Tuesday, June 10, 2025

                                 

የጸ ዲቃላ ፪ኛ በግእዝ ኣልፍ ሴት በአበገደ በተራ ቍጥር ፲፱ኛ ሲኾን ስሙ ፀጰ፡ በአኃዝነት 600 ይባላል ጻፎችም ፀሓይ ይሉታል ነገር ግን በፊደልነት መደ በኛው ፲፱ኛ ነው
ፀሓየ ልዳ ዐዲስ አበባ በቅድስት ሥላሴ አጥቢያ የነበሩ ሳታት ቋሚ የብሉይ መምር የሺዋ ተወላጅ በአድዋ ዘመቻ ጊዜ ዐጤ ምኒልክ ጣሊያንን ድል ያደርጉታል፡ ነገር ግን ባርባ ዓመት ተመልሶ ዘርዎን ይገ ዛዋል ብለው በጸሓፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ አማካይነት ትንቢት የተናገሩ
ፀሓየ ልዳ የልዳ ፀሓይ (የቅዱስ ጊዮርጊስ የግብር ስም ")
ፀሓዩ የርሱ ፀሓይ
ፀሓያም የፀሓይ ሙቀት የሚበዛበት ስፍራ
ፀሓይ (ጸሐየ) ጣይ የበራ የሚ በራ (የዓለም መብራት ") "ቀን በአፍሪቃና በእስያ ባውሮጳ ፲፪ ሰዓት፡ ሌሊት ባሜሪካ ፲፪ ሰዓት ያበራል" "ፀሓይ" የግእዝ ስሙ ነው፡ ባማ ርኛ "ጀንበር" ይባላል
ፀሓይ ሰገድ ያጤ ዮስጦስ ስመ መንግሥት (ፀሓይ የሰገደለት ማለት ነው ")
ፀሓይ ጻፎች "ጸሓይ" በማለት ፈንታ "ፀሓይ" ብለው ስለሚጽፉ ፀጰ ፀን ፀሓይ ይሉታል (ተረት) "ልማድ ይከብዳል ከግንድ"
ፀሓይዋ (ፀሓዪቱ) ያች ፀሓይ
ፀሓይዋ የርሷ ፀሓይ ("(ኤር. ፲፭፥ )")
ፀሓዮች (ፀሓያት) ፀሓይን የመሰሉ እንደ ፀሓይ የሚያበሩ ኮከቦች ቅዱሳን "ፀሓይ ወጣ" ብቅ አለ፡ እውነት ተፈረደ
ፀምር ሱፋላ የበግ ጠጕር፡ ወይም በርኖስ ("(ግእዝ)") ዛሬ ግን አለስሙ ሱፍ ይሉታል
ፀረ መናፍቃን ጠላቶች መናፍቆች ማለት ነው፡ አፅራር መናፍቃን ቢል በቀና ነበር "ከሰማየ ሰማያት አልወረደም፡ ከድንግል ማርያም አልተወለደም የሚሉ ፀረ መናፍቃ ንን እምገጸ ምድር ያጥፋልን" እንዲል የባላጎር ቄስ
ፀረ ማርያም (አንድሪማጢስ) ጠረ ማሪያም የማሪያም ጠላት ("(ድኅረ ወለደት ክርስቶስሀ ተደመረት ምስለ ዮሴፍ)") እያለ የመቤታችንን ድንግልናዋንና ቅድስናዋን ንጽሕናዋን የሚክድ መናፍቅ ይሁዲ በዘመናችንም ክርስቲያኖች ነን እያሉ ይህን ክሕደት በስውር የሚሰብኩ እንደ አይሁድም የሚያስ ተምሩ የውጭ አገር ሰዎች ባገራችን ይገኛሉ፡ እነዚህም ወንጌልን ወንጀል ያሠኛሉ።
ፀረ ታንክ ታንክን የሚያበላሽ ድፍ
ፀረ አንቄ ሲላ
ፀረሰ ተቸረቸመ ጠረሰ
ፀረረ (ፀሪር ፀረረ) ጠላ ጠላት አደረገ "ጠረረን" አስተውል "ፀረረ" የግእዝ፡ "ጠረረ" ያማርኛ ነው
ፀረረ ዕሩር ሠራ አለበሰ
ፀረፈ (ፀሪፍ ፀረፈ) ክፉኛ ሰደበ አዋረደ "ጨረፈን" ተመልከት
ፀር ከል (ከላኤ ፀር) የግንብ ዐጥር መከታ ጠላተ ከልክል (ያጐዶ ደንጊያ ")
ፀር ከልበጋር ፀርከል። ፀረ መናፍቃን የመናፍቃን ጠላት (እለእስክንድሮስ ጢሞቴዎስ ቄርሎስ ዲዮስቆሮስ ")
ፀር ጠር ጠላት "ለዲያብሎስ ፀሩ መታገሥ" "ለረኃብ ፀሩ ማረስ"
ፀር ፀረረ
ፀነሰ (ፀንሰ) ጠነሰ ጠነሰሰ "ረገዘ" ብለኸ "አረገዘን ከበደን" እይ
ፀነሰች (ፀንሰት) ደም በሆዷ ቀረ፡ ጠነሰች ጠነሰሰች ያዘች ቋጠረች
ፀዳ ነጣ ጸዳ
ፀጰ (ፀጳ) የፊደል ስም "እሳትማ ፀሓይማ" ማለት ነው
ፀፍር (ፀፈረ) ጠፍር "ፀፍርና መሥ ነቅት እንዳለ ተማሪ"
ፃሰርጔ (ፀሓይ ሽልማቴ - ሰርጕየ) ፀሓይ ሽልማቴ (ከፍተኛ የማዕርግ ስም ") "ያጤ ዘርዐ ያዕቆብ ታሪክ" "አምኃ ኢየሱስ ፃሰርጔ ገብረ ዋሕድ ፃሰርጔ መርቆሬዎስ ፃሰርጔ" "እሉ ፃዕርጔ ሠለስቱ ፃሰርጔ ቤተ ፃዕርጔ መንበረ ማርያም ፃሰርጔ" እንዲል "ገጽ ፹፬ ፹፭ ፻፷፬ ፻፸፪ ፻፸፯ ፻፹፩" እይ
ፃሰርጓ (ፀሓይ ሰርጓ - ሰርጕሃ) ፀሓይ ሽልማቷ ጌጧ (የንግሥቲቱ የይተጌዪቱ ") ይኸውም ነጭ ሐርን ላንቃንና ወርቅን ያሳያል ("(ራእ. ፲፪፥ )") የተረሳ ቋንቋ ነው "ሰረፃ" ብለኸ "ሰርጓይን" እይ ዳግመኛም "ፃሰርጓ ( ሓፌ ሰርጓ)" ቢል፡ የግምጃ ቤቷ ጸሓፊ ("(ሹም)") ተብሎ ይተረጐማል።
ፃት ጣት
ጻድቅ (ቃን) ደግ ቅን ገር ዋህ እውነተኛ ሰው (ምግባሩ የቀና ሃይማ ኖቱ የጸና የግዜር ወገን ለነፍሱ ያደረ ") "ጻድቁ" ጻድቅ
ፃግታ (ፀግዐ) ጥግ መከታ ጋሻ
ፅሩር የጦር ልብስ ሐምበል "ፅሩር" የካህናት፡ "ጥሩር" የሕዝብ አነጋገር ነው "ዕሩር" ቅጽል ሲኾን በጥሬነት መነገሩን አስተውል
ፅራር ዝኒ ከማሁ
ፅርር የተፀረረ
ፅርፈት መስደብ ስድብ
ፅንሰቱ በመጋቢት ፳፱ ቀን የጌታ ችን ያለዘር መፀነሱ (የመፀነሱ በዓል ")
ፅንሰታ በነሐሴ ቀን የመቤታ ችን መፀነሷ በዓል ርግጠኛው ግን ታኅሣሥ ቀን ነው "ወለደ" ብለኽ "ልደታን" እይ
ፅንሰት መፅነስ መፀነስ
ፅንስ የቍርባን ርሾ
ፅንስ ጥንስ ጥንስስ (የተንቀሳቃሽ ፍጥረት የአካል ውጥን ጥንት ዥምር ሽል የማሕፀን ፍሬ ")

No comments:

Post a Comment

ሽፋን

  ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ