Friday, June 6, 2025

                                
፬ኛ ፊደል በአበገደ "በፊደልነት ስሙ ድል() በቍጥርነት ደ፬ ይባላል።"
የዘጠተ ተወራራሽ (ማስረጃ) " ፈቀ፡ ዘፈቀ፡ ጨቦደ፡ በጠ፡ ቦደሰ፡ ጠሰ፡ ለደፈ፡ ለጠፈ፡ ገረደፈ፡ ከረተፈ።"
ፍልቅ አለ፡ እጅግ አማረች
ደኃራ (ደኃራይ) በቀዳማ አንጻር በስተኋላ ያለ ("የኮርቻ ጫፍ")
ደኅነኛ፡ ጤናማ ባለጤና (ጤነኛ "ደኅነኞች ጤነኞች" )
ደኅኒት፡ ደጓ ማለፊያዋ
ደኅና (ዳኅነ) ንኡስ አገባብ (ጤና በጎ ሰላም "ከኀላፊና ከትንቢት ከትእዛዝ ከነ ባር አንቀጽ አስቀድሞ እየገባ ይነገራል" )
ደኅና (ድኅነ፡ ዳኅና) ቅጽል (ደግ ማለፊያ የጠባይ የግብር የሰውነት "ደኅኖች ደጎች ማለፊያዎች" )
ደኅና መጣ፡ በሰላም በጤና በሕይ ወት
ደኅና ሰንብት፡ ከእሑድ እስከ ' ዳሜ ("ወይም ብዙ ሳምንት ረፈደን ዋለን መሸን ዐደረን ከረመን ሰነበተን በየስፍራው ተመልከት ከስም እየቀደመ በቅጽልነት ሲነገር")
ደኅና ሰው፡ እውነተኛ ደግ ቅን ትሑት ("እሰው ጠባይ የማይደርስ")
ደኅና ቀን፡ ዝናም የሌለበት ወለል ያለ ሰዓት
ደኅና ቀን፡ የሰላም የደስታ የጥ ጋብ ጊዜ ዘመን
ደኅና ነው፡ እሱ ደኅና ነው ("ምንም የለበት በቅርብ ትእዛዝ ሲነገር")
ደኅና ነገር፡ ማለፊያ ወሬ
ደኅና አምሽ፡ ከምሽቱ ፲፪ እስከ ሌሊቱ ሰዓት
ደኅና አርፍድ፡ ከጧቱ ፲፪ እስከ ሰዓት
ደኅና ዕደር፡ ከማታ እስከ ጧት
ደኅና ክረም፡ ከዕለት እስካመት
ደኅና ኹን፡ ለብዙ ጊዜ
ደኅና ዋል፡ ከጧት እስከ ማታ
ደኅና ያሳድርኸ፡ ዝኒ ከማሁ
ደኅና ያውልኸ፡ ዝኒ ከማሁ
ደኅና ገባ፡ ያለችግር ያለሁከት ወደ ቤቱ ተመለሰ
ደኅኔ፡ የሰው ስም ("የደኅና ማለት ነው")
ደኅንነት፡ ደኅና መኾን ጢንነት
ደለለ (ዐረ) መራ/አመለከተ/ ቈመ/አሳየ ("ሸያጭና ገዢን አስማማ")
ደለለ (ደልሎ ደለለ/ጸልሎ ለለ) አሞኘ/አታለለ/ሸነገለ ("የማያደርገ ውን አደርጋለኹ አለ") (መዝ. ፲፰፡ ፵፬፡ ኤር. ፬፡ )
ደለለ ሸነገለ አሞኘ እዘነጋ አቄለ (በነገር/በስብከት - ኤር. ፳፡ ፯፡ ዘካ. ፲፫፡ ) በውስጥ ጭቃ እበት ዐመድ በላይ ማር ቅቤ ዶቄት አድርጎ ሼጠ ለወጠ
ደለለ፡ ጫነ/ከመረ/ሸፈነ/አለበሰ/አጠለቀ
ደለለኝ፡ የሰው ስም ("አሞኘኝ ሸነገ ለኝ ማለት ነው")
ደለላም/ደለልማ፡ ደለል ያለበት/የበዛበት ("ባለዶለል ስፍራ")
ደለል፡ ያፈር/የደንጊያ/ያሸዋ/የሣር/የንጨት ክምር "ጐርፉ በቡቃያው ላይ ደለል ነበት"
ደለመ (ጸልመ) ጠለመ/ጨለመ/ወደመ/ጠፋ/ተሰወረ ("የዐይን የመብራት የስለት የትዳር")
ደለመጠ (ደመጠ ለመጠ) ሥጋ ያዘ/ወፈረ ("ከቅጥነት ከክሳት ራቀ ተጠረነቀ ፈረጠመ")
ደለማ፡ ጭለማ/ስወራ "ሳይሰማ በደ ለማ" እንዲሉ
ደለሠ ቀባ ደለሰ
ደለሠ ዶለተ
ደለሰ (ደለዘ) ቅቤን በራስ ላይ አድርጎ ላከከ ("አብዝቶ ቀባ መረገ ትግሬ ግን ደለሰን ሰበሰበ ይለዋል ደለፈሰን እይ የዚህ ዘር ነው")
ደለሽ፡ የእኸል ማነባበሪያ ("ከሰፌድ የሚበልጥ ሥሥ ምርጊት")
ደለቀ (ደሊቅ ደለቀ) መታ/ደሰቀ/ጐሰመ/አስጮኸ ("የከበሮ የዠርባ የደረት")
ደለቀ፡ ቈነነ ("በዝግታ አስኬደ ቶሎ ቶሎ ምን ይደልቅኻልእንዲል ባላገር)
ደለቀቀ (ለቀቀ) ዛቀ ("የቅቤ")
ደለቀቀ፡ ባለ እንደ ልቡ ኾነ ("የልጅ")
ደለቀቅ/ደልቃቃ፡ ባለጌ/ቅምጥል/እንቅብር ("አያት ያሳደገው ሞልቃቃ")
ደለበ፡ ተዘገበ/ተሰበሰበ/ተጠራቀመ/ተከማቸ ("ብዙ ጊዜ ተቀመጠ ቈየ ዘገየ ከዚሀ የተነሣ ጠቈረ ደነበሸ ሻገተ ዛገ የእኸል የገንዘብ")
ደለበ፡ ወፈረ/ሠባ ("የበሬ")
ደለንቲ፡ ደነዝ/ፈዛዛ ሰው ("ወይም ' ከብት")
ደለኸ (ደሊኅ ደልኀ) በርበሬ ቀጠ ("በሽንኵርት ደለዘ ከጨው ጋራ ፈጮ ሰለቀ አላቈጠ አላመ ድልኸ ኣዘጋጀ አደ ራጀ ደለኸ በትግሪኛ ደለኄ ይባላል")
ደለዘ (ዶለሰ) በርበሬን ከሽንኵርት ጋራ ወቀጠ
ደለዘ፡ መረገ በየደ ደፈነ ብረትን (ተመልከት፡ ፪ኛውን ገበዛ)
ደለይ ነፋስ፡ የነፋስ ደለይ ("ያባይ ' ጠንቋይ ባህል ነው")
ደለይ፡ ከዐዘቅት ከጕድጓድ የውሃ መቅጃ መጐተቻ ("ከንጨት ከብረት የተበጀ ዕቃ ባልዲ ባለማንጠልጠያ በግእዝ ደለው ማሕየብ ይባላል")
ደለይ፡ የኮከብ ስም ("በደለይ ውሃ ቀጂ የሚመሰል የጥር ኮከብ መዝገበ ፊደል እይ")
ደለደለ (" በበ ገደበ አገደ አቆመ አበዛ ውሃን ከተረ ነገርን በልብ ያዘ አሳደረ አምላክ ሆይ በየለቱ የምናደርገውን በይል አትክተርብን ከታሪ ") (ሮች)
ደለደለ (ደለለ) መላ ጨመረ/ትክክል አደረገ/መደመደ መሬትን (ኢሳ. ፳፯፡ ) ("ጐዘጐዘ አነጠፈ ድልድልና ድልድይ አበጀ")
ደለደለ፡ ሰሐቅ ከፈለ/መደበ/ተነተነ (ርስትን ገንዘብን)
ደለደለ፡ አሳበጠ/ቅል አስመሰለ ገላን
ደለደለ፡ ገደበ/ከበበ/አገደ/ከተረ ውሃን "በሬ ሆይ እኔ ላንተ ብዬ ገለባ ቈልዬ ውሃውን ደልድዬ" እንዲል ገበሬ
ደለጐም (ዘልጉም) ዝምተኛ አል ጉም
ደለፈሰ፡ ዛቀ/ሰረረ
ደለፈስ/ደልፋሳ፡ የተደለፈሰ/የተ ዛቀ መሬት
ደላ ደላጎ
ደላ (ተደልወ) ተሰፈረ/ተመዘነ
ደላ (ደለወ) ተመቸ/ተሰማማ/ኾነ/ተገባ
ደላ (ድሕለ) ሸሸ/ተናደ/ኼደ/ነጐደ
ደላላ (ሎች) አመልካች/ጠቋሚ/ኣስማሚ
ደላማ፡ የደለመ/የጠፋ ዐይን
ደላሽ፡ የደለሰ/የሚደልስ (ቀቢ)
ደላቂ፡ የደለቀ/የሚደልቅ ("ደሳቂ ' ጐሳሚ ሰም")
ደላቢ፡ የሚደልብ (ሠቢ)
ደላንታ፡ በየጁ ውስጥ ያለ አገር ("የዋ ድላ ጎረቤት ዋድላ ደላንታእንዲሉ)
ደላኺ (ዎች) የደለኸ/የሚደልኸ ("አላቋጭ")
ደላዥ (ዦች) የደለዘ/የሚደልዝ (ወቃጭ መራጊ በያጅ)
ደላይ (ዮች) የደለለ/የሚደልል (" ታሳይ ሸንጋይ እፈ ቅቤ ልበ ጩቤ") (መዝ. ፲፪፡ )
ደላደለ፡ ጐዛጐዘ/አነጣጠፈ
ደላጎ (ዎች) የቈርበት/የማስ/የነት/የዳባ ዕላቂ/ቅዳጅ
ደላጎ፡ ጅል/ቂል/ሞኝ/ከርፋፋ ሰው
ደል (መድሎት) ቍና እኸል የሚይዝ ጕርዝኝ ("ወይም ቅርጫት ልክ")
ደል/ዶል (ድልው) የተገባ/የሚ ኾን ነገር ሥራ
ደልማጣ/ድልምጥ፡ የዶለመጠ ("ወፍ ራም ጥርንቅ")
ደልዳላ፡ ትክክል ሰው ("በሰውነቱ በው ቀቱ ወይም ቦታ") (ዘዳ. ፬፡ ፵፫፡ መዝ. ፳፮፡ ፲፪፡ ዘካ. ፬፡ )
ደልዳይ (ዮች) የደለደለ/የሚደለ ድል/የሚጨምር ("ከታሪ")
ደልድል፡ የራስ ዘውዴ የፈረስ ስም ("አባ ደልድልእንዲሉ) "አስተካክል ማለት ነው"
ደልገን (ዘልጕን) የድብኝት ስም ("ቅጥልጥል ድብኝት")
ደልጊ፡ በጣና ውስጥ ያለ የመቤታችን ደብር
ደልጐም፡ የማሽላ ስም ("እንጀራው የማያምር የማይሰምር ቀይ ማሽላ")
ደመ መራር፡ ቍጡ ጠበኛ "ደሙ መሪራት ዕከክ ፈረሳቤት ቍጡ ደም ማለት ነው"
ደመ ሰች (ሰታዬ ደም) የዶሮ ያሞራ የወፍ ጭራ በነቀሉት ጊዜ ደም የሚጠጣ የሚጐርሥ
ደመ ቢስ፡ ክቾ ለዛ ሙጥጤ
ደመ ነፍስ (ነፍሰ ዶም) በዶም የምታድር የእንስሳ ነፍስ ("ደም ሲደርቅና ሲያልቅ የምትጠፋ እንደ ሰው ነፍስ ትን ሣኤ የሌላት")
ደመ ነፍስ፡ በዶማዊት ነፍስ የቆመ' እንስሳ
ደመ ከልብ፡ ተበቃይ የሌለው የወንጀለኛ ደም ("ደሙ ከልብ ይባላል")
ደመ ወዘኛ (ኞች) ባለደመ ወዝ ("በደመ ወዝ ዐዳሪ") (ዘሌ. ፳፪፡ )
ደመ ወዙ ተቈረጠበት - ተቈረጠለት) ተቀነሰበት ተወሰነለት
ደመ ወዝ (ደመወዝ) ወዘ ደም ("የደም ወዝ ጥሮ ግሮ ላብን አፍሶ የሚገኝ ገንዘብ") (፩ቆሮ. ፱፡ ፳፬)
ደመ ግቡ፡ ደሙ (መልኩ) እሰው ዐይን የሚገባ የሚያምር ("እዩኝ አዩኝ የሚል ውብ መልከ መልካም")
ደመለለ (ደበለ) ጠቀለለ ("ብዙውን አንድ አደረገ") (ተመልከት፡ ጀመለን እይ)
ደመመ (ደሚም ደመ ዕብ ማም ዝም አለ) ደነቀ/ገረመ
ደመመ፡ መደምም/መደንን ı አበጀ ("ቀበረ ዘጋ መረገ ደፈነ ዐፈር አለበሰ አስ ጣጣ ኣስተካከለ")
ደመመ፡ አጮኸ/አስፈራ (ተመልከት፡ ተመመን)
ደመመን፡ ዝኒ ከማሁ
ደመሰ (ደሚስ ደመሰ) ተመሰ/ለከሰ ("ደበሰን እይ የዚህ ለውጥ ነው")
ደመሰሰ (ደምሰሰ) ፋቀ/አጠፋ (" ንዳልነበረ አደረገ አበላሸ") (ዘዳ. ፱፡ ፲፬) "እንደ መስቀሉ ይበሳሳኝ እንደ ወንጀሉ ይደምሰኝ" እንዲል ማለኛ
ደመሰሰ፡ ጠቀለለ ("የበላይ ገዢ ኾነ")
ደመሳሰሰ፡ አጠፋፋ
ደመስማሳ፡ የተድመሰመሰ ("ደበስባሳ")
ደመረ (ደምሮ ደመረ) ሰበሰበ/ ከበ/አከማቸ ("አንድ ላይ አደረገ ባንድነት አቆመ ጠመጠመ የንጨት የቍጥር የሻሽ")
ደመራ፡ መደመር ("አንድነት ማድረግ ማቆም")
ደመራ፡ ብዙ ርጥብ ዕንወት ተሰ ብስቦ የሚቆምበት የመስቀል ዋዜማ ("የመስከ ረም ፲፮ኛ ቀን")
ደመርጽማ፡ ደም ዕርጥ የሚመስል (ተመልከት፡ መዠመሪያውን ዐረጠ እይ)
ደመቀ (ደሚቅ ደመቀ) ገነነ ("ጐላ አማረ") (ዘፀ. ፳፮፡ ፴፮፡ ፳፰፡ ፯፡ መሳ. ፭፡ ፴፩፡ ዳን. ፲፪፡ ) ("በዛ ከበረ ቀለጠ የማሕሌት ' የዘፈን ' የልብስ ' ያጀብ")
ደመቅ (ደሚቅ) መድመቅ
ደመቅ አለ፡ ጐላ አለ
ደመቅ ደመቅ አለ፡ መላልሶ ደመቀ
ደመነ/ዳመነ (ደምኖ ደመነ) ጠቈረ/ጨለመ/ደመና ኾነ/ከበደ
ደመና ጠቀሰ፡ ደመናን ' ኣዘዘ ("በደ መና ተጫነ ተቀመጠ ቶማስ ደመና ቅሶ መጣ")
ደመና/ዳመና፡ ከምድር ወደ ማይ የሚበን የውሃ ላበት እንፋሎት ዝናም የሚኾን ("በምድር ላይ ሲታይ ጉም ይባላል")
ደመናዋ፡ ደመናዪቱ ("ያችደመና") (ኢዮ. ፳፮፡ )
ደመን/ድመን፡ ድመም ድራር ("መና' ይወራረሳሉና ድመም በማለት ፈንታ ድመን ' ይላል ዳግመኛም ውስጡ መጨለ ሙን ያሳያል")
ደመኖች (ደመናት) ላበቶች/እን ፋሎቶች (ኢዮ. ፴፭፡ ፭፡ ፴፮፡ ፳፰)
ደመኛ (ኞች) ደበኛ/ባለደም/ጠላት/ባለጋራ ("የገዳይ ወይም የጝች ወገን") (መዝ. ፭፡ )
ደመኛነት፡ ባለጋራነት/ጠላትነት
ደመደመ (ትግ. ደምደመ፡ ደነዘ) ረገጠ/አስተካከለ ምድርን ("ዘሩ ደመመ ' ነው ተመተመን ተመልከት")
ደመደመ፡ አደነዘ ("ሹለትና ስለት ' ኣላጣ")
ደመደመ፡ ጨረሰ/ፈጸመ/ቈረጠ ("ግን ብን ግድግዳን ጣራን ኣላጣ")
ደመጠ ደመመ
ደመጠ (ደሚፅ ደምፀ ተሰማ) ጮኸ/ድምጥ ሰጠ
ደመጠ፡ ፈገፈገ/አለሰለስ/አለዘበ (ብራናን)
ደሙ ፈላ) ተበሳጨ ተናደደ ተቈጣ አመረረ "ሞቀንና ነፈረን" እይ
ደሙ ፈላ፡ ተቈጣ
ደሙ፡ ደም ("የርሱ ደም")
ደሚ፡ የደማ/የሚደማ
ደሚና (ኖች) የገራዳ ዋስ ("ተጠሪ ማለት ነው ይህ ስም ከሐረርጌ በቀር በሌላ አገር አይነገርም በዐረብ ደሚን ' ይባላል ጎራዳን እይ")
ደማ (ደመወ) ደም ኾነ ("ደም ጣው ፈሰሰው ገላው ሰውየው")
ደማ፡ የርሷ ደም
ደማሚ፡ የደመመ/የሚደምም
ደማሚት፡ አሲድ ከሚባል ከድኝ ባሕርይ የተሠራ ማር መሳይ ("እሳት ሲነካው ደንጊያ የሚሰብር ተራራ የሚፈነቅል ሲጮኸ 1 ድም የሚል ፈረንጆች ዲናሚት ይሉታል")
ደማም፡ ውብ ቈንዦ ("ደሙ ፍልቅ ያለ")
ደማስ፡ ቀይነትና ብጫነት ያለው የደማስቆ ሥራ ባለቀለም ልብስ ("ለበቅሎ ግላስ የሚኾን ደም አስተኔ")
ደማስቆ፡ የላይኛው ሶርያ ክተማ
ደማሪ፡ የደመረ/የሚደምር ("ጠምጣሚ")
ደማቂ፡ የሚደምቅ/የሚያምር ("ጕልሕ በሩቅ የሚታይ")
ደማቅ/ድምቅ (ድሙቅ) የደመቀ ("ድምቅ ቀይእንዲሉ)
ደም መለሰ፡ ተበቀለ ("ገዳይን ገደለ")
ደም መላሽ፡ ተበቃይ ("የደም ብድር ከፋይ") (ዘኍ. ፴፭፡ ፳፭)
ደም መታት፡ ብዙ ደም ወረዳት ሴትዮዋ
ደም ረግጦ ገባ፡ በደም ላይ ዐለፈ ("ታቦቱ ሙሽራው")
ደም በደም ኾነ፡ ብዙ ሰው ተፈ ነከተ ("ቈሰለ")
ደም ተቃባ፡ ባለደም ተኳዃነ
ደም ተፋሰሰ፡ ተጋደለ/ተጝተ
ደም አስተኔ፡ የደም ዐይነት
ደም አስተፊ፡ ሥረ ቀይ ቅጠል ("የጥፈት መማሪያ")
ደም አስተፊት፡ የማይበላ እንጕዳይ
ደም አፈ ሰሰ) ጭዳ አለ (ሠዋ ነፍስ ገደለ ")
ደም አፈሰሰ፡ ሰው ገደለ ("ከብት ዶሮ ዐረደ ጭዳ አለ")
ደም አፈታበት፡ ደሙ ከመውረድ አልቆመም ("አልታገደም")
ደም ዐፋሽ (ለዐት) ውላጋ ("የአፋ እጄታ ክንፍ የታራጅን ደም የሚቀባ")
ደም ዐፋሽ (ደማፋሽ) ልጅ ከተ ወለዶ በኋላ ደም ደምታፍሥ ሴት
ደም እሰከረው) አሳበደው፡ አጠገበው (ሐርበኛውን ውሻውን)
ደም ዕርጥ (የደም ዕርጥ) ቀይና' ሳንባ መሳይ ሞላላ ዶቃ ("የደም ኣብነት ነስ")
ደም ያፈላል፡ ያስቈጣል
ደም ይጐርሣል፡ መጠጥ የሌለበት ምግብ ደም ይስባል
ደም ደረቀ፡ ቂም ጠፋ ("ዕርቅ ኾነ ሰላም ስምምነት ተደረገ የገዳይ ወገን ከማች ዘመድ በመጋባቱ")
ደም ገሣ፡ ደም ተፋ/አፈሰሰ
ደም ጋን (የደም ጋን) የሽንጥና የዳሌ መገናኛ ("ደም የሚታቈርበት")
ደም ግባት፡ ላሕይ ወዝ ማማር ቍንዥና ውበት (ዳን. ፬፡ ፴፮)
ደም ጥልቀት፡ የደም (የዘር) መቀ ላቀል "ደም ጥልቀት ሥጋ ልደት" እንዲሉ
ደም ጥሪ፡ ከደም መጥራት ("የሴት ግዳጅ መቆም አለመውረድ")
ደም፡ ከሰው ከእንስሳ ከተንቀሳቃሽ ኹሉ ከዕፀዋትም የሚወጣ ቀይና ነጭ ፈሳሽ "የበለስ የቍልቋል የወርካ የቅንጭብ ደም" እንዲሉ
ደም፡ የዘቢብ ጭማቂ
ደምለው፡ የሰው ስም ("ጠቅለው . ነው")
ደምላይ፡ የቍጥር ስም (" ")
ደምላይ፡ የደመለለ/የሚደመልል (" ቅላይ")
ደምማ፡ ድምቅ ቀይ
ደምሰው፡ ዝኒ ከማሁ ("አጥፋው ለት ነው")
ደምሳሳ፡ ምሉ/ጠቅላላ ("አንድ ሳይ ቀር")
ደምሳሽ (ሾች/ደምሳሲ) የደመ ሰሰ/የሚደመስስ ("አጥፊ")
ደምሳሽ፡ ጠቅላይ የበላይ ዳኛ ("ሌላው የፈረደውን የሚሽር የሚገለብጥ")
ደምሴ/ደምስ፡ የሰው ስም
ደምበጫ፡ በጐዣም ውስጥ ያለ
ደምቡራ፡ ከጥጥና ከጭረት የተሠራ መናኛ ልብስ ("ኰስኳሳ ሻድሬ ደም ቡራ የደመረ ዘር ነው አመከዝን እይ")
ደምቢያ፡ በበጌምድር ክፍል ያለ ' አገር ("ደምቢያና ፎገራእንዲሉ) "በግእዝ ድንቢ ይባላልና ደንቢያ ተብሎ ሊጻፍም ይቻላል።"
ደምዳሚ (ዎች) የደመደመ/የሚ ደመድም ("አስተካካይ ጨራሽ")
ደምዳማ፡ ደነዝ/ስለት አልባ ("የእ ብድ ጐራዴ")
ደሞ ደመደመ
ደሞ ደግሞ ደገመ
ደሞ፡ ደግሞ "ደሞ ደሞ" እንዲል ዘፋኝ "ደሞ የባላገር ደግሞ የከተማ ዐማርኛ ነው"
ደሞዬ ገብስ ደማ
ደሞዬ፡ ወደ ቀይነት የሚያደላ ገብስ ("ደም አስተኔ")
ደሠመ መታ ደሰመ
ደሰመ፡ በሾኸ ዐጠረ/ዘጋ/ደፈነ
ደሰመ፡ ገጨ/ለመተ/ተመተመ
ደሰማ፡ በመራቤቴ ውስጥ ያለ አገር
ደሰሰ (ደሲስ ደሰ ደሰሰ) ዘመመ/ዘነበለ/ተኛ/ዐጪር ኾነ
ደሰስ አለ፡ ዘንበል አለ
ደሰቀ፡ በጕልበት በጩ በክርን መታ
ደሰቀ፡ ተጫነ/ደበተ/አሞቀ
ደሰተ (ደሰየ) ደላ/ተመቸ/ተስማማ ("ጊዜው አገሩ ኑሮው")
ደሳ፡ ከሣር የተበጀ ዳውጃ ("የሱማሌ ዘላን ጐዦ መደረቢያ የሚነቀልና የሚተከል አጐበር ያለው") (ተመልከት፡ ዳስን ደሰሰን እይ)
ደሳለኝ (ደስ አለኝ) (ተፈሣሕኩ) የሰው ስም ("ተደሰትኩ ልጅ ብወልድ ደሳለኝ")
ደሳሚ፡ የደሰመ/የሚደስም ("የሚጋጭ ለታሚ ተምታሚ")
ደሳሳ፡ የዘመመ/የዘነበለ ቤት ("ዐጪር የድኻ ጐዦ ጐንባሲት")
ደሳቂ፡ የደሰቀ/የሚደስቅ ("የሚመታ ሌባሻይ ወይም ሌላ")
ደሴ የወሎ ከተማ፡ ደሰተ
ደሴት ጅብ አለ
ደሴት (ቶች) በባሕር ውስጥ ያለ ደረቅ ስፍራ ("በውሃ የተከበበና የታጠረ አገር ሰፊ ወይም ጠባብ ዟይን ሐይቅን ቀን የመሰለ ደሴት ግእዝኛ ነው")
ደስ የደስታ ከፊል፡ ደሰተ
ደስ ተሠኘ፡ ተደሰተ (ተመልከት፡ ሠኘን እይ)
ደስ አለ፡ ኾነ/ተደረገ ("ደስታው")
ደስ አለው (ተፈሥሐ ተሐሥየ) ደስ ተሠኘ ("ደላው ተመቸው")
ደስ አሠኘ (አሥመረ) አስደሰተ
ደስ ይበልኸ፡ ፈንድቅ (ዘዳ. ፲፮፡ ፲፬)
ደስ ፈቅ አለው (ተደለወ ጹመ) ፈጽሞ ደስ አለው ("ሐዘን ትካዜ ቀው የልብ ተድላ አገኘ")
ደስሜ፡ የሰው ስም
ደስቃም፡ እንቅልፋም/ሙቀታም ስፍራ
ደስቅ () የንቅልፍ ጋኔን ደባች/ደባስ ("ወይም እንቅልፍና ሙቀት")
ደስተኛ (ኞች) ደስታ ያለው/ባለ ደስታ (ዘዳ. ፳፮፡ ፲፭ = ኢሳ. ፳፬፡ )
ደስተኛዋ፡ ደስተኛዪቱ ("ደስ ያላት የተደሰተች") (ሶፎ. ፪፡ ፲፭)
ደስታ፡ በቶሎ የምትለቅ ኩፍኝ
ደስታ፡ ተድላ/ድሎት/ፍሥሓ/ምቾት ("ሐዘን ትካዜ የሌለበት") (ኢሳ. ፳፬፡ )
ደስታ፡ የሚያስለቅስ የከብት በሽታ ("ከማመም በቀር የማይገድል")
ደስታ፡ የንጉሥ ግምጃ ድንኳን (" ጕዞ ጊዜ በጧት የምትነቀል በቀትር የምት ተከል በርሷ መተከል መንገድ ያደከው ሰራዊት ስለሚደሰት ደስታ ተባለች በቀድሞ ዘመን ደበና ትባል ነበር") (ተመልከት፡ መሬትን እይ)
ደስታ፡ የወንድና የሴት መጠሪያ ስም ("አቶ ደስታ እመት ደስታ")
ደስቶች፡ ደስታ ድንኳን ጫኞች
ደስክ ጋኔን ደሰቀ
ደረመሰ (ደረሰመ) ደረባ ወደ ታች አፈረሰ/ናደ/አወደቀ/አሠረገ ("የመሬት የመቃብር")
ደረመናም፡ ዕከካም/ፎከታም
ደረመን (ድራሞ) ዕከክ/ፎከት/ፈረ ሳቤት
ደረሞኛ፡ እንቅልፋም/ጋኔን የሚያሳክክ
ደረሰ (ዐረ) ተማረ/ትምርት ጠና/አነበበ ("ሌሎች የጻፉትን የደረሱትን")
ደረሰ (ደሪስ ደረሰ በጽሐ ጸቀ ትግ ሐባ ደርሰ ተቀኘ) ዐጕልና ገቢር ("አደገ ጐለመሰ በቃ አከለ ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ ለፈረስ ደረሰ")
ደረሰ፡ መላ ተጨረሰ/ተፈጸመ (መዝ. ፵፬፡ ፲፯)
ደረሰ፡ ሴት ዐወቀ/ነካ
ደረሰ፡ ኼደ/መጣ/ተመለሰ/ቀረበ/ከተፍ አለ/ተጠጋ/ገባ
ደረሰ፡ ድርሰት ተናገረ/ቅኔ ተቀኘ
ደረሰመ (ደሰመ) ደረመሰ/ደነቀፈ
ደረሰኝ (ኞች) የገንዘብ መቀበያ ወረቀት ጽፈትና ማኅተም ፊርማ ያለበት
ደረሰኝ፡ ተቀበልኩ/ተረከብኩ
ደረሰው፡ አገኘ/ተቀበለ
ደረሳ፡ መድረስ/ድርሰት
ደረስጌ (ደራስጌ) የደራስ ምድር/የደራስ ስፍራ ("በስሜን ውስጥ ያለ አገር ሌላም አፈታት ይኖረዋል")
ደረቀ ("ልስላሴና ጣዕም ዐጣ የጠባይ የሌላም ነገር ከቸቸ ደነገጠ ከቻቻ የከቸቸ ደረቅ ክችሌ ክቾ ዝኒ ከማሁ ለዛ ቢስ ለሙጥጤ ቅጠል የለሽ ክች አለ ድርቅ አለ ክች አለ ደነገጠ ከቸች ከተፍ ከቸች አለ ሳይታሰብ ድንገት ከተ አለ መጣ ደረሰ ከች ከባሕር የመጣ ልብስ ቈቦን' ጥፍራንዶን ከመሰለ ዕንጨት የተሠራ ሲጋኩት የሚሻክር አከቸቸ አደረቀ ጣም አሳጣ ከቸ ለንና ከቸመን ተመልከት አከቻቸች አደራረቅ መከቸት ካፓ ካባ ") (ማር. ይሥ. )
ደረቀ (ደረከ) ከለለ/ከቸለ/ከቸረ/ከቸቸ/ከሸለለ/ከረረ ("ርጥበት ዐጣ ከልም ላሜ ራቀ") (ኢሳ. ፵፩፡ ፲፯) (ተመልከት፡ ነጠፈን ደምን እይ)
ደረቀ፡ ጨከነ ("ጨካኝ ኾነ")
ደረቀች፡ ከሳች/ኰሰመነች
ደረቅ (ድሩክ) የደረቀ ክቾክችሌ ከራራ ("ውሃ ያልነካው ነገር") (ተመልከት፡ ልብንና ቀልብን)
ደረቅ ምች፡ ደም የሚያስተፋ ምታት በሽታ
ደረቅ ምድር፡ የብስ ("ውሃ የሌለባት ዝናም ያልጣለባት")
ደረቅ ሳል) አክታ የሌለው።
ደረቅ ሴት፡ ንፉግ/ሥሥታም/ ካኝ ("እጇን ቢሏት የማይወድቃት ጠብ ማይላት ቀጪን የከሳች ተብሎም ይተረጐ ማል")
ደረቅ ትንቢት፡ ስውር ያይዶለ ንግር ግልጥ ("ዕርገተ ኢሳይያስ ራእየ ኤልያስ ተረፈ ኤርምያስ")
ደረቅ እንጀራ፡ መባያ የሌለው ("ኣለወጥ")
ደረቅ ዕንጨት፡ ቅጠል/ልምላሜ የሌለው ("የቆመ ወይም የወደቀ")
ደረቅ ወዝ፡ ሸቀን/ፎረፎር
ደረቅ ግንባር፡ ጌታችን በምራቁ ጭቃ አላቍጦ ዐይን ያፈካበት (ዮሐ. ፱፡ , )
ደረቅ ጠጅ፡ የተጣራ ሲጠጡት ሚያሰክር ("የቈየ የኖረ የከረረ የወጣለት ንዱ በቃኝ")
ደረቅ ጥይት፡ ቱባ/ክልስ/ያይዶለ
ደረቅ ጦር፡ መሣሪያ ያሊያዘ ሰው ("ወረጋ ባዶ እጅ ወግቶ ደም የማያወጣ ማለት ነው እከሌ ደረቅ ጦሩን መጣእንዲሉ)
ደረቅ፡ ምድር/መሬት (ዘፍ. ፩፡ , )
ደረቅነት፡ ደረቅ መኾን/ጨካኝነት
ደረቅያ፡ ኰቻሮ/እንኵርኵሪት ("የመ ነኵሴ መኖ")
ደረቆት፡ ተቀቅሎ የደረቀ የጠላ - ፍሮ
ደረበ፡ ካበ/አነባበረ/በላይ አደረገ ("በልብስ ላይ ልብስን ጫነ አለበሰ ጨመረ!") (ሕዝ. ፲፮፡ ፲፰)
ደረበ፡ ደርብ/ደረባ/ድርብ ሠራ ("ዕጥፍ አደረገ")
ደረበ፡ ጓድ አበጀ
ደረባ (ዎች) የጐታ/የጐተራ/የድ ብኝት/የኵበት ጣራ ከነክዳኑ ("በጋልኛም ደባል ማለት ነው")
ደረባ ቤቴ፡ ፯ኛ ባሪያ ("የማን ቤቴ ልጅ ደረባ ደፍቶ በጓሮ የሚያድር")
ደረባ ቤት፡ በታችኛው ወግዳ ያለ አገር
ደረቤ፡ በጐዣም ክፍል ያለ አገር ("ጓዴ ማለት ነው")
ደረብ (ትግ) ሆድ/ከርሥ
ደረብ/ደረባ (ቢጽ) ጓድ/ጓደኛ/ባልንጀራ/ወዳጅ
ደረቦች፡ ጓዶች/ባልንጀሮች
ደረተ (ደርዐ ጠቀበ ትግ ረተ ወሰነ) ደበደበ/ጠቃቀመ/መላልሶ ሰፋ ("ደረትን አስመሰለ አደረገ") (ተመልከት፡ ደረዘንና ጠረ ዘን እይ)
ደረተ ሰፊ፡ ዝኒ ከማሁ
ደረተ ሳንቃ፡ ደረቱ/ደረቷ ሳንቃ የሚመስል
ደረተ ጠባብ፡ ደረቱ/ደረቷ የጠበበ
ደረታም፡ ደረተ ሰፊ
ደረት (ቶች) ትግ. ወሰን/ድን በር) በቁሙ ከማንቍርት በታች ከሆድ ላይ ያለ ገላ ("ያጥንቱ መጠጋጋት እንደ ሪቶ የኾነ ፍርምባ የእጅና የክንፍ የወ ርች ወሰን") (ዮሐ. ፲፫፡ ፳፭)
ደረት፡ በድጓ ተጽፎ የሚገኝ ምል ክት ("ካጪርነቱ በቀር የሀን ቅርጽ የሚመ ስል")
ደረት፡ የመሬት ' ዕርከን
ደረቷን ጣለች፡ አራቈተች
ደረነቀ፡ ዐመቀ/ተጫነ/ረጠጠ ("የስ ፍር") (ተመልከት፡ ጠረነቀን እይ)
ደረከ፡ ጠና ("ጥኑ ኾነ") (ግእዝ)
ደረከክ/ደርካካ፡ የተንደረከከ/ያጠረ/ፀር የኾነ ("ወፍራም")
ደረዘ (ጠረዘ ደረተ) ክርን ዐጥፎ መልሶ ልብስን ጠቀመ ("ስፌትን ለጐመ በ፪ መርፌ መጫሚያ ሰፋ በትግ ሪኛ ግን ደረዘ ገላን ዐሸ ማለት ነው ምስጢሩ መመላለስን ያሳያል")
ደረደረ (ትግ. ደርደረ አነባበረ) ሰደረ/ኰለኰለ/ደከነ ("በተራ በመደዳ አስቀ መጠ አነባበረ ከመረ")
ደረደረ፡ በገና መታ (፩ነገ. ፩፡ )
ደረደረ፡ አሰለፈ/አቆመ/ገረገረ
ደረደረ፡ ዕርቅን አዘጋጀ
ደረጀ (ደረገ) ደንጊያ ጠረበ/ደረጃ ሠራ/አበጀ/ጸፈጸፈ/አነጠፈ/ገጠመ/ደረበ ("አድራጊ")
ደረጀ፡ ተደላደለ/ተመቻቸ/በሀብት ላይ ሀብት ጨመረ/ወገን አበዛ/ሥር ሰደደ ጸና ("ተደራጊ")
ደረጃ
ደረጃ (ጆች) ጸፍጸፍ ("ባደባባይ ሰበሰብ በቤት ውስጥ የተነጠፈ ጥርብ ደን ጊያ")
ደረጃ፡ ማዕርግ ("የማዕርግ ስም")
ደረጃ፡ ዕርከን ("መውጫና መውረጃ")
ደረገ ደራጎን
ደረገ (ደርጎ ደረገ) ገጠመ/አንድ ኾነ/ዐበረ
ደረገመ (ረገመ) በጥፊ መታ/ ረጎተ
ደረገመ፡ አባ ጠረቀመ/ዘጋ
ደረገመ፡ ዐይንን/መብራትን አጠፋ/አወደመ
ደረገመ፡ ከንባብ የሚጣላ ትርጓሜ ተና ገረ
ደረጠ (ትግ. ደረጸ) ተልባን ዐሸ/መታ/ሊጥ አደረገ
ደረጠ፡ በጠበጠ/አወከ/ነቀነቀ ("አገ ሮን ሰውነትን") (ተመልከት፡ ናጠን እይ)
ደረጣ፡ ብጥበጣ/ሁከት
ደረፎ (ዘረፍኦ) በጐላ ክፍል ያለ ተራራ
ደረፎጪ፡ ተኰሰተረ/ተሰበሰበ
ደሪ፡ የሚደራ ("ዘቢ ተለማጭ")
ደራ (ደርዖ ደርዐ) ዘባ/ተለመጠ ("እንደ ሰፌድ ኾነ ማስጫ መሰለ የዚህ ቤት ጣራው ደርቷል")
ደራ፡ ሠማ/ጋለ ("ምጣዱ ደራ እን")
ደራ፡ ሰፋ/በዛ/ደመቀ ("ገበያው ደራ ጨዋታ ሲደራ እናቴ ባሪያ ነች ያሠኛል")
ደራ፡ ሻፈደ/ሠየ/ጐመዠ ("እንደ የቦ ሰልቶ እንደ ቈንዦ ደርቶእንዲሉ)
ደራ፡ በመርሐ ቤቴ ባሻገር በወንጭት ዳር ያለ አገር ዐምባ (ተራራ) ያለው
ደራሳ፡ ያገር ስም ("በሲዳሞ ክፍል ያለ አገርና ነገድ")
ደራስ፡ ጮሌ ፈረስ ("ቶሎ የሚደርስ") (ተመልከት፡ ባልን)
ደራረበ፡ ካካበ/ጨማመረ
ደራሽ (ደራሲ በጻሒ) የደረሰ/የሚደርስ ("መጪ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሃ ፈሳሽ ባለቅኔ መምር ሊቅ")
ደራሾች (ደራስያን) የቅኔ መም ሮች ("ሊቃውንት")
ደራቂ፡ የሚደርቅ
ደራቃ/ደራቍቻ፡ ከሲታ/ጣጋ/ጠጋ/ቋንጣ/ብረ/ሸሽ
ደራቢ (ዎች) የደረበ/የሚደርብ ("ድርብ ሠሪ ወይም ለባሽ ዐጣፊ")
ደራች (ቾች) ጠቃቢ) የደረተ/የሚደርት ("ደባደቦ ሰፊ ጠቃቃሚ")
ደራዥ (ዦች) የደረዘ/የሚደርዝ ("በመኪና ሰፊ")
ደራደረ፡ ኰላኰለ
ደራጎን፡ የዘንዶ ስም ("በዛፍ ላይ ተጠምጥሞ የልጃገረድ ድርጎ ተቀባይ እግርና ክንፍ ቀንድ ያለው አውሬ")
ደራጭ፡ የደረጠ/የሚደርጥ ("ዐሺ በጥ ባጭ ነቅናቂ")
ደሬ (ደርዐ) ጠንካራ የቈላ ግራር ከሰሌ ("በሐረርጌ ሀሎ ይባላል ነዋሪ የማይበ ላሽ የማይነቅዝ ማለት ነው")
ደር ("ችፍግ ያለ ከተማ ርግጫ የበዛበት መሬት")
ደርሰኒ፡ የሽቱ ስም ("የጥንት ሽቱ ቀረፋ")
ደርሰኸ/ደርሰሽ፡ የወንድና የሴት ስም ("አድገኸ አድገሽ ማለት ነው")
ደርሶ መልስ፡ እቅርብ ስፍራ ኺዶ መመለስ (ተመልከት፡ ዋለ ብለኸ ውሎን እይ)
ደርሶ፡ ንኡስ አገባብ ("ድንገት")
ደርበት (ጐዣም) እንስራ ውሃ የሚይዝ ማድጋ
ደርቡሽ (ሾች) የነገድ ስም ("የሱ ዳን ሕዝብ የኖባ ዘር ባረብኛም ደርዊሽ ዘላን ማለት ነው አንዳንድ ሰዎች ግን የመሕዲ ወታደር ስም ነው ይላሉ")
ደርባባ/እንድርብ፡ የተንደረበበ/የረጋ/ጭምት/ዝምተኛ
ደርባቦች፡ ጭምቶች/ዝምተኞች
ደርብ (ቦች) ላይኛ ቤት/ሰገነት/ፎቅ ("በሳንቃና በመረባርብ በስሚንቶ የተሠራ እሳተ ከል") (ዘፍ. ፮፡ ፲፯፡ ፩ነገ. ፮፡ , )
ደርቦ ገዳይ፡ ባንድ ጊዜ ጠላት የገደለ ("ዳጃች ብጡልን የመሰለ") (ተመልከት፡ ዋንታን እይ)
ደርቦ፡ አነባብሮ
ደርናቂ፡ የደረነቀ/የሚደረንቅ ("ዐማቂ ረጣጭ")
ደርከክ፡ ደርከክ አለ ("የውፍረትና የድንክ አካኼድ ኼደ")
ደርዘን፡ የዝርዝር ወይም የጥቅል ዕቃ ስም ("፲፪ ማለት ነው ደርዘን የፈረንጅ ቋንቋ ሲኾን ባማርኛም ስለ ተለመደ ጻፈ")
ደርዘኛ (ኞች) ነገር ዐዋቂ ሰው/ቋጣሪ/ውለኛ
ደርዝ (ዞች) የሱሪ/የእጀ ጠባብ/የጥብቆ/የሽብሽቦ/የመጫሚያ/የበቅሎ ዕቃ ስፌት ("በእጅ ወይም በመኪና የተሰፋ የቍና የጕርዝኝ የንቅብ ያገልግል የመሶብ ልጕማት")
ደርዝ'ውግ፡ ዕጥፍ ስፌት
ደርዳሪ (ዎች) የደረደረ/የሚደረድር ("ሰዳሪ ኰልኳይ በገና መቺ")
ደርገ ሙሴ፡ ዐሥራ ኹለት ወይም ኻያ አራት ማኅበረተኞች
ደርጋሚ፡ የደረገመ/የሚደረግም ("አጥፊ")
ደርጋንበሳ
ደርጋንበሳ (ደርገ አንበሳ) አንበሳዊ/አንበስማ/አንበሳ መሳይ አውሬ ኀይለ
ደርግ፡ አንድጋ/አንድነት/ኅብረት ኅበር
ደርፋጫ፡ ኵስትር/ዐጪር/ሽክና/አንኮላ
ደሽ፡ ብዙ ድርሻ/ዕጣ የለሽ
ደቀ መዛሙርት፡ የዳዊት ተማሮች ("ሐዋርያት አርድእት") (ዮሐ. ፱፡ ፳፯, ፳፰)
ደቀ መዝሙር፡ ዳዊት የሚማር ልጅ ("የዳዊት ተማሪ") (ማቴ. ፲፡ ፵፪፡ ዮሐ. ፱፡ ፳፰)
ደቀ ሳፍ (አውፋሪ) ሊቀ አርድ እት ("ተማሮችን የሚያስገባና የሚያስወጣ ተማሮች አለቃ")
ደቀ እስጢፋ፡ ርሱ ራሱ ደቅ ("በጣና ባሕር የሚገኝ የእስጢፋኖስ አጥቢያ መቅደስ በውስጡ ብዙ ምትሀትና ኣስማት")
ደቀ እስጢፋ፡ ባጤ እስክንድር መን የነበረ ፈላስፋ አስማተኛ ምትሀተኛ
ደቀለ/ዴቀለ፡ ዲቃላ ወለደ/አመጣ
ደቀል የመርከብ ምሰሶ ደን ቀል
ደቀሰ (ደቅሶ ደቀሰ) ተኛ/አንቀ ላፋ
ደቀቀ (ደቂቅ ደቀ) ተሰበረ/ ከተ/ተፈጨ/ተሰለቀ/ላመ/ለዘበ/እነሰ
ደቀበትን በማሽተት ዐውቆ ወገኖቹን የሚጠራ አውሬ በዱር የሚኖር ያህያ ጠላት
ደቀነ፡ አቀረበ/አስጠጋ/አቋተ/ደከረ
ደቀደቀ (ደደቀ ትግ ደግደገ) ወቀጠ/ወቃቀጠ/ወጋ/ወጋጋ/ጠቀጠቀ ("ቍል ቍል ቍልቍል አለ ለማድቀቅ ለመጥረግ መወልወል")
ደቀደቀ፡ መላልሶ ከረና
ደቂ (ደቃሒ) የደቃ/የሚደቃ ("መድቃት መምታት መውጋት")
ደቂቀ ሴት፡ ፊት በደብር ቅዱስ የነ በሩ መላእክት ("የግዜር ልጆች የተባሉ ኋላም በስሕተታቸው የሰይጣን አሻንጕሊት የኾኑ") (ሔኖ. ፭፡ ዘፍ. ፮፡ )
ደቂቀ ነቢያት፡ ከሆሴዕ እስከ ሚል ክያስ ያሉ የነቢያት መጻሕፍት
ደቂቀ ነቢያት፡ የነቢያት ልጆች ("ወይም ተማሮች")
ደቂቃ (ዎች) ባ፭ ባ፭ የተወሰነ የሰዓት ክፍል ("ስሳው ነጥብ አንድ ሰዓት ነው በግእዝ ካልኢት ይባላል ከዋናው ሰዓት ነጥብ ስላነሰ ደቂቃ ተባለ")
ደቂቅ ርባታ) ባ፲ መደብ የሚረባ ነባር አንቀጽ ጥሬ ዘር "መጽሐፍ ግን በረብና በርባና ፈንታ ርባታ ይላል" ("(፩ነፃ. ፲፬፥ ፲፬ ኢሳ. ፳፫፥ ፲፰)")
ደቂቅ ቅጽል) ይህ
ደቂቅ አገባብ፡ አንቀጽ የማያስቀር (ተመልከት፡ ገባ ብለኸ አገባብን እይ)
ደቂቅ፡ ልጅ ("ተኰልኰሎ ውሪ ውር ጋጥ ኵታራ ከሊቅ እስከ ደቂቅእንዲሉ)
ደቃ (ደቅሐ) ምድርን በእግሩ መታ/ወጋ ("ደቅ አደረገ የፍየል የጋማ ከብት አውሬ ባየ ጊዜ ለሰውም ይነገራል") (፩ዜና. ፲፯፡ )
ደቃቂ፡ የሚደቅ ("ለዛቢ")
ደቃቃ/ደቃቅ/ድቃቂ፡ የደቀቀ ("ስልቅ ልዝብ ዶቄት ገለባ ዐሠር አሸዋ ዐቧራ") (፪ዜና. ፴፬፡ )
ደቃኝ (ኞች) የደቀነ/የሚደቅን (" ቅራቢ አቋች ደካሪ")
ደቈሰ፡ በጣም መታ ("በክርን ደበደበ በድጅኖ ዳመጠ")
ደቈሰ፡ እጅግ ዐመመ
ደቈሰ፡ ፈጩ/ሰለቀ/አደቀቀ/አላመ/አለዘበ ("የኮሶ የቅመም የበርበሬ የመድኀኒት")
ደቅ በቁሙ ደቀቀ
ደቅ አደረገ፡ ደቃ
ደቅ፡ መድቃት
ደቅ፡ ከጣባ የሚበልጥ ከዋዲያት የሚያ ንስ ዐቃፋ የሸክላ ዕቃ ("ሲበዛ ደቆች ይላል")
ደቅ፡ ዝኒ ከማሁ ለደቂቅ (ግእዝ)
ደቅ፡ የደሴት ስም ("በጣና ውስጥ ያለ ታላቅ ደሴት ደቅ የሚሠራበት")
ደቅደቅ አለ፡ ተንደከደከ ("ዶዮው")
ደቅዳቂ፡ የደቀደቀ/የሚደቀድቅ ("ወጊ ጠቅጣቂ")
ደቋሽ (ሾች) የደቈሰ/የሚደቊስ (" ድቃቂ አላሚ አለዛቢ")
ደቋቈሰ፡ ዐማመመ
ደበለ (ደቢል ደበለ) አከለ/ጨመረ/ደረበ/ሰበሰበ/ዕጥፍ አደረገ/ሸረበ/ ሞረ
ደበለ፡ ቀየጠ/ቀላቀለ/ደባለቀ
ደበለ፡ እቤቱ ባዕድ ሰው አኖረ
ደበላ፡ ለራስ ጥምጥም ለወገብ መቀ ነት የሚኾን ከባሕር የመጣ ዐርበ ጠባብ ልብስ (ከመሐሙዲ የሚሣሣ ከሻሽ የሚወፍር)
ደበል፡ ደበን
ደበሎ (ዎች) በለምድ ዐይነት የተበጀ የበግ ዐጐዛ (ከነጠጕሩ የለፋ መደረ ቢያ በልብስ ላይ የሚጠለቅ) (ተመልከት፡ ቅጥልጥል)
ደበሎ) በካባ አምሳል ተቀጣጥሎ የተሰፋ ረዥም ደበሎ (የተማሪ ልብስ)
ደበሏም፡ ደበሎ ለባሽ ባለደበሎ (አባ ደበሎ እረኛ ተማሪ መነኵሴ)
ደበሰ (ደመሰ) ገሰሰ/ለቀቀ/ጠፋ/አልታይ አለ (የጽፈት) "በትግሪኛ ግን በረዘ ማለት ነው የሙቀትን ማነስና መቀነስ ያሳ ያል"
ደበሰ፡ ዶቄት ጨመረ/አጐበገበ
ደበሰስ/ደብሳሳ፡ ደበዘዝ/ደብዛዛ
ደበረ (ደቢር ደበረ) ደብር አደ ረገ/ገደመ/አከበረ/አበለጠ/አላቀ
ደበረ፡ ደበለ/ደረበ/አነባበረ/ሰደረ/ደረደረ (በተራ አኖረ ዕቃን)
ደበሸ፡ ሰነፈ/ችላ አለ/ፈዘዘ/ተንደ በዘዘ
ደበሽ/አዲበሽ፡ ትጋትና ንቃት የሌ ለው ሰነፍ ችላ ባይ ፈዛዛ ደበዘዝ ሰው በሬ
ደበቀ፡ ከተተ/ሸጐጠ/ዐባ/ሰወረ/ሸሸገ
ደበቅ ጦር፡ የደበቅ ጦር
ደበቅ፡ ስውር ቦታ
ደበቅ፡ ራሱን ሰውነቱን የደበቀ
ደበበ (ደቢብ ደበ) ድባብ ሠራ/ዘረጋ/ወጠረ/ገተረ/አጠላ/አጠየመ "የጊዜና ኀላፊ ትንቢቱም ይደብብ ይደብባል ይላል መዠመሪያውን ሰለለ እይ።"
ደበተ (ደበወ ድቡት) ጨቈነ/ተጫነ/ከበደ ("መንቃትና መስማት ከለከለ")
ደበተረ፡ ደብተር ዘረጋ/ጻፈ/ከተበ ("ደብተራ ደብተር አደረገ")
ደበነ፡ ከረረ/ጥብቅ ኾነ/አነሰ "በትግሪኛ ግን አደፈ ቈሸሸ ማለት ነው።"
ደበና፡ ከማቅ የተሰፋ ሰቀልኛና ላልኛ የንጉሥ ድንኳን "ያውታሩን መክረ ርና መወጠር ያሳያል ዳግመኛም የድሩንና የማጉን ጠጕርነት ያመለክታል።"
ደበና፡ ደበረ
ደበናንሣ (ደበን አንሣ) ጠይብ ባለጅ ፋቂ (የቈዳን ጠጕር በመጥረቢያ ፍቆ የሚያነሣ ደደቡን እድፉን የሚያሶግድ)
ደበኔ (ዋኖስ) ሱያ ዋኔ ዋሊያ "የኔ ደበን ደበናዊ ማለት ነው ከርግብ ማነ ሷን ያሳያል።"
ደበን (ሐረር ጢም) የጠጕር ስም (ጠጕር እድፍ ቍሻሻ)
ደበኛ፡ ደመኛ (ተመልከት፡ ደማን)
ደበከከ፡ (ደበከ) ደጊመ ቃል ( ረኃ ኾነ)
ደበከክ/ደብካካ፡ ወረኃ
ደበዘዝ/ደብዛዛ፡ ሰነፍ ደንጊያ (በግሩ የፍጥነት ጠላት ደደብ)
ደበየ (ደብይ ደበየ ደበወ) (ትግ. ደበየ ደፈነ ቀበረ)
ደበየ፡ ደቦ አዋለ
ደበደ፡ ደረቀ/ደደረ
ደበደ፡ ደረቀ/ደደረ
ደቡል (ሎች) (ጥካካ) አካል አካ ልማ ሥጋማ ሰው ("ጭቃው ብዙ")
ደቡብ፡ ፬ኛ የምድር ማእዘን (የሰሜን አንጻር በስተቀኝ ያለ)
ደባ (ዲፓ) ሽመቃ/ደፈጣ/ተን ኰል/እከይ/ክፋት (ዘረፋ ቅሚያ ንጥቂያ) "ስለት ድጕሱን ደባ ራሱን" እንዲሉ (እስ. ፯፡ ) (ተመልከት፡ ደጐሰ ብለኽ ድጕስን፡ ሳለ (ሰሐለ) ብለኸ ስለትን እይ)
ደባ ሠራ፡ ዝኒ ከማሁ
ደባ ዋለ (ደበየ) ተተነኰለ/ተጠ በበ/ዘረፈ/ቀማ/ነጠቀ
ደባል (ሎች) በሌላ ሰው ቤት ተጨማሪ ኹኖ የሚኖር አንድ ባዕድ ሰው (ተመልከት፡ ድልባንን እይ ከዚህ ጋራ አንድ ነው)
ደባሳ (ድሙስ) የደበሰ/የገሰሰ ( ጠፋ ጥፉ)
ደባስ፡ በጠፍ በወና በባዶ ከተማ የሚቀመጥ ጋኔን (ወይም ሰላቢ ሰይጣን ለራሱ ጠፍቶ የሰውን በረከት የሚያጠፋ) (ተመልከት፡ ደስቅን እይ)
ደባሪ፡ የደበረ/የሚደብር (ኣክባሪ)
ደባርቅ፡ ያገር ስም (በበጌምድር አው ራጃ ያለ አገር) "ደባ አርቅ ማለት ይመስ ላል።"
ደባሽ፡ የሚደብስ (ጠፊ)
ደባቂ፡ የሚደብቅ (ሰዋሪ ሸሻጊ)
ደባቃ፡ ሰዋራ ቦታ አሳቻ
ደባበቀ፡ ሰዋወረ
ደባቢ፡ የደበበ/የሚያብብ (ዘርጊ )
ደባብቆ፡ ሰዋውሮ
ደባት፡ ጥርጥር (የደባ ፍራት)
ደባክድ፡ ቀጠጥና ያህያ ዦሮ
ደባያት፡ በቀል ፍዳ (የክፉ ብድር "እንደ ሠራው መሥራት እንዳደረገው ማድረግ።") (ተመልከት፡ ፪ኛውን ደባይ ተመልከት ከዚህ ጋራ አንድ ነው)
ደባይ (ደባዪ) ወራሪ/ዘራፊ/ደባ ሠሪ
ደባይ፡ መረሬ (ጐንደር)
ደባይ፡ ሰፊ ነጋሪት "ደባይ ምታ አታመንታ" እንዲሉ ወደ ዘመቻ ሲኼዱ "ከዘረፋና ከወረራ ሲመለሱ መመታቱንና በሙሉ ግብር ቀን መጐሸሙን ያሳያል።"
ደባይ፡ የሰው ስም
ደባይ፡ ድንገተኛ አደጋ "ቢኾን ይኾናል ባይኾን አይተነው አንኼደውሞይ ደባይ መተነው" እንዲል ሐርበኛ
ደብ
ደብረ () ዐባይ፡ በትግሬ ያለ ልቅ ገዳም
ደብረ ሊባኖስ፡ አስቀድሞ አባ ሊባኖስ የጸለየበት (ኋላም አባ ተክሌ ያቀኑት እግራቸው እስኪሰበር የቆሙበት ገዳም እት ጋፊኝ ዜጋመል)
ደብረ ማርቆስ፡ በጐዣም ያለ የማ ርቆስ ቤተ ክሲያን
ደብረ ሲና፡ የሲና ተራራ (ሙሴ ፲ቱ ቃላትን ከግዜር የተቀበለበት) "በይፋት ያለ ያቡነ አረጋይ መቅደስ አጥቢያ።"
ደብረ በግዕ፡ ያባ ሕፃን ሞአ ዳም የሚገኝበት አገር (ሺዋ በጠራ ወረዳ) "በግዕ የተባሉ ጻድቁ ናቸው።"
ደብረ በጥብጥ፡ ቤተ ክሲያን ዋኪ አስቸጋሪ በጥባጭ ክፉ ደብተራ
ደብረ ቢዘን፡ በላዩ ገዳም ቤተ ክሲያን ያለበት የትግሬ ተራራ "ደብረ ባዜን ማለት ነው ይላሉ።"
ደብረ ብርሃን፡ ያገር ስም (በላይኛው ተጕለት መዠመሪያ ያለ አገር ዐጤ ዘርዐ ያዕቆብ የቅድስት ሥላሴን መቅደስ የሠሩበት) "ብርሃን ስለ ወረደበት በመቅደሱ ስም ብረ ብርሃን ተባለ ይላሉ ሌላም ሐተታ አለው።"
ደብረ ታቦር፡ የበዓል ስም (በነሐሴ ፲፫ ቀን የሚውል በዓል) (ተመልከት፡ ቡሔን እይ)
ደብረ ታቦር፡ የታቦር ተራራ (ጌታ ችን የግዜር ልጅነቱን ያስመሰከረበት) "በበ ጌምድር ያለ አገር።"
ደብረ ነጐድጓድ፡ ሐይቅ (የሐይቅ መቅደስ ደሴት)
ደብረ ዐስቦ (ደብረ ዐጸባ ብረ ዐስብ) የደብረ ሊባኖስ ፊተኛ ስም "የጭንቅ የምንዳቤ የረኃብ የጥም የጾም የጸ ሎት ስፍራ ማለት ነው ዐሰብ ዐሰቦት ጭንቅ ማለት ነውና። ፪ኛም ዐጸባው ዋጋ ያለው ስለ ኾነ ዋጋ የሚያሰጥ ገዳም ማለት ይኾናል"
ደብረ ከርቤ፡ ከርቤ የበቀለበት ያለበት ተራራ
ደብረ ወርቅ፡ በጐዣም ያለ የቅድ ስት ማርያም መቅደስ የቅባቶች ሰበካ
ደብረ ዘይት፡ በኢየሩሳሌም አቅራ ቢያ የሚገኝ ዘይት (ሴቴ ወይራ) የበቀለበት (ጌታችን ለሐዋርያት የምጽኣትን ነገር ያስተ ማረበት ተራራ)
ደብረ ዘይት፡ የበዓል ስም (በዓል ያርባ ሑዳዴ እኩሌታ እሑድ ለት የምጽ አት መታሰቢያ ማሰቢያ) "በሰንበት ላይ ደብረ ዘይት" እንዲሉ
ደብረ ዝቋላ፡ በሺዋ ያለ ረዥም ተራራ ያቦ ገዳም
ደብረ ዳሞ፡ ያቡነ አረጋይ ገዳም ያለበት የትግሬ ተራራ
ደብረ ድኁኃን፡ ጥንታዊ የአንጎት (ወሎ) ታላቅ ደብር መቅደስ
ደብረ ገነት፡ በኢየሩሳሌም ያለ ኢትዮጵያ ገዳም
ደብረ ገነት፡ ከግራኝ በፊት በወሎ የነበረ ቤተ ክሲያን
ደብረ ጽዮን፡ የጽዮን ተራራ ደብር ቅዱስ (ከማየ አይኅ በፊት ደቂቀ ሴት የነበሩበት የተቀደሰ ተራራ) (ተመልከት፡ ትቤ ትን)
ደብረ ጽጌ፡ አበባ ያለበት ተራራ
ደብሪቱ፡ የሴት ስም ("ታላቂቱ ማለት ነው" )
ደብራሆም፡ ሐሚና ተናጋሪ ለፍላፊ ለማኝ ላሊበላ "ግእዝ ደበራ አንደበራ ካለው በምስጢር ይገጥማል።"
ደብር፡ መወድስ የሚቆምበት ከለት እስካመት የሚቀደስበት ገዳም (ታላቅ ቤተ ክሲያን ተራራ የሚመስል ዐጸዳም) (ተመልከት፡ ጢምን አይ) "የቀድሞ ሰዎች ቅዱሳን አበው ነቢያት መናንያን መነኮሳት ባሕታውያን በደብር ላይ ስለ ኖሩ በዚህ ምክንያት የከተማ ቤተ ክሲያን ኹሉ ደብር ተባለ። ዋና ምስጢሩ ግን ከገጠር መቅደስ የበለጠና በተራራ ላይ"
ደብር፡ በሞረት ያለ ያቡነ ዜና ማርቆስ ገዳም (ወይም ቤተ ክሲያን ሰበካ አጥቢያ አገር)
ደብር፡ የተራራ ስም (ተራራ) "ደብር የግእዝ ተራራ ያማርኛ ነው በጋልኛ ጋራ ይባላል።"
ደብሮች፡ ገዳሞች/ታላላቆች ቤተ ክሲያኖች
ደብብ፡ ያገር ስም (አዳባይ አቅራ ቢያ ያለ አገር የወግዳ ክፍል ድባብ ዘርጋ ወጥር ማለት ነው) "ደብብ የጠጋ ልጅ" እንዲል (ዘር ቈጣሪ)
ደብተራ
ደብተራ ኦሪት፡ የሙሴ መቅደስ (የታቦት የጽላት መኖሪያ)
ደብተራ፡ ዜማ ቅኔ ሳታት የሚያ ውቅ (በደብተራ (በድንኳን) ውስጥ የሚመራ የሚቀኝ የሚዘምር መንፈሳዊ አገልጋይ ካህን አወዳሽ ሳታት ቋሚ)
ደብተራ፡ የድንኳን ስም (ድንኳን እዝ) "ሲበዛ ደባትር ይላል።" ()
ደብተር፡ መሥመር ያለው ባንድነት የተጠረዘ (ገቢና ወጪ ወይም ሌላ ቃል መጸ ፊያ ብራና ወረቀት ትንሹም ትልቁም የነገር የጕዳይ መዝገብ) "ቢጻፍበትም ባይጻፍበ ትም ደብተር ይባላል።"
ደብተርነት፡ ድብትርና ካህንነት አወዳሽነት (ደብተራ መኾን)
ደብተሮች (ደባትር) ካህናት መዘም ራን አወዳሾች ድንኳን ዐዳሪዎች ("ካህናተ ደብተራ" )
ደብቴ፡ ከፊለ ስም ወይም ቍልምጫ (የደብተራ ወገን "የኔ ደብተራ ማለት ነው" )
ደብያት፡ ዝኒ ከማሁ "ደቦ በሺዋ ደብያት በጐንደር ነው"
ደብደቦ፡ በይፋት ክፍል ያለ ቀበሌ
ደቦ ጅጊ ደበየ
ደቦ፡ ብዙ ሰው ተሰብስቦ እንደ ረራ ላንድ ሰው የሚሠራው የኅብረት ሥራ ጅጊ
ደቦል (ሎች) ገላው ጥርንቅ ያለ ያንበሳ የውሻ የዝንጀሮ የሰው የከብት ልጅ ሲያዩት የሚያምር (መሳ. ፲፩፡ , ፮፡ መዝ. ፻፬፡ ፳፩፡ ምሳ. ፳፰፡ ) (ተመልከት፡ ወጠምሻን እይ)
ደቧቡል (ሎች) ዝኒ ከማሁ ( ፋሬ ድንዳኔ ያለው ሞንዳላ መንደላት) (ኢዮ. ፳፩፡ ፲፩) "ደቧቡል ውስጠ ብዙነትም አለው"
ደቸኛ (ኞች) ባለምድር ("ዋና ሰው")
ደች (ኦሮ) ምድር ("የምድር ስም") (ተመልከት፡ ደጭን እይ ከዚህ ጋራ አንድ ነው)
ደነ ጋና/ደነጀ፡ አንድ ናቸው
ደነሰ (ደንሶ ደነሰ) ዘለለ/ጨፈረ ("ተወዘወዘ ተረገረገ")
ደነሰረ፡ አሸራሽቶ አስቀመጠ ("ቸሰረ ")
ደነቀ (ደኒቅ ደነቀ) ገረመ/ መመ/ዕጹብ ኾነ
ደነቀረ (ነቀረ) ደከረ ("አጕራን መስቀልኛ አድርጎ በበር አቆመ ወነከረ መዝ ጊያን በደንጊያ ደገፈ በአጣና ሸጐረ ቀረ ቀረ እሾኸን ጋረጠ ተከለ ሰካ")
ደነቀረ፡ ደንቃራ በመንገድ ላይ ጣለ/አስቀመጠ ("ዕርድ ዐርዶ ድር አድርቶ")
ደነቀፈ (ነቀፈ) ዐነቀፈ/ወለከፈ
ደነቀፍ/ደንቃፋ፡ ወለከፍ/ወልካፋ ("ዕንቅፋታም")
ደነቈለ፡ ጠነቈለ/ዘነቈለ ("ወጋ ዛቀ አነቈረ")
ደነቈረ (ነቈረ ደንቀወ አብደ) ወለነ ("ዦሮው ተዘጋ ተደፈነ አልሰማ ኣለ")
ደነቈረ፡ ሰነፈ/ዕውቀት ዐጣ ("አላ ዋቂ ኾነ ጀለ")
ደነበ፡ ፈጽሞ ደነዘ/ፈዘዘ/ለገመ (" ተኛ ' አባያ ኾነ እንቢ አልኼድም አለ")
ደነበረ (ደበረ ነበረ) ደነገጠ/ፈራ/በረገገ ("አገረገረ ወገሸ አፈገፈገ ሸሸ ዘለለ ወደ ጐን ኼደ ወነበደ")
ደነበረ፡ ለካ ወሰነ ደካ ("(ገቢር)")
ደነበረ፡ ታወረ/ጠነበረ ("(ተገብሮ)")
ደነበር/ደንባራ፡ ዝኒ ከማሁ ("ጠነ በር ጠንባራ ዕውር")
ደነበሸ፡ ታመገ/ደለበ/ሻገተ (ተመልከት፡ ዐማ ብለኸ ታማን እይ)
ደነበቀ (ደበቀ) አብዝቶ ቀዳ ("አን ኮላን በማጥለቅ")
ደነበዘ (ደበሰ ነበዘ) ጨለመ/ ነበዛ
ደነበዝ/ደንባዛ/ድንብዝ፡ የደነበዘ ' የጨለመ ሰውየው ("ወይም ዐይኑ")
ደነባ (ትግ. ደንበወ) እጅና እግሩ ዐበጠ/ተድበለበለ
ደነባ፡ ሐጎ ወሰነ/ደነገገ ("ደንብ ቆመ ሥራት ሠራ ዐወጀ") (ተመልከት፡ ዐገገን እይ)
ደነባ፡ ያልጋ ጋድም ዐነጸ/ጠረበ (" ልክ በመጠን በማስተካከል")
ደነብ()ስ፡ ዳት ልግም ዝምታ
ደነብስ አለ፡ ዝም አለ ("ነገር ልመልስም አለ ከነፍስ መጥቶ ተጨም ሯል በደነ ብለኸ በደነፍስን ተመልከት")
ደነነ (ደኒን ደነ) ናቸ/በዛ/ችፍግ አለ ("ዘነበለ ጐነበሰ ዘመመ")
ደነከ (ደነቀ) ዐጠረ/ዐጪር ኾነ
ደነከለ (ትግ. ደንከለ) ጣለ/ፈነገለ/አሰናከለ
ደነከረ (ደነቀረ ደነገረ) ወለገደ/አጠመመ ("ሥሩ ደከረ ነው")
ደነከረ፡ ወዲያና ወዲህ ግራና ቀኝ ማሰ ኳተ ቈፈረ (ተመልከት፡ ደነጐረን እይ)
ደነከረ፡ ዘለለ/አረገደ
ደነዘ (ደንዘዘ) ደና/በረደ ' ጠረሰ ' ስለት ዐጣ ("አልቈርጥ አለ") (ኤፌ. ፬፡ ፲፱)
ደነዘዘ (ደንዘዘ) ፈዘዘ/ዳተኛ ኾነ ("አልኼድ አልሰማ አለ በደነ ደበዘዘ ልማዱ ግን አፈዘዘ ነው እግሬን ደነዘዘኝእንዲሉ)
ደነዘዝ/ደንዛዛ፡ ፈዛዛ ደብዛዛ በድን
ደነዝ (ዞች) የደነዘ/የደና ("ዐር የማይቈርጥ ካራ ከባለጅ ደጅ የተሰረቀ ደነዝ ደንቈሮ ደደብ")
ደነደነ (ትግ. ደንደነ ሞከረ ተነ) ወፈረ/ገዘፈ/ረጋ ("የጭቃ የሊጥ የቡሖ") (፪ዜና. ፲፡ ) (ተመልከት፡ ደለመጠንና ፈረጠመን እይ)
ደነጀ (ደንገገ) ደነገገ/ወሰነ
ደነገለ (ደንገለ) ጠበቀ ("በድንግልና አኖረ ድንግል አደረገ")
ደነገረ (ለበየ) ሳተ/ዐጣ/ረሳ
ደነገተ (ደዲቅ ደደቀ ደኒቅ ነቀ) ድንገት ኾነ ï መጣ/ተደረገ ("ሳያስቡት አለብኝ ሳይሉት")
ደነገዘ፡ ስሯጽ ነው ("በርጅና ዘዘ ጨለመ ላይን ያዘ") (ተመልከት፡ ደገዘን እይ)
ደነገዝ/ደንጋዛ (ዞች) የደነገዘ ("ፈዛዛ ዳፍንታም")
ደነገገ (ደንገገ) ሥራት ሠራ ' ሰነ/ሐገገ/ደነባ/ጠነቀቀ
ደነገጠ (ደንገፀ) ፈራ/ባባ/ተንቀጠቀጠ ("ነው አለ ዐዘነ ከሳ")
ደነገጠ፡ ሣሣ/አነሰ ("ገበታው ደነገጠእንዲሉ)
ደነጋ (አበነ) ደንጊያ ኾነ ("ወደ ደንጊያነት ተለወጠ ከረረ ጠነከረ ፈዘዘ") (ዘፀ. ፲፭፡ , , ፲፮)
ደነጐረ፡ ደደቀ/ቈፈረ/ፈነቀለ/ገለ በጠ ("አደንጓሬ ዘራ")
ደነፈቀ (ደፈቀ) ሳያቋርጥ ፈጽሞ አለቀሰ ("ነፈረቀ ተስረቀረቀ ፊቱን በንባ ዘፈቀ ተንሠቀሠቀ")
ደነፋ (ደፍዐ ወክሐ ትግ. ደን ፍዐ) ተንቈራጠጠ/ዘለለ/አወካ/ፎከረ/ተን ደቀደቀ ("ዘራፍ እዚህ ገዳይ አለ")
ደና፡ ደነዘ/ተቸረቸመ
ደናም፡ ደን የበዛበት ስፍራ ("ባለደን ዱር")
ደናራ (ዲናር) የገንዘብ ስም ("የቀ ድሞ ገንዘብ")
ደናሽ፡ የደነሰ/የሚደንስ
ደናቂ፡ የሚደንቅ ("ገራሚ")
ደናቢ፡ የደነበ/የሚደንብ ("ደናዥ ")
ደናብ፡ በመራቤቴ ውስጥ ያለ አገር
ደናዥ፡ የሚደንዝ ("በራጅ")
ደን (ኖች) ብዙ ዛፍና ቅጠላቅጠል ዎማ ጫካ ውድማ
ደን ደነነ
ደንሳራ/ድንስር፡ የተደነሰረ ("ቅምጥ")
ደንሳገነን፡ የሚሸት ቅጠል የምች መድኀኒት
ደንሴ፡ ዐመለ ልስልስ ሰው ("ገራም ከብት የማይዋጋ የማይራገጥ የደንስ ደንሳዊ ማለት ነው")
ደንስ፡ የቀበሌ ስም ("ካንኮበር በታች ያለ ስፍራ ደናም ዛፋም ትርጓሜው ደግ ማለፊያ")
ደንሶ፡ ዝኒ ማከሁ ("ደንዞ ከዚህ ወጣ ነው")
ደንቀል/ደቀል፡ የመርከብ ምሰሶ (ኢሳ. ፴፫፡ ፳፫)
ደንቀዝ፡ የከተማ ስም ("ከጐንደር ስቀድሞ በበጌምድር የነበረ ከተማ")
ደንቃሪ፡ የደነቀረ/የሚደነቅር ("ወንካሪ ሸጓሪ ቀርቃሪ")
ደንቃራ (ሮች) ጦስና ርት ("በጐ ዳና ላይ የታረደ በግ ፍየል ዶሮ የተደራ ድር በበሽተኛ ራስ የዞረ ውጥንቅጥ እኸ ልና ቅቤ በመተላለፊያ መንገድ የተጣለ")
ደንቈሬ፡ የደንቈሮ ወገን ("ጐበዝ መቱት የማይሰማ ፍንክች የማይል ኣይፈር ለፊቱ")
ደንቈር (ጐረጥ) ቍልቋል ቈር ቍሮ የሚገባ አረንጓዴ ዐይነት ወፍ ("ደረተ ወይባ ዕሽ ሲሉት ከማሽላ ላይ ቶሎ ስለ ማይበር ደንቈር ተባለ") (ተመልከት፡ ጐረጥን ዱንቄን)
ደንቈሮ (ድንቅው ጽሙም ብድ) የደነቈረ ("ውለናም አላዋቂ ሰነፍ ልኀት ዕርሙ ጅል") (ማቴ. ፭፡ ፳፪፡ ፩ቆሮ. ፲፬፡ ፲፩)
ደንቈሮ፡ በባላ ኣንጻር ያለ ዕንጨት ("እንደ ባላው ድር የማይሠባጠርበት ብልኀት አልባ")
ደንቈሮነት፡ ውለናምነት
ደንቈሮዎች/ደንቈሮች/ደናቍርት፡ ውለናሞች/ዕውቀተ ቢሶች (ኢሳ. ፵፪፡ ፲፰፡ ኤር. ፲፡ )
ደንቋሪ፡ የሚደነቍር
ደንቋይ፡ የደነቈለ/የሚደነቍል ("ዘንቋይ አንቋሪ ዛንቂል")
ደንበር ደንበር አለ፡ እንዳገኘ ገጠ ("ዕውርኛ ኼደ ተራመደ")
ደንበር/ድንበር (ዘንቡር) በርስት/በመሬት/በርሻና በርሻ/ባገር/በወረዳ/ባው ራጃ/በቀበሌ መካከል ያለ የማይታረስ የማ ይፈልስ የምድር ወሰን ("ትክል ደንጊያ ራራ ባሕር") (ምሳ. ፳፫፡ )
ደንበር፡ መደንበር
ደንበርበር አለ፡ ተግተመተመ
ደንበሾ፡ ድልብ/ሻጋታ እኸል
ደንበቆ፡ መቃ መስዬ በዥረት አቅ ራቢያ የሚበቅል
ደንበኛ (ኞች) ዋና ሰው í ("ወይም ለሥራው ደንብ ያለው ሠራተኛ ወታደር በደንብ የሚሠራ የሚተዳደር ባለደንብ")
ደንበኛ ሰው፡ ታማኝ/ቁም ነገራም/ሐቀኛ
ደንበኛ፡ ዘወትር ካንድ መደብር ዕቃ የሚገዛ ሰው
ደንበጃን፡ የብርሌ ገንቦ
ደንበጫ አገር ደምበ
ደንቢ (ዎች) የደነባ/የሚደነባ (" ንብ ኣውጪ ሐጋጊ ወሳኝ")
ደንቢያ አገር ደምቢያ
ደንባሪ፡ የደነበረ/የሚደነብር/የሚሸሽ
ደንባቂ፡ የደነበቀ/የሚደነብቅ ("ቀጂ")
ደንብ (ቦች) ሕግ/ውሳኔ/ትእዛዝ/ዐዋጅ ("የመንግሥት ሥራ")
ደንብ እግር፡ እግሩ ያበጠ/የደነደነ/የተድበለበለ ሰው
ደንብ፡ ወታደር ወር ተራ የሚገፋበት የዘብ ("ወይም የሥራ ክፍል ቤተ ደንብእንዲሉ)
ደንብ፡ ያልጋ ራስጌና ግርጌ ጋድም ("በቁመት በውፋሬ ልክ ትክክል ኹኖ ፍና ጫፉ ሹለት ከሸንኰር የተዋደደ")
ደንቧ ደንቧ አለ፡ መላልሶ ጮኸ ("የከበሮ የነጋሪት")
ደንቧ፡ መጮኸ (ተመልከት፡ ጠነባን እይ) "ዳግመ ኛም ደንቧ የርሷ ደንብ ተብሎ ይተረጐማል ደንቧ አለ ጮኸ"
ደንታ፡ ተስፋ/ጥቅም/አለኝታ
ደንከሊ (ዎች) የነገድና ያገር ስም ("የደንከል ደንከላዊ") (ተመልከት፡ አዳልን እይ ደንከሊ ' ረብኛ አዳል ዐማርኛ ነው)
ደንከል (ትግ.) ውል/ገደብ/ዕድር
ደንካራ (ሮች) ወልጋዳ ወረኃ እግረ ድር
ደንዞ፡ ካፄ ሠርጸ ድንግል በፊት የነበሩት ነገሥታት ደንዞ ይባሉ ነበር ("ጃን ሆይ እንደ ማለት") (ተመልከት፡ ደንሶን እይ)
ደንደሎ (ገንዶራ) ያባያ መቅጫ የንዶድ ግንድ ("ወይም ላንቊሶ")
ደንደሳም/ደንደሳማ (ሞች) ባለ ደንደስ ("የበሬ አውራ ወይም ዥብ መስታድ ርት ዥብ ደንደሳማእንዲል)
ደንደሳም፡ በማዥራቱ ግድ ያለበት ሰው
ደንደሳምነት፡ ደንደሳም መኾን
ደንደስ (ትግ. አፋፍ) ያልተወቀጠ ወይፈን ወፍራም ማዥራት ትከሻ ጫንቃ ለሰውም ይነገራል (፩ዜና. ፲፭፡ ፲፭)
ደንደስ፡ ያሞሌ ጠርዝ ዳር
ደንደሶች፡ ትከሾች/ጫንቆች
ደንደሬ (ደንደራዊ) ለስላሳ ሴቴ ኰሸሽላ ("ወይም ሌላ")
ደንደር፡ ኰሸሽላ ኹለንተናው እሾኸ የኾነ ዕንጨት ("ደንደር የግእዝ ስሙ ነው")
ደንደሮ (ዎች) ወፍራምና ሻካራ ደደብ ሴት ("ዘሩ ደደረ ነው")
ደንዳና፡ የደነደነ ("ወፍራም ልብን መልከት")
ደንዳኔ፡ ወፍራምና ሰፊ አንዠት ("የደ ንዳና ደንዳናዊ ማለት ነው")
ደንዳኖች፡ የደነደኑ ("ወፍራሞች") (ኢሳ. ፲፡
ደንዳኝ፡ የሚደነድን ("ወፋሪ")
ደንገላሳ (ኦሮ) በሶምሶማና በሽምጥ መካከል ያለ ግልቢያ ገር
ደንገል (ሎች) የመንኰራኵር ልታ ("ዕንብርቱ መካከሉ") (፩ነገ. ፯፡ ፴፫)
ደንገል፡ በውሃ ውስጥ የሚበቅል የገሣ ዐይነት ("ወፍራም ሣር እንደ መቃ ታንኳ የሚኾን")
ደንገሎ (ደንግ ) ደረቅ የገብስ ቂጣ ጨው ያለበት ("ጥጥር የፈረስ የበቅሎ መኖ")
ደንገጥር ገረድ ደነጋ
ደንገጥር/ደንገጡር (ጸዋሪተ ጌጽ) የመቤቷን ጌጥ ባንገቷ አጥልቃ ምትሸከም ገረድ ("አሳሳች እመቤት መሳይ በግእዝ አመት ትባላለች") (ተመልከት፡ ላቀ ብለኸ ሊቀ መኳስን)
ደንገጥር፡ በጥበብ ዳር የሚጣል ለት ("የጥበብ ኣሽከር")
ደንገጥሮች (አእማት) የንግሥታትና የወይዛዝር ገረዶች ("አሳሳቾች") (ዘፀ. ፪፡ )
ደንጊያ (ዎች) በመሬት ውስጥ የሚገኝ ጠንካራ የምድር ዐጥንት ("ጥቍርና ነጭ ብና አረንጓዴ ባለብዙ ሕብር ቦረ ቦጭ")
ደንጊያ ልብሱ፡ ደንጊያ የለበሰ ዔሊ የሚባል አውሬ
ደንጊያ በግሩ፡ ሰነፍ ሰው ፍጥነት ዕርሙ
ደንጊያ ከሰል፡ (ተመልከት፡ ከሰለን)
ደንጊያ/ድንጋይ በቁሙ ነጋ ደነገየ
ደንጋጊ (ዎች) የደነገገ/የሚደነግግ ("ወሳኝ ሒጋጊ")
ደንጋጭ/ደንጋጣ፡ የሚደነግጥ (ዘዳ. ፳፡ )
ደንግ/ደንጊያ/ደነጋም ሳይቀር ደንገገ ካለው ከግእዝ አንቀጽ ይወጣሉ (ተመልከት፡ (ፈራ ፈረየ) ብለኸ አፈራን)
ደንግ፡ ከወርቅና ከብር የተሠራ የን ግሥታትና የወይዛዝር ያንገት ጌጥ ሽልማት ("ቀለበት መስቀል አንባር ድሪ ጠልሰም ኰት ግርጃ ማርዳ የመሰለው ኹሉ")
ደንግ፡ ከደንጊያ የሚገኝ ፈርጥ አልማዝ ("ከሰደፍ ከብርጋና የሚወለድ ዕንቍ")
ደንጐለት (ደንግ ሎቱ) ዝኒ ማሁ ("ለደንጐላጕል ወጣ ገባ")
ደንጐሊጥ (የሊጥ ደንጊያ) ዐጕል ሰው ዐመለ መጥፎ (ተመልከት፡ ብርኵታን)
ደንጐላጕል (ደንጐል ዐጕል) ዐጕል ደንጐል ያለበት ስፍራ ("ሲረግጡት የሚያስቸግር ሥርጓጕጥ")
ደንጐል (ትግ. ደንጐላ) ገለብ
ደንጐሎ፡ ባለትልቅ ፍሬ ዐይነት ጥቍር ነጭ ኢየሩሴ መሳይ አደንጓሬ ("በይ ፋትና በሐረርጌ የሚበቅል ዐረቦች ፈሱሊያ ይሉታል")
ደንጐራ፡ በጫፉ ማረሻ በሥሩ ደን ጊያ የተዋደደበት አጣና
ደንጎች፡ ደንጊያዎች/ጌጦች/አልማዞች/ፈርጦች (ዘፀ. ፳፰፡ ፲፩, ፲፫፡ ፴፭፡ ፱፡ ኢሳ. ፵፪፡ ፲፩)
ደንጎዜ፡ በሺዋ አውራጃ በመንዝ ስጥ ያለ አገር ("ደንገዜ ሀብተ ሥላሴእንዲሉ)
ደንጓሪ፡ የደነጐረ/የሚደነጕር ("ደዳቂ ፈንቃይ")
ደንጓራ፡ ዘንኳራ ("ነገሩ ከሰው የማ ይሰማማ")
ደንፊ፡ የደነፋ/የሚደነፋ ("ፎካሪ")
ደንፋቂ፡ የደነፈቀ/የሚደነፍቅ ("አልቃሽ")
ደንፍ (ፎች) ታሕታይ ጒበን ርበኛ እየደነፋ የሚገባበትና የሚወጣበት ("በግእዝ መርፈቅ መድረክ ይባላል") (ተመልከት፡ ደፍን እይ ከዚህ ጋራ አንድ ነው)
ደከመ (ዶኪም ደክመ) ለፋ/ጣረ/ታከተ/ሰነፈ/ላመ/ሰለቸ ("መኼድ መሥ ራት መናገር አቃተው ተሳነው ኀይል ዐጣ ዛለ ለሞት ቀረበ ስልም አለ") (ዮሐ. ፬፡ ) (ተመልከት፡ ዳከረንና ማሰነን እይ)
ደከረ፡ ደቀነ/ገተረ/አቆመ/አዘገበ/ለጠጠ/አነጣጠረ/አቀረበ ("የጦር የቀስት የእ ስኪት የጠመንዣ")
ደከር (ዐረ. ዘከር፡ እስኪት. ተባ ዕት፡ ዕብ. ዛካር፡ ወንድ) ጥኑ/ጠን ካራ "ደከር ጐበና" እንዲሉ ሐረርጌዎች
ደከነ (ደቀነ) ሰደረ/ደረደረ/አነ ባበረ/ደራረበ
ደከከ (ደኅኀ) ዐጠረ/ድንክ ኾነ/ወፈረ
ደከደክ/ደክዳካ፡ የተንደከደከ
ደካ (ደቅሐ፡ ደወለ) ደቃ/ለካ/ረገጠ/ወሰነ/ከለለ (ተመልከት፡ ደነበረን እይ)
ደካ፡ ዠለጠ/ኣለፋ
ደካሚ፡ የሚደክም/የሚታክት (ኢሳ. ፩፡ )
ደካማ (ሞች) የደከመ (ታካች ' ሰነፍ ስልቹ ቈማጣ) (መዝ. ፻፭፡ ፴፯፡ ኢሳ. ፲፬፡ ፲፡ ሕዝ. ፲፮፡ ፴፡ ማቴ. ፲፩፡ ፳፰፡ ሮሜ. ፲፬፡ ፪፡ ፩ቆሮ. ፩፡ ፳፯)
ደካማ፡ ዐቅመ ቢስ ሰውነት
ደካማነት፡ ደካማ መኾን ("ታካችነት ሰነፍነት ዝለት")
ደካሪ፡ የደከረ/የሚደክር (ገታሪ አዝ ጋቢ አቅራቢ)
ደካኝ (ኞች) የደከነ/የሚደክን ( ዳሪ ደርዳሪ ኣነባባሪ እክር)
ደካካ፡ ድኁርና ወፍራም ("ሲኼድ መን ገድ ጠብ የማይልለት ልጅ ወይም ዐዋቂ")
ደኬ ዶዮ ደከደከ
ደኬ፡ ውሃ ያነሰው ' ዶዮ ("የሹሮ ወጥ ዐል")
ደክደክ አለ፡ ተንደከደከ
ደኮ፡ የለፋ ደበሎ ድብዳብ
ደኳኳ፡ ብርኵማ/መዳኺያ/መንፈቀቂያ
ደኸየ (ደኀየ) ዐጣ/ተቸገረ/ድኻ ኾነ ("ከሌላው አነሰ")
ደወረ (ዘወረ) አዞረ/አሽከረከረ ("በጭን በጣት ጸፋ ማዳወሪያን እንዝርትን")
ደወረ፡ ጠቀለለ/አቀለመ/አጠነጠነ ("የጥጥ የጠጕር የማግ የሐር የጥለት")
ደዋሪ (ሮች) የደወረ/የሚደውር ( ዟሪ አጠንጣኝ አቅላሚ)
ደዘለ (ደለዘ) ጠዘለ
ደዘደዘ (ጠዘጠዘ) ከበሮ መታ/ ዘለ/ወቀጠ
ደዘደዝ/ደዝዳዛ፡ ምድርን በርግጫ የሚደዘድዝ ("ደውዳዋ ቀጥ")
ደዝዳዥ፡ የደዘደዘ/የሚደዘድዝ (መቺ)
ደይን (ደየነ) ሲኦል ("የኵነኔ ስፍራ በግእዝ ግን ፍርድ ማለት ነው ዕለትን ተመልከት")
ደይን ወረደ፡ ሲኦል ወረደ ገባ "ነፍሴ ደይን ትውረድ" እንዲል ማለኛ
ደደቀ (ደዲቅ ደደቀ) ወጋ/ፈነቀለ/ደነጐረ/ገለበጠ/ዕዳሪ አወጣ
ደደቆ፡ ኵልኵልት ወዶማ ("የበግ ዐን ገት ዕብጠት ዶዶት")
ደደብ (ስድብ) ሲነግሩት የማይሰማ ዕውቀት የማይገባው ልበ ድፍን ሰው
ደደብ (ቦች) ከቈዳ ጋራ ' ያለ ረቅ ሥጋ ዐብሮ የተገፈፈ
ደዳቂ (ዎች) የደደቀ/የሚደድቅ (ፈንቃይ ደንጓሪ)
ደጀ ሰላም፡ ከተም በር ደጅ ሠኘው ዐውዱ አደባባዩ ነው (መሳ. ፲፮፡ ፫፡ ሕዝ. ፵፡ , )
ደጀ ሰላም፡ የሰላም ደጅ (መሳለሚያ የቤተ መቅደስ የቤተ ክሲያን መሳሚያ የወን ዶች መግቢያ የሰላምታ መቀባበያ የመክፈ ልት መሳተፊያ ቤት ደጅ የተባለው ማርገ ጃው ነው ሲበዛ ደጅ ሰላሞች ይላል)
ደጀ ብርሃን (አንቀጸ ብርሃን) በስተምሥራቅ ያለ የቤተ ክሲያን ጓሮ በር (የካህናት መግቢያ)
ደጀ ብርሃን፡ ቤተ ልሔም ምስጢር
ደጀ ጠኒ (ጸናሒ) በደጅ የሚቀ መጠ የሚቈይ (ሥራ ፈላጊ)
ደጀኔ፡ የሰው ስም ("የኔ ደጀን ደጀኖች ተከታዮች ጭፍሮች")
ደጀን (ደጊን ደገነ) በስተኋላ የሚጠብቅ ("የኋላ ዘበኛ ረዳት ጦር ሰራዊት ትርጓሜው (ዴጋኒ) ተከታይ ማለት ነው") (፪ዜና. ፳፡ ፳፪) (ተመልከት፡ ወቦን)
ደጃች፡ ዝኒ ከማሁ ለደጃዝማች ("የጽ ሑፍና የቃል ማሳጠሪያ ኹለት ፊደል በመ ጕረድ ፊደሎቹም ዝማ ናቸው")
ደጃዝማች (ደጅ አዝማች) የሹመት ስም ("በራስና በፊታውራሪ መካከል ያለ የጦር አለቃ ትርጓሜው ዋና ትልቅ አዝማች ማለት ነው ጀና ይወራረሳሉና ደግ አዝማችእንዲል ትግሬ)
ደጃዝማቾች፡ ሻለቆች የጦር መኰንን
ደጃፍ (ደጅ አፍ) በመቃን ካከል ያለ (ኅዋ) ክፍት በር ("የደጅ መን ገድ አፈ ደጅ በራፍ ደጃፍ የመለሰው ማጀት የጐረሠውእንዲሉ)
ደጃፍ፡ መዝጊያ (ዘፍ. ፲፱፡ )
ደጅ (ዴዴ) ውጭ ሜዳ ("ከቅጥር በአፍኣ ያለ ስፍራ ገገምተኛው እደጅ እቤት ይላል እሰር በፍንጅ ጣል በደጅእንዲሉ) "ሲበዛ ደጆች ያሠኛል" (መዝ. ፹፯፡ ፪፡ ኢሳ. ፵፭፡ , )
ደጅ መታ፡ መዝጊያን አንኳኳ (" ጁን ጸፋ")
ደጅ አጋፋሪ፡ የውጭ ያደባባይ ልካይ
ደጅ ይጥኑ፡ የሴት ስም
ደጅ ጠና (ጸንሐ) በደጅ ተቀ መጠ ቈየ ("ሹመት ሽልማት ፈለገ ዘወትር በደጅ ታየ ተገኘ")
ደጅ ጥናት (ጽንሐት) በንጉሥ በመኰንን አደባባይ መገኘት አለመታጣት
ደጅ፡ መዝጊያ በር ("ደጅ ምቱ ይከፈ ትላችኋል") (ማቴ. ፯፡ , ፰፡ ዘፍ. ፮፡ ፲፮፡ ፲፱፡ , , ፲፩፡ ዮሐ. ፲፡ , ፱፡ ፳፡ ፲፱, ፳፮)
ደጅ፡ አደባባይ (ዘፍ. ፲፱፡ )
ደገለ (ዐረ. ደጀለ፡ ሸሸገ/ደበቀ) ቂምን በልቡ አሳደረ/አኖረ
ደገለለ፡ ጠቀለለ/ጠመጠመ ("ዘንዶ ስመሰለ አከበበ")
ደገላ (ኦሮ) ቋያ ሣር ቅጠላቅጠል (ዳዋ ክረምት አፈራሽ)
ደገሌ ማቶት ደገለለ
ደገሌ ደገመ
ደገሌ፡ የጋን የጣራ የዳቦ ማቶት ("ጫፍና ጫፉ የገጠመ ክብ ጥምጥም ሥራ") (ተመልከት፡ ፪ኛውን ዘንዶ እይ)
ደገል ገባ፡ ቂም ያዘ
ደገል፡ ቂም በቀል
ደገመ (ደጊም ደገመ) በቀስታ በለኊሳስ ድምጥ ሳያሰማ አነበበ/ጸለየ
ደገመ፡ መለሰ/አከለ/ጨመረ "ጣመኝ ድገመኝ" እንዲሉ
ደገመ፡ ኹለተኛ ዐረሰ/ዐየመ/ቀበቀበ
ደገመ፡ ዘለቀ/ወጣ/ተማረ/ለመደ/ጨረሰ/ዐወቀ "ዳዊት ደገመ" እንዲሉ
ደገማ/ድግሚያ፡ መድገም (እከላ መራ)
ደገሠ አዘጋጀ ደገሰ
ደገሰ፡ ቈላ ፈጨ/ጠመቀ/ጋገረ/ ብል መጠጥ አዘጋጀ/አሰናዳ/አቀናበረ
ደገነ (ዴገነ) ደጋንን ቀስትን አጐ በጠ ("በዥማት በገመድ አሰረ አበጀ አዘጋጀ አዘገበ ደከረ") "ጠመንዣን አጐረሠ ቃታ ያዘ ዐለበ አነጣጠረ ነፍጥን የቀስት ጥይትን የወ ስፈንጠር ቃታን የገመድ ምሳሌ አደረገ።"
ደገኛ (ኞች) የደጋ (በደጋ ተወልዶ የሚኖር አውሬ ከብት ሰው)
ደገዘ (ደነገዘ) መሸ/ጨለመ ("ላይን ያዘ")
ደገዛ፡ ኵብኵባ ("የኵብዙባ ወገን")
ደገደገ (ትግ. ደግደገ) ወቀጠ/ ደቀቀ (ተመልከት፡ ደቀደቀን)
ደገደገ (ደግደገ) ደከመ/ከሳ/ ሰሰ/ተጐዳ/ጠቈረ (የሰውነት) (ግእዝ)
ደገደገ፡ ተጣበቀ/ተላከከ (የሞራ የቅቤ)
ደገደገ፡ አደፈ/ቸከ/ልማም ያዘ ( ጥርስ)
ደገደገ፡ ወየበ/ፈዘዘ (ያይን)
ደገገ፡ አላቀ/አበለጠ/አኰራ/ዐጀረ (ገቢር)
ደገገ፡ ደግ ኾነ ("ከክፋት ከተንኰል ከሐሜት ከሥሥት ከክፉ ነገር ኹሉ ራቀ") (ተገብሮ)
ደገፈ ደገሰ
ደገፈ፡ የገደፈ ተቃራኒ (ዐቀበ/ያዘ/ዐግዘ/ረዳ "እንዳይወድቅ አደረገ")
ደገፉ፡ ደገፌ ("የሰው ስም ደገፋው የኔ ደገፍ ማለት ነው")
ደገፋ፡ ኀይል ጥንካሬ ብርታት ረከት ረድኤት ("ከንጀራና ከውሃ የሚገኝ") (ኢሳ. ፫፡ )
ደገፋ፡ ደግፌ ድጋፌ ("የወንድ ጠሪያ ስም ድጋፌ ግን ለሴትም ይኾናል")
ደገፋ፡ ድጋፍ (ባላ ወጋግራ ምሰሶ ተራዳ ያልጋ ሸንኰር ትራስ መከዳ ግንብ ግድግዳ ወንበር) (፩ነገ. ፯፡ ፳፰, ፴፡ ፴፪)
ደገፍ (ናህብ ድንጋግ) ዐቃባ ቃሊብ ("የወንዝ ዳርና ዳር ዠማው ካፍ እስከ ደገፉ ጢም ብሎ መልቷል")
ደገፍ አለ፡ ተደገፈ
ደገፍ አደረገ፡ ደገፈ
ደገፍ፡ ያዝ/መደገፍ
ደገፎች፡ ድጋፎች (አርድእት) ወጋግሮች ("የቤተ መቅደስ የቤተ ክሲያን ሰበሰብ ጣራ ተሸካሞች") (ኤር. ፳፯፡ ፲፱)
ደጊመ ቃል፡ ቃልን ፊደልን መመ ለስ ኹለተኛ መናገር "ወንዛወንዝ ቅጠላቅ ጠል ኼደ ነጐደ ዐረገ ወጣ ነደዶ ነበበ የመሰለው ኹሉ ነደደንና ነበበን የመሰለ ግስ የጊዜና ኀላፊ ትንቢቱ በረረ ይበር ይበራል ገረረ ይገር ይገራል ጠመመ ይጠም ይጠማል ተመመ ይተም ይተማል ቢል እንጂ ይበርር ይበርራል ይጎርር ይገርራል ይጠምም ይጠምማል ይተምም ይተምማል አይልም ቢልም የስሕተት ስሕተት ነው ፊደልን ጐርዶና አሳጥሮ መናገር ስንኳን ማርኛ በግእዝ አለና።"
ደጊም፡ መድገም
ደጋ ደገደገ
ደጋ (ትግ. ደጕዓ) አስታ/ጓሳ/ጦስኝ (ያበባ እኸልና የብር እኸል የሚበቅል በት ላይኛ ከፍተኛ አገር) "እንደ ጣርማበርና እንደ መገዘዝ ያለ የመንግሥተ ሰማይ ምሳሌ ወይም በቈላና በዋና ደጋ መካከል የሚገኝ እንቧጮ ከስክሶ ብሳና ከወሎ ወይራ ጥድ ነት የሚገኝበት እኸል በያይነቱ ኣገዳ ጭምር የሚኾንበት ወይናደጋ (ጮቄ)"
ደጋሚ (ሞች) የደገመ/የሚደግም/የሚያነብ (አንባቢ ጸላይ ካህን ተማሪ "ዳዊት ደጋሚ" እንዲሉ)
ደጋሚ፡ አስማተኛ/መሠሪ/ዐዚማም (መክ. ፲፡ ፲፩)
ደጋሽ (ሾች) የደገሰ/የሚደግስ (አዘጋጂ አቀናባሪ)
ደጋን (ኖች) (ዲጋን) የጐበጠ ዕን ጨት (ጥጥ ጠጕር መንደፊያ ቅስት ቅሥፍ መሳይ)
ደጋን ወገብ፡ ጐባጣ ሰው ("ወገበ")
ደጋኝ (ኞች) (ዴጋኒ) የደገነ/የሚ ደግን (አጕባጭ አነጣጣሪ)
ደጋገመ፡ የደገመ ድርብ (አነባበበ መላለሰ ጨማመረ)
ደጋገፈ፡ መላልሶ ደገፈ
ደጋጋ (ኦሮ) ጥርሱ ያደገ የረዘመ
ደጋግ (ጎች) መልካካም የግብር የጠባይ "ደጋግ ሰዎች" እንዲሉ
ደግ (ቀዳሚ) ትልቅ ዋና ባላባት "አንድ ከደግ ተወለድ አንድ ከደግ ተጠጋ" እንዲሉ "ትግሬም ትልቅ ሲል ደግ ይላል።" (ተመልከት፡ ደጅን)
ደግ (ጎች) ቸር ነባይ ማለፊያ ልካም ቁም ነገራም ሐቀኛ ቅን እውነተኛ ሰው ("ዐጥንቱን የሚቈራኙት")
ደግ ሠራ፡ መልካም አደረገ (ለተ ራበ አበላ ለተጠማ አጠጣ ለታረዘ ለበሰ የታሰረ አስፈታ)
ደግ ሰው) ከንጀራው ቈርሶ ከወጡ አጥቅሶ የሚያጐርሥ።
ደግ ሰው፡ የሰው መጨረሻ (ጻድቅ አይቈረቊሬ)
ደግ ቸር ደገገ
ደግ ነው፡ በጎ ነው/ተሽሎታል
ደግ ነው፡ ጥሩ ነው/ማለፊያ ነው
ደግ አደረገ፡ አበጀ/አሳመረ
ደግ፡ የትዛዝ መልስ ("ዕሺ በጎ በጄ")
ደግሞ፡ ተምሮ አንብቦ ዐውቆ
ደግሞ፡ ዳግመኛ (ንኡስ አገባብ)
ደግነት፡ ቅንነት/ትሑትነት/ታዣዥ ነት
ደግዳጊ፡ የሚደገድግ (ተላካኪ)
ደግዳጋ (ድግዱግ) የደገደገ/የከሳ (የኰሰሰ የተላከከ ያደፈ)
ደግፍ፡ የዦሮ ግንድ በሽታ (ዕብጠት "ዦሮ ደግፍ" እንዲሉ)
ደጐለ (ትግ) አዳፈነ/ቀበረ (ተመልከት፡ ጀጐለን እይ የዚህ ዘር ነው)
ደጐመ ደገፈ
ደጐመ (ጠቈመ) ረባ/ጠቀመ/ ገዘ/ረዳ/ደገፈ ("ዐልፎ ዐልፎ ሰጠ በልክ መጠን")
ደጐሠ አስጌጠ ደጐሰ
ደጐሰ (ደጐጸ) የመጽሐፍን ገበታ ነት አለበሰ ("ወይም በተንቤን በባሕር ዐረብ አስጌጠ ሸለመ ለሰገባ ሲኾን ሸመጠጠ ይላል")
ደጐባ (መሓዝ) ጐበዝ ወጣት ሦታ (ትምርት ያልገባው ያልዘለቀው ሰው ወገበ ነጭ ጸናጽል መቋሚያ አቀባይ በከበሮ' ቤት የሚቆም)
ደጐባ (ደጐብያ) ኵብኵባ ክንፍ የሌለው አንበጣ ("ከማኰብኰብ በቀር መብረር የማይችል ያንበጣ ተወራጅ")
ደጐቤ (ደጐባዊ) የደጐባ ወገን ዐይነት (ዮኤ. ፩፡ )
ደጐቦች፡ ብኵቦች ጐበዛዝት
ደጎጎ (ኦሮ) ጐታ/ጐተራ (ከንጨት ከጭቃ የተበጀ)
ደጓሚ (ሞች) የደጐመ/የሚደጕም (ዐጋዥ ረዳት ደጋፊ ሰጪ)
ደጓሳ፡ ወፍራም ቋራም ዱላ
ደጓሽ (ሾች) የደጐሰ/የሚደጕስ ( ላሚ አስጊያጭ ተማሪ ደብተራ ካህን)
ደጭ (ኦሮ) መሬት ("የመሬት ስም ደችን እይ")
ደጭ መረጭ፡ የቅጠል ስም ("ፍሬው አንዠት የሚመስል የዕባጭ መድኀኒት ደጭ መሬት መረጭ አንዠት የመሬት አን ዠት ማለት ነው መረጭን ተመልከት")
ደፈ፡ ራሰ/ጨቀየ/ተጨማለቀ
ደፈ፡ እብቅ/ገርገመጥ
ደፈረ (ደፊር ደፈረ) ጨከነ/ ደበ/ነጠበ/ናቀ/አቀለለ/አዋረደ ("አላቅሙ ሠራ") (ዮሐ. ፳፩፡ ፲፪፡ ሮሜ. ፲፡ )
ደፈረ፡ ሴትን ነካ/ደረሰ/አለውድ በግድ
ደፈረ፡ አበዛ/ቈለለ ("ደብር አስመሰለ")
ደፈረሰ (ደፈረ ፈረሰ) ተበጠ በጠ/እተለ/ጐሸ/አደፈ/ጐደፈ ("ቀላ ተበላሸ ካልደፈረሰ አይጠራምእንዲሉ)
ደፈረሰ፡ ታወከ/ተሸበረ ("አገሩ ከተ")
ደፈረሱ፡ የሰው ስም ("ጠላቶች ታወኩ ተሸበሩ ማለት ነው")
ደፈራ፡ መድፈር (፪ሳሙ. ፯፡ ፳፯)
ደፈር (ሮች) የተራራ የገመገም ራስ ጫፍ ("ከፍታው ምንም ቢርቅ በማየት የሚደፈር ሰማይ ደጋፊ የሚመስል ጠፈር ደፈር" እንዲሉ) (ተመልከት፡ አንበጣን)
ደፈቀ፡ ቈበርን ዐረፋን ካፍ አወጣ "ዐረፋ ደፈቀ" እንዲሉ
ደፈቀ፡ ዘፈቀ/እውሃ ውስጥ ነከረ/አገባ ("ወደ ታች አለ ሰውን ሌላ ነገርን")
ደፈቀ፡ የምስር ንፍሮን ዳጠ/ፈጨ ("በመጠኑ አላመ")
ደፈነ (ደፊን ደፈነ) ቀበረ/መረገ/መላ ጠቀጠቀ/ሸፈነ/ወተፈ/ዘጋ/ጨፈነ/አለበሰ ("የውሃ የገንዘብ የነገር የሬሳ የዦሮ የዐይን") (ዘፍ. ፳፮፡ ፲፭, ፲፰)
ደፈነ ደፈቀ
ደፈና፡ መረጋ/ጭፈና
ደፈና፡ ጠቅላላ/ሙሉ ("መክፈልና ጕደል መለየት ሳይኖር ሰውን በደፈናው ጥራእንዲሉ)
ደፈደፈ (ደፍደፈ ዐፈር ከደነ አለበሰ የእድሞ) ለጠፈ/ቀባ/መረገ/ ስልን በመድኀኒት
ደፈደፈ፡ ጥንስስንና ቂጣን እንኵሮን ቀላቀለ/አዋዋደ ("ውሃ ጨምሮ ባንድነት ዐሸ ለወሰ ድፍድፍ አደረገ") (ተመልከት፡ ዘፈዘፈን እይ)
ደፈደፈ፡ ጥፋቱን በሰው ላይ አደረገ
ደፈደፍ/ደፍዳፋ፡ የተንደፋደፈ/የሚ ንደፋደፍ ("ርብትብት")
ደፈጠ፡ ሰካ/አዋደደ/ገጠመ
ደፈጠ፡ የተልባ ነዶን በደንጊያ ዐሸ/ፈለፈለ
ደፈጠ፡ ጐነበሰ/ተደበቀ/ሸመቀ
ደፈጠጠ፡ ረገጠ/ዳመጠ/ረመጠጠ ("ዝንጀሮ አስመሰለ አፍንጫን")
ደፈጠጠ፡ ጨቈነ/አስተኛ/ተጫነ/ ፈለቀ/
ደፈጠጥ/ደፍጣጣ/ድፍጥ፡ የተደ ፈጠጠ ("ዳመጦ ዐይጥ ሰው አፍን፵ ደፍ ጣጣእንዲሉ)
ደፈጣ፡ ተጐንብሶ የሚገቡበት የራስጌ በር መሿለኪያ
ደፈጨ (ፈጪ) ደቀቀ ("የገለባ")
ደፈጩ፡ (This seems to be a heading leading into the next word)
ደፊ (ዎች) የደፋ/የሚደፋ ("አፍሳሽ ገልባጭ ዘርጋፊ")
ደፊ፡ ዘርፍን አስቀድሞ ባለቤትን የሚያስከትል ፊደል "አምላከ ሰማይ ንጉሠ ኢትዮጵያ ያለው የሰማይ አምላክ የኢትዮጵያ ንጉሥ የሚያሠኝ ምስጢሩ ዛዋሪ እንደ ማለት ነው"
ደፋ (ደፍዐ) አወደቀ/ፈነገለ/አፈ ሰሰ/ከነበለ/ዘቀዘቀ/ገለበጠ/ዘረገፈ
ደፋ ቀና አለ፡ ወደቀ/ተነሣ
ደፋ አደረገ፡ ከንበል አደረገ
ደፋ ደፋ አለ፡ ቸኰለ ("ቶሎ ቶሎ")
ደፋ፡ በራሱ ላይ ዘውድን ራስ ርን ጫነ/አደረገ/ተቀዳጀ (፩ሳሙ. ፲፯፡ )
ደፋ፡ አስቀመጠ/አኖረ/ተወ "አህያዬ ቢደክምብኝ እኸሌን እከሌ ቤት ደፍቼው መጣኹ" ("የስልቻው አፍ መዘቅዘቁን ያስረዳል")
ደፋ፡ አንድ ነገር ለመግዛት ብዙ ገንዘብ ከፈለ
ደፋ፡ ወዳንድ ፊት አመዘነ ("ዐንገቱን አዘነበለ አቀረቀረ")
ደፋ፡ ዳቦ ጋገረ ("ያክንባሎን በላዬ መደፋት ያሳያል")
ደፋሪ፡ የሚደፍር ("አዋራጅ")
ደፋር (ሮች) ዝኒ ከማሁ ("የደፈረ ጨካኝ") (መዝ. ፲፱፡ ፲፫፡ ምሳ. ፳፩፡ ፬፡ መክ. ፯፡ )
ደፋርነት፡ ደፋር መኾን
ደፋቂ (ቆች) የደፈቀ/የሚደፍቅ ("ዘፋቂ ነካሪ አላሚ")
ደፋና/ደፈነት፡ ማየት የማይችል/የማትችል ("ጨፋና")
ደፋኝ (ኞች) የደፈነ/የሚደፍን (" ባሪ መራጊ ዘጊ ሸፋኝ ጉም")
ደፋጭ፡ የደፈጠ/የሚደፍጥ ("ሸማቂ")
ደፋጮች፡ ሸማቂዎች
ደፋፈነ፡ ቀባበረ/መራረገ
ደፋፋ፡ መላልሶ ደፋ/አፈሳሰሰ
ደፍ (ፎች) ታሕታይ ጕበን መቃ ኖች በላዬ የተዋደዱበት ("በግእዝ መርፈቅ መድረክ ይባላል ዶፍ ለላዕላይ ጕበንም ይነገራል")
ደፍ አለ፡ ሳይበላ ሳይጠጣ ጦም
ደፍረስ አለ፡ ጥቂት ጐሸት አለ ("ወፈረ ኣካሉ")
ደፍረስ፡ አተል/ወፈር
ደፍራሳ፡ የደፈረሰ/የጐሸ
ደፍራሽ፡ የሚደፈርስ ("ውሃ መጠጥ")
ደፍደፍ አለ፡ ተንደፋደፈ ("ክንፉን አማታ አርገበገበ")
ደፍደፍ አለ፡ ቸኰለ/ተጣደፈ
ደፍዳፊ (ዎች) የደፈደፈ/የሚደፈ ድፍ ("ለጣፊ ቀቢ መራጊ")
ደፍጣጭ፡ የደፈጠጠ/የሚደፈጥጥ/የሚ ዳምጥ
ደፍጥ/ድፍጥ፡ ያይጥ ወጥመድ የሚ ጫን ("ተጫኝ ጨቋኝ ድንጋይ")
ደፎጭ፡ የዓሣ ስም
ዱሓ (ትግ. ድኋ፡ ቦዳ) ሜዳ ረባዳ ዘባጣ ጐድጓዳ ሸለቆ ቈላ ታች (፩ነገ. ፳፡ ፳፰፡ ፪ነገ. ፳፫፡ )
ዱኃ ረባዳ ዱሓ
ዱለታ፡ ነገር ቋጠራ
ዱለት ጨጓራና ጕበት ለተ
ዱለት፡ መዶል/አዷዷል ጀመራ
ዱለቻ (ኦሮ) ያረጀ ከብት
ዱለኛ (ኞች) ባለዱላ (ተማች ብዳቢ)
ዱላ በትር ደወለ
ዱላ (ዎች) ወፍራም በትር መደ ወያ መምቻ መመድወቻ ("በሎታ ጐመድ ሜንዶ ቈመጥ በጋልኛ ዘመቻን ዱላ (አባ ዱላ) ማለት ከዚህ ይሰማማል")
ዱላ ቀረሽ፡ ከፍ ያለ ጥል ("ዱላ የቀረው ክፍል")
ዱላ፡ ያገር ስም ("የሚገኘውም በሜጫ")
ዱላብ (ዐረ) ቁም ሣጥን ("የገንዘብ ማድለቢያ")
ዱልዱም፡ ሹለቱ የተቀነጠበ የተ ዋጊ በሬ ቀንድ
ዱልዱም፡ ዝርዝር ያይዶለ የዶሮ ኰኰኔ ("የሥጋ ቍንጮ")
ዱማች (መራቤቴ) የጦም ምሳ
ዱስ ማንዱስ፡ ያንበሳ ንጉሥ
ዱስ፡ የፈስ ድምፅ
ዱሪ፡ ጥቍር ፈረስ (ዘካ. ፮፡ , )
ዱራ ቀድሞ አካን
ዱራ፡ ያቡጀዲ የሻሽ የሌላም ልብስ መለኪያ ብረት ("የሜትር እኩሌታ የክንድ ልክ ባረብኛ ዚራዕ ይባላል በግእዝ መሠረቱ ዘርዐ ነው")
ዱራም፡ ዱር የበዛበት ደናም ቀበሌ (ተመልከት፡ ገዳምን እይ)
ዱር (ዐረ. ዴር) ከመንደርና ካምባ የራቀ የተለየ ስፍራ ("ጠፍ መሬት ሲበዛ ዱሮች ይላል") (ተመልከት፡ ዐደረ ብለኸ ዐዳሪን)
ዱር፡ ቤቴ ("ለውላጅ ፰ኛ ለፍናጅ ፯ኛ የባሪያ ዘር የማን ቤቴ ልጅ ቤቱ ዱር የኾነ ዱር ዐዳሪ")
ዱር፡ ደን/ዎማ/ጨለማ
ዱርር፡ የተዶረረ ("ኵሩ ቍጡ")
ዱርሽት (ዱር ሸተት) የሐረግ ስም ("ያረግ ሬሳ ዐይነት የተስቦ መድኀኒት ግማታም ክርፋታም ቅጠል")
ዱሮ ዘመን፡ የዱሮ ዘመን
ዱሮ፡ ፊት/ቀድሞ/አስቀድሞ/ጥንት (ተመልከት፡ ዘንድሮን አስተውል)
ዱሽ (ሾች) የእጅና የእግር ጣት የሌለው ሰው ("ስለት ወይም ምች ቍምጥና የቈረጠው ቈማጣ") (ተመልከት፡ ኵንትሽን)
ዱቄት በቁሙ ደቀቀ
ዱቄት/ዶቄት፡ ተፈጭቶ ተሰልቆ የደቀቀ ("የላመ የለዘበ ኖራን ዐመድን ጥንጣ ንን የመሰለ እኸል ክርትፉም ሽምሽሙም አንደ ስልቁ ዶቄት ይባላል")
ዱቅ()ዱቂት፡ ዐመድማ ትል ("ከም ድር ወጥቶ እንደ ትዃን ሰው የሚበላ እግር የሌለው እዦሮና ዕንጨት ውስጥ ገብቶ የሚደቀድቅ")
ዱቅ()ዱቅ፡ በትረ ቃቃን ድጅኖ አለት የሚወጋ/የሚደቀድቅ/የሚበሳ/የሚነ ድል
ዱቅንዱቂት ዐመድማ ትል ቀደቀ
ዱቅንዱቅ በትረ ቃቃን ደቀ ጥብጥ
ዱቅዱቄ፡ ሲኼድ የሚንደቀደቅ (" ለ፪ እግር መኪና ሠረገላ በኤሌትሪክና ቤንዚን ኀይል የሚሽከረከር")
ዱበር (ኦሮ) የወንዝ ስም (ከጋራ ጐርፎ ተነሥቶ ወደ ሙገር ቈላ የሚወርድ ታላቅ ዥረት) (ተመልከት፡ ወገረ ብለኸ ሙገርን እይ)
ዱቢት (ደባ) ዐጪርና ጐባጣ አፋ (፩ነገ. ፲፰፡ ፳፰)
ዱቢት፡ የሽንብራ ባቡቴ እንክብል ("ዱባዊት ማለት ነው" ) (ተመልከት፡ ዱባን እይ)
ዱባ (ዐረ. ዱባህ) ክብና ሞላላ የኾነ ባር ቅል (ቡጡ ተቀቅሎ ፍሬው ታምሶ የሚበላ) "ዱባ ዐይነት ነው ፩ኛው አረን ጓዴ ፪ኛው ይመስላል።"
ዱባለ (ዕብ. ዙብ) የሰው ስም ("ጠብ አለ ማለት ነው" )
ዱባለ (ዱብ አለ) እንደ ድብ ለለ/ወረደ ("ጡብ አለ")
ዱቤ (ዱባዊ) የዱባ ዐይነት የማ ይፋጅ (ያገራችን ወይም የፈረንጅ በርበሬ) "ዱቤ ትልልቅ የፈረንጅ ሽንብራ።"
ዱብ ዱብ አለ፡ ጨፈረ ("ጠብ ጠብ ጡብ ጡብ አለ") "ልጁ እንባው በረ ዶው ዱብ ዱብ ይላል"
ዱብ፡ ከላይ ወደ ታች መውረድ
ዱብሌ (ዱብላዊ) ጊዜ ቀንድ ያለው በግ
ዱብሌ፡ ዐርቡ ወርዱ ስምንትያ የኾነ ልብስ
ዱብሌ፡ የበግ ዐይነት (የዱር በግ) "ምስጢሩ በቤት ላለው በግ ፪ኛ ማለት ነው በጕራጌ አገር ይገኛል። ኦሮም ድኵላን ዱብሌ ይለዋል።"
ዱብል፡ ዕጥፍ መንታ ፊደል (በረደደ ሰገደደ ገሰሰ ፈሰሰ እያለ ተጽፎ የሚገኝ ደጊመ ቃል)
ዱብራ (ኦሮ) የደረሰች ልጃገረድ
ዱብታ፡ ዱብ ማለት (ዝላይ)
ዱብዳ (ዱብ ዕዳ) ያልታሰበ ዕዳ (ድንገተኛ ጥል ቍጣ)
ዱኒ፡ በጣም ታናሽ ብራብሮ ("መልከ ጠቃጠቆ")
ዱን ዱን አለ፡ እንደ ዱኒ ኼደ ("ብር ብር ክንፍ ክንፍ አለ ሕፃኑ")
ዱንቄ፡ ቍልቋል ፈልፍሎ የሚገባ ወፍ ("እጅግ የሚያምር አረንጓዴና ብጫ መልክ ደንቈር")
ዱካ፡ ፍለጋ ("አሠረ ሰኰና የኰቴ የጫማ ምልክት")
ዱያት ደዌ (ደወየ)
ዱዳ ደደቀ
ዱዳ ደደቀ
ዱዳ፡ መናገር የማይችል (ራሱ ትክክል ያይዶለ ሰው "ድዳን እይ" )
ዱዳ፡ ዘንድ ' አጠገብ ቀበሌ (ተመልከት፡ ደጅን)
ዱዳሌብ() የምድር ዕንብርት ኢየ ሩሳሌም "መሬትን ከዱዳሌብ ውሃን ከናጌብ" እንዲሉ
ዱድማ የማይናገር ዱዳ
ዱድማ፡ ዝኒ ከማሁ
ዱድማ፡ ዝኒ ከማሁ
ዱግ ታናሽ ሹም ዶገዶገ
ዱግ (ጎች) (ኮሬ) ያቡን ወኪል "ሙሉና ዱግ" እንዲሉ "ግእዝ ኀዱግ ካለው ቢወጣ ግን በወኪልነት የተተወ ማለት ነው።"
ዱግ፡ የሻለቃ እንደራሴ የበታች ዳኛ (ወይም በምስለኔና በጭቃ ሹም መካከል ያለ አዛዥ)
ዱጭ (ዳጠ) ድው ("የሕፃን ኣካ ኼድ ከመዳኸ በኋላ ዱጭ ዱጭ አለ ሲኼድ ድው ' ድው አለ")
ዱፍና፡ መልከ ቢስ ሴት
ዲማ (ኦሮ) ቀይ ከብት
ዲሞትፎር፡ የነፍጥ ስም ("የቀድሞ ዘመን ጠመንዣ")
ዲር ግንብ ደራ
ዲር (ዐረ. ዲርዕ) ጥሩር ("በግእዝ ድርዕ ይባላል")
ዲር/ድር (ትግ. ደር) የካብ ዐጥር
ዲር፡ በሰንጠረዥ መጫወቻ ውስጥ ያለ ግንብ (ማኅፈድ)
ዲር፡ ፈረሰኛ
ዲቃላ (ሎች) የምንዝር ወይም የበረት ልጅ ("ማንዘራሽ በሕግ በሥርዐት ከሚስት ያል ወለደ በስርቆሽ የመጣ") (ዘዳ. ፳፫፡ )
ዲቃላ ግስ፡ ከጥሬ መስም የወጣ አንቀጽ ("ኣከለ መካከል አማከለ ዘገበ መዝ ጎብ መዘገበ ዐጠነ ማጠን ኣማጠነ ዐተበ ማተብ አማተበ የመሰለው ኹሉ")
ዲቃላ፡ የማይበስል ትንንሽ ባቄላ
ዲቃላ፡ የዛፍ ተቀጽላ ("ወይም ተገ ድራ ትግሬ")
ዲበል (ሲሲት) ዘማች አሞራ በው ዳቂ ላይ የሚደበል
ዲብ (ደየበ) አነስ ያለ ቍልልታ (ያፈር ያሸዋ ክምር ይሳ)
ዲቦች፡ ቍልልቶች (ከምድር ጥቂት ከፍ ያሉ ኵይሶች)
ዲቱ ታናሽቱ ዕንጨት በግራና በቀኝ ተሰ ቅላ ያለች፡ ከ፫ ላይ ክርክር ያላት የመን ውጫና ማውረጃ
ዲና መታ፡ አደጋ ጣለ/ወረረ/ዘረፈ
ዲና፡ የሣህለ ሥላሴ የፈረስ ስም ("አባ ዲና" እንዲሉ)
ዲና፡ የሴት ስም ("የያዕቆብ ልጅ ዘሩ ደየነ ነው")
ዲና፡ ጠላት/ደመኛ ("አደጋ የሚጥል ዲና ጋልኛ ነው ባማርኛም ተለምዷል")
ዲናሚት ደማሚት ደመመ
ዲናሞ፡ እንደ ቡላድ ለመኪና (ለሞ ተር) ኹሉ እሳትን መብራትን ኀይልን የሚ ሰጥ ("በጫፉ ከሰል ያለበት ብረት")
ዲኖ፡ የባሕር ጐሽ/የጋኔን በሬ
ዲኖ፡ ጅን - ጋኔን ጣዖት (ተመልከት፡ ታሪከ ዘርዐ ያዕቆብ አስተውል በትግሪኛ ግን ዐጐዛ ማለት ነው)
ዲዋኒ ዳዊት
ዲዋኒ (ገመስ) ታናሽ መጨረሻ ገንዘብ ("እንደ ቤሳ ያለች") (ማቴ. ፭፡ ፳፮፡ ሉቃ. ፲፪፡ ፶፱)
ዲያ ከፊለ ስም የዲያ
ዲያቆናዊት፡ ሴት ዲያቆን ("የስሳ ' ዓመት ባልቴት ዳቈነንና ዛቈነን አስተውል")
ዲያቆን፡ የቅዳሴ አገልጋይ ("ተንሥኡ ጸልዩ ባይ ነፈቀ ብለኸ ንፍቅን እይ")
ዲያቆኖች (ዲያቆናት) ኹለትና ከኹለት በላይ ያሉ ብዙዎች
ዲያብሎስ፡ ሳጥናኤል ("ያጋንንት አለቃ")
ዲደን፡ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ሲኼድ ድድድ የሚል
ዲግዲግ፡ ትግሪት (ታናሽ የበረሓ ሠሥ ስትኼድ ድቅድቅ የምትል) (ተመልከት፡ እንሹን) "ዲግዲግ የሐረርጌ ቋንቋ ነው"
(ሀዲእ) በሥራ በነገር ባካኼድ አለመፍጠን
አለ (ሀድአ) ዝግ/ቀስ/ቸል አለ (ተመልከት፡ ዳትን እይ)
ዳኄራ ባሩድ ዳኼራ
ዳሔራ ባሩድ ዳኼራ
ዳለቻ (ኦሮ) ዐመድማ ፈረስ
ዳለጠ (ዳሌጥ) ዳጠ/ለጠ ("የተ ላገ መዝጊያ ሳንቃ መሰለ")
ዳላጣ፡ የዳለጠ (ድጥ ላጣ ወፍጮ)
ዳሌ፡ የገላ ስም ("ከጭን በላይ ከወገብ በታች ያለ የሙሓይት ሥጋ") (ማሕ. ፯፡ )
ዳሌጥ፡ የፊደል ስም (" ድልት")
ዳልጋ (ጎች) በበሬና በላም በጐሽ በቶራ ዐንገት ከማንቍርት እስከ ፍርንባ የተንጠለጠለ ቈዳ "ደላጎና ዳልጋ ግእዝ ለገ ካለው የወጡ ናቸው"
ዳልጋ፡ የጤፍ ዛላ
ዳልጋንበሳ ያውሬ ስም
ዳመና/ዳመኑ፡ የወንድና የሴት ጠሪያ ' ስም
ዳመጠ፡ ረገጠ/ዳጠ/ደፈጠጠ ("ለሰቀ ለጥ ቀጥ አደረገ ኣስተካከለ ጥጥን ከፍሬ ለየ") (ተመልከት፡ መከረን እይ)
ዳመጣ፡ ረገጣ/ልሰቃ
ዳመጦ፡ ኣፍንጫ ደፍጣጣ ወንድ ("ወይም ሴት ዝንጀሮ መሳይ")
ዳመጦ፡ የተዳመጠ ("ፍሬው የወጣ ጥጥ")
ዳሙሬ፡ ድሪቶ ("በላዩ ብዙ ክር የሚገኝበት ደምቡራን እይ ከዚህ ጋራ አንድ ነው")
ዳማ ከለለኝ፡ ሰፊ የምድር ይዘታ ("ያባ ሰንጋ መሬት በዳማ ፈረስ የተከለለ (የተወሰነ)")
ዳማ ከሴ፡ ቀይ ከሴ ("ለምች መድኀ ኒትነት ቈርጠው ዐሽተው ሲጨምቁት ሃው ዕርድ ደም የሚመስል")
ዳማ ፈረስ፡ ቀይ ፈረስ
ዳማ፡ የደም ዐይነት (ቀይ)
ዳማ፡ ደም አዋጣ አፋሰሰ
ዳማ፡ ጠይም ወንድ ("ወይም ሴት የቀይ ዳማእንዲሉ) "በጋልኛ ግን ዳማ የሚባል ፈረስ ነው"
ዳማጭ (ጮች) የዳመጠ/የሚ ዳምጥ ("ደፍጣጭ ለሳቂ ፈረስ")
ዳምዛ፡ የንጨት ስም ("ዐጣጥ የሚመ ስል ዕንጨት")
ዳምጠው፡ የንጉሥ ኀይለ መለኮት
ዳምጤ/ዳምጠው፡ የሰው ስም
ዳሞት ወይራ፡ እንደ ወይራ ጠን ካራ የኾነ ዛፍ ("ጥቍር ዕንጨት መሳይ የዳ ሞት ወይራ ማለት ይመስላል")
ዳሞት፡ በጐዣም ክፍል ያለ አገር
ዳሞትራ (ሮች) የሚናደፍ መርዘኛ ጥቍር ከሰልማ ባለጠጕር ሸረሪት
ዳሞቶች፡ የዳሞት ሰዎች ("የዳሞት ተወ ላጆች")
ዳሰ (ትግ. ደሀሰ ናደ አፈረሰ ዐረ. ዳሰ) ረገጠ/ዳጠ/ዳመጠ/ደፈጠጠ (ኢሳ. ፳፰፡ ፲፯)
ዳሰ፡ ዐሻሮ ፈጨ/አደቀቀ ወረዳውን
ዳሰሰ (ትግ. ዳሕሰሰ) ነካ/ዳበሰ (ዘዳ. ፳፰፡ ፳፱፡ ዳን. ፰፡ , ፲፰፡ ፱፡ ፳፩፡ ኢሳ. ፶፱፡ ፲፡ ማቴ. ፰፡ , ፲፭)
ዳሰሳ፡ ዳበሳ
ዳሰሳ፡ ፍለጋ (የመዳሰስ ሥራ "ዕውር በዳበሳ ይኼዳል" )
ዳሳሽ፡ የዳሰሰ/የሚዳስስ ("ዳባሽ")
ዳስ (ሶች) ሰቀላ ("የቅጠል ቤት የሰርግ የዝክር የተዝካር የማኅበር ድግስ የሚበላበትና የሚጠጣበት") (ዘዳ. ፲፮፡ ፲፫)
ዳስ፡ የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ ("ዐሻሮ ፍጭ")
ዳረ (ደኀረ) ሙሽራውንና ሙሽራዪ ቱን ባረከ/መረቀ ("ውለድ ክበድ ውለጂ ክበጂአለ)
ዳረ (ደሐረ) ወንድ ልጁን ሰረገ/ሞሸረ/ሚስት አጋባ/ንብረት ትዳር አሲያዘ ("ሴት ልጁን ከቤት አወጣ ለባል ሰጠ")
ዳረገ (ዳርጎ ዳረገ አሥበጠ) ድርጎ ፈቀደ/ኣዘዘ ("ከእከሌ ተቀበልአለ)
ዳረገ፡ ለካ/ሰፈረ/መጠነ/ቈነነ/ሰጠ
ዳረጎት (ሥበጥ) ከንጀራ ከዳቦ ተቈ ርሶ ለሰው የሚሰጥ ጕርሻ ("የረኛ መክሠሥ ዕንጐቻ የውሻ እራት")
ዳሩ እሳት፡ መኻሉ ገነት ("በዙ ሪያው መስቀል የዞረበት ገዳም ታላቅ ደብር የከተማ ቤተ ክሲያን") (ዘፍ. ፫፡ ፳፬)
ዳሩ ግን፡ (ኢሳ. ፵፡ )
ዳሩ፡ ንኡስ አገባብ
ዳሩ፡ ዳርቻው/ጫፉ/መጨረሻው
ዳሪ (ደሓሪ ደኃሪ) የዳረ/የሚድር ("ሰራጊ ሞሻሪ ባራኪ መራቂ")
ዳራ ዶሮ
ዳራ (ደኃራይ) በቀዳማ አንጻር ያለ የኮርቻ ኋለኛ ድጋፍ
ዳራጊ፡ የዳረገ/የሚዳርግ ("ሰጪ አሰጪ")
ዳር አገር (ዳራገር) በዳር ያለ አገር
ዳር፡ ዳርቻ ("ከውስጥ ከመካከል የራቀ ወሰን ደንበር ወደብ ገደብ አፋፍ ጠረፍ ጠርዝ ጫፍ መጨረሻ") (ዘፀ. ፳፫፡ ፴፩፡ ኢሳ. ፲፫፡ ) (ተመልከት፡ ዳረገን እይ)
ዳርም የለሽ፡ የሴት ስም ("ወሰን መጨረሻ የለሽም ማለት ነው")
ዳርቻ ደሰመ
ዳርቻ ጠረፍ ዳረ ዳር
ዳርና ዳር፡ ጠርዝና ጠርዝ ("ፍና ግፍ")
ዳርጌ (ጌ፡ ዳር) የዳር ምድር ረፍ (ተመልከት፡ ዳረ ብለኸ ዳርን እይ)
ዳርጌ፡ የሰው ስም ("ዳርግ ወይም የዳ ራጊ ወገን ማለት ነው")
ዳሮች፡ ወሰኖች/ጠርዞች (ዘፍ. ፳፭፡ ፲፱)
ዳሸቀ፡ ተረገጠ/ዳከረ
ዳሸን ደሰተ
ዳሸን፡ የስሜን ተራራ ቧሒት
ዳሽ፡ የዳሰ/የሚድስ/የሚፈጭ ("ፈጪ")
ዳቈነ፡ ዛቈነ/ተካነ ("ዲያቆን ኾነ ቍና ተቀበለ")
ዳቈን (ዲያቆን) የዳቈነ/የተካነ ምስጢር ያየ ቀዳሽ
ዳቋኝ (ኞች) የሚዳቍን ("ዛቋኝ ካኝ ክህነት ተቀባይ")
ዳበሰ፡ ዳሰሰ/ነካ/ፈለገ "ማሪያም ትዳብስሽ" እንዲሉ
ዳበስ አደረገ፡ ዳበሰ
ዳበስ፡ መዳሰስ
ዳበረ ደበሰ
ዳበረ፡ አደገ/ወፈረ/ገዘፈ/አሞላ/ ካለ መጠን አደረሰ/ሰፋ/ሰፊ ኾነ/አማረ
ዳበሩ፡ የሰው ስም "እናት ለልጇ ስም ስታወጣ አባትኸ ትልቅ ኾኑ እንደ ማለት ዳበሩ ትላለች።"
ዳቢት (ደበለ) የሥጋ ስም (የበሬ ትከሻ ሥጋ ከብራኳ ጋራ የጐድን ዘርፍ) "ጐድን ተዳቢት" እንዲሉ
ዳባ (ዎች) ቈዳ/ጀንዲ/ቈርበት/ነት/ተንቤን/ማስ/ሌጦ (ዐጽ(ጥፍ ምንጣፍና መደረቢያ ቀሚስ የሚኾን)) "አባ ልብሱ ዳባ ውስጡ ደባ" እንዲሉ
ዳባ ለባሽ፡ መናኝ/መነኵሴ (አረ መኔ)
ዳባ ሳም፡ ከድርበብ በታች ያለ ስፍር ("ዳባ ነክ ማለት ነው" ) "ዳባ የተባለው የቍናው ክፈፍ።"
ዳባሪ፡ የዳበረ/የሚዳብር (ያደገ)
ዳባሼ፡ የኔ ዳባሽ (ጐብኚዬ ጠያቂዬ)
ዳባሽ፡ የዳሰሰ/የሚዳብስ/የሚዳስስ (ሐኪም ወጌሻ ነኪ ፈላጊ)
ዳባት፡ በበጌምድር ውስጥ ያለ አገር
ዳቤ (ዎች) (ዳባዊ) ወፍራም የማኅበር እንጀራ (ተመልከት፡ ጐራ ብለኽ ጕሬን እይ)
ዳብሬ፡ ከዶጮና ከገንቦ የሚበልጥ ከንስራ የሚያንስ የሸክላ ዕቃ
ዳብዛ፡ ፍለጋ ጭገሬታ ምልክት "ይህ ነገር ዳብዛው ጠፋ። ዘሩ ደበሰ ነው"
ዳቦ ደበበ
ዳቦ (ዎች) በቅጠል ተጠቅሎ ገበር ምጣድ የተጋገረ (በላይ በታች እሳት የሚነድበት ትልቅነትና ስፋት ከውፋሬ ጋራ ያለው ኅብስት)
ዳቦ ሽሮ፡ በዘይት በቅቤ የተቀቀለ ሽንብራ ከዳቦ ጋራ የሚበላ
ዳቦ ቈሎ፡ ከስንዴ ሊጥ የተቈላ (የዳቦ ቈሎ ድብልብል እንክብል ዳቦነትን ከቈሎነት ያስተባበረ ምግብ ሥንቅ) (ሳሙ. ፩፡ ፳፭፡ ፲፰)
ዳቦ በሊት፡ የሴት ስም
ዳቦ በሌ፡ የሚጣቅ ወንዝ "ዳቦ ስለ ወሰደ በዚህ ስም ተጠራ ይላሉ።"
ዳቦት፡ የችቦ ስም (ሽግ ሽጕ)
ዳተኛ (ኞች) ቸልተኛ/ልግመኛ ("ደበዘዝ ገበሬ መጣኝ")
ዳተኛነት፡ ቸልተኛነት/ልግመኛነት
ዳታ/ዳት (ሀድአ ህድአት) ጸጥታ/ዝምታ/ርጋታ ("ቸልታ ልግም")
ዳታን፡ ሰን ኵስኵስት ባለማንቈርቈ ሪያ ከብር ከንሓስ የተሠራ ወርቅ ቅብ (" ነገሥታት እጅ መታጠቢያ ትርጓሜው ምን ጫም ማለት ነው ዳታን መካከለኛ ስም ስለ ኾነ ለብርትም ይነገራል")
ዳታን፡ የሰው ስም ("በሙሴ ጊዜ እንደ አቤሮን ምድር ተከፍታ የዋጠችው")
ዳነ (ድኅነ) ጤና አገኘ/ተፈወሰ/ተረፈ ("ከተያዘና ሳይያዝ አመለጠ ጻድቅ በሃ ይማኖት ይድናል") (ዕን. ፪፡ ፬፡ ዕብ. ፲፡ ፴፰)
ዳነተ፡ ዛተ/ዘበተ/ፎከረ/ተቈጣ/
ዳን፡ የሰው ስም ("ካ፲፪ቱ ነገደ እስራ ኤል፩ዱ ትርጓሜው ፈራጅ ማለት ነው ፍርድም ይኾናል")
ዳንስ፡ የፈረንጅ ጭፈራ ("ውዝዋዜ ")
ዳንኤል፡ ከታላላቆቹ ነቢያት ኣንዱ ("በባቢሎን የተነሣ ነቢይ ዳን ዳኛ ኤል አምላክ በተገናኝ ያምላክ ዳኛ ማለት ነው ሶስናን በዳኝነቱ ከሞት አድኗልና")
ዳንኪራ/ዳንኬራ (ፃሕስ) ሽብ ሸባ ርግዶሽ ጭፈራ ("እግርን እያወላመሙና እያወላገዱ ዕጥፍ ዘርጋ እያሉ የሚደረግ")
ዳንኬራ መታ (አፅሐሰ) አሸበሸበ/አረገደ/ጨፈረ
ዳንዳ፡ ማማ ያዝመራ መጠበቂያ ቄራ የዱር ዐልጋ ("ወይም ቈጥ")
ዳንዴ፡ ዳንዳዊ የዳንዳ ("ወንበዴ ማኛ በትግሪኛ ግን ሞኝ ቂል ማለት ነው")
ዳንግላ፡ በጐዣም ጠረፍ ያለ አገር
ዳንግሌ፡ ቀይ በግ እሳትማ ("ዳንግላዊ የዳንግላ ማለት ይመስላል ዳግመኛም ተባት አውራ በግ ተብሎ ይተረጐማል") (ኤር. ፶፩፡ ፵፡ ዳን. ፯፡ , , )
ዳንግሎች፡ ተባት በጎች (ዘኍ. ፳፱፡
ዳኘ (ዳነየ) ከሳሽ ተከሳሽን ዋስ አስጠራ ("አስቻለ አነጋገረ ፈረደ በየነ")
ዳኘ ቃኘ፡ ዳኝነት እየ ("ሕዝብን ዳኘኝ ዳኛ ኹነኝ ቅረብ ተከሰኻል በልልኝ")
ዳኘው፡ ዝኒ ከማሁ
ዳኛ (ኞች) የዳኘ/የሚዳኝ ("ፈራጅ ቀዳጅ አገረ ገዥ አለቃ ሹም")
ዳኛ ማሪያም፡ የማሪያም ዳኛ ("እንደ ራሴ ኢትዮጵያ የመቤታችን ዐሥራት በመ ኾኗ ፈራጁ ዳኛ ማሪያም ተባለ")
ዳኛ ሲቀመጥ፡ ሲያስችል ሲያነጋግር ("አቀርባለኹ")
ዳኛ ረገጠ፡ አልዳኝም እንቢ አለ
ዳኛ ቀጠነኝ፡ ዳኛን መናቅ ("ማስተ ሐቀር")
ዳኛ ኾነ፡ ዳኝነት ተሾመ
ዳኛው፡ ያጤ ምኒልክ የፈረስ ስም ("አባ ዳኛውእንዲሉ)
ዳኜ፡ የሰው ስም ("ዳኛዬ የኔ ዳኛ ዳኛ ወገን ማለት ነው")
ዳኝ፡ የሚድን/የሚተርፍ ("ዳኝና ዳኛ ባማርኛ ይተባበራሉ።")
ዳኝነት ገባ፡ በቅሎ ፈረስ ማር እሰጥ ብሎ ተረታ (" ብር ' ከፈለ የዳኝነት ብር ሰጠ")
ዳኝነት፡ ለዳኛ የሚከፈል የውርርድ ዕዳ
ዳኝነት፡ ዳኛ መኾን ("ፈራጅነት")
ዳከ - (ድሕከ) በደረት ተሳበ/ተጐተተ ("ምድርን በጕልበትና በመዳፍ ረገጠ አጐንብሶ በእጅና በእግር ኼደ የሕፃን")
ዳከመ፡ ቈፈረ/ጫረ/ኰተኰተ ("ያገዳ ዛሬ ቈላ ወርጄ አገዳ ስዳክም ውዬ መጣኹ")
ዳከረ (ትግ. ደከረ፡ መታ) ተለወሰ/ላቈጠ/ተረገጠ/ተወቀጠ/ደከመ/ለፋ
ዳካ ዋዲያት
ዳካ (ዐይገን) ዋዲያት/ደቅ/ትልቅ ሳሕን ጻሕል ("ከተረገጠ ቀይ ዐፈር የተሠራ") (ዘፀ. ፳፬፡ ፮፡ ኤር. ፶፪፡ ፲፰) "ሲበዛ ዳኮች ይላል" (፩ነገ. ፯፡ , ፵፭)
ዳክዬ (ዮች) (ዳከ) በውሃ ላይ የምትድሽ ዋነተኛ አሞራ ዝዪ "ዳክዬ ማለት ጋልኛ ነው"
ዳኺ፡ የዳኸ/የሚድሽ "ባለቅኔዎች ግን ጓያ ይሉታል"
ዳኼራ፡ ከጨውና ከከሰል ተወቅጦ የሚዘጋጅ ("በቀለሕ ውስጥ ከዐረር በታች የሚቀመጥ ባሩድ የጠመንዣ የመድፍ ቃታ በከምሱር ሲመታው ተተኵሶ ርሳስን የሚያ በር")
ዳወለ፡ ተፈተፈተ/ተለወሰ
ዳወሮ፡ የቀድሞ የሐረጌ ስም ("ይኸ ውም በግእዝ መጻሕፍት ይገኛል")
ዳዊት (ቶች) የመጽሐፍ ስም ("ሙሴ ሳይቀር ዳዊትና ሌሎች መዘምራን በየጊዜው የደረሱት (የዘመሩት) ፻፬ መዝሙር ያለበት የጸሎት መጽሐፍ ዳዊትና ውዳሴ ማርያምእንዲሉ)
ዳዊት ደገመ፡ ጨረሰ ዐወቀ
ዳዊት ደጋሚ (ደጋሜ ዳዊት) ዳዊት የሚደግም ("በዳዊት የሚጸልይ (ተማሪ) ካህን ፪ኛውን ደገመ ተመልከት")
ዳዊት፡ የሰው ስም ("የእሴይ ልጅ የእስራኤል ንጉሥ በገና ደርዳሪ ዳዊት በገናውን ዕዝራ መሰንቆውን ዳዊትና ሰሎሞን")
ዳውላ (ጐንደር) እንቢ' ነገር ("ከስ ልቻ ከሌላም ቈዳ የተበጀ በውስጡ 'ሣርና ገለባ ያለበት የጭነት መደላድል")
ዳውሌ፡ በጠራ አጠገብ የሚገኝ ቀበሌ
ዳውንቴ፡ የዳውንት ተወላጅ ("የዳው ንት ወገን")
ዳውንት፡ ያገር ስም ("በሣይንት አጠ ገብ ያለ አገር")
ዳውንቶች፡ የዳውንት ሰዎች
ዳዳ (ዕብ. ዳዴህ) አስከጀለ አሳ ሰበ ("የርምጃ የሩካቤ የመናገር")
ዳዴ ዳዴ አለ፡ የሕፃንን እጅ ይዞ እያለ መኼድን አስለመደ አስተ ማረ "አቱ ሥግራ ታቱ ሥግራ አለ ወን ከር ወንከር አደረገ።"
ዳዴ ዳዴ አለ፡ የሕፃንን እጅ ይዞ እያለ መኼድን አስለመደ አስተ ማረ "አቱ ሥግራ ታቱ ሥግራ አለ ወን ከር ወንከር አደረገ።"
ዳዴ፡ የሕፃን ርምጃ ("እጁን ተይዞ እየተወናከረ የሚኼደው አካኼድ")
ዳዴ፡ የሕፃን ርምጃ ("እጁን ተይዞ እየተወናከረ የሚኼደው አካኼድ")
ዳገተ፡ ዳገት ኾነ
ዳገት (ቶች) ዐቀበት (ሽቅብ ሽቅ በት)
ዳገት ዕርሙ፡ ሜዳ ወንድሙ (" ነፍ ዳውላ ሐሞት")
ዳገትና ቍልቍለት፡ የደጋና የተ ራራ የቈላ መንገድ
ዳጕሳ (ሶች) የእኸል ስም ("ዛላው ሙርዬ ፍሬው የወፍ ዘረር የሚመስል ባገ ዳም በፍሬም ከጤፍ የሚዳጕስ እኽል በሐረ ርጌና በትግሬ በሌሎችም ባንዳንድ አገሮች የሚበቅል")
ዳጋ ደሴት ደገገ
ዳጋ፡ በጣና ውስጥ ያለ ትልቅ ደሴት
ዳጌ ሙክት ደገገ
ዳጌ፡ ሙክት
ዳግመኛ (ዳግማይ ) የዳግም (ኹለተኛ)
ዳግማ ተንሣይ (ዳግም ትንሣኤ) የትንሣኤ ፪ኛ እሑድ
ዳግማ፡ ዳግም/ዳግመኛ
ዳግም፡ ኹለት (ኹለት ጊዜ)
ዳግሞሽ፡ ዝኒ ከማሁ
ዳጐሠ ወፈረ ዳጐሰ
ዳጐሰ፡ ወፈረ ("ከቅጥነት ራቀ")
ዳጐስ አለ፡ ወፈር ኣለ ("በእጅ መላ")
ዳጐስ፡ ወፈር
ዳጎን፡ የጣዖት ስም (በዓሣ ዐይነት የተሠራ የፍልስጥኤም ጣዖት)
ዳጠ (ድኅፀ) ዳለጠ/ድጥ ኾነ
ዳጠ ርጥ ብን፡ ዳሰ ' ደረቅን ነው
ዳጠ፡ ረገጠ/ደፈጠጠ/ጨፈለቀ/አጨ ማለቀ
ዳጠ፡ ቅመምን ተልባን ኮሶን የምስር ንፍሮን ፈጪ አላመ
ዳጥ፡ ዝኒ ከማሁ ለድጥ ("መሰናክል ዕንቅፋት ትእዛዝ አንቀጽ ፍጭ አልም")
ዳጪ () የዳጠ/የሚድጥ (ረጋጭ ፈጪ ())
ዳጪ፡ ዝኒ ከማሁ (ተመልከት፡ ዳመጠን እይ)
ዳፈ (ደሐፈ) ገፋ/አዳፋ/ገፈተረ/አጣደፈ
ዳፈለ፡ ጨጐረ/ጠጕራም ኾነ
ዳፈን ከፈለ፡ ባለመሥራቱ ዕዳ ቀጮ ከፈለ
ዳፈን፡ እጕል ("ያልተቀደሰ ያልተሠራ ሳይገበር የቀረ")
ዳፋ (ዳሕፍ) ግፍ ' ጡር ' ጥፋት
ዳፍል፡ ጠጕር/ጭገር/ጐፍላ
ዳፍሎ፡ የውሻ ስም ("ጠጕራም ውሻ")
ዳፍንታም (ሞች) ዳፍንት ያለበት/የሠለጠነበት ("ባለዳፍንት የቈሎ ተማሪ ጕዳ ተኛ ሰው")
ዳፍንታም፡ ደንቈሮ ("ዕውቀት የማይገ")
ዳፍንት፡ ያይን በሽታ ("ጀንበር ስት ጠልቅ ማየት የሚከለክል ምድርን ባሕር አስመስሎ የሚያሳይ ከጕዳት የሚመጣ በግእዝ ግን ርሚጦ ማለት ነው")
ዴሮ (ኦሮ) ዝንጕርጕር የዱር ድመት ("ዶሮና ወፍ ዐይጥ የሚበላ ቁመቱ ክንድ ከጭራው እስከ ራሱ ክንድ ይኾ ናል ባማርኛ አነር ይባላል")
ዴበ (ዴፐ) ተደበቀ/ሸመቀ " ዴበ እንጂ ዴበ አልተለመደም።"
ዴንሳ፡ በጐዣም ውስጥ ያለ አገር
ዴንዳ፡ የብሄሞት ፪ኛ ስም ("ዳንዴ ከዚህ የወጣ ይመስላል")
ዴግሬ፡ ደረጃ/ዕርከን/ማዕርግ ("ከፍ ታና ዝቅታ የትምርት የውቀት የመድኀኒት ወይም የሙቀት የብርድ ልክና መጠን ዴግሬ ፈረንጅና ነው")
()ከን (ኖች) ብዙ' ዕቅፍ ("የጤፍ የብር እኸል የሽንብራ ነዶ በላዩ ደንጊያ የተጫነበት")
ድኁር (ሮች) ዐጪር ሰው ("ከማ ደግ ወደ ኋላ ያለ")
ድኅነት፡ መዳን ሽረት
ድሕንጻ፡ ከቀንድ ከዝኆን ጥርስ ከጥ ቍር ዕንጨት የተበጀ የበገና መምቻ መደ ርደሪያ ("ምስጢሩ የታነጸ ማለት ነው")
ድኋን (ዐረ. ድኁን) ብልቱግ
ድለላ፡ ሽንገላ ("የሽንገላ ነገር")
ድለቃ/ድልቂያ፡ ምት/ድሰቃ/ጕሰማ
ድላል፡ ለጠቋሚ/ለስማሚ የሚሰጥ ገንዘብ
ድሌ፡ የኔ ድል ("አያ ሆሆ ማታ ነው ድሌእንዲል ገና ተጫዋች)
ድሌ፡ የድል ድላዊ ("ድል አድራጊ")
ድል (ዳሕል) መሸነፍ/ሽሽት
ድል ተነሣ፡ ድል ኾነ ("በጦር ተሸ ነፈ ተረታ")
ድል ተነሺ (ሾች) ተሸናፊ (ዘፀ. ፴፪፡ ፲፰)
ድል ነሣ፡ ድል አደረገ ("ድል ስም")
ድል ነሤ፡ ድል ነሣኹ ("የሰው ስም")
ድል ነሺ (ሾች) አሸናፊ (ዘፀ. ፴፪፡ ፲፰)
ድል ነዓድ፡ ባ፲፻ . . የነበረ የሐበሻ ንጉሥ ስም ("ድልን የሚንድ የሚያ ፈርስ ማለት ነው ናደን እይ")
ድል አለ፡ ልጅን በጣት ነካ ("ነክቶ ሸሸ ድላም ድል ያለበት")
ድል አደረገ (አድሐለ ሞኣ) አሸነፈ/አሸሸ
ድል አድራጊ (ጎች) አሸናፊ ሐር በኛ ጐበዝ ' የጦር ገበሬ
ድል ኾነ (ተድሕለ ተሞአ) ተሸነፈ/ተፈታ/አሳጣ
ድል ድልቅ አለ፡ መላልሶ ተመታ/ተደሰቀ ("ጮኸ ነጋሪቱ ከበሮው")
ድል፡ የልጆች ጨዋታ
ድል፡ የቍምጥና ምልክት ("በገላ ላይ መስሎ የሚታይ አካልን የሚያበላሽ ሕዋሳትን ይልቁንም ጣቶችን ድል የሚመታ")
ድልል (ሎች) የተደለለ/የተሸነገለ ("ሽንግል ምልስ ንገል")
ድልም አለ፡ ጭልም/ጥፍት/ዕልም
ድልም፡ የደለመ ("ውድም")
ድልምጥ አለ፡ ደለመጠ ("ጥርንቅ")
ድልስ፡ የተደለሰ ራስ ("ወይም ቅቤ")
ድልቅ፡ የተደለቀ ("ድስቅ ጕስም")
ድልባም፡ ድልብ ያለው ("ባለድልብ")
ድልባን (ወሎ) ደባል
ድልብ (ቦች) የደለበ ("ደንበሾሻጋታ እኸል ብር ወፍራም ሰንጋ ፍሪዳ ገች")
ድልኽ በሊት፡ አቃጣሪ/አሳባቂ/ነገረኛ ሴት ("በሌላዪቱ ሴት ማጀት የምትገኝ ከድልኽ ዠምሮ ኹሉን የምትቀምስ የምትበላ አደላለኽ አሰላለቅ አለቋቈጥ መደ ለኸ")
ድልኽ፡ የተፈጨ/የተደለኸ የበርበሬ ዶቄት ("ወይም ልቍጥ ብትን ድልኽ ድል ኸና ቅቤእንዲሉ)
ድልዝ፡ የተደለዘ/የተወቀጠ (በርበሬ)
ድልዝ፡ ግብዝ/ብይድ/ምርግ/ድፍን (ብረት ሸክላ ውስጠ ሰባራ)
ድልድል (ሎች) የተደላደለ ("ቅም ጥል ሀብታም ጌታ ትክክለኛ ክፍያ")
ድልድል አለ፡ ዕብጥ አለ
ድልድል ዘንፋላ ብዙ ምግብና ልብስ አማ ራጭ ጌታ ወይዘሮ ("(ኢሳ. ፵፯፥ - )") ።ሴትን ከወንድ ለመለየት
ድልድል፡ የተደለደለ ስፍራ ("ዐባጣ ጐባጣ የሌለበት") (፪ሳሙ. ፳፡ ፲፭፡ ፪ነገ. ፲፱፡ ) "ዦር ክትር የውሃ መከማቻ የኩሬ መሰብሰቢያ ግድብ ድልድል ያሠኘው ጕድ ጓዱን የከበበ ዐፈር ነው"
ድልድይ
ድልድይ (ዮች) የዠማ የዥረት ' የወንዝ ላይ መንገድ ("በንጨት በግንብ በብረት የተሠራ ከወዲህ ወዲያ ከወዲያ ወዲህ መሻገሪያ መሸጋገሪያ ላዬ የተደለደለ ታቹ ባዶ ክፍት")
ድሎት (ድልወት) ምቾት/ተድላ
ድመም፡ መደምም/መደንን
ድመራ (ድማሬ) ስብሰባ/እከባ/ጥምጠማ
ድመት (ቶች) የሴት አውሬ ለማዳ ዕቃ ዘበኛ ("ድብርቅ ዐይን ያይጥ ጠላት ዐይ")
ድመት ቅዱስ ነው፡ ንዋየ ቅድ ሳትና መንበረ ታቦት ስለሚጠብቅ እንዲህ ይባላል
ድመት የቤት አውሬ ("ደመመ")
ድመና፡ ጥቍረት/ጥቍርነት
ድማ፡ ምርት መጨመሪያ መስፈሪያ
ድማ፡ የዛፍ ስም ("በከረን ያለ ዕን ጨት ቀይ ፍሬው የሚበላ")
ድማም፡ ድንቂያ
ድም አለ ጮኸ ደመመ
ድም አለ፡ ጮኸ/ፈነዳ/አስተጋባ
ድም ድም አለ፡ መላልሶ ጮኸ ("ተተኰሰ")
ድም፡ የሴት ስም ("ድንቋ ድንቂቱ' ትክክሿ")
ድምም፡ የተደመመ/የተስጣጣ ("ትክ ክል የመደምም ክዳን")
ድምም፡ የተደነቀ ("ድንቅ")
ድምሰሳ (ድምሳሴ) ፍቆሽ
ድምስስ አለ፡ ተደመሰሰ ("ጥፍት አለ (ጥደ)")
ድምስስ/ድምስ (ድምሱስ) የተ ደመሰስ/የጠፋ/የማይታይ ("ዐይን የሌለው እን ጀራ ዕውር ዕከክ")
ድምር (ድሙር) የተደመረ/አንድ ላይ ያለ ቍጥር ("የደመራ ዕንጨት ትልቅ ጥምጥም")
ድምር ሥሉሴ፡ ሦስትዮ ድርድር ("በንጉሥና በንግሥት ቅሎ ዐንገት የሚጠለቅ የወርቅ ጌጥ ሾጣጣ ቍርጥ ንብብር መገ ናኛው ዐልፎ ዐልፎ የወርቅ ሽቦ የተሰካበት ታቹ ባሕር ረብ መደቡ ቀይ ከፈይ ነው")
ድምሮች፡ የተደመሩ ("ርጥ ቦች ዕንጨቶች")
ድምቅ ቀይ) ደምማ
ድምቡ፡ የድንቡጭ ወገን
ድምቡጭ አለ፡ ዝም አለ
ድምቡጭ፡ አካለ ጥብቅ ("እንደ ድም ቢጥ ዝምተኛ")
ድምቢጥ (ቢጸ ደም) የደም ዐይ # ነት ("ታናሽ መጨረሻ ቀይ ወፍ ጤፈ ' በል ሲበዛ ድምቢጦች ይላል") (ኤር. ፰፡ ፯፡ ማቴ. ፲፡ ፴፩, ፳፱)
ድምታ (ድመት) ጩኸት ' ድም ' ማለት ("ድመት ግእዝኛ ነው")
ድምንምን (ደመንሚን) ጨለማ ' ድግዝታ/ዐፈና
ድምንምን አለ (ኮነ ደመንሚነ) ጥቍርቍር/ጭልምልም አለ
ድምደማ፡ የመጨረስ/የማስተካከል ሥራ ("ፍጸማ")
ድምድማት (ቶች) የግንብ/የግድ ግዳ/የማንኛውም ሥራ ጫፍ መጨረሻ (መዝ. ፻፳፱፡ )
ድምድም፡ የተደመደመ ("ትክክል ወጣ ገባ የሌለበት")
ድምጠ መልካም፡ ድምጠ ማለፊያ ("ሲዘፍን ሲያዜም ወዝና ጣዕም ላሕይ ያለው")
ድምጠ ሰላላ፡ ድምጠ ቀጪን ("ሴት ድምጥ ሽማግሌ")
ድምጠ ቢስ፡ ድምጠ መጥፎ (" ምጡ የማያምር")
ድምጠ ጐርናና፡ ድምጠ ' ወፍራም ጕልማሳ ("ወይም ሌላ ምት")
ድምጡ የማይሰማ ("ዝምተኛ ")
ድምጣም (ድምፃዊ) ጯኺ (" ምጠ ረዥም ድምጠ ጕልሕ")
ድምጥ (ድምፅ) ካፍ የሚወጣ የሰው ' ቃል ("የእንስሳ ያውሬ የወፍ የደመና የውሃ የገደል ማሚቶ የሙዚቃ ጩኸት ጓታ ሲበዛ ድምጦች ይላል")
ድምጥ መለሰ (ዐለወ) እንደ ጮኹ ጮኸ ("እንደ ተናገሩ ተናገረ ገደሉ")
ድምጥ ሰጠ፡ ቃል አሰማ ("እህ አለ ተናገረ")
ድምጥማጡ ጠፋ፡ ማጥ እንደ ጠው ኾነ ("የደረሰበት ታጣ") (ተመልከት፡ ደረሰ ብለኸ ድራሽን እይ)
ድምጥማጥ (የማጥ ድምጥ) ጭም ጭምታ ወሬ ("ፍለጋ")
ድምጫ (ድምፀት) ስሚ ("መስማት")
ድምጽ በቁሙ ድምፅ
ድምፅ ድምጥ ደመጠ
ድምፅን ስለበ) ቃልን ዘጋ።
ድሰቃ፡ የቡጢ ምት
ድስም፡ ቅጽልና ስም መኾኑን አስተ ውል
ድስም፡ በሾኸ የታጠረ የዘላን ዐጥር ("ወዘፍ")
ድስም፡ የተዘጋ/ዝግ/ድፍን ("የበረት የሾኸ መዝጊያ ከላይ በንጨት ተንጠልጥሎ ከታች በባላ የሚከፈት")
ድስም፡ የተደሰመ/የተለተመ ("ልትም")
ድስቅ፡ የተደሰቀ/የተደቃ ("ዠርባ ደረት")
ድስት (ቶች) ከሸክላ ከብረት ንሓስ ከመዳብ የተሠራ ወጭት ("የወጥ ሥሪያ ትንሹም ትልቁም") (ተመልከት፡ አፍን)
ድረ ገብ፡ አንድ ወንድ ያወቃት/የደረሰባት ሴት ("ፍት")
ድረስ (እስከ) ደቂቅ አገባብ - እን ወይም እስከን ("ከአንቀጽና ከስም ጋራ እያስቀደመ ይነገራል ኤልያስ እስኪጠግብ ድረስ መብል በላ እቤቴ ድረስ መጥተሽ እንገናኝ እስከ የግእዝ ï ድረስ ያማርኛ ነው")
ድረስ/ድረሴ፡ የሰው ስም
ድረስ፡ ትእዛዝ አንቀጽ ("ቅረብ")
ድረስ፡ ንቃ/ተነሣ/ብድግ በል
ድረታ፡ የመደረት ሥራ
ድሪ ጌጥ ደራ
ድሪ፡ የወርቅና የብር ፈትል በሐር ላይ የተጠመጠመ የልጃገረድ ዐንገት ጌጥ ("ማተብ ሲበዛ ድሪዎች ይላል") (ዘፀ. ፳፰፡ , ፲፫, ፲፬)
ድሪም (ድርህም) የፋርስ ገንዘብ ስም (" ቀመት ድሪም ነው ሚዛኑም ገንዘቡም ድሪም ይባላል ሲበዛ ድሪሞች ያሠኛል")
ድሪቶ (ትግ. ድርዕቶ) ያዲስና ያሮጌ ልብስ ደባደቦ (" ጣት ዐለፍ የተሰፋ")
ድሪቷም፡ ድሪቶ ለባሽ/ባለድሪቶ
ድሪያ መቃበጥ ደራ
ድራር (ደሪር/ደረ) መደንን የሬሳ ቤት ("የመሬት ቅርጽ በግእዝ ግን እራት ማለት ነው ይኸውም ማች የመቃብር እራት መኾኑን ያሳያል")
ድራር ዐቃፊ፡ ሥሥ ደንጊያ በድ ራር ዙሪያ ተደርድሮ የሚቆም የሬሳ ሣጥን
ድራሽ አምላኩ ጠፋ፡ በሴዴቅያስ ጊዜ ቤተ መቅደስ ተቃጠለ (፪ዜና. ፴፮፡ ፲፱)
ድራሽ አምላክ፡ የአምላክ ምልክት ("ወይም አምላክ የደረሰበት ተገልጦ የታየበት ቤተ አብርሃም ደብተራ ኦሪት")
ድራሽ፡ አሠር/ፍለጋ/ድምጥማጥ/ ገሬታ
ድራተኛ፡ ባለድራት ("ሻፋዳ")
ድራት (ምርዐት) ሽፍጃ
ድራት፡ ለማጣነት፡ ደራ
ድራት፡ መድራት ("ለማጣነት")
ድሬ ዳዋ፡ ከሐረርጌ በታች በበረሓ ውስጥ ያለ ከተማ ("የባቡር ጣቢያ ድሬ ሜዳ ዳዋ መማቻ ማለት ነው በዙሪያው ያሉ ዘላኖች ለመንጋቸው ውሃ ሲያጠጡ ይደባደ ቡበት ነበርና በዚህ ስም ተጠራ ይባላል")
ድር ዝሓ ደራ
ድር (ደራ) የደራ/የተለመጠ ("ለማጣ ልምጥ እግር ጣራ እግረ ድርእንዲሉ)
ድር (ድርዕ) የተደራ ("ቀኝ ዝሓ ጠን ካራ ፈትል ዝርግ ዳግመኛም በግእዝ ስፍሕ ይባላል")
ድር ቈጠረ) በቅል በቅል አደረገ
ድር፡ እስኪት ብልት የወንድነት ልክት
ድርምስ፡ የተደረመሰ ("ውድቅ")
ድርምቢታም፡ ግዳም/ወፍራም
ድርምቢት (ደረበ) ግድ ድርብርብ ሥጋ
ድርሰት (ቶች) መልክ/ሰላምታ/ቅኔ/ዐርኬ/ግጥም/ቃል/ነገር/ስብከት/ገድል/ድርሳን/ታምር ("የመሰለው ኹሉ")
ድርሳነ መድኀኔ ዓለም፡ የመድኀኔ ዓለም ድርሳን ("አባ መባአ ጽዮን የጻፈው")
ድርሳነ ሚካኤል፡ የሚካኤል ድር ሳን
ድርሳነ ማሕየዊ፡ የጌታችንን ነገረ መስቀል የሚናገር
ድርሳነ ማርያም፡ ነገረ ማርያም
ድርሳነ ሰንበት፡ የሰንበት ድርሳን ("ያዕቆብ ዘስሩግ የደረሰው")
ድርሳነ ሥላሴ፡ የሥላሴ ድርሳን
ድርሳነ ራጉኤል፡ የራጉኤል ' ድር ሳን
ድርሳነ ኡራኤል፡ የኡራኤል ድር ሳን ("የኢትዮጵያን መጻእያት የሚናገር")
ድርሳነ ገብርኤል፡ የገብርኤል ' ርሳን
ድርሳን (ኖች) በሥላሴ በማርያም በጌታችን በመላእክት ስም ስለ ሃይማኖትና ስለ ምግባር ከሊቃውንት የተደረሰ መጽሐፍ
ድርስ (ሶች) ለማርገዝ የደረሰች ጊደር ("ረባ አራት ሸረፍ ከብት")
ድርስ ርጉዝ፡ ልትወልድ የቀረበች ክበድ ላም ("ርግዝናዋ ከ፰ ወር በላይ የኾነ ወይም ወረ ግቡ")
ድርስ፡ ርግጥ/እውነት/ጭራሽ
ድርስ፡ የዛፍ ስም ("በሉጥ")
ድርስ፡ የዜማ ምልክት (ርስ) ("በዜማ መጽሐፍ ተጽፎ የሚገኝ")
ድርሻ፡ ክፍል/ዕድል/ፈንታ/ዕጣ ("የቦታ የርስት የገንዘብ የከብት የማንኛውም ነገር") (መክ. ፱፡ , )
ድርሽ፡ ዝር/ትርው
ድርቀ ሐዋርያት፡ ሐምሌ ፪ኛና ፫ኛ ፬ኛ ፭ኛ ቀን ዝናም ተግ የሚልበት ፀሓይ የሚታይበት ("የሐዋርያት በዓል")
ድርቀት፡ መድረቅ/ደረቅነት ("የሆድ በሽታ ዐይነ ምድርን እንደ በጠጥ የሚያደ ርግ")
ድርቄ (ዎች) ያልተሸመጠጠ/ያል ተሸለመ ዐረብ ያለበሰ የጐራዴ መክተቻ ("በንጨት ላይ ተሰፍቶ የደረቀ ከተጌጠ በኋላ ግን አፎት ሰገባ ይባላል")
ድርቅ፡ በረሓ/ምድረ-በዳ (መዝ. ፷፫፡ )
ድርቅ፡ በጋ/ቦና ("ዝናም የጠፋበት የታጣበት ዘመን")
ድርቅና፡ ደረቅነት/ጭከና
ድርቆሽ፡ ደረቅ ሣር ("የተወቀጠ ቸሮ")
ድርቋ (ትግ) ድርቆሽ ("የከብት መኖ") (ኢሳ. ፭፡ ፳፬፡ ሆሴ. ፲፩፡ )
ድርበብ፡ ከዳባ ሳም በላይ ከመንተር ፈፍ በታች ያለ ስፍር ይዘውት ሲኼዱ የማይፈስ
ድርብ (ቦች) ሰፊ ጥበብ ያለው ዋጋው ፫፻ ጥሬ ብር የኾነ ጌጠኛ የማዕርግ ልብስ ("ዝቅዝቅ ድርብ ተሸለመ ድርብ ለበሰ ድርብ ሠሪእንዲሉ) (ተመልከት፡ ረገፈ ብለኸ መርገፍን እይ)
ድርብ ታቦት፡ የዋናው ታቦት ኹለ ተኛ
ድርብ ትርጓሜ፡ ብዙ አወራረድ ያለው ፍች
ድርብ ዜማ፡ ንባቡ አንድ ሲኾን ዜማው ዕጥፍ የኾነ
ድርብ ጃኖ፡ ዳርና ዳሩ የድርብ በብ ያለበት ጃኖ
ድርብ ጥርስ፡ በኋላ የበቀለ ላይኛ ጥርስ
ድርብ፡ ቍና የሚይዝ ጕርዝኝ
ድርብ፡ የተደረበ ("ዕጥፍ የኾነ ብርድ ልብስ") (ሩት. ፫፡ )
ድርብርብ፡ የተደራረበ ("ንብብር ሥራ")
ድርት፡ የተደረተ/የተደበደበ/የተጠቃ ቀመ ("ጥቅምቅም")
ድርና ማግ፡ ቀኝና ግራ
ድርንቅ፡ የተደረነቀ/የታመቀ/የተረ ጠጠ ("ዕምቅ ርጥጥ")
ድርንቅ፡ ድርጭት (ግእዝ)
ድርዝ፡ የተደረዘ/የተለጐመ ("ልጕም")
ድርደራ/ድርዳሮ፡ ስደራ/ኵልኰላ/ግርገራ
ድርደራ፡ የበገና ምት
ድርድር (ሮች) የተደረደረ የመ ደብር ዕቃ ("ስድር ኵልኵል") (፪ነገ. ፲፱፡ ፳፭፡ መዝ. ፸፱፡ ፩፡ ምሳ. ፳፮፡ )
ድርድር፡ የዕርቅ ውል/ስምም
ድርጅት፡ ዝግጅት/መደራጀት
ድርጅቶች፡ ዝግጅቶች/መደራጀት/መዘጋጀት/መቀናበር/ ሰናዳት
ድርገት፡ አንድነት/ማኅበር/ሸንጎ/ ባኤ/ብዙ ሕዝብ/ገበያተኛ/ሰርገኛ/ዱለተኛ/ልቅሶኛ ("አንድ መኾን ግጥሚያ ቅዳሴው ድርገት ወረደእንዲሉ)
ድርጊያ/ድርጊት፡ ሥራ/ብጀታ/አድራጎት
ድርግ (ድሩግ) የተደረገ ("ብጁ")
ድርግም፡ የተደረገመ ("የጠፋ")
ድርጎ (ዎች) በርቦ በመቍነን ሚለካ ንፍሮ ("ኵርማን ጕርሻ ምግብ የን ፊት የውሃ የርድ የማንኛውም ጥቅም የመጠን ስጦታ በዕለትና በወር ባመት የሚደረግ")
ድርጎ፡ ርቦ ታናሽ መስፈሪያ
ድርጎኛ (ኞች) ድርጎ ተቀባይ/ባለ ድርጎ
ድርጥ፡ የተደረጠ/የታሸ ("የተልባ ሊጥ የማር ብጥብጥ የተልባ ድርጥእንዲሉ)
ድርጭቱ፡ ድርጭት ("የርሱ ድር ጭት")
ድርጭት (ቶች) ከርግብ የሚያንስ ወፍ ("ሥጋው ንብብር ድርብርብ የኾነ ተባ ቱም እንስቱም ድርጭት ይባላል") (ዘፀ. ፲፮፡ ፲፫፡ መዝ. ፻፭፡ )
ድርጭቶች
ድርጭቷ፡ ያች ድርጭት ("የርሷ ርጭት")
ድርፉጭ አለ፡ ሰውነቱን ሰብስቦ ተቀመጠ ("ቍጭ አለ")
ድርፉጭ፡ የተሰበሰበ/የተቀመጠ ("ስብ ስብ ቅምጥ")
ድሮች፡ የተደሩ ዝሓዎች
ድሮች፡ የደሩ/የተለመጡ እግሮች ራዎች
ድቀት መውደቅ ወደቀ
ድቀና፡ ድከራ ("የማቅረብ ሥራ")
ድቍስ አደረገ፡ ደቈሰ ("ድቅቅ ላም ልዝብ አደረገ")
ድቁስ፡ የተኛ/እንቅልፋም (ግእዝ)
ድቍስ፡ የተደቈሰ ("የላመ የለዘበ ዝብ ደቃቅ ብትን ድልኸ ትኵስ በድቍስእንዲሉ)
ድቍና፡ ዲያቆንነት/ዲያቆን መኾን ("ክህነት ድቍና ቅስናእንዲሉ)
ድቄታም፡ ባለድቄት/እንቅልፋም ("ያዞ")
ድቄት፡ ከባድ እንቅልፍ ("ሰውነት አድ ቃቂ") (ተመልከት፡ ደስቅን እይ)
ድቅ (ድቁቅ) የደቀቀ
ድቅስቃሽ፡ ዝኒ ከማሁ
ድቅስቅስ አለ፡ ተድቀሰቀሰ
ድቅስቅስ፡ የተድቀሰቀሰ/የዛለ ("ደካማ ደቃቃ ዐቅም የለሽ")
ድቅቅ አለ፡ ፈጽሞ ደቀቀ ("ዐመድ ኾነ ደከመ")
ድቅቅ አደረገ፡ ፍጭት አደረገ
ድቅን አለ፡ ተደቀነ
ድቅን፡ የተደቀነ ("የቋት እኸል ድክር")
ድቅደቃ፡ ወቀጣ/ጥቅጠቃ
ድቅድቅ (ደቃ) የሕፃን ኣካኼድ/ሩጫ ዠመረ ("ሕፃኑ")
ድቅድቅ አለ፡ የቅል ውሃና መጠጫ ሲጠጣ አስጮኸ ("ከረ")
ድቅድቅ፡ የተደቀደቀ/የተጠቀጠቀ (" ቅጥቅ ውድቅት ድቅድቅ ጨለማእንዲሉ) (ኢሳ. ፰፡ ፳፪፡ ዮኤ. ፪፡ )
ድቋ (ትግ) ያልጠራ መጠጥ ("ጕሽ ሲፈላ ጋን የሚደቃ")
ድበላ፡ ያበባ እኸል (ባቄላ ዐተር ሽንብራ ጓያ ምስር አደንጓሬ አገዳ የገብስ የስንዴ መቀየ አደፍ ቀሊል)
ድበላ፡ ጭመራ ቅየጣ
ድበቃ፡ ስውራ ሽሸጋ
ድበታ፡ ጭቈና/ጫና
ድቡ፡ የሰው ስም ("አዛዥ ድቡ" እንዲሉ)
ድቡ፡ ድብ (የርሱ ድብ)
ድቡሽት፡ በዠማ በዥረት ዳር ሚገኝ ደቃቅ አሸዋ ድንቡልቅኝ (ተመልከት፡ ፪ኛውን በሰ እይ)
ድባ፡ ትልቅና ክብ ዶቃ (ቀይ ብጫ ቅጠልያና አረንጓዴ ዐመድማ ሌላም ሕብር ያለው) (ተመልከት፡ ዘለለ ነደደ ብለኸ ዘሎ ባይኔን ድን ተመልከት) "ዳሴና ዳቦ ድባ የደበደበ ዘሮች ናቸው ደበደበ አወፈረ ተብሎ ይፈታ ልና። ዳባም የድብዳብ ከፊል ነው።"
ድባርዋ፡ በሐማሴን ክፍል ያለ አገር
ድባርዋ፡ ጥንብራ
ድባቡ/ድባቤ፡ የወንድና የሴት ስም ("የርሱ ድባብ የኔ ድባብ ማለት ነው" )
ድባብ (ቦች) የታቦት የንጉሥ ጥላ (ከቀርክሓና ከግምጃ ከባለቀለም ልብስ የተሠራ ጕልላትና አጫዋች ዘርፍ ያለው የጃን ጥላ ዐይነት) (ተመልከት፡ ወለዶ ብለኸ ወላድን፡ ጫረ ብለኸ አጫረን እይ)
ድባኖ (ዐረ. ድባን፡ ዝንብ) የደ በነ ትንሽ (ዝንብ አከል)
ድቤ፡ ታናሽ ነጋሪት፡ ደበ ደበ
ድብ በቁሙ ደባ
ድብ (ቦች) (ድብ ድባት) ኣድ ብቶ ሸምቆ የሚነጥቅ ብርቱ ኀይለኛ አውሬ (የዥብ ወገን ነጭና ጥቍር) (ኢሳ. ፶፱፡ ፲፱) (ተመልከት፡ ዶባን እይ ከዚህ ጋራ አንድ ነው) "ተባቱንና እንስቱን ለመለየት"
ድብ አንበሳ፡ ታላቅ የንጉሥ ነጋ ሬት (የአንበሳ ድቤ)
ድብ፡ በሰሜን በኩል ጅብ ብለው የሚታዩ ኮከቦች (እነሰባቶ መርከበኞች የሚመ ለከቷቸው መርከብ የሚመሩባቸው) (ኢዮ. ፱፡ )
ድብል፡ የተደበለ ሽርብ
ድብስ፡ የተደበሰ (ጕብጕብ ሊጥ)
ድብርቅ (.በረቅ) አበባው በሩቅ ሲያዩት በረቅ ወይም የድመት ዐይን የሚመ ስል በወይናደጋ የሚበቅል ቅጠል "ፍሬው ከብቅልና ከጥቍር ስንዴ ጋራ አንተክትኮ ሲጠጡት ለጕንፋን መድኀኒት ይኾናል"
ድብርቅ ዐይን፡ ዐይጥ ድመትን የሰደበው ስድብ (ተረት)
ድብቅ (ቆች) የተደበቀ ያደፈጠ ጦር (ዕቡ ስውር ሽሽግ) (መሳ. ፳፡ ፴፫, ፴፮)
ድብቅ ብዬ፡ የቀበሌ ስም (በቡልጋ ውስጥ ያለ ስፍራ)
ድብቅ አለ፡ ተደበቀ
ድብቅ ድብቅ አለ፡ መላልሶ
ድብቅታ፡ ድብቅ ማለት (ስውር ቦታ)
ድብቆሽ፡ ዝኒ ከማሁ
ድብብ፡ የተደበበ/የተዘረጋ (ዝርግ )
ድብት፡ ትንሽ ድግስ (የቈራቢ እራት) (ላስታና ዋድላ)
ድብት፡ የተደበተ (የማይሰማ)
ድብን አለ፡ ሙትት ክርር አለ
ድብን አደረገ፡ ግድል አደረገ (" ኀይል ገረፈ ቈነጠጠ")
ድብን፡ የደበነ
ድብኝት (ቶች) ከጭቃ ተበጅቶ የደረቀ የእኸል ማስቀመጫ መክተቻ በር ሚል መሳይ (ተመልከት፡ ጐሰጐሰን እይ)
ድብክብክ፡ የተድበከበከ (አተላማ)
ድቧ፡ ያች ድብ (የርሷ ድብ)
ድንሰራ፡ ችሰራ
ድንስር አለ፡ ተደነሰረ/ተረፈቀ
ድንቀኛ፡ ድንቅ አድራጊ ("ባለድንቅ")
ድንቁ/ድንቄ፡ ዝኒ ከማሁ ("ዝርዝሩ ፈጣሪንና ወላጅን ያሳያል")
ድንቍል፡ የተደነቈለ ("ውግ ንቍር")
ድንቍርና፡ ደንቈሮ መኾን ("አላዋቂነት መደንቈር መዘጋት መወለን መደ ፈን አለመስማት ዕውቀት ማጣት")
ድንቂቲ፡ የፈንጣጣ ስም ("ልጅን ኹሉ የምትሸልም ስለ ኾነች ድንቂቱ ተባለች")
ድንቂያ፡ ድንቅነት ("ድማም")
ድንቅ ነኸ/ነሽ፡ የወንድና የሴት ስም
ድንቅ አደረገ፡ ታምር ሠራ ("ሙት አነሣ ዕውር አበራ")
ድንቅ፡ የደነቀ ("ጉድ ግሩም ዐጀብ ዕጹብ ታሪክ ታምር") (ዘዳ. ፳፮፡ ፰፡ መዝ. ፻፮፡ ፳፪፡ ኢሳ. ፱፡ ፮፡ ሉቃ. ፭፡ ፳፮) (ተመልከት፡ ድንክን እይ)
ድንቅር፡ የተደነቀረ ("ሽጕር ቅርቅር")
ድንቅነት፡ ድንቅ መኾን
ድንቅፍቅፍ፡ ውልክፍክፍ/ስንክልክል
ድንቆች፡ ጉዶች/ታምሮች
ድንበረተኛ (ኞች) ወሰነተኛ ("በድ ንበር አጠገብ ያለ አዋሳኝ")
ድንበረኛ (ኞች) ወሰነኛ (ዘዳ. ፩፡ )
ድንበራ፡ ፍራት/ሽሽት/ዝላይ
ድንበሮች፡ ወሰኖች (ኢሳ. ፲፡ ፲፫)
ድንቡልቅኝ ዐቧራ ደባለቀ
ድንቡሎ ድምቡጨ ደበለ
ድንቡሽ፡ የደነበሸ/የሻገተ
ድንቡጨ አካለ ጥብቅ ድም ቡጨ
ድንቡጭ አለ፡ ዝም አለ፡ ምቡጭ አለ
ድንብላል ቅመም ደበለ
ድንብርብር፡ ጥንብርብር
ድንብዝብዝ አለ፡ ጭልም አለ
ድንት (ድልት) ንኡስ አገባብ (" ላለም ዝንት ድንት ያኑርኸ ድንት እስከ ንትእንዲሉ)
ድንት፡ የፊደል ስም ("ዘላለምነትን ሳይለቅ መዝጊያ ማለት ነው ድልት የግእዝ ድንት ያማርኛ")
ድንች፡ የተክል ስም ("የእንቅርብጭ ዐይነት ተክል በሥሩ የሚያፈራ ፍሬው ተቀቅሎና ተጠብሶ የሚበላ ሲበዛ ድንቾች ይላል")
ድንን (ድኑን) የተያያዘ ጠጕር (" ርና ዕንጨት")
ድንከን፡ የጤፍ ድርድር ("")
ድንኩል (ትግ. ጓል) አሰናካይ መሬት (ኢዮ. ፴፰፡ ፴፰)
ድንኩል ድንኩል አለ፡ ሕፃንኛ ኼደ ("ድቅድቅ ስንክል ስንክል አለ እመ ቤታችን ድንኩል ድንኩል እያለች ወደ ቅዱስ ፋኑኤል ቀረበች") (ትርጓሜ ቅዳሴ ማር ያም)
ድንክ (ኮች) ዐጪር አልጋ ("የዙ ፋን ርካብ መቀመጫና መወጣጫ")
ድንክዬ (ድንቃዊ) ድንካዊ " የድ ንክ ዐይነትና ወገን ("ቁመተ ዶሮ ዐጪርነቱ የሚያስደንቅ ዣርት ቅልጥም ሰው")
ድንኳኑ፡ ድንኳን ("የርሱ ድንኳን")
ድንኳኒቱ፡ ድንኳኗ ("ያች ድንኳን") (ዘፀ. ፴፮፡ ፲፰፡ ፪ዜና. ፭፡ )
ድንኳን
ድንኳን (ዐረ. ዱካን) ከዝተት ' ከሸማ ' ካቡጀዲ ' ከሐር ' ከሸራ የተበጀ (የተ ሰፋ) የነጋዴና የዘማች የመንገደኛ ቤት ("ተራዳ ዋልታ አውታር ካስማ ያለው የሚነ ቀልና የሚተከል ጐዴ ቤተ ንጉሥ ሞላልኛ መላጃን ደስታ መደረቢያ ያለውና የሌለው ድንኳን ቤት ድንኳን ሰፊእንዲሉ)
ድንኳኗ፡ የርሷ ድንኳን
ድንዘዛ/ድንዛዜ/ድንዛዥ፡ የደም መርጋት ("ፈዛዛነት አለመስማት")
ድንዛዣም፡ ባለድንዛዥ ("ድንዛዜ የማ ያጣው")
ድንዝ አለ፡ ደነዘ ("ጥርስ አለ")
ድንዝ፡ ዝኒ ከማሁ
ድንዝዝ (ድንዙዝ) የደነዘዘ
ድንዝዝ አለ፡ ደነዘዘ
ድንዳኔ፡ ውፈራ/ውፋሬ/ውፍረት (ዘኍ. ፴፩፡ ፳፯፡ ኢሳ. ፲፯፡ ፬፡ ፶፭፡ ፪፡ ኤር. ፶፪፡ ፳፩፡ ሕዝ. ፲፮፡ ፴፱)
ድንድን (ኖች) ውፍረት ያለው ዐጪር መቀነት ("የሴቶች ቀሚስ መታጠቂያ")
ድንጁ (ድንጉግ) ድንግግ ውስን
ድንጁድ፡ ያገር ስም ("በተጕለት ረዳ ከደብረ ብርሃን በታች የሚገኝ ቀበሌ ዙሪያው ገደል ድንጁድ አቦእንዲሉ)
ድንጃን (ደነጀ) በላይኛው ወግዳ ያለ አገር
ድንገላ (ድንጋሌ) የሰውነት ጥበቃ
ድንገተኛ (ኞች/ግብታዊ) የድ ንገት ባለድንገት ("ያልታሰበ ነገር አደጋ ሞት")
ድንገት (ድንቀት ግብት) ያል ታሰበ ጊዜ "ንኡስ አገባብ ሲኾን ድንገት ኼደ ድንገት ሞተ ይላል" (መዝ. ፮፡ ፲፡ ምሳ. ፮፡ ፲፭፡ ሉቃ. ፪፡ ፲፫)
ድንገቶ/ድንጋታዊ፡ ዘክዛካ የጧፍ ሸማ ባለ፪ በቅል
ድንገጋ (ድንጋጌ) ውሳኔ/ውሰና/ጥንቀቃ
ድንጉላ፡ ያልተኰላሸ ቍላው ያልወጣ ፈረስ ' ግመል
ድንጉል (ሎች) የማይናደፍ ንብ ውሃ ቀጂ
ድንጉል፡ ድምፀ ወፍራም የበገና ማት ("እንደ ንብ ድንጉል የሚጮኸ")
ድንጕር፡ ዐባጣ ጐባጣ ጕራንጕር ደን ጐላጕል (ዓሞ. ፯፡ ፲፪)
ድንጕር፡ የተደነጐረ ("ድድቅ ፍንቅል ግልብጥ")
ድንጕርጕር፡ ፍንቅልቅል/ግልብጥብጥ ዐይነት ("ወጣ ገባ መንገድ መጥፎ ስፍራ ማዕበል ያበላሸው")
ድንጉጥ (ጦች/ድንጉፅ) የደነገጠ ("ፈሪ ቀጥቃጣ")
ድንጋይ (ዮች) ደንጊያ የካህናት ("ድንጋይ የሕዝብ ቋንቋ ነው")
ድንጋይ ዳቦ፡ የድንጋይ ዳቦ "ቅዱስ ያሬድ ጌታ የተወለደ ለት ተራሮች የሕይ ወት ኅብስት ኾኑ የባሕር ውሃ ወተትና ማር ኾነች ዛፎች የበረከት ዘለላ አፈሩ ይላልና ድንጋይ ዳቦ ማለት ከዚህ የመጣ ነው"
ድንጋግ፡ ዐቃባ/ደገፍ/ቃሲም (ግእዝ)
ድንጋጤ (ድንጋፄ) ፍራት/ዐዘን
ድንጋጤ የልቡና ነው፡ "እንደ ዕንጨት ያደር ቃል እንደ ደንጊያ ያፈዛል"
ድንግላይ (ዮች/ዎች) የድንግል ወገን ("ባለድንግል")
ድንግል መሬት፡ ያልተማሰ/ያልተቈ ፈረ/ሰው ያልተቀበረበት ስፍራ (ዮሐ. ፲፱፡ ፵፩)
ድንግል ማርያም፡ ከመውለድ አስ ቀድሞ በመውለድ ጊዜ ከመውለድ በኋላ ድን ግል የኮነች ማሪያም
ድንግል አጠፋ፡ ዐወቀ/ገሰሰ/ዳሰሰ/ጠረቈሸ "ያለስምና ከስም በፊት ሲነገር በቂና ቅጽል ይኾናል"
ድንግል፡ ሴት ያላወቀ ወንድ ("ወንድ ያላወቃት ልጃገረድ") (ዘሌ. ፳፩፡ ፲፫)
ድንግል፡ ክብርና ሕግ ማኅተም (፩ቆሮ. ፴፮, ፴፰)
ድንግልነት፡ ዝኒ ከማሁ ("ልጃገረድነት") (ዘዳ. ፳፪፡ ፲፯)
ድንግልና፡ ድንግል መኾን/መጠበቅ ("ወይም ክብርና")
ድንግሎች (ደናግል) ወንዶች ጆች ("ልጃገረዶች")
ድንግሎች፡ ክብርናዎች
ድንግር፡ የተደናገረ/የተሳተ
ድንግርግር፡ የተደነጋገረ/የተሳሳተ (" ድንግርግር አለው ተሳሳተው መላ")
ድንግዝ አለ፡ ጭልም አለ ጊዜው
ድንግዝ፡ የደነገዘ
ድንግዝግዝ አለ/ድግዝግዝ እለ፡ ፈጽሞ ጨለመ ("ዐይን ቢወጉ የማይታይ ኾነ")
ድንግዝግዝ፡ ድግዝግዝ/ጭልምልም
ድንግዝግዝታ/ድግዝግዝታ፡ ጭልምል ምታ
ድንግግ (ድንጉግ) የተደነገገ (" ስን ጥንቅቅ")
ድንፋታ (ወክሕ) ውካታ/ፉከራ/ዝላይ "የሹሮ ድንፋታ እንጀራ እስኪመጣ" እንዲሉ
ድኝ፡ ከምድር የሚገኝ ብጫዊ ዐፈር መድኀኒት የሚኾን ("የሚቃጠል")
ድኵላ (ሎች) የዱር ፍየል ("በወ ይናደጋና በበረሓ የሚገኝ ሥጋው የሚበላ ተባቱም እንስቱም የዋላ የብሖር ዐይነት")
ድኵሌ፡ የሃሌታ ዜማ ቤት ("ምልክቱ ነው")
ድኵል፡ ዐጪርና ጐነ ሰፊ ከብት
ድኩዬ፡ ዐጪር ዘንጋዳ ("ወይም ሽላ ጥቃቅን ፍሬ ያለው")
ድካ፡ እብነ ወሰን ("የወሰን ደንጊያ")
ድካም፡ ልፋት/ጥረት/ስንፍና/ሀኬት
ድክመት፡ ዝኒ ከማሁ ("ምስነት")
ድክም (ደኪም) መድከም
ድክም አለ፡ ደከመ
ድክር (ሮች) የተደከረ ("ድቅን ' ግትር ሰልፈኛ የማይላላ የማይረግብ የማይደ ክም ጐበዝ ብርቱ")
ድክር፡ ያቶ በዛብኸ የፈረስ ስም "በዙ አባ ድክር" እንዲሉ
ድክን፡ የተደከነ ("ስድር ድርድር ንብ ብር ድርብርብ")
ድኰት፡ የእግር ጌጥ ("የገምባሌ ዐይ ነት ቢተዋ መሳይ መካፈቻና መጋጠሚያ ያለው ከንሓስ ከብር የሚሠራ") (ተመልከት፡ ግርጃን እይ)
ድኳ ግርምቡድ ደካ
ድኳ (ትግ) የራስ ብርኵማ ("ግርም ዑድ በርጩማ የሰው መቀመጫ የሽባ መንፋ ቀቂያ የዋንጫ መቆሚያ ፍልፍል ዕንጨት የሸክላ ዐንገት በልክ በመጠን የተበጀ ድኳ ሉሕ ምንጣፍ የእግር ማረፊያ") (ማር. ፲፮፡ ፴፮፡ ሉቃ. ፳፡ ፵፫፡ ግብ. ሐዋ. ፪፡ ፴፭፡ ፯፡ ፵፱)
ድኺት፡ አንዲት ብቻ ቂጥኝ ("ከጕያ በቀር እፊት ላይ የማትወጣ")
ድኺት፡ ዐጪርና ቀን የዋልታ ዙሪያ ማገር
ድኻ በቁሙ ደኸየ
ድኻ (ኾች) ነዳይ/ምስኪን/ዕጦ ተኛ/ችግረኛ/ለማኝ/ቧጋች/ተመጽዋች ("የሰው እጅ ጠብቆ ጥሮ ግሮ ዐዳሪ አይቶ ዐጣ የሰው ታናሽ ባይተዋር") (መከ. ፱፡ ፲፭፡ ምሳ. ፴፡ ፲፬) "ድኻ ጥኑ ድኻ ይበላው እንጂ ይከፍለው አያጣም ድኻ ቢናገር አያደምቅ! ቢጨብጥ እያጠብቅ ውሃን በሶን ተመልከት"
ድኻ ሰብሳቢ፡ ድኻን እየሰበሰበ ቤቱ የሚያኖር የሚያበላ የሚያለብስ
ድኻ ቀባሪ፡ ድኻ ጐጂ ጨቋኝ
ድኻ ነቀል፡ አቀንጭራ የሚባል
ድኻ ዐረም
ድኻ አክባሪ፡ ድኻ ጠቃሚ ደግ ሰው
ድኻ አደግ (ድክቱም) የሙት ልጅ ("እናት አባት አልባ ጕልቻ የላቀው ዐመድ ያጠለቀው በድኽነት ያደገ") (ሆሴ. ፲፬፡ )
ድኻ አደግ ኾነ (ደክተመ) ድኻ ኹኖ አደገ ("አባት እናት ዐጣ")
ድኻ አደጎች (ድክቱማን) የሙት ልጆች (ኢዮ. ፳፪፡ ፱፡ ፳፬፡ ፫፡ ምሳ. ፳፫፡ )
ድኽነት፡ ንዴት ዕጦት ችግር ("ድኻ መኾን") (ዘዳ. ፲፭፡ ፯፡ ምሳ. ፮፡ ፲፩፡ ማር. ፲፪፡ ፵፬)
ድውር (ሮች) የተደወረ ("የማግ የጥለት የሐር የጥሙር ጥቅል ጥንጥን")
ድዝደዛ፡ ጥዘላ ወቀጣ ("የከበሮ ምት")
ድዝድዝ፡ የተደዘደዘ ("ሥራው የማያ ምር ጸናጽል መስቀል ጻሕል")
ድደቃ፡ ፍንቀሳ/ድንጐራ/ግልበጣ
ድደቃ፡ ፍንቀሳ/ድንጐራ/ግልበጣ
ድዳ፡ መናገር ሲያስብ ቃል መስጠት የማይችል እእ የሚል አፈ እስር አንደበተ ዝግ ("እንደ እንስሳ የማይናገር ሰው") (ኢሳ. ፴፭፡ ) (ተመልከት፡ አፍን)
ድዳ፡ መናገር ሲያስብ ቃል መስጠት የማይችል እእ የሚል አፈ እስር አንደበተ ዝግ ("እንደ እንስሳ የማይናገር ሰው") (ኢሳ. ፴፭፡ ) (ተመልከት፡ አፍን)
ድዳም፡ ድደ ወፍራም ድደ ፈጣጣ ሰው ችኮ
ድዳም፡ ድደ ወፍራም ድደ ፈጣጣ ሰው ችኮ
ድድ (ዶች) (ወደደ) የጥርስ ሥር መሠረት መገኛ መብቀያ
ድድ (ዶች) (ወደደ) የጥርስ ሥር መሠረት መገኛ መብቀያ
ድድብ፡ የደረቀ (ድድር) ( መልከት፡ ደበደበን የደደበ ዘር ነው)
ድድብ፡ የደረቀ (ድድር) ( መልከት፡ ደበደበን የደደበ ዘር ነው)
ድድኾ (ደደካዊ) የንጨት ' ስም ("አገዳው ቀልጣማ ቅጠሉ ለስላሳ የኾነ በወ ይናደጋ ቈላ የሚበቅል ታናሽ ዛፍ የማሪ ያም ጥላ")
ድድኾ (ደደካዊ) የንጨት ' ስም ("አገዳው ቀልጣማ ቅጠሉ ለስላሳ የኾነ በወ ይናደጋ ቈላ የሚበቅል ታናሽ ዛፍ የማሪ ያም ጥላ")
ድድድ አለ፡ ሮጠ/ተንደረደረ (ተመልከት፡ ዲደንንን እይ)
ድድድ አለ፡ ሮጠ/ተንደረደረ (ተመልከት፡ ዲደንንን እይ)
ድድድ፡ ሩጫ መንደርደር
ድድድ፡ ሩጫ መንደርደር
ድዶች፡ የማይናገሩ ቃል የማይሰጡ ሰዎች (ኢሳ. ፴፪፡ )
ድዶች፡ የማይናገሩ ቃል የማይሰጡ ሰዎች (ኢሳ. ፴፪፡ )
ድጅኖ (ዎች) በትረ ቃቃን ("የደንጊያ መስበሪያ መንደያ መፈንቀያ ንጥር ብረት ዘንግ መሳይ ቀጪንና ወፍራም") (፩ነገ. ፮፡ )
ድጅኖ (ዎች) በትረ ቃቃን ("የደንጊያ መስበሪያ መንደያ መፈንቀያ ንጥር ብረት ዘንግ መሳይ ቀጪንና ወፍራም") (፩ነገ. ፮፡ )
ድገመና፡ ጨምርልና/አድርሰና (" ቃለ አጋኖ ነው ዓመት ዐውዳመት ድገመናእንዲሉ ልጆች)
ድገመኝ፡ መልሰኸ ምታኝ ("ጨምር ልኝ")
ድገመኝ፡ አድርሰኝ/አብላኝ ("ዓመት ዓመት ድገመኝእንዲል ገበሬ)
ድገፋ፡ የመደገፍ ሥራ (ዕገዛ ርዳታ)
ድጕልጕል፡ የተድጐለጐለ (ወፍራም ዐጓጕል ቅጥ የለሽ እጅ እግር አልባ ቅንቡ ርስ ዐይነት)
ድጕም፡ የተደጐመ/የተረዳ (ዕግዝ)
ድጕሰት/ድጕሳት፡ የድጕስ ሥራ (ጌጥ ሽልማት ሐረግ አበባ)
ድጕስ፡ ሰገባ ሽፋፍ አፎት "ስለት ድጕሱን ደባ ራሱን" እንዲሉ
ድጕስ፡ የተደጐሰ/የተጌጠ
ድጕስ፡ ጌጠኛ (የመጽሐፍ ገበታ ልብስ ወይም የማኅደሩ ውግ ስንብር በተን ቤኑ ላይ የሚታይ)
ድጋሚ፡ ፪ኛ ሥራ ምላሽ ዕርሻ
ድጋም (ሞች) የለኊሳስ ንባብ ሎት
ድግ መቀነት ደገደገ
ድግ (ጎች) ክንድ መቀነት ወገብ ላይ የሚታሰር የሚጠመጠም ደበላ ቤት ሥር (፩ሳሙ. ፲፰፡ ፬፡ ኢሳ. ፫፡ ፳፬)
ድግል፡ የተደገለለ (ትልቅ ጥምጥም ፌዶ የደገሌ ዐይነት)
ድግም፡ የተደገመ/የተመለሰ (፪ኛ የተ)
ድግምታም፡ አስማታም ጠንቋይ መተ
ድግምት፡ የተደገመች (ድጋም አስማት መስታድርት)
ድግስ (ሶች) የተደገሰ (ዝግጁ ድርጁ ስንዱ እንጀራ ወጥ ጠላ)
ድግር (ሮች) (ድጉር) ከግራር ተጠርቦ የተበጀ የበሬ ዕቃ ("በስተሥር በቅትርት ከሞፈር ጋራ የተዋደደ በስተጫፍ ከዕርፍ ከማረሻ ጋራ በወገል የተረገጠ እንደ መቅዘፊያ ኹኖ ፈር የሚያሰፋ")
ድግና (ዴጋኒ) በ፯፻ . የነበረ የሐበሻ ንጉሥ ስም ("ተከታይ አሽከር ማለት ነው ድግና ሚካኤልእንዲል ክብረ ነገሥት)
ድግን፡ መጋዝ) ቀስት፡ የሚመስል
ድግን፡ መትረየስ ("እግራም ባለእግር መትረየስ አግሬ ባላ የማያሻ")
ድግን፡ የተደገነ/የታሰረ/የጐረሠ
ድግዝታ፡ ምሽት ጭልምታ "በግእዝ ሕዋይ ይባላል።"
ድግዝግዝ አለ፡ ጭልምልም እለ
ድግዝግዝ፡ የጨለመ/ጭልምልም
ድግዝግዝታ፡ ጭልምልምታ ("ፍጹም ድግዝታ")
ድግድጋት፡ የሸማ ትጥቅ አስራት ("የማደግደግ አኳኋን")
ድግድግ አለ፡ ልክክ አለ
ድግድግ፡ የተደገደገ የሸማ ትጥቅ
ድግድግ፡ የደገደገ/የተላከከ/ያደፈ (ልማም ችክ ሞራ)
ድግጣ (ጦች) ቀጥታነት ያለው ንጨት "ከማነሱና ከመገርጣቱ በቀር ነገረ ሥራው ብርብራ ይመስላል ዕጣ በድግጣ ንዲሉ"
ድግፍ፡ የተደገፈ የተያዘ (ዕቅብ)
ድግፍግፍ፡ የተደጋገፈ/የተያያዘ (ቅር ብርብ "የከሌና የከሌ ዕድሜ ድግፍግፍ ነው" )
ድጓ በቁሙ ደገደገ
ድጓ (ሐማሴን ድጕዓ) ሙሾ ቍዘማ የሐዘን ዜማ (ተመልከት፡ ዐዘለ ብለሽ ፫ኛውን ዕዝል እይ ሐዲሱን መጽሐፈ ሰዋስው ገጽ ፫፻፴፱ አስተውል)
ድጓ (ዎች) የዜማ መጽሐፍ ስም (ቅዱስ ያሬድ የደረሰው ካመት እስካመት በ፫ ዐይነት ዜማ የሚጸለይ መንፈሳዊ ድር ሰት ጽፈቱ ደቃቅ ረቂቅ በመኾኑ ድጓ ተባለ "ድጓ ጾመ ድጓ" እንዲሉ) (ተመልከት፡ ዶገዶገን እይ) "ዳግመኛም ደገደገ የደገገ ደጊም ስለ"
ድጓ ውሃው፡ ድጓ ዐዋቂ
ድጓ፡ እብቅ ደቃቅ ገለባ
ድጣም፡ ድጥ ያለው ("ባለድጥ ስፍራ መንገድ")
ድጥ (ዳኅፅ) ዝናም የመታው ጥብ መሬት ("ተዳፋት አንሻታች አንሸራታች ድጥ ኾነ ዳለጠ ሙልጭልጭ አለ")
ድጦ/ድጦሽ፡ የተዳጠ/የተፈጨ ( ስር ያተር ክክ ንፍሮ ወጥ የሚኾን)
ድፊት፡ የወንፊት ወጥመድ ወፍ ያዣ (ሆሴ. ፱፡ )
ድፋ፡ የጠነከረ ስንደዶ ሳይታጨድ ተተወ
ድፋርሳ/ድፋሳ፡ የበረሓ እንስሳ ("የበሬ ዐይነት ቀንዱ ከሥር እስከ ጫፍ ክርክር ያለው")
ድፋርሳ፡ (Repeated from above, likely a continuation)
ድፋት (ድፍዐት) መድፋት/መደ
ድፋት፡ መጨረሻ ግጥም ("ወይም ንኝ") (ተመልከት፡ ግድግዳን)
ድፋት፡ የከረጢት ቀሚስ የዱሮ መን ዐንገትጌ የሌለው ("በ፪ ወገን ክፍት")
ድፋት፡ የዜማ ምልክት ("ዝቅዝቅ ጽፈት የደረት ተቃራኒ")
ድፋት፡ ያገባብ ስም ("ነጠላ ድፋት ድርብ ድፋትእንዲሉ) (ተመልከት፡ የቅኔ አገባብ)
ድፋዬ፡ የሰው ስም
ድፌት፡ ቍንናት ያለው የራስ ጕር ("በራስ ላይ የተደፋ ቆብ የሚመስል ምጥም ሥራ")
ድፍ (ድፉዕ) የተደፋ/የፈሰሰ
ድፍረሳ፡ መደፍረስ
ድፍረት፡ ጭካኔ/አለማፈር (ግብ. ሐዋ. ፬፡ ፲፫, ፳፱, ፴፩) "ሲያውቁ በድፍረት ሳያውቁ በስሕተት" እንዲሉ
ድፍርስ፡ ዝኒ ከማሁ ("ያተለ ጕሽ ")
ድፍርስነት፡ ድፍርስ መኾን
ድፍቅ፡ የተደፈቀ ("ዝፍቅ የተፈጨ ምስር ወጥ")
ድፍት አለ፡ ተደፋ
ድፍት አደረገ፡ ክንብል አደረገ
ድፍት፡ መደፋት
ድፍነት፡ መድፈን/መደፈን (ግእዝ)
ድፍነት፡ ቀበራ/ደፈና
ድፍን (ኖች) የተደፈነ ("ዝግ ልበ ድፍን አፍንጫ ድፍንእንዲሉ)
ድፍን ቅል፡ ያልተቈረጠ/ያልተከፈተ
ድፍን አለ፡ ዝግት አለ
ድፍን አቋራሽ፡ ወንድም ተካፋይ
ድፍን ዓመት፡ ምሉ ዓመት ("፲፪ ወር")
ድፍን እንጀራ፡ ያልተሸረፈ ' ያልተ ቈረሰ
ድፍን ጥቍር፡ ድመት ("ኹለት ይነት ቍራ የደጋና የቈላ")
ድፍን፡ ኹሉ/መላው/ጠቅላላው (" ድለት የሌለበት ድፍን ጐንደር ድፍን ሺዋእንዲሉ)
ድፍንት፡ አፍንጫ ቢስ = ሴት
ድፍንት፡ የተደፈነች ቤት ("መተናፈሻ መስኮት የሌላት")
ድፍንፍን፡ የተድፈነፈነ ("ጭፍንፍን")
ድፍደፋ፡ መረጋ ልወሳ
ድፍድፍ፡ የተደፈደፈ ("በውሃ የራሰ ዝፍዝፍ የጠላ ቡሖ ሊጥ")
ድፍጥፍጥ፡ ፍርጥርጥ
ዶለ (ደዊል ዶለ) ጨመረ/አገባ/ከተተ/አሰናዳ
ዶለተ (ዶለ) ሰበሰበ/ዐደመ ("ከንቱ ዐሳብ ዐሰበ ክፉ ምክር መከረ አሤረ ነገር ቋጠረ")
ዶለተ፡ ጨመረ/ቀላቀለ
ዶለቾሜ፡ የዶለችም ዐይነት
ዶለቾም፡ ዐጕል ሰው ደነዝ
ዶለዝ (ዞች) ደነዝ መጥረቢያ (" ደብ ወፍራም ሰው ልበ ደንቈሮ")
ዶለዶመ፡ ፈጽሞ ደነዘ/ጐለደፈ/ተደመደመ
ዶለዶሜ፡ የዶለዶም ዐይነት
ዶለዶም፡ የዶለዶመ/የደነዘ
ዶላች (ቾች) የዶለተ/የሚዶልት ("መካሪ ኣሢያሪ ቋጣሪ ሤረኛ ነገረኛ")
ዶል፡ ያፈር ስም ("ቀይ ዐፈር ለሥዕ ልና ለጽፈት የሚኾን")
ዶልዷላ፡ የሚንዶለዶል ("ብዛት ብዘ ነት ያለው የቦይ የመስኖ ውሃ")
ዶልዷሌ፡ የዶልዷላ = ዐይነት ("ለስጦ ታው ልክና መጠን ወሰን የሌለው ቸሩ ኣምላክ")
ዶልዷማ፡ የዶለዶመ ("ደነዝ ጐልዳፋ የዱልዱም ወገን ደመ")
ዶልዷሜ፡ የዶልዷማ ዐይነት
ዶመኛ (ኞች) ባለዶማ ቈፋሪ ("ድኻ ጥማድ የለሽ በዶማ ቈፍሮ የሚበላ")
ዶማ (ዎች) (ደምሐ መድምሕ) መማሻ/መቈፈሪያ ("ዛቢያ ያለው ባለጕረሮ")
ዶሰ (አፅወሰ) ለመሸ/ሽባ አደረገ/አጥመለመለ
ዶሰ (ፀዊስ ፆሰ ትግ ደወሰ ዕብ. ዳሽ እኽል አኼደ) ኣማሰለ/ ባለቀ
ዶሰ፡ ብረትን/ደንጊያን ቀጠቀጠ/ ሣሣ/አጠፈጠፈ/አደቀቀ
ዶሰ፡ ዐየለ/በረታ
ዶሰ፡ ጣሰ/ጠመሰሰ
ዶሰኛ (ኞች) ኀይለኛ/ጣሽ/ጠም ሳሽ ("ባደባባይ ተናጋሪ አይፈር ለፊቱ")
ዶሴ፡ የኔ ዶስ
ዶስ፡ ኀይል/ብርታት/ዕጥፍ/ድርብ
ዶሪ፡ የሰው ስም ("የትግሬ ተወላጅ የቅኔ መምር ወርቃዊ ወርቅማ ማለት ነው ዶሪ ዶሪ ቅኔ ፈጣሪ እንዳለ ዕቡይ ካሳ")
ዶራሪ፡ የሽቱ ዕንጨት ስም
ዶራር፡ ማሽላ ("የማሽላ ስም")
ዶር፡ ጥሩ ወርቅ
ዶርዜ (ዎች) የነገድና ያገር ስም ("በኦሮ ቤት በወላሞ አጠገብ ያለ አገር ወይም ሸማኔ ሕዝብ")
ዶሮ (ዎች/ዶርሆ) ለማዳ የቤት አሞራ ("ነጭ ቀይ ጥቍር ወሰራ ገብስማ ዛጐልማ ተባቱም እንስቱም") (ተመልከት፡ አውራን ዐቀፈን እይ)
ዶሮ (የህንድ ዶሮ)
ዶሮ ማታ፡ ጧት ለኮሶ ጠጪ ሚነገር ፈሊጥ ዘዬ
ዶሮ ማነቂያ፡ በአዲስ አበባ ዐራዳ ውስጥ ያለ ስፍራ
ዶሮ በሌ፡ የበሬ በሽታ ("የሚያፈዝ የሚያደነግዝ ዶሮውን በራሱ ላይ አዙሮ ሥጋውን ቀቅሎ ከንጀራ ጋራ ቢያበሉት በሬው ስለሚድን በሽታው ዶሮ በሌ ተባለ")
ዶሮ በጋን፡ ትንሹን ጥቂቱን በት ልቅ በሰፊ ውስጥ መጨመር
ዶሮ ዋጭ፡ ዶሮ ነጣቂ አሞራ ("ጭል ፊትን ገዲን ሲላን የመሰለ")
ዶሮ ዳቦ (የዶሮ ዳቦ) ከዶሮ ወጥ ጋራ የተጋገረ ዳቦ
ዶሮ ጩኸት፡ እኩለ ሌሊት
ዶሮ ጮኸ፡ ኵኵሉ አለ
ዶሮዋ፡ ዶሮዪቱ ("ያች ዶሮ የርሷ ዶሮ")
ዶሮው፡ ዶሮ ("የርሱ ዶሮ")
ዶቀረ፡ ሰምቶ ዝም አለ ("ወይ ሳይል ቀረ")
ዶቃ (ደቀቀ) የልጆች ዐንገት ' ጌጥ ("ውስጠ ቀዳዳ ከሸክላ ተሠርቶ ሰማያዊ ቀለም እየተቀባ ̇ ̇ ሺንና ከህንድ አገር የሚ መጣ")
ዶቅማ፡ የዛፍ ስም ("ፍሬው የሚበላ ዕንጨት የእስላም ሴቶች ጪሱን ይሞቁታል ፪ኛ ስሙ አዝጋሮ ነው")
ዶበዶብ፡ ክርፋታም የበልግ አንበጣ (መብረርና መመሠጥ የማይችል)
ዶቢ (ኦሮ) ሳማ (የሳማ ስም)
ዶባ (ዕብ. ዶብ፡ ድብ) የበሬ ስም (ያዳል የበረሓ ቀንደ ረዥም በሬ ጋዘን ዐይነት)
ዶባች፡ የደሰተ/የሚደብት (የሚጫን ከባድ እንቅልፍ ድቄት ደስቅ)
ዶብማ (ድብማ) ድብ ዥብ የሚመስል በሬ ያጋዘን ዲቃላ (የጅን ዘር)
ዶቲ፡ ወደ ቅላት የሚያደላ ከላድማ ፍየል
ዶቶን፡ የነፍጥ ስም ("ከናስ ማሰር አነስ የሚል ጠመንዣ")
ዶች) በዛፉ ላይ የፈነዳ
ዶኬ፡ ዝኒ ከማሁ
ዶዮ ቀቃይ፡ ዶዮ የምትቀቅል ("ዶዮ ሠሪ ሴት ሥራ ቤት ዶዮ ቀቃይ ትሙትእንዲል ወታደር)
ዶዮ፡ ተራና መናኛ ወጥ ("ቅቤና ቅመም የሌለበት ዘሩና ምንጩ በግእዝ ወደየ ነው")
ዶገዶገ፡ ወረ ሞወረ/አቀጠነ/አረቀቀ/አሳነሰ (የጽፈት የማዕርግ የመጠን)
ዶጉ፡ የበሬ ስም
ዶግ ዕንጨት ዶገዶገ
ዶግ (ጎች) የንስላል ዐይነት እን ዳገዳ የቀለለ ዕንጨት ("ቀጫጭን ቅጠሉ የፈረስ ጭራ የሚመስል ዶግ ዐመድእንዲሉ)
ዶግ ዐመድ ኾነ፡ ድራሹ ጠፋ
ዶግማ፡ በጥቍርና በቀይ መካከል ያለ የከብት መልክ
ዶግዷጋ፡ ሙጭርጭር ጽፈት (የድጓ ምልክት ዐይነት ረቂቅ)
ዶግዷጌ፡ የዶግዷጋ ወገን ("ሙጭርጭሬ ድጓ ዶግዷጌእንዲሉ) (ተመልከት፡ (ቀኘ) ብለኸ ቅኔን እይ)
ዶጮ (ዎች) ከመስቴ ከቻች ከብ ጕሪት ከቡይት የሚበልጥ ከገንቦ የሚያንስ የሸክላ ዕቃ ("የጠጅ የጠላ የውሃ ማኖሪያ ዶጮ በወላምኛ ሆድ ማለት ነው")
ዶፈዶፈ፡ ገዘፈ/ወፈረ/ከበደ ("እንደ ድፍድፍ")
ዶፈዶፍ/ዶፍዷፋ፡ የዶፈዶፈ ("ወፍ")
ዶፍ (ሐረር ዱፍ ነፋስ) የማያቋርጥ ኀይለኛ ዝናም ("ከነፋስ ጋራ የሚዘ ንም ዘሩ በግእዝ ጸፍጸፈ ነው")
አለ፡ ጮኸ፡ (ዷዷ)
አለ፡ ጠንሷ አለ ጮኸ
አለ፡ ጠንሷ አለ ጮኸ

No comments:

Post a Comment

ሽፋን

  ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ