Friday, June 6, 2025

                                

(): ፫ኛ ፊደል በአበገደ። ስሙ ገምል (ግመል) ነው። አኃዝ: ይባላል።

ገ፡ የቀ ወራሽ።ወቀጠእናወገጠዘቀጠእና ዘገጠ ማስታወሻ:ወቀጠ፣ ዘቀጠየሺዋ ሲሆን፣ወገጠ፣ ዘገጠየጐንደር ነው።

ገሃ፡ ርሚጦ፣ ብርኩታ፣ በአመድ በመሬት ውስጥ ተዳፍኖ ወይም ሊጡ በድንጋይ ተድበልብሎ የበሰለ።

ገሃ፡ ነጭ ጠመኔ፣ ገሃ።

ገሃ፣ ግሃ (ገህህ፣ ገህግሀ)፡ በረቅ፡ ወይም ነጭና ቀይ ብሓ። ዐፈር ያነሰው መሬት የብሓ ቦረቦር።

ገሃነመ እሳት፡ የእሳት ጕድጓድ፣ የኃጥኣን መኖሪያ፡ ክፉዎች የሥራቸውን ዋጋ፣ ቅጣት የሚያገኙበት፣ የሚሣቀዩበት ስፍራ፡ የወህኒ ምሳሌ።

ገሃነም፡ ሄኖም የሚባል፡ ሰው ያቀናው ጐድጓዳ ቈላ፣ ሸለቆ ከኢየሩሳሌም በስተ ደቡብ ያለ፣ እስራኤል ልጆቻቸውን ለሞሎኸ ይሠዉበት የነበረ ቦታ።

ገሃድ፡ ግልጥ፣ ጋድ።

ገለለ፡ ተዘረጋ፣ ጠፍጣፋ ኾነ (ተገብሮ)

ገለለ፡ ዐወደ፣ ቈረጠ፣ ነቀለ፡ አጠራቀመ (ገቢር)

ገለል"ራቅ" "ፈቅቅ" "ዕልፍ" (፪ዜና:፳፫:፲፭)

ገለል አለ፡ ራቅ አለ፡ ተገለለ።

ገለል አደረገ፡ ራቅ አደረገ።

ገለል፡ የራቀ፣ የተወገደ፡ ውግድ።

ገለል ገለሌ፡ የገዳይ፣ ያርበኛ ሽለላ፣ ዘፈን፣ ቅርርት።

ገለል ገለል አለ፡ ፈቀቅ ፈቀቅ አለ።

ገለልተኛ (ኞች)፡ የተለየ፣ የራቀ፣ በገለልታ የሚቀመጥ፡ ብቸኛ። የቦታ ቅጽልም ይኾናል፡ "ገለልተኛ ስፍራ" እንዲሉ።

ገለልተኛነት፡ ውግድነት፣ ብቸኛነት።

ገለልታ፡ ልዩ ስፍራ፡ ደባቃና ሰዋራ ቦታ።

ገለልታ፡ ፈቀቅታ፣ ርቀት።

ገለሚጡ፡ ዲያቆን መሥዋዕት ሲሠራ የሙጋድ ወላፈን የሚገለምጠው። የቅኔ ቤት ዐማርኛ ነው።

ገለማ፡ ጣመ ቢስ ኾነ፣ ተበላሸ፣ እጅ እጅ አለ (የንፍሮ)

ገለማጠ፡ ኣሞቀ፣ ኣጋለ፣ ኣላበ፣ ኣተኰሰ።

ገለሞተ (ጋለ)፡ ወንደ ላጤ ፈት ኾነ፡ ብቻውን አለሚስት ተቀመጠ፣ ኖረ።

ገለሞተች፡ ባል አልባ ኖረች፡ አመነዘረች (ዘፍ፴፰:፳፬)

ገለሞታ፣ ጋለሞታ (ቶች) (ጋለ፡ ሞቷ)፡ ባል የሌላት፡ አመንዝራ፣ ሸርሙጣ (ባንድ ወንድ የማትጸና፣ የማትኖር) ኻያጅ፣ ቅንዝረኛ፡ "ሞቷ የጋለ፣ የተቃጠለ" (ዘፍ፴፰:፲፭:፳፩:፳፪) (ተረት)"በጋለሞታ ቤት ኹሉ ይጣላበት"

ገለሰሰ፡ ገለፈፈ (ድዱን)፡ በለሰሰ፣ ገለጠ፣ አሰጣ።

ገለስላሳ፡ ግልስልስ (ቀለሰ)፡ የተኛ፣ የተመሳቀለ፡ ቀለስላሳ፣ ቅልስልስ (ሣር፣ ጤፍ፣ ጠጕር)

ገለበ (ገሊብ፣ ገለበ። ዐረ፡ ቀለበ)፡ ገለጠ፣ ገለበጠ (የጭን፣ የቋጥኝ)

ገለበ፡ መግለቦ ሠራ፡ ሸሸገ፣ አጠመደ፡ ሳበ፣ ጐተተ (ዓሣን)

ገለበ፡ አቀለለ፡ ፍሬ ቢስ አደረገ።

ገለበ፡ አቃጠለ፣ አሳረረ (እህልን) "እሳቱ ዐሻሮውን ገለበው" እንዲሉ።

ገለበጠ፡ ማስገልበጫ፡ ማስደፊያ፣ ማስጨመሪያ።

ገለበጠ፡ ቀዳ፣ ጨመረ፣ አጋባ፡ ደፋ፣ አፈሰሰ፡ ጨርሶ ጠጣ (ከለበሰ፣ ከነበለ) (ኤር፴፰፡ ፲፪)

ገለበጠ፡ ተረጐመ (ካንዱ ቋንቋ ወደ ሌላው)፡ ከቀኝ ወደ ግራ መለሰ፡ ከፈተ፣ ገለጠ (የጽሁፍ፣ የብራና፣ የመዝጊያ)

ገለበጠ፡ ከ"ገለጠ" የወጣ ስርዋጽ ግስ ነው።

ገለበጠ፡ የላዩን በውስጥ፣ የውስጡን በላይ አደረገ፡ አፈረሰ፣ ቀየረ፣ ለወጠ፣ አዛወረ (ኢዮ፲፪፡ ፲፭፣ ማቴ፳፩፡ ፲፪)

ገለበጠ፡ ጣለ፣ አወደቀ፣ አጋደመ፣ ገደለ። "ወታደሩ ዝንጀሮውን በጥይት ገለበጠው"

ገለበጠ፡ ፈነቀለ፣ አስገለለ (ዘፍ፳፱፡ ፫)

ገለበጥ (ገልባጣ)፡ ገላላ፣ ሰፌድ፣ ሳሕን፡ ዝርግ ወጭት።

ገለባ (ቦች)፡ የአገዳ፣ የብር ድቃቂ፣ ንፋሽ፣ እንግውላይ፣ ዐሠር፣ ከልብ፣ እብቅ፡ ቀላል ነገር ሁሉ (ኢዮ፵፩፡ ፲፱፡ ፳፣ ማቴ፫፡ ፲፪)

ገለባ ቤት (የገለባ ቤት)፡ በውስጡ የገለባና የድርቆሽ ቍልል ያለበት ዐጥራም ቦታ።

ገለባም፡ ከፍሬው ገለባው የሚበዛ።

ገለባበጠ፡ ቀያየረ፣ ለዋወጠ፡ አነኳኰረ፡ አፈራረሰ (ዘፍ፲፱፡ ፳፭፣ ፩ነገ፡ ፲፰፡ ፲፯፡ ፲፰)

ገለባት፡ በበለው አገር ውስጥ ያለ ነገድ።

ገለባት፡ የከተማ ስም፡ በበጌምድር ክፍል ያለ ከተማ።

ገለባት፡ ጀማ፣ ነጋዴ፣ ቅፍለት፡ የነጋዴ ማኅበር።

ገለብ (ላለ)፡ ከኋላ ቤት፣ በገሙ ክፍል ያለ አገር።

ገለብ፡ ከገደል፣ ከተራራ ተገምሶ፣ ተገልብጦ የወረደ ቋጥኝ ገዎቻ። በትግርኛ ግን "ጋሻ" ማለት ነው፡ "" አይጠብቅም (፪ዜና፡ ፳፫፡ ፱)

ገለቦች፡ ቋጥኞች።

ገለተመ (ለተመ)፡ ቸኰለ፣ ጠደፈ፡ ገጯ፣ ገለበጠ፡ አምታታ።

ገለታ) አንገላታ፣ አጕላላ፣ ጐዳ፣ አጠቃ፣ አስራበ፣ አስራቈተ።

ገለወደ፡ ሥራ ፈታ፡ ተንቀዋለለ። "ገለደወን" እይ።

ገለየ) ግልየት ግእዝኛ ናቸው።

ገለየ) ገለጠ፣ ከፈተ። "እገሌን ተመልከት፡ የዚህ ዘር ነው።"

ገለደ (ትግ)፡ ጠረበ፣ ሸለተ። በግእዝ፡ ግን "ደጐሰ" "አለበሰ" "ሸፈነ" ማለት ነው።

ገለደመ) (ገሊድ፣ ገለደ) አገለደመ፣ በሱሪና በቀሚስ በጥብቆ ፈንታ ታጠቀ፣ አሸረጠ፣ በወገብ ላይ አሰረ (ዳባን፣ ልብስን) "ጠረቀመ ብለሽ አጠረቀመን እይ።"

ገለደወ (ገለወደ)፡ አወደቀ፣ አጋደመ፣ አስተኛ።

ገለዶ፡ የበግ ጠጕር መሸለቻ እንደ መቃድ ያለ ጐባጣ ቢላዋ ካራ።

ገለጀጀ) አንገለጀጀ፣ እንሰለጀጀ፣ አንሰዋለለ፣ አንቀዋለለ።

ገለጀጅ፣ ገልጃጃ (ጆች)፡ ሰለጀጅ፣ ሰልጃጃ፣ ቀውላላ።

ገለገለ (ገልገለ)፡ በደረቅ በበጋ ወይም በበልግ ጊዜ መጀመሪያ ገመሰ፣ ዐረሰ።

ገለገለ፡ ለመነ፣ ጋበዘ፣ አባበለ።

ገለገለ፡ ሎሌ ቀጠረ፣ አሽከር አሳደረ።

ገለገለ፡ ነቀለ፣ ነቅሎ ወሰደ (የችግኝ)

ገለገለ፡ ወለደ፣ ፈለፈለ (የግልገል፣ የጩት)

ገለገፍታ (ገል፡ ገፍታ)፡ ገልፋጣ፣ ሣቂታ፣ ጋለሞታ፣ ሥራ ፈት።

ገለገፍቶች፡ ገልፋጦች፣ ጋለሞቶች።

ገለጠ (ገሊጽ፣ ገለጸ)፡ ገፈፈ፣ ገለበ፣ ከፈተ፡ አራቆተ፡ አሳየ (ነገረ፣ ተረጐመ፣ አስረዳ፣ ከሰተ፣ አበራ፣ አጠራ፣ አወጣ፣ ለቀቀ) (የደረትን፣ የአፍን፣ የመጽሐፍን፣ የአይንን፣ የሰማይን፣ የምስጢርን፣ የመንገድን) (፪ነገ::፲፯፣ ዮሐ፳፩:) (ያባቱን ኀፍረት ገለጠ)፡ ያባቱን ቁባት ደፈረ።

ገለጠመ (ቀለጠመ)፡ ናቀ፣ ነቀፈ፣ አኰሰሰ፣ ሰደበ፣ አዋረደ። "እከሌ የሰው አባት ይገለጥማል"

ገለጠጠ (ቀለጠጠ)፡ ጥርስን፣ ፍምን ፈጽሞ ገለጠ፣ ዛቀ፡ ገለፈጠ፣ ሣቀ።

ገለጠጥ፣ ገልጣጣ፡ መገለጢጥ፡ ገልፋጣ።

ገለጣ፡ ከፈታ፣ ገፈፋ።

ገለጸ፡ ገለጠ፣ ከሠተ።

ገለፈ (ገሊፍ፣ ገለፈ)፡ ተቈጣ፣ ወፈፈ፡ አመረረ።

ገለፈት (ግልፋፊ)፡ የሽንኵርት ልላጭ፣ ወይም ገለባ።

ገለፈት፡ የባቄላ በቈልትና ኣሹቅ ጥራጣሪ።

ገለፈት፡ ያሣ፣ የእባብ ቅርፊት፡ በግእዝ "ቅሣር" ይባላል።

ገለፈንት፡ ርባና ቢስ ወንድ፣ ወይም ሴት (በኾነ ባልኾነው የሚሥቅ፣ የምትሥቅ)

ገለፈንት፡ የሚሥቅ።

ገለፈጠ፡ ዝንጀርኛ ሣቀ፡ ከንፈሩን ገለጠ፣ ገለፈፈ።

ገለፈጥ፣ ገልፋጣ (ጦች)፡ ዝኒ ከማሁ፡ ጥርሱን የማይከድን።

ገለፈፈ፡ ላጠ፣ ላፈ፣ ገፈፈ፣ ፋቀ (የሽንኵርት፣ የእባብ፣ የብራና)

ገለፈፈ፡ ሣቀ፡ ድዱን አሰጣ።

ገለፈፍ፣ ገልፋፋ፡ የተላጠ፡ የሣቀ።

ገሊላ፡ በይፋትና በጠራ ክፍል ያለ ቀበሌ።

ገሊላ፡ ያገር ስም፡ በፍልስጥኤም ውስጥ የሚገኝ አገር። ትርጓሜው "ዙሪያ" ማለት ነው (::)

ገላ (ዎች) (ገልዐዊ)፡ የገል ተፈጥሮው እንደ ገል ከመሬት የሆነ ከራስ እስከ እግር ያለ ቁመት፣ ቁመና፣ አካል፣ ኹለንተና፣ ሰውነት። (አዝማሪ)"እዚያ ላይ ያለች ሸክላ ሠሪ ድኻ ናት አሉ ጦም ዐዳሪ፣ ማን አስተማራት ጥበቡን፣ ገላፈር መኾኑን (ገላ ዐፈር)"

ገላ ሳሙና፡ የአካል መታጠቢያ፣ ባለሽቱ የገላ ሳሙና።

ገላ ነክ፡ ኀበር፡ የቀሚስ ውስጥ።

ገላለጠ፡ ገላለበ፣ ከፋፈተ፣ አብራራ።

ገላላ፡ ዝርግ፣ ሰታታ (ሰፌድ ዐይነት)

ገላልት፡ ገሎች፣ ስባሪዎች።

ገላመጠ፡ በክፉ ዐይን ከፍና ዝቅ አድርጎ አየ፣ ተኰረ፡ ገሠጸ፣ ተቈጣ፣ ገረመመ።

ገላማ፡ አካል ወፍራም፣ ደንዳና።

ገላማጭ (ጮች)፡ የገላመጠ፣ የሚገላምጥ፡ ተኳር፣ ቍጡ፣ ገርማሚ።

ገላበጠ፡ ወላወለ፣ ዘላበደ፣ አነኰረ።

ገላቢ፡ የገለበ፣ የሚገልብ፣ የሚገልጥ፣ የሚያጠምድ፣ የሚያሳርር፣ የሚያቀል፡ ገላጭ፣ አጥማጅ፣ አሳራሪ፣ አቅላይ።

ገላቢጦሽ፡ እንደ ግልብጮ፡ ወንዱን "አንቺ" ሴቱን "አንተ" ማለት።

ገላባጭ (ጮች)፡ ወላዋይ፣ ወረተኛ (ምሳ፲፫፡ ፳፫)

ገላባጭነት፡ ወላዋይነት፣ ዘላባጅነት።

ገላን፡ የኦሮ ነገድና አገር፡ ትርጓሜው "ጐርፍ" ማለት ነው፡ ብዛትን ያሳያል። "አብቹናገላን" እንዲሉ።

ገላው ነውር አወጣ፡ ዐበጠ፣ ቈሰለ።

ገላውን ሰደደ፡ ዐረፈ፣ ተዘለለ፡ ፍር አልባ ተቀመጠ።

ገላገለ፡ ከለከለ፣ አስጣለ፣ አስተወ፣ አስለቀቀ፡ አስታረቀ፣ አሰማማ።

ገላገለ፡ ዘረገፈ፣ ባዶ አደረገ፣ ለየ፣ ነጠላ፡ አሶለደ።

ገላጋይ (ዮች)፡ የገላገለ፣ የሚገላግል፡ አስጣይ፣ አስታራቂ፣ አዋላጅ፣ ዳኛ፣ ዘመድ፣ ሽማግሌ፣ ጨዋ፣ ሐኪም። "ተው በገላጋይ" እንዲሉ ልጆች።

ገላጋይነት፡ አስታራቂነት፡ ሽምግልና።

ገላግል፡ ገላግሌ፡ የሰው ስም።

ገላግልት (ቶች)፡ ታናናሽ ዶሮዎች (ከጫጩት በላይ፣ ከዘረንቦ በታች ያሉ) "ገላግልት" ለጥቂትና ለብዙ ይሆናል፡ "ገላግልቶች" ግን የብዙ ብዙ ናቸው። ትግርኛ "ውርንጭላ (ሎች)" ሲል "ገልገል ገላግል" ይላልና፡ "ገላግልት" "ገልገል" ብዛት ነው።

ገላጣ፡ ሣር ቅጠል የሌለበት ባዶ ስፍራ፣ መላጣ።

ገላጣዋ (ገላጣይቱ)፡ የተገለጠች፡ አንዳች አልባ (ኢሳ፵፩:፲፰)

ገላጭ (ጮች)፡ የገለጠ፣ የሚገልጥ፡ ከፋች። "መጽሐፍ ገላጭ" እንዲሉ።

ገል (ሎች) (ገልዕ)፡ የንስራ፣ የማድጋ፣ የጋን፣ የምጣድ፣ የማንኛውም ሸክላ ስባሪ። (ተረት)" ቢታለብ፣ እኔ በገሌ" አለች ድመት።

ገልማጣ፡ የተገላመጠ።

ገልማጭ፡ የገለመጠ፣ የሚገለምጥ፡ የሚያሞቅ፣ የሚያተኵስ።

ገልማጭ፡ ገላማጭ (ካህንኛ)

ገልበጥባጣ፡ ዘላባጅ (ዘዳ፴፪:፭፣ ሉቃ፱:፵፩)

ገልባጭ (ጮች)፡ የገለበጠ፣ የሚገልብጥ፡ ቀጂ፡ አጋቢ፣ ደፊ፣ አፍሳሽ፡ ለዋጭ፣ ቸርቻሪ፣ አንሸራታች፡ ብራና መላሽ፣ ተማሪ።

ገልባጭነት፡ ለዋጭነት፣ ቸርቻሪነት።

ገልብጥ፡ እንደ ገልባጭ፡ ዳግመኛም ለቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ ይሆናል። "ኮርቻ ገልብጥ" እንዲሉ።

ገልተምተም አለ፡ ቸኩሎ ሠራ፡ ተምታታ።

ገልቱ (ዎች) (ኦሮ)፡ ያ ቢስ፣ ያልሠለጠነ፣ ሥራ የማያውቅ።

ገልታማ፡ ችኵል፣ ጥዱፍ።

ገልዋዳ፡ ሥራ ፈት፣ ምናውዬ፣ ቀውላላ።

ገልጋይ (ዮች)፡ የገለገለ፣ የሚገለግል፡ ገማሽ፣ ዐራሽ።

ገልጣሚ፡ የገለጠመ፣ የሚገለጥም፡ ሰዳቢ፣ አዋራጅ።

ገልፋጭ፡ የገለፈጠ፣ የሚገለፍጥ፡ ሣቂታ፣ ዝንጀሮ ዐይነት።

ገልፋፊ፡ የገለፈፈ፣ የሚገለፍፍ፡ የሚልጥ፣ የሚገፍ፣ የሚሥቅ፡ ፋቂ፣ ገፋፊ፣ ሣቂ።

ገመለ፡ ለበለበ፡ ግመልና ለምጽ አስመሰለ (የእግር፣ የቂጣ)

ገመመ (ከመመ)፡ የሸክላ ዕቃን ዐንገት ሰበረ፣ ጐረደ።

ገመመ፡ ቈረጠ፣ ላጣ፣ ከረከመ። "ጋማ" "ጋሜ" ከዚህ የወጣ ነው።

ገመሞ ራስ፡ ራሰ ትልቅ፣ ራሰ ሰፊ (ሰው)

ገመሞ፡ ዐንገቱ የተሰበረ እንስራ።

ገመሰ (ገሚስ፣ ገመሰ)፡ ተለመ፣ አቦየ፣ ዐረሰ፡ ቈረሰ፣ ከፈለ፡ ፈነከተ (ኹለት አደረገ) (የመሬት፣ የዳቦ፣ የራስ፣ የንጀራ)

ገመሰ: በቀበቀ። "በዝቶ የበቀለ አገዳን ነቀለ።"

ገመሳ (ግምሻ)፡ ተለማ፣ ቈረሳ፣ ፍንከታ።

ገመረ (ገሚር፣ ገመረ)፡ ላቀ፣ ትልቅ ኾነ፡ ከፍ አለ፣ በለጠ።

ገመረ፡ አስቋፈ፡ በቀስታ አስኬደ።

ገመሬ፡ ዝኒ ከማሁ፡ የገመር ወገን ዐይነት።

ገመር (ሮች)፡ ትልቅ አውራ ዝንጀሮ (የጅር መሪ፣ አሳዳሪ)፡ ታላቅ ሰው፣ ዋና ጐምቱ፣ ሽማግሌ፣ ያገር ቀንድ፣ ዐዛውንት፡ ሊቅ፣ መምር። "መምሩ ገመሩ" እንዲሉ።

ገመር ገልብጥ፡ የሣህለ ሥላሴ ስም፡ ገመሩን ገልብጦ በላይ የኾነ ማለት ነው። "ገበረ"ብለኸ "ገበርን" እይ።

ገመሮች(የጋሜ ወገን)

ገመተ (ገሚት፣ ገመተ)፡ አሰላ፣ ገመገመ፡ ዋጋ ቈረጠ፡ "ይህ ይህን ያኸል ያወጣል" አለ፡ ሸለገ። ("ገመሰ" እና "ገመተ" አንድ ዘር ናቸው)

ገመታ፡ ርቦ፣ ሢሶ፡ ተጋዥ ለባለመሬት የሚከፍለው የርሻ ክራይ።

ገመነ (ገምኖ፣ ገመነ፣ ተገመነ)፡ ነደደ፣ ተቃጠለ፣ ዐረረ፣ ተከነ፣ በገነ፣ ጠቈረ፣ ከሰለ፡ ዐዘነ።

ገመነ፡ ተነወረ፣ ረከሰ።

ገመና፡ ነውር፡ የማያምር አግር፡ የተረከዝ ፈለግ፣ ንቅ፣ ሥንጥቅ።

ገመና ከታች፡ ባለተረከዝ መጫሚያ (የእግርን ነውር የሚከት)፡ ያየውን፣ የሰማውን የሚደብቅ ወዳጅ።

ገመናው ተገለጠ፡ ነውሩ ታየ፣ ታወቀ፡ ሚስት ልጅ ሞቱበት።

ገመደ፡ ቈረጠ (ግእዝ) "ጐመደን" እይ።

ገመደ፡ ፈተለ፣ አከረረ፣ ጠሞረ፣ ሸረበ፣ ጠመዘዘ፣ ደበለ።

ገመደለ (ገመደ፡ ገመጸ)፡ አብዝቶ ቈረሰ፣ ገመሰ (ዳቦን)

ገመደለ፡ ፍርድን አጐደለ፣ ቀመጠለ፡ አጠመመ፣ አደላ። ('' ከበደለ መጥቶ በገመደ ላይ ተደርቧል)

ገመደደ፡ ተቋጠረ፣ ተኰመተረ፣ ተኰሰተረ፣ ተጨመደደ፣ ተጨመተረ (የፊት)

ገመድ፡ ቅጣት፣ እስራት፣ ስቅላት (አስቴ፯::) "ግባ በገመዴ" እንዲል ተከሳሽ።

ገመድ፡ ከጓሳና ከስንደዶ፣ ከናጫና ከቃጫ፣ ከእንሰት፣ ከሳማ ልጥ፣ ከፈትል፣ ከሐር፣ ከተልባ እግር፣ ከሽቦ የተጠሞረ (ማሰሪያ፣ መማገሪያ የሚኾን) (ቀላድ፣ ደበል፣ ወደሮ)፡ መታጠቂያ ጥብጣብ።

ገመዶች፡ ቀላዶች፣ አውታሮች (ዘፀ፴፭:፲፰)

ገመገመ (ዐይኖ፣ ዐየነ)፡ ገመተ፣ ሸለገ፣ አሰላ፡ ዋጋ ቈረጠ (ዘሌ፮:)

ገመገመ፡ ተመመ፣ ጮኸ። "ጎመጎመን" እይ።

ገመገመ፡ አያያዘ፣ አረዘመ፣ ከፍ አደረገ፣ አቆመ።

ገመገመ፡ የገገመ ደጊም ነው።

ገመገም (ሞች)፡ እንደ ሰንሰለት የተያያዘ ተራራ (የብዙዎች አገሮች መካከለኛ ወሰን) (ጣርማበርን የመሰለ) ፈረንጆች "ሼን ደሞንታኝ" ይሉታል።

ገመጠ (ገምጾ፣ ገመጸ)፡ ነከሰ፡ በጥርስ ቈረሰ፣ ሰበረ፣ ሸረፈ፣ በላ።

ገመጠጠ፡ በክፉ ዐይን አየ፣ ነቀፈ፣ አጥላላ፣ አንጓጠጠ፣ አሽማጠጠ፡ ጕይዲ ግን "ቀነፈ፣ ቀለበሰ" ብሎታል። "ገረጠጠን" እይ።

ገመጠጠ፡ የ'ገመጠ' 'ገጠጠ' ዲቃላ ነው።

ገሙ፡ ያገር ስም፡ በኦሮ ቤት፣ በወላሞና በጎፋ መካከል ያለ አገር።

ገሚ፡ የሚገማ፣ የሚጠነባ።

ገሚስ፡ ግማሽ፡ ያንድ ወይም የብዙ እኩሌታ (ኑስ፣ ጐደሎ፣ ሕጹጽ) "የሰው ገሚስ" "ግማሽ እንጀራ" "ግማሽ አሞሌ" እንዲሉ።

ገሚሶች፡ ግማሾች፡ እኩሌቶች።

ገማ (ገሚእ፣ ገምአ)፡ በከተ፣ በሰበሰ (ክፋኛ)፡ ሸተተ፣ ጠነባ፣ ከረፋ፣ ቀረና፣ ተበላሸ (አፍንጫው፣ ኣፉ፣ ብብቱ፣ ሥጋው፣ ሬሳው፣ ዕንቍላሉ)፡ ማንኛውም ነገር።

ገማ: ነፈገ።

ገማመሰ፡ ተላለመ፣ ዐራረሰ፡ ቈራረሰ፣ ከፋፈለ፣ ፈነካከተ።

ገማሳ፡ የተፈነከተ (ፍንክት) "ራሰ ገማሳ" እንዲሉ።

ገማሽ (ሾች)፡ የገመሰ፣ የሚገምስ፡ ወራሽ፣ ቈራሽ።

ገማች (ቾች)፡ የገመተ፣ የሚገምት፡ የሚያሰላ፡ አስሊ፣ ገምጋሚ።

ገማይ፡ የገመለ፣ የሚገምል፡ ለብላቢ።

ገማጅ (ጆች)፡ የገመደ፣ የሚገምድ፡ ሸራቢ፣ ጠምዛዥ።

ገማጣ፡ የተገመጠ፡ ሸራፋ፣ ገመሞ።

ገማጭ (ጮች)፡ የገመጠ፣ የሚገምጥ፡ የሚነክስ፡ ነካሽ፣ ሸራፊ።

ገምል፡ የፊደል ስም፡ ፫ኛ ፊደል ()፡ ግመል ማለት ነው።

ገምባሌ፡ በቁሙ (ገነበለ)

ገምቤላ፡ ያገር ስም፡ በዳር አገር ያለ የኢሉባቦር ጠረፍ፡ "ገምቤሎ" ከማለት ጋራ ይስማማል። ዛሬ ግን እንደ ፈረንጅ "ጋምቤላ" ይሉታል።

ገምቤሎ፡ የዛፍ ስም፡ በኃላ ቤት የሚገኝ ለሳንቃ የሚኾን ዕንጨት።

ገምብ (ትግ ገምቢ፣ ጥንብ)፡ ያሞራ ስም፡ ጥንበ በላ አሞራ (ዘዳ፲፬:፲፰)

ገምና (ሐረር ግሙና)፡ ነውረኛ (በምንዝር የረከሰች ዘማ)

ገምናኔ (ግሙናዊ)፡ የገምና ወገን፡ ያመንዝራ፣ ኵሩ፣ ትቢተኛ፣ ተጐማሪ።

ገምዳላ፡ ግምድል፡ የተገመደለ፣ የተቈረሰ፡ ቅምጥል።

ገምዳይ (ገማዲ፡ ገማጺ)፡ የገመደለ፣ የሚገመድል፡ ቈራሽ፣ ገማሽ።

ገምዳዳ፡ ቋጣራ፣ ኰምታራ፣ ጨምታራ። "ፊተ ገምዳዳ" እንዲሉ።

ገምድል፡ አድላዊ፣ አጥማሚ። "ፍርደ ገምድል" እንዲሉ።

ገምጋሚ፡ የገመገመ፣ የሚገመግም፡ ገማች፣ አስሊ።

ገምጣጣ፡ የተገመጠጠ፡ ንቁፍ።

ገምጣጭ፡ የገመጠጠ፣ የሚገመጥጥ፡ ነቃፊ፣ አንጓጣጭ።

ገምጦ፡ ነክሶ፣ ቈርሶ፣ ሸርፎ።

ገምጦ ወጥ፡ መረን ዕገውጡ፡ ገምጦ ወጥ የሚያወጣ፡ ወይም ግማጩን ከወጥ የሚያገባ ባለጌ።

ገሞራ፡ በውሃ የማይጠፋ እሳት (ከምድር የሚፈልቅ)"ገሞራን እሳት" ማለት "ኀዳሪ" በማኅደር ነው። "ፈንታሌን" ተመልከት።

ገሞራ፡ ብርቱ፣ ኀይለኛ፣ ጐበዝ፡ አደጋና መከራ ቻይ። "ገሞራው ወልዴ" እንዲሉ።

ገሞራ፡ ያገር ስም፡ ከሰዶም ጋራ እሳትና ድኝ የዘነበበት አገር።

ገሞራዊት፡ በገሞራ የተወለደች አውሬ።

ገሰለ (አአርወየ): ግስላ አደረገ (ጠባይ በግብር)

ገሰሰ (ዐረ፡ ጀለስ)፡ ተቀመጠ፣ ቍጭ አለ።

ገሰሰ (ገሲስ፣ ገሰሰ): አጠፋ፣ ወረቈሸ፣ ዳበሰ፣ ዳሰሰ፣ ደመሰሰ (ክብርናን)

ገሰሰ: ላጠ፣ ለወጠ፣ ገለበጠ፣ ሻረ (ፍርድን)

ገሰሰ: ቀተለ፣ ቀደስ፣ ባረከ፣ ወደሰ (እያለ) የሩቁን ወንድ አንቀጽ አረባ፣ አበዛ፡ ከመጽሐፍ ቃል ጠቅሶ ወረበ፣ ተቀኘ (ገቢር) የጊዜና ኀላፊ ትንቢቱም "ይገስ" "ይገሳል" በል እንጂ፡ "ይገስስ" "ይገስሳል" አያሠኝም።

ገሰሰ: አዋረደ፣ ዝቅተኛ አደረገ።

ገሰሰ: ደበሰ፣ ለቀቀ (የወርቅ፣ የቀለም) (ተገብሮ)

ገሰስ: ብርድ የመታው ያጠፋው የገብስና የስንዴ ፍሬ፡ ወይም ገለባ። "ዐሠሥ ገሰስ" እንዲሉ።

ገሰረ (ቀተረ): አብዝቶ ጠጣ፣ ለገሸ (የበሬ፣ የሰው)

ገሰሪ ጐሰረ ገተረም ሳይቀር የቀተረ ዘሮች ናቸው።

ገሰበ (ትግ ገሰመ): ጠጣ (ግጥም፣ ሽምጥጥ፣ ዥው አደረገ)፡ ጨለጠ። "ገተመን" እይ።

ገሠገሠ (ገሥገሠ፣ ጌሠ)፡ ማለደ፡ በማለዳ ጨለማ ሳለ ኼደ፡ አረበደ፣ ቸኰለ፣ ተጣደፈ፣ ፈጠነ። (ተረት)"ገዳይ ቢያረፍድ ' ይገሠግሣል"

ገሠገሠ፡ ቶሎ ቶሎ አደገ (የጠጕር)

ገሰገሰ: ማልዶ ኼደ፣ ገሠገሠ።

ገሠገሡ፡ የሴት ስም፡ "ሰዎች ወደ ርሷ ማለዱ" ማለት ነው።

ገሠጠ (ገሠጸ)፡ ሳለ (ዐነጠሰ) (የበሬ) "ወይፈኑ ዐልቅት ስለ ያዘው ይገሥጣል"

ገሠጠ፡ የሕዝብ፡ ገሠጸ የካህናት አነጋገር ነው።

ገሠጠ፡ ገሠጸ፣ ቀጣ።

ገሠጸ (ገሥጾ)፡ ተቈጣ፣ ዘለፈ፡ ሠራ፣ ቀጣ፡ መከረ።

ገሠጸ: (ቈጣ)

ገሣ (ጐሥዐ)፡ አዠ፡ አፈሰሰ፣ አወረደ፡ ተፋ። "ልቡ፣ አፉ፣ ቍስሉ ደም ይገሣል"

ገሣ፡ እንደ ሰይፍ ስለት ያለው፡ ስፋቱ ጋት የሚያኽል ሣር (በረግረግ ውስጥ የሚበቅል)፡ እንደ ግንብ መመለሻ ዐጣፋ ቀናፋ።

ገሣ፡ ከጐሣና ከቀጤማ የተሠራ የዝናም ልብስ (እረኛ በዝናም ጊዜ የሚደርበው) ዘሩ "ገሠገሠ" ነው።

ገሳ: ሣር፣ ገሣ።

ገሣሠጸ፡ ተቈጣጣ፣ መካከረ።

ገሳሪ: የገሰረ፣ የሚገስር፡ ጠጪ።

ገሳሽ (ሾች): የገሰሰ፣ የሚገስ፡ አጥፊ፣ ደምላሽ፡ ለዋጭ፣ ገልባጭ፣ ሻሪ፣ አርቢ፡ ጕልማሳ፣ ዳኛ፣ የቅኔ መምር።

ገሳሽ: ደባሽ፣ ለቃቂ።

ገሣጭሣጺ።

ገሣጭ፡ የገሠጠ፣ የሚስል፣ የሚያነጥስ (ከብት)

ገሣጺ፡ የገሠጸ፣ የሚገሥጽ፡ ገሣጭ (ተቈጪ) (ኢሳ፳፱:፳፩፣ ሮሜ፪:)

ገሥጋሽ (ሾች)፡ ለሣልስት የሚገሠግሥ፡ ማላጅ (በጧት ኻያጅ) (፩ነገ:፲፬:፳፯:፳፰)

ገሥጋሽነት፡ ፈጣንነት፣ አዳጊነት።

ገሥጥ (ገሥጽ)፡ የራስ አበበ አረጋይ የፈረስ ስም፡ "ቅጣ" ማለት ነው (አባን እይ)

ገሦ፡ እጀታው (ዕርፉ) ፩፣ አፍሬው (ጫፉ) ጣምራ የኾነ የጕራጌ መደደቂያ።

ገረ()ገሬገራ()ገሬ (ግራ)ገራገሬ፡ የገራገር ወገን፡ ጥንካሬ የሌለው ዕንጨት (ሙጫው ማረ) (ግላ እደርጝር) (የዶሮ ማር የሚባል)

ገረመ (ገሪም፣ ገረመ): ደነቀ፡ ተፈራ፡ ተለየ። "ይገርማል" "ይደንቃል" (መዝ፷::) (ተረት): "ይገርማል፡ አህያ ከዥብ ይከርማል"

ገረመ (ገርሀ): ገር ኾነ፣ ለሰለሰ፡ ቍጡነትን ተወ፡ ጨመተ። ይህ ቅጽላዊ ግስ ይባላል። "ለበመን" ተመልከት።

ገረመመ (ገረመ): ገላመጠ (ከንፈሩን ነክሶ፣ በክፉ ዐይን ከላይ እታች አየ)፡ አስፈራራ፡ ዐይኑን አፈጠጠ። "ገረፈን" እይ።

ገረማ: የዱር ሲናር፡ የስሙ ምስጢር "ልዩ" ማለት ነው።

ገረሠሙ: ገረሰመ።

ገረሠሙ: ገጨ፣ ለተመ፣ ወለከፈ።

ገረሰሰ (ዕብ ጋራስ፣ ለየ): ዛፍን ነቀለ፣ አነገለ፣ አፈለሰ፣ ጣለ፣ እወደቀ፣ አጋደመ። "ገረሠሠ" ተብሎ ሲጻፍም ይቻላል። "ገነደሰን" እይ።

ገረሠሠ: ሰበረ፣ ገረሰሰ።

ገረረ (ገሪር፣ ገረረ): ጠረረ፡ ጋለ፣ በጣም ሞቀ፣ ተኰሰ፣ ተፋጀ (የፀሓይ) ሠማ፣ ጠበረረ (ለእሳት ተገዛ) (የምጣድ)

ገረረ: ተሳበ፣ ተጐተተ፡ ታለበ።

ገረረ: ተጮኸ። "ቀረረን" እይ።

ገረራ: ሙቀት፣ ጩኸት።

ገረሸ (ገረሠ፣ ዕብ ጋራሽ፣ ሚስት ፈታ): ተመለሰ፣ ታደሰ (የበሽታ)

ገረበበ (ቀረበበ): አንገረበበ፡ መዝጊያን ሳይገጥም ተወ፡ መለስ አደረገ። አንከረፈፈ (ሰውን)

ገረበብ፣ ገርባባ: ግጥም ልጥቅ ልክክ ያላለ ማንኛውም መክደኛ፡ ያልተጠጋ፣ ያልቀረበ፣ የተለየ ሰው (ገረበበ)

ገረበደ: በጣም ከፈተ፣ ወለለ፣ በረገደ። "ገረበደና በረገደ" አንድ ዘር ናቸው።

ገረበድ፣ ገርባዳ: የተከፈተ፡ ክፍት፣ ውልል፣ ብርግድ።

ገረነ (ቀረነ): ወጋ፣ አተኰሰ፣ አቃጠለ፡ አሳመመ (ፀሓይና ንዳድ ሰውን)

ገረን: በመራቤቴ ክፍል ያለ አገር።

ገረንገሬ: የንጨት ስም፣ ገራ።

ገረኘ (ረጊን፣ ረገነ): ቈረኘ፡ አግር ተወርች አሰረ፡ ወይም የኋላ እግርን ከፊት እግር ገጥሞ ባንድነት ጠፈረ (ኰደኰደ) ለመተኰስ፣ ለመብጣት፣ ለማረድ።

ገረዘ (ገዘረ): የወሸላን (የሽፍንን) ጫፍ በክር አስሮ ቀነጠበ፣ ቈረጠ።

ገረዘዘ (ገረሰሰ): አሸለበ፣ ተነ፡ አንቀላፋ፡ አሸነፈ፣ አዘመመ (ሰውን)፡ ነፋስ ዛፍን እንደሚገረስስ። "እከሌን እንቅልፍ ገረዘዘው" እንዲሉ።

ገረዘዘ: ገረደደ፣ ከረዶዶ፡ ጠና፣ ጠነከረ (ሥጋው) "ደና" "" ባማርኛ ይወራረሳሉ! "ደፈቀ" "ዘፈቀ" "ገነተረን" እይ።

ገረደ: ኣጦለ፣ ለየ (ግርድን)

ገረደ: ገረድ ቀጠረ፣ አሳደረ።

ገረደመ: ገመጠ፣ ሰበረ፣ አነከተ፣ አደቀቀ (በላ) (የጋማ ከብት ዕንጨትን) "ዛሬ ሌሊት አጋሰሶቹ ግድግዳውን ሲገረድሙ ዐደሩ"

ገረደደ (ከረደደ): ደረቀ፣ ጠነከረ፡ አልታኘክ አለ።

ገረደደ: አጠረሰ፣ ቸረቸመ፣ ኣበላሸ (ጥርስን፣ ሥጋው፣ ስንደዶው፣ አክርማው)

ገረደፈ (ገረደ፣ ገደፈ): አጐረሠ (መዠመሪያ ፈጩ) ከረተፈ። "ከረተን" "ሸረከተን" እይ።

ገረድ (ዶች) (አመት): ሚስት ያይዶለች (በምንዳ የተቀጠረች) ሴት አሽከር፣ ሎሌ፡ ወይም ሴት ባሪያ (ደንገጥር) (ዘዳ፲፭:፳፩፣ ምሳ፳፯:፳፯፣ ኢሳ፲፬:) በጕራጌ ግን ሴት ልጅ ማለት ነው።

ገረድነት፣ ግርድና: ገረድ መኾን፣ ቅጥርነት (ዘዐ፳፩:)

ገረጀፈ (ገረገፈ): ወፈረ፣ ከበደ፡ ዘፈዘፈ።

ገረገመ (ረገመ፣ ገረመ): ጥርስን ጨርሶ ሸረፈ፣ ሰበረ። "ገረገመ" ብሎ "ሰበረ" ማለት ዕብራይስጥ "ጋራም" ካለው የመጣ ነው።

ገረገመ: ግርግም ሠራ፣ አበጀ።

ገረገረ (ገርገረ): ቀረቀረ፣ ገደገደ፣ ደረደረ፣ ተከለ (ዕንጨትን፣ ኵበትን)

ገረገረ: ሻከረ፣ ደነበረ።

ገረገረ: ከለከለ፣ አገረ፣ አወከ፣ አገደ፣ አቆመ (ሰውን) (ኢዮ፴፱:፳፬)

ገረገራ (ዎች): የቤተ ክሲያን ዐጥር ቅጥር (ከደረቅ ዕንጨት የተበጀ)

ገረገራ: ዐጠድ፡ እንዳጥር ኹኖ የተተከለው (የተሰደረው፣ የተደረደረው) ማንኛውም ዛፍ። (ግጥም): "የቤተ ክሲያን ዐጠድ ስሙ ገረገራ፡ እንዳትወስድብኝ ወዳጄን ዐደራ"

ገረገበ (ረገበ): አንገረገበ፡ ባቄላን፣ ዐተርን፣ ሽንብራን፣ ምስርን፣ ጓያን (ከጤፍ በቀር ሌላውንም እኸል) ሳይቈላ (እኩል ሰዓት ደቂቃ ያኸል) የፍሬው ገለባ ጨምደድ ምደድ እስኪል በጥቂቱ አፈላ፡ በተደራጊነትም ይፈታልም።

ገረገንብ: ግድንግድ።

ገረገፈ (ገረፈ፣ ረገፈ): አንገረገፈ፡ በረደ፣ አቀዘቀዘ፣ አንጠበጠበ፣ አንቀጠቀጠ (መታ ብርዱ፣ ወባው)

ገረጠጠ (ገመጠጠ): አንገራጠጠ፡ ናቀ፣ ኣኰሰሰ።

ገረጣ (ጻዕደወ): ነጣ፣ ነጭ ኾነ (የእኸል፣ የሰው) (ከፀሓይ፣ ከበሽታ የተነሣ)

ገረጨ (ገረጣ): ግራጭ መሰለ፡ ወይም ጥቍረቱና ንጣቱ መሣ ኾነ (የበቅሎ)

ገረፈ (ገሪፍ፣ ገረፈ): በጅራፍ፣ ባለንጋ፣ በጠፍር፣ ባርጩሜ፣ በመንገር ተገተገ፣ መታ፣ ቈነደደ፣ ገጋ፣ ለመጠጠ፣ ቈጋ፣ ለቈጠጠ፣ ሸመተረ፣ ሾጥ አደረገ፣ ሸነቈጠ፣ ቀጣ፣ ጠበጠበ (ሰውን፣ ከብትን) (ዘፀ፭:፲፬፣ ፩ነገ:፲፪:፲፩-፲፬፣ ፪ዜና::፲፩:፲፬፣ ማቴ፳፯:፳፮)

ገረፈ: በመቃ ሥንጣቂ፣ በቢላዋ፣ ደንደስ፣ ባንኮላ አፍ አሰነበረ፣ ሸለመ፣ አስጌጠ፣ ዐተመ፣ ሠረጐደ፣ ጐበጐበ (ድፎን)

ገረፈ: በቀላል ተኰሰ፡ ፈጀ። "(ባርባስ ስምንት ገረፈ)""ላ፬ ብር ዋስ አስጠራ"

ገረፈ: በእሳት ተኰሰ።

ገረፈ: ኣቀና (ወይፈንን)፡ ኣሠለጠነ (ልጅን፣ አሽከርን)

ገረፈ: ገላመጠ። "ድኻውን የሀብታሙ ፊት ገረፈው። "

ገረፋ: ግርፊያ፡ ጥብጠባ፣ ሽንቈጣ።

ገረፍታ: የፀሓይ፣ የጨረቃ ምታት፣ ሽውታ።

ገሪ (ዎች) (ረያፂ): የገራ፣ የሚገራ፡ አስተማሪ፣ አስለማጅ፣ አሠልጣኝ። "ወንድን" እይ።

ገሪ፡ የሚገጭር፣ አስቋፊ።

ገሪማ: የኢትዮጵያ ጻድቅ ስም፡ ከተስዐቱ ቅዱሳን ኣንዱ፡ የፈረንጅ አገር ሰው፡ ጧት ዘርቶ በሠርክ ስላልደና፣ ዛፎችም ቃሉን ሰምተው ስለ ተወገዱ፡ ሌላም ብዙ ተኣምር በመሥራቱ "ገሪማ" ተባለ (ድንቁ እንደ ማለት)፡ ጥንታዊ ስሙ ይሥሐቅ ነው።

ገሪፍ: በግእዝ ያሣ ወጥመድ መያዣ ነውና፡ በምስጢር ከዚህ ጋራ ይገጥማል። ዳግመኛም "ግራፍ" "ጅራፍ""አግራፍ" "ጅራፎች" ተብሎ ይተረጐማል።

ገራ (ረየፀ፣ አግርሀ): ለፈረስ፣ ለበቅሎ፣ ለግመል፣ ለስናር፣ ለአህያና ለዝኆን መቀመጫነትን፣ ግልቢያን፣ ሥግሪያን፣ አረማመድን አስተማረ፣ አስለመደ፡ ወይም እነሱን ፈተነ፣ ሠራ፣ ቀጣ፣ አሠለጠነ፡ አሮ ኣስኬደ (ገቢር)

ገራ (ገሪህ፣ ገርሀ)፡ ለዘበ፣ ላላ፣ ገር ኾነ (ጥናት ዐጣ) (ተገብሮ) መጽሐፍ ግን "ጎራ" ፈንታ "ተገራ" ይላል፡ ስሕተት ነው (፪ሳሙ:፲፰:)

ገራ (ገሪዕ፣ ገርዐ፣ ዕብ ጋራዕ): ከፈለ፣ ከፍሎ ሰጠ፡ አጐደለ፣ አሳነሰ። "ግራን" እይ፡ የዚህ ዘር ነው። "ገርዐ" ጥንታዊ ዐማርኛ መኾኑን አስተውል፣ ልብ አድርግ።

ገራ (ገር)

ገራሚ: የሚገርም፣ የሚደንቅ።

ገራም (ገርሃዊ፣ ልቡብ): ደግ ሰው (ምሳ፳፭:፲፭) ደንሴ፡ አውሬ ያይዶለ (ዐመለ ልስልስ) ከብት፡ የገር ባለገር (ገራዊ) ማለት ነው። መዠመሪያውን "ገራ" እይ።

ገራም ፋሲል: ያፄ ሱስንዮስ አባት፡ ደግ፣ የዋህ ማለት ነው።

ገራሪ: የሚገር፡ ምጣድ።

ገራራ: የገረረ፡ ጠራራ።

ገራዥ (ዦች): የገረዘ፣ የሚገርዝ፡ ቈራጭ። "እከሌና እከሌ ተጣሉና ለያዥ ለገራዥ አስቸገሩ" (ተረት): "የክፉ ቀን ገራዥ አነባበሮ ዐዘለችና፡ እንዲህ ቢያደርጉት እንትን ይኾናል፡ እንዲህ ቢያደርጉት እንትን ሰፊ ይኾኛል፡ ምን ይሻላል?" ብትል... ሌላዪቱ ባልቴት " እቴ ቢቸግርሽ" አለቻት፡ "ቢቸግርሽ ሞተች፡ ረ አላልኩሽም፡ አላልኩሽም" ተደገመች አለችና ደረቷን እየመታች ኼደች ይባላል። ይህም ምሳሌ ሰው በማያውቀው ነገር ገብቶ እንዳያጭበረብር ያስጠነቅቃል።

ገራዳ (ገራዳዊ): ገራድ የተከለው የሐረርጌ ባላባት፡ እንደ መልከኛ የሚታሰብ ባለምድር፡ በርስቱ ውስጥ ብዙ ገባር ያለው፡ ለመንግሥት የሚገብርና የሚያስገብር። የርሱም ተጠሪ "ዋሱ ደሚና" ይባላል።

ገራድ: የሐረርጌ አውራጃ የቀድሞ የማዕርግ ስም። ዐረብ "ጀረደ" ብሎ "ሰይፍ መዘዘ" ይላልና፡ ምስጢሩ "ሰይፈኛ አዝማች" ማለት ይመስላል፡ "ግራኝን" "መሐመድ ገራድ" ይሉታልና።

ገራገር፡ የገር ገር (የየዋህ የዋህ)

ገራፊ (ፎች): የገረፈ፣ የሚገርፍ፡ የሌባ፣ ያባያ ቀጪ (ኢሳ፶:)

ገሬ (ገርሃዊ)፡ ወባ ያለበት ሰው (የወባ ጐራ)፡ ሰውነተ ልል።

ገሬንጭ: በምድር ላይ ደርቆ የቆመ የበርበሬ ዕንጨት።

ገር (ሮች) (ገርህ)፡ የገራ፡ የዋህ፣ ደግ ሰው (ቂም፣ በቀል፣ ተንኰል፣ ሽንገላ የሌለው)፡ የጐመን ዕርሻ (መዝ፳፭:፱፣ ማቴ፭:) "መዠመሪያውን ገረመ" እይ።

ገርማሚ: የገረመመ፣ የሚገረምም፡ አስፈራሪ።

ገርማማ: ያገር ስም (ባዲስ አበባ ምሥራቅ፣ በቡልጋ ያለ) አገርና ዠማ ወገን።

ገርማሜ: የገርማሚ ስም፡ "ደጃች ገርማሜ" እንዲሉ።

ገርሰምሰም አለ: ውልክፍክፍ፣ ድቅፍቅፍ አለ።

ገርሣ: የገደል ላይ ሣር፡ ዘሩ ጐረሠ ነው። "ለሸለሸ" ብለህ "ልሻን" እይ።

ገርሳማ: የገርሳም ወገን፡ ደንቃፋ።

ገርሳም: የሚገጭ፡ ለታሚ።

ገርሳሽ: የገረሰሰ፣ የሚገረስስ (ነፋስ፣ ውሃ፣ ናዳ)

ገርበብ አለ: ተንገረበበ።

ገርበብ አደረገ: በጥቂቱ ዘጋ፡ አንገረበበ።

ገርነት፡ የዋህነት፣ ደግነት (፪ቆሮ::፩፣ ኤፌ፬:፪፣ ያዕ፩:፳፩) "እንዶድን" ተመልከት።

ገርኚ: የገረኘ፣ የሚገረኝ፡ አሳሪ፣ ኰድኳጅ።

ገርዋ: ጠማማ፣ ዐመለ ቢስ፣ ክፉ፣ መጥፎ ሰው፡ ጠባዩ ከሌላ የማይሰማማ።

ገርዳሚ: የገረደመ፣ የሚገረድም፡ ሰባሪ።

ገርዳማ: ገማጣ፣ ሰባራ።

ገርዳሳ (ኦሮ): ጠጕርን ወደ ላይ ደግፎ በራስ ዙሪያ የታሰረ ሻሽ። "ጋሜን" "ናኑን" እይ።

ገርዳዳ: የገረደደ፣ የሚገረድድ፡ ጠንካራ ሥጋ።

ገርዳፊ: የገረደፈ፣ የሚገረድፍ፡ ከርታፊ፣ አጕራሽ።

ገርጀሞ (ጐዣም): ሣር።

ገርጃፋ: ወፍራም፣ ወዘፍዛፋ፡ ቶሎ የሚያረጅ (ሰው)

ገርገመጥ (ግርግመ መጥ): ወደ ግርግም የሚመጣ የባቄላና የሽንብራ (የምስር) አገዳ እግር ስብርባሪ።

ገርገብ አለ: ንዴቱ፣ ቍጣው በረደ።

ገርገብ: መለስ፣ በረድ።

ገርጋሪ: የገረገረ፣ የሚገረግር፡ ቀርቃሪ፣ ተካይ፡ አዋኪ፣ አጋሪ።

ገርጋራ: መሳል፣ ሻካራ (ደንጊያ፣ ሞረዳይ)

ገርጋር: ደንባሪ፣ ሁከተኛ (ድንጉጥ) (ከብት፣ ሰው)

ገሮ፡ በተጕለት ውስጥ ያለ አገር።

ገሸለጠ (ገለጠ): ላጠ፣ መለጠ፣ ገፈፈ።

ገሸለጠ: ገለፈፈ () ገለፈጠ።

ገሸለጥ፣ ገሽላጣ: ጥርሱን የማይከድን፡ ሣቂታ ሴት።

ገሸረ (ዕብ ጋሻር፣ መሰላል ሠራ): አስቀመጠ፣ ቍጭ አደረገ፣ ረፈቀ (ሰውን) "ተነሣ እዚህ ምን ገሽሮኻል" እንዲል ባላገር።

ገሸረ: ተወ፣ አቈየ (ሥራን፣ ውሃን)

ገሸሸ (ገሰሰ): ናቀ፣ አቀለለ፡ ፍቅርን አጐደለ።

ገሸሽ አደረገ: ችላ አለ፡ ነቀፈ፣ ተወ።

ገሸገሸ (ገሥገሠ): አንገሸገሸ (አንገሥገሠ)፡ ነቀነቀ፣ ወዘወዘ፡ አንገፈገፈ (ዐንገቱን አዋቃ)

ገሽላጭ: የገሸለጠ፣ የሚገሸልጥ፡ ገፋፊ፣ ገልፋፊ።

ገበሎ(ዎች)፡ የላሽ፡ ወገን፡ ባላ፬፡ እግር፡ አረንጓዴ፡ ቀለም፡ ራሱን፡ የሚያንቀጠቅጥ፡ አውሬ ጕበና፡ እንቃቅላየአስቆሮቱ፡ ይሁዳ ምሳሌ።

ገበሎጐበለ(ዕብ፡ ጋባል፡ ወሰነ፡ ደንጊያ፡ አቆመ) ቍጭ፡ አደረገ፡ አስቀመጠ።

ገበሰ፡ ገብስ መሰለ፣ ነጣ፣ ፈገገ።

ገበረ ያደረ፣ ደረቀ፣ ጕጥ፣ አባ፣ የገብራ፣ የእጅ የገባ።

ገበረ(ገብሮ ገበረ፡ ገቢር ገብረ፡ ጸብሐ)፡ በቁሙ፣ ሠራ፣ አዘመረ፣ ዐረሰ።

ገበረ፡ ባሪያ፣ ዜጋ ኾነ፡ ግብር ሰጠ፣ ከፈለ፣ አስቀረጠ (፬ነገ :፲፫)

ገበራርት፡ በጐዣም ውስጥ ያለ ቀበሌ።

ገበሬ (ገባር ገባራዊ)፡ ዐራሽ፣ ቈፋሪ፣ ባላዝመራ።

ገበሬ መጣኝ፡ ገበሬን የሚንቅ፣ በቀንበር ቀዳዳ የሚያይ፣ ልግመኛ በሬ፣ አውልግ።

ገበሬ ሸንጎ፡ የገበሬ መሰብሰቢያ፣ ማሤሪያ፣ መዶለት፣ ማደሚያ ስፍራ።

ገበሬ አስደንግጥ፡ የእባብ ዓይነት፡ ገራም እባብ። አታላይ ሰው ወይም ነገር፣ ማስፈራራቱ እውነት ያይደለ።

ገበሬ፡ ገ፡ ገዢ። በሬ፡ ገዢ። በሬን የሚገዛ፣ ጠማጅ፣ አቅኒ፣ ገራፊ ማለት ነው። (ዘፍ፱:, ያዕ፭:)

ገበሬነት፡ ግብርና፣ ዐራሽነት።

ገበሬዎች፣ ገበራርት፡ ዐራሾች፣ ቈፋሪዎች፣ ለፍቶ ዐደሮች።

ገበር (ገመር)፡ ዋና ትልቅ ወፍራም፣ ደንዳና፣ ጠንካራ።

ገበር (ገበሬ)፡ ዐርሶ በላ።

ገበር (ገበዝ)፡ ውሳጣዊ ልብስ፣ ወይም ገላ ነክ፣ ከሐር ልብስ ጋራ በስተውስጥ የተሰፋ።

ገበር ምጣድ፡ ብዙ ሊጥ የሚያምር (የሚችል) ትልቅና ወፍራም ዳቦ የሚጋግር፣ አንድ ጕርዝኝ፣ ሀሻሮ የሚነዛ፣ የሚያነኵር፣ የሚያበስል።

ገበር ዕቃ፡ የገበሬ ዕቃ፡ ሞፈር፣ ቀንበር፣ ዕርፍ፣ ቅትርት፣ ድግር፣ ወገል፣ ማረሻ፣ መርገጥ (ጠፍር ልጥ) ምራን፣ ማነቆ (ጠፍር ዕንጨት) የበሬ ዕቃም ይባላል።

ገበር እንቧይ፡ ታላቅ እንቧይ፣ ከዘርጭና ከምድር እንቧይ የሚበልጥ የእንቧይ ገመር።

ገበር፡ የኦሮ አምባራ፡ ኦሮነቱን ትቶ አማራ የኾነ፡ ወይም በኦሮና በአማራ መካከል የተቀመጠ፣ የአማራ ከለላ፡ "ኦሮ መጣላችኹ" የሚል፡ የኦሮን ምስጢር ለአማራ የሚነግር። ትርጓሜውም "መጻተኛነት" ነው።

ገበር፡ የጥራዝ ልብስ ጣፎችጥራዙን በርሱ ይዘው አስደግፈው የሚጥፉበት፡ የተጣፈውን የሚያስቀምጡበት።

ገበርማ፡ በር ያለው ልብስ።

ገበርማ፡ በጐዣም ክፍል ያለ የአርና የነገድ ስም፡ "የገበሬ ገበራም የገበር ባለገበር" ማለት ነው። (ላማ) ገበርማ፡ በትግሬ ውስጥ የሚገኝ ቀበሌ።

ገበርሾ (ገበር ርሾ)፡ የርሾ መተመጫ፣ ዳቦ ማቡኪያ፣ እንደ ዋዲያት ያለ አፈ ለቃቃ ሸክላ፣ ሰፊ ቡሖቃ።

ገበሮች፡ ጋሎች፣ የአማራ ከለላዎች።

ገበታ (ገበታ፣ ማእድ)፡ የመቃ፣ የሳንቃ፣ የስፌት፣ ሰደቃ፣ የእንጨት፣ የወርቅ መሶብ፣ የእንጀራ፣ የሥጋ ማቅረቢያ። (ተረት)"ሹመት በተርታ፣ ሥጋ በገበታ"

ገበታ (ገበጣ)፡ የገበጣ እንጨት ለጨዋታ ጠጠር የሚመላበት።

ገበታ ሠራ): ዘረጋ፣ እንጀራ ጣለ፣ አቀረበ።

ገበታ ረጋጭ፡ ገበታ ሳይነሣ የኼደ ባለጌ፣ ነውረኛ።

ገበታ ቤት፡ መኻል ሜዳ፣ መታደያ።

ገበታ ዐቃፊ፡ ገበታን ዐቅፎና ከቦ የሚበላ፣ የሚመገብ ሰው።

ገበታ፡ ከግንድ ተጠርቦ የተበጀ ዋልታ። "የባጥ ገበታ" እንዲሉ።

ገበታ ዘረጋ: አስቀመጠ፣ ደረደረ።

ገበታ፡ የዕንቍ፣ የእብነ በረድ፣ የእንጨት፣ የልብ ሰሌዳ፣ ጽላት (ኤር፲፯:)

ገበታ፡ ጠፍጣፋና ዝርግ፣ ልዝብ የመጽሐፍ ዳርና ዳር፣ የዋንዛ፣ የኮሶ ሉሕ፡ በሉሑ አምሳል የተበጀ ካርቶን።

ገበታን ከፍ አደረገ፡ አነሣ፡ ላሽከር አቀረበ።

ገበታዋሪያ፡ በ፲፱፻፳፰ .. ደስታ ተክለ ወልድ ያሳተመው የአማርኛ ግስና ርባታ፣ ተረት፣ ምሳሌ፣ ታሪክ ነው።

ገበታዋርያት (ገበታ ሐዋርያት)፡ የመጽሐፍ ስም፡ ባንድነት የተጠረዘ ፯ቱ የሐዋርያት መልክት። ይህም ሐዋርያት ተሰብስበው ማታ ማታ ባንድ ገበታ የሚመገቡትን (ሰአልናከ) ጸሎተ ማእድ ያሳስባል። መጽሐፉን ገበታ ያሰኘው በ፪ ወገን ያለው ሉሕ ነው ብለዋል ---ክ።

ገበታው ደነገጠ፡ የተጣለው እንጀራ ሣሣ፣ አነሰ።

ገበቴ (ገበታዊ፣ ዋልታዊ)፡ ከእንጨት የተነጠ፣ የተቀረጠ ወጭት፣ ደቅ፣ ዋዲያት፣ ዳካ፣ ሳሕን። መምህራን ግን ገበታ ይሉታል (ዘኍ፯:፴፩:፴፳፯:፶፭:፷፩:፲፯:፸፫, ማር፲፬:) ሲበዛ ገበቴዎች ይላል። መጠናቸውም የቍና፣ የጕርዝኝ ነው። ትንሹ 'ቈሬ' ይባላል።

ገበቶች፡ ሰሌዶች፣ ጽላቶች (ዘፀ፴፩:፲፰, ፴፬:)

ገበቶች፡ ሰደቃዎች፣ መሶቦች። በግእዝ ገባትው ይባላሉ።

ገበና ነውር ገመና።

ገበዘ (ገቢዝ፣ ገበዘ): ግብዝናን (ጠባቂነትን) ሾመ።

ገበዘ ብለኸ ግብዝን እይ።

ገበዘ አኵስም: የአኵስም ገበዝ ጽዮን ወይም ካህን።

ገበዘ: ደለዘ (ለሰነ፣ መረገ፣ ለቀለቀ)፡ ሰባራውንና መጥፎውን ደህና አስመሰለ፡ ቀላቀለ፡ ግብዝ አደረገ (መዝሙር ፳፭፥፫)

ገበዘዘ: አረጀ አፈጀ

ገበዝ (a garment): የሐር ቀሚስ ውስጣዊ ክፈፍ (በዳር የተሰፋ)

ገበዝ (ዞች): የቤተ ክርስቲያን ሹም (ጠባቂ)፡ መንፈሳዊ ዘበኛ፡ በረኛ፡ አስተንታኝ (የሰሞነኛ አለቃ) ምሳሌ:ቄሰ ገበዝእንዲሉ። ተመልከት: "ወሰጠ" ብለህ "ውስጥን" እይ።

ገበዝ ዓምባ: የገንቢዎች አለቃ (መሐንድስ) ማስታወሻ: "ገበዝ ሹሙ፣ ዓምባ መንደሩ"

ገበዝነት: ግብዝና፡ በቁሙ የቤተ ክርስቲያን ሹመት (ግምጃ ቤትነት) ምሳሌ:ከበሽታ ክፉ ቍምጥና፡ ከሹመት ክፉ ግብዝናእንዲሉ።

ገበየ: ኼደ፣ ገዛ፣ ለወጠ፣ ሸመተ፣ አቀና፣ ወሰደ፣ እጅ አደረገ። ግጥም: "አላየናት እንዲያው ገበየናት። " ትርጉም: "ገበየናት" ማለት ጥሎሹንና ማውን ያሳያል።

ገበየኹ፡ የሰው፡ ስም።

ገበየኹ፡ ያጤ፡ ምኒልክ፡ የጦር፡ አበጋዝ፡ (ፊታውራሪ)፡ በዐድዋ፡ ጦርነት፡ የሞቱ።

ገበያ (ዮች): መግዣ፣ መሸጫ፣ መለወጫ ስፍራ (መደብር፣ ሱቅ) ተረት: "ኮሶ ለማላጅ፣ ገበያ ላርፋጅ። " የሥጋ ገበያ: ሥጋያ።

ገበያ ቆመ: መሸጥና መግዛት ተጀመረ።

ገበያ፡ ነሽ የሴት፡ ስም።

ገበያ ወጣ: ከቤት ወደ ገበያ ኼደ። ተረት: "ይሉሽን ባወቅሽ ገበያም ባልወጣሽ። "

ገበያ: ገበያተኛ

ገበያተኛ(ኞች)፡ ገበያ፡ የሚኼድ፡ በገበያ፡ የሚውል፡ የሚቀመጥ፡ ገዢና፡ ሸያጭ።

ገበያው፡ ተፈታ፡ ተበተነ፡ በደግ፡ በክፉ።

ገበያየ፡ ገዛዛ፡ ለዋወጠ፡ ሸማመተ።

ገበይ(ትግ፡ ሐባ፡ መንገድ)፡ አማካይ፡ የምራን፡ ያ፡ የቀንበር፡ መካከል፡ የጠፍሩን፡ ብዛት፡ ያሳያል።

ገበደ: ወፍራም አድርጎ ፈለጠ ሠነጠቀ ከፈለ ተመልከት: ገበዘን

ገበገበ (ገብቦ፣ ገበበ): ተመኘ ፈለገ፣ ነፈገ ሠሠተ (ሣሣ) ማስታወሻ: ከዚህ የተነሳ ምግቡን ሰበሰበ፡ ወደ ሆድ አገባ፣ ከተተ። ተመልከት: ቀበቀበን እና ሰገበን ሌላ ትርጉም: ታገለ ተናነቀ።

ገበገበ: ነገረ (ትርጓሜ)፡ አስተማረ፡ ሰበሰበ።

ገበገባ: ፍለጋ ፍላጎት፣ ምኞት

ገበገባኒ (አመ ከመ ዮም):ዓመታመት ድገመኝእዛሬ ዓመት አድርሰኝማለት፡ እሸትን ቀምሶ አጣጥሞ።

ገበጠ: መታ ለየ፣ ከመረ አከማቸ ሌላ ትርጉም: ግብጣ አወጣ ሌላ ትርጉም: ዝበጣ ተጫወተ

ገበጣ (ገበታ): የጠጠር ጨዋታ (ጊዜ ማሳለፊያ) ፮፥፮ ጉድጓድ ያለው፣ ሁለት የእንጨት ሉሕ ወይም ጠፍጣፋ ሰሌዳ። የጠሩ ቍጥር ፵፰ ነው። ሰሌዳውም ጠጠሩም በአንድነት "ገበጣ" ይባላል። በጨዋታው የተሸነፈውን "ዐይጥበላ" ይሉታል። ጠሩም ከድንጋይና ከእርሳስ ነው። ተመልከት: ጅምን ሥሉስን ውግን ተረት: "ገበጣ ላዋቂ፣ ወሬ ለጠያቂ" "ሲበዛ ገበጦች" ይላል።

ገበጣ ገበጥባጣ (ገበጥባጥ ወስፋት ሹጥ): የስሙ እኩይ የሆነ የገበጣ አይነት። ወስፋትና ሹጥ ሰው የበላውን እንዲበላ የገበጣ ጠጠርም ከአንዱ ተጫዋች ወደ ሌላው ይተላለፋል። ተረት: "ገበጣ ገበጥባጣ፣ ከየሩሳሌም የመጣ" ማስታወሻ: ገበጣ የስቅለት ዕለት እንደነበረ በሕማማተ መስቀል ይነገራል።

ገቢ (ገባኢ): የገባ (የተመለሰ)፡ ተመላሽ (መጪ)፡ ጥቅም (ረብ) ምሳሌ:ለገቢህ ተንገብገብገቢህን ስታይይሉኝአትበል ሌላ ትርጉም: ኹነኛ ዘመድ፡ በደስታና በመከራ የሚገኝ፡ ጠቃሚ (ዃኝ) ምሳሌ:ገቢውን ባለቤት ያውቃልእንዲሉ። ተመልከት: ቃልን

ገቢር፡ ል፣ ፍቱን መድኀኒት፣ አብነት (ለይኩን)

ገቢር፡ ማድረግ (ግእዝ) "በኀልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር" እንዲል ናዛዥ ቄስ።

ገቢር፡ የተገብሮ ተቃራኒ ፊደል፡ ይኸውም '' ነው። (ማስረጃ)"እግዜር በስድስተኛ ቀን አዳምን ፈጠረ" አንዳንድ ጊዜም ገቢር '' ሳይጨምር ሊነገር ይችላል። (ማስረጃ)"እከሌ ሥጋ በላ፣ ጠጅ ጠጣ"

ገቢርና ተገብሮ''ያለበትና የሌለበት ነገር። አንቀጽም ገቢርና ተገብሮ ይባላል፡ ማድረግና መደረግ ማለት ነው።

ገቢና ወጪ (ገባኢ ወወፃኢ): ወደ ሣጥን ገብቶ የሚወጣ፡ ወጥቶ የሚገባ ተመላሽ ገንዘብ፡ በግብር (በቀረጥ፣ በንግድ) ምክንያት።

ገባ (የወንዝ ስም): በኦሮሞ ቤት ያለ ዥረት።

ገባ (የዛፍ ስም): ፍሬው የሚበላ፣ ወደ ሆድ የሚገባ፡ እሾኸ (ቈላፋ) እንጨት። ማስታወሻ:ገባና ቍርቍራአንድ ስለሆነ ሐረርጌዎችና ሌሎችም ገባውንቍርቍራይሉታል።

ገባ (ገቢእ፣ ገብአ): በቁሙ ወደ ውስጥ ጠለቀ (ዘለቀ፣ ሰጠመ)፡ ተጨመረ (ተዶለ፣ ተከተተ) (ዘጸአት ፲፭፥፲፱፣ ኤርምያስ ፲፭፥፱) ሌላ ትርጉም: ተመለሰ (ተመልሶ መጣ)፡ ወደ ኋላ ዞረ (ታጠፈ) ምሳሌ:እዩው ወሮ ሲገባእንዲሉ ሴቶች ታቦት ሲነግሥ።ዥብ እሰር ብሎ ተሰሮ ገባ ሌላ ትርጉም: ጠቀመ (ሆነ) ሌላ ትርጉም: ወጠነ (ዠመረ) ሌላ ትርጉም: ጨረሰ (ፈጸመ) ሌላ ትርጉም: ታወቀ (ተረዳ)፡ ነገሩ (ትምህርቱ) አገባብ: በጥሬና በቦዝ፣ በቅጽልና በነገርም ሁሉ መጨረሻ ይነገራል። ማስረጃ:እባሕር ገባእቤት ገባእዱር ገባ እሆድ ገባ: ተዘነጋ (ተረሳ)፡ ነገሩ። እሰው አፍ ገባ: ስሙ ተነሳ (ታማ) በሽታ ገባ ግብር ገባ ገደል ገባ ገዳም ገባ ግራ ገባው ደኅና ገባ ወዶ ገባ ውል ገባ ውሎ ገባ ወሸባ ገባ ጥብቅ ገባ ጣልቃ ገባ ጦም ገባ ክራይ ገባ ክረምት ገባ ልቡ ገባ መከራ ገባ ንስሐ ገባ ሥራ ገባ ዕዳ ገባ ቅዳሴ ገባ ቀለም ገባ: ተነከረ (ታለለ) ሱባዔ ገባ: ከሰው ተለየ። ገቢእ: መግባት።

ገባ አለ: ቶሎ ገባ።

ገባሪ፡ የሚሠራ፣ ሠሪ፣ አድራጊ (ግእዝ)

ገባሪ፡ ገባር (ሮች)፡ የገበረ፣ የሚገብር፣ የሚያምር፣ የሚያስስ፣ ዜጋ፣ ተገዥ፣ ሠራተኛ፣ ባለርስት፣ የሸማምት መወቻ፣ ሢሶ፣ ማጅ።

ገባሬ ሰናይ፡ ዋና ቂስ፣ "ነአኵቶ ሰገባሬ ሰናያት" ብሎ የሚቀድስ፡ ትርጓሜውም "ደግ አድራጊ" ማለት ነው።

ገባር፡ ገበሬ (ግእዝ)

ገባርነት (ግብርናት)፡ ባርነት፣ ተገዥነት፣ ሠራተኛነት።

ገባባ: መላልሶ ገባ (ገባ ገባ)ጥልቅ ጥልቅዘው ዘውአለ።

ገባዥ: የገበዘ (የሚገብዝ)፡ ገበዝ ሹሚ። ሌላ ትርጉም: ደላዥ (ለሳኝ፣ መራጊ፣ ቀቢ፣ ቀላቃይ)

ገባጅ (ጆች): የገበደ (የሚገብድ)ፈላጭ (ሠንጣቂ)

ገባጭ: የሚገብጥ፣ ግብጣ አውጪ።

ገብ: የገባ (የሚገባ) ምሳሌ:እኹል ገብድረ ገብእንዲሉ። ተመልከት: ኹልን እና ድርን

ገብሰ በላ፡ ድምጽ ረዥም ሰው፣ ደገኛ።

ገብሳም፡ ገብስ ያለበት፣ የመላበት ስፍራ፣ መሬት፣ ባለገብስ።

ገብስ (ሰገም)፡ በቁሙ፣ እንጀራ፣ ጠላ፣ በሶ፣ ጥረሾ፣ ቈሎ፣ ገንፎ፣ እንከት የሚሆን ዋና እህል ነው። (ተረት)"ገብስ የእህል ንጉሥ" (ግጥም)"አትኩራ ገብስ፣ ጐመን ባወጣው ነፍስ"

ገብስ፡ ቀላል ነገር፣ በቅርብ የሚገኝ። "ይህ ነገር ዕዳው ገብስ ነው" እንዲሉ።

ገብስማ፡ ዓይነቱ፣ መልኩ፣ ላባው፣ ጠጕሩ፣ ሕብሩ፣ ቀለሙ ገብስ የሚመስል ዶሮ። ጠንቋዮች ለዛር የሚፈልጉት።

ገብረ መስቀል፡ የመስቀል ባሪያ። በ፮፻ .. የነበረ የኢትዮጵያ ንጉሥ።

ገብረ መንፈስ ቅዱስ፡ የመንፈስ ቅዱስ ወዳጅ፣ አቦ።

ገብረ ማሪያም፡ የማርያም ሎሌ፣ የማርያም ወዳጅ።

ገብረ አብ፡ የክርስትና ስም፣ በገባር በ፲፫ኛ ቀን የእግዚአብሔር አብ ዕለት የተሰየመ።

ገብረ እግዚሐር፡ የእግዚአብሔር ሰው፣ ራሱን ለእግዚአብሔር የሚያስገዛ፣ ነቢይ፣ ሐዋርያ፣ ጻድቅ፣ ሰማዕት፣ እውነተኛ ባሕታዊ፣ መናኝ፣ መነኵሴ።

ገብረ ኪዳን፡ የክርስትና ስም፣ በኪዳነ ምሕረት ዕለት የተሰየመ።

ገብረ ጕንዳን(ቃሕም)፡ የጕንዳን ባሪያ፡ እህል እያጋዘ ጉድጓድ የሚያገባ፣ የሚከት፣ የገባር ዓይነት (ምሳ፮፡ ፯)

ገብሩ፡ ባሪያው፣ ሎሌው፣ አገልጋዩ፣ ወዳጁ።

ገብራምላክ (ገብረ አምላክ)፡ የአምላክ ሎሌ፣ የአምላክ አገልጋይ።

ገብሬ (ገብርየ)፡ ባሪያዬ፣ ሎሌዬ፣ የኔ ባሪያ።

ገብሬል (ገብርኤል)፡ የአምላክ ባለሟል፣ የአምላክ ሐርበኛ፣ የቅዱስ ሚካኤል ጓደኛ። ጌታችንም ገብሬል ይባላል።

ገብሬል ያየው ምስጢር፡ የቃል ሥጋ መልበስ ከድንግል ማርያም መወለድ።

ገብሬሎች፡ የገብሬል ካህናት።

ገብሬሏ፡ የሴት ስም።

ገብር (ጸብሕ)፡ የታላቅ ነጋሪት ድምጽ፡ ሲጮኽ ግብር ገብር ያለ የሚመስል። ታዘዝ፣ ተገዛ፣ ግብር ስጥ ማለት ነው።

ገብር፡ ባሪያ፣ ተገዥ፣ አልጋይ።

ገብር፡ አሽከር፣ ሎሌ፣ ባለል።

ገብርዬ ዝኒ ከማሁ፡ የሰው ስም፡ ያጤ ቴዎድሮስ አበ ጋዝ። እሳቸውም ዐፄ ቴዎድሮስን ለመሻርና ልጃቸውን ደጃች መሸሻን ለማንገሥ ከመኳንንቱ ጋራ በመከሩ ጊዜ፣ ንጉሡ ጠርተው "አንተ የኔ ገብርዬ ነኸ፣ የመሻሻ ገብርዬ ግን ሌላ ነው" አሏቸው። ከርሳቸው ጋራ የመከሩትን መኳንንት እየጠሩ አሰሯቸው ይባላል።

ገብሮናሂ (ገብሮንሂ)፡ ሂ ዋዌ ነው። ባሪያቸውም ያሰኛል። ባለቅኔዎች ግን መለከተኛ ይሉታል።

ገብታ፡ ጕባ፣ ጐበበ።

ገብዛዛ: ያረጀ ፊተ ጨምዳዳ

ገብዪ (ዎች): የሚኼድ፣ የሚገበይ፣ የሚገዛ፣ የሚለውጥ፡ ገዢ፣ ለዋጭ።

ገብገብ: ጎብጋባ ንፉግ፣ ሥሡ (ሥሥታም) ደረቅ፡ የማይጠግብ፣ የማይረካ። ተረት:ከሰው ቀለብላባ፣ ከመሬት ገብጋባ

ገብገቦ: የአጋቦስ ገዳይ፣ የመጀመሪያው የትግሬ ገዢ፣ የሐማሴን ሰው።

ገተለ): (ቀጠለ) አግተለተለ: አያያዘ፣ አስተሳሰረ፣ አቅጠለጠለ (እንደ ግመል) "ገና፣ ቀ፣ ተና፣ " መወራረሳቸውን አስተውል።

ገተመ (ገጠመ፣ ትግ ጐሰመ): ባፉ ሙሉ ቃመ፣ ቻመ። "እረኛው አሹቅ ይገትማል"

ገተም: በወግዳ ውስጥ ያለ ቀበሌ።

ገተረ (ቀተረ): ሳበ፣ ለጠጠ፣ ወጠረ፣ ወተረ፣ ገደገደ (መዝ፯:፲፪) አቆመ፣ ቀሰረ፣ ደከረ።

ገተርታራ፣ ግትርትር: የተግተረተረ፡ እንግድግድ።

ገተርታራ፣ ግትርትር: የተግተረተረ፡ እንግድግድ።

ገተተ (ገቲት፣ ገተ): ዐለቀ፣ ግትቻ ኾነ፡ ተንከረፈፈ፣ ተሞኘ።

ገተነ (ነትገ፣ አንተገ): ነጨ፣ ቦጨቀ፣ ዘነተረ፣ ዘበተረ፡ በላ፣ ዋጠ። "በምጽኣት ጊዜ ዥብ የገተነው፣ አሞራ የበተነው የሰው አስከሬን ኹሉ ይነሣል"

ገተገተ (ቀጠቀጠ): ነከሰ፣ ገጠገጠ፣ ዐኘከ፣ ዐኝ ዐኝ አለ፡ ቈረጠመ።

ገቲ: ዝኒ ከማሁ፡ "ጥሬን" እይ።

ገታ (ገቲዕ፣ ገትዐ): ያዘ፣ ከለከለ፣ አገረ፣ አቆመ፣ አገደ፡ የበቅሎ፣ የፈረስ። ትግሪኛ "ገትዐን" "ገትዔ" ይለዋል። "ገተነ" ብለህ "ገታኝን" እይ።

ገታሚ: የገተመ፣ የሚገትም፡ ቃሚ፣ ቻሚ።

ገታሪ: የገተረ፣ የሚገትር፡ ለጣጭ፣ ወጣሪ፣ አቋሚ።

ገታራ: የተገተረ፣ የቆመ፡ አይወሳወስ።

ገታራ: የተገተረ፣ የቆመ፡ አይወሳወስ።

ገታተረ: ወጣጠረ፣ ሳሳበ።

ገታኝ (ገትዐኒ): ኣገረኝ፡ አላስኬድ አለኝ።

ገታኝ: የገተነ፣ የሚገትን፡ ቦጫቂ፣ ዘንታሪ።

ገት ፊት፡ ፊተ መጥፎ፡ አስቀያሚ።

ገትም: ቃም።

ገትጋታ: የያዘውን የማይለቅ፡ ጥብቅ፣ እውነተኛ ሰው።

ገትጋች: የገተገተ፣ የሚገተግት፡ ነካሽ፣ ዐኛኪ (ውሻ፣ ቍርጥማት)

ገቸገቸ: አንገቸገቸ፡ ዘከዘከ፣ ነቀነቀ።

ገቸገች፣ ገችጋቻ: ሥግሪያ የሌለው በቅሎ፣ ፈረስ፣ አጋሰስ (መጋዣ)

ገቺ (ገታዒ): የገታ፣ የሚገታ፡ ከልካይ፣ ኣጋጅ።

ገች: ታላቅ ጋን (ዐዋሽ) እውስጡ ባለው መጠጥ ማኅበረተኛን የሚያረካ፡ ትልቅ ፍሬዳ፣ ሰንጋ (ድልብ ሥጋው ላንድ ዳስ ሰው የሚያጠግብ) የ፪ቱም ምስጢር፣ ጥማትንና የሥጋ አምሮትን መግታት ነው።

ገችገች አለ: እንገፍ እንገፍ አለ፡ መጥፎ እካኼድ ኼደ።

ገቾች: ጋኖች፡ ሰንጎች፡ የሠቡ ፍሪዶች፣ ድልቦች (መዝ፳፪:፲፪፣ ማቴ፳፪:)

ገነበለ (ገንጰለ)፡ ገለበጠ፣ አጋደመ፣ አስተኛ።

ገነበለ፡ ገንባሌ ለበሰ።

ገነበረ (ቀነበረ)፡ ጠና፣ ጠነከረ፡ ግንባር ኾነ። "እከሌ የግንባር ሥጋ ነው" እንዲሉ።

ገነበበ፡ ውሃ ስለ ወጋው ፍሬ አልባ ቀረ (ያገዳ እኽል)

ገነበጠ፡ አገዳው የፍሬ ምልክት አወጣ፣ አሳየ።

ገነተረ (ገተረ)፡ በጥቂቱ ላይ ላዩ በሰለ፡ ኵምትር ስብስብ አለ፡ ገረደደ፣ ጠነከረ።

ገነታ (ገንሐ)፡ ድምጡን አበርትቶ በኀይል ጮኸ፣ ተቈጣ፡ ሰበከ።

ገነቴ፡ ያገር ስም፡ የጁ። "የገነት" "ገነታዊት"፡ ወይም "ገነትየ" "የኔ ገነት" ማለት ነው።

ገነት(በቁሙ) እና ጕነት።

ገነት፡ በቁሙ ገነነ።

ገነት፡ በያይነቱ ተክል ያለበት ምቹ ስፍራ፡ ቀድሞ አዳምና ሔዋን የነበሩበት (ዛሬም የጻድቃን ነፍሳት እስከ ምጽአት ድረስ የሚኖሩበት) የተድላና የደስታ ቦታ።

ገነት፡ የከተማ ስም፡ ካዲስ አበባ በስተምዕራብ ያለ ቀበሌ።

ገነነ (ገኒን ገነ)፡ ከፍ አለ፣ ታላቅ ኾነ፡ ዐየለ፣ በረታ፡ በጣም ከበረ፣ ጌተየ፡ በዛ፣ ናቸ፣ ለማ። "ቤቱ ገነነ" "እሳቱ ገነነ" እንዲሉ።

ገነነ፡ ዐጠረ፣ ቀጠረ፣ ጀጐለ (የተክል)

ገነን፣ ገናና፣ ገናን፡ የገነነ (ጌታ) (ከበርቴ) (ሀብቱ እዱኛው እጅግ የበዛ) (የተረፈ) "ዐምባ ገነን" እንዲሉ። ሐረርጌዎች ግን "ገነነ አብሲት ጣለ" "ገናና አብሲት" ይላሉ። ምስጢሩ ብዛትን፣ ብርታትን ያሳያል።

ገነዘ (ገኒዝ፣ ገነዘ)፡ የእጅን፣ የእግርን አውራ ጣት በክር ገጠመ፡ ከፈነ፣ ሸፈነ፣ ጠቀለለ፣ አለበሰ፡ ሰፋ፣ ሸለለ። በፈትል፣ ገመድ ዐልፎ ዐልፎ ጠለፈ፣ አሰረ፣ ቋጠረ።

ገነዘበ፡ ዐሰበ፣ ዐወሰ፣ ልብ አለ፣ አጢነ።

ገነዠበ፡ አረጀ (ገነጀበ)

ገነደሰ፡ ከመንታ ግንድ አንዱን ሰበረ፣ ሠነጠቀ፡ አጋደመ፣ አስተኛ፣ አወደቀ። "ገረሰሰን" እይ።

ገነደሰ፡ ገደለ። (የቧልት ግጥም)"ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ትልቅ ትልቁን ገንድስ፡ ባ፵ በ፴ እንድንቀምስ"

ገነደረ (ገነበረ)፡ ወፈረ፣ ደነደነ። ዘሩ "ግንድ" ነው፡ '' ተቀጽላ ኹኖበታል።

ገነጀረ (ገዘረ)፡ ዐረደ፣ ጠባ።

ገነጀበ፡ ፈጽሞ አረጀ፡ ዘነጋ፣ ረሳ (ገንዘብን፣ ሰውነትን) "ገነጀበ" "ገነዘበ" ተቃራኒ ነው፡ "ዝነዠበ" ተብሎ ሊጻፍም ይችላል።

ገነጀብ፣ ገንጃባ፡ የገነጀበ፣ ያረጀ፡ ዝንጉ።

ገነገነ (ገነነ)፡ ፈራ፣ ጠረጠረ፣ ታዘበ፡ ነቅቶ ተጠበቀ፡ "ያርዱኛል፣ ይወጉኛል፣ ይገድሉኛል" ብሎ ሠጋ። "ከነከነን" እይ።

ገነጠለ (ነጠለ)፡ አለስለት ቍልቍል (ወይም ወደ ጐን) በእጅ ስቦ ጐትቶ ቈረጠ፣ ሰበረ (የዐጽቅ) ለየ፣ ኣበላሸ (የመጣፍና የማንኛውም ነገር) "ቈነጠለን" እይ።

ገነጣጠለ፡ የገነጠለ ድርብ፡ ፈጽሞ ቈራረጠ፣ ሰባበረ፣ ለያየ፣ አበለሻሸ።

ገነፈለ (ገንፈለ)፡ ፈላ፣ ፈለቀ፣ ፈልቶ ፈሰሰ። "ቡናው" "ወጡ" "ጠላው" "ሊጡ" "ገነፈለ" እንዲሉ።

ገነፈለ፡ ተሸ፡ በውስጡ ዶቄት ፈላበት፡ መዠመሪያ ተቀቀለበት ንፍሮው።

ገነፈለ፡ የሰው ስም፡ በሣህለ ሥላሴ ጊዜ የነበረ መንፈሳዊ እብድ፡ ፈሊጡ "ግፉ በዛ ገነፈለ! ሆዴን በልቶኝ ጐኔን ቢያኩኝ አይገባኝ አይገባኝ" ማለት የነበረ።

ገነፋ (ገንፈለ)፡ ፈላ፣ ተጠበሰ፣ በሰለ።

ገኑ (ኦሮ)፡ ከዳተኛ።

ገና (ዓዲ)፡ የጊዜ ንኡስ አገባብ፡ ያልተዠመረና ያልደረሰ ሰዓት።

ገና (ጌና)፡ ታላቅ በዓል (በክርስቲያን ኹሉ ዘንድ የከበረ)፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት የታኅሣሥ ፳፱ኛ ቀን። "የወንዶች ገና" "የሴቶች ገና" እንዲሉ። "የገና ለት የተገዛች ባሪያ ዘወትር ገና ይመስላታል" "ካለ እንደ ገና ነው" (ተረት)"በትር ለገና፡ ነገር ለዋና"

ገና ለገናው፡ አስቀድሞ፣ ለሚመጣው፣ ለወደ ፊቱ።

ገና፡ ቀድሞ፣ አስቀድሞ፣ ፊት (ዛር፣ ልመና)"ሳይያዙ ገና"

ገና በርቆ፣ ገና ዘንሞ፡ ያልተወጠነ ሥራ (እንዲህ ይባልለታል)

ገና፡ በ'' ሲጨመርበት 'በገና' ጋራ ዐማርኛ ይኾናል። (ግጥም)"ዳዊት እንዴት ይሙት ሳንተዋወቀው፡ የሚመጣውን ቀን በገና የሚያውቀው"

ገና፡ ዕሩር፣ ጥንግ። "ገና መምቻ" እንዲሉ።

ገና፡ የ'አገና' ከፊል ነው።

ገና፡ የገና ለት በጥንግ ጨዋታ የተሸነፈውን ወገን የሚሳደብ።

ገና ጥዶ፣ ገና ግሞ፡ ዝኒ ከማሁ።

ገናሌ፡ የዠማ ስም፡ እንደ ዳዋ ካሩሲ ተራራ የሚፈልቅ ትልቅ ዥረት።

ገናነዘ፡ ከፋፈነ፣ ጠቃለለ።

ገናና፡ ግዛተ ሰፊ ንጉሥ።

ገናናነት፡ ገናና መኾን።

ገናን ሰባ፡ የቀበሌ ስም፡ በላይኛው ወግዳ ያለ የቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ፡ "የገነኑ ሰባ ሰዎች" ማለት ይመስላል።

ገናንነት፡ ዝኒ ከማሁ (ኢዮ፵:፲፣ ራእ፬:)

ገናኝ፡ የሚገን።

ገናዥ (ዦች)፡ የገነዘ፣ የሚገንዝ፡ ሸፋኝ፣ ጠቅላይ፣ አሳሪ።

ገን (ጥና)፡ ልደት (ገነነ)

ገን ሆይ"ትልቀቱ ሆይ"፡ የአቤቶ አንጻር ነው። "ጃን ሆይ (ጋን ሆይ)" ከማለት ጋራ በምስጢር ይሰማማል።

ገን፡ ትልቅ (ገነነ)

ገን፡ ትልቋ እመቤት (በድሜና በማዕርግ)

ገንባሌ፡ እግርን ከቍርጭምጭሚት እስከ ቋንዣ የሚሸፍን፣ የሚሸበልል (ባለዘለበት) ተንቤን ሸራ፡ ወይም ሌላ ወፍራም ትልታይ ሹራብ።

ገንቦሬ፡ ቀይ ዐፈር፡ ወይም መሬት።

ገንታ፡ ቀንዳ (መለከት) (ቱልቱላ) (ጩኸቱ በሩቅ የሚሰማ)

ገንታ ገንታ አለ፡ ጮክ ጮክ አለ።

ገንታሪ፡ የሚገነትር።

ገንታራ (ሮች)፡ በነገሩ ከሌላ የማይሰማማ (ዐመለ ሻካራ) ሰው።

ገንትቶ ተናገረ፡ ቃሉን ከፍ አድርጎ አሰማ።

ገንትቶ፡ ጩኾ፣ አሰምቶ፣ ተቈጥቶ።

ገንቺ፡ የገነታ፣ የሚገነታ፡ ጯኺ።

ገንዘባም፡ ባለገንዘብ፣ ሀብታም።

ገንዘብ (ቦች)፡ ዕንቍ፣ አልማዝ፣ ወርቅ፣ ብር፣ አሞሌ። (ተረት)"ገንዘብ በስተርጅና ወዴት ትገኚና፡ በልጅነት ይይዝሽና " "የራስሽኝ አትበዪ ገንዘብ የለሽ፡ የሰው አትበዪ ዐመል የለሽ"

ገንዘብ፡ በገንዘብ የተገዛ (በድካም የተገኘ) ከብት፣ ዕቃ (ማንኛውም ለሰው ጠቃሚ የሚኾን ነገር ኹሉ)

ገንዘብ፡ ዐቢይ ኣገባብ፡ ከአንቀጽ ጋራ '' እየቀደመው ማሰሪያ ሲያስቀር "እከሌ እከሌን ባዋረደ ገንዘብ ተዋረደ" ይላል። ምስጢሩም "ስላዋረደ" "እንዳዋረደ" "ያዋረደ ያኸል" ማለት ነው። በግእዝ መሠረቱ "በዘ"

ገንዘብ አደረገ፡ ወረሰ፣ ያዘ፣ ረዘዘ፣ ገዛ፣ ነዳ።

ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ፡ በጥያራ መብረር ይቻላል፡ "በምጿት ገነት መንግሥተ ሰማይ ይገኛል"

ገንደስ፡ ዘንበል፣ ጋደም።

ገንደስ ገንደስ አለ፡ ግንድኛ ኼደ፣ ተራመደ (የወፍራም ሰው)

ገንዳ፡ መካከሉን ጠርበው አጐድጕደው ለከብት ውሃ የሚያጠጡባት ብሓ ደንጊያ። በግእዝ "ገብላ" ይባላል።

ገንዳ፡ ከግንድ ተፈልፍሎ የተበጀ ሞላላ የቤት ዕቃ (ማቡኪያና ጠጅ ማሳረፊያ)

ገንዳሳ፡ ጋድሚያ (ውድቃን)፡ እንቅልፋም (ዐዞ)

ገንዳሽ፡ የገነደሰ፣ የሚገንድስ፡ ሰባሪ።

ገንዴት፡ ምርቀ (ትንሽ ዐጪር ገብስ)

ገንዶራሂ'' 'ዋዊ' ነው የእግሯ ማሰሪያም ያሠኛል። ባለቅኔዎች ግን "ነጋሪት መቺ" ይሉታል።

ገንዶር፡ የእግር ማሰሪያ (ግንድ) (ግእዝ)

ገንጃሪ፡ የገነጀረ፣ የሚገንጅር፡ ዐራጅ፣ በጋማች።

ገንገበት፡ ቀቀበታም፣ ገብጋባ፣ ሥሥታም፡ ግርግራ። ዘሩ "ገበገበ" ነው።

ገንጋና፡ ዝኒ ከማሁ።

ገንጋኝ (ኞች)፡ የገነገነ፣ የሚገነግን፡ ፈሪ፣ ጠርጣሪ፣ ታዛቢ፣ ሥጉ።

ገንጣላ፡ የተገነጠለ፡ ሰባራ።

ገንጣይ (ዮች)፡ የገነጠለ፣ የሚገነጥል (የሚያበላሽ)

ገንጥል፡ የሚለይ፡ ሰባሪ። "ዛቢያ ገንጥል" እንዲሉ። "ገንጥል" ትእዛዝ ሲኾን በቅጽልነት መፈታቱን አስተውል።

ገንፋይ፡ የሚገነፍል፣ የሚፈላ።

ገንፎ፡ ከፍና ከገብስ (ከዐጃ ዱቄት) የተዘጋጀ ቅቤና ዐዋዜ የገባበት የላመ (የጣመ) ለስላሳ ምግብ። (ተረት)"ገንፎ እፍፍ ቢሉኸ ሊውጡኸ ነው"

ገኘ (ገነኘ) (ገንይ፣ ገነየ)፡ አገኘ (አግነየ፣ ረከበ)፡ ደረሰ፣ ነካ፣ ዳሰሰ፡ ያዘ፣ ጨበጠ፣ ገንዘብ አደረገ፡ ወሰደ።

ገኘ፣ ገነኘ'ገነነ' በውስጠ ምስጢር አንድ ናቸው፡ ሰው የሚገነው ሲያገኝ ነውና።

ገኘ)ን፡ እይ፡ አካኼዱ፡ ከዚህ፡ ጋራ፡ አንድ፡ ነው። "

ገወለለ (ጓለለ፣ ጓለበ)፡ አንገዋለለ፡ እህልን በሰፌድ ከቀኝ ወደ ግራ አዞረ፡ ገለባን በላይ ፍሬን በታች አደረገ።

ገወለል፡ ገውላላ፡ የተንገዋለለ፣ የዞረ።

ገወራ፡ በጐዣም ውስጥ ያለ አገር። ትርጓሜው "ጉርብትና" ማለት ነው።

ገውዝ (ዐረ፡ እልጀውዛ)፡ ሥዕሉ፣ ባልና ሚስት፣ ወንድና ሴት የሚመስል የግንቦት ኮከብ፡ ዕጥፍ፣ ጥንድ፣ መንታ ማለት ነው። "ገውዝ ነፋስ" እንዲል ጠንቋይ። ወሩን ኮከቡ ስለ ያዘው ሽማግሎች በግንቦት መጋባት አይገባም ይላሉ።

ገውዝ (ዞች)፡ የተክል ዛፍ ስም፡ ፍሬው የሚበላ፣ መንታነት ያለው። "ገውዝ ለውዝ" እንዲሉ።

ገውዝ ነፋስ፡ የነፋስ ገውዝ፡ በግቦት ኃይለኛ ነፋስ መንፈሱን ያሳያል።

ገውጋዋ (መንጎግው)፡ ዘዋሪ፣ ቀውላላ፡ ሞኝ። ኦሮ "ጥዋ" የሚለው ከዚህ ጋር አንድ ነው።

ገውጡ፡ መረን፣ ዐገገ።

ገዎች ፡ ገለብ፣ ቋጥኝ፡ ታላቅ የደንጊያ ቍልልታ።

ገዎች ዐምባ፡ ቋጥኝ ያለበት መንደር፡ ወይም ቀበሌ ተራራ።

ገዘመ (ገዚም፣ ገመ)፡ ቆረጠ፣ ከፈለ፣ አመመ።

ገዘመ፡ ናቀ፣ ነቀፈ፣ አሸነፈ፣ አዋረደ፣ ገዛ፣ ገረዘዘ።

ገዘረ (ገር፣ ገዘረ)፡ ገረዘ፣ ቆረጠ፣ ቀነጠበ። "ገዘረ" የግእዝ፣ "ገረዘ" የአማርኛ ነው።

ገዘራ፡ መግረዝ፣ ቆረጣ።

ገዘተ (ወጊዝ፣ ወገዘ)፡ በቃል፣ በመንፈሳዊ ሥልጣን ያዘ፡ አሰረ። ክፉ ነገር እንዳይሰራ፣ እውነተኛ ሃይማኖት እንዳይካድ አገደ፣ ከለከለ። "ሠርቶ ክዶ ቢገኝ ከሕዝብ ከማኅበር ለየ፣ እወገዘ" (ቄሱ፣ ጳጳሱ)

ገዘዘ (ገዚዝ፣ ገዘ፣ ገዘዘ)፡ ጀጐለ፡ ዐጥር ዐጠረ፣ ቀጠረ፣ ጋረደ፣ ከለለ፣ መከተ።

ገዘገዘ (ገዚዝ፣ ገዘ፣ ገዘዘ፣ ገዝዐ፡ ወሠረ)፡ ከረከረ፣ መዘ፣ ከረከመ፣ ከመመ።

ገዘገዘ፡ አደከመ፣ አሰለተ። "እከሌን በሽታ ገዝግዞታል"

ገዘገዘ፡ ከበደ፣ አረጀ። "ሰውነቱ ገዝግዟል"

ገዘፈ (ገዚፍ፣ ገዝፈ)፡ አጐራ፣ አጓራ፣ አጋፈተ፡ "ሂያ ሂያ" አለ (የዛር) አካል ገዛ፣ ዳጐሰ፣ ደነደነ፣ ወፈረ፣ ጐላ፡ ዛርም ቢሆን በሰው ዐድሮ ሥጋ ለብሶ ማለት ነው።

ገዘፋ፡ ድንደና፣ ውፈራ።

ገዛ (ገዚእ፣ ገዝአ)፡ ማንኛውንም ነገር በገንዘብ፣ በእህል ገዛ ወይም ሸመተ፡ እስረኛን ዋጀ።

ገዛ፡ ራስ። የስም ዘርፍ ሆኖ ይነገራል፡ በመነሻውም "" ያስቀድማል።

ገዛ፡ አገርን በጦር ኃይል ያዘ፣ አስገበረ፡ ጌታ ሆነ፣ ሠለጠነ፣ ወይም አዘዘ።

ገዛሚ፡ የገመ፣ የሚገዝም፣ የሚያመም፣ የሚገረዝዝ፡ አማሚ፣ ገርዛዥ፣ አሸናፊ፣ እንቅልፍ ሰው።

ገዛሪ፡ የገዘረ፣ የሚገዝር፡ ገራዥ።

ገዛች፡ የገዘተ፣ የሚገዝት፣ የሚያስር፣ የሚለይ፣ የሚያወግዝ፡ አውጋዥ።

ገዛቾች፡ አውጋዦች፣ ቄሶች፣ ጳጳሶች።

ገዛዛ፡ መላልሶ ገዛ፣ ገበያየ፣ ሸማመተ።

ገዛፊ (ፎች)፡ የሚገዝፍ፣ የሚያጐራ፣ የሚያጓራ (ቃልቻ)

ገዛፍ፡ ደጓሳ፣ ወፍራም።

ገዜ፡ ወለደ፣ አገኘ። "ወንድም ጊዜ" እንዲሉ።

ገዝ ገዠሞ (ዎች) (ገዛሚ፣ መግዝም፣ ጕድብ)፡ ባለቂ ጫፍ መሣሪያ፣ ዶማ፡ በአንድ ወገን ሹል በሌላው በኩል ስለት ያለው፣ መቂፈሪያና መቆረጫ።

ገዝሙ፡ የሰው ስም፣ የሴት ስም። ቃዳው፣ ተለላው፣ ክፍሉ፣ ድርሻው ማለት ነው።

ገዝም፡ እመም፣ ቃዳ፣ ተለላ፣ ፈፋ፣ መዛሪያ፣ ትልም። በትግርኛ ግን "ገዝሚ" መዳሪያ ማለት ነው፡ ርስቱ ገንዘቡ ተከፍሎ መሰጠቱን ያሳያል።

ገዝት፡ ለገዛች። "ወፍ ገዝት" እንዲሉ።

ገዝት፡ በመንዝ ውስጥ ያለ ቀበሌ ስም።

ገዝገዝ፣ ገዝጋዛ፡ ለዝጋዛ፣ ገትጋታ ነገር የማይቆርጥ።

ገዝጋዥ (ዦች) (ገዛዚ፣ ገዛዒ፣ ወሣሪ)፡ የገዘገዘ፣ የሚዝግዝ፡ የሚመግዝ፡ መጋዥ፣ ከርካሪ፣ ከርካሚ።

ገዠለ (አግዠለዠለ)፡ አረዘመ፣ ሳበ፣ ጐተተ።

ገዢ (ዥ፣ ዦች) (ገዛኢ)፡ የሚገበይ፣ የሚገዛ፣ ጌታ፣ ሹም፣ መኰንን (ዘዳ፩፡ ፲፭፣ ምሳ፮፡ ፯) "አገረ ገዢ"

ገዢነት፡ ገዢ መሆን፣ ጌትነት።

ገይድ (ገዪድ፣ ጌደ)፡ ጮሌ ፈረስ። "ገይድ" የሰው ስም፣ "ፈጣን" ማለት ነው።

ገደ ቢስ፡ ዕድለቢስ፣ ሀብተ ቢስ፡ ዕድሉ ማጣት የኾነ።

ገደለ (ገዲል፣ ገደለ፡ ቀቲል፣ ቀተለ)፡ ዐደነ፣ መታ፣ ደበደበ፡ ወጋ፣ አቈሰለ፡ ዐረደ፣ ዐነቀ፣ ነፍስ አሳለፈ፣ አጠፋ፣ ቀተለ ሌላውን ወይም ራሱን። "እግሬን ድንጋይ ገደለኝ" ማለት "መታኝ"

ገደለ፡ ወደ ገደል ጣለ፣ አሽቀነጠረ።

ገደለ: ጨረሰ፣ ጠነገደ።

ገደሉ ገደል ገባ፡ ፈረሰ፣ ተናደ፣ ወረደ።

ገደላም፡ ገደል ያለበት፣ የበዛበት ስፍራ።

ገደላገደል፡ የገደል ገደል።

ገደል (ሎች)፡ የተራራና የኰረብታ ደረት፡ የደጋና የቈላ የላይና የታች መካከል የሚያዝ የሚጨበጥ ነገር የሌለበት፣ የመጥፎ ነገር መጣያ (ሕዝ፮:) (ተረት)"እባብ ግደል፡ ከነበትሩ ገደል"

ገደል ሰደደ፡ አንከባለለ።

ገደል ገባ (ጸድፈ)፡ ተንከባለለ፣ ወደቀ።

ገደልጌ፡ በይፋት ያለ ቀበሌ፡ ገደላም ምድር።

ገደመ (ገዲም፣ ገደመ)፡ ገዳም አደረገ፣ ለገዳም ሰጠ፣ ጐለተ፣ ከለለ፣ ወይም መስቀል አዞረ።

ገደማ፡ ዘንዳ፣ ዘንድ፣ ቀበሌ፣ ወይም አጠገብ። እንዲሁም በታችኛው ወግዳ ወረዳ ያለ የአገር ስም ሲሆን "ገደማ ጊዮርጊስ" ተብሎ ይጠራል።

ገደማ፡ ጊዜ ወይም ሰዓት። "ወደ ማታ ገደማ እመጣለሁ"

ገደም አለ፡ ወደ ጎን ሄደ።

ገደረ (ዕብ: ጋዳር፡ ዐጠረ፡ ቀጠረ፡ ከተረ። ዐረ፡ ቀደረ፡ ቻለ)፡ አስቸገረ፣ አሳጣ፡ በችግር፣ በዕጦት ከበበ።

ገደረ፡ ቻለ፡ ቀጠለ።

ገደረ፡ አሽማጠጠ፣ አላገጠ።

ገደራ፡ የሺዋ ክፍል ያለ አገር ስም።

ገደበ (ጐዲብ፣ ጐደበ)፡ ከተረ፣ እገደ፣ ወሰነ፣ ከለከለ፣ ወደበ፣ ደለደለ፣ ዞር ሠራ፣ አበጀ።

ገደበ፡ ዕድር፣ ዐደረ።

ገደበ፡ ደገፈ፣ አጎዘ፣ ረዳ።

ገደበ: ገደብ እደረገ።

ገደብ፡ ዕድር፣ ማገጃ፣ ውሳኔ፣ ዕርቅ፣ አፍራሽ የሚከፍለው ዕዳ። "የተጣሉት ሰዎች በገደብ ታረቁ" (ተረት)"ዐጢን መደብ ይተ፣ ጌን ገደብ"

ገደብ፡ ወሰን፣ ወደብ፣ ዐቃባ፣ ደገፍ (ኢዮ፳፰:፲፩)

ገደደ (ገዲድ፣ ገደ)፡ ግድ፣ ግዴታ ኾነ፡ ጠመመ፣ ተጠመዘዘ።

ገደደ፡ ቸገረ፣ ጠፋ፣ ታጣ፡ ተሳነ (ሉቃ፳፪:፴፭) (ተረት)"ካንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም (አይቸግርም)" "የአፍ ዘመድ በገበያም አይገድ" "ያስቡት አይገድ""አይጠፋ፣ አይታጣ" ማለት ነው። (ላምጪ ይግደደው)"ይቸግረው"

ገደፈ (ገዲፍ፣ ገደፈ)፡ ጊዜ ሳይደርስ በላ፣ ጦምን ተወ፣ ሻረ፣ ወይም ፈሰከ።

ገደፈ፡ ቃል ወይም ትምህርትን ረሳ፣ ጣለ፣ ሳተ፣ ዘለለ፣ ወይም አጐደለ (ሲጽፍና ሲያነብ ይሳሳታል)

ገደፋ፡ ግድፈት፣ ርሳታ፣ ዝንጋታ፣ ወይም መግደፍ (መክ፲፭)

ገደፍ፡ ዐቃባ፣ ደገፈ፣ ወይም ደገፍ።

ገደፎ፡ ትቶ ("በዓል ሽሮ የከበረ፡ ጦም ገድፎ የወፈረ የለም" የሚለው ተረት)

ገዲ (ዶች)(አንቄ)፡ አሞራ፡ ጭላት፡ የዶሮና የወፍ ጠላት፡ መልኳ በስተኋላ ቅልያ፣ በስተፊት ነጭ የኾነ። የባላገር ማረፍያ፡ ዠርባዋ የክፉ፣ ደረቷ የበጎ (ደግ) ምሳሌ።

ገዳሚ፡ የሚገድም ወይም ገዳም የሚያደርግ።

ገዳም ሆነ፡ በብዙ ዘበኛ ታጀበ ወይም ተከበበ።

ገዳም፡ ታላቅ ደብር፣ በዙሪያው መስቀል የዞረበት የከተማ ቤተ ክርስቲያን።

ገዳም አባት: አበ ምኔት፡ የገዳም ሹም፡ የመነኮሶች አስተዳዳሪ።

ገዳም፡ የመናኞች፣ ባሕታውያንና መነኮሳት መኖሪያ፡ ከዓለም የተለየ ስፍራ እንደ ዋልድባና ደብረ ሊባኖስ ያለ ዱር፣ በረሃ፣ ወይም ደን።

ገዳም፡ የቤት አሽከር ወይም የንጉሥ ዘበኛ።

ገዳም ገባ፡ ዓለምን ናቀ፣ ተወ፣ መነነ፣ ወይም ከዓለም ተለየ።

ገዳምጌ፡ በታች ወግዳ ያለ "የገዳም ምድር" ማለት ነው።

ገዳሞች (ገዳማት)፡ ዱሮች፣ መናኞች፣ መነኮሴዎች።

ገዳሞች፡ መሸሻዎች ወይም መማጠኛ ስፍራዎች (ዘኍ፴፡ ፭፡ ፯)

ገዳቢ፡ የገደበ፣ የሚገድብ፣ የሚያግድ፡ ጋጅ፣ ዐጋዥ፣ ረዳት፣ ደጀን፣ የኋላ ጦር።

ገዳዎ፡ ጉዳይ ሆይ።

ገዳይ (ገዳሊ፡ ቀታሊ)፡ የሚመታ፣ የሚገድል፡ አዳኝ፣ ነፍስ አጥፊ (ዘዳ፬:፵፪፣ ማቴ፳፪:፯፣ ሉቃ፲፫:፴፬) "ነፍሰ ገዳይ" "ሰው ገዳይ" እንዲሉ። (ተረት)"እህል ከበዩ፣ ሰው ከገዳዩ"

ገዳይ፡ የጉደለ፣ የገደለች። ሴትን ከወንድ ለመለየት "ገዳዪት" ይሏል።

ገዳይ፡ የፉከራ ቃል ነው። "እዚህ ገዳይ" እንዲል ፎካሪ። ተደጋግሞ ሲነገር "ገዳይ ጉዳይ" ይባላል።

ገዳይነት (ቅትለት)፡ አዳኝነት፡ ገዳይ መኾን።

ገዳዮች፡ የገደሉ፣ የሚገድሉ፡ ወንዶችና ሴቶች።

ገዳደለ፡ የገደለ ድርብ፣ መላልሶ ፈጽሞ ደባደበ፣ ገደለ።

ገዳዳ (ዶች)፡ የገደደ፣ ጠማማ፣ ጠምዛዛ፣ ወልጋዳ፣ ዘዋራ።

ገዳጅ፡ የሚገድ፣ ጠማሚ፣ ቸጋሪ።

ገዳፊ፡ የገደፈ፣ የሚገድፍ፣ ጦምን የሚተው፣ ወይም ያለሰዓቱ የሚበላ ("መገዳፊ" እንደሚባለው)

ገዳፋ፡ ጥፋት፣ በደል፣ ሰበብ፣ ወይም ዳፋ ("ባፈፋ በጐደፋ" እንደሚባለው)

ገዳፍ ቃል፡ የሚገድፍ ወይም የሚጥል (መጽሐፍ ወይም ሰው)

ገድ በለኝ፡ በጧት የኔን ዕቃ ግዛ።

ገድ፡ ዕድል፣ ክፍል፣ ሀብት፣ በረከት።

ገድለኛ፡ ገድል ያለው፣ ባለገድል፣ ሰማዕት፣ ጻድቅ።

ገድል (ሎች)፡ የሰማዕታትንና የጻድቃንን መጋደል የሚነግር መጽሐፍ። "ገድለ ጊዮርጊስ" "ገድለ ተክለ ሃይማኖት" "ያቦ ገድል" እንዲሉ።

ገድል፡ ሰማዕታት ስለ ክርስቶስ እጅ እግራቸውን ለስለት፣ ዐይናቸውን ለፍላት ሰጥተው በሰውነታቸው የፈጸሙት መንፈሳዊ ትግልና ግድያ። ጻድቃን የመዓልት ሐሩር የሌሊት ቍር ታግሠው፣ ዳዋ ለብሰው፣ ደንጊያ ተንተርሰው፣ ጤዛ ልሰው ያደረጉት ስግደት፣ ጾም፣ ጸሎት፣ ትሩፋት፣ መልካም ሥራ ሁሉ ነው።

ገድጋጅ (ጆች)፡ የገደገደ፣ የሚገደግድ፣ የሚተክል፡ ተካይ፣ ወጣሪ። (ተረት)"ያባት ወዳጅ፣ የደንጊያ ገድጋጅ"

ገጀለ (ገደለ፣ ተገደለ)፡ ልበ ሙት ሆነ፣ ቄለ።

ገጀሞ፡ መቍረ፣ ገዠሞ።

ገገመ፡ ከጉዳት፣ ከክሳት፣ ከመገርጣት ጥቂት ዳነ፣ አሸለተ፡ ደሙ ተመለሰ፣ ተሻለው።

ገገም አለ፡ ገገመ፡ በረታ፣ ዐቅም አገኘ።

ገገምተኛ (ኞች)፡ ያገገመ፣ ያሸለተ፣ የተሻለው።

ገገምተኛነት፡ ገገምተኛ መኾን።

ገገምታ፡ ጤና፣ ድኅነት።

ገገረ፡ አፈጠጠ።

ገገረ፡ አፈጠጠ፡ ዐይኑን አፍጦ አየ (ጀጀረ)፡ አጐረጠ።

ገገጭ፡ ገጭጋጭ፣ የሚል፣ የሚጮህ።

ገጋ (ኦሮ)፡ ወለላ የሌለበት የንብ ቀለብ፣ ደረቅ ቀለሕ፣ ሰፈፍ።

ገጠ ቢስ፡ ፊተ መጥፎ፣ ግንባረ ፈጣጣ፣ አፍንጫ ደፍጣጣ፣ መልኩ የማያምርና ደስ የማያሰኝ ሰው።

ገጠመ፡ በመንገድ አገኘ።

ገጠመ፡ አንድ ሆነ፣ አበረ። "የባልና የሚስቱ ኮከባቸው ገጥማል"

ገጠመ፡ ዘጋ፣ አተመ፣ ልክክ አደረገ (ማር፲፭፡ ፲፮)

ገጠመ፡ ዘፈነ፡ የዘፈንን ጫፍ አንድ ዐይነት ፊደል አደረገ፡ ቤት መታ (፪ዜና፡ ፴፭፡ ፳፭)

ገጠመ፡ ጀመረ፣ ያዘ። "ውጊያ፣ ሙግት፣ ጦርነት ገጠመ" እንዲሉ።

ገጠመት (ጥመ)(ገጸ፡ መት፣ መታሄ ገጽ)፡ ግንባረ መቺ፣ ባለጌ።

ገጠመት፡ ፊተ መት፣ ገጥ።

ገጠም፡ የገጠሙ። "ኩታ ገጠም" እንዲሉ።

ገጠረ፡ ዋንጫ ሆነ። "ይህ መሬት ገጥሯል"

ገጠረ፡ ፈረሰ፣ ወደቀ፣ ተፈታ፣ ጠፋ (የአገር፣ የከተማ)

ገጠር (ሮች)፡ ባላገር፡ የባላገር ቤተ ክርስቲያን አጥቢያና ሰበካ ቀበሌ፡ ጭንጫ።

ገጠበ (ትግ፡ ገጸበ፣ ተገጠበ)፡ ነካ፣ አቆሰለ፣ መለጠ፣ ላጠ፣ ላፈ፣ ጋጠ (ገላን በጭነት፣ ባለንጋ፣ ሣርን በጥርስ፣ በማጭድ)

ገጠገጠ (ቀጥቀጠ)፡ ቀጠቀጠ፣ መደበደበ (የክትክታ፣ የፍየለፈጅ)

ገጠገጠ፡ ብዙ ቤት ሠራ፣ ፀያድ ድንኳን ተከለ።

ገጠጠ፡ በአይን ቂጥ በክፉ ገጽ እየተኮረ፡ ፊት ነሣ፣ አጐጠጠ (ገቢር)

ገጠጠ፡ ገጣጣ ሆነ፡ ፈነገጠ፣ ፈነረ፡ ወደ ገጽ (ግንባር) ቀና አለ (ተገብሮ)

ገጡ ለጣይ፡ ጥርሱን የማይከድን፣ ሣቂ። "ገጣጣ ጥርሰ ጣይ ሞቴ"

ገጣለ፡ ገጥ አለ (ገጸወ)፡ ፊት ለፊት ተገለጠ፣ ታየ፡ መጣ፣ ከተፍ አለ።

ገጣሚ (ሞች)፡ የሚገጥም፡ ዐናጢ፣ ዘፋኝ፣ ግጥም ዐዋቂ።

ገጣበረ (አገጣበረ)፡ ናቀ፣ ነቀፈ፣ አኰሰሰ፡ ፀረፈ፣ ሰደበ፣ አዋረደ፣ አቃለለ፡ ገጠጠ፣ አጥላላ።

ገጣበረ፡ እንደ "ገላገለ" ባደራጊነት ቢፈታ፣ "አገጣበረ" ባደራራጊነት፣ "ተገጣበረ" በተደራራጊነት ይተረጐማሉ።

ገጣቢ፡ የገጠበ፣ የሚገጥብ፡ ኦቍሳይ።

ገጣቢት፡ የተገጠበች። (ተረት)"ወደሽን ገጣበት ንጉሥ ትመርቂ"

ገጣባ (ቦች)፡ የተነካ፣ የተገጠበ (የጋማ ከብት፣ የጭነት አጋሰስ፣ ወቀሬ፣ ግመል) "ገጣባ አህያ" እንዲሉ።

ገጣባ፡ በጋማ ከብት ዠርባ ላይ ያለ ቍስል።

ገጣጠመ፡ መላልሶ፣ ብዙ ጊዜ ገጠመ፣ ዘጋ፣ ዘጋጋ፡ ዘፋፈነ።

ገጣጣ (ጦች)፡ የገጠጠ፡ ጥርሰ ረዥም፣ ጣረ ሞት፡ ፍልፈል፣ ዕሪያ። (ተረት)"ገጣጣ ሲሞት የሣቀ ይመስላል"

ገጣጣሚ፡ የገጣጠመ፣ የሚገጣጥም (ዕቃን፣ ግጥምን)

ገጣጭ፡ የሚገጥ፡ አጐጣጭ።

ገጥ (ገጽ)፡ ግንባር፣ ፊት፣ ከግንባር እስከ አገጭ ያለ የፊት መልክ።

ገጥ፡ በፈረስና በበቅሎ ግንባር ላይ የሚውል መካከለኛ የልባብ ጠፍር።

ገጥ፡ የፊት ጥርስ።

ገጥታ (ገጽ)፡ ገጥ፣ ፊት፣ አርኣያ፣ ምስል፣ ወረራ፣ መልክ። "ይህ ሰው ገጥታው አያምርም"

ገጥታ (ግጻዌ)፡ የፊት፣ የግንባር መገለጥ፣ መታየት።

ገጥጋጭ፡ የገጠገጠ፣ የሚጋግጥ፡ ቃጭ።

ገጨ (ጐጠየ)፡ መታ፣ ኰረኰመ፡ ለተመ፣ ተመተመ (ገጽን)

ገጨረ፡ ደነሰረ፣ ጐበለ።

ገጨገጯ (ቀጯቀል)፡ መላልሶ ገጯገጯ፡ ጮኸ፡ ድምጹ፣ ጩኸቱ ተሰማ (ከመጋጨት የተነሣ)፡ የድንጋይ፣ የብረት፣ የንጨት፡ የደረቅ ነገር ሁሉንም ይጨምራል።

ገጭ፡ መግጨት።

ገጭ አደረገ፡ ገጨ፣ መታ።

ገጭገጭ አለ፡ ተንገጫገጨው።

ገጭገጭ አደረገ፡ አንገጫገጨው።

ገጯ፡ የ፣ የሚገጭ፡ ለታሚ።

ገጸ ላሕም፡ ፊቱ በሬ የሚመስል መልአክ።

ገጸ ሰብእ፡ ፊቱ ሰው የሚመስል መልአክ። እነዚህ ኹሉ የግዜርን መንበር ተሸካሞች ናቸው፡ ነገዳቸውም "ኪሩብ" ይባላል (ሕዝ፩:፲፣ ራእ፬:)

ገጸ በረከት (በረከተ ገጽ)፡ እጅ መንሻ፣ መተያያ (ለጳጳስ፣ ለንጉሥ፣ ለባለማዕርግ ኹሉ የሚሰጥ) ገንዘብና ማንኛውም ስጦታ (ጥቂቱ እንደ ብዙ ኾኖ በተቀባዩ ፊት ስለሚቀርብ በረከተ ገጽ ተባለ)

ገጸ ንስር፡ ፊቱ አሞራ የሚመስል መልአክ።

ገጸ አንበሳ፡ ግንባሩ (ፊቱ) አንበሳ የሚመስል መልአክ፡ ፊተ አንበሳ።

ገጸ ከልብ፡ ውሻ ፊት፡ ውሻ መሳይ ሰው (የቅዱስ መርቆሬዎስ ጋሻ ዣግሬ) "እንድሪስን" እይ።

ገጽ፡ በአርእስት የተጻፈ አኃዝ (የገጽን ብዛት የሚነግር)

ገጽ፡ ከአርእስት እስከ ኅዳግ (ከምስማክ እስከ ግልየት) የሚታይ የመጽሐፍ መልክ።

ገጽ፡ ግንባር፣ ፊት። "ገጥን" እይ።

ገጾች፡ ግንባሮች፣ ፊቶች።

ገፈለ (ገነፈለ)አግፈለፈለ፡ የንጀራና የዳቦ ድርቆሽ አፈላ፡ ወጥ ሠራ።

ገፈለለአንገፈለለ፡ ፍሬ ኣሳጣ።

ገፈል (ዐረ ጀፈል)፡ የቡና ገለባ። ገፈል ትግሪኛ ነው።

ገፈረ፡ ቸፈረ፣ ቃመ፣ ቻመ፣ በላ።

ገፈረ፡ ገፈራ ከፈለ፣ ገበረ።

ገፈረና ገበረ፡ አንድ ናቸው፡ መገፈር ለሆድ ለመገበር ነውና። "" "" ተለውጧል።

ገፈራ፡ ቃሚያ፣ ቅሞሽ። "የገፈራ እኸል" እንዲሉ።

ገፈራ፡ የሹም የመንግሥት ፈረስ (በቅሎ) የሚገፍረው የሚበላው ገብስ፡ ይህነንም ባላገር ይሰፍራል።

ገፈተ፡ ኣቅለሸለሸ፡ "ልውጣ ልውጣ" አለ፡ ፈጀ፣ አቃጠለ፣ ዐመመ። "ይህ ኮሶ (እንቆቆ) ልብ ይገፍታል"

ገፈተ፡ ፈትን፣ ገፈፈ፡ ቀመሰ፣ ጠጣ፣ ዠመረ። "ዘኮንኪን ገፍትልኝ" እንዲል (ተማሪ)"ዠምርልኝ" ሲል።

ገፈተረ(ገፈተ፣ ፈተረ)፡ በኅይል ገፋ።

ገፈታ፡ ዝኒ ከማሁ፡ እስኩታ።

ገፈት፡ ያሻሮ የብቅል ገለባ፡ በጠላ ላይ የሚሰፍ ዐሠር።

ገፈን (ትግ)፡ ፈፋ፣ ፈረፈር።

ገፈገፈ (ገፈፈ)፡ ትግ ገፍገፈ፡ ሥራን ኹሉ ብቻውን ሠራ፣ ገፋ።

ገፈገፈ (ጐፈጐፈ), ጐፈጠጠ

ገፈገፈ፡ ላጠ፣ ላጫ፣ ዐጨደ፣ ጠረገ፣ ቀረደደ፣ ሰበሰበ።

ገፈገፈ፡ በላ፣ ጨረሰ።

ገፈገፈ፡ ብዙ ዕዳ ከፈለ።

ገፈገፍ፡ በመንዝ ውስጥ ያለ አገር። ምስጢሩ የካፊያን ብዛትና ደጋነትን ያሳያል።

ገፈጠ (ትግ)፡ ለቀመ፣ ሰበሰበ፣ አከማቸ።

ገፈጠጠአንገፈጠጠ፡ ነፋ፣ እሰፋ፣ አንጠረዘዘ፣ አንዘረጠጠ፣ አንቀበደደ። በተደራጊነትም ይፈታል።

ገፈጠጥገፍጣጣ(እንግፍጥ)፡ የተንገፈጠጠ፡ ጠረዘዝ፣ ቀበዴድ፡ ጠርዛዛ፣ ቀብዳዳ፣ ዘርጣጣ።

ገፈጥ (ትግ)፡ ግባስ ማገዶ።

ገፈፈ (ቀፈፈ)፡ ቈዳን ከሥጋ (ዐበላን ከዐይን) (ልብስን ከገላ) (ክዳንን ከጣራ) (ገፈትን ከጠላ ላይ) ሰነዘረ፣ ሸለቀቀ፣ ለየ፣ አስገለለ፣ ነጠቀ፣ ቀማ፣ ሞሸለቀ፣ አራቈተ፣ አነሣ፡ ጠጕርን ላጩ፡ ዛፍን ላጠ (ዘፀ፲፪:፴፮፣ ሚክ፫:፫፣ ማቴ፳፯:፳፰፣ ፩ቆሮ:፲፩:፰፣ ቈላ፪:፲፭)

ገፈፋ (ትግ ሐባ)፡ ምርኮ፣ ምርኮኛ።

ገፈፋ፡ የመግፈፍ ሥራ (ቅሚያ)

ገፈፎ፡ መብራት አብሪ (ዲያቆን በመቅዶስ ውስጥ የሚንጋፈፍ) (መሶበ ወርቅ ተሸካሚ)

ገፈፎ፡ የወይን ዘለላ ዐሠር (ዘኍ፮:)

ገፈፎ፡ ግባስ ደረቅ ሣርና ቅጠል (ጭራሮ) (ኢዮ፲፫:፳፭፣ ኢሳ፵:፳፬፣ ፵፩:)

ገፊ (ዎች) (ገፋዒ)፡ የገፋ፣ የሚገፋ፡ በዳይ፣ ጉዳይ፣ አጥፊ። "ወስንን" "ዐፈርን" እይ።

ገፊ፡ አሻራው ግንባሩ የኾነ ልጅ፡ አባት እናቱ የሞቱበት (ዘመዶቹ ያለቁበት)

ገፋ (ገፊዕ፣ ገፍዐ)፡ ማንኛውንም ነገር ካለበት ስፍራ ዕልፍ አደረገ፣ አገለለ። (ተረት)"እንዳያማኸ ጥራው፡ እንዳይበላ ግፋው" "ነበረ" ብለኸ "ወንበርን" "ገፈተረን" ተመልከት።

ገፋ ቢል፡ ቢያክል፣ ቢጨምር፣ ቢበዛ።

ገፋ፡ ናጠ፣ ወዘወዘ (ወተትን)

ገፋ፡ ዐመፀ፣ በደለ።

ገፋ፡ ዐበጠ፣ አደገ፣ ሰፋ፣ በዛ፣ በረከተ (የሆድ፣ የቀን) አድራጊና ተደራጊ መኾኑን አስተውል። (ተረት)"ሽልም እንደኾን ይገፋል (ያድጋል)፡ ቂጣም እንደኾን ይጠፋል"

ገፋ አደረገ፡ ዕልፍ አደረገ።

ገፋ ገፋ አደረገ፡ ዕልፍ ዕልፍ (ገለል ገለል) አደረገ፡ ገፋፋ።

ገፋሪ፡ የገፈረ፣ የሚገፍር፡ ቃሚ፣ ምስንጅር።

ገፋች (ቾች)፡ የገፈተ፣ የሚገፍት፡ ገፈት ጠጪ፣ ዐቃቢ ()

ገፋፊ (ዎች)፡ የገፈፈ፣ የሚገፍ፡ የማለይ፡ ቀማኛ (ወንበዴ) ያፈ፣ መምር፣ አሽከር፣ የማች፣ ልብስ ወሳጅ። "ልብስ ገፋፊ" እንዲሉ።

ገፋፋ (ፎች)፡ ሞኝ፣ ቂል፣ ቀርፋፋ፡ ልብሱን ያሶሰደ።

ገፋፋ፡ የገፋ ድርብ፡ መላልሶ ገፋ። አድርግ አድርግ በል በል፡ አትፍራ አለ፡ አስደፈረ (ኢሳ፫:)

ገፍ፡ ከጳጕሜ መጨረሻ ያለፈ ዝናም። "የዘንድሮ ክረምት ካምና ይልቅ ገፍ ነው" ምስጢሩ ብዛትንና መግፋትን ያሳያል።

ገፍ፡ ዝኒ ከማሁ። "ወንበር ገፍ" እንዲሉ።

ገፍ፡ የስጦታ ብዛት (ልክ የሌለው) "እከሌ ቸር ነው፡ በገፍ ይሰጣል"

ገፍታሪ፡ የገፈተረ፣ የሚገፈትር፡ ገፊ! ነፋስ፣ ውሃ፣ ሰው።

ገፍጋፊ፡ የገፈገፈ፣ የሚገፈግፍ፡ ገፊ፣ ዐጅ፣ ቀርዳጅ።

፡ የማር መስፈሪያ፡ ብዙውን ጕንዶ አንድ የሚያደርግ ማድጋ።

unda፡ መልከ ቀይ፣ ማረ በላ፣ ፈጣን። የስሙ ምስጢር ጐናዴነት ነው። ከነዚም አግዝ ደገኛና ቈለኛ፡ ተናካሽ ደገኛ፡ ሻሻቴና ማረ በላ ቈለኞች ናቸው።

unda፡ ዘማች፣ ሻሻቴ፣ ችስችሳ፣ ምሥጠ በል።

undሾች፡ እጀ ቍርጦች (ሉቃ፲፬:፲፫:፳፩) "ኰነተሽ" ብለኸ "ኵንትሽን" እይ።

ጕለላ፡ የመጐለል ሥራ፡ ከደና።

ጉለሌ፡ የቀበሌ ስም፡ ባዲስ አበባና በሰላሌ ይገኛል፡ "ጉለሌ አቅኒው ነው"

ጕለማ፡ የመክፈል ሥራ፡ ቈረጣ፣ ልየታ።

ጕለሻ (ሾች)፡ ደካማ፣ ዐቅመ ቢስ።

ጕለሻ ደካማ፡ ጐለሰሰ።

ጕለታ፡ ተከላ፣ ጥምዘዛ (የጕልቻ)

ጕለንታ፡ በርሻ ዳር ያለ የቦይ ዐፈር (ጓል፣ ድድቅ)

ጕለንታ፡ ጥምጥም ጠጕር።

ጕሊት፡ የሠባች ወፍራሚቱ መሬት።

ጕላላ፡ የግንድና የደንጊያ ክምር (የውሃ መገደቢያ)

ጕላስ፡ ዐሸን፣ ብዙ ጕንዳን፣ ሰራዊት (ምድርን የሚያለብስ፣ የሚሸፍን)

ጕላንጆ፡ ያልሠባ፣ ያልጮመየ (ጕፋያ ሥጋ)

ጕል፡ እንደ ጓል ነው።

ጕልሕ (ሖች) (ጐሊሕ፣ ጐልሐ)፡ የጐላ፣ ግዙፍ፣ ወፍራም (ቁም ጽሁፍ)፡ ወይም ረቂቅ (ያይዶለ ሌላ ነገር)

ጕልላት (ቶች) (ጐላት)፡ በዘውድና በአክሊል ምሳሌ የተሠራ ሸክላ፣ የቤት ቆብ፡ ኳስ የሚመስል ክብ እንክብል (በድንኳን ጫፍ የሚሰካ ፪ና ዕንጨት) (ኢሳ፶፬:፲፪፣ ዘፀ፴፮:፴፰) "ማዘንትን" እይ።

ጕልል፡ ተከድኖ ያለቀ፡ የተጐለለ።

ጕልመሳ፡ ጕልማሳ መኾን።

ጕልማ (ሞች)፡ ላሽከር፣ ለሎሌ፣ ለዘመድ፣ ለወዳጅ ተከፍሎ የተሰጠ ማሳ። "ይህ ዕርሻ የጕልማዬ ነው"

ጕልማ፡ የወንድና የሴት ስም።

ጕልማሳ፡ የጐለመሰ፡ ለጋ፣ ጐበዝ፣ ወጣት፣ ሶባ፣ ሥታ፣ ለማልሞ፣ ዐፍለኛ፣ ጐረምሳ፡ ሠላሳ ዓመት የመላው መናዎ።

ጕልማስነት፡ ዝኒ ከማሁ።

ጕልማሶች፡ ዐፍለኞች (ዘዳ፫::፲፰)

ጕልም፡ የተጐለመ፡ ጕልማ የኾነ።

ጕልምስና፡ ጕልማሳነት፣ ጕርምስና፣ ጕብዝና፣ ዐፍላ።

ጕልስስ አለ፡ ተጐለሰሰ።

ጕልስስ አደረገ፡ ጐለሰሰ።

ጕልስስ፡ ዝኒ ከማሁ።

ጕልሻ ከለላ፡ ጐለሰሰ።

ጕልሻ፡ የኀፍረት፣ የብልት ከለላ (ጨሌ)

ጕልበተኛ፡ እንደ ጕልበታም፡ ሐርበኛ።

ጕልበቱን አፈሰሰ፡ ወዙን ማለት ነው፡ ሥራ ሠራ።

ጕልበታም፡ ኃይለኛ፣ ጐበዝ፣ ብርቱ፣ ጠንካራ።

ጕልበት (ቶች) (ብርክ፣ አብራክ)፡ በጭንና በቅልጥም መካከል ያለ የእግር አንጓ ዐጥቅ፡ ሎሚታ ታጥፎ የሚዘረጋ፣ ተዘርግቶ የሚታጠፍ።

ጕልበት፡ ኃይል፣ ብርታት፣ ጥንካሬ። "ድኻ በጕልበቱ፡ ባለጠጋ በሀብቱ" "ከብዙ ጕልበት ጥቂት ብልሃት" እንዲሉ።

ጕልበት አወጣ፡ ኃይል አገኘ፡ ጐለበተ።

ጕልባን፡ የባቄላ ክክና የፍትግ ስንዴ ንፍሮ በጸሎተ ሐሙስ የሚበላ የዕዝን። "ጕልባን" "ጐለበ" "ቀለበ" ዘር ነው።

ጕልብ (ጥል)፡ የተጐለበ፣ ልብድ፣ ሽፍን፣ ልጕምም።

ጕልቴ፡ የሰው ስም፡ "የኔ ጕልት" ማለት ነው።

ጕልቴና ሰሎሞን፡ በሣህለ ሥላሴ ጊዜ የነበሩ ሊቃውንት (በማታለልና በመታለል የታወቁ)፡ አንዱ ያስፈራኻል፣ ሁለተኛው "ተጠንቀቅ" እያሉ ሌላውን የሚያታልሉ፡ ርስ በርሳቸውም የሚታለሉ፡ ቀልደኞች፣ የንጉሥ ባለማሎች፣ አጫዋቾች።

ጕልት (ቅጽል)፡ የተጐለተ፡ ቅምጥ፣ ርፍቅ፣ ሰነፍ።

ጕልት (ቶች) (ጥሬ) የመልከኛና የባላባት፣ የገዳም ርስት (ለወንድ መኰንን፣ ለሴት ወይዘሮ፣ ለቤተ መቅዶስ የተከለለ) (ዘዳ፲፫:፲፬)

ጕልትሽባ

ጕልት ቀለም፡ ፊደል (በግእዝ "እግዚኡ እዴሁ" እያለ ገቢር ተገብሮ የሚከት)

ጕልት አለ፡ ተጐለተ። "ገደመ"ብለኸ "ግድም አለን" ተመልከት።

ጕልት አደረገ፡ ጐለተ።

ጕልት፡ የወሰን ደንጊያ (ባራት ወገን የተተከለ)

ጕልቻ (ቾች)፡ ከሸክላና ከብሓ ደንጊያ፣ ከብረት የተበጀ (የድስት፣ የምጣድ፣ የማሰሮ፣ የጋን መጣጃ) (ባለ፫ ቍጥር)

ጕልቻ፡ ሹለትና ክንፍ ያለው የመርከብ ማቆሚያ መልሕቅ።

ጕልድማ (ሞች)፡ ጫፈ ድብልብል የማውድ ዐጥንት።

ጕልድማ፡ ቍርጭምጭሚት፣ ኵርማ፣ ጕልበት አንጓ፣ መለያያ።

ጕልድም፡ የተጐለደመ፣ የተናጋ፣ የተለየ፡ ንግ፣ ልዩ።

ጕልድፍ አለ፡ ድንዝ አለ፡ ዶለዶመ።

ጕልድፍድፍ፡ ፍጹም ዱልዱም፡ አፈ እስር።

ጕልጕላ (ጕልጓሎ)፡ ቍንጫቶ፣ ለቀማ፡ የመጐልጐል ሥራ።

ጕልጕል፡ የተጐለጐለ፣ የተበላሸ (ልቃቂት)

ጕልጓይ፡ ንፍጣም፣ መንጐላም፡ ወይም ንፍጥ፣ የተናደ ፈትል።

ጕልጥምት (ቶች)፡ በመሬት ውስጥ ያለ ደረቅ የንጨት ቅሬታ።

ጕልጥምት፡ ቍርጭምጭሚት፣ ኵርማ፣ ጕልበት አንጓ፣ መለያያ።

ጕሎ (ዎች) (ትግ፡ ጕልዕ)፡ የዛፍ ስም፣ ቢጫዊ ፍሬው ቅባትና ዘይት የሚሆን ዕንወት። ፍሬውም "ጕሎ" ይባላል፣ መጠኑ ከእህል ቅንጣት መብለጡን ያሳያል።

ጕሎ (ጥሎ) ጕሎ፡ ቢጫ መልክ ፈረስ። የራስ ዐሊ ፈረስ ስም (አባ ጕሎ)

ጕሎ፡ በቁሙ፣ ጐላ።

ጕመላ(የወንዝ ስም)

ጕመላ፡ እንደ ግመል መውጋት የማይችል (ጐዳ በሬ)፡ በጭራሽ ቀንድ ያላበቀለ፡ በጋልኛ "ሞግሎ" ይባላል።

ጕመራ፡ መጐመር።

ጉመር፡ የጕራጌ አገርና ነገድ፡ ከ፯ቱ ወንድማማቾች አንዱ።

ጉመሮ፡ የቀንጠፋ ዐይነት ዕንጨት።

ጕመይ፡ የቀበሮ ዐይነት አውሬ።

ጉማ (ጉማዕ)፡ ሙዳ ሥጋ ቍራጭ (፩ነገ:፲፮:)

ጉማ፡ በኦሮ ቤት ያለ አገር።

ጉማ፡ የነፍስ ዋጋ (ገመገመ)

ጉማ፡ የነፍስ ዋጋ፣ ገንዘብ፡ ወይም ቁም ከብት። (ጉማ ጋልኛ ነው፡ በግእዝ ግን ታላቅ ጩኸት ማለት ነው) ጋልኛውም ቢኾን በቀንበር ተጠምዶ የሚደረገውን እግዚኦታ ያሳያል።

ጉማ፡ የኦሮ ባላባት ነው።

ጉማም፡ ጉም የሸፈነው ተራራ፡ ደን፡ ጉም የማይለየው፣ ባለጉም።

ጕማራ፡ የወንዝና የቀበሌ ስም፡ በበጌምድር ውስጥ ያለ ዠማ።

ጕማሬ (ሮች)፡ ወፍራም፣ ደንዳና፣ ታላቅ የባሕር እንስሳ (በዟይና በጣና የሚገኝ)፡ በበላበት የሚያራ (አፍ ቂጡ)፡ ዘፈንና ጨዋታ፣ ነጋሪት ወዳድ፡ የጕምር ዐይነት (ክምር መሳይ)

ጕማሬ፡ ከጕማሬ ቈዳ ተጠርቦና ተሸልቶ የተበጀ ዐለንጋና አኰርባጅ። "ርኰትን" ተመልከት።

ጕማርዮስ፡ የዛር አዛዥ፡ ብር ዐለንጋን ያስተረጕማል።

ጕማርዮስ፡ የጅን በሬ (እንደ ጕማሬ በባሕር የሚኖር)

ጕማጅ፡ ጕራጅ፣ ቍራጭ።

ጉሜ (ጉማዊ)፡ በብርና በወርቅ የተጌጠ ያንበሳ አንፋሮ፡ የነጭ ፍየል ሎፊሳ። በጋልኛ ግን "አንባር" ማለት ነው።

ጉሜ፡ ሚስት፣ ቤተ ሰብ።

ጉሜ፡ አንፋሮ (ጎመ)

ጉም (ጊሜ)፡ ምድርን የሚያፍን፣ የሚሸፍን፣ ንድፍ መሳይ ነጭ ደመና (ከምድርና ከባሕር ላይ ወዳየር ወደ ሰማይ እየበነነ (እየተነነ) የሚወጣ)

ጉም ለበስ፡ ዝኒ ከማሁ፡ ጉም የለበሰ።

ጉም፡ ነጭ ደመና (ጎመ)

ጉም አለ፡ ለብቻው ተቀመጠ፡ ጉማ መሰለ፡ ኰራ።

ጉም አስጎምጉም"ጉም ልጁ፣ አስጎምጉም አባቱ"

ጉም፡ የሰው ስም፡ በ፰፻ ዓመተ ምሕረት የነበረ የኢትዮጵያ ንጉሥ።

ጉምሩክ (ዐረ ጅምሩክ)፡ በዋና ከተማና በያገረ ገዢው መኖሪያ የተሠራ ቤት (የነጋዴና ያጣሪ፣ የቸርቻሪ፣ የመሸተኛ፣ የሸቃጭ ግብርና ቀረጥ መቀበያ) በግእዝ "ምጽባሕ" ይባላል።

ጕምር፡ የተጐመረ፡ ንፍ፣ ኵሩ፣ ኵራተኛ።

ጉምብራ፡ ዕንብርት (ጕንብራ)

ጕምዘዛ፣ ጕምዛዜ፡ ምረት፣ ኩምጣጤ።

ጕምዝዝ አለ፡ ጐመዘዘ።

ጕምዠታ፡ ዝኒ ከማሁ።

ጕምዡ፡ የጐመዥ፡ ቋማጭ።

ጕምዣን (ፍትወተ መብልዕ)፡ ሥየታ፣ ምኞት፡ "ባገኘኹት" ማለት። "ጕረሮን" ተመልከት።

ጕምድ አለ፡ ቍርጥ አለ፡ ተጐመደ።

ጕምድ፡ የተጐመደ፡ ጕርድ፣ ቍርጥ፣ ዱሽ።

ጕምድማጅ፡ ዝኒ ከማሁ፡ የተጐማመደ።

ጕምድምድ፡ ቍርጥርጥ፣ ጕርድርድ፣ ብጥስጥስ።

ጕምድምድ አለ፡ ብጥስጥስ አለ።

ጕምጕም አለ፡ ጥቂት በጥቂት፣ በቀስታ ተናገረ (ስለ ቅርታ)

ጕምጕምታ፡ ጒምጕም ማለት።

ጕስማት: የጐን ላይ ምት።

ጕስማዬ: ዘመን አመጣሽ ዘፈን፡ "የኔ ጒስም" ማለት ነው። "ጕስማዬ እንዳለ ሙዚቃ"

ጕስም: የተጐሰመ፣ የተመታ (ነጋሪት)

ጕስምታም: ጕስምት ያለበት፣ የበዛበት (ሰው)

ጕስምት: እውክታ፣ ስርቅታ (የሆድ ዕቃ በትር)

ጕስር: እብቅ የመላበት የጥጃ ስልቻ፡ ጐፍላ እንበጣ።

ጕስቈላ: ክሳት፣ ጥቍረት።

ጕስጕስ: የተጐሰጐሰ፣ የገባ፣ የተከተተ፡ ጥቅጥቅ። "የሜዳ ንስንስ የቤት ጕስጕስ" እንዲሉ።

ጕስጕሻ: የጭቃ፣ የአበት ድብኝት፡ ዶቄት ማኖሪያ (ወታቦ፣ ቅጥልጥሉ "ደልገን" ይባላል)

ጕስጐሳ: ጐረሣ፣ ጥቅጠቃ፣ ጕትጐታ።

ጕረሮ (ጕርዔ): በስተፊት በኩል ባንገት ውስጥ ያለ የመብልና የመጠጥ አሸንዳ፡ ሰፊ የሥጋ ቀሠም (ምግብን ኹሉ ከአፍ ተቀብሎ ወደ ሆድ የሚያወርድ)፡ የነገር፣ የቃል፣ የድምፅ መውጫ ማለት ነው (መነዠኸ ብለህ ምንዣኸን፡ ዐረዶ ብለህ ታራጅን እይ)

ጕረሮኸን ይክፈትልኸ: ሰው ወደ ግብዣ ሲኼድ የሚነገር ቃል፡ በፈረንጅኛ "ቦን አፐቲ" ይባላል።

ጕረንጆ: ያገዳ ስም፡ ጥቍሬታ፣ ራሰ ብትን፣ ተቀምጨ።

ጕረኖ (ዎች): በጭቃና በደንጊያ የተሠራ የግልገሎች የቡችሎች ቤት፣ መከማቻቸው። "ጐረተን" እይ፡ የጐራ ዘር ነው።

ጕረኖ: የግልገል ቤት፣ ጐራ።

ጕረኛ (ኞች): ባለጕራ፣ ጕራ ተናጋሪ፣ ፎካሪ፡ ይስሙልኝ ባይ፣ ጕራ ወዳድ፣ አንጀበኛ፡ አንቧታሪ፣ አንፋሻሪ። "ጐረረ" "ቀረረ" "ገረረ" ዘሮች ናቸው።

ጕራ: ያልተፈጸመ ፉከራ፣ ዛቻ። "ይህ ድብርቅ ዐይን እኔ ልጆቼን ከቈጥ እባጥ እያልኹ አሳደግኹና ለሱ መገበር ኾነን፡ ቈይ ብቻ" (አቶ ዐይጦ ድመትን)

ጕራ: ፉከራ (ጐረረ)

ጕራማይሌ (ዎች): የወፍ ስም፡ ሰማያዊነትና አረንጓዴነት ያላት (ሐር የምትመስል) ወፍ (የምታብረቀርቅ) "ድንቃዊት" "ድንቅ ላቲ" ማለት ነው።

ጕራማይሌ: አንድ ዐለፍ የጥርስ ንቅሳት።

ጕራማይሌ: ወፍ፣ ገረመ።

ጕራሽ: አፍ የሚመጥነው ዳቦ፣ እንጀራ።

ጕራች (ኦሮ): ጥቍር፣ ጠቋራ ፈረስ፣ ሰው፡ ወይም ሌላ ነገር።

ጕራንጕር: የጕር ጕር፡ ዐባጣ፣ ጐበጣ፣ ወጣ ገባ፣ ሥርጓጕጥ (ደንጊያማ ስፍራ) " ስሯጽ ነው"

ጕራንጕር: የጕር ጕር፣ ጐራ።

ጕራዕ: በትግሬ ውስጥ በሐማሴን ክፍል ያለ አገር፡ "ጕር" ከማለት ይሰማማል። "ጕራጌን" ተመልከት።

ጕራጅ: ቍራጭ፣ ጕማጅ።

ጕራጌ ( ጕራዕ): ምድረ ጕራዕ (ድንጋያም ምድር) በትግሬ አውራጃ ያለ የጕራዕ አገር።

ጕራጌ (ጎች): ከትግሬ ወረዳ ከጕራዕ መጥቶ በሺዋ የተቀመጠ፡ ፯ ነገድ ( ወንድማማች) (ባለብዙ ቋንቋ)

ጕራጌ: ፯ቱ ክፍል የጕራጌ አገር። " ቤት ጕራጌ" እንዲሉ። በዝርዝር ሲቈጥሩት ግን ነገዱና አገሩ እስከ ፳፭ ይደርሳል።

ጕራጌም: የሞጋሳ ልጅ ሲል "ዋወራ" ይላል፡ በወላጆቹ ዘንድ የተረሳ፣ የተዘነጋ ማለት ነው።

ጕሬዛ (ዎች): ነጭና ጥቍር የዛፍ ላይ አውሬ (የጦጣና የዝንጀሮ ወገን)፡ ጠጕረ ረዥም፡ ቈዳው በቤት ውስጥ በግድግዳ ላይ ይለጠፋል፡ በወንበር ላይ ይነጠፋል (ጥቍረቱን ንጣት፣ ንጣቱን ጥቍረት የገረዘው (የቈረጠው) ማለት ነው) (ተረት): "ከጦጣ የዋለ ጕሬዛ እኸል ፈጅቶ ገባ" ባላገሮች "ካርብ ማታ እስከ ሰኞ ጧት ከዛፍ አይወርድም" ይላሉ።

ጕሬዝ (ዞች): የበሬ መጥሪያ ስም።

ጕሬዝማ (ጕሬዛዊ): የጕሬዛ ዐይነት ወገን፡ መልኩና ጠጕሩ ጕሬዛ የሚመስል (በሬ፣ ፍየል፣ በግ) (ወፈ ያሬድ)

ጕር (ሮች): የደንጊያ ክምር፣ ክምቹ፣ ኣረንዛ፣ ስብስብ፣ ቍልል (በግእዝ ጕርዕ ይባላል (ገድ ተክ)) "ጕራጌን" "ዘንዶን" ተመልከት።

ጕር ዐምባ: የጕር ዐምባ፡ መዠመሪያ ዐጢ ቴዎድሮስ የሸፈቱበት ቀበሌ (ጕራም)

ጕር: በቁሙ (ጐራ)

ጕር: ያገር ስም (ጕር ያለበት አገር) "ጕር ሥላሴ" እንዲሉ።

ጕርማጅ: የዳቦ ቍራጭ፡ ታናሽ ክፍል ለሰው የሚሰጥ (የሚታደል) ቍራሽ።

ጕርምስና: ጕልምስና።

ጕርምርሜ: የጕርምርም ወገን፡ "የኔ ጕርምርም"

ጕርምርም: ድምፀ ወፍራም ሰው።

ጕርምርምታ (ነጐርጓር): የድምፅ ውፋሬ፡ ክፉ ነገር (ኢዮ፴፯:)

ጕርሥ (ፋእም፣ ላእፍ): ቀለብ፣ ምግብ፣ መብል። "ልብስ ጕርሥ" እንዲሉ።

ጕርሥ አደረገ: ብልት አደረገ፡ ጐረሠ።

ጕርሥ: የተጐረሠ (አፍ ውስጥ የገባ) እንጀራ፣ ትንባኾ።

ጕርሥ: የትምትም ኹለተኛ ስም።

ጕርሦ: ከርትፍ፣ ሽምሽም፡ ያልደቀቀ ዶቄት።

ጕርሻ: የመብልና የገንዘብ ታናሽ ስጦታ፡ አፍ ሙሉ ቍራሽ፣ ዳረጎት፡ ማግ፣ ዐረር።

ጕርብ (ቍቁዕ): የጐረበ፣ የረገበ፡ ቋጣራ ፈትል፡ ቍርብጭ እጅ፡ ያልደቀቀ የገብስ ፍትግ፡ ንድፍና ኣኺዶ።

ጉርብትና: ዝኒ ከማሁ፡ ጎረቤት መኾን።

ጕርብጥ: የተጐረበጠ።

ጕርብጥብጥ: የጕርብጥ ጕርብጥ።

ጕርት: የተጐረተ፡ ጕር (የደንጊያ ቍልል) "ኰረተን" ተመልከት፡ የዚህ ዘር ነው።

ጕርና (ጕርን፣ ዐውድማ): የወተት ዕቃ መግፊያ፣ መናጫ።

ጕርናታም: ቅርናታም፡ የማይጣፍጥ፡ ብላሽ ወጥ።

ጕርናት: ቅርናት፡ መጥፎ ሽታና ጣዕም።

ጕርዝኝ (ኞች): የስፌት ስም፡ በንቅብና በቍና መካከል ያለ ስፌት። አንዱን እንቅብ ኹለት፡ ዐምስቱን ቍና አንድ የሚያደርግ መስፈሪያ።

ጕርደማ: ቍርጠማ።

ጕርዳ በሺ: ማሕፀን ዳባሽ፣ ወጌሻ፡ ጕርዳን የሚጠርግና የሚያስወግድ ሐኪም። "ጕርዳ" ጋልኛ ነው፡ ባማርኛም ይነገራል።

ጕርዳ: ማርገዝና መውለድ የሚከለክል (የሚያቈርጥ) ማሕፀን (ደፋኝኛ፣ ዘጊ) (ውፋሬ)

ጕርድ: ዐጪር ጠመንዣ።

ጕርድ: ከወገብ በታች የተለበሰ የሴት ጥብቆ።

ጕርድ: የተጐረደ ዛፍ፡ ወይም ሌላ ነገር። ቀሪና ኻያጅ (የደረሰኝ ወረቀት ከመካከሉ የተቈረጠ)

ጕርድርድ አለ: ቍርጥርጥ አለ፡ ተጐራረደ።

ጕርድርድ: ቍርጥርጥ፣ ብጥስጥስ።

ጕርዶ: የተፈተገ ስንዴ (እንቅጥቃጥ) (ዘፀ፳፱:፪፣ ፪ነገ:::፲፯) "ጕርዶ" "ግርድን" ያስተረጕማል።

ጕርጅ (ጆች): የቤት ውስጥ ቅይድ (ጓዳ ክፍል) (በያይነቱ ዕቃ የሚቀመጥበት) (ዘፍ፮:፲፬) የንጉሥ ጐተራ (እኸል ቤት) (ባለመከታ)

ጕርጕራ: የነገድ ስም፡ በሐረርጌ አውራጃ "ኢሳ" በሚባለው ሱማሌ አጠገብ የሚገኝ የኦሮ ጐሣ፡ አገሩም "ጕርጕራ" ይባላል።

ጕርጕጭ (ጠጣ)

ጕርጕጭ አደረገ (ሐዘዘ፣ ሠረበ): ማገ፣ ጠጣ። አጠጣጡ የሕፃን ወይም የበሽተኛ ነው።

ጕርጕጭ: ማማግ (ወደ ማንቍርት መግባት)፡ አንድ ጊዜ ማጠጣት። "ጕር" (ጕርዔ)"ጕጭ" (ጕጡ፣ ጕብሩ) ማለት ይመስላል። "ጕርዔ" በግእዝ "ጕረሮ" ማለት ነው።

ጕርጐራ፣ ጕርጓሮ: ብርበራ፣ ፍለጋ፡ የመጐርጐር ሥራ።

ጕርጥ (ጓጕንቸር): ዐይነ ትልቅና ከፍተኛ እንቍራሪት (ታናናሽ ዓሣና ያይጥ ዓሣ የሚውጥ፣ የሚሰለቅጥ)፡ ድምፀ ወፍራም።

ጕርጥ ዐይን: ዐይነ ፈጣጣ ሰው።

ጕርጥ: (መዋጥ)

ጕርፍርፍ: የተጕረፈረፈ፡ ዝርክርክ፣ ዝርፍርፍ።

ጕርፎ: ካመድ ጋራ የታሸ ሱረት፡ ሥንቀን ጠጪው በሞተ ጊዜ ካፍንጫው የሚጐርፍ።

ጕሸማ: ድሰቃ፣ ድሰማ።

ጕሽ (ጻዕፍ): ድፍርስ (አተላውና አንቡላው ያልተለየ)፡ ጥሩ ያይደለ፣ ብጥብጥ፣ ዝልል መጠጥ (ግብ ሐዋ፪:) "ጕሽ ጠላ" "ጕሽ ጠጅ" እንዲሉ። ጕሽ የጌሾ ምስጢር አለበት።

ጕሽም: የተጉሸመ፡ ጕጕም።

ጕሽም: የጡ፣ የቡጢ ምት፣ በትር። "በጕሽም መታው" እንዲሉ።

ጕበት፡ በሆድ ዕቃ መካከል ለብቻው ጕብ ብሎ የሚገኝ ለምለም ደማዊ ሥጋ። ዘሩ ጐባ ነው (ስቍ፪:፲፩)

ጕበትን አየ፡ በጕበት አረተ፣ ጠነቈለ (ሕዝ፳፩:፳፩)

ጕበና (ዎች)() መርዛም፣ ተንቀሳቃሽ ገበሎ፣ የክፉ ሰው ምሳሌ (ዘሌ፲፩:, ሉቃ፫:)

ጕበን (ኖች)፡ በደንፍ አንጸር፣ በመቃን ላይ ያለ፣ ከመቃን የተዋደደ አራት ማዕዘን ዕንጨት። መቃንና ጕበን እንዲሉ።

ጕበኛ (ኞች)(ሰብአ ዐይን)፡ ሰላይ መርማሪ (ዘፍ፵፪::፲፩:፲፮)

ጉባ (ኦሮሞ): ያገሰስ ዠርባ መተኰሻ ጐባጣ ብረት።

ጕባ (ዎች)/ቍባ: በምድር ላይ ያለ የመሬት እምብርት (ቍልልታ)

ጕባ (ዎች): በምድር ላይ ያለ የመሬት እምብርት ቍልልታ ሌላ ትርጉም: ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ።

ጉባኤ (ገብአ): መስብሰብ ስብሰባ አሰባሰብ ሌላ ትርጉም: ጉባይ ዐውድ አደባባይ ሺንጎ ታላቅ ተማሪ ቤት

ጉባኤ ቃና: የቅኔ ስም። ባለሁለት ቤት የሆነ የመጀመሪያ ቅኔ ነው። በቡልጋ ቃና በሚባል ቀበሌ የተወሰነ ነው። ወይም (ቃና ጉባኤ): ጣዕም ያለው ቅኔ (የጉባኤ ጣዕም) ተመልከት: ኅብሮን

ጉባኤ ነጋሪ: ሊቅ ታላቅ መምህር፣ ሰባኪ፣ አስተማሪ

ጉባኤ: የትርጓሜ ክፍል፣ ማንሻና ማረፊያ። ሌሎች ትርጉሞች: ሰርገኛ ዱለተኛ፣ ገባያተኛ፣ ለቅሶኛ፡ ብዙ ሕዝብ፣ ሰራዊት (ዘጸአት ፲፯፥፫) የደቀ መዛሙርት ስብሰባ፡ የብሉይ፣ የሐዲስ፣ የሊቃውንትና የመጽሐፈ መነኮሳት ትርጓሜ የሚማሩበት። "አራቱ ጉባኤ" እንዲሉ። ጉባኤ ሐዋርያት: ቤተ ክርስቲያን። ጉባኤ መላእክት: የመላእክት አንድነት። ጉባኤ ነቢያት: የነቢያት ማኅበር።

ጉባይ(ጉባኤ) እንደ፡ ገበያ፡ ብዙ፡ ሕዝብ፡ የሚሰበሰብበት፡ ሸንጎ፡ ዐውድ፡ አደባባይ፡ (ኢሳ፬ ' )

ጉባይ፡ ስብሰባ፡ ክምቸታ።

ጉባይ፡ የወንድና፡ የሴት፡ ስም።

ጉባዮች፡ ስብሰባዎች፡ ሸንጎች፡ አደባባዮች፡ (ዘሌ፳፫፡ ፴፯። መክ፲፪፡ ፲፩)

ጕብ (ቦች): ታላቅ የሸማ ጮጮ ከግራምጣ የተሰፋ እንደ ጉድጓድ ያለ።

ጕብ አለ: ተጐበለ ቍጭ አለ እንደ ጕብ ተቀመጠ

ጕብል(ሎች)(ጥል) ጥጃ፡ ጠባቂ፡ ወንድ፡ ወይም፡ ሴት፡ ልጅ።

ጕብል(ጥብ) የተጐበለ፡ ጕብ፡ ያለ፡ የመፃጕዕ፡ ሻኛ።

ጕብሰታም፡ የሚጐበስት፣ ሳላም፣ ጕንፋናም።

ጕብሰት፡ ክፉና ደረቅ ሳል፣ ከምች፣ ከነፋስ፣ ከብርድ፣ ከፀሐይ የሚነሣ፡ አክታ ቢስ።

ጕብታ: ቍጭ ማለት መጐበል፣ መቀመጥ ሌላ ትርጉም: ጕባ ምሳሌ:እጕብታው ላይ ተቀመጥ

ጕብንጭር (ሮች)፡ የሸማ መጠቅለያ የሚሰካበት፣ በቀኝ የተተከለ ሹል ዕንጨት፡ ወንዳወንዴ።

ጕብኝ፡ የተጐበኘ፣ የተሰለለ።

ጕብኝታ (ሕዋጼ)፡ ጥየቃ፡ ስለላ፡ የመሰለል ሥራ።

ጕብዝና: ዝኒ ከማሁ፣ ጥናት ብርታት ጥንካሬ (ኢዮብ ፴፫፥፳፭፣ ምሳሌ ፭፥፲፰)

ጕብጕባ: የስሚንቶ ዓይነት አፈር፡ የመሬት ስሚንቶ። በሰንበሌጥ ፈንታ በአፈር ቤት (በእድሞ) ላይ የሚፈስ፣ የሚነሰነስ፣ የሚከዶን።

ጕብጕባት: ሽልማ (የጕብጕብ ሥራ) ጌጥ፣ ሽልማት።

ጕብጕብ: የተጐበጐበ አብሲት፣ የጉባባት ሊጥ፣ ቡሖ። ሌላ ትርጉም: በጋሻና በለምድ ሳንቃ ወይም በዙሪያው ላይ ያለ ጌጥ (የጥንብራና የመጣብር ዓይነት)

ጕብጓቢ: ዝኒ ከማሁ፣ ያብሲት ጨማሪ

ጕብጠት: ጐባጣነት።

ጕብጥብጥ: ዝኒ ከማሁ፡ ሥርጓጕጥ ዐባጣ ጐባጣ ድንጕርጕር

ጕብጭ: ፍላጻ፡ በጐባጣ ቀስት የሚወረወር (የሚነደፍ)

ጕቦ (ሕልያን): ፍርድን ለማጥመም እና ሐሰትን እውነት ለማስመስል ለዳኛ የሚሰጠው መማለጃ

ጕቦኛ (ዎች): ጕቦ ሰጪ እና ተቀባይ፣ ጕቦ ወዳጅ

ጕተታ: ስቦሽ።

ጕተና: ያደገ፣ የረዘሙ ጐፈሬ (፩ቆሮ፲፩:፲፬)

ጕተና: ጐሚት (የብላጊ አበባ)፡ እጅግ የሚያምር ቀይ ደማቅ የሬት ዐይነት። "ጕተና አበባ" እንዲሉ።

ጕተናማ: ጕተናም፣ ባለረዥም ጕተና።

ጕታ: ቍግ (ጐተነ)

ጕታ: ከና፣ ከቃጫ፣ ከጥፍራንዶ፣ ካክርማ፣ ከስንደዶ፣ ከሳማ፣ ከንሰት፣ ከማንኛውም ጭረት የተበጀ ቍግ፡ የጅራፍ (ውልብልቢት) ነፋስን በመጥለፍ የሚጮኸ፡ ጕተና መሳይ።

ጕት: ቅኔ (ጐተተ)

ጕት: የመረብ ቂጥ (መወጠኛው)

ጕት: የቅኔ ስም፤ የዜማ ልክ የሌለው ድርድር (የቀድሞ ቅኔ)

ጕትት: የተጐተተ፡ አዝጋሚ (ዝግ ብሎ ኻያጅ)፡ የእባብ፣ የዘንዶ፣ ያዞ፣ የዔሊ ዐይነት።

ጕትቻ: ከወርቅና ከብር፣ ከንሓስ፣ ከሌላም ማዕድን የተሠራ የዦሮ፣ ያፍንጫ ጌጥ።

ጕትቻ: የነገር ሳቢያ፡ ንዝንዝ፣ ውዝግብ።

ጕትን: ብጥር፣ ምይድ ጠጕር።

ጕትዬ: ቍንጪም ወፍ (እንድርማሚት)፡ ጕተናም አሞራ።

ጕትዬ: ቍንጯም ወፍ (ጐተነ)

ጕትጐታ: ንቅነቃ፣ ውትወታ።

ጕቶ: የተቈረጠ ግንድ፡ በምድር ላይ የቆመ የንጨት ጕራጅ። "ማዶጉን መቈረጥ የጌታው" ጕቶ: (ጋተ)

ጕቶ: የግንድ ቅሬታ (ገታ)

ጕቺ (ኦሮ): ሰጐን በሩቅ ሲያይዋት ጕቾ መሳይ።

ጕች አለ: ቍጭ አለ፡ ተቀመጠ።

ጕች: ቍጭ መቀመጥ።

ጕቾ: የተጐቸ፡ ክምር፣ ዘመመን፣ ቍልል (የእኸል፣ የሣር)

ጕነት፡ ንሮሽ (ጓነ)

ጕነጣ፡ የመጐነጥ ሥራ፡ ንቅነቃ።

ጕነፋ፡ ዐጠባ፣ ዕጀላ፣ ጠረባ፣ ድጐሳ።

ጕኒና፡ ከጠጕር (ከፈትል) (ከሣር) (ከሰሌን) የተበጀ የተቈነነ ቍንን ቆብ።

ጕናጕኒት፡ በደብረ ብርሃን እቅራቢያ ያለች አገር (ኮባ ያለባት) "ጕናጕናሚት" "መስኗሚት" ማለት ነው።

ጕናጕና፡ ቅጠለ ድርብርብ (ንብብር) (ኮባ)፡ ጭረቱ (ቃጫው) የሚጐነጐን።

ጕንም፡ ጕንጪ ትልቅ ሰው።

ጕንቍል፡ የጐነቈለ (የበቀለ) በቈልት፡ የተነከረ ዐተር (ባቄላ) (ሽንብራ)

ጕንብስ(ቅጽልና ጥሬ)

ጕንብራ፡ ዕንብርት (ጐበረ)

ጕንዳን (ኖች) (ጐነደ)፡ ጥሬ እኽል ለቀለቡ ባፉ እየያዘ ወደ ጕድጓድ የሚያገባ (የሚከት) (የሚጐደጕድ) (ጥቍር ተንቀሳቃሽ)፡ እንዳይነቅዝበት እየከካ በውጭ በፀሓይ ላይ የሚያሰጣ (አግዝ) (ገብረ ጕንዳን) በግእዝ "ቃሕም" ይባላል።

ጕንዳን፡ ተናካሽ፣ ተቈናጣጭ፡ ሥጋና ቅባት ወዳድ።

ጕንዳጕንዲት (ትግ ጐዳጕዲ)፡ ዐጤ ዮሐንስ ቱርክን ድል ያደረጉባት ጐድጓዳ ስፍራ።

ጕንድል (ሎች)፡ የተጐነደለ (ቍላው የወጣ)፡ ኵልሽ፣ ስልብ (ዶሮ)፡ እያስካካ እንደ እንስቷ ከነፋስ ዕንቍላል የሚወልድ (የሚጥል)

ጕንድሽ (ጐነደ)፡ እጁ ካንባር ያው የተቈረጠ ሰው (ማቴ፲፰:)

ጕንድብ፡ ዝኒ ከማሁ፡ የተጐነደበ፣ የተቈረጠ፡ ቍርጥ።

ጕንድብድብ፡ ጕርድርድ፣ ቍርጥርጥ።

ጕንዶ (ዎች) (ግንዶ)፡ ከግንድና ከቀንድ የተበጀ (ጥንታዊ) የማር መስፈሪያ፡ ቀንዶ። "ጕንዶ ማር እሰጥ" እንዲል ተጋች።

ጕንጕናት፡ የጕንጕን ሥራ።

ጕንጕን፡ ሽሩባ (መሳ፲፮:፲፫:፲፱)

ጕንጕን፡ የተደራረበ፣ የተነባበረ (ኢዮ፵:)

ጕንጕን፡ የተጐነጐነ (የተወሰበ) ጠፍር፣ ገመድ፣ ሽቦ፣ ፈትል፣ ጠጕር፣ ዥማት፣ ሢር፣ ሰርዶ፣ ሰሌን፡ ትት፣ ቍንን።

ጕንጕን፡ ድፍድፍ።

ጕንጕኖች፡ የተጐነጐኑ ገመዶች፣ ጌጦች (፩ነገ::፵፩:፵፪)

ጕንጐና፡ ጠለፋ፣ ቋጠራ፣ ድፍድፋ።

ጕንጥ፡ የተጐነጠ፣ የተነካ።

ጕንጨ፡ የሰው ስም፡ ጕንግም።

ጕንጨ፡ የኔ ጕንጭ።

ጕንጨፋ፡ ሽምጠጣ፣ ዥምገጋ።

ጕንጩን ወጠረ፡ ነፋ (በውሃ፣ በትንፋሽ)

ጕንጪት፡ ጕንጫሚት።

ጕንጭ (መልታሕት)፡ ያፍ ጓዳ (የምግብ፣ የመጠጥ መያዣ ቋት) (ኢሳ፶:፮፣ ሰቈ፩:)

ጕንጭ አለ፡ ካፍ ወደ ጕንጭ፣ ከጕንጭ ወደ ጕረሮ አገባ (ውሃን)

ጕንጭና ጕንጭ፡ ባፍ ግራና ቀኝ ያሉ ኹለቱ (ማሕ፬:፫፣ ::፲፫)

ጕንጮች፡ ኹለትና ከኹለት በላይ ያሉ (ዘዳ፲፰:)

ጕንፋት፡ ዕጥበት፣ ዕጅላት፡ ሕንጻ (ቅርጽ)፡ ድጕሰት፣ ድጕሳት።

ጕንፋናም፡ ባለጕንፋን፡ "ኡሁ ኡሁ" የሚል።

ጕንፋን (ትግ ጕንፋዕ)፡ የበሽታ ስም፡ በክፉ ሽታና በብርድ የሚነሣ (የሚያስል) (የሚያስነጥስ) (ትኵሳታም) (ንፍጣም) ሕመም፡ እስከ ቀን ከጭንቅላት ንፍጥን የሚያወርድ (ባፍንጫ የሚያንቈረቍር) (ከዚያ በኋላ የሚበስል)

ጕንፍ፡ የተጐነፈ ሸክላ፡ የዘንጋዳ ጠቈርት፡ ጥርብ የመጣና ገበታ ድጕስ።

ጕኝር፡ የተጐኘረ (በስልቻ የተመላ) (ዘኬ)

ጕዉ፡ ጕብሯ፣ የርሷ ጕጥ።

ጕዛ፡ የአሞራ ስም፣ ቀደደ።

ጕዝጕዝ አለ፡ ተጐዘጐዘ፡ ንስንስ አለ።

ጕዝጕዝ፡ የተጐዘጐዘ፣ የተነሰነሰ፣ ንስንስ፣ የተሿሚ ማረፊያ ቤት።

ጕዝጐዛ፡ ብተና፣ ምንዘራ፣ ንስነሳ።

ጕዝጓዝ (ዞች) (ጐዘጐዝ)፡ ደረቅና ርጥብ ሣር።

ጕዞ፡ የግሥገሣ ተቃራኒ። ዘገምታ፣ ቀስታ፣ ቀስ፣ ዝግ ብሎ መኼድ። ነገሥታትና መኳንንት ጧት ከ፪ ሰዓት እስከ ሰዓት የሚያደርጉት ርምጃ። (ተረት)"ምን ይዞ ጕዞ"

ጕዞ ፍታት፡ የጕዞ ፍታት ባለ፯ ማረፊያ።

ጕያ፡ በግእዝ "ሽሽት" ማለት ስለ ሆነ፣ የሕፃን መሸሻና መደበቂያ መሆኑን ያስረዳል። "አንተ ልጅ ዛሬ እናትህ ጕያ ብትገባም አታመልጠኝም" እንዲል ባላገር። (ተረት)"ወዳጅ ይመጣል ከራያ፣ ጠላት ይወጣል ከጕያ" (፪ሳሙ፡ ፲፭--፲፪)

ጕያ፡ የተጕለት ውስጥ በታችኛው ወግዳ ባሻገር ያለ አገር ስም። "ሽሽ፣ ሩጥ" ማለት ነው።

ጕያ፡ የጭንና የጭን ውስጥ መካከል። "እናት ጕያ" እንዲሉ።

ጕይ ማጋ (ጕይማጋ)፡ ማጋ ጕይ፡ "ወደ ማጋ ሽሽ" አቀማመጡ የማግ ልታቂት የሚመስል ባናቱ የጊዮርጊስ ታቦት ያለበት ረዥምና ሾጣጣ ዐምባ፣ የጕይ ተራራ "ወደ ሰማይ የተንጠራራ" "ጕይ ማጋ ጊዮርጊስ" እንዲሉ።

ጕይዲ ጎን በለው፡ የባሌ ንጉሥቍንዶ በርበሬይለዋል።

ጕደሪ፡ የመከር ዐውሎ ነፋስ፣ ክረምት ውጭ ከሰሚን የሚነፍስ። ሥሩ ጐደራ ስለ ሆነ ጩኸቱን ያሳያል።

ጉዲት፡ ጕዲት (ይሁዲት፣ ዮዲት)፡ በ፰፻፺ .. የኢትዮጵያን መንግሥት በተንኰሏ ነጥቃ ዓመት ስለ ነገሠችና ከርሷ በፊት የነበረውን እውነተኛውን የሳባ፣ የግእዝ ታሪከ ነገሥት እያቃጠለች ባላባቶቹን ስለ ኀደለች፣ "ጉደኛዋ ጉደኚት" እንደ ማለት፣ "እሳት" ጉዲት ተብላለች።

ጕዳሌ፡ አእምሮን የሚያጐድል በሽታ ወይም ጋኔን።

ጉዳምጕደኛ (ኞች)፡ ድንቀኛ፣ ታምረኛ፣ ጉድ አድራጊ፡ ባለጉድ፣ ነውረኛ።

ጕዳተኛ (ኞች)፡ ራብተኛ፣ ችጋረኛ፣ ከሲታ፣ ዕርዝተኛ።

ጕዳት (ጕድዐት)፡ ችጋር፣ ራብ፣ ክሳት፣ ንጣት (ኢሳ፶፱:)

ጕዳይ (ዮች)፡ የጐደለ ክፍል (ለምሳሌ፡ - "ለ፯ ሰዓት ሩብ ጕዳይ እመጣለሁ")

ጕዳይ፡ ቁም ነገር (፪ዜና ፱፡ ፳)

ጕዳይ፡ ተፈላጊ ሥራ ወይም ነገር። "አንተ ዘንድ ጕዳይ አለኝ" እንደሚባለው።

ጕዳይ ፈጻሚ፡ ነገር ጨራሽ።

ጉዳጉድ፡ የጉድ ጉድ፡ ፈናፍንት።

ጉዴላ፡ በከንባታ ወረዳ ያለ የነገድና የአገር ስም።

ጉድ (ጕድ ድሮች)፡ ተኣምር፣ ግሩም፣ ዕጡብ፣ ድንቅ፣ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ፣ ዐዲስ ነገርና ሥራ።

ጉድ፡ ኀላፊ ወሬ። (ግጥም)"እቴ ብንጋባ ምነው፡ ጉድ አንድ ሰሞን ነው"

ጉድ፡ ነውር፣ መጥፎ ነገር፣ ከሰውና ከእንስሳ ሆድ የሚወጣ፣ የሚወሰድ ወሬውን ሊሰሙት፣ ኹናቴውን ሊያዩት የማይገባ። "ጉድ ኾነ! ጉድ ፈላ፣ ጉድ ተወለደ፡ ጉድ ታየ፡ እከሌ በገድ ወጣ" እንዲሉ። በቃለ አጋኖ ሲነገር "ወይ ጉድ፡ ወይ ጉዴ፡ ላግባሽ አለኝ ነጋዴ" ይላል።

ጉድ አወጣ፡ የሰውን ነውር ገለጠ።

ጉድ አደረገ፡ ሰረቀ፣ አታለበ።

ጕድለት፡ ጐደሎነት ወይም የጠባይ ስህተት።

ጕድል (ጐዲል)፡ ቅምጥል ወይም መጕደል።

ጕድል አለ፡ ቅምጥል አለ፣ ጐደለ፣ ወይም ተቀመጠለ።

ጕድሩ፡ በወለጋ ክፍል የሚገኝ አገር ስም። "ጕድሩ ቢጋልኛ" ቍንጮ ማለት ነው።

ጕድባ (ቦች)፡ ዕርድ፣ ፈፋ፣ ሰው ወይም ውሃ ያረያው፣ ያጐደጐደው።

ጕድብ (ጥድ)፡ የተጐደበ፣ የጐደጐደ፣ ዕርድ፣ ቍፍር፣ ፈፋ።

ጕድብ፡ ስለትና ሹለት ያለው ዶማ (ግእዝ)

ጕድኝ (ኞች)፡ በወንዝ ዳር የሚበቅል የደጋ ቅጠል ሲሆን ከብት ሲበላው ይገድላል። በቁስል ላይ ሲታሰርም ህመም ይፈጥራል። "ጕደኛ" ከሚለው ቃል ጋር ይመሳሰላል።

ጕድጕድ፡ ሥርጕድ።

ጕድጕድ፡ ሮጥ ሮጥ።

ጕድጕድ አለ፡ በጓዳ ሮጠ፣ ተንጐዳጐደ።

ጕድጕድ አለ፡ ጐደጐደ፣ ተሠረጐደ።

ጕድጓድ (ዶች)፡ የተማሰ፣ የተቈፈረ፣ የተጐደበ፣ ያውሬ፣ የእህል፣ የሬሳ ቤት፣ ውሃ የሚቀዳበት፣ ዐዘቅት፣ ሸማኔ ሸማ የሚሠራበት።

ጕድፈራ፡ ቍፈራ፣ ምንቀራ፣ ብተና።

ጕድፋም፡ ጕድፍ ያለበት ወይም እድፋም።

ጕድፍ (ፎች)፡ የሣር፣ የገለባ፣ የእንጨት፣ የቅጠል፣ የድንጋይ፣ ወይም የአፈር ድቃቂ። በተጨማሪም በምግብና በመጠጥ ውስጥ የሚገባ ማንኛውም ነገር።

ጕድፍ መጣያ፡ ቆሻሻ ማኖሪያ ስፍራ (ኤር፳፭፡ ፴፫)

ጕድፍ፡ ፍግ፣ ፋንድያ፣ በጠጥ፣ ዐመድ፣ ወይም የቤት ጥራጊ የፈሰሰበት ደጅ ("ባዶ እልፍ የመምሬን ጠላት አንጠልጥሎ ወደ ጕድፍ እንዳይመለስ በብረት ቍልፍ" እንደሚባለው)

ጕዶ፡ አፋ ጩቤ፡ ማረጃና መጕጃ ማለት ነው።

ጕጆ፡ የዛፍ ስም፡ የግራዋ ዐይነት እንጨት።

ጕጉ (ጕጉእ)፡ የጓጓ፣ የከጀለ፣ ጐምዢ።

ጕጕ (ጕጋ)፡ ስትጮኽ የምትቸኩል የሌሊት አሞራ፣ ድመት መሳይ። ሌሊት ቀኑ፣ ቀኑ ሌሊቱ። በጩኸቷ "ጐትት" የምትል፣ ስለዚህ ባላገሮች ሰው ይሞታል ይላሉ (መዝ፻፪:)

ጕጕ() (ቶች)፡ ጕጕእት።

ጕጕለት፡ የደም መርጋት፣ ጓጓላነት።

ጕጕማት፡ ቀላል ውግታት፣ አወጋግ።

ጕጕም፡ የተጐጐመ፣ የተወጋ፡ ልትም።

ጕጕት (ጕጓኤ)፡ ክጀላ፣ ሥየታ፣ ጕምዠታ፣ ፍላጎት።

ጕጕት፡ አሞራ (ጓጓ)

ጉጉግ፡ የአሞራ ስም (ዘሌ፲፩:፲፮)

ጉግሳ፡ የሰው ስም፡ "የጁዬ ጉግስ ዐዋቂ፣ ባለጉግስ" የጉግስ ጌታ ማለት ይመስላል። "ጉግሳ አርአያ" እንዲሉ።

ጉግስ (ጎግ)፡ የጨዋታ ስም፣ የፈረሰኞች ጨዋታ፡ የጦርነት ምሳሌ (ማሸነፍና መሸነፍ፣ ማሳደድና መሻሽ፣ በዘንግ በሸንበቆ መውጋትና መወጋት ያለበት)

ጕጐማ፡ ልተማ።

ጕጠታፍ (ጕጠት አፍ)፡ ሹላፍ፣ ነገረኛ፣ በነገሩ ሰውን የሚነካና የሚጐዳ ክፉ ሰው።

ጕጠት (ቶች) (ጐጠየ)፡ በእሳት የጋለ ብረት መያዣ፣ መቆንጠጥ፣ በስተፉ በምስማር የታጋጠመ መንታ ብረት።

ጕጠት፡ ችንካር፣ መንቀያ፣ ፈቸል።

ጕጣ (ቍጥ)፡ ዕላቂ ማረሻ። (ተረት)"በጕጣ ያረሰ፡ ሲፈራ የከሰሰ"

ጕጣ፡ ንአስ እስኪት።

ጉጣ፡ ዕላቆ፣ ማረሻ።

ጕጣ፡ ዕላቆ፣ ማረሻ፣ ጐጠጐጠ።

ጕጣም፡ ጕጥ ያለው ዕንጨት፣ እጅ፣ ባለጕጥ።

ጕጣጕጥ፡ የጕጥ ጕጥ፣ ገ።

ጕጥ፡ የንጨት ዐይን፣ ጐጠጐጠ።

ጕጥ፡ ጕብር፣ የንጨት ዐይን። በስተውስጥ ዐብጦ የደረቀ የውስጥ እጅ ሥጋ፡ የድር ቋር።

ጉጥ፡ ጕብር፣ ጐጠጐጠ፣ ጕጥ።

ጕጥር፡ የተጐጠረ፣ ጕስር፣ ጕኝር።

ጕጥጐጣ፡ መዘዛ፣ ነቀላ።

ጕጦች፡ ጕብሮች፣ ቋሮች።

ጕጭ፡ ማንቍርት።

ጕጭ፡ ማንቍርት፣ ጐጠጐጠ።

ጕጭማ (ሞች)፡ የጕጭ፣ የዶማ ዕላቂ ብረት።

ጕጮ፡ አጭር ሣር፣ ጠጕር፣ ጠፍ።

ጉፋ፡ የደጋ አባሎ፡ ፍሬውን አሳርሮ ከቅቤ ጋራ ቢቀቡት (ቅጠሉን ዘፍዝፎ ብልትን እንዳይነካ ተጠንቅቆ ቢታጠቡበት) ለዕከክ መድኀኒት ይኾናል።

ጕፋያ (ዮች)፡ ዕብ፣ ጉፍ፣ ሥጋ)፡ ያልሠባ፣ ያልጮመየ ቀይ ሥጋ፡ ወይም በሬ።

ጉፍታ፡ የስላም ሴት ራስ ማሰሪያ (ቀለም የገባ ወይም ቅቤ ጠገብ ጨርቅ) (የጠጕር መሸፈኛ) "ኩፌትን" እይ።

ጕፍጥጥ አለ፡ ጭብጥ አለ።

ጕፍጥጥ፡ ዝኒ ከማሁ።

ጊሆን፡ የደጋ አባሎ፡ ጉፋ።

ጊሚራ፡ በከፋ ክፍል ያለ የሻንቅላ ነገድና አገር። "ሺዋን" ተመልከት።

ጊሚሮች፡ የጊሚራ ሰዎች።

ጊኒ (ዐረ ጀኒህ)፡ የወርቅና የወረቀት ገንዘብ፡ በምንዛሪ ያንዱ ዋጋ ካሥር ብር ይወጣል፣ ይወርዳል። "የምስር" "የንግሊዝ" "የቱርክ ጊኒ" እንዲሉ።

ጊኒ (ጥኒ)፡ ያገር ስም (ገነነ)

ጊኒ፡ ያገር ስም፡ አሳግርት አጠገብ ያለ (ወረዳ) "ጊኒ አገር" እንዲሉ።

ጊንር፡ በባሌ ክፍል ያለ ተራራ።

ጊንጣም፡ ጊንጥ ያለበት (የበዛበት) ስፍራ።

ጊንጥ፡ በዥራቱ የሚነድፍ፣ ባፉ የሚነክስ (ባለ፯ ክርክር) (መርዛም) (ተንቀሳቃሽ) (የምድር አውሬ)፡ ዘሩ "ጐነጠ" ነው (ዘዳ፰:፲፭) "ሴትና ጊንጥ በቂጥ" እንዲሉ።

ጊንጦች፡ ተናዳፎች (መርዘኞች)፡ የክፉዎች ሰዎችና ያጋንንት ምሳሌዎች (ሕዝ፪:)

ጊዜ (ዎች)፡ ዘመን፣ ዓመት፣ ወር፣ ቀን፣ ሰዓት፣ አፍታ።

ጊዜ፡ ፀሐይ ሳለ፣ ሳይመሽ፣ ሳይጨልም። "እንግዳ በጊዜ መጣ"

ጊዜዋ (ጊዜሃ)፡ ያች ጊዜ፡ የርሷ ግዜ፣ የርሷ ዘመን።

ጊዜው፣ ጊዜዋ፡ ያች ጊዜ፡ የርሷ ግዜ፣ የርሷ ዘመን።

ጊዮርጊስ፡ የሰው ስም፣ የጽርእ ሰው በልዳ የተወለደ ሰማዕት፣ ባለዐምባላይ ፈረስ፡ የሰማዕታት አለቃ፣ ቢሩታይትን ከደራጎን አፍ ያዳነ። ትርጓሜው "ዐራሽ ገበሬ" ማለት ነው ይላሉ።

ጊዮርጊሶች (ጊዮርጊሳውያን)፡ የጊዮርጊስ መቅደስ አወዳሾች፣ ካህናት።

ጊደራች፡ በይፋት ውስጥ ያለ አገር።

ጊደር (ሮች)፡ አውራ ለመሸከምና ለመጠቃት፣ ዘር ለመቀበል የምትችል ድርስ ከብት (፩ሳሙ ፲፬፡ ፴፪) በጕራጌ "ጐበዝ" ትባላለች።

ጊድረኛ፡ ተንኰለኛ፣ ጥመመኛ።

ጊድራ (ኦሮ)፡ ተንኰል፣ ክፋት፣ ጥመት።

ጊጋር፡ የሰው ስም፡ ሰማዕት፡ እመቤታችን በተሰደደች ጊዜ ስንቅ ሰጥቶ የሸኛት የሶርያ መስፍን።

ጊጋር፡ የአንጥረኛ ወረንጦ፣ መቈንጠጫ።

ጊጤ (ዎች) (ጐጠየ፡ ጋየጸ)፡ በሹል ዘንግ የሚወጋ ቍልቋልና የእንዶድ ወይም የሬት ሥር። "ጊጤ" በግእዝ "ቃፍ መጠራ" ይባላል። እንደ ይላማ የጦር አወራወርና አወጋግ ልጆች ይማሩበታል።

(እነት): አንድ ጋ።

: በቃል መጨረሻ እየገባዘንድና አጠገብስፍራ ይሆናል። ምሳሌ:እኔ ጋ፣ አንተ ጋ፣ እሱ ይላል። ጌን ይመልከቱ፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።

ጋለ (ጕሒል፣ ጐሐለ) (ዕብ፡ ጋሓል)፡ ጋመ፣ ሞቀ፣ ሠማ፣ ተኰሰ፣ እሳት መሰለ። "ጋየን" እይ፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።

ጋለ፡ ከበረ፣ ገነነ። "ያቶ እከሌ ቤቱ ገሏል"

ጋለሞታ፡ እይ፣ ገለሞተ።

ጋለበ፡ ሸሸ፣ በረረ፣ ሮጠ፡ ፈረጠጠ፣ ወነበደ፣ ሸመጠጠ (በፈረስ፣ በበቅሎ ተቀምጦ) (ቂጡን ገልቦ)፡ ሰው፡ ዥራቱን፣ ጭራውን ለብሶ (ከብቱ)

ጋለባ፡ ሶምሶማ፣ ሽምጥ። (ተረት)"ልባልማ ታጥቆ ዐዛባ፣ ሱሪ አውልቆ ፈረስ ጋለባ"

ጋሊት፡ ብረት (ኦሮ)

ጋል (ግሒል)፡ መጋል።

ጋል፡ መሃል እጅ ውስጥ እጅ፡ ገላ ጠፍጣፋ ማለት ነው፣ "ገለለን" እይ።

ጋል ጋል አለ፡ ባለማቋረጥ ኃይለ ቃል ተናገረ።

ጋልማ፡ እንደ ጋል፡ የጋለ። ፈረንጆች "ጋሌ" ይሉታል።

ጋልማ፡ ውስጥ እጅ፣ ጋል።

ጋሎች፡ የያዙትን አገር ሁሉ በአባቶቻቸው ስም ሰይመውታል። "የጻድቁ ዮሐንስ ታሪክ ግራኝ አማራን በወጋ ጊዜ አሮ የአማራን አገር ሁሉ ያዘ" ይላል።

ጋመ (ግሒም፣ ግሕመ)፡ ፋመ፣ ጋለ፣ ሞቀ፣ ተኰሰ፣ ተቃጠለ። ትግሬ ግን "ገሐመን ጠፋ" ይለዋል፡ መክሰልን፣ መጥለስን ያሳያል። "ሠማን" እይ።

ጋመረ፡ አደገ (ገመረ)

ጋመረ፡ አደገ፣ ጐለመሰ፣ ጠና።

ጋመረች፡ ዘር ለመቀበልና ለማርገዝ ደረሰች፣ ጠናች፡ ልጅነቷ ዐለቀ፣ ተፈጸመ። ("ጋመረች" "አሳጣች" ከማለት ይስማማል)

ጋመን (ጋበን)፡ ግመት (ሐሩር፣ ሙቀት፣ ወበቅ)

ጋመኛ፡ የሜዳ ስም፡ ባንኮበር ክፍል ያለ ስፍራ።

ጋሙዳ፡ ራብተኛ፣ ችጋራም፣ በገ ፈጅ፣ ቍና ፈጅ።

ጋሙድ፡ ራብ (አንዠት የሚገምድ፣ የሚያጥመለምል)

ጋሚ፡ የሚግም፣ የሚፍም (ዕንጨት፣ ኵበት፣ ከሰል)

ጋሚቶ፡ የማሽላ በሶ (ኑግና በርበሬ ያለበት) (ሻሜት)፡ የፈረሳቤት መድኃኒት።

ጋማ (ሞች)፡ የግመል፣ የፈረስ፣ ያህያ፣ የበቅሎ ማዥራት ጠጕር፡ ወይም ጭራ።

ጋማ ከብት (የጋማ ከብት)፡ ፈረስን፣ አህያን የመሰለ የቤትና የዱር እንስሳ (ኣውሬ) (ያውሬው ከብትነት ተይዞ ለማዳ ሲኾን ነው)

ጋማ፡ የገብስ ስም ("ጋማ" የሚመስል ገብስ)

ጋማ፡ የፊደል ስም ''

ጋማ፡ ግመል (የቤት እንስሳ)

ጋማማ፡ ጋማም (ብዙ ጋማ ያለው)፡ ባለጋማ። "አንበሳ ጋማማ" እንዲል መስታዽርት።

ጋሜ (ትግ ጋማ)፡ ገርዳሳ። "ጉሜን" እይ (ጎመ)

ጋሜ (ዎች)፡ መካከሉ ተላጭቶ በራስ ዙሪያ ያለ (እንደ ጋማ የቆመ)፡ ጋማዊ (የወንድና የሴት ልጅ ጠጕር)

ጋሜ፡ የዛፍ ስም፡ ደጋን የሚኾን ዕንጨት። "ጋሜ ያሠኘው መጕበጡ ነው"

ጋሜ፡ ጋሜ ያለው (ባለጋሜ)፡ ታናሽ ልጅ፣ አሽከር። (ግጥም)"አያችኹት ቢያ ይኸን እብድ፡ ዐምስት ጋሜ ኹኖ ጕር ዐምባ ሲወርድ" (ጋሜ ለሴት ልጅም ይነገራል)

ጋምጨ፡ ጅር የሌለው ዝንጀሮ (ስጥ)፡ የሚቀማ፡ ቢይዙት የሚገምጥ ቦለዴ።

ጋሰሰ: ነቀለ፣ ጋፈፈ፡ ደፈረ።

ጋረ (ግዒር፣ ገዐረ): ተጨነቀ፡ የጭንቅ ጩኸት ጮኸ፡ ጣረ፣ አለቀሰ። "ገረረን" ተመልከት።

ጋረኛ: የተጨነቀ፣ ጣረኛ።

ጋረኛነት፣ ጋረኝነት: ጣረኝነት።

ጋረደ (ገልዶ፣ ገለዶ): ከለለ፣ ጠለለ፣ ሸፈነ፣ ሰወረ፡ መከተ፣ ዘረጋ። "ቀየደን" እይ።

ጋረዴ: ጋረደው፡ የሰው ስም፡ "ክልሌ" "ከለለው" "ሰወረው" ማለት ነው።

ጋረድ: ዝኒ ከማሁ።

ጋረጠ (ጐረጸ): ወጋ፣ ሰካ፣ ሻጠ፡ ተከለ፡ ቀደደ፣ ፈቃ፣ በጣ፣ ቈራ።

ጋሪ (ዎች): በመንኰራኵር የሚኼድ (በቅሎ፣ ፈረስ፣ ግመል፣ ባቡር) የሚስበው፣ የሚጐትተው፡ የሰው መቀመ፵፣ የዕቃ መጫኛ (ከብረት ከሳንቃ ባጐበርና በቤት አምሳል የተሠራ) ሠረገላ (፪ና ከዚህም በላይ እግር ያለው) ዘሩ "ገረረ" ነው።

ጋሪ (ገዓሪ): የጋረ፣ የሚግር፡ ጯኺ።

ጋሪባልዲ: የምድርን መዞር የፀሓይን አለመዞር የተናገረ የጣሊያን ፈላስፋ፡ እንደ ፈረንጅ አቈጣጠር ባ፲፰፻፯ . . ተወለደ፡ እስካ፲፰፻፹፪ . . ነበረ።

ጋሪያታሞ: ባለጋሪያት፡ ጯኺ፣ ቍጡ።

ጋሪያት ቍጣ: ጋረ።

ጋሪያት: ቍጣ፣ ብስጭት።

ጋራ (ምስለ): አንድነት፣ ማኅበር፣ ሱታፌ፣ ጭምር (ዘዳ፳::፫፣ ማቴ፭:፳፬) "" በማድረጊያነት፣ "" በቅጽልነት፣ "" በመነሻነት ቀድመው እየገቡ ይሰማሙታል።

ጋራ አንድነት: ገራ (ገርዐ)

ጋራ: በጋልኛ ተራራ ይኾናል፡ "ጋራ ሙለታ፣ ጋራ ቁፋ" እንዲሉ (የሐረርጌ አውራጃ ሰዎች)

ጋራ: እጋልኛ መኾኑን ያላወቁ አንዳንድ ጻፎች ግን ዐማርኛ መስሏቸው "ከማክበር ሰላምታ ጋራ" በማለት ፈንታ "ጋር" እያሉ ይጽፋሉ። "ጋር" ጩኸት ማለት ነው እንጂ እንደነሱ ሐሳብ አንድነት ማለት አይዶለም።

ጋራጅ (ጆች): የጋረደ፣ የሚጋርድ አሽከር፡ ከላይ ሰዋሪ። "አንጣፊ ጋራጅ" እንዲሉ።

ጋራጭ: የጋረጠ፣ የሚጋርጥ፡ ወጊ፣ በጪ።

ጋሬ (ዎች) (ገዓራዊ): የዘንጋዳና የገብስ ቅይጥ (መናኛ እንጀራ) (በመያዣ ሥር አስቀድሞ የሚጣል) የገበታ ጕዝጓዝ፡ "ጥሮ ግሮ የሚበላ" ማለት ነው።

ጋሬ (ገዓርየ): ጩኸቴ፣ የኔ ጩኸት፡ የወፍጮውንም ድካምና እምምታ ያሳያል።

ጋሬዳ (ግዝእ): ጐዶ ውርርድ፡ የዋዛ ፈዛዛ መብል መጠጥ፡ "ዳስ ተጥሎ ቅጠል ተጋርዶ""ነገ ባንዱ ቤት ተነግ ወዲያ በሌላው ቤት የሚበላ"፡ ድኻ አይቀምስሽ ምግብ፡ ርኩስ ማኅበር (ዘዳ፳፩:)

ጋሬጣ: ሥንጥር፣ ሥንጣቂ (የግራጭ (ዣርት) ወስፌ) እሾኸ (እግርን፣ ልብስን የሚቀድ፣ የሚሸረክት)

ጋሬጣ: አፈኛ፣ ነገረኛ፣ ክፉ ሰው።

ጋር (ገዓር): ጋራ (ምስለ)

ጋር (ገዓር): ጭንቅ ጩኸት፣ ጣር (የመከራ ድምፅ)

ጋርኖ: በበጌምድር ውስጥ ያለ ተራራ። "አርኖ ጋርኖ" እንዲሉ።

ጋርዱላ: ያገር ስም፡ በኦሮ ቤት በገሙ ክፍል ያለ አገር።

ጋርዱሎች: የጋርዱላ ተወላጆች።

ጋሸበ: አደገ፣ ረዘመ፡ ወደቀ፣ ተኛ። ከዚህ የተነሣ ፍሬ ዐጣ፡ ፍሬ ቢስ ኾነ።

ጋሸኛ (ኞች): ጋሻም፣ ባለጋሻ፡ ኀይለኛ፣ ጦረኛ፣ ስመ ጥር፡ በግእዝ "ያርብሓዊ" "አጋራዊ" ይባላል።

ጋሸኛነት: ዠግንነት፣ ሐርበኝነት።

ጋሻ (ሾች): ወልታ፣ ሐገፋ (ዮሐ፲፰:)፡ ከጐሽና ከጕማሬ፣ ካውራሪ፣ ከዝኆን ቈዳ የተበጀ የዠግና መከታ። ትልቁ "አግሬ" ይባላል።

ጋሻ (የረኛ)

ጋሻ (ገያሣ): ገሥጋሽ ከማለት የወጣ ነው፡ ትግሬ "አንግዳ" ሲል "ጋሻ" ይላልና። "ጣፋን" "ሻንቆን" እይ።

ጋሻ ለበሰ: ጋሻን በላይ ሰውነቱን በታች አደረገ።

ጋሻ ዣግሬ (ዣግሬ ጋሻ): የንጉሥ፣ የሻለቃ ጋሻ ተሸካሚ ጐበዝ። "ጋሻ ዘአግሬ" ቢል፡ "አግሬ" የሚሳል፡ ወይም "ዣግር" (ጋሻና ዘገር ያዥ) (፩ነገ፴፩:-) "አግሬን" "ዣግሬን" ተመልከት።

ጋሻ ዣግሬዎች: ብዙዎች ጋሻ ተሸካሞች፡ የጋሻ ዣግሬ ጭፍሮች።

ጋሻ: ኀይል፣ ጕብዝና፣ ወኒ። "እከሌ የእከሌን ጋሻ አነሣ (ወረሰ)"

ጋሻ: በገመድ ተለክቶ ለዘማች የተሰጠ ቀላድ መሬት። ዘመቻው "ዘገር ነጥቆ ጋሻ አንግቦ" ስለሆነ መሬቱ "ጋሻ" ተባለ። "ቀላድን" ተመልከት።

ጋሻ: በጦርነት ጊዜ የጋሻ መካች ምድር።

ጋሻ: እንጕዳይ። "የረኛ ጋሻ" እንዲሉ። በትግሪኛም (ዋልታ ምድሪ) "የምድር ጋሻ" ይባላል።

ጋሻ: ዘማች ወታደር (ነፍጠኛ) ሚስት፣ ልጅ፣ ቤተሰብ ያሉት። "ጠልጠሌ ወንደ ላጤ ያይደለ" "ጓዝ ተጋሻ" እንዲሉ።

ጋሻ: የደረሰ አሽከር፣ ልጅ፣ እግር። "ማር ተጋሻ" እንዲሉ። ማር መብላቱንና ጋሻ መሸከሙን ያሳያል።

ጋሻ: የጦር ዠብዱ። "እከሌ እከሌን በጋሻ ይበልጠዋል" "ወይ ጋሻ፣ ዱሮ ቀረሻ"

ጋሼ: የታላቅ ወንድም መጠሪያ ስም። "ጋሻዬ" "የኔ ጋሻ" ማለት ነው።

ጋሾ ዐምባ: ያገር ስም (በይፋት ወረዳ ያለ) አገር። "ጋሼ" የሚባል ሰው ዐምባ (መንደር) የነበረበት።

ጋሾጥ (ጋሾ ጥግ): ያገር ስም (በላይኛው ወግዳ፣ በገደል ሥር ያለ) ቀበሌ። ጥንት "ጋሼ" የሚባል ሰው የነበረበት። "ጋሾጥ ማሪያም" እንዲሉ።

ጋበሰ) አጋበሰ፣ ጋፈፈ፣ አጓለበ፣ ሰበሰበ (የሣር፣ የገለባ፣ የጭራንፎ)

ጋበን(ጋመን)፡ ሐሩር፣ ሙቀት፣ ወበቅ።

ጋበን፡ ዕሩር። በና፡ መ፡ ተወራራሾች ስለ ኾኑ፡ በጋበን ፈንታ ጋመን ይላል።

ጋበዘ (ሰዋስው): በራብዕ ተነሥቶ በመደራረግና በማደሪረግ ጊዜ ሥርወ ቀለሙ ግእዝ እንደሆነ ልብ ይሏል።

ጋበዘ (ገበዘ): ወደ ማዕድ ጠራ (አበላ፣ አጠጣ፣ አስተናገደ) ተረት:ባለቤት ቢያፍር እንግዳ ይጋብዝ ማስታወሻ: "ጋበዘ" ማለት ለምግብ ብቻ ጠራ ማለት ነው፡ ለሌላ አይሆንም። ሌላ ትርጉም: ጠብን ከለከለ (ተው ይቅርብህ አለ)፡ ገላገለ፡ ሰላምን ሰጠ

ጋቢ: ወፍራም ሸማ፡ የሌሊትና የቀን ተገቢ ልብስ፡ ጥለት የሌለው ረዥም ኩትኛ ወይም ዝቅዝቅ።

ጋቢ: የልብስ ስም ነው።

ጋባዤ: ዝኒ ከማሁ፡ የኔ ጋባዥ።

ጋባዥ (ዦች): የጋበዘ (የሚጋብዝ)የሚያመሳአስታራቂ (አብላ፣ አጠጪ፣ አስተናጋጅ)ከልካይ (ተው ባይ) ሌላ ትርጉም: የሰው ስም።

ጋባዥነት: አብላ አጠጪነት።

ጋብ (ጋብኦ): መመለስ (መተው፣ ምላሳ)

ጋብ አለ: ተመለሰ (ተወ፣ ቆመ)፡ ቍጣው በረደ።

ጋብር (ትግ)፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አቦ።

ጋብቻ፡ በቁሙ፣ ገባ።

ጋብቻ: ተክሊል (ሩካቤ፣ ዕምረት) ሙሽራው ወደ ሙሽራዋ ቤት፣ ሙሽራይቱ ወደ ሙሽራው ቤት መግባታቸውንም ያሳያል።

ጋተ (ገዐተ): ለሕፃን፣ ለበሽተኛ፣ ለጥጃ ውሃን፣ ወተትን በጋት፣ በቅል ዐንገት ግዴታ ጭምር አጠጣ፣ አስጐነጩ (፩ቆሮ፫:)

ጋተ: በጥፊ መታ፡ የጋት ምስጢር አለበት።

ጋተለ: ተሰበሰበ፣ ታከበ፣ ተያዘ።

ጋተሎ: ግትል፡ ስብስብ፣ ታላቅ ሸክም።

ጋተው: የፈረስ ስም። "አባን" እይ።

ጋቴራ: ጣፋ ጋሻ፡ ቁመት ሙሉ (ሾጣጣ)፡ አግሬ (ከጕማሬ ቈዳ የተበጀ)፡ ሲሰጐድ የተወጠረ፡ ወይም ተሸላሚው ይዞት የሚቆም።

ጋት (ጋዕት): ውስጥ እጅ፣ መዳፍ፣ ጥርኝ፡ የክንድ ፮ኛ ልክ (ዘፀ፳፭:፳፭)

ጋች (ገዓቲ): የጋተ፣ የሚግት፡ አጠጪ።

ጋነ ገብ፡ የመንግሥት ምስለኔዎች ግዛት (ዐላባው ኹሉ በወር ተራ ወደ ንጉሥ ማድ ቤት የሚገባ) "ጋነ ግብ" ያሠኘው ማሩ፣ ጌሾው፣ ዐሻሮው ነው።

ጋኔል፡ ጋኔን (ገነነ)

ጋኔናም፡ ጋኔን ያደረበት።

ጋኔን (ኖች)፡ ክፉ መንፈስ (ጅን)"ይህን ዓለም በጨለማ የሚገዛ" (በክፋት የገነነ)፡ የግዜርና የሰው መዠመሪያና መጨረሻ ጠላት፡ በላይ በታች የሚገኝ ("ያየር ጋኔን"፡ ባየር የሚኖር) ("የጕድፍ ጋኔን"፡ ልክስክስ በጕድፍ የሚውል) ሰይጣን። በን ፈንታ ባላገር "ጋኔል" ይላል።

ጋኔን ሳቢ፡ ጋኔን ጐታች።

ጋኔን ዐደረበት፡ ገባበት፣ ተዋሓደው።

ጋኔን፡ ክፉ ሰው።

ጋኔን ጐታች፡ አስማተኛ፣ ጠንቋይ። "እሰግድ ለግልፎ" ብሎ ማተቡን በጥሶ ዕራቍቱን ኹኖ ጋኔን የሚስብ፡ ሳቢ፣ ኣነጋጋሪ።

ጋኔን ጣለው፡ ሰውየውን ጋኔኑ ከመሬት አወደቀው፣ መታው፣ አንደባለለው፣ አንከባለለው፣ ቈበር አስደፈቀው፣ አስጮኸው፣ አስለፈለፈው።

ጋን (ኖች) (ገንዕ)፡ የጠላ መጥመቂያ፣ የጠጅ መጣያ፣ የቡሖ ማቡኪያ፣ የሸማ መክተቻ (ታላቅ የሸክላ ዕቃ)፡ ማድጋ፣ ሳሌ፣ ዝንግሪር፣ ገች፣ ዐዋሽ።

ጋን ሆይ፡ ገናና ሆይ፡ ጃን ሆይ።

ጋን ሰበር፡ የገብስ ስም፡ ጠላው ጋን የሰበረ (ጥቍር ገብስ)

ጋን ታረደ፣ ሙክት ተዘነበለ፡ ገላቢጦሽ ነገር።

ጋን፡ ከታችኛው ወግዳ በስተቀኝ በተጕለት ክፍል ያለ አገር።

ጋን፡ የገነነ ዘር ነው። ደንጊያም ጋን ይኾናል (ዮሐ፪::)

ጋንና ጋኔን፡ ባማርኛ ይገጣጥማሉ። "ልጆች ሲጫወቱ ጋኔን ሰበሩብኝ"

ጋንዣ፡ ያንገት መትን (ዥማት)፡ ራስን ከትከሻና ከደረት ጋራ የሚያያይዝ።

ጋንድያ (ዮች)፡ ወፍራም አህያና የበቅሎ አጋሰስ (ምስንጅር)፡ ግንድ የሚጭን፣ የሚደበለል፡ ጐነደበ (ጐደበ)

ጋንድያ፡ ምስንጅር (ግንድ)

ጋንገኛ፡ ኀይለኛ፣ ዶሰኛ (ብዙ ሰው የሚመታ) በፈረንጅኛ "ጋንግስተር" ይባላል።

ጋንጋት፡ ጋጋኖ (ድምፀ ጋንገኛ)፡ የሚንጋጋ ብዙ ማለት ይመስላል።

ጋንግ (ትግ ሐባ ጊንግ፣ ግንድ)፡ ኀይል፣ ብርታት። ግእዝ "ጋጋ" ከሚለው የወጣ ነው። "ቀንበርን" እይ።

ጋንጢጥ (ጋጠጥ)፡ ደፋር (ይሉኝ አይል)

ጋንጩር፡ ሰይጣናም ሰው።

ጋንጩር፡ ጋኔን፣ ሰይጣን።

ጋንፉር (ሮች)፡ እንደ መጅ ያለ ጨው።

ጋኖች፡ ትልልቆች ሰዎች፣ ዋኖች፣ ጨዎች፣ ጐምቱዎች፣ አባቶች፣ ዐዛውንቶች።

ጋዛ፡ የይሁዳ ክፍል፣ ከአምስቱ የኢሎፍሊ አገሮች አንዲቱ የሆነ የአገር ስም።

ጋዜጠኛ (ኞች)፡ ባለጋዜጣ፣ ጋዜጣ ጻፊ፣ ጋዜጣ ወዳድ፣ አንባቢ።

ጋዜጣ (ጦች)፡ የቀን፣ የሳምንት፣ የወር፣ የአመት ወሬ ጽሑፍ፣ ዕትም፣ ወይም ወሬው የተጻፈበትና የታተመበት ወረቀት፣ መጻፍ። የኢትዮጵያ ጋዜጦች ምሳሌዎች፡ - አእምሮ፣ ብርሃንና ሰላም፣ ተሐደሰት ኢትዮጵያ (በጣሊያን ጊዜ) የሮማ ብርሃን፣ ሰንደቅ ዐላማችን፣ ዐዲስ ዘመን፣ የኤርትራ ድምፅ፣ ነጋሪት ጋዜጣ፣ ተክለ ሃይማኖት፣ ዜና ቤተ ክርስቲያን፣ የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ድምፅ፣ መነን፣ ኅብረት፣ ወታደርና ዐላማው፣ ወታደርና ጊዜው፣ ፖሊስና ርምጃው፣ ፈለገ ብርሃን፣ ኑሮ በዘዴ፣ የወንጂና የሺዋ ዜና

ጋዝ (ዐረ፡ ቃዝ)፡ ላምባ፡ መብራት የሚሆን የምድር ዘይት፡ ወይም ቅባት። በግእዝ "ነፍጥ" ይባላል።

ጋዝ (ጋእዝ)፡ ጠብ፣ ክርክር፣ ንዝንዝ፣ ውዝግብ፣ ጭቅጭቅ፣ ጦርነት። "አበ ጋዝ" እንዲሉ።

ጋዝ (ግዕዘ፣ ጋዕዝ)፡ ዕቃ፣ ጓዝ፣ ጭነት፣ ሲራራ። "ወደል ጋዝ" እንዲሉ።

ጋዝ: ዘይት፣ ፍት፣ ቤንዚን፣ ሌላም ቅባት በያይነቱ ከውጭ የሚመጣበት ሥሥ ቈርቈሮ። ትንሹ ጣሳ ይባላል።

ጋዠ (ቃዠ)፡ አረጀ፣ አፈጀ፡ ረሳ፣ ዘነጋ፡ አእምሮ ዐጣ፡ ዣዠ።

ጋዠ፡ ከፋ፣ ተበላሸ፣ መጥፎ ሆነ (ዐመሉ፣ ጠባዩ)

ጋዣ፡ የሣር ስም፡ ማለፊያ ሣር፣ የፈረስ መኖ፡ ቅልጥሙን ሲመጡት "ማር ማር" የሚል፡ "የጋዣ ማር" እንዲሉ።

ጋየ፡ ጋለ፡ ፋመ፣ ነደደ፣ ተቃጠለ፣ ቀላ፣ ሸክላ መሰለ።

ጋይ (ዮች)፡ የጋየ፣ የጋለ (ያፈር፣ የመሬት) "ፍም ጣረት የጋይ መሬት" እንዲሉ።

ጋይ፡ የጋለ፣ የሚግል ብረት።

ጋይንቴ፡ የጋይንት ተወላጅ፡ የጋይንት አገር ሰው።

ጋይንት (ቶች)፡ በበጌምድር ክፍል ያለ የነገድና ያገር ስም፣ ትርጓሜው "ትልቅ"

ጋደ (ገሀደ)፡ ተገለጠ፣ ታየ።

ጋደለ፡ ዘነበለ ወይም ወዳንድ አቅጣጫ መዘነ።

ጋደል አለ፡ ዘንበል አለ።

ጋደል፡ ዘንበል።

ጋደም፡ ረብ።

ጋደም አለ፡ ተኛ።

ጋዱ (ዎች)፡ ዝኒ ከማሁ፡ የሚከለክል፣ አዋኪ፣ ሽፍታ፣ ላምን ጋድቶ ወተቷን እንደ ማለብ ሰውን ይዞ የፊጥኝ አስሮ ገንዘቡን የሚቀማ። ጋዱ በጋልኛም ይነገራል።

ጋዱ፡ ሽፍታ፣ ጋዳ።

ጋዱ፡ ጐደበ።

ጋዲ፡ ባንድ በኩል ቍጥር ያላት ዐጪር ጠፍር፡ የላም እግሮች ማሰሪያ።

ጋዲሎ፡ ጋዲሎ፣ አፄ ምኒልክና አቶ በዛብኽ የተዋጉበት ቦታ፣ የመንዝ ክፍል ነው።

ጋዳ ለጦ፡ ለጦ (ዳነት) ግልጥነት ይግባውና፡ "ትላንትና ዐሙስ ጮማ በላን"

ጋዳ ለጦሙ(ጾመ ገሃድ) በጾም ቀን የሚነገር ቃል።

ጋዳ፡ አሰረ፣ ወደረ፡ አዋሰዐ (እንደ ባላ ድር ጠለፈ)፡ ከለከለ፣ አገደ፡ እንዳይኼድ አደረገ። ጋዳ ከአገደ የወጣ ነው።

ጋዳ፡ ጋድ፣ (ገሃድ) የወንዶች ገና (የጥምቀት ከተራ፣ የገና የጥምቀት ዋዜማ፣ እንደ ረቡዕና እንደ ፍልሰታ፣ እንደ ሑዳዴ የሚጾም) ትርጓሜው "የሚገለጥ፣ ተገላጭ፣ ግልጥ" ማለት ነው። ጌታችን እንደ ሰውነቱ በአጭር ቁመትና ጠባብ ደረት ተወስኖ መታየቱን ያስረዳል።

ጋዳይ፡ የሚጋድል ወይም ዘንባይ።

ጋድ (ገደወ)፡ የሰው ስም፡ የያዕቆብ ልጅ፡ ትርጓሜው "እጅ መንሻ"

ጋድሚያ፡ እንቅልፋም ሰው ወይም ዐዞ።

ጋድም (ሞች)፡ የአፈር ቤት መረባርብ ተሸካሚ እንጨት።

ጋድም፡ ከግንብ እስከ ግንብ የተጋደመ ሰረገላ።

ጋድርኤል፡ የጋኔን ስም፡ ሔዋንን ያሳተ ሰይጣን (ሔኖ፲፱፡ ፲፱)

ጋጂ፡ የጋዳ፣ የሚጋዳ፣ ላም ዐላቢ።

ጋገረ፡ ሊጥን በምጣድ ላይ አዞረ፡ አሰረረ፣ አሰፋ፣ ደፋ፣ አበሰለ፡ የእንጀራ፣ የቂጣ፣ የዳቦ፣ የድፎ፣ የጥረሾ፣ የብርኩታ፣ የማር።

ጋገራ፡ የመጋገር፣ የማብሰል ሥራ።

ጋጋ (ገህግሀ፣ ጎገወ)፡ ገረፈ፡ በጥፊ መታ፣ አጮለ።

ጋጋ፡ ለየ፣ ከላ፣ ከለከለ ከዝሪት።

ጋጋ፡ ዝኒ ከማሁ፡ ከፊለ ስም። (ትርጓሜ መቅደመ ወንጌል)

ጋጋ፡ ግር ግር አደረገ፡ አራቀ፣ አስገለለ ከቤት።

ጋጋሪ (ሮች)፡ የጋገረ፣ የሚጋግር፡ አብሳይ፣ ዐበዛ።

ጋጋታ (ተዋክቶ)፡ ጃጃታ፣ ግርግርታ።

ጋጋታ፡ ግርግርታ (ጋጋ)

ጋጋኖ (ዎች)(ጓጓ)፡ ርኩምና የወንዝ አመቴ መሳይ፡ የአሞራ መንጋ በምድር በሰማይ የሚንጋጋ፡ ጯኺ፣ ድምጽ ረዥም፡ የነቢያት ምሳሌ።

ጋግርታም (ሞች)፡ የጋግርት ወገን፣ ባለጋግርት፣ አፍጣጭ፣ አጕራጭ።

ጋግርት (ቶች)፡ የጐረጠ የሚያይ፣ የደጋ ቆቅ ሲነሣ "ግር" የሚል።

ጋግርት፡ የደጋ ቆቅ።

ጋጠ (ትግ፡ ገሐጸ)፡ በጥርስ ላጠ፣ መለጠ፣ ገጠበ፡ ነጨ፣ በላ፣ ሰበረ (የአጥንት፣ የሣር፣ የጨው፣ የብክካ)

ጋጠ፡ ሰውን ዐማ።

ጋጠረ፡ ለፋ፣ ደከመ (በገጠር)

ጋጠረ፡ የገረ ዘር ነው። "ገጠረ" የስፍራን መበላሸት፣ "ጋጠረ" የሰውነትን መጐዳት ያሳያል።

ጋጠወጥ፡ ባለጌ፣ ጋጠ።

ጋጠወጥ፡ የጋጠውን ወጥ የሚያስነካ፡ ግጦ ከወጥ፡ ባለጌ፣ መረን፣ አግድሞ አደግ።

ጋጠጠ፡ ሥጋን ከአጥንት ላይ ቆረጠ፣ ገፈፈ፣ ጥቂት ሳያስቀር ጨርሶ ጠረገ፣ ደደ፣ ጠጠ።

ጋጠጥ፡ የጋጠጠ፣ የሚጋጥጥ፡ ባለጌ፣ ደድ።

ጋጣ (ጋጥ) (ጋሕጽ)፡ የፈረስ፣ የበቅሎ፣ የአህያ፣ የበግ፣ የፍየል ጓዳ፣ መጠጊያና ማደሪያ፡ ሲርባቸው ግድግዳውን፣ መሬቱን የሚግጡ ስለ ሆነ "ጋጣ" ተባለ (ኢሳ፩፡ ፫)

ጋጣ፡ ከብት ግጦ ያበጀው ዋሻ።

ጋጤ፡ የተጋጠ፣ የተመለጠ፣ ዐምቦ።

ጋጥ፡ ትእዛዝ አንቀጽ፡ ላጥ፣ ምለጥ፣ ንጭ፣ ብላ። "ጋጣ ጋጥ" ግእዝ "ዕጋዕ ምፅንጋዕ" ካለው ይሰማማል።

ጋጯጭ፡ የጋጠ፣ የሚልጥ፣ የሚነጭ፣ የሚበላ፡ ሰው፣ አውሬ፣ ከብት፣ በረሮ።

ጋፈ (ግሒፍ፣ ገሐፈ)፡ ዐፈሠ፣ ጠረገ (ከምጣድ አወጣ)፡ እንደ በሬ አብዝቶ ጠጣ። "ጋፈፈን" እይ።

ጋፈረ (ቀፈረ)አጋፈረ፡ አርጩሜ ያዘ፡ አጋፋሪ ኾነ፡ ከለከለ፣ አቆመ። ሰውን ለግብር ወይም ለሌላ ነገር ወደ ሹም ቤትና ወደ ቤተ መንግሥት አስገባ፡ ከዚ ያም አስወጣ።

ጋፈተአጋፈተ፡ ጕልበቱን ዐጥፎ በኹለት እጆቹ ጕልበቶቹን ተመርኵዞ (ቍጢጥ ብሎ) እያኰበኰሰ ባፉ ትንፋሽ ተጫወተ።

ጋፈጠተጋፈጠ፡ ተጨመረ፣ ተማገደ፣ ተዠገደ (ግንዱ ከእሳት)

ጋፈፈ፡ አብዝቶ በላ፣ ጨረሰ።

ጋፈፈ፡ ዐወደ፣ ጠረገ፡ ሰበሰበ፣ ወሰደ (የደረቅ ሣር) (ያሣ) (ተረት)"የተማሪ ጋፍ መልክ ይጋፍፍ (ይሰበስብ)"

ጋፈፎ፡ ዐጨዳ፣ ጠረጋ፣ ስብሰባ፡ ውሃ ሲመላ በሸማ ዓሣ መያዝ።

ጋፊ (ዎች)፡ የጋፈ፣ የሚግፍ፡ ጠራጊ (ጠጪ)

ጋፊኛ፡ በቀጥታ ቀንበርን አለመሳብ፡ ወደ ጐን የበሬ ጫንቃ ግፊያ።

ጋፊኛ፡ የበሬ ግፊያ (ገፋ)

ጋፋት፡ የነገድና ያገር ስም፡ በጐዣም አጠገብ በዳሞት ውስጥ ያለ አገር።

ጋፋቶች፡ የጋፋት ሰዎች፡ ነገደ ጋፋት።

ጋፋፊ፡ የጋፈፈ፣ የሚጋፍፍ፡ ዐጫጅ፣ ሰብሳቢ፣ ዓሣ ያዥ፣ ዘኬ ተሸካሚ።

ጋፍ (ገሐፍ)፡ ዕፈሥ፣ ጥረግ።

ጋፍ (ጋሕፍ)፡ የባሕር ዔሊ (ግእዝ)

ጋፍ፡ ሞኝ፣ ቂል፣ ግትቻ።

(ከፊለ ስም):ባለጌማለት ነው። ተመልከት: ትርጓሜ መቅድመ ወንጌል።

: እንደበቃል መጨረሻ እየገባምድር፣ ቦታ፣ ስፍራተብሎ ይተረጐማል። ማስረጃ: እጅጌ፣ ባለጌ፣ ገደልጌ፣ ገዳምጌ፣ ጕራጌ፣ ግርጌ፣ ደረስጌ፣ ወገብጌ፣ ዋንዛጌ፣ ሐረርጌ፣ ይተጌ፣ ላምጌ፣ ንብጌ፣ ዓዲስጌ፣ ዕጨጌ (ሐፄጌ) ዓምባላጌ፣ ዓንገትጌ፣ ፍንጥርጌ፣ ቅዱስጌ፣ ራስጌ፣ ሰላምጌ። የሁሉንም ትርጓሜ በየስፍራው ይመለከቷል። ማስታወሻ: ትግሬ (ሐባብም) አገርንድጌይለዋል።

ጌሥ (ጊሥ)፡ የገበጣ ጨዋታ፡ "የያዝኸውን ይዘኸ ኺድ ገሥግሥ ባትመለስ" ማለት ነው።

ጌሥ፡ በመንዝ ውስጥ ያለ አገር።

ጌስ: ያገር ስም፣ ጌሥ።

ጌሦች፡ የጌሥ ሰዎች (የጌሥ ተወላጆች) (መንዞች)

ጌራ: የሰው ስም፡ ከመንዝ ባላባቶች አንዱ። አገሩም "ጌራ" ይባላል።

ጌራ: የራስ ወርቅ (የራስ ቍር) (የብረት ቆብ) (ግእዝ)

ጌራ: የገንዘብ ስም፡ ታናሽ ገንዘብ። "ሐዲሱን መጽሐፈ ግስ ገጽ ፫፻፲፬" እይ።

ጌራ: ያገር ስም፡ የሻንቅላ አገር። "የጌራ ንግሥት" እንዲሉ።

ጌርጊስ: የመናፍቅ ስም፡ ያባ ተክሌ ጠላት፡ ከመንገድ ላይ ተቀምጦ ወደ ዜጋ መል የሚኼዱትን ጠበለተኞች ኹሉ "ባገራችኹ ቤተ ክሲያንና ውሃ የለምን?" እያለ የሚያውክ። መቃብሩ በደብረ ሊባኖስ ባሻገር ካቢ ሰሚባል አገር ይገኛል፡ መሬንዝ በቅሎ በታል፡ በዚያ የሚያልፍ መንገደኛ ምን ጊዜም ቢኾን ደንጊያ ይጥልበታል። ስለ ርሱ ሌላም ብዙ አፈ ታሪክ ይነገራል፡ እውነት መኾኑን እንጃ።

ጌርጌሴኖን: ያገር ስም፡ በምድረ ፍልስጥኤም ያለ አገር።

ጌሾ (ትግ ጌሦ): የታወቀ ተክል ስም። ከጥንስስ ዠምሮ ቅጠሉና ዐጥንቱ እየተወቀጠ ጠላ፡ ዐጥንቱ ተልጦ ሳይወቀጥ ጠጅ የሚኾን። በርሱ ምክንያት ጠላውና ጠጁ አብዝቶ ሲጠጡት የሚያሰክር፣ ራስ የሚያዞር፣ የሚያንገደግድ፣ አእምሮ የሚያሳጣ፣ አንዱን ኹለት አድርጎ የሚያሳይ፣ ሰው ኣዋራጅ ይኾናል። በደም ሥር ወደ ራስ ስለሚገሠግሥ ጊሾ (ገያሢ) "ገሥጋሽ" ተባለ።

ጌተየ (ገይተየ): ከበረ፣ በለጠገ፣ ተሾመ፣ ተሸለመ፡ ገዛ፣ ነዳ፣ ገነነ።

ጌታ (ቶች) (እግዚእ): ባለጠጋ፣ ሀብታም፣ ገንዘባም፣ ከበርቴ፣ ባለእዱኛ፡ ሹም፣ መስፍን፣ መኰንን፣ አለቃ፣ አሳዳሪ፣ ባለማረግ፣ ዳኛ፣ ገዢ፡ እግዜር። ዘርፍ ይዞ ሲነገር: ብላቴን ጌታ ግራ ጌታ ቀኝ ጌታ የኔታ። ቅጽል ሲቀድመው: መሪ ጌታ ይላል። (የጌታ ጌታ): የሀብታም ሀብታም፣ ያለቃ አለቃ፣ የበላይ አዛዥ። "ውሻ የጌታዋን ጌታ አታውቅም" እንዲሉ። (የጕልማሳ ጌታ): የጐበዝ አለቃ (ባላገር መርጦ የሾመው) (የቅሬ ጌታ): ያጣሪ፣ የመሸተኛ ግብር ተቀባይ። (የሰራዊት ጌታ): የመላእክት ፈጣሪ፣ አዛዥ (ኢሳ፩:፳፬) "" ብለህ "ኣሻን" ተመልከት።

ጌታ ሆይ ( እግዚኦ): አምላክ፣ ፈጣሪ ሆይ።

ጌታ መሳይ: ተግደርዳሪ፣ ራሱን የማይጥል ሰው።

ጌታ: ባለቤት። "የዚህ ጌታ" እንዲሉ። "አባን" እይ።

ጌታ: ከ፯ቱ የጕራጌ ወንድማማቾች አንዱ፡ ነገዱም አገሩም "ጌታ" ይባላል።

ጌታችን (እግዚእነ): የኛ ጌታ፡ ፈጣሪያችን፣ መምራችን ኢየሱስ ክርስቶስ።

ጌታዋ: የርሷ ጌታ።

ጌታው (እግዚኡ): የሀብት፣ የእዱኛ ባለቤቱ፡ የሰማይ፣ የምድር፣ የዓለም ፈጣሪው።

ጌታው: ጌታ፡ የርሱ ጌታ።

ጌታዬ (እግዚእየ): የኔ ጌታ፣ አሳዳሪዬ፣ አዛዤ።

ጌት: በኢየሩሳሌም አቅራቢያ በፍልስጥኤም ውስጥ ያለ አገር።

ጌትነት (እግዚእና): ጌታ መኾን፣ ባለጠግነት፣ ሹምነት፣ ንጉሥነት፣ ኣምላክነት (ኢሳ፴፫:፲፯፣ ይሁ:) "የኔታን" እይ።

ጌትኛ: የጌታ ኹኔታ፣ አነጋገር፣ አስተያየት።

ጌትዬ: የሰው ስም፡ አስቀድሞ የንጉሥ ተክለ ሃይማኖት፣ ኋላም ያጢ ምኒልክ ሸላይ የነበረ፡ ትርጓሜው "ጌታዬ" ማለት ነው።

ጌቶ (እግዚኦ): አቤቱ፣ አቤቶ።

ጌቶች: በባላገር ከንጉሥ ዠምሮ ስላንድ ባለሥልጣን ይነገራል።

ጌኔ፡ የጎፋ ባላባትና ንግሥት። "ጎፋ ጌኔ" እንዲሉ። "ገን" ጋራ አንድ ነው።

ጌንጭ፡ እንደ ጤፍ ዳልጋ ያለው ሣር (ዐረም)

ጌጠኛ (ኞች)፡ ያጌጠ፣ የተጌጠ፣ የተሸለመ፣ ሽልም፣ ባለጌጥ፣ ጌጣም፣ ጌጥ ያለው፣ ጌጥ ወዳድ።

ጌጣት፡ ጌጦች፣ በተጕለት አርባ ያህል ያለ ቀበሌ። "የጣት ምድር" ተብሎም ይተረጐማል (በእጅ ዐደር ማለት ነው)

ጌጣጌጥ፡ የጌጥ ጌጥ፡ ብዙ ዐይነት ጌጥ።

ጌጥ (ጌጽ)፡ የሚያምር ልብስ፡ ሓር፣ ዕንቍ፣ ፈርጥ፣ ወርቅ፣ ብር፣ ቀለበት፣ አንባ፣ ጕትቻ፣ ግርጃ፣ ድኰት፣ ሽልማት፣ ጥልፍ፣ ሻት፣ ዝምዝም፣ የመሰለው ሁሉንም ይጨምራል።

ጌጥ፡ በቁሙ፣ ገየጠ።

ጌጦች፡ ማዕድኖች፣ ጥልፎች።

ጌጽ፡ በቁሙ፡ ሽልማት። "ገየጠ (ጌጠ)" ብለኸ "ጌጥን" ተመልከት።

ግሃ፡ በሽተኛ፣ ፈርካሳ ጥርስ። "ግሃ ጥርስ" እንዲሉ።

ግሑሣን፡ መናኞች፣ ባሕታዊዎች ከሰው የማይገናኙ።

ግሑሥ (ግሒሥ፣ ገሐሠ)፡ የተወገደ፣ ውግድ፡ ከሰው ተለይቶ በበዓት (ዋሻ) ተከቶ የሚኖር መናኝ፣ ባሕታዊ።

ግለት፡ ግመት፣ ሙቀት፣ ትኵሳት።

ግላሎ፡ ከርሻ፣ ከዝሪት ውስጥ ተነቅሎ የሚወገድ ዐረም።

ግላስ (ሶች)፡ ከተንቤን፣ ከነት፣ ከጀንዲ፣ ከሐር፣ ከግምጃ የተበጀ (በኮርቻ ላይ የሚደረግ መቀመጫ)

ግላቢ፡ የእግር ግላጭ ሥጋ።

ግላጭ፡ ብቻ፡ ሌላ ሰው ሳይኖር። "ነጋዴው በግላጭ ብዙ ትርፍ አገኘ"

ግላጭ፡ ወበቅ፣ የፀሓይ ሙቀት። "የደመና ግላጭ" እንዲሉ።

ግላጭ፡ የተገፈፈ፣ ግፋፊ። "እግር ግላጭ" እንዲሉ።

ግል፡ ልዩ ገንዘብ፣ ከብት (ባል ለሚስቱ ያልቈጠረው፣ ያላገባው) "የግሉ ነው" "የግሏ ነው" እንዲሉ።

ግል፡ የመለየት ሥራ፡ ብቻ ቈይታ። "እከሌና እከሌ ስለ ተጣሉ ሽማግሎች ግል ይዘዋቸዋል"

ግል፡ የተገለለ፣ የተለየ፣ የራቀ፡ ሩቅ።

ግል፡ የተገለለ፣ ገለለ።

ግል()ምቢጥ (ግፍትዒት)፡ ግልብጮ። "የዥብ ገበሬ፣ የአህያ በሬ፡ የጦጣ ዘር አቀባይ፣ የዝንጀሮ ጐልጓይ፡ ሁሉም እንብላ ባይ"

ግልሙትና፡ ፈትነት፣ ብቻነት፡ ምንዝር (የምንዝር ሥራ፣ ብልግና) ባል አልባነት (ዘፍ፴፰:፳፬፣ ኢሳ፳፫:፲፯)

ግልም፡ ትኰራ፣ ቍጣ፣ ፍጥጫ፣ ግርማ።

ግልምቢጥ፡ ግልብጮ፣ ገለበጠ።

ግልምት፡ መገልማት፡ እክክ ማለት።

ግልምት አለ፡ ፈጽሞ ገለማ።

ግልስልስ አለ፡ ቅልስልስ አለ፡ ተኛ፣ ተመሳቀለ።

ግልበጣ፡ ልወጣ፣ ቅየራ፣ ትርጐማ፣ ምልሳ፣ ክንበላ።

ግልቢያ፡ ሽሽት፣ ሩጫ፣ ፍርጠጣ።

ግልባጭ፡ እንደ ግልብጥ።

ግልባጭ፡ የተቀዳ፣ የተተረጐመ፣ ቅድ፣ ትርጒም፣ ፪ኛ ጽሁፍ።

ግልብ፡ የተገለበ፣ የተገለጠ።

ግልብልብ፡ የተግለበለበ፡ ገለባ ዐይነት፣ እንብልብል።

ግልብጥ፡ የተገለበጠ፡ በላይ ወይም በውስጥ የሆነ፡ ልውጥ፣ ቅይር። (ተረት)"ተወኝ ተወኝ፡ ዐዲስ ግልብጥ ነኝ"

ግልብጥብጡ ወጣ፡ ቅጡ ጠፋ።

ግልብጥብጥ አለ፡ ተገለባበጠ፡ ታወከ፣ ታመሰ።

ግልብጥብጥ፡ የተገለባበጠ፣ የተለዋወጠ፣ ልውጥውጥ።

ግልብጦሽ፡ በአጅና በእጅ መካከል ወደ ኋላ እየተገለበጡ ወጣቶች የሚጫወቱት የጢሎሽ ጨዋታ። ፈረንጆች "ባር ፓራሌል" ከሚሉት ጋራ ይገጥማል።

ግልብጮ፡ ደቂቅ አገባብ፡ ግርምቢጥ፣ የኋሊት። (ተረት)"ዶሮ ከጋጥ፡ በሬ ከቈጥ። ቍርባን ውጪ ክርስትና"

ግልየት፡ የመጽሐፍ መግለጫ (በጥፈት ዳርና ዳር በስተጠርዝ በኩል ያለ)

ግልድመኛ፡ እንደ ግልድማም።

ግልድማም፡ ባለግልድም፣ እስላም፣ በረኸኛ።

ግልድም (ግልድሞሽ) (ገልድ)፡ ትጥቅ፣ ሽርጥ።

ግልድሞች፡ ሽርጦች።

ግልድው፡ መውደቅ፣ መጋደም።

ግልድው አለ፡ ወደቀ፣ ተጋደመ።

ግልገላ፡ ግልጋሎ፡ መሳ (የበጋ ዕርሻ)

ግልገል (ሎች)፡ የበግ፣ የፍየል፣ የፈረስ ልጅ። (የዥብ ግልግል)፡ ቡችላ።

ግልገል መሪ፡ የአማጭ ምክትል።

ግልገል ሙሴ፡ ምክትል ሙሴ፡ ፪ኛ የማኅበረተኛ ሹም፣ አዛዥ፣ አለቃ፣ አሳዳሪ።

ግልገል ሚዜ፡ ፪ኛ ሚዜ፡ የዋና ሚዜ ተወራጅ፣ ዝቅተኛ።

ግልገል ሞራ፡ ከወተት አንጀት ጋራ የሚገኝ።

ግልገል ሰኰና፡ ከወደ ኋላ ከሰኰና በላይ ያለ የከብት ጥፍር።

ግልገል በቅሎ፡ አህያ ከፈረስ የወለደው።

ግልገል አህያ፡ ውርንጭላ (ዘፍ፴፪:፲፭፣ ሉቃ፲፱:-፴፫:፴፭)

ግልገል አንሣ፡ የሎስ ታላቅ አሞራ፣ ንስር፡ ጐሢ ግልገል አንሥቶ የሚወስድ።

ግልገል፡ ከጐርዝ የሚበልጥ፣ ከግንቡል የሚያንስ ዓሣ።

ግልገል፡ የሙቀጫ ልጅ፣ ዘነዘና።

ግልገል፡ የግብግብ ጥብቆ፣ ሕዕንግል።

ግልገል፡ የጐሽ እንቦሳ፣ ጥጃ። "የጐሽ ግልገል የመሰለ ልጅ" እንዲሉ።

ግልግል (ሎች)፡ ከመደቡ ተነቅሎ በሌላ ስፍራ የተተከለ የጌሾ፣ የበርበሬ፣ የዛፍ፣ የማንኛውም ተክል ችግኝ።

ግልግል፡ ዕርቅ፣ ስምምነት።

ግልጥ (ጦች)፡ የተገለጠ፣ የታወቀ፣ የጐላ፣ የተረዳ፡ ክሱት።

ግልጥ ሆነ፡ ጐላ፣ ታወቀ፡ ከመሰወር፣ ከመርቀቅ ራቀ።

ግልጥ ነገር፡ ያልተሰወረና ምስጢር የሌለው ወሬ፡ ወይም ሌላ።

ግልጥ አለ፡ ተገለጠ።

ግልጥ አደረገ፡ ገለጠ።

ግልጥልጥ፡ የተገላለጠ፡ ክፍትፍት።

ግልጥነት፡ ግልጥ መሆን፣ አለመሰወር፣ አለመታባት።

ግልጸ፡ በመነሻው '' ያለበት ግእዛዊ ቅጽል፡ በዐማርኛም '' ነው።

ግልጽ፡ ግልጥ፣ ክሡት።

ግልፊያም፡ የግልፍ ወገን፣ ባለግልፍ።

ግልፋጭ፡ የተገለፈጠ፡ ግልፋፊ።

ግልፋፊ፡ የብራና ፍቄት።

ግልፌ፡ በድንገት የምትመላ ባዲስ አበባ ያለች የሥላሴ አጥቢያ ፈፋ፡ ዳግመኛም ግንፍሌ ትባላለች።

ግልፍ አለኝ፡ ፪ኛ የግልፌ ስም።

ግልፍ አለኝ፡ ተቈጣኹ፡ ቍጣ ገጠመኝ።

ግልፍ አለው፡ ቍጡ ኾነ፡ ቍጣ አገኘው።

ግልፍ፡ የተቈጣ፣ ቍጡ።

ግልፍተኛ (ኞች)፡ በጥቂት ነገር የሚቈጣ፣ ወፈፍተኛ፣ አምራሪ።

ግልፍተኛነት፡ ቍጡነት፣ ወፈፍተኛነት።

ግልፍታ፣ ግልፍት፡ ቍጣ፣ ወፈፍታ።

ግልፍጥ፡ ዝኒ ከማሁ፡ ግልፍፍ።

ግልፍፍ፡ የተገለፈፈ፣ የተላጠ፣ የተላፈ።

ግሎብ (ሮማይ፡ ግሎቡስ)፡ ክብ፣ እንክብል፣ የዓለም ሥዕል በብረት ላይ የተሳለ። የመጋለብና የመዞር ምስጢር አለበት።

ግመለኛ (ገመላዊ)፡ ግመል ጫኝ፣ ግመል ሳቢ።

ግመላም፡ ባለግመል፣ ጠባሳም፡ በገላው የብጫ ነጠብጣብ ያለበት።

ግመል (ሎች) (ገመል)፡ የጋማ ከብት፡ እንደ ፈረስ ጋማ፣ እንደ በሬ ሻኛ ያለው፡ የሚያመሰኳ፣ ቁመቱና ዐንገቱ ረዥም፡ ታዛዥ (ተንበርክኮ የሚን)፡ ያ፬ በቅሎ ጭነት የሚያነሣ፡ በረሓ ደፋር፣ ውሃ ጥም ቻይ የቤት እንስሳ (ዘፍ፳፬:፲፩፣ ፴፩:፴፬)

ግመል አወጣ፡ ጠባሳ አበጀ፣ አደረገ።

ግመል ዠርባ፡ መፃጕዕ።

ግመል፡ የጭን፣ የቅልጥም ብዊ ጠባሳ።

ግመት፡ ግለት፣ ሙቀት፣ ቃጠሎ።

ግመኒ፡ ጥንበኒ ( እንደ '' እንደ '' መኖርንና ባለቤትነትን ያሳያል)

ግማታም (ሞች)፡ ጥንባታም፣ ክርፋታም፣ ቅርናታም።

ግማት፡ ጥንባት፣ ክርፋት፣ ቅርናት፡ ክፉ ሽታ (ኢሳ፫:፳፬)

ግማደ መስቀል፡ ዐጤ ዳዊት ከኢየሩሳሌም ያስመጡት የጌታችን መስቀል ቍራጥ።

ግማድ፡ ጕማጅ (ግእዝ)

ግማጭ፡ ከጥርስ የተረፈ ቍራሽ፡ የዳቦ፣ የንጀራ ቅሬታ።

ግም (ሞች) (ግሙእ)፡ የገማ፣ የጠነባ፡ ጥንብ፣ የተበላሸ፡ ውዳቂ።

ግም፡ መጥፎ ሰው፡ ሥራ።

ግም አለ፡ አስተጋባ (ገመገመ)

ግም አለ፡ ድም ኣለ፡ ጮኸ፣ ድምፅ ሰጠ፣ አስተጋባ (የሳንቃ፣ የነጋሪት፣ የሰማይ)

ግም፡ የመንቀፍና የማዋረድ ቃል።

ግምላም፡ ልብልባታም፣ ጠባሳም።

ግምል፡ የተገመላ፣ የተለበለበ (ልብልብ)፡ ቅርፊቱ የሚወድቅ (ለጠላ የሚኾን) የማሽላ አብሲት ቂጣ።

ግምሳት፡ የመግመስ፣ የመፈንከት ሥራ፡ ወይም ፍንክት።

ግምስ፡ የተገመሰ፣ የታረሰ፡ ትልም።

ግምት (ቶች)፡ ሒሳብ፣ ግምጋሚ፣ ስሌት፡ ያንድ ነገር ዋጋ (ጥሬ)

ግምት፡ መግማት።

ግምት አለ፡ ፈጽሞ ገማ።

ግምት የለሽ(የሴት ስም)

ግምት የለኸ(የሰው ስም)፡ ላንተ ዋጋ የሚሆን የለም ማለት ነው።

ግምት፡ የተገመተ፣ የተገመገመ (ቅጽል)

ግምነት፡ ንዴት፣ ቅጥለት።

ግምን (ግሙን)፡ የገመነ፣ ያረረ።

ግምን አለ፡ ንድድ፣ ቅጥል፣ ዕርር፣ ክስል አለ።

ግምንምን አለ፡ የግምን አለ ድርብ።

ግምንምን፡ የተግመነመነ።

ግምደላ፡ ቈረሳ፣ ገመሳ።

ግምድ፡ የእግር ቍርጥማት (እግርን እንደ ገመድ የሚያደርግ)፡ በግእዝ ግን ቍራጭ ዕራፊ ማለት ነው።

ግምድል አለ፡ ቍርስ አለ፡ ተገመደለ።

ግምዶ፡ ያራስ ጥሪ።

ግምጃ ሱሪ፡ ከግምጃ የተዘጋጀ ሱሪ።

ግምጃ ቀሚስ፡ ከግምጃ የተሰፋ ቀሚስ (እጀ ጠባብ፣ ዐብደላ ካኒ)

ግምጃ ቤት፡ በጐንደር ግንብ ውስጥ ያለ የማሪያም አጥቢያ።

ግምጃ ቤት፡ የግምጃ ቤት ሹም (በዥሮንድ)

ግምጃ ቤት፡ የግምጃ፣ የገንዘብ ቤት።

ግምጃ፡ ከጥጥ ከሐር ተፈትሎ የተሠራ (በያይነቱ ባለቀለም) ልብስ (የሚያስጐመዥ) (ዘፀ፳፯:) "ሶራን" "ሱቲን" እይ።

ግምገማ፡ ገመታ፣ ስሌት።

ግምጋሚ፡ ግምት፣ ሸለግ፣ ሒሳብ (ዘፀ፭:፲፰፣ ፩ነገ::፴፱፣ ኢሳ፯:፳፫)

ግምግም አለ፡ ድምድም አለ፡ መላልሶ ጮኸ።

ግምግም፡ ዝኒ ከማሁ፡ ፪ኛውን '' አጥብቅ።

ግምግም፡ የተገመገመ፣ የተገመተ። (የላይኛው ጥሬ የታችኛው ቅጽል መኾኑን አስተውል)

ግምግምታ፡ ግምግም ማለት፡ ጩኸት።

ግምጥ አደረገ፡ ገመጠ።

ግምጥ፡ ዝኒ ከማሁ።

ግምጥምጥ፡ የተገማመጠ፡ ስብርብር፣ ሽርፍርፍ።

ግሠጻ (ግሣጼ)፡ ቍጣ፣ ዘለፋ።

ግሱ አነሣ እንደ አገባቡ የተለያዩ ትርጉሞች አሉት:

ግሣት (ጕሥዐት)፡ ካፍ የሚወጣ ክፉና መልካም ሽታ።

ግሴት (ግሰት): የሚያዝና የሚዳሰስ የቤት ቈሳቍስ። "ዕቃ ግሴት" እንዲሉ።

ግስ: የሩቅ ወንድ አንቀጽ፡ "ዐወቀ" "ነበረ" "አለ" "ነው" እያለ የሚገሰስና የሚነገር ኹሉ፡ ይኸውም "ነጠላ ግስ" ይባላል። የግእዝ ኣገባብም የግስን ዐይነት "ከተማ ግስ" "መንደር ግስ" "ተራ ግስ" ይለዋል። "መስምን" ተመልከት።

ግስ: የቋንቋ መጻፍ በፊደል ተራ ማንኛውም ቃልና ነገር በጠቅላላው ዘርና ነባር (ስምና ግብር) ከእልፍ እስከ ታው ተጽፎ የሚገኝበት መዝገበ ቃላት።

ግስ: ያንዱን ላንዱ በማወራረስ የሚባል የወረብና የቅኔ ጥቅስ።

ግስ: ጓዝ፣ እክት። "ሰማይ ከነግሱ ምድር ከነልብሱ" እንዲሉ።

ግስላ (ሎች): እጅግ ቍጡ አውሬ (የነብር ዐይነት)፡ እልከኛ። (ተረት): "ዐዳኝ በጕድጓድ ውስጥ ተቀምጦ ጋሻ ለብሶ ሲሰድባት፣ ጋሻውን መንጠቅና ዐዳኙን መግደል ባቃታት (በተሳናት) ጊዜ በገዛ እጇ ታንቃ ትሞታለች" ይላሉ። ተባቱም እንስቱም "ግስላ" ይባላሉ። (ግጥም): "ዝኆንና ጐሽ አውራሪሥ ገድዬ፣ አንበሳና ነብር ቀጪኔም ገድዬ፣ አንድ አውሬ ቀርታለች፡ ወይ እገድላታለኹ፡ ወይ ትገድለኛለች። "

ግስላ: የጐበዝ ጐበዝ፡ ጨካኝ ሰው።

ግስንግሳም: ኮተታም፣ ባለብዙ ኮተት።

ግስንግስ: ብዙ ዐይነት ዕቃ፣ ጥርቃሞ (በራፍ የመለሰው፣ ማጀት የጐረሠው)

ግስንግስ: ኮተት፣ ገሰሰ።

ግሥገሣ፡ ዐጤ ምኒልክ ራስ መንገሻ ዮሐንስን ለመያዝ ያደረጉት ዘመቻ።

ግሥገሣ፡ ግሥጋሤ (ጊሠት)፡ ውሎ ሳያደርጉ ሲነጋ ዕለት ዕለት ለጦርነት ፈጥኖ መኼድ (መራመድ)፡ ሩጫ (ጥድፊያ) (ችኰላ)

ግሥግሥ፡ የገሠገሠ፡ ተሳቢና ባለቤት ከቅጽል ሲቀድም "ግሥግሥ" ይባላል፡ ይኸውም የግእዝ አገባብ ነው።

ግሶች: አንቀጾች፣ የቋንቋ መጻፎች፡ ጓዞች።

ግረት (ግዕረት): ጭንቀት፣ ጩኸት።

ግሩማን: የተፈሩ፣ የሚፈሩ። "ግሩማን አራዊት" "ግሩማን መላእክት" እንዲሉ።

ግሩም አንተ: ቃለ አንክሮ፡ ወይም አጋኖ።

ግሩም እምግሩማን: ከተፈሩ ይልቅ የተፈራ።

ግሩም: በቁሙ፡ ድንቅ፣ ዐጀብ፣ ዕጹብ (መዝ፻፯:፳፪) ልዩ፣ የተፈራ፣ ገናና፣ ታላቅ፡ እግዜር ሳይወጋ የሚገድል፣ ሳይታገል የሚጥል።

ግሪ፣ ግሪያ (ርያፄ): ቅጣት፣ የሥግሪያ ርምጃ ትምርት፣ ልማድ።

ግሪሳ: መቄ ነጐዴ (ብዙ ወፍ ወይም ዝንብ) ግር ብሎ የሚነሣ።

ግሪሳ: መቄ፡ ገረገረ።

ግሪክ (ኮች): የነገድ ስም፡ የጽርእ አገር ሰው፡ የያፌት ዘር፡ የያዋን ተወላጅ።

ግሪዶ: ዝኒ ከማሁ።

ግራ (ፅግም): በግራ በኩል ያለ ስፍራ።

ግራ ቢስ: ሥራ የለሽ፣ ዕውቀት የለሽ፣ ከርታታ፣ ችግረኛ።

ግራ አገባ: አስቸገረ፣ አወከ፡ ዕረፍት ነሣ።

ግራ አግቢ: አስቸጋሪ፣ አዋኪ።

ግራ እጅ: በስተግራ ያለ ፪ኛ እጅ (ደካማ፣ ሰነፍ) (ከቀኝ እየተጋራ የሚሠራ) ፫ኛውን "ገራ" እይ፡ ዘሩ እሱ ነው።

ግራ ገባው: ተቸገረ፣ የሚያደርገውን ዐጣ፡ ታወከ፣ ተጨነቀ። (ግጥም): "ግራ የገባው ያጣው መላውን፡ ግራ ያገባል ደግሞ ሌላውን" ምስጢሩ መሥራት እንደማይችል "ግራ ኾነ" ማለት ነው።

ግራ ጌታ (የግራ ጌታ): በካህናት አለቃ ግራ የሚቀመጥ የደብተሮች ሹም (የቅዱስ ገብርኤል ምሳሌ)

ግራ፡ ግእዝ ነው።

ግራ ጐንደር: ዳር አገር።

ግራ: ችግር፣ ጭንቅ።

ግራ: እንደ ድር ጠንካራ ያልኾነ ማግ (የግራ ፈትል) "የጥንት ግብጦች ማግን ወደ ግራ ይፈትሉ ነበር" ይላል ሔሮዶቱስ።

ግራ: ደካማ፣ ጐደሎ፣ ከቀኝ የሚያንስ፣ ጸጥተኛ።

ግራ: ጠማማ (ቀና ያይዶለ) "ያቶ እከሌ ነገር ግራ ነው" እንዲሉ።

ግራም: የሚዛን ስም፡ ታናሽ ክፍል (የኪሎ ሺሕኛ)

ግራምጣ: ማእዘን ያለው ጠንካራ ሣር (እንደ ገሣ በረግረግ ውስጥ የሚበቅል) ሴቶች እየሠነጠቁ ጕብና፣ ጮጮ ይሰፉታል። የትግሬም ልጃገረዶች እሱን እያሸረጡ ባውዳመት ይጨፍራሉ።

ግራሞች: ኹለትና ከኹለት በላይ ያሉ ብዙዎች።

ግራር (ሮች): የዛፍ ስም፡ የታወቀ ዕንጨት (እሾኻም)፡ ፍልጡ ሲማግዱት እንኵሮ ምጣድ የሚያጎር (የሚያግል)፡ ወይም ለዕቃ መጥረቢያ የሚገር (የሚገዛ)፡ በድግርነት ከሞፈር ጋራ የሚሳብ፣ የሚጐተት ማለት ነው (ዘፀ፳፭:) "ሀሎን" እይ።

ግራርያ (ግራራዊ): ያገር ስም (በበጌምድር ያለ) አገር። "ግራራም" "ባለግራር"፡ ብዙ ግራር የበቀለበት፣ ያለበት ማለት ነው። ይህ ስም በግእዝ መጻሕፍት ይገኛል፡ በሺዋም (ሰላሌ) ግራር ወንዝ ነው። "ገድለ ፊልጶስ" ተመልከት።

ግራት፡ ገርነት፣ መግራት።

ግራናማ: የቀንድ መብቀያ።

ግራንጃ: ክፉ ቃል፡ የሸፍጥ ንግግር፡ የአንጃ መልስ። "አንጃ" የቀኝ አሉታ፡ "ግራንጃ" የግራ አሉታ፡ "እንጃ" "አላውቅም" መባባል ነው። "አንጃን" ተመልከት።

ግራንጃ: ክፉ ቃል፣ ግራ።

ግራኝ (ኞች) (ፀጋማይ): "" ከቀኝ መጥቶ ተደርቧል፡ በግራው የሚሠራና የሚበላ ሰው፡ ግራ ቀኙ። "አባን" እይ።

ግራኝ፡ ድንጋይ፡ ስረ፡ ወጥ፡ አራት፡ ማእዘን፡ የጥንት፡ ሰዎች፡ ያቆሙት፡ የምዕራፍ፡ (ኪሎ፡ ሜትር)፡ ልክ።

ግራኝ: የሰው ስም፡ በሐረርጌ አውራጃ የተወለደ መሓመድ ገራድ ኢትዮጵያን ባፄ ልብነ ድንግል ጊዜ ፲፭ ዓመት በጦርነት ያስጨነቀ፡ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ አቃጣይ (የስላም መሪ)

ግራዋ (ዎች): የዛፍ ስም (ባዲስ አበባ እንደ ሰንሰል በዝቶ የሚገኝ) የጕጆ ዐይነት ዕንጨት፡ ጣዕሙ መራራ ኹኖ አፍ ስለሚያዋዋ ወይዛዝሮች ቅጠሉን ቀጥቅጠው ከአጓት ጋራ ይጠጡታል።

ግራዝማች (የግራ አዝማች): በንጉሥ ግራ ጭፍራውን የሚያዘምት የጦር አለቃ።

ግራዬ ሆይ: የገና ስድብ ዘፈን አዝማች።

ግራጫ: የበቅሎ መልክ (ግራጭ (ዣርት) የሚመስል) በቅሎ፡ እያደር የሚነጣ። ዳግመኛም ግራ በቅሎን ሲጠሩ "ግራጭ" ይላሉ።

ግራጭ (ጮች): ዣርት፡ የዣርት ስምና መልክ (የገላው ጠጕር (እሾኸ) ንጣት ከጥቍረት ያለው) አውሬ (ጠጕረ ወስፌ) የእኸልና ያትክልት ጠላት። ቁመቱ ዐጪር ስለ ኾነ በማሳ እኸል ላይ እየተንደባለለ ፍሬውን ይበላል።

ግራፍ: ጅራፍ።

ግሬራ: አኮሌ፣ ጮጮ፣ የግልገል አቍማዳ። የላም ጡት እየጐተቱ ማለቢያ ስለ ኾነ "ግሬራ" ተባለ።

ግሬት: በመራቤቴ ውስጥ ያለ አብር።

ግር (ርዩፅ፣ ግሩህ): የተገራ፣ የተገረፈ፣ የተማረ፣ የለመደ።

ግር ሲል እወፍጮ ሥር: ፈሪ ሴታውል (ገዳይ)

ግር ሲል ገዳይ: ጐበዝ የወንዶች ባል።

ግር ሲል: ሲነሣሣ፣ ሲታወክ፣ ሲተራመስ፣ ሲደበላለቅ።

ግር አለ: በብዛት ተነሣ (ግው አለ)፡ የሕዝብ፣ የባለክንፍ ኹሉ ነው።

ግር አለ: ተነሣ፣ ገረገረ።

ግር አለው: ቅር አለው፡ አልገባውም፡ አልተረዳውም (ቀረን እይ)

ግር()ግሪት: ኋሊት፣ ፊጥኝ። "የግርንግሪት ታሰረ" "ወደቀ" እንዲሉ።

ግርመማ: ግልምጫ።

ግርመት: መግረም፣ ድንቅነት።

ግርማ መለኮት: የመለኮት ግርማ።

ግርማ መንግሥት: የመንግሥት ግርማ።

ግርማ ሞገስ (ሞገሰ ግርማ): መወደጃ፣ ባለል መኾኛ፡ መኳንንት በደረታቸውና በክንዳቸው የሚያንጠለጥሉት (በንጉሥ ዘንድ መወደድን፣ በሕዝብ በኩል መፈራትን የሚሰጥ) ያስማት ክታብ (እውነት መኾኑን እንጃ)

ግርማ: መፈራት፣ አስፈሪነት (የንጉሥ፣ የሞት፣ የምጽአት)

ግርማም (ግርማዊ): ግርማ ያለው፣ ባለግርማ፡ ተፈሪ፣ አስፈሪ።

ግርማዊ፣ ግርማዊት: የንጉሥና የንግሥት የስም ቅጽል (ማዕረግ)

ግርማዊነትዎ፣ ግርማዊትነትዎ: አስፈሪነትዎ፣ መፈረትዎ።

ግርምቡድ (ጐረመደ): የግንድ ቍራጭ (መቀመጫ በርጩማ)

ግርምቢጥ: ግልብጦ፣ ገለበጠ።

ግርስስ አለ: ፍልስ አለ፡ ተገረሰሰ።

ግርስስ: የተገረሰሰ፡ ንቅል፣ ፍልስ ውድቅ።

ግርር (ገሪር): መግረር።

ግርር አለ: አለልክ ሠማ፣ ጋለ፡ ጥብርር አለ።

ግርሻ: ኹለተኛ ዕመም።

ግርሻ: የራስ ዳርጌ ፈረስ ስም (አባን ተመልከት)

ግርሽ (ዐረ): የገንዘብ ስም፡ አንድ መሐለቅ። "ቅርስን" አስተውል።

ግርሽጥ (ጦች): የቅጠል ስም፡ ሴቶች ሥሩን ቀቅለው በእንፋሎቱ እግራቸውን የሚያቀሉበት የወይናደጋ ቅጠል። "እንሶስላን" "ሒናን" ተመልከት።

ግርባብ (ትግ ፈርጅ): ኰረጃ፣ አቍፋዳ፡ "አፈ ከፋታ መኾኑን ያሳያል"

ግርንቡድ: በርጩማ፣ ግርምቡድ።

ግርንድስ: ወፍራም፡ ግንድ ዐይነት ሰው።

ግርንግሪት: የኋሊት፣ ገረገረ።

ግርንግያ: ያልጋ ጠፍር።

ግርኘታ: አሰራ፣ ኵድኰዳ።

ግርዛት (ግዝረት): ዝዘራ፡ መግዘር፣ መገዘር።

ግርዝ (ግዙር): የተገረዘ (ይሁዲ፣ ፈላሻ፣ ዐማራ፣ ዐረብ)፡ ሽፍን ያይዶለ ማንኛውም ነገድ።

ግርድ (ጥድ): የጠረሰ (ችርችም)

ግርድ: በማጦያ ከምርት የተለየ መናኛ እኽል (ገለባና ሰበር ያለበት) የምርት ምክትል። "ሚስትና ምርት፣ ገረድና ግርድ" በምስጢር አንዳንድ ወገን ናቸው። "እንቡርቧይን" "እንችፍን" እይ።

ግርድ: የጥርስ በሽታ (ጥሮሶችን ሸራርፎ የሚጨርስ)

ግርድም: የተገረደመ ስብር።

ግርድፍ: የተገረደፈ፡ ክርትፍ፣ እንቀት፣ ሽርክት፣ ሽርንክት፣ ጕርሦ።

ግርዶ፣ ግርዶሽ: መጋረጃ።

ግርጃ: የእግር አንባር (እግርን በጌጥነቱ የሚጋርድ)

ግርገራ: ቅርቀራ (ግድግዳ)፡ ድርደራ፣ ተከላ፡ የመገርገር (የመደርደር) ሥራ።

ግርጌ (ትርጋጽ): እንደ "ራስጌና ግርጌ" እንደሚባለው። "ጌን" ተመልከት። "ግርጌ" ማለት "እንደ ጎርዶ" ነው። ሲበዛ "ግርጌዎች" ይላል።

ግርጌ: የእግር ስፍራ (እግር)

ግርግም (ሞች): ከብቶች ሣርና ገለባ (እኸል) የሚበሉበት (የሚቅሙበት) በግንብ ወይም በግድግዳ የተሠራ ሞላላ የበረት የጋጣ ቋት።

ግርግም: ጫፍ ጫፉ የተሸረፈ (ሸራፋ፣ ሰባራ) "ግርግም ጥርስ" እንዲሉ።

ግርግራ: ጭንጫ መሬት (ማረሻን የሚገረግር)፡ ገበሬ አዋኪ።

ግርግራት (ስያሕ): ሴቶች ጪስ የሚሞቁበት እግራም ሸክላ፡ ወይም ከንሓስ የተበጀ (እንደ ጥዋና እንደ ጥና ያለ) ዕቃ።

ግርግራት: የደረቅ ኵበት ጥፍጥፍ አቋቋም በምድጃ።

ግርግር (ሮች): በካብ ላይ የቆመ ዕንጨት (ያልተማገረ)፡ ቢማገርም ያልተሸመጠጠ ዐጥር።

ግርግር አለ: ሊሸበር ቀረበ፡ ታወከ፣ ተነሣሣ፣ ተተራመሰ፡ ዕረፍትና ጸጥታ ዐጣ።

ግርግር፣ ግርግርታ (ወክሕ): ሁከት፣ ውካታ፣ ትርምስ። "የገበያ ግርግርታ ለሌባ ተመቸው"

ግርግር: በሜዳ ተደጋግፎ የቆመ ጥፍጥፍ።

ግርግር: እብድ፣ አስተኔ፣ ወፈፌ። "እከሌ ግርግር ነው" እንዲሉ።

ግርጣት: ንጣት፣ ነጭነት።

ግርፋት: መግረፍ፣ መገረፍ፡ ጥብጥባት (የጅራፍ ቅጣት) (ዘሌ፲፱:፳፣ ዘዳ፳፭:፫፣ ፪ቆሮ:፲፩:፳፬)

ግርፋት: የጨረር ምች፣ ትኵሳት፡ ሽፍ ያለ ዕከክ፡ ጅራፍ ያቈሰለው ያሰነበረው ገላ።

ግርፍ (ግሩፍ): የተገረፈ፣ የተመታ፣ የተቀጣ፡ ቍንድድ፣ ልቍጥጥ፣ ትኵስ (የተተኰሰ) ወይፈን፣ አሽከር፣ ማደጎ፣ ድፎ፣ ጠባሳ።

ግርፍ አደረገ: ገረፈ።

ግሼ (ግሼቅ ገድ ተክ): ያገር ስም፡ የመንዝ መዠመሪያ አገር። "ግሼ ያው ሳቤ ልጅ" እንዲል ዘር ቈጣሪ። አንቀጹ "ገሣ" ሲኾን ትርጓሜው "ምንጭ" ይባላል።

ግሼ አባይ: በሰከላ ዳሞት ያለ የአባይ መፍለቂያ። "ግሼንን" እይ።

ግሼን (ግሼ): ያገር ስም። ዐጤ ዳዊት ግማደ መስቀል ያኖሩበት (የቀበሩበት) ዐምባ ተራራ። "ግሼን ማሪያም" እንዲሉ። ግሼን ያሠኘው በላዬ ያለው ኩሬ ነው። አገሩ የሚገኝበት አውራጃ ዐምባሰል (ዐምባ ዐሰል) "ዐጢን" ተመልከት፡ "ሞኝን" እይ።

ግሼኖች (ግሼናውያን): የግሼን ሰዎች፣ የግሼን ተወላጆች።

ግሽልጥ አደረገ: ግፍፍ አደረገ፡ ልብስን ቀማ።

ግሽልጥ: የተገሸለጠ፣ የተላጠ፣ የተመለጠ፣ የተገፈፈ፡ መለመላ፡ ዕራቍት።

ግሽር (ሮች): የተገሸረ፡ ቅምጥ።

ግሽር: የጋን፣ የማድጋ ውሃ።

ግቡ (ግቡእ): ዝኒ ከማሁ። ተመልከት: ደምን ሌላ ትርጉም: ገቢ (ተገቢ) (ዕዝራ ፬፥፲፫) ሌላ ትርጉም (ግብኡ): ትእዛዝ አንቀጽ። ምሳሌ:ሰዎች! አቤት ግቡ

ግቢ (ዐጸድ): ውስጥ፡ በአጥርና በቅጥር የተከበበ ቦታ። ምሳሌ:ዐጥር ግቢእንዲሉ። ሌላ ትርጉም: የጋብቻ ሥርዐት ወይም ጋብቻ። ግጥም:እንቢልታ መለከት የሚነፋው የት ነው፡ አንድም በስርቆሽ በር አንድም በግቢ ነው

ግቢ (ግብኢ): በቁሙ። የዜማ ምልክት።

ግቢ ነፍስ (ግብኢ ነፍስ):ነፍስ ወደ ሥጋሽ ግቢ” (ተመለሺ)፡ ወይምሥጋ ወደ መሬትነትሽ ተመለሺ

ግቢ ነፍስ ውጪ ነፍስ: በጣረ ሞት ጊዜ ይባላል።

ግባ በገመዴ:እኔ በምቀጣበት ቅጣት ተቀጣ” (አስቴር ፯፥፱፣ )

ግባሳም፡ ግባስ ተሸካሚ፣ ባለግባስ።

ግባስ፡ ግባሶ፣ ድቃቂ ሣር፣ ገለባ፣ ቈሻሻ፣ ጭራንፎ።

ግባተ መሬት (ግብአተ መሬት): ሬሳ ወደ መቃብር ሲገባ የሚደረግ ፍታት። ትርጓሜውም "ወደ መሬት መግባት" ማለት ነው። ግጥም:ግብአተ መሬቱን አትድገሙ እናንተ፡ ታዞ ኺዷል እንጂ ልጄ መቼ ሞተ?” ሌላ ትርጉም: "ግባ ተመሬት""እመሬት ግባ" (ተቀበር) ግጥም:በተማረው ድጓ በጣፈው ግንዘት፡ ድረስ ድረስ አሉት፡ ግባ ተመሬት።

ግባት (ግብአት): የንጉሥ ግብር (መብል፣ መጠጥ)(ጐንደር) ተመልከት: "ደምን" ሌላ ትርጉም: ክተት (ሰራዊት) ሌላ ትርጉም: ሚዛን፡ ሁለት አሞሌ መሣ። ሌላ ትርጉም: ብዙ የጠመንጃ ተኩስ ሳያቋርጥ እየተመላለሰ የሚተኮስ።

ግቤ: የዛፍ ስም፡ ዓሣ ማስከሪያ የበረሓ እንጨት። ሌላ ትርጉም: ከመኻል የኦሮምኛ አገር የሚነሳ ዠማ፡ ብዙ ፈሳሽ የሚገባበት። እርሱም ጅማንና ጕራጌን የሚያዋስን ታላቅ ወንዝ ነው። ሌላ ትርጉም:የኔ ግብ

ግብ (ግቡእ): የገባ (በውስጥ የሆነ) ሌላ ትርጉም: የኳስና የሩር ማረፊያ፡ ኳስና ሩር የሚገቡበት ስፍራ፡ የሜዳ (ግፍ) ዳር ድንበር፡ ወይም ምልክትና የጥንግ አስተራረፍ። ሌላ ትርጉም: የነገር መልስ (አመጣጥ) ሌላ ትርጉም: መጨረሻ (መዳረሻ፣ ልክ) ምሳሌ:ነገር ከግቡ፣ ጋሻ ከንግቡእንዲሉ።

ግብስብስ፡ የተግበሰበሰ፡ ብዙ ግባስ፣ ገለባ፡ ጕትት፣ ክብስብስ ሰው።

ግብረ ሐዋርያ፡ የመጽሐፍ ስም፡ ሐዋርያት የሠሩትን ሥራና ያስተማሩትን ትምህርት የሚናገር መጽሐፍ።

ግብረ መርፌ፡ ወፍራምና ጠጕራም ባለዘርፍ ስጋጃ፣ ምንጣፍ፡ ለሱ በሚሆን ወፍራም መርፌ ስለተሠራና ስለተታታ 'የመርፌ ሥራ' ተባለ።

ግብረ መርፌ፡ ደባደቦ ጨርቅ ወይም የድሪቶ ምንጣፍ።

ግብረ ሥጋ፡ የሥጋ ግብር፡ ወንድና ሴት የሚሠሩት ዕምረት፣ ሩካቤ።

ግብረ በላ፡ በንጉሥ ወይም በመኳንንት ቤት ዘወትር መብል የሚበላ ካህን፣ ወታደር፣ ወይም ማንኛውም ሰው።

ግብረ ገብ፡ ፍጹም፣ ምግባረ መልካም፣ ምግባሩ የቀና፣ ሃይማኖቱ የጠና፣ እውነተኛ ደግ (ጻድቅ) ሰው፣ ሕግ ፈጻሚ፣ ትሑት፣ ነባይ።

ግብረ ጠል፡ በርስቱ ለመንግሥት ያልገበረ፣ ግብርን ጠልቶ የኼደ።

ግብራ፡ የዛፍ ስም፡ በጣና ዳር የሚበቅል ዕንጨት።

ግብር መጣጃ ከ፲ ሰዓት በኋላ።

ግብር በግእዝ ጸባሕት ይባላል።

ግብር፡ ዐሥራት፣ ቀረጥ (ማቴ፲፯:፳፬)

ግብር አቀለጠ፡ ሳይከፍል ቀረ።

ግብር እስከ መቃብር፡ ሙቶ እስኪቀበሩ ድረስ ግብር አይቀርም፣ አይታጐልም።

ግብር ውሃ፡ ሴቶች ማታ ማታ ይዘውት የሚወጡት መታጠቢያ።

ግብር፡ የማይቀር ግዴታ ሥራ፣ ቅዳሴ፣ የአባት ዕዳ፣ ለባሕርይ የሚስማማ መብልና መጠጥ። "ለተራበ በግብር ለተበደለ በነገር ተገኘ" እንዲሉ ።

ግብር ገባ፡ በላ፣ ጠጣ (ሰራዊቱ)

ግብር ገባ፡ ከሰው ተለየ፣ በዋሻ ተከተተ፣ ተዘጋ፣ ሱባዔ ያዘ።

ግብርና፡ ገበሬነት፣ ማረስ፣ መቈፈር፣ የገበሬ ሥራ። በግእዝም ግብርናት ባርነት ማለት ነው።

ግብት አለ: ፈጥኖ ገባ (ጥልቅ አለ፣ ዘው አለ)

ግብት: መግባት (በውስጥ መሆን)

ግብዝ (ተምያን): ድልዝ (ውስጠ ሰባራ፣ ብይድ፣ ቅልቅል፣ ቂራጥ)፡ ጥኑና ጠንካራ ያልሆነ፡ ጥሩ ያልሆነ፡ የተንኮልና የማታለል ሥራ ወይም ነገር። ምሳሌ:ግብዝ ወርቅግብዝ ፍርድእንዲሉ።

ግብዝ (ዞች): መደልው (ፈሪሳዊ)ሰነፍ (ይሉኝታ ቢስ፣ ዋሾ)፡ ለራሱ የሚያደላ (ናዝራዊ፣ ባሕታዊ)፡ ላዩ ደህና፣ ውስጡ ቀጣፊ፡ ወይም ላዩ ዳባ፣ ውስጡ ደባ (ማቴዎስ ፯፥፭፣ ኢሳይያስ ፴፫፥፲፬፣ ማቴዎስ ፮፥፪-)

ግብዝ ሆነ: ተገበዘ ተደለዘ፣ ተቀላቀለ፡ አፈ ጻድቅ ልበ ኃጥእ አድላዊ ሆነ

ግብዝነት: ዋሾነት አታላይነት ቀጣፊነት፡ ቅልቅልነት (ሉቃስ ፲፪፥፩፣ ሮሜ ፲፪፥፬፣ ፩ኛ ጢሞቴዎስ ፩፥፭) (ጥብ) ግብዝና: ዝኒ ከማሁ፡ ውሸት ተንኰል አድልዎ

ግብዣ: ጥሪ፡ መብል፣ መጠጥ፣ ምግብ።

ግብየታ፡ ግዥ፡ ሸመታ።

ግብድ (ዶች): ወፍራም እና ሰፊ ፍልጥ፡ ያልቀጠነ፣ ያልተሠነጠረ፣ ያልተሸነሸነ።

ግብግብ (ቦች): እጅጌ የሌላት አጭር ቍምጣ ጥብቆ የደረቅ ልብስ። ተመልከት: ግብጣን

ግብግብ አለ: ትግል ገጠመ፣ ጀመረ።

ግብግብ: ሠመር ገብቶ ደረት ለደረት ተጋጥሞ የሚተናነቁት ትንንቅ

ግብጣ (ጦች): ታናናሽ የጐድን አጥንት ከኩላሊት ጋራ። ሌላ ትርጉም: ሕፃን ሾለቅ፣ ሠላጤ፣ ቅድ፣ ወሽመጥ።

ግብጥ (ግብጽ፣ ቅብጥ): የነገድና የሀገር ስም፡ የካም ዕጣ፡ የእስያና የአፍሪቃ ወሰን ወይም ድንበር።

ግብጥ (ጥብ): የተገበጠ፡ ልዩ፡ ክምር፣ ክምቹ፡ ጓል፣ ሸክም።

ግብጥ ምስር: ሻሞች (ዐደስ ምስር) የሚሉት፡ ከግብጥ የመጣ የግብጥ ምስር ወጥ። "ብርስነ ግብጽ" ማለት ነው።

ግብጦ (ተርሙስ): የደንጐሎ ዓይነት መራራ እህል፡ ግብጣዊ ማለት ነው። ሌላ ትርጉም: ጠጠር ጣዮች በግብጦ የሚቆጥሩት የግብጦ ቍጥር (ጥንቆላና መላ)

ግብጦች (ግብጻውያን): የግብጥ ሰዎች፡ ቅብጦች።

ግቦ: እየጣፈጠ ወደ ሆድ የሚገባ የመኳንንት ምግብ።

ግተም: የንጨት ስም፡ ሎል የሚመስል ዛፍ፡ ፍሬውን ጦጦና ዝንጀሮ የሚገትመው፡ ቅጠሉ ሰበከተ ነጭ፣ ወዙ አረንጓዴ።

ግተት (አብድ): ከርፋፋ፣ ሞኝ፣ ቂል።

ግታም: ግተ፣ ትልቅ ላም፣ ፍየል፣ ሚስት።

ግት (ግቱዕ): የተገታ፣ የታገደ፡ እግድ፣ ውስን፣ ክልክል።

ግት (ግዕት): በጡት ውስጥ የታቈረ፣ የተቋጠረ ወተት፡ ያራስ፣ የንቦሳ፣ የግልገል፣ የውርንጭላ ምግብ።

ግት: በቁሙ፣ ጋተ።

ግትልትላም: ቅጥልጥላም፣ ቍጥርጥራም።

ግትልትል: የተግተለተለ፣ የተያያዘ፡ ቅጥልጥል።

ግትም አደረገ: ጨርሶ ቃመ። "፬ኛውን እይ"

ግትም: የተገተመ፣ የተቃመ።

ግትር አለ: ውጥር አለ፡ ቅስር አለ፡ ተገተረ።

ግትር ግትር አለ: ውጥር ውጥር፣ ውትር ውትር አለ።

ግትር ግትር አለ: ውጥር ውጥር፣ ውትርትር ውትርትር አለ።

ግትር: "ይስበረኝ፣ ይሠንጥረኝ" የማይል። ፊት ለፊት እውነቱን እቅጩን ተናጋሪ ሰው (ነገረ ጠንካራ)

ግትር: ልጥጥ፣ ውጥር፣ ቅስር፣ ድክር።

ግትር: ስል ያይዶለ (ዕርፍ፣ ማረሻ፣ ወይም ስበት)

ግትርትር አለ: ውጥርጥር፣ ውትርትር አለ።

ግትቻ (ግተት): የማንኛውም ስፌት ዕላቂ (ዐመድና ጥራጊ)፡ ፍግ ማውጫ፡ ኣሮጌ የኾነ። "ግተት" ግእዝ፣ "ግትቻ" ዐማርኛ ነው።

ግትን: የተገተነ፡ ቡጭቅ፣ ዝንትር።

ግትግት: የተገተገተ፡ ንክስ፣ ዕኝክ።

ግቻ (ግጫ): የስንደዶና ያክርማ የሌላውም ሣር ቅሬታ፡ የማጭድ፣ የከብት ትራፊ።

ግቻ: የሣር ቅሬታ (ገታ)

ግነዛ (ግንዘት)፡ ጥቅለላ፣ አሰራ፡ የመገነዝ ሥራ።

ግናዝ፣ ግንዛት፡ እስራት፣ ቍጥራት።

ግንቡል (ሎች) (ግንጱል)፡ ወፍራም፣ ደንዳና ዓሣ (የተጋደመ) (ጋድሚያ)

ግንባረ ቦቃ፡ ፊተ ነጭ (ከብት)

ግንባረ ደረቅ፡ ዕፍረተ ቢስ፣ "ይሉኝ አይል"

ግንባራም፡ ግንባረ ፈጣጣ።

ግንባራም፡ ጠላት የማይቆምለት (ዕድላም)፡ ድል አድራጊ፣ አሸናፊ።

ግንባር (ሮች)፡ ገጽ (ከሰርንና ከሽፋል በላይ ያለ ገላ)፡ ፊት፣ ስፍራ (የጐሽ ግንባር)፡ የስንዴ ስም (ነጭ ስንዴ) (ዐጪር) "ግንባርን ገጽ" ማለት በከፊል ነው።

ግንባር ለግንባር፡ ፊት ለፊት።

ግንባር ቀደም፡ በኵር፣ አለቃ፣ ዋና፣ አንጋፋ።

ግንባር፡ ዕድል፣ ሀብት፣ ገድ።

ግንባር ጸያፍ፡ ወርቅ ቀድሞ ከሠም ሲናበብ "ግንባር ጸያፍ" ይባላል።

ግንብል፡ የተገነበለ፡ ግልብጥ።

ግንብል ግንብል አለ፡ ግልብጥ ግልብጥ አለ።

ግንብብ፡ የዝነበበ፡ ባዶ አገዳ (ጣራ እንደሌለው ግንብ የተገተረ)

ግንብጥ፡ ከድብድብነት ያለፈ (ያገዳ፣ የበቈሎ፣ የብር) እኽል ፍሬ ብቅ ያለ።

ግንብጥ፡ የገነበጠ (የጐን፣ የገቦ) ቅጥይ (ፍሬያዊ)

ግንቦቴ፡ የግንቦት፡ በግንቦት የሚዘራ ገብስ፣ አንበዲያት፣ ጠበል።

ግንቦት፡ የወር ስም (ገነባ)

ግንትር፡ የነተረ ሥጋ (ጭብጥ ያለ)፡ ገርዳዳ፣ ዐኞ።

ግንኙ (ዎች)፡ የተገናኘ፣ የተጋጠመ፣ የተያያዘ፡ ድርብርብ፣ ንብብር፡ ቅልቅል።

ግንኙ፡ የተጋጠመ (ገኘ፣ ገነኘ)

ግንኙነት፡ መገናኘት፣ ተገናኝ።

ግንኝ፡ ግንኙ፡ ግጥም።

ግንኝት፡ ዝኒ ከማሁ።

ግንኝነት፡ ግንኙነት።

ግንዘት (ቶች)፡ የመጣፍ ስም፡ ለሞቱ ሰዎች ስለ ፍታት የሚደገም፣ የሚጸለይ መጣፍ (ከቅዱስ አትናቴዎስ የተደረሰና የተጣፈ) ባለ፯ ምዕራፍ።

ግንዝ (ግኑዝ)፡ የተገነዘ፡ ጥቅልል፣ ሽፍን፣ እስር፣ ክፍን።

ግንደ ቈርቍር፡ ግንድ ቈርቍሮ የሚበሳ (የቅንቡርስ ዐይነት ቡልማ ትል) "ደንቈር" የሚባልም ወፍ ትሉን ለመብላት ግንድ ይቈረቍራል።

ግንደ በል፡ የዘመቻ መሬት ያለው ጭፍራ (በጦርነት ጊዜ ሥንቅና ድንኳን ጝኝ፣ ተራዳ፣ ተሸካሚ)

ግንደ በረት፡ ከሙገር በስተግራ ያለ አገር።

ግንዲላ፡ ያልተጠረበ ዕንጨት (ግንድነት ያለው)

ግንድ (ዶች) (ጕንድ)፡ በሥርና በዐጽቅ መካከል ያለ ያልተቈረጠ ወፍራም ዕንጨት (ርጥብ)

ግንድ፡ መደብ፣ ሥር፣ መብቀያ። "ዦሮ ግንድ" እንዲሉ።

ግንድ፡ ተቈርጦ ሥራ ያሊያዘና የያዘ ደረቅ ዕንጨት፡ ደንዳና፡ የእግር ማሰሪያ።

ግንድ ዐመድ (የግንድ ዐመድ)፡ የሰራዊት ብዛት፣ ብዙነት።

ግንድ፡ የትውልድ መዠመሪያ አባት።

ግንድስ፡ ዝኒ ከማሁ፡ የተገነደሰ፡ ስብር፣ ሥንጥቅ።

ግንዶሽ፡ በቁሙ ግንድ።

ግንዶሽ፡ የጅራፍ፣ የዥራት ግንድ (አኒሳ)

ግንጃር (ሮች)፡ በሱዳን ቈላ ያለ ሻንቅላ።

ግንገና፡ ፍራት፣ ጥርጠራ፣ ጥርጣሪ፣ ሥጋት።

ግንጠላ፡ ቈረጣ፣ ሰበራ፡ የመገንጠል ሥራ።

ግንጣር፡ ቅንጣር።

ግንጣይ፡ ዝኒ ከማሁ።

ግንጥል (ሎች)፡ ከቃታው አጠገብ የሚገነጠል ባለ፪ አፍ ማደኛ ጠመንዣ።

ግንጥል አለ፡ ተገነጠለ፡ ወደ ጐን ወረደ።

ግንጥል፡ የባላ ዛቢያ ሲቈፍሩበት "ግንጥል" የሚል። "ወደደን" እይ።

ግንጥል ጌጥ፡ የማያምር (ልዩ) ጌጥ (ለሰውነት የማይስማማ)

ግንጥል: ጌጥ።

ግንጥልጥል አለ፡ ተገነጣጠለ።

ግንጥልጥል፡ የተገነጣጠለ፡ ብጥስጥስ።

ግንጭል (መንሰክ)፡ ልዩነት ያለው (ታችኛ መንጋጋ) (ማላመ) (አገጭ)

ግንፈላ፡ ፍላት፣ ፍልቅ ማለት።

ግንፊጥ (ጦች)፡ ታዛ፣ ታዛይ፡ የሰበሰብ ቅይድ፡ ልጥፍ ቤት። ዘሩ "ገነበጠ" ነው።

ግንፍሌ፡ የገነፈለች፡ ግልፌ።

ግንፍል አለ፡ ፍልቅ አለ፡ ፍስስ አለ።

ግንፍል፡ የገነፈለ (የባቄላ በቈልት) (ሙዳ) (ሥጋ)፡ ወይም እንፊሎ።

ግንፍል ግንፍል አለ፡ ፍልቅ ፍልቅ፣ ፍስስ ፍስስ አለ፡ መላልሶ ፈላ (ጠላው፣ ጠጁ፣ ቡናው፣ ውሃው)

ግዕዘ ብሔር፡ ያገር ልማድ።

ግዕዘ፡ ነጻ ወጣ፣ ተጓዘ።

ግዕዛን፡ ነጻነት፣ ሐርነት። "ግዕዛን የሌለው እንስሳ" እንዲሉ።

ግእዜ (ገዝአ፣ ግዝእ): ጐዶ (ጋሬዳ)፡ ድግስ (መሰናዶ)፡ ፍሪዳ ያለበት የመብልና የመጠጥ፣ የምሳ በዓል (ኢዮብ ፩፥፬) ምሳሌ:ግዝኡ ባለ በቀና ነበር

ግእዝ (ንባብ): የንባብ ስም። ከወርድ ንባብ የሚቀድም፡ ሕፃናት የፊደልን ቍጥር እጅና እግሩን ከለዩ በኋላ ከነቍጥ እስከ ነቍጥ የሚያግዙት ማጋዝ።

ግእዝ (ዜማ): የዜማ ስም። አንደኛ ስልት፡ መዠመሪያ ዜማ (የአብ ምሳሌ)

ግእዝ (ግኢዝ፣ ግእዘ፣ ገአዘ): የቋንቋ ስም፡ ሴማዊ (አዳማዊ) ልሳን፡ ከሱርስትና ከዕብራይስጥ፣ ከዐረብ የሚገጥም። ዘይቤው አንድ መዠመሪያ፡ ምስጢሩ ጥንታዊ (አዳማዊ) ማለት ነው። ማስታወሻ: ግእዝአንድመባሉ ምክንያት መሆኑን አስተውል።

ግእዝ (ፊደል): የፊደል ስም። አንድ ወጣት፣ አንድ ቅንጣት፣ ዕዝል፣ ቅጥል፣ ነቍጣ፣ ምክትል (ዋየል) የሌለው፡ ቀንጃ (ነጠላ) ፊደል። ከአ እስከ ያለአ፣ በ፣ ገ፣ ደ፣ ሀ፣ ወ፣ …” አንድ (አንደኛ፣ መዠመሪያ) ማለት ነው። ምሳሌ: ግእዝ፣ ግእዝ፣ ግእዝእንዲሉ። ተመልከት: የአን አፈታት።

ግዕዝ፡ ባህል፣ ልማድ።

ግእዝኛ (ግእዛዊ): ዝኒ ከማሁ፡ ፊተኛና ኋለኛ። ምሳሌ:ፊተኛው ነገሠ ረመሓየ፣ ኋለኛው ንጉሥ ረምሓይእያለ በአኵስም መሐልቅና ሐውልት ላይ ተቀርጾ የሚታይ።

ግው (ጎግዎ፣ ጎገወ)፡ ግር፣ ግም፣ ብው።

ግው አለ፡ ግር አለ፣ ግም አለ፣ ብው አለ።

ግዘታ፡ ውግዣ፣ ውግዘት፡ ልየታ፣ ክልከላ።

ግዙ፣ ግዝ (ግዙእ)፡ የተገዛ፣ ተገዥ፣ ባሪያ፣ መግዞ።

ግዙር፡ የተገዘረ፡ ግርዝ።

ግዙርነት፡ ግርዝነት፣ ይሁዲነት፣ ፈላሻነት።

ግዙፍ፡ የገዘፈ፣ የደነደነ፣ ደንዳና።

ግዛ (ትግ፣ ግዛዕ)፡ አንዳች፣ ምናምን።

ግዛ ምዛ (ትግ፡ ግዛዕ፡ ምዛዕ)፡ ምናምን ነገር፣ ጣጣ፣ ሰበብ፣ ምክንያት። "ይህ ሰው ግዛ ምዛ ያበዛል"

ግዛት (ቶች) (ግዝአት)፡ ወረዳ፣ አውራጃ፣ ቀበሌ፣ ይዘታ፣ ርስት፣ ጕልት፡ መንግሥት (መክ፮፡ ፪፣ ሕዝ፳፱፡ ፲፰)

ግዛው፡ የሰው ስም፡ "አገሩን ወይም ሕዝቡን አንተ ግዛው"

ግዜ፡ ዝኒ ከማሁ።

ግዝረት፡ መግዘር፣ መገዘር፣ ገዘራ።

ግዝረት፡ በጥር ቀን የሚውል የጌታችን የኢየሱስ በዓል።

ግዝራት፡ ግርዛት።

ግዝት (ውጉዝ)፡ የተገዘተ፣ የተወገዘ፣ የተለየ፣ የተከለከለ፡ ክልክል። "አንተ ይህን እንዳታደርግ ግዝት ነህ"

ግዝት (ግዘት)፡ መገዘት፣ መገዘት፡ ማላ፣ ክልከላ፡ ውግዣ፣ ርግማን። "እከሌ ግዝት አፍራሽ ነው" እንዲሉ።

ግዝገዛ፡ ክርከራ፣ ምገዛ፣ ክርከማ።

ግዝግዝ (ግዙዝ፣ ግዙዕ፣ ውሡር)፡ የተገዘገዘ፣ የተመዝዘ፡ ክርክር፣ ምግዝ፣ ክርክም።

ግዝፈት፡ ውፍረት፣ ድንዳኔ።

ግዝፊያ፡ መግዘፍ።

ግዞተኛ (ኞች)፡ የተጋዘ፣ የተሻረ፣ የታሰረ፡ ሽር፣ እስረኛ።

ግዞተኛነት፡ ሽር መሆን፣ እስረኛነት።

ግዞት (ግእዘት)፡ ሽረት፣ እስራት፣ ቅጣት፣ ውርደት፣ ወህኒ (ዘፍ፴፱፡ ፳፡ ፳፪፡ ፳፫፣ ኢሳ፵፪፡ ፯፣ ማቴ፭፡ ፳፭)

ግዡ፡ የጋዥ፣ የከፋ፣ ክፉ፡ የተበላሸ፣ ብልሹ፣ መጥፎ፣ ዥዡ።

ግዥ፡ ግብየታ፣ ሸመታ።

ግዥል፡ ገጀለ፣ ግጅል።

ግዥልዥል፡ ረዥም፣ ጕትት፣ ውዥምጉም፣ ውዳቂ።

ግዮን፡ ነጭ አባይ (ግእዝ)

ግደ በል) በግድ ጭኖ የሚበላ።

ግዱፍ፡ የተገደፈ፣ የተጣለ፣ ወይም ዝልጉስ።

ግዳም፡ ግድ ያለው፣ ባለግድ፣ ወፍራም፣ ቦርም።

ግዳይ (ግዱል፣ ቅቱል)፡ የተገደለ፣ የሞተ፣ ሬሳ፣ በድን፣ ወይም ሰለባ (ሕዝ፲፩፡ ፮)

ግዳይ፡ መግደል። "ነፍሰ ግዳይ" እንደሚባለው።

ግዳይ ጣለ፡ ሰለባ አሳየ ወይም ፎከረ።

ግዳዮች፡ ሬሶች ወይም በድኖች (ኤር፳፭፡ ፴፫)

ግዳጅ (ትክቶ)፡ የሴቶች አበባ፣ በወር በወር የሚፈስ ደም። ባላገሮች ግን በኦሪት ሕግ "አደፍ" ካህናትም "መርገም" ይሉታል።

ግዳጅ፡ ችግር፣ መፍቀድ፡ በግድ የሚፈለግ ነገር፣ ጕዳይ። "ግዳጅ አለኝና አንተ ዘንድ እመጣለሁ"

ግዴታ (ዎች)፡ ማስገደድ፣ መገደድ፣ ግድ፣ ግድነት። በግእዝ "ግደት" ይባላል።

ግድ (ጥድ)፡ በቁሙ፣ ገደደ።

ግድ፡ ሥብ የማዥራት ሥጋ፣ እንደ ዕርከን ኾኖ የሚታይ፣ መተንፈስና መኼድ የሚከለክል ነው።

ግድ አለ(አገበረ)፡ በግድ አዘዘ፣ አስቸገረ፣ ወጥሮ ያዘ።

ግድ አሠኘ፡ አስባለ፣ አናገረ፣ በግድ።

ግድ፡ እንደ "" እና "" ሲሰማማው "የግድ" ይላል።

ግድ፡ ውድና ፈቃድ የሌለበት ሥራ፣ ነገር፣ ግብር (፩ሳሙ :፳፰) (ግጥም)"ግድ የለም፣ ግድ የለም፣ ሰው እንዳይኾን የለም"

ግድ የለሽ፡ ዐሳብ የለሽ፡ "ምን ቸግረኝ" ባይ።

ግድ፡ የተጋዳ፣ የተጠለፈ።

ግድል (ጥል)፡ ድብን፣ ሙትት።

ግድል አደረገ፡ አደበነ።

ግድመት፡ እንደ ግድም (ኢሳ፲፭፡ ፭)

ግድም (ጥድ)፡ የተገደመ ወይም ገዳም የሆነ።

ግድም አለ፡ ጎኑ መሬት ነካ።

ግድም፡ ገደማ፣ ዘንዳ፣ ወይም በመንዝ ውስጥ ያለ አገር። "ግድምና ኤፍራታ" እንደሚባለው።

ግድርድር፡ የተግደረደረ፣ ኵሩ፣ ግብዝ። ሲበዛ "ግድርድሮች" ያስገኛል።

ግድብ፡ የተገደበ፣ የተከተረ፣ ክትር፣ ድልድል፣ የታገደ፣ እግድ። መሬትንና ውሃን ባንድነት ያሳያል።

ግድቦች፡ ክትሮች፣ ዦሮች።

ግድነት፡ ግድ መኾን።

ግድንግዲ፡ የአሞራ ስም ሲሆን ግድግዲ ተብሎም ይጠራል።

ግድንግድ (ዶች)፡ በሜዳ ላይ ያለ ከፍተኛ ቦታ። ረጅም እና ወፍራም ዛፍ ወይም ሰው። ሥሩ ገደገደ ነው፣ ከግንድም ጋር ይሰማማል።

ግድያ (ቀትል)፡ ሰልፍ፣ ውጊያ፣ ውጊት፣ ጦርነት፣ ትግል፣ ወይም ትንንቅ።

ግድገዳ፡ ተከላ፣ ውጠራ።

ግድግዲ፡ ግድንግዲ፣ ታላቅ አሞራ፣ ነጣቂ፣ ግልገል አንሣ፣ የሎስ ጐሢ፡ እንደ ግድንግድ በምድር ቁሞ ተገትሮ የሚታይ (ዘሌ ፲፩:፲፱)

ግድግዳ (ዶች)(ገድገድ) ቦግንብ ፈንታ ቁሞ የተማገረ፣ ጣራ ተሸካሚ፣ ብዙ ዕንጨት (ዘፀ፴፯:፳፯)

ግድግዳ፡ መጀመሪያ ስንኝ።

ግድግዳ፡ የብሽሽትና የብብት ዕብጠት ወይም እንደ ቂጥኝ ያለ የሕፃናት ሶከክ።

ግድግዳውን ጨርሶ እጣራው ተጋባ፡ በጣም ራበ፣ ልብን አደከመ፡ ራስን አዞረ።

ግድግድ፡ የተገደገደ፣ የተተከለ፣ የቆመ፣ ውጥር።

ግድፈተ ጸሓፊ፡ የጸሐፊ ቃልን መዝለል።

ግድፍት፡ ፍስክ፣ ፋሲካ፣ ወይም ማንኛውም ሥጋ የሚበላበት ቀን።

ግጃዋ (ጊዜዋ)፡ የንጨት ስም፣ ጠላ እንዳይበላሽ፣ ሴቶች እጥንስስ የሚያገቡት ዕንጨት።

ግጅል (ግዱል)፡ አእምሮ ቢስ፣ ሞኝ፣ ቂል፣ ወይም ውዳቂ።

ግጋም፡ ግጉ፣ የሚነቀል፣ የሚመነገል ልጅ፣ ወይም ዘር፣ ነገድ። መንቀያውም ታናሽ ቈላፋ ብረት ናት።

ግግ፡ መጀመሪያ ድድን ሠንጥቆ በላይና በታች የሚወጣ፣ የልጆች ጥርስ። የሚያስቀምጣቸው፣ የሚያስቀዝናቸው የወተት ጥርስ፣ ካደገ በኋላ ክራንቻ ይባላል።

ግግ የመነገገና የሞገገ ዘር ነው።

ግግ፡ ጋጋኖ።

ግግር አለ፡ ተጋገረ፡ ልክክ አለ፡ ተሰጣ።

ግግር፡ ዝምተኛ ሰው።

ግግር፡ የተጋገረ፣ የረጋ፣ የጠና (ሠም፣ ሞራ፣ ደም፣ ቅባት፣ የመሰለው ሁሉ) (ተረት)"ንግርና ግግር ሳይደርስ አይቀር"

ግጠኸ ውጣ፡ በጭንቅ በችግር ሠርተህ ወረስ።

ግጣም (ሞች)፡ ለጠብ መግጠሚያ።

ግጣቢ፡ ቅንነት የሌለው፣ ሲጠሩት "ወይ" የማይል። ክፉና አልምጥ ልጅ፣ ለዛ ቢስ፣ መታዘዝና ትሕትና አልባ።

ግጥሚያ፡ መግጠም፣ አገጣጠም፣ ነኛ፣ ተሰማሚ፣ ውድ፣ ግንኝነት፣ ቀረቤታ።

ግጥም (ሞች)፡ የተገጠመ፣ የተዘጋ፣ የታተመ፣ የታሸገ፡ ዝግ፣ እሽግ፡ የዘፈን ስንኝ (፪ዜና፡ ፴፭፡ ፳፭)

ግጥም፡ ሙሉ ዕቃ፣ ርስ በርሱ የሚገጥም።

ግጥም አለ፡ ልክክ አለ፡ ሞተ (ዐይኑ ተከደነ፡ አፉ ተዘጋ) "እከሌ ሳይታመም ድንገት ግጥም አለ፡ ሞላ፣ ሙሉ ሆነ"

ግጥም አለ፡ ጨለመ። "ሰዓቱ ግጥም ቢል ይህን ነገር አላደርገውም"

ግጥም አደረገ፡ በጥፊ መታ፡ አጥብቆ አሰረ፡ ጨልጦ ጠጣ። "መላ ሙሉ አደረገ"

ግጥም: "ዐራዳ ለኪራይ ቤት የፈሊጋችሁ ዘማለች፣ ምናልባት በውል እያያችሁ። ዘማለች እያልነ ምክር እየናቁ፣ ምን ይጠቀማሉ እየገቡ ቢያልቁ። "

ግጥም: "እየጠጡ ዝም፡ የጋን ወንድም። "

ግጥም: "የዝንጀሪትዬ የዝንጀሪት፡ እናትሽ ሞተች በነጋሪት" እንዲሉ ሴቶች ልጆች።

ግጥም:እንጅልኝ ወዲያልኝ ሰው መሆን ሰለቸኝ፡ በላይ ቤት አልሠራሁ፡ በምድር አልተመቸኝ።

ግጥምጥም አለ፡ ተገጣጠመ፡ ተሳካ።

ግጥምጥም፡ የተገጣጠመ።

ግጥብ አለ፡ ተገጠበ።

ግጥብ አደረገ፡ ምልጥ አደረገ፣ ገጠበ።

ግጥብ፡ የተገጠበ፣ የተመለጠ፡ ሣር፣ ቅጠል የሌለበት መሬት፣ ንክ (የሥና፣ የከብት ዠርባ)

ግጥብጥቢ፡ ግጥብጥብ፣ የተገጣጠበ፡ በብዙ ስፍራ ተገጥቦ የቈሰለ፣ ምልጥልጥ።

ግጥብጥብ አለ፡ ተገጣጠበ።

ግጥግጣ፡ ቅጥቀጣ፣ ምት።

ግጥግጥ፡ የተገጠገጠ፡ ቅጥቅጥ፣ የመብራት ዕንጨት፣ ክትክታ፣ ፍየለፈጅ።

ግጦ፡ በቡልጋ ክፍል ያለ ቀበሌ።

ግጦ፡ ግጦሽ፣ ለቀም፣ ሣር፣ ደንጊያ።

ግጫ (ግቻ)፡ ከብት የነጨው፣ የጋጠው በመሬት ላይ ያለ ያጭር ሣር ቅሬታ።

ግጫ፡ እንግጫ (ጮች)፡ የንቁጣጣሽ ሣር፣ እንቁጣጣሽ (ኢሳ፲፱፡ ፲፭)

ግጭ፡ ትእዛዝ አንቀጽ፡ ምታ፣ ለትም፣ ኰርኵም።

ግጭ፣ አገጭ፡ በታችኛ ከንፈር ሥር ያለ ሾጣጣ ገላ።

ግጭር (ሮች)፡ የተገረ፣ ዝግ ብሎ ኼያጅ፣ ድንስር።

ግጭት (ቶች) (ድድቅ)፡ መግጨት፣ መገጨት፡ ድንገተኛ ጥል፣ ዕለተ ጠብ፣ ያልታሰበ አደጋ፣ የጊዜ ጦርነት።

ግፈኛ (ኞች)፡ ዐመፀኛ፣ በደለኛ፣ ክፉ አድራጊ፣ ቀማኛ (መዝ፻፵:::፲፩፣ ምሳ፫:፴፩፣ ሉቃ፲፮:፲፣ ሮሜ፫:)

ግፈኛነት፡ ዐመፀኛነት፣ በደለኛነት።

ግፈኝነት፡ ዝኒ ከማሁ (ሮሜ፪:)

ግፉዓን፡ የተገፉ ሰዎች፡ የደብረ ሊባኖስ ጠበል ("ግፉዕና ግፉዓን" ግእዝኛ ነው) "ግፉዓን ጠበለተኞች ናቸው፡ ሲጠመቁ ይገፋሉና"

ግፉዕ፡ የተገፋ፣ የተበደለ።

ግፊ፡ ግፊያ፡ የመግፋት ሥራ።

ግፋ ወሰን፡ የሰው ስም።

ግፋን፡ የቍርጥና የመት የፍጥነት (የቀጥታ) መንገድ፡ ሳያመነቱ ግራ ቀኝ ሳይሉ መኼድ፡ ርምጃ መቀጠል።

ግፋፊ፡ የተገፈፈ፡ ገለፈት፣ ልጥ፣ ሰፈፍ፣ ዐሠር፣ የወተት ስልባቦት፣ የመጠጥ ዐረፋ፣ የዳቦ ልብስ፣ እንጀራ።

ግፍ (ግፍዕ)፡ በቁሙ፡ በደል፣ ዐመፅ፣ ክፉ ሥራ (ሉቃ፲፮:)

ግፍ ሠራ፡ ነፍስ አጠፋ፣ ገደለ።

ግፍ ሠራ): ዐመፀ፣ በደለ (ሰውን)

ግፍ፡ ቅርፊት።

ግፍ፡ ቅርፊት (ገፈፈ)

ግፍ ተዋለበት፡ ተሠራበት፣ ተደረገበት።

ግፍልፍል፡ ተጫዋች ሰው።

ግፍልፍል፡ የተግፈለፈለ (የድርቆሽ ወጥ)

ግፍት አገር፡ ገፈተ።

ግፍት፡ የተገፈተ፣ የተቀመሰ፡ ዥምር።

ግፍት፡ ያገር ስም፡ በታችኛው ወግዳና በተጕለት ውስጥ ያለ አገር። "ግፍት ከወይና ሲናበብ የንጨት ስም ይኾናልና ወይናን እይ" የግፍት ትርጓሜ ማቃጠልንና መግፈፍን ያሳያል።

ግፍንት፡ ገልቱ (ዕውቀተ ቢስ) ሴት።

ግፍንት፡ ገልቱ ሴት (ጋፈ)

ግፍገፋ፡ ዐጨዳ፣ ጠረጋ፣ ቅርደዳ።

ግፍጥፍጥ፡ የተግፈጠፈጠ፡ በምድጃ እየጨሰ የሚነድ ግንድና ኵበት።

ጎሐ ጽባሕ፡ የብላቴን ጌታ ኅሩይ መጽሐፍ ስም። ማተሚያ ቤቱም "ጎሐ ጽባሕ" ይባል ነበር።

ጎሐ ጽባሕ፡ የንጋት ውጋገን።

ጎሐ ጽዮን፡ በሰላሌ አውራጃ ያለ አገርና መቅደስ። የጽዮን ጎሕ ማለት ነው።

ጎሕ (ገዊሕ፣ ጎሐ)፡ ከንጋት በፊት ደም መስሎ የሚታይ ብርሃን፣ የመንጋት ምልክት።

ጎሕ ሲቀድ፡ ጎሕ ሲያበራ፣ ሲያሳይ። "መንገደኛው ጎሕ ሲቀድ ተነሥቶ ኼደ"

ጎሕ ቀደደ፡ አየሩን፣ የሌሊቱን ጨለማ ከፈለ፣ ሠነጠቀ፡ አበራ፣ አሳየ።

ጎሕን፡ አስተውል፡ "የጊዜና፡ ኀላፊ፡ ትንቢቱም፡ ይቀድ፡ ይቀዳል፡ እያለ፡ ጠብቆ፡ ይነገራል፡ እንጂ፡ ይቀድድ፡ ይቀድዳል፡ አይልም፡ ቢልም፡ ስሕተት፡ ነው። "

ጐለለ (ቈለለ)፡ ጕልላት ሠራ፣ አበጀ፡ በቤት ቍንጮ ላይ ነ፣ አኖረ፡ ክዳን ጨረሰ።

ጐለለ፡ ቀለም አበዛ (ሲጽፍ)

ጎለልታ፡ ገለል ማለት።

ጐለመ፡ ከፈለ፣ ለየ፣ ቈረጠ፣ ሰጠ (መሬትን) በትግሪኛም "ገመጠ" ማለት ነው፡ ከፈለ ካለው ይገባል።

ጐለመሰ፡ አሞላ (አካለ መጠን አደረሰ)፡ ጐረመሰ፣ ጐበዘ፡ ሪዝ አወጣ፣ አቀመቀመ፣ ጸና፣ በረታ።

ጐለሰ፡ በዛ፣ ፈደፈደ።

ጐለሰሰ፡ ፈጥኖ አሸነፈ፣ አደከመ፣ ጣለ፡ ተጫነ፣ ጨቈነ፣ ጐለፈጠ፣ ጐለፈፈ፣ ረፈቀ፣ ኣሳፈረ።

ጐለሰስ፣ ጐልሳሳ፡ የተጐለሰሰ፡ ሽንፍ፣ ጭቍን፡ ደካማ፣ አሮጌ።

ጐለበ (ገለወ)፡ በቈዳ ለጐመ፣ ለበደ፣ ሸፈነ፣ ጠፈረ (የከበሮ፣ የሌላም ነገር) ትግርኛ ግን "ጐለበን" "ተቀለሰ" "ጐበጠ" ይለዋል።

ጐለበተ፡ በረታ፣ ጠና፣ ጠነከረ፣ ዐየለ።

ጐለተ (ጐልቶ፣ ጐለተ)፡ ጕልቻን ተከለ፣ ጠመዘዘ፣ አቆመ፡ ለካህናት፣ ለመኳንንት፣ ለወይዛዝር ጕልትን ከለላ ሰጠ፡ ሰውን አስቀመጠ፣ ረፈቀ።

ጐለት፡ ጭጐት።

ጐለንዳ፡ እባብ፣ ከይሲ።

ጐለንዳ፡ ወምበርቲ።

ጐለደመ፡ አናጋ፣ ለየ፣ ዐጠፈ፣ ኰረተመ፣ አወጣ።

ጐለደፈ (ለደፈ)፡ ፈጽሞ ደነዘ፣ ላሸ (ስለትና ሹለት)፡ ጥፍር ትባት ዐጣ፡ ለንባዳ ሆነ (፩ሳሙ:፲፫:፳፩፣ መክ፲:) (ተረት)"ያደፈ በንዶድ፡ የጐለደፈ በሞረድ"

ጐለደፍ፣ ጐልዳፋ፣ ጕልድፍ፡ ደነዝ፡ ዕውር ጣት፡ ለንባዳ አንደበት።

ጐለጐለ፡ ቈነጨ፣ ነሰነሰ፣ ለቀመ (ዐረምን፣ ሰርዶን) (ኢዮ፴፱:፲፣ ሆሴ፲::፲፩)

ጐለጐለ፡ ናደ፣ አበላሸ (ልቃቂትን)

ጐለጐለ፡ አወጣ (ምላስን፣ ንፍጥን፣ አንዠትን)

ጐለጐለ፡ አፈጠጠ፣ አጐረጠ (ዐይንን)

ጐለጐል፡ ከዋሻ የወጣ ነብር፡ አነር (የነብር ዲቃላ)፡ ከልብሱ ውስጥ እግሮቹንና ዐንገቱን ብቅ ያደረገ ዔሊ (የልጆች ማስፈራሪያ)

ጐለጠመ፡ ሰበረ፣ አነከተ፣ ቀለጠመ።

ጐለፈጠ፡ ጐለፈፈ።

ጐለፈፈ፡ በርጅና ከሳ (ተገብሮ)

ጐለፈፈ፡ ጐለሰሰ (ገቢር)

ጐላ (ስም)፡ ታላቅ የብረት ጋን ወይም ድስት፣ ፍሪዳ፣ ዳውላ እህል የሚቀቅል።

ጐላ (ጐሊሕ፣ ጐልሐ)፡ ከመቅጠን፣ ከርቀት፣ ራቀ፣ ጕልሕ ሆነ፡ ገዘፈ፣ ወፈረ፡ ከሩቅ ታየ፣ ደመቀ (የጥፈት፣ የጥቃቅን ነገር)

ጐላ (ጐሊሕ)፡ መጕላት።

ጐላ ሰፈር፡ በአዲስ አበባ የሚገኝ የጐላ አካባቢ ሰው ሰፈር።

ጐላ፡ በባሶ ወረዳ ያለ ቀበሌ ስም።

ጐላ አለ፡ ጐላ።

ጐላሚ፡ የጐለመ፣ የሚጐልም፡ ምድር ሰጪ።

ጐላቢ፡ የጐለበ፣ የሚጐልብ፡ ለባጅ።

ጐላች (ቾች)፡ የጐለተ፣ የሚጐልት፡ ጕልት ሰጪ፣ ተካይ፣ ከላይ።

ጐላዎች፡ ታላላቆች ጋኖች፣ ድስቶች።

ጐላይ (ዮች)፡ የጐለለ፣ የሚጐልል፡ የሚጭን፡ ከዳኝ።

ጐሌ፡ የሰው ስም፡ በመንዝ የአፍቀራ ባላባት። "ጕልላቴ" ማለት ነው።

ጐልማሽ፡ የሚጐለምስ።

ጐልደያ፡ በኦሮ ቤት፣ በከፋ ክፍል ያለ አገር።

ጎልጎታ፡ የራስ ዐጥንት (ራስ ቅል)፡ ጌታ የተሰቀለበት ስፍራ፣ የአዳም መቃብር።

ጎልጎታ፡ የጸሎት መጽሐፍ በመቤታችን ስም የተጻፈ።

ጐልጓይ (ዮች)፡ የጐለጐለ፣ የሚጐልጕል፡ የሚቈነጭ፡ ለቃሚ፣ አውጪ።

ጐልፋጣ፡ ጐልፋፋ።

ጐልፋፋ፡ ጐልሳሳ፡ ከሲታ።

ጎመ (ገዪም፣ ጌመ)፡ ጉም ኾነ፡ ዐፈነ፣ ሸፈነ፣ ጠቀጠቀ።

ጐመ፡ ዐለቀ፣ አነሰ፡ ጕ፣ ጕጣ፣ መሰለ፣ አከለ።

ጐመለለ፡ አንበስኛ፣ ዝንጀርኛ ኼደ። "ጐደደን" እና "ጀነነን" እይ።

ጐመረ፡ ነፋ፣ አሳበጠ፡ አኰራ።

ጐመራ (ጻዕደወ)፡ በሰለ፣ ነጣ፣ ገረጣ (የሰብል)

ጐመርታ፡ ሽበት የወረረው (ያርባና ያምሳ ዓመት ሐርበኛ)፡ ብስል ሰው፣ የጦር ገበሬ።

ጐመተ፡ ርጥብ ሥጋን ሙዳ እያደረገ ጭብጦ ያካክል (ጐመደ) ቈረጠ፣ ከፈለ። ('' '' ለውጥ መኾኑን አስተውል)

ጐመተ፡ ትልቅ አደረገ።

ጐመን (ኖች)፡ የተክል ስም፡ ተክል (ተቀቅሎ የሚበላ) ቅጠል፡ ፍሬው ማሠሻ ሲያደርጉት የሚያር፣ የሚገምን፡ አባጀኸኝ (አይ ደርቄ) የወፍ ዘረር፣ ሥንቆ፣ የጕራጌ ጐመን።

ጐመን በጤና፡ በሽተኛ ኹኖ ሥጋ ከመብላት ጤንነት ካለ ጐመን ይሻላል።

ጐመን ዘር፡ የጐመን ዐይነት (ዘረር)

ጐመን ዘር፡ የጐመን ፍሬ (ዘር የሚኾን)

ጐመዘዘ፡ መረረ፣ መረገገ፣ ኮመጠጠ፡ በምረትና በኩምጣጤ መካከል ኾነ (የንጆሪ፣ የኰሽም)

ጐመዘዝ፣ ጐምዛዛ፡ የጐመዘዘ፡ ኮምጣጣ፣ መርጋጋ፡ ዦሮ ግንድ የሚወጋ።

ጐመዠ፡ ሺዋ (የሴት ስም)

ጐመዥ (ተመነየ፣ ፈተወ)፡ ሠየ፣ ጓጓ፣ ቋመጠ፣ ተቃረ፡ "አኹን አኹን" አለ፡ ማግኘትን ቍርጥ አደረገ። ('' '' ተወራራሾች ስለ ኾኑ መጽሐፍ "ጐመጀ" ይላል) (ዘፍ፴:፴፰:፵፩፣ ኤር፭:)

ጐመደ (ገምዶ፣ ገመደ)፡ ቈረጠ፣ ጐረደ፣ ጐነደበ፣ በጠሰ፣ ሰለበ። "ጐመተን" እይ።

ጐመደ፡ በጐመድ መታ፣ ደበደበ።

ጐመደ፡ ዐሰለ፣ ዋሸ።

ጐመደ፡ ገመጠ (በላ ዳቦን)

ጐመዳም ዱላ፡ ጐመድ የለበሰ፣ ያጠለቀ፣ ባለጐመድ በትር።

ጐመድ (ዶች) (ትግ) ቈመጥ (መንደርቶ ከዛፍ ላይ ተጐምዶ ሳይጠረብ፣ የሚያዝ ወፍራም ዱላ) (በሎታ) (ሕዝ፴፱:፱፣ ማቴ፳፮:፵፯:፶፭፣ ማር፲፬:፵፰:፵፰)

ጐመድ፡ ከበግና ከፍየል እግር ተገፎ (እንደ ቀለበትና ) የሚወጣ ቈዳ (ማፈኛ) (በዱላ ላይ የሚሰካ) (የበትር ቤዛ፣ ጂና)

ጐመድ፡ ፍጹም ዐባይ፣ ሐሰት ጽድቁ።

ጐመጀ፡ ሠየ (ጐመዠ)

ጎመጎመ (ጎመ)፡ ሸፋፈነ፣ ዐፋፈነ።

ጐመጐመ (ጐጐመ)፡ ወጣ፣ ብቅ አለ፡ በቀለ፣ ታየ።

ጐመጐመን እይ።

ጐመጠ፡ ውሃን ፉት አለ፡ ዐጠበ፣ አጠዳ፣ አጠራ (አፍን)

ጐመጠጠ (ትግ ጐምጠጠ)፡ ደን ልብስን ሳበ፣ ጐተተ፡ ሰው እሸትን ላሰሰ፣ ሰሰ።

ጐመጭ፡ ከዳ። "ዕጭ ጐመጭ" እንዲሉ።

ጐመጭ፡ የሣር ስም፡ አገዳው ቀጪን የኾነ ሣር (ባለብዙ ዛላ)፡ ርጥቡን ከብት የሚበላው (የሚያጓምጠው)፡ ዝንጀሮ የሚያኝከው፣ የሚመገበው።

ጐሚት (ቶች) (ፍሕሶ)፡ እጅግ የሚያምር ዕጥፍ አበባ (በበልግ ዝናም የሚለመልም)፡ ክብ የምድር ጕተና፡ ደማቅ ቀይ።

ጐሚት ገና፡ የእባብ ስም፡ ዠርባው የጐሚት ዕንጨት (ላንፋ) ሆዱ ብልጭልጭ የሚመስል፣ ቁመቱ የጥንግና የሩር መምቻ ገና የሚያኸል፣ ትልቅና ተልብማ አባብ (የገና ለት ወደ ሄሮድስ የኼደው የሰይጣን ምሳሌ)፡ ማደሪያው መደበቂያው (ጎሜእ) የሚባል ቀርክሓ ስለ ኾነ "ጎሚት ገና" የተባለ ይመስላል።

ጎማ፡ ድዳ፣ የማይናገር ሰው። "አፈ ጎማ" እንዲሉ።

ጎማ፡ ጕመላ፡ ቀንድ አልባ ጐዳ በሬ፡ እንስት የዱር ፍየል።

ጎማ፡ ጠንካራ ላስቲክ።

ጐማ) አጕማማ፣ ያልተረገጠ ወሬ ዐፍኖ፣ ሸፍኖ፣ ውስጥ ውስጡን አወራ፣ አሾከሾከ፣ ህምህም አለ።

ጎማመደ፡ ሸራረበ።

ጐማመደ፡ ቈራረጠ፣ ጐራረደ፣ በጣጠሰ።

ጐማሪ፡ የጐመረ፣ የሚጐምር፡ ነፊ፣ አኵሪ።

ጐማች፡ የጐመተ፣ የሚጐምት፡ የሚቈርጥ፡ ጐማጅ፣ ከፋይ።

ጐማዳ (ዶች)፡ ስልብ (አፍንጫ ዐጪር) (ዘሌ፳፩:)

ጐማዴ፡ ዝኒ ከማሁ፡ ጃን ደረባ ጠባቂ፡ የጐማዳ ወገን። "አባን" ተመልከት።

ጐማጅ (ገማዲ)፡ የጐመደ፣ የሚጐምድ፡ የሚቈርጥ፣ የሚጐርድ፡ ቈራጭ፣ ጐራጅ።

ጐምላላ (መካሕ)፡ ቈናና፣ ኰፍናና፡ ጕልማሳ አንበሳ፣ ገመር።

ጐምር (ሮች)፡ የበሰለ እሸት (አገዳው ብሩ የነጣ፣ የገረጣ)

ጐምቱ (ዎች)፡ ጨዋ፣ ትልቅ ሰው፣ ዐዛውንት።

ጐምዛ፡ መራራ ሴት (ዐመለ መጥፎ)

ጐምዛ፡ ክፉ ሴት (ጐመዘዘ)

ጐምዢ፡ የሚጐመዥ፣ የሚጓጓ።

ጐምዤ፡ ዘንጋዳ (ጐመዘዘ)

ጐምዤ፡ የሚጐመዝዝ፡ ዘንጋዳ።

ጎሞር፡ አንድ መገበሪያ ዶቄት የሚይዝ (የሸክላ ወይም የስፌት) ዕቃ (ንዋየ ቅድሳት)፡ ልብም።

ጐሰመ (ትግ ጐሰመ፣ ቃመ፣ ልብስ አጣፋ): ነጋሪት መታ (ድም ድም አደረገ)"ደለቀን" እይ።

ጐሰመ ንና፡ ጐሸመን፡ እይ።

ጐሰመ: ወጋ፣ ጓጐጠ (በሬን፣ ኣህያን)

ጐሰሰ (ቈሰሰ): ኰሰሰ፣ ከሳ፣ ደከመ።

ጐሰሰ እና ቈሰስ የጐተተ ዘሮች ናቸው፡ ይህም ቈ፣ መወራረሳቸውን ያሳያል።

ጐሰረ: ሰብዙ ጨመረ፣ መላ፣ ጠቀጠቀ፣ ዐመቀ፣ ዐጨቀ፣ ነፋ፣ ወጠረ (ሆድን በመብል)፡ ስልቻን (በእብቅ)

ጐሰረት: ሆደ ክርብ (የቦና ጥጃ)

ጐሰቈለ (ሐርተመ): ጠፋ፣ ተበላሸ፣ ከሳ፣ ጠቈረ፣ ወራዳ ኾነ፣ ቈሸሸ፣ ከሰረ (ከበሽታና ከክፉ ዐመል፣ ከችጋር የተነሣ) (ኤር፲፭:፱፣ ፴፩:፲፱)

ጐሰጐሰ (ትግ ጐስጐሰ፣ በረበረ፣ ጐተጐተ): እንደ በሬ አብዝቶ ጐረሠ፣ በላ፣ ጠቀጠቀ፡ የግሥገሣ አበላል ነው።

ጐሠጐሠ፡ አብዝቶ ጐረሠ።

ጐሰጐሰ: እድብኝት ውስጥ አገባ፣ ከተተ።

ጐሰጐሰን እይ፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው፡ ጐተጐተ የሺዋ፣ ጐሰጐሰ የጐንደር።

ጐሢ (ጐሣዒ)፡ ያሞራ ስም፡ ጥቍር አሞራ (ግልገል)፡ አንሣ፡ በአየር መጥቆ የሚያገሣ። በግእዝ "ንስር" ይባላል።

ጐሣ (ኦሮ)፡ ዘር፣ ትውልድ፣ ወገን፣ ነገድ።

ጐሳሚ: የጐሰመ፣ የሚጐስም፡ መቺ።

ጐሳሳ: ደካማ ሰው፡ ኰሳሳ ጥጃ።

ጐሳሪ: የጐሰረ፣ የሚጐስር፡ ዐቂ።

ጐሳራ፣ ጕስር (ሮች): የተጐሰረ፡ ውጥር፣ ንፍ፣ ጥቅጥቅ፣ ክርብ፣ እንቅብ (ሆድ፣ ዘርጣጣ)

ጐስቋላ (ሎች): ጕስቋይ፣ ጕስቍል (ሕርቱም)፡ የጐሰቈለ (መጥፎ፣ ወራዳ፣ ምናምንቴ፣ ልክስክስ)፡ ዐመለ ውዳቂ፡ የሰው ታናሽ (ምሳ፲፱:፳፯፣ ሮሜ፯:፳፬፣ ፊልጵ፫:)

ጐስቋል()ነት: ጕስቍልና (ሕርትምና)፡ ብላሽነት፣ ምናምንቴነት፣ ውርደት፣ ጥፋት፣ ጕዳት፣ አደጋ፣ መከራ (ኤር፵፮:፲፪፣ ሰቈ፫:)

ጐስቋይ: የሚጐሰቍል።

ጐስጓሽ: የጐሰጐሰ፣ የሚጐሰጕስ፡ በላተኛ፡ ጐትጓች።

ጎረ ገነት: የገነት አቅራቢያ ረዥም ተራራ።

ጐረመ (ጐርጐረ፣ አንጐርጐረ): ወፍራም ድምፅ ሰጠ፣ አሰማ።

ጐረመመ (ጐርመመ): የትግሬ፡ "ፎነነ" የአማራ ነው።

ጐረመመ: አፍን፣ ከንፈርን ቈረጠ፡ ፎነነ።

ጐረመሰ: የሕዝብ፡ "ጐለመሰ" የካህናት ነው።

ጐረመሰ: ጐለመሰ። "" "" ተወራራሽ መሆናቸውን አስተውል።

ጐረመደ: ጐመደ፣ ጐረደ፣ ገመሰ፡ ተነተነ፣ ሸነሸነ፣ ከፈላ፣ ሰበረ፣ ቈረሰ፣ ቈረጠ (ዳቦን)

ጐረምሳ (ሶች): ጕልማሳ (ጎረ ኅምሳ ለብእሲት)

ጐረሠ (ገረሠ): ወዳፍ አገባ፣ ከተተ፡ በላ፣ ተመገበ (ምግብን)፡ ትንባኾን ባፉ ያዘ። (ተረት): "ለወጡም ዕዘኑለት፡ ከንጀራውም ጕረሡለት። " "ምን ቢያርሱ እንደ ጐመን ኣይጐርሡ። "

ጐረሣ: የመጕረሥ ሥራ።

ጐረረ (ትግ አጕረረ): ፎከረ፣ ዛተ፣ አንገራበደ፡ ተላገደ፣ ተመካ፣ ታጀረ፡ ወሬ ነዛ፣ አንቧተረ፣ አንፋሸረ፡ ራሱን አከበረ፣ ሌላውን ናቀ፣ አኰሰሰ። "አንተን አንድ ነገር ሳላደርግ የቀረኹ እንደ ኾነ ሰው አትበለኝ" አለ። "ጓሮ" ማለት ከዚህ የወጣ ነው።

ጐረበ (ቈቍዐ): ረገበ፣ ተቋጠረ፣ አጐበጐበ፣ ቈረበጨ፣ ተመደደ (የውስጥ እጅ፣ የእንግርግብ፣ የድር) "ቀረበን" ተመልከት።

ጎረበተ (ገዊር፣ ጎረ): ተጎራበተ (ተጋወረ): አጠገብ ላጠገብ፣ ቅርብ ለቅርብ ቤት ሠራ፡ ጎረቤት ኾነ፡ ተቃረበ፡ ሰፈረ፣ ተቀመጠ።

ጐረበጠ: ነካ፣ ቈረቈረ፣ ወጋ፡ አልመች አለ፡ አስቸገረ (ጐንን፣ ሆድን)

ጎረባብት (ቶች): ዝኒ ከማሁ።

ጎረቤላ: ያገር ስም፡ ካንኮበር በላይ ያለ አገር።

ጎረቤት (ጎር፣ ጎረ ቤት): የቤት ኣጠገብ፡ ወይም ቤቱን በሰው ቤት ጐን የሠራ ሰው። (ተረት): "ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት" "ደግ ጎረቤት ውሻ ያሳድጋል፡ ክፉ ጎረቤት ግን ዶሮ ያረባል" "ባለቤት ካልጮኸ ጎረቤት አይረዳም"

ጎረቤትነት: የቤት አቅራቢያነት፣ አጠገብነት።

ጎረቤቶች (አግዋር): የቤት አጠገቦች፡ ዐምባቸው መንደራቸው አንድ የኾነ ሰዎች።

ጐረተ: ጐራ፣ ከመረ።

ጐረነነ (ጐረና): ወፈረ፣ ደነደነ (የድምዕ)

ጐረና: ቀረና፣ ተበላሸ (የቅቤ፣ የወጥ) ሳይማሰል ስለ ቀረ።

ጐረንጐሬ: ሽፋፍ፣ ጐራ።

ጐረንጐሬ: የጐሬ ጐሬ፡ የፍላጻ የስለት መክተቻ፣ ማከማቻ (ከቈዳ የተበጀ) (ኰረጆ ሽፋፍ) " ስሯጽ ነው (ዐብድ፩:)" በግእዝ "ምጕንጳ" ይባላል።

ጐረደ (ገረዘ፣ ቀረፀ): ከጫፍ ከመኻል ጐመደ፣ ቈረጠ (መቀስ)፡ ጐነደበ፣ ዐረደ፣ አሳጠረ፡ ቀየደ፣ ከፈለ፡ ፈተገ። "ዘና፣ " በዐረብ "" ተብለው ስለሚነገሩ፡ "ጐረደ" የገረዘና የቀረፀ ዲቃላ ነው፡ ገና ቀም መወራረሳቸውን ባማርኛው ገበታዋሪያ መቅድም ተመልከት።

ጐረደ: ፊደል ዘለለ፡ አስቀረ፣ ዋጠ።

ጐረደመ: ቈረጠመ፣ ሸረደመ (በቅሎና አህያ ጥሬ ያበባ እኸልን)

ጐረደማን (ኖች): የነጋዴ ሎሌ ጫኝ። ምስጢሩ አቈርጣሚነትን ያሳያል።

ጐረደደ (ቈረጠጠ): ተንጐራደደ (ተንቈራጠጠ): ወዲህና ወዲያ፣ ግራና ቀኝ ተመላለሰ (ለመፎከር፣ ለመስበክ) (ጐራዴውን ታጥቆ) (አፈንግጦ)

ጐረደድ (ጐርዳዳ): ቈረጠጥ፣ ቈርጣጣ።

ጐረድ ጐረድ አደረገ: ከላይ ከላይ መላልሶ ጐረደ፡ በቀላል ወቀጠ፣ ዠብ ዠብ ኣደረገ።

ጐረድ: የጐረደ፡ ቀጣፊ፣ ዐባይ።

ጐረዶ: ተዠምሮ የቀረ (ያላለቀ) ሥራና ነገር (ውዝፍ)

ጐረጐመ: ጥርስን ዐልፎ ዐልፎ አወለቀ፣ ነቀለ።

ጐረጐማ (ሞች): ጥርሰ ወላቃ።

ጐረጐሜ: የጐረጐማ ወገን፡ ወይም ጥርስ ጐደሎ።

ጐረጐረ (ጐርጐረ): ኰረኰረ፣ ፈተሸ፣ በረበረ፣ ጓጐጠ፣ ሻ፣ ፈለገ (የኵክ፣ የቅቤ፣ የድልኸ፣ የዓሣ፣ የጥርስ)

ጐረጐጯ: አማገ፣ እጠጣ፡ ከጕንጭ ወደ ጕረሮ ሲያወርድ ገጭ ሲያደርግ ተሰማ (ውሃን፣ መጠጥን)

ጐረጠ (ጐረጸ): ወጣ፣ ፈጠጠ (ያይን) (ተገብሮ)

ጐረጠ: ጫረ፣ ወረ (ገቢር) ትግሬ ግን "ጐረጸን" "በቡጢ መታ" ይለዋልና፡ የቀኝ እጅ አውራ ጣትን ጥፍር ያሳያል።

ጐረጥ (ደንቈር): ግንድ በሺ፣ ሆደ። ወይብማ ወፍ ዐይኑን አጕርጦ የሚያይ። "የጐረጥ አየ" እንዲሉ።

ጐረፈ (ጐሪፍ፣ ጐረፈ): ወረደ፣ ፈሰሰ (በዝቶ)፡ ደንጊያን፣ ዐፈርን፣ ሣርን፣ ቅጠልን፣ ግንድን፣ ግባስን፣ ቍሻሻን ኹሉ ይዞ (ማቴ፯:፳፭፣ ፳፯)

ጐረፈ: መዠመሪያ ታጠበ።

ጐሪ: የጐራ፣ የሚጐራ፡ ድንጋይ ከማሪ።

ጐራ (ሳራ): ከፍተኛ ቦታ።

ጐራ (ጐርዐ፣ ዕብ ጋር): ደንጊያ ሰበሰበ፣ አከማቸ፣ ከመረ፣ ጐረተ፣ ቈለለ። "ጐርዐ" ጥንታዊ ግእዝ ነው።

ጐራ (ጓራ) (ጐርዐየ፣ ዐነቀ): አጐራ፣ አጓራ፡ በጕረሮው ጮኸ። "ሲጠባ ያደግ ጥጃ ቢይዙት ያጓራል" "በሬው ስለ ታረደ ያጓራል" "ከብቶቹ በፈርስ ላይ ያጓራሉ (ያለቅሳሉ)"

ጐራ ማለት (ግሒሥ): መንገድ ለቆ እግር መንገዱን ወደ ቤት መምጣት፣ መግባት።

ጐራ በል: ገባ በል፣ ግባ።

ጐራ አለ (ገሐሠ): መጣ፣ ገባ። "ጐደኘ" ብለኸ "ተጐዳኘን" እይ።

ጐራ: በጋልኛ ቀጋ ማለት ነው።

ጐራ: የጦር ሜዳ (የጭንቅ የመከራ ስፍራ) "የጐራው ባላ" (እከሌ ላንድ ጐራ የሚበቃ ጐበዝ ነው) እንዲሉ።

ጐራ: የፊታውራሪ ገበየኹ የፈረስ ስም። "የጐራው ገበየኹ" እንዲሉ።

ጐራ: ጠባብ መንገድ (ዐንገት፣ ዐራዳ፣ መተላለፊያ)

ጐራ: ፊና፣ አኳያ። "በጐራኸ" እንዲል።

ጐራሥ: ጋን (የሸማና የዕቃ መክተቻ)

ጐራረደ: ቈራረጠ፣ ጐነዳደበ፡ ጠጕርን ሲቈርጥ አበላሸ (ረዥምና ዐጪር አደረገ)

ጐራሸሽ: ሰን፣ ኵስኵስት (ፊልክስ ዩስ ፻፲፪)

ጐራሽ (ሾች): የጐረሠ፣ የሚጐርሥ፡ በላተኛ። (ተረት): "ከኛ ወዲያ ጐራሽ እኸል አበላሽ። "

ጐራቢ: የሚጐርብ፣ የሚቈረብጭ።

ጐራዝመን: ርጥበትና ደረቅነት ሰው ዕንጨት፡ ያልታጨደ እኸል።

ጐራዝመን: ጥቍር አይሉት ነጭ።

ጐራዳ (ዲት): ከጫፉ የተሰበረ ዕቃ፡ አፍንጫ ዐጪር ሰው። (ግጥም): "ኣፍንጫ ጐራዳ ከወደደልኸ፡ እኔም ካፍንጫዬ ልጐረድልኸ"

ጐራዴ (ጐራጅ): የሰይፍ ዐይነት (አንድ አፍ) የጦር መሣሪያ (ሐኔ፣ ዋልሴ፣ ሾተል)፡ የጠላትን ዐንገት ዐራጅ "ጐራጅ" ማለት ነው።

ጐራዴ: በመሬት ላይ ከራሱ ዘንበል የሚል (የሚዘናፈል) ባለዳልጋ ጤፍ አቋቋመ (ጐራዴ) "ቈንደልን" እይ።

ጐራድ: ዐንገት የሌለው ማድጋ፡ መስፈሪያ።

ጐራጅ (ጆች): የሚጐርድ፡ ቈራጭ።

ጐራጅ: በመካከልና በመጨረሻ በግእዛዊ ቃል ሲገባ ራሱን ጐርዶ ሌላውን ፊደል ባማርኛ ራብዕና ሳብዕ በማድረግ የሚታጣ ፊደል (ኣዐ፣ ሀሐኀ፣ ወ፣ ) ማስረጃ፡ "ለአከ" "ላከ" "ሰዐመ" "ሳመ" "ነሀረ" "ናረ" "ሰሐበ" "ሳበ" "ድኅነ" "ዳነ" "ነሥአ" "ነሣ" "በልዐ" "በላ" "ተግህ" "ተጋ" "ሠብሐ" "ሠባ" "በዝኀ" "በዛ" "ጸረየ" "ጠራ" (ጥሩ ኾነ) "ወም" በግእዝና ባማርኛ ራሱን ጐርዶ ሌላውን ሳብዕ ያደርጋል። "ዘዊር" "ዞረ""ነዊር" "ኖረ""ዘዋሪ" "ኗሪ""ዟሪ" "ኗሪ" ሳብዕም ሳያደርግ ተጐርዶ ይቀራል፡ "ሀለወ" "አለ" "ሰጠወ" "ሰጠ" ራብዕም ሲያደርግ፡ "ደለወ" "ደለ" "ጠበወ" "ጠበ" ይላል። በመድረሻውም ደጊመ ቃል ያለው የ፫ ፊደል ግስ በጊዜና በኅላፊ ትንቢት ፫ኛው ፊደል ይታጣል። ይህም "በረረ" "ይበር" "ይበራል""ነደደ" "ይነድ" "ይነዳል""ቀደደ" "ይቀድ" "ይቀዳል""ፈሰሰ" "ይፈስ" "ይፈሳል""ሰደደ" "ይሰድ" "ይሰዳል" እያለ ጐራጅነቱን ያሳያል።

ጐራጅነት: ጐራጅ መኾን፣ ቈራጭነት።

ጐራጐረ: ኰራኰረ።

ጐራጣ: የጐረጠ፣ ፈጣጣ።

ጐራጭ (ጐራጺ): የሚጐርጥ፡ ፈጣጭ፡ ጝሪ።

ጐራፊ: የጐረፈ፣ የሚጐርፍ፡ ፈላሽ፣ ታጣቢ።

ጐሬ: በኢሉባቦር ክፍል ያለ አገር።

ጐሬ: ጕድጓድ፣ ዋሻ (ያውሬ፣ የንብ መኖሪያ)፡ ደንጊያም፣ ቋጥኛም ማለት ነው (የጌሾ ወቃጭ ግጥም)"ለወቀጣ አንድም ሰው አልመጣ፡ ለመጠጡ ከየጐሬው ወጡ"

ጎር (ግእዝ): ጎረቤት።

ጐርማሚ: የጐረመመ፣ የሚጐረምም፡ ፎናኝ።

ጐርማማ: የተጐረመመ ፉን።

ጐርምድ: የሚጐረምድ፡ ቈራሽ።

ጐርምጥ (ቁስል)

ጐርምጥ (ጐርምድ): ባለብዙ እግር የባሕር ተንቀሳቃሽ (ጓጕንቸር) (ሸርጣን) (መቀስ ያለው)፡ ዐረቦች "ኣቡ መቀስ" የሚሉት።

ጐርምጥ: "ብዙ እጅና እግር ያለው የባሕር ተንቀሳቃሽ አቡ መቀስ።"

ጐርምጥ: ቈላ፣ ቍስል (እግር የሚቈርጥ፣ የሚጐረምድ) " ጐረጠ" ብለህ "መጐራጕርጥን" እይ።

ጐርበጥባጣ: የጐርባጣ ጐርባጣ፡ ወጣ ገባ።

ጐርባጣ: መጥፎ መኝታ፣ አስቸጋሪ።

ጐርባጭ: የጐረበጠ፣ የሚጐረብጥ፡ ቈርቋሪ፣ ነኪ።

ጐርብጥ: ያለፋ የበሬ ቈዳ፡ "ቈርቍር ወጋ ማለት ነው""እንግዳ ጐርብጥ" እንዲሉ።

ጐርናና: ቃለ ወፍራም ጕልማሳ።

ጐርዝ፣ ጐርዞ: የዓሣ ስም (ከግልገል የሚያንስ ዓሣ) "ጐርዝ" ያሠኘው የሆዱና የጐኑ ንጣት (የዠርባው ጥቍረት፣ ጠይምነት) ነው። "ሦርዞ ጐርዞ" እንዲሉ።

ጐርደድ ጐርደድ አለ: ቈርጠጥ ቈርጠጥ አለ።

ጐርደድ: ቈርጠጥ።

ጐርዳሚ: የጐረደመ፣ የሚጐረድም፡ ቈርጣሚ፣ ሸርዳሚ።

ጐርዶማ: ያገር ስም፡ ከደብረ ሊባኖስ በላይ ዕልፍ ብሎ ያለ አገር።

ጎርጎ (ዎች): የንጨት ስም፡ እሾኻም፣ ሻካራ ዛፍ፡ ፍሬው ቀይ፡ ለሕፃናት ቍንጮ ጌጥ የሚኾን የኮርች ዐይነት፡ ወይም ርሱ ራሱ ኮርች።

ጐርጐራ: በበጌምድር ክፍል በደንቢያ ውስጥ ያለ አገር።

ጎርጎርዮስ: የኑሲስ ኤጲስቆጶስ (ባለታምራት)

ጎርጎርዮስ: የአርማንያ ሊቀ ጳጳሳት (ከውነተኞቹ ሊቃውንት አንዱ)፡ ድርሰቱና ትምርቱ ሐሰት ስሕተት የሌለበት ጥሩ እውነት፡ የአርመንን ንጉሥ በክርስቲያን ሃይማኖት ያሳመነ እሱ ነው።

ጐርጓማ: የተጐረጐመ፡ ጐረጐማ።

ጐርጓሪ (ሮች): የጐረጐረ፣ የሚጐረጕር፡ በርባሪ፣ ፈላጊ። "ዓሣ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል፡ የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል"

ጐርጠብ: የቅጠል ስም፡ በመረሬ የሚበቅል ቅጠል፡ እሱን ቀጥቅጦ በውሃ ቢጨምቁት የታመመ ዐይን ያድናል፡ ለቍስልም መድኀኒት ይኾናል።

ጐርፉ፣ ጐርፌ: የሰው ስም፡ የዘሩን ብዛትና ኀይሉን ያሳያል። ዳግመኛም "ጐርፉ" የርሱ ጐርፍ፡ "ጐርፌ" የኔ ጐርፍ ተብሎ ይተረጐማል።

ጐርፍ (ጐረፋ): ድፍርስና ብጥብጥ (የክረምት፣ የብላጊ) ውሃ፣ አንፎርሻ (ማቴ፯:፳፭-፳፯)

ጐርፎ: የቀበሌ ስም፡ እስላምን ለማጥቃት ኦሮን ስቦ፣ ጐትቶ ወደ መኻል ያገባ ጐርፉ። "ጋራ ጐርፎ" እንዲሉ፡ "ሙሎን" እይ።

ጐሸ (ትግ ጐሰየ፣ ኰራ፣ ናቀ): ደፈረሰ፣ አተለ፣ ተዘለለ፣ ተበጠበጠ፡ ጕሽ ኾነ፡ ወፈረ።

ጐሸመ (ጐሰመ): ደሰቀ፣ ደሰመ፣ ጐጐመ (በጕልበት፣ በክርን፣ በቡጢ) "ሌባሻይ ሰውን ይጐሽማል" እንደ ጐሰመ ለነጋሪትም ይነገራል።

ጐሸመጠ (ጐሸመ): በነገር ነካ፣ ጐነጠ፣ ነጠበ።

ጐሹ ባዶ: በታላቅ ዐምባ ውስጥ የሚገኝ የጐሹ ወና።

ጐሹ: የሰው ስም። "አራት ዐይና ጐሹ" እንዲሉ።

ጐሹ: የበሬ ስም። ጐሽ የሚመስል በሬ (የጐሽ ዲቃላ)

ጐሻሚ: የጐሸመ፣ የሚጐሽም፡ ደሳቂ፣ ይሳሚ፣ ጐጓሚ።

ጐሽ (ጋሙስ): (ጐሥዐ ጐሣዒ) ያሣ፡ የሚያገሣ፣ አግሺ፡ ሰውን በምላሱ የሚቃወም፡ ቈርበተ ወፍራም የዱር (የበረሓ) በሬ (ኢዮ፴፱:) በህንድና በምስር ግን ለማዳ ነው፡ ተባቱ ያርሳል፡ እንስቷ ትታለባለች። (ተረት): "ይኾናል ብዬ ጐሽ ጠመድኹ፡ ባይኾንልኝ ፈትቼ ለቀቅኹ። "

ጐሽ መቃ (የጐሽ መቃ): ቅጠሉን ጐሽ የሚበላው እንደ መቃ አንጓ ያለው (ከቅጥነቱ በቀር ሽመል የሚመስል)፡ መዝጊያና መከታ የሚኾን የመቃ መስዬ ዐይነት። ጐንደሮች "ቀለም" ይሉታል።

ጐሽ ዐረስ: ከባለምድሩ ሳይጋዛና ሳያስፈቅድ አንድ ሌላ ሰው ያረሰው መሬት። "ጉሽ ምድርን በቀንዱ በማረሱ በመፈ ለሱ ዋጋ የለሽ ስለኾነ አለባለቤቱ ፈቃድ የታረሰው ማሳ ጐሽ ዐረስ ተባለ"፡ ለባለርስቱ ጥሎ ከመኼድ በቀር ሌላ ጥቅም የለውምና።

ጐሽ ውሃ: በላይኛው ወግዳ ያለ አገር። "ጐሹ" የሚሳል ሰው ያቀናው፡ በቡልጋም "ጐሽ ውሃ" የሚባል ቀበሌ አለ።

ጐሽ ግንባር: የገብስ ስም።

ጐሽ ጠጕር (የጐሽ ጠጕር): ቀይ የልጅ ጠጕር (ካ፲፭ ዓመት በኋላ የሚጠቍር)

ጐሽ: የሚባል ተባቱም እንስቱም ነው። "ጐሽ ለልጇ ተወጋች" እንዲሉ። "ገሣ" ብለህ "ጐሢን" እይ።

ጐሽ: የምስጋና፣ የምርቃት ቃል፡ "ወሰው የኰርማ ወንድም ይውጣብሽ""ወጣን" እይ። "ጐሽ ልጄ" እንዲሉ።

ጐሽመቃ ቀለም: ጐሽ።

ጐሽማጭ: የጐሸመጠ፣ የሚጐሸምጥ፡ ጐናጭ።

ጐሽሜ: የሰው ስም። የጐሻሚ ወገን፡ ወይም "ጐሽም" ማለት ነው።

ጐበሰተ፡ ሠጠ፡ ሳለ (ኡሁ ኡሁ አለ)

ጐበበ (ገብቦ፣ ገበበ): ጐነበሰ ተቀለሰ፣ እንደ ቀስት ወይም እንደ ደጋን ሆነ።

ጐበብ አለ: ቀለስ አለ።

ጐበና(ኦሮ) የሰው፡ ስም፡ በሙሉ ጨረቃ፡ የተወለደ፡ ማለት፡ ነው፡

ጐበና፣ ዳጪ፡ የዳጯ፡ ልጅ፡ ራስ፡ ጐበና፡ ያጤ፡ ምኒልክ፡ አበ፡ ጋዝ፡ የታወቁ፡ ስመ፡ ጥር፡ ዠግና፡ ባባታቸው፡ ከኦሮ፡ በናታቸው፡ ካማራ፡ ያወለዳሉ የፈረስ፡ ስማቸው፡ አባ፡ ጥጉ።

ጐበኘ(ሐወጸ)፡ ዐወቀ፡ አየ፡ ተመለከተ፡ ፈቀደ፡ ጠየቀ፡ ሰለለ፡ መረመረ (በክፉም ይሁን በበጎ፣ በጠላትነት ወይም በወዳጅነት) (ዘፍ፳፮:፲፰, ዘኍ፲፫::፳፩, ኢሳ፳፮:፲፬)

ጐበዘ: አደገ፣ ጐለመሰ (ጐረመሰ) ዐየለ በረታ ጠና ጠነከረ ጐለበተ ወንድ ሆነ፣ ወጣው፣ ዠብዱ ሠራ

ጐበዛዝት: "ጐበዝ" ብዜት (ዮኤል ፩፥፲፣ ዓሞጽ ፪፥፲፩)

ጐበዛየኹ (ጐበዝ አየኹ): የድሮ ነፍጥ ስም። ተረት: "ካሽከር ገበየኹ፣ ከነፍጥ ጐበዛየኹ"

ጐበዜ: የሰው ስም፡ የጐበዝ ወገን ወይም "የኔ ጐበዝ"

ጐበዝ (ዞች): ጕልበታም ኃይለኛ ብርቱ ጨካኝ ጕልማሳ፣ ምሉዕ ሰው

ጐበዝ፡ ብለኸ፡ ጐበዝን፡ እይ።

ጐበዝነት: ኃይለኛነት ጠንካራነት

ጎበደደ: ተሰበሰበ፡ ሊያልቅ ቀረበ፡ ጥቂት ቀረ፡ አንድ ወገን ሆነ (የሥራ) ተመልከት: ሀዘንን

ጐበደደ: ጐበጠ (ጐነበሰ፣ ተንጐበረረ፣ ዘነበለ)፡ ጐበበ (ደጋን መሰለ)

ጐበደድ/ጐብዳዳ (ዶች): የጐበደደ፡ ጐባጣ (ተርካሳ፣ ፈንዳዳ)

ጐበጐበ (ቈበቈበ): ሸለመ (አስጊጠ)"ጕብ ጕብ" "ቍብ ቍብ" አደረገ (ጋሻን) ሌላ ትርጉም: ውሃ ያዘ (ቋጠረ)፡ እቈረበ (የጣት) ሌላ ትርጉም: ጐመደሰ (መታ) ሰውን። ሌላ ትርጉም (ትግሪኛ: ጐብጐበ): አግደረደረ ሌላ ትርጉም: ግብዝ አደረገ

ጐበጠ: ደነነ፣ ጸነነ፣ ጐነበሰ ዘባ ደጋንና ቀስት፣ ሙጭና፣ ከዘራ፣ አጐበር መሰለ፡ ተቀሰተ ተደገነ ተቀለሰ (መዝሙር ፵፬፥፳፭)

ጐበጥባጣ: የጐባጣ ጐባጣ፡ ወጣ ገባ አስቸጋሪ መንገድ (ደንጐላጕል፣ ድንጕር)

ጐቢ: የጐባ (የሚጐባ)፡ የሚደግፍ፡ ጕቦ ሰዋሽ።

ጐቢ: የጐባ፣ የሚደግፍ፣ ጕቦ ሰዋሽ

ጐቢል(ጥሲ) የዛፍ፡ ስም፡ ታቦት፡ የሚኾን፡ እንጨት፡ ፍሬው፡ ሎሚ፡ የሚያካክል።

ጐቢጥ: የአረቄ ስም፡ ኃይለኛ መጠጥ፡ አብዝቶ ቢጠጡት የሚያጐብጥ።

ጐባ: ደገፈ (ጣራን)፡ አነሣ (ወደ ላይ)፡ ገፋ። ሌላ ትርጉም: ጕቦ ሰጠ (አስበሰተ) ሌላ ትርጉም: አስቀመጠ (ቍልልታ አደረገ) ሌላ ትርጉም: ጕብ ሰፋ።

ጐባ: ጣራን ደገፈ ወደ ላይ አነሣ ገፋ ሌሎች ትርጉሞች: ጕቦ ሰጠ አስበሰተ። ልልታ አደረገ አስቀመጠ። ጕብ ሰፋ

ጐባባ: የጐበበ (ጐባጣ፣ ጐንባሳ፣ ቀላሳ) ተመልከት: ቈበበን

ጐባታ: ለጕባ ተመሳሳይ ቃል ነው።

ጐባን(ኖች)፡ የሰው፡ ሚስት፡ ያገባ ጣውንት።

ጐባን፡ የሌላዪቱን፡ ባል ' ያገባች ሴት (፩ሳሙ፡ ፩፡ ፮)

ጐባንነት፡ ጣውንትነት፡ የሌላ ባል ወይም ሚስት መውሰድና ማግባት።

ጐባጣ: ጐባጥ ቀላሳ ተርካሳ ደጋን ወገብ (ዘሌዋውያን ፳፩፥፳) ማስታወሻ: "ሲበዛ ጐባጦች" ይላል (ዮሐንስ ፭፥፫)

ጐባጣነት: ጐባጥነት፣ ቀላሳነት፣ ተርካሳነት።

ጐባጤ: የጐባጣ ወይም የተርካሳ ዓይነትና ወገን።

ጐባጭ: የሚጐብጥ፣ ዘቢ።

ጐቤ: ግብዝ (አስመሳይ፣ ወሬኛ)

ጐቤ: ግብዝ (ጐበጐበ)

ጎብሩና ገብሬ ከፊለ ስም ይሆናሉ።

ጎብር፡ የግእዝ ሲሆን፣ ባሪያ የአማርኛ ነው።

ጐብኚ (ዎች)(ሐዋጺ)፡ የጐበኘ፣ የሚጐበኝ፣ የሚጠይቅ፣ የሚያይ፣ ፈቃጅ፣ ተመልካች።

ጎብደድ አለ: ገበደደ (ተወገደ፣ ተሰለሰ)

ጐብጓቢ: የጐበጐበ (የሚጐበጕብ)ጕብጕብ ሠሪ (ሸላሚ፣ ደጓሽ)

ጐተመ (ጐመተ): አጕተመተመ፡ አጕረመረመ፣ አድረመረመ። "ጐመተ" ከዚህ ጋራ አንድ ነው፡ ከመዛወር በቀር ልዩነት የለውም።

ጐተራ: ሰፊ ኹኖ በግንብ የተሠራ የመንግሥት እኸል መክተቻ (ማስቀመጫ) ቤት፡ ባለብዙ ጕርጅ (ሚል፫:)

ጐተራ: የግድግዳ ጐታ (ከሪቅ የሚበልጥ) ሲበዛ "ጐተሮች" ይላል (ዮኤ፩:፲፯)

ጐተተ: ሳበ፣ ስቦ ወሰደ፡ አበዛ፣ አረዘመ፡ ጠራ፣ አቀረበ (የሞፈር፣ የሠረገላ፣ የሰው፣ የመረብ፣ የነገር፣ የጋኔን) (ምሳ፳፫:፴፭፣ ሕዝ፴፪:፳፣ ዮሐ፳፩:፲፩)

ጐተተ: ጕትቻ ሠራ፣ አበጀ።

ጐተታ: መጐተት።

ጐተታ: ክብ ያይደለ (ሞላላ ንብ የጋገረው የማር እንጀራ ከቀፎ ተጐትቶ የሚወጣ)

ጐተት: የቀበሌ ስም፡ በታችኛው ወግዳ ባሻገር በስተግራ ያለ ገደል። "ክፉ ልጅ ዕድሜያም አባቱን ጐትቶ ስለ ጣለበት ጐተት ተባለ" ይላሉ። "እሱም በፈንታው አባቴን ከዚህ አላሳለፍኩትምና አታሳልፈኝ አለ" ይባላል። ይህ ታሪክ በሐተታ ወልደ ሕይወት ተጽፎ ይገኛል።

ጐተነ: አደገ፣ ረዘመ፣ ቆመ፡ ፍሕሶ መሰለ፡ ተበጠረ፣ ተመየደ።

ጐተጐተ (ትግ ጐስጐሰ): ነቀነቀ፣ አተጋ፣ አጣደፈ፣ አስቸኰለ፡ ዕረፍት ነሣ፡ ወተወተ፣ ኰረኰረ፣ ነዘነዘ፣ ዘበዘበ (በሥራ፣ በነገር)

ጐታ (ለጐተ): ከክትክታና ከቀጨሞ፣ ከመቃ፣ ከቀርክሓ፣ ከሌላም ዕንጨት እንደ ቅርጫት የተታታ የእኸል መክተቻ፣ ማስቀመጫ (ማቴ፫:፲፪) ሲበዛ "ጐቶች" ይላል (ዮኤ፩:፲፯) "ደረባን" እይ፡ "ጐተራንና ሪቅን" ተመልከት። "እጐታ ውስጥ የሚገቡ ያልባለቀ ልጅና ልጃገረድ ናቸው"

ጐታታ: ረዥም ቀሚስ፡ የታቦት ልብስ (መጐናጸፊያ)

ጐታች (ቾች): የጐተተ፣ የሚጐትት፡ ሳቢ (በሬ፣ ፈረስ፣ በቅሎ፣ ግመል፣ ባቡር)፡ ጠንቋይ። "ጋኔን ጐታች" እንዲሉ።

ጐታጐተ: ኰራኰረ።

ጐትት (ሳብ): የጕጕት ጩኸት (ማማረቻ) "ዛሬ ሌሊት ጕጕቷ ጐትት ስትል ዐደረች"

ጐትት: ዝኒ ከማሁ፡ የምትጉትት። "አሮጊት ነገረ ጐትት" እንዲሉ።

ጐትጓች: የጐተጐተ፣ የሚጐተጕት፡ አጣዳፊ፣ ኣስቸኳይ፡ ወትዋች።

ጐቸ: ከመረ፣ ዘመመ፣ ቈለለ፣ አስቀመጠ፡ ገዎቻ አስመሰለ።

ጐቺ: የጐቸ፣ የሚጐች፡ ከማሪ፣ ቈላይ።

ጐነ ሰፊ፡ ሰፊ ጎን ያለው።

ጐነቈለ፡ መብቀል ዠመረ፡ ወጣ፣ ፈጠጠ።

ጐነበ (ጐነጰ)፡ ከነበ፣ ጐነፈ።

ጐነበሰ፡ ዘነበለ፣ ተዘለሰ፣ ተቀለሰ (በእጁ ጭምር)፡ እንሰስኛ ቆመ (ለመቈፈር፣ ለማረም፣ ለማጨድ፣ አንድ ነገር ለማንሣት)

ጐነበጠ፡ ቦጨቀ፣ ነጯ።

ጐነተለ፡ ባፍ ወይም በእጅ ወዳንድ ስፍራ ለማድረስ ነካ፣ ጐነጠ፣ ገፋ።

ጐነተረ(ጐነተለ)፡ ቈነጠረ።

ጐነነ፡ ቈነነ፣ ታታ፡ በራስ ልክ ቆብ ሠራ። "ጐነጐነን" ተመልከት፡ ከዚህ የወጣ ነው።

ጐነዘለ (ነዘለ)፡ ረዘመ (በትከሻ ላይ ተኛ)፡ አማረ (የጠጕር)

ጐነደ (ጐኒድ፣ ጐነደ)፡ ወፈረ፣ ደነደነ።

ጐነደ፡ ካባት፣ ከናቱ ቤት ተለየ (ጐዦ ወጣ)፡ ከግንድ ተቈርጦ እንደሚተከል ዕንጨት (ለራሱ የትውልድ ግንድ፣ አባት፣ ለመኾን)

ጐነደለ (ቈነጸለ)፡ ነደለ፣ ቀደደ፣ ሰለበ፣ አጐደለ፣ ሰነጋ፣ ኣኰላሸ (የዶሮ) "ጐነደለ" "ነደለ" "ጐደለ" ዘር ስለ ኾነ '' ሲቀር "ነደለ"'' ሲቀር "ጐደለ" ይኾናል።

ጐነደበ (ጐደበ)፡ ግንድን ከወገቡ በላይ ጐረደ፣ ቈረጠ፣ ጐመደ።

ጐነዳደበ፡ ጐራረደ፣ ቈራረጠ፣ ጐማመደ።

ጐነጐነ (ጐነነ)፡ ታታ፣ ቈነነ፣ ጠለፈ፣ ጠላለፈ (ገመድን ከገመድ፣ ጠጕርን ከጠጕር ጋራ)፡ የቀኙን ከግራ፣ የግራውን ከቀኝ ወሰበ፣ ጠመረ።

ጐነጐነ፡ ነገር ሠራ፣ ቋጠረ (ሚክ፯:)

ጐነጐነ፡ ደፈደፈ፡ ጌሾን፣ ብቅልን፣ እንኵሮን አዋዋደ፣ ቀላቀለ፣ ደባለቀ።

ጐነጠ (ትግ ጐነጸ)፡ ደፈረ፣ ነካ፣ ገፋ፣ ነቀነቀ።

ጐነጠፈ)ተጐናጠፈ፡ የጐነጠና የነጠፈ (ነጸፈ) ዲቃላ፡ ረዥምና ሰፊ የሐር ግምጃ (ሶራ) (የወርቀ ዘቦ ልብስ) ከእግር እስከ ራስ ኣጣፋ፣ ደረበ፣ ለበሰ፣ ተከናነበ። "ጐነጸፈን" ተመልከት።

ጐነጥ፡ መጐነጥ።

ጐነጥ አደረገ፡ ጐነጠ፡ (ላካፋ) ነካ፣ ገፋ፣ ነቅነቅ አደረገ።

ጐነጨ (ለትሐ)፡ ጕንጭ አወጣ፡ አማረበት።

ጐነጨፈ፡ በጥቂቱ ሸመጠጠ (ዠመገገ)

ጐነጩ፡ በጕንጭ ያዘ፡ ጠጣ። "ማገንን" እይ።

ጐነጸፈተጐናጸፈ፡ ተጐናጠፈ (ዘፍ፴፰:፲፬)

ጐነፈ (ገኒፍ፣ ገነፈ)፡ ረመጥ ጨመረ፡ በፍል ውሃ ዐጠሰ (ቅባት የነካውን ድስት)

ጐነፈ፡ ዘንጋዳን ባመድ ኹለት ቀን ዐጀሰ።

ጐነፈ፡ ጠረበ፣ ዐነጠ፣ ቀረጻ፡ ኣለበሰ፣ ደጐሰ። "ቀረጸ" "ደጐሰ" የህናት ትርጓሜ ነው። "ጐነፈን" "አለበሰ" "ደጐሰ" ማለት የጐነበ ምስጢር አለበት።

ጐነፈረ (ጐነፈ፣ ጐፈረ፣ ጐረፈ)፡ ገነፈለ፣ ከመጠን ዐለፈ፣ ተረፈ።

ጐኒ፡ ግንድ ቈረጠ (ጐመደ)

ጐናም፡ ወርዳም።

ጐናዴ (ዎች)፡ ዝኒ ከማሁ፡ የጐናድ ወገን ዐይነት፡ ወይም ርሱ ራሱ።

ጐናድ (ዶች)፡ የጐነደ፣ የሚጐንድ፡ ዐዲስ ጐዦ ወጪ።

ጐናጭ (ጮች)፡ የጐነጠ፣ የሚጐንጥ፡ ደፋር፣ ነኪ፣ ነቅናቂ።

ጐናፊ (ገናፊ)፡ የጐነፈ፣ የሚጐንፍ (የሚቀርጽ)፡ ዐጣቢ፣ ደጓሽ።

ጐን (ኖች)፡ ከብብት እስከ ማውድ ያለው ገላ። እንዲሁም በስተቀኝና በስተግራ ያለ ስፍራ፣ ወርድ ወይም ስፋት። ቅርበትን ለመግለጽም ያገለግላል ("ጐን ለጐን" ማለት አጠገብ ለአጠገብ)

ጐን: አጠገብ።

ጐንቋይ፡ የሚጐነቍል።

ጐንበስ፡ መጐንበስ።

ጐንበስ ቀና አለ፡ ወደ ታችና ወደ ላይ አለ፡ ሰገደ፣ ወደቀ፣ ተነሣ።

ጐንበስ አለ፡ ጐነበሰ፣ ተጐነበሰ፡ ዘንበል፣ ዘለፍ አለ።

ጐንበስ ጐንበስ አለ፡ ደፋ ደፋ አለ፣ አጐንብሶ ሮጠ። "ሌሊት የት ጐንበስ ጐንበስ እንዲል ነጋዴ"

ጐንባሲት፡ ታናሽ ጐዦ (ቀላሲት)፡ ዐጪር በር (ጐንብሶ የሚገቡባት)

ጐንባሳ (ሶች)፡ የጐነበሰ (ዘንባላ) (ቀላሳ)

ጐንባሳ፡ የመጐንበስ ኹኔታ። "ሕፃኑ በጕንብሱ ይኼዳል"

ጐንባሽ፡ የሚጐነብስ፡ ዘንባይ።

ጐንታይ፡ የጐነተለ፣ የሚጐነትል፡ ገፊ።

ጐንቸል፡ አህያ፣ ጐናጭ፣ ዥብ።

ጐንና ጐን፡ ግራና ቀኝ (ኢዮ፴፩፡ ፳)

ጐንአጠገብ፡ ጐደነ።

ጐንዛላ፡ የተመቸው (የደላው) ቈንዳላ።

ጐንደራ (ትግ)፡ የወስፋት ስም፡ ወስፋት።

ጐንደሬ (ሮች)፡ የጐንደር ሰው፡ የጐንደር ተወላጅ።

ጐንደሬ፡ ለስላሳ ጥጥ (ሳይነደፍ የሚፈተል)

ጐንደሬ፡ ነጭ ዐተር በሳል፡ መጠኑ ኢየሩሴን የሚያኸል።

ጐንደር (ጕንደ ሀገር)፡ ዋና አገር (ያገር ግንድ) (ያገር ቀንድ)፡ ፋሲል የሠ ራው መናገሻ (የበጌምድር ራስ ከተማ) መዲና፡ ባለ፵፬ ደብር። "ግራን" ተመልከት።

ጐንደርኛ: ጐዣምኛ እንዲሉ።

ጐንዳ (ጕንዳዊ) (ጐምዳ)፡ ጐማዳ፣ ቈራጣ፣ ቈማጣ (ጣቱ የረገፈ) "ላሊበላ ኣባ ጐንዳ" እንዲሉ።

ጐንዳ ፈረስ፡ ጭራው ተቈርጦ የዥራቱ ግንዶሽ የቀረ።

ጐንዳቢ፡ የጐነደበ፣ የሚጐነድብ፡ ጕራጅ።

ጐንዳባ፡ ጐራዳ፣ ጐማዳ።

ጐንጊት፡ በደብረ ሊባኖስ ቤተ ክርስቲያን ግራና ቀኝ ያሉ የወንዞች ስም። "ትልቋ ጐንጊት፣ ትንሿ ጐንጊት" እንዲሉ። ውሃ በመላ ጊዜ የምትንጓጓ ማለት ነው።

ጐንጊት፡ የወንዝ ስም (ጓጓ)

ጐንጓኝ (ኞች)፡ የጐነጐነ፣ የሚጐነጕን፡ ነገረ ሠሪ።

ጐንጣፋ፡ የተጐናጠፈ፡ ጐታታ።

ጐንጤ፡ የሰው ስም፡ ጐናጭ ወይም ጐንጥ ማለት ነው።

ጐዘለ (ዘጐለ)፡ አነሰ፣ ኰሰሰ፡ ተናቀ፣ ቀለለ።

ጐዘጐዘ (ጐዝጐዘ)፡ ሣርና ቅጠል በተነ፣ መነዘረ፣ ነሰነሰ፣ አነጠፈ፣ አመቻቸ፣ አስቀመጠ።

ጐዛጐዘ፡ በታተነ፣ ነሳነሰ።

ጐዝጓዥ (ዦች)፡ የሚጐዘጕዝ፣ ነስናሽ፣ አንጣፊ።

ጐዝጓዥነት፡ ነስናሽነት፣ አመቻቺነት።

ጐዠሬ፡ የጐዠር ዐይነት መሣሪያ፡ ወይም ርሱ ራሱ ጐዠር።

ጐዠር (ገዛሪ)፡ መጥረቢያ፣ ቦለድ፣ ጠገራ፣ የእንጨት መቆረጫ።

ጐዣሜ (ጐዣማዊ)፡ የጐዣም ሰው።

ጐዣም (ጐገና)፡ ጐም፣ ዘላን፣ ባለጐዦ። አቅኒዎቹን ያሳያል።

ጐዣም፡ የአማሮች አገር አንዱ ክፍል።

ጐዣሞች፡ የጐዣም ተወላጆች።

ጐዦ (ዎች) (ግዕዘ)፡ በዱር በመንደር ያለች ቅልስ ወይም ታናሽ ቤት።

ጐዦ አወጣ፡ አባት ለልጁ ቤት ሠርቶ ገንዘብና ከብት ከፍሎ ሰጠ፡ አጐነደ። የጐዦ ምስጢር ተነቅሎ መጓዝ ነው።

ጐዦ ወጣ፡ ከአባት ከእናቱ ቤት ተለየ፣ ትዳር ያዘ፣ ጐነደ።

ጐዦ ወጪ፡ ትዳር ጀማሪ።

ጐዦና ጕልቻ፡ ንብረት፣ ትዳር።

ጐደለ (ጐዲል፣ ጐደለ)፡ አነሰ፣ ተቀነሰ፣ ዐጸጸ፣ ዐጠጠ፣ ወይም ያልተሞላ ቀረ (ዘፍ፰፡ ፩፣ ኢሳ፰፡ ፳)

ጐደል፡ የጐደለ። "ዋና ጐደል" እንደሚባለው።

ጐደሎ (ዎች)፡ ባላንድ አካል (ለምሳሌ፡ - ዐይን፣ ጆሮ፣ እጅ) ወይም ቍጥሩ ያልሞላ።

ጐደሎ ቀን: ሰዓቱ ከ፲፪ ያነሰ።

ጐደሎነት፡ ጐደሎ መሆን ወይም ታናሽነት።

ጐደራ፡ ጮኸ፣ ቀተራ (የበሬ)

ጐደሬ፡ የድንች ዐይነት ተክል።

ጐደበ (ጐዲብ፣ ጐደበ)፡ ማሰ፣ ተፈረ፣ መነቀረ፣ ቈረጠ፣ ዐረደ፣ አጐደጐደ። "ጐደበ" የግእዝ፡ "ገደበ" የአማርኛ ነው።

ጐደነ፡ መንገድ ጠረገ ወይም አሰፋ።

ጐደነ፡ ወደ ጎን ሄደ።

ጐደደ፡ ተላከከ፣ ተጣበቀ፣ ተጋገረ።

ጐደደ፡ ዝግ፣ ቀስ አለ።

ጐደዳ፡ በጥፍጣፍ ደንጊያ ላይ የተጣበቀ፣ እንደ እንጀራ የተጋገረ የበግና የፍየል በጠጥ፡ ጠቦት።

ጐደጐደ (ጐድጐደ)፡ ጐድጓዳ፣ ጕድጓድ፣ ዘባጣ ኾነ (ተደራጊ)

ጐደጐደ፡ እጕድጓድ አገባ፣ ከተተ፣ ረገረገ፣ ቀበረ፣ ደፈነ (አድራጊ)

ጐደፈ (ጐዲፍ፣ ጐደፈ)፡ ፋ፣ ጕድፍ ሆነ፣ አደፈ፣ ቈሸሸ፣ ወሰከ፣ ወይም ረከሰ።

ጐደፈረ (ጐጽፈረ)፡ ጫረ፣ ማሰ፣ ቈፈረ፣ መነቀረ፣ ዛቀ (ዐፈርን፣ ጕድፍን)፡ በተነ (ያውራ፣ ያውሬ፣ የሰው፣ የበሬ)

ጐደፋ፡ በማይገባ ሥራ፣ በአመጽ ወይም በቅሚያ መጐደፍ ወይም መርከስ።

ጐዳ (ጕዱዕ) (ላዳ)፡ የተጐዳ፣ ዘላሳ ቀላሳ።

ጐዳ (ጐዲዕ፣ ጐድዐ)፡ በጣም በኀይል መታ፣ ደሰቀ፣ ሰበረ፣ ቀጠቀጠ፣ አደቀቀ፣ አከላ።

ጐዳ በሬ፡ ተንዱ የተዘለሰ፣ የተቀለሰ በሬ።

ጐዳ፡ በደለ፣ ጨቈነ፣ አስጨነቀ (ራእ፲፩:)

ጐዳ፡ ባዶ አደረገ፡ አሳጣ።

ጐዳ ኩታ፡ ጥለት የሌለው ኩታ።

ጐዳ ኩታ: ያለ ጥለት የተሠራ፡ ጥለት የሌለው ኩታ።

ጐዳቢ፡ የጐደበ፣ የሚጐድብ፣ ማሽ፣ ቈፋሪ።

ጐዳና"መንገድ ሰው እንዳይሄድ የለም" ወይም "ሰው እንዳይሄድ" እንዳለ የበገና መቺ።

ጐዳና (ዎች)፡ ጥርጊያ ወይም ሰፊ መንገድ። "ጐዳናዋ" ወይም "ጐዳናዪቱ" ሲባል "ጥርጊያዋ" ማለት ነው።

ጐዳና፡ የበገና ምት ወይም ስልት።

ጐዳይ፡ የሚጐድል ወይም አናሽ።

ጐዳዳ፡ ዝግተኛ፣ ቀስተኛ።

ጐዳዴ፡ የጐዳዳ ወገን፡ ወይም "የኔ ጐዳዳ፣ ጐዳዳዬ" "ዐይናማው ጐዳዴ" እንዳለ ዘፋኝ።

ጐዳፊ፡ የሚጐድፍ ወይም የፍግ/ጥራጊ ማፍሰሻ መሬት።

ጐዳፋ፡ የጐደፈ፣ ጕድፋም፣ ቆሻሻ፣ ወይም የአሳማ አይነት።

ጐዴ፡ የጐዳ፣ ጐዳዊ፡ የጐዳ ወገንና ዐይነት።

ጐዴ ድንኳን፡ ትልቅና ሞላልኛ ድንኳን፣ ዳርና ዳሩ ክብ፡ ጕልላት የሌለው።

ጐድር፡ የሣር ስም፡ ለቤት ክዳንና ጕንጕን የሚሆን ሣር (ጐዣም)

ጐድን (ኖች)፡ የጎን ዐጥንት (ቁጥሩ እና ፮፣ በአጠቃላይ ፲፪) በተጨማሪም የተጫነ አህያን ወደ ጎን እንዲሄድ ለማድረግ የሚነገር ቃል ነው።

ጐድን ከዳቢት፡ የሥጋ ብልት ስም ሲሆን ጐድን ከዳቢት ጋራ የሚለው የብራኳ ዐጥንትና ሻኛ አንድነትን ያመለክታል።

ጐድጓዳ፡ ዐቃፋ፣ ወጭት፣ ድስት።

ጐድጓዳ፡ የጐደጐደ፣ ፈፋ፣ ፈረፈር፡ በግደልና በተራራ መካከል ያለ የምድር ዋዲያት። "ጐድጓዳ ስፍራ" እንዲሉ።

ጐድጓጅ፡ የሚጐደጕድ፡ ከታች።

ጐድፋሪ (ጐጽፋሪ)፡ የጐደፈረ፣ የሚጐደፍር፡ ማሽ፣ ቈፋሪ፣ ጫሪ፣ መንቃሪ።

ጎዶ፡ ቸግሮ፣ ጠፍቶ፣ ታጥቶ። "ምን ገዶ፣ ምን ገዶት" እንዲሉ።

ጐዶ፡ ጐበዛዝት በዋሻ በሰቀላ ውስጥ ሥጋ እየበሉ የሚያደርጉት ዕረፍትና በዓል፡ ከጕዳት ከድካም የሚያርፉበት፣ ትልቅነትንና ጌትነትን የሚቀምሱበት።

ጐጀሬ፡ ገዠሞ፣ ጐዠሬ።

ጐጀብ፡ የዠማ ስም፣ በከፋና በጌራ መካከል የሚወርድ ታላቅ ወንዝ።

ጐጂ (ጐዳዒ)፡ የጐዳ፣ የሚጐዳ፣ የሚያከሳ።

ጐጋ (ጕጋ)፡ የጕጕት ወገን፣ ፈሪ፣ አንበልጋ፣ ቡከን።

ጎግ (ቃውቃዝ)፡ የነገድና ያገር ስም።

ጎግ (ጎገወ)፡ የያፌት ልጅ፣ የመስኮቦች አባት።

ጎግ ማጎግ፡ ጎግ ጀርመን፣ ማጎግ መስኮብ። ምስጢሩም ብዛትንና አሕዛብነትን ያሳያል። "ጎግ ሕዝብ፣ ማጎግ አሕዛብ" ማለት ነው (: : ) ባላገር ግን "ጉግ ማንጉግ" ይላል።

ጐጐመ (ቀቀበ)፡ በጦር፣ በቀንድ ጥቂት ለተመ፣ ወጋ፡ አላቈሰለም።

ጐጓ (ጐጕኦ ጐጕአ)፡ አጣደፈ፣ አስቸኰለ።

ጐጓ፡ ቋቅ አሰኘ፡ ባለማቋረጥ አስታወከ፣ አስመለሰ፣ አቀረሸ፣ አስፈለቀ፣ አስተፋ።

ጐጓሚ፡ የጐጐመ፣ የሚጐጕም፡ ወጊ።

ጐጠ ጕጣ፡ ጐጠ።

ጐጠረ (ገየጠ ጌጠ)፡ ተገሪ፡ የሚገር፣ ተቋፊ።

ጐጠረ፡ ጐሰረ፣ ጐኘረ፣ መላ፣ ጠቀጠቀ፣ ወጠረ።

ጐጠጐጠ (ቈጠቈጠ)፡ ወጣ፣ በቀለ፣ ጐመጐመ (የጐጥ፣ የጕጥ፣ የጡት)

ጐጠጐጠ (ትግ፡ ጐጥጐጠ)፡ ዐይንን ወጋ፣ አወጣ፣ ቦጠቦጠ። "ዐይኖቹን ጐጠጐጡት" "የወንዝ ዳር ቍሮች ይጐጠጕጧታል" (፪ነገ፡ ፳፭፡ ፯፣ ምሳ፡ ፲፯)

ጐጠጐጠ (ትግ፡ ጐጽጐጸ፡ ተጕመጠመጠ)፡ ወጣ ገባ ሆነ፣ ከፍና ዝቅ አለ።

ጐጠጐጠ፡ በጕጣ ዐረሰ።

ጐጠጐጠ፡ ገጠጠ፣ ጕራጅ።

ጐጠጐጠ፡ ጥርስን መዘዘ፣ ነቀለ።

ጐጠጠ (ቈጢጥ፣ ቈጠጠ)፡ አነሰ፣ ኰሰሰ፣ ቀጠነ፡ ተናቀ።

ጐጣጕጥ (ጐጻጕጽ)፡ ዐባጣ፣ ጐባጣ፣ ሻካራ፣ ወጣ ገባ፣ አስቸጋሪ፡ ሥርጥ፣ ሰንከልካሳ፣ ደንጐላጕል፣ ሥርጓጕጥ፡ ብዙ ጐጥ ተደራርቦ ያለበት፣ የበዛበት ስፍራ።

ጐጥ (ጦች)፡ የምድር ጕጥ፡ ታናሽ፣ ዝቅተኛ ጕባ ከፍታ። "የጐጥ አለቃ" እንዲሉ።

ጐጥ፡ የሰጐጥ ከፊል ስለሆነ፣ ታላቅ ቋጥኝ ገዎቻ ሊባልም ይቻላል።

ጐጥ፡ ጕባ፣ ጐጠጐጠ።

ጐጥጓጭ፡ የጐጠጐጠ፣ የሚጐጠጕጥ፡ አውጪ፣ መዛዥ፣ ነቃይ።

ጐጯጯ (ቈጪጪ)፡ ቀጨጩ፣ አጠረ፣ አጭር ሆነ።

ጐፈለ፡ ጐፈረ።

ጐፈለለአንጐፈለለ፡ አረዘመ (ጠጕርን)

ጐፈረ (ቀፈረ)፡ ረዘመ፡ ጐፈሬ ኾነ፡ ቆመ፡ ተመየደ፣ ተበጠረ።

ጐፈረ፡ ጨቈነ፣ ረፈቀ፡ ጫረ፣ ማጨረ።

ጐፈሪያም፡ ጐፈሬ ያለው (ባለጐፈሬ)

ጐፈሬ (ጐፈራዊ)፡ የጐፈር ዐይነት፡ በመቀስ ጫፍ ጫፉ የሚከረከም የማይላጭ መጠነኛና ረዥም የራስ ጠጕር (ጕተና) (ብርንጎ) (የጐፈር)፡ ገዳይ ወይም የሌላ።

ጐፈሬ፡ የመሬት ጥቅም (ሣር) (እኽል)

ጐፈር፡ ያንበሳ ለምድ። "ወታደሩ ጐፈር ለብሷል"

ጐፈር፡ ጠጕረ ረዥም አህያ (ውሻ)

ጐፈር፡ ጠጕራም አንበሳ። "ዐዳኙ ጐፈር ገደለ"

ጐፈነነ (ቈፈነነ)፡ ቀፈፈ፣ መረረ፡ ክፉኛ አገሣ፣ አቀመ፣ ሰቀጠጠ (የኮሶ)

ጐፈየ፡ ከላ (ማንጆ) ኾነ፡ ሥባት ዐጣ። "ሠባ እንረደው፡ ጐፈየ እንስደደው" እንዲሉ።

ጐፈጐፈ (ጐፈፈ)አንጐፈጐፈ፡ እንደ ዶሮ አስኬደ፣ አሮጠ።

ጐፈጐፍጐፍጓፋ፡ የተንጐፈጐፈ። (ተረት)"እመዬቴ ጐፈጐፍ ወረደች እጕድፍ"

ጐፈጠጠ፡ ፈጽሞ ኣረጀ፣ አፈጀ፣ ደከመ፡ ሰውነቱ ተጨበጠ፣ ጐነበሰ፣ ጐበጠ፡ መኼድ አቃተው።

ጐፈጠጥጐፍጣጣ፡ የጐፈጠጠ፡ ደካማ፣ ያረጀ፣ ያፈጀ፣ አሮጌ፣ ሽማግሌ።

ጐፈፈአንጓፈፈ፡ አደከመ፣ አታከተ፡ አንቈረሰሰ፣ አዘገመ።

ጐፈፍ አለ፡ ዘገም አለ።

ጎፋ፡ ያገር ስም፡ በኃላ ቤት ያለ ክፍል አገር።

ጎፋ ጌኔ፡ የጎፋ ንግሥት።

ጐፋፋ፡ ደካማ፣ ሽማግሌ፣ ቈርሳሳ።

ጐፍላ (ሎች)፡ ረዥምና ብዙ የውሻ ጠጕር፡ ወይም ጠጕራም ባለረዥም ጠጕር። "ጐፍላ ውሻ" እንዲሉ።

ጐፍላ፡ እንቡጣ ከነጠጕሩ ስልቻ የወጣ (ሣርና ገለባ የመላበት) (የተጐሰረበት) (ባ፬ የንጨት እግር የቆመ) የጥጃ ቈዳ፡ ላም እሱን እየላሰች ወተት ትሰጣለች። "ላም በጐፍላ ትታለባለች" እንዲሉ። (ግጥም)"አባቴ ጌታ ነው እናቴ እመቤት ነች እያሉ ጨዋታ! በጐፍላ ማለብ ነው ላም ጥጃዋ ሞታ"

ጐፍናና፡ ፊቱን ያቀጨመ፣ ያከፋ።

ጐፍናኝ፡ የጐፈነነ፣ የሚጐፈንን፡ መራራ ነገር።

ጐፍጐፍ አለ፡ ተንጐፈጐፈ።

(ቆዕ): ጓሚያ (ያልበሰለ ፍሬ፣ ጨረቋ፣ ቃሪያ) በትግሪኛ:ጉዕይባላል። ተመልከት: ጓይን፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።

አለ: ጮኸ (ጓጓ)

፡ እጓ አለ ( እቋ አለ)፡ ተንጓጓ አለ፣ ጓጓ።

ጓ፣ ጓይ፣ ጓሚያ፣ ጓዕ፡ ኹሉም 'ቆዕ' የወጣ ነው።

ጓለለ) (ትግ ጐለለ) አንጓለለ፣ አንገዋለለ። "ገወለለን እይ።"

ጓለበ፡ ተንገዋለለ፡ ተመረጠ፣ ተለየ።

ጓል (ሎች)፡ የተድበለበለ ዐፈር በመሬት ላይ እንደ ድንጋይ ጐልቶ የሚታይ፣ ድብልብል መከሎ።

ጓመጠ፡ ታኘከ፣ ተበላ።

ጓሚያ (ጓዕ)፡ ያልበሰለ የተክል፣ የዕንጨት ፍሬ፡ ጠንካራ ቃሪያ።

ጓሣ፡ ሣር (ጓሳ)

ጓሳ: የሣር ስም። የታወቀ ሣር (እንደ ጣርማበር ባለ በጉም ለበስ ተራራ ላይ ከአስታ ጋራ የሚበቅል)፡ አንጓ የለሽ፣ ሻካራ፣ መላላ። ለቤት መክደኛ፣ ገመድ፣ ለወፍጮ መጥረጊያ "ሙሬ" ይኾናል። አንቀጹ "ጐሰሰ" ነው።

ጓረኛ: ዝኒ ከማሁ።

ጓሮ (ገዊር፣ ጎረ፣ ጎር): ከቤት በስተኋላ ያለ ዐጥር ግቢ (ሕዝ፵:፲፬:፲፯:፲፱) "ባለቤት ጓሮ ዞረ" (ግጥም): "አንቱም አንቱም አትዋሹ፡ ወደ ጓሮ ልትሸሹ" (እንስት ዶሮ አውራ ዶሮን)

ጓሮ (ጐረረ፣ ጐረጐረ): ጠብ፣ ጥል፣ ክርክር። "ዐምባ ጓሮ" እንዲሉ። "ዐምባን" ተመልከት።

ጓሮ ቤት: በጓሮ ያለ ሠገራ ቤት።

ጓሮ ገዳይ: በቅርብ በጓሮ አጠገብ የገደለ። የዝኆን ገዳይ ዘፈን አዝማች።

ጓሮኛ (ኞች): ጠበኛ (ጥል ያለሽ) (ዳቦ የሚል)፡ ጠብ ወዳድ። "ጓሮ" "ጠብ" ተብሎ ሲተረጐም፣ ግእዝ "ጐርጐረ" "አንጐርጐረ" "ነጐርጓር" ካለው ይወጣል።

ጓታ (ገብጥ)፡ የሆድ በሽታ፣ ብስና፣ እሕታ፣ የሚቈርጥ፣ የሚጐረብጥ።

ጓታ፡ የመብረቅ ጩኸት፡ "" ማለት።

ጓታ: የሆድ፣ የመብረቅ ጩኸት (ጓጓ)

ጓንጕል (ትግ)፡ ሕብረ ዕንቍ (ጨሌ) (ሽልማት)፡ ዝንጕርጕር ነገር፡ ነጭና ቀይ በሬ፡ ሴደር፣ ሴደርማ።

ጓንጕል፡ የሰው ስም፡ "ጌጤ ነኸ" እንደ ማለት ነው። "ጓንጕል ዘገየ" እንዲሉ።

ጓንጓ፡ የንጨት ዋሻ፡ ውስጠ ክፍት ዛፍ (ማጓ፣ ቀባ) የሚገኝበት። "ጓንጓ" ትግሪኛ ነው።

ጓዕ (ቆዕ)፡ ጓሚያ።

ጓዝ (ዞች)፡ ገዓዝ፣ ጋዕዝ፡ ዕቃ።

ጓዝ ተጋሻ፡ አንድ ወታደር ከነቤተሰቡ። "ጓዝ ሚስት፣ ልጅ፣ አሽከር፣ ጋሻ" ባለቤት ነው።

ጓዝ ጠባቂ፡ የጓዝ ዘበኛ።

ጓያ (ዮች) (ጐይይ፣ ጐየ)፡ በክፉ ቀን የበሉትን ሰዎች ወገብ ሰብሮ ቋንዣቸውን ያሽመደመደ ባለሐረግ እህል ነው። ከዚህ የተነሳ ብዙዎች ሰዎች ፈርተው እሱን ከመብላት ይሸሻሉና "ጓያ" ማለት ፍራትን፣ ሽሽትን ያሳያል። ትግርኛ "ነበረ" ይለዋል።

ጓይ፡ የጥጥ ጓሚያ፡ ጓዕ።

ጓደና፡ ዘላንነት ወይም በዱር መቀመጥ።

ጓደኛ (ኞች)፡ ጓድ፣ ወይም ጓድ ያለው፣ ባለጓድ። ሚስትም ለባሏ ጓደኛ ናት።

ጓደኛ፡ ባልንጀራ።

ጓደኛ()ነት፡ ባልንጀርነት፣ ባልደረብነት።

ጓደደ (ትግ ጓዕደደ፣ ኰራ)፡ ዐበረ፣ ገጠመ፣ ባልንጀራ ኾነ።

ጓዳ (ዎች፣ ዶች)፡ የዕቃ፣ የምግብ መክተቻ፣ መጐድጐጃ፡ በቤት ዙሪያ ተያይዞ ወይም ተቀጥሎ የተሠራ ማጀት።

ጓዳ፡ ተጨማሪ ቤት፣ ጐደጐደ።

ጓዳ ጐድጓዳ፡ እንደ መታደያ ያልተደለደለ፣ የቤት ሥርቻ፣ ውስጣውስጥ የጐድጓዳ ጓዳ።

ጓዴ፡ ባልንጀራዬ፣ ባልደረባዬ፣ ቢጤ፡ የኔ ጓድ።

ጓድ (ዶች)፡ ባልደረባ፣ ዐብሮ አደግ፣ ጭፍራ።

ጓድ፡ ባልንጀራ፣ ጓደደ።

ጓጕንቸር (ሮች)፡ ትልቅ እንቍራሪት፣ ጕርጥ፡ ወይም ሸርጣን፣ ጐርምጥ (ዘፀ፰:፫፻ :, :, ራእ፲፮:፲፫)

ጓጕንቸር፡ ሜንጦው የእንቍራሪቱን እግር የሚመስል ትልቅ የመዝጊያ ቍልፍ።

ጓጒ፡ የሚጓጓ፣ ከጃይ፣ ሠዪ፣ ጐምዢ።

ጓጐለ፡ ረጋ፣ ተቋጠረ (የደም)

ጓጐለ፡ ተድበለበለ፣ ድብልብል ኾነ (የቡሖ፣ የሊጥ)

ጓጐረ፡ ከመያዝ፣ ከመጋት፣ ከጭንቅ የተነሣ ጮኸ፣ አጓራ። (ተረት)"ሲጠባ ያገጠ ጥጃ ቢይዙት ይጓጕራል። "

ጓጐት፡ ወንዴ፣ ቋቍቻ፣ ቅርፍርፍ፣ ሽርክርክ፡ ከቀይ ወደ ቀይ፣ ከጠይም ወደ ጠይም ገላ የሚጋባ፣ ተላላፊ፣ ተረማማጅ የቍንቍን ወገን። ካፍለኛ በቀር ሽማግሌ የማይዝ። ቋቍቻና ጓጐት አንድ ስም ነው።

ጓጓ (ጐጕአ)፡ ከጀለ፣ ተመኘ፣ ሠየ፣ ጐመዠ፣ ቶሎ ለማግኘት ተስፋ አደረገ።

ጓጓ አደረገ፡ አንጓጓ።

ጓጓ አደረገ፡ አጓጓ።

ጓጓላ፡ የጓጐለ፣ ድብልብል፣ የረጋ፣ የተቋጠረ፣ ቋጣራ፣ ጭን።

ጓጓላነት፡ ጓጓላ መኾን፡ ቋጣሪነት።

ጓጓሪ፡ የጓጐረ፡ በሬኛ፣ ጯኺ።

ጓጓራ፡ ዝኒ ከማሁ፡ የሚጓጕር።

ጓጓታ (ዎች)፡ መንጓጓት፣ ጩኸት። "የጋሻ ጓጓታ" እንዲሉ።

ጓጓታ፡ መንጓጓት (ጓጓ)

ጓጓአለ፡ ተንጓጓ።

ጓጓይ፡ የሚጓጕል፣ ተድበልባይ።

ጓጓጠ (ጐጽጐጸ)፡ ወጋ፣ ሸቀሸቀ፣ ቈሰቈሰ።

ጓጓጭ (ጮች)፡ የጓጐጠ፣ የሚጓጕጥ፣ የሚሸተሽቅ፣ ሸቅሻቂ።

ጓጠጠ (አንጓጠጠ)፡ አጐጠጠ፣ አሽሟጠጠ፣ አቃለለ፣ አዋረደ፣ ሰደበ።


No comments:

Post a Comment

ሽፋን

  ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ