ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ኘ: የነ ድቃላ።
ኚኣ: በሺዋ ክፍል ያለ ገጠር።
ኛ (ኒያ): ማጥኛ፡ ማጥኒያ።
ኛ (ዊ): ወገን፡ ቅጽልንና ግብርን፣ ባለቤትነትን አመልካች። በስም መጨረሻ እየገባ:
ኛ: በነገድ ስም መጨረሻ እየገባ ቋንቋ፣ ልሳን ተብሎ ይተረጐማል።
ኛ: የቃል፣ የነገር ዘዬ (ፈሊጥ)።
ኛ: የተራ ቍጥር ምእላድ። ፩ኛ፣ ፪ኛ፣ ፲ኛ፣ ፻ኛ።
ኛምኛም: የሻንቅላ ነገድ፡ አገሩም
"ኛምኛም"
ይባላል።
ኛምኛሞች: የኛምኛም ሰዎች፡ ሻንቅሎች።
ኝ (ኒ):
"እኔ"
ለሚል የአንቀጽ ዝርዝር፡ በሩቅ ወንድ በኀላፊ የሚነገር።
"እሱ እኔን ወደደኝ፣ አመነኝ፣ አመሰገነኝ።
"
ኝ: በ"ነ" የሚጨርስ ግስ፣ የሣልስ (ሳድስ) ቅጽል መድረሻ።
ኝ: ወገን ቅጽል (ግራ፣ ግራኝ፡ አውራ፣ አውረኝ፡ ሙዝ፣ ሙዝኝ)።
No comments:
Post a Comment