ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ፈለል፡ ዝኒ ከማሁ (የሠባ ") ።
ፈላሽ፡ አፍላሽ ።
ፈላቂ (ጥል)፡ የሚፈልቅ (ሠንጣቂ ቀዳጅ ") ።
ፈከክ፡ የፈከከ/የተራራቀ ።
ፉን፡ ከንፈረ ሥንጥቅ ።—ፎነነ ። ፊና/ፍና (ፈነወ)፡ መንገድ ስፍራ በኩል ወገን አንጃ ሚና ጐራ ። "ፍናዋትን" ተመልከት፡ የ "ፍና" ብዢ ነው ።
ፉን፡ ፈነዳ፡
ፋዳ፡ ዐንገታም ዓሣ ።
ፍልቅ፡ የተፈለቀ/የተቀደደ (ቅድ ሥን ጥቅ ") ።
ፍርቅ፡ የተፈረቀቀ (የራቀ - ፍንቅል ሥን ጥቅ ") ።
ፍጥም (ፍጹም/ፍፁም)፡ የተፈ ጠመ ያለቀ የተወረሰ (ዝግ ") ።
ፈ ፡ ፲፯ኛ ፊደል በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ ተራ ቍጥር ። በፊደልነት ስሙ ፈፍ (በአኃዝነት ፈ ፹ ይባላል ") ።
ፈ፡ የመ ተወራራሽ ። "ፈነጪ መነጨ፡ ፈለሰመ ፈለሰፈ፡ ፊና ሚና" ።
ፈ፡ የፐ ተለዋጭ ። "ፋናን" ተመልከት ("ኰረብታን" እይ ") ።
ፈለለ፡ ወፈረ ደነደነ ሠባ (ተከፈለ ተ ለየ ") ።
ፈለለ፡ ፈለፈለ፡
ፈለል ፈለል አለ፡ እለይ እለይ አለ (ድልብኛ ገችኛ ኼደ ") ።
ፈለመ፡ ቀደመ ዠመረ (ከሌሎች በፊት መታ ወጋ ኣቈሰለ፡ በጥይት በጦር አንበ ሳን ዝኆንን ጐሽን አውራሪሥን ግስላን ") ።
ፈለማ፡ ቅድሚያ ዥመራ ።
ፈለሰ (ፈሊስ/ፈለሰ)፡ ተናደ ተፈነ ቀለ ነገለ ተነቀለ ወጣ (ወደ ባዕድ አገር ኼደ ተሰደደ - ፪ነገ. ፲፯፥ ፳፫፡ ዓሞ. ፩፥ ፭) ።
ፈለሰ፡ ታደሰ ተለወጠ ("(ተገብሮ)") ።
ፈለሰ፡ አፈለሰ መነቀረ እፈረሰ ("(ገቢር)") ።
ፈለሰ፡ ፈለሰፈ፡
ፈለሰመ፡ ፈለሰፈ ።
ፈለሰሰ)፡ አንፈላሰሰ፡ አጋደመ አስተኛ (አንከባለለ አገላበጠ - በቅርብ ") ።
ፈለሰሰ)፡ ፋመ፡
ፈለሰስ/ፈልሳሳ፡ ዝኒ ከማሁ (የተ ንፈላሰሰ እንዳፈቀደው የሚተኛ ") ።
ፈለሰፈ፡ ጠበበ አራቀቀ ሥጋዊ ጥበ ብን ዕውቀትን ብልኀትን ፈተነ መረመረ (ግ ብር እምግብር ከወነ ") ። ስልክን ራዲዮንን መርከ ብን ሱማራን ባቡርን ኦቶሞቢልን አይሮ ፕላንን ታንክን (የንጨት የብረት የሸክላ ") ።
ፈለቀ (ፈሊቅ/ፈለቀ)፡ መነጨ ወጣ ፈሰሰ " እከሌ አምልኮ ባዕድ ስለሚ ወድ ዛር ፈለቀበት፡ ወጣበት ።
ፈለቀ፡ ሰረቀ ብልጭ አለ (በራ እን ጸባረቀ ") ። "በምሥራቅ በኩል ሰማዩ ይፈል ቃል (ይበርቃል) (ተገብሮ)" ።
ፈለቀ፡ በጥቂቱ ቀደደ ሠነጠቀ ("(ገቢር)") ። "ፈለቀ" የሚነገረው ለቀሚስና ለጥብቆ ዐን ገት ማግቢያ ነው ። "ፈለገን" ተመልከት ።
ፈለቀ፡ የወንድ ስም ።
ፈለቀቀ (ፈለቀ/ለቀቀ)፡ ኣፍታታ ለየ (በተነ የጥጥን ፍንድ በጣት ") ።
ፈለቀቀ፡ ኣላላ ከፈተ ። "እስረኛው የሰ ንሰለቱን ፍንጅ ፈለቀቀና አመለጠ" ። "ፈረቀቀን" አስተውል ።
ፈለቀጠ፡ ፈለሰ፡
ፈለቀጠ፡ ርጥብ ፍሬን ከፈለ ።
ፈለቄ፡ ፈለቀች (የሴት ስም ") ።
ፈለከ (ፈለክ/ሰማይ)፡ ጠረበ አጐ ደጐደ ። "ፈለቀን" - እይ ።
ፈለገ (ፈሊግ/ፈለገ)፡ ሻ ፈቀደ " ("(ዘፀ. ፲፪፥ ፴፭)") ።
ፈለገ፡ ከፈለ አነተበ ሠነጠቀ ።
ፈለጋም፡ እግሩ ፈለግ ያለበት (የበዛ በት ሰው ") ።
ፈለግ፡ መካከሉ የተከፈለ የፍየል ጥ ፍር ሰኰና ። "ፍየል ፈለግ" እንዲሉ ። በግእዝ ግን ወንዝ ማለት ነው ። "ፍየልን" እይ ።
ፈለግ፡ የነተበ የተላጠ የተሠነጠቀ (የተረከዝ ቈዳ = አለመጫሚያ ስለ ኼድኩ እግሬ ፈለግ አወጣ ") ።
ፈለጠ (ፈሊጥ/ፈለጠ/ፈለጸ)፡ ሠነ ጠቀ ሠነጠረ ፈነከተ ተረከከ ሰበረ ሸነሸነ ። "ለየን ወለለን ከፈለን" ተመልከት ።
ፈለጠ፡ ቀደደ ተረተረ ። "(ተረት)" - ባልን ጀራዬ ሲበልጠኝ ቍንጣን ይፍለጠኝ ።
ፈለጠ፡ ዐወቀ ዘየደ ።
ፈለጠ፡ ፈለከ፡
ፈለጣ፡ የመፍለጥ ሥራ (ሥንጠቃ ሽን ሸና ") ።
ፈለፈለ (ፈልፈለ/መነጪ)፡ ማሰ ፈረፈረ መሬትን ።
ፈለፈለ፡ ቀረጸ ሰረሰረ በሳ ነደለ ዕን ወትን ።
ፈለፈለ፡ እሸትን ከንቡጥ ጫጩትን ትልን ከንቍላል ቀፈቀፈ አወጣ (ረባ ብዙ ወለደ ") ።
ፈለፍል፡ እግርን፡ በነከሰች፡ ጊዜ፡ አለመጠን' የምታንገበግብ፡ የምታሳክክ፡ የሰነፍን፡ ሰው፡ እግር፡ ጣት፡ የምትቈምጥ። (ግጥም); እመት፡ ሞያሊት፡ ተይ፡ አገርሽ፡ ግቢ፡ የጩዋን፡ ልጅ፡ ኹሉ፡ ዘር፡ አታሰድቢ። እኔና፡ ሞያሌ፡ ያመጣነው፡ ፍቅር፡ አጋም፡ እሾኸ፡ ይዞ፡ ምንቅርቅር፡ ምንቅርቅር።
ፈሊጠ ቢስ፡ ፈሊጠ መጥፎ (ፈሊጥ የሌለው ") ።
ፈሊጠኛ፡ ፈሊጥ ዐዋቂ ባለፈሊጥ ዘ ዴኛ ።
ፈሊጥ፡ ዕውቀት ዘዴ ቃንጤ ። "ዐዲስ ፈሊጥ አመጣ፡ በፈሊጥ ተናገረ" እንዲሉ ።
ፈሊጥ፡ ዘዬ ። "ውሻ ያገኘው ሊጥ፡ ሞኝ ያገኘው ፈሊጥ" ' እንዲሉ ።
ፈላ (ፈልሐ)፡ ተፍለቀለቀ ተንተከ ተከ (ጠላው ጠጁ ውሃው ቡናው ") ። "(ተረት)" - ተጥዶ የማይፈላ፡ ተሹሞ የማይበላ ።
ፈላ፡ መነጩ ፈለቀ ("(ዘዳ. ፰፥ ፯፡ ሕዝ. ፵፯፥ ፪)") ።
ፈላ፡ በቀለ ሽፍ አለ ችግኙ ።
ፈላ፡ በብዛት ወጣ (ጕንዳኑ ምሥጡ ዘመሚቱ ዐሸኑ ") ።
ፈላ፡ እሳት መሰለ ጋለ ። "(ተረት)" - ብረት ካልፈላ አይላላ ።
ፈላለገ፡ ፈቃቀደ ።
ፈላለጠ፡ ሠነጣጠቀ ሸናሸነ ።
ፈላላ፡ የፈለለ (ወፍራም ደንዳና' ሥብ ጐነ ሰፊ ") ።
ፈላሚ (ዎች)፡ የፈለመ/የሚፈልም (ቀዳሚ ዠማሪ ") ።
ፈላስማ፡ ፈላስፋ ።
ፈላስፋ (ፎች)፡ አስተዋይ ብልኅ ዐ ዋቂ ባለአእምሮ ተራቃቂ (የዓለማዊ ጥበብ መሪ አስተማሪ ኮከብ ቈጣሪ - ይህ ይኾናል ይህ ይመጣል ብሎ ተናጋሪ ") ። ባላገርም "ፈላስማ" ይላል ።
ፈላስፋ ኾነ፡ ዐወቀ ተራራቀ ።
ፈላስፋ፡ ዓለም ዐላፊ ጠፊ መኾኑን ስላወቀ ከሰው ተለይቶ በበኣት (ዋሻ) ተከቶ ድንጋይ ተንተርሶ ዳዋ ለብሶ ቤዛ ልሶ የሚኖር (ሔኖክን ኤልያስን ቡዳሃን ዲዮጋንስን አቢብን እንጦንስን ማር ይሥ ሐቅን የመሰለ እውነተኛ ባሕታዊ መንፈ ሳዊ ዕውቀት ማስተዋልና ጥበብ ያለው መናኝ መነኵሴ ግሑሥ ") ።
ፈላስፋነት፡ ፈላስፋ መኾን ።
ፈላሻ፡ ካገሩ ከወገኑ ተሰዶ በባዕድ አገር የሚኖር ስደተኛ (የአይሁድ ዘር፡ ባ ለጅ ሠራተኛ ") ። ይኸውም በአብርሀ አጽብሐ ጊዜ ጥምቀትን ያልተቀበለ ነው ።
ፈላሻነት፡ ፈላሻ መኾን (ስደተኛነት ") ።
ፈላሽ (ፈላሲ)፡ የፈለሰ/የሚፈልስ (ነጋይ ተነቃይ ") ።
ፈላሾች (ፈላስያን)፡ ስደተኞች ጠይ ቦች ባለጆች ።
ፈላሾች፡ በግዜር በኦሪት አምነው እስራኤልን ተከትለው ከፋርስ ከባቢሎን የወጡ አሕዛብ ("(ሕዝ. ፵፯፥ ፳፪)") '
ፈላቂ፡ የፈለቀ/የሚፈልቅ (በራቂ ") ።
ፈላጊ (ጎች)፡ የፈለገ/የሚፈልግ (የሚሻ ") ። "ነገር ፈላጊ" እንዲሉ ።
ፈላጭ (ጮች)፡ የፈለጠ/የሚፈልጥ (ሠንጣቂ ሸንሻኝ ") ።
ፈላጭ ቈራጭ፡ የሚፈልጥ/የሚቈርጥ ። "ቈራጭ ፈላጭ ቢል"፡ "የሚቈርጥ የሚፈልጥ ንጉሥ ባለወግ ማለት ነው" ። ፈላጭ፡ "ሰውን ከግንባሩ እስከ መጋፊያው" ።
ፈላጭነት፡ ፈላጭ መኾን ።
ፈልሰስ ፈልሰስ አለ፡ ገልበጥ " ገ ልበጥ አለ ።
ፈልሳፊ፡ የፈለሰፈ/የሚፈለስፍ (ጠባቢ አራቃቂ ") ።
ፈልቃ፡ ሣቂታ ሴት (ሥቃ የምታሥቅ ") ።
ፈልቃቂ፡ የፈለቀቀ/የሚፈለቅቅ ።
ፈልቅ፡ ብራቅ ከመታው መሬት የ ሚገኝ የመብረቅ ብረት፡ ማግኔት ። ጋሎች ከሌቻ ይሉታል ።
ፈልፈላ (ፋል)፡ ርት የተደፈነ " ሥ ራሥር ዕንቍላል ።
ፈልፈላ፡ ፈለቀ፡
ፈልፈልቱ፡ ምድር ምሶ ክፉ መድኀ ኒት የሚቀብር ርተኛ ሰው ። "ፈልፈላ ፈልፈልቱ ሥሩ በግእዝ ፋል ሲኾን በጋልኛ ይነገራል፡ ባማርኛም ተለምዷል" ።
ፈልፋይ (ዮች)፡ የፈለፈለ/የሚፈለፍል (ዕንቍላል ያለው ፍጥረት አንበጣ፡ ወላድ ሰው ") ።
ፈሎ ቢስ፡ ርባና ቢስ ።
ፈሎ፡ ፋይዳ ረብ ጥቅም ትርፍ ።
ፈሰ ከንቱ (ቲ)፡ የፈሱ ሽታ ራስ የሚበጠብጥ (ሆድ የሚቈርጥ የሚያም ቍና ሳም ") ።
ፈሰለቀ)፡ አንፈሳለቀ/አንፈላሰሰ፡ አ ላጋጭ አደረገ ።
ፈሰሰ (ፈሲስ ፈሰ)፡ ተደፋ ተቸ ለሰ ተከነበለ ወረደ ተዘቀዘቀ (ኮለል አለ ") ።
ፈሰሰ፡ ተነገረ ። "ኑዛዜው ፈሰሰ" እንዲሉ ።
ፈሰሴ (ፈሰሳዊ)፡ ባገር ላይ የተጣለ ዕዳ መቻያ (ባላገር አዋጥቶ ላገረ ገዢ የሚ ከፍለው ") ("(፪ ነገ. ፳፫፥ ፴፫፡ ፪ ዜና. ፴፮፥ ፫)") ።
ፈሰሴ፡ የሽንብራ ቂጣ ኩፍታ (የሊጡን በምጣድ ላይ መፍሰስ ያሳያል ") ።
ፈሰስ አለ፡ ፈሰሰ (ዟ ሰተት አለ ሰውየው ") ።
ፈሰስ አደረገ፡ ፍልቅ ጠብ አደረገ ።
ፈሰስ ከንበል አለ፡ ድፍት ውድቅ አለ ።
ፈሰስ፡ ከጣራ የፈሰሰ የዝናም ውሃ ከአጥር ግቢም ተሰብስቦ በግንብና በግድግዳ ሥር የሚፈስ "ፈሰስ" ይባላል ።
ፈሰስ፡ ዝኒ ከማሁ (ለ "ፈሳሽ ") ። "ካናት የፈ ሰስ እስከ እግር ድረስ" እንዲሉ ።
ፈሰከ፡ ጦምን ተወ ገደፈ ሥጋ በላ ። "ፈሰገ" የሕዝብ፡ "ፈሰከ" የካህናት ዐማርኛ ነው ።
ፈሰገ፡ ፈሰከ ።
ፈሰፈሰ (ትግ. ፈስፈሰ - ዞረ)፡ አስ ፈራራ (በክርን መታ ደበደበ አስፈሳ ") ። "ዘሩ ፈሰሰ" ነው ።
ፈሰፈስ/ፈስፋሳ፡ የተፈሰፈሰ (ፈሳም ፈሪ ወስዋሳ ዘዋሪ ") ።
ፈሱን ቀደደ)፡ ፈሳ ላጥ አደ ረገ ። "ጎሕን" አስተውል ። "የጊዜና ኀላፊ ትንቢቱም ይቀድ፡ ይቀዳል እያለ ጠብቆ ይነገራል እንጂ፡ ይቀድድ፡ ይቀድዳል አይልም፡ ቢልም ስሕተት ነው" ።
ፈሲታ፡ የፈሳች ።
ፈሳ (ፈሰወ - ዐረ. ፈሳ)፡ በታች ተነፈሰ (ፈሱን ለቀቀ - ዘረጥ አደረገ - አንጣረረ ") ።
ፈሣ (ፈሥሐ)፡ ተደሰተ ። የካህናት ዐማርኛ ነው ።
ፈሳ፡ ሸሸ (የቅል የቀይ ሽንኵርት ") ።
ፈሳ፡ ብብቱን በመዳፉ ዐፍኖ እንደ ቂጥ አስጮኸ ።
ፈሳ፡ የተማረውን ረሳ ዘነጋ አጠፋ ዐጣ ።
ፈሳም (ሞች)፡ ኹል ጊዜ የሚፈሳ የሚያንዛርጥ (ፈሱን የማይቋጥር ፈሪ ") ።
ፈሳሽ (ሾች)፡ የፈሰሰ/የሚፈስ (ወ ራጅ ቀላጭ - ውሃ ሠም ዘይት ቅባት ዐረቄ ደም፡ የመሰለው ኹሉ ") ("(ኢሳ. ፵፬፥ ፬፡ መዝ. ፩፥ ፫፡ ኢሳ. ፲፱፥ ፮፡ ሕዝ. ፴፪፥ ፪)") ። "የግዜር ቃል እንደ ውሃ ፈሳሽ እንደ እንግዳ ደራሽ አይዶለም፡ ከጥንት ካባቶች ሲያያዝ ፥ የመጣ ነው እንጂ" ። (ተረት)፡ "የተጠማ ከፈሳሽ፡ የተበደለ ከነጋሽ" ።
ፈሳሽቱ፡ ያች ፈሳሽ (ውሃዪቱ ") ("(ኤር. ፲፰፥ ፲፬)") ።
ፈስ (ፈስው)፡ ታችኛ ትንፋሽ (ግም ያይነ ምድር ወላፈን ") ።
ፈስማ፡ ፈሶሌ ።
ፈስንዱስ፡ ዝኒ ከማሁ ። "ፈሱን ዱስ አደረገ" (በወፍራሙ ፈሳ ") ።
ፈሶሌ፡ ተበጣሽ ጠፍር ገመድ ልጥ ፈትል ("ፈስማ ") ።
ፈረመ (ፈፀመ፡ ዘጋ)፡ በደብዳቤና በውል በስምምነት በስሌት በማንኛውም ጽፈት መጨረሻ "ፈቅጃለኹ ልክ ነው" ሲል ስሙን ጻፈ፡ ምልክት አደረገ ("ዐተመ") ።
ፈረመ፡ ፈለመ ወጠነ (ሥራን በትጋት በጥራት ") ።
ፈረሰ (ፈሪስ ፈረሰ)፡ ተናደ ወደቀ ጠፋ ተበላሸ ተቈመጠ ተሻረ (እንዳልተሠራና እንዳልነበረ ኾነ ") ።
ፈረሰ እሳት፡ ከእሳት የተፈጠረ የእሳት ፈረስ ("(፪ ነገ. ፪፥ ፲፩)") ።
ፈረሰ፡ ተበተነ ተዘረዘረ (ዱለቱ ሤራው ሸንጎው ") ።
ፈረሰ፡ ጋለበ ነጐደ (ወጣ ወረደ ") ("(ኪ. ወ. ክ.)") ።
ፈረሰ፡ ፈነዳ ። "ልቡ ፈረሰ" እንዲሉ ።
ፈረሰኛ (ኞች)፡ በፈረስ ተቀምጦ የሚጋልብ (ግልቢያ ዐዋቂ ") ።
ፈረሰኛ፡ በሰልፍ ኹኖ እንደ ፈረስ እየዘለለ የሚኼድ (ፈረስ የተቀመጠ የሚ
ፈረሰኛ፡ የዶሮ ፍርንባ ።
ፈረሱ፡ ያ ፈረስ (የርሱ ፈረስ ") ።
ፈረሱላ፡ ከርሳስ የተበጀ የሚዛን ጕ ልቻ (የዝኆን ጥርስ የቡና የቈዳ መመዘኛ ") ። አንዱ ፈረሱላ በኪሎ 17 በነጥር 20 ይኾ ናል ። በአረብኛ "ፈራሲላ" ይባላል ።
ፈረሳቤት (አቤት ፈረስ)፡ ንኡስ አገባብ (የሐዘንና የአንክሮ ቃል ") ። "አቤት ፈረሱ ምንኛ ድንቅ ነው" ማለት ነው ።
ፈረሳቤት፡ የዕከክ ስም (በሙሉ ጨ ረቃ ማታ ማታ የሚያሳክክ ቀን የሚጠፋ ዕከክ ") ። ፪ኛም ደመ መራሪት ይሉታል ። ፫ኛም የፈረስን ገላ ስለሚያለብስ "ፈረሳቤት" ተባለ ።
ፈረስ (ሶች)፡ ከቤት እንስሶች አንዱ ! የጋማ ከብት ሰው በዠርባው ኮርቻ ጭኖ የሚቀመጥበት ። ተባቱም እንስቱም ፈረስ ይባ ላሉ ። ኹለቱን ለመለየት ብትፈልግ፡
ፈረስ መፈተኛ)፡ ሜዳ ።
ፈረስ ዘበኛ፡ የፈረስ ዘበኛ (የባልደ ራስ ጭፍራ የንጉሥ ፈረስ ጠባቂ ") ።
ፈረስ፡ ከሰንጠረዥ መጫወቻ አንዱ፡ ይኸውም የፈረስ መልክ ያለው ነው ።
ፈረሷ/ፈረሲቱ፡ ያች ፈረስ ።
ፈረሷ፡ የርሷ ፈረስ ። (ተረት)፡ "ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም።" "ባዝራንና ድንጕላን" ተመልከት ።
ፈረረ (ትግ. ሐባ)፡ ፊር አለ ። "ፈነነን" እይ ።
ፈረቀ (ፈሪቅ ፈረቀ)፡ ለየ ከፈለ ። (ፈረከ)፡ ከዚህ የወጣ ነው ።
ፈረቀቀ (ፈረቀ)፡ ፈነቀለ ፈለቀቀ ሠ ነጠቀ ለያየ "
ፈረቃ፡ የሥራ የሸክም የጥበቃ ተራ ፈንታ ። "ወታደሮች በፈረቃ ዘብ ያድራሉ።"
ፈረነሰ (ግእዝ - ፈርነሰ)፡ አስተኛ አ ጋደመ ዘረረ ፈነደሰ ።
ፈረንሳዊ/ፈረንሳይ (ዮች)፡ "ዊ" የግ እዝ ልማድ ነው፡ የፈረንስ "(ፍራንስ)" ተወ
ፈረንስ (ፍራንስ)፡ የነገድ ስም (ባ ውሮጳ ውስጥ ያለ ሕዝብ - ሥልጣኔ ካላቸው ወገኖች አንዱ ") ። "ከተገዢነት ወጥቶ ራሱን ስለ ቻለ ፍራንስ (ፍራንክ) ተባለ" ይላሉ፡ "ነጻ" ማለት ነው ። "ፈረንጅ" ለመባል መሠረቱ ፍራ ንስ "(ፍራንቼ)" ሳይኾን አይቀርም፡ እንግሊዞች ፍራንስን "ፍሬንች" ይሉታልና ። በአረብኛ "ቸ" ፊደል ስለሌለ "ፈረንች" በማለት ፈንታ "ፈረ ንጅ" ተባለ ። ዳግመኛም ከ2ኛው የዓለም ጦር ነት በፊት አውሮጶች ኹሉ በአረብና በሐበሻ አገር የፈረንሳይ ቋንቋ ስለ ተናገሩ "ፈረንጅ" የተባሉ ይመስላል ።
ፈረንጅ (ጆች)፡ የነገድ ስም (መልኩ ዐውቆ ነጭ የኾነ ያውሮጳ ሰው - የያፌት ዘር ") ። "ፈረንጅ" እንዲሉ ። በአረብኛም "ፈረንጅ" ይባላል ። "ፈረንስን" አስተውል ።
ፈረንጅ ቀመስ፡ ከፈረንጅ ጋራ የ በላ የኖረ ሰው ።
ፈረንጅ፡ ደማቅ ቀይ ሰው ።
ፈረንጅኛ፡ የፈረንጅ ቋንቋ ።
ፈረከ)፡ አፍረከረከ፡ ፈረፈረ ሸራረፈ አፈራረሰ ። "ፈረቀን" ተመልከት ።
ፈረከሰ (ፈረከ)፡ ሰበረ አደቀቀ ብክ ካን ።
ፈረከከ/ፈረቀቀ)፡ አንፈረከከ፡ እግ ርን አለያየ ።
ፈረከክ/ፈርካካ፡ የተንፈረከከ/የሚን ፈረከክ ("በጕያው ቂጥኝ ዕባጭ ወይም ሌላ ቍስል ያለበት ሰው ") ።
ፈረዘ፡ እዳር ደረሰ ወጣ ።
ፈረዘዘ/ፈርዘዘ)፡ አንፈረዘዘ፡ አጠ ገበ ቀበነነ ነፋ አሳበጠ (አስደሰተ አቀማ ጠለ ") ። በተደራጊነትም ይፈታል ። "(ከረጠጠ)ን" ተመልከት ።
ፈረዘዝ/ፈርዛዛ፡ የተንፈረዘዘ (የጠ ገበ - ደስተኛ ጸጥተኛ ") ። (ተረት)፡ "እኸል የያዘ ፈርዛዛ፡ ወርቅ የያዘ ቀበዝባዛ" ።
ፈረደ (ፈሪድ ፈረደ)፡ በየነ ከሳ ሽንና ተከሳሽን ለየ (የተያዘውን ነገር ርስ ትና ገንዘብ አስለቀቀ፡ ለሚገባው ሰጠ፡ ነፍሰ ገዳይን ቋንዣ ቈራጭን ቤት አቃጣ ይን "ይሙት በቃ" "ይቀጣ በቃ" አለ ") ። (ተረት)፡ "ዐይን አይቶ ልብ ይፈርዳል" ። "ቈረጠን" እይ ።
ፈረደለት፡ በየነለት ።
ፈረደበት፡ በየነበት ።
ፈረድ፡ የጕድባ የፈፋ የወንዝ ወሰን ። "ውሃ ፈረድ" አንዲሉ ።
ፈረጀ (ዐረ)፡ ከጭንቅ ከመከራ አ ወጣ አዳነ ።
ፈረጀ (ፈረገ)፡ እኩል ትክክል አደ ረገ (በወርድ በቁመት ") ።
ፈረገ (ፈረቀ)፡ ለየ ' አስገለለ ። "ፈገ ረን ፈረጀን" እይ ።
ፈረገጠ/ፈገጠ ረገጠ)፡ አንፈራ ገጠ)፡ እጆቹን እግሮቹን አንቀሳቀሰ ዐጠፈ ዘረጋ ።
ፈረገጥ/ፈርጋጣ፡ የተንፈራገጠ/የሚ ንፈራገጥ ።
ፈረጎ፡ የጋኔን የሰይጣን ስም ("በታች ኛው ወግዳ መጥቈሪያ በሚባል አገር - አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሊያስታቸው ቢመጣ ይህን ገለብ ጫኑበት" እያሉ ባላገሮች ያሳያሉ ") ። "የ ስሙ ትርጓሜ ከቅዱሳን መላእክት የተለየ ልዩ ማለትን ያሳያል" ።
ፈረጠ (ፈረጸ)፡ ተጣለ ወደቀ ተሰበረ ተፈነከተ ("ደንጊያው እንስራው ሰዉ ") ።
ፈረጠ፡ ተገለጠ ተረዳ ታወቀ (ነገሩ ") ።
ፈረጠ፡ ወጣ (ፈርጡ ") ።
ፈረጠ፡ ፈነዳ መገለ ፈሰሰ (የቍስል ያይን የንቍላል የልብ ") ።
ፈረጠመ፡ ገላው ጠበቀ ተጠረነቀ ሥጋ ያዘ ሠባ ። "ደለመጠን" እይ ።
ፈረጠጠ (ረጠጠ)፡ ሮጠ ሸሸ ጋለበ ወነበደ ሸመጠጠ (ጭራውን ለበሰ ኰበለለ ") ። (ተረት)፡ "አህያ እንዳባቱ ይፈርጥጥ፡ ዥብም እንዳባቱ ይዘርጥጥ" ።
ፈረፈረ (ፈርፈረ)፡ አደቀቀ አጠቀነ እንጀራን ። "ቈረሰንና ሸረፈን" እይ ።
ፈረፈረ፡ ፈለፈለ ሸረሸረ ማሰ ቈፈረ ኣጐደጐደ ።
ፈረፈር (ሮች)፡ ውሃ የቈፈረው ያጐ ደጐደው ጕድባ ("(ኤር. ፲፬፥ ፮)") ።
ፈሪ (ዎች/ፈርሂ)፡ የፈራ/የሚ ፈራ (ብቡ ሥጕ ጠርጣሪ ቡከን እንበልጋ አንቡጋድ ጡርቂ ") ። (ተረት)፡ "ፈሪን እውሃ ውስጥ ያልበዋል" ። "ለፈሪ ሜዳ አይነሡም" ። "ዘመቻ ፈሪ ሑዳድ ፈሪ" እንዲሉ ። "ደገደገ" ብለኸ "ድግድግን አርባን ሥጋን ሠላሳን" ተመልከት ። (አዝማሪ)፡ "ከፈሪም ፈሪ ፈሪ ይበ ልጣል፡ እኒያ ሲመጡ ሸሽቶ ያመልጣል" ።
ፈሪህ፡ መፍራት ("(ግእዝ)") ። "ፈሪሀ መለ ኮት" እንዲሉ ።
ፈሪሳዊ (ውያን)፡ ንጹሕ ድንግል መናኝ ("(ኪ. ወ. ክ.)") ።
ፈሪሳዊ፡ ግብዝ ባሕታዊ አፈ ጻድቅ ልበ ኃጥእ ተመጻዳቂ ። (ተረት)፡ "አባ ልብሱ ዳባ፡ ውስጡ ደባ" ።
ፈሪነት፡ ፈሪ መኾን ።
ፈራ - ፈረየ)፡ ብለኸ "ፍሬን" እይ ።
ፈራ (ፈርሀ)፡ ልቡ ጠረጠረ ባባ ገነ ገነ ሠጋ ታወከ ። (ተረት)፡ "ፈሩ ፈሩ ማጀት ዐሩ" ። "የውሻን ጥርስ ባጥንት ይፈሯል" ። "ሴት የላከችው ሞት አይፈራም" ።
ፈራ, ተንቀጠቀጠ, ተብረከረከ (ፈራ, ተንቀጠቀጠ, ተብረከረከ).
ፈራ/ፈርየ/ፈርኅ)፡ አፈራ፡ " ፍሬ አገኘ ወለደ አወጣ ሰጠ አንዠረገገ አንጨረገገ ("(ዘፀ. ፩፥ ፯)") ። (ተረት)፡ "አገር ሲያ ረጅ ዣርት ያፈራል" ። (ገንዘብ አፈራ)፡ አገኘ ። (ጠላት አፈራ)፡ አበጀ ። (ዕዳ አፈራ)፡ አመጣ ። (ያፈራ ድንጋይ)፡ በላዩ ዕንጨትና ሣር የበ ቀለበት ቋጥኝ ገለብ ገዎቻ
ፈራሚ (ዎች)፡ የፈረመ/የሚፈርም ።
ፈራረሰ፡ ተናናደ ወዳደቀ ተበታተነ ።
ፈራሽ (ሾች)፡ የሚፈርስ (ጠፊ ") ።
ፈራሽ በስባሽ፡ ሰው (ሥጋዊ ፍጥረት ኹሉ ") ።
ፈራሽነት፡ ፈራሽ መኾን ።
ፈራጅ፡ የፈረደ/የሚፈርድ (እግዜር ንጉሥ አገረ ገዥ ዳኛ ሹም መኰንን አለቃ ባለሥልጣን ሊቀ ካህናት ") ("(መዝ. ፯፥ ፲፩)") ። "ፈራጅ ቀዳጅ"፡ "የመነኵሴ ፈራጅ" እንዲሉ ።
ፈራጅነት፡ ፈራጅ መኾን ።
ፈራጆች፡ ዳኞች ሹሞች ("(ዘፀ. ፳፩፥ ፳፪፡ ምሳ. ፰፥ ፱፥ ፲፮)") ።
ፈራጭ፡ የሚፈርጥ ።
ፈር፡ ትልም፡ ወፈረ ።
ፈርሳም (ሞች)፡ ፈርሰ ብዙ (ሆዳም ከርሣም ") ።
ፈርስ፡ የምግብ አተላ (ከጨጓራ ውስጥ የሚወጣ ") ።
ፈርስ፡ የባት ውሳጣዊ ሥጋ (ወይም አስኳል ") ።
ፈርሶ (ኦሮ)፡ ጠላ ። (ግጥም)፡ "ለሣህለ ሥላሴ ከኾንኩት ወዳጅ እኔ ፈርሶ አልጠጣም፡ እጥላለኹ ጠጅ" ።
ፈርሶ፡ ተንዶ ወድቆ ።
ፈርቃቂ፡ የፈረቀቀ/የሚፈረቅቅ (ፈን ቃይ ሠንጣቂ ") ።
ፈርናሳ/ፍርንስ (ፍርኑስ)፡ የተፈረ ነሰ/የተኛ/የተጋደመ (ጋድሚያ ") ።
ፈርዖን (ኖች)፡ የምስር ንጉሥ ስም፡ ሰው በሞተ ቍጥር የመቃብር ዋጋ ስለ ተ ቀበለ "ፈርዖን" ተባለ ይላሉ፡ "ሙት አስገባሪ" ማለት ነው ። እሱም ከፋርስ ወደ ግብጽ የመጣ ፈላስፋ ነው ።
ፈርከሻ (ትግ)፡ ብክካ (ነጭ ድንጋይ ") ።
ፈርከክ አለ፡ ተንፈረከከ -
ፈርከክ ፈርከክ አለ፡ ተንፈርክኮ ኼደት ኼደት አለ ።
ፈርኵስ፡ ሥጋው ገር የኾነ ዓሣ ።
ፈርካሳ፡ የተፈረከሰ (ደቃቅ ") ።
ፈርካሽ፡ የፈረከሰ/የሚፈረክስ (ሰባሪ አድቃቂ ") ።
ፈርኬ፡ የገብስ ስም ።
ፈርጅ (ጆች)፡ አንድ ዘንግ ፥ አንድ ' ዐርብ የነጠላ ግማሽ ሸማ ።
ፈርጣማ፡ የፈረጠመ (ሥብ ") ።
ፈርጣጣ፡ ሆዱ ሊፈርጥ የቀረበ ዘፍ ጣጣ ።
ፈርጣጭ (ጮች)፡ የፈረጠጠ/የሚፈ ረጥጥ (ሯጭ ሸምጣጭ ኦሮቢ፡ ኰብላይ ከብት ") ።
ፈርጥ (ዐረ)፡ ሽጕጥ ።
ፈርጥ (ጦች)፡ ከደንጊያ የሚገኝ አልማዝ (እንደ ዕንቍና እንደ ሉል የከበረ - በዘ ውድ በቀለበት ላይ የሚደረግ ብርሃናዊ ማዕ ድን ") ። በግእዝም "ፈርጽ" ይባላል ።
ፈርጥ፡ በሐር ልብስና በከፈይ ሠቅ በድባብ በጃን ጥላ የሚለጠፍ ከወርቅ ከመ ዳብ የተሠራ ጌጥ፡ ፈርጥ የሚመስል ጥልፍ ።
ፈርፋሪ፡ የፈረፈረ/የሚፈረፍር (አድቃቂ ሸርሻሪ ") ።
ፈሺ፡ የፈሳ/የሚፈሳ ።
ፈቀረ (ፈቂር ፈቀረ)፡ ወደደ ።
ፈቀረኝ፡ ወደደኝ ። "(ምን ፈቀረኝ)"፡ ም ንኛ እንዴት ወደደኝ ። ምስጢሩ ግን "ፈቀር" እንጂ "ፈቀረኝ" አያሠኝም ። "ምንን" ተመ ኩት ልከት ።
ፈቀቀ (ፈገገ)፡ ዕልፍ አለ (ጥቂት ራቀ ተገለለ ተለየ ተወገደ ") ።
ፈቀቅ አለ፡ ገለል አለ (ስፍራ ለቀቀ ") ("(ሉቃ. ፰፥ ፴፯)") ።
ፈቀቅ አደረገ፡ አገለለ ።
ፈቀቅ፡ ዝኒ ከማሁ (ለ "ፈቅ" - ገለል ") ።
ፈቀቅታ፡ ገለልታ ።
ፈቂ (ዎች)፡ የ "ፈቃ" /የሚፈቃ (በጪ ") ።
ፈቃ (ፈቅዐ)፡ ቈራ በጣ ሠነጠቀ ተፈተፈ ጋረጠ ።
ፈቃሪ፡ የሚፈቅር/የሚወድ ።
ፈቄ፡ የ "ፈቅ ይበሉ" ከፊል ።
ፈቅ ይበሉ፡ የሰው ስም ("ካንተ ፊት ጠላቶቻችን ገለል ይበሉ ማለት ነው") ።
ፈቅ፡ ዕልፍ ራቅ ። "ደስታን" ተመልከት ።
ፈቅ፡ ዕልፍ፡ ፈቀቀ ።
ፈቅታ፡ ዝኒ ከማሁ (ዕልፍታ ") ።
ፈተለ (ዐረ)፡ አቃጠረ አገናኘ ። "ደራ" ብለኸ "ድርና ማግን" አስተውል ።
ፈተለ (ፈቲል ፈተለ)፡ በጭን ጠፋ ወዘገ መዘዘ ሳበ እነዘረ አከረረ (ገመደ ጠመረ ፪ቱን ክር አንድ አደረገ ") ። "የተፈተለ ከኹለት፡ የተታታ ከሦስት" እንዲሉ ። ሐማ ለመርዶክዮስ በተከለው ግንድ በፈተለው ገመድ ተሰቀለ ("(አስቴ. ፯፥ ፱፥ ፲)") ።
ፈተለከ)፡ አፈተለከ፡ ፈታ አሾለከ አወጣ (ራሱን ወይም ሌላውን ") ።
ፈተለክ/ፍትላካ፡ የተፈተለከ (ሾላካ ") ።
ፈተላ፡ የመፍተል ሥራ መዘዛ ።
ፈተረ፡ ዐነቀ አስጨነቀ ወጠረ (በ ሥራ በነገር ") ።
ፈተሸ፡ ቀነቀነ መረመረ በረበረ ። "ፈተነን" ተመልከት ።
ፈተተ (ፈትቶ ፈተተ)፡ ቈረሰ ገ መሰ ከፈለ ተነተነ ።
ፈተተ፡ ተረጐመ ገለጠ አስረዳ ። "የ ሐር ' ዐምባው መምር ክፍሌ ብሉይ ተሐ ዲስ ይፈትቱ ነበር" ።
ፈተነ (ፈቲን ፈተነ)፡ ሞከረ ፈተሸ መረመረ ጠየቀ ፈተና ሰጠ ("(ዳን. ፩፥ ፲፪፥ ፲፬፡ ሉቃ. ፬፥ ፲፱)") ። ጠበሰ አቀለጠ አፈሰሰ፡ ጥቂት ጻፈ አበላ ጋለበ ። መድኀኒትን ማዕድን ንን በሽተኛን ፈረስን ወርቅን በኵየት ብርን በጽፈት ፈተነ እንዲሉ ።
ፈተነ፡ መከራ አሳየ ።
ፈተና፡ ሙከራ ፍተሻ ጥያቄ ምር መራ ። "የፈተና ደንጊያ" እንዲሉ ። "ፈተናውን ዐለፈ" (የተጠየቀውን ዐ ወቀ ") ።
ፈተገ፡ ላጠ መለጠ (ደንጊያ እግርን ") ።
ፈተገ፡ ልጦ ጕርዶ አወጣ (ስንዴን ገብስን በውሃ እያራሰ ሸከሸከ ዠብ ዠብ አደረገ ወቀጠ ከገለባ ለየ ") ። ተልባን በጭድ ዐሸ፡ ቈዳን ዠለጠ አለፋ፡ ዐጪር ሣርን ዐደ ። በግእዝም "ለተመ" "ፈተገ" ተብሎ ይተረጐማል ።
ፈተፈተ (ፈተተ)፡ እንጀራን አራሰ (ከውሃ ከጠላ ከጠጅ ከወጥ ከወተት ከቅቤ ጋራ አደቀቀ አዳወለ አዳከረ ") ።
ፈተፈተ፡ አዋሸከ ነገር አበዛ ።
ፈታ (ፈትሐ)፡ ተረተረ አወለቀ ከ ፈተ (ጠፍርን ገመድን ሰንሰለትን እግር ብረ ትን ቍልፍን ") ።
ፈታ ፈታ አለ፡ ፈጥኖ ተናገረ ቀ ለጠፈ ።
ፈታ, አወለቀ, አወረደ ዕቃን (ዕቃን ፈታ/አወለቀ/አወረደ).
ፈታ፡ ኀጢአተኛን ከኀጢአት ማሰሪያ "እግዜር ይፍታ" አለ (ናዘዘ ") ።
ፈታ፡ ለቀቀ ሰደደ አበረረ ተወ (እስረ ኛን ሚስትን ሥራን ") ።
ፈታ፡ ስለ ሞተ ሰው ጸለየ ። (ተረት)፡ "የዘመድ ቄስ እየፈታ ያለቅስ" ።
ፈታ፡ አሸነፈ ድል አደረገ ። "ጦር ከፈ ታው ወሬ የፈታው ይበዛል" ።
ፈታ፡ አዘዘ ፈቀደ ።
ፈታ፡ አጠፋ አፈረሰ ሻረ በተነ ጠፍ ባድማ ወና አደረገ (አገርን ሸንጎን ቤትን ኀበያን ከተማን አስማትን መድኀኒትን ") ።
ፈታ፡ ገለጠ ተረጐመ (ምስጢርን ቅኔን ") ("(ማር. ፬፥ ፴፬)") ።
ፈታ፡ ግዝትን አስወገደ ።
ፈታ፡ ፈረደ ፍርድ ሰጠ ዐደለ በየነ ። "አፍን" እይ ።
ፈታል (ዐረ)፡ አቃጣሪ (ወንድና ሴት የሚያገናኝ ") ።
ፈታሪ፡ የፈተረ/የሚፈትር (ዐናቂ አ ስጨናቂ ") ።
ፈታሽ (ሾች)፡ የፈተሸ/የሚፈትሽ (ቀ ንቃኝ መርማሪ ") ።
ፈታሽነት፡ ፈታሽ መኾን (ቀንቃኝነት ") ።
ፈታተለ፡ መላልሶ ፈተለ ገማመደ መደ ።
ፈታተገ፡ ወቃቀጠ ሸካሸከ ። "ያጤ ቤት ገረዶች ፈተጉ ፈታተጉ፡ በቍልቢጥ አስ ቀመጡ" እንዲሉ ልጆች ።
ፈታች (ቾች)፡ የፈተተ/የሚፈትት (ቈራሽ ተንታኝ ቄስ ሊቅ ") ።
ፈታኝ (ፈታኒ)፡ የፈተነ/የሚፈትን (ሞ ካሪ ፈታሽ መርማሪ ጻፊ ") ("(ኤር. ፮፥ ፳፯፡ ማቴ. ፬፥ ፫፡ ፩ ተሰ. ፫፥ ፭)") ።
ፈታኝ (ፈትሐኒ)፡ ለቀቀኝ ተወኝ ።
ፈታኞች፡ የፈተኑ/የሚፈትኑ (መርማሪ ዎች ") ።
ፈታይ (ዮች)፡ የፈተለ/የፈተለች/የሚ ፈትል/የምትፈትል (አንዛሪ አቅጣኝ ሴት ሸረ ሪት ") ።
ፈታይነት፡ ፈታይ መኾን ። "የፈታይ ምንዳ" (ዋጋ ቀለብ ደመ ወዝ ") ። "የፈታይ ግብሩ" (ፍትል የኾነ መሬት ርስት ") ።
ፈታጊ (ዎች)፡ የፈተገ/የሚፈትግ (ወቃጭ ዐሺ አልፊ ዐጫጅ ") ።
ፈታፈተ፡ አደቃቀቀ ።
ፈት (ቶች)፡ ያጠፋ አጥፊ (የተወ የ ለቀቀ የሚለቅ ") ። "አገር ፈት"፡ "ሥራ ፈት" እ ንዲሉ ።
ፈት፡ የፈታች/የተወች ። "ይህች ሴት ባል የላትም፡ ፈት ነች" ።
ፈትቶ (ቦዝ)፡ ቈርሶ ገምሶ ("(ዐማርኛ)") ።
ፈቸለ፡ ያዘ ነቀለ ። "ፈተረን" እይ ።
ፈቸል (ሎች)፡ ጕጠት የምስማር ንቀያ ።
ፈቺ (ዎች)፡ የፈታ/የሚፈታ (ለቃቂ ተርጓሚ ") ። "አግቢ ፈቺ"፡ "ሰንሰለት ፈቺ" እንዲሉ ።
ፈነረ፡ ተወ ጣለ ወረወረ አሽቀነጠረ ርግፍ አደረገ ። "ፈገጠን" እይ ።
ፈነረ፡ አደገ ገጠጠ ረዘመ ፈነገጠ ።
ፈነቀ (ነፈቀ)፡ እነቃ ሠነጠቀ ተረ ረ ።
ፈነቀለ (ፈንቀለ)፡ ገለበጠ ለየ ቀረፈ ስፍራ አስለቀቀ (የላዩን በውስጥ የውስጡን በላይ አደረገ - የድንጋይ የጓል ") ። "ፈነገለን" አስተውል ።
ፈነቃቀለ፡ ገለባበጠ ቀራረፈ "
ፈነተተ (ትግ. ፈንተተ፡ ዕልፍ አለ፡ ፈቀቀ)፡ ዐጠረ ፈጽሞ ዐጪር ኾነ አነሰ (አልደርስ አልበቃ አለ ") ።
ፈነተወ (ትግ. ፈንተወ፡ ለየ)፡ ጠረገ አጠራ ገለጠ አገለለ (ፈንቶን ") ።
ፈነተወ፡ ከፈለ ለየ ተነተነ ደለደለ መደበ (ዐደለ ሰጠ - ፈንታን ") ።
ፈነቸረ (ፈነከረ)፡ ወደ ኋላ ጣለ ' ገደለ ' ኣዶበነ ።
ፈነነ (ትግ. ሐባ. ፈረረ)፡ ፊን አለ ። "ነና ረ መወራረሳቸውን አስተውል" ።
ፈነከረ (ፈከረ)፡ ጨርሶ ገለጠ ከ ፈተ ዘረጋ ።
ፈነከተ (ነከተ)፡ ፈለጠ ከፈለ ገ መሰ ሰበረ ተረረ ተረከከ ሠነጠቀ ወለለ ራስን (ጨፈለቀ ዕዳሪን ") ።
ፈነካከረ፡ ገላለጠ ከፋፈተ ዘረጋጋ ።
ፈነወ፡ ተበሳ ተቀደደ ተከፈተ (መ ነጨ ወጣ ፈር አለ ") ።
ፈነዘ፡ ጐንበስ ቀና አለ (ተንቀጠቀጠ ተ ነቃነቀ - ፈንዛው ") ።
ፈነደሰ (ትግ. ፈደሰ፡ ቈራ. በጣ. ጋረጠ)፡ ሠነጠቀ ፈነከተ አነቃ እግርን "
ፈነደሰ፡ ኣስተኛ አጋደመ ።
ፈነደረ ካንድ ፊት በለጠ (ወደ ኋላ አለ - ጣራው ግድግዳው ") ። "ፈነገጠን" እይ ።
ፈነደቀ፡ ፈጽሞ ተደሰተ (ዘለለ ፈ ነ ፈነጠዘ ") ።
ፈነደደ፡ ጐነበሰ ተመከተ ዠርባው ።
ፈነደደ፡ ፈነደሰ፡
ፈነደድ/ፈንዳዳ/የፈነደዶ፡ ቂጠ ት ልቅ ። "ፈነደረን" እይ ።
ፈነዳ (ፈንደወ)፡ ዷ አለ (ወከከ ፈረሰ ተበተነ ተተረተረ ፈረጠ ተሠነጠቀ - ልቡ ሆዱ ዕባጩ ጋኑ ደንጊያው ቦምቡ ") ።
ፈነዳ፡ ፈካ (አበባው ፈርጡ ጥጡ እንዱሽዱሹ - ፪ዜና. ፩፥ ፭) ።
ፈነጀረ፡ ተለየ ራቀ ጠመመ (ወጣ ገባ ኾነ ") ።
ፈነገለ (ጰንገለ)፡ ከቅምጥ ጣለ አወ ደቀ ደበለለ ገለበጠ (ባሪያ ሼጠ ") ። "ነገለን" እይ ።
ፈነገጠ (ፈገጠ)፡ ፈነረ ወጣ ገ ጠጠ (የጥርስ የደንጊያ የብረት ") ።
ፈነጠ፡ በጥቂቱ ናረ ። "ፈነጯን" እይ ።
ፈነጠረ (ትግ. ሐባ. ፈንጠረ፡ በ ተነ)፡ ፈነረ ፈገጠ ተወ ' ለየ ። "ነጠረን ፈ ነጠን" እይ ።
ፈነጠቀ (ፈነጠ/ነጠቀ)፡ ረጪ ነዛ በተነ በቀላል ጣል ጣል አደረገ (ዘርን ቈሎን ተልባን ጮራን ለምጽን ደምን ") ።
ፈነጠቀ፡ —ፈነጠረ፡
ፈነጠዘ፡ ተደሰተ ደስ ተሠኘ (በበ ዓል ቀን ከመብል ከመጠጥ የተነሣ ") ። "ፈነ ጠዘ" ከግሪኮች የተወረሰ ነው ።
ፈነጠጠ (ትግ. ፈንጠጠ፡ ቂጥኝ አወጣ)፡ ወጣ ተገለበጠ ቈሰለ ።
ፈነጣጠቀ፡ ረጫጨ በታተነ ።
ፈነጨ፡ ቦረቀ ዘለለ ተወረወረ ።
ፈነፈነ (ትግ. ሐባ. ፈንፈነ)፡ i አጸየፈ ጠላ ነቀፈ ። "ነፈነፈን" ተመልከት ።
ፈናጅራ፡ ጠማማ ወልጋዳ ጥርስ ።
ፈናፍንታም፡ ፈናፍንት ያለበት (ባለ ፈናፍንት - የፈናፍንት ወግን ወይም ርሱ ራሱ ፈናፍንት ነውረኛ ") ።
ፈናፍንት (ቶች)፡ የተባትና የእንስት ምልክት ያለው (ወንድ አይሉት ሴት ጕድ ጢም አልባ ሴት ድምጥ ዐጓጕል - በሰው ዘንድ የተጸየፈ የተጠላ የተነቀፈ ") ። "ፈናፍንት በእንስሳትና በአራዊትም ይልቁንም በዥብ ይገኛል" ። "ወንድን/ገረድን" እይ ።
ፈንረው፡ ተወው ጣለው ።
ፈንቃላ፡ የተፈነቀለ ።
ፈንቃይ (ዮች)፡ የፈነቀለ/የሚፈነቅል (ገልባጭ ") ።
ፈንቅል፡ ዝኒ ከማሁ (ትእዛዝ ሲኾን ገልብጥ ማለት ነው ") ።
ፈንታ፡ የሰው ስም ። "ሹም ዳኅና ፈንታ" እንዲሉ ።
ፈንታ፡ ድርሻ ዕድል መክፈልት (ተራ ምትክ ለውጥ ") ("(ዘፀ. ፴፭፥ ፭፥ ፳፩፡ ኢሳ. ፶፯፥ ፮፡ ዳን. ፬፥ ፲፭)") ።
ፈንታሌ፡ የተራራ ስም (ካዋሽ ወንዝ በስተግራ የሚገኝ እሳተ ገሞራ ያቀለጠው ተራራ ") ። "ከውስጡ የተተፋው ያፈርና የደን ጊያ ከሰል እበታቹ ባለው ሜዳ ላይ በሰ ፊው ተንጣሎ ይታያል" ። "እንደ ፈንታሌ ትቀልጣለኽ" እንዲሉ ።
ፈንታሌ: ፡ ፈጸመ፡
ፈንታታ/ፍንትት፡ የፈነተተ (ዐጪር ") ።
ፈንቶ፡ የማይረባ ምናምን ነገር (ይህ የማይባል ጥራጊ ጕድፍ ") ። "እንቶ ፈንቶ" እን ዲሉ ። "ፈንታና ፈንቶ" ከ "ፈነተወ" ይወጣሉ ።
ፈንቶች፡ ድርሻዎች ምትኮች ለውጦች ።
ፈንኦሮ፡ የተፈነገለ (ወዳቃ ") ።
ፈንካሪ፡ የፈነከረ/የሚፈነክር (ገላጭ ከፋች ዘርጊ ") ።
ፈንካራ፡ የተፈነከረ (ግልጥ ክፍት ዝ ርግ ") ።
ፈንካታ፡ የተፈነከተ (ራስ ቅል ደን ጊያ ወይም ሌላ ") ።
ፈንካች፡ የፈነከተ/የሚፈነክት ።
ፈንዛ፡ የበሬ ስም ።
ፈንዜ፡ ቀጪንና ጐባጣ የኾነ ረዥም ጐራዴ (ታጥቀውት ሲኼዱ የሚነቃነቅ ") ።
ፈንዝ/ፈንዛ፡ የወፍ ስም (ዓሣ ለ ቃሚ ነጭና ጥቍር ወፍ ቀጥቃጣ ዥራታም ") ።
ፈንዝማ፡ የ "ፈንዝ/ፈንዛ" ዐይነት (ጭ ራው ነጭ የኾነ በሬ ") ።
ፈንዞ፡ ዥራተ ነጭ ፈረስ ።
ፈንዞ፡ ያሣ ስም (ነጭነት ከጠይምነት ያለው ዓሣ ") ።
ፈንዳ ፈንዳ አለ፡ ፈታ ፈታ አለ (ደስ ተሠኘ ") ።
ፈንዳራ/ፍንድር፡ የፈነደረ ።
ፈንዳቂ፡ የፈነደቀ/የሚፈነድቅ (በላይ ፈንጪ ልጅ ጥጃ ") ።
ፈንዳጅ፡ የሚፈነድድ "
ፈንጂ፡ የፈነዳ/የሚፈነዳ (ጥንብ ደማ ሚት ") ።
ፈንጋይ (ዮች)፡ የፈነገለ/የሚፈነግል (ጣይ ባሪያ ሸያጭ ") ። "ባሪያ ፈንጋይ" እንዲሉ ።
ፈንጋይነት፡ ፈንጋይ መኾን ።
ፈንግል፡ ትልቅ ጥዋ ዋንጫ "
ፈንግል፡ ድንገት የሚገድል በሽታ (ባጤ ቴዎድሮስ ጊዜ የነበረ ") ።
ፈንጠራ፡ የተለየ ልዩ ።
ፈንጠራ፡ ፌንጣ ።
ፈንጠር አለ፡ ለየት አለ ።
ፈንጠር፡ ዐፈር ሳይለብስ የቀረ የዘር ፍሬ ።
ፈንጠቅ አለ፡ ተፈነጠቀ ።
ፈንጠዝያ፡ በጽርእ "ፋንቲሲያ" ይባላል (ዝንጕርጕር ሽል ማት ጌጣጌጥ ማለት ነው ") ።
ፈንጠዝያ፡ ፍጹም ደስታ ።
ፈንጣሪ፡ የፈነጠረ/የሚፈነጥር ።
ፈንጣቂ (ዎች)፡ የፈነጠቀ/የሚፈነ ጥቅ (ረጪ በታኝ ") ።
ፈንጣዥ፡ የሚፈነጥዝ/የሚደሰት (ተደ ሳች ") ።
ፈንጣጣ (ዎች)፡ እንደ ቂጥኝ የም ታቈስል የቍስል በሽታ (አንድ ጊዜ ከወ ጣች ኹለተኛ አትመለስም ") ። "ጣጣ ፈንጣጣ" እንዲሉ ። "ባዘተ ደነቀ" ብለሽ "ባዘቶን ድን ቂቱን" እይ ።
ፈንጥረው/ፈንረው/ፈግጠው፡ ተወው ።
ፈንጥቄ፡ የሰው ስም ("የጠላትን ደም ፈንጥቅ ማለት ነው") ።
ፈንጪ፡ የፈነጩ/የሚፈነጭ (ቦራቂ ዘላይ ") ። "ያዳይ ጠጪ የግመል ፈንጪ" እን ዲሉ ።
ፈከረ/ፎከረ (ፈክሮ/ፈከረ/ተረ ጐመ)፡ ሞያውን ዠብዱን ገለጠ ቈጠረ አስረዳ (ደነፋ ዐካኪ ዘራፍ ገዳይ - እዚህ ገዳይ አለ ") ። "ፈከረ" የግእዝ፡ "ፎከረ" ያማርኛ ነው '
ፈከከ) ዐረ/ፈከ፡ አንፋከከ፡ እግ ሮችን አራራቀ (ወዲያና ወዲህ አስረገጠ መ ጥፎ አካኼድ አስኬደ ") ። "ፈቀቀን" አስተውል ።
ፈከክ ፈከክ አለ፡ ተንፋከከ '
ፈከፈከ (ፈከከ)፡ ነተበ ተሠነጠቀ ተ ነሣ ተላጠ ። ከአፈከፈከ በቀር ፈከፈከ አል ተለመደም ።
ፈኪ፡ የሚፈካ/የሚያብብ ።
ፈካ (ፈግዐ/ዐረ/ፈኪሀ)፡ ተከፈተ ፈነዳ (የውስጡ በላይ ኾነ ") ። አበበ ።
ፈካ፡ ደስ ተሠኘ (ፈጽሞ ሣቀ ") ።
ፈካሪ/ፎካሪ (ዎች)፡ የፈከረ/የፎከረ/ የሚፈክር/የሚፎክር (ግዳይ ተናጋሪ ") ።
ፈወሰ (ፈውሶ/ፈወሰ)፡ ዐከመ አዳነ ኣሻረ አተረፈ ከሕማም ከደዌ (ጠገነ - ሉቃ. ፯፥ ፳፩፡ ፲፫፥ ፲፬) ።
ፈወተ (ጥንታዊ አማርኛ)፡ ጠጣ ።
ፈዋሽ (ፈዋሲ)፡ የፈወሰ/የሚፈውስ (አዳኝ ሐኪም ባለመድኀኒት ወጌሻ ") ።
ፈዋሾች (ፈዋስያን)፡ የሚፈውሱ ሐኪሞች ("(ሉቃ. ፰፥ ፵፫)") ።
ፈውሰ ቢስ፡ የማይፈወስ ሰው (ቢፈ ወስም በሽታው የሚመለስበት ") ።
ፈውስ መንፈሳዊ፡ የመጻፍ ስም (ብዙ የነፍስ አብነት የሚኾን ምክር ያለ በት መጻፍ - የሲኖዶስ ዐይነት ") ።
ፈውስ፡ ድኅነት ጤና ("(ግብ. ሐዋ. ፬፥ ፳፪)") ።
ፈዘዘ፡ ዘነጋ ቀዘዘ ደነዘዘ ቦዘ ሰው ነቱ (ተሰቀጠጠ ተሸመቀቀ ዥማቱ - ዘፍ ")
ፈዛዛ (ዞች)፡ የፈዘዘ (ዝንጉ ") ። "ዋዛን" ተመልከት ።
ፈዛዛነት፡ ፈዛዛ መኾን ።
ፈየተ፡ ቀማ ነጠቀ ("(ግእዝ)") ።
ፈየተ፡ ቀደመ ተገለጠ ታየ (ሰው ሲወ ለድ ራሱ ፊቱ - ዐማርኛ ") ። "መቅደም" ጊዜን፡ "መታየት" ፊትን ያስተረጕማል ። "ፊት" ቅሉ ከዚህ የወጣ ነው ።
ፈየተ፡ ፈከረ
ፈየዘ/ፌዘ) አፌዘ፡ አላገጠ አቧ ለተ ("(ኢሳ. ፳፰፥ ፳፪፡ ኤር. ፲፱፥ ፰)") ።
ፈየደ (ፈደየ)፡ ረባ ጠቀመ አተረፈ ።
ፈየጠ/ፌጠ)፡ ወጣ በላይ ኾነ (ፈጀ አቃጠለ ") ። "ፊጥንና ፌጦን" እይ፡ የዚህ ዘሮች ናቸው ።
ፈያ፡ የውሃ መኼጃ።
ፈያጅ፡ የፈየደ/የሚፈይድ (ጠቃሚ አ ትራፊ ") ።
ፈደለ (ፈዲል/ፈደለ)፡ ጣፈ ለፈለፈ ዋሸ ቀጠፈ ።
ፈደነ (ደፈነ)፡ አጥብቆ እሰረ ወደነ ቀፈደደ ።
ፈደነ፡ ፈዘዘ፡
ፈደፈደ (ፈድፈደ)፡ በዛ ተረፈ በ ለጠ ። "(ብርድ ፈደፈደኝ - በዛብኝ በረታብኝ ") ።
ፈዳኝ (ኞች)፡ የፈደነ/የሚፈድን '
ፈድፋጅ፡ የሚፈደፍድ (በዢ ") ።
ፈጀ (ፈገ/ፈደየ)፡ አቃጠለ ገደለ ጠነገደ አጠፋ ፈጸመ ጨረሰ (ቻለ - ዘዳ. ፱፥ ፫፡ ሉቃ. ፳፬፥ ፳፰) ። "(ተረት)" - እሳት ለፈጀው ምን ይብጀው ። "(ዐምሳ ኾነው ዐምሳ በግ ፈጁ)"፡ ጨረሱ ። "(ለብሰሽ ፍጀው)"፡ ጨርሰው ። "(የጫረው እሳት ፈጀው)"፡ ሰውን የሠራው ሥራ ጐዳው አጠፋው ።
ፈጀታ፡ የፈጀች/የምትፈጅ/የምትጨ ርስ ሴት ።
ፈጅ፡ የፈጀ/የሚፈጅ (ጨራሽ ቻይ ") ። "አህያ ፈጅ በገ ፈጅ ኹለተ ፈጅ ላመ ፈጅ ነገረ ፈጅ ዐሥረ ፈጅ ፍየለ ፈጅ ሸማ ፈጅ" እንዲሉ ።
ፈገመ (ደበየ)፡ ባፍ ጢም ደፋ አወደቀ ።
ፈገረ (ትግ/ሐባ/ፈግረ)፡ ወጣ ብቅ አለ ። በትግሪኛ ግን "ፈገረ" - ሰረቀ ማለት ነው ።
ፈገገ (ትግ)፡ ጐፈነነ ።
ፈገገ (ፈጊግ/ፈገ/አክሞሰሰ)፡ በጥቂቱ ሣቀ ከንፈሩን ገለጠ ።
ፈገገ፡ ፊቱ ፍሙ በራ ("(መዝ. ፲፰፥ ፰)")
ፈገገን፡ ውጋገን (ብርሃነ ገጽ ") ።
ፈገግ (ፈጊግ)፡ መፍገግ ።
ፈገግ አለ፡ ወገግ አለ (በራ ገጹ ሰማዩ ") ።
ፈገጠ፡ ፈነረ ጣለ ተወ "
ፈገፈገ (ፈገገ)፡ ፋቀ ጠረገ ለማጥ ራት ፥ ለማሣሣት ። ላይኛ መልክን ወይም ኹና ቴን ለወጠ ። "ሞረድን ሰነገለን" እይ ።
ፈገፈገ፡ ፋገረ፡
ፈጋሚ፡ የፈገመ/የሚፈግም (ደፊ ") ።
ፈጋራ፡ ሬብ የኵስ መውጫ ።
ፈጋጊ፡ የፈገገ/የሚፈግ/የሚበራ ።
ፈጋፈገ፡ ፋፋቀ ጠራረገ ።
ፈግግታ/ፍግግታ፡ ወገግታ (ሣቅ የጥ ርስ ብልጭታ ") ።
ፈግጠው/ፈግጪው፡ ጣለው/ጣዪው (ተወው/ተዪው መባባል - የባልና የሚስት ") ።
ፈግፋጊ፡ የፈገፈገ/የሚፈገፍግ (ጠራጊ ") ።
ፈጠመ (ፈጸመ/ፈፀመ)፡ ጨረሰ አ ሳለቀ ጠነገደ ቈረጠ ደመደመ ዘጋ ። "ፈጸ መን" አስተውል ።
ፈጠም፡ ዝኒ ከማሁ፡ የነገር የሙግት መግቻ (ወይም ማሰሪያ መቍረጫ ማኅተ ምን ፊርማን የመሰለ ሰማኒያ ") ። (ጥሪ) መፈጠም፡ መጨረስ መጠንገድ ።
ፈጠረ (ፈጢር/ፈጠረ)፡ ካለመኖር ወደ መኖር አመጣ አስገኘ ሠራ አደረገ ወለደ ። "ዛሬ ምን ስትፈጥር ዋልክ"፡ "ስትሠራ ስታደርግ" ። "እናቴ ከፈጠረችኝ እንደዚህ ያለ ነገር አይቼ ኣላውቅም"፡ "ከወለደችኝ ማለት ነው" ።
ፈጠረቀ) አፈጠረቀ፡ አፈነዳ አወጣ የቍላ ፍሬን ። "በጠረቀንና (ፈተለከ)ን" እይ ።
ፈጠራ፡ ልብ ወለድ ነገር '
ፈጠነ (ፈጢን/ፈጠነ)፡ በመኼድ በመሥራት በመናገር በማንኛውም ጒዳይ ቸኰላ ቀለጠፈ (ከዝግታና ከቀስታ ፈጽሞ ተለየ ራቀ ") ።
ፈጠን (ፈጢን)፡ መፍጠን ።
ፈጠን ፈጠን አለ፡ ቶሎ ቶሎ ኼደ ሠራ ተናገረ ።
ፈጠጋር፡ በቡልጋና በምንጃር መካከል ያለ አገር ።
ፈጠጠ፡ ጐነቈለ ወጣ ጐረጠ ተጐለ ጐለ ። "ፈጠፈጠ" ብለኸ "አፈጠፈጠን" እይ ።
ፈጠጤ፡ የፈጠጥ ዐይነት ወገን (ያው ድማ ዳር ጕንቍል ባቄላ ዐተር ሽንብራ ") ።
ፈጠጥ፡ ዝኒ ከማሁ ።
ፈጠፈጠ (ትግ/ፈጽፈጸ/ፈተ ፈተ)፡ ፈነከተ ሰባበረ (በብዙ ወገን አቈ ሰለ ራስን ") ። "ሕፃናቶቻቸውንም ትፈጠፍጣለኸ" ("(፪ነገ. ፰፥ ፲፪፡ መዝ. ፻፴፯፥ ፱)") ።
ፈጠፈጠ፡ ፈጨረ፡
ፈጣሚ፡ የፈጠመ/የሚፈጥም (ጨራሽ ") ።
ፈጣሪ (ዎች)፡ የፈጠረ/የሚፈጥር (አ ስገኝ ሠሪ አምላክ እግዜር ") ።
ፈጣሪ ተቈጣ)፡ ዐባር ቸነፈር ሰይፍ ማራኪ አመጣ ። "እግዜር ሲቈጣ በዝናም ዐር ያመጣ" ።
ፈጣሪነት፡ ፈጣሪ መኾን (አምላክነት መለኮትነት ") ።
ፈጣን ("ፈጥኖ ደራሽ - ከተፍ አለ በድንገት ደረሰ መጣ ከ ቸቸን ተመልከት መክተፍ መቍረጥ መሸከፍ መክተፊያ ሉሕ ቢላዋ በውስጡ ጭ ርስ ያለው መኪና አስከተፈ አስቈረጠ አስደቀቀ ሥጋን አስከታፊ ያስከተፈ የሚያስከትፍ ማስከተፍ ማስቈረጥ ማስደቀቅ ማስከተፊያ ጊዜና ወጥ ቤት ተከተፈ ተመተረ ተቈረጠ ጠቀነ ሸከፈ ደቀቀ ተከታፊ የሚከትፍ ብርንዶ ቅቅ ክትፍ የተከተፈ በስለት የደቀቀ ክትፎ ደቃቅ ሥጋ በቅቤና በድልኸ በቅመም ታሽቶ የሚበላ ዝግንን አስተውል ክትፋት ክትፍነት የክትፎ ሥራ በ ብጥታት ፈንታ ክትፋት ይላል ") (ኤር. ፵፰፡ ፴፯) ።
ፈጣን (ኖች)፡ የፈጠነ/የሚፈጥን ("(መክ. ፱፥ ፲፩)") ።
ፈጣጣ፡ የፈጠጠ ። "ዐይነ ፈጣጣ" እን ዲሉ ።
ፈጣጭ፡ የሚፈጥ/የሚጐርጥ ።
ፈጥኖ ደራሽ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ።
ፈጥኖ፡ ቶሎ ብሎ ቸኵሎ ። "ፈጥኖ ኼደ፡ ፈጥኖ መጣ" እንዲሉ ።
ፈጥፋጭ፡ የፈጠፈጠ/የሚፈጠፍጥ (ፈን ካች ") ።
ፈጨ፡ በጥቂቱ መገለ አዠ ። "ፈጨ ፈን" እይ ።
ፈጨረ/ፋጨረ፡ በብርቱ ሥራ ለፋ ደከመ ። "ፋገረን" ተመልከት ።
ፈጨፈጪ) ፈጪጪ (ጨፈጨፈ)፡ አንፈጨፈጨ፡ አፈላ አወረዛ ።
ፈጨፈጭ፡ የተንፈጨፈጨ/የሚንፈ ፈጭ (ጨቆ የምድር እዥ ") ።
ፈጪ (ፈጻሒ)፡ የፈጪ/የሚፈጭ (ከርታፊ ሰላቂ ") ። ሲበዛ "ፈጪዎች/ፈጮች" ይላል ("(መክ. ፲፪፥ ፫)") ።
ፈጪ (ፈጽሐ)፡ እኸልን ከካ ከረ ተፈ አጐረሠ አደቀቀ ሸመሸመ ሰለቀ ደቈሰ ዳጠ አለዘበ አላመ ዳሰ ጣሰ ("(፪ሳሙ. ፳፪ - ፵፫ - ፪ዜና. ፲፭፥ ፲፮)") ።
ፈጪታ፡ ፈጪ ለወንድ (ፈጪታ ለ ሴት ይነገራል - የፈጨች/የምትፈጭ ማለት ነው ") ።
ፈጫ (ፍጹሕ)፡ ደቃቅ አሸዋ ጠ ጠር (በፀሓይ ጊዜ እግርን የሚያቃጥል ") ።
ፈጫይ (ዮች)፡ ዝኒ ዓዲ ከማሁ ። "የፈይ" - ፈጫይ አንድ ቍና እኸል ፈጭታ የቍና አጋማሽ (ኹለት ቍና ጥሬ ፈጭታ አንድ ቍና የጕልበት ዋጋ ታገኛለ ችና - የፈይ የሚባል ይህ ነው ") ።
ፈጭ፡ ዝኒ ከማሁ ። "ዐመደ ፈጭ" እን ዲሉ ።
ፈጯጯ ፈጠነ፡
ፈጯጯ፡ መላልሶ ፈጨ ከረታተፈ ።
ፈጸመ (ፈጽሞ ፈጸመ)፡ ጨረሰ ከወነ ቈረጠ ደመደመ ። "ፈጠመንና ከተመን" ተመልከት ።
ፈጻሚ (ሞች)፡ የፈጸመ/የሚፈጽም (ጨራሽ ") ። "ጕዳይ ፈቃድ ፈጻሚ" እንዲሉ ። "ፈጻምያነ ፈቃድ"፡ "ፈቃድ ፈጻሞች" (ነፋስ እሳት ውሃ ") ።
ፈጽሞ ደረቀ ("ቀ ለዘ የንጨት ክችሌ ሳይቈረጥ ተልጦ በጣም የደረቀ ዕንጨት ለዛ ሙጥጤ ሰው ከቸቸን ተመልከት ከተለበ ከለበ ከትላባ ከላባ ተከታለበ ተካለበ መከታለብ መካለብ መከታለቢያ መካለቢያ አከታለበ አካለበ ማከታለብ ማካለብ ማከታለቢያ ማካለቢያ ካቶሊክ የቤተ ክሲያን ስም ከኹሉ በላይ ማለት ነው ካቶሊክ የሃይማኖት ስም የሮማውያን ሃይማኖት በግእዝም ፊተኛው ኮቶሊክ ኋለኛው ኮቶሊካ ይባላል ኮተሊክ ") (ኮች) ።
ፈፋ (ፎች)፡ የውሃ መኼጃ መው ረጃ (ከጕድባ ያነሰ ሸንጥሮ ") ።
ፈፍ፡ የፊደል ስም "ፈ" (ትርጓሜው አፍ ማለት ነው ") ። "ፈፋና ፈፍ አፍ" አንድ ዘር ናቸው፡ ኹሉም ከአፈፈ ይወጣሉ ።
ፉ አለ ፈገመ፡
ፉ አለ፡ በቍጣ ተነፈሰ ("በሬው እፍ ኝቱ ") ። አንቀጹ ነፋ ("(ነፍኀ)") ነው ።
ፉሲ፡ ከንቱ ብላሽ ።
ፉሲ፡ ፈሰሰ፡
ፉር አለ፡ በአፍንጫው ጮኸ (የጋማ ከብት ከፍራት የተነሣ ") ።
ፉር ፉር አለ፡ በነፋስ ኀይል ድ ምፅ ሰጠ (ፉርቴው ") ።
ፉር፡ የበቅሎ ያህያ ጕንፋን ።
ፉርሽ አለ፡ "አትያዝ አትቅለብ" አለ (አ ሰናከለ ") ።
ፉርሽ፡ ያሊያዘ/ያልጨበጠ/ያላገኘ (ከ ንቱ ብላሽ እንዲያው መና የቀረ ") ።
ፉርቃን (ዐረ)፡ የእስላም መጽሐፍ ቍርኣን (ከኦሪት ከወንጌል ተከፍሎ የወጣ ") ።
ፉርቴ (ዎች)፡ የመጫወቻ ስም (በመካከል ባለው ቀዳዳዋ ልጆች ዕጥፍ ገመድ አግብተው ግራና ቀኝ ሲዘውሯት በነፋስ ኀይል ፉር ፉር የምትል ታናሽ ጠፍጣፋ ዕ ንጨት፡ ቁመቷ መካከለኛ ጣት ያኸላል ") ። "እ ውዋን" አስተውል ።
ፉሮ (ኦሮ ፉሪ፡ ንፍጥ)፡ የጋማ ከብት ያፍን ውስጥ በሽታ የሚያስል የሚያስነጥስ ።
ፉቅራ፡ የስላም ቃልቻ (ዛር ፈረስ ") ።
ፉት (ፈወተ - ትግ. ፋየተ)፡ መ ማግ መቅመስ መጠጣት ። "ፈወተን" አስተውል ።
ፉት ቢሉ ጭልጥ፡ ንብረቱ በጣም ያነሰ ሰው እንዲህ ይባላል ።
ፉት አለ፡ ማገ (በጥቂት ጠጣ - በ ፍጥነት አነበበ ጨረሰ ") ።
ፉት አደረገ፡ አማገ ።
ፉነቲ፡ አፍንጫ ደፍጣጣ፡ ፎ ነነ ።
ፉነቲ፡ አፍንጫው ዋ ያጠረ ፉንጋ ወንድ ሴት ።
ፉነቴ፡ የ "ፉነቲ" ወገን (አፍንጫ ደፍ ጣጣ ቅድስና ያላት ባሪያ ") ። "ርሷ ከተሰወረች በኋላ የምትለብሰው ጨርቅ ታምራት ስለ ሠራ በተረት የፉነቴ ጨርቅ ሲባል ይኖ ራል" ። (፩)
ፉነና፡ ሥንጠቃ ቈረጣ ።
ፉን/ፉንን፡ ከንፈረ ሥንጥቅ ። ግመ ልም "ፉን" እየኾነ ይወለዳል ።
ፉንቅ፡ የገደል ሳን አጣብቂኝ ።
ፉንታሮት፡ እዚህ ይግባ የማይባል '
ፉንጋ፡ ፊተ ዐጪር በቅሎ አህያ ሰው ። "ሲበዛ ፉንጎች ያሠኛል" ።
ፉኖ፡ ከንፈረ ዐጪር ሰው (የጋማ ከብት ") ።
ፉካ፡ ውላ ቀዳዳ ታናሽ መስኮት ። "ፉካ" ' የ(ፈከከ) ዘር ነው '
ፉዲድ ፉዲድ አለ፡ ፋደደ ።
ፉዲድ፡ መፋደድ ።
ፉገርታ፡ ጐበዝ ፋጋሪ ።
ፉጋ፡ የነገድ ስም (በጕራጌ ክፍል ያለ ሕዝብ ')
ፉጠራ፡ አሰራ ሽበባ ።
ፉጥ፡ የሰው ስም ።
ፉጥ፡ ፈጠጠ፡
ፉጥር፡ የተፎጠረ (አፈ እስር ሽብብ ") ።
ፉጨታ፡ ዝኒ ከማሁ ("(ኢሳ. ፭፥ ፳፮)") ።
ፉጨት (ፋጻ)፡ እጅግ የሚያምር የትንፋሽ ዘፈን ዜማ ጥሪ ።
ፊላ፡ የረግረግ ዳር የወንዝ አጠገብ ቅጠል እንደ ችግኝ በዝቶ የሚበቅል የሚ ፈላ ።
ፊላማ፡ የፊላ ወገን (ፊላ መሳይ ማለት ነው ") ።
ፊላስ ፊላስ አለ፡ ፍንቅል ፍንቅል ብድግ ብድግ አለ (መጋለብ ዠመረ ") ።
ፊላዊ፡ እፊላ ዐይነት ቀለም የገባ ቈዳ ።
ፊር (ትግ. ሐባ. ፈረረ)፡ ፊን (መ ውጣት - የሽንት የደም ") ።
ፊር አለ፡ ፊን አለ (ወጣ ") ።
ፊርማ (ዎች)፡ የጽፈት ያውራ ጣት ምልክት ። "ፊርማ" ጣሊያንኛ ነው፡ ከዐድዋ ጦር ናት ወዲህ በአማርኛ ተለምዶ ይሠራበታል ። "ጋዜጣን" እይ ።
ፊቅ፡ በሐረርጌ አውራጃ ያለ ቀበሌ ።
ፊተ መጣጣ፡ ደረቅ ሰው ከሲታ ሴት ።
ፊተ ገምዳዳ፡ ፊቱ የተቋጠረ ።
ፊተ ጨምዳዳ፡ ፊቱ የተጨመደደ (የከሳ ወይም ሽማግሌ ዞ ") ።
ፊተኛ (ኞች)፡ የፊት (በፊት ያለ የነበረ - ፊት የመጣ የተወለደ በኵር ቀዳሚ ግንባር ቀደም ") ።
ፊቱ ተሸበሸበ)፡ ተጨማደደ ።
ፊቱ፡ የርሱ ፊት ።
ፊታውራሪ (ፊት አውራሪ)፡ የፊት አዝማች (በስተፊት ጦርነት የሚያደርግ የጠ ላትን አገር የሚያስወርር የሚያስወጋ ") ። ማዕርጉ ከደጃዝማች በታች የኾነ (የሻለቃ ፥ ፊታውራሪ ") ። ሲበዛ "ፊታውራሪዎች" ይላል ።
ፊታውራሪ፡ አበ ' ጋዝ (የመንግሥት ጠቅላይ ጦር አዛዥ ") ። ማዕርጉ ከራስና ከደጃ ዝማች በላይ ከንጉሥ በታች የኾነ ("(፪ ሳሙ. ፲፥ ፲፮)") ።
ፊት (ትካት)፡ ንኡስ አገባብ (ቀ ድሞ አስቀድሞ ዱሮ ያለፈ ጊዜ ") ("(መክ. ፫፥ ፲፭)") ። (ተረት)፡ "ፊት የደረሰን ወፍ ይበላው" ። "ፊት የተናገረን ሰው ይጠላው" ። "የፊት ወዳጅ ኸን በምን ቀበርከው በሻሽ፡ የኋለኛው እንዳ ይሸሽ" ።
ፊት (ቶች - ፈየተ - ቀማ)፡ ገጽ ግንባር (ካንገት በላይ ያለ መልክ ገላ ") ። (ተረት)፡ "ከፍትፍቱ ፊቱ" ። "ለውሽማ ሞት ፊት አይነጭ ለት" ።
ፊት ለፊት፡ አንጻር ለአንጻር አቅ ጣ፵ ላቅጣጫ ።
ፊት መመለሻ፡ የሹምን መልካም አስተያየት ለማግኘት የሚሰጥ ገንዘብ ።
ፊት መን፡ የጕንጭ ጫፍ (የ ዦሮ አጠገብ ") ። "ነጩን" እይ ።
ፊት መግለጫ፡ እጅ መንሻ መተ ደያ ("(ማስደሰቻ)") ።
ፊት በር፡ የፊት በር (የስርቆሽ በር አቅጣጫ ") ።
ፊት ነሣ፡ ጠላ (በክፉ ዐይን አየ ") ።
ፊት አሳየ፡ ወደደ አፈቀረ አቀ ረበ ።
ፊት፡ በስተግንባር ያለ ስፍራ (የኋላ አንጻር ትይዩ ") ። "እዩ ለኤልያስ እፊቱ ወድቆ ሰገደለት" ።
ፊት፡ በኩል ወገን ። "ጭነቱ ወዳንድ ፊት ዘነበለ" እንዲሉ ።
ፊናጥ መር፡ ፈነጠ ። ፌንጣ ተንቀሳቃሽ ፈነጠ ።
ፊናጥ አለ፡ መር አለ ። ፈናጥ/ፊናጥ አለ፡ ብድግ ብድግ ' አለ (በቅሎው ") ።
ፊናጥ ፈነጠቀ፡
ፊናጥ፡ ብድግ መር ።
ፊን አለ፡ ፊር አለ (ከፊኛ ወጣ ") ። ፊን ፊን አለ፡ ፊር ' ፊር አለ ። "ፈነነንና ፈረረን አስተውል" '
ፊን አደረገ፡ ፊር አደረገ (በትንሽ በቀጪን ሸነ አፈሰሰ ") ።
ፊንቀራ፡ ቅማንት ያለበት አገር ።
ፊንጥጣ፡ ፈጋራ ሬብ እበትና ኵስ መውጫ መቀመጫ ።
ፊኛ (ትግ. ፍሒና)፡ ሥጋዊ የሽ ንት ከረጢት ሥሥ ረቂቅ ("(ዘሌ. ፩፥ ፲፮)") ።
ፊኛ ሆድ፡ ሆደ ጠባብ ። ፊን (ፈነነ)፡ ፊር መውጣት መፍ ሰስ ።
ፊኛ፡ በነፋስ በትንፋሽ የሚነፋ ላስ ቲክ (የንዶድ የሳሙና ዐረፋ ") ።
ፊው (አፊው/አፈወ/ፈዐወ)፡ ፉጨት (ማፋጨት ") ።
ፊው አለ፡ አፋጩ በትንፋሽ ድምፁን አሰማ (ለመጥራት ለማስጠንቀቅ ") ።
ፊደላዋሪያ (ፊደለ ሐዋርያ)፡ ልጆች ከፊደል በኋላ የሚማሩት መዠመሪያው የዮሐ ንስ መልክት ("(፩ዮሐ. ፳፯)") ። ፊደል መባሉ እንደ ፊደል ስለ ተጻፈ ነው ።
ፊደል ("(ኢሳ. ፳፱፥ ፲፩)")፡ መዠመሪያ ትም ርት (ተቀዳሚ ጥፈት ") ። ከአልፍ እስከ ፐ ያለ ፴፯ ኅርመት ባለ፯ ቅንጣት ። ከዚሁ ደግሞ እነጐኈኰቈ ባላ፭ ቅንጣት ናቸው ። "አበገደን" ተመልከት ። "የፊደል ትርጓሜ የነ ገር የቃል ምልክት ሥዕል ማጕሊያ መግ ለጫ ማለት ነው" ። "መዝገበ ፊደል" እይ ።
ፊደል ቈጠረ፡ ትምርት ዠመረ (አበ ገደ ወይም አኡ አለ ") ።
ፊደሎች (ፊደላት)፡ ኹለትና ከኹለት በላይ ያሉ ብዙዎች ።
ፊዶ (ኤፉድ)፡ ቍምጣ ጥብቆ ሴደ ርያ ማጠቆ እድፈ ከል ።
ፊጋ (ኦሮ)፡ የሚሸሽ የሚሮጥ የሚ ፈረጥጥ በሬ (ሸሺ ' ሯጭ ' ፈርጣጭ ' ወንባጅ ") ።
ፊጥ (ፈየጠ)፡ አንድ ነገር ላይ መ ውጣት ።
ፊጥ አለ፡ ወጣ ተቀመጠ በላይ ኾነ ።
ፊጥኝ፡ የኋሊት እስራት ግርንግሪት ። "የፊጥኝ አሰረ"፡ ኹለት እጆችን ወደ ኋላ ገጥሞ ቀፈደደ ("(ግብ. ሐዋ. ፳፪፥ ፳፭)") ።
ፋ) ፋጸየ)፡ አፋጩ አፉን አሞ ጠሞጠ (በትንፋሽ ድምፅ ጮኸ ዘፈነ ") ። "ዛሮ ችም በርሷያፋጫሉ" ("(ኢሳ. ፴፬፥ ፲፬)") "
ፋሌ፡ በአዲስ አበባ ምዕራብ ያለ ገጠር ።
ፋሌቅ፡ የሰው ስም ። "ፋሌግ" ።
ፋሌግ (ፋሌቅ)፡ የሰው ስም (የዔቦር ፥ ልጅ - ካዳም ፲፮ኛ ትውልድ ") ። በዘመኑ ምድር ስለ ተከፈለች "ፋሌግ" ተባለ ("(ዘፍ. ፲፥ ፳፭)") ። ዳግመኛም ገና ቀ ተወራራሾች ስለ ኾኑ በ "ፋሌግ" ፈንታ "ፋሌቅ" ይላል ።
ፋል (ፈልፈለ)፡ መስኖ ቦይ ። በግእዝ ግን "ርት" ተብሎ ይተረጐማል ።
ፋልማ፡ ውሃ ገብ መሬት (ፋል ") ።
ፋልማ፡ ውሃ ገብ ወፍራም መሬት ለም (የዠማ ዳር ምድር ") ።
ፋልቱ፡ የዕቃ ማመላለሻ ባቡር (አመ ንዝራ ሴት ") ።
ፋመ (ፍሕመ)፡ ጋመ በሰለ ተን ደረከከ መረተ (እሳት መሰለ ኾነ ") ።
ፋሚ (ፈሓሚ)፡ የሚፍም (ጋሚ ከ ሰሌ ሀሎ ደሬ ") ።
ፋሲለደስ፡ ከታወቁት ሰማዕታት አንዱ (የጽርእ - ግሪክ - ተወላጅ ") ።
ፋሲል፡ የሰው ስም (የጐንደር ንጉሥ ") ። ይህ ስም የሰማዕቱ ፋሲለደስ ከፊል ነው። "ፋሲል ይንገሥ፡ ሃይማኖት ይመለስ" ("(ዐፄ ሱስንዮስ)") ።
ፋሲካ፡ ከትንሣኤ ሌሊት 1 ሰዓት ወይም ቅዳሴ ውጭ ዠምሮ እስከ ዳግም ትንሣኤ ያለው ስምንት ቀን ። የፋሲካ ምስጢር ከግብጽ ወደ ፍልስጥኤም ከሲኦል ወደ ገነት መሻገር ነው ። ለፋሲካ የሚታረደውም በግ "ፋሲካ" ይባላል ("(ዘዳ. ፲፮፥ ፪፥ ፭፥ ፮)") ።
ፋሲጋ፡ ፋሲካ ።
ፋስ (ዐረ)፡ ዕንጨት የሚፈለጥበት ደ ንጊያ የሚጠረብበት ቦለድ ምሣር ወይም መጥረቢያ (የፈረንጅ ሥራ ") ።
ፋረ (ፈሐረ)፡ ውስጥ ውስጡን ታች ታቹን ጫረ ቈፈረ ማሰ ጐደፈረ (በጥ ፍር በዶማ ") ።
ፋሪ (ዎች/ፈሓሪ)፡ የ "ፋረ" /የሚ ፍር (ቈፋሪ ") ።
ፋራ፡ የሰው ማ (የከብት ሰኰና የረገጠው ዱካ ፍለጋ ") ። "አንዳንድ ሰዎች በፋራ ፈንታ ፋና ይላሉ፡ ስሕተት ነው" ።
ፋሬስ፡ የይሁዳ ልጅ (የዛራ መንትያ - ትርጓሜው ጣሽ ማለት ነው ") ።
ፋር ፋር አደረገ፡ ጫር ጫር አደ ረገ ።
ፋር፡ ጫር ።
ፋርስ፡ በእስያ ውስጥ ያለ አገር ። ዛሬ ግን "ኢራን" ይባላል ።
ፋርሶች፡ የፋርስ ተወላጆች ።
ፋርጣ፡ በበጌምድር ያለ ተራራ ።
ፋሮ (ዎች)፡ ዐረ እልፋእር (ዐ ይጥ ")፡ እንደ ፍልፈል ምድር የሚቈፍርና እቤት ውስጥ ገብቶ ወተት የሚደፋ (ቅቤ የሚበላ ጕሬዝማ አውሬ - ጐፍላ የፋደት ወገን ") ። "እግሮቹ ዐጫጭር ናቸው፡ ቈዳውን የፈረንጅ ሴቶች እየቀጣጠሉ ይለብሱታል" ። በትግሪኛም "አውጭ ፍሒራ" ይባላል ።
ፋሸረ - ፎከረ)፡ አንፋሸረ፡ አንገራ በደ ጕራ አበዛ ።
ፋሸከ (ተፈሥሐ)፡ ፈጽሞ ደስ ተ ሠኘ (አፍ ቂጡ ሣቀ - በፍስክ ሰዓት ") ።
ፋሸገ፡ ተከፈተ ተላቀቀ ። "አፋሸገ" እንጂ "ፋሸ" አልተለመደም ። "ፋሸከን" እይ ።
ፋሺስት ወደ ኢትዮጵያ በዘመተ ጊዜ የሰራዊቱ ብዛት ምድር ያላብስ ነበር ("አላባሽ ያላሰሰ የሚያላብስ አካዳኝ ") ።
ፋሽኮ፡ በቅል አምሳል የተሠራ ጠር ሙስ ። በጣሊያንኛ "ፊያስኮ" ይባላል ።
ፋሽኮ፡ አንኮላ ("ጐንደር") ።
ፋቀ (ፈሐቀ)፡ እድፍን ችክን ከጥ ርስ ላይ ወ ፈገፈገ ጠረገ (ጠጕርን ከብ ራና፡ ጭረትን ከእንሰት ከቃጫ ከሳማ ከና ") ።
ፋቀ/ፈሀቀ)፡ አፋቀ፡ ወደ ላይ ተነፈሰ (ሕቅ ሕቅ አለ ") ።
ፋቂ (ቆች/ፈሓቂ)፡ የፋቀ/የሚ ፍቅ (ደበናንሣ ቈርበት አልፊ ") ("(ግብ. ሐዋ. ፱፥ ፵፫፡ ፲፥ ፲፪)") ።
ፋቂታ (ፈሓቂት)፡ የምትፍቅ ሴት ።
ፋቂነት፡ ፋቂ መኾን ።
ፋቂያ/ፍቄት፡ የብራና ገለፈት (የሳ ንቃ የንዝርት ልላጊ ") ።
ፋቃ (ፈካ)፡ መንዶልዶያ የዦር የድልድል ፍንጭ ቀዳዳ ፉካ ።
ፋቅ (ፋህቅ)፡ ሕቅታ ስርቅ ስር ቅታ ።
ፋቅ (ፍሒቅ)፡ መፋቅ መራብ ።
ፋቅ አደረገ፡ በፍጥነት ፋቀ፡ ራበ ።
ፋታ፡ ፈንታ ዕረፍት ትንፋሽ ።
ፋቶ (ፈታ)፡ ባዘቶ ።
ፋነነ (ትግ. ፋሕነነ፡ ኰራ)፡ ተ ነሣ ቀና (ተቀሰረ ቆመ ") ። ጭራውን ለበሰ፡ ሮጠ ፈረጠጠ ("(፪ሳሙ. ፮፥ ፮)") ።
ፋነነ፡ ሳይታዘዝ ባሳቡ ዘመተ "
ፋና (ፓና)፡ ወፍራም ጧፍ ("(ኢሳ. ፷፪፥ ፩፡ ዮሐ. ፲፰፥ ፫)") ።
ፋና ወጊ፡ በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት የተሰቀለ ፋናን (ሻማን) በዘንግ እየወጋ (እየለኰሰ) የሚያበራ የመብራት ' ሹም ።
ፋና፡ ጭፍን ("የተጨፈነ ዐይን፲ ወይም አሞራ ሰው") (፪ ጴጥ. ፩፡ ፱) ።
ፋናኝ፡ የፋነነ/የሚፋንን (ሯጭ ፈር ጣ ") ።
ፋንታ፡ ዝኒ ከማሁ (ለፈንታ ") ። "ፋታን" እይ፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው ።
ፋንታዬ፡ የሰው ስም ("የኔ ፋንታ ድ ርሻዬ ማለት ነው፡ ለሴትም ይነገራል") ።
ፋንድያ፡ ደረቅ የሰው ዐር ("(ሕዝ. ፬፥ ፲፪፡ ፲፭)") ።
ፋንዶ/ፋንድያ (ዎች)፡ የጋማ ከብት ዙስ ። "የሜዳ አህያን የመሰሉ ጋማ ያላቸው የዱር እንስሶች ኹሉ ፋንዶ ይጥላሉ" ("(ሚል. ፪ - ፫)") ። "ዎች" ፋንዶን "ዮች" ፋንድያን ይከተላል ።
ፋኖ (ዎች)፡ አለቃ የሌለው ዘማች፡ በፈቃዱ የዘመተ ወያኔ ጦር ጠማሽ ።
ፋኖ፡ ወዶ ዘማች ።—ፋነነ፡
ፋኖ፡ የግስ ስም (ጠሞረ ተቤተ የ ሚል አንቀጽ ") ።
ፋኖስ (ሶች)፡ ከብርጭቆና ከመስ ተዋት ከነጭ ስኒ የተሠራ (ዘይት ቅባኑግ ጋዝ ነፍት ኤሌትሪክ ማብሪያ - የመቅረዝና የቀንዲል ዐይነት ") ። "የጣራ የግድግዳ የመን ገድ ፋኖስ" እንዲሉ ። "ፓና" የግእዝ፡ "ፋና/ፋኖስ" ያማርኛ ' ("(ዮሐ. ፲፰፥ ፫)") ። በጽርእ "ፓኖስ" በአረብኛም "ፋኑስ" ይባላል ።
ፋኖስ፡ መብራት ማብሪያ ፋና ።
ፋይዳ ቢስ፡ ረበ ቢስ (ያገኘው ፋይዳ መጥፎ የኾነ ") ።
ፋይዳ፡ ረብ ጥቅም ትርፍ ።
ፋይድ (ግእዝ ፋውድ)፡ መከራ ሥ ቃይ ፍዳ ውርደት ርግማን ። "አዳም ከፈጣሪ ከተጣላ በኋላ ምድረ ፋይድ ወረደ" ።
ፋደሸ) አፋደሸ፡ በሰው ነገር ገባ (አጐበጐበ ") ።
ፋደት (ቶች)፡ ግማታም ክርፋታም አውሬ (መልከ ጥርኝ ዥራተ ጐፍላ - ኹለተ ኛም ቀፎ ስለሚደፋ ዐራጅ ይባላል ") ። "ዐረ ደን" እይ ።
ፋደደ፡ ደፋ ደፋ አለ (ዥብኛ ኼደ ") ።
ፋገ (ፈአገ)፡ ወጣ ፈሰሰ ።
ፋገ፡ ሰፋ ሰፊ ኾነ (በዛ ቍስሉ ") ።
ፋገረ (ዕብ/ፋጋር/ደከመ)፡ እንደ ውሻ ረ ጐደፈረ (ፋረ ማሰ ቈፈረ - ለፋ ደከመ ") ።
ፋጕሎ (ዎች)፡ የሠም ዝቃጭ (ወይም አተላ - ባንድነት የተወቀጠ ድብልብል ከዳና ሰፈፍ ምጣድ ማሠሻ ") ።
ፋጕሎ፡ የማይረባ ሰው ("እዚህ ይግባ የማይባል ") ።
ፋጕሎ፡ የበሰበሰ ግንድ "
ፋጋ (ትግ/ፈግአ/ከፈለ/ፋግኣ)፡ የሸክላ የቅል ስባሪ (የግንድ ፍንካች - ወይም ቀራፎ ጐድጓዳ ዕንጨት ") ።
ፋጋ፡ ከላይ አንድ ከታች መንታ የኾነ ፈሳሽ ዠማ ።
ፋጋሪ፡ የፋገረ/የሚፋግር (ሰፊ ደካሚ ") ።
ፋጡማ፡ የሴት ስም (የእስላሞች ነቢይ የመሐመድ ልጅ ") ።
ፋጪ፡ ጦር ።
ፋጮ፡ ዳመጦ ሳይባዘት የሚፈተል ።
ፋፊ፡ የሚፋፋ/የሚዳብር ።
ፋፋ (ትግ. ፈሕፍሐ፡ መገመገ)፡ ወፈረ ዳበረ ደነደነ (ገላው አማረ - እንደ ልቡ ጡት ስለ ጠባ ስለ መገመገ ") ።
ፋፋቀ፡ ደመሳሰሰ አጠፋፋ (መላልሶ ላገ አለዛዘሰ ") ።
ፋፋቴ (ዎች)፡ የተንፋጁ/የሚንሿሿ (ሿሿቴ ኀይለኛ የገደል የተዳፋት ፈሳሽ ") ።
ፋፋቴ፡ ወተታም ላም ።
ፋፍ፡ ቧቧ) ። አንፋፋ/አንቧቧ ' በኀይል በብዛት ዐለሰ አወረደ አፈሰሰ ወተ ትን ውሃን ።
ፌ፡ የፊደል ስም ' ፈ ።
ፌልቲ፡ ፍልስጥኤማዊ (የዳዊት ጭፍራ - ኪ ወ ። ክ ") ።
ፌራ (ግእዝ)፡ ቸነፈር ወረርሽኝ ተላላፊ የተስቦ በሽታ ። "ፊር" ከዚህ ጋራ ይሰማማል ።
ፌሾ፡ ቶሎ የሚደርስ ገብስ ።
ፌቆ (ዎች)፡ የሠሥና የምዳቋ ዐይ ነት የዱር ፍየል (ከተራራና ከገደል ላይ የምትዘል የምትወረወር እንስሳ - መልከ ዳለቻ "(ባና)"፡ ዦሮዎቿ ከፍ ከፍ ያሉ ናቸው ") ። "ተባቱም እንስቱም ፌቆ ይባላል" ። "መጽሐፍ ግን በሽኮኮ ፈንታ ፌቆ ይላል፡ ስሕተት ነው" ("(ዘዳ. ፲፬፥ ፯፡ መዝ. ፻፬፥ ፲፰)") ።
ፌንጣ (ጦች)፡ ወዲያው ወዲያው ' ቶሎ ቶሎ የምትዘል ተንቀሳቃሽ ። (ተረት)፡ "ፌንጣ ብትቈጣ እግሯን ጥላ ኼደች" ። "ከወ ገኑ የተለየ አንበጣ ይኾናል ፌንጣ" ። "ተባቱንና እንስቱን ለመለየት" '
ፌንጣዋ፡ ፌንጣዪቱ (ያች ፌንጣ ") ።
ፌንጣው፡ ያ ፌንጣ ።
ፌዘኛ (ኞች)፡ ለግጠኛ ቧልተኛ ፌዝ ወዳድ ዋዘኛ ("(ምሳ. ፲፫፥ ፩፡ ኢሳ. ፳፱፥ ፳)") ።
ፌዝ፡ ለግጥ ቧልት ዋዛ ("(ኤር. ፲፱፥ ፰)") ።
ፌዝ፡ ቧልት ("(ፈየዘ)") ።
ፌጠኛ (ኞች)፡ ቀልደኛ ፌዘኛ "
ፌጥ፡ ቀልድ ለግጥ ፌዝ ።
ፌጦ፡ የቅመም ስም (ሲቀምሱት የሚ ለበልብ የሚፋጅ የሚያንገበግብ ፍሬ መድ ኀኒትነት ያለው ") ። "ፌጦ" የ(ፈየጠ) ዘር ነው ።
ፍሕሶ፡ ያበባ ስም (በበልግ ጊዜ የሚ ታይ ቀይ አበባ - የሬት ዘር ጒተናማ ") ። "ጐሚ ትን" ተመልከት፡ "ፍሕሶ" ግእዝኛ ነው ።
ፍሕሶ፡ ፈጨ፡
ፍለማ፡ ዝኒ ከማሁ ።
ፍለቃ፡ ቀደዳ ሥንጠቃ ።
ፍለጋ፡ መፈለግ ለማግኘት ። "ዛሬ ማታ ከብቶች ስለ ጠፉ ፍለጋ ኼጄ ' ነበር" ።
ፍለጋ፡ እግር የረገጠው (የጫማ የሰ ኰና ዱካ ፋራ ምልከት - ዘፍ. ፴፯፥ ፲፯፡ መዝ. ፳፭፥ ፬፡ ኢሳ. ፰፥ ፲፬፡ ኤር. ፶፪፥ ፰) ። በግ እዝ "አሠር" ይባላል ።
ፍሉስ (ዐረ)፡ ገንዘብ (ካንዱ ወደ ሌላው የሚፈልስ የሚዛወር ") ።
ፍላሎት፡ ዝኒ ከማሁ ለፍላት ።
ፍላሽ፡ ልውጥ ብረት (ኹለተኛ የተ ሠራ ' የታደሰ የብር ጌጥ ") ።
ፍላቂ፡ የፈሰሰ ፈሳሽ (የውሃ ፥ የጠላ የወተት ጠብታ ከላይ ካናት የወረደ ") ። "የል ጃገረዲቱ ጥርስ የርጎ ፍላቂ ይመስላል" ።
ፍላቃ፡ የተዳጠ/የተደፈጠጠ ።
ፍላት (ፍልሐት)፡ ሙቀት ትኵሳት (መፍላት ፍልነት - ኢሳ. ፩፥ ፴፩) '
ፍላት፡ ግለት ። "የአሕዛብ ነገሥታት ዐ ይን በፍላት ያፈሳሉ" ።
ፍላጎት (ቶች)፡ መፍቅድ ተፈላጊ ነ ገር ጕዳይ "
ፍላጭ፡ የፍልጥ ሥንጣሪ ። "(ያጥንት ፍ ላጭ፡ የሥጋ ቍራጭ)"፡ "ወንድም ቅርብ ዘመድ" ("(፪ሳሙ. ፭ ፮ ፩)") '
ፍላጻ '
ፍላጻ (ፈለጸ)፡ ጫፉ ስለትና ሹለት ያለው ዐጪር የብረት ቍራ (የቀድሞ ሰዎች በንወት ጫፍ አዋደው በቀስት እየነደፉ የሚወረውሩት ባለመርዝ የጦር መሣሪያ የበዳ ጸብት - ዘካ. ፱፥ ፲፬፡ ኤፌ. ፮፥ ፲፯) ። በግእዝ "ሐጽ" ይባላል ። ትግሬ ሐባብም ፍላጻን መንፈጽ ይለዋል፡ ቀስቱ ከነፍጥ ፍላጻው ከጥይት ጋራ አንድ ነውና ። ፈረ ንጆችም "ፍሌሽ" ይሉታል ።
ፍላጻ፡ የቅኔ አገባብ ስም (ነጠላና ድ ርብ ") ። "መጽሐፈ ሰዋስው" እይ ።
ፍላጾች፡ ኹለትና ከኹለት በላይ ያሉ ብዙዎች ("(ኢሳ. ፲፫፥ ፲፰)") ።
ፍል (ፍሉሕ)፡ የፈላ/የተፍለቀለቀ ።
ፍል ውሃ፡ ሙቅ ትኵስ ንፍር ውሃ (የቤት የበረሓ ") ።
ፍል፡ ችግኝ ።
ፍልማት፡ የፈለማ ኹኔታ ።
ፍልም፡ የተፈለመ የተመታ የቈሰለ ።
ፍልሰታ፡ በነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታ ችን ከመቃብር ተነሥታ ወደ ሰማይ መ ውጣቷ (የመውጣቷ የማረጓ በዓል - ፍልሰታ ለማርያም ") ።
ፍልሰት፡ መነቀል መውጣት ስደት (መ ") ።
ፍልሰፋ (ፍልሳፌ)፡ የጥበብ ምር መራ ጥልቅ ረቂቅ ሐሳብ ።
ፍልስ አለ፡ ፍንቅል ' አለ ።
ፍልስ ፍልስ አለ፡ ንቅል ንቅል አለ (ተነቃነቀ ተወዛወዘ ") ።
ፍልስ፡ የተነቀለ የተፈነቀለ (ንቅል ፍ ንቅል ጥርስ ደንጊያ ጕቶ ") ።
ፍልስልሱ ወጣ፡ ፈጽሞ ፈለሰ (ሥሩ ታየ ") ።
ፍልስልስ፡ ንቅልቅል ፍንቅልቅል ።
ፍልስጣ (እምከንቱ ውስተ ከንቱ)፡ "ከብላሽ ወደ ብላሽ ማለት ነው"፡ ሊቃውንትም "እኩይ ፍልስጣ ጸሓፌ ተምያን" ይሉታል ።
ፍልስጣ፡ የሰይጣን ስም (ሰው የሠ ራውን ኀጢአት በየቀኑ የሚጽፍ አሳጪ ጋኔን ") ።
ፍልስፍ (ፍልሱፍ)፡ የፈለሰፈ ።
ፍልስፍ፡ የተፈለሰፈ የፍልስፍና ሥራ ።
ፍልስፍና፡ ፈላስፋነት ።
ፍልቀቃ፡ የመፈልቀቅ ሥራ (ብተና ል የታ ") ።
ፍልቃቂ፡ ዝኒ ከማሁ ለፍልቅቅ (የተ ለየ የተከፈለ፡ ልዩ ክፍል ") ። "ያጤ ካሌብ ልጅ ዘእስራኤል የወርቅ ፍልቃቂ ይመ ስል ነበር" ።
ፍልቅ አለ፡ ፍስስ አለ ።
ፍልቅ አደረገ፡ ፍስስ አደረገ ።
ፍልቅ፡ የፈለቀ ምንጭ ።
ፍልቅልቅ አለ፡ ተፍለቀለቀ ።
ፍልቅልቅ፡ የተፍለቀለቀ/የሚፍለቀለቅ (ብዙ ምንጭ በያለበት በብዙ ወገን የሚ ፈላ ") ።
ፍልቅልቅታ፡ የመብረቅ ብልጭልጭታ ብርቅርቅታ ።
ፍልቅልቅታ፡ ፍልቅልቅ ማለት ።
ፍልቅቅ አለ፡ በጥቂቱ ሣቀ (ጥርሱን ገለጠ ") ።
ፍልቅቅ፡ የተፈለቀቀ/የተበተነ (ፍሬው ያልወጣ ጥጥ ብትን ") ። "የላላ የተከፈተ እግር ብረት ልል ክፍት" ።
ፍልክልክ አለ፡ ተፍለከለከ ።
ፍልክልክ፡ የተፍለከለከ ውንጅር ።
ፍልኳ፡ ሞላላ የገንዳ ታንኳ ። "የፍልኳ ምስጢር ላይኛነት ነው" ።
ፍልግ (ፍልቅ)፡ የተፈለገ የተሻ የ ተከፈለ ።
ፍልጠት፡ መለየት ልየታ ልዩነት ።
ፍልጠት፡ እኩሌታ ራስ ምታት (የራ ስን ግማሽ ለይቶ የሚያም ") ። "ራስ ፍልጠት ሆድ ቍርጠት" እንዲሉ ።
ፍልጥ (ጦች) (ፍሉጥ)፡ የተፈለጠ/የተሠነጠቀ ዕንጨት ። "(ተረት)" - የሺ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ ።
ፍልጥ አለ፡ ሥንጥቅ ፍንክት አለ ተ ፈለጠ ።
ፍልጥልጥ አለ፡ ተፈላለጠ ።
ፍልጥልጥ፡ የተፈላለጠ (ፍንክትክት ") ።
ፍልጹት (ፍላጹት)፡ የገዲ ዐይነት አሞራ (እንደ ፍላጻ የምትወረወር የምትበር ጥፍረ ፍላጻ ሲላ ወይም ሌላ ") ።
ፍልፈላ፡ ፍርፈራ ስርሰራ ነደላ ቅፍ ቀፋ (መፈልፈል ") ።
ፍልፈል (ሎች)፡ ምድር የሚምስ የሚ ፈረፍር የሚነድል' ዐፈር የሚቈልል ጥርሳም የዱር ዐይጥ ትልቅ ባለጠጕር ("(ኢሳ. ፪፥ ፳)") ።
ፍልፋይ (ዮች)፡ የንቡጥ ገለባ ።
ፍልፍሉ፡ የወንድ ስም (ሉ አባትን ያያል ") ።
ፍልፍሌ፡ የፍልፍል ወገን ("የኔ ፍልፍል ማለት ' ነው"፡ የወንድና የሴት ስም ይኾናል ") ።
ፍልፍል አለ፡ ተፈለፈለ (አማረበት ") ።
ፍልፍል፡ የተፈለፈለ (ቅርጽ ብስ ነዳላ፡ እሸት ጫጩት ዕንጨት ") ።
ፍልፍሏ፡ የሴት ስም (ሏ እናትን ያስ ተረጕማል ") ።
ፍማም፡ ባለፍም (ወይራ ግራር ፍም የሚወርደው ") ።
ፍም (ሞች) (ፍሕም)፡ የእሳት ምርት ቍልል ("(ዮሐ. ፳፩፥ ፱)") ።
ፍም ጫሪ (ፍንጫሪ)፡ ከቤተ ልሔም ፍም የሚጭር ዲያቆን (ፍሬ ሰሞ ነኛ፡ ከሰሞነኞች ፭ኛው ቀዳሽ ") ።
ፍሳሽ (ሾች)፡ ቤት ያፈሰሰው ውሃ "ፍሳሽ" (ከስፍር የተንጠባጠበ እኸል ወይም ሌላ ነገር ") ።
ፍስ፡ የነገር ጭብጥ (በዳኛ ፊት የፈ ሰሰ/የሚፈስ ") ።
ፍስ፡ የፈሰሰ ።—"ፈሰሰ" ።
ፍስ፡ የፈሰሰ/የቀለጠ/የነጠረ ወርቅና ብር ።
ፍሥሓ፡ ደስታ ።
ፍሥሕ፡ የአይሁድ ፋሲካ ።
ፍስስ አለ፡ ፈሰሰ ።
ፍስስ አደረገ፡ አፈሰሰ ።
ፍስክ (ፍሥሕ)፡ የተፈሰከ (ብሎት ሥ ጋና ቅቤ የሚበላበት ቀን ") ።
ፍስጥቅ (ጵስጥቂስ - ዐል)፡ የሽቱ ስም (ሽቱ ") ።
ፍረማ፡ ምልከታ ።
ፍረድ፡ በይን ("(ሚክ. ፮፥ ፩)") ።
ፍሪት፡ እጅግ ታናሽ (ወይም ጥቂት የኾነች ") ። "አንድ ፍሪት" እንዲሉ ።
ፍሪዳ (ዶች)፡ ለመታረድ ከመንጋ መካከል የተለየ በሬ (የሥጋ ከብት ሰንጋ ገች ") ።
ፍራሽ (ሾች - ዐረ. ፈርሽ)፡ በው ስጡ ጠጕር ጥጥ ቃጫ አበባ ያለበት (በሰው ቁመት ልክ የተሰፋ ከረጢት - መደላድል ምቹ መኝታ የሚደላ ") ።
ፍራሽ፡ ከጣራ ከግድግዳ ከግንብ የፈ ረሰ ዕንጨት ደንጊያ ። "የቤት ፥ ፍራሽ" እንዲሉ ("(መዝ. ፻፪፥ ፲፬፡ ፻፵፬፥ ፲፬)") ። ሲበዛ "ፍራሾች" ይ ላል ("(ኢሳ. ፲፯፥ ፱)") ።
ፍራት (ፍርሃ)፡ ትእዛዝ አንቀጽ ("ሰውዮ ይህችን ሴት ፍራት ") "
ፍራት (ፍርሀት)፡ መፍራት (ሥጋት ጥርጥር ") ። "ፍራት የናላ ነው፡ ከቁም ይጥላል" ።
ፍራት አልባ፡ አለፍራት የሚኖር ብሄሞት ("(ኢዮ. ፵፩፥ ፳፭)") "
ፍራት ፍራት አለው፡ ባር ባር አለው (ፈጽሞ ፈራ ") ።
ፍራት, ብርክ, እንቅጥቅጥ (ከቅምጥ የሚፈነቅል) - ፍርሃት, ብርክ, እንቅጥቅጥ (ከወገብ የሚጀምር).
ፍራት፡ ሥጋት፡ ፈራ ።
ፍራት፡ የቍስል ስም (በልጆች ራስ ላይ የሚወጣ ክፉ ቍስል - ሲያዩት ፍራትን የሚያመጣ ") ።
ፍራቻ፡ ዝኒ ከማሁ (ለ "ፍራት") ።
ፍራንክ (ፍራንስ)፡ የገንዘብ ስም (በወርቅና በብር ፈንታ የሚገበይበት - የፈረን ሳይ መንግሥት የወረቀት የናስ የኒኬል ገን ዘብ ") ። ከ1936 ዓ.ም. ወዲህ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ በስሕተት፡ የመንግሥቱን ገንዘብ 10ሩን ብር ፓውንድ አላዱን 1 ሺሊንግ ፥ 1ዱን ብር 2 ሺሊንግ ሩቡን ስሙኒ እያለ እንደሚ ጠራው፡ ዝርዝሩንም 2 መሐለቅ 4 መሐለቅ በማለት ፈንታ 2 ፍራንክ 4 ፍራንክ ይለ ዋል ።
ፍራጣ፡ ጥሬ ገንዘብ ።
ፍራፍሬ፡ የፍሬ ፍሬ (ብዙ ዐይነት ፍሬ ውጥንቅጥ ") ።
ፍሬ (ዎች)፡ የማንኛውም ዕንጨትና ተክል ዘር (ከሥር ወይም ከጫፍ የሚገኝ ክብ ሞላላ ጠፍጣፋ - የሣር የቅጠል የእ ኸል የቅመም ቅንጣት፡ ያውሬ ቡችላ፡ የን ስሳ እንቦሳ፡ ያሞራ የወፍ ጫጩት፡ የሰው ልጅ ") ። (ተረት)፡ "የልጅ ነገር ኹለት ፍሬ፡ አንዱ ብስል፡ አንዱ ጥሬ" ።
ፍሬ ሰሞነኛ፡ ከእሑድ "(ቅዳሴ ውጭ)" እስከ እሑድ ሙሉ ሳምንት ከቤተ ክሲ ያን የማይለይ የማይታጣ ቍልፍ "(መክፈቻ)" ያዥ፡ ካ፬ቱ ሰሞነኞች አስቀድሞ ወደ ቤተ ልሔም ይመጣና የሚላክ "(ኅብስተ ቍርባን የሚያዘጋጅ)"፡ ዋና ሰሞነኛ መሧዕት እየሠራ መሶበ ወርቅ የሚሸከም፡ መብራት ያዥ ። "ገፈፈ" ብለኸ "ገፈፎን" ተመልከት ።
ፍሬ ሰው፡ ቁም ነገራም ውለኛ ።
ፍሬ ቅዳሴ፡ በየበዓሉ እየተለዋወጠ በቅዳሴ ጓዝ ውስጥ እየገባ የሚነገር ዋና ቅዳሴ (ሐዋርያት የእስክንድርያ የአንጾኪያ የቍ ስጥንጥንያ ሊቃነ ጳጳሳት የቂሳርያው ባስል ዮስ የኢትዮጵያ ሊቃውንት በየጊዜው የደረ ሱት ፲፬ ቅዳሴ ") ።
ፍሬ ቢስ፡ ዐረማሞ ።
ፍሬ ቢስ፡ ከንቱ ብላሽ ሰው (ቁም ነገር የሌለው ") ።
ፍሬ ቢስ፡ ፍሬው የማይበላ ዕፅ ።
ፍሬ ነገር፡ የነገር ዋና አርእስት ።
ፍሬ ከርሥ፡ የሆድ ፍሬ (ልጅ ኹኖ የሚወለድ - ያባት ዘር ") ።
ፍሬ ግብር፡ ዋና ዐይነተኛ ግብር ዓሥራት ።
ፍሬ ፈርስኪ፡ የማይረባ ፈሎ የሌ ለው ። "ያቶ እከሌ ነገር ፍሬ ፈርስኪ ነው" እንዲሉ ። "ኪ" ግእዛዊ ዝርዝር ነው ("የፈርስሽ ፍሬ" ያሠኛል ") ። "በፈርስ ውስጥ የተገኘ ፍሬ እንዳይረባ ይህም እንደዚያ ነው" ። ዳግመኛም በግእዝ "ፍሬ ከርሥኪ" የተባለውን ማይምን "ፍሬ ፈርስኪ" ይላል ።
ፍሬ፡ ቍላ ቈለጥ ።
ፍሬ፡ በወጥ ውስጥ ያለ ሥጋ ።
ፍሬምናጦስ፡ የከሣቴ ብርሃን ሰላማ ጥንታዊ ስም፡ ግሪኮች "ፍሩሜንቴዎስ" ይሉታል ።
ፍሬያማ፡ ባለፍሬ (ብዙ ፍሬ የሚሰጥ መሬት ") ።
ፍሬያም፡ ዝኒ ከማሁ ።
ፍርም፡ የተጻፈ/የተፈረመ ውል ደብዳቤ ።
ፍርምርም፡ የተፍረመረመ (ትጉህ ") ።
ፍርምባ/ፍርንባ፡ የእንስሳትና የአራዊት ደረት ። "እን ቢያን" ተመልከት ።
ፍርምባ፡ የሥጋ ስም (የቅዱስ ከብት ደረት ሥጋ ") ("(ዘፀ. ፳፱፥ ፳፮፥ ፳፯)") ። በግእዝ "ተላዕ" ይባላል ።
ፍርስ አለ፡ ፈረሰ ።
ፍርስ፡ ዝኒ ከማሁ ።
ፍርስራሽ (ሾች)፡ ዝኒ ከማሁ (ለ "ፍርስ ርስ ") ።
ፍርስርስ አለ፡ ብትንትን አለ ።
ፍርስርስ፡ የፈራረሰ (ብትንትን ") ።
ፍርሻ፡ መፍረስ ። በግእዝ "ፍርሰት" ይባ ላል ።
ፍርቀቃ፡ ፍንቀላ ሥንጠቃ ።
ፍርቃ፡ በበጌምድር ክፍል ያለ አገር ።
ፍርቃ፡ አባሎ ። "ፍርቃ" ማለት ፍልጡን ያሳያል ።
ፍርቅ ጸያፍ፡ አለደንቡ የተጻፈ የተነ ገረ የቅኔ አገባብ፡ ተሳቢ ኹኖ ከሳቢው፡ ቅጽ ልም ኹኖ ከባለቤት የራቀ ማለት ነው ።
ፍርቅ፡ ግማሽ እኩሌታ ("በትግሪኛ ፍ ርቂ ይባላል ") ።
ፍርቅርቅ፡ የተፍረቀረቀ (ስብርብር ንፍ ርቅርቅ ") ።
ፍርኑስ፡ የሴት ስም ።
ፍርንስ አለ፡ ትኝት አለ (ተፈረነሰ ") ።
ፍርንትት፡ ንፍፊት (የጕያ ዕብጠት ") ።
ፍርንችት (ትግ)፡ ቍላ ቈለጥ ።
ፍርንድስ፡ ወፍራም ሰው ። "ግርንድስን" ተመልከት ።
ፍርኵታ (ፈረከሰ)፡ የተቦረቦረ ዋሻ ግንድ ንቃቃት ጐሬ ።
ፍርኵታ፡ የዕጨ ዮሐንስ ገዳም በመ ንዝ ክፍል ያለ ።
ፍርክስ አለ፡ ድቅቅ አለ ።
ፍርክስ፡ ዝኒ ከማሁ (ለ "ፈርካሳ") ።
ፍርክስክስ አለ፡ ስብርብር ' አለ ።
ፍርክስክስ፡ የተፈረካከሰ ።
ፍርክርካም፡ ባለፍርክርክ ።
ፍርክርክ አለ፡ ሽርፍርፍ አለ ።
ፍርክርክ፡ የተፍረከረከ (ሽርፍርፍ ቅር ፍርፍ ") ።
ፍርክርክነት፡ ቅርፍርፍነት ።
ፍርዝ (ዐረ)፡ ሰንጠረዥ ።
ፍርዝ፡ በዳርቻ ያለ የቆመ የሰንጠ ረዥ መጫወቻ (የንግሥት ተምሳሊት ") ።
ፍርዝዝ አለ፡ ተንፈረዘዘ ።
ፍርዝዝ፡ ቅብንን ።
ፍርደት፡ ፍርጃ (መፈረድ ") ።
ፍርድ ለበሰ፡ ሕግን ደንብን ወግን ልማድን ተከተለ (የተፈረደበትን ፍርድ ተቀ በለ ") ።
ፍርድ ቀጠነ)፡ ጐደለ ። (ተረት)፡ "ከውሃ የቀጠነ ከዐይን የፈጠነ" ።
ፍርድ ቤት፡ ፈራጆች ዳኞች ወንበ ሮች ፍርድ የሚያድሉበት ቤት ። "ጠቅላይ ፍርድ ቤት"፡ "ከፍተኛ ፍርድ ቤት" እንዲሉ ።
ፍርድ፡ ብይን ፍት ("(ሚክ. ፮፥ ፪)") ።
ፍርዶ ገምድል፡ አድላዊ ጕቦኛ ዳኛ (ፍርድን የሚገመድል ") ።
ፍርጃ፡ ድንገተኛ አደጋ (ከሰማይ የታ ዘዘ - ምክንያቱ ያልታወቀ ") ።
ፍርግርግ፡ የተፍረገረገ (ቅዝምዝም ው ዝግዝግ ") ።
ፍርግጥ አለ፡ ተንፈራገጠ ።
ፍርግጥ፡ ዝኒ ከማሁ (ለ "ፈርጋጣ") ።
ፍርጠጣ፡ ሩ ግልቢያ ሽሽት ኵብ ላላ ።
ፍርጣጣ፡ የዛፍ ስም ("(ፊልክስዩስ ገጽ ፳)") ።
ፍርጥ (ፍሩጽ)፡ የፈረጠ/የመገለ ።
ፍርጥ አለ፡ ፈረጠ ።
ፍርጥ ፍርጥ አለ፡ መላልሶ ፈረጠ ።
ፍርጥም አለ፡ ፈረጠመ ።
ፍርጥም፡ ዝኒ ከማሁ (ጥርንቅ ") ።
ፍርጥርጥ አለ፡ ተፍረጠረጠ ።
ፍርጥርጥ፡ የተፍረጠረጠ (ድፍጥፍጥ ") ።
ፍርፈራ፡ ፍልፈላ ሽርሸራ ምሰት ቍ
ፍርፋሪ (ሮች)፡ የንጀራ የዳቦ ድቃቂ ("(ሉቃ. ፲፮፥ ፳፩)") ። በግእዝ "ፍርፍር" ይባላል ። "ለጐ በዝ ሰንጋ ፈረስ፡ ለፈሪ ፍርፋሪ" እንዲሉ ልጆች ።
ፍርፋሪት፡ ጥቃቅኒት ።
ፍርፍር አለ፡ ተንፈራፈረ (ወፍኛ ተን ቀሳቀሰ ") ።
ፍርፍር አለ፡ ተፈረፈረ (ድቅቅ አለ ") ።
ፍርፍር፡ የተፈረፈረ/የደቀቀ ። "ፍርፋሪ" ጥሬ፡ "ፍርፍር" ቅጽል መኾኑን አስተውል።
ፍርፍርት (ግእዝ)፡ ድርጭት ።
ፍሽካ፡ ስለ ድንገተኛ ጥሪ ማጫ ታናሽ ብረት ። ጣሊያኖች "ፊስኪዮ" ይሉታል ። "ፍሽካ ነፋ"፡ "ፍሽካ አስጮኸ"፡ "በፍሽካ አፋጯ ጠራ" ።
ፍሽካና/ፍንሽካና፡ ፍጹም ደስታ ። ና፡ ምእላድ ፲ ን ስሯጽ ነው ።
ፍቀት (ፍሕቀት)፡ ጽፈትን የማጥ ፋት የመደምሰስ ሥራ ።
ፍቁር፡ የተፈቀረ የተወደደ ። "ይህ ቃል ግእዝ ሲኾን ባማርኛም ይነገራል" ። "መሰለ" ብለኸ "ምስለን" እይ ።
ፍቅ (ፍሑቅ)፡ የተፋቀ (ልዝብ ") ።
ፍቅ (ፍቁዕ)፡ የተፈቃ (ብጥ ሥን ጥቅ ትፍትፍ ") ።
ፍቅረኛ፡ ሰው ወዳድ ፍቅር ዐዋቂ ሰላማዊ ።
ፍቅሩ ጥኑ፡ ጭጐጐት የጥጥ ፍንድ የሚያካክል ነጭ የንጨት አበባ (ልብስንና ጠጕርን ከያዘ የማይለቅ፡ ዳግመኛም የካህን ቂም ይባላል ") ።
ፍቅሩ፡ እንደ ' "ፍቅሬ" ያለ ከፊለ ስም ።
ፍቅሩ፡ የርሱ ፍቅር '
ፍቅሬ ግንብ፡ ባንኮበር የሚገኝ ቀ በሌ ።
ፍቅሬ፡ የሽቱ ስም ("ፍቅሬ የሚባል ሰው መዠመሪያ የሼጠው ሽቱ ") ።
ፍቅሬ፡ የኔ ፍቅር ።
ፍቅሬ፡ የክርስትና ከፊለ ስም ።
ፍቅር (ፍቁር)፡ ወዳጅ ። "እከሌና ' እከሌ ፍቅር ናቸው" ።
ፍቅር፡ ውድ ሰላም ስምም ። (ተረት)፡ "ሆዳም ሰው ፍቅር አያውቅም" ።
ፍቅታት (ፍቅዐት)፡ ስለት ያለፈ በት (የሰው ፊት ሰንበር ቍርታት ብጥታት ትፍትፋት፡ የዘር መለያ ቅርጽ ") ።
ፍቆሽ፡ ዝኒ ከማሁ ።
ፍተራ፡ ውጠራ ።
ፍተሻ፡ ብርበራ ምርመራ ቅንቀና ።
ፍተታ (ፍታቴ)፡ ቈረሳ ገመሳ ት ንተና ።
ፍተጋ፡ ወቀጣ ሽክሸካ ዐወዳ ።
ፍቱ ርቱ ሥላሴ፡ ፍርዱ ቅን ("(ቀ ጥታ)") የኾነ ሥላሴ ። በግእዝ ሲነገር "ዘፍትሑ ርቱዕ"፡ "ርቱዐ ፍትሕ" ያሠኛል ።
ፍቱን፡ የተፈተነ/የተመረመረ (አብነት ገቢር ኹነኛ ዋና መድኀኒት ል ' ለይኩን ") ።
ፍታል (ትግ)፡ የቤት ፈትል ።
ፍታቴ (ጥተ) መፈተት ። (ጥፈ) መፈተት፡ ቈረሳ ፍተታ ። "የቅዱስ ቍርባን" ("(ግእዝ)") ። "ፈትቶ" ("(ዘር)") መቍረስ ። "ጸሎተ 'ፈትቶ'" እንዲል ቅዳሴ ።
ፍታት (ፍትሓ)፡ ልቀቃት ስደዳት ። (ግጥም)፡ "ምን ያሉ ቄስ ናቸው ተዝካር የለ መዱ፡ አስታርቁኝ ብላቸው ፍታት ብለው ኼዱ" ።
ፍታት (ፍትሐት)፡ የሙታን ጸሎት፡ ትርጓሜው ከኀጢአት ማሰሪያ መፍታት መፈ ታት ።
ፍታች (ፍት)፡ የዳቦ የንጀራ ቍ ራሽ (አፍ የሚመጥነው ") ።
ፍታነገሥት (ፍትሐ ነገሥት)፡ የመ ጻፍ ስም ። ትልቁ ቈስጠንጢኖስ ያስጣፈው ባለ፪ ክፍል መንፈሳዊና ሥጋዊ መጻፍ ። እንደ ጊዜው የክርስቲያን ነገሥታት የሚፈርዱት ፍርድ በውስጡ ስለ ተጻፈ "ፍትሐ ነገሥት" ተባለ ።
ፍታውጪ (ፍት አወ ጪ)፡ እው ነት ፈራጅ ።
ፍታይ፡ የጥጥ የፈትል ውጤት ።
ፍታጎ፡ ዐጪር ጕጮ ሣር ።
ፍት (ፍትሕ)፡ ፍርድ ብይን ።
ፍት ርት (ፍትሕ ርትዕ)፡ ቅን ፍርድ ።
ፍትሐ ብሔር፡ የመጻፍ ስም (ሥጋዊ ያገር ፍርድ ማለት ነው ") ።
ፍትሕ፡ ፍርድ ፈታ ።
ፍትለክ አለ፡ ፍትት ሹልክ ውጥት አለ (ውሉ እስራቱ ") ።
ፍትል፡ የተፈተለ/የተጠመረ/የተገመደ ። በግእዝ "ፍቱል" ይባላል ።
ፍትል፡ ድርና ማግ ዝሓ ግራ (ክር ወፍራምና ቀጪን ") ። "የቤት ፈትል"፡ "የባሕር ፈትል" እንዲሉ ።
ፍትልት፡ የተጠመዘዘች/የተጠመረች (ደረቅ ምራን ፥ የግንባር ቈዳ ") ።
ፍትልትል፡ የተፍተለተለ (ቀስ ብሎ ኻያጅ ጕትት ") ።
ፍትር አደረገ፡ ውጥር አደረገ ።
ፍትር፡ የተፈተረ/የታነቀ/የተጨነቀ (ው ጥር ") ።
ፍትሽ፡ የተፈተሸ/የተበረበረ/የተመረመረ (ብርብር ምርምር ") ።
ፍትት (ፍቱት)፡ የተፈተተ/የተቈረሰ (ጕርማጅ ዳቦ ") ።
ፍትወተ ሥጋ፡ የሥጋ መሻት (ሥ የታ የዘር ፈቃድ ") ("(ዘፍ. ፲፰፥ ፲፪)") ።
ፍትወተኛ፡ ፍትወት ያለበት/የበዛ በት (ባለፍትወት ሰው ፍየል ") ።
ፍትወት (ፈተወ)፡ ያልተሰጠውን መሻት መፈለግ መውደድ ።
ፍትጋት፡ ፍተጋ ።
ፍትግ፡ የተፈተገ (ልጦ ጕርዶ የወ ጣለት ቈሎ ዳቦ የሚኾን ስንዴ ገብስ ") ። በግእዝ "ልቱም" ይባላል ።
ፍትፈታ፡ የመፈትፈት ሥራ ።
ፍትፋች (ቾች)፡ የፈተፈተ/የሚፈ ተፍት ። (ተረት)፡ "የዋስ ተማጋች፡ የቈማጣ ፈትፋች" ።
ፍትፋች፡ አዋሻኪ ነገር አመላላሽ ።
ፍትፍት፡ የተፈተፈተ (ደቃቅ እን ጀራ በውሃ የራሰ ") ። (ተረት)፡ "ከፍትፍቱ ፊቱ" ። "ማቶትን" እይ ። (ያቃቢት ፍትፍት)፡ ጠላና ወጥ ያነሰው ደረቅ ።
ፍቹ፡ ዝኒ ከማሁ (ፍራሽ ወና ") ("(ዘኍ. ፴፫፥ ፶፪)") ።
ፍቼ (ኦሮ. ሠሥ)፡ ከደብረ ሊባ ኖስ በስተደቡብ አፋፍ ላይ ያለ ቀበሌ ። "ፍ ቼና ተፋ" ባማርኛ ይተባበራሉ ። (ግጥም)፡ "በ ላኹ በላኹና ሆዴን ጨነቀው፡ እንደ ምን አ ድርጌ ተፍቼ ላውጣው" ("(ባሻ ባሪያው)") ።
ፍች (ቾች - ፍቱሕ)፡ የተፈታ (ባ ድማ ባዶ ጠፍ ") ("(ሕዝ. ፳፱፥ ፲፥ ፲፱፡ ኢሳ. ፶፪፥ ፱)") ።
ፍች/ፍቺ፡ መፍታት/መፈታት ። "በሙሴ ሕግ ሚስቱን የሚፈታ የፍችዋን መጻፍ ይ ሰጣታል" ።
ፍች፡ ትርጓሜ ።
ፍናዋተ ቢስ፡ ልክስክስ ምናምንቴ ሰው ።
ፍናዋት (ፈነወ)፡ መንገዶች ጥርጊያ ዎች ጐዳናዎች መዳረሻዎች ።
ፍናዋት፡ ዐመሎች ሥራዎች ፍለጋዎች ።
ፍናጅ፡ የባሪያ ስም (የውላጅ ልጅ ፪ኛ ባሪያ ") ።
ፍን ።
ፍንሽካና፡ ፍጹም ደስታ፡ ፋ ሸከ ።
ፍንቀላ፡ ግልበጣ ቀረፋ ።
ፍንቃይ፡ የመሬት የምርጊት የቍስል ልጣጭ ቅራፊ ።
ፍንቅል አለ፡ ግልብጥ አለ (ተፈነቀለ ") ።
ፍንቅል፡ ዝኒ ከማሁ (የተገለበጠ ግል ") ።
ፍንቅልቅል አለ፡ ቅርፍርፍ አለ (ተፈነቃቀለ ") ።
ፍንቅልቅል፡ የተፈነቃቀለ ግልብጥብጥ ።
ፍንትት አለ፡ ዕጥር አለ ።
ፍንትው አለ፡ ቅልጥጥ አለ (ግልጥ ") ።
ፍንትው፡ የተጠረገ የተገለጠ (ግልጥ ጥሩ ስፍራ ቤት ") ።
ፍንችር አለ፡ ውድቅ ሙትት ድብን አለ ።
ፍንችር፡ የተፈነቸረ የሞተ ።
ፍንከራ፡ ገለጣ ከፈታ ።
ፍንከታ፡ ፈለጣ ገመሳ ጭፍለቃ ።
ፍንካች (ቾች)፡ ግማሽ የባቄላ ክክ፡
ፍንክር፡ ዝኒ ከማሁ ("(ኅፍረተ ብእ ሲት)") ።
ፍንክርክር አለ፡ ተፈነካከረ ።
ፍንክርክር፡ የተፈነካከረ (ግልጥልጥ ክ ፍትፍት ") ።
ፍንክት አለ፡ ፍልጥ ክፍል አለ (ተፈነከተ ") ።
ፍንክት፡ ዝኒ ከማሁ (ስብር ") ።
ፍንክትክት፡ የተፈነካከተ/የተሰባበረ (ፍልጥልጥ ስብርብር ") ።
ፍንክች አለ፡ ተደፈረ ተነካ ተበ ገረ ።
ፍንክች፡ ንክች ። "ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ" እንዲሉ ።
ፍንክንክ፡ የተፍነከነከ/የተደሰተ (ደስ ") ።
ፍንዝንዝ፡ የተፍነዘነዘ (ቅንዝንዝ ክን ፍንፍ ክልፍልፍ ") ።
ፍንደቃ፡ ፍጹም ደስታ ዝላይ ።
ፍንዱቅ፡ የንግድ ቤት መብል መ ጠጥ ያለበት ("(ግእዝ)") ።
ፍንዳታ፡ ሥንጥቃት ፍካት (ወከክ ማለት ") ።
ፍንድ፡ ጥጥ ከነፍሬው ።
ፍንድር አለ፡ ፈነደረ ።
ፍንድቅ አለ፡ ጭራሽ ተደሰተ (ፍ ንጥዝ ' አለ ") ።
ፍንድቅ፡ የፈነደቀ ደስ ያለው የተ ደሰተ ።
ፍንድድ፡ ጕንብስ (የኳስ ጨዋታ ") ።
ፍንጃል፡ ዐረብኛ ነው፡ በግእዝ "ፍያል" ይባላል ("(መሳ. ፭፥ ፳፭)") ። "ስኒን" እይ ።
ፍንጃል፡ እግራም ጥዋ ትልቅ ስኒ ' የሻይ የቡና የወተት መጠጫ "
ፍንጃሎች፡ ጥዎች ስኒዎች ("(ዘፀ. ፳፭ '
ፍንጅ፡ ኹለት የሰንሰለት ቀለበት ። "እ ሰር በፍንጅ ጣል በደጅ" እንዲሉ ።
ፍንጅር፡ የፈነጀረ የጠመመ ።
ፍንጅርጅር፡ ውልግድግድ (የተራራቀ ላይና ታች ' የኾነ ") "
ፍንገላ፡ ግልበጣ ጥሎሽ ።
ፍንጋ፡ ብላሽ ("(ግእዝ)") ።
ፍንግል አለ፡ ውድቅ አለ (ተፈነ ገለ ") ።
ፍንግል፡ ዝኒ ከማሁ (የተጣለ ውድቅ ") ።
ፍንግልግል አለ፡ ተፈነጋገለ ።
ፍንግልግል፡ የተፈነጋገለ "
ፍንጠቃ፡ የመፈንጠቅ ሥራ (ብተና ") ።
ፍንጠዛ፡ የመፈንጠዝ ሥራ '
ፍንጣሪ፡ የተፈነጠረ (ታናሽ የፍም ቍራጭ ስባሪ - ፍንካች ") ። "የእሳት የደንጊያ የቦምብ ፍንጣሪ" እንዲሉ ።
ፍንጣቂ፡ የውሃ የደም የወጥ የቀለም የዘይት የቅባት ቅንጣት ጠብታ ።
ፍንጥር አለ፡ ተፈነጠረ ።
ፍንጥር፡ ዝኒ ከማሁ ።
ፍንጥርጌ፡ በጠራ ውስጥ ያለ ቀበሌ ("የፍንጥር ምድር" ማለት ነው ") ።
ፍንጥቅ አለ፡ ብትን አለ ። "ጨረሯ ፍንጥቅ ' አለች" እንዲሉ ።
ፍንጥቅ፡ የተፈነጠቀ የተረጨ ብትን ።
ፍንጥቅጣቂ፡ የተፈነጣጠቀ (ብትንትን ") ።
ፍንጥቅጥቅ አለ፡ ብትንትን አለ (ተ ፈነጣጠቀ ") ።
ፍንጥቅጥቅ፡ ዝኒ ከማሁ (ነጠብጣብ ") ።
ፍንጥዝ አለ፡ ፈነጠዘ ።
ፍንጥዝ፡ የፈነጠዘ የተደሰተ ።
ፍንጥጫ፡ የመፈናጠጥ ኹኔታ (አቀማ መጥ ") ።
ፍንጨታ፡ ዝላይ ቡረቃ ።
ፍንጫሪ፡ ፍም ጫሪ፡ ፋመ ። ፍንጭት፡ ክፍት፡ ፈነጩ ። (ፈነከ)፡ አፍነከነከ፡ አስደሰተ ።
ፍንጭ (ጮች)፡ የቀፎ ያፍን የጡት የእስኪት የምንጭ የዕባጭ አፍ ቀ ዳዳ ።
ፍንጭት (ቶች)፡ በጥርስና በጥርስ መካከል ያለ ክፍት ባዶ ("ጥርሰ ፍንጭት" እንዲሉ ") ።
ፍንጭት፡ ሞርስ ።
ፍንፍን አለ፡ ተፈናፈነ (ተፍጨረጨረ ወዲያና ወዲህ አለ ተጋ ተረ ") ።
ፍንፍን፡ የተፈናፈነ ።
ፍከራ/ፉከራ፡ ዘራፍ ማለት (ድንፋታ ዠብዱ ቈጠራ ") ።
ፍካሬ፡ ትርጓሜ ። ከዳዊት አርእስት አን ደኛው መዠመሪያው ።
ፍካሬየስ (ፍካሬ ኢየሱስ)፡ ጌታችን ለሐዋርያት የነገራቸው ትንቢት ።
ፍካት፡ የማሽላ ቈሎ ኹኔታ ፍንዳታ፡ የፊት ወለልታ ።
ፍክ፡ የፈካ ቈሎ (የጥጥ ፍንድ አበባ ") ።
ፍክክር/ፉክክር፡ ውድድር ክርክር ። "(ተረት)" - የፍክክር በር ሳይዘጋ ዐደር ።
ፍወሳ (ፍዋሴ)፡ የመፈወስ ሥራ ።
ፍዝ፡ ዝኒ ከማሁ ለፈዛዛ ።
ፍዝ፡ የዜማ ምልክት ስም ። "ዝን" ተመ ልከት ።
ፍዝዝ አለ፡ ፈዘዘ ።
ፍየለ ፈጅ፡ የንጨት ስም (በወይ ናደጋ የሚበቅል ዕንጨት መቍጠሪያ የሚ ኾን - ቀጥቅጠው ሲያደርቁት እንደ ክትክታ ይበራል ") ። "ፍየለ ፈጅ" መባሉ ቅጠሉን ፍየል ስለማይበላው ይመስላል ።
ፍየሉ፡ ያ ፍየል (የርሱ ፍየል ") ።
ፍየላፍ (ፍየል አፍ)፡ አፈኛ ለፍ ላፊ ቀባጣሪ ሰው ።
ፍየል (ሎች)፡ ከበዳ ፍየል የተለየ ' የቤት እንስሳ ከብት ። "(ተረት)" - ፍየል ከመ ድረሷ ቅጠል መበጠሷ ። "ሜ ባልኩ ፍየል"
ፍየል ፈለግ፡ የማኅደር የመጣፍ መ ደጐሻ ግፉ የፍየል ጥፍር የመሰለ ዕንወት ። "ፈለገን" ተመልከት ።
ፍየሏ፡ የርሷ ፍየል ። (ሜዳ ፍየል)፡ የ ዱር የበረሓ የሜዳ ፍየል በያይነቱ ።
ፍየሏ፡ ፍየሊቱ (ያች ፍየል ") ።
ፍየዳ፡ የመርባት የመጥቀም ' ሥራ ።
ፍዳ (ፈደየ)፡ የክፉ ብድራት ፍርድ ቅጣት ።
ፍዳውን አየ፡ መከራውን ተቀበለ (ብ ድሩን አገኘ ") ።
ፍድል፡ አካለ ደጓሳ ጕልሕ ሰው ።
ፍድፈዳ (ፍድፋዴ)፡ ብዛት ብዙነት ብልጫ ላቂያ ።
ፍድፋጅ፡ ተረፍ ትራፊ ርዝራዥ (የዶ ቄት ወይም የሌላ ") ።
ፍጅ፡ ጨርስ ፈጽም ።
ፍጅብኝ፡ ጠበቃ ነገረ ፈጅ ። ቀናው "ፍጅልኝ" ሲኾን "ፍጅብኝ" ይባላል ።
ፍጅት (ፍድየት)፡ ጭቅጭቅ ንዝንዝ ጩኸት ውዝግብ ("(ግብ. ሐዋ. ፲፪፥ ፲፰)") ።
ፍጅት አደረገ፡ ጭርስ ጥንግድ አ ደረገ ።
ፍጆታ፡ የሙግት የክርክር ፈንታ ተራ ፈረቃ ።
ፍጉ፡ ተቃ ጠለ ጐደፈ ' መሬቱ ። "ፈአገ" ጥንታዊ አማርኛ ነው ።
ፍጋም፡ ፍገ ብዙ ባለፍግ ።
ፍግ (ፈገ)፡ የእበት የፋንዶ የበጠጥ የጠቦት ደረቅ ድቃቂ ።
ፍግም አለ፡ ድፍት ሙትት ድብን '
ፍግም፡ የተፈገመ የተደፋ የወደቀ (ውድቅ ") ።
ፍግምግም አለ፡ ርግድግድ አለ ("(ኤር. ፳፫፥ ፲፪)") ።
ፍግምግም፡ የተፍገመገመ (እንግድግድ ርግድግድ ") ።
ፍግምግምታ (ትንታኔ)፡ የመንገድ ገድ ኹኔታ ።
ፍግርግር አለ፡ ውስብስብ አለ (ተፍ ገረገረ ") ።
ፍግርግር፡ የተፍገረገረ (ስያፍ ማገር ውስብስብ መናኛ ዐጥር ") ።
ፍግርግር፡ ጫታሪ ተጣጣሪ ።
ፍግግ አለ፡ ሣቅ አለ ።
ፍግግ ፍግግ አለ፡ ሣቅ ሣቅ አለ ።
ፍግፈጋ፡ ፍቀት ጠረጋ ።
ፍግፍጋት፡ ፍቆሽ ።
ፍግፍግ፡ የተፈገፈገ ።
ፍጡር (ሮች)፡ የተፈጠረ (የፈጣሪ ሥራ ") ።
ፍጡርነት፡ ፍጡር መኾን ።
ፍጥ፡ የመፍጠጥ ኹኔታ ።
ፍጥ፡ ፈጣጣ ፈጠጤ ።
ፍጥም አለ፡ ዕልቅ ጭርስ አለ ።
ፍጥም፡ ቀጠሮ ባጤ ይሙቱ የተወሰነ ። "ፍጥም አፍራሽ ቤተ ክሲያን ተኳሽ" እን ዲሉ ።
ፍጥምጥም አለ፡ ፈጽሞ አለቀ ፥ ተከ ናወነ ።
ፍጥምጥም፡ ዝኒ ከማሁ ።
ፍጥሞ፡ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ራእ ዩን በደሴቱ የጻፈበት አገር ።
ፍጥረታለም (ፍጥረተ ዓለም)፡ በዓ ለም የሚኖር ማንኛውም ፍጥረት ኹሉ ።
ፍጥረት (ቶች)፡ ሰማይና ምድር መ ሬት ውሃ ነፋስ እሳት ብርሃን ጨለማ መ ልአክ ዘር ተክል ዕንጨት ፀሓይ ጨረቃ ኮከብ እንስሳ አውሬ ወፍ ሰው ።
ፍጥረት፡ ተፈጥሮ መፈጠር ። "ዕውቀትና ፍጥረት አንድ ቀን ነው" እንዲሉ ።
ፍጥሪያ፡ የመፍጠር ሥራ አድራጎት ።
ፍጥርቅ አለ፡ ፍንድት ውጥት አለ ።
ፍጥርቅ፡ የተፈጠረቀ/የፈነዳ ።
ፍጥርጥር፡ ዐመል ጠባይ ብጤት ። "ፍ ጥጥር ቢል በቀና ነበር" ። "ሰው ኹሉ እንደ ፍጥርጥሩ ይኖራል" ።
ፍጥነት፡ ዝኒ ከማሁ ።
ፍጥኒያ፡ ችኰላ ጥድፊያ ።
ፍጥጥ አለ፡ ጕርጥ አለ (ፈጠጠ ") ።
ፍጥጥም፡ የቃል የማተብ ማሰሪያ (የጋ ብቻ ውል ") ።
ፍጭርጭር፡ የተፍጨረጨረ (ትጉ ታ ታሪ ተትኰርኳሪ ") ።
ፍጭጭ አለ፡ ዝኒ ከማሁ ።
ፍጸማ፡ ድምደማ ።
ፍጹም (ሞች)፡ የተፈጸመ (ሕጸጽ ጕድለት ነውር እንከን የሌለበት - ንጹሕ ቅዱስ ጻድቅ የበቃ - ከንጽሐ ልቡና ማዕ ርግ የደረሰ - እንደ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያለ መንፈሳዊ ግሑሥ ") ።
ፍጹምነት (ፍጽምና)፡ ፍጹም መ ኾን (ብቃት ቅድስና ") ።
ፍጻሜ፡ መጨረሻ ምጽአት ("(ማቴ. ፳፬፥ ፲፬)") ።
ፍጽም (ፍጹም)፡ ያለቀ የተጨረሰ ።
ፍጽም አለ፡ ዕልቅ ጭርስ አለ ።
ፎለለ፡ አብዝቶ ተጫወተ (በጕልሕ'ድ ምፅ እንዳገኘ ተናገረ ") ።
ፎለፎል (ፈልፈለ)፡ ቦሬ ገር ሰው ሸክ የሌለበት (ጨዋታው ደስ የሚያሠኝ ") ።
ፎላይ (ዮች)፡ የፎለለ/የሚፎልል (ተ ጫዋች ") ።
ፎሌ (ኦሮ)፡ ሲያውቅ አበድ አመንዝራ ወንድን ይዞ የሚደበድብ ።
ፎሌ፡ አፈ ሰፊ ኣንኮላ ። "ፎለፎልን" ተመ ልከት ።
ፎረፎር፡ ሸቀን ደረቅ ወዝ ፎከት ።
ፎሸፎሸ)፡ አንፎሸፎሸ፡ ወሬ አስነዛ ።
ፎሸፎሽ/ፎሽፋሻ፡ የተንፎሸፎሸ/የሚ ንፎሸፎሽ (ወሬኛ ቀላል አባ ንፋው ") ።
ፎቀቀ)፡ አንፋቀቀ፡ በቂጥና በእጅ አስኬደ ።
ፎቃቃ (ቆች)፡ ዝኒ ከማሁ (የተንፋ ቀቀ - አዋሻኪ ") ።
ፎተተ፡ ነገር አበዛ አንጁቀቀ ።
ፎታች፡ የፎተተ/የሚፎትት (አንፋ ቃቂ ") ።
ፎቶ ግራፍ፡ ጽሕፈተ ብርሃን (የብ ርሃን ጽፈት - ሥዕል ") ። "ፎቶና ግራፍ" የጽርእ ልሳን ነው ።
ፎቶ፡ ብርሃን ጸዳል ።
ፎነቀ፡ ዝኒ ከማሁ ።
ፎነነ፡ ላይኛ ከንፈርን ሠነጠቀ (አፍን ጫን ቈረጠ ጐረደ አሳጠረ ") ።
ፎናና፡ አፍንጫ ጐራዳ ። ባለቅኔዎች "ፋጌ" ይሉታል ።
ፎናኝ (ኞች)፡ የፎነነ/የሚፎንን (ሠን ጣቂ ቈራጭ ") ።
ፎከተ፡ ባ፭ ጣት ዐካከ ፋቀ አካልን ።
ፎከተ፡ ዐወደ ፈተገ ዐጪር ሣርን ።
ፎከተ፡ ፈላ፡
ፎከታም (ሞች)፡ ፎከት ያለበት (የበ ዛበት ባለፎከት ") ።
ፎከት፡ ነጭ ዕከክ እብቅ መሳይ፡ በ ግእዝ "ኣበቅ" ይባላል ።
ፎከት፡ የዕከክ ትቢያ (የገላ ፍቄት፡ ጕማጮ ሣር ") ።
ፎከፎከ) አንፎከፎከ፡ አብዝቶ፥ሸነ ኣንዠቀዠቀ ።
ፎካች፡ የፎከተ/የሚፎክት (ዐካኪ ዐ ጅ ") ።
ፎደፎደ) አንፎደፎደ፡ አንበደበደ አስፈራ አንቀጠቀጠ ።
ፎደፎድ፡ እንብድብድ እንቅጥቅጥ ።
ፎገራ፡ በበጌምድር ግዛት ውስጥ ያለ አገር (ከብት የሚረባበት ") ።
ፎጠረ (ጠፈረ)፡ የከብትን ' አፍ ' አ ሰረ ሸበበ ።
ፎጠረ፡ ፍየል፡
ፎጠና፡ ፈጥኖ የሚያድግ የሚሠራ ወጣት (ለሴትም ይኾናል ") ።
ፎጢማ፡ ታናሽ ዋሽንት ።
ፎጣ፡ የፊት መጥረጊያ የእጅ ማበሻ የገሳ ማምጠጫ ባለዘርፍ ነጠላ ጠጕራም ። በአረብኛ "ፉጣ" ይባላል ።
ፎጣሪ፡ የፎጠረ/የሚፎጥር (አሳሪ ") ።

No comments:
Post a Comment