ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
- አ (ሀ)፡ በሀ ፈንታ የሚነገር የሀ ተለዋጭ ከግእዝ ወዳማርኛ ። ሀገር ፥ አገር ። ሀጕለ ፥ አጐለ ።
- አ (ያ)፡ የአንቅጽና የዝርዝር እያያዥ ። በየ ተራ ፭ኛውን ያ ተመልከት ።
- አ፡ በአዐ (በማይነሣ ግስ) የሳቢ ዘር ኹሉ መነሻ ። በቀለ ፥ አበቃቀል ። ገደለ ፥ እገዳደል ። ኣስተን እይ ።
- አ፡ ካደራራጊና ካድራግ ግስ ለሚወጣ ስም ባዕድ መነሻ ። ደበለ ፥ አዳበለ ፥ አዳባይ ፥ አደባበለ ፥ አደባባይ ። ጠገበ ፥ እጠግበ ፥ አጠገብ ። ከረመ ፥ አከረመ - አክርማ ። ቀጠጠ ፥ አቀጠጠ ፥ አቅጣጫማ ።
- አ፡ የማደራረግ ልማድ ። ገደለ ፥ አጋደለ ፥ ኣገዳደለ ። ገለጠ ፥ እጋለጠ - አገላለጠ ።
- አ፡ የማድረግ ልማድ ። ቆመ ፥ አቆመ ። በቀለ ፥ አበቀለ ። ናረ ፥ እናረ ። ይህ በተግብሮ ግስ ነው ። አስን ተመልከት ። በገቢርም በላ ፥ አበላ፡ ጠጣ ፥ አጠጣ ይላል ።
- አ፡ ደቂቅ አገባቦች፡ በ ፥ የ ፥ ከ ፥ ለ ሲቀድመት ራሱን ጐርዶ ኹሉንም ራብዕ ሲያደርግ ። አገር ባገር ፥ ያገር ፥ ካገር ፥ ላገር ይላል ።
- አ፡ ግእዝ፡ ፳ኛ አንደኛ ድምፅ፡ እንደ ኛነቱ ለአ ኡ ካዕብ ።
- አኃዘ ቢስ፡ ዘብዛባ ነገር ። አብዢአኃዝ ለሌላው ቅጽል ሲኾንና ርስ በራሱ ሲቀጻጸል፡ ፩ ሰው፡ ፪ ሰው፡ ፳፲፡ ፪፲፡ ፩፻፡ ፪፻፡ ፲፻፡ ፲፩፻ ይላል ።
- አኃዝ፡ (አኀዘ)፡ የቍጥር ስም፡ በጥቅል ፩፡ ፪፡ በዝርዝር አንድ፡ ኹለት እየተባለ የሚጻፍና የሚነገር ቍጥር ። አኃዝ በገጽ ሲጻፍ ነጥብ አይከተለውም።
- አኃዝ ቅጽል)፡ ፩ ፪ ። ከዚህም በቀር የቅርብ ሴት ትንቢትና ኀላፊ አንቀጽ ሲኾን በሩቅ ወንድ ቅጽልነት የሚፈታ ቃል አለ ። "ውሻ አይበላሽ፡ ዱላ ቀረሽ፡ ላባ ቀረሽ" ። ስትፈታም "አይበላሽ የማይበላው፡ ቀረሽ የቀረው በል" ። ቅጽል ለቅጽል ሲቀጸል፡ "ድፍን ጥቍር" ይላል ። ከዚህ የቀረውን ባገባብ ተመልከት ።
- አኃዝ፡ ዐቅድ፡ ውሳኔ፡ ልክ፡ መጠን። አኃዝ የሌለው ነገር እንዲሉ።
- አሓያ፡ ሓያ፡ (ሐይወ)፡ በዠማና በረግረግ ዳር የሚበቅል ዛፍ፡ ዕንጨቱ ለስላሳ መፋቂያ የሚኾን (መዝ፻፴፯፡ ፪ ። ኤር ፵፱፡ ፲፬)። በክረምት ውሃ በላዩ ይኼድበታል፡ አረንዛ ይጭንበታል፡ በበጋ ግን ተመልሶ ይለመልማልና ፥ ሕይወታዊ እንደ ማለት አሓያ ተባለ ይላሉ ። ሲበዛ አሓዮች ያሠኛል ። መጽሐፍ ግን በአሓያና በሓያ ፈንታ ህያ' ይላል።
- አሀያ፡ የዛፍ ስም ፥ —አሓያ ።
- አሁ፡ ሆ ሆታ ። አሁ በል፡ አሁ በል ጃሌ እንዲል ሐርበኛ ።
- አሁን፡ ይህ ጊዜ፡ አኹን ።
- አሕዛብ (ቦች)፡ ቍጥራቸው የበዛ አረመኔዎች ("በፍጡር የሚያመልኩ ለጣዖት የሚሰግዱ ሕዝቦች ጨካኞች ሐዛቦች አሕዛቦች ያማርኛ አሕዛብ የግእዝ ነው") ።
- አህያ፡ አላዋቂ ሰው ደንቈሮ ።
- አህያ ዐረደ)፡ በወንድሙ ላይ ግፍ ሠራ ("ያልወለዶ አጋ ድሞ ዐረደ ") ።
- አህያ፡ የቤት እንስሳ ዐመደ በል፡ ጭነት ተሸካሚ የጋማ ከብት ሲጮኸ ሀሀሀ የሚል ። (ተረት)፡ ያህያ ባል ከዥብ አያስጥል ። ዥብ ሊወጉ በአህያ ይጠጉ ። በግእዝ አድግ ይባላል ። ዐመድን እይ ። ተባቱንና እንስቱን ለመለየት ፥
- አህያ ፈጅ፡ ከወንጭት በላይ ከጃማ በታች ያለ ዳገት ። አህያ ገዳይ የት ነው አገርኸ፡ አህያ ፈጅ ። ከማዞር ከመጠምጠሙ እንዲያው ዥብ ነኝ አትልምን ።
- አህያ ፈጅ፡ ዥብ አህያ ጨራሽ ።
- አህያዋ አህያዪቱ፡ ያች አህያ ።
- አህያዋ፡ የርሷ አህያ ።
- አህያው፡ ያ አህያ፡ የርሱ አህያ ።
- አህዮ፡ ነጭ እንዶድ ።
- አህዮች፡ ፪ና ከ፪ በላይ ያሉ ብዙዎች ። (ዘፀ ፱ ፥ ፫) ።
- አሖመጠጠ፡ ኣቦካ/አሸመጠረ ።
- አሆማ፡ የዛፍ ስም፡ የዋንዛ ዐይነት ዕንጨት ። ሲበዛ አሆሞች ይላል ። (ዘካ ፲፩ ፥ ፪) ።
- አሖረጠ፡ እንዲፋጅ እንዲያቃጥል አደ ረገ ወጥን ።
- አለ፡ (እንበለ)፡ ደቂቅ፡ አገባብ። ለስምና፡ ለግብር፡ ለነገር፡ ኹሉ፡ በመነሻ፡ እየገባ፡ አሉታ፡ ይኾናል። (ማስረጃ)፡
- አለ፡ ል፡ በትንቢትና፡ በቦዝ፡ መጨረሻ፡ እየገባ፡ የቅርብ፡ ኀላፊ፡ ይኾናል ።ያውቃል፡ ዐውቋል ።ኺዷል፡ ሙቷል፡ ቢል፡ በደረሰበት፡ ስፍራ፡ በተቀበረበት፡ ቦታ፡ አለ፡ ማለት፡ ነው ።አለ፡ በኀላፊ፡ ብቻ፡ በ፰፡ መደብ፡ እየጠበቀ፡ ይረባል፡ ይዘረዘራል፡ መጥበቁም፡ ሀለወን፡ ተከትሎ፡ ነው።
- አለ፡ መታ፡ ደወለ፡ ደበደበ፡ ጠዘለ። አለ፡ በከፊለ፡ ቃልና፡ በሳድስ፡ ቅጽል፡ በሳቢ፡ ዘርም፡ ጫፍ፡ ማሰሪያ፡ ኹኖ፡ ሲነገር፡ ገባ፡ ወጣ፡ ቆም፡ ብድግ፡ ከፍ፡ ዝቅ፡ ብቅ፡ ጥልቅ፡ ስብር፡ ግብት፡ ዝግት፡ ዝርግት፡ አለ፡ እያለ፡ የግስ፡ ጽንዕና፡ አዳባሪ፡ ይኾናል ።በ፰፡ መደብ ሲረባና፡ ሲዘረዘር፡ አልኸ፡ አሉ፡ አላችኹ፡ አለች፡ አልሽ፡ አልኹ፡ አልን። አለው፡ አለኸ፡ አላቸው፡ አላችኹ፡ አላት፡ አለሽ፡ አለኝ፡ አለን፡ እያለ፡ በመላላት፡ ይነገራል።
- አለ፡ አልሞተም፡ ደኅና፡ ነው። ከፈነ፡ ብለኸ፡ ከፈንን፡ እይ።
- አለ፡ ኼደ፡ ወጣ፡ ወረደ፡ ዞረ፡ ናወዘ፡ ተቅበዘበዘ፡ ጠንቋይና፡ ቃልቻ፡ ጠየቀ፡ ልጅ፡ ዘመድ፡ ወዳጅ፡ ስለ፡ ታመመበት። ከዛር፡ እካህን፡ አለ፡ እንዲሉ ።
- አለሓ፡ ለሐጭ፡ ቀባ፣ ከለሐጭ፡ ጋራ፡ አልጐመጐመ።
- አለሐጯ -ለሐጭ፡ ቀባ፡ -ለሐጭ ።
- አለለ፡ (አልሎ፡ አለለ) ፣ሻ፡ ፈለገ፡ ዘለለ፡ ፊጥ፡ አለ፡ ተከመረ፡ በላይ፡ ኾነ፡ ታዘለ፡ ቀነዘረ፡ አመነዘረ፡ መታ፡ ሰረረ ።
- አለለ ቀለም፡ አገባ፡ ዐለለ ።
- አለለት፡ ተቀመጠለት፡ ኖረለት፡ ለሱ ።
- አለላ፡ በቁሙ፡ ዐለላ ።
- አለሌ፡ (ዎች)፡ እለሌ)፡ የፈረስ፡ የግመል፡ ድንጕላ፡ ወይም፡ ፈረስን፡ በቅሎ፡ የሚያስወልድ፡ የስናር፡ አህያ ።
- አለል፡ ዘለል፡ አለ፡ (አንዛህለለ) ሥራ፡ ፈታ፡ ተሞዣለጠ፡ ዞላ፡ ዋለ ።
- አለል፡ ዘለልታ፡ ዞላነት፡ ንዝህላልነት ። ዘለለን፡ ተመልከት ።
- አለል፡ የሚያልል፡ የሚዘል፡ የሚከመር ።
- አለልክ፡ በላ፡ ጠገበ።
- አለልክ፡ አላልኩሽም፡ ገረዘን፡ እይ። አልተናገርኩሽም ።
- አለልክ)፡ አለመ ጠን፡ አለወሰን።
- አለመ፡ ዕልም፡ አየ፡ ዐለመ ።
- አለመለመ፣ አለምለመ)፡ አጠደቀ - ለምለም፡ አደረገ። እንደ፡ ቀጤማ፣ ያለምልምምእንዲል፡ ተማሪ ።
- አለመዛዘግ፡ አቈነጣጠጥ፡ መለምዘግ ላምዛንአነባበሮ ፣ለመዘ።
- አለመደ፡ አስለመደ፡ (ኣልመደ)፡ አስተማረ፡ አስጠና፡ መራአሳወቀ ።
- አለመደና፡ አስለመደ፡ ምንም፡ በትርጓሜ፡ አንድ፡ ቢኾኑ፡ በውስጠ፡ ምስጢራቸው፡ ልዩነት፡ አላቸው፡ አለመደ፡ ፈቃድን፡ አስለመደ፡ ግዴታን፡ ያሳያል ።በግእዝም፡ አልመደ፡ አለመደ፡ አስለመደ፡ ተብሎ፡ ይፈታል።
- አለመጠ፡ (አልመጸ)፡ ምላሱን፡ አውጥቶ፡ አላገጠ፡ ኣልታዘዝ፡ እለ።
- አለመጠ፡ ለምጥ፡ አደረገ።
- አለመጠ አሉታ ፣
- አለመጠ አላገጠ፡ ለመጠ ።
- አለመጠን፡ አለመጠን፡ ጠጣ፡ ሰከረ።
- አለመጣጠጥ፡ አዝራረፍ፡ መለምጠጥ።
- አለማ፡ (አልምዐ)፡ አለመለመ፡ አበጀ፡ አሳመረ፡ አበዛ፡ ("ዘሌ. ፳፮፡ ፱") ።
- አለማ፡ ኰሰተረ፡ ተረኰሰ፡ ቈነጸለ፡ አ
- አለማለም፡ አጠዳደቅ፡ መለምለም።
- አለማመን፡ አቀፋፈፍ፡ መለመን።
- አለማመድ፡ አስተዋወቅ፡ መልመድ።
- አለማመጠ፡ አለማመነ።
- አለማመጥ፡ አዘባብ፡ መለመጥ።
- አለማም፡ አለማለም፡ መልማት።
- አለማዘገ፡ አቈናጠጠ ።
- አለሰለሰ፡ ላገ፡ ፋቀ፡ አለዘበ፡ ሳንቃን ።
- አለሰለሰ፡ የታጠበ ፣ልብስን፡ በማስ፡ ው ስጥ፡ አድርጎ፡ በእግር፡ ረገጠ፡ በእጅ፡ ተመተመ ።
- አለሰው፡ አቢብ፡ አለሰው፡ ብቻውን፡ ኖረ ።
- አለሳለሰ፡ ለስላሳ፡ አኳዃነ፡ አለዛዘበ ፣ (ኣደራራጊ) ።
- አለሳለሰ፡ ቀስ፡ ብሎ፡ ዐመመ፡ ብዙ፡ ጊዜ፡ ቈየ፡ በሽታው፡ (አድራጊ) ።
- አለሳለሰ፡ እለዛዘበ። ማለሳለስ፣ ማለዛዘብ።
- አለሳለስ፡ ኣለዛዘብ፡ መለስለስ።
- አለሳሰስ፡ አነቃቀል፡ መላሰስ።
- አለሳሰቅ፡ ኣለጣጠቅ፡ መለሰቅ።
- አለሳሰን፡ አለቃለቅ፡ አስተሣሠሥ፡ መ፡
- አለስላሽ፡ ያለሰለሰ፡ የሚያለሰልስ፡ ባዛች፡ ወናጢ፡ ፋቂ፡ አለዛቢ።
- አለሻለሽ፡ አስተኛኘት፡ መለሽለሽ።
- አለሽ፡ (ሀሎኪ)፡ አንቺ፡ አለሽ።
- አለሽ፤(ሀለወኪ)፡ ጥበብ፡ አለሽ።
- አለቀ ተጨረሰ፡ ዐለቀ ። አበደረ ፣(ለቃ) ።
- አለቀሰ -እንባ፡ አፈሰሰ፡ (ለቀሰ)፡
- አለቃ፡ ማንኛውም፡ ሹም፡ የበላይ፡ እዛዥ ፣ዳኛ ፣ባለሥልጣን፡ መኰንን ።ተመልከት፡ ዐላማኸን፡ ተከተል፡ አለቃኸን ።መቶን፡ እይ ።የቤተ፡ ክሲያን፡ አለቃ፡ የጦር፡ አለቃ፡ የገበሬ፡ አለቃ፡ የሽፍታ፡ አለቃ፡ የነጋዴ፡ አለቃ፡ የሰይጣን፡ አለቃ፡ ሻለቃ፡ እንዲሉ። (የዥብ፡ አለቃ)፡ ወቸገል፡ ቀመር። (ያለቃ፡ አለቃ)፡ የበላይ፡ በላይ። (የዛር፡ አለቃ)ቃልቻ፡ አረጋጋጭ። ፈረንጆች፡ አለቃን፡ ፕሬዚዳን፡ ይሉታል ።
- አለቃ፡ ንጉሥ፡("ሕዝ. ፲፪፡ ፲፪")
- አለቃ፡ አጋዳጅ (የሚያበድር/አበዳሪ/አዋሽ)።
- አለቃ፡ ኾነ፣ (ተመልአከ)፣ ሹመት፡ መብት፡ ሥልጣን፡ አገኘ፡ አዘዘ።
- አለቃ፡(ቆች)፡ ዋና፡ በኵር፡ አንጋፋ፡ ግንባር፡ ቀደም፡ ("፪ነገ. ፱፡ ፭ ። ምሳ. ፯፡ ፯") ።አለቃና፡ ምንዝር፣ የመሬት፡ አለቃ፡ እንዲሉ።
- አለቃቀም፡ አሰባሰብ፡ መልቀም።
- አለቃቀሰ፡ መላልሶ፡ አለቀሰ።
- አለቃቀስ፡ አነባብ፡ ማልቀስ።
- አለቃቀቅ፣ አከፋፈት፡ መልቀቅ።
- አለቃቅ፡ አበዳድር፡ ማለቃት።
- አለቅሶስ (አለ ክርስቶስ)፡ ክርስቶስ፡ አለ፡ ማለት፡ ነው ። አለቅሶስ፡ እንጽደቅ፡ ምንተ፡ ኣብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ፡ ቅዱስ፡ እንዲሉ፡ ሙሴና፡ ማኅበረተኞች፡ (ማቴ፲፡ ፵፪)፡ ተመልከት ።
- አለቅርታ፡ አለቅርታ፡ ኼደ።
- አለቅነት ፣ አለቃ፡ መኾን፡ ሹምነት፡ አዛዥነት፡ ("ዘኍ. ፬፥ ፲፯ ። ሮሜ. ፲፪፡ ፰") ።
- አለቆች፡ ዳኞች፡ ሹሞች፡ አራት፡ ማዕርግ፡ ያላቸው፡ ("ዘፀ. ፲፰፡ ፳፩, ፳፭ ። ምሳ. ፰፡ ፲፮")፡
- አለቋቈጥ ፣ አራራስ፡ መላቈጥ።
- አለበ፡ ዕልባት፡አደረገ፡ ዐለበ
- አለበ፡ ወተት፡ አወጣ፡ ዐለበ ።
- አለበት፡ ሰፈረበት፡ ተቀመጠበት፡ ዐደረበት፡ ኖረበት፡ በሱ።(በያለበት)፡ በብዙ፡ ስፍራ፡ በብዙ፡ ወገን።
- አለባለብ አተኳኰስ መለብለብ ("ለባልብ ለምለም ወጣት ለባልብ ዕብራይስጥ ላብሌብ ካለው የወጣ ነው፡ ልባልማ፡ የሴት ሱሪ፡ ልብ ለበመ ") ("ለቢብ/ለበ/ለበወ") ።
- አለባሚ ("(አለባዊ) ያለበመ የሚያለ ብም ለባሚ ወአለባሚ እንዲል ትርጓሜ ቅዳሴ ማርያም ማለበም ማጨመት ማለበሚያ ማመቻ አስለበመ ") ("አለበወ") ።
- አለባበሰ ደራረበ ("ሸፋፈነ ደባበቀ ዐ ረም ነ አለባብሶ ሸፋፍኖ ደባብቆ ") ።
- አለባበስ የማጣፋት የማጥለቅ ኹናቴ መልበስ ("ሌበቻ እወደል ጋዝ አጋሰስ ዥራት የሚገባ የመጫኛ ሥር ግንዶሽ በቈዳና በጨርቅ የተደገለለ ዳግመኛም ወዴላ ይባላል ለጋ ") ("ትግ፡ ለግዐ፡ እንገርን፡ ዐለበ") ።
- አለብላቢት፡ በቁሙ፡ ለበለበ ።
- አለተ፡ ፈጽሞ፡ አረጀ፡ ብዙ፡ ዘመን፡ ኖረ፡ እንደ፡ ቋጥኝ፡ እንደ፡ አለት፡ ሸበተ ።
- አለተተ፡ አለፋ፡ አለሰለሰ፡ አደከመ፡ አሰነፈ ።
- አለተኛ ፣ አሉታ፡ ወዳድ፡ የነገር፡ ተቃራኒ፡ ሸፍጠኛ፡ ዐሎኛ ።
- አለታም፡ አለት፡ ያለበት፡ የበዛበት ስፍራ። አለት ዐልጋ ዐለት ።
- አለታተት፡ አለፋፍ፡ መለተት።
- አለት፡ (ኰኵሕ)፡ በወንዝ፡ በዠማ፡ ውስጥ፡ ያለ፡ ጥኑ፡ ጠንካራ፡ የደንጊያ፡ ምንጣፍ ፣ ግራና፡ ቀኝም፡ የቆመው ።
- አለች፡ (ሀለወት)፡ እሷ፡ አለች ።
- አለነቀጠ፡ ለነቀጠ።
- አለነቃቀጥ፡ አፈጫጨት፡ መለንቀጥ።
- አለን፡ (ሀለወነ)፡ ዕውቀት፡ አለን።
- አለን፡ (ሀሎነ)፡ እኛ፡ አለን።
- አለንጋ፡ በቁሙ፡ ዐለንጋ ።
- አለኝ፡ (ሀለወኒ)፡ ሥራ፡ አለኝ።
- አለኝታ፡ ተስፋ አለ፡ አለኝ ።
- አለኝታ፡ አለኝ፡ ማለት።
- አለከ፡ (ትግ፡ ሐለከ። ዕብ፡ ሀላኸ)፡ ጨከነ፡ በረታ፡ ደፈረ፡ ተከራከረ፡ እልከኛ፡ ኾነ፡ ሞገደ፡ አላናግር፡ አላስኬድ፡ አለ፡ ወደረ፡ ጋዳ ።
- አለከለከ፡ ምላሱን፡ እንዘለዘለ፡ ትንፍስ፡ ትንፍስ፡ አለ፡ ግልገሉ፡ ውሻው፡ ዶሮው፡ ከፀሓይ፡ ሙቀት፡ የተነሣ ።
- አለከለከ ትንፍስ፡ ትንፍስ፡ አለ፡ ለከለከ ።
- አለከለከ፡ አጠጣ፡ አዋጠ።
- አለከፈ፡ አቀመሰ፡ አፍን፡ አስነካ።
- አለካለክ፡ አጠጣጥ፡ አዋዋጥ፡ መለክ
- አለካከም፡ አወራር፡ መለክም።
- አለካከክ፡ አቀባብ፡ መላከክ።
- አለካከፈ፡ አቀማመሰ፡ አነካካ።
- አለካከፈ፡ አዠማመረ።
- አለካከፍ፡ አቀማመስ፡ መልከፍ።
- አለካኪ፡ ያለካካ፡ የሚያለካካ።
- አለካካ፡ አከነዳዳ፡ አመጣጠነ።
- አለካክ፡ አመጣጠን፡ መለካት። ኦሮም፡ ቈጠረ፡ ሲል፡ ለካዬ፡ ይላል።
- አለክላኪ፡ ያለከለከ፡ የሚያለከልክ።
- አለኳኰሰ፡ አቀጣጠለ፡ አተኳኰሰ።
- አለኳኰስ፡ አተኳኰስ፡ መለኰስ።
- አለኳኰፍ፡ አተነኳኰስ፡ መለኰፍ፡ ፡
- አለኳኳሽ፡ አቀጣጣይ።
- አለኸ፤(ሀለወከ)፡ ዕውቀት፡ አለኸ።
- አለኹ፡ (ሀሎኩ)፡ እኔ፡ አለኹ።
- አለኽ፡ (ሀሎከ)፡ አንተ፡ አለኸ።
- አለወዘዘ፡ አለዘዘ።
- አለዋወስ፡ አለቋቈጥ፡ መለወስ።
- አለዋወጠ፡ አሻሻጠ ፥ አገዛዛ።
- አለዋወጠ፡ አዘዋወረ፡ አቀያየረ ።
- አለዋወጥ፡ አቀያየር፡ መለወጥ።
- አለዋዋጭ፡ ያለዋወጠ፡ የሚያለዋውጥ፡
- አለዋዛ፡ ኣለዋዛው፡ ዋዛ፡ ቅቤም፡ አያወዛ ።
- አለው፡ (ሀለዎ)፡ ለርሱ፡ ዕውቀት፡ አለው ።
- አለው፡ መታው፡ ደበደበው። (ተረት)፡ አለው፡ አለውና፡ ሳይመታው፡ ቀረ።
- አለው፡ ነገረው ።እከሌ፡ እከሌን፡ ምን፡ አለው ።
- አለውቀት፡ አለ(ባለ)ውቀት፡ በደለ።
- አለዘበ፡ አደቀቀ፡ አላመ፡ አለሰለሰ፡ ("ምሳ. ፪፡ ፲፯") ።
- አለዘበ፡ ወረበ፡ እየመላለሰ፡ እመ።
- አለዚህ፡ ሌላ፡ አይቅመስ።
- አለዚህ፡ አለይህ፡ አለ ።
- አለዚያ፡ አለያ፡ አለ ።
- አለዚያ፡ አለይህ ። አለዚህ፡ በቀር፡ ኣለያ፡ ኣለርሱ፡ ወይም። ይምጣ፡ አለዚያ፡ ይቅር።
- አለዛለዝ፡ አጠባብ፡ መለዝለዝ።
- አለዛቢ፡ ያለዘበ፡ የሚያለዝብ፡ ሰላE፡ ዐናጢ፡ ደብተራ፡ መሪ፡ ጌታ ።
- አለዛዘበ ፣ ኣደቃቀቀ፡ አለሳለሰ።
- አለዛዘብ፡ አለሳለስ፡ መለዘብ።
- አለዛዘዝ፡ አራራስ፡ መለዘዝ።
- አለዛዘግ፡ አጐታተት፡ መላዘግ።
- አለዛዥ፡ ያለዘዘ፡ የሚያለዝ።
- አለያየ፡ አነጣጠለ፡ አፈራቀቀ።
- አለያየት፡ አነጣጠል፡ መለየት
- አለያዪ፡ ያለያየ፡ የሚያለያይ፣ አፈራቃቂ።
- አለይሉኝታ፡ አለይሉኝታ፡ ኖረ።
- አለደ፡ (ኣልዶ፡ አለደ)፡ ሰበሰበ፡ አከማቸ፡ (ግእዝ)
- አለደለደ፡ አለሰለሰ፡ አሰማማ፡ አዋዋደ፡ አወፈረ።
- አለደንብ፡ አለወግ፡ አለደንብ፡ ሠራ። አለወግ፡ አነሣ።
- አለዳለድ፡ አወፋፈር፡ መለድለድ።
- አለዳደፍ፡ አለጣጠፍ፡ መለደፍ።
- አለገ፡ አንድ ዐይኑን ገድሎ ("ባንድ ዐይኑ እየ አወለገ አነጣጠረ") ።
- አለገገ፡ (አሥወነ)፡ ልጋግ፡ ለቀቀ፡ ኣወጣ፡ መለለ።
- አለገገ፡ ልጋግ፡ አወጣ፡ ለገገ።
- አለጋገስ፡ አሰጣጥ፡ መለገስ።
- አለጋገድ፡ አቀራቀር፡ መለገድ።
- አለጋግ፡ ኣመታት፡ መለጋት። ቈረቈ ሰን፡ እይ።
- አለጓጐም፡ አጐራረሥ፡ አሰፋፍ፡ መለ
- አለጓጐድ፡ አለዳደፍ፡ መለጐድ ።
- አለጠ ዐልጫ፡ ኾነ፡ ዐለጠ ።
- አለጠ፡ አዳለጠ/አለዘበ/አማገጠ።
- አለጣጠጠ፡ ኣወጣጠረ።
- አለጣጠጥ፡ አነጣጠል፡ አሳሳብ፡ መለ
- አለጥርጥር፡ አለጥርጥር፡ አመነ።
- አለጨ፡ አዳጠ።
- አለጫጨ፡ አንደ፡ ላጨኸ፡ ላጪው፡ አለ፡ ተላጪውን፡ ላጪ፡ ላጪውን፡ ተላጪ፡ አኳዃነ።
- አለጫጩት፡ አጠራረግ፡ መላጨት።
- አለፈ፡ (አሊፍ፡ አለፈ)፡ ተማረ፡ ፊደል፡ ቈጠረ፡ አ፡ አሌፍ፡ አለ ። አበዛ፡ አረባ፡ እልፍ፡ አደረገ ።
- አለፈ ፣ኼደ፡ ዐለፈ ።
- አለፈ፡ ወጥን በጭልፋ አቃዳ ።
- አለፈዳደድ፡ አጨመላለቅመለፍደድ።
- አለፋ፡ አጣረ፡ አደከመ።
- አለፋለፈ፡ ልፍለፋን፡ አመላለስ።
- አለፋለፍ፡ አቀበጣጠር፡ መለፍለፍ።
- አለፋደደ ፣እጨማለቀ፡ ከንቱ፡ ነገር፡ አናገረ ።
- አለፋጨቀ፡ አነዛነዘ፡ አጨቃጨቀ።
- አለፋፍ፡ አዠላለጥ፡ አደካከም፣መልፋት።
- አለፍርድ፡ ናቡቴ፡ አለፍርድ፡ ሞተ።
- አሉ፡ (ሀለዉ)፡ ሰዎች፡ አሉ ።
- አሉ፡ (ብህሉ)፡ ተናገሩ፡ ቃል፡ ሰጡ፡ አዘዙ ። ሠለስቱ፡ ምእት፡ እንዲህ፡ አሉ።
- አሉ፡ መቱ፡ አለ፡ አመነታ ።
- አሉ፡ ባልተኛ፡ አሉ፡ ባልታ፡ ወዳድ።
- አሉ፡ ባልታ፡ (ብሂሎተ፡ ብህሉ)፡ የሐሜት፡ ወሬ፡ የቅጂ፡ ቅጂ፡ ነገር፡ እንዲህ፡ አሉ፡ ማለት፡ ያንዱን፡ ለሌላው፡ ማውራት፡ ነገር፡ ማመላለስ፡ ማዛመት ።
- አሉላ፡ (ዐረ፡ አልዑላ)፣ የወረ፡ ሸኆች፡ ስም፡ ትርጓሜው፡ በላይ፡ እንደ፡ ማለት፡ ነው ።
- አሉማ፡ የቅጠል፡ ስም፡ ሲበሉት፡ ሆድ፡ የሚያለሰልስ፡ ሰውነትን፡ የሚያልም፡ ቅጠል።
- አሉታ ፣ ዐሌ፡ ማለት፡ ማስተባበል ።
- አሉታ፡ (አል፡ ኢ)፡ በቁሙ፡ የቃል፡ የነገር፡ የጽድቅ፡ የአወንታ፡ አፍራሽ፡ ተቃዋሚ፡ መልስ፡ ሸፍጥ፡ የለም፡ አይዶለም፡ ማለት ።
- አሉታ፡ አይ፡ አን፡ አት ። ኹሉንም፡ በየተራቸው፡ እይ ።
- አሉታና፡ ጽድቅ፡ ክደትና፡ እምነት፡ ሸፍጥና ፥ እውነት ። ጽድቅ፡ ነው፡ አሉታ፡ አይዶለም ። መረነን፡ እይ ።
- አሊ፡ ልዑል፡ ዐሊ።
- አሊ፡ ኤሎሄ ፣
- አላህ፡ (ዐረ)፡ አምላክ፡ እግዜር። (ተረት)፡ ካላህ፡ አልኾንኩ፡ ከነቢ ።
- አላለ፡ (አልአለ)፡ አልተናገረ፡ ቃል፡ አልሰጠ ። ዘካርያስ፡ ዮሐንስ፡ እስኪወለድ፡ ምንም፡ አላለ ።
- አላለ፡ አልተናገረ፡ ፡ አል ።
- አላሊ፡ (አላሕላሒ፡ አላኅላኂ)፡ ያላላ፡ የሚያላላ፡ አርጋቢ።
- አላላ፡ (አላሕልሐ፡ አላኅልኀ)፡ አራሰ፡ አለሰለሰ፡ አረገበ፡ ሳያጠብቅ፡ ቀረ፡ ("ማቴ. ፲፭፡ ፮") ለጐመ፡ ብለኸ፡ ልጓምን፡ አስተውል። ባል፡ ላላ ፡ አለ፡ ባማርኛ፡ ይተባበራሉ ። (ግጥም)፡ ምን፡ ያ ላት፡ አሽከር፡ ናት፡ ቀልድ፡ የለመደች፡ ባጠብቃት፡ ዝም፡ አለች፡ ባላላት፡ ኼደች ።
- አላላመ፡ አዳቀቀ፡ አለዛዘበ ።
- አላላም፡ ኣለዛዘብ፡ መላም።
- አላላሰ (አስተላሐሰ) ፡
- አላላሰ፡ (አስተልሀሰ)፡ ባከነ፡ አጠፋ) ።
- አላላስ፡ አጠራረግ፣ መላስ።
- አላላቀ፣ አበላለጠ።
- አላላቂ፡ የሚያላልቅ፡ አበላላጭ።
- አላላቅ፡ አበላለጥ፣ መላቅ።
- አላላከ፡ አጻጻፈ፡ መልክት፡ አቀባበለ፡ ኣመላለሰ ።
- አላላኪ፡ ያላላከ፡ የሚያላልክ፡ አቀባባይ።
- አላላክ፡ አሰዳደድ መላክ።
- አላላጠ፡ ልጥን፡ ከዛፍ፡ አለያየ፡ አጋፈፈ።
- አላላጥ፡ አገፋፈፍ፡ መላጥ።
- አላላጭ፡ ያላላጠ፡ የሚያላልጥ፡ (ባንድ፣በኩል፡ የሚልጥ) ።
- አላላፈ፡ አጋፈፈ፡ አላላጠ ።
- አላላፍ፡ አላላጥ፡ አገፋፈፍ፡ መላፍ።
- አላል፡ (አልዕል)፡ የጭነት፡ ማስተካከያ፡ ተጨማሪ፡ ጭነት፡ መጣያ ። (ተረት)፡ ከሰው፡ ክፉ፡ ደባል፡ ከጭነት፡ ክፉ፡ አላል ።
- አላመ፡ (አልሐመ)፡ ሰለቀ፡ ለነቀጠ፡ ኣደቀቀ፡ አለዘበ፡ አለሰለሰ
- አላመነ አለማመነ፡ አማለደ፡ እቃፈፈ፡ አቧገተ እባኽ፡ አባባለ፡ አለማመጠ ።
- አላመደ፣ አለማመደ፡ አስተዋወቀ፡ አቃረበ፡ አቀራረበ፡ አሰማማ ።
- አላመጠ፡ ሰውን፡ ዐማ፡ ነቀፈ።
- አላመጠ፡ ዐኘከ፡ ለመጠ ።
- አላመጠ፡ ዐኘከ፡ አመሰኳ፡ አመነዠኸ፡ አለዘበ፡ አለነቀጠ፡ አላመ፡ ("ዘኁ. ፲፩፡ ፴፫") (ተረት)፡ እኸልን፡ አላምጦ፡ ነገርን፡ አዳምጦ ።አላምጠኸ፡ አላምጠኸ፡ ወደ፡ ወገንኸ፡ ዋጥ ።አላመጠን፡ ዐኘከ፡ ማለት፡ የልማድ፡ ትርጓሜ፡ ነው ።
- አላመጠ፡ አዛባ፡ አጓበጠ።
- አላሚ፡ ያላመ፡ የሚያልም፡ ለንቃጭ።
- አላማ፡ አኰሳተረ፡ አቈናጸለ።
- አላማ፡ አያያዘ፡ አጋጠመ፡ (በመላሚያ፡ አሰረ፡ ጠገነ) ።
- አላማኝ፣ አለማማኝ፡ ያላመነ፡ የሚያላምን፡ የልመና፡ ጓድ፡ ያለማመነ፡ የሚያለማምን። ዛር፡ አለማማኝ፡ እንዲሉ።
- አላማጅ ፣ አለማማጅ ያላመደ፡ የሚ ያላምድ፡ ያለማመደ፡ የሚያለማምድ፡ አስተዋዋቂ።
- አላማጣ፣ በሰቈጣ፡ ውስጥ፡ ያለ፡ አገር።
- አላማጣ፣ ባዲስ፡ አበባ፡ ቤተ፡ መንግሥት፡ በፊት፡ በር፡ በኩል፡ የሚገኝ፡ የኹለተኛ ቅጥር፡ በር፡
- አላማጭ፣ ያላመጠ፡ የሚያላምጥ፡ ዐኛኪ።
- አላሰ፡ ማርን፡ እጅ፡ አግባ፡ ድፍድፍን፡ እቅራሪ፡ ጨመረ።
- አላሰ፡ ጨውን፡ ለከብት፡ በምላስ፡ መ
- አላሰነ፡ ልስን፡ አሣራ፡ (ረዳ)፡ አለቃለቀ፡ አቀባ።
- አላሳመ (አስተሳዐመ)፡ አማረ ። አሳሳሚ፡ ያላሳመ/የሚያሳስም ። ማሳሳም፡ ማማጪም ። ማሳሳሚያ፡ ማጨማሚያ ።
- አላሸቀ፡ አለፋ፡ አላላ፡ አለጠ።
- አላሽ፣ ያላሰ፡ የሚያልስ፡ ለጓሚ፡ እረኛ ።
- አላቀ፡ (አልሀቀ)፡ አሳደገ፡ አበለጠ፡ ሾመ፡ አከበረ፡ አለቃ፡ አደረገ፡ ("ፊልጵ. ፪፡ ፱") ።
- አላቀሰ፡ እለቅሶ፡ ደረሰ፡ አዋየ፡ አስተዛዘነ፡ ዐብሮ፡ አለቀሰ፡ ሐዘንን፡ ተካፈለ፡ እንባ፡ ኣፋሰሰ፡ ኦናባ ።
- አላቀቀ፡ አለያየ፡ አካፈተ፡ አፋታ፡ ባልና፡ ሚስትን፡ ፍንጅን፡ እግር፡ ብረትን። አፋሸ፡ አዛጋ፡ ኣ፡ አለ፡ አፍን ።
- አላቀቀ አላቃቂ፡ ያላቀቀ፡ የሚያላቅቅ፡ አለያዪ፡
- አላቂ፡ (አልሃቂ)፣ ያላቀ፡ የሚያልቅ፡ አሳዳጊ፡ ሿሚ፡ ኣክባሪ።
- አላቂ የሚወረስ፡ ዐለቀ።
- አላቃሚ፡ ያላቀመ፡ የሚያላቅም፡ አሰባ
- አላቃሽ፡ ያላቀሰ፡ የሚያላቅስ፣ አስተዛ
- አላቈጠ ፣ አራሰ፡ ረገጠ፡ ለወሰ፡ ጭቃናሊጥ፡ አደረገ ።
- አላቋጭ፡ ያላቈጠ፡ የሚያላቍጥ፡ ጭቃ፣ረጋጭ፡ አቡኪ ።
- አላባሽ አግሬ ("ሐገፋ ታላቅ ጋሻ' ያርበኛን ገላ የሚደብቅ ማላበስ ማካደን ማሻፈን ") ።
- አላባት፡ አለደንብ፡ አላገባብ። አባትን፡ ተመልከት ።
- አላባት፡ አባት፡ ሳይኖረው፡ አለዘር። ክርስቶስ፡ ከድንግል፡ ማርያም፡ አላባት፡ ተወለደ።
- አላባ፤ነጭ፡ ማዕድን፡ ዐላባ።
- አላት፡ (ሀለዋ)፡ ብልኀት ' አላት ።
- አላቸው፡ (ሀለዎሙ፡ ን)፡ ለነዚያ፡ ትጋት፡ አላቸው።
- አላቻ፡ አለኩያ። አላቻ፡ ጋብቻ፡ ቈይ ፥ ብቻ፡ ቈይ፡ ብቻ ።ያለን፡ ተመልከት፡ ከዚህ፡ ጋራ፡ አንድ፡ ነው ።
- አላችኹ፡ (ሀለወክሙ፡ ን)፡ ለናንተ፡ ደግነት አላችኹ። ነውን፡ ተመልከት።
- አላችኹ፡ (ሀሎክሙ፡ ን)፡ እናንተ፡ አላችኹ ።
- አላከከ፡ አቃባ፡ አጋጠመ ።
- አላከፈ፡ አቃመሰ፡ አናካ።
- አላከፈ፡ አዣመረ፡ እያያዘ።
- አላካ፡ አከናዳ፡ አሳፈረ፡ አሻለገ።
- አላኰሰ፡ አታኰሰ፡ አጣላ።
- አላኳሽ፡ ያላኰሰ፡ የሚያላኵስ።
- አላወሰ፡ አስኬደ፡ አራመደ፡ (አድራጊ) ።
- አላወሰ፡ አንቀሳቀሰ፡ አነቃነቀ፡ አዛመረ፡ አወሳወሰ፡ አወላዳ፡ (አደራራጊ) "
- አላወጠ፡ (አስተዋለጠ)፡ አዛወረ፡ አቃየረ፡ (ለወጠ) ። (ተረት)፡ ባለቤት፡ የወደደው፡ አህያ፡ ፈረስ፡ ያላውጣል ።
- አላዘበ፡ አለዛዘበ፡ አዳቀቀ፡ አሳለቀ፡ አላላመ፡ አለሳለሰ፡ (አደራራጊ)
- አላዘበ፡ አዋረበ፡ አባባለ።
- አላዘበ፡ እንደ፡ ዘበት፡ ያዘ፡ በእጁ፡ ላይ፡ ምራቁን፡ እንትፍ፡ እንትፍ፡ እያለ፡ በቀላል፡ ሠራ፡ (አድራጊ) ።
- አላዘነ፡ አንቋረረ፡ (ላዘነ) ።
- አላዘገ፡ ሳበ፡ ጐተተ።
- አላዛኝ፡ ያላዘነ፡ የሚያላዝን፡ አንቋራሪ፡
- አላድ፡ (ዶች)፡ የገንዘብ፡ ስም፡ የብር፡ ግማሽ፡ እኩሌታ፡ ፲፡ መሐልቅ፡ የሚያነሣ ' ፰ ' መሐልቅ፡ ፩፡ ተሙን፡ የሚመነዘር። አበትን፡ እይ፡ ፭፡ ድሪም፡ ፩፡ አላድ፡ ነው ።
- አላገባብ፡ አለሥርዐት፡ እንዳለወገን ።አላገባብ፡ ተናገረ፡ ጻፈ።
- አላገደ፡ አላገጠ፡ ("መሳ. ፰፡ ፲፭") ።
- አላገደ፡ አቀራቀረ፡ አዋተፈ ።
- አላገጠቀለደ፡ ለገጠ።
- አላጊ፡ ያላጋ፡ የሚያላጋ፡ አቈራቋሽ ።
- አላጋ ዕሩርን፡ አቈራቈሰ፡ ኣማታ፡ አጋጯ ።ሰውየው፡ ሰውየውን፡ ማሪያምን፡ ትወዳ ታለኸን፡ ቢለው፡ ከግንድ፡ የሚያላጋ፡ ልጅ፡ አላት፡ አለ፡ ይላሉ ።
- አላጐመ፡ አቀራቀረ፡ አጫመረ፡ አጋባ፡ ልጓምን፡ እፈረስ፡ እበቅሎ፡ አፍ፡ ውስጥ።
- አላጐመ፡ ኣሳፋ፡ ኣላበደ ።
- አላጐደ፡ አላጠፈ ።
- አላጠጠ፡ አሳሳበ፡ አዋጠረ።
- አላጨ፡ አፈጋፈገ፡ አጣረገ፡ ጠጕርን።
- አላጭ፡ ያለጠ/የሚያልጥ።
- አላፈደ ፣አለፋ፡ አጋጠረ፡ አደከመ።
- አላፋ፡ (አስተላፍዐ)፣ አፋተ፡ እራገጠ፡ አዣለጠ፡ እጝወተ ።
- አላፋጅ፣ ያላፈደ፡ የሚያላፍድ፡ አድካሚ፡
- አላፋፋ ፣ ዐሻሸ፡ ዠላለጠ።
- አሌአይዶለም፡ ዐሌ።
- አሌጠ አላገጠ (ሌጠ) ።
- አሌፋት፡ ፊደሎች፡ ከአ፡ እስከ፡ ተ፡ ያሉ ። አለቃቸው፡ አሌፍ፡ ስለ፡ ኾነ፡ በርሱ፡ ስም፡ አሌፋት፡ ተብለው፡ ይጠራሉ ።
- አሌፍ፡ (ዕብ)፡ ፊደል፡ የፊደል፡ ስም፡ መዠመሪያ፡ ፊደል፡ አ ። (ግጥም)፡ አሌፍ፡ ብሂል፡ ብዬ፡ እታው፡ ድረስ፡ ሳውቀው፡ ቤት፡ እመኻል፡ ገብቶ፡ ልቤን፡ አስጨነቀው ።
- አል፡ (አል፡ ኢ)፡ በቁሙ፣ አሉታ፡ አፍራሽ ። በኀላፊ፡ አንቀጽ፡ አልበላም፡ አልጠጣም፡ አላየም፡ አልሰማም፡ አልኼደም፡ አልመጣም፡ እያለ፡ አሉታነቱን፡ ያሳያል። እኔ፡ በሚል፡ ግን፣ በትንቢትና፡ በትእዛዝ፡ አልሰንፍ፡ አልሰንፍም፡ አልስነፍ፡ እያለ፡ ይነገራል ።አል፡ መነሻው፡ ረ፡ በኾነ፡ ግስ፡ ሲገባ፡ ል፡ ተጐርዶ፡ ረገጠ፡ አረገጠም፡ ረዘመ፡ አረዘመም፡ እያለ፡ ረ፡ ይጠብቃል።
- አልመዘመዘ፡ ዐሽ፡ አፍተለተለ፡ አጥመ
- አልመዘመዘ አፍተለተለ፡ ለመዘ።
- አልሚ፡ ያለማ፡ የሚያለማ፡ አለምላሚ፡
- አልሚና፡ ለሚ፡ ኮከባቸው፡ የገጠመ፡ ባልና፡ ሚስት።
- አልሚና፡ ለሚ፡ ውሃና፡ ተክል።
- አልማ፡ ዐልባ፡ ልብ ።
- አልማዝ፡ (ዞች)፡ (ዐረ፡ አልማስ)፡ የድንጋይ፡ ንጉሥ፡ ጥኑ፡ ጠንካራ፡ አለት። ዕንቍ ፈርጥ፡ ክቡር፡ ደንጊያ፡ (ዘካ፯፡ ፲፪)። ዕንቍና፡ ሉል፡ ፈርጥና፡ አልማዝ፡ አንዳንድ፡ ወገን፡ ናቸው፡ ፈርጥ፡ ከድንጋይ፡ ሉል፡ ከባሕር፡ ይገኛል ።
- አልማጅ፡ አስለማጅ፡ ያለመደ፡ የሚያለምድ ፣ያስለመደ፡ የሚያስለምድ፡ አስተማሪ፡ መሪ ።
- አልማጭ፡ (ጮች)፡ ያለመጠ፡ የሚያለምጥ ፣ አላጋጭ፡ ዝንጀሮ።
- አልማጭ፡ መኾን፡ አለ
- አልማጭነት መታዘዝ ።
- አልምጥ፡ አልማጭ፣ ዝንጀሮ፡ ዐይነት አልምጥ፡ ኣላግጥ።
- አልሞት፡ ባይ፡ ተጋዳይ፡ ከተመታና፡ ከተወጋ፡ በኋላ፡ ጠላቱን፡ መልሶ፡ ወግቶ፡ የገደለ ።
- አልሰሜ፡ ያልሰማ፡ ያልተረዳ። ዘከረ፡ ብለኽ፡ ተዝካርን፡ እይ።
- አልቃሽ፡ (ሾች)፣ ያለቀስ፡ የሚያለቅስ፣ ለቅሶኛ፡ ቈዛሚ፣ የለቅሶ፡ ቀንቃኝ፡ ግጥም፡ ገጣሚ፡ አውራጅ፡ አልቅሶ፡ የሚያስለቅስ፡ ("ኤር. ፱፡ ፲፯") ።
- አልቃሾ፡ የተጫነ፡ አህያ፡ መውጊያ፡ መጓጐ፡ ሽመል፡ ሹል፡ ብረት፡ ያለበት፡ በትግሪኛ፡ አርቃይ፡ በግእዝ፡ መቅርዕ፡ ይባላል ። ለና፡ ረ፡ ተወራራሾች፡ ስለ፡ ኾኑ፡ በአርቃሾ፡ ፈንታ፡ አልቃሾ፡ ይላል ። በአልቃሾም፡ ዘይቤ፡ ቢፈቱት፡ መጕዳቱንና፡ ማስለቀሱን፡ ያሳያል ። ዳግመኛም፡ የግእዝ፡ መጽሐፍ፡ መድጐጽ፡ ይለዋል ።
- አልቅሺን ፣ (መስቈቅው)፡ የሚያለቅስ፡ ልጅ፡ ላንቊሶ ፣እንደ፡ ኤርምያስ፡ ያለ፡ ለቅሶ፡ ወዳድ ።
- አልቅት በቁሙ፡ ዐልቅት ። እልቅት፣የደረት፡ ጫፍ፡ ዕልቅት።
- አልቢን፡ የጣሊያን፡ ጠመንዣ ።
- አልባ፡ የላት። አንዳች፡ አልባ፡ ልጅ፡ አልባ፡ እናት፡ አልባ። ልብንና፡ ለማን፡ እይ። አልባ፡ ለወንድም፡ ይነገራል፡ ትርጓሜውም፡ አለ፡ ያለ፡ ይባላል፡ (ዘፍ፵፪፡ ፴፮)።
- አልባሌ፡ የአልባል፡ ወገን፡ ዐይነት። አልባሌ፡ መሰለ፡ ልብሱን፡ ለወጠ፡ አሳቻ፡ ኾነ፡ (፩ነገ፡ ፳፪፡ ፴)።
- አልባል፡ (ኢይትበሀል)፡ ያልታወቀና፡ በክብር፡ የማይጠራ፡ ተርታ፡ ሰው። ስሜ፡ አይታወቅ፡ እከሌ፡ አይበሉኝ፡ ማለት፡ ነው ።
- አልባብ፡ (ልብን)፡ ዕጣን፡ ልባንጃ ' የጪስ፡ ዕንጨት ።ደን፡ ኹሉ፡ በጥቅምት፡ አልባብ፡ አልባብ፡ ይሸታል።
- አልባብ፡ ያጋምና፡ ያዞ፡ ዐረግ፡ የርጐፍት፡ አበባ፡ ሽታ ።መዐዛው፡ ልብ፡ የሚመሥጥ፡ ስለ፡ ኾነ፡ አልባብ፡ ተባለ፡ አልባብ፡ በግእዝ፡ ልቦች፡ ማለት፡ ነውና ።
- አልባት፡ (አልባቲ)፡ ዝኒ፡ ከማሁ። ምናልባትን፡ እይ።
- አልባት (አልባቲ)፡ የላት ማለት ነው።
- አልቦ (አል፡ ቦ)፡ የለም፡ አልኖረም፡ አልነበረም። አልቦና፡ ዐልቦ፡ ባማርኛ፡ ይገጥማሉ።አንጥረኛው፡ ብዙ፡ በቴዎድሮስ፡ ቤት፡ ባላልቦ፡ ኣደረጉት ፥ ይኸን፡ ኹሉ፡ ሴት፡ እኔስ፡ የሚገርመኝ፡ የዚህ፡ አብነቱ፡ ባላልቦ፡ ወለደች ልጃገረዲቱ፡ (ማቴ፩፡ ፲፰ ።ሉቃ፩፡ ፴፬) ። (ባል፡ አልቦ፡ ባለዐልቦ) ።ዐለበን፡ እይ ።
- አልቦ፡ የጌጥ፡ ስም፡ ዐልቦ።
- አልተሰባኝም)፡ አልተገለጠልኝም፡ አልገባኝም።
- አልተሳካም)፡ አልተቀናበረም፡ አልኾነም፡ አልበጀም፡ አልሰለጠም።
- አልታየ፡ የወንድና የሴት ስም ።
- አልቴት፡ (ዐረ፡ ሀልቲት)፡ የዛፍ ፥ ሙጫ፡ የራስ፡ ምታትና፡ የውጋት፡ መድኀኒት ።
- አልከሰከሰ፡ ቅጥ፡ አሳጣ፡ እንዳይሠራ፡ እንዳይኾን፡ አደረገ፡ ጣለ፡ በተነ፡ ረገጠ፡ አሳደፈ፡ አቈሸሸ፡ አረከሰ ።ፈረሱ፡ ድርቆሹን፡ አልከሰከሰ ሰው፡ እንጂ፡ አልበላውም።
- አልከሰከሰ -በተነ፡ ረገጠ፡ ለከሰ ።
- አልከስካሽ፡ ያልከሰከሰ፡ የሚያልከሰክስ፡ አሳዳፊ ።
- አልከፈከፈ፡ ቅምስ፡ ቅምስ፡ አስደረገ፡ አልከሰከሰ ።
- አልከፈከፈ፡ አልከሰከሰ፡ ለከፈ።
- አልካፊ፡ ያለከፈ፡ የሚያለክፍ፡ አቅማሽ።
- አልኰሰኰሰ፡ (አልኈሰሰ)፡ ረገጠ፡ አላወሰ ። ለከሰን፡ እይ።
- አልኰሰኰሰ፡ በለኈሳስ፡ ደገመ።
- አልኰሰኰሰ አላወሰ፡ ለኰሰ።
- አልኰስኳሽ፡ ያልኰሰኰሰ፡ የሚያልኰስኵስ፡ አላዋሽ።
- አልኰፈኰፈ፡ ምራቅ አስነካ፡ ለኰፈ ።
- አልኰፈኰፈ፡ ምራቅና፡ ለሐጭ፡ አስነካ፡ ሳይበላ፡ ሳያኝክ፡ ተወ፡ ኣኵለፈለፈ " አልኰፍኳፊ ፣አኵለፍላፊ ።
- አልኹ፡ (ብህልኩ)፡ ተናገርኹ፡ ቃል፡ አሰማኹ።
- አልኹ፡ ባይ፡ ብዬ፡ ነበር፡ የሚል።
- አልኹ፡ አላልኹ፡ የ፪፡ ውሻ፡ ጩኸት።
- አልገዘገዘ፡ አንገታገተ፡ (ለገዘ)።
- አልገዝጋዥ፡ የሚያልገዘግዝ፡ አንገታ ጋች ።
- አልጕም፡ መስተሐምም፡ መናገር፡ የሚከለክል፡ አስማት፡ መድኀኒት ።
- አልጕም፡ ዝምተኛ፡ ሰው።
- አልጋ፡ በቁሙ፡ ዐልጋ።
- አልጐመጐመ፡ በቀላል፡ ዐኘከ፡ ለጐመ።
- አልጐመጐመ፡ ባፉ፡ ውስጥ፡ ዐጥንትን፡ እያዛወረ፡ በቀላል፡ ልጓምኛ፡ ዐንከ፡ ቈረጠመ ።
- አልጐምጓሚ፡ ያልጐመጐመ፡ የሚያል ጐመጕም ።
- አልፈሰፈሰ አዝለፈለፈ፡ (ለፈሰ)።
- አልፊ፡ (ዎች)፡ ያለፋ፡ የሚያለፋ፡
- አልፋ፡ (ጽርእ)፡ ዝኒ፡ ዓዲ፡ ከማሁ፡ ለአሌፍ ። አልፋ፡ ቤጣ(ታ)፡ አልፍ፡ ቤት ።
- አልፋ፡ ስመ፡ አምላክ ። ቅድስት፡ ሥላሴ፡ አ፡ አብ፡ ል፡ ወልድ፡ ፋ፡ መንፈስ፡ ቅዱስ፡ ማለት፡ ነው፡ ይላሉ ።
- አልፋ፡ ወዖ፡ አሌፍ፡ ወታው፡ (ራእ ፩፡ ፰) ። ትርጓሜው፡ ፊተኛና፡ ኋለኛ፡ መዠመሪያና፡ መጨረሻ፡ ማለት፡ ነው ። ፆን፡ እይ ።
- አልፍ፡ (ግእዝና፡ ዐረብ)፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ ለአሌፍ፡ ዞ አልፍ፡ አ፡ እንዲሉ ። አልፍ፡ ቤት፡ የአና፡ የበ፡ ስም ።
- አሎ ፣ የስልክ፡ ጥሪ፡ ሰማኸ፡ ስማ፡ እንደ፡ ማለት።
- አሎ (ጥሎ)፡ (ሀሎ)፡ የሰው ስም፡ ትርጓሜው፡ አለ፡ ማለት፡ ነው፡ ሌላም፡ አፈታት፡ ይኖረዋል።
- አሎ፡ ሐሰት ˓፡ ዐሎ ።
- አሎ፡ በረት፡ በላይኛው፡ ወግዳ፡ ያለ፡ ቀበሌ ።
- አሎሎ፡ ድንብልብል፡ ደንጊያ፡ የኮሶና፡ የቅመም፡ መደቈሻ፡ ስምነቱ፡ በላይ፡ መኾንን፡ ያሳያል ።
- አመ፡ ጊዜ፡ ሰዓት፡ አመ፡ ሠላሳ፡ እንዲሉ። አመ፡ ሠላሳ፡ የወር፡ መጨረሻ፡ ቀን ።
- አመለለጠ (አምለጠ/አምሠጠ)፡ ከተያዘ በኋላ ነጠቀ/ወጣ/ዳነ/ተረፈ፡ ሸሸ (ዘዳ. ፫፥፳፩፡ ኢሳ. ፬፥፪፡ ሕዝ. ፴፫፥፳፩፡ ዮሐ. ፲፥፴፱፡ ፪ቆሮ. ፲፩፥፴፫) ። "ከጠላት አመለጠ፡ ከአሥር ቤት አመለጠ" እንዲሉ። (ተረት)፡ "ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም"። በላን እይ።
- አመለመለ (አሕመልመለ)፡ ሸበለለ/ጠቀለለ (የኮባንና የእንሰትን/የሙዝን/የዘንባባን ሙሽራ አስመሰለ)፡ አምልማሎ አደረገ።
- አመለመለ አምልማሎ፡ አደረገ፡ -መለመለ ።
- አመለመለ/ዐመል ማለ፡ እነዚህ ሦስቱ በአማርኛ ይተባበራሉ (ግጥም)፡ "ጥጡን ነድፈሽ ነድፈሽ ባልጋ ቈልለሻል፡ ይህን አመልምለሽ (ዐመል ምለሽ) ብተይ ይሻልሻል"።
- አመለከ (አምለከ)፡ አምላክ አደረገ፡ ኣምላክነት ሰጠ፡ አመነ፡ ኣከበረ፡ አመሰገነ፡ ወዳምላክ ጸለየ/ሰገደ። "ከኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ"።
- አመለከ፡ አመሰለ፡ ክፉ ምልክት አሳየ፡ ጣዖትን አምላክ እንደ ማለት።
- አመለከ፡ አምላክ፡ አደረገ፡ ለከ ።
- አመለከተ፡ ለእኛ ክርስቲያኖች የትንሣኤ ምልክት ነው (ይህ ከላይ ካለው "መለከት" ጋር የተያያዘ ይመስላል) ።
- አመለከተ፡ በበረቅ አሠመረ፡ ነደፈ/በገረ (ኢሳ. ፵፬፥፲፫) ።
- አመለከተ፡ በዜማ መጻፍ ላይ ምልክት ጻፈ።
- አመለከተ፡ ጠቈመ፡ (መለከተ)።
- አመለካች፡ የጠቆመ/የነገረ/የገለጠ/የአሳየ።
- አመለካከተ፡ ከአንድ ኹለት ጊዜ አመለከተ።
- አመለካከት፡ አስተያየት፡ መመልከት።
- አመለገ፡ ሳበ፡ ጐተተ፡ አወለገ፡ አሾ ለከ።
- አመለጠ፡ ነጥቆ በረረ፡ መለጠ።
- አመለጠነ፡ -አንገርጋሪ፡ መራ፡ -(መለጠነ) ።
- አመለጣጠን፡ ያንገርጋሪ አመራር፡ ማመልጠን።
- አመለጥ፡ ባሪያ፡ መለጠ።
- አመለጥ፡ የባሪያ ስም፡ ፭ኛ ባሪያ የእሠለጥ ልጅ።
- አመላለሰ፡ (ከዚያ ወደዚህ አመጣ/እጋዘ፡ ከዚህ ወደዚያ ወሰደ) ።
- አመላለሰ፡ ብድርን አከፋፈለ።
- አመላለሰ፡ አለዋወጠ።
- አመላለሰ፡ አመጣጣ/አወሳሰድ።
- አመላለስ፡ አዟዟር፡ መመለስ።
- አመላለድ፡ የጧት አገሣገሥ፡ መማለድ።
- አመላለግ፡ ኣመጋገጥ፡ መምለግ/መማለግ።
- አመላለጠ፡ አስተጪደ/አላላጠ/አቀራረፈ።
- አመላለጥ፡ አላላጥ፡ መምለጥ።
- አመላላሽ፡ ያመላለሰ/የሚያመላልስ (አከፋፋይ፡ አምጪና ወሳጅ፡ አንጥረኛ) ። "ነገር ኣመላላሽ" እንዲሉ።
- አመላላሽነት፡ አመላላሽ መሆን (አሳባቂነት) ።
- አመላል/አሞላል፡ አጨማመር፡ መምላት/መሙላት።
- አመላመለ፡ አማረጠ።
- አመላመለ፡ አኰታኰተ/አቋረጠ።
- አመላመል፡ አኰታኰት፡ መመልመል። ቈጠቈጠን ተመልከት።
- አመላማይ፡ ያመላመለ/የሚያመላምል (አኰታኳች/አማራጭ) ።
- አመላከተ፡ አስተያየ፡ ምልክት አጻጻፈ፡ አመለካከተ፡ አጠቋቈመ።
- አመል ጠባይ፡ ዐመል ።
- አመልማይ (ዮች)፡ ያመለመለ/የሚያመለምል (ሸብላይ/ጠቅላይ) ።
- አመልካች (ቾች)፡ ያመለከተ/የሚያመለክት፡ ጠቋሚ/አቤት ባይ።
- አመልካች፡ ምልክት ጻፊ።
- አመልጣኝ፡ ያመለጠነ/የሚያመለጥን (መሪ) ።
- አመመ፡ (አምሞ፡ አመመ)፡ አነተ፡ እናት፡ አደረገ፡ እማማ፡ አለ ። (ግጥም)፡ ያምማል፡ ዝኆን፡ የኛ፡ ወገን፡ ሊኾን።
- አመመ፡ በዛ፡ ዐመመ።
- አመመ፡ አማሚ፡ ኾነ፡ ቀመደ፡ ያረም፡ ያጨዳ፡ የቊፋሮ።
- አመመ፡ አጮኸ፡ አተመመ።
- አመመበሸተ፡ ዐመመ።
- አመሰ አገላበጠ፡ ዐመሰ።
- አመሰሰ፡ መዘዘ/አረዘመ።
- አመሰሰ፡ አንገዋለለ/አወጣ/ለየ።
- አመሠራረት፡ መሠረት አጣጣል፡ መመሥረት።
- አመሰቃቀለ፡ አዘበራረቀ/አገለባበጠ ።
- አመሰቃቀል፡ አዘበራረቅ፡ ማመሳቀል፡ አሰቃቀል፡ አነሣሥ፡ መስቀል። ሰቀቀሰ/ለቸ/ሠቀቀ ። ሰቈቃው (ቈቀወ)፡ ሙሾ ቍዘማ ።
- አመሰቃቃይ፡ ያመሰቃቀለ/የሚያመሰቃቅል ።
- አመሰኳ (መሰኳ/ሰኵዐ)፡ ወንከ/አመነዠኸ/አለነቀጠ/አላመጠ (ቀን የለቀመውን በ፪ኛ ጕሮሮ ከሆዱ እያወጣ) ።
- አመሰኳ -አመነዠኸ (መሰኳ)።
- አመሰኳኵ፡ አመነዣዠኸ፡ ማመስኳት።
- አመሰገነ ፣አወደሰ፡ (መሰገነ)።
- አመሰጋገነ፡ አወዳደሰ/አሞጋገሰ።
- አመሰጋገነ፡ አወዳደሰ/ኣሞጋገሰ። አመሰጋገን፡ አሞጋገስ፡ ማመስገን። መሳድ፡ የሸማ መወጠኛ ቀጪን ዕንጨት በቍቲት ውስጥ ያለች (ከመጠቅለያ አትለይም) ።
- አመሰጠረ (አመስጠረ)፡ አረቀቀ/ሐባ ሰወረ/ደበቀ/ሸሸገ ነገርን።
- አመሰጠረ፣፡ አረቀቀ፡ ምስጢር።
- አመሰጣጠር፡ አረቃቀቅ (የምስጢር አነጋገር/መመስጠር/ማመስጠር) ።
- አመሳ (አምስሐ)፡ አበላ/ጋበዘ/መገበ። "ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቢራቡ ያመሳል ቢሞቱ ያስነሣል" (ዮሐ. ፮፥፲፩-፲፪፡ ፲፩፥፵፬) ። ማምሳት፡ ምሳ ማብላት/መጋበዝ።
- አመሳ (አምስሐ)፡ አበላ/ጋበዘ/መገበ። "ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቢራቡ ያመሳል ቢሞቱ ያስነሣል" (ዮሐ. ፮፥፲፩-፲፪፡ ፲፩፥፵፬) ። ማምሳት፡ ምሳ ማብላት/መጋበዝ።
- አመሳሰለ፡ አነጻጸረ/አስተባበረ (ምስል አባጀ) ።
- አመሳሰለ፡ አንድ አደረገ/አመሳሰለ።
- አመሳሰል፡ አሣሣል/አተራረት፡ መምሰል/መመሰል።
- አመሳሰን፡ አለፋፍ፡ መማሰን።
- አመሳሳሊ፡ የሚያመሳስል።
- አመሳሳል፡ አንድ ማድረግ/ማመሳሰል።
- አመሳሳይ፡ ያመሳሰለ/የሚያመሳስል (እነጻጻሪ/አስተባባሪ) ።
- አመሳስ፡ የምሳ አበላል፡ መምሳት።
- አመሳሶ -መናኛ ውጤት፡ -መሰሰ ።
- አመሳሶ፡ እንግውላይ/መናኛ ውጤት ("የልጅ አመሳሶ የለውም ለናት ላባቱ ኹሉም እኩል ነው" - "እከሌ የነገር አመሳሶ ያወጣል") ።
- አመሳቀለ፡ አዘባረቀ፡ ሰቀለ።
- አመሳቀለ፡ አዘባረቀ/አጣላ (ተክልን በተክል ከተበ መስቀልኛ ቈረጠ አራከበ) ። አመሳቃይ፡ ያመሳቀለ/የሚያመሳቅል (አዘባራቂ አጣይ) ።
- አመሳቀለ፡ እንቢ፤
- አመሳቃይነት፡ አመሳቃይ መኾን (አዘባራቂነት) ።
- አመሳከረ/አመሰካከረ፡ ምስክርንና ምስክርን/ባለጋራንና ባለጋራን አናገረ/አነጋገረ።
- አመሳገነ፡ አገሰ።
- አመሳጠረ፡ አራቀቀ (በምስጢር አነጋገረ/አጨዋወተ) ።
- አመሳጣሪ፡ ያመሳጠረ/የሚያመሳጥር (የምስጢር አነጋጋሪ) ።
- አመሳጣሪነት፡ አመሳጣሪ መኾን።
- አመስኲ (ሰኳዒ)፡ ያመሰኳ/የሚ፡(ያመሰኳ/የሚያመነዥኸ አመንዣኺ - በሬን/በግን/ፍየልን/ግመልን/ጥንቸልን/ሽኮኮን/ዕሪያን የመሰለ እንስሳ/አውሬ - አመስኲ አልተለመደም) ።
- አመስጋኝ፡ ያመሰገነ/የሚያመሰግን (በውነት ወይም ባሰት - "አመስጋኝ አማሳኝ" እንዲሉ) ።
- አመስጋኞች፡ የሚያመሰግኑ/አወዳሾች/መዘምራን (ነሐ. ፲፪፥፴፰) ።
- አመረ፡ (አሚር፡ አመረ)፡ ዐወቀ ' ወደደ፡ (ግእዝ) ።
- አመረ፡ (አምሮ፡ አመረ)፡ አሳየ ' አመለከተ፡ ታምር፡ ሠራ፡ (ግእዝ)።
- አመረረ፡ መራራ አደረገ (ኢዮ. ፳፯፥፪፡ ራእ. ፲፥፱-፲) ። "ማሩን አምርሮ ወተቱን አጥቍሮ" እንዲሉ።
- አመረረ፡ ተቈጣ/ጥል አነሣ ("እከሌ በጨዋታ ያመራል።")
- አመረቀዘ፡ ዐደሰ/አቀበረ/ኣባሰ/አቄመ።
- አመረቀዘ፤አቄመ፡ መረቀዘ ።
- አመረቃ፡ አጣፈጠ (ጣዕም ሰጠ/አዋዋ) ።
- አመረቃ አጣፈጠ፡ መረቃ።
- አመረቈተ፡ አበጠረ/አጐፈረ/አጐተነ።
- አመረተ፡ ላይዳ አለ/አዘራ (ፍሬን ከገለባ ለየ/አጠራ) ።
- አመረተ፡ ኣዛገ/መሬት አስመሰለ።
- አመረኳኰዝ፡ አደጋገፍ መመርኰዝ።
- አመረገደ፡ መረገደ።
- አመረጋገድ፡ የመረግድ አባባል፡ መመራገድ።
- አመራ (አምርሐ)፡ ፊቱን ወዳንድ በኩል መለሰ/አቀና።
- አመራመረ፡ አጠያየቀ/አፋተሸ/አቋፈረ።
- አመራመር፡ አጠያየቅ፡ መመርመር።
- አመራማሪ፡ ያመራመረ/የሚያመራምር (የምርመራ ረዳት) ።
- አመራማሪነት፡ አመራማሪ መኾን።
- አመራረር፡ የምሬት አኳዃን፡ መምረር።
- አመራረቀ፡ አበራረከ (ምርቃት አቀባበለ በምርቃት ላይ ምርቃት ጨመረ) ።
- አመራረቅ፡ አበራረክ፡ መመረቅ።
- አመራረት፡ አዛዛግ፡ ዝገት፡ መመረት፡ መምረት።
- አመራረን፡ አስተሳሰር፡ መመረን።
- አመራረክ፡ አዘራረፍ፡ መማረክ።
- አመራረግ፡ አለጣጠፍ፡ መምረግ።
- አመራረጥ፡ አለያየት፡ መምረጥ።
- አመራራ፡ ዕውርን አከታተለ (ያንዱን እጅ ከሌላው ትከሻ እያያዘ) ።
- አመራሮ፡ ዛፍ፡ መረረ።
- አመራሮ፡ የዛፍ ስም (መራራነት ያለው ታናሽ ዛፍ በቀመሱት ጊዜ አፍን የሚያመር) ።
- አመር፡ (ምዕር)፡ አንደዬ ።
- አመር፡ ዘራፍ፡ አንድ፡ ጊዜ፡ ፊት፡ መዠመሪያ፡ ዘምቶ፡ የዘረፈ፡ መራውን፡ የወጣ፡ ማለት፡ ነው ።አንቷን፡ ዳባዲና፡ ጕይዲ፡ ግን፡ ጦር፡ ነቀል፡ ብለውታል ።ሐመርን፡ ዐከከ፡ ብለኽ፡ ዐካኪን፡ እይ ።
- አመርቃዥ፡ ያመረቀዘ/የሚያመረቅዝ።
- አመርጋጅ፡ ያመረገደ/የሚያመረግድ (መርጋጅ) ።
- አመሸ (አምሰየ)፡ በምሽት ከ፲፪ ሰዓት እስከ ፪ና ፫ ሰዓት በአንድ ስፍራ ተቀመጠ/ቈየ (አጨለመ - የባለጌ ግጥም)፡ "ዝንጀሮ ጠባቂ ላያድር ያመሻል፡ ብፈራሽ ነው እንጂ ልቤስ ከጅሎሻል"።
- አመሸከ፡ ፈጥኖ ዐጨደ/ቈረጠ (የመስክ ሣርን/እጅን/ሥጋን/ቅጠልን) ።
- አመሸከ፣፡ዐጪደ፡ መሸከ ።
- አመሻሸ/አምሻሸ፡ በምሽት ጊዜ ቈያየ ("አያድሩበት ቤት ያምሻሹ") ።
- አመሻሸት፡ ዝኒ ከማሁ።
- አመሻሸት፡ የመሸታ አሠራር፡ መመሸት።
- አመሻሸግ፡ አስተጣጠር፡ መመሸግ።
- አመሻሽ፡ የምሽት አኳዃን (መምሸት) ።
- አመቀ፡ ረጠጠ፡ ዐመቀ ።
- አመቀ፡ አጠማዘዘ/አጠናፈፈ/አ ጣራ ።
- አመቀመቀ ፣አቅማማ ፣(መቀመቀ) ።
- አመቀኛኘ፡ አቀናና።
- አመቀኛኘት፡ አቀናን፡ መመቅኘት።
- አመቃቀቅ፡ አለፋፍ፡ መማቀቅ።
- አመቃኘ፡ አቃና።
- አመቃኘ፡ አቃና፡ (መቀኘ)።
- አመቅማቂ፡ ያመቀመቀ/የሚያመቀምቅ (አመንቺ) ።
- አመተ፡ አከሰለ፡ ዐመተ።
- አመተ፡ ጭምት አደረገ ("አረጋ") ።
- አመታት፡ አደባደብ/መምታት።
- አመታት፡ ኣወጋግ/አገዳደል (፩ሳሙ. ፲፱፥፰) ።
- አመቴ፡ (አመትየ)፡ ገረዴ፡ ባሪያዬ፡ የኔ፡ ባሪያ፡ ከፊለ፡ ስምም፡ ይኾናል። አመቴ፡ ያሞራ፡ ስም፡ ቤተ፡ ሠሪ፡ አሞራ፡ ወንዝ፡ አመቴ፡ እንዲሉ።
- አመት፡ ገረድ፡ ሴት፡ ባሪያ፡ ደንገጥር ።
- አመቸ አስደላ፡ (መቸ)
- አመቻቸ፡ አደላደለ/አሸራሸ/አስተካከለ/አሰማማ።
- አመቻቸት፡ አደላደል፡ መመቸት።
- አመነ፡ (አሚን፡ አምነ)፡ በቁሙ፡ ተቀበለ፡ ተስፋ፡ አደረገ፡ ወደደ፡ አከበረ፡ ወከለ። ደንደስን፡ እይ።
- አመነ፡ ታዘዘ፡ ገበረ።
- አመነ፡ እውነት፡ ነው፡ አለ፡ እማኝ፡ ኾነ፡ መሰከረ።
- አመነመነ፡ አኰሰመነ/አቀጠነ/አሰለሰለ። "ምነው ያመነመነኸ ጥሬ ጓያ ነው?" እንዲል እረኛ።
- አመነሸ -በመንሽ፡ ወጋ፡ (መነሸ)።
- አመነታ (አመንተወ)፡ ላድርግ/አላድርግ አለ፡ አወጣ/አወረደ፡ ልቡን ኹለት አደረገ፡ አወላወለ።
- አመነታ -አወጣ አወረደ፣መነታ።
- አመነታተግ፡ አነጣጠቅ፡ መመንተግ።
- አመነታተፍ፡ አቀማም፡ መመንተፍ።
- አመነቸከ፡ አመነጀዘ/አሳደፈ።
- አመነቻቸክ፡ አጨቃጨቅ/አስተዳደፍ፡ መመንቸክ። መነጩቀንና ነተረከን እይ፡ የጨንና የቸን መወራረስ ልብ አድርግ።
- አመነኰሰ (አመንኰሰ)፡ ቆብ ሰጠ፡ መነኵሴ አደረገ።
- አመነኳኰስ፡ የቆብ አደራረግ (መመንኰስ) ።
- አመነዘረ (ትግ. መንዘረ)፡ ሴሰነ/ሸረሞጠ/ከሰው ሴት ኼደ/ቀነዘረ (መሳ. ፲፱፥፳፭፡ ማቴ. ፭፥፴፪፡ ራእ. ፲፰፥፫) ።
- አመነዘረ፡ ሴሰነ፡ መነዘረ ።
- አመነዘረች፡ "አንተ ውጣ/አንተ ግባ" አለች።
- አመነዛዘረ፡ አበታተነ/አለዋወጠ።
- አመነዛዘር፡ ኣሸራረፍ፡ መመንዘር።
- አመነዠኸ፡ -አመሰኳ፡ -(መነዠኸ)።
- አመነዣዠኸ፡ አመሰኳኵ፡ ማመንዠኸ።
- አመነዳደብ፡ አመታት/አቈራረጥ፡ መመንደብ።
- አመነዳደግ፡ አነጣጠቅ፡ መመንደግ።
- አመነጋገል፡ አነጋገል፡ መመንገል።
- አመነጓጐል፡ አነፋፈጥ፡ መመንጐል።
- አመነጣጠር፡ አስተጫወድ፡ መመንጠር።
- አመነጣጠቅ፡ አነጣጠቅ፡ መመንጠቅ። ነጠቀን እይ።
- አመነጨ፡ አፈለቀ/አወጣ/አፈሰሰ።
- አመነጫጨረ፡ አበታተነ።
- አመነጫጨር፡ አበታተን፡ መመንጨር።
- አመነጫጨት፡ አፈላለቅ (መመንጨት) ።
- አመናሸ፡ መንሽ አጣጣለ/አባባለ።
- አመናሸ፡ አዋጋ።
- አመናቸከ፡ አጨቃጨቀ/አነዛነዘ።
- አመናነን፡ አናናቅ፡ መመነን።
- አመናኘ፡ አስተዳደለ፡ ናኘ።
- አመናኘ፡ አስተዳደለ/አቀባበለ።
- አመናዘረ፡ አባተነ/አሻረፈ/አላወጠ።
- አመናደበ፡ አማታ/አቋረጠ።
- አመናጐለ፡ መጥፎ ነገር አናገረ/አነኋረጠ።
- አመናጠረ፡ አጣረገ/ኣስተጫጨደ።
- አመናጠቀ፡ አናጠቀ/አቃማ።
- አመናጨረ፡ አባተነ።
- አመናጨቀ፡ አመናቸከ/አጨቃጨቀ/አነዛነዘ።
- አመንማኝ፡ ያመነመነ/የሚያመነምን (አቅጣኝ/አሰልሳይ/ሳል) ።
- አመንሺዋ፡ የሰው፡ ስም፡ ሺዋ፡ አመነ፡ ማለት፡ነው።
- አመንቺ፡ ያመነታ/የሚያመነታ (ያዝ) ።
- አመንኳሽ (ሾች)፡ ያመነኰሰ/የሚያመነኵስ (ቆሞስ/ጳጳስ) ።
- አመንኳሽነት፡ አመንኳሽ መኾን።
- አመንዛሪ፡ ያመነዘረ/የሚያመነዝር።
- አመንዝራ (ሮች)፡ ሸርሙጣ/ቅንዝረኛ/ዘማዊ/ሴሰኛ/ጋለሞታ (ማቴ. ፭፥፴፪) ። በግእዝ መንዚር (መንዚራን) ይባላል።
- አመንዝራነት፡ አመንዝራ መኾን (ሴሰኝነት) ።
- አመንዝራው (ዋ/ዪቱ/ቷ)፡ ያ ኣመንዝራ (ኤር. ፫፥፯) ።
- አመንዣኺ፡ ያመነዠ/የሚያመነዥኸ (አመስኲ) ።
- አመንጪ፡ ያመነጩ/የሚያመነጭ (አፍላቂ) ።
- አመኛኘ፡ አከጃጀለ።
- አመከመከ፡ መከመከ።
- አመከመከ፡ በቀላል ፈተለ፡ መከመከ ።
- አመከረ፡ በራብና በጥም ብዛት በምንዳቤ ሰውነቱን ፈተነ/ጐዳ።
- አመከነ፡ መውለድ ከለከለ፡ ዘር አሳጣ፡ መካን አደረገ፡ ማሕፀን ዘጋ።
- አመከነ፡ ኮሶን ከሆድ አጠፋ።
- አመከኛኘ፡ ስሕተቱ/ጥፋቱ የኔ አይደለም ያንተ ነው አባባለ።
- አመከኛኘት፡ አሰባበብ፡ ማመካኘት።
- አመከዝ፡ ከገሣ፡ የተሠራ፡ የመናኞች፡ ልብስ ።
- አመካመክ፡ አለሳለስ፡ መመክመክ።
- አመካሪ፡ ያመከረ/የሚያመክር፡ ረድ ጥቍር ራስ፡ ራሱን የሚፈትን።
- አመካኘ ምክንያት፡ ሰጠ፡ (መከኘ) ።
- አመካከረ፡ ምክር አዋጣ/አለዋወጠ/አቀባበለ፡ እንዲህ ይኹን/ይደረግ አባባለ።
- አመካከር፡ የምክር አሰጣጥ፡ መምከር።
- አመካከተ፡ አቀያየደ፡ አገራረደ።
- አመካከቴ፡ እንደ ወንድ፡ አጨካከኔ እንደ ሴት፡ አፈጣጠኔ እንደ ጕንዳን (ግራኝ) ።
- አመካከት፡ አከላለል፡ መመከት።
- አመካከን፡ ዝኒ ከማሁ፡ መምከን።
- አመዘበረ፡ መዘበረ።
- አመዘባበር፡ አፈራረስ፡ መመዝበር።
- አመዘነ፡ ወዳንድ፡ ፊት፡ ደፋ፡ መነዘለ፡ ኣጋደለ።
- አመዘነ፡ የወንድ፡ መጠሪያ፡ ስም።
- አመዘነች፡ የሴት፡ መጠሪያ፡ ስም።
- አመዛመዘ፡ ዐሰበ፡ ገመተ፡ አወጣ፡ እወረደ፡ ነገርን፡ መዘነ፡ (አድራጊ) ።
- አመዛመዘ፡ አተላተለ' አተራተረ፡ አራዘመ፡ (አደራራጊ)
- አመዛመዝ፡ ኣመዛዘዝ፡ መመዝመዝ።
- አመዛኝ፡ ያመዘነ፡ የሚያመዝን፡ አጋዳይ ።
- አመዛዘነ፡ አለካካ፡ አሰፋፈረ፡ ግራና፡ ቀኙን፡ አስተካከለ።
- አመዛዘን፡ አለካክ፡ መመዘን።
- አመዛዘዘ፡ አነቃቀለ።
- አመዛዘዝ፡ አሳሳብ፡ አነቃቀል፡ መም
- አመዛዛኝ፣ ያመዛዘነ፡ የሚያመዛዝን፡ ትክክለኛ፡ ዳኛ፡ አመዛዛኙ፡ ጌታ፡ እንዲሉ።
- አመዠራረጥ፡ አነቃቀል፡ መመዥረጥ ።
- አመያ፡ ያገር፡ ስም፡ በጨቦ፡ ውስጥ፡ ያለ፡ አገር ።
- አመደ፡ ዐመድ፡ አደረገ፡ ዐመደ።
- አመዳመድ፡ አቈራረጥ፡ መመድመድ።
- አመድ፡ በቁሙ፡ ዐመደ ።
- አመጃ አምጃ -የንጨት፡ ስም፡ ዐመጃ ።
- አመገ፡ መሰገ፡ ዐመፃ ።
- አመገለ፡ በኹለት፡ ጣቱ፡ ይዞ፡ አፈረጠ፡ ኣወጣ፡ ኣፈሰሰ፡ መግልን ።
- አመጋመግ፡ አጠባብ፡ መመግመግ።
- አመጋገለ፡ አፈራረጠ፡ አድፈጠፈጠ።
- አመጋገል፡ አፈራረጥ፡ መምገል። (ጥግ)ምግል፡ በተጕለት፡ ክፍል፡ ያለ፡ ቀበሌ ።
- አመጋገዝ፡ አገዛገዝ፡ መመገዝ።
- አመጋገድ፡ አጨማመር፡ መማገድ።
- አመጋገጥ፡ ኣወሰላለት፡ መማገጥ።
- አመጠ፡ በደለ፡ ዐመጠ ።
- አመጠቀ፡ አረዘመ።
- አመጠዋወት፡ አመጸዋወት፡ የምጧት፡ አሰጣጥ፡ መመጥወት ።
- አመጠጠ፡ አደረቀ፡ ርጥበትን፡ አራቀ፡ ተመተመ፡ የውስጡን፡ ወደ፡ ላይ፡ የላዩን፡ ወደ፡ ውስጥ፡ አደረገ፡ የንፍሮ።
- አመጠጠ፡ አጠባ።
- አመጠጠ፡ ጠማ፡ (ጸምአ)።
- አመጣ አተረፈ - "ተረት - ኹሉ ወረሰ ማ...ይሸምት") ።
- አመጣ፡ አጋዘ፡ አደረሰ፡ አቀረበ፡ ("ኢሳ. ፯፡ ፲፯") ።
- አመጣሽ፡ ያመጣሽ፡ ያመጣው። ዘመን፡ አመጣሽ፡ እንዲሉ።
- አመጣደቀ፡ አመጻደቀ ።
- አመጣዳቂ፡ አመጻዳቂ ።
- አመጣጠነ፡ አለካካ፡ አመዛዘነ።
- አመጣጠን፡ አለካክ፡ መመጠን።
- አመጣጠጥ፡ አጠጣጥ፡ መምጠጥ ።
- አመጣጣ፡ መላልሶ፡ አመጣ፡ አቀራረበ ።
- አመጣጣ፡ አያያዘ፡ አሸካከመ።
- አመጣጥ፡ አረማመድ፡ መምጣት።
- አመጨመጪ፡ አጨመጨመ ወመን፡ እይ።
- አመጻደቀ፡ ገበዘ ራሱን አመሰገነ ሌላውን አመሳገነ ። "አዎን እከሌን የሚያኸለው የሚመስለው የለም" ኣባባለ ።
- አመጻዳቂ፡ ያመጻደቀ/የሚያመጻድቅ (አ መስጋኝ አመሳጋኝ ") ።
- አሙለጨለጨ የማይጨበጥ፡ አደረገ፡ ለወለወ ።
- አሙለጨለጫ፡ የማይጨበጥ/የማይረገጥ አደረገ፡ እግርን መልሶ መላልሶ አንሸራተተ።
- አሙስ፡ ፭ኛ፡ ቀን፡ ዐመሰ፡ ዐሙስ ።
- አሙኝት (ቶች)፡ ዔሊ (ደንጊያ ለብሳ አይታዋን የምታሞኝ) ።
- አሙኝት፡ -ክረምት፡ አፈራሽ፡ -(ሞኘ)።
- አሙኝት፡ ወስፋት የሚመስል የምድር ተንቀሳቃሽ (ክረምት አፈራሽ የሕፃናት ማሞኛ/ማስፈራሪያ) ።
- አሙካ፡ ሞራ ከከ ።
- አሙካ፡ በሰው ራስ ላይ ብዙ ጊዜ የተላከከ ቅቤ፡ ዕጥበት ያልነካው እድፍ። በድስትና በማሰሮ ውስጥ የደገደገ ቅባት ሞራ።
- አሙካ፡ ጸያፍ፡ እንደ አሙካ የሚያጸይፍ መጥፎ ንግግር።
- አሚ፡ ያ የሚያሻማ (አቅላጭ) ።
- አሚ፡ ያ የሚያሻማ (አቅላጭ) ።
- አሚን፡ (ኖች)፡ አማኝ፡ እሙን፡ የታመነ፡ ምስክር፡ (ራእ፫፡ ፲፬) ።አሚንኸን፡ ቍጠር፡ እንዲሉ።
- አሚን፡ ማመን፡ ሃይማኖት፡ ሕግ። ያሚን፡ ባል፡ ያሚን፡ ሚስት፡ እንዲሉ።
- አሚዛ፡ እንጀራ፡ ዐሚዛ ።
- አማ፡ አቀለጠ (ውሃ አደረገ) ።
- አማ፡ አቀለጠ (ውሃ አደረገ) ።
- አማለ (አምሐለ)፡ ስመ እግዚሐር አስጠራ፡ በሰሌን ገንዞ ጐተተ፡ "ያጥፋኝ/እያኑረኝ" አሠኘ (፪ዜና. ፴፯፥፲፫፡ ዕዝ. ፲፥፭) ።
- አማለለ (ኣማሕለለ)፡ አስረሳ/አዘነጋ/አሠየ/አጐመዠ። "ዛሬ ማታ ጨዋታ አማለለኝና ቶሎ ሳልመጣ ቀረኹ"።
- አማለለ፡ አላመነ/አጻለየ።
- አማለለ፡ አራዘመ፡ ኣንዛዛ።
- አማለሰ፡ ወደ ነበረበት ኣማጣ/አዋሰደ (ከብትን/ሌላ ነገርን) ።
- አማለደ፡ የጐደለውን መልቶ/የጠመመውን አቅንቶ "እንዲህ ቢኾን እንዲህ ነው" ብሎ ከጣጣ/ከዕዳ አዳነ፡ አሰማማ/አስታረቀ።
- አማለደ፡ ጧት አገሠገሠ/አመጣ/ሠራ።
- አማለገ፡ ኣማገጠ፡ ሥራ አስፈታ፡ አለ።
- አማለጠ፡ አቋረጠ/አስተላለፈ፡ ጣልቃ አግብቶ ሠራ።
- አማለጠ፡ ኣናጪ/አፋተግ/አቃረፈ።
- አማላ፡ አላ፡ አራጩ፡ አመረ፡ ትክክል አደረገ/አስተካከለ/አደላደለ።
- አማላይ፡ ያማለለ/የሚያማልል (አዘንጊ ጠጅ) ።
- አማላጅ (ጆች)፡ ያማለደ/የሚያማልድ፡ የነፍስ/የሥጋ አስታራቂ፡ መካከለኛ፡ ዘመድ/ወዳጅ (ኢየሱስ ክርስቶስ - ፩ዮሐ. ፪፥፩)፡ ማርያም/ነቢያት/ሐዋርያት/ጻድቃን/ሰማዕታት/መላእክት።
- አማላጅነት፡ አማላጅ መሆን፡ አስታራቂነት።
- አማላጭ፡ ያማለጠ/የሚያማልጥ።
- አማልቶ ሰጠው፡ ዕውቀትን/ሀብትን/መውለድን/ጤንነትን/ዕድሜን ባንድነት ዐደለው።
- አማልቶ፡ አስተካክሎ፡ አደላድሎ።
- አማመዘ፡ አሖመጠጠ/አሸመጠረ።
- አማመዘ፡ አሖመጠጠ/አሸመጠረ።
- አማሚ፡ ያመመ፡ የሚያምም፡ የሚያንት፡ የሚቀድም ፣ቀዳሚ ።
- አማሚነት፡ ቀዳሚነት፡ ዠማሪነት።
- አማማለ (አስተማሐለ)፡ ማላ እከፋፈለ/አመላለሰ/አገዛዘተ።
- አማማል፡ ራስን አረጋገም፡ መማል።
- አማማስ፡ አቈፋፈር፡ መማስ።
- አማማይ፡ ያማማለ/የሚያማምል፡ አገዛዛች።
- አማማግ፡ አጠጣጥ፡ መማግ፡ ማማግ።
- አማማጠ፡ ምጥን፡ ረዳ፡ የወላድን፡ ወገብ፡ ያዘ፡ ዐብሮ፡ ተጨነቀ፡ ማሪያም፡ ማሪያም፡ አለ፡ አዋለደ ።እከሌ፡ ዛር፡ ስቶልድ፡ ቢያይ፡ ያማምጣል፡ እንዲሉ።
- አማማጥ፡ አጨናነቅ፡ ማማጥ።
- አማማጭ፡ ያማማጠ፡ የሚያማምጥ፡ አዋላጅ፡ ሐኪም።
- አማሰለ፡ አገላበጠ/አቀላቀለ/አደባለቀ/አዋሐደ (አንድ አደረገ - ዐረረንን ተመልከት) ።
- አማሰነ፡ አለፋ/አደከመ/አጠፋ (ጕልበትን/ስምን በከንቱ) ።
- አማሳኝ፡ ያማሰነ/የሚያማስን (አልፊ/አድካሚ/አጥፊ - "አመስጋኝ አማሳኝ" እንዲሉ) ።
- አማሳይ (ዮች)፡ ያማሰለ/የሚያማስል) ።
- አማረ ፣ አማረች፡ የወንድና፡ የሴት፡ ስም ።
- አማረ፡ (አደመ፡ ሠነየ፡ ቀደወ)በቁሙ፡ ተዋበ፡ በጀ፡ ሸገነ፡ ቈነዠ፡ ሰመረ፡ ተወደደ፡ ደስ፡ አሠኘ፡ ውል፡ አለ፡ (አስ፪፡ ፬ ።መዝ፻፮፡ ፲፬ ።ዳን፩፡ ፲፭) ። (ተረት)፡ ልፋት፡ ቢያምርኸ፡ መሬት፡ ግዛ፡ ችግር፡ ቢያምርኸ፡ ልጅ፡ ኣብዛ " ያምራል፡ ብሎ፡ ከመናገር፡ አያምርም፡ ብሎ፡ መተው። ያምሯል፡ ይታደሏል። ደመቀን፡ እይ ።
- አማረ (አጽሐረ፡ አፅረረ)፡ ጦር
- አማረ፡ መራ/እዞረ/ጠመዘዘ/ቀለሰ። ሥሩ መወረ ነው።
- አማረረ፡ ማሩን ከመራራ አመሳሰለ/አ—።
- አማረረ፡ ዐማ/ወቀሡ/አሳጣ።
- አማረረ፡ አቋጣ/አጣላ።
- አማረቀ፡ አባረከ ("ምሩቅ ኹን" አባለ) ።
- አማረተ፡ ላይዳ አባባለ/አራገበ።
- አማረነ፡ አስተሳሰረ/አጠማጠመ።
- አማረከ/አመራረከ፡ አያያዘ/አማለሰ ምርኮን።
- አማረገ፡ አላጠፈ።
- አማረጠ/አመራረጠ፡ አሻሻለ/አመላመለ።
- አማሪ፡ አሽሙር/ጠምዛዥ።
- አማሪ፡ ያማረ፡ የሚያምር።
- አማሪት፡ (ቶች)፡ የምታመለክት፡ የምታምር፡ የከበሮ፡ ቂጥ፡ መኰርኰሪያ፡ ድምፀ- ቀጪን፡ የበገና፡ ዥማት፡ አንዲቱ ።
- አማሪት፡ ዘፋኝ፡ ቀንቃኝ፡ አረኾ ።አማሪት፡ ገንቦኛ፡ እንዲሉ።
- አማራ፡ (ሠነየ)፡ ነገሩ፡ እንዲህ፡ ከኾነማ፡ አማራ " አማረና፡ ዐማራ፡ ባማርኛ፡ ሲገጥሙ፡ የት፡ ገደልክ፡ አንጎለላ፡ እንግዲያው፡ ኣማራ። በልቼ፡ መጣኹ፡ ከስላም፡ ጋራ፡ እንግዴህ፡ ምኔ፡ አማራ ።
- አማራ፡ ምራትን አዚያዚያመ።
- አማራ፡ ሰውንና ውሃን ኣዋሰደ።
- አማራ፡ ነጻ፡ ሕዝብ፡ ዐማራ።
- አማራሪ፡ ያማረ/የሚያማርር (ወቃሽ/አሳጣው) ።
- አማራች፡ ያማረተ/የሚያማርት።
- አማራጊ፡ ያማረገ/የሚያማርግ (የምርግ ረዳት) ።
- አማራጭ/አመራራጭ፡ ያማረጠ/የሚያማርጥ (አመላማይ) ።
- አማሬ፤ስንዴ፡ ዐማሬ።
- አማሮ አገር፡ ዐማሮ።
- አማሸ፡ ጨርሶ እስኪመሽ አጫወተ/አነጋገረ።
- አማቀቀ፡ አለፋ/አከሳ/ማቅ አለበሰ።
- አማቃቂ፡ ያማቀቀ/የሚያማቅቅ (ኣልፊ) ።
- አማቄጦ፡ ማገጥ፡ ማገጠ ።
- አማተ፡ አጋደለ፡ አገዳደለ፡ አስተላለቀ።
- አማተበ (አማዕተበ)፡ ጣቱን አመሳ ቅሎ በመስቀል ምልክት ፊቱን ባረከ (ሰይ ጣንን ለማራቅ ለመጸለይ - በስመ አብ ወወ ልድ ወመንፈስ ቅዱስ አለ ") ።
- አማተበ ፊቱን፡ ባረከ፡ ዐተበ።
- አማታ፡ አማጣ ዕመምን (አጋረፈ በሶው ተልባው ቅመሙ እንኵሮው) ።
- አማታ፡ አባባለ/አጋጩ/አደባደበ (አንቦጫረቀ/አበጣበጠ) ።
- አማታቢ፡ ያማተበ/የሚያማትብ (የሚባ ርክ - ባራኪ ") ።
- አማት የሚስት፡ አባትና፡ እናት፤ዐማት ።
- አማት -የባል፡ አባትና፡ እናት፡ -ዐማት ።
- አማቺ፡ ያማታ/የሚያማታ።
- አማች የልጅ፡ ባል፡ ዐማች።
- አማነነ፡ አቀጠነ (ቀጪን ፈተለ) ።
- አማናዊ፡ እውነተኛ፡ ርግጠኛ፡ መደበኛ፡ ዋና፡ ደገኛ፣ ከምሳሌነት፡ የራቀ።
- አማን፡ በአማን፡ እውነት፡ በውነት።
- አማን፡ እውነት፡ ደኅና፡ ሰላም፡ ጸጥታ፡ አገር፡ አማን፡ ኾነ ።ሤራን፡ ተመልከት ።
- አማን፡ የራስ፡ ጐበና፡ ከተማ። (ቅኔ)፡ ወንጌል፡ ጐበና፡ በአማን፡ ቅዱስ፡ (ደብተራ፡ ሀብተ፡ ወልድ፡ የወይራ፡ ዐምባው)። (ግጥም)፡ ይታመሳል፡ አሉ፡ ከፋና፡ ቦረና፡ አማን፡ አይደሉም፡ ወይ፡ እነራስ፡ ጐበና ።መዠመሪያውን፡ አማን፡ እይ ።
- አማኝ፡ (አማኒ)፡ ያመነ፡ የሚያምን፡ የሚወድ፡ የሚወክል፡ እውነተኛ።
- አማኞች፡ ያመኑ፡ የሚያምኑ፡ ወንዶችና፡ ሴቶች ።
- አማከለ፡ (ኣማእከለ)፡ ከበበ፡ እመኻል አገባ ።
- አማከለ፡ በመካከል፡ አደረገ፡ አከለ ።
- አማከለች፡ (አማእከለት)፡ የሴት ስም ።
- አማከለው፡ (አማእከሎ)፡ የሰው ስም፡ በባባቱ ግራ የሚቀመጥ ኹለተኛ ልጅ፡ አባቱን ከታላቅ ወንድሙ ጋራ የሚያማክር ።
- አማከረ፡ ምክር ጠየቀ፡ አወጣ፡ አካፈለ፡ ምን ይሻላል አለ (መከረ) ።
- አማከረ፡ አፋተነ፡ አዣመረ፡ አባባለ።
- አማከተ፡ አቃየደ፡ አካለለ።
- አማካሪ (ሮች)፡ ያማከረ/የሚያማክር (መካሪ) ።
- አማካሪነት፡ አማካሪ መሆን።
- አማካይ፡ (አማኻይ)፡ መካከል የሚያደርግ፡ የቀንበር መኻል ምራን ያ ።
- አማካይነት፡ ከባቢነት፡ በውስጥ ማድረግ ፥ ግራ ቀኝ መቀመጥ ፥ መገኘት ። መካከለኛነት በማለት ፈንታ ኣማካይነት ማለት ስሕተት ነው ።
- አማኰተ ተስፋ፡ ሰጠ (aqኰተ)።
- አማኳች፡ ያማኰተ/የሚያማኵት።
- አማወቀ፡ አመዋወቀ፡ አቀ። ጌታችን፡ በተወለደ፡ ጊዜ፡ አህያና፡ ላም፡ በትንፋሻቸው፡ አማወቁት።
- አማዘነ፡ አላካ፡ አሳፈረ፡ አማጠነ።
- አማዘዘ፡ አሳሳበ፡ አጓተተ፡ አናቀለ።
- አማዛኝ፡ ያማዘነ፡ የሚያማዝን።
- አማዛዥ፡ ያማዘዘ፡ የሚያማዝዝ።
- አማገ፡ ምግብን፡ በመጠጥ፡ አወረደ።
- አማገ፡ በመጠጥ፡ ዋጠ፡ ማገ ።
- አማገ፡ ኹለት፡ አደረገ፡ ማግ፡ ፈተለ፡
- አማገ، መልሶ፡ ሰደበ። ብታደራልኝ፡ አማግኹልኸ፡ እንዲል፡ ባላገር ።
- አማገዘ፡ አገዛገዘ፡ አከራከረ፡ አከራከመ፡
- አማገደ፡ ማጋጅ፡ አደረገ፡ ዕንጨቱ፡ ሰውየውን ።ይህ፡ ፍልጥ፡ ብዙ፡ ቀን፡ ያማግደኛል፡ (ማገዶ፡ ይኾነኛል)
- አማገጠ፡ ሥራ፡ አስፈታ፡ ከንቱ፡ ጨዋታ፡ አጫወተ፡ አወሰለተ፡ አመንዝራ፡ አደረገ ።
- አማጊጦ፡ (አማቄጦ)፡ የማገጥ፡ ዐይነት፡ ቅጠል፡ በክፉ፡ ቀን፡ ፍሬው፡ የተበላ፡ ቅጠልነቱ፡ ዋዥማ፡ ቅንጣቱ፡ አብሽ፡ ይመስላል ።
- አማጋጭ፡ ያማገጠ፡ የሚያማግጥ፡ አወስላች።
- አማጠ፡ ዕሕ፡ አለ፡ ከሆድ፡ ውስጥ፡ ወደ፡ ውጭ፡ ገፋ፡ ("ኢሳ. ፲፫፡ ፰፡ ፷፮፡ ፰") ።
- አማጠነ (አማሕፀነ)፡ በግዜር በማ ሪያም ይዤኻለኹ (በንጉሥ አምላክ አለ - አ ዳኘ ከለከለ አረዳ - ዘፍ. ፵፪፥፳፩ - በግእዝ ግን ዐደራ ሰጠ ማለት ነው ") ።
- አማጠነ፡ ሙትን ገዘተ (ጠራ - ፩ሳሙ. ፳፰፥፯) ። "አከለ/ዐተበ" ብለሽ "አማከለንና አማ ተበን" እይ ("አካኼዳቸው ከዚህ ጋራ አንድ ነው ") ።
- አማጠነ፡ አዳኘ፡ ዐጠነ ።
- አማጠነ፡ ኣላካ፡ አማዘነ።
- አማጠጠ፡ ውሃን፡ አሻማ፡ አለጠ።
- አማጣ፡ አጋጋዘ፡ አስተ፵ጨ፡ (አግባት፡ አግቢው፡ ማለፊያ፡ ነው፡ ማለፊያ፡ ናት፡ አለ)፡ አጋባ።
- አማጣኝ (ኞች)፡ ያማጠነ/የሚያማ ጥን (ገዛች ጠሪ - ፪ዜና. ፴፫፥፮ - "ሙት አ ማጣኝ" እንዲሉ) ።
- አማጣጭ፡ ያማጠጠ፡ የሚያማጥጥ፡ የውሃ፡ ዕላቂ፡ አጣጪ።
- አማጪ፡ ጭ፡ ያማጣ፡ የሚያማጣ፡ የጋብቻ፡ መካከለኛ፡ ክፉና፡ ደግ። አማጪን፡ መጦር፡ አማጪን፡ በጦር። አማጭ፡ ረማጭ፡ እንዲሉ።
- አማጪም፡ አሳሳም/አመጋገር ("መ ጨምጪም") ።
- አማጭ፡ ያማጠ፡ የሚያምጥ።
- አሜሪካ፡ እንደ፡ ፈረንጅ፡ አቈጣጠር፡ ባ፲፬፻፺፪፡ ዓ፡ ም፡ የተገኘ፡ ዐዲስ፡ ዓለም ።
- አሜራ፡ ለንቅሳት፡ የሚኾን፡ ያረግ፡ ቀለም፡ የእጅና፡ ያንገት፡ ማሳመሪያ፡ መሸለሚያ፡ ምልክት፡ ማድረጊያ ።
- አሜን፡ እውነት። ይኹን፡ ይደረግ።
- አምኃ ፣(አምኆ፡ አምኀ)፡ የሰው፡ ስም፡ እጅ፡ መንሻ፡ ገጸ፡ በረከት፡ ማለት፡ ነው ። ዘርፍ፡ ይዞ፡ ሲነገር፡ አምኃየስ፡ አምኃ፡ ጊዮርጊስ፡ ይላል ።
- አምለገለገ፡ አሙለጨለጨ፡ መለገ።
- አምለገለገ፡ አሙለጨለጩ።
- አምለግላጊ፡ ያምለገለገ/የሚያምለገልግ።
- አምላከ ሐሰት፡ እውነት የሌለበት ጣዖት/ሰይጣን (የአሕዛብ አምላክ ከወርቅና ከብር ተሠርቶ በሐሰት የሚመለክ) ።
- አምላከ ጽድቅ፡ ሐሰት የሌለበት የውነት አምላክ (ክረምትንና በጋን/ሌሊትንና መዓልትን/ፀሓይንና ጨረቃን የሚያፈራርቅ፡ ክፉ ቢሠሩ ፍዳ፥ ደግ ቢሠሩ ዋጋ የሚሰጥ) ።
- አምላኪ፡ ያመለከ/የሚያመልክ (አማኝ) ።
- አምላኬ (አምላኪየ)፡ የማሽላ ስም ("የኔ አምላክ" ማለት ነው) ።
- አምላክ፡ እግዚአብሔር (ሰማይንና ምድርን ፈጥሮ የሚገዛ፡ ፍጡር ኹሉ እሱን የሚያመልከውና ለሱ የሚሰግድ) ። (ና በንጉሥ በኀይለ ሥላሴ አምላክ አለ)፡ ከሰሰ/አማጠነ።
- አምላክ፡ ጠባቂ። "ላይን አምላክ አለው" እንዲሉ።
- አምላክ፡ ፈጣሪ፡ መለከ ።
- አምላክነት፡ አምላክ መሆን/ፈጣሪነት። "ለሰው ብሎ መሞት አምላክነት ያሻል" እንዲሉ። (በአምላክነቱ)፡ አምላክ በመኾኑ/በመለኮቱ።
- አምላክና ሰው (አምላክ ወሰብእ)፡ ኢየሱስ ክርስቶስ (ፈጣሪና ፍጡር) ።
- አምላኮች (አማልክት)፡ ካህናት/ዳኞች (መዝ. ፹፪፥፩, ፮)፡ ጣዖቶች/ምስሎች።
- አምላጭ፡ ያመለጠ/የሚያመልጥ።
- አምሌ፡ የወር፡ ስም፡ ዐምሌ።
- አምልማሎ (ዎች)፡ የተሸበለለ/የተጠቀለለ ንድፍ (የጥጥ ነዶ ድር የሚኾን) (ምሳ. ፴፩፥፲፱) ።
- አምልማሎ የተሸበለለ፡ ንድፍ፡ መለመለ።
- አምልኮ፡ ማምለክ፡ መለከ።
- አምልኮ ባዕድ፡ ጣዖትን/ምስልን/ማንኛውንም ፍጡር ማምለክ። ቡሓ/ነጭ/ቀይ በግ፡ ገብስማ ወሰራ ዶሮ ማረድ፡ ለቃልቻ መታዘዝ/ለሰይጣን መገበር። አምልኮ ባዕድን ለማጥፋት ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የመቤታችንን ልደት ግንቦት ፩ ቀን አደረገው።
- አምልኮ/ማምለክ፡ ሃይማኖት።
- አምልኮኛ፡ ባለአምልኮ/ሃይማኖተኛ (ያዕ. ፩፥፳፮) ።
- አምሳ፡ ዐምስት፡ ዐሥር፡ -0 መሰ፣ ዐምሳ።
- አምስት፡ በቁሙ፡ ዐመሰ፡ ዐምስት ። (ግእዝ)
- አምራሪ፡ ያመረረ/የሚያመር (ቍጡ) ።
- አምራች፡ ያመረተ/የሚያመርት (ዐራሽ ገበሬ) ።
- አምሮ፡ (ትግ፡ ሐባ፡ አምር)፡ ዕውቀት፡ ፈሊጥ፡ ማስተዋል። ባምሮ፡ ቃል፡ ተናገረ፡ እንዲል፡ ባላገር። አምሮ፡ አጊጦ፡ ተሽኰንትሮ። ኣምሮት፡ ማማር፡ ውልታ፡ ፈቃድ፡ ውድ፡ ውዴታ፡ ጕምዠታ፡ ሥየታ፡ (ኤር፲፪፡ ፲) ። (ተረት)፡ እንግዴህ፡ ለርጥ፡ ኣምሮቴ፡ ቍርጥ ።አምሮት፡ ውል፡ ብሎት ።
- አምሸከሸከ፡ በጣጠሰ/ቈራረጠ/ሰበረ።
- አምበላይ ባለጥሩር፡ ዐምበላይ ።
- አምበል -የጭፍራ፡ አለቃ፡ ዐምበል ።
- አምበልጋ፡ ፈሪ፡ አንበልጋ ።
- አምበር፡ ሽቱ፡ ዐምበር ።
- አምባ መንደር፡ ዐምባ ።
- አምባላ፡ ነጭ፡ ወፍ፡ ዐምባላ ።
- አምባላይ፡ ነጭ፡ ፈረስ፡ ዐምባላይ ።
- አምባር፡ ማልደያ፡ ፡ ነበረ ።
- አምባሻ - የትግሬ፡ ኅብስት -አንባሻ ።
- አምባቀቀ አፉን፡ ከፈተ፡ በቀቀ፡ አንባቀቀ ።
- አምባት፡ ዐምቦች፡ ዐምባ ።
- አምባዛ፡ ዓሣ፡ ነበዘ ።
- አምቦ፡ ጪው፡ ጨው፡ የሚል፡ ዐፈር፡ ዐምቦ ።
- አምቧተረ -አንገራበደ (ቧተረ)፡ አንቧተረ ።
- አምታታ፡ አፋጀ/አሸበረ/በጠበጠ።
- አምታቴ፡ የሰው ስም።
- አምታቺ፡ ያምታታ/የሚያምታታ (አሸባሪ/በጥባጭ) ።
- አምነሸነሸ አስጌጠ፡ (መነሸ)።
- አምነሸነሸ፡ አስጌጠ፡ ደስ አሠኘ፡ አሽሞነሞነ/አሽኰነተረ።
- አምና፡ (አሚና)፡ ተቀብላ ' ወዳ ።የጻድቅ፡ ነፍስ፡ ክርስቶስን፡ አምና፡ ዐረፈች።
- አምና፡ ያለፈ ዓመት፡ ዓምና ።
- አምኜ፡ (አሚንየ)፡ የስንዴ፡ ስም፡ እንደ፡ ሽንብራ፡ በመስከረም፡ ዝናም፡ ካለፈ፡ በዋና፡ ደጋ፡ መረሬ፡ የሚዘራ፡ ስንዴ። ጠቀመ፡ ብለኸ፡ ጠቀምሽኝን፡ እይ ።
- አምካኝ፡ ያመከነ/የሚያመክን።
- አምዘገዘገ አቅዘመዘመ፡ -መዘገ ።
- አምዘገዘገ፡ ኣውዘገዘገ፡ ኣንዘገዘገ፡ እመዘጋ፡ ጣለ።
- አምድ ምሰሶ፡ ዐመደ ።
- አምጃር፡ (ነገረ፡ አንገረ፡ አንጋር)፡ ያቡን፡ አነጋጋሪ፡ ትርጁማን ።
- አምጃርነት፡ አስተርጓሚነት ። ምና፡ ን፡ ጃና፡ ጋ፡ እንደ፡ ተወራረሱ፡ አስተውል ።
- አምጃሮች፡ አነጋጋሪዎች፡ ትርጁማኖች ።
- አምጋይ፡ ያመገለ፡ የሚያመግል፡ አፍራጭ፡ ጨካኝ፡ ሰው፡ ሾኽ ።
- አምጣ፡ አታምጣ፡ የጠብ፡ ንግግርና፡ መልስ። አምጣዕሺ በልአታምጣ እንቢበል፡ አቅርብ፡ አታቅርብ።
- አምጣ፡ ወዲህ፡ በል፡ አቅርብ።
- አምጣጭ፡ ያመጠጠ፡ የሚያመጥ።
- አምጪ፡ ለቅርብ፡ ሴት፡ ትእዛዝ፡ አንቀጽ ።
- አምጪ፡ ያመጣ፡ የሚያመጣ፡ አቅራቢ። ላምጪ፡ ይግደደው፡ እንዲሉ።
- አሞለለ፡ ሞላላ አደረገ (ክብነትን ነሣ/አራቀ) ።
- አሞለሞለ፡ አከበበ፡ ሞለሞለ።
- አሞለሞለ፡ አከበበ/ክብ አደረገ፡ ሙልሙል ጋገረ።
- አሞለሞለ፡ ኣሳበጠ። ልማዱ ግን ዐበጠ ነው።
- አሞለቃቀቅ፡ ኣቀመጣጠል፡ ማሞላቀቅ።
- አሞለጪ (ሞለጩ)፡ ሳይታወቅ ሰረቀ/አወጣ።
- አሞለፋፈጥ፡ ሥራ አፈታት መሞላፈጥ።
- አሞላ፡ አደገ፡ አካለ መጠን አደረሰ (ድልድል ኾነ)
- አሞላሞል፡ የሙልሙል አገጋገር፡ ማሞልሞል ።
- አሞላቀቀ፡ አናቀለ/አጋፈፈ።
- አሞላቀቀ፡ አንደላቀቀ/አቀማጠለ/አንቀባረረ (አባለገ
- አሞላቀቀ፤አንደላቀቀ -ሞለቀቀ።
- አሞላጀጀ፡ አንሰዋለለ።
- አሞላፈጠ፡ አሞዣለጠ።
- አሞሌ (ዎች)፡ ሞላላነት ያለው ጨው (የተጠረበ/የተቀረጸ) ። (ተረት)፡ "ጌታ ለሎሌው፡ ነጋዴ ለአሞሌው"።
- አሞሌ መሣ፡ "አሞሌ በነሣ ባነሣ" ማለት ነው፡ መሣን እይ።
- አሞሌ፡ በቁሙ፡ ሞለለ ።
- አሞልይ፡ ያሞለሞለ/የሚያሞለሙል (ሙልሙል ጋጋሪ) ።
- አሞራ፡ (ሮች)፡ በቂሙ፡ ባየር፡ ዟሪ፡ ቍልቍል፡ ተወርዋሪ፡ ቅልጥም፡ ሰባሪ፡ በዛፍ፡ በገደል፡ ላይ፡ ዐዳሪ፡ የነፋስ- ቋትለኛ፡ የአየር፡ ዋነተኛ፡ ንስር፡ የሎስ፡ ጐሢ፡ ጥንበ፡ በላ፡ ማንኛውም፡ ኹሉ፡ (ኤር ፴፬፡ ፲፭)። አሞራውም፡ በረረ፡ ቅሉም፡ ተሰበረ፡ እንዲሉ ።ያሞራ፡ ትርጓሜ፡ አመልካች፡ ተመልካች፡ ማለት፡ ይመስላል ። (ዘማች፡ አሞራ)፡ ሰው፡ ሲሞት፡ ለመብላት፡ ዐይን፡ ለመጥቃት፡ ከጦር፡ ሰራዊት፡ ጋራ፡ ዐብሮ፡ የሚዘምት ።አሞራ፡ ባማርኛ፡ ንስር፡ በግእዝ፡ የወል፡ ስሞች፡ ናቸው ።
- አሞራረተ፡ ርትን አወጣጣ/አጠነቋቈለ።
- አሞራረት፡ አጠነቋቈል፡ ማረት።
- አሞራረድ፡ አዘራዘር፡ መሞረድ። "ሞረደ" ከመረደም ሊወጣ ይችላል።
- አሞሸ ቈዘመ፡ ፡ (ሞሸ) ።
- አሞሸላለቅ፡ አገፋፈፍ፡ መሞሽለቅ።
- አሞሻሸር፡ አሸፋፈን/አመጋገብ፡ መሞሸር።
- አሞቀ አተኰሰ አ ወዛ ("ላብ አወጣ አፈሰሰ ") ።
- አሞቀላለል፡ አረዛዘም፡ መሞቃለል/ማሞቃለል ለመለመ።
- አሞቀሞቀ፡ ሙቅ አስመሰለ።
- አሞቃለለ -አረዘመ -(ሞቀለለ) ።
- አሞቃለለ፡ አረዘመ (አራዘመ) ።
- አሞተ፡ አደከመ፡ አሰነፈ።
- አሞት በቁሙ፡ ዐሞት ።
- አሞናደለ፡ አሳመረ አካልንና አካኼድን።
- አሞኘ፡ ፡ አማረ፤
- አሞኘ አታለለ፡ (ሞኘ) ።
- አሞኛኘ፡ አዳለለ/አሸናገለ።
- አሞካሸ ሞክሼ፡ አደረገ፡ (ሞከሸ) ።
- አሞካከረ፡ ኣፈታተነ።
- አሞካከር፡ አፈታተን፡ መሞከር።
- አሞካከት፡ አቀላለብ፡ መሞከት።
- አሞዣለጠ፡ አላፋ፡ አሞላፈጠ።
- አሞዣለጠ፡ አላፋ፡ አሞላፈጠ።
- አሞዣዠቅ፡ አጠራረግ፡ አሞጫጨር፡ መሞዠቅ ።
- አሞዣዠት፡ አፈጋፈግ፡ መዠት፡
- አሞዳሞደ፡ በስውር፡ አመካከረ፡ አደማደመ ።
- አሞዳሞደ፡ አመካከረ - ሞደሞደ ።
- አሞጃጀር፡ አጨማመር፡ መሞጀር።
- አሞገሰ፡ አመሰገነ፡ ሞገሰ ።
- አሞጋገስ፡ አመሰጋገን፡ ማሞገስ።
- አሞጋገት፡ አጠያየቅ፡ መሞገት።
- አሞጠሞጠ፡ አሾለ፡ አፍን፡ ("ምሳ. ፲፫፡ ፫") ። (ተረት)፡ ፊት፡ ያሞጠሙጧል፡ ኋላ፡ ያፋጫል ።
- አሞጣጠጥ፡ አጠራረግ፡ መጠጥ።
- አሞጨላለፍ፡ አነጣጠቅ፡ መሞጭለፍ ።
- አሞጫጨር; አጫር፡ መጨር።
- አሞጭ -የቅጠል፡ ስም፡ ዐሞጭ ።
- አሰለለ፡ ሰላይ ልኮ አሳየ፡ አስገመተ፡ አስመረመረ፡ አስጐበኘ።
- አሰለለ፡ ኣመነመነ፡ አቀጠነ፡ አስኰበለለ ።
- አሰለመ (አስለመ)፡ ማተብ አስበጠስ እስላም አደረገ። በ"ሰለመ" ፈንታ "አሰለመ" ማለት ስሕተት ነው። "ላመና ሰለመ" በአማርኛ ይተባበራሉ። (ግጥም)፡ "የበጌምድርን ዱቄት ክርትፍ ነው እያለ ራስ ዐሊ መጡ አስል ሊበሉ"።
- አሰለማመጥ/አሰለቃቀጥ፡ መሰልመጥ።
- አሠለሰ፡ ሦስተዬ አሳረሰ።
- አሠለሰ፡ በሦስተኛ ቀን መጣ (ወይም ኼደ ሠራ) ።
- አሠለሰ፡ አስመሰገነ ("ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ" አሠኘ) ።
- አሰለሰለ (አሰሰለ)፡ አቀጠነ፡ አሰለተ፡ አመነመነ፡ ኣኰሰሰ (ውፋሬን ኣስወገደ) ።
- አሰለሰለ፡ ግዝትን ፈታ።
- አሰለቀ፡ አስደቈሰ፡ አስላመ፡ አስለዘበ። አሰላቂ፡ ያሰለቀ/የሚያሰልቅ (አስለዛቢ) ። ተሰለቀ፡ ኹለተኛ ተፈጨ/ደቀቀ/ተደቈሰ/ላመ/ለዘበ።
- አሰለቃቀጥ፡ አዋዋጥ፡ መሰልቀጥ።
- አሰለበ (ሰለበ/አስሐወ)፡ ገፈፈ/አወለቀ ልብስን (አድራጊ) ።
- አሰለበ (አስለበ)፡ አስቈረጠ፡ አስጐወደ፡ አስደደ (ኣስደራጊ) ።
- አሰለተ፡ አለተተ፡ አደከመ፡ እቀጠነ፡ አመነመነ፡ አደረቀ (ኣድራጊ) ።
- አሰለተ፡ ኣዘቀዘቀ፡ ሰለታ አስደረገ፡ አስከደነ (አስደራጊ) ።
- አሰለቸ፡ አስጠላ/አንገፈገፈ ።
- አሰለቸ፡ አታከተ/አደከመ ።
- አሰለቻቸት፡ አጠላል/መሰልቸት ።
- አሰለከ፡ አቀጠነ፡ ቀጥ አደረገ።
- አሠለጠ፡ አሠለጠነ።
- አሰለጠ፡ አቀና፡ ከወነ፡ ጨረሰ። ሰሊጥ (ጦች)፡ ቅባት የሚወጣው ቅመም (ከናገዳው) ።
- አሠለጠነ (አሠልጠነ)፡ መብት ሰጠ (ዕውቀትን ያን አስተማረ አሳወቀ አሳደገ ከተምኛ አደረገ - መዝ. ፻፴፮፥፰, ፱) ።
- አሠለጣጠን፡ የሥራ አስተዋወቅ (መ ሠልጠን) ።
- አሠለጥ፡ ባሪያ ሠለጠ።
- አሠለጥ፡ አሠልጣኝ (ጌታው ያሠለጠነው ፬ኛ ባሪያ የቅናጅ ልጅ ") ።
- አሰለፈ፡ በተራ አቆመ/ሰደረ/ደረደረ፡ ሰልፍ አስተማረ/አሳየ ።
- አሰለፈች፡ የሴት ስም ("ሰልፍ አሳየች፡ በሰልፍ ባጀብ ኼደች" ማለት ነው) ። አሰላፊ (ዎች)፡ ያሰለፈ/የሚያሰልፍ (የጭፍራ ኣለቃ) ።
- አሰላ (ሰሐለ)፡ ሳለ፡ ስል አደረገ፡ እተባ፡ አሾለ (ብረትን/አንደበትን) ።
- አሰላ (ሠርሐ)፡ (ዘፍ. ፴፱፡ ፫)፡ አበጀ፡ አዘጋጀ፡ አደራጀ፡ አሳመረ፡ ከወነ፡ አቀና፡ አቀለ ጠፈ።
- አሰላ፡ ሒሳብ ዐሰበ፡ ስሌት አደረገ/ቈጠረ (በባሳብና በቃል) ።
- አሰላ፡ ሩሲ ውስጥ ያለ እግርና ከተማ። አስሊ፡ ያሰላ/የሚያሰላ (ቈጣሪ) ። አስሊነት፡ አስሊ መኾን። ማስላት፡ መሳል (ስለት ማውጣት/መቊጠር) ።
- አሰላ፡ በልብ ተሳበ (ድምጥ ሳይሰማ ለመያዝ/ለማነቅ - ነብሩ/ድመቱ) ። "መለገን" ተመልከት።
- አሰላ፡ እንደ ሸላ/እንደ ዋልጋ በደን ውስጥ ኼደ (በስለት ለመምታት) ።
- አሰላለል፡ አመራመር/መሰለል ። ጐበኘ ለደግም ለክፉም ይነገራል፡ "ሰለለ" ግን ለክፉ ብቻ ነው።
- አሰላለል፡ እመናመን፡ መስለል።
- አሰላለም፡ የማተብ አበጣጠስ፡ መስለም ።
- አሠላለስ፡ ሦስት አደራረግ (አመሰጋገን መሠለስ) ።
- አሰላለቅ፡ አደቋቈስ፡ መሰለቅ።
- አሰላለብ፡ ኣቈራረጥ፡ መስለብ።
- አሰላለተ፡ አከዳደነ።
- አሰላለት፡ የሰለታ እከዳደን፡ መሰለት/መስለት ።
- አሰላለክ፡ ኣሾላለክ፡ መስለክ ።
- አሰላለፈ፡ አቀራረበ/አቋቋመ። ማሰላለፍ፡ ማቀራረብ።
- አሰላለፍ፡ አቀራረብ። (ጥለ) መሰለፍ፡ መሰለፍ ።
- አሰላል፡ የስለት አወጣጥ፡ መስላት።
- አሰላሰለ፡ አመናመነ፡ አመዛመዘ፡ ዐሰበ፡ አሰላ (አወጣ/አወረደ ነገርን በልቡ) ።
- አሰላሰል፡ አመናመን፡ አነጣጠል፡ ሰልሰል ።
- አሰላሳይ፡ ያሰላሰለ/የሚያሰላስል (ዐሳቢ) ። ማሰላሰል፡ ማመናመን፡ ማመዛመዝ፡ ማሰብ/ማስላት/ማውጣት/ማውረድ (የኅሊና ዕረፍት ማጣት) ።
- አሠላሽ፡ ያሠለሰ/የሚያሠልስ።
- አሰላቢ፡ ያሰለበ/የሚያስልብ (እስቈራጭ አስጐማጅ) ።
- አሰላቸ፡ አጣገበ/አጣላ።
- አሰላች፡ ያሰለተ/የሚያሰልት (ባለቤት) ። ማሰለት፡ ማዘቅዘቅ/ማስከደን ። ተሰለተ፡ ተዘቅዝቆ ተከደነ፡ ሣሣ ክዳኑ። ተሰለተ፡ ተከፈለ/ተለየ። ተሰላች፡ የሚሰለት (ጣራ) ። (ጥል) ስልት፡ የተሰለተ/ሰለታ የኾነ (ቅጽል) ።
- አሰላይ፡ ያሰለለ/የሚያሰልል (የሰላዮች አለቃ) ።
- አሰላፊነት፡ አሰላፊ መኾን ።
- አሰል፡ በአዳል መሬት ያለ የጨው ባሕር ። የቈላ !
- አሰልሳይ፡ ያስለሰለ/የሚያሰለስል (አመ ንማኝ/አቅጣኝ/ችጋር/ሳል/የልብ በሽታ/ናፍቆት) ።
- አሰልሳይነት፡ ኣሰልሳይ መኾን።
- አሰልቺ፡ ያስለት/የሚያሰለች (አስጠሊ ኣታካች/አድካሚ) ።
- አሠልጣኝ (ኞች)፡ ያሠለጠነ/የሚያ ሠለጥን (አሳዳጊ አስተማሪ) ።
- አሠልጣኝነት፡ አሠልጣኝ መኾን (አስ ተማሪነት) ።
- አሠመረ፡ መሥመር፡ አደረገ፡ ሠመረ ።
- አሠመረ፡ በብራና ላይ ወስፌን በወረቀት ላይ ርሳስን አሳለፈ/አስኬደ/አሰነበረ/ነደፈ/በገረ (መሥመር አደረገ/ጣለ/አበጀ/አዘጋጀ - "(አድራጊ)") ። (ጥሠ) አሠመረ፡ አስወደደ/አስፈቀደ/ዕሺ አሠኘ ("(ኣስደራጊ)") ።
- አሰመራ፡ አሠራጪ ፥ —(ሰመራ) ።
- አሰመራር፡ አሠረጨት፡ ማሰምረት/መሰምረት ።
- አሰመጠ፡ አሰጠመ።
- አሰመጣጠጥ፡ አጨላለጥ፡ መሰምጠጥ ።
- አሰሚ፡ ያሰማ/የሚያሰማ (መጽሐፍ ነጋሪ/ሰባኪ) ።
- አሰሚነት፡ ነጋሪነት/ሰባኪነት።
- አሰማ (አስምዐ)፡ ነገረ፡ ሰበከ፡ ተረጐመ፡ አስረዳ፡ አስደመጠ (ዘዳ. ፬፡ ፲፡ ሕዝ. ፴፮፡ ፲፰) ።
- አሠማ (አሥምዐ/አርሰነ)፡ አሞቀ ' አጋለ ' አጋመ (ምጣድን) ' አቀለጠ ' አፈሰሰ ' ሠምን ።
- አሰማመል፡ አዠላለጥ፡ መሰመል።
- አሰማመረ፡ አበጃጀ፡ ሰመረ ።
- አሰማመረ፡ አበጃጀ/ሸላለመ።
- አሰማመር፡ አበጃጀት፡ መስመር። "አማረን" ተመልከት ።
- አሰማመጥ፡ አሰጣጠም፡ መስመጥ። "ሰመጠ" ያማርኛ "ሰጠመ" የግእዝ መኾኑን አስተውል ።
- አሰማሚ፡ ያሰማማ/የሚያሰማማ (ኣፈቃቃሪ/አዋዋይ) ።
- አሰማማ (አስተሳምዐ)፡ አደማመጠ፡ አስተራረቀ፡ አፈቃቀረ፡ አዋዋለ፡ ቸነከረ፡ አዋደደ (ዘፀ. ፵፡ ፲፰፡ ኤር. ፲፡ ፬) ።
- አሰማም፡ አደማመጥ/መስማት።
- አሠማም፡ አጋጋል/አቀላለጥ (መሥማት መቅለጥ) ።
- አሰምሪ፡ ያሰመራ/ያሰማራ (የሚያሰመራ/የሚያሰማራ እረኛ) ።
- አሰምሬ፡ የሰው ስም (የሕዝብ መሪ/ጠባቂ ማለት ነው) ።
- አሠሠ፡ ጠረገ፡ ዐሠሠ።
- አሰሰለ፡ ወገደ/አራቀ ።
- አሠሠተ፡ ፪ቱንም ሠ አጥብቅ (አስነፈገ አስቀቀተ) ።
- አሠሠተ፡ ፪ኛውን ሠ አጥብቅ (ሥሥታም አደረገ) ።
- አሠሣሠት፡ አነፋፈግ (መሠሠት) ።
- አሰስልልኝ፡ ወግድልኝ...አርቅልኝ ።
- አሰረ (አሲር አሰረ)፡ ያዘ፡ ቀፈ ደደ ቈረን ኣበተ ገረን፡ ጠመረ ዘወı ተበተበ ። (ባውራ ጣት ላይ ክር አሰረ)፡ ጕዳይ እንዳይረሳ ማስታወሻ አደረገ ። (አንዠቱን ኣሰረ)፡ ሆዱን በመቀነት ጠመጠመ፡ ዘወትር ሳይበላ ዋለ፡ ምግብ ቈጠበ ።
- አሠረ፡ ምድር፡ በታች፡ ወግዳ፡ ከዠማ፡ በስተግራ፡ ያለ፡ ቀበሌ ።
- አሠረ፡ ቀፈደደ፤አሰረ ።
- አሰረሰረ፡ አስበሳ/አስነደለ ።
- አሰረረ (አስደራጊ)፡ አስጠቃ/አስመታ ።
- አሰረረ (አድራጊ)፡ ከፍ አደረገ (ምጣድ ጣደ ሊጥን አሰፋ ጋገረ) ።
- አሰረቀ (አስረቀ)፡ ሌባ መራ (የሰው ገንዘብ በስውር አስነሣ አስወሰደ) ። "ለመደ ብለኸ ልማድን" ተመልከት ።
- አሠረቀ፡ አባተ፡ ሠረቀ።
- አሠረቀ፡ አባተ/አገባ ወርን።
- አሠረተ፡ መሠረት ሠራ/አኖረ።
- አሠረተ ምድር፡ የምድር መሠረት አኖረ።
- አሰረናነቅ፡ አስተፋፈን፡ መሰርነቅ።
- አሰረጃጀት፡ አጠላለፍ፡ መስርጀት።
- አሰረገ፡ አስኳለ/አስጌጠ/አስዳረ ።
- አሰረገ፡ አስደገሰ ።
- አሠረገ፡ አከሰረ/ወረሰ ገንዘብን።
- አሠረገ፡ አከሰረ/ወረሰ ገንዘብን።
- አሠረገ፡ ወደ ውስጥ አለ (አገባ ደበቀ - "(ተረት)" - ቢያዩኝ አሠርግ ባያዩኝ እሰርቅ) ።
- አሠረገ፡ ወደ ውስጥ አለ (አገባ ደበቀ - "(ተረት)" - ቢያዩኝ አሠርግ ባያዩኝ እሰርቅ) ።
- አሠረጸ (አሥረጸ)፡ አወጣ/አበቀለ ።
- አሰሪ (ዎች)፡ የሚያሰራ (የስራ ሹም - ዘፀ. ፭፡ ፲፫) ።
- አሠሪ (ዎች)፡ ያሠራ/የሚያሠራ (የሕግ ባለሥልጣን) ።
- አሠሪነት፡ አሠሪ መኾን (አዛዥነት ሕጋዊ ሹመት) ።
- አሰራ (አስርሐ)፡ አሳረሰ/አስቈፈረ/አሳወደ/አስከመረ ።
- አሠራ (አሥርዐ)፡ አስወሰነ/አሳ ገገ/አስደነገገ/አስደነባ (ደግ ወይም ክፉ አስደረገ - ፪ነገ. ፲፯፥፳፩) ።
- አሠራ፡ አሳነጠ/ኣስገነባ/አሰፋ።
- አሰራ፡ የማሰር ሥራ፡ ትብተባ ።
- አሰራሰረ፡ አባሳ/አናደለ ።
- አሰራሰር፡ አበሳስ፡ መሰርሰር።
- አሰራረር፡ አወጣጥ/እጠቃቅ፡ መስረር።
- አሰራረቀ፡ አሞጨላለፈ ።
- አሰራረቅ፡ አሞጨላለፍ፡ መስረቅ።
- አሠራረብ፡ አማማግ (መሥረብ) ።
- አሠራረብ፡ አማማግ (መሥረብ) ።
- አሰራረገ፡ አዳዳረ ።
- አሰራረግ፡ አደጋገስ፡ መሰረግ።
- አሠራረግ፡ አገባብ (መሥረግ) ።
- አሠራረግ፡ አገባብ (መሥረግ) ።
- አሠራሪ፡ አደራራጊ ።
- አሰራሪ፡ ያሰረረ/የሚያሰርር (አስጠቂ አስመቺ ባለጊደር ባለባዝራ) ።
- አሠራሪነት፡ አደራራጊነት (የሥራ ረ ዳትነት ") ።
- አሠራራ፡ ኣወሳሰነ/አደራረገ ።
- አሰራር፡ አስተራረስ፡ መስራት። ሠርዐና ሰርሐ በግእዝ ልዩዎች ሲኾኑ ይህ ከዚህ በላይ የጻፍነው ቃል ኹሉ በልማድና በሞክሼነት ምክንያት በሠውት ሠ ይጻፋል፡ "ሠራን" እይ። ሠራ ሥርዐትን ጥበብን፡ ሰራ የጕልበት ስራን ያሳያል።
- አሠራር፡ አደራረግ (መሥራት) ።
- አሰራቂ፡ ያሰረቀ/የሚያሰርቅ (የሌባ ሸሪክ ምስጢረኛ) ።
- አሰራቂነት፡ አሰራቂ መኾን ።
- አሰራጀ፡ አጣለፈ/አጣጣለ ።
- አሠራጩ፡ አወራኘ፡ (ሠረጪ)።
- አሰር፡ አስር፡ ዝኒ ከማሁ ። ቈጥ እስር እንዲሉ ።
- አሠር፡ ገለባ፡ ዐሠር።
- አሠር፡ ፍለጋ፡ ዱካ፡ (ግእዝ) ።
- አሰርሳሪ፡ ያሰረሰረ/የሚያሰረስር ።
- አሰርኩሽ፡ ተበተብኩሽ፡ ያረግ ስም፡ በዛፍ በቅጠል ላይ የሚጠመጠም መናኛ ዐረግ ።
- አሰቀለ (አስቀለ)፡ አንዲሰቀል እንዲንጠለጠል አስደረገ ።
- አሠቀቀ፡ አስጠላ/አሰለት/አሰቀጠጠ ።
- አሠቃሠቅ፡ ኣበሳስ (መሠቅሠቅ) ።
- አሠቃቀቅ፡ ኣሰለቻቸት (ማሠቀቅ መሠቀቅ ") ።
- አሠቃቀይ፡ የጭንቅ አሰጣጥ (መሣ ቀይ ") ።
- አሠቃቂ (ቆች)፡ ያሠቀቀ/የሚያሠ ቅቅ (አስጠሊ አሰቅጣጭ) ።
- አሰቃይ፡ ያሰቀለ/የሚያሰቅል (ባለደም ወንጀል) ።
- አሰበ፡ አስታወሰ ፥ —ዐሰበ ።
- አሰበሰበ፡ አስለቀሙ፡ አሳከበ፡ አስከተተ።
- አሰበረ (አስበረ)፡ አስነከተ፡ አስደቀቀ።
- አሰበረ፡ አስነደለ፡ አስጣሰ፡ ኣስፈረሰ።
- አሰበረ፡ ኣሳወደ፡ አስቈረጠ።
- አሰበቀ፡ አስነገረ (ሰብቅን) ።
- አሰበቀ፡ አስወዘወዘ፡ አስነቀነቀ።
- አሰበቀለ፡ ከወነ፡ አቀለጠፈ፡ አሳጠረ፡ እጣፈጠ።
- አሰበቃቀለ፡ አቀለጣጠፈ፡ አመሰቃቀለ።
- አሰበቃቀል፡ አቀለጣጠፍ፡ መሰብቀል ።
- አሰበከ፡ "ስበኩ" አለ፡ አስነገረ።
- አሠባ (አሥብሐ)፡ አወፈረ/አደነደነ ' ኣደለበ ' አጮመየ (ሥብ አደረገ) ።
- አሰባሰበ፡ አጠራራ፡ አለቃቀመ፡ አጠረቃቀመ፡ አከመቻቸ (አበጀ) ።
- አሰባሰብ፡ አጠረቃቀም፡ መሰብሰብ።
- አሰባሳቢ፡ ያሰባሰበ፡ የሚያሰባስብ።
- አሰባሪ፡ ያሰበረ፡ የሚያሰብር።
- አሰባቀለ፡ አቀላጠፈ፡ አዘናፈለ፡ አመሳቀለ።
- አሰባቃይ፡ አዘናፋይ፡ አመሳቃይ።
- አሰባበረ፡ አቀለጣጠመ።
- አሰባበር፡ አቀለጣጠም፡ መስበር ።
- አሰባበቅ፡ አወዛወዝ፡ አስተሻሸት፡ መስበቅ።
- አሰባበብ፡ አመካኘኘት፡ መሰበብ።
- አሰባበክ፡ አነጋገር፡ መስበክ።
- አሰባበዝ፡ አሸጓጐጥ፡ መሰበዝ።
- አሠባብ፡ አወፋፈር (መሥባት) ።
- አሠባጠረ (አሠበጣጠረ)፡ አዋሰበ ' አዛነቀ ' ጣልቃ ' አገባ ።
- አሠባጣሪ፡ ያሠባጠረ/የሚያሠባጥር (አዛናቂ) ።
- አሰብ፡ ወደብ ዐሰብ ።
- አሰብሳቢ፡ ያስበሰበ፡ የሚያሰበስብ (አስለቃሚ) ።
- አሰቦት፡ ተራራ ፥ —ዐሰቦት ።
- አሰታተረ፡ አዘረጋጋ ።
- አሰታተር፡ አዘረጋግ፡ መሰተር ።
- አሰታተፍ፡ አቈራረስ፡ መሳተፍ ።
- አሰት፡ ውሸት ፥ —ዐሰት ።
- አሠነቀ፡ ሠንቁ አለ ("እንዲሠንቁ አ ዘዘ አስቈላ አስፈጪ አስጋገረ") ።
- አሰነቃቀር፡ አገራረጥ፡ መሰንቀር።
- አሰነበረ፡ ሰንበር አደረገ/አስመሰለ ።
- አሰነበተ፡ ሳምንት ወይም ብዙ ጊዜ አስቀመጠ ኣቈየ ። "እግዜር ያሰንብትልኝ" እንዲል ባላገር።
- አሰነባበተ፡ ተሰናባችንና አሰናባችን አነጋገረ ("ደኅና ኹን" አባባለ) ።
- አሰነባበተ፡ አፋታ/አላቀቀ/አለያየ።
- አሰነባበት፡ አቈያየት፡ መሰንበት።
- አሰነባበግ፡ አራረፍ፡ መሰንበግ ።
- አሠነባበጥ፡ አሠነጣጠር (መሠንበጥ) ።
- አሠነተረ፡ አስበጣ/አሠነጠቀ።
- አሠነታተር፡ አበጣጥ (መሠንተር) ።
- አሰነከለ፡ ኣስመታ እግርን።
- አሰነካከለ፡ ወለካከፈ/አስተጓጐለ/አነጓጐለ ።
- አሰነካከል፡ የአግር አመታት መሰን...ከል ።
- አሰነካከል፡ የአግር አመታት መሰን...ከል ።
- አሰነካካይ፡ አስተጓጓይ ።
- አሰነካካይ፡ አስተጓጓይ ።
- አሰነዘረ፡ አሠነተረ/ኣስበጣ ።
- አሰነዘረ፡ አስለካ/አስመጠነ ።
- አሰነዘረ፡ አስቃጣ ።
- አሰነዛዘር፡ አለካክ/አሠነታተር፡ መሰ...ንዘር ።
- አሰነደቀ፡ ሰንደቅ አስቀረጸ ።
- አሰነደቀ፡ አሳሰረ አንድነት አስደረገ ።
- አሰነደቀ፡ አስጓዘ/ኣስቋፈ ።
- አሰነደደ፡ ስንድድ አሠራ/አሰካ/አስደረደረ ።
- አሰነዳደቅ፡ አስተሳሰር፡ መሰንደቅ።
- አሰነዳደብ፡ አመታት፡ መሰንደብ። "ዘነደበን" እይ።
- አሰነዳደድ፡ አደራደር፡ መሰንደድ ።
- አሰነዳዳ፡ አዘገጃጀ/አደረጃጀ ።
- አሰነዳድ፡ አዘገጃጀት/ማሰናዳት ።
- አሰነገ፡ አስበሳ/አስነደለ/አሸነቈረ/አስገባ/አሻጠ/አስጨመረ ።
- አሰነገለ፡ አሳለ/አስወለወለ።
- አሰነጋ፡ አስወጣ/አስጐነደለ/አስቀጠቀጠ/አስወቀጠ ("ሰንጋ ጕንድል" አስደረገ) ።
- አሰነጋገል፡ አሳሳል፡ መሰንገል።
- አሰነጋግ፡ አኰለሻሸት፡ መሰንጋት።
- አሠነጠቀ፡ አሰበረ/አስተረተረ/አስከፈለ ።
- አሠነጣጠር፡ አሠነባበጥ (መሠንጠር) ።
- አሠነጣጠቅ፡ አቀዳደድ (መሠንጠቅ) ።
- አሰነፈ፡ ሰነፍ አደረገ/አታከተ/አቦዘነ (ሥራ አስፈታ) ።
- አሰነፋፈጥ፡ አፈጃጀት መሰንፈጥ ።
- አሰናሰን፡ አሸናሸን፡ መሰንሰን።
- አሠናቂ፡ ያሠነቀ/የሚያሠንቅ (የሠናቂዎች አዛዥ) ።
- አሰናበተ (ሠርሐ)፡ ፈታ/ለቀቀ ("ኺድ አገርኸ እቤትኸ ግባ" አለ - ፩ሳሙ. ፳፡ ፭, ፳፪፡ ማቴ. ፲፫፡ ፴፮) ።
- አሰናባች፡ ያስናበተ/የሚያሰናብት (ቄስ "ንዑና ሑሩ" ባይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ) ።
- አሠናተረ፡ ኣባጣ/ኣቃደደ።
- አሠናነቅ፡ የሥንቅ አዘገጃጀት (መሠ ነቅ ") ።
- አሰናነግ፡ አቀራቀር፡ መሰነግ።
- አሰናነፈ፡ አስተናነሰ/አበላለጠ ።
- አሰናነፍ፡ አቦዛዘን፡ መስነፍ።
- አሰናኘ፡ አጋጠመ/አሰማማ፡ አስተላ...ለፊ ።
- አሰናኘ፡ አጋጠመ/አሰማማ፡ አስተላ...ለፊ ።
- አሰናከለ፡ አወላከፈ ፥ —ሰነከለ ።
- አሰናከለ፡ ጠለፈ/ሰረጀ/እወላከፈ/አጪናጐለ (እንዳይኼድ እንዳይሠራ አደረገ፡ አወከ/ኦጐለ - ምሳ. ፬፡ ፲፮፡ ማቴ. ፲፰፡ ፮) ።
- አሰናካይ፡ ያሰናከለ/የሚያሰናክል (ጠላፊ/አዋኪ/አጓይ/አጨናጓይ) ።
- አሰናካይ፡ ያሰናከለ/የሚያሰናክል (ጠላፊ/አዋኪ/አጓይ/አጨናጓይ) ።
- አሰናካይነት፡ አሰናካይ መኾን።
- አሰናዘረ፡ አላወሰ/አዛወረ/አወላዳ/አዛመረ ።
- አሰናዘረ፡ አሠናተረ/አባጣ ።
- አሰናዘረ፡ ኣላካ/አማጠነ ።
- አሰናዳ፡ አገባ/ጨመረ/ከተተ (በውስጥ አደረገ - አድራጊ) ።
- አሰናዳ፡ እዘጋጀ/አደራጀ ።
- አሰናዳ፡ ጨመረ አገባ ፥ —(ሰነዳ) ።
- አሰናጂ፡ ያሰናዳ/የሚያሰናዳ (ተጨማሪ ከታች - ዘፀ. ፴፯፡ ፳፱) ።
- አሰናጂነት፡ አዘጋጂነት/አደራጂነት ። "ኣሸንዳን" ተመልከት ።
- አሠናጠቀ፡ አቃደደ/አፋለጠ/አማገዘ/አካፈለ ።
- አሠናጣቂ፡ ያሠናጠቀ/የሚያሠናጥቅ (አቃዳጅ) ።
- አሰንባሪ፡ ያስነበረ/የሚያሰነብር ።
- አሰንባች፡ ያሰነበተ/የሚያሰነብት (ሥ ንቅ ዘመድ ሥራ) ።
- አሰንዳሪ፡ የጩጌ አጋፋሪ ቢትወደድ ። አሳዳሪ ማለት ይመስላል ።
- አሠንጣቂ፡ ያሠነጠቀ/የሚያሠነጥቅ።
- አሰኘ፡ አሳሰበ ፥ —(ሠኘ) ።
- አሠኚ፡ ያሠኘ/የሚያሠኝ (ያስባለ ያና ገረ አናጋሪ) ።
- አሠኛኘ፡ አባባለ/አነጋገረ።
- አሠኛኘት፡ አባባል/አነጋገር (ማሠኘት - "ደስ አሠኘ ደስ ተሠኘ ቢል አስደሰተ ተደሰተ ማለት ነው" - "ደስታን" ተመልከት) ።
- አሰከለ፡ አሳሰረ (ፍሬ አሰጠ) ።
- አሰከረ (አስከረ)፡ አጠነበዘ፡ አሳበደ፡ አዞረ፡ አቃዠ፡ እዘለለ (ኤር. ፳፫፡ ፲፫).
- አሰከነ፡ አሳጣ፡ አደኸየ።
- አሰከነ፡ አወረደ፡ አዘቀጠ፡ አረጋ።
- አሰካ፡ አሻጠ፡ አስወጋ።
- አሰካከል፡ አስተሳሰር፡ መሰከል።
- አሰካከን፡ ኣዘቃቀጥ፡ መስከን።
- አሰካክ፡ አደራደር፡ መሰካት።
- አሰወረ፡ አሸፈነ፡ እስከለለ፡ አስደበቀ። አስገለበጠ (ወደ ውስጥ እስደረገ) ።
- አሠዋ፡ አሳረደ/አስተጠበሰ/አስቀረበ።
- አሰዋወረ፡ ኣደባበቀ።
- አሰዋወር፡ አደባበቅ፡ መሰወር።
- አሠዋው፡ አስተራረድ (መሠዋት) ።
- አሰየፈ፡ በሰይፍ አስመታ፡ አስቈረጠ፡ አስጐመደ፡ አስጐረደ፡ አስክለለ፡ ኣስገደለ።
- አሰየፈ፡ አሾጠጠ (በሾጣጣ መንገድ ኼደ) ።
- አሰያየም፡ ስም አወጣጥ፡ መሰየም። "ስምን" ተመልከት።
- አሠያየም፡ ኣመላል (መሠየም) ።
- አሠያየት፡ አጐመዣዠት (መሠየት) ።
- አሰያየፍ፡ አቈራረጥ፡ መሰየፍ።
- አሰያፊ፡ አሾጣጭ።
- አሰያፊ፡ ያሰየፈ/የሚያስይፍ (እስቈራጭ አስገዳይ) ።
- አሰደረ፡ ኣስደረደረ፡ አስኰሰኰለ፡ ኣስረደፈ።
- አሰደበ፡ ኣስወረፈ፡ ኣስነቀፈ፡ ኣዘለፈ። "ክፉ ልጅ አባቱን ያሰድባል" (ምሳ. ፳፰፡ ፯፡ ናሆ. ፫፡ ፮).
- አሰደደ፡ ካገር አስወጣ፡ ወደ ሌላ አገር አስኬደ።
- አሰዳ (ወሰደ)፡ መሬትን ጠርጎ የሚወስድ ያምሌና የናሴ ጐርፍ ።
- አሰዳቢ (ዎች)፡ ያሰደበ/የሚያሰድብ (ባለጌ ነውረኛ) ። "ዘር አሰዳቢ" እንዲሉ።
- አሰዳቢነት፡ አሰዳቢ መሆን።
- አሰዳደር፡ አደራደር፡ መሰደር።
- አሰዳደበ፡ አወራረፈ፡ አነቃቀፈ።
- አሰዳደድ፡ አላላክ፡ አለቃቀቅ፡ መስደድ።
- አሰዳጅ፡ ያሰደደ/የሚያሰድድ።
- አሰድ (ዐረ)፡ አንበሳ፡ ያምሌ ኮከብ አንበሳ የሚመስል ።
- አሰድ እሳት፡ ኮከቡ ዕድሉ ዕጣው አሰድ የኾነ ኀይለኛ አሸናፊ ድል አድራጊ፡ አንበሳ እሳት ማለት ነው ። አሰድ የያዘውን ኣይሰድ እንዲሉ ።
- አሰጅ፡ እንግዴ ሥጋ ከልጅ በኋላ የሚመጣ፡ በግእዝ ሰይል ይባላል ።
- አሰጅ፡ ወሽ የላም ጡት ።
- አሰጅ፡ የጐድን ሥጋ ።
- አሰገሰገ፡ አሰበሰበ፡ ጠባብ አስደረገ።
- አሰገሰገ፡ አስገባ፡ አሳወቀ።
- አሠገረ (አሥገረ)፡ አንድ ቀን አዘ ለለ ' አሳለፈ ።
- አሠገረ፡ በወጥመድ ያዘ (ዓሣን) ።
- አሠገረ፡ አሳለፈ/አራመደ (በሥግሪያ እንዲኼድ አደረገ - "በቅሎ እንዳሠገሯት ትኼዳለች") ።
- አሰገደ (አስገደ)፡ "ስገዱ" አለ፡ ኣስጐነበሰ፡ አንበረከከ።
- አሰገደች፡ የሴት ስም።
- አሰገደደ፡ ኣሰበሰበ፡ እስከለለ፡ ኣስደበቀ።
- አሰገዳደድ፡ ኣደባበቅ፡ መሰግደድ ።
- አሰገገ፡ አቀና፡ አንጋጠጠ፡ አረዘመ።
- አሰገጠ፡ አሰፋ፡ አስቀመቀመ፡ አሀመዘመ።
- አሰጋሰግ፡ አሰባሰብ፡ መሰግሰግ።
- አሠጋሪ፡ ያሠገረ/የሚያሠግር (በቅሎኛ) ።
- አሰጋደደ፡ አደባበቀ፡ አካለለ ።
- አሰጋጅ (አስጋዲ)፡ ያሰገደ/የሚያሰግድ (ቄስ/የመስጊድ ሹም) ።
- አሠጋገር፡ አረማማድ (ሥግሪያ መሥ ገር) ።
- አሰጋገድ፡ ኣጐነባበስ፡ መስገድ።
- አሰጋገግ፡ አረዛዘም፡ መስገግ።
- አሰጋገጥ፡ አሰፋፍ፡ መሰገጥ።
- አሰግዴ፡ የሰው ስም።
- አሰግድ ባላምባራስ አሰግድ፡ በራስ ቢትወደድ ተሰማ ጊዜ ወሰን ለመካለል ወደ ቦረና ኼደው ከዳዊት በቀር ምንም ሳይዙ የመነኑ መንፈሳዊ ሐርበኛ ናቸው። ሚስታቸውም ወደ ኢየሩሳሌም መንነው ዐረፉ ይባላል።
- አሰጐደ፡ አሳጠፈ፡ አስቀነፈ፡ ጋሻ አስበጀ፡ አስደጐሰ፡ አሸለመ።
- አሰጓጅ፡ ያሰጐደ/የሚያሰጕድ (አሳጣፊ፡ አስቀናፊ) ።
- አሰጓጐድ፡ አቀናነፍ፡ መሰጐድ።
- አሰጠ፡ አስቸረ፡ አስለገሰ።
- አሰጠመ (አስጠመ)፡ አገባ፡ አጠለቀ፡ አዘቀጠ፡ አጠፋ (መዝ. ፻፴፮፡ ፲፭).
- አሠጠቀ፡ ጨመረ/ቀላቀለ ("አክታው ደም አሠጠቀ" እንዲሉ) ።
- አሠጠጠ፡ አስቀደደ።
- አሰጣ (አስጥሐ)፡ አዘረጋ፡ አዘረረ፡ እስተረ (አስደራጊ) ።
- አሰጣ፡ ሰተረ (ሰጣ) ።
- አሰጣጠመ፡ መላልሶ አሰጠመ።
- አሰጣጠም፡ አጠላለቅ፡ መስጠም ።
- አሠጣጠጥ፡ አቀዳደድ (መሠጠጥ) ።
- አሰጣጣ፡ አዘረጋጋ።
- አሰጣጣ፡ ዘረጋጋ፡ ሰታተረ።
- አሰጣጥ፡ መስጠት፡ ሰጠ።
- አሰጣጥ፡ አለጋስ፡ መስጠት (ምሳ. ፲፰፡ ፲፮፡ ሉቃ. ፳፩፡ ፲፫).
- አሰጣጥ፡ እዘረጋግ፡ ማስጣት።
- አሰጪ፡ ያሰጠ/የሚያሰጥ።
- አሰጪነት፡ አሰጪ መሆን።
- አሰጫጨቅ፡ አበጣጠስ፡ መበጨቅ ።
- አሰፈሰፈ፡ አቀረበ/አሰለፈ (ራሱን በራሱ) ። ልማዱ ግን ቀረበ ተሰለፈ ነው ። (ግጥም)፡ "ረ ነጋ ነጋ ወፎች ለፈለፉ ጠላት አሰፍስፎ ምንድነው እንቅልፉ"።
- አሰፈረ (አስደራጊ)፡ አስለካ/አስመጠነ (ድርጎን/ቀለብን) ።
- አሰፈረ (አድራጊ)፡ ዶሮን እቈጥ ላይ ሰቀለ፡ ሰራዊትን በሜዳ አስቀመጠ፡ ንብን በወስከንባይ ውስጥ አሳረፈ ።
- አሰፈፈ፡ አንካፈፈ (በላይ አደረገ - ፩ነገ. ፭፡ ፱) ።
- አሰፊ፡ ያሰፋ/የሚያስፋ (ባለሸማ) ።
- አሰፋ (አስፈየ)፡ ሱሪ እጀ ጠባብ ቀሚስ ጥብቆ አስጠቀመ አስደረሀ ።
- አሰፋ (አስፍሐ)፡ ዘረጋ/አፋገ/አጠፈጠፈ/ጋገረ/አንቦረቀቀ (ማቴ. ፳፫፡ ፭) ።
- አሰፋ፡ የሰው ስም ።
- አሰፋሪ (ሮች)፡ ያሰፈረ/የሚያሰፍር (ዓሥራት አይ...ጭቃ ሹም) ።
- አሰፋፈር፡ አለካክ፡ መስፈር።
- አሰፋፈፍ፡ አረባበብ፡ መስፈፍ/መን...
- አሰፋፋ፡ አጠቃቀመ/አደራረተ።
- አሰፋፍ፡ አጠቃቀም፡ መስፋት።
- አሰፋፍ፡ የስፋት አጨማመር መስፋት ወሲፍ የዚህ ዘር ነው።
- አሲል (ሎች)፡ ተወርዋሪ እባብ፡ ቀጪን ረዥም፡ ከዛፍ ላይ እየዘለለ ሰውን ይነክሳል (ይነድፋል)፡ ዐንገቱን አቅንቶ እያሰገገና እያፋጩ ይኼዳል ። (ኢሳ ፴፬ ፥ ፲፭) ። ፈረንጆች ኮብራ ይሉታል ።
- አሲያ፡ ያሲያዘች የምታሲዝ ("ያች አሲያዥ") ።
- አሢያሪ፡ ያሤረ/የሚያሤር (ሤረኛ ዐዳሚ) ።
- አሲያዘ (አእኀዘ)፡ አስጨበጠ ("እጅ አስደረገ (በሽታ ኣሲያዘ) አጋባ (የውሻ በትር አሲያዘ) ቢያክ ቢያክ አለ አረከሰ") ።
- አሲያዘ፡ መያዣ ሰጠ አደረገ (ነሐ. ፭፡ ፬) ።
- አሲያዡ፡ ያ አሲያዥ ።
- አሲያዥ (ዦች)፡ ያሲያዘ/የሚያሲዝ ("ወንድና ሴትን ለመለየት") ።
- አሲዳም (አሲዳዊ)፡ ያሲድ ወገን ዐይነት አሲድ ያለበት፡ ሆዳም ከርሣም ብዙ የሚበላ፡ አንድ ዋዲያት ፍትፍት ውጦ አኹንም አኹንም ራበኝ የሚል ከሲታ በሽተኛ ጥጋብ የለሽ ።
- አሲዳሞች፡ በልተው የማይጠግቡ ሰዎች ሆዳሞች ።
- አሲድ (ዐረ ሀሲድ)፡ ምቀኛ ።
- አሲድ፡ ብረትን ከዝገት ልብስን ከእድፍ የሚያስለቅቅ የሚያጠራ የሚወለውል የሚሰነግል፡ ልብስን እንደ እሳት የሚያቃጥል የሚበላ የሚነድል፡ ሖምጣጤ ብረት አክስል መርዝ ።
- አሲድ ክፉ በሽታ ። ወደደ ብለኸ አስወደደን እይ ።
- አሳሑርታ፡ በትግሬ ውስጥ ያለ እገር ። አሳ ሰው፡ ሑርታ ሐርነት ይመስላል ።
- አሳሑርቶች፡ የአሳሑርታ ሰዎች ወይም ተወላጆች ።
- አሣለ (አሥዐለ)፡ ሥዕል አሠራ ' አስመሰለ ' አስነቀሰ ።
- አሳለለ፡ አጐበኛኘ፡ አላላከ፡ አጠያየቀ፡ አመራመረ፡ አመሳጠረ።
- አሳለመ (አስተሳለመ)፡ መስቀል አሳሙ/ባረከ። ሬሳን በወንዶች ወይም በሴቶች መግቢያ ቤተ ክርስቲያን ያሳልሙታል፡ ዳግመኛም ወደ መቃብር ይወስዱታል። "አሳለመ" አደራራጊ ሲኾን ባስደራጊነትና ባድራጊነት መተርጐሙን አስተውል።
- አሳለቀ (አኅለቀ)፡ አስጨረሰ አስፈጸመ አስጠነገደ ።
- አሳለቀ፡ ኣዳቈሰ፡ ኣላላመ፡ ኣላዘበ።
- አሳለበ (አሕለበ)፡ ሰውየው እንዲያ ልብ ላማ እንድትታለብ አስደረገ ።
- አሳለበ፡ አቋረጠ፡ አጓመደ።
- አሳለፈ (አኅለፈ)፡ ኣስኬደ/አራመደ/አሻገረ/አዘለለ ("(መዝ. ፻፴፮፥፲፬)")
- አሳለፈ፡ ማንኛውንም ምግብ ዐደለ (መ ጠጥ ሰጠ ወጥ አወጣ - እንጀራ አጠገበ ") ።
- አሳለፈ፡ በደልን ተወ አቀለለ (ይቅር አለ ") ።
- አሳለፈ፡ ችግርን አራቀ ።
- አሳለፈ፡ ነፍስ ገደለ ።
- አሳለፈ፡ ኣቃረበ/አፋጠጠ።
- አሳለፈ፡ እንዳልነበረ አደረገ እግዜር ዓለምን ።
- አሳለፈ፡ ዋቢ አመጣ ።
- አሳሊ፡ ያሳላ/የሚያሳላ (አቈጣጣሪ) ።
- አሳላ፡ አስተሳሰበ፡ አፋሰሰ፡ አቈጣጠረ።
- አሳላ፡ አከናወነ፡ እቃና፡ አቀናበረ፡ አሳካ።
- አሳላሚ፡ ያሳላመ/የሚያሳልም (አሳሚ/ባራኪ ቄስ) ።
- አሳላሚነት፡ አሳሚነት/ባራኪነት።
- አሳላቂ፡ ያሳለቀ/የሚያሳልቅ።
- አሳላቢ፡ ያሳለበ/የሚያሳልብ (ያቢ ላም ያላቢ አለቃ ") ።
- አሳላይ፡ ያሳለለ/የሚያሳልል (አመራማሪ) ።
- አሳላፊ (ዎች)፡ ያሳለፈ/የሚያሳልፍ (ዐዳይ - ዘፍ. ፵፥፩፥፪) ።
- አሳላፊነት፡ ዐዳይነት "
- አሳላፎች፡ አሳላፊዎች ዐዳዮች ።
- አሳልፎ ሰጠ (አግብአ)፡ እሰሩት ግደሉት ብሎ እሌላ ሰው እጅ አግባ ጣለ ("(ማቴ. ፳፮፥፳፩—፳፫፡ ሉቃ. ፳፪፥፳፩)") ።
- አሳልፎ ሰጠ)፡ ለቅጣት/ለመከራ ተገቢ አደረገ (በዳኛ ፊት) ።
- አሳልፎ፡ ዐድሎ ሰጥቶ ።
- አሳመ (አስዐመ)፡ አሳለመ/አስጨመ...
- አሳመመ (አሕመመ)፡ አስበሸተ ።
- አሳመሰ (አሐመሰ)፡ ዐምሱ አለ (አስ
- አሳመረ፡ መልካም አደረገ—አ...
- አሳመረ፡ አሸገነ፡ አማረ ።
- አሳመረ፡ አበጀ፡ አሰመረ፡ መልካም፡ አደረገ፡ አስጌጠ፡ አሸገነ፡ አከናወነ፡ አቀለጠፈ፡ (ኤር፳፮፥ ፲፫። ማር፯፡ ፴፯። ዮሐ፯፡ ፲፭)። አማረ፡ በማስደረግ፡ ጊዜ፡ ማ፡ ግእዝ፡ መኾኑን፡ አስተውል፡ ሰመረን፡ ተመልከት ።
- አሳመሩ፡ ማለት ነው። "አሥመራ" ተብሎ ቢጻፍ ግን "ደስ አሠኛት/አሠኙ" ተብሎ ይተረጐማል። ("ውእቱ አሥመራ፡ አንስት አሥመራ") ። አዳሎች ግን አስመራን (አሳሒመራ) ትርጓሜውንም ቀይ ሰው ይሉታል ።
- አሳመቀ፡ አሳበቀ አስረጠጠ ።
- አሳመነ፡ (አእመነ)፡ በቁሙ፡ አስረዳ፡ አስቀበለ፡ ሐሰትን፡ ክሕደትን፡ አራቀ፡ አወን፡ አሠኘ፡ አስገበረ ።
- አሳመነ፡ አሳምነው፡ የወንድ፡ ስም።
- አሳመነች፡ የሴት፡ ስም።
- አሳመገ (አሕመገ)፡ አሰበሰበ አስ
- አሳመጠ፡ ዐመጠኛ አደረገ/አስደረገ (ኣስከዳ ኣሸፈተ - "ዐመፀን" እይ - "ዐመጠ የሕዝብ ዐመፀ የካህናት" ነው ") ።
- አሳመፀ፡ አሳመጠ ።
- አሳሚ (አሕማዪ)፡ ያሳማ/የሚያ ሳማ (አስነቃፊ ") ።
- አሳሚ፡ ያሳመ/የሚያስም... (አሳላሚ) ።
- አሳሚነት፡ አሳሚ/አሳላሚ መኾን ።
- አሳማ (ኣሕመየ)፡ አስነቀፈ ("እንዲያ ሙት እንዲታማ አስደረገ ") ።
- አሣማ፡ በቁሙ፡ ዐሣማ ።
- አሳማሚ (አሕማሚ)፡ ያሳመመ/የሚ ያሳምም ።
- አሳማሪ
- አሳማሪ የሚያሳምር፡ የሚያስውብ፡ በጅ፡ የሚያሰምር፡ አከናዋኝ። ደገደገ፡ ብለኸ፡ ድግድግን፡ እይ።
- አሳማኝ (አሕመየኒ)፡ ስሜን፡ የሰውን፡ ስም፡ በክፉ፡ አስነሣኝ። ዐማን፡ እይ።
- አሳማኝ፡ (አእማኒ)፡ ያሳመነ፡ የሚያሳምን፡ የሚያስረዳ፡ አስቀባይ።
- አሳማጭ፡ ያሳመጠ/የሚያሳምጥ (አስከጂ ") ።
- አሳምሮ፡ አስጊጦ፡ አሽግኖ። አሳምሮ፡ ሠራ፡ አቀለጠፈ፡ ከወነ ' አስዋበ፡ አሸገነ ።
- አሳሠሠ (አኅሠሠ)፡ አስጠረገ አስ ወለወለ ።
- አሳሰረ (አእሰረ)፡ ኣሲያዘ አስጋ አስቀፈደደ ።
- አሳሰበ (አሐሰበ)፡ የተረሳ ነገርንና ወደ ፊት ስለሚደረግ ጕዳይ ልብ አስደ ረገ (አስታወሰ - ቲቶ. ፫፥ ፳) ። "አስታወሰ ፥ የዐሰ በና የአሳሰበ መፍቻ መኾኑን ልብ አድ ርግ" ።
- አሳሰበ ልብ ኣስደረገ አሳወቀ አስረዳ ("አስጨመተ አስለበመ አሠየመ አስመላ አስለባሚ ያስለበመ የሚያስለብም አ ሳዋቂ አስረጅ አሠያሚ ማስለበም ማስጨመት ማሳወቅ ማስ መላት ማሠየም ማስለበሚያ ማሳወቂያ ማስጨመቻ ማስመሊያ ተለበመ ") ("ተለበወ") ።
- አሣሠተ፡ አናፈገ።
- አሣሣ፡ አሠሠተ/አሳነሰ።
- አሣሣ፡ አጠፈጠፈ/አረቀቀ (ሥሥ አደረገ - ዘኍ. ፲፮፥፴፰፡ ኢሳ. ፵፩፥፯ - "ስንዴና ጤፍ ገበታ ያሣሣል" እንዲል ባላገር) ።
- አሣሣለ፡ ቀለም አቃባ ("(የሥዕልን ሥራ ረዳ)") ' አመሳሰለ ።
- አሣሣል፡ አመሳሰል (መሣል) ።
- አሳሳል፡ አሰነጋገል፡ መሳል።
- አሳሳል፡ አጐብሳሰት፡ መሳል።
- አሳሳሪ (አእሳሪ)፡ ያሳሰረ የሚያሳስር፡ አስቀፍዳጅ ።
- አሣሣቀ፡ መላልሶ አሣቀ ("(ዐብሮ ቀ)") ' አጨዋወተ ።
- አሣሣቂ፡ ያሣሣቀ/የሚያሣሥቅ።
- አሣሣቅ፡ አፈጋገግ ' መሣቅ ።
- አሳሳበ፡ (አስተሳሐበ)፡ አጓተተ፡ አማዘዘ፡ አለካካ።
- አሳሳቢ፡ ያሳሰበ/የሚያሳስብ (አስታ ማሳሰብ ") ።
- አሳሳቢ፡ ያሳሳበ፡ የሚያሳስብ (አጓታች፣ አለካኪ) ።
- አሳሳብ፡ አጐታተት፡ መሳብ።
- አሳሳተ (አስተሳሐተ)፡ አሳከረ/አደናገረ (አጭበረበረ) ።
- አሳሳተ፡ ኣለያየ። "ጠንቋይ ከግዜር ያሳስታል"።
- አሳሳት፡ አዘላለል፡ መሳት።
- አሳሳች (ቾች)፡ ያሳሳተ/የሚያሳስት (አደናጋሪ አጭበርባሪ) ።
- አሳሳች፡ የሴት ሙሽራ መሰል (የሴት ወይዘሮ የንግሥት ደንገጥር) ።
- አሳሳግ፡ አሰካክ፡ አጨማመር፡ መሳግ።
- አሳረመ (አሕረመ)፡ አስተወ አስ ከለከለ ።
- አሳረመ፡ ዐረምን አስነቀለ (አስኰተ ኰተ አገዳን ተክልን ") ።
- አሳረመ፡ የመጻፍን የደብዳቤን ቃል ጕድለት አስመላ ።
- አሳረሰ (አሕረሰ)፡ አስገመሰ አስገለ ገለ አስቀበቀበ ።
- አሳረረ (ኣሕረረ/ኣሕለለ)፡ ኣቃ ጠለ አገመነ አጠቈረ አከሰለ (ዐሩር አደረገ ") ። "ዛሬ ጨው የበዛበት ወጥ በልቼ ውሃ ጥም አሳረረኝ" ።
- አሳረረ፡ በጅራፍ ባለንጋ ገረፈ (በት ይት መታ ") ።
- አሳረረ፡ አስተዛዘለ/አገናኘ ።
- አሳረረ፡ ዋጋ አበለጠ አሳደገ (ርግጠኛው ግን አበላለጠ ነው) ።
- አሳረቀ (አስተሳረቀ)፡ አናሣ/አዋሰደ/አሞ፵ለፈ ።
- አሳረቀ (አዕረቀ)፡ ቀጥ አስደረገ ።
- አሳረዘ፡ አስጐደለ አሳነሰ አሳለቀ ልብስን (አስራቈተ ገላን ") ።
- አሳረደ (አሕረደ)፡ አስገዘገዘ አስ ከረከረ አስቈረጠ አስቀረደደ ።
- አሳረደ፡ አስማሰ አስጐደበ ።
- አሳረገ (አዕረገ)፡ ከጸሎትና ከመ ብል ከመጠጥ በኋላ ጸለየ አመሰገነ ("ጸሎ ታችንን ከደመና በታች አያስቀርብን - የበ ላነውን ኅብስተ በረከት - የጠጣነውን ጽዋዐ ሕይወት ያድርግልን - በሬን ገበሬን አውሎ ያግባ - ኣቡነ ዘበሰማያት ሰላሙ ገብርኤል አለ ") ። የተጸለየውን ጸሎት የተሰጠውን ምጿት ፈጣሪ ጌታ ያስምረው ያሳርገው ይቀበለው እያለ ተናገረ ።
- አሳረገ (አዕረገ)፡ ከጸሎትና ከመ ብል ከመጠጥ በኋላ ጸለየ አመሰገነ ("ጸሎ ታችንን ከደመና በታች አያስቀርብን - የበ ላነውን ኅብስተ በረከት - የጠጣነውን ጽዋዐ ሕይወት ያድርግልን - በሬን ገበሬን አውሎ ያግባ - ኣቡነ ዘበሰማያት ሰላሙ ገብርኤል አለ ") ። የተጸለየውን ጸሎት የተሰጠውን ምጿት ፈጣሪ ጌታ ያስምረው ያሳርገው ይቀበለው እያለ ተናገረ ።
- አሳረገ፡ መሥዋዕት አቀረበ ሰጠ (እ ሳት ላይ አደረገ አቃጠለ አሳረረ - ዘሌ. ፰፥ ፲፯ - ፳፩፡ ፩ሳሙ. ፲፫፥ ፱) ።
- አሳረገ፡ መሥዋዕት አቀረበ ሰጠ (እ ሳት ላይ አደረገ አቃጠለ አሳረረ - ዘሌ. ፰፥ ፲፯ - ፳፩፡ ፩ሳሙ. ፲፫፥ ፱) ።
- አሳረፈ (አዕረፈ)፡ አስቀመጠ ዕረ ፍት ሰጠ ("(ዘዳ. ፫፥ ፳፡ ምሳ. ፳፭፥ ፲፫)") ።
- አሳረፈ፡ ሸክምን አስቀበለ ("ተቀበለ") ።
- አሳረፈ፡ በቶሎ ገደለ (ከሥቃይ ለየ ") ።
- አሳረፈ፡ ዝም አሠኘ ጠበቀ ("አፍኸን አሳርፍ" እንዲሉ) ።
- አሳሪ፡ ያሰረ የሚያስር የሚቈረኝ የሚ ገረኝ፡ አጋዥ ። (ማቴ ፭ ፥ ፳፭) ።
- አሳሪ፡ ያሳራ/የሚያሳራ (ደብዳቢ ") ።
- አሳሪዎች፡ አሳሮች፡ ያሰሩ የሚያስሩ ። (ግብ ሐዋ ፲፮ ፥ ፴፭ ፥ ፴፰) ።
- አሳራ (አስተሳርሐ)፡ አስተራረሰ/አቋፈረ/አስተጫጨደ ።
- አሣራ (አስተሣርዐ)፡ አዋሰነ/አደና ገገ/አደናባ ።
- አሳራ፡ አስኰሳ (በጣም ደበደበ መታ ") ።
- አሣራ፡ አዳረገ ("(ሥራን ረዳ)") ' አገናባ ።
- አሳራሚ፡ ያሳረመ/የሚያሳርም (አስነ ቃይ ያራሚ አዛዥ ") ።
- አሳራሪ፡ ያሳረረ (አገናኝ አገና...ጨማሪ) ።
- አሳራቂ፡ ያላረቀ/የሚያሳርቅ ።
- አሳራጅ፡ ያሳረደ፥የሚያሳርድ አስጐዳቢ ።
- አሳራጊ (ጎች)፡ ያሳረገ/የሚያሳርግ (ቄስ ቆሞስ ኤጲስቆጶስ ጳጳስ ሊቀ ጳጳሳት ") ። "ወደሰ" ብለኸ "ውዳሴ ከንቱን" ተመልከት ። አሳራጊነት፡ አሳራጊ መኾን ።
- አሳራጊ (ጎች)፡ ያሳረገ/የሚያሳርግ (ቄስ ቆሞስ ኤጲስቆጶስ ጳጳስ ሊቀ ጳጳሳት ") ። "ወደሰ" ብለኸ "ውዳሴ ከንቱን" ተመልከት ።
- አሳራጊነት፡ አሳራጊ መኾን ።
- አሳራፊ፡ ያሳረፈ/የሚያሳርፍ (አስቀ ማጭ ገዳይ ") ።
- አሳር፡ ውርደት ፥ —ዐሳር ።
- አሳር፡ ውርደት ፥ ዐሳር ።
- አሣር፤ውርደት፡ ዐሳር።
- አሳሸ (አሕሰየ)፡ ስለወሰ አስደረጠ' አስለፋ ።
- አሳሸለ (አእከለ)፡ አስጨመረ አሳ ከለ፡ እስለካ አስከነዳ አስቀጠበ ።
- አሳሸመ መ፡ አሠራ አስጐነጐነ አስደበለ ።
- አሳሸገ፡ አዘጋ አስደፈነ አስመረገ ።
- አሣሺ፡ ያሣሣ/የሚያሣሣ (አጠፍጣፊ አ ርቃቂ) ረግ ።
- አሳሻጊ፡ ያሳሸገ የሚያሳሽግ የሚያስደፍን የሚያስመርግ ።
- አሣቀ፡ አስፈገገ/አንከተከተ (በኹናቴው ባነጋገሩ እንዲሥቁ አደረገ አጫወተ) ።
- አሳቀለ፡ ሻፈደ ።
- አሳቀለ፡ አናሣ/ኣማዘነ (ወደ በላይ አሳጣ) ።
- አሳቀለች፡ ሻፈደች (ዥራቷን ሰቀለች ተባት ፈለገች አውራ ላይ ወጣች ተከመረች ጊደሯ) ።
- አሣቀቀ፡ አሳይቶ ሰጥቶ ነሣ (ከለከለ ") ፋሪ ።
- አሣቀየ፡ ሥቃይ አስቀበለ።
- አሳቀደ (አዕቀደ)፡ ዐቅዱ አለ (ዐ ቅድ አስበጀ ") ።
- አሳቀፈ ግዴታን፡ አስታቀፈ ፈቃድን ያሳያል ። "ዕን ቍላልን ለዶሮ አስታቀፈ" እንዲሉ ።
- አሳቀፈ/አስታቀፈ (አሕቀፈ)፡ በጕያ በልብስ አሲያዘ አሸከመ ።
- አሣቂ፡ ያሣቀ/የሚያሥቅ ።
- አሣቃቂ፡ ያሣቀቀ/የሚያሣቅቅ (አሳ ፋሪ) ።
- አሳቃፊ/አስታቃፊ፡ ያሳቀፈ/የሚያ ሳቅፍ/ያስ ያስታቀፈ/የሚያስታቅፍ (አሲያዥ አ ሸካሚ ") ።
- አሳቈረ (አዕቈረ)፡ አስቋጠረ አሳ
- አሳበ (አስሐበ)፡ አስጐነበሰ፡ በመሬት ውስጥ ቀበረ፡ ዐፈር አለበሰ፡ ወደ ጎን አስኬደ፡ አዘመተ (ተክልን) ።
- አሳበ፡ አስመጣ፡ አስቀረበ።
- አሳበ፡ አስወጠረ፡ አስለጠጠ፡ አስገተረ (አስደራጊ) ።
- አሳበ፡ አስጐተተ፡ አስመዘዘ፡ አስረዘመ።
- አሳበ፡ አረዘመ (መንገድን - አድራጊ) ።
- አሳበለ (አሕበለ)፡ አስዋሸ (ዐባይ አ ደረገ - ሐሰት አናገረ) ።
- አሳበሰ፡ አስጠረገ፡ አስበደለ ።
- አሳበረ (አስተሳበረ)፡ አማታ፡ አቀላጠመ (ሽመልመሌን የደመራ ለት) ።
- አሳበረ፡ መንገድን አቋረጠ፡ አግድም/መስቀልኛ ኼደ።
- አሳበረ፡ ዐይንንና ዐይንን አሸናነፈ፡ አረታታ።
- አሳበቀ፡ ሰበቀ፡ አዋሸከ፡ አሳጣ።
- አሳበቀ፡ አሳመቀ፡ እስጨመረ ፥ አስመላ አስረጠጠ ወ ።
- አሳበቀ፡ አስወጋ ።
- አሳበቀ፡ አበጣበጠ፡ አስተሻሸ።
- አሳበቀ፡ ዕንጨትንና ዕንጨትን አፈጋፈገ፡ አፋጨ።
- አሳበበ፡ አፈካ ፥ አፈነዳ ፥ አበባ አስወጣ ፥ አስፈነዳ ።
- አሳበዘ (አኅበዘ)፡ አስጋገረ።
- አሳበደ (አእበደ)፡ እብድ አደረገ፡ አስጮኸ ፥ አስቈጣ ፥ አስመሸ ። (ኢዮ ፲፪ ፥ ፲፯ ። መከ ፰ ፥ ፳) ።
- አሳበጠ (አሕበጠ)፡ ነፋ/ቀበተተ/ ነረተ ።
- አሳቢ፡ ቀጪን አደንጓሬ።
- አሳቢ፡ ያሳበ፡ የሚያስብ፡ ተክል አዝማች።
- አሳቢ፡ ያሳበ፡ የሚያስብ፡ አስጐታች።
- አሳባ (አኅብአ)፡ አሸሸገ/አስደበቀ ።
- አሳባሪ (ዎች)፡ ያሳበረ/የሚያሳብር።
- አሳባሪ፡ ያሳበረ፡ የሚያሳብር (አቋራጭ) ።
- አሳባሪነት፡ አሳባሪ መኾን ።
- አሳባቂ (ቆች)፡ ያሳበቀ፡ የሚያሳብቅ (ሰባቂ፡ ሰብቀኛ፡ አዋሻኪ) ።
- አሳባቂነት፡ ሰብቀኛነት።
- አሳባይ፡ ያሳበለ/የሚያሳብል።
- አሳባጅ (አባዲ)፡ ያሳበደ የሚያብድ ፥ አስቈ ፥ አስጯኺ ።
- አሳባጅ፡ ኣብሾ ፥ ብርብራ የዕፀ ፋርስ ፍሬ (እንዶድ የገባበት ጠጅ) ።
- አሳባጭ፡ ያሳበጠ/የሚያሳብጥ (የሚነፋ) ።
- አሳተ (አስሐተ)፡ ክፉ ሥራ አሠራ፡ ጣዖት አስመለከ፡ መንፈሳዊውን ዓለማዊ እውነተኛውን ሐሰተኛ ጻድቁን ኃጥእ ንጹሑን ርኩስ አደረገ፡ አስነወረ (፪ነገ. ፳፬፡ ፱፡ ምሳ. ፯፡ ፳፩) ።
- አሳተመ (አኅተመ)፡ ማኅተም አስ ደረገ (በማተሚያ ቤት አጻፈ ") ።
- አሳተረ፡ አዘራጋ ።
- አሳተበ (አዕተበ)፡ አስቈረጠ ዕትብ ትን ።
- አሳተተ (አሕተተ)፡ አስመረመረ፥ ስተቸ ።
- አሳተተ (አእተተ)፡ አስራቀ አስገ ለለ አስለየ ።
- አሳተፈ፡ አገናኘ/አቋረስ/አፋተተ/አካፈለ (ባንድነት አበላ) ።
- አሳታሚ፡ ያሳተመ/የሚያሳትም (ባለደ ብዳቤ የመጻፍ ጌታ ") ።
- አሳታፊ፡ ያሳተፈ/የሚያሳትፍ (ቄስ) ።
- አሳቺ/ች (አስሓቲ)፡ ያሳተ/የሚያስት (መጥፎ ሰው ሰይጣን - ፪ዮሐ. ፯) ።
- አሳቻ፡ ስላች ፥ —ሳተ ።
- አሳቻ፡ ተራ ሰው አልባሌ (ስላች) ።
- አሳችነት፡ አሳች መኾን ።
- አሳቾች፡ በነገር በሥራ በሃይማኖት የሚያስቱ ተንኰለኞች ሰዎች አጋንንት (፪ቆሮ. ፬፡ ፬፡ ፪ጢሞ. ፫፡ ፲፫፡ ፪ዮሐ. ፯) ።
- አሳነሰ፡ (አእነሰ)፡ ዝቅ፡ አደረገ፡ አዋረደ፡ አስቀነሰ፡ አሳጠረ፡ አጐደለ። ለራስ፡ ሲቈርሱ፡ አያሳንሱ ።
- አሳነቀ (አሕነቀ)፡ ጕረሮን አሲያዘ አሳሰረ ።
- አሳነገ፡ አባሳ/አቀራቀረ።
- አሳነጠ (አሕነጸ)፡ አስጠረበ - አሸለተ አስላገ አስመገዘ አስፈለፈለ አስበሳ አስቀረጸ ።
- አሳነፈ፡ አዳከመ ።
- አሳናሽ፡ ያሳነስ ፣የሚያሳንስ፡ አዋራጅ፡ አኰሳሽ ።
- አሳናቂ፡ ያሳነቀ/የሚያሳንቅ ።
- አሳናፊ፡ ያሳነፈ/የሚያሳንፍ።
- አሳኘከ (አሕነከ)፡ አስቈረጠመ አስ በላ አስመነዠኸ ።
- አሳከመ (አሕከመ)፡ አላገመ (አስ በጣ - የተቀደደ የተፈነከተ ገላን እሰፋ - ቍስ ልን አሳሰረ አስጠገነ ") ።
- አሳከረ፡ አሳሳተ፡ አዛነቀ፡ አዘባረቀ፡ አቃወሰ።
- አሳከከ (አሕከከ)፡ አስፈገፈገ (አስ ፋቀ አስጠቈመ ") ።
- አሳኪ፡ ያሳካ/የሚያሳካ (አዋዳጅ/አቀናባሪ) ።
- አሳካ (አስተሳክዐ)፡ አዋደደ፡ አቀናበረ፡ አሳላ፡ አሠባጠረ (ጣትን) ።
- አሳካሚ፡ ያሳከመ/የሚያሳክም (የበሽተኛ ዘመድ ") ።
- አሳካሪ፡ ያሳከረ/የሚያሳክር (አሳሳች አዘባራቂ) ።
- አሳካኪ፡ ያሳከከ/የሚያሳክክ ተባይ
- አሳክክ፡ የእንጕዳይ ዐይነት (የምድር
- አሳወረ (አዖረ)፡ ዐይንን አስወጣ አስፈሰሰ (ዕውር አስደረገ - ዮሐ. ፲፪፥፵) ።
- አሳወረ፡ አዳበቃ፡ እሻሸገ።
- አሳወቀ (አዖቀ)፡ አስተማረ/አስጠና/ አስለመደ/ኣስለየ/አሠለጠነ ።
- አሳወቂ፡ ያሳወቀ/የሚያሳውቅ (አስ ተማሪ ") ።
- አሳወከ (አሆከ)፡ አስነቀነቀ አስበጠበጠ ።
- አሳወደ (አዕጸደ)፡ ዕጨዱ አለ (እ ስቈረጠ ") ።
- አሳወደ (ጥዞ)፡ አዞረ (በዙሪያ አስኬደ ") ።
- አሳዋሪ፡ ያሳወረ/የሚያሳውር ።
- አሳዋኪ፡ ያሳወከ የሚያሳውክ፡ አስነቅናቂ አስበጥባጭ ።
- አሳዘለ (አሕዘለ)፡ በዠርባ አሸ ከመ (አሲያዘ ") ።
- አሳዘነ (አሕዘነ)፡ አስተከዘ/ኣጸጸተ/አራራ (አስቀየመ አስከፋ አበሳጨ - ምሳ. ፳፪፥፳፫) ።
- አሳዘዘ፡ (አአዘዘ፡ አስተአዘዘ)፡ እዘዝ " አለ፡ አዛዥነት፡ ሾመ፡ ወከለ።
- አሳዛኝ፡ ያሳዘነ/የሚያሳዝን ።
- አሳዛዥ፡ ያሳዘዘ፡ የሚያሳዝዝ፡ ያዛዦች ፥
- አሳዛይ፡ ያሳዘለ/የሚያሳዝል (ኣሸካሚ ") ።
- አሳየ፡ (አርአየ)፡ አመለከተ ፥ ገለጠ ፥ አስረዳ ፥ አሳወቀ (ዮሐ፲፬፡ ፪) ።
- አሳየ፡ የሰው ስም ።
- አሳዪ፡ (አርኣዪ)፡ ያሳየ ፥ የሚያሳይ ፥ የሚነግር ፥ የሚያስረዳ፡ አመልካች ፥ ገላጭ።
- አሣይ፡ ያሣለ/የሚያሥል።
- አሳደለ፡ ባዳይ እጅ አሰጠ ።
- አሳደመ፡ ዐድማ አስደረገ (ሰውን አሳ በረ - ክፉ አስመከረ ") ።
- አሳደረ (አኅደረ)፡ ዕደሩ አለ (ማያ ሪያ ሰጠ - "አያሳድረኝ አላሳድረው እኔ የክርስ ቶስ ባሪያ እንዳሉ" - ዐጤ ቴዎ) ።
- አሳደረ፡ መሬቱን ሳይታረስ ሳይዘራ ተወ ።
- አሳደረ፡ አሽከር አደረገ ።
- አሳደረ፡ ኣደራደረ፡ ኣኰላኰለ።
- አሳደበ (አስደራጊ)፡ አሰደበ። "ምን ያሳድብኻል?" እንዲሉ። ("ተሳደበ"ና "አሳደበ" ተደራራጊና አስደራጊ ሲኾኑ ስለ ልማድ ባድራጊነትና ባስደራጊነት መፈታታቸውን አስተውል) ።
- አሳደበ፡ ኣዋረፈ፡ አኳሰሰ፡ አናቀፈ።
- አሳደነ፡ እደን አገባ ሰውን (አሲያዘ ፥ አስወጋ አስገደለ አውሬን ") ።
- አሳደደ፡ አባረረ (መዝ. ፵፬፡ ፪፡ ፩ቆሮ. ፲፭፡ ፴).
- አሳደገ፡ አበለጠ አላቀ በሹመት በማዕርግ ። (ዳን ፩ ፥ ፭ ። ፩ቆሮ ፫ ፥ ፮) ።
- አሳደገ፡ ከፍ አደረገ አረዘመ በማቀፍ በማጥባት በመመገብ ።
- አሳደፈ፡ አጨማለቀ እረከሰ አስነወረ፡ ነቀፈ ዘለፈ፡ ሰድቦ ለሰዳቢ ሰጠ ። (ሕዝ ፴፪ ፥ ፪ - ፲፫) ።
- አሳዳሚ፡ ያሳደመ/የሚያሳድም (አሳባሪ ") ።
- አሳዳሚነት፡ አሳዳሚ መኾን ።
- አሳዳሪ (ሮች)፡ ያሽከር/የሎሌ/የገ ረድ ጌታ (የሰርግ ቤት አዛዥ አለቃ - በግእዝ ሊቀ ምርፋቅ ይባላል - ዮሐ. ፪፥ ፰, ፱ - ሳታት በተቆመ ጊዜ የቅስና ቀለም የሚል ቄስ - የድቍና ቀለም - "(ተንሥኡ ጸልዩ)" - የሚል ዲያቆን - "(ባሳዳሪዬ)" - በጌታዬ ባለቃዬ - ባሳዳሪዬ እንዲል ተከሳሽ ") ።
- አሳዳሪነት፡ አሳዳሪ መኾን ።
- አሳዳኝ (ኞች)፡ ያሳደነ/የሚያሳድን (የሚያሲዝ የሚያስገድል - መሪ አስገዳይ ") ።
- አሳዳይ፡ ያሳደለ/የሚያሳድል ።
- አሳዳጅ (ጆች)፡ ያሳደደ/የሚያሳድድ (አባራሪ - መዝ. ፯፡ ፩፡ ፊልጵ. ፫፡ ፮፡ ፩ጢሞ. ፩፡ ፲፫).
- አሳዳጅነት፡ አሳዳጅ መሆን (አባራሪነት) ።
- አሳዳጅና ተሳዳጅ፡ አባራሪና ተባራሪ። "እሳዳጅና ተሳዳጅ እኩል አይሮጡም።"
- አሳዳጊ (ጎች)፡ ያሳደገ የሚያሳድግ ። አባት ሞግዚት ። (ኢሳ ፵፱ ፥ ፳፫) ።
- አሳዳጊ፡ የበደለው ያልተሠራ ያልተ ቀጣ ባለጌ ልጅ ስድ መረን ።
- አሳዳፊ፡ ያሳደፈ የሚያሳድፍ፡ አርካሽ አስነዋሪ ።
- አሳጀለ፡ አሸፈነ/አስለበሰ/አስጠቀለለ (ከባድ ነገር አስ፵ነ ") ስለስ ።
- አሳጀበ፡ አስከተለ/አስከበበ።
- አሳጅ፡ ያሳወደ/የሚያሳጭድ ።
- አሳገለ (አዕገለ)፡ አስጫረ/ኣስኰተ ኰተ ።
- አሳገመ (አሕገመ)፡ አስጠባ/አስመ ጠጠ/አስወጣ ደምን ።
- አሳገተ (አዕገተ)፡ ዕጎቻ ሰጠ/አሲ ያዘ ።
- አሳገዘ (አሕገዘ)፡ አስረዳ ("ርዱት ተቀ በሉት አለ - አሳረፈ ") ረዳ ።
- አሳገደ፡ አስገታ አስከለከለ እስከተረ አስቆመ አስጠበቀ ።
- አሳጋች፡ ያሳገተ/የሚያሳግት (ዋስ) ።
- አሳጋዥ፡ ያሳገዘ/የሚያሳግዝ።
- አሳጋይ፡ ያሳገለ/የሚያሳግል (አስኰትኳች) ።
- አሳጋጅ፡ ያሳገደ የሚያሳግድ፡ አስከል ካይ አስጠባቂ ።
- አሳጐረ፡ በረትን አዘጋ ።
- አሳጠረ (አሕጸረ)፡ ዐጥር አሠራ (አስከበበ አስከለለ አስቀጠረ አስጀጐለ ") ።
- አሳጠረ (ኣኅጸረ)፡ ዐጪር አደረገ (አሳነሰ - ዳን. ፯፥፩) ።
- አሳጠበ (አኅፀበ)፡ ዕጠቡ አለ (አስ ጐረፈ አስለቀለቀ ") ።
- አሳጠፈ (አዕጸፈ)፡ ዕጠፉ አለ (ሸ ማን መጣፍን ቈርበትን ወረቀትን ብራናን እ ንጀራን ") ።
- አሳጣ (አኅጥአ)፡ አደኸየ/አስቸገረ ።
- አሳጣ (አስተሳጥሐ)፡ አዘራጋ፡ አሳተረ።
- አሳጣ፡ አጣላ፡ ኣካሰሰ። ልማዱ ግን ኣድራጊነት ነው።
- አሳጣ፡ ከሰሰ፡ ስም አከፋ (ዘዳ. ፳፫፡ ፱፡ ዮሐ. ፰፡ ፲፡ ሮሜ. ፰፡ ፪). "ዳኘ" ብለኽ "አዳኘን" አስተውል።
- አሳጣሪ (አኅጻሪ)፡ ያሳጠረ/የሚያሳ ጥር (ቁመትን ነገርን ቀናሽ አሳናሽ ") ።
- አሳጣሪ (አሕጻሪ)፡ ያሳጠረ/የሚያሳ ጥር ፲ ቅጥር አሠሪ ።
- አሳጣቢ፡ ያሳጠበ/የሚያሳጥብ (ያጣቢ ዎች አለቃ ") ።
- አሳጣች፡ አደገች ልጃገረድ ሳትታጭ ቈየች እናት አባቷን ኣሳሰበች።
- አሳጣነ (አዕጠነ)፡ ዕጠኑ አለ (አስ ጨሰ ጪስ ኣሰጠ ኣስቀበለ ") ።
- አሳጣኝ (አኅጥአኒ)፡ ባዶዬን አስቀ ረኝ ("ዐጣ" ብለኸ "ኣሳጣን" አስተውል ") ።
- አሳጣኝ (አዕጣኒ)፡ ያሳጠነ/የሚያሳ ጥን (ንፍቅ ዲያቆን ቄስ እያጠነ ሲዞር እ ፊት እፊት የሚቀድም ") ።
- አሳጣፊ፡ ያሳጠፈ/የሚያሳጥፍ ።
- አሳጨቀ (አዕጸቀ)፡ አስገባ/አስከ ተተ/አሳጀበ ።
- አሳጪ፡ እንዲያጭ እንድትታጭ አስ ደረገ ("እወዳታለኹ እወደዋለኹ ቃሌ ነው ፈቃዴ ነው" አሠኘ ") ።
- አሳጪ፡ ያሳጣ/የሚያሳጣ (ስም አጥፊ) ። "ካሳጪ ማራኪ ይሻላል" እንዲሉ። "ፍልስጣን" እይ።
- አሳፈረ (አኅፈረ)፡ አዋረደ አሰቀጠጠ ("(፪ሳሙ. ፲፫፥ ፳፪፡ መዝ. ፵፬፥ ፯ - ፱፡ ሉቃ. ፲፫፥ ፲፯)")
- አሳፈረ፡ ሰውን ወደ ተሽከርካሪና ወደ በራሪ መኪና ላይ አወጣ ።
- አሳፈረ፡ አላካ/አማጠነ።
- አሳፈረ፡ አስፈራ አስከበረ ።
- አሳፈፈ፡ አስከረከመ ኣስቀፈፈ አስክመመ አስቈረጠ ።
- አሳፋ (አስተሳፈየ)፡ አጣቀመ/አደረተ/አዘማዘመ ።
- አሳፋሪ (ሮች)፡ ያሳፈረ/የሚያሳፍር/የምታሳፍር (አዋራጅ - ምሳ. ፲፪፥ ፬) ።
- አሳፋሪ፡ ያሳፈረ/የሚያሳፍር (የተሳፋሪ ሸኚ) ።
- አሳፋፊ፡ ያሳፈፈ የሚያሳፍፍ፡ አስከርካሚ ባለመጣፍ ።
- አሴሰነ፡ አቀነዘረ/አሸረሞጠ ።
- አሤረ፤ዐደመ (ሠየረ፡ ሤረ)።
- አስ (አ)፡ የማስደረግ ልማድ፡ ፍችው በቁም ቀሪ ። በላ አስበላ፡ ጠጣ አስጠጣ፡ ተነከረ ኣስተነከረ ። ይኸውም ግዴታንና ጥናትን ያሳያል ።
- አስሖደደ፡ አሳረሰ/አዘራ/አሳረመ/ አሳጨደ/አስወቃ ።
- አስሖደደ፡ አስጦመ/አስራበ/አስጠማ ።
- አስሖዳጅ፡ ያስሖደደ/የሚያስሖድድ ("አ ስጧሚ") ።
- አስለመነ፡ አስማለደ፡ ለምኑልኝ፡ ኣስቀፈፈ፡ አስቧገተ ።
- አስለመጠ፡ (አልመጸ)፡ ለማጣ፡ አስደረገ ፣ አስጐበጠ።
- አስለመጠ፡ አስለዘበ፡ አስለሰለሰ።
- አስለመጠጠ፡ አስፈጀ፡ አስገረፈ፡ ሰፊ፡ አስደረገ ።
- አስለማ፡ ለም፡ አስደረገ ።
- አስለማኝ፡ ያስለመነ፡ የሚያስለምን ማስለመን፡ ማስተፈፍ፡ ማስቧገት ።
- አስለሰቀ፡ አስጨፈቀ።
- አስለሰነ፡ ለስኑ፡ አለ፡ አስቀባ፡ አስለቀለቀ ፣የልስን፡ ሥራ፡ አሠራ።
- አስለሳቂ፣ ያስለሰቀ፡ የሚያስለስቅ፡ አስመፋቂ ።
- አስለሳኝ፣ ያስለሰነ፡ የሚያስለስን ።
- አስለቀቀ፡ አስከፈተ፡ አስፈታ፡ አተወ፡ አስጣለ።
- አስለቃሽ ፣ ያስለቀሰ፡ የሚያስለቅስ።
- አስለቃቂ፡ ያስለቀቀ፡ የሚያስለቅቅ አስጣይ ።
- አስለቈደ፡ ድዳ፡ አስደረገ።
- አስለበጠ አስለጠፈ ("አስለጠጠ ማስለበጥ ማስለጠፍ ተለበጠ ተለጠፈ ተሸፈነ ለበሰ ተ ጌጠ ") ("ኢሳ. ፴፡ ፳፪") ።
- አስለነቀጠ፣ ለንቅጡ፡ አለ፡ አስፈጬ፡ ኣስላመ፡ አስለዘበ።
- አስለንቃጭ፡ ያስለነቀጠ፡ የሚያስለነ
- አስለከለከ፡ አስጠጣ ፥ —ለከለከ ።
- አስለከለከ፡ አስጠጣ፡ አስዋጠ።
- አስለከለከ፡ አስጠጣ/አስዋጠ/ለከለከ ።
- አስለከለከ፡ አሹለከለከ ፥ —ሰለከ ።
- አስለከለከ አሹለከለከ፡ ሰለከ።
- አስለከለከ፡ ኣፍለከለከ፡ ኣሹለከለከ።
- አስለከፈ፡ አስቀመሰ፡ አስነካ።
- አስለከፈ፡ አዠመረ፡ እሲያዘ።
- አስለኪ፡ ያስለካ፡ የሚያስለካ፡ አሸላጊ ።
- አስለካ፡ አስመጠነ፡ አሰፈረ፡ አሸለገ፡ እስከነዳ፡ አስረተመ።
- አስለኰሰ፡ አስተኰሰ።
- አስለኰፈ፡ ተመቺውን፡ የማይጐዳ፡ መቺውን፡ የማያስደስት፡ ምት፡ አስመታ።
- አስለኳሽ፡ ያስለኰሰ፡ የሚያስለኵስ፡ አስ
- አስለወሰ፡ አስላቈጠ፡ አሳሸ፡ አስቦካ።
- አስለወጠ፡ አሼጠ፡ አስቀየረ።
- አስለዋሽ፣ ያስለወሰ፡ የሚያስለውስ፡
- አስለዋጭ፡ ያስለወጠ፡ የሚያስለውጥ፡ አስዋያሪ ።
- አስለዘበ፡ አስደቀቀ፡ አሰለቀ፡ አስላመ።
- አስለዛቢ፡ ያስለዘበ፡ የሚያስለዝብ።
- አስለየ፡ አሳወቀ፡ አስለመደ፡ አስረዳ፡
- አስለየ፡ ኣስነጠለ፡ እስከፈለ ።
- አስለዪ፡ ያስለየ፡ የሚያስለይ፡ አስተማሪ ።
- አስለደፈ፡ አስለጠፈ።
- አስለገሰ፡ አሰጠ፡ አስቸረ።
- አስለገደ፡ ኣስወተፈ፡ አስቀረቀረ፡ ኣስ መረገ ።
- አስለገገ፡ አስወጣ፡ አስለቀቀ፡ ልጋግን።
- አስለጊ፡ ያስለጋ፡ የሚያስለጋ፡ አስመቺ።
- አስለጋ፡ አስቀላ፡ አስመታ።
- አስለጐመ ("አስለባጅ ያስለበደ የሚያስለብድ አስ ለጓሚ ማስለበድ ማስለጐም ማሰፋት ማስለበጃ ጊዜና መሣሪያ ዋጋ ተለበደ ") ("ተለበጠ") ።
- አስለጐመ፡ ልጓም፡ አስጐረሠ፡ ጥይት፡ ኣስቀረቀረ።
- አስለጐመ፡ አሰፋ፡ አስለበደ።
- አስለጐደ፡ አስለደፈ፡ አስለጠፈ።
- አስለጓሚ፡ ያስለጐመ፡ የሚያስለጕም፡ የለጓሚ፡ ጌታ፡ አለቃ፡
- አስለጠጠ፡ አሠነበጠ፡ አስነጠለ።
- አስለጠጠ፡ አሳበ፡ አስጐተተ።
- አስለጣጭ፡ ያስለጠጠ፡ የሚያስለጥጥ፡ አስነጣይ፡ አስጐታች።
- አስለፈለፈ፡ አስቀባጠረ፡ ብዙ፡ አናገረ።
- አስለፊ፡ ያስለፋ፡ የሚያስለፋ።
- አስለፋ፡ (አልፍዐ)፡ አስረገጠ፡ እዚ
- አስለፍላፊ፡ ያስለፈለፈየሚያስለፈልፍ።
- አስለፍልፍ፡ አናጋሪ፣ መድኀኒት፡ እስ
- አስላሊ፡ ያስላላ፡ የሚያስላላ ።
- አስላላ፡ ልል አስደረገ ፥ —ላላ ።
- አስላላ ልል አስደረገ፡ ማስላላት፡ ማሰላሰል ።
- አስላላ፡ ልል፡ አስደረገ ።ሰላን፡ እይ ።
- አስላላ፡ መላልሶ አሰላ (አወጣ/አወረደ/አሰላሰለ) ። "ዛሬ ሌሊት እከሌ ነገር ሲያስላላ ዐደረ።"
- አስላላ፡ አሰላሰለ ፥ —ሰላ ።
- አስላመ፡ አስደቈሰ፡ አሰለቀ፡ አስለዘበ፡ ኣስለነቀጠ ።
- አስላሚ፡ ያሰለመ/የሚያሰልም ("አስላሚ የሚያስልም ላመ") ።
- አስላሰ፡ ላሱ፡ አለ፡ አስመገበ።
- አስላሰ፡ መሬትን፡ አሳመ።
- አስላሰ፡ አስጨመረ፡ አስገባ።
- አስላቀቀ፡ አስፈቀደ፡ ማገትን።
- አስላከ፡ መልክቱ፡ እንዲላክ፡ አስደረገ።
- አስላከከ፡ አስቀባ፡ አስደለሰ፡ አስገጠመ።
- አስላገ፡ ኣስፋቀ፡ ኣስለዘበ፡
- አስላጠ፡ (አልሐጸ)፡ አስገፈፈ፡ ዕራቍት፡ አስደረገ፡ ዛፍን፡ ሰውን።
- አስላጩ፡ ራስ፡ ቅልን፡ አስፈገፈገ፡ ጠጕርን፡ አስጠረገ ።
- አስላጪ፡ ያስላጩ፡ የሚያስላጭ፡ ልጁን ።
- አስላጭ፡ ያስላጠ፡ የሚያስልጥ።
- አስላፈ ፣ አስፈጀ፡ አስላጠ፡ ገላን።
- አስላፈ፡ አስለየ፡ አስገፈፈ፡ ልጥን።
- አስል፡ አመንምን፡ ኣቅጥን።
- አስል፡ ያስኰበለለ/የሚያስኰበልል።
- አስመለመለ፡ አስለየ/አስመረጠ።
- አስመለመለ፡ አስኰተኰተ/አስቈረጠ/አስቀነጠበ።
- አስመለሰ፡ ቋቅ አሠኘ/አስተፋ/አስቀረሸ።
- አስመለሰ፡ አስታወከ (ቋቅ አለ/ተፋ/ቀረሸ)፡ የበላውን በገባበት አስወጣ (እንደ ጕማሬ) ።
- አስመለሰ፡ አስጠመዘዘ/አዞረ። "የናት ልመና ፊት አያስመልስ ዐንገት አያስቀልስ" እንዲሉ።
- አስመለሰ፡ የተወሰደን ነገር እንዲመለስ አስደረገ፡ ወደ ወጣበት አስመጣ (፩ሳሙ. ፴፥፲፰-፲፱) ።
- አስመለከ፡ አስከበረ/አመሰገነ፡ ወዳምላክ አስለመነ።
- አስመለከተ፡ ምልክት አጻፈ።
- አስመለከተ፡ አሳሰበ/አስጠቈመ/አስገለጠ። "ምን አስመለከተኸና (አሳሰበኸና) እንዲህ ያለ ሥራ ሠራኸ?"
- አስመለከተ፡ አስጠቈመ/አስነገረ/አስገለጠ/አሳየ።
- አስመለካች፡ ያስመለከተ/የሚያስመለክት።
- አስመለጠ፡ አስነጠቀ/አስፈተገ/አሳወደ/አስላጠ/አስቀረፈ።
- አስመለጠነ፡ ዜማ አሳወቀ/አስመራ።
- አስመላ/አስሞላ፡ አስጨመረ፡ ምሉ/ሙሉ አስደረገ።
- አስመላሽ፡ ያስመለሰ/የሚያስመልስ (አስታዋኪ) ።
- አስመላኪ፡ ያስመለከ/የሚያስምልክ (አስመስጋኝ) ።
- አስመላጭ፡ ያስመለጠ/የሚያስመልጥ።
- አስመልማይ፡ ያስመለመለ/የሚያስመለምል (አስኰትኳች/አስመራጭ) ።
- አስመልካች፡ ያስመለከተ/የሚያስመለክት (አሳሳቢ) ።
- አስመልጣኝ፡ ያስመለጠነ/የሚያስመለጥን (የዜማ መምር) ።
- አስመሠረተ (አመሥረተ)፡ መሠረት አስጣለ/አስበጀ/አሠራ/አስገነባ።
- አስመሰከረ፡ ሊያስተምር ይችላል አሠኘ።
- አስመሰከረ፡ ምስክርን አስነገረ (ነሐ. ፲፫፥፳፩፡ ምሳ. ፲፫፥፲፡ ኤር. ፮፥፲) ።
- አስመሰገ፡ አስተኛ።
- አስመሰገ፡ አስገባ/አስጨመረ።
- አስመሰገነ፡ ምስጋና አሰጠ/አስሞገሰ ("እኔ አባቴን አስመሰግነዋለኹ" እንዳለ ሬሳ አውጭ ልጅ - አባቱ መቃብር እየከፈተ ሬሳ ይገፋል ልጁ ግን ሬሳውን ወስዶ እወጣበት ቤት በር ላይ ይጥለዋል ይባላል) ።
- አስመሳይ (ዮች)፡ ያላደረገውን ያደረገ መስሎ የሚናገር/የሚሠራ (ግብዝ) ።
- አስመሳይ፡ ያላደረገውን ያደረገ መስሎ የሚናገር/የሚሠራ (ግብዝ) ።
- አስመሳጊ፡ ያስመሰı/የሚያስመስግ።
- አስመሥራች፡ ያስመሠረተ/የሚያስመሠርት።
- አስመስካሪ፡ ያስመሰከረ/የሚያስመክር።
- አስመስጋኝ፡ ያስመሰገነ/የሚያስመስግን (ደግ ልጅ/አሽከር) ።
- አስመረመረ፡ አስጠየቀ/አስፈተነ/አስፈተሸ/አስፈለገ/አስቈፈረ።
- አስመረረ፡ አጠቃ/አሳዘነ/አስቈጣ (መዝ. ፸፯፥፲፯፡ ኢሳ. ፷፫፥፲፡ ዕብ. ፫፥፲፮) ።
- አስመረቀ፡ አስባረከ ("ዐዲስ ቤትን ያለም የደስታ ቤት ይኹን" አሠኘ - ዘዳ. ፳፥፭) ።
- አስመረቀ፡ ወድቆ ጠፍቶ ያገኘውን አስፈቀደ ("ውሰደው ላንተ ይኹን" አስባለ) ።
- አስመረተ፡ ምርት አስደረገ።
- አስመረዘ፡ መርዝ አስጨመረ/አስደነገረ/አስጠላ።
- አስመረገ፡ አስለጠፈ/አስደፈነ።
- አስመረገገ፡ አስጐመዘዘ።
- አስመረጠ፡ "ምረጡ" አለ፡ አስወደደ/አስለየ/አስመለመለ።
- አስመሪ፡ ያስመራ/የሚያስመራ (የመሪና የተመሪ አዛዥ) ።
- አስመራ (አምርሐ)፡ መሪን በመሪ ፊት አስቀደመ።
- አስመራ፡ በሐማሴን ውስጥ ያለ ከተማ። "አስመራ" በግእዝ "አሳመራት" ወይም ሴቶች...
- አስመራሪ፡ ያስመረረ/የሚያስመርር (አሳዛኝ) ።
- አስመራቂ፡ ያስመረቀ/የሚያስመርቅ (አስፈቃጅ) ።
- አስመራዥ፡ ያስመረዘ/የሚያስመርዝ (እስጠሊ) ።
- አስመራጊ፡ ያስመረገ/የሚያስመርግ (አስለጣፊ/አስደፋኝ) ።
- አስመራጭ፡ ያስመረጠ/የሚያስመርጥ።
- አስመርማሪ፡ ያስመረመረ/የሚያስመርምር (አስፈታሽ) ።
- አስመርኳዥ፡ ያስመረኰዘ/የሚያስመረኵዝ።
- አስመሸ፡ እንዲመሽ አስደረገ (ጊዜ አሳለፈ - ለፍ) ።
- አስመሸተ፡ መሸታ አስደረገ (መሽቱ አለ፡ መሸታ አሼጠ) ።
- አስመሸገ፡ መሽጉ አለ (ዐጥር አሳጠረ/ቅጥር አስቀጠረ/አስካበ/አስከበበ/አስማሰ/አስጐደበ/ዕርድ አስበጀ) ።
- አስመታ፡ አሰረረ።
- አስመታ፡ አስበጠበጠ።
- አስመታ፡ አስወጋ/አስገደለ።
- አስመታ፡ አስጠዘለ/አስወገረ/አስደበደበ (ጠበል አስመታ፡ አስጠመቀ - እሳት አስመታ፡ አንቃቃ፡ ሙቀት አስቀበለ) ።
- አስመቺ፡ ያስመታ/የሚያስመታ (አስደብዳቢ) ።
- አስመነመነ፡ አድቀሰቀሰ።
- አስመነሸ፡ አስወጋ/አስወረወረ።
- አስመነተፈ፡ አስቀማ/አስነጠቀ።
- አስመነታ፡ መንታ ኹለት ዐሳብ አስደረገ።
- አስመነቸከ፡ አስጨቀጨቀ/አስነዘነዘ።
- አስመነነ፡ አስናቀ/ኣስተወ (ትዳርን/ንብረትን) ።
- አስመነዘረ፡ አስበተነ/አሸረፈ (አንዱን ገንዘብ ለጥቃቅን ነገር አስለወጠ) ።
- አስመነዘረ፡ ኣሸረሞጠ (ሸርሙጣ/አመንዝራ አደረገ - ፪ዜና. ፳፩፥፲፫) ።
- አስመነደረ፡ አሳነጠ/አስገነባ/አሠራ።
- አስመነደበ፡ አስመታ/አስደበደበ።
- አስመነደበ፡ አስቈረጠ/አስመደመደ።
- አስመነደገ፡ አስነጠቀ።
- አስመነገለ፡ አስነገለ።
- አስመነገገ፡ አሲያዘ/አሳሰረ (የከብትን መንጋጋ) ።
- አስመነጠረ፡ አስጠረገ/አሳወደ/አሳጠበ/አስገረፈ።
- አስመነጠቀ፡ አስነጠቀ/አስቀማ/አስወሰደ።
- አስመነጠቀ፡ አስወጣ/አስኬደ።
- አስመነጨረ፡ አስጫረ/አስበተነ።
- አስመነጨቀ፡ አስመነቸከ/አስቀጨቀ/አስነዘነዘ።
- አስመነጨቀ፡ አስመነጠቀ/አስለቀቀ።
- አስመናኝ፡ ያስመነነ/የሚያስመንን (አስናቂ) ።
- አስመንታፊ፡ ያስመነተፈ/የሚያስመነትፍ (አስቀሚ) ።
- አስመንቻኪ፡ ያስመነቸከ/የሚያስመነችክ (አስጨቅጫቂ) ።
- አስመንዛሪ፡ ያስመነዘረ/የሚያስመነዝር (አሸራፊ) ።
- አስመንጣሪ፡ ያስመነጠረ/የሚያስመነጥር (አስጠራጊ/አሳጣቢ/አስገራፊ) ።
- አስመንጣቂ፡ ያስመነጠቀ/የሚያስመነጥቅ (አስነጣቂ) ።
- አስመኚ፡ ያስመኘ/የሚያስመኝ (አስከጃይ) ።
- አስመከረ፡ ምከሩ/ምከሩት አለ፡ ምክር አስደረገ/አሰጠ።
- አስመከተ፡ አስቀየደ፡ አስጋረደ፡ አስከለለ።
- አስመከነ፡ መካን አስደረገ።
- አስመኪ፡ ያስመካ፡ የሚያስመካ፡ አስከባሪ ።
- አስመካ፡ ማያን አስነገረ (መካ) ።
- አስመካሪ፡ ያስመከረ/የሚያስመክር፡ መኰንን/ንጉሥ።
- አስመካች፡ ያስመከተ/የሚያስመክት፡ አስጋራጅ/አስከለል ።
- አስመዘመዘ፡ አስለዘለዘ፡ አስራሰ ።
- አስመዘመዘ፡ አስለዘለዘ፡ አስራሰ ።
- አስመዘመዘ፡ አስቀጠነ፡ አስረዘመ።
- አስመዘመዘ፡ አስተለተለ፡ አስተረተረ፡ ኣሳበ፡ ኣስመዘዘ ። እሾኻም ።
- አስመዘመዘ፡ አስተለተለ፡ አስተረተረ፡ ኣሳበ፡ ኣስመዘዘ ። እሾኻም ።
- አስመዘቀ፡ አስነቀለ።
- አስመዘበረ፡ አስፈረሰ፡ አስናደ።
- አስመዘነ፡ በሚዛን፡ አስለካ፡ አሰፈረ፡ እስመጠነ ።
- አስመዘዘ፡ አስጐተተ፡ አስነቀለ፡ ("ዘሌ. ፳፮፡ ፴፫") ።
- አስመዘዘ፡ ኣስቈጠረ፡ ዘርን።
- አስመዘገበ፡ አመዝገብ አስገባ/አጻፈ ።
- አስመዛኝ፡ ያስመዘነ፡ የሚያስመዝን።
- አስመዛዥ፡ ·ያስመዘዘ፡ የሚያስመዝዝ፡ አስነቃይ ።
- አስመዝማዥ፡ ያስመዘመዘ፡ የሚያስመዝምዝ፡ አስተልታይ፡ አስረዛሚ።
- አስመየደ; አስበጠረ፡ አስጐተነ።
- አስመደመደ ፣ አስቈረጠ · አስጠረገ፡ ኣስናደ፡ አስፈረሰአስደለደለ፡ ትክክል፡ አስደረገ ።
- አስመደበ፡ አስወሰነ፡ አስደነገገ።
- አስመደበ፡ አስደለደለ፡ መደብ፡ አሠራ።
- አስመዳቢ፡ ያስመደበ፡ የሚያስመድብ፡ አስወሳኝ
- አስመገመገ፡ አስጠባ፡ አስለገለገ።
- አስመገዘ፡ (አግዝዐ)፡ አስገዘገዘ፡ አስከረከረ፡ በመጋዝ፡ አስቈረጠ፡ አሠነጠቀ ።
- አስመጋዥ፡ ያስመገዘ፡ የሚያስመግዝ፡ አስገዝጋዥ፡ አስከርካሪ።
- አስመግማጊ፡ ያስመገመፃ፡ የሚያስመገምግ ።
- አስመጠነ፡ አስለካ፡ አስመዘነ፡ አስገመተ፡ አስገመገመ ።
- አስመጠወተ፡ አስመጽወተ፡ ምጧት፡ አሰጠ፡ አሳደለ።
- አስመጠጠ፡ አሳበ፡ አስጐተተ፡ አስጠጣ፡ አስጨለጠ፡ አስጠባ ። (ተረት)፡ ወጥ፡ ቢጣፍጥ፡ እጅ፡ ያስመጥጥ፡ ጥጥ ።
- አስመጣ፡ አስጋዘ፡ አስገባ፡ አስቀረበ፡ ("፪ዜና. ፳፱፡ ፬፡ ግብ. ሐዋ. ፲፡ ፭") ።
- አስመጣኝ፡ ያስመጠነ፡ የሚያስመጥን, አስለኪ ።
- አስመጣጭ፡ ያስመጠጠ፡ የሚያስመጥጥ ።
- አስመጥዋች፡ አስመጽዋች፡ ያስመጠወተ፡ የሚያስመጠውት ።
- አስመጪ፡ ጭ፡ ያስመጣ፡ የሚያስመጣ ።
- አሥሚ፡ ያሠማ/የሚያሠማ (አጋይማሥማት፡ ማሞቅ/ማጋል/ማጋም ።
- አስማለ (አምሐለ)፡ አማለ፡ አስገዘተ፡ አዘጋ ሳንቃን።
- አስማሚ፡ ያስማማ/የሚያስማማ (አስታሪቂ ሽማግሌ/ጨዋ/ደላላ) ።
- አስማማ፡ ለወሰ፡ አዋሐደ፡ አዋዋደ።
- አስማማ፡ ዕርቅ አደረገ፡ ፍቅር አወረደ፡ እስታረቀ፡ ገላገለ።
- አስማማ፡ ገዢና ሸያጭን አገናኘ ("አንተ በዚህ ሽጥ፡ አንተም በዚህ ግዛ" አለ፡ ይህን ነገር በ፪ቱም ወገን አስወደደ) ።
- አስማሰ፡ አስኳተ/አስቈፈረ/አስጐደፈረ/አስጐደጐደ።
- አስማረ (አምሐረ)፡ አማለደ/ምሕረት አሰጠ/አስተወ/አስለቀቀ (ሮሜ. ፰፥፴፬) ።
- አስማረከ፡ እሲያዘ/አዘረፈ/አስወሰደ።
- አሥማሪ፡ ያሠመረ/የሚያሠምር (ጸፊ) ።
- አስማሪ፡ ያስማረ/የሚያስምር (አማላጅ) ።
- አስማሪ፡ ያስጨረ የሚያስጭር፡ አስቧጫሪ።
- አስማራኪ፡ ያስማረከ/የሚያስማርክ (ዘራፊ) ።
- አስማሽ፡ ያስማሰ/የሚያስምስ (እስቈፋሪ) ።
- አስማቀቀ፡ አስደከመ (መከራ አስቀበለ) ።
- አስማተኛ (ኞች)፡ ዝኒ ከማሁ (አስማት ደጋሚ/ዐዚመኛ/ርተኛ/አጋንንት ጠሪ/ሙት አማጣኝ - ዘዳ. ፲፰፡ ፲፡ ሚክ. ፭፡ ፲፪) ።
- አስማተኛነት፡ አስማተኛ መኾን (ናሖ. ፫፡ ፬) ።
- አስማታም፡ ባለአስማት ጠንቋይ ዐዚ...
- አስማት፡ ስሞች (ግእዝ) ።
- አስማት፡ ስሞች ስም ።
- አስማት፡ ያጋንንት ስሞች (የጠንቋይ ክታብ - ጀጀጀ/ጨጨጨ/ሸሸሸ የሚል) ። "ጨርጮቤ ዐይነ ጥላ መፍትሔ ሥራይ። መንድግ መስተፋቅር ግርማ ሞገስ መግረሬ ፀር፡ ሩሕ ከናንህ የስጡ ስጡ" የመሰለው ኹሉ።
- አስማይ፡ ያስማለ/የሚያስምል፡ አማይ።
- አስማገደ፡ እፍም፡ ላይ፡ አስጨመረ፡ ኣስገባ፡ አስዶለ።
- አስማጠ፡ ዕሕ፡ ኣሠኘ።
- አስማጭ የሚያስምጥ፡ (ማጠ)፡ አስማጠ ።
- አስማጭ፡ ያሰመጠ/ያሰጠመ (የሚያሰጥም አስጣሚ) ።
- አስሞለቀቀ፡ አዛቀ/አስነቀለ።
- አስሞረደ፡ አስፈገፈገ/አሳለ/አስለዘበ/አዘረዘረ።
- አስሞራጅ፡ ያስሞረደ/የሚያስሞርድ (አስለዛቢ) ።
- አስሞሸለቀ፡ አስገፈፈ/አስፈጀ/አስላጠ/አሰረቀ።
- አስሞሸረ፡ ሞሽሩ አለ (አሸለመ/አስጌጠ) ።
- አስሞተ፡ ሞት፡ አስፈረደ፡ አስገደለ። ያስሞትኻል፡ አያስሞተኝም፡ እንዲል፡ ባለዶምና፡ ገዳይ ።
- አስሞከረ፡ አስፈተነ/አስበገረ/አዠመረ።
- አስሞከተ፡ አስወቀጠ/አስቀጠቀጠ/አስቀለበ ሙክት አስደረገ።
- አስሞካሪ፡ ያስሞከረ/የሚያስሞክር፡ አስበጋሪ።
- አስሞካች፡ ያስሞከተ/የሚያስሞክት።
- አስሞዠቀ፡ አስጠረገ፡ አስጨረ፡ አስፈገፈገ ።
- አስሞዣቂ፡ ያስሞዠቀ፡ የሚያስሞዥቅ፡ አስጫሪ።
- አስሞጀረ፡ አስጨመረ።
- አስሞጃሪ፡ ያስሞጀረ፡ የሚያስሞጅር፡ ያስጨመረ፡ የሚያስጨምር ።
- አስሞገተ፡ አስጠየቀ፡ አስነዘነዘ፡ አስጮቀቀ።
- አስሞገደ፡ አስወገጠ፡ አሳወከ
- አስሞጋች፡ ያስሞገተ፡ የሚያስሞግት።
- አስሞጨለፈ፡ አሰረቀ፡ አስነጠቀ፡ አስቀማ፡ አስወሰደ።
- አስሰሰ፡ አስላሰሰ/አስነቀለ።
- አስሶኪ፡ ያስቦካ የሚያስቦካ የሚያስለውስ፡ አስለዋሽ ።
- አስረመመ፡ ዝም አሠኘ፡ አርምሞ ኣሲያዘ።
- አስረመሰ፡ አስለወሰ፡ አስቦካ።
- አስረመሰ፡ አስወሸቀ፡ አስነከረ፡ እዘፈቀ፡ አስራሰ።
- አስረመረመ፡ አስጠቀጠቀ፡ አስረገጠ።
- አስረመደ፡ አስነካ፡ አስረገጠ።
- አስረመደደ፡ አስረመጠጠ።
- አስረመጠ፡ አሸጐጠ፡ አስጠበሰ፡ ርሚጦ አስበጅ።
- አስረመጠጠ፡ አስረገጠ፡ አስደፈጠጠ።
- አስረምራሚ፡ ያስረመረመ፡ የሚያስረመርም፡ ኣስጠቅጣቂ።
- አስረሳሽ፡ የሴት ፣ ስም ።
- አስረስ፡ ሴ፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ የሰው፡
- አስረሽ፡ (አርሳዒ)፡ ያስረሳ፡ የሚያስ
- አስረሽ፡ ከፍ አድርገሽ ።
- አስረቀረቀ፡ አስመታ አስለቀሰ፡ ረ ቀረቀ ።
- አስረቀረቀ፡ አስመታ፡ አስደቀደቀ። አስረቀረቀ፦ እንሠቀሠቀ፡ አስለቀሰ።
- አስረቀረቀ/አስመታ/አስለቀሰ፡ ረቀረቀ ።
- አስረቀቀ፡ ረቂቅ አስደረገ፡ አስጣፈ።
- አስረበረበ፡ አስረጫ ።
- አስረበረበ፡ አስደረደረ ።
- አስረበደ፡ ኣስቸኰለ አረበደ ።
- አስረበዶ፡ አስቸኰለ አስቈጣ አስለፈለፈ ።
- አስረቢ፡ ያስረባ/የሚያስረባ ("የቅኔ መምር፡ አስጠቃሚ ") ።
- አስረባ (አርብሐ)፡ አስወለደ/አስበዛ ።
- አስረባ፡ አስጠቀመ ("ጥቅም አሰጠ ") ።
- አስረባየ፡ አስረገጠ/አስረመረመእስጠ ቀጠቀ ።
- አስረተ (አማረየ/አስተማረየ)፡ አስጠነቈለ (ርት አስደረገ) ።
- አስረታ፡ አንዱ እንዲረታ እንዲያሸንፍ ሌላው (ጥረ) እንዲረታ እንዲሸነፍ አስደረገ።
- አስረቺ፡ ያስረታ፡ የሚያስረታ፡ ክስ ጠበቃ አውለኝ።
- አስረከሰ፡ (አርኰሰ) ርካሽ አስደረገ ዋጋ አሳጣ፡ አስናቀ።
- አስረከረከ፡ አስጐበጠ፡ ኣስወለገደ።
- አስረከበ፡ ሰጠ፡ አቀበለ፡ እሰው እጅ።
- አስረካሽ፡ ያስረከሰ፡ የሚያስረክስ፡ ኣስናቂ። (ሴት አስረካሽ) ገለሞታ ቀን የባሕር፡ ድር ውሃ የሚመስል።
- አስረካቢ (ቦች)፡ ያስረከበ፡ የሚያስረክብ፡ ሰው አቀባይ።
- አስረካቢነት፡ አስረካቢ መሆን።
- አስረካቢው፡ ያ ወይም የርሱ አስረ።
- አስረዘመ፡ አስበለጠ፡ አስበዛ ("(ኢዮ. 7፡ ")፡ "(ማቴ. 23፡ 5)") - አስበለጠ፡ አበዛ ("(ኢዮ. 7፡ ")፡ "(ማቴ. 23፡ 5)").
- አስረዛሚ፡ ያስረዘመ/የሚያስረዝም፡ ኣብላይ - ያስረዘመ/የሚያስረዝም፡ በላዩ ላይ ያለ።
- አስረዳ፡ ለጠ፣ አስጠና፣ አሳወቀ።
- አስረጀ (አእረገ)፡ አሮጌ አደረገ፡ አሸመገለ ።
- አስረጅ፡ የነገር አስተንካሪና። አዳም ከሲኦል ወጣ ስለ ርሱ ፈጣሪ ሙቷልና።
- አስረጅ፡ ያስረዳ፣ የሚያስረዳ፣ አሳዋቂ። (ባዕድ አስረጅ)፡ ከመደበኛው ቅኔ ሐሳብ የማይገጥም።
- አስረገመ፡ አስለየ/አስካደ ።ርጉም አሠኘ ።
- አሥረገረገ (አሕዘዘ)፡ ዋጠ ' አሰ ጠመ ።
- አሥረገረገ (አሕዘዘ)፡ ዋጠ ' አሰ ጠመ ።
- አስረገረገ፡ አሰጠመ ፥ —ሠረገ ።
- አስረገረገ፡ አሳወቀ, አስከተተ, አስመላ ("ሠረገን ተመልከት" - "ሠረገን ተመልከት").
- አስረገረገ፡ አስነቀነቀ ፥ —ረገረገ ።
- አስረገረገ፡ አስነቀነቀ, አስወዘወዘ.
- አስረገበ፡ አስላላ / አስጐረበ
- አስረገዘ፡ ኣፀነሰ/አስቋጠረ/እሲያዘ ።
- አስረገደ፡ አስጨፈረ / አዘለለ / አስረገጠ
- አስረገደ፡ አንቀጠቀጠ / አስፈራ / አራደ
- አስረገጠ (አርገፀ)፡ በርግ አስ መታ እስደበደበ ሰውን ።
- አስረገጠ፡ መሬትን አስጠቀጠቀ/አስረ መረመ ።
- አስረገጠ፡ አስጨፈረ/አዘለለ ።
- አስረገጠ፡ እውነት አስደረገ/እስቲነከረ/አስተካከለ ። (ተረት)፡ "ሳያስረግጡ ወሬ ሳይገድሉ ጐፈሬ ።አንድ ምስክር አያስደነግጥ አንድ ዐይን እያስረግጥ" ።
- አስረገፈ፡ አስወደቀ/አስጣለ ።
- አስረጋሚ፡ ያስረገመ/የሚያስረግም ("ክፉግብር አስካጅ ") ።
- አስረጋዥ፡ ያስረገዘ/የሚያስረግዝ ወንድ ተባት ። (ተረት)፡ "ላስረጋዥም ያምረዋል" ።
- አስረጋጅ፡ ያስረገደ / የሚያስረግድ ("እስጨፋሪ አስረጋጭ")
- አስረጋጭ (ጮች)፡ ያስረገጠ/የሚያ ስረግጥ ("አስጨፋሪ ኣሸብሳቢ ደብተራ ጕኔ መኰንን ") ።
- አስረጋጭነት፡ አስረጋጭ መኾን ("አስ ሠፋሪነት ") ።
- አስረጋፊ፡ ያስረገፈ/የሚያስረግፍ ("አስ ጣይ ") ።
- አስረጠበ፡ ርጥብ አስደረገ። አስረጠበ፦ ርጥባን አሰጠ፡ አስቀለተ፡ አስረዳ፡ አሳገዘ።
- አስረጠጠ፡ ኦሳመቀ፡ አስጨቈነ፡ አስወ።
- አስረጣቢ፡ ያስረጠበ፡ የሚያስረጥብ፡ እቀላች።
- አስረጨ (አርቀየ)፡ አስፈነጠቀ፡ አስበተነ፡ አስነዛ፡ አስወረወረ - አስረጨ፡ አስበተነ፡ አስነዛ፡ አስወረወረ።
- አስረጪ፡ ያስረጫ/የሚያስረጭ (ቤትን ዐራስን) - የሚያረጭ (ቤትን/ራሱን) ።
- አስረፈረፈ፡ አስነሰነሰ፡ አስረበረበ፡ አስጐዘጐዘ።
- አስረፈቀ፡ ቸል አሠኘ፡ ጋብ አስደረገ ሰውን ነገርን።
- አስረፈደ፡ ረፋድ እስኪኾን አስቈየ፡ አዘገየ።
- አስረፋቂ፡ ያስረፈቀ፡ የሚያስረፍቅ።
- አስረፋጅ፡ ያስረፈደ፡ የሚያስረፍድ።
- አስራመመ፡ አስጠረገ፡ አስፈገፈገ፡ አሳጠበ።
- አስራማሚ፡ ያስራመመ፡ የሚያስራምም፡ አሳጣቢ።
- አስራሰ፡ (አርሐሰ)፡ ፡ አስነከረ፡ አስረ
- አስራሶ (አስራባዊ)፡ ከፈሳሽ ከረግረግ አጠገብ የሚነሣ ነጭ የወባ ትንኝ። ሲበዛ "አስራቦች" ይላል ።
- አስራሪ፡ ያሰረረ/የሚያሰር (ጣጂ) ።
- አስራቀ፡ አስገለለ፡ አስወገደ፡ አስለየ፡ አስነጠለ። እከሌ እከሌን ውቃቢ አስራቀው።
- አሥራቂ፡ ያሠረቀ/የሚያሠርቅ (ቄስ) ።
- አስራቂ፡ ያስራቀ፡ የሚያስርቅ፡ አስገላይ አስወጋጅ ያየ።
- አስራቈተ (አዕረቀ)፡ አስገፈፈ አሳ ረዘ (ባዶ ገላ አስደረገ ") ።
- አስራቈተ፡ አሳረዘ ዐረቀ ።
- አስራበ (አርኀበ)፡ መብል ከለከለ ባዶ አደረገ ("ምግብ ኣሻ አስፈለገ ብላ ብላ አሠኘ ") ("(ምሳ. ፴፥ ፫)") ።
- አስራቢ (አርኃቢ)፡ ያስራበ/የሚያ ስርብ ሰው/መጠጥ ።
- አስራብ፡ ፈሳሾች ።
- አስራቦ፡ የወባ ትንኝ ፥ —ሰረበ ።
- አሥራጊ፡ ያሠረዝ/የሚያሠርግ።
- አሥራጊ፡ ያሠረዝ/የሚያሠርግ።
- አሥራጺ፡ ያሠረጸ/የሚያሠርጽ (የአብ አካል) ።
- አሥር፡ በቁሙ፡ ዐሥር።
- አሥርግ፡ አክሳሪ/ወራሽ ("ሰርግ አ ሥርግ" እንዲሉ) ጠመ ።
- አስሮጠ፡ አስበረረ, አስጋለበ, አስፈረጠጠ - አስሮጠ, አስጋለበ, አፋጠነ።
- አስሯጭ፡ ያስሮጠ/የሚያስሮጥ፡ አስኦሮቢ - የሚያስሮጥ፡ ፈጣን ሮጣሪ።
- አስቀለለ (አቅለለ)፡ ቀላል አስደረገ አስጐደለ ።
- አስቀለሰ፡ አስመለሰ አስጐበጠ ። "የናት አማላጅ ዐንገት አያስቀልስ፡ ፊት አያስመልስ" እንዲሉ።
- አስቀለበ፡ አሲያዘ አስጨበጠ ።
- አስቀለበ፡ አስረዳ አስመገበ ።
- አስቀለበሰ፡ አሳጠፈ አሸነቀረ አስ
- አስቀለተ፡ አስረጠበ አሳገዘ ኣስረዳ ።
- አስቀለደ፡ አስተረበ አስፌዘ ።
- አስቀለጠ፡ አስመታ አስደበደበ ።
- አስቀለጠ፡ አስፈሰሰ፡ አስናደ አስፈረሰ ።
- አስቀለጠመ፡ አስመታ አሰበረ፡ ቅልጥ ምን ዕንጨትን ።
- አስቀለጠፈ፡ አስፈጠነ፡ በቶሎ አሠራ አ
- አስቀላ (አቅልዐ)፡ አስመታ አስለጋ ።
- አስቀላ፡ ቀይ አስደረገ ።
- አስቀላ፡ አስቈረጠ ።
- አስቀላሽ፡ ያስቀለሰ/የሚያስቀልስ (አስ ጐባጭ ") ።
- አስቀላወጠ፡ የሰው ማድ አስከጀለ ።
- አስቀላጅ፡ ያስቀለደ/የሚያስቀልድ ።
- አስቀልባሽ፡ ያስቀለበሰ/የሚያስቀለብስ (አስቀናፊ ") ።
- አስቀመለ፡ ቅማል አስለቀመ/አስገደለ ።
- አስቀመመ፡ ቀምሙ አለ፡ አስደባለቀ አስቀላቀለ ።
- አስቀመሰ፡ አስለከፈ ።
- አስቀመሰ፡ አስመታ ።
- አስቀመረ፡ አስቈጠረ፡ አስመደበ አስለየ አስከፈለ ።
- አስቀመቀመ፡ አሰፋ አዘመዘመ ።
- አስቀመጠ፡ አስቀዘነ ።
- አስቀመጠ፡ አኖረ ፥ —(ቀመጠ) ።
- አስቀመጠለ፡ አሳረደ አስጐመደ ።
- አስቀመጠለ፡ አስጐደለ ።
- አስቀሚ፡ ያስቀማ/የሚያስቀማ (አስነጣቂ ") ።
- አስቀማ (አቅምሐ)፡ አስነጠቀ አስወ ሰዶ ።
- አስቀማሚ፡ ያስቀመመ/የሚያስቀምም ።
- አስቀማይ፡ ያስቀመለ/የሚያስቀምል (አስ ለቃሚ አስገዳይ ") ።
- አስቀማጭ (ጮች)፡ ያስቀመጠ የ ሚያስቀምጥ (አኗሪ ሰው አስቀዛኝ ኮሶ አን ግሊዝ ጨው ጕሎ ዘይት ሙስና መተሬ እንቆቆ ")፡ የመሰለው ኹሉ።
- አስቀማጭነት፡ አስቀማጭ መኾን፡ አኗሪነት ።
- አስቀምቃሚ፡ ያስቀመቀመ/የሚያስቀ መቅም (አዘምዛሚ ") ።
- አስቀምጣይ፡ ያስቀመጠለ/የሚያስቀመ ጥል (አስጐዳይ ") ።
- አስቀሠመ፡ አስለቀመ አሰበሰበ አስ መጠጠ ።
- አስቀሰረ፡ አስገተረ/አስቆመ ።
- አስቀሰቀሰ፡ አስበረበረ/አስፈተሸ ።
- አስቀሰቀሰ፡ አስነቀነቀ ።
- አስቀሠፈ፡ አስቀጪ አስቀጠፈ አስ ገደለ ።
- አስቀሣፈተ፡ አሳበለ አስቀባዠረ ።
- አስቀሣፊ፡ ያስቀሠፈ/የሚያስተሥፍ (አስገዳይ ") ።
- አስቀስቃሽ፡ ያስቀሰቀስ/የሚያስቀሰቅስ ።
- አስቀረ፡ አተረፈ አዳነ ("(ዘፍ. ፲፱፥ ፴፪ - ፴፬)") ።
- አስቀረ፡ እንዳይመጣ እንዳይሰጥ አደረገ፡ ከለከለ ።
- አስቀረረ፡ አስጠለለ አስቀዳ ።
- አስቀረቀረ፡ አስገባ ኣሸጐረ ።
- አስቀረቀበ፡ አሳሰረ አስወደነ አስጠ መረ ።
- አስቀረበ፡ ባጠገብ አስቀመጠ አስኖረ ።
- አስቀረበ፡ አስነዳ አስወሰደ ።
- አስቀረነተ፡ አሳሰረ አስቀረቀበ ።
- አስቀረደደ፡ አስቈረጠ አስቈረሰ አስገ መሰ ።
- አስቀረጠ፡ ከዕቃ ወይም ከገንዘብ ላይ አስከፈለ አስገበረ ዳኛው ። እንደ "አቀረጠም" ሲፈታ ይችላል ።
- አስቀረጠፈ፡ አስቈረጠ አስጠቀነ/አስ ደቀቀ ።
- አስቀረጪጪ፡ አስነከሰ ።
- አስቀረጸ፡ አስቀረጠ አስነጠጠ፡ አስፈ ለፈለ አስነቀሰ ።
- አስቀረፈ፡ አስላጠ አስመለጠ፡ አሰበረ ኣስፈለጠ ።
- አስቀሪ፡ ያስቀረ/የሚያስቀር ።
- አስቀራሪ፡ ያስቀረረ/የሚያስቀርር ።
- አስቀራቢ፡ ያስቀረበ/የሚያስቀርብ (አስ ነጂ ") ።
- አስቀራጭ፡ ያስቀረጠ/የሚያስቀርጥ (ቀረጥ አስከፋይ ") ።
- አስቀራፊ፡ ያስቀረፈ/የሚያስቀርፍ ።
- አስቀርቃሪ፡ ያስቀረቀረ/የሚያስቀረቅር (አሸጓሪ ") ።
- አስቀርዳጅ፡ ያስቀረደደ/የሚያስቀረ ድድ ።
- አስቀርጣፊ፡ ያስቀረጠፈ/የሚያስቀር ጥፍ ።
- አስቀቀለ፡ አስሞቀ አስፈላ አስበሰለ ኣስነፈረ፡ ወጥ አሠራ ።
- አስቀቀረ፡ ዦሮን አስመለሰ አስጣለ ።
- አስቀቀተ፡ አስነፈገ አሠሠተ ።
- አስቀቃይ፡ ያስቀቀለ/የሚያስቀቅል (አስፈሊ ") ።
- አስቀበለ፡ ስጥ እለ አስጠ ።
- አስቀበረ (አቅበረ)፡ ቅበሩ አለ (አስ ደፈነ በመቃብር አስኖረ ዐፈር አስመለሰ ") ።
- አስቀበቀበ፡ አሳረሰ አሳየመ አስለሰ
- አስቀበቀበ፡ አስቀጠቀጠ አሳደሰ ።
- አስቀበቀበ፡ አስተከለ አስቸከለ ።
- አስቀበተተ፡ አሳበጠ አስነፋ አስወጠረ ።
- አስቀቢ፡ ያስቀባ/የሚያስቀባ (አስለቅላቂ ") ።
- አስቀባ (አቅብዐ)፡ አስላከከ አስለ ቀለቀ አስደለሰ ።
- አስቀባሪ፡ ያስቀበረ/የሚያስቀብር (አስደ ፋኝ ") ።
- አስቀባይ፡ ያስቀበለ/የሚያስቀብል (አ ሰጪ ") ።
- አስቀባጠረ፡ አስለፈለፈ አናገረ ።
- አስቀብቃቢ፡ ያስቀበቀበ/የሚያስቀበቅብ (የሚያሳርስ አስቀጥቃጭ አሳዳሽ አስቸ ካይ ") ።
- አስቀተራ፡ አስጮኸ/አስጥሣ/አስጐ ደራ ።
- አስቀነሰ፡ አስጐደለ ።
- አስቀነቀነ፡ አስመረመረ አስፈተሸ ።
- አስቀነቀነ፡ አዠመረ አስቃኘ ።
- አስቀነተ፡ አስታጠቀ ።
- አስቀነዘፈ፡ አሳረደ አስቀነጠሰ አስመ ለመለ ።
- አስቀነዘፈ፡ አስፈሰሰ እንባን ።
- አስቀነደለ፡ አስበጣ አስቈረጠ ።
- አስቀነደበ፡ አስመታ ።
- አስቀነደበ፡ አስቀነደለ ።
- አስቀነጠሰ፡ አስቀነጠበ አስቈረጠ አስ ።
- አስቀነጠበ፡ አስቈረጠ አስበጠሰ አስቀ ነጠሰ ።
- አስቀነፈ፡ አሳጠፈ አስቀለበሰ አሸ በለለ ።
- አስቀና፡ ቀና አስደረገ፡ አስመቀኘ ምቀኛ አስነሣ፡ ቅናት አሳደረ ("(ሮሜ. ፲፩፥ ፲፩)") ።
- አስቀናሽ (አቅንአኪ)፡ ቀናተኛ አ ስደረገሽ ። "ቀናን" እይ ።
- አስቀናሽ፡ ያስቀነሰ/የሚያስቀንስ (አስጐዳይ ") ።
- አስቀናፊ፡ ያስቀነፈ/የሚያስቀንፍ (አስ ቀልባሽ ") ።
- አስቀንቃኝ፡ ያስቀነቀነ/የሚያስቀነቅን (አስመርማሪ ") ።
- አስቀንዳይ፡ ያስቀነደለ/የሚያስቀነድል ።
- አስቀንጣሽ፡ ያስቀነጠሰ/የሚያስቀነጥስ ።
- አስቀንጣቢ፡ ያስቀነጠበ/የሚያስቀነጥብ (አስበጣሽ ") ።
- አስቀኝ፡ ያስቀና/የሚያስቀና ።
- አስቀኝ፡ ያስቀኘ/የሚያስቀኝ (የቅኔ መምህር ") ።
- አስቀዘነ፡ አስቀመጠ ነዳ ።
- አስቀዘፈ፡ አስገፋ ኣስገለጠ አስከፈለ ።
- አስቀዛኝ፡ ያስቀዘነ/የሚያስቀዝን (ኮሶ የኖረ ቅቤ ሌላም በያይነቱ መድኅኒት፡ እንግሊዝ ጨው ጕሎ ዘይት ") ።
- አስቀዛፊ፡ ያስቀዘፈ/የሚያስቀዝፍ (የመርከብ አዛዥ ") ።
- አስቀየመ (ጥጸ)፡ አጸየፈ አስከፋ አሳ ዘነ አስኰረፈ ።
- አስቀየሰ፡ ኣስለካ አስመጠነ አስነደፈ አስበገረ ።
- አስቀየረ፡ አስለወጠ ።
- አስቀየደ፡ አሰከለ አስጋዳ ።
- አስቀየደ፡ አስከፈለ አስመከተ አስጋረደ ።
- አስቀየጠ፡ አዘነቀ አስቀላቀለ ኣስደ
- አስቀያሚ፡ ያስቀየመ/የሚያስቀይም (አጸያፊ አሳዛኝ ") ።
- አስቀያሚነት፡ አስቀያሚ መኾን ።
- አስቀያሪ፡ ያስቀየረ/የሚያስቀይር (አስ ለዋጭ ") ።
- አስቀያሽ፡ ያስቀየሰ/የሚያስቀይስ (አስ ለኪ ባለሕንጻ ") ።
- አስቀያጅ፡ ያስቀየደ/የሚያስቀይድ (አስ መካች አስጋራጅ ") ።
- አስቀያጭ፡ ያስቀየጠ/የሚያስቀይጥ ።
- አስቀደመ፡ ወደ ፊት አስደረገ አስኬደ አሳለፈ (በፊት አሠራ ") ።
- አስቀደሰ፡ አስቈረበ ።
- አስቀደሰ፡ አስባረከ ኣስከበረ አስመሰገነ ።
- አስቀደደ፡ አሸረከተ አሠነጠቀ አሸነቈረ ኣስነደለ ።
- አስቀዳ (አቅድሐ)፡ አስደነበቀ አስጠ ለቀ አስጨለፈ አስገለበጠ ።
- አስቀዳ፡ አጻፈ ።
- አስቀዳሚ፡ ያስቀደመ/የሚያስቀድም ።
- አስቀዳሽ (ሾች)፡ ያስቀደሰ/የሚያስቀድስ (አስባራኪ አስቈራቢ ") ።
- አስቀዳጅ፡ ያስቀደደ/የሚያስቀድድ (አ ሠንጣቂ ") ።
- አስቀድሞ፡ ንኡስ አገባብ (በፊት በመዠመሪያ ") ("(ዮሐ. ፩፥ ፩ - ፪)") ። "አስቀድሞ ማመ ስገን ለሐሜት ያስቸግራል።"
- አስቀጂ፡ ያስቀዳ/የሚያስቀዳ ።
- አስቀጠለ፡ አስጨመረ (አስቋጠረአሰፋ አስረዘመ (ቤትን ") ።
- አስቀጠረ (አቅጸረ)፡ ቅጥር አሠራ አስከበበ አሳጠረ ።
- አስቀጠቀጠ፡ ብረት አሠራ ።
- አስቀጠቀጠ፡ አስመታ አስደበደበ አስ
- አስቀጠቀጠ፡ አስወቀጠ ።
- አስቀጠበ፡ አስከነዳ አስለካ አስመ ጠነ፡ አስመለከተ ምልክት አስደረገ ።
- አስቀጠነ፡ ቀጪን አስደረገ ድርን ።
- አስቀጠጠ፡ አስቈረጠ አሳወደ አሸለተ ።
- አስቀጠፈ፡ አስቈረጠ አስቀነጠበ ።
- አስቀጠፈ፡ አስገደለ አስቀሠፈ ።
- አስቀጣ፡ ቅጣት አስፈረደ አሳሰረ አስመታ አስገረፈ ።
- አስቀጣ፡ አስጐመደ አስቈረጠ ።
- አስቀጣሪ፡ ያስቀጠረ/የሚያስቀጥር ።
- አስቀጣቢ፡ ያስቀጠበ/የሚያስቀጥብ (ያስመጠነ/የሚያስመጥን፡ አስመጣኝ ") ።
- አስቀጣይ፡ ያስቀጠለ/የሚያስቀጥል (አስፈላጊ አስቋጣሪ ") ።
- አስቀጣይነት፡ አስቀጣይ መኾን፡ አስ ረዛሚነት ።
- አስቀጣፊ፡ ያስቀጠፈ/የሚያስቀጥፍ (አ ስቈራቹ ") ።
- አስቀጥቃጭ፡ ያስቀጠቀጠ/የሚያስቀ ጠቅጥ ።
- አስቀጪ፡ ያስቀጣ/የሚያስቀጣ (ኣበሳ ኀጢአት ") ።
- አስቀጯ፡ አስቀሠፈ አስገደለ ።
- አስቀጯ፡ አስቈረጠ አስነጯ አስገነ
- አስቀጸለ፡ አስተማረ ነገረ ።
- አስቀጻ (አቅጽዐ)፡ አሳፈፈ አስቀ ፈፈ ።
- አስቀጻይ፡ ያስቀጸለ/የሚያስቀጽል (ነ ጋሪ አስተማሪ ") ።
- አስቀጻይነት፡ አስተማሪነት ።
- አስቀፈረ፡ አስቆመ አስቀቀረ ።
- አስቀፈቀፈ፡ አስበሳ አሰበረ አስፈለ ፈለ ።
- አስቀፈቀፈ፡ አስከረከረ ዕንወትን ።
- አስቀፈደ፡ አስበሳ/አሳሰረ ።
- አስቀፈደደ፡ አሳሰረ ።
- አስቀፈፈ፡ አስለመነ አስጠየፈ ።
- አስቀፈፈ፡ አስቈረጠ አስከረከመ ።
- አስቀፋፊ፡ ያስቀፈፈ/የሚያስቀፍፍ (አ ስከርካሚ አስለማኝ ") ።
- አስቍጠረ (አቍጸረ)፡ ኣኡ አሠን፡ ፊደልና ቍጥር አስተማረ፡ አንድ ኹለት ኣስ ባለ ።
- አሥቂኝ (ኞች)፡ አጫዋች/ድንክ/ ቀልደኛ ካታ (ጥርስ የማያስከድን) ።
- አስቃመ፡ አስበላ አሳፈሠ አስገተመ አ ስገፈረ ።
- አስቃሚ፡ ያስስቃመ/የሚያስቅም (ቸልተኛ ") ።
- አስቃረ፡ አሳለ አስጐመዠ ።
- አስቃረመ፡ አስለቀመ፡ አሰበሰበ።
- አስቃራሚ፡ ያስቃረመ፡ የሚያስቃርም፡ አስለቃሚ ።
- አስቃተተ፡ አስለፋ/አስደከመ ("ቍና ቍና አስተነፈሰ ") ።
- አስቃኘ፡ አሰለለ አስጐበኘ ።
- አስቃኘ፡ አስቀነቀነ አዠመረ ።
- አስቃኘ፡ አስጠበቀ አስላላ ።
- አስቃጣ፡ አስደከረ አስደቀነ አዘረጋ
- አስቈለለ፡ እስከመረ አስጐቸ ።
- አስቈለመመ፡ አስቀለሰ አስጐበጠ አስ ጠመዘዘ ።
- አስቈለፈ፡ አስጐበጠ አስቀለሰ ።
- አስቈለፈ፡ አዘጋ ኣሸጐረ ።
- አስቈላ፡ አሳመሰ አስጠበሰ ።
- አስቈላ፡ አስወዘወዘ አስነሰነሰ ።
- አስቈላይ፡ ያስቈለለ/የሚያስቈልል (አስ ከማሪ ") ።
- አስቈላፊ፡ ያስቈለፈ/የሚያስቈልፍ (አ ዘጊ አስቀላሽ ") ።
- አስቈልማሚ፡ ያስቈለመመ/የሚያስቈለምም (ኣስቀላሽ አስጐባጭ ") ።
- አስቈመደ፡ አስደረተ አስደበደበ አስ
- አስቈመጠ፡ አስቈረጠ አስጐመደ ።
- አስቈሰለ፡ አስደማ አንዲቈስል አስደረገ ።
- አስቈሰቈሰ፡ አስጠቀሰ አስገፋ አስጨ መረ ።
- አስቈስቋሽ፡ ያስቈሰቈሰ/የሚያስቈሰቍስ (አስጨማሪ ") ።
- አስቈረመ፡ አስመታ፡ አስኰረኰመ።
- አስቈረሰ፡ አስፈተተ አስገመደለ አስቀረደደ አስከፈለ ።
- አስቈረረ፡ አስጫነ አስደረበ ።
- አስቈረቈረ፡ አሳዘነ አጸጸተ ።
- አስቈረቈረ፡ አስማሰ አስመሠረተ ።
- አስቈረቈረ፡ አስደፈነ አስጠቀጠቀ ።
- አስቈረቈረ፡ አስጐረበጠ አስወጋ ።
- አስቈረበ፡ አስቀደሰ አሠለሰ፡ የማችን ስም በቅዳሴ አስጠራ ።
- አስቈረኘ፡ አሳሰረ አስጠመደ ።
- አስቈረኘተ፡ አስነፋ አስጐሰረ ።
- አስቈረጠ፡ ነገርን አስጨረሰ አስፈ ጸመ ።
- አስቈረጠ፡ አስጐረደ አስጐመደ አስመደመደ ኣሸለተ (ዕንወትን ሥጋን እጅን ጠጕርን ሌላውንም ") ።
- አስቈረጠመ፡ አስጐረደመ አሳንከ አ ስበላ ።
- አስቈረፈ፡ አስጨረፈ አስለኰፈ ።
- አስቈሪ፡ ያስቈራ/የሚያስቈራ (አስበዉ አስፈቂ ") ።
- አስቈራ፡ አስበጣ አስፈቃ አስጋረጠ፡ ኣስተኰሰ አስነቀሰ ኣስቀባ ኣስመለከተ፡ አስመታ አስቈረመ ።
- አስቈራሚ፡ ያስቈረመ፡ የሚያስቈርም፡ አስኰርኳሚ "
- አስቈራሽ፡ ያስቈረስ/የሚያስቈርስ (አስ ፈታች ") ።
- አስቈራቢ (ዎች)፡ ያስቈረበ/የሚያስ ቈርብ (አስቀዳሽ ") ።የች ልጅ ወይም ወራሽ ።
- አስቈራጭ (ጮች)፡ ያስቈረጠ/የሚያ ስቈርጥ (ሥጋ ያዥ ") ።
- አስቈራጭነት፡ አስቈራጭ መኾን ።
- አስቈርቋሪ፡ ያስቈረቈረ/የሚያስቈረቍር† አሳዛኝ ።
- አስቈርጣሚ፡ ያስቈረጠመ/የሚያስቈረ ጥም ።
- አስቈርጣሚ፡ ያስቈረጠመ/የሚያስቈረ ጥም ።
- አስቈነነ፡ አስለካ አሰፈረ አስመጠነ ።
- አስቈነነ፡ አስኰራ አስቋፈ ።
- አስቈነነ፡ አስጐነጐነ አሸረበ ።
- አስቈነደደ፡ አስደረቀ ዐጪር አስደረገ ።
- አስቈነደደ፡ አስገረፈ አስለቈጠጠ ።
- አስቈነጠረ፡ ቈንጥራችኹ ውሰዱ አለ ።
- አስቈነጠረ፡ አስወጋ አስነከሰ አስጫረ ።
- አስቈነጠጠ፡ አስለመዘገ አስቀጣ ።
- አስቈነጠጠ፡ አስረገጠ ።
- አስቈነጠጠ፡ አስነከሰ አስበላ ።
- አስቈነጠጠ፡ አስጠቀለለ አሸበለለ አስ ማገረ ።
- አስቈነጨ፡ አስለቀመ አስጐለጐለ ።
- አስቈነጸለ፡ አስቈረጠ አስገነጠለ ።
- አስቈነጸለ፡ አስኰሰተረ አሰበረ ።
- አስቈናኝ፡ ያስቈነነ/የሚያስቈንን (ኣስ ጐንጓኝ አሰፋሪ ") ።
- አስቈንጣሪ፡ ያስቈነጠረ/የሚያስቈነጥር ።
- አስቈንጣጭ፡ ያስቈነጠጠ/የሚያስቈን ጥጥ (አስለምዛጊ ") ።
- አስቈየ፡ እንዲቈይ እንዲዘገይ አስደረገ ።
- አስቈጋ፡ አስገረፈ አስቈነደደ ።
- አስቈጠቈጠ፡ አስለበለበ ።
- አስቈጠቈጠ፡ አስቈረጠ/አስመለመለ ።
- አስቈጠበ፡ እንዲቀመጥ አስደረገ፡ አስበዛ አስበረከተ ።
- አስቈጠጠ (አቍጠጠ)፡ አስኰሳ ቍጣጥ አስጣለ ።
- አስቈጣ፡ አናደደ አስጮኸ ቍጡ አደረገ አስደረገ አበሳጩ ("(ዘዳ. ፱፥ ፯፡ ዘካ. ፰፥ ፲፬፡ ሮሜ. ፲፥ ፲፱)") ።
- አስቈጣ፡ አዘለፈ (ቈጣ) ።
- አስቈጣሪ፡ ያስቈጠረ/የሚያስቈጥር (አስተማሪ ") ።
- አስቈጣቢ፡ ያስቈጠበ/የሚያስቈጥብ (የቍጠባ ሹም ") ።
- አስቈጪ፡ አጸጸተ አሳዘነ አስተከዘ ።
- አስቈጪ፡ ያስቈጣ/የሚያስቈጣ ።
- አስቈፈረ፡ አስማሰ አስማረ አስኳተ ("(ዘፍ. ፳፮፥ ፲፰)") ።
- አስቈፋሪ፡ ያስቈፈረ/የሚያስቈፍር (አ ስማሽ ") ።
- አስቆመ፡ አስገታ ኣሳገደ አስገተረ ።
- አስቋመጠ፡ አስጐመዠ (ጥሠ) ኣሠየ ።
- አስቋሚ፡ ያስቆመ/የሚያስቆም ።
- አስቋተ፡ አስደቀነ ።
- አስቋጠረ፡ አስቀጠለ፡ በልብስ በስልቻ በማሕፀን አሲያዘ ።
- አስቋጣሪ፡ ያስቋጠረ/የሚያስቋጥር (ባለ
- አስቋጩ፡ "ቋጩልኝ" አለ፡ አስጠመዘዘ አስከረረ አስገመደ አስጠመረ ።
- አስቋጪ፡ ያስቋጪ/የሚያስቋጭ (ባለልብስ ") ።
- አስቋፈ፡ በቀስታ አስኬደ/አስቈነነ ።
- አስበለቀጠ፡ ኣስገለጠ አስከፈተ ።
- አስበለተ፡ አስለየ፡ አስነጠለ፡ አስቈ
- አስበለጠ፡ አስረዘመ አስከበረ ።
- አስበለጠጠ፡ አስገለጠ አስቀለበሰ ።
- አስበሊ፡ ያስበላ የሚያስበላ የሚያስነክስ ።
- አስበላ (አብልዐ)፡ አስጐረሠ አስዋጠ ። (ኢሳ ፵፱ ፥ ፳፳፫) ። ኣበላ ፈቃድን፡ አስበላ ግዴታን ያሳያል ።
- አስበላ፡ አስነከሰ አስቦጨቀ ።
- አስበላጭ፡ ያስበለጠ የሚያስበልጥ የሚያስረዝም የሚያስከብር ።
- አስበሰለ፡ አስቀቀለ፡ አስቈላ አስጋገረ ።
- አስበሠረ (አብሠረ)፡ የምሥራች አሠኘ አስነገረ ።
- አስበሰበሰ፡ አስራሰ አሳሸ ።
- አስበሰከ፡ አስበተከ አስበጠሰ ።
- አስበሳ፡ አሰረሰረ አስፈለፈለ አስቀደደ አስነደለ ።
- አስበረረ፡ አስሮጠ አስጋለበ ።
- አስበረቀሰ፡ አስጣሰ አስፈረሰ ።
- አስበረበረ፡ አዘረፈ ኣስበዘበዘ፡ አስገለበጠ ።
- አስበረከከ (አብረከ)፡ አስጐነበሰ አስተኛ ግመልን ወይም ሰውን ። (ዘፍ ፳፬ ፥ ፲፩) ።
- አስበረኰተ፡ አስደፈነ አስቀበረ አስ ረመጠ ።
- አስበረዘ፡ በሪድ አስደረገ ኣስቀዘቀዘ፡ አስበጠበጠ ።
- አስበረየ፡ አስደነበረ አስበረረ ።
- አስበረደ (አብረደ)፡ አስቀዘቀዘ፡ አስበረዘ፡ እንዲበርድ እንዲቀዘቅዝ አስደረገ ።
- አስበረገደ፡ አስከፈለ አስተረረ አስፈለጠ ።
- አስበረገገ፡ አስደነገጠ አስፈራ አስደነበረ አስፈገፈገ ።
- አስበረገገ፡ አስፈነከተ አስወለለ ።
- አስበራ (አብርሀ)፡ አስገለጠ፡ ብልጭ አስደረገ፡ ፋና አስወጋ ።
- አስበራየ፡ አስኼደ፡ አስረገጠ ።
- አስበራጅ፡ ያስበረደ የሚያስበርድ የሚ ያስበርዝ ።
- አስበርባሪ፡ ያስበረበረ የሚያስበረብር፡ አስበዝባዥ ።
- አስበሸተ፡ አሳመመ ጤና አሳጣ ።
- አስበሺ፡ ያስበሳ የሚያስበሳ የሚያስ ነድል ።
- አስበቀለ፡ ዐሎ አስከፈለ፡ ደመኛን አስገደለ ።
- አስበቀለ፡ እንዲበቅል እንዲወጣ አስ ደረገ ።
- አስበቀተ፡ አስነዘነዘ አስነተረከ አስቀቀ ።
- አስበቃ፡ ልክ እንዲኾን እንዲበቃ አስደረገ ።
- አስበቃች፡ ያስበቀተ የሚያስበቅት እስ ጨቅጫቂ ።
- አስበቃይ፡ ያስሰቀለ የሚያስበቅል፡ አስ ገዳይ ።
- አስበበተ፡ በብብት ኣሲያዘ፡ ከብብት አስገባ ።
- አስበተበተ፡ አስቦጠቦጠ አስፈለፈለ አስበገበገ ።
- አስበተነ፡ አዘራ አስለየ አስወረወረ አዘረዘረ አስፈነጠቀ አስነሰነሰ ።
- አስበተከ (አብተከ)፡ አስበሰከ ኣስ በጠሰ ።
- አስበታኝ፡ ያስበተነ የሚያስበትን ።
- አስበከለ፡ አስኰለፈ አስቈሸሸ አስ ጠፋ ።
- አስበከረ (አብኰረ)፡ አሶለደ፡ በካር አስደረገ፡ አስተወ አስቀረ ።
- አስበካይ፡ ያስበከለ የሚያስበክል የሚያሳድፍ የሚያስኰልፍ ።
- አስበዘበዘ፡ አዘረፈ አስቀማ አስበረበረ ። (ሕዝ ፳፭ ፥ ፪ ። ዓሞ ፭ ፥ ፱) ።
- አስበዝባዥ፡ ያስበዘበዘ የሚያስበዘብዝ የሚያዘርፍ የሚያስቀማ፡ አዘራፊ አስቀሢ ።
- አስበየነ፡ አስፈረደ አስለየ ።
- አስበየደ፡ አስደለዘ አስመረገ አስደ ፈነ ።
- አስበያኝ፡ ያስበየነ የሚያስበይን የሚያስፈርድ፡ ራሱን ከባለጋራው የሚያስለይ ።
- አስበያጅ፡ ያስበየደ የሚያስበይድ የሚያስደፍን፡ አስመራጊ ።
- አስበደለ፡ አሳመፀ አስፋ፡ በሰው ላይ ግፍ አሠራ ።
- አስበደረ (አብደረ)፡ ወለድ አሰጠ፡ አስቀበለ አስለቃ ። በወለድ አለ ።
- አስበደነ (አብደነ)፡ አስፈዘዘ አስደ ነገዘ፡ ሬሳ አስደረገ ።
- አስበጀ፡ አሠራ ማለፊያ አስደረገ አስከወነ ።
- አስበገረ፡ አስሞከረ አስፈተነ፡ አስነደፈ አስለካ አስመጠነ አሣለ ።
- አስበገረ፡ አስደፈረ ።
- አስበገበገ፡ አስፈጀ አስገረፈ አስቈሰለ ።
- አስበጋሪ፡ ያስበገረ የሚያስበግር፡ የሚያስነድፍ አስሞካሪ ።
- አስበጠሰ፡ አስጐመደ አስቦደሰ አስ ቀነጠሰ ።
- አስበጠረ፡ አስነፈሰ አስጐተነ አስነ ቀሰ ።
- አስበጠረቀ፡ አስነደለ አስበሳ አሸነ ቈረ ።
- አስበጠበጠ፡ አስጠመቀ አስበረዘ አስመሸተ ።
- አስበጣ (አብጥሐ)፡ አስፈቃ አስቈራ አሠነተረ አስጋረጠ ።
- አስበጣሪ፡ ያስበጠረ የሚያስበጥር የ ሚያስነፍስ፡ አስነፋሽ ።
- አስበጣሽ፡ ያስበጠሰ የሚያስበጥስ የሚያስቀነጥስ፡ አስቀንጣሽ ።
- አስበጥባጭ፡ ያስበጠበጠ የሚያስበጠብጥ የሚያሳውክ ።
- አስበጨቀ፡ አስበጠሰ አስበሰከ ።
- አስበጪ፡ ያስበጣ የሚያስበጣ፡ አስፈቂ ።
- አሥቢ፡ ያሠባ/የሚያሠባ (ሙክትና ገች ቀላቢ) ለብ ።
- አስባለ (አብሀለ)፡ አሠኘ፡ አናገረ ።
- አስባለ፡ አስመታ አስደበደበ ።
- አስባሰ (አብአሰ)፡ አስከፋ አስቀየመ ኣሳዘነ ።
- አስባረከ፡ አስመረቀ ኣስቀደሰ ።
- አስባራኪ፡ ያስባረከ የሚያስባርክ የሚያስቀድስ፡ ኣስቀዳሽ ።
- አስባብ፡ ሰበቦች ፥ ሰበበ ።
- አስባብ፡ ሰበቦች። "የከተማ አታላዮች ከባላገር ላይ በሰበብ ባስባብ ገንዘብ ይቀማሉ።"
- አስባዘተ፡ አስፈለቀቀ አስቦጨቀ አስ ።
- አስባዛች፡ ያስባዘተ የሚያስባዝት፡ አስቦጫቂ ።
- አስቤዠ (አቤዘወ)፡ ቤዛ አሰጠ ኣስለወጠ ኣስገዛ አስዳነ አስጣለ አስተወ ኣስለቀቀ ኣስዋጀ ።
- አሥብቶ ዐራጅ፡ እያሠባ የሚያርድ (ሰውን በገንዘብ እያታለለ የሚገድልም አሥብቶ ዐራጅ ይባላል) ።
- አሥብቶ፡ አወፍሮ/አደንድኖ።
- አስቦረቀ፡ አስወረበ ።
- አስቦረቀ፡ አዘለለ ጮቤ አስመታ ።
- አስቦረቦረ (አስበረበረ)፡ አስጐረጐረ አስፈለፈለ ።
- አስቦቀረ፡ ጠጕርን ሳዱላ አስወጣ ።
- አስቦቃሪ፡ ያስቦቀረ የሚያስቦቅር የሚ ያስላጭ ።
- አስቦተረፈ፡ ኣስነከሰ አስቦጨቀ ።
- አስቦዘነ፡ ዞላ አስዋለ፡ ሥራ አስፈታ ።
- አስቦጠቦጠ፡ አስቦረቦረ አስጐረጐረ አስጐጠጐጠ ።
- አስቦጨቀ (አስበጨቀ)፡ አስባዘተ አሳጨደ አስቈረጠ ።
- አስቦጫቂ፡ የሚያስቦጭቅ የሚያሳጭድ ።
- አስቧለተ፡ አስተረበ አስቀለደ ።
- አስቧል፡ አስጐንብሷል፡ አዝምቷል።
- አስቧወረ፡ አስወረ አሰነዘረ ኦሳከከ ።
- አስቧገተ፡ አስቀለተ አስለመነ፡ ቧጋች አደረገ አስደረገ፡ አዘገነ ።
- አስቧጠጠ፡ አስጠጠ፡ አስጨረ፡ አስጠረገ ።
- አስቧጣጭ፡ ያስቧጠጠ የሚያስቧጥጥ፡ የሚያስጝጭር ።
- አስተ (አስ ተ)፡ አንዳንድ ጊዜ በጕል ግስ የማድረግ የቅጽል ልማድና መነሻ ። ዋለ አስተዋለ አስተዋይ ። በአዐ በሚነሣ በገቢር ግስ ሲገባም የማድረግና የማደራረግ የሳቢ ዘር ልማድና መነሻ ይኾናል ። ዐወቀ አስታወቀ አስተዋወቀ አስተዋወቅ ። አዕማድን ተመልከት፡ ቍጥር ፱ ። አንዳንደዬም መነሻው አዐ ባልኾነ ግስ፡ ነበረ አስተናበረ፡ ነገደ አስተናገደ፡ ነፈሰ ፥ አስተነፈሰ ሲል ይገኛል ። ይኸውም ከግእዝ የመጣ ነው ። አስተ ባ፩ ቃል የማድረግና የማስደረግ ልማድ መኾኑ ንም በአወከና በ(ዐወሰ) እይ ።
- አስተለመ፡ እዠመረ አሳረሰ እስከመሰ ።
- አስተለተለ፡ አስቀደደ አሠነጠቀ እስ...አስተልታይ ያስተለተለ/የሚያስተለትል ።
- አስተለተለ፡ አስፈታ አስተረተረ አስ...መዘዘ እስለየ ።
- አስተላለል፡ ዐለላ አነካከር (ማለል ") ።
- አስተላለም፡ የዕልም አስተያየት (ማ
- አስተላለቀ (አስተኃለቀ)፡ አጋደለ ኣተ "
- አስተላለቅ፡ አት (ማለቅ ") ።
- አስተላለበ (አስተሓለበ)፡ ጡትን አ ሳሳበ ("(ላም ስትታለብ ጥጃ ያዘ ማለብን ረዳ)") ።
- አስተላለብ፡ አሳሳብ (ማለብ ") ።
- አስተላለከ፡ አደፋፈረ፡ አጨካከነ፡
- አስተላለክ፡ አጨካከን፡ አደፋፈር፡ አወዳደረ ። አበረታት ።
- አስተላለጥ፡ ያልጫ አኳዃን (ማለጥ ") ።
- አስተላለፈ (አስተኃለፈ)፡ አረማ መደ አሸጋገረ (አዛመተ አጋባ - "(አደራራጊ)") ።
- አስተላለፈ፡ ለሌላ ጊዜ አደረገ ጕዳ ይን ("(አድራጊ)") ።
- አስተላለፍ፡ አካኼድ (ማለፍ ") ።
- አስተላላቂ፡ ያስተላለቀ/የሚያስተላልቅ አጋዳይ ።
- አስተላላፊ፡ ያስተላለፈ/የሚያስተላልፍ (መንገድ መሪ ") ።
- አስተላላፊነት፡ አስተላላፊ መኾን ።
- አስተላሚ፡ ያስተለመ/የሚያስተልም (እ...መሰ) ።
- አስተመመ፡ አስጮኸ ።
- አስተመተመ፡ አስመታ አስለተመ አ...ስገጨ አስወጋ ።
- አስተመተመ፡ አስደመደመ ።
- አስተማመመ፡ መድኀኒት አደራረገ ።
- አስተማመም ፣ኣዠማመር፡ ማመም።
- አስተማመም፡ የበሽታ አያያዝ (ማመም ") ።
- አስተማመሰ (አስተሓመሰ)፡ አገለባ በጠ (አተረማመሰ ") ።
- አስተማመስ፡ ኣገለባበጥ (ማመስ ") ።
- አስተማመቅ፡ አረጣጠጥ (ማመቅ ") ።
- አስተማመት፡ አከታተፍ (ማመት ") ።
- አስተማመቸ (አስተሓመወ)፡ ኣጋባ አዛመደ ።
- አስተማመነ (አስተኣመነ)፡ ኣዋደደ፡ አሰማማ፡ እውነት፡ ርግጥ፡ ሐቅ፡ ነው፡ አባባለ፡ አሠኛኘ። አረጋገጠ፡ ኣማማለ፡ አገዛዘተ።
- አስተማመን፡ አቀባበል፡ ማመን።
- አስተማመድ፡ አቈራረጥ (ማመድ ") ።
- አስተማመግ፡ አመሳሰግ (ማመግ ") ።
- አስተማመፀ (አስተዓመፀ)፡ አበዳ
- አስተማሚ (አስተሓማዪ)፡ ያስተ ማማ/የሚያስተማማ (አነቃቃፊ
- አስተማማ (አስተሓመየ)፡ አነቃቀፈ ።
- አስተማማኝ፡ ያስተማመነ፡ የሚያስተማምን፡ አረጋጋጭ።
- አስተማረ፡ ነገረ (ማረ) ።
- አስተሰረየ (አስተስረየ)፡ ሰረየ። "የአስተሰረየና የሰረየ ትርጓሜ ባማርኛ እንጂ በግእዝ አንድነት የለውም"።
- አስተሣሠሠ (አስተኃሠሠ)፡ አጣ ረገ አወላወለ ።
- አስተሣሠሥ፡ አጠራረግ { ማሠሥ ።
- አስተሳሰረ/አስተኣሰረ፡ አዋሰበ፡ አያያዘ፡ አቈራኘ፡ አቈላለፈ፡ አጣመረ።
- አስተሳሰር፡ አቀፈዳደድ፡ ማሰር።
- አስተሳሰበ (አስተሓሰበ)፡ አሳላ (አረዳዳ ") ።
- አስተሳሰብ፡ ያሳብ አደራረግ (ማሰብ ") ።
- አስተሳሳሪ፡ ያስተሳሰረ፡ የሚያስተሳስር፡ አቈራኚ።
- አስተሳሳቢ፡ ያስተሳሰበ/የሚያስተሳ ስብ ዳኛ ።
- አስተስራዪ፡ የሚያስተሰርይ (ሰራዪ) ።
- አስተረረ፡ አሠነጠቀ ።
- አስተረበ፡ አስቀለደ አስፌዘ ።
- አስተረተ፡ አስመሰለ አስነገረ አስወጋ (አውግዐ) ።
- አስተረተረ፡ አሠነጠቀ አስፈነከተ ። አስተረተረ፡ ኣስጨፈለቀ ።
- አስተረተረ፡ ኣስፈታ አስለየ ።
- አስተረከ፡ አስወጋ አስነገረ አስወራ ታሪክን ።
- አስተረከከ፡ አስጠረቀቀ አሠነጠቀ አ...ስፈነከተ ።
- አስተረጐመ፡ ተረጐመ አነጋገረ (እ...ድራጊ) ።
- አስተረጐመ፡ ኣስገለበጠ አስፈታ አስገለጠ (አስደራጊ) ።
- አስተረፈ፡ አስዳነ እስተወ አስቀረ ። ("አላስተረፈኝም" - እጅግ በጣም ጐድቶኛል) ።
- አስተረፈ፡ አተረፈ።
- አስተረፈሰ፡ አዘገነ አሳፈሠ አስቃመ ።
- አስተራረመ (አስተሓረመ)፡ እና ቀለ አኰታኰተ ።
- አስተራረሰ (አስተሓረሰ)፡ አታለመ አገላገለ አቀባቀበ ።
- አስተራረሰ (አስተኃረሰ)፡ ወላድን አማገበ አቃለበ ።
- አስተራረስ፡ አመጋገብ (ማረስ ") ።
- አስተራረስ፡ አተላለም (ማረስ ") ።
- አስተራረር፡ አከሳሰል (ማረር ") ።
- አስተራረቀ (አስተዓረቀ)፡ አጐናበሰ፡
- አስተራረቅ፡ አቀናን (ማረቅ ") ።
- አስተራረብ፡ አጠላለቅ (ማረብ ") ።
- አስተራረደ (አስተሓረደ)፡ አቀራ
- አስተራረድ፡ ያንገት አቈራረጥ (ማረድ ") ።
- አስተራረግ፡ አወጣጥ (ማረግ ") ።
- አስተራረፈ (አስተዓረፈ)፡ አስተጋ ገዘ ሥራን ።
- አስተራራፊ፡ ያስተራረፈ/የሚያስተራ ርፍ (አስተጋጋዥ ") ።
- አስተራር፡ አኰሳስ (ማራት ") ።
- አስተራቢ፡ ያስተረበ/የሚያስተርብ (አስቀላጅ) ።
- አስተራች፡ ያስተረተ/የሚያስተርት ።
- አስተራኪ፡ ያስተረከ/የሚያስተክ ።
- አስተራፊ፡ ያስተረፈ/የሚያስተርፍ (አስቀሪ ") ።
- አስተርታሪ፡ ያስተረተረ/የሚያስተረ...ትር (እሠንጣቂ) ።
- አስተርእዮ (ርእየ)፡ የበዓል ስም፡ በጥር ፳፩ ቀን የሚከበር የመቤታችን ዕረፍት፡ ትርጓሜው መገለጥ መታየት ። ባላገርም አስተሮ ይለዋል ።
- አስተርጓሚ (ሞች)፡ ያስተረጐመ...የሚያስተርጕም (አነጋጋሪ ቋንቋ ዐዋቂ ስማ...) ።
- አስተርጓሚነት፡ አነጋጋሪነት ።
- አስተርፎ፡ ትርፍ።
- አስተሻሸል፡ አለካክ፡ ማሸል ።
- አስተሻሸም፡ አጐናጐን (ማሸም ") ።
- አስተሻሸት፡ አለዋወስ አዘዋወር (ማ ሸት ") ።
- አስተሻሸግ፡ አደፋፈን ማሸግ ።
- አስተቃቀብ፡ አጠባበቅ አደጋገፍ ማ
- አስተቃቀድ፡ አለካክ ማቀድ ።
- አስተቃቀፈ (አስተሓቀፈ)፡ ኣስተቋ ቈረ (አደጋገፈ አገናኘ አጋጠመ አናከሰ አ ያያዘ - ፪ዜና. ፫፥ ፭) ።
- አስተቃቀፍ፡ አስተቋቈር (ማቀፍ ") ።
- አስተቋቈረ (አስተዓቈረ)፡ አስተቃ
- አስተቋቈር፡ አስተቃቀፍ (ማቈር ") ።
- አስተበተበ፡ አስወረረ አስከበበ ።
- አስተበተበ፡ አስጠመጠመ አሳሰረ ።
- አስተባበለ (አስተሓበለ)፡ አካካደ/ኣሸፋፈጠ ("ቍርኣን ብሉይንና ሐዲስን ያስተባብላል - (የተነገረውን የተደረገውን እንዳልተነገረ እንዳልተደረገ መልስ ሰጠ ሐሰት አለ)") ።
- አስተባበል፡ አወሻሸት (ማበል) ።
- አስተባበስ፡ አጠራረግ፡ እበዳደል፡ ማበስ ።
- አስተባበረ (አስተኃበረ)፡ አነጻጻረ/ አመሳሰለ/አዋሐደ/አሰማማ/አገጣጠሙ/አሻረከ ።
- አስተባበር፡ አመሳሰል (ማበር) ።
- አስተባበቅ፡ አስተማመቅ፡ ማበቅ ።
- አስተባበት፡ አጠላለፍ ማበት ።
- አስተባበድ፡ አኸ ማበድ ።
- አስተባበጥ፡ የዕብጠት አኳዃን (ማበጥ) ።
- አስተባባሪ፡ ያስተባበረ/የሚያስተባብር (አንድ ያኳዃነ ") ።
- አስተባባይ፡ ያስተባበለ/የሚያስተባብል።
- አስተቤተ፡ አስኰራ።
- አስተብታቢ፡ ያስተበተበ/የሚያስተብ...ትብ (አሳሳሪ) ።
- አስተተገ፡ አስመታ አስወጋ ።
- አስተታተል፡ አደፈራረስ፡ ማተል ።
- አስተታተመ (አስተኃተመ)፡ የማ ተም የማኅተም ሥራን ረዳ ' ዐገዘ ።
- አስተታተር፡ አቈረባበጭ (ማተር ") ።
- አስተታተብ፡ አቈራረጥ (ማተብ ") ።
- አስተታተት፡ አወጋገድ፡ ማተት ።
- አስተቸ፡ አሳተተ ሐተታ አስነገረ ።
- አስተቺ፡ ያስተት/የሚያስተች ።
- አስተነባ፡ አስነበየ።
- አስተነተነ (አስተሐመመ)፡ ተጋ ዐሰበ ነገርን በልቡ አወጣ አወረደ ጥቂቱን ብዙ ለማድረግ ለማብቃቃትና ሥራን ኹሉ ለማከናወን ።
- አስተነተነ፡ አስለየ አስከፈለ አስመደበ አስደለደለ ኤስቈነነ አሳደለ ።
- አስተነከረ፡ አስጠነከረ መረመረ አስረገጠ (ወሬን ነገርን - "ተና ጠ ተወራራሽ መኾናቸውን አትርሳ") ።
- አስተነከረ፡ ወሬን አስረገጠ፡ ተ ነከረ ።
- አስተነከረ፡ ወሬን አስረገጠ፡ተ ነከረ።
- አስተነኰሰ፡ አስለኰፈ አስነካ ።
- አስተነፈሰ (አስተንፈሰ)፡ ፋታና ትንፋሽ ሰጠ (አሳረፈ እፎይ አሠኘ አናገረ በቅጣት የሚመረመር ሰውን አስተነፈሰ) ። አስተነፈሰ፡ ከተነፋ ስልቻና ደንዳኔ ላስቲክ ከሚናጥ ወተት አየርን አወጣ።
- አስተነፈሰ፡ እፎይ አሠኘ፡ ነ ፈሰ ።
- አስተነፈገ፡ አስገማ/አስከረፋ።
- አስተናበረ፡ እንጀራ ኣቀረበ/ሰደረ/ደረደረ (ሰውን ጐን ለጐን አስቀመጠ መጠ) ።
- አስተናባሪ፡ ያስተናበረ/የሚያስተናብር (ዐዳይ/አሳላፊ ጋባዥ) ።
- አስተናባሪነት፡ አሳላፊነት/ጋባዥነት።
- አስተናባሪዎች፡ ዐዳዮች/አሳላፎች።
- አስተናነሰ፡ አጓደለ፡ አቀናነሰ ።
- አስተናነስ፡ አጐዳደል፡ ማነስ።
- አስተናነቀ (አስተኃነቀ/አስተቃ ለሰ)፡ አያያዘ አስታገለ ።
- አስተናነቅ፡ አስተሳሰር (ማነቅ ") ።
- አስተናነጥ፡ አጠራረብ (ማነጥ ") ።
- አስተናናቂ፡ ያስተናነቀ/የሚያስተናንቅ (አስታጋይ ") ።
- አስተናገደ (አአንገደ)፡ እንግዳ ተቀበለ/ጋበዘ/አበላ/አጠጣ/አስተናበረ/ሸኘ።
- አስተናጋጅ፡ ያስተናገደ/የሚያስተናግድ (እንግዳ ተቀባይ/ጋባዥ/አስተናባሪ) ።
- አስተናግር፡ ዕፀ ፋርስ ("አናግር አስለፍልፍ" ማለት ነው - የቀመሰውን ሰው ወደ ፊት የሚኾነውንና የሚያገኘውን ስለሚያናግር "አስተናግር" ተባለ) ።
- አስተኔ፡ ሕብር ዐይነት ። ደረቅ አስተኔ፡ ርጥብ አስተኔ ዕንጨት እንዲሉ ። አስተ ዐይነት መባሉ ኔ ከዐይን መጥቶ በምእላድነት ስለ ተጨመረበት ነው ።
- አስተንታኝ (ኞች)፡ ያስተነተነ/የሚያስተነትን (ትጉህ ዐሳቢ እንቅልፍ የለሽ የገዳም የቤተ ክሲያን መጋቢ) ።
- አስተንካሪ፡ ያስተነከረ/የሚያስተነክር (ነገር አስረጋጭ) ።
- አስተንፋሽ፡ ያስተነፈሰ/የሚያስተነፍስ (ፋታ ሰጪ) ።
- አስተኚ፡ ያስተኛ/የሚያስተኛ (አንጣፊ ጋራጅ አጋዳሚ) ።
- አስተኚነት፡ እስተኚ መኾን ።
- አስተኛ፡ ጠጕርን።
- አስተኛኘክ፡ አመሰኳኵ (ማኘክ ") ።
- አስተከለ፡ ቀላድ አሰጠ ።
- አስተከለ፡ አስመሠረተ አስለማ ።
- አስተከለ፡ አስቸከለ እስከሰመ አስቆመ ።
- አስተኪ፡ ያስተካ/የሚያስተካ (አስከፋይ) ።
- አስተካ፡ አሰጠ አስከፈለ አስረጠበ አ...ስወከለ ።
- አስተካከለ፡ (አስተኣከለ)፡ አመሳሰለ ፥ አነጻጸረ ፥ አወዳደረ፡ አደላደለ፡ ትክክል አደረገ፡ (ኢዮ ፳፰፡ ፳፭ ። ኢሳ ፵፡ ፳፭ ። ዮሐ ፭፡ ፲፰ ። ቈላ ፬፡ ፩) ።
- አስተካከል፡ አጨማመር፡ ማከል።
- አስተካከም፡ አስተጋገም (ማከም ") ።
- አስተካከብ፡ አሰባሰብ፡ ማከብ ።
- አስተካከት፡ አሰባሰብ፡ ማከት።
- አስተካከክ፡ አፈጋፈግ (ማከክ ") ።
- አስተካካይ፡ ያስተካከለ ፥ የሚያስተካክል ፥ የሚያወዳድር ።
- አስተካዥ፡ ያስተከዘ/የሚያስተክዝ (አሳ...ዛኝ) ።
- አስተካይ፡ ያስተከለ/የሚያስተክል።
- አስተኰሰ፡ ቃታን አሳበ ።
- አስተኰሰ፡ አስለኰሰ አስለበለበ ።
- አስተኰሰ፡ አስዳመጠ ቀጥ አስደረገ ።
- አስተኰሰ፡ ኣስላከከ አስቀባ አስገጠመ ።
- አስተኰሰ፡ ኣስካሰ አስቀበለ ካሳን ።
- አስተኰሰ፡ እስሞቀ አስወበቀ ።
- አስተኰረ፡ ኣስመለከተ ።
- አስተኳሽ፡ ያስተኰሰ/የሚያስተኵስ (አስለኳሽ - "የትኵስ አዛዥ") ።
- አስተኳሽነት፡ አስተኳሽ መኾን ።
- አስተወ፡ አስለቀቀ አስረገፈ አስጣለ እስማረ (መዝ. ፻፴፩፡ ፪፡ ኢሳ. ፲፬፡ ፳፯፡ ሕዝ. ፵፬፡ ፲) ። ማስተው፡ ማስለቀቅ ማስጣል።
- አስተዋለ (አስተውዐለ ለበወ)፡ አየ/ተመለከተ/ተኰረ ("ዐይነ ልቡን ባንድ ነገር ላይ ጣለ ልብ አለ ልብ አደረገ አጤነ") ።
- አስተዋለ፡ ተኰረ ፥ —ዋለ ።
- አስተዋወስ፡ አስተሳሰብ (ማስታወስ ") ።
- አስተዋወር፡ ያይን አጠፋፍ ("መታ ወር ") ።
- አስተዋወቀ (አስተዓወቀ)፡ ተዋ ወቁ አለ (አላመደ አለማመደ ") ።
- አስተዋወቅ፡ አለማመድ (ማወቅ ") ።
- አስተዋወክ፡ አበጣበጥ፡ ማወክ ።
- አስተዋወድ፡ አዟዟር/አሸታተት (ማ ወድ ") ።
- አስተዋወጅ፡ አለፋፈፍ (ማወጅ ") ።
- አስተዋዋቂ፡ ያስተዋወቀ/የሚያስተዋ ውቅ (አለማማጅ ") ።
- አስተዋዋቂነት፡ አስተዋዋቂ መኾን ።
- አስተዋይ (ዮች) (ለባዊ)፡ ያስተዋለ/የሚያስተውል ("ያስ አስተዋለች የምታስተውል ተመ ልካች ተኳር ልብ አድራጊ ያየውን የሰማ ውን ቶሎ የሚቀበል") (ዘዳ. ፳፱፡ ፬፡ ፩ ሳሙ. ፲፰፡ ፴፡ ምሳ. ፲፪፡ ፬፡ ሮሜ. ፩፡ ፳፪) ።
- አስተዋይነት፡ ተመልካችነት/ተኳርነት/ ልብ አድራጊነት ።
- አስተዋፅኦ (ወፅአ)፡ መዋጮ ገንዘብ፡ ምእላድ ።
- አስተዛዘለ (አስተሐዘለ)፡ አሸካከመ/ አደራረበ/ኣነባበረ ።
- አስተዛዘለ፡ በኹለት ወገን አለ ("(ተ ቀባበለ)" - አቀባበለ አፈራረቀ አመላለሰ - የን ባብ የዜማ የዘፈን ") ።
- አስተዛዘል፡ በዠርባ አሸካከም (ማ ዘል ") ።
- አስተዛዘበ (አስተሓዘበ)፡ አጠራ ጠረ/አናናቀ/አነቃቀፈ ("(ግጥም)" - ዐርኩም ይኼ ድና ሊሬውም ያልቅና ያስተዛዝበናል ይኸ ቀን ያልፍና ") ።
- አስተዛዘብ፡ አጠላለፍ (ማዘብ ") ።
- አስተዛዘነ (አስተሐዘነ)፡ አላቀሰ = ኣዋየ ፥ አረጋጋ (አስተራረፈ ኣከፋፈለ - ኣረዳዳ ") ።
- አስተዛዘን፡ አተካከዝ (ማዘን ") ።
- አስተዛዘዘ፡ (አስተኣዘዘ)፡ ተዛዘዙ፡ አለ፡ ትዛዝ፡ አቀባበለ።
- አስተዛዘዝ፡ የትዛዝ፡ አሰጣጥ፡ ማዘዝ።
- አስተዛዛቢ፡ ያስተዛዘበ/የሚያስተዛ ዝብ (አጠራጣሪ ") ።
- አስተዛዛኝ፡ ያስተዛዘነ/የሚያስተዛዝን (አረጋጊ - "ይብላኝ ለሞተ እግዜር ያጥናኸ" የሚል ") ።
- አስተዛዛይ (ዮች)፡ ያስተዛዘለ/የሚ ያስተዛዝል (ተማሪ - አደራራቢ አነባባሪ ") ።
- አስተዣዠት፡ አወረዛዝ፡ ማዠት።
- አስተያየ፡ (አስተራአየ)፡ አነጻጸረ ፥ ፊት ለፊት ፥ ዐይን ላይን፡ (፩ሳሙ ፲፫ - ፲፰) ።
- አስተያየር፡ ኣቀላቀል (ማየር ") ።
- አስተያየት፡ አተያይ፡ አመለካከት፡ ማሰብ ።
- አስተዳደለ (አስተዓደለ)፡ ተፈላጊ ነገርን አሰጣጠ/አቀባበለ ።
- አስተዳደለ፡ ፍረዱ አለ (አፈራረደ) ።
- አስተዳደል፡ የዕድል አሰጣጥ (ማደል ") ።
- አስተዳደሰ (አስተሓደሰ)፡ አጠጋገነ ።
- አስተዳደስ፡ አጠጋገን (ማደስ ") ።
- አስተዳደረ (አስተኃደረ)፡ አሰማማ/አኳዃነ ("(ኣደራራጊ)") ።
- አስተዳደረ፡ አስተነተነ ("ይህ ለዚህ ይበቃል" አለ - "(አድራጊ)") ።
- አስተዳደረ፡ ዐብሮ ዐደረ ("(ተገብሮ)") ።
- አስተዳደር፡ የኑሮ አኳዃን (ማደር - ኢሳ. ፶፯፥፲ - ያለፈው ተገብሮ የሚመጣው ገቢር መኾኑን አስተውል ") ።
- አስተዳደብ፡ አቀጣጥ፡ ማደብ ።
- አስተዳደነ፡ ኦፈላለገ እያያዘ (አጋደለ ኣገዳደለ ") ።
- አስተዳደን፡ አገዳደል (ማደን ") ።
- አስተዳደግ፡ አለቃቀቅ (መታደግ ") ።
- አስተዳደግ፡ አረዛዘም፡ ማደግ ።
- አስተዳደፈ፡ አጨመላለቀ ።
- አስተዳደፍ፡ አስተሣሠሥ (ማደፍ ") ።
- አስተዳደፍ፡ አጐዳዶፍ፡ ማደፍ ። ደፈረሰን እይ ።
- አስተዳዳሪ (ሮች)፡ ያስተዳደረ ፥ የሚ ያስተዳድር (አስተንታኝ ሹም ") ።
- አስተዳዳሪነት፡ አስተዳዳሪ መኾን (አስተንታኝነት ዋናነት ") ።
- አስተዳዳይ፡ ያስተዳደለ/የሚያስተዳድል።
- አስተጃጀል፡ ኣሸፋፈን (ማጀል ") ።
- አስተጃጀብ፡ አከባበብ (ማጀብ ") ።
- አስተገተገ፡ አስገረፈ አስተኰሰ ።
- አስተገነ፡ አስጠጋ አስጠለለ ።
- አስተገነ፡ ዐጥር ቅጥር አሠራ አስጀጐለ አስጋረደ አስከለለ ።
- አስተጋ፡ ትጉህ አስደረገ ።
- አስተጋባ (አስተጋብአ)፡ አሳለፈ አዛወረ፡ አስጮኸ ።
- አስተጋባ፡ ባንድነት ሰበሰበ አከማቸ ።
- አስተጋባ፡ አስጮኸ ፥ —ገባ ።
- አስተጋገለ፡ አኰታኰተ።
- አስተጋገል፡ አኰታኰት (ማገል) ።
- አስተጋገም፡ የደም አሳሳብ (ማገም) ።
- አስተጋገሠ (አስተዓገሠ)፡ አቻቻለ/ አጸናና ።
- አስተጋገሥ፡ አቻቻል (ማስታገሥ ") ።
- አስተጋገር፡ አስተዋወክ፡ ማገር ።
- አስተጋገተ (አስተዓገተ)፡ ኣካበበ (ዋስን አያያዘ ") ።
- አስተጋገት፡ በዋስትና አያያዝ (ማገት ") ።
- አስተጋገዘ (አስተሓገዘ)፡ አቀባበለ/ አረዳዳ/አስተራረፈ ።
- አስተጋገዝ፡ አረዳድ (ማገዝ ") ።
- አስተጋገደ፡ አካተረ አከታተረ አዋ ሰነ አወሳሰነ አጠባበቀ ።
- አስተጋገድ፡ አገታት ማገድ ።
- አስተጋጋዥ፡ ያስተጋገዘ/የሚያስተጋግዝ (አቀባባይ አስተራራፊ ") ።
- አስተጓጐለ (አስተሃጐለ)፡ አጠፋፋ አሰነካከለ ።
- አስተጓጐል፡ አሰነካከል፡ ማስታጐል ።
- አስተጓጐር፡ አሰባሰብ፡ ማጐር ።
- አስተጓጓይ፡ ያስተጓጐለ የሚያስተጓጕል፡ አሰነካካይ ።
- አስተጣጠረ (አስተሓጸረ)፡ አታከለ/ አገራገረ/አማገረ/አካካበ/አገናባ ።
- አስተጣጠር፡ አስተናነስ (ማጠር ") ።
- አስተጣጠር፡ ያጥር አሠራር (ማጠር ") ።
- አስተጣጠቀ (አስተዓጠቀ)፡ አስተ ሳሰረ/አጠማጠመ ።
- አስተጣጠቅ፡ አጠማጠም (መታጠቅ ") ።
- አስተጣጠበ (አስተኃፀበ)፡ ኩታና ቀሚስን ሱሪና እጀ ጠባብን ("(በማጠብ ረዳ ዐገዘ)") - አስተሻሸ/አጓረፈ/አለቃለቀ/አጠማ ዘዘ ።
- አስተጣጠብ፡ አለቃለቅ (ማጠብ ") ።
- አስተጣጠነ (አስተዓጠነ)፡ እጫጫሰ (ጪስን አቀባበለ - "(ማጠንን ረዳ)") ።
- አስተጣጠን፡ የጪስ አሰጣጥ (ማጠን ") ።
- አስተጣጠፈ (አስተዓጸፈ)፡ ("(ማጠ ፍን ረዳ)") - አጠቃለለ ።
- አስተጣጠፍ፡ አኰረማመት (ማጠፍ ") ።
- አስተጣጣቢ፡ ያስተጣጠበ/የሚያስተጣ ጥብ (የዕጥበት ረዳት ") ።
- አስተጣጣፊ፡ ያስተጣጠፈ/የሚያስተጣ
- አስተጣጥ፡ አደኸያየት/አረሳስ (ማጣት ") ።
- አስተጫጨቅ፡ አከታተት (ማጨቅ ") ።
- አስተጫጨደ፡ አቋረጠ/አጣረገ ።
- አስተጫጨድ፡ አቈራረጥ (ማጨድ ") ።
- አስተጫጫጅ፡ ያስተጫጨደ/የሚያስ ተማጭድ ።
- አስተፈተፈ፡ አስበጣ አስፈቃ አስቈራ አስቈረጠ (ፊትን ገላን የሚጠበስ ሥጋን) ።
- አስተፈተፈ፡ አስቸኰለ አጣደፈ ።
- አስተፊ፡ ያስተፋ/የሚያስተፋ ("ደም ኣስተፊ" - ሊበሉት የማይገባ እንጕዳይ) ።
- አስተፊታ፡ የምታስተፋ ሴት ።
- አስተፋ (አትፍአ)፡ አስቀረሸ አስ...ወ ።
- አስተፋ፡ በፍጥነት አስመጣ አስከፈለ ።
- አስተፋሳ፡ እፎይ አለ (ከሞት ኣፋፍ ተመለሰ - አፋረሰ ") ።
- አስተፋሳ፡ እፎይ አለ ፈሳ ።
- አስተፋፈረ (አስተኃፈረ)፡ አፈራራ አከባበረ ።
- አስተፋፈር፡ አፈራር (ማፈር ") ።
- አስተፋፈግ፡ አስተጃጀብ፡ ማፈግ ።
- አስተፋፈፍ፡ አቀፋፈፍ ማፈፍ ።
- አስተፍታፊ፡ ያስተፈተፈ/የሚያስተፈ...ትፍ ።
- አስታ ት፡ የንጨት ስም፡ አንደ ጣርማበር ባለ ተራራ ላይ ከጓሳና ከጦስኝ ጋራ የሚበቅል፡ ሲሰብቁት እሳት የሚወጣው ዕንጨት ።
- አስታመመ (አስተሐመመ)፡ በሽተ ኛን ረዳ (ፈተነ እኸል አቀመሰ ውሃ ጋተ አነሣ አቀና ደገፈ አስተኛ ") ።
- አስታመመ፡ ዐሰበ (ቀስ አለ፥ዝግ ብሎ ") ።
- አስታመነ (አስተአመነ)፡ አሳመነ ።
- አስታማሚ (ዎች/አስተሐማሚ)፡ ያስታመመ/የሚያስታምም (የበሽተኛ ጠባቂ ") ።
- አስታማሚነት፡ አስታማሚ ፥ መኾን ።
- አስታረቀ (ዐሪቅ/ዐረቀ)፡ አንተም ተው አንተም ተው አለ (አስማማ ከቂም ከበቀል አራቀ ባዶ አደረገ አፋቀረ - ቈላ. ፩፥ ፳) ።
- አስታረበ (አሥበጠ)፡ እበላ መገበ ጋበዘ እራትን (ጥቂት ቈርሶ ዳረጎት ሰጠ አጐረሠ - ራብን ከላ ") ። በጦም ቀን ምሳ እራት ሲኾን "አስታረበ ምሳ አበላ" ተብሎ ይተረጐማል ።
- አስታረበ (አሥበጠ)፡ እበላ መገበ ጋበዘ እራትን (ጥቂት ቈርሶ ዳረጎት ሰጠ አጐረሠ - ራብን ከላ ") ። በጦም ቀን ምሳ እራት ሲኾን "አስታረበ ምሳ አበላ" ተብሎ ይተረጐማል ።
- አስታረበ፡ አጠለቀ ጀንበርን ።
- አስታረበ፡ አጠለቀ ጀንበርን ።
- አስታራቂ (ዎች)፡ ያስታረቀ/የሚያ ስታርቅ (አስማሚ ጨዋ ሽማግሌ ") ።
- አስታራቂነት፡ አስታራቂ መኾን ።
- አስታራቢ፡ ያስታረበ/የሚያስታርብ (አጕራሽ ") ።
- አስታራቢ፡ ያስታረበ/የሚያስታርብ (አጕራሽ ") ።
- አስታር ቦሸሽ፡ የማታ ኮከብ ። ቧሽሸንና ዐረበን ተመልከት ።
- አስታር፡ የኮከብ ስም፡ ኮከብ ። ሉልን እይ ።
- አስታርቦ ሸሽ፡ ፀሓይ ሳትጠልቅ ታይቶ ስትጠልቅ የሚጠፋ ኮከብ ("አጥልቆ የሸሸ" ማለት ነው ") ። "አስታር ቦሸሽም" ተብሎ ይነገራል ። "ቧሸሸን" ተመልከት ።
- አስታርቦ፡ አጥልቆ አግብቶ ።
- አስታርቦ፡ አጥልቆ አግብቶ ።
- አስታቀረ፡ ነቀፈ፡ (ዐቀረ) ።
- አስታበየ፡ አስመካ ፥ —ዐበየ ።
- አስታበየ፡ ኣስተቤተ/አስመካ/አስደገገ/አጓደደ ።
- አስታታ፡ አስጠፈረ አስጠለፈ ።
- አስታከለ፡ (አስተአከለ)፡ አሳከለ ፥ አስመሰለ ። ፈጣሪ ከፍጡር አስታከልከኝ አይበለኝና፡ የፈረንጅ ሥራ የፈጣሪን ይመስላል ።
- አስታከከ (አስተሐከከ)፡ አቀረበ አስጠጋ ።
- አስታካኪ፡ ያስታከከ/የሚያስታክክ (አስጠጊ ") ።
- አስታኰተ፡ (አኰተ)፡ ጸለየ፡ የማታ፡ ጸሎት፡ ምስጋና፡ አቀረበ፡ የለት፡ ውዳሴ፡ ማሪያም፡ አዜመ ።
- አስታኰተ/አኰተ፡ ጸለየ፡ የማታ ጸሎት ምስጋና አቀረበ፡ የለት ውዳሴ ማርያም አዜመ።
- አስታኳች፡ ያስታኰተ፡ የሚያስታኩት፡ የሚያመሰግን፡ አመስጋኝ።
- አስታኳች፡ ያስታኰተ፡ የሚያስታኩት፡ የሚያመሰግን፡ አመስጋኝ።
- አስታወሰ፡ አሳሰበ ፥ —(ዐወሰ) ።
- አስታወቀ (አስተዐወቀ)፡ ነገረ/አስ ረዳ ("(፩ሳሙ. ፳፰፥፲፭)") ።
- አስታወከ፡ ቋቅ አለ፡ አወጣ ተፋ ቀረሸ አፈሰሰ የበላውን የጠጣውን (አድራጊ) ።
- አስታወከ፡ አስመለሰ ፥ —አወከ ።
- አስታወከ፡ አስመለሰ ኣስተፋ (አስደ ራጊ) ።
- አስታዋሽ (ሾች)፡ ያስታወሰ/የሚ ያስታውስ (ዐሳቢ አሳሳቢ ") ።
- አስታዋሽነት፡ ዐሳቢነት/አሳሳቢነት ።
- አስታዋቂ፡ ያስታወቀ/የሚያስታውቅ (ነጋሪ አስረጅ ") ።
- አስታዋኪ፡ ያስታወከ የሚያስታውክ፡ ቋቅ የሚል የሚያስመልስ፡ አስመላሽ አፍሳሽ ።
- አስታዘበ (አስተሐዘበ)፡ አስጠረ ።
- አስታየ፡ (አስተርአየ)፡ አሳየ።
- አስታገለ (አስተዓገለ/አስተቃ ለሰ)፡ አስተናነቀ ።
- አስታገለ፡ አስተናነቀ ፥ —ዐገለ ።
- አስታገሠ፡ አስቻለ፡ (ዐገሠ) ።
- አስታጋሽ፡ ያስታገሠ/የሚያስታግሥ።
- አስታጐለ (አስተሀጐለ)፡ አዳፈነ አጠፋ አስቀረ ቅዳሴን ጸሎትን ግብርን ።
- አስታጓይ (ዮች)፡ ያስታጐለ የሚያስ ታጕል፡ አዳፋኝ ገባር ሰሞነኛ ።
- አስታጓይነት፡ አስቀሪነት አዳፋኝነት ።
- አስታጠቀ (አስተዐጠቀ)፡ ታጠቅ አለ (አስቀነተ - እንዲታጠቅ አደረገ አስደረገ - ኢዮ. ፲፪፥፲፥፲፰፡ ኢሳ. ፵፭፥፭ - ጐበዝ ") ።
- አስታጠቀ፡ አስቀነተ፡ (ዐጠቀ) ።
- አስታጠበ (አስተኀዘበ)፡ በእጅ ላይ ውሃ ጨመረ/አፈሰሰ ።
- አስታጣቂ፡ ያስታጠቀ/የሚያስታጥቅ ።
- አስታጣቢ (ዎች)፡ ያስታጠበ/የሚ ያስታጥብ (አሽከር ብላቴና ") ።
- አስታጣቢ፡ የቤተ መንግሥት ደንብ ።
- አስታጣቢነት፡ አስታጣቢ መኾን ።
- አስታጥቄ፡ የሰው ስም ።
- አስቴ ፥ ባስቴ የተተኮሰ ጠባሳ በክንድ በጡንቻ ላይ ያለ ።
- አስቴ (አስታዊ)፡ ያስታ ወገን፡ ያስታ እሳት የሚወጣው ማንኛውም ዕንጨት ወይም ካስታ የወጣ እሳት ።
- አስቴር፡ የሴት ስም፡ የታባች የተሰወረች ሽሽጓ ማለት ነው ።
- አስቶረበ፡ አስወሰወሰ ኣሸደሸደ አሽ...ለለ ኣሸከሸከ ።
- አስቶራቢ፡ ያስቆረበ/የሚያስቶርብ ።
- አስቶች፡ አስታዎች፡ ኹለትና ከኹለት የሚበዙ ።
- አስቸለሰ፡ አስከነበለ አስገለበጠ አስ...ፈሰሰ ።
- አስቸመቸመ፡ አስበዛ ።
- አስቸመቸመ፡ አስቸረቸመ አስጠረሰ ።
- አስቸሰረ፡ አስረፈቀ አስደነሰረ ።
- አስቸረ፡ እሰጠ አስናን እስለገሰ ።
- አስቸረቸመ፡ አሰበረ አሸረፈ አስጠ...ረሰ አሳጠረ ።
- አስቸረቸረ፡ አስበተነ አስተነተነ አዘረዘረ በዝርዝር አሼጠ ።
- አስቸርቻሪ፡ ያስቸረቸረ/የሚያስቸረችር ።
- አስቸበቸበ፡ አሳረደ አስቈረጠ ።
- አስቸበቸበ፡ አስራበበ ።
- አስቸበቸበ፡ አስጣለ አስመታ አስደ...በደበ አስወቃ ።
- አስቸበቸበ፡ ኦሼ አስለወጠ ።
- አስቸቸረ፡ አስገፈረ አስቃመ ።
- አስቸነነ፡ አስጀነነ አስኰራ አስቈነነ ።
- አስቸነከረ፡ አስመታ አስወጋ በምስ...ማር ።
- አስቸንካሪ፡ ያስቸነከረ/የሚያስቸነክር ።
- አስቸከለ፡ አስተከለ አስቀበቀበ ።
- አስቸካይ፡ ያስቸከለ/የሚያስቸክል (አስማስቸከል - ማስተከል ማስቀብቀብ) ።
- አስቸኰለ (ኣትከለ)፡ ኣስጠደፈ ኣስጐተጐተ አስፈጠነ ።
- አስቸኳይ (ዮች)፡ ያስቸኰለ/የሚያስቸል (አስጠዳፊ አስጐትጓች - ዘፀ. ፭፡ ፮, ፲) ።
- አስቸኳይነት፡ አስጐትጓችነት ።
- አስቸገረ፡ አስጨነቀ አሳጣ እስራበ ።
- አስቸጋሪ (ሮች)፡ ያስቸገረ/የሚያስቸግር (አስጨናቂ - ፪ነገ. ፪፡ ፬) ። አስቸጋሪነት፡ አስጨናቂነት ።
- አስቸፈረ፡ አስቃ...መ ።
- አስቻለ (አክሀለ)፡ አሸከመ አስወሰነ...አስታገሠ ። ("ያስችልኸ" - ትዕግሥት ይስጥኸ) ። ("እያ ስችለውም" - አይታገሥም) ።
- አስቻለ፡ ልጃገረድን በጠለፋት ሰው ሚስትነት እንድትኖር አስደረገ ።
- አስቻለ፡ በችሎት ተቀመጠ ከሳሽ ተከሳሽን አነጋገረ ኣተ አነጣጠረ አከራከረ አበጣጠረ ።
- አስቻመ፡ አስቃመ ።
- አስቻይ፡ ያስቻለ/የሚያስችል (አጋች አነጋጋሪ ዳኛ) ።
- አስነሰነሰ፡ አስበተነ ' አዘራ ' አስጐዘጐዘ ።
- አስነሡተ፡ አስነዘነዘ/አስበቀተ።
- አስነሣ፡ ቀሰቀሰ/አነቃ (ከንቅልፍ ከመቃብር - ዮሐ. ፲፩፥፲፩ - "ርጥብ ሬሳ ደረቁን አስነሣ" እንዲሉ - "ክርስትናን" ተመልከት - ባስ ደራጊነትም ይፈታል - ኣስቀሰቀሰ) ።
- አስነሣ፡ አሲያዘ/አስጨበጠ ("እጅን" ተመልከት - "(ፈረሱን አስነሣ)" - ኰረኰረ ግልቢያ ዠመረ ሽምጥ ጋለበ) ።
- አስነሣ፡ አሸከመ/አስወሰደ (ዕቃን ሸ ክምን) ።
- አስነሣ፡ ኣወጣ/አስወጣ/አስለቀቀ ("ጌታ በዚህ ዓለም ሳለ ጋኔን ያስነሣ ነበር ይህም የሰውየውን ከወደቀበት መነሣቱን ያሳያል") ።
- አስነስናሽ፡ ያስነሰነሰ/የሚያስነሰንስ (አ ስጐዝጓዥ) ።
- አስነረተ፡ አስመታ/አስጠዘለ።
- አስነረተ፡ አስነፋ/አስቀበተተ።
- አስነሽ/ሺ፡ ያስነሣ/የሚያስነሣ (ቀስቃሽ አንቂ አውጪ) ።
- አስነቀለ፡ አስመዘዘ/ኣስመነገለ/አስወለቀ ' አስለቀቀ።
- አስነቀሰ፡ አስመሰከረ።
- አስነቀሰ፡ አስመሰከረ።
- አስነቀሰ፡ አስቀነሰ/አስጐደለ።
- አስነቀሰ፡ አስነቀለ/አስወጣ።
- አስነቀሰ፡ አስጠቀጠቀ/አስወቀረ/አስ ቈረ ።
- አስነቀበ፡ አስበላ/አሰፋ።
- አስነቀነቀ፡ አስቀሰቀሰ/አስወዘወዘ።
- አስነቀፈ፡ አሰደበ/አስነወረ/አስቈጣ ' አስወቀሠ ።
- አስነቀፈ፡ አሰደበ/አስነወረ/አስቈጣ ' አስወቀሠ ።
- አስነቃ፡ አስቀሰቀሰ/አስነሣ ("ነሣን" እይ " አነቃቅ" - አተጋግ - መንቃት) ።
- አስነቃሽ፡ ያስነቀሰ/የሚያስነቅስ።
- አስነቃይ፡ ያስነቀለ/የሚያስነቅል (ኣበሳ ኀጢአት ነፍሰ ግዳይ አለመገበር አለመዝመት) ።
- አስነቃፊ፡ ያስነቀፈ/የሚያስነቅፍ (እሰ ዳቢ) ።
- አስነቈጠ፡ አስጣፈ (ነቍጣን) ።
- አስነቅናቂ፡ ያስነቀነቀ/የሚያስነቅንቅ።
- አስነበበ፡ ንባብ አስተማረ (በንባብ ፈ) ።
- አስነበዘ፡ አሰለበ/አስቈረጠ።
- አስነበዘ፡ አስመረዘ/አስቀለመ።
- አስነበዘ፡ አስቀማ/አስገፈፈ።
- አስነባ፡ አስለቀሰ/እንባ አስፈሰሰ።
- አስነባቢ፡ ያስነበበ/የሚያስነብብ (ንባብ አስተማሪ ዛቋኝንና ቀሳሽን የሚፈትን አቡነ ቀሲስ) ።
- አስነከሰ (አሐንከሰ)፡ ዐንካሳ አደረገ
- አስነከሰ፡ አስጠላ/አስመረዘ።
- አስነከሰ፡ ዐንካሳ አደረገ (ፀነ ንታሪ) "
- አስነከሰ፡ ያዝ ኵቲ አለ (አዘነተረ አስቦጨቀ አስበላ) ።
- አስነከረ፡ እውሃ አስገባ/አዘፈቀ/አስ ራሰ/አስጠመቀ።
- አስነከነከ፡ አስበላ።
- አስነኪ፡ ያስነካ/የሚያስነካ "
- አስነካ፡ ቀባ (ዘፀ. ፲፪፥፯) ።
- አስነካ፡ አስዳበሰ/አስዳሰሰ (አስላጠ አስገጠበ አስቈሰለ) ።
- አስነካ፡ አስገኘ/አሲያዘ።
- አስነካሪ፡ ያስነከረ/የሚያስነክር።
- አስነካሽ፡ ያስነከሰ/የሚያስነክስ (አዘ ተነከሰ) ።
- አስነኰረ፡ አንኵሩ አለ (እንኵሮ አስ ደረገ አስበሰለ) ።
- አስነኳሪ፡ ያስነኰረ/የሚያስነኵር።
- አስነወረ፡ ልጃገረድን ደፈረ/አበላሸ (ከክብር አሳነሰ - ፪ሳሙ. ፲፫፥፲፬) ።
- አስነዋሪ፡ ያስነወረ/የሚያስነውር።
- አስነዘነዘ፡ አስጨቀጨቀ/አስነተረከ።
- አስነዘዘ፡ ትን አሠኘ።
- አስነዛ፡ አስበተነ/አስረጪ።
- አስነዝናዥ፡ ያስነዘነዘ/የሚያስነዘንዝ (አስጨቅጫቂ) ።
- አስነደለ፡ ኣስፈለፈለ/አስበሳኣሸነቈረ/ኣስቀደደ/አስፈረሰ።
- አስነደቀ፡ አስገነባ/አስናሰ።
- አስነደደ፡ እሳትን እፍ አሠኘ።
- አስነደፈ፡ አስለካ/አስበገረ።
- አስነደፈ፡ አስበተነ/አስጠዘጠዘ/አስወጋ።
- አስነዳ፡ አስቀረበ/አስወሰደ።
- አስነዳይ፡ ያስነደለ/የሚያስነድል (አስፈልፋይ) ።
- አስነዳጅ፡ ያስነደደ/የሚያስነድድ።
- አስነዳፊ፡ ያስነደፈ/የሚያስነድፍ (አስወጊ የምታስነድፍ የፈታይ አለቃዋ) ።
- አስነጂ፡ ያስነዳ/የሚያስነዳ።
- አስነገለ፡ ንቀሉ አለ (አስነቀለ/አስፈለሰ) ።
- አስነገረ፡ አስባለ/አስወራ/አሳወጀ (አስተነባ) ።
- አስነገተ፡ አሲያዘ አሸከመ ባንገት ።
- አስነገደ፡ አስገዛ/አሼጠ/አስለወጠ/አሸቀጠ (ንግድን ባሽከር በወኪል አሠራ) ።
- አስነጋሪ፡ ያስነገረ/የሚያስነግር።
- አስነጋች፡ ያስነገተ/የሚያስነግት ።
- አስነጋጅ፡ ያስነገደ/የሚያስነግድ።
- አስነጐረ፡ አስፈላ/አስቀለጠ።
- አስነጐተ፡ አስጋገረ ዕንጐቻን ።
- አስነጓች፡ ፡ ያስነጐተ/የሚያስነጕት እረኛ።
- አስነጠለ፡ አስለጠጠ/ኣስለየ (ነጠላ አስ ደረገ) ።
- አስነጠሰ (አዕጠሰ)፡ እንዲያነጥስ አስ ደረገ (ዕንጥስ አሠኘ ") ።
- አስነጠረ፡ አስናረ/አዘለለ/አስጓነ።
- አስነጠረ፡ አስፈላ/አስቀለጠ/አስፊ ሰሰ።
- አስነጠቀ፡ አስቀማ/አስወሰደ።
- አስነጠበ፡ አስደፈረ/አስነቀፈ።
- አስነጠበ፡ ጠብ አስደረገ።
- አስነጠጠ፡ አስፋቀ አሰነጠ ።
- አስነጠፈ፡ አስተካ።
- አስነጠፈ፡ አዘረጋ ("አንጥፉ ዘርጉ") ።
- አስነጣ፡ ነጭ አስደረገ።
- አስነጣሪ፡ ያስነጠረ/የሚያስነጥር።
- አስነጣሽ፡ ያስነጠሰ/የሚያስነጥስ (ዐቧራ ደረቅ በርበሬ ") ።
- አስነጣቂ፡ ያስነጠቀ/የሚያስነጥቅ (አስ ቀሚ) ።
- አስነጣይ፡ ያስነጠለ/የሚያስነጥል።
- አስነጣጭ፡ ያስነጠጠ/የሚያስነጥጥ (ያ ንጣጭ አለቃ ") ።
- አስነጣፊ፡ ያስነጠፈ/የሚያስነጥፍ ("ያን ጣፊ አለቃ ራስጌ ቤት") ።
- አስነጨ፡ አስነቀለ።
- አስነጯ፡ አስላጠ/አስመለጠ/አስቈሰለ።
- አስነፈሰ፡ አንፍሱ አለ (እንዲያነፍሱ አስደረገ) ።
- አስነፈገ፡ አትስጥ አለ/አስከለከለ (አ ሠሠተ) ።
- አስነፊ (አንፋኂ)፡ ያስነፋ/የሚያስ ነፋ (እንቢልታን መለከትን) ።
- አስነፊ (አንፋዪ)፡ ያስነፋ/የሚያስ ነፋ (የፈይ አለቃ) ።
- አስነፋ (አንፈየ)፡ እንዲነፉ አዘዘ (ዐሠርንና ዱቄትን አስለየ) ።
- አስነፋ (አንፍኀ)፡ እፍ አሠኘ (እን ዲነፋ አስደረገ - ማቴ. ፮፥፪ - "ሻለቃው ግብር ሲያበላ መለከት ያስነፋል") ።
- አስነፋ፡ አሳበጠ።
- አስነፋሽ፡ ያስነፈሰ/የሚያስነፍስ።
- አስናሰ፡ አሠራ/አስገነባ። ተናሰ፡ ተሠራ/ተገነባ (ናሱ ግንቡ) ።
- አስናረ፡ አስጓነ/እዘለለ።
- አስናቀ፡ እንዲናቅ አስደረገ (አስጠላ - አስናቀ/አስናቀች የወንድና የሴት መጠሪያ ስም) ።
- አስናቂ፡ ያስናቀ/የሚያስንቅ (አስጠሊ) ።
- አስናኘ፡ አሳደለ/አሰጠ/አስበተነ።
- አስናደ፡ አስጐተተ/አዘረጠጠ/አስፈረሰ።
- አስናጠ፡ አስገፋ/ኣስወዘወዘ/ኣስነቀነቀ።
- አስናፈቀ፡ አሻ/አስፈለገ/አስመኘ።
- አስናፊ፡ ያሰነፈ/የሚያሰንፍ (አቦዛኝ ሥራ አስፈች) ።
- አሥኔት፡ (ሠነየ፡ አሠነየ)፡ አበባ፡ በያይነቱ፡ (ግእዝ)። ባለቅኔዎች፡ ግን፡ አገር፡ ይሉታል።
- አስንዳቦ (ዎች)፡ በወይናደጋ በርሻ ውስጥ የሚበቅል ሣር ፍሬያም ።
- አስኖረ፡ አስቈየ/አስከረመ።
- አስኦሮቢ፡ የሚያስጋልብ/የሚያስሮጥ (አስፈርጣቹ) ።
- አስከለለ፡ አስቈረጠ ("አሰየፈ") ።
- አስከለለ፡ አስወሰነ ("አስገደመ") ።
- አስከለለ፡ ኦስጋረደ ("አስመከተ አስቀ የደ አሳጠረ አስቀጠረ ") ።
- አስከለሰ፡ ዳግመኛ አሠራ ("አስተማረ አስከለሰ አስጨመረ አሳከለ አስከለሰ አስጨረሰ አስመላ ") ።
- አስከለከለ፡ አሳገደ ("አስጠበቀ አስተወ አስከልካይ ያስከለከለ የሚያስከለክል የከልካዮች አለቃ ዕልፍኝ አስከልካይ እን ዲሉ ") ።
- አስከለፈ፡ አስቀማ ("አስነጠቀ") ።
- አስከላ፡ ኣስከለከለ ።
- አስከላሽ፡ ያስከለሰ/የሚያስከልስ ("፪ኛ ጊዜ አስተማሪ አስጠኒ ") ።
- አስከላይ፡ ያስከለለ/የሚያስከልል ("አስ ጋራጅ ") ።
- አስከልካይነት፡ አስከልካይ መኾን ("ሊ ጋባነት ") ።
- አስከመረ፡ አስደረደረ ("አስጐቸ አስቈ ለለ ") ።
- አስከማሪ፡ ያስከመረ/የሚያስከምር ("አስጐቺ አስቈላይ ") ።
- አስከሠተ፡ አስገለጠ ።
- አስከሬናም፡ ጣጋ ጠጋ ሰው ።
- አስከበረ፡ አሲያዘ፡ አስጠበቀ፡ የሰውን ቤት ንብረት። አስከበረን አሲያዘ ማለት ከጣሊያን ወዲህ የመጣ ዐማርኛ ነው። አስከባሪ፡ ያስከበረ፡ የሚያስከብር። ሕግ አስከባሪ እንዲሉ።
- አስከበረ፡ ክብር፡ ሹመት፡ ሽልማት፡ ማዕርግ፡ አሰጠ።
- አስከበበ፡ አስከበረ፡ አኰራ፡ አላሳብ አስቀመጠ፡ አቈየ፡ ይህ ገንዘብ ብዙ ጊዜ ያስከብበኛል ።
- አስከበተ፡ አስደበቀ ("አሳባ ") ።
- አስከበደ፡ ከባድ አስደረገ፡ አስጨቁን።
- አስከባሪ፡ አሲያዥ፡ አስጠባቂ።
- አስከባቢ፡ ያስከበበ፡ የሚያስከብብ፡ አዝማች የጦር መሪ ፊታውራሪ ዞ
- አስከተረ፡ አስደለደለ ("አስከበበ አሳገደ እንዳይኼድ እንዳይወርድ አስደረገ አስበዛ አስከታሪ ያስከተረ የሚያስከትር አሳ ጋጅ ስፍራ ማስከተር ማስከበብ ማሳጋድ ማስከተሪያ ማስከበቢያ ማሳገጃ ጊዜ ተከተረ ተደለደለ ተከበበ ተገደበ ታገደ በዛ ባጤ ይሙቱ የተከተረ በስለት የተመተረ ተከተረ በልብ ተያዘ ዐደረ ተከታሪ የሚከተር ተከባቢ ክትር ") (ክቱር) ።
- አስከነበለ፡ አስደፋ ("አስገለበጠ አስከነበለ አስከደነ አስገጠመ አስከነበለ ወስከንባይ አሰፋ ") ።
- አስከነከነ፡ አስቀነቀነ ("አሳወከ ዐሳብን ") ።
- አስከነዳ፡ አስለካ ("አስመጠነ አስከነዳ አስከፈለ አሰጠ ዕዳን ") ።
- አስከንባይ፡ ያስከነበለ/የሚያስከነብል ("አስደፊ ኣስከዳኝ ") ።
- አስከንጂ፡ ያስከነዳ/የሚያስከነዳ ("አስ ለኪ አስከፋይ ከፈል ") ።
- አስከኪ፡ ያስከካ/የሚያስከካ ።
- አስከካ፡ ኣስፈነከተ ("አሰበረ") ።
- አስከየ፡ አስለገመ ፥ —(ከየ) ።
- አስከደነ፡ አሰለተ ("አስከፈከፈ አስለበሰ አስገጠመ ") ።
- አስከዳ (አክድዐ)፡ ከዳተኛ አደረገ ("አሸፈተ ይዞ ኼደ ከደነ አስከደነ ብለኸ ኣስከዳኝን ተመልከት መካር ") ።
- አስከዳኝ (ኞች)፡ ያስከደነ/የሚያስከድን ("የከዳኞች አዛዥ የቤት ጌታ ") ።
- አስከዳኝ (አክድዐኒ)፡ የከዳ አስደራጊ አንቀጽ ("የሩቅ ወንድ ") ።
- አስከጀለ፡ አሳሰበ ("አሠኘ አስመì አስፈለገ ") ።
- አስከጂ፡ ያስከዳ/የሚያስከዳ ("መጥፎ ") ።
- አስከጃይ፡ ያስከጀለ/የሚያስከጅል ("እ ሳሳቢ ") ።
- አስከፈለ፡ ዕዳን አስገባ ("አሰጠ አስ ቀበለ ") ።
- አስከፈከፈ፡ አስከደነ ("አስመታ አስከፈከፈ አስበጠረ አስከመከመ ") ።
- አስከፈፈ፡ ክፈፍ አስደረገ/አሰፋ ።
- አስከፊ፡ ያስከፋ/የሚያስከፋ ("አሳዛኝ") ።
- አስከፊታ፡ የምታስከፋ ሴት ("አስቀያሚ ነገር ") ።
- አስከፋ፡ አስቀየመ ("አሳዘነ ") (ግብ. ሐዋ. ፲፬፡ ፪) ።
- አስከፋች፡ ያስከፈተ/የሚያስከፍት ።
- አስከፋይ (ዮች)፡ ያስከፈለ/የሚያስከ ፍል ("አስቀባይ ዋስ ዳኛ ") ።
- አስከፋፊ፡ ያስከፈፈ/የሚያስከፍፍ ።
- አስኪያጅ (ጆች)፡ ያስኬደ ("ስኬድ አዛዥ አሠሪ ሥራ መሪ ሥራ አስኪያጅ እንዲሉ ") ።
- አስካለ ማርያም፡ ለሴት ልጅ የሚሰጥ የክርስትና ስም።
- አስካል፡ የወይን ዘለላ፡ ሰከለ ።
- አስካል፡ የወይን/የበለስ/የሌላውም ተክል ዛላ/ዘለላ።
- አስካሰክ፡ አሰራረር፡ መሰክሰክ።
- አስካሪ፡ ከዚህ በላይ የተጻፈውን ለሰው/ለዓ... ሰጥቶ የሚያሰክር ሰው።
- አስካሪ፡ ያሰከረ/የሚያሰክር (ጠላ፡ ጠጅ፡ ዐረቄ፡ ብርብራ፡ እንቧይ፡ ቀጥና፡ ቍልቋል፡ እንዶድ የመሰለው ኹሉ) ። (ውርድ)፡ "ከጠጅ ወዲያ አስካሪ፡ ከባለቤት ወዲያ መስካሪ፡ ከእግዚአብሔር ወዲያ ፈጣሪ።"
- አስካሪነት፡ አስካሪ መኾን።
- አስካበ፡ ካቡ አለ፡ አሠራ ካብን። አስካቢ፡ ያስካበ፡ የሚያስክብ። ማስካብ፡ ካብ ፥ ማሠራት ።ማስካቢያ፤ትእዛዝ፡ የቤት ዙሪያ፣ ም
- አስካነ (አክሀነ)፡ አስዳቈነ ("ድቍና አስቀበለ ካህን አስደረገ ክህነት አሰጠ ") ።
- አስካኝ፡ ያስካነ/የሚያስክን ("አዳቋኝ ") ።
- አስካኪ፡ ያስካካ/የሚያስካካ ("ዶሮ ቆቅ ሲካካ የምታስካካ ቄብ ዶሮ ዕንቍ ላል መውለድ የምትች ") ።
- አስካካ፡ እንስት ፈለገ ፥ —(ካካ) ።
- አስካካ፡ ድምጥ ሰጠ ("ተጣራ ምግብ እንስት ሻ ፈለገ የፈረስ ያህያ የበቅሎ የዥብ ዛሬ ሌሊት ዥቡ ስሪያ ይዞ ሲያስካካ ዐደረ ") ።
- አስካካች፡ (ዘፈነች) አውራ ፈለገች ዶሮዪቱ ።
- አስካደ (አክሐደ)፡ ከሓዲ አደረገ ("እምነትን አስለቀቀ አስተወ") (ማር. ፱፡ ፵፪) ።
- አስካደ፡ አስለየ ("አስረገመ") ።
- አስካደ፡ አሸፈጠ ("ያየውን አላየኹም የሰማውን አልሰማኹም አሠኘ") ።
- አስካጅ (ጆች)፡ ያስካደ/የሚያስክድ ("ሰይጣን መናፍቅ ገንዘብ") ።
- አስኬደ (አኬደ)፡ አስረገጠ ("አሳለፈ አራመደ ስፍራ አስለቀቀ የሚያ አስኬደ አዘዘ እሠራ") ።
- አስክርት (አስክሮት)፡ ዓሣ ማስከሪያ ቀን።
- አስኰለፈ፡ አስነካ ("አስበከለ አስጠፋ ") ።
- አስኰላ፡ አሳጠበ ("አስወለወለ አሳደሰ በኮመር አስነከረ ") ።
- አስኰልኳይ፡ ያስኰለኰለ/የሚያስኰለኵል ("አስደርዳሪ ኣስተካይ ") ።
- አስኮበ፡ አስደወረ፡ አስጠነጠነ፡ አስጠቀ
- አስኰበለለ፡ ወንድ ልጅንና ልጃገረድን አስከዳ ።
- አስኰብላይ (ዮች)፡ ያስኰበለለ " የ ሚያስኰበልል ("የልጅ ሌባ") ።
- አስኰነነ፡ አስፈረደ ("አስቀጣ ቅጣት አሰጠ አስቀበለ በነፍስ ") (ሮሜ. ፲፬፡ ፳፫) ።
- አስኰናኝ (ኞች)፡ ያስኰነነ/የሚያስ ኰንን ("አስፈራጅ አስጐጂ ድኻ ምስኪን የተገፋ የተበደለ ") ።
- አስኰኳ፡ አስመታ ("ኣስፈነከተ") ።
- አስኰኳ፡ አስጣለ ("አስወደቀ") ።
- አስኰኳ፡ አሼጠ ("አስለወጠ") ።
- አስኰፈሰ፡ አስመየደ ("አስበጠረ አስ ሰገነ ") ።
- አስኰፈሰ፡ የማይረባ ምስጋና አሰጠ ።
- አስኳለ፡ አስቀባ ("አስጌጠ ሸፋሽፍትን") ።
- አስኳል (ሎች)፡ የዶሮ/የወፍ/ያሞራ ዕንቍላል ፍሬ (ብጫ መልክ) ።
- አስኳል፡ ሰባት ውስጥ ያለ ዕጢ፡ ዳግመኛም ፈርስ ይባላል።
- አስኳል፡ በቁሙ ፥ —ሰከለ ።
- አስኳይ፡ ያስኳለ/የሚያስኵ ።
- አስወለለ፡ እስከፈለ ፥ አሠነጠቀ ("አስከ ፈተ") ።
- አስወለቀ፡ አስበጠበጠ/አስመታ ።
- አስወለቀ፡ አሶለቀ/አስነቀለ/አስፈ ለሰ/አስወጣ/አስመነገለ ።
- አስወለወለ፡ በጥፊ አስመታ/አስጠፈ ጠፈ ።
- አስወለወለ፡ አስጠረገ/አላሠሠ/አሳበሰ ።
- አስወለደ፡ አሶለደ ("ሚስቱን እንድት ወልድ አስደረገ ወንድ ወይም ሴት ልጅ አስገኘ አስረባ") ።
- አስወለዶ፡ አስከፈለ ።
- አስወላቂ፡ ያስወለቀ/የሚያስወልቅ ("አስነቃይ") ።
- አስወላጅ፡ ያስወለደ/የሚያስወልድ ("አ ባት አውራ") ።
- አስወሰነ፡ አስደነገገ/አስደነባ/አስገ ደበ/አስከለከለ/አስከለለ ።
- አስወሰወሰ፡ አስዋኘ ("በባሕር ውስጥ አስኬደ") ።
- አስወሰወሰ፡ አሸደሸደ/አሸከሸከ ።
- አስወሰደ/አሶሰደ፡ አስጋዘ/አስነዳ/አስቀረበ/አስቀማ/አስጠፋ ።
- አስወሣ/አሶሣ፡ አሳሰበ/አናገረ/አ ስመለሰ ("ቃል አሰጠ") ።
- አስወሳጅ፡ ያስወሰደ/የሚያስወስድ ("አ ስነጣቂ አስጠፊ") ።
- አስወረሰ፡ አለፈቃድ ርስትን ንብረትን ኣስወሰደ ።
- አስወረሰ፡ አስፈጸመ/አሳለቀ/አስከ ወነ ።
- አስወረረ፡ አስከበበ/አዘረፈ/አስበዘበዘ/ኣስበረበረ/አስማረከ ።
- አስወረቀ፡ አስቦረቀ/አዘለለ/አስጨፈረ ።
- አስወረበ፡ አሳወደ/አስላዉ ።
- አስወረበ፡ ወረብ አስደረገ/አስቀነቀነ ።
- አስወረበ፡ ውርባ አስጣለ ።
- አስወረወረ፡ አስቀረቀረ/አሸጐረ/አስ ቈለፈ ።
- አስወረወረ፡ አስጓነ/አስጣለ ።
- አስወረደ/አሶረደ፡ (ግብ. ሐዋ. ፳፪፡ ፴) ኣሽቈለቈለ ("ወደ ታች አስመጣ አስለቀቀ አስለየ አስወገደ እከሌ ዋስትናውን ከራሱ አሶረደ” እንዲሉ) ።
- አስወረፈ፡ አሰደበ/ኣፀረፈ ።
- አስወራ፡ አስነገረ/አስባለ ወሬን ("እንዲህ ቢኾን እንዲህ ነው አሠኘ") ።
- አስወራሪ፡ ያስወረረ/የሚያስወርር ("አ ስከባቢ አዘራፊ") ።
- አስወራሽ፡ ያስወረሰ/የሚያስወርስ ("ዳኛ ወንጀል") ።
- አስወራቂ፡ አስቦራቂ/አስጨፋሪ ።
- አስወራቢ፡ ያስወረበ/የሚያስወርብ ("አስቀንቃኝ") ።
- አስወራጅ፡ ያስወረደ/የሚያስወርድ ("በ ሽታ መድኀኒት") ።
- አስወራፊ፡ ያስወረፈ/የሚያስወርፍ ("አ ሰዳቢ") ።
- አስወርዋሪ፡ ያስወረወረ/የሚያስወረውር ("አስቀርቃሪ") ።
- አስወሸለ፡ አስወከለ/አስወተፈ ("አስገባ") ።
- አስወሸለ፡ ኣሸፈነ ("የማይታይ አስደ ረገ") ።
- አስወሸመ፡ ውሽማ ኣሲያዘ ("አቃጠረ") ።
- አስወሸከተ፡ አስቀባጠረ/አስለፈለፈ ።
- አስወሻሚ፡ ያስወሸመ/የሚያስወሽም ("አቃጣሪ") ።
- አስወቀሠ/አሶቀሠ፡ አስገሠጸ/አዘ ለፈ/አስቈጣ/አስመከረ ።
- አስወቀረ/አሶቀረ፡ አስነቀሰ/አስ ጠረበ ("ስል ሻካራ አስደረገ") ።
- አስወቀጠ፡ አስቀጠቀጠ/አስመታ ።
- አስወቀጠ/አሶቀጠ፡ አስፈተገ/አሸ ከሸከ ።
- አስወቃ/አሶቃ፡ አስጣለ/አስመታ/አስደበደበ ("አስኼደ አስፈለፈለ") ።
- አስወቃሪ፡ ያስወቀረ/የሚያስወቅር ("አ ስነቃሽ አስጠራቢ") ።
- አስወቃሽ፡ ያስወቀሠ/የሚያስወቅሥ ("እስነቃፊ አስቈጭ አስመካሪ") ።
- አስወቃጭ፡ ያስወቀጠ/የሚያስወቅጥ ("አስቀጥቃጭ ኣስፈታጊ አሸክሻኪ") ።
- አስወተተ፡ አስባከነ ("ዕረፍት ነሣ") (መቅ. ወን. ገጽ ፲፯) ።
- አስወተፈ፡ አሸጐጠ/አስከደነ ።
- አስወነበደ፡ አሳተ/አስነጠቀ/አስቀማ ።
- አስወነበደ፡ አስደነበረ/አሸሸ/አስጋ ለበ/አስሮጠ ።
- አስወነጀለ፡ ወንጀለኛ አስደረገ ("በኀ ጢአት አስከሰሰ") ።
- አስወነጨፈ፡ በወንጭፍ አስወረወረ/አስመታ ።
- አስወንጃይ፡ ያስወነጀለ/የሚያስወነጅ ።
- አስወከለ፡ ተጠሪ አሰጠ ("ቶፋ አስ ደረገ") ።
- አስወዘመ፡ ዋዜማ አስደረገ/አቆመ ።
- አስወዘተ፡ በነዲድ አጠገብ ቍጭ አስደረገ ።
- አስወዘወዘ፡ እሰበቀ/አስነቀነቀ ።
- አስወዘፈ፡ አስወዘተ/አስረፈቀ ("አስ ተወ") ።
- አስወየዘረ፡ አሸለመ ("ጌጠኛ አስደረገ") ።
- አስወደለ፡ አስወፈረ/አስደነደነ ።
- አስወደለ፡ ውዴላን አስጫነ/አስጨመረ ።
- አስወደረ፡ አስገመደ/አስጠመረ ።
- አስወደረ፡ አስጠመጠመ/አሳሰረ/አስ ሳሳሪ ።
- አስወደረ፡ እሰጥ አሠኘ ።
- አስወደቀ፡ አስጣለ/አስጋደመ/አስረ ከሰ ።
- አስወደበ፡ ወደብ አሠራ ("ዳር አስ") ።
- አስወደነ፡ አሳሰረ/አስቀረቀበ ።
- አስወደነ፡ አስቦደነ/አስደገደገ ።
- አስወደደ (አሶደደ)፡ አስፈቀረ/አስ ፈቀደ ።
- አስወደደ፡ አስቈረጠ/አሠነጠቀ ።
- አስወደደ፡ አስከበበ/አሳገደ ።
- አስወዳሪ፡ ያስወደረ/የሚያስወድር ("አ ሳሳሪ") ።
- አስወዳቂ፡ ያስወደቀ/የሚያስወድቅ ።
- አስወዳጅ፡ ያስወደደ/የሚያስወድድ ("የሚያስፈቅድ አስፈቃጅ") ።
- አስወገረ፡ አስመታ/አስደበደበ ።
- አስወገረ፡ አስጣለ/አስከመረ ።
- አስወገሸ፡ አስቈጣ/አስወነበደ/አስፈ ረጠጠ ።
- አስወገዘ፡ አስገዘተ ("ውጉዝ አሠኘ አስ ለየ አስወገደ") ።
- አስወገጠ፡ አሳወከ/አስወጠረ ።
- አስወገጠ፡ አስወቀጠ ።
- አስወጊ (ዎች)፡ ያስወገደ/የሚያስወግድ ("የሚያርቅ አግላይ") ።
- አስወጊ፡ ያስወጋ/የሚያስወጋ ("አስጠሊ አስመራዥ") ።
- አስወጋ (አውግዐ)፡ አስወራ/አስነ ገረ ወግን ።
- አስወጋ፡ አስለተመ/አስተመተመ/አስ ነደፈ/አስጠቀጠቀ ።
- አስወጋ፡ አስጠላ/አስመረዘ ።
- አስወጋ፡ አጻፈ/አስመለከተ ("ግንባሩን አስወጋ አሳየ መኖሩን አስረዳ") ።
- አስወጋሪ፡ ያስወገረ/የሚያስወግር ("አስ ደብዳቢ ኣስመቺ") ።
- አስወጋዥ፡ ያስወገዘ/የሚያስወግዝ ("እ ስገዛች") ።
- አስወጋጅ፡ ያስወገደ/የሚያስወግድ ("አስገላይ") ።
- አስወጠረ፡ አስነፋ/አስቀበተተ/ኣዘረጋ/ አሳበ/አስለጠጠ/አስገተረ ።
- አስወጠረ፡ አስኰራ/አስቈነነ/አስቋፈ ።
- አስወጠረ፡ አስጠየቀ/አስወገጠ ።
- አስወጠቀ፡ አስጠቀጠቀ ("አላወቀ") ።
- አስወጠነ/አሶጠነ፡ አዠመረ/አስፈ ለመ ("ዠምሩ አለ") ።
- አስወጣ፡ አሶጣ ("እንዲያወጡ አስደ ረገ ከቤት ከበረት ካጥር ግቢ ከቤተ ክሲ ያን ካትክልት ከዝሪት ሰውን እንስሳን ከለ ከለ ነዳ ሐይ አለ (ተረት) ጦጣ ባለቤቱን ' ታሶጣ ወይ ጣጣ በዚህም አያሶጣ (ካገር አስወጣ) ክፉ ሰውን አበረረ አሰደደ ዕድር ተኛው") ።
- አስወጣሪ፡ ያስወጠረ/የሚያስወጥር ።
- አስወጣኝ (አውፅአኒ)፡ ከውስጥ ወደ ውጭ አስኬደኝ ።
- አስወጣኝ፡ ያስወጠነ/የሚያስወጥን ("አዠማሪ") ።
- አስወጭ፡ ያስወጣ/የሚያስወጣ ("ነጂ እረኛ ከልካይ") ።
- አስወጭ፡ ግብር አስከፋይ (፪ ሳሙ. ፳፡ ፳፬) ።
- አስወጭና አስገቢ፡ አጋፋሪ ሊጋባ መጨኔ ።
- አስወፈረ፡ ወፋር አስደረገ/አስደነደነ ።
- አስዋለለ፡ አስዋዠቀ ።
- አስዋሰ፡ ዕቃ አሰጠ/አስበደረ ።
- አስዋሰ፡ ዋስ አስጠራ ።
- አስዋሸ፡ አሳበለ/አስቀጠፈ ("ሐሰት ው ሸት አናገረ") ።
- አስዋበ፡ አሰጠ/አስቀበለ ።
- አስዋበ፡ አስቈነዠ ("ቈንዦ አስደረገ") ።
- አስዋኘ/አሷኘ (አጽበተ)፡ አስወ ሰወሰ ("ዋና አስተማረ አንሳፈፈ አንካፈፈ በባሕር ላይ ኣስኬደ") ።
- አስዋጀ፡ አስገዛ/ኣስዳነ/ኣስተረፈ ("ከግዞት ከመታሰር") ።
- አስዋጠ፡ አሷጠ ("ያለውድ በግድ አ ስጐረሠ አስበላ የኮሶ የመድኀኒት") ።
- አስዋጭ፡ ያስዋጠ/የሚያስውጥ ("ዐለ ንጋ ይዞ አስፈራርቶ") ።
- አስደለለ፡ ኣስሞኘ/ኣሸነገለ ።
- አስደለሰ፡ አስላከከ/አስቀባ ።
- አስደለቀ፡ አስመታ/አስደሰቀ/አስጐ ሰመ ።
- አስደለበ፡ አዘገበ/አሰበሰበ/አስቈየ ።
- አስደለኸ፡ አስፈጪ/አስላቈጠ/አስ ።
- አስደለዘ፡ አስወቀጠ/አስወገጠ ።
- አስደለዘ፡ ኣስመረገ/አስደፈነ/አስበየደ ።
- አስደለደለ፡ አሳገደ/አስከተረ ።
- አስደለደለ፡ አስመላ/አስጨመረ ፥ አስ መደመደ ።
- አስደለፈሰ፡ እዛቀ/አሰረረ ።
- አስደላይ፡ ያስደለለ/የሚያስደልል ።
- አስደልዳይ (ዮች)፡ ያስደለደለ/የሚ ያስደለድል ("አስከታሪ") ።
- አስደመመ፡ አስደነቀ/አስገረመ ።
- አስደመመ፡ አዘጋ/አስደፈነ ።
- አስደመሰሰ፡ አስፋቀ/አስፈገፈገ/አስ ጠፋ ።
- አስደመረ፡ አሰበሰበ/አንድ ላይ አስ ደረገ/አስቆመ/አስጠመጠመ ።
- አስደመደመ፡ አስረገጠ ("ትክክል አስ") ።
- አስደመደመ፡ አስጨረሰ/አስፈጸመ/አስቈረጠ ።
- አስደመጠ (አድመፀ)፡ አሰማ ።
- አስደማሚ፡ ያስደመመ/የሚያስደምም ("አስደናቂ አስደፋኝ") ።
- አስደማሪ፡ ያስደመረ/የሚያስደምር ("አስጠምጣሚ") ።
- አስደምዳሚ፡ ያስደመደመ/የሚያስደ መድም ("አስጨራሽ") ።
- አስደሰመ፡ አስጎ/አስለተመ ።
- አስደሰመ፡ ዐጥር አሳጠረ ("እሾኽ አ ስወዘፈ አዘጋ አስደፈነ") ።
- አስደሰቀ፡ አስመታ/አስደቃ ።
- አስደሰቀ፡ አስሞቀ/አስደበተ ።
- አስደሰተ (አስተፍሥሐ)፡ ደስታ ሰ በሥራ በነገር ።
- አስደሳች፡ ያስደሰተ/የሚያስደስት ።
- አስደረመሰ፡ አስደረባ/አስፈረሰ/አስናደ ።
- አስደረቀ፡ ፀሓይና እሳት አስመታ ("ደ ረቅ አስደረገ") ።
- አስደረበ፡ አስካበ/ድርብ አሠራ/አስ ለበሰ/አሳጠፈ ("ዕጥፍ አስደረገ") ።
- አስደረባ፡ አስናደ/አስወደቀ ።
- አስደረተ፡ አስደበደበ ("ደባደቦ አሰፋ") ።
- አስደረነቀ፡ አሳመቀ/አስረጠጠ ።
- አስደረዘ፡ ደርዝ አሰፋ/አስደረገ ("አ ስለጐመ") ።
- አስደረደረ፡ በገና አስመታ ።
- አስደረደረ፡ አሰደረ/አስኰለኰለ/አስ ደከነ/አስገረገረ ።
- አስደረገ (ባንድ እግር አስረገጠ አስኬደ - ፪ሳሙ. ፰፥ ፬) ።
- አስደረገ (አድረገ)፡ አሠራ/አስበጀ/አስከወነ/አስፈጸመ ።
- አስደረገመ፡ አስመረገተ/አስጠፋ ።
- አስደረጠ፡ አሳሸ/አስመታ ።
- አስደረጠ፡ አስበጠበጠ/አሳወከ/አስ ነቀነቀ ።
- አስደራ፡ አስለመጠ ።
- አስደራ፡ አስተረተረ/አዘረጋ ።
- አስደራቢ፡ ያስደረበ/የሚያስደርብ ።
- አስደራች፡ ያስደረተ/የሚያስደርት ።
- አስደራጊ፡ ፪ኛ ዐምድ ("አስገደለ አ ሠሪ አካል አስገዳይ") ።
- አስደራጊ፡ ያስደረገ/የሚያስደርግ/የሚ ያስበጅ ።
- አስደርዳሪ፡ ያስደረደረ/የሚያስደረድር ።
- አስደርጎ፡ አሠርቶ/አስበጅቶ ።
- አስደቀቀ፡ አስፈጪ/አሰለቀ/አስላመ/አስለዘበ ።
- አስደቀነ፡ አስቀረበ/አስቋተ/አስደከረ ።
- አስደቀደቀ፡ አስወቀጠ/አስወጋ/አስጠ ቀጠቀ ("አስከረና") ።
- አስደቂ፡ ያስደቃ/የሚያስደቃ ።
- አስደቃ፡ አስመታ/አስወጋ ("ደቅ አስ") ።
- አስደቈሰ፡ አስመታ/አስዳመጠ ።
- አስደቅዳቂ፡ ያስደቀደቀ/የሚያስደቀድቅ ።
- አስደቋሽ፡ ያስደቈሰ/የሚያስደቍስ ።
- አስደበለ፡ አስጨመረ/አስደረበ/ኣሸ ረበ/አስጠሞረ/አስቀየጠ ።
- አስደበረ፡ ደብር አስደረገ/አስገደመ/አስከበረ/ኣስበለጠ ።
- አስደበቀ፡ አስከተተ/አሸጐጠ/አሳባ/አሰወረ/ኦሸሸገ ።
- አስደበበ፡ አዘረጋ/አስወጠረ ።
- አስደበተ፡ አስጨቈነ/አስከበደ ።
- አስደበደበ ።
- አስደባ፡ አስደበቀ/አስደፈጠ (ጥሸ) አሸ ።
- አስደባሪ፡ ያስደበረ/የሚያስደብር ።
- አስደባቂ፡ ያስደበቀ/የሚያስዶብቅ (አ ሸሻጊ) ።
- አስደነሰረ፡ አስቸሰረ/አስረፈቀ ።
- አስደነቀ፡ አስገረመ/አስደመመ (መሳ. ፬፡ ፲፭) ።
- አስደነቀረ፡ አሸጐረ/አስቀረቀረ/አስ ።
- አስደነቈለ፡ አስጠነቈለ/አስወጋ/አስነ ።
- አስደነበ፡ ኣስደነዘ/ኣስፈዘዘ ።
- አስደነበረ፡ አስደነገጠ/አስፈራ/አስ ፈገፈገ ፥ አሸሸ ("አዘለለ") ።
- አስደነበቀ፡ አስቀዳ/ኣስጠለቀ ።
- አስደነባ፡ አሳገገ/አስወሰነ/አሳወጀ ።
- አስደነከረ፡ አዘለለ/አስረገደ ።
- አስደነዘ፡ ደነዝ አስደረገ ("አስጠረሰ") ።
- አስደነደነ፡ ደንዳና አስደረገ ("አስወፈረ") ።
- አስደነገለ፡ አስጠበቀ (ልጃገረድን) ።
- አስደነገገ፡ አስወሰነ/አሳገገ/አስደነባ/አስጠነቀቀ ።
- አስደነገጠ (አደንገፀ)፡ አስፈራ ' አ ባባ/አሳዘነ (ሉቃ. ፭፡ ፱) ።
- አስደነገጠ፡ ታየ/ተጣባ ("ኮሶ አስደ ነገጠኝ” እንዲሉ) ።
- አስደነጐረ፡ አስደደቀ/አስቈፈረ/አስ ፈነቀለ/አስገለበጠ ።
- አስደነፈቀ፡ አስለቀሰ/አንሠቀሠቀ አ ስረቀረቀ ።
- አስደነፋ፡ አስፎከረ/ዐካኪ/ዘራፍ አ ሠኘ ("ግዳይ አስቈጠረ") ።
- አስደናቂ (ቆች)፡ ያስደነቀ/የሚያስ ደንቅ ("አስገራሚ") ።
- አስደንቢ፡ ያስደነባ/የሚያስደነባ ።
- አስደንባሪ፡ ያስደነበረ/የሚያስደነብር ("አስፈሪ አስደንጋጭ") ።
- አስደንጋጊ፡ ያስደነገገ/የሚያስደነግግ ("አስወሳኝ") ።
- አስደንጋጭ (ጮች)፡ ያስደነገጠ ' የ ሚያስደነግጥ ("አሳዛኝ") ።
- አስደንግጥ፡ ዝኒ ከማሁ ("የሚያስፈራ አድባር አስደንግጥ ገበሬ አስደንግጥ” እንዲሉ) ።
- አስደንጓሪ፡ ያስደነጐረ/የሚያስደነጕር ("አስደዳቂ አስፈንቃይ") ።
- አስደንፊ፡ ያስደነፋ/የሚያስደነፋ ("አስ ፎካሪ") ።
- አስደከረ፡ አስደቀነ/አስገተረ/አስ ቆመ ("አሰለፈ") ።
- አስደከነ፡ ኣሰደረ/አስደረደረ ።
- አስደካኝ፡ ያስደከነ/የሚያስደክን ።
- አስደወለ፡ አስመታ/አስጠዘለ ።
- አስደወረ፡ አዘወረ/አስጠነጠነ/አስጠ ቀለለ/አስቀለመ ።
- አስደዋሪ፡ ያስደወረ/የሚያስደውር (አ ስጠንጣኝ) ።
- አስደዋይ፡ ያስደወለ/የሚያስደውል ።
- አስደዘደዘ፡ ኣስመታ/አስወቀጠ ።
- አስደደቀ፡ አስወጋ/ኣስፈነቀለ ፥ አስደ ነጐረ/አስገለበጠ ።
- አስደደቀ፡ አስወጋ/ኣስፈነቀለ ፥ አስደ ነጐረ/አስገለበጠ ።
- አስደዳቂ፡ ያስደደቀ/የሚያስደድቅ (አ ስፈንቃይ ኣስደንጓሪ) ።
- አስደዳቂ፡ ያስደደቀ/የሚያስደድቅ (አ ስፈንቃይ ኣስደንጓሪ) ።
- አስደገለ፡ አስቀየመ ("ቂም ኣሲያዘ") ።
- አስደገለለ፡ አስጠቀለለ/አስጠመጠመ ("ክብ አስደረገ") ።
- አስደገመ፡ አሳከለ/አስጨመረ ("፪ኛ አሰጠ አስቀበለ") ።
- አስደገመ፡ አስነበበ/አስተማረ/አሳወቀ/አስጨረሰ/አጸለየ ።
- አስደገሰ፡ አስቈላ/አስፈጪ/አሶቀጠ/አስጠመቀ/አስደለሽ ።
- አስደገደገ፡ አስወደነ/አስታጠቀ ።
- አስደገደገ፡ አስፈራ/አራደ ፥ አንቀጠ ።
- አስደገገ፡ አስኰራ/እሳጀረ ("ሌላውን ኣስናቀ አስነቀፈ") ።
- አስደገፈ፡ ኣሳቀበ/ኣሲያዘ/አሳገዘ/አ ስጠጋ/አንተራሰ ።
- አስደጋሚ፡ ያስደገመ/የሚያስደግም (አስነባቢ ኣስተማሪ) ።
- አስደጋሽ፡ ያስደገሰ/የሚያስደግስ ።
- አስደጋጊ፡ ያስደገገ/የሚያስደግግ ።
- አስደጋፊ፡ ያስደገፈ/የሚያስደግፍ (አሳ ጋዥ) ።
- አስደግዳጊ፡ ያስደገደገ/የሚያስደገድግ (አስታጣቂ አስፈሪ) ።
- አስደጐሰ፡ አስለበሰ/አሸለመ ።
- አስደጓሽ፡ ያስደጐሰ/የሚያስደጕስ (ባለ መጽሐፍ) ።
- አስደፈረ፡ አስበዛ/እስቈለለ ።
- አስደፈረ፡ አስከነ/ኣስናቀ/አሰደበ/አስነጠበ ።
- አስደፈቀ፡ ቈበር አስወጣ ።
- አስደፈቀ፡ አስነከረ/አዘፈቀ ።
- አስደፈቀ፡ አስፈጩ/ኣስላመ ።
- አስደፈነ፡ አስቀበረ/አስመረገ/አስመላ/አዘጋ ።
- አስደፈደፈ፡ አስለጠፈ/አስቀባ/አስመ ረገ ("ድፍድፍ አስደረገ") ።
- አስደፈጠ፡ አሸሸገ/ኣሸመቀ/አስደባ ።
- አስደፈጠጠ፡ አስረገጠ/አስዳጠ/አስ ጨቈነ/አስጨፈለቀ ።
- አስደፊ፡ ያስደፋ/የሚያስደፋ ("አስገል ባጭ አስጋጋሪ") ።
- አስደፋ፡ አስፈሰሰ/አስገለበጠ/አስጋገረ ።
- አስደፋሪ፡ ያስደፈረ/የሚያስደፍር ("አሰ ዳቢ") ።
- አስደፋቂ፡ ያስደፈቀ/የሚያስደፍቅ ።
- አስደፋኝ (አድፍዐኒ)፡ አስፈሰሰኝ ። (ተመልከት፡ ደፋን እይ) ።
- አስደፋኝ፡ ያስደፈነ/የሚያስደፍን ("አ ስቀባሪ አዘጊ") ።
- አስደፍዳፊ፡ ያስደፈደፈ/የሚያስደፈድፍ ።
- አስዳመጠ፡ አስረገጠ/አስለሰቀ ("ዳ መጦ አስደረገ") ።
- አስዳሰ፡ አስፈጪ/አስደቀቀ ።
- አስዳሰሰ፡ አስነካ/አስዳበሰ ።
- አስዳረ፡ አሰረገ ("ለባል አሰጠ") ።
- አስዳረገ፡ ኣሰጠ ድርጎን ።
- አስዳበሰ፡ አስዳሰሰ/አስነካ ።
- አስዳነ፡ አስፈወሰ ("እንዲድን አስደረገ") ።
- አስዳነ ጤና
- አስዳነተ፡ ኣዘበተ/አስፎከረ/አስቈጣ/አሰደበ ።
- አስዳኘ፡ አስከሰሰ ("እዳኛ ፊት አስቀ") ።
- አስዳወረ፡ አስደወረ ።
- አስዳዋሪ፡ አስደዋሪ ።
- አስዳጠ (አድኀፀ)፡ አስረገጠ ("አስ ደፈጠጠ") ።
- አስዳጠ፡ አስፈጪ/አስላመ ።
- አስዳጭ፡ ያስዳጠ ' የሚያስድጥ ፈረሰኛ ።
- አስዶለ፡ አስጨመረ/አስገባ/አስከተተ ።
- አስዶለተ፡ አሳደመ/አስመከረ/ሤራ አስደረገ/ነገር አስቋጠረ ።
- አስዶለዶመ፡ አስደነዘ/አስጐለደፈ ።
- አስዶላች፡ ያስዶለተ/የሚያስዶልት ("አሳዳሚ አስመካሪ") ።
- አስዶበረ፡ አስከፋ/አስቀየመ/አስኰ ረፈ ("ዝም አሠኘ") ።
- አስዶገዶገ፡ አስመረ/አስቀጠነ/አ ስረቀቀ ።
- አስጀጐለ፡ አስካበ/አስገረገረ/አሳጠረ/ኣስቀጠረ/አስማረ/አሸመጠጠ ።
- አስገለለ፡ አሳወደ/አስቈረጠ ።
- አስገለለ፡ አስለየ/አስወገደ/አስራቀ ።
- አስገለበጠ፡ አስቀዳ/አስፈሰሰ/አስከነበለ/አስጨመረ ።
- አስገለበጠ፡ አስተረጐሙ/አስገለጠ ።
- አስገለበጠ፡ አስፈረሰ/አስለወጠ ።
- አስገለበጠ፡ አስፈነቀለ/አስፈቀቀ ።
- አስገለደመ፡ እንደ እስላም ኣስታጠቀ/አስለበሰ ።
- አስገለገለ፡ አስገመሰ/አሳረሰ/አሠራ ።
- አስገለገለ፡ ውሃ አሰጠ/አስጠጣ ።
- አስገለጠ፡ አስገፈፈ/አስከፈተ/አስራቈተ/አስለቀቀ ።
- አስገለፈጠ፡ አሣቀ (ከንፈርን ኣስገለጠ) ።
- አስገለፈፈ፡ አሣቀ (ከንፈርን አስገለጠ) ።
- አስገለፈፈ፡ አስላጠ/አስገፈፈ/አስፋቀ ።
- አስገላመጠ፡ አስገረመመ ።
- አስገላማጭ፡ ያስገላመጠ/የሚያስገላምጥ (አስገርማሚ) ።
- አስገላይ፡ ያስገለለ/የሚያስገልል (አስወጋጅ) ።
- አስገላጭ፡ ያስገለጠ/የሚያስገልጥ (አስገላቢ) ።
- አስገልባጭ፡ ያስገለበጠ/የሚያስገለብጥ (አስደፊ) ።
- አስገልጋይ፡ ያስገለገለ/የሚያስገለግል/የሚያሠራ (አሠሪ) ።
- አስገመለ፡ አስለበለበ (ብ አስመሰለ) ።
- አስገመሰ፡ አስተለመ/አሳረሰ/አስቈረሰ/አስከፈለ ።
- አስገመተ፡ ኣሰላ/አስገመገመ ።
- አስገመነ (አግመነ)፡ አስነደደ/አስበገነ/አስጠቈረ ።
- አስገመደ፡ አስፈተለ/አስከረረ/አሸረበ/አስጠሞረ/አስደበለ ።
- አስገመደለ፡ አስቈረሰ/አስገመሰ ።
- አስገመደለ፡ አስጐደለ/አስቀመጠለ ።
- አስገመገመ፡ አስገመተ/አሸለገ ።
- አስገመገመ፡ አተመመ/አስጮኸ/አስተጋባ ። "ልማዱ ግን ጮኸ ነው።"
- አስገመጠ፡ አስነከሰ/አስቈረሰ/አስበላ ።
- አስገመጠጠ፡ አስነቀፈ/አስናቀ ።
- አስገማሽ፡ ያስገመሰ/የሚያስገምስ (የሚያሳርስ አስተላሚ አስቈራሽ) ።
- አስገማች፡ ያስገመተ/የሚያስገምት (አስገምጋሚ) ።
- አስገማይ፡ ያስገመለ/የሚያስገምል (ኣስለብላቢ) ።
- አስገማጅ፡ ያስገመደ/የሚያስገምድ (አሸራቢ ቤተ ሠሪ) ።
- አስገማጭ፡ ያስገመጠ/የሚያስገምጥ ።
- አስገምዳይ፡ ያስገመደለ/የሚያስገመድል (አስቈራሽ) ።
- አስገምጋሚ፡ ያስገመተ/የሚያስገምት (አስገማች አሰሊ አሳሳቢ) ።
- አስገምጋሚ፡ ያስገመገመ/የሚያስገመግም (ሰማይ ዝናም) ።
- አስገሰለ፡ አነሣሣ/አስቈጣ/አናደደ/አስጮኸ ።
- አስገሰሰ፡ ቀተለ/ገደለ/አሠኘ/አስረባ ።
- አስገሰሰ፡ አስለወጠ/አስገለበጠ/አሻረ ።
- አስገሰሰ፡ አስጠፋ/አስደመሰሰ ።
- አስገሠገሠ፡ አሳደገ/አስረዘመ ።
- አስገሠገሠ፡ አስማለደ (ማለዳ አለዕረፍት በፍጥነት አስኬደ አራመደ) ።
- አስገሠጠ፡ አሳለ/አስነጠሰ ።
- አስገሠጠ፡ አስቀጣ ።
- አስገሠጸ፡ አስቈጣ/ኣዘለፈ ።
- አስገሣ (አጕሥዐ)፡ አስፈሰሰ/አስ ።
- አስገሣ፡ ምግብን አስቀበለ/አሰማማ ።
- አስገሳሽ፡ ያስገሰሰ/የሚያስገስስ (አስ ጠፊ ባለጋራ ሚዜ ቅኔ ተቀባይ) ።
- አስገረመ፡ አስደነቀ/አስፈራ (ዕብ. ፲፪፡ ፳፩) ።
- አስገረመመ፡ አስገላመጠ (ባይን ቂጥ አስተየ) ።
- አስገረሰሰ፡ አስነቀለ/እስፈለሰ/ኦስ ።
- አስገረዘ፡ አስቈረጠ/አስቀነጠበ ።
- አስገረደመ፡ አስገመጠ/አሰበረ/አስ ።
- አስገረገረ፡ አሳወከ/አስቆመ ።
- አስገረገረ፡ አስቀረቀረ/አስገደገደ/አስተከለ ።
- አስገረፈ፡ አስመታ/አስቈነደደ/አስለቈ ጠጠ/አስቀጣ ።
- አስገሪ፡ ያስገራ/የሚያስገራ (የፈረስ የበቅሎ ባለቤት ባልደራስ) ።
- አስገራ (አረየፀ)፡ እንዲቀመጥ እንዲያስለምድ አስደረገ ።
- አስገራሚ፡ ያስገረመ/የሚያስገርም (አ ስደናቂ) ።
- አስገራዥ፡ ያስገረዘ ይዞ የሚያስገርዝ (አባት እናት) ።
- አስገራፊ (ፎች)፡ ያስገረፈ/የሚያስ ገርፍ (ሹም ዳኛ) ።
- አስገርማሚ፡ ያስገረመመ/የሚያስገረ ምም (አስገላማጭ) ።
- አስገሸለጠ፡ አሣቀ/አስገለፈጠ/አስገ ።
- አስገሸለጠ፡ እስላጠ/አስገፈፈ ።
- አስገበረ (አጸብሐ)፡ አሠራ፡ ግብር አስከፈለ/አስቀረጠ። "ጌታችን እንደ ሰውነቱ ገበረ፡ እንዳምላክነቱ ባሕርን አስገበረ" (ማቴ. ፲፯፡ ፳፯) ።
- አስገበረ፡ ባሪያ/ዜጋ/ተገዥ አደረገ/አስደረገ።
- አስገበዘ፡ አስደለዘ፡ ግብዝ አስደረገ።
- አስገበዘ፡ ግብዝና ኣሾመ።
- አስገበየ፡ አስገዛ፡ አስለወጠ።
- አስገበደ፡ በሰፊው አስፈለጠ፡ አስተረጠቀ።
- አስገበገበ፡ አስቸኰለ (ተመልከት፡ ሰገበ)።
- አስገበገበ፡ አስቸኰለ ሰገበ ።
- አስገበገበ፡ አስቸኰለ፡ አጣደፈ (በምግብ ጊዜ) ።
- አስገበጠ፡ አስመታ፡ አስለየ፡ አስከመረ።
- አስገቢ፡ ያስገባ የሚያስገባ፡ አስከታች አስጨማሪ ።
- አስገባ (አግብአ)፡ አስከተተ አስጨመረ አስዶለ፡ ወደ ውስጥ ኣስመጣ ። (ዮሐ ፲፰ ፥ ፲፮) ። ባድራጊነትም ኣገባ ተብሎ ይፈታል ።
- አስገባሪ (መጸብሕ)፡ የሚያሠራ/የሚያስገብር (ግብር እስከፋይ/ኣስገቢ/አስቀራጭ) (፩ነገ. ፫፡ ፯፡ ፪ዜና. ፲፡ ፲፰) ።
- አስገብጋቢ፡ ያስገበገበ፡ የሚያስገበግብ (አስቸኳይ ራብ/ሥሥት) ።
- አስገተመ፡ አስቃመ/አስቻመ ።
- አስገተረ፡ አስለጠጠ/አስወጠረ (አስ ቆመ አስቀሰረ አስደከረ) ።
- አስገተነ፡ አስቦጨቀ/አዘነተረ/አስበላ ።
- አስገተገተ፡ አስነከሰ/አሳኘከ/አስገጠ ገጠ/አስቈረጠመ ።
- አስገታ (አግትዐ)፡ አሲያዘ/አስከለ ከለ/ኣስቆመ ።
- አስገታሚ፡ ያስገተመ/የሚያስገትም (አስቃሚ) ።
- አስገታሪ፡ ያስገተረ/የሚያስገትር (አስ ወጣሪ) ።
- አስገቺ፡ ያስገታ/የሚያስገታ ።
- አስገነታ፡ በኀይል አስጮኸ/አስቈጣ ።
- አስገነነ፡ አስከበረ/አስጌተየ/አስበዛ ።
- አስገነዘ (አግነዘ)፡ አስከፈነ/አሸፈነ/ኣሸለለ/አሳሰረ/አስቋጠረ ።
- አስገነዘበ፡ አሳሰበ (ገንዘብን ወይም ሌላ ነገር ኣስታወሰ ልብ አስደረገ) ።
- አስገነደሰ፡ ኣሰበረ/አሠነጠቀ/አስጣለ ።
- አስገነገነ፡ አስፈራ/አስጠረጠረ/አሠጋ ።
- አስገነጠለ፡ አስቈረጠ/አሰበረ/ኣስለየ ።
- አስገነፈለ፡ አስፈላ/አስሸተተ/አስፈሰሰ ።
- አስገነፋ፡ ገንፎ አስበጀ/አስጠበሰ/አስበሰለ ።
- አስገናዥ፡ ያስገነዘ/የሚያስገንዝ ።
- አስገንዛቢ፡ ያስገነዘበ/የሚያስገንዝብ (አስታዋሽ) ።
- አስገንጋኝ፡ ያስገነገነ/የሚያስገነግን (አስጠርጣሪ) ።
- አስገንጣይ፡ ያስገነጠላ/የሚያስገነጥል ።
- አስገኘ፡ አስነካ/ኣሲያዘ "ይህ ነገር እኔን ያስገኘኛል።"
- አስገኘ፡ ፈጠረ/ወለደ/አመጣ/አቀረበ ።
- አስገኚ(ኝ)፡ ያስገኘ/የሚያስገኝ (ታቦት ፈጣሪ ወላጅ) ።
- አስገዘመ፡ አስቈረጠ/አስከፈለ ።
- አስገዘመ፡ አስነቀፈ/አስገዛ/እስገረዘዘ ።
- አስገዘረ፡ አስገረዘ ።
- አስገዘተ፡ ኣስከለከለ/ሰለየ/አስወገዘ/አስራቀ ።
- አስገዘዘ (አግዘዘ)፡ አስጀጐለ/አስጋረደ/አስከለለ/አስመከተ ።
- አስገዘገዘ (አግዘዘ/አግዝዐ/አወሠረ)፡ አስከረከረ/አስመገዘ/አስከረከመ ።
- አስገዘፈ (አግዘፈ)፡ አስጓራ/አስጋፈተ ።
- አስገዛ (ኣግዝአ)፡ አስገበየ/ኣሸመተ/አስዋጀ ።
- አስገዛ፡ ሾመ/ሸለመ/አገር ሰጠ/አከበረ/አጌተየ/እሠለጠነ (ሕዝ. ፳፱፡ ፲፰፡ ሮሜ. ፮፡ ፲፪) ። #2
- አስገዛሪ፡ ያስዝዘረ/የሚያስገዝር።
- አስገዛች፡ ያስገዘተ/የሚያስገዝት (አስወጋዥ) ።
- አስገዛፊ፡ ያስገዘፈ/የሚያስገዝፍ (ዛር) ።
- አስገዝጋዥ፡ ያስዝገዘ/የሚያስዝዘግዝ/አስመጋዥ ።
- አስገዢ (ዥ)፡ የሚያስገበይ (ሿሚ/ሸላሚ የሚያስገዛ ዕቃን/አገርን) ።
- አስገደለ (አግደለ/አቅተለ)፡ ኣሳደነ/አስመታ/አስወጋ/አስደበደበ/አሳረደ/አስሞተ ።
- አስገደበ፡ እስከተረ/አሳገደ/አስወሰነ/ድልድል አስበጀ።
- አስገደደ (አገበረ)፡ አለውድ በግድ አሠራ ።
- አስገደገደ፡ አስተከ/አላቆመ/አሳወከ ።
- አስገደፈ፡ ጦምን አሻረ/እኸል አበላ። "ኣገደፈ በፍስክ አስገደፈ በጦም ቀን ነው። ይኸውም ግድና ፈቃድ አለበት።"
- አስገዳቢ፡ ያስገደበ/የሚያስገድብ/አስ ።
- አስገዳይ (አግዳሊ/አቅታሊ)፡ የሚያሳድን/የሚያስገድል (አሳዳኝ) ።
- አስገዳይነት፡ አሳዳኝነት/አስደብዳቢነት።
- አስገዳጅ (ጆች)፡ ያስገደደ/የሚያስገድድ (አለፈቃድ የሚያሠራ)።
- አስገዳፊ፡ ያስገደፈ/የሚያስገድፍ (አለጊዜ የሚያስበላ) ።
- አስገድጋጅ፡ ያስገደደ/የሚያስገደግድ (አስተካይ) ።
- አስገገረ፡ አስፈጠጠ/አስጐረጠ።
- አስገጠመ፡ አዘጋ/አሳተመ/እዘፈነ ።
- አስገጠበ፡ አስነካ/አስላጠ ።
- አስገጠገጠ፡ አስቀጠቀጠ/አስመደበደበ ።
- አስገጣሚ፡ ያስገጠመ/የሚያስገጥም (አዘፋኝ) ።
- አስገጣቢ፡ ያስገጠበ/የሚያስገጥብ።
- አስገጨ፡ አስመታ/አስለተመ/አስኰረኰመ ።
- አስገፈረ፡ አስቸፈረ/አስቃመ/አስቻመ ።
- አስገፈረ፡ ገፈራ አስገበረ ።
- አስገፈተ፡ አስገፈፈ/አስቀመሰ/አስጠጣ/አዠመረ ።
- አስገፈተረ፡ አስገፋ ።
- አስገፈገፈ፡ አሠራ/አስገፋ ሥራን ።
- አስገፈገፈ፡ አስላጠ/አስላጨ/አሳወደ ።
- አስገፈገፈ፡ አስበላ/አስጨረሰ ።
- አስገፈገፈ፡ አስከፈለ ዕዳን ።
- አስገፈፈ፡ አስለየ (የሰው ልብስ አስወሰደ አስቀማ) ።
- አስገፊ፡ ያስገፋ/የሚያስገፋ (አስበዳይ) ።
- አስገፋ፡ በሰው ላይ ግፍ አሠራ (ድኻን ኣስበደለ) ።
- አስገፋ፡ አስናጠ/አስወዘወዘ ።
- አስገፋ፡ አስፈቀቀ/አስገለለ ።
- አስገፋፊ፡ ያስገፈፈ/የሚያስገፍፍ (የቀማኛ አለቃ) ።
- አስጊያጭ፡ ያስጌጠ/የሚያስጌጥ (አሸማ) ።
- አስጋለ፡ አስጋመ/እስሞቀ/አስተኰሰ ።
- አስጋለበ፡ አሸሸ/አስበረረ/አስሮጠ/አስወነበደ/አስፈረጠጠ ።
- አስጋመ፡ አስፋመ/አስጋለ ።
- አስጋረደ፡ አስከለለ/ኣስመከተ/ኣሀ ረጋ ።
- አስጋረጠ፡ አስተከለ/አስፈቃ/አስቈራ ።
- አሥጋሪ፡ ያሠገረ/የሚያሠግር (ያዥ - "ዓሣ አሥጋሪ" እንዲሉ) ።
- አስጋራጅ፡ ያስጋረደ/የሚያስጋርድ ።
- አስጋበሰ፡ አስጋፈፈ/አሰበሰበ።
- አስጋተ (አግዐተ)፡ አስጠጣ/አስጐ ።
- አስጋዘ (አግአዘ)፡ አስጠላ/አስነቀፈ/ኣሳሰረ ።
- አስጋዘ (ኣግዐዘ)፡ አስወሰደ/አስመጣ ።
- አስጋዥ (አግኣዚ)፡ አስነቃፊ/እሳሪ ።
- አስጋዥ (አግዓዚ)፡ የሚያስግዝ (ኦ ስወሳጅ አስመጪ) ።
- አስጋዳ፡ አስጠለፈ/አሳሰረ (እንዳይኼድ/እንዳይላወስ/እንዳይራመድ አስደረገ) ።
- አስጋገረ፡ አስደፋ/አበሰለ።
- አስጋጋሪ፡ ያስጋገረ/የሚያስጋግር (የጋጋሮች አዛዥ) ።
- አስጋጠ፡ አስነጬ/አስጠበ/አስበላ ። "እከሌ ጠላቱን ዐፈር አስጠው።"
- አስጋጠጠ፡ አስቈረጠ/አስገፈፈ/አስዶዶ/አስጠጠ ።
- አስጋጭ፡ ያስጋጠ/የሚያስግጥ ።
- አስጋፈ፡ አሳፈሠ/አስጠረገ/አስጠጣ ።
- አስጋፈፈ፡ አሳወደ/አስጠረገ/አሰበሰበ ።
- አስጌጠ፡ ኣስለበስ/እሸለመ ጌጥን ።
- አስግድ፡ አሰግድ። "ባሕረ ኣስግድ" እንዲሉ።
- አስጐለለ፡ ክዳን አስጨረሰ/ጕልላት አሠራ/አስነበረ/አስኖረ ።
- አስጐለመ፡ አስከፈለ/አስቈረጠ/አሰጠ ።
- አስጐለበ፡ አስለጐመ/አስለበደ/አሸፈነ/አስጠፈረ ።
- አስጐለት፡ ጕልቻን አስቆመ (ጕልት አስደረገ አስከለለ) ።
- አስጐለጐለ፡ አስቈነጩ/አስለቀመ ።
- አስጐለጐለ፡ አስናደ/ብላሽ አስደረገ ።
- አስጐለጐለ፡ አስወጣ/አዘረገፈ ።
- አስጐለጐለ፡ ኣስፈጠጠ/አስጐረጠ ።
- አስጐላቢ፡ ያስጐለበ/የሚያስጐልብ (አስለባጅ) ።
- አስጐላች፡ ያስጐለተ/የሚያስጐልት (የሚያስቆም ኣስከላይ) ።
- አስጐላይ፡ ያስጐለለ/የሚያስጐልል (አ) ።
- አስጐልጓይ፡ ያስጐለጐለ/የሚያስጐለጕል (አስለቃሚ) ።
- አስጐመረ፡ አስነፋ (አንፍኀ) አስኰራ ።
- አስጐመተ፡ አስጐመደ/አስቈረጠ/አስከፈለ ።
- አስጐመዘዘ፡ መራራ አስደረገ/አስኮመጠጠ ።
- አስጐመዠ (አመነየ/አፍተወ)፡ ኣስቋመጠ "ዋይ ባገኘኹት አሠኘ" (አስቃረ) (ዘፍ. ፫፡ ፮) ።
- አስጐመደ፡ አስቈረጠ/አስጐረደ/አስጐነደሰ/አስበጠሰ ።
- አስጐመጎመ፡ ፈጽሞ አሸፈነ/አስገመገመ ።
- አስጐማጅ፡ ያስጐመደ/የሚያስጐምድ (አስጐራጅ) ።
- አስጐምዢ፡ ያስጐመዠ/የሚያስጐመዥ (አስቋማጭ) ።
- አስጎምጉም፡ አባቱ ጉም የሚባል በ፰፻ ዓ. ም. የነበረ የኢትዮጵያ ንጉሥ ስም (ማስገምገምንና መጮኸን ያሳያል) ። "ጉም አስጎምጉም" እንዲል ዘር ቈጣሪ ።
- አስጐሰመ፡ አስመታ/አሳዘነ ።
- አስጐሰመ፡ አስወጋ/አስጓጐጠ ።
- አስጐሰጐሰ፡ ልቅ ልቅ ያኸል አስ ጕረሠ/አስበላ/አስጐተጐተ ።
- አስጐሳሚ፡ ያስጐሰመ/የሚያስጐስም ።
- አስጐረመመ፡ አስቈረጠ/አስፎነነ ።
- አስጐረሠ፡ አፍ ውስጥ አስገባ/ኣስከ ።
- አስጐረበጠ፡ አስነካ/አስቈረቈረ/አስወጋ ።
- አስጐረተ፡ አስጐራ/አስከመረ ።
- አስጐረና፡ አስቀረና ።
- አስጐረደመ፡ አስቈረጠመ ።
- አስጐረዶ፡ አስጐመደ/አስቈረጠ/አስ ጐነደበ/አስቀየደ/አስከፈለ/አስፈተገ ።
- አስጐረጐረ፡ አስበረበረ/አስጓጐጠ/አስፈለገ ።
- አስጐረጐጪ፡ አስማገ/አስጠጣ ።
- አስጐረጠ፡ አስጨረ/አስቧጠጠ ።
- አስጐረጠ፡ አስፈጠጠ ።
- አስጐሪ፡ ያስጐራ/የሚያስጐራ (አስከማሪ ደንጊያን) ።
- አስጐራ፡ አስከመረ/አስጐረተ/አስቈለለ ።
- አስጐራጅ፡ ያስጐረደ/የሚያስጐርድ (አስቈራጭ) ።
- አስጐርጓሪ፡ ያስጐረጐረ/የሚያስጐረጕር (አስፈላጊ) ።
- አስጐሸ፡ አስደፈረሰ መጠጥን ።
- አስጐሸመ፡ አስደሰተ/አስደሰመ ።
- አስጐሸመጠ፡ አስነካ/አስጐነጠ ።
- አስጐበኘ፡ አስጠየቀ፡ አስፈቀደ፡ አሰለለ/አስመረመረ ።
- አስጐበዘ፡ ጐበዝ አስደረገ፡ አስጐለመሰ ።
- አስጐበደደ፡ አስጐበጠ፡ አስጐነበሰ።
- አስጐበጐበ፡ ዶቄት ወይም አብሲት አስጨመረ።
- አስጐበጐበ፡ ጕብጕብ አሠራ፡ እሸለመ፡ አስጌጠ።
- አስጐበጠ፡ አስጐነሰሰ፡ አስቀለሰ/አስደገነ/አስቀሰተ ።
- አስጐባ፡ አስደገፈ፣ አስነሣ።
- አስጐባ፡ ጕሶ (ጉቦ) አሰጠ፣ ኣስቀበለ።
- አስጐብኚ፡ ያስጐበኘ/የሚያስጐበኝ፡ የሚያሰልል (አሰላይ/አስጠያቂ) ።
- አስጐብዳጅ፡ አስጐንባሽ፡ አስፈንዳጅ።
- አስጐብጓቢ፡ አስደጓሽ፡ አስጊያጭ/አስለዋሽ።
- አስጐተተ፡ አሳበ/አስረዘመ/አስጠራ ።
- አስጐተጐተ፡ አስነቀነቀ/አስወተወተ ።
- አስጐታች፡ ያስጐተተ/የሚያስጐትት (ገበሬ ባለሠረገላ) ።
- አስጐቸ፡ አስከመረ/አስቈለለ ።
- አስጐቺ፡ ያስጐቸ/የሚያስጐች (አስማሪ አስቈላይ) ።
- አስጐነበሰ፡ አስቀለሰ/አስጐበጠ (የሙጭ የገና የከዘራ) ።
- አስጐነተለ፡ አስጐነጠ/አስገፋ ።
- አስጐነደ፡ ግንድ ጐናዴ አስደረገ ።
- አስጐነደለ፡ አሰለበ/አሰነጋ ።
- አስጐነጐነ፡ ነገር አስቋጠረ ።
- አስጐነጐነ፡ ጕንጕን አሠራ/አስበጀ ።
- አስጐነጠ፡ አስደፈረ/አስነካ/አስገፋ ።
- አስጐነጨ (አልትሐ)፡ ውሃን በጕንጭ አሲያዘ/አስጠጣ ።
- አስጐነፈ፡ አሳጠበ/አሳጀለ/አስጠረበ/አስደጐሰ ።
- አስጐናጭ፡ ያስጐነጠ/የሚያስጐንጥ ።
- አስጐንዳይ፡ ያስጐነደለ/የሚያስጐነድል ።
- አስጐንጓኝ፡ ያስጐነጐነ/የሚያስጐነጕን (አስቈናኝ) ።
- አስጐንጪ፡ ያስጐነጩ/የሚያስጐነጭ ።
- አስጐኘረ፡ ኣስመላ/አስነፋ/አስጐሰረ ።
- አስጐዘጐዘ፡ አስበተነ/አስነሰነሰ/አስነጠፈ ።
- አስጐዝጓዥ፡ ያስጐዘጐዘ/የሚያስገዘጕዝ (አስነስናሽ/አስነጣፊ) ።
- አስጐደለ፡ ጐደሎ አስደረገ/አስቀነሰ/አሳረዘ ።
- አስጐደራ፡ አስጮኸ/አስቀተራ።
- አስጐደበ፡ አስማዕ/አስቈፈረ/አስመነቀረ/እስጐደጐደ (ጕድባ አሠራ) ።
- አስጐደጐደ፡ አስማሰ/አስቈፈረ/አስጐደበ/ኣስመነቀረ (ጕድጓድ አሠራ/አስበጀ) ።
- አስጐደጐደ፡ አስገባ/አስከተተ።
- አስጐደፈ፡ ጕድፋም አስደረገ/ፍግ አስፈሰሰ ።
- አስጐደፈረ፡ አስማሰ/አስማረ/አስመነቀረ/አዛቀ - አስበተነ ።
- አስጐዳ (አጕድዐ)፡ አስመታ/አስወቀጠ/አስደበደበ/አስበደለ ።
- አስጐዳ፡ አስቀጣ/አስኰነነ።
- አስጐዳቢ፡ ያስጐደበ/የሚያስጐድብ (አስቈፋሪ)።
- አስጐጂ፡ ያስጐዳ/የሚያስጐዴ/የሚያስኰንን ።
- አስጐጐመ፡ አስለተመ/አስወጋ ።
- አስጐጓሚ፡ ያስጐጐመ/የሚያስጐጕም (አስለታሚ/አስወጊ) ።
- አስጐጠጐጠ፡ አስመዘዘ/አስነቀለ ጥርስን ።
- አስጐጠጐጠ፡ አስወጋ/አስወጣ/አስቦጠቦጠ ዐይንን ።
- አስጐጠጠ፡ አስናቀ/አስገጠጠ ።
- አስጐፈነነ፡ አስቀየመ/አስከፋ/አሰቀጠጠ (ኢዮ. ፮፡ ፯) ።
- አስጐፈጮረ፡ አስጨቈነ/አስረፈቀ/አስጨረረ ።
- አስጓሪ፡ ያስጓራ/የሚያስጓራ (አስገዛፊ) ።
- አስጓራ፡ አስጮኸ/አስገዘፈ ።
- አስጓዘ (አግዐዘ)፡ አዘገመ/በዝግታ አስወሰደ/አስነዳ (ዘፀ. ፲፭፡ ፳፪) ።
- አስጓጐረ፡ አስጮኸ ።
- አስጓጐጠ፡ አስወጋ/አስቈሰቈሰ።
- አስጠለለ (አጽለለ)፡ ከጥላ አስጠጋ ("አሳረፈ አስጋረደ አስከለለ") ።
- አስጠለቀ አስ ታጠቀ ("አስለባሽ ያስለበሰ የሚያስለብስ ማስለበስ ማስጠለቅ ማስታጠቅ ተለበሰ ") ("ተለብሰ") ።
- አስጠለቀ፡ አስለበሰ ።
- አስጠለቀ፡ አስጠቀሰ/አስቀዳ ።
- አስጠለፈ፡ አሲያዘ/አሳሰረ ።
- አስጠለፈ፡ አስነጠቀ/አስወሰደ ።
- አስጠለፈ፡ ጥልፍ አሰፋ (ዘፀ. ፳፮፡ ፴፩) ።
- አስጠሊ፡ ያስጠላ/የሚያስጠላ ("አሠቃቂ") ።
- አስጠላ (አጽልኦ)፡ አስነቀፈ/አስረከሰ/አሠቀቀ ("እንዳይወደድ አደረገ አስደረገ ነገር ሠርቶ ስም አክፍቶ አይ በሉ በሎ አሠኘ") ።
- አስጠላቂ፡ ያስጠለቀ/የሚያስጠልቅ ።
- አስጠላፊ፡ ያስጠለፈ/የሚያስጠልፍ ("አሲያዥ አስነጣቂ") ።
- አስጠመመ፡ አስጠመዘዘ ("ጠማማ ወል ጋዳ አስደረገ") ።
- አስጠመሰሰ፡ አስጣስ/አስለጠሰ/አስ ተኛ ።
- አስጠመቀ (አጥመቀ)፡ ውሃ እስ መላ አስበጠበጠ ።
- አስጠመቀ፡ አስነከረ/ኣሳጠበ ።
- አስጠመቀ፡ ክርስትና አስነሣ ።
- አስጠመቀ፡ ጠበል አስመታ "
- አስጠመነ፡ መሬቱን አጋዛ ("ለተጋዢ ሰጠ ጠመኔውን ወይም ሌላውን") ።
- አስጠመዘዘ፡ አስጦዘ/አስከረረ/አስጠ ממ ።
- አስጠመደ (አፅመደ)፡ ጥመዱ አለ ("ቀንበር አስጝነ አስገዛ ማነኸ ባለሳምንት ያስጠምድሽ ባሥራ ስምንት እንዲል ሙሴ") ።
- አስጠመደ፡ አስጠላ/አስመረዘ ።
- አስጠመጠመ፡ አስጠቀለለ/አሳሰረ/አስከበሰ/አስደመረ ።
- አስጠሚ፡ ያስጠማ/የሚያስጠማ ("ጨው ፀሓይ ትኵሳት") ።
- አስጠማ (አጽምአ)፡ ውሃ ' ነሣ ፥ ከለ ከለ ("ኣሻ አስፈለገ") ።
- አስጠማቂ፡ ያስጠመቀ/የሚያስጠምቅ ("ኣስነካሪ") ።
- አስጠማጅ፡ ያስጠመደ/የሚያስጠምድ ("አስጠሊ") ።
- አስጠምዛዥ፡ ያስጠመዘዘ/የሚያስጠ መዝዝ ።
- አስጠሞረ፡ ባንድነት አስከረረ/አስደ ወረ ።
- አስጠረረ፡ አስጠለቀ/አስለበሰ ጥሩርን ።
- አስጠረቀ፡ አስመታ/አስቸነከረ ("ብረት አስለበሰ") ።
- አስጠረቀመ፡ በጥብቅ አሳሰረ ("አዘጋ") ።
- አስጠረበ፡ ኦሳነጠ/አስቀጠነ ሥሥና ጠፍጣፋ ቀጪን አስደረገ ።
- አስጠረነቀ፡ አሳሰረ ("ጥብቅና ወፍራም አስደረገ") ።
- አስጠረኘ፡ በጥርኝ አዘገነ/አሲያዘ/አስጨበጠ ("ጥርኝን ሌላ ነገርን") ።
- አስጠረኘ፡ ጥርኝ አስመሰለ ።
- አስጠረዘ፡ አሰፋ/አስጠለፈ/አስታታ/አስደረዘ ("አስጠፈረ") ።
- አስጠረዘ፡ አስመታ/አስደወለ ።
- አስጠረገ፡ አሳወደ/አስቈረጠ/አስመነጠረ ።
- አስጠረገ፡ ጥረጉ ዛቁ አለ ("አስገለለ") ።
- አስጠሪ፡ ያስጠራ/የሚያስጠራ ("ሕንጻ ሣት") ።
- አስጠራ፡ ስምን አስነሣ ("በደግ ወይም በክፉ") (ዘፍ. ፲፩፡ ፬) ።
- አስጠራ፡ ችን አሳሰበ ("አስቀደሰ አ ስቈረበ ልጅ") ።
- አስጠራ፡ አስጮኸ ("እንዲመጣ አስደ ረገ ና ኣሠኘ") ።
- አስጠራሪ፡ ያስጠረረ/የሚያስጠርር ።
- አስጠራቂ፡ ያስጠረቀ/የሚያስጠርቅ ።
- አስጠራቢ፡ ያስጠረበ/የሚያስጠርብ ("የሚያሳንጥ") ።
- አስጠራጊ፡ ያስጠረገ/የሚያስጠርግ ("አሳጅ አስቈራጭ የጽዳት ሹም") ።
- አስጠቀለለ፡ አሰበሰበ/አሸበለለ/አስ ጠመጠመ/አሸፈነ ።
- አስጠቀለለ፡ አስፈጸመ/አስጨረሰ ።
- አስጠቀመ፡ አሰፋ/አስጣፈ/አስደረተ ።
- አስጠቀመ፡ አስረባ/አሰጠ ጥቅምን ።
- አስጠቀሰ፡ ማጥቀሻ ሰጠ ("አጥቅሱ አለ አስነከረ") ።
- አስጠቀሰ፡ አስባለ/አስነገረ ጥቅስን ።
- አስጠቀሰ፡ አስጠራ ("ና አሠኘ") ።
- አስጠቀነ፡ አስከተፈ/አስፈረፈረ ።
- አስጠቀጠቀ፡ አስረገጠ/አስረመረመ ።
- አስጠቀጠቀ፡ አስበላ/አስወጠቀ/አስ መላ ።
- አስጠቀጠቀ፡ አስወጋ/አስነቀሰ ።
- አስጠቀጠቀ፡ አስደፈነ/አስደበቀ/ኣሸ ሸገ/አሸፈነ ።
- አስጠቂ፡ ያስጠቃ/የሚያስጠቃ ("የሚያሰርር ጥቃት አስገቢ") ።
- አስጠቃ፡ አስወጋ/አሰረረ ።
- አስጠቃ፡ አስገፋ/አስበደለ/አስጐዳ/ አስጯቈነ ።
- አስጠቃሚ፡ ያስጠቀመ/የሚያስጠቅም ("ልብስ አሰፊ ጥቅም አሰጪ አጽዳቂ") ።
- አስጠቃሽ፡ ያስጠቀሰ/የሚያስጠቅስ ።
- አስጠቈመ፡ አሳመለከተ/አስነገረ ።
- አስጠቈመ፡ አስጫረ/አሳከከ ።
- አስጠቈረ፡ አስነቀሰ/አስወቀረ ጥርስን ።
- አስጠቈረ፡ ዘንጋዳን አስጐነፈ ።
- አስጠቈረ፡ ጥቍር አስደረገ ("ከል አስ ነከረ እጥቍር ቀለም አስገባ") ።
- አስጠቅላይ፡ ያስጠቀለለ/የሚያስጠተ ልል ("ኣሸብላይ") ።
- አስጠቅጣቂ፡ ያስጠቀጠቀ/የሚያስጠቀ ጥቅ ("አስደፋኝ አስረምራሚ") ።
- አስጠቋሚ፡ ያስጠቈመ/የሚያስጠቍም ("፩ አስመልካች") ።
- አስጠበሰ፡ አስተኰሰ/አስፈተነ ።
- አስጠበሰ፡ አስፈላ/አስቈላ ።
- አስጠበረ፡ አሠራ ጠበራን መጠብ ።
- አስጠበቀ (አዕቀበ)፡ አስከለከለ/አሳገደ (፪ ቆሮ. ፲፩፡ ፴፪) ።
- አስጠበቀ፡ አስቈየ ("ለሌላ ጊዜ") ።
- አስጠበቀ፡ ጥብቅ አስደረገ ("አስጠነ ከረ") ።
- አስጠበበ (አጥበበ)፡ ጥበብ አስ ጣለ/አሠራ/አሳወቀ ።
- አስጠበበ (አጽበበ)፡ ጠባብ አስደ ረገ ("አስጨነቀ") ።
- አስጠበበ (አጽበበ)፡ ጠባብ አስደ ረገ ("አስጨነቀ").
- አስጠበጠበ፡ አስበለተ/አስጠባ ።
- አስጠበጠበ፡ አስቸኰለ/አስገሠገሠ ።
- አስጠበጠበ፡ አስገረፈ/አሸነቈጠ ።
- አስጠቢ፡ ያስጠባ/የሚያስጠባ ።
- አስጠባ (አጥብሐ)፡ አስገፈፈ/አስበለተ ("ብልት አስወጣ") ።
- አስጠባ (አጥብሐ)፡ አስገፈፈ/አስበለተ ("ብልት አስወጣ").
- አስጠባ፡ አስመጠጠ/አስመጠመጠ/አስመገመገ ።
- አስጠባሪ፡ ያስጠበረ/የሚያስጠብር ።
- አስጠባቂ፡ ያስጠበቀ/የሚያስጠብቅ ("እስከልካይ") ።
- አስጠባቢ፡ ያስጠበበ/የሚያስጠብብ ("አስጨናቂ") ።
- አስጠባቢ፡ ያስጠበበ/የሚያስጠብብ ("አስጨናቂ").
- አስጠብጣቢ፡ ያስጠበጠበ/የሚያስጠበ ጥብ ("አስገራፊ") ።
- አስጠነሰሰ፡ ጥንስስ አስደረገ ("አስበጠ በጠ") ።
- አስጠነቀለ፡ አስቈነጠረ ።
- አስጠነቀለ፡ አስነከሰ ("ዐንካሳ አስደ ረገ") ።
- አስጠነቀቀ፡ አስታወቀ/አስረዳ (ዘፍ. ፵፫፡ ፫) ።
- አስጠነቀቀ፡ አስኰሰተረ/አስጠበቀ ።
- አስጠነቈለ፡ አስወጋ/አስደነቈለ/አስ ነቈረ ።
- አስጠነቈለ፡ ጠንቋይ አስጠየቀ ("መላ አስመታ አስረተ") ።
- አስጠነከረ፡ አስበረታ/አስጠጠረ ።
- አስጠነጠነ፡ አስነቀዘ ("ጥንጣን አስበላ") ።
- አስጠነጠነ፡ አስጠቀለለ/አስጠመጠመ/አስኮበ/አስደወረ ።
- አስጠነፈፈ፡ አጠንፍፉ አለ ("አስፈሰሰ") ።
- አስጠኒ (ዎች)፡ ያስጠና/የሚያስጠና ("አስተማሪ አስቀጻይ ነጋሪ") ።
- አስጠና (አጽንሐ)፡ አስማለደ ("በደጅ አስቀመጠ አስቈየ እከሌ ልጁን በቤተ መንግሥት ደጅ ያስጠናል") ።
- አስጠና (አጽንዐ)፡ አስጠነከረ/አስ ጨከነ ።
- አስጠና፡ አስተማረ/አስቀጸለ/አሳወቀ ።
- አስጠንቃቂ፡ ያስጠነቀቀ/የሚያስጠነ ቅቅ ።
- አስጠንቋይ (ዮች)፡ ያስጠነቈለ/የሚ ያስጠነቍል ።
- አስጠንጣኝ፡ ያስጠነጠነ/የሚያስጠነ ጥን ("አስደዋሪ") ።
- አስጠየቀ፡ አስመረመረ ።
- አስጠየቀ፡ አስሞገተ፡ ተጠየቅ፡ አሠኘ ።
- አስጠየቀ፡ አስጐበኘ፡ አስፈቀደ ። አስጠያቂ፡ ያስጠየቀ፡ የሚያስጠይቅ፡
- አስጠየተ፡ አሠራ ("አንድነት አስደረገ አስጠየተ አስመታ አስደበደበ በጥይት") ።
- አስጠያች፡ ያስጠየተ/የሚያስጠይት ("አሳሳሪ አሠሪ ኣስገዳይ") ።
- አስጠደፈ፡ አስቸኰለ ።
- አስጠዳፊ፡ አስቸኳይ ።
- አስጠጀ፡ አስበጠበጠ ("ጠጅ አስደረገ") ።
- አስጠገረረ፡ አስደበለለ ("ታላቅ ሸክም አሸከመ") ።
- አስጠገተ፡ አላለበ ።
- አስጠገነ፡ አስጠቀለለ/አስፈወሰ ("አሳ ደሰ") ።
- አስጠገነ፡ አስጠቀመ/አሳገዘ/አስረዳ ።
- አስጠገገ፡ አሰበሰበ/አስዳነ ።
- አስጠገገ፡ ጠገግ አሠራ/አስጠፈረ ።
- አስጠጊ፡ ያስጠጋ/የሚያስጠጋ ("አሳዳሪ አስጠጊ የቅርብ ሴት ትእዛዝ አን ቀጽ") ።
- አስጠጋ፡ አቀረበ/አስለጠቀ/ጥግ አሲያዘ/አስደገፈ/አሳደረ ቀጽ ።
- አስጠጋኝ (ጸወነነ)፡ አቀረበኝ ("አከሌ ወደ ቤቱ አስጠጋኝ ጠጋን እይ") ።
- አስጠጋኝ፡ ያስጠገነ/የሚያስጠግን ("አሳዳሽ አስጠቃሚ") ።
- አስጠጠ፡ አስጠረገ፡ አስጨረሰ።
- አስጠጠተ፡ አስቈጪ/አሳዘነ/አስተከዘ ።
- አስጠጣ፡ አስጐነጨ/አስማገ/አስጨለጠ ("አጠጣ ፈቃድን አስጠጣ ግዴታን ያያል") ።
- አስጠጣ፡ ውሃ አስጨመረ/አስፈሰሰ ።
- አስጠጣች፡ ያስጠጠተ/የሚያስጠጥት ("የሚያሳዝን አሳዛኝ") ።
- አስጠጪ፡ ያስጠጣ/የሚያስጠጣ ።
- አስጠፈረ፡ አሳሰረ/አስማገረ/አስጠለፈ/አስገረፈ/አስጐለበ ።
- አስጠፈጠፈ (አጸፍጸፈ)፡ አዘረጋ/ አ ስነጠፈ/አስለበጠ ።
- አስጠፈጠፈ፡ በጥፊ አስመታ ("በለው ድገመው አለ አስወለወለ") ።
- አስጠፊ፡ ያስጠፋ/የሚያስጠፋ ("አስኰ ብላይ አስገዳይ") ።
- አስጠፋ፡ አስቀሠፈ/አስገደለ/አስደመ ሰሰ/አስገሰሰ ።
- አስጠፋ፡ አስኰበለለ/አስራቀ "
- አስጠፋሪ፡ ያስጠፈረ/የሚያስጠፍር ("አስማጋሪ አሳሳሪ") ።
- አስጠፍጣፊ፡ ያስጠፈጠፈ/የሚያስጠፈጥፍ ("አስነጣፊ") ።
- አስጣለ (አኅደገ)፡ አስለቀቀ/አስተወ/አዳነ/አተረፈ (ዘፀ. ፮፡ ፮፡ ነሐ. ፬፡ ፲፩) ።
- አስጣለ፡ አዘረጠጠ/አስወደቀ ።
- አስጣሚ፡ ያሰጠመ/የሚያሰጥም።
- አስጣሰ፡ አስወደደ/አስከፈለ/አስነደለ አስፈረሰ ።
- አስጣሽ፡ ያስጣሰ/የሚያስጥስ ።
- አስጣቈሰ፡ አስጐሸመጠ/አስደፈረ ።
- አስጣቈሰ፡ ዘር አስደገመ ።
- አስጣይ (ዮች)፡ ያስጣለ/የሚያስጥል ("አስለቃቂ ጡት አስጣይ እንዲሉ") ።
- አስጣደ (አጽዐደ)፡ ምጣድ ጣዱ አለ ("አዘዘ") ።
- አስጣደ፡ አስቀረበ/አስደቀነ ።
- አስጣጅ፡ ያስጣደ/የሚያስጥድ ።
- አስጣጣ፡ ገላለጠ፡ አገላበጠ።
- አስጣፈ፡ አስጠቀመ/አሰፋ/አስለጠፈ ።
- አስጣፈ፡ አጻፈ/አስከተበ ።
- አስጣፊ፡ ያስጣፈ/የሚያስጥፍ ።
- አስጥል፡ ዝኒ ከማሁ ("የሚያስተው እማስጥል ቆባስጥል እንዲሉ") ።
- አስጦመ፡ ጡሙልኝ ("ጦም ያዙልኝ አለ እኸል ውሃ ነሣ ከለከለ ጦም አዋለ ኣስዋለ") (ሉቃ. ፭፡ ፴፬) ።
- አስጨለጠ፡ ውሃን/ጠላን/ጠጅን/ወተትን/ኮሶን አስጠጣ ("አስጨረሰ") ።
- አስጨለፈ፡ አስጠለቀ/አስቀዳ ወጥ አስወጣ ።
- አስጨላፊ፡ ያስጨለፈ/የሚያስጩልፍ ("አስቀጅ") ።
- አስጨመረ፡ አሳከለ/አስደበለ ።
- አስጨመረ፡ አስገባ/አስዶለ ("እስከ ተተ") ።
- አስጨመተ፡ ዝም አሠኘ ("አስረመመ ማስጯመት ዝምተኛ ማስደረግ ምቶ ዝም ብሎ ረግቶ") (ማር. ፭፡ ፲፩) ።
- አስጨማመረ፡ አካከለ ("በላይ በላዬ") ።
- አስጨምari፡ ያስጨመረ/የሚያስጨምር ።
- አስጨሰ፡ ኣስኖረ ።
- አስጨሰ፡ ጪስ አስደረገ ("አሳጠነ") ።
- አስጨረ፡ አስጫረ፡ አስቧጨረ ።
- አስጨረተ፡ አስፋቀ ("ጭረት ጭርት አስደረገ") ።
- አስጨረነቀ፡ አሳጠረ/ዐጪር አስደ ረገ ("አስጨቈነ") ።
- አስጨረገደ፡ አሳወደ/አስቈረጠ ።
- አስጨረፈ፡ ላመል አስመታ/አስቈረ ።
- አስጨራሽ፡ ያስጨረሰ/የሚያስጨርስ ("አስፈጻሚ") ።
- አስጨራፊ፡ ያስወረፈየሚያስጨን ።
- አስጨቀጨቀ፡ አስነዘነዘ/ኣስነ ።
- አስጨቀጨቀ፡ አስወቀጠ ።
- አስጨቀጨቀ፡ አስጠቀጠቀ/አስፊነ ።
- አስጨቈነ፡ አስጫነ/አስወፈቀ ።
- አስጨቅጫቂ፡ ያስጨቀጨቀ/የሚያ ቤቀጭቅ ("አስደፋኝ አስነዝናዥ አስወቃ ") ።
- አስጨቋኝ፡ ያስጨቈነ/የሚያስጨቍን ።
- አስጨበጨበ፡ ነገሩን ስብከቱን አስወ ደደ/አስመሰገነ ("በጭብጨባ") ።
- አስጨበጨበ፡ አጨብጭቡ አለ ("ጭብ ባን አስተማረ") ።
- አስጨብጫቢ፡ ያስጨበጨበ/የሚያስ ጨበጭብ ("ዘፋኝ አልቃሽ ዛር ፈረስ") ።
- አስጨነቀ፡ አስጠበበ/አስቸገረ ("ጭንቀ አሳየ") (ኢሳ. ፷፫፡ ፲፡ ኤር. ፲፱፡ ፱፡ ሕዝ. ፲፰፡ ፯፡ ዳን. ፩፡ ፩) ።
- አስጨነገፈ፡ አስመለመለ/አስጣለ ።
- አስጨነገፈ፡ አስወረደ/አስወጣ ("ባጓጕል አስቀረ") (፪ ነገ. ፪፡ ፲፱) ።
- አስጨናቂ፡ ያስጨነቀ/የሚያስጨንቅ ("አስጠባቢ ' አስቸጋሪ") (ኢሳ. ፲፬፡ ፬፡ ፳፱፡ ፳) ።
- አስጨንጋፊ፡ ያስጨነገፈ/የሚያስጨን ግፍ ("የሚያስወርድ አጠናዋች") ።
- አስጨከነ፡ አስቻለ/አስታገሠ ።
- አስጨካኝ፡ ያስጨከነ/የሚያስጨክን ።
- አስጨፈለቀ፡ አሠራ/አስቀጠቀጠ ።
- አስጨፈለቀ፡ አስረገጠ/አስዳጠ/እስ ደፈጠጠ ።
- አስጨፈለቀ፡ ጨፍልቁ አለ ("አሳረሰ አስተረተረ") ።
- አስጨፈረ፡ አዘለለ/አስረገደ ("እስረ ገጠ") ።
- አስጨፈቀ፡ አስጠቀጠቀ ።
- አስጨፈቀ፡ ድንጋይ አስጫነ ("አስለሰቀ") ።
- አስጨፈነ፡ አስከደነ/አሸፈነ ።
- አስጨፈጨፈ፡ አስመታ/አስቈረጠ ።
- አስጨፋሪ፡ ያስጨፈረ/የሚያስጨፍር ("አዘላይ አስረጋጅ አስረጋጭ") ።
- አስጨፋቂ፡ ያስጨፈቀ/የሚያስጨፍቅ ("አስለሳቂ") ።
- አስጨፍላቂ፡ ያስጨፈለቀ/የሚያስጨማ ስጨፍለቅ ("ማስዳጥ ማሳረስ ማስቀ ፈልቅ ጥቀጥ") ።
- አስጨፍጫፊ፡ ያስጨፈጨፈ/የሚያስ ጨፈጭፍ ("አስቈራጭ") ።
- አስጪ (ዎች)፡ ያሰጣ/የሚያሰጣ (ዘርጊ፡ ዘራሪ፡ ሰሪ) ።
- አስጫረ (አጽሓረ)፡ አስጨረ/አስቈፈረ/አስኳተ/አስፋረ/አስጐደፈረ ።
- አስጫረ፡ እሳትን አስወሰደ/አስመጣ ።
- አስጫሪ፡ ያስጫረ/የሚያስጭር ።
- አስጫነ፡ ኑ አለ ("ጫኞችን አዘዘ") ።
- አስጫነ፡ አስጨቈነ/አስጨፈቀ/አስለ ሰቀ ።
- አስጫኝ፡ ያስጫነ/የሚያስጭን ፡ የነ ኞች አለቃ ።
- አስጫወተ፡ ማንኛውንም ጨዋታ እስ ደረገ ።
- አስጮኸ፡ ቍቁ አሠኘ ("አስተመመ ውሃን ምን ያስጮኸዋል ቢሉ ድንጋይ") ።
- አስጯ፡ አስፋቀ፡ አስፈገፈገ።
- አስጯኺ፡ ያስጮኸ/የሚያስጮኸ ።
- አስፈለመ፡ አስቀደመ አዠመረ (አስ መታ አስወጋ አስቈሰለ ") ።
- አስፈለሰ፡ አስፈነቀለ አስነገለ ።
- አስፈለሰፈ፡ ፈልስፉ አለ (ዕውቀትን አስመረመረ እስከወነ ") ።
- አስፈለቀ፡ አስመነጨ (አስረጪ አስፈ ነጠቀ ") ።
- አስፈለቀ፡ አስቀደደ አሠነጠቀ ።
- አስፈለቀቀ፡ አስላላ አስከፈተ ።
- አስፈለቀቀ፡ ጥርስን አስገለጠ ።
- አስፈለቀቀ፡ ፈልቅቁ አለ (ኣስበተነ ") ።
- አስፈለገ፡ አስከፈለ አስነተበ (አሠነጠቀ ") ።
- አስፈለገ፡ ፈልጉ አለ (አሻ ") ። "(በግር ' ተፈረስ አስፈለገ)"፡ "እግረኛ ፈረሰኛ ልኮ ማለት ፥ ነው" ።
- አስፈለጠ፡ አሠነጠቀ አሸነሸነ ።
- አስፈለፈለ፡ አስማሰ አስፈረፈረ ።
- አስፈለፈለ፡ አስቀረጸ አሰረሰረ አስበሳ አስነደለ ።
- አስፈለፈለ፡ ፍሬን ከገለባ ኣስለየ (ዶ ሮን አስቀፈቀፈ፡ ልጅን አስወለደ ") ።
- አስፈሊ፡ ያስፈላ/የሚያስፈላ ።
- አስፈላ፡ አፍሉ አለ (አስሞቀ ") ።
- አስፈላሚ፡ ያስፈለመ/የሚያስፈልም (አዠማሪ ") ።
- አስፈላጊ (ጎች)፡ ያስፈለገ/የሚያስፈ ልግ ።
- አስፈላጊነት፡ ኣስፈላጊ መኾን ።
- አስፈላጭ፡ ያስፈለጠ/የሚያስፈልጥ (አ ሠንጣቂ ") ።
- አስፈልቃቂ ያስፈለቀቀ/የሚያስፈልቅቅ ።
- አስፈልፋይ፡ ያስፈለፈለ/የሚያስፈልፍል።
- አስፈሰሰ፡ አስቀለጠ አስነጠረ ("(፪ ዜና. ፬፥ ፲፯)") ።
- አስፈሰሰ፡ አፍሱ አለ (አስደፋ አስቸ ለሰ እስከነበለ ") ።
- አስፈሲታ፡ የምታስፈሳ ። "አስፌስ" የወ ንድ፡ "አስፈሲታ" የሴት ቅጽልና በቂ መኾኑን አስተውል #
- አስፈሣ (አስተፍሥሐ)፡ ደስ አሠኘ አስደሰተ ።
- አስፈሳ፡ እስኪፈሳ መታ ደበደበ (ፈስ አስወጣ ") ።
- አስፈረመ፡ ፊርማ አስደረገ አጻፈ ።
- አስፈረቀቀ፡ አስፈነቀለ ኣስፈለቀቀ አ ሠነጠቀ አስራቀ ።
- አስፈረደ፡ ፍረዱ አለ (አስበየነ ") ።
- አስፈረጀ፡ አዞረ (ነፋስ አስቀበለ አገር አሳየ ") ።
- አስፈረጠ፡ አስመገለ ።
- አስፈረጠጠ፡ አስሮጠ አሸሸ አስጋ ለበ አስወነበደ አስኰበለለ ።
- አስፈረፈረ፡ አስደቀቀ አስጠቀነ ።
- አስፈረፈረ፡ አሸረሸረ አስማሰ ።
- አስፈሪ (ዎች)፡ ያስፈራ/የሚያስፈራ (አሥጊ ባለግርማ፡ ጠላት ወንበዴ መንገድ ") ("(ኢሳ. ፵፱፥ ፳፭)")
- አስፈሪታ፡ ያስፈራች/የምታስፈራ ።
- አስፈሪነት፡ አስፈሪ መኾን ።
- አስፈራ (አፍረየ)፡ ፍሬ አስደረገ ። "አፈራ" እንጂ "(ፈራ)"ና "አስፈራ" ኣልተለመ
- አስፈራ (አፍርሀ)፡ አባባ አሠጋ ኣስጠረጠረ ኣሳሰበ ("(ሕዝ. ፴፫፥ ፳፰)") ። "ባሕርን" እይ ።
- አስፈራሚ፡ ያስፈረመ/የሚያስፈርም ።
- አስፈራሚነት፡ አስፈራሚ መኾን ።
- አስፈራሪ፡ ያስፈራራ/የሚያስፈራራ ።
- አስፈራራ፡ ወግዱ ሽሹ ዘወር በሉ አለ ("(ዕዝ. ፬፥ ፬)") ። (ተረት)፡ "በገዛ ዐረ እባብ ይዛ ታስፈራራ" ። "ረዥም ጦር ባይወጉበት ያስ ፈራሩበት" ።
- አስፈራጅ፡ ያስፈረደ/የሚያስፈርድ (አስበያኝ ") ።
- አስፈርጣጭ፡ ያስፈረጠጠ/የሚያስፈረ ጥጥ (አስኰብላይ ") ።
- አስፈርፋሪ፡ ያስፈረፈረ/የሚያስፈረፍር ።
- አስፈሺ፡ ያስፈሳ/የሚያስፈሳ ።
- አስፈቀረ (አፍቀረ)፡ አስወደደ (እን ዲወድ እንዲወደድ አስደረገ ") ።
- አስፈቀቀ፡ ዕልፍ አሠኘ ።
- አስፈቂ፡ ያስፈቃ/የሚያስፈቃ (እስበጪ ") ።
- አስፈቃ (አፍቅዐ)፡ አስቈራ አስበጣ አስጋረጠ ።
- አስፈተለ፡ አስከረረ አስጠመረ አስገ መደ ።
- አስፈተለከ፡ በፍጥነት አስፈታ አስ ወጣ ("(ጥሾ)") አሾለከ ።
- አስፈተረ፡ አሳነቀ አስወጠረ ።
- አስፈተሸ፡ አስበረበረ አስመረመረ አ ስቀነቀነ ።
- አስፈተተ፡ አስቈረሰ አስገመሰ አስከ ፈለ አስተነተነ ።
- አስፈተነ (አፍተነ)፡ አስሞከረ አ ስፈተሸ አስመረመረ፡ መከራ አስቀበለ ፈ ተና አሰጠ፡ አስጠየቀ፡ አስጠበሰ ("(ሉቃ. ፭፥ ፲፬)") ።
- አስፈተገ፡ አስወቀጠ አሳወደ ።
- አስፈተፈተ፡ አስራስ አስደቀቀ ።
- አስፈታ፡ ስለ ች ፍታት አስደረገ (ሰዓተ ሌሊት አሲያዘ ስም ' አስጠራ ") ።
- አስፈታ፡ አስከፈተ አስለቀቀ አስተወ ። "ዐባይ ጠንቋይ ቤት ያስፈታል ያስለቅቃል" ።
- አስፈታ፡ አስገለጠ አስተረጐመ ።
- አስፈታ፡ አስጠፋ እስፈረሰ አስበተነ ።
- አስፈታሽ (አፍትሐኪ)፡ አስለቀቀሽ ።
- አስፈታሽ፡ ያስፈተሸ/የሚያስፈትሽ (አ ስመርማሪ ") ።
- አስፈታች፡ ያስፈተተ/የሚያስፈትት (አ ስቈራሽ ") ።
- አስፈታኝ (አፍታኒ)፡ ያስፈተነ/የ ሚያስፈትን (ያስመረመረ ") ።
- አስፈታኝ (አፍትሐኒ)፡ ከእስር ቤት አስለቀቀኝ ። "ፈታን" አስተውል ።
- አስፈታይ፡ ያስፈተለ/ያስፈተለች/የ ሚያስፈትል/የምታስፈትል (የፈታይ አለቃ ") ። ወንድና ሴትን ለመለየት "አስፈታዬ" "አስፈታ ይዋ" ይሏል ።
- አስፈታይነት፡ አስፈታይ መኾን ።
- አስፈታጊ፡ ያስፈተገ/የሚያስፈትግ (አ ስወቃጭ አሳጫጅ ") ።
- አስፈቺ፡ ያስፈታ/የሚያስፈታ/የሚያስ ተው ። "ሥራ አስፈቺ" እንዲሉ ።
- አስፈነቀለ፡ ኣስገለበጠ አስቀረፈ ።
- አስፈነቸረ፡ አስጣለ አስወደቀ አስገ ደለ ።
- አስፈነከረ፡ ኣስገለጠ ኣስከፈተ ኣዘረጋ ።
- አስፈነከተ፡ አስፈለጠ አስገመሰ አስ ተረረ ።
- አስፈነደሰ፡ አሠነጠቀ ኣስፈነከተ ።
- አስፈነደቀ፡ አስደሰተ አዘለለ አስፈ ነጠዘ ።
- አስፈነደደ፡ አስጐነበሰ (ቂጥን ለኳስ' አስመከተ አስመቸ ") ።
- አስፈነገለ፡ አስጣለ አስወደቀ ።
- አስፈነጠረ፡ አስወለቀ አስወጣ በፍጥ ነት ።
- አስፈነጠቀ፡ አስረጪ እስነዛ አስበተነ ።
- አስፈነጠዘ፡ አስደሰተ (በልብስ በጌጥ በምግብ በመጠጥ ") ።
- አስፈነጯ፡ አዘለለ አስቦረቀ ።
- አስፈንቃይ፡ ያስፈነቀለ/የሚያስፈነቅል (አስገልባጭ ") ።
- አስፈንካች፡ ያስፈነከተ/የሚያስፈነክት ።
- አስፈንዳጅ ያስፈነደደ/የሚያስፈነድድ (አስጐንባሽ ") ።
- አስፈንጋይ፡ ያስፈነገለ/የሚያስፈነግል ።
- አስፈንጣሪ፡ ያስፈነጠረ/የሚያስፈነጥር (ቀለሕን ፍምን ") ።
- አስፈንጣቂ፡ ያስፈነጠቀ/የሚያስፈነጥቅ (አስረጪ ") ።
- አስፈከረ/አስፎከረ፡ አስደነፋ (ግዳይ' አስቈጠረ ") ።
- አስፈካሪ/አስፎካሪ፡ ያስፈከረ/የሚ ያስፈክር/የሚያስፎክር (አስደንፊ ") ።
- አስፈወሰ፡ አሳከመ (አሰጠ ") ።
- አስፈዘዘ፡ ፈዛዛ አስደረገ ።
- አስፈየደ፡ አስረባ አስጠቀመ ።
- አስፈደነ፡ አሳሰረ አስቀፈደደ አስወደነ ።
- አስፈጀ፡ እንዲቃጠል አስደረገ (አስጨ ረሰ አሳለቀ አስበላ ") ።
- አስፈጅ፡ ያስፈጀ/የሚያስፈጅ (አስጨ ራሽ አስበሊ ") ። "እልክ አስፈጅ የልጅ ልጅ እኸል ፈጅ በኋላም ዥብ አስፈጅ" እንዲሉ ።
- አስፈገመ፡ አስደፋ አስወደቀ ።
- አስፈገፈገ፡ አስፋቀ አስጠረገ ።
- አስፈገፈገ፡ ወደ ኋላ አሠኘ ።
- አስፈግፋጊ፡ ያስፈገፈገ/የሚያስፈገፍግ (አስጠራጊ ") ።
- አስፈጠመ፡ አስጨረሰ ። "ንጉሥ ይሙት" አስባለ አሠኘ ።
- አስፈጠረ፡ አስደረገ አሠራ ።
- አስፈጠነ (አፍጠነ)፡ አስቸኰለ አ ሰቀለጠፈ ።
- አስፈጠጠ፡ አስጐረጠ አስቸኰለ ።
- አስፈጠፈጠ፡ አስፈነከተ አስቈሰለ ።
- አስፈጣሚ፡ ያስፈጠመ/የሚያስፈጥም ።
- አስፈጣኝ፡ ያስፈጠነ/የሚያስፈጥን (እስ ቸኳይ ") ።
- አስፈጣጭ፡ ያስፈጠጠ/የሚያስፈጥጥ ።
- አስፈጪ (አፍጽሐ)፡ አስከረተፈ አሸ መሸመ አሰለቀ ።
- አስፈጪ፡ ያስፈጩ/የሚያስፈጭ (የፈ ጫይ አለቃ ባለእኸል ") ።
- አስፈጪነት፡ አስፈጪ መኾን ።
- አስፊ፡ ያሰፋ/የሚያሰፋ።
- አስፋ፡ ሰፊ አድርግ።
- አስፋ ወሰን፡ የሰው ስም (ባ፲፰፻ ዓ.ም የነበሩ የሺዋ ባላባት) ።
- አስፋልት፡ የመጫ ቅጥራን ። አስፋልት በግእዝ አስፈሊጦስ ይባላል፡ በዘመናችን ግን ከምድር ዘይት የሚገኝ አተላ ነው ።
- አስፋሪ፡ ያሰፈረ/የሚያሰፍር (ስቃይ አስቀማጭ) ።
- አስፋቀ (አፍሀቀ)፡ ስርቅ ' አሠኘ ።
- አስፋቀ (አፍሐቀ)፡ አስጩ አስ ጠረገ አስጠፋ አስላገ አስለዘበ ።
- አስፋቂ፡ ያስፋቀ/የሚያስፍቅ (አስላጊ ") ።
- አስፋው፡ የሰው ስም ("ሰፊ አድርገው አታጥበው ትዳሩን ወሰኑን ድንበሩን") ።
- አስፋጪ (አፍጽሐ/አሕቀየ)፡ ሢጥጥ ሢጥጥ አስደረገ ። "አስፋጩን አስደ ራጊ ለማድረግ በፈጪ ፈንታ ፋጪ ብሎ ይነሧል" ።
- አስፌስ፡ መናኛ ኮሶ ፈሳ ።
- አስፌስ፡ በፈስ ብቻ የሚቀር የማያስ ቀምጥ የማያስቀዝን መናኛ ኮሶ ።
- አስፍሐ፡ ፊት በ፫፻ ኋላም በ፬፻ ዓ.ም የነበረ የኢትዮጵያ ንጉሥ።
- አስፎነነ፡ አሠነጠቀ አስቈረጠ ዐጪር አስደረገ ።
- አስፎናኝ፡ ያስፎነነ/የሚያስፎንን (እስ ቈራጭ ") ።
- አስፎከተ፡ አሳከከ ኣስፋቀ ።
- አስፎከተ፡ አሳወደ አስፈተገ ።
- አስፎጠረ፡ አሳሰረ አሸበበ ።
- አሶ (አሰወ)፡ ወባ ንዳድ ትኩሳት እሳታዊ በሽታ ።
- አሶመሶመ፡ አረተረተ ፥ (ሶመ ሶመ) ።
- አሶምሷሚ፡ ያሶመሶመ/የሚያሶመሱም (አረጥራጭ/አኰትኳች) ።
- አሶረደ፡ ፅንስን ሽልን አስጨነገፈ ("ከማሕፀን አለ ጊዜው አሶጣ ሴትዮዋን ምች አሶረዳት") ።
- አሶር፡ ፪ኛው የሴም ልጅ፡ ሶርያንና ሱርስትን እይ ። አገሩም ነገዱም አሶር ይባላል ።
- አሶከሶከ፡ እንደ ውሻ ኼደ፡ (ሶ ከሶከ) ።
- አሶክሷኪ፡ ያሶከሶከ/የሚያሶከሱክ ።
- አረ፡ የፈቃድ እብድ አደረገ ራሱን።
- አረመ፡ ነቀለ ፥ —ዐረመ ።
- አረመመ፡ ፥ —ዝም አለ ፥ —ረመመ ።
- አረመሰ፡ ረመሰ።
- አረመኔ (አረሚ አረማዊ)፡ አራማዊ፡ የአራም ነገድና ወግን፡ ፊት በኦሪት ኋላም በወንጌል ያላመነ ማንኛውም ሕዝብ፡ ቁመተ ገፋፋ ልብሰ አዳፋ፡ ለንት ለደንጊያ ለውሃ ለፀሓይ ለጨረቃ ለኮከብ የሚሰግድ፡ ጣዖት አምላኪ ሐዛብ ጨካኝ ። (ግጥም)፡ የኦሮ ልጅ ኦሮ ከቶም አረመኔ፡ እንቅልፍ ወሰደሽ ወይ ተለይተሽ ከኔ ።
- አረመኔ፡ ሐዛብ ፥ —አራም ።
- አረመኔነት፡ አረመኔ መኾን፡ ጨካኝነት የአሕዛብ ሥራ መሥራት ።
- አረመኔዎች (አረማውያን)፡ የኦራም ወገኖች፡ ጣፆት አምላኪዎች፡ ጨካኞች ክፉዎች አሕዛብ ።
- አረመደ፡ በንጀራ በሥጋ ድልኸን ብትን ድልኽን ተነ ቈነ ተመተመ ደመደመ።
- አረመደ፡ በውስጥ እግሩ ብዙ እሾኸ።
- አረመደ፡ አስነካ ፥ —ረመደ ።
- አረመጠ፡ (አርመፀ) ረመጥ አደረገ፡ አጋለ።
- አረማመም፡ አፈጋፈግ፡ መራመም።
- አረማመስ፡ አወሻሸቅ፡ መረመስ።
- አረማመደ፡ አስተላለፈ፡ አጋባ፡ አሸጋገረ።
- አረማመድ፡ አካኼድ፡ መራመድ (ምሳ፭' ፭። ፴፡ ፳፱) ። ረመደ እንደ ለመጠ ከሌላው ግስ ተለይቶ በ፰ ዐምድ መገሰሱን አስተውል።
- አረማመጥ፡ አሸጓጐጥ፡ መረመጥ።
- አረማማጅ፡ ያረማመደ፡ የሚያረማምድ፡ አስተላላፊ።
- አረማረም፡ አረጋገጥ፡ መረምረም።
- አረም (ትግ ሐባ)፡ አሕዛብ ። (መዝ ፪ ፥ ፩ ፥ ፰) ።
- አረም፡ ዝኒ ከማሁ፡ ኣራም ግእዝኛ፡ አረም ዐማርኛ ።
- አረሰ፡ ቀለበ ፥ —ዐረሰ ።
- አረሰረሰ፡ አራሰ አወረዛ አጨቀየ።
- አረሰገመሰ፡ ዐረሰ ።
- አረሳሳ፡ (አስተራስዐ)፡ አዘነጋን፡ አ
- አረሳረሰ፡ አራራሰ።
- አረሳረስ፡ አራራስ፡ መረስረስ።
- አረሳሺ፡ ያረሳሳ፡ የሚያረሳሳ ። ማረሳሳት፡ ማነጋጋት፡ ማስተጣጣት ። ማረሳሻ፡ ማነጋጊያ ። ርሳታ፡ (ርስዐት)፡ ዝንጋታ ። ርስት፡ ዝንግት፡ ተወት ። ርስት፡ አደረገ፡ ፈጽሞ፡ ረሳ ። አረሳስ ፣ አዘነጋግ፡ መርሳት ። ረሽ ጠመንዣ ፣ ረሸነ ። ራሰ ፣ (ርሕሰ ። ዕብ፡ ራስ አራሰ፡ ለ ወሰ)፣ ተነከረ፡ ተዘፈቀ፡ ተዘፈዘፈ፡ ረጠበ ። ረሰ
- አረረ (አሪር አረረ)፡ ዐወደ ሰበሰበ ለቀመ፡ ጠቀለለ ። ማረረን እይ ።
- አረረ፡ ጠቈረ ፥ —ዐረረ ።
- አረረ፡ ጮኸ ገነታ ። እሪን ተመልከት፡ የዚህ ዘር ነው ።
- አረር፡ ርሳስ ፥ —ዐረረ ።
- አረቀቀ፡ (አርቀቀ) አቀጠነ፡ አሣሣ፡ አሳነሰ፡ አደቀቀ፡ እላመ፡ እለዘበ።
- አረቀቀ፡ ቃል አወጣ፡ ረቂቅ ጽፈት ጻፈ።
- አረቃረቅ፡ አመታት፡ መረቅረቅ።
- አረቃቀቅ፡ አቀጣጠን፡ መርቀቅ።
- አረቄ፡ የሚያሰክር መጠጥ ፥ —ዐረቄ ።
- አረበ፡ ጠለቀ ፥ አቀላ፡ ዐረበ ።
- አረበረበ፡ አረበደ ("በላይ በላዬ ተናገረ ") ።
- አረበረበ፡ አርከፈከፈ አረበደረ በረበ ።
- አረበረበ፡ አካፋ አንጠባጠበ።
- አረበደ (ሀርበደ)፡ ቸኰለ ተቈጣ፡ እብድ እብድ ሰው ልፍጅ አለ፡ ባለማቋረጥ ለፈለፈ ተናገረ፡ አረበረበ ። ረበደን ተመልከት ።
- አረበደ፡ ቸኰለ ።
- አረባ (አርብሐ)፡ ከብትን እንዲወልድ እንዲረባ አደረገ ።"ኣንዱን ግስ ባ፲ ሰራ ዊት በ፹ መደብ አበዛ ዘረዘረ፡ ርባታ ተማረ" ።
- አረባረበ፡ አራጨ ።
- አረባረበ፡ አደራረበ/አነባበረ ።
- አረባረብ፡ አደራደር/መረብረብ ።
- አረባበብ፡ እዞረግ/መርበብ ።
- አረባበክ፡ ኣወዛዘፍ/መረባክ ።
- አረባብ፡ አወላለድ/አጠቃቀም/መር ባት ።
- አረባየ፡ ረገጠ ። (ረበየ) ።
- አረባጅ (ጆች)፡ ያረበደ የሚያረብድ፡ የሚቸኵል የሚያብድ፡ ቍጡ ለፍላፊ አረብ ራቢ ቸኳይ ።
- አረባጅነት፡ አረባጅ መኾን፡ ለፍላፊነት ።
- አረብራቢ፡ ያረበረበ/የሚያረበርብ ("አ አረብራቢነት ኣረብራቢ መኾን እረ ባጅነት ") ።
- አረተ፡ መድኀኒት አቃበረ/አጠናቈለ።
- አረተ፡ አራት አደረገ ።
- አረተ፡ አራት አደረገ፤—አራት።
- አረተ፡ አከበ ከበበ ጐረሠ እራት በላ ። ወቃ፡ ቀረቀበ አሰረ ወደነ ። አከተን እይ ።
- አረተ፡ አፋፋቀ/አቀጣቀጠ/ኣባተነ/አለያየ ።
- አረተ፡ ደንቃራ፡ ጣለ (ረተ)።
- አረተረተ፡ አሶመሶመ (ረተ ረተ) ።
- አረታ/አርትዐ፡ አቀና፡ ቀጥ አደረገ፡ አሰላ ነገርን።
- አረታታ፡ ኣሸናነፈ።
- አረታት፡ አሸናነፍ፡ አቀናን፡ መርታት።
- አረትራች፡ ያረተረተ፡ የሚያረተርት።
- አረነ (ረሐነ)፡ ጫነ፡ ላገ ሳበ አ ጠበቀ ።
- አረነ፡ ነዳ፡ ኣሰማራ፡ ኣገደ፡ ጠበቀ፡ ኣስወጣ ኣስገባ ።
- አረንቋ፡ ማጥ ረግረግ ወልቅ ጭቃ ።
- አረንዛ (ዞች)፡ መሬትን ውሃን የሚያለብስ ብዙ ደንጊያ ።
- አረንጓዴ (ዎች)፡ የውሃ ልብስ፡ የኩሬ ሰፈፍ ቅጠልያ ። በትግሪኛ ሐምላይ ይባላል ። ፪ኛውን አለ ተመልከት ።
- አረንጓዴነት፡ አረንጓዴ መኾን ።
- አረከሰ፡ (አርኰሰ) አሳደፈ፡ ርኩስ አደረገ (ሰቈ፪፡ ፪) ።
- አረከሰ፡ ዋጋ ሰበረ፡ ናቀ፡ አዋረደ፡ ጣለ። አረከሰ፦ ኣባረሰ፡ አበረደ፡ ሻረ፡ አጠፋ።
- አረካ፡ አጠጣ፡ እራሰ፡ አጠገበ (መዝ ፻፯፡ ፱) ።
- አረካረክ፡ አወለጋገድ፡ መረክረክ።
- አረካከሰ፡ ጣልጣል አደረገ ሰውን።
- አረካከስ፡ አበራረስ፡ መርክስ።
- አረካከበ፡ አሳሳጠ፡ አቀባበለ።
- አረካከብ፡ አወጣጥ መርከብ።
- አረካካቢ፡ ያረካካበ፡ የሚያረካክብ፡ አተባባይ ዳኛ።
- አረካካቢነት፡ አቀባባይነት።
- አረካክ፡ አጠጣጥ፡ መርካት።
- አረኸ (አርኀ ዕብ አራኸ ረዘመ)፡ ከገደልና ከተራራ በታች ያለ ተዳፋት፡ ወዳቃ ዘቅዛቃ ቍልቍለት ስፍራ፡ ሲበዛ አረኾች ይላል ።
- አረኾ (ዎች)፡ ዘፋኝ አማርያት ቀንቃኝ አውራጅ፡ ባረኸ ላይ ኹና ዘፈን የምትፈጥር የምታንጐራጕር ድምፀ ረዥም ሴት ።
- አረዋወጥ፡ አሯሯጥ, አበራሪር - አሯሯጥ, ማባረር።
- አረዘ፡ አነሰ ፥ —ዐረዘ ።
- አረዘመ (አርዘመ)፡ ኣበለጠ፡ አበዛ፡ አተረፈ፡ ቁመትን ነገርን ("(ግብ. ሐዋ. 20፡ 7)") - በለጠ፡ አበዛ፡ አተረፈ፡ ቁመትን/ነገርን ("(የሐዋ. ሥራ 20፡ 7)").
- አረዛዘም፡ አባላለጥ, መርዘም - ማራዘም, ርዝመት።
- አረደ፡ ዐንገት ቈረጠ ፥ —ዐረደ ።
- አረደ/አሞራረደ፡ አዘራዘረ/አሳሳለ።
- አረዳ (ኦሮ)፡ ከአባት የወረደ ርስት፡ ባዶ ወና ጕድፋም መሬት ።
- አረዳ፡ መርዶ ነገረ ፥ —ረዳ ።
- አረዳ፡ ንብ ዐጥር ላይ ዐረፈ ሰፈረ መኼዱን ኣስታወቀ። ንብ ላጥር ሳያረዳ ኣይኼድም እንዲሉ። ዐጥር የተባለ ባለቤትነው ።
- አረዳ፡ የችን ነገር ነገረ አወራ ዕርምኽን አውጣ አለ። (ተረት) ማን ይንገር፡ የነበር ።ማን ያርዳ ! የቀበር።
- አረዳደፍ፡ አሰዳደር፡ መረደፍ - አሰላለፍ፡ መደርደር። መርዱፋንን አስተውል፡ የረደፈ ዘር ነው - መርዱፋንን አስተውል፡ የተደረደረ/የተደረበ ዘር ነው።
- አረዳዳ፡ አስተጋዝ፣ አደጋገፈ።
- አረዳድ፡ ኣስተጋዝ፣ መርዳት።
- አረጀ (አሪግ አረገ)፡ አሮጌ ኾነ፡ ሸመገለ አፈጀ ። (ኢዮ ፳፩ ፥ ፯) ። ዋጀን እይ ። (ተረት)፡ ሲያረጁ አይበጁ ። አንበሳ ቢያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይኾናል ። (ፈራ) ብለኸ አፈራን እይ ።
- አረጃጀት፡ አሸመጋገል፡ ማርጀት ።
- አረገ ሠራ፡ ፥ —ደረገ ።
- አረገ፡ ወጣ ፥ —ዐረገ ። (ረ) ።
- አረገረገ (ረገረገ)፡ አንቀጠቀጠ. "ልማዱ ግን ተነቃነቀ ተወዛወዘ ነው ። የክትክታ ሞፈር ያረገጋል" - "ልማዱ ግን ተነቃነቀ ተወዛወዘ ነው ። የክትክታ ሞፈር ያረገጋል".
- አረገረገ፡ ተወዛወዘ ረገረገ ።
- አረገበ፡ አላላ / አጐረበ
- አረገዘ ቂም ያዘ ("(መዝ. ፯፥ ፲፬)") ።"ነገር እረግ" እንዲሉ ።
- አረገዘ፡ ተንዘረጠጠ/ተንጠረዘ/ተንቀ በያያ ("የሆድ የማሕፀን ") ።"ተንጠለጠለ ሊናድ ተረበ እዘበዘበ የግንብ የካብ(ተገብሮ )" ።
- አረገዘ፡ ፀነሰ ፥ —ረገዘ ።
- አረገዘ፡ ፀነሰ/ቋጠረ ("(ቢር)") ።
- አረገዘች፡ ፀነሰች/ቋጠረች/ያዘች/ሙሉ ኾነች/ከበደች ("(ዘፍ. ፬፥ ፩ ። ሮሜ ፬፥ ፲)") ። (ተረት)፡ "ያረገች ታስታውቅ ከደረቷ ትታጠቅ (ገቢር )" ።"ባላገርም ሴትን አርግዛለች ለማለት ታማለች ይላል፡ ይኸውም የምጥ ትንቢትነው ። ዐመመ ብለኸ ታመመን እይ" ።
- አረገደ (ረገደ)፡ መር መር አለ ("እሸበሸበ") - (ተረት) "ላለው ቅንጭብ ያረግዳል"
- አረገደ፡ ጨፈረ ፥ —ረገደ ።
- አረገፈ (አርገፈ)፡ አወደቀ/ጣለ/አን ጠባጠበ ("(ኢሳ. ፶፪፥ ፪ ። ዳን. ፬፥ ፲፬)") ።
- አረጋ፡ አረጋኸ/አረጋኸኝ ።"የሰው መጠሪያ ስም ። እናት ልጅ ከወለደች በኋላ ልቧ ረግቶ በባሏ ቤት መኖሯን ያሳያል" ።
- አረጋ፡ አቆመ/አሳረፈ/አደረቀ/አጸና ።አረጋ፡ ደለደለ/አገደ ።"ክተረ የምስጢር ትርጓሜ ነው" ።
- አረጋረግ፡ አወዛወዝ, መረግረግ.
- አረጋሽ፡ የሴት ስም ።
- አረጋዊ (ይ)፡ የአረግ ያሮጌ ወገን ሮማዊ፡ ከተስዐቱ ቅዱሳን አንዱ፡ ደብረ ዳሞ ላይ የዘንዶ ዥራት ይዘው የወጡ፡ ጥንተ ስማቸው ዘሚካኤል ። ካነጋገራቸው የተነሣ በሕፃንነት ስለ መነኰሱ አረጋዊ ተባሉ ይባላል፡ የልጅ ዐዋቂ እንደ ማለት ። አቡነ ኣረጋይ እንዲሉ ።
- አረጋዊ፡ መንፈሳዊ፡ የሶርያ ቅዱስ ።
- አረጋገም፡ አካካድ/መርገም ።
- አረጋገብ፡ አጐራረብ / መርገብ
- አረጋገዝ፡ አፀናነስ/ማርገዝ ። "ምርጕዝን አስተውል የዚህ ዘር ነው" ።
- አረጋገድ፡ አጨፋፈር/መርገድ ።
- አረጋገጠ፡ አደላደለ/አረጋጋ ("የዛር ") ።
- አረጋገጥ፡ በመንገድ ላይ የእግር እጣጣል/መርገጥ ("(መዝ. ፯፥ ፭ ። ፲፰፥ ፴፯ ። ኢሳ. ፳፯፥ ፮)") ።
- አረጋገፈ፡ ብዙ ጊዜ አረገፈ ።
- አረጋገፈ፡ አፋታ ጭነትን ባንድ በኩል ይዞ አዋረደ (ጭነትን በአንድ በኩል ይዞ አወረደ).
- አረጋገፈ፡ የምንጣፍን ዐቧራ አባነነ (የምንጣፍን ዐቧራ አባነነ).
- አረጋገፍ፡ አወዳደቅ, መርገፍ.
- አረጋጊ፡ ያረጋጋ/የሚያረጋጋ ("አረጋጋጭ መካር ቃልቻ ") ።
- አረጋጋ፡ አስተዛዘነ/አወያየ/አጸናና/አ በረታታ ዐዘነተኛን ።
- አረጋጋ፡ አረጋገጠ ዛርን ።
- አረጋጋ፡ አጽናና ("አይዞሽ አለ ") ።
- አረጋጋጭ፡ ያረጋገጠ/የሚያረጋግጥ ("አደላዳይ ዛር አረጋጊ ቃልቻ ") ።
- አረግ (አሪግ አረገ አረጀ)፡ ኦሮጌ ።
- አረግ፡ በቁሙ ዐረግ ።
- አረግ፡ የግእዝ ቃል ነው ።
- አረግራጊ፡ ረግራጊ, አንቀጥቃጭ, ተነቃናቂ ተወዛዋዥ.
- አረጠ፡ አሸሸ/አከሳ።
- አረጠ፡ አቈረጠ ዐረጠ ።
- አረጠ፡ አተረፈ፡ ዐረጠ ።
- አረጠረጠ፡ ሮጠ፡ አዘጠዘጠ፡ አረተረተ፡ አነጠነጠ።
- አረጠረጠ፡ አዘጠዘጠ ረጠ ።
- አረጠበ፡ (አርጠበ)፣ እራሰ፡ አለመለመ።
- አረጣጠበ፡ መላልሶ አረጠበ።
- አረጣጠበ፡ ኣሰጣጠ፡ አረዳዳ፡ አስተጋ።
- አረጣጠብ/አራራስ/አሰጣጥ፡ መርጠብ።
- አረጣጠጥ፡ አስተማመቅ፡ መረጠጥ።
- አረጥራጭ፡ ዘብዛቢ ጥልቅ ብዬ።
- አረጥራጭ፡ ያረጠረጠ፡ የሚያረጠርጥ፡ አዘጥዛጭ፡ አረትራች፡ አነጥናጭ።
- አረጨ፡ አፈነጠቀ, አበታተነ - አረጨ, በተነ።
- አረጭ፡ ኹለተኛ የጭሪ ስም ።
- አረጮች፡ ጭሪዎች ።
- አረፈ፡ እፎይ አለ ፥ —ዐረፈ ።
- አረፈረፈ፡ (ረፈረፈ) ነሰነሰ፡ አርከፈከፈ (ይሁ፡ ፲፫) ።
- አረፈረፈ፡ ነሰነሰ ፥ —ረፈረፈ ።
- አረፈረፍ፡ ዝኒ ከማሁ። (ግጥም) የጊዮርጊስ የለምዱ ዘርፍ ወርቅ አረፈረፍ።
- አረፈቀ፡ ዐቅም ወጣ፡ ደከመ በፈር ላይ ተኛ በሬው።
- አረፈቀ፡ አበቃ፡ እቤት ዋለ ሽማግሌው። አገባቡ ግን አድራጊነት ነበር።
- አረፈደ፡ ጊዜው እስኪረፍድ ቈየ፡ ዘገየ፡ ሳይኼድ ሳይሠራ።
- አረፋ፡ የንዶድ መረቅ ፥ —ዐረፋ ።
- አረፋረፍ፡ አጣጣል፡ መረፍረፍ።
- አረፋቂ፡ ያረፈቀ፡ የሚያረፍቅ፡ ደካማ።
- አረፋፈቅ፡ አቋቈንእተማመጥ (ጥፈ) መረፈቅ (ጥረ) መረፈቅ።
- አረፋፈደ፡ የአረፈደ ድርብ።
- አረፋፈድ፡ ኣቈያየት፡ መርፈድ።
- አረፋፈጥ/አረፋፈቅ፡ መረፈ።
- አረፍራፊ፡ ያረፈረፈ የሚያረፈርፍ ነሳሽ።
- አረፍተ ነገር፡ ፍጹም ቃል፡ የተላ ዞ ንግግር ።
- አረፍት (ግእዝ፡ ግድግዳ ግንብ)፡ የቤተ ክሲያንን ግድግዳ ወይም ግንብ ተጠግቶ በስተውስጥ ዐልፎ ዐልፎ የተበጀ የካህናት የሕዝብ የሴቶች ማረፊያ መቀመጫ ።
- አሩሲ፡ የኦሮ ነገድና አገር፡ ከአዋሽ ወንዝ ቀጥሎ የሚገኝ፡ ከ፲፪ቱ ጠቅላይ ግዛቶች አንዱ ።
- አሩት (ረዐወ ጠመደ አርዑት)፡ ቀንበር፡ ማኅበር፡ በወር በወር የሚደገስ ድግስ፡ በእያንዳንዱ ማኅበረተኛ ባመት ባመት የሚደርስ፡ ማኅበረተኛ ባ፬ ሳምንት የሚገባበት የሚጠመድበት ። ማነሽ ባለሳምንት፡ ያስጠምድኸ ባሥራ ስምንት፡ እኔ ነኝ የምትል የማሪያም ወዳጅ እንዲል ሙሴ ። አለቅሶስን እይ ።
- አሩት፡ አጣማጅ አቻ ወደር እኩያ ። አባትና እናት ለልጃቸው ስም ሲያወጡ ማን ኣሩትኸ እንዲሉ ።
- አሪ (ዕብ)፡ አንበሳ፡ ያንበሳ ቡችላ ።
- አሪ ዘንባባ ዬ፡ ልጃገረዶች ዐንገት ላንገት ተያይዘው የሚዘፍኑት ዘፈን ። ምስጢሩ ጠላትን ድል አድርጎ በተመለሰ ጊዜ ዘንባባ ይዘው የሚቀበሉትን ንጉሥ ያሳያል ። ባለዘንባባ የዘንባባ አንበሳ (ንጉሥ) ማለት ነው ። (ዮሐ ፲፪ ፥ ፲፫) ።
- አሪ፡ ያማረ/የሚያሙር (ያኺዶ/መሪ/ቀላሽ/አዟሪ/አባት/በሬ/አማሪና አሯጭ) ። "ማርንና ማሮጥን ሰው ሳያስተምራቸው በተፈጥሮ ባሕርይ ተምረው ይገኛሉ"።
- አሪማጥ፡ ሞያ ቢስ ሴት ፥ —ረ መጠ ።
አሪማጥ፡ የረመጥ ዐመድ የበነነባት ጽዳት የሌላት ሞያ ቢስ ሴት፡ ገልቱ ጥላት ፊት።
አሪባራ፡ የወፍ ስም፡ ካካቴ ።
አሪታ፡ ያራች፡ ሀራ ።
አሪዛዞ፡ ሰማያዊ የጥንቈላ ብርሌ ። ዘሩ ረዘዘ ይመስላል ።
አራ፡ ኰሳ ፥ —ዐራ ።
አራመመ፡ አጣረገ፡ አስተጣጠበ፡ አፌጋ።
አራመደ፡ አሳለፈ ፥ —ረመደ ።
አራመደ፡ አስኬደ፡ አሳለፈ፡ እሠፃረ፡ አገሠገሠ፡ አስፈጠነ። (ዐይኑን አራመደ) አሻገረ አሻግሮ አየ። አደራራጊ ሲመስል ባስደራ ጊነት መተርጐሙን ልብ አድርግ።
አራማጅ፡ ያራማደ፡ የሚያራምድ፡ አሠጋሪ፡ አገሥጋሽ፡ መንገድ መሪ።
አራም፡ የሴም ፭ኛ ልጅ ። (፩ዜና ፩ ፥ ፲፯) ። አገሩም ነገዱም አራም ይባላል ።
አራምዴ፡ የሰው ስም፡ አራምድ ከሚለው ከቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ የወጣ ነው። አስኪድ፡ አሳልፍ፡ አገሥግሥ።
አራሰ፡ (አርሐሰ)፡ ነከረ፡ ዘፈዘፈ፡ አ ረጠበ፡ (ሉቃ፯ ፥ ፵፬ ።
አራስ፡ በቁሙ ፥ —ዐራስ፡ ዐረሰ ።
አራሪ፡ ዐጫጅ ሰብሳቢ ። (ተረት)፡ ኣራሪ ለማራሪ፡ ማራሪ ለበራሪ ይተው ።
አራሪ/አራኅራኂ፡ ያራራ፡ የሚያራራ።
አራራ/አራኅርኅ፡ ርኅሩኅ አደረገ፡ አሳዘነ።
አራራሰ ፣ (አስተራሐሰ)፡ አናከረ፡ አ
አራራስ፡ አረጣጠብ ፣ መራስ ።
አራራቀ፡ (አስተራሐቀ) አነጣጠለ አለያየ።
አራራቂ/አስተራሓቂ፡ ያራራቀ የሚያራርቅ።
አራራቅ፡ አገላለል፡ መራቅ፡ ርቀት።
አራራብ፡ ኣሞራሞር/መራብ ።
አራራት፡ የተራራ ስም፡ የአርማንያ ተራራ፡ የኖኅ መርከብ ያረፈችበት ። (ዘፍ ፰ ፥ ፬) ።
አራራይ፡ የዜማ ስም፡ ፫ኛ ዜማ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ።
አራሽ፡ (አርሓሲ፡ ያራሰ፡ የሚያርስ፡ ነካሪ፡ አጣቢ ።
አራቀ፡ (አርሐቀ) አገለለ፡ ወገደ፡ ነጠለ፡ ለየ (፪ዜና፡ ፴፫፡ ፲፭) ።
አራቀ፡ ከፍ አደረገ፡ አመጠቀ። ኣምላክ ባወቀ ሰማዩን አራቀ እንዲሉ።
አራቀቀ፡ ብልኀ ጥበበኛ አደረገ፡ አስፈለሰፈ፡ ረቂቅ አኳዃነ።
አራቂ/አርሓቂ፡ ያራቀ፡ የሚያርቅ፡ አግላይ ወጋጅ ለየት።
አራቃቂ፡ ያራቀቀ፡ የሚያራቅቅ።
አራቈተ፡ ባዶ ገላ አደረገ፡ ዐረቀ ።
አራቈተ፡ ገፈፈ ልብስ ነሣ ከለከለ አወለቀ ("(አጋፈፈ)") ።
አራቋች፡ ያራቈተ/የሚያራቍት (ገፋፊ ") ።
አራቢ፡ መላጭ —ዐረበ/ዐራቢ ።
አራቢ፡ ያራባ/የሚያራባ ("አባዢ አጣ ቃሚ ") ።
አራባ (አስተራብሐ)፡ አዋለደ/አ ባዛ ።
አራባ፡ አጣቀመ ።
አራባ፡ የባሕር ድርና ማግ፡ የሐር የጥለት ቱባ ክፍል፡ በባለ ቀለም ክር የተለየ ። አንዱ ቱባ በአሥር አራባ፡ አንዱ ኣራባ በሰባት ወረር ይከፈላል ። ኣራባ በጋልኛ ምላስ ማለት ነው ።
አራባ፡ ጠላንና አንደኛ ቅራሪን ቀላቀለ ደባለቀ አባረዘ አላማ ።
አራተኛ (ራብዓዊ)፡ ያራት ወገን፡ ባራት ክፍል ረድፍ ያለ፡ ሩብን ርቦን የመሰለ፡ በአኃዝ ሲጣፍ ፬ኛ፡ ሲዘረዝርም አራተኛው አራተኛዪቱ አራተኛዬ እያለ እስከ ስምንት ይዘምታል ።
አራተኛው፡ ያ አራተኛ በተራ ቍጥርነት ላይ ለማንኛውም ነገር በከፊል በቂ ይኾናል፡ ጊዜንም ያሳያል ። ካቱ ባሕርያት እንደኛው መሬት፡ ፬ኛው ነፋስ ነው ።
አራቱ ሊቃነ ጳጳሳት፡ በሮም በእስክንድርያ በአንጾኪያ በኤፌሶን የተሾሙ፡ ጴጥሮስ ማርቆስ አግናጥዮስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ።
አራቱ ባሕርያት፡ መሬት ውሃ ነፋስ እሳት ።
አራቱ ወንዞች፡ ጥቍር አባይ ነጭ አባይ ኤፍራጥስ ጤግሮስ፡ ኹለቱ በአፍሪቃ ኹለቱ በእስያ ይገኛሉ ።
አራቱ ወንጌላውያን፡ ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ዮሐንስ ።
አራቱ ጉባኤ፡ ብሉይ ሐዲስ ሊቅ መጽሐፈ መነኮሳት ።
አራቲያ፡ ርቢት ።
አራታ፡ አቃና፡ አሳላ።
አራት (ረብዐ አርባዕት)፡ ከ፫ በላይ ያለ ሙሉ ቍጥር፡ ኹለት ጊዜ ኹለት አራት፡ የስምንት እኩሌታ ። በአኃዝ ሲጣፍ ፬ ይባላል ።
አራት ሕብር፡ ነጭ ቀይ ብጫ ጥቍር ቀለምና መልክ ያለው የአዳም ዘር ምሳሌ ቀስተ ደመና ።
አራት ማእዘን፡ ምሥራቅ ምዕራብ ሰሜን ደቡብ ።
አራት ማእዘን፡ አራት ገጽ ያለው ዕንጨት ደንጊያ መንሰር፡ ባራት ወገን ትክክል የኾነ ቤት ።
አራት ራስ አሞራ፡ ኪሩብ ከወገቡ በታች አንድ ከወገቡ በላይ አራት መኾኑን ያሳያል ። (ሕዝ ፩ ፥ ፮) ።
አራት ዐቅ፡ እራት ክንድ ቅጥብ ልክ ። አራት ዐቅ ሸማ እንዲሉ ።
አራት ዐይና፡ ፍጹም ሊቅ መምር (ዲፕሎማቲክ) አራቱን ጉባኤ ያወቀ ። አራት ዐይና ጐሹ፡ አራት ዐይና ክፍሌ እንዲሉ ።
አራት ዐይን፡ ዕጥፍ ዐይን፡ ዐዋቂ፡ አራት ዐይን (ዕውቀት) ያለው ጭራቅ በጨለማ እንዳውሬ ሰውን የሚሰርቅ፡ ሰው በሌ በላዔ ሰብእ ።
አራት አደረገ (ረብዐ)፡ ካራት ከፈለ፡ አራት አለ ።
አራት እግር፡ ባራት እግር የሚኼድ እንስሳ አውሬ ከብት ።
አራት ገጽ፡ ኪሩቤል፡ አርባዕቱ እንስሳ፡ ገጸ ሰብእ ገጸ ላሕም ገጸ ንስር ገጸ አንበሳ ።
አራትነት፡ አራት መኾን ።
አራትያ፡ ፬፻ ጥርስ ያለው፡ ዐርብ ፬፻ ድር የሚቋጥር፡ ድሩም አራትያ ይባላል ።
አራትጌ፡ በጕራጌ አገር ያለ ፬ ክፍል የወታደር ሰፈር ።
አራቶ፡ አራትዮ፡ አራት የኾነ ውስጠ ብዙ ።
አራች፡ ያረተ/የሚያማርት (ጠንቋይ) ።
አራኝ (ረሓኒ)፡ የሚጭን የሚልግ የሚስብ የሚያጠብቅ፡ ጫኝ አጥባቂ ። (ተረት)፡ ያባያ ልጅ ወዳቂ፡ ያራኝ ልጅ አጥባቂ ።
አራኞች (ረሓንያን)፡ ጫኞች፡ አጥባቂዎች፡ ጐረደማኖች ።
አራከሰ፡ (አረከሰ) አስተዳደፈ፡ አቃለለ፡ አናናቀ።
አራከበ፡ (ከተበ) ኣመሳቀለ ተክልን። አራከበ፦ እቀራመተ፡ አካፈለ፡ ኣቃማ፡ አ።
አራከበ፡ አገናኘ፡ አጋጠመ፡ አዳረሰ።
አራካሽ፡ ያራከሰ፡ የሚያራክስ፡ አታላይ፡ አናናቂ።
አራኰተ፡ አስተናነቀ፡ አስታገለ፡ ኣጋፋ።
አራኰተ፡ አጣላ፡ አከራከረ፡ አተ።
አራኰተከራከረ፡ አስታገለ ፥ —(ረ ኰተ) ።
አራኳች፡ ያራኰተ፡ የሚያራኵት፡ አከራ።
አራወጠ፡ አሯሯጠ (ዐብሮ ጠ) - አባረረ, አሽቀዳደመው።
አራዊት፡ አራዪት፡ ከላይ ጥርስ ያላቸው አውሬዎች ። እነሱም ቀን ይደበቃሉ ሌሊት ይወጣሉ ። (መዝ ፻፬ ፥ ፳ ፥ ፳፪) ። ሌሊት ለአራዊት፡ ቀን ለሰራዊት እንዲሉ ። (የቤት አራዊት)፡ ውሻ ድመት ዐይጥ ። ወና የ ተወራራሾች ስለ ኾኑ ባላገር ኣራዪት ይላል ።
አራዋጭ፡ አሯሯጭ፡ ያራወጠ/የሚያራውጥ, ያሯሯጠ/የሚያሯሩጥ፡ አሽቀዳዳሚ - አሯሯጭ፡ ያባረረ/የሚያባርር, ያሽቀዳደመ/የሚያሽቀዳድም።
አራዘመ፡ አባለጠ፡ አበላለህ፡ አባዛ፡ አበራከተ - አበለጠ፡ አበዛ።
አራዛሚ፡ ያራዘመ/የሚያራዝም, አባዝ/አባራካች - ያረዘመ/የሚያረዝም, አብዝቶ የሚያበዛ።
አራዠ፡ ተየ፡ ነዘነዘ፡ አስጨነቀ፡ ዕረፍት ነሣ - ተወ፡ ነዘነዘ፡ አስጨነቀ፡ ዕረፍት ነሣው። ዛሬ ዓይኔን ዐሞኝ ሲያራዠኝ ሀደረ - ዛሬ ዓይኔ ታሞ ስታስጨንቀኝ ዋለ።
አራዠ፡ አናወዘ፡ ራዠ ።
አራያ (ርእየ አርአየ አርኣያ)፡ መልክ ምስል ።
አራያ በለል፡ መልከ መልካም ሰው ግብረ መጥፎ ሲኾን እራያ በለል ይባላል ።
አራደ (አርዐያ)፡ አስፈራ, አንቀጠቀጠ, አብረከረከ (አስፈራ, አንቀጠቀጠ, አብረከረከ).
አራደፈ፡ አከታተለ.
አራገመ/አረጋገመ፡ እካካደ/አለያየ ("(ዐብሮ ረገመ)") ።
አራገጠ (አስተራገፀ)፡ በርግጫ ኣ ማ ።
አራገጠ፡ አንፈራገጠ ("(ማር. ፱፥ ፲፰)") ።
አራገጠ፡ አዳካ/ኣዋሰነ/ኣካላለ ።
አራገፈ (አረገፈ)፡
አራጊ፡ ያራጋ/የሚያራጋ ("አጻኚ ") ።
አራጋ፡ አዋየ/አጻና/አበራታ ።"አራጋው የሰው ስም" ።
አራጋሚ/አረጋጋሚ፡ ያራገመ/የሚያ ራግም ("ያረጋገመ የሚያረጋግም አለያዪ አካካጅ ") ።
አራጋቢ፡ ያራገበ / የሚያራግብ ("ገበሬ ልቅሶኛ")
አራጋጭ፡ ያራገጠ/የሚያራግጥ አካ ላይ አዋሳኝ ። የወሬ ።
አራጋፊ፡ ያራገፈ/የሚያራግፍ ("ፈቺ አውራጅ" - ፈቺ ወይም አውራጅ).
አራጠበ፡ ርጥባን አቀባበለ።
አራጠበ፡ አራራሰ (የሽንት ውሃ አፈሰሰ፡ አረጠበ፡ ምጥ ዠመረ) ። ገ።
አራጠጠ፡ አስተማመቀ፡ አማቈነ። አራጠጠ፦ አሸራሸረ፡ ብዙ ጊዜ ጐረሠ፡ በላ፡ ተመገበ (ዓሞ፯፡ ፯) ።
አራጣ፡ ትርፍ ፥ —ዐራጣ ።
አራጣቢ/አራጠበ፡ የሚያራጥብ።
አራጨ (አስተራቀየ)፡ አፈናጠቀ, አበተነ, አወራወረ - አረጨ, በተነ, ወረወረ።
አራፈደ፡ የጧትን ሰዓት አስተላለፈ።
አሬራ (ኦሮ)፡ አዥራሮ ውሃ የተጨመረበት ወተት፡ ባዶ ።
አሬሮ፡ ያገር ስም፡ በወለጋ ክፍል ያለ አገር ።
አሬዘ፡ አቀነቀነ፡ ሪዝ ።
አሬዘ፡ አወጣ, አቀነቀነ ሪዝን - ሪዝን አወጣ/አበቀለ።
አርመሰመሰ፡ አንቀሳቀሰ ረ መሰ ።
አርመሰመሰ፡ አንቀሳቀሰ፡ አነቃነቀ፡ ግራና ቀኝ አላወሰ እባብን ጅራፍን።
አርመን (ኖች)፡ የነገድ ስም፡ ከአርያ የወረደ ዘር፡ በእስያ ውስጥ በፋርስና በመስኮብ በቱርክ አገር አጠገብ ያለ ሕዝብ ።
አርመን፡ የግንብ የካብ ስፋት፡ ጐን ። (ዐማርኛ) ።
አርመጠመጠ፡ ከረመጥ ከአመድ መላልሶ አገባ፡ በአመድ በጥላት አለፈለፈ፡ አልከሰከሰ።
አርማሚ፡ ያረመመ፡ የሚያረምም፡ ዝምተኛ ጭምት ባሕታዊ።
አርማንያ፡ የአርመን አገር፡ ይኸውም በግእዝ ነው ። በይፋትም ኣርማንያ የሚባል ቀበሌ አለ ።
አርማጅ፡ ያረመደ፡ የሚያረምድ፡ ተጫኝ ጨቋኝ።
አርማጭሆ፡ ያገር ስም፡ በበጌምድር ክፍል ያለ አገር ።
አርምሞ፡ ዝምታ፡ ጸጥታ።
አርምዳቸው፡ ተጫናቸው ቍናቸው።
አርምድ/አርምዴ፡ የሰው ስም፡ ተጭን ጨቍን ማለት ነው።
አርሞጠሞጠ፡ ዝኒ ከማሁ።
አርስ፡ እንዲለ ።
አርስ፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ ለአራሽ ። አንዠት፣
አርስ፡ የቅርብ፡ ወንድ፡ ትእዛዝ፡ አን
አርቃሾ (ትግ አርቃይ)፡ ሽመል የላም መንጃ ። (መድጐጸ ላሕም) ። አልቃሾን እይ፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ።
አርቃቂ፡ ያረቀቀ፡ የሚያረቅቅ፡ ረቂቅ ጻፊ።
አርበተበተ፡ አንተባተበ፡ ረ በተ ።
አርበተበተ፡ አፍን እንተባተበ እጅን ኣንቀጠቀጠ ።
አርበኛ፡ ተጋዳይ ፥ —ዐርበኛ ።
አርበደበደ፡ አስፈራ ፥ —ረበደ ።
አርበደበደ፡ እስፈራ እንበደበደ እን ቀጠቀጠ ።
አርቢ (ዎች)፡ ያረባ/የሚያረባ ።ከ በት አርቢ እንዲሉ ።
አርባ (አርብዓ ፵ ረብዐ)፡ የቍጥር ስም፡ አራት ዐሥር፡ ወይም ዐሥር ጊዜ አራት፡ ኹለት ጊዜ ኻያ ። ኻያና ኻያ አርባ እንዲሉ ።
አርባ ስምንት፡ በሙግት ላይ ነገርን ያጣረሰ (ያቃወሰ) የሚከፍለው ዕዳ አራት ብር ።
አርባ አንድ (፵፩)፡ እርባና አንድ ።
አርባ፡ የች አርባኛ ቀን፡ ተዝካር የሚወጣበት፡ ኑዛዜ የሚፈስበት፡ ሐዘን የሚቀርበት ። (ተረት)፡ ከሜዳ ወዲያ ፈረስ፡ ካርባ ወዲያ ቄስ ።
አርባ ጦም (ጾመ አርብዓ)፡ ያርባ ቀን ጦም፡ ሑዳዴ ።
አርባ ፈሪ፡ ሠላሳ ዘጠኝ (፴፱) ። አርባ ሲመላ አንድ የጐደለው ።
አርባኛ (አርብዓዊ)፡ አራተኛ ዐሥር፡ ወይም ሌላ ነገር አራትንና ኹለተኛውን ። ረባ እይ ።
አርባዕቱ እንስሳ፡ አራት እንስሶች የግዜርን መንበር ተሸካሞች ። ገጽን እይ ።
አርባዕት (ቱ)፡ (ረብዐ)፡ የቍጥር ስም፡ ኣራት በግእዝ ።
አርባዕት፡ የዜማ ስም፡ ባ፭ኛው መዝሙር ቃልየ እያለ የሚዠምር ዜማ ።
አርባጫ (ጮች)፡ የምሥጥ ቤት፡ ኩይሳ ያፈር ቍልል ።
አርቤ፡ ያርበኛ ወገን ፥ —ዐርቤ ።
አርቲ ቡርቲ ቅባጥርሴ ። ቡርቲን እይ ።
አርነት፡ ነጻነት፡ ዐርነት ።
አርና፡ ጭነት ጭቈና፡ መጫን ማጥበቅ መጨቈን ። ይህ ነገር ያርና ነው ።
አርኖ፡ የተራራ ስም፡ በበጌምድር የሚገኝ ተራራ ። አርኖ ጋርኖ እንዲሉ ።
አርእስተ ነገር፡ ሥረ ነገር ።
አርእስት፡ ራሶች ርእስ ።
አርእስት፡ ራሶች/አለቆች ("(ግእዝ)") ።
አርእስት፡ በመጽሐፍ ገጽ ላይ የተ ጻፈ ቃል ።
አርእስት፡ አባት/ዘር ("መግደል ማ ወቅ ") ።
አርእስት፡ የመጽሐፍ ገጽ ራስ ("በኅዳግ ኣንጻር ያለ ") ።"ኣርእስት ባማርኛ ብዛት እንደሌለው አስተውል" ።
አርእስት፡ የቃል/የንባብ መነሻ/መዠመሪያ ።"ኦሪት ዘፍጥረት ወንጌል ዘማቴዎስ ራእየ ዮሐንስ ሞአ አንበሳ እንደ ማለት ያለ ኹሉ" ።
አርከፈከፈ፡ አረበረበ ፥ —(ረከፈ) ።
አርከፍካፊ፡ ያርከፈከፈ፡ የሚያርከፈክፍ ረብራቢ።
አርኪ፡ ያረካ፡ የሚያረካ።
አርካሽ፡ ያረከሰ፡ የሚያረክስ፡ ነውረኛ ሻር።
አርካታ፡ ረኸጥ መጥፎ ሴት ሞያ ቢስ ምጣድ የለሽ ቂል ሰነፍ ።
አርኳታ፡ ጥዳት አልባ ዐር ኳታ ።
አርዋ፡ ሰማያዊ የሐር ግምጃ ወይም ሐር ።
አርዋጺ፡ የድጓ ምልክት - የድጓ (የቤተ ክርስቲያን መዝሙር) ምልክት።
አርዌ ብርት፡ ሙሴ የሠራው የንሓስ እባብ፡ በግእዝ ኔስታሊ ይባላል ።
አርዌ፡ አውሬ ።
አርዛሚ፡ ያረዘመ/የሚያረዝም፡ ኣብላዩ - ያረዘመ/የሚያረዝም፡ በላዩ ላይ ያለ።
አርዝ (ዞች)፡ የንጨት ስም፡ እንደ ጥድና እንደ ዝግባ ያለ የሊባኖስ ዛፍ ።
አርዝም አደንድን፡ የመድኅኒት ስም፡ እስኪትን የሚያረዝምና የሚያደነድን - የመድኃኒት ስም፡ እስትንፋስን የሚያረዝምና የሚያጠናክር። በዚህ ዕዕ ራስ አሉላ ጥርሱን ሲፍቅ ወደ ሆዱ ገብቶ ግደለው ይላል ያጢ ቲዎድሮስ ታሪክ - በዚህ... ራስ አሉላ ጥርሱን ሲነቅል ወደ ሆዱ ገብቶ ግደለው ይላል... የቴዎድሮስ ታሪክ።
አርያ፡ የነገድ ስም፡ በህንድ ነገር የነበረ ሕዝብ ። ፪ኛውን ዐራ እይ ።
አርያም፡ የሰማይ ስም፡ መጨረሻ ሰማይ ። ዘሩ በግእዝ ረዪም ሬመ ነው ።
አርያም፡ የዜማ ስም፡ ከአርባዕት ቀጥሎ የሚባል ዜማ፡ ቅዱስ ያሬድ በተመስጦ የደረሰው ።
አርዮሳዊ፡ የአርዮስ ወገን፡ በአርዮስ ሃይማኖት የሚያምን ከሓዲ ።
አርዮስ፡ የሰው ስም፡ ወልድ ፍጡር በመለኮቱ ብሎ የካደ የግብጥ ቄስ ። ከዚህ የተነሣ ክፉ ሰው አርዮስ ይባላል ።
አርዴም (ሞች)፡ መጥፎ ሰው፡ አርዳሚሳዊ ጣዖታዊ ።
አርድ፡ አንቀጥቅጥ፡ ሲያዩት የሚያንቀጠቅጥ (ልብሰ በቀል, ሞጣሕተ ግርማ) - አንቀጥቅጥ፡ ሲያዩት የሚያንቀጠቅጥ (የበቀል ልብስ, የግርማ ምልክት).
አርድእት፡ በ፲፪ቱ ሐዋርያትና ከ፸፪ቱ አርድእት ስም የተጻፈ ልብ ወለድ ያስማት የጸሎት መጽሐፍ።
አርድእት፡ የጌታችን ተከታዮች ፲፪ና ፸፪ ሰዎች ሌሎችም ክርስቲያኖች። አርድእት የቤተ ክርስቲያን ሰበሰብ ደገች።
አርጂ፡ የሚያረጅ አረጀ።
አርጂ፡ ያረዳ፣ የሚያረዳ፣ እከሌ ሞተ ባይ።
አርጃኖ (ዐንጉግ)፡ ገላው ሻካራና ቅርፍርፍ የኾነ ያዞ ወይም የገበሎ ዐይነት አውሬ ። (ዘሌ ፲፩ ፥ ፴) ። አርጃኖ ገላ እንዲሉ ። ሲበዛ አርጃኖዎች ይላል ።
አርጃኖ፡ ጨው የሚገኝበት፡ ያዳል (የጥ ልጣል) አገር፡ የትግሬ በረሓ ።
አርጆ፡ በወለጋ ክፍል የሚገኝ አገር ።
አርገበገበ፡ አንዘፈዘፈ ፥ —ረገበ ።
አርገበገበ፡ አንዘፈዘፈ / ወዘወዘ / ነቀነቀ / አንቀጠቀጠ ("እጅን ክንፍን ሸፋሽፍትን") - "ነጠበ ብለኸ አንጠበጠበን ተመልከት"
አርገብጋቢ፡ ያርገበበ / የሚያርገበግብ ("አንዘፍዛፊ")
አርገደገደ፡ አንገደገደ ፥ —ረገደ ።
አርገደገደ፡ እንገደገደ / አፍገመገመ
አርገፈገፈ፡ በአፉ ይዞ ወዘወዘ ("ለማራገፍ ለመብላት" - ለማራገፍ ወይም ለመብላት).
አርገፈገፈ፡ ወዘወዘ ፥ —ረገፈ ።
አርጊ፡ ያረጋ/የሚያረጋ ("ርጎ የሚያዘጋጅ ") ።
አርጋቢ፡ ያረገበ / የሚያረግብ ("አላሲአጕራቢ")
አርጋኖ፡ የመጽሐፍ ስም፡ የጸሎት መጽሐፍ፡ የኢትዮጵያ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ከቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሱ በመቤታችን ስም የደረሱት ።
አርጋኖ፡ የዜማና የዘፈን መሣሪያ ባለ፯ ረድፍ፡ ምልክቱ ኖት የሚባል፡ ሙዚቃ ።
አርጋኖዎች፡ ሙዚቆች፡ መጽሐፎች ።
አርጋው፡ የጦርነት ጊዜ ዐልቆ ሰላም ሲዠመር የተወለዱ ልጆች ።"አረጋሽ አርጋው ይባላሉ" ።
አርጋጅ፡ ያረገደ / የሚያረግድ ("ፋሪ ዘላይ") - "ያርጋጅ አናጓጅ" እንዲሉ
አርጋፊ፡ ያረገፈ/የሚያረግፍ ።
አርግፍ፡ ጠይብ ቡዳ ። "ወፍ እርግፍ" እንዲሉ ።
አርጎባ፡ ያገር ስም፡ ባዳል አዋሳኝ ያለ አገር ። ሕዝቦቹም አርጎቦች ይባላሉ ።
አርጎቤ፡ አርጎባዊ፡ ያርጎባ ተወላጅ፡ ያርጎባ ቋንቋ፡ ግእዝን ትግሬን የመሰለ ። ኣርጎቦችና ሐረርጌዎች ከትግሬ የመጡት አንድ ጊዜ ነው ይባላል ።
አርጣቢ፡ ያረጠበ፡ የሚያረጥብ፡ አለምል።
አርጣጣ፡ ሰነፍ፡ ውዝፍ ሴት ከተቀመጠችበት የማትነሣ። (ተረት) እህል ከዘባጣ ልጅ ካርጣጣ።
አርጣጣ፡ ውዝፍ ረጠጠ ።
አርጩሜ፡ ለመግረፊያ መሸምተሪያ ለበቅ አሽንቋጦ ።
አርጴ፡ ጣብ ።
አርፋጃ፡ ረፋድ።
አርፋጅ፡ ያረፈደ፡ የሚያረፍድ። (ተረት) ቤተ ክሲያን ለማላጅ ገበያ ላርፋጅ።
አሮጊት (አረጊት)፡ ከ፷ ዓመት በላይ ያለች ባልቴት ። ሲበዛ አሮጊቶች ያሠኛል ። መጽሐፍ ግን ባሮጊት ፈንታ ሽማግሊት ይላል ። (፩ጢሞ ፭ - ፪ ። ቲቶ ፪ - ፫) ።
አሮጊቷ፡ ያች አሮጊት ።
አሮጋግት፡ አሮጊቶች ።
አሮጋግቶች፡ ዝኒ ከማሁ፡ የቧልት አነጋገር ። (ተረት)፡ ስምሽ ማነው፡ ላገር አይመች፡ ማን አወጣልሽ፡ አሮጋግቶች ።
አሮጌ (አረግ)፡ ሽማግሌ ሸበቶ ፸ ዓመት ያለፈው ዕድሜ የጠኀበ ለሞት የቀረበ ። ትግሮች ግን አረጊት ይሉታል፡ ጠበልን እይ ። ሲበዛ አሮጌዎች ይላል ።
አሮጌ ቤተ ክሲያን፡ የቤተ ክሲያን ባድማ ጠፍ ባዶ ።
አሮጌ ውሻ፡ እቤት የዋለ ያረፈቀ፡ መጮኸ ያቃተው ውሻ ።
አሮጌነት፡ አሮጌ መኾን፡ ሽማግሌነት ።
አሮጌው፡ ያ አሮጊ ሽማግሌው ።
አሮጌዪቱ፡ የቀድሞዪቱ የጥንቲቱ ኦሪት ። (፩ዮሐ ፪ ፥ ፯) ።
አሮጠ (አሮጸ)፡ አበረረ, አፈጠነ - አሮጠ፡ አፋጠነ።
አሯጭ፡ ያሮጠ/የሚያሮጥ፡ እብራሪ - ያሮጠ/የሚያሮጥ፡ ዙሪያውን የሚዞር በሬ (ባማሬ አንጻር ዳር ዳሩን የሚዞር በሬ፡ እሱ ሲሮጥ ሌሎቹ ይሮጣሉና፡ በዚህ ምክንያት እሯጭ ተባለ) - በጋጣ ውስጥ ዳር ዳሩን የሚዞር በሬ፡ እሱ ሲሮጥ ሌሎቹ ይሮጣሉ። (ማረ)፡ ብለኸ አማረን እይ - በጋጣ ውስጥ ያለውን በሬ ተመልከት።
አሯጭነት፡ እሯጭ መኾን - ሯጭ መሆን።
አሯጮች (አርዋጽያን)፡ የሚያሮጡ - የሚያሮጡ።
አሸ፡ ቍርስ በላ ("ደኅና አውለኝ" አለ) ።
አሸ፡ በቁሙ ፥ —ዐሸ ።
አሸ አገነፈለ፡ (ሸ) ።
አሸለ (አኪል ኣከለ)፡ እከለ ጨመረ፡ አቀላ አነጣ፡ መጠነ ለካ ከነዳ ቀጠበ ።
አሸለለ፡ ሽለላ አስደረገ ።
አሸለለ፡ አስወሰወሰ አስቆረበ አሰፋ ።
አሸለመ፡ ሽልማት አሰጠ ።
አሸለመ፡ አሣለ አስመሰለ (ምስል አሠራ አስነቀሰ) ።
አሸለቃቀቅ፡ አላላጥ መሸልቀቅ ።
አሸለበ፡ አንቀላፋ ፥ —ሸለበ ።
አሸለበ፡ ዠበብ አደረገ (አንቀላፋ አንጐ...ላቸ) ።
አሸለተ (ቢር)፡ አዳነ አሳመረ ።
አሸለተ (ተገብሮ)፡ ዳነ አማረ አሸበ...ረቀ (ታሞ የነበረ ሰው) ። "አሸለተን ዳነ ብሎ መተርጐም የስሕተት ልማድ ነው"።
አሸለተ (ኣስደራጊ)፡ አስቈረጠ (የበግን ጠጕር) ። መጽሐፍ ግን "አስሸለተ" ይላል እያሠኝም (ዘፍ. ፴፩፡ ፲፱፡ ፪ሳሙ. ፲፫፡ ፳፫-፳፬) ። ኣሸለተ፡ አስረበ አስላገ ሹል አስደረገ (ሽብልቅን ውሻልን) ።
አሸለገ፡ አስገመተ ። (በቀድሞ ዘመን ባለ ምድር የሚከፍለው ሲያጣ ልጁን አሸልጎ ለመንግሥት ይሰጥ ነበር) ።
አሸላለመ፡ አሣሣለ አጊያጊያጠ ።
አሸላለም፡ አሣሣል መሸለም ።
አሸላለብ፡ የዐይን አከዳዶን ማሸለብ ።
አሸላለተ፡ መጠራረበ አላላ ።
አሸላለገ፡ አገማገመ አገማመተ ።
አሸላለፍ፡ አሸነጋገል መሸለፍ ።
አሸላል፡ የሽለላ አባባል መሸለል ።
አሸላሚ፡ ያሸለመ/የሚያሸልም (አለቃ ሥራ) ።
አሸላች፡ ያሸለተ/የሚያሸልት (አስቈ...ራም) ።
አሸላይ፡ ያሸለለ/የሚሸልል (እስቶራቢ) ።
አሸላጊ፡ ያሸለገ/የሚያሸልግ (አስገማች) ።
አሸመ፡ ጐነጐነ፡ ዐሸመ ።
አሸመቀ (አድራጊ)፡ ደበቀ ከለለ ራ...ሱን ።
አሸመቀ፡ ደበቀ ።
አሸመቀቀ፡ አሳጠረ (አስጠበበ አስጨ...መደደ) ።
አሸመቃቀቅ፡ ኦሳሳባ አመዳደድ መሸምቀቅ ።
አሸመተ፡ አስገዛ አጄጠ አስለወጠ ።
አሸመታተር፡ ኣሸነቋቈጥ መሸምተር ።
አሸመገለ፡ ሽማግሌ አደረገ (አስረጀ ኣሸበተ) ።
አሸመጋገል፡ አረጃጀት መሸምገል ።
አሸመጠጠ፡ አሸለመ አስደጐሰ ።
አሸመጠጠ፡ አዠመገገ አስፈተለ ።
አሸመጠጠ፡ ዐጥር አሳጠረ በማቀ...ሰብ ።
አሸመጣጠጥ፡ ዝመግ መሸምጠጥ ።
አሸማመቀ፡ አደፋፈጠ ።
አሸማመቅ፡ አደፋፈጥ መሸመቅ ።
አሸማመተ፡ አገዛዛ እለዋወጠ ።
አሸማመት፡ አገዛዝ መሸመት ።
አሸማሸመ፡ አከራተፈ አፋፊ ።
አሸማሸም፡ አፈጫጨት መሸምሸም ።
አሸማቀቀ፡ አሳሳበ አጣበበ አማ...
አሸማቂ፡ ያሸመቀ/የሚያሸምቅ (አስደ...ፋጭ እስደባቂ) ።
አሸማቂ፡ ያሸመቀ/የሚያሸምቅ (ደባቂ ወጥ) ።
አሸማች፡ ያሸመተ/የሚያሸምት (አስ...ገዥ) ።
አሸማጠጠ፡ አስተጣጠረ አሳሳበ ሽም...ጥን ።
አሸማጠጠ፡ ኣዠማገገ ኣፋተለ ።
አሸማጣጭ፡ ያሸማጠጠ/የሚያሸማጥጥ (የስምጥ ረዳት አማጋ ኣፋታይ) ።
አሸምጣጭ፡ ያሸመጠጠ/የሚያሸመጥጥ (አዠም ኣስፈታይ) ።
አሸረሞጠ፡ ሸርሙጣ አደረገ ።
አሸረሞጠ፡ አሠረጓጐደ ።
አሸረሞጠ፡ ኣመንዝራ አስደረገ ።
አሸረሞጥ፡ አቀነዛዘር መሸርሞጥ ።
አሸረረ (አስረረ)፡ እዠርባ ላይ ኣወጣ ዐዘለ (እንቡቡ ኣለ) ።
አሸረቋቈጥ፡ አቀለጣጠፍ መሸርቈጥ ።
አሸረበ፡ አስደበለ አስጠሞረ ።
አሸረከተ፡ አስቀደደ አዘረከተ (አስደ...ራጊ) ።
አሸረከተ፡ አጠፋ በደለ (እድራጊ) ።
አሸረካከተ፡ አቀዳደደ አዘረካከተ ።
አሸረካከት፡ ኣቀዳደድ መሸርከት ።
አሸረደመ፡ አቈረጠመ እበላ ።
አሸረገደ፡ አጠፋ አጐደለ አከፋ በደለ ። "ምን ኣሸረገድኩ" እንዲል ባላገር ።
አሸረጠ፡ አገለደመ ፥ —(ሸረጠ) ።
አሸረፈ፡ አስመነዘረ ።
አሸረፈ፡ አስነቀለ አስመዘዘ ።
አሸረፈ፡ ከመንገድ ወጥቶ ወደ ጐን ኼደ ።
አሸራሞጠ፡ አሸሸ አጓደለ ሠረጐደ ።
አሸራረጥ፡ አገለዳደም ማሸረጥ ።
አሸራረፈ፡ አሰባበረ አቈራረሰ ።
አሸራረፍ፡ አቈራረስ መሽረፍ ።
አሸራሸ፡ አደላደለ ፥ —(ሸረሸ) ።
አሸራሸ፡ አደላደለ አመቻቸ አንዘራ...ፈጠ ።
አሸራሸረ፡ ኣበራበረ አፈራፈረ አፋረሰ ።
አሸራሸረ፡ ኣጓደለ አቃለለ አፈፈገ ።
አሸራሸር
አሸራሻሪ፡ ያሸራሸረ/የሚያሸራሽር (አጓዳይ ኣቃላይ) ።
አሸራቢ፡ ያሸረበ/የሚያሸርብ ።
አሸራከተ፡ አቃደደ አዘራከተ ።
አሸራጭ (ጮች)፡ ያሸረጠ/የሚያሸ...ርጥ (አገልዳሚ) ።
አሸራጭ፡ ያሸራሞጠ/የሚያሸራሙጥ ።
አሸራፊ፡ ያሸረፈ/የሚያሸርፍ (አስቈራሽ አስመንዛሪ) ።
አሸርዳሚ፡ ያሸረደመ/የሚያሸረድም (አቈርጣሚ) ።
አሸርድማ፡ ሆዳም (ሴት - "ገረድመ እገረደመ" ብለሽ "አፃርድማን" እይ) ።
አሸሸ (አስደራጊ)፡ አስፈገፈገ ፊት አስመለሰ አስበረረ አስሮጠ አስፈረጠጠ አስኰበለለ (ዕብ. ፲፩፡ ፴፬) ።
አሸሸ (አድራጊ)፡ አራቀ ወደ አኰ...በለለ (ዘፀ. ፱፡ ፳) ።
አሸሸ፡ አደረቀ (ንሽን) ።
አሸሸ፡ አጐደለ/አበላሸ/አደረቀ።
አሸሸገ፡ አስደፈነ አሰወረ አስደበቀ ።
አሸሻሸግ፡ አደባበቅ መሸሸግ ።
አሸሻጊ፡ ያሽሽገ/የሚያሸሽግ (አስደባቂ) ።
አሸቀሸቀ፡ ተነቃነቀ ተንጠለጠለ (አዘበዘበ አረገዘ - ግንቡ ካቡ - እርግጠኛው ትርጓሜ ግን "ነቀነቀ አንጠለጠለ" ነው) ።
አሸቀሸቀ፡ አዘበዘበ ሸቀሸቀ ።
አሸቀጠ፡ ሸቀጥ አሺጠ አስለወጠ ።
አሸቃሸቅ፡ ኣወጋግ መሸቅሸቅ ።
አሸቃቀጥ፡ አለዋወጥ መሸቀጥ ።
አሸቈረረ፡ አስጠየፈ አሠቀቀ ።
አሸቈረረ፡ ዐፋር አደረገ ።
አሸቅሻቂ፡ ያሸቀሸቀ/የሚያሸቀሽቅ ።
አሸበለለ፡ አስጠቀለለ ።
አሸበላለል፡ አጠቀላለል፡ መሸብለል ።
አሸበላለቅ፡ አወጋግ፡ መሸብለቅ ።
አሸበረ፡ በጠበጠ ፥ —(ሸበረ) ።
አሸበረቀ (አንጸብረቀ)፡ አጠራ/አበራ/አሳመረ/አብረቀረቀ/አወለወለ ።
አሸበረቀ፡ አበራ ፥ —ሸበረቀ ።
አሸበረከ፡ አበረከ/አንበረከከ ።
አሸበሸበ (አስደራጊ)፡ አሸነሸነ (ሽብ...ሽቦ አሰፋ) ።
አሸበሸበ (አድራጊ)፡ ጨፈረ/አረገደ/ተነቃነቀ/ተወዛወዘ (፬ነገ. ፫፡ ፴) ።
አሸበበ፡ አሁጭን አፍን አስጠለፈ አሳሰረ ።
አሸበተ፡ ጠጕርን አነጣ ነጭ አደረገ ።
አሸበደደ፡ አጐነበሰ/አጐበደደ ።
አሸባለለ፡ አጠቃለለ ።
አሸባሪ (ሮች)፡ ያሸበረ/የሚያሸብር (አዋኪ በጥባጭ) ።
አሸባሪነት፡ አሸባሪ መኾን (አዋኪነት) ።
አሸባሸበ፡ አሸናሸነ ።
አሸባሸብ፡ አሸናሸን፡ መሸንሸን ።
አሸባበር፡ አስተዋወክ፡ ማሸበር ።
አሸባበት፡ አነጣጥ፡ መሸበት ።
አሸብር፡ አሸበር (የሰው ስም - በጦርነት ጊዜ የተወለደ ልጅ "አሸብር" ይባላል) ።
አሸብሻቢ (ዎች)፡ ያሸበሸበ/የሚያ...
አሸቦ፡ ጨው ዐሸቦ ።
አሸተ (አሥወየ)፡ አፈራ ኣበሰለ እደ...ረሰ ።
አሸተተ (ዘፍ. ፳፯፡ ፳፯)፡ ባፍንጫ ሳበ ማገ አነፈነፈ (አድራጊ) ። ("ተረት - ዐይጥ ለሞቷ የድመት አፍንጫ ታሸታለች") ።
አሸተተ፡ ኣሽት አለ አሳበ አስማተ (አስደራጊ) ።
አሸታተር፡ አሸላለም መሸተር ።
አሸታተት፡ በትንፋሽ አሳሳብ ማሽ...ተት ።
አሸነ፡ ከቀፎ ወደ ውጭ አጣ (ነፋስኣስቀበለ ንብ እውራውን) ።
አሸነ፡ የሽንት ውሃ አስፈሰሰ አስፈራ ።
አሸነሸነ (አስደራጊ)፡ አሸበሸበ፪ አሠነ...ጠቀ ።
አሸነሸነ (አድራጊ)፡ ሸነሸነ አጠጋጋ ታጠቀ (ቀሚስን በመቀነት) ።
አሸነቀጠ፡ ኰሰተረ ሰበሰበ (ባጪር አለ...በሰ አስታጠቀ አቀለጠፈ ቀልጣፋ አደረገ ልብስን ሰውነትን) ።
አሸነቃቀር፡ አቀናነፍ መሸንቀር ።
አሸነቃቀጥ፡ አኰሰታተር መሸንቀጥ ።
አሸነቈረ፡ አስበሳ አስነደለ አስቀደደ ።
አሸነቈጠ፡ ኣስገረፈ ኣስመታ ።
አሸነቋቈር፡ አበሳስ መሸንቈር ።
አሸነቋቈጥ፡ አገራረፍ መሸንቈጥ ።
አሸነታተር፡ አበጣጥ መሸንተር ።
አሸነካከፍ፡ አስተጣጠፍ መሸንከፍ ።
አሸነደረ፡ አንሸዋረረ ፥ —ሸነደረ ።
አሸነዳደር፡ አዘዋወር ማሸንደር ።
አሸነፈ፡ ድል አደረገ ፥ (ሸ ነፈ) ።
አሸነፈጠ፡ አደገደገ (የጨዋ የማይምን) ።
አሸነፈጠ፡ ዘቅዝቆ ታጠቀ (ሸ ነፈጠ) ።
አሸነፋፈጥ፡ አዘቃዘቅ አስተጣጠቅ ማሽንፈጥ ።
አሸናሸነ፡ አሸባሸበ አሠናጠቀ ።
አሸናሸን፡ አሸባሸብ መሸንሸን ።
አሸናነዋ፡ የሽንጥ አወጣጥ መሸነጥ ።
አሸናነፈ፡ ድል አነሣሣ አረታታ ።
አሸናነፍ፡ አረታት ማሸነፍ ።
አሸናከፈ፡ አስተጣጠፈ አኰራተመ አስተሳሰረ ።
አሸናፊ (ፎች)፡ ያሸነፈ/የሚያሸንፍ (ድል አድራጊ ጐበዝ) ።
አሸናፊ፡ የሰው ስም ።
አሸናፊነት፡ አሸናፊ መኾን ።
አሸን ጕላስ፡ ዐሸን ።
አሸንሻኝ፡ ሸንሻኝ ።
አሸንዳ (ዶች)፡ (ሰነዳ)፡ በውስጡ ውሃ ዐረቄ ጠጅ የሚወርድበት ደረቅ ቍልቋል ቀርክሓ መቃ ቦምባ ።
አሸንዳሪ፡ ያሸነደረ/የሚያሸነድር ።
አሸንፋጭ፡ ያሸነፈጠ/የሚያሸነፍጥ (ዘቅዝቆ ታጣቂ) ።
አሸኘ፡ ሸኚ ሰጠ ።
አሸኛኘ፡ አሰነባበተ ።
አሸኛኘት፡ ወደ መንገድ ኣመራር...መሸኘት ።
አሸከ 1፡ አሸደሽደ እዘረዘረ ።
አሸከመ፡ ራስ ላይ አደረገ፡ (ሸ ከመ) ።
አሸከመ፡ ክፉኛ ሰደበ ።
አሸከካ፡ እስወቀጠ ።
አሸካሚ (ሞች)፡ ያሸከመ/የሚያሸክም (ነሐ. ፬፡ ፲፯) ።
አሸካሚ፡ ሰዳቢ ።
አሸካሚነት፡ አሸካሚ መኾን ።
አሸካሸከ፡ አሸዳሸደ ።
አሸካሸከ፡ አዋቀጠ ።
አሸካሸክ፡ ኣወቃቀጥ/አሸዳሸድ/መሸ...ክሸክ ።
አሸካከመ፡ ሸክምን አያያዘ አስተጋገዘ አረዳዳ አወሳሰደ አስተዛዘለ ።
አሸካከረ፡ ሆድ ለሆድ አቃቃረ አቀ...ያየመ ።
አሸካከር፡ እንደ አሽክርት መኾን መ...ሻከር ።
አሸካካሚ፡ ያሸካከመ/የሚያሸካክም (አወ...ሳሳጅ) ።
አሸኳኰት፡ አጸፋፍ፡ መሻኰት ።
አሸዋ (ዎች)፡ ጠጠር ጅጀት ታናናሽ ጥቃቅን የደንጊያ የጭንጫ ቅንጣት እንደ ጤፍ ምርት እንደ ክርትፍ ዶቄት ያለ፡ በወንዝ ዳር በባሕር ጠረፍ በምድረ በዳ በበረሓ የሚገኝ፡ ከኖራ ጋራ ለግንብ የሚኾን ። (ዕብ ፲፩ ፥ ፲፪) ። አሸዋና ኆጻ ባማርኛ ፪ ሲኾኑ በግእዝ አንድ ናቸው ። ኆጻን ተመልከት ።
አሸዋም፡ አሸዋ የበዛበት ስፍራ ባለ ።
አሸያየት፡ አጣጣል፡ መሸየት ።
አሸያየጥ፡ አሻሻጥ አለዋወጥ መሼጥ ። በ"ሐ"ና በ"የ" ምክንያት የሻጠና የሼ ተደራራጊና ኣደራራጊ አንቀጽ መግጠሙን አስተውል ።
አሸደሸደ፡ እስወሰወሰ/አሸከሸከ/አሸ...ለለ ።
አሸዳሸደ፡ አወሳወሰ ።
አሸዳሸድ፡ አወሳወስ፡ መሸድሸድ ።
አሸገ፡ ዘጋ፡ ዐተመ፡ ደፈነ፡ ላከከ፡ መረገ እንዳይከፈት አደረገ፡ የቤት የሣጥን የመዝገብ የደብዳቤ ።
አሸገሸገ፡ አፈገፈገ ፥ ሸገሸገ ።
አሸገነ፡ አሳመረ/ኣስዋበ/አቈነዠ ።
አሸጋሸገ፡ አፈጋፈገ/አራራቀ/አቀራረበ/አጠጋጋ ።
አሸጋሸግ፡ አፈጋፈግ፡ ማሸግሽግ ።
አሸጋሻጊ፡ ያሸጋሸገ/የሚያሸጋሽግ (ኣፈጋፋጊ አራራቂ አጠጋጊ አቀራራቢ) ።
አሸጋገረ፡ አስተላለፈ (አደረሰ - "እንኳዕ ከዘመን እዘመን አሸጋገረዎ" እንዲሉ) ።
አሸጋገር፡ የውሃ ላይ አካኼድ፡ መሻ...ገር ።
አሸጋገት፡ አበሳበስ፡ መሻጋት ።
አሸጋገነ፡ አሰማመረ ።
አሸጋገን፡ ኣቈነዣዠት፡ መሽገን ።
አሸጋጋሪ፡ ተራዛሚ መድፍ (ከወንዝ ባሻገር የሚመታ) ።
አሸጋጋሪ፡ ያሸጋገረ/የሚያሸጋግር (አስ...ተላላፊ) ።
አሸግሻጊ፡ ያሸገሸገ/የሚያሸግሽግ (ኣፈ...ግፋጊ) ።
አሸጐረ፡ አስቀረቀረ/አስደነቀረ ።
አሸጓሪ፡ ያሸጐረ/የሚያሸጕር (አስቀ...ርቃሪ) ።
አሸጓጐር፡ አቀራቀር፡ መሸጐር ።
አሸጓጐብ፡ ኣቀላለስ፡ መሸጐብ ።
አሸፈተ፡ አስከዳ ሽፍታ አስነሣ ።
አሸፈነ፡ አስለበሰ አስከለለ አስጋረደ...አስጨፈነ አስከደነ ።
አሸፈጠ፡ አስካደ አስከዳ አሳበለ (ክፉ አሳሰበ አስነሸጠ) ።
አሸፋሸፍ፡ አስተድ መሻፍሸፍ ።
አሸፋች፡ ያሸፈተ/የሚያሸፍት (እስከጂ) ።
አሸፋጭ፡ ያሸፈጠ/የሚያሸፍጥ (አሳባይ) ።
አሸፋፈት፡ አከዳድ መሸፈት ።
አሸፋፈን፡ አከላለል መሸፈን ።
አሸፋፈድ፡ አሠያየት መሻፈድ ።
አሸፋፈጠ፡ አከዳዳ አካካደ ።
አሸፋፈጥ፡ አከዳድ መሸፈጥ ።
አሹለከለከ፡ ኣለመንገድ በሣር በቅጠል መካከል አስኬደ ።
አሹራ፡ ታሥር አንድ ፥ —ዐሹራ ።
አሹቅ፡ ተቈልቶ የተቀቀለ ሾቀ ።
አሹቅ፡ ተቈልቶ የፈላ የተቀቀለ ያበባ...እኸል (እየተጠረጠረና ሳይጠረጠር የሚበላ) ።
አሹቅ፡ ትእዛዝ አንቀጽ (ለቅርብ ወንድ የሚነገር) ።
አሻ፡ አስፈለገ ፥ —ሻ፡ ሻየ ።
አሻ፡ አስፈለገ/አስፈቀደ/አሠኘ (ነሐ. ፱፡ ፳፩፡ ማር. ፲፡ ፳፩፡ ቲቶ ፫፡ ፲፬) ። (ተረት)፡ "ጌታ ትኾን እንዳሻኸ ትናገር"።
አሻለ (አስሻለ)፡ አሻረ አዳነ (አስዳነ) ጤና ሰጠ (አሰጠ) ።
አሻለተ፡ አቋረጠ አጣረበ ።
አሻለገ፡ አስተሳሰበ አሳላ አጋመተ ።
አሻል (ሎች)፡ ተጨማሪ ድር፡ በኋላ የተደራ ።
አሻል፡ ቀይና ነጭ ጨው ዐሸቦ፡ በዋንጫ ዐይነት በተሠራ ባለመክደኛ ገሣ ።
አሻል፡ በመረሬና በቀይ ዐፈር መካከል ያለ አቦልሴ መሬት ዕይር፡ ለስላሳ ምድር ።
አሻል፡ ኣራት እግሩ ነጭ የኾነ ቀይ ወይም ሌላ ዐይነት ፈረስ፡ በጋልኛ ሙጣ ይባላል ።
አሻልማ (አሻላዊ)፡ ያሻል ዐይነት፡ ጥቍር ወይም ቀይ በሬ ፍየል በግ ባራት እግሩ ፍ ንጣት ያለበት የተጨመረበት፡ ድሩን ፈረሱን ጨዉን የሚመስል ባለአሻል ።
አሻመቀ፡ አዳፈጠ ።
አሻመተ፡ አጋዛ አላወጠ ።
አሻመደ፡ ዐኘከ ፪ (ሻመደ) ።
አሻሚ፡ ያሻማ/የሚያሻማ (አሚ - የሚያሽም ዐሸመ) ።
አሻማ (አስተማሠጠ)፡ አናጠቃ አቃማ ጋራ ኣፋለመ ("ለኒ ነገረ ለኔ ነገረ እሠኛኘ የምስክርን ቃል") ።
አሻማ፡ አናጠቀ ፥ —ሻማ ።
አሻማጅ፡ ያሻመደ/የሚያሻምድ (አጋሰስ ምስንጅር ወደል ጋዝ) ።
አሻረ (አስዐረ)፡ አስጠፋ አስፈታ...ኣስፈረሰ ።
አሻረ (አሥዐረ)፡ አዳነ ፈወሰ ።
አሻረ፡ ሹመትን አሶሰደ (ማዕርግን አስገፈፈ) ።
አሻረ፡ ኮሶን ገደለ አስወጣ ቀና ።
አሻረበ፡ አጋመደ ።
አሻረከ፡ አወዳጄ አስተባበረ እጋጠመ ።
አሻረፈ፡ አመናዘረ ።
አሻረፈ፡ አሳበረ አቋረሰ ።
አሻሪ (አሥዓሪ)፡ ያሻረ/የሚያሽር...አዳኝ ፈዋሽ ።
አሻሪ (አስዓሪ)፡ ያሻረ/የሚያሽር...ግፍ (አድልዎ ድኻ መበደል ፍርድ ማጕደል) ።
አሻራ (ዎች) (አሠር)፡ አንድነት የተያያዘ የተሳሰረ የተጠመዘዘ የቍንጮ ያ ጠጕር፡ ምልክት እምር ። ዐረብ አሸረ ብሎ አመለከተ ይላልና፡ አሻራ ማለት ከዚህ የወጣ ነው ።
አሻራ ቢስ፡ ዕድለ ገደ ሀብተ ቢስ፡ አሻራው በግንባሩና በማዥራቱ የሚታይ፡ ዘመዱ ወገኑ ዐልቆ ብቻውን የቀረ ። ይህ ኹሉ የጠንቋይ ባህል ነው ።
አሻራ፡ የውስጥ እጅ ጭረት ። ጠነቈለን እይ ።
አሻራኪ፡ ያሻረከ/የሚያሻርክ (አስተ...ባባሪ) ።
አሻራፊ፡ ያሻረፈ/የሚያሻርፍ (አመና...ዛሪ) ።
አሻሮ፡ በቁሙ ፥ —ዐሻሮ ።
አሻሸገ፡ አዳበቀ ።
አሻሻ፡ ዐሾ Hዐሸ ።
አሻሻለ፡ አማረጠ ፥ —ሻለ ።
አሻሻለ፡ ዐደሰ ጠገነ አማረጠ ለዋወጠ (አለዋወጠ አሳመረ) ። "አሻሻለ" የአሻለ ድርብና አደራራጊ መኾኑን አስተውል ።
አሻሻል፡ አዳዳን መሻል ።
አሻሻር፡ አዳዳን መሻር ።
አሻሻት፡ አበሳሰል መሸት ።
አሻሻይ፡ ያሻሻለ/የሚያሻሽል (ዐዳሽ ጠጋኝ አሳማሪ) ።
አሻሻይነት፡ ዐዳሽነት/አሳማሪነት ።
አሻሻጠ (አስተሳሐወ)፡ አታከለ/አ
አሻሻጠ (አስተሣየጠ)፡ አገበያየ/አገዛዛ/ኣለዋወጠ (ለሸያጭና ለገዢ መካከለኛ ኾነ) ።
አሻሻጠ፡ አለዋወጠ (ሸየጠ) ።
አሻሻጥ፡ አሰካክ፡ መሻጥ ።
አሻሻጭ (ጮች)፡ ያሻሻጠ/የሚያሻ...ሽጥ (አዋዋይ ደላላ) ። ያሻሻጠች የምታሻሻጥ መልከ ቀና ሴት ።
አሻሻጭነት፡ አሻሻጭ መኾን ።
አሻቀበ (አንቃዕደወ)፡ ፊቱን አቀና አንጋጠጠ (ሰማይ ሰማይ ኣየ - ዘፍ. ፲፭፡ ፭) ።
አሻቀበ፡ አንጋጠጠ ፥ —ሸቀበ ።
አሻቅቦ፡ አቅንቶ ወደ ዳገት ደጋ ላይ ። "እረኛው ከብቶቹን አሻቅቦ ነዳ ወሰደ"።
አሻበ፡ አስመዘዘ/አስጠመዘዘ/አስጠመጠመ ።
አሻተረ፡ አጫረ (ሻተረ) ።
አሻተተ፡ አስተጣጠነ አጫጫስ አነ...ነፈ ።
አሻታሪ፡ ያሻተረ/የሚያሻትር (አጫሪ) ።
አሻታች፡ ያሻተተ/የሚያሻትት ።
አሻንጕሊት፡ የሕፃን ተምሳሊት ሸነገለ ።
አሻኝ፡ ያሸነ/የሚያሸን ።
አሻከመ፡ አናሣ አዋሰደ ።
አሻከረ፡ ሻካራ አደረገ ። (ተረት)፡ "ጥሬና ነገር ሆድ ያሻክር"።
አሻካሪ፡ ያሻከረ/የሚያሻክር ።
አሻኰተ፡ አጻፋ ሸኰተ ።
አሻኰተ፡ እጅ ለጅ እማታ አጻፋ አወ...ዳደረ አፈካከረ ።
አሻኳች
አሻዳ፡ እግረ ወልጋዳ ዐሻዳ ።
አሻገረ፡ ሙላትን አሳለፈ (ሻ ገረ) ።
አሻገረ፡ ወንዙን ሙላቱን ፈፋውን ፈረፈሩን ጕድባውን አሳለፈ (እጅ ይዞ ዐዝሎ ተሸክሞ - ዘፍ. ፴፪፡ ፳፫) ።
አሻገር (ሮች)፡ ማዶ መካከሉ ዠማ ኹኖ ግራና ቀኝ ያለ ስፍራ አንዱ ለአንዱ አሻገር ይባላል ። "ባሻገሩ ባሻገርኸ" እያለ ይዘረዝራል ።
አሻገተ፡ አበሰበሰ/ለወጠ/አበላሸ (ጉም አስመሰለ) ።
አሻጊ (ዎች)፡ ያሸገ የሚያሽግ፡ ዐታሚ ዘጊ ደፋኝ መራጊ ።
አሻጊነት፡ ዐታሚነት መራጊነት ።
አሻጋሪ፡ ያሻገረ/የሚያሻግር (ዋነተኛ) ።
አሻጋች፡ ያሻገተ/የሚያሻግት (አበስ...ባሽ) ።
አሻግር/ሬ፡ የሰው ስም ።
አሻጐጠ፡ አዋተፈ አዳበቀ ።
አሻጠ (አስሐጠ)፡ አስተከለ/እሰካ/ኣ...ስቆመ ።
አሻጠረ፡ አዋዋለ/አሰማማ (ሸያጭና ገዢን) ።
አሻፈረኝ፡ እንቢኝ (ሻፈረ) ።
አሻፈረኝ፡ እንቢኝ እንቢዮ (አልታዘዝም ልሠራው ላደርገው አልፈቅድም - "ግጥም" - እኔ እንቢ አሻፈረኝ እወጣለኹ ደጋ ዐንገቷ ይመስላል የጠንበለል ለጋ) ።
አሻፈተ፡ አካዳ (ሽፍታን ተከተለ) ።
አሻፈነ፡ አላበሰ ።
አሻፈደ፡ አሠየ አጐመዠ አሻ አስ...ፈለገ ።
አሻፈጠ፡ አካዳ ።
አሻፋጅ፡ ያሻፈደ/የሚያሻፍድ ።
አሼጠ፡ አስለወጠ ።
አሽ (አስ)፡ የማድረግና የማደራረግ ልማድ ። በለበለ አሽበለበለ፡ ቈጠቈጠ አሽቈጠቈጠ፡ ቀደመ አሽቀዳደመ ። ተሽን ተመልከት ።
አሽመደመደ፡ ፥ —አጥመለመለ ፥ —ሸ መደ ።
አሽመደመደ፡ አቅመደመደ እጥመለሙለ (ውህኛ እባብኛ ኣስኬደ) ።
አሽመደመደ،—፡ አጥመለመለ ሸ
አሽመድማጅ፡ ያሽመደመደ/የሚያሽመይምድ (አጥመልማይ ጓያ ምች ተስቦ) ።
አሽሙረኛ (ኞች)፡ ባሽሙር የሚሳደብ (ባላሽሙር አግቦኛ) ።
አሽሙር፡ ተዛዋሪ ነገር አግቦ ምፀት (ለበጣ ውሻን ሰድቦ ሰውን እንደ መስደብ ያለ) ።
አሽሙር፡ አግቦ ፥ —ሽሙር ።
አሽሙቅ (መቃይጽ)፡ የደባ የቅ...ጣት መሪያ ።
አሽማጠጠ፡ ሸረደደ ፥ —ጠጠ ።
አሽማጠጠ፡ ሸረደደ፡ በንቀት፡ ሰደበ፡ አቃለለ፡ ቀለደ፡ አለመጠ።
አሽማጣጭነት፡ አላጋጭነት።
አሽሞለሞለ፡ ፥ —አላዘገ ፥ —ሞለሞለ ።
አሽሞለሞለ፡ በውስጥ እጁ ወሸ/አላዘፃ አሞለለ ጭቃን፡ እጅ እግር አወጣ (የወፍ/የሕፃን ምሳሌ አበጀ እረኛው) ።
አሽቀረቀረ፡ ሸለመ አስጌጠ (ሰውነቱን በጌጥ ውስጥ አደረገ ") ።
አሽቀርቃሪ፡ ያሽቀረቀረ/የሚያሽቀረቅር (ሸላሚ እስኪያጭ ") ።
አሽቀነደረ፡ አስደሰተ አቀናጣ አዘለለ ።
አሽቀነጠረ፡ ወረወረ ፥ —(ቀነጠረ) ።
አሽቀንዳሪ፡ ያሽቀነደረ/የሚያሽቀነድር (አስደሳች ") ።
አሽቀንጣሪ፡ ያሽቀነጠረ/የሚያሽቀነጥር (ወርዋሪ ") ።
አሽቀዳደመ፡ አቀዳደመ አሯሯጠ (በ ሩጫ አበላለጠ ") ።
አሽቀዳዳሚ፡ አቀዳዳሚ (ያሽቀዳደመ/የሚያሽቀዳድም የሩጫ አዛዥ ") ።
አሽቃቃ፡ ክፉ ኾነ ።
አሽቃበበ፡ አሽጓበበ (ከነገር ለመግባት ዳር ዳር አለ አሽማጠጠ አሽጓበጠ ") ።
አሽቃበበ፡ አሽጓበጠ ቃበበ ።
አሽቃባቢ፡ ያሽቃበበ/የሚያሽቃብብ (አሽጓባቢ አሽጣጭ ") ።
አሽቃነጠ፡ አረገደ (ቃነጠ) ።
አሽቃናጭ (ጮች)፡ ያሽቃነጠ/የሚያ ሽቃንጥ (ዘፈን አድማቂ አትኮኝ የለሽ ") ።
አሽቃጠረ፡ ዘፈነ ገጠመ አወረደ ለፈለፈ ጮኸ ።
አሽቈለቈለ፡ አቈለቈለ አዘቀዘቀ ወደ ታች አስኬደ ።
አሽቈመቈመ፡ ፥ —ጠራ (ቈመ ቈመ) ።
አሽቈመቈመ፡ አልበላም አሠኘ ። "ገደረ" ብለኸ "አግደረደረን" እይ ።
አሽቈመቈመ፡ ጠራ ኑ ኑ አለ፡ አውራ ዶሮ ጫጩቶችን ምግብ ሊሰጣቸው ።
አሽቈጠቈጠ፡ አስፈራ ቈጠ ቈጠ ።
አሽቈጠቈጠ፡ አስፈራ አንቀጠቀጠ፡ እንዲለማመጡት አደረገ ።
አሽቈጥቋጭ፡ ያሽቈጠቈጠ/የሚያሽቈጥቍጥ (አስፈሪ ") ።
አሽቋንዳ፡ ሰውነተ ደረቅ ቈነ ደደ ።
አሽቋንዳ፡ ሰውነተ ደረቅ ክሥዲያም ።
አሽበለበለ (ባበለ)፡ ለመነ ደለለ አባበለ አቈላመጠ፡ ይስበረኝ ይሠንጥረኝ አለ ።
አሽበለበለ፡ አቈላመጠ ፥ —በለበለ ።
አሽበልባይ (ዮች)፡ ያሽበለበለ የሚያሽበልብል የሚደልል የሚያባብል የሚያቈላምጥ፡ አባባይ አቈላማጭ ።
አሽበልባይነት፡ ኣባባይነት አቈላማጭነት ።
አሽታተተ፡ መላልሶ አሸተተ ።
አሽታች፡ ያሸተተ/የሚያሸት (አነፍ...ናፊ) ።
አሽኔ ኪዳነ ማርያም፡ ብላታ አሽኔ (ካጤ ምኒልክ እስከ ቀዳማዊ ዐጤ ኀይለ ሥላሴ የነበሩ መንግሥትን በፍጹም ልባቸው የሚያከብሩ እግዚአብሔርንም የሚፈሩ የዘርና የሃይማኖት ልዩነት ሳያደርጉ ሰውን ኹሉ የሚያፈቅሩ ትሕትናንና ታማኝነትን ቸርነትን ገንዘብ ኢድርገው የኖሩ ናቸው) ።
አሽኔ፡ የሰው ስም (ጠላትን አሽን ማለት ነው) ።
አሽንቋጦ፡ ፥ —ጨንገር ፥ —ሸነቈጠ ።
አሽንቋጦ፡ አርጩሜ ፊንገር ልምጭ ።
አሽከረከረ፡ ወረወረ በሰማይ አዞረ አሾረ ("በመሬት ላይ አስኬደ አንደረደረ - አን ") ።
አሽከር (ሮች/አሻክርት)፡ ከ፯ እስከ ፲፭ ዓመት ያለ ልጅ (ብላቴና ታዛዥ ሎሌ አገልጋይ ተከታይ ወታደር ጭፍራ) ።
አሽከር፡ ሎሌ ፥ —ሸከረ ።
አሽከርነት፡ አሽከር መኾን (ታዛዥነት - "አሽከር ቢያጡ የማይረባ አሽከር መጥሪያ") ።
አሽኩቲ፡ ዐጡንባር፡ ኹኔታው በሶብላ አበባው ብማ የሚመስል ቅጠል፡ ሽታው ጣፋጭ ።
አሽካካ፡ ፎከረ ("ደነፋ ጮኸ ተበተ አሽካካ አስካካ ") ።
አሽካካ፡ ፎከረ (ካካ) ።
አሽክላ (ሎች)፡ ከሥር እስከ ጫፍ አንጓና ቈላፋ እሾኽ ያለው፡ ለቀፎ የሚኾን አረንጓዴ መልክ ዐረግ ፍሬያማ ። በርሱ ዐይነት የተሠራ ወጥመድ ። (መዝ ፲ ፥ ፱ ። ፻፵፫ ፥ ፭ ፥ ፱ ። ዐብድ ፩ ፥ ፯ ። መክ ፯ ፥ ፳፮) ። ዘሩና አንቀጹ ስከለ ነው፡ ፍሬውን ልጃገረዶች የእጅ ጌጥ ያደርጉታልና ። (ግጥም)፡ ያሽክላ መፋቂያ ይላል ጠጅ ጠጅ፡ እንዴት ነሽ በሉልኝ ያችን ጠይም ልጅ ።
አሽክማ/ዋይክማ (ወሎ)
አሽክርት፡ አሰመራ ።
አሽክርት፡ አሽክት ፥ —ሻከረ ።
አሽክርት፡ የቅጠል ስም (ፍሬውን ልጃገረዶች ለእጃቸው ጌጥ የሚያደርጉት ኹለንተናው ሻካራ የኾነ ሐረጋዊ ቀጪን ቅጠል) ። "አሸክትን" እይ ።
አሽክት (አሰከ አሰክት)፡ ጭጕኝ የጕያ ጠጕር ሻካራ ቍርንድድ ።
አሽክት፡ አሽክርት ። ሻከረን እይ ።
አሽኰመኰመ፡ አሽቈመቈመ ("ባፉ ምግብ ይዞ ጠራ የቀኝ ክንፉን ዘረጋ ዞረ አሽኰረመመ አጫወተ አዳራ አውራ ዶሮው ") ።
አሽኰመኰመ፡ አሽቈመቈመ ኰ መኰመ ።
አሽኰረመመ፡ አዳራ ፥ (ኰረመመ) ።
አሽኰረኰረ፡ ጓሚያ አበጀ ኰ ረኰረ ።
አሽኰነተረ፡ አስጌጠ፡ ኰነተረ ።
አሽኰንታሪ፡ ያሽኰነተረ/የሚያሽኰንትር ("አስጊያጭ ") ።
አሽኮኮ፡ ሽኮኮ ።
አሽኮኮ እንኮኮ (ኮኮ) ።
አሽኮኮ፡ እንኮኮ (ኮኮ) ።
አሽኮኮ፡ ያውሬ ስም ሽኮኮ ።
አሽኮኮች፡ ሽኮኮዎች (መዝ. ፻፬፡ ፲፰፡ ምሳ. ፴፡ ፳፮) ። "አሽኮኮ አሽኮኮች" የካህናት ነው ።
አሽጋኝ፡ ያሸገነ/የሚያሸግን (አሳማሪ) ።
አሽጐደጐደ/አዥጐደጐደ (ዠጐደ) ።
አሽጓበበ፡ ነገርን አጠመመ፡ አሽቃበበ፡ አሽጓበጠ።
አሽጓበጠ፡ አሽጠጠ፡ አሽጓበበ፡ አላገጠ ።
አሽጓባቢ፡ ያሽጓበበ/የሚያሽጓብብ፡ አጥማሚ፡ አሽቃባቢ፡ አሽጓባጭ።
አሽጓባቢነት፡ አጥማሚነት፡ አሽቃባቢነት፡ አሽጓባነት።
አሽጓባጭ (ጮች)፡ የሚያሽጓብጥ/ኣሽጣጭ/አላጋጭ።
አሽጓባጭነት፡ አሽጣጭነት/አላጋጭነት ።
አሽጣጭ፡ (ጮች)፡ ያሽማጠጠ፡ የሚያሽጥጥ፡ ሸርዳጅ፡ ሰው፡ ናቂ፡ አቃላይ፡ ቀልደኛ፡ አላጋጭ።
አሽጣጭ፡ ከሐኔ፡ በላይ፡ ያለ፡ ቀና፡ ያለ፡ የሰገባ፡ ፍ፡ ባለሎሚታና፡ ሎሚታ፡ የሌለው ።
አሽጣጭ፡ ጐራዴ፡ እንዲሉ።
አሾለ (ሰሐለ)፡ ሹል አደረገ (አቀጠነ እሾጠጠ - "አፉን ምላሱን ኣሾለ" - ለነገር ኣቈተመ) ።
አሾለ (አስሐለ)፡ ሹል አስደረገ ።
አሾለ፡ ሥልጣኑን አሳደሰ ።
አሾለ፡ የቄስን ሥልጣን ዐደሰ ።
አሾለቀ፡ ሾለቅ አደረገ (እሾጠ) ።
አሾለከ (አድራጊ)፡ በፉካ ኣሳለፈ ኣ...ወጣ ።
አሾለከ (ኣስደራጊ)፡ እንዲወጣ አስደረገ አስወጣ አሳለፈ ።
አሾላለክ፡ ኣወጣጥ መሹለክ ።
አሾላኪ፡ ያሾለከ/የሚያሾልክ (አስወጪ ንቃቃት ቀዳዳ) ።
አሾመ፡ ማዕርግ አሰጠ ኣስበጀ እስ...መላ ።
አሾረ፡ ኣዞረ አሠግረ አሽከረከረ (እንዝርትን በቅሎን መዘውርን) ።
አሾቀ፡ ቀቀለ አራሰ አረሰረሰ ።
አሾተለ፡ አደባ ፥ —ሾተል ።
አሾተለ፡ አደባ ሾተል ይዞ ሸመቀ...ደፈጠ ።
አሾታይ፡ ያሾተለ/የሚያሾትል (አድቢ...ሸማቂ) ።
አሾከሾከ፡ በዦሮ ነገረ ፥ —(ሾከሾከ) ።
አሾካሾከ፡ በዦሮ አነጋገረ ።
አሾካሿኪ፡ ያሾካሾከ/የሚያሾካሹክ ።
አሾክሿኪ፡ ያሾክሾክ/የሚያሾክሹክ (ጋ...ኔን ባለቅኔ) ።
አሾክሿኪነት፡ ኣሾክሿኪ መኾን ።
አሾጠጠ፡ አቀጠነ/አሾለቀ ።
አሾፈ፡ አላገጠ ፥ (ሾፈ) ።
አሿሚ፡ ያሾመ/የሚያሾም ።
አሿሪ፡ ያሾረ/የሚያሾር (አዟሪ አሽከ...ርካሪ) ።
አሿሿል፡ አቀጣጠን መሾል ።
አሿሿመ፡ ሹመት አቀባበለ አሸላለመ ።
አሿሿም፡ የሹመት አሰጣጥ መሾም ።
አሿሿቅ፡ አራራስ መሾቅ ።
አሿቂ፡ ያሾቀ/የሚያሾቅ ።
አሿይ፡ ያሾለ/የሚያሾል (አቅጣኝ ባለጅ ዐናጢ) ።
አሿፊ፡ ያሾፈ/የሚያሾፍ (ቀላጅ አላ...ጋጭ) ።
አሿፊነት፡ አላጋጭነት ።
አቀለ፡ ዐዘለ፡ ቀለ ።
አቀለለ (ኣቅለለ)፡ አሳነሰ አጐደለ አላላ ዕዳን ግዞትን ንስሓን ሐዘንን ። (መርከብን አቀለለ)፡ ዕቃን ጭነትን ሸክምን ወደ ባሕር ጣለ ("(ዮና. ፩፥ ፭፡ ግብ. ሐዋ. ፳፯፥ ፲፰)") ።
አቀለለ፡ ኣኰሰሰ ሰውን ።
አቀለመ (ሤረየ)፡ ቀለም እገባ ነከረ
አቀለመ፡ ደወረ አዳወረ አጠነጠነ፡ በቀለም (ቀሠም ላይ) ጠቀለለ ።
አቀለማመድ፡ አቀሠፋፈት መቀላመድ ።
አቀለማመጥ፡ አጣጣም/ማቀላመጥ ።
አቀለባበስ፡ አቀናነፍ/መቀልበስ ።
አቀለዋወጥ፡ አከጃጀል/መቀላወጥ ።
አቀለዘ፡ አደረቀ አከቸለ ።
አቀለጠ፡ መታ አሰማ ።
አቀለጠ፡ ነሣ ከለከለ አስቀረ ግብርን ።
አቀለጠ፡ አ አፈሰሰ፡ ናደ አፈረሰ ("(ኢዮ. ፳፪፡ ኤር. ፱፥ ፯)") ።
አቀለጠ፡ አሠባ አጮመየ ።
አቀለጠ፡ አደመቀ አሳመረ ። "ፈርዖን በሰጠመ ጊዜ እስራኤል እልልታውን አቀለጡት" ።
አቀለጠ፡ ወሰደ አጠፋ፡ ሰረቀ አሠ ረገ ።
አቀለጠፈ፡ ባጪር ሠራ፡ አፈጠነ ከወነ ።
አቀለጣጠም፡ አሰባበር/መቀልጠም ።
አቀለጣጠጥ፡ አገላለጥ/ማንቀልጠጥ/ መንቀልጠጥ ።
አቀለጣጠፈ፡ አከነዋወነ አጣጣመ ።
አቀለጣጠፍ፡ አፈጣጠን/መቀልጠፍ ።
አቀላ፡ ቀይ አደረገ ።
አቀላለል፡ አጐዳደል/መቅለል ። "ሞቀለለን" እይ፡ የዚህ ዘር ነው ።
አቀላለም፡ አነካከር አደዋወር መቅለም ።
አቀላለስ፡ አመላለስ/መቀለስ ።
አቀላለብ፡ አመጋገብ አያያዝ/መቀለብ/ መቅለብ ።
አቀላለተ፡ አረጣጠበ ።
አቀላለት፡ አረጣጠብ/መቀለት ።
አቀላለዝ፡ አደራረቅ/መቅለዝ ።
አቀላለድ፡ ኣለጋገጥ/መቀለድ ።
አቀላለጥ፡ አፈሳሰስ/መቅለጥ ።
አቀላል፡ ደም በርበሬ አመሳሰል/መ
አቀላመደ፡ ቀልማዳ አደረገ ።
አቀላመጠ፡ አጣጣመ ፥ —(ቀለ መጠ) ።
አቀላማጭ፡ ያቀላመጠ/የሚያቀላምጥ (አ ጣጣሚ ") ።
አቀላበሰ፡ አቃነፈ አሸናቀረ ።
አቀላወጠ፡ ለቀላዋጭ ሰጠ አጐረሠ ።
አቀላጠፈ፡ አከናወነ ጨረሰ ።
አቀላጣፊ፡ ያቀላጠፈ/የሚያቀላጥፍ (አከናዋኝ ጨራሽ ") ።
አቀል፡ አከላለል/መቃጠል ።
አቀልጣፊ፡ ያቀለጠፈ/ የሚያቀለጥፍ (አፍ ጣኝ ") ።
አቀመ፡ ፊቱን ቋጠረ አጠቈረ አ ከፋ (ቀጨሞ እንደ ቀመሰ ሰው ") ።
አቀመሰ፡ በጥፊ በበትር መታ ።
አቀመሰ፡ አጣመ አለከፈ ።
አቀመሰ፡ ጣለ አወደቀ ። "የምድር ቂጣ አቀመሰ" እንዲሉ።
አቀመቀመ፡ መልሶ መላልሶ መጠጥ ሰጠ ዐደለ ቸረ አጠጣ ።
አቀመቀመ፡ ወሬ ነገረ ።
አቀመቀመ፡ ጠጕር አወጣ አቀነቀነ ።
አቀመጣጠል፡ አጐዳደል/መቀምጠል ።
አቀማመም፡ አቀላቀል/መቀመም ።
አቀማመሰ፡ መታታ ።
አቀማመሰ፡ ኣለካከፈ ።
አቀማመስ፡ አለካከፍ/መቅመስ ።
አቀማመር፡ አቈጣጠር/መቀመር ።
አቀማመጠ፡ ቍጭ አባባለ፡ አስተራረፈ አሸካከመ፡ አኗኗረ ።
አቀማመጥ፡ አኗኗር/መቀመጥ ("(ማሕ. ፯፥ ፪)") ።
አቀማማጭ፡ ያቀማመጠ/የሚያቀማምጥ (ዳኛን የሚያማክር ") ።
አቀማም፡ አነጣጠቅ/መቀማት ።
አቀማቀመ፡ መብል አላመደ ።
አቀማቀመ፡ አሳፋ አዘማዘመ ።
አቀማቀም፡ አዘማዘም/መቀምቀም ።
አቀማቃሚ፡ ያቀማቀመ/የሚያቀማቅም (አዘማዛሚ ") ።
አቀማጠለ፡ አንቀባረረ ፥ —ቀመ ጠለ ።
አቀማጠለ፡ አጓደለ አንደላቀቀ አንቀ ባረረ አዘናፈለ ።
አቀማጣይ፡ ያቀማጠለ/የሚያቀማጥል (አንደላቃቂ አንቀባራሪ ") ።
አቀምቃሚ፡ ያቀመቀመ/የሚያቀመቅም (አቀንቃኝ አጠጪ ") ።
አቀሠመ፡ አለቀመ አመጠጠ ።
አቀሠመ፡ ደወረ ኣዳወረ አቀለመ በቀሡም አጠነጠነ ጠቀለለ ።
አቀሰሰ፡ ቅስና ሰጠ (ቄስ አደረገ ") ።
አቀሠፋፈት፡ አቀለማመድ/መቀሣፈት ።
አቀሳሰስ፡ ቅስና አቀባበል/መቅሰስ ።
አቀሳሰር፡ አገታተር/መቀሰር ።
አቀሳሰት፡ አደጋገን/መቀሰት ።
አቀሳሰት፡ አደጋገን/መቀሰት ።
አቀሳሰን፡ አጐመዣዠት/መቃስን ።
አቀሣሠፍ፡ አገዳደል/መቅሠፍ ። "ቀሣፈተን" ተመልከት ።
አቀሳቀስ፡ አነቃነቅ/መቀስቀስ ።
አቀረማመት፡ አከፋፈል/ማቀራመት ።
አቀረረ፡ ባይኑ ውስጥ እንባ አሳየ ("(ታየ)") ።
አቀረረ፡ ጠላን ቅራሪን ከላይ ቀዳ አጠለለ፡ ጨረሰ ።
አቀረሸ፡ አስቀረሸ፡ አስፈሰሰ አስተፋ ።
አቀረሻሸት፡ አተፋፍ/መቀርሸት ። "አንቀርሻ ከቀረሸ ሊወጣ ይችላል"፡ "ነቀረን" እይ ።
አቀረቀረ፡ አዘነበለ ደፋ ዐንገትን (ምድር ምድር አየ ") ። "ቀቀረን" ተመልከት ።
አቀረበ (አቅረበ)፡ አስጠጋ አገናኘ፡ ባጠገብ አቆመ አስቀመጠ፡ ባለል አደረገ ወደደ ።"እሳትና ውሃ አቀረብኩልሽ፡ አጅኸን ወደ ወደድኸው ጨምር (፩መቃ. ፯፥ ፯)" ።
አቀረና፡ በጥፊ መታ ።
አቀረና፡ አሸተተ አገማ ።
አቀረናን፡ አገማም/መቀርናት ።
አቀረጠ (ፀ)፡ ፍሬ ሰጠ አዝመራው ።
አቀረጠ፡ ቀረጥ ግብር ከፈለ ገበያተኛው ።
አቀረጣጠፈ፡ አጠቃቀነ።
አቀረጣጠፍ፡ አቈራረጥ፡ መቀርጠፍ።
አቀረጫጩም፡ አጠረቃቀም/ማቀራ
አቀረጫጩም፡ አጠረቃቀም/ማቀራ
አቀራመተ፡ አቃረጠ አተናተነ አራ ከበ አካፈለ ።
አቀራሚ ! ያቀራመ፡ ጭም፡ ሰብሳቢ/አጠራቃሚ ።
አቀራማች፡ ያቀራመተ/የሚያቀራምት ("አካፋይ ") ።
አቀራረም፡ አለቃቀም/መቃረም።
አቀራረር፡ አቀዳድ/ማቅረር ።
አቀራረበ፡ አጠጋጋ አገነኛኘ ።
አቀራረበ፡ ጠጋ ጠጋ አደረገ ።
አቀራረብ፡ አጠጋግ አነዳድ/መቅረብ ።
አቀራረጠ፡ አሰጣጠ አከፋፈለ ግብ ሮን ።
አቀራረጥ፡ አሿሿል/መቅረጥ ።
አቀራረጽ፡ አፈላፈል/መቅረጽ ። "ቀረጠን" እይ፡ "ቀረጸ የካህናት" "ቀረጠ የሕዝብ ዐማርኛ" ነው ።
አቀራረፍ፡ አላላጥ/መቅረፍ ።
አቀራራቢ፡ ያቀራረበ/የሚያቀራርብ (አጠጋፂ ") ።
አቀራር፡ አተራረፍ/መቅረት ።
አቀራቀር፡ አሸጓጐር/መቀርቀር ።
አቀራቀበ፡ አስተሳሰረ አጠማመረ ።
አቀራቀብ፡ አወዳደን/መቀርቀብ ።
አቀራቀፍ፡ አከራከር/መቀርቀፍ ።
አቀራጠፈ፡ አቋረጠ፡ አጣቀነ።
አቀራጣፊ፡ ያቀራጠፈ፡ የሚያቀራጥፍ።
አቀራጨመ፡ ሰበሰበ፡ (ቀረ መ) ።
አቀራጪመ፡ ሰበሰበ አጠራቀመ አጠ ናቀረ ።
አቀራጪመ፡ ሰበሰበ አጠራቀመ አጠ ናቀረ ።
አቀራጪጨ፡ አናከሰ ።
አቀርቃሪ፡ ያቀረቀረ/የሚያቀረቅር ።
አቀሸማመድ፡ አሰባበር/መቀሽመድ ።
አቀሻሸር፡ አከሻሸን አነፋፍ/መቀሸር ።
አቀቃቀል፡ አፈላል/መቀቀል ።
አቀቃቀር፡ አመላለስ/መቀቀር ።
አቀቃቀት፡ አነፋፈግ/መቀቀት ።
አቀበ፡ ጠበቀ ፥ —ዐቀበ ።
አቀበለ፡ ሰጠ (ቀበለ) ።
አቀበለ፡ አጐረሠ አጠጣ (የክርስቶስን ሥጋና ደም ") ። "ክርስቶስን" እይ ።
አቀበረ፡ ለገመ (ላዩ የሻረ መስሎ በውስጥ ቈሰለ መግል ያዘ አመረቀዘ ቍስል ") ።
አቀበታተት፡ አነፋፍ/መቀብተት ።
አቀበናነን፡ አነፋፍ/መቀብነን ።
አቀበዣዠር፡ አዘበራረቅ/መቀባዠር ።
አቀበጠ (አቅበጸ)፡ አጫወተ ቅብ ጠት አስተማረ ቀበጥ አደረገ ።
አቀበጣጠር፡ አለፋለፍ/መቀባጠር ።
አቀባቀበ፡ አስተራረሰ አለሳለሰ ።
አቀባቀበ፡ አቀጣቀጠ አስተዳደሰ ።
አቀባቀበ፡ አታከለ አቻከለ ።
አቀባቀብ፡ አቸካከል/መቀብቀብ ።
አቀባበለ፡ አሰጣጠ አረካከበ ።
አቀባበለ፡ ደግሞ ደጋግሞ አቀበለ ።
አቀባበለ፡ ጥይትን በቃታ አማካይነት ከጠመንዣ አገነኛኘ ።
አቀባበል፡ አሰጣጥ ማቀበል መቀ በል ።
አቀባበረ፡ እመቃብር ውስጥ አጨማመረ አደፋፈነ ። "የሠራኸኝ ሥራ አያቀባብርም" እንዲል ባላገር ።
አቀባበር፡ አደፋፈን/መቅበር ።
አቀባበጠ፡ መላልሶ አቀበጠ ።
አቀባበጥ፡ እዘላለል/መቅበጥ ።
አቀባቢ፡ ያቀባባ/የሚያቀባባ ።
አቀባባ (አስተቃብዐ)፡ አለቃለቀ አደላለሰ ።
አቀባባሪ፡ ያቀባበረ/የሚያቀባብር (ጎረቤት ዘመድ ") ።
አቀባባይ፡ ያቀባበለ/የሚያቀባብል (አረካካቢ ያቀባይና የተቀባይ መካከለኛ ") ።
አቀባባይነት፡ አቀባባይ መኾን (አረካ ካቢነት ") ።
አቀባብ፡ አደላለስ መቀባት ።
አቀባይ (ዮች)፡ ያቀበለ/የሚያቀብል (ስጪ ") ። "ስንበሌጥ እቀባይ ጭቃ አቀባይ ነገር አቀባይ" እንዲሉ ።
አቀባይነት፡ አቀባይ መኾን (ሰጪነት ") ።
አቀብሎ፡ ሰጥቶ አስረክቦ ።
አቀብሎ ሸሽ፡ በንባብ ተነግሮ በት ርጓሜ የሚታጣ ፊደል "ለ" ። ይኸውም በግእዝ አገባብ "ለይበል ለይኩን" የተባለውን "ይበል ይኩን" እያሠኘ ይነገራል።
አቀተራ፡ እጮኸ ።
አቀታተረ፡ አወዳደረ አከራከረ ኣፈካ ከረ አቋቋመ ።
አቀታተር፡ አወጣጠር/መቀተር ።
አቀታተት፡ ኣደካከም/መቃተት ።
አቀታታሪ፡ ያቀታተረ/የሚያቀታትር ("አፈካካሪ ") ።
አቀነቀነ፡ ጢም አበቀለ አቀመቀመ ።
አቀነበረ፡ አደረቀ አጠና ።
አቀነባበረ፡ አዘገጃጀ አደረጃጀ አከነዋ
አቀነባበር፡ አደራረቅ እጠናን/መቀን
አቀነባባሪ፡ ያቀነባበረ/የሚያቀነባብር (አከነዋዋኝ ") ።
አቀነዛዘር፡ አረዛዘም/መቀንዘር ።
አቀነዛዘፍ፡ አስተራረድ/መቀንዘፍ ።
አቀነዳ፡ አደረቀ አከረረ ።
አቀነዳደል፡ አበጣጥ አቈራረጥ/መቀን
አቀነጃጀት፡ አጠማመድ/ማቀናጀት ።
አቀነጣጠስ - አቀነጣጠብ - መቀንጠስ ።
አቀነጣጠበ፡ አቀነጣጠሰ ።
አቀነጣጠብ፡ አቀነጣጠስ/መቀንጠብ ።
አቀነጨረ፡ አደረቀ አጠነከረ ።
አቀነጫጨር፡ አጠነካከር/መቀንጨር ።
አቀና፡ ራስን ወደ ላይ አነሣ ቀና አ
አቀና፡ በጦር ኀይል ያዘ ተገዥ አደረገ አገርን ።
አቀና፡ አለማ አሳመረ ጠፍ መሬትን ።
አቀና፡ አበጀ አሰላ ነገርን ።
አቀና፡ ገረፈ ገራ ወይፈንን፡ ዕርሻ አለ
አቀና፡ ገዛ ሼጠ ለወጠ ።
አቀና፡ ፊቱን መለሰ አመራ ("(ዘፍ. ፲፰፥ ፲፮፡ ፳፪)") ።
አቀናቀነ፡ ሙሾን አዣመረ ።
አቀናቀነ፡ አመራመረ አፋተሸ ።
አቀናቀን፡ አመራመር አበላል/መቀን ቀን ።
አቀናቃኝ፡ ያቀናቀነ/የሚያቀናቅን (እ መራማሪ ") ።
አቀናበረ፡ አዘጋጀ አደራጅ አከናወነ አቋቋመ ።
አቀናባሪ (ዎች)፡ ያቀናበረ/የሚያቀናብር (አከናዋኝ ") ።
አቀናነስ፡ አነሣሥ/መቀነስ ።
አቀናነት፡ አስተጣጠቅ/መቀነት ።
አቀናነፍ፡ አቀለባበስ/መቀነፍ ።
አቀናና፡ ቀና ቀና አደረገ አነሣሣ፡ የጐደለን መላ አስተካከለ ("(ማር. ፱፥ ፲፪፡ ፳ተሰ. ፭፥ ፲፬)") ።
አቀናና፡ አመቀኛኘ ።
አቀናን፡ አነሣሥ/መቅናት/ማቅናት ።
አቀናዘረ፡ አዋሸመ ።
አቀናጀ፡ አንዱን ከራሱ ኹለተኛውን ከሌላ አምጥቶ ጠመደ ዐረሰ ።
አቀናጀ፡ ጠመደ ቀነጀ ።
አቀናጂ፡ ያቀናጀ/የሚያቀናጅ (ባላንድ ባሪያ ") ።
አቀናጠሰ - አቀናጠበ - እባጠሰ ። አቀናጣሽ፡ ያቀናጠሰ/የሚያቀናጥስ ።
አቀናጠበ፡ አቀናጠሰ ።
አቀናጣ፡ አወበራ ፥ —ቀነጣ ።
አቀናጣ፡ አወበራ አጠገበ አዘለለ አላፋ ።
አቀንጭራ፡ ድኻ ነቀል አባ ዳማ ።
አቀኛኘት፡ የቅኔ አሰጣጥ/መቀኘት ።
አቀኛኘት፡ የዜማ አዠማመር አፈቃ ቀድ/መቃኘት ።
አቀዋወሰ፡ አዘበራረቀ ።
አቀዘቀዘ፡ አበረደ (ቀዝቃዛ አደረገ ") ።
አቀዛቀዝ፡ አበራረድ/መቀዝቀዝ ።
አቀዛዘን፡ አለቃቀቅ/መቅዘን ።
አቀዛዘዝ፡ አፈዛዘዝ/መቅዘዝ ።
አቀዛዘፍ፡ አገፋፍ/መቅዘፍ ።
አቀዝቃዥ (ዦች)፡ ያቀዘቀዘ/የሚያቀዘቅዝ (አብራጅ ") ።
አቀዣዠት፡ አጯጯኸ/መቃዠት ።
አቀየመ፡ ፊቱን
አቀየመ፡ ፊቱን አከፋ ፥ —(ቀ የመ) ።
አቀያየም፡ አኰራረፍ/መቀየም ።
አቀያየስ፡ አለካክ/መቀየስ ።
አቀያየረ፡ አለዋወጠ አዘዋወረ ።
አቀያየር፡ አለዋወጥ/መቀየር ።
አቀያየድ፡ አገራረድ አሰካከል/መቀ የድ ።
አቀያየጥ፡ አቀላቀል/መቀየጥ ።
አቀያያሪ፡ ያቀያየረ/የሚያቀያይር (አለ ዋዋጭ እዘዋዋሪ ") ።
አቀደ፡ ውሳኔ አደረገ፡ ዐቀደ ።
አቀዳደመ፡ አስተላለፈ ።
አቀዳደም፡ አስተላለፍ/መቅደም ።
አቀዳደሰ፡ አበራረከ አመሰጋገነ ።
አቀዳደስ፡ አበራረክ/መቀደስ ።
አቀዳደደ፡ አሸረካከተ አሠነጣጠቀ አበ ጫጨቀ ።
አቀዳደድ፡ አሠነጣጠቅ/መቅደድ ።
አቀዳዳሚ፡ ያቀዳደመ/የሚያቀዳድም ።
አቀዳጂ፡ ያቀዳጀ/የሚያቀዳጅ (ካህን ነ
አቀጠለ (አቍጸለ)፡ ከተቈረጠና ከ ተመለመለ በኋላ ቅጠል አወጣ ለመለመ (አለመለመ) አቈጠቈጠ ።
አቀጠነ፡ ቀጪን አደረገ፡ ኣነነ እሣሣ አረቀቀ ።
አቀጠጠ፡ አኳያ አደረገ ።
አቀጠፈ፡ ቀንበጥና ቅጠል ሰጠ ።
አቀጣቀጠ፡ ብረት አሣራ ።
አቀጣቀጠ፡ አማታ አደባደበ አዳቀቀ ።
አቀጣቀጠ፡ አዋቀጠ ።
አቀጣቀጥ፡ አመታት/መቀጥቀጥ ።
አቀጣቃጭ፡ ያቀጣቀጠ/የሚያቀጣቅጥ (አዋቃ ") ።
አቀጣይ፡ ያቀጠለ/የሚያቀጥል (ለምላሚ ") ።
አቀጣጠለ፡ አቈጣጠረ አሰፋፋ ።
አቀጣጠለ፡ አያያዘ አናደደ ። ተደራራጊውና አደራራጊው ከቀጠለና ከ(ቃጠለ) መውጣቱን አስተውል ።
አቀጣጠል፡ አጨማመር አቈጣጠር አሰፋፍ/መቀጠል ።
አቀጣጠበ፡ አጠቃቀሰ (አከነዳዳ አለ
አቀጣጠብ፡ አለካክ/መቀጠብ ።
አቀጣጠነ፡ ጠራረበ ሸላለተ ።
አቀጣጠን፡ አሞናነን/መቅጠን ።
አቀጣጠጥ፡ አቈራረጥ አስተባበጥ/ መ ቀጠጥ ።
አቀጣጠፈ፡ አስተባበለ ።
አቀጣጠፈ፡ አቀነጣጠበ ።
አቀጣጠፍ፡ አቈራረጥ/መቅጠፍ ።
አቀጣጣይ፡ ያቀጣጠለ/የሚያቀጣጥል (አያያዥ ") ።
አቀጣጣይነት፡ አቀጣጣይ መኾን ።
አቀጣጥ፡ አቈራረጥ/መቅጣት ።
አቀጫቀጭ፡ አቈረጣጠም/መቀጭቀጭ ።
አቀጫጩም፡ የቅጫም አፈራር/መቀ
አቀጫጩት፡ አቈራረጥ አቀሣሠፍ/ መቅጨት ።
አቀጮ፡ አክርማና ስንደዶ ሰጠ መ
አቀጯጯ (አቍጠጠ)፡ አቀጠነ አ ኰሰመነ ኣሰለተ ።
አቀፈ፡ በክንድ ያዘ፡ ዐቀፈ ።
አቀፈዳደድ፡ ኣስተሳሰር/መቀፍደድ ።
አቀፈፈ፡ አለመነ (ለተማሪ ተዘከረ ") ።
አቀፋቀፈ፡ አባሳ አፈላፈለ ።
አቀፋቀፍ፡ አፈላፈል/መቀፍቀፍ ።
አቀፋፈር፡ አዘረጋግ/መቀፈር ።
አቀፋፈፍ፡ አከራከም አለማመን/መቅ ፈፍ ።
አቍለጨለጨ፡ ዐይኑን አንከባለለ ፥ —ቈለጨ ።
አቍለጨለጩ፡ ዐይኑን አንከባለለ፡ መለስ ቀለስ አደረገ ።
አቍላ፡ የጅራፍ ዕንጨት ቀለበት ።
አቍላሊ፡ ያቍላላ/የሚያቍላላ ።
አቍላላ፡ ሽንኵርትን ቅመምን ቅቤን ሥጋን ባንድነት ጠባበስ፡ ወጥ መሥራት ዠመረ ።
አቍላጥ፡ ኹለትነት ያላቸው ቈለጦች/ቍላዎች ።
አቍላጥ የካህናት፡ ቈለጦች የሕዝብ አነጋገር ነው ።
አቍል፡ ብዙ ጊዜ እንዲቈጭ አደረገ ።
አቍማዳ (ዶች)፡ ስልቻ ለቈታ ቀ ልቀሎ ጭልጊ ካንድ በኩል በስፌት የተደፈነ ።
አቍማዳ፡ ስልቻ ፥ —ቈመደ ።
አቍማዳ፡ ርኰት ራዎት ቀርበታ የውሃ የጠጅ መያዣ ("(ዘፍ. ፳፩፥ ፲፬፡ ፲፭፡ ፲፱፡ ሉቃ. ፭፥ ፴፯፡ ፴፰)") ።
አቍሳይ፡ ያቈሰለ/የሚያቈስል (መጫሚያ ኮርቻ ቀንበር ጭነት ") ።
አቍስል፡ ዝኒ ከማሁ ("አትክር ጨቅጫቃ ") ።"ልብ አቍስል" እንዲሉ ።
አቍስጣ (ጦች)፡ በረግረግ በባሕር ዳር የሚገኝ የድመት ዐይነት አውሬ ዓሣ በል ።
አቍራቢ (ዎች)፡ ያቈረበ/የሚያቈርብ ቄስ ።
አቍነጠነጠ፡ አቅበጠበጠ ቈ ነጠ ።
አቍነጠነጠ፡ አቅበጠበጠ ወዘወዘ ።
አቍዳማ፡ የገዳይ ምልክት፡ ቍ ዳማ ።
አቁፋዳ፡ የተማሪ ኰረጆ ፥ ቀ ፈደ ።
አቂያሚ፡ ያቄመ/የሚያቄም ።
አቃ፡ በቁሙ,—ዕቃ፣ እልቅና፡ አለቅነት፡ በኵርነት ታላቅነት
አቃ፡ በጦር፡ ሰራዊት፡ ክፍል፡ የማዕርግ፡ ስም፡ አለቃ፡ ማለት፡ ነው ።
አቃ፡ አለቃ ፥ —ላቀ ።
አቃ፡ ዕቃ ፥ —ዐቃ ።
አቃ፡ ገብሩ፡ እ ንዲሉ።
አቃለለ (አስተቃለለ)፡ አዋገደ አገባ ደደ ።
አቃለለ (አቀለለ)፡ ናቀ አዋረደ ("(ኢሳ. ፩፥ ፬፡ ሰቈ. ፩፥ ፰፡ ሉቃ. ፳፫፥ ፲፩)") ።
አቃለመ፡ እዳወረ አጠናጠነ አጠቃለለ ።
አቃለሰ፡ አጓበጠ አዳገነ ።
አቃለተ፡ አራጠበ ።
አቃለደ፡ አዋዛ አታረበ ።
አቃለጠ፡ አዳመቀ ።
አቃለጠ፡ ኣማታ አደባደበ ።
አቃለጠ፡ ኣፋሰሰ አናናደ ።
አቃላይ (ዮች)፡ ያቃለለ/የሚያቃልል (ናቂ አዋራጅ ") ።
አቃላጅ፡ ያቃለደ/የሚያቃልድ ።
አቃላጭ፡ ያቃለጠ/የሚያቃልጥ (አማቺ አደባዳቢ ") ።
አቃልጣ፡ ወሬ አዳማቂ አጣፋጭ፡ ካገኘው ሰው የሚጫወት ።
አቃመ (አቅሐመ)፡ ጥሬን ገለባን እ በላ፡ አቻመ አገፈረ ።
አቃመመ፡ ቅመምን ከቅመም መድኀኒትን ከመድኀኒት አገናኘ አቀላቀለ አደባ ለቀ አዋዋደ ።
አቃመሰ፡ አላከፈ አዳረሰ አባቃ ።
አቃመሰ፡ አማታ አደባደበ ።
አቃሚ (አቅሓሚ)፡ ያቃመ/የሚያቅም (እረኛ ለጓሚ ") ።
አቃሚ፡ ያቃማ/የሚያቃማ (አናጣቂ ") ።
አቃማ (አስተቃምሐ)፡ አናጠቀ አ ሻማ ።
አቃማሚ፡ ያቃመመ/የሚያቃምም (የ ቀማሚ ረዳት ") ።
አቃማሽ፡ ያቃመሰ/የሚያቃምስ (አማቺ ") ።
አቃሰተ፡ አቃተ ቀለሰ ።
አቃሰተ፡ ኣቃተተ ኣቃዘነ ኣጣረ አስ ጨነቀ ።
አቃሰተ፡ ኣቃተተ ኣቃዘነ ኣጣረ አስ ጨነቀ ።
አቃሰነ፡ አጐመዠ አቃቃ ።
አቃሳች፡ ያቃሰተ/የሚያቃስት/አቃታች ።
አቃሳች፡ ያቃሰተ/የሚያቃስት/አቃታች ።
አቃረ፡ አቃጠለ፡ ቃረ ።
አቃረ፡ አተኰሰ አቃጠለ ። "ልብን አቃረ"፡ አጐመዡ ("አግኝቼ በበላኹት በጠጣኹት አሠኘ፡ ለሐጭን አንጠባጠበ ") ።
አቃረመ፡ አላቀመ፡ አሰባሰበ።
አቃረረ፡ አቃዳ አጫለጠ ።
አቃረበ፡ አላጠቀ አጣጋ አገናኘ ።
አቃረበ፡ አናዳ አዋሰደ ።
አቃረበ፡ አዳረሰ አዋገደ ።
አቃረጠ፡ መጻፊያ ብርን አሿሿለ ኣበጀ ።
አቃረጠ፡ ቀረጥ ተቀባይን ረዳ ።
አቃረጠ፡ አቀራመተ አካፈለ ።
አቃረጸ፡ አቃረጠ አፈላፈለ አናቀሰ ።
አቃረፈ፡ አላላጠ አማለጠ ።
አቃራሚ፡ ያቃረመ፡ የሚያቃርም፡ እ ላቃሚ ።
አቃራሪ፡ ያቃረረ/የሚያቃርር (አጫላጭ ") ።
አቃራቢ፡ ያቃረበ/የሚያቃርብ (አገናኚ ") ።
አቃራጭ፡ ያቃረጠ/የሚያቃርጥ (አቀራማች አካፋይ ") ።
አቃቀለ፡ ኣፋላ አባሰለ፡ ወጥ አሣራ ።
አቃቂ፡ ያቃቃ/የሚያቃቃ (አጐምዢ ") ።
አቃቃ፡ አጐመዠ አሠየ ።
አቃቃም፡ አገታተም/መቃም ።
አቃቃር፡ አሳሳል/መቃር ።
አቃቅማ፡ ኵርንችት፡ ዐቃቅማ ።
አቃበረ (አስተቃበረ)፡ ሬሳን ኦያያዘ መሬትን አማለሰ አዳፈነ ።
አቃበጠ፡ አላፋ አቈናጠጠ አቈላመመ ።
አቃቢ፡ ያቃባ/የሚያቃባ ።
አቃባ፡ አዳለሰ ኣላከከ ።
አቃባ፡ ደም አፋሰሰ አጋደለ ።
አቃባሪ፡ ያቃበረ/የሚያቃብር ።
አቃባጭ (ጮች)፡ ያቃበጠ/ የሚያቃ
አቃተተ፡ አዞረ አለፋ አደከመ ።
አቃታች፡ ያቃተተ/የሚያቃትት ("አልፊ አድካሚ ") ።
አቃች፡ ያቃተ/የሚያቅት (ተሳኝ ") ።
አቃች፡ ያቃተ/የሚያቅት (ተሳኝ ") ።
አቃና (አስተራትዐ)፡ አሳላ አሳካ አስተካከለ ።
አቃና (አስተቃንአ)፡ አመቃኘ ።
አቃናሽ፡ ያቃነሰ/የሚያቃንስ (አጓዳይ ") ።
አቃኚ፡ ያቃና/የሚያቃና (አስተካካይ ") ።
አቃወመ፡ አጣላ አከራከረ አገተ ።
አቃወሰ፡ አለያየ (አንድነትን ኅብረትን አሳጣ ")፡ አሳሳተ አጣመመ አሳከረ አዋሰበ አዘባረቀ (ምክርን ጸጥታን ") ።
አቃዋሽ፡ ያቃወሰ/የሚያቃውስ (አሳሳች ") ።
አቃዘነ፡ አባዘነ ፥ —ቃዘነ ።
አቃዘነ፡ አንከራተተ አባዘነ ።
አቃዘፈ፡ አጋፋ አጋለጠ ።
አቃዠ፡ አስጮኸ አስለፈለፈ ።
አቃየሰ፡ ገመድ አዘራጋ አላካ ።
አቃየረ፡ አላወጠ አዛወረ ።
አቃየደ፡ አስተሳሰረ ኣጋዳ ።
አቃየዶ፡ አጋረደ ኣካለለ ።
አቃየጠ፡ አዛነቀ አቀላቀለ አደባለቀ ።
አቃያጅ፡ ያቃየደ/የሚያቃይድ ።
አቃይ፡ ያቃጨለ/የሚያቃጭል (ዲ ያቆን ") ።
አቃደሰ፡ አቋረበ ።
አቃደሰ፡ አባረከ አመሳገነ ።
አቃደደ፡ አሠናጠቀ አተናተነ ።
አቃዳሽ፡ ያቃደሰ/የሚያቃድስ (አባራኪ ") ።
አቃዳጅ፡ ያቃደደ/የሚያቃድድ (አተና
አቃጠለ፡ ተኰሰ እነደደ አሳረረ አገመነ ("(ዘሌ. ፲፥ ፮፡ ፪ዜና. ፴፩፥ ፭)") ።
አቃጠለ፡ አነደደ ቀጠለ፡ (ቃ ጠለ) ።
አቃጠለ፡ ኣቋጠረ አሳፋ ።
አቃጠረ፡ ቀጠሮ አቀባበለ፡ ወንድና ሴትን አነጋገረ፡ "እንድትመጪ/እንድትመጣ ብሎሻል/ብላኻለች" አለ፡ አማጣ አገናኘ ።
አቃጠበ (አስተቃጸበ)፡ አከናዳ አ
አቃጠነ፡ መቃጥን ጣለ፡ ቀ ጠነ ።
አቃጠነ፡ መቃጥን ጣለ አወረደ ።
አቃጠነ፡ አሊጥ ውስጥ ውሃ ኣጫመረ ኣማስለ ።
አቃጠነ፡ አፋተለ ቀጪንን ።
አቃጠጠ፡ አቋረጠ አሻለተ ።
አቃጠፈ፡ አቋረጠ አቀናጠበ ።
አቃጣ (አስተቃጽዐ)፡ አማታ ኣ
አቃጣ፡ አቋረጠ አማቀሰ ።
አቃጣሪ (ሮች)፡ ያቃጠረ/የሚያቃጥር (አገናኚ ") ። "አመንዝራ ሲያረጅ አቃጣሪ ይኾናል" እንዲሉ።
አቃጣሪነት፡ አቃጣሪ መኾን ።
አቃጣኝ፡ ያቃጠነ/የሚያቃጥን (አዋ
አቃጣይ (ዮች)፡ ያቃጠለ/የሚያቃጥል (አንዳጅ ") ("(ዓሞ. ፯፥ ፲)") ።
አቃጣይነት፡ አቃጣይ መኾን ።
አቃጣፊ፡ ያቃጠፈ/የሚያቃጥፍ ።
አቃጨለ፡ ቃጭልን መታ ፥ —ቀ ጨለ ።
አቃጨለ፡ ቃጭልን ወዘወዘ መታ አከለለ አስጮኸ ።
አቃጨለ፡ አማታ አጋጨ ።
አቃጩ፡ አጋጨ አላተመ ።
አቃፈፈ፡ አላመነ ።
አቃፈፈ፡ አከራከመ ።
አቃፊ፡ ኣቋረጠ አናጩ አገናጠለ ።
አቄለ፡ ቂል አደረገ፡ አሞኘ አታለለ እንደ ልጅ ።
አቄመ፡ ለገመ አቀበረ አመረቀዘ፡ የቍስል ።
አቄመ፡ ቂም ያዘ ።
አቄመ፡ ቂም ያዘ ፥ —(ቀየመ ቄመ) ።
አቄደረ፡ አኰራ አተቤተ ።
አቄዳደር፡ አኰራር/መቄደር ።
አቈለ፡ ገለጠ አጠራ አበራ አጐላ ።
አቈለማመም፡ አቀላለስ/መቈልመም ።
አቈለማመጥ፡ አመሰጋገን/ማቈላመጥ ።
አቈለቈለ፡ ዘቀዘቀ (ቈለቈለ) ።
አቈለባበጥ፡ አስተናነስ/መቈልበጥ ።
አቈላ፡ ቍላ አኰረተ አሳየ ዘረጋ አወረደ አንጠለጠለ ።
አቈላለል፡ አከማመር/መቈለል ።
አቈላለፈ፡ አገነኛኘ አጣላ ።
አቈላለፍ፡ አዘጋግ/መቈለፍ ።
አቈላላፊ፡ ያቈላለፈ/የሚያቈላልፍ (አጣይ ነገረ ሠሪ ") ።
አቈላል፡ አስተማመስ/መቍላት ።
አቈላመመ፡ አጠማዘዘ እቃለሰ አዳራ ።
አቈላመጠ፡ ውዳሴ ከንቱ ሰጠ (ቈለመጠ) ።
አቈላማሚ፡ ያቈላመመ/የሚያቈላምም ።
አቈላማጭ፡ ያቈላመጠ/የሚያቈላምጥ (አመስጋኝ ተለማማጭ ") ።
አቈላማጭነት፡ አመስጋኝነት ተለማማ
አቈላማጮች፡ አመስጋኞች ተለማማ
አቈላቈል፡ አዘቃዘቅ/ማቈልቈል ።
አቈላዘመ፡ አጐናዘለ፡ (ቈለ ዘመ) ።
አቈላዘመ፡ አጐናዘለ አዘናፈለ አጠ
አቈልቍሎ፡ ዘቅዝቆ አዘቅዝቆ አጐን ብሶ ("(መዝ. ፻፪፥ ፲፱)") ።
አቈልቋይ፡ ያቈለቈለ/የሚያቈለቍል (ዘ
አቈልቋይ ገበታ፡ አውራጅ፡ ከላይ ወደ ታች የሚዘረጋ ሞላላ ገበታ፡ ባላ፬ እግር፡ ፪ና ፫ እግር ያለውም አለ ።
አቈማመድ፡ አደራረት/መቈመድ ።
አቈማመጥ፡ ኣቈራረጥ/መቍመጥ ።
አቈሰለ፡ ነካ ላጠ እደማ ("(፪ነገ. ፰፥ ፳፱ ። ፱፥ ፲፭)") ።
አቈሰለ፡ አሳዘነ ።
አቈሳሰለ፡ መላልሶ አቈሰለ፡ የቍስሉን ብዛት ያሳያል ።
አቈሳሰል፡ አደማም/መቍሰል ።
አቈሳቈሰ፡ አዋጋ አጋደለ ።
አቈሳቈሰ፡ አጋፋ አመረ ።
አቈሳቈስ፡ አጨማመር/መቈስቈስ ።
አቈሳቋሽ፡ ያቈሳቈሰ/የሚያቈሳቍስ (አ ዋጊ ") ።
አቈረ፡ ዐቀፈ ፥ —ዐቈረ ።
አቈረማመደ፡ አጨባበጠ/አኰረማመተ ።
አቈረማመድ፡ አኰረማመት/ማቈራ መድ ።
አቈረቈዘ፡ አሳነሰ አሳጠረ ።
አቈረበ (አቅረበ)፡ ለባለጤና ወይም ለበሽተኛ ሥጋ ወደሙ ሰጠ አቀበለ ።
አቈረበጨ፡ አጐረበ ፥ —ቈረበ ።
አቈረበጯ፡ አጐረበ ።
አቈረኛኘት፡ አስተሳሰር/ማቈራኘት ። "ቈ ረኘተን" እይ ።
አቈረጠ፡ አቆመ ተወ (ስጦታን ዝናምን ደምን መውለድን ") ።
አቈረጠመ፡ ቈሎ አበላ ። "በቁምኸ፪ ማሪያም ቈሎ ታቈርጥምኸ" እንዲሉ ።
አቈረጣጠም፡ አከረታተስ/መቈርጠም ።
አቈረፈደ፡ አደረቀ አሻከረ ።
አቈረፋፈድ፡ አደራረቅ/መቈርፈድ ።
አቈራመደ፡ ጨበጠ፡ (ቈረ መደ) ።
አቈራማጅ፡ ያቈራመደ/የሚያቈራምድ ።
አቈራረም፡ አመታት፡ መቈረም ።
አቈራረሰ፡ አገማመሰ አከፋፈለ ።
አቈራረብ፡ አቀዳደስ/መቍረብ ።
አቈራረዝ፡ አሸራረብ/መቈረዝ ።
አቈራረጠ፡ አጠሳላ አለያየ ("(ብዙ ጊዜ መንገድን አቋረጠ)") ።
አቈራረጥ፡ አጐማመድ/መቍረጥ ።
አቈራረፍ፡ አጨራረፍ/መቈረፍ ።
አቈራራጭ፡ ያቈራረጠ/የሚያቈራርጥ (አሳባቂ ዥብ እማስጥ ") ።
አቈራር፡ አበጣጥ/መቈራት ።
አቈራቈሰ፡ አፋተነ ፥ —ቈረቈሰ ።
አቈራቈሰ፡ አፋተነ አከራከረ አከረ አዣመረ አማታ አዋጋ አጋጩ (ሰውን ዱላን ") ።
አቈራቈስ፡ አዠማመር/መቈርቈስ ።
አቈራቈር፡ አመሠራረት/መቈርቈር ።
አቈራቈዝ፡ አስተናነስ/መቈርቈዝ ።
አቈራቋሽ፡ ያቈራቈሰ/የሚያቈራቍስ (አማቺ አዋጊ ") ።
አቈራኘ (አድራጊና አደራራጊ)፡ አሰረ ኣስተሳሰረ አያያዘ ።
አቈራኘ፡ አሳደረ አዋሐደ ።
አቈራኚ፡ ያቈራኘ/የሚያቈራኝ (አስተሳሳሪ አያያዥ ") ።
አቈራፈደ፡ አዳረቀ አሸካከረ ።
አቈሸሸ፡ አሳደፈ በከለ አለፈለፈ ።
አቈሻሸሽ፡ አስተዳደፍ/መቈሸሽ ።
አቈቈጭ፡ አስተጋገል/መቈጭቈጭ ።
አቈበረ፡ አበሳጨ (ዐመለ ቍርንጭ አደረገ ") ።
አቈበቈበ (አጐሰጐበ - አኰበኰበ)፡ አጐረበ አቈረበ ።
አቈበቈበ፡ ሰለፈ ፥ —ቈበቈበ ።
አቈበቈበ፡ ሰለፈ (ዳር ዳር አለ ለመኼድ ለመናገር ") ።
አቈባቈብ፡ አጐራረብ/ማቈብቈብ ።
አቈብቋቢ፡ ያቈበቈበ/የሚያቈበቍብ (ሰላፍ አጐብጓቢ ") ።
አቈተመ፡ አጓጓ ፥ —ቈተመ ።
አቈታተም፡ አሰላለፍ/መቈተም ።
አቈታተም፡ አሰላለፍ/መቈተም ።
አቈታተም፡ አሰላለፍ/መቈተም ።
አቈታቸ፡ አወራረደ ("እሰጥ አገባ አባ ባለ ") ።
አቈታቺ፡ ያቈታቸ/የሚያቈታች (አወ ራራጅ ") ።
አቈነዠ፡ አሳመረ አስዋበ፡ ቈንዦ አደ
አቈነዣዠት፡ የውበት አኳዃን/መቈን ዠት ።
አቈነዳደድ፡ አገራረፍ/መቈንደድ ።
አቈነጣጠር፡ አነካከስ/መቈንጠር ።
አቈነጣጠጥ፡ አለመዛዘግ/መቈንጠጥ ።
አቈነጫጨት፡ አለቃቀም/መቈንጨት ።
አቈነጻጸል፡ አኰሰታተር/መቈንጸል ።
አቈናቈነ፡ አሣሠተ አቋጠሰ አንቈጣ ቈጠ ።
አቈናቈነ፡ አካተፈ አተናተነ ።
አቈናቈን፡ አቈጣጠብ/መቈንቈን ።
አቈናነስ፡ አገማም/መቈነስ ።
አቈናነን፡ አጐናጐን አሰፋፈር/መቈ
አቈናደደ፡ አጋረፈ ።
አቈናጠረ፡ አቅበጠበጠ አቍነጠነጠ አ ፈናጠረ ።
አቈናጠረ፡ አናከሰ ።
አቈናጠጠ (ሥራ ትዳር ኣሲያዘ) ።
አቈናጠጠ፡ አለማዘገ አቃጣ ።
አቈናጠጠ፡ አናከሰ አባላ ።
አቈናጠጠ፡ አጠቃለለ አማገረ ።
አቈናጠጠ፡ እግርንና ርካብን አገናኘ አያያዘ ።
አቈናጣሪ፡ ያቈናጠረ/የሚያቈናጥር (አና ካሽ አፈናጣሪ ") ።
አቈናጣጭ፡ ያቈናጠጠ/የሚያቈናጥጥ ("(ትዳር አሲያዥ)") ።
አቈዛዘም፡ አስተዛዘን/መቈዘም ።
አቈዛዘር፡ አጐሳሰር/መቈዘር ።
አቈየ፡ አስቀመጠ አዘገየ ።
አቈያየት፡ አዘገያየት/መቈየት ።
አቈጋግ፡ አገራረፍ/መቈጋት ።
አቈጠቈጠ፡ የቈጠቈጠ ተቃራኒ፡ አለመለመ ጨበጨበ አፈጠፈጠ አጀፈጀፈ ቍጥቋጦ ኣወጣ፡ አቀጠለ ።
አቈጣቈጥ፡ አቈራረጥ/አስባለብ/መቈ
አቈጣጠረ፡ አስተሳሰበ አሳላ ።
አቈጣጠር፡ አስተሳሰር/መቋጠር ።
አቈጣጠር፡ የቍጥር አደራረግ አሠ ራር፡ መቍጠር ።
አቈጣጠብ፡ የገንዘብ አያያዝ/መቈ
አቈጣጠጥ፡ አኰሳስ/መቈጠጥ ።
አቈጣጣሪ፡ ያቈጣጠረ/የሚያቈጣጥር (አስተሳሳቢ ") ።
አቈጣጥ፡ አገሣሠጽ/መቈጣት ።
አቈጨባበር፡ ኣበሰጫወት/መቈጫበር ።
አቈጨጭ፡ አስተናነስ/መቈጨጭ ።
አቈጫበረ፡ አበሳጩ ፥ —ቈጨበረ ።
አቈጫጨት፡ አጸጻጸት/መቈጨት ።
አቈፈናነን፡ አስተጣጠፍ/መቈፍነን ።
አቈፋጠነ፡ አዘጋጀ ኣደራጀ አሳመረ አስጌጠ ።
አቈፋፈር፡ አማማስ/መቈፈር ።
አቅ፡ ልክ ፥ —ዐቅ ።
አቅለሰለሰ፡ አደከመ ።
አቅለሰለሰ፡ አደከመ አሰለተ ።
አቅለሸለሸ፡ አጥወለወለ ፥ —(ቀ ለሸ) ።
አቅለበለበ፡ አስገበገበ ፥ —ቀለበ ።
አቅለበለበ፡ አክለበለበ አስገበገበ ።
አቅለብላቢ፡ ያቅለበለበ/የሚያቅለበልብ (ኣስገብጋቢ ") ።
አቅለጠለጠ፡ አወዛ ፥ —ቀለጠ ።
አቅለጠለጠ፡ አወዛ ወዛም አደረገ ።
አቅሊ፡ ያቀላ/የሚያቀላ ።
አቅላሊ፡ ያቅላላ/የሚያቅላላ (ሸላሚ አዥጐርጓሪ ") ።
አቅላላ (አቅየሐይሐ)፡ ደም ኣስ መሰለ ወደ ቀይነት ለወጠ፲ ሸለመ አዥጐረጐረ ("(ዘፍ. ፴፪፥ ፳፮)") ።
አቅላሚ፡ ያቀለመ/የሚያቀልም (ቀለም አግቢ ነካሪ ዐላይ ") ።
አቅላሚ፡ ደዋሪ አዳዋሪ አጠንጣኝ ።
አቅላይ፡ ያቀለለ/የሚያቀል ።
አቅላጭ፡ ያቀለጠ/የሚያቀልጥ (አፍሳሽ ") ("(ምሳ. ፳፭፥ ፬)") ።
አቅሌሳ (አቅሌስያ)፡ ቤተ ክሲያን ።
አቅሌሳ፡ የሴት ስም፡ ያቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እናት ። ቤተ ክሲያን ስላሳደገቻቸው እናቴ አቅሌሳ ናት፡ አባቴ ስም ፆን (ጴጥሮስ) ነው አሉ ይላል ገድላቸው ።
አቅሌሳ፡ የዝንብ ስም፡ እጠላ ውስጥ የገባች ዝንብ በካህናት ፈሊጥ አቅሌሳ ትባላለች ።
አቅል፡ ዕውቀት ፥ —ዐቅል ።
አቅልጥ፡ ሌባ እጀኛ አጥፊ እሥራጊ ።
አቅልጥ፡ ዝኒ ከማሁ ። "ብርድ አፍንጫ አቅልጥ" እንዲሉ።
አቅመደመደ፡ እባብኛ አስ ኬደ ። (ቀመደ) ።
አቅመድማጅ፡ ያቅመደመደ/የሚያቅመደምድ (በሽታ ወገብ ሰባሪ ዥብሪ ") ።
አቅማሚ፡ ያቅማማ/የሚያቅማማ (አመ
አቅማማ፡ አመነታ ፥ —ቀማ ።
አቅማማ፡ አመነታ አመቀመቀ፡ ልቀማ ልተው ላድርግ አላድርግ አለ ።
አቅማሽ (ሾች)፡ ያቀመሰ/የሚያቀ ምስ (የወጥ ቤት ያሳላፊ አለቃ ") ።
አቅማሽነት፡ አቅማሽ መኾን ።
አቅሳሽ፡ ያቀስሰ/የሚያቀስ ።
አቅራሪ፡ ያቀረረ/የሚያቀር (አጥላይ ") ።
አቅራሪ፡ ያቅራራ/የሚያቅራራ/የሚሸ ልል (ሸላይ ") ።
አቅራሪነት፡ አቅራሪ መኾን (ሸላይነት ") ።
አቅራራ፡ ሸለለ፡ ቀረረ ።
አቅራራ፡ አክላላ ሸለለ ። "ገረረ" ብለኸ "አገረረን" እይ ።
አቅራቢ (ዎች)፡ ያቀረበ/የሚያቀ ርብ (አስጠጊ አገናኚ ") ።
አቅራቢነት፡ ኣቅራቢ መኾን ።
አቅራቢያ፡ ሩቅ ያልኾነ ስፍራ ።
አቅበዘበዘ - ኣቅነዘነዘ፡ አናወዘ አባከነ አዞረ ("(ኢዮ. ፲፪፥ ፳፬ - ፳፭)") ።
አቅበዘበዘ፡ አናወዘ ፥ —ቀበዘ ።
አቅበዝባዥ፡ ያቅበዘበዘ/የሚያቅበዘ ብዝ (አቅነዝናዥ አባካኝ ") ።
አቅበጠበጠ፡ አቍነጠነጠ በጠ ።
አቅበጠበጠ፡ አቍነጠነጠ አወራጨ ወዘወዘ ነቀነቀ (ኣበሳጩ ") ። "ማር ቢሰጡት ወተት፡ ጠጅ ቢሰጡት ጠላ አሠኘ" ።
አቅባሪ፡ ያቀበረ/የሚያቀብር (ልግመኛ ") ።
አቅባጭ (ጮች)፡ ያቀበጠ/የሚያ
አቅባጭነት፡ አቅባጭ መኾን ።
አቅነዘነዘ፡ አፍነዘነዘ፡ (ቀነዘ) ።
አቅነዘነዘ፡ አፍነዘነዘ አክለፈለፈ አንቀ ዠቀዠ ።
አቅኒ (ኚ - ኝ)፡ ያቀና/የሚያቀና (አ ልሚ ሸያጭ ") ።
አቅኒነት፡ አቅኒ መኾን ።
አቅኒዎች፡ ያቀኑ/የሚያቀኑ (ነገሥታት መኳንንት፡ ሸያጮች ገበያተኞች ") ።
አቅዘመዘመ፡ አምዘገዘገ፡ (ቀ ዘመ) ።
አቅዘምዛሚ፡ ያቅዘመዘመ/የሚያቅዘመዝም (አምዘግዛጊ ሜዳ ") ።
አቅጠለጠለ፡ አከታተለ ።
አቅጠለጠለ፡ አከታተለ ፥ —ቀጠለ ።
አቅጣኝ (ኞች)፡ ያቀጠነ/የሚያቀጥን (ያቀጠነች/የምታቀጥን ሴት ሸረሪች ") ። (ተረት)፡ "አፍጣኝና አቅጣኝ እመዳሮ እንገናኝ ዞ ሊጥን" ።
አቅጣጫ፡ አንጻር አፍዛዣ ። "ገጠጠን" አስተውል ።
አቅጣጫ፡ አኳያ ፥ —ቀጠጠ ።
አቅጨለጨለ፡ መላልሶ አቃጨለ፡ ቅጭል ቅጭል አደረገ ።
አቆመ (አቀመ)፡ ታ መ ኼድ ከለከለ ገተረ አገደ ።
አቋለለ፡ አካመረ አጓቸ ።
አቋለፈ፡ አገናኘ አያያዘ ።
አቋላ፡ አጋረፈ አማታ ።
አቋላ፡ አጣበሰ አባሰለ ።
አቋላይ፡ ያቋለለ/ያካመረ/የሚያቋልል (አካማሪ ") ።
አቋላፊ፡ ያቋለፈ/የሚያቋልፍ (አገናኝ አያያዥ ") ።
አቋመጠ፡ አጐመዠ አሠየ ።
አቋሚ (ዎች)፡ ያቆመ/የሚያቆም (ገቺ ") ።
አቋማጭ፡ ያቋመጠ/የሚያቋምጥ (አጐ ምዢ ") ።
አቋም፡ በግድግዳ መካከል ዐልፎ ዐልፎ የቆመ ወጋግራ ፬ ማእዘን ።
አቋም፡ የ ቋም ብዢ ነው ።
አቋም፡ የማንኛው ሥራ የሕንጻ ኹኔታ አኳዃን ።
አቋም፡ የቆመ ውሃ ኩሬ ።
አቋሰለ፡ አማታ አዋጋ አፈናከተ አዳማ ።
አቋረሰ፡ አፋተተ አጋራ አካፈለ አሳ ተፈ ።
አቋረጠ፡ መንገድ አሳጠረ አሳበረ መስቀልኛ ኼደ ።
አቋረጠ፡ ተወ አስቀረ ።
አቋረጠ፡ ኣዋዋለ አጻጻፈ ("(በቍርጥ ሰጠ ሥራን)") ።
አቋረጠ፡ የቤትን ውስጥ ከፈለ መከተ ጋረደ ።
አቋረጠ፡ የያዘውን ትቶ ሌላውን ጣ ልቃ አግብቶ ሠራ ።
አቋራሽ፡ ያቋረሰ/የሚያቋርስ (አካፋይ ዐብሮ በላ ") ። "ድፍን አቋራሽ" እንዲሉ ።
አቋራሽነት፡ ኣቋራሽ መኾን ።
አቋራጭ፡ የቤትን ወለል የሚከፍል ግንብ ግድግዳ መከታ ።
አቋራጭ፡ ያቋረጠ/የሚያቋርጥ ሰው (አዋዋይ ") ።
አቋሸ፡ ዐኘከ ። (ቋሸ) ።
አቋቋመ፡ መቆምን አስተባበረ ("(ተባበረ)") ። "ልጄን ክርስትና ሳስነሣ እንድታቋቁሙኝ ትላለች እናት" ።
አቋቋመ፡ አበጀ አሳካ አቀናበረ ።
አቋቋሚ (ዎች)፡ ያቋቋመ/የሚያቋ ቁም (ኣቀናባሪ ") ።
አቋቋም፡ አነሣሥ (መቆም ቁመና ") ("(፩ነገ. ፲፥ ፭)") ።
አቋቋም፡ ዝማሜና ጽፋት መረግድ ዚቅ ሥርዐተ ማሕሌት ቁመው የሚሉት ።
አቋች፡ ያቋተ/የሚያቍት (ደቃኝ ") ።
አቋች፡ ያቋተ/የሚያቍት (ደቃኝ ") ።
አቋነነ፡ አላካ አሳፈረ ።
አቋነነ፡ አሻረሰ አጐናጐነ ።
አቋደሰ፡ አቋረሰ አካፈለ አሳተፈ መቋ
አቋዳሽ፡ ያቋደስ/የሚያቋድስ (አቋራሽ አካፋይ ") ።
አቋጠረ፡ ፩ - ፪ - አባባለ ። (መቊጠርን ረዳ) ። "ጐንደሮች ግን አቋጠረን ዐሰበ ይሉታል" ።
አቋጠረ፡ አስተሳሰረ ("መቋጠርን ረዳ ") ።
አቋጣ (አስተቋጥዐ)፡ አጋሠጸ አገላ
አቋጣሪ፡ ያቋጠረ/የሚያቋጥር ።
አቋጨ፡ አካረረ (ቍቲትን ") ።
አቋጩ፡ ቍጭትን አሳሰበ አነሣሣ ። "ቋጨን" ተመልከት ።
አቋፈ፡ ቈነነ ፥ —(ቋፈ) ።
አቋፈረ፡ አማማሰ ኣኰታኰተ ። አቋፋሪ፡ ያቋፈረ/የሚያቋፍር (የቍፋሮ ረዳት ") ።
አበ፡ (አብ)፡ መነኵሴ / የመነኵሴ ስምና መጥሪያ ። አባ ። አበ አመ እንዲሉ - ሕፃናት ።
አበ ልጅ፡ የክርስትና አባትና እናት ቀኝ አውራጣት የሚይዝ የምትይዝ የሃይማኖት ባለቃል ኪዳን ። ሴትን ኣበ ልጅ ማለት ባልና ሚስት አንድ አካል አንድ አምሳል ስለሚባሎ ነው ።
አበ ማኅበር፡ ሙሴ የማኅበረተኛ ሹም።
አበ ማኅበር፡ የማኅበር መምር የነኮሳት አሳዳሪ፡ (ግእዝ) ።
አበ ምኔት፡ ዝኒ ከማሁ፡ የገዳም እባት፡ (ግእዝ) ።
አበ ሱዳ፡ ጥቍር አዝሙድ፡ ፍጹም ጥቍር ፥ ከሱዳን የመጣ ቅመም ።
አበ ሱዳን፡ የጥቍሮች ጌታ፡ ጊዮርጊስ ፥ ንጉሠ ኖባን የመሰለ ። ሱዳንን እይ ።
አበ ነፍስ፡ የነፍስ የንስሓ አባት ።
አበ ደም፡ ባለደም ፥ ደመኛ (ደበኛ ነፍሰ ገዳይ ወይም የቕ ወገን ተበቃይ) ።
አበ ጋዝ፡ (አበ ጋእዝ)፡ የንጉሥ በጦር ዋና አዛዥ ፥ አዝማች ፥ አለቃ ፥ ደምሳሽ ፥ ጠቅላይ ፈታውራሪ፡ የሰልፍ ፥ የዘመቻ ፥ የጠበ ፥ የጥል መሪ፡ የክርክር ጌታ ፥ ባለቤት ። ጋዘ ብለኸ ጋዝን እይ ።
አበ ጋዝነት፡ አበ ጋዝ መኾን ፥ ያበ ጋዝ ሹመት ። ጠጅ የሌለበት-አበጋዝነት እንዲሉ።
አበ ጋዞች፡ የጦር አለቆች ፥ ፊታውራሪዎች የአዝማቾች ።
አበለ ዋሻ፡ ዐበለ ።
አበለሰ፡ ኣበለዘ፡ በለስ፡ አስመሰለ ።
አበለሻሸ፡ (አደራራጊ)፡ አጣፋ፡ አጠፋፋ ። ማበለሻሸት፡ ማጣፋት፡ ማጠፋፋት ። አበለሻሸት፡ አጠፋፍ፡ መበላሸት ። በለሰሰ፡ ቅንድብን፡ ወደ፡ ታች፡ አለ፡ ገለጠጠ፡ በለጠጠ፡ ነጠለ፡ የውርዴነት ።
አበለቃቀጠ፡ ኣከፋፈተ አፈራቀቀ ።
አበለቃቀጥ፡ አለያየት አከፋፈት፡ መበልቀጥ ።
አበለዘ፡ ኣዘጐነ ዛጐል፡ አስመሰለ፡ እበረሰ አበለሰ ።
አበለገ፡ አዘነመ፡ በልግ ሰጠ ።
አበለጠ፡ አረዘመ አላቀ፡ አከበረ ከፍ አደረገ፡ አበዛ አፈደፈደ ። (መክ ፪ ፥ ፬) ።
አበለጠገ፡ አከበረ፡ አጌተየ፡ ሀብታም አደረገ ።
አበለጣጠጥ፡ አገላለጥ አከፋፈት፡ መበልጠጥ ።
አበለጥ፡ ያበለጠ ያበዛ ያፈደፈደ ። ዐውድማ ለመለጥ፡ ምስክር ላበለጥ ።
አበለጨ (አብረጸ)፡ አበራ፡ ብልጭ አደረገ፡ ገለጠ ።
አበለጬ ።
አበላ (አብልዐ)፡ አጐረሠ አዋጠ ሴሰየ መገበ አመሳ ። (ተረት)፡ ለሰው ልጅ ሲያበሉ ለውሻ ልጅ ያብሉ ። (ከዕርም አያበላም)፡ ያየውን የሰማውን በቶሎ ይናገራል ።
አበላ (ኣብልኀ)፡ አፈጠነ አሰላ አሾለ፡ ስለት አወጣ ። ኣፌን አበላኹ፡ አንደበቴን ኣሰላኹ፡ ትርጓሜ ሕዝቅኤል (፪ ፥ ፲፪) ። (ዐይጥ ኣበላ)፡ በገበጣ ጨዋታ አሸነፈ ። (ዐሩን ኣበላው)፡ ክፉኛ ደበደበው ።
አበላ ፈሳሽ፡ ዐበላ ።
አበላለት፡ አነጣጠል አለያየት አከፋፈል፡ መበለት ማደኸየት ።
አበላለዝ፡ አዘጓጐን አጠቋቈር፡ መብ ለዝ ።
አበላለጠ፡ አላላቀ አራዘመ ።
አበላለጥ፡ አስተዳደግ አላላቅ አረዛዘም፡ መብለጥ ብልጫ ብልጠት ።
አበላላ፡ አብላላ፡ መላልሶ አበላ፡ ብዙ ጊዜ እንዲበላ አደረገ፡ ምግብ አስደፈረ ። የበላን ያብላላዋል፡ የለበሰን ይበርደዋል እንዲሉ ።
አበላላጭ፡ ያበላለጠ የሚያበላልጥ የሚያላልቅ ።
አበላል፡ አጐራረሥ አስተኛኘክ አዋዋጥ፡ መብላት ። (ግጥም)፡ ከመከራ ኋላ ምክር መገኘቱ ዳቦዬ ተበላ ኣበላለ ከንቱ ።
አበላሸ አጠፋ፡ በለሸ ።
አበላሺ፡ ሽ፡ ያበላሸ፡ የሚያበላሽ፡ የሚ ያጠፋ፡ ኣጥፊ ። ስምንተኛው፡ ሺ፡ ሰው፡ አበ ላሺ፡ (መዝ፲፩፡ ፩፬) ። ጐረሠ፡ ብለኸ፡ ጐራሽን፡ ተመልከት ።
አበላቀጠ፡ አጋለጠ አለያየ ኣካፈተ አላቀቀ ።
አበላጩ፡ ደንጊያን በደንጊያ ገጯ መታ ሰበረ፡ አጋጨ አሳበረ አለያየ፡ ሻፎ አደረገ ።
አበል፡ ለሹም ለሠራተኛ የሚገባ ገንዘብ ወግ ።
አበል፡ ወግ (በላ) ።
አበሰ (አብሶ አበሰ)፡ በቁሙ፡ ጠረገ፡ እማጠጠ፡ ወለወለ ። (ኢሳ ፳፭ ፥ ፰ ። ሉቃ ፯ ፥ ፵) ። (ፊቱን በቅቤ አበሰ አወዛ) ። ዐሠሠን ተመልከት ። ተረቴን መልስ፡ አፌን በጨው አብስ ። የራሷን አበሳ በሰው አብሳ ። ጳጕሜ ቢወልስ ጐተራኸን እብስ ።
አበሰ፡ በደለ ፥ ደፈረ ፥ ከዳ፡ ኀጢአት ሠራ፡ ሲያውቅ በድፍረት ።
አበሰለ (አብሰለ)፡ ተኰሰ ጠበሰ ቀቀለ ጋገረ አነፈረ፡ አደረቀ ።
አበሰለ፡ በጣም ተማረ ።
አበሰለ፡ ዐየመ ቀበቀበ አለሰለሰ ዕር ሻን ።
አበሰለ፡ እጅግ ዐመመ ጐዳ፡ በሽታ ሰውን ።
አበሰቈለ፡ አጐሰቈለ ።
አበሰቋቈል፡ አጐሰቋቈል፡ መበስቈል ።
አበሰበሰ፡ አረጠበ አራሰ፡ በሶን በውሃ ዐሸ አገላበጠ፡ ለምግብነት አበጀ አዘጋጀ ።
አበሰበሰ፡ አበሸቀጠ አበላሸ ። (ዳን ፬ ፥ ፴፫) ።
አበሰና፡ ለወጠ አገማ አከረፋ ።
አበሰኛ (ኞች)፡ ያበሰ የበደለ ፥ ኃጥእ ወንጀለኛ ።
አበሰጪ፡ አጣላ አቋጣ አጋጨ ።
አበሰጫጩት፡ አስተዛዘን አቈጣጥ፡ መ በሳጨት ።
አበሳ፡ በቁሙ፡ ዕዳ ፥ በደል ፥ ጥፋት ፥ ኀጢ እት ፥ ክሕደት ።
አበሳሰል፡ አጐመራር፡ መብሰል ።
አበሳሰስ፡ አሰባበቅ መስበቅ ማሳበቅ ።
አበሳሰክ፡ ኣቈራረጥ አበጣጠስ፡ መበ ስክ ።
አበሳስ፡ ኣሰራሰር አፈላፈል አሸነቋቈር፡ መብሳት ።
አበሳበሰ፡ አራራሰ ኣስተሻሸ ።
አበሳበስ፡ አራራስ አረጣጠብ አሸጋገት አለዋወጥ፡ መራስ መበስበስ ።
አበሳውን ታይ ተቀበለ፡ (፩ጴጥ ፬ ፥ ፳) ።
አበሳጪ፡ ያበሳጩ የሚያበሳጭ የሚያስቈጣ፡ አሳዛኝ አስቈጪ ።
አበስ፡ ዝኒ ከማሁ ። ሀይቦ የሚባል በፊ ቀንዱ ሰማይ ጠቀስ፡ ጭራው ምድር ኣበስ እንዲሉ ።
አበስ ገበርኩ (አበሳ ገበርኩ)፡ በይልኹ፡ አጠፋኹ ።
አበስባሽ፡ ያበሰበሰ የሚያበሰብስ የሚ ያርስ ።
አበረ፡ አንድ ኾነ ዐበረ ።
አበረሰ (በረዘ)፡ ሻረ አጠፋ አረከሰ ።
አበረሰ፡ አበረደ አቀዘቀዘ ።
አበረረ፡ አሮጠ ኣከነፈ አስቸኰለ አጣደፈ አሸሸ አስጋለበ ።
አበረቀ (አብረቀ)፡ ብልጭ አደረገ አበራ አጸደለ አንጸባረቀ ።
አበረቃቀሰ፡ እበታተነ አለያየ ።
አበረቃቀስ፡ አነዳደል አጣጣስ፡ መበ ርቀስ ።
አበረቈጠ፡ አበረከተ አበዛ ጨመረ አከለ አረዘመ፡ ዐደሰ ። እከሌ ነገር ያበረቍ ጣል እንዲሉ ።
አበረቋ፡ አነጣ አገረጣ፡ አበሰለ አደረሰ ።
አበረታ፡ አጠና አጠነከረ አጐለበተ አባሰ ። (ሕዝ ፳፬ ፥ ፳፭) ።
አበረታታ፡ አጠናና አጠነካከረ ።
አበረከ (አብረከ)፡ በጕልበት አቆመ ራሱን ሰውነቱን ወይም ሌላውን ። በረከ ተንበረከከ፡ አበረከ አንበረከከ አንዳንድ ወገን ናቸው ።
አበረከተ፡ አቀረበ ሰጠ፡ ትንሹን እንደ ትልቅ ። (፩ሳሙ ፲፯ ፥ ፲፰) ። (ተረት)፡ መሶብ ሰፍቼ ለዐጤ አበርክቼ ።
አበረከተ፡ አበዛ አረባ፡ አተረፈ አፈደፈደ፡ አደለበ፡ ጥቂቱን ብዙ አደረገ፡ በጸሎት በታምራት ።
አበረካከት፡ አበዛዝ አደላለብ አረ ባብ፡ ብርከታ መበርከት ።
አበረየ፡ አበረገገ አወገሸ አበረረ ።
አበረደ፡ ጠብን ጥምን አስታገሠ ።
አበረደደ፡ አበረታ አጸና አከበደ ።
አበረዶ (አብረደ)፡ ኣቀዘቀዘ፡ በረዶ አደረገ ። እግዜር አለእሳት አነደደ፡ አለውሃ አበረደ ።
አበረገገ፡ አበረየ ገታ፡ ወደ ኋላ አለ ።
አበረጋገድ፡ አከፋፈት አከፋፈል፡ መበርገድ መፍለጥ ።
አበረጋገግ፡ አደነጋገጥ አደነባበር፡ መ በርገግ ።
አበራ (አብርሀ)፡ አሳየ ገለጠ አስረዳ ። (ማቴ ፲፯ ፥ ፪) ። ጨለማን አራቀ፡ ዐይንን አዳነ ።
አበራ፡ አንድ የውጭ አገር ሰው ላበደረው ኢትዮጵያዊ የሚከፍለው ቢያጣ ማታ መብራት ያዘ፡ (አታለለ) ።
አበራ፡ የሰው ስም ።
አበራረስ፡ አረካከስ አበራረድ አቀዛቀዝ፡ መብረስ ። በረዘና በረሰ አንድ ዘር ናቸው ።
አበራረር፡ አሯሯጥ አሸመጣጠጥ አጠዳደፍ፡ መብረር ። ፪ኛውን ብር እይ፡ የዚህ ዘር ነው ።
አበራረከ (አስተባረከ)፡ አመሰጋገነ አመራረቀ ።
አበራረክ፡ አመራረቅ አቀዳዶስ፡ መባ ረክ መቀደስ ።
አበራረደ፡ መላልሶ አበረዶ፡ እፍፍ አለ ።
አበራረድ፡ አቀዛቀዝ፡ መብረድ በረዶ መኾን ።
አበራር፡ ብርሃን መኾን፡ መብራት ።
አበራሽ፡ የሴት ስም ።
አበራበረ፡ አበዛበዘ አዛረፈ፡ ብርባሮ ረዳ፡ ኣገላበጠ ።
አበራበር፡ አበዛበዝ ኣወራረር አዘራረፍ ኣገለባበጥ፡ መበርበር መገልበጥ ።
አበራባሪ፡ ያበራበረ የሚያበራብር ።
አበራታ፡ አጣና አጠናከረ ።
አበራከተ፡ አባዛ አታረፈ አራባ አዋለደ ።
አበራካች፡ ያበራከተ የሚያበራከት የሚያባዛ ።
አበራየ፡ አኼደ ረገጠ፡ በነዶ ላይ በሬ ነዳ እዞረ ።
አበራየ ያውድማ፡ አረባየ የርሻ ነው ። ረበየን ተመልከት ።
አበራገገ፡ አደናገጠ ኣደናበረ ።
አበራገገ፡ አፈናከተ አሳበረ ።
አበርቋጭ፡ ያበረቈጠ የሚያበረቍጥ፡ ጨማሪ ነገር አብዢ ።
አበርባራ፡ የሳማ ዐይነት ፥ —በረ ።
አበርባራ፡ የሳማ ዐይነት ቅጠል፡ እንደ በርበሬ የሚለበልብ የሚያንገበግብ፡ ልጡ ገመድ የሚኾን ጋሎች ዶቢ የሚሉት ረዥም ሳማ ።
አበርቺ፡ ያበረታ የሚያበረታ የሚያጠና፡ መጥኔ ።
አበርካች፡ ያበረከተ የሚያበረክት የሚ ያደልብ፡ አድላቢ ።
አበርክታ፡ የምታበረክት፡ አበርካች ቈጣቢ፡ ጥቂቱን ብዙ የምታደርግ የምታብቃቃ ሴት ።
አበሸራረክ፡ አቀዳደድ አሸረካከት፡ መበሽረክ ።
አበሸቀ፡ አሳዘነ አበሳጨ አናደደ ።
አበሸቀጠ፡ ፈጽሞ አራሰ አረሰረሰ አበሰበሰ አበከተ፡ አረከሰ ።
አበሸቃቀጠ፡ አነቃቀፈ አሰዳደበ ።
አበሸቃቀጥ፡ አረሳረስ መበሽቀጥ ።
አበሻ፡ የነገድ ስም ፥ —ሐበሻ ።
አበሻቀጠ፡ ናቀ ነቀፈ አቃለለ፡ ኣጸየፈ አዋረደ አራከሰ ።
አበሻቃጭ፡ ያበሻቀጠ የሚያበሻቅጥ፡ አቃላይ አዋራጅ ።
አበሽቃጭ፡ ያበሸቀጠ የሚያበሸቅጥ የሚያርስ፡ አጸያፊ አርካሽ ዋረጃ ።
አበቀ፡ በኀይል ወጋ ። እቶ እከሌ ደህናውን እዱር ቢያገኘው በጦር እበቀው ።
አበቀ፡ ታመመ፡ ከከ፡ (ግእዝ) ።
አበቀ፡ እደቀቀ ፥ ዐመቀ ፥ መረ መላ ረጠጠ፡ እብቅን ፥ ዶቄትን ፥ ኣሸዋን ፥ ደቃቅ ነገርን ኹሉ። (ምን ላብቅበት)፡ ልጫምርበት ፥ ለምላበት ረጣ ።
አበቀለ (አብቈለ)፡ አቀነቀነ አቀመቀመ፡ አጐመጐመ አወጣ አሠረጸ፡ አጸደቀ፡ አስገኘ ። ጥል አበቀለ እንዲሉ ። መጣ ብለኸ ፪ኛውን መጭ እይ ። (ሕዝ ፴፩ ፥ ፬) ።
አበቀለ፡ ጨለለ ።
አበቃ (አብቍዐ)፡ ጠገበ ተወ ፲አ ደረሰ ጨረሰ ። (በልቶ ሲያበቃ)፡ ሲጠግብ ሲጨርስ ሲተው ። (ሰው ለመኾን ቢያበቃኝ)፡ ቢያደርሰኝ ።
አበቃ፡ ደከመ አረጀ አፈጀ አረፈቀ (ተገብሮ) ።
አበቃ፡ ጻድቅ ቅዱስ ፍጹም ኣደረገ (ገቢር) ።
አበቃቀለ፡ መላልሶ አበቀለ ።
አበቃቀል፡ አወጣጥ አጸዳደቅ፡ መብቀል ።
አበቃቀት፡ አነዛነዝ፡ መበቀት ። ኦሮም በቀቴ ብሎ ሸሸ ይላል ።
አበቃቃ (አብቃቃ)፡ የአበቃ ድርብ፡ እንዳያንስ እንዳይጐድል ጥቂቱን እንደ ብዙ አደረገ፡ አስተነተነ ። ፈጀ ብለኸ አፍጃጀን ተመልከት ።
አበቃቅ፡ አስተዳደግ አጠቃቀም፡ መብቃት ። አከለን ጠቀመን ረባን አንቃን እይ ።
አበቅ፡ እብቅ፡ ነጭ ዕከክ፡ (ግእዝ) ። (ዳን ፪ ፥ ፬፭) ። ፎከተን ተመልከት ።
አበቅቴ፡ ጭማሪ ተውሳክ፡ የቍጥር ማማያ ማስተካከያ (ያመት ትራፊ ትርፍ ፍድፋጅ) ። አበቅቴና መጥቅ እንዲሉ በረ ።
አበበ፡ (አቢብ አበ ጸገየ)፡ ፈካ ፥ ፈነዳ፡ እበባ ያዘ፡ ለበሰ፡ ሳበባ፡ አጌጠ ፥ ተሸለመ ፥ ተቀዳጀ፡ አማረ ፥ ደመቀ ፥ አሸበረቀ፡ ለማፍራት ሰመውለድ፡ የዓት የትክቶ (ግዳጅ)፡ የሙሽራ የልብስ የጌጥ (መክ ፲፪ - ፳) ። (ማሕ ፪ ፥ ፲፪ ። ፪ ፥ ፲፫ ። ሕዝ ፯፡ ፲ ፱) ። (ግጥም)፡ አበበች መስከረም ጠባቕ ። እቴ ሸንኰሬ፡ ጕላሽ አብቧል፡ ዛሬ አባና አብ የአበበ ዘሮች ናቸው ።
አበበ፡ የሴት ልጅ ስም ።
አበበ፡ የወንድ መጠሪያ ስም ። አበበ አረጋይ አበባ ቢቂላ እንዲሉ ።
አበበች፡ የሴት መጠሪያ ስም ።
አበቡት፡ ይህ በእንስት ሲነገር ነው ። አበቡቴ አበባ የተቀረጸባት ትንሽ ጠብኛ ዳቦ ። ቈሎባቡቴ ቢል ግን እንደ ዔሊ ያለች እንክብል ኀብስት ማለት ነው ። አበቡቴ ነጭ የቈላ ስንዴ፡ ጣይ ሶፊ ያቡን እግር ።
አበቢላ (አበባ ላቲ)፡ አበባ አላት፡ ያበባ ባላሰባ ። አበቢላ የመስከረም ጠላ እንዲሉ።
አበባ፡ (በቁሙ) ጽጌ፡ ከፍሬ የሚቀድም የዕፀዋት ጌጥ፡ (ማሕ ፪ ፥ ፲፪) ። ሻሽን እይ ። አበባዬ ሆይ አበባዬ፡ ርግፍ በሸማዬ ። አበባ ስቫ ስሻ ስሻ፡ ሊበላኝ ነበር የባብ ውሻ ። አበባ ስሻ በየዱሩ፡ ባልንጀሮቼ ወልደው ዳሩ ። (ልጃገረዶች የንቍጣጣሽ ለት) ። አበባዬ አበባዬ ሆዬ፡ መስከረም ጠባዬ እንዲሉ ወንዶች የደመራ ለቅ ። (ተረት)፡ ላበባ የለው ገለባ ።
አበባ፡ (ትክቶ) ግዳጅ፡ ልጅ ። አበባሽ በሳ ፥ አልል ብዬ ልግባ እንዲል የመስቀል ዘፋኝ ።
አበባ ምንጣፍ፡ አበባ ያለበት የተሣለበት የተጠለፈበት ምንጣፍ ስጋጃ ።
አበባ ሸያጭ (ጮች)፡ አበባን ችቦና ማቶት አክሊል እያስመሰለ የሚሼጥ ያበባ ነጋዴ ። በፈረንጅኛ ፍሎሪስት ይባላል ።
አበባ፡ ታላቅ እት ። እቴ አበባሽ ። አቴ አበባዬ እዩ ። እቴ አበባዬ እንዲሉ ልጃገረዶች ።
አበባም፡ ዐደይን ፥ ጽጌ ፥ ረዳን የመሰለ ማንኛውም ቍጥቋጦ ወይም ዛፍ አበባ እየተናበበ የዘርፍነትና የቅጽል እፈታት ይፈታል ። አበባ ጎመን፡ ኣበባ ያለው ባላበባ (የባሕር ጎመን) ።
አበባዊት፡ (የኔ አበባ ማለት ነው) ።
አበባዋ፡ አበባዬቱ፡ ያች አበባ ፥ አበባዋ፡ የርሷ አበባ ።
አበባው፡ ያ አበባ ፥ የርሱ አበባ ።
አበቦች፡ በቁሙ አበባ ቅርጾች ጌጦች፡ (ማቴ ፮ ፥ ፳፰ ። ሉቃ ፲፪ ፥ ፳፯ ። ፩ነገ ፲ ፥ ፰) ።
አበተ (ዕብ ዐቤት ወፈቀ ጨመረ)፡ በቁሙ፡ ጠለፈ ፥ ኣሰረ ፥ አንጠለጠለ ፥ ሰቀለ ።
አበተ፡ አባባ አለ፡ አባት አደረገ ።
አበተ፡ አባባ እለ አበታ፡ ታላቅ ጦር ቅጠለ ሰፊ ያባት ምስጢር አለበት ። አበታ ጦር እንዲሉ። ለሰውም ይነገራል። በጦርነት ጊዜ አሰታ አበታው ዐልቆ ጭንጋፍ ጭንጋፉ ይቀራል ።
አበተሬ፡ መተሬ ።
አበታተነ፡ አዘራዘረ አራጩ አፈና ጠቀ ።
አበታተከ፡ አበጣጠሰ ኣቈራረጠ ።
አበታተክ፡ አቈራረጥ፡ መበሰክ፡ ቈረጣ ብጠሳ ።
አበት፡ ታናሽ የሚዛን ። ከ ፪ አበት ፩ ተረን፡ ፪ ተረን ፩ ቀመት ፲፬ ቍሙት ፩ ድሪም ፲፭ ድሪም ፩ እላድ፡ ፪ አላድ ፩ ወቄት ነው ይላል ጕይዲ ።
አበነነ አቦነነ አተነነ ኣበለለ፡ አጨሰ ለነፋስ ሰጠ አጠፋ ።
አበነነ, አስወገደ ትቢያን ("(ሉቃ. ፲፥ ፲፩)") - ትቢያን አበነነ/አስወገደ ("(ሉቃ. 10፡ 11)"). "ሌላው መጽሐፍ ግን በእራገፈ ፈንታ አረፈ ይላል" ("(ነሐ. ፭፥ ፲፫ ። ማቴ. ፲፥ ፲፬)") - ሌላው መጽሐፍ ግን በእራገፈ ፈንታ አረፈ ይላል (ነህ. 5፡ 13፡ ማቴ. 10፡ 14)").
አበናነን፡ አጠፋፍ መብነን መበተን ።
አበከረ (አብኰረ)፡ ወንድ ሴትን ተወ፡ ተራክቦን አቈረጠ ።
አበከረ፡ ሥጋ ማሪያም አጠለቀ ።
አበከረች (አብኰረት)፡ ወንድ ተወች፡ ምንኵስና ፈለገች ።
አበከተ፡ ተዝካር ሳይበላ ቀረ፡ አበላሸ ።
አበከተ፡ አራሰ አበሸቀጠ አገማ አሸተተ ።
አበከከ፡ አፈረሰ፡ አበላሸ ።
አበካከል፡ አኰላለፍ፡ መበከል።
አበካከር፡ አወላለድ፡ ማብከር ።
አበካከት፡ አራራስ አበሳበስ፡ መብከት ። በተከን እይ፡ በከተ ያማርኛ፡ በተከ የግእዝ ነው ።
አበካከነ፡ አቅበዘበዘ አጐዳደለ በተነ ።
አበካከን፡ አበታተን አዘራር፡ መባከን ማባከን ።
አበዛ (ኣብዝኀ)፡ አተረፈ አፈደፈደ አረባ አበረከተ ። አማረንን እይ ።
አበዛ፡ ጋጋሪ፡ ዐበዘ ።
አበዛበዘ፡ አዛረፈ አቃማ ።
አበዛዘቅ፡ አዘበራረቅ፡ መባዘቅ ።
አበዛዘት፡ አፈለቃቀቅ አቦጫጨቅ መ ባዘት ማባዘት ።
አበዛዝ፡ አረባብ አወላለድ አበረካከት፡ መብዛት ።
አበዣገደ፡ አሳሳተ ቅጥ አሳጣ ።
አበያየድ፡ አደላለዝ አመራረግ አደፋ ፈን፡ መበየድ ።
አበይ፡ ሌሊት ከ፲ እስከ ፲፪ ሰዓት ከብት ጠባቂ ዘበኛ ። ጊዜውም ኣበይ ይባላል ።
አበደ፡ (አቢድ አብደ)፡ በቁሙ፡ ኽ ተቈጣ፡ አእምሮ ወጣ፡ ተማረ፡ ላባና ስሪቱ በራሱ ላይ ሻጠ ወበሸ ተነሣሣ፡ አፈፍ አፈፍ አለ፡ ወፈፈጠፋ፡ ተበላሸ ልቡና ላው፡ ራሱ ዞረ፡ ከስካርና ከበሽታ ካስማት ከመዳኒት የተነሣ ልብሱን ጣለ፡ ሮጠ ሓረጠጠ ። (ኤር ፶፩ ፥ ፯ ። ሉቃ ፰ ፥ ፴፫ ። ግብ ሐዋ ፳፮ ፥ ፳፬ ፥ ፳፩) ። ኳስ አበደች እንዲሉ ። ወፈፌን እይ ። አበደበት፡ ጮኸበት ፥ ተቈጣው ። አበደ ሰንጋ አለ፡ ጠብ እነሣ ።
አበደረ (አብደረ)፡ ዐረጠ አለቃ ሰጠ፡ አጋደደ አዋሰ ። (ዘዳ ፳፰ ፥ ፲፪ ። ሉቃ ፮ ፥ ፴፭) ።
አበደረ፡ አለቃ፡ በደረ ።
አበደነ (አብደነ)፡ አፈዘዘ አደነዘዘ፡ ሬሳ አደረገ ።
አበዳሪ (ሮች)፡ ያበደረ የሚያበድር የሚያርጥ የሚያጋድድ የሚያውስ ። (ምሳ ፳፪ ፥ ፯ ። ኢሳ ፳፬ ፥ ፪ ። ሉቃ ፯ ፥ ፵፩) ።
አበዳደለ፡ አጐዳዳ አጨቋቈነ ።
አበዳደል፡ አስተማመፅ አገፋፍ፡ መበ ደል ።
አበዳደረ (አስተባደረ)፡ አዋዋለ አስማማ አቀባበለ ።
አበዳደረ፡ መላልሶ አበደረ ።
አበዳደር፡ አለቃቅ፡ ማበደር መበደር ።
አበዳደን፡ አፈዛዘዝ፡ መብደን፡ በድንነት ።
አበድ፡ ዝኒ ከማሁ፡ የሚጮኸ የሚለፈልፍ፡ ሲያውቅ አበድ እንዲሉ ።
አበጀ፡ ሠራ አዘጋጀ አሰመረ አሳመረ አስዋበ ። (ኢሳ ፷፩ ፥ ፭ ። ዕብ ፲፩ ፥ ፯) ። (ተረት)፡ አባት ያበጀው ለልጅ ይበጀው ። አንቺ አበጀሽ አበጀሽ ዛሬ እንዲል ሰርገኛ ። አበጀ፡ ደግ አደረገ ። (አላበጀም)፡ ደግ አልሠራም፡ አጥፍቷል ።
አበጀ፡ የሰው ስም ።
አበጀኹ፡ እንኳን ሠራኹ ። ባል ብለኸ ባለጊዜን እይ ።
አበጃጀ፡ መላልሶ ሠራ እሰማመረ አከናወነ ኣሻሻለ ።
አበጃጀት፡ አሠራር አከናወን፡ ማበጀት በጀ ማለት እጅን ያሳያል ።
አበገነ፡ አደረቀ አከረረ፡ አገመነ አሳረረ ።
አበገደ፡ ከሰላማ በፊት የነበረ ጥንታዊ የግእዝ ፊደል ።
አበጋበግ፡ አገራረፍ፡ መበግበግ ።
አበጋዝ፡ አባያ ።
አበጋዝ የጦር አለቃ ።
አበጋገር፡ አሞካከር አፈታተን አነዳደፍ አመጣጠን፡ መበገር መድፈር ።
አበጋገን፡ አደራረቅ አከራረር አገማ መን፡ መብገን ። በገነ ያማርኛ፡ ገመነ የግእዝ ነው ።
አበጠ፡ ተቀበተተ ወበጠ ።
አበጠለለ (አባጠለ)፡ አባጩ ነቀፈ አጸየፈ ።
አበጠረ፡ አነፈሰ አጠራ እኸልን፡ ስንዴን ከንክርዳድ ገብስን ከሲናር ለየ ። መየደ አጐተነ አቆመ፡ ጠጕርን ።
አበጠራረቅ፡ አነዳደል አበሳስ፡ መበ ጥረቅ ።
አበጣሪ፡ ያበጠረ የሚያበጥር፡ የሚያነፍስ፡ መያጅ ተን ።
አበጣበጠ፡ አጣመቀ አባረዘ አማታ፡ አጣላ አፋጀ ።
አበጣበጥ፡ አጠማመቅ አበራረዝ፡ ብጥበጣ መበጥበጥ ።
አበጣጠሰ፡ አቈራረጠ፡ አጣላ አለያየ ።
አበጣጠስ፡ ኣቈራረጥ፡ መበጠስ ።
አበጣጠረ፡ አነጣጠረ አነጋገረ አለ ያየ ።
አበጣጠር፡ አነፋፈስ አነቃቀስ፡ ማበጠር ። አበጠረ በሰፌድ፡ አነፈሰ በነፋስና በትን ፋሽም ጭምር ነው ።
አበጣጣሽ፡ ያበጣጠሰ የሚያበጣጥስ፡ አቈራራጭ አሳባቂ ።
አበጣጥ፡ አፈቃቅ አቈራር አተፋተፍ አሠነታተር፡ መብጣት ።
አበጨጨ፡ ብጫ አስመሰለ አወረቀ ።
አቡ መቀስ፡ ባለመቀስ፡ የመቀስ ጌታ፡ እግሩና እጁ እንደ መቀስ ያለ ጐርምጥ ፥ ሸርጣን ፥ የባሕር ተንቀሳቃሽ ።
አቡ ሻህር፡ ባለወር ፥ ወር ቈጣሪ፡ የወር ጌታ መጽሐፍ፡ የመጽሐፍ ስም።
አቡ ቅዳዴ፡ ባለቅዳጅ፡ የቅዳጅ ጌታ ። በራሱ ሳይ ቀይ የሚያስር የተሸለ ሐርበኛ ወታደር፡ ዐላማ የሚጠመጥም ዝኆን ግዳይ በወገቧ ብ የምትታጠቅ የዝኆንግዳይ ሚስት ።
አቡ፡ አቢ፡ አባ፡ አብ፡ አባት ፥ ባለቤት ፥ ጌታ ፥ አዛዥ ። አራቱ ኹሉ እየተናበበ ይነገራሉ። ባልን ተመልከት ። አብ እንደ ግእዝ ልማድ ዘርፍ ይዞ ሲነገር ።
አቡ ጀዲድ፡ ባላዲስ ፥ ዐዲስ ልብስ ።
አቡ ጀጂ፡ ባለፍየል፡ የፍየል ጥቦት በላዬ ያለበት የተሣለበት ልብስ ከባሕር የመጣ ። በአረብኛ ማን አቡ አባቴ ማለት ነው ።
አቡነ (አቡ አብ)፡ አባታችን ጌታችን ያስተማረው ጸሎት መዠመሪያ ። አባታችን የተባለም እግዜር ነው ።
አቡነ ሰላማ፡ ከሣቴ ብርሃን ፍሬምናጦስ፡ ብርሃነ ኣብ ካልእ ሰላማ ።
አቡነ ቀሲስ (ቀሲሰ አቡን)፡ የአቡን ቄስ እስነባቢ ቄሳሹንና ዛቋኙን የሚመረምር በግእዝ ንባብ ።
አቡነ አረጋይ፡ ዘሚካኤል (የደብረ ዳሞው) ።
አቡነ ዘለብ (እቡ ዘነብ)፡ ባለዘለበት ወዴላ ባለዥራት ። ዘሐብን እይ ።
አቡነ ዘበሰማያት፡ በሰማዮች የምትኖር አባታችን ። ይኸውም የጸሎት ኹሉ መጨረሻና መደምደሚያ ነው ።
አቡነ ዜና ማርቆስ፡ የሞረቱ የደብሩ ።
አቡን፡ አስቀድሞ እየተነገረ የስም ቅጽል ሲኾን መንፈሳዊ አባትነትና መምርነት ምንኵስና ቅስና ቅድስና ላለው ይነገራል ።
አቡን አቡን አለ፡ አቡነ ዘበሰ ማያትን ደገመ ፥ ዘከረ ፥ አሳረገ ።
አቡን፡ የዜማ ስም፡ የድጓ መዝሙር ።
አቡን፡ የጳጳስና የኤጲስቆጶስ ስም፡ ፍች አባት ። ያቡን የ ጌ ከብት በየወገኑ ይከተት ።
አቡንነት፡ አቡን መኾን፡ ጳጳስነት ።
አቡኖች፡ አባቶች ፥ ጳጳሶች ።
አቡዳ፡ የተማሪ ዕዳ እንዲሉ።
አቡድ (ዐረ አብየድ)፡ ባንኮበር ሚካኤል የሚገኝ ነጭ የፍየል በጐዛ ከባሕር የመጣ ደረ ።
አቡጊዳ፡ ዝኒ ከማሁ (መነሻውን ሳይለብጥ ሌላውን በማሰፍኖ - በማነቅ የተጸፈ) ።
አቢ ላም፡ (አበ ላሕም)፡ ሰለላም ላም ፥ ዐሳቢ ፥ ላም ጠባቂ እረኛ የላም ጌታ ሹም (ጸሓፌ ላሕም) ። ሲበዛ አቢ ላሞች ይላል ። በዕብራይስጥና በአረብኛ ግን አቢ እባቴ ማለት ነው ።
አቢሲኒያ (አቢሳዊ)፡ የአቢስ (ያ ማራ) አገር፡ ሐበሻ ። ይኸውም ስም ከ፸ ሊቃናት በፊት ነበረ ። አቢሲኒያ ማለት ፈረንጅኛ ነው ።
አቢስ አቢሳ (ከለው)፡ የሰው ስም፡ የኵሽ ሰባተኛ ልጁ፡ የናምሩድ ታናሽ፡ የነ ሂድ ስም ።
አቢብ፡ የስውስም አሳ ቡላ፡ ፍችው የሚያብብ የሚያፈራ ። አቡነ አቢብ እንዲሉ።
አባ ሆይ፡ (ቃለ አክብሮና የስም ምትክ ለቅርብ መነኵሴ) ። አባ ሆይ ትወዱኛለኾይ፡ እንዳል ታቦት ዘፋኝ ።
አባ ለነፍሱ፡ መንፈሳዊ (መናኝ መነሲ) ።
አባ ለከርሡ፡ ሥጋዊ ዓለማዊ መነኵሴ ።
አባ መላ፡ (የውቀት የጥበብ የማስተዋል ባለቤት) ። አባ ምኑ ታውቆ ያዘው ።
አባ፡ መነኲሴ፡ የመነኵሴ ስም፡ ፍችው አባት ። (ተረት)፡ ለይቶት አባ ንጉሧ ። አባ ሲኖበብ የፈረስ ስም ፥ ሳይናበብ የስም ቅጽል ይኾናል ።
አባ ሞገድ፡ ሞገደኛ ፥ ኀይለኛ ፥ እልከኛ ሰው ።
አባ ሰላማ፡ (ቅጽል)፡ መዠመሪያ የኢትዮጵያ ሐዋርያ ቅዱስ ፍሬምናጦስ ከሣቴ ብርሃነ ። በዚህ ጊዜ አባ አባት መነኵሴ ተብሎ ይተረጐማል ።
አባ ሰላማ፡ ንኡስ ዕላማ ፥ ብርሃነ አዜብ ባጤ ሰይፈ አርዓድ ጊዜ ወደ ሐበሻ የመጣ ጳጳስ ።
አባ ሰራን፡ የሰራን ባለቤት ፥ የሰራን ጌታ ።
አባ ሰንጋ፡ የሰንጋ ባለቤት (ሰንጋ ገባሪ) ። በሰንጋ (ፈረስ) ተቀምጦ ርስቱን ስለሚካለል የኦሮው ባላባትነት አባ ሰንጋ ተባለ ። ዳማን እይ ።
አባ ሰንጋ፡ ድንገተኛ በሽታ መጋኛ ።
አባ ሰይጣን፡ የሰይጣን ጌታ ፥ ደጃች ወልደ ገብሬ ።
አባ ሰጕድ፡ የሰጕድ ባለቤት፡ ንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ ።
አባ ሻንቆ፡ የሻንቆ ጌታ፡ ንጉሥ ሚካኤል።
አባ ሻውል፡ የሰው ስም፡ የሻውል አባት ፥ የሻውል አዛዥ ማለቅ ነው ።
አባ ቀማው፡ የሺዋ ክፍል ባላባት ራስ ቢትወደድ ተሰማ ።
አባ ቀማው፡ የቀማው ጌታ የጐዣም ባላባት ራስ ደስታ ።
አባ ቀስቅስ፡ ልዑል ራስ እምሩ ኀይለ ሥላሴ ።
አባ ቀስቅስ፡ የቀስቅስ ጌታ፡ ልዑል ራስ ካሳ ኀይሉ ።
አባ ቃኘው፡ ልዑል ራስ መኰንን (የቃኘው ባለቤት) ።
አባ በዝብዝ፡ ዮሐንስ ርባና ቢስ ፈሎ ወይም ሌላ አይረባ፡ የበዝብዝ ጌታ ፥ ዐጤ ።
አባ ቡላ፡ (ቅጽል)፡ ቡላ (ጳውሎስ) የሚባል እንደኛ መዠመሪያ የክርስቲያን ባሕታዊ ፥ የባሕታዊዎች አባት ። አቢብን እይ ።
አባ ቢላዋ፡ ባለቢላዋ፡ የቢላዋ ጌታ፡ በጕያው ቢሳዋ ደብቆ የያዘ ባለሾተል ። ፈነ ከተ ብለሽ ፍንክችን አስተውል ።
አባ ባሕርይ፡ የኦሮን ታሪክ በግእዝ የጻፈ፡ የብርብር ማሪያም መነኵሴ ዘ ።
አባ ብያ፡ ያገር አባት ፥ ዋኖ ያገር ቀንድ ፥ አሳዳሪ የጕልማሳ ጌታ ። ብያን ተመልከት ። (ግጥም)፡ ዐማቻችን አባ ብያ ነው፡ አባ ብያ ዐመድ ይቅማል እንዴህያ ።
አባ ተክሌ፡ (ቅጽል)፡ አቡነ ተከለ ሃይማኖት የእቲሳው ጻድቅ መነኵሴ፡ በ፯፻ ዓመተ ምሕረት የነበሩ ። አባዬን እይ ።
አባ ታቦር፡ የታቦር ጌታ፡ ደጃች አባ ታቦር (የመጠሪያ ስም) ።
አባ ታጠቅ፡ የታጠቅ ባለቤት (የታጠቅ ጌታ) ዐጤ ቴዎድሮስ ። ከዚህ የቀረውን የፈረስ ስም ክቡር ብላቴን ጌታ ኅሩይ በጻፉት የሕይወት ታሪክ ተመልከት ።
አባ ነብሮ፡ የነብሮ ባለቤት ፥ ፊታውራሪ አባ ነብሮ (የመጠሪያ ስም) ።
አባ ነጋ፡ የነጋ ጌታ ራስ አሉላ ።
አባ ነፍሶ፡ የነፍሶ ባለቤት ደጃች ባልቻ ምዷታቸውንም ያሳያል ። ሮዛ አብ አበበ ።
አባ ናዳ፡ የናዳ ባለቤት እቶ ክብረት የመራቤቴ ሐርበኛ ።
አባ ንፋው፡ የንፋው ጌታ፡ ወሬኛ ፥ ወፊ ወዳድ ።
አባ አይረባ፡ ቢስ ፥ ዓለመኛ መነኵሴ ለአባ ቅጽል ነው ።
አባ ኵራራ፡ የራራ ጌታ፡ የደራ ባላባት ወሰኑ ወዳጅ ። ዳሌን እይ ።
አባ ክብሪት፡ ቍጡ ትንታግ መነኵሴ ወይም ሌላ ።
አባ ኰራን፡ የኰራን ባለቤት ፊታውራሪ አባ ኰራን (የመጠሪያ ስም) ።
አባ ወራ፡ ባለቤት ፥ የቤት ጌታ ፥ ኣሳዳሪ ፥ ቤት አባት፡ (ጋልኛ) ። (ግጥም)፡ አባ ወራሽ ክፉ ውሻሽ ፥ ተናካሽ፡ ሹልክ ብዬ ልግባ ባተካሪስሽ ።
አባ ዋጠው፡ የዋጠው ጌታ የወሎ ባላባት ።
አባ ዘባሪቆ፡ (ዘባራቂ)፡ ሲናገር የሚዘባርቅ ሰው ።
አባ ዝናብ፡ የዝናብ ጌታ (ቸር ሊጋስ) ።
አባ ይትረፍ፡ የይትረፍ ጌታ (ቸር) ራስ አባተ ።
አባ ደልድል፡ የደልድል ባለቤት ራስ ዘውዴ ።
አባ ደበሎ፡ ዶበሎ ለባሽ መነኵሴ ።
አባ ደባደቦ፡ ድሪቷም ባለድሪቶ ።
አባ ደፋር፡ የደፋር እባት ዓለማዊ ሰው ወይም መነኵሴ ።
አባ ዱላ፡ አብ ጋዝ፡ የዘመቻ ጌታ ባለዘመቻ የጦር አዛዥ ፥ አዝማች (ጋልኛ አባ ደላጎ፡ ደላጎ ለባሽ ባለደላጎ መነኵሴ) ።
አባ ዲና፡ የዲና ጌታ፡ ሣህለ ሥላሴ ንጉሡ ሺዋ ።
አባ ዳማ፡ የዳማ ጌታ አፌ ንጉሥ ነሲቡ ። በርበሬ የሚመስል ቅጠል ዐረም፡ አቀንጭራ ድኻ ነቀል አንበጣ ዐራሽ ። ሐረርጌዎች ዐረመ ባልቻ ይሉታል ።
አባ ዳምጠው፡ የዳምጠው ባለቤት ኀይለ መለኮት ንጉሠ ሺዋ ።
አባ ዳኛው፡ የዳኛው ባለቤት ዐጤ ምኒልክ ።
አባ ድክር፡ የድክር ጌታ ፥ ኣቶ በዛብኸ ።
አባ ጅፋር፡ የጅፋር ጌታ ባላባት (የጅማ አባ ጅፋር እንዲሉ) ። ጌጣም ባለጌጥ ማለት ነው ።
አባ ገሥጥ፡ የጎሥጥ ጌታ፡ የግጥ ባለቤት ራስ ። አበበ አረጋይ አባ ግራኝ ! የግራኝ ጌታ (እንደ ግራኝ ያለ ጐበዝ ግራ ቀኙ (ቅዱስ ገብርኤል) የደጃች ሰባ ጋዲስ ፈረስ ስም ነው ይላሉ ። አባ ግራኝ ሞተ የሆዴ ወዳጅ የሚያበላኝ ሥጋ የሚያጠጣኝ ጠጅ እንዳለ በገና መቺ ።
አባ ጊዮርጊስ፡ (ቅጽል) የኢትዮጵያ ተወላጅና ሊቅ ባለብዙ ድርሰት፡ አገራቸው ጋሥጫ (ዐምባሰል) ።
አባ ጋተው፡ የጋተው ባለቤት ፥ ቀኛዝማች መኰንን ወልደ ገብሬ ።
አባ ግርሻ፡ የግርሻ ጌታ ራስ ዳርጌ ።
አባ ጐማዴ፡ ስልብ መነኵሴ ።
አባ ጐንዳ (ቈማጣ)፡ የቈማ አለቃ ፥ የጁና የግሩ ት ረግፎ ግንዶሹ ብቻ የቀረ፡ ላሊበላ ።
አባ ጠቅል፡ የጠቅል ጌታ፡ የጠቅል ባለቤት ፥ ቀዳማዊ ዐጤ ኀይለ ሥላሴ ።
አባ ጠና፡ የጠና ባለቤት ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ፥ ደጃች ይልማ ፥ መኰንን ።
አባ ጠጣው፡ የጠጣው ባለቤት ራስ ወሌ ።
አባ ጢጋዛብ፡ አባ ቅጽል ፥ ጢጋዛብ ስም ። ጠጋኝ እይ ።
አባ ጣለው፡ የጣለው ጌታ ጐበዝ (ጋኔን) ።
አባ ጣርማ፡ እባ ሕፃን ሞአ የደብረ በግዑ ። አባ ጣርማ ያማርኛ፡ ሕፃንሞአ የግእዝ ስም ነው ። ከበሬ ጋራ ተጠምደው ምስት ፌር ስላወጡ አባ ጣርማ ተባሉ። ጣርማን እይ ።
አባ ጥጉ፡ የጥጉ ጌታ፡ የጥጉ ባለቤት ራስ ጐበና ።
አባ ጨብራሬ፡ ጠጕራም ትል፡ ባለ ጠጕር ። (አባ ጨጓሬ) ።
አባ ጨጓሬ፡ ጭገራም ትል፡ ጠጕሩ እንደ ጨጓራ የኾነ ። (አባ ጨብራራ) ።
አባለ፡ ዘር፡ ኅፍረት፡ የወንድ ብልት፡ ሙርጥ ። በግእዝ አባለ ዘርዕ ይባላል፡ የዘር ብልት ዘር የሚዘራ ማለት ነው ።
አባለቀ፡ አጠለቀ፡ አፈለቀ፡ ዘር አርፈሰሰ ።
አባለተ፡ ዐሠሠ ወለወለ ዐደፈ ።
አባለገ፡ ባለጌ አደረገ፡ ሳይቀጣ አሳደገ፡ አበላሸ ከሕግ አራቀ አስወገደ ።
አባለጠ፡ አዛነፈ ።
አባላ (አስተባልዐ)፡ አያያዘ አናከሰ አጋመጠ አናጪ አቋረሰ ።
አባላ መታ፡ ቋንዣ ቈረጠ ተከበሰ ። (መቃ ፭ - ፲) ።
አባላ ቋንዣ፡ ፩ዋና የደም ሥር ።
አባላ ተመታ፡ ቋንዣው ተቈረጠ ። (ለመቃ ፲፯ ፥ ፬) ።
አባላሽኝ፡ ችጋር፡ ዘመነ ረኃብ ። ሴት ባሏን ስላናፈገችው ነው ይባላል ።
አባላጊ፡ ያባለገ የሚያባልግ ።
አባሎ፡ የንጨት ስም ፍልው፡ ለጠላና ለወተት ዕቃ የሚታጠን ዛፍ ።
አባሰ (አብአሰ)፡ አጠና አከፋ፡ ክፉ መጥፎ አደረገ ።
አባሰለ፡ አቃቀለ፡ አጋገረ አጣበሰ ።
አባሳ፡ አሸናቈረ አናደለ አቃደደ ።
አባረረ (አበረረ)፡ አሳደደ አሸሸ አከነፈ ። (ዘፀ ፲፬ ፥ ፱ ። መሳ ፬ ፥ ፲፮ ። ኢሳ ፷፮ ፥ ፭) ።
አባረቀ፡ ተኰሰ አጮኸ ። ሆድን በጥ ይት በካራ በጦር አማሰለ፡ አበላሸ ቀደደ ።
አባረከ (አስተባረከ)፡ አቃደሰ አማረቀ ።
አባረዘ፡ አቀላቀለ አደባለቀ አካለሰ ።
አባረደ፡ አባረዘ አቀዛቀዘ፡ አዳከመ ።
አባራ፡ አቆመ፡ ቀጥ ተግ አደረገ ። ዝናሙ አባራ እንዲሉ ። ልማዱ ግን ተገብሮ ነው ።
አባራሪ (ዎች)፡ ያባረረ የሚያባርር የሚያሸሽ፡ አሳዳጅ አጣዳፊ አሸናፊ ። አባራሪ ጐበዝ እንዲሉ ።
አባራሪነት፡ አባራሪ መኾን፡ ጕብዝና ጐበዝነት ሐርበኛነት ።
አባራኪ፡ ያባረከ የሚያባርክ፡ አቃዳሽ ።
አባራዥ፡ ያባረዘ የሚያባርዝ፡ አቀላቃይ ።
አባሽ (አባሲ)፡ ያበሰ የሚያብስ፡ ጠራፂ በዳይ ።
አባሽ (አብኣሲ)፡ ያባሰ የሚያብስ የሚያበረታ ።
አባቀተ፡ አጨቃጨቀ አነታረከ ።
አባቍልቶች (ትግ አባቅል)፡ በቅ ሎዎች ። (፩ነገ ፬ ፥ ፳፰) ።
አባቂ፡ የሚያባቃ የሚያሰላች ። አበቀንን ተመልከት ።
አባቂ፡ ያበቀ የሚያብቅ ፥ ዐማቂ ፥ ጨማሪ ።
አባቃ፡ አዳከመ አሰላቸ አጣገበ፡ አጣቀመ አስተካከለ አዳረሰ ።
አባበለ፡ ለመነ፡ ባበለ ።
አባበለ፡ አሽበለበለ አቈላመጠ እንደ ድመት በወተት እንደ ልጅ በቀለበት ለመነ ። ዕሽባቦ አለ ። (ምሳ ፩ ፥ ፲ ። ሆሴ ፪ ፥ ፲፮ ። ማቴ ፳፯ ፥ ፳ ። ግብ ሐዋ ፲፰ ፥ ፲፫) ።
አባበሰ፡ ጠራረገ ፥ ወላወለ ።
አባቢ፡ የሚያብብ ፥ ፌኪ ።
አባባ፡ (አባ አባ) አበ አብ)፡ ያባት አባት ወንድ አያት ወይም አባት ።
አባባ (አባሕብሐ)፡ አስፈራ አሠጋ አባነነ አገነገነ ። (ኢዮ ፳፫ ፥ ፲፮) ።
አባባ አለ፡ መናገር ዠመረ፡ አባቱን ራ ሕፃኑ ። ዳባን እይ ።
አባባለ (አስተባሀለ)፡ አነጋገረ አገተ አከራከረ ።
አባባለ፡ አማታ አደባደበ አዋጋ ።
አባባሰ (አስተባአሰ)፡ አጣላ አጠ ላላ፡ አከፋፋ አማረረ ።
አባባሰ (አባ ባሰ)፡ (ግጥም)፡ ይሻላታል ብዬ ገዳም ብሰዳት፡ ያዝ ረድ እያሉ አባባሱባት (አባ ባሱባት) ።
አባባስ፡ አጠናን አከፋፍ አበረታት፡ መባስ ።
አባባሽ፡ ያባባስ የሚያባብስ የሚያ ጣላ የሚያጠላላ ።
አባባባ፡ ሕፃናት አፋቸውን በውስጥ እጃቸው እየተመተሙ የሚያሰሙት የጨዋታ ድምፅ፡ ፫ቱም ባ ይላል ።
አባባዬ (አባ አባየ፡ አበ አቡየ)፡ ያባቴ አባት አያቴ ወይም አባቴ ።
አባባይ (ዮች)፡ ያባበለ የሚያባብል የሚያሽበለብል የሚያቄላምጥ የሚለማመጥ ። ቤት ዐባይ፡ ቤት ኣባባይ እንዳለ ታቦት ዘፋኝ ።
አባባይ፡ ያባባለ የሚያባብል የሚያግት የሚያማታ፡ አነጋጋሪ ።
አባባይነት፡ አሽበልባይነት ደላይነት ።
አባብዬ፡ ዝኒ ከማሁ፡ የኔ አባባ ።
አባተ (አብሐተ)፡ አሠረቀ አገባ ዠመረ፡ ወርን፡ ሌሊትን በጨረቃ፡ መዓልትን በፀሓይ ቈጠረ ።
አባተ፡ ሾመ አሠለጠነ ።
አባተ ታናሽ፡ የድኻ የመናጢ የለ ማኝ የቧጋች ልጅ ።
አባተ፡ አሸነፈ በላይ ኾነ፡ ዐየለ በረታ ።
አባተ፡ አሸነፈ ባተ ።
አባተ፡ የሰው ስም ።
አባተለ፡ ብቸኛ አደረገ አለፋ አደከመ ።
አባተነ፡ አዛራ አለያየ አሠራጩ ።
አባታችን (አቡነ)፡ ወላጃችን መም ፊችን ጌታችን ሽማግሊያችን አቡናችን ጳጳሳችን ።
አባታነስ (አባት አነስ)፡ ልጁ ዐም ባራስ፡ አባቱ ንጉሥ ።
አባታደግ (አባት አደግ)፡ ልጁ ንጉሥ፡ አባቱ ዐምባራስ ።
አባቴ (አቡየ)፡ የግብርና የነብር ስም ። ወላጅነት ሽበትና ማዕርግ ምንኵስና ላለው ከልጆች ከታናናሾች አፍ የሚሰጥ፡ የኔ አባት ማለት ነው ። በትግሪኛ አቦይ ይባላል ። አባቴዋ አባቴ ሆይ ።
አባት፡ ሴት የቤት (አዛዥ መጋቢ አሳዳሪ) ። ይኸውም በእናት ፈንታ - የሃባ ነው ። ቤት አባት እንዲሉ። አመመ ብለኽ እሙን እይ ።
አባት በሬ፡ አሪ ወይፈን አቅኒ ።
አባት ነፍጠኛ፡ ትልቅ ዋና፡ ሽማ ግሌ ወታደር ።
አባት አልባ፡ አባቱ ያልታወቀ ልጅ ።
አባት ዐርቶ፡ አባት ያልሠራው ያላቈ የው፡ ባባት የሌለ ደንብና ሥራ ትእዛዝ፡ እንደ ዐይነ ምድር የተጣለ ማለት ነው ።
አባት ዘር፡ አርእስት መኼድ መምጣት ።
አባት፡ ደንብ አገባብ ሥርዐት ። ከአባት ሲያያዝ የመባ ። አላባት ጎመን ባጓት ። አላባት ዦሮ በጡጫ ።
አባትነት (አብና)፡ አባት መኾን ።
አባትና እናት፡ አዳምና ሔዋን፡ ሞግ ዚቶች፡ ወላጅነት ላለው ፍጡር ኹሉ ይነገራል።
አባትያ፡ የጋረዳ ጌታ፡ ዋና የኀዋት ዳኛ ። አባቴና፡ ቃለ መሐላ ።
አባቶቻችን (አበዊነ)፡ ወላጆቻችን፡ ቅዱሳን አብርሃም ይሥሐቅ ያዕቆብ ነቢያት ።
አባቶቼ (አበውየ)፡ ወላጆቼ ሽማግሎቼ መምቼ ጴጥሮስ ጳውሎስ ሰላማ ከሣቴ ብርሃኑ ተክለ ሃይማኖት ዜና ማርቆስ ።
አባቶች (አበው)፡ ወላጆች የቀድሞ ሰዎች፡ አያት ቅድም አያት ያር ሽማግ ሎች ሠምራን ሊቃውንት ።
አባች፡ ያበቀ የሚያብት፡ ጠላፊ ።
አባነነ፡ አጫጫሰ ።
አባከነ፡ አባዘነ አቃበዘ አዛበረ ዘራ በተነ አጐደለ፡ ገንዘብን ልብን ። (ምስጢር አባከነ)፡ አወጣ ገለጠ፡ ለማንም ነገረ ።
አባካኝ (ኞች)፡ ያባከነ የሚያባክን የሚያባዝን፡ በታኝ ። (ግጥም)፡ አባካኝ አለችኝ፡ አባካኝስ እሷ፡ እያበካከነች ባይንና በጥርሷ ።
አባዘቀ፡ አቀላቀለ አደባለቀ አዘባረቀ አማሰለ ።
አባዘተ፡ ዐማ ነቀፈ ስም አከፋ ።
አባዘነ፡ አዞረ አንከራተተ አዛበረ ።
አባዛ (አስተባዝኀ)፡ ተበራከተ ኣዋለደ ኣራሳ አበራከተ ። እምብዛንን እይ ።
አባዛቂ፡ ያሳዘቀ የሚያባዝቅ የሚያደባልቅ የሚያዘባርቅ ።
አባዛች፡ ያባዘተ የሚያባዝት የሚቦ ጭቅ፡ እጀ ሥራ አግቢ፡ ባዛች፡ ዐሚተኛ ።
አባዛኝ፡ ያሳዘነ የሚያባዝን፡ አንከራታች ።
አባዜ (አብ አኃዜ)፡ (አባዜ ይዞታል፡ አዛዚያም እንዲሉ) ።
አባያ (ኣበየ አባዪ)፡ እንቢተኛ ፥ ዳተኛ ፥ በፌር ላይ የሚተኛ ፥ ያልቀና ወይፈን ። (ኤር ፴፩ ፥ ፲፰) ። አባያ ቢቀኖ ቤት ያቀኖ ። ሰውም በስንፍናው አባያ ይባላል ። (ምሳ ፯ ፥) ።
አባዬ (አባየ አቡየ)፡ አባቴ የኔ ።
አባይ (ሐረር)፡ እት ።
አባይ (ኤፌሶን)፡ አባያ የወንዞች አባት ። ከ፬ቱ ወንዞች እንደኛው መዠመሪያው መንዝ ፥ ታላቅ ዠማ ። በግእዝ አዋልድ ፈለማ አባዊ ይባላል ። እሱም በዳሞት ሰከላ ሚካኤል ከሚባል አገር ከደንገዛ ተራራ ሥር ፈልቆ ጐምን ይከባል ። ምንም ግሼ አባይ ይባላል፡ በጣና ላይ ዐልፎ ወደ ከርቱም ከዚያም ወደ ምከር ይኼዳል ። ፈሳሹም ሰማይ መስሎ ስለሚታይ ጥቍር ኣባይ ይሉታል ። (ተረት)፡ አባይ ማደሪያ የለው ፥ ግንድ ይዞ ይዞራል ። አባይን ያላየ ምንጭ ያመሰግናል ። ኤፍራጥስንና ሣሮስን እይ ።
አባይ (ጊዮን)፡ በደቡብ አፍሪቃ ኒያንዛ ከሚባል ሐይቅ የሚወጣ ወንዝ፡ ከ፬ቱ ወንዞች ኹለተኛው፡ ውሃው ነጭ የኾነ ። ነጭ አባይ እንዲሉ። እሱም ከጥቍር አባይ ጋራ በከርቱም ይገጥማል ።
አባይ መስኩ፡ ዋነተኛ አባይን በዋና የሚቈርጥ፡ በአባይ ላይ የሚንፈላሰስ ።
አባይ ነሽ፡ የሴት ስም ።
አባይ ነኸ፡ የወንድ ስም ።
አባይ፡ የወንድና የሴት ስም ። አቶ አባይ እመት አባይ እንዲሉ።
አባይ ጋረደሽ፡ የሴት ስም ።
አባይ ጣና፡ የጣና አባይ፡ ከነጭ አሳይ ለመለየት አባይ ጣና ይባላል ።
አባዮች፡ ኤፌሶን - ማዮን፡ ፭ቱ ዝሞች ።
አባደ (አብዐደ)፡ ለየ ነጠለ አራቀ ወገደ ።
አባደለ፡ አጓዳ አጫቈነ ።
አባጀ፡ አሣራ ።
አባጀ፡ አስቀመጠ አቈየ ።
አባጀኸኝ፡ የጐመን ስም፡ የበጋ ጐመን አይደርቄ ። በጋውን ኣቈየኸኝ ኣሳለፍከኝ ማለት ነው ።
አባጀኸኝ ጐመን፡ ባጀ ።
አባጅ (አባዲ)፡ የሚያብድ የሚወገሽ ።
አባጠለ (ኣብጠለ)፡ እጠፋ አፈረሰ ፈታ ሻረ ።
አባጠለ፡ ዐማ፡ ስም አከፋ ።
አባጠሰ፡ አቋረጠ አማተረ ።
አባጠረ፡ አናፈሰ ።
አባጠጠ፡ አዘለለ አስፈነጪ፡ አቀማጠለ ።
አባጣ (አስተባጥሐ)፡ አተፋተፈ አሠናተረ ።
አባጣይ፡ ያባጠለ የሚያባጥል የሚያፈርስ የሚያበላሽ፡ አጥፊ ።
አባጨበ፡ ተባበረ/አዳመቀ ("ጭብጨባን ረዳ አስ") ።
አባጯ፡ ለየ ከፈለ፡ በተነ፡ አላገጠ ።
አቤ፡ (ኦሮ)፡ አባትሽ ። አሳ ላፊ - አሴ እንዲሉ።
አቤል፡ የሰው ስም፡ የአዳም ፪ኛ ልጅ ። መስክ አልቃሽ ። (ኪ ወ ክ አቤልና ቃል እንዲሉ) ።
አቤሜሌክ፡ የሰው ስም፡ አ ንጉሥ የንጉሥ አባት ማለት ነው ። ዐብድን እይ ።
አቤተኾን (አበ ቤት ኮነ)፡ ቤት አባት ባለቤት ጌታ የነገድ የወገን አባት አሳዳሪ መሪ ኾነ፡ ከበረ ገነነ ።
አቤቱ (እግዚኦ)፡ ንኡስ አገባብ፡ ቃለ አጋኖ ወይም ቅጽል ። አቤቱ ጌታዬ ማረኝ ። (ኤር ፲፬ ፥ ፳) ።
አቤቱ አቤቱ፡ ጌታው ጌታው ። (ማቴ ፳፭ ፥ ፲፩) ።
አቤቱታ፡ አቤት ማለት፡ የተበደለ ድኻ ለበላይ ዳኛ ወይም ለንጉሥ የሚያቀርበው ጩኸት፡ ይግባኝ ምጥንታ፡ እግዜር ያሳይዎ መልአኩ ያመልክትዎ ።
አቤቱታዎች፡ ጩኸቶች ይግባኞች ።
አቤት (አበ ቤት)፡ ሆይ ወይ፡ ተጠሪ ለጠሪው የሚመልሰው የከበሬታ ቃል፡ ቤት አባት ባለቤት ጌታ ሲጠሩኸ አቤት፡ ሲልኩሽ ወዴት እንዲሉ ። እየተደጋ ገመ ሲነገርና በአንቀጽ ሲሳብ፡ አቤት አቤት አለ፡ ወደ ፈጣሪ ጸለየ ተማለለ ። አቤት አለ፡ ወይ አለ ፥ ጮኸ ለዳኛ ነገረ አሰማ በደሉን ።
አቤት ባይ፡ አቤት የሚል፡ ወይ ባይ፡ ጯኺ ።
አቤቶ ኹን (አበ ቤት ኩን)፡ የቤት አባት የቤት ጌታ ኹን፡ እደግ ግዛ ንዳ ፥ ብዛ፡ ተባዛ ። አቶን ተመልከት፡ የዚህ ዘር ነው ።
አቤቶ፡ የስም ቅጽል ። አቤቶ ሣህለ ሥላሴ ፥ ኣቤቶ ዳርጌ ፥ ኣቤቶ ሰይፉ ። ጌቶ ጌታው ማለት ነው ።
አብ፡ እግዜር፡ የግዜር ስም፡ ከቅድስት ሥላሴ አንዱ መዠመሪያው አካል ። ዓለም ሳይፈጠር ወልድን አለ ። እናት ስለ ወለደ አብ ይባላል፡ አባት ማለት ነው ። (ግጥም)፡ አብን ተዉትና ንፃሩት ለወልድ፡ ተወግሯል ተሰቅሏል፡ እሱ ያውቃል ፍርድ ። አቡንን አብነትን አባትን አስተውል ። አብና ወልድ፡ አባትና ልጅ ። ፪ ዮሐ ፩ - ፱ ።
አብለጠለጠ፡ የአበለጠ ድርብ፡ አካቶ ፈጽሞ መላልሶ አበለጠ፡ ብልጥ አደረገ፡ አትኰረኰረ ።
አብለጨለጨ፡ የአበለጨ ድርብ፡ አሸበረቀ አብረቀረቀ ። (ሉቃ ፱ ፥ ፳፱) ።
አብሊ (አብላዒ)፡ ያበላ የሚያበላ የሚመግብ የሚቀልብ ።
አብላሊ፡ የሚያበል፡ አጥፊ ።
አብላሊት አለብላቢት፡ በለለ ።
አብላሊት፡ አለብላቢት፡ አብላሊት ግእዝኛ ነው ።
አብላሊት፡ አለብላቢት፡ለበለበ ።
አብላጭ (ጮች)፡ የሚያበልጥ የሚያረዝም የሚያልቅ፡ አለቃ የሚያደርግ ።
አብሰለሰለ፡ ቈጩ አንገበገበ ኣትከነከነ፡ ኣወጣ አወረደ ።
አብሰከሰከ፡ አንበሸበሸ አቀማጠለ ።
አብሲት (አብኣሲት)፡ ቡሖን የሚያበረታ እንጀራን የሚያሳምር፡ በፍል ውሃ የተላቈጠ በማማሰያ ተልጎ በጣባ የተጣለ ገንፎ መሳይ ።
አብሲት፡ በቁሙ፡ ባሰ ።
አብሳይ፡ ያበሰለ የሚያበስል የሚቀቅል፡ ቀቃይ ጋጋሪ ሊጥ አፍሳሽ ወጭት ጠባሽ፡ ዐበዛ፡ ወጥ ቤት ።
አብሳዲ፡ የሰው ስም፡ በእንሳሮ የነበረ ሊቅ ።
አብስል፡ የሚያቃጥል የሚያናድድ፡ አቃጣይ አናዳጅ ። ልብ አብስል እንዲሉ ።
አብሶ፡ አጥንቶ አክፍቶ፡ ይልቅ ማለት ነው ። ንኡስ አገባብም ይኾናል ።
አብረቀረቀ፡ አብለጨለጩ ኣፍለቀለቀ አንተገተገ አንጸባረቀ፡ ውሃና መስተዋት ጥሩ ብረት ከፀሓይ ሲገናኝ ነው ።
አብረቅራቂ፡ ያብረቀረቀ የሚያብረቀ ርቅ፡ ነጭ ልብስ ሐር ወርቅ ኖራ ።
አብረንታንት፡ የገዳም ስም —ሀ ረዥ ።
አብረከረከ፡ መላልሶ ፈጽሞ አበረከ፡ ዕጥፍ ዕጥፍ አደረገ፡ ጕልበትን አንቀጠቀጠ፡ ኀይል አሳጣ፡ አዛለ አደከመ ።
አብረዠረዠ፡ ረዥ በረ ።
አብረዠረዠ፡ ጨፈነ አጥበረበረ፡ አንገደገደ አንቦዠቦዠ ።
አብሪ (አብርሂ)፡ የቅርብ ሴት ትእዛዝ አንቀጽ ። (ኢሳ ፰ ፥ ፩) ።
አብሪ (ዎች) (አብራሂ)፡ ያበራ የሚያበራ፡ ፋና ወጊ፡ ገላጭ አስረጅ ። መብራት አብሪ እንዲሉ ።
አብሪነት፡ መብራት ያዥነት፡ ፋና ወጊነት ።
አብራ (አብራሂ)፡ ያያን ሐኪም ። ዐይን አብራ እንዲሉ ።
አብራ ቅዳ (አብርህ ቅዳሕ)፡ መብራት አብራ፡ መጠጥ ቅዳ ። አብራ ቅዳ ሲል ዐደረ እንዲሉ ።
አብራሪ፡ ያበረረ የሚያበር የሚያከንፍ የሚያሮጥ ጥያራ ነጂ ።
አብራራ፡ ገላለጠ መላልሶ አስረዳ ።
አብራሽ፡ ያበረሰ የሚያበርስ፡ አርካሽ ።
አብራከ ሥላሴ፡ የሥላሴ ኀይልና ጸጋ በጥምቀት ልጅነትን የሚሰጥ ።
አብራክ፡ ጕልበቶች ።
አብራጃ፡ አየር፡ ነፋሻ ቦታ፡ ቀዝቃዛ ስፍራ ።
አብራጅ፡ ያበረዶ የሚያበርድ የሚያቀዘቅዝ፡ አቀዝቃዥ ።
አብርሀ፡ የሰው ስም ። አብርሀ አጽብሐ እንዲሉ ። ትርጓሜው አበራ ማለት ነው ።
አብርሃም፡ ታላቅ አባት ። በዕብራይስጥ አብራሃም ይባላል ።
አብርል፡ የገነት ወፍ ።
አብርር፡ ጠንቋይ በሥጋ ደግሞ ላሞራ የሰጠው አስማተኛ መድኀኒት ሰውን የሚያበር የሚያንከዋርር ።
አብርቅ፡ ተላላፊ የከብት በሽታ ከፀሓይ ሙቀት የሚመጣ፡ እንደ አባ ሰንጋ በፍጥነት ይገድላል ።
አብሻት፡ ጥዋ ዐፈሠ ።
አብሽ፡ ምረቱ የባሰ፡ እንደ ኮሶ የኾነ ቅመም፡ ልጅን የሚያፋፋ የሚያወፍር ። አብሽ ወጭት፡ ምንቸት አብሽ የሚሠራበት ድስት፡ እንደ ጣባ ያለ ክብ ባለዦሮ ።
አብሽ ቅመም፡ ባሰ ።
አብሽ ወጭት፡ ድስት ፥ —ባሰ ።
አብሽሎ፡ ቀለጦ በሰለ ።
አብሽሎ፡ የጠላ ቂጣ ቀለጦ ጥሬው ተንተብትቦ የተፈጨ ።
አብሽሬ (ጕራጌ)፡ አስደሳች ።
አብሽር፡ ትልቅ ብራብሮ ቀለመ ነጭ ።
አብሽቅ፡ አሳዛኝ አናዳጅ ። ልብ አብሽቅ እንዲሉ ።
አብሾ፡ በቁሙ ፥ —ባሰ ።
አብሾ፡ አብሽ መሳይ፡ ፍሬውን ሲቀምሱት የሚያስወገሽ ወፈፍ የሚያደርግ የሚያስቈጣ የሚያሳብድ አእምሮ ለዋጭ ቅጠል ።
አብሿም፡ አብሾ የጠጣ፡ ባላብሾ በጥቂት መጠጥ የሚሰክር፡ ሰካር እብድ ቍጡ ወፈፍተኛ ደፋር ተማሪ ደብተራ ።
አብቂ፡ ያበቃ የሚያበቃ፡ ልክ ትክክል የሚያደርግ ።
አብቃቂ፡ ያብቃቃ የሚያብቃቃ፡ አስተንታኝ ።
አብቃይ (ዮች)፡ ያበቀለ የሚያበቅል፡ የሚያጸድቅ ።
አብቃይነት፡ አጽዳቂነት አስገኝነት ።
አብተከተከ፡ በታተከ በጣጠሰ ቈራረጠ ። ዐይን አበጀ አሳመረ፡ የንጀራ ።
አብታ (ቶች)፡ ያረግ ስም፡ በንጨት ኹሉ ላይ የሚታበት የሚንጠለጠል ዐረግ፡ የጠንበለል ዐይነት ።
አብቹ፡ የኦሮ ባላባት፡ የሱ አገርና ዘር በስሙ ይጠራል ። አብቹና ገላን እንዲሉ ።
አብቺው፡ የሴት ስም ።
አብነት (አብና)፡ አባትነት (አባት መ) ።
አብነት፡ ምሳሌነት ፥ መምርነት ።
አብነት ቀምሷል፡ ኮሶ ወይም ሌላ መዳኒት ጠጥቷል ውል ።
አብነት ነሣ፡ ከሥነ ፍጥረት የሥፈን ምሳሴና ዐይነት ወሰደ ፥ እስመስሎ ሠራ ።
አብነት፡ የትርጓሜ ባህል ልዩነት ።
አብነት፡ ፍቱን መዳኒት፡ (መድኀኒት)፡ ገቢር ል ይኩን ። (የዶም ኣብነት)፡ ደም ዕርጥ ያለው ።
አብነቶች፡ መዳኒቶች ።
አብናኝ፡ ያበነነ የሚያበን፡ አጫሽ ።
አብከነከነ፡ የአበካከነ ድርብ ።
አብካሪ፡ ያበከረ የሚያበክር የሚያቈርጥ የሚተው የሚያቆም ።
አብዛኛ (ኞች)፡ ያብዢ ወገን ብዙ ። አብዛኛውን አትናገር ።
አብዝቶ በሰ ረካ ("ጠጣ ከለ ለበሰ ወዶ'ተቀበለ እከሌ ስድቡን ለብሶት ዐደረ እንዲሉ። ሠራ ብለኸ ሥራ ትን ፈረደ ብለኸ ፍርድን እይ ለብሰኸ ፍጀው ዐዲስ ልብ የለበሰውን ሰው እንዲህ ይሉታል ፍጀው ጨር ሰው ማለት ነው ለባሽ ") ("ሾች") ።
አብዢ (አብዛኂ)፡ የሚያበዛ የሚያተርፍ የሚያበረክት የሚያረባ፡ አትራፊ አርቢ ። አብዢ፡ ተጨማሪ ፊደል ምእላድ ። ዎችን ተመልከት ።
አብዢነት፡ አትራፊነት አበርካችነት ።
አብዢዎች፡ የሚያበዙ፡ አትራፎች ።
አብዬ፡ የጋሼ ታላቅ ወንድም ስም፡ በ፫ኛ ልጅ አፍ የሚነገር አባቴ ማለት ነው ። ኣቡ ብለኸ እብን እይ ።
አብዱ፡ የድኝ ጭቃ ።
አብጅር፡ የነጋሪት ድምጥ ።
አብጅር፡ የነጋሪት ድምፅ፡ ሩጥ ቅደም ማለትን ያሳያል ። አብጅር ቀብዥር እንዲሉ ። ዳግመኛም አብጅር ከበገረ ቢወጣ አስበግር ተብሎ ይፈታል ።
አብጋኝ፡ ያበገነ የሚያበግን የሚያደርቅ የሚያከር የሚያገምን፡ አክራሪ ።
አብግን፡ ዝኒ ከማሁ፡ አግምን ። ልብ አብግን እንዲሉ ።
አብጠለጠለ፡ በጫጨቀ ቈራረጠ ቀ ጠቅ ።
አብጠሰጠሰ፡ አበላሸ ከንቱ አደረገ፡ ዐመልን ጠባይን ።
አቦ፡ (ኣባት ሆይ)፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ። በጋልኛ ግን ሰውዮ ማለት ነው፡ ትግሮችም አባት ሲሉ ኣቦ ይላሉ ። አቦዬን እይ ።
አቦ ሰጡኝ፡ ዝኒ ከማሁ፡ እናት ያቦን ገድል ዐዝላ ተስላ የወለደችው የወለደቻት ልጅ ።
አቦ ረቱኝ፡ የወንድና የሴት ስም (ምክነቴን አሸነፉልኝ ማለት ነው) ።
አቦ አቦ አለ፡ ኣክሪ - አኀነነ፡ ከፍ ከፍ አደረገ፡ ያባትነትና የጌትነት የመምርነት ማዕርግ ሰጠ ።
አቦ እገሌ፡ ስመ ጥር መነኵሴ ።
አቦለድ (ዶች)፡ ወገን፡ ዐይነት፡ ተመሳሳይ ። ዝንጀሮ ከእንዳሞድ፡ ጕሬዛ ከጨኖ፡ ቀበሮ ከተኵላ እንዲመሳሰሉ፡ ይህም እንደዚያ ነው ። ነገዱ አንድ ሲኾን መለያየቱን ያሳያል ።
አቦል (ዐረ አወል)፡ አንደኛ መዝሙ ራያ ፥ ፊት ። አቦል ዘራፍ ። አቦል ቡና እንዲሉ ።
አቦልሴ፡ ሰርገኛ፡ የሚባል፡ ጤፍ፡ ዕ ይር፡ መሬት ። በረዘን፡ እይ
አቦልሴ፡ ድብልቅ በለሰ ።
አቦልዜ፡ አቦልሴ፡ በለሰ ።
አቦራረቅ፡ አዘላለል አፈነጫጨት፡ መቦረቅ ቡረቃ ።
አቦራቦር (አበራበር)፡ አጐራጐር አፈላፈል፡ መቦርቦር ባዶ ማድረግ ።
አቦቃቀር፡ አለጫጩት፡ መቦቀር ። ወረ በንን እይ ።
አቦብላት፡ ብልኀተኛ፡ አቦ ።
አቦነነ፡ እንዳህያ መታ ጠዘለ ።
አቦካክ፡ ኣለዋወስ አስተሻሸት፡ መቡ ካት ።
አቦኸየ፡ መለጠ ገለጠ ቡሓ አደረገ፡ አነጣ ።
አቦዘ፡ አዘነጋ አፈዘዘ ። ቦዘነንን ተመልከት፡ የዚህ ዘር ነው ።
አቦዘነ፡ አሰነፈ አሳረፈ ዞላ አዋለ ሥራ አስፈታ፡ ከለከለ አስቀረ አስታጐለ አቆመ አቈረጠ ።
አቦዘነ አቦዘነች፡ የወንድና የሴት ስም ።
አቦዛኝ፡ ያቦዘነ የሚያቦዝን የሚያሰንፍ፡ ሥራ አስፈች ።
አቦዛዘን፡ ኣሰናነፍ፡ መቦዘን ።
አቦየ፡ ማሰ ቈፈረ ገመሰ፡ ቦይ አወጣ ።
አቦዬ (አቡየ)፡ የሰው ስም፡ አባቴ የኔ አባት ። ያቦ ነኽ የኔ አቦ ተብሎም ይተረጐማል ። ቆቅ፡ ማሪ፡ እቦዬ፡ እንዲሉ ።
አቦዳደስ፡ አለማመስ አጐማመድ፡ መቦደስ ።
አቦጋገት፡ አለማመን፡ መቧገት ።
አቦጣጠጥ፡ አሞጣጠጥ፡ መቧጠጥ ።
አቦጫጨር፡ አሞጫጨር፡ መቧጨር ።
አቦጫጨቅ፡ አስተጫጨድ፡ መቦጨቅ ።
አቧለተ፡ አፌዘ፡ ቧለተ ።
አቧለተ፡ አፌዘ ተረበ ዘበተ ቀለደ፡ ዋዛ ፈዛዛ ተናገረ ።
አቧላች፡ ያሷለተ የሚያቧልት የሚተርብ፡ ተራቢ ቀላጅ ።
አቧራ፡ ያፈር ብናኝ ዐቧራ ።
አቧደነ፡ እጣመረ አያያዘ አቀናጅ፡ አጋጠመ ።
አቧዳኝ፡ ያቧደነ የሚያቧድን፡ ቡድን መራጭ ና ወዲህ የሚል ።
አቧገተ፡ አቀለተ አለመነ፡ ዘግኖ ሰጠ ከምርት ።
አቧጋች፡ ያቧገተ የሚያቧግት የሚያቀልት የሚዘግን፡ አቀላች ዘጋኝ ።
አቧጨቀ፡ አባዘተ አናከሰ አባላ አቃማ ።
አተ፡ (ማችን፡ ረዳ፡ ዐገዘ)አማች፡ ያተ፡ የሚያሙት ።
አተለ (አንተለ ጥሕለ ትግ ሐተለ)፡ ደፈረሰ፡ አተላ ኾነ ከላይ ወደ ታች ወረደ፡ ዘቀጠ ዘገጠ ።
አተለለ (አጽለለ)፡ አጠራ እጠለለ ።
አተለለ፡ ኣወረደ አፈሰሰ ።
አተለቀ፡ አላቀ፡ ትልቅ፡ አደረገ።
አተላ (ትግ ሐተላ)፡ የጠላ የጠጅ የቅቤ የኮሶ የብረት ዝቃጭ፡ አንቡላ ዐር ወደ ውጭ የሚፈስ የሚጣል ። (ኤር ፵፰ ፥ ፲፪) ።
አተላ፡ አወጣ አፍለከለከ ኣርመሰመሰ ትልን (ዘኍ. ፭፡ ፳፩) ። "ዕጭን" አስተውል ። አተላ፡ አበዛ አተረፈ አፈደፈደ ።
አተላለመ፡ እዠማመረ ኣስተራረሰ ።
አተላለም፡ ኣስተራረስ መትለም ።
አተላል፡ የትል ተፈጥሮ አኳዃን መ...ትላት ።
አተላም፡ አተላ የፈሰሰበት ያለበት ስፍራ ።
አተላተለ፡ ኢቃደደ አሠናጠቀ አባጣ ።
አተላተላ፡ ኦተራተረ አማዘዘ ።
አተላተል፡ አተራተር መተርተር ።
አተል (ጥሒል)፡ ማተል መደፍረስ ።
አተል አለ፡ አተለ፡ ደፍረስ አለ ።
አተመ፡ በቁሙ ዐተመ ።
አተመመ፡ አጮኸ አናረ ።
አተመከ፡ ሰገደ ሠረጐደ ።
አተማመም፡ እኸል መትመም ።
አተማተመ ።
አተማተመ፡ አላተመ አጋጨ አዋጋ ።
አተማታሚ፡ ያተማተመ/የሚያተማትም (ኣላታሚ አዋጊ ቲቲቲ ባይ እረኛ) ።
አተረ፡ ተቋጠረ ፥ —ዐተረ ።
አተረማመሰ፡ አበጣበጠ አመሰቃቀለ ።
አተረማመስ፡ አበጣበጥ ማተራመስ ።
አተረማማሽ፡ ያተራማመሰ/የሚያተረማምስ (አበጣባጭ) ።
አተረተረ፡ ዘር ዘር አደረገ በተራ አቆመ ሰደረ ደረደረ አሰለፈ ። ልማዱ ግን ተገብሮ ነው ("ተሰደረ ተደረደረ") ።
አተረተረ፡ ደረደረ፡ ተረተረ ።
አተረካከክ፡ አሠነጣጠቅ መተርከክ ።
አተረኳኰስ፡ አኰሰታተር መተርኰስ ።
አተረጓጐመ፡ አመላለሰ ።
አተረጓጐም፡ አፈታት መተርጐም ።
አተረፈ (አትረፈ)፡ ኣዳነ ፈታ ፈ...ወስ ተወ ኣስቀረ ።
አተረፈ፡ አበዛ ትርፍ ሰጠ ኣከለ ጨመረ (፪ነገ. ፬፡ ፵፫, ፵፬፡ ኤር. ፵፰፡ ፮) ። ("ቂም አተረፈ" - አቈየ) ።
አተረፋፈስ፡ አዘጋገን መተርፈስ ።
አተራመሰ፡ አሸበረ ፥ —(ተረመሰ) ።
አተራመሰ፡ ኣወከ በጠበጠ አሸበረ ዐመሰ አፋጀ አመሳቀለ ።
አተራማሽ፡ ያተራመሰ/የሚያተራምስ (አዋኪ በጥባጭ ዐማሽ ኣመሳቃይ) ።
አተራረር፡ አሠነጣጠቅ መተረር ።
አተራረብ፡ አቀላለድ መተረብ ።
አተራረት፡ አመሳሰል መተረት ።
አተራረክ፡ የታሪክ አነጋገር መተረክ ።
አተራተረ፡ አጨፋለቀ ።
አተራተረ፡ አፋታ አለያየ ። አተራተረ፡ አሠናጠቀ አፈናከት ።
አተራተር፡ አፈታት መተርተር ።
አተራከመ፡ ሰበሰበ አጠራቀመ ።
አተራካሚ፡ ያተራከመ/የሚያተራክም (ሰብሳቢ አጠራቃሚ) ።
አተራጐመ፡ አገላበጠ አማለሰ አፋታ ።
አተርትሮ፡ ሰድሮ ደርድሮ ("ተሰድሮ ተደርድሮ" - "ዐረፈ" ብለኸ "ምዕራፍን" ተመልከት) ።
አተበ፡ ቈረጠ፡ ዐተበ ።
አተባ (ኣትብዐ)፡ ሞረደ ጨው...ነሰነሰ እውሃ አገባ ነከረ አጠነከረ አሰላ ኣሾለ ።
አተባብ፡ አፈጣጠን መትባት ።
አተባተበ፡ አጠላለፈ አስተሳሰረ አያያዘ አወሳሰበ ።
አተባተብ፡ አጠላለፍ መተብተብ ።
አተቤተ፡ አኰራ።
አተተ (አቲት አተተ ራቀ)፡ ወገደ አራቀ ነጠለ አስገለለ ።
አተተ፡ ተቸ ዐተተ ።
አተቻቸት፡ አስተታተት መተቸት ።
አተነነ፡ አበነነ አጨሰ ። አትናኝ፡ ያተነነ/የሚያተን (አብናኝ ") ።
አተነኳኰል፡ አጐዳድ መተናኰል ።
አተነኳኰስ፡ አለኳኰፍ መተንኰስ ።
አተናተነ፡ አካፈለ አከፋፈለ ።
አተናተን፡ አከፋፈል መተንተን ።
አተናታኝ፡ ያተናተነ/የሚያተናትን (አ...ከፋፋይ) ።
አተንክ (ኮች)፡ ፈጣን ክፉ ጠንቀኛ ተንኰለኛ ።
አተንክ፡ ሙቀት ሐሩር ።
አተንክ፡ ጠንቀኛ፡ ተንክ ።
አተኛ፡ አስተኛ አጋደመ (መክ. ፭፡
አተኛኘት፡ አስተኛኘት አገዳደም መተኛት ።
አተከረ፡ ነዘነዘ ፥ —ተከረ ።
አተከረ፡ ጨቀጨቀ ነዘነዘ ።
አተከነ፡ አበገነ አናደደ አቃጠለ ። አትካኝ፡ ያተከነ/የሚያተክን (አቃጣይ...አናዳጅ) ።
አተከዘ/አስተከዘ፡ አሳዘነ ወዘን አሳደረ ።
አተካረኛ፡ ዝኒ ከማሁ ።
አተካሪስ፡ ድንድን፡ ተካሪስ ።
አተካራ/አተኻራ፡ ንዝንዝ ጭቅጭቅ ።
አተካራም፡ ጭቅጭቃም (ልብ አቍስል) ።
አተካተክ፡ አጠቃጠቅ መተክተክ (ቶክቶከ) ።
አተካከል፡ አቸካከል መትከል ።
አተካከር፡ አነዛነዝ ማትከር ።
አተካከት፡ አደካከም መታከት ።
አተካክ፡ አወካከል መተካት ።
አተኰሰ፡ እሞቀ ኣወበቀ ።
አተኰረ፡ ተኰረ ።
አተኰነ፡ ትዃን አፈራ አበጀ ።
አተኳሪ፡ ተኳር ።
አተኳኰሰ፡ ላኳኰሰ አቀጣጠለ...አ የያዘ ።
አተኳኰስ፡ አለኳኰስ መተኰስ ።
አተኳኰር፡ የጥንቃቄ አስተያየት መተ...ኰር ።
አተኳኰን፡ የትዃን አፈጣጠር መተ...ኰን ።
አተጋ (አትግሀ)፡ አሠጋ አነቃ ጐተጐተ (ዕረፍት ነሣ - መክ. ፩፡ ፲፫) ። አትጊ (አትጋሂ)፡ ያተጋ/የሚያተጋ (አሥጊ ጐትጓች) ።
አተጋተግ፡ አራረፍ መተግተግ ።
አተጋገብ፡ አቀዛቀዝ መተገብ ።
አተጋገን፡ ኣጀጓጐል መተን ። "ችግኝን እይ - የተገነ ዘር ነው"።
አተጋጋ፡ አነቃቃ አሳሰበ ።
አተጋግ፡ አሠጋግ መትጋት ።
አተፈተፈ፡ ቸኰለተፈተፈ ።
አተፋተፈ፡ አባጣ አቋረጠ አሠናተረ ።
አተፋፍ፡ ኣቀረሻሸት መትፋት ።
አተፍተፍ፡ አሰጣጥ መተፍተፍ ።
አተፍታፊ፡ ያተፈተፈ/የሚያተፈትፍ (ተፌ ከተፎ) ።
አቱ (አቲው አተወ)፡ መምጣት መግባት ። መምጣት ከናት ወዳባት፡ መግባት ።ካባት ወደናት ነው ። በአባትና በእናት መካከል ቁሞ መመላለስን ያሳያል ።
አቱ ሥግራ፡ ታቱ ሥግራ፡ (አቲወ ተአቱ፡ ሥግርአ)፡ መምጣት ትመ ጣለኸ፡ መግባት ትገባለኸ ። ሥገራ ተራመዳ፡ ሥር ተራመድ ።
አቱች (ቾች)፡ የቅጠል ስም፡ ሥሩ ለጠጅና ለንጥል መድኀኒት የሚኾን፡ የጠጅን መበላሸት የንጥልን መውረድ የሚያርቅ የሚያሶግድ ።
አቲከም (ኦሮ) (ኣቲ ከሚ)፡ አንተ የየት ነኸ ። መንገሻ አቲከም እንዲሉ ።
አታለለ፡ አሞኘ፡ (ታለለ) ።
አታለመ፡ አዣመረ ፈር አዋጣ ።
አታላሚ፡ ያታለመ/የሚያታልም።
አታላይ፡ ያታለለ/የሚያታልል (ደላይ ሸንጋይ ዋሾ ቀጣፊ መልቲ - "አታላይ ሌባ" እንዲሉ) ።
አታላይነት፡ አታላይ መኾን ።
አታላዮች...ቲዎች (ሮሜ. ፩፡ ፴) ።
አታሞ (ዎች)፡ የክበሮ ቂጥ እማሪት ።
አታሞ፡ አማሪት ተመመ ።
አታሞ፡ ኣፉ በለፋ ቈዳ የተለጐሠ (የታሰረ) እንስራ ገንቦ ።
አታሞ፡ ዋሻ (እረኞች ደበሎ ጠቅለው በውስጧ ሲመቱ እንደ አታሞ የምትጮኸ ዋሻ - ይህችውም በላይኛው ወግዳ ክፍል "ጐሽ ውሃ" በሚባል አገር ትገኛለች) ።
አታረተ፡ ተረት አነጋገረ ምሳሌ አመ...ሳሰለ ።
አታረፈ፡ አባለጠ አባዛ ።
አታተተ (ተሐተ)፡ ተመረመረ ተተቸ ።
አታት፡ ዐራጣ ወለድ፡ ሰው ካገሩ ተወግዶ እባዕድ አገር ኺዶ የሚያተርፈው ትርፍ ላበዳሪ የሚከፍለው ገንዘብ ። ውርኝ ትትን እይ ።
አታች፡ ያተተ የሚያትት፡ አስገላይ ።
አታከለ፡ አቻከለ አካሰሙ (አትክልት...መትከልን ረዳ) ።
አታከተ፡ አለፋ አደከመ እሰነፈ አስ...ለቐ (ሚል. ፪፡ ፲፯፡ ማቴ. ፳፮፡ ፲) ። አታካች...አስናፊ ።
አታካይ፡ ያታከለ/የሚያታክል።
አታክልት፡ አትክልት ዛፎች ኵትኵቶች ። "አትክልት" የግእዝ "አታክልት" ያማርኛ ነው (በባላገር ግን ስለ ተክል ይነገራል) ።
አታኰሰ፡ አላኰሰ አለባለበ ።
አታኳሽ፡ ያታኰሰ/የሚያታኵስ (አዋጊ) ።
አታጊ፡ ያታጋ/የሚያታጋ (አነቃቂ) ።
አታጋ (አስተታግህ)፡ (ጥነ) አነቃቃ ።
አቴቴ (ዶሮ) ዛር፡ በሴት ስም የምትጠራ ውቃቢ፡ ዐማሮተ ከጋሎች የወረሷት፡ ጨሌ የሚያጠልቁላት፡ አቴቴ ግንቢ አቴቴ ሐራ አቴቴ ዱላ እያሉ እንቀት የሚቀቅ ሉላት አምልኮ ባዕድ ። ትርጓሜው ጠባቂ ማለት ይመስላል ። ወሌን ተመልከት ።
አቴት፡ ሀብት ዕድል ገንዘብ ከብት፡ ባል ። ሚስትም ለባሏ አቴት ትባላለች ።
አቴና (ኖች)፡ ከመቃና ከቀርክሓ የተሠራ ሣጠራ የመሬት ልባጥ ። ሥራው ከአቴና ስለ መጣ አቴና ተባለ ይላሉ ። ደብተራ ወገቡን ረግራጊ፡ አቴና ወጊ ። (ዐጤ ቴዎ) ።
አቴና፡ የጣዖት ስም፡ ሴት አምላክ ።
አቴና፡ ያገር ስም፡ የግሪክ አገር ።
አቴፈ፡ አነሣ አንሳፈፈ አንካፈፈ ።
አቴፈው፡ አንሳፈፈው ።
አት ፣ የነፍስ፡ አወጣጥ፡ መሞት።
አት (ኢት)፡ በትንቢትና በትእዛዝ አንቀጽ የሚገባ አሉታና አፍራሽ ። አትወርድ አትወጣ፡ አትኼድ አትመጣ፡ (አንተ እሷ) ። አትስረቅ አታመንዝር፡ አትንካ አትቅመስ አትቅረብ ። (ቈላ ፪ ፥ ፩) ። ኮነን እይ ።
አት፡ ለሩቅ ሴት የአንቀጽ ዝርዝር ። እሱ እሷን ዐወቃት ። ፭ኛውን ያ እይ ።
አትሊ፡ ያተላ/የሚያተላ ።
አትላንቲክ፡ ባውሮጳና በአሜሪካ በአፍሪቃ መካከል ያለ ውቅያኖስ፡ ስፋቱ ሦስት ሺ ማይል (ዐምስት ሺ ኪሎ ሜትር) ነው ።
አትላይ፡ ያተለለ/የሚያተል (እጥላይ) ።
አትመሰመሰ፡ አድበሰበሰ አድመሰመሰ...አመቀመቀ እርበተበተ ።
አትመከመከ፡ አድበስበስ ሳያሰማ ተና...ገረ ("መከመከን" እይ) ።
አትማሚ፡ ያተመመ/የሚያተም (ከበሮ...መቒ) ።
አትምጣ፡ (ኢትምጻእ)፡ ባለኸበት፡ ርጋ፡ እዚያው፡ ኹን።
አትራፊ (ፎች)፡ ያተረፈ/የሚያተርፍ (አዳኝ ኣብዢ ነጋዴ) ።
አትሮንሰ ማርያም፡ ከግራኝ በፊት የነበረች የወሎ ቤተ ክሲያን ።
አትሮንስ፡ መንበር (ግእዝ) ።
አትሮንስ፡ ዐጪርና ረዥም የመጽሐፍ ወንበር የቅምጥ የቁም ባለኹለት መልሕቅ ባላራት እግር፡ መጽሐፍ ተዘርግቶ የሚደገ ምበትና የሚነበብበት፡ ታጥፎ የሚቀመጥበት ። (ኪ ወ ክ) ። በግእዝ ግን ዙፋን ማለት ነው ።
አትቢ፡ ያተባ/የሚያተባ (ኣስሊ ነካሪ አጠንካሪ ባለጅ ጠይብ) ።
አትባራ፡ በሱዳን ክፍል ያለ አገር፡ ተከዚ የሚወርድበት ። የግእዝ መጽሐፍ ፈለገ አትባራ እንዲል ።
አትንኩኝ፡ የፈትል ስም (ቀጪን የባ ሕር ድር) ።
አትከነከነ (ከነከነ)፡ አብስለሰለ አግ...መነመነ (በልብ ውስጥ እጕላላ) ።
አትከነከነ፡ ተትከነከነ ("አብሰለ ሰለ ተብሰለሰለተከነ ") ።
አትከነከነ፡ አብሰለሰለ ፥ —ተከነ ።
አትካሪ፡ ያተከረ/የሚያተክር (ነዝናዥ) ።
አትክልተኛ (ኞች)፡ ያትክልት ሠራተኛ (ባላትክልት ኰትኳች ዐጋይ) ።
አትክልት፡ ተካይ (ዮች)፡ አትክልት የሚተክል ። ፈረንጆች "ዣርዲኜ" ይሉታል ።
አትክልት፡ ተክሎች ።
አትክር፡ ዝኒ ከማሁ (ጨቅጫቃ ነዝናዛ ልብ አውልቅ) ።
አትክን፡ ዝኒ ከማሁ ("ልብ አብግን...") ።
አትኮኝ፡ የለሽ ("እንደ ዶሮ አንዳውሬ እንደ በሬ የሚጮኸ ሰው ተምሳሊተ ብዙ በፈረንጅኛ ባንትሪሎግ ይባላል ") ።
አትኳር (ሮች)፡ የንጨት ስም፡ ያን ፋር ዐይነት ዛፍ የተኰረ ዘር ይመስላል ።
አትጋፊኝ፡ ወደ ግፉዓን ጠበል መውረጃ የደብረ ሊባኖስ ጠባብ ሥርጥ "በዚህ ገደል ባል ሚስቱን አትጋፊኝ አለ ይላሉ።"
አቶ (አቤቶ)፡ በዕድሜና በማዕርግ ከፍታ ላለው ሰው የሚሰጥ የስም ቀዳሚ ቅጽል፡ በአያና በአቤቶ መካከል ያለ፡ ፍችው ጌታ ባለቤት፡ ምስጢሩ ቃለ አጋኖ ነው ። አ አባት፡ ቶ ቤት (ኣበ ቤት) ከማለት የመጣ ነው ። እመትን ተመልከት፡ አመመ ።
አቶ በዛብኸ የተዋጉበት አሽከሮቻቸው የተጋደሉበት ሜዳ (የመንዝ ክፍል) ።
አቶመቆመ፡ አጕረመረመ ፥ —(ቶ መቶመ) ።
አቶምቷሚ፡ ያቶመቶመ/የሚያቶመቱም (አጕረምራሚ) ።
አቶሰቶሰ፡ አቶከቶከ አሳበቀ ።
አቶሰከ፡ በቀስታ ፈሳ ።
አቶሳል (አቶ ሳል)፡ የስንዴ ስም፡ ሙቁ እንትክትኩ ከብቅልና ከድብርቅ ፍሬ ጋራ ለሳል ለጕንፋን መድኀኒት የሚኾን ጥቍር ስንዴ ማር ማር የሚል ። አንዳ ንድ ሰዎች ሣህሌ የሚባል ሰው ከሌላ ስፍራ ወደ ሺዋ ስላመጣው ኣቶሣል ተባለ ይላሉ፡ እውነት መኾኑን እንጃ ።
አቶስቲሽ፡ አሳባቂ ።
አቶራረብ፡ አሸዳሸድ መቶረብ ። ተረገ፡ ሠረግ ተንቀጠቀጠ ።
አቶከቶከ፡ አሾከሾከ፡ (ቶከቶከ) ።
አቶከቶከ፡ ከሰው በታች ኹኖ ድምፁን በማሳነስ ተናገረ ነገርን ደገፈ እሥር እሥር አለ አሾክሾክ አሳበቀ ።
አቶክቷኪ፡ ያቶከቶከ/የሚያቶከቱክ (አሾ...ክሿከ) ።
አቷረበ፡ አወሳወሰ አሸዳሸደ ።
አቸላለስ፡ አከነባበል መቸለስ ።
አቸማቸም፡ ኦቸራቸም መቸምቸም ።
አቸሳሰር፡ ኣደኒሳሰር መትሰር ።
አቸረ (አኄረወ)፡ ቸር አደረገ ።
አቸረቸረ (ቸረረ)፡ ላይ ላዩን ዐለፈ ተንደረደረ ሳይ...የጦር ያንካሴ ።
አቸረቸረ፡ ሳይወጋ ዐለፈ ፥ —ቸ ረቸረ ።
አቸራቸም፡ አሰባበር መቸርቸም ።
አቸራቸር፡ ኦተናተን መቸርቸር ።
አቸራቻሪ፡ የቸራቸረ/የሚያቸራችር (አሻሻጭ) ።
አቸርቻሪ፡ ያቸረቸረ/የሚያቸረችር ።
አቸባቸብ፡ አመታት አወቃቅ መቸብቸብ ።
አቸነካከር፡ አወጋግ መቸንከር ።
አቸናቧ፡ አማታ አንቦጫረቀ ውሃን...በእግሩ ።
አቸናቧ፡ አንቦጫረቀ፡ (ቸነቧ) ።
አቸናቧ፡ እናፈረ ገላን ።
አቸናኘን፡ እጀናነን መቸነን ።
አቸናከረ፡ ችንካርን ልብ ውሃትን አማታ አታከለ ።
አቸኛ፡ አቻም ባላቻ፡ እኩያነት ያለው ወደረኛ ።
አቸካቸክ፡ አወጋግ መቸክቸክ ።
አቸካከል፡ አቀባቀብ መቸከል።
አቸኰለ፡ ኣፈጠነ ጐተጐተ ።
አቸኳኰል፡ አጠዳደፍ መቸኰል ።
አቸጋገር፡ አጨናነቅ መቸገር ።
አቸፈር፡ በአገው ውስጥ ያለ አገር ።
አቸፋቸፈ፡ አጨቃጨቀ እነዛነዘ ።
አቸፋቸፍ፡ አጨቃጨቅ መቸፍቸፍ ።
አቻ (ቾች) (ወላሞ ጥርስ)፡ ጓድ ወደር እኩያ ባልንጀራ ግጥሚያ፡ የፍቅሩ ኹናቴ እንደ ጥርስ የተጋጠመ የተካከለ ። (ተረት)፡ ኣላቻ ጋብቻ፡ ቈይ ብቻ ቈይ ብቻ ። አቻ ግእዝ አተወ አታዊ ካለው የወጣ ነው ። አቻም፡ ኦቻ ያለው ።
አቻለሰ፡ አከናበለ አዳፋ አፋሰስ ።
አቻላሽ፡ ያቻለሰ/የሚያቻልስ (እፋሳሽ) ።
አቻመ፡ እቃመ ።
አቻሜ፡ የወንድና የሴት ስም፡ የአቻም ወገን ማለት ነው ።
አቻም የለሽ፡ አቻሽ ማነው፡ የሴት ስም ።
አቻም የለኽ፡ የወንድ ስም ።
አቻቻለ (አስተካሀለ)፡ እሸካከመ...አወሳሰነ አስተጋጉ ።
አቻቻለ፡ አጣወረ አካልን ሰውነትን ።
አቻቻለ፡ አጣጣ አማላ ዕዳን ።
አቻቻል፡ አወሳሰን መቻል።
አቻቻም፡ አቃቃም መቻም ።
አቻቻይ፡ ያቻቻለ/የሚያቻችል ።
አቻቻይነት፡ አቻቻይ መኾን ።
አቻከለ፡ አታከለ አቀባቀበ ።
አቻኰለ፡ አጣደፈ አፋጠነ አጐታጐተ ።
አቻኳይ፡ ያቻኰለ/የሚያቻኵል (አጣዳፊ...አፋጣኝ አጐታጓች) ።
አነሰ፡ (አኒስ፡ አነሰ)፡ በቁሙ፡ ኰሰሰ፡ ቀጠነ፡ ተዋረደ፡ ዝቅ፡ አለ፡ ጐደለ፡ ዐጠረ፡ የመጠን፡ ያካል፡ የማዕርግ ።አነሰ፡ ሲሉት፡ ተቀነሰ ።ባ፭ኛው፡ ዓለም (ኦስያንያ)፡ ክፍል፡ በፓሲፊክና፡ በህንድ፡ ውቅያኖስ፡ ውስጥ፡ የነበሩ፡ ጥንተ፡ ባላገሮች፡ ፈረንጆች፡ ከገቡባቸው፡ በኋላ፡ ባረቄና፡ በጨብጥ፡ በልዩ፡ ልዩ፡ ተንኰል፡ ዐልቀው፡ ቍጥራቸው፡ አነሰ።
አነሰ ጐደለ ' ዐጸጸ ዐለቀ ሣሣ ።
አነሣ፡ መዘነ/ሰቀለ/አንጠለጠለ።
አነሣ፡ ሾመ/አከበረ/አጌተየ።
አነሣ፡ በቃ/አገመረ/ቻለ/አስቀመጠ (ዘፍ. ፴፮፥፯፡ ፩ነገ. ፯፥፴፰, ፰፥፷፬፡ ፪ዜና. ፯፥፯) ።
አነሣ፡ ብድግ አደረገ (ከዳቦ ከሥጋ ወገን - "የወደቀን አንሣ የሞተን ቅበር" እን ዲሉ - "(እማኝ አነሣ)" - ቈጠረ - "(ስም አነሣ)" - በደግ ወይም በክፉ አመሰገነ ዐማ) ።
አነሣ፡ ብድግ፡ አደረገ፡ ነሣ።
አነሣ፡ አስታወሰ/አሳሰበ ("ነገርን ነገር ያነሣዋል" እንዲሉ - ዘፍ. ፵፩፥፱, ፲፫) ።
አነሣ፡ አቀና ("ዐይኑን አነሣ" እንዲሉ) ።
አነሣ፡ አንሳፈፈ/አንካፈፈ።
አነሣ፡ ዕዳውን አመነ/ተቀበለ ("እከሌ ስለ ተረታ ዳኝነቱን አነሣ") ።
አነሣ፡ ከመሪ ቀጥሎ በቀኝ በግራ አንገርጋሪን አዜመ።
አነሣ፡ ዠመረ ("ነገር አነሣ ጦር'አ ነሣ" እንዲሉ) ።
አነሣ፡ ጨረሰ ("ይህ ዱቄት ብዙ ውሃ ያነሣል") ።
አነሣሣ (አስተናሥአ ወሐከ)፡ ጐተጐተ ("በል አድርግ አትተው አለ አደፋፈረ") ።
አነሣሣ፡ መላልሶ አነሣ።
አነሣሣ፡ አከላከለ።
አነሣሥ፡ አከላከልመንሣት ("መሣን" ተመልከት የዚህ ዘር ነው) ።
አነሣሺ፡ ያነሣሣ/የሚያነሣሣ (አደፋ ፋሪ) ።
አነሳነስ፡ አበታተን ' መነስነስ ።
አነስ፡ አለ፡ ጐደል፡ አለ፡ አነሰ።
አነስ፡ ያነሰ፡ የተዋረደ። አባት፡ ኣነስ፡ እንዲሉ ።
አነስ፡ ጐደል።
አነስተኛ ምጣድ፡ ከመኩብሽ የምትበልጥ - ከመኩብሽ የምትበልጥ ትንሽ ምጣድ። ዘሩ ረጋ ነው - ቅርፁ ክብ ነው።
አነስተኛ፡ የትንሽ፡ ወገን፡ ዝቅተኛ፡ መለስተኛ።
አነረነረ፡ አነጠነጠ፡ (ነረነረ)።
አነረነረ፡ አደዘደዘ ' አነጠነጠ ።
አነር፡ (ሮች)፡ የነብር፡ ዲቃላ፡ ኹለተኛ፡ ስሙ፡ ጐለጐ ነው። (ተረት)፡ ጕድባ፡ መዝለል፡ ስላቃተው፡ ከናቱ፡ ከነብር፡ ተለየ፡ ይባላል። ዴሮን፡ እይ።
አነሻሸጥ፡ አነሣሥ ' መነሸጥ ።
አነቀ ዐንገትን፡ ያዘ፡ ዐነቀ።
አነቀረ፡ ጨርሶ፡ ቀዳ፡ (ነቀረ)።
አነቀሸ ፣ሰበረ፡ ነቀሸ።
አነቀሸ፡ ሰበረ/ቀለጠመ ።
አነቀበ፡ ዝኒ ከማሁ ("ለነቀሰ") ።
አነቀተ እንቀት፡ ቀቀለ፡ (ነቀተ) ።
አነቀዘ፡ ነቀዝ አስበላ (ጥንጣን አደረገ - ማቴ. ፮፥፲፱, ፳)
አነቀፈ አሰናከለ፡ ዐነቀፈ ።
አነቀፈ፡ እግርን መታ —ዐነቀፈ።
አነቀፈ፡ እግርን መታ —ዐነቀፈ።
አነቃ (አንቅሀ)፡ ቀሰቀሰ/አስነሣ።
አነቃ (አንቅዐ)፡ ሠነጠቀ/ለየ/ከፈለ ("ቄሱ ኅብስቱን ከላይ ወደ ታች ያነቃዋል።")
አነቃ፡ አመነጨ/አወጣ/አፈለቀ/አስገኘ (ነሐ. ፯፥፰ - "አከሌ ነገርን ከልቡ አንቅቶ ካፉ አውጥቶ ይናገራል") ።
አነቃ፡ አተጋ።
አነቃቀል አመነጋገል፡ መንቀል።
አነቃቀስ፡ አቀናነስ ' መንቀስ ።
አነቃቀር፡ አጨላለጥ (ማንቀር) ።
አነቃቀት፡ አከረታተፍ/አቀቃቀል ("ማን ስከር") ።
አነቃቀዝ፡ አጠናጠን (መንቀዝ) ።
አነቃቀፈ፡ አሰዳደበ/አወቃቀሠ።
አነቃቀፈ፡ አሰዳደበ/አወቃቀሠ።
አነቃቀፍ፡ አሰዳደብ ' መንቀፍ ("ነከፈን" ' አስተውል) ።
አነቃቀፍ፡ አሰዳደብ ' መንቀፍ ("ነከፈን" ' አስተውል) ።
አነቃቃ፡ ቀሳቀሰ/አተጋጋ/ጐተጐተ።
አነቃቃፊ፡ ያነቃቀፈ/የሚያነቃቅፍ።
አነቃቃፊ፡ ያነቃቀፈ/የሚያነቃቅፍ።
አነቃቅ፡ አሠነጣጠቅ (መንቃት) ።
አነቃነቀ፡ አንቀሳቀሰ/አወዛወዘ።
አነቃነቅ፡ አወዛወዝ ' መነቅነቅ ("ነወጠን/ቀነቀነን" ተመልከት) ።
አነቃናቂ፡ ያነቃነቀ/የሚያነቃንቅ (አወ ዛዋዥ አንቀሳቃሽ) ።
አነቈረ (ነቈረ)፡ ደነቈለ/አወጣ ዐይ ንን ("በደን ውስጥ ስኼድ ድንገት ዕንጨት ዐይኔን አነቈረኝ") ።
አነቈረ፡ ደነቈለ፡ ነቈረ።
አነቈጠ፡ አነጠበ (ነቍጣ ጣፈ) ።
አነቋቈር፡ አነካከስ መንቈር ' ማንቈር ።
አነበረ፡ አስቀመጠ/አቈየ/አኖረ።
አነበረረ፡ አስረጀ/አከሳ/አደረቀ/አሰለ።
አነበራረር፡ አረጃጀት (መነብረር) ።
አነበበ (አንበበ)፡ ንባብ ተማረ/አ።
አነበበ፡ ሠነጠቀ/ተረተረ።
አነበነበ፡ ለፈለፈ፡ ነበነበ።
አነበነበ፡ ፈጥኖ አነበበ (ነገር ኣበዛ/ለፈለፈ) ።
አነበዘ፡ አመነቸከ/አቀለመ (ጥራትና ጽዳት አሳጣ) ።
አነበጃጀል፡ አነኈራረጥ፡ መነባጀል፡
አነባ (አንብዐ)፡ አለቀሰ/አፈለቀ/አፈሰሰ (፪ሳሙ. ፩፥፲፪፡ መክ. ፬፥፳) ።
አነባ፡ አለቀሰ፡ ነባ ።
አነባረረ፡ ዐጒልኛ አስጮኸ/አስለቀሰ/አንዠባረረ።
አነባበሰ፡ አጫጫሰ ።
አነባበረ፡ አደራረበ/አገጣጠመ (ዕቃን/ጠላትን) ።
አነባበረ፡ አደነጋገረ ።
አነባበር፡ አኗኗር/አደራረብ (መንበር ማነባበር - ድንበርን ተመልከት) ።
አነባበሮ (ዎች)፡ ኹለቱንና ሦስቱን እንጀራ አነባብረው የጋገሩት ወይነብሩት።
አነባበብ፡ የንባብ አነጋገር (ማንበብ) ።
አነባበዝ፡ ኣቀማም፡ መንበዝ።
አነባባሪ፡ ያነባበረ/የሚያነባብር (አደራራቢ ደርቦ ገዳይ) ።
አነባብ፡ አለቃቀስ፡ ማንባት።
አነባነበ፡ እነዛነዘ/አለፋለፈ።
አነባነብ፡ አነዛነዝ፡ ማነብነብ።
አነባጀለ፡ አነኋረጠ።
አነባጀለ፡ አነኋረጠ፡ ነበጀለ ።
አነብናቢ፡ ያነበነበ/የሚያነበንብ።
አነተ፡ (አመመ)፡ እናት፡ አደረገ፡ እማማ፡ አለ። ነትን፡ እይ
አነተሰ፡ አንከሰ።
አነተራረክ፡ አነዛነዝ ' መነትረክ ።
አነተፈ፡ አነፋ።
አነታረከ፡ አጨቃጨቀ/አባቀተ።
አነከለ፡ ዐነከሰ፡ ነከለ ።
አነከሰ፡ ባንድ እግሩ ረገጠ፡
አነከሰ፡ ዐንካሳ፡ ኾነ፤ዐነከሰ ።
አነከረ (አንከረ)፡ አደነቀ (ዕጹብ) ።
አነከረ፡ አደነቀ፡ ነከረ።
አነከተ፡ ሰበረ/አደቀቀ።
አነከተ፤ሰበረ፡ ነከተ ።
አነካነክ፡ አበላል (መነክነክ) ።
አነካከል፡ ኣነካከስ (ማንከ) ።
አነካከሰ፡ አዘበታተረ/አቦጫጨቀ።
አነካከስ፡ አዘነታተር (መንከስ) ።
አነካከስ/አነካከል፡ ማንከስ ። ባስደራጊ ውና በሳቢ ዘሩ ዐ መጐረዱን አስተውል ("ነከሰን" እይ ") ።
አነካከር፡ አዘፋፈቅ (መንከር) ።
አነካከተ፡ ሰባበረ/አደቃቀቀ
አነካከት፡ ኣደቃቀቅ (መንከት - "ከተከ ተን" እይ) ጣይ።
አነካካ (ዎች)፡ ያነካካ/የሚያነካካ (ኣቀያያሚ - "በረከን" እይ) ።
አነካካሽ፡ ያነካከሰ/የሚያነካከስ።
አነካክ፡ አደሳሰስ (መንካት) ።
አነኰረ፡ ገለበጠ፡ (ነኰረ)
አነኰተ አቃጠለ፡ ነኰተ ።
አነኰተ፡ አቃጠለ/አበሰለ (አነከተ) ።
አነኳኰረ፡ ገለባበጠ።
አነኳኰር፡ አገለባበጥ (ማንኰር - "ኰረ ኰረን" እይ) ።
አነኳኰተ፡ አበሳሰለ (አነካከተ) ።
አነኳኰት፡ የንኵቶ አደራረግ (መንኰት ማንኰት) ፍሬ።
አነኾለለ (አንኮለለ)፡ አደነቈረ አዞረ።
አነኾለለ፡ አዞረ፡ ነኾለለ።
አነኾላለል፡ አደነቋቈር (መነኹለል - "ነጐለለን" እይ) ።
አነዃለለ፡ አደናቈረ።
አነወረ (አንወረ)፡ ክፉ ስም ሰጠ ነውረኛ አደረገ።
አነወረ፡ ነውረኛ፡ አደረገ፡ ነወረ።
አነዋሪ፡ ያነወረ የሚያነውርስም (አጥፊ) ።
አነዋወረ፡ አወጣጣ ገመናን።
አነዋወር፡ ዝኒ ከማሁ (የነውር አወራር ማነወር) ።
አነዋወዝ፡ አዟዟር (መናወዝ) ።
አነዋወጥ፡ እነቃነቅ (መናወጥ/ማናወጥ) ።
አነዘረ (አንዘረ)፡ እንዝርትን በጭኑ ጸፋ/አሾረ (ድር ፈተለ ወዘገ) ።
አነዘረ፡ በገናን/ክራርን መታ/አስጮኸ።
አነዘረ፡ ፈተለ፡ ነዘረ ።
አነዘዘ (አሕዘዘ)፡ ባፍንጫ አወጣ (ምግብን መጠጥን ሰረነቀ) ።
አነዘዘ፡ ባፍን፡ አወጣ፡ ነዘዘ።
አነዛ (አንዝሀ)፡ ነሰረ/አፈሰሰ።
አነዛነዘ፡ አጨቃጨቀ/አነታረከ።
አነዛነዝ፡ አነተራረክ (መነዝነዝ) ።
አነዛናዥ፡ ያነዛነዘ የሚያነዛንዝ (አጨቃ ቂ) ።
አነዛዘር፡ ኣወራወር (መንዘር) ።
አነዛዘዝ፡ የኑዛዜ አነጋገር (መናዘዝ) ።
አነዛዝ፡ አበታተን (መንዛት) ።
አነደ፡ (አኒድ፡ አነደ)፡ አንድ፡ እለ፡ አንድ፡ ኣደረገ፡ ቍጥር፡ ዠመረ።
አነደደ (አንደደ)፡ ቦግ/ቧ አደረገ (አቃጠለ) ።
አነዳደል፡ አሸነቋቈር (መንደል) ።
አነዳደቅ፡ አገነባብ (መንደቅ) ።
አነዳደድ፡ እቀጣጠል (መንደድ - "በለበለን" እይ) ።
አነዳደፍ፡ አጠዛጠዝ (መንደፍ) ።
አነዳድ፡ አቀራረብ (መንዳት) ።
አነገለ፡ ነቀለ = አፈለሰ።
አነገሠ፡ ቀሳ ንጉሥ አደረገ (አሠለጠነ/አገነነ/አከበረ - ፪ዜና. ፴፮፥፬) ።
አነገሠ፡ በቤተ ክሲያን ዙሪያ ታቦት አዞረ።
አነገሠ፡ አበዛ/አበረታ።
አነገረ፡ እንገር ዐለበ።
አነገረ፡ እንገር፡ ዐለበ፡ ነገረ።
አነገረ፡ ኰሽምን የቅሞ ፍሬን በመሬት ውስጥ ቀብሮ ጠበሰ/አበሰለ (እንገር ኣስመሰለ) ላቢ።
አነገበ፡ ያዘ (አብዝቶ ተሸከመ - ሐርበኛው ጋሻውን በክንዱ አንግቧል) ።
አነገበ፡ ያዘ፡ ነገበ ።
አነገተ፡ ባንገት፡ ተሸከመ፡ ዐነገተ ።
አነገነገ፡ አኖቀኖቀ/ጮኸ (ወፍራም የሚያስፈራ ድምጥ ሰጠ/አሰማ - ነብሩ አንበሳው ሰጐጡ ዐዶ ከቢሩ) ።
አነገነገ፡ ድምጥ፡ አሰማ፡ ነገነገ ።
አነጋ፡ አጠባ (ሌሊቱን አሳለፈ ክረምቱን - ፪ሳሙ. ፪፥፴፪) ።
አነጋ፡ የሰው ስም።
አነጋገል፡ አፈላለስ (መንገል - "መነገለን" ተመልከት የነገለ መስም ግስ ነው) ።
አነጋገሡ፡ አከባበረ/አደናነቀ/አዘመነ።
አነጋገሥ፡ አሠለጣጠን (መንገሥ) ።
አነጋገረ መልካም፡ ስብቅል ተለማማጭ።
አነጋገረ፡ አባባለ/አገተ/አከራከረ።
አነጋገረ፡ አጫወተ/አጨዋወተ (ኣስተ ረጐመ) ።
አነጋገር፡ አወራር ("ካያያዝ ይቀደዳል ካነጋገር ይፈረዳል" - ወስላታና ደኅና ሰው ባነጋገሩ ይታወቃል) ።
አነጋገብ፡ አሸካከም (ማንገብ) ።
አነጋገት፡ የደረት አያያዝ (ማንገት ") ። ባ ስደራጊውና በተደራጊው በሳቢ ዘሩ ዐ መጐ ረዱን አስተውል ("ዐነጠጠንና ዐነከሰን" እይ ") ።
አነጋገድ፡ ኣገዛዝ/አሻሻጥ (መነገድ) ።
አነጋገፍ፡ አጠነዋወት/መጨንገፍ ።
አነጋጋሪ (ዎች)፡ ያነጋገረ/የሚያነጋግር/የሚያጫውት (አጫዋች/አስተርጓሚ "ስማ በለው") ።
አነጋጋሪነት፡ አጫዋችነት/አስተርጓሚነት።
አነጋግ፡ አጠባብ (መንጋት) ።
አነግናጊ፡ ያነገነገ/የሚያነዝንግ (በጩኸቱ ምድርን የሚያነቃንቅ) ።
አነጐላለል፡ አደነቋቈር (መነጕለ) ።
አነጐረ፡ አቀለጠ፡ ነጐረ ።
አነጐረ፡ አፈላ/አቀለጠ/አፈሰሰ።
አነጐተ ዕንጐቻ፡ ጋገረ፡ ዐነጐተ።
አነጐደ፡ በኀይል መታ/አጨናፈረ (የጥፊ/የምች/የንቅፋት) ።
አነጐጠ፡ ነጐለ ። ነካ ነጐጠ ።
አነጐጠ፡ ዐነቀፈ/ነካ/ወጋ (በነገር) ።
አነጓ (አንጕዐ)፡ ሰበረ/ቀለጠመ/ኣፈሰሰ።
አነጓ፡ ቀለጠመ፡ ነጓ ።
አነጓለለ፡ አደናቈረ/አነፋለለ።
አነጓጐል፡ አሰነካከል/ማጨናጐል ።
አነጓጐር፡ አፈላል (መንጐር) ።
አነጓጐት፡ የዕንጐቻ አገጋገር (ማንጐት ") ። ባስደራጊውና በተደራጊው በሳቢ ዘሩ ዐ መ ጐረዱን ልብ አድርግ ።
አነጓጐድ፡ አካኼድ (መንጐድ - "ጐነደን" ተመልከት) ።
አነጓጐጥ፡ አወጋግ (ማንጐጥ) ።
አነጠ፡ ጠረበ፥ ላገ፡ ዐነጠ ።
አነጠሰ፡ በቁሙ፡ ዐነጠሰ ።
አነጠረ (አንጠረ)፡ ወረወረ (እመሬት ላይ መታ አናረ አዘለለ አጓነ) ።
አነጠረ (አንጸረ)፡ አሳየ/አመለከተ አስረዳ (እውነት አደረገ አሳመነ - "እከሌ የእከሌን ሌብነት አነጠረበት") ።
አነጠረ፡ በቅመም አፈላ/አቀለጠ/እፈሰሰ/ለየ/አጠራ/አጣፈጠ (ቅቤን) ፈተነ/መረመረ (ማዕድንን ልብን ኵላሊትን - መዝ. ፲፯፥፫, ፳፯፥፪) ።
አነጠበ፡ ነጥብ ጣለ ጸፈ።
አነጠነጠ፡ አረጠረጠ፡ ነጠነጠ።
አነጠነጠ፡ አዘጠዘጠ/አረጠረጠ ("ንግዴ ዳር ዳሩን ያነጥንጥ ሣህለ ሥላሴም ካልጋው አይናወጥ") ።
አነጠዘ፡ ከቁም ጣለ (እስኪሰበርና እስኪሠነጠቅ ድረስ) ።
አነጠዘ፡ ጣለ፡ ነጠዘ ።
አነጠጠ፡ ፋቀ፡ ዐነጠጠ።
አነጠፈ፡ በተወሰደ መሬት ፈንታ ሌላ ተካ ሰጠ።
አነጠፈ፡ ዘረጋ፡ (ነጠፈ)።
አነጠፈ፡ ጣለ/ገደለ (ጠላትን) ።
አነጣ፡ አጠራ/ነጭ አደረገ/አጸዳ ("ያ ነጣ ወዳድ" - ድኻን ወርቀ ለባሽን የማይወድ - ያዕ. ፪፥፬) ።
አነጣነጥ፡ አደባደብ (መነጥነጥ/ማነጥነጥ - የነጠነጠ ሥር በግእዝ ነጢጥ/ነጠ ነው) ።
አነጣጠል፡ አለያየት/አለጣጠጥ (መነ ጠል) ።
አነጣጠስ፡ ዕንጥስታ (ማንጠስ ") ። በጥሬ ውና ባስደራጊው በሳቢ ዘሩ ዐ መጐረዱን ተመልከት ።
አነጣጠረ (አስተናጸረ)፡ ነገርን ከነገር አስተያየ/አመሳሰለ (አገተ አከራከረ አስተማመነ አለያየ) ።
አነጣጠረ፡ ፊት ለፊት አኳዃነ (አደረገ ዐለበ ቀስትን ጠመንዣን) ።
አነጣጠር፡ አናናር (መንጠር) ።
አነጣጠቀ፡ አቀማማ።
አነጣጠቅ፡ አቀማም (መንጠቅ - "ነጠቀ የመነጠቀ ከፊል ነው") ።
አነጣጠብ፡ ኣወዳደቅ (መንጠብ) ።
አነጣጠፈ፡ እዘረጋጋ።
አነጣጠፈ፡ ዘረጋጋ/አሰጣጣ።
አነጣጠፍ፡ አዘረጋግ (ማንጠፍ) ።
አነጣጠፍ፡ አደራረቅ (መንጠፍ) ።
አነጣጣ፡ አጸዳዳ።
አነጣጣሪ፡ ያነጣጠረ/የሚያነጣጥር (ዐዳኝ ተኳሽ አጋች አከራካሪ ዳኛ) ።
አነጣጣፊ፡ ያነጣጠፈ/የሚያነጣጥፍ።
አነጣጥ፡ ኣጸዳድ (መንጣት) ።
አነጥናጭ፡ ያነጠነጠ/የሚያነጠንጥ (አረጥራጭ አዘጥዛጭ) ።
አነጨ፡ አነቃቀለ።
አነጨቀ፡ ከጡንቻ ወደ ትከሻ/ከራስ ወደ ንቃ ከፍ ዝቅ አደረገ (ወይም በትከሻና በራስ ላይ ሚዛን አድርጎ ተሸከመ ያዘ ዕንወትን) ።
አነጨቀ ከፍ፡ አደረገ፡ ነጨቀ ።
አነጩት፡ አነቃቀል (መንጨት መ ላጥ) ።
አነጫነጨ፡ ኣበሳጩ/አጨቃጨቀ።
አነጻ (አንጽሐ)፡ ኣጠራ ' አጠዳ (ነጭ ንጹሕ አደረገ ከኀጢአት ለየ) ።
አነጻ፡ ከለምጽ አዳነ/ፈወሰ ("የሰውን ገላ አቀላ እጠየመ አጠቈረ - ይህ ቃል ለምጽ በኦሪት ርኩስ መባሉን ያሳስባል።") ማንጻት፡ ማጥራት/ማጥዳት።
አነጻጸረ፡ አስተያየ/አመሳሰለ።
አነጻጻሪ፡ ያነጻጸረ/የሚያነጻጽር (አመሳሳይ ") ።
አነፈላለል፡ አደነቋቈር (መነፍለል) ።
አነፈሰ (አንፈሰ)፡ ፍሬን ከገለባ በሰፌድ ለየ እፍ እፍ አለ ለነፋስ ሰጠ አበ ጠረ።
አነፈረ፡ አለመጠን አፈላ/አሞቀ/አፍለቀለቀ (አበሰለ) ።
አነፈረ፡ አፈላ፡ ነፈረ።
አነፈረቀ፡ አመለ/አሞቀሞቀ።
አነፈረቀ፡ ኣስለቀሰ/አንሠቀሠቀ/አስረቀረቀ።
አነፈረቀ፡ ፈረቀ ።
አነፈራረቀ፡ አመጋገለ።
አነፈራረቅ፡ አለቃቀስ (መነፍረቅ) ።
አነፈነፈ (አነፈ)፡ ኣፈነፈነ o ኣሸተተ (ለመብላት ለመተኛት ለመጣላት - ግብ. ሐዋ. ፱፥፳ - "ፈነፈነን" እይ - "አነፈነፈ የሕዝብ አፈነፈነ የካህናት ነው") ።
አነፈነፈ፡ አሸተተ፤ነፈነፈ ።
አነፈነፈ፡ አጋጠ/ኣበላ።
አነፋ፡ በኀይል አገሣ/ተነፈሰ (አንበ ሳው) ።
አነፋለለ፡ አደናቈረ።
አነፋረቀ፡ አላቀሰ (ልማዱ ግን አስ ለቀሰ ነው) ።
አነፋረቀ፡ አነኋረጠ።
አነፋነፈ፡ አሻተተ።
አነፋነፈ፡ አነኋረጠ (ባፍንጫ አናገረ) ።
አነፋነፍ፡ አነኈራረጥ (መነፍነፍ ማነ) ፍነፍ።
አነፋፈሰ፡ አበጣጠረ።
አነፋፈስ፡ የነፋስ አካኼድ (መንፈስ) ።
አነፋፈረ፡ አጣላ/አማረረ ' አባባሰ
አነፋፈር፡ አረጋገጥ (ማናፈር) ።
አነፋፈር፡ አፈላል (መንፈር) ።
አነፋፈቀ፡ አፈላለገ ("የሠራኸኝ ሥራ አያነፋፍቅም") ።
አነፋፈቅ፡ አፈላለግ (መናፈቅ) ።
አነፋፈግ፡ አሠሣሠት (መንፈግ) ።
አነፋፈጥ፡ የንፍጥ አወጣጥ (መናፈጥ) ።
አነፋፍ፡ የነፋስ/የትንፋሽ አሰጣጥ (መ
አነፋፍ፡ የወንፊት አዟዟር (መንፋት) ።
አነፍራቂ፡ ያነፈረቀ/የሚያነፈርቅ (አምጋይ አስለቃሽ) ።
አነፍናፊ፡ ያሸተተ/የሚያሸት (አሽታች እንስሳ ኣውሬ) ።
አነፍናፊ፡ ያነፈነፈ/የሚያነፈንፍ (የሚ ያበላ የሚያግጥ) ።
አኒሳ፡ (ሶች)፡ ከዥራት፡ አንጓ፡ እስከ፡ ጭራ፡ ያለው፡ ግንዶሽ፡ ጥንካሬው፡ ከአጥንት፡ ያነሰ፡ እንደ፡ ሥጋ፡ ልል፡ እንዳጥንት፡ ጥጥር፡ ያይዶለ።
አናሣ፡ (ካንድ በኩል ማንሣትን ረዳ) አቃና (የሳንሳ እያያዘ አዋሰደ) ።
አናረ፡ አነጠረ/አጓነ።
አናረተ፡ እማታ/አጣዘለ።
አናሪ፡ ያናረ/የሚያንር (አጓኝ ") ።
አናሸረ፤አማረረ፡ ነሸረ።
አናሸቀ፡ አጋጠመ ' አጣላ ' አቀያየ ' አ ናሸረ ።
አናሸቀ አጣላ፡ ነሸቀ።
አናሺ፡ ያናሣ/የሚያናግ
አናሽ፡ የሚያንስ፡ ጐዳይ ።
አናቀለ/አነቃቀለ፡ አማዘዘ/አመናገለ መንቀል ' መንቀል ' መንቀያ ጊዜ ምክንያት ዶማ ዐንካሴ ' ሹል ብረት።
አናቀሰ፡ አመሳከረ።
አናቀሰ፡ አናቀለ።
አናቀሰ፡ አጠቃጠቀ/አጣቈረ።
አናቀዘ፡ አጠናጠነ።
አናቀፈ፡ አሳደበ/ኢናወረ/አቋጣ/አዋቀሡ።
አናቀፈ፡ አሳደበ/ኢናወረ/አቋጣ/አዋቀሡ።
አናቃሽ፡ ያናቀሰ/የሚያናቅስ (አመሳካሪ) ።
አናቃፊ፡ ያናተፈ/የሚያናቅፍ።
አናቃፊ፡ ያናተፈ/የሚያናቅፍ።
አናቈረ፡ አጣላ/አናከሰ/አዋጋ ።
አናበ፡ ንብ፡ አረባ፡ ናበ ።
አናበለ፡ እዘለለ/አስጨፈረ።
አናበበ፡ መጻፍን ከመጻፍ አስተያየ።
አናበበ፡ ቃልን ከቃል አዛረፈ።
አናባ (አስተናብዐ)፡ አላቀሰ።
አናባቢ፡ ያናበበ/ያያያዘ/የሚያናብብ (አያያዥ) ።
አናተረከ፡ አነዘነዘ/አጨቃጨቀ/አበቃ።
አናት፡ ማድረግ፡ አናት፡ ቍንጮ፡ ያ፡ ዐናት።
አናትርኪ፡ ያናተረከ/የሚያናትርክ።
አናች፡ አናካሽ።
አናና (አናሕንሐ)፡ አበዛ (ኣፈላ አ) ።
አናና፡ አሠየ/አጐመዡ።
አናና፡ አጐመዠ፡ (ናና)።
አናናሰ፡ አባጀ/አገናባ።
አናናስ፡ የተክል፡ ስም፡ ሥጋማ፡ ተክል፡ ጣፋጭ ።
አናናስ፡ የናስ አሠራር/አገነባብ ("መናስ" - ፪ዜና. ፮፥ ፲፰) ።
አናናረ፡ አዛለለ/አጓጓነ። ናር (ንሂር)፡ መናር።
አናናር፡ አዘላለል (መናር) ።
አናናቀ፡ አጠላላ/እኳሰሰ ("አደገ" ብለኸ ማደግን እይ) ።
አናናቅ፡ አጠላል (መናቅ) ።
አናናደ፡ አዘራጠጠ/እፋረሰ።
አናናድ፡ አዘረጣጠጥ (መናድ) ።
አናናጥ፡ አገፋፍ (መናጥ - "ዋለለን" እይ) ።
አናከሰ፡ አዘናተረ/አባላ/አቧጨቀ።
አናከሰ፡ አጋጠመ/አገናኘ/አያያዘ (አጣላ) ።
አናከረ፡ አዛፈቀ/አዳፈቀ/አራራሰ።
አናኪ፡ ያናካ/የሚያናካ (ኣጋጣሚ) "
አናካ፡ አረመደ ("በድልኸ እያናካ በላ") ።
አናካ፡ አጣላ/አጋጠመ።
አናካሽ፡ ያናከሰ/የሚያናክስ።
አናኮ፣ በደብረ፡ ሊባኖስ፡ ገዳም፡ ዕንጨት፡ የሚፈልጥ፡ ውሃ፡ የሚቀዳ፡ ዓለማዊ፡ ረድኤት፡ ደጐባ።
አናኰረ፡ አገላበጠ ("ማንኰርን ዐገዘ ረዳ") ።
አናኮዎች፡ (አናኵዕ)፡ ረድኤቶች፡ ደጐቦች ።
አናኳሪ፡ ያናኰረ/የሚያናኵር።
አናወረ፡ የነውርን ወሬ አዋጣ/አዋራ።
አናወተ፡ ኣንከራተተ።
አናወዘ፡ ኣዞረ/ኣባከነ/አዋተተ።
አናወጠ/አነዋወጠ፡ አናጋ/አነቃነቀ።
አናወጠ፤አናጋ፡ ነወጠ።
አናወጥ፡ የሰው ስም (አገር በተናወጠ ጊዜ የተወለደ ልጅ ነውጡ/ነውጤ/ነውጠኛ/አናወጥ ተብሎ ይሰየማል) ነቅ።
አናዋዥ፡ ያናወዘ/የሚያናውዝ (አባካኝ) ።
አናዋጭ/አነዋዋጭ፡ ያናወጠ/የሚያናውጥ ያነዋወጠ/የሚያነዋውጥ (አናጊ/አነቃናቂ) ።
አናዎር፡ አኗኗር።
አናዘረ፡ አዛዘነ/ኣዞረ/አስጮኸ።
አናዘዘ፡ የሠሩትን እናገረ (የኅጢአት ስርየት ሰጠ) ።
አናዛዥ (ዦች)፡ ያናዘዘ/የሚያናዝዝ (ባለሥልጣን የንስሓ አባት) ።
አናደለ፡ አለመጠን ጠገበ (ከዚህ የተነሣ ዘለለ/ጨፈረ ወር/መር አለ አነጠነጠ - "ነደረን" ተመልከት ከዚህ ጋራ አንድ ነው) ።
አናደለ፡ ኣባሳ/አሸናቈረ።
አናደለ ዘለለ፡ ናደለ።
አናደደ፡ አያያዘ/አቀጣጠለ።
አናደደ፡ ኣበሳጩ።
አናደፈ፡ አባተነ/አጠዛጠዘ/አዋጋ።
አናዳ (አስተናድአ)፡ አቃረበ/አዋሰደ።
አናዳይ፡ ያናደለ/የሚያናድል (ጥጋበኛ ዘላይ - "አናዳይ እንቧይ ጥሶ ገዳይ" - "ይሁዳ - ኣናዳይ ጌታውን ጉዳይ" እንዲሉ) ።
አናዳጅ፡ ያናደደ/የሚያናድድ "
አናገሠ፡ አባዛ/አበራታ።
አናገሡ፡ አቃባ/አጋነነ/አዳነቀ።
አናገረ፡ (አስደራጊ) ነገር አስወጣ/አስቀባጠረ/አስለፈለፈ/አስለፈፈ/አስነገረ (ኣስ. ፩፥፳፪ - "ዐዋጅ አናግረ" እንዲሉ) ።
አናገደ፡ አገዛዛ/አሻሻጠ/አለዋወጠ።
አናጋ፡ አነቃነቀ፡ ነጓ ።
አናጋሪ፡ ያናገረ/የሚያናግር (ዐለንጋ/ጅራፍ) ።
አናጋሪነት፡ አስለፍላፊነት።
አናጋሽ፡ ያናገሠ/የሚያናግሥ (አጋናኝ) ።
አናጋጅ፡ ያናገደ/የሚያናግድ (አሻሻጭ/ኣለዋዋጭ ሸሪክ) ወጥ።
አናጐረ፡ አፋላ/አቃለጠ።
አናጐደ፡ አካኼደ/አማታ/አፈረ/አበራታ።
አናጓጅ፡ ኣካኺያጅ/ኣማቺ (አጫፋሪ - "ያርጋጅ አናጓጅ" እንዲሉ) ።
አናጠለ/አነጣጠለ፡ አለያየ።
አናጠረ (ጥና)፡ አቃለጠ/አፋሰሰ።
አናጠረ፡ ዘለለ፡ (ናጠረ)
አናጠቀ፡ አቃማ/አሻማ።
አናጠጠ፡ አዘለለ/አስፈነጨ።
አናጠፈ፡ አዘራጋ/አሳተረ።
አናጣ፡ እናጻ።
አናጣሪ፡ ያናጠረ/የሚያናጥር (ዘላይ ወፋሪ) ።
አናጣቂ፡ ያናጠቀ/የሚያናጥቅ (አሻሚ) ።
አናጣይ/አነጣጣይ፡ ያናጠለ/የሚያናጥል ያነጣጠለ/የሚያነጣጥል) ።
አናጣፊ፡ ያናጠፈ/የሚያናጥፍ።
አናጯ፡ አበሳጨ/አጨቃጨቀ።
አናጯ፡ አናቀለ።
አናጻ፡ ዐጠበ/አስታጠበ/አስተጣጠበ "
አናፈለ፡ አወደቀ/ጣለ (አስጨነቀ ትንፍስ ትንፍስ አደረገ ዕረፍት ነሣ - "እከሌ ብርቱ በሽታ ይዞት ያናፍለዋል (ያስጨንቀዋል)") ።
አናፈሰ፡ ልብስን ግምጃን ማንኛውንም ብል የሚበላው ዕቃ ኹሉ ከተከተተ በት ወደ ውጭ አወጣ (በገመድ ላይ ሰቀለ በሜዳ ዘረጋ ከነፋስ አገናኘ) ።
አናፈሰ፡ አባጠረ ("(ማንፈስን ረዳ)") ።
አናፈረ፡ በእግሩ ዐፈር ጫረ (በቀንዱ መነቀረ ውጊያ ፈለገ ጠብ አሸተተ ቧጠጠ መላልሶ ወጋ ረገጠ በሰው በከብት ላይ ጨፈረ ውሻው በሬው ጋቦ) ።
አናፈረ፡ ዐፈር፡ ግረ፡ ናፈረ።
አናፈገ፡ አነፋፈገ/አሣሠተ/አከላከለ (ኣቋረሰ ፥ ኣሻማ) ።
አናፈጠ፡ አለውድ በግድ ገንዘብ አስከፈለ።
አናፈጠ፡ አስከፈለ፡ ነፈጠ ።
አናፈጠ፡ እንፍ አሠኘ (አናጻ - የልጅን አፍንጫ - "እከሌ የተወጋ አያናፍጥም") ። አናፈጠ፡ የተወቃ እኸልን ኣዘራ ለነፋስ ሰጠ (አጣራ) ።
አናፈጠ፡ እንፍ፡ አሠኘ፡ ነፈጠ ።
አናፊ፡ ያናፋ/የሚያናፋ (ጯኺ) ።
አናፋ (ነቀወ)፡ ኣፉን ከፈተ/ጮኸ (ሀ ሀ አለ አህያው) ።
አናፋ፡ ሀሀ አለ፣፡ ነፋ (ነፍኀ)።
አናፋሪ፡ ያናፈረ/የሚያናፍር (ወጊ ' ረ) ።
አናፋሽ፡ ያናፈሰ/የሚያናፍስ (አባጣሪ) ።
አናፋጊ፡ ያናፈገ/የሚያናፍግ (አከላካይ አሻሚ ዐብሮ በል አቋራሽ) ።
አናፋጭ፡ ያናፈጠ/የሚያናፍጥ (አስከ ፋይ) ።
አን፡ (ኢን)፡ እኛ፡ ለሚሉ፡ የትንቢትና፡ የትእዛዝ፡ አንቀጽ፡ አፍራሽ፡ አሉታ ።አንዘነጋ፡ አንዘነጋም፡ አንዘንጋ ።
አን፡ የማድረግ፡ ልማድ። ይኸውም፡ ደጊመ፡ ቃል፡ ባለው፡ ግስ፡ ገበገበ፡ አንገበገበ፡ ገፈገፈ፡ አንገፈገፈ፡ ደበደበ፡ እንደበደበ፡ ጠፈጠፈ፡ አንጠፈጠፈ፡ ቀረቀበ፡ አንቀረቀበ፡ ተከተከ፡ አንተከተከ፡ በማለቱ፡ ይታወቃል ።ቀሰቀሰ፡ አንቀሳቀሰ፡ ቢል፡ አደራራጊነትን፡ ያሳያል። አዕማድን፡ ተመልከት፡ (ቍጥር - ፱)። እንን፡ እይ፡ የዚህ፡ ዘር፡ ነው። እንደዚሁም፡ ተን፡ ኣን፡ በገባበት፡ በተደራጊነት፡ ይገባል።
አንሖጫሖጪ፡ አንሿሿ አቃጨለ ("የ ብር ድምፅ አሰማ") ።
አንሰለጀጀ፡ አደከመ፡ ኣፈዘዘ፡ አንሰዋለለ። በተገብሮነትም ይፈታል።
አንሰለጀጀ አፈዘዘ፡ ሰለጀጀ።
አንሰረሰረ፡ ቀቀለ፡ ሰረሰረ ።
አንሰረሰረ፡ በጣም ቀቀለ አበሰለ አነፈረ (ሰረሰርን ሌላውንም ዐጥንት) ። በተገብሮነትም ይፈታል ።
አንሰረተተ፡ ልብስን፡ ጐተተ፡ (ሰረተተ) ።
አንሰራራ፡ ከድካም ከሞት ዳነ ተመለሰ ነፍስ ዘራ ።
አንሰራፋ አሰፋ፡ (ሰረፋ) ።
አንሰርሳሪ፡ ያንሰረሰረ/የሚያንሰረስር (ቀቃይ አንፋሪ) ።
አንሠቀሠቀ፡ አስረቀረቀ/ካንዠት አስ ለቀሰ/አንፈቀፈቀ ።
አንሠቀሠቀ፣፡አስለቀሰ፡ ሠቀሠቀ ።
አንሰዋለለ፡ አንቀዋለለ፡ (ሰወለለ) ።
አንሰዋለለ፡ እንቀዋለለ፡ እንከዋረረ፡ አንሰለጀጀ።
አንሰገሰገ፡ አስገበገበ፡ ሰገሰገ ።
አንሰገሰገ፡ ኣስገበገበ፡ ቶሎ ቶሎ ኣስበላ/አስዋጠ።
አንሰፈሰፈ፡ አንዘፈዘፈ ሰፈፈ ።
አንሢያጠጠ፡ አስጮኸ (ቀጪን ድ ምፅ አሰማ) ።
አንሣ፡ ብድግ አድርግ።
አንሣ/አንሺ፡ ብድግ አድራጊ ("ቤት አንሣ ግልገል አንሣ" እንዲሉ) ።
አንሳተተ፡ ሰፊ አደረገ (ዘረጋ) ።
አንሳፈፈ፡ አንካፈፈ፡ ሰፈፈ ።
አንሳፈፈ/አሰፈፈ ።
አንሳፋፊ፡ ያንሳፈፈ/የሚያንሳፍፍ ።
አንስተኛ፡ ሴታዊ፡ ሴትማ፡ ሴትኛ።
አንስት፡ ሴት፡ ከወንድ፡ የምታንስ፡ (ግእዝ) ።
አንሶ፡ ተዋርዶ። ማን፡ ከማን፡ አንሶ፡ እንዲሉ ።
አንሶከሶከ፡ አስኬደ።
አንሶከሶከ እንደ፡ ውሻ፡ አስኬደ፡ (ሶከሶከ)።
አንሸልፋ እንሻፎ፡ ብርድ፡ የመታው፡ እኸል፡ ወሰስ ፣ቀላል፡ ዘሩ፡ ሸፈፈ፡ ነው ።
አንሸልፋ፡ ዝኒ ከማሁ ።
አንሸረሸረ አሠገረ፡ ሸረሸረ ።
አንሸረሸረ፡ ኣሠገረ (በቅሎን) ።
አንሸረሸረ፡ ኣሾረ (እንዝርትን) ።
አንሸረሸረ፡ ወደ መንገድ ይዞ ኼደ (አዞረ እናፈሰ ነፋስ አስቀበለ - ሚስቱን ወይም ሌላዋን) ።
አንሸራተተ፡ አዳለጠ፣፡(ሸረተተ)።
አንሸራታች፡ ያንሸራተተ/የሚያንሸራትት (ተዳፋት ገልባጭ እኸል ሸያጭ) ።
አንሸርሻሪ፡ ያንሸረሸረ/የሚያንሸራሽር...ገር ።
አንሸቀሸቀ፡ አስፈራ አራደ አንቀጠ...ቀጠ ።
አንሸቀሸቀ አራደ፡ ሸቀሸቀ።
አንሸቅሻቂ፡ ያንሸቀሸቀ/የሚያንሸቀ...ሽቅ (አስፈሪ አንቀጥቃጭ) ።
አንሸዋረረ፡ አጣመመ ሸወለለ ።
አንሸዋረረ፡ አጣመመ/አንጋደደ ።
አንሺ፡ ቈስቋሽ/ዠማሪ ("ጠብ አንሺ" እንዲሉ) ።
አንሺ/ሽ፡ ያነሣ/የሚያነሣ (አዚያሚ ደብተራ) ።
አንሺነት፡ አንሺ መኾን።
አንሻለለ፡ አንሯቀቀ እንሻረረ (በፍጥነት አስኬደ) ።
አንሻረረ፡ ወረወረ፡ ሸረረ ።
አንሻረረ፡ ወረወረ አንሻለለ (ከመ ቅጽበት አሳለፈ) ።
አንሻተተ አንሸራተተ (ሻተተ)።
አንሻፈፈ፡ አስነከሰ ዐንካሳ አደረገ ።
አንሻፈፈ፡ ወደ፡ ጐን፡ አስረገጠ፡ ሸፈፈ ።
አንሾካሾከ፡ አሾካሾከ ።
አንሾካሿኪ፡ አሾካቯኪ ።
አንሿከከ አሳበቀ ሾከከ።
አንሿከከ፡ አሳበቀ ነገር ሠራ ሾካካ አደረገ ።
አንሿካኪ፡ ያንሿከከ/የሚያንሿክክ (አሳባቲ ነገረ ሠሪ) ።
አንቀለቀለ፡ ልብሱን ነበልባል አስመ
አንቀለቀለ፡ በጣም አረዘመ ።
አንቀለቀለ፡ አንበለበለ፡ አናወዘ፤(ቀለቀለ)።
አንቀለቀለ፡ አዞረ አንቀዠቀዠ አንቀወ ቀወ፡ እናወዘ ።
አንቀለጠጠ፡ ገለጠ፡ ቀለጠጠ ።
አንቀላበሰ ደገፈ፡ ቀለበሰ ።
አንቀላበሰ፡ ደገፈ አንተራሰ፡ ራስጌና ግርጌ አለ ።
አንቀላባሽ፡ ያንቀላበሰ/የሚያንቀላብስ
አንቀላፊ፡ ያንቀላፋ/የሚያንቀላፋ (ሰው ድካም ምሽት ") ።
አንቀላፊኝ፡ የቀበሌ ስም፡ በተጕለት ክፍል ያለ ሜዳ ።
አንቀላፋ፡ ዐረፈ ሞተ ("(፩ነገ. ፪፥ ፲፡ ግብ. ሐዋ. ፯፥ ፷፡ ፩ቆሮ. ፲፭፥ ፳)") ።
አንቀላፋ፡ አሸለበ (ቀለፋ) ።
አንቀላፋ፡ አሸለበ ገረዘዘ አንጐላቸ እንቅልፍ ሰውን ።
አንቀልቃይ፡ ያንቀለቀለ/የሚያንቀለቅል (አንዳጅ አናዋዥ ") ።
አንቀልባ (ዎች)፡ የልጅ ማዘያ መሸፈኛ ከለፋ ቈዳ የተሰፋ ከወደ ላይ ግራና ቀኝ መጥለፊያ (ማሰሪያ) ጠፍርና ዘለበት ያለው ።
አንቀልባ፤የልጅ፡ ማዘያ፡ ቀለበ ።
አንቀሳቀሰ፡ አነቃነቀ አላወሰ ("(፪ሳሙ. ፳፬፥ ፩ ። ኢዮ. ፵፩፥ ፪ ። ኤር. ፲፰፥ ፲፮ ። ዮሐ. ፭፥ ፴፫፥ ፴፰)") ።
አንቀሳቃሽ፡ ያንቀሳቀሰ/የሚያንቀሳቅስ (አነቃናቂ ኣላዋሽ ") ።
አንቀረሰሰ፡ አንቈረሰሰ፡ ኣዘገመ፡ (ቀረሰሰ፡ ቈረሰሰ)፡
አንቀረቀበ፡ አንቀጠቀጠ አናወጠ አ ንጠረጠረ (ብድግ ብድግ አደረገ ምድርን ") ። ወዘወዘ አንገዋለለ፡ ክርትፍን ከደቃቅ ሰበርን እብቅን ከጤፍ በሰፌድ ለየ ። በተገብሮነትም ይፈታል ።
አንቀረቀበ፡ አንጠረጠረ፡ ቀረቀበ ።
አንቀረበበ፡ አንቀረደደ፡ (ቀረበበ)።
አንቀረደደ፡ አንቀረፈፈ፡ ቀረደደ ።
አንቀረፈፈ፡ አረዘመ፦ (ቀረፈፈ)።
አንቀራበጠ፡ አዛወረ (ቀረበጠ)
አንቀራባጭ፡ ያንቀራበጠ/የሚያንቀራ ብጥ (ኣዛዋሪ ") ።
አንቀራባጭነት፡ አንቀራባጭ መኾን (አዛዋሪነት ") ።
አንቀራጩ፡ ቈረጠመ፡ (ቀረጨ) ።
አንቀራጪ፡ ያንቀራጩ/የሚያንቀራጭ (ቈርጣሚ ") ።
አንቀር፡ አሸዋ ሻክላ ።
አንቀርሻ፡ ደም ቅልቅል ሽንትና እውክታ (ጥቍር የዘንጋዳ ውሃ - "ደመናው ሠራ ዊቱ አዝመራው አንቀርሻ መስሎ ይታያል" - "እከሌ የኾነውን እንጃ አንቀርሻ የሚመስል ነገር አስታወከው" - "ጥቀርሻን" እይ) ።
አንቀርሻ፤የዘንጋዳ፡ ውሃ፡ (ነቀረ) ።
አንቀርቃቢ፡ ያንቀረቀበ/የሚያንቀረቅብ (እንገዋላይ ") ።
አንቀርባቢ፡ የሚያንቀረብብ ።
አንቀርፋፊ፡ ያንቀረፈፈ/የሚያንቀረፍፍ (አንከርፋፊ ") ።
አንቀሸረረ፡ አከሳ አደረቀ ሰውነትን ።
አንቀሸረረ፡ አደረቀ፡ ቀሸረረ።
አንቀሻቀሸ፡ ሰባበረ፡ (ቀሸቀሸ)።
አንቀሻቀሸ፡ ሰባበረ/አንከታከተ ። በተገብሮነትም ይፈታል ።
አንቀበቀበ፡ አሠሠተ፡ ቀበቀበ።
አንቀበቀበ፡ አንገበገበ አስነፈገ አሠ
አንቀበደደ፡ ሆድን፡ ነፋ፡ ቀበደደ ።
አንቀበደደ፡ አስረገዘ ነፋ አሳበጠ ። በተደራጊነትም ይፈታል።
አንቀባረረ፡ አቀማጠለ፡ (ቀበረረ) ።
አንቀባራሪ፡ ያንቀባረረ/የሚያንቀባርር (አያት ሞግዚት ") ።
አንቀወቀወ፡ አንከወከወ፡ (ቀወቀወ)፡
አንቀዋለለ (አንገዋለለ)፡ አዞረ አን ከዋረረ አንሰዋለለ፡ አረዘመ ።
አንቀዋለለ፡ አዞረ፡ (ቀወለለ)።
አንቀዋላይ፡ ያንቀዋለለ/የሚያንቀዋልል ።
አንቀዠቀዠ፡ አክለፈለፈ፡ (ቀዠቀዠ)።
አንቀጠቀጠ (አንቀጥቀጠ)፡ አንጠ ረጠረ አንጠበጠበ ነቀነቀ ወዘወዘ አንዘፈዘፈ አብረከረከ አራደ አስፈራ ("(ኢሳ. ፲፬፥ ፲፮)") ። በተደራጊነትም ይፈታል ።
አንቀጠቀጠ፡ አንዘፈዘፈ፡ ቀጠቀጠ ።
አንቀጥቃጢ፡ የዜማ ምልክት፡ (ጢ) ሲያዜሙት የሚያንቀጠቅጥ ።
አንቀጥቃጭ፡ ያንቀጠቀጠ/የሚያንቀጠ ቅጥ (ንጉሥ ኀይለኛ ሰው ወባ ") ።
አንቀጥቅጥ፡ ዝኒ ከማሁ ። "አርድ አንቀጥቅጥ ዕምስ አንቀጥቅጥ" እንዲሉ።
አንቀጫቀጨ፡ ቈሎ ቈረጠመ ።
አንቀጫቀጨ፡ ጥርሱን አጋጨ አፋጩ ።
አንቀጸ፡ ብርሃን፡ የጸሎት፡ ስም፡ ቅዱስ፡ ያሬድ፡ በውዳሴ፡ ማርያም፡ መጨረሻ፡ የጨመረው፡ ድርሰት ።ቅዳሴ፡ ማርያምም፡ የርሱ፡ ሳይኾን፡ አይቀርም።
አንቀጸ፡ ብርሃን፡ ደጀ፡ ብርሃን፡ የቤተ፡ ልሔም፡ በር፡ በስተምሥራቅ፡ ያለ፡ (ሉቃ፪፡ ፬)።
አንቀጸ፡ ተዐቅቦ፡ ስለ፡ ጌታችን፡ ባሕርያት፡ አለመቀላቀል፡ አለመደባለቅ፡ የሚናገር፡ የሃይማኖተ፡ ኣበው፡ ክፍል ።
አንቀጸ፡ ተዋሕዶ፡ ስለ፡ ጌታችን፡ አካል፡ ፩፡ መኾን፡ የሚናገር፡ የሃይማኖተ፡ አበው፡ ክፍል።
አንቀጺ፡ ዐበዘ፡ (ኀበዘ)፡ ነው ።
አንቀጽ፡ (ነቂጽ፡ ነቅጸ፡ ደረቀ)፡ በር፡ መግቢያ። አንቀጽ፡ መቃንና፡ ጕበንን፡ ያሳያል ።
አንቀጽ ፲ የመጻፍ፡ ክፍል፡ ትርጓሜው፡ የንባብ፡ የቃል፡ በር፡ ማለት፡ ነው።
አንቀጽ፡ ሃሌታ፡ ቍጥሩ፡ ከአንድ፡ እስካሥር፡ የሚደርስ፡ ሥረይነት ' ያለውና፡ የሌለው፡ ሃሌታ ። የዜማ፡ በር፡ ስለ፡ ኾነ፡ አንቀጽ፡ ተባለ ።
አንቀጽ፡ መዠመሪያ፡ በሩቅ፡ ወንድ፡ ቀጥሎ፡ በሰባት፡ ሰራዊት፡ በኀላፊና፡ በትንቢት፡ በዘንድ፡ በትእዛዝ፡ የሚነገር፡ ግስ፡ የቃል፡ ማሰሪያ ።ዘማች፡ አንቀጽ፡ ነባር፡ አንቀጽ፡ እንዲሉ (ዐቢይ፡ አንቀጽ)፡ ገደለ። (ንኡስ፡ አንቀጽ)፡ መግደል፡ አገዳደል። (ቦዝ፡ አንቀጽ)፡ ገድሎ። (የወንድና፡ የሴት፡ አንቀጽ)፡ ዐወቀ፡ ዐወቀች።
አንቀጽ፡ ተቀባይ፡ ባለቤት፡ ይኸውም፡ የነገር፡ የጕዳይ፡ ነው።
አንቀጽ፡ አስቀረ፡ እንዳያስር፡ አደረገ፡ ዐቢይ፡ አገባብ፡ ግስን።
አንቀጽ፡ አኰቴት፡ አንቀጸ፡ ብርሃን፡ ተደግሞ፡ የሚደረግ፡ ተረፈ፡ መሥዋዕት።
አንቀፈረረ አረዘመ፡ ቀፈረረ።
አንቀፈደደ፡ አንቀረደደ ። በተደራጊነትም ይፈታል ።
አንቀፈደደ፡ አንቀረደደ፡ ቀፈደደ ።
አንቍር፡ ዝኒ ከማሁ ("ወፍን" እይ) ።
አንቂ (አንቃሂ)፡ ያነቃ/የሚያነቃ (ቀስቃሽ አስነሺ አትጊ) ።
አንቂ (አንቃዒ)፡ የሚያነቃ/የሚሠነ ጥቅ (አመንጪ - "አንቃን" እይ) ።
አንቂ፡ ከደብረ ሊባኖስ በስተሰሜን ያለ አገር (የቅዱስ ሚካኤል ኣጥቢያ) ።
አንቂ፤ያገር፡ ስም፡ ነቃ።
አንቂደኛ (ኞች)፡ ታሪከኛ ድንቅ አ ድራጊ ተናጋሪ።
አንቂደኛ ታሪከኛ፡ ነቀደ ።
አንቂድ፡ ታሪክ፡ ነቀደ ።
አንቂድ፡ ታሪክ ድንቅ ነገር በትጋት የሚገኝ።
አንቃ፡ (አንቅዕ)፡ የዛፍ፡ ስም፡ ቀላል፡ ዕንጨት ። (ተረት)፡ አንቃ፡ ለራሱ፡ አይበቃ ።ዘሩ፡ ነቃ (ነቅዐ)፡ ይመስላል ።የሙጫው፡ ሽታ፡ ከዕጣን፡ ይበልጣል፡ ይባላል፡ ከዚህ፡ የተነሣ፡ አንቃ፡ አመንጭ፡ ተብሎ፡ ሊተረጐም፡ ይችላል ።
አንቃረረ፡ ጮኸ ቀረረ።
አንቃረረ፡ ጮኸ አገረረ ("አንቃሩ እስኪ ታይ ድረስ ") ።
አንቃሪ፡ ያነቀረ/የሚያነቅር (ጨላጭ) ።
አንቃሪ፡ ያነቀረ/የሚያነቅር (ጨላጭ) ።
አንቃራሪ፡ ያንቃረረ/የሚያንቃርር (ፊኺ አግራሪ ") ።
አንቃር (አንቀር)፡ የእንጥል ስም (
አንቃር፡ ላይኛው የጕረሮ አፍ።
አንቃር መታው፡ አስታወከው ("እውክታው በኀይል አንቃሩን እየመታ ወጣ") ።
አንቃር፡ የሚዛን መርፌ ' ወይም ልሳን።
አንቃቂ፡ ያንቃቃ/የሚያንቃቃ ።
አንቃቃ፡ አሞቀ አመጠጠ አደረቀ አቀነበረ፡ አጕላላ ።
አንቃች፡ ያነቀተ/የሚያነቅት (ፈጪ ' ቀቃይ) ።
አንቃች፡ ያነቀተ/የሚያነቅት (ፈጪ ' ቀቃይ) ።
አንቃዥ፡ ያነቀዘ/የሚያነቅዝ ") ።
አንቃፈፈ - አንጋፈፈ - አንከረፈፈ ።
አንቃፈፈ፡ አንከረፈፈ፡ ቀፈፈ።
አንቄ፡ ጭላት፡ ጭልፊት፡ ገዲ ።
አንቈላለጠ፡ ላይሰጥ አሳየ፡ አሳይቶ ነሣ፡ ኣሠየ አጐመዠ ።
አንቈላለጠ፡ አሠየ፡ ቈለጠ።
አንቈላላጭ፡ ያንቈላለጠ/የሚያንቈላ
አንቈላጰላጠሰ፡ አከበረ፡ (ቈለጰለጠሰ) ።
አንቈረቈረ፡ መረ፡ ቈረቈረ።
አንቈረቈረ፡ አስተካክሎ አዜመ ።
አንቈረቈረ፡ አፈሰሰ አወረደ ጨመረ ቀዳ መላ አሳለፈ ዐደለ ሰጠ መጠጥን ።
አንቈረበበ አቈረበጪ (ቈረበበ)።
አንቈረዘዘ፡ አንጠለጠለ፡ (ቈረዘዘ)
አንቈራባ፡ ቈዳን አንኳኳ አንኰራፋ ።
አንቈራባ፡ አንኳኳ፡ ቈረባ።
አንቈራጠጠ፡ አላሳርፍ፡ አለ፡ (ቈረጠጠ) ።
አንቈራጣጭ፡ ያንቈራጠጠ/የሚያንቈራጥጥ (አንጐራዳጅ ") ።
አንቈራፋ - አንኰራፋ - አንቈራባ፡ መቋ ረፊያውን ።
አንቈራፋ፡ አንኰራፋ፡ ቈረፈ።
አንቈርቋሪ፡ ያንቈረቈ/የሚያንቈረቍር (አሳላፊ ዐዳይ ") ።
አንቈሻበለ፡ ለመነ፡ (ቈሸበለ)
አንቈጠቈጠ፡ ሸለመ፡ -ቈጠቈጠ ።
አንቈጠቈጠ፡ ካባ ላንቃ ድርብ ሽለመ አስጌጠ ። በተገብሮነትም ይፈታል ።
አንቈጣቈጠ - አቈናቈነ፡ አሠሠተ ።
አንቈጨቈጪ አደቀቀ፡ ቈጪ ።
አንቈጫቈ፡ ኣነጫነጩ ።
አንቈጫቈጪ፡ አነጫነጩ፡ ቈጨቈል ።
አንቈጯቈል፡ አደቀቀ አንከታከተ ።
አንቋለጠ (አፍተወ)፡ አቋመጠ ወ ነገ ወሰጠ ወዘወዘ ።
አንቋለጠ፡ ወነገ፡ ቈለጠ።
አንቋለጠች፡ ወደ ቈለጥ አስጠጋች ወዘወዘች ገላዋን ።
አንቋሊት፡ ዐይብ።
አንቋሊት፡ ዐይብ።
አንቋሊት፡ ዐይብ፡ ነቀለ ።
አንቋላጭ፡ ያንቋለጠ/የሚያንቋልጥ ።
አንቋሰሰ - አንቈረሰሰ፡ ጐተተ ።
አንቋሰሰ ጐተተ፡ (ቈሰሰ)
አንቋረረ፡ በንቅልፍ ልብ እንቍራሪትኛ ጮኸ፡ ቃዠ አላዘነ ።
አንቋረረ፡ አላዘነ፡ ቈረረ።
አንቋሪ፡ ያነቈረ/የሚያነቍር።
አንቋራሪ፡ ያንቋረረ/የሚያንቋርር (አላ ዛኝ ") ።
አንቋር (አንኳር)፡ ድብልብል ዕጣን ወይም እንኵሮ ። "ነኰረን" ተመልከት ።
አንቋቊ፡ ያንቋቋ/የሚያንቋቋ (ተጫኝ ጠምዛዥ ") ።
አንቋቋ፡ አጮኸ ! ወገብን ጣትን አሰ ማማ ።
አንቋቋ ጣትን አጮኸ፡ ቋቋ።
አንቋጠጠ፡ አኰራ፡ ቈጠጠ።
አንቋጠጠ፡ ኰሰተረ፡ አኰራ ከመድራት አራቀ ።
አንበለበለ (አንበልበለ)፡ አንቦገቦገ፡ ቦግ ቦግ አደረገ፡ አነደደ ኣቃጠለ ።
አንበለበለ፡ አነበበ፡ ኣነበነበ ።
አንበለበለ፡ አነደደ፡ በለበለ።
አንበላይ፡ ባለጥሩር፡ ዐምበላይ።
አንበላጠጠ፡ አገላመጠ አስፈራ ።
አንበል ፣የጭፍራ፡ አለቃ፡ ዐምበል።
አንበልጋ፡ ፈሪ፡ ቡከን፡ ሴታውል ።
አንበሲት፡ ወንዲት፡ ዐጅሪት ።
አንበሳ፡ (በስበሰ)፡ በዱር፡ በበረሓ፡ የሚኖር፡ የድመትና፡ የነብር፡ ወገን፡ አውሬ፡ ልበ፡ ሙሉ፡ ደፋር፡ በኵርማው፡ የበሬ፡ ዠርባ፡ የሚሰብር፡ አሸናፊ፡ የዠግና፡ የሐርበኛ፡ የንጉሥ፡ ምሳሌ ።ተባቱም፡ እንስቱም፡ አንበሳ፡ ይባላል ።ለይቶ፡ ለመናገር፡
አንበሳ፡ መደብ፡ ዐዘቅተ፡ ኵስሕ፡ ዘንጉሥ ።
አንበሳ፡ ውድም፡ ባ፲፻፡ ዓ፡ ም፡ የነበረ፡ የኢትዮጵያ፡ ንጉሥ፡ የውድማ፡ አንበሳ፡ ማለት፡ ነው ።
አንበሳ ያለው የተሰጠው ("መጠኑ የነብር ኦሮ ' በጕዳ ' ይለዋል በጋራ ጐርፎ ይገኛል") ።
አንበሳዋ፡ የርሷ፡ አንበሳ። አንበሳዋ፡ አንበሳዪቱ፡ ያች፡ አንበሳ፡ (ኢዮ፴፰፡ ፴፱)።
አንበሳው፡ ያ፡ አንበሳ፡ የርሱ፡ አንበሳ ።
አንበሴ፡ አንበሳዊ፡ የኔ፡ አንበሳ። የወንድና፡ የሴት፡ ስም ።
አንበስ፡ አንበሳ፡ መሳይ፡ በሬ ።
አንበስ፡ የሰው፡ ስም፡ አባ፡ አንበስ፡ (ስንክሳር)።
አንበስማ፡ ያንበሳ፡ ዐይነት፡ አንበሳ፡ መልክ ።
አንበሶች፡ (አናብስት)፡ ፪ና፡ ከ፪፡ በላይ፡ ያሉ፡ ተባቶችና፡ እንስቶች፡ (ማሕ፬፥፰) ።
አንበሶች፡ ዠግኖች፡ ሐርበኞች ።
አንበረበረ፡ በረበረ ።
አንበረከከ (አብረከ)፡ አበረከ አሸ በረከ አስተኛ ።
አንበሪ፡ ታላቅ፡ ዓሣ፡ ዐንበሪ።
አንበራሌ፡ የዋሊያ፡ ዐይነት፡ የበረሓ፡ ፍየል፡ ቀንዱ፡ የረዘመ፡ የተጠመዘዘ ። አንበራሌ፡
አንበራጠጠ፡ አጓደደ፡ አንበጣረረ ።
አንበራጠጠ፣አጓደደ፡ በረጠጠ።
አንበርብር፡ የሰው፡ ስም፡ በረበረ ።
አንበርብር፡ የሰው ስም፡ በርብር ውረር ዝረፍ ማለት ነው ።
አንበርካኪ፡ ያንበረከከ የሚያንበረክክ የሚያስተኛ የሚያሸበርክ ግመለኛ ።
አንበሸበሸ፡ ደስ አሠኘ አስደሰተ ። መላልሶ ሰጠ፡ በብዙ አጠጣ አጠገበ ።
አንበሸከከ፡ -አንቀባረረ፤-(በሸከከ)።
አንበቀበቀ (አንበቅበቀ)፡ አጮኸ፡ ሳጥ ጣጥ ቈረጥ አደረገ፡ አንዛረጠ፡ መላልሶ ፈሳ ።
አንበከበከ፡ አንደከደከ አንደገደገ አፈላ አዘለለ ።
አንበደበደ፡ ፡ አስፈራ ፣በደበደ።
አንበደበደ (አንበድበደ)፡ አስፈራ አንቀጠቀጠ፡ በተደራጊነትም ይፈታል ።
አንበዲያት፡ የገብስ፡ ስም፡ በግንቦት፡ ተዘርቶ፡ በጳጕሜ፡ የሚደርስ፡ የሚታጨድ፡ ገብስ፡ ግንቦቴ።
አንበጠረረ፡ አኰራ አስታበየ ።
አንበጠረረ፣አኰራ ፣በጠረረ ።
አንበጣ፡ (ጦች)፡ (ዐረ፡ ነበጠ፡ ፈላ፡ ገነፈለ፡ በዝቶ፡ ወጣ)፡ በቁሙ፡ በበረሓ፡ አሸዋ፡ ውስጥ፡ ተፈልፍሎ፡ የሚፈላ፡ አኰብኳቢ ' ባላ፬፡ እግር፡ ባለ፪፡ ክንፍ፡ ክንፉ፡ ሲጠና፡ ባየር፡ የሚበር፡ ሣርና፡ ቅጠል፡ እኸል፡ የሚበላ ።አንበጣ፡ ሆዳም፡ ሰው፡
አንበጣ፡ ደፈር፡ አንበጣ፡ የሚመጣበት፡ ከፍታ፡ ይኸውም፡ በደብረ፡ ብርሃን፡ ኣቅራቢያ፡ ይገኛል።
አንበጨበጨ፡ አፈለቀ እመነጨ፡ አስ ጮኸ ።
አንቡላ፡ አንብላ፡ (ትግ፡ ቡላ)፡ የጠጅ፡ አተላ ።ቡላን፡ ተመልከት ።
አንቡጋድ፣(ትግ፡ በገድ ፣ኀፍረተ ብእሲት)፡ ፈሪ፡ ሴታውል፡ ቡከን።
አንባ፡ መንደር፡ ዐምባ ።
አንባ፡ ራስ፡ ያምባ፡ ራስ፡ ዐምባ፡ ራስ።
አንባ፡ ገነን፡ ያምባ፡ ጌታ፡ ዐምባ፡ ገነን ።
አንባ፡ ጓሮ፡ ጠብ፡ ክርክር፡ ዐምባ፡ ጓሮ ።
አንባ፡ ጓሮኛ፡ ጠበኛ፤ዐምባ፡ ጓሮኛ ።
አንባላ ነጭ፡ ወፍ፡ ዐምባላ ።
አንባላይ፡ ነጭ፡ ፈረስ፡ ዐምባ ላይ ።
አንባሰል፡ አገር፡ ዐምባሰል።
አንባረቀ -በኀይል፡ ጮኸ፡ ባረቀ።
አንባር (ሮች)፡ የእጅ ጌጥ (ክብና ሰፊ ወፍራም ቀለበት ከወርቅና ከብር ከንሓስ ከመዳብ የተበጀ ማልደያ ቢተዋ የእጅ ቦራ የልካ - ዘፍ. ፳፬፥፳፪፡ ፴፰፥፲፰ - ተረት፡ "ሲያረጁ አንባር ይዋጁ" - ብርን እይ - የአንባር ምስጢር ከጥንት የነበረ መኾኑን ያሳያል) ።
አንባር ማያ፡ አንባር የሚውልበት/የሚደረግበት የእጅ ክፍል።
አንባር የእጅ ጌጥ፡ ነበረ።
አንባሻ፡ የትግሬ፡ ኅብስት፡ ጢብኛ፡ ሙልሙል፡ ጌጠኛ፡ ድፎ፡ (፩ሳሙ ፲፡ ፫) ።
አንባቀቀ (አብቀወ አንባሕቀወ)፡ አዛጋ አፋሸገ፡ ኣ አለ፡ አፉን አለልክ ከፈተ አላቀቀ ።
አንባቀቀ፡ አዛጋ፡ በቀቀ።
አንባቢ (ቦች)፡ ያነበበ/የሚያነብ (ማቴ. ፳፬፥፲፭ - "ሃይማኖተ ኣበው አንባቢ"፡ "ፍታነገሥት አንባቢ" እንዲሉ) ተነ።
አንባቢነት፡ አንባቢ መኾን።
አንባባ (አንቤበየ)፡ አሠየ እጐመዥ አናወዘ አቅበዘበዘ፡ አስጮኸ ለስሪያ ለዝሙት ። ያንባባኸ ኵ(ቍርንቢ እንዲሉ ። ዳግመኛም በ ተገብሮነት ይፈታል ።
አንባባ ጮኸ፡ አስጮኸ፡ ባባ።
አንባዛ፡ ቅርፊት የሌለው ታላቅ ዓሣ (ሌላውን ታናሽ ዓሣ የሚውጥ/የሚሰለቅጥ - ምዥልግን እይ) ።
አንባዛ፡ ዓሣ፡ ነበዘ።
አንብር፡ የምልክት ስም (የዜማ ምልክት - "ባጭር ተው አስቀምጥ" ማለት ነው - ርን እይ) ።
አንቦ፡ የማዕድን፡ ዐፈር፡ ዐምቦ።
አንቦ፡ ጨው ጨው የሚል ዐፈር ወይም ውሃ ("ዐምቦ" ተብሎ ቢጻፍ ግን ትርጓሜው ሌላ ነው) ።
አንቦረቀቀ አሰፋ፡ (ቦረቀቀ) ።
አንቦዠቦዠ አስደሰተ፡ (ቦዠቦዠ)።
አንቦገቦገ -አንበለበለ፡ -(ቦገቦገ) ።
አንቦጨቦጪ፡ በጠበጠ ወዘወዘ፡ አፈ ሰሰ ።
አንቦጫረቀ፡ አንደፋደፈ፡ አንደፋረሰ አማታ አንቧቸ ።
አንቦጫቦጨ አወዛወዘ፡ ቦጪ ቦል ።
አንቦጫቦጨ፡ ኣወዛወዘ አማታ፡ ኣፋ ሰሰ ።
አንቧለለ፡ አሰፋ ሰፊ አደረገ ። አሰ አትጐለጐለ ።
አንቧለለ፡ አሰፋ፡ አጨሰ፡ ቦለለ።
አንቧቀሰ፡ አደከመ አሰለተ አጠወ ለገ ።
አንቧቧ አንፋፋ (ቧቧ)፡
አንቧተረ፤- አንገራበደ (ቧተረ) ።
አንቧታሪ፡ የንቧተረ የሚያንቧትር፡ እንገራባጅ አንፋሻፊ ጕረኛ ።
አንተ ሆይ፡ ሰውዮ፡ ቃለ፡ አጋኖ፡ ነው።
አንተ፡ ት፡ የቅርብ፡ ወንድ፡ ዐጸፋና፡ ቅጽል፡ በቂ። አንተ፡ ና፡ ዐጸፋና፡ በቂ። አንተ፡ ሰው፡ ቅጽል። ትርጓሜው፡ እስኸ፡ ርስኸ፡ ራስኸ፡ ቅልኸ ።በግእዝም፡ እንደዚሁ፡ አንተ፡ ይባላል ።
አንተ፡ ትብስ፡ አንተ፡ ትብስ፡ ተባባለ፡ ተከባበረ፡ በሥራ፡ በነገር፡
አንተላከሰ፡ አመቀመቀ፡ አመነታ።
አንተላከሰ፡ አደከመ፡ ለከሰ ።
አንተላከሰ፡ አደከመ፡ አሰነፈ፡ አታከተ ።
አንተሰተሰ፣ አስፈራ፣ (ተሰተሰ)።
አንተረከረከ፡ አንከባለለ።
አንተረከከ፡ አሠባ አወፈረ (ሙክትን...ፍሪዳን) ።
አንተረከከ አፈራ፡ ተረከከ።
አንተረከከ፡ አፈራ ኣበሰለ ("ደረከከ" ብለኸ "አንደረከከን" እይ) ።
አንተረፈ (አንትርፎ)፡ አተረፈ፡ አበዛ፡ አስረፈ ።
አንተረፈረፈ፡ አትረፈረፈ።
አንተረፈፈ፡ መላ፡ (ተረፈፈ)፡
አንተራሰ፡ ትራስ ሰጠ፡ አስደገፈ፡ ቀና አደረገ።
አንተራሰ፣ራስን አስደገፈ፡ ራሰ ።
አንተራሽ፡ ያንተራሰ፡ የሚያንተርስ፡ ኣሽከር ሎሌ ልጅ እናት።
አንተራፋ፡ ሰበረ ፈለቀ ኣማለቀ (ውሃ ያለበት እንስራን የሰውን ራስ) ። ("የዱሮ ግጥም" - ድንጋይ ካፋፍ ወርዶ እዘ ብጥ ያርፋል - አዎን ያርፋል - ሰው ያገኘ እንደኹ ያንተራፋል - አዎን ያንተራፋል) ።
አንተራፋ፣፡ሰበረ፡ (ተረፋ)።
አንተርፋ፣ ወተታም፡ ቅጠል፣ (ተረፋ) ።
አንተርፋ፡ የቅጠል ስም (ለመጋኛ በጠጡት ጊዜ የሚያስቀምጥና የሚያስታውክ ዐረፋ የሚያወጣ ዐረግ) ።
አንተበተበ፡ በቀላል ቈላ (ተቈላ) ።
አንተበተበ፡ በቀላል፡ ቈላ፡ ተበተበ።
አንተባተበ፡ ለንባዳ አደረገ (ኣኰላ...ተፈ) ።
አንተባተበ፡ አኰላተፈ፣፡ተበተበ ።
አንተብታቢ፡ ያንተበተበ/የሚያንተብ...ትብ ።
አንተከተከ (አንሳዕስዐ)፡ አሞቀ አፈላ እነፈረ አንጠቀጠቀ (ኢዮ. ፵፩፡ ፳፫) ። በተገብሮነትም ይፈታል ።
አንተከተከ አነፈረ፡ ተከተከ።
አንተክታኪ፡ ያንተከተከ/የሚያንተከትክ (ኣፍሊ) ።
አንተገተገ አብረቀረቀ፤ተገተገ ።
አንተገተጉ (ነቲግ/ነትግ)፡ ኣብረ ቀረቀ ኣብለጨለመ ቦግ ቦግ አደረገ አበራ ።
አንቱ፡ የቅርብ፡ ወንድና፡ ሴት፡ ከበሬታ፡ እስዎ፡ ርስዎ ። ደረገመን፡ እይ ።
አንቱም፡ ርስዎም ።ኣንቱም፡ አንቱም፡ አትዋሹ፡ ወደ፡ ጓሮ፡ ልትሸሹ ።
አንቱታ ፣ ርስዎታ፡ ከበሬታ፡ አንቱ፡ ማለት።
አንቱዬ፡ የኔ፡ አንቱ።
አንታታ፡ በጠሰ ባለማቋረጥ ጥይት ተኰሰ ("አንጣጣ") ።
አንታፊ፡ አነፋፊ።
አንትርክራኪ፡ የሚያንከባል።
አንትርፍራፊ፡ የሚያተርፈረፍ።
አንቸለቸለ አነበበ፡ (ቸለቸለ)።
አንቸሰቸሰ አጨሰ፡ (ቸሰቸሰ)።
አንቸረፈፈ፣፡አስኰረፈ፣፡(ቸረፈፈ) ።
አንቸበቸበ አንተገተገ፡ ጠበሰ ቸበቸበ ።
አንቸበቸበ፡ ጠበሰ አበሰለ አቃጠለ ።
አንቸከቸከ፡ ሥጋን በቅቤ በዘይት ጠበሰ ("ተከተከ" ብለኸ "አንተከተከን" እይ) ።
አንቸከቸከ፡ ሸነ አንፎከፎከ ።
አንቸከቸከ፡ ጠበሰ ፥ሸነ፡ ቸከቸከ ።
አንቺ፡ ሆይ፡ ሴትዮ፡ ቃለ፡ አጋኖነው ።
አንቺ፡ ች፡ (አንቲ)፡ የቅርብ፡ ሴት፡ ዐጸፋና፡ ቅጽል፡ በቂ። እስሽ፡ ርስሽ። ባላገርም፡ ጠንቋይን፡ አምኖ፡ ሴቷን፡ አንተ፡ ወንዱን፡ አንቺ፡ ይላል።
አንቺዬ፡ የኔ፡ አንቺ ።
አንቻረረ፡ አዘለለ (ቸረረ)።
አንቻሮ፡ በወሎ ክፍል ያለ አገር ("አዘልሎ" ማለት ነው) ።
አንቻቻ አስጮኸ፡ (ቻቻ)።
አንኦሮይ፡ ሐኪም/ወጌሻ (ወይም ሌላ) ።
አንከሊስ፡ የኵፍኝ ስም ("በሽታው ከፈንጣጣ የሚያንስ ስለ ኾነ እንከሊስ ተባለ አንከሊስ ደካማ ጕልበቱ ያለቀ ሰው ዐቅመ ቢስ ") ።
አንከሊስ፡ ደካማ፡ ከለሰ ።
አንከሊሶች፡ ደካሞች ("ዐቅሙ ቢሶች") ።
አንከላወሰ፡ አንጠራወዘ፡ (ከለወሰ) ።
አንከረደደ አዞረ፡ ከረደደ ።
አንከረጠጠ ሆድን፡ ነፋ (ከረጠጠ) ።
አንከረፈፈ፡ አንቀረፈፈ (ከረፈፈ) ።
አንከራበተ፡ አንገላታ፡ ከረበተ።
አንከራተተ፡ አዞረ (ከረተተ)
አንከርት፡ ምድጃ፡ ዋግንቦ (ከረተተ)
አንከሸለለ፡ አደረቀ ከሸለለ።
አንከበለለ፡ አድበለበለ ("አከበበ") ።
አንከበከበ፡ አድበለበለ ("አንከበለለ የፍትፍት የቅቤ የማር የሊጥ የኮሶ የመድኀኒት የጭቃ ክብ አደረገ ") ።
አንከበከበ ከበበ ።
አንከባለለ፡ ናዳ ሰደዶ አገላበጠ ("እን ደባለለ የጋማ ከብትን") ።
አንከባለለ፡ አቍለጨለጨ ("አዥገረገረ ዐይኑን") ።
አንከባለለ፡ አገላበጠ፡ ከበለለ።
አንከባላይ (ዮች)፡ ያንከባለለ/የሚያ ንከባልል ("አገላባጭ እንደባላይ") ።
አንከብካቢ፡ ያንከበከበ/የሚያንከበክብ ("አድበልባይ ሥሥት የተባለ ተንቀሳቃሽ አንከብካቢ ") ።
አንከተከተ፡ አሣቀ ከተከተ።
አንከታከተ፡ ሰባበረ ከተከተ።
አንከዋተተ፡ አንከራተተ፡ (ወተተ) ።
አንከዋታች፡ ያንከዋተተ/የሚያንከዋ ትት ("አንከራታች ") ።
አንከፈረረ፣፡አደረቀ፡ ከፈረረ ።
አንከፈከፈ አላስረግጥ፡ አለ፡ ከፈከፈ ።
አንካላ (ሎች)፡ ያነከለ/የሚያነክል (ዐንካሳ) ።
አንካሴ በቁሙ፡ ዐነከሰ።
አንካረረ፡ አንጋለለ፡ ከረረ ።
አንካሪ፡ ያነከረ/የሚያነክር (አድናቂ) ።
አንካቦ ("ዎች")፡ ፬ ብርሌ ጠላ ወይም ጠጅ የሚይዝ ("የሚችል") ከቀንድና ከን ጩት የተበጀ ዋንጫ።
አንካቦ፡ በአንካቦ ዐይነት የተሠራ ረዥም ኩባያ ተሳክቶ ተደራርቦ የሚቀመጥ።
አንካቦ፡ ትልቅ፡ ዋንጫ፡ ካበ።
አንካቦ፣ ከገሣ የተታታ አዳሎችና ሱማሌዎች ዐሸቦ የሚያመጡበት ዋንጫ መሳይ ሞላላ አኩፋዳ "
አንካች፡ ያነከተ/የሚያነክት (ሰባሪ አድ) ።
አንካካ፡ ዐሰበ ("ጠረጠረ ያለፈው እን ቀጽ የሚመጣው ስም መኾኑን አስተውል አንካካ ዐሳብ ቅርታ ጥርጥር እከሌ አንካካ ገብቶታል።") ።
አንካካ፡ አሣቀ ("አንከተከተ") ።
አንካካ፡ ገደል፡ ሰደደ (ካካ)።
አንካካ፡ ጥርጥር፤(ካካ)።
አንካፈፈ (አጽለለ)፡ ኣቀለለ ("እነሣ አሰፈፈ አንሳፈፈ በላይ አደረገ ታንኳ ") ።
አንካፈፈ፡ አንሳፈፈ፡ ከፈፈ ።
አንካፋፊ፡ ያንካፈፈ/የሚያንካፍፍ ።
አንክሮ፡ ሥነ ፍጥረትን እያዩ ፈጣሪን ማድነቅ (መዝ. ፻፬፥፬, ፳፭)
አንክሮ፡ ንኡስ አገባብ (ሆይ ዎ) ።
አንኮ፡ (አንኵዕ)፡ ኵብኵባ፡ ግልገል፡ አንበጣ፡ ፡
አንኮ፡ የዝንጀሮ፡ ጅር።
አንኮላ፡ (ሎች)፡ የዕቃ፡ ስም፡ ውሃ፡ መቅጃ፡ ሞላላ፡ ቅል ።አንቀጹ፡ ነቀለ፡ ነው ።
አንኮላ፡ ሞኝ፡ ቂል፡ እንከፍ፡ እንቆል ።
አንኰላኰለ፡ ወይፈንን አቀና ("ሥራ ዠመረ ") ።
አንኰላኰለ ወይፈንን፡ አቀናኰለኰለ ።
አንኰረኰረ (አንኰርኰረ)፡ ኣገላበጠ ("አሽከረከረ በዙሪያ አስኬደ ") (ምሳ. ፳፡ ፳፮) ።
አንኰረኰረ፡ አገላበጠ፡ ኰረኰረ ።
አንኰረፈፈ፡ አስኰረፈ፡ (ኰረፈፈ) ።
አንኰራኰረ ሰባበረ፡ ኰረኰረ።
አንኰራኰረ፡ አደቀቀ ("ሰባበረ ፈረፈረ በተገብሮነትም ይፈታል ነኰረን ተመ ልከት አንኰራኳሪ ያንኰራኰረ የሚያንኰ ራኵር የሚሰባብር ፈርፋሪ እንኵርኵር የተንኰራኰረ የተሰባበረ ድቃቂ ስብርባሪ ፍርፋሪ ላባት ለናቱ አንድ የኾነ ልጅ መጥፎ ሲኾን ያንድ እንጀራ እንኵርኵር እንዲሉ እንኵርኵሪት ደረቅ ጭብጦ የተሰባበረች የማኅበረ ሥላሴ መነኮሳት እየሰበሩ በውሃ አርሰው የሚመገቧት ይህችንም ባመት አንድ ጊዜ ያዘጋጇታል ይባላል ፈረ ተንኰራኰረ ደቀቀ ተሰባበረ ተፈረ አኰራኰር አጐራጐር አጐታጐት መኰርኰር ከርከሩሜ ያሞራ ስም ሥጋው የሚበላ አሞራ እሱም በቈላ አገር ይገኛል ከርከሩሜ ከርካሳ ዕላቂ አሮጌ ደንቃፋ ከረመ (ከሪም ከረመ) ክረምትን ዓመትን ባንድ አገር ተቀመጠ ቈየ ዝናም እስኪያልፍ መስከረም እስኪጠባ ኖረ ነበረ “ ።
አንኰራኳ፡ አንከባለለ፣፡(ኰረኳ)
አንኰራፋ -አንገራበደ (ኰረፋ)፡
አንኮበር፡ (በረ፡ አንኵዕ)፡ የከተማ፡ ስም፡ (ተረት)፡ የትም፡ ተወለድ፡ አንኮበር፡ እደግ ።አንኮ፡ ከበረሓ፡ የሚመጣውን፡ ኵብኵባ፡ ያሳያል ።
አንኮበሮች፡ ያንኮበር፡ ሰዎች፡ ወይም፡ ተወላጆች "
አንኰታኰተ አደቀቀ፡ ኰተኰተ ።
አንኰፈኰፈ፡ አስቈጣ ("አስኰረፈ አስ ተንኰፈኰፈ ተቈጣ አኰረፈ ሮጠ ሽማግሌው ") ።
አንኰፈኰፈ፡ አስኰረፈ፣፡(ኰፈኰፈ) ።
አንኳለለ (አንኮለለ)፡ ኮለል አደረገ ።
አንኳለለ አፈሰሰ (ኮለለ)።
አንኳረፈ (ከረፈፈ)፡
አንኳሪ (ዎች)፡ ያነኰረ/የሚያነኵር (ገልባጭ) ።
አንኳራ፡ ጠበኛ ሰው ("ሰንኰርቱን" እይ) ።
አንኳራጠበኛ (ነኰረ)።
አንኳር (ሮች)፡ ድብልብል (ጨው ዕጣን ድኝ) ።
አንኳር፡ ድብልብል፡ (ነኰረ)።
አንኳች፡ ያነኰተ/የሚያነኵት (አቃ) ።
አንኳኲ፡ ያንኳኳ ' የሚያንኳኳ ።
አንኳኳ፡ በር፡ መታ፡ ኳኳ)።
አንኳፈፈ፡ አሰፈፈ፡ (ኰፈፈ)።
አንዘለዘለ፡ አንጠለጠለ፡ ዘለለ ።
አንዘለዘለ፡ አንጠለጠለ ዝልዝልን ።
አንዘለዘለ፡ አዞረ/ኣባለገ ("ባለጌ አደረገ አለቅጣት አሳደገ መረን ሰደደ ለቀቀ በተደራጊነትም ይፈታል") ።
አንዘልዛይ፡ ያንዘለዘለ/የሚያንዘለዝል ("አንጠልጣይ") ።
አንዘረበበ፡ - አንጠለጠለ (ዘረበበ) ።
አንዘረበበ፡ አንጠለጠለ ወደ ታች አለ ("የከንፈር ፥ የለንቦጭ ' በተደራጊነትም ይፈ ታል") ።
አንዘረዘረ፡ አዘራ፡ ዘረዘረ።
አንዘረዘረ፡ እንደ ቆመ በወንፊት ነፋ/እንቀጠቀጠ/እዞረ/አዘራ ።
አንዘረገገ፡ ጐተተ ("ተጐተተ") ።
አንዘረጠጠ፡ አንቀበደደ፡ ዘረጠጠ ።
አንዘረጠጠ፡ አንጠረዘዘ/አንቀበደደ/አስረገዘ/ነፋ ("(ነፍኀ) በተደራጊነትም ይፈ ታል") ።
አንዘረፈፈ፡ አረዘመ፡ ዘረፈፈ።
አንዘራጋ በዠርባ፡ ጣለ፡ ዘረጋ ።
አንዘራጋ፡ ክፉኛ በዠርባ ጣለ/አወደቀ/አንፈራገጠ ("ጋኔን ሰውን ካታ") ።
አንዘራፈጠ፡ አሸራሸ፡ ዘረፈጠ።
አንዘራፈጠ፡ አደላድሎ አስቀመጠ ("አሸራሸ አሰፋ አንሰራፋ") ።
አንዘገዘገ/አምዘገዘገ/ኣውዘገዘገ/አቅ ዘመዘመ፡ ወረወረ/ለቀቀ ።
አንዘፈዘፈ (አንዘፍዘፈ)፡ አርገበኀበ/እንቀጠቀጠ (ማር. ፩፡ ፳፯) ።
አንዘፈዘፈ፡ አንቀጠቀጠ፡ ዘፈዘፈ ።
አንዘፍዛፊ፡ ያንዘፈዘፈ/የሚያንዘፈዝፍ ("አርገብጋቢ") ።
አንዛረጠ፡ ሀረጥ አደረገ ("ዘለለ") ።
አንዛረጠ፡ ፈሳ፡ ዘለለ፡ ዘረጠ።
አንዛሪ (መአንዝር)፡ ያነዘረ/የሚያነዝር (ፈታይ ክራር መቺ) ።
አንዛራጭ፡ ያንዛረጠ/የሚያንዛርጥ ("ዘ ማንዛረጥ መፍሳት መዝለ") ።
አንዛዛ፡ አንከዋረረ፡ አዞረ ።
አንዛዛ፡ አንከዋረረ/አዞረ ።
አንዛፈፈ፡ አሰፋ/አንሰራፋ/ዘረጋ ("ዛፍ አደረገ አሳደገ አረዘመ") ።
አንዠረገገ፡ ብዙ አፈራ ("አንጨረገገ አወረደ አንጠለጠለ እንዘረፈፈ በተደራጊነትም ይፈታል") ።
አንዠረገገ፡ አንረገገ፡ ዠረገገ ።
አንዠቀዠቀ አፈሰሰ (ዠቀዠቀ)።
አንዠባረረ፡ አሰከረ፡ ዠበረረ ።
አንዠባረረ፡ አስቸረ/አለገሰ ("አንቀ ባረረ") ።
አንዠቱ፡ ቅቤ፡ ጠጣ፡ ጠላቱን፡ ስለ፡ ጐዳ፡ ተደሰተ።
አንዠቴን፡ አርሰው፡ ምታልኝ፡ በልልኝ፡ ደስ፡ አሠኘኝ ።
አንዠት፡ (ቶች)፡ (ማዑት)፡ በቁሙ፡ በሆድ፡ ውስጥ፡ ያለ፡ የመብልና፡ የመጠጥ፡ ውሳጣዊ፡ አሸንዳ፡ ቀሠም፡ መተላለፊያ ።ወተትን፡ እይ ።የበግና፡ የፍየል፡ እንዠት፡ ይከርና፡ ሲደርቅ፡ ዥማት፡ ዠገዠግ፡ ይባላል፡ ለጥጥም፡ መንደፊያ፡ ይኾናል ። (ተረት)፡ ካንዠት፡ ካለቀሱ፡ እንባ፡ አይገድም ።
አንዠት፡ ራቀው፡ መናገር፡ አቃተው፡ ደከመሰለተ፡ ከምግብ፡ ማጣት፡ ከበሽታ፡ የተነሣ ።
አንዣለለ፡ አሾጠጠ፡ (ዠለለ)።
አንዣረረ፡ ሸነ/ለቀቀ/አፈሰሰ/አወ ረደ ("አቀጠነ") ።
አንዣረረ፣ሸነ፡ ዠረረ ።
አንዣበበ (ጸለለ ደበበ)፡ ክንፉን ዘረጋ/ወጠረ/አርገበገበ ("በአየር አዞረ አሰፈፈ አስኬደ ኹለንተናውን") ።
አንዣበበ፡ በአየር፡ ዞረ፡ ዠበበ።
አንደላቀቀ፡ አሞላቀቀ፣ ደለቀቀ።
አንደላቀቀ፡ አቀማጠለ/አንቀባረረ/ኣሞላቀቀ/አባለገ ("አያት የልጅ ልጁን") ።
አንደረሰሰ፡ አዘገመ፡ (ደረሰሰ) ።
አንደረበበ፡ አመተረበ (ደረበበ) ።
አንደረከከ፡ አመረተ/አንገለጠጠ ።
አንደረደረ፡ ቍልቍል አስሮጠ፡ ደረደረ ።
አንደረደረ፡ ቍልቍል አሮጠ ።
አንደርሶ፡ 3፡ ጦር፡ ነቀል፡ ሐርበኛ፡ ጋሻውን፡ መክቶ፡ 3፡ ጦር፡ የመለሰ፡ ማለት፡ ነው።
አንደርቤ፡ (ደርበየ)፡ በቁሙ፡ ምትሀት፡ በጨለማ፡ የሚወረወር፡ ደንጊያ፡ ወርዋሪው፡ የማይታይ፡ የማይታወቅ። በማእድ፡ ላይ፡ የሚወድቅ፡ ፋንድያ፡ ዐይነ፡ ምድር፡ ዐፈር፡ ጕድፍ ።አንደርቤ፡ ተደገመበት ። (ጸሎት፡ በአንተ፡ አንደርቤ)። ደረባን፡ እይ።
አንደርቦሽ፡ ዝኒ፡ ከማሁ።
አንደርዳሪ፡ ያንደረደረ/የሚያንደረድር ።
አንደርዶ፡ አጐንብሰው በተደረደሩ ልጃገረዶች ላይ ተንደርድሮና ዘሎ መውጣት ("የዝላይ ጨዋታ") ።
አንደርዶ፡ ዝላይ፡ -ደረደረ።
አንደቀደቀ፡ ሰውን አስቈጣ/አስፎከር ።
አንደበሰሰ፡ አንደበዘዘ፤(ደበሰሰ) ።
አንደበቱ ተዘጋ)፡ መናገር አቃተው (ሉቃ. ፩፡ ፳፪) ።
አንደበታም፡ ምላሰኛ፡ ነገረኛ፡ ለፍላፊ፡ ተናጋሪ።
አንደበት፡ (ነደበ)፡ ልሳን፡ ምላስ፡ ተናጋሪ፡ ሕዋስ። የሰይፍ፡ የመጥረቢያ፡ የጦር፡ ስለት። ያንደበት፡ ምስጢር፡ ጥበት፡ ነው።
አንደበቶች፡ ምላሶች፡ ስለቶች።
አንደበዘዘ፡ አሰነፈ፡ ደበዘዘ።
አንደበደበ (አደብደበ)፡ አሳከከ ("ደባ ደቦ አስመሰለ ኣጕረበረበ ሳማ አባ ጨጓሬ አለብላቢት ገላን አካልን ኾነ።") ።
አንደበደበ፡ አጕረበረበ፡ ደበደበ ።
አንደባለለ፤አንከባለለ፡ ደበለለ ።
አንደኛ፡ (ኣሐድ)፡ መዠመሪያ፡ ፊተኛ፡ በኵር ። ሴም፡ ከኖኅ፡ ልጆች፡ አንደኛ፡ ነው።
አንደኛቸው፡ (ኣሐዲሆሙ)፡ መዠመሪያቸው፡ ፊተኛቸው። ለሐዋርያት፡ አንደኛቸው፡ ቅዱስ፡ ጴጥሮስ፡ ነው ።
አንደኛዋ፡ አንደኛዪቱ፡ (ኣሐት)፡ መዠመሪያዪቱ፡ ፊተኛዪቱ። ከትእዛዞች፡ አንደኛዪቱ፡ ፍቅረ፡ እግዚኣብሔር፡ ናት ።
አንደኛው፡ መዠመሪያው፡ ፊተኛው። ከያዕቆብ፡ ልጆች፡ አንደኛው፡ ሮቤል፡ ነበረ።
አንደዬ፡ አለ፡ መታ፡ ጠዘለ።
አንደዬ፡ አንድ፡ ጊዜ፡ አንድ፡ አፍታ። እባክኸ፡ ኣንደዬ፣ ና።
አንደገደገ፡ ቈላ ("አንደቀደቀ") ።
አንደፋረሰ አቸናቧ፡ ደፈረሰ።
አንደፋረሰ፡ አቸናቧ/አበጣበጠ/አማታ ውሃን ።
አንደፋራ፡ አንደፋደፈ፡ (ደፈራ)።
አንደፋደፈ፡ አንፈራፈረ፡ ደፈደፈ ።
አንደፋደፈ፡ አንፈራፈረ/አንፈራገጠ/አንዘፈዘፈ/ኣንደፋራ ።
አንደፋዳፊ፡ ያንደፋደፈ/የሚያንደፋድፍ ("አንፈራጋጭ") ።
አንዱ፡ (አሐዱ)፡ ሌላው፡ አንዱም፡ አንዱ አንዱ፡ ባንዱ፡ እንዱ፡ ላንዱ አይቦዝንም። መለዮ፡ የተባለው፡ ካዕሱ፡ እንደ፡ ኾነ፡ ኣስተውል ። (እያንዳንዱ)፡ እየራሱ ። (እያንዳንዳቸው) እየራሳቸው።
አንዱ፡ በቃኝ፡ የሚያሰክር፡ መጠጥ፡ ለመናኛም፡ ይነገራል።
አንዱን ያለ አባ መቻል፡ የመቻል ጌታ (ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (አባ መላ)) ።
አንዱን፡ ያዢው፡ ምጡን፡ ወይም፡ መብሉን ።
አንዲቱ፡ ቷ፡ አንዷ። ከሎጥ፡ ዘንድ፡ አንዲቱ፡ ስቶጣ፡ አንዲቱ፡ ገባች። አንዲቱን፡ ባንዲቱ፡ ይዤ። አንድ፡ ምእላዶች፡ ኛ፡ ው፡ በመድረሻው፡ ተጨምረው፡ የተራ፡ ቍጥር፡ ሲኾን፡
አንዲት፡ (ኣሐቲ)፡ የሴት፡ ቅጽልና፡ በቂ። አቤሜሌክን፡ አንዲት፡ ሴት፡ ገደለችው። አንዲት፡ ቀረችኸ።
አንዲዮ፡ አንድነትያለው፡ ውስጠ፡ ብዙ።
አንዳሰሰ፡ በቀስታ አስኬደ ።
አንዳሰሰ፡ አደራ ለመጠ ዳስ አስ መሰለ ።
አንዳሪያ፡ የገብስ፡ ስም፡ ፍሬው፡ ትልልቅ፡ የኾነ፡ ገብስ ።
አንዳርጋቸው፡ ረኃብ፡ የችጋር፡ ስም።
አንዳርጋቸው፡ አንድ፡ አድርጋቸው። ከፈረሰኞች፡ የምናውቃቸው፡ በሻኸ፡ አቦዬ፡ ኀይሌ፡ አንዳርጋቸው ።
አንዳርጌ፡ የሰው፡ ስም፡ ፍችው፡ አንድ፡ አድርግ። (ጥሩር፡ አንዳርጌ)፡ የጥሩር፡ አንዳርጌ።
አንዳቅ፡ (አንድ፡ ዐቅ)፡ 4፡ ክንድ፡ ሸማ ።
አንዳቸው፡ (አሐዶሙ)፡ ከሦስቱ፡ አንዳቸው፡ ይምጣ።
አንዳች፡ ምናልባት (ማቴ፳፮፡ ፳፪) ።
አንዳች ምንም፡ አንድ ።
አንዳች፡ አይፈታሽ፡ አንዳች፡ አልባ፡ ባዶ፡ እጅ፡ (ኢዮ፳፪፡ ፱)።
አንዳች፡ አይፈታሽ፡ እግር፡ ብረት፡ ዥቦ፡ ከሞረድ፡ በቀር፡ ምንም፡ የማይፈታው "
አንዳች፡ የብትን፡ ኹሉ፡ ቅጽልና፡ በቂ፡ ፍችው፡ ምንም፡ (ዘፀ፳፪፡ ፲፬። ፴፬፡ ፳)አንዳች፡ ነገር፡ እንዲሉ ።
አንዳችን፡ (አሐድነ)፡ አንዳችን፡ በቀኝኸ፡ አንዳችን፡ በግራኸ፡ እንቀመጥ ።
አንዳንድ፡ ጊዜ፡ አንዳንደግዜ፡ ድርብ፡ ቅጽልና፡ ንኡስ፡ አገባብ፡ ነው፡ አለማዘውተርን፡ ያስረዳል። አንድ፡ አንድ፡ ጊዜ፡ ተብሎ፡ ቢጻፍ፡ ግን፡ ዐማርኛው፡ ብትክ፡ ይኾናል።
አንዳከከ፡ በቅርብ በቅርብ እዚያው እዚያው አስረገጠ/አስኬደ ("እንደ ቈፋሪ ዶማ") ።
አንዳይና፡ (አንድ፡ ዐይና)፡ ባላንድ፡ ዐይን፡ ባንድ፡ ዐይን፡ የሚያይ። ናኦስ፡ አንዳይና፡ ነበረ።
አንዳጅ፡ ያነደደ/የሚያነድ (አቃጣይ - "እሳት አንዳጅ" እንዲሉ) ።
አንድ፡ (እሒድ፡ አሐደ፡ አሐድ)፡ የቍጥር፡ ስም፡ መዠመሪያ፡ ቍጥር፡ የቍጥር፡ ኹሉ፡ ጥንትና፡ መሠረት፡ መነሻ። መዠመሪያነቱ፡ ከ፪፡ እስከ፡ ዝም፡ ላለ፡ ቍጥር፡ ኹሉ፡ ነው ።በአኃዝ፡ ሲጻፍ፡ 1፡ ይባላል ። (ተረት)፡ አንድ፡ ያላት፡ እንቅልፍ፡ የላት ።አንድ፡ ከስምና፡ ከግብር፡ ከነገር፡ አስቀድሞ፡ እየገባ፡ ቅጽል፡ ብቻ ውን፡ ሲነገር፡ በቂ፡ ይኾናል። አንድ፡ በሬ፡ ስቦ፡ አንድ፡ ሰው፡ ዐስቦ፡ ቅጽል። አንድ፡ አይነድ፡ አንድ፡ አይፈርድ፡ በቂ "
አንድ፡ ላንድ፡ ብቻ፡ ለብቻ። ዳዊት፡ ጎልያድን፡ አንድ፡ ላንድ፡ ገደለው።
አንድ፡ ላይ፡ አንድ፡ ቅጽል፡ ላይ፡ ስፍራ። ሳኦልና፡ ዮናታን፡ አንድ፡ ላይ፡ ሞቱ።
አንድ ሠሪ መኾን ፍጹም አምላክነትና ፍ ጹም ሰውነት ("፪ ልደት ፪ ባሕርይ ፪ ግብር እንዳለው የሚያስረዳ የሐዋርያትና የ፫፻፲፰ ሊ ቃውንት እምነት በጽርእ ኦርቶዶክስ ይባላል") ።
አንድ፡ ሠሪ፡ ፍጹም፡ አምላክና፡ ፍጹም፡ ሰው፡ የኾነ፡ ጌታችን፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ አንድ፡ ሠሪ (አሐዱ፡ ገባሪ)፡ ነው ።
አንድ፡ ሰው፡ በመዠመሪያ፡ አዳም፡ አንድ፡ ሰው፡ ነበረ ።
አንድ፡ ቀንጃ፡ ነጠላ።
አንድ፡ ቃል፡ የገጠመ፡ የተባበረ፡ የብዙ፡ ሰው፡ ነገርና፡ ድምፅ። ሠለስቱ፡ ምእት፡ እንዳንድ፡ ቃል፡ ተናጋሪ፡ እንዳንድ፡ ሰው፡ መስካሪ፡ ናቸው ።
አንድ፡ በቀል፡ ታናሽና፡ ታላቅ፡ የሌለው፡ ልጅ፡ አንድ፡ ለጊዜ፡ ሲቀጸል፡
አንድ፡ ባሕርይ፡ እግዜር፡ ቅድስት ' ሥላሴ፡ ባለሦስት፡ አካል፡ ባላንድ፡ ባሕርይ ።ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ባምላክነቱ፡ ከአብ፡ ጋራ፡ አንድ፡ ባሕርይ፡ በሰውነቱ፡ ከኛ፡ ጋራ፡ አንድ፡ ባሕርይ ።ኹለትን፡ እይ ።
አንድ፡ ባሕርይ፡ የጌታችን፡ የኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሰውነት፡ ወዳምላክነት፡ ተለወጠ፡ ተቀላቀለ፡ የሚል፡ አውጣኪ፡ ያወጣው፡ ሃይማኖትና፡ ባህል፡ ቅዱስ፡ ዲዮስቆሮስ፡ በታሰረ፡ ጊዜ፡ ግብጦች፡ ኋላም፡ ባገራችን፡ ቅባቶችና፡ ያልተማሩ፡ ሰዎች፡ የተቀበሉት፡ (ቱሳሔ፡ ውላጤ)።
አንድ፡ ነገር፡ በቁሙ፡ ዕቃ። አንድ፡ ነገር፡ ተናገረ፡ አንድ፡ ነገር፡ ይዞ፡ መጣ።
አንድ፡ አማራጭ፡ ቃል፡ ወይም ።አንድ ከደግ፡ ተወለድ፡ አንድ፡ ከደግ፡ ተጠጋ።
አንድ፡ አምላክ፡ አብ፡ ወልድ፡ መንፈስ፡ ቅዱስ፡ አንድ፡ አምላክ፡
አንድ፡ አምሳል፡ አንድ፡ መልክና፡ አንድ፡ አርኣያ። ዳዊትና፡ ሰሎሞን፡ አንድ፡ አምሳል ።
አንድ፡ አንድ፡ ሕፃን፡ እጁን፡ ተይዞ፡ የሚራመደው ' ርምጃ፡ ቍጥር፡ ፪፡ ጊዜ፡ 1፡ 2።
አንድ፡ አካል፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ አንድ፡ አካል፡ ነው።
አንድ፡ ዐይነት፡ ሕብሩ፡ ቀለሙ፡ አንድ፡ የኾነ፡ ሌላ፡ 2ኛ፡ 3ኛ፡ ያልተደባለቀበት ።
አንድ፡ አደረገ፤(አሐደ)፡ ጠመረ ' አዋሐደ፡ መንታነትን፡ አጠፋ።
አንድ፡ ኾነ፡ ተባበረ፡ ተዋሐደ፡ ተሰማማ፡ ተሳተፈ ።ኣምላክ፡ ከማርያም፡ ሥጋ፡ ነሥቶ፡ ከኛ፡ ጋራ፡ አንድ፡ ኾነ ።
አንድ፡ ወጣት፡ ዘንባባ።
አንድ፡ ዘንግ፡ አንድ፡ ፈርጅ፡ የነጠላ፡ እኩሌታ፡ 6፡ ክንድ፡ የቀሚስ፡ 12።
አንድ ጊዜ፡ አንደግዜ፡ አንድ፡ ወር፡ አንድ፡ ዘመን፡ አንድ፡ ሌሊት፡ አንድ፡ ዕለት፡ አንድ፡ ዓመት፡ አንድ፡ ቀን፡ አንድ፡ ሳምንት፡ አንድ፡ ሰዓት፡ እንዲህ፡ ኾነ፡ ተደረገ፡ ይላል፡ (ፊልጵ፬፡ ፲፯)፡ ተደራርቦ፡ ሲነገር፡
አንድ ፍሬ)፡ ዕድሜው መጠኑ በጣም ያነሰ ሕፃን ። "አንድ ፍሬ ልጅ" እንዲሉ ።
አንድም፡ ም፡ ዋዌ፡ ነው፡ ፍችው፡ ስንኳ ። (ግጥም)፡ ለወቀጣ፡ አንድም፡ ሰው፡ አልመጣ፡ ለመጠጡ፡ ከየጐሬው፡ ወጡ ።
አንድም፡ የልዩ፡ ልዩ፡ ትርጓሜና፡ ምስጢር፡ መነሻ፡ ፍችው፡ ወይም ።ሦስተኛውን፡ አንድ፡ እይ።
አንድስ፡ ቅጤ፡ ያንድስ፡ ወገን፡ ፍጥረቱ፡ ዐይነቱ፡ ቅጡ፡ እንደ፡ አንድስ፡ የኾነ፡ እባብ፡ የእባብ፡ ዐይነት፡ ኹሉ። ቀጣን፡ እይ።
አንድስ፡ ትልቅ፡ ዘንዶ፡ አንድ ።
አንድስ፡ ያውሬ፡ ስም፡ ያልታወቀ፡ አውሬ፡ ወይም፡ ትልቅ፡ ዘንዶ። አንድስ፡ መሳይ፡ ኣንድስ፡ ያኸላል፡ እንዲሉ ።አንድስ ፣መጥፎ፡ ለኾነና፡ ለማያምር፡ ይነገራል ።
አንድነት፡ (ኅብረት)፡ የሐዋርያት፡ ንብረት፡ ጽኑ፡ የገዳም፡ ሥርዐት፡ አንድ፡ ዐይነት፡ ልብስ፡ መልበስ፡ ባንድ፡ ገበታ፡ ዐብሮ፡ መብላት፡ መጠጣት፡ ጥሪት፡ ቍሪት፡ አለመለየት፡ እንደ፡ ማኀበረ፡ ሥላሴ።
አንድነት፡ (ዋሕድና)፡ አንድ፡ መኾን፡ በባሕርይ፡ በግብር፡ መሳተፍ፡ መተባበር፡ መጣመር፡ (ዘካ፲፩፡ ፯፡ ፲፬ ።ኤፌ፬፡ ፫) ።ለፈጣሪ፡ የባሕርይ፡ አንድነት፡ ያካል፡ ሦስትነት፡ አለው፡
አንድና፡ ብዙ፡ አጫፋሪ። ሰው፡ ሰዎች፡ ቤት፡ ቤቶች ።አንድ፡ በመለዮ፡ መድበል፡ ቍጥርና፡ በቂ፡ ሲኾን፡
አንድያ፡ አንድ፡ ብቻ፡ ጭራሽ ።አንድ ያውን፡ ኼደ።
አንድዬ፡ በባሕርዩ፡ አንድ፡ የኾነ፡ አምላክ፡ አንድ፡ ብዬ፡ የማምንበት፡ ፈጣሪ፡ የኔ፡ አንድ ።አንድዬ፡ ያውቃል፡ ሳለ፡ አንድዬ ።
አንድድ፡ ዝኒ ከማሁ (መጠጥ - "አንድ ልብ አንድድ ኹለት ልብ አብርድ" እንዲሉ - "ቈሽትን" ተመልከት) ።
አንድጋ፡ (ኅቡረ)፡ አንድነት፡ ኅብረት፡ አንድ፡ ዘንድ፡ አንድ፡ ስፍራ። ዳግመኛም፡ ጋ፡ ጋራ፡ ከማለት፡ ሊወጣ፡ ይችላል ።አንድጋ፡ በሉ፡ አንድጋ፡ ሞቱ ።
አንዶ ፣ እንዶ፡ እንደ። ጥፍርን፡ ተመልከት ።
አንዶ፡ አንድያ ።
አንዶለዶለ አወረደ፡ (ዶለዶለ)።
አንዷ፡ (አሐቲ)፡ ከብዙ፡ ቈንዦ፡ አንዷን፡ ምረጥ፡ ካንዷ፡ ጋራ፡ ኑር።
አንጀበኛ፡ (ኞች)፡ አንገራባጅ፡ ጕረኛ፡ የሚዝት ።ይህ፡ ቋንቋ፡ በሐረርጌ፡ አውራጃ፡ ይነገራል።
አንጀባ፡ (ዐረ፡ ሀንጀመ፡ ፎከረ)፡ ማንገራበድ፡ ፉከራ፡ ዛቻ፡ ጕራ።
አንጃ፡ (አንጕዕ)፡ የተለየ፡ ልዩ፡ ስፍራና፡ ፊና፡ ወገን፡ በኩል ። (ባንጃው፡ ባንጃኸ)፡ የሰው፡ ስም፡ በፊናው፡ በፊናኸ፡ ማለት፡ ነው ።
አንጃ፡ (እንዳዒ)፡ እንጃ፡ አላውቅም እከሌና፡ እከሌ፡ አንጃ፡ ግራንጃ፡ ተነጋገሩ።
አንጆ፡ (አነዳ)፡ የከሳ፡ የኰሰሰ'ሥጋው፡ ዐልቆ፡ በቈዳና፡ በዥማት፡ ባጥንት፡ የቆመ፡ ከሻዋ፡ ከሲታ፡ በሬ ።
አንገለጀጀ አንሰዋለለ፡ (ገለጀጀ)።
አንገለጠጠ፡ አመረተ/አንቀለጠጠ ፍምን (በተገብሮነትም ይፈታል።)
አንገለጠጠ፡ አንቀለጠጠ፡ ገለጠጠ ።
አንገላታ፡ አጕላላ፡ (ገለታ)።
አንገላቺ፡ ያንገላታ/የሚያንገላታ (ጐጂ ጨቋኝ) ።
አንገላወደ፡ ሥራ አስፈታ/አንቀዋለለ ።
አንገላወደ አንቀዋለለ፡ -ገለወደ ።
አንገረር፡ የበጋ ጐመን "አባጅኸኝ አይደርቄ።"
አንገረር፡ የበጋ ጐመን፡ ገረረ።
አንገረበበ፡ አንከረፈፈ፡ (ገረበበ)።
አንገረብ፡ የወንዝ፡ ስም፡ የበጌምድር፡ ዠማ ።
አንገረገረ (አንገርገረ)፡ አንገደገደ/አፍገመገመ/አዘመመ (ወለም ዘለም አደረገ) ።
አንገረገበ፡ ሳይቈላ፡ አፈላ፡ (ገረገበ)።
አንገረገበ፡ ጠላትን በውጊያ ጐዳ ።
አንገረገፈ፡ አንቀጠቀጠ፡ (ገረገፈ)።
አንገራ፡ አሳሳተ/አጭበረበረ (ጥል ዐሰበ አልታዘዝ አለ) ።
አንገራበደ፡ አንኰራፋ፡ ገረበደ።
አንገራበደ፡ አፉን ከፍቶ ፎከሪ አስፈራራ አንኰራፋ ጕራ ተናገረ አንቧተረ አገኝ ዐጣውን ቀባጠረ ለፈለፈ ።
አንገራባጅ (ጆች)፡ ያንገራበደ/የሚያንገራብድ (አንቧታሪ ጕረኛ ፎካሪ አንጀበኛ) ።
አንገራገረ፡ አመነታ፡ ገረገረ ።
አንገራገረ፡ አጕረመረመ/አመነታ/አወላወለ/አወጣ/አወረደ ። "ቅን ሰው በታዘዘ ጊዜ አያንገራግርም።"
አንገራገረ፡ አጠራጠረ (አላሰማ አለ "እከሌ ዦሮው ያንገራግረዋል።") ።
አንገራጋሪ፡ ያንገራገረ/የሚያንገራግር (አጕረምራሚ አመንቺ አወላዋይ አጠራጣሪ) ።
አንገራጠጠ፡ አኰሰሰ፡ ገረጠጠ።
አንገራጣጭ፡ ያንገራጠጠ/የሚያንገራ ጥጥ (ናቂ አኰሳሽ) ።
አንገራጨ አሳሳተ፡ ገረጨ ።
አንገርበብ አለ፡ ተንገረበበ ።
አንገርባቢ፡ ያንገረበበ/የሚያንገረብብ ።
አንገርጋሪ፡ የዜማ ስም (ፊት መስቀል ይዞ የሚመራ ኋላም በመቋሚያ የሚዘመም ምልጣን ደብተራን ግራ ቀኝ የሚያንገረግር አዝማሚ አንገድጋጅ ማለት ነው) ።
አንገርጋቢ፡ ያንገረገበ/የሚያንገረግብ (የሚጐዳ ጐጂ) ።
አንገሸገሸ ነቀነቀ፡ (ገሸገሸ)።
አንገበገበ፡ አቃጠለ፡ ገበገበ ።
አንገበገበ፡ እታጠለ፡ ለበለበ፡ ቈጠቈጠ፡ አስገበገበ።
አንገብጋቢ፡ የሚያንገበግብ፡ የሚያቃጥል፡ እቃጣይ፡ ለብላቢ (እሳት)፡ ዐለንጋ፡ ጅራፍ፡ አርጩሜ፡ ኢበት፡ ልምጭ (ወንዝ)፡ ችጋር፡ ራብ።
አንገታገተ፡ አመላለሰ/አንገዛገዘ ።
አንገት በቁሙ፡ ዐንገት።
አንገቸገቸ ዘከዘከ፡ (ገቸገቸ) ።
አንገዋ፡ የወረዳ፡ ስም፡ በመንዝ፡ ማማ፡ ምድር፡ ያለ፡ ቀበሌ ።
አንገዋለለ፡ ለየ፣፡ገወለለ።
አንገዋለለ፡ ዐይኑን መለስ ቀለስ እያረገ ።
አንገዋላይ፡ ያንገዋለለ/የሚያንገዋልል/የሚለይ (ለዪ) ።
አንገዛገዘ፡ አንገታገተ/ለንባዳ አደረገ (እእ አሠኘ) ።
አንገደገደ፡ አግተረተረ፡ ገደገደ።
አንገደገደ፡ ወዘ/ነቀነቀ/አግተረተረ/አፍገመገመ/አርጎደጎደ/አንቀጠቀጠ (እንዳልተማገረ ግድግዳ ማለት ነው)። "በተገብሮነትም ይፈታል።"
አንገዳገደ፡ አወዛወዘ/አነቃነቀ ።
አንገድጋጅ፡ ያንገደገደ/የሚያንገደግድ ።
አንገገ፡ አጋጨ/አንቀጫቀጨ፲ ቀንድ ለቀንድ ወይም ቀንዱን ከቀንበር ጋራ አማታ አስጮኸ ።
አንገፈለለ፡ አረዘመ፡ -(ገፈለለ) ።
አንገፈገፈ፡ ሰለቸ/ጐፈነነ/አሠቀቀ/ነቀነቀ/አንገሸገሸ (ፊት አስቋጠረ) ።
አንገፈገፈ፡ ጐፈነነ፡ ገፈገፈ።
አንገፈጠጠ አነደ፤
አንገፈጠጠ አንቀበደደ፡ (ገፈጠጠ) ።
አንገፍጋፊ፡ ያንገፈገፈ/የሚያንገፈግፍ (ኮሶ መራራ ነገር አሠቃቂ) ።
አንጕላ፡ ዝኒ ከማሁ ለአንጐል ("አንጕሎውንጅር" - ጓለለ) ።
አንጕሎ፡ ያይጥ ዓሣ ውንጅር ።
አንጕሎውንጅር (ጓለለ)።
አንጕዝ፡ ጠባሳ ።ነጐደ፡ ብለኸ፡ አነጐደን፡ እይ።
አንጕይ፡ (ጐየ)፡ በታችኛው፡ ወግዳ ' ያለ፡ አገር፡ የማሪያም፡ አጥቢያ። አንጕይ፡ ማሪያም፡ እንዲሉ።
አንጕጥ፡ ዝኒ ከማሁ።
አንጋለለ፡ አንካረረ (በዠርባ አስተኛ) ።
አንጋሪ፡ ያነገረ/የሚያነግር (እንገር ዐላቢ) ።
አንጋራ፡ (ሮች)፡ ወዳጅ፡ ባልንጀራ፡ ጓደኛ፡ ወንፈለኛ። አን፡ ከኣንድ፡ መጥቶ፡ ከጋራ፡ ተደርቧል፡ (ሉቃ፭፡ ፲) ።
አንጋራ፡ ምንደኛ፡ ሎሌ። በግእዝ፡ ዐሳብ፡ ይባላል ።
አንጋራ፡ በጣና፡ ውስጥ፡ ያለ፡ ያቡነ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ አጥቢያ፡ (ገዳም)፡
አንጋሬ፡ ተጐትቶ የተወጠረ ደረቅ የፍየል ቈዳ ።
አንጋሬ የፍየል፡ ቈዳ፡ ገረረ።
አንጋር፡ በመንዝ፡ ክፍል፡ ከጌሥ፡ በታች፡ ያለ፡ ዘባጣ፡ ቀበሌ።
አንጋሽ፡ ያነገሠ/የሚያነግሥ (አሠልጣኝ - "ዛር አንጋሽ" እንዲሉ) ።
አንጋቢ፡ ያነገበ/የሚያነግብ (ተሸካሚ) ።
አንጋተት፡ አንጋፈፈ/አንከረፈፈ ።
አንጋይ፡ ያነገለ/የሚያነግል (ነቃይ) ።
አንጋደደ፡ አጣመመ/አወላገደ/አወላቀመ ።
አንጋዳ፡ ገዳዳ፡ ገደደ።
አንጋዳ፡ ገዳዳና ጠማማ ጕድጓድ ።
አንጋዳጅ፡ የሚያንጋድድ (አጣማሚ)።
አንጋጋ (አንጎገወ/አንጃጃ)፡ ረባ/ኣበዛ፡ ኣብዝቶ ነዳ/አሰመራ ።
አንጋጋ፡ አቃጠለ/አነደደ።
አንጋጠጠ፡ አሰገገ፡ ገጠጠ።
አንጋጠጠ፡ አሻቅቦ፡ አየ፡ ገጠጠ ።
አንጋፈፈ፡ አንቀረፈፈ፡ ጋፈፈ ።
አንጋፈፈ፡ አንቃፈፈ/አንቀረፈፈ ።
አንጋፋ፡ (ኦሮ☞መዠመሪያ፡ ልጅ)፡ በኵር ።
አንግሥ፡ የመጠጥ ስም ("ሞኝ እንግሥ" እንዲሉ) ።
አንግዳ መቀበያ)፡ ቤት ምግብ ።
አንጐለ ቢስ፡ ዕውቀት/ማስተዋል የሌለው።
አንጎለላ፡ ያገር፡ ስም፡ በላይኛው፡ ወግዳ፡ ያለ፡ ቀበሌ። ንጉሥ፡ መጡ፡ ካንጎለላ፡ ምን፡ ሊበሉ፡ የማር፡ ወለላ፡ እንዲሉ፡ ልጆች።
አንጐላቸ (በፀወ)፡ ተቀምጦ አንተላፋ (ዐንገቱን ደፋ ቀና አደረገ) ።
አንጐላቸ አንቀላፋ፡ ጐለተ ።
አንጐል (ናላ)፡ በራስ ቅል ው ስጥ ያለ ወፍራም ቅባት (የዕውቀት ምንጭ - አንጐላም፡ ካፍንጫው ንፍጥ የማይልይ - "መነጐለን" ተመልከት - "መነገለ" የነገለ መስም ግስ እንደ ኾነ "መነጐለም" የነጐለ መስም አንቀጽ ነው) ።
አንጐል፡ በቁሙ
አንጐራደደ፡ አንቈራጠጠ (መለስ ቀ ለስ አደረገ) ።
አንጐራደደ፡ አንቈራጠጠ፤(ጐረደደ) ።
አንጐራዳጅ፡ ያንጐራደደ/የሚያንጐራ ድድ (አንቈራጣ) ።
አንጐራጐረ (አንጐርጐረ)፡ አጕረመረመረ (ሰቈ. ፫-፴፱) ። "ብዙ ጊዜም መጽሐፍ በአንጐራጐረ ፈንታ አንጐረጐረ ይላል" (ዘፀ. ፲፭፡ ፳፬፡ ፲፯፡ ፪፡ ሉቃ. ፲፭፡ ፪፡ ዮሐ. ፯፡ ፴፪) ።
አንጐራጐረ፡ ዘፈነ፡ ጐረጐረ ።
አንጐራጐረ፡ ዘፈነ/ቈዘመ ።
አንጐራጓሪ፡ ያንጐራጐረ/የሚያንጐራጕር (አጒረምራሚ ዘፋኝ ቈዛሚ) ።
አንጐር፡ ያገር፡ ስም፡ በደብረ፡ ሊባኖስ፡ ደቡብ፡ ያለ፡ ቀበሌ።
አንጐርባ፡ የሰውና የከብት በሽታ ባለቈበር (ጠጕርን የሚያቆም ገላን የሚያሳብጥ መድኀኒቱ ጥፍር አንዶ) ።
አንጐርባ፡ የከብት፡ በሽታ፡ ጐረበ ።
አንጐበደደ፡ አጐበደደ።
አንጎት፡ የወሎ፡ ጥንታዊ፡ ስም፡ (ድርሳነ፡ መድኀኔ፡ ዓለም) ።
አንጐደጐደ (አንጐድጐደ)፡ ኣስጮኸ/አሰማ (የነጐድጓድ) (ኢዮ. ፴፯፡ ፭፡ መዝ. ፲፰፡ ፲፫) ።
አንጐደጐደ፡ አመጣ/አወረደ (የቅኔ)።
አንጐዳጐደ፡ በማጀት አሮጠ/አመላለሰ ።
አንጐፈጐፈ፡ -አሮጠ፡ -(ጐፈጐፈ) ።
አንጐፈጠጠ፡ አስረጀ/አደከመ (ጨባጣ አደረገ በተደራጊነትም ይፈታል) ።
አንጓ (አንጕዕ/መሌሊት)፡ የእጅ አንባር/ያ ኵርማ/የጣት ክፍል/የእግር ቍርጭምጭሚት/ጕልበት።
አንጓ፡ ዐጥቅ፡ ነጓ ።
አንጓ፡ የመቃ/የሽመል/የቀርክሓ/የጐሽ መቃ/ያገዳ/የሸንኰራገዳ ዐጥቅ መለያ (ከዐጥቅ እስከ ዐጥቅ ያለውም ቀጥታ መለ ልታ ባንድነት ኣንጓ ይባላል) ።
አንጓለለ፡ አንገዋለለ፡ (ጓለለ)።
አንጓላይ፡ ያንጓለለ/የሚያንጓል ።
አንጓሌ፡ የሰው ስም "አንጓል ማለት ነው።"
አንጓሰሰ፡ አንቋሰሰ/አንቈረሰሰ/ጐተተ ።
አንጓሪ፡ ያነጐረ/የሚያነጕር (ቅቤ አቅላጭ) ።
አንጓበበ፡ ጐንባሳ/ቀላሳ አደረገ።
አንጓጅ፡ ያነጐደ/የሚያነጕድ (መቺ) ። አንጕድ/አንጕዝ "
አንጓጒ፡ ያንጓጓ/የሚያንጓጓ (ጐርባጭ) ።
አንጓጓ (አንኳኳ/አንቋቋ)፡ ሆድን ጐረበጠ፡ ደንጊያን እገላበጠ፡ አስጮኸ።
አንጓጓ፡ ቈዳን፡ አስጮኸ፡ ጓጓ ።
አንጓጠጠ -አሽማጠጠ፡ -(ጓጠጠ)።
አንጓጣጭ፡ ያንጓጠጠ/የሚያንጓጥጥ/የሚያሽጥጥ (አጐጣጭ/አሽጣጭ/አቃላይ) ።
አንጓጭ፡ ያነጐጠ/የሚያነጕጥ (ነኪ) ።
አንጠለጠለ፡ ሰቀለ፡ (ጠለጠለ)።
አንጠላጠለ፡ ኣወጣ/አስተዛዘለ ።
አንጠልጣይ፡ ያንጠለጠለ/የሚያንጠለጥል ("ሰቃይ ሰቅጣጭ አንዘልዛይ") ።
አንጠልጥሎ፡ ሰቅሎ/አንዠርጎ (ማሕ. ፯፡ ፲፫) ።
አንጠሰጠሰ፡ ቈላ፡ ጠሰጠሰ ።
አንጠሰጠሰ፡ ዐመሰ ቈላ ።
አንጠረረ፡ አቈረጠ።
አንጠረበበ አከበደ ፣(ጠረበበ)።
አንጠረዘዘ፡ አንገፈጠጠ፡ (ጠረዘዘ) ።
አንጠረጠረ፡ አንቀረቀበ ("ለየ የተወቀጠ ተልባን") ።
አንጠረጠረ አንቀረቀበ፡ ጠረጠረ።
አንጠረጠረ፡ አንቀጠቀጠ/አንጠበጠበ ።
አንጠረጠረ፡ አጮኸ ።
አንጠራራ፡ በእግር ጣት አቆመ ("እጅን ወደ ላይ አዘረጋ አንድ ነገር ለማሲ ያዝ ለማስጨበጥ (የነብርና የጦጣ ተረት) አአ አንጠራራኝ እኔንም ሰው ጠራኝ") ።
አንጠራወዘ፡ አንከላወሰ፡ (ጠረወዘ)
አንጠራወዘ፡ አወጫመደ/አንከላወሰ ።
አንጠርጣሪ፡ ያንጠረጠረ/የሚያንጠረጥር ("አንቀጥቃጭ አንቀርቃቢ") ።
አንጠቀጠቀ፡ አንተከተከ፡ ጠቀጠቀ።
አንጠቀጠቀ፡ አንተከተከ/አፈናጠረ ።
አንጠቀጠቀ፡ አንተገተገ/አብረቀረቀ/ኣስጌጠ/ሸለመ/አንቈጠቈጠ ።
አንጠቀጠቀ፡ አፈላ/ኣበሰለ ።
አንጠበጠበ (አንጠብጠበ)፡ አንቀጠ ቀጠ/አንጠረጠረ/አንቀረቀበ ("ዛሬ ሌሊት እከሴን ብርድ ሲያንጠበጥበው ዐደረ") ።
አንጠበጠበ፡ አንቀጠቀጠ ነ ።
አንጠበጠበ አንቀጠቀጠ፡ ነጠበ ።
አንጠባጠበ (አንጠብጠበ)፡ ጠብ ጠብ አደረገ (ጥቂት ጥቂት አዘነበ አንጠፈጠፈ በቀላል ዘራ - በተደራጊነትም ይፈታል - መጽሐፍ ግን በአንጠባጠበ ፈንታ አንጠበ ጠበ ይላል - መዝ. ፷፰፥፰፡ ኢሳ. ፵፭፥፰) ።
አንጠባጠበ፡ ጠብ ጠብ አደ ረገ ነጠበ ።
አንጠባጠበ፡ ጠብ፡ ጠብ፡ አደረገ፡ ነጠበ ።
አንጠባጣቢ፡ ያንጠባጠበ/የሚያንጠባጥብ (ደመና ቤት) ።
አንጠፈጠፈ (አንጸፍጸፈ)፡ አፈሰሰ/ አንጠባጠበ ("ጠብ ጠብ አደረገ ውሃን ደምን ማርን በተገብሮነትም ይፈታል።") ።
አንጠፈጠፈ፡ አፈሰሰ፡ ጠፈጠፈ ።
አንጠፍጣፊ (ዎች)፡ ያንጠፈጠፈ/የ ሚያንጠፈጥፍ ("አንጠባጣቢ") ።
አንጡራ፡ ሰው ጥሮ ግሮ ወዙን አፍስሶ ያገኘው ጥሩ ገንዘብ (ኦሮ) ።
አንጣ፡ መና፡ ነ፡ ተወራራሽ፡ ስለ፡ ኾኑ፡ አምጣ፡ በማለት፡ ፈንታ፡ አንጣ' ይባላል ።ባላንጣ፡ እንዲሉ።
አንጣ፡ ነጭ አድርግ።
አንጣ፡ ነጭ፡ አድርግ፡ ነጣ።
አንጣ፡ አምጣ—መጣ።
አንጣለለ (ጦለለ/አንጦለለ)፡ አፈሰሰ/መሬት አለበስ/ኣሰፋ/ዘረጋ/ኣስተኛ/አበዛ/ኣበረከተ ።
አንጣለለ፡ አሰፋ፡ ጠለለ ።
አንጣረረ ፣ፈሳ፡ ጠረረ ።
አንጣረረ፡ ፈሳ ፈሱን ለቀቀ ("አስጮ ማንጣረር መፍሳት") ።
አንጣሪ (ዎች)፡ ያነጠረ/የሚያነጥር ("ቅቤ አንጣሪ" እንዲሉ) ።
አንጣሪ፡ የሚያቈርጥ።
አንጣሪያ (አንጻራዊ)፡ የእንጻር (በመሬት ላይ በቀጥታ በያንጻሩ እያደገ የሚ ዘምት ቅጠል ተቀቅሎ የሚበላ - "አንጣሪያ ላንጣሪያ ቢደጋገፍ ተያይዞ ዘፍ" - ተረት)
አንጣሪያ ሆድ፡ አንጣሪያ በልቶ ሆዱ የተጐሰረ ሰው (ሆደ አንጣሪያ) ።
አንጣሪያ፡ ቅጠል፡ ነጠረ ።
አንጣር (አንጻር);ትይዩ/አኳያ/አፍዛዣ (ፊት ለፊት ያለ ስፍራ አቅጫጫ) ።
አንጣር ጣይ (አንጻረ ፀሓይ)፡ በፀሓይ አንጻር ያለ ጊዜ (፮ ሰዓት ቀትር ጠራራ ዳግመኛም ፀሓይ በአንጻር የሚታይ በት የሰማይ መካከል ማለት ነው - "ባንጣር ጣይ ኣትኺድ" እንዲል ባላገር) ።
አንጣጣ (አንጣእጥአ)፡ ቈላ/አናረ ("አዘለለ") ።
አንጣጣ፡ ቈላ፡ ጣጣ።
አንጣጣ፡ ፈሳ ("ፈሱን ለቀቀ አጮኸ አንጣጣ አስቀባጠረ አስለፈለፈ") ።
አንጣፊ (ዎች)፡ ያነጠፈ/የሚያነ ጥፍ ("አንጣፊ ጋራጅ" እንዲሉ) ።
አንጣፊነት፡ አንጣፊ መኾን።
አንጥረኛ (ኞች)፡ አንጥር ያለው (ባለአንጥር የአንጥር አለቃ ወይም ርሱ ራሱ ወርቅና ብር አፍሳሽ አቅላጭ የማዕድን ጌጥና ሽልማት ፥ ዐልቦና ድኰት አንባርና ቀለበት ድሪና ማርዳ ሙጣና ጣፋ ጫሜ አክሊል ዘውድ ሠራተኛ ጃን ሸላሚ - ኢሳ. ፶፬፥፲፮፡ ዘካ. ፩፥፳) ።
አንጥረኛ ወርቅና፡ ብር፡ አፍሳሽ ፣ነጠረ ።
አንጥረኛነት፡ አንጥረኛ መኾን።
አንጥር፡ ዝኒ ከማሁ (ዳግመኛም "አንጥር" ለቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ ይኾናል ትርጓሜውም "አንር አቅልጥ" ማለት ነው) ።
አንጦለጦለ፡ አንቀዠቀዠ (ጦለጦለ) ።
አንጦርጦስ፡ የታች፡ ታች፡ መጨረሻ፡ ታች፡ ሲኦል፡ ገሃነም።
አንጦዘጦዘ አንከወከወ (ጦዘጦዘ) ።
አንጨረገገ፡ አጠቈረ ("የፊት በተደራጊነትም ይፈታል") ።
አንጨረገገ፡ አፈራ፡ (ጨረገገ)።
አንጨረጨረ፡ አለምጣድ፡ በፍም፡ ላይ፡ ቈላ፡ (ጨረጨረ) ።
አንጨረጨረ፡ አስጮኸ ።
አንጨርፋፊ፡ ያንጨረፈፈ/የሚያንጪረፍፍ ("ጠጕር አሳዳጊ") ።
አንጨበረረ፡ አቃጠለ፡ በበረረ ።
አንጨበረረ፡ አቃጠለ/አደረቀ/አቆመ ("አንጨፈረረ") ።
አንጨፈጨፈ (አንጠፈጠፈ)፡ በአ ለት ላይ መናኛ ዕጥበት ዐጠበ ።
አንጨፈጨፈ፡ አወዛ/አቅለጠለጠ ።
አንጨፈጨፈ፡ ዐጠበ፡ አቅለጠለጠ፡ ጨፈጨፈ ።
አንጨፈጨፈ፡ ወቀሠ/ዘለፈ ።
አንጨፍጫፊ፡ ያንጨፈጨፈ/የሚያን ጨፈጭፍ ("ዐጣቢ") ።
አንጪ ቈረር)፡ በግወዳ ዋዩ በሚባል አገር ውስጥ ያለ ገበያ ።
አንጫ፡ አንቻቻ፡ (ጫ)።
አንጫረረ፡ አሳረረ፡ ወረረ።
አንጫረረ፡ አሳረረ/አንጨበረረ/አገመነ/አኰማተረ ("ገረፈ አጮኸ") ።
አንጭት፡ (አንቄ)፤ገዲ፡ ደረተ፡ ነጭ፡ አሞራ፡ ወይም፡ ሳቢሳ። ድንኳኑ፡ አንጭት፡ መስሏል፡ እንዲሉ ።
አንጸባረቀ፡ አብረቀረቀ (ጸበረቀ) ።
አንጻር (ሮች)፡ ፊት ለፊት ያለ ስፍራ (አንጣር) ሳሳይ።
አንጻር፡ አቅጣጫ፡ ነጸረ።
አንጻር፡ ያገባብና የቅኔ ስም።
አንፈላሰሰ፡ አገላበጠ፡ (ፈለሰሰ)።
አንፈላሳሽ፡ ያንፈላሰሰ/የሚያንፈላስስ ።
አንፈሳለቀ አንፈላሰሰ፡ (ፈሰለቀ) ።
አንፈረከከ፡ ጭኑን፡ አለያየ፡ (ፈረከከ)
አንፈረዘዘ፡ አጠገበ፡ (ፈረዘዘ)
አንፈረፈረ፡ አግፈለፈለ፡ ፈረፈረ ።
አንፈረፈረ፡ እንጀራ ፈርፍሮ በወጥ ሠራ አግፈለፈለ ።
አንፈራገጠ፡ ዕጥፍ፡ ዘርጋ፡ አደረገ፤(ፈረገጠ)።
አንፈራጠጠ፡ እግሩን አራራቀ አዋ ቀረ (ብዙ ስፍራ ያዘ ") ። (አዝማሪ)፡ "ከጐበዝ ደግሞ ጐበዝ ይበልጣል፡ እኒያ ሲመጡ፡ ያን ፈራጥጣል" ።
አንፈራጠጠ፡ እግሩን፡ አራራቀ፡ ፈረጠጠ።
አንፈራጣጭ፡ ያንፈራጠጠ/የሚያንፈራ ጥጥ (እልከኛ ሞገደኛ ") ።
አንፈራፈረ፡ አንደፋደፈ አንዘፈዘፈ አ ንቀጠቀጠ ("ጋኔን ወባ ሰውን፡ ድመት ወፍን ዐይጥን ") ።
አንፈራፈረ፡ አንደፋደፈ፡ ፈረፈረ ።
አንፈራፋሪ፡ ያንፈራፈረ/የሚያንፈራፍር (አንደፋዳፊ አንዘፍዛፊ ") ።
አንፈቀፈቀ፡ አፈላ፡ ፈቀፈቀ ።
አንፈጨፈጨ፡ አፈላፈጨ ፈጪ ።
አንፋለለ፡ አወደቀ፡ ፈለለ ።
አንፋለለ፡ ኣረዘመ አወረደ አወደቀ ጡትን ።
አንፋሰሰ፡ እንደ ፈሳሽ አስኬደ ።
አንፋሪ፡ ያነፈረ/የሚያነፍር (ቀቃይ አብሳይ) ።
አንፋር፡ (ሮች)፡ የዛፍ፡ ስም፡ ዐመድማ፡ ዕንጨት።
አንፋሮ፡ (ዎች)፡ ያንበሳ፡ ጠጕር፡ የራስ፡ ጌጥ፡ (፩ሳሙ፡ ፲፯፡ ፴፭) ።ጐፈርን፡ እይ ።
አንፋሸረ፡ አንገራበደ (ፋሸረ) ።
አንፋሻሪ፡ ያንፋሸረ/የሚያንፋሽር (አ ንገራባጅ ጕረኛ ") ።
አንፋሽ፡ ያነፈሰ/የሚያነፍስ ("የወቃጭ አንፋሽ" እንዲሉ) ።
አንፋሽነት፡ አንፋሽ መኾን።
አንፋቀቀ በቂጥ፡ አስኬደ፤(ፎቀቀ)።
አንፋቀቀ፡ ነገር አዛመተ አዋሰደ አዋሸከ አሳበቀ ።
አንፋቃቂ (ዎች)፡ ያንሯቀቀ/የሚ ያንፍቅቅ (ነገረኛ አሳባቂ አዋሻኪ ") ።
አንፋከከ፡ ወዲያና፡ ወዲህ፡ አስረገጠ፡ (ፈከከ)
አንፋፋ ዐለበ አወረደ፡ (ፋፍ)።
አንፎርሻ፡ ድፍርስ ውሃ (መሬት ፈርሶ ተንዶ የወደቀበት - ብጥብጥ ፈሳሽ ") ("(ኢሳ. ፳፬፥ ፫)") ።
አንፎርሻ፡ ድፍርስ፡ ፈረሰ።
አንፎሸፎሸ አቀለለ፡ (ፎሸፎሸ)
አንፎከፎከ፡ ሸነ (ፎከፎከ)።
አኖረ፡ አስቀመጠ/አቈየ/አከረመ (ግብ. ሐዋ. ፭፥፪ - "ድንት ያኑርኸ" እንዲሉ) ።
አኗሪ፡ ያኖረ/የሚያኖር (አስቀማጭ) ።
አኗኗር፡ አቈያየት (መኖር) ።
አኘከ አላመጠ፡ ዐኘከ።
አኞ፡ አንጆ፡ ዐኘከ።
አአ፡ ከመጋኛና ከውጋት ከጭንቅ የተነሣ መኸ ማቃሰት ። አአ ወጋኝ ። አአአንጠራራኝ እንዲሉ።
አኡ፡ ፈዷል ፥ ቈጠራ ።
አእ በል ኡኡ፡ (ቊቁ)፡ የሐዘንና የጭንቅ የመከራ ጩኸት ። ኡኡና ቊቁ በግእዝ ኦኦ ይባላል ።
አእላፋት፡ (፻፻፻)፡ መቶ፡ ጊዜ፡ እልፍ ፣ ዐሥር፡ መቶ፡ ሺ፡ (ሚሊዮን) ።
አእላፍ ፣ ብዙ ። ወፍን፡ እይ ።
አእላፍ፡ (፲፻፻)፡ እልፍ፡ ጊዜ፡ እልፍ፡ ወይም፡ መቶ፡ ሺ ።
አዕማደ ምስጢር፡ የምስጢር ምሰሶ ዎች ("(ዐይነተኞች ዋኖች)" - እነዚሁም ምስጢረ ሥላሴ' ምስጢረ ሥጋዌ' ምስጢረ ጥምቀት' ምስጢረ ቍርባን' ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን ናቸው ") ።
አዕማድ፡ ዐምዶች ምሰሶዎች ደገፎች "
አዕማድ፡ አድራጊ አስደራጊ ተደራጊ '
አእምሮ፡ ዕውቀት ።
አእምሮ፡ ዕውቀት፡ (ማሳወቅ) ።አእምሮ፡ ገዛ፡ ልቡ፡ ተመለሰለት፡ ዕውቀትን፡ ገንዘብ፡ አደረገ (ሉቃ፰፡ ፴፭)።
አእምሮ፡ ጠባይዕ፡ የባሕርይ፡ ዕውቀት፡ ሰው፡ ከእንስሳ፡ የሚለይበት ።ፈረንጆች፡ ሞራል፡ የሚሉትን፡ ይመስላል ።
አኦሮጭ (ጮች)፡ ያጋለጠ/የሚያጋልጥ (ጥሎ ሸሺ) ። "ፈረንጆች 'ደዜርተር' ይሉታል።"
አከለ፡
አከለ፡ ልክ ፥ ትክክል ኾነ ። አባትና እናት ልጆቻቸውን ማን ያኸልኻል ማን ያኸልሻል እንዲሉ።
አከለ፡ በላ ፥ ተመገበ ፥ ጐረሠ ፥ ቃመ ፥ አላመጠ ፥ ዋጠ ፥ ሰለቀጠ ።
አከለ፡ ጨረሰ ፥ ፈጸመ ፥ ደመደመ ።
አከለለ (አሕለለ)፡ እከል አገባ ("ነከረ አጠቈረ ትርጓሜ አረጋዊ መንፈሳዊ ገጽ ፲፪ ተመልከት ከላ ብለኸ ፪ኛውን ከል አስተውል ከዚህ የወጣ ነው ደቀ ") ።
አከለለ፡ አቀዳጀ ("በራስ ላይ አደረገ አክሊል (ሎች) የነገሥታት ተወላጅነት ያላቸው መኳንንትና ወይዛዝር በቤተ ክ ህነትም መምህራንና ዲያቆናት የሚቀዳጁት ከብርና ከወርቅ የተሠራ ክብ የራስ ዙሪያ ጌጥ ማዕርጉ በዘውድና በራስ ወርቅ መካከል የኾነ በግእዝ ግን ዘውድ አክሊል ይባ ላል ") ።
አከለለ፡ አደረቀ ("አቀለለ አጮኸ") ።
አከለበ፡ ውሻ አደረገ ("አሮጠ አቸኰረ አቀለለ ") ።
አከላለል፡ አደራረቅ ("አጯጯኸ መክ ") ።
አከላለል፡ አገራረድ ("መከለል ደነበ ረን አስተውል ") ።
አከላለስ፡ አጨራረስ ("መከለስ") ።
አከላለብ፡ አቸኳኰል፡ መክለብ። ኰልባ፡ (ዎች)፡ የጋሻ፡ ዋንጫ፡ ከጐሽ፡ ከበሬ፡ ቀንድ፡ የተሠራ፡ ታላላቅ፡ ሰዎች፡ መንገድ፡ ሲኼዱ፡ የሚያሲዙት፡ የመንገድ፡ ራዎት።
አከላለፍ፡ አቀማም ("መከለፍ") ።
አከላል፡ አከላከል ("መክላት") ።
አከላከለ፡ ተው ተው አባባለ ("(ይህን ብትሰጥ ምን ትውጥ አለ ንፍገት አስተማረ ") ።
አከላከል፡ አከላል ("መከልከ ") ።
አከላካይ (ዮች)፡ ያከላከለ/የሚያከላ ክል ።
አከመ፡ መድኀኒት አደረገ፡ ዐከመ ።
አከመቻቸ፡ አጠረቃቀመ ።
አከመቻቸት፡ አስተካከብ ("ማከማቸት") ።
አከማመር፡ አጐቻቸት ("መከመር") ።
አከማቸ፡ ሰበሰበ ("አከበ አጠራቀሙ ሰራዊትን ገንዘብን ") (፪ ዜና. ፳፰፡ ፳፬) ።
አከማቸ፡ ሰበሰበ፡ (ከመቸ) ።
አከማቺ፡ ያከማቸ/የሚያከማች ("ሰብሳቢ ኣካቢ ፥ አጠራቃሚ ") ።
አከማከም፡ አከፋከፍ ("መከምከም") ።
አከሣሠት፡ አገላለጥ ("መከሠት") ።
አከሳስ፡ አቀጣጠን ("መክሳት ከሴ (ዎች) ንጣት ያለው ቅጠለ ሻካራ ዕንጨት ሽታው ጣፋጭ ስለ ኾነ ባላገሮች ቅጠሉን አወተት ውስጥ ይጨምሩታል (ዳማ ከሴ) ቀይ ከሴ ይኸውም ቅጠሉ ይቀቀልና ገገምተኛ ይታጠብበታል በሽታው እንዳያገረሽ ይከለክላል ይላሉ ከሽ ቀላል ከሸከሸ ከሽ አደረገ፡ በጥርስ ሰበረ፡ ከ ሸከሸ ከሾ ያገር ስም በጋልኛም የትን ባኾ ቅጠል ማለት ነው ኰሳ (ኰስሐ) ስ ጣለ ዐራ ኵስ (ኵስሕ) የዶሮ ያሞራ የወፍ ዐር የዶሮ ኵስ እንዲሉ በግእዝ ግን ለኹሉም ይነገራል ኵስ ሠገራ ኵሳም (ኵስሓዊ) ሰ ብዙ ባለ መኵሳት መጣል ማንጠባጠብ ማራት መኵሻ የቈጥ የዛፍ የገደል ሥር አስኰሳ አሳራ ኵስ አስጣለ ማስኰሳት ማሳራት ተኰሳ (ተኰስሐ) ታራ ተጣለ ተን ጠባጠበ አኰሳስ አስተራር መኵሳት ") ።
አከረ፡ (እኂር፡ አኀረ ።ዕብ፡ ሀካር፡ ቈፈረ)፡ ለወጠ፡ አቈየ፡ አዘገየ፡ ወደ፡ ኋላ፡ አደረገ፡ የርሻ፡ ያዝመራ። ያበባ፡ እኸል፡ ዘራ፡ ዐደሰ፡ መሬትን።
አከረተ፡ አቃጠለ፡ ከረተ ።
አከርካሪ፡ የሽንጥ፡ ዐጥንት፡ ከረከረ ።
አከበረ፡ ሾመ፡ ሸለመ፡ አበለጠገ፡ ከዕ ጦት ከችግር አራቀ፡ ከበሬታ ሰጠ፡ ከሰው አላቀ።
አከበረ፡ ዐረፈ፡ ሥራ ተወ፡ በዓል አደረገ ።
አከበበ፡ ("ከበበ")፡ ክብ ሥራ ሠራ። አስከበበ፡ በዙሪያ አስቆመ፡ በመካከል አስደረገ ።
አከባበስ፡ አጠማጠም ("መከበስ") ።
አከባበረ፡ እንዲከባበሩ አደረገ። ክብረት፡ ሀብት ብልጥግና ከበሬታ ።ክብረት፤የወንድና የሴት ስም ።ክበር ተመስገን፤ባላገር ለፈጣሪ የሚያቀርበው ምስጋና ።
አከባበር፡ አበለጣጠግ፡ መክበር። (ላ)ከበር፡ ("ዐረ፡ ኸበር")፡ ወሬ ነገር ።
አከባበብ፡ አስተጃጀብ ("መክበብ") ።
አከባበት፡ አደባበቅ ("መከበት ") ።
አከባበድ፡ መደበት ።
አከባከበ፡ አሰራረገ ("አመጋገበ") ።
አከባከብ፡ አሰራረግ ("መከብከብ") ።
አከተ፡ (ትግ፡ ዛገ፡ አደፈ፡ ቸከ)፡ ሰበሰበ፡ አከማቸ፡ አጠራቀመ፡ አረተ፡ ጠበቀ።
አከተ፡ ልክ፡ ትክክል፡ አድርጎ፡ ቈረጠ፡ ዕንጨትን።
አከተመ፡ ጨረሰ፡ ደከመ፡ ከተመ።
አከተመ፡ ጨረሰ ፥ደከመ፡ ከተመ ።
አከታተለ ("አለጣጠቀ አቀጣጠለ አራደፈ አጠባበቀ አከታታይ ያከታተለ የሚያከታትል አለጣጣቂ አጠባባቂ ማከታተል ማለጣጠቅ ማራዶፍ ማከታተያ ማለጣጠቂያ ክትሊ ታናሽ ማንቈርቈሪያ ዐይኑት የምታኸል ለሕፃን አብሽና ወተት ማፍሊያ ባረብኛ ኩትል ትባላለች አከታተል አለጣጠቅ መከተ ከቸለ ") (ቀጨለ) ።
አከታተመ ("አለጣጠቀ አቀጣጠለ አራደፈ አጠባበቀ አከታታይ ያከታተለ የሚያከታትል አለጣጣቂ አጠባባቂ ማከታተል ማለጣጠቅ ማራዶፍ ማከታተያ ማለጣጠቂያ ክትሊ ታናሽ ማንቈርቈሪያ ዐይኑት የምታኸል ለሕፃን አብሽና ወተት ማፍሊያ ባረብኛ ኩትል ትባላለች አከታተል አቈራቈር አሰፋፈር መከ ከቸመ ከቸቸ ደረቀ የጠባይ አከቸመ አከቸቸ አደረቀ አከች ድርቅና አከቻማ ክቾ ለዛ ቢስ ሞዛዛ ኰቸመ ኰሰተረ ዕንጨትን ኰቻሚ የኰቸመ የሚኰችም ኰስታሪ መኰቸም መኰስተር መኰቸሚያ መኰስተሪያ አስኰቸመ አስኰሰተረ ማስኰቸም ማስኰስተር ተኰቸመ ተኰሰተረ ኵችም የተኰቸመ ኵስትር ቀልባጫ የደረቅ ዕንጨት ሸክም ኵችም አለ ቍስትር አለ ተኰቸመ አኰቻቸም አኰሰታተር መኰቸ ኳተነ ሮጠ ለፋ ደከመ ኳተነ የኰቴ ምስጢር አለበት ኳታኝ የኳተነ የሚኳትን የሮጠ የደ ከመ ሯጭ ስፍራ መኳተን መሮጥ መልፋት መድከም መኳተኛ መልፊያ መድከሚያ ጊዜ አኳተነ አሮጠ አለፋ አደከመ አኳታኝ ያኳተነ የሚያኳትን አድካሚ ማኳተን ማሮጥ ማልፋት ማድከም ማኳተኛ ማድከሚያ አኰታተን አደካከም መኳተን ክታን የተልባ እግር ልብስ ") (ግእዝ) ።
አከቴ ፣የቸከ፡ ችካም፡ እድፋም፡ ፡ ጥርሱ፡ ቃሞ ።
አከት፣ ችክ፡ የጥርስ፡ እድፍ ።
አከቻማ፡ ክቾ፡ ከቸመ።
አከቻማ፡ ክቾ፤—ከቸመ።
አከነበለ፡ አክንባሎ አደረገ ("አበጀ ሠራ አጠፈጠፈ ") ።
አከነባበል፡ አደፋፍ ("መከንበል") ።
አከነታተር፡ አገዳደል ("መከንተር") ።
አከነዋወነ፡ አቀለጣጠፈ ።
አከነዋወን፡ አቀለጣጠፍ ("ማከናወን") ።
አከነዳዳ፡ አለካካ ።
አከነዳድ፡ አለካክ ("መከንዳት") ።
አከነፈ፡ በክንፍ አበረረ ("አስቸኰለ አጣደፈ አሮጠ ") ።
አከነፈሰ፡ ቀባጠረ፡ (ከነፈሰ) ።
አከናነበ፡ አጐናነሰ ("አሸፋፈነ አከናነበ ብዙ ስድብ ሰደበ አከናናቢ ያከናነበ የሚያከናንብ ") ።
አከናነብ፡ አሸፋፈን ("ማከናነብ") ።
አከናከን፡ ኣለባለብ ("መከንከን") ።
አከናወነ (ኣጣእጥአ ስለጠ)፡ አቃና ("አሳካ አሳላ አቀላጠፈ ፈጸመ አጣጣመ ተከናወነና አከናወነ ተደራራጊና ኣደራራጊ ሲመ ስል በተደራራጊና በተደራጊ ባደራራጊና ባድራጊ መፈታቱ ሥርወ ቀለሙ ግእዝ ተከታዩ ራብዕ ስለ ኾነ ነው ") ።
አከናወነ፡ ዐረደ ("በለተ ጠባ አወራረደ አዘጋጀ ") (መሳ. ፮፡ ፲፱) ።
አከናወነ፡ አቀላጠፈ፡ (ከነወነ)።
አከናዋኝ፡ ያከናወነ/የሚያከናውን ("አ ጣጣሚ ") ።
አከናዳ፡ አላካ ።
አከንፋሽ (ሾች)፡ ያከነፈሰ/የሚያከ ነፍስ ("ቀባጣሪ ሸውሻዋ ቀባ ብለኸ ቅቤን እይ ") ።
አከከ፡ አበሰለ፡ ሙክክ አደረገ።
አከከ፡ ፎከተ፡ ዐከከ ።
አከካክ፡ አፈነካከት ("መከካት") ።
አከየ፡ (አክይ፡ አከየ)፡ ከፋ ፥ ክፉ ኾነ፡ ለገመ ።
አከዳደነ፡ አሰላለተ ("አከፋከፈ") ።
አከዳዳ፡ አካካደ ።
አከዳድ፡ አሸፋፈት ("መክዳት") ።
አከጃጀለ፡ አመኛኘ ("አፈላለገ ") ።
አከጃጀል፡ አፈላለግ ("መከጀ ") ።
አከፈ፡ ዐፈሠ፡ ዛቀ፡ ጠረገ፡ ጋፈ።
አከፈከፈ፡ አኰፈኰፈ ውስጥ እግር ።
አከፋ፡ አባሰ ("አጠና አጨከነ ክፉ አደረገ ስም አጠፋ (ፊቱን አከፋ) አቀጨመ ቋጠረ አጠቈረ ") ።
አከፋከፈ፡ አካደነ ("አማታ ክፍክፋትን አንከፈከፈ አላስረግጥ አለ አሠቀቀ አንገፈገፈ ካከመን ተመልከት ") ።
አከፋከፍ፡ የክዳን አመታት ("መከፍከፍ") ።
አከፋፈለ፡ ኣለያየ ("ዕዳን ልቆን ደምን አመላለሰ አቀባበለ አከፋፋይ ያከፋፈለ የሚያከፋፍል ብድር አመላላሽ ") ።
አከፋፈል፡ አለያየት ("መክፈል") ።
አከፋፈት፡ ኣወላለል ("መክፈት ") (ሕዝ. ፵፪፡ ፬) ።
አከፋፈን፡ አጠቀላለል ("መከፈን") ።
አከፋፈፍ፡ የክፈፍ አሠራር ("መከፈፍ") ።
አከፋፊ፡ ያከፋፋ/የሚያከፋፋ ("አቀያ ያሚ ") ።
አከፋፋ፡ ሆድ አባባሰ ("አቀያየመ አ ካከነ ") ።
አከፋፋ/አክፋፋ፡ የአከፋ ድርብ ።
አከፋፍ፡ አጨካከን ("መክፋት") ።
አኵለፈለፈ፡ በካከለ፡ ኰለፈ ።
አኵለፈለፈ፡ ብዙ ጊዜ መልሶ መላ ልሶ ኰላለፈ ("በካከለ አጠፋፋ አጥረከረከ ") ።
አኵላላ፡ ፈጋፈገ ("አለዛዘበ ዐዲስ ሸ ክላን ") ።
አኵስማይ የአኵስም፡ ሰው ።
አኵስም፡ ኵሻውያን፡ የኵሽ፡ ልጆች፡ ኵሽን፡ እይ።
አኵስም፡ ጥንታዊት፡ የነገደ፡ ኵሽ፡ መዲና፡ በትግሬ፡ ያለች።
አኵስም፡ ጽዮን፡ (የአኵስም፡ ጽዮን)፡ በቅዱስ፡ አትናቴዎስ፡ እጅ፡ ተባርካ፡ ከታቦተ፡ ሚካኤል፡ ጋራ፡ ለከሣቴ፡ ብርሃን፡ ሰላማ፡ የተሰጠች፡ የማሪያም፡ ታቦት፡ በአኵስም፡ ዐምባ፡ ያለች፡ ነብሪድ፡ ይሥሐቅ፡ ግን፡ የሙሴ፡ ጽላት፡ ይላታል ።አኵስም፡ የጽዮን፡ ዘርፍ፡ ነው ።ጽዮነ፡ ኣኵስም፡ እንደ፡ ማለት፡ ጽዮንን፡ ተመልከት።
አኵስሞች፡ የአኵስም፡ ተወላጆች ።
አኵሪ፡ ያኰራ/የሚያኰራ ("አጓዳጅ ሴት አኵሪ እንዲሉ ") ።
አኵራሪ፡ ያራራ/የሚያራራ ("የልብ ልብ ሰጪ ") ።
አኵነሰነሰ፡ በያይነቱ ልብስ ኣለባበሰ ("ሸላለመ አሽቀረቀረ አሻንጕሊት አስመሰለ ") ።
አኩነሰነሰ፡ አሽቀረቀረ፡ ኰነሰ።
አኩፋዳ፡ አቁፋዳ፡ ቀፈደ ።
አካለ መጠን፡ የ፴ ዓመት ጕልማሳ ፥ ያ፲፭ ዓመት ቈንዦ ፥ ፍጹም ምሉእ አካል፡ ዐቅመ አዳም ፥ ዐቅመ ሔዋን ።
አካለ ጐደሎ፡ ዐይኑ የጠፋ ፥ አፍንጫው ፥ ከንፈሩ የተፎነነ ፥ ዦሮው ፥ እጅ ፥ እግሩ የተቈረጠ ።
አካለለ፡ አጋረደ ("አቃየደ አካለለ አዋሰነ አዳካ ") ።
አካለበ፡ አሯሯጠ ("አቻኰለ አጣደፈ አፋጠነ ") ።
አካላሽ፡ ያካለሰ/የሚያካልስ ("አቀላቃይ ") ።
አካላቢ፡ ያካለበ/የሚያካልብ ("አቻኳይ አጣዳፊ ") ።
አካላት፡ አካሎች፡ ገላዎች ። አካላት የግእዝ፡ አካሎች ያማርኛ ። (የሠራ አካላት)፡ ኹለመና ።
አካላዊ ቃል፡ ወልድ ።
አካላዊ፡ አካልማ ፥ አካላም ።
አካላይ (ዮች)፡ ያካለለ/የሚያካልል ("አዋሳኝ የወሰን የድንበር ዳኛ ") ።
አካል (ሎች)፡ ፍጹም ገጽ ፥ ፍጹም መልክ ያለው፡ ራሱን የቻለ ፥ ለራሱ የበቃ ፥ እኔ የሚል ነባቢ፡ ቁመት ፥ ቁመና ፥ ገላ ፥ ኹለንተና - ከራስ ጠጕር እስከ እግር ጥፍር ያለ ህላዌ የባሕርይ የግብር የስም ባለቤት ። አካል ባማርኛ ለእነባቢ እንስሳም ይነገራል ።
አካል ገዛ፡ አበጀ፡ ሙቶ ተነሣ ።
አካመረ/አከማመረ፡ አደራደረ ("አጓቸ አቋለለ ") ።
አካማሪ፡ ያካመረ/የሚያካምር ("አቋላይ ") ።
አካሰሙ፡ አታከለ ("አቀባቀበ አገዳገደ አዋጠረ ማካሰም ማታከል ማቀባቀብ አከሳሰም አተካከል መከሰም ከሰመ ቅርፊት ያዘ ሻረ ዳነ ጠፋ ጠቈረ የኩፍኝ የፈንጣጣ የጕድፍ የቂጥኝ የዕከክ ") (ተገብሮ) ።
አካበበ፡ ክበብን አሣራ ("አባጀ") ።
አካበበ፡ በጠላት ባውሬ ዙሪያ አ ቋቋመ ።
አካበተ (አመክዐበ/አካዕበተ)፡ እየቈጠበ ከተተ ("አጠራቀመ አጠናቀረ ኣደለበ ") ።
አካበደ፡ ("አስተካበደ")፡ ሸክምን ባዛ፡ አመናዘለ፡ ርስ በርሱ እንዲካበድ አደረ ። አከባበደ፡ አጨቋቈነ፡ አመነዛዘለ ። አከባበድ፡ አጨቋቈን፡ መክበድ ። ኩባያ፡ ኵባያ፡ ("ዐረ")፡ በዋንጫ ህይ ነት ከብረት ዐፈር ተሠርቶ ነጭና ጥቍር ፣
አካቢ፡ ያከበ ፥ የሚያክብ፡ ሰብሳቢ ።
አካባቢ፡ በወሰን ዙሪያ ያለ ስፍራ ቀበሌ ።
አካባቢ፡ ያካበበ/የሚያካብብ ።
አካባቢዎች፡ የሚያካብቡ ("ባካባቢ ያሉ ሰዎች") ።
አካባች (ቾች)፡ ያካበተ/የሚያካብት ("አጠራቃሚ ") ።
አካብሪኝ፡ ለሀብታም የሚሰጥ። አካ ብሪኝ፡ የቅርብ ሴት ትእዛዝ አንቀጽ ነው። ተመልሰኸ መዠመሪያውን ክብር ተመልከት።
አካተበ፡ ኣጻጻፈ ("ኣባጣ አሠናተረ አካታቢ ያካተበ የሚያካትብ የተከታቢን እጅ የሚይዝ ማካተብ ማጻጻፍ ማባጣት ማሠናተር አከታተብ አጻጻፍ ኣበጣጥ መክተብ ኮቲባ ጌታችንን ከመቤታችን እጅ ነጥቃ እምድር የጣለች የግብጽ ሴት ባሪያ ካቲካላ፡ ዐረቄ፡ ከተከተ ከተከተ ") (ከተተ) ።
አካተበ፡ ኣጻጻፈ ("ኣባጣ አሠናተረ አካታቢ ያካተበ የሚያካትብ የተከታቢን እጅ የሚይዝ ማካተብ ማጻጻፍ ማባጣት ማሠናተር አከታተብ አጻጻፍ ኣበጣጥ መክተብ ኮቲባ ጌታችንን ከመቤታችን እጅ ነጥቃ እምድር የጣለች የግብጽ ሴት ባሪያ ካቲካላ፡ ዐረቄ፡ ከተከተ ከተከተ ") (ከተተ) ።
አካተፈ አማተረ ("አቋረጠ አዳቀቀ አካታፊ ያካተፈ የሚያካትፍ ማካተፍ ማማተር ማዳቀቅ አክተፈተፈ አጣደፈ አቻኰለ ማክተፍተፍ ማጣደፍ ማቻኰል ተክተፈተፈ ተጣደፈ ተቻኰለ አከታተፍ አቈራረጥ መክተፍ ሸከ ፈን እይ ከተረ ") (ከቲር/ከተረ) ።
አካት፡ (ትግ፡ ሐባ)፡ የደጓዕሌ፡ ፍሬ፡ አዝራር፡ የሚኾን። ዛፉን፡ ሱማሌዎች፡ ቆኔ፡ ይሉታል።
አካች፡ ሌሊት፡ ከሰባት፡ እስከ፡ ዘጠኝ፡ ሰዓት፡ ከብት፡ ጠባቂ፡ ዘበኛ ።ጊዜውም፡ አካች፡ ይባላል ።
አካች፡ ያከተ፡ የሚያክት፡ አጠራቃሚ።
አካንዱራ፡ መጫወቻ፡ ልጆች፡ ባጥንት፡ በሥንጥር፡ እየወጉ፡ የሚጫወቱበት፡ ልትና፡ ቱልት፡ ይኸውም፡ የጦርነት፡ ምሳሌ፡ ነው ።በጋልኛ፡ aka dura፡ እንደ፡ ፊተኛው፡ ማለት፡ ነውና፡ ከጋልኛ፡ የመጣ፡ ይመስላል ።
አካከለ፡ ጨማመረ ።
አካከመ፡ ጐዳ ("አሳመመ አንከፈከፈ ቅባት ሆድ ያካክማል ") ።
አካኪ፡ የሚያክ፡ ዐከከ ።
አካካበ፡ አመሰጋገነ።
አካካበ፡ የካብ ሥራ አሣራ፡ ደንጊያን አንዱን ባንዱ ላይ አዳረገ አዳረበ።
አካካደ (አስተካሐደ)፡ አረጋገመ ("አለያየ ") ።
አካካደ፡ አሸፋፈጠ ።
አካካድ፡ አረጋገም ("መካድ") ።
አካካጅ፡ ያካካዶ/የሚያካክድ ("አረጋ ጋሚ ") ።
አካኺያጅ፡ ያካኼደ/የሚያካኺድ ("ሥራ ' አቀናባሪ አፋጣኝ ") ።
አካኼደ፡ አቃና ("አቀናበረ አፋጠነ") ።
አካኼድ፡ አረማመድ ("መኼድ") (ምሳ. ፭፡ ፮) ።
አካወሰ፡ አነቃነቀ ("አበጣበጠ ኮሶን እይ የዚህ ዘር ነው ") ።
አካየደ (አስተካየደ)፡ አዋዋለ ("አማማለ ቃል ኪዳን አጋባ ") ።
አካይ፡ ያከለ ፥ የሚያክል ፥ የሚጨምር፡ ጨማሪ ።
አካይስት (አክይስት)፡ እባቦች ።
አካደነ ("አሻፈነ ") ።
አካደነ፡ አሳለተ ("አከፋከፈ እድሞ ኣሣራ ቈርቈሮ ኣማታ ") ።
አካዳ፡ አሻፈተ ።
አካዳኝ፡ ያካደነ/የሚያካድን ("የክዳን ረዳት ዐጋዥ") ።
አካጀለ፡ አፋቀደ ("አፋለገ ") ።
አካፈለ፡ አጋራ ("አፋለመ አዳረሰ አራ ከበ አተናተነ ዋዩን ነገረ አዋየ ") ።
አካፈተ፡ መክደኛን አያያዘ ("(መክፈትን ረዳ) አካፋች ያካፈተ የሚያካፍት ቢከፍቱ ተልባ ርባና ቢስ ትዳር ውስጠ ባዶ ") ።
አካፋ (ነፍነፈ)፡ ካፊያ ጣለ ("እዘነመ በአ ተራ አካፋን እይ ") ።
አካፋ፡ ማፈሻ፡ የላይዳና፡ የማንካ፡ ዐይነት፡ ብረት፡ መዛቂያ ።ሥሩ፡ ወከፈና፡ ካፍ፡ ነው ።
አካፋ፡ ባካፋ፡ ቈፈረ፡ ኰተኰተ ።ይህ፡ ቋንቋ፡ በሐረርጌ፡ ይነገራል ።
አካፋ፡ ካፊያ፡ ጣለ፡ ካፋ።
አካፋይ፡ አጋማሽ ቍና ።
አካፋይ፡ ያካፈለ/የሚያካፍል ("አለቃ ርስት ሰጪ ") (ሉቃ. ፲፪፡ ፲፬) ።
አካፋዮች፡ ያካፈሉ/የሚያካፍሉ ("(መሳ. ፭፡ ፲፩) አካፋይነት አካፋይ መኾን ") ።
አኬለ (አዔለ)፡ አዞረ ("አሽከረከረ") ።
አክ፡ (አህ)፡ የጕረሮ ድምፅ ። አክ አለ፡ ምራቁን በትንፋሽ ከጕረሮ ለየ አወጣ ።
አክ እንትፍ አለ፡ አክ እንትፍ ብሎ ተፋ ። (ግጥም)፡ አያበቅለው የለ ሠኔና ግንቦት፡ አክ እንትፍ አክ እንትፍ ምኑን በላኹት ።
አክለበለበ፡ የአከለበ ድርብ ("እክለፈለፈ ") ።
አክለፈለፈ፡ ክልፍልፍ አደረገ ("አክለ በለበ ") ።
አክለፍላፊ፡ ያክለፈለፈ/የሚያክለፈልፍ ("ኣክለብላቢ ") ።
አክሊለ ሦክ፡ አይሁድ የስቅለትለት ለጌታችን ያቀዳጁት የሾኸ አክሊል ።
አክሊለ ብርሃን፡ የብርሃን አክሊል ።
አክሊለ ጽጌ፡ ያበባ አክሊል ("ልጃገረዶች የደመራ ለት በራሳቸው ላይ የሚያደ ርጉት ዐደይ ") ።
አክሊል፡ በምርት ላይ ያለ ምልክት ("በላይዳ የተሸለመ ") ።
አክሊል፡ በቁሙ ፥ —ከለለ ።
አክላላ፡ ሸለለ ("፡ከለለ ") ።
አክላላ፡ አቅራራ ("ሸለለ ለና ረ ተወራራሾች ስለ ኾኑ አቅራራ በማለት ፈንታ አክላላ ይላል ከላን አስተውል ") ።
አክላላ፡ እንዳይሰጥ አደረገ ("መካከረ") ።
አክሳይ (ዮች) ያከሰለ የሚያከስ ።
አክስል፡ ዝኒ ከማሁ ("አናዳጅ ልብ ኣክስል እንዲሉ ማክሰል ማጥቈር ማግመን ማናደድ ማክሰያ ከሰል ማድረጊያ እሳት ጕድጓድ ውሃ አስከሰለ ከሰል አስደረገ አስጠቈረ አስከሰለ በከሰል አስመለከተ በጽ ፈት ሥርና ጫፍ ዐጥር አስደረገ አሠረዘ ማስከሰል ማስፋም ማስጠቈር ማስመልከት ማሠረዝ ማስከሰያ ዱር የከሰል ስፍራ ተከሰለ በከሰል በርሳስ ተመለከተ ተጻፈ ታረመ ተሠረዘ ") ።
አክሥት (ቶች)፡ ያባትና የናት እት' በኹለት ወገን ዝምድናዋ የተገለጠ ("አክሥቴ የኔ አክሥት ") ።
አክሥት፡ ያባት፡ ወይም፡ የናት፡ እኅት፡ ከሠተ ።
አክረጠረጠ፡ አድበለበለ ("ተክረጠረጠ ዐተረ ተድበለበለ ጓጐለ ተቋጠረ ክርጥርጥ የተክረጠረጠ ዕጢ ጓጓላ ከረ (ቀረጸ) የወፍጮ ውቃሪ ደቃቅ ደንጊያ አሸዋ ") ።
አክረጠረጠ፡ አድበለበለ፡ (ከረጠ) ።
አክርማ፡ የሣርስም፡ ከረመ።
አክሽ፡ ያክታ ዐይነት ብላሽ፡ ዐይነ ምድር ። አክሽ ነው እንዲል ሕፃን ።
አክበሰበሰ፡ ረዥምና ብዙ ልብስ ለብሶ ጐተተ ("መሬት አበሰ አግበሰበሰ") ።
አክባሪ ("ዎች")፡ ያከበረ የሚያከብር ትሑት ታዛዥ ።እከሌ ሰውን አክባሪ እግዜ ርን ፈሪ ነው እንዲሉ። ደኸየን ተመልከት። አክባሪነት፡ አክባሪ መኾን ።
አክባጅ፡ ያከበደ፡ የሚያከብድ፡ ጨካኝ፡ ጨቋኝ ።
አክብሮ፡ ማክበር፡ ሥራ አለመሥራት። አክብሮ ሰንበት እንዲሉ።
አክብሮ፡ ንኡስ አገባብ፡ ሆይ ዎ።
አክብሮ፡ የሩቅ ወንድ ቦዝ አንቀጽ። እከሌ መጋቢት መስቀልን አክብሮ ዋለ።
አክተፈተፈ፡ አጣደፈ፡ ከተፈ ።
አክተፈተፈ፡ አጣደፈ፤—ከተፈ።
አክታ፡ በቁሙ፡ አክ ።
አክታ፡ በቁሙ፤—አክ።
አክታ፡ ከሳልና ከጕንፋን ምክንያት የሚመጣ የንፍጥ ዐይነት መጥፎ የሚያጸይፍ ምራቅ ።
አክነዘነዘ፡ ኣቅነዘነዘ፡ (ከነዘ) ።
አክነፈነፈ፡ አክናፍን ወዘወዘ ("አርገበገባ ኣቅነዘነዘ ነዘነዘ ") ።
አክናፊ፡ ያከነፈ/የሚያከንፍ ("አብራሪ") ።
አክናፍ፡ ኹለት ክንፎች ።
አክንባሎ (ዎች)፡ የምጣድ/የገበር ምጣድ መክደኛ/መግጠሚያ ከእበት/ከሸክላ የተበጀ ("እንጀራና ዳቦ በተጋገረ ጊዜ ከሊጥ በላይ ይደፋል በግእዝ መድፍዕ ይባላል ሞግ ድን እይ ") ።
አክንባሎ፡ የምጣድ መክደኛ፡ ከነበለ ።
አክንፍ/አክነፍንፍ፡ ድግምት ("አስማት አብርር አቅነዝንዝ ማለት ነው አከናነፍ አቸኳኰል መክነፍ ") ።
አክአብ፡ (ኣኅ ኣብ፡ እኅወ አብ)፡ የሰው ስም፡ ያባት ወንድም ፥ አጎት ማለት ነው ።
አክፊ፡ ያከፋ/የሚያከፋ ("ክፉ አድራጊ") ።
አክፋይነት፡ አክፋይ መኾን ("ጦመኛነት") ።
አክፍለተኛ (ኞች)፡ ባላክፍለት/አክ ፋይ/ጦመኛ ።
አክፍለት፡ የ፫ ቀን ጦም ።
አኮ፡ (ትግ)፡ የናት ወንድም ፥ አጎት ማለት፡ ከዚህ የወጣ ነው ።
አኰለታተፍ፡ አጸያየፍ ("መኰልተፍ") ።
አኰላለፍ፡ አበካከል ("መኰለፍ") ።
አኰላል፡ አስተጣጠብ ("መኰላት") ።
አኰላሸ፡ ሰነጋ፡ (ኰለሸ) ።
አኰላተፈ/አኰለታተፈ፡ አንተባተብ ("አስተሳሰረ ") ።
አኰላኰለ፡ አደራደረ ("ደንጊያን አታ ") ።
አኰላኰል፡ አደራደር መኰልኰ ።
አኮሌ፡ ማለቢያ ፥ ቄጆ ፥ ጮጮ ፥ የወተት መጨመሪያ ። አኮሌው ዘንዶ ጋዲው እባብ ነው፡ ያንን ተሻግሮ ዐላቢው ማነው አኮሌ ጋልኛ ነው ።
አኮሌዎች፡ ማለቢያዎች ፥ ጮጮዎች ።
አኰመታተረ፡ አጯመታተረ ("አመ ዳደደ ") ።
አኰመታተር፡ አጨመዳደድ ("ማኰማ ተር ") ።
አኰመኰመ፡ እሸትን/መጠጥን አብዝቶ አበላ ("አጠጣ እጅግ ወሬ አወራ ኣሰማ አኰምኳሚ ያኰመኰመ የሚያኰመ ም ዙም አብሊ አጠጪ ") ።
አኮመጠጠ፡ አሸመጠረ ("ኮምጣጣ አደ ረገ አስቈጣ ") ።
አኮመጣጠጥ፡ አሸመጣጠር ("መኮምጠጥ") ።
አኰማተረ፡ አጨማተረ ("አጨማደደ አ ጨባበጠ ") ።
አኰማታሪ፡ ያኰማተረ/የሚያኰማትር ("አማታሪ ") ።
አኮማጠጠ፡ አሸማጠረ ("አበሳጩ አሳዘነ ") ።
አኮምጣጭ፡ ያኮመጠጠ/የሚያኮመጥጥ ("ብዙ ብቅ ") ።
አኰሰታተር፡ አጠነቃቀቅ ("አሰባሰብ መኰስተር ከት አለ፡ ፈጽሞ ሣቀ፡ ከተከተ ከቶ፡ ጭራሽ ከተተ ከች የልብስ ስም ከቸቸ ኰቴ፡ ሰኰና፡ ኰተኰተ ኩቲ፡ የውሻ ስም፡ ኰተኰተ ኩታ/ኵታ ") (ክታን) ።
አኰረማመት፡ አስተጣጠፍ ("መኰርመት ኰረምቱ የዝኆን አውራ ኰርማ ከረና (ኰርዐ) በክርን መታ ደ ሰቀ ወጋ ክርን (ኵርናዕ) ኵርማ የእጅ ማጠፊያ እንደ ጕልበት ያለ "ሐባቦችም ቀን ድን ክርን ይሉታል ጋት መከርናት በክርን መምታት መው አስከረና አስመታ በክርን ተከረና በኵርማ ተደሰቀ ተወጋ አከረናን አደሳሰቅ መከርናት ከረን የተራራ ስም በትግሬ አውራጃ በብሌን ውስጥ ያለ ዐምባ (ተራራ) አገሩም ከረን ይባላል የምድር ቀንድ እንደ ማለት ኵርንቢ ቍርንቢ የፍየል ወጠጤ ያንባባኸ ኵርንቢ ይወጥርኸ ዶቢ እንዲል እረኛ ኵርንባጥ ኵርምባጥ ክሪንካ ጭንጫ ጣፎንጋ ከረኬማ መሬት ኰርናፋ ኣጕረምራሚ በጥቂት ነገር ኩፍ የሚል ባፍንጫው የሚናገር የሚያኰርፍ አንቀጹ ኰረፈ ነው ኰርናፌ ዳቦ የዳቦ ዐይነት ኩፍ ሲል የተጋገረ ከረነተ አጥብቆ አሰረ ጠፈረ ክርንን ሌላውንም ነገር ") ።
አኰረተ፡ በስተሥሩ፡ አፈራ፣፡ ኰረተ ።
አኰረፈ፡ ተከፋ፡ ኰረፈ።
አኰረፈ፡ ኰረፈ ።
አኰራ (አኵርዐ)፡ ኵራት አሳደረ ("ቈነነ አጓደደ አኰፋነነ አኰራ አንቋጠጠ ከመድራት ከመለመጥ አራቀ ") ።
አኰራኰመ፡ አማታ ("አጋጨ አሳበረ አሻረፈ ") ።
አኰራኰም፡ አሸራረፍ ("መኰርኰም") ።
አኰርባጅ፡ ዐለንጋ፡ ከረበጀ።
አኮበ፡ አብዝቶ አጠነጠነ፡ ደወረ ጠቀ ለለ፡ ኩብ አደረገ፡ ኮባ አስመሰለ።
አኮበ፡ አጠነጠነ፡ ኮበ ።
አኰበለለ፡ ኰብላይ አደረገ ("ሰርቆ ወ ") ።
አኰበላለል፡ አጠፋፍ ("መኰብለል") ።
አኰበተ፡ አደረቀ ("ኵበት አስመሰለ አፍን") ።
አኰበኰበ፡ ዱብ ዱብ አለ፡ (ኰበኰበ) ።
አኰብላይ፡ ያኰበለለ/የሚያኰበል ።
አኰብኳቢ (ዎች)፡ ያኰበኰበ/የሚያኰበኵብ ("ተንደርዳሪ አንበጣ አሞራ ዶሮ") ።
አኰተ፡ (አኲት፡ አኰተ)፡ አመሰገነ፡ ባረከ፡ መረቀ ። (ማኰተን፡ እይ።)
አኰተኰተ፡ ቶሎ ቶሎ ኼደ ኰተኰተ።
አኰተኰተ፡ ቶሎ፡ ቶሎ፡ ኼደ፡ ኰተኰተ ።
አኰቴት (ቶች)፡ ምስጋና፡ ተረፈ መሥዋዕት አመስግነው የሚመገቡት።
አኰቴት፡ (ቶች)፡ ምስጋና፡ ተረፈ፡ መሥዋዕት፡ አመስግነው፡ የሚመገቡት ።
አኰናነን፡ አቀጣጥ ("መኰነን") ።
አኰያየስ፡ አቈላለል ("መኰየስ") ።
አኰዳኰድ፡ አገረኛኘት ("መኰድኰያ") ።
አኰፈንች፡ የማያምር፡ መልከ፡ ጥፉ ።
አኰፈኰፈ፡ ሊላጥ፡ ቀረበ፡ (ኰፈኰፈ) ።
አኰፋነነ፡ አኰራ ።
አኰፋነነ፡ አኰራ፡ (ኰፈነነ) ።
አኳሰ፡ አድበለበለ፡ (ኳሰ)
አኳቢ፡ ያኮበ፡ የሚያኩብ፡ አጠንጣኝ፡ ደዋሪ፡ ጠቅላይ።
አኳኳለ (አስተኳሐለ)፡ አቃባ ("አቀ ባባ ዐይንን በኵል ") ።
አኳኳል፡ ኵል አቀባብ ("መኳ ") ።
አኳዃነ፡ አጠማመረ ("አፋቀረ አዋደደ አሰማማ ") ።
አኳዃን/አኳኾን፡ አደራረግ ("ተፈጥሮ ኹናቴ ኹኔታ ሥረት ኾነን እይ ኮነ የግ እዝ ኾነ ያማርኛ ነው ") ።
አኳያ፡ አንጻር፡ አከለ ።
አኳያ፡ አፍዛዣ ፥ ኣንጻር ፥ ትይዩ ፥ አቅጣጫ ፥ ፊት ለፊት ያለ ።
አኹን፡ -ተዠምሮ ያለ ጊዜ ኾነ።
አኺዶ ("(ሆሴ. ፲፡ ፲፩) ኼደት ") (ኪደት) ።
አወ፡ ቃል አሰረ፡ ዐጪ ።
አወሓሐደ፡ ኣዋዋደ/አገነኛኘ/ኣዛ መደ/አሰማማ ።
አወሓሐጅ፡ አዋዋጅ ።
አወለመጠ፡ አካሉን አሸሸ/አላወሰ/አንቀሳቀሰ ።
አወለቀ፡ ነቀለ/አፈለሰ/አወጣ/ለየ ("የጥርስ የልጓም የልብስ") ።
አወለቀ፡ አደከመ/አስለቸ ("የልብ") ።
አወለቃቀመ፡ አወለጋገመ ።
አወለቃቀም/አወለጋገም፡ ማወለቃ ቀም ።
አወለበ፡ አበጀ/መዘዘ ።
አወለበ፡ ጠረጠረ ፥ —ወለበ ።
አወለበ፡ ጠረጠረ/አጐለበ/አወጣ ።
አወለነ፡ ዘጋ/ደፈነ/አደነቈረ ።
አወለካከፍ፡ አሰነካከል ("መወልከፍ ማወላከፍ") ።
አወለወለ፡ አበጠ/ላላ ("ፍም መሰለ ፊቱ አወለወለ” እንዲሉ) ።
አወለወለ፡ ፍም መሰለ ፥ —ወለወለ ።
አወለገ፡ አጨለገ ("ሰርቆ ዐይኑን አሾ ልኮ አየ አዩኝ አላዩኝ አለ አልማጭ ኾነ በሥራ ጊዜ") ።
አወለገ፡ አጮለገ፡ ወለገ ።
አወለጋገመ፡ አወለቃቀመ ።
አወለጋገም/አወለቃቀም፡ መወልገም ።
አወለጋገደ፡ ውልግድግድ አደረገ ("አወ ለጋገመ") ።
አወለጋገድ/አወለጋገም፡ መወልገድ ("ማጕበጥ") ።
አወላለል፡ አከፋፈት/መወለል ።
አወላለስ፡ የብዙ ዝናም አጣጣል ("አስ ተፋፈን መወለስ") ።
አወላለቀ፡ የአወለቀ ድርብ ("ነቃቀለ አፈላለሰ አወጣጣ") ።
አወላለቅ፡ አወጣጥ/መውለቅ ።
አወላለበ፡ ጠራጠረ ።
አወላለደ፡ አዘማመደ ።
አወላለድ፡ አረባብ ("መውለድ") ።
አወላመመ፡ አጣመመ/አዛወረ ።
አወላመጠ፡ አዘዋወረ ።
አወላቀመ፡ አወላገመ ።
አወላቀመ፡ አወላገመ፡ ወለቀመ ።
አወላከፈ፡ አደናቀፈ ፥ —ወለከፈ ።
አወላከፈ፡ አደናቀፈ/አሰናከለ ።
አወላካፊ፡ ያወላከፈ/የሚያወላክፍ ("አሰናካይ") ።
አወላወለ፡ አወዛወዘ ፥ —ወለወለ ።
አወላወለ፡ አዞረ/አወዛወዘ ("ጅራፍን") ።
አወላወለ፡ አጠራጠረ/አመነታ ።
አወላወለ፡ አጣረገ/አስተሣሠሠ ።
አወላወለ፡ ኣማታ/አጠፋጠፈ ።
አወላወል፡ አጠራረግ/መወልወል ።
አወላዋይ (ዮች)፡ ያወላወለ/የሚያወ ላውል/የሚያመነታ ("ኣወዛዋዥ አጠራጣሪ") ።
አወላዳ፡ አዛመረ/አሰናዘረ/አፈናፈነ ።
አወላገመ፡ አወላቀመ ።
አወላገመ፡ አጣመመ ፥ —ወለገመ ።
አወላገደ፡ አጓበጠ፡ ወለገደ ።
አወላገደ/አወላገመ፡ አጓበጠ ።
አወላጋጅ፡ ያወላገደ/የሚያወላግድ ("እ ወላጋሚ") ።
አወልማጭ፡ ያወለመጠ/የሚያወለምጥ ዝንጀሮ ።
አወሰለተ/አወሳለተ፡ ኣሰነፈ/አባ ለገ/አማገጠ ።
አወሰላለት፡ አመጋገጥ/መወስለት ።
አወሣ፡ መልስ ሰጠ፡ (ወሣ) ።
አወሳሰበ፡ አጠላለፈ/አጠማመረ/ኣወ ታተበ/አተባተበ ።
አወሳሰብ፡ አጠላለፍ/መወሰብ ።
አወሳሰነ፡ አደነጋገገ/አደነባባ ("ወሰን ኣቋቋሙ") ።
አወሳሰን፡ አገዳደብ/መወሰን ።
አወሳሰክ፡ አጨማመር/መወሰክ ።
አወሳሰደ፡ ኣጋጋዘ/አቀማማ/አነጣጠቀ ።
አወሳሰድ፡ አነዳድ/መውሰድ ።
አወሳሳኝ፡ ያወሳሰነ/የሚያወሳስን ።
አወሳሳጅ፡ ያወሳሰደ/የሚያወሳስድ ።
አወሣሥ፡ የነገር አመላለስ/ማውሣት ።
አወሳወሰ፡ አሸዳሸደ ።
አወሳወሰ፡ አወዛወዘ/አነቃነቀ/አዛ መረ/አወላዳ/አፈናፈነ ።
አወሳወስ፡ ኣሸዳሸድ/መወስወስ ።
አወስላች፡ ያወሰለተ/የሚያወሰልት ("አ ማጋጭ") ።
አወረ፡ ዕውር አደረገ ፥ —ዐወረ ።
አወረሰ፡ አባት ወይም ሌላ ሰው ርስቱን/ጕልቱን/ሀብቱን/ንብረቱን ለወራሹ ተናዘዘ/ሰጠ ("የጄን ለልጄ አለ") ።
አወረረ፡ ሽበት ጣል ጣል አደረገ ("አበቀለ") ።
አወረረ፡ አስወረረ ።
አወረቀ፡ አወራ/ዐደሰ/አሳመረ ("ወ ርቅ ኣስመሰለ አወየበ አበል") ።
አወረዛ፡ አራሰ/አረጠበ/አፈሰሰ ("በመ ጠኑ") ።
አወረዛዝ፡ አስተዣዠት/መወርዛት ።
አወረደ፡ ቀነቀነ/ዘፈነ/ግጥም ገጠመ ።
አወረደ፡ ቍልቍል ወደ ቈላ ነዳ/አመጣ/አስኬደ ።
አወረደ፡ አንቈረቈረ/መላ ዐደለ/ሰጠ/ለገሰ/ቸረ ("ዛሬ ማታ እከሌ ጠጅ አወ ረደ") ።
አወረደ፡ አዘነመ/አፈሰሰ ("ኤልያስ ከሰማይ እሳት አወረደ") ።
አወረደ፡ አዜመ ("ዚቅ አወረደ” እን ዲሉ) ።
አወረደ፡ ከላይ ወደ ታች አምጣ ("አቀረበ አዋረደ አሳነሰ") ።
አወረጋገድ፡ አስተጫጨድ ("መጪር") ።
አወራ (ወራ)፡ ወሬ ተናገረ (ማቴ. ፰፡ ፴፫፡ ግብ. ሐዋ. ፫፡ ፳፬) ።
አወራ፡ ነገረ፡ አወረቀ ፥ —ወራ ።
አወራ፡ ኣወረቀ ብጫ አስመሰለ ።
አወራረሰ፡ ርስትን አቀባበለ/አዘዋወረ/አስተላለፈ ።
አወራረሰ፡ አገነኛኘ/አገነዛዘበ/አቈላ ለፈ ።
አወራረስ፡ የርስት ኦያያዝ/መውረስ ።
አወራረር፡ አዘራረፍ/መውረር ።
አወራረቅ፡ አረቃቀቅ/መሣሣት ።
አወራረቅ፡ አቦራረቅ/መወረቅ ።
አወራረብ፡ አስተጫጨድ/መወረብ ።
አወራረደ፡ በየተራ አወረደ ።
አወራረደ፡ ኣገተ/አከራከረ/አነጣ ጠረ/አበጣጠረ ("እሰጥ አገባ ኣባባለ") ።
አወራረደ፡ ጠባ/በለተ/ብልት አ ወጣ/ቈራረጠ (ሚክ. ፫፡ ፪) ።
አወራረድ፡ ብዛት ያለው ያንድ ን ባብ ትርጓሜ ።
አወራረድ፡ አፈሳሰስ/መውረድ ።
አወራረፍ፡ አሰዳደብ/መወረፍ ።
አወራራ፡ መላልሶ አወራ ።
አወራራሽ፡ ያወራረሰ/የሚያወራርስ ("አ ቀባባይ አስተላላፊ አገናዛቢ") ።
አወራራጅ፡ ያወራረደ/የሚያወራርድ ("ዳኛ በጋማች") ።
አወራር፡ አነጋገር/ማውራት ።
አወራኘ (ዐዘረ)፡ በተነ/አሠራጪ/አሰማራ/አስተላለፈ/አገናኘ/አጋጠመ ("የሕዝብ የሰራዊት") ።
አወራኘ፡ አሠራጪ (ወረኘ) ።
አወራወረ፡ አሻጐረ/አቀራቀረ/አቋለፈ ።
አወራወረ፡ አጓጓነ ("እንዲወራወሩ ኣደ ረገ") ።
አወራወር፡ አጣጣል/መወርወር ።
አወራጨ፡ አቅበጠበጠ/አበጣበጠ ("አበ ሳጨ ዕረፍት ነሣ") ።
አወራጩ፡ አበሳጩ ፥ —ወረ ።
አወሸናገረ፡ አጣመመ፡ ሸነገረ።
አወሸካከት፡ አቀበዣዠር/መወሽከት ።
አወሻሸል/አወካከል/መወሸል፡ ዋስላ (ዐረ) የትንባኾ ቅጠል ።
አወሻሸመ፡ አገነኛኘ ።
አወሻሸም፡ የማመንዘር ዘዴ ("መወ ሸም") ።
አወሻሸቅ፡ አሸጓጐጥ/መወሸቅ ።
አወሻገረ/አወናገረ/አወናከረ፡ ማወሻገር/ማወናገር/ማወናከር ።
አወቀ፡ በቁሙ ዐወቀ ።
አወቃቀሠ፡ አቈጣጣ ("ወቀሣን ኣመ ላለሰ አነጋገረ አመካከረ") ።
አወቃቀሥ፡ አገሣሠጽ/መውቀሥ ።
አወቃቀር፡ አነቃቀስ/አጠራረብ/መ ውቀር ።
አወቃቀጥ፡ አቀጣቀጥ/መውቀጥ ።
አወቃቃሽ፡ ያወቃቀሠ/የሚያወቃቅሥ ("አመካካሪ አከራካሪ") ።
አወቃቅ፡ አመታት/መውቃት ።
አወባነነ፡ አኰራ/አጓደደ/አዘባነነ ።
አወባነነ፡ አዘባነነ ፥ —(ወበነነ) ።
አወተተ/አዋተተ፡ አባከነ/አዞረ/አ ንከራተተ ።
አወታተብ፡ አጠማጠም/መወተብ ።
አወታተፍ፡ አከዳደን/መወተፍ ።
አወነባበደ፡ አደነባበረ/አነጣጠቀ ።
አወነባበድ፡ አገላለብ/መወንበድ ።
አወነካከረ፡ አወነጋገረ/አራራቀ ።
አወነካከር/አወነጋገር፡ ማወናከር ።
አወነጃጀል፡ አከሳሰስ/መወንጀል ።
አወነጃጀረ/አወነጋገረ/አፈነጃጀረ፡
አወነጃጀር/አወነጋገር/አፈነጃጀር፡
አወነጨፈ፡ ወነጨፈ ።
አወነጨፍ፡ ኣወራወር/ማወንጨፍ ።
አወናቀፈ፡ አወላከፈ ፥ —ወነቀፈ ።
አወናቀፈ፡ አወላከፈ/አደናቀፈ ።
አወናበደ፡ አሳሳተ/አናጠቀ/አቃማ ።
አወናበደ፡ አደናበረ/አሯሯጠ ።
አወናባጅ (ጆች)፡ ያወናበደ/የሚያ ወናብድ ("አደናባሪ አሳሳች") ።
አወናከረ፡ አራራቀ ፥ —ወነከረ ።
አወናከረ፡ ግራ ቀኝ አስረገጠ ("አው ተረተረ") ።
አወናከረ/አወናገረ፡ አለያይቶ አራ ርቆ ተከለ/አቆመ ።
አወናወነ፡ ኦወዛወዘ/አወላወለ/አነቃ ነቀ/አወሳወሰ ።
አወናደመ (አስተኣኀወ)፡ ወንድም' አዳረገ ("አኳዃነ አቀናጀ") ።
አወናጀለ፡ ኣካሰሰ/አነጋገረ ("ወንጀልን") ።
አወናጀረ/አወናገረ/አፈናጀረ፡ አራ ራቀ ።
አወናጀበ፡ ኣወላከፈ/አደናቀፈ ።
አወናጃይ፡ ያወናጀለ/የሚያወናጅል ("ሌባ ቢልኸ ሽፍታ በለው የሚል") ።
አወናጨፈ፡ አስተላለፈ/አራመደ ።
አወናጨፈ፡ ኣወራወረ/ኣማታ ።
አወናፈለ፡ አስተጋገዘ ፥ —ወነፈለ ።
አወናፈለ፡ አስተጋገዘ/ዕርሻን ሀ ዳን ("ማንኛውንም ሥራ") ።
አወን (እወ)፡ ነባር አንቀጽ፡ የጽድቅና የእምነት ቃል፡ አሉታና ሸፍጥ የሌለበት፡ ደጉን ደግ ክፉውን ክፉ ማለት ። (፪ሳሙ ፪ ፥ ፳) ። (ተረት)፡ ኣወን ባይ ዕዳ ክፋይ ።
አወን አለ፡ አመነ፡ አልካደም ።
አወንታ፡ የአሉታ ተቃራኒ፡ ኣወን ማለት ።
አወንጫፊ፡ ያወነጨፈ/የሚያወነጭፍ ("ወንጫፊ ሰብል ጠባቂ") ።
አወከ (ሆከ)፡ ነቀነቀ በጠበጠ፡ አተራመሰ፡ አስቸገረ አስጨነቀ አሳዘነ፡ አስፈራ አስደነገጠ ። (ዘፀ ፲፬ ፥ ፳፬) ። አንዳንድ መጽሐፍ ግን በአወከ ፈንታ አስታወከ ይላል፡ ስሕተት ነው ። (ግብ ሐዋ ፲፯ ፥ ፰) ።
አወከ ዐበጠ ። አነፈሰ ፥ አጐተነ (በ ጠረ) ።
አወከፈ፡ ወከፈ ።
አወካ፡ ጮኸ (ወካ) ።
አወካከል፡ አተካክ ("መወከል") ።
አወካከብ፡ አጠዳደፍ ("ማዋከብ") ።
አወካከፈ፡ ኣቀባበለ/አሰጣጠ/አረካከሰ ።
አወወ፡ ጮኸ፡ የዥብ የእውዋ ።
አወዛ፡ ኣላበ ("ወዝ ሰጠ አራሰ አያወዛ ወዝ አይሰጥ") ። (ተመልከት፡ ዋዛን እይ) ።
አወዛወዘ፡ አናጋ/አነቃነቀ/አወላወለ/ ኣንቦጫቦጨ ።
አወዛወዝ፡ አነቃነቅ/መወዝወዝ ።
አወዛዋዥ፡ ያወዛወዘ/የሚያወዛውዝ ("አናጊ አነቃናቂ") ።
አወዛዘም፡ አዘነባበል/መወዘም ።
አወዛዘት፡ አቀማመጥ/መወዘት ።
አወዛዘግ፡ አመዛዘዝ/አሳሳብ/አፈታ ተል ("መወዘግ") ።
አወዛዘፍ፡ አረፋፈቅ/መወዘፍ ።
አወዛዛ፡ የኣወዛ ድርብ ("ቀባባ ኣባበሰ") ።
አወዛገበ፡ አነዛነዘ ፥ —ውዝግብ ።
አወዛገበ፡ አጨቃጨቀ/አነዛነዘ/አነ ታረከ ።
አወዣበረ፡ ኣሳሳተ/አደናገረ/አጭ በረበረ ።
አወዣባሪ፡ ያወዣበረ/የሚያወዣብር ("አሳሳች አደናጋሪ አጭበርባሪ") ።
አወየበ፡ ወይባ ነከረ/አቀለመ ("አወ ረቀ አወራ ኣበል ብ ወይም ወይባ አስመሰለ") ።
አወየዘረ፡ አስጌጠ/ሸለመ/አንቈጠ ቈጠ ("ወይዘሮ አደረገ") ።
አወያየብ/አወራረቅ፡ መወየብ ።
አወይ አወይ፡ ወየው ወየው ።
አወይ አወይ ወይ እኔ ወይ እኔ፡
አወይ፡ ከሐዘንና ከጭንቅ የተነሣ የሚባል ቃል ("ፍችው ወየው ተደጋግሞ ሲ ነገር") ።
አወይ፡ የሐዘን ቃል ፥ —ወይ ።
አወደ፡ ቈረጠ፡ ዐደ ።
አወደ፡ ዞረ ሸተተ ፥ —ዐወደ ።
አወደለ፡ አወፈረ/አደነደነ ("ወደል አ") ።
አወደመ፡ አጠፋ/ደመሰሰ ("እንዳልነበረ አደረገ") ።
አወደሰ (ወደሰ)፡ ሳታትና ማሕሌት ቆመ ("ዳዊት ደገመ") ።
አወደቀ፡ ጣለ/አንካረረ/አጋደመ (ሰቈ. ፪፡ ፪) ።
አወዳሽ፡ ያወደሰ/የሚያወድስ ("ቤተ ክሲያን አገልጋይ ካህን ደብተራ ኣንባቢ ደጋሚ አዚያሚ") ።
አወዳሽነት፡ አወዳሽ መኾን ("ደብተ ርነት") ።
አወዳሾች፡ ዳዊት ደጋሞች/ሳታት ቋሞች/መዘምራን ።
አወዳደል፡ አወፋፈር/መወደል ።
አወዳደም፡ አጠፋፍ/መውደም ።
አወዳደሰ፡ አመሰገነ ።
አወዳደሰ፡ አመሰጋገነ ("መላልሶ ደጋ ግሞ") ።
አወዳደስ፡ አመሰጋገን/መወደስ/ማ ወደስ ።
አወዳደረ፡ አስተሳሰረ/አጋመደ ።
አወዳደረ፡ አስተካከለ ።
አወዳደረ፡ አፈካከረ/አስተላለከ/አማ ገተ/አወራረደ ("እሰጥ አገባ አባባለ") ።
አወዳደር፡ አስተሳሰር/መወደር ።
አወዳደቀ፡ አጣጣለ/አገዳደመ ።
አወዳደቅ፡ አከሳሰር/መውደቅ (ማቴ. ፯፡ ፳፯) ።
አወዳደነ፡ ዝኒ ከማሁ ።
አወዳደን፡ አቦዳደን/አቀራቀብ/መወ ደን ።
አወዳደድ፡ አፈቃቀር/መውደድ ።
አወዳዳሪ፡ ያወዳደረ/የሚያወዳድር ("አፈካካሪ") ።
አወዳጀ፡ አዋደደ ("ወዳጅ አኳዃነ") ።
አወዳጂ፡ ያወዳጀ ' የሚያወዳጅ ("አዋዳጅ") ።
አወጀ፡ ዐዋጅ ነገረ ፥ —ዐወጀ ።
አወገነ (አውገነ)፡ ቈረጠ/ለየ ("አራቀ") ።
አወገዘ (አውገዘ)፡ ገዘተ ("ክፉ ሥ ራን ክሕደትን ከለከለ ተው አለ እንቢተ ኛን መናፍቅን ከሕዝብ አንድነት ለየ ወገደ") ።
አወጋ፡ ወግ ተናገረ ፥ —(ወጋ) ።
አወጋገር፡ አመታት/አጣጣል/መው ገር ።
አወጋገዘ፡ አገዛዘተ ("ቃልዎ ይድረ ሰኝ አባባለ") ።
አወጋገዝ፡ አገዛዘት/ማውገዝ ።
አወጋገድ፡ አገላለል/መወገድ ።
አወጋገጥ፡ አስተዋወክ/መውገጥ ። (ተመልከት፡ ሞገ ደንና ሞገተን) ።
አወጋገፍ፡ አረጃጀት/መወገፍ ።
አወጋግ፡ አነዳደፍ/መውጋት ።
አወጝባሪ፡ ያወበረ/የሚያወጫብር ("አሳሳች አደናጋሪ") ።
አወጠጠ፡ ወጠጤ አደረገ ።
አወጣ፡ ልብስን አወለቀ (ነሐ. ፬፡ ፳፫) ።
አወጣ፡ ስም ሰጠ/ሰየመ ።
አወጣ፡ ነቀለ/መዘቀ ("ከውስጥ ለየ አራቀ እሾኽ አወጣ” እንዲሉ) ።
አወጣ፡ አስለቀቀ ።
አወጣ፡ አበቀለ ።
አወጣ፡ አዳነ/አተረፈ ።
አወጣ፡ አፈሰሰ/አጠፋ ።
አወጣ፡ ወለደ/አገኘ ።
አወጣ፡ ገዛ/ለወጠ ።
አወጣ፡ ገፈፈ ።
አወጣጠረ፡ አዘረጋጋ/አለጣጠጠ ።
አወጣጠር፡ አሳሳብ/አዘረጋግ/መወ ጠር ።
አወጣጠቅ፡ አስተጫጨቅ/መወጠቅ ።
አወጣጠነ፡ አዠማመረ/አፈላለመ ።
አወጣጠን፡ አዠማመር/መወጠን ።
አወጣጠጥ፡ አገታተር/መወጠጥ ።
አወጣጥ፡ አበቃቀል/አስተዳደግ ("ወደ ውጭ አካኼድ መውጣት") (መዝ. ፲፱፡ ፮) ።
አወጨባበር፡ አደነጋገር ("ማወጫበር") ።
አወጫመደ፡ አውተረተረ/አግተረተሪ ተር ።
አወጫበረ፡ አሳሳተ/አደናገረ ።
አወፈረ (አውፈረ)፡ አገዘፈ/አደነ ደነ/አሰፋ/አጐላ/አሠባ/አደለበ ።
አወፋሪ፡ ያወፈረ/የሚያወፍር ("አደንዳኝ አሥቢ አድላቢ") ።
አወፋፈር፡ አደናደን/መወፈር ።
አዋሐደ፡ አንድ አደረገ፡ (ዋሐደ) ።
አዋሓጅ፡ ያዋሐደ/የሚያዋሕድ ("አንድ አድራጊ") ።
አዋሓጅነት፡ አዋሓጅ መኾን ("አንድ አድራጊነት በመንፈስ ቅዱስ ኣዋሓጅነት እን ዲሉ ተርጓሞች") ።
አዋለ፡ በቀላል አሰረ/ቋጠረ ("ውል አደረገ") ። (ተመልከት፡ ነፈሰ ብለኸ ነፍስን ዕጭን ወደ ፊት ውሎን እይ) ።
አዋለ/አስዋለ (አውዐለ)፡ ቀን ' ሙሉ ጠበቀ/አቈየ/አዘገየ ("ከብትን ለቅሶን") ።
አዋለቀ፡ አሳደበ/አዋጋ/አጋደለ ።
አዋለቀ፡ እናቀለ/አፋለስ ።
አዋለደ፡ አማማጠ ("ወላድን ያዘ ደገፈ ረዳ ዐገዘ ዐቀፈ") ።
አዋለደ፡ ኣራባ/አዛመደ ።
አዋላቂ፡ ያዋለቀ/የሚያዋልቅ ("እናቃይ አሳዳቢ አዋጊ") ።
አዋላጅ (ጆች)፡ ያዋለደ/የሚያዋልድ/የምታዋልድ ("አማማጭ ሐኪም ባልቴት ማ ሪያም ፡ ማሪያም የምትል") (ዘፀ. ፩፡ ፲፭, ፲፯, ፲፱-፳፩) ።
አዋላጅነት፡ አማማጭነት ፥ ዐቃፊነት ፥ ደጋፊነት ።
አዋላጇ/አዋላጅቱ፡ ያች አዋላጅ (ዘፍ. ፴፰፡ ፳፰) ።
አዋልድ፡ ሴቶች ልጆች (ግእዝ) ።
አዋሰ፡ – የሚመለስ፡ ዕቃ ሰጠ፡ (ዋሰ) ።
አዋሰ፡ ዋስ ጠራ ።
አዋሰበ፡ አጣለፈ/አጣመረ/አተባተበ ።
አዋሰነ፡ አደናገገ/አደናባ ("ወሰን አካ ለለ ደንጊያ አታከለ አዳካ ሥራት አሣራ") ።
አዋሰደ፡ አዛወረ/አዛመተ/አሳበቀ ።
አዋሰዶ፡ አቃማ/እናጠቀ/አናዳ/አቃ ረበ ።
አዋሳቢ፡ ያዋሰበ/የሚያዋስብ ("አጣማሪ") ።
አዋሳኝ (ኞች)፡ ያዋሰነ/የሚያዋስን ("ዳኛ ወሰነተኛ") ።
አዋሳጅ (ጆች)፡ ያዋሰደ/የሚያዋስድ ("አሳባቂ") ።
አዋረሰ፡ አዛወረ ርስትን ።
አዋረሰ፡ ኦያያዘ/አገናኘ/አገናዘበ/አቋ ለፈ ("ዘለበትን") ።
አዋረረ፡ አካበበ/አዛረፈ/አበዛበዘ/አ ማረከ ።
አዋረበ፡ አስተጫጨደ/አለጯጯ ።
አዋረበ፡ አዚያዚያመ/አቀናቀነ ።
አዋረደ፡ ሻረ/አደኸየ/አሳጣ ("ዝቅ አደረገ ሰደበ ዐጥንት አሳደፈ አጐሰቈለ") (ኢዮ. ፲፪፡ ፲፱፡ መዝ. ፻፯፡ ፲፪፡ ፊልጵ. ፪፡ ፰) ።
አዋረደ፡ አዋረሰ ("አደከመ") ።
አዋረደ፡ ከላይ ወደ ታች አናሣ አያ ያዘ/ኣዋሰዶ ("ማውረድን ረዳ - ዐገዘ") ።
አዋሪ፡ ያዋራ/የሚያዋራ ።
አዋራ፡ ወሬን አናገረ/አዳረሰ/ላል ሰማ/አሳማ ("ነዛ አሰማ") ።
አዋራሽ፡ ያዋረሰ/የሚያዋርስ ("አገናዛቢ") ።
አዋራቢ፡ ያዋረበ/የሚያዋርብ ("አስተ ጫጫጅ የወረብ ረዳት") ።
አዋራጅ (ጆች)፡ ያዋረደ/የሚያዋርድ ("ተሳዳቢ") ።
አዋራጅ፡ የሚያዋርድ ("አደካሚ") ።
አዋሸመ፡ ውሽምነት ኦያያዘ ("እዋደደ አገናኘ") ።
አዋሸከ፡ አሳበቀ፡ ወሸከ ።
አዋሸከ፡ አሳበቀ/አዋሰደ ።
አዋሻኪ፡ ያዋሸከ/የሚያዋሽክ ("አሳ ባቂ ነገረ ሠሪ") ።
አዋሽ፡ ወንዝ፡ (ዐወሰ)።
አዋሽ፡ የሚያውስ ("አበዳሪ") ።
አዋሽ፡ የሚያውስ፡ (ዋሰ)።
አዋሽ፡ ጋን፡ (ዐወሰ)።
አዋቀሠ፡ አከራከረ/አቋጣ ።
አዋቀረ፡ አናቀሰ/አጠቃጠቀ ! አጣረበ ።
አዋቀረ፡ ጣራ ወጠነ ፥ —ወቀረ ።
አዋቀረ፡ ጣራ ወጠነ/ዠመረ ("በዋልታ ላይ ጠረቀ አሰረ") (፩ ነገ. ፮፡ ፱) ።
አዋቀጠ፡ አቀጣቀጠ/አማታ/አደባ ደበ ።
አዋቀጠ፡ አፋተገ/አሸካሸከ ።
አዋቂ፡ ያዋቃ/የሚያዋቃ/የሚያማታ ("አደባዳቢ አፈላፋይ") ።
አዋቃ፡ አነቃነቀ/አንገሸገሸ ("ፈረሱ ' ዐንገቱን ' ያዋቃል") ።
አዋቃ፡ ኦማታ/አደባደበ ("አፈላፈለ") ።
አዋቃሪ፡ ያዋቀረ/የሚያዋቅር ("አጣ ራቢ ውቅር ዐዋቂ በልብ ውጋት በምስማር ጠራቂ") ።
አዋቃሽ፡ ያዋቀሠ/የሚያዋቅሥ ("አከራ ካሪ") ።
አዋቃጭ፡ ያዋቀጠ/የሚያዋቅጥ ("የወ ቃጭ አጣማጅ ዘነዘና አፈራራቂ") ።
አዋተፈ፡ አሻጐጠ/አካደነ ።
አዋታች፡ ያዋተተ/የሚያዋትት ("አንከ ራታች") ።
አዋከበ፡ አጣደፈ ፥ —ወከበ ።
አዋከበ፡ ኣቻኰለ/አጣደፈ/ኣዳፋ ።
አዋኪ (ሀዋኪ)፡ ያወከ የሚያውክ፡ በጥባጭ አስቸጋሪ ። ሲበዛ አዋኪዎች ያሠኛል ።
አዋካቢ፡ ያዋከበ/የሚያዋክብ ("አጣዳፊ አዳፊ ዐራጅ ደብዳቢ") ።
አዋዋ (አምዐረ)፡ ጣዕም ተወ/ሰጠ ("አጣፈጠ አፍ ያዋዋል” እንዲሉ) ።
አዋዋ፡ አጣፈጠ፡ ዋዋ ።
አዋዋለ (አስተዋዐለ)፡ አሰማማ/አጻ ጻፈ/አፈራረመ ።
አዋዋል፡ መዋል/ማዋል ።
አዋዋሰ፡ አሰዳደረ/አቀባበለ ዕቃን ።
አዋዋሰ፡ ዋስ እጠራራ ።
አዋዋስ፡ አበዳዶር/ማዋስ ።
አዋዋሽ፡ ያዋዋሰ/የሚያዋውስ ።
አዋዋበ (አስተዋሀበ)፡ አሰጣጠ ፥ አረ ካከበ/አቀባበለ ።
አዋዋብ፡ አሰጣጥ/መዋብ ።
አዋዋይ (ዮች)፡ ያዋዋለ/የሚያዋ ውል ("አጻጻፊ ዳኛ ምስክር ጸሓፊ") ።
አዋዋዶ፡ ኣሰማማ ።
አዋዋጅ፡ ያዋዋደ/የሚያዋውድ ("አሰ ማሚ") ።
አዋዋጠ፡ አሰላሰለ/አወጣ/አወረደ ("ነገርን") ።
አዋዋጠ፡ አባላ/አበላላ/አስለቃቀጠ ("አወራረደ") ።
አዋዋጥ፡ አበላል/አሰለቃቀጥ/መዋጥ ።
አዋዛ፡ ኣዛበተ/ኣቃለደ ("አላላ እንደ ዘበት ሠራ") ።
አዋዜ፡ ብትን ድልኸ፡ ዐዋዜ ።
አዋዜ፡ ብጥብጥ ድልኽ ፥ —ዐዋዜ ።
አዋዠቀ፡ አነቃነቀ/አወዛወዘ ።
አዋየ፡ አስተዛዘነ ፥ —ዋየ ።
አዋየ፡ አስተዛዘነ ("ይብላኝ ለሞተ አለ አላቀሰ ሐዘንን ከሐዘን አነጻጸረ አንቺ ተ ዪነ ሌሎቹ ያዋዬነ እንዳሉ መምር ዕዝራ") ።
አዋዪ፡ ያዋየ/የሚያዋይ ("የሚያስተዛ ዝን አስተዛዛኝ") ።
አዋይ፡ በሴት አንቀጽ የምትጠራ የ ቤት ውቃቢ ።
አዋይ፡ የቤት ውቃቢ ፥ —ዋለ ።
አዋይ፡ ያዋለ/የሚያውል ።
አዋደረ፡ አጋመደ/አጣመረ ።
አዋደቀ፡ አዋረደ/አራከሰ ("ይህን ያ ኸል አያወጣም ኣባባለ") ።
አዋደነ፡ አስተሳሰረ/አቀራቀበ ።
አዋደደ፡ አሳካ/አጋጠመ ("የመኪና የ ጦር የዶማ ፥ የመጥረቢያ ያንካሴ የበሬ ዕቃ") ።
አዋደደ፡ አፋቀረ/ኣሰማማ አስተማመነ ።
አዋዳጅ፡ ያዋደደ/የሚያዋድድ ("አፋቃሪ አሳኪ አጋጣሚ") ።
አዋገረ፡ አማታ/አደባደበ ።
አዋገነ፡ አዛመደ ("ወገን አኳዃነ") ።
አዋገዘ፡ አጋዘተ ።
አዋገደ፡ ከኩሌታ አሳለፈ/አገባደደ/አቃለለ/አቃረበ ።
አዋጊ (ዎች)፡ ያዋጋ/የሚያዋጋ ("የ ጦር አዛዥ አበ ጋዝ የሚያጣላ") ።
አዋጋ (አስተዋግዐ)፡ ዳኛ ኹኖ ' ወ ግን አነጋገረ ("ዋጋን አሳላ") ።
አዋጋ፡ አጣላ/አላተመ/አጋጩ/አታ ኰሰ/አሸራከተ ።
አዋጋሽኝ፡ ጋለሞታ/አመንዝራ ሴት ("ወዳጇ በመጣ ጊዜ በደጇ ብዙ ወንድ ቢያይ አዋጋሽኝ አላት ይላሉ (ወግዳ ማገዋሻ)") ።
አዋጋጅ፡ ያዋገደ/የሚያዋግድ ("አገባ ዳጅ") ።
አዋጠ፡ ቅቤ አጐረሠ/አበላ/መገበ ።
አዋጠረ፡ አዘራጋ/አሳሳበ/አጋተረ/አ ላጠጠ ።
አዋጠቀ፡ አጠቃጠቀ/አባላ ።
አዋጠነ፡ አዣመረ/አፋለመ ።
አዋጣ፡ ሕዝብ ጥቂት ጥቂት ገንዘብ ሰጠ (ነሐ. ፯፡ ፸) ።
አዋጣ፡ አማረጠ/አሻሻለ ("ምክርን ነገርን") ።
አዋጣ፡ አዛለቀ ("እስከ መጨረሻ ደረሰ") ።
አዋጣ፡ አገላለጠ/አናገረ ።
አዋጣ፡ የሳንሳ ይዞ አወጣ ("ማውጣ ትን ረዳ") ።
አዋጪ፡ ያዋጣ/የሚያዋጣ ("የሚያዛልቅ") ።
አዋጭ፡ ያዋጠ/የሚያውጥ/የሚያበላ ("አጕራሽ አብሊ") ።
አው ንጉሥ፡ የንጉሥ አባት፡ የሐረርጌ እስላሞች በዚህ ስፍራ ከነጓዙ ተሰው ሯል እያሉ ያከብሩታል፡ ገዳሙም ኖሌ በሚባል አገር ይገኛል፡ ንጉሡም ክርስቲያን ነው ይላሉ ።
አው አዋ (ሐረር)፡ አባት፡ ኦዊ አባቴ ። ከአይዋ ከማለት ጋራ ይገጥማል ።
አውለቀለቀ፡ የአወለቀ ድርብ ("ፈታታ ለያየ") ።
አውለበለበ (ለውለወ)፡ ወዘወዘ/ነቀ ነቀ ("ምላስን ነበልባልን ነጠላን ላንፋን") ።
አውለበለበ፡ ወዘወዘ ፥ —ወለበ ።
አውለብላቢ፡ ያውለበለበ/የሚያውለበ ልብ ("ወዝዋዥ ነቅናቂ ነፋስ ትንፋሽ") ።
አውለኝ፡ የሸንጎ ተቺ ("የሙግት ረዳት") ።
አውለኝ፡ ጠብቀኝ ("ከጧት እስከ ማታ አድርሰኝ ደኅና አውለኝ” እንዲል ባላገር) ።
አውሊያ (ዐረ)፡ ወልዮች ("የተመ ረጡ ምርጦች") ።
አውሊያ፡ ዛር ፥ —ወለየ ።
አውላ (አውል)፡ ቀሥም የረጋ ያበባ ውሃ፡ ንብና ጣዝማ ጥንዝዛ ከዕፀዋት ኹሉ የለቀሙት የሰበሰቡት የተሠሙት የማር ርሾ ።
አውላላ ሜዳ፡ ርዝመቱ ከአንዱ አገር ወደ ሌላው ብዙ ጊዜ የሚያስኬድ ("በግራ በቀኝ ገመገምና ተራራ ይታይበታል ፈረን ጆች ሬፍት ባሊ ይሉታል") ።
አውላላ፡ ግልጥ ስፍራ ፥ —ወለለ ።
አውላላ፡ ጠላላ/የተንጣለለ ("ግልጥና ሰፊ ስፍራ ባሕር") (ኢዮ. ፴፯፡ ፲) ።
አውላቂ፡ ያወለቀ/የሚያወልቅ/የሚነ ቅል ("ነቃይ") ።
አውላቸው፡ የሰው ስም ("እረኛ ጠባቂ ኹናቸው") ።
አውላዶ (መቍዐል)፡ ወረሞ ("ወፍራምና ሥብ የበግ ሙክት") ።
አውላጊ፡ ያወለጎ/የሚያወልግ ("ገበሎ ዐይነት") ።
አውላጋ፡ የሰው ስም ። (ተመልከት፡ ፊልክስዩስ) ።
አውልቅ፡ ዝኒ ከማሁ ("አድካሚ እሰ ልቺ ልብ አውልቅ” እንዲሉ) ።
አውልግ፡ ዝኒ ከማሁ ("ልግመኛ") ።
አውሎ፡ ጥቅል ነፋስ ፥ —ዐውሎ ።
አውስ፡ ስጥ/አበድር ።
አውስ፡ ዋስ ጥራ ።
አውረኝ፡ ከቀኝ ወደ ግራ ትልቅ ጅራፍ ማጮኸ ።
አውረኝ፡ ያውራ ።
አውሪ (ዎች)፡ ያወራ/የሚያወራ ("ወ ሬኛ") ።
አውሪያም፡ አውሬያለበት የበዛበት ዱር ።
አውራ (አሑር)፡ ኰርማ ወይፈን አግዳማይ ዘዋሪ ። (ተረት)፡ የላሜ ልጅ ያውራዬ ውላጅ ። አውራ ከስም አስቀድሞ እየገባ ቅጽል ይኾናል፡ ፍችውም ዋናነትን መደብ አድርጎ ትልቅነትን ያሳያል ። ያገር አውራ እንዲሉ ።
አውራ መንገድ፡ ትልቅና ሰፊ መንገድ፡ የንጉሥ ጐዳና፡ ብዙ ሰራዊትና ከብት የሚኼድበት ።
አውራ ሙሽራ፡ ከሙሽሮች የሚልቅ ዋና ሙሽራ ።
አውራ ምስክር፡ ዋና ምስክር፡ ወይም እውነተኛ፡ ከዝርዝር ምስክር የሚበልጥ ።
አውራ በሬ፡ ኰርማ ። (ኢዮ ፳፩ ፥ ፲) ።
አውራ በግ፡ ዋና በግ፡ ወይም ያልተቀጠቀጠ የበግ አውራ ።
አውራ ተሲያት፡ ቀትር ስድስት ሰዓት፡ ውሃ ጠጪ ።
አውራ ነገር፡ ዐይነተኛ ሥረ ነገር ። (ዳን ፯ ፥ ፳) ።
አውራ ንብ፡ የንብ ንጉሥ የንግሥት ባል ። ባገራችን ግን ለዓሣና ለንብ ተራክቦ የላቸውም ይባላል ። (ግጥም)፡ እንዳሣ በጥላ እንደ ንብ በድምጥ እኔ አንቺን አርግዤ ተይዣለኹ ምጥ ።
አውራ፡ ንገር ፥ —ወራ፡ አወራ ።
አውራ ዐዘል፡ ድርስ ጊደር ።
አውራ ዶሮ፡ ዋና ዶሮ ኵኵሉ የሚል፡ ወይም ያልተሰነጋ የዶሮ አውራ ።
አውራ ጐዳና፡ ጐነ ሰፊ መንገድ፡ ጥርጊያ ።
አውራ ጣቱን ይጠባል፡ ሕፃን ነው፡ አላዋቂ ነው ።
አውራ ጣት፡ ዋና ጣት፡ ዐጪርና ወፍራም ።
አውራ ፍየል፡ ያልተወቀጠ የፍየል ኣውራ ። (ዘካ ፲ ፥ ፫) ።
አውራ ፍጥረት፡ የፍጥረት አውራ ዋና ትልቅ ብሄሞት ። (ኢዮ ፵ ፥ ፲፱) ።
አውራሪ (ዎች)፡ አስወራሪ ("ፊታው ራሪ” እንዲሉ) ።
አውራሪ፡ የሚያስከብብ ፥ —ወረረ ።
አውራሪሥ (አርዌ ሐሪሥ)፡ በቁሙ፡ አፍን ቀንድ፡ ቀንዱ ባፍንጫው ላይ የበቀለ፡ የጐሽ ዐይነት የበረሓ በሬ ። (መዝ ፳፪ ፥ ፳፩ ። ፳፱ ፥ ፮) ። ተርጓሞች ግን አለስሙና አለመልኩ ርኤም ጽኢም ይሉታል ። ርኤምን ተመልከት፡ ከረከንድን እይ ።
አውራሪስ፡ አፍን ቀንድ፡ አውራሪሥ ።
አውራሪሥ፡ ያውራሪሥ፡ ቀንድ፡ ለጐ ራዴ፡ እጀታ፡ የሚፈለግ፣ ክቡር፡ ውድ።
አውራሪሦች፡ የበረሓ፡ በሮች፡ ያፍን፡ ቀንዶች ።
አውራሽ (ሾች)፡ ያወረሰ/የሚያወርስ ።
አውራሽነት፡ አውራሽ መኾን ።
አውራጃ፡ ፬ ማእዘን ዕንጨት ("አው ራጃ መብሻ” እንዲሉ) ።
አውራጃ፡ በጠቅላይ ግዛትና በወረዳ መካከል ያለ አገር ግዛት ("ወይም የዳኝነት ቤት የምክትል አገረ ገዢ መቀመጫ ብዙ ቀበሌ ወረዳ እንዲባል ብዙ ወረዳም አው ራጃ ይባላል የወረዳና ፥ ያውራጃ ትርጕም ከራስ ከተማ ከጠቅላይ ግዛት ዠምሮ ወራጅ ወንዝ በመለስ ማለት ነው") ።
አውራጃ፡ ብዙ ወረዳ ። (ወረደ) ።
አውራጃ፡ የቈርቈሮ ማገር ተሸካሚ ድፍን ዕንጨት ("በባላገር ግን ማዋቀሪያ ውቅር ይባላል") ።
አውራጃዎች፡ ምክትል አገር ግዛ ቶች ።
አውራጅ፡ አቈልቋይ/ሞላላ ("የመቃና የሳንቃ ገበታ በ፪ቱ ወይም በ፫ቱ ያንድ አነስተኛ አውራጃ ሕዝብ በከፊል ሊመገብ በት የሚችል") ።
አውራጅ፡ የሚያወርድ ("አሳሳች") ።
አውራጅ፡ ያወረደ/የሚያወርድ ("አፍሳሽ ቀንቃኝ ዘፋኝ ግጥም ዐዋቂ") ።
አውራጆች፡ የሚያወርዱ ("ዘፋኞች") ።
አውሬ (አርዌ)፡ በቁሙ፡ ጠባየ ክፉ፡ ደም ልሶ ብርንዶ ጐርሦ ዐጥንት ከስክሶ የሚኖር፡ የሚያድንና የሚታደን ነጣቂ በረ ኸኛ የሰው የእንስሳ ደመኛ፡ በየስሙና በያይነቱ፡ በየነገዱ ። (የቤት አውሬ)፡ ውሻ ድመት ዐይጥ ። አርዌን ተመልከት ።
አውሬ፡ በየብስ፡ ካሉት፡ አራዊት፡ ኹሉ፡ የሚ በልጥ፡ ረዣዥሞች፡ ቀንድ፡ የሚመስሉ፡ ጥር ሶቹ፡ በውድ፡ ተሼጠው፡ በያይነቱ፡ የጌጥ፡ መሣ ሪያ፡ ይኾናሉ ። (ተረት)፡ ዝኆንም፡ ለሆዱ፡ ድም ቢጥም፡ ለሆዱ፡ ወደ፡ ወንዝ፡ ወረዱ ።
አውሬ፡ የሚወገሽ በሬ ። የዱር እንስሳ ጐሽን አጋዘንን ድኵላን የመሰለ ። (ተረት)፡ ያውሬ ሥጋ ለወሬ ። ክፉ ሰውም አውሬ ይባላል ።
አውሬዎች (አራዊት)፡ ዐዳኞች ነጣቆች ቍጡዎች፡ አንበሳን ነብርን ዥብን ተኵላን ዘንዶን ዐዞን የመሰሉ፡ ከላይ የፊት ጥርስ ያላቸው ።
አውር፡ ከባድ ጨው፡ ጋንፉር፡ ኹለት ልመደው አራት አሞሌ የሚያነሣ ።
አውሮች፡ ኰርሞች አግዳማዮች ዋኖች ። (፩ዜና ፲፩ ፥ ፲) ።
አውሮፓ፡ ጳ፡ የእስያ፡ ምዕራብ፡ የያፌት፡ ዕፃ፡ የነጮች፡ አገር ።እንደ ፈረንሳይኛ፡ Europe ቢባል፡ ግን፡ ከዐረበ፡ የወጣ፡ ይመስላል።
አውሮፖች፡ የአውሮፓ፡ ተወላጆች፡ ነጮች፡ ፈረንጆች
አውሸለሸለ፡ –ሳያጠብቅ፡ አሰረ፡ ወሸለ ።
አውሸለሸለ፡ አውተፈተፈ ("ሳያጠብቅ ሠራ") ።
አውተረተረ፡ አግተረተረ ("መናኛ ቤ ትና ዐጥር ሠራ አወናከረ") ።
አውተበተበ፡ አውተፈተፈ/አውሸለ ሸለ ።
አውተፈተፈ፡ አውሸለሸለ፣፡ወተፈ።
አውተፈተፈ/አውተበተበ/አውሸለ ሸለ፡ ማውተፍተፍ/ማውተብተብ/ማውሸ ልሸል ።
አውታር (ሮች)፡ የበገና ዥማት ("የድንኳን የጀልባ የቀስት ገመድ በግእዝ ግን አውታር የወተር ብዢ ነው") (መዝ. ፲፩፡ ፪፡ ኢሳ. ፴፫፡ ፳) ።
አውታር፡ ዥማት፡ ገመድ፡ ወተረ።
አውታታ፡ ባካና/ዘዋሪ/ከርታታ/ቀ ውላላ ።
አውታታ፡ ዘዋሪ፣ወተተ፡ ዋተተ ።
አውናን፡ የሰው ስም፡ የመዠመሪያው ይሁዳ ልጅ ተቀሥፎ የሞተ ።
አውዘገዘገ፡ አምዘገዘገ፡ ወሀገ ።
አውዘገዘገ፡ ኦምዘገዘገ/አቅዘመዘመ ። (ተመልከት፡ ዘገዘገንና መዘገን) ።
አውደለደለ፡ አለል ዘለል አለ ፥ —ወደለ ።
አውደለደለ፡ አለል ዘለል አለ ("አደ ዘደዘ ወደልኛ ሮጠ") ።
አውደልዳይ፡ ያውደለደለ/የሚያውደለ ድል ("አደዝዳዥ ሥራ ፈት") ።
አውደልድል (ጐዣም)፡ ቶፋ አ ይቻል ።
አውደሰደሰ፡ ዞረ ("ሥራ ፈታ") ።
አውደስዳሽ (ሾች)፡ ያውደሰደሰ/ የሚያውደሰድስ ("ዘዋሪ የካህን ሥራ ፈት ቀላዋጭ") ።
አውዳሚ፡ ያወደመ/የሚያወድም ("አጥፊ") ።
አውዳቂ፡ ያወደቀ/የሚያወድቅ ("አጋ ዳሚ") ።
አውድል፡ ጠብደል ።
አውድልት፡ ወፍራሞች/ጠብደሎች ።
አውድም፡ ዝኒ ከማሁ ።
አውጊ፡ ያወጋ/የሚያወጋ ("ወገኛ") ።
አውጋር (አውግር)፡ ቍልልቶች/ኰ ረብቶች ።
አውጋር፡ ኰረብቶች ፥ ወገረ፡ ወግር ።
አውጋዥ (ዦች)፡ ያወገዘ/የሚያወ ግዝ/የሚለይ ("ገዛች ቄስ ጳጳስ አስማተኛ") (፪ ዜና. ፴፫፡ ፮) ።
አውግቼው፡ የሰው ስም ("በክፉ ቀን የተወለደ ልጅ አውግቼው ይባላል") ።
አውግቼው፡ ይህ ጊዜ ዐልፎ ተናግ ሬው ("አውርቼው") ።
አውጠነጠነ፡ ነገርን በልቡ ዐሰበ ("አጕላላ አስላላ") ።
አውጣ፡ ዝኒ ከማሁ ("የሚያወጣ የሚ ያበቅል ባለጌ ዛጐል ልብሱ ዐይን አውጣ ቀንድ አውጣ” እንዲሉ) ።
አውጣጣ፡ እንዲያወጣ አደረገ ("መረመረ") ።
አውጣ'ጦሬን፡ ጠበኛ ኀይለኛ ሰው ("ምሁረ ጸብእ") ።
አውጥ፡ የቅጠል ስም ፥ —ዋጠ ።
አውጥ፡ የቅጠል ስም ("ፍሬው የሚ በላ የሚዋጥ መጠኑ ዐተር የሚያካክል ብጫ መሳይ ቀይ ቀለም የሚኾን ሲበስል ይቀ ላል ሲደርቅ ይጠቍራል (ጥቍር አውጥ) ቅጠለ መራራ ከሥንቆ ከሥጊሚና ከአ ሉማ ጋራ ተቀቅሎ ባንድነት የሚበላ") ።
አውጪ፡ ያወጣ/የሚያወጣ ("ገዳይ ለዪ ነፍስ አውጪ” እንዲሉ) ።
አውጪ፡ ጭ ("ከውስጥ ወደ አፍኣ ከታች ወደ ላይ የሚወስድ ማሽ ፋሪ ቈፋሪ መቃብር አፍራሽ አውሬ ሬሳ በል በግእዝ ጽዕብ በትግሪኛ ፍሒራ ይባላል") ። (ተመልከት፡ ዥራትን እይ) ።
አውጪኝ እግሬ፡ አድኚኝ ("እንዳመ ልጥ አድርጊኝ") ።
አውጫጭኝ፡ አፈርሳታ ("ሕዝብ ተሰ ብስቦ ምሎ ሥዕል ወግቶ ጥፋተኛን የሚያወ ጣበት የሚገልጥበት ምርመራ") ።
አውፋሪ፡ የቤተ መንግሥት ምድረ' ግቢ ሠራተኛ ("በቀድሞ ዘመን የጨዋ ልጆች አሰምሪ ደቀቀ ብለኸ ደቀ ሳፍን እይ") ።
አዉ፡ የዥብ ጩኸት ። (ዥቡ ኣዉ አለ)፡ ጓደኞቹን ጠራ ።
አዉ፡ የዥብ ጩኸት፡ አወወ ።
አዎን፡ ዝኒ ከማሁ ለአወን ። (ሮሜ ፫ ፥ ፳፱ ። ያዕ ፭ ፥ ፲፪) ።
አዘለ፡ በዠርባ፡ ተሸከመ፡ ዐዘለ ።
አዘለለ፡ አስበለጠ/አስተወ ።
አዘለለ፡ አናረ/አነጠረ/አጓነ ("አስጩ ፈረ") ።
አዘለለ፡ ደንጊያን/ዘንግን በዛፍ ላይ አሳለፈ ።
አዘለሰ፡ አስቈጠቈጠ/አስመለመለ/አስ ለሸለሸ ።
አዘለቀ፡ (ኣስደራጊ) አስነበበ/አስጨረሰ ።
አዘለቀ፡ ብቅ አደረገ ።
አዘለቀ፡ አገባ/ዝልቅ አደረገ/አወጣ/ አሳለፈ (ኢዮ. ፳፯፡ ፬) ።
አዘለዘለ፡ አሠነጠቀ/አሸነሸነ ።
አዘለዘለ፡ አስነከሰ/አዘነተረ ።
አዘለጓጐስ፡ አገዳደፍ/መዘልጐስ ።
አዘለፈ፡ አስገሠጸ/አስነቀፈ/አሰደበ ።
አዘላለል፡ አጠማመቅ/መዘለል ።
አዘላለል፡ አጨፋፈር/አናናር/መዝለል ።
አዘላለስ፡ አቈጣቈጥ/መዘለስ ።
አዘላለቅ፡ አጨራረስ/መዝለቅ ።
አዘላለግ፡ አረዛዘም/ማደግ ።
አዘላለፍ፡ አነቃቀፍ/መዝለፍ ።
አዘላዘለ፡ አሠናጠቀ/አሸናሸነ ።
አዘላዘለ፡ አናከሰ/አዘናተረ ።
አዘላዘል፡ አሸናሸን/አነካከስ/መዘል ዘል ።
አዘላይ፡ ያዘለለ/የሚያዘልል ("አስጨፋሪ") ።
አዘልዛይ፡ ያዘለዘለ/የሚያዘለዝል ("አስ ረዘመ") ።
አዘሎ፡ ተራራ፡ ዐዘሎ ።
አዘመመ (አስደራጊ)፡ ዝማሜ አስተማረ/አስደረገ ("ዘና መዠመሪያው መ ይጠብቃል") ።
አዘመመ (አድራጊ)፡ አዘነበለ/አጋደለ ("መዠመሪያው መ ይጠብቃል ባይ") ።
አዘመመ፡ አስከመረ/አስጐቸ ።
አዘመረ (ዘመረ)፡ ማሲንቆ ከረከረ/ መታ ("አያ ሌሌ ሌሌ ዕሠይ ናማ ምነው አለ") ።
አዘመረ፡ የርሻ ሥራ ሠራ ("ዐረሰ ቈፈረ ዘራ ዐደ ቈረጠ") ።
አዘመረ፡ ጮኸ/ፎከረ ።
አዘመተ (አስደራጊ)፡ ወታደር አስላከ ።
አዘመተ፡ ከምድር አስተኛ/ለለጠሰ ("አሳበ ዐፈር አለበሰ የተክል") ።
አዘመተ፡ ጭፍራን/ሰራዊትን ወደ ዘመቻ ላከ/ሰደደ ።
አዘመዘመ፡ አሰፋ/አስቀመቀመ/አስጠ ለፈ ።
አዘማመም፡ አዘነባበል/መዝመም/መ ዘመም ።
አዘማመር፡ አመሰጋገን/መዘመር ።
አዘማመት፡ አካኼድ/አገሣገሥ/መዝ ሙት ።
አዘማመደ፡ ኣገነኛኘ/አገነዛዘበ ።
አዘማመድ፡ ኣገነኛኘት/ማዛመድ ።
አዘማሚ፡ ያዘመመ/የሚያዘምም ("የዝማሜ መምር አስተማሪ አስከማሪ") ።
አዘማዘመ፡ ኣሳፋ/አጣቀመ/አጣለፈ/ አቀማቀመ ።
አዘማዘም፡ አቀማቀም/መዘምዘም ።
አዘማዛሚ፡ ያዘማዘመ/የሚያዘሃዝም ("አቀማቃሚ") ።
አዘምዛሚ፡ ያዘመዘመ/የሚያዘምዝም ("አስቀምቃሚ") ።
አዘረረ፡ ኣሰተረ/አዘረጋ ።
አዘረካከተ፡ አቀዳደደ/አሸረካከተ ።
አዘረካከት፡ አቀዳደድ/መዘርከት ።
አዘረኳኰት፡ አዘለጓጐስ/መዘርኰት ።
አዘረዘረ፡ አስመነዘረ/አሸረፈ ።
አዘረዘረ፡ አስሞረደ/አስፈገፈገ ።
አዘረዘረ፡ አስበተነ/አስለየ ።
አዘረዘረ፡ አሸከሸከ/ኣዘከዘከ ።
አዘረገፈ፡ አስወጣ/አስፈሰሰ ።
አዘረጋ፡ አሰተረ/አዘረረ/አስከፈተ/ አስገለጠ/አስወጠረ ።
አዘረጋገፍ፡ አቦጫጨቅ/መዘርገፍ ።
አዘረጋግ፡ አሰታተር/መዘርጋት ።
አዘረጠ (ዘረጠ)፡ ሰደበ/አዋረደ ።
አዘረጠ፡ አሳጠረ ("ቁመትን") ።
አዘረጠ፡ ፈሳ ("ፈሱን ለቀቀ") ።
አዘረጠ፡ ፈሳ፤ዘረጠ ።
አዘረጠጠ፡ አሳበ/አስጐተተ ።
አዘረጠጠ፡ አስናደ/አስፈረሰ ።
አዘረጣጠጥ፡ አናናድ/መዘርጠጥ ።
አዘረፈ (አስደራጊ)፡ አስቀማ/አስበዘበዘ/አስነጠቀ/አስወሰደ ።
አዘረፈ (አድራጊ)፡ አብዝቶ ሰጠ ("አዘረፈኝ የሰው ስም") ።
አዘሪ፡ ያዘራ/የሚያዘራ ።
አዘራ (አዝርዐ)፡ አስበተነ/አስነሰ ነሰ ።
አዘራ፡ ለነፋስ፡ ሰጠ፡ (ዘራ)።
አዘራ፡ በዱላ መታ ("ደሙ እስኪበተን ድረስ እከሌ እከሌን በዱላ አዘራው") ።
አዘራ፡ አወረደ/ነዛ/አፈሰሰ ።
አዘራ፡ ክፉኛ ሰደበ/አዋረደ ።
አዘራረር፡ ኣዘረጋግ/መዘረር ።
አዘራረፈ፡ አቀማማ/አነጣጠቀ ።
አዘራረፍ፡ አቀማም/መዝረፍ ።
አዘራር፡ አበታተን/መዝራት ።
አዘራር፡ አነቃነቅ/አለያየት/ማዝራት ።
አዘራከተ፡ አቃደደ/አሸራከተ ።
አዘራዘረ፡ አመናዘረ/አሻረፈ ።
አዘራዘረ፡ አባተነ/አለያየ ።
አዘራዘረ፡ ኣረደ/አፈጋፈገ/አሳሳለጥርስ አዋጣ ።
አዘራዘር፡ አበታተን/አሞራረድ/መዘር ዘር ።
አዘራገፈ፡ አቃደደ/አሸራከተ/አዘራከተ/ አዋጣ/አፋሰሰ ።
አዘራጊ፡ ያዘራጋ/የሚያዘራጋ ("አሳታሪ") ።
አዘራጋ፡ ኣሳተረ/አዛረረ/አሳጣ/አካ ፈተ/አዋጠረ/አናጠፈ ።
አዘራጠጠ፡ አሳሳበ/አጓተተ ።
አዘራጠጠ፡ አናናደ/አፋረሰ ።
አዘራፊ፡ ያዘረፈ/የሚያዘርፍ ("አስበዝ ባዥ") ።
አዘርዛሪ፡ ያዘረዘረ/የሚያዘረዝር ("ባለ ማጭድ") ።
አዘቀዘቀ፡ አስቈለቈለ/አስፈሰሰ/አስደፋ ("(አስደራጊ) ፪ቱንም ዘ አጥብቅ") ።
አዘቀዘቀ፡ ወደ ታች አመራ/ኼደ ("(አድራጊ) ፩ኛውን ዘ አላላ") ።
አዘቀጠ (ዘቀጠ)፡ ወደ ኋላ አለ ("ቀረ እዘበጠጠ (ተገብሮ)") ።
አዘቀጠ፡ አሰጠመ/አሠረገ/አስቀረ ("ራሱን ሰውነቱን (ገቢር)") ።
አዘቃቀጥ፡ አሠራረግ/መዝቀጥ ።
አዘቃዘቀ፡ ራስን ወደ ታች እግርን ወደ ላይ አያያዘ ።
አዘቃዘቅ፡ አቈላቈል/መዘቅዘቅ ።
አዘቃጭ/አዝቃጭ (ጮች)፡ ያዘ ቀጠ/የሚያዘቅጥ ("አዘብጣጭ") ።
አዘቋቈን፡ አደቋቈን/መዛቈን ።
አዘበ፡ ጠለፈ፡ ዐዘበ።
አዘበላለል፡ አስተራር/መዘብለል ።
አዘበተረ፡ አዘነተረ ።
አዘበታተር፡ አዘነታተር/መዘብተር ።
አዘበነ፡ ዘበናይ አደረገ ("አጌተየ") ።
አዘበዘበ፡ ተንጠለጠለ/ተንጠረበበ ("ሊ ፈርስ ሊናድ ሊወድቅ ቀረበ") (ተደራጊ) ።
አዘበዘበ፡ አስነዘነዘ/ኣስነተረከ (አስ ደራጊ) ።
አዘበዘበ፡ አንጠለጠለ/አንጠረበበ (አ ድራጊ) ።
አዘበጠ፡ ለመጠ/አደራ ("ዘባጣ አደ ረገ") ።
አዘበጠጠ አስቀረ፡ ዘበጠጠ።
አዘበጠጠ፡ አዘቀጠ ("የኋላ አደረገ አስ ቀረ ልማዱ ግን ተደራጊ ነው") ።
አዘባ፡ አደራ/ለመጠ ("ጫፍና ጫፍን ወደ ላይ መካከልን ወደ ታች አደረገ") ።
አዘባበተ፡ አዛዛተ/እፎካከረ ።
አዘባበት፡ ኣዛዛት/መዘበት ።
አዘባበጥ፡ አለማመጥ/መዝበጥ ።
አዘባብ፡ አደራር/መዝባት ።
አዘባነነ፡ ትዕቢትኛ አናገረ ("አኰራ አጓደደ") ።
አዘባነነ አኰራ፡ (ዘበነነ) ።
አዘባዘበ፡ እነዛነዘ/አነታረከ/አጨቃ ጨቀ/አጓተተ ።
አዘባዘብ፡ አነዛነዝ/መዘብዘብ ።
አዘብዛቢ፡ ያዘበዘበ/የሚያዘበዝብ ("አን ጠልጣይ ተንጠልጣይ") ።
አዘብጣጭ፡ ያዘበጠጠ/የሚያዘበጥጥ ("ያዘብጣጭ የቀሪ ዕዳ") ።
አዘቦ፡ ያገር ' ስም ።ራያና፡ አዘቦ፡ እን ዲሉ። አዘቦ፡ አቅኒው፡ ነው።
አዘቦት፡ ሥራ፡ የሌለበት ቀን፡ ዐዘቦት ።
አዘነ፡ ተከዘ፡ ዐዘነ።
አዘነበ፡ አወረደ/አመጣ/አንጠባጠበ ("ዝናብ ጣለ ሌላውንም") (መዝ. ፸፰፡ ፳፬, ፳፯) ።
አዘነበለ (አስደራጊ)፡ አስጐነበሰ ።
አዘነበለ፡ (ዘመ) ።
አዘነበለ፡ አጋደለ/እጐነበሰ/አዘመመ ("ዝቅ አደረገ ደፋ አቀረቀረ") (ዘፍ. ፳፬፡ ፲፬፡ ዘፀ. ፴፯፡ ፱፡ ፪ ሳሙ. ፲፱፡ ፲፬) ።
አዘነባበል፡ አጐነባበስ/መዘንበል ።
አዘነተረ፡ አስነከሰ/አስበላ ።
አዘነታተር፡ አነካከስ/መዘብተር ።
አዘነኳኰረ፡ ኣበለሻሸ/አዘነጓጐለ ።
አዘነኳኰር፡ አበለሻሸት/መዘንኰር ።
አዘነጋ፡ ከዳ/አታለለ ("ከወደ ኋላ ነከሰ መታ የውሻ የባለጋራ") ።
አዘነጋ፡ ዝንጉ አደረገ/አስረሳ ።
አዘነጋጋ፡ አረሳሳ ።
አዘነጋግ፡ አረሳስ/መዘንጋት ።
አዘነጓጐለ፡ አለያየ/አበለሻሸ ።
አዘነጓጐል፡ አለያየት/ማዘናጐል ።
አዘነጠለ፡ አስነደለ/አስበሳ/አስቀደደ ።
አዘነጣጠለ፡ አበሳሳ/አነዳደለ/አቀዳ ደደ ።
አዘነጣጠል፡ አፈነቃቀል/መዘንጠል ።
አዘነጣጠፍ፡ አሸመጣጠጥ/መዘንጠፍ ።
አዘነፋፈል፡ አዘነባበል/መዘናፈል ።
አዘና (አዝኀነ)፡ አሳረፈ/አረጋ ።
አዘናበለ፡ አጐናበሰ/አደናቀፈ/አጣ መመ ።
አዘናነቅ፡ አቀያየጥ/መዘነቅ ።
አዘናነብ፡ አወራረድ/መዝነብ ።
አዘናነፈ፡ አበላለጠ ።
አዘናነፍ፡ አተራረፍ/መዝነፍ ።
አዘናን፡ አደራር/መዝናት ።
አዘናኰረ፡ ነገር፡ አበላሸ፡ ዘነኰረ ።
አዘናኰረ፡ አዘናጐለ ።
አዘናጋ፡ አራሳ ።
አዘናጐለ፡ አጣረሰ፡ ዘነጐለ ።
አዘናጐለ፡ አፈቸለ/አቃወመ/አከራከረ ("አጣረሰ አበላሸ") ።
አዘናጓይ፡ ያዘናጐለ/የሚያዘናጕል ("አከ ራካሪ") ።
አዘናጠለ፡ አባሳ/አቃደደ ።
አዘናጠፈ፡ አዠማገገ ።
አዘናፈለ፡ አንፈላሰሰ፡ ዘነፈለ።
አዘናፈለ፡ አጋደመ/አንፈላሰሰ/አቈላ ዘመ ።
አዘንባይ (ዮች)፡ ያዘነበለ/የሚያዘነ ብል ("ኣጋዳይ አጐንባሽ") ።
አዘንብል በሌ፡ የሰርግ ዘፈን ።
አዘንታሪ፡ ያዘነተረ ("አስነካሽ") ።
አዘንጊ (ዎች)፡ ያዘነጋ/የሚያዘነጋ ("ከዳተኛ አታላይ") ።
አዘከረ፡ ዝክር አደረገ ("ባንድ ታቦት ስም ደግሶ ለነዳያን ለካህናት ኣመሳ ኦበላ አጠጣ") (አድራጊ) ።
አዘከረ፡ የታቦትን ስም አስጠራ ("በዓ ሉን አሳሰበ አስባረከ አስቈረሰ ጠዲቅን") (አስደራጊ) ።
አዘካከር፡ አደጋገም/መዝከር ።
አዘካዘክ፡ አነቃነቅ/መዘክዘክ ።
አዘወተረ (አውተረ)፡ ዘወትር/ዕለት ዕለት/በየጊዜው/በየቀኑ መላልሶ ሠራ ("ደ ጋገመ ዐሳቡን ባንድ ነገር ላይ አደረገ") ።
አዘወተረ፡ መላልሶ፡ ሠራ፡ ዘ ወትር።
አዘዋወረ፡ አጠማዘዘ/መዘውር አሣራ አባጀ ("አለዋወጠ አቀያየረ አስተላለፈ") ።
አዘዋወር፡ አጠመዛዘዝ/መዘወር ።
አዘውታሪ፡ (ሮች)፡ ያዘወተረ፡ የሚያዘ ወትር፡ ዘወትር፡ ሠሪ፡ አድራጊ ። ማዘውተር፡ መመላለስ ። ማዘውተሪያ፡ መመላለሻ ። ተዘወተረ፡ ዘወትር፡ ተሠራ፡ ኾነ፡ ተደ ረገ ።
አዘውታሪ (ሮች)፡ ያዘወተረ/የሚያዘ ውትር ("ዘወትር ሠሪ አድራጊ") ።
አዘዘ፡ (አዝዞ፡ አዘዘ)፡ በሥራ፡ በገንዘብ፡ በርስት፡ ላይ፡ ቍርጥ፡ ቃል፡ ሰጠ፡ አድ ርግ፡ አታድርግ፡ ይኹን፡ አይኹን፡ አለ፡ በቃል፡ በጥፈት፡ የሹም፡ የቄስ፡ ያባት፡ የባለቤት። (ተረት)፡ ያልተሾመ፡ አያዝ፡ ያልቀሰሰ - አይናዝዝ።
አዘዘ፡ አመናቸከ።
አዘዞ፡ የገዳም፡ ስም፡ በጐንደር፡ መንግሥት፡ ዕጨጌ፡ የሚኖሩበት፡ መንፈሳዊ፡ ትእዛዝና፡ እውነተኛ፡ የተዋሕዶ፡ ሃይማኖት፡ የሚነገርበት፡ ያቡነ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ ገዳም፡ በአዘዞ፡ ውስጥ፡ ያለ። (ተረት)፡ አዘዞ፡ አንድም፡ ተናዞ፡ አንድም፡ ሥንቅ፡ ይዞ፡
አዘዞ፡ ያገር፡ ስም፡ በጐንደር፡ ኣቅራቢያ፡ ያለ፡ አገር።
አዘዞዎች፡ የአዘዞ፡ መነኵሴዎች፡ ደብረ፡ ሊባኖሶች፡ የሃይማኖት፡ ተቀናቃኞች
አዘዪ፡ ያዘገየ/የሚያዘገይ ("የሚያ ቈይ") ።
አዘያየር፡ ኣጐበኛኘት/መዘየር ።
አዘያየድ፡ አጨማመር/አስተዋወቅ/መ ዘዴ ።
አዘገመ፡ አስጓዘ ።
አዘገመ፡ አጓዘ፡ ዘገመ ።
አዘገመ፡ ኣጓዘ/ወሰደ ።
አዘገበ (ትግ. አዝገበ) (አድራጊ)፡ ዐለበ/ሳበ/ገተረ/ለጠጠ/ደከረ ቀስትን ("የፍ ላጻን ማረፊያና መግቢያ ተኰረ ኣነጣጠረ") ።
አዘገበ (ኣስደራጊ)፡ አሰበሰበ/አስደለበ ("ደለበ") ።
አዘገበ አነጣጠረ፡ ዘገበ ።
አዘገነ፡ ሰጠ/አቀረበ/አቃመ/አበላ (አድራጊ) ።
አዘገነ፡ ዝገኑ አለ ("አስጠረን በጥርኝ አሲያዘ አስጨበጠ አስቃመ") (ኣስደራጊ) ።
አዘገየ፡ አቈየ/አዋለ/አሳደረ/አሰነበተ (ኢሳ. ፵፰፡ ፱፡ ሉቃ. ፲፰፡ ፬፡ ፩ ተሰ. ፪፡ ፲፰) ።
አዘገያየት፡ ኣቈያየት/መዘግየት ።
አዘገጃጀ፡ አደረጃጀ/አሰነዳዳ/እቀነባ በረ ።
አዘገጃጀት፡ አደረጃጀት/ማዘጋጀት ።
አዘገጠ፡ ኣዘቀጠ ።
አዘጊ፡ ያዘጋ/የሚያዘጋ ("አስማይ የዘጊ ዎች አለቃ ከደን") ።
አዘጋ (አስደራጊ)፡ አስገጠመ ("አስማለ") ኣስደፈነ/አስከደነ (ግብ. ሐዋ. ፲፮፡ ፳፬) ።
አዘጋ (አድራጊ)፡ ዘረጋ/አደራ ("ድሩን ከድር በማቃረብና በመግጠም መጽሐፍ ግን ዘጋ ይላል ርግጠኛው ይህ ነው") (ኢሳ. ፶፱፡ ፭) ።
አዘጋኝ (አዝግሐኒ)፡ "ነፋሱ ቤቴን አዘጋኝ ተብሎ ይተረጐማል ዘሩ ዘጋ ነው" ።
አዘጋኝ፡ ያዘገነ/የሚያዘግን ("ጥሬ ቈሎ ንፍሮ ዐዳይ አስቃሚ") ።
አዘጋጀ (አድራጊ)፡ አደራጀ/አሰናዳ/አቀናበረ (ዮሐ. ፲፬፡ ፪ - ፫) ።
አዘጋጀ አደራጀ፡ ዘገጀ።
አዘጋጂ (ጆች)፡ ያዘጋጀ/የሚያዘ ጋጅ ("አደራጂ አሰናጂ አቀናባሪ") ።
አዘጋገም፡ አጓጓዝ/ማዝገም ።
አዘጋገብ፡ አሰባሰብ/መዝገብ/መዘገብ ።
አዘጋገን፡ አቃቃም/መዝገን ።
አዘጋጋ፡ አገጣጠመ/አከዳደነ/አደፋፈነ ።
አዘጋግ፡ አከዳደን/መዝጋት ።
አዘጐነ፡ ዛጐል አስመሰለ ("አበለዘ አጠቈረ") ።
አዘጓጐን፡ አበላለዝ/መዝጐን ።
አዘጠዘጠ፡ አነጠነጠ፡ (ዘጠዘጠ)።
አዘጣጠን፡ ዝጠና/መዘጠን ።
አዘጥዛጭ፡ (ጮች)፡ ያዘጠዘጠ፡ የሚያ ዘጠዝጥ ፣ አነጥናጭ ።
አዘጥዛጭ (ጮች)፡ ያዘጠዘጠ/የሚያ ዘጠዝጥ ("አነጥናጭ") ።
አዘፈቀ፡ ኣስደፈቀ/አስነከረ ።
አዘፈነ፡ አስቀነቀነ/አስገጠመ/ኣዘለለ ።
አዘፈዘፈ (አስደራጊ)፡ አስነከረ/አስራሰ/ አስወዘፈ ።
አዘፈዘፈ (አድራጊ)፡ አከበደ/አሰፋ ("ሰፊ አደረገ አረዘመ") ።
አዘፋዘፍ፡ አነካከር/መዘፍዘፍ ።
አዘፋፈቅ፡ አደፋፈቅ/መዝፈቅ ።
አዘፋፈን፡ አቀናቀን/መዝፈን ።
አዙሪቴ፡ ልጆች እየዞሩ የሚጫወቱት ጨዋታ ።
አዙሪት (ነኮላል)፡ ባሪያ/የበግ/የ ሰው በሽታ ("ራስ እያዞረ የሚጥል") ።
አዙሪት፡ ኵርፊት/ዐውሎ ነፋስ ("ባሕ ርን ዐቧራን የሚያዞር የሚያጥወለውል") ።
አዚያሚ፡ ያዜመ/የሚያዜም ("ዘማሪ ካ ህን ደብተራ") ።
አዚያዚያመ፡ አጯጯኸ/አባባለ ዜማ ።
አዚፋ፡ ከምስር፡ የተሠራ፡ የጦም፡ ወጥ፡ ምስሩ፡ ድፍኑን፡ ከተቀቀለ፡ በኋላ፡ ኰረሪማ፡ ዝንጅብል፡ አዝሙድ፡ ሰናፍጭ፡ ቀይ፡ ሽንኵርት፡ ቅባኑግ፡ ይገባበታል ።
አዛለ (አዝሐለ)፡ አደከመ/አዝለፈለፈ ።
አዛለ/አዛለች፡ የወንድና የሴት ስም ።
አዛለቀ፡ አዋጣ/አፋጸመ ("እስከ መጨረሻ አዳረሰ ይህ ነገር አያዛልቅም” እንዲሉ) ።
አዛመ፡ አተኰሰ/አንቀጠቀጠ/አዞረ ።
አዛመረ፡ አሣራ አስተራረሰ/አስተ ወደ ።
አዛመረ፡ አወላዳ/አላወሰ/አስተላለፈ ።
አዛመረ፡ አዚያዚያመ/አመሳገነ ።
አዛመተ፡ አስተላለፈ/አዋራ/አዳረሰ ።
አዛመደ፡ አዋሐደ/አራከበ/አገናኘ ("እያያዘ አሰማማ አገናዘበ") ።
አዛማች፡ ያዛመተ/የሚያዛምት ("አዋሪ") ።
አዛማጅ፡ ያዛመደ/የሚያዛምድ ("አዋ ሓጅ") ።
አዛምር (አዝመር)፡ የንጨት ስም ("የቅጠሉ ሰበከት አረንጓዴ ወዙ ብጫ የሚ መስል ዐጪር ዛፍ") ።
አዛምር፡ ዛፍ፡ ዘመረ።
አዛረፈ፡ ቅኔ አማጣ ።
አዛረፈ፡ አበዛበዘ/አቃማ/አናጠቀ ።
አዛረፈ፡ ዘርፍ አያያዘ/አናበበ ።
አዛራ (አስተዛረወ)፡ በሳንሳ አነቃ ነቀ/ኣፋሰሰ ("አለያየ") ።
አዛራ (አስተዛርዐ)፡ አባተነ " እነ ሳነሰ ።
አዛቀ፡ አስጠረገ/አስጋፈ/አስረ ወሰደ ።
አዛቂ፡ ያዛቀ/የሚያዝቅ ።
አዛቈነ፡ አዳቈነ ።
አዛቋኝ፡ ያዛቈነ/የሚያዛቍን ("አዳቋኝ") ።
አዛበረ፡ አስዋለለ/አስቃሰተ ("ወለሌ አለ") ።
አዛበተ፡ አቃለደ/አዋዛ ።
አዛበተ፡ ኦፋከረ ።
አዛባ፡ በቁሙ፡ ዐዛባ።
አዛባ፡ አዳራ/አላመጠ ("አቃወሰ አሳ ሳተ") ።
አዛባሪ፡ ያዛበረ/የሚያዛብር ።
አዛነቀ፡ አቃየጠ/አሠባጠረ/አደባለቀ ።
አዛነፈ፡ አባለጠ/አታረፈ/አራዘመ ።
አዛና፡ አዳራ ("በብልግና አጫወተ አ ቃበጠ") ።
አዛናቂ፡ ያዛነቀ/የሚያዛንቅ ("አቃያጭ") ።
አዛወረ፡ አላወጠ/አቃየረ ።
አዛወረ፡ ኣጋባ/ገለበጠ ።
አዛወቀ፡ አዛነቀ/አዘባረቀ/አሳሳተ ።
አዛወገ፡ አዋገነ/አጣመረ ።
አዛዋሪ፡ ያዛወረ/የሚያዛውር ("አላዋጭ") ።
አዛውር፡ በበጌምድር ክፍል ያለ አገር ("የኪዳነ ምሕረት አጥቢያ") ።
አዛውንት፡ ጨዋ፡ ዐዛውንት ።
አዛዘነ፡ አስጮኸ፡ አዞረ ።
አዛዘነ፡ አስጮኸ/አዞረ ።
አዛዛቀ፡ አዋጣ/አሰባሰበ ።
አዛዛቀ፡ አጣረገ/አጠራረገ ።
አዛዛቅ፡ አጠራረግ/መዛቅ ።
አዛዛተ፡ አፋከረ/አዘባበተ/አወዳደረ ።
አዛዛት፡ አፎካከር/መዛት ።
አዛዛግ፡ ኣስተዳደፍ/መዛግ ።
አዛዜ የስንዴ፡ ስም ዐዘዘ ።
አዛዥ፡ (ዦች)፡ አዛዚ)፡ ያዘዘ፡ የሚያዝ፡ ዳኛ፡ ጌታ፡ ባለሥልጣን፡ አሠሪ፡ የሥራ፡ ሹም፡ (ምሳ፮፡ ፯) ።ወህኒ፡ ቤት፡ አዛዥ፡ አዛዥ፡ ወልደ፡ ጻድቅ፡ እንዲሉ ።
አዛዥ፡ የቤት፡ የንብረት፡ መጋቢ፡ አስተዳዳሪ፡ (ዘፍ፳፬፡ ፪)
አዛዥነት፡ አዛዥ፡ መኾን፡ አሠሪነት፡ ሹምነት፡ መጋቢነት፡ አስተዳዳሪነት፡ ኀላፊነት።
አዛገ፡ አሳደፈ/አበላሸ/አጠቈረ ።
አዛገ፡ የሰው ስም ።
አዛገመ/አዘጋገመ፡ አጓጓዘ ።
አዛጊ፡ ያዛጋ/የሚያዛጋ ("አፋሻጊ") ።
አዛጋ (አንባሕቀወ)፡ አፋሸግ/አላ ቀቀ/አንባቀቀ ኣፍን ።
አዛጋ፡ አጋጠመ/አካደነ/አዳፈነ ("እ ማማለ") ።
አዛጋ፡ ድርን አዳራ ።
አዛጐለ፡ ኣዘጐነ ።
አዛፈቀ፡ አዳፈቀ/አሳጠመ ።
አዛፈነ፡ አዚያዚያመ/አጨዋወተ/አፈረ/አባጨበ ።
አዜመ፡ ሃሌ፡ አለ፡
አዜመ፡ አዘነበለ ("እንቅልፍ ሰውን") ።
አዜመ፡ ግጥም ገጠመ/አመሰገነ (ኤፌ. ፭፡ ፲፱) ።
አዜብ፡ የማእዘን፡ ስም፡ ንኡስ፡ ማእዘን፡ የአፍሪቃ፡ ወገን፡ በምዕራብና፡ በደቡብ፡ መካከል፡ ያለ፡ የደቡብ፡ ግራ፡ የመስዕ፡ ትይዩና፡ አንጻር፡ ፊት፡ ለፊት፡ ያለ፡ ፮ኛ፡ የምድር፡ ማእዘን። ንግሥተ፡ አዜብ፡ እንዲል፡ ወንጌል ።
አዜገ፡ ዜጋ አደረገ ("ኣስገበረ") ።
አዝ፡ የስንዴ፡ በሽታ፡ ፡ አዘዘ።
አዝ፡ የስንዴ፡ በሽታ፡ በገብስና፡ ባገዳም፡ ራስ፡ ላይ፡ ከሰል፡ መስሎ፡ ይታያል፡ አንዳንድ፡ ዓመት፡ በስንዴ፡ ላይ፡ የሚታዘዝ፡ ዐረማሞ፡ ነው ።
አዝለሰለሰ፡ አዝለፈለፈ/አቅለሰለሰ ።
አዝለገለገ፡ አምለገለገ/አዝረበረበ ።
አዝለገለገ፡ አዝረበረበ፡ ዘለገ።
አዝለግላጊ፡ ያዝለገለገ/የሚያዝለገልግ ("አዝረብራቢ") ።
አዝለፈለፈ፡ አጥመለመለ ("እንደ ሞተ እባብ አደረገ አዛለ") ።
አዝላቂ፡ ያዘለቀ/የሚያዘልቅ/የሚያገባ/የሚያሳልፍ ።
አዝልቃቸው፡ ዝኒ ከማሁ ("አሳልፋቸው ወደ ውስጥ አግባቸው") ።
አዝልቅ/አዝልቄ፡ የሰው ስም ።
አዝመራ፡ ዕርሻ/ቍፋሮ/ዐጨዳ ("መ ከር ፍሬ") ።
አዝመራ፤የርሻ ሥራ፡ ዘመረ።
አዝሙድ (ዶች)፡ የነጭና የጥቍር ቅመም ስም ("መልኩ ፪ ሲኾን በጣዕሙ አንድነት ባንድ ስም ተጠራ ነጭ አዝሙድ ጥቍር አዝሙድ” እንዲሉ) ።
አዝሙድ፡ የቅመም፡ ስም፡ ዘመደ ።
አዝማሚ፡ ያዘመመ/የሚያዘም ("አዘን ባይ") ።
አዝማሚያ፡ ዝንባሌ/ኹናቴ/አኳዃን/አመጣጥ/ስልት/አጣጣል ("አወዳደቅ የነገር አዝማሚያ” እንዲሉ) ።
አዝማሪ (ሮች)፡ ያዘመረ/የሚያዘምር ("ዘፋኝ ባለማሲንቆ ባለክራር አረኾ ጯኺ") (ነሐ. ፯፡ ፷፯) ።
አዝማሪ)፡ "ከፈረሰ ኞች የምናውቃቸው ፥ በሻሽ አቦዬ ኀይሌ አን ዳርጋቸው ። ከፈረሰኞች አሉ በልዩ፡ መኻል አገዳ የሚለያዩ" ።
አዝማሪ)፡ የጐበና አሽከሮች ጠፍር የት ያውቃሉ (በነጋ በጠባ ባረብ ይጭናሉ ") ። ሰማያዊ ዐረብም ከጥቍር ይቈጠራል ።
አዝማሪነት፡ አዝማሪ መኾን ("ዘፋኝነት") ።
አዝማች (ቾች)፡ ያዘመተ/የሚያዘምት ("ኣበ ጋዝ የጦር አለቃ ወይም መሪ ፊታውራሪ ' አዝማች ስብሐት ግራ አዝማች ደጅ አዝማች መርድ አዝማች ቀኝ አዝማች' እንዲሉ) ።
አዝማች፡ አንድ ጊዜ በዜማ/በዘፈን መዠመሪያ ("ብዙ ጊዜ እየተመላለሰ በመጨረሻ የሚባል ቃል ወይም ግጥም ለበገና ድርደራ ለማሲንቆ ክርክራ ለክራር ምት ልዩ ልዩ አዝማች አላቸው") ።
አዝማችነት፡ አዝማች መኾን ።
አዝማድ፡ ዘመዶች ("አዝማድ የግእዝ ነው ዘመድ አዝማድ” እንዲሉ) ።
አዝምቴ፡ የሰው ስም ("አዝምት ማለት ነው") ።
አዝረበረበ፡ አንጠባጠበ ("ጠብ ጠብ አደረገ አዝረከረከ የለሐጭ") ።
አዝረበረበ፡ አንጠባጠበ፡ ዘረበ።
አዝረከረከ፡ ምስጢር አባከነ ።
አዝረከረከ፡ አዝረፈረፈ፣፡ (ዘረከ)።
አዝረክራኪ፡ ያዝረከረከ/የሚያዝረከርክ ("አዝረፍራፊ") ።
አዝረጠረጠ፡ አዝረከረከ፡ ዘረጠ ።
አዝረጠረጠ፡ አዝረከረከ/አስቀረ ።
አዝረፈረፈ፡ አዝረከረከ/አወደቀ/ጣለ/ አቈናዘለ ።
አዝሪ (ዎች)፡ ያዘራ/የሚያዘራ ።
አዝራር፡ የልብስ ቍልፍ፡ ዘረረ።
አዝርል፡ የገነት፡ ወፍ።
አዝበደበደ፡ አስፈራ/አርበደበደ ።
አዝቢ፡ ያዘባ/የሚያዘባ ("አድሪ ለማጭ") ።
አዝባጭ፡ ያዘበጠ/የሚያዘብጥ ("ከባድ ሸክም") ።
አዝብጤ/አዝብጥ፡ የሰው ስም ።
አዝቦጠቦጠ፡ አወፈረ፡ (ዘቦጠ)።
አዝናና (አስተዝያነወ)፡ እንደ ልብ አናገረ ("ሳይፈር ሳያፍር አቅበጠበጠ") ።
አዝካሪ፡ ያዘከረ/የሚያዘክር ("አሳሳቢ ስም አስጠሪ ጠበል ጠዲቅ አድራጊ አብሊ ' አጠጪ") ።
አዝጊ፡ ያደራ/የሚያደራ ("አድሪ ዝሓ ኣዝጊ” እንዲሉ) ።
አዝጋሚ (ዎች)፡ ያዘገመ/የሚያዘ ግም ("አጓዥ") ።
አዝጋሮ፡ የዛፍ፡ ስም፡ ዶቅማ ።
አዝጋቢ፡ ያዘገበ/የሚያዘግብ ("ደካሪ") ።
አዞ፡ የባሕር፡ አውሬ፡ ዐዞ።
አዞረ፡ በራስ ዙሪያ አሳለፈ ዶሮን ።
አዞረ፡ በዙሪያ አፈሰሰ/አከበበ ሊጥን ።
አዞረ፡ አንቀዋለለ/አንከዋረረ ("ፊቱን መለሰ ዠርባውን ሰጠ ጠመጠመ ጠመዘዘ") ።
አዞረ፡ አጥወለወለ/አሰከረ/አናወጠ/አሳ በደ ራስን/ናላን ("በመጠጥ በመድኀኒት በሕ መም") (ሕዝ. ፴፱፡ ፪) ።
አዟሪ (ልጐት)፡ የባሕር ጕድጓድ ("የ ውሃ አሻራ") ።
አዟሪ ሥጋ (ሕልቅ)፡ የጕረሮ ቀ ለበት ("ዐልፎ ዐልፎ ያለው ዙሮ የሚገጥ መው") ።
አዟሪ፡ የእጅ ፥ የራስ አሻራ ።
አዟሪ፡ ያዞረ/የሚያዞር/የሚያንከዋርር ("አስካሪ") ።
አዟዟረ፡ አስተላለፈ ("በዙሪያ አካኼደ") ።
አዟዟር፡ አመላለስ/መዞር ።
አዠ፡ (አዚኅ፡ አዝኀ)፡ ወረዛ፡ ፈሰሰ።
አዠለዠለ፡ አረዘመ፣፡ ዠለዠለ።
አዠለዠለ፡ አረዘመ/አግዠለዠለ ("አዠገዠገ") ።
አዠላለጥ፡ አረጋገጥ/መዠለጥ ።
አዠመረ፡ አስወጠነ/አስፈለመ ።
አዠማመረ፡ አወጣጠነ/አፈላለመ ።
አዠማመር፡ አወጣጠን/መዠመር ።
አዠማሪ፡ ያዠመረ/የሚያዠምር ("አስ ፈላሚ") ።
አዠረጋገግ/አዠመጋገግ፡ መዠርገግ ።
አዠነጣጠፍ/አዠመጋገግ፡ መዠንጠፍ ።
አዠናነቅ/አጨማመር፡ መዠነቅ ።
አዠገዠገ፡ አረዘመ፡ ዠገዠገ።
አዠገዠገ፡ አበዛ/አረዘመ/አንጠለጠለ ።
አዣመረ፡ አዋጠነ/አፋለመ ።
አዣረገ፡ ሰበሰበ፡ ፡ ፡ ዣረገ ።
አዣራ፡ የወንዝ/የዥረት ጠጠር ("ውስጠ ክፍት መሬት ሲያርሱት የሚንቻቻ") ።
አዣራ፣የዥረት ጠጠር፡ ዣራ።
አዥራሮ፡ ውሃ የገባበት መጠጥ፡ ዠረረ።
አዥበረበረ፡ አንጸባረቀ/አጥበረበረ ("ዐይንን በዘበዘ") ።
አዥጐርጓሪ፡ ያዥጐረጐረ/የሚያዥጐረጕር ("ቀለም ቀቢ ሸላሚ") ።
አዥጐደጐደ፡ ብዙ ወለደ ።
አዥጐደጐደ፡ አወረደ፡ (ዠጐደ)።
አየ፡ (ርእየ)፡ ተመለከተ ፥ ተኰረ ፥ አስተዋለ፡ ዐይኑን፡ ልቡን፡ ባንድ፡ ነገር፡ ላይ፡ ጣለ ፥ ተከለ፡ (ዘፍ፩፡ ፩ ። ዮሐ፲፬፡ ፱)። (ተረት)፡ በኔ ሲያዩብኝ ባንቺ ይዩብሽ፡ እያየኋት የምታሥቀኝ ሚስት አገባኹ ። (ባይኑ ቂጥ እየ)፡ ገረመመ። (በጠላት ዐይን ኣየ)፡ ጠላትን ባየበት ወይም እንደ ጠላት ዐይን እየ። (የሰው እጅ አየ)፡ ከጀለ፡ በሰጡኝ አለ ። (የጐድን ኣየ)፡ ዐይኑን አጣሞ አየ።
አየ፡ ነካ። እሳት ካየው ምን ለየው እንዲሉ።
አየ፡ አገኘ። አይቶ ዐጣ እንዲሉ።
አየ፡ ፈረደ። ሰው ኣየ፡ እግዜር ኣየ እንዲሉ።
አየለ፡ በረታ፡ ዐየለ።
አየረ፡ ቀላቀለ፡ ዐየረ።
አየረ አየራት፡ የሰማዮች ሰማይ፡ መጨረሻ ላይ ።
አየር፡ (ኅዋ)፡ ክፍት ከምድር በላይ ከጠፈር በታች ባዶው መካከል። ባላገር ግን አይር ይላል።
አየር፡ ላይ ፥ ሰማይ ።
አየር፡ የረጋ ነፋስ፡ በአየር የመላ፡ የሰማይ ።
አየበት፡ ዐይኑ ጠገበበት፡ መብላት ከለከለው፡ ሳይበላ ጠገበ ።
አየበት፡ ፈረደበት ።
አየት፡ (ርእየት)፡ ማየት ። አየት አደረገ፡ አየ ።
አዩባን፡ እንገባን። አዩባን የካህናት ዐማርኛ ነው ።
አዩኝ አላዩኝ አለ፡ በሥራ ሰነፈ ።
አዪት፡ (አያዪት)፡ የባል እትን የምትመስል ።
አዪት አከለ፡ ትንሿን አባትን የምትመስል። ኦሮ እዮ፡ ሱማሌ ሆዮ የሚሉት ከዚህ ጋራ ይሰማማል። የአያት ምስጢር አዳም የሔዋን አባትና እናት መኾኑን ያሳያል ። ሲበዛ አያቶች ይላል።
አዪት፡ ዋርሳ፡ የወንድም ሚስት። አዪት የአያ አንጻር ናት። ሲበዛ ኣይቶች ይላል።
አያ፡ (አ አባት፡ ያ ሆይ)፡ በባላገር የሚነገር ቃለ አክብሮ የአቶ ተወራጅ፡
አያ፡ (ኣየየ፡ አያይ)፡ ያባት ምሳሌ፡
አያ ሌሌ ሌሌ፡ የማሲንቆ ዘፈን አዝማች ። ሌሌን አስተውል ።
አያ ወሸባ፡ የዘፈን አዝማች ። ወሸባን እይ ።
አያ(ይ)ዋ፡ ዝኒ ከማሁ፡ ዋ ከወይ መጥቶ ምእላድ ኹኗል፡ ይኸውም የጐዣም አጠራር ነው ። ኹለተኛውን ዋ ተመልከት ።
አያላውስም፡ አያዛምርም፡ አያሰናዝርም፡ አያፈናፍንም።
አያሰናዝርም፡ አያላውስም/አያወላዳም/አያዛምርም ።
አያስቀይሜ፡ ሰውን የማያስቀይም ደግ
አያሻም፡ አያስፈልግም ።
አያት፡ (ሐረር፡ አይ፡ እናት)፡ የናትና ያባት እናት፡ ሴት አያት፡ እሚታ እናት ።
አያንጓልሌ፡ ድኻ አክባሪ ደግ ሰው ።
አያየ፡ ተመለካከተ። እንዲያውም ባያያችኹ የተንኰል መዝገብ ናችኹ (ዐጤ'ቴዎ)።
አያያዘ (አስተኣኀዘ)፡ አገናኘ/አጣመረ/አቈላለፈ/አዋሰበ/አጣበቀ/አቀጣጠለ/እነ ደደ/አጣላ/አስተናነቀ ።
አያያዝ፡ አጨባበጥ ("መያዝ (ተረት)ካያያዝ ' ይቀደዳል፡ ካነጋገር፡ ይፈረዳል።") ።
አያያዥ፡ ያያያዘ/የሚያያይዝ ("አቈላላፊ አቀጣጣይ ዘረፈ ብለኸ ዘርፍን ተመልከት") ።
አያድርስ፡ አያምጣ/አያጋጥም/አያድ ርግ ።
አዬ፡ (አይ ዬ)፡ ንኡስ አገባብ ። አንክሮና ሐዘን፡ አክብሮ ወይም ቃለ አጋኖ ። ትርጓሜው፡ ወየው ፥ ሆይ ። (መክ፪ ፣ ፲፮) ። አዬ ጕድ አዬ ጕድ፡ የቦራ እሱ እንዳለው፡ የማረከው ኦሮ መልሶ ገደለው ። አዬ እቴ አበባዬ ። አይ ዬ በግእዝ ፪ ቃል ሲኾን፡ ይ ተጐርዶ በአማርኛ ኣዬ ተብሏል ።
አይ፡ (ኢይ)፡ ያሉታና የነቀፌታ ቃል፡
አይ፡ (ዘኢ)፡ የትንቢት አሉታ ቅጽል መነሻ፡ ፍችው፡ የማ ። በላን በረረን ደረቀን ቻለን እይ ። (ተረት)፡ አይበሉት እኸል ካፈር አንድ ነው ።
አይ፡ (የሚ)፡ በትንቢት መነሻ እየገባ ቅጽል ይኾናል ። አያርም ዐራሽ፡ አያጥብ ለባሽ ።
አይ፡ ያየ ፥ የሚያይ ፥ የሚያስተውል ፥ የሚመለከት ። ዓሥራት አይ እንዲሉ።
አይሁድ፡ አይሁዶች፡ ይሁዳ ።
አይሁዶች፡ ዝኒከማሁ ("አይሁድ የግ እዝ አይሁዶች ያማርኛ ነው") ።
አይኅ፡ ጥፋት ፥ ድምሳሴ፡ (ግእዝ)። ማይን እይ ።
አይለመድ)፣አይደገም ፣ኹለተኛ፡ አይደረግ ።
አይመለል፡ የጕራጌ ነገድና አገር፡ ከ፯ቱ ወንድማማቾች ፩ዱ ምን አለ ሲል ምን ባለ የሚል። ባለን እይ ።
አይመስሉ፡ መሰለ፡ ከሳ ፥ ጠቈረ፡ ጐሰቈለ ።
አይሞላለት)፡ ኣይሳካለት፡ አያልፍለት።
አይሰንፌ፡ ስንፍና የሌለበት (ሠራተኛ ትጉህ ጐበዝ) ።
አይሰንፎ፡ የቀድሞ ጭፍራ ስም (ደምሳሽ አጥፊ ማለት ነው) ።
አይሰጥ፡ የማይሰጥ ። ታለ አይሰጥ እንዲሉ።
አይስማ፡ የሰው ስም (የደስታ ተክለ ወልድ ቅድም አያት የየምሩ ውሃ ሥንቁ አባት) ።
አይረባ)፡ የማይረባ/የማይጠቅም ።
አይራ፡ የተራራ ስም፡ በይፋት ቈላ ያለ ተራራ፡ በዚያም ወገብ መሞከር ስለማይቻል ኣይራ ተባለ ይላሉ ። በወለጋም ክፍል አይራ የሚባል ቀበሌ አለ ።
አይራራ፡ በባንኮበርና በጐላ መካከል ያለ ዥረት። እናት ልጇን ስለ ወሰደባት አይራራ አለችው ይባላል።
አይሮፕላን፡ ጥያራ።
አይቀር፡ ያሉታ ትንቢት (ሞት ቢፈ ሩት አይቀር ") ።
አይቀጡ ቅጣት ቀጣ)፡ ከራስ በታች በቁም ቀበረ ።
አይቈረቍሬ፡ ፍጹም ደግ ሰው (ሰላማዊ ገራም በሥራ በነገር ማንንም የማይነካ ") ።
አይቅር፡ ያሉታ ትእዛዝ ። "የኢትዮጵያ ሕዝብ ጣሊያን በመጣ ጊዜ ባንድ አይቅር ዘመተ" ።
አይበሮ፡ ሙዳ፡ በረረ።
አይበሮ፡ የሥጋ ቍራጭ ሙዳ ።
አይበትአቍማዳ፡ ዐይበት።
አይበደም፡ ወተታም ዕንጨት፡ ወተቱ ለቋቍቻና ለችፌ መድኀኒት ይኾናል። መጽሔተ ጥበብ ፺፩ ገጽ ተመልከት ።
አይብ፡ በቁሙ ዐይብ ። አይበሉብሽ፡ የውስጥ እጅ ዠርባበላ ።
አይተንፍሱ፡ የሰው ስም፡ ጠላቶች ዝም ይበሉ፡ ጥቂትም አይናገሩ ማለት ነው ።
አይታ፡ ያየች ፥ የምታይ ።
አይቴ፡ (አይ) የንቀት ቃል ። በግእዝ ግን የት ፥ ወዴት ማለት ነው ።
አይቸግረው፡ የሰውና የበራ ስም (አይገደው አይሳነው) ።
አይቻል፡ ትልቅ ቶፋ፡ ቻለ ።
አይችሉኸ/ኣይችሉሽ፡ የወንድና...የሴት ስም ።
አይኑት፡ ትንሽ ማሰሮ፡ ዐይኑት ።
አይናገር፡ አይጋገር፡ ድዳ ፥ ዱድማ ።
አይክማ፡ ዋይክማ ፥ ኣሽክማ።
አይዋ አያዋ፡ አያ ።
አይዙር፡ በ፯፻፸፪ ዓ ም ፯ ሰዓት የነገሠ የኢትዮጵያ ንጉሥ ።
አይዞኸ (ኢይእኅዘከ)፡ ንኡስ አገባብ ("የማጽናትና የማበርታት ቃል። አይዝኸም አይነካኸም ቢነካኸም አይጐዳኸም በርታ ጽና ማለትን ያሳያል አይዞኸ ወንድሜ ተሠራው ጋሜ እንዲል ሐርበኛ የጥምቀት ለት አይዞሽ ፥ አይዟችኹ እያለ በቅርብ በቅርቦቹ ብቻ ይነገራል።") ።
አይዞኸ ባይ፡ ረዳት/ደጋፊ ("የሚያ ጽናና") ።
አይዞኸ፡ የማበርታት ቃል፡ ያዘ።
አይደለም፡ አይገባም፡ ደላ።
አይደለም/አይዶለም (ወኢይ ደሉ)፡ አይገባም/አይኾንም ("የነው አሉታ አፍራሽ ነው") (ሮሜ. ፮፡ ፲፭፡ ፯፡ ፯፡ ያዕ. ፭፡ ፲፪) ።
አይደል/አይዶል (ኢድልው፡ ኢይደሉ)፡ አይገባ/አይኾን ("አይደላ አይመች አይሰማማ አይደረግ") ።
አይደርቄ፡ አባጀኸኝ፡ ደረቀ።
አይደርቄ፡ የበጋ ጐመን አባጀኸኝ ።
አይዳምጥ፡ የላሊበላ ሚስት ያሚታ ስም ("እጇ የማይዳምጥ በልመና ዐዳሪ ማለት ነው") ።
አይገባም (ኢይትገባእ)፡ መግባት አይቻልም ።
አይገባም (ወኢይደሉ)፡ ፈጣሪን ትቶ ፍጡርን ማመን አይገባም ።
አይጠቅመኝም፡ አይረባኝም ።
አይጥ፡ የቤት አውሬ፡ ዐይጥ።
አይጨስ ነደድ፡ የንጨት ስም ጥ ቡን ከእሳት ሲጨምሩት ሳይጨስ የሚነድ ታናሽና ቀጪን ዕንጨት ።
አይጨስ፡ የማይጨስ ።
አይፈራም ጋሜ አይፈራም፡ የዘፈን ማድመቂያና ማጨብጨቢያ ከበሮ ወምቻ እስክስታ መውረጃ ።
አይፈራም ጋሜ አይፈራም)፡ የእስክስታ አዝማች ።
አይፈር ለ ፊቱ)፡ ግንባሩን ቢሉት የማይፈራ የማይመለስ ጐበዝ ።
አደለ፡ ሰጠ ፥ —ዐደለ ።
አደለመ፡ አጠለመ/አጨለመ/አጠፋ ።
አደለመጠ፡ አወፈረ ፥ —ደለመጠ ።
አደለመጠ፡ አወፈረ/አሳመረ ("ጠረ ነቀ አፈረጠመ") ።
አደለበ፡ አወፈረ/አሠባ ።
አደለበ፡ ዘገበ/አከማቸ/አቈየ/አጠ ቈረ/ኣዛገ ።
አደላ (አድለወ)፡ ፍርድን አጠመመ ("ገመደለ አንዱን በድሎ ሌላውን ጠቀመ ላንዱ ብዙ ለኹለተኛው ጥቂት ሰጠ") (ዘዳ. ፳፫፡ ፫) ።
አደላ፡ በቁሙ ፥ —ደላ ።
አደላለል፡ አሸነጋገል/መደለል ።
አደላለም፡ አጠፋፍ/መድለም ። (ተመልከት፡ ወደ መን) ።
አደላለስ፡ አቀባብ/መደለስ ።
አደላለቅ፡ አደሳሰቅ/መደለቅ ።
አደላለብ፡ አሸጋገት/መድለብ ።
አደላለዝ፡ ኦወቃቀጥ/አበያየድ/መደ ለዝ ። (ተመልከት፡ ደዘለን) ።
አደላለጥ፡ አዳዳጥ/መዳለጥ ።
አደላል፡ አመቻቸት/መድላት ።
አደላደለ፡ አስተካከለ/አመቻቸ/አሰ ማማ/አከፋፈለ ።
አደላደል፡ ኣስተካከል/መደልደል ።
አደላዳይ (ዮች)፡ ያደላደለ/የሚያ ደላድል ("አከፋፋይ አስተካካይ እግዜር እውነ ተኛ ጌታ ዳኛ") ።
አደሌ፡ ጥጥ ፥ —ዐደሌ ።
አደመ፡ አሤረ ፥ —ዐደመ ።
አደመሳሰስ፡ አፋፋቅ/መደምሰስ ። (ተመልከት፡ ሠረ ዘን እይ) ።
አደመቀ፡ አገነነ/አጐላ/አበዛ/አከበረ ።
አደመነ፡ አጠቈረ/አጨለመ ("ደመና ' አደረገ ጋረደ") ።
አደመደመ፡ ጠቀራ መሰለ ፥ —ደመደመ ።
አደመደመ፡ ጨለመ/ጠቀራ መሰለ ("በዛ ምድር አላበሰ እንዳፈር እንዳሸዋ እንደ ደመና") ።
አደመጠ (ኣድመፀ አሰማ)፡ ሰማ' አዳመጠ ።
አደመጠ፡ ሰማ ፥ —ደመጠ ።
አደማ (አድመወ)፡ ደም አደረገ ("አቈሰለ") ።
አደማመም፡ አደናነቅ { መድመም መ ደመም ።
አደማመር፡ አሰባሰብ/አጠማጠም ("መ ደመር") ።
አደማመቅ፡ አጐላል/አገናነን ("መድ መቅ") ።
አደማመን፡ አጠቋቈር/አጨላለም ("መ ደመን መዳመን") ።
አደማመጠ፡ አሰማማ ።
አደማመጥ፡ አሰማም/ማድመጥ ።
አደማመጥ፡ አደፈጣጠጥ/መዳመጥ ።
አደማም፡ አፈሳሰስ/መድማት ።
አደማደመ፡ አመሳጠረ/አሞዳሞደ ።
አደማደመ፡ አፋጸመ/አጫረሰ ("ድም ድማትን") ።
አደማደም፡ አጨራረስ/መደምደም ። (ተመልከት፡ መደመደን እይ የዚህ ግልባጭ ነው) ።
አደምድሞ፡ በዝቶ ብዙ ኹኖ ። "ጦር አደምድሞ መጣ" እንዲሉ ።
አደሰ፡ ዐዲስ አደረገ ፥ —ዐደሰ ።
አደሳሰም/አለታተም፡ መደሰም ።
አደሳሰስ፡ አዘማመም/መድራት ።
አደሳሰስ/አደባበስ፡ መዳሰስ ።
አደሳሰቅ/ኣደቃቅ፡ መደሰቅ ። (ተመልከት፡ ጐሰመ ንና ጐሸመን እይ) ።
አደሳሰት/አደላል፡ መደሰት ።
አደስ (ዕብ ሀዳስ)፡ በቁሙ፡ የሽቱ ቅጠል ስም፡ ሴቶች ከቅቤ ጋራ የሚቀቡት ከዳቦ ጋራ የሚጋግሩት ባርሰነት (የባሕር ሽነት) ። አዶስ ዶቄቱ፡ ባርሰነት ዕንጨቱ ።
አደረ፡ ሥራት ሠራ ፥ —ዐደረ ።
አደረ፡ በቁሙ ፥ —ዐደረ ።
አደረሰ፡ አመጣ/አቀረበ/አስጠጋ/አጋጠመ ።
አደረሰ፡ አሳደገ/አጐለመሰ/አበቃ/ኣሞላ ።
አደረሰ፡ አደረገ/ፈጸመ/ኣከናወነ (ኢሳ. ፶፡ ፰) ።
አደረቀ፡ መታ/ደሰቀ ።
አደረቀ፡ ነዘነዘ/ነተረከ/ጨቀቀ ።
አደረቀ፡ አጨከነ ("ልብን አጠና") ።
አደረቀ፡ ደረቅ አደረገ ("አከለለ አክ ቸለ አከረረ") ።
አደረጀ፡ አደላደለ/አጼና/አበረታ ("እንደ ከር") ።
አደረጃጀ፡ አዘገጃጀ/አዳገሰ/አቀነባበረ/አሰነዳዳ ።
አደረጃጀት፡ አዘገጃጀት/መደርጀት/ማ ደራጀት ።
አደረገ (አድረገ ገብረ ረሰየ)፡ ሠራ/አበጀ/ከወነ/ፈጸመ (ዘፀ. ፳፡ ፬፡ ዮሐ. ፲፬፡ ፲፬) ።
አደረገ፡ ለወጠ/ሌላ አስመሰለ ("ውሃን ወይን አደረገ") ።
አደረገ፡ መለሰ (መዝ. ፳፭፡ ፲፮) ።
አደረገ፡ ሠራ ፥ —ደረገ ።
አደረገ፡ ተካ - ሰጠ ("ወኪል አደረገ") ።
አደረገ፡ አስቀመጠ/አኖረ (፪ዜና. ፴፯፡ ፯) ።
አደረገ፡ ጐዳ ("ከግዜር ካልኾነ ሰው ምን ያደርጋል") ።
አደረገ፡ ፊቱን አቀና/አመራ/ዐለፈ ።
አደሩ፡ የሰው ስም፡ የ፯ ቤት አገው ባላባት ።
አደራ (ጥራ)፡ አዘባ አዘጋ ፥ —ደራ ።
አደራ፡ ሰበቀ/ነቀነቀ/ወዘወዘ ጦርን ("ይኸውም በጐንደር ይነገራል") ።
አደራ፡ ተረተረ/ዘረጋ ("ድር አደረገ አ ዘጋ (ባጪር አደራ) ዕድሜ አሳጠረ") ።
አደራ፡ አዘባ/ለመጠ ።
አደራ የተጠበቀ (ላራ)፡ ዐደረ ።
አደራሰመ፡ አገራሰመ/አደናበረ/አደ ናቀፈ ።
አደራረሰ፡ አቀራረበ/አገነኛኘ ።
አደራረስ፡ አመላል/አጨራረስ/መድ ረስ/ማድረስ ።
አደራረስ፡ የታላቅ በዓል ማሕሌት ("የክሥተት አርያም አባባል አፈጻጸም ለመ ወድስም ይነገራል") ።
አደራረቀ፡ መላልሶ አደረቀ ።
አደራረቅ፡ አከቻቸል/መድረቅ ።
አደራረበ፡ አነባበረ/አለባበሰ/አስተጣ ጠፈ ።
አደራረብ፡ አካካብ/መደረብ ።
አደራረት፡ አደባደብ/መደረት ።
አደራረዘ፡ አሰፋፋ/አጠቃቀመ ።
አደራረዝ፡ አለጓጐም/መደረዝ ።
አደራረገ፡ አሠራራ/አበጃጀ ።
አደራረገ፡ ድርጎ አስተላለፈ ("ሰጪና ተቀባይን አገናኘ አቀባበለ አሰጣጠ") ።
አደራረግ፡ አሠራር/ማድረግ (፩ነገ. ፲፮፡ ፭፡ መዝ. ፱፡ ፲፩) ።
አደራረግ፡ ድርጎ አሰጣጥ/መዳረግ ።
አደራረጥ፡ አስተሻሸት/መድረጥ ።
አደራራቢ፡ ያደራረበ/የሚያደራርብ ("አ ነባባሪ") ።
አደራራጊ፡ ፭ኛ ዐምድ ("አሳሳቢ አን ቀጽ አጋደለ አገዳደለ ፪ አካልን የሚያጋ ድል ፩ አካል አጋዳይ አገዳዳይ") ።
አደራራጊ፡ ያደራረገ/የሚያደራርግ ("አ ሠ ራሪ") ።
አደራራጊነት፡ ፡ አሠራሪነት አኳዃኝነት ።
አደራር፡ አለማመጥ/አዘረጋግ/መድ ራት/ማድራት ።
አደራደረ፡ አሰማማ/አዋዋለ ።
አደራደረ፡ አሳደረ/አኰላኰለ ።
አደራደር፡ አሰዳደር/መደርደር ።
አደራዳሪ፡ ያደራደረ/የሚያደራድር ("የድ ርዳሮ ረዳት") ።
አደራጀ፡ አዘጋጀ ፥ —ደረጀ ።
አደራጀ፡ አዘጋጀ/አቀናበረ/ደገሰ/አሰ ናዳ ("አድራጊ") ።
አደራጂ፡ ያደራጀ/የሚያደራጅ ("አዘጋጂ አቀናባሪ ደጋሽ አሰናጂ") ።
አደራጎተ፡ ዳረጎት ሰጠ ።
አደር፡ እሾኻም የቈላ ዛፍ ።
አደርር፡ የዶሮ ማር የገረንገሬ ሙጫ ።
አደርጂ፡ ያደረጀ/የሚያደረጅ ("አደላዳይ ኣጽኒ") ።
አደሸደሸ፡ አደዘደዘ፡ (ደሸደሸ) ።
አደሽዳሽ/አደዝዳዥ/አውደልዳይ፡ ።
አደቀቀ፡ ሰበረ/አነከተ/ፈጪ/ሰለቀ/አለዘበ (፪ዜና. ፴፬፡ ፬፡ ኢሳ. ፵፭፡ ፪) ።
አደቃቀስ፡ አተኛኘት/መዛል ።
አደቃቀቀ፡ ሰባበረ/አነካከተ ።
አደቃቀቅ፡ አለዛዘብ/መድቀቅ ። (ተመልከት፡ ዶቃን እይ የደቀቀ ዘር ነው) ።
አደቃቀን፡ አቀራረብ/መደቀን ። (ተመልከት፡ ደከ ነን እይ) ።
አደቃቅ፡ የኰቴ አመታት/መድቃት ።
አደቃደቅ፡ አወቃቀጥ/መደቅደቅ ።
አደቋቈስ፡ አፈጫጨት/መደቈስ ።
አደበ (ዐረ ከለከለ ወሰነ)፡ ሥርዐት ሠራ፡ ቀጣ መቀጮ ጣለ ። አገደ ዐደረ፡ ወሰነ ደነገገ ።
አደበ፡ ዝም ዕክም አለ፡ አረመመ ጨመተ ረጋ ።
አደበለ (ደበለ)፡ ዘነቀ ("ድበላን ከ ጥሩ" (ጐንደር)) ።
አደበሰ፡ ኣጠፋ ("እንዳይታይ አደረገ") ።
አደበነ፡ አከረረ/አጠበቀ (አጥብቆ ቋ ጠረ ፈተለ) ።
አደበነ፡ ከመ ቅጽበት ገደለ/አደ ረቀ ።
አደባ፡ አሸመቀ ፥ —ደባ ።
አደባበለ፡ አደራረበ/አገነኛኘ/አከመ ቻቸ/አጠጋጋ ሰውን ።
አደባበስ፡ አደሳሰስ/መዳበስ ።
አደባበስ፡ ኣጠፋፍ/መድበስ ።
አደባበር፡ አገዳደም/መደበር ።
አደባበቀ፡ አሰዋወረ ።
አደባበቅ፡ አሰዋወር/መደበቅ ።
አደባበን፡ ኣከራረር/መሞት/መድበን ።
አደባባይ፡ መሰብሰቢያ ፥ —ደበለ ።
አደባባይ አዋለ፡ አሳዘነ/አስለቀሰ ።
አደባባይ፡ የሰው መሰብሰቢያ ማቻ ጉባይ ጉባኤ ሸንጎ ዐውድ ወለል (የነገር የሙግት የችሎት ሰፊ ስፍራ) (ኢሳ. ፶፱፡ ፲፬፡ ዘካ. ፰፡ ፭) ።
አደባብ፡ አሸማመቅ/ማድባት ።
አደባየ፡ ረገጠ ፥ —ደበየ ።
አደባየ፡ በሙግት አሸነፈ/ረታ ።
አደባየ፡ ካፈር ከድቤ ላይ ጣለ/ረገጠ/በርግጫ ደበደበ/አረባየ ኣኼደ/አስፈ ገመ ።
አደባይ፡ ያደባየ/የሚያደባይ (ረጋጭ) ። "የበላይ አደባይ" እንዲሉ ።
አደባደብ፡ ኣመታት/መደብደብ ።
አደብ፡ ሥርዐት ቅጣት መቀጮ ። አደብ ጣለ ፥ አደብ ከፈለ እንዲሉ ።
አደብ፡ ዝምታ አርምሞ ። አደብ ግዛ እንዲሉ ።
አደነ፡ አውሬን ገደለ ፥ —ዐደነ ።
አደነሳሰር፡ አቸሳሰር/መደንሰር ።
አደነቀ፡ ግሩም ዕጹብ ድንቅ አለ ("አነከረ") (ዕን. ፩፡ ፭፡ ማቴ. ፰፡ ፳፯) ።
አደነቃቀር፡ አወነካከር/መደንቀር ።
አደነቃቀፈ፡ አወለካከፈ/አሰነካከለ ።
አደነቃቀፍ፡ አወለካከፍ/ማደናቀፍ ።
አደነቈረ፡ አሰነፈ/አጀለ ("አላዋቂ እ") ።
አደነቈረ፡ አወለነ/ዘጋ/ደፈነ ።
አደነቋቈል፡ አነቋቈር/መደንቈል ።
አደነቋቈር፡ አወላለን/መደንቈር/መ ጀል ።
አደነበ፡ አደነዘ ("መናገር ከለከለ") ።
አደነበሸ፡ ዐመገ/አደለበ/አሻገተ ።
አደነባበረ፡ አለካካ/አወሳሰነ ።
አደነባበረ፡ አጨነባበረ/አወነባበደ ።
አደነባበር፡ አዘላለል/መደንበር ።
አደነባበቅ፡ አጠላለቅ/አቀዳድ ("መደ ንበቅ ተመልከት ደነፈቀን") ።
አደነባበዝ፡ አጨላለም/መደንበዝ ። (ተመልከት፡ ጠ ነበዘን እይ) ።
አደነባብ፡ አወሳሰን/መደንባት ።
አደነነ (አድነነ)፡ እናቸ/አበዛ ("ደን አደረገ አዘነበለ") ።
አደነዘ/አደና፡ አጠረሰ ።
አደነዘዘ፡ አፈዘዘ/አደበዘዘ/አበደነ ("በ ማሽተት መርፌ በመውጋት") ።
አደነዛዘዝ፡ አፈዛዘዝ/መደንዘዝ ። (ተመልከት፡ ደነገ ዘን እይ) ።
አደነደነ፡ አወፈረ/አገዘፈ/አሰፋ/አጨ ከነ (ዘዳ. ፴፪፡ ፴፡ ኤር. ፲፯፡ ፳፫፡ ዮሐ. ፲፪፡ ፵) ።
አደነገተ፡ ድንገት አደረገ/ሠራ ።
አደነገዘ፡ አፈዘዘ/አጨለመ ።
አደነገየ፡ ዝኒ ከማሁ ።
አደነጋ (አእበነ)፡ ደንጊያ አደረገ/አደረቀ/አፈዘዘ ።
አደነጋገል፡ አጠባበቅ/መደንገል ።
አደነጋገር፡ አሳሳት/ማደናገር ።
አደነጋገዝ፡ ኣፈዛዘዝ/መደንገዝ ።
አደነጋገገ፡ አወሳሰነ ።
አደነጋገግ፡ አወሳሰን/መደንገግ ።
አደነጋገጥ፡ ኣፈራር/መደንገጥ ።
አደነጓጐር፡ አደዳደቅ/መደንጐር ።
አደነፋፈቅ፡ አለቃቀስ/መደንፈቅ ።
አደነፋፋ፡ አፎካከረ ።
አደነፋፍ፡ አፎካከር/መደንፋት ።
አደና፡ አደነዘ/ቸረቸመ ።
አደናቀፈ፡ አሰናከለ ፥ —ደነቀፈ ።
አደናቀፈ፡ ኣወላከፈ/አስናከለ ።
አደናቃፊ፡ ያደናቀፈ/የሚያደናቅፍ ("አ ሰናካይ") ።
አደናቈለ፡ ኣዘናቈለ/አናቈረ ።
አደናቈረ፡ አጯጯኸ/አለፋለፈ ።
አደናበረ፡ አላካ/ኣዋሰነ/አዳካ ።
አደናበረ፡ ኣሳሳተ/አጨናበረ/አወና በደ ።
አደናባሪ፡ ያደናበረ/የሚያደናብር ("አ ሳሳች ኣናባሪ አወናባጅ") ።
አደናነቅ፡ አገራረም/መድነቅ ።
አደናነዝ፡ አጠራረስ/መደነዝ ።
አደናከረ (አደናገረ)፡ አወላገደ/አጣ መመ/አወላመመ/አደናቀፈ ።
አደናዥ፡ ያደነዘ/የሚያደንዝ ።
አደናደን፡ አወፋፈር/መደንደን ።
አደናገረ/አደነጋገረ፡ አሳሳተ ።
አደናገገ፡ አዋሰነ ።
አደናገጠ፡ ኣፋራ ።
አደናጋሪ፡ ያደናገረ/የሚያደናግር ("አሳ") ።
አደናፋ፡ ኣሯከረ ።
አደን፡ አውሬን መግደል ዐደን ።
አደን፡ አገር ፥ —ዓደን ።
አደንቋሪ፡ ያደነቈረ/የሚያደነቍር ("ጯኺ") ።
አደንካሬ (ዎች)፡ ታላቅ እንቅርብጭ የድንች ዐይነት ("ሳይቀቀልና ሳይጠበስ ጥሬ ውን የሚበላ የምድር ፍሬ እረኞች ቈፍረው የሚያገኙት ሐረጉ በበጋ ደርቆ በክረምት ይበቅላል") ።
አደንካሬ፡ እንቅርብጭ ፥ —ደነከረ ።
አደንዛዥ፡ ያደነዘዘ/የሚያደነዝዝ ("አፍ ዛዥ ሐኪም ባለመዳኒት") ።
አደንጋዥ፡ ያደነገዘ/የሚያደነግዝ ።
አደንግዝ፡ ዝኒ ከማሁ ("መርዝ ያለው ዓሣ") ። (ተመልከት፡ ፈዘዘ ብለኸ አፈዘዘን) ።
አደንጓሬ፡ ያበባ እኽል ፥ —ደነጐረ ።
አደንጓሬ/አዳጕራ፡ መጠኑ ካተር ጥቂት የሚያንስ ባለሐረግ ያበባ እኸል ("ባ ማራ አገር የሚበቅል") (ሕዝ. ፬፡ ፱) ።
አደኛኘት፡ አፈራረድ/መዳኘት ።
አደከመ (አድከመ)፡ አለፋ/አጣረ/ኣታከተ/አለተተ/አሰለቸ ።
አደካከም፡ አኰታኰት/መዳከም ።
አደካከም፡ አዛዛል/መድከም ።
አደካከር፡ አገታተር/መደከር ።
አደካከን፡ አደራደር/መደከን ።
አደካክ፡ ኣወሳሰን/መድካት ።
አደኸየ፡ አሳጣ/አስቸገረ/አሳነሰ ("ድኻ አደረገ ባዶ አስቀረ") ።
አደኸዪ፡ ያደኸየ/የሚያደኸይ (ስን ፍና ጦርነት) ።
አደዋወል፡ አመታት/መደወል ።
አደዋወር፡ አጠናጠን/መደወር/ማዳ ወር ።
አደዘደዘ፡ አውደለደለ ፥ —ደዘደዘ ።
አደዘደዘ፡ አደሸደሸ/አውደለደለ (ሥራ ፈታ) ።
አደዛዘል፡ ኣጠዛዘል/መደዘል ።
አደዛደዝ፡ ኣወቃቀጥ/መደዝደዝ ።
አደዝዳዥ፡ ያደዘደዘ/የሚያደዘድዝ (አ ደሽዳሽ ኣውደልዳይ ሥራ ፊት) ።
አደይ፡ በቁሙ ፥ —ዐደየ ።
አደዳ ነፋስ፡ ዐደዳ ።
አደገ (አዲግ አደገ)፡ ረዘመ በለጠ ላቀ ተመነደገ ወጣ፡ ቁመትና ጐን ጨመረ ። (ዘፀ ፪ ፥ ፲ ። ሉቃ ፪ ፥ ፵) ።
አደገ፡ ሹመት ሽልማት ማዕርግ አገኘ ።
አደገ፡ በዛ ተረፈ ።
አደገ፡ ገዛ መለሰ ፥ —ዐደገ ።
አደገ፡ ጐለመሰ (ጐረመሰ)፡ ዐየለ፡ በረታ፡ ጠና፡ ጠነከረ፡ ጐለበተ፡ ወንድ ወጣው፡ ዠብዱ ሠራ።
አደገላለል፡ አጠቀላለል/መደግለል ።
አደገኛ (ኞች)፡ መከረኛ ባለመከራ፡ ወይም አደጋ የሚያመጣ አደጋ የማይርቀው የማይለየው ሰው ቀበሌ ።
አደገደገ (አደግደገ)፡ አደከመ/አ ከሳ/ኣኰሰሰ/አጠቈረ ።
አደገደገ፡ ታጠቀ ፡ ደገደገ ።
አደገደገ፡ አዞረ/ጠመጠመ/ቦደነ/ወ ደነ/አሰረ/ታጠቀ/አሸነፈጠ/ተላበሰ/አ ሸረጠ ።
አደጋ፡ ታላቅ መከራ ሳይታሰብ የመጣ፡ ጦር ናዳ ጐርፍ የሰማይ ቍጣ ። አደጋ ጣለ፡ አደጋ ወደቀበት እንዲሉ ። አደጋ ድንገት መደረጉን ያሳያል ።
አደጋ ጣይ (ዮች)፡ ጦረኛ ኀይለኛ ። (፪ነገ ፭ ፥ ፪) ።
አደጋደገ፡ አጠማጠመ/አስተጣጠቀ ።
አደጋደገ፡ አጠቃ/ገፋ/አበሳቈለ/አጣ ።
አደጋደግ፡ አለካክ/መደግደግ ።
አደጋገመ፡ አመላለሰ/አጨማመረ ።
አደጋገም፡ አጸላለይ/መድገም ።
አደጋገስ፡ አዘገጃጀት/መደገስ ።
አደጋገን፡ አጐባበጥ/ማጕበጥ/መደገን ።
አደጋገፈ፡ አያያዘ/አጠጋጋ/አገጣጠመ/አቀራረበ ።
አደጋገፍ፡ አስተቃቀብ/መደገፍ ።
አደጋጋፊ፡ ያደጋገፈ/የሚያደጋግፍ ።
አደግ፡ ያደገ የላቀ የበለጠ ከፍ ያለ የገነነ ። አባት አደግ ፥ ዐብሮ አደግ እንዲሉ ።
አደግሽነት፡ ዐብሮ አደግነት ።
አደግዳጊ፡ ያደገደገ/የሚያደገድግ (ታ ጣቂ ዐዳይ አሳላፊ ተጋች) ።
አደጎች፡ ያደጉ ። ደኸየ ብለኸ ድኻን እይ ።
አደጓጐም፡ አስተጋገዝ/መደጐም ።
አደጓጐስ፡ አወፋፈር/መዳጐስ ።
አደጓጐስ፡ ኣሸላለም/መደጐስ ።
`አደፈ (ረስሐ)፡ ጐደፈ ተጨማለቀ ቈሸሸ ወሰከ ረከሰ፡ ተበከለ ተኵለፈለፈ፡ ነውረኛ ኾነ ።
አደፈ፡ ጠረገ ፥ —ዐደፈ ።
አደፈረሰ፡ በጠበጠ/አጐሸ/አሳደፈ/አጐደፈ/አቀላ/አበላሸ (ሕዝ. ፴፪፡ ፪) ።
አደፈራረስ፡ አስተታተል/መደፍረስ ።
አደፈነ፡ አቀበረ/ለገመ ።
አደፈጠ (ደፈጠ)፡ አጐነበሰ/ዐባ ሸሸገ/አደባ/አዴበ ።
አደፈጠ፡ ተሸሸገ ፥ —ደፈጠ ።
አደፈጣጠጥ፡ አረጋገጥ/መደፍጠጥ ።
አደፋም፡ አደፈኛ፡ አደፍ ያለው ባለ አደፍ ።
አደፋደፍ፡ አለጣጠፍ/መደፍደፍ ።
አደፋጩ፡ አራሰ/አጨቀየ/አማ ለቀ ። "ክረምቱ ሳያደፋጭ ቶሎ ና" ።
አደፋጯ፡ አልቀየ፡ ደፈጨ ።
አደፋፈረ፡ አጨካከነ/አሰዳደበ/አነጣ ጠበ ።
አደፋፈር፡ አጨካከን/አነጣጠብ/መ ድፈር ። (ተመልከት፡ በገረን እይ) ።
አደፋፈቅ፡ አነካከር/መድፈቅ ።
አደፋፈን፡ አቀባበር/መድፈን ።
አደፋፈጠ፡ አሸማመቀ ።
አደፍ፡ የሴቶች ግዳጅ (ትክቶ)፡ አበባ ። አደፋ መጥቷል ። ረገመ ብለኽ መርገምን እይ ።
አደፍ፡ ያበባ እኸል፡ ቀሊል ተርታ መናኛ ንፋሽ ገለባ ዐሠር ያለው ድበላ፡ ዐተር ባቄላ ሽንብራ ምስር ጓያ አደንጓሬ ። ጥሩ ታደፍ እንዲሉ ። አገዳም ድበላ ይባላል ።
አደፍራሽ (ሾች)፡ ያደፈረሰ/የሚያደ ፈርስ ("በጥባጭ") ።
አደፍርስ/አደፍርሰው፡ የሰው ስም ("በጥብጥ ኣውክ ኣሸብር ኣሸብረው ማለት ነው") ።
አዱኛ እዱኛ (አዶናዊ)፡ ጌትነት ክብር ልዕልና ማግኘት፡ ሀብት ብልጥግና ከ ጌታ ከፈጣሪ የሚገኝ ።
አዲስ፡ በቁሙ ፥ —ዐደሰ ።
አዳ፡ ካዲስ አባ በስተደቡብ ያለ ቀ በሌ ። በጋልኛ አደአ ይባላል ።
አዳለለ፡ አሞኛኘ/አሸናገለ ።
አዳለቀ፡ አዳሰቀ/አጓሰመ ።
አዳለጠ፡ አዳጠ/አለጠ (ርጥብ መሬት) ።
አዳላ፡ አመቻቸ ("ፍርድን ወደ ወደ ደው አጣመመ እውነትን ኣጓደለ ዶል") ።
አዳላጭ፡ ያዳለጠ/የሚያዳልጥ (ልጅ) ።
አዳል (ሎች)፡ የነገድ ስም፡ በዐሰብና በዐውሳ በትግሬ በረሓ የሚኖር ሕዝብ ። በአዛል ዘይቤ ቢተረጕሙት ግን ብርቱ ማለ ትን ያሳያል ። ደንከሊን እይ ።
አዳልኛ፡ የአዳል ቋንቋ፡ ወይም አፍ ።
አዳመረ፡ አሰባሰበ/አቋቋመ ("ድምር አጻጻፈ ጥምጥም አጠማጠመ") ።
አዳመቀ፡ አጋነነ/አባዛ/አካበረ ።
አዳመጠ (አደራራጊ)፡ አሳማ ("ልማዱ ግን ' አደመጠ ሰማ ' ነው") (ኢዮ. ፳፫፡ ፮) ። "እኸል አላምጦ ነገር አዳምጦ የነገር ወጡ ማዳ መጡ" እንዲሉ ።
አዳመጠ (አደራራጊ)፡ አደፋጠጠ/አላ ሰቀ ("ጥጥ ፍሬን አዋጣ") ።
አዳሙ፡ የሰው ስም ።
አዳማቂ (ቆች)፡ ያዳመቀ ' የሚያዳ ምቅ ("አጋናኝ") ።
አዳማቂ፡ ትርጓሜ የሌለው ተጨማሪ ' ፊደል ("ዘ ከመ ለ የግእዝ አገባብ አስተውል") ።
አዳማጭ፡ ያዳመጠ/የሚያዳምጥ ("አድ ማጭ ሰሚ") ።
አዳሜ (አዳማዊ)፡ የአዳም ዘር ሰው፡ የአዳም ወገን ።
አዳም (ትግ ሐባ)፡ ሰው ።
አዳም (አዲም አደመ ቀላ ቀይ ኾነ ። አድሞ አደመ አማረ)፡ በቁሙ፡ መዠመሪያ ሰው፡ የሰው ኹሉ አባት፡ ቀይ ውብ መልከ መልካም የሚያምር ማለት ነው ። አዳምና ሔዋን እንዲሉ ።
አዳም ዐሙስ፡ ያዳም ዐሙስ፡ ከትን ሣኤ ዐምስተኛ ቀን አምላከ አዳም ተብሎ እስመ ለዓለም የሚመራበት ።
አዳሰመ፡ አጋጨ/አላተመ ።
አዳረሰ (አደረሰ)፡ አቃረበ ("ለኹሉ ሰጠ ኣካፈለ") ።
አዳረሰ፡ አዋገደ/አገባደደ ።
አዳረቀ፡ አነዛነዘ/አጨቃጨቀ ።
አዳረቀ፡ ደረቅ አዳረገ ።
አዳረበ፡ ኣካካበ/አጫመረ ።
አዳረተ፡ ድሪቶ ኣሳፋ/አጣቀመ/አደ ባደበ ።
አዳረዘ፡ አሳፋ/አጣቀመ/አላጐመ ።
አዳረገ፡ ሥራ አሣራ - አባጀ ።
አዳሪ፡ ያዳራ/የሚያዳራ ድርን ።
አዳራ፡ አቃጠበ/አላፋ ።
አዳራ፡ አተራተረ/አዘራጋ ዝሓን ።
አዳራ፡ አዛባ/አላመጠ ።
አዳራሽ (ሾች)፡ ያዳረሰ/የሚያዳርስ ("ዐዳይ አሳላፊ ኣዋጋጅ") ።
አዳራሽ ተገኘ፡ ተቀመጠ/ግብር አበላ/ጠጅ አጠጣ/ጮማ አስቈረጠ/ለገሰ/ቸረ ።
አዳራሽ፡ ታላቅ ቤት ብዙ ሰው የሚያገባ/የሚከት ("ይኸውም ክብ ወይም ሞላላ (ሰቀልኛ) ነው") (ሉቃ. ፳፪፡ ፶፭) ።
አዳራሽ፡ ትልቅ ቤት ፥ —ደረሰ ።
አዳራቂ፡ ያዳረቀ/የሚያዳርቅ ("አነዛ ናዥ") ።
አዳሸቀ፡ ረገጠ/አዳከረ ።
አዳቀለ፡ አራከበ/አገናኘ ።
አዳቀለ፡ አጋባ/አቀላቀለ/አዋለደ/አ ዛመደ ።
አዳቀቀ፡ አሳበረ/አሳለቀ/አዳከመ ("ዐ ቅመ ቢስ አደረገ") ።
አዳቈሰ/አደቋቈሰ፡ አፋጩ/አዳቀቀ/ኣላላመ/ኣላዘበ/ኣለዛዘበ ።
አዳበለ (ደበለ)፡ ከቤቱ ደባል እ ስጠጋ አስቀመጠ ።
አዳበለ፡ አገናኘ/አከማቸ ።
አዳበረ፡ አሳደገ/አወፈረ/አሰፋ/ጨ መረ/አሳመረ ። "ሹመት ያዳብር" እንዲሉ ።
አዳበቀ፡ አሳወረ/አሻሸገ ።
አዳባሪ፡ ያዳበረ/የሚያዳብር (አሳማሪ) ።
አዳባይ፡ አከማቺ ፥ —ደበለ ።
አዳባይ፡ ዥረት (የብዙ ዠማ መገ ናኛ ታላቅ ወንዝ በወግዳና በተጕለት ግፍ ያለ ፪ኛ ስሙ ሰመጎ ዥረት ይባላል) ። "በዚያም የሚገናኙ ዋና ዋኖቹ ፵ ሱላይ (በሬሳ) ጕናጕኒት አይሠራውም (ጋዱ) ሞፈር ውሃ ሌ ሎችም ብዙዎች። ከተጋጠመም በኋላ በመርሐ ቤቴ ዠማ ይሉታል።"
አዳባይ፡ ያዳበለ/የሚያዳብል (የሚያገ ናኝ አከማቺ) ።
አዳነ (አድኀነ)፡ ፈወሰ/አሻረ/አስ ጣለ/አተረፈ ።
አዳነ/አዳነች፡ የወንድና የሴት ስም ።
አዳነቀ (አደነቀ)፡ ድንቅ ኣባባለ ("አጋረመ አጋነነ") ።
አዳነቁ፡ የወንድና የሴት ስም ።
አዳናቂ (አድናቂ)፡ ያዳነቀ/የሚያዳ ንቅ ("አጋናኝ") ።
አዳኘ፡ ለዳኛ ነገረ ("አቤት አለ ዳኛ አወጣ አማጠነ ከሰሰ አሳጣ ረበ") ።
አዳኝ (አድኃኒ)፡ ያዳነ/የሚያድን ("ፈዋሽ እግዜር ሐኪም ባለመድኀኒት") (፪ሳሙ. ፳፪፡ ፫) ።
አዳከመ፡ አሰላቸ/አሳነፈ (ሉቃ. ፲፰፡ ፭) ።
አዳከረ፡ ለወሰ ረገጠ ፥ —ዳከረ ።
አዳከረ፡ ለወሰ/አላቈጠ/አዳወለ/ረ ገጠ/ወቀጠ ("ከጭቃ ጋራ ኣዳሸቀ") ። (ተመልከት፡ ዳወለንና ፈተፈተን እይ) ።
አዳከነ፡ አሳደረ/አደራደረ ።
አዳካ፡ አላካ/አዋሰነ/አካለለ ።
አዳካሪ፡ ያዳከረ/የሚያዳክር (ረገጭ) ።
አዳወለ (ላዳ)፡ አዳከረ ፥ —ዳወለ ።
አዳወለ (ጥዳ)፡ አማታ ደወለ ።
አዳዋሪ፡ ደዋሪ ።
አዳዳሰ፡ አፋጩ/አዳቀቀ ።
አዳዳስ፡ አፈጫጨት/መዳስ ።
አዳዳረ፡ አሰራረገ ።
አዳዳር፡ አሰራረግ/መዳር ።
አዳዳነ፡ ኣፈዋወሰ ።
አዳዳጥ፡ አረጋገጥ/መዳጥ ።
አዳገመ፡ ፪ኛ እሠራ ("አሣራ ይህ ሥራ ያዳግመኛል") ።
አዳገመ፡ አናበበ/አጸለየ ።
አዳገሰ፡ አቋላ/አፋጩ/አዋቀጠ/አጣ መቀ/አዳለኸ ።
አዳገተ፡ አቃተ፡ ዳገተ ።
አዳገተ፡ ዳገት አደረገ ("አስቸገረ ተሳነ አቃተ አላልቅ አለ") ።
አዳገነ፡ አጓበጠ ።
አዳገፈ፡ አቃረበ/አገናኘ ("ካንድ በ ኩል ያዘ መደገፍን ረዳ") ።
አዳጊ፡ የሚያድግ የሚረዝም የሚመነደግ ።
አዳጋ፡ ከፍ ያለ የረዘሙ ስፍራ፡ ቍልልታ ። አዳጋ ቦታ እንዲሉ ።
አዳጋሚ፡ ያዳገመ/የሚያዳግም (አናባቢ) ።
አዳጋች፡ ያዳገተ/የሚያዳግት (አስቸጋሪ) ።
አዳጐሰ፡ አወፈረ ("ወፍራም አደረገ") ።
አዳጐሰ፡ ኣላበሰ/አጊያጊያጠ/አሻለመ ።
አዳጠ (አድኀፀ)፡ አዳለጠ/ድጥ አ ደረገ ("ዐነቀፈ አሰናከለ ሰረጀ ዘረጠጠ አን ሻተተ አንሸራተተ ምጣድ አዳጠኝ አክን ባሎ ዳጠኝ” እንዲሉ ልጆች) ።
አዳጠ፡ አሳተ ("እከሌን አፉ ያድጠዋል") ።
አዳጪ፡ ያዳጠ/የሚያድጥ (አዳላጭ) ።
አዳፈረ፡ አጫከነ/ኣሳደበ/አናጠበ ("ኣለአኩያ አናገረ") ።
አዳፈቀ፡ አዛፈቀ/አናከረ/አሳጠመ ።
አዳፈቀ፡ አፋጩ/አላላመ ።
አዳፈነ (አድራጊ)፡ ደፈነ/ቀበረ ("ዐመ ድና ዐፈር ነ ጨመረ") ።
አዳፈነ (ኣደራራጊ)፡ አቃበረ/አማ ረገ/አማላ ።
አዳፈነ፡ በጥይት መታ/ገደለ ።
አዳፈነ፡ አስቀረ/አስታጐለ ።
አዳፈጠ፡ አስተሻሸ/አፈላፈለ ።
አዳፈጠ፡ አሻመቀ ።
አዳፈጠ፡ ኣሳካ/አጋጠመ ።
አዳፊ፡ የሚያድፍ፡ እድፍ የሚቀበል ።
አዳፊ፡ ያዳፋ/የሚያዳፋ ("አጣዳፊ") ።
አዳፋ (አትከለ)፡ አጣደፈ፥አቻኰለ (ዓሞ. ፭፡ ፲፪) ።
አዳፋ፡ አፋሰሰ/አከናበለ ።
አዳፋ፡ እድፋም ልብስ፡ ወይም ሌላ ነገር ።
አዳፋሪ፡ ያዳፈረ/የሚያዳፍር ።
አዳፋቂ፡ ያዳፈቀ/የሚያዳፍቅ ።
አዳፋኝ፡ የእጕል ዕዳ አሞሌ ብር ።
አዳፋኝ፡ ያዳፈነ/የሚያዳፍን ("ያስታጐለ የሚያስታኍል አስታጓይ") ።
አዳፍሬ፡ ብርቱ መጠጥ ።
አዳፍሬ፡ የሰው ስም ("አዳፍር ማለት ነው") ።
አዳፍኔ፡ የከባድ መድፍ ስም ("በተተ ኰሰ ጊዜ ጥይቱ ጠላትን እመሬት የሚደ ፍን ስለ ኾነ አዳፍኔ ተባለ ትርጓሜው ቅበር ኣቃብር ማለት ነው") ።
አዴበ፡ አደባ (ላሸ) ኣሸመቀ ። "ልማዱ ግን ተገብሮ ነው" ።
አዴበ፡ ደፈጠ ዴበ ።
አድሊ (አድላዊ)፡ ያደላ/የሚያደላ ("ፍርደ ገምድል ጕቦኛ") ።
አድላሚ፡ ያደለመ/የሚያደልም ("አጥፊ") ።
አድላቢ (ዎች)፡ ያደለበ/የሚያደልብ ("አከማቺ ኣወፍሪ") ።
አድመሰመሰ፡ አትመሰመሰ አልከሰከሰ ።
አድመነመነ፡ አጠቋቈረ/አጨላለመ ።
አድሚ፡ ያደማ/የሚያደማ ("አቍሳይ") ።
አድማሰ ወርቅ፡ የሴት ስም፡ አጥናፈ ወርቅ እንደ ማለት ነው ።
አድማሱ አድማሴ፡ የሰው ስም፡ የርሱ የኔ አድማስ ማለት ነው ።
አድማስ ሰገድ፡ ያጤ ሚናስ ስመ መንግሥት ።
አድማስ፡ ርሳስ ወይም ብረት የግንብ ጠርዝልክ፡ የማእዘኑ ማስተካከያ ቱንቢ ።
አድማስ፡ የማእዘን ስም፡ የምድር ዳር ድንበር ። ከኣድማስ እስከ ኣድማስ እንዲሉ ።
አድማቂ (ቆች)፡ ያደመቀ ፥ የሚያደ ምቅ ("አሳማሪ") ።
አድማጭ፡ ያደመጠ/የሚያደምጥ/የሚ ሰማ ("ሰሚ ቃል ተቀባይ") (ኢዮ. ፴፩፡ ፴፭) ።
አድማጮች፡ የሚያደምጡ ("የጉባኤ ' ሰዎች") (መዝ. ፻፴፡ ፪) ።
አድምቅ፡ ዝኒ ከማሁ ። (ተመልከት፡ ወንዝን) ።
አድረመረመ፡ አጕረመረመ ፥ —(ደረመ) ።
አድረቀረቀ፡ እንደ መብረቅ አጮኸ/አስጮኸ ።
አድሩስ፡ እስላሞች ቡና ሲጠጡ ምኞታችንን አድርስ እያሉ የሚያጨሱት ዕጣን ።
አድሪ፡ ያደራ/የሚያደራ ("አዝጊ") ።
አድራሻ፡ ሰው የሚገኝበት ቦታ ወይም መሥሪያ ቤት ስምና መልክት ጕዳይ የያዘ ወረቀት የሚደርስበት ።
አድራሽ፡ ያደረሰ/የሚያደርስ/የሚፈ ጽም ("አብቂ አቅራቢ") ።
አድራቂ፡ ያደረቀ/የሚያደርቅ ።
አድራጊ፡ የገቢር ሳቢ አንቀጽ ("ገደለ አረዘመ ሠሪ አካል ገዳይ ገደለ ፩ኛ ዐ ምድ አረዘመ ፪ኛ ' ዐምድ ነው") ።
አድራጊ፡ ያደረገ/የሚያደርግ/የሚያ በጅ ("ሠራተኛ") (ዕብ. ፲፩፡ ፲፡ ፪ጢሞ. ፪፡ ፲፭) ።
አድራጎት፡ ማድረግ (ዘፀ. ፴፡ ፴፭) ።
አድርሰናል፡ ሰጥተናል/ተዘክረናል/ጨርሰናል ።
አድርቅ፡ ዝኒ ከማሁ ("ነዝናዛ ፊት ፵ቃ ነገረኛ ልብ አድርቅ እንባ አድርቅ ቅቤ አድርቅ” እንዲሉ) ። (ተመልከት፡ ልብን ነባን ቀባን እይ) ።
አድርጎ፡ ሠርቶ/አበጅቶ/ለውጦ ።
አድርጎ፡ አቅንቶ/አምርቶ/ዐልፎ ።
አድቀሰቀሰ፡ ፥ —አዛለ ፥ —ደቀሰ ።
አድቀሰቀሰ፡ አስተኛ/አዛለ/አደከመ/ተጫጫነ ("የበሽታ የንቅልፍ") ።
አድቃቂ (ቆች)፡ ያደቀቀ/የሚያደቅ ("ፈጪ ሰላቂ") ።
አድበለበለ፡ አሳበጠ ፥ —ደበለ ።
አድበለበለ፡ አርበተበተ ።
አድበለበለ፡ ከበበ ።
አድበለበለ/አድቦለቦለ፡ አንከበከበ/ኣከበበ (የጭቃ የኮሶ የፍትፍት አሳበጠ ነፋ የገላ) ። "አድበለበለ ደበለን አድቦለቦለ ደቦልን ያ ያል ።"
አድበልባይ (ዮች)፡ ያድበለበለ የ ሚያድበለብል (አንከብካቢ ሥሥት የሚባል ዕንዝዝ መሳይ አሳባጭ በሽታ) ።
አድበሰበሰ፡ የሰውን ነገር አደናገረ/አሳሳተ/አጭበረበረ/አበላሸ ።
አድበስባሽ፡ ያድበሰበሰ/የሚያድበሰብስ (አደናጋሪ አሳሳች) ።
አድበከሰከ፡ አወፈረ ፥ —(ደበከ) ።
አድቢ፡ ያደባ/የሚያደባ (አድፋጭ አሸማቂ (ሸማቂ)) ።
አድባር ሰገድ፡ ያጤ ዳዊት ፫ኛ ስመ መንግሥት ።
አድባር፡ በሴት አንቀጽ የምትጠራ የማትታይ ያገር ውቃቢ ። "አድባር ትቀበልኸ" እንዲሉ ። (ተመልከት፡ ዋለ አዋለ ብለኸ አዋይን እይ) ።
አድባር፡ ተራሮች ። "አድባር ፥ አውጋር" እንዲሉ ።
አድባር፡ ተራሮች ዛፎች ፥ —ደበረ ።
አድባር አስደንግጥ፡ አድባርን የሚ ያስደነግጥ (ጯኺ) ።
አድባር አውጋር፡ ተራሮች ኰረብ ቶች ።
አድባር፡ የበቁ ሰዎች ግሑሣን በተ ራሮች ላይ የሚኖሩ ።
አድባር፡ ግንቦት ፩ ቀን በተራራ ላይ ከጥንት ሲያያዝ የመጣ ኣምልኮ ባዕድ የሚደረግበት ጭዳ የሚባልበት ብዙ ዛፍ የማይቈረጥ ደን ። "ካህናት ግን ዐጸድ ይሉ ታል" (፪ነገ. ፳፫፡ ፲) ።
አድባሮች (አድባራት)፡ የብዙ ብዙ ተራሮች (የአምልኮ ዛፎች) ።
አድነው (አድኅኖ)፡ የሰው ስም ("ኣምላክ ይህን ልጅ አትግደለው ከሞት ኣትር ፈው አሳድገው ማለት ነው") ።
አድናቂ (ዎች)፡ ያደነቀ/የሚያደንቅ ("አንካሪ") ።
አድናቆት፡ አንክሮ ።
አድካሚ፡ ያደከመ/የሚያደክም (አታ ካች አልፊ አስናፊ) ።
አድዋ፡ ያገር ስም ፥ —ዐድዋ ።
አድጎ፡ ከፍ ብሎ ።
አድጐለጐለ፡ አወፈረ ("አንቀሳቀሰ አላወሰ") ።
አድጎልኝ፡ የሰው ስም ።
አድፈነፈነ፡ አጭፈነፈነ ("ማየት ከለከለ") ።
አድፈጠፈጠ፡ አፍረጠረጠ ("መግል") ።
አድፈጥፋጭ፡ ያድፈጠፈጠ/የሚያድፈ ጠፍጥ ("አፍረጥራጭ") ።
አድፋጭ (ደፋጭ)፡ ያደፈጠ/የሚ ያደፍጥ ("ሸሻጊ ተሸሻጊ አድቢ ድመት ነብር ቀበሮ የመሰለው ኹሉ") ።
አድፋፋ፡ ቶሎ ቶሎ ጨረሰ/ጨራረሰ ።
አዶ፡ በረሓ፡ ዐዶ ።
አዶለዶመ፡ አደነዘ/አጐለደፈ/ደመ ።
አዶማይ (ኤዶማዊ)፡ የዔሳው ዘር የኤዶምያስ ሰው፡ ጨካኝ ክፉ ጠማማ ።
አዶማዮች (ኤዶማውያን)፡ የዔሳው ልጆች፡ ጨካኞች ክፉዎች ። (መዝ ፻፴፯ ፥ ፯) ።
አዶም (ኤዶም)፡ የዔሳው ኹለተኛ ስም፡ ቀይ ማለት ነው ። (ዘፍ ፳፭ ፥ ፴) ።
አዶቀረ፡ ዝም አሠኘ ራሱን ።
አዶባሪ፡ ያዶበረ/የሚያዶብር (አኵራፊ) ።
አዶናይ፡ ስመ አምላክ፡ ጌታዬ ጌቶቼ ማለት ነው ።
አዶን (ዕብ)፡ ጌታ ፈጣሪ ።
አዶን ጼዴቅ፡ የጽድቅ (የውነት) ።
አዶንያስ፡ የሰው ስም፡ አዶን እግዚእ ያስ፡ እግዚኣብሔር ።
አዷዷል፡ አጨማመር/መዶል ። (ተመልከት፡ ዶለ ተን እይ የዶለ ሳቢ ዘር ነው) ።
አጀለ፡ በቅጠል ሸፈነ ዐጀለ ።
አጀለ፡ አቄለ/አሞኘ ።
አጀረ፡ አኰራ ፥ —ዐጀረ ።
አጀራ (ዐረ ሀጀር ደንጊያ)፡ የሸክላ መተኰሻ ማብሰያ ምድጃ፡ በግእዝ ሞፍጥ ይባላል ። አጀራ ማለት በጕድጓዱ ውስጥ በዙሪያ ያለውን ድንጋይ ያሳያል ። ዣራን ተመልከት ።
አጀበ፡ ከበበ ፥ —ዐጀበ ።
አጀብ፡ ግሩም ፥ —ዐጀብ ።
አጀናነን፡ አኰራር/መጀነን ። (ተመልከት፡ ቈነነን) ።
አጀናጀን፡ ኣመላል/መጀንጀን ።
አጀጓጐል፡ አስተጣጠር/መጀጐል ።
አጀፈጀፈ፡ አቀጠለ/አለመለመ/አፈ ጠፈጠ ።
አጃ፡ በቁሙ ዐጃ ።
አጅባር፡ የከተማ ስም ("በሣይንት ያለ ከተማ ባላ፩ ተራራ እሱም አስታምባ ይባላል አጅባር ትልቅ ድንኳን በሩቅ ሲያ ዩት ደብር የሚመስል") ።
አጅባር፡ ድንኳን ፥ —ጅባር ።
አገለ፡ ኰተኰተ፡ ዐገለ ።
አገለለ፡ ለየ/ወገደ/አራቀ (እየብቻ አደረገ ለምርምርና ለማስታረቅ) ።
አገለለ፡ ወገደ፡ ገለለ ።
አገለማ፡ ጣም አሳጣ/አበላሸ ።
አገለማመጠ፡ አገራመመ ።
አገለማመጥ፡ አተኳኰስ/መገልመጥ/መገላመጥ ። (ተመልከት፡ በለጠጠን) ።
አገለማም፡ አበለሻሸት/መገልማት ።
አገለሞተ፡ ሴትን ከባሏ ከተፋታች በኋላ እያበላ እያጠጣ በቤቱ አስቀመጠ (ጋለሞታ አደረገ) ።
አገለደመ፡ አሸረጠ፡ (ገለደመ) ።
አገለዳደም፡ ኣስተጣጠቅ/አሸራረጥ/ማገልዶም ።
አገለገለ፡ ረባ/ጠቀመ/አጠጣ ።
አገለገለ፡ ቀደሰ/አወደሰ/ዘመረ/አመሰገነ (የክህነት ሥራ ሠራ) (ሕዝ. ፵፬፡ ፲፭–፲፮, ፲፯) ።
አገለገለ፡ ተገዛ/ታዘዘ (ማንኛውንም ሥራ ሠርቶ ጌታውን ደስ አሠኘ ዐገዘ ረዳ) (ዘፍ. ፳፱፡ ፲፭፡ ሚል. ፫፡ ፲፯) ።
አገለፋፈጥ፡ አሣሣቅ/መገልፈጥ ።
አገለፋፈፍ፡ አላላጥ/አሣሣቅ/መገልፈፍ ። (ተመልከት፡ ገለፈጠን) ።
አገላለል፡ አራራቅ/ማግለል ።
አገላለብ፡ አበራረር/መጋለብ ።
አገላለጠ፡ አገፋፈፈ/አገላለበ/አጥፍቻለኹ አባባለ/በድያለኹ አሠኛኘ ።
አገላለጥ፡ አገፋፈፍ/መግለጥ ።
አገላላጭ፡ ያገላለጠ/የሚያገላልጥ (የዘመድ ዳኛ ሽማግሌ) ።
አገላመጠ፡ አቋጣ/አጋሠጸ (አደራጊ) ።
አገላመጠ፡ የፍርሀትና የነፍሰ ጉዳይ አስተያየት አሳየ (ፊትን መለሰ ቀለሰ) (አድራጊ) ።
አገላማጭ፡ ያገላመጠ/የሚያገላምጥ ።
አገላተመ፡ አቻኰለ/አጣደፈ/አገላበጠ/አጋጨ/አማታ ። "ዐይጡ ሌሊቱን ዕቃ ሲያገላትም ዐደረ።"
አገላታሚ፡ ያገላተመ/የሚያገላትም (የሚያጋጭ አጋጪ) ።
አገላገለ፡ ማሪያም ማሪያም አለ/አዋለደ ።
አገላገለ፡ አላቀቀ/አለያየ/አስተራረቀ/አሰማማ ።
አገላገለ፡ አጋመሰ/አስተራረሰ ።
አገላገል፡ አገማመስ/አስተራረስ/መገልገል/ማገልገል/መገላገል ።
አገላጋይ፡ ያገላገለ/የሚያገላግል (አሰማሚ አዋላጅ) ።
አገልች፡ ያገለሞተ/የሚያገለሙት ወንድም ።
አገልዳሚ፡ ያገለደመ/የሚያገለድም (ኣሸራጭ) ።
አገልድም፡ የሰው ስም (ግልድም ወዳጅ ግልድመኛ) ። "አገልድም ኢያሱ" እንዲሉ።
አገልድም፡ የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ "ታጠቅ አሸርጥ ማለት ነው።"
አገልጋይ፡ ያገለገለ/የሚያገለግል (ቅን ሎሌ ኣሽከር ምንደኛ ባሪያ ገረድ አወዳሽ ካህን ዐዳይ አሳላፊ) (ኢዮ. ፯፡ ፪) ።
አገልጋይነት፡ ሎሌነት/ሠራተኛነት ።
አገልጋዮች፡ ዐዳዮች/አሳላፎች/አስተናባሮች/አሽከሮች (፩ዜና. ፳፱፡ ፮፡ ዮሐ. ፪፡ ፭, ፱) ።
አገልግል (ሎች)፡ የተለጐመና ያልተለጐመ ባለመክደኛ ስፌት በውስጡ ገንዘብና ዕቃ የሚቀመጥበት የምግብ መያዣ ። "ዐናጢዎችም የንጨት አገልግል ያበጃሉ።"
አገልግል፡ የስፌት ዕቃ፡ ገለገለ ።
አገልግል፡ የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ (ሥራ ቀድስ አወድስ) ።
አገልግሎት፡ ዕርሻ/ቍፋሮ (ማንኛውም ሥጋዊና መንፈሳዊ የማገልገል ሥራ ዕንጨት መስበር ውሃ መቅዳት እንጀራ መጋገር ወጥ መቀቀል ጠላ መጥመቅ ስፌት መስፋት ቅዳሴ ውዳሴ የመሰለው ኹሉ) (፪ዜና. ፰፡ ፲፬) ።
አገመ፡ ደምን ሳበ ዐገመ ።
አገመሰ፡ ሰው እንዳያየው ሸሸ/ተደበቀ ።
አገመነ (ገመነ)፡ አነደደ/አቃጠለ/አሳረረ/አበገነ/አጠቈረ/አከሰለ (አሳዘነ) ።
አገመነ፡ አሳደፈ/አለፈለፈ/አረከሰ ።
አገመደደ (ፀወገ)፡ ፊቱን ቋጠረ/አጠቈረ/ጨመተረ ።
አገመዳደል፡ አቈራረስ/መገምደል ።
አገመጠ፡ በጥርስ እንዲቈርስ አደረገ ።
አገመጠ፡ ተቈጣ/አኰረፈ ።
አገመጣጠጥ፡ አነቃቀፍ/መገምጠጥ ።
አገማ፡ አበከተ/አበሰበሰ/አበላሸ/አጠነባ/አከረፋ/አቀረና/አበሰና ።
አገማ፡ ዝክርን ተዝካርን ሳይበላ ቀረ ።
አገማ፡ ፈንጣጣ ልጅን ሳይዝ ተወ ።
አገማመል፡ ኣለባለብ/መገመል ።
አገማመሰ፡ አተላለመ/አስተራረሰ/አቈራረስ/አከፋፈለ ።
አገማመስ፡ አተላለም/አስተራረስ/አከፋፈል/መግመስ ።
አገማመተ፡ አስተሳሰበ (ግምትን ረዳ አሸላለገ) ።
አገማመት/አገማገም፡ አሰላል/መፃት ።
አገማመን፡ አስተራረር/መግመን ።
አገማመደ፡ አጠማመረ/አሸራረበ ።
አገማመድ፡ አፈታተል/መግመድ ።
አገማመጠ፡ አነካከሰ/አሰባበረ/አሸራ ።
አገማመጥ፡ አነካከስ/መግመጥ ።
አገማም፡ አጠነባብ/አከረፋፍ/መግማት ።
አገማች፡ ዕንቍላሏን ሳትፈለፍል ቀረች ዶሮዪቱ ።
አገማገመ፡ አጋመተ/አገማመተ/አሻለገ/ኣሸላለገ/አስተሳሰበ ።
አገማገም፡ አማመት/መገምገም ።
አገማጋሚ፡ ያገማገመ/የሚያገማግም (አጋማች አሳሊ) ።
አገማጠጠ፡ አነቃቀፈ/አናናቀ ።
አገምዳጅ፡ ያገመደደ/የሚያገመድድ (ፊተ ቋጣሪ ኰምታሪ) ።
አገሠገሠ፡ አማለደ (በጧት ወሰደ) ።
አገሠገሠ፡ አሳደገ/እረዘመ ።
አገሣ (ጐሥዐ ጥሕረ)፡ ጮኸ (' ጩኸት አሰማ - የበሬ ያንበሳ የከበሮ) ። "መጽሐፍ ግን በአገሣ ፈንታ ገሣ ይላል (ሆሴ. ፲፩፡ ፲፡ ዓሞ. ፫፡ ፰) 'ሚጣቅ እሾላው ሥር ዐማኔል ቢያገሣ በሽታዬ ኹሉ እክቱን አነሣ' (ታቦት ዘፋኝ)"
አገሣ፡ ምግብ ተቀብሎ ድምጥ ሰጠ ። "መብል በልቶ መጠጥ ሲጠጡ ሆድ ያገሣል ያዋሕዳል ያሰማማል ማለት ነው።"
አገሣ፡ በሬ ጮኸ ገሣ ።
አገሳሰል፡ አቈጣጥ/መገሰል ።
አገሳሰስ፡ አጠፋፍ/አረባብ/አለቃቀቅ/መግሰስ ።
አገሳሰር፡ አጠጣጥ/መገስር ።
አገሣሠጥ፡ አሳሳል/አነጣጠስ/መገሠጥ ።
አገሣሥ፡ አፈሳሰስ/አወራረድ/መግሣት/ማግሣት ።
አገሣገሥ፡ አረዛዘም/መገሥገሥ (የችኰላ የፍጥነት አካኼድ) ።
አገሥጋሽ፡ ያገሠገሠ/የሚያገሠግሥ (መንገድ መሪ የሚያረዝም ዞሚያ) ።
አገረ (አጊር አገረ ። ትግ ሐባ አግረ)፡ እግር አወጣ፡ እግረኛ ኾነ፡ በእግር ኼደ ተራመደ ።
አገረ መርፌ፡ መርፌ የሚመስል እንደ መርፌ የሾለ፡ በሞፈር ውሃ አጠገብ ያለ አገር፡ ሾጣጣ ሾለቅ ዥራትማ የምድር ሠላጤ ወንዝ ያሾለው ያሞጠሞጠው ። (ሀገረ መርፍእ)፡ የመርፌ አገር ።
አገረ፡ መከተ ከለለ ።
አገረ ሰብ (ሰብአ ሀገር)፡ ባላገር ።
አገረ ብርቁ፡ አገር ወዳድ፡ አገሬ አገሬ ባይ፡ ላገሩ የሚያስብ የሚቈረቈር አገሩን የሚናፍቅ ። (ግጥም)፡ አገር አገር አለች ይች አገረ ብርቁ፡ እኛም አገር አለን ይታያል በሩቁ ። (ለም አገር)፡ የወይኑ ዘለላ ጋን የሚመላ፡ የስንዴው ዛላ ዕፍኝ የሚመላ ።
አገረ፡ አወከ አስቸገረ አቆመ ። ገረ ገረን እይ ።
አገረ ወገብ፡ ያገር ወገብ፡ በደጋና በቈላ መካከል ያለ ቀበሌ ።
አገረ ገዥ ዢ (ገዛኤ ሀገር)፡ አገር የሚገዛ መስፍን ራስ ደጃዝማች መኰንን፡ ፊታውራሪ ቀኛዝማች ግራዝማች ባላም ባራስ ባለሥልጣን እንደራሴ ሻለቃ ባልደራስ ።
አገረመ (አግርሀ)፡ አገራ (ገር አደረገ) ።
አገረማመም፡ አገለማመጥ/መገርመም ።
አገረሳሰስ፡ አነቃቀል/መገርሰስ ።
አገረረ (ትግ. አግረረ ዐለበ)፡ አጋለ/አሠማ/አጠበረረ ።
አገረረ፡ አጠበረረ ፥ ጮኸ ፥ —ገረረ ።
አገረረ፡ ጮኸ/ሸለለ/አቅራራ/ፎከረ ።
አገረሸ፡ መለስ ዐደሰ (ልማዱ ግን ተመለሰ ታደሰ ነው) ።
አገረሸ፡ ዐደሰ ፥ —ገረሸ ።
አገረደ፡ ፈናፍንት አደረገ/አሰደበ ። "አገረዶች የሴት ስም ላሌዋን ገረድ አደረገች።"
አገረዳደም፡ አሰባበር/መገርደም ።
አገረዳደፍ፡ አከረታተፍ/መገርደፍ ።
አገረድ (ልጅ አገረድ/ልጃገ ረድ)፡ (ተመልከት፡ ወለደ ብለኸ ልጅን እይ) ።
አገረድ (ወንድ አገረድ/ወንዳ ገረድ)፡ የሚያገርድ ። (ተመልከት፡ ወንድን ተመልከት) ።
አገረዶ፡ ግርድ አወጣ ።
አገረዶመ፡ አገመጠ/አበላ ።
አገረገረ፡ በረገገ ፥ —ገረገረ ።
አገረገረ፡ በረገገ/ታወከ (ሊደነብር ሊያብድ ፈለገ ቀጥ ብሎ ቆመ ዦሮውን ቀፍሮ አየ አልኼድ አለ) ። "ካበደው ያገረገረው ይበዛል" እንዲሉ ። "አገረገረን በረገገ ቆመ ማለት ልማድ እንጂ የቋንቋው ሕግ አይዶለም።"
አገረጣ፡ አነጣ (ነጭ አደረገ) ።
አገሪት (ሀገሪት)፡ ያገር ስም፡ በመ ራቤቴ ያለች አገር፡ እናት አገር ማለት ነው፡ ባላገር ተብሎም ይተረጐማል ።
አገራ (አግርሀ)፡ ገር አደረገ/አለዘበ/አላላ ።
አገራመመ፡ አገለማመጠ ።
አገራሰመ፡ አጋጨ/አላተመ/እገላተመ አወላከፈ/አደናቀፈ ።
አገራረመ፡ አደናነቀ/አፈራራ ።
አገራረም፡ አደናነቅ/መግረም ።
አገራረር፡ አሠማም/አጯጯኸ/መግ ።
አገራረዝ፡ አቈራረጥ/መግረዝ ።
አገራረደ፡ አመካከተ ።
አገራረድ፡ አዘረጋግ/አከላለል/መጋረድ ።
አገራረፍ፡ አቈነዳደድ/መግረፍ ።
አገራር፡ ሥግሪያን ማስለመድ/መገራት ።
አገራር፡ አለዛዘብ/መግራት ።
አገራደመ፡ አጋመጠ/አሳበረ ።
አገሬ (ሀገርየ ሀገራዊ)፡ የኔ አገር፡ ያገር ሰው ያገር ተወላጅ ባላገር ። አገሬ፡ ጥቃቅን ዐተር ።
አገር (ሀገር)፡ በቁሙ፡ ከተማና መንደር፡ ዐምባ ያለበት ብዙ ሕዝብ የሰፈረበት፡ አውራጃ ወረዳ ቀበሌ ገጠር ትንሹም ትልቁም ክፍል፡ ሲበዛ አገሮች ይላል ። ያማራ ያረብ የጥቍር የቀይ የብጫ የነጭ አገር እንዲሉ ። እናትን እይ፡ ቸረ ብለኸ ቸርን ተመ ልከት ። (የነጋሪት አገር)፡ ባለነጋሪት የሚገዛው ። (ፈራ ብለኽ አፈራን እይ) ።
አገር፡ ሕዝብ ። ማገረ ብለኸ ማገርን ተመልከት ።
አገር ላገር፡ ከ የቀረው ነው፡ ካገር ወዳገር ።
አገር ምድር (ምድረ ሀገር)፡ እጅግ በጣም ብዙ ።
አገር ቂጥ፡ እጅግ የራቀ ታችኛ ።
አገር በጄ፡ አገር በጄ ኾነ፡ ሥልጣን አገኘኹ ።
አገር ቤት (ቤተ ሀገር)፡ ከከ ተማ ውጭ በገጠር ያለ ቤት፡ ወይም ቤት ያለበት አገር ። አገር ቤት ኼደ፡ አገር ቤት ከረመ ።
አገር፡ ብዙ እጅግ ። እከሌ ቸር ነው፡ አንድ አገር እንጀራ ሰጠኝ ። ዳግመኛም ያንድ አገር እንጀራ ተብሎ ይተረጐማል ።
አገር አማን ነው፡ አገር ደኅና ነው፡ ክፉም የለ ።
አገር አወጣ፡ ተሾመ፡ ገባር ዜጋ ተቀበለ ።
አገር አዋይ፡ አገርን ከጠላት ጠብቆ የሚያውል ሐርበኛ ጐበዝ ።
አገር አጥፊ፡ አገር የሚያጠፋ ክፉ ሰው ወራሪ ዘራፊ ቀማኛ ።
አገር ዘዋሪ፡ አገርን እየዞረ የሚያይ፡ ጐብኝ ። ፈረንጆች ቱሪስት ይሉታል ።
አገር ግዛት (ሀገረ ግዝአት)፡ ባንድ መኰንን የሚገዛ የሚተዳደር አገር አውራጃ፡ የግዛት አገር፡ ወይም ያገር ግዛት (ግዝአተ ሀገር) ።
አገር ፍቅር (ፍቅረ ሀገር)፡ የማኅበር ስም፡ በከበሮ በማሲንቆና በበገና በክራር፡ በዋሽንት በእንቢልታ በያይነቱ ያር ጨዋታና ዘፈን ጭፈራ የሚያሳይ ማኀበር፡ ያገር ፍቅር ።
አገርድማ፡ ባላተኛ ሴት ነፋ ሥራ የማይፈታ ። "አሸርድማ ብትኼድ አገርድማ መጣች።"
አገርጋሪ፡ ያገረገረ/የሚያገረግር (የሚቆም ፈረስ) ።
አገሸላለጥ፡ አገፋፈፍ/አሣሣቅ/መገ ሽለጥ ።
አገሻሸር፡ አቀማመጥ/መገሸር ።
አገበረ (አግበረ)፡ ቻለ/ወሰነ ።
አገበረ፡ ግድ አለ፡ አስገደደ፡ በግድ/ያለውድ አሠራ። "አገበረ የግእዝ አስገደደ ያማርኛ ነው።" (ተመልከት፡ ገደደን)
አገበር፡ እረኛ/ከብት ጠባቂ (ይኸውም በሐረርጌ ምድር ይነገራል)።
አገበያየ፡ አገዛዛ፡ አሻሻጠ፡ አቀባበለ።
አገበያየት፡ አገዛዝ፡ አለዋወጥ፡ መገብየት (መሸጥ/መለወጥ)።
አገበገበ፡ ቸኰለ፡ ገበገበ ።
አገባ (አግብአ)፡ ጨመረ ከተተ ዶለ አሰናዳ ።
አገባ፡ በሺ ሰርገኛ በሥሉስ ዳኛ ሚስት አመጣ አስጠጋ፡ በቤቱ አስቀመጠ፡ ቆበተ፡ ገረድ ቀጠረ ። (ተረት)፡ እናቷን አይተኸ ልጇን አግባ ። እናቴን ያገባ ኹሉ አባቴ ነው ። አታግባና ስትዘል ኑር ። ቸገረን እይ ።
አገባ፡ ዕሩርን ጥንግን እዳር አደረሰ አሳረፈ ።
አገባበስ፡ ገብስ መምሰል፡ ማጋገስ፡ አሰባሰብ፡ ስብሰባ።
አገባበዘ፡ "አንተ ብላ አንተ ብላ" አሠኛኘ፡ አጐራረሡ።
አገባበዝ፡ አጠራር፡ መጋበዝ፡ ግብዣ ማድረግ፡ ማስተናገድ።
አገባበዝ፡ ኣሿሿም፡ መዝበዝ/ገበዝ መሾም፡ ግብዝ ማድረግ።
አገባበድ፡ አፈላለጥ፡ እሠነጣጠቅ፡ መገበድ።
አገባባ፡ አዘማመደ አቀነጃጀ አገነኛኘ ።
አገባብ (ቦች)፡ (ኢዮ ፳፩ ፥ ፴፬) ። የቋንቋ ሥርዐትና ሕግ ደንብ፡ በብትን ሰዋስው ኹሉ እየገባ የሚነገር ቃልና ፊደል ። (ዐቢይ አገባብ)፡ አንቀጽን (ግስን) እንዳያስር የሚያደርግ ። (ንኡስ አገባብ)፡ ማሰሪያነትን የማያስለ ቅቅ፡ ጥያቄና አንክሮ፡ ደስታና ሐዘን፡ ልመናና ምኞት፡ አሉታና አፍራሽ፡ ዕሺታና እንቢታ ። (ደቂቅ አገባብ)፡ በብትን ሰዋስው ላይ የሚ ጨመር ቃል ።
አገባብ፡ ሥርዐት፡ ገባ ።
አገባብ፡ ወደ ውስጥ አመጣጥ እካኼድ፡ መግባት መመለስ፡ አመላለስ ምለሳ ።
አገባች፡ ባልን ወደ ቤቷ ወደ ሰውነቷ አስጠጋች ።
አገባየ፡ አጋዛ፡ አሻመተ።
አገባደደ፡ አዋገደ፡ አቃረበ።
አገባደደ፡ አዋገደ፡ ገበደደ ።
አገባዳጅ፡ ያገባደደ/የሚያገባድድ፡ አዋጋጅ።
አገብጋቢ፡ ቸኳይ፣ ችኩል፣ ተዳፊ።
አገብጋቢ፡ ጤፍ ውቂያ ዠማሪ/መሪ።
አገተ፡ የዋስን ዕቃ ወሰደ ዐገተ ።
አገታተም፡ አቃቃም/መገተም ።
አገታተር፡ አሳሳብ/አወጣጠር/መገተር ።
አገታተን፡ አዘነታተር/መገተን ።
አገታገት፡ አነካከስ/መገትገት ።
አገነበረ፡ አጠና ፥ —ገነበረ ።
አገነበረ፡ አጠና/አጠነከረ (ግንባር አደረገ) ።
አገነበረ፡ ጐራዴ ታጠቀ/አገነደረ ።
አገነበበ፡ ፍሬ አሳጣ (አገዳና ላንፋ ብቻ አደረገ) ።
አገነበጠ፡ ሰይፍ ታጠቀ ፥ —ገነበጠ ።
አገነበጠ፡ ሰይፍ ታጠቀ (በረዥሙ ለቀቀ ወደ ላይ አቀና ወይም በጐኑ (በትከሻው) አንጠለጠለ) ።
አገነተረ፡ ቀቀለ/አገረደደ/አጠና/ኰመተረ ።
አገነታ፡ አጮኸ (ኀይለ ቃል ሰጠ) ።
አገነታተር፡ አገረዳደድ/ኣኰመታተር/መጎንተር ።
አገነታት፡ አጯጯኸ/መገንታት ።
አገነነ፡ አከበረ/አበዛ/አናቸ/አበረታ (ኀይል ሰጠ) (ሉቃ. ፩፡ ፶፰) ።
አገነኛኘ፡ አቀራረበ/አገጣጠመ/አቀነባበረ/አጠማመረ ።
አገነኛኘት፡ አገጣጠም/ማገናኘት ።
አገነዛዘብ፡ አወራረስ/ማገናዘብ ።
አገነደረ፡ ሰይፍ ታጠቀ/አገነበረ/አገነበጠ/አቀና ።
አገነደረ፡ አገነበረ ፥ —ገነደረ ።
አገነዳደስ፡ አሰባበር/አጣጣል/መገን ።
አገነጃጀብ፡ አረጃጀት/አዘነጋግ/መገ ።
አገነገነ፡ አሠጋ/አነቃ ።
አገነጣጠለ፡ አለያየ/አበታተነ/አበለሻሸ (በብዙ ወገን) ።
አገነጣጠል፡ አሳሳብ/አቈራረጥ/አሰባበር/መገንጠል ።
አገነፈለ፡ ባቄላን ሥጋን አንድ ጊዜ አፍልቶ ውሃውን አፈሰሰ ።
አገነፈለ፡ ዐዲስ ሸክላን በተበጠበጠ ዶቄት አሸ ።
አገነፋ፡ አፈላ ፥ —ገነፋ ።
አገነፋ፡ አፈላ/ጠበሰ (እሳት አስመታ ላገ ኣማሰለ ኣበሰለ) ።
አገነፋፈል፡ አፈላል/አፈሳሰስ/መ ።
አገና (ሐገነ)፡ ርግጥ ቍርጥ ድርስ ቃል።
አገና ተማታ፡ ተሻኰተ ተጣፋ ዕቃን ለመሼጥ ለመግዛት ።
አገና አማታ፡ አሻኰተ አጣፋ ። (ምሳ ፳፪ ፥ ፳፮) ።
አገናነዝ፡ አከፋፈን/አስተሳሰር/መገ ።
አገናኘ፡ አቃረበ/አስተዋወቀ ።
አገናኘ፡ አዋዋደ/አማሰለ/አነደ ።
አገናኘ፡ አጣመረ/አያያዘ/አገናዘበ/አጋጠመ (መክ. ፱፡ ፲፩) ።
አገናኘ፡ ጥጃን አጠባ/ላምን ዐለበ ።
አገናኚ፡ ያገናኘ/የሚያገናኝ (የሚያልብ ላም ዐላቢ) ።
አገናዘበ፡ አያያዘ ፥ —ገነዘበ ።
አገናዘበ፡ ያንዱን ለሌላው አደረገ/አወራረሰ/አገናኘ/አያያዘ ።
አገናዛቢ፡ ያገናዘበ/የሚያገናዝብ (አያያዥ) ።
አገናገን፡ ኣፈራር/አጠራጠር/አሠጋግ/መገንገን ።
አገናጠለ፡ አቋረጠ/አባጠሰ/አሳበረ ።
አገንታሪ፡ ያነተረ/የሚያገነትር (ቀ) ።
አገንፊ፡ ያገነፋ/የሚያገነፋ ።
አገንፋይ፡ ያገነፈለ/የሚያገነፍል ።
አገኘ፡ በቁሙ (ገኘ ገነኘ) ።
አገኘ፡ ገጠመ/ዐወቀ/ተረዳ (ዘዳ. ፳፰፡ ፪፡ ዮሐ. ፲፩፡ ፲፯) ። (ተመልከት፡ ተኛን) ።
አገኘበት፡ ከበረበት/ሀብታም ኾነበት (ባገሩ በሥራው) ።
አገኘኸ/አገኘሽ፡ የሰርግ ዘፈን ። "አንተ አገኘሽ አገኘኸ ዛሬ አንች አገኘሽ አገኘሽ ዛሬ" እንዲል ሰርገኛ ።
አገኘኹ እንግዳ፡ ከሐበሻ ሠዓሊዎች አንደኛው (የቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ባለል) ።
አገኘኹ፡ የሰው ስም "ልጅ ወለድኹ ማለት ነው።"
አገኛኘት፡ አቀራረብ/ማግኘት ።
አገኝ ባይ፡ አገኛለኹ የሚል ሰው (ባላለኝታ ባለተስፋ) ።
አገው፡ የነገድና ያገር ስም፡ በሰቈጣና በጐዣም ከዳሞት ቀጥሎ ይገኛል ። አገው ልቡ ዘጠኝ ስምንቱን ትቶ አንዱን አጫወ ተኝ ። ሰባት ቤት አገው ። የጐዣም አገው ከሰቈጣ አገው የመጣ ነው፡ ባላባቱ አደሩ ይባላል ። የአገው ሰው የወፍ ቋንቋ ያውቃል ይላሉ ።
አገውኛ፡ የአገው ቋንቋ አገዎች ብቻ የሚናገሩት፡ ቄሶቻቸው ግን እንደ ትግሬና እንደ አማራ በግእዝ ይቀድሳሉ ። ከዚህ የቀረውን የአገውን ነገር በኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ተመልከት ።
አገዎች፡ የአገው ሰዎች፡ የአገው ተወ ላጆች ።
አገዘ፡ ረዳ ፥ —ዐገዘ ።
አገዘፈ (አግዘፈ)፡ አዳጐሰ/አደነደነ/አወፈረ/አጐላ ።
አገዛዘም፡ አቁራረጥ/አከፋፈል/መግዘም ።
አገዛዘር፡ አገራረዝ/እቈራረጥ/መግዘር።
አገዛዘተ፡ አወጋገዘ ።
አገዛዘት፡ አለያየት/አወጋገዝ/መገዘት ።
አገዛዘፍ፡ አደናደን/አወፋፈር/መግዘፍ ።
አገዛዛ፡ አገበያየ/አሸማመተ/አለዋወጠ (ሸያጭና ገዢን አገናኘ/ኣዋዋለ) ።
አገዛገዘ፡ አማዝዘ ።
አገዛገዝ፡ አከራከር/ኣመጋገዝ/መገዝገዝ ።
አገደ (ኣጊድ አገደ)፡ በቁሙ፡ ገታ ከለከለ ፥ አቆመ ፥ ገደበ ፥ ከተረ ፥ ደለደለ ፥ አሰረ፡ ጠበቀ ። እንዳይሠራ እንዳይኼድ እንዳይበላ እንዳይጠፋ አደረገ፡ የሰው የውሃ የእሳት የከብት ።
አገደመ (አመግደመ)፡ አግድም ባቋራጭ መስቀልኛ ኼደ/ዐለፈ (ዘፍ. ፴፰፡ ፲፮) ።
አገደም፡ ገደማ ። "በዚያ አገደም ኺድ።"
አገደደ፡ ጠመዘዘ/አጠመመ (ዐንገትን)። "በሬው አገደደ" እንዲሉ። "በአስገደደ ፈንታ 'አገደዶ' ይላል። ምን አግዶኸ ምን አግዶኝ" እንዲሉ።
አገዳ (ዶች)፡ በቁሙ፡ ማሽላ ዘንጋዳ ሸንኰር በቈሎ ከሥር እስከ ጫፍ አንጓ ።
አገዳ (ዶች)፡ የመቅረዝ ዐጽቅ ፮ ቅጥይ የዘይትና የፈትል መቀመጫ ከናስ የተበጀ ። (ዘፀ ፴፯ ፥ ፲፰ ። ኢዮ ፵ ፥ ፲፰) ።
አገዳ ሰበር፡ ቅልጥም ሰባሪ አሞራ ።
አገዳ፡ ጡንቻ ክንድ ከክርን እስከ አንባር ያ ። (ኢዮ ፴፩ ፥ ፳፪) ። ጭን ቅልጥም ከቋንዣ እስከ ቍርጭምጭሚት ያለ የእጅና የእግር መደበኛ ዐጥንት ። (ተረት)፡ ዐሎ ብሎ የተረታ መኻል አገዳውን የተመታ ። አከለን ተመልከት ።
አገዳዋ፡ አገዳዪቱ፡ ያች አገዳ ።
አገዳዋ፡ የርሷ አገዳ፡ ዐጽቋ ። ዋ መቅ ረዝን ያያል ። (ዘፀ ፴፯ ፥ ፳፩ ፥ ፳፪) ።
አገዳው፡ ያ አገዳ፡ የርሱ አገዳ ።
አገዳደለ፡ የአጋደለ ድርብ (አደባደበ/አስተላለቀ/አስተራረደ/አቀራደደ)።
አገዳደል፡ አመታት/አወጋግ/መግደል ።
አገዳደረ፡ አወዳደረ/አፈካከረ/አነቃቀፈ ።
አገዳደር፡ አቻቻል/መገደር ።
አገዳደብ፡ አከታተር/አስተጋገድ/አውሳሰን (መገደብ/መወደብ)። "ትግሬ ግን 'ገደበ' ብሎ ደሙ ወዝ ቈረ ይላል።"
አገዳደድ፡ አጠማመም/መግደድ/ማግደድ ።
አገዳደፍ፡ አጣጣል/አዘላለል/አረሳስ/መግደፍ/ማጕደል ።
አገዳዳሪ፡ ያገዳደረ/የሚያገዳድር (አወዳዳሪ/አፈካካሪ) ።
አገዳገደ፡ ግድግዳን አታከለ/አቋቋመ።
አገዳገድ፡ አተካከል/መገድገድ።
አገገመ፡ አዳነ/አሻለ። "ልማዱ ግን ዳነ ተሻለ ነው።"
አገገመ፡ ደሙ ተመለሰ፡ ገገመ ።
አገጋሚ፡ ያገገመ/የሚያገግም።
አገጋገር፡ አሰፋፍ/አዟዟር/አደፋፍ (መጋገር/መሳብ/ማውጣት)። (ተመልከት፡ እንጌራን የዚህ ዘር ነው) ።
አገጠመት (ቶች)፡ ዝኒ ከማሁ (ችኮ ዕፍረተ ቢስ ዐይናውጣ ኣገጨ መት ቢል በቀና ነበር) ።
አገጠመት፡ ችኮ ፥ —ገጥ ።
አገጠጠ፡ አፈነረ ፥ —ገጠጠ ።
አገጣባሪ፡ ያገበረ/የሚያገባብ - ሰዳቢ/አዋራጅ ።
አገጣገጠ፡ አቀጣቀጠ (የግጥግጥ ሥራ አማራ) ።
አገጣገጥ፡ አቀጣቀጥ/ኣመታት/መገጥ ።
አገጣጠመ፡ አቀራረበ/አገነኛኘ/አቀናበረ/አቀነባበረ/አከናወነ/አከነዋወነ/አዘጋጀ/አዘገጃጀ ።
አገጣጠም፡ አዘጋግ/መግጠም ።
አገጣጠብ፡ አነካክ/አቈሳሰል ።
አገጣጣሚ፡ ያገጣጠመ/የሚያገጣጥም (አቀናባሪ/አቀነባባሪ/አከናዋኝ) ።
አገጫጭ፡ ጨት/አለታተም/መግጨት ። (ተመልከት፡ ቀን) ።
አገጭ፡ በቁሙ ፥ —ገጨ ።
አገፈረ፡ አቃመ/አበላ ገፈራን ።
አገፈታተር፡ አገፋፍ/መገፍተር ።
አገፋፈር፡ አቃቃም/መገፈር ።
አገፋፈት፡ ኣቀማመስ/መገፈት ።
አገፋፋ፡ አጨናነቀ ።
አገፋፍ፡ የግፍ አሠራር/አበዳደል/አስተዳደግ/መግፋት ።
አጕሊ፡ የሚያጐላ/የሚያገዝፍ (አግዛፊ) ።
አጕላላ፡ በጕልሕ (በግልጥ) ጐዳ/መከራ አሳየ/አንገላታ/አስጨነቀ/አስቸገረ/አንቃቃ/በደለ ።
አጕላላ፡ አንገላታ ፥ —ጐላ ።
አጕላሲ፡ ያጕላላ/የሚያጕላላ (አንገላቺ አስቸጋሪ ጐጂ) ።
አጕል፡ መጥፎ Á ፥ —ዐጕል ።
አጕመተመተ፡ አጕረመረመ ፥ ጐመተ ።
አጕመተመተ፡ አጕረመረመ/አድረመረመ ። (ተመልከት፡ ጐተመ) ።
አጕመጠመጠ፡ በምላስና በትንፋሽ ውሃን እያንቀሳቀሰ የጕንጭን ውስጥ አሳጠበ/አስታጠበ/አስለቀለቀ/አስጠዳ ።
አጕመጠመጠ፡ አፍን አሳጠበ ፥ —ጐመጠ ።
አጕማማ፡ በስውር አወራ ጐማ ።
አጕረመረመ፡ አስገመገመ ሰማዩ ።
አጕረመረመ፡ አንጐራጐረ ፥ —ጐረመ ።
አጕረመረመ፡ አድረመረመ/አቶመ ቶመ (ክፉ ቃል አናገረ አስቈጣ) (መዝ. ፪፡ ፩፡ ኢሳ. ፰፡ ፱፡ ኤር. ፶፩፡ ፴፰) ። "ጐረጐረ ብለኸ አንጐራጐረን እይ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።"
አጕረምራሚ (መንጐርጕር)፡ ያጕረመረመ/የሚያጕረመርም (አቶምቷሚ) ።
አጕረምራሞች፡ ያጕረመረሙ/የሚያጕ ረመርሙ (ክፉዎች) (ዘኍ. ፳፡ ፲) ።
አጕረፈረፈ፡ አዝረከረከ/አዝረፈረፈ (እንደ ጐርፍ በያለበት አስቀረ ጣለ አወደቀ) ።
አጕሪ/አጓሪ፡ ያጓራ/የሚያጐራ/የሚያጓራ (ገዛፊ) ።
አጕራ (ዎች)፡ ብዙ አጣና የበረት መዝጊያ ማወናከሪያ ። ክርክር ሙግት ። ባንድ አጕራ ኹለት አውራ ። ኣጕራኸ ጠናኝ አጕ ራዬ ጠና እንዲሉ ።
አጕራ ዘለል፡ ከባሏ ቤት ጠፍታ ኰብልላ የኼደች ሴት ።
አጕራራ፡ ገዛዘፈ ።
አጕራራ፡ ገዛዘፈ ፥ —(ጐራ) ።
አጕራራ፡ ጯጯኸ (መላልሶ አገሣ) (ዓሞ. ፫፡ ፬) ።
አጕራሽ፡ ያጐረሠ/የሚያጐርሥ (ሰጪ ፈጫይ) ።
አጕራቢ፡ ያጐረበ/የሚያጐርብ (አርጋቢ) ።
አጕራዶ፡ ባጪር ባጪሩ የተመገዘ ግንድ (ማገዶ) ።
አጕራጭ፡ ያጐረጠ/የሚያጐርጥ (አፍ ጣ) ።
አጕራፊ፡ ያጐረፈ/የሚያጐርፍ (ዐጣቢ) ።
አጕሬሣ፡ ወገዝ ከበሬና ከወይፈን እየተሻማ ሣር የሚጐርሥ ።
አጕር፡ አወናክር ዝጋ ክፉ ተናጋሪ ደፋር ። (ወልደኸ አጕር)፡ ጨካኝ ቂል ደንቈሮ ሰው ።
አጕርጥ፡ ዝኒ ከማሁ (አፍጥጥ) ።
አጕባጭ፡ ያጐበጠ/የሚያጐብጥ፡ ደጋኝ/ቀላሽ ።
አጕተመተመ፡ አጕረመረመ (ጐተመ) ።
አጕተምታሚ፡ ያጕተመተመ/የሚያጕ ተመትም (አጕረምራሚ) ።
አጕደፈደፈ፡ የአጐደፈ ድርብ አኵለፈለፈ ።
አጕዳይ፡ ያጐደለ/የሚያጐድል/የሚቀንስ/የሚያሳንስ (ቀናሽ/አሳናሽ)። "ኣተርፍ ባይ ኣጕዳይ" እንዲሉ።
አጕዳፊ፡ ያጐደፈ/የሚያጐድፍ (ጕድፍጥራጊ የሚያፈስ/አፋጊ) ።
አጊያጊያጠ፡ አሸላለመ (የጌጥ ሥራ) ።
አጊያጭ፡ ያጌጠ/የሚያጌጥ/የሚሸልም (አልባሽ/ሸላሚ) ።
አጋለ፡ ሠማ ።
አጋለ፡ አከበረ/አገነነ ።
አጋለ፡ አጋመ/አሞቀ/አሠማ ።
አጋለጠ፡ ሰው የሠራውን ነውር አወጣ/አወራ ።
አጋለጠ፡ በጠብ በጦርነት ጊዜ ጥሎ ሸሸ/ብቻ አደረገ/አጋፈፈ/አራቈተ ።
አጋመ፡ አፋመ/አጋለ/አሞቀ/አቃጠለ (አጋም አስመሰለ) ።
አጋመሰ፡ አታለመ/አቋረስ/አጋራ/አካፈለ/አፈናከተ (እኩሌታ አደረገ ሥራን እንጀራን) ።
አጋመረ፡ አሳደገ/አጐለመሰ/አጠና ።
አጋመተ፡ አሳላ/አሻለገ/አዋጋ (ዋጋን አነጋገረ) ።
አጋመነ፡ አናደደ/አጣቈረ ።
አጋመደ፡ አፋተለ/አካረረ/አሻረበ/አጣመረ ።
አጋመጠ፡ የጋማ ከብትን ርስ በርሱ ኣጣላ/እናከሰ/አባላ ።
አጋሙዳ፡ ምስንጅር ፥ —ገመደ ።
አጋሙዳ፡ ታላቅ ምስንጅር ሆዳም በቅሎ (ብዙ ሣርና እኽል የሚበላ የሚደብል) ።
አጋሚ፡ ያጋመ/የሚያግም (አቂ) ።
አጋሚዶ፡ ሽፍታ፡ ገመደ ።
አጋማ፡ ኣበሳበሰ/አበለሻሸ/አጠናባ ።
አጋማሽ (ሾች)፡ አንዱን ኹለት የሚያደርግ (አካፋይ ቍና) ።
አጋማጅ፡ ያጋመደ/የሚያጋምድ (የሚያሻርብ) ።
አጋሜ፡ የኔ አጋም ።
አጋሜ፡ የአጋሜ ተወላጅ ።
አጋሜ፡ ያገር ስም በትግሬ ውስጥ ያለ አገር ። አጋም ያለበት የበዛበት፡ አጋማም አጋ ማዊ ተብሎ ይተረጐማል ። ሹም አጋሜ እንዲሉ።
አጋም (ሞች)፡ የንጨት ስም፡ ፍሬው የሚበላ እሾኻም ዕንጨት ። (የባለጌ ግጥም)፡ ያንን ነጕላ ባሏን ነብር በቧጠጠው፡ መሹለ ኪያዬን አይቶ አጋም ሸመጠጠው ።
አጋም አስመሰለ፡ የባቄላ ቈሎን አጠቈረ ።
አጋም አዙርበት፡ ጥርሱ ለማያምር ሣቅ ለሚያበዛ ሰው የሚነገር፡ ጥርስኸን ተነ ቀሰው ባጋም ተወቀረው ማለት ነው ።
አጋም ጣስ፡ የዛር ስም፡ የቀይ ዝር ዝር ዶሮ የሚገብሩለት ዛር ።
አጋም፡ ጥቍር ያጋም ፍሬ ።
አጋሰሰ፡ አዳፈረ ።
አጋሰስ (ሶች)፡ የጭነት ከብት በ ቅሎ ምስንጅር ። "አጋሰስ ያሠኘው ጓዝ መሸከሙና ዠርባው መገጠቡ ከጭን በቅሎ በ ታች መኾኑ ነው" ።
አጋሰስ፡ በቁሙ ፥ —ገሰሰ ።
አጋሣ፡ አገሣሣ/አፋሰሰ/አጯጯኸ ። (ተመልከት፡ ጐሽን እይ "የዚህ ዘር ነው።")
አጋረ፡ አስጮኸ/አስጨነቀ/አስለ ።
አጋረመ፡ አዳነቀ/አፋራ ።
አጋረዘ፡ መግረዝን ረዳ (ሕፃንን ያዘ) ።
አጋረደ፡ አካለለ/አማከተ ።
አጋረጠ፡ አሳካ/አባጣ ። (ተመልከት፡ ግራጭን ተመልከት ከገረጨና ከጋረጠ የወጣ ነው) ።
አጋረፈ፡ አቈናደደ (ምች አማታ) ።
አጋሪ፡ ያገረ የሚያግር፡ አዋኪ መካች ።
አጋሪ፡ ያጋራ/የሚያጋራ (አካፋይ) ።
አጋራ (አስተራየፀ)፡ የሚገራውን ከብት በሽቢያ አያያዘ (መገራትን ረዳ) ።
አጋራ፡ አካፈለ ፥ —ገራ ።
አጋራ፡ አካፈለ —(ተመልከት፡ ገራ ጋራ) ።
አጋራ፡ አካፈለ/አተናተነ/አፋለመ ።
አጋራ፡ አዳረሰ ።
አጋራ፡ የገበሎ ስም፡ በእግሩ ሸረር ብሎ የሚኼድ ማለት ነው ።
አጋራረጥ፡ አሰካክ/አፈቃቅ/መጋረጥ ።
አጋራዥ፡ ያጋረዘ/የሚያጋርዝ ።
አጋራይ (አጋራዊ)፡ የአጋር ያርበኛ ወገን ።
አጋራይ መንገድ፡ ብዙ እግረኛ ሰል ፈኛ የሚኼድበት ኣውራ ጐዳና ።
አጋራፊ፡ ያጋረፈ/የሚያጋርፍ (የገራፊ) ።
አጋር፡ እግረኛ ተራማጅ ሐርበኛ ። እስ ራኤል ከግብጽ ሲወጡ ፰፻፻ አጋር ነበሩ ።
አጋር፡ የሚረዳ የሚያግዝ፡ ዐጋዥ ረዳት ዘመድ ወገን ጥግ ። እከሌ አጋር የለውም እንዲሉ ። (ግጥም)፡ አንተም ሠርተኸ ብላ አን ቺም ሠርተሽ ብይ፡ አላጋር እንጀራ አይበ ላም ወይ ። (ወልደ ጻድቅ ጋሼ) ።
አጋር፡ ያብርሃም ገረድ፡ የይስማኤል እናት ። በዕብራይስጥ ሀጋር ትባላለች፡ መጻተ ኚት ስደተኚት ማለት ነው ። (ኪ ወ ክ) ።
አጋሮች፡ ዐጋዦች ረዳቶች ወገኖች ።
አጋሸበ፡ አሳደገ/አረዘመ ።
አጋበሰ፡ ጋፈፈ፡ (ጋበሰ) ።
አጋቢ፡ አዛዋሪ አስተላላፊ በሽታን ።
አጋቢ፡ ያጋባ የሚያገባ፡ አማጭ ሚ ስትን ።
አጋባ፡ አዛመደ ሚስት አማጣ፡ አቀ ናጀ አራከበ እገናን፡ አዛወገ ። (ዕዝ ፲ ፥ ፲) ።
አጋባ፡ ገለበጠ ባዶ አደረገ፡ አዛወረ አስተላለፈ ።
አጋባሽ፡ ያጋበሰ/የሚያጋብስ/የሚጋፍፍ (ሰብሳቢ)።
አጋቦስ፡ የትግሬን ሕዝብ እያጋበሰ የሚበላ ዘንዶ (ታሪከ ነገሥት)።
አጋተ (አግዐተ)፡ ወተት ቋጠረ/ዐቈረ/አወረደ/አንጠለጠለ/ዘረጋ/አድበለበለ/አከበደ (የፊት) ።
አጋተ፡ ወተት ቋጠረ፡ ጋተ ።
አጋተለ፡ ሰበሰበ/አከበ/ያዘ/ተሸ ከመ ። "እከሌ ከዠማ ብዙ ዓሣ አጋትሎ መጣ።"
አጋተለ፡ ሰብስቦ ያዘጋተለ ።
አጋተረ፡ አሳሳበ/አዋጠረ ።
አጋት፡ የወንዝ ስም ፥ —ጋተ ።
አጋት፡ የወንዝ ስም (ዜጋመልን ወደ ግራ ትቶ የሚወርድ ዥረት ፋፋቴው ባትጋ ፊኝ አፋፍ ተንጠልጥሎ የሚታይ) ።
አጋች፡ ያጋተ/የሚያግት (የላም ጡት) ።
አጋነነ (አገነነ)፡ ትንሹን ነገር ትልቅ አደረገ/አነሣሣ/አመሳገነ/አመሰጋገነ ።
አጋነዘ፡ አካፈነ/አሻፈነ/አጠቃለለ/አስተሳሰረ ።
አጋናኝ (ኞች)፡ ያጋነነ/የሚያጋንን (አመሳጋኝ) ።
አጋናዥ፡ ደጋነዘ/የሚያጋንዝ ።
አጋንንት፡ ጋኔኖች (ግእዝ) ።
አጋንዱር (ሮች)፡ ወፍራም ቂጣም ሴት ባለጌ ።
አጋንዱር፡ ወፍራም ሴት ገነደረ ።
አጋኖ፡ ንኡስ አገባብ (የሩቅ ወንድ ቦዝ ኣንቀጽ "ከፍ አድርጎ አበርትቶ ማለት ነው ዳግመኛም ማጋነን ማበራታት ተብሎ ይተረጐማል 'ቃለ አጋኖ' እንዲሉ።") (ተመልከት፡ ሆይን) ።
አጋዕዝተ ኪነት፡ የእጅ ጥበብ ጌቶች (ባለያዎች) ።
አጋዕዝት፡ ጌቶች (ነገደ መላእክት ሥላሴ) ።
አጋዘ (ግእዘ/ገአዘ)፡ ግእዝ ተማረ ። "ሣር ሥንጥር ይዞ አ ግእዝ በ ግእዝ መልእክተ ዮሐንስ አለ ጕት ንባብ አነበበ ተማሪው ቍጥር ዐውቆ ያግዛል። እኔና ሞት ባንድነት ገብተን ተማሪ ቤት እኔ ገና ስቈጥር እሱ ያግዝ ዠመር" (አዝማሪ) ።
አጋዘ (ግእዘ/ገአዘ)፡ ጠላ/ነቀፈ/ሻረ/አዋረደ/እወህኒ ቤት አገባ/አሰረ/ቀጣ ። "ንጉሡ ባለሉን አጋዘው።"
አጋዘ፡ አመጣ ወሰደ ፥ —(ጋዘ) ።
አጋዘ፡ አሰረ (ጋዘ) ።
አጋዘተ፡ አዋገዘ ።
አጋዘን፡ የዱር የበረሓ በሬ የደጋ የቈላ፡ ቀንዳም ቀንደ ረዥም ። (፩ነገ ፬ ፥ ፳፫) ። ዶባን እይ ። (አጋዘን)፡ አመጣን ወሰደን አሰረን ።
አጋዛ (አስተጋዝአ)፡ አገባየ/አሻሻጠ/አሻመተ (አደራራጊ) ።
አጋዛ፡ መሬቱን ለተጋዢ ሰጠ (አድራጊ) ።
አጋዠ፡ አስረጀ/አስረሳ/አዣዠ ።
አጋዢ፡ የሚያገባይ/የሚያሻምት (የሚደጋዛ ባለርስት) ።
አጋዥ (ዦች)፡ ያጋዘ/የሚያግዝ (የሚወስድ/የሚያመጣ ወሳጅና አምጪ) ።
አጋዥ፡ ማጭድ ። ዐገዘ ።
አጋዥ፡ ረዳት፡ ዐገዘ ።
አጋዥ፡ የግዞት ሹም/አሳሪ (ሉቃ. ፲፪፡ ፻፰) ።
አጋየ፡ አጋለ = አነደደ/አቃጠለ "ጋይ አደረገ።" (ተረት)፡ "እንዳየን ጤፍ ኢጋየን።"
አጋይ፡ በጋ፡ ዐጋይ ።
አጋይ፡ ያጋለ/የሚያግል ።
አጋደ (አግሀደ)፡ ገለጠ/አሳየ።
አጋደለ (አስተጋደለ/አስተቃተለ)፡ አስተዳደነ/አማታ/አዋጋ/አተ ።
አጋደለ፡ አዘነበለ/አመዘነ/አከበደ/ደፋ/መነዘለ (ጭነትን)።
አጋደረ፡ አፋከረ/አናቀፈ ። "ተጋደረና አጋደረ አልተለመዱም።"
አጋደደ፡ አበደረ/አዋሰ ።
አጋዳ፡ አስተሳሰረ/አያያዘ ።
አጋዳይ (ዮች)፡ ያጋደለ/የሚያጋድል (ኣዋጊ "አትለውም ወይ ባይ ጋለሞታ።")
አጋዳይ፡ የሚያጋድል/የሚያዘነብል (እህያ/አጋሰስ/ወደል ጋዝ)።
አጋጅ (ጆች)፡ ያገደ የሚያግድ፡ ገቺ ከልካይ ከታሪ አሳሪ ጠባቂ እረኛ ። ከብት አጋጅ እንዲሉ ።
አጋጅ፡ የሰው ስም ።
አጋገረ፡ እንጀራን አባሰለ፡ እሳትን አቈሳቈሰ፡ ዳቦን አዳፋ።
አጋጋለ፡ አጋነነ/አነሣሣ/አዳመቀ ።
አጋጋለ፡ አጋጋመ/አቀጣጠለ/አታኰሰ ።
አጋጋል፡ አጋጋም/አቅ/መጋል ።
አጋጋመ፡ አፋፋመ/አጋጋለ/አቀጣጠለ ።
አጋጋም፡ አፋፋም/አጋጋል/መጋም ።
አጋጋተ፡ አጣጣ/አጐናጩ (የሕፃንን እጅ የጥጃን አፍ በመያዝ መጋትን ረዳ) ።
አጋጋት፡ የወተት የውሃ አሰጣጥ መ ጋት ።
አጋጋዝ፡ አወሳሰድ/አስተሳሰር (መውሰድ/ማጋዝ) ።
አጋጋይ፡ ያጋጋለ/የሚያጋግል/የሚያጋግም (አጋናኝ) ።
አጋጋጥ፡ አላላጥ/አመላለጥ/እነጫ ጨት/አበላል/መጋጥ ።
አጋጋፈ፡ አስተፋፈሠ/አጣረገ ።
አጋጋፍ፡ አጠራረግ/አጠጣጥ/መጋፍ ።
አጋጠ፡ ለከብት ሣር አበላ/እለቀመ ።
አጋጠመ፡ አቃረበ/አገናኘ/አሳካ/አዋደደ/እሰማማ/ኣጣመረ/አያያዘ/አቋለፈ/አገናዘበ/አዋረሰ (ዘፀ. ፴፮፡ ፲፯፡ ማር. ፲፡ ፱፡ ሉቃ. ፲፡ ፴፬) ።
አጋጠመ፡ አጣላ/አዋጋ ።
አጋጠመ፡ ጥርስን በከንፈር/ዐይንን በሸፋሽፍት ከደነ/አማወተ/ገነዘ ።
አጋጣሚ፡ ያጋጠመ/የሚያጋጥም (የላይ ፈሪ/የታች ፈሪ ባይ የሚያጣላ አሳባቂ ዦሮ ጠቢ አዋሻኪ ድንገተኛ ነገር አማዋችገናዥ) ።
አጋጣሚነት፡ ኣጣይነት/አማዋችነት ።
አጋጣሞች፡ አሳባቆች/ገናዦች ።
አጋጣረ፡ አለፋ/አደከሙ ።
አጋጨ፡ አጣላ/አማታ/አላተመ/አዋጋ (ኤር. ፶፩፡ ፳–፳፫) ።
አጋጭ (ጮች)፡ ያጋጠ/የሚያግጥ/የሚያበላ (አብሊ) ።
አጋጭ፡ የባልደራስ ደንብ (የመንግሥት ፈረስ በቅሎ ኣብሊና ጠባቂ ጭፍራ) ።
አጋጭነት፡ አጋጭ መኾን/ፈረስ ዘበኝነት ።
አጋጯ፡ ያጋጨ/የሚያጋጭ/የሚያጣላ (አማቺ/አላታሚ/አዋጊ) ።
አጋፈረ፡ ከለከለ ፥ —(ጋፈረ) ።
አጋፈተ፡ ገዘፈ ፥ —(ጋፈተ) ።
አጋፈተ፡ ገፈ (የዛራም) ።
አጋፈተች፡ ተጫወተች (ልጃገረዲቱ) ።
አጋፈጠ፡ ሰውን ወደ ጠብ አሳለፈ ።
አጋፈጠ፡ ወፍራም ዕንጨትን ጥፍጥፍን ጨመረ/ማገደ/ዠገደ ።
አጋፈፈ፡ ልብስን ኢቃማ ገፈፈ ።
አጋፋ (አስተጋፍዐ)፡ ግፍ አሣራ/አባደለ (ሉቃ. ፰፡ ፵፭) ።
አጋፋ፡ አናሣ ። "ይህን ጣራ እባክኸ አጋፋኝ።"
አጋፋ፡ አዳፋ (ዘፍ. ፲፱፡ ፱) ።
አጋፋ፡ አጣበበ/አጫነቀ ።
አጋፋሪ (ሮች)፡ ያጋፈረ/የሚያጋፍር (ከልካይ አስገቢና አስወጭ) ። (ተመልከት፡ የሺ አጋፋሪ - የሻምበል ምክትል አዛዥ ደጅን እይ) ።
አጋፋሪነት፡ ከልካይነት ።
አጋፋች፡ ያጋፈተ/የሚያጋፍት (የሚጋፍት ገዛፊ) ።
አጋፋጭ፡ ያጋፈጠ/የሚያጋፍጥ (ማጋጅ አንዳጅ) ።
አጌተየ፡ ኣከበረ/አላቀ/ሀብታም አደ ረገ/አስገዛ/አስነዳ/እገነነ ።
አጌጠ፡ ሸለመ (ገየጠ ጌጠ) ።
አጌጠ፡ ጸዐዳ ልብስ ለበሰ ። (ተረት)፡ "ጀንበር ሳለ ሩጥ አባት ሳለ አጊጥ።"
አግ፡ ሐግ፡ ዐገገ ።
አግለበለበ፡ ወዘወዘ ፥ —ገለበ ።
አግላይ፡ ያገለለ/የሚያገል (አራቂ) ።
አግመነመነ፡ የአገመነ ድርብ (አትከንከን) ።
አግሚ፡ ያገማ/የሚያገማ/የሚያጠነባ ።
አግማማ፡ የአገማ ድርብ (ብዙ ጊዜ አገማ) ።
አግማሪ፡ ያገበረ/የሚያገምር (የሚችል ቻይ ወሳኝ) ።
አግማጭ፡ ያገመጠ/የሚያገምጥ ።
አግምቶ፡ አበስብሶ/አበላሽቶ ። "አግምቶ በል እያገማ የሚበላ ሥ ሥታም ሰው ወይም ነብር።"
አግምን፡ ያገመነ/የሚያገምን (ልብ አንድድ አብግን) ።
አግሪ (ሐረር)፡ ዝኒ ከማሁ ።
አግሪ (ትግ ሐባ)፡ መንገደኛ ።
አግራሪ፡ ያገረረ/የሚያገር/የሚያሠማ (አሥሚ ጯኺ አቅራሪ ሸላይ) ።
አግራራ፡ አለዛዘበ ።
አግራፍ (ፎች)፡ ከቀጪን ብረትና ከንሓስ ሽቦ ከሌላም የተበጀ የልብስ የእጀ ጠባብ የኮት የካባ ቍልፍ ማያያዣ ።
አግሬ (ዘአግር አግራዊ)፡ ዝኒ ከማሁ ለአግር ቁመት ሙሉ ጋሻ ። አላባሽ አግሬ እንዲሉ ። ዣግሬን ተመልከት ።
አግሬ ባላ (ባላ አግሬ)፡ የአግሬ ባላ፡ የጋሻ መስቀያ ሽመል ነፍጠኛ ይዞት የሚዞር፡ ዐንካሴ ያለው ባለብዙ ሜንጦ ማነጣጠሪያ፡ ሥጋ ማንጠልጠያ ።
አግሬ፡ የአግር ባለአግር ጋሸኛ ።
አግሬዎች፡ ሰፋፊዎችና ረዣዥሞች ጋሾች ።
አግር (ወልታ)፡ ታላቅ ጋሻ የአጋር ያርበኛ መከታ ከለላ ።
አግርዴ፡ የሰው ስም ።
አግርድ፡ ግርድ አውጣ ።
አግሺ፡ ያገሣ/የሚያገሣ ።
አግበሰበሰ፡ ልብስን ጐተተ/አክበሰበሰ ።
አግበሰበሰ፡ ሰበሰበ፡ (ጋበሰ) ።
አግበሰበሰ፡ የአጋዐሰ ድርብ (አብዝቶ ሰበሰበ)።
አግቢ፡ የሚያገባ፡ ሚስት የሚያመጣ፡ አምጪ ።
አግቢ ፈቺ፡ ባንዲት ሴት የማይረጋ ወረተኛ ወንድ ።
አግባ (አግብእ)፡ ክተት ዱል ጨምር፡ ወደ ኋላ በል ።
አግባ መልስ አለ፡ ከሸሸ ካፈገፈገ በኋላ፡ ጠላትን ተቋቋም ውጋ አለ ።
አግባቢ፡ ያግባባ የሚያግባባ፡ ጐትጓች፡ በል በል የሚል ።
አግባባ፡ አድርግ አድርግ አለ፡ ጐተጐተ አስደፈረ ።
አግባብ፡ መግባት አገባብ፡ የመግባት ምክንያት ።
አግባብ፡ ዕውቂያ ልማድ ወዳጅነት ። እከሌ እከሌ ቤት አግባብ የለውም ።
አግቦ (አግብኦ ት)፡ አሽሙርና ለበጣ ነገር፡ በራስ አስመስሎ ሌላውን መስደብ ። ምፀትን እይ ።
አግቦ፡ ስድብ፡ ፡ ገባ ።
አግቦኛ (ኞች)፡ አሽሙረኛ፡ ባላግቦ አግቧም ።
አግተለተለ፡ አቅጠለጠለ፡ (ገ ተለ) ።
አግተልታይ፡ ያግተለተለ/የሚያግተለ ትል (አቅጠልጣይ) ።
አግተመተመ፡ አምታታ/አገላተመ/አ ጋጨ ዕቃን ከዕቃ ።
አግተመተመ፡ አገላተመ፡ ገተመ ።
አግተምታሚ፡ ያግተመተመ/የሚያግተ መትም (አገላታሚ) ።
አግተረተረ፡ አውተረተረ/አንገደገደ ።
አግተረተረ፡ የገተረ ድርብ (ብዙ ጊዜ ገታተረ የመትን የሥር የዥማት የቋን) ።
አግናኝ፡ ያገነነ/የሚያገን ።
አግኚ፡ ያገኘ/የሚያገኝ (ያዥ) ።
አግዓዚ፡ ጌታ (ነጻ አውጭ ነገደ ለኵሽ ከመገዛት ሬሱን ነጻ ያወጣ) ።
አግዓዝያ/አግዓዚት፡ ሐበሻ የአግዓዚ አገር ።
አግዛፊ፡ ያገዘፈ/የሚያገዝፍ/የሚያጐላ (አጕሊ ረቂቁንና የሩቁን አጕልቶ የሚያሳይ መነጥር) ።
አግዝ (ዞች)፡ ገብረ ጕንዳን (የእኸልን ቅንጣት ከሜዳ ወደ ጕድጓድ የሚያ ግዝ)። "በግእዝ 'ቃሕም' ይባላል።"
አግዝ፡ ገብረ ጕንዳን ፥ —(ጋዘ) ።
አግዠለዠለ፡ ጐተተ፡ (ገዠለ) ።
አግደረደረ፡ አኰራ/አስታበየ/አስገበዘ/ወላዋይ አደረገ ።
አግደርዳሪ፡ ያግደረደረ/የሚያግደረድር/የሚያኰራ (አኵሪ) ።
አግደው፡ ጠላትን ግታው ከልክለው ።
አግዳሚ፡ ኩትኛ/አጣፊኝ ሸማ ዝቅዝቅ ያይዶለ ።
አግዳሚ፡ የመቂናጦች መንጠልጠያ (አጣና በ፪ ባላ ላይ የተቀመጠ)።
አግዳሚ፡ የግድግዳና የጣራ ማገር በምስማር አግድም የሚመታ ።
አግዳሚ፡ ያገደመ/የሚያገድም (መንገድ አቋርጦ አግድሞ የሚያልፍ)። "ዐላፊ አግዳሚ" እንዲሉ።
አግዳሚ፡ ጫፍና ጫፉ ዋልታ ያለበት የድንኳን ሠረገላ ።
አግዳማ፡ ዘዋሪ አውራ ፍየል የማንንም መንጋ ተከትሎ ለስሪያ የሚያገድም ።
አግዳማይ (ዮች)፡ የአግዳማ ዐይነት/ወገን (ዞሮ ተመልሶ እወጣበት ቤት የሚገባ)።
አግዳጅ፡ ያገደደ/የሚያገድ (አጥማሚ)።
አግዳፊ፡ ያገደፈ/የሚያገድፍ (ጦም አስጣይ/ሥጋ እብለ)።
አግዴ፡ የሰው ስም፡ ከልክሌ ጠብቄ ወስኔ ።
አግድ፡ ትእዛዝ አንቀጽ፡ ከልክል ጠብቅ፡ ሐይ በል ። ወለደ ብለኸ ወለድን እይ ።
አግድም/አግድመት፡ ጐን (የቀኝ ወይም የግራ ስፍራ ሽቅብና ቍልቍል ቀጥታ ያልኾነ) ።
አግድሞ አየ፡ በንቀት ተመለከተ ።
አግድሞ አደግ፡ ባለጌ ያልተቀጣ ዕገውጡ መረን ስድ ።
አግድሞ/አግድሞሽ፡ ዝኒ ከማሁ ።
አግጀለጀለ፡ ጐተተ፡ (ገዠለ) ።
አግፈለፈለ፡ አፈላ፡ (ገፈለ) ።
አግፈልፋይ፡ ያግፈለፈለ/የሚያግለፈልፍ ።
አግፈጠፈጠ፡ አጨሰ/አጫሰ/አነደደ ።
አጐለ (ሀጕለ)፡ አጠፋ ፥ አወከ ፥ እሰ ናከለ ።
አጐለመሰ፡ እጐረመሰ/አጐበዘ/አጸና/አበረታ ።
አጐለማመስ፡ አጐባበዝ/አበረታት/መጐልመስ ።
አጐለሳሰስ፡ አጣጣል/አጨቋቈን/መጐልሰስ ።
አጐለበ፡ ሽንብራን ከእንቡጥ/አሹቅን ከገለባ አወጣ/ጠረጠረ/አወለበ ። (ተመልከት፡ ቀለበን የአጐለበ ዘር ርሱ ነው) ።
አጐለበተ፡ ጕልበታም አደረገ/አበረታ ።
አጐለባበት፡ አበረታት/መጐልበት ።
አጐለደመ (ጐለደመ)፡ አፈነገጠ/አፈጠጠ ።
አጐለደፈ፡ አደነዘ/አላሸ/አዶለዶመ ።
አጐለዳደም፡ አለያየት/መጐልደም/ማናጋት ።
አጐለዳደፍ፡ አደናነዝ/መጐልደፍ ።
አጐላ (አጕልሐ)፡ ጕልሕ አደረገ/አገዘፈ/ኣወፈረ ።
አጐላለል፡ የጕልላት አሠራር/አጫጫን (የክዳን አጨራረስ/መጐለል) ።
አጐላለም፡ አከፋፈል/መጐለም ።
አጐላለብ፡ ኣለጓጐም/መጐሰብ ።
አጐላለት፡ ኣተካከል/አከላለል/መትከል/ማቆም ።
አጐላል፡ አገዛዘፍ/መጕላት ።
አጐላመሰ፡ አዳመቀ/አዳራ/አበራታ/አጋነነ ።
አጐላማሽ፡ ያጐላመሰ/የሚያጐላምስ (ተጨማሪ ፊደልና ቃል ማ ለካ አኮ) ። "እኔማ ለካ እንዲህ ኑሯልን አንተ እኮ።" "ይኸውም ንኡስ አገባብ ነው።"
አጐላጐለ፡ አቈናጩ/አላቀመ ።
አጐላጐለ፡ አናናደ/አተራተረ/አበለሻሸ ።
አጐላጐለ፡ አዋጣ/አዘካዘከ ።
አጐላጐል፡ አቈነጫጨት/አለቃቀም/መጐልጐል ።
አጐልማሽ፡ ያጐለመሰ/የሚያጐለምስ (አጐባዥ) ።
አጐልባች፡ ያጐለበተ/የሚያጐለብት (አበርቺ) ።
አጐመላለል፡ አቈናነን/መጐማለል ።
አጐመራር፡ አበሳሰል/አገረጣጥ/መጐምራት ።
አጐመዘዘ፡ ጐምዛዛ አደረገ/አመረረ ።
አጐመዛዘዝ፡ አመራረር/መጐምዘዝ ።
አጐመዠ (አመነየ)፡ አሠየ/አቋመጠ/አቃረ ።
አጐመዣዠት፡ አሠያየት/መጐም ።
አጐመጐመ፡ አበቀለ ጐመ ጐመ ።
አጐመጐመ፡ አወጣ/አበቀለ ።
አጐማለለ፡ ቈነነ/አኰፋነነ ።
አጐማመር፡ አነፋፍ/አስተባበጥ/መጐመር ።
አጐማመደ፡ አቈራረጠ/አበጣጠሰ/እለያየ ።
አጐማመድ፡ አጐራረድ/መጕመድ ።
አጐማማጅ፡ ያጐማመደ/የሚያጐማምድ (አቈራራጭ አበጣጣሽ) ።
አጐምዢ፡ ያጐመዠ/የሚያጐመዥ ።
አጐሰቈለ፡ ብላሽ አደረገ/አጠፋ/ጐዳ/አከሰረ (የሰው በታች አደረገ) (ምሳ. ፲፱፡ ፲፱፡ ሰቈ. ፭፡ ፲፩፡ ግብ. ሐዋ. ፳፬፡ ፭) ።
አጐሰቋቈለ፡ አበለሻሸ ።
አጐሰቋቈል፡ አከሳስ/አጠቋቈር/መ ጐስቈል ። (ተመልከት፡ በሰቈለን እይ ከዚህ ጋራ አንድ ነው) ።
አጐሳሰም፡ አመታት/መጐሰም ።
አጐሳሰር፡ አመላል/መጐሰር ።
አጐሳቈለ (አጐሰቈለ)፡ አጣቈረ/እ በላሸ/አዋረደ (፩መቃ. ፲፱፡ ፱) ።
አጐሳጐስ፡ አጐራረሥ/መጐስጐስ ።
አጐስቋይ፡ ያጐሰቈለ/የሚያጐስቍል (አጥፊ አዋራጅ) ።
አጐረ (አጊር አገረ)፡ በቁሙ፡ ሰበ ሰበ አከማቸ ዐጀበ፡ አወናከረ ዘጋ፡ የንጨት የከብት የገንዘብ ። ክፉ ተናገረ ተከራከረ ።
አጐረማመስ፡ አጐለማመስ/መጐርመስ ። "ጐረመሰ የሕዝብ ጐለመሰ የካህናት ነው።"
አጐረሠ፡ ባፍ ልክ መብልን ለሠራ ተኛ ጥቂት ገንዘብ ጥሬ እኸልን ለወፍጮ ሰጠ (መዠመሪያ ፈጨ ከረተፈ ሸመሸመ ጤፍን) ። (ተመልከት፡ ገሣ ብለኸ አገሣን እይ) ።
አጐረሠ፡ ጠመንዣን ለጐመ (ጥይት ቀረቀረ) ።
አጐረበ፡ አረገበ/አሳበጠ/አቈረበ (በቀላል ወቀጠ ነደፈ አኼደ) ።
አጐረባበጥ፡ አቈራቈር/አወጋግ/መጐርበጥ ።
አጐረና፡ አቀረና/አበላሸ ።
አጐረናን፡ አቀረናን (አበለሻሸት መጐርናት) ። (ተመልከት፡ ገለማን እይ) ።
አጐረደመ፡ አቈረጠመ ።
አጐረዳደም፡ አቈረጣጠም/መጐርደም ።
አጐረጠ፡ ዐይኑን አወጣ/አፈጠጠ ።
አጐረፈ፡ ልብስን ዐጠበ (እንዶድን ሳሙናን ለማውጣት) ።
አጐረፈ፡ ቅቤና ድልኸ ቀላቀለ (ደ ባለቀ አዋሐደ ዐሸ በጠበጠ ባንድነት መታ) ።
አጐረፈ፡ ጐርፍ አደረገ (ኣወረደ አፈሰሰ ዝናቡ) ።
አጐራ አጓራ፡ በጕረሮው ጮኸ ፥ —(ጐራ ጓራ) ።
አጐራ፡ ገዘፈ (ሂያ ሂያ አለ "ዛሬ ሌሊት እከሌ ዛር ፈልቆበት ሲያጐራ ዐደረ።") (ተመልከት፡ ጋረን ተመልከት) ።
አጐራ/አጓራ፡ በጕረሮው ጮኸ ። "ሲጠባ ያደግ ጥጃ ቢይዙት ያጓራል በሬው ስለ ታረደ ያጓራል ከብቶቹ በፈርስ ላይ ያጓራሉ (ያለቅሳሉ)።"
አጐራረሠ፡ ጕርሻ አቀባበለ/አመጋ ።
አጐራረሥ፡ አበላል/አከረታተፍ/መጕ ረሥ/ማጕረሥ ። (ተመልከት፡ ሳበ ብለኸ ሳቢ ዘርን እይ) ።
አጐራረብ፡ አረጋገብ/አቈረባበጥ/መጕረብ ።
አጐራረድ፡ አቈራረጥ/አፈታተግ/ኣዘ ለል/መጕረድ ።
አጐራረጥ፡ አወጣጥ/አፈጣጠጥ/መጕረጥ/ማጕረጥ ።
አጐራረፍ፡ አወራረድ/አፈሳሰስ/አስ ተጣጠብ/መጕረፍ ።
አጎራበተ (አስተጋወረ)፡ ጐን ለጐን ዐጥር ለአጥር በቀኝ በግራ በፊት በኋላ ጎረቤት አደረገ (አኳዃነ አቃረበ አኗኗረ) ። "ትግሬም አጎርበተ ብሎ አፈናጠጠ ይላልና አቃረሰ ካለው ይገባል።"
አጎራበተ፡ አቃረበ ፥ —ጎረቤት ።
አጎራባች፡ ያጎራበተ/የሚያጎራብት (አቃራቢ) ።
አጐራጐረ፡ አፋተሸ/ኣበራበረ/አፋ ።
አጐራጐር፡ አበራበር/አፈላለግ/መጐርጐር ።
አጐሸ፡ አደፈረሰ ።
አጐሸመጠ፡ ብጫ መስሎ መብቀል ዠመረ (ብቅ አለ ብቋያው) ። "ርግጠኛው ትር ጓሜ ግን አበቀለ ነው" ።
አጐሸማመጥ፡ አጐናነጥ/መጐሽመጥ ።
አጐሻመጠ፡ አናካ/አጓነጠ/አናጠበ ።
አጐሻሸም፡ አደሳሰቅ/መጐሸም ።
አጐበራረር፡ አደራረቅ/አጐባበጥ፡ መጐብረር/መድረቅ ።
አጐበር፡ በቁሙ፡ ጐበረ ።
አጐበበ፡ ጐባባ አደረገ።
አጐበተ፡ ጕበት አበጀ ።
አጐበኛኘ፡ አጠያየቀ፡ አፈቃቀደ ።
አጐበኛኘት፡ አስተያየት፡ አፈቃቀድ፡ አሰላለል፡ መጐብኘት።
አጐበዘ፡ ኣጐለመሰ፡ አበረታ፡ አጠና፡ እጠነከረ ።
አጐበደደ፡ አጐነበሰ፡ አጐበጠ፡ አፈነደደ ።
አጐበደደ፡ አጐነበሰ፡ ጐበደደ ።
አጐበዳደድ፡ አጐባበጥ፡ አጐነባበስመ ጐብደድ።
አጐበጐበ፡ አብሲት ጨመረ፡ ጐበጐበ ።
አጐበጐበ፡ አብሲትን ከቡሖ ደባለቀ።
አጐበጐበ፡ እቈበቈበ፡ አቶከቶከ፡ አረገደ ።
አጐበጠ፡ አጐነበሰ፡ እዘባ፡ ደጋን አደረገ፡ ቀለሰ/መለሰ/ቀሰተ።
አጐባበል፡ አቀማመጥ፡ ማስቀመጥ ።
አጐባበዝ፡ አበረታት፡ አጠናን፡ መጐብደድ ።
አጐባበጥ፡ አጐነባበስ፡ አዘባብ፡ መጕበጥ ።
አጐባኘ፡ አጣየቀ፡ አፋቀዶ ።
አጐባዥ፡ የሚያጐብዝ፡ የልብ ልብ የሚሰጥ ።
አጐባጐበ፡ አማታ፣ አዳሰቀ፣ አጓሸመ።
አጐባጐበ፡ ዶቄትና አብሲት አመረ፡ አላወሰ።
አጐባጐብ፡ አሸላለም፡ መጐብጐብ፡ ማጐብጐብ፡ መጨመር፡ መደባለቅ።
አጐባጓቢ፡ የሚያጐባጕብ፣ አዳሳቂ።
አጐብዳጅ (ጆች)፡ ያጐበደደ/የሚያጐበድድ፡ አጐንባሽ፡ አዘንባይ።
አጐብጓቢ፡ ያጐበጐበ/የሚያጐበጕብ፡ ኣቈብቋቢ፡ አቶክቷኪ፡ አርጋጅ።
አጐብጓቢነት፡ አቈብቋቢነት፡ አቶክቷኪነት።
አጐተነ፡ አሳደገ/አጐፈረ/አበጠረ/መየደ/አቆመ (ጐሚት እስመሰለ) ።
አጐተነ፡ አጐፈረ ፥ —ጐተነ ።
አጐታተት፡ አሳሳብ/መጐተት ።
አጐታተን፡ አስተዳደግ/አረዛዘም/ማ ጐተን ።
አጐታኝ፡ የሚያጐትን መያጅ ።
አጐታጐተ፡ አቻኰላ/አዘባዘበ/እነሣሣ ።
አጐታጐት፡ አወታወት/መጐትጐት ።
አጎት (ቶች)፡ ያባትና የእናት ወንድም ። (ዘሌ ፳ ፥ ፳) ። አጎት ከአኮ፡ ኣኮ ከአኅ የወጣ ነው ። ኣኮን እይ ።
አጐቻቸት፡ አከማመር/መጐቸት ።
አጐነቈለ፡ ኣበቀለ/አወጣ/አፈጠጠ ።
አጐነቋቈል፡ አበቃቀል ሙጐንቈል ።
አጐነበሰ፡ ዐንገቱን ደፋ/አቀረቀረ/እዘነበለ ።
አጐነታተል፡ አጐናነጥ/አነካክ/አገፋፍ/መጐንተል ።
አጐነታተር፡ አቈነጣጠር/መጐንተር ።
አጐነደ፡ ኣወፈረ/አደነደነ ።
አጐነደ፡ ጐናዴ አደረገ (ጐዦ አወጣ) ።
አጐነዳደል፡ አሰላለብ/አሰነጋግ/መጐ ።
አጐናተረ፡ ኣቈናጠረ/አበሳ/አስቈጣ ።
አጐናነበ፡ አከናነበ/አጐናጸፈ/ጀቦነ ።
አጐናነጥ፡ አደፋፈር/አነካክ/መጐነጥ ።
አጐናነፍ፡ አስተጣጠብ/አስተጃጀል/አቀራረጽ/አደጓጐስ/መጐነፍ ።
አጐናዘለ፡ አዘናፈለ ፥ —ጐነዘለ ።
አጐናዘለ፡ አዘናፈለ/አቈላዘመ ።
አጐናጅ፡ ያጐነደ/የሚያጐንድ (አባት ዘመድ) ።
አጐናጐነ፡ አታታ/አቋነነ/አቈላለፈ/አጠላለፈ/ኣዋሰበ/አወሳሰበ ።
አጐናጐን፡ አጠላለፍ/ኦጠማመር/መጐንጐን ።
አጐናጓኝ፡ ያጐናጒነ/የሚያጐናጕን ።
አጐናጠፈ፡ አለበሰ/አከናነበ ።
አጐናጣፊ፡ ያጐናጠፈ/የሚያጐናጥፍ ።
አጐናጸፈ፡ አጐናጠፈ ።
አጐናፈረ፡ እንዳፈር እንደ ራስ ጠጕር አብዝቶ በላይ በላዬ ቤት ሙሉ ሰጠ (አለልክ ቸረ ለገሰ) ።
አጐናፍር፡ የሰው ስም ፥ —(ጐነፈረ) ።
አጐናፍር፡ የሰው ስም (ሀብታም ልጅ ቸር ዕድሉ እንደ ጐርፍ እንደ ዠማ የኾነ) ። "ያቶ እከሌ ቤት አጐናፍር ነው" እንዲሉ ።
አጐንቋይ፡ ያጐነቈለ/የሚያጐነቍል (አብቃይ) ።
አጐንባሽ (ሾች)፡ ያጐነበሰ/የሚያጐንብስ (እንስሳ ሰው) ። "ዐፋሽ አጐንባሽ" እንዲሉ ።
አጐንብሶ፡ አቀርቅሮ ። "አጐንብሶ የሚህላን ተኝተኸ ቀላውጠው።"
አጐዘለ፡ ናቀ ፥ —ጐዘለ ።
አጐዘለ፡ ኣኰሰሰ/ናቀ/አቀለለ ።
አጐዛ፡ ደበሎ ፥ —ዐጐዛ ።
አጐዛይ፡ ያጐዘለ/የሚያጐዝል (ኣኰሳሽ/ናቂ/አቅላይ) ።
አጐዛጐዘ፡ አነሳነሰ/አናጠፈ ።
አጐዛጐዝ፡ አበታተን/አነሳነስ/መጐዝጐዝ ።
አጐዛጓዥ፡ ያጐዛጐዘ/የሚያጐዛጕዝ ።
አጐደለ (ዘፀ. ፲፬፡ ፳፩)፡ አሳነሰ/ቀነሰ/ነቀሰ/ቀመጠለ/አስቀረ/አጐዳ ። "ቃሉን አጐደለ" (የተናገረውን አልፈጸመም)።
አጐደነ፡ ወደ ጐን አስኬደ/ጐድን አለ ።
አጐደጐደ፡ ማሰ/ቈፈረ/ፋረ/ሸረሸረ/ጐደበ (ውሃ/ሰው/መሬትን) (ዘኍ. ፳፩፡ ፲፰) ።
አጐደፈ፡ ጦምን አስተወ/ሥጋ አበላ ።
አጐደፈ፡ ፍግ/ፋንድያ/በጠጥ አፈሰሰ/አፋፃ/አረከሰ/ስም አጠፋ/አሳደፈ ። (ተመልከት፡ ኰለፈን) ።
አጐደፋፈር፡ አማማስ/መጐድፈር።
አጐዳ (ጐድዐ/አጕድዐ)፡ ጐዳ/አስጐዳ ።
አጐዳ፡ ሰኰና ጐዳ ።
አጐዳ፡ አጐደለ። "ጮሌውን በሠጋር ብለውጠው አያጐዳኝም" (አንቀጽ) ።
አጐዳኘ፡ ከብትን አዛወረ/ኣስገለለ።
አጐዳደለ፡ ቀናነሰ/ነሣሣ።
አጐዳደል፡ አስተናነስ/መጕደል።
አጐዳደብ፡ አማማስ/አቈፋፈር/መደብ ። "ትግሬም 'ጐደበን' ደነዘ ይለዋል።"
አጐዳደፍ፡ አስተዳደፍ/መጕደፍ።
አጐዳዳ፡ እበዳደለ።
አጐዳድ፡ ክፉ አመታት/መጕዳት።
አጐዳጐድ፡ አከታተት/መጐድጐድ/መክተት/ማጐድጐድ።
አጐድጓጅ፡ ያጐደጐደ/የሚያጐደጕድ (ማሽ ቈፋሪ) ።
አጐዶ፡ በውስጡ ሊጥ እየለጠፉ ቂጣ የሚጋግሩበት ሸክላ (የዘላን ምድጃ) (ዘሌ. ፪፡ ፬)።
አጐዶ፡ እሳት/ከሰልና ብረት የሚገባበት የጠይብ ጕድጓድ ።
አጐዶ፡ የማታምር ሴት አፍንጫ ጐራዳ - ደፍጣጣ። "እኸል ከባዶ ልጅ ከአጐዶ" እንዲሉ።
አጐዶ፡ የከሰል ጕድጓድ ፥ —ጐ ደጐደ ።
አጐጠጐጠ (አቈጠቈጠ)፡ አወጣ/አበቀለ/አጐመጐመ ።
አጐጠጐጠ፡ አበቀለ፡ ጐጠጐጠ ።
አጐጠጐጤ፡ በደረቷ ጡት ያወጣች ያበቀለች የአሥራ አምስት ዓመት ልጃገረድ ።
አጐጠጐጤ፡ አጐጥጓጭ (ያጐጠጐጠ/የሚያጐጠጕጥ ያፍለኛ ሴት ልጅ ደረት) ።
አጐጠጠ (አቍጠጠ)፡ "ምን ይመስላል አለ ፊቱን አጠቈረ ግንባሩን ቋጠረ አሳነሰ የሰው በታች አደረገ አኰሰሰ ናቀ አቀለለ።"
አጐጠጠ፡ ናቀ ፥ —ጐጠጠ ።
አጐጣጐጥ፡ ኣመዛዘዝ/መጐጥጐጥ።
አጐጣጭ (ጮች)፡ ያጐጠጠ/የሚያጐጥጥ (አኰሳሽ/ናቂ) ።
አጐጤ (ዎች)፡ ልጃገረዲቱ ወይም ጕጥ የሚመስለውና ያልወደቀው ጡቷ ። "አጐጤ የአጐጠጐጤ ከፊል ነው።"
አጐፈረ፡ አጐተነ ፥ —ጐፈረ ።
አጐፈረ፡ ጠጕሩን አሳደገ/አረዘመ/አጐተነ/መየደ/አበጠረ ።
አጐፈነነ፡ አመረረ/አቀየመ/አከፋ/ፊትን አኮሳተረ ።
አጐፈየ፡ አከሳ (ጕፋያ አደረገ) ።
አጐፈጣጠጥ፡ ኣረጃጀት/መጐፍጠጥ ።
አጐፋሪ፡ ያጐፈረ/የሚያጐፍር (አጐታኝ) ።
አጐፋፈር፡ አረዛዘም/መጐፈር ።
አጓለበ፡ አንገዋለለ (ከላይ ከላይ አነሣ የሣር የገለባ) ።
አጓለተ፡ አቋቋመ/አጠማዘዘ/አታከለ/አካለለ ።
አጓመተ፡ አጓመደ/አቋረጠ/አካፈለ ።
አጓመደ፡ አማታ/አደባደበ ።
አጓመደ፡ አቋረጠ/አጓረደ/አባጠሰ/አሳለበ (ለያየ) ።
አጓመጠ፡ ባፉ ሙሉ ይዞ ዐኘከ/በላ እንደ ከብት ።
አጓመጠ፡ ዐኘከ ጓመጠ ።
አጓማጭ (ጮች)፡ ያጓመጠ/የሚያጓምጥ (የሚያኝክ ዐኛኪ) ።
አጓረሠ፡ ኣባላ አማገበ/አከራተፈ/አ ሸማሸመ/አፋጩ ።
አጓረበ፡ አራገበ/ኣጨማደደ ።
አጓረፈ፡ አስተጣጠበ/አስተሻሸ ።
አጓሪ፡ ያጐረ የሚያጕር፡ ሰብሳቢ አከ ማቺ ዘጊ፡ የጭቃ ሹም ምክትል ቱኪ ።
አጓሸመ፡ አዳሰተ/አዳሰመ ።
አጓበበ፡ ዳር ዳር አለ፡ ጐበበ ።
አጓበበ፡ ዳር ዳር እለ፡ አጊጦ ታየ (ሐዋ. ፳፭፡ ፳፬)።
አጓበጠ፡ አቃለሰ፡ አዛባ።
አጓባቢ፡ ያጓበበ/የሚያጓብብ "እዩኝ"
አጓተተ፡ አሳሳበ/አዋሰደ ።
አጓታች፡ ያጓተተ/የሚያጓትት (አሳ) ።
አጓት፡ የወተት ውሃ ያይብ ቅራሪ ። (ተረት)፡ አጓቱን ሲያዩት ዐይቡን ጨለጡት ።
አጓዘ፡ ቀስ ብሎ ወሰደ ፥ —(ጓዘ) ።
አጓዥ (አግዓዚ)፡ ያጓዘ/የሚያጕዝ/የሚያዘግም (አዝጋሚ) ።
አጓይ፡ ያጐለ የሚያጕል፡ የሚያጠፋ፡ አጥፊ አዋኪ አሰናካይ ።
አጓደለ፡ ኣስተናነሰ/አቀናነሰ/አቆመ/አቋረጠ ።
አጓደደ፡ አኰራ ፥ —ጓደደ ።
አጓደደ፡ አኰራ/አስደገገ/አስታበየ ።
አጓደፈ፡ ጕድፍ አፋሰሰ/አፋፋገ/አስተዳደፈ/ኣራከሰ ።
አጓዳ፡ ኣባደለ።
አጓዳይ፡ ያጓደለ/የሚያጓድል/የሚያቋርጥ ።
አጓዳጅ፡ የሚያጓድድ (አዙሪ/አስደጊ) ።
አጓጒ፡ ያጓጓ/የሚያጓጓ (አሳይቶ ነሺ) ።
አጓጐለ፡ አድበለበለ/አረጋ/ቋጠረ ።
አጓጐታም፡ አጓጐት የወጣበት/ያለበት ።
አጓጐት፡ ቋቍታ፡ ጓጐት ።
አጓጐት፡ ዝኒ ከማሁ።
አጓጓ (አጐጕአ)፡ አሠየ/አጐመዠ/አሳይቶ ነሣ/አሣቀቀ "ላይሰጥ እሰጣለኹ አለ።"
አጓጓዘ (አስተጋዐዘ)፡ አዛገመ/አዘጋገመ ።
አጓጓዝ፡ አዘጋገም/ማዝገም (የሰራዊት የጌትነትና የሕመም የድካም አካኼድ) (ዘኍ. ፴፫፡ ፩) ።
አጓጓዥ፡ ያጓጓዘ/የሚያጓጕዝ (አዛጋሚ/አዘጋጋሚ) ።
አጓጓይ፡ ሴት መንገድ ሊጥን ጭንን የምታጓጕል/የሚያጓጉል ።
አጠለለ (አጥለለ)፡ አረጠበ/አራሰ ።
አጠለለ (አጽለለ)፡ አሰፈፈ/አተለለ/አቀረረ/ለየ/አጠራ ("ቀስ ብሎ ቀዳ የጠላ የቅቤ የቅባ ኑግ አሰፈፈ ማለት መቅጃውን (አንኮላውን) ያሳያል") ።
አጠለሰ፡ አጠቈረ/አከሰለ/አጠፋ ("ዐ መድ አደረገ") ።
አጠለቀ፡ ለበሰ/አለበሰ ።
አጠለቀ፡ አስታረበ/አገባ ።
አጠለቀ፡ አረቀቀ ።
አጠለቀ፡ አዘለቀ/አሰጠመ/አዘቀጠ ።
አጠለቀ፡ አጐደጐደ ።
አጠለቀ፡ ዋጠ ።
አጠላ (አጽለለ)፡ ጥላ ጣለ/ገተረ/ወጠረ/ዘረጋ/ረበበ ("ፀሓይን ከለለ ጋረደ") ።
አጠላለል፡ አከላለል/ማጥለል ።
አጠላለም፡ አጠቋቈር/አሰጣጠም/መጥለም ።
አጠላለስ፡ አከሳሰል/መጥለስ ።
አጠላለቀ፡ ለባበሰ ።
አጠላለቀ፡ አገባባ/አሰጣጠመ ።
አጠላለቅ፡ አዘላለቅ/አገባብ/አለባበስ
አጠላለዝ፡ አጠላለስ ("መድከም") ።
አጠላለፈ፡ አወሳሰበ/አቈላለፈ ።
አጠላለፍ፡ አሰረጃጀት/መጥለፍ ።
አጠላላ፡ አነቃቀፈ/አሰለቻቸ ።
አጠላላፊ፡ ያጠላለፈ/የሚያጠላልፍ ("አቈላላፊ") ።
አጠላል፡ አነቃቀፍ/መጥላት ።
አጠልጣይ፡ አዋሻኪ ።
አጠልጣይ፡ የሥሥ ሞራ ከረጢት ሆድ ዕቃ ዐቃፊ ።
አጠመላለል፡ አቈለማመም/መጠምለ ።
አጠመመ፡ ጠመዘዘ/አገደደ ("ፊትን መንገድን") (ምሳ. ፪፡ ፲፭፡ ኤር. ፫፡ ፳፩፡ ሰቈ. ፫፡ ፱) ።
አጠመሳሰስ፡ አለጣጠስ/መጠምሰስ ።
አጠመቀ (አጥመቀ)፡ በሰው/በዕቃ ላይ ውሃ አፈሰሰ ("በውሃ ነከረ ዘፈቀ ዐጠበ አጠመቀ ክርስትና ኣነሣ") ።
አጠመዛዘዝ፡ አከራረር/መጠምዘዝ ።
አጠመደ (አፅመደ)፡ ወጥመድ አዘ ጋጀ ("ሸምቀቆ አበጀ ሸሸገ አኖረ") ።
አጠመደ፡ ወጥመድ አዘጋጀ፡ ጠመደ ።
አጠማ (አጽምአ)፡ ጠመዘዘ/ጠመቀ/ ወመቀ/አመጠጠ ("የውሃንና የወጥን እንጥፍጣፊ አራቀ") ።
አጠማ፡ ምአ)።
አጠማ፡ ጠመዘዘ ።
አጠማለለ፡ አቈላመመ ።
አጠማመም፡ ኣወለጋገድ/መጥመም ።
አጠማመረ፡ አገነኛኘ ("አንድ አኳዃነ አጠማመደ") ።
አጠማመር፡ አጠማመድ/መጠመር ።
አጠማመቅ፡ አበጣበጥ/አጠመዛዘዝ/ መጥመቅ ።
አጠማመደ፡ ፪ ፫ ጊዜ አጠመደ ።
አጠማመደ፡ አቈረኛኘ/አስተሳሰረ ("አጠላላ") ።
አጠማመድ፡ አቈረኛኘት/መጥመድ/ማ ጥመድ ።
አጠማማጅ፡ ያጠማመደ/የሚያጠማ ምድ ።
አጠማም፡ መጥማት/መጠማት
አጠማረረ፡ አጠረረ ("አለፋ አደ ከመ አጣወረ") ።
አጠማዘዘ፡ አዘዋወረ/ኣጋመደ/አጣመመ/አካረረ ("መጠምዘዝን ረዳ የልብስን ' ውስጥ ውሃ አፋሰሰ") ።
አጠማዛዥ፡ ያጠማዘዘ/የሚያጠማዝዝ ("ያጣቢ ረዳት") ።
አጠማጠመ፡ አሸባለለ/አጠቃለለ ("ሻሽ አስተሳሰረ") ።
አጠማጠም፡ አደማመር/መጠምጠም ።
አጠሳሰቅ፡ ኣወጣጠቅ/መጠሰቅ ።
አጠረ፡ ዐጪር ኾነ፡ ዐጠረ።
አጠረሰ (አፅረሰ)፡ ቸረቸመ/ሰበረ/ሸ ረፈ/አደነዘ (ኤር. ፴፩፡ ፳፱, ፴፡ ሕዝ. ፲፰ = ፪) ።
አጠረቀመ፡ አሸረጠ፡ ጠረቀመ።
አጠረቀመ፡ አገለደመ/አሸረጠ/አሸነፈጠ ("ሸብ አደረገ ወርቅ አጠርቅሞ መስ ቀል ተሸክሞ እንዲሉ") ።
አጠረቃ፡ አሻረ/ኣሻለ ።
አጠረቃቀመ፡ ሰባሰበ/አከመቻቸ ።
አጠረቃቀም፡ ኣወጋግ/መጠርቀም ።
አጠረቃቅ፡ አገጋገም/መጠርቃት ።
አጠረኘ፡ አጐለመሰ/አጠነከረ ።
አጠራ (አጽረየ)፡ ጥሩ አደረገ/አጠለለ ።
አጠራ፡ ስም ዐደሰ ("ጥሩ ነሽ አለ አከበረ ሰየመ በደግ ስም ጠራ ካህናት ግን ጸራ ኣጸራ ይላሉ") (ኢሳ. ፵፰፡ ፲፮) ።
አጠራ፡ ትምርትን/ቋንቋን በትክክል ዐወቀ ።
አጠራ፡ አነጻ/አጠዳ ።
አጠራረስ፡ አደናነዝ/መጥረስ ።
አጠራረቅ፡ አቸነካከር/መጠረቅ ።
አጠራረብ፡ አስተናነጥ/መጥረብ ።
አጠራረግ፡ አስተባበስ/መጥረግ ።
አጠራራ፡ ና አባባለ ("ጥሪን አረዳዳ") ።
አጠራራ፡ አጠዳዳ ።
አጠራር፡ አነሣሥ/አወሣሥ ("ስም አጠራር እንዲሉ") ።
አጠራር፡ አጠዳድ/መንጻት ።
አጠራር፡ አጯጯኸ ("መጥራት") ።
አጠራቀመ፡ አጠናቀረ/ሰበሰበ/አከማቸ/ዘገበ (ሚክ. ፪፡ ፲፪) ።
አጠራቀመ፡ ዘገበ፡ ጠረቀመ።
አጠራቃሚ፡ ያጠራቀመ/የሚያጠራቅም ("አጠናቃሪ ሰብሳቢ አከማቺ") "
አጠራጠሰ፡ ከደንጊያ አማታ አጋጩ መስቈርን ።
አጠራጠር፡ አወላለብ/መጠርጠር ።
አጠርቂ፡ ያጠረቃ/የሚያጠረቃ ።
አጠቀላለል፡ አሸበላለል/መጠቅለል ።
አጠቀሰ፡ እንጀራን እወጥ አገባ/ነከረ ለመብላት ("አጠለቀ") ።
አጠቀነ፡ ትንንሽ አድርጎ ቈረጠ ("ከ ተፈ ፈረፈረ አሳነሰ") ።
አጠቃ፡ ገፋ/በደለ/አጕላላ ("መታ መላልሶ ጐዳ አሸነፈ አዋረደ ጨቈነ") (ነሐ. ፩፡ ፲፱) ።
አጠቃ፡ ጐዳ፡ ጠቃ።
አጠቃለለ (ጠቀለለ)፡ ከናወነ ("ገደለ አሳረፈ ከፈነ ገነዘ") ።
አጠቃለለ፡ ኣሸባለለ/አጠማጠመ/እካ ፈነ/ኣጋነዘ ።
አጠቃላዩ (ዉ)፡ አሳራፊው ጌታ ("ፈጣሪ") ።
አጠቃላይ፡ ያጠቃለለ/የሚያጠቃልል ።
አጠቃቀመ፡ አገነኛኘ/አሰፋፋ/አጣ ጣፈ ።
አጠቃቀመጥቅም፡ አከፋፈለ/አመላ ለሰ ።
አጠቃቀም፡ ኣበቃቅ/አሰፋፍ/መጥቀም ።
አጠቃቀሰ፡ አመለካከተ/አገነኛኘ/አነ ካካ ።
አጠቃቀስ፡ አነካከር/መጥቀስ/ማጥ ቀስ ።
አጠቃቀነ፡ መላልሶ አጠቀነ ("እያሳነሰ ቈራረሰ ገማመሰ ከፋፈለ ሰባበረ የዳቤ የዳቦ") ።
አጠቃቀን፡ አስተናነስ/መጠቀን ።
አጠቃቃሚ፡ ያጠቃቀመ/የሚያጠቃ ቅም ።
አጠቃቅ፡ አበዳደል/መጥቃት/ማጥቃት ።
አጠቃጠቀ፡ አባላ/አዋጠቀ ።
አጠቃጠቀ፡ አባሳ/አናቀሰ ።
አጠቃጠቀ፡ አደፋፈነ/አደባበቀ ።
አጠቃጠቅ፡ አወጋግ/አደፋፈን ("መጠ ቅጠቅ") ።
አጠቈረ፡ አጐሰቈለ ።
አጠቈረ፡ ጥቍር አደረገ ("ፊቱን ለወጠ አጨለመ ጥንስስ ኣስመሰለ ልብሱን ከል ነከረ") ።
አጠቋቈም፡ አመለካከት/መጠቈም ።
አጠቋቈስ፡ አጐሸማመጥ/መጣቈስ ።
አጠቋቈር፡ የጥቍረት ኹናቴ ("መጥቈር") ።
አጠበ፡ አጐረፈ፡ ዐጠበ።
አጠበረረ፡ አጋለ፡ ጠበረረ ።
አጠበረረ፡ ኦጋለ/አገረረ ።
አጠበቀ፡ አከረረ/አጠነከረ ።
አጠበበ (አጽበበ)፡ ጠባብ አደረገ ("አቀረበ") ።
አጠበበ (አጽበበ)፡ ጠባብ አደረገ ("አቀረበ").
አጠባ (አጥበወ)፡ ጡት/አውራ ጣት ሰጠ/አጐረሠ ("ወተት አጠጣ መገበ") ።
አጠባ (አጽብሐ)፡ አነጋ/አፈገገ ።
አጠባ፡ ሰበከ/ገዛ ።
አጠባ፡ አባተ ኣገባ ወርን ።
አጠባበስ፡ አተኳኰስ/መጥበስ ።
አጠባበቀ፡ መላልሶ አጠበቀ ("አጠነከረ") ።
አጠባበቀ፡ አከላከለ/አስተጋገደ ።
አጠባበቅ፡ አስተጋገድ/መጠበቅ ።
አጠባበቅ፡ አከራረር/መጥበቅ ።
አጠባበብ፡ አጣጣል/መጠበብ ።
አጠባበብ፡ አጨናነቅ/መጥበብ ።
አጠባብ፡ አመጣጠጥ/መጥባት ።
አጠባብ፡ አበላለት/መጥባት ።
አጠባብ፡ አበላለት/መጥባት.
አጠባጠበ፡ አባለተ/አጣባ ።
አጠባጠበ፡ አጋረፈ/አሸናቈጠ ።
አጠባጠብ፡ አገራረፍ ("መጠብጠብ መ በለት") ።
አጠነ፡ በቁሙ፡ ዐጠነ።
አጠነሳሰስ፡ አበጣበጥ/መጠንሰስ ።
አጠነቃቀል፡ ኣቈነጣጠር/መጠንቀል ።
አጠነቃቀረ፡ አጠረቃቀመ/አከመቻቸ ።
አጠነቃቀር፡ አጠረቃቀም/ማጠናቀር ።
አጠነቃቀቅ፡ ኣኰሰታተር/መጠንቀቅ ።
አጠነቋቈለ፡ አነቋቈረ ።
አጠነቋቈል፡ ኣወጋግ/መጠንቈል ።
አጠነባ፡ አገማ ("ጥንብ አደረገ") ።
አጠነባብ፡ አገማም/መጠንባት ።
አጠነነ (አጽነነ)፡ አዘነበለ ።
አጠነከረ፡ አጠና/ጥኑ አደረገ/አበሪታ/አከረረ/አደረቀ/አጠጠረ (፪ ዜና. ፴፪፡ ፭) ።
አጠነካከረ፡ አጠናና/አበረታታ ።
አጠነካከር፡ አጠናን/መጠንከር ።
አጠነዛ፡ አጠነከረ/አበላሸ ።
አጠነዛዝ፡ አጠነካከር/መጠንዛት ።
አጠነጋ (አፀንግዐ)፡ ጥንግ አበጀ/ ሠራ ' ታታ/አዋሰበ/ጠፈረ ("መታ ለጋ") ።
አጠነጋ፡ ለጋ ፥ ገደለ፡ ጠነጋ ።
አጠነጋ፡ ብዙ ሰው ገደለ ("በጦር በሰይፍ") ።
አጠነጋገር፡ አጠነባበር/ማጠናገር ።
አጠነጠነ (አጸንጸነ)፡ አነቀዘ/ሰለቀ/ አደቀቀ ።
አጠነጠነ፡ አነቀዘ፡ ደወረ፡ ጠነጠነ ።
አጠነጠነ፡ ወሬ ቀሠመ/አጠራቀመ ።
አጠነጠነ፡ ጠቀለለ/ጠመጠመ/እኮደወረ/አዳወረ ("ድርን ማግን ጥለትን") ።
አጠነፈ (አጥነፈ)፡ ጠንፍ አበጀ/ አዘጋጀ ።
አጠነፈፈ፡ የንፍሮ ውሃን እፈሰሰ፡ (ጠነፈፈ) ።
አጠነፋፈፍ፡ አፈሳሰስ/ማጠንፈፍ ።
አጠና (አጽንዐ)፡ አጠነከረ/አበረታ/ አጨከነ ።
አጠና፡ ተማረ/ቀጸለ/አረጋገጠ/ዐወቀ/ ተረዳ ("ልብ አደረገ") ።
አጠናሰሰ፡ ሸክላን አስተጣጠበ/አስተ ጣጠነ ("ጥንስስን ረዳ አበጣበጠ") ።
አጠናቀረ፡ አከማቸ፡ (ጠነቀረ)።
አጠናቀረ፡ አጠራቀመ/ሰበሰበ/አከማቸ ("(ግጥም) ቢነግሩሽ ቢነግሩሽ አታጠና ቅሪ እንደ ተርኪስ ባቡር ተገትረሽ ቅሪ") ።
አጠናቀቀ፡ አከናወነ/አጣጣመ ("ጨ ረሰ") ።
አጠናቃሪ፡ ያጠናቀረ/የሚያጠናቅር ("አጠራቃሚ") ።
አጠናቃቂ፡ ያጠናቀቀ/የሚያጠናቅቅ ("አከናዋኝ") ።
አጠናቈለ፡ መላ አማታ/አዋጣ ።
አጠናቈለ፡ አናቈረ ።
አጠናቅር፡ የተራራ ስም ("ባንኮበር በኩል ያለ ተራራ አጠራቅም ማለት ነው") ።
አጠናበረ፡ አደናበረ ("በጥፊ መታ") ።
አጠናባ፡ አጋማ ።
አጠናና፡ አረጋጋ/አበረታታ ' እጫካ ነገር ።
አጠናን፡ አጠነካከር/መጥናት ።
አጠናከረ፡ አጣና/አበራታ ።
አጠናወተ፡ አስጨነገፈ ' አሶረደ ።
አጠናወተ፡ አተናኰለ/አቃወመ ።
አጠናገረ፡ አጠናበረ ።
አጠናጠነ፡ አጠቃለለ/አዳወረ ።
አጠናጠነ፡ አጤነ/ዐሰበ/አወጣ/እወ ረደ ።
አጠናጠነ፡ ኦናቀዘ ።
አጠናጠን፡ አነቃቀዝ ("ማርጀት መጠ ንጠን ማጠንጠን") ።
አጠናጣኝ፡ ያጠናጠነ/የሚያጠናጥን ("ዐሳቢ") ።
አጠናፋፊ፡ ያጠናፈፈ/የሚያጠናፍፍ ።
አጠንቢ፡ ያጠነባ/የሚያጠነባ ("አግሚ") ።
አጠንካሪ፡ ያጠነከረ/የሚያጠነክር ("አ ጥኒ") ።
አጠንጣኝ (ኞች)፡ ያነቀዘ/የሚያነ ቅዝ ("ኣንቃዥ አድቃቂ") ።
አጠንጣኝ፡ ያጠነጠነ/የሚያጠነጥን ("ጠቅላይ ደዋሪ አዳዋሪ አኳቢ ሴት ሸረሪት አጠንጣኝ ወሬ ማዱ አጠልጣይ") ።
አጠንፋፊ፡ ያጠነፈፈ/የሚያጠነፍፍ ።
አጠወለገ፡ ለወጠ/አጠቈረ ።
አጠወላለግ፡ ኣለዋወጥ/መጠውለግ ።
አጠዋለገ፡ ኣለዋወጠ/አጣቈረ ።
አጠዋወር፡ አለማመድ/መጣወር ።
አጠውላጊ፡ ያጠወለገ/የሚያጠወልግ ("ችጋር") ።
አጠዛዘል፡ አመታት/መጠዘል ።
አጠዛጠዘ፡ አናደፈ/አዋጋ ።
አጠዛጠዝ፡ አነዳደፍ/አነዛዘር/መጠ ዝጠዝ ።
አጠየመ፡ ጠይም፡ አደረገ፡ ጠይማት
አጠያሚ፡ ያጠየመ፡ የሚያጠይም ። ማጠየም፡ ጠይም፡ ማድረግ፡ አጠያየም፡ ጠይምነት፡ መጠየም ። ጠየፈ፡ ጸየፈ፡ ጸያፍ፡ ኾነ ። አጠየፈ፡ አጸየፈ፡ ጠላ፡ ነቀፈ ። አስጠየፈ፡ አስጠላ፡ አስነቀፈ፡ አስቀየመ አስጠያፊ፡ ያስጠየፈ፡ የሚያስጠይፍ፡ አ
አጠያየር፡ አበራረር/ማክነፍ ።
አጠያየቀ፡ አመራመረ ።
አጠያየቀ፡ አጐበኛኘ፡ አፈቃቀደ ።
አጠያየት፡ አሠራር/አስተሳሰር/መጠ የት ።
አጠያያቂ፡ ያጠያየቀ፡ የሚያጠያይቅ፡
አጠደፈ (አጽደፈ)፡ ገደል ሰደደ አገባ ("አንከባለለ") ።
አጠዳ (አጻዕደወ)፡ ዐጠበ/አጠራ/ አነጣ/አሳመረ ("ጥሩ አደረገ") ።
አጠዳደቅ፡ ኣጸዳደቅ ።
አጠዳደፍ፡ አቸኳኰል/መጥደፍ ።
አጠዳዳ፡ አጠራራ/አነጣጣ/ኣሰማመረ ወለወለ ።
አጠዳድ፡ አነጣጥ/መጥዳት ።
አጠገበ፡ ሆድን መላ አሰለቸ ።
አጠገበ፡ መሬትን አረካ/አራሰ ("ዝናሙ") ።
አጠገበ፡ አስረገዘ/አከበደ ።
አጠገበ፡ አቀረበ/ቅርብ አደረገ ።
አጠገብ ላጠገብ፡ ቅርብ ለቅርብ ጐን ለጐን ።
አጠገብ፡ ቅርብ/አቅራቢያ/ጐን ጋ ዘንድ (ዘፍ. ፮፡ ፲፯፡ መክ. ፯፡ ፲፬፡ ዮሐ. ፰፡ ፳) ።
አጠገብ፡ ጐን፡ ጠገበ።
አጠገቦች፡ ቅርቦች/ጐኖች ።
አጠገገ፡ አደረቀ/ሰበሰበ ("አዳነ") ።
አጠገገ፡ ጠገግ ሠራ/አበጀ/አደረገ ታታ ጠፈረ ።
አጠጋ፡ አቃራረበ/አደጋገፈ ("(ሰገሰገ)") ።
አጠጋገብ፡ አሰለቻቸት/መጥገብ ።
አጠጋገት፡ አስተላለብ/መጠገት ።
አጠጋገን፡ አስተካከም/አስተጋገዝ/መ ጠገን ።
አጠጋገግ፡ አደራረቅ/መጥጎግ ።
አጠጋጊ፡ ያጠጋጋ/የሚያጠጋጋ ("አቀ ራራቢ") ።
አጠጋግ፡ አቀራረብ/አጨፈላለቅ ("መጠ ጋት") ።
አጠጠ፡ አነሰ፡ ጐደለ፡ ዐጠጠ።
አጠጠ፡ ጠጠ። እባክኸ፡ ጃል፡ ፍቅር፡ አታጣጥ፡ እንዲል፡ ባላገር ።
አጠጠረ፡ አጠና/አጠነከረ/አበረታ ("ጥጥር አደረገ") ።
አጠጣ፡ መጠጥ ሰጠ ("ጠጡ አለ አጠጣ ጨመረ አፈሰሰ አንቈረቈረ") (ዘፀ. ፪፡ ፲፱፡ ፩ ቆሮ. ፲፡ ፴፮) ።
አጠጣ፡ ማግን ወረወረ ("ከድር ጋራ አዋሰበ (ውጉን አጠጣ) ባ፬ የገበጣ ጠጠር ላይ ፭ኛ ጠጠር ጨመረ አስቀመጠ አኖረ") ።
አጠጣሪ፡ ያጠጠረ/የሚያጠጥር ("አጥኒ አጠንካሪ") ።
አጠጣጠር፡ አጠናን/መጠንከር ።
አጠጪ (ዎች)፡ ያጠጣ/የሚያጠጣ ("መጠጥ ሰጪ") ።
አጠፈ፡ ዕጥፍ አደረገ፡ ዐጠፈ።
አጠፈጠፈ (አጸፍጸፈ)፡ አሣሣ/ዘረጋ/አሰፋ ("ዝርግ ጠፍጣፋ አደረገ ሸክላን ጭ ቃን ደንጊያን ብረትን ማዕድንን") (ዘፀ. ፲፱፡ ፫) ።
አጠፋ (አጥፍአ)፡ ቀሠፈ/ገደለ ("ነፍስ ኣሳለፈ") ።
አጠፋ፡ ሰረቀ/በላ ።
አጠፋ፡ ረሳ'ዘነጋ ("የሚያውቀውን ዐጣ") ።
አጠፋ፡ አወደመ/ደረገመ/ደመሰሰ/ፋቀ/ገሰሰ/አበላሸ/አከፋ ።
አጠፋጠፈ፡ በጥፊ አማታ ።
አጠፋጠፈ፡ አዘራጋ ("የጥፍጥፍን ሥራ ረዳ") ።
አጠፋጠፍ፡ አዘረጋግ/ኣለባበጥ/መጠ ፍጠፍ/ማጠፍጠፍ ።
አጠፋፈር፡ አስተሳሰር/መጠፈር ።
አጠፋፈር፡ አቈራረጥ/መከርከም ።
አጠፋፈጠ፡ መላልሶ ብዙ ጊዜ አጣ ፈጠ ።
አጠፋፈጠ፡ አጣጣመ ("ጣም አቀባበለ") ።
አጠፋፈጥ፡ አጣጣም/መጣፈጥ ።
አጠፋፋ፡ አገዳደለ ።
አጠፋፋ፡ ደመሳሰሰ/ፋፋቀ ።
አጠፋፍ፡ አማት/መጥፋት ።
አጠፍጣፊ፡ ያጠፈጠፈ/የሚያጠፈጥፍ ።
አጣ፡ ሳያገኝ ቀረ፡ ዐጣ።
አጣለለ፡ አጣራ/አቃረረ ።
አጣለቀ፡ አሳጠመ ።
አጣለቀ፡ አቃዳ/አጫለፈ ።
አጣለፈ፡ ኣሰራጀ/አዋሰበ/አቋለፈ/ኣያያዘ ("ጥልፍን ፍሪዳን") ።
አጣላ (አስተጻልአ)፡ እናቀፈ/አሰ ለቸ/አለያየ ።
አጣላፊ፡ ያጣለፈ ' የሚያጣልፍ ("አያ ያዥ") ።
አጣመ (አጥዐመ)፡ አቀመሰ ።
አጣመ (አጥዐመ)፡ አጣፈጠ ።
አጣመመ፡ አጠማዘዘ/አንጋደደ/አወላገደ (ዘፀ. ፳፫፡ ፮, ፰፡ ኢዮ. ፴፫፡ ፳፯፡ ዓሞ. ፪፡ ፯) ።
አጣመረ (አስተፃመረ)፡ አገናኘ/አ ጣመደ/አዋደደ/አሰማማ/አያያዘ ("አነባበረ እከሌ በበዓል ቀን እጅና እግሩን አጣምሮ ዋለ") ።
አጣመቀ፡ አጫመቀ/አጠማዘዘ ።
አጣመቀ፡ ውሃ አጫመረ/አማላ/ኣበ ጣበጠ ።
አጣመተ (አጻመተ)፡ በልቶ ጨረሰ/ ፈጀ/አቃጠለ/አጠፋ ("ዐመድ አደረገ") ።
አጣመተ፡ በልቶ ጨረሰ፡ (መተ) ።
አጣመተ፡ ፈጩ አደቀቀ ።
አጣመደ (ዐብሮ ተጠመደ)፡ ቀንበርን አሸካከመ ።
አጣመደ፡ በሬን ወደ ቀንበር አቀረበ ("ቀንበርን አጫጫነ") ።
አጣመደ፡ አጣላ/ኣማረዘ ።
አጣማሚ፡ ያጣመመ/የሚያጣምም ("አንጋዳጅ አወላጋጅ") ።
አጣማሪ፡ ያጣመረ/የሚያጣምር ("አያ ያዥ") ።
አጣማቂ፡ ያጣመቀ/የሚያጣምቅ ።
አጣማች፡ ያጣመተ/የሚያጣምት ("ጨ ራሽ አቃጣይ") ።
አጣማጅ (ጆች)፡ ያጣመደ/የሚያጣ ምድ ("የሰው የበሬ ጓድ ቀንጃ (ግጥም) አጣማጁን ሲያጣ እንቧ ይላል በሬ አልተ ሻለሽሞይ ከትላንቱ ዛሬ") ።
አጣረ (አጽዐረ)፡ አስጨነቀ/አለፋ/አደከመ ("በሽታ ሰውን (ጣራ ጣራ አየ ዐይኑን አፈጠጠ እግሩን አንፈራገጠ እሞት አፋፍ ደረሰ ውጪ ነፍስ ግቢ ነፍስ አለ)") ።
አጣረሰ፡ አሳሳተ/አበላሸ/አቃወሰ ጥይቅን ።
አጣረሰ፡ አጋጨ አማታ ።
አጣረቀ፡ ምስማር አማታ አቸናከረ ።
አጣረበ (አስተጻረበ)፡ አስተናነጠ/አሻለተ/አቃጠነ ("ጠርብ አባጀ") ።
አጣረገ፡ አስተጫወደ/አመናጠረ ።
አጣረገ፡ አወላወለ/አስተባበሰ ።
አጣሪ (አጽዓሪ)፡ ያጣረ/የሚያጥር ("የሚያስጨንቅ አልፊ አድካሚ") ።
አጣሪ መሸተኛ፡ ቀራጭ ("ቸር ቻሪ ዐጠረ") ።
አጣሪ፡ ዐጥር የሚያጥር ።
አጣሪ፡ ያጣራ/የሚያጣራ ("በሙሉ ያጭ አጥሪ") ።
አጣራ (አስተጣርአ/አስተጻርሐ)፡ አጯጯኸ ("መጥራትን ረዳ") ።
አጣራ (አስተጻረየ/አስተናጽሐ/አጣለለ/እናጻ/ጥሩ አዳረገ (አደረገ))፡ ጨርሶ ሼጠ ።
አጣራቢ፡ ያጣረበ/የሚያጣርብ ።
አጣራጊ፡ ያጣረገ/የሚያጣርግ ።
አጣቀመ፡ አሳፋ ("የተለያየ ነገርን አያያዘ አገናኘ") ።
አጣቀመ፡ አባቃ/አማላ/አራባ ።
አጣቀሰ፡ አቃጠረ ("ሰውን በሓሳብ ባ ሥራ አገናኘ አሳሳበ") ።
አጣቀነ፡ አቀራጠፈ/ኣካተፈ ።
አጣቃሚ፡ ያጣቀመ/የሚያጣቅም ("የሚያሳፋ አያያዥ") ።
አጣቃሽ፡ ያጣቀሰ/የሚያጣቅስ ።
አጣቈረ፡ አጐሳቈለ ።
አጣበሰ፡ አቋላ/አባሰለ ።
አጣበቀ፡ አዋደደ/አሰማማ/አጋጠመ/አያያዘ ("ቸነከረ ቀረቀረ ልክክ አደረገ ከምድር ሰፋ ለመጠ") (ዘዳ. ፳፰፡ ፰፡ ፩ ሳሙ. ፲፰፡ ፲፩፡ ፳፮፡ ፰፡ ፪ ሳሙ. ፪፡ ፳፪፡ ኢሳ. ፵፩፡ ፯) ።
አጣበበ (አስተጻበበ)፡ ኣጠጋጋ/እ ጫነቀ ።
አጣበበ (አስተጻበበ)፡ ኣጠጋጋ/እ ጫነቀ.
አጣቢ፡ ያጣባ/የሚያጣባ ።
አጣባ (አስተጣበወ)፡ አመጋመገ/ አማጠጠ ።
አጣባቂ፡ ያጣበቀ/የሚያጣብቅ ("አያ ያዥ") ።
አጣባቢ፡ ያጣበበ/የሚያጣብብ ("አጫ ናቂ") ።
አጣባቢ፡ ያጣበበ/የሚያጣብብ ("አጫ ናቂ").
አጣብቂኝ (ኞች)፡ ዐርኩ መንታ ብረት ("ወይም ዕንጨት ፈረንጆች ኤቶ ይሉታል ሠንጣቃ ደንጊያ በዝቋላና በደብር ያለ") ።
አጣና (ኖች)፡ ጠንካራ ዕንጨት ("ቤትን የሚያጣና ውፍረቱ በጭብጥ የሚመላ ለግድግዳ ማገር ለጣራ ሳጋ ይኾናል") ።
አጣና (አስተጸንዐ)፡ አበራታ/አ ከነ ።
አጣና፡ ዕንጨት፡ ጠና።
አጣወረ፡ እቻቻለ/አላመደ ።
አጣዘለ፡ አማታ/አጣረዘ ።
አጣየቀ፡ አጐባኘ፡ አፋቀደ ።
አጣዪ፡ ያጣላ/የሚያጣላ ።
አጣደፈ፡ አቻኰለ፡ ጠደፈ ።
አጣደፈ፡ አቻኰለ/አፋጠነ/አዋከበ ።
አጣዳፊ፡ ያጣደፈ/የሚያጣድፍ ("አቻኳይ አዋካቢ አዛዥ ጣረ ሞት ተቅማጥ") ።
አጣገበ፡ አባቃ/አሰላቸ ።
አጣጋ (አስተጣግዐ/አስተፃግዐ)፡ አቃረበ/አዳገፈ ("(አደረቀ እከሳ ለመጠ)") ።
አጣጣለ (አስተጻዐለ/አስተጣሐለ)፡ አዋደቀ/አገዳደመ ("ፍሪዳን ዛፍን") ።
አጣጣለ፡ አናናደ/አዘራጠጠ ("ክምርን አጣጣለ አበጣበጠ ጠጅን") ።
አጣጣል፡ አገዳደፍ/መጣ ።
አጣጣል፡ አጻጻፍ ።
አጣጣመ፡ አጠፋፈጠ/አፋቀረ/አሰማማ ።
አጣጣመ፡ ፈጸመ/አከናወነ ።
አጣጣሚ፡ በጐንደር ክፍል ያለ አገር ።
አጣጣሚ፡ ያጣጣመ/የሚያጣጥም ("አፋ ቃሪ ፈጻሚ አከናዋኝ") ።
አጣጣም፡ አቀማመስ/መጣም ።
አጣጣም፡ አጠፋፈጥ/መጣም ።
አጣጣስ፡ አነዳደል/መጣስ ።
አጣጣረ (አስተጸዐረ)፡ አጨናነቀ ("ነፍስና ሥጋን አታጋ አዳከመ") ።
አጣጣር፡ አጨናነቅ/መጣር ።
አጣጣይ፡ ያጣጣለ/የሚያጣጥል ።
አጣጣደ፡ ምጣድን ለመጣድ አያያዘ/አጫነ ።
አጣጣድ፡ አጫጫን/መጣድ ።
አጣጣፈ፡ አጋጠመ/አገናኘ/አሰማማ/አፋቀረ ።
አጣጣፈ፡ አጣቀመ/አሳፋ ።
አጣጣፈ፡ አጻጻፈ/አዋዋለ ("ደብዳቤን ኣላላከ (የጥፈትን ሥራ ረዳ)") ።
አጣጣፊ፡ ያጣጣፈ/የሚያጣጥፍ ("አዋ ዋይ") ።
አጣጣፍ፡ አጠቃቀም/መጥቀም ።
አጣጣፍ፡ የጥፈት አጣጣል/መጣፍ ።
አጣጥ፡ ዕንጨት፡ ዐጣጥ።
አጣጭ፡ ጣጭ።
አጣፈረ (አስተጣፈረ/አስተፃፈረ)፡ አስተሳሰረ/አጋረፈ ("ጠፈርን ዐልጋን አባጀ አሣራ ከበሮን ኣጓለበ") ።
አጣፈረ፡ በባይበሉብሽ አማታ ("መታ") ።
አጣፈረ፡ አስተሳሰረ ፥ መታ፡ ጠፈረ ።
አጣፈረ፡ ጥፍር ለጥፍር አቋረጠ ።
አጣፈጠ፡ ጣም ሰጠ ።
አጣፊ (አስተጣፋሒ)፡ ያጣፋ' የሚ ያጣፋ ("ለባሽ") ።
አጣፊ (አስተጣፋኢ)፡ ያጣፋ/የሚ ያጣፋ ("አጋዳይ") ።
አጣፊኝ (ኞች)፡ ኩትኛ ልብስ ("መላበሻ") ።
አጣፋ (አስተጣፍሐ)፡ ኩታ'ለበሰ ("ጫፍና ፵ፉን አጋጠመ") ።
አጣፋ (አስተጣፍአ)፡ አጋደለ/አማ ዳይ ።
አጣፋ፡ አሻኰተ/አገና/አማታ ።
አጣፋ፡ ኩታ ለበሰ፡ ጠፋ፡ (ጠፍሐ) ።
አጣፋ፡ ክንፍና ክንፍን አጋጨ (ኢሳ. ፲፡ ፲፬) ።
አጣፋሪ (አስተጣፋሪ)፡ ያጣፈረ/ የሚያጣፍር ("አስተሳሳሪ") ።
አጣፋሪ (አስተጻፋሪ)፡ ያጣፈረ/የሚያጣፍር ("በቃሪያ ጥፊ የሚመታ") ።
አጣፋጭ (ጮች)፡ ያጣፈጠ/የሚያጣ ፍጥ ("ሽቱ አጣፋጭ እንዲሉ") ።
አጤ፡ ንጉሠ ነገሥት፡ ዐጪ ።
አጤቀ፡ በከለ፡ ጤቀ ።
አጤቀ፡ በከለ/አሳደፈ/አበላሸ ።
አጤቀ፡ አስጨነቀ ("መላ ዓሣ መረብን") ።
አጤቀው፡ በከለው ("አስጨነቀው መ ላው") ።
አጤነ፡ አስታወሰ፡ (ጤነ)።
አጥለቀለቀ፡ አንጣለለ ("ምድር አለበሰ ሸፈነ በላይ አስተኛ") ።
አጥለቀለቀ፡ አንጣለለ፡ ጠለቀ።
አጥለቅላቂ፡ ያጥለቀለቀ/የሚያጥለቀልቅ ("መሬት አልባሽ ጐርፍ") ።
አጥሊ፡ ያጠላ/የሚያጠላ ("ጥላ ያዥ") ።
አጥላላ፡ አጸያየፈ/አረካከሰ ("ቢያክ ቢያክ አለ") ።
አጥላስ፡ ካባ፡ ጠለሰ ።
አጥላስ፡ ጠለስ የሚመስል ያረንጓዴ መጐናጸፊያ ("ካባ እማሎሚ ከል የሐዘን ልብስ") ።
አጥላቂ፡ ያጠለቀ/የሚያጠልቅ ("አስጣሚ ለባሽ አልባሽ") ።
አጥላባቸው፡ የሰው ስም ("ጥላኸን ጣልባቸው የበላይ ኙንባቸው ማለት ነው") ።
አጥላይ (መጥለሊ/መጥልል)፡ ዘይት/ቅባት ቀጂ ።
አጥላይ (መጽለሊ/መጽልል)፡ ያጠለለ/የሚያጠል ("የሚያቀር የሚያጠራ አጥሪ") ።
አጥሌ፡ የአጥላባቸው ከፊል ።
አጥመለመለ፡ አዝለፈለፈ (መለ) ።
አጥመልማይ፡ ያጥመለመለ/የሚያጥመ ለምል ("በሽታ") ።
አጥመዘመዘ፡ አልመዘመዘ፡ (ጠመዘ)
አጥሚ፡ ያጠማ/የሚያጠማ ("ጠምዛዥ") ።
አጥሚት፡ በውሃ ርሶ የተቀቀለ የዐጃ ክክ ("እንትክትክ የበሽተኛን አንዠት የሚያርስ የሚያረሰርስ ምግብ (የዶሮ አጥሚት) ሥጋና መረቅ") ።
አጥሚት፡ እንትክትክ ጠማ፡ (ጠምዐ) ።
አጥማሚ፡ ያጠመመ/የሚያጠም ።
አጥማቂ (ዎች)፡ ያጠመቀ/የሚያጠ ምቅ ("ቄስ ጳጳስ") ።
አጥማቂነት፡ አጥማቂ መኾን ።
አጥማጅ (ጆች)፡ ያጠመደ/የሚያጠምድ ("ዐዳኝ ዓሣ ወጋሪ") ።
አጥም፡ ዐጥንት፡ ዐጥም።
አጥረበረበ፡ አሽቈጠቈጠ፡ ጠረበረበ ።
አጥረበረበ፡ አሽቈጠቈጠ/አለማመጣ ("ይስበረኝ ይሠንጥረኝ አሠኘ አርገበገበ") ።
አጥረከረከ፡ አኵለፈለፈ፡ ጠረከ።
አጥረኸረኸ፡ አዋረደ/አሳፈረ ።
አጥሪ፡ ያጠራ/የሚያጠራ ("ልብስ ዐጣቢ እኽል ለቃሚ") ።
አጥቍሪት፡ የዐለላ ቅጠል ።
አጥቍሮ፡ ጥቍር አድርጎ ።
አጥቂ (ዎች)፡ ያጠቃ/የሚያጠቃ ("ገፊ ጐጂ የላም ኣሸናፊ በተጠቂም አጥቂ ባጥቂም አጥቂ አለበት አሰንብተኝ አምላክ ባይኔ ጕድ ልይበት (ኣዝማሪ ዘለቀ በጣሊ ያን ጊዜ)") ።
አጥቂት፡ የደም ምች ።
አጥቂነት፡ አጥቂ መኾን ("ጨቋኝነት") ።
አጥቃሽ (ሾች)፡ ያጠቀሰ/የሚያጠቅስ ።
አጥቋሪ፡ ያጠቈረ/የሚያጠቍር ።
አጥበረበረ፡ አንጸባረቀ፡ ጠበረ።
አጥበረበረ፡ አንጸባረቀ/አብለጨለጫ/አብረቀረቀ ("ማየት መመልከት ከለከለ ፀሓዩ መጣብሩ ውሃው ልብሱ") ።
አጥበርባሪ፡ ያጥበረበረ/የሚያጥበረብር ("ባሕር መስተዋት ጥሩ ብረት ከዐይን የራቀ አገር ውሃና ጭጋግ መሳይ") ።
አጥቢ፡ ያጠባ/የሚያጠባ ("ያጠባች የምታጠባ አባት እናት እመጫት ሞግዚት እረኛ ጥገት") ።
አጥቢያ (ዎች)፡ ሰበካ ("የታቦት ግዛት እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን በትም ርቲ የምታበራበት አገር ማለት ነው") ።
አጥቢያ (ጽባሕ)፡ ንጋት/ጧት ።
አጥቢያ፡ ንጋት፡ ሰበካ፡ ጠባ (ጸብሐ) ።
አጥባቂ፡ ያጠበቀ/የሚያጠብቅ ("አጠንካሪ (ተረት) ያራኝ ልጅ አጥባቂ ያባያ ልጅ ወዳቂ") ።
አጥባቂ ፈረስ፡ ልጓም የማይመልሰው ("ሯጭ ሸምጣጭ") ።
አጥባቂነት፡ አጥባቂ መኾን ።
አጥባቢ፡ ያጠበበ/የሚያጠብ ("የማያሰፋ እንትንን አስተውል") ።
አጥባቢ፡ ያጠበበ/የሚያጠብ ("የማያሰፋ እንትንን አስተውል").
አጥብቆ፡ ንኡስ አገባብ ("እጅግ በጣም በኀይል በብዙ ክፉኛ") (፪ ዜና. ፴፭፡ ፳፫) ።
አጥኒ (አጽናዒ)፡ ያጠና/የሚያጠና/ የሚያጠነክር ("አጠንካሪዞ") ።
አጥናኒ፡ ያጠናና/የሚያጥናና ("ሐዘን አቅላይ") ።
አጥናና፡ አጠናና/አበረታታ ("አይዞኸ አይዞኸ እለ አረጋጋ") ።
አጥናፈ ምድር (አጽናፈ ምድር)፡ የምድር ዳር (ዳሮች) ።
አጥናፈ ዓለም (አጽናፈ ዓለም)፡ የዓለም ዳር (ዳሮች) ።
አጥናፈ ዓለም፡ የወንድና የሴት ስም ።
አጥናፈ ወርቅ፡ የሴት ስም ።
አጥናፈ ወርቅ፡ የወርቅ ዳር ።
አጥናፍ (አጽናፍ)፡ ዳሮች/ዳርቾች ።
አጥናፍ ሰገድ፡ የሰው ስም ።
አጥንት፡ በቁሙ፡ ዐጥንት ።
አጥወለወለ፡ አዞረ፡ (ጠወለ)።
አጥጋቢ፡ ያጠገበ/የሚያጠግብ ("የሚበቃ ምግብ ሥራ ነገር") ።
አጥጋጊ፡ ያጠገገ/የሚያጠግ ("መድኀ ኒት") ።
አጥግቢኝ (ኞች)፡ ሆዷ የተነፋ/ያበጠ/የተንዘረጠጠ ("የምድር ተንቀሳቃሽ") ።
አጥግቢኝተንቃሳቃሽ፡ ጠገበ።
አጥፊ (ዎች)፡ ያጠፋ/የሚያጠፋ ("ቀሣፊ ገዳይ አበላሺ አክፊ") (ምሳ. ፳፰፡ ፳፬፡ ኤር. ፮፡ ፳፮፡ ሕዝ. ፱፡ ፳) ።
አጥፊነት፡ አጥፊ መኾን ።
አጥፊና ጠፊ፡ ውሃና እሳት ("ገዳይና ች") ።
አጥፍ፡ ዳባ፡ ዐጥፍ።
አጦለ (ትግ. ጨለወ)፡ ጠረገ/ገፈፈ/ ለየ/ኣስገለለ ("ግርድን ሰበርን ገለባን ከፍሬ ላይ") ።
አጦለ፡ ጠረገ፡ ጦለ።
አጦዘ፡ ጠመዘዘ/አከረረ/አደበነ ።
አጦፈ፡ ኣሳበደ "
አጦፈ፡ ጧፍ አበጀ ("አነደደ አቃጠለ አንቀለቀለ") "
አጧይ (ዮች)፡ ያጦለ/የሚያጦል ("ጠ ራጊ ገፋፊ") ።
አጧጧም፡ ጦም አዋዋል/መጦም ።
አጧጧር፡ አሸካከም/መጦር ።
አጨ፡ ፋቀ፡ አጨ ።
አጨለለ፡ ጨለለ ።
አጨለገ፡ ባንድ ዐይን አየጨለገ ።
አጨላለቅ፡ አበጣበጥ/መጮለቅ ።
አጨላለፍ፡ አቀዳድ/መጨለፍ ።
አጨመላለቀ፡ የአጨማለቀ ድርብ ("አስተዳደፈ") ።
አጨመላለቅ፡ አስተዳደፍ/ማጨማለቅ ።
አጨመታተረ፡ ኣኰመታተረ/አጨመ ዳደደ ።
አጨመታተር/አጨመዳደድ፡ ማጨማ ተር ።
አጨማለቀ፡ አደፋጪ (መለቀ)።
አጨማለቀ፡ አጨቀየ/አደፋጩ/አራሰ ("ጭቃ አደረገ አሳደፈ ፥ አለፈለፈ ወፈለቀን አስተውል") ።
አጨማላቂ፡ ያጨማለቀ/የሚያጨማ ልቅ ።
አጨማመ፡ አሳሳመ ።
አጨማመ፡ ጮምሞአስተሳሰረ ("አማገረ አባጀ") ።
አጨማመር፡ አሰነዳድ/መጨመር ።
አጨማመቅ፡ አጠመዛዘዝ/መመት ።
አጨማመት፡ አረማመም/መጨመት ።
አጨማተረ፡ ኣኰማተረ/አጨማደደ ።
አጨማታሪ፡ ያጨማተረ/የሚያጨማትር ("አጨማዳጅ") ።
አጨሰ፡ ትንባኾ (ስጃራ) ጠጣ ።
አጨሰ፡ አሳዘነ/አናደደ/አቃጠለ/አገ መነ ።
አጨሰ፡ አበነነ/አተነነ ("ዕጣንን የጪስ ዕንጨትን ዐጠነ") ።
አጨሰ፡ ጪሰኛ ኾነ ("በሰው ምድር ተቀመጠ መነ") ።
አጨረማመተ፡ አጨመታተረ/አጨ መዳደደ ።
አጨረማመት፡ አጨመታተር ("ማ !") ።
አጨረቀ (አሥረቀ)፡ ሽንቱን ወረወረ/ረጨ/ፈነጠቀ ("እንደ ጮራ ") ።
አጨረተ፡ ቀጠቀጠ/በተነ/አባዘተ ("አ ነጣ ጭርት አደረገ ጭራ አስመሰለአንድ የነበረውን ለያየ አበዛ") ።
አጨረተ፡ ፋቀ/ፈገፈገ ።
አጨረናነቅ፡ አጨቋቈን/መጨርነቅ ።
አጨራመመ፡ አጣመመ ።
አጨራመተ፡ አማተረ አጨማደደ ።
አጨራረሰ፡ አፈጻጸመ/አስተላለቀ/አከ ነዋወነ ።
አጨራረስ፡ አፈጻጸም/መጨረስ ።
አጨራረፍ፡ ቀላል አመታት ።
አጨቀየ፡ ውሃ አጠገበ/አራሰ/አረካ ("ጭቃ አደረገ አላቈጠ") ።
አጨቀጨቀ፡ ጨመረ፡ ዐወቀ።
አጨቃጨቀ፡ አነዛነዘ/አነታረከ ።
አጨቃጨቀ፡ አዋቀጠ ።
አጨቃጨቀ፡ አጠቃጠቀ/አዳፈነ ።
አጨቃጨቅ፡ አደፋፈን/እነዛነዝ/መጨቅጨቅ ።
አጨቃጫቂ፡ ያጨቃጨቀ/የሚያጨቃጭቅ ("አነዛናዥ የጭቅጭቅ ዳኛ ") ።
አጨቋቈነ፡ አጨናነቀ/አጠጋጋ/አጣ በበ ።
አጨቋቈን፡ አጫጫን/መጨቈን ።
አጨበራረር፡ አደራረቅ/መጨብረር ።
አጨበጨበ (ጠፍሐ)፡ የቀኙንና የግራ ውስጥ እጁን አማታ ("ቸብ ቸብ አደ ረገ") (ኢሳ. ፶፭፡ ፲፪፡ ሕዝ. ፮፡ ፲፩፡ ማቴ. ፲፩፡ ፲፯) ።
አጨበጨበ፡ ቸብ፡ ቸብ፡ አደረገ፡ ጨበጨበ ።
አጨባበጠ፡ አኰረማመተ ።
አጨባበጥ፡ አያያዝ/መጨበጥ ።
አጨብጫቢ (ቦች)፡ ያጨበጨበ/የሚ ያጨበጭብ ።
አጨብጫቢ፡ የነገር ረዳት/አዳማቂ ።
አጨነቀረ፡ አደፈጠ ።
አጨነቈረ፡ አጨለገ/አወለገ ።
አጨነቋቈር፡ የግራ ዐይን አጨፋፈን የቀኝ ዐይን አስተያየት ።
አጨነባበስ፡ አጫጫስ/ማጨናበስ ።
አጨነባበር፡ አደነጋገር/ማጨናበር ።
አጨነጓጐለ፡ አስተጓጐለ/አሰነካከለ ።
አጨናቈረ፡ ጨንቋራ አኳዃነ ዐይንን አጫፈነ ("ቅንድብን አጠጋጋ") ።
አጨናበሰ፡ አወከ/ኣጨሰ ("እንዳያይ እንዳይነድ አደረገ") ።
አጨናበሰ፡ አጨሰ፡ ነበሰ ።
አጨናበረ፡ አሳሳተ፡ ጮነበረ።
አጨናበረ፡ ኣሳሳተ/አደናገረ ("ኹለት ነገር አሳየ") ።
አጨናባሪ፡ ያጨናበረ/የሚያጨናብር ("አሳሳች አደናጋሪ") ።
አጨናነቀ፡ አጠጋጋ/አቀራረበ/አደራ ረበ ።
አጨናነቅ፡ አቸጋገር/መጭነቅ ።
አጨናገፈ፡ አሰናከለ ።
አጨናጐለ፡ አሰናከለ ።
አጨናጐለ፡ አሰናከለ፡ ጪነፈረ ።
አጨናጓይ፡ ያጨናጐለ/የሚያጨናጕል ("አሰናካይ") ።
አጨናፈረ፡ ክፉኛ መታ፡ (ጩነፈረ)።
አጨንቅራ፡ በተነቀለ ማግስት የሚበቅል መጥፎ ዐረም ።
አጨከነ፡ አበረታ ("ጨካኝ አደረገ አ ከፋ") ።
አጨካከነ፡ መተዛዘንን አጣፋ ።
አጨካከን፡ አበረታት/መጨከን ።
አጨካካኝ፡ ያጨካከነ/የሚያጨካክን ።
አጨዋወተ፡ ጨዋታን አለዋወጠ ("አቀ ባበለ") ።
አጨዋወት፡ አነጋገር/መጫወት ።
አጨጐረ፡ ጠጕር ጭገር አበቀለ ("ዐ ረም አወጣ") ።
አጨጓጐል፡ አጀጓጐል/መጪጐል ።
አጨፈላለቀ፡ አዳዳጠ/አደፋጠጠ ("እ ጨመላለቀ") ።
አጨፈላለቅ፡ አቀጣቀጥ/መጨፍለቅ መ
አጨፋለቀ፡ ብረት ኣሣራ አባጀ ("አት ጣቀጠ") ።
አጨፋለቀ፡ አስተራረሰ ("ዕዳሪ አዋጣ") ።
አጨፋጨፈ፡ አማታ/አቈራረጠ ።
አጨፋጨፍ፡ አቈራረጥ/መጨፍጨፍ ።
አጨፋፈር፡ አዘላለል/መጨፈር ።
አጨፋፈቅ፡ አለሳሰቅ መጨፈቅ ።
አጨፋፈነ፡ አከዳደነ/አሸፋፈነ ።
አጨፋፈን፡ አከዳደን/መጨፈን ።
አጫለጠ፡ አቃረረ ("ከዚያም ከዚያም አቃዳ") ።
አጫላጭ፡ ያለጠ/የሚያማልጥ ("የሚ ማለጥ ማቃዳት ማቃረር ማሣረስ") ።
አጫመረ/አጨማመረ፡ አጋባ/አዷ ዷለ/አካተተ/አሰነዳዳ ።
አጫማሪ፡ ያጫመረ/የሚያጫምር ።
አጫሰ፡ እያያዘ አፋፋመ ።
አጫረ፡ አሾተለ/አደባ/ሸመቀ ።
አጫረሰ፡ አጋደለ/አፋጸመ ("አደማደመ") ።
አጫረተ፡ ዋጋ አሳረረ/አባዛ/አበላለጠ ("አፈካከረ") ።
አጫሪ (ዎች)፡ ያጫረ/የሚያጭር ("የጦር ቀንቃኝ ተቈራቋሽ") (፩ ሳሙ. ፲፯፡ ፬) ።
አጫራሽ፡ ያጫረሰ/የሚያጫርስ ("አፋ ጻሚ") ።
አጫራች (ቾች)፡ ያጫረተ/የሚያጫ ርት ("አፈካካሪ አበላላጭ ኀራጅ ባይ") ።
አጫር፡ አቈፋፈር ("መር") ።
አጫሽ (ሾች)፡ ያጨሰ/የሚያጨስ ።
አጫሽ፡ ያጫጫሰ/የሚያጫጭስ ።
አጫሽነት፡ አጫሽ መኾን ("ጪሰኛነት ደድ") ።
ዐጫቂ (ዐጻቂ)፡ ያጨቀ/የሚያጭቅ (ከታች ዐጃቢ ") ።
አጫቈነ፡ አጫጫነ ("ወደ ታች አባባለ አጫፈቀ በበ") ።
አጫብር፡ በጐዣም አውራጃ ያለ አገር ።
አጫብር፡ የዜማ ስም፡ ከአጫብር የተገኘ ዜማ።
አጫተረ (ጫተረ)፡ አሾተለ/አደባ ።
አጫተረ፡ አለፋ/አደከመ ።
አጫታሪ፡ ያጫተረ/የሚያጫትር ("አልፊ አድካሚ") ።
አጫነ፡ ጭነትን እከብት ዠርባ ላይ አዋጣ/አስተሳሰረ ("የሚጭነውን ከብት አያያዘ (ያዘ)") ።
አጫነቀ (አስተጻዐቀ)፡ አጣበበ/አጋፋ ("መተናፈሻ አሳጣ") (ዘዳ. ፳፡ ፲፪፡ ኢሳ. ፲፩፡ ፲፫፡ ዮኤ. ፪፡ ፰፡ ማር. ፫፡ ፱) ።
አጫናቂ፡ ያጫነቀ/የሚያንቅ ("አጣ ባቢ") ።
አጫወተ (አስተጻወተ)፡ ወሬ አወራ/ወግ አወጋ/ነገር አነጋገረ ("አላፋ አ ሣቀ ደስ አሠኘ") (ምሳ. ፮፡ ፳፪፡ ግብ. ሐዋ. ፲፭፡ ፬) ።
አጫወተ፡ አነጋገረ፡ ጨወተ።
አጫዋች (ቾች)፡ ያጫወተ/የሚያጫውት ("አነጋጋሪ አሥቂኝ ጥርስ የማያስከድን አለቃ ገብረ ሐናን አባ ምን ይዋብን ከሉን የመሰለ የጨዋታ ፈላስፋ አዝማሪ ሲያውቅ አበድ ቀልደኛ") ።
አጫዋች፡ የቤተ ክሲያን ጕልላትና ሰበሰብ የበቅሎ ዐልቦ መርገፍ ("በነፋስ ርስ በርሱ እየተጋጨ ድምፅ የሚሰጥ") ።
አጫዋች፡ የወንድና የሴት ስም ።
አጫውተኝ፡ የሰው ስም ።
አጫጪ (አፃእፅአ)፡ አሳነስ/አኰሰሰ/አቀጠነ/አመነመነ ።
አጫጫረ፡ አዋሰደ ፍምን ።
አጫጫረ፡ አዣመረ ጠብን ።
አጫጫኝ፡ ያጫጫነ/የሚያጫጭን የ ኝ ረዳት ።
አጫፈረ፡ አዛለለ ("አቃረበ አያያዘ አቀናጀ") ።
አጫፋሪ (ዎች)፡ ያጫፈረ/የሚያጫፍር ("ፊት ለፊት በአንጻር ያለ የጭፈራ ጓድ") ።
አጫፋሪ፡ አያያዥ/አቀናጂ ("ቃልን ከቃል (ነገርን ከነገር) የሚያያይዝ ራብዕ ፊደል እና ሲነገርም እ ተጐርዶ ይቀራል እከሌና እከሌ ሰማይና ምድር እንዲሉ እናን በስፍራው ተመልከት") ።
አጭላጊ፡ ያጨለገ/የሚያጨልግ ("አው ላጊ አነጣጣሪ") ።
አጭልግ፡ ዝኒ ከማሁ ("አውልግ") ።
አጭበረበረ (ትግ. ጠበረ አባበለ ሸነገለ)፡ አጥበረበረ/አንጸባረቀ ("እንደ ጨበሬ ዐይንን በዘበዘ ማየት ከለከለ") ።
አጭበረበረ፡ አታለለ/አሳሳተ/አደናገረ ("አላዋቂነቱን በመንቀፍ ሰወረ ጠበረን አስተውል") ።
አጭበረበረ፡ አደናገረ፡ በረ።
አጭበርባሪ (ሮች)፡ ያጭበረበረ/የሚ ያጭበረብር ("አሳሳች አደናጋሪ ገረዘ ብለኸ ገራዥን እይ") ።
አጭበርባሪነት፡ አጭበርባሪ መኾን ("አሳሳችነት") ።
አጭፈነፈነ፡ ኣጭበሰበሰ ።
አጮለ፡ በጥፊ መታ (፬ ነገ. ፳፪፡ ፳፬) ።
አጮለ፡ በጥፊ መታ፡ ጮለ።
አጮለ፡ አፈጠነ/ነዳ እጅ ።
አጮኸ፡ የጅራፍን/የጣትን/የማንኛውንም ነገር ድምጥ አሰማ ።
አጮኸ፡ ገረፈ ("ምች መታ") ።
አጯ፡ ጨ ።ማጨት፡ መጨት።
አጯኺ፡ ያጮኸ/የሚያጮኸ ።
አጯጨረ፡ አጠጠረ/አጠና/አጠነከረ ።
አጯጯኸ፡ ቍቁ አባባለ ("ጩኸትን ኣዛመተ አፋጀ") "
አጯጯኸ፡ አተማመም/መጮኸ ።
አጰጰሰ፡ ጳጳስ አደረገ ሾመ ።
አጰጰሽ፡ ያኋጶሰ/የሚያጶጶስ (ሊቀ ጳጳሳት) ።
አጰጳጰስ፡ በአንብሮተ እድ መሾም...“ማጰጰስ ።
አጵሎን፡ የጽርእ ጣዖት ስም፡ የቍንዥና አምላክ ።
አጶሊጡ (አቦሊጡ)፡ የሊጡ ባለቤት፡ ሊጥን የሚያሽ የሚለውስ ። ባለቅኔዎች ግን የምጣድ ብልጭልጭታ ይሉታል ።
አጶራግዛ፡ የማይበላ መጥፎ ዓሣ ።
አጸና (አጽንዐ)፡ እጠና ጽኑ አደረገ ።
አፀናነስ፡ ኣረጋገዝ መፅነስ ። "ጠነሰ ጥንስ" ማለት የሕዝብ አነጋገር ነው ።
አጸናና፡ አረጋጋ አበረታታ ("(ኢሳ. ፷፮፥ ፲፫፡ ዘካ. ፲፥ ፪)") ።
አጸናን፡ አጠናን መጽናት ።
አጸየፈ (አድራጊ)፡ ጸያፍ አደረገ (ኣከፋ ጠላ ናቀ ነቀፈ አቃለለ ") ። "ቢያክ ቢያክ አለ" ("(ተሠቀቀ ተሸቈረረ)") ።
አጸያፊ፡ ያጸየፈ/የሚያጸይፍ (ናቂ ነ ቃፊ ") ።
አጸደቀ (አጽደቀ)፡ አከበረ ጽድቅ ("(እውነተኛ)") አደረገ፡ ጽድቅ አሰጠ፡ አለመለመ ("(፩ ነገ. ፲፰፥ ፴፪)") ።
አጸዳ፡ አጠዳ ።
አጸዳደቅ፡ አለማለም መጽደቅ ።
አጸዳዳ፡ አጠዳዳ ።
አጸፋ፡ የስም ምትክ ፥ —ዐጸፈ ።
አፃረረ (አስተፃረረ)፡ አጣላ ።
አጻና (አስተጻንዐ)፡ አበራታ አጣና ።
አጻኚ፡ ያጻና/የሚያጻና (አበራቺ ") ።
አጻጻፈ (አስተጻሐፈ)፡ አጣጣፈ'ጽፈ ትን ረዳ አላላከ አቀባበለ ።
አጻጻፍ፡ አጣጣፍ መጻፍ ።
አጼ፡ ንጉሠ ነገሥት ፥ —ዐፄ ።
አጽናና፡ መካከረ ተስፋ ሰጠ ኣይ ዞኸ አለ ።
አጽናፍ፡ ዳርቾች ።
አጽደለደለ (አጽደልደለ)፡ አበራ አሸበረቀ አብረቀረቀ አጥበረበረ ። "እመቤታችን ጌታን ከፀነሰች በኋላ ፊቷ ያጽደለድል ነበር" ። ማጽደልደል፡ ማሸብረቅ ማብረቅረቅ ።
አጽዳቂ (ቆች)፡ ያጸደቀ/የሚያጸድቅ (ጠቃሚ አለምላሚ ") ።
አጽድቆ፡ አለምልሞ አልምቶ ። "ዕርፍ አርቆ ተክል አጽድቆ" እንዲሉ ።
አጽፍ፡ ዳባ ፥ —ዐጸፈ ።
አፈ፡ ሕፃን፡ በብርሌ፡ ውስጥ፡ ባለ፡ ውሃ፡ ታይቶ፡ በሕፃን፡ ኣንደበት፡ የሚናገር፡ ዛር፡ ምትሀት።
አፈ፡ ለቃቃ፡ አፈ፡ ሰፊ።
አፈ፡ ሊቅ፡ የሊቅ፡ ወኪልና፡ ምትክ፡ በሊቅ፡ ፈንታ፡ የሚሰብክ፡ የሚከራከርና፡ የሚተች፡ እንደ፡ ቄርሎስ፡ እንደ፡ ዲዮስቆሮስ፡ ያለ፡ እውነተኛ ደቀ፡ መዝሙር፡ አፈቻላ። ለሊቅ፡ ላፈ፡ ሊቅ፡ እንዲል፡ ሙሴ።
አፈ፡ ላማ፡ ከብት፡ ዝሪት፡ ሲበላ፡ የሚከፈል፡ ዕዳ። ላማ፡ ለምለም፡ ወይም፡ ላም።
አፈ፡ ልስልስ፡ ሻካራ፡ ነገር፡ የማይናገር፡ ሰው።
አፈ፡ መምር፡ የመምር፡ ነገረ፡ ፈጅ፡ ልብስ፡ ገፋፊ ።
አፈ፡ ሙዝ፡ የጠመንዣ፡ አፍ፡ ወይም፡ ርሳስ፡ ዐረር ።ሙዝን፡ እይ ።
አፈ፡ ምሣር፡ ኦፉ፡ እንደ፡ ምሣር፡ ስለት፡ ያለው፡ ወስፌ፡ ወሳፍቻ
አፈ፡ ሰፊ፡ አፋም፡ አፈ፡ ለቃቃ፡ ሰው፡ የሸክላ፡ ዕቃ።
አፈ፡ ሸራፋ፡ እንስራ- ጋን ፥ አፉ፡ የተሸረፈ፡ የተሰበረ ።
አፈ፡ ሾሌ፡ ከንፈሩ፡ የበሰለ፡ ሾላ፡ የሚመስል፡ ፈረስ ።
አፈ፡ ቅቤ፡ ነገረ፡ ልስልስ።
አፈ፡ በረከት፡ የቅዱስ፡ ኤፍሬም፡ የስም፡ ሽልማት፡ ስመ፡ ስርጋዌ፡ (ቅጽል)
አፈ፡ ብልጥ፡ ንግግር፡ አሳማሪ።
አፈ ታሪክ (ታሪከ አፍ)፡ ጽሐፍ ሳይኖር በቃል ብቻ የሚነገር፡ ከአባቶች ሲወርድ ሲዋረድ ሲያያዝ የመጣ ያፍ ታሪክ ።
አፈ፡ ንጉሥ፡ በንጉሥ፡ ፈንታ፡ የሚፈርድ፡ የፍርድ፡ ባለሥልጣን፡ የመንግሥት፡ ዋና፡ ዳኛ ።
አፈ፡ እስር፡ የማይናገር፡ ሽብብ።
አፈ፡ ከፋታ፡ ያልተከደነ ።
አፈ፡ ወሪሳ፡ ያፍ፡ ዘረፋ፡ አፍ፡ እንዳመጣ፡ እንደ፡ ተገኘ፡ ወሬ፡ ማውራት ።
አፈ፡ ወርቅ፡ የሰው፡ ስም፡ መንፈሳዊ፡ ድርሰቱ፡ በዓለም፡ የተደነቀ፡ የጽርእ፡ ሊቀ፡ ጳጳሳት ።ዮሐንስ፡ አፈ፡ ወርቅ፡ ቢል፡ ግን፡ ቅጽል፡ ይኾናል ።
አፈ፡ ዋሾ፡ የዋሾ፡ ነገር፡ የሐሰተኛ፡ አፍ። የቀሚስ፡ ዝምዝም፡ ወይም፡ ጥልፍ።
አፈ፡ ዘርጣ፡ ተሳዳቢ።
አፈ፡ ድስት፡ አፉ፡ ድስት፡ የሚመስል፡ ብርሌ፡ መውዜር፡ ጠመንዣ።
አፈ፡ ድዳ፡ መናገር፡ የማይችል፡ ሰው።
አፈ፡ ጉባኤ፡ የጉባኤ፡ አፍ፡ የማኅበር፡ ጠበቃ፡ የብዙ፡ ሰው፡ ነገረ፡ ፈጅ።
አፈ፡ ግም፡ አፉ፡ የሚገማ።
አፈ፡ ጎማ፡ ድዳ
አፈ፡ ጨዋ፡ የሊቅ፡ የመምር፡ የደቀ፡ መዝሙር፡ ሳይኾን፡ ያልተማረ፡ ሰው፡ ማይምን፡ የሚናገረው፡ ነገር፡ ቃል፡ ወግ፡ ታሪክ።
አፈ፡ ጭቃ፡ ከንፈረ፡ ጥቍር፡ ሰው፡ በቅሎ፡ አህያ፡ ውሻ።
አፈ፡ ጮሌ፡ አፈ፡ ብልጥ።
አፈ፡ ጸያፍ፡ ኰልታፋ።
አፈ፡ ጻድቅ፡ አፉ፡ እውነተኛ፡ ልቡ፡ ሐሰተኛ፡ የኾነ፡ አታላይ፡ ግብዝ፡ የተናገረውን፡ የማያደርግ፡ ከንፈረ፡ መጣጭ፡ (ሉቃ፲፮፡ ፲፭)።
አፈለ፡ ጐለመሰ ፥ —ዐፈለ ።
አፈለለ፡ አሰፋ (ትልቅና ሰፊ አደረገ ") ።
አፈለሰ (አፍለሰ)፡ ቈፈረ፥ደደቀ ማሰ ደነጐረ ናደ ፈነቀለ አነገለ ነቀለ ሻረ አወጣ፡ ወደ ሌላ አገር ወሰደ ("(ኤር. ፳፪፥ ፲፪፡ ዳን. ፪፥ ፳፩)") ።
አፈለሰ፡ ዐደሰ ለወጠ ።
አፈለሳሰፍ፡ አረቃቀቅ (መፈልሰፍ ") ።
አፈለቀ (አፍለቀ)፡ አመነጩ አወጣ አፈሰሰ ጠበልን ("(ምሳ. ፲፭፥ ፪፡ ኤር. ፮፥ ፯)") ። "ሙሴ በምድረ በዳ ለእስራኤል ውሃ ከአለት አፈ ለቀ" ።
አፈለቀ፡ ቀረሸ ሕፃኑ ።
አፈለቀ፡ ከጠላ ከጠጅ ከማንኛውም መጠጥ ላይ ጠብ አደረገ ።
አፈለቃቀጥ፡ አከፋፈል (መፈልቀጥ ") ። "በ ለቀጠን" እይ ።
አፈለቃቅ፡ አበታተን (መፈልቀቅ ") ።
አፈላ (አፍልሐ)፡ አሞቀ አንተከተከ ፥ አነፈረ አፍለቀለቀ (በእሳት በጸሎት ") ።
አፈላ፡ አመነጨ አፈለቀ አፈሰሰ ("(ዘዳ. ፴፩፥ ፳)") ።
አፈላ፡ አበቀለ ችግኝን ።
አፈላ፡ ዝናምና ዘር ፈለገ (መሬቱ ነቃ ኩፍ አለ ") ።
አፈላለል፡ አወፋፈር አሰፋፍ (መፍለል ") ።
አፈላለመ፡ አቀዳደመ አዠማመረ ።
አፈላለም፡ አቀዳደም (መፈለም ") ።
አፈላለስ፡ አመነቃቀር (መፈለስ ") ።
አፈላለስ፡ አነጋገል (መፍለስ ") ።
አፈላለቅ፡ አመነጫጨት (መፍለቅ ") ።
አፈላለቅ፡ አቀዳደድ (መፈለቅ ") ።
አፈላለገ፡ አፈቃቀደ ።
አፈላለግ፡ አፈቃቀድ (መፈለግ ") ።
አፈላለጠ፡ አሠነጣጠቀ አፈነካከተ ።
አፈላለጥ፡ አሠነጣጠቅ (መፍለጥ ") ።
አፈላላ፡ መላልሶ አፈላ ።
አፈላላጊ፡ ያፈላለገ/የሚያፈላልግ ።
አፈላል፡ አቅ (መፍላት ") ።
አፈላሎ፡ ያሣ ቋንጣ ቅቅል ።
አፈላሾ፡ ችግኝ ግልግል ከመደቡ ' የ ፈለሰ የተነቀለ ።
አፈላሾ፡ ግልግል ፥ —ፈለሰ ።
አፈላቀቀ፡ አለያየ አፈራቀቀ አላቀቀ ።
አፈላቃቂ፡ ያፈላቀቀ/የሚያፈላቅቅ (ጥ ጥን ፍንጅን ") ።
አፈላፈለ፡ አቀፋቀፈ (ፍሬን አዋጣ ") ።
አፈላፈለ፡ አቃረጸ አባሳ ።
አፈላፈል፡ አቀፋቀፍ (መፈልፈል ") ።
አፈሠ፡ ዘገነ ፥ —ዐፈሠ ።
አፈሰ፡ ዘገነ ፥ —ዐፈሠ ።
አፈሰሰ፡ ኑዛዜን ነገረ ።
አፈሰሰ፡ አከሳ አቀጠነ (ገላን ") ። አጠፋ (ሥባትን ") ። "ሙክቱ አፈሰሰ" እንዲሉ ።
አፈሰሰ፡ አፈረሰ አረከሰ ። "ቄሱ ሥል ጣኑን አፈሰሰ" ።
አፈሰሰ፡ ደፋ ቸለስ ከነበለ ("(ኢሳ. ፶፯፥ ፮)") ። አወረደ አንጠባጠበ (ክዳኑ ዝናምን ") ። አቀ ለጠ አነጠረ (ጃን ሸላሚው ወርቅን ብርን ") ።
አፈሳሰስ፡ አወራረድ አቀላለጥ መፍሰስ ።
አፈሳስ፡ በታች አተነፋፈስ (መፍሳት ") ።
አፈረሰ (አፍረሰ)፡ ናደ እጠፋ ሻረ ("(፪ ነገ. ፳፫፥ ፰፥ ፲፪፥ ፲፭፡ ዮሐ. ፭፥ ፲፰)") ። (ግጥም)፡ "ዐይናማ ሰው ቤቴን አፈረሰው" ። "ባ፲፫ኛ ተራ ቤትን" ተመልከት ።
አፈረሰ፡ ቈመጠ ገላን አበላሸ ።
አፈረሰ፡ በተነ ዘረዘረ ።
አፈረሰ፡ ተወ ጣለ (ቅስናን ድቍናን ቆብን ") ።
አፈረሰ፡ ዐሎ አለ (ቃሉን ለወጠ ") ።
አፈረቀ (አፍረቀ)፡ አስለየ አስከፈለ ።
አፈረቃቀቅ፡ አለያየት (መፈርቀቅ ") ።
አፈረኵምሽሽ አለ፡ ፥ —ዐፈረ ።
አፈረካከስ፡ አሰባበር (መፈርከስ ") ።
አፈረጠ (አፍረጸ)፡ ጣለ ሰበረ ፈነ ከተ ።
አፈረጠ፡ አወጣ ።
አፈረጠ፡ አፈነዳ አመገለ አፈሰሰ ።
አፈረጠ፡ ገለጠ አበራ አስረዳ ። "አቶ እከሌ ነገሩን አፍርጦ ይናገራል" ።
አፈረጠመ፡ አጠበቀ አሠባ ጠረነቀ ።
አፈረጣጠም፡ አሠባብ (መፈርጠም ") ።
አፈረፈረ፡ ፍርፋሪን ሹሮን በወጥ ላይ ነሰነሰ ጨመረ ።
አፈራ፡ ፍሬ ሰጠ ። (ፈራ፡ ፈረየ፡ ፈርኀ) ።
አፈራረም፡ የፊርማ አጻጻፍ (መፈረም ") ።
አፈራረሰ፡ በታተነ አጠፋፋ ። (ግጥም)፡ "ቤት እሠራ ብለሽ አታዋሪ ለሰው፡ መጣ ሙሶሊኒ የሚያፈራርሰው" ።
አፈራረስ፡ አጠፋፍ (መፍረስ ") ("(ኢሳ. ፳፬፥ ፲፫)") ።
አፈራረቀ (አስተባረየ)፡ አስተጋገዘ አስተራረፈ (አዘዋወረ እለዋወጠ ") ። "ገበረው አንድ ጥንድ ከቀንጃ ስላለው በሮቹን እያፈራ ረቀ ዕርሻውን ያርሳል ። ያቶ እከሌ ሚስት እያፈራረቀች ወንድና ሴት ትወልዳለች" ።
አፈራረቀ፡ አስተራረፈ ፥ —ፈረቀ ።
አፈራረቅ፡ አከፋፈል (መፍረቅ ") ።
አፈራረድ፡ አበያየን (መፍረድ ") ።
አፈራረጠ፡ አመጋገለ ።
አፈራረጥ፡ አመጋገል (መፍረጥ ") ።
አፈራራሚ፡ ያፈራረመ/የሚያፈራርም (አጻጻፊ አዋዋይ ") ።
አፈራራቂ፡ ያፈራረቀ/የሚያፈራርቅ (አ ስተጋጋዥ አለዋዋጭ ") ።
አፈራር፡ አሠጋግ (መፍራት ") ።
አፈራር፡ የፍሬ አሰጣጥ (ማፍራት ") ።
አፈራቀቀ፡ አላቀቀ አለያየ አራራቀ ።
አፈራቃቂ፡ ያፈራቀቀ/የሚያፈራቅቅ (አ ላቃቂ አለያዪ ") ።
አፈራከሰ፡ አሳበረ አዳቀቀ ።
አፈራፈረ፡ አሸራሸረ አማማሰ ።
አፈራፈረ፡ አዳቀቀ አጣቀነ ።
አፈራፈር፡ ፍርፈራ (መፈርፈር ") ።
አፈር መሬት፡ ዐፈር ።
አፈርሳታ (ፈርሰወ)፡ አውጫጭኝ፡ ባላገር ሥዕል ወግቶ ምሎ ተገዝቶ በጥፋተኛ ላይ የሚናገረው ምስክርነት ።
አፈርሳታ አወጣ፡ አጥፊን ገለጠ አስታወቀ ።
አፈርሳታ፡ ወጣ ።
አፈርፋሪ፡ ያፈረፈረ/የሚያፈረፍር (ነስ ናሽ ጨማሪ ") ።
አፈቀ፡ በጨፈቃ ላይ ደንጊያ አ ጫጫነ፲ አላሰቀ ።
አፈቀረ (ፈቀረ)፡ ወደደ ወዳጅ አደ ረገ አቀረበ ።
አፈቀረ፡ ወደደ ፥ —ፈቀረ ።
አፈቃቅ፡ አቈራር (መፍቃት ") ።
አፈተለተለ፡ አጥመዘመዘ፡ ፈ ተለ ።
አፈተለከ፡ ፈታ ። (ፈተለከ) ።
አፈተላለክ፡ አሾላለክ ማፈትለክ ።
አፈተተ (አፍተወ)፡ አሻ አስፈ ለገ አፈቀደ ።
አፈተተ፡ አፈቀደ ፥ —ፈተተ ።
አፈታ፡ ደምን አበዛ አፈሰሰ አወረደ (ባለማቋረጥ ") ። "እከሌ በጦር ስለ ተወጋ ደም አፈታበትና ሞተ" ።
አፈታተል፡ አወዛዘግ መፍተል ።
አፈታተር፡ አስተናነቅ መፈተር ።
አፈታተሽ፡ አመራመር መፈተሽ ።
አፈታተት፡ አቈራረስ መፈተት ።
አፈታተነ፡ አፈታተሸ አመራመረ አ ሞካከረ ።
አፈታተን፡ አሞካከር መፈተን ።
አፈታተገ፡ አወቃቀጠ አስተወደ አመላለጠ ።
አፈታተግ፡ አወቃቀጥ መፈተግ ።
አፈታት፡ አተራተር አከፋፈት (መፍ ታት ") ።
አፈታፈተ፡ አራራሰ ፥ ኣዳቀቀ ።
አፈታፈት፡ አራራስ መፍትፈት ።
አፈትላኪ፡ ያፈተለከ/የሚያፈተልክ (አሹላኪ ") ።
አፈቸለ፡ ልጅ በሽማግሌ መካከል ተ ናገረ (ለፈለፈ ተቸ ተከራከረ ወገጠ አላና ግር አለ ") ። "ጌታችን በተወለደ በ12 ዓመቱ በሊቃውንት መካከል ሲያፈችል ተገኘ" ("(ሉቃ. ፪፥ ፵፪፥ ፵፯)") ።
አፈቸለ፡ ተረተ ።
አፈቸለ፡ ወገጠ፡ ፈቸለ ።
አፈቻላ፡ ለፍላፊ ተቺ ተከራካሪ ወጋጭ አሉተኛ ።
አፈቻላ፡ ተራች ተረተኛ ።
አፈቻቸል፡ አነቃቀል መፈቸል ።
አፈቻይ፡ ያፈቸለ/የሚያፈችል (የነገር ተቃራኒ ") ።
አፈነ፡ ሸፈነ ፥ —ዐፈነ ።
አፈነ፡ ኣካደነ/አሻፈነ "
አፈነረ፡ ኣገጠጠ አፈነገጠ ጥርስን ። ልማዱ ግን እንደ ኹለተኛው ተገብሮ ነው ።
አፈነቃቀለ፡ አገለባበጠ አለያየ ።
አፈነቃቀል፡ አገለባበጥ (መፈንቀል ") ።
አፈነተተ፡ አሳጠረ ዐጪር አደረገ ። ልማዱ ግን ተገብሮ ነው ።
አፈነቻቸር፡ አጣጣል (መፈንቸር ") ።
አፈነካከር፡ አከፋፈት (መፈንከር ") ።
አፈነካከተ፡ አፈላለጠ አሰባበረ "
አፈነካከት፡ አፈላለጥ (መፈንከት ") ።
አፈነደረ፡ ወገቡን ዐጠፈ (ደረቱንና ' ጕልበቱን ገጠመ፡ ቂጡን ትርፍ አደረገ፡ ልጥቅ ሳይል ቀረ ") ። "በመኝታ ላይ ማፈንደር"፡ "ሰውነትን ማጠፍ" ።
አፈነደረ፡ ወገቡን ዐጠፈፈ ነደረ ።
አፈነደቀ፡ አፈነጠዘ ።
አፈነደደ፡ አጐነበሰ ቂጡን ሰጠ መከተ ለኳስ ። "፱ኛውን ሸመጠጠ" ተመልከት ።
አፈነዳ፡ ተረተረ ሠነጠቀ አፈረሰ በተነ ።
አፈነዳ፡ አፈካ ።
አፈነዳደቅ፡ አደሳሰት (መፈንደቅ ") ።
አፈነዳደድ፡ አጐነባበስ (ማፈንደድ ") ።
አፈነዳድ፡ አፈካክ (መፈንዳት ") ።
አፈነጀረ፡ ለየ አራቀ አጠመመ ።
አፈነጀረ፡ አጠመመ ፥ —ፈነጀረ ።
አፈነጃጀረ፡ ኣወለጋገደ አወነጋገረ ።
አፈነገጠ፡ አፈነረ አወጣ አገጠጠ ።
አፈነጋገል፡ አጣጣል (መፈንገል ") ።
አፈነጠ፡ አናረ ።
አፈነጠዘ፡ አበላ አጠጣ (እንዲደሰቱ ") ።
አፈነጣጠር፡ አበታተን (መፈንጠር ") ።
አፈነጣጠቀ፡ አረጫጨ አበታተነ ።
አፈነጣጠቅ፡ አረጨት (መፈንጠቅ ") ።
አፈነጣጠዝ፡ አደሳሰት (መፈንጠዝ ") ።
አፈነጣጠጥ፡ አወጣጥ (መፈናጠጥ ") ።
አፈነጣጣቂ፡ ያፈነጣጠቀ/የሚያፈነጣ ጥቅ ።
አፈነጫጨት፡ አቦራረቅ (መፈንጨት ") ።
አፈነፈነ፡ አነፈነፈ ።
አፈነፈነ፡ አነፈነፈ ፥ —ፈነፈነ ።
አፈናሪ፡ ያፈነረ/የሚያፈንር (አግጣጭ አፈንጋጭ ") ።
አፈናቀለ፡ ኣገላበጠ አለያየ ።
አፈናቃይ፡ ያፈናቀለ/የሚያፈናቅል (አ ገላባጭ ") ።
አፈናከተ፡ ኣፋለጠ አሳበረ ።
አፈናካች፡ ያፈናከተ/የሚያፈናክት ።
አፈናጀረ፡ አራራቀ አወላገደ አጣመመ ።
አፈናጠረ፡ በተነ ፥ —ፈነጠረ ።
አፈናጠቀ፡ አራጪ አናዛ አባተነ ("(ፈነጠቀ)") ።
አፈናጠጠ፡ በወዴላ ላይ አስ ቀመጠ ፈነጠጠ ።
አፈናጠጠ፡ ባንድ በቅሎ ላይ ኹለ ተኛ ። ሰው አስቀመጠ (አዳበለ ") ።
አፈናጣቂ፡ ያፈናጠቀ/የሚያፈናጥቅ ።
አፈናጣጭ፡ ያፈናጠጠ/የሚያፈናጥጥ ።
አፈናጪ፡ አዛለለ አቧረቀ ።
አፈናፈነ፡ አነፋነፈ (አወላዳ አዛመረ ") ።
አፈናፈን፡ አነፋነፍ (ማፈንፈን ") ።
አፈንዳቂ፡ ያፈነደቀ/የሚያፈነድቅ ።
አፈንዳጅ፡ ያፈነደደ/የሚያፈነድድï አ ጐንባሽ ።
አፈንጂ፡ ያፈነዳ/የሚያፈነዳ (ተርታሪ ሠንጣቂ ") ።
አፈንጋጭ (ጮች)፡ ያፈነገጠ/የሚ ያፈነግጥ (አግጣጭ ") ።
አፈንጣዥ፡ ያፈነጠዘ/የሚያፈነጥዝ (አ ብሊ ' አጠጪ ") ።
አፈንፋኝ፡ አነፍናፊ ።
አፈኛ (ኞች)፡ (አፋዊ) አፋም ለፍላፊ ነገረኛ ጨቅጫቃ።
አፈኛነት፡ ለፍላፊነት ተናጋሪነት፡ አፈኛ መኾን።
አፈከፈከ፡ አነተበ ፈከፈከ ።
አፈከፈከ፡ ኣነተበ (ፈለግ አወጣ ሠነ ጠቀ ") ።
አፈካ፡ አስደሰተ አሣቀ ።
አፈካ፡ አፈነዳ አሳበበ ።
አፈካከረ/አፎካከረ፡ አወዳደረ አከራ ከረ አቀታተረ ("እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ" አባባለ ") ።
አፈካከር/አፎካከር፡ አደነፋፍ (መፈ ከር/መፎከር ") ።
አፈካካሪ/አፎካካሪ፡ ያፈካከረ ' ያፎካ ከረ፡ የሚያፈካክር/የሚያፎካክር (አወዳዳሪ ") ።
አፈካክ፡ አፈነዳድ (መፍካት ") ።
አፈዋወስ፡ የጤና አሰጣጥ (መፈወስ ") ።
አፈዘዘ፡ ዐዘመ አቦዘ አደነዘዘ አደነ ገዘ ("(ዘፍ. ፴፪፥ ፴፪)") ።
አፈዛዘዝ፡ ኣዘነጋግ (መፍዘዝ ") ።
አፈየ (አፍይ አፈየ ጋገረ አበሰለ)፡ ከደነ ገጠመ ልክክ አደረገ፡ ዐፈነ ።
አፈያየድ፡ አረባብ (መፈየድ ") ።
አፈደፈደ (አፈድፈደ)፡ አበዛ አተ ረፈ አበለጠ "
አፈዳደን፡ አስተሳሰር (መፈደን ") ።
አፈዳፈደ፡ አባዛ አባለጠ ።
አፈዳፈድ፡ ኣበዛዝ (መፈድፈድ ") ።
አፈጀ፡ አረጀ ። "አፈጀ ከ፸ ዓመት በላይ መኾንንና የብርታትን ፈጽሞ ማለቅ ያሳያል" ።
አፈጃጅ/አፈጃጀት፡ አቀጣጠል አጨ ራረስ (መፍጀት ") ።
አፈገ፡ ዐጀበ አከማቸ፡ ብዙውን አንድነት አደረገ፡ መሰገ ።
አፈገገ፡ ኣበራ (ጥርስ ኣስገለጠ ") ።
አፈገፈገ (ገገጸ)፡ ወደ ኋላ አለ ኼደ (ከፍራት የተነሣ አሸገሸገ ") ። "(ተረት)" - ምንም ብታፈገፍጊ ከግድግዳ አታልፊ ። አፈግፋጊ፡ ያፈገፈገ/የሚያፈገፍግ (አ ውራ በግ ጦረኛ ") ።
አፈገፈገ፡ ወደ ኋላ አለ፡ ፈ ገፈገ ።
አፈጋገም፡ አደፋፍ (መፈገም ") ። "ገተረን" አስተውል ።
አፈጋገግ፡ አሣሣቅ (መፍገግ ") ።
አፈጋገጥ/አጣጣል/መፈገጥ ። "ፈነገጠን" ተመልከት ።
አፈጋፈገ፡ አሸጋሸገ ጥቂት አራራቀ ።
አፈጋፈገ፡ አፋፋቀ አጣረገ ።
አፈጋፈግ፡ አፋፋቅ (መፈግፈግ ") ።
አፈጋፋጊ፡ ያፈጋፈገ/የሚያፈጋፍግ (አ ሸጋሻጊ አፋፋቂ አራራቂ ") ።
አፈጠረቀ፡ አፈነዳ፡ (ፈጠረቀ) ።
አፈጠነ (አፍጠነ)፡ አቀለጠፈ እቸ ኰለ ("(ሉቃ. ፳፬፥ ፲፪)") ።
አፈጠጠ፡ ሲበላ ሲጠጣ አየ ቀላ ወጠ ከጀለ ።
አፈጠጠ፡ አጐረጠ (ዐይኑን ጐለጐለ ") ። "ዐይኑን አፍጥጦ እስኪያፍር ድረስ ተመለ ከተው" ("(፪ነገ. ፰፥ ፲፩)") ።
አፈጠፈጠ፡ አቈጠቈጠ ጨበጨበ ል ምላሜ ዠመረ ። "ጐመጐመን" እይ ።
አፈጠፈጠ፡ አቈጠቈጠ ፈጠ ።
አፈጣጠመ፡ አቃጠረ አዋዋለ ("ንጉሥ ይሙት" አባባለ ") ። "ሙግቱ በዚህ ቀን፡ ሰርጉ ለገና ወይም ፋሲካ ውጭ ይኹን እሠኛኘ" ።
አፈጣጠም፡ አጨራረስ (መፈጠም ") ።
አፈጣጠር፡ አሠራር (መፍጠር ") ።
አፈጣጠን፡ አቸኳኰል (መፍጠን ") ።
አፈጣጠጥ፡ አጐራረጥ (መፍጠጥ ") ።
አፈጣጣሚ፡ ያፈጣጠመ/የሚያፈጣጥም (ሹም ") ።
አፈጣፈጠ፡ አፈናከተ አቋሰለ ።
አፈጣፈጥ፡ አፈነካከት (መፈጥፈጥ ") ።
አፈጫጭ፡ አፈጫጨት፡ አከረታተፍ አሰላለቅ (መፍጨት ") ።
አፈፈ (አፊፍ አፈፈ)፡ ከረከመ ።
አፈፈ፡ ቀፈፈ፡ ከመመ፡ ቀረደደ፡ ቈረጠ፡ ዐረደ፡ አነሣ፡ ያዘ፡ ጫፍን፡ አፍን፡ ዐንገትን፡ ዕቃን ። ፈፋንና ፈፍን ተመልከት፡ የዚህ ዘሮች ናቸው ። ቀረጠፈን እይ ።
አፈፋ፡ ቀፈፋ ቅርደዳ ዐረዳ ። ባፈፋ በጐደፋ እንዲሉ ።
አፈፍ (አፊፍ)፡ መያዝ መጨበጥ ማንሣት ።
አፈፍ አለ፡ ብድግ አለ፡ ፈጥኖ ተነሣ ።
አፈፍ አደረገ፡ ለቀም አደረገ፡ ባፍ በፍጥነት ያዘ ጨበጠ እነሣ በጅ ።
አፈፍ አፈፍ አለ፡ ብድግ ብድግ አለ ።
አፉን ነጠበው፡ ሳያስበው ድፍረት ተናገረ ።
አፉን አጠፋ፡ የተናገረው ሳይኾንለት ቀረ ።
አፉን ከፈተ፡ ተናገረ፡ ዝም አላለም ።
አፉን ያዘ፡ ዝም ዕክም ጸጥ አለ ።
አፉን ይበላዋል፡ ተናገር ተናገር ይለዋል ።
አፉን ይይዘዋል፡ ትክክል አይናገርም ።
አፉን ፈታ፡ መናገር ቻለ ዠመረ ። ዳግመኛም ከስምና ከቅጽል ተናቦ፡ እሾኻፍ እሳታፍ ክፍታፍ ሙጢ አፍ ሙሬ አፍ ፍየላፍ ሹላፍ እያለ ዘርፍ ይዞ ሲነገር በቂ ይኾናል፡ ኹሉንም በተራው ተመልከት ።
አፉፉ፡ የዘፈን አዝማች፡ ባጤ ምኒልክ ጊዜ የተዘፈነ ዘፈን ።
አፊያዥ (ዦች)፡ ያፌዘ/የሚያፌዝ (አላጋጭ ") ።
አፊያጭ፡ ያፌጠ/የሚያፌጥ (ቀላጅ ") ።
አፊያፊያዘ፡ አዋዛ አላገጠ ።
አፊያፊያጠ፡ አቃለደ ።
አፋ፡ ማረጃ፡ አፈፈ።
አፋ፡ ሰፊ ሙሴ ከግፉ ቀና ያለ ካራ ማረጃ፡ እጀታው ደም ዐፋሽ ይባላል ። (ግጥም)፡ ቆመሽ ስትገት ዳኛው እያደላ፡ ባፋረዱኸ እንጂ እትኸ ምን ልበላ ። ቀነተ ብለኸ ቅናትን እይ ።
አፋ፡ አፈጋፈገ አሳሳለ አንቀ ቀጨ ብረትን ጥርስን ("(መዝ. ፻፲፪፥ ፲፡ ሰቈ. ፪፥ ፲፮፡ ማር. ፱፥ ፲፰)") ።
አፋለመ፡ አዣመረ አቃደመ ።
አፋለመ፡ አጋራ አካፈለ ።
አፋለሰ (አስተፋለሰ)፡ አሳሳተ እቃ ወሰ አዛወረ ኦለዋወጠ ።
አፋለሰ፡ አጣላ አገተ፡ አማታ አዋለቀ ።
አፋለገ፡ አፋቀደ ።
አፋለጠ (አስተፋለጠ)፡ አሠናጠቀ አፈናከተ ።
አፋላ (አስተፋልሐ)፡ ኣቀ አና ፈል ።
አፋላሚ፡ ያፋለመ/የሚያፋልም (አዣ ማሪ ኣካፋይ ") ።
አፋላሽ፡ ያፋለሰ/የሚያፋልስ (አቃዋሽ ") ።
አፋላጊ፡ ያፋለገ/የሚያፋልግ '
አፋላጭ፡ ያፋለጠ/የሚያፋልጥ (አሠና ጣቂ አፈናካች ") ።
አፋመ (አፍሐመ)፡ አጋመ አበሰለ አንደረከከ ፍም አወረደ አመረተ ቈለለ ።
አፋሚ (አፍሓሚ)፡ ያፋመ/የሚያ
አፋሰሰ፡ አስተሳሰበ አሳላ ።
አፋሰሰ፡ አተላን አዳፋ አከናበለ አቻለሰ ።
አፋሰሰ፡ ያንዱን ትርፍ ወደ ሌላው ወሰደ አማላ ።
አፋሰሰ፡ ደም አቃባ ።
አፋሳሽ፡ ያፋሰሰ/የሚያፋስስ ።
አፋረመ/አፈራረመ፡ አጻጻፈ አዋዋለ አቀባበለ (ፊርማን ") ።
አፋረሰ፡ አናናደ አባተነ ።
አፋረሰ፡ ከሞት ዳነ ተመለሰ አስተፋሳ ።
አፋረሰ፡ የገበያን ውል አካካደ ።
አፋረደ፡ አባየነ ። "አፋረደና ባፋ ዐረደ" በአማርኛ ይገጥማሉ ። "ቆመኸ ስትገት ዳኛው እያደላ ባፋረዱኸ እንጂ፡ እትኸ ምን ልበላ" ።
አፋራ፡ ማካፋት ዠመረ ። (ፋራ) ።
አፋራ፡ ፋራን ተከተለ አነፈነፈ ።
አፋራ/አፈራራ፡ አጠራጠረ ።
አፋራሽ፡ ያፋረሰ/የሚያፋርስ (አናናጅ ") ።
አፋራጅ፡ ያፋረደ/የሚያፋርድ ።
አፋር (ሮች)፡ የአዳል ነገድ ስም ።
አፋሸከ፡ አስደሰተ ።
አፋሸገ፡ አዛጋ፡ ፋሸገ ።
አፋሸገ፡ አፉን ከፈተ አላቀቀ አዛጋ ።
አፋሻጊ፡ ያፋሸገ/የሚያፋሽግ (ሰው ወ ይፈን አውራ ") ።
አፋቀ (ዕብ. አፋቅ)፡ በረታ ጠና ጠነከረ ። "ያፋቀ ያፋቀውን ለሞት ይሰጥ ዠመረ" ("ልብ ወለድ - አፈ ወርቅ ገ. ኢ.") ።
አፋቀ፡ ሕቅ ሕቅ አለ ። (ፋቀ) ።
አፋቂ፡ ያፋቀ/የሚያፍቅ (ብርቱ ጨካኝ ") ።
አፋተለ (አመግደመ)፡ እግሩን አመ ሳቀለ አጣመረ ።
አፋተለ፡ አቃጠረ አገናኘ ።
አፋተለ፡ ፈትልን ረዳ አጋመደ ።
አፋተሸ፡ አበራበረ አመራመረ አቀና ቀነ ።
አፋተተ፡ አቋረሰ አካፈለ አተናተነ አሳተፈ ።
አፋተነ (አስተፋተነ)፡ አማከረ አ ፋተሸ አስታገለ ።
አፋተገ፡ ኣሸካሸከ አዋቀጠ አስተሻሸ አላፋ አላላጠ ።
አፋታ፡ አለያየ አላቀቀ ። (ተረት)፡ "ሥራ ስፈታ ልጄን ላፋታ" ።
አፋታ፡ አተራጐመ ።
አፋታሽ፡ ያፋተሸ/የሚያፋትሽ (አመራ ማሪ ") ።
አፋታኝ (አስተፋታኒ)፡ ያፋተነ/የ ሚያፋትን (አስታጋይ ") ።
አፋታይ (ዮች)፡ ያፋተለ/የሚያፋትል (አቃጣሪ ") ።
አፋታይነት፡ ኣፋታይ መኾን ።
አፋታጊ፡ ያፋተገ/የሚያፋትግ (አዋ ቃጭ ") ።
አፋቺ፡ ያፋታ/የሚያፋታ (ባልና ሚ ስትን የሚያለያይ የነገር አባት ") ።
አፋነነ፡ አነሣ አቀና ቀሰረ አቆመ ዥራትን፡ አሮጠ ሰውን ከብትን ።
አፋከረ/አፋከረ፡ አደናፋ (ግዳይ አቋ ጠረ ") ።
አፋወሰ/አፈዋወሰ፡ ኣስተካከመ ፈው ስን አሰጣጠ (አዳዳነ # ") ።
አፋዘዘ፡ ኣንጻር ለአንጻር (አኳዃነ አስ ተያየ ") ።
አፋዛዥ፡ ያፋዘዘ/የሚያፋዝዝ ።
አፋደሸ፡ በሰው ነገር ገባ፡ (ፋ ደሸ) ።
አፋዳሽ (ሾች)፡ ያፋደሸ/የሚያፋድሽ (አጐብጓቢ ጥልቅ ብዬ ነገር አመላላሽ ") ።
አፋጀ፡ አጨቃጨቀ አጯጯኸ "
አፋጀሽን፡ አመንዝራ ገለሞታ ሴት "
አፋጂ፡ ያፈጀ/የሚያፋጅ (አጨቃጫቂ ") ።
አፋገ፡ አሰፋ አበዛ "
አፋገ፡ አፈሰሰ አቃጠለ አጐደፈ ።
አፋገረ፡ አለፋ አደከመ ።
አፋጊ፡ ያፈገ የሚያፍግ፡ ዐጃቢ መሳጊ ።
አፋጠነ (አስተፋጠነ)፡ አቻኰለ አ ጣደፈ ።
አፋጠጠ፡ አጓረጠ ("(ጥሳ)") አሳለፈ አቻ ኰለ ኣፋዘዘ አጣደፈ ።
አፋጣኝ፡ ያፋጠነ/የሚያፋጥን (አቻኳይ ") ።
አፋጣጭ (ጮች)፡ ያፋጠጠ/የሚያፋ ጥጥ (አጣዳፊ ጠላት ሽንት ዐይነ ምድር ") ።
አፋጨ፡ በትንፋሽ ዘፋነ ፥ —(ፋል) ።
አፋጩ (አስተፋጽሐ)፡ ኣከራተፈ አዳዳስ ።
አፋጪ፡ ያፋ/የሚያፋጭ (አሳሳይ ") ።
አፋፊ፡ ያፈፈ የሚያፍፍ፡ ቀፋፊ ከርካሚ ።
አፋፊ፡ ያፋፋ/የሚያፋፋ (አዳባሪ ") ።
አፋፋ፡ አወፈረ አዳበረ አደነደነ አሳመረ (ሕፃንን ግልገልን ጥጃን ") ።
አፋፋመ (አስተፋሐመ)፡ አጝቀ አጣደፈ አበራታ አቃረበ ምጥን ጦርን ።
አፋፋሚ፡ ያፋፋመ/የሚያፋፍም ።
አፋፋም፡ አጋጋም (መፋም ") ።
አፋፋር፡ አጫጫር (መፋር ") ።
አፋፋቀ (አስተፋሐቀ)፡ አጣረገ አላ ላገ አላዘበ ።
አፋፋቅ፡ አላላግ (መፋቅ ") ።
አፋፍ (ፎች)፡ የገደል አፍ፡ የተራራ ጫፍ ። በግእዝ አፈ ጸድፍ ይባላል ። አፋፍ ላፋፍ ኼደ ። ካፍ ከወጣ አፋፍ እንዲሉ ።
አፌ፡ የኔ አፍ፡ ነገረ ፈጅ ።
አፌዘ፡ አላገጠ፡ (ፈየዘ ፌዘ) ።
አፌጠ፡ ቀለደ አሌጠ (በሰው ላይ አፌዘ አላገጠ ") ። "ዘበተን" እይ፡ ከአፌጠና ከአ ፌዘ ጋራ አንድ ነው ።
አፌጠ፡ አሌጠ፡ (ፈየጠ ፌጠ) ።
አፍ ፣ ስለት። ኹለት፡ አፍ፡ ሰይፍ፡ እንዲሉ፡ (መዝ፻፵፱፡ ፮) ።
አፍ ፣ አስተርጓሚ፡ ስማ፡ በለው፡ ትርጁማን፡ አምጃር፡ አነጋጋሪ፡ ጠበቃ፡ ወኪል፡ የነገር፡ አባት። ባፌ፡ እንዲል፡ ተከሳሽ።
አፍ፡ (አፈወ፡ አፈፈ)፡ በቁሙ፡ በከንፈርና፡ በከንፈር፡ መካከል፡ ያለ፡ ክፍት፡ መተንፈሻና፡ መናገሪያ፡ የቃል፡ የትንፋሽ፡ የመብል፡ የመጠጥ፡ የነገር፡ ኹሉ፡ መውጫ፡ መግቢያ፡ የሚከፈትና፡ የሚዘጋ፡ የሕዋሳት፡ በር ።በለፈለፉ፡ ባፍ፡ ይጠፉ። በርን፡ ደጅን፡ ተመልከት። (የዥብ፡ አፍ)፣ ቀጩማ።
አፍ፡ ላፍ፡ (አፈ፡ በአፍ)፡ ቃል፡ ለቃል ። አብርሃምና፡ እግዜር፡ አፍ፡ ላፍ፡ ተነጋገሩ።
አፍ፡ መፍቻ፡ አባባ፡ እማማ።
አፍ፡ ሰጠ፡ ነገር፡ መለሰ።
አፍ፡ ሲከዳ፡ ከሎሌ፡ ይብሳል፡ ከታላቅ፡ ጕዳት፡ ያደርሳል።
አፍ፡ ሳቻ፡ (ስሕተተ፡ አፍ)፡ ያፍ፡ ስሕተት፡ ያልታሰበ፡ ስድብ፡ ነቀፋ።
አፍ፡ ቂጡ፡ ሸበተ፡ ፈጽሞ፡ አረጀ።
አፍ፡ ቂጥ፡ (አፈ፡ ቂጥ)፡ ፈጋራ ።አፍ፡ ቂጡ፡ ሣቀ፡ ፈካ፡ እጅግ፡ ተደሰተ ።
አፍ፡ ቃል፡ ነገር፡ ቋንቋ። የኦሮ፡ አፍ፡ የፈረንጅ፡ አፍ፡ እንዲሉ።
አፍ፡ ተጅ፡ (አፍ፡ ምስለ፡ እድ)፡ ቅርብ፡ አጠገብ። በምግብ፡ ጊዜ፡ አፍና፡ እጅ፡ እንዳይተጣጣ፡ ይኸም፡ እንደዚያ፡ ነው።
አፍ፡ አሲያዘ፡ ዝም፡ አሠኘ፡ መልስ፡ አሳጣ።
አፍ፡ አወጣ፡ ጠበቃ፡ እያለው፡ ተናገረ ።
አፍ፡ አፉን፡ አሉት፡ የተናገረው፡ እንዳይሰማ፡ አደረጉት፡ ኹሉም፡ መለሱለት።
አፍ፡ አፍ፡ ሌላ፡ ልብ፡ ሌላ፡ ሸንጋይ፡ አታላይ፡ ደላይ፡ (ዘፍ፫፡ ፩፭) ።
አፍ፡ ያለው፡ ጤፍ፡ ይቈላል፡ ነገር፡ አሳማሪ፡ እውነትን፡ ለሐሰት፡ ይለውጣል ።
አፍ፡ ፈርጅ ፱ ፫ቱን ቋጭቼ አንድ አፍ ቀርቶኛል።
አፍለቀለቀ (አንሳዕስዐ)፡ አፈላ አን ተከተከ አዘለለ አስጨፈረ ።
አፍለቀለቀ (ጥሠ)፡ አሠገረ አንሸረሸረ ።
አፍለቀለቀ፡ አብለጨለጨ አብረቀረቀ (ተግ ተግ አደረገ ") ።
አፍለኛ፡ ጕልማሳ ዐፈለ ።
አፍለከለከ፡ አላወሰ አንቀሳቀሰ አስለ ከለከ ።
አፍለከለከ፡ አስለከለከ ፥ —ፈለከ ።
አፍሊ (ዎች)፡ ያፈላ/የሚያፈላ ።
አፍላል (ሎች)፡ ከማሰሮ የሚበልጥ ሸክላ (የንስራ አጋማሽ ") ።
አፍላል፡ በቁሙ፡ ፈለለ ።
አፍላሽ (ሾች)፡ ያፈለሰ/የሚያፈልስ (አንጋይ ነቃይ ") ።
አፍላቂ፡ ያፈለቀ/የሚያፈልቅ (አፍሳሽ ") ።
አፍሌታ (ቶች)፡ ጥዋ፡ የጥዋ ዐይነት ።
አፍልሖ፡ ለትምርት የሚደገም አስማት ።
አፍሳሽ (ሾች)፡ ያፈሰሰ/የሚያፈስ (ቸላሽ ከንባይ ኣቅላጭ አንጥረኛ ") ("(ኤር. ፮፥ ፳፱)") ። "ብር አፍሳሽ" እንዲሉ ።
አፍሳሽነት፡ አፍሻሽ መኾን አንጥረኛ ነት ።
አፍረመረመ፡ በላ ጋጠ፡ አተጋ ፥ —ፈረመ ። (ፈረከ) ።
አፍረመረመ፡ በአፉ ይዞ በመሬት ላይ አጋድሞ ወዲያና ወዲህ አለ (ወዘወዘ መላ ልሶ ነከሰ በላ ጋጠ ነፈነፈ ") ።
አፍረመረመ፡ አተጋ (እንዲጣጣር አደ ረገ፡ አፍጨረጨረ ") ።
አፍረምራሚ፡ ያፍረመረመ/የሚያፍረመ ርም (አትጊ ") ።
አፍረቀረቀ፡ ሰባበረ (ግንብን ") ።
አፍረቀረቀ፡ አነፈረቀ አፍረጠረጠ (ዕባ ጭን ") ።
አፍረቀረቀ፡ ዳማ ።
አፍረከረከ፡ ፈረፈረ ።
አፍረገረገ፡ አቅዘመዘመ አረገረገ ወዘ ዘወዘ ።
አፍረጠረጠ፡ አድፈጠፈጠ (መላልሶ ተጫነ ጨቈነ ") ።
አፍረጥራጭ፡ ያፍረጠረጠ/የሚያፍረጠ ርጥ (አድፈጥፋጭ ") ።
አፍሪ፡ ያፈራ/የሚያፈራ "
አፍሪቃ (አፍራቅያ)፡ ኹለተኛው የ ዓለም ክፍል (የካም ዕጣ ወይም ድርሻ ") ። ግእዝ የማያውቁ ሰዎች ግን እንደ ፈረንጅ "አፍሪካ" ይሉታል ።
አፍሪቃ፡ በቁሙ ፥ —ፈረቀ ።
አፍራሽ (ሾች)፡ ያፈረሰ/የሚያፈርስ (ናጂ አጥፊ ") ። "ሠርቶ አፍራሽ" እንዲሉ ።
አፍራሽ፡ አይ አን አት ። ፫ቱንም በ የስፍራቸው አስተውል ።
አፍራሽ፡ የነገር ተቃራኒ አሉታ ("አል - አ ") ። "ኾነ ፥ ይኾን ኖረ ይኖር" ተብሎ ሲነገር፡ "አልኾነ አይኾን አልኖረ አይኖር" ማለት ።
አፍራሽነት፡ አፍራሽ መኾን አሉታነት ።
አፍራዲቆ፡ በድንኳን ጣራ ዙሪያ ዐልፎ ዐልፎ ያለ ብስ አውታር የሚገባበት፡ በማስ የተለበደ ከናስ ቀለበት የተዋደደ ነዳላ ።
አፍራጭ፡ ያፈረጠ/የሚያፈርጥ (አም ጋይ ") ።
አፍሬ (ዎች)፡ የማረሻ ጫፍ ሹለቱ (ፍሬ ሰጪ ማለት ነው ") ።
አፍሬ፡ የማረሻ ጫፍ፡ (ፈራ፡ ፈረየ፡ ፈርኀ) ።
አፍሬ፡ የጦር መሣሪያ አፍ (ወይም ስለት ") ("(ኢዮ. ፳፥ ፳፬)") ።
አፍርንጅ፡ ንጣቱ ነበልባል የሚመስል ድቍስ (የበርበሬ ፍሬ ርጥብ ሥጋ መብሊያ ") ።
አፍርንጅ፡ የበርበሬ ፍሬ፡ ፈ ረንጅ ።
አፍርንጅ፡ ፈረንጆች ። "አፍርንጅ" የግእዝ' አነጋገር ነው ። "ታሪከ ነገሥት" እይ ።
አፍሮ አይገባ፡ የደብረ ሊባኖስ መስቀል መነኮሳቱ ላማላጅነት ይዘውት የ ሚኼዱ (ሰላምን ሳያገኝ የማይመለስ ማለት ነው ") ።
አፍሻት፡ ጥዋ ፥ —ዐፍሻት ።
አፍቃሪ (ፈቃሪ)፡ ያፈቀረ/የሚያፈ ቅር (ወዳጅ ") ።
አፍቃሪነት፡ አፍቃሪ መኾን (ወዳጅ ነት ") ።
አፍቃሪዎች፡ የሚያፈቅሩ/የሚወዱ ።
አፍቅሮ፡ ማፍቀር ("(ግእዝ)") ። "አፍቅሮ ንዋይ"፡ ገንዘብ መውደድ ።
አፍተለተለ፡ አጥመዘመዘ አልመዘመዘ ሆድን ።
አፍተለተለ፡ ኣለፋ ቈዳን፡ ጐተተ ሰውን ።
አፍተለተለ፡ ገላን ዐሸ እድፍን አ ወጣ አጥመለመለ ።
አፍተልታይ፡ ያፍተለተለ/የሚያፍተለ ትል (አጥመዝማዥ አልመዝማዥ የሆድ በሽታ ") ።
አፍታ (አፍ)፡ ጊዜ ፈንታ ዝም እመም ተለላ ቃዳ ። እከሌ አፍታ አይሰጥም ። ጊዜ ፈንታ መጥቶ ነበር ። አንድ አፍታ ሠርቶ ኼደ ። ገዝም እመም ። አፍታ ማለት የአፍን መከፈትና መዘጋት ያሳያል ። አፈፈን እይ ።
አፍታታ፡ ነገርን መረመረ ቍቲትን ዘረዘረ ገላን ዐሸ (ደምን በተነ ") ።
አፍታቺ፡ ያፍታታ/የሚያፍታታ (መርማሪ ዳኛ በታኝ ") ።
አፍነከነከ፡ አስደሰተ ፥ —(ፈነከ) ።
አፍነዘነዘ፡ አቅነዘነዘ ፥ —ፈንዝ ።
አፍነዘነዘ፡ አቅነዘነዘ ኣክነፈነፈ አክ ለፈለፈ ወዘወዘ አወከ አሮጠ ።
አፍነዝናዥ፡ ያፍነዘነዘ/የሚያፍነዘንዝ ።
አፍነዝንዝ/አክነፍንፍ/አክለፍልፍ፡ ድ ግምት አስማት '
አፍና አፍኣ፡ ግእዝ አፈወ ከሚለው ይወጣሉ ።
አፍንጫ '
አፍንጫ (ጮች)፡ በተንቀሳቃሽ ፍጥ ረት ኹሉ በኹለት ዐይኖቹ መካከል የተ ተከለ የማሽተት ሕዋስ (የትንፋሽ የነፋስ መውጫና መግቢያ ባለኹለት ፍንጭ ") ። በግ እዝ "አንፍ" ይባላል ። "ላፍንጫ ግም አፍንጫ ድፍን ያዝለታል" እንዲሉ ። "ወጣን" ተመል
አፍንጫ ሰልካካ፡ አፍንጫው ዋ ስልክ የሚመስል ።
አፍንጫ ስንደዶ፡ አፍንጫው ዋ ቀጥታ የኾነ ስንደዶ መሳይ ።
አፍንጫ፡ በቁሙ ፈነወ ።
አፍንጫ አቅልጥ፡ ውርጭ ብርድ ።
አፍንጫ ደፍጣጣ፡ ዳመጦ (ዐዳ ዝንጀሮ ") ።
አፍንጫ፵ ጐማዳ፡ አፍንጫው ያጠረ ።
አፍንጮ፡ የንቀት አጠራር (አግቦ አፍ ንጫ የለሽ ማለት ነው ") ።
አፍኣ ወጣ፡ ዕዳሪ ተቀመጠ ።
አፍኣ፡ ውጭ ዕዳሪ፡ ደጅ ወልወል፡ ሜዳ ከቤት ከቅጥር ከመንደር በውጭ ያለ፡ በውስጥ ያይዶለ ልዩ ቦታ ።
አፍኣዊ፡ የውጭ፡ ሥጋዊ ዓለማዊ ።
አፍኣውሰንሰለት፡ ውስጡ፡ ዐውደ ነገሥት፡ ሐሰተኛ ባሕታዊ ጠንቋይ ።
አፍኸ ይረፍ፡ አትናገር፡ ዝም በል ።
አፍዛዣ፡ አቅጣጫ አንጻር ፊት ለፊት አኳያ ።
አፍዛዣ፡ አቅጣጫ ፈዘዘ ።
አፍዛዥ፡ ፪ ' የበገና ዥማት ።
አፍዛዥ፡ ያፈዘዘ/የሚያፈዝ ።
አፍዝ፡ ዐዚም አስማት መድኀኒት ።
አፍዝ አደንግዝ፡ መርዝነት ያለው ዓሣ ሲይዙት የሚያፈዝ የሚያደነግዝ ። ጠን ቋይ በቈዳው ክታብ ይጽፍበታል ።
አፍደደ፡ ዥብኛ አስኬደ ።
አፍጃጀ፡ የአብቃቃ ተቃራኒ (ብዙ ወጪ አደረገ - በተነ ገንዘብ ጨረሰ አባከነ ") ።
አፍገመገመ (አተንተነ)፡ አንገደገደ አርገደገደ (ለማውደቅ ") ። "ወተረ" ብለኸ "አውተረ ተረን" እይ ።
አፍገመገመ፡ አንገደገደ፡ ፈ ገመ ።
አፍገምጋሚ፡ ያፍገመገሙ/የሚያፍገመ ግም (አንገድጋጅ ስካር ") ።
አፍገረገረ፡ አዋሰበ ፥ —ፈገረ ።
አፍገረገረ፡ አጣመረ አዋሰበ ዕንጨ ትን ።
አፍገረገረ፡ አፍጨረጨረ አጫተረ ።
አፍገርጋሪ፡ ያፍገረገረ/የሚያፍገረግር (አጣማሪ አዋሳቢ ") ።
አፍጋብ፡ ኦሮ፡ የኦሮ ነገድና አገር ።
አፍጣኝ (ኞች)፡ ያፈጠነ/የሚያፈጥን (ቶሎ የሚሠራ የሚፈጽም ") ። "(ተረት)" - አፍጣኝና አቅጣኝ እመዳሮ እንገናኝ ።
አፍጣጭ (ጮች)፡ ያፈጠጠ ፥ የሚያ ፈጥ (አጕራጭ ቀላዋጭ ") ።
አፍጣጭነት፡ አፍጣጭ መኾን (ቀላዋ ጭነት ") ።
አፍጥጥ፡ ዝኒ ከማሁ ለአፍጣጭ ' አ ጕርጥ ።
አፍጨረጨረ፡ አተጋ ፥ —ፈረ፡ ፋረ ።
አፍጨረጨረ፡ አተጋ አጣረ አትከረ ኰረ ።
አፍጨርጭሪ፡ ያፍጨረጨረ/የሚያፍጨ ረጭር ።
አፍጮ፡ አተራመሰ ፥ —ፈጩ ።
አፍጮ፡ ወረረ ዐመሰ አተራመሰ አፋጀ (ዘረፈ ቀማ ነጠቀ ") ።
አፎቄ (ዎች) (ወቃዬ አፍ ወ ጋኤ አፍ)፡ በቁሙ፡ ሰውን በወጋ ጊዜ እንደ አፋ ባፉ (በስለቱ) የሚቈርጥ የሚቀድ ቅጠለ ሰፊ ታላቅ አበታ ጦር ።
አፎት (ቶች)፡ የሰይፍ የጐራዴ ቤት ድርቄ ሰገባ አፍ ። (፩ሳሙ ፲፯ ፥ ፯ ። ኢሳ ፳፪ ፥ ፱ ። ኤር ፵፯ ፥ ፮ ። ሕዝ ፳፩ ፥ ፲ ፥ ፬) ። ነገር ቢሳሳት ከጥንቱ፡ ሰይፍ ቢመለስ ካፎቱ ። አፍ ከአፈወ እንደ ወጣ እፎትም ከአፈፈ ይወጣል። ምስጢሩም አፍነትን ሳይለቅ መክበብንና ማቀፍን ያመለክታል ። (ተረት)፡ እጅግ ስለት ይቀዳል አፎት፡ እጅግ ብልኀት ያደርሳል ከሞት ።
አፎት፡ ሽፋፍ ጐረንጐሬ ። (ዘፍ ፳፯ ፥ ፫ ። ሰቈ ፫ ፥ ፲፫) ።
አፎች፡ (አፈዋት)፡ በቁሙ፡ ክፍቶች፡ ፍንጮች፡ (ኤር፭፡ ፲፮)። አፍ፡ እየተናበበ፡ ቅጽልና፡ በቂ፡ ኹኖ፡ እንደሚያምርለት፡ ይፈታል፡ በተሳቢነትም፡ ይነገራል ።
አፎናነን፡ አቈራረጥ (መፎነን ") ።
አፎንቻ፡ መልከ ጥፉ ፉንጋ አፍን ቢስ ።
አፎካከት፡ አስተካከክ (መፎከት ") ።
አፎጣጠር፡ አስተሳሰር አሸባበብ (መፎ ጠር ") ።
ኡ ካዕብ፡ ፪ኛ፡ ኹለተኛ ድምፅ፡ ኹለተኛነቱ ለአ አ ግእዝ ። ዳግመኛም ካዕብነቱን ከወ ካዕብ ዉ ነሥቶ ለሌላው ፊደል ያራክባል ። በ ኡ ፥ ቡ ። ጐ ኡ ፥ ጉ ።
ኡሁ፡ የሳል የጕንፋን ድምፅ ። ኡሁ ኡሁ አለ፡ ሳለ ጐበሰተ ።
ኡራኑስ፡ ከፀሓይ ብርሃን ከሚነሡ ከ፯ቱ ኮከቦች ፯ኛው ኮከብ ።
ኡራኤል፡ የመልአክ ስም፡ ብርሃነ አምላክ፡ ያምላክ ብርሃን ማለት ነው ።
ኡኡ አለ፡ ቍቱ አለ፡ ጮኸ ።
ኢ ሳልስ፡ ፱ኛ (ሦስተኛ ድምፅ)፡ ሳልስነትን ከየ ሳልስ ዪ ወስዶ ሌላውን አ ፊደል ሳልስ ያደርጋል ። በ ኢ ፥ ቢ ። ገ ኢ ፥ ጊ ።
ኢ፡ በቁሙ፡ የንቀትና የማኰሰስ የማዋረድ ቃል ። እዪ ።
ኢምንት፡ ምንም፡ ያይደል፡ ከቍጥር፡ የማይገባ፡ የተናቀ፡ ስም፡ የለሽ፡ ነገር። ኢምንት፡ ግእዝኛ፡ ነው ።
ኢሳ (ሶች)፡ የነገድ ስም፡ በሐረርጌ ቈላ ኣዳል አጠገብ ያለ የሱማሌ ሕዝብ፡ አገሩም ኢሳ ይባላል ።
ኢሳይያስ፡ የሰው ስም፡ በዖዝያንና በኢዮአታም በአካዝ በሕዝቅያስ ዘመን የነበረ ነቢይ ።
ኢትዮጵ፡ ኢትዮጲስ፡ ኹለተኛ የኵሽ ስም፡ በጽርእ ኢትዮፕስ ይባላል ።
ኢትዮጵያ (ጽርኢቲዖፒኣ)፡ ያገር ስም፡ የኖባ ልጆች የሱዳኖች አገር፡ መላው ጠቅላላው፡ ከግብጽ ቀጥሎ ያለው፡ ትርጓሜው ቈላ በረሓ ምድረ በዳ ። (ዘፍ ፲ ፥ ፲፫ ። መዝ ፸፪ ፥ ፱ ። ፸፬ ፥ ፲፬ ። ኢሳ ፴፯ ፥ ፱) ።
ኢትዮጵያ፡ የመልክና የሕብር ስም፡ ጥቍር ጠቋራ ከሰልማ ማለት ነው፡ በዐረብ ሱዳን በዕብራይስጥ ኵሽ ይባላል ። ዳግመ ኛም በኵሽ ልጆች በሳባ ሳባ በአቢስ ኣቢሲኒያ የተባለችው የትግሬና የአማራ አገር ከሮ ሊቃናት በኋላ ኢትዮጵያ ተብላለች፡ በአግዓዚ አግዓዝያ በሐበሻት ሐበሻ እንደ ተባለች ። አቢስን ተመልከት፡ ሐዲሱን መጽሐፈ ሰዋስው እይ ። በቂና ቅጽል ኹኖ ሲነገር፡ ቅጽልነቱም ከስም ጋራ ሲጻፍ ነው ።
ኢትዮጵያዊ፡ የኢትዮጵያ ሰው ።
ኢትዮጵያዊት፡ የኢትዮጵያ ሴት ።
ኢትዮጵያውያት፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ።
ኢትዮጵያውያን፡ የኢትዮጵያ ሰዎች ።
ኢነባቢ፡ የማይናገር (እንስሳ/አውሬ/ወፍ/ተንቀሳቃሽ ኹሉ) ።
ኢየሱስ ክርስቶስ፡ የጌታችን ድርብ ስም፡ ክርስቶስን እይ ። ኢየሱስ የተዋሕዶ፡ ክርስቶስ የተቀብዖ ስሙ ነው ።
ኢየሱስ፡ የመጠሪያ ስም፡ (ስመ ተጸውዖ)፡ መድኅን ፥ መድኀኒት ማለት ነው ።
ኢየሩሳሌም ሰማያዊት፡ ከጠፈር ወደ ላይ ዐምስተኛ ሰማይ ።
ኢየሩሳሌም፡ ያገር ስም፡ የዳዊት ከተማ ። የሴዱ ልጅ ሳሌም ስለ ነገሠባት በዕብራይስጥ ይሩሻሌም (ሀገረ ሰላም) ተብላለች፡ (ኪ፡ ወ፡ ክ)።
ኢየሩሳሌሞች፡ የኢየሩሳሌም ሰዎች ።
ኢየሩሴ፡ ዐተር፡ ኢየሩሳሌም ።
ኢየሩሴ፡ ያተር ስም፡ መጠኑ ካገራችን ዐተር የሚበልጥ፡ መልኩ አቦልሴ ። ከኢየሩሳሌም ስለ መጣ ኢየሩሴ ተባለ ።
ኢዮሃ፡ (ኢዮ እይ፡ ሃ ውሃ)፡ ወንዶች የደመራ ለት እየዘፈኑ ድምሩን የሚዞሩበት ያበባ ዘፈን፡ የደስታ ቃል ። ኢዮሃ አበባዬ፡ ውሃ ያደረገውን እይ ።
ኢዮሄ ኢዮሄ አለ፡ ጮኸ ከጭንቅ የተነሣ ። እከሌ በጠና ስለ ታመመ ዛሬ ሌሊት ኢዮሄ ኢዮሄ ሲል ዐደረ ።
ኢዮሄ፡ ጩኸት ፥ ወለሌ ፥ ኤሎሄን የመሰለ ።
ኢዮር፡ ከጠፈር እስከ መንበር ያሉ ሰባቱ ሰማያት ።
ኢጣሊያ፡ የጣሊያን አገር፡ (ዕብ ፲፫፡ ፳፬)። ይኸውም፡ ኢታሎ፡ ከሚባል፡ ሰው፡ ስም፡ የመጣ፡ ነው።
ኣ፡ (አንባሕትዎ)፡ ማዛጋት ፥ ማፋሸግ ፥ ማላቀቅ ፥ መክፈት ።
ኣ ራብዕ፡ ፬ኛ (አራተኛ ድምፅ) ። የራብዕን ሥረይነት ከሀ ራብዕ ሃ እየተጋራ ሌላውን ፊደል ራብዕ ያደርጋል ። በ ኣ ፥ ባ ።
ኣ፡ ባድራጊ ግስ የትንቢትና የዘንድ አንቀጽ መነሻ እኔ በሚል ። እወጣኹ ፥ አወጣ ፥ ኣወጣ ዘንድ ። አወረድኹ ፥ ኣወርድ ፥ ኣወርድ ዘንድ ። ይኸውም ፥ ሌሎቹ አሥራው ፥ ያ ፥ ታ በመኾናቸው ይታወቃል ።
ኣ አለ፡ አዛጋ ፥ አፋሸገ ፥ አላቀቀ ። ኣ በል ኣፍኸን ክፈት፡ (ሕዝ ፪፡ ፳) ።
ኣለሻሸቅ፡ ኣለፋፍ፡ መላሸቅ።
ኣለዘዘ፡ በመጠኑ፡ አራሰ።
ኣማዘ፡ (አምዐዘ)፡ አሸተተ፡ አጣፈጠ።
ኣማይ (አምሓሊ)፡ ያማለ/የሚያምል ጠላት/ባለጋራ ወይም ሌላ።
ኣምሸከሸከ፡ ሰባበረ፡ መሸከ ።
ኣሰመረ (አስመረ)፡ አበጀ/አሳመረ ።
ኣሰካከር፡ አጠነባበዝ፡ መስከር።
ኣሰፋፈረ፡ አለካካ/አመጣጠነ።
ኣሰፋፋ/አስፋፋ፡ ሰፋፊ አደረገ፡ ዘረጋጋ ።
ኣሳለ (አስዐለ)፡ ኡሁኡሁ አሠኘ፡ አስጐበሰተ (በርበሬ/ዐቧራ/ትንፋን ሰውን) ።
ኣሳለለ (ኣዕለለ)፡ አስነከረ በቀለም ።
ኣሳከለ፡ ከፍ አስደረገ፡ አስጨመረ ።
ኣስተበተበ፡ አስደገመ ።
ኣስተታተም፡ በማኅተም አረጋገጥ (ማተም ") ።
ኣስተነኰለ፡ ተንኰል አስተማረ አሠራ ።
ኣስከሬን (ኖች)፡ የሰው ዐጥንት በመቃብር ውስጥና ከመቃብር ውጭ የሚገኝ ዐፅም፡ ለሬሳም ይነገራል።
ኣስኰለኰለ፡ ኵልኵል አስበጀ ("አስ ደረደረ አስተከለ ") ።
ኣስያ ሰ፡ አስፈጪ/አስላመ ።
ኣራት ፈርጅ)፡ ኩታ ጋቢ ።
ኣርዕድ)፡ የግዕዝ, አንቀጥቅጥ ያማርኛ ነው - የግዕዝ ሲሆን አማርኛው አንቀጥቅጥ ነው። ይህን ልብስ የዱሮ ነገሥታት የሞት ፍርድ በሚፈርዱበት ቀን ይለብሱታል ግርማ ይሰጣቸዋል - ይህን ልብስ የድሮ ነገሥታት የሞት ፍርድ በሚፈርዱበት ቀን ይለብሱት የነበረ ሲሆን ግርማ ይሰጣቸዋል።
ኣሸለቀቀ፡ አስቀደደ እስላጠ እስፃፈፈ ።
ኣሸለተ፡ ሊጡ በታች ቀረራው በላይ ኾነ (ጥቅልል አለ አቀረረ) ።
ኣሸላለት፡ ኦቈራረጥ መሸለት ።
ኣሸላለግ፡ አገማገም፡ መሸለግ ።
ኣሸመጠ፡ አኰረፈ፡ (ሸመጠ) ።
ኣሸረዳደድ፡ አነቃቀፍ መሸርደድ ።
ኣሸረፈ፡ አሰበረ አስቈረሰ ።
ኣሸራረብ፡ አደራረብ መሸረብ ።
ኣሸባበብ፡ አስተባበት፡ መሸበብ ።
ኣሸንዳ (ትግ)፡ ርጥብ ገሣ፡ የትግሬ ልጃገረዶች በበዓል ቀን ያሸርጡታል ።
ኣሸካከም፡ ባናት በንቃ ላይ አያ...ያዝ መሸከም ።
ኣሸጓጐጥ፡ ኦወታተፍ፡ መሸጐጥ ።
ኣሸፋፈነ፡ ኣከናነበ ።
ኣሻለ፡ አዳነ ፥ —ሻለ ።
ኣሻል (ትግ አሽዓል)፡ በለጭ ግንባረ ነጭ ከብት ።
ኣሽቃጣሪ (ዎች)፡ ያሽቃጠረ/የሚያሽቃጥር (ዘፋኝ ") ።
ኣሽከረከረ፡ አንደረደረ ፥ ከረከረ ።
ኣሽጓበጠ፡ አሽማጠጠ ጐ በጠ ።
ኣቍስጣ፡ አቃተተ ቃሰተ ። ተሳነ ። (ቃተ) ።
ኣቈራመደ፡ ጨበጠ/አኰራመተ ።
ኣቈራረስ፡ አፈታተት/መቍረስ ።
ኣቈታሚ፡ ያቈተመ/የሚያቈትም (አ ጓጒ ") ።
ኣበ ተኸራ፡ የጭቅጭቅና የንዝንዝ ባለቤት ፥ ጌታ ። ተከረን ተመልከት ።
ኣበለለ (አብለለ)፡ አጠፋ አበላሸ፡ ከንቱ ብላሽ አደረገ ።
ኣበረዘ፡ አበረደ አበረሰ ኣቀዘቀዘ ።
ኣበተከ (አብተከ)፡ ከንቱ አደረገ አበላሸ ነገርን ።
ኣበታተን፡ አዘራር አዘራዘር፡ መበተን ።
ኣቡነ ተክለ ሃይማኖት፡ አባ ተክሌ (የእቲሳው) ።
ኣቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፡ ኣቦ የዝቋላው ።
ኣቡጀዲ፡ የልብስ ስም ።
ኣባል፡ ብልት፡ የገላ ክፍል፡ (ግእዝ) ።
ኣባት (አብ)፡ ወላጅ፡ አስገኝ ፥ አሳዳጊ ሞግዚት መነኵሴ ።
ኣቤሴሎም፡ የሰው ስም፡ አበ ሰላም፡ የሰላም አባት ።
ኣብርጣሞ (ኦሮ)፡ ሽሩባ ።
ኣብተው፡ ዝኒ ከማሁ ። አሸንፈው ማለት ነው ።
ኣብዬ፡ የሰው ስም፡ ባ፲፰፻ ዓ ም የነበረ የሺዋ ባላባት ።
ኣቦክ፡ በዐሰብና በጅቡቲ መካከል ያለ ወደብ ።
ኣተማተመ፡ አደማደመ ።
ኣተርፍ፡ ኣበዛ ኣክል እጨምር ። ("ኣተርፍ ባይ አጕዳይ" እንዲለ) ።
ኣታኰሰ፡ ዋጋ አጋደለ ።
ኣቸራቸረ፡ አተናተነ ኣዘረዘረ...በችር ጓሮ አሻሻጠ ።
ኣነራረት፡ አመታት ' መነረት ።
ኣናከረ፡ አዳነቀ (ዕጹብ ድንቅ አባባለ) ።
ኣንቈረፈፈ፡ ቈፈነነ፡ (ቈረፈፈ)።
ኣንከወከወ፡ አዞረ፡ (ከወከወ)።
ኣንከዋረረ፡ አንቀዋለለ፡ (ከወረረ)።
ኣከለ፡ (አኪል፡ አከለ)፡ ዐጕልና ገቢር ። በቁሙ፡ አደገ ፥ ላቀ ፥ ከፍ አለ ፥ ጐለመሰ፡ አካል ጨመረ ።
ኣከለ፡ ኾነ ፥ መሰለ ። (ተረት)፡ ያለ ልጅ አከለ ።
ኣከል፡ አካል፡ የሚያኸል ከፍየሚል፡ ዋና ፥ ትልቅ ፥ ከፍተኛ ። ባለቤት አከል፡ አካል ዳኛ እንዲሉ።
ኣከበ፡ (ከዐበ)፡ ሰበሰበ ፥ አከማቸ ።
ኣከፈለ (አክፈለ)፡ ከእኸል/ከውሃ ተለይቶ ፫ ቀን ያኸል ጦመ ።
ኣክሽ፡ ብላሽ፡ አክ ።
ኣወለካከፈ፡ አሰነካከለ/እደነቃቀፈ ።
ኣወረቀ፡ አሳለቀ/አሣሣ ።
ኣወዛ፡ ላሚ።
ኣዘፈነ፡ አንቀጠቀጠ/አንዘፈዘፈ ።
ኣዘፋኝ፡ ያዘፈነ/የሚያዘፍን ("አዘላይ አስጨፋሪ የዘፈን መሪ") ።
ኣዜብ
ኣየኹኽ፡ አየኹሽ፡ የሕፃናት ጨዋታ ።
ኣዪ፡ (አይ)፡ ቃለ አኀስሮ፡ የማዋረድ ቃል፡ ለመናቅ ፥ ለማኰሰስ ፥ ለማቃለል የሚነገር ዘዬ ። ኣዪ አንተ እኔን ታኸለኛለኸን ። ንኡስ - አገባብ ነው ።
ኣያት፡ (አይይ፡ አየየ)፡ ያባትና የናት አባት፡ ወንድ አያት፡ አባትንና እናትን የሚመስል ።
ኣይለምደኝም)፡ በዚህ፡ ጥፋት፡ ኹለተኛ፡ አልመለስም።
ኣይለምደውም)፣አይደግመ ውም።
ኣደባ፡ ደበቀ/አደፈጠ (ላሸ) አሸመቀ ። "ልማዱ ግን ተደበቀ ሸመቀ ነው" (ዘፍ. ፬፡ ፯፡ ኤር. ፭፡ ፮, ፯፡ ሰቈ. ፬፡ ፲፱፡ ሉቃ. ፮፡ ፯፡ ግብ. ሐዋ. ፳፡ ፭, ፫) ።
ኣደናግር፡ ዥጕርጕር የሸማ ጥለት ("ኣሳስት ማለት ነው") ።
ኣገነባበር፡ አጠናን/አጠነካክር/መገን ።
ኣግድም፡ በቁሙ ፥ —ገደመ ።
ኣጡንባር፡ የሽቱ ቅጠል፡ ዐጠነ።
ኣጥቢያ ኮከብ፡ ለእሑድ አጥቢያ እንዲሉ ።
ኣጨረቀ፡ አወጣ/አነጣ ።
ኣጨራረት፡ አሰዛዘት ("ማጭረት ") ።
ኣጻፈ (ኣጽሐፈ)፡ አስጣፈ አስከተበ አሳተመ ።
ኣጽናፍ ሰገድ፡ ያጤ ገላውዴዎስና ያጤ ዘድንግል ስመ መንግሥት ።
ኤ ኃምስ፡ ፩ኛ (ዐምስተኛ ድምፅ) ። ኃምስነትን ከየ ኃምስ ዬ ተቀብሎ ሌላውን ፊደል ኃምስ ያደርጋል ። በ ኤ ፥ ቤ ። ገ ኤ ፥ ጌ ።
ኤ፡ ቃለ አንክሮ፡ ዬ ።
ኤሊ፡ የሰው፡ ስም፡ ፡ ዔሊ።
ኤሊ፡ ደንጊያ፡ ልብሱ፡ ዔሊ።
ኤሌትሪክ፡ የብርሃን፡ የመብራት፡ ስም፡ የሚበርቅ፡ የሚያንጸባርቅ፡ ማለት፡ ነው፡ በግእዝ፡ እለቄጥሩ፡ ይባላል፡ (ሕዝ፩፡ ፬፡ ፳፯) ። ባ፲፯፻፡ ዓ፡ ም፡ የፈለሰፈው፡ (የመረመረው)፡ እንግሊዛዊው፡ ጊልበር፡ ነው፡ ይባላል፡ ዳግመኛም፡ ቦልታ፡ የሚባል፡ ጣሊያን፡ በሥራ፡ ላይ፡ እዋለው፡ ይላሉ።
ኤል፡ አምላክ፡ ፈጣሪ። ገብርኤልንና፡ ሚካኤልን፡ እይ፡ ኤሎሄን፡ ተመልከት።
ኤልሞሌ፡ (ኦሮሞ) ፥ የዝኆን፡ ግልገል፡ ጥጃ፡ ወይም፡ ወገዝ፡ (ኰርማ) ። (ግጥም)፡ ከገደሉም፡ አይቀር፡ ይገድሏል፡ ኤልሞሌ፡ ባለብዙ፡ ጭፍራ፡ ባለብዙ፡ ሎሌ ።
ኤሎሄ፡ አምላኬ። ኤልን፡ እይ። ኤሎሄ፡ ኤሎሄ፡ አለ፡ (ጽራሐ፡ መስቀል)፤አምላኬ፡ አምላኬ፡ አለ ።
ኤረር፡ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ያለ ተራራ ። የረረን እይ፡ ኤረር ግእዝኛ፡ የረር ዐማርኛ ።
ኤረር፡ ከጠፈር በላይ ከራማ በታች ያለ ብሩህ ሰማይ ።
ኤረጨት፡ አፈነጣጠቅ, መርጨት - መረጨት።
ኤርትራ፡ በአፍሪቃና በእስያ መካከል ያለ ቀይ ባሕር፡ እስራኤል ሙሴ ከፍሎላቸው የተሻገሩበት፡ ፈርዖን ከነሰራዊቱ የሰጠመበት ። በኛም በኩል ወደቦቹ ምጥዋ ዐሰብ ኦቦክ ናቸው ።
ኤባ፡ ዝንጀሮ፡ የዝንጀሮ ባት ። ኤባ ገደል ገባ እንዲሉ ልጆች ።
ኤክላ፡ አካይ ፥ ጮማሪ ። ባሕረ ኤክላ እንዲል ክብረ ነገሥት ።
ኤድን፡ ምቹ ስፍራ ፥ —ዔድን ።
ኤዶምያስ፡ የዔሳው አገር ።
ኤጲስቆጶስ፡ መንፈሳዊ የቤተ ክሲያን ሹም፡ አቡን ቄስን ዲያቆንን የሚሾም፡ ትርጓሜው ጠባቂ ማለት ነው ።
ኤፌሶን፡ ያገር ስም፡ በእስያ ውስጥ ያለች አገር፡ ጳውሎስ ዮሐንስ ያስተማሩባት፡ ንስጥሮስ የተወገዘባት ።
ኤፌሶን፡ ጥቍር አባይ ። (ግእዝ) ።
ኤፍራጥስ፡ ካራቱ ታላላቆች ወንዞች አንዱ፡ ከአርመን አገር ፈልቆ በአሶር ላይ ወደ ባቢሎን ይወርዳል፡ በዚያም ከጤግሮስ ጋራ ገጥሞ ወደ ፋርስ ባሕር ይገባል ። (ኪ ወ ክ) ።
እ ሳድስ፡ ፮ኛ (ስድስተኛ ድምፅ)፡ የሳድስነትን ሥረይ ከሀ ሳድስ ህ እየተጋራ ሌላውን ፊደል ሳድስ ያደርጋል ። በ እ ፥ ብ ።
እ፡ በ ። (ግጥም)፡ ድንጋይ ካፋፍ ወርዶ እዘብጥ ያርፋል፡ ሰው ያን እንደኹ ያንተ ራፋል ።
እ፡ አ በአኃዝነት ፩ እንደ ተባለ እ ደግሞ በ (አንድ እልፍ) ወይም ዐሥር ሺሕ ይኾናል ። መዝገበ ፊደል ተመልከት ።
እ፡ እኔ ለሚል የትንቢት ሥር ። ሠራኹ ፥ እሠራ ፥ እሠራለኹ ። ጻፍኹ ፥ እጽፍ ፥ እጽፋለዀ ። በአዐ የሚነሣ ግስ ማን አመንኹ ፥ አምን ፥ አምናለኹ፡ ዐወቅኹ ፥ ዐውቅ ፥ ዐውቃለኹ እያለ ራሱን ይችላል እንጂ እን አይፈልግም ።
እ፡ ወደ ። ዐመል ያገባል እመኻል ዐመል፡ ያወጣል ከመኻል ። በግእዝ መሠረቱ እስከ ነው፡ ይኸውም መገሥገሻና መድረሻ ማለት ነው ። ደቂቅ አገባብ እይ ።
እ፡ የ ። እናንተ እምታዩኝ እኔ እማሳያችኹ እንዲል ዐይነ ስውር ሲለምን ።
እሑድ፡ (እሒድ፡ አሐደ)፡ የዕለት ስም፡ አንደኛ መዠመሪያ ቀን።
እህ (አህ)፡ የሐዘን የጭንቅ አሉታ የነቀፌታ ቃል፡ መታመም መጐሰም ። አይ ኣዬ ዋይ ወዮ ወዲያልኝ ወዲያ ። (ግጥም)፡ ሰው ኹሉ ገብቶ አገሩን፡ አሀናኔ ቀረን ።
እህ ማለት፡ መጠየቅ ።
እህ አለ፡ በሐዘን ታመመ ተጐሰመ ።
እህ አለ፡ አማጠ ፥ —ዕሕ ።
እህ አለ፡ ወሬ ጠየቀ ።
እህ፡ የጥያቄ ቃል ። እህ ነገሩ እንዴት ኾነ ።
እህህ (ዕብ አሀህ)፡ ዝኒ ከማሁ ለእህ ። (ግጥም)፡ እህህ ነው እንጂ ያከሳው ደረቴን፡ ሳልበላ መች ዐደርኩ አንድ እንጀራ እራቴን ።
እህህ አለ፡ አቃሰተ ዛበረ ዋለለ ።
እህህ አለ፡ ፈረስ ምግብ ፈለገ ።
እህህታ፡ ትከዛ ትካዜ ።
እህታ ምጥ፡ ዕሕታ ።
እህታ፡ ዝኒ ከማሁ፡ ጥያቄ ።
እህታ፡ ጥያቄ ፥ —እህ ።
እለዚህ፡ (እሉ)፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ ለእሊህ፡ የብዙ፡ ወንዶችና፡ ሴቶች፡ ቅጽልና፡ ዐጸፋ ። ባለ ቤት፡ ሲኖር፡ ጭብጥ፡ ቅጽል፡ ሲቀር፡ ዐጸፋና፡ በቂ፡ ይኾናል ። እነን፡ ተመልከት ። እለ፡ የግእዝ፡ እነ፡ ያማርኛ፡ አብዢ፡ ነው፡
እለዚያ፡ (እሙንቱ፡ እማንቱ)፡ የሩቆች፡ ወንዶችና፡ ሴቶች፡ ዐጸፋና፡ ቅጽል፡ እነዚያ፡ ርሳቸው ። ዚህንና፡ ዚያን፡ እይ ።
እሊህ፡ (ዕብ፡ ኤሌህ)፡ ዐጸፋና፡ በቂ፡ ቅጽል ። እኒህ፡ እነዚህ፡ እሊሆች፡ እሊኸኞች ።
እሊያ፡ (እለ፡ ያ)፡ አለዚያ፡ የሴቶች፡ ዐጸፋና፡ ቅጽል፡ በቂ፡ ለወንዶችም፡ ይኾናል ። እሊህና፡ እለዚህ፡ እለዚያና፡ እሊያ፡ አንዳንድ፡ ወገን፡ ናቸው ። እሊህ፡ እለዚህ፡ ባይን፡ የሚታዩ፡ በጅ፡ የሚዳሰሱ፡ እለዚያ፡ እሊያ፡ ባይን፡ የሚታዩ፡ በጅ፡ የማይዳሰሱ ። እኒያን፡ እይ ።
እሊያኞች፡ እሊያኞቹ፡ ዝኒ፡ ከማሁ ።
እላንት፡ (አንትሙ፡ ን)፡ የቅርቦች፡ ወንዶችና፡ ሴቶች፡ የስም፡ ምትክ፡ ወይም፡ ዐጸፋና፡ በቂ፡ እናንተ፡ እናንት፡ ማለት፡ ነው፡
እሌት፡ ከወፍጮ፡ አለት፡ ላይ፡ በመጨረሻ፡ የሚጠረግ፡ ዶቄት፡ ለውሻ፡ እራት፡ ርሚጦ፡ የሚያደርጉት ። አለትና፡ እሌት፡ የእለ፡ (ሀለወ) ፣ ዘሮች፡ ይመስላሉ ።
እልል፡ (ኣልሎ)፡ የደስታ፡ ጩኸት ። እልል፡ አለ፡ (አለለ)፡ መላልሶ፡ ሦስት፡ ጊዜ፡ ጮኸ፡ ዕሠይ፡ ዕሠይ፡ አለ፡ እልል፡ በይ፡ ጉሜ፡ እንዲል፡ ዘማች ።
እልልታ፡ በቁሙ አለለ ።
እልልታ፡ እልል፡ ማለት፡ ዕሠይታ፡ ፍጹም፡ ደስታን፡ መግለጥ፡ በግእዝ፡ ይባቤ፡ ይባላል ። እልልታ፡ የሚደረገው፡ ልጅ፡ ሲወለድ፡ ታቦት፡ ሲነግሥ፡ ዘማች፡ በደኅና፡ ሲገባ፡ ንጉሥ፡ ሲታይ፡ የሰርግ፡ የሹመት፡ ለት፡ ማሕሌትና፡ ዘፈን፡ ሲደምቅ፡ ነው ።
እልልታው፡ ቀለጠ፡ ደመቀ፡ በዛ ።
እልቅና አለቅነት ፣ ላቀ ።
እልበት፡ የጦም፡ ወጥ፡ ዐለበ።
እልከኛ፡ (ኞች)፡ ጨካኝ፡ ኀይለኛ፡ ደፋር፡ ተጋፊ፡ ወደረኛ፡ ተከራካሪ፡ ሞገደኛ፡ (ዘዳ፳፩፡ ፲፰) ።
እልከኛነት፡ ደፋርነት፡ ኀይለኛነት እኔ፡ ያልኩት፡ ይኹን፡ ማለት፡ (፩ሳሙ፡ ፲፭፡ ፳፫)።
እልክ፡ ጭከና፡ ብርታት፡ ድፍረት፡ ሞገድ ። እልክ፡ ምላጭ፡ ያስውጣል፡ እንዲሉ ።
እልፍ፡ (፻፻)፡ ሺ፡ ጊዜ፡ ዐሥር፡ ወይም፡ ዐሥር፡ ሺ ። ጐደፈ፡ ብለኸ፡ ጕድፍን፡ እይ ።
እልፍ፡ ብዙ፡ ባላገር፡ የንጉሥን፡ ከባድ፡ ዕቃ፡ ተሸክሞ፡ ካንዱ፡ ቀበሌ፡ ወደ፡ ሌላው፡ የሚያሳልፍ ።
እልፍ፡ ነኽ፡ እልፍ፡ ነሽ፡ የወንድና፡ የሴት፡ መጠሪያ፡ ስም፡ ትርጓሜውም፡ ብዙ፡ ነኸ፡ ብዙ፡ ነሽ፡ ያሠኛል ።
እልፍ፡ አእላፍ፡ ውሳኔ፡ የሌለው፡ ቍጥር፡ ብዛቱ፡ እንዳሸዋና፡ እንደ፡ ኮከብ፡ ያለ፡ የብዙ፡ ብዙ ። ከዚህ፡ የቀረውን፡ የእልፍ፡ ነገር፡ በመዝገበ፡ ፊደል፡ ተመልከት ።
እልፍ፡ ዛላ፡ ፍሬ፡ አንድ፡ ራስ፡ ስንዴ፡ አንድ፡ ራስ፡ ማሽላ ። እልፍ፡ መባሉ፡ አንዷ፡ ቅንጣት፡ ብዙ፡ ስለ፡ ወለደችና፡ ስለ፡ በዛች፡ ነው ።
እልፍ፡ ይከንዱ፡ የሴት፡ ስም፡ እልፍ፡ ወቄት፡ ይክፈሉ፡ ማለት፡ ነው ።
እልፍኝ ፣ጌጠኛ፡ ቤት፡ ፡ ዐለፈ።
እልፎች፡ ዛላዎች፡ ፳፡ ሺሖች ።
እመ መነኵሲት፡ ፡ አመመ ።
እመ፡ መነኵሲት፡ መንፈሳዊት፡ እናት፡ ይቶት። አበን፡ እይ።
እመ፡ ምኔት፡ የገዳም፡ እናት፡ የሴት፡ ደብር፡ አሳዳሪ።
እመ፡ ብርሃን፡ የብርሃን፡ እናት፡ ማሪያም ።
እመም፡ (ዐረ፡ አማም፡ ፊት)፡ በቁሙ፡ አፍታ፡ ወረራ፡ ፊት፡ ለፊት፡ አቅንቶ፡ የሚሠራ።
እመር፡ መዝለል፣መረረ፡ መር።
እመበለት፡ (እም፡ መበለት)፡ እመ፡ የምትባል፡ መበለት፡ መነኵሲት፡ ባልቴት። በለተን፡ እይ ።
እመቤቲቱ፡ ቱ፡ እዱኛን፡ ቤተ፡ ሰብን፡ ያሳያል፡ ወይም፡ ያች፡ እመቤት፡ ያሠኛል፡ (ገላ፬፡ ፳፫)።
እመቤት፡ (ቶች)፡ (እመ፡ ቤት)፡ ባልተ፡ ቤት፡ ሀብታም፡ ሴት፡ ወይዘሮ፡ (፪ዮሐ፡ ፳)። እመቤቴ፡ እመቤታችን፡ የኔ፡ የኛ፡ እመቤት፡ ማሪያም።
እመቤት፡ ባልተ፡ ቤት -አመመ ።
እመቤትኛ፡ የመቤት፡ ኹኔታ፡ አለባበስ፡ አነጋገር ።
እመት፡ ሴት፡ ስትጠራ፡ የጥሪ፡ መልስ፡ የአቤት፡ አንጻር፡ ወይ፡ ማለት።
እመት፡ እመቤት፡ አመመ ።
እመት፡ እመቤት፡ ገንሆይ፡ የአቶ፡ አንጻር ።እመት፡ እከሊት፡ እንዲሉ።
እመት የዕጣን፡ ዐመድ፡ -ዐመተ ።
እመዬቴ፡ እመቤቴ፡ የኔ፡ እመቤት።
እመጫት፡ (ቶች)፡ (እመ፡ ፃት)፡ የጨቅላ፡ የለጋ፡ እናት፡ ዐራስ። እመጫት ዕዝል፡ ቅጽል፡ ጽፈት ።
እመጫት፡ ዐራስ፡ አመመ ።
እሙን፡ ታማኝ፡ የታመነ፡ ሰው፡ የተረዳ፡ ርግጥ፡ እውነት፡ ነገር።
እሙኝ፡ አለ፡ አመመ፡ ጮኸ፡ ዥቡ ።
እሚሚ፡ (እሚ፡ እሚ)፡ የሴት፡ ልጅ፡ ስም፡ የናቴ፡ እናት፡ ማለት፡ ነው።
እሚታ፡ ሴት፡ አያት፡ አመመ።
እሚታ፡ የናትና፡ ያባት፡ እናት፡ ሴት፡ አያት፡ (፪ጢሞ፡ ፩፡ ፭)። ወንድ፡ አያትም፡ የናት፡ አባት፡ በአዳምና፡ በሎጥ፡ አንጻር፡ እሚታ፡ ይባላል።
እማ፡ እም፡ እናት፡ (እናቷ)።
እማሆይ፡ እመ፡ ሆይ፡ መነኵሲት፡ ሆይ፡ ይቶት፡ ሆይ፡ እናት፡ ሆይ።
እማሎሚ፡ አጥላስ፡ አመመ፤
እማሎሚ፡ አጥላስ፡ ካባ፡ ሎሚ፡ መሳይ።
እማማ፡ (እመ፡ እም)፡ የናት፡ እናት፡ ወይም፡ እናት።
እማማዬ፡ (እመ፡ እምየ)፡ የናቴ፡ እናት፡ አያቴ፡ ወይም፡ እናቴ "
እማምሳይ፡ (አምሳለ፡ እም)፡ እናቷን፡ የምትመስል፡ ጥጃ፡ ቅቤውም፡ በዚሁ፡ ስም፡ ይጠራል ።
እማስጥል (እም፡ አስጥል)፡ የናትን፡ ጡት፡ የሚያስጥል፡ (የሚያስተው)፡ መራራ፡ ቅጠል፡ አቈራራጭ።
እማኝ፡ (ኞች)፡ ያየ፡ የሰማ፡ ምስክር፡ እውነተኛ ። (ርጥብ፡ እማኝ)፡ ዐዲስ፡ እማኝ፡ እበላይ፡ ዳኛ፡ ዘንድ፡ የሚነሣ ።
እማኝነት፡ ምስክርነት።
እማግልግሌ፡ የሕፃናት፡ ጨዋታ፡ ፍችው፡ የግልገሌ፡ ባልተ፡ ቤት፡ እረኛ፡ ማለት፡ ነው ።ጨዋታውም፡ በመዳፍ፡ በጣት፡ እስከ፡ ብብት፡ ይደረጋል ።አካኼዱ፡ እባብኛ፡ አኰራ ኰሩ፡ ድንገተኛ።
እም፡ ቄስ፡ ምሁር፡ ቄስ፡ በታላላቅ፡ በዓል፡ እየዞረ፡ በያድባራቱ፡ የሚቀድስ፡ ገባሬሠ ናይ፡ (ጐዣም)። በግእዝ፡ ካህን፡ ዘየዐቢይ፡ ይባላል ።
እም፡ አለ፡ ተመመ፡ ጮኸ፡ አስተጋባ።
እም፡ እመ፡ እናት፡ ወላጅ፡ መገኛ። ባለን፡ ተመልከት፡ ከዚህ፡ ጋራ፡ አንድ፡ ነው።
እምኀበ፡ አልቦ፡ ኀበ፡ ቦ፡ ካለመኖር፡ ወደ፡ መኖር ።
እምማት፡ ያረም፡ ያጨዳ፡ አቅጣጫ ።
እምም፡ አለ፡ መላልሶ፡ ጮኸ። (ግጥም)፡ እምም፡ ይላል፡ ወፍጮ፡ ይከተላል፡ መጅ፡ ሌላ፡ ምን፡ ሥራ፡ አለኝ፡ አንተን፡ ላበጃጅ።
እምም፡ የተዠመረ፡ ዥምር ።
እምምታ፡ እምም፡ ማለት፡ የወፍጮ፡ ድምፅ ።
እምሩ፡ እምሯ፡ የወንድና፡ የሴት፡ መጠሪያ፡ ስም፡ ምልክቱ፡ ምልክቷ፡ ቍንጮው፡ ቍንጮዋ፡ ጫፉ፡ ጫፋ፡ አሻራው፡ አሻራዋ፡ ዐናቱ፡ ዐናቷ፡ ማለት፡ ነው።
እምር፡ (እሙር)፡ የተመለከተ፡ ምልክት፡ የአክሊል፡ ኹናቴ፡ ያለበት፡ ላይዳ፡ የቆመበት፡ የምርት፡ ቍንጮ፡ ጫፍ፡ አሻራ፡ ዐናት "
እምር፡ ታኸል፡ እጅግ፡ በጣም፡ ትንሽ፡ ምልክት፡ አሻራ፡ የምታኸል፡ የምልክት፡ ዐይነት (ዕርም፡ ታኸል)።
እምሽክ አደረገ፡ ዕጭድ አደረገ።
እምሽክሽክ አለ፡ ብጥስጥስ/ስብርብር አለ።
እምሽክሽክ፡ የተምሸከሸከ።
እምቡጣ፡ ጐፍላ፡ እንቡጣ ።
እምቡጣጥያ ግልገል፡ እንቡጣ ።
እምብዛ፡ (እምብዝኀ)፡ ከብዛት፡ በብዛት ። እምብዛ፡ አይፈለግም ።
እምብዛም፡ ከብዛትም፡ የተነሣ ። (ተረት)፡ እምብዛም፡ ብልኅት፡ ያደርሳል፡ ከሞት፡ እምብዛም፡ ስለት ፥ ይቀዳል፡ አፎት ።
እምቧ፡ የላም፡ ጩኸት፡ -እንቧ ።
እምቧይ፡ የንጨት፡ ስም፡ ፡ እንቧይ ።
እምቧጮ፡ የንጨት፡ ስም፡ እንቧጮ ።
እምነተ፡ ቢስ፣ ሃይማኖተ፡ መጥፎ፡ መናፍቅ።
እምነት፡ በቁሙ፡ ሃይማኖት፡ ማመን፡ መታመን።
እምነት፡ ክደት፡ ነው፡ አይዶለም፡ ኾነ፡ አልኾነም፡ አዎንታና፡ አሉታ ።
እምዬ፡ (እምየ)፡ እናቴ፡ ወላጄ፡ የኔ፡ እናት ።
እምዬ፡ ቅሌት፡ የባላገር ' ፈሊጥ፡ የነቀፌታ፡ ቃል። (ግጥም)፡ እምዬ፡ ቅሌት፡ ያብሽ፡ ገለባ ፲ ሜዳ፡ ነው፡ ብዬ፡ ገደል፡ ልገባ።
እሞ፡ አጐላማሽ። እሞ፡ ስሚኝ፡ እሞ፡ እማሆይ፡ ማሪያሞ።
እሰይ፡ በቁሙ ፥ —ዕሠይ ።
እሠይ፡ በቁሙ፡ ዕሠይ።
እሰጥ አለ፡ በፈረስ/በበቅሎ/በማር ተወራረደ።
እሰጥ አገባ፡ ውርርድ። "እሰጥ" የከሳሽ ቃል፡ "አገባ" የተከሳሽ መልስ። (ግጥም)፡ "ተጠየቅ ጠይቀኝ ማር እሰጥ አገባ፡ እንዴት ይዘለቃል የጎረቤት ሌባ?"
እሱ (ርእሱ ለሊሁ)፡ የተገብሮ ዐጸፋና በቂ ። ርሱ ራሱ ቅሉ፡ ባለቤቱ እንቶ ያ ያው ። የገቢር ዐጸፋ ሲኾን እሱን ይላል ። (የሱ)፡ የዚያ ።
እሣ፡ የነቀፌታ፡ ቃል፡ ንሣ ።
እሳተ ከል፡ የዕቃ ቤት ደርብ፡ በላዩ መዠመሪያ ሰሌን የተዘረጋበት ኹለተኛም ዐፈር የተደለደለበት ዝርግ ሳንቃ በሠረገላ ላይ የተነጠፈ ። እሳተ ከልክል ማለት ነው ።
እሳተ ገሞራ፡ ተራራን ነድሎ ፈንቅሎ የሚወጣ እሳት ። ፈረንጆች ቦልካ ይሉታል።
እሳታዊ፡ ከእሳት የተፈጠረ፡ የእሳት ባሕርይ ያለው መልአክ ።
እሳታፍ (እሳት አፍ)፡ ለፍላፊ ።
እሳት (ቶች) (አሲው አሰወ)፡ በቁሙ፡ አጥፍቶ ጠፊ፡ የሚነድ የሚበራ፡ የሚያቃጥል የሚበላ የሚፈጅ የሚልጥ የሚለመጥጥ፡ ደረቅ የሚቃጠል ብሩህ፡ ካራቱ ባሕርያት ኣንዱ፡ በኹሉ የሚገኝ፡ በደረቅነቱ ከነፋስ በመቃጠሉ ከመሬት በብርሃኑ ከውሃ የሚስማማ ። እሳት ለፈጀው ምን ይብጀው እንዲሉ ።
እሳት ለብሶ እሳት ጐርሦ መጣ፡ ፈጽሞ ጨከነ ተቈጣ ።
እሳት ባለጅን እንዳያቃጥል የሚከለክል።
እሳትማ፡ እሳት መሳይ ቀለም፡ ወይም በግ ዳንግሌ ።
እሳትና ጭድ፡ እስተ (እስከ)፡ በቁሙ ኹለት የወ ደደ እስታንዱም ያጣል። አጥፊና ጠፊ ።
እሳቶ፡ የጕዲት የግብር ስም ። እሳቶ ጕዲት እንዲሉ ።
እሳቸው (ርእሶሙ ለሊሆሙ)፡ ርሳቸው ራሳቸው ቅላቸው ባለቤታቸው፡ እነዚያ ወንዶች ።
እሳቸው (ርእሶን ለሊሆን)፡ ዝኒ ከማሁ፡ እሊያ ሴቶች ።
እሳቸው፡ እኒያ ሰው ። (ተረት)፡ ዐደራ ቢሏቸው ይብሳሉ እሳቸው ።
እሳችን (ርእስነ ለሊነ)፡ ርሳችን ራሳችን ቅላችን ባለቤታችን፡ እኛ ።
እሳችኹ (ርእስክሙ ለሊክሙ)፡ ርሳችኹ ራሳችኹ ቅላችኹ ባለቤታችኹ፡ እናንት ተ ።
እሳችኹ (ርእስክን ለሊክን)፡ ዝኒ ከማሁ፡ እላንት ።
እሴ (ርእስየ ለልየ)፡ ርሴ ራሴ ቅሌ፡ ባለቤቴ እኔ እኔው ።
እሴይ፡ የሰው ስም፡ የዳዊት አባት ።
እስ (ርእስ ለል)፡ ርስ ራስ የናላ ቅል፡ ባለቤት ።
እስላም (ሞች)፡ ሠመድ በቍርኣን የሚያምን (ማተብ የሌለው በአረብኛ የሚጸልይ ሰው/ባልም) ። (ጥም ወይፈኑ ቢታም ጊደሯ መች ረ...ለመኾኑ ያችስላም እንዴት ነች?) ካንዲት እስም ጋራ የስግን ክርስቲያን የ...ነው።
እስላም፡ ማተብ የሌለው ፥ —ሰ ለመ ።
እስላምነት፡ ከኒ ከማሁ።
እስልምና፡ ስላም መኾን።
እሥሥት፡ ዘለባብዳ፡ ዐሠሠ።
እስረኛ (ኞች) (እሱራዊ)፡ የእስር ወገን፡ ግዞተኛ።
እስራት (እስረት)፡ አሰራ፡ ማሰር፡ መታሰር (ምሳ፯፡ ፳፪ ። ኤር፶፪፡ ፴፫ ። ፊልጵ፩፡ ፲፫) ።
እስራት፡ ቍጥራት (፩ሳሙ፡ ፴፡ ፲፪) ።
እስራኤል (ሎች)፡ ፊት ለያዕቆብ ኋላም ለልጆቹ ለ፲፪ቱ ነገድ ከፈጣሪ የተሰጠ ስም፡ ከአምላክ ጋራ የሚታገል (መስተ ቃልሰ አምላክ) ማለት ነው ። (ዘፍ ፴፪ ፥ ፳፬ ፥ ፳፰ ። ፵፭ ፥ ፲) ። በዕብራይስጥ ዪስራኤል ይባላል ።
እስር (ሮች) (እሱር)፡ የታሰረ፡ የተቀፈደደ (ኤፌ፬፡ ፩) ። (የቁም እስር) ሳይታሰር በሹም ሥልጣን ከዚህ አትለፍ የተባለ (፩ነገ፡ ፪፡ ፴፮) ።
እስር ቤት፡ እስረኛ ያለበት ወህኒ ዘብጥያ የእስር ቤት።
እስር አደረገ፡ ቅፍድድ አደረገ።
እስርስር፡ የተሳሰረ፡ ኵልትፍትፍ ተባለ።
እስሽ (ርእስኪ ለሊኪ)፡ ርስሽ ራስሽ ቅልሽ ባለቤትሽ፡ አንቺው ።
እስተ (ውስተ)፡ ወገን አጠገብ በኩል ጐን ። ጻድቃን በስተቀኝ ኃጥኣን በስተግራ ይቆማሉ ። በስተዚያ በስቲያ በስተ ኋላ ። ማድረጊያ ሲወድቅበት እ እንደ ተጐረደ አስተውል ። ዳግመኛም ተና ከ ተወራራሽ ስለ ኾኑ በስከ ይላል ። (፩ሳሙ ፲፯ ፥ ፫) ። (በስቲያ)፡ ወዲያ ። ከትላንት በስቲያ ከነግ በስቲያ ። (፩ሳሙ ፴ ፥ ፲፫) ። ፊትና ኋላም ተብሎ ይተረጐማል ። (ዘዳ ፬ ፥ ፵፪) ።
እስቲ፡ እስኪን እይ ።
እስት፡ እስክን ተመልከት ።
እስትሌ፡ መካከለኛ የዳስ ወጋግራ ።
እስትንፋስ፡ ትንፋሽ ፥ —ነፈሰ ።
እስትንፋስ፡ ትንፋሽ (ግእዝ) ።
እስከ፡ ዐቢይ አገባብ ። ከአንቀጽ አስቀድሞ በቁሙ ቀሪነቱን ሳይለቅ ከአንቀጽ በኋላ በትርፍ ዐማርኛ ድረስ እየኾነ ፍጻሜ በሌለው ሲነገር ። የበክር ልጇን እስከ ወለደች ድረስ አላወቃትም ። ቍራ የጥፋት ውሃ እስከ ጐደለ ድረስ ወደ ኖኅ አልተመለሰም ይላል ። (ማቴ ፩ ፥ ፳፭ ። ዘፍ ፰ ፥ ፮ ፥ ፯) ። ፍጻሜ ባለው ሲነገር ከ ኪ ተብሎ በትንቢት ይገባል ። ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ መበለት ኹነሽ ተቀመጪ ። በትር ከይሁዳ አይጠፋም ሴሎም የሰላም ንጉሥ እስኪመጣ ድረስ ። (ዘፍ ፴፰ ፥ ፲፩ ። ፵፱ ፥ ፲) ። መዠመሪያውን እስኪ እይ ።
እስከ የሌለው፡ መጨረሻ አልባ ። እ እስከ የሌለው ነገር እንዲሉ ።
እስከ፡ ደቂቅ አገባብ ። መገሥገሻና መድረሻ ። ጳውሎስ እስከ ፫ኛ ሰማይ ወጣ ። እመቤታችን እስከ ግብጽ ተሰደደች ። (ተረት)፡ ሲታጠቡ እስከ ክንድ፡ ሲታረቁ ከሆድ ድረስን፡ እንደ ላይኛው ጨምር ። ከዐጸፋና ከጊዜ ጋራ ሲነገር፡ እስከዚህ እስከዚያ፡ እስከ ዛሬ እስካኹን ይላል ።
እስኩታ (እስከ)፡ የመጠጥ ዐሠር፡ ገፈታ ገፈት ።
እስኪ (እስኩ)፡ ንኡስ አገባብ ። የጥ ያቄና የምክር የልመና ቃል፡ ፍችው በቁሙ ቀሪ ። በፈጣሪ ፊት መቆምን እስኪ ዐስብ ። ከመስቀልኸ እስኪ ውረድ ። እስቲን ተመልከት ።
እስኪ፡ ዐቢይ አገባብ ። የትንቢት መነሻ ኹኖ በሩቅ ወንድና በሩቆች ወንዶች ሲነገር፡ እስኪበረታ እስኪያድግ፡ እስኪበረቱ እስኪያድጉ ይላል ።
እስክ፡ ዐቢይ አገባብ፡ አንተ አንቺ እናንተ እሷ በሚባሉትና እኔ በሚል እኛ በሚሉ የትንቢት መነሻ ሲኾን፡ እስክትደክም (አንተ እሷ) እስክትደክሚ እስክደክም እስክ ንደክም ይላል ። እስከ የግእዝ፡ እስኪ እስክ ያማርኛ ። (ተረት)፡ ያፌን እስክውጥ ዕድሜ ይስጠኝ ይላል ርኩም ።
እስክስ፡ እስክስታ፡ በዘፈን ጊዜ የሚደረግ የአካል ውዝዋዜ ንቅናቄ ። እስክስታ ወረደ እንዲሉ ።
እስክስተኛ፡ እስክስታ ዐዋቂ፡ አረግ ራጊ ።
እስክስታ መታ፡ ሰውነቱን ሰበቀ፡ ወዘወዘ፡ ትከሻውን ከፍ ዝቅ አደረገ፡ አረገ ረገ ። (ተረት)፡ የመዝሙር መዠመሪያ ሃሌታ፡ የዘፈን መዠመሪያ እስክስታ ።
እስክንድር፡ የሰው ስም፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ፫፻፶፮ ዓመት በግሪክ አገር የተወለደ፡ ስመ ጥር ንጉሥ ኀይለኛ ።
እስክንድርያ፡ በግብጽ ወደብ እስክንድር የሠራት ከተማ ።
እስኸ (ርእስከ ለሊከ)፡ ርስኸ ራስኸ ቅልኸ፡ ባለቤትኸ አንተ ።
እስዎ (እስ)፡ ርስዎ ራስዎ ቅልዎ ባለቤትዎ አንቱ ።
እስያ፡ ካ፭ቱ የዓለም ክፍሎች አንደኛው፡ የብጮችና የቀዮች የመዳቦች አገር፡ የሴም ዕጣ ።
እስጢፋ፡ ከፊለ ስም፡ ደቀቀን እይ ። እስጢፋ ለማርያም ስግደት አይገባም ቢሉ ዐጤ ዘርዐ ያዕቆብ በደብረ ብርሃን ከሰቀሏቸው ኹለት ሊቃውንት አንደኛው የደቀ እስጢፋ መምር ።
እስጢፋኖስ፡ የሰው ስም፡ ከሰባ ኹለቱ አርድእት አንዱ፡ ሊቀ ዲያቆናት ።
እስጢፋኖስ፡ የታቦት ስም፡ ታቦት ።
እስጢፋኖሶች፡ የእስጢፋኖስ ካህናት፡ በዚህ ስም የሚጠሩ ፪ ፫ ሰዎች ።
እስጢፎ፡ የሰው ስም፡ የእስጢፋኖስ ከፊል ። እስጢፎ እስጢፎ ገደል ተለጥፎ እንዲሉ ልጆች ። እስጢፎ ቃለ አጋኖም ይኾናል ።
እሶ፡ ዕሠይ ፥ —ዕሦ ።
እሦ፡ የደስታ፡ ቃል፡ ዕዎ ።
እሷ (ርእሳ ለሊሃ)፡ ርሷ ራሷ ቅሏ፡ ባለቤቷ፡ ያች ያቻት ። በሩቆችና በቅርቦች እኛ በሚሉም እሳቸው እሳትኹ እሳችን እያለ ይዘረዝራል፡ ኹሉንም በተራው ተመልከት ።
እረኛ (ኞች)፡ አጋጅ ጠባቂ፡ ዘላን ደሳ ገሣ ጫኝ ። (ተረት)፡ ሰነፍ እረኛ ከሩቅ ይመልሳል ። (የሕዝብ እረኛ)፡ በመንፈሳዊ ጳጳስ፡ በሥጋዊ ንጉሥ ።
እረኛ ኣኰማኰም አበላል አጠጣጥ መኰ ምኰም ") ።
እረኝነት፡ አጋጅነት ጠባቂነት ።
እሩር፡ ጥንግ ፥ —ዐረረ ።
እሩብ፡ ሩብ፡ ረባ ። (ረብዐ) ።
እሪ (አረረ)፡ ታላቅ ጩኸት ቅርርት፡ ክፉ አውሬ ወይም ጠላት በመጣ ጊዜ የሚደረግ ። እሪ በሉ ሰዎች እሪ በሉ እንዲል አቅራሪ ።
እሪ በከንቱ፡ የስፍራ ስም፡ በጐንደር ቀበሌ ያለ የቀማኛ ስፍራ ። ዐጋዥ ረዳት የማይደርስበት ስለ ኾነ እሪ በከንቱ ተባለ ይላሉ ።
እሪ አለ፡ ከተራራ ወይም ከቅጥር ላይ ወጥቶ ጮኸ ።
እሪታ፡ እሪ ማለት፡ መጮኸ ማቅራራት መገንታት ሰውን ለመጥራትና ለመሰብሰብ ።
እሪታ፡ ጩኸት ፥ —እሪ ።
እሪዝ፡ ዐጪር ጢም ፥ —ሪዝ ።
እራት፡ በቁሙ፡ ማታ የሚጐረሥ የሚበላ ። (ራእ ፫ ፥ ፳) ። በራት ዋዛ ምሳ ይመስል ። እራትና እሳት፡ ዐማትና ምራት፡ ሳይስማሙ መሬት ። (ያውራ አራት)፡ ዐዲስ ማር ።
እራቻ፡ የታከበ፡ የተሰበሰበ፡ አለጊዜው ለራት በበትር የተወቃ እኽል።
እሬት፡ ሬት፡ መረረ ።
እር፡ ፍየልን ለመከልከልና ለማገድ ለማብረር ከሰው የሚወጣ ድምፅ ።
እርሱ፡ እሱ ፥ —ርሱ ።
እርሳስ፡ በቁሙ ፥ —ርሳስ ።
እርሾ፡ የቡሖ ቅሬታ ፥ —ርሾ ።
እርቦ ርቦ፡ ረባ ። (ረብዐ) ።
እርት፡ የተከበበ፡ የታረተ፡ የታሰረ፡ የተበላ፡ ቅርቅብ፡ ውድን።
እርት፡ የታረተ፡ አራት የኾነ ።
እርችት፡ የመድፍ ጥይት ፥ —ር ችት ።
እርኩም፡ ያሞራ ስም ፥ —ርኩም ።
እርኰት፡ ውሃ መያዣ ፥ —ረካ ።
እርያን፡ ነጭ ሽቶ ፥ —ርያን ።
እርጅት፡ ሽምግል ።
እርጅት አለ፡ ፈጽሞ አረጀ፡ ሽምግል አለ ።
እርጅና (እርግና)፡ እሮጌነት ሽምግልና ። (ኢሳ ፵፯ ፥ ፬) ። እርጅና ብቻኸን ና እንዲሉ ።
እርግዝና፡ እርጉዝነት ("እርጉዝ መኾን ቅሪትነት ") ።
እርጥ፡ የጤፍ አነባበሮ ጠጠ ።
እሮት (ኣለለ)፡ በቁሙ፡ የአራዊት ስሪያ ።
እሸቱ፡ የሰው ስም (ቱ አባትን ያያል - "የርሱ እሸት" ማለት ነው) ።
እሸቴ፡ የወንድና የሴት ስም (ትርጓሜውም "የኔ እሸት" ያሠኛል) ።
እሸት (ሠዊት)፡ ዛላ ዘለላ እንቡጥ...ጐምር ("የስንዴ እሸት የወይን እሸት" እንዲሉ) ።
እሸት፡ በቁሙ ፥ —ሸተ ።
እሸትነት፡ እሸት መኾን (ጐምርነት) ።
እሺ፡ በጄ ዕሺ ።
እሺታ፡ መታዘዝ ፥ —ዕሺ ።
እሼ (ኮሞል)፡ ሸዬ፡ ፍሬው የሚበላ ዕንጨት ።
እሽ፡ የስም ባዕድ መነሻ ። ኮለሌ እሽኮለሌ፡ ቀደመ አሽቀዳደመ፡ እሽቅድድም ።
እሽላት፡ ልክ መጠን፡ የዝሓ ።
እሽል (ሎች)፡ የታሸለ የተጨመረ የቀላ የነጣ፡ ጭምር ።
እሽል፡ አንድ ክንድ መቃ፡ በመቃው የተለካ ፮ ክንድ ድር ። ዘንግን እይ ።
እሽርር፡ ልጅን ያዘለ ኣንቀልባ ያለ...በሰ ።
እሽርር/እሽርሩ፡ ልጅ ታዝሎ ባለቀሰ ጊዜ የሚዘፈንለት ዘፈን ("እሽርር ማሙዬ" እንዲሉ) ።
እሽቅድድም፡ በውድድር የሚደረግ (እግብ ድረስ ግልቢያ ሽምጥ ሩጫ ") ። "የፈረስ የአግር እሽቅድድም" እንዲሉ።
እሽባቦ፡ እንዳልክ ዕሺ ።
እሽካካ፡ ጩኸት ፥ —(ካካ) ።
እሽካካ፡ ጩኸት ("የገና ጨዋታ አሽካክቶ መጣ ፎክሮ ደንፍቶ ማለት ነው ") ።
እሽክም፡ የዘፈን አዝማች (በጣሊያን ጊዜ የተባለ - ሐርበኛ)፡ "እሽክም እንደ ምን ነሽ እኔ መምጣቴ ነው ክርስትና ተነሽ"።
እሽኮለሌ፡ ስድብ፡ ኮለለ ።
እሽኮለሌ፡ የኹለት ወገን ስድብ ("እንደ ሚዛን ኮለሌ ወዲያና ወዲህ ከፍና ዝቅ የሚል ") ።
እሽጋት፡ የመታሸግ ሥራ ኹኔታ ።
እሽግ መታሸግ ።
እሽግ አደረገ፡ ዝግት ድፍን አደረገ ።
እሽግ፡ የታሸገ የተዘጋ የተደፈነ፡ ድፍን ምርግ ።
እሾኸ አፍ፡ ተሳዳቢ ሰው (በነገር ሰውን ጠቅ የሚያደርግ) ።
እሾኻም፡ እሾኸ ያለበት የበዛበት (ዛፍ ስፍራ) ።
እሾኽ፡ በቁሙ ሾኽ ።
እቀጭ እቋ አለ፡ ጮኸ ተሰማ ። "ሙ ክቱ ሲኼድ እግሩ እቀጭ እቋ ይላል" ።
እቀጭ፡ እባጭ ።
እቃ፡ በቁሙ ዕቃ ።
እቅጭ፡ ርግጥ ቀጪ ።
እቅጭ፡ ርግጥ እውነት ቍርጥ ። "እቅጩን ተናገረ፡ ቍርጡን ገለጠ ኣስረዳ" ።
እበት፡ የበሬና የላም ስ፡ ላውድማና ለቤት ለጐታ ለድብኝት መለቅለቂያ ይኾ ናል፡ ካመድ ጋራ እየደባለቁም ወታቦና አክ ንባሎ ይሠሩታል ። ጐሽ አውራሪሥ ወደቢ ቶራ ድፋርሳ እነዚህንም የመሰሉ የዱር እንስሶች ኹሉ እበት ይጥላሉ ። (ሕዝ ፬ ፥ ፲፭) ። የጠገራ ላም ባደረችበት በረት እበት አይ ገኝም ።
እባቡ፡ ያ እባብ፡ የርሱ እባብ ።
እባብ (ቦች)፡ በቁሙ፡ ከይሲ ፥ አንድስቅ ፥ ጐሚቅ ፥ ገና አፍነት እግር አልባ ፥ መሬቱ በል በምድር የሚሳብ ፥ የሚጐተት ፥ የሚሰልክ በደረቱ የሚኼድ ፥ የሚዘል ፥ የሚሆ ረወር፡ መርዘኛ ፥ አውራ የሰው ጥንተ ጠላት ። (ተረት)፡ እባብን ልቡን አይቶ እግር ነሣው ። (ዘፍ ፫ ፥ ፩ ፥ ፪ ፥ ፬ ፥ ፱) ። እባብ ግደል ከነበትሩ ። ገደል እባብ ያየ ልጥ ቢያይ በረየ ። እባብ ለባብ ይተያያል በካብ ።
እባብ፡ ክፉ ተንኰለኛ ሰው ፥ ነገረ መርዝ ። አከሌ ኣባብ ነው መኼጃው እይታ ወቅም እንዲሉ።
እባብ ወረዴ፡ ዘፈን ስም፡ ልጃገረዶች ሀንፃት ላንገት ተያይዘው የሚዘፍኑት፡ ዘፈን አራ ዘንባባዬዓ የመሰለ ። (ራእ ፲፪ ፥ ፱ ፥ ፲) ። እባብ ኾነ፡ ተለወጠ ። የሙሴ በትር እባብ ኾነች ።
እባብ ዋጭ፡ እባብ የሚውጥ አሞራ ርኩም ወይም ሌላ ።
እባብነት፡ ተንኰለኛነት ፥ መሠሪነት ።
እባቧ፡ እባቢቱ እባቢቷ፡ ያች እባብ ። (ዘፍ ፫ ፥ ፪ ፥ ፲፬) ።
እባካችኹ ስጡኝ፡ እያለ በሦስቱ ቅርቦች ከትእዛዝ አንቀጽ አስቀድሞ ይነገራል ።
እባክኸ፡ ንኡስ አገባብ ። አለዋጋ በብላሽ በከንቱ ለማግኘትና ለመቀበል የሚነገር የልመና ቃል ። ሲዘረዘርም፡ እባክዎ እባክሽ ።
እባክኸ፡ የልመና ቃል ። —በከከ ።
እብሪተኛ (በዓለ እብሬት)፡ ባለፈንታ ባለተራ ጊዜው ፈረታው የሱ የኾነ፡ ጥጋበኛ የወበራ ። ሲያበዛ እብሪተኞች ይላል ።
እብሪት (ባረየ እብሬት)፡ ፈረቃ ፈንታ ተራ ሰሞን ፥ የጊዜ ክፍል ፥ ጥጋብ ፥ መብራት ።
እብቅ (ቆች)፡ ደቃቅ ገለባ (ስም) ።
እብቅ፡ የደቀቀ የበቀ (ዕምቅ ርጥጥ) (ቅጽል) ።
እብብ፡ ያይጥ ተረትና ዘፈን ። ዐይጥና ድመት ሊጋቡ፡ ድመት ወበብ መበብ ዳር ዳሩን ክበብ ባለ ጊዜ፡ ዐይጦች እብብ እብብ እኛም አለን ከልብ አሉ ይባላል ። ትርጓሜውም እንደ እባብ ወደ ጕድጓድ ጥልቅ ማለትን ያሳያል ።
እብት፡ የታበተ የተጠለፈ የታሰረ የተንጠለጠለ ፥ እስር እንጥልጥል ልጥ ገመድ ጠፍር ። የታረደ በግ ወይም ፍየል ።
እብነ በረድ፡ በረዶ የሚመስል ነጭ ደንጊያ ጽላትና ጸፍጸፍ የሚኾን ፪ ዐይነት ።
እብነ በረድ፡ የበረዶ ጠጠር ትንሹም ትልቁም ፥ የበረዶ ሎሕ ።
እብን፡ ደንጊያ ፥ ድንጋይ፡ (ግእዝ) ።
እብደት (እበድ)፡ ቍ ጩኸት ወፈፍታ ሀሳባ ዘ ።
እብዱ፡ ያ እብድ (ቀበጡ ዕርፊተ ቢሱ) ።
እብድ (እቡድ)፡ (ያበደ የሰከረ የወዝሽ፡ ራሰ ቢስ ቍጡ ብስጩ ጯኺ) ። (ዘዳ ፳፰ ፥ ፴፬ ። ኤር ፳፭ ፥ ፳፯) ። እብድና ዘመናይ የልቡን ይናገራል። ለካ ብለሽ መልክን እይ ። በጋልኛ እሳትን እቢዳ ማለት ከዚህ ይሰማማል ።
እብድ ሀሙስ፡ የእብድ ሀሙስ፡ ሰዎች እንደ እብድ እየኾኑ የተጫወቱበትና ተደሰቱበት ከነነዌ ቀን ተጥሎ ያለው ዐሙስ ። ፈረንጆች ካርኖባል ከሚሉት ይሰማማል ።
እብድ ቀን፡ የእብድ ቀን፡ እብድ ዐሙስን የመሰለ ። እብድ ቀን ኣይመሽ፡ እብድ ለእብድ ቀን ይበጁል እንዲሉ።
እብድ አስተኔ፡ እብድ ዐይነት፡ ዘባራቂ ላባ ቀረሽ ።
እብድ እብድ አለ፡ ወፈሳ ወፈፍ ።
እብድ፡ ከሰንጠረዥ መጫወቻ አንዱ የንጉሥና የንግሥት አጫዋች - አለ ።
እብድ ውሻ፡ አንጐሉ የተበላሸ ዘዋሪ ውሻ ። በሽታውም ሲዠምረው ዥራቱን ይሸጕባል፡ ለሐው ይዝረበረባል፡ ውሃ አይጠጣም፡ ወንዝ አይሻገርም፡ ያገኘውን ኹሉ ይነክሳል፡ እሱ የነከሰውም በጥቂት ጊዜ ያብዳል ። ለዚህ ፍቱን መድኀኒቱ የቀበሮ ሥጋ ቀቅሎ መብላትና ማብላት ነው ።
እብድ የያዘው መልክ አይበረክትም፡ የእብድ (የቀበጥ መልክ አይሰነብትም አይቈይም አይዘገይም) ።
እብድ የጣለው፡ ሚስቱ የተወችው ደግ ባል፡ ባሏ የተዋት ባለያ ሴት ።
እብድ ገብረ ኪዳን፡ ያ ቴዎድሮስ ያሚታ ስም ።
እብድነት፡ እብድ መኾን፡ ጨርቅ መጣል ። (ምሳ ፳፩ ፥ ፳፬ ። ዘካ ፲፪ ፥ ፬) ።
እብዶች፡ ያበዱ የወገሹ ። (መክ ፲ ፥ ፳፭ ። ማቴ ፰ ፥ ፳፰) ።
እብዷ፡ እብዲቱ፡ ያች እብድ ተብላ ።
እቦኛ፡ ክፉ ልበ ደንጊያ ደረቅ ካኝ ።
እተከዘ፡ የግእዝ "ኣስተከዘ" ያማርኛ ነው ።
እተጌ (እግዝእተ ጌ)፡ የምድር እመቤት ።
እተጌ (ዎች) (እኅተ ሐፄጌ)፡ ይተጌ፡ ንጉሥ እቴ የምትላት የንጉሥ ሚስት፡ ባለኩል ርስቱን ጕልቱን እንደ እት ተካፍላ የምትገዛ የሴት ንግሥት ። (ግጥም)፡ ዐሊ ማን ይላታል ሲጠራ እናቱን፡ እኛስ እንላለን እተጌ መነን ። እተጌ ሰብለ ወንጌል እተጌ ጣይቱ እንዲሉ ። ጌን ተመልከት ። አና የ ተወራራሽ ስለ ኾኑ እተጌ ይተጌ ተብሎ ይነገራል ።
እተጌ ይተጌ፡ እት ።
እተጌዋ፡ እተጌይቱ፡ ያች ይተጌ፡ እሷ ። (አስ ፩ ፥ ፲፩ ፥ ፲፪ ፥ ፲፭ ፥ ፲፯) ።
እቲሳ፡ የቀበሌ ስም፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተወለዱበት ስፍራ በቡልጋ ውስጥ ያለ ። በጋልኛ ከልካይ ማለት ነው፡ በግእዝ ጽላልሽ ይባላል ።
እቴ (እኅትየ)፡ የኔ እት ። (ግጥም)፡ አቴ ነች እላለኹ፡ ወንድሜ ነው በይ፡ የነፍስማ ነገር ቀርቶ የለም ወይ ። (ዘፍ ፲፪ ፥ ፲፫ ። ፳፮ ፥ ፯) ።
እቴዋ (ኦ እኅትየ)፡ እቴ ሆይ፡ የኔ እት ሆይ ። ዋ ከወይ የመጣ ነው ።
እት (እኅት)፡ የናት ምሳሌ፡ ካባት ከናት የተወለደች እንደ ወንድም ያለች፡ የቅርብ ዘመድ፡ ወዳጅ እኩያ ሚስት ዐብሮ ኣደግ ። (ግጥም)፡ እቴ ብንጋባ ምነው፡ ጕድ አንድ ሰሞን ነው ። ቁመኸ ስትገት ዳኛው እያደላ፡ ባፋረዱኸ እንጂ እትኸ ምን ልበላ ። ትዳር እይዝ ብዬ ልጅ አሳድግ ብዬ ለቅቄለት ዐደርኩ ለዚያ ለሰውዬ ሚስቴን እቴ ብዬ ። (ቀድሞ ዘመን ወታደር ያጠቃው ባላገር) ። እትና እናት ባማርኛ ይገጥማሉ ። እስቲ ጠይቁልኝ ርቃ ሳትኼድ፡ ይተጌ ተዋ በች እትናት ዘመድ ። ሽንኰሬንና አበባን እይ ።
እትማ፡ እትማም፡ (እትማሞች)፡ እታም ባለእት፡ እት ያለቻት፡ ማና ም አንድ ወገን ።
እትማማት (እትም ዐማት)፡ እንደ ኦሪት ሥርዐት ልጆቻቸው ስለ ተጋቡ እትም ዐማት ተባሉ ።
እትማማቶች (አኃት ወሐማታት)፡ እቶች፡ ሴቶች ዐማቶች ።
እትማማች (አኃት)፡ ታናሽና ታላቅ፡ ያንድ አባት ያንዲት እናት ሴቶች ልጆች ። (እትም ዐማች)፡ ወንድ ልጇ የእቷን ሴት ልጅ ያገባ ማለት ነው ።
እትማማቾች (እትም ዐማቾች)፡ ከኹለት በላይ ያሉ ብዙዎች ሴቶች ያክሥቶቻቸውን ሴቶች ልጆች ያገቡ ወንዶች ልጆች ያሏቸው እቶች ማለት ነው፡ ወንድ ምን እይ ።
እትት (እቱት)፡ ከልብስ የተለየ ዕራቍት ገላ ። (ግጥም)፡ እትቱ በረደኝ ቀዘቀዘኝ ነቱ፡ አስለምዶኝ ነበር ያ ልጅ በደረቱ ። ዕችክን እይ ።
እትዬ (እኅትየ)፡ ያባት የናቴ ልጅ የሽንኰሬና ያበባ ታላቅ ።
እቶች (አኃት)፡ የናት አምሳዮች፡
እቶን (አተወ)፡ ዕንጨት የሚማገድበት እሳት የሚነድበት እንጀራና ዳቦ የሚጋገርበት ወጥ የሚሠራበት ምድጃ በማዘንት የተከበበ ። (ሚል ፬ ፥ ፩) ።
እቶን፡ ከአኰቴትና ከባለቤት ከፍ ያለ ኅብስት፡ ተረፈ መሥዋዕት የሳል የጕንፋን መድኀኒት ።
እቶን ኾነ፡ ዐመድ ትቢያ ዐቧራ ኾነ፡ ነከተ ደቀቀ ።
እቶን፡ የእሳት ጕድጓድ ። (ዳን ፫ ፥ ፮ ፥ ፲፩) ።
እነ፡ (እለ)፡ በስም፡ ምትክና፡ በተጸውዖ፡ ስም፡ በጥያቄም፡ መነሻ፡ እየገባ፡ አብዢ፡ ይኾናል ።እነዚህ፡ እነዚያ፡ እኒያ፡ እነኛ፡ እናንተ፡ እነሱ፡ እነጳውሎስ፡ እነማን። ከ፡ ተ፡ መነሻ፡ ሲኾኑት፡ እ፡ ይጐረዳል፡ ከነ፡ ተነ። ኹለቱንም፡ በየስፍራቸው፡ ተመልከት።
እነማን፡ (እለ፡ መኑ)፡ የጥያቄ ንኡስ፡ አገባብ። እነማን፡ መጡ። እነን፡ እይ።
እነሞር፡ የጕራጌ፡ ነገድና፡ አገር፡ ከ፯ቱ፡ ወንድማማቾች፡ አንዱ።
እነሱ፡ (እሙ(ማንቱ)፡ እነርሱ፡ የሩቆች፡ ወንዶችና፡ ሴቶች፡ ዐጸፋና፡ ቅጽል፡ በቂ ።እነዚያ፡ እሊያ፡ እሳቸው፡ ርሳቸው
እነሣሥቶ ላዘመን አዝም ላስፈጸመን እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው በውነት እንበለ ሐሳት ።
እነሴ፡ ዘር፡ ትውልድ፡ ሸረሪት፡ በሸነችበት፡ ገላ፡ ላይ፡ ምስር፡ ዐኝኮ፡ የሚተፋ፡ አባታችን፡ ከሸረሪት፡ ጋራ፡ ተወልዷል፡ እያለ፡ ሸረሪት፡ የማይገድል፡ ነገድ ።
እነሴ፡ ያገር፡ ስም፡ በጐዣም፡ ውስጥ፡ ያለ፡ አገር።
እነሴዎች፡ የእነሴ፡ ዘሮች፡ የአነሴ፡ ትውልዶች ።
እነርሱ፡ (እነ፡ ርሱ)፡ እነሱ፡ እነዚያ ።
እነት፡ (ና)፡ ባሕርይ፡ መኾን ።አምላክነት፡ ሰውነት፡ አብነት።
እነኛ፡ (እነ፡ እኛ)፡ (እሙንቱ፡ እማንቱ)፡ የሩቆች፡ ወንዶችና፡ ሴቶች፡ ዐጸፋና፡ በቂ፡ ቅጽል። እነዚያ፡ እኒያ፡ እሊያ፡ እነሱ። እኛ፡ እነ፡ መነሻ፡ ሲኾነው፡ ለሩቆች፡ የስም፡ ምትክ፡ መኾኑን፡ አስተውል።
እነዋሪ፡ በወግዳ፡ ውስጥ፡ ያለ፡ አገር፡ ዋሪን፡ እይ።
እነዚህ፡ (እነ፡ ዚህ)፡ እኒህ፡ እሊህ ። ዚህን፡ እይ።
እነዚያ፡ (እነ፡ ዚያ)፡ እኒያ፡ እሊያ። እነን፡ ዚያን፡ ተመልከት።
እነጐታም፡ ካትጋፊኝ ' በስተሰሜን፡ ያለ፡ ቀበሌ፡ ጐታ፡ ያላቸው፡ ማለት፡ ይመስላል። በዚህ፡ ስፍራ፡ መስቀል፡ ከሰማይ፡ ወረደ፡ እየተባለ፡ ይወራል ።
እነጐፌ፡ ያገር ' ስም፡ በመራቤቴ፡ ውስጥ፡ ያለ፡ አገር ።ዕችክን፡ እይ ።
እኒሁ እኒሁና፡ በቅርብ፡ ባጠገብ፡ አሉ።
እኒህ፡ (እነ፡ ይህ)፡ እነዚህ፡ እለዚህ፡
እኒያ፡ እነዚያ። ያ፡ ሲበዛ፡ እኒያ፡ ይባላል፡ እነያ፡ እንደ፡ ማለት ።
እኒያው፡ ው፡ ቦታን፡ ያሳያል፡ በሩቅ፡ አሉ።
እኒያውና፡ ው፡ እንዳለፈው፡ ና፡ እንሆ። እነሱ፡ እዚያ፡ አሉ።
እና፡ (ወ)፡ በስምና፡ በግብር፡ መካከል፡ እየገባ፡ አጫፋሪ፡ ይኾናል ።ሰማይና፡ ምድር፡ ጨለማና፡ ብርሃን፡ ጽድቅና፡ ኵነኔ፡ ሰውና፡ መላእክት። ሰማይ፡ እና፡ ምድር፡ ተብሎ፡ ቢጻፍ፡ ስሕተት፡ ነው።
እናሪያ፡ በወላሞ፡ በሲዳሞ፡ በኩሎ፡ በኮንታ፡ በዐማሮ፡ በዛንጅሮ፡ የሚኖር፡ ነገድ፡ የካም፡ ዘር። የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ታሪክ፡ ገጽ፡ ፴፱፡ ተመልከት።
እናቱ፡ እንደ፡ ወለደችው፡ ልብስ፡ አልባ፡ መኾን።
እናቲቱ፡ እናትዮዋ፡ ያች፡ እናት፡ (ማቴ፪ - ፳፡ ፳፩ ።
እናቲት፡ አንስት፡ አህያ፡ ውርንጭላ፡ ያስከተለች ።እናቲት፡ አህያ፡ እንዲሉ ።
እናታችን፡ (እምነ)፡ ወላጃችን ' አስተናጋጃችን፡ የኛ፡ እናት፡
እናቴ፡ (እምየ)፡ የኔ፡ እናት፡ እምዬ ።
እናት፡ (ቶች)፡ (እም)፡ በቁሙ፡ ከአባት፡ ዘር፡ ተቀብላ፡ ዘጠኝ፡ ወር፡ ካምስት፡ ቀን፡ አርግዛ፡ ከባሕርይዋ፡ ልጅን፡ የምትወልድ፡ የምታስገኝ፡ (ዘፀ፳፡ ፲፪። ፩ጢሞ፭፡ ፪) ።ከናት፡ ወዲያ፡ ዘመድ፡ ከቃጫ፡ ወዲያ፡ ገመድ ።የንጀራ፡ የቆብ፡ የክርስትና፡ የቀለም፡ የጡት፡ የሞጋሳ፡ እናት፡ የውሃ፡ እናት፡ እንዲሉ ። (ያገር፡ እናት)፡ በባላገር፡ ዛሬ፡ አንዱ፡ ቤት፡ ነገ፡ እሌላው፡ ቤት፡ እያደረች፡ የምትጦር፡ አሮጊት፡ ልጅ፡ አልባ ።
እናት፡ ባልቴት፡ እመበለት፡ መነኵሲት፡ የናትነት ' ሥራ፡ የምትሠራ፡ ሞግዚትን፡ እይ። (የገዳም፡ እናት)፡ እመ፡ ምኔት።
እናት፡ አይምሬ፡ የክፉ፡ ክፉ፡ መካኝ፡ ደረቅ፡ ሰው'ክርስቶስ፡ ሲወገር፡ ድንጋይ'ያቀበለ።
እናት፡ አደግ፡ እንደ፡ ንግሥተ፡ ነገሥታት፡ ዘውዲቱና፡ እንደ፡ ግርማዊት፡ እተጌ፡ መነን፡ አስፋው ' ያለች፡ ልጅቷ፡ ንግሥት፡ እናቷ፡ ወይዘሮ ።አመቤታችንም፡ አምላክን፡ በመውለዷና፡ በቅድስናዋ፡ እናት፡ አደግ፡ ትባላለች።ሐናን፡ እይ ።
እናት፡ አገር፡ (ሀገሪት)፡ ኣገሪት፡ ያባት፡ የናት፡ አገር፡ የተወለዱባት፡ እንግዴ፡ ልጅ ፥ የተቀበረባት ።በፈረንጅኛ፡ ፓትሪ፡ ትባላለች።
እናት፡ ጕያ፡ በቁሙ፡ ያገር ' ስም፡ በተጕለት፡ ውስጥ፡ ያለ፡ አገር።
እናትነት፡ (ከዊነ፡ እም)፡ እናት ' መኾን፡ ወሓድነት።
እናትና ልጇ እመቤታችንና፡ ጌታችን፡ ማነት፤
እናትኸ፡ ውሃ፡ ትጋትኸ፡ አለ፡ የድካምን፡ ዋጋ፡ ነሣ፡ ከለከለ፡ አስቀረ፡ (ያዕ፭፡ ፬) ።
እናትያ፡ (እማዊት)፡ እናትኛ፡ የጨዋታና፡ የመታዘል፡ ዳኛ፡ አንደርዶ፡ የሚዘሉ፡ ልጃገረዶች፡ ዋና፡
እናትዬ፡ ዝኒ፡ ከማሁ ። (ግጥም)፡ እናትዬ፡ ቈይ፡ ታዪኛለሽ ፥ ተሰቅዬ።
እናንተ (እነ፡ አንተ)፡ (አንትሙን)፡ የቅርቦች፡ ወንዶችና፡ ሴቶች፡ ዐጸፋና፡ በቂ፡ ቅጽል። እላንት፡ ርሳችኩ። አንተ፡ እነ፡ መነሻ፡ ሲኾነው፡ ለቅርቦች፡ የስም፡ ምትክ፡ መኾኑን፡ አትርሳ።
እናንት፡ ዝኒ፡ ከማሁ።
እኔ፡ (አነ)፡ በስምና፡ በአካል፡ ፈንታ፡ የሚነገር፡ የነባቢና፡ የነባቢት፡ በቂና፡ ቅጽል። እኔ፡ ጐበዙ፡ እኔ፡ ልጅት፡ ቅጽል። እኔ፡ አምናለኹ፡ በቂ ። እኔ፡ ራሴ፡ ቅሌ፡ ባለቤቴ። ደቂቅ፡ አገባቦች፡ በ፡ የ፡ ከ፡ ለ፡ ሲሰማሙት፡ እን፡ ጐርዶ፡ በኔ፡ የኔ፡ ከኔ፡ ለኔ፡ ይላል ።
እኔቶች፡ (እነ፡ የቶች)፡ የየት፡ ስፍራ፡ ሰዎች፡ እነን፡ ተመልከት።
እን፡ አን፡ በገባበት፡ ግስ፡ የተደራጊ፡ ቅጽል፡ መነሻ፡ ሲኾን፡ ዘፈዘፈ፡ አንዘፈዘፈ፡ እንዝፍዝፍ፤(ቀለቀለ)፡ አንቀለቀለ፡ እንቅልቅል፡ ይላል። ዳግመኛም፡ ለጥሬ፡ መነሻ፡ እየኾነ፡ ዐልፎ፡ ዐልፎ፡ ይገኛል፡ ይኸውም፡ ትርፍ፡ ጭማሪ፡ አዳማቂ፡ ነው ።ከአን፡ ተለይቶ፡ ሲነገር፡ ጫጨ፡ አጫጪ፡ ብሎ፡ እንጭጭ፡ እንጮጭ ፡ እንጭላ፡ ይላል።
እን፡ እኛ፡ ለሚሉ፡ የትንቢትና፡ የትእዛዝ፡ አንቀጽ፡ መነሻ፡ ሲኾን፡ እንማራለን፡ እንማር፡ እናውቃለን፡ እንወቅ፡ እያለ፡ ይገባል። በግእዝ፥ መሠረቱ፡ ን፡ ነው።
እንሆ፡ (ናሁ፡ ነዋ)፡ ንኡስ፡ አገባብ። የቅርብ፡ ጊዜ፡ የጨበጣ፡ ዐጸፋ። አኹን፡ ቶሎ፡ ይኸው፡ ይኸውና። እንሆ፡ እኔ፡ እንደ፡ ሌባ፡ ድንገት፡ እመጣለኹ። እንሆት፡ እንኋቸው፡ እንኋት፡ እንሆኝ፡ እንሆን፡ እያለ፡ ይዘረዝራል ።እነሆ፡ ማለት፡ ስሕተት፡ ነው፡
እንሆ፡ ዕንኩ፡ ዕንኾ።
እንሰስ፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ የሀገረ፡ ሰብ፡ ቋንቋ፡ ነው።
እንሰስማ፡ እንሰስኛ፡ የንስሳ፡ ባሕርይ፡ ግብር፡ የንስሳ፡ ዐይነት፡ ወገን፡ (መዝ፵፱፡ ፳) ።
እንሰት፡ (ቶች)፡ የኮባና፡ የሙዝ፡ ዐይነት፡ ቅጠል፡ ሴቴ፡ ኮባ፲ ጕናጕና፡ የጕራጌ፡ መና።
እንሰት፡ የቅጠል፡ ስም፡ አነሰ።
እንሱትርያ፡ ተግዳሮት አንጀባ ትም ክት ጕራ ።
እንሳሮ፡ ያገር፡ ስም፡ ከዠማ፡ በስተግራ፡ ያለ፡ አገር።
እንስ፡ (አኒስ)፡ ጕድል፡ መጕደል። እንስ፡ አለ፡ ጕድል፡ አለ። እንስንስ፡ አለ፡ ፈጽሞ፡ ብዙ፡ ጊዜ፡
እንስ፡ ያነሰ፡ የጐደለ፡ (ቅጽል) ።
እንስላል (ሎች)፡ (ሲላን)፡ (ማቴ. ፳፫፡ ፳፫)፡ የእፅዋት ስም (ዕንተ ቀጪን ቅጠሉ ዐረቄ ይኾናል) ። ስለዚህ ፈረንጆች "ወረቄን አኒስ" ይሉታል።
እንስላል፡ በቁሙ፡ ሰለለ።
እንስልጅ፡ ያፈዘዘ/የፈዘዘ።
እንስሳ፡ (ሶሰወ፡ አንሶሰወ)፡ የዱር፡ የቤት፡ ከብት፡ ባላራት፡ እግር፡ ሣር፡ ነጭቶ፡ ውሃ፡ ተጐንጭቶ፡ የሚያድር፡ የሚበላና፡ የማይበላ፡ (ዘይትበላዕ፡ ወዘኢይትበላዕ)፡ የሚያመሰኳ፡ የማያመሰኳ ።ባላገር፡ ግን፡ እንሰሳ፡ ይላል ። ተባቱንና፡ እንስቱን፡ ለመለየት፡
እንስሳ፡ ገር፡ የዋህ፡ ሰው፡ እንደ፡ ሕፃን፡ ያለ ።
እንስሳዋ እንስሳዪቱ፡ ያች፡ እንስሳ፡ (ዘሌ፳፡ ፲፭)።
እንስሳው፡ ያ፡ እንስሳ፡ (ዘሌ፳- ፲፮) ።
እንስሶች፡ ኹለትና፡ ከኹለት፡ በላይ፡ ያሉ፡ ብዙዎች።
እንስራ (ንስራሕ)፡ የዕቃ ስም (የውሃ መቅጃና ማኖሪያ ሸክላ) ።
እንስራ ልብም ጋን ስልቻ ።
እንስራ፡ የሸክላ፡ ዕቃ፡ ሰራ።
እንስርስር፡ የተንሰረሰረ/የበሰለ ሥጋ ከናጥንቱ ።
እንስተኛ፡ የእንስት፡ ወገን።
እንስት፡ በቁሙ፡ በሥራና፡ በኀይል፡ በተፈጥሮ፡ ከተባት፡ ያነሰች፡ የጐደለች፡ ሴቴ። ተባትና፡ እንስት፡ አደረጋቸው፡ (ማር፲፡ ፮)። እንስት፡ ማለት፡ ለኣራዊትና፡ ለእንስሳት፡ ለአዕዋፍ፡ ለተንቀሳቃሽ፡ ኹሉ፡ ለሰውም፡ ለንጨት፡ ለደንጊያ፡ ለምድር፡ ሳይቀር፡ ይነገራል። (ተረት)፡ ከገንዘብ፡ ርስት፡ ከከብት፡ እንስት።
እንስቶች፡ ኹለትና፡ ከኹለት፡ በላይ፡ ያሉ፡ ከብቶች፡ እንስሶች፡ (፩ሳሙ፡ ፱፡ ፫)።
እንሶስላ፡ (ዎች፡ ሎች)፡ የቅጠል፡ ስም፡ ተወቅጦና፡ ፈልቶ፡ እንፋሎቱ ' የሴቶችን፡ እጅና፡ እግር፡ የሚያቀላ ። " እንሶስላ፡ ቅጠሌ፡ አብቧል፡ ዛሬ፡ እንዲሉ፡ ልጃገረዶች ።ሀሩ፡ ሰሰለ፡ ነው ።ከቅጥነቱ፡ በቀር፡ ቅሉ፡ ግርሽጥን፡ ሥሩ፡ መቅመቆንና፡ ካሮትን፡ ይመስላል ።
እንሹ፡ (ዎች)፡ ታናሽ፡ የበረሓ፡ ሠሥ፡ ዲግዲግ፡ ድቅድቅ፡ የምትል። ትግሪትን፡ ተመልከት ።
እንሻ፡ ጕድለት፡ ሕጸጽ፡ ማነስ፡ መኰሰስ፡ መጕደል፡ መዋረድ፡ (ምሳ፲፫፡ ፳፬)።
እንሽላሊት፡ ተንቀሳቃሽ፤ሸለፈ ።
እንሽላሊት፡ የተንቀሳቃሽ ስም (ራሷ እባብ የሚመስል የምድር አውሬ አራት እግር ከጣት ጋራ ያላት) ። ተባትና እንስትን ለመለየት "እንሽላሊቱ እንሽላሊቷ" ይሏል ።
እንቀታም፡ እንቀት ያለው (ባለእንቀት) ።
እንቀት፡ የጥሬ ገብስ ክክ ("(አንቅጥቃጭ)" - የተቀቀለና ያልተቀቀለ) ኾነ " ቀት።
እንቍ፡ በቁሙ፤ዕንቍ ።
እንቍላል፡ በቁሙ፡ ዕንቍላል።
እንቍል፡ ውነጋ ውዝወዛ ።
እንቍልልጦሽ ላይሰጡ፡ ማሳየት፤ቈለጠ ።
እንቍልልጦሽ፡ ከሰጭ ወደ ተቀባይ የማይተላለፍ ማንኛውም ነገር ። "እንቍልልጦሽ የውሻ ርሚጦሽ" እንዲሉ ልጆች ።
እንቍራሪት (ቶች)፡ በውሃ ውስጥና ዳር የሚቀመጥ ተንቀሳቃሽ አረንጓዴ መልክ፡ ተባቱንና እንስቱን ለመለየት እንቍራሪቱ እ ንቍራሪቷያሠኛል ። በየብስ ያለው በበጋ ይሞትና በክረምት ይታደሳል ።
እንቍራሪት በቁሙ፡ ቈረረ።
እንቍራሪትኛ፡ እንደ እንቍራሪት ።
እንቁር/እንቁራ (ፅፍሮ)፡ የጠፍር ኳስ ጥንግ በወስፌ የተበጀ።
እንቍርባ፡ ያተር የሽንብራ ፍሬ መታቈሪያ ገለባ ፍልፋይ ጥርጣሪ ።
እንቍርብ፡ ሌላውን ያንቈረበበ (ለራሱ የተንቈረበበ ") ።
እንቍርዝ፡ እንጥልጥል (የተንጠለጠለ ጤዛ ") ።
እንቍርጥ፡ ቈርጣጣ ።
እንቍጣጣሽ፡ ባንድነት የታሰረ እንግጫና ዐደይ አበባ (የደስታና የምሥራች ምል ክት ርግብ ለኖኅ ያመጣችለት ዘይት (ወይራ) ምሳሌ ከታናናሾች ለታላላቆች የሚሰጥ በረከት)
እንቍጣጣሽ፡ እንግ፵፡ ነቈጠ።
እንቍጣጣሽ፡ የበዓል ስም (ዘመን መለወጫ መስከረም ፩ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ የበዓል ኹሉ ራስ አንደኛ መዠመሪያ በዓል - "እንቍጥ እንቍጣጣሽ በያመቱ ያምጣሽ") ። እንቊጣ
እንቍጥ፡ የእንቍጣጣሽ ከፊል።
እንቍጥቍጥ፡ ያንቈጠቈጠ/የተንቈጠቈጠ (ያጌጠ ሽልም ") ። "ነቈጠ" ብለሽ "እንቍጣ ጣሽን" እይ ።
እንቃቅላ (ሎች)፡ ዐራስ ልጅ/ጨቅላ ' እንጭላ ።
እንቃቅላ ዐራስ፡ ልጅ፡ ነቀለ።
እንቃቅላ፡ ዝበሎ፡ የገበሎ ዐይነት ላሽ (ዘሌ. ፲፩፥፳፱) ።
እንቅልቅል፡ ዝኒ ከማሁ፡ የተንቀለቀለ፡ እንብልብል ጠራራ ። "እንቅልቅል ፀሓይ" እንዲሉ።
እንቅልጣጭ፡ ዝኒ ከማሁ ።
እንቅልጥ፡ ያንቀለጠጠ/የተንቀለጠጠ
እንቅልፋም (ሞች)፡ እንቅልፍ የሚበዛበት ኹል ጊዜ የሚተኛ ፈዛዛ ሰው፡ ዐዞ ።
እንቅልፋምነት፡ እንቅልፋም መኾን ፈዛዛነት ።
እንቅልፍ፡ ዐይንን የሚጨፍን ዦሮን የሚደፍን አፍን የሚገጥም እግር እንዳይኼድ እጅ እንዳይጨብጥ የሚያደርግ ሰውን የሚያጋድም ሌሊታዊ ዕረፍት፡ የሕዋሳት ቍልፍ ። (ተረት)፡ "እንቅልፍ ታበዢ፡ ከነብር ትፋዘዢ ።እንቅልፍና ሞት አንድ ነው ።አንድ ያላት እንቅልፍ የላት" ።
እንቅልፍ እንቅልፍ አለው፡ መኝታ ፈለገው ኣሠኘው ።
እንቅልፍ ወሰደው፡ አስተኛው አጋደመው እንዳይሰማ አደረገው ።
እንቅልፍ ዲና ነው፡ የቤትን ዕቃ ያስበዘብዛል ።
እንቅስቃሴ - ቅስቃሴ - ንቅናቄ፡
እንቅርቃቢ፡ የተልባ የኑግ ክክ ።
እንቅርቅብ፡ የተንቀረቀበ (ደቃቅ ተልባ ") ።"እንቅርቅብ አደረገ"፡ አንቀረቀበ ።
እንቅርብ፡ ያንቀረበበ/የተንቀረበበ ።
እንቅርብጭ (ጮች)፡ የምድር ፍሬ (እንደ ድንች ያለ ") ። በክረምት ቅጠሉ ስለሚበቅል እረኞች ከመሬት ቈፍረው እያወጡ ሳይ ጠብሱና ሳይቀቅሉ የሚበሉት አደንካሬ ።
እንቅርብጭ፡ የምድር፡ ፍሬ፣(ቀረበጠ) ።
እንቅርት ያንገት፡ ዕብጠት፡ ዕንቅርት ።
እንቅርፍ፡ ያንቀረፈፈ/የተንቀረፈፈ (እ ንክርፍ ") ።
እንቅሽ አለ፡ ስብር አለ (ነቀሸ) ።
እንቅሽ አለ፡ ስብር አለ (ነቀሸ) ።
እንቅሽ አደረገ፡ ስብር አደረገ (አነቀሽ) ።
እንቅሽቅሽ፡ አንክትክት ።
እንቅብ (ቦች)፡ የታወቀ ትልቅና ሰፊ የስፌት ዕቃ (፪ ጕርዝኝ ወይም ፲ ቍና እኸል የሚይዝ ላዳን - ዘዳ. ፳፮፥፪, ፬፡ ማቴ. ፭፥፲፭)
እንቅብ፡ ሆድ ።
እንቅብ ሆድ፡ ዘርጣጣ።
እንቅብ፡ ስፌት፡ ነቀበ ።
እንቅብር (ሮች)፡ ሌላውን ያንቀባረረ ለራሱ የተንቀባረረ ።
እንቅብድ፡ ሌላውን ያንቀበደደ ለራሱ የተንቀበደደ (ሆዱ ያበጠ ንፍ እርጉዝ ") ።
እንቅጥቃጭ፡ በሰፌድ እያንቀጠቀጡ ያንጠረጠሩት የገብስ እንቀት ስብርባሪ ።
እንቅጥቃጭ የተቀጠቀጠ፡ ፡ ቀጠቀጠ ።
እንቅጥቅጣም፡ ገላው የሚንቀጠቀጥ ወባም ንዳዳም ።
እንቅጥቅጥ - እንቅጥቅጥታ፡ መንቀ ጥቀጥ ። በግእዝ "ነቀጥቃጥ" ይባላል ።
እንቅጥቅጥ፡ ሌላውን ያንቀጠቀጠ ለ ራሱ የተንቀጠቀጠ (መሬት እጅ ") ።
እንቅጥቅጥ የተንቀጠቀጠ፡ ቀጠቀጠ ።
እንቅፋት፡ መሰናክል፡ ዐነቀፈ።
እንቅፍር፡ ያንቀፈረረ/የተንቀፈረረ (ረ ዥም ") ።
እንቅፍድ - እንቅፍዳጅ፡ ያንቀፈደደ/የተንቀፈደደ (ቀርዳዳ ") ።
እንቆል፡ ሞኝ፡ ነቀለ።
እንቆል፡ ሞኝ/ቂል (እንኮላ) ።
እንቆቅልሽ፡ ለሴት፡ የሚነገር፡ ጥያቄ፡
እንቆቅልሽ፡ ምን፡ ዐውቅልሽ። ላዩ፡ በድን፡ የታቹ፡ በድን፡ መካከሉ፡ ነፍስ፡ አድን። መጽሐፍ፡ ግን፡ በእንቆቅልኸ፡ ፈንታ፡ እንቆቅልሽ፡ ይላል፡ (፩ነገ፡ ፲፡ ፳)።
እንቆቅልኸ፡ (አንቆቅሖ፡ ለከ)፡ የተረት፡ የምሳሌ፡ አነጋገር፡ እንደ፡ ዕንቍላል፡ ድፍን፡ የኾነ፡ ፈተና፡ ላንተ፡ ሰጠኹኽ፡ አቀረብኩልሽ፡ ማለት፡ ነው። እንቆቅልኸ፡ ምን፡ ዐውቅልሽ። ዞሮ፡ ዞሮ፡ መዝጊያው፡ ጭራሮ፡ እንዲሉ።
እንቆቆ፡ የዛፍ፡ ስም፡ ፍሬውን፡ ፈልፍለው፡ ሲቅሙት፡ ኮሶ፡ የሚያሽር፡ ዕንጨት ።ኮሞርን፡ እይ።
እንቡስ፡ (ሶች)፡ የንጨት፡ ስም፡ ዕርፍ፡ ማነቆ፡ የሚኾን፡ የወይናደጋ፡ ዛፍ።
እንቡር፡ መዝለል መቦረቅ ።
እንቡር አለ፡ ዘለለ ቦረቀ፡ ጥጃው ልጁ ።
እንቡር፡ ዝላይ፡ በረረ ።
እንቡርቧይ፡ ተበርብሮ የወጣ፡ ያልደቀቀ ገለባ፡ እንግውላይ ። እንችፉን ጋማ ከብት ከውስጡ የበላው የስንዴና የገብስ ብር አንጓ ጕልበት ሰበር ።
እንቡርቧይ እንግውላይ፣፡በረበረ ።
እንቡርችት፡ እንፉቅቅ፡ በቂጥ መኼድ ።
እንቡሽቡሽ ያልፈላ፡ ጕሽ፡ በሸበሸ ።
እንቡሽቡሽ፡ ጌሾ የሌለው ጕሽ፡ ያልፈላ ቢጠጡት የማያሰክር ።
እንቡቡ፡ (ዕብ፡ ቡባ፡ አሻንጕሊት)፡ ማዘል፡ መሸከም።
እንቡቡ፡ አለ፡ ዐዘለ፡ በዠርባ፡ ተሸከመ ፣በልብስ፡ ባንቀልባ፡ አሰረ ።
እንቡትርያ፡ አንጀባ፡ (ቧተረ)።
እንቡካ የሆድ፡ ቡኬት፡ ፡ ቦካ።
እንቡግቡግ፡ የሚንቦገቦግ፡ እንብል ብል ።
እንቡጣ፡ (ዎች)፡ ጐፍላ፡ የጥጃ፡ ቈዳ ።ጥጃ፡ በሞተ፡ ጊዜ፡ ስልቻ፡ አውጥተው፡ በውሥጡ፡ ሣር፡ ገለባ፡ ጐስረው፡ (መልተው)፡ ጨው፡ ነስንሰው፡ በላ፡ ፊት፡ ያቆሙታል፡ እሷም፡ ያን፡ እያየች፡ እየላሰች፡ ትታለባለች ።
እንቡጣጢት፡ ሴት፡ ልጅ፡ እንስት፡ እንስሳ፡ ለጋ ።
እንቡጣጥያ፡ (ዮች)፣ ጨቅላ፡ ዐራስ፡ ግልገል፡ ከማሕፀን፡ የወጣ፡ የተፈለፈለ።
እንቡጥ፡ (ጦች)፡ የባቄላና ' ያተር፡ የሽንብራ፡ የጓያ ፣ያደንጓሬ፡ የደንጐሎ ፣ያበባ፡ እኸል፡ ኹሉ፡ መታቈሪያ ።ፍሬ፡ ሲዠምር፡ ጨርቋ፡ ካፈራ፡ በኋላ፡ እንቡጥ፡ ይባላል ።
እንቡፍና፡ ዝኒ ከማሁ ።
እንቡፍና ያልፈላ፡ ጕሽ፡ ቡና ።
እንቢ፡ (እንብየ)፡ ነባር፡ አንቀጽ፡ አሉታ። በቁሙ፡ አሻፈረኝ፡ አልሰማም፡ አልታዘዝም ፣አልቀበልም፡ አይኾንም፡ ኣይኹን ።ሲዘረዝርም፡ እንቢዮ፡ እንቢኝ፡ እንቢልኝ፡ ይላል።
እንቢ፡ ነገር፡ ባጋሰስና፡ ባህያ፡ ዠርባ፡ ከጭነት፡ በታች፡ የሚደረግ፡ መደላድል፡ በውሥጡ፡ ሣርና፡ ገለባ፡ ስላለበት፡ ጐንደሮች፡ ዳውላ፡ ይሉታል።
እንቢ፡ አለ፡ (አበየ)፡ እንቢተኛ፡ ኾነ፡ አልታዘዘም ።
እንቢ፡ ጣጣ፡ ያገር፡ ስም፣ በይፋት፡ ውስጥ፡ ያለ፡ ቀበሌ።
እንቢልተኛ (ኞች)፡ እንቢልታ ነፊ፡ ባለእንቢልታ ።
እንቢልታ፡ የዘፈን መሣሪያ፣ በለተ ።
እንቢልታ፡ ድምፁ ወፍራምና ቀጪን የኾነ፡ በአፍ የሚነፋ የዘፈን መሣሪያ፡ በድምፁ የእስክስታንና የዘፈንን ኹናቴ ለይቶ የሚያስታውቅ ።
እንቢተኛ፡ (ኞች)፡ (አባዪ)፡ የማይታዘዝ፡ የማይሰማ፡ እንቢ፡ ባይ፡ አባያ፡ (ሕዝ፲፪፡ ፫፡ ፪) ።
እንቢተኛነት፡ ሞገደኛነት፡ አፈቻይነት።
እንቢታ፡ (እበይ)፡ አለመታዘዝ፡ አለመቀበል፡ ዕሺ፡ በጎ፡ አለማለት ።
እንቢያ፡ ደረት፡ ፍርንባ፡ ካንገት፡ በታች፡ በወርችና፡ በብራኳመካከል፡ ያለ። በንቢያው፡ ገፍቶኝ፡ ኼደ ።
እንቢያጕሥ፡ እንቢያ፡ ጕርሥ፡ እንቢያ፡ የሚጐርሥ፡ እንቢያ፡ ጐረሥ፡ የተሰፋ፡ ጠፍር፡ በፈረስ፡ በበቅሎ፡ ባህያ፡ በግመል፡ በዝኆን፡ እንቢያ፡ የሚውል፡ በስተዠርባ፡ ቀዳማይ፡ በስተሆድ፡ ቅናት፡ የሚገባበት። እንቢያ፡ ጕስ፣ ቢል፡ እንቢያ፣ የሚጐስም፡ የሚነካ፡ የሚፈገፍግ፡ የኮርቻ፡ ሚዛን፡ ማለት፡ ነው። ሲበዛ፡ እንቢያጕሦች፡ ይላል ።
እንባ (እንብ/አንብዕ)፡ ከኹለት ዐይን የሚፈልቅ የሐዘን ፈሳሽ ("ካንዠት ካለቀሱ እንባ ኣይገድም") ።
እንባ ቀረሽ፡ ሊያለቅስ ጥቂት የቀረው።
እንባ፡ በቁሙ፣፡ ነባ።
እንባ በንባ ተራጩ፡ ኹሉም ተላቀሰ።
እንባ አቀረረ፡ ባይኑ ውስጥ እንባ አሳየ።
እንባ ዐነቀው፡ በፍጥነት አለቀሰ (ከበደልና ከሐዘን የተነሣ) ።
እንባ አድርቅ፡ በሬሳ ፊት የሚኼድ እንጀራና ጠላ እንባ የሚያደርቅ (ከቀብር በኋላ ስለሚበላ "እንባ አድርቅ" ተባለ) ።
እንባ እንባ አለው፡ ማልቀስ ፈለገው።
እንባ ወጣው፡ አለቀሰ።
እንባ ጠባቂ፡ ፍርድ ጐደለ ድኻ ተበደለ የሚል እውነተኛ ሰው።
እንባማ፡ ባለብዙ እንባ (ለማንም የሚያለቅስ አልቃሽ) ።
እንብልብል፡ ነብ፡ በለበለ ።
እንብልብል፡ ነብ ነዲድ ።
እንብርት፡ በቁሙ፡ ዕንብርት።
እንብርክ፡ የጐነበሰ ያጐነበሰ የበ ረከ የተንበረከከ በጕልበት የቆመ ።
እንብድብድ፡ የሚፈራ የሚንቀጠቀጥ፡ ፈሪ ።
እንቦሳ፡ በቁሙ፣ ከወተት፡ በቀር፡ ውሃ፡ የማይጠጣ፡ ሣር፡ የማይበላ፡ የላም፡ ልጅ፡ (፩ሳሙ፡ ፮፡ ፲) ።ቤት፡ ለንቦሳ፡ እንቦሳ፡ እሰሩ፡ እንዲሉ።ተባትንና፡ እንስትን፡ ለመለየት፡
እንቦሳዋ፡ የርሷ፡ እንቦሳ፡ እንቦሳዋ፡ እንቦሳዪቱ፡ ያች፡ እንቦሳ።
እንቦሳው፡ ያ፡ እንቦሳ፡ የርሱ፡ እንቦላ።
እንቦሶች፡ በእንቦሶች፡ አምሳል፡ የተሠሩ፡ ጣዖቶች፡ (፪ዜና - ፲፩፡ ፲፭)።
እንቦሶች፡ ጥጆች፡ ተባቶችና፡ እንስቶች።
እንቦቀቅላ (ሎች)፡ አበባው ቅላት ያለው ቅጠል በወይናደጋ የሚበቅል ።
እንቦቀቅላ፡ ለጋ ቀንበጥ፡ ሕፃን ። (ላቀ) ።
እንቦቀቅላ፡ የቅጠል፡ ስም፡ ቀለ ።
እንቦጭ፡ መጮኸ መሰማት ። (ተረት)፡ ውሃ ቢወቅጡ እንቦጭ ።
እንቦፍ፡ መውደቅ፡ ቦፍ።
እንቦፍ አለ፡ ወደቀ፡ ድምፁ ተሰማ፡ ውሃ ያለበት ሸክላ ወይም ቅል ።
እንቦፍ፡ ዝኒ ከማሁ ።
እንቧ (ነብሐ)፡ የበሬ፡ የላም፡ የጥጃ ፥ ጩኸት። አገሯ፡ መረሬ፡ እንቧ፡ እንደ፡ በሬ፡ እንዳለ፡ ዘፋኝ። መና፡ ነ፡ ተወራራሾች፡ ስለ፡ ኾኑ፡ እምቧ፡ ይላል።
እንቧ፡ አለ፡ አለች፡ በሬ፡ አጣማጁን፡ ላም፡ ጥጃዋን፡ ጠራ፡ ጠራች፡ (፩ሳሙ፡ ፯፡ ፲፪)
እንቧ(ባ)ጮ፡ (ዎች)፣ (ባጦስ)፡ የንፊት፡ ስም፡ ለጋውን፡ ቀንበጡን፡ ልጆች፡ የሚበሉት፡ ውሃው፡ የሚሖመጥጥ፡ የሚሸመጥር። መብሉ፡ እንቧጮ፡ እንቧጮ፡ አለኝ። መና፡ ነ፡ ተወራራሾች፡ ስለ፡ ኾኑ፡ እምቧጮ፡ ተብሎ፡ ሊጣፍም፡ ይቻላል።
እንቧይ፡ (ዮች)፡ ዓሣ፡ የሚያስክር፡ ፍሬው፡ እንደ፡ ሎሚና፡ እንደ፡ ገባ፡ያለ፡ ትልቅና፣ትንሽ፡ እሾኻም ፣ዕንጨት ።ገበር፡ እንቧይ፣ ዘርጭ፡ እንቧይ፡ እንዲሉ፡ (፪ዜና፡ ፳፬፡ ፲፰)። (የምድር፡ እንቧይ)፡ ሻካራ፡ ሐረግ፡ ያለው፡ እንቧይ፡ ምድር፡ ለምድር፡ የሚሳብ ።ካበ፡ ብለኸ፡ ካብን፡ እይ ።
እንቧይ፡ ሰበከት፡ አካለ፡ ሻካራ፡ ሴት። ባዘተ፡ ብለኸ፡ ባዘቶን፡ እይ።
እንተኔ፡ (እንቲኣየ)፡ እንተ፡ እኔ፡ የኔ፡ ወገኔ፡ ዘመዴ።
እንተን፡ (እንተ)፡ ለሩቅና፡ ለቅርብ፡ ወንድና፡ ሴት፡ በቂ ።እከሌ፡ እከሊት፡ እሱ ' እሷ፡ አንተ፡ አንቺ።
እንቱሽ፡ (እንተ፡ ወሽ)፡ ልጆች፡ እንዳህያ፡ የሚራገጡት፡ ርግጫ።
እንቲያኽ፡ (እንቲኣከ)፡ ምን፡ እንቲያኸ፡ እንዲሉ፡ ልጆች።
እንትብትብ፡ የተንተበተበ ቈሎ ።
እንትና፡ ላገር፡ ስም፡ በቂ፡ ይኾናል።
እንትን፡ (ኖች)፡ የስምና፡ የግብር፡ የነገር፡ በቂ። ዘወር፡ በል፡ እንትን፡ መጣብኸ። እባክሽ፡ ወንድሜ፡ እንትን፡ ስጠኝ። እንትኑን፡ በንትን፡ አደረገው፡ ብትንትን። እንትን፡ ባልኩበት፡ እንትን፡ ገባበት፡ አንትን፡ አምጪልኝ፡ እንትን፡ እልበት፡ አንቺም፡ ነዪልኝ፡ እንትን፡ ትይልኝ ።የኔን፡ እንትን፡ የሚያሰፋ፡ እንጂ፡ የሚያጠብ፡ አይመጣም፡ ትቤ፡ ብእሲት።
እንትክትክ፡ የተንተከተከ ሙቅ ።
እንትፍ፡ መትፋት ።
እንትፍ መትፋት ፣ተፋ።
እንትፍ አለ፡ ተፋ ።
እንትፍ እንትፍ አለ...ጥላቻውን ተወ ።
እንትፍታ፡ እንትፍ ማለት ትፍታ (ኢዮ. ü፡ ፲) ።
እንትፍትፍ አለ፡ ዝኒ ከማሁ ። ትፋት (ትፋእ)፡ ቅርሻት ምላሽ (ምሳ. ፳፮፡ ፲፩፡ ኢሳ. ፲፱፡ ፲፬፡ ኤር. ፵፰፡ ፳፮) ። ("ተረት - ልጅ የቈሎ ትፋት ያምረዋል") ።
እንቶ፡ አንተን፡ ያ።
እንቶ፡ እየተጠበሰ፡ የሚበላ፡ እንጕዳይ። እንቶ፡ እንትኖ፡ ምናምኖ። እንቶፈንቶ እንዲሉ ።
እንቶኔ፡ ዝኒ፡ ከማሁ። ፫ኛውን፡ እንቶ፡ እይ ።
እንችርፍ ያኰረፈ፡ (ቸረፈፈ)።
እንችፍ፡ የስንዴና፡ የገብስ፡ እንሻፎ፡ ወሰስ፡ ቀላል፡ የግርድ፡ ተወራጅ ።
እንከን፡ (እንትን)፡ ነውር፡ አደፍ፡ ጕድፍ፡ ስሓ።
እንከን፡ የለሽ፡ የሴት፡ ስም፡
እንከፍ፡ ዝኒ ከማሁ (አላዋቂ ነጕላ ነፈዝ) ።
እንከፍቂል፡ ነከፈ።
እንኩ ተቀበሉ፡ ዕንኩ።
እንኵርኵሪት፡ የተሰባበረች፡ ኰረኰረ ።
እንኵርኵር፣፡ስብርብር፣፡ኰረኰረ ።
እንኵሮ፡ በውሃ ርሶ ወይም ላቍጦ እየተገለበጠ በገበር ምጣድ የበሰለ የገብስ ዐሻሮ (ያገዳ ዱቄት ሊጥ) ።
እንኵሮ፡ የበሰለ፡ ዐሻሮ፡ (ነኰረ) ።
እንኵቶ፡ በቁሙ በመሬት ላይ ተቃጥሎ ከነገለባው የበሰለ የረኛ ምግብ ("እንኵቶ ኾነ" - ደቀቀ) ።
እንኪያ፡ (እንከ)፡ ንኡስ፡ አገባብ፡ እንግዲያ ። እድግስ፡ ቤት፡ ካልበላኸ፡ ካልጠጣኸ፡ እንኪያ፡ ለምን፡ መጣሽ። ማ፡ ሲያጐላምሰው፡ እንኪያማ፡ ይላል፡ (ማቴ፲፱፡ ፳፭ ።ዮሐ፩፡ ፳፭)።
እንኪያስ፡ (እንከሰ)፡ (ዮሐ፩፡ ፳፩)፡ በግፍ፡ ነፍስ፡ ከገደለ፡ እንኪያስ፡ ይሞት፡ በቃ። ስ፡ አፍራሽ፡ ወይም፡ ትች፡ ያ፡ ምእላድ፡ መኾኑን፡ አስተውል፡ እንግድን፡ ተመልከት።
እንካ፡ ተቀበል፡ ዕንካ።
እንክል እንክል አለ፡ ዕንክስ ዕንክስ ጥንቅል ጥንቅል አለ፲ ዥብኛ ረገጠ ኼደ።
እንክርት፡ ከርታታ፡ (ከረተተ)።
እንክርዳድ (ክርዳድ)፡ ከስንዴ'ጋራ ዐብሮ የሚበቅል ዥራታም ፍሬ ("እንጀራውን በበሉትና ጠላውን በጠጡት ጊዜ ራስ የሚያዞር አእምሮ የሚለውጥ ናላ የሚበጠብጥ ") (ማቴ. ፲፫፡ ፳፭, ፳፱) ።
እንክርፍ፡ የተንከረፈፈ፡ (ከረፈፈ)፡
እንክብል (ሎች)፡ ክብ ' ድብልብል ' ነገር ።
እንክብል፡ በንቍላል/በሎሚ አምሳል ከብረት የተበጀ የዓለም ሥዕል ("ግሎብ") ።
እንክብል፡ ድብልብል፡ ከበለለ።
እንክብክብ (ቦች)፡ የተንከበከበ ("ድ ብልብል ነገር ርጥብ") ።
እንክብክብ የተንከበከበ ከበበ ።
እንክት አለ፡ ድቅቅ አለ።
እንኮኮ፡ በቁሙ፡ (ኮኮ) ።
እንኮኮ አለ (ኀንገረ)፡ ልጅን በት ከሻው ላይ አስቀመጠ ("ተሸከመ እንኮኮ ተባለ በጫንቃ ተያዘ አሽኮኮ እንኮኮ አሽኮኮ አለ እንኮኮ አለ አሽኮኮ የካህናት እንኮኮ የሕዝብ ነው ሽኮኮን እይ ") ።
እንኮዬ፡ ከሠላሳ ዓመት በላይ ያለች ሴት የስማ ቅጽል ("አያ እንኮዬ ዘመነ እን ኮዬ" እንዲሉ) ።
እንኮዬ የኔ፡ እንኮይ፡ ነካ ።
እንኮዬ፡ የኔ እንኮይ ወይም የእንኮይ ዐይነትና ወገን።
እንኮይ (ዮች)፡ ፍሬው የሚበላ የበረሓ ዕንጨት (የትፋሕ ዐይነት - ዘፍ. ፴፥ ፲፬, ፲፭, ፲፮፡ ማሕ. ፪፥፫, ፰፥፭) ።
እንኮይ፡ የዛፍ፡ ስም፡ ነካ።
እንኳ፡ (ጓ፡ ጥቀ)፡ ንኡስ፡ አገባብ። የማበላለጥ፡ ቃል፡ (መዝ፻፴፰፡ ፯) ።የፈጣሪን ባሕርይ፡ ሰው፡ ይቅርና፡ መልአክ፡ እንኳ፡ አያውቀውም ።እንኳና፡ እንኳን፡ ስንኳና፡ ስንኳን፡ አንዳንድ፡ ወገን፡ ናቸው።
እንኳን፡ (ስንኳን)፡ የማበላለጥና፡ የማማረጥ፡ የማዋረድና፡ የማሳነስ፡ ቃል። እንኳን ' ጠላና፡ ይቀራል፡ ጠጅ፡ እንዲያው፡ ነገሩ፡ ይቈል፡ እንጅ(ጂ)፡ (አዝማሪ)፡ የገርማሜን፡ ምክር፡ የሰማኸ፡ እንደኾን፡ እንኳን፡ ንጉሥና፡ ዐምባ፡ ራስም፡ ኣትኾን ።እንኳን፡ ለሙቅ፡ ለገንፎም፡ አልደነግጥ ።
እንኳን፡ (አኮ)፡ ነባር፡ አንቀጽ፡ አሉታ። አይዶለም፡ አይኾንም፡ አይደረግም፡ (፩ሳሙ፩፡ ፲፭) ።በዘመናችን፡ ግን፡ እንኳን፡ በእንኳዕ፡ ፈንታ፡ ይነገራል ።እንኳዕን፡ እይ ።ተደጋግሞ፡ ሲነገር፡
እንኳን፡ እንኳን (አኮ፡ አኮ)፡ አይ ዶለም፡ አይዶለም። (ግጥም)፡ ላንተ፡ ይብላኝ፡ እንጂ፡ ለኔስ፡ እንኳን፡ እንኳን፡ የትም፡ ይተከላል፡ ፍቅርና፡ ድንኳን። እንኳን፡ እንኳን፡ ሐሰቱን፡ ትተኸ፡ እውነቱን፡ ተናገር፡ (ማቴ፭፡ ፴፯)።
እንኳዕ፡ (እንቋዕ)፡ ንኡስ፡ አገባብ፡ የደስታ፡ ቃል። ዕሠይ፡ ወሰው፡ ይበጅ፡ ያድርግ። እናት፡ የልጇን፡ ሞት፡ ሳትሰማ፡ እንኳዕ፡ ሞተች። እከሌ፡ ከዘመቻ፡ እንኳዕ፡ ደኅና፡ ገባ። እንኳዕ፡ ከዘመን፡ እዘመን፡ አሸጋገረዎ። እንኳዕ፡ ካማርኛ፡ ይልቅ፡ በትግሪኛ፡ ይነገራል።
እንኳዕ፡ እንኳዕ (እንቋዕ፡ እንቋዕ)፡ ዕሠይ፡ ዕሠይ፡ ወሰው፡ ወሰው።
እንኾ ተቀበሉ፡ ዕንኾ።
እንዘረዘይ፡ ቅጠል፡ ዘረዘረ ።
እንዘረዘይ፡ የቅጠል ስም ("ሥሩ እንደ ሽንኵርት ላዩ እንደ ፊላ የኾነ ልዩ ልዩ ነት ያለው ቅጠል ለዕባጭ መድኀኒት ይኾናል ይበትነዋል") ።
እንዘጥ፡ መውደቅ፡ (ዘጠዘጠ)።
እንዘጥ አለ፡ ወደቀ ("ቂጡን መሬት መታው") ።
እንዚራ፡ በበገና ብርክማ ላይ ያለ የጠፍር ቍርጥራጭ ("በግእዝ ግን ማሲንቆ በገና ክራር የዘፈን መሣሪያ ማለት ነው") ።
እንዛዝላ (ሎች)፡ ደንደሎ ("ያባያ መ ቅጫ ረዥም ግንድ ወይም እንዶድ") ።
እንዛዝላ፡ ባለጌ፡ ልጅ፡ ስድ ።
እንዛዝላ፡ ባለጌ ልጅ/ስድ ።
እንዛዝላ፡ ደንደሎ፡ ዛዘለ።
እንዝልዝል/እንዝልዛይ፡ የሚንዘለዘል ("እንጥልጥል") ።
እንዝርብ፡ እንጥልጥል ።
እንዝርት (ቶች)፡ በቁሙ እጀታው ቀርክሓና ወይም ወይራ የኾነ (በራሱ ላይ ቀንድ ከሽቦ ቋንጣ ጋራ ያለበት የፈትል መሣሪያ - ምሳ. ፴፩፥፲፱) ።
እንዝርት፡ የፈትል፡ መሣሪያ፡ ነዘረ።
እንዝርግ፡ የሚንዘረገግ ("ጐታታ") ።
እንዝርጣጭ፡ ዝኒ ከማሁ ("እንቅብድ") ።
እንዝርጥ፡ የተንዘረጠጠ ("እንጥርዝ") ።
እንዝርፍ፡ የሚንዘረፈፍ/የሚጐተት ።
እንዝዝ፡ ሥሥት፤ዕንዝዝ ።
እንዝግዝግ፡ ቅዝምዝም፡ ዘገዘገ።
እንዝግዝግ/ምዝግዝግ/ውዝግዝግ/ቅዝ ምዝም፡ ጫፉን ይዞ የወረወሩት በትር ወይም ብረት ።
እንዝግዝጎሽ፡ የበትር ውርወራ ።
እንዝፍዝፍ (ፎች)፡ የተንዘፈዘፈ ("ርግብግብ እንቅጥቅጥ ቀጫ") ።
እንዞርዬ፡ ዕፀ፡ ሳቤቅ፡ ያረግ፡ ሬሳ። እንጆሪንም፡ ያሳያል።
እንዡባን፡ ዐጡንባር፡ የሚመስል፡ ቅጠል፡ መልካም፡ አበባና፡ ጣፋጭ፡ ሽታ ያለው።
እንዥርግ/እንጥልጥል/እንጭርግ፡ የዛፍ/የተክል/የእኸል ፍሬ ።
እንዥቦ፡ (እንጅቦ)፡ የቅጠል፡ ስም፡ ወተታም፡ ቅጠሉ፡ ሳይቀቀል፡ ከንጀራ፡ ጋራ፡ የሚበላ። በና፡ መ፡ ዠና፡ ጀ፡ ተወራራሾች፡ ስለ፡ ኾኑ፡ ካህናት፡ እንጅሞ፡ ይሉታል።
እንደ፡ (ከመ)፡ ዐቢይ፡ አገባብ፡ ፍችው፡ በቁም፡ ቀሪ። እንደ፡ ኾነ፡ እንዲኾን፡ እንድትኾን።እንዳያማኸ፡ ጥራው፡ እንዳይበላ፡ ግፋው ።እንዳ የን፡ ጤፍ፡ አጋየን።
እንደ፡ ምን፡ (ከመ፡ ምንት)፡ በሽተ ኛው፡ እንደ፡ ምን፡ ነው፡
እንደ፡ ምንም፡ (ከመ፡ ምንትኒ)፡ እንደ፡ ምንም፡ ብዬ፡ ዕዳዬን፡ ከፈልኩ። በጥሬ፡ ሲገባ፡
እንደ፡ ራሴ፡ (ከመ፡ ርእስየ)፡ ባልንጀራዬን፡ እንደ፡ ራሴ፡ እወዳለኹ።
እንደ፡ ሻሽ፡ እንደ፡ በፍታ። የኩታው፡ ቅጥነት፡ እንደ፡ ሻሽ፡ ኾነ ።ስም፡ ከቅጽል፡ ሲናበብ፡ እንደን፡ ያመጣል።
እንደ፡ ነገሩ፡ እንደ፡ ተገኘ። እንደ፡ ቂጡ፡ ደኅና፡ ነውር፡ አልባ፡ ሳይኾን፡ ሌላውን፡ ለሚነቅፍ፡ ሰው፡ ይነገራል ።
እንደ፡ ዋለ፡ ቀረ፡ ወደ፡ ቤቱ፡ አልተመለሰም፡ የደረሰበት፡ አልታወቀም ።
እንደ፡ ደቂቅ፡ አገባብ። እንዳገሩ፡ይኖሩ፡ እንደ፡ ወንዙ፡ ይሻገሩ ።እንደ፡ ገና፡ ይመታል፡ በገና፡ ይህ፡ ኣንጻር፡ ሲኾን፡ ነው ።በስም፡ ምትክ ሲገባ፡
እንደ ድር ጠንካራ ያልኾነ ማግ (የግራ ፈትል) ። "የጥንት ግብጦች ማግን ወደ ግራ ይፈትሉ ነበር ይላል ሔሮዶቱስ።"
እንደሆህላ፡ እንዳሁላ፡ የታወቀ፡ ቅጠል፡ በወይናደጋ፡ የሚበቅል፡ ዕንጨቱ፡ ጠንካራ፡ ያይዶለ፡ ቅጠሉ፡ ለስላሳ ።
እንደራሴ፡ በቁሙ፡ እንደ ።
እንደራሴ፡ ኾነ፡ ተወከለ፡ ተሾመ።
እንደራሴ፡ የማዕርግ፡ ስም፡ የንጉሥ፡ የሻለቃ፡ ያገረ፡ ገዢ፡ ወኪል፡ ባለሥልጣን። ምስለኔን፡ ተመልከት።
እንደራሴነት፡ እንደራሴ፡ መኾን።
እንደራሴዎች፡ ወኪሎች፡ ዳኞች፡ ሹሞች ።
እንደርታ፡ በትግሬ፡ ውስጥ፡ ያለ፡ አገር።
እንደሻሽ፡ የሴት፡ ስም፡ እንደ፡ ፈለገሽ፡ እንደ፡ ፈለግሽ።
እንደሻው፡ የሰው፡ ስም፡ እንደ፡ ፈለገው፡ ማለት፡ ነው ።ሻን፡ እይ ።
እንደነዚህ፡ (ከመ፡ እለ፡ ዝ)፡ እንደነዚህ፡ እንጂ፤
እንደነዚያ፡ (ከመ፡ እለ፡ ዘህየ)፡ እ እንደነዚያ፡ መኾን፡ አይገባም። ዚህንና፡ ዚያን፡ ተመልከት።
እንደኔ፡ (እንደ፡ እኔ)። ምስለኔ፡ ኹን፡ እንደኔ ።
እንደኹ፡ እንደ፡ ኾነ፡ እንደኾን። ሰው፡ ያገኘ፡ እንደኹ፡ . . . . ። በጥያቄ፡ ሲገባ፡
እንደዚህ፡ (ከመ፡ ዝ)፡ እንደ፡ ይህ።
እንደዚያ፡ (ከመዘህየ)፡ እንደ፡ ያ፡
እንደዚያው፡ እንደ ' ያው ።ዛሬም፡ እ ንደዚያው፡ ነው።
እንደጋኝ፡ የጕራጌ፡ ነገድና፡ አገር፡ ከ፯ቱ፡ ወንድማማቾች፡ አንዱ ።
እንዱሽዱሽ ቈሎ፡ (ዶሸዶሸ)
እንዱሽዱሽ፡ የተንዶሸዶሸ/የሚንዶ ሸዶሽ ("ቈሎ") ።
እንዲ፡ ለሩቅ፡ ወንድ፡ ለሩቆች፡ ወንንዲ፡ ለሩቅ፡ ወንድ፡ ለሩቆች፡ ወንዶችና፡ ሴቶች፡ የዘንድ፡ አንቀጽ፡ መነሻ። እንዲያውቅ፡ እንዲያውቁ ።በስም፡ ምትክ፡ ገብቶ፡ አንጻር፡ ሲኾን፡
እንዲሁ፡ እንደዚሁ።
እንዲህ፡ (እንደ፡ ይህ)፡ እንደዚህ ' (፩ቆሮ፡ ፯፡ ፯) ።እከሌ፡ እንዲህ፡ አለኝ፡
እንዲህ፡ ነው፡ ማለፊያ፡ ነው፡ ሥራው፡ ነገሩ።
እንዲህ፡ አይደለም፡ አላማረም፡ አልሰመረም፡ አልበጀም።
እንዲያ፡ (እንደ፡ ያ)፡ እንደዚያ፡ (፪ዜና፡ ፲፰፡ ፲፱ ።፩ቆሮ፡ ፯፡ ፯) ። ደው ።
እንዲያ፡ በለው፡ ምታው፡ አስወግደው ።
እንዲያማ፡ እንደ ' ያማ። ማ፡ አጐላማሽ፡ ነው ።
እንዲያው፡ ባዶ፡ አጅ፡ አንዳች፡ አልባ፡ (ሉቃ፳፡ ፲) ።
እንዲያው፡ የዝም፡ ብሎ። ምንም፡ ሳላጠፋ፡ እንዲያው፡ ተጣላኝ፡ (፩ቆሮ፡ ፲፬፡ ፲፯) ።
እንዳለ፡ የሰው፡ ስም፡ ፈጣሪ፡ እንዳዘዘ፡ እንደ፡ ፈቀደ ።
እንዳለ፡ ያለ፡ በቋፍ፡ የተቀመጠ፡ ሕመምተኛ፡ ግልፍተኛ፡ ሰው፡ አትንኩኝ፡ ባይ፡
እንዳለወገን፡ አደረገ፡ አላገባብ፡ ሠራ፡ አጕላላ፡ ጐዳ፡ አበላሸ።
እንዳላማው፡ ልጅ፡ ነሣኝ፡ እንዳልለው፡ ማለት፡ ነው ።
እንዳልኾነ፡ ኾነ፡ እንዳልተፈጠረ፡ እንዳልነበረ፡ ተደረገ፡ ጠፋ፡ ታጣ፡ (ኢሳ፵፩፡ ፲፪) ።
እንዳሞድ፡ ነጭ፡ ዝንጀሮ፡ እንዳመድ፡ ያለ፡ ወይም፡ እንዳፍንጫ፡ ዐዳው፡ ጥቍሬ፡ ዝንጀሮ፡ የኾነ፡ ማለት፡ ነው።
እንዳባት የሚጠራ፡ የእንኰዬ አንጻር ። እያ እንኰዬ እንዲሉ። (ተረት)፡ የሞተውን አያ ይለዋል ።
እንዳይላሉ፡ የሰው፡ ስም፡ ነቅተው፡ ተግተው፡ ጠንክረው፡ ይኑሩ፡ ማለት፡ ነው ።
እንዳፈተተ)፡ እንዳፈቀደ ።
እንዴ፡ (እፎ)፡ ንኡስ፡ አገባብ ።እንዴ፡ ይህ፡ ሰው፡ ምን፡ ማለቱ፡ ነው። ጥያቄና፡ የብስጭት፡ አንክሮ፡ ነው ።
እንዴታ፡ (እፎአ)፡ ሰውዮ፡ የግስ፡ ተራ፡ ታውቃለኽን፡ እንዴታ፡ አሳምሬ፡ ዐውቃለኹ ።
እንዴት፡ (እንደ፡ የት)፡ ዝኒ፡ ከማሁ። እንዴት፡ አንተ፡ አይሁዳዊ፡ ስትኾን፡ ከኔ፡ ውሃ፡ ትለምናለኸ። የጥያቄ፡ ቃል፡ ኹኖ፡ በ፰፡ መደብ፡ ሲነገር፡
እንዴት ሰነበትክ)፡ አንተ ለሚባል የቅርብ ወንድ በደብዳቤ ወይም ባንደበት የሚሰጥ የሰላምታ ቃል።
እንዴት፡ ነሽ፡ (እፎ፡ አንቲ)፡ አንቺ፡ እንዴት፡ ነሽ፡ ነሻ፡ እንዴት፡ አለሽ፡ (ሮሜ ፲፯፡ ፲፪)።
እንዴት፡ ነች፡ ናት (እፎ፡ ይእቲ)፡ እሷ፡ እንዴት፡ ናት፡ እንዴት፡ አለች።
እንዴት፡ ነኽ፡ (እፎ፡ አንተ)፡ አንተ እንዴት፡ ነኸ፡ እንዴት፡ አለኸ፡ (ሮሜ፲፯፡ ፯፡ ፲፩)።
እንዴት፡ ነው፡ (እፎ፡ ውእቱ)፡ እሱ፡ እንዴት፡ ነው፡ እንዴት፡ አለ።
እንዴት፡ ነዎ፡ ርስዎ፡ እንዴት፡ ነዎ፡ አንዴት፡ አሉ።
እንዴት፡ ናችኹ፡ (እፎ ኣንትሙ)፡ እናንተ፡ እንዴት፡ ናችኹ፡ እንዴት፡ አላችኹ፡ (ሮሜ ፲፯፡ ፫፡ ፲፩፡ ፲፪፡ ፲፭)። እኔ፡ ደኅና፡ ነኝ።
እንዴት፡ አመሸኸ፡ (እፎ፡ አምሰይከ)፡ አንተ፡ እንዴት፡ አመሸኸ ።
እንዴት፡ ዐደሩ፡ (እፎ፡ ኀደሩ)፡ እነሱ፡ (ርስዎ)፡ እንዴት፡ ዐደሩ።
እንዴት፡ ዐደርኸ፡ (እፎ፡ ኀደርከ)፡ ኣንተ፡ እንዴት፡ እንደ፡ ምን፡ ዐደርኸ፡ እኔ፡ እግዜር፡ ይመስገን፡ በጎ፡ ነኝ። ተመላልሶ፡ ሲነገር፡ እንዴት፡ እንዴት፡ ይላል ።
እንዴት እንደ፡ ምን፡ እንደ ።
እንዴት፡ ዋልኸ፡ (እፎ፡ ወዐልከ)፡ ኣንተ፡ እንዴት፡ ነኸ፡ እንዴት፡ ዋልኸ።
እንዴትናቸው፡ (እፎ፡ እሙንቱ)፡ እነሱ፡ እንዴት፡ ናቸው፡ እንዴት፡ አሉ።
እንድ፡ (እንዲ)፡ ለሩቅ፡ ሴትና፡ ለቅርቦች፡ ኹሉ፡ እኔ፡ ለሚልና፡ እኛ፡ ለሚሉም፡ የዘንድ፡ አንቀጽ፡ መነሻ ።እንድታውቅ፡ አንተ፡ እሷ)፡ እንድታውቂ፡ እንዳውቅ፡ እንድታውቁ፡ እንድናውቅ ።እኔ፡ በሚለው፡ በዐ፡ ምክንያት፡ ድ፡ ራብዕ፡ መኾኑን፡ አስተውል ።
እንድ፡ የታነደ፡ አንድ፡ የኾነ።
እንድሊዝ፡ የሚያስፈራ፡ ደሴት።
እንድሪስ፡ በመደገስካር፡ ደን፡ የሚገኝ፡ አውሬ፡ ገጸ፡ ከልብ፡ ቁመናው፡ የሰው፡ ፊቱ፡ የውሻ። ሠኔ፡ 7፡ ቀን፡ 1953፡ ዓ፡ ም፡ በወጣው፡ ዐዲስ፡ ዘመን፡ ጋዜጣ፡ ቍጥር፡ 141 ገጽ፡ 563፡ እይ።
እንድሬ፡ ክታቤ፡ የሰው፡ ስም፡ ቀድሞ፡ የንጉሥ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ ኋላም፡ ያጤ፡ ምኒልክ፡ አጫዋች፡ የነበረ፡ ሰው፡ አሥቂኝ፡ ባነጋገሩ፡ ስሙ፡ የተጠራ።
እንድር፡ ዛጕፍ፡ ዋሽንት፡ የዘፈን፡ መሣሪያ፡ እየዘለሉ፡ የሚነፋ፡ እንቢልታ፡(ናብሊስ)። እንድር፡ ትግሪኛ፡ ነው፡ ጕራጌም፡ ዋሽንትን፡ አንድር፡ ይለዋል። ነደረን፡ እይ።
እንድርማሚት፡ (ቶች)፡ ቍንጪም፡ ወፍ፡ ዝንጕርጕር፡ አፈ፡ ረዥም፡ ጃንጁላቴ፡ (ዘሌ፲፩፡ ፲፱)።
እንድርስ፡ የተንደረሰሰ/የሚንደረሰስ ("ኣዝጋሚ") ።
እንድርብ/ደርባባ፡ የተንደረበበ ።
እንድርክ፡ የበሰለ/ዐጪር ።
እንድርያስ፡ የሰው፡ ስም፡ ካ፲፪ቱ፡ ሐዋርያት፡ አንዱ።
እንድኪ፡ የግምጃ፡ ስም፡ ቀይ፡ ግምጃ " ህንዳዊ፡ ማለት፡ ይመስላል።
እንዶዴ፡ ያገር፡ ስም፡ እንዶዳም፡ የኔ፡ እንዶድ፡ ማለት፡ ነው።
እንዶድ (ነደደ)፡ ያረግ፡ ስም፡ ፍሬው፡ ልብስን፡ የሚያነጣና፡ የሚያጠራ፡ ነድ፡ የሚያስመስል፡ እድፍን፡ የሚከላ፡ ነጭና፡ ቀይ፡ ነጩ፡ እህዮ፡ ቀዩ፡ ዐረቢ፡ ይባላል ።(ተረት)፡ እንዶድን፡ በገርነቷ፡ ውሃ፡ ወሰዳት። (መካን፡ እንዶድ)፡ ፍሬ፡ አልባ።
እንዶዶች፡ የንዶድ፡ ዐረጎች።
እንጀ(ጄ)ራ፡ (ትግ፡ ሐባ፡ እንጌራ)፡ በቁሙ፡ ሴቶች፡ በምጣድ፡ ላይ፡ አስፍተው፡ የሚጋግሩት፡ የሰው፡ ኹሉ፡ መኖ፡ ባለብዙ፡ ዐይን። እንጀራ፡ አገኘ ።እንጀራ፡ በወጥ፡ በላኹ ።ለወጡ፡ ዕዘኑለት፡ ከንጀራውም፡ ጕረሡለት ።ጋገረንና፡ ነገረን፡ ተመልከት ። (ተረት)፡ እንጀራን፡ ከባዕድ፡ መከራን፡ ከዘመድ። (የንብ፡ እንጀራ)፡ ማር፡ ዐይነ፡ ብዙ፡ (የተርብ፡ እንጀራ)፡ አንዳች፡ አልባ ።
እንጀራ፡ በግእዝ፡ ኅብስት፡ ይባላል፡ ባልን፡ ተመልከት።
እንጀራ፡ ቤት፡ ዐበዛ፡ እንጀራ፡ ጋጋሪ፡
እንጀራ፡ ቤት፡ የንጀራ፡ ቤት፡ እንጀራ፡ የሚጋገርበት፡ ማድ፡ ቤት ።
እንጀራ፡ ወጣለት፡ ሀብት፡ አገኘ፡ ተሰጠው ።
እንጀሮች፡ ኹለትና፡ ከኹለት፡ በላይ፡ ያሉ፡ ብዙዎች፡ (ዘሌ፯፡ ፲፫። ዮሐ፮፡ ፲፩)።
እንጂ፡ (ባሕቱ)፡ ዐቢይ፡ አገባብ። አብ፡ ወልድን፡ ይወልደዋል፡ እንጂ፡ አይቀድመውም።(ግጥም)፡ ዐራዳ፡ ደግ፡ ነው፡ ሥጋ፡ በልቶ፡ ጠጅ፡ ጥቂት፡ የሚያስፈራው፡ ዘብጥያው፡ ነው፡ እንጅ(ጂ) ።
እንጂ ዐማርኛ አይዶለም ። "ጣፈን ከለለ" ብለኸ "ተክሊልን" እይ ።
እንጃ፡ (እንጋ፡ እንዳዒ)፡ አሉታ። አላውቅም፡ አላየኹም፡ ኣልሰማኹም ።የጥርጥር፡ ቃል፡ ሲኾን፡ (ግጥም)፡ ያራዳ፡ ሸርሙጣ፡ መጋረጃሽ፡ ግምጃ፡ በምድርስ፡ ደልቶሻል፡ የሰማዩን፡ እንጃ። (ተረት)፡ የእኸል፡ ክፉ፡ ዐጃ፡ የሣር፡ ክፉ፡ ሙጃ፡ የነገር፡ ክፉ፡ እንጃ። በ፰፡ መደብ፡ ሲነገር፡
እንጃ፡ ባፍኸ ሙሉ ዥብ ይንጃጃ ("እ እንዲል እረኛ (ጃጃ)ና ጋጋ አንድ ናቸው") ።
እንጃለት/እንዳዒ ሎቱ፡ ለርሱ እንጃለት፡ እንጃለት ለርሱ።
እንጃላት/እንዳዒ ላቲ፡ ለርሷ እንጃላት፡ እንጃላት ለርሷ።
እንጃላቸው/እንዳዒ ሎሙ ን፡ ለነሱ እንጃላቸው፡ እንጃላቸው ለነሱ።
እንጃላችኹ/እንዳዒ ለክሙ ን፡ ለናንት እንጃላችኹ፡ እንጃላችኹ ለናንት።
እንጃልሽ/እንዳዒ ለኪ፡ ላንቺ እንጃልሽ፡ እንጃልሽ ላንቺ።
እንጃልን፤(እንዳዒ፡ ለነ)፡ ለኛ፡ እንጃልን፡ እንጃልን፡ ለኛ ።
እንጃልኝ፡ (እንዳዒ፡ ሊተ)፡ ለኔ፡ እንጃልኝ፡ እንጃልኝ፡ ለኔ፡
እንጃልኸ፡ (እንዳዒ፡ ለከ)፡ ላንተ ' እንጃልኸ፡ እንጃልኸ፡ ላንተ። እንጃልኸ፡ ኣላውቅልኸም።
እንጅላት፡ ሰባተኛ አያት።
እንጅልሽ፡ ምን ዐውቅልሽ።
እንጅልሽ፡ ዝኒ ከማሁ። መጨረሻ ቍጥር ከዝም የሚቀድም።
እንጅልኝ፡ ዝኒ፡ ከማሁ። (ግጥም)፡ እንጅልኝ ወዲያልኝ ሰው መኾን ሰለቸኝ! በላይ ቤት አልሠራኹ በምድር አልተመቸኝ።
እንጅሞ፡ እንዥቦ።
እንጅቦ፡ የቅጠል፡ ስም፡ እንጅቦ ።
እንጅዋ፡ እንጅሞ።
እንጆሪ (እንጌራዊ)፡ ፍሬው፡ የሚበላ፡ እሾኻም፡ ዐረግ። ይህ፡ በሽተኛ፡ ፊቱ፡ እንጆሪ፡ ይመስላል። በምግብነቱ፡ እንጆሪ፡ እዦር፡ አጠገብ፡ በመብቀሉ፡ እንዦሪ፡ ተብሎ፡ ሊጣፍ፡ ይቻላል ።
እንገር፡ መዠመሪያ ወተት ወፍራም ዝልግልግ ("እንጌራን" እይ) ።
እንገር፡ ያልበሰለ ወተት፡ ነገረ።
እንገፍ እንገፍ አለ፡ ዘክ ዘክ አለ/ገፍ ገፍ አለ (ዝኒ ከማሁ) ።
እንጕልቻ፡ የቅምጥ እንቅልፍ (ምሳ. ፮፡ ፬) ።
እንጕርጕሮ ዘፈን፡ ጐረጐረ ።
እንጕርጕሮ/ሽ፡ የደስታና የሐዘን ዘፈን ቍዘማ ።
እንጕይ፡ (ጐያዪ)፡ የሸሸ፡ የራቀ ።
እንጕይ፡ አለ፡ ፈጽሞ፡ ጠላ፡ ሸሸ፡ ዐይኑን፡ አያሳየኝ፡ አለ፡ ጕይን፡ እይ።
እንጕዳይ (ዮች)፡ አሳክክ/እንቶ ደም አስተፊ ቍቻ (የሚበላና የማይበላ መጥፎና ደኅና በበጋ ደርቆ ኵምሽሽ ብሎ የሚጠፋ ካለበት ስፍራ የሚጐድል የሚታጣ በክረምት ግን የሚበቅል የምድር ድባብ ወይም የረኛ ጋሻ) ።
እንጕዳይ፡ በቁሙ፡ ጐደለ ።
እንጋበዝ፡ ከገበታ እንነሣ፡ ላልበላ ስፍራ እንልቀቅ።
እንጌራ፡ (ትግ፡ ሐባ)፡ በቁሙ፡ እንጀራ ።
እንግሊላ፡ የዠርባ መኝታ (የምንዝር ሥራ ምንዝር) ።
እንግሊዙ፡ ያ፡ እንግሊዝ።
እንግሊዝ፡ (ዞች)፡ የንግሊዝ፡ ተወላጅ፡ አንድ፡ ሰው።
እንግሊዝ፡ የነገድ፡ ስም፡ ባውሮጳ፡ ከሠለጠኑት፡ መንግሥታት፡ አንደኛው፡ ቅዱሳት፡ መጻሕፍትን፡ ባ፲፩፻፡ ቋንቋ፡ ያስተረጐመ፡ (ማቴ፳፬፡ ፲፬)
እንግሊዝኛ፡ የንግሊዝ፡ ቋንቋ።
እንግሊዞች፡ እነዚያ፡ አንግሊዞች።
እንግሊዟ፡ ያች፡ እንግሊዝ።
እንግልጣር፡ (አንግሌቴር)፡ የንግሊዝ፡ አገር፡ አድማሳዊ፡ ማእዘንማ፡ ምድር፡ ማለት፡ ነው፡ እንግልጣር፡ ግእዝኛ፡ መኾኑን፡ ዕወቅ።
እንግልጥ፡ የተንገለጠጠ (አንቅልጥ) ።
እንግርግሮሽ፡ ፍግምግምታ/ትግል/ትንንቅ ። "በግእዝ ነገርጋር ይባላል።"
እንግርግብ (ቦች)፡ የተንገረገበ እኽል (በጥርስ የማይጠረጠር) ። (ተመልከት፡ ሾቀ አሾቀ ብለኸ አሹቅን ተመልከት) ።
እንግርግፎ፡ የምድር ፍሬ ።
እንግርግፎ፡ የምድር፡ ፍሬ ́፡ (ገረገፈ) ።
እንግብ (ነገበ)፡ የተነገበ/የተያዘ (ጋሻ/ሸክም - "እንዥቦን" እይ የዚህ ዘር ነው - "እንግብ አደረገ"፡ አነገበ) ።
እንግብግብ (ቦች)፡ የተንገበገበ፡ የተቃጠለ፡ ልብልብ፡ ስግብግብ፡ ተቀብታም።
እንግብግቦት፡ ሕፃን ተቀጥቶ ካለቀሰ በኋላ የሚተነፍሰው ትንፋሽ።
እንግውላይ፡ ገለባ/ጕድፍ ሰበር።
እንግዲያ፡ እንኪያ።
እንግዲያው፡ እንግዲያውስ፡ እንግዲያስ፡ ማለቱን፡ ያሳያል ።ደቂቅ፡ አገባቦች ' ከ፡ ለ፡ በመነሻ፡ ወደ፡ በመድረሻ፡ ሲሰማሙት፡ ከንግዴህ፡ ለንግዴሁ፡ እንግዴህ፡ ወዴህ፡ አይለምደኝም፡ ይላል ።ሲናበብ፡ ጫፉ፡ ኃምስና፡ ሣልስ፡ መኾኑን፡ አስተውል ።
እንግዳ (ዶች/ነግድ)፡ ባዕድ/ባይተዋር (የሌላ አገር ሰው አገሩ ሩቅ ጭብጦው ደረቅ - ተረት፡ "ላገሩ ባዳ ለሰዉ እንግዳ" - "እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሃ ፈሳሽ" - "ጠቈረ" ብለኸ "ጥቍርን" እይ) ።
እንግዳ መቀበያ፡ እንግዳ የሚያርፍበት/የሚያድርበት ቤት።
እንግዳ ሰው፡ በቁሙ የሰው ስም።
እንግዳ፡ ባዕድ፡ ሰው ́፡ ነገደ።
እንግዳ ቤት (የንግዳ ቤት)
እንግዳ ተቀበለ)፡ በቤቱ አሳደረ አስተናገደ ("(ማቴ. ፲፥ ፵)") ።
እንግዳ ነገር፡ ታይቶ ተሰምቶ የማያውቅ።
እንግዳ አምላክ፡ ጣዖት (ኤር. ፯፥፮) ።
እንግዳ ወርቅ፡ የሰው ስም።
እንግዳ፡ የሰው ስም ("ዋልድቤ እንግዳ ዙራምቤ እንግዳ" እንዲሉ) ።
እንግዳ ጐርብጥ፡ ያልተለፋ ቈዳ (እንግዳን የሚጐረብጥ እንቅልፍ የሚነሣ) ።
እንግዳዋ፡ ያች እንግዳ (የርሷ እንግዳ) ።
እንግዳዪቱ፡ ዝኒ ከማሁ (ሌላዪቱ - ዕብ. ፲፫፥፪) ።
እንግዴ፡ ልጅ፡ እንግዳ፡ ልጅ፡ የንግዴህ፡ ልጅ ።ልጅ፡ ከተወለደ፡ በኋላ፡ እንደ፡ ልጅ፡ ከወላድ፡ ማሕፀን፡ የሚመጣ፡ የሚወለድ፡ ስለ፡ ኾነ፡ የልጅ፡ እንግዳ፡ እንደ፡ ማለት፡ እንግዴ፡ ልጅ፡ ተባለ። ነገደን፡ እይ፡ ሥሩ፡ ርሱ፡ ነው።
እንግዴ፡ ሥጋ፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ እንግዳ፡ ሥጋ፡ አሰጅ።
እንግዴህስ፡ (፩ቆሮ፡ ፲፬፡ ፲፭)።
እንግድ፡ (እንከ)፡ ንኡስ፡ አገባብ። በኀላፊና፡ በመጪ፡ ጊዜ፡ መካከል፡ ያለ፡ ሰዓት፡ አኹን። ህ፡ ያ፡ ው፡ ትራስ፡ ማ፡ አጐላማሽ፡ ም፡ ዋዌ፡ ስ፡ ትች፡ አፍራሽ፡ እየኾኑላት፡ ሲነገር፡ እንግዴህ፡ ዳግመኛ፡ ኸለተኛ፡ ሌላ፡ ጊዜ ።እንግዴህ፡ ለጋን፡ ውሃ፡ አለች፡ ዐይጥ ።እንግዴህማ፡ እንግዴህም፡ (፩ቆሮ፡ ፲፮፡ ፲፰) ።
እንግድነት፡ እንግዳ መኾን (ግብ. ሐዋ. ፲፥፯, ፲፰, ፳፫, ፴፪ - እንግዳን ተመልከት የነገደ ዘር ነው) ።
እንግድግድ፡ የተንገደገደ (ግትርትር/ፍግምግም/ርግድግድ)።
እንግጫ ሣር፡ ጋጠ።
እንግፍጥ፡ ሆዱ የሰፋ/የከበደ (እርጉዝ መሳይ እንጥርዝ እንዝርጥ እንቅብድ ቅርጫት ሆድ) ።
እንጐቺት፡ ያረግ፡ ስም፡ ዕንጐቺት።
እንጐቻ ታናሽ፡ እንጀራ፡ ዕንጐቻ ።
እንጣጢት፡ ተልባ በተቈላ ጊዜ የሚ ዘል የሚንጣጣ ።
እንጣጢት፡ ተልባ፡ ጣጣ ።
እንጣጥ፡ መናር/መዝለል ።
እንጣጥ፡ መዝለል፡ ጣጣ።
እንጣጥ አለ፡ መር አለ ("ዘለለ ወደ ላይ ተወረወረ") ።
እንጥል (ሎች)፡ አንቃር ("በጕረ ጫፍ ከወደ ላይ ተንጠልጥሎ የሚታይ ሥጋ የመዋጥና የድምፅ ሚዛን") ።
እንጥል፡ (ነቀረ)።
እንጥል በቁሙ፡ (ጠለጠለ)
እንጥልጣይ፡ የእንጥልጥል ዐይነት ።
እንጥልጥል (ሎች)፡ ዐሸን/ክታብ/ያፍንጫ ቀለበት ("ያንገት የዦሮ ጌጥ የተንጠለጠለ") (ዘፍ. ፳፬፡ ፵፯፡ ኢሳ. ፫፡ ፲፱) ።
እንጥልጥል፡ በፍየል ማንቍርት ያለ ጥንድ መንታ ነገር ።
እንጥልጥል፡ የተንጠለጠለ፡ (ጠለጠለ) ።
እንጥር፡ መናር።
እንጥር እንጥር አለ፡ ናር ናር ገንታ ጎንታ አለ።
እንጥርጣሪ፡ እንቅጥቃጭ ("የተልባ ፍሬ ስብርባሪ ብጣሪ") ።
እንጥብጣቢ፡ የተንጠባጠበ (ዐልፎ ዐልፎ የወደቀ የቀረ ሰው ወይም ሌላ ነገር) ።
እንጥፍጣፊ፡ የተንጠፈጠፈ/የሚንጠፈጠፍ ("እንጥብጣቢ") ።
እንጦ፡ ቀሠብ፡ ዕንጦ ።
እንጦጦ፡ በአዲስ፡ አበባ፡ ከተማ፡ ሰሜን፡ ያለ፡ የትልቅ፡ ተራራ፡ ስም፡ ጋሎች፡ ዲልዲላ፡ ይሉታል። የንጦጦ፡ መምር፡ ቢናገር፡ ባመት፡ ያውም፡ ሬት። (በልቼ፡ ልቍረብ፡ አለ፡ ይላሉ)።
እንጧ፡ የሕፃናት፡ ቋንቋ እንጀራ፡ ማለት፡ ነው ።
እንጭላ (ሎች)፡ እንቃቅላ/ዐራስ ልጅ ("ርጥብ ለጋ ቡችላ ውጭ ውሪ ሙሊ የሰው የዝንጀሮ ልጅ") ።
እንጭላ፡ ዐራስ፡ ልጅ፡ ጪ ።
እንጭራር (ሮች)፡ ማታ ማታ የሚጮኸ ድምጠ ብዙ ጥቊር ተንቀሳቃሽ በክንፍ በራሪ ("እግሮቹ ፮ ሲኾኑ በራሱ ላይ ጭራ የሚመስል ፪ ቀንድ አለው ፪ኛ ስሙ ቢያርዱ አይሞት ነው ጭራ") ።
እንጭራርተ ንቀሳቃሽ፡ ወረረ።
እንጭርግ፡ ያንጨረገገ/የተንጨረገገ ("እንዥርግ እንጥልጥል") ።
እንጭርጭር፡ የተንጨረጨረ ("የጥሬ ባቄላ ቈሎ፪ ጥብስ ሥጋ ") ።
እንጭርፍ፡ የተንጨረፈፈ ያደገየረዘመ ("የሽፍታ የናዝራዊ ጐፈሬ ረቅ") ።
እንጭቅ አደረገ፡ ዝኒ ከማሁ ለአ ነቀ።
እንጭብሌ፡ ዘንጋዳ፡ ጨበረረ።
እንጭብሬ (ሌ)፡ ራሰ ብትን/ዘንጋዳ ደረቅ መሳይ ("አንጭፍሬ") ።
እንጭብር፡ የቅጠል፡ ስም፡ ጪበረረ።
እንጭብር/ጭብር፡ የታናሽ ቅጠል ስም ("ደሙ ቀይ ጨበሬ የሚመስል ሐረግ ቅጠለ ሻካራ ሥሩ ከቅቤ ጋራ ለሳል መድ ኀኒት ይኾናል እንጭብርና ምንጭርር አንድ ስም ነው") ።
እንጭጭ (ጮች)፡ ጥቃቅን ፍሬ ("ጨርቋ ማንኛውም ያልበሰለ እሸት") ።
እንጭጭ ያልጠና፣ ፍሬ ጫጪ።
እንጭፍሬ፡ የእንጭፍር ዐይነት ("እንጭ ብሌ") ።
እንጭፍር/እንጭርፍ፡ ጠጕር እንጭ ብሌ ።
እንጭፍጫፊ፡ ዕጣቢ እድፍ ።
እንጮቴ፡ ፍሬው፡ የሚዘራ፡ ሥሩ፡ የሚበላ፡ ዐረግ። እሱም፡ በወለጋ፡ ይገኛል፡ ሥሩም፡ ግርሽጥ፡ ይመስላል።
እንጮጭ፡ መራራ፡ ጯጯ።
እንጮጭ፡ ዝኒ ከማሁ ("መራራ የማይጣፍጥ እንጕይ እንጮጭ የቀጨሞ ፍሬ እንዲሉ") ።
እንጯ፡ እንጯ፡ አለ፡ ለፍጫቃ፡ ኾነ፡ ያስተኛኘክ ።
እንፉቅቅ፡ የቂጥ የቅምጥ መንገድ ። "ሽባ በንፉቅቁ ይኼዳል" ።
እንፉጭ፡ መናኛ ግርድ —ዕንፉጭ።
እንፉጭ ቀላል፡ ፍሬ፡ ዕንፉጭ ።
እንፋሎት፡ ላበት፤ፈላ ።
እንፋሎት፡ የውሃ ጪስ ላበት ።
እንፍ፡ (አነፈ)፡ መናፈጥ፡ ማውጣት፡ መክላት ።
እንፍ፡ አለ፡ ተናፈጠ፡ አወጣ፡ ከላ፡ ንፍጥን ።
እንፍሌ ሥጋ ፈላ። በወጥ፡ የተነከረ፡
እንፍሌ፡ በፈላ ወጥ ውስጥ የተነከረ ዝልዝል ሥጋ ።
እንፍርዛዥ፡ ዝኒ ከማሁ (የተቀበነነ ") ።
እንፍርዝ፡ ሆዱ የጠገበ (ጥጉብ ") ።
እንፍርፍር ሽሮ፡ "ፍርፍር" የሚል የ ሽሮ ወጥ ።
እንፍርፍር፡ የንጀራ ወጥ ግፍልፍል ።
እንፍርፍር፡ የንጀራ፡ ወጥ፡ ፈረፈረ ።
እንፍርፍሮሽ፡ ዝኒ ከማሁ ።
እኛ፡ (ንሕነ)፡ የነባብያንና፡ የነባብያት፡ በቂና፡ ቅጽል ።ራሳችን፡ ቅላችን፡ ባለቤታችን፡ ማለት፡ ነው። ደቂቅ፡ አገባብ፡ ሲቀድመው፡ በኛ፡ የኛ፡ ከኛ፡ ለኛ፡ እያለ፡ እን፡ ይጐርዳል። እነኛን፡ እይ።
እኛ፡ (እኒያ)፡ እሳቸው። እኛስ፡ መስጠታቸው፡ እሱስ፡ መቀበሉ፡ ከነልቡ፡ ነወይ፡ ከናደፋፈሩ። (አልቃሽ)፡ ስላቶ፡ በዛብኸ፡ ፈረሶች። ፈካሪም፡ እነኛ፡ በማለት፡ ፈንታ፡ እኛ፡ ይላል። ላጠ፡ ብለኸ፡ ተላጠን፡ እይ።
እኛ ለሚሉ የአንቀጽ ዝርዝር ("አንተ እኛን አመንኸን ወደድኸን ! ሰጠኸን ነሣኸን ኾራ ") ("ኩሬ") ።
እኛን፡ ምሰል፡ በምግብ፡ ጊዜ፡ ለመጣ፡ ሰው፡ የሚነገር፡ ቃል። ከኛ፡ ጋራ፡ መብል፡ ብላ፡ ተጋበዝ፡ ማለት፡ ነው፡ በትግሪኛ፡ ተቀደም፡ ይባላል።
እኛው፡ በኛ፡ ርስ፡ በርሳችን።
እእ፡ ያፈ ድዳ ድምፅ ወይም ፈሊጥ ።
እከሊት፡ (እገሊት)፡ ያች ሴት፡ አንቺ ።
እከላ፡ ጭመራ ።
እከሌ፡ (ገልይ፡ ገለየ፡ እገሌ)፡ የስም ለውጥና ምትክ፡ በስም ፈንታ የሚነገር ቃል ። እንተኔ ፥ እንተን፡ ያ ፥ ርሱ፡ አንድ ሰው፡ አንተ ሰውዬ ፥ ሰዌ ። አካሉ ታውቆ ስሙ ላልታወቀ ለሩቅም ለቅርብም ዐጸፋ እየኾነ ይነገራል። እከሌ ማለት አካላዊ ስም ስለ ኾነ ከአከለም ጋራ ይሰማማል ። ሲበዛ እነከሌ፡ ሲጫፈር እከሌና እከሌ ይላል ።
እከባ፡ ስብሰባ ፥ ክምቸታ ።
እከከሽ፡ ከብስጭት የተነሣ የሚነገር ዘዬ ።
እከከከ፡ (ቆቀወ)፡ የቆቅ ጩኸት ። ያማርኛ ገበታዋሪያ ገጽ ፶፮ እይ ።
እከየኛ (ኞች)፡ ክፋተኛ ፥ ጥፋተኛ ፥ ልግመኛ ፥ ተንኰለኛ ።
እከየኛነት፡ ልግመኛነት ።
እከይ፡ ክፋት ፥ ጥፋት ፥ ልግም ፥ ተንኰል፡ የተንኰል ሥራ ።
እከደከ (እክሕደከ)፡ እክድኻለኹ ("እከደከ ሰይጣን እንዲሉ") ።
እከደከድ፡ ዝኒ ከማሁ ።
እከደከድዬ፡ ንኡስ አገባብ ("የቃል ጭማሪ (ግጥም) እከደከድዬ ነገር ተበላሸ እሥጋ ገበያ ስልከሰከስ መሸ ዬ ' ሐዘንን ጸጸትን ያሳያል ፬ኛውን ዬ ተመልከት ") ።
እከድዬ፡ ንኡስአገባብ፡ ካደ።
እከድዬ፡ ዝኒ ከማሁ ("የአከደከድዬ ከፊል") ።
እኩለ ሌሊት፡ መንፈቀ ሌሊት፡ የሰዓተ ሌሊት ግማሽ ።
እኩለ ቀን፡ ቀትር፡ ስድስት ሰዓት፡ የሰዓተ መዓልት ገሚስ ።
እኩለ ጦም፡ ደብረ ዘይት ።
እኩሌታ፡ ክፍል ፥ ግማሽ ፥ መንፈቅ ፥ ኑስ ፥ አላድ፡ (ዘፀ ፳፬፡ ፮ ። ዘዳ ፳፱፡ ፬) ።
እኩሌታ/ኑስ/ጐደሎ/ሕጹጽ ። "የሰው ገሚስ ግማሽ እንጀራ ግማሽ አሞሌ እንዲሉ።" (ተመልከት፡ ዐረገ ብለኸ ማረግን እይ) ።
እኩሌቶቹ፡ ግማሾቹ ።
እኩሌቶች፡ ግማሾች ፪ ካ፲ ፭ቶች እንደ ማለት ነው፡ (ኤፌ ፬፡ ፲፩) ።
እኩል ለነፍስ፡ እኩል ለሥጋ፡ መፍቅደ ነፍስ፡ መፍቅደ ሥጋ ።
እኩል በኩል፡ ግማሽ በግማሽ ፥ ኑስ በኑስ ።
እኩል፡ ትክክል ። እከሌና እከሌ አይበላለጡም፡ እኩል ናቸው ። (ተረት)፡ እናቱ ውሃ የኼደችበትና የሞተችበት እኩል ያለ ቅሳሉ።
እኩል፡ የተከፈለ ፥ የተገመሰ፡ ግማሽ ፥ አጋማሽ፡ (ማር ፮፡ ፳፫) ። ሙሉና እኩል፡ አንድ ተኩል እንዲሉ። ሠነጠቀ ብለኸ ሥንጥቅን እይ ።
እኩሎች፡ ትክክሎች ።
እኩያ፡ ባልንጀራ ፥ ጓደኛ ፥ አምሳያ ፥ ቢጤ ፥ ዐብሮ አደግ፡ በድሜ ፥ በቁመት ፥ በኀይል ፥ በጕልበት ፥ በገንዘብ ፥ በሥራ ፥ በያ በማንኛውም ነገር የተካከለ የተማዘነ፡ የፈረስ ዦሮ አቻ ፥ ግጥሚያ ።
እኩይ፡ የከፋ ፥ ክፉ፡ መጥፎ ፥ ጥፉ ። ከየን እይ ።
እኩዮች፡ ትክክሎች ፥ መንቶች፡ (ዳን ፩፡ ፲) ። በእኩዮች ፈንታ እኩያቶች ይላል፡ ስሕተት ነው፡ (፪ዜና ፲፡ ፲) ።
እካሎ፡ የጭራሮ ስብርባሪ ፥ እሳት ማንደጃ ።
እክል፡ ዐዘን፡ ዐከለ ።
እክል፡ የታከለ ፥ የተጨመረ፡ ጭምር ።
እክር፡ (ሮች)፡ የታከረ፡ ልውጥ፡ ባቄላ፡ የተሰበረበት፡ ዐተር፡ ሽንብራ፡ ጓያ፡ ምስር፡ የተነቀለበት፡ መሬት ።የእክር፡ መደበኛው፡ ባቄላ፡ ነው ።የባቄላ፡ ማሳ፡ የገደለ፡ አይነሣ፡ እንዲሉ ።መለወጥ፡ የባቄላ፡ ማዘግየት፡ የሽንብራ፡ ነው፡ ሽንብራ፡ ከእኸል፡ ኹሉ፡ በኋላ፡ በመስከረም፡ ይዘራልና ።
እክብ፡ የታከበ ፥ የተሰበሰበ ፥ የተከማቸ፡ ስብስብ ፥ ክምቹ ።
እክታም፡ ዝባዝንኪያም፡ ዝግንትላም፡ እርታም።
እክት፡ (ቶች)፡ የታከተ፡ ጥርቅም፡ እርት፡ ቅራቅንቦ፡ ዕቃ፡ ግሴት። አለዳኛ፡ ሙግት፡ አለገመድ፡ እክት፡ እንዲሉ ።ሚጣቅ፡ እሾላው፡ ሥር፡ ዐማኔል፡ ቢያገሣ፡ በሽታዬ፡ ኹሉ፡ እክቱን፡ አነሣ፡ (ታቦት፡ ዘፋኝ) ።
እክክ፡ (አሀህ)፡ ስልቸታ ። እክክ አለኝ፡ ሰለቸኝ ንፍሮው ።
እኮ፡ (እስመ አኮ ጓ)፡ ንኡስ አገባብ ። ከአንቀጽ አስቀድሞ እየገባ የስም አጐላማሽ ሲኾን፡ ኤልያስ እኮ ወደ ሰማይ ዐረገ ይላል ። ዐቢይ አገባብ ሲኾን፡ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ዐረገ እኮ ማለቱን ያሳያል ።
እኮን፡ (አኮኑ)፡ ዝኒ ከማሁ ። የተጠሩት ብዙ ናቸው፡ የተመረጡት ጥቂቶች ናቸው እኮን ።
እኮን፡ ዐቢይ አገባብ፡ እኮ ።
እኸሉን ቀጭ መታው)፡ አለፍሬ አስቀረው ።
እኸል፡ (እክል)፡ የሚበላ ምግብ ፥ መኖ ፥ ቀለብ የሚኾን ያልበሰለ፡ ስንዴ ፥ ዐጃ ፥ ገብስ ፥ ባቄላ ፥ ዐተር ፥ ሽንብራ ፥ አደንጓሬ ፥ ጓያ ፥ ምስር ፥ ማሽላ ፥ ዘንጋዳ ፥ በቈሎ ፥ ደንጐሎ ፥ ዳጒሳ ፥ ጤፍ ፥ ሩዝ ፥ ድኋን ። ጥሬ እኸል፡ ያበባ ያገዳ ፥ የብር እኸል እንዲሉ። (ተረት)፡ እኸልን በጥቅምት፡ ልጅን በጡት ። ሲበዛ እኸሎች ይላል ። (የወፍጮ እኸል)፡ ሊፈጭ የተዘጋጀ ። (የልመና እኸል)፡ ውጥንቅጥ ።
እኸል፡ እንጀራ ። እኸል ውሃ እንዲሉ። እኸል በኸል፡ ሥጋና ቅቤ የሌለበት የጦም ምግብ እኸል በኸል ይባላል ።
እኹል ገብ፡ -የቅጠል ስም ኹል።
እወከተኛ (ሁከታዊ)፡ ሽብረኛ አስጨናቂ አተራማሽ ። መምህራን ግን ሁከተኛ ይላሉ ። ሁከትን እይ ።
እወካ፡ የማወክ ግብር፡ ብጥበጣ ንቅነቃ ።
እወደድ ባይ፡ ከንቱ ውዳሴ ሰጪ ("ኣከንፋሽ ኰፋሽ") ።
እው፡ የናዳ ድምፅ ። (ናዳው እው አለ)፡ አስተጋባ ።
እው፡ የናዳ ድምፅ ፥ —አወወ ።
እውነተኛ (ኞች) (አማናዊ ጻድቅ)፡ ቅን መልካም ደግ በጎ ንጹሕ ጥሩ ።
እውነተኛነት (ከዊነ ጻድቅ)፡ ቅንነት ደግነት ገርነት፡ አውነተኛ መኾን ።
እውነት (አማን ጽድቅ)፡ ርግጥ፡ ሐሰት የሌለበት፡ የግዜር ሥራና ነገር ።
እውነት አወጣ፡ ርግጡን ተናገረ ።
እውነቶች፡ ከውሸት የራቁ ነገሮች ።
እውን (አማንኑ)፡ ጥያቄ ። እውን እንዲህ ኾነ ።
እውን፡ እውነት ንቃት ። በሕልም ነውን፡ ወይም በውን ።
እውከት (ሁከት)፡ መታወክ መታመስ መተራመስ፡ ሽብር ።
እውከት፡ ምላሽ ትፋት ቅርሻት ። ዳግመኛም ባላገር ትውከት ይላል ።
እውኪያ (ሀውክ)፡ ንውጽውጽታ መከራ ጭንቅ ሽብር ድብልቅልቅ ።
እውክ (ህዉክ)፡ የታወከ ድንጉጥ ።
እውክታ፡ ዝኒ ከማሁ ለእውከት ።
እውዋ፡ እው እው የምትል ታናሽ ጠፍጣፋ ዕንጨት፡ ልጆች ባንድ ወገን ባለው ቀዳዳዋ የክር ገመድ አግብተው (አስረው) ሲያወላውሏት (ሲያወዛውዟት) በነፋስ ኀይል ወፍራም የነብርና የዥብ ድምፅ ታሰማለች ። ፉርቴን እይ ።
እውጪ፡ ደግ ማለፊያ መልካም ። (ጐአውጭኝ ንደር) ።
እዚህ፡ በቁሙ፡ ፡ ዚህ ።
እዚኻች፡ ላይን የራቀ ስፍራ ።
እዚያ (ህየ)፡ የቦታና የአካል በቂ ።
እዚያ፡ (ህየ)፡ የቦታና፡ የአካል፡ በቂ ። እዚያው፡ ው፡ ስፍራንና፡ ዕቃን፡ ያሳያል ።
እዚያ፡ ላይ፡ እዚያ፡ ማዶ ፣ እዚያ፡ ታች፡ ቅጽል ።
እዚያ፣፡በቁሙዚያ ።
እዚያች፡ የሴት የእንስት በቂ ።
እዚያች፡ የሴት፡ የእንስት፡ በቂ ። እዚኻች፡ ላይን፡ የራቀ፡ ስፍራ ። እስከዚያ እስከዚያው፡ የቦታና፡ የጊዜ፡
እዚያው፡ በዚያው፡ ርስ፡ በርሱ፡ ክስ፡ በክሱ ። እንዲህ፡ እዚያው፡ በዚያው፡ ያቀጣቅጥ ልኝ፡ እንጂ፡ ባሪያን፡ ባሪያ፡ በጣለው፡ ጊዜ፡ ጌታው ።
እዚያው፡ ው ስፍራንና ዕቃን ያሳያል ።
እዚያው፡ ፈላ፡ እዚያው፡ ሞላ ፣ ትርፍ፡ አልባ፡ ሥራ፡ በቂ ።
እዛብ፡ ፡ ዛብ፡ ዐዘበ ።
እዛዊ ቅጽል "ባማርኛም የ ነው።"
እዝ፡ (እዙዝ)፡ የታዘዘ፡ የተገባ፡ የተሠራ፡ የተወሰነ፡ የተጻፈ፡ የተነገረ፡ ደንብ፡ መዓት ።
እዝ፡ አለጮኸ፡ ዕዝ።
እዝ፡ የታዘዘ፡ አዘዘ።
እዝል፡ የዜማ፡ ስም፡ ዐዘለ፡ ዕዝል ።
እዝጊያራ፡ (እግዚእ፡ ኀረያ)፡ የሴት፡ ስም፡ ያቡነ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ እናት፡ ትርጓ ሜው፡ ጌታ፡ መረጣት፡ ማለት፡ ነው።
እዞች፡ የታዘዙ፡ ነገሮች፡ ሰዎች።
እዡን፡ ጨረሰ፡ ቅጣቱን፡ መከራውን፡ ሥቃዩን፡ ፈጸመ።
እዣ፡ ጕራጌ፡ የጕራጊ፡ ነገድና፡ አገር፡ ከ፯ቱ፡ ወንድማማቾች፡ አንዱ፡ ምን፡ በማለት፡ ፈንታ፡ ምር፡ የሚል፡ የእዣ ¡ ትርጓሜ፡ እይ፡ ማለት፡ ነው፡ ይላሉ ።
እዥ፡ (እዝኅ)፡ የደም፡ ውሃ፡ ቅራሪ፥ ጥንፋፊ፡ እንጥፍጣፊ፡ የመግል፡ ትራፊ፡ ከተበጣ፡ ወይም፡ እሳት፡ ከፈጀው፡ ካበጠ፡ ከቈሰለ፡ ገላ፡ ከሐዲስና፡ ከሰባራ፡ ሸክላ፡ የሚፈስ፡ (ኪ፡ ወክ) ።
እየ፡ (ኀበ)፡ ደቂቅ አገባብ ። ወደ ን ። እየቤትኸ ግባ፡ እየራስኸ ተቀባ ። ደጊመ ቃል ሲኾን፡ እየለት እየለቱ፡ እየራስ እየራሱ ይላል። ይህም እየ ከማለት በየ ቢል ያምርለታል። ከ ለ መነሻ ሲኾኑት፡ ከየቤቱ ለየፊናው ይላል። ዐማን እይ ።
እየ፡ (ለለ)፡ ዐቢይ አገባብ ። ከአንቀጽ አስቀድሞ እየገባ አንቀጽ ያስቀራል። እየሰበረ ሰጠው ላሞራ ። እያንጐራጐረ ጋራውን ዞረ ።
እየ፡ (በበ)፡ ደቂቅ አገባብ ። በስም ሲገባ ማድረጊያ እየቀደመው እንጐርዶ ይነገራል። የንጉሥ የወጌ ከብት በየወገኑ ይከተት ።
እየለሌ፡ እየለየ፡ (ለሌ) ።
እየራሱ አይሠራም፡ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ መልስ፡ ክርስቶስ አንድ አካል ከኾነ እየራሱ አይሠራም፡ እየራሱም ከሠራ አንድ አካል አይኾንም ። አንድ አካል አንድ ልጅ አንድ ሠሪ ነው እንጂ ።
እየራሱ ይሠራል፡ የማኅበረ ኬልቄዶን ስሕተት፡ ቃል የቃልን ሥራ ሥጋ የሥጋን ሥራ ለየብቻው ይሠራል ማለት ።
እየቀደም)፡ እያደር ።
እየቅል እየቅሉ)፡ እየብቻ እየብቻው፡ እየራስ እየራሱ ። "ዱባና ቅል አበቃቀሉ እየቅል" ። "ቅሉ ቅልኸ እያለ ይዘረዝራል። ራሱ ራስኸ ማለት ነው" ። "ራስን" እይ ።
እየው፡ (ርአዮ)፡ አስተውለው፡ ተመልከቱው። እየው ወሮ ሲገባ እንዲሉ ሴቶች ታቦት ሲነግሥ።
እዩ፡ (ርእዩ)፡ ተመልከቱ፡ አስተውሉ ።
እዪ፡ (ርእዪ)፡ ተመልከቺ፡ አስተውሊ።
እዪ እቴ፡ (ርእዪ እኅትየ)፡ የድንጋፄ ቃል ። ተመልከቺ፡ አስተውሊ።
እያደር፡ አያደረ እየሰነበተ እየቈየ ("ያቶ እከሌ በሽታ እያደር ይብሳል ") ።
እዬዬ፡ ዝኒ ከማሁ ("የሐዘንና የለቅሶ ቃል። ዬ ዬዬ የግእዝ እዬዬ ያማርኛ ነው እዬዬ ቢዳላ ነው እዬዬ ብሎ ማልቀስ ባገር አማን ነው ደላ ብለኸ ተዳላን አስተውል") ።
እዬዬ፡ የለቅሶ ቃል፡ ዬዬ።
እይ፡ (ርኢ)፡ ተመልከት፡ አስተውል ።
እይታ፡ ምልከታ ፥ ትኰራ።
እዱኛ፡ የወንድና የሴት ስም ።
እዳ፡ በቁሙ ፥ —ዐደየ፡ ዕዳ ።
እድሞ (ዎች)፡ ያፈር ቤት፡ ጣራው የንጨት ክዳኑ ዐፈር መሬት ። በትግሪኛ ህድሞ ይባላል ።
እድሞ፡ የበር ጣራ ባለሣር ክዳን (ሺዋ) ። ዝንቦን ተመልከት ።
እድሞ፡ የካብ የግንብ ዐጥር ድምድ ማት፡ ባጥር በበር ላይ የተሠራ ቤት፡ የኹሉም ክዳን ዐፈር ነው ። ናስን እይ ።
እድብ፡ የታደበ የተሠራ የተደነገገ፡ ውስን ድንግግ ዕድር ።
እድያት፡ ጥለት፡ ዐደየ ።
እድጊያ፡ እድገት፡ ርዝማኔ ከፍታ ብልጫ ላቂያ ።
እድግ፡ ዝኒ ከማሁ ለአደግ፡ ያደገ ።
እድግና፡ እድግ መኾን፡ ከፍተኛነት ።
እድፈት፡ እድፍነት፡ ማደፍ ።
እድፋም (ሞች)፡ ያደፈ የረከሰ የተበከለ፡ ብክል ጨምላቃ ኵልፍልፍ ዐሣማ ልብስ ።
እድፍ፡ በቁሙ፡ ጭቅቅት ቈሻሻ ወሰክ ነውር ገመና ። (ራእ ፲፯ ፥ ፬) ። እድፍ ጕድፍ እንዲሉ ። (ለጋ እድፍ)፡ ባዲስ ልብስ ላይ ያለ ቀላል እድፍ ።
እድፍ አለ፡ አደፈ ።
እድፍነት፡ እድፍ መኾን ።
እጀ መርዝ፡ መቶ ያቈሰለው የማይሽር ።
እጀ መናኛ፡ ባለቤትነት ሳይኖረው የሰው ገንዘብ የወሰደ ሰው እጀ መናኛ ይባላል፡ እጀ መጥፎ ማለት ነው ።
እጀ ሰላላ)፡ እጁ መያዝ/መጨበጥ የማይችል ልምሾ።
እጀ ሰባራ፡ ግብዝ ሥራ የሠራ ሰው ።
እጀ ሰብ (እደ ሰብእ)፡ ክፉ ሰው በጁ ሥር ምሶ ቅጠል በጥሶ በሰው ላይ የሚያደርገው ተንኰልና ደዌ፡ ወይም ቡዳ ።
እጀ ሰፊ፡ ቸር ለጋስ ደግ ።
እጀ ሰፊ፡ እጅጌው ሰፊ የኾነ መቋረፊያ ።
እጀ ሥራ፡ የእጅ ሥራ፡ ባዘቶ ቡጭቅ ።
እጀ ርጥብ፡ እሱ የቈረጠው ተክል በቶሎ የሚለመልም፡ ቸር ገንዘብ የማያጣ ።
እጀ ብልኅ፡ ሥራ ዐዋቂ ባለያ፡ የብልኅ እጅ ተብሎም ሊተረጐም ይቻላል ።
እጀ ደረቅ፡ የቈረጠው ተክል የሚ ደርቅ ።
እጀ ጠባብ፡ እጅጌው የጠበበ የቀ ጠነ፡ የወንድና የሴት ቀሚስ ።
እጀ ጠብቅ፡ ሰው ጠላቱን እንዳይ መታ የሚጠራው ዋስ ።
እጀ ጥበብ (ጥበበ እድ)፡ የእጅ ብልኀት፡ ማንኛውም የሥራ ዘዴ ። ጽፈት ስ ፌት ሥዕል ሕንጻ ቅጥቀጣ ፈትል ሸማ ሥራ፡ የመሰለው ኹሉ ።
እጀታ፡ መያዣ መጨበጫ ። የጋሻ የጐራዴ የማጭድ የቢላዋ የጅራፍ እጀታ እንዲሉ ። ላትን እይ ።
እጀኛ፡ ሌባ፡ እጁ የማያርፍ የሰው ገንዘብ የሚሰርቅ የሚያሠርግ ።
እጀኛ ሰራቂ ("የሰውን ገንዘብ እንደ ወተት የሚያልብ የሚያነሣ የሚሰርቅ የሚወስድ እንደ እሸት የሚ ያወልብ ") ("ዮሐ. ፲፡ ፩") ።
እጁ ዐመድ ዐፋሽ ነው፡ ያበላው ያጠጣው ይከዳዋል ።
እጁ አቆመ፡ ገንዘብ መስጠት ተወ ።
እጁ አቆመ)፡ መስጠትን ተወ (ገንዘብን ያዘ ") ።
እጁ ዐጠረ፡ አንድ ነገር ለማድረግ ገንዘቡ አነሰበት ጐደለበት አልበቃ አለው ።
እጁ ጣለው፡ ሰው ያበላው መብል በልቶ ካድን አጠፋው ።
እጁን ለኔ ከብቱን ላንተ፡ በወን ጀለኛ ላይ የተነገረ የንጉሥ ዐዋጅ ።
እጁን ሰጠ፡ ተያዘ፡ እጠላት እጅ ገባ ተማረከ ።
እጁን ከብብቱ አገባ፡ ፈጽሞ ሰነፈ፡ ሳይሠራ ቀረ ።
እጁን ጫነበት፡ ያዘው፡ የራሱ አደ ረገው ።
እጃም፡ ረዘም ያለ ሞላላ ደንጊያ ።
እጅ (እድ)፡ የገላ ክንፍ ሥራ መሥ ሪያው መሣሪያው ። እጅና እግር ፥ እጅና ፍንጅ ፥ እጅ በጅ ፥ እጅ ለጅ እንዲሉ ። ባልን ወርችን ውስጥን ፪ኛውን ሰለለ እይ፡ በጄን ተመልከት ።
እጅ ለጅ፡ የኵስኵስት ትግል ቍጭቋጮ ።
እጅ መንሻ (ምንሣአ እድ)፡ እጅ መያዣ መጨበጫ ።
እጅ መንሻ (አምኃ)፡ ገጸ በረከት መተያያ እጅ ነሥቶ ወዲያው የሚሰጡት የዕቃ የገንዘብ የከብት ስጦታ ። (ዘፍ ፴፬ ፥ ፲፪) ።
እጅ ማሟሻ፡ የዳግም ትንሣኤ ማግ ስት ሰኞ እጀ ሥራ የሚዠመርበት፡ ኲበት ወረራ ።
እጅ በዛበት፡ ብዙ ሰው ወሰደው ።
እጅ በጅ፡ የዋጋና የዕቃ ወዲያው መቀባበል ።
እጅ ተነሣሣ (እደ ተናሥአ)፡ እጅ ለጅ ተያያዘ ተጨባበጠ ተገናኘ፡ ሰላ ምታ ተሰጣጠ ተሰነባበተ፡ ታቦትና ታቦት፡ ጻድቅና ጻድቅ ።
እጅ ነሣ (ነሥአ እደ አምኀ)፡ እጅን በጅ ያዘ ጨበጠ፡ ሰላምታ አቀረበ ሰጠ ። ሳመ ተሳለመ፡ ሰገደ ተንበረከከ ። ፪ኛውን ነሣ እይ ። ዳግመኛም እጅ ነሣ ማለት በዘመናችን የፈረንጅ ወታደር እጁን አንሥቶ ላለቃው ሰላምታ ሲሰጥ እንደምናየው ነው ።
እጅ ነሺ፡ ሰላምታ አቅራቢ ሰጪ ።
እጅ አላስገባም፡ አልታረመም ኣል ታጨደም አዝመራው ።
እጅ አስነሣ፡ ሰውን እንጉሥ እመ ኰንን ዘንድ አቅርቦ ሰላምታ ኣሰጠ አስቀ ረበ፡ እጅን በጅ አሲያዘ እስጨበጠ ።
እጅ አስነሺ፡ ሹም ባለል ።
እጅ አውሰኝ፡ ምታልኝ በልልኝ ማለት ።
እጅ አዛወረ፡ ለከሳሽ ለቀቀ ሰጠ ተከሳሽ ይዘታውን ።
እጅ አደረገ፡ ተቀበለ ተረከበ ያዘ ጨበጠ ።
እጅ እጅ አለ፡ ሰለቸ ጣም ዐጣ ምግቡ እጅ ስለ በዛበት ።
እጅ ከፍንጅ፡ ሌባ ከሰረቀው ዕቃ ጋራ ሲያዝ እጅ ከፍንጅ ይባላል፡ በሰንሰ ለት መታሰሩን ያሳያል ።
እጅ፡ ክፍል ። ፩ እጅ ፥ ፪ እጅ ፥ ዐሥር እጅ እንዲሉ ።
እጅ ጸፋ፡ በር መታ፡ ድምፅ አሰማ፡ አጨበጨበ ቸብ ቸብ አደረገ ።
እጅብኝ፡ ረፋድ፡ ዐጀበ ።
እጅጉ፡ የወንድ ስም ።
እጅጌ (ጌ እድ)፡ የእጅ ስፍራ እጅ የሚያርፍበት የሚይዘው የሚጨብጠው፡ እጅ የሚያጠልቅ የእጅ ቤዛ ቈዳ ልብስ ። ቤዛን እይ ።
እጅጌ፡ የእጅ ማግቢያ ፥ —እጅ ።
እጅጌው ያጠረ ባ ለጥለት ሰፊ ጥብቆ የኮት ያኸል ርዝማኔ ያለው ("ይህ ስም የሚነገረው በባላገር ነው ኪቶች ጥብቆዎች ካቲ፡ ስንድድ ከተከተ ካታ የሚሥቅ ከተከተ ኳተ ") (ኰዐተ) ።
እጅግ (ጎች)፡ የበዛ የተረፈ የተትረፈረፈ ዐያሌ ብዙ ። ንኡስ አገባብ ። እጅጉን በጅጉ እንዴት ከርመኻል፡ እጅጉን ብዙውን እንደ ምን አለኸ ።
እጅግ በጣም፡ ብዙ፡ ብዛቱ ከልክ ያለፈ ።
እጅግ ነው፡ ብዙ ነው፡ ሞልቷል ። (መዝ ፳፭ ፥ ፲፩) ።
እጅግ አየኹ፡ የወንድና የሴት ስም፡ ብዙ አየኹ ማለት ነው ።
እጅግ አየኹ፡ የዳግማዊ ምኒልክ እናት ።
እጅጓ፡ የሴት ስም ።
እጆች (እደው አእዳው)፡ የገላ ቅጥዮች ዐጽቆች ክንፎች ።
እገሌ፡ የስም ምትክ ፥ —እከሌ ።
እገዳ፡ ከተራ ጥበቃ ።
እጕል (ህጉል)፡ የታጐለ የጠፋ የቀረ የተዳፈነ፡ ዳፈን ።
እጕል ገባ፡ ዳፈን ሊከፍል ዐደረ ።
እጕር (ሮች)፡ የታጐረ የተዘጋ ዝግ፡ የተሰበሰበ የተከማቸ ከብት ዕጅብ ።
እጕር፡ ዕዳ የሚያመጣ ክፉ ነገር ። እጕር ገባ እንዲሉ ።
እግረ ኅሊና፡ ያሳብ እግር ሳይኼዱ የሚኼዱበት ።
እግረ መልስ፡ ባሪያን ከኼደበት የ ሚመልስ የጠንቋይ ድጋም አስማት ።
እግረ ሙቅ (ሞቅሐ እግር)፡ የእግር ማሰሪያ መዘንጀሪያ ሥራ የማይከለክል። እግር ብረት፡ ፍንጁ ኹለት ጠገጉ ኹለት ።
እግረ ሰላላ)፡ እግረ መንማና።
እግረ ቀላል፡ ቀልጣፋ ፈጣን ።
እግረ ድር፡ እግረ ለማጣ ወደ ጐን የሚረግጥ ።
እግረ ፀሓይ፡ ጮራ ። በግእዝ ማዕዘር ይባላል ። ተልባን ተመልከት ።
እግረኛ (ኞች) (አጋር)፡ ሯጭ ገሥጋሽ በእግር ኻያጅ ጐበዝ ጕልማሳ ወታደር ሰልፈኛ ዘማች ።
እግረኛ፡ ዕርፊተ ቢስ ዘዋሪ ።
እግሩን አነሣ፡ ነቀለ፡ መኼድ መራ መድ ዠመረ ።
እግራም፡ እግር ያለው ዕቃ ። እግራም ጥዋ እንዲሉ ።
እግር (ሮች)፡ በቁሙ፡ መቆሚያ መርገጫ መኼጃ መራመጃ ከጭን እስከ ሰኰና ያለው ። የሰውና የአዕዋፍ ኹለት ኹለት፡ የአራዊትና የእንስሳት አራት አራት ነው ። የፊት እግር የኋላ እግር፡ እግር ጣለው፡ ምን እግር ጣለኽ፡ ያልጋ የወንበር የገበታ እግር እንዲሉ ። ደንብን ዝኆንን ኰብሽን እይ፡ ጣለን ተመልከት ። (ያቡን እግር)፡ ነጭ ስንዴ ጣይ ሶራ ። (የዳኛ እግር)፡ ምስክር አለ በት ኺዶ ለሚያመሳክር ዳኛ የሚከፈል ገን ዘብ ። (የመዝጊያ እግር)፡ ወንዳወንዴ የመዝ ጊያ ቍላ ። ውስጥን እይ፡ ዐምሳንና ሺን ተመ ልከት ። (የታ ት እግር)፡ ቄስ ታቦት ተሸ ካሚ ። ከሺ ምስክር የታቦት እግር እንዲሉ ።
እግር መመለሻ፡ የመልክተኛ ድካም ዋጋ ።
እግር መንገዱን ጠየቀ፡ ሲኼድ ሳለ መንገዱን ለቆ ለወዳጁ ሰላምታ ሰጠ ። ፫ኛውን ጐራ እይ ።
እግር መንገድ ኼደ (አገረ መልዐ)፡ ድንገት ሳያስበው በእግሩ ኼደ፡ ዐለፈ ነጐደ አንድ ነገር ይዞ ።
እግር መንገድ፡ የእግር መንገድ ።
እግር በግር፡ ተከታትሎ ።
እግር ብረት (ብርተ እግር)፡ የእግር ብረት፡ እግር ማሰሪያ ዥቦ ቀለበት ያለውና የሌለው፡ ፍንጁ ኹለት፡ ዘንጉ (ቅር ቃሩ) አንድ ። (ኢሳ ፵፭ ፥ ፲፬) ።
እግር ተወርች፡ የሰውን እግሩን በ ግር ብረት እጁን በሰንሰለት አንድነት ማ ሰር ።
እግር ተፈረስ፡ ቀጪንና ወፍራም ሽሩባ ።
እግር ተፈረስ፡ የጠፋ ነገር ቶሎ መፈለጊያ ።
እግር ዐልቦ፡ የእግርጌጥ ። ዐልቦን እይ ።
እግር አወጣ፡ መኼድ ዠመረ ቻለ ኼደ ተራመደ ።
እግር ዛል፡ ጭን ።
እግር ግላጭ፡ ከበሬ ከበግ ከፍየል እግር ላይ የተቈረጠ የተለጠጠ ሥጋ ።
እግር ጣለው፡ አመጣው አደረሰው ።
እግርጌ (ትርጋፅ)፡ ዝኒ ከማሁ ። ራስ ጌና ግርጌ እንዲሉ ። ጌን ተመልከት ። ግርጌ ማለት እን ጐርዶ ነው፡ ሲበዛ ግርጌዎች ይላል ።
እግርጌ (ጌ እግር)፡ የእግር ስፍራ የእግር መቆሚያ እግር የሚያርፍበት በስተ እግር በኩል ያለ ታች ።
እግርጌ፡ በግርጌ ። እግርጌ ኹን ።
እግዚሐራብ (እግዚአብሔር አብ)፡ የቅድስት ሥላሴ አንደኛው መዠመሪያው አካል ። አብን ተመልከት ።
እግዚሐራብ፡ የታቦት ስም ።
እግዚሐር፡ እግዜር ።
እግዚእ (ገዝአ)፡ ጌታ እግዜር መኰንን ።
እግዚኦ፡ አቤቱ፡ ጌቶ ጌታው፡ ጌታ ሆይ ። እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ።
እግዚኦታ፡ እግዚኦ ማለት፡ አቤቱታ፡ ጸሎት ምሕላ ልመና ። ፵፩ እግዚኦታ እንዲሉ ። ያድኅነነ ከመዓቱ ይሰውረነ በምሕረቱ ምንተ ማሪያም ወላዲቱ ። እማሆይ ማሪያም ስልሽ ሣህል ወምሕረት ወልደሽ ወዴት አገኝሽ ፥ ዐሳቤን እነግርሽ ትካዜን እነግርሽ፡ ዎ ይለ መነና ልጅሽ፡ ዎ ይታደገና ልጅሽ እንዲሉ ባልቴቶች ።
እግዜር (እግዚአብሔር)፡ የባሕርይ አንድነት ያካል ሦስትነት፡ ምላት ስፋት ርቀት ያለው የሰማይና የምድር የዓለም ጌታ ፈጣሪ ። (፩ዮሐ ፭ ፥ ፯) ። እግዜር ያሳይዎ እንዲል አቤት ባይ ።
እግዜር፡ በቁሙ ፥ —እግዚእ ።
እግዜር የሌለበት አገር የለም፡ በኹሉ ምሉ ነው በሰማየ ሰማያት በዕመቀ ዕመቃት ይገኛል ። (መዝ ፻፴፱ ፥ ፰ ፥ ፲) ።
እግዝእት፡ እመቤት ባልተ ቤት ወ ይዘሮ ።
እግዝእትነ ማርያም፡ እመቤታችን ማሪያም ።
እግድ፡ የታገደ የተገታ የተከተረ፡ ው ስን ክልክል እስር ጥብቅ ዝግ ክትር ።
እጓ፡ በቁሙ፡ ጓጓ ።
እጠድቅ ባይ፡ እጸድቅ ባይ ።
እጢ፡ ዕብጠት፡ ዕጢ ።
እጣቆ፡ በበልግ ዘመን ባገዳ ቡቃያ ላይ ከማር ጋራ የሚገኝ ትል ("ከብት በበላው ጊዜ ሆድን ይነፋና እንደ መርዝ በቶሎ የሚገድል ነገረኛም ሰው እጣቆ ይባላል") ።
እጣቆ፡ ያገዳ ትል፡ ጠቃ ።
እጨጌ፡ የምድር ዕጮኛ፡ ዐጪ፡ ዕጨጌ ።
እጭ፡ የንብ ዕንቍላል፡ ዕጭ።
እፈፋ፡ ቅርጠፋ ክርከማ ።
እፊያ (ዎች)፡ የድስት፡ የመሶብ፡ የማንኛውም ዕቃ መክደኛ፡ ወስከንባይ፡ ከሸክላ ከስፌት የተዘጋጀ ።
እፋፊ፡ ቅፋፊ ቍራጭ ።
እፍ፡ መንፋት መተንፈስ ።
እፍ አለ፡ መብራት ኣጠፋ ።
እፍ አለ፡ ነፋ አነፈሰ ተነፈሰ፡ በትንፋሽ ጠረገ ኣስገለለ፡ ያይን ያቧራ የዶቄት የደቃቅ ነገር ።
እፍ አለ፡ እሳት አነደደ፡ እሳቱ እንዳይጠፋ እንዳይጠልስ አደረገ ።
እፍ አይሉሽ፡ ማሽላ፡ የማሽላ ስም ።
እፍ ያለ፡ ነፋስ የጠረገው ለጥ ያለ ሜዳ፡ ምንም የሌለበት ።
እፍ ያለች፡ ዋና ሸርሙጣ፡ ያበደ ያበደች የነደደ የነደደች ።
እፍራን፡ ቀይ የንጨት አበባ ቀለም የሚኾን ።
እፍታ፡ በወጥ ላይ የሰፈፈ ወይም የጠለለ የቅቤና ያዋዜ ስልባቦት ። እፍታ በልቼ ልቤን ያቅረኛል ።
እፍታ፡ አፍ ማለት ። (ኢሳ ፴ ፥ ፴፫) ።
እፍታ፡ እፍ ማለት ፥ —አፍ ።
እፍኝት (ቶች) (አፍዖት ፈዐወ)፡ ዝንጕርጕር እባብ ኵርፋፍያ፡ መርዙን በትንፋሹና በጥርሱ የሚናኝ፡ ሰውንና ከብትን የሚጐዳ፡ ዥራተ ጐንዳ ። ጕበናን ተመልከት ።
እፍዳ፡ ከእበት የተበጀ የቀፎ መክደኛ መግጠሚያ ።
እፍግ አለ፡ ታፈገ ።
እፍግ፡ የታፈገ የተከማቸ ። ፪ ክምቹ ።
እፍግፍግ፡ የተፋፈገ የተጠጋጋ፡ ንብብር ።
እፍፋት፡ ክርክማት ክምማት ።
እፍፍ አለ (እፍ እፍ አለ)፡ መላልሶ አነደደ፡ በትንፋሽ ኣበረዶ፡ አከባበረ ፈጽሞ ወደደ ። (ተረት)፡ ገንፎ እፍፍ ቢሉኸ ሲውጡኸ ነው ።
እፍፍ አለ፡ መላልሶ አነደደ ፥ —አፍ ።
እፍፍ፡ የታፈፈ የተከረከመ፡ ክርክም መጣፍ ደብተር መዝገብ ።
እፎይ (አፈወ እፎ)፡ በቁሙ፡ መተንፈስ ማረፍ ።
እፎይ አለ፡ ዐረፈ ተነፈሰ አስተፋሳ ። ሲዘረዝር እፎዬ እፎዬው ይላል ። ው ሥራውንና ድካሙን ያሳያል ።
እፎይታ፡ እፎይ ማለት፡ ዕረፍት ማግኘት መተንፈስ ።
ኦ ! አባ ።
ኦ ሳብዕ፡ (፳ኛ) ሰባተኛ ድምፅ፡ ሳብዕነትን ከወ ሳብዕ ዎ ተረክቦ ሌላውን ፊደል ሳብዕ ያደርጋል ። በ አ ፥ ቦ ። ጐ አ ፥ ጎ ።
ኦ ስመ አምላክ !፡ ፆ ።
ኦ፡ ንኡስ አገባብ፡ ቃለ አጋኖ፡ ፍችው፡ ሆይ ። ኦ አምላክ ፥ ኦ ክርስቶስ ። ዎን አስተውል ።
ኦሳጋሚ፡ ያሳገመ/የሚያሳግም።
ኦሪተ ሊቃናት፡ በበጥሊሞስ ዘመን ሰባ ሊቃናት ከዕብራይስጥ ወደ ጽርእ የተረጐሙት፡ መላው ብሉይ ከነአዋልዱ ።
ኦሪተ ሌዋውያን፡ ፊት ሙሴ የጻፈው ኋላም ሌዋውያን በየጊዜው እየጻፉ ለሕዝብ ያስተምሩት የነበረ ፭ቱ ብሔረ ኦሪት ።
ኦሪተ ሳምራውያን፡ በስልምናሶር ጊዜ የሰማርያ ካህን ምናሴ በሰማርያ ለሚኖሩ ሕዝብ አሕዛብ የጻፈው ፭ቱ ክፍል ኦሪት ብቻ ።
ኦሪተ አይሁድ፡ በሐዋርያት ጊዜ አይሁድ ጉባኤ አድርገው ዘመነ አበውን በመፋቅ እያጐደሉ የጻፉትና ያበላሹት (ብጡል) ።
ኦሪት፡ ሕግ ፍርድ ትእዛዝ፡ ዐሠርቱ ቃላት ። ሕግ አድርግ አድርግ፡ ትእዛዝ አታድርግ የሚለው ነው ።
ኦርቶ (ርቱዕ) የቀና፡ ዶክስ (ስብሐት) ምስጋና ማለት ነው ይላሉ ። (ኪ ወ ክ) ።
ኦርቶዶክሳዊ፡ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት የሚያምን ።
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን፡ ሃ ይማኖት ።
ኦርቶዶክስ፡ የሃይማኖት ስም፡ ከሐዋርያት ዠምሮ እስከ ጉባኤ ኬልቄዶን የነበረ እምነት፡ በግእዝ ተዋሕዶ ይባላል ። ዛሬም በሶርያና በአርማንያ ቤተ ክርስቲያን የሚገኝ፡ በምስጢረ ሥላሴ ፫ ኣካል ፩ ባሕርይ፡ በምስጢረ ሥጋዌም ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፩ አካል ፩ ልጅ፡ ፪ ባሕርይ፡ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው ፪ የባሕርይ ልደት፡ ፫ኛ የግብር ልደት፡ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ፲ ፩ ሠሪ፡ ፪ ሥራ ፲ ወልደ አብ ወልደ ማርያም በተዋሕዶ ከበረ ብሎ የሚያስተምር፡ ከቱሳሔና ከውላጤ የራቀ የቄርሎስና የዲዮስቆሮስ ባህል ። ትርጓሜውም፡
ኦርቶዶክሶች (ኦርቶዶክሳውያን)፡ ግሪኮች መስኮቦች ሩማንያዎች ሶርያዎች የደቡብ ህንዶች አርመኖች ግብጦች ኢትዮጵያውያን ።
ኦሮ ቤት፡ የኦሮ ነገድና ስፍራ ዳር አገር (ኢሉባቦር አሩሲ ቦረና ገሙ ጐፋ ጋርዱላ ጅማ ወለጋ (ወላሞ ከንባታ) ከፋ ሊሙ ሲዳሞ ባሌ ሌላውም በዚህ ያልተጻፈው የሻንቅላ አገርና ወገን ኹሉ።)
ኦሮሞ (ዎች)፡ የነገድ ስም (በኢትዮጵያ በዝቶ የሚገኝ ሕዝብ ወረሞ የጭፍራም ስም ይኾናል) ። (ተመልከት፡ ወፈረ ብለኸ ሞፈርን) ። "ኦሮሞች የያዙትን አገር ኹሉ በአባቶቻቸው ስም ሰይመውታል። የጻድቁ ዮሓንስ ታሪክ ግራኝዐማራን በወጋ ጊዜ ኦሮ ያማራን አገር ኹሉ ያዘ ይላል።"
ኦሮቢ፡ የጋለበ/የሚጋልብ/የሚሸሽ (በራሪ/ሯጭ/ፈረሰኛ) ።
ኦሮቢነት፡ በራሪነት/ፈረሰኛነት ።
ኦበዛበዝ፡ ኣዘራረፍ አበራበር፡ ብዝበዛ መበዝበዝ ።
ኦከ ሞት)፡ የኀጢአተኛን ነፍስ ከሥጋ የሚለይ ("አስከሬናም ጥርሳም መስሎ የሚታይ ካህናት ግን ጸረ ሞት ይሉታል") (፪ ዜና. ፳፩፡ ፲፱) ።
ኦኵረፈረፈ፡ ቈበር፡ ደፈቀ፡ ኰረፈ ።
ኦፊር፡ ወርቅ እንዳፈር የሚታፈሥበት አገር በእስያ ውስጥ ያለ ። (ዘፍ ፲ ፥ ፳፱ ። ፫ነገ ፱ ፥ ፳፰) ።
No comments:
Post a Comment