰዎች፡ የላስታ ተወላጆች።

ላሸ: ትግ፡ ላሸወ። ለስሐ፡ ላላ፣ ጥብቀት ዐጣ፣ ለጠ፡ የምላስ፣ የጠመንዣ፣ የወፍጮ። (መክ. ፲፪፡ ፬) ላሸ የላሸቀ ከፊል ነው።

ላሸቀ: ቀን ተመልከት። በጣም ለፋ፡ ቈዳው ላላ፣ ለጠ ቃታው። ላሸን እይ።

ላሽ: ለሓሲ፡ የላሰ፣ የሚልስ። "ላሺ" ተብሎ ሊጻፍም ይችላል።

ላሽ: ላሺት፡ መርዝ ያላት ታናሽ ዝንብ፡ "ሳትታይ፣ ሳትሰማ የራስን ጠጕር እየላሰች ትመልጣለች" ይላሉ። ሐኪሞች ግን በደም መበላሸት ምክንያት መኾኑን ያስረዳሉ።

ላሽ: ቋያን።

ላቀ: ልህቀ፡ አደገ፣ ጐለመሰ፣ አካለ መጠን እደረሰ፣ ከፍ አለ፣ በለጠ።

ላቀ: አረጀ፣ ሸመገለ።

ላቀ: ከበረ፣ ተሾመ፣ አለቃ ኾነ።

ላቀቀ: ነገር ሳትካፈል፣ ሳትይዝ ባዶ እጇን ኼደች ነውረኛዪቱ ሴት።

ላቀቀ: ዕብ፡ ላቃቅ፣ ላሰ፡ ፈቀደ፣ መብት ሰጠ፣ አሰናበተ፣ ዋስን ዐግት አለ።

ላቀች: የሴት ስም፡ "በለጠች" ማለት ነው።

ላቀው: የሰው ስም፡ "በለጠው" ማለት ነው።

ላቂ: ለሃቂ፡ የላቀ፣ የሚልቅ፡ የበለ፡ የሚበልጥ።

ላቂ: የዟይ ደሴት ፭ቱ ኹሉ፣ በጋልኛ "ቀዛፊ" ማለት ነው።

ላቂያ: ብልጫማ፣ ማዕርግ ከፍታ።

ላቃ) ነቃ (ነቂህ): መንቃት።

ላቃቂ: የላቀቀ፣ የሚላቅቅ፡ ዳኛ።

ላቈጠ: ፈጽሞ ራሰ፡ ተረገጠ፣ ታሸ፣ ተለወሰ።

ላቅ አለ: በለጠ አለ።

ላቅ: ልሂቅ፡ መላቅ።

ላበ (ልህበ): ሞቀ፡ ተኰሰ፡ ወዛ ወጣ፡ ጭፍጭፍ አለ፡ ፈሰሰ።

ላበት/ላቦት (ልህበት): ሙቀት፡ እንፋሎት፡ በዝናም ጊዜ ከመሬት ብርድ ሲኾን ከሆድ ከፈላ ውሃ የሚወጣ ጭስ (ለምሳሌ በኢሳይያስ :፳፬ ላይ እንደተጠቀሰው)

ላባ ሞረድ: ሥሥና ቀጪን ሞረድ፡ የማጭድ መዘርዘሪያ፡ "ላባ" ያሠኘው መሣሣቱ ነው።

ላባ ቀረሽ: በራሱ ጠጕር ላይ ላባ ሊሽጥ ጥቂት የቀረው እብድ።

ላባ: በካብ፣ በግንብ ዐጥር፣ ዐሰላ ላይ የተተከለ ብረት፡ ሹለትና ስለት ያለው (ጠላትን ከልክል፡ በግእዝ 'መብኀል' ይባላል) በዘመናችን ግን የጠርሙስና የብርጭቆ ስባሪ ነው። "በላይ የመጣውን በላባ ይከለክሉታል" (ትርጓሜ: ትህርተ ኅቡኣት) "ዲርን" ተመልከት።

ላባ: የወፍ፣ የአሞራ ጠጕር፡ ልብሳቸው። ሲበዛ "ላባዎች" ያሠኛል። በጋልኛ 'ባሊ' ይባላል።

ላባም: ላበ ብዙ፡ ባለላብ። "ላባን" እይ።

ላባም: ላባ ያለው፡ ባለላባ።

ላብ (ላህብ): ሙቀት ያለው የገላ ወዝ፡ የደም ዐረቄ ከድካም የተነሣ፡ የሚፈስ።

ላብ ላብ አለው: ሞቀው፡ ሙቀት ተሰማው።

ላተ፡ ኳስን፡ ጥንግን፡ ሳይቀልብ፡ ሳይመታ፡ ቀረ፡ ቸኰለ፡ ተጣደፈ፡ (ጐዣም)

ላተ: ለዐተ፡ ላት አወጣ፣ ሠራ።

ላተነ: ሸግ አለ፡ ተገነፋ፣ ተዋዋደ፣ ተሰማማ።

ላቲን: በግእዝ "ሮማይስጥ" የሚባል አሮጌው የሮማውያን ቋንቋ።

ላቲን: የሮማውያን ዘር ስም።

ላቲኖች: ከላቲን ነገድ የተከፈሉ፡ ፈረንሳዮች፣ ፑርቱጌዞች፣ እስጳኞች፣ ሌሎችም በአሜሪካ አገር በ፩ ክፍል ያሉ ወገኖች "ላቲኖች" ይባላሉ፡ አገራቸውም "ሜክሲኮ" ነው።

ላት: ለዐት፡ የበግ ዥራት። (. ፳፬፡ ፳፪)

ላት: ላቲ፡ ለሩቅ ሴት የአንቀጽ ዝርዝር። "እከሊት ልጇ ከዘመቻ ደኅና ገባላት፡ ብዙ ምርኮ አመጣላት። አሽከሯ ውሃ ቀዳላት፣ ዕንጨት ሰበረላት"

ላት: ላት የሚመስል የጐራዴ እጀታ ዳር ማገጃ፡ "ኹለተኛ ስው ደም ዐፋሽ" ይባላል። መክድን እይ።

ላት: የጠመንዣ ሰደፍ።

ላቸው: ሎሙን፡ ለሩቆች ወንዶችና ሴቶች የንቀጽ ዝርዝር። "ኢየሱስ ክርስቶስ ለእስራኤል ወንጌልን ሰበክላቸው፡ ዕውሮቻቸውን አበራላቸው፡ የሞቱትንም አስነሳቸው"

ላችኹ: ለክሙ፡ ን፡ ለቅርቦች ወንዶችና ሴቶች የአንቀጽ ዝርዝር። "ነቢያት ሆይ ደስ ይበላችኹ፣ ክርስቶስ ተወለደላችኹ፣ ብርሃን ተገለጠላችኹ"

ላንሴታ: ላንሴታዎች፡ የሚዛን ምላስ ፍትውልብልቢት፡ በግእዝ "ለጽሊጽ" ይባላል። ኮለሌን እይ።

ላንቍሶ: ላንቍሶዎች፡ ያረግ ስም። ወፍራም ዐረግ። ባላገሮች በመጥረቢያ እየሸነሸኑ ዐጥርና ግድግዳ ይማግሩበታል፡ ልጡ ከተልባ ይልቅ ይማልጋል።

ላንቍሶ: የሚያለቅስ ልጅ።

ላንቃ ነዲድ: ነበልባል፣ ውልብልቢቱ። (ኢሳ. ፶፡ ፲፩) "የእሳት ላንቃ" እንዲሉ።

ላንቃ: ባለመደረቢያ ካባ። "ካባ ላንቃ" እንዲሉ።

ላንቃ: ትናጋ፡ ያፍ ዋሻ ላይኛው። "አፌን ስለ ተጋረፈኝ ላንቃዬን ዐሞኛል"

ላንባ ጋዝ: ላምባ።

ላንተ (ለአንተ): ላንተ።

ላንተ ይደሩ: የሰው ስም። "ላንተ አሽከር ይሁኑ" ማለት ነው።

ላንቴ: ከፊለ ስም።

ላንፋ: ላንፋዎች፡ የመቃ፣ የጐሽ መቃ፣ የፊላ፣ ያገዳ ቅጠል፣ የሬት ዕንጨት። "የሬት ላንፋ" እንዲሉ። የላንፋ ምስጢር መቅለልና አለመክበድ ነው።

ላከ: ለአከ፡ ሰደደ፣ አመጣ፣ አወረደ። "በትና ለት ሲሰማሙት ላከበት፣ ላከለት" ይላል። (ምሕረቱን ይላክልሽ) ያምጣል፣ ያውርድልህ።

ላከ: ምግብን ወደ ሆድ አገባ፣ ዋጠ፡ ሰለቀጠ። (ሲበሉ የላኩት) ችኩል፣ ጥዱፍ።

ላከከ: ለሕሐ፡ ረጠበ፡ ቀሳ፣ ደለሰ፣ ለጠፈ፡ አጣበቀ፣ ገጠመ፡ አመካኘ። (ግጥም) "አባ ተቈጡልኝ እማ ቈንጥጡልኝ፡ እሷ በፈሰሰችው በኔ ላከከችው" ለደፈንና ደፈደፈን ተመልከት።

ላኪ: ላኪዎች፡ ለአኪ፡ የላከ፣ የሚልክ፡ ሰዳጅ።

ላኪነት: ላኪ መሆን።

ላካኪ: የላከከ፣ የሚላክክ፡ ቀቢ።

ላክ አደረገ: በፍጥነት ዋላ፡ ገንፎን፣ ፍትፍትን።

ላክ: ልኢክ፡ ዋጥ፡ መዋጥ።

ላወሰ: ዞረ፣ ኳተነ፣ ለፋ፣ ደከመ። ለምሳሌ፣ "ዛሬ እንዲያው በከንቱ ስላውስ ውዬ መጣሁ" እንዲሉ።

ላዊ: የፊደል ስም '' ጠማማ፣ ቈልማማ ማለት ነው። "መዝገበ ፊደል" እይ።

ላዘገ: (ዘለገ) እንደ ላስቲክ ሆነ፡ ተሳበ፣ ተጐተተ።

ላዙና: የሐሞት ወርቅ፡ ከበሬ ሆድ የሚገኝ፡ በውስጡ ወርቅ ውሃ ያለበት ብጫ የሚመስል የልፋጭ ከረጢት፡ በደረቀ ጊዜ ፈረንጆች "ሱካር" ለሚሉት በሽታ ከሻይ ጋራ እየተጠጣ መድኃኒት ይሆናል ይላሉ። ላዙና የሚነገረው በሐረርጌ፡ የሚገኘውም በኦሮ ቤት ነው።

ላዛ: ልስላሴ፣ ለስላስነት፡ የጠጉር።

ላይ ሄደ: አፋፍ፣ አፋፉን፣ ላይ ላዩን፣ ደጋ ደጋውን አለፈ፡ ነጐደ።

ላይ ቤት: በመራቤቴ ያለ ቀበሌ።

ላይ ቤት: በጐንደር የነበረ የጉባኤ፣ የመጻፍ ትርጓሜ ትምርት ቤት።

ላይ ቤት: የላይ ቤት፡ ደርብ፣ ሰገነት።

ላይ ቤት: ገነት፣ መንግሥተ ሰማይ።

ላይ: ላዕል፡ ለዐለ፡ ደቂቅ አገባብ፡ ደጋ፣ ሰማይ፣ ሽቅብ፣ ዐቀበት፣ ከፍታ፡ በታች፣ በግርጌ፣ በሥር አንጻር ያለ ከፍተኛ ስፍራ፣ ራስ፣ ራስጌ፣ ጫፍ፣ ውልብልቢት፡ በ፡ ማድረጊያ፡ ወደ፡ መገስገሻ፡ ከ፡ መነሻ ሁነው፡ ያለስምና ከስም ጋራ በመነሻው እየገቡ ሲነገሩ "በላይ፣ በሰማይ ላይ፣ በሰው ላይ፣ ወደ ላይ፣ ወደ ዛፍ ላይ፡ ከላይ፣ ከተራራ ላይ፡ ከላይ ወረደ፣ ከላይ መጣ" ይላል። (ተረት) "ከራስ በላይ ነፋስ" እንጃን ተመልከት።

ላይና ታች: ሰማይና ምድር፡ ደጋና ቈላ፡ ራስጌና ግርጌ።

ላይኛ: ላዕላይ፡ የላይ፣ የሰማይ፡ በላይ ያለ፣ የሚኖር፡ ሲዘረዝር "ላይኛው" ይላል።

ላይኞች: ደገኞች፡ በላይ የሚኖሩ መላእክት፣ ጻድቃን።

ላይዳ አለ: በላይዳ እኸልን ወደ ላይ ወረወረ፣ በተነ፣ ለነፋስ ሰጠ፡ ፍሬን ከገለባ ለየ፡ አመረተ።

ላይዳ: ላሜዳ፡ ላዩ ሜዳ፡ ከእንወት የታነጸ ዝርግ ሾጣጣ ያውድማ ማንካ። ሲበዛ "ላይዶች፣ ላሜዶች" ይላል። ላሜዳ ከለመደም ሊወጣ ይችላል።

ላዳን (ኖች): የመስፈሪያ ስም ሲሆን የዳውላ እኩሌታ፣ ቁና የሚይዝ ቅርጫት፣ ማድጋ፣ እንቅብ ማለት ነው።

ላገ (ልሕገ። ትግርኛ: ለሐገ): ላከ፡ ዐነጠ፡ ዐነጠጠ፡ ፋቀ፡ አለዘበ፡ እለሰለሰ። "ልሕገ" ጥንታዊ ዐማርኛ ነው።

ላገ: ሳባ አጠበቀ (መጫኛን)

ላገ: ዐለበ። (የረኛ ግጥም) "የክትክታ ሞፈር የሚያረገው፡ እመቤቴ ማሪያም፡ አንጀትኸን ትላገው። "

ላገ: አማሰለ (ገንፎን)

ላገ: ጠባ፡ ለገለገ።

ላጊ (ለሓጊ): የላገ ወይም የሚልግ፡ ዐናጢ፡ ፋቂ፡ ጠቢ። "ላም ላጊ" እንዲሉ።

ላጊ: ጕንዳን፡ የጤፍን ፍሬ ከነገለባው የሚያጠፋ፡ ኣገዳውን ባዶ የሚያስቀረው፡ የተፋቀ የሚያስመስለው።

ላጋ) ለጋ (ትግርኛ: ለጋዕ): ያረገዘች ጊደር፡ ወይም ቄብ በግ፡ ፍየል።

ላጠ: (ልሕጸ) ዛፍን ገፈፈ፣ አራቆተ፣ ባዶ አደረገ፡ ልጥን ከቅርፊት ጋራ ወሰደ። (ዘፍ. ፴፡ ፴፯) አማ፣ ስም አጠፋ። ሻረ፣ ለወጠ። እንዳህያ ፈሳ፡ ፈሱን ለቀቀ። መዘዘ ጐራዴውን።

ላጣ (ጦች): የለጠ፣ የሚልጥ፡ ዳላጣ (ወፍጮ)ሥራ ፈት ማጋጣ

ላጤ መላጤ: ልብስ ያረረበት ፍጹም ድሃ፡ ትፈሳ ዶሮ የሌለችው የተላጠ፣ የተመለጠ ግንድ የሚመስል።

ላጤ: ብቸኛ። "ወንደላጤ" እንዲሉ።

ላጤ: ፈሳም፡ ዕፍረተ ቢስ። የተላጠ፣ የተገፈፈ።

ላጥ ላጥ አለ: ልጥኛ ጮኸ፡ ተፈሳ።

ላጥ አደረገ: በኃይል ፈሳ።

ላጥ: (ልሒጽ) መላጥ።

ላጩ: ላጸየ፡ ጠጕርን በምላጭ ከራስ፣ ከጕንጭ፣ ከአገጭ፣ ከኀፍረት ላይ ፈገፈገ፣ ገፈፈ፣ ጠረገ፣ አስወገደ። (በደረቅ ላጭ) አታሰለ።

ላጩ: ረባ፣ ጠቀመ፣ ውለታ መለሰ።

ላጪ: "የላጪን ልጅ ቅማል በላት" እንዲሉ። በግእዝ ላጻዪ (ላጸይት) ይባላል።

ላጪ: ላጮች፡ የላጨ፣ የሚላጭ ራስ።

ላጪታ: (ላጻዪት) የላጨች፣ የምትላጭ፡ ለሴት ብቻ ይነገራል።

ላጭ: (ለሓጺ) የላጠ፣ የሚልጥ፡ ሐሜተኛ ሰው።

ላጲስ: ላፒስ፡ በደረቅ ርሳስ የተጻፈ ጽፈት ማጥፊያ። እውነተኛ ስሙ "ጎማ" ይባላል። ጣሊያኖች ግን "ላፒስን" "ርሳስ" ይሉታል፣ ዐማሮችም ጎማውና ርሳሱ ባንድነት ስለተገኙ የጎማውን ስም በስሕተት ለርሳሱ ሰጥተውታል።

ላፈ: ለአፈ፡ ቅርፊትን ከልጥ ለየ፣ ገፈፈ። ላፈፈን ተመልከት።

ላፈ: በፍጥነት በላ፣ ጠጣ ሙቅ ምግብ።

ላፈ: አቃጠለ፣ ፈጀ፣ ላጠ አካልን።

ላፈን: ፈጀን፣ አቃጠለን፣ ላጠን።

ላፈደ: ለፋ፣ ጋጠረ፣ ደከመ።

ላፈፈ: ላፈ፣ ነጠለ።

ላፊ: የላፈ፣ የሚልፍ፣ የሚጠጣ።

ላፋ ገፋ (ገፊዕ) መግፋት።

ላፍንጫ ግም፡ አፍንጫ ድፍን ያዝለታል እንዲሉ።

ሌለ: የለ፡ የአለ አሉታ፡ የየለ መንትያ። አልነበረ፡ አልተገኘ። "" "" ተወራራሽ ስለ ኾኑ "የለ" በማለት ፈንታ "ሌለ" ይላል። "" መነሻ ሲኾነው በቂና ቅጽል ይሆናል።

ሌሊት: ሌሊቶች፡ የጨለማ ስም፡ ፲፪ የጨለማ ሰዓት ከማታ እስከ ጧት የሚቆጠር የዕለት (የቀን) እኩሌታ፡ ከመዓልት (ቀን) የተለየ ጊዜ ነው። (ዘፍ. ፩፡ ፭)

ሌላ ሌላ አለ: ጣዕም ለወጠ፡ ምግቡ፣ መጠጡ።

ሌላ ትርጉም: ሆድን በጥይት፣ በካራ፣ በጦር አማሰለ (አበላሸ፣ ቀደደ፣ ሸረከተ) "መብረቅ የመታው እንዳይረባ እንደዚያ አደረገ" ማለት ነው።

ሌላ: ሎች፡ ኹለተኛ፣ ልዩ፣ ባዳ። "ሌላ ነገር፣ ሌላ ሰው" እንዲሉ።

ሌላ: በቀር። (ዘፀ. ፲፪፡ ፴፯፣ ኢሳ. ፷፬፡ ፬፣ ፷፭፡ ፳፪)

ሌላኹለተኛ: ለየ።

ሌሌ አለ: አዘመረ፡ በማሲንቆ ዘፈነ፡ ቀነቀነ።

ሌሌ: ሌለየ፡ ዕብ፡ ሀሎል፡ የማሲንቆ ዘፈን አዝማች። "አያ ሌሌ ሌሌ" እንዲል አዝማሪ። ሌሌ ዘፋኝ፣ አመስጋኝ ማለት ነው።

ሌሎችም በዚህ ስም የሚጠሩ ሰዎች አሉ። "ይሁዳ የጌታችን ወንድም""ይሁዳ አስቆሮታዊ" እንዲሉ።

ሌማት: ለም ማት፡ መዓተ ለምለም የንጀራ ብዛት።

ሌማት: ሌማቶች፡ ልሔምት፡ የንጀራ፣ የኀብስት ማስቀመጫ፡ መሶብ ሲከደን ግጥም የሚል ዝንበ፡ ከልክል።

ሌማት: ዕብ፡ ሌሔማት፡ ኅብስቶች፣ አንጀሮች።

ሌቃ: በኦሮ ቤት ያለ አገር። "ሌቃያቅኒው" ስም ነው።

ሌበቻ: እወደል፣ ጋዝ፣ አጋሰስ፣ ዥራት የሚገባ የመጫኛ ሥር ግንዶሽ፡ በቈዳና በጨርቅ የተደገለለ። ዳግመኛም "ወዴላ" ይባላል።

ሌባ (ሐለበ፣ ወለበ): እጀኛ፡ ሰራቂ፡ የሰውን ገንዘብ እንደ ወተት የሚያልብ፡ የሚያነሣ፡ የሚሰርቅ፡ የሚወስድ፡ እንደ እሸት የሚያወልብ (ለምሳሌ በዮሐንስ : ላይ እንደተጠቀሰው) (ተረት) "ሌባ እናት ልጇን አታምንም። " "ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል። " "ከሌባ ሌባ ቢሰርቀው ምን ይደንቀው?" ሲበዛ "ሌቦች" ይላል (ለምሳሌ በኤርምያስ ፵፰:፳፯፣ ዮሐንስ : ላይ እንደተጠቀሰው) "ወለበ" ብለኸ "ወሊባን" አስተውል።

ሌባ ሚዛን: የሌባ ሚዛን በስጡ ተንኰልና ጕደለት ያለበት (ለምሳሌ በዓሞጽ : ላይ እንደተጠቀሰው)

ሌባ ውጋት: ድንገተኛ የውጋት በሽታ።

ሌባ ዝናም: መከር አጥፊ።

ሌባ ጣት: ካውራ ጣት ቀጥላ ያለች ጣት፡ ኹለተኛ ስም "ማመልከቻ" ይባላል። "ሌባ" መባሏ ቀድማ በመንካቷ ነው።

ሌባ: በፍልጥና በፍልጥ መካከል ያለ ሥንጣሪ።

ሌባሻይ (ዮች) (ሌባ ሻይ): ፈላጊ። የውሸት መድኃኒት ጠጥቶ ወገበን በመቀነት ይያዝና ሌባ ይሻል፡ ወይም ተንኰል እሰው ቤት ገብቶ ይተኛል፡ በውሃም ይታጠባል። "ያማርኛ ገበታዋሪያ" ተመልከት፡ "ሻየን" እይ፡ "ቍናን" አስተውል።

ሌብነት: ሌባ መኾን፡ ሰራቂነት።

ሌቦ ሣህሉ: የታወቀ ሌባ በሥደር መንግሥት የነበረ። አንዲት አሮጊት "ሌቦ ሣህሉ እንዳይወስድብኝ ስልቻዬን ብቅልኝ" ብትለው፡ "ወይ አለመተዋወቅ፡ ሌቦ ሣህሉ ይሉሻል እኔ ነኝ፡ ዕንቺ ስልቻሽ" አለ ይላሉ።

ሌቦ: ቃለ አኅስሮ፡ የማዋረድ ቃል።

ሌታ: ሌት፡ ሌሊት ለየ።

ሌታቀን: ህብረ ከብድ፡ ጕበት የሚመስል ግምጃ፡ የቀንና የሌት ሁናቴ (ብርሃንና ጨለማ) የሚታይበት።

ሌት ቀኑ: ሌት እንደ ቀን የሚያይ የሌት ወፍ፣ ጕጕት። ሊልንና ሲሎን እይ፡ የዚህ ዘሮች ናቸው።

ሌት ቀኑ: የአሜሪካ ኣዝርና፡ ህዝብ።

ሌት ተቀን: ሌት ከቀን ጋራ ወይም ሌትና ቀን። "እከሌ ሌት ተቀን ይሠራል"

ሌት: ሌት ያማርኛ፡ ሌሊት የግእዝ።

ሌንቦ: ለንቦጭ።

ሌንቧም: ለንቦም።

ሌንች: በአካንዱራ ጨዋታ ጊዜ የሚነገር ቃል፡ ይኸውም አንዲቱን የልት ወይም የቱልት ቀንበጥ እንዲሁም ሌሎቹን በሹል ዐጥንት አጣምሮ ለመውጋት "ሌን" ይባላል፣ "ላንች" ማለት ይመስላል። ወይም በሊያንኛ "ላንቻ" ጦር ማለት ነውና የጦርነትን ምስጢር ያሳያል።

ሌዊ: የሰው ስም። ከ፲፪ቱ ነገደ እስራኤል አንዱ። ሀብተ ክህነት የተሰጠው። ትርጉሙ "ልጹቅ" ማለትም የቀረበ ማለት ነው (ኪደ እና ክዳን)

ሌዋታን: የአውሬ ስም፡ በዓለም ዙሪያ በባሕር በኩል ተጋድማ ያለች እንስት ዓሣ ነባሪ። (ኢዮ. ፵፡ ፳፭፣ ሱቱ ዕዝ. ፮፡ ፵፱-፶፪) ዳግመኛም ዘንዶ ትባላለች። "ክፉ ቀን ዙሪያው ዘንዶ" ማለት ከዚህ የመጣ ነው። (ቢሂሞትን እይ።)

ሌዋታን: የአውሬ ስም፡ በዓለም ዙሪያ በባሕር በኩል ተጋድማ ያለች እንስት ዓሣ ነባሪ። (ኢዮ. ፵፡ ፳፭፣ ሱቱ ዕዝ. ፮፡ ፵፱-፶፪) ዳግመኛም ዘንዶ ትባላለች። "ክፉ ቀን ዙሪያው ዘንዶ" ማለት ከዚህ የመጣ ነው። (ቢሂሞትን እይ።)

ሌዋዊ (ውያን): የሌዊ ወገን ወይም ነገድ።

ሌዋውያን: ከአምስቱ ኦሪት ሦስተኛው ክፍል (መጽሐፈ ሌዋውያን)

ሌጣ: ትግኛ፣ ሐበሻ፡ ብቻ፡ ልጅ የማታጠባ፣ የማታዝል ሴት፡ ልጅ ከዠርባዋ የወረደላት።

ሌጣ: ጭነት፣ ኮርቻ በዠርባው የሌለ ፈረስ፣ በቅሎ፣ አህያ። ወረጋንን አስተውል።

ሌጦ: የተለፋ የበግ ቈዳ ዕላቂ፡ ጠጕሩ የበነነ። በግእዝ መሊጦ ይባላል፡ ስለዚህ ዘሩ መለጠ ሊሆን ይችላል። (እከሌ ከቍንጫ ሌጦ ያወጣል) ይቀልዳል፣ ይነቅፋል።

: ፲፪ኛ ፊደል፡ በግእዝ አልፍ ቤት፡ በአበገደ። በፊደልነት ስሙ 'ላዊ'፡ አኃዝ ሲኾን '' ይባላል።

: የዘንድ አንቀጽ መነሻ ሲኾን ከሩቁ ወንድና ከሩቆቹ በቀር በኹሉ፡ በትእዛዝ ግን "እኔ" በሚል ብቻ ይገባል። "ልትጥፍ" (እሷ)"ልትጥፍ" (አንተ)"ልትጥፊ""ልጥፍ እወዳለሁ""ልጣፍ" "ልትጥፉ""ልንጥፍ እንወዳለን" የሣልሱና የሳድሱ (ሊ፣ ) በግእዝ መሠረቶቻቸው የተአነ ናቸው።

ልለሳለስ: የሴት ባሪያ ስም።

ልላጭ: የሽንኩርት፣ የድንች ልብስ፣ ገለባ።

ልል: ልሕሉሕ፣ ልኅሉኅ፡ የላላ፣ የራሰ፣ የረገበ፡ ልስልስ፡ ጥብቅ ያይደለ።

ልል: ልእል፡ "እኔ" ለሚል ፫ኛ ዘንድ አንቀጽ። "አልኹ እል፡ እል ዘንድ እንድል ልል እፈቅዳለሁ" አለን ተመልከት።

ልሎች: ልሕሉሓን፣ ልኅለኃን፡ የላሉ፣ የረገቡ ገመዶች፣ ሰዎች።

ልመት: ልሕመት፡ ልዘባ፡ ደቃቅነት፣ ልዝብነት፣ ልስላሴ።

ልመና: ምልጃ፣ ጸሎት፣ መለመን፣ ፈፋ፣ ቧገታ። (፩ነገ. ፰፡ ፵፭፣ ዳን. ፮፡ ፲፫፣ ኤፌ. ፲፰)

ልመደው: ያሞሌ ስም። አሞሌ የሚያነሣ - አሞሌ።

ልሙጥ ብርሌ: ሰንበር አልባ።

ልሙጥ: ልሙጽ፡ ጌጥ የሌለው የበቅሎ ዕቃ ዝናር።

ልሙጥ: አለጥለት የተሠራ ሸማ።

ልማም ያዘ: ለመመ፣ ቈሸሸ።

ልማም: ሰው ብዙ ጊዜ ሲታመም ከትኵሳት ብዛት የተነሣ በጥርስዎ ላይ የታይ እድፍ ብ። ቸክን ተመልከት።

ልማት: ልምላሜ፣ ብጀታ፣ ብዛት።

ልማደ ሀገር: ያገር ልማድ ካባት የወረደ። በፈረንጅኛ "ኩቲም" ይባላል። ግዕዝን እይ።

ልማደኛ: ልማደኞች፡ ልማዳም፣ ባለልማድ፣ ልማድ ያለው ዐመለኛ፡ ይኸውም ክፉና በጎ ነው።

ልማዱ፡ ግን፡ ተገብሮ፡ ነው (ተሰደረ፡ ተደረደረ)

ልማድ: ልማዶች፡ ዐመል፣ ደንብ፣ ሕግ፣ ወግ።

ልማድ: በኀላፊ አንቀጽ መነሻ የሚጨመር ፊደል፡ "" "አን" "አስ" "አስተ" "አሽ" "" "ተን"

ልማድ: ትንባኾ፣ ጫት፣ ቡና፣ ጠጅ፣ ዐረቄ፣ ልዩ ልዩ መብልና መጠጥ፣ በያንዳንዱ ሰው ዘንድ ዘወትር ተፈላጊ የኾነ ነገር ሁሉ "ልማድ" ይባላል። (ተረት) "ክፉ ልማድ ያሰርቃል ከማድ"

ልም ዕቃ: ምራን፣ የመርገጥ፣ የማነቆ ጠፍር።

ልም: ልሑም፡ የላመ፡ ልዝብ፣ ልስልስ፡ የድመት ጠጕር፡ ደቃቅ።

ልም: ልሙዕ፡ የለማ፡ ዐዲስ ግብር፣ ባባት የሌለ፡ ከተዠመረ እየለማ የኼደ።

ልም: የለማ፣ ለማ።

ልም: የደከመ፣ ደካማ። "ዐይነ ልም" እንዲሉ።

ልምለማ: መለምለም።

ልምላሜ: ዝኒከማሁ፡ ጠል፣ ርጥበት፣ ለምለምነት።

ልምምጥ: መለማመጥ።

ልምስስ አለ: ተለመሰሰ።

ልምስስ: የተለመሰሰ፡ ልሽልሽ።

ልምሹ: ልምሾዎች፡ የለመሸ፣ ጥምልምል፡ አምልማሎ እግር፣ ሽባ፣ እጀ ሰላላ።

ልምሽቅ አለ: ለመሸቀ።

ልምሽቅ: የለመሸቀ።

ልምሾ አደረገ: አዕወሰ፡ አጥመለመለ፡ ሽባ አደረገ።

ልምሾነት: ልምሾ መኾን፡ ሽባነት።

ልምን: የተለመነ፣ የተቀፈፈ የልመና እኽል ወይም ሌላ ነገር።

ልምክክ አለ: ልክክ፡ ምርግ አለ።

ልምክክ: የተለመከከ፣ የተላከከ።

ልምዘጋ: ቍንጠጣ፣ ቍንጥ።

ልምዝግ አደረገ: ቍንጥጥ አደረገ።

ልምዝግ: የተለመዘገ፡ ቍንጥጥ።

ልምድ: ልማድ፡ የተለመደ፣ የተጠና፣ የታወቀ፡ ዕውቅ።

ልምጥ አለ: ጕብጥ አለ።

ልምጥምጥ አለ: ብዙ ጊዜ ተለመጠ።

ልምጥምጥ: የተለማመጠ።

ልምጥጥ አለ: ውዕየ፡ ቅጥል አለ፡ ተለመጠጠ።

ልምጥጥ: ዝኒ ከማሁ።

ልምጭ አይነካሽ: የሥጋ ስም፡ ጡንቻ፣ ነብሮ።

ልምጭ: ልምጮች፡ ከእሓያና ከወይራ፣ ከቀጨሞ፣ ከሌላውም ቀጥታ ካለው ዕንጨት የተቈረጠ ቀጫጪን አርጩሜ፣ አሽንቋጦ፣ ጨንገር።

ልምጭ: ልብኔ፡ የንጨት ስም፡ ልጠ ጥቍር ዛፍ፡ እየተቀረጸ መስቀል ይኾናል፡ አቋቋሙ ድግጣ ይመስላል። የስሙ ምስጢር መለመጥንና መለስለስን ያሳያል።

ልምጭጭ አለ: ተለመጨጨ።

ልምጭጭ አለ: እንደ ሙጫና እንደ ቅቤ ኾነ፣ ሞቀሞቀ ዳቦው።

ልምጭጭ: የተለመጨጭ፣ ለጣሳ።

ልሰቃ: የመለሰቅ ሥራ፡ ጭፈቃ።

ልሰና: የመለሰን ሥራ፡ ልቅለቃ።

ልሳሽ: ለውጥ፣ ድጋሚ። "የነገር ልሳሽ" እንዲሉ።

ልሳሽ: በመስከረም የታጨደውን የብስ ብር ወዲያው እየላሰሱ የሚዘሩት የሽንብራና የጓያ ዘር።

ልሳነ ምድር: ወደ ባሕር የገባ የምድር ሠላጤ።

ልሳነ ባሕር: ወደ የብስ ወይም ወዳገር የገባ የባሕር ሠላጢ። ፈረንጆች "ጎልፍ" ይሉታል።

ልሳነ ዓለም: መንፈስ ቅዱስ ያንዱን ቋንቋ ለሌላው ገልጦ የሚያናግር።

ልሳነ ዓለም: ሰው ኩሉ በያገሩ የሚናገርበት ቋንቋ።

ልሳነ ዓለም: የዓለም መገናኛ ቋንቋ። ከ፲፱፻፴፫ .. በፊት ፈረንሳይኛ ከዚያ ወዲህ እንግሊዝኛ።

ልሳኑ ተዘጋ: መናገር አቃተው፡ ዝም አለ።

ልሳን: ልሳኖች፡ ምላስ፣ አንደበት፡ የነገር ሕዋስ። "እከሌ ልሳኔን ይዝጋው!" ብሎ ማለ።

ልሳን: ቋንቋ፡ በልሳን (ምላስ) የሚነገር። ላዝማሪና ለሐሚና ከግእዝና ካማርኛ የማይገጥም ሌላ የምስጢር ልሳን አላቸው።

ልሳን: የመጥረቢያ ጕረሮ። "ይህ ምሣር ልሳኑ ጠቧል፡ ዛቢያ አያስገባም" ልሳን መባል የሚገባው ለስለቱ ነበር።

ልሳን: የሚዛን መርፌ።

ልሳን: የሰይፍ ስለት። (ራእ. ፪፡ ፲፪)

ልሳኖ: ትግ፡ ትርፍ ምላስ።

ልስ: የተላሰሰ ንቅል።

ልስለሳ: ልዘባ።

ልስላሴ: ልዝብነት።

ልስልስ አለ: ልዝብ አለ።

ልስስ አለ: ንቅል አለ፣ ተላሰሰ።

ልስቅ አለ: ተለሰቀ፡ ልጥቅ አለ፣ እጅጉ ጥቂት መሰለ።

ልስቅ: ልጹቅ፡ የተለሰቀ፣ ለጥ ቀጥ ያለ።

ልስን: ስም፡ የምርግ ወይም የልጥፍና የትምትም መጨረሻ ሥራ። "የዚህ ቤት ልስኑ ያምራል"

ልስን: ቅጽል፡ የተለሰነ፣ ቅብ፣ ልቅልቅ።

ልሻ ጠጕር: ጠጕሩ እንደ ልሻ ቍልቍል የሚያድግ ሰው።

ልሻ: ለስላሳ፣ ያረኸ፣ የገደል ሣር፡ እንደ ጭድ ከጭቃ ጋር የሚስማማ እንስት ገርሣ።

ልሻ: ሣር ለሸለሸ።

ልሻን: ሽልማት፡ ኒሻን።

ልሽ: ለኪ፡ ለቅርብ ሴት የአንቀጽ ተጠቃሽ። (ማስረጃ) "ሴትዮ ልጅሽ ተማረልሽ፣ ዐወቀልሽ፣ ከባልንጀሮቹ በለጠልሽ"

ልሽልሽ: የተለሸለሸ፣ የተኛ።

ልቍጥ በርበሬ: ውሃ የገባበት ድልኅ፣ የታሸ፣ የተለወሰ።

ልቍጥ: የላቈጠ፡ ልውስ ጭቃ፣ ሊጥ፣ መድኀኒት።

ልቍጦሽ: ዝኒ ከማሁ፡ ለልቍጥ።

ልቃቂት: ልቃቂቶች፡ ክንዝርት የወጣ፣ የወለቀ፣ የተለየ የድርና የማግ ፈትል።

ልቅ: ስድ፡ ለቅዳ፡ ለግዳ፡ ቅምሖ።

ልቅ: ከፍ ያለ።

ልቅለቃ: ልቅላቄ፡ የመለቅለቅ ሥራ፡ ዐጠባ፣ እስክስታ፣ ውዝዋዜ። "ዋንጫ ልቅለቃ" እንዲሉ።

ልቅላቂ: ዕጣ።

ልቅልቃት: የመለቅለቅ ኹናቴ፡ ዕጥበት።

ልቅልቅ አለ: ዕብጥ፣ ግጥም አለ የጕረሮ።

ልቅልቅ: የተለቀለቀ ቤት፣ መኻል ሜዳ ዐውድማ።

ልቅሶ: ዝኒ ከማሁ። (፪ዜና. ፴፭፡ ፳፭፣ ኤር. ፱፡ ፲፰) በግእዝ "ብካይ" ይባላል።

ልቅና: ልህቅና፡ ዝኒ ከማሁ፡ አለቃ መኾን።

ልቆ: ልቃሕ፡ ብድር።

ልቆኛ: ኹል ጊዜ የሚበደር፣ ከልቆ የማይወጣ።

ልበ ሙሉ: አይፈር ለፊቱ፡ ደፋር።

ልበ ሙት: ሰነፍ፡ ደካማ።

ልበ ሰፊ: ቻይ፡ ታጋሽ። "ልበ ሰፊ ነገር ዐላፊ" እንዲሉ።

ልበ ቍላ: ከተወቀጠና ከተቀጠቀጠ በኋላ የሚሰር በሬ፡ ልቡ ያልሞተ፡ ያላለቀለት መነኵሴ፡ ሴት ፈላጊ።

ልበ ቈራጥ: የማያመነታ።

ልበ ቅን: ደግ፡ ትሑት፡ ታዛዥ።

ልበ ቢስ (ሶች): ቀልበ ቢስ፡ ዝንጉ።

ልበ ብርቱ: የማይፈራ፡ የማይፈታ፡ ጨካኝ።

ልበ ክፍት: ብልኅ፡ ማንኛውም ሥራና ነገር ቶሎ የሚገባው።

ልበ ውልቅ: ስልቹ።

ልበ ደረቅ: ዐዘኔታና ርኅራኄ የሌለው።

ልበ ደንዳና: ዐሳብ የለሽ። ሲበዛ "ልበ ደንዳኖች" ይላል (ለምሳሌ በኢሳይያስ ፵፯:፲፪ ላይ እንደተጠቀሰው)

ልበ ደንጊያ: የነገሩትን የማይሰማ።

ልበ ደፋር: ጐበዝ፡ ኀይለኛ።

ልበ ድፍን: ደደብ፡ ደንቈሮ።

ልበ ጡል: ልቡ የዞረ፡ እብድ ዐይነት።

ልበ ጥኑ: ጨካኝ፡ ወርጅ።

ልበ ጨካኝ: ዝኒ ከማሁ (ልክ እንደ ልበ ደረቅ)

ልበል: ልናገር፣ ልምታ። ማስታወሻ: "ዐበለን" ተመልከት።

ልበል: ዕብለት ልናገር። "ባለን" አስተውል።

ልበማ: ዕውቂያ፡ ሥየማ።

ልበባ: መለበብ።

ልበኛ (ኞች): ልባም፡ ዐዋቂ።

ልበኛነት: ልባምነት።

ልበኢ: ልብ የለሽ።

ልበጣ: ልጠፋ፡ ሽፈና፡ ሥንበጣ።

ልቡ ሠባ: ተቤተ።

ልቡ ተሰቀለ: ባንድ ሐሳብ ተያዘ።

ልቡ ተሰወረ: አበደ፡ አእምሮ ጠፋ።

ልቡ ገባ: አእምሮው ተመለሰ።

ልቡ ፈረሰ: ፈነዳ።

ልቡሰ ሥጋ: ሥጋ የለበሰ ጋኔን (በሰው ያደረ)

ልቡስ: የለበሰ (ግእዝ)

ልቡና/ልቦና: ልብ፡ ልብነት፡ የልብ ማስተዋል፡ ትግሥት። "ልቦና ይስጥኸ" እንዲሉ። "ልቡና" የግእዝ፡ "ልቦና" የአማርኛ ነው።

ልቡና/ልቦና: በቁሙ፡ ልብ።

ልቡን ሰረቀው: ከዳው፡ ነሣው።

ልቡን ሰወረው: እብድ አደረገው።

ልቡን ከዳው: አወፈፈው፡ ወንጃ አለው።

ልባልማ: የሴት ሱሪ፡ ልብ።

ልባልባ (ልብ አልባ): ዝንጉ ሰው። '' '' ተወራራሽ ስለ ኾኑ "ልባልማ" (ልብ አልማ) ተብሎም ይነገራል፡ "ልብን በደስታ አልማ፡ አለምልም" ማለት ነው።

ልባልባ (ዐልባ ልብ): በሐርና በወርቅ የተጠለፈ፡ ባለማዕርግ ሴት የምታጠልቀው ጌጠኛ ሱሪ። "ልብ ዐልባ" መባሉ "ገንዘብ የልብ ሥር" ስለ ተባለ ነው። "ልብ አልባ" ተብሎ ቢጻፍ ግን "እሱን ያጠለቀች ሴት ልብ የላትም" ማለት ነው፡ ዝምዝማቱንና ጥልፉን ተኵራ በማየቷ ሌላውን ሁሉ ትዘነጋለችና። ዳግመኛም "የልብ ምሳሌ ሠላጤ የሌለው" ያሠኛል። 'ዐልባ' ትርጓሜው "ልብስ" ማለት ነውና፡ "ዐለበን" እይ።

ልባም (ሞች) (ለባዊ): ልብ አድራጊ፡ አስተዋይ፡ የማይዘነጋ፡ ዠግና፡ ሐርበኛ። "ለበመን" ተመልከት፡ ከዚህ የወጣ ቅጽላዊ ግስ ነው።

ልባም: ባሬታ መክፈያ፡ በውስጡ የበሽተኛ ዐይነ ምድርና ሽንት ያለበት የመላበት። "ለበበ" ግእዝኛ፡ "ለበመ" ዐማርኛ ነው።

ልባምነት (ልባዌ): ልባም መኾን (ለምሳሌ በሮሜ ፲፪: ላይ እንደተጠቀሰው)

ልባስ: የጕቾ፣ የግንብ ክዳን። "ተንበረክን" ተመልከት፡ "በረከ"

ልባብ (ቦች): ከፈረስና ከበቅሎ ዕቃ አንደኛው የታወቀው የገጽ ጌጥ፡ ከልጓም አስቀድሞ የሚደረግ የልጓም መደብ። በጋልኛ "ፉሎ" ይባላል።

ልባብ ገባበት: በልባብ ተያዘ (ፈረሱ)

ልባንጃ (ልብን): የዕጣን ሙጫ፡ ከቅርፊት ጋራ ዐብሮ የደረቀ፡ መናኛ ዕጣን እንደ ጪስ ዕንጨት ሴቶች የሚሞቁት፡ የሚታጠኑት።

ልባጥ: የጣራ፣ የግንብ፣ የግድግዳ መሸፈኛ (ሉሕ፣ ግምጃ)፡ የሣጥን፣ የታቦት ተለጣፊ ማዕድን ሥሥ። "ብላጥን" እይ።

ልባጭ: ሥንባጭ፡ ልጣጭ።

ልብ (ቦች) (ለበበ፣ ለበወ): ከውስጥ አካላት አንዱ፡ የደም መመላለሻ፡ ያሳብ መፍለቂያ (ለምሳሌ በመዝሙረ ዳዊት : ላይ እንደተጠቀሰው) "አልባብን" ተመልከት። (ግጥም) "ያውና እዚያ ማዶ ፍሪዳ ተጥሏል፡ ቢላዋው ደንዞ ልብ አልቈርጥ ብሏል። "

ልብ ለልብ: ዐሳብ ላሳብ፡ ሆድ ለሆድ። "እከሌና እከሌ ልብ ለልብ ይተዋወቃሉ። "

ልብ ቀረው: ዐሳቡ ወደ ወጣበት ተመለሰ እንደ ሎጥ ሚስት።

ልብ ተባለ: ታሰበ፡ ተጤነ።

ልብ ነሣ: አሳበደ።

ልብ አለ: ዐሰበ፡ ኣስታወሰ፡ አጤነ።

ልብ አሳጣ: ኣፈዘዘ፡ ኣሞኘ፡ አታለለ።

ልብ አስደረገ: አሳሰበ።

ልብ አቍስል: ጨቅጫቃ፡ አተካራም።

ልብ አብርድ: ውሃ ወተት።

ልብ አብሽቅ: አሳዛኝ።

ልብ አብግን: አናዳጅ።

ልብ አንድድ: ዐረቄ፡ መጥፎ መጠጥ።

ልብ አውልቅ (ቆች): አሰልቺ፡ ነዝናዛ።

ልብ አደረገ (ለበወ): አጤነ፡ በልብ አዋለ፡ አሳደረ፡ አቈየ፡ ኣኖረ። "ዋለ" ብለኸ "አስተዋለን" እይ።

ልብ አድራጊ: ያየውን፣ የሰማውን፣ የተማረውን የማይረሳ፡ የማይዘነጋ።

ልብ አድርቅ: መንቻካ ሰው።

ልብ አድርግልኝ: እማኝ ነኸ።

ልብ አጠፋ: ቀልበ ቢስ አደረገ።

ልብ ዐጣ: ራሰ ቢስ ኾነ።

ልብ ወለድ: ፈጠራ፡ መጽሐፈ ጨዋታ፡ "ወዳጄ ልቤ""ጦቢያው"

ልብ ወረደው: ደከመ (በሬው)

ልብ ውጋት: ዱሮ ባገራችን ይሠራ የነበረ ችንካር፡ ምስማር እንደ ካስማ ያለ፲፪ቱን ማእዘን ያገናኛል።

ልብ ገዛ፡ አእምሮ አገኘ።

ልብ: ሆድ፡ ደረት። "እከሌ አሽከሩን በልቡ አስተኛና ገረፈው። "

ልብ: ዕውቀት፡ ማስተዋል (ለምሳሌ በመዝሙረ ዳዊት ፴፪: ላይ እንደተጠቀሰው)

ልብ: እውነት፡ ሐቅ። "ልብ ሳይዙ ነገር አያበዙ። "

ልብ: ውስጥ፡ ቡጥ። (ተረት) "በገዛ ዳቦዬ ልብ ልቡን ዐጣኹት። "

ልብ: ውጋት።

ልብለባ: ትኰሳ፡ ሽንገላ።

ልብላቢ: የበርበሬ ፍሬ መገኛ መቀምጫ፡ ቋሚው መካከሉ ድልኸ ሲያደርጉት የሚለበልብ። "ክንክናን" እይ።

ልብልባት: ቀላል ቃጠሎ፡ የእሳት ግርፋት፡ ትኵሳት።

ልብልብ: የተለበለበ፡ ርጥብ ዕንወት (ሥጋ፣ ቅልጥም)

ልብማት: ዕውቀት፡ ምሉነት።

ልብም: የተለበመ፡ የመገበሪያ ዶቄት የመላበት ጕብ ሸክላ።

ልብሰ ብርሃን: የብርሃን ልብስ፡ ልብሰ ማርያም። በሰማያዊና በቀይ ከፈይ ቀለም የሚሣል የማሪያም ሥዕል ካባ።

ልብሰ ተክህኖ: ለጸሎትና ለቅዳሴ ቄስ በቤተ መቅደስ የሚለብሰው ግምጃ።

ልብሳት: ያለባበስ ኹኔታ።

ልብስ (ሶች): ሸማ፡ ኩታ፡ ነጠላ፡ ጋቢ፡ ልግም፡ በገላ ዝቅዝቅ፡ ጃኖ፡ ድርብ፡ ቀሚስ፡ ኪታ፡ ግምጃ፡ መጐናጸፊያ፡ እጅ ጠባብ፡ ጥብቆ፡ ካባ፡ ለምድ፡ ለምደኛ፡ ቡልኮ፡ በርኖስ፡ ዝተት፡ ደበሎ፡ ዳባ፡ ዐጽፍ፡ ሌጦ፡ ሱሪ።

ልብስ ገፋፊ: የሬሳ ልብስ ወሳጅ፡ ያፈ መምር፡ አሽከር።

ልብስ: የተለበሰ፡ የሰው ገላ የነካው፡ ዐዲስና ዐርበ ወጥ ያይደለ።

ልብስንና፡ ማንኛውንም ዕቃ በጭቃ፡ በወጥ፡ በቅቤ፡ በቀለም፡ በእድፍ ነገር ዐልፎ ዐልፎ በከለ፡ አበላሸ፡ አጠፋ። ("ለኰፈን" የሚለው ቃል ዘር ነው።)

ልብባት: የልባብ አገባብ፡ አደረግ።

ልብብ: የተለበበ፡ ልባብ የገባባት።

ልብደ ሠሪ: ልብድን የሚሠራ፡ የሚያበጅ፡ የሚሰፋ።

ልብድ (ዶች): በኮርቻ ላይ የተሰፋ ድብዳብ (ጥሬ)

ልብድ: የብረት ቀሚስ፡ ውስጤ ነት፡ ያርበኛን ገላ መለበጃ (ለምሳሌ በ፩ኛ ነገሥት ፳፪: ላይ እንደተጠቀሰው) "ጥሩርን" ተመልከት።

ልብድ: የተለበደ፡ ቅጽል።

ልብጣት (ልብጠት): ልጥፋት፡ ሽፍናት (ለምሳሌ በኢሳይያስ :፳፪ ላይ እንደተጠቀሰው)

ልብጥ (ልቡጥ): የተለበጠ፡ የተጌጠ፡ የተሠነበጠ።

ልተማ: ትምተማ፡ የመለተም፣ የመግጨት ሥራ።

ልቴማም: ልቴም ያለበት፡ ባለልቴም

ልቴም: የፈንጣጣ ቍስል፡ ዕብጠት፣ መጅ፡ ዕመም፡ የለተመው ማለት ነው።

ልት: ልቶች፡ የቅጠል ስም፡ ዕንጨቱ ጥንካሬ የሌለው፡ የደረቀ ቍስል የሚያለሰልስ፡ ማላጋ ቅጠል። የታወቀ፣ ዕውቅ። እንደ ጐመን እየቀቀሉ ሲበሉት ለሆድ መድኀኒት ይኾናል።

ልት: ቅጠል፣ ለተተ።

ልትለታ: መወዝወዝ፣ ውዝዋዜ።

ልትም: የተለተመ፣ የተገጨ።

ልትት አለ: እንደ ልት ኾነ፡ ድክም አለ፡ ባዘተ።

ልትት: የለተተ። መዠመሪያው ይጠብቃል።

ልቼ: ኦሮ፡ ልምጭ፡ በደብረ ብርሃን አጠገብ ያለ ቀበሌ።

ልነት: ስምምነት፣ ወዳጅነት።

ልን: ለነ፡ "እኛ" ለሚሉ የአንቀጽ ዝርዝር። "ከሣቴ ብርሃን ሰላማ ከጽርእ ወደ ግእዝ ቅዱስ መጽሐፍን ተረጐመልን፣ የክርስቲያንን ሃይማኖት ሰበከልን"

ልንቀጣ: የመለንቀጥ፣ የማላም ሥራ።

ልንቅጥ: የተለነቀጠ፣ የተላመ ሊጥ።

ልንበጣም: ልንቡጥ ያለው፡ ባለልንቡጥ።

ልንቡጥ: ለበጠ፡ ወሸላ፣ ሽፍን፣ ቍርዝ፣ ሸለፈት። "ልንቡጥ" በግእዝ "ልቡጥ" (ቈላፍ) በአማርኛ "ልብጥ" ይባላል።

ልኝ: ሊተ፡ "እኔ" ለሚል የአንቀጽ ዝርዝር። "ኢየሱስ ክርስቶስ የልቤን ዐይን አበራልኝ፣ ሕገ ወንጌልን ሠራልኝ"

ልዑላን: ልዑላት፡ ከፍተኞች ወንዶችና ሴቶች።

ልዑል እምልዑላን: ከከፍተኞች።

ልዑል: ለዐለ፡ የነገሥታት ብላጆች፣ የታላላቆች፣ መሳፍንትና ባላባቶች የስነ ቅጽል ትርጓሜውም "ከፍ ያለ" "በላይ የኾነ" "ላይኛ" "ከፍተኛ" ማለት ነው። "ልዑል ወል ወራሽ" "ልዑል መኰንን" "መስፍነ ሐረር" እንዲሉ።

ልዕልት: ከፍ ያለች፣ ከፍተኛዋ ኵናኛዪቱ።

ልዕልና: ከፍታ።

ልከኛ: ምጡን፡ የልክ አይነት፡ ልክ ያለው፣ ባለልክ፣ መጠነኛ፣ እኩያ።

ልኵስ አደረገ: ትኵስ አደረገ።

ልኵስ: የተለኰሰ።

ልኵስኵስ: የተልኰሰኰሰ መስክ፣ ዝሪት።

ልኵፍ: የተለኰፈ፡ ትንኰስ።

ልኵፍኵፍ አለ: ኵልፍልፍ አለ። ኰለፈን እይ።

ልኵፍኵፍ: የተልኰፈኰፈ፡ ኵልፍልፍ።

ልክ ሆነ: መላ ደረሰ፣ ገጠመ።

ልክ ነው: ምሉ ነው፡ አልጐደለም፡ አልተረፈም።

ልክ ናቸው: መንቶች ልጆች ትክክል ናቸው፡ አይበላለጡም።

ልክ የለሽ: የሴት መጠሪያ ስም።

ልክ የለኸ: የወንድ መጠሪያ ስም፡ ለሰውነትህ አቻ፣ ለሀብትህ ወሰን የለውም ማለት ነው።

ልክ: መጠን፣ ስፍር። (ነሐ. ፫፡ ፲፱፣ ፳፣ ፳፩) ሲበዛ "ልኮች" ይላል። ውሃን ተመልከት።

ልክ: ዐቅም፣ ቅጥብ፣ ዕለተ ሞት። "ሰው ከልኩ አያልፍም"

ልክስክስ ነገር: የማይረባ፣ ፈሎ ቢስ።

ልክስክስ አለ: ተልከሰከሰ።

ልክስክስ: ልክስክሶች፡ ዝኒ ከማሁ፡ አመንዝራ፣ ርኩስ ዐሣማ፣ ውሻ፣ ዝንብ።

ልክስክስ: ሰልቢባ፡ የሚዞር፣ የሚጥወለወል ባንድ ስፍራ ቀጥ ብሎ የሚቆም ዐውሎ ነፋስ።

ልክና መልክ: የሕዋሳትን ኹለትነትና ትክክልነት አንድ አይነት መኾንን ያሳያል።

ልክክ አለ: ግጥም አለ።

ልክክ አደረገ: ግጥም አደረገ።

ልክክ: የተላከከ። ፩ኛውን አጥብቅ።

ልክፍ አለ: ድቅን አለ፡ ተለከፈ፣ ሰለፈ።

ልክፍ: ላክ፡ የተዠመረ፡ ዥምር።

ልክፍ: ጥክ፡ ድቅን፣ ሰላፍ።

ልክፍት: ጥንተ ደዌ፣ የበሽታ ዥምር፣ ውጥን። በግእዝ ግን "የተለከፈች" ማለት ነው።

ልክፍክፍ አለ: ልክስክስ አለ።

ልክፍክፍ: የተልከፈከፈ፣ የተልከሰከሰ፡ ልክስክስ የውሻ፣ ያሣማ አይነት።

ልኰሳ: ትኰሳ።

ልኮሽ: መላክ፡ "እሱ አንቺን ልኮሽ" ቢል ቦዝ ይሆናል።

ልኰፋ: ትንኰሳ።

ልወሳ: የማላቆጥ፣ የማዋዋድ ሥራ።

ልወጣ: ቅየራ፣ የመለወጥ ሥራ።

ልውስ አለ: ቅስቅስ፣ ንቅንቅ አለ።

ልውስ: (ቅጽል) ዝኒ ከማሁ ለለዋሳ፡ ቅልቅል፣ ልቁጥ፣ ሊጥ፡ ቅቤና አዶስ።

ልውጡ: የራስ ወሌ ዘዬ ፈሊጥ።

ልውጣ፡ ልውጣ፡ አለ፡ ምግቡ፡ እንባው።

ልውጥ አደረገ: ለወጠ።

ልውጥ: (ቅጽል) (ውሉጥ) የተለወጠ፣ ቅይር። ለምሳሌ፣ "ልውጥ ግልብጥ" እንዲሉ።

ልውጥነት: ልውጥ መሆን።

ልውጥውጥ አለ: ተለዋወጠ።

ልውጥውጥ: (ቅጽል) የተለዋወጠ።

ልዘባ: ልስለሳ።

ልዝብ (ልዝቦች): (ቅጽል) የለዘበ፡ ልስልስ፣ ልም፣ ደቃቅ። ለምሳሌ፣ አይን ቢጨምሩት የማይቆረቁር ዶቄት፡ የድመት ጠጕር፡ ሰላማዊ ሰው።

ልዝብ፡ ትንቡሼ።

ልዝብ አለ: ላመ፣ ልስልስ፣ ድቅቅ አለ።

ልዝብ ደንጊያ: ልሙጥ፣ የለሰለሰ አለት። (ኢሳ. ፶፯፡ ፮)

ልዝብ ጠርብ: በዕቃ መጥረቢያ የተጠረበ፣ በመላጊያ የተላገ ሰፊና ጠባብ የእንጨት ሉህ።

ልዝብ: (ቅጽል) (ብዙ ቁጥር: ልዝቦች) የለዘበ፡ ልስልስ፣ ልም፣ ደቃቅ። ለምሳሌ፣ አይን ቢጨምሩት የማይቆረቁር ዶቄት፡ የድመት ጠጕር፡ ሰላማዊ ሰው።

ልዝብነት: ልዝብ መሆን።

ልዝብነት: ልዝብ መሆን።

ልየታ: ንጠላ፣ ሥንጠቃ፣ ከፈላ።

ልዩ ልዩ: ዘዘ፣ ዚኣሁ፡ የልዩ ልዩ፡ እየብቻ፣ እየብቻው፣ እየራስ፣ እየራሱ፣ እየቅል፣ እየቅሉ የሆነ ነገር።

ልዩ ፍጥረት: የሌት ወፍ።

ልዩ: ሊሉይ፡ የተለየ፣ እንግዳ፣ ባዕድ፡ ከሌላው የዘር፣ የልማድ አንድነት፣ ህብረት የሌለው። (ዘሌ. ፳፬፡ ፲፩) "ልዩ ነገር፣ ልዩ ሥራ" እንዲሉ። "የሥላሴ ባሕርያቸው አንድ ሲሆን አካላቸው ልዩ ነው" ሲበዛ "ልዩዎች" ይላል።

ልዩ: ባሕታዊ፣ ግሑሥ።

ልዩነት: ልዩ መሆን፡ ባዕድነት።

ልያ: የሴት ስም፡ የላባ ልጅ፣ የያዕቆብ ሚስት።

ልይት አለ: ክፍል አለ፡ ተለየ።

ልይት አደረገ: ክፍል አደረገ፡ ለየ።

ልይት: ልዩ፣ የተለየ፣ የተከፈለ።

ልይትይት አለ: ንጥልጥል አለ።

ልይትይት: የተለያየ፣ የተፈራቀቀ፣ የተነጣጠለ።

ልደተ ሥጋ: በግዙፍ አካል ከአባት ከናት መወለድ። ሥጋን እይ።

ልደተ ነፍስ: በምግባር፣ በሃይማኖት፣ በጥምቀት፣ በቍርባን የሚገኝ የእግዚአብሔር ልጅነት፡ ታድሶ፣ ረቆ፣ በነፍስ መደብ ከመቃብር መነሣት፣ መውጣት።

ልደተ ወልድ: የወልድ መወለድ፡ የክርስትና ስም።

ልደቱ: መወለዱ፡ የርሱ ልደት። ዝርዝሩ ጌታችንን ያያል።

ልደታ (ልደታ ለማርያም): መወለዷ፡ የርሷ ልደት። የማርያም መወለድ በግንቦት ፩ኛ ቀን የሚከብር፡ ርግጠኛው ግን መስከረም ቀን ነው። ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የመቤታችንን ልደት በግንቦት መባቻ ያደረገበትና ፊደልን ሀለሐመ ብሎ የዠመረበት ምስጢሩ ኣንድ ነው።

ልደታ: የታቦት ስም። "ወለደ" እይ።

ልደታ: የታቦት ስም። ዘርፍ ቀድሞት ሲነገር "ግንቦት ልደታ" ይላል።

ልደቴ: የልደተ ወልድ ከፊል። "የኔ ልደት" ተብሎም ይተረጐማል።

ልደት: መወለድ። "ወለደ" እይ።

ልደት: መውለድ፣ መወለድ። ልደት፣ ልደት እንዲሉ። ፪ቱ የባሕርይ፡ ፫ኛው በመቀበል ነው።

ልዳ: የቦታ ስም ሲሆን በእስያ ውስጥ የሚገኝ የቅዱስ ጊዮርጊስ ከተማ ነው።

ልድላዴ: ልስላሴ ውፍረት

ልድፋት: ልጥፋት።

ልድፍ አለ: ልጥፍ አለ።

ልድፍ: ልጥፍ።

ልጃልቅሶ: የገብስ ስም፡ በችግር ጊዜ ተዘርቶ ቶሎ የሚደርስ ገብስ እንደ አንበዲያት ያለ፡ የሚያለቅስ ልጅ መፈተኛ በፍጥነት እንዲዘጋጅ፡ ይህም የዚያ ምሳሌ ነው።

ልጃገረድ (ዶች): ያ፲፭ ዓመት ቈንዦ፣ ባለክብርና፡ እናት አባቷን ወይም ሌላውን ሰው የምታገለግል፡ ልጅነት ከገረድነት ያላት፡ የልጅ ገረድ እንደ ርሷ የማይሠሩትን የምታገርድ፡ ለወንድ የደረሰች። ከጣሊያን ወዲህ ግን ወይዘሪት ትባላለች።

ልጄ ዘመዴ: እናቱ ከዘመዷ የወለደችውን "ልጄ ዘመዴ" ትለዋለች።

ልጄ: የኔ ልጅ።

ልጅ (ጆች) (ወልድ): የራስ፣ የጨቅላ፣ የሕፃን፣ የትንሹም፣ የትልቁም፣ የወንዱም፣ የሴቱም የባሕርይ ስም፡ ሰው ተወልዶ እስኪያድግ ድረስ የሚጠራበት። "አንተ ልጅ" "አንቺ ልጅ""ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ" እንዲሉ።

ልጅ በልጅ ኾነ: በላይ በላዬ፣ ራስ በራስ ወለደ።

ልጅ አልባ: አለልጅ።

ልጅ ኢያሱ: ልጅ ገብረ ሩፋኤል እንዲሉ።

ልጅ ኢያሱ: ልጅ ገብረ ሩፋኤል እንዲሉ።

ልጅ እንደናቷ ኾነች: ተዳሰሰች፣ ተገሰሰች፣ ታወቀች። (ሕዝ፲፮:፵፬)

ልጅ እግር (ሮች): አካለ መጠን ያላደረሰ፣ አድጎ ያልጨረሰ፣ ገና ወጣት፣ ታዳጊ፣ ለጋ።

ልጅ ከስም አስቀድሞ እየተነገረ: ለነገሥታትና ለመኳንንት ልጆች የማዕርግ ስም ይኾናል።

ልጅ ወልዶ እረኝነት የሰደደ: ትልቅ ሰው፣ ዐዋቂ።

ልጅ ወንድሜ: እንደ ዐሞንና እንደ ሞአብ አባቱ አያቱ፡ እናቱ እቱ የኾነች ልጇን "ልጅ ወንድሜ" ትለዋለች።

ልጅ ደረሰ፡ ቤት፡ ፈረሰ።

ልጅ: በቁሙ ሲተረጎም "ወለደ" ማለት ነው።

ልጅቱ/ልጅቷ: ያች ልጅ። (ዘሌ፲፰:)

ልጅት: የሴት ፉከራና ጕራ። "እኔ ልጅት" እንድትል አንዳንዷ ሴት።

ልጅነቱን ያልጨረሰ: ዐዋቂ ሲኾን ከልጆች ጋራ እንደ ልጆች የሚጫወት፣ የሚሠራ።

ልጅነት: ልጅ መኾን። "የሰው ልጅነት አያኰራም፡ ጊዜ ነው እንጂ ቁም ነገርም ነው። " (አዝማሪ)

ልጅነት: ገርነት፣ የዋህነት፣ ሞኝነት፡ ከውቀት ከማስተዋል መራቅ። "ልጅነት ጅልነት" እንዲሉ።

ልጇ: የርሷ ልጅ።

ልገማ: ቸልታ።

ልገሳ: ስጦታ፡ ችሮታ።

ልጕማት: የመለጐም ስፌት አኳዃን።

ልጕም: የተለጐመ (በቅሎ፣ ፈረስ፣ አህያ)፡ አገልግል፡ የስፌት ዕቃ፡ ጕልብ፡ ተንቤን የለበሰ።

ልጕድ: የተለጐደ፡ ልድፍ።

ልጕጥ: ዝኒ ከማሁ፡ ውትፍ።

ልጋጋም (ሞች): ለሐጫም።

ልጋግ (ሠወን): ለሐጭ፡ እንደ ድር ያለ ካፍ ካንጓ የሚወጣ (ለምሳሌ በ፩ኛ ሳሙኤል ፳፩:፲፫ ላይ እንደተጠቀሰው)

ልግ (ልጉዕ): የተለጋ፡ የተቀላ ጥንግ።

ልግ: ዝኒ ከማሁ ለለግጥ (ለምሳሌ በ፩ኛ ሳሙኤል ፲፯:፳፮፣ ምሳሌ :፳፪፣ ዮሐንስ :፲፯-፲፱፣ ሚክያስ :፲፮ ላይ እንደተጠቀሰው)

ልግመኛ: ሀኬተኛ፡ ጠማማ (ለምሳሌ በ፩ኛ ጴጥሮስ :፲፭ ላይ እንደተጠቀሰው)

ልግመኛነት: ልግመኛ መኾን፡ ጠማምነት።

ልግመኞች: ቸልተኞች፡ ጠማሞች፡ እከየኞች (ለምሳሌ በ፩ኛ ጢሞቴዎስ :፲፫ ላይ እንደተጠቀሰው)

ልግም በገላ: ፈርጅ ኩታ፡ ፵፯ ክንድ ባለሰፊ ጥለት (ለምሳሌ በኢሳይያስ :፳፪ ላይ እንደተጠቀሰው)

ልግም: ሀኬት፡ ጥመት፡ እከይ። (ተረት) "ልግም እግዜር አይወድም"

ልግስና: ዝኒ ከማሁ፡ ቸርነት (ለምሳሌ በ፪ኛ ቆሮንቶስ :፲፩፣ ፩ኛ ጢሞቴዎስ :፲፯ ላይ እንደተጠቀሰው)

ልግዕ (ትግርኛ: ልግዒ): እንገር፡ ዐዲስ ወተት። "ልግዕ" ለግእዝም ሊኾን ይችላል።

ልግድ: የተለገደ፡ በፈፋ መካከል የተቀረቀረ ቋጥኝ፡ ገለብ።

ልጐማ: የመለጐም ሥራ።

ልጎሽ: ንጣጭ፡ ሊፍ፡ የሳንቃ፣ የማእዘን ፍቄት።

ልጓም (ሞች): የከብት አፍ መዝጊያ፡ እንዳይኼድ፣ እንዳይበላ መከልከያ፡ መግቻ፡ መመለሻ (ለምሳሌ በምሳሌ ፳፮: ላይ እንደተጠቀሰው) (ተረት) "ጠፍር በሊታ ብትኼድ ልጓም በሊታ መጣች። "

ልጓም ለቀቀ: በቀላል ያዘ፡ ጨበጠ።

ልጓም አላላ: ወደ ፊት ያዘ (ሽምጥ ለመጋለብ)

ልጓም አወለቀ: ከፈረስ፣ ከበቅሎ አፍ አወጣ።

ልጓም አጥባቂ: ልጓምን ዐኝ እያለ ሽምጥ የሚጋልብ (ለምሳሌ በ፪ኛ ዜና መዋዕል ፳፰:፲፱ ላይ እንደተጠቀሰው)

ልጓም ጣሰ: አልመለስ፣ አልገታ አለ (ፈረሱ)

ልጓጥ: ዋይክማ (ሣይንት)

ልጠቃ: ክተላ፣ ልሰቃ።

ልጠየቅ፡ የተጠያቂ መልስ፡ የሙግት አዝማች።

ልጠፋ: የመለጠፍ ሥራ፣ መረጋ።

ልጡ የተራሰ: መቃብሩ የተማሰ: በጣም ያረጀ፣ ያፈጀ፣ የደከመ ሽማግሌ።

ልጣም: ብዙ ልጥ የሚወጣው ዛፍ። ለጠመንን ተመልከት።

ልጣም: ክዳን፣ ግጣም፣ ለጠብ።

ልጥ (ልጦች): (ልሕጽ) በቂዳ፣ እምሳል ከእንጨት ሁሉ ላይ የሚገፈፍ፣ በቅርፊት ውስጥ ያለ፡ ማሰሪያ የሚሆን። "የሺ - ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ" እንዲሉ። (የብረት ልጥ) ሥሥ ብረት፡ የሳንቃና የእንጨት ማእዘን ማያያዣ፡ የጣቃ መቀፈጃ።

ልጥም ልጥም አለ: ጠጋ ጠጋ አለ።

ልጥም አለ: ጠጋ፣ ግጥም አለ።

ልጥም: የተለጠመ፡ ግጥም።

ልጥስ አለ: ትኝት አለ፡ ተለጠሰ።

ልጥስ: የተለጠሰ፣ የተኛ።

ልጥቅ አለ: ልስቅ አለ።

ልጥቅ: የተለጠቀ፡ ልስቅ።

ልጥፋት: የልጥፍ ሥራ አኳዃን።

ልጥፍ አለ: ምርግ አለ፡ ተለጠፈ።

ልጥፍ: ሬ፡ ከትምትም በፊት የሚሆን የጭቃ ሥራ።

ልጥፍ: ቅጽል፡ የተለጠፈ፣ የተጣበቀ፡ ምርግ።

ልጦ ጕርዶ አወጣ: ፈተገ፣ አነፈሰ፣ አበጠረ።

ልጦ ጕርዶ: ጕርዶ እንቅጥቃጭ፡ ልጦ እንዳለፈው። ስንዴ እንደ ቀይ፣ ሽንጥጥ ተልጦ የሚያልቅ ስለ ሆነ ንፋሹ ልጦ ተባለ። ኅዕቦን እይ።

ልጦ: የፍትግ ስንዴ እብቅ ገለባ፡ ዐሠር።

ልጨኛ: ውለታ ከፋይ፣ ላጪ፣ ልጭ።

ልፊያ: የጨዋታ ምት፣ ቍልመማ።

ልፋም: ልፋጭ ያለው፡ ባለልፋጭ ጕፋያ።

ልፋት: ልፍዐት፡ ጥረት፣ ድካም። አማረን አስተው።

ልፋጭ: ንፍጥ መሳይ ሥጋ።

ልፋፈ ጽድቅ: የጽድቅ ልፋፍ፡ ጥፎ ተጠቅሎ በሰውነት የሚንጠለጠል መጻፍ።

ልፋፊ: የልጥ ቅሬታ፡ ለስላሳ።

ልፋፍ: የመጻፍ ስም፡ የተጠቀለለ ጽሑፍ።

ልፍ: ልፉዕ፡ የለፋ፣ የተለፋ፡ ደበሎ፣ ስልቻ፣ ቈርበት።

ልፍለፋ: የነገር ብዛት።

ልፍስፍስ: የተልፈሰፈሰ፡ ዝልፍልፍ፣ ጥምልምል፡ ደካማ፣ ዐቅመቢስ።

ልፍት አለ: ድክም አለ።

ልፍት: ምግብ የሚኾን ቅጠላት ወይም ሌላ።

ልፍት: ድክም።

ልፍትት: ዝኒ ከማሁ፡ የለፈትታ። ፈደደን እይ።

ልፍጥ: ልፉጽ፡ የተለፈጠ፡ ልውስ። ሞለፈጥን አስተውል።

ልፍፍ: የተለፈፈ ጥቅል።

ሎላልት: ዝኒ ከማሁ። (ኢሳ. ፲፬፡ ፪፣ ዮሐ. ፯፡ ፵፭፡ ፵፮)

ሎሌ በትን: ታናሽ ዋንጫ።

ሎሌ: ወዓሊ፡ ምንደኛ፣ ታዛዥ፣ አሽከር። (ተረት) "ቅልና ድንጋይ ተማቶ ሎሌና ጌታ ተግቶ"

ሎሌነት: ሎሌ መኾን፡ ምንደኛነት፣ አሽከርነት።

ሎሌዎች: ወዐልት፡ ምንደኞች፣ ታዛዦች።

ሎል: ልዑል፡ የታላቅ ዛፍ ስም፡ ዕንጨትነቱ ክብደት ያለው፡ በጊዜው ከተቈረጠ ጽላት ይኾናል። ሲበዛ "ሎሎች" ይላል።

ሎሚ: ሎሚዎች፡ ለመለመ፡ የተክል ስም፡ የታወቀ ተክል፣ ሽታው የሚጣፍጥ፣ ለሥራይና ለመርዝ መድኀኒት የሚኾን፡ ዕንጨቱም ፍሬውም ሎሚ ይባላል። (ተረት) " ሎሚ ላ፩ ሰው ሸክም ነው፡ ላ፶ ሰው ጌጥ ነው" በከረን እይ። በትግሪኛ ግን "ሎሚ" ዛሬ ማለት ነው፡ ዮማዊ እንደ ማለት።

ሎሚታ: ሎሚታዎች፡ እንደ ሎሚ ክብ ኹኖ የሚታይ ጕልበት።

ሎሚታ: በሙጣ ጫፍ ላይ ያለ ወይም የብር እንክብል።

ሎሚታ: ጕልበት፣ ሎሚ።

ሎሚናት: መጠጥ።

ሎሚናት: ከሎሚ የሚወጣ መጠጥ፡ ፈረንጆች "ሎሚናድ" ይሉታል፡ በግእዝም "ሎሚዎች" ማለት ነው።

ሎም ሎም አለ: ላላ፡ እንደ ሎሚ ኾነ።

ሎምቢ: ያሣ ስም፡ ጌታችን ከሰባት እንጀራ ጋራ ሺሕ ሰው ያጠገበበት ዓሣ። (ማቴ. ፲፭፡ ፴፬፣ ፴፭)

ሎሴ: ለወሰ፡ የአንድ አሞሌ ክፍል ፲፪ ቍራጭ ወይም ኵርኳሚ።

ሎቲ: ሎቲዎች፡ ከወርቅና ክብር ከንሓስ ከሌላም ማዕድን፣ ከዝኆን ጥርስና ከአውራሪሥ ቀንድ የተበጀ ሰፊ ቀለበት፡ አንበሳ፣ ዝኆን፣ ግስላ፣ አውራሪ ጉዳይ በዦሮው የሚያንጠለጥለው። ሎቲ ጋልኛ ነው።

ሎቴር: የሰው ስም፡ በ፲፭፻ .. የተነሣ የጵሮተስታኖች አባት፣ የጀርመን ተወላጅ፣ ወንጌላዊ ሊቅ። ሰው ሠራሽ ትምርትን ተቃራኒ። እንደ አውሮፓ አቈጣጠር በ፲፱፻፹፱ .. ተወለደ፣ በ፲፭፻፵፯ ሞተ። ወገኖቹ "ማርቲን ሉቴር" ይሉታል፡ "ሰማዕት" ማለት ነው።

ሎች: ውዶች፣ ፍቅሮች።

ሎክሎክ አለ: ላሕልሐ፡ ላላ፡ ከመጠጠር ራቀ ፍሬው፣ ዕባጩ።

ሎክሏካ: ልል።

ሎዛ: የአገር ስም፡ በፍልስጥኤም ያለ አገር፡ ያዕቆብ በህልሙ ከምድር እስከ ሰማይ የተተከለ መሰላል ያየባት ምድረ ለውዝ።

ሎዜ ገብሩ: ባጤ፡ በቴዎድሮስ ዘመን በጐንደር የነበሩ ያሬዳዊ ሊቅ።

ሎዜ: ለውዛዊ፣ ዘለውዝ፣ የለውዝ ባለለውዝ።

ሎጋ (ሊወጋ): ረዥምና ጠንካራ ጦር ከነሶማያው።

ሎጋ ወጣት: ያደገ ረዥም ወታደር፡ መለሎ።

ሎጋ: ቁመተ ረዥም ሰው።

ሎጋው ሽቦ: በጦር ጕረሮ ላይ ያለ ሽቦ፡ ሎጋ የተባለ ጦሩ ነው።

ሎጋው ሽቦ: የጦረኛና የሐርበኛ ዘፈን፡ ሽቦ ያለበት፡ የተጠመጠመበት፡ ባለሽቦ "ሎጋ" ማለት ነው። "ሎጋው ሽቦ አመጣው ስቦ" እንዲሉ።

ሎግ (ለወገ): ለካ፡ ሰፈረ፡ እረዘመ፡ የሳንሳ ያዘ፡ ተሸከመ።

ሎጠሎጥ: ለወጠ፡ ለተለት፡ ዕርፈ ቢስ፣ ከውካዋ።

ሎጤ: ቀላዋጭ፡ ሎፌ፡ ሥራውን ለቅልውጥ የለወጠ።

ሎጥሎጥ አለ: ሎጥኛ ሄደ።

ሎጥሏጣ: ዝኒ ከማሁ ለትላታ።

ሎፊሳ: ባለጥቍር ጠጕር፡ የወሎ፣ የበሎ። ዘሩ "ላፈ" ነው።

ሎፊሳ: ከታናሽ እስያ የመጣ የሚፍየል ቈዳ፣ ለምድና ግላስ የሚኾን 1-ዐጐዛ ጠጕረረዥም።

ሎፌ: ለአፈ፡ ሎጤ፣ ቀላዋጭ።

ሎፍ አለ: ሰለፈ፣ ቀረበ፣ ተደቀነ። ሎፊሳን ተመልከት።

ሎፍ: ድቅን።

(ሎልዎ): መቃጠል።

አለ (ሎለወ): ጋለ፡ ተኰሰ፡ ተቃጠለ።

No comments:

Post a Comment

ሽፋን

  ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ