ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ሰ : ፳፩ኛ ፊደል በግእዝ እልፍ ቤት በአበገደ። "በፊደልነት ስሙ ሳት አኃዝ ሲኾን ሰ−፫፻ ይባላል።"
ሰ: የዘና፣ የከ፣ የጸ ተለዋጭ። "ግእዝ አመዝገነ ምስጋና፣ መከነ መካን፣ ጸልመ ጸለለ ጸጥ የሚለውን ዐማርኛ አመሰገነ ምስጋና፣ መሰነ መሲና፣ ሰለመ ሰለለ ሰጥ በተከ፣ ቀተረ ወዘወዘ ያለውን በሰከ ቀሰረ ወሰወሰ ማለቱን ያሳያል።" "፪ኛውን ሰለመ፣ ፫ኛውን ስለለ ተመልከት።"
ሰሐራ (ዐረ፡ ጻሕራእ): የበረሓ ስም፡ ከግብጽ ቀጥሎ ያለ እጅግ ታላቅ ሰፊ ምድረ በዳ። "ጥንት፡ ከተማ፡ ነበር፡ ይላል፡ መጽሐፈ፡ መነኮሳት፡ (ፊልክስዩስ)።"
ሰሐጢ (ሰሐጠ): በትግሬ ክፍል ያለ በረሓ። "ትርጓሜው፡ ቈንጣጭ፡ ማለት፡ ነው፡ ትንኙን - ያሳያል።"
ሰለሔ: መለሔ፡ ሰለሔ፡ እንዳለፈው፡ መለሔን፡ እይ።
ሰለሔ: ገንፎ በቅቤ።
ሰለለ (ትግ፡ ሰለለ፡ ኰበለለ): መነመነ፣ ቀጠነ፣ ከውፋሬ ራቀ፣ ያካል የቃል (መሳፍንት ፫፡ ፲፭። ማቴዎስ ፲፪፡ ፲። ዕብራውያን ፲፪፥ ፲፪)። "የጌዜና ኀላፊ ትንቢቱ ይሰል ይሰላል ይላል።"
ሰለለ (ጸለለ፡ ተንኳፈፈ): ጠለለ።
ሰለለ: ሰው ኹሉ የሚናገረውን ሰማ፣ ወሬ ጠበቀ።
ሰለል ብሎ ገባ: እንደ ሰላይ፣ እንደ ውሃ ሳይታይ ሳይታወቅ ማለት ነው።
ሰለል አለ: ስተት አለ።
ሰለልታ: ጠለልታ፣ ጠላ ከተመላ በኋላ በላይ የሚታየው ውሃና ዐሠር። "ዳግመኛም ዐሠር ውሃ ይባላል።"
ሰለልኩላ: በላስታ ውስጥ ያለ አገር፣ የቅዳሴ ዜማ መምራን የሚገኙበት። "ሰለልኩላ ባንኮበርም አለ።"
ሰለመ (ሰለም፡ ሰለመ): ማተቡን በሰ፣ እስላም ኾነ፣ ኦሪትን ወንጌልን ወይም ሌላውን ሃይማኖት ተወ፣ ካደ፣ የእስላምን እምነት ተባለ።
ሰለመ (ጸልመ): ጨለመ።
ሰለመ: አፈቀረ፣ አመሰገነ፣ አሳረፈ፣ አዳነ።
ሰለመጠ (ሰለጠ): ሳያኝክ ዋጠ፣ ሰለቀጠ።
ሰለሰለ (ትግ ሰንሰነ፡ ከሳ): ቀጠነ፣ ስለተ፣ መነመነ፣ ኰሰሰ (ኢዮብ ፴፫፡ ፳፩)። "ሥሩ፡ ሰለለ፡ ነው፡ (ተገብሮ)።"
ሰለሰለ: ሸነሸነ፣ ነጠለ፣ ሠነጠቀ (ሰሌንን፣ ግራምጣን (ገቢር))። "ስነሰነን፡ እይ።"
ሰለቀ (ሠለቀ): ጕርሃን ጤፍን ፈ፣ አደቀቀ፣ ደቈሰ፣ አላመ፣ አለሀበ።
ሰለቀ: በጣም ዐመመ፣ መታ፣ አደከመ ሰውነትን።
ሰለቀጠ: ሳያኝክ ዋጠ። "ሰለመጠን፡ እይ።"
ሰለበ (ሰሊብ፡ ሰለበ፡ ገፈፈ። ዐለገ): የወንድን ብልት ቈረጠ፣ ጐመደ፣ ደደ እስከ ዕንብርት ገሸለጠ፣ ጃን ደርባ አደረገ።
ሰለበ: ምትሀት ባስማት በሚዛን የሰውን ምርት ቡሖ ቅቤ ጥጥ ሳበ፣ ወሰደ። "የሌላውን፡ ጥቅም፡ አሳነሰ፡ ኣጐደለ፡ የራሱን፡ መላ፡ አበዛ።"
ሰለባ: ማንኛውም የተቀማና የተገፈፈ፣ የተሰረቀ ዕቃ። "ሌባ፡ ከነሰለባው፡ ተያዘ፡ እንዲሉ።"
ሰለባ: ቈረጣ።
ሰለባ: የተቈረጠ ቍላ፣ የግዳይ፣ የድል ምልክት (፩ኛ ሳሙኤል ፲፰፡ ፳፭)።
ሰለተ (ሰልቶ፡ ሰለተ፡ ዘበተ): ሰንበሌጥን ዘቀዘቀ፣ እንደ ዘበት በቀላል ከደነ፣ ክዳንን አሣሣ።
ሰለተ: ለተተ፣ ደከመ፣ ከሳ፣ ቀኑ መነመነ፣ ፍሬ አልባ ቀረ፣ ደረቀ (ተገብሮ)።
ሰለተ: ከፈለ፣ ለየ (ገቢር)።
ሰለታ: ሥሥ ክዳን፣ ዝቅዝቅ።
ሰለቸ: ታከተ፣ ደከመ።
ሰለቸ: ጠበ፣ ጠላ፣ ነቀፈ፣ ተሠቀቀ፣ ተንገፈገፈ (ዘጸአት ፰፥ ፲፯። ዘኍልቍ ፲፩ - ፳። ኢዮብ ፲፡ ፩፡ ሕዝቅኤል ፮፡ ፱)።
ሰለንዳ (ሰነዳ): ዝግጅት፣ መቀናበር።
ሰለንዳ ቢስ: ዝግጅተ መጥፎ።
ሰለከ: ቀጠነ፣ ቀጥ አለ፣ ወደ ውስጥ ኼደ፣ ሰልቶ ገባ። "ሾለከን፡ እይ።"
ሰለከከ: አማረ፣ ተዋበ፣ ሸገነ፣ ከኣለማማር ራቀ።
ሰለጀጅ: ሰልጃጃ፣ የተንስለጀጀ፣ የሚንሰለጀጅ፣ እንስልጅ፣ ፈዛዛ።
ሰለጠ (ሰልጦ፡ ሰለጠ): ቀና ኾነ፣ በጀ፣ ተከወነ፣ ተጨረሰ፣ ቀለጠፈ። "፪ኛውን ሰላ ተመልከት።"
ሰለጡ (ሰልጦ፡ ሰለጠ): ቀና ኾነ፣ በጀ፣ ተከወነ፣ ተጨረሰ፣ ቀለጠፈ። "፪ኛውን፡ ሰላ፡ ተመልከት።"
ሰለፈ (ዐረ): አበደረ፣ በዱቤ ሰጠ።
ሰለፈ: ቀረበ፣ ቸኰለ፣ አቈተመ ለምግብ፣ ለወሬ።
ሰለፈ: ተጠረረ፣ ተዘጋጀ ለውጊያ (ተገብሮ)።
ሰለፈ: ደከረ፣ ደቀነ ጸብትን (ገቢር)።
ሰሊጥ (ጦች): ቅባት የሚወጣው ቅመም፣ ከናገዳው።
ሰሊጥ: ሰላጣ።
ሰላ (ተስሕለ): ስለታም ኾነ፣ ተባ፣ ሾለ፣ ሾለከ።
ሰላ (ትግ፡ ሰልሐ። ዐረ፡ ጸለሐ። ግእዝ፡ ተሠርሐ): በጀ፣ አማረ፣ ሰመረ፣ ቀና፣ ቀለጠፈ፣ ተከወነ (፪ኛ ዜና መዋዕል ፳፡ ፳። ሉቃስ ፰፡ ፲)። "ወሰላ፡ ወሰልሰላ፡ ዐንገቱ፡ በምን፡ ሰላ፡ ነጭ፡ ጤፍ፡ እየበላ፡ እንዲሉ፡ አባትና፡ እናት፡ ልጃቸውን።"
ሰላ፡ ገደድ: ቅን፣ ጠማማ ወይም ቀና ጠመመ። "እከሌ፡ ሰላ፡ ገደድ፡ ያውቃል፡ እንዲሉ።"
ሰላላ: መላላ፣ ትክክል ያልኾነ ፈትል፣ ቅጥነትና ጥቂት የቀጥታ ውፍረት ባንድነት ያለው "የዝንብ አንዠት የሰዶ ጕልበት የመሰለ።"
ሰላላ: የሰለለ፣ የመነመነ።
ሰላሌ (ኦሮ): የነገድና ያገር ስም፡ "ሰላሌ አቅኒው ነው።"
ሰላመ ገብርኢል: ቅዱስ ገብርኤል ለመቤታችን ያቀረበው ምስጋና፣ ከአቡነ ዘበሰማያት ጋራ የሚጸለይ።
ሰላሚ: የሚልም።
ሰላማ፣ ብርሃነ አዜብ፣ ንኡስ ሰላማ: በ1000 ዓ.ም የነበረ የሐበሻ ጳጳስ፣ ያገር ተወላጅ።
ሰላማ: አንደኛው መዠመሪያው የኢትዮጵያ ጳጳስ፣ ከሣቴ ብርሃን ፍሬምናጦስ፣ በ409 ዓ.ም የነበረ። "ማ ያገሪቱ ዝዝ - ነው።"
ሰላማዊ: የሰላም ባለሰላም ሰው፣ ደንሲ፣ ራም፣ ከብት፣ እንስሳ። "ሰላማዊ የግእዝ ነው ባማርኛ ሰላመኛ ሊባል ይኵላል።"
ሰላም ላንተ: ምስጋና፣ ደኅንነት ላንተ ይኹን፣ ይደረግ።
ሰላም: አጭ፣ ደጭና ደኅንነት፣ ጤና፣ ሤራ፣ ዕረፍት፣ ጸጥታ፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ ምስጥና።
ሰላም: የዜማ ስም፣ የቁም ዜማና የማሕሌት ክረም።
ሰላምተኛ: ባለሰላምታ ሰው፣ ጠያቂ።
ሰላምታ ሰጠ: ጠየቀ፣ እንዴት ነኸ አለ።
ሰላምታ: በሰባቱ ጊዜያት የሚጸለይ የአባ ጊዮርጊስ ድርሰት።
ሰላምታ: የፍቅር ምስጋና ደብዳቤ። "የተላከ ከይድረስ ለካለ በኋላ እንዴት ሰንብተኻል (ከመኻል) ብሎ የሚዠምር።"
ሰላምታ: ጤና ይስጥልኝ ማለት፣ እጅ መንሣት፣ ከበሬታ መስጠት (ሉቃስ ፲፩፡ ፵፫)።
ሰላቂ: የሰለቀ፣ የሚሰልቅ፣ አላሚ፣ አለዛቢ፣ ደቋሽ።
ሰላቢ (ዎች): የሰለበ፣ የሚሰልብ፣ ጠንቋይ፣ ምትሀተኛ፣ ጝርተኛ።
ሰላቢነት: ሰላቢ መኾን።
ሰላች (ቾች): የሰለተ፣ የሚሰልት፣ ከዳኝ።
ሰላኪ: የሰለከ፣ የሚሰልክ፣ ዐልቅት።
ሰላይ (ዮች): የሰለለ፣ የሚሰልል፣ ጕበኛ፣ ተመልካች፣ ነገር ጠባቂ፣ አገር ምን ይላል ባይ (ኢያሱ ፪፡ ፩። ፪ኛ ነገሥት፱፡ ፲፯፡ ፲፰፡ ፰። ሉቃስ ፳፡ ፳)።
ሰላይ: ከሰንጠረዥ መጫወቻ አንዱ።
ሰላይነት: ሰላይ መኾን፣ ጕበኛነት።
ሰላጢን: ጦር፣ ሠለጠ።
ሰላጣ: የጐመን ዐይነት ቅጠል፣ ሳይቀቀል የሚበላ።
ሰላጤ: ሕፅን፣ ሠለጠ።
ሰላፋ: ሰላፍ፣ የሰለፈ፣ የሚሰልፍ፣ ችኵል፣ እቈታሚ።
ሰላፋ: ብድር፣ ልቆ፣ ዱቤ።
ሰሌን (ኖች): የዘንባባ ሙሽራ ሸለም። "ከዚሁ የተሠራ ምንጣፍ (ኢሳያስ ፲፱፡ ፲፭)።"
ሰሌዳ: ሉሕ፣ ያልተቀጻ ብራና፣ ወረቀት፣ ዝርግ ጠፍጣፋ ሥራ፣ ጡብ፣ ብረት፣ እብነ በረድ፣ ደንጊያ፣ ንሓስ፣ የዝኆን ጥርስ፣ በላዩ ጽፈት የሌለበት። "ሲበዛ፡ ሰሌዳዎች፡ ሰሌዶች፡ ይላል።"
ሰልሰል: ሰልሳላ፣ የሰለሰለ፣ መንማና።
ሰልሳይ: የሚሰለስል፣ ሸንሻኝ፣ መንማኝ።
ሰልቀጥ፡ ስልቅጥ: አደረገ፣ ዋጥ፣ ተሰላቀጠ።
ሰልቃጭ: የሰለቀጠ፣ የሚሰለቅጥ፣ ዋጭ ገባ።
ሰልቶ፡ ገባ: ሾልኮ ገባ።
ሰልቶ: ስል ኹኖ፣ ሾሎ፣ ሾልኮ።
ሰልቷል: ቀና ብሏል፣ በጅቷል፣ ዕምሯል፣ ስል ኹኗል፣ ሾልኳል፣ ስበቱ፣ መጥረቢያው ፈሰሱ።
ሰልቺ: የሰለቸ፣ የሚሰለች።
ሰልካካ: ስልክክ፣ መልከቀና፣ አፍንጫ፣ ስንደዶ። "ፊተ፡ ሰልካካ፡ እንዲሉ።"
ሰልፈኛ (ኞች): ሰልፍ የሚያሳይ፣ ባለሰልፍ፣ ወታደር፣ ጭፍራ።
ሰልፈኛነት: ሰልፈኛ መኾን።
ሰልፍ: የጦርነት ዝግጅት፣ የደመራ ለትና በዘመቻ ጊዜ የሚደረግ ከነጦር መሣሪያው የሰራዊት መታየት።
ሰልፍ: ጦርነት፣ ውጊያ (፩ኛ ሳሙኤል ፲፯፡ ፵፯፡ ፵፰። ፳፯፡ ፲። ፴፩፡ ፫)። "በግእዝ ጸብእ ቀትል ይባላል።"
ሰልፎ: የሚጤ መውጊያ ሹል ዘንግ።
ሰሎሞን: የሰው ስም፣ የዳዊት ልጅ፣ የእስራኤል ንጉሥ፣ ብልኀ፣ ዐዋቂ፣ ፈላስፋ። "ምሳሌን መክብብን ጥበብን መሓልይን የደረሰ።" "ትርጓሜው ፍቅርን ሰላምን ያሳያል።"
ሰመለ: ዠለጠ፣ አለፋ፣ አለሰለሰ (ቈዳን)፣ ላገ፣ ፋቀ (ዕንወትን)።
ሰመለለ: ጠጣ፣ ዥው አደረገ፣ ሰመጠጠ።
ሰመመ (ዘመመ): አሸለበ፣ አንቀላፋ።
ሰመመናም: ባለሰመመን።
ሰመመን: ሽልብታ፣ እንቅልፍ።
ሰመረ (ሰምረ): በጀ፣ አማረ፣ ማለፊያ ኾነ (ያዝመራ፣ የሥራ)። "ዲያቆኑ፡ መሥዋዕት፡ ይሰምርለታል።"
ሰመነ (ሰምኖ፡ ሰመነ): ስምንት አደረገ፣ በስምንት ከፈለ።
ሰመነ ዥረት: ዳር ዳሩን ሰመግ የሚበቅልበት ዠማ፣ አዳባይ። "የዱሮ፡ ሰዎች፡ በየሳምንቱ፡ ቅዳሜ፡ ጦርነት፡ የሚያደርጉበት፡ የጦር፡ ተማሪ፡ ቤት፡ ሰመጎ፡ ዥረት፡ ያለሽ፡ ዕዳሪ፡ መች፡ ትቀሪያለሽ፡ ሳትሞከሪ፡ ሰመዕ፡ ዥረት፡ ያለሽ፡ አሞራ፡ ሥጋውን፡ በልተሽ፡ ለምዱን፡ ዐደራ፡ እንዳለ፡ ወያኔ።"
ሰመነ: ሰመረ።
ሰመነ: ከበደ፣ ተጫነ።
ሰመከ: ተጠጋ (ግእዝ)።
ሰመግ፡ ዐይን: ዐይነ፡ ትንሽሽ፡ ሰው።
ሰመግ: በቈላ የሚበቅል ዐረግ። "ፍሬውን፡ ሴቶች፡ በክር፡ እየሰኩ፡ በእግራቸውና፡ በእጃቸው፡ በአንገታቸው፡ ላይ፡ ያስሩታል፡ ያጌጡታል።" "ሲበዛ፡ ሰመጎች፡ ይላል።"
ሰመግ: የሰመግ ፍሬ፣ ስንድድ፣ ዐንገት (የዦሮና የእጅ ጌጥ)። "ስመግ፡ ዐንገት፡ መባሉ፡ ውስጠ፡ ክፍትና፡ ያንገት፡ ጌጥ፡ በመኾኑ ነው።" "ክሣድን፡ ተመልከት።"
ሰመግማ: ጠጕሩ እንደ ሰመግ ፍሬ ጥቍረትና ንጣት ያለው በሬ፣ ፍየል፣ ፈረስ፣ ጠቃጠቆ። "ዳግመኛም፡ ስሙ፡ ሰመግ፡ ይባላል።"
ሰመጎ: ቃለ አጋኖ ወይም አክብሮና ኣንክሮ።
ሰመጠ: ሰጠመ።
ሰመጠጠ (መጠጠ): ሸመጠጠ፣ ጠጣ፣ ዥው አደረገ፣ ጨለጠ።
ሰሚ (ሰማዒ): የሰማ፣ የሚሰማ፣ አድማጭ (ያዕቆብ ፩፡ ፳፭)።
ሰሚ: በቶሎ ስለት የሚያደርስ ታቦት ወይ ብላ።
ሰሚ: አንተ እየተባለ ቅኔና ምስጋና የሚነገርለት የቅርብ ወንድ።
ሰሚ: የተማሪን ቅኔ ሰምቶ የሚያርም የቅኔ ምር።
ሰሚነት: ሰሚ መኾን።
ሰሚዎች: ሰሞች፡ የሚሰሙ፣ አድማጮች (ያዕቆብ ፩፡ ፳፫)።
ሠማ (ሠምዐ፡ ረስነ): ሞቀ፡ ጋለ፡ ጋመ፡ ቀለጠ፡ ፈሰሰ። ነገር ግን በልማድ ምክንያት በሳት ሰ ይጻፋል።
ሰማ (ሰምዐ): አደመጠ፣ ነገርን ተቀበለ (፪ኛ ሳሙኤል ፲፱፡ ፲፱)።
ሰማ: ጋለ፣ ሰማ።
ሰማማ: አደማመጠ።
ሰማኒያ (፹፡ ሰማንያ): የቍጥር ስም፡ "በሰባና፡ በዘጠና፡ መካከል፡ ያለ፡ ያሥር፡ ቤት፡ አኃዝ፡ ስምንት፡ ዐሥር።"
ሰማኒያ፡ አወረደ: ሚስቱን ፈታ፣ ለቀቀ፣ በዳኛ ፊት ተፈጥሞ።
ሰማኒያ፡ ከነዳ: ተፈጥሞ ስለ ቀረ ፲፭ ብር ከፈለ።
ሰማኒያ: የሳምንት ቀጠሮ ፈጠም።
ሰማኒያ: የች ኹለት አርባ።
ሰማኒያ: የውል የጋብቻ ቃል ማሰሪያ፣ እንደ ፊርማ ያለ፣ ፊርማን የመሰለ። "ይኸውም፡ ንጉሥ፡ ይሙት፡ ማለት፡ ነው።"
ሰማዕት (ሰዐም): ስለ ሃይማኖት የሞተ፣ የሃይማኖት ምስክር። "ሲበዛ፡ ሰማዕታት፡ ያሠኛል።"
ሰማዕትነት: ሰማዕት መኾን። "በሰይፍ፡ በእሳት፡ በክፉ፡ ሥቃይ፡ መሞት።"
ሰማየ፡ ሰማያት: ላይኛ መጨረሻ፣ ከሰማዮች በላይ ያለ ሰማይ (መዝሙር ፻፲፭ - ፲፮። ፻፵፰፡ ፬)። "ኣርያምን፡ እይ።"
ሰማያም: ባለሰማይ፣ የሰማይ ጌታ።
ሰማያዊ: ሰማይማ፣ ሰማይ የሚመስል ቀለም፣ ጥለት፣ ልብስ፣ ካባ።
ሰማያዊ: የሰማይ፣ በሰማይ ያለ፣ የተቀመጠ፣ እግዜር፣ መልአክ።
ሰማያይ: ዝኒ ከማሁ።
ሰማይ (ሰመየ): ከምድር በላይ ያለ የውሃ ባጥ ጣራ። "ያለባላ፡ ያለምሰሶ፡ ያላንዳች፡ ድጋፍ፡ በፈጣሪ፡ ትእዛዝ፡ የተሰቀለ፡ ጠፈር፡ የሌሊት፡ የቀን፡ መብራቶች፡ ጨረቃ፡ ኮከብ፡ ፀሓይ፡ በበታቹ፡ የሚታዩ።" "ሰማይ፡ ያለባላ፡ ምድር፡ ያለካስማ፡ እንዲሉ።"
"ሲበዛ፡ በግእዝ፡ ሰማያት፡ ባማርኛ፡ ሰማዮች፡ ያሠኛል፡ እነዚሁም፡ ሰባት፡ ናቸው፡ (ኢሳያስ ፵፰፡ ፲፫። ማቴዎስ ፫፡ ፲፮)።"
ሰማይ፡ በሰማይ: የሚኖር አምላክ፣ ፈጣሪ። "የሰማይ፡ ቍጣ፡ እንዲሉ።"
ሰማይ፡ ቤት (የሰማይ፡ ቤት): በሰማይ ያለ ቤት፣ ገነት፣ መንግሥተ ሰማይ።
ሰማይ፡ ዳሱ: ረዥም ሰው፣ ደመና ገፊ (ሔኖክ ፯፡ ፪፡ ፬። ዘዳግም ፪፡ ፳፡ ፳፬)።
ሰማይ፡ ጠቀስ: ዐይቦ የሚባል የነጭ በሬ ቀንድ። "ቀንዱ፡ ሰማይ፡ ጠቀስ፡ ጭራው፡ ምድር፡ አበስ፡ እንዲሉ።" "የዚህም፡ ምስጢር፡ የጌታችንን፡ አምላክነትና፡ ሰውነት፡ ያስረዳል።"
ሰማይና፡ ምድር: የተለያየ፣ የተራራቀ ነገር፣ አንድነት የሌለው።
ሰሜን: የማእዘን ስም። "ካራቱ፡ የዓለም፡ ማእዘኖች፡ ሦስተኛው፡ የምድር፡ ጎፍ፡ ራስጌ፡ በስተግራ፡ ያለ።"
ሰምዛ: ሰንሰል (ዮሐንስ ፲፱፡ ፳፱)። "በግእዝ፡ ግን፡ ስማዝ፡ ሸንበቆ፡ ጐሽ፡ መቃ፡ ተብሎ፡ ይተረጐማል።"
ሰሞነኛ (ኞች): "ከእሑድ፡ እስከ፡ እሑድ፡ በቤተ፡ መቅደስ፡ የሚያገለግል፡ ቀዳሽ፡ ሠላሽ፡ ቄስ፡ ዲያቆን።" "(ፈራ)፡ ፈረየ)፡ ብለኸ፡ ፍሬን፡ እይ።"
ሰሞነኛነት: ሰሞነኛ መኾን።
ሰሞን (ሰሙን): የስምንት ቀን ስም። "ዳግመኛም፡ ሰውን፡ በግእዝ፡ ያንድ፡ ዕለት፡ ቅጽል፡ ይኾናል፡ ትርጓሜውም፡ ስምንተኛ፡ ይባላል።"
ሰሰለ (ሰስሎ፡ ሰሰለ): ተወገደ፣ ራቀ ።
ሰስ: በቁሙ ሠሥ።
ሰረም: ቈለቈለ።
ሰረሰር: ያከርካሪ መትረብ ከማዥራት እስከ ወገብ በታች ያለ ደል።
ሰረሪን: የተክል ስም፣ "ሥሩ መቅመቆ ቅጠሉ ቀረሻሽንቦ የሚመስል ተክል።"
ሰረቀ (ሰሪቅ፡ ሰረቀ): ቀማ፣ ነጠቀ፣ እንደ ውሻ ነጥቆ በረረ። ("ከተለፈንና"፡ "ለከፈን" የሚሉት ቃላት ይዛመዳሉ)።
ሰረቀ: አከሳ።
ሰረቀ: ጠቀሰ።
ሰረበ: ማገሠረበ።
ሰረተተ/ሰርታታ: የተንሰረተተ፣ የሚንሰረተት፣ ጐታታ።
ሰረነቀ: ለበለበ፣ አቃጠለ (አፍንጫን)።
ሰረየ (ሰርይ፡ ሰረየ): እቀለለ፣ ተወ፣ ይቅር አለ ኀጢኣትን፣ በደልን።
ሰረገ (ሰሪግ፡ ሰረገ): አደራጀ፣ ደገሰ።
ሰረገ: ልጅን አስጌጠ፣ ኳላ ዳረ።
ሰረገላ: የመንኰራኵር ጋድም፣ ሀረገላ።
ሰረፈ: የካህናት ሸረፈ የሕዝብ ዐማርኛ ነው።"
ሰሩር: የዐይን ግርማ።
ሰሪ (ዎች): ሰራሒ)፡ የሰራ፣ የሚሰራ፣ ዐራሽ፣ ቈፋሪ።
ሰሪቴ: ሻጠ። "ሰሪቴ በራሱ ላይ አሰረ፣ አደረገ፣ ሲያውቅ አበደ።"
ሰራ (ሰርሐ፡ ደከመ): ዐረሰ፣ ቈፈረ፣ ገበረ፣ አዘመረ፣ ዐጨደ፣ ከመረ፣ ወቃ።
ሰራረቀ: አነሣሣ፣ ወሳሰደ።
ሰራሪ: የሰረረ፣ የሚሰር፣ ጠቂ፣ አውራ፣ አለሌ።
ሰራራ: ዐራረሰ፣ ቈፋፈረ።
ሰራቂ (ቆች): የሰረቀ፣ የሚሰርቅ፣ ሌባ፣ ሙጥልቅ፣ እጀኛ።
ሰራኖች: ዝንጕርጕሮች ፈረሶች (ዘካርያስ ፮፡ ፮)።
ሰራዊት: ዘጠኙ የስም ምትኮች፡ "እነዚሁም ርሱ፣ ርሷ፣ አንተ፣ አንቺ፣ እኔ፣ ርስዎ፣ ርሳቸው፣ እናንተ፣ እኛ ናቸው።"
ሰራዊት: የመላእክት ጭፍሮች፣ ያለቃ አለቃ ያላቸው (ኢሳይያስ ፩፡ ፳፬)።"
ሰራዊት: የጭፍራ ስም፣ የዠግና፣ የሐርበኛ፣ የጦረኛ ማኅበር፣ "በያለቃውና በያበጋዙ የሚታዘዝ ብዙ ወታደር።"
ሰራዪ: የሰረየ፣ የሚሰርይ ቄስ።
ሰራዪት: በባላገር ይነገራል፡ "ሰራዊትና ሰራዪት ውስጠ ብዙ ነው። አራዊትን ተመልከት።"
ሰራዪት: ጭፍራ፣ ሰርዌ።
ሰራዬ: ያገር ስም፡ "ሠራዬ ሶርያ፣ በእስያ ክፍል ያለ ታችኛውና ላይኛው የአሶር የአራም አገር።"
ሰራጊ (ዎች): የሰረገ፣ የሚሰርግ፣ ደጋሽ፣ ዳሪ።
ሰራፊ (ፎች): የሰረፈ፣ የሚሰርፍ፣ መንዛሪ (ማቴዎስ ፳፩ - ፲፪። ፳፭፡ ፳፯)።
ሰር: የሞፈር ቂጥ፣ ድግርና ቅትርት የተዋደዱበት።
ሰር: የተጠመደ በሬን ቁም ማለት።
ሰርሳሪ (ዎች): የሰረሰረ፣ የሚሰረስር ሌባ።
ሰርብ: ፈሳሽ ሿሿቴ።
ሰርተት ሰርተት አለ: ጐተት ጐተት አለ፣ ሥራ ፈታ።
ሰርተት: ጐተት፣ ሥራ አልባነት።
ሰርነ: ረዥም ሰው።
ሰርናቂ: የሰረነቀ፣ የሚሰረንቅ፣ ሰንፋጭ።
ሰርካማ: ያገር ስም።
ሰርክ ምሽት: ዘወትር ሠርክ።
ሰርዌ (ሰረወ፡ አሸነፈ): "ሠርዌን አስተውል።"
ሰርዲታ: አንዲት ሽሩባ።
ሰርገኛ (ኞች): ባለሰርግ፣ የወንድ ሙሽራ ተከታይ።
ሰርገኛ መባሉ: ነጩ የሙሽራውንና የሚዜዎቹን አቦልሴው የተከታዮቹን ልብስ ያሳያል።"
ሰርገኛ: ነጭና አቦልሴ ጢፍ ተፈጥሮው ቅይጥ ውጥንቅጥ የኾነ።
ሰርግ (ጎች): የጋብቻ ድግስ፡ "የሙሽራውና የሙሽራዪቱ አባትና እናት የሚደግሱት መብልና መጠጥ (ዮሐንስ ፪፡ ፩፡ ፪። ራእይ ፲፱፡ ፯ ' ፱)።"
ሰርግና ምላሽ: በጦም ምክንያት ተከታትሎ የሚደረግ ሰርግና ቤት ማያ።
ሰርግና ምላሽ: ባለቤት ሳይኖር እንደ ልብ መብላት መጠጣት፣ በሰው መሰናዶ መደሰት።
ሰርግና: በመራቤቱ ክፍል ያለ አገር።
ሰርጓይ (በዓለ፡ ሰርጕ): "በ፪፻ ዓመተ ምሕረት የነበረ የሐበሻ ንጉሥ ትርጓሜው ባለ ሽልማት ማለት ነው።"
ሰርፍ (ዘርፍ): ጌጠኛ የንጉሥ ምንጣፍ፣ ሰፊ፣ ባለዘርፍ፣ ቀጪን ያልጋ ልብስ። "በሬሳ አጐበር ላይ የሚደረግ የሐር መጐናጸፊያ ዐይነ ርግብ መሳይ (ምሳሌ ፯፡ ፲፯)።"
ሰቀላ፡ ስቅሎሽ: የማንጠልጠል ሥራ።
ሰቀላ፡ ቤት: አንደ ሰቀላ የተሠራ ቤት። "(ተረት)፡ የልጅ፡ ክፉ፡ ዲቃላ፡ የእኸል፡ ክፉ፡ ባቄላ፡ የልብስ፡ ክፉ፡ ነጠላ፡ የቤት፡ ክፉ፡ ሰቀላ።"
ሰቀላ፡ ዳስ: "ግድግዳውና፡ ጣራው፡ ቅጠል፡ የለበሰ፡ የተሸፈነ፣ ሰርግ፡ ማኅበር፡ ተዝካር፡ ማንኛውም፡ ድግስ፡ በውስጡ፡ የሚበላበት።"
ሰቀላ፡ ድንኳን: በሰቀላ አምሳል የተሰፋ ድንኳን።
ሰቀላ: የበላይ። "የሰቀላ፡ ዳኛ፡ እንዲሉ። (የሰቀላ፡ መሬት)፡ መትከያ፡ መንቀያ፡ መሾሚያ፡ መሻሪያ፡ ምድር።"
ሰቀል (ሎች): ዝኒ ከማሁ። "በገዳም፡ ውስጥ፡ ከሚኖረው፡ መነኵሴ፡ የሚበዛው፡ ዶማ፡ ሰቀል፡ ነው።"
ሰቀልት: በጋይንት ክፍል ያለ አገር። "ትርጓሜው፡ ሰቃዮች፡ ማለት፡ ነው።"
ሰቀልኛ: ሞላልኛ፣ ወገርኛ፣ የዳስ ዐይነት ሕንጻ ወይም ሌላ። "ከሰቀላ፡ ወደ፡ ጥላ፡ ከክብር፡ ወደ፡ ኀሳር።"
ሰቀሰ: ለቸ ሠቀቀ።
ሰቂለ ኅሊና: ዐሳብን ሰማያዊ ማድረግ።
ሰቂለ፡ አዕይንት: በጸሎት ጊዜ ሰማይን ትክ ብሎ ማየት።
ሰቂል: መስቀል።
ሰቃቀለ: መላልሶ ሰቀለ።
ሰቃይ (ዮች): የሰቀለ፣ የሚሰቅል፣ አንጠልጣይ። "በቀለ፡ ብለኸ፡ ብቅልን፡ እይ።"
ሰቈረ (ሰቊር፡ ሰቈረ): በሳ፣ ሸነቈረ።
ሰቈረ): በሳ፣ ነደለ፣ ቀደደ።
ሰቈቃወ፡ ኤርምያስ: "ስለ፡ ኢየሩሳሌም፡ መጥፋት፡ የኤርምያስ፡ ሙሾ። የመጽሐፍ፡ ስም።"
ሰቈቃወ፡ ድንግል: የግጥም ድርሰት፣ ዐምስት ቤት ያለው። "እመቤታችን፡ በስደቷ፡ ጊዜ፡ የተናገረችውን፡ ሙሾ፡ ያለቀሰችውን፡ ለቅሶ፡ አምልቶ፡ አስፍቶ፡ በግእዝ፡ ቋንቋ፡ የሚናገር። መሠረቱ፡ ነገረ፡ ማርያም፡ ነው።"
ሰቈቃው (ቈቀወ): ሙሾ፣ ቍዘማ።
ሰበሰበ: ለቀመ፣ አጠራቀመ፣ አከበ፣ አከማቸ፣ አንድ ላይ አደረገ፣ ከተተ (ዘፀአት ፴፭፡ ፩። ፪ኛ ዜና መዋዕል ፴፫፡ ፯)። "ወሰበን እይ የዚህ ሥር ነው።"
ሰበሰበ: ዐጠፈ፣ ቀነፈ፣ ሸጐጠ። "የሱሪን የቀሚስን ጝፍ ውሃና ጭቃ እድፍ እንዳይነካው።"
ሰበሰበ: ጌታ መለሰ፣ ዐጠፈ፣ ኰረተመ፣ አሳጠረ (አኅጸረ)፣ ሰቀጠጠ፣ ሸነቀረ፣ አሳረፈ እጅን፣ እግርን፣ ልብስን። "(ተረት)፡ ሰርቆ ከማሰብ እጅን መሰብሰብ (ማሳረፍ)።"
ሰበሰብ/ስብሳብ (ቦች): በቤት ዙሪያና በራፍ በኩል ብቻ ከጣራ በታች ያለ ስፍራ፣ እንግዳ ወይም ዕቃ ተሰብስቦ የሚቀመጥበት። "ባኹኑ ዘመን እነጋገር በረንዳ ይባላል፣ ይኸውም የህንድ ቋንቋ ነው ይላሉ።"
ሰበረ: ኰሰተረ፣ ኣለማ፣ መብተርኳሽ፣ የተረኰሰ፣ የሚተረስ፣ ኰስታሪ።
ሰበራ: ቈረጣ፣ ዐዳ። "ባቄላ ሰበራ እንዲሉ።"
ሰበር (ሮች): የበላይ ዳኛ፣ በታች የተፈረደውን ፍርድ የሚለውጥ፣ የሚገለብጥ። "ሰበር ዳኛ እንዲሉ።" "(ደኅና ሰበር)፣ መጥፎ ሰው።" "ቀነበረ ብለኸ ቀንበርን ተመልከት።""(ላበ)ሰበር: የስንዴና የገብስ የጤፍ አገዳ ገለባ ባኺዶ ጊዜ የከብት እግር የሰበረው።"
ሰበቀ (ሰቢቅ፡ ሰበቀ): ወዘወዘ፣ ነቀነቀ ጦርን። "ጐንደሮች ግን ጦር ሰበቀ ሲሉ አደራ ይላሉ።"
ሰበቀ: በጠበጠ፣ አማሰለ፣ አምታታ ደርጎን።
ሰበቀ: ብዙ ጊዜ ወሸ፣ በመዳፍ መታ የጤፍ ዶቄትንና ሊጥን።
ሰበቀ: ነከረ፣ ዐለለ።
ሰበቀ: ነገር ሠራ፣ አሳጣ፣ አጣላ። "ሰበከን ተመልከት።"
ሰበቀ: አዋሸከ። "ወሸከን እይ።"
ሰበቀ: ወደ ፊትና ወደ ኋላ እመላለሰ እሽክርክሪት።
ሰበቀ: ጣለ፣ አስተኛ፣ አጋደመ፣ አያያዘ።
ሰበበ (ሰቢብ፡ ሰበ): ምክንያት፣ ምክኛት ፈጠረ፣ አመካኘ።
ሰበበም: ሰበብ ያለው።
ሰበበኛ (ኞች): የሰበብ ባለሰበብ ሰው፣ ሰበብ ወዳድ። "ምክንያተኛ ለቍጣ፣ ለስካር፣ ለጥል፣ ለመውደቅ፣ ለመታመም ጥቂት የሚበቃው።"
ሰበብ: ሳቢያ፣ ምክንያት።
ሰበቦች: ምክንያቶች።
ሰበተ (ሰብዐ): ሰባት አደረገ።
ሰበተ (ትግ): ረገጠ፣ እሰረ፣ ስበት።
ሰበተ: አብስሎ ዐረሰ፣ ገለገለ።
ሰበከ (ሰቢክ፡ ሰበከ): ነገረ፣ አወራ፣ አሰማ፣ አስተማረ።
ሰበከ (ሰብሐ፡ ተሰብሐ): ወገግ አለ፣ ነጋ፣ በራ፣ ወጣ፣ ታየ። "ፀሓይ ሲሰብክ ትኼዳለኸ።"
ሰበከ (ትግ): በንጉሥ አለ፣ እማጠነ።
ሰበከ/ሰበቀ: አሳበቀ፣ ዋሸ። "ሰበከን ሰበቀ ማለት ከና ቀ ተወራራሽ ስለ ኾኑ ነው ውስጠ ምስጢሩም ስብኮን ያሳያል።"
ሰበከም: ባለሰበከት፣ ሻካራ።
ሰበከተ: ሰበከት ባለው ጅራፍ ገረፈ።
ሰበከተ: ጠጣ፣ ዥው አደረገ።
ሰበከት: ነገረች፣ አስተማረች (ግእዝ)።
ሰበከት: የቍርበት፣ የንጀራ፣ የቅጠል፣ ያውሬ ሻካራ ዠርባ (ኢዮብ ፵፩፡ ፯)። "ሰበከት ማለት ግልጥነትን ያሳያል።" "ወዝን እንቧይን እይ።"
ሰበካ: የታቦት ያቡን ግዛት፣ አጥቢያ ሀገረ ስብከት።
ሰበዘ: ሻጠ፣ ሸጐጠ፣ ጨመረ፣ አገባ።
ሰበዝ (ዞች): ስንደዶ፣ ግራምጣ፣ የስፌት ዙር፣ ማብዣ፣ ማሳደጊያ።
ሰበገናም: ከሲታ፣ ደረቅ ሰው፣ ሰበገኑ የሚታይ።
ሰበገን: የጐን ዐንጥት በግራና በቀኝ ያለ።
ሰበጠራ: ያገዳ ቅርጫት፣ ሠበጠረ።
ሰባ (ሰብሐ): ገለጠ፣ አስረዳ።
ሰባ (ሰብዐ): የቍጥር ስም ፸። "ሰባት ዐሥር ወይም ዐሥር ጊዜ ሰባት በስሳና በሰማኒያ መካከል ያለ ያ፲ ቤት አኃዝ።" "ተራ ቍጥር ሲኾን ሰባኛ ሰባኛው ይላል።" "ሰባትን አስተውል።"
ሰባ ሊቃናት: ለግብጽ ንጉሥ በጥሊሞስ ብሉያትን ከዕብራይስጥ ወደ ጽርእ የተረጐሙ ሰባ ሊቃውንት። "ከነሱም አንዱ ሽማግሌው ስምዖን ነበረ (ሉቃስ ፪፡ ፳፭-፴፭)።"
ሰባ አንድ (፸፩): ስባና አንድ፣ ሰባ አንደኛ የማዕርግ ወይም ተራ ቍጥር።
ሰባ፡ ጮማ ኾነ: ሠባ።
ሰባሰበ: ለቃቀመ፣ አግበሰበሰ።
ሰባሰገል (ሰብአ፡ ሰገል): የጥንቈላ፣ የውቀት፣ የፍልስፍና ሰዎች፣ ኮከብ ቈጣሮች።
ሰባሪ (ሮች): የሰበረ፣ የሚሰብር (ሚክያስ ፪፡ ፲፫)። "(የሰላበትን ወጭት ሰባሪ)፡ ጥጋበኛ ሰው፡ ዕገውጡ።"
ሰባሪ (ትግ፡ ሰበረ): ጓያ ወገብን፣ ቋንዣን የሚያሽመደምድ። "ጓያ ሰባሪ እንዲሉ።"
ሰባራ ሥንጥር: መናኛ የቤት ዕቃ።
ሰባራ ዘንግ: ሐሰተኛ ነገር፣ ሙግት።
ሰባራ: የተሰበረ ዕቃ ወይም ሌላ። "ዐንተ ሰባራ እንዲሉ።"
ሰባራነት: ሰባራ መኾን።
ሰባቂ: የሰበቀ፣ የሚሰብቅ፣ ነገረኛ፣ አሽሙርተኛ።
ሰባተኚት: ሰባተኛዪቱ ክፍልል።
ሰባተኛ ቀን: ቅዳሜ (ዘፍጥረት ፪፡ ፪-፫)።
ሰባተኛ: የማዕርግ ቍጥር። "ሲዘረዝር ሰባተኛው ይላል።"
ሰባቱ ቀለማት: ጥቍር፣ ቀይ፣ ብጫ፣ አረንጓዴ፣ ሰማያዊ፣ ነድ፣ ወርቅ ቀለሞች።
ሰባቱ ዕለታት: ከእሑድ እስከ ቅዳሜ ያሉ ቀኖች።
ሰባቱ ከዋክብት: ከፀሓይ ብርሃን የሚነሡ ኮከቦች።
ሰባቱ ፊደላት: ከግእዝ እስከ ሳብዕ ያሉ ፊደሎች። "ከዋክብት ዕለታት ፊደላት የግእዝ ኮከቦች፣ ቀኖች ፊደሎች ያማርኛ መኾናቸውን አስተው።"
ሰባት (ሰብዐት): የቍጥር ስም ፯። "በስድስትና በስምንት መካከል ያለ አኃዝ።"
ሰባት ቀንዶ፡ የበረሓ እንስሳ: ቀንድ።
ሰባት አደረገ (ሰብዐ): እስከ ሰባት ቈጠረ፣ በሰባት ከፈለ። "ሰባት ከስም አስቀድሞ እየተነገረ ቅጽል ሲኾን ሰባት በረት የከብት አንዠት።"
ሰባትያ: ሰባት መቶ ድር።
ሰባትያ: ከሰባት አንድ።
ሰባትዮ: ሰባትነት ያለው፣ ውስጠ ብዙ።
ሰባትዮሽ: ከሰባት አንድ የኾነ ገመድ፣ ፈትል፣ ሌላም ነገር።
ሰባቶ/ሰባቶች: "ች" ስለተጐረደ "ሰባቶ" እየተባለ ይነገራል።
ሰባኪ/ሰባቂ/አሳባቂ/ውሸተኛ/ነቢየ ሐሰት: (፩ኛ ነገሥት ፲፫፡ ፲፰)። ባላገር ግን "ሰባኺ" ይላል። (ኮች): የሰበከ፣ የሚሰብክ፣ እግር ላገር እየዞረ፣ በአደባባይ ቆሞ የሚነግር፣ የሚያስተምር፣ ሐዋርያ፣ መምህር፣ ነጋሪ፣ አስተማሪ (መክብብ ፩፡ ፲፪። ኤፌሶን ፬፡ ፲፩)።
ሰባዥ: የሰበዘ፣ የሚሰብዝ፣ ሸጓጭ፣ ጨማሪ።
ሰባጊ: የሰገየ፣ የሚሰግይ፣ ሰፊ፣ ወሽካካ።
ሰባጌ: የቀበሌ ስም በመራቤቴ ክፍል ያለ ገጠር። "የምድር ሰው ወይም የሰው ምድር ፸ ምድር ማለት ነው።"
ሰብ (ሰብእ): ሰው፣ ባለግዕዛን። "አገር ሰብ፣ እጅ ሰብ፣ ቤተ ሰብ እንዲሉ።"
ሰብለ ወንጌል: የአጤ ልብነ ድንግልና የጻድቁ ዮሐንስ ሚስቶች ስም። "ይተጌ ሰብለ ወንጌል እንዲል (ታሪከ ነገሥት)።" ትርጓሜውም "የወንጌል እሸት" ማለት ነው።
ሰብሌ (ሰብልየ): የኔ ሰብል፣ እሸቴ።
ሰብሌ: የወንድና የሴት መጠሪያ ስም።
ሰብል (ሰብለ): እህል፣ ዛላ - ዘለላ፣ እሸት፣ የማንኛውም (ሰብል።)
ሰብሳቢ (ቦች): የሰበሰበ፣ የሚሰበስብ፣ ለቃሚ፣ አጠራቃሚ። "ዘመድ ሰብሳቢ እንዲሉ።"
ሰብሳቢነት: ለቃሚነት፣ አካቢነት።
ሰብሳብ: ግቢ፣ ጋብቻ (ግእዝ)።
ሰብስቤ: የሰው ስም። "የዘመድ፣ የወገን ሰብሳቢ ማለት ነው።"
ሰብስብ: የሪያ ጥርስ ዕባጭ መተኰሻ። "(ብረ ሰብስብ): ሴቶች ከክታብ ጋራ የሚይዙት የሚያንጠለጥሉት ብር፣ ሌላውን ብር ሁሉ እከብ አከማች አጠራቅም ማለት ነው።"
ሰብስብ: የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ።
ሰብራዳ: ከጭቅና ጋራ ያለ ኹለት የበሬ ጐድን።
ሰብር: የሽቱ ስም፣ ውድ ከሬት የተዘጋጀ። "በግእዝ ዐልው ይባላል (ዮሐንስ ፲፱፡ ፴፬)።"
ሰብቀኛ (ኞች): ሰብቃም፣ ሰባቂ፣ ሰብቅ ወዳድ፣ ባለሰብቅ፣ አሾክሿኪ፣ ዦሮ ጠቢ።
ሰብቀኛነት: ሰብቀኛ መኾን።
ሰብቃላ: ዝኒ ከማሁ ለስብቅል።
ሰብቅ: ክፉ ነገር፣ ሹክታ፣ ሐሜት፣ ሰውን ከሰው የሚለይ። "ሸውክን እይ።"
ሰቦች: ሰዎች።
ሰተረ (ሰቲር፡ ሰተረ):
ሰተፈ (ሳትፎ፡ ሳተፈ):
ሰታሪ (ሮች): የሰተረ፣ የሚሰትር፣ ዘርጊ፣ አስጪ።
ሰት: ቀጤማ (ግእዝ)።
ሰቸ: "ረበን እይ።"
ሰች (ሰታዪ): የጠጣ፣ የሚጠጣ፣ ጠጪ። "ደመ ሰች እንዲሉ።"
ሰነመኪ: የታናሽ ዕንወት ስም። "ቅጠሉ፡ የሽቱ፡ ቅመም፡ ይኾናል፣ በጠጡትም፡ ጊዜ፡ ያስቀምጣል፡ (ዘጸአት ፲፡ ፳፬። ሕዝቅኤል ፳፯፡ ፲፱)።"
ሰነሰለ (ሰንሰለ): አጠጋጋ፣ አያያዘ፣ አቀጣጠለ፣ አቈራኘ፣ አጠላለፈ።
ሰነሰነ (ሰነነ): ሰለሰለ፣ ሸነሸነ፣ ተነተነ፣ ነጠለ፣ አበዛ።
ሰነቀረ (ደነቀረ): ሻጠ፣ ሰካ፣ ወጋ፣ ጋረጠ፣ አገባ። "ሸነቀረን፡ እይ።"
ሰነቀረ: አንድ ነገር ነገረ፣ አሰማ።
ሰነቃ (ሰንቀወ): ጠረበ፣ ዓነጠ፣ ላገ፣ አለዘበ (ሳንቃን)።
ሰነቃ: መታ፣ ከረከረ፣ ገረፈ (ማሲንቆን)።
ሰነተረ: በጣ፣ ሠነተረ።
ሰነኘ (ሰኒን፡ ሰነ): ገጠመ፣ ደረደረ፣ ቤት መታ።
ሰነከለ (ሰከለ): እግርን መታ፣ ጐዳ። "የበሬን፡ ስንድድ፡ ቈረጠ፡ የባሪያን፡ ሥር፡ በጠሰ።"
ሰነኰረ: ዘነኰረ።
ሰነዘረ (ሰዚር፡ ሰዘረ): በስንዝር ለካ፣ መጠነ።
ሰነዘረ: ሠነተረ፣ ሠነጠቀ፣ በጣ (የታረደ ከብትን)።
ሰነዘረ: በትርን ወደ ሰው ቃጣ። "ሳይንጠራራ፡ በቅርብ፡ ማለት፡ ነው፡ ነዘረን፡ ተመልከት።"
ሰነገ (ሰነጐ): በሳ፣ ነደለ፣ ሸነቈረ (አፍንጫን)፣ አገባ፣ ሻጠ፣ ቀረቀረ (ላባን፣ ሽቦን)።
ሰነገ: አስጨነቀ፣ አስጠበበ።
ሰነገ: ጠመጠመ፣ አጥብቆ አሰረ።
ሰነገለ (ዐረ፡ ሰሕገለ): ፈገፈገ፣ ወለወለ፣ ጠረገ፣ አጠራ፣ አብለጨለጨ፣ ሳለ፣ አሰላ (ጦርን፣ ሰይፍን) (ኤርምያስ ፵፮፡ ፬)።
ሰነገጩ: ነቀነቀ፣ ዘከዘከ፣ አደናቀፈ።
ሰነጋ (ትግ፡ ሰንገወ): "አኰላሸ፡ ኣወጣ፡ ጐነደለ፡ የፈረስ፡ የበቅሎ፡ የዶሮ፡ ቍላን፡ ወቀጠ፡ ቀጠቀጠ፡ አስሮ፡ ገደለ፡ የወይፈንን፡ ሠነጠቀ፡ ኣፈሰሰ፡ የበርበሬ፡ ፍሬን፡ የሰው፡ ሲኾን፡ ዐሸ፡ ሰለበ፡ ያሰኛል።"
ሰነጋ: ሰነገ።
ሰነጠ (ሰነጸ): አሳመረ፣ አስጌጠ፣ መልክ ሰጠ፣ ነቀሰ፣ ፋቀ፣ አለዘበ።
ሰነጠበ: ሠነጠረ፣ ሠነበጠ።
ሰነፈ: ሥራን ተወ ወይም ጠላ፣ ከተ፣ ደከመ፣ ሐሞቱ ዳውላ አከለ፣ ቦዘነ፣ ቍር ብሎ ዞላ ዋለ (ኤርምያስ ፲፡ ፬። ሕዝቅኤል ፵፭፡ ፳)። "(ተረት)፡ በሰጡኸ፡ አትስነፍ፡ ከሰጡኸ፡ አትለፍ።"
ሰነፈጠ: በጥንቃቄ በሳ፣ ነደለ፣ ውስጥ ለውስጥ ኼደ።
ሰነፍ (ፎች): የሰነፈ፣ የሚሰንፍ፣ ሥራ ያለ ሰው፣ ተቀምጦ የሚውል። "ሰነፍ፡ ባል፡ ያበዛል፡ እንዲሉ። ሰነፍ፡ ለባለአእምሮ፡ ይገዛል፡ (ምሳሌ ፲፩፡ ፳፱። ፳፮፡ ፯፡ ፲፱)።"
ሰነፍ መረቅ: ከጨው በቀር ቅቤና ቅመም ያልገባበት ቀላል መረቅ። "ዐልጫን" ተመልከት።
ሰነፍ፡ ምርት: ላይዳ ያልተባለ።
ሰነፍ፡ ሴት: ረኸጥ።
ሰነፍ፡ ቈሎ: ሲቈሉት በቶሎ የሚፈካ፣ ለጥርስ የሚገራ ገብስ።
ሰነፍ፡ ዕርቅ: እንዳይፈርስ ማሰሪያ ውል፣ ማገጃ ያልተበጀለት ዕርቅ፣ የጊዜ።
ሰናሰነ: ተናተነ፣ ነጣጠለ። "(ግጥም)፡ አቶ፡ ይነሡልኸ፡ በሰላ፡ መጥረቢያ፡ በዚያች፡ በጥልቆ፡ ቢሰናስኑት፡ አነስ፡ አነስ፡ ያለው፡ በወጣው፡ ስምንት። ያንተን፡ ቂጥ፡ የሚያኸል፡ በነበረኝ፡ ምድር፡ እጅጋየኹ፡ ትሙት፡ አለጠጅ፡ አላድር፡ (ቍንጪ)።" "ትግሬ፡ ግን፡ ሰንሰነ፡ ብሎ፡ ከሳ፡ ይላል፡ ከሰለሰለ፡ ጋራ፡ አንድ፡ ነው።"
ሰናዳ: ትግ፡ ሰንደወ፣ ወረወረ።
ሰናድር (ሮች): የነፍጥ ስም። "ባጤ፡ ዮሐንስ፡ ጊዜ፡ የነበረ፡ ጠመንዣ። በጀርመንኛ፡ ሽናይደር፡ ይባላል።"
ሰናድር፡ ያዥ: ሰናድር የሚይዝ፣ የሚሸከም ጭፍራ፣ ወታደር።
ሰናጊ: የሰነገ፣ የሚሰንግ፣ በሺ ቀርቃሪ።
ሰናጭ: የሰነጠ፣ የሚሰንጥ፣ አሳማሪ።
ሰናፊ: የሚሰንፍ፣ ታካች።
ሰናፊል (ሎች): የዱሮ ዘመን ሱሪ፣ ቦላሌ፣ ተነፋነፍ (ዘሌዋውያን ፯፡ ፲። ሕዝቅኤል ፵፬፡ ፲፰)።
ሰናፍጭ (ስናፔ): የቅመም ስም። "አፍንጫን፡ የሚለበልብ፡ ጕረሮን፡ የሚያቃጥል፡ ቅመም።" "(ተረት)፡ የፌጦ፡ መስሎሽ፡ ሰናፍጭ፡ ትቀምሽ።"
ሰንሰለት (ቶች): "የተቀጣጠለ፡ ብዙ፡ የብረት፡ ቀለበት፡ ሞላላ። ጫፍና፡ ፵ፉ፡ ፍንጅ፡ አለበት፡ ይኸውም፡ ያመፀኛ፡ ማሰሪያ፡ ማቈራኛ፡ ነው፡ (ማርቆስ ፭፡ ፬። የሐዋርያት ሥራ ፲፪፡ ፯)።"
ሰንሰል (ሎች): ብዙ ኹኖ ተያይዞ የሚበቅል ዕንጨት፣ ስምዛ።
ሰንቃሪ: የሰነቀረ፣ የሚሰንቅር፣ ሻጭ፣ ጋራጭ።
ሰንተል፡ ነጋሪት: ከማዕድን የተሠራ ሳንቲም፣ የብር ፪ኛ ሳንቲም።
ሰንተል: ሰፋ፣ ተክል።
ሰንተል: የብረት ሥራ።
ሰንከልካላ: ስንክልክል፣ የተሰነካከለ፣ ወጣ ገባ፣ ደንጐላጕል፣ ሥርጓጕጥ።
ሰንካላ: ስንክል፣ የተሰነከለ፣ እግሩ የተመታ። "እንደ፡ ልቡ፡ መኼድ፡ መራመድ፡ የማይችል።"
ሰንካይ: የሰነከለ፣ የሚሰንከል፣ መቺ።
ሰንኬት: ታናሽ የእጅ ጣት፣ ዐምስተኛዪቱ።
ሰንኬቶ: የታናሽ ጣት ቀለበት። "በግእዝ፡ ገመስ፡ ትባላለች። ዲዋኒን፡ እይ።"
ሰንኰፋም: ባለሰንኰፍ፣ ቍስል።
ሰንኰፍ: የዕባጭ፣ የብጕንጅ ጥርስ።
ሰንኳራ: ሰንኰርቱ፣ ነገረ ብላሽ፣ ዘንኳራ።
ሰንዛሪ: የሰነዘረ፣ የሚሰነዝር፣ ለኪ፣ ሠንታሪ።
ሰንደል፡ ሣጥን: ከሰንደል የተሠራ ሣጥን፣ ባለመዐዛ።
ሰንደል: ታቹ መርገጫው የሰንደል ሉሕ የኾነ መጫሚያ።
ሰንደል: የህንድ አገር ዛፍ ስም። "ክልካዩ፡ (ፍርፋሪው)፡ በውድ፡ የሚሸጥ፡ የጪስ፡ ዕንጨት።"
ሰንደል: የሽቱ ስም፣ ቅጥነቱ እንደ ሰንበሌጥ ያለ። "ሰንደልን፡ የተቀባ፡ ዕፅ፡ ሲያጨሱት፡ የሚሸት። ዑድን፡ አስተውል።"
ሰንደሮስ: ነጭ ዕጣን (ግእዝ)።
ሰንደቀ (ሰደቀ): አሰረ (ነዶን)። "ጠየተን፡ እይ።"
ሰንደቀ: አጓዘ፣ አቋፈ።
ሰንደቀ: ከበበ፣ ክብ አደረገ፣ ኳስ፣ ሎሚ አስመሰለ (ከላይ)።
ሰንደቅ (ቆች): "ከቀንድ፣ ከዝኆን ጥርስ፣ ከብር፣ ከዞጲ፣ ከልምጭ፣ ከቀረጥ የተቀረጸ፣ በላይ ክብ እንክብል፣ በታች ጕረሮ ያለው መቋሚያ (፪ኛ ዜና ፲፯፡ ፲፫)።"
ሰንደቅ፡ ዐላማ (መዝሙር ፳፡ ፭): "በሰንደቅ ላይ የተሰቀለ፣ የተንጠለጠለ፣ ባለአረንጓዴና ብጫ ቀይ ቀለም የመንግሥት ምልክት፣ ባንዲራ። በመካከሉ ጽሑፍና ያንበሳ ሥዕል ከዘውድ ጋራ ይታይበታል። አንበሳውም ሰንደቅ ዐላማ ይዟል።" "ሰንደቅ ዘንጉ፡ መቋሚያው ከነእንክብሉ፡ ዐላማ ሐሩ። ርግጠኛው አጻጻፍ ግን (ዐላማ ሰንደቅ) የሰንደቅ ዐላማ ነው።"
ሰንደቅ፡ ጓዝ።
ሰንደቅ: የጭራ፣ የመነሳንስ ዕንወት።
ሰንደደ: ሰካ፣ ደረደረ (ሰመግን፣ ጨሌን)፣ የስንደዶ ጌጥ አበጀ።
ሰንደደ: ሥራን አቀና፣ አቅንቶ ሠራ።
ሰንዳቂ: የሰነደቀ፣ የሚሰንድቅ፣ አጓዥ።
ሰንዳቢ: የሰነደበ፣ የሚሰነድብ፣ መቺ።
ሰንዳዳ: ቀጥ ያለ አፍንጫ።
ሰንዳጅ: የሰነደደ፣ የሚሰነድድ፣ ሰኪ፣ ደርዳሪ።
ሰንዳፋ: "ባዲስ አበባ ምሥራቅ በቅርብ ያለ ቀበሌ፣ ስሙን ከሣሩ ወስዳ።"
ሰንዳፋ: በግእዝ መጽሐፍም ይገኛል (ታምራት፡ ማርያም)።
ሰንዳፋ: የሣር ስም። "እንደ ሰርዶ አንጓ ያለው የሜዳ ሣር፣ ወፍራም፣ በረግረግ ወይም በውሃ ውስጥና ዳር ይበቅላል።"
ሰንጊ: የሰነጋ፣ የሚስነጋ፣ አኰላሺ፣ ጐንዳይ፣ ወቃጭ፣ ቀጥቃጭ።
ሰንጋ (ጎች): የተስነጋ፣ የተኰላሸ፣ የተጐነደለ፣ የተቀጠቀጠ፣ ኵልሽ፣ ጕንድል፣ ቅጥቅጥ።
ሰንጋ፡ ምት: "ና ቼ ቼ ቼ የሚል የሰንጋ ፈረስ ዘፈን አዝማች።"
ሰንጋ፡ ሰንጋ: የሰንጋ ሰንጋ ጮሌ ፈረስ። "ደጊሙ ቃልም ይኾናል።"
ሰንጋ፡ ቦካ: በቡልጋ አፋፍ ያለ ቀበሌ።
ሰንጋ፡ ቦካ: ወፈረ፣ ሠባ፣ ደለበ፣ መኼድ አቃተው።
ሰንጋ፡ ፈረስ: ታፍኖ በቤት የሚውል ኦሮቢ ፈረስ፣ ድንጕላ ያይዶለ።
ሰንጋ: አዝማሪ። "ሰንጋ ሰንጋ እያለ ሐርበኛን የሚያመሰግንበት የማሲንቆ ምት።"
ሰንጋ: የተቀለበ በሬ፣ ድልብ፣ ገች፣ ፍሪዳ።
ሰንጋ: የኦሮ ባላባት ግዛት፣ ዳማ ከለለኝ። "አባ ሰንጋ እንዲሉ። አባን፣ ዳማን ተመልከት።"
ሰንጋይ (ዮች): የስነገለ፣ የሚሰነግል፣ ሳይ (ሕዝቅኤል ፳፩፡ ፲፩)።
ሰንጌ: የቍልምጫ ቃል። "የኔ ሰንጋ እንደ ማለት።"
ሰንጎ፡ መገን: ሰንጎ ፈረስ፣ መገን ጋሻ ነው። "ሰንጎ መገን ተው ሰንጎ መገን ከፈረሰኞች የምናውቃቸው በሻኸ አቦዬ ኀይሌ አንዳርጋቸው እንዳለ አዝማሪ።"
ሰንጎ: ሰንግዮ፣ ቃለ አጋኖ። "ሰንጋ ሆይ ማለት ነው።"
ሰንጎ: አስጨንቆ፣ አስጠብቦ።
ሰንጠረ: ሠነበጠ፣ ሠነጠረ።
ሰንጠረዥ (ዦች): የመጫወቻ ስም። "ስድስት ዐይነት ምስል ያለው መጫወቻ። ምስሉም ንጉሥ፣ ንግሥት፣ ፊታውራሪ፣ ፈረስ፣ ግንብ፣ አሽከር ይባላል።" "ነጭና ጥቍር መደብ አለው። ጨዋታው የጦርነት ምሳሌ ነው። ያወጡትም ፋርሶች ናቸው ይላሉ።"
ሰንጠረዥ: የቍጥር መደብ። "አግድምና ቍልቍል የተሠመረ መሥመር፣ በውስጡ አኃዝ ያለበት ክብ ሲኾን ዐውድ ይባላል።"
ሰንጠፈ: ከፈለ ሠነጠፈ።
ሰንጢ (ዎች): "የታናሽ ቢላዋና የምላጭ ዐይነት ታጣፊ መሣሪያ፣ ባለኹለት አፍ። ትልቁ ሥጋ መብሊያ፣ ራስ መላ። ትንሹ ጥፍር መቍረጫ፣ ብር፣ ርሳስ መቅረጫ መሰኛ።"
ሰንጣ: "አሳምሮ እንደ ልብ (፩ኛ ሳሙኤል ፲፬፡ ፴)።"
ሰንጣ: ወለል ያለ ሜዳ፣ የሚያምር።
ሰንፋጣ: ዝኒ ከማሁ።
ሰንፋጭ: የሰነፈጠ፣ የሚሰንፍጥ (ሰናፍጭ፣ በርበሬ፣ ዝንጅብል የመሰለው ኹሉ።)
ሰአልናከ: የተረፈ መሥዋዕት፣ የኦኰቴት ምክትል ጠዲቅ ዳቦ። "ትርጓሜው ለንኸ ማለት ነው።" "ሰአልናከ መባልን ከጸሎቱ ወስዷል፣ ባላገር ግን ሳሊነክ ይለዋል።"
ሰዓ፡ ሰዓት (ሰዐወ): የጊዜ ስም። "ሰዓት ሲበዛ ቀን፣ ቀን ሲበዛ ወር፣ ወር ሲበዛ ዓመት፣ ዘመን ይኾናል። ደግ ሰዓት፣ ክፉ ሰዓት እንዲሉ።"
ሰዓተ፡ ሌሊት: ከማታ እስከ ጧት ያለ ጊዜ፣ ፲፪ ሰዓት። "ካህናት በቤተ ክርስቲያን እያደሩ በሰባቱ ጊዜያት የሚጸልዩት የፍታት ጸሎት ሰዓተ ሌሊት ያሠኘው የሚዠመረው በመንፈቀ ሌሊት ስለ ኾነ ነው። መላን አስተውል።"
ሰዓተ፡ መዓልት: ከጧት እስከ ማታ ያለ ጊዜ፣ ፲፪ ሰዓት። "ተሲያትን፣ ሳትንና፣ ሳታትን ተመልከት።"
ሰዓቱን ሞላ): ዘወረ፣ ጠመዘዘ፣ እንዲንቀሳቀስ፣ እንዲዞር አስተካከለ (ገቢር)።
ሰዓት፡ አደረሰ: በ፯ቱ ጊዜያት ጸለየ፣ አቍጣሮ ያዘ፣ አደረገ።
ሰዓት: የሰዓት መሣሪያ፣ ክብ መኪና፣ ባለ፳፬ ክፍል። "በላዩ ያለው መርፌ የላይኛው በቀን ፳፬፣ የታችኛው ፪ ጊዜ ይዞራል። የደቂቃው ቍጥር አንድ ሺ አራት መቶ አርባ፣ የካልኢቱ (ሰጏንዱ) ሰማኒያ ስድስት ሺ ካራት መቶ ነው።"
ሰዓት: ጊዜ። "ሰዓትን ተመልከት።"
ሰዓቶች (ሰዓታት): ጊዜዎች፣ ዘመኖች፣ የሰዓት መሣሪያዎች።
ሰከለ (ሰኪል፡ ሰከለ): አፈራ፣ ፍሬ ሰጠ (ግእዝ)። "ሰነከለን፡ እይ።"
ሰከለ: ዐንገትንና የኋላ እግርን ወይም የፊት እግርንና የኋላ እግርን አሰረ፣ ቈረኘ። "ምስጢሩም የተክል ፍሬ ዐጽቅን መዝኖ ከግንድ ቅርንጫፍን ከዐጽቅ እንዲያገናኝ ማለት ነው።"
ሰከላ: በጐዣም አውራጃ ያለ አገር፣ ኣባይ የሚፈልቅበት።
ሰከመ): አሸከመ። "ከምድር አንሥቶ በሰው ራስና ትከሻ ላይ አደረገ፣ ነ፣ አሳዘለ፣ አሲያዘ፣ አስነገተ (፩ኛ ነገሥት፡ ፲ ' ፪። ሉቃስ ፲፩፡ ፵፯)።" "ሰውነቱን ይሰርቀዋል።"
ሰከመ: ተሸከመ (ግእዝ)። "ወስከምት ማለት ከዚህ የወጣ ነው።"
ሰከም፡ ሰከም፡ አለ: ሲኼድ እንደ ተሸካሚ ፈጠን ፈጠን አለ።
ሰከሰከ (ሰገሰገ): ሰረረ።
ሰከረ (ሰኪር፡ ሰክረ): ጠነበዘ፣ አበደ፣ ራሱ ዞረ፣ ቃዠ፣ ጮኸ፣ ለፈለፈ፣ ዘለለ፣ ተንገደገደ፣ ወደቀ፣ አንዱ ኹለት ኾነበት (ከመጠጥ ብዛት የተነሣ)።
ሰከቴ: የተደቀነ፣ ሠከተ።
ሰከነ (ሰኪን፡ ሰከነ): ወደ ታች ወረደ፣ ዘቀጠ፣ ረጋ (የቡናው አተላ)።
ሰከነ: ተዋረደ፣ ዐጣ፣ ነጣ፣ ደኸየ።
ሰከከ: ቀና፣ ሰገገ።
ሰኵዐ (ሰኳ): "(መሰኳ)ን፡ አስተውል፡ የዚህ፡ ዘር፡ ነው።"
ሰኪ (ሰካዒ): የሰካ፣ የሚሰካ፣ ሻጭ።
ሰካ (ሰክዐ): ሻጠ፣ ሳገ፣ አገባ፣ ወጋ፣ በተራ አቆመ፣ ደረደረ (ጦርን፣ ዕንጨትን፣ ዶቃን፣ ዐልቦን፣ ወሌን፣ ሰመግን) በክር፣ በሢር፣ በሽቦ ላይ። "(ዐይኑን ሰካ)፡ ተኰረ፡ ትክ ብሎ አየ።"
ሰካላ: ገመድ፣ ጠፍር።
ሰካሪ: ሰካር፣ የሰከረ፣ የሚሰክር፣ የጠነ በህ (ምሳሌ ፳፮፡ ፱። ፩ኛ ቆሮንቶስ ፩፡ ፲፩)።
ሰካሪዎች: ሰካሮች፣ የሰከሩ፣ የሚሰክሩ፣ ጠንባዞች (ኢሳያስ ፳ፈ፡ ፩ ' ፫)።
ሰካራም: ሰካር ያለበት፣ የሚያድርበት መሸታ ቤት።
ሰካይ (ዮች): የስከለ፣ የሚሰክል፣ አሳሪ።
ሰክ፡ አለ: ተደቀነ፣ ሠከተ።
ሰኰና (ግእዝ): የሰው ጫማ ውስጥ እግር፣ ኰቴ፣ የከብት ጥፍር፣ መርገጫ፣ መኼጃ። "ገለገለ፡ ብለኸ፡ ግልገልን፡ እይ።"
ሰወለለ: ተንሰዋለለ፣ ተንቀዋለለ፣ ተንከዋረረ፣ ተንሰለጀጀ።
ሰወለል: ሰውላላ፣ ቀወለል፣ ቀውላላ - ሰልጃጃ።
ሰወረ: አረቀቀ።
ሰዋ: ዐረደ፣ ሠዋ።
ሰዋም: ሰው ያለበት፣ የበዛበት፣ ባለሰው ስፍራ።
ሰዋስው (ሶሰወ): የመሰላል ስም (ግእዝ)።
ሰዋስው፡ ጨዋታ: የግእዝ ንግግር። "(ቀን)፡ ብለኸ፡ ቅኔን፡ አስተውል።"
ሰዋስው: ነጠላ ግስ ከነርባው፣ ሀርና ነባር ወይም ስምና ግብር።
ሰዋስው: የነገር፣ የቃል፣ የቋንቋ እገባብ፣ ሥርዐት፣ ደንብ። "የግእዝን፡ ምስጢር፡ ካለማወቅ፡ ወደ፡ ማወቅ፡ መወጣጫ፡ ማለት፡ ነው።"
ሰዋስውኛ: የሰዋስው ጭውውት፣ ዘይቤ፣ ነገረ ደብተራ። "በተነ፡ ብለኸ፡ ብትንን፡ እይ፡ ጥሬን፡ ተመልከት።"
ሰዋረ (ሰውሮ፣ ሰወረ): ሸፈነ፣ ጋረደ፣ ከለለ፣ ዐወረ (ዐይንን)፣ ነሣ (አሳበደ ልብን)። "ወባ፡ ሸሸጉ፡ ደበቀ፡ ገለበጠ፡ የሚታየውን፡ እንዳይታይ፡ በስተውስጥ፡ አደረገ።" "ሱረትን፡ እይ፡ የዚህ፡ ዘር፡ ነው።"
ሰዋሪ: የሰወረ፣ የሚሰውር፣ ሸፋኝ፣ ደባቂ።
ሰዋራ: ደባቃ ስፍራ።
ሰዋወረ: ደባበተ።
ሰዋውሮ: ደባብቆ።
ሰው (ሶሰወ): ኣዳም፣ ያዳም ልጅ፣ የፈጣሪ ምሳሌ (ነባቢ፡ ለባዊ፡ ሕያው)። "በሥጋው ከእንስሳት፣ በነፍሱ ከመላእክት አንድነት ያለው ፍጥረት፣ ባለግዕዛን።" "ምናልባት፡ ሰው፡ ለመኾን፡ ቢያበቃኝ፡ ውለታኸን፡ እከፍላለኹ።"
"ሰው፡ ማለት፡ በሔዋን፡ ኣንጻር፡ ለሴትም፡ ይነገራል።" "አንቺ፡ ሰው፡ እንዲል፡ ባላገር።"
"(ተረት)፡ ለሰው፡ ሞት፡ ኣነሰው።" "(ደግ፡ ሰው) ከንጀራው ቈርሶ ከወጡ አጥቅሶ የሚያጐርሥ።"
"(የሰው፡ አገር፡ ሰው) የሩቅ የውጭ አገር።"
ሰው፡ መሳይ: ሰውን የሚመስል (ዝንጀሮ፣ ጦጣ፣ ጕሬዛ፣ ዓሣ (ስሬን))።
ሰው፡ መሳይ: በሸንጎ ወስላታ፣ ምናምንቴ፣ ነውረኛ።
ሰው፡ ሠራሽ: ግብር እምግብር፣ ሰው የሠራው ሥራ፣ የግዜር ያይደለ።
ሰው፡ ሰውኛውን፡ ኖረ: እንደ ሰው ከሰው ጋራ፣ ፍጹም ሰው ኹኖ እየበላ እየጠጣ ማለት ነው።
ሰው፡ በሌ: ሰውን የሚበላ ጭራቅ አውሬ።
ሰው፡ በሩቁ: የውሻ ስም።
ሰው፡ ብሎ፡ ዝም፡ ነው: "እሰው ጠባይ የማይደርስ እንዲህ ይባልለታል።"
ሰው፡ አይዶለም፡ ክፉ፡ ነው። "ሰው እተፈጠረበት አልተፈጠረም ጨረሻ።" "ዕቡይ፡ እከየኛ፡ ተንኰለኛ፡ የክፉ፡ መሰው፡ ባገሩ፡ ሰው፡ ነው፡ ክብር፡ አለው፡ አይናቅም፡ አይዋረድም።"
ሰው ኹሉ እንደ ፍጥርጥሩ ይኖራል።
ሰው፡ ኾነ (ተሰብአ): ነፍስና ሥጋ ያለው ኾነ፣ ተዋሐደ፣ የሰውን ባሕርይ ነሣ።
ሰው፡ ጤፉ: ሰውን የሚንቅ፣ የሚያኰስስ፣ ከመ ጤፍ የሚቈጥር።
ሰው (ሶሰወ) ፡ ኣዳም (ያዳም ልጅ) ፡ የፈጣሪ ምሳሌ (ነባቢ፡ ለባዊ፡
ሕያው) ፡ በሥጋው ከእንስሳት በነፍሱ ከመላእክት አንድነት ያለው ፍጥረት (ባለግዕዛን)” ። ምናልባት ሰው ለመኾን ቢያበቃኝ ውለታኽን እከፍላለኹ” ። ሰው ማለት በሔዋን ኣንጻር ለሴትም ይነገራል” ። አንቺ ሰው!" እንዲል ባላገር ። (ተረት) ፡ "ለሰው ሞት ኣነሰው " ።
ሰው: ሌላ፣ ባዕድ። "ይህ፡ ገንዘብ፡ የሰው፡ ነው፡ የኔ፡ አይዶለም።" "ዳረንና፡ ቃጣን፡ እይ።" (የሰው፡ ሰው): የሌላ ሌላ፣ የባዕድ ባዕድ።
ሰው: ጌታ፣ ጨዋ፣ ባላባት፣ ክቡር፣ ባለማዕርግ (መዝሙር ፵፱፡ ፳)። "ጊዜ ነው እንጂ ቁም ነገራም የሰው ልጅነት አያኰራም - (አዝማሪ)።"
ሰውማ: ሰው መሳይ።
ሰውር (ተውር፣ ሶር): በሬ።
ሰውር፡ መሬት: ጠንቋይ። "ላንዳንድ አስጠንቋይ ኮከብኸ ሰውር መሬት ነው ይላል።"
ሰውር: የኮከብ ስም፣ በሬ የሚመስል የማዚያ ኮከብ።
ሰውነተ፡ ቢስ: የነገሩትን የሚረሳ ዝንጉ።
ሰውነት: ሰው መኾን፣ የነፍስ ባሕርይ፣ አካል፣ ገላ (ሉቃስ ፲፪፡ ፲፱)። "ዛሬ በመንገድ ውዬ ሰውነቴ ልትት ብሏል።" "በዘመናችን ግን የውሻው የፈረሱ የመኪናው ሰውነት እየተባለ በስሕተት ይጻፋል።"
ሰውን ሰበሰበ: ኣከበ፣ አበጀ፣ አዘጋጀ፣ ሸንጎን።
ሰውኛ: የሰው ጠባይ፣ ባሕርይ።
ሰውየው: በሰውዬ አንጻር፣ የርሱ ሰው ማለት ነው።
ሰውዬ: የኔ ሰው።
ሰውዮ (ኦ፡ ብእሲ): ሰው ሆይ፣ ዮ፡ በጥሪ ጊዜ ማግነንንና ማክበርን ያሳያል።
ሰዉ፡ ዋቢ: ኀላፊ። "ሰጪኸን፡ አምጣ፡ እንዲሉ።"
ሰየመ (ሰመየ): ስም ለሌለው ስም አወጣ፣ ሰልጅ የተወለደና ክርስትና የተነሣ ለት። "ሠየመን፡ እይ።"
ሰየጐመዠ።
ሰየፈ (ሰይፎ፡ ሰየፈ): በሰይፍ መታ፣ ቀላ፣ ቀነጠሰ፣ ቈረጠ፣ ጐመደ፣ ጐረደ፣ ከለለ፣ ገደለ።
ሰያሚ: የሰየመ፣ የሚሰይም፣ የሰየመች፣ የምትሰይም፣ ስም አውጪ (አባትና እናት፣ ቄስ፣ ሴት ዐማት)።
ሰያሚነት: ሰያሚ መኾን።
ሰያፊ: የሰየፈ፣ የሚሰይፍ፣ ቈራጭ፣ ባለወግ።
ሰያፍ: ዝኒ ከማሁ።
ሰይጣናም (ሞች): ሰይጣን ያለበት፣ ያደረበት፣ ባለሰይጣን (ክፉ ሰው፣ እባብ)።
ሰይጣን: ሴጣን፣ ዲያብሎስ፣ ክፉ መንፈስ፣ ጋኔን፣ የግዜርና የአዳም መጀመሪያና መፍረሻ ጠላት፣ ባለጋራ። "ሲበዛ፡ ሰይጣኖች፡ ሴጣኖች፡ ይላል።" "ጋንጩርን፡ አስተውል።"
ሰይጣን: እንደ ጪስ ተኖ፣ እንደ ጉም በኖ ጠፋ።
ሰይጣንነት: ሰይጣን መኾን፣ ክፉነት።
ሰይፈ፡ ሥላሴ: የመጽሐፍ ስም። "ምስጢር ያላገመረ ካህን በግእዝ ቋንቋ የደረሰው ነው።" "ይኸንንም የመሰለ ከወንጌል የማይሰማማ ፈጠራ ድርሰት አርድእት ነው።" "(ተረት)፡ የልጅ፡ ጥፉ፡ በስም፡ ይደግፉ።"
ሰይፈ፡ ነበልባል: ከነበልባል የተዘጋጀ የመልአክ ሰይፍ።
ሰይፈ፡ አርዓድ (አርዓዴ፡ ሰይፍ): በ፲፱፻ ዓ.ም የነበረ የኢትዮጵያ ንጉሥ፣ በሰይፍ አንቀጥቃጭ ማለት ነው።
ሰይፈ፡ ዣግሬ (ዣግሬ፡ ሰይፍ): የንጉሥ፣ የመስፍን፣ የመኰንን ሰይፍ ያዥ፣ ተሸካሚ (፩ኛ ሳሙኤል ፴፩፡ ፬)። "ዳግመኛም፡ ዣግሬ፡ (ዘእግር፡ ዘአጋር)፡ ማለት፡ ነው።" "ሦስተኛም፡ አግሬን፡ ያሳያል።"
"አራተኛም፡ ሰይፍንና፡ ዘገርንም፡ ያስተረጕማል።" "ጋሻንና፡ ዣግሬን፡ እይ።"
ሰይፈ፡ ዣግሬዎች: ብዙዎች ሰይፍ ተሸካሞች፣ የሰይፈ ዣግሬ ጭፍሮች።
ሰይፈኛ (ኞች): ሰይፍ ታጣቂ፣ ሰይፍ መዛዥ።
ሰይፉ: ሴፉ፣ የሰው ስም።
ሰይፋም: ባለሰይፍ ማለት ነው።
ሰይፋይ: በዘመነ ብለይ የነበረ የኢትዮጵያ ንጉሥ።
ሰይፍ (ሴፍ): የጦር መሣሪያ ስም። "ይኸውም በ፪ ወገን ስለት ያለው፣ በወገብ የሚታሰር፣ በትከሻ የሚንጠለጠል ነው።" "ጐራዴንና፡ ሾተልን፡ ሐኔን፡ ዱቢትን፡ አስተውል።"
ሰይፍ፡ ፬፡ ጣት: በሽቻ መቀስ የሚረስ።
ሰደስ: ስድስት አደረገ (ግእዝ)።
ሰደረ (ትግ፡ ሰነዘረ): ወለደ፣ ደረደረ፣ ረደፈ፣ መደደ፣ ኰሰኰለ፣ በተራ አስቀመጠ፣ አቆመ።
ሰደቀ: አብዝቶ ቀባ፣ ደለሰ፣ እፊማለቀ (ዐማርኛ)። "ሰነደቀን፡ እይ፡ የዚህ፡ ጣልቃ፡ ነው።"
ሰደቀ: ገበታ ዘረጋ (ግእዝ)።
ሰደቃ: እግሪ ረዥም ስፌት፣ የንጀራ ማቅረቢያና መብሊያ። "ባረብኛ ግን ጸደቃ፣ ለድኮች የሚያበሉት ጠዲቅ ስለ ጽድቅ የሚሰጡት ገንዘብ ወይም ሌላ ምጽዋት ተብሎ ይተረጐማል።"
ሰደቃ: ከሳንቃ የተበጀ ገበታ (ዘፀአት ፳፭፡ ፳፫። ዮሐንስ ፪፡ ፲₅)።
ሰደበ (ትግ፡ ሰደበ፣ ወሰነ፡ ደነገገ): ወረፈ፣ ነቀፈ፣ ዘለፈ፣ አዋረደ፣ አሳነሰ፣ አቃለለ፣ አኰሰሰ፣ አረከሰ፣ ክፉ ስም ሰጠ። "(ተረት)፡ አባቱን፡ የጠላ፡ የሰው፡ አባት፡ ይሰድባል።"
ሰደደ (ሰዲድ፡ ሰደደ): ላከ፣ ፈታ፣ ተወ፣ ለቀቀ፣ አወጣ፣ አበረረ (ዘፍጥረት ፰፡ ፮፡ ፰። ኤርምያስ ፩፡ ፯። ፳፰፡ ፱። ፩ኛ ቆሮንቶስ ፯፡ ፲፪፡ ፲፫)። "ያባትን፣ ሞቱን፡ አይወዱ፣ ረጃቱን፡ አይሰዱ፡ (ኦ ይለቁ)።"
ሰደደ: አረዘመ። "ሥርን፡ እይ።"
ሰደደ: አንከባለለ። "የአይሁድ፡ ሴቶች፡ በጥጦስ፡ ጊዜ፡ ልጆቻቸውን፡ ገደል፡ ሰደዷቸው።"
ሰደደ: ጨመረ፣ አገባ፣ ዶለ። "(-4-2-4-): በሰው፡ ቍስል፡ ዕንጨት፡ ስደድበት።"
"የጊዜና፡ ኀላፊ፡ ትንቢቱም፡ ይሰድ፡ ይሰዳል፡ ቢል፡ እንጂ፡ ይሰድድ፡ ይሰድዳል፡ አይልም፡ ቢልም፡ ስሕተት፡ ነው።"
ሰደድ (ባሪያ፡ ሰደድ): የገብስ ስም። "ሲፈጩት የሚጠና፣ የሚጠነክር ገብስ።"
ሰደድ: ቋያ፣ የዱር፣ የበረሓ ሣር። "የሰደድ፡ እሳት፡ እንዲሉ።" "ዳግመኛም፡ ዕንጨት፡ ለንጨት፡ ተፋጭቶ፡ የሰደደው፡ እሳት፡ ማለትን፡ ያሳያል።"
ሰደፍ: የባሕር እንስሳ፣ ዕንቍን፣ ሎልን የምትወልድ (ግእዝ)። "ሲበዛ፡ ሰደፎች፡ ይላል።" "ብርጋናን፡ ተመልከት።"
ሰደፍ: የጠመንዣ ላት። "ሰደፍ፡ ዕንቀን፡ በሆዷ፡ እንደምታቅፍ፡ ይህም፡ ጠመንዣን፡ በስተታች፡ በኩል፡ በውስጡ፡ መያዙን፡ ያሳያል።"
ሰዱቃዊ: የሳዶቅ ወገን፣ ተመጻዳቂ፣ አፈ ጻድቅ።
ሰዱቃውያን: ተመጻዳቆች።
ሰዳ: ባዶ፣ ሰደደ።
ሰዳ: ዐጥር፣ ቅጥር የሌለበት ባዶ ስፍራ።
ሰዳሪ: የሰደረ፣ የሚሰድር፣ ደርዳሪ፣ ኰልኳይ።
ሰዳሽ: የሰደሰ፣ የሚሰድስ።
ሰዳቢ: የሰደበ፣ የሚሰድብ፣ አዋራጅ።
ሰዳቢዎች: ሰዳቦች፣ የሰደቡ፣ የሚሰድቡ (፩ኛ ጢሞቴዎስ ፫፡ ፲፩)።
ሰዳዳ: ራሰ በራ፣ ጠጕሩ ከፊቱ ወደ ኋላው የተሰደደ።
ሰዳጅ (ጆች): የሰደደ፣ የሚሰድ፣ ላኪ፣ ፈቺ፣ ለቃቂ፣ አንከባላይ።
ሰዴቻ (ኦሮ): መንቀጥቀጥ፣ መንዘፍዘፍ።
ሰዴቻ፡ መታው: አንቀጠቀጠው፣ አንዘፈዘፈው።
ሰድቦ፡ ለሰዳቢ፡ ሰጠ: መተረቻ አደረገ።
ሰድቦ: ነቅፎ፣ ዘልፎ።
ሰዶ፡ ማሳደድ፡ ቢሻኸ፡ ዶሮኸን፡ ለቆቅ፡ ለውጥ።
ሰዶም (ሎጣዊ): ሰዶማዊ፣ ግብረሰዶም የሚያደርግ፣ የሎጥ አገር ሰው።
ሰዶም: በእስያ ውስጥ በዮርዳኖስ ማዶ ያለ አገር፣ የገሞራ ጎረቤት። "ሰዶም፡ ገሞራ፡ እንዲሉ።" "ትርጓሜውም፡ (ሲድ)፡ ኖራ፡ የሚወጣበት፡ ማለት፡ ነው፡ ይላሉ፡ (ኪ፡ ወ፡ ክ)።"
ሰገለ ቢስ: ሰግላባ፣ ነገሌ።
ሰገለ ቢስ: ዕውቀተ መጥፎ፣ ፀባይ ጠንቋይ።
ሰገሌ: የቀበሌ ስም ካንጎለላ በላይ ያለ ሜዳ። "ባ፲፱፻፱ ዓ.ም፣ የርስ በርስ ጦርነት የተደረገበት።"
ሰገል: ጥንቈላ፣ ዕውቀት (ግእዝ)።
ሰገሰገ: ሰበሰበ፣ አጠጋጋ፣ አቀራረበ፣ አጠበበ ጥለትን፣ ማግን፣ ቍቲትን ለመቋጨት።
ሰገሰገ: ጠቀጠቀ፣ አብዝቶ በላ፣ እሆድ አገባ፣ ዐጨቀ።
ሰገረ: ስናርኛ ኼደ፣ ሠገረ።
ሰገበ (ዘገበ): ሰገባ፣ አበጀ፣ ሰፋ (ገቢር)።
ሰገበ: ሰለፈ፣ ተደቀነ (ተገብሮ)። "ገበገበን እይ።"
ሰገባ (ቦች): የሰይፍ ቤት፣ የጐራዴ መክተቻ። "አፎትንና ድርቄን ተመልከት።"
ሰገነተ: በጠጉሩ ወሽካካ ኾነ።
ሰገደ (ሰጊድ፡ ሰገደ): አጐነበሰ፣ ተንበረከከ፣ በኹለት ጕልበቱና በኹለት እጁ ምድርን ተመረኰዘ፣ ተደፋ፣ በግንባሩ መሬት ነካ፣ ወደቀ፣ ተነሣ።
ሰገዳ: ስግዶሽ፣ የመስገድ ኹኔታ።
ሰገገ (ትግ): ፊት ነሣ፣ አበረረ፣ ኣባረረ (፩ኛ ሳሙኤል ፳፭ ' ፲፬)።
ሰገገ: ቀና፣ ተንጋጠጠ፣ ረዘመ፣ በረረ። "የግመልና የቀጪኔ የሰጐን ዐንገት መሰለ (ሆሴዕ ፲፫፡ ፰)።"
ሰገጋ: የመሰገግ ሥር።
ሰገጠ: የቅልን ግፍና ለጠብ ባክርማ በስንደዶ ገመድ ሰፋ፣ ተመተመ። "(ፊቱን ሰገጠ)፣ አከፋ፣ መጥፎ፣ አስተያየት እየ።" "ካባን በክር ዘመዘመ።"
ሰገጥ: የቅል፣ የካባ ስፌት፣ ቅምቅማት፣ ዝምዝማት።
ሰጊድ: መስገድ (ግእዝ)።
ሰጋጊ: የሰገገ፣ የሚሰግ፣ ዐንገቱን አቅንቶ የሚሠግር። "ሰጋጊ በቅሎ እንዲሉ።"
ሰጋጭ: የሰገጠ፣ የሚሰግጥ፣ ሰፊ፣ ቀምቃሚ፣ ዘምዛሚ።
ሰግሳጊ: የሰገሰገ፣ የሚሰገስግ፣ ሰብሳቢ፣ አቀራራቢ፣ አጥባቢ፣ ዐጝቂ።
ሰግደድ አለ: ተሰገደደ። "ከታዳጊ ጌታ ሰግደድ ያለ ቦታ እንዲሉ።"
ሰግደድ አደረገ: ሰገደደ።
ሰግዳጅ: የሰገደደ፣ የሚሰገድድ፣ መላሽ፣ ሰብሳቢ፣ ደባቂ።
ሰጐኑ: ያ ሰጐን፣ የርሱ ሰጐን።
ሰጐን (ሰገኖ): ዐንገቱና ቅልጥሙ የረዘመ ኣሞራ። "ክንፎቹን ዘርግቶ፣ በእግሮቹ ይሽከረከራል እንጂ እንደ ሌላው በአየር አይበርም፣ ተመሥጦ የለውም።" "ሲበዛ ሰጐኖች ያሠኛል።"
"ተባቱንና እንስቱን ለመለየት ሰጐን።"
ሰጎንድ ካልኢት: ፷ ቅጽበት።
ሰጐኗ: ሰጐኒቱ፣ ያች ሰጐን።
ሰጐኗ: የርሷ ሰጐን።
ሰጐጥ (ጦች): ሰግ በመሬት ላይ ተተክሎ የማይነቃነቅ ደንጊያ፣ የምድር ስገጥ።
ሰጠ (ሰጠወ): (ሉቃስ ፯፡ ፳፩)፡ አቀበለ፣ አስረከበ፣ ዐደለ፣ ቸረ፣ ለገሰ። "(ተረት)፡ የሰጠ፡ ቢነሣ፡ የለበት፡ ወቀሣ።" "ካልሰጡ፡ ኣይዕደቡም።"
"፩፡ ወንድ፡ ለዘጠኝ፡ ያውም፡ እግዜር፡ ሰጠኝ።" "(አሳልፎ፡ ሰጠ)፡ ለቅጣት፡ ለመከራ፡ ተገቢ፡ አደረገ፡ በዳኛ፡ ፊት።" "(ቤት፡ ሙሉ፡ ሰጠ)፡ አለልክ፡ ናኘ።" "(መልስ፡ ሰጠ)፡ ተናገረ፡ አወሣ።"
"(ቃል፡ ሰጠ)፡ ዕሺ፡ አደርጋለኹ፡ አለ።" "ሰጠ፡ የ፪፡ ፊደል፡ ግስ፡ ኹኖ፡ መጥበቁ፡ ሰጠወን፡ ተከትሎ፡ ነው።" "(ላይችል፡ አይሰጠውም)፡ እግዜር፡ ለሰው፡ ከዐቅሙ፡ በላይ፡ ጭንቅ፡ አያመጣበትም።"
"(የጁን፡ ይስጠው)፡ ጡር፡ ይድረስበት።"
ሰጠመ (ሰጥመ): ገባ፣ ጠለቀ፣ ጠለመ፣ ዘቀጠ፣ ጠፋ። "ሰመጠን፡ ተመልከት፡ ከዚህ፡ ጋራ፡ አንድ፡ ነው።" "መጽሐፍ፡ ግን፡ በሰጠመ፡ ፈንታ፡ ተሰጠመ፡ ይላል፡ ስሕተት፡ ነው (ዕብራውያን ፲፩፡ ፳፱)።"
ሰጠሰጠ (ጠሰጠሰ): ደበደበ፣ ገረፈ።
ሰጠሰጠ: ሰየፈ፣ መታ።
ሰጠረ: አረቀቀ፣ ሰወረ። "ምስጢርን፡ እይ፡ የዚህ፡ ዘር፡ ነው።"
ሰጠጠ: ቀደደ፣ ሠጠጠ።
ሰጣሚ: የሚሰጥም፣ ጠላቂ።
ሰጥ፡ ለመጥ፡ አለ: ርግት፣ ለጥ እለተ ለመጠ፣ ተኛ፣ ዠርባውን ኣስመቸ።
ሰጥ: ጸጥ፡ ሰጥ፡ አለ፣ ጸጥ፡ አለ፣ ረጋ፣ ተገዛ።
ሰጥር: ቀጪን፣ የጐድን ዐጥንት፣ ሠጥር።
ሰጥቶ፡ ዕንካ፡ ብሎ: አስረክቦ።
ሰጥቶ፡ ይለምን: ቸር፣ ደግ፣ የዋህ ሰው፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (ዮሐንስ ፬፡ ፯፡ ፲)።
ሰጪ፡ ጭ (ዎች): የሰጠ፣ የሚሰጥ፣ ቸር፣ ሊጋስ።
ሰጪታ: የምትሰጥ፣ ዘራፍ ሴት።
ሰፈሰፈ (ሰፈፈ): ቀረበ፣ ተሰለፈ።
ሰፈረ (ሰፊር፡ ሰፈረ) (ገቢር): ለካ፣ መጠነ (ምድርን፣ አኸልን፣ ውሃን፣ ቅቤን፣ ማርን፣ ማንኛውንም ነገር ኹሉ) (ሕዝቅኤል ፵፡ ፳፡ ፳፫)።
ሰፈረ (ተገብሮ): ዐረፈ፣ ተቀመጠ (ጭፍራው፣ ንቡ)፣ ተሰቀለ (ዶሮው፣ ወፉ) (፪ኛ ዜና መዋዕል ፴፪፡ ፩። ማቴዎስ ፲፫፡ ፴፪)።
ሰፈረተኛ (ኞች): ሰፈር ያለው፣ ባለሰፈር፣ በሰፈር ያለ፣ የተቀመጠ፣ የሰፈር ሰው።
ሰፈራ: ስፍሮሽ፣ የመስፈር ሥራ፣ ምጠና።
ሰፈር (ሮች): የጦር ሰራዊት ድንኳን ተክሎ፣ ዳስ ጥሎ የሚያድርበትና የሚውልበት ስፍራ። "በቀን፡ ብዛት፡ ግን፡ ዐምባ፡ መንደር፡ ይባላል።"
ሰፈርጃል (ዐረ): የተክል ስም። "ፍሬው ላዩ ብጫ፣ ውስጡ ብርንዶ የሚመስል ተክል። ግእዝ ሰፈርጐል ይለዋል።"
ሰፈነ (ሰፊን፡ ሰፈነ): ተሾመ፣ ገዛ፣ ሠለጠነ፣ የበላይ ኾነ።
ሰፈፈ (ሰፊፍ፡ ሰፈፈ): በላይ ኾነ፣ ተዘረጋ፣ ረበበ (ዘፍጥረት ፩፡ ፪)። "ተንካፈፈ፣ ተንኳፈፈ፣ ዋኘ (አሞራው፣ መርከቡ)። ጠለለን፡ እይ።"
ሰፈፍ፡ አለ፡ ሰፈፈ (፪ኛ ነገሥት ፮፡ ፮)።
ሰፈፍ፡ የለሽ፡ የሴት ስም። እንከን፣ ነውር፣ ነቀፋ፣ እድፍ፣ ጕድፍ የለሽ ማለት ነው።
ሰፈፍ፡ የጠጅ ገፈት ወይም ግፋፊ፣ ደረቅ የማር እንጀራ ድቃቂ ከሠም የተደባለቀ፣ ዐዲስ ሸክላ ማማሻ። "ፋጕሎን፣ አስተውል።"
ሰፊ (ሰፋዪ): የሰፋ፣ የሚሰፋ፣ ጠቃሚ፣ ዘምዛሚ። "ልብስ፡ በርኖስ፡ መጝሚያ፡ ጠፍር፡ መኪና፡ ሰፊ፡ እንዲሉ። ሲበዛ፡ ሰፊዎች፡ ይላል።"
ሰፊ (ስፉሕ): የሰፋ፣ የተንቦረቀቀ፣ ቦርቃቃ፣ ቦላሌ። "ሰፊ፡ ቤት፡ ሰፊ፡ ሱሪ፡ ሰፊ፡ መንገድ፡ እንዲሉ። እጅን፡ ገበረ፡ ብለኸ፡ ግብርን፡ ሆድን፡ ልብን፡ እይ።"
ሰፊ፡ ሜዳ፡ "በባቢሎን አገር በሰናዖር ምድር የሚገኝ ሜዳ፣ የተንጣለለ (ዘፍጥረት፡ ፲፩፪)።" "ወገደ፡ ብለኸ፡ ወግዳን፡ አስተውል።"
ሰፊ፡ ሰፈር፡ የድንኳን፣ የልብስ፣ የኮርቻ ሰፊ ቦታ።
ሰፊ፡ ኾነ: ሰፋ፣ አልጠበበም።
ሰፊ: ጠባብ፣ ቦላሌ፣ ተነፋነፍ ሱሪ፥ ኢያሱ ሱሪ፣ ተፈሪ ሱሪ፣ ቍምጣ ሱሪ እንዲሉ።
ሰፊታ (ሰፋዪት): "የመሶብንና የሌላውንም ስፌት የምታውቅ፣ የምታፈጥን፣ በቶሎ የምትቈርጥ ሴት።"
ሰፊነት: ሰፊ መኾን፣ ጠቃሚነት።
ሰፊዋ: ሰፊዪቱ፣ የሰፋች፣ ከጥበት የራቀች (ዘጸአት ፫ ' ፰)።
ሰፋ (ሰፈየ): ጠቀመ፣ ዘመዘመ፣ ደረዘ፣ ደረተ፣ ደበደበ፣ ወሰወሰ፣ ሸደሸደ፣ ሸከሸከ፣ ሸለለ። "(ተረት)፡ ለስ፡ መጥሪያ፡ ቍና፡ ስፋች።"
ሰፋ (ሰፍሐ): ተዘረጋ፣ ፋገ፣ ተንቦረቀቀ፣ ከጥበት ራቀ፣ ረዘመ (በጐን፣ በወርድ)።
ሰፋ (ዐረ፡ ጸፋ): ጠራ፣ ጥሩ ኾነ፣ ነጣ።
ሰፋ: ሽፋፍ አበጀ፣ ሸለመ፣ አስጌጠ።
ሰፋ: በዛ፣ እየጨመረ ኼደ።
ሰፋ: የታናሽ ዛፍ ስም። "ዘንግና ሶማያ የሚኾን ዕንወት፣ ቀጥታ መለልታ ያለው። ፪ኛ ስሙ ጠዬ ይባላል። ይኸውም ተባትና እንስት ነው፤ ወንዴ ሰፋ፣ ሴቴ ሰፋ እንዲሉ።" "ጐዣሞች ግን ሱማያ ይሉታል፤ ሶማያ ከማለት ጋራ ይሰማማል። ሰፋ ማለፊያ ጥሩ ማለት ነው፤ ፋ እይነሣም።"
ሰፋሪ: የሰፈረ፣ የሚሰፍር፣ የሚለካ፣ ተቀማጭ። "ዓሥራት፡ ሰፋሪ፡ ቀለብ፡ ሰፋሪ፡ መኻል፡ ሰፋሪ፡ እንዲሉ።"
ሰፋሪዎች: የሚሰፍሩ፣ ተቀማጮች።
ሰፋፊ: ብዙ ሰፊ (የኮባን፣ የንሰትን፣ የሙዝን ቅጠል፣ ቈርበትን የመሰለ ነገር)። "(ግጥም)፡ ይወለድና፡ ቂጠ፡ ሰፋፊ፡ ያባቱን፡ ምድር፡ ወሰን፡ አስገፊ።"
ሰፋፊ: የሰፈፈ፣ የሚሰፍ።
ሰፋፋ: ጠቃቀመ።
ሰፌድ (ዶች) (ሰፋ፣ ሰፈየ): "ሰታታ ዝርግ ስፌት፣ እኽል ማበጠሪያ፣ ከምጣድ ላይ ትኩስ እንጀራ ማውጫ። በትግሪኛ ሰተታ ይባላል።"
ሰፌድ፡ ሰፌዶ: የዓሣ ስም፣ ጠፍጣፋ ዓሣ።
ሰፌድ፡ እግር: እግሩ ለማጣ ጠፍጣፋ የኾነ ሰው።
ሰፌዶ: መርከብ የሚገለብጥ የባሕር ዘንዶ።
ሰፌዶ: ሰፌድን የመሰለ፣ እንደ ሰፌድ ያለ ነገር።
ሰፌዶ: ዝርግ ጋሻ።
ሰፍነግ: "እንደ ኳስ ክብ ኹኖ በባሕር ውስጥ የሚበቅል ብቋያ። ኹለንተናው ዐይን፣ ውሃ መጣ የባሕር እንጕዳይ፣ ዐይነ በጎ መሳይ።"
ሱላይ: የዠማ ስም፣ በወግዳና በተጕለት መካከል ያለ ወንዝ።
ሱሌማ: ከደንጊያ የሚገኝ ማዕድን፣ ሌሎችን ማዕድኖች የሚያሰማማ፣ የሚያጠራ።
ሡልጣን (ዐረ): ንጉሥ (በሕዝብ ላይ ሥልጣን ያለው)።
ሱሎ: የብ ነጭ ፈረስ።
ሱማሌ (ዎች): የነገድ ስም። "በሐረርጌ አውራጃ በውጋዴና በኢሳ የሚኖር ዘላን ሕዝብ። በምሥራቅ አፍሪቃም አለ።"
ሱማሌ: ሱማልኛ ።
ሱማሌ: ወገን ቅጽል ይኾናል።
ሱማል: ሶማል፣ ላም ዕለብ።
ሱማል: ዐረብኛ ሶማል፣ ሱማልኛ ነው።
ሱማልኛ: የሱማሌ ቋንቋ፣ የሱማሌ አፍ።
ሱማልያ: የሱማሌ አገር።
ሱሳ: በወይናደጋ የሚበቅል ዛፍ፣ ቅጠለ ብዙ ዕንጨት።
ሱሳን: በቀድሞ ዘመን በቤተ መንግሥት የሚሣል ባላበባ ሐረግ።
ሱስ፡ ልማድ: ሡሥ።
ሱረት (ሰወረ): በስውር የሚያዝ ማለት ነው።
ሱሪ: ምስጢረኛ፣ ውስጥ ዐዋቂ ሰው። "ሱሪ ታጠቀ ወንድ ወጣው ሞያ።"
ሱራፌል: የነገድ ስም። "የግዜርን መንበር የሚያጥኑ መላእክት፣ ካህናተ ሰማይ ፮፡ ፮ ክንፍ ያላቸው።"
ሱርስት:
ሱባዔ (ሰብዐ): አንድ ወይም ኹለት ሰባት ከሰው ተለይቶ በበኣት ተከቶ የሚደረግ ጾምና ጸሎት። "የሱባዔ ትርጕም ሰባት ሰባትነት ማለት ነው።"
ሱባዔ ገባ: ከሰው ተለየ፣ ዘጋ፣ ብቻውን ተቀመጠ።
ሱቲ: መናኛ ግምጃ፣ ሐርነት የሌለው።
ሱት (ስሑት): የሳተ፣ የሳተች፣ ደካማ። "ሴት ሱት እንዲል ባላገር። ሔዋንን ያሳያል።"
ሱካ: ኀፍረተ ብእሲ። "ሹካን፡ እይ።"
ሱካረ፡ ነቢያት: ቀይ ሱካር። "በግእዝ ሶከረ ነቢያት ይባላል። የመቤታችን ምሳሌ ነው።"
ሱካር (ሶከር): የሸንኰራገዳ እንቀት ክርትፍ፣ በያይነቱ ክብ እንክብል፣ ድብልብል፣ አራት ማእዘን ኹኖ የተዘጋጀ፣ ከሻይና ከቡና ጋራ የሚጠጣ ምግብ፣ ጣፋጭ። "ሸንኲርን፡ እይ።" "ሱካር፡ ሸንኰር፡ ዐማርኛ፡ ሶከር፡ ግእዝኛ።"
ሱካር: የበሽታ ስም፣ ከሱካር የሚመጣ ሕመም። "ብዙ፡ ውሃ፡ ያስጠጣል፡ በሰው፡ ገላ፡ ላይ፡ ቍስል፡ ያበዛል።"
ሱካርና፡ ወተት: የመጽሐፍ ስም። ብላቴን ጌታ ኅሩይ ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የተረጐሙት ታናሽ የተረት መጽሐፍ።
ሱክሱክ፡ አለ: ተንሶከሶክ፣ ውሽኛ ኼደ።
ሱዳ (ሱድ) (ዐረ፡ አስወድ): ጥቍር። "ኣበ፡ ሱዳ፡ እንዲሉ።" "ሲበዛ፡ ሱዳን፣ ይላል።"
ሱዳኔ (ሱዳናዊ): የሱዳን ሰው፣ የሱዳን ተወላጅ።
ሱዳን (ኖች): ያገር፣ የነገድ ስም። "ሱዳን ባረብኛ ጥቍሮች ማለት ነው። በግእዝ ግን አገሩ ኖባ ይባላል።" "በ፲፬፻ ዓ.ም ጊዮርጊስ ንጉሠ ኖባ የሚባል ክርስቲያናዊ ንጉሥ ነበራቸው።"
ሱፋላ (ሱፍ): ከበግ ጠጕር የተሠራ ጸዐዳ ካባ። "ሱፍና ሱፋላ ባማርኛ ይተባበራሉ። (ግጥም)፡ ቅባኑጉ፡ ወጥቶ፡ ሲተርፈው፡ ለይፋት፡ ሱፋላጣኹ፡ እኔ፡ ያሰናጂ፡ ጥፋት። ሱፍ፡ አላጣኹ፡ ሱፋላ፡ ዐጣኹ፡ ማለት፡ ነው።"
ሱፋላ: የበርባሬ ብጫ ጥለት፣ የሱፍ ኣበባ መሳይ።
ሱፋላ: የነጭ በግ ጠጕር፣ እንደ ሱፍ ንጣት ነጭነት ያለው። "ሎፊሳን፡ አስተውል።"
ሱፋጭ (ሰፈጠ): ስለት ያለው ጥቍር ደንጊያ፣ ተሰብሮና ተፈንክቶ ሻፎ የኾነ አለት።
ሱፍ (ዐረ፡ ጹፍ): ጠጕር። "ጥብቆና ሱሪ ቀሚስ የሚኾን ከጠጕር የተሠራ ልብስ፣ እንደ በርኖስ ያለ፣ በርኖስን የመሰለ። ሱፋላን ተመልከት።"
ሱፍ (ፎች): የቅመም ስም፣ ዘይት የሚወጣው ነጭ ቅመም፣ ባላገዳ።
ሲ በለው/ሲሲ በለው: "ነገረ ብለኸ ነገርን አስተውል።"
ሲ: ዐቢይ አገባብ። በትንቢት ገብቶ አንቀጸ እያስቀረ በቁም ቀሪነቱን ያሳያል። "(ማስረጃ): መብራት ሲበራ ጨለማ ይጠፋል፣ ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም።"
"ሲያውቅ የተኛን ሲሰማ ቅበረው።" "ሰን ሲ ያሠኘው የትንቢት መነሻ ይ ነው።" "አ ሲከተለው ሳ ይኾናል፣ ዓለም ሳይፈጠር ፈጣሪ ነበር።" "ሰነፍ ሳይከብር ይሞታል።"
"እኔ፣ አንተ፣ እናንተ፣ እሷ፣ በነዚህ ባ፬ቱ ሰራዊት በትንቢት ገብቶ ስ ሲኾን ስጥፍ፣ ስትጥፍ (አንተ፣ እሷ)፣ ስትጥፉ ይላል።" "በግእዝ መሠረቱ እንዘ ነው።"
ሲ: የስም ባዕድ መነሻ፣ ካስደራጊ አንቀጽ የሚወጣ። "(ካካ): አስካካ ሲካካ።"
ሲሉ (እንዘ፡ ይብሉ): "ፈረንጆች እጨረቃ ላይ እንወጣለን ሲሉ ይወድቃሉ።"
ሲላ (ሰላ) (ዘዳግም ፲፬፡ ፲፱): የአሞራ ስም፣ ፀረ እንቄ፣ ዐይነተ ጭልፊት፣ ቁመተ ዐርአሞራ፣ ጥፍሩ የሾለ፣ የሰላ፣ የወፍ፣ የዶሮ ጠላት ነው። "ሌሎቹ፡ አሞሮች፡ የያዙትን፡ ይቀማቸዋል፡ ስለዚህ፡ ጐበዝ፡ ሰው፡ ሲላ፡ ይባላል።" "ሾተልን፡ እይ።"
ሲላ፡ ሲል: ሳለ።
ሲላ፡ በዳሳ: የሰው ስም። "ዐጤ ቴዎድሮስ በጦርነት ጊዜ ይዘው የሰቀሉት የንጉሥ ሣህለ ሥላሴ አሽከር፣ ሐርበኛ ጐበዝ።" "በዳሳ በጋልኛ ቸር ማለት ነው።"
ሲላዮ: ታናሽ መስፈሪያ፣ ርቦ።
ሲል (እንዘ፡ ይብል): ሲ፡ ከሰ፡ ል፡ ከኣለ፡ ትንቢት፡ ይል፡ መጥቶ፡ ሲል፡ ተብሏል። "ሙሴ ዐመሌ ዐመሌ ሲል በደብረ ሲና ያየው እሳት በልቶት ይኾናል።"
ሲል፡ አለ: ታንቆ ሞተ። "ይህ ዐማርኛ ከሲላ በዳሳ ተሰቅሎ መሞት የመጣ ነው።"
ሲሎንዲስ: ቀድሞ ዘመን ዕፀ ሕይወትን ያገኘ ፈላስፋ (ቅዳሴ ማርያም)።
ሲመሽ: የሰው ስም፡ አባት ካረጀ በኋላ የወለደውን ልጅ "ሲመሽ" ይለዋል።
ሲምር (ያስተምር): "በልጅ ኢያሱ ጊዜ ፊታውራሪ ይብሳ ሰፈር ሁለት ሌቦች ሌሊት እሰው ቤት ገብተው መብራት አብርተው በባለቤቱ ራስጌ ሰይፍ ሰይፋቸውን መዘው ግራና ቀኝ ቆሙና ዕቃውን ሲያስግዙ ሚስቱ ነቅታ ምንድነው ብትል፡ ባልዮው ተይ ዝም በይ ሚካኤልና ገብርኤል ናቸው አለ፡ ሌቦቹም ሣቁና ዕቃውን ጥለውለት ኼዱ ይባላል።"
ሲሳያም/ሲሳየ: ብዙ አገር፣ ምግባም።
ሲሳይ: ምግብ፣ መብል፣ ቀለብ፣ ጕርሥ፣ እንጀራ፣ የለት እራት።
ሲራራ: ጭነት፣ ቀርቃባ አጋሰስ ዠርባ ላይ የሚወጣ።
ሲር ሲር አለ: ጮኸ፣ ተንሰረሰረ።
ሲር: የተጣደ ማሰሮና የልብ ጩኸት።
ሲሻኝ: ሲያምረኝ፣ ሲፈልገኝ። "(ተረት): እንባ ሲሻኝ ዐይኔን ስ ወጋኝ።"
ሲሻው: ሲያምረው።
ሲበዛ "ነብሮች" ያሰኛል።
ሲበዛ "ዕሪያዎች" ያሠኛል (የብዙ ቁጥር)።
ሲበዛ: ሱሪዎች ያሠኛል። ሠራ።
ሲባጎ (ዎች): ቀጪንና ወፍራም የፈረንጅ ክር፣ ወይም ገመድ።
ሲኒማ: በመብራት (በኤሌትሪክ) ኀይል በተዘጋ ቤት ጐልቶ የሚታይ የማንኛውም ፍጥረት ሥዕል፣ ጥላ፣ የማይናገርና የሚናገር። "ይህን ጥበብ ያወጡ የዘር ስማቸው ሉሜር የሚባል ወንድማማቾች ፈረንሳዮች ናቸው ይባላል። ጊዜውም ፲፱፻ ዓመተ ምሕረት ነው።"
ሲኒጋል (ሎች): ያገር፣ የነገድ ስም። "በምዕራብ አፍሪቃ ውስጥ የሚኖር ሻንቅላ፣ የሱዳን ቍራጭ፣ የፈረንሳይ ቅኝ የነበረ። የሚገኘውም በአትላንቲክ ውቅያኖስ አጠገብ ነው።"
ሲናር (ሮች): "ከገብስ ጋራ የሚበቅል የገረማ ዐይነት። ፍሬው ለፈረስ ቀለብ ይኾናል።"
ሲናር: ስናር፣ በሰሜን አፍሪቃ በሱዳን ክፍል ያለ አገር።
ሲኖዶስ: የካህናት ጉባኤ፣ ሸንጎ፣ አደባባይ፣ ዓውድ። "የጉባኤ መጽሐፍ በየጊዜው የተጻፈ። ሲኖዶስ የጽርእ ቋንቋ ነው።"
ሲኦል: የቅጣት፣ የንስሓ ስፍራ፣ እስከ ፍርድ ቀን ኃጥኣን የሚኖሩበት፣ ታችኛ ጐድጓዳ፣ የጨለማ ቦታ፣ የዘብጥያ ምሳሌ።
ሲካ፡ ርጎ (ጐንደር): "ሲካ፡ መስበቂያውን፡ ያያል።"
ሲካካ: ቄብ ዶሮ (ካካ)።
ሲካካ: የምታስካካ ቄብ ዶሮ፡ ዕንቍላል መውለድ የምትችል።
ሲው: ጭው፣ የወፍ፣ የጫጩት፣ የከይሲ ጩኸት። "ሲውሲዋን፡ ተመልከት።"
ሲውሲዋ: ከዘረምቦና ከሻሻቴ ከፍ ያለ ዶሮ።
ሲያውቅ፡ የተኛ፡ ቢጠሩት አይሰማ።
ሲደልል: ዝኒ ከማሁ፡ "ሲያሞኝ፣ ሲሸንግል፡ መግደሉ ላይቀር"።
ሲዳማ: በሲዳሞ ውስጥ ያለ አገር። በጋልኛ ዐማራ፣ ሐበሻ ማለት ነው። "ይኸውም ስም ዐማራ አስቀድሞ በዚህ ክፍል መኖሩን ያስረዳል።"
ሲዳሞ: በኃላ ቤት ያለ አገር።
ሲጥ: መጮኸ፣ ሠጠጠ።
ሲፈራ ሲቸር: "ልስጥ እልስጥ"፣ "ላድርግ እላድርግ"፣ "ልምታ አልምታ" እያለ፣ የሞት ሞቱን።
ሳ: እንደ ን በመጨረሻ እየገባ የጥያቄ ቃለ አጋኖ ይኾናል፣ እሱንም ማ ያጐላምሰዋል። "(ጥያቄ): ሳኦል ሺ ገደለ፣ ዳዊት ሳ።" "(መልስ): ዳዊትማ እልፍ ገደለ።" "ኢዮአብ ከዘመቻ ደኅና ገባ፣ ኦርዮ ሳ።" "ኦርዮማ ሙቶ ቀረ በማለቱ የመሰለውን ሁሉ ያሳያል።"
"በግእዝ መሠረቶቹ ሰ፣ ኬ ናቸው።"
ሳ: ዝኒ ከማሁ ንኡስ ኣገባብ። "ደግ ሳንሠራ ሞት ቢመጣሳ እንዴት እንኾናለን።"
ሳሕን (ዐረ፡ ጻሕን): ጻሕል፣ ወጭት፣ ጣባ፣ ደቅ (ከሽክላ፣ ከማዕድን የተሠራ)፣ ትንሹም ትልቁም።
ሳሕን፡ ስፍራ።
ሳለ (ሰሐለ): ሞረደ፣ ፈገፈገ፣ ስነገለ፣ አሰላ፣ ለመጠ (መዝሙር ፻፵፡ ፫)። "በሳልከው፡ ተመተር፡ እንዲሉ።" "ሰላና፡ ሳለ፡ ከሰሐለ፡ መውጣታቸውን፡ ልብ፡ አድርግ።"
ሳለ (ሰአለ): ለመነ፣ ጠየቀ።
ሳለ (ሰዐለ): ኡሁ ኡሁ አለ፣ ጐበሰተ።
ሳለ (እንዘ፡ ሀሎ): ሳይሞት፣ ሳያልፍ። "(ተረት)፡ አባት፡ ሳለ፡ አጌጥ፡ ጀንበር፡ ሳለ፡ ሩጥ።"
ሳለ፡ ሶለግ፡
ሳለ፡ አይሰጥ: ሰረሰር፣ ደንደስ (ቢቈርጡት ቢግጡት ሥጋው የማይጠቅም)። "መጀመሪያውን፡ አለ፡ እይ።"
ሳላ: መልኩ ወደ ጥቍረት የሚያደላ ወፍራም ስንዴ። "ሳላ፡ ያሠኘው ምርቁ፡ ይኾናል።"
ሳላ: ቀንዱ የሾለ፣ የሰላ የበረሓ እንስሳ። "በግእዝ፡ ብዕዛ፡ ይባላል።"
ሳላም: ሳል የያዘው ወይም ያለበት፣ ያደረበት፣ ባለሳል።
ሳላይሽ: በወግዳና በተጕለት ክፍል ያለ ቀበሌ።
ሳላይሽ: የቀስሌ ስም፡ የፈረንጅ ፈረስ።
ሳላይሽ: የፈትል ስም፣ የፈረንጅ ማግ።
ሳሌ: ካዋሽ የሚያንስ ጋን፣ ዝንግሪር። "ቻልን፡ አስተውል፡ ከዚህ፡ ጋራ፡ አንድ፡ ነው።"
ሳሌ: የበሬ ስም።
ሳሌም: ሰላም። "ኢየሩሳሌምን እይ።"
ሳል (ሰዓል): ከነፋስ፣ ከብርድ፣ ከክፉ ሽታ፣ ከጕንፋን፣ ከመጠጥ የሚመጣ ጥዳቂ የሳንባ በሽታ፣ ትክትክ፣ አክታ ያለው።
ሳመ (ሰዐመ): ጨመጨመ፣ ተሳለሙ (ሉቃስ ፳፪፡ ፵፯)።
ሳሙና፡ ፈገግ፡ ያለ: የበቅሎ መልክ። "(ገላ፡ ሳሙና)፡ የገላ መታጠቢያ ባለሽቱ ሳሙና።"
ሳሙና: "ኮስቲክ ሶዳ ከሚባል የምድር ጨው ጋራ ተቀላቅሎ የተበጀ ቅባት (ዘይት፣ ሞራ)። በእንዶድ ፈንታ ልብስ ማጠቢያ፣ እድፍ ማስለቀቂያ (ሚልኪያስ ፫፡ ፪)።" "ኮስቲክ ሶዳም ነጥሮን ሳይኾን አይቀርም።"
"ሳሙና በአረብኛ ሳቡን ይባላል።"
ሳሚ (ዎች): የሳመ፣ የሚስም፣ ተሳላሚ፣ ጨምጫሚ። "ቤተ ክርስቲያን ሳሚ፣ ዐላዋቂ ሳሚ፣ ንፍጥ ይለቀልቃል እንዲሉ።"
ሳሚነት: ሳሚ መኾን።
ሳማ (ሞች): የቅጠል ስም፣ ረቂቅ የኾነ እሾኹ እንደ እሳት የሚለበልብ፣ የሚያቃጥል፣ የሚያንገበግብ ቅጠል (ኢዮብ ፬። ኢሳያስ ፴፬፡ ፲፫)። "በጦም ቀን እየተቀቀለ ይበላል፣ በጋልኛም ዶቢ ይባላል።"
ሳማ (ሰማ) (ጥሰሰ): የሚያስማ፣ የሚሰማ።
ሳማ (ሰዐምአ): የቅርብ ወንድ ትእዛዝ እንቀጽና ቃለ መልእክት። "በበዓል ቀን ተቀምጠሽ ከመዋል ቤተ ክርስቲያን ሳማ።"
ሳማ (እንዘአሐሚ): "ጠላቴን ሳማ፣ እኔ እጐዳለኹ እንጂ እሱ አይጐዳም።"
ሳማ ሰንበት (ሰምዐ፡ ሰንበት): "በምንጃር አውራጃ የተተከለ የሰንበት ታቦት።" "ትርጓሜው ሰንበት ሰማ ይመስላል።"
ሳማ ቅቤ: "ሰባት ዓመት የኖረ ቅቤ፣ ሖምጣጣ፣ ጥቂቱ የሚበቃ የሆድ መድኀኒት።"
ሳም (ስዒም): መሳም።
ሳም ሳም አደረገ: ሳሳመ፣ ጭምጭም አደረገ።
ሳም አደረገ: አጥብቆ ሳመ።
ሳምንት፡ አንድ ወር ሠላሳ ቀን። "ማነኸ፡ ባለሳምንት፡ እንዲል፡ ሙሴ።" "የዚህም፡ ምስጢር፡ ሰንበቴን፡ ያሳያል።"
ሳምንት: ስምንት ቀን። "በግእዝ ግን ያንዲት ሴት ተራ ቍጥር ነው። ትርጓሜውም ስምንተኛዪቱ፣ ስምንተኛዋ ያሠኛል።"
ሳሳመ: መላልሶ ሳመ።
ሳበ (ሰሐበ): ጐተተ፣ መዘዘ፣ እረዘመ። "(ተረት): በሬ ወዳገሩ ይስባል (ይጐትታል)።"
ሳበ: ወጠረ፣ ገተረ፣ ለጠጠ ቈዳን፣ ድንኳንን።
ሳበ: ይፋት የሴት ስም።
ሳበ: ጠራ፣ አወጣ፣ አመጣ፣ አቀረበ ጋኔንን።
ሳበው ጠመንዣ: "ባፉ ባሩድ ከተመላበት በኋላ መጣቀሻው በቋድ ተስቦ የሚተኰስ የዱሮ ነፍጥ።"
ሳቢ (ዎች): የሳበ፣ የሚስብ፣ ጐታች፣ አምጪ፣ አቅራቢ፣ በሬ፣ ፈረስ፣ ግመል፣ ባቡር። "ሳቢውን ግረፈው እንዲሉ።" "(ጋኔን ሳቢ): ጋኔን ጠሪ፣ አነጋጋሪ።"
ሳቢ ዘር: ሳቢ ርጥበት፣ ዘር መርጠብ። "የርጥበት ትርጓሜ መርጠብ መኾኑን ያሳያል።" "፪ኛው ያማርኛ ሳቢ ዘር አስተራረስ አጐራረሥ ይላል።"
"(ግጥም): በኔ አስተራረስ ባንቺ አጐራረሥ፣ እንኳን እሠኔ እማዚያም አንደርስ።"
ሳቢ ግመል: የቀድሞ አቡ፣ ጀዲ ምልክት።
ሳቢሳ (ዎች): ነጭ አሞራ፣ በዠማ ዳር በዝቶ የሚለኝ። "በበሬ ዠርባ ተቀምጦ ወንዝ ይሻገራል፣ ከከብት ጋራ ይሰማራል።" "ጫትን እይ።"
ሳቢና ተሳቢ: ጐታችና ተጐታች፣ ኣንቀጽና ጥራ።
ሳቢያ: ሰበብ፣ ምክንያት።
ሳቢያ: ቀጥታ ሞፈር።
ሳቢያ: ኹለተኛ ዐረቄ፣ መናኛ ተወራጅ።
ሳባ: ሰበከ።
ሳባ: የሰው ስም፣ የኵሽ ልጅ፣ የትግሮች አባትና አገር (ዘፍጥረት ፲፡ ፯)። "ሳባ ኖባ እንዲሉ።"
ሳባ: የየመኑ ሣባ።
ሳቤላ: የሴት ስም፣ ብቃት ያላት የጽርእ ፈላስፋ በጣፆት ምኵራብ የምትቀመጥ። "ባንድ ሌሊት የታየ የፈላስፎችን ሁሉ ራእይ ከመተርጐም በላይ እመቤታችን በፀሓይ አምሳል ወንድ ልጅ እንደ ታቀፈች በራእይ አይታ ተናግራለች።" "የነበረችውም በታላቁ እስክንድር ዘመን ነው።" "የትንቢት መጽሐፉም በግእዝ ይገኛል፣ አባቷ ህልቃስ ይባላል።"
ሳቤላ: ጐበዝ በሬ፣ ብርቱ፣ ፈጣን፣ ሳቢ (ዐማርኛ)።
ሳቤቅ: ያረግ ሬሳ በመሬት ላይ የተጋደመ። "ዕፅን ተመልከት።"
ሳብ (ስሒብ): መሳብ።
ሳብ ረገብ አለ: ተገተረ፣ ላላ።
ሳብ አለ: ተሳበ።
ሳብ አደረገ: ጐተት አደረገ።
ሳብዕ: ሰባተኛ ፊደል። "ኦ ሳብዕ፣ ቦ ሳብዕ እንዲል ፊደል ቈጣሪ።"
ሳብዕነት: ሰባተኛነት።
ሳተ: ሕግን፣ ትእዛዝን አፈረሰ። "ሃይማኖትን ካደ፣ ኀጢአት አደረገ፣ የማይገባ ሥራ ሠራ (ዘሌዋውያን ፭፡ ፲፰። ኢሳይያስ ፳፰፡ ፯። ሕዝቅኤል ፵፭፡ ፳)።"
ሳተ: ቅዘኑን፣ ዘሩን ለቀቀ፣ አፈሰሰ።
ሳተ: ዐጣ። "እባብ ጕድጓዱን አይስትም እንዲሉ።"
ሳተ: ዘነጋ፣ ገደፈ፣ አጠፋ የሚያውቀውን።
ሳተና/ሳታና (ሳጥና): የሳተነ፣ የሚሳትን፣ ብርቱ ሯጭ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋ።
ሳተናው: የክራር መቺ፣ ዘፈን ኣዝማች።
ሳተናው: ያ ሳተና፣ ፈጣኑ፣ ቀልጣፋው።
ሳቱ ሰ: እንዲሉ።
ሳታተ ግብጽ: የጸሎት ኣስተዋፅኦ ወደ ግእዝ የተተረጐመ።"
ሳታት (ሰዓታት): ቋሚ (ቀዋሜ፡ ሰዓታት): "ሌሊት በቤተ ክሲያን ውስጥ ቆሞ ሳታት የሚያደርስ አወዳሽ።"
ሳታትን እይ: የዚህ ብዢ ነው።"
ሳት (ስሒት): መሳት።
ሳት አለው: ነገር አመለጠው።
ሳት: የፊደል ስም፣ ሰ።
ሳቻ (ስሕተት): ኀጢአት፣ ክሕደት፣ ነውር። ሳች: የሚስት።
ሳንሳ (ምዝላል): የጋራ ሸክም። "መሸከሚያውም አጣና መሎጊያ ይባላል። የሳንሳ ያዘ፡ የሳንሳ ተሸከመ፡ እንዲሉ።"
ሳንቃ፡ ተጠርቦና ተልጎ የተቀመጠ የእንጨት ሉሕ (፩ኛ ነገሥት ፯፡ ፱)።
ሳንቃ፡ ከዕንቍና ከወርቅ፣ ከብር፣ ከንሓስ የተሠራ የለምድ መጋጠሚያ፣ በስተደረት ያለ። "(የደረት፡ ሳንቃ) ጌጠኛ የደረት ልብስ፣ ሴደርያ (ዘጸአት ፳፭፡ ፯። ፳፰፡ ፬)።"
ሳንቃ፡ የበር መዝጊያ መግጠሚያ። "(ታቦት፡ ዘፋኝ)፡ ተክልዬ፡ ተክልዬ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ ሳንቃው፡ መከፈቻው፡ የሚካኤል ለት፡ ትምሩኝ፡ እንደኾን፡ ልምጣ፡ በግንቦት።"
ሳንቆች፡ መዝጊያዎች (ዘጸአት ፳፮፡ ፳፯ ' ፳፱)።
ሳንቲ፡ የሜትር ፪ኛ፣ አንዲት ጭረት።
ሳንቲ፡ የዋሽንት ዐይነት የዘፈን መሣሪያ።
ሳንቲም (ሞች): የብር ፻ኛ፣ የምትርጓሜ ኛ ነው።
ሳንከኛ (ኞች): ሰበበኛ፣ ሁከተኛ።
ሳንክ፡ ጕትቻ፣ ሰበብ፣ ሁከት፣ ክፉ ሐሳብ።
ሳንኮች፡ ቅባቶች (በዘፋኝ ዳዊት ጊዜ ለተዋሕዶዎች ሳንክ የኾኑ በቅባት "ሃይማኖት የሚያምኑ ሰዎች")።
ሳንኳ፡ ሰኰና፣ ቍርጭምጭሚት፣ ስንድድ።
ሳንጃ፡ በጠመንዣ ጫፍ የሚሰካ የጦር መሣሪያ፣ ሽፋፉ ብረት። "መጠኑ የጩቤ ሲኾን ጫፉ ሹል ነው፤ የጨበጣ ውጊያ ይደረግበታል።"
ሳንጃ፡ ተርብ፣ የተርብ መርዝ ወይም ሳንጃ የሚባል ተርብ፣ ተቈናጣጭ ዝንብ።
ሳንፊል፡ የነፋስ ስልክ። "አለሽቦ ድምፅ የሚሰጥና የሚቀበል መኪና (ራዲዮ)። ማርኮኒ የሚባል ጣሊያን ያወጣው። ሳንፊል ፈረንሳይኛ፣ ራዲዮ ጣሊያንኛ ነው።"
ሳኦል: የሰው ስም፣ በእስራኤል ላይ መዠመሪያ የነገሠ ንጉሥ።
ሳካ (ስሕከ፡ ሳሕክ): እንከን፣ የገላ ነውር፣ ቋቍቻ፣ ዕከክ።
ሳካም፡ የለሽ፡ የሴት ስም። "እንከንም የለሽ ማለት ነው።"
ሳያጠሩ): የውሻ ስም። "ነገርን ሳያጠሩ ተለባብሶ መኖርን ያሳያል።"
ሳይ (ሰሓሊ): የሳለ፣ የሚስል፣ ሞራጅ፣ ሰንጋይ።
ሳይ (እንዘ፡ እሬኢ): እኔ ሳስተውል፣ ስመለከት። "አየን፡ እይ።"
ሣይ (ዮች፣ ሠዓሊ): የሣለ፡ የሚሥል (በእጅ፣ በመኪና)። "ሥዕል ሣይ" እንዲሉ።
ሳይታይ: የሰው ገንዘብ አነሣ፣ ወሰደ፣ ሞጨለፈ፣ ቤትን ቈፍሮ፣ ሰርስሮ፣ ነድሎ፣ ኪስን በርብሮ።
ሳይንት፡ ያገር ስም።
ሳይዳ፡ እመቤት። "ሴዱን፡ እይ፡ ከዚህ፡ ጋራ፡ ዘሩ፡ አንድ፡ ነው።"
ሳደረ፡ አመረቀዘ፣ ቍስሉ ተበላሸ፣ ጠመመ (መቃብሩ፣ ነገሩ፣ የቀንበሩ ብስ)።
ሳደፍ: መበከል፣ ማኵለፍለፍ፣ ማበሽጠቅ።
ሳዱላ (ኦሮ): ሴት ልጅ፣ ልጃገረድ።
ሳዱላ፡ በብር በመዳፍ ልክ የተቦቀረ ያናት ቡቅራት፣ ባል ባላገባች ልጃገረድ መኻል ራስ (ቍንጮ፡ ያ) ላይ የሚታይ ክብ ልጭታት።
ሳድስ ቅጽል): ንግር። (ሣልስ ቅጽል): ነጋሪ። (ደቂቅ ቅጽል): ያ፣ ይህ። (አኃዝ ቅጽል): ፩፣ ፪። "ከዚህም በቀር የቅርብ ሴት ትንቢትና ኀላፊ አንቀጽ ሲኾን በሩቅ ወንድ ቅጽልነት የሚፈታ ቃል አለ።" "ውሻ አይበላሽ፡ ዱላ ቀረሽ፡ ላባ ቀረሽ።" "ስትፈታም አይበላሽ የማይበላው፡ ቀረሽ የቀረው በል።"
ሳድስ፡ የፊደል ስም፣ ስድስተኛ ፊደል። እ፡ ሳድስ፡ ብ፡ ሳድስ፡ እንዲል ፊደል ቈጣሪ። "ትጽልን፡ ተመልከት።"
ሳድስነት፡ ስድስተኛነት።
ሳዶቅ፡ የሰው ስም፣ ጻድቅ ማለት ነው።
ሳገ/ሳጋ (ሰሐገ): ሻጠ፣ ሰካ፣ ጨመረ፣ አገባ። "ላፃ የካህናት ሳጋ የባላገር።" "መሰገን እይ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።"
ሳገ: የሳገ፣ የሚስግ፣ ሻጭ።
ሳጋ: ባንድ በኩል እየሾለ እባጥ እግድግዳ የሚገባ ጠርብ ሽብልቅ።
ሳጠራ፡ አቴና፣ ሣጠራ።
ሳጥ)፡ ጡጥ፣ ጥጥ (ግእዝ)።
ሳጥናኤል (ሰይጣነ፡ ኤል): ሰይጣን፣ ጠላት፣ ኤል፡ አምላክ። "በተገናኝ ፀረ አምላክ፣ ያምላክ ጠላት፣ ባለጋራ ማለት ነው።"
ሳጥን፡ በቁሙ ሣጥን።
ሳጻ) ነጻ (ነጻሒ፡ ሐራ፡ ግዑዝ): ጌታው የለቀቀው፡ ባርነት የቀረለት፡ በራሱ ሐሳብ ዐዳሪ።
ሳፍ (ዐረ፡ ጻፊ): ጥሩ፣ የጠራ።
ሳፍ፡ ሹል ዐጥንት፣ ሰፋ (ሰፈየ)።
ሳፍ፡ ያካንዱራ መውጊያ፣ ሹል ዐጥንት ወይም ዕንጨት።
ሳፍራ፡ የነፋስ ባሕርይ (ግእዝ)።
ሳፍራን፡ "አበባው ዐደይ መሳይ የሽቱ ቅጠል። በግእዝ መጽርይ ይባላል (ማሕልየ፡ መሓልይ ፩፡ ፲፬)።"
ሳፍወርቃ፡ የሴት ስም፣ ጥሩ ወርቅ ማለት ነው። "ይህችውም በመርሐ ቤቴ የግሬት ባላባት ነች።"
ሳፍጅ፡ በጠራ ውስጥ ያለ ቀበሌ።
ሴ፡ ምእላድ። "አንድ - አንድስ፡ ማን - ማንትስ፡ ማንትሴ፡ ምን - ምንትስ፡ ምንትሴ፡ ቅባጥር - ቅባጥርሴ።"
"የኹሉንም ፍች በየስፍራው እይ።"
ሴላ፡ ድንቅ ማለት ነው።
ሴሎ፡ በእስያ ክፍል ያለ አገር።
ሴም: የሰው ስም፣ ከኖኅ ልጆች አንዱ፣ በኵሩ። "የርሱም ዕጣ ክፍል እስያ ነው።"
ሴሰን: ምንዝር፣ ቅንዝር፣ ሽርሙጥና።
ሴሰኛ (ኞች): የሴሰን፣ ባለሴሰን፣ እመንዝራ፣ ቅንዝረኛ፣ ኻያጅ።
ሴሰኛነት: ቅንዝረኛነት።
ሴሰኝነት: ዝኒ ከማሁ (ሮሜ ፲፫፡ ፲፫)።
ሴታሴት: የሴት ሴት። "መልኳ እናቷን ብቻ የሚመስል ሴት።"
ሴታውል (ሴት፡ አውል): ላም ዐንገት፣ የሴት እረኛ፣ ከሴት ጋራ የሚውል ወንድ፣ ደካማ፣ ዐቅመ ቢስ፣ ፈሪ።
ሴቴ ሰፋ: ጕጥ አልባ፣ ጠዬ።
ሴቴ ሬት: ጥርስ የሌለው የቍስል መድኀኒት።
ሴቴ ቍልቋል: ለስላሳ፣ መላላ፣ ቀጥተኛ ቍልቋል።
ሴቴ ብር: የሴት ሥዕል ያለባት ብር፣ ብረ ሰብስብ።
ሴቴ ብርጕድ: ያልተመጠነ፣ ያልተቀላቀለ ብርጕድ።
ሴቴ ዐፈር: ቀይ መሬት፣ ሸክላ ያፈር፣ ወይዘሮ።
ሴቴ ዐፈር: ቀይ መሬት፡ ያፈር ወይዘሮ፡ ገንቦሬ (ቀይ አፈር)።
ሴቴ ወገን: ቅጽል፣ የሴት፣ ሲታዊ፣ ሴትማ፣ ሴት ዐይነት፣ እንስታዊ።
ሴት፡ ልጁን፡ ከቤት፡ አወጣ፡ ለባል፡ ሰጠ። (ተረት)፡ በሰው፡ ምድር፡ ልጇን፡ ትድር።
ሴትነት: ሴት መኾን፣ የሴት ያ። "ሴትነቱ ጣጣ ነው እንዲሉ።"
ሴትኛ: ዐዳሪ።
ሴትዮ: (ኦ፡ ብእሲቶ)
ሴቶች: ሚስቶች፣ ባልተ ቤቶች።
ሴቷ/ሴቲቱ: ያች ሴት (ራእይ ፲፪፡ ፬ = ፮፡ ፲፬፡ ፲፭፡ ፲፮፡ ፲፯)።
ሴክል፡ የአመት ዘለላ፣ ፻ ዓመት።
ሴደር፡ ቀይና ነጭ የበሬ መልክ፣ ቅላትና ንጣት እንደ መቀነት እየኾነ ገላውን የከበበው። "ነጭና፡ ጥቍር፡ ሲኾን፡ ጕሬዝ፡ ይባላል።"
ሴደርማ፡ የሴደር ወን፡ ባካሉ ላይ ሴደር ያለበት ከብት።
ሴደርያ (ዐረ፡ ጸደይሪያህ): ዐጪር የደረት ጥብቆ፣ ባለጌጥ።
ሴዱ፡ የሰው ስም፣ ጌታ ማለት ነው። "ሳይዳን፡ ተመልከት።"
ሴጣን፡ ጋኔን፣ ሰይጣን።
ሴፍ፡ ሰይፍ፣ ሰየፈ።
ስሓ (ሳካ): እንከን። "በግእዝ ዘሩ ሴሐ ነው።"
ስሓ (ትግ): ዕከክ።
ስሃ፡ እንከን፣ ስሓ።
ስኂን (ሰኀነ): የጪስ ዕንጨት፣ ምጥን፣ ልባንጃ፣ ዕጣን፣ ጥሩ ሽታ ያለው።
ስሒን፡ ልባንጃ፣ ስኂን።
ስለ (ሰአለ): ዐቢይ፣ እገባብ። "ዠግና ስሙን ማስጠራት ስለ ወደደ ዝኆን ዐደን ኼደ።"
ስለ፡ ምን፡ በምን ምክንያት፣ በምን ሰበብ። "ስለ ፍቅር፡ በስመ አብ፡ ይቅር፡ የሰይጣን፡ ነገር።"
ስለ፡ ሺ (ስለሺ): የሰው ስም። "በሺ ፈንታ አንተ ትበቃለኸ ማለት ነው።"
ስለ፡ እንደ። "ጥቍሬታ፡ ስለ፡ ጤፍ፡ ነው።"
ስለ፡ ከተናባቢ ሳድስ ቅጽል ሲገኝ ታቦት ዘፋኝ ይላል።
ስለ፡ ደቂቅ፡ አገባብ።
ስለ: ያለፈና የጊዜ ነገን እውነት አስመስሎ አወጋ።
ስለላ፡ የመሰለል ሥራ።
ስለሚሣሣ ሥጋው ቀይ ሽንኵርት ይመስላል!" ተባቱም እንስቱም ሠሥ ይባላል። "ሠሥና ድኵላ" እንዲሉ።
ስለቃ: ድቈሳ።
ስለታ፡ የመሰለት ሥራ።
ስለታም፡ ስለት ያለው፣ ባለስለት (ብረት ወይም ሰው) (፪ኛ ሳሙኤል ፪፡ ፲፮)።
ስለት (ስሕለት): ስልነት፣ ሹለት። "(ተረት) እምብዛም፡ ብልኀት፡ ያደርሳል፡ ከሞት፡ እምብዛም፡ ስለት፡ ይቀዳል፡ እፎት።"
ስለት (ስእለት): መለመን፣ ልመና፣ ማታ፣ ብፅዐት፣ ተሳይ፣ የሚሰጠው ወርቅ፣ ብር፣ ግምጃ፣ መጽሐፍ፣ ከብት ወይም ሌላ ስጦታ (ዘፍጥረት ፳፰፡ ፳። ግብረ ሐዋርያት ፳፩፡ ፳፫)።
ስለት፡ ልመና (ሳለ፡ ሰአለ)።
ስለት፡ ማረጃ።
ስለት፡ ማረጃ፡ ሳለ (ሰሐለ)።
ስለት፡ ማረጃ፡ ካራ፣ ቢላዋ፣ ኣፋ፣ ጩቤ፣ ዱቢት፣ ሾተል፣ ሰይፍ፣ ጐራዴ፣ ሐኔ፣ ፈንዜ፣ ዋልሴ፣ ወንበርቲ (፪ኛ ዜና መዋዕል ፳፫፡ ፯፡ ፲)።
ስለት፡ አወጣ: አሰላ።
ስለት፡ ድጕሱን ደባ፣ ራሱን ይቀዳል፣ ይጐዳል።
ስለፋ: ችኰላ፣ ቍተማ።
ስላች፡ ከብት የማይኼድበት ጠባብ የዱር መንገድ፣ አሳቻ፣ እጐዳና የሚያደርስ።
ስላች፡ የነገር ጭላንጭል፣ አንድ ሰው በሌላ ሰው ጕዳይ የሚገባበት ሰበብ፣ ምክንያት።
ስላንቲያ: የመልሱ መጨረሻ ስድብ የኾነ የልጆች ጥያቄ። "ስላንተ ዘለፋ ማለት ን ያሳያል።"
ስሌት፡ ሒሳብ፣ ቍጥጥር።
ስል (ሥሩሕ): የቀና ማረሻ፣ ግትር ያይደለ፣ ስበት። "በትግሪኛ ስሉሕ ይባላል።"
ስል (እንዘ፡ እብል): ደግ መሥራቴ እጸድቅ ስል ነው።
ስል፡ የሰላሳለ።
ስል፡ የበጀ፣ የሰላ፣ ሰላ (ሳለ)።
ስል: የሰለለ፣ ሰላላ።
ስልም (ጽሉም): የጨለመ።
ስልም አለ: ጭልም አለ፣ ዐይኑ ዛለ፣ ደከመ ሰውነቱ።
ስልምልም አለ: ተስለመለመ።
ስልምልም: የተስለመለመ፣ ዝልፍልፍ፣ ጭልምልም።
ስልምልምታ: ጭልምልምታ፣ ዝልፍልፍታ።
ስልምታ: ጭልምታ፣ ድካም።
ስልምጥ አደረገ: ሰለመጠ።
ስልምጥ: የተሰለመጠ፣ ስልቅጥ።
ስልሰላ፡ ምንመና፣ ንጠላ፣ ሽንሸና፣ ሥንጠቃ።
ስልስል (ዕዉስ): ዝኒ ከማሁ፣ ልምሾ።
ስልስል፡ አለ: ምንምን አለ።
ስልቃት: ስለቃ።
ስልቅ አደረገ: ድቅቅ አደረገ፣ ጐዳ በሽታ፣ ድጅኖ ሰውን።
ስልቅ: የተስለቀ፣ ድቍስ፣ ልዝብ።
ስልቅጥ፡ የተሰለቀጠ፣ የተዋጠ፣ ውጥ።
ስልባቦታም፡ ስልባቦት ያለው፣ ባለስልባቦት።
ስልባቦት፡ በፈላ ወተት ላይ የሰፈፈ ቅቤ። "በትግሪኛ ላሕመት ይባላል፤ ፈረንጆች ክሬም ይሉታል።"
"ምስጢሩ፡ ከወተት፡ ላይ፡ ተገፎ፡ መነሣት፡ ነው።"
ስልብ (ቦች): የተሰለበ፣ የተቈረጠ፣ ጕምድ፣ ጃን፣ ደርባ፣ ጠባቂ።
ስልቦሽ፡ ዝኒ ከማሁ።
ስልቦት፡ ጋዣ።
ስልት፡ ቀጠና፣ ጠኔ።
ስልት፡ አለ: ልትት፣ ድክም አለ።
ስልት፡ ክፍል፣ ወገን (የነገር ስልት)፣ ዐቅድ፣ መልስ።
ስልት፡ የተሰለተ፣ ሰለታ የኾነ (ቅጽል)።
ስልቹ፡ የሰለቸ፣ የተሰለቸ፣ ታካች።
ስልቻ (ቾች): የበግና የፍየል ቀልቀሎ፣ አቍማዳ፣ ዳውላ፣ ቀርበታ። "ትንሹም ትልቁም የወይፈን ሲኾን ጭልጊ፣ ዐይበት ይባላል።" "ሥሩ፡ ዕለተ፡ ይመስላል።"
ስልችት፡ አለ: ተሰለቸ።
ስልከኛ (ኞች): ስልክ ጠባቂ፣ ሳለ ስልክ፣ ሰውን በስልክ አሎ እያለ የሚጠራና የሚያነጋግር።
ስልከኛነት፡ ስልከኛ መኾን፣ የስልክ ሥራ መያዝ። "ስልክን መጀመሪያ በ1876 ዓ.ም ያወጣው እስክንድር ግራሐም በል የሚባል አሜሪካዊ ነው ይላሉ።" "ፈረንጆች ቴሌፎን ይሉታል።"
ስልክ (ኮች): የብረት፣ የመዳብ፣ የናስ ቀጥተኛ ሽቦ፣ የቃል፣ የኤሌትሪክ መኼጃ፣ መመላለሻ።
ስልክ፡ ያገር ስም፣ ሥልቅ።
ስልክክ፡ አለ: ስልክ መሰለ፣ ቈነዠ።
ስልጆ፡ ከባቄላና ከሰናፍጭ የተዘጋጀ የጦም ወጥ (ምግብ)። "ነጭ ሽንኵርትም አለበት።"
ስሎሽ፡ ሙረዳ፣ ፍግፈጋ፣ ስንገላ።
ስመ ጥር (ሩ): በዠግንነት፣ በደግ ሥራ፣ በውቀት ስሙ የተጠራና የታወቀ ባለዝና። "በግእዝ ስሙይ ይባላል።"
ስመ: ተጸውዖ: የመጠራት ስም።
ስመኛ (ኞች): ስም አክራ፣ የስም ባለስም፣ ተብሎም ይተረጐማል።
ስመኝ: የወንድና የሴት ስም።
ስሙ ኢያሱ ሲኾን በግብሩ "ሢራክ" ተብሏል ይላሉ። ጊዮርጊስ ወልደ ሐሚድ ግን ፪ቱን ፩ አድርጎ ኢያሱን የሢራክ ልጅ ይለዋል።
ስሙር፡ እረኛ እንዲሉ።
ስሙኒ፡ ሩብ፣ ፳፭ ሳንቲም። "ከጣሊያን ወዲህ የተለመደ ቋንቋ ነው።" "የተሙን፡ ተሙናዊ፡ ማለት፡ ነው፡ ባ፩፡ ተሙን፡ ፪፡ ይመነዘር፡ ነበር።"
ስሙን ለሰው አወረሰው: የራሱን ነውር በሌላ ላከከው።
ስሙን፡ ተከለ): አስጠራ።
ስሚ: መስማት፣ ወሬ፣ ጭምጭምታ።
ስማ (ስማዕ፡ መስክር): የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ፣ አድምጥ።
ስማ ምስክር፡ ዕወቅልኙን ስማ: "ያየኸውን የሰማኸውን መስክር ማለት ነው።"
ስማ ስማ፡ ያዋጅ ቃል መዠመሪያ: "ስማ ስማ መሰማሚያ ይንሣው ያድባርን ያውጋርን ጠላት እንዲል ዐዋጅ ነጋሪ።"
ስማ በለው: ተርጕመኸ ንገረው።
ስማ በለው: አስተርጓሚ።
ስማንፋር (ዐረ፡ ሱም፡ እልፋር): ያይጥ መርዝ። "ዐይጥን የሚገድል የቈለቈል ዐይነት መድኀኒት።"
ስሜት: መገረን፣ በውስጥ ያለ ደዌ በስተው ሲሰማ ስሜት ይባላል። "ትርጓሜውም መሰማት ነው።"
ስሜነኛ (ኞች): የስሜን ተወላጅ፣ የስሜን አገር ሰው።
ስሜን (ስምየ): የኔን ስም፣ ስምና ስሜን፣ በገቢር ጊዜ ይገጥማሉ። "ስሜን ስሜን እነግርኻለኹ (ዐጤ፡ ቴዎ)።"
ስሜን፡ በጐንደር ሰሜን ያለ አገር። "ስሜን የተባለው በቧሒት (የያሬድ ተራራ) ምክንያት ይመስላል።"
ስም (ሰመየ): የቦታና የአካል መጠሪያ። "ማንኛውም የሚታይና የማይታይ ነገር ሁሉ የሚጠራበትና የሚታወቅበት ስም ይባላል።"
ስም ሰጠ: ቀኛዝማች፣ ግራዝማች አለ።
ስም ቀቢ: በሰው ስም ላይ ነውርን የሚቀባ፣ የሚላክክ።
ስም አወጣ: የማዕርግ ስም ሰጠ ወይም ተቀበለ፣ ተሾመ።
ስም አውጪ: ለሰው ክፉ ወይም ደግ ስም የሚያወጣ።
ስም አጠራር: "የሰውን ስም ሲኾን በደግ ሳይኾን በክፉ ማንሣት።"
ስም አጥፊ: ስምን የሚያጠፋ፣ የሚያበላሽ።
ስም እኩይ: የሐሜት ስም።
ስም ጠራ: እከሌ አለ።
ስም: ከአንቀጽ በፊት ተነግሮ በተሳቢነት፣ ከቅጽል ተናቦ በዘርፍነት፣ ከጥሬ ተናቦ በባለዘርፍነት ይነገራል።
ስምል: የተሰመለ፣ ልፍ፣ ልዝብ።
ስምም: የተስማማ፣ ወዳጅ። "እከሌና እከሌ ስምም ናቸው እንዲሉ።"
ስምም: ፍቅር፣ ሰላም (አሞጽ ፫፡ ፫)።
ስምምነት: ስምም መኾን፣ ወዳጅነት።
ስምር፡ የሰመረ፣ የበጀ፣ ማለፊያ፣ ኵስ ትር።
ስምና ግብር: ነባርና አባት ዘር።
ስምን (ስሙን): የተሰመነ።
ስምን መልአክ ያወጣዋል/ይሰጠዋል/ይስይመዋል: (ማቴዎስ ፩ ' ፳፩)።
ስምንምን፡ አለ: ተስመነመነ።
ስምንምን፡ አደረገ: አስመነመነ።
ስምንምን፡ የተስመነመነ፣ ድቅስቅስ።
ስምንተኚት፡ ስምንተኛዪቱ ክፍል
ስምንተኛ (፰ኛ)፡ የተራ ወይም የማዕርግ ቊጥር፣ የስምንት ወገን።
ስምንተኛዋ፡ ስምንተኛዪቱ፣ ያች ስምንተኛ።
ስምንተኛው፡ ሺ፡ የዘመን ስም። "ሽንገላና ተንኰል፣ ክሕደት፣ ክፋት፣ ጥመት የበዛበት ጊዜ። ከአጤ ምኒልክ አሽከሮች አንዱ መኰንን ስምንተኛው ሺ ብለው ሲጠሩ አገልጋያቸው ሰው አበላሺ ይል ነበር ይባላል (አርእስተ፡ መዝ፡ ፲፩)።"
ስምንተኛው፡ ያ ስምንተኛ፣ የርሱ ስምንተኛ።
ስምንቲያ፡ ከስምንት አንድ።
ስምንት (፰)፡ የቍጥር ስም። "በሰባትና በዘጠኝ መካከል ያለ መድበል ወይም ጅምላ ቍጥር ያንድ ቤት።"
ስምንቶ፡ ስምንትዮ፡ ስምንትነት ያለው፣ ውስጠ ብዙ።
ስምዐበር: ሞክሼ።
ስምዖን፡ የሰው ስም፣ የያዕቆብ ልጅ። "ካ፲፪ቱ ነገደ እስራኤል አንዱ።" "በዕብራይስጥ ሺምዖን ይባላል።"
ስምጥ፡ አለ፡ ስጥም አለ።
ስምጥ፡ የሰመጠ፣ የሰጠመ። "ዕጥ የኾነ ስምጥ ታጣ እንዲሉ።"
ስሞሽ (ስዕመት): መሳም። "ራስ ስሞሽ እንዲሉ።"
ስሞተኛ: ስሞታ ወዳድ ነጋሪ።
ስሞታ: "እከሌ እንዲህ ሠራኝ፣ እንዲህ ኣደረገኝ ብሎ ለዋ የሚያሰሙት ወቀሣ።"
ስሞች: ኹለትና ከኹለት በላይ ያሉ መጠሪያዎች።
ስረጌ: ተሰረገች፣ ተጌጠች፣ ተሸለመች፣ ተዳረች ለባል፣ ተሰጠች፣ ባል አገባች። የማንም ከብት መዋያ፣ ሥር።
ስሪያ: ያውሬ፣ የንስሳ፣ ያሞራ ሩካቤ፣ እሮት፣ ግንኝት።
ስራ (ስራሕ): ዕርሻ፣ ቍፋሮ፣ ዐዳ። "ስራ መስራት የማይወድ አይብላ (፪ኛ ተሰሎንቄ ፫፡ ፲)።"
ስርሰራ: ስንፈጣ፣ ነደላ።
ስርስራ: የሣር ስም። "ቀጪን ሰንበሌጥ (ጐዣም)።"
ስርቂያ: ስርቆሽ፣ ስርቆት፣ መስረቅ፣ ሌብነት (ምሳሌ ፱፡ ፲፯)።
ስርቅ (ስሩቅ): የተሰረቀ፣ ከባለቤቱ የራቀ። የሆድ ጕስምት።
ስርቅ አለው: ሆዱን ጐሰመው፣ ሸቀበው።
ስርቅታ: ስርቅ ማለት፣ ፋቅ፣ ሕቅታ።
ስርቆሽ በር: "በፊት በር አንጻር ካዳራሽ ከልፍኝ በስተኋላ ያለ በር፣ ነገሥታት መኳንንት ለሕዝብ ሳይታዩ የሚወጡበት።"
ስርነቃ: ስንፈጣ፣ ትንታዞ።
ስርንቅ አደረገ: ሰረነቀ።
ስርንቅ: የተሰረነቀ፣ ዕፍን።
ስርወት፡ ከርሰ እምድ ይትኰነ ፍጥረት።
ስርዋጽ (ሰርወጸ):
ስርየት (ስሬት): የኀጢአት ይቅርታ።
ስርጀታ: ጠለፋ።
ስርጋዌ: አፈ በረከት፣ አፈ ወርቅ።
ስርግ (ስርግው): የተስረገ፣ የተጌጠ፣ የተዳረ።
ስርጓጕጥ: ወጣ ገባ፣ ሥርጓጕጥ፣ ሠረጐደ።
ስሯጽ: ሽብልቅ፣ ጣልቃ፣ ሠላጤ። "አለሥራውም የገባ ሰው ሽባጥ ይባላል።"
ስሻሽ: የሴት ስም፣ ስፈልግሽ።
ስሻኸ: የሰው ስም፣ ስፈልግኸ ማለት ነው።
ስቅለት፡ ሰቀላ፣ መስቀል፣ መሰቀል (ግእዝ)።
ስቅለት፡ የታላቅ በዓል ስም። "ጌታችን ዓለምን ለማዳን በመስቀል ላይ የተሰቀለበት መጋቢት ፳፯ ቀን።"
ስቅላት፡ ዝኒ ከማሁ፣ ለስቅለት መሰቀል (ዐማርኛ)።
ስቅል (ስቁል): የተሰቀለ፣ የተንጠለጠለ፣ እንጥልጥል፣ ዝልዝል ሥጋ፣ ርጥብ ልብስ። "ባላገር ግን ሥዕልን ስቅል ይለዋል።"
ስቅል፡ አለ፡ ተሰቀለ።
ስበረ: ቈረሰ፣ ዕቃን፣ ዳቦን፣ ከፍ።
ስበብ: ሰበብ። "በስበሱ መምሬ ተሳቡ እንዲሉ።"
ስበት (ስሕበት): እየተረገጠ በጠፍር አንድነት የታሰረ፣ የተቈራኘ ማረሻ፣ ድግር፣ ሞፈር፣ ቅትርት፣ ዕርፍ፣ መርገጥ፣ ወገል፣ ሰባትነት ያለው።
ስበዛ: ሽጐጣ፣ ጭመራ።
ስባሪ: የሸክላ፣ የብርጭቆ ሽራፊ፣ ድቃቂ (ኢሳይያስ ፶፰፡ ፲፬። ፴፩፡ ፬። ግብረ ሐዋርያት ፳፯፡ ፵፬)። "(የሰማይ ስባሪ): ሰፊ ምድር።" የቈሎ ክርታሽ፣ ፍንካች። ጣልቃ ገብ፣ ሥንጣሪ፣ ለቃልም ይነገራል።
ስባቅ: ቀለም ባንድነት የታሸ ዕይር።
ስብሐተ ነግህ: የጧት ምስጋና። "ቅዱስ ያሬድ በዜማ የደረሰው።"
ስብሐተ ፍቁር: ሦስተኛ የሳታት ክፍል ባለ፫ ስንኝ፣ "የወዳጅ ምስጋና ማለት ነው።"
ስብሐት (ሰብሐ): ምስጋና፣ ማመስገን።
ስብሐት ለአብ: ለአብ ምስጋና ይገባል "ይገባል ማለትን ያመጣ ለ ነው።" ከማእድ በኋላ የሚባል ጸሎት። የሰው ስም። "ባ ኢያሱ አድያም ሰገድ ጊዜ መልክአ ሥላሴን የደረሱ ፍጹም ሊቅ።"
ስብሰባ: ለቀማ፣ እከባ።
ስብሰባ: ጉባይ፣ ጉባኤ።
ስብሰባዎች: ጉባኤዎች፣ ጉባዮች።
ስብስባት: ስብስብነት።
ስብስብ አለ: ተሰበሰበ።
ስብስብ: የተሰበሰበ፣ ጥርቅም፣ እክብ፣ ክምቹ።
ስብራት: መሰበር፣ ሰባራነት (ኢሳይያስ ፴፡ ፳፮። ኤርምያስ ፶፩፡ ፻፬)።
ስብራት: ዕጥፋት፣ ቅንፋት፣ የልብስ፣ የቈዳ።
ስብር (ስቡር): የተሰበረ፣ ሥንጥቅ፣ ልብጥ።
ስብር አለ: እንክት ቅልጥም አለ።
ስብርባሪ: ስብርብር፣ የተሰባበረ፣ እንክትካች፣ ቅልጥምጥም።
ስብርብር አለ: እንክትክት አለ።
ስብቀላ: ቅልጠፋ።
ስብቀት: ስብቅ ማሳበቅ።
ስብቅ: ዱቄቱ የተሰበቀ፣ የታሸ፣ ጤፍ እንጀራ።
ስብቅል (ሎች): የሰበቀለ፣ ጣፋጭ፣ ቀልጣፋ ቃል ሰው።
ስብቅል አለ: ሰበቀለ።
ስብቅልቅል አለ: ቅልጥፍጥፍ፣ ምስቅልቅል አለ።
ስብቅልቅል: ቅልጥፍጥፍ፣ የተሰበቃቀለ፣ የተመሰቃቀለ።
ስብቅልነት: ቀልጣፋነት፣ ጣፋጭነት።
ስብቆ: ስብቆሽ፣ ታሽቶ ተሰብቆ የፈላ የጥቍር ስንዴ፣ ሙቅ፣ እንትክትክ ያጃ አጥሚት።
ስብት: የተሰበተ፣ የታረሰ፣ የተገለገለ፣ ግልግል።
ስብከተ ገና: ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ልደት፣ የስብከት እሑድ ከታኅሣሥ ፯ እስከ ፲፫ ያለ።
ስብከት: ቃል፣ ነገር፣ ትምርት ከሰባኪ አንደበት የሚወጣ።
ስብዛት: የሰበዝ አገባብ ኹኔታ።
ስብዝ: የተሰበዘ፣ የተሻጠ፣ የተሸጐጠ፣ ሰበዝ።
ስቦሽ: ጐተታ።
ስቱፋን: የሳቱ፣ ያልመቱ። "ልጆችም አንዱን ልጅ ስቱፋን ይሉታል።"
ስቱፍ: የሳተ፣ ያልቀለበ፣ ያልመታ፣ ፉርሽ፣ ችኩል፣ ጥዱፍ።
ስትል (አንተ፡ እሷ): ስትሉ፣ ስትዪ፣ ስል፣ ስንል እያለ በ፰ ሰራዊት ይዘረዝራል። "ሰን ተመልከት።"
ስትር (ስቱር): የተሰተረ፣ ዝርግ፣ ስጥ (ጥስ)።
ስነጋ፡ ነደላ፣ ቅርቀራ።
ስናም፡ ነፈሊያም አፍንጫ፣ ነፍናፋ።
ስናር፡ በቅሎ። "ስናር አህያ ከእንስት ፈረስ የዴቀለው፤ ሲኼድ እንደ እንዝ የሚሾር የሚሽከረከር።"
ስናር፡ አህያ፡ ቁመቱ ፈረስ የሚያኸል ረዥም የስናር አህያ።
ስናቅ (ስናግ): ትናግ አፍንጫ ወይም ውሳጣዊ ያፍንጫ ቀዳዳ። "ሕፃኑ የጠባው ወደ ስናቁ ወጣና ትን አለው።"
ስናን፡ በጐዣም ክፍል ያለ አገር።
ስናን፡ የሕፃን በሽታ፣ ተውሳክ፣ ግግን የመሰለ።
ስናን፡ ያንድ ክፍል ጭፍራ ስም (በዱሮ ዘመን)።
ስናጋ (ስናግ): ንፎ የከብት አፍንጫ ቀለበት። "በግእዝ ዝማም ይባላል (፪ኛ ነገሥት ፲፱፡ ፳፰። ኢዮብ ፵፡ ፳፮)።"
ስናጋ፡ በልጥ የታሰረ ሰባራ አሞሌ።
ስናግ (ትናግ): ከላንቃ በስተኋላ ያለ ቀዳዳ፣ ወዳፍንጫ የሚደርስ። "ስናቅን፡ እይ።"
ስናግ፡ እዶሮ አፍንጫ የገባ ላባ።
ስናግ፡ የመጋረጃ ዘንግ (ከብረት ዋ የተሠራ)። "በግእዝ ሰንጐጕ ይባላል።"
ስናግ፡ ያፍንጫ መካከለኛ ጫፍ። "በግእዝ ሕልበት ይባላል።"
ስናጭ፡ ለገድ፣ ነፈል። "ያፍንጫ ትንፋሽ በቀጥታ እንዳይወጣ የሚከለክል ሥጋ።"
ስናፍቅሽ: የሴት ስም።
ስናፍቅኽ: የወንድ መጠሪያ ስም፡ "ስሻኸ፣ ስፈልግሽ አገኘኹኸ" ማለት ነው።
ስናፒክ፡ የተክል ስም (የባሕር አገር)።
ስንቅር፡ አለ፡ ተሰነቀረ።
ስንቅር፡ አደረገ፡ ሰነቀረ።
ስንቅር፡ የተሰነቀረ፣ የተሻጠ፣ የተጋረጠ ሥንባጭ።
ስንተኛ (ኞች): የተራ ቍጥርን መጠን ለማወቅ የሚነገር ጥያቄ። "ሲጫፈር፡ ስንትና ስንት ይላል፤ ብዛትንም ያመለክታል።"
ስንተኛው (ስንተኛቸው): የጊዜና የማንኛውም ነገር ዐጸፋና በቂ።
ስንታየኹ፡ የወንድና የሴት ስም።
ስንት (ስፍን): የቍጥርን ልክ ለመጠየቅ የሚነገር ንኡስ አገባብ፣ ምን ያኸል። "ይሁዳ ጌታችንን 'ለስንት ብር ሼጠው? ጴጥሮስ ስንት ጊዜ ካደው? አይሁድ ስንት ጊዜ ገረፉት? ጌታችን ስንት ተኣምራት አደረገ?'"
ስንቶች (እስፍንቱ): ምን ያኽሎች።
ስንቾ፡ የሚጥሚጣ ስም፣ ሚጥሚጣ።
ስንን (ኖች): ፪ኛው ን ይጠብቃል፣ ቅንቅን ገዳይ ቅጠል።
ስንኝ (ኞች): የመልክ፣ የሰላምታ፣ የዐርኬ፣ የዘፈን ቤት፣ ግጥም።
ስንከላ፡ የእግር ላይ ምት።
ስንኩል፡ ዝኒ ከማሁ፣ ጐደሎ። "ሀብተ ስንኩል፡ መብሉ እኩል፡ ሥራው ስንኩል እንዲሉ።"
ስንክልክል፡ አለ፡ ተስነካከለ።
ስንክሳር፡ የመጽሐፍ ስም። "የመላእክትን ማዕርግና ሹመት የሚያስረዳ፣ የነቢያትንና የሐዋርያትን፣ የጻድቃንንና የሰማዕታትን፣ የደናግልንና የመነኮሳትን ምግባር፣ መከራና ዕረፍት ከዕለት እስካመት የሚነግር መጽሐፍ፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ። የመቤታችንን ዜና፣ የልጇንም በጎ ሥራ ሁሉ በሰፊው ይናገራል።"
"ትርጓሜውም በጽርእ የተሰበሰበ ስብስብ ማለት ነው።"
ስንክሳሮች፡ ኹለትና ከኹለት በላይ ያሉ መጽሐፎች።
ስንኳ፡ ንኡስ አገባብ፣ የማማረጥ ቃል። "ስንኳን፡ እንኳ፡ (ዘጸአት ፲፬፡ ፳፰። ዘዳግም ፪፡ ፭። መዝሙር ፻፴፱ - ፲፮። ኢሳይያስ ፴፫፡ ፳፫። ፴፭ ' ፰። ሕዝቅኤል ፳፬፡ ፲፪)።"
ስንኳን (ጥቀ፡ ጓ): ንኡስ አገባብ። "የማማረጥና የማሻሻል፣ የማበላለጥና የማላላቅ ቃል ይኾናል። ስንኳ ከእንኳ፣ ስንኳን ከእንኳን ጋራ አንድ ነው። ስንኳ ስንኳን የካህናት፣ እንኳ እንኳን የሕዝብ አነጋገር ነው።" በእንኳና በስንኳ ላይ ን ምእላድ ኹኖ ተጨምሯል።
ስንዘራ፡ የመሰንዘር ኹኔታ።
ስንዛሪ፡ የተሰነዘረ፣ የተሠነተረ።
ስንዝር (ስዝር): "ካውራ ጣት ጫፍ እስከ መካከለኛ ጣት መጨረሻ ያለ ልክ መጠን። ስንዝር ተጋት እንዲሉ (ስም)።"
ስንዝር፡ አለ፡ ዕልፍ አለ።
ስንዝር፡ የተለካ፣ የተመጠነ፣ ሥንትር፣ ሥንጥቅ (ቅጽል)።
ስንደዶ፡ ስፌትና ገመድ የሚኾን ሣር። "(የውሻ፡ ስንደዶ) ስንደዶ የሚመስል ዋና የመስክ ሣር ሰል።"
ስንዱ፡ የሴት ስም።
ስንዱ፡ የተሰናዳ፣ የተዘጋጀ፣ ዝግጁ።
ስንዱነት፡ ዝግጁነት፣ ድርጁነት።
ስንዴ (ስንዳሌ): የእኽል ስም። ዳቦና እንጀራ የሚኾን የብር እኽል። "አምኜ፡ አቶሳል፡ ጐዣሜ፡ ጣይ፡ ሶራ፡ ዐዛዜ፡ መንዜ፡ ሸመጥ፡ ተኸሬ፡ ከዚህም በቀር ብዙ ዐይነት ስንዴ አለ።" "(ተረት) ስንዴ በጭንቅ፡ ባለጌ በጥብቅ።"
ስንዴ፡ ማና፡ የነጭ ገብስ ስም። "እንጀራው የስንዴ መና የሚመስል።"
ስንድቅ፡ የተሰነደቀ፣ የታሰረ ነዶ። "(ጥሰ) መሰንደቅ፡ መታሰር፡ መጓዝ።"
ስንድድ፡ አለ፡ ቀጥታ ኾነ፣ አማረ (አፍንጫው)።
ስንድድ፡ ከተረከዝ ተያይዞ በስተላይ ያለ ሥር።
ስንድድ፡ የስንደዶ ቀለበት፣ የዦሮ ደግፍ መድኀኒት።
ስንድድ፡ የተሰነደደ፣ ሰመግ።
ስንድድ፡ ጨሌ፡ የሴት እጅና እግር ጌጥ፣ መጋረጃና የመሶብ ቀሚስም ይኾናል።
ስንገላ፡ ፍግፈጋ፣ ውልወላ።
ስንጋት፡ ስነጋ፣ የመሰነግ ሥራ። "(ጥሰ) መሰነግ፡ መበሳት፡ መቀርቀር፡ መጨነቅ፡ መታሰር።"
ስንግ፡ የተሰነገ፣ አፍንጫው ዋ፣ በስናግ የተያዘ (በሬ፣ ዶሮ)።
ስንግ፡ የንግዴ ልጅ (የሴትን ማሕፀን በወሊድ ጊዜ ሰንጎ የሚያስንቅ)።
ስንግል፡ የተሳለ፣ የተሰነገለ፣ ውልውል፣ ጥሩ ብልጭልጭ፣ ባለስለት መሣሪያ። "(ጥዕ) መሰንገል፡ መወልወል፡ መጠረግ።"
ስንጥ፡ የተሰነጠ፣ ያማረ፣ ልዝብ።
ስንፈጣ፡ ስርነቃ፣ ስርሰራ፣ ልብለባ።
ስንፍ፡ ስንፍና፡ ስንፈት፡ ሥራ መፍታት፣ ሰነፍነት (ምሳሌ ፳፮፡ ፬፡ ፭። ማርቆስ ፯፡ ፳፪። ፩ኛ ቆሮንቶስ ፩፡ ፳፡ ፳፩፡ ፳፫፡ ፳፭)።
ስንፍ፡ አለ፡ ሰነፈ።
ስንፍ፡ የዶባ ላም (የጋለሞታ እንዲሉ።)
ስንፍ፡ ገባው፡ ስንፍና አደረበት፣ ተጠቃ።
ስዒሮኪ)፡ "በታችኛው ወግዳ ውስጥ ያለ ቀበሌ። ሸመትሽን ወስዶብሽ ወይም ያንቺ ሽሮ ማለት ነው።"
ስኣ: የኢፍ ፫ኛ።
ስከላ፡ አሰራ፣ የመሰከል ሥራ።
ስካራም፡ ዘወትር ሰክሮ የሚታይ፣ ሳይስክር የማይውል ሰው፣ ቅዠታም። "ሰካራም፡ ማለት፡ ግን፡ ያልታረመ፡ ዐማርኛ፡ ነው።" "ስካር፡ ልብ፡ አያሳጣም፡ ቍርሾን፡ ያናግራል፡ ቂምን፡ ይገልጣል።"
ስካር፡ የመጠጥ እብደት፣ ቅዠት። "ስካር፡ ሰውን፡ ከእንስሳ፡ በታች፡ ያደርጋል፡ የሚሰክርም፡ ሰው፡ በቁሙ፡ የሞተ፡ ነው።"
ስክ (ስኩዕ): የተሰካ፣ የተሻጠ። "ስክ፡ መዝጊያ፡ እንዲሉ።"
ስክል (ሎች): የተሰከለ፣ የታሰረ (ፈረስ፣ በቅሎ፣ ግመል፣ አህያ)።
ስክል፡ አስተካክል።
ስክረት፡ መስከር፣ ሰካርነት።
ስክር (ስኩር): ስካሪ፣ የሰከረ።
ስክር፡ አለ፡ ጥንብዝ አለ።
ስክርክር: የውሃ እድፍ፣ ዝቃጭ፡ አተላ ወይም ቍሻሻ።
ስክርክር: የውሃ ዝቃጭ።
ስክተት (ሰክተተ): ዝርግ ጠፍጣፋ ሉሕ፣ የወጋግራ መቆሚያ። "ክባስን፡ እይ።"
ስወራ (ስዋሬ): ሽፈና፣ ክለላ፣ ድበቃ።
ስዊስ፡ በፈረንሳይና በጀርመን በጣሊያን መካከል ያለ አገር፣ ሰዓት የሚሠራበት። "ሕዝቡ በ፫ ኣንጻር ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛ፣ ጣሊያንኛ ይናገራል።"
ስውር (ሮች): የተሰወረ፣ የማይታይ፣ ድብቅ (ፈጣሪ፣ መልአክ፣ ሰይጣን፣ ነፍስ) (መዝሙር ፲፩፣ ፪። ማቴዎስ ፯፡ ፬፥፯)። "ረቂቅ ነገር፣ ምስጢር፣ የቀሚስ፣ የጋቢ፣ የኩታ ስፌት።" "ዐይንን፡ ተመልከት።"
ስውር፡ ቦታ፡ ድብቅና ሽሽግ ስፍራ።
ስውር፡ አለ፡ ድብቅ አለ፣ ዕቡ ኾነ።
ስየማ፡ ስያሜ፣ ስም አጠራር።
ስያፍ፡ ቀጥታ ያይደለ፣ ከታች ሰፊ ከላይ ቀጪን፣ ሾጣጣ ወይም ጐደሎ የኾነ ዕቃ፣ ልብስ። "መቅንን፡ ተመልከት።"
ስይም (ስሙይ): የተሰየመ፣ እከሌ የተባለ።
ስይም፡ ልብም ሠየመ።
ስይጣኔ፡ ዝኒ ከማሁ (ተንኰለኛነት)።
ስይፍ፡ የተሰየፈ፣ ዐንገቱ የተቈረጠ።
ስደራ፡ ድርደራ፣ ኵልኵላ።
ስደተኛ (ኞች) (ዘፍጥረት ፳፰፡ ፩። ዘፀአት ፳፫፡ ፱): በስደት ያለ፣ የኖረ፣ ላገሩ እንግዳ፣ ለሰዉ ባዳ፣ ባይተዋር፣ መጻተኛ። "(ተረት)፡ ሐሰተኛ፡ በቃሉ፡ ስደተኛ፡ በቅሉ፡ (ይታወቃል)።"
ስደት፡ መሰደድ። "ስደት፡ ለወሬ፡ ይመቻል፡ እንዲሉ።"
ስዱብ፡ የተሰደበ፣ ውርፍ፣ ንቁፍ።
ስዱኝ፡ ስደዱኝ።
ስዱኝ፡ አለ፡ ሰውን ለመጣላት፣ ለመምታት ተዉኝ፣ ልቀቁኝ አለ።
ስዱዳም፡ የስዱድ ወገን፣ ስዱድ ያለበት።
ስዱዳን፡ ስደተኞች።
ስዱድ፡ የተሰደደ፣ ካገሩ ወጥቶ የኼደ፣ ፈላሻ።
ስዳጅ፡ መረን፣ የመከር መካተቻ፣ የካቲት።
ስድ፡ ልቅ፣ አግድሞ አደግ፣ ባለጌ።
ስድሳ፡ ስሳ (፰): የቍጥር ስም። "ባምሳና በሰባ መካከል ያለ ያሥር ቤት አኃዝ፣ ስድስት ጊዜ ዐሥር ወይም ዐሥር ጊዜ ስድስት።"
ስድስ፡ የተሰደሰ።
ስድስተኚት፡ ስድስተኛዪቱ ክፍል፣ ስድስት አደረገ፣ እስከ ስድስት ቈጠረ፣ በስድስት ከፈለ። "(ጥሰ) መሰደስ፡ ስድስት፡ መኾን።"
ስድስት (፮): ባምስትና በሰባት መካከል ያለ ቍጥር ያንድ ቤት። "ስድስተኛ፣ ስድስተኛው እያለ ተራ ቍጥር ይኾናል።"
ስድስት ዐሥር: ሰደሰ።
ስድስትነት፡ ስድስት መኾን።
ስድስትያ፡ ስድስት መቶ ድር።
ስድስትያ፡ ከስድስት አንድ።
ስድስቶ፡ ች፡ ባንድነት ጅብ ብለው የሚታዩ ኮከቦች፣ ስድስትነት ያላቸው።
ስድራ (ትግ): ባል፣ ሚስት፣ ልጆች፣ ቤተሰብ።
ስድራት፡ ድርድራት።
ስድር፡ የተሰደረ፣ ድርድር፣ ክልል።
ስድብ፡ ዘለፋ፣ ነቀፋ (ሕዝቅኤል ፳፪፡ ፬። ማርቆስ ፯፡ ፳፪)። "በሌባ ቤተሰብ ላይ የተነገረ (ስድብ)።" "የሚስቱ ባልትና ኺዱ ምን አለና የማጭዱ ስም ተው ቈያ ይጨልም የልጆቹ አልተኙም ሰዎቹ።"
ስጃራ (ዐረ): በወረቀት ተጠቅሎ ፊሱ የሚጠጣ ደረቅ ትንባኾ። "(የገለሞታ ግጥም)፡ ስጃራ እማይጠጣ ትንሽ ልጅ ወድጄ በምን አመካኝቶ ይደርሳል እደጄ።" "በፈረንጅኛ ሲጋሬት ይባላል።"
ስጃጃ (ስጋጃ): የፉቅራ፣ የቃልቻ መቀመጫ ምንጣፍ።
ስጕድ: የንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ ፈረስ ስም። "አባ ሰጕድ ወልዴ እንዳለ አዝማሪ።"
ስጋጃ (ጆች): (ዐረ፡ ሱጋጃ)፣ ከጠጕር ከቃጫ የተዘጋጀ ምንጣፍ፣ መስገጃ፣ መቀመጫ፣ ግብረ መርፌ፣ የፋርስ ሥራ (ምሳሌ ፴፩፡ ፳፪)። "ስጋጃና ወላንሳ እንዲሉ።"
ስግ: የሰጋ፣ ሠጋ።
ስግ: የተሳገ ዕንጨት።
ስግሰጋ: የመሰግሰግ ሥራ፣ ስብሰባ ዕቃ።
ስግስጋት: መጠጋጋት።
ስግስግ አለ: ጥቅጥቅ አለ።
ስግስግ: የተሰገሰገ፣ የተቀራረበ።
ስግብግብ (ቦች): የተስገበገበ፣ ችኵል፣ ጥዱፍ፣ ቀቀበታም፣ ሰላፍ።
ስግብግብ አለ: ተስገበገበ።
ስግደት: መስገድ፣ ሰገዳ፣ መውደቅ፣ መነሣት።
ስግደዳ: ምለሳ፣ ስብሰባ፣ ድበቃ፣ ስውራ።
ስግድድ አለ: ድብቅ አለ፣ እንደ ዔሊ።
ስግድድ: የተሰገደደ፣ ሰዋራ፣ ድብቅ ስፍራ፣ ገለልታ።
ስጐደብ፡ ማስማስ፣ ማስጐድጐድ።
ስጥ (ስጡሕ): የተሰጣ፣ ዝርግ፣ ስትር፣ ለፀሓይ የተሰጠ ቅይጥ።
ስጥ፡ አቀብል፣ ሰጠ።
ስጥ፡ የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ፣ አቀብል፣ አስረክብ።
ስጥ፡ የተሰጣ (ሰጣ)።
ስጥም (ስጡም): የሰጠመ፣ የዘቀጠ፣ ጥልም።
ስጥም፡ አለ፡ ስጠሙ።
ስጦታ፡ ስጥወታ፡ መስጠት፣ ችሮታ፣ ልገሳ (ዘፀአት ፴፭ ' ፭። ምሳሌ ፳፭ - ፲፬። ሮሜ ፭ ' ፲፭፡ ፲፯)። "በሴት ለመናገር ብትፈልግ ስጦታዋ፣ ስጥወታዪቱ ያች ስጥወታ በል (ሮሜ ፭፡ ፲፮)።"
ስጦታዋ፡ የርሷ ስጦታ። ቀረ ብለኸ ይቅርታን እይ።
ስፋት፡ ሰፊነት፣ ጐን።
ስፌት፡ "ካክርማ ከስንደዶ ከአለላ ከግራምጣ የተሰፋ ሰፌድ፣ ቍና፣ ጕርዝኝ፣ እንቅብ፣ መሶብ፣ ሌማት፣ ሙዳይ፣ አገልግል፣ ጮጮ፣ ጕብ የመሰለው ኹሉ።"
ስፌት (ቶች) (ስፍየት): መስፋት። "እከሊት፡ ስፌት 'ታውቃለች።"
ስፌት፡ የሸማ፣ የሱሪ፣ የበርኖስ፣ የዐጽፍ የማንኛውም ልብስ መጋጠሚያ። "ደርዝ፡ ተኵስ፡ ውስውስ፡ ስፌት፡ እንዲሉ።"
ስፌት፡ ጥልፍ፣ ዝምዝማት። ማሪያምን፡ አስተውል።
ስፌትን ጥምጥምን ፈታ: ለየ፣ ክርን፣ ሢርን መዘዘ፣ በጠሰ።
ስፍ (ስፉይ): የተሰፋ፣ ድርዝ፣ ዝም።
ስፍ (ስፍይት): የሐረርጌ ኦሮና የሱማሌ ልጃገረድ የተሰፋች።
ስፍሕ፡ ድር፣ ዝሓ (ግእዝ)። ምስጢሩ፡ ስፋትና ዝርግነት ነው።
ስፍረ፡ ሰዓት፡ ሰው ጥላውን በማው እየሰፈረ የሚያውቀው የሰዓት ቍጥር።
ስፍራ (ዎች): ቦታ፣ ቀበሌ (መዝሙር ፻፴፭፡ ፪)።
ስፍር (ስፉር): የተሰፈረ፣ የተለካ (ቅጽል)።
ስፍር፡ ልክ፣ መጠን። "ስፍር የሌለው፣ ስፍር ቍጥር እንዲሉ (ስም)።"
ሶለላ (ጸለለ፡ ጋረደ): አግሬ (፩ኛ ዜና መዋዕል ፲፪፡ ፲፡ ፴፬። ፪ኛ ዜና መዋዕል ፲፩፡ ፲፪)።
ሶለላ: ወሰራ (ጐም)።
ሶለሶለ)፡ አንሶለሶለ፣ እዞረ፣ እንቀዠቀዠ፣ አንቀለቀለ።
ሶለሶል፡ ሶልሷላ፡ ሶልሶልቱ፡ የተንሶለሶለ፣ የሚነሶለሶል፣ ዘዋሪ።
ሶለግ (ጎች) (ሰለከ): ከግንዶሽ በላይ ከቍግ በታች ያለ የጅራፍ ክፍል። "ከታች ወደ ላይ እየቀጠነ ይኼዳል።" "ሾለቅን፡ ተመልከት።"
ሶለግ፡ ውሻ፡ ቀጪን ረዥም የፈረንጅ ውሻ፣ ሽንጣም ዐዳኝ።
ሶለግ፡ የውሻ ቅጽል ነው።
ሶል፡ ፀሓይ፣ ጀንበር (ሮማይስጥ)።
ሶል)፡ ፀሓይ ጧት በምሥራቅ፣ ቀትር ሲኾን በሰማይ መካከል። ማታ በምዕራብ እንድትታይ፤ ይህም እንደዚያ ማለት ነው።
ሶልዲ፡ ገንዘብ (ጣሊያንኛ)።
ሶማያ፡ (ሰው፡ ማያ): በላይ ጦር በታች ጀንፎ የተዋደደበት ዘንግ፣ ጠዬ ወይም ሌላ ዕንጨት። "በጐዣምም ብዬ (ሰፋ) ሱማያ ይባላል።"
ሶስና: የሴት ስም። "አበቡት ማለት (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ)።"
ሶረናዊ: የሶረን፣ ፍጹም ቅላት ያላት የቈላ ቆቅ።
ሶሪት ቀይ ወፍ: ሶራ።
ሶሪት: የእንስት በግ ስም።
ሶራ: በአረብኛ ጹራ፣ በዕብራይስጥ ጹራት ይባላል (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ)።
ሶሮሮ: ነጭ ጤፍ።
ሶብይ: ጐበዝ፣ ጕልማሳ፣ ወጣት፣ ሦታ።
ሶከሶከ)፡ አሶከሶከ፣ በዝግታና በሩጫ መካከል ያለ ኣካኼድ ኼደ (ውሻው)።
ሶክሷካ፡ የተንሶከሶከ፣ የሚንሶከሶክ።
ሶዳ፡ የመጠጥ ስም። "ጠርሙሱን ሲከፍቱት የሚጨስ፣ የሚፈላ ቀላል የባሕር አገር መጠጥ።"
ሶፍያ፡ ሕልመ ዝሙት፣ ተጻብኦ። "በሴት አምሳል የሚታይ ምትሀት፣ ፍትወታዊ የሰይጣን ጥበብ። ሶፍያ መታችኝ እንዲል ተማሪ። አራተኛውን ጠባ እይ።"
ሶፍያ፡ የሴት ስም፣ የጽርእ ሰማዕት።
ሶፍያ፡ ጥበብ ማለት ነው።
No comments:
Post a Comment