Friday, June 6, 2025

                                 

: የዘ ዲቃላ፡ ዐማርኛ ፊደል (መጪረሻው በሆነ ግስ ሳድሱ በሣልስ ቅጽል ሲነገር፡ አዘዘ - አዛዥ፡ ገረዘ - ገራዥ፡ ናዘዘ - ናዛዥ ይላል። ራብዑም ማዘዣ፣ መግረዣ፣ መናዘዣ፣ መያዣ እያለ ይገባል። ዐማርኛ ከግእዝ ባሕርይ መውጣቱ በዚህ ይታወቃል።)

: የጀ ወራሽ (ጀማን ዠማ እንዲሉ)

ዠለለ (ዘለለ): አንዣለለ (የበግ ላት አስመሰለ አሾለቀ አሞለለ አሾጠጠ ሰለ) ።

ዠለተ/ጀለተ: ናቸ ጀለተ 

ዠለዠለ (ዠለለ): ረዘመ፣ ረዥም ሆነ፣ ተግዠለዠለ።

ዠለዠል/ዠልዣላ: ረዥም፣ ላት፣ ግዥልዥል።

ዠለጠ : አጐደለ፣ ዘቀዘቀ፣ ወዳንድ በኩል ደፋ፣ አጋደለ።

ዠለጠ: ቈዳን በሁለት እጅ ይዞ ቍልቍል በእግሩ ረገጠ፣ አለፋ።

ዠላላ: ሞላላ፣ ሾለቃዊ፣ ሾጣጣ፣ አገረ መርፌ፣ ዥራትማ።

ዠላጣ: ተዳፋት ስፍራ ወይም ድንጋይ፣ ግንድ፣ ዘመመን።

ዠላጭ: የዠለጠ፣ የሚዠልጥ፣ አልፊ።

ዠመረ (ዘምሮ፣ ዘመረ): ወጠነ፣ ፈለመ፣ ቀደመ፣ መራ።

ዠመተ (ዘመተ): ከሠደ፣ የፍየልና የበግ አንዠት ዐለበ፣ ዥማት አወጣ፣ አከረረ።

ዠመት (ብዙ ቁጥር: ዠመቶች): ከባሕር ወደ ባሕር የሚዘምት ታላቅ ዓሣ። ከግንቡል የሚበልጥ። በትከሻ ላይ ሲሸከሙት ራሱና ጭራው እግር የሚነካ።

ዠመገገ: ጐተተ፣ ሸመጠጠ፣ ዠረገገ፣ ሳበ፣ ዐለበ፣ መናኛ ፈትል ፈተለ።

ዠማ : ቸር ሰው፣ ሳይቈጥብ የሚሰጥ።

ዠማ : ከተጕለትና ከወግዳ መካከል ዠምሮ መርሐ ቤቴን ወደ ቀኝ እየተወ የሚወርድ ያዳባይ ዥረት።

ዠማ (ዐረብኛ: ጀማዐህ፣ ማኅበር): ብዙ ወንዝ፣ ዥረት። (ላንድም ይነገራል። ዤማ ተብሎ ቢጻፍ ግን ትርጓሜው ጯኺ ያሠኛል)

ዠማ ነሽ: የሴት መጠሪያ ስም። (ዠና፣ ተወራራሾች ስለሆኑ ጀማ በማለት ፈንታ በግእዝ መጽሐፍ ዠማ እየተባለ ተጽፎ ይገኛል። ፈለገ ዠማ እንዲል (ገድለ ተክለ ሃይማኖት))

ዠማ ነኸ: የወንድ መጠሪያ ስም፣ ብዙ ነኸ ማለት ነው።

ዠማ ነጋዴ: የነጋዴ ማኅበር ብዛት፣ ብዙነት ያለው፣ በየነጋድራሱ ዠማ ተሻግሮ ወደ ንግድ የሚኼድ፣ የሚነጕድ። (ፈረንጆች ኩባንያ (ኮምፓኚ) ይሉታል፡ ባልንጀራ ከማለት ጋራ ይሰማማል)

ዠማ ነጋዶች: ብዙዎች የንግድ ማኅበሮች (፪ኛ ዜና ፩፡ ፲፯)

ዠማመረ: ፈላለመ።

ዠማሪ (ብዙ ቁጥር: ዠማሪዎች): የዠመረ፣ የሚዠምር፣ ወጣኒ፣ ፈላሚ፣ ቀዳሚ።

ዠምጋጊ: የዠመገገ፣ የሚዠመግግ፣ ሸምጣጭ።

ዠሞች: ወንዞች፣ ዥረቶች።

ዠረረ (ዘረረ): ትግርኛ: ዛረየ። መነጨ፣ ፈሰሰ፣ ብዙ ውሃ ጨመረ፣ ዘለለ፣ በጠበጠ።

ዠረር አለ: ፈሰስ አለ።

ዠረገ: ዠለጠ፣ አለፋ፣ ሞዠቀ።

ዠረገደ : ብዙ ወለደ፣ ፈለፈለ።

ዠረገደ : አረዘመ።

ዠረገደ (ረገደ): መታ፣ ደበደበ።

ዠረገድ/ዠርጋዳ/ዥርግድ: ሽንጣም፣ አቋቋሙ መልካም ወንድ ወይም ሴት።

ዠረገገ: ዠመገገ፣ በጠሰ (እሸትን)

ዠረገግ/ዠርጋጋ: የተንዠረገገ፣ የተንጠለጠለ፣ የተንጨረገገ (ዛላ፣ ዘለላ)

ዠራረገ: ዠላለጠ፣ አለፋፋ።

ዠር: የቤት ግንብና ህንጻ (በቀድሞ አነጋገር)

ዠር: ገር፣ ጣል፣ ወርውር ማለት ነው።

ዠርባ (ብዙ ቁጥር: ዠርባዎች): የገላ ስም። ከትከሻ ዠምሮ እስከ ወገብ በታች ያለ አካል፡ ከሆድ የተለየ አንጻር። (ለምሳሌ: "እከሌና እከሌ ሆድና ዠርባ ናቸው" እንዲሉ) በስተፊት ያለ ስፍራ ፊት እንዲባል በስተዠርባም በኩል ያለ ቦታ ዠርባ ይባላል። ትርጓሜውም ድርብ ተደራቢ ሲኾን፡ ጀርባ ተብሎ ሊጻፍ ይችላል። (የወጣበት ሥር ቢመረመር እንደ ግእዝ ዘረበ፣ እንዳማርኛ ደረበ ኹኖ ይገኛል)

ዠርባ ሰፋሪ: ከንጉሥ ድንኳን በስተኋላ የሚሰፍር ሰራዊት፡ ደጀን።

ዠርባውን ሰጠ: ፊቱን መለሰ።

ዠርጋጊ: የዠረገገ፣ የሚዠረግግ፡ ዠምጋጊ።

ዠቀዠቀ (ዘቀዘቀ):

ዠቀዠቅ/ዠቅዣቃ: የተንዠቀዠቀ፣ የሚንዠቀዠቅ (ፈሳሽ፣ የጣራ ውሃ)

ዠቅ አለ: እንደ ፈሰስ በዝቶ መጣ (የንግዳ)

ዠቅዠቅ አለ: ፈሰስ ፈሰስ፣ ወረድ ወረድ አለ።

ዠበረ (ዘበረ): ዥበር ሰበረ። (በረ ዠን አስተውል)

ዠበረ (ዘበረ): ይህ ዥበር ሰበረ ማለት ነው።

ዠበረረ (ዛበረ): አንዠባረረ፣ ልብ አሳጣ፣ አሰከረ፣ አዘነጋ፣ ፈጽሞ አስረጀ፣ አዦዠ፣ አዣዠ። (ነበረረን እይ)

ዠበረር/ዠብራራ: የተንዠባረረ፣ የሚንዠባረር፣ እጅግ ቸር፣ ለጋስ፣ አባ መስጠት።

ዠበርባራ: የተዥበረበረ።

ዠበበ (በፀወ): አሸለበ፣ ዘመመ። (ግእዝ ዘቢብ ዘበ ካለው የወጣ ነው።)

ዠበብ አደረገ: አንቀላፋ (በጥቂቱ)

ዠበደ: በጥቂቱ መታ፣ ለኰፈ።

ዠበደ: በጥቂቱ መታ ወይም ለኰፈ ማለት ነው።

ዠበድ ዠበድ አደረገ: በቀላል ወቀጠ ወይም ሸከሸከ ማለት ነው።

ዠበድ ዠበድ አደረገ: ዝኒ ከማሁ (በቀላል ወቀጠ፣ ሸከሸከ)

ዠባባ: የተንዣበበ ወይም የሚንዣበብ ነገር፡ ለምሳሌ አሞራ፣ ወፍ፣ አይሮፕላን።

ዠባባ: የተንዣበበ፣ የሚንዣበብ (አሞራ፣ ወፍ፣ አይሮፕላን)

ዠባባዬ: የዘፈን አዝማች፣ የኔ ዠባባ፣ የዠባባ ዐይነት ወገን። (ለምሳሌ: እንዲያው ዠባባዬ እንዳለ የዱሮ ዘፋኝ)

ዠባባዬ: ይህ ቃል በዘፈን አዝማችነት ጥቅም ላይ ይውላል፡ ዘፋኞች በዘፈናቸው ውስጥ የሚጠቀሙበት የፍቅር ወይም የናፍቆት ቃል ሲሆን 'የኔ ዠባባ' የሚል ትርጉም አለው። እንዲሁም እንደ ቅጽል ስም የሚያገለግል ዠባባ የሚል ቅጽል ስም ላለው ሰው ሊያገለግል ይችላል። 'እንዲያው ዠባባዬ' የሚለው ደግሞ የድሮ ዘፋኞች ብዙ ጊዜ የሚጠቀሙበት የዘፈን አባባል ነው።

ዠብ ዠብ አደረገ: ዠበደ። (የክንፍን መጋጨት ያሳያል)

ዠብ ዠብ አደረገ: ዠበደ፣ ዠበበ።

ዠብ ዠብ አደረገ: ይህ ማለት ዠበደ ማለት ሲሆን፣ የክንፍን መጋጨት ድምፅ ያሳያል።

ዠብዱ ጋልኛ ነው: በአማርኛም ተለምዷል።

ዠብዱ: የወንድ ልጅ ሞያ፣ ግዳይ።

ዠብዱ: ይህ የወንድ ልጅ ሞያ ወይም ግዳይ ነው። ቃሉ ከጋልኛ ቋንቋ የመጣ ቢሆንም በአማርኛም ተለምዷል።

ዠነቀ (ዘነቀ): አብዝቶ ጨመረ፣ አገባ (የውሃ፣ የፈሳሽ)

ዠነቀ: የሕዝብ።

ዠነቄ: በወግዳ ውስጥ ያለ ገጠር የማሪያም አጥቢያ።

ዠነጠፈ (ዘነጠፈ): እሸት ቈረጠ፣ ዠመገገ።

ዠናቂ: የዠነቀ፣ የሚዠንቅ፣ ጨማሪ።

ዠን: ይህ ቃል አስተውል ማለት ነው።

ዠንበር: ፀሓይ (ጀንበር)

ዠንዲ: ተንቤን (ጀንዲ)

ዠንፍ: ጠበቃ፣ ደጀን።

ዠንፎ (ጀንሮ): (ዘነፈ) የዘንግ፣ የሶማያ፣ የመቋሚያ ቀለበት። ከብረት የተሰራ። በትሩ እንዳይሠነጠቅ ጠባቂ፣ ቤዛ። በተዛነፍ ተጠምዞ የተበጀ።

ዠንፎቅ: የአረግ ስም። በዛፍ ላይ የሚዘረጋ፣ የሚንዛፈፍ ዐረግ።

ዠወለለ (አንዠዋለለ): አረዘመ፣ ጐተተ። (መሠረቱ ገወለለ ነው)

ዠወለል/ዠውላላ: ረዥም፣ ጕትት።

ዠውዣዋ (ጀውጃዋ): ገውጋዋ፣ ሞኝ፣ ቀውላላ።

ዠዠ: የጠንቋይ ጽፈት። (ጩጪን ተመልከት)

ዠዠነ (ዘጊን፣ ዘገነ): ገነነ፣ በረታ፣ ጐበዘ።

ዠደመ: ጨረሰ፣ ፈጸመ።

ዠደበ: መታ፣ ሰረረ። (ዘነደበን ተመልከት)

ዠደደ (ገደደ): በዛ፣ ብዙ ሆነ።

ዠደድ አለ: ተነቀ።

ዠደድ አለ: ድንገት በዝቶ ወደ ቤት ገባ።

ዠደድ: የበዛ፣ ብዙ።

ዠዲ (ዐረብኛ: ጀዲ): የፍየል ጥቦት። (በግእዝ ዠደይ ይባላል። ጀና፣ ተወራራሽ ስለሆኑ ጀዲ በማለት ፈንታ ዠዲ ይላል። ጀንዲን እይ)

ዠድብ: ነዊኅ አስኪት።

ዠጂ: የፍየል ወጠጤ የሚመስል የታኅሣሥ ኮከብ። (ለምሳሌ: ዠዲ መሬት እንዲል ጠንቋይ)

ዠገረ (ዠጐረ): አዥገረገረ (ዥግራ አስመሰለ አንከባለለ መለስ ቀለስ አደረገ ነጭና ጥቍርን አሳየ ይህ ሰውዐይ ኑን ያዥገረግራል ። ከባለል

ዠገዠገ : ተንጠለጠለ፣ አሸቀሸቀ፣ ሊናድ ቀረበ (የግንብ፣ የካብ)

ዠገዠገ (ዘገዘገ): ተረፈ፣ ተትረፈረፈ፣ በዛ፣ ረዘመ (የዥማት፣ የነገር)

ዠገዠግ: ረዥም የደጋን ዥማት፣ ትርፉ፣ ጥምጥሙ።

ዠገደ: ሞገደ፣ ማገደ፣ ሞጀረ፣ ጨመረ (የማገዶ)

ዠግና (ብዙ ቁጥር: ዠግኖች): ኀይለኛ፣ ጐበዝ፣ ብርቱ፣ ጦረኛ፣ ሐርበኛ፣ አሳዳጅ፣ አባራሪ፣ አሸናፊ፣ ሞት አይፈሬ፣ የጦር ገበሬ።

ዠግና ሆነ: ሞያ፣ ዠብዱ ሠራ፣ ዐየለ።

ዠግንነት: ዠግና መኾን፣ ጕብዝና፣ ሐርበኝነት።

ዠጐረ (ዘጐረ): ዠግና መኾን (ጕብዝና ሐርበኝነት) ።አዥጐረጐረ (ነብር አስመሰለ አነጣ አጠቈረ)

ዠጐደ (ጐደጐደ): አዥጐደጐደ (አመጣ አወረደ የቅኔ የነገር)

ዠጠዠጠ: አብዝቶ አስፍቶ ከተማ ሠራ፣ ድንኳን ተከለ። (ገጠገጠን እይ)

ዡህ/ዥው (ትግርኛ: ዘውሐ): ስምጥጥ፣ ቀጥ፣ ሰተት።

ዣረ (ዘኀረ): ተዣረ (ተዝኅረ) ራሱን ኰፈሰ ሌላውን ናቀ ኣኰሰሰ ኰራ ታበየ ዐዲስ ልብስ ለብሶ ተሽኰንትሮ)

ዣረገ (ዘኀረ): አዣረገ: ቈረጠ፣ አከበ፣ ሰበሰበ፣ አከማቸ (የፍሬ፣ የዛላ፣ የዘለላ፣ የጥጥ፣ የዓሣ)

ዣራ (ትግርኛ: ዛራ): ፈሳሽ። የመርሐ ቤቴ ወንዝ መዋጊያ ስፍራ።

ዣራ: ወንዝ (ዠረረ)

ዣርት (ብዙ ቁጥር: ዣርቶች): ጋረጠ። እሾኻም የዱር አውሬ፣ ድኍር። ካፍንጫው በቀር በጠጕር ፈንታ ኹለንተናው ነጭና ጥቍር ጋሬጣ የሆነ። ጠላት በመጣበት ጊዜ እሾኹን ያራግፋል (ይነዛል) (ለምሳሌ: "የዣርት ወስፌ" እንዲሉ) (ፈራ ብለኸ አፈራን እይ) ተባቱም እንስቱም ዣርት ይባላል። ጃርት ተብሎም ሊጻፍ ይችላል።

ዣርት ቅልጥም: ዐጪር ሰው፣ ድንክ።

ዣን: ትልቅ (ጃን)

ዣንዦ (ኦሮምኛ): የበግ አዙሪት፣ ባሪያ።

ዣዠ: ፈጽሞ አረጀ፣ ጋዠ፣ ተንዠባረረ። (ዦዠን እይ)

ዣዣ (ዛሕዝሐ): አንዣዣ (አበዛ ለገሰ አንቻቻ

ዣገረ (ረጊዝ፣ ረገዘ፣ ወጋ): አነሣ፣ ያዘ፣ ተሸከመ (የበዳ፣ ጸብትን)

ዣግሬ: የነገሥታትና የመሳፍንት፣ የመኳንንት ታማኝ አሽከር፣ ጋሻና ሰይፍ ያዥ፣ ተሸካሚ። (ለምሳሌ: ጋሻ ዣግሬ፣ ሰይፈ ዣግሬ እንዲሉ) (፩ኛ ነገሥት ፲፡ ፴፩፡ ፬፡ ፭፡ ፮)

ዣግሬ: የዣግር፣ ባለዣግር።

ዣግሬዎች/ዣግሮች: ተሸካሞች። (ጋሻና ሰይፍን እይ)

ዣግር: የተሸከመ፣ የሚሸከም (ዣግር፣ ዘገር፣ ንዋየ፣ ሐቅል)

ዥለጣ: ረገጣ፣ ዝቅዘቃ።

ዥልጥ: የተዠለጠ፣ የተረገጠ፣ በትክክል ያልተቀመጠ።

ዥመራ/ዥማሬ: ፈለማ፣ ቀደማ፣ የመዠመር ሥራ።

ዥማታም: ከሲታ፣ ክሥዳው የሚታይ ሰው፣ ከብት።

ዥማት (ብዙ ቁጥር: ዥማቶች): ዐጥንትንና ሥጋን ከእግር እስከ ራስ የሚያያይዝ የደም ሥር። (በግእዝ መትን ይባላል፡ ውስጠ ክፍት ነው) (ኤፌሶን ፬፡ ፲፮)

ዥማት: የአንዠት ክር ለክራር፣ ለበገና፣ ለደጋን የሚሆን።

ዥምራት: ውጥናት።

ዥምር (ብዙ ቁጥር: ዥምሮች): የተዠመረ፣ ውጥን፣ ፍልም።

ዥምባዥምቦ: ርዳ፣ ተራዳ፣ ፊትና ኋላ ኹኖ የሚያዝ የሳንሳ ሸክም።

ዥምገጋ: ሽምጠጣ፣ ሽምጣጦ።

ዥምግ: የተዠመገገ፣ ሽምጥጥ፣ መናኛ ፈትል።

ዥረት (ትግርኛ: ሐባ፣ ዘራት): ፈሳሽ። አሸዋ፣ ጅጀት ያለበት ዠማ፡ ታላቅ ወንዝ፣ ፈሳሽ። (ሲበዛ ዥረቶች ይላል)

ዥራሮ/አዥራሮ: ውሃ የበዛበት መጠጥ ወይም ወተት። (ተረት: "ምን ሲል ተዠምሮ ያጓት አዥራሮዞ")

ዥራሮ/አዥራሮ: ውሃ የበዛበት መጠጥ ወይም ወተት። (ተረት: ምን ሲል ተዠምሮ ያጓት አዥራሮዞ)

ዥራተ ቀጪን: ዥራቱ የቀጠነ፣ ቀጪኔ።

ዥራታም ኮከብ: ዥራት ያለው፣ ባለ ዥራት ኮከብ። አንዳንድ ዘመን ራሱ ወደ ምዕራብ፣ ጭራው ወደ ምሥራቅ ኹኖ እየወጣ የሚታይ።

ዥራታም: አውጭ፣ ሬሳ በል (ጋሎች አዋል ዲጌሳ (መቃብር አፍራሽ) ይሉታል) ረዥም ዥራት ያለው፣ ባለ ዥራት (አውሬ፣ እንስሳ፣ ወፍ፣ እንክርዳድ)

ዥራት (ዘራት): ዘለብ። በተንቀሳቃሽ ገላ ሁሉ በራሱ በማዥራቱ አንጻር ያለ ሹል የአካል ፍ፡ ግንዶሹ፣ ሶለጉ፣ ጭራውም ባንድነት ዥራት ይባላል (ዘዳግም ፳፰፡ ፲፫፡ ራእይ ፱፡ ፲፡ ፲፱)

ዥራት አንጓ: የዥራት ሥር፣ ዐጥቅ፣ መብቀያው፣ መጋጠሚያው፣ መገናኛው፣ ከሬ።

ዥራትማ : በተጕለት ውስጥ በሁለት ወንዝ መካከል ያለ ሾጣጣ፣ ሞጥጣ ቀበሌ። ወንዞቹም ሱላይና ጋዱ (አይሠራውም) ናቸው።

ዥራትማ: የበረሓ ጐሽ። (በግእዝ ዘራት ይባላል) (ዘዳግም ፲፬፡ ፭)

ዥራፍ: መግረፊያ (ጅራፍ)

ዥራፍ: መግረፊያ (ጅራፍ)

ዥበራም: ዥበረ ትልቅ ሰው፣ ከብት፣ ሽንጣም።

ዥበር (ብዙ ቁጥር: ዥበሮች): የሽንጥ ዐጥንት፣ ወገብ።

ዥበር አንጓ: የዥበር አንጓ፣ ልዩ ልዩነት ያለው የሽንጥ የወገብ ዐጥቅ አከርካሪ። (ዥራትን ተመልከት)

ዥቡ: ዥብ።

ዥባም: ዥብ የበዛበት ስፍራ።

ዥብ (ዝእብ): የእንስሳ ስም፡ የውሻ፣ የድብ፣ የተኵላ፣ የቀበሮ ዐይነት፡ ጥንብ የወደቀበትን በማሽተት ዐውቆ ወገኖቹን የሚጠራ አውሬ፣ በዱር የሚኖር፣ ያህያ ጠላት።

ዥብ አፍ: በቤት መግቢያ ጣራ ጫፍ ላይ ያለ ተጨማሪ ሰቀላ።

ዥብ አፍ: አፈ ሰፊ ሰው።

ዥብ ኦሮቢ (ብዙ ቁጥር: ዥብ ኦሮቦች): አስማተኛ፣ ምትሀተኛ ሰው በዥብ የሚጋልብ።

ዥብማ: ዥብ የሚመስል፣ መልከ ዥብ እንስሳ።

ዥብሪ: የአሞራ ስም። በጥላው የከብትን ዥበር የሚሰብር አሞራ። ዐይኑ ሲያዩት የሚያዥበረብር፣ አፉ ቀይ፣ ክንፉ በስተላይ ጥቍር፣ በስተውስጥ ነጭ የሆነ። ጯኺ፣ ድምፁ ረዥም፣ ጩኸቱ እየር የሚመላ። (ዘበረ፣ ዘባሪ ከማለት የወጣ ይመስላል)

ዥብነት: ዥብ መኾን።

ዥቦ ወልደ ሥላሴ: አራቱን ጉባኤ የሚያውቁ ያንኮበር ሊቅ።

ዥቦ: እግር ብረት በመዶሻ (ባሎሎ) የሚመታ፣ በሞረድ ተፈግፍጎ የሚፈታ፡ ሊሰብሩት የማይቻል ማሰሪያ።

ዥቦች (አዝእብት፣ ዝእባት): ብዙዎች የዱር አውሬዎች፣ ተባቶችና እንስቶች፣ አህያ ፈጆች።

ዥቧ: ያች ዥብ።

ዥንጐዶ: በተጕለት ውስጥ ያለ አገር። (የጅን ዋሻ ማለት ይመስላል)

ዥዋት: መራራ ቅጠል።

ዥዋዥዌ: ጢሎሽ።

ዥው አለ : ሰተት አለ ለመግባት።

ዥው አለ : ቀጥ ብሎ በቀጥታ ወዲያ ወዲህ ሳይል ኼደ።

ዥው አለ: ገደል ገባ፣ ድምፁ ተሰማ።

ዥው አደረገ: ሰመጠጠ፣ ስምጥጥ አደረገ፣ ባንድ ትንፋሽ ጨለጨለ።

ዥው ያለ ገደል: ዕልም ያለ፣ መያዣ መጨበጥ የሌለው።

ዥዡ: የዣዠ፣ ዠብራራ፣ ልጡ የተራሰ፣ ሰሌኑ፣ የተደገሰ፣ ጕድጓዱ የተማሰ።

ዥጕርጕር (ብዙ ቁጥር: ዥጕርጕሮች): የተዥጐረጐረ፣ ዝንጕርጕር፣ ነብርማ (የነብር ዐይነት ከብት ወይም ሌላ ነገር፣ ዕቃ፣ ቀለም)

ዥጕድጕድ: የተዥጐደጐደ፣ ብዛት ያለው።

ዥግል (ትግርኛ): የሰው፣ የውሻ ጨብጥ። (ጅግል ተብሎ ቢጻፍ ግን ድግልነቱንና ዕብጠትነቱን ያሳያል)

ዥግሪቴ: የኔ ዥግራ። (ለምሳሌ: ዥግሪቴ ዥግሪቴ ዐመለ ደኅኒቴ እንዳለ እረኛ)

ዥግሪት : የጨሌ ጥብቆ። (ዥግራዊት ዥግራ መሳይ ማለት ነው)

ዥግሪት: እንስት ዥግራ።

ዥግራ (ብዙ ቁጥር: ዥግሮች): የዱር፣ የበረሓ ጠቃጠቅማ ዶሮ፣ የቆቅ ወገን፣ ሥጋው የሚበላ።

ዥግርማ: የዥግራ ዐይነት ጠቃጠቋም ዶሮ።

ዥግርግር: የተዥገረገረ፣ አንድ ዕቃ።

ዦር: ከምንጭ ቀጥሎ ያለ የውሃ መፍሰሻ፣ መጠራቀሚያ፡ ድልድል። (እንዦሪ ማለት ከዚህ የወጣ ነው)

ዦርድልድል: ዠረረ።

ዦሮ ለዦሮ: ቅርብ ለቅርብ፣ አጠገብ ላጠገብ።

ዦሮ ቈራጭ: በአጕስ የልጆች ማስፈራሪያ።

ዦሮ ቈራጭ: ባጕስ የልጆች ማስፈራሪያ።

ዦሮ ዐጋሚ: እንደ ዦሮ ጠቢ። ወሬን በዦሮ የሚስብ፣ የሚያግም፣ ሰብቀኛ።

ዦሮ ዐጋሚ: ዝኒከማሁ ለዦሮ ጠቢ። በዦሮ ወሬን የሚስብ፣ የሚያግም፣ ሰብቀኛ።

ዦሮ ደግፍ: በዦሮ ሥር ይበቅልና ዦሮን የሚደግፍ የዕብጠት በሽታ።

ዦሮ ግንድ (የዦሮ ግንድ): ዦሮ የበቀለበት፣ የተተከለበት ገላ፣ ሥሩ፣ መሠረቱ።

ዦሮ ጠቢ: አሳባቂ። ሰው ሲናገር ነገርን ሁሉ በዦሮው የሚጠባ (የሚሰማ) በዦሮ ሹክ የሚል (ምሳሌ ፳፮፡ ፳-፳፪)

ዦሮ: ምነው አታድግ ቢሉት፡ ጕድ እየሰማኹ በየት ልደግ አለ።

ዦሮ: በሰውና በእንስሳ፣ በአራዊትና በአዕዋፍ ራስ ግራና ቀኝ የተተከለ የመስማት ሕዋስ። የማያድግ የዐይን ጓሮ።

ዦሮ: የመርፌ ቀዳዳ (ሉቃስ ፲፰፡ ፳፭)

ዦሮ: የዠረረ ዘር ነው። ይኸውም የቃል፣ የነገር መፍሰሻ መሆኑን ያሳያል። (ዦርን ተመልከት)

ዦሮ: የጋን፣ የንስራ፣ የገንቦ፣ የዳብሬ፣ የማሰሮ፣ የድስት፣ የሌላውም ሸክላ ወይም ዕቃ መያዣ ቀለበት።

ዦሮዎች/ዦሮች: ሁለትና ከሁለት በላይ ያሉ ብዙዎች (ኢሳይያስ ፵፰፡ ፰)

ዦሯም: መጨበ ያለው የብረት፣ የንጨት ዕቃ።

ዦቴ: ሐበሻ።

ዦዠ (ዣዠ): ዘነጋ፣ ረሳ፣ እንደ ሕፃን ሆነ። ማር ሲሰጡት ወተት፣ ወተት ሲሰጡት ማር አለ ከርጅና ብዛት የተነሣ። (ዣዠ (ዣዣ) ዦዠ አንድ ዘር ናቸው)

ዦፌ: አሞራ (ጀፈጀፈ)

መንዧ አለ (ዛሕዝሐ): እንደ ልቡ ሆነ፡ በገፍ ሰጠ፣ ለገሰ፣ ቸረ።

አለ (ትግርኛ: ዘውሐ፡ አፈሰሰ): ዘነበ፣ ፈሰሰ፣ በዝቶ ወረደ፣ ተበተነ።

: (ዘዊሕ) መዝነብ፣ መፍሰስ፣ መበተን።

No comments:

Post a Comment

ሽፋን

  ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ