ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ጰ ፡ የበ ዲቃላ
በግእዝ አልፍቤት በአበገደ ተራ ቍጥር ፳፩ኛ ፊደል ። ጰን ፳፩ኛ ማለት ከታች የጠን ፱ኛነት ለኀ የቀኝ ፲፱ኛነት ለጸ ሰጥቶ
በማፌጋፈግ መኾኑን አስተውል ። በፊደልነት ስሙ ጰይት አኃዝ ሲኾን ጳ ፯፻ ይባላል ።
ጰ ፡ በበና በፐ ፈንታ ይነገራል የኹለቱም ተወራራሽ ነው” ። መዝገበ ፊደል" ተመልከት ።
ጰራቅሊጦስ (የመንፈስ ቅዱስ ቅጽል): "መጽንዒ"፣ "መንጽሒ"፡ የሚያጸና የሚያነጻ ማለት ነው። አማላጅ፡ አስታራቂ። (ዮሐ ፪)።
ጰንጠቈስጤ ትርጉም: ከትንሣኤ እስከ ጰራቅሊጦስ ያለው ዐምሳ ቀን።
ጰንጤናዊ: የጴንጤን ተወላጅ (ነው)።
ጲላጦስ: በጌታችን ጊዜ ኢየሩሳሌምን ይገዛ የነበረ የካም መንግሥት።
ጳልታን ትርጉም: የርኩምና የመረቡ ዓይነት። (ዕብራይስጡ) ማብራሪያ: መያዣ ከረጢት ያለው። (የውዳሴ ማርያም ተርጓሚዎች) የአዳምን መከራ የተቀበለ የጌታችን ምሳሌ ያደርጉታል። (ፈረንጆችም) ፔሊካን ይሉታል። የጥርስ ሐኪም መማሪያም በርሱ ስም ይባላል።
ጳኵሚስ: በምንኩስና ለእንጦንስ የተስፋ ቃል የሆነ ጻድቅ።
ጳውሎስ (የሰው ስም): አስቀድሞ መምህረ ኦሪት የነበረ፡ ኋላም መምህረ ወንጌል የሆነ፡ ቁጥሩ ከአርድእት ሲሆን ማዕርጉ እንደ ጴጥሮስ ነው። (ከዚህ የተነሣ) የአገራችን ሰዎች "ጴጥሮስ ጳውሎስ" የሐዋርያት አለቆች ይሏቸዋል።
ጳጕሜ (የወር ስም): ፲፫ኛ ወር፡ ተረፈ ዓመት። በነሓሴ መጨረሻ በ፫ ዓመት ፭ ቀን፣ በአራተኛው ዓመት ግን ፮ ቀን ይኾናል። (ትርጓሜው) ጭማሪ ማለት ነው።
ጳጳስ (ሶኻ): ቄስ፡ ካህን፡ የሚሠልስ፡ የሚተያስ። (ቲቶ ፩፡ ፩ጢሞ ፫፡ ፩)። "ጳጳስ" ከጽርእ "ፓስ" (እረኛ) ማለት ነው። የቤተ ክርስቲያን አባት፡ ማዕርጉ ከሊቀ ጳጳሳት በታች፡ ከኤጲስቆጶስ በላይ የኾነ አቡን።
ጳጳስ ኤጲስቆጶስ: የጠቅላይና የውራ ግዛት አቡኖች፡ የሃይማኖት አባቶች።
ጳጳስነት: ከጵጵስና ጋር ተመሳሳይ ነው።
ጴጥሮስ ጳውሎስ (የታቦት ስም): በጴጥሮስና በጳውሎስ ስም የተቀረጸ ጽላት። (ይከም በሐምሌ ፭ ቀን በአያመቱ ይገባሃል)።
ጴጥሮስ: ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ፡ አለቃቸው። ጌታ ከትንሣኤ በኋላ "በጎቼን ጠብቅ" ብሎ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሾመው። "ጴጥሮስ ኰኵሓዊ" ማለት "አለታዊ" ማለት ነው ይላሉ። ኰኵሕ የተባለም ክርስቶስ ነው።
ጵጰሳ: ከላይ ካለው ጋር ተመሳሳይ።
ጵጵ: የከንፈር ድምፅ።
ጵጵስና: ጳጳስ መሆን።
ጶያት (የፊደል ስም): "ጳ ቤት" ማለት ነው።
No comments:
Post a Comment