ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ነ ፡ ፲፬ኛ ፊደል በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ (በፊደልነት ስሙ "ነሐስ" በአኃዝነት "፶" ይባላል) ።
ነ፡ በጫፉ ዝርዝር እየጨመረ ነባር አንቀጽ ይኾናል ("ነውን" እይ) ።
ነ፡ አገዛዝ አጸና፡ ከነ
ነ፡ ዝርዝር፡ ን።
ነ፡ የለ ተለዋጭ ከግእዝ ወዳማርኛ ("ወልድ/ወንድ") ።
ነ፡ የረና የመ ተለዋዋጭ ("አጠናቀረ/አጠራቀመ"፡ "ንስር/ምስር") ።
ነሐሴ፡ የወር ስም (ናሴ ፲፪ኛ ወር ሥሩ በግእዝ ነሐሰ ነው) ።
ነሐስ፡ የፊደል ስም ነ (ሽቦ ማለት ነው) ።
ነኈረጥ/ነኍራጣ፡ የተነኋረጠ/የሚነኋረጥ።
ነኆለለ፡ ደነቈረ፡ነኾለለ።
ነኆረጠ (ንኅረ)፡ ነፍናፋ ኾነ (ባፍንጫው ተናገረ - "ሖረጠን" እይ) ።
ነምሳ፡ በአውሮፓ እጀርመን አጠገብ ያለ አገር።
ነሰረ (ነሲር/ነሰረ)፡ ወረደ/ፈሰሰ ' ደሙ ።
ነሰረ፡ በዛ/ፈደፈደ/ተንጣለለ ("ይህ ወጥ ቅቤ ነስሮታል።")
ነሰረ፡ ከሰማይ ቍልቍል ተወረወረ አሞራው ።
ነሠረ፡ ወረደ፡ነሰረ።
ነሰረኝ፡ ወረደኝ/ፈሰሰኝ ("ዛሬ ፀሓይ መታኝና ነሰረኝ") ።
ነሰበ (ዐረ. ነጸበ)፡ ዐደለ/ዕድል ሰጠ።
ነሠበ፡ ዐደለ፡ነሰበ።
ነሠተ፡ ነዘነዘ (በቀተ አስቸገረ) ።
ነሰነሰ (ነስነሰ)፡ በቀላል/በተነ ዘራ ' ጐዘጐዘ ("እከሌ ወዳጁ ስለ ሞተ ማቅ ለብሶ ዐመድ ነስንሶ ተኛ" - ፩ሳሙ. ፩፥፲፪፡ ኤር. ፮፥፳፮ " ማቴ. ፲፩፥፳፩፡ ራእ. ፲፰፥፲፱) ።
ነሰነሰ፡ ወዘወዘ/አንቀሳቀሰ ("ውሻ ጌታውን ባየ ጊዜ ዥራቱን ይነሰንሳል" - "ቈላን" እይ) ።
ነሲቡ (አፈ ንጉሥ ነሲቡ)፡ ያጤ ምኒልክ የፍርድ አንደራሴ ልጅ (አባቱን በኀጢአት ከሶ በርሳቸው ዳኝነት በረታ ጊዜ ያባት ዕዳ ለልጅ ነውና ጣለው ብለው በተወራረደበት አርባ ጅራፍ ልጁን ገረፉ። ዳግመ ኛም አንድ ሰው አንዷን ሴት ላንድ ሌሊት ባንድ አሞሌ ተዋውሎ ወሰዳትና ሚስት ኹና ፴ ዓመት ከተቀመጠች በኋላ አንድ አሞሌ ሰጥቶ ባባረራት ጊዜ ላፈ ንጉሥ አቤት እለች እሳቸውም ነገሩን ሽማግሌ ይየው ቢ ሉት እንቢ ስላለ በወር ፴ ሒሳብ ፩፻፻፰፻ (ዐሥር ሺ ስምንት መቶ) ጨው እንዲሰጣት ፈረዱበትና ትዳሩን ለቆ ኼደ ይባላል) ።
ነሲቡ፡ የሰው ስም ("ለአባቱ ዕድሉ ኹኖ የተሰጠው" ማለት ነው) ።
ነሲብ፡ ዕድል (ግምት - "በነሲብ ግዛ" እን ዲል እስላም) ።
ነሣ (ነሥአ)፡ ከለከለ/ወሰደ/አራቀ ("እግዜር ሰጠ እግዜር ነሣ - የሰጠ ቢነሣ የለበት ወቀሣ - ሥጋ ሰጥተው ቢላዋ ነሡ - ለፈሪ ሜዳ አይነሡም - (የባልቴት ግጥም) እኒህ ሥሙ ለዝናም ጌታ ውሃ ነሡ" - "ድ ልን ኅብርን ፊትን" ተመልከት) ።
ነሣ፡ ቀነሰ/አጐደለ ("(ሥጋ ነሣ)" - ተፀነሰ ሰው ኾነ ሥጋ ለበሰ) ።
ነሣ፡ ተቀበለ/ወሰደ ("ይህ ኅብስት ሥጋዬ ነው í ንሡ ብሉ እንዳለ ጌታ በወ ንጌል") ።
ነሣ፡ ቻለ/ወሰነ (፪ዜና. ፪፥፮) ።
ነሣ፡ ያዘ/ጨበጠ ("በ፳፮ኛ ተራ እጅን" አስተውል) ።
ነሣሣ፡ ወሳሰደ/ቀናነሰ/አጐዳደለ ("ነሣሣለትና አመጣው" እንዲል ተርጓሚ) -
ነሳነሰ፡ በታተነ ' ጐዛጐዘ ።
ነስር፡ ካፍን የሚወርድ የደም ፈሳሽነስር ።
ነስናሽ (ሾች)፡ የነሰነሰ/የሚነሰንስ (በታኝ ጐዝጓዥ ወዝዋዥ) ።
ነረተ፡ መታ/ጠሀለ/ደበደበ።
ነረተ፡ ነፋ/ቀበተተ (ሆድን) ።
ነረነረ)፡ ነርነር አለ፡ በኀይል ተሰማ ' ወፍራም ድምጥ ሰጠ (በገናው ከበሮው) ።
ነራች፡ የነረተ/የሚነርት (ነፊ መቺ) ።
ነርነርቱ፡ ኣደዝዳዥ ' አነጥናጭ (ዐፍለኛ ኰረዳ) ትር።
ነሸቀ ' ነሰቀ)፡ ተናሸቀ፡ በክፉ ፥ ተጋጠመ ' ተጣላ ' ተቀያየመ ' ተናሸረ ("በሸቀን" ተመ ልከት) ።
ነሸጠ፡ አሳሰበ/አነሣሣ (ጠብን መጥፎ ነገርን "በል በል" አለ - "ሸፈጠን" አስተውል) ።
ነሸጥ፡ ሸፈጥ።
ነሺ፡ የነሣ/የሚነሣ (ከልካይ ተቀባይ ወሳጅ) ።
ነሺነት፡ ከልካይነት/ተቀባይነት።
ነሽ (ነየኪ)፡ አንቺ ነሽ አለሽ።
ነሽ፡ የቅርብ ሴት ነባር አንቀጽ ("ውን" እይ) ።
ነቀለ (ነቂል/ነቀለ)፡ መዘዘ/መነገለ/ኣፈለሰ/አነıለ/አወጣ/አወለቀ (ያበባ እኸልን እንግጫን ጥርስን የእጅና የእግር ዐጥንትን ማንኛውንም ነገር) ።
ነቀለ፡ ሰውን ከርስቱ ከመሬቱ ላይ አራቀ/አስወገደ።
ነቀለ፡ ኣነሣ/ያዘ።
ነቀለ፡ እግሩን አነሣ (ስፍራ ለቀቀ) ።
ነቀላ፡ የመንቀል ሥራ (መዘዛ) ።
ነቀል ተከል፡ የዘላን ጐዦ ።
ነቀል፡ ዝኒ ከማሁ ("ለነቃይ" - ያነሣ የያዘ - "ብር ነቀል ጦር ነቀል" እንዲሉ) ።
ነቀልቃል፡ ወላፈን ነበልባል ነብ ነድ (ግእዝ) ።
ነቀምቴ፡ የነቀምት ተወላጅ (የነቀምት ሰው - "ነቀምቴ በጋልኛ ተከተተች" ማለት ነው) ።
ነቀምት፡ የከተማ ስም (በወለጋ ክፍል ያለ አገር - ዐማሮች ግን ለቀምት ይሉታል) ።
ነቀሰ፡ መሰከረ (ያየውን ተናገረ ነገርን አሻሻለ "ይኸ ቢኾን ይኸ ነው" አለ) ።
ነቀሰ፡ ቀነሰ (ዋጋ አጐደለ - "ነቀሰ ዐረብኛ" - ቀነሰ ዐማርኛ ነው) ።
ነቀሰ፡ እሾኸን ነቀለ/አወጣ ("ሾኸን" እይ) ።
ነቀሰ፡ ወርቅንና ብርን ዕንጨትን የጌጥ ዕቃን አስጌጠ/ሸለመ ።
ነቀሰ፡ ጠቀጠቀ/ወቀረ/ወጋ/አጠቈረ (ጥርስን ገላን - "(ተረት)" - ያልወጋኝ ነቀሰኝ) ።
ነቀሰ፡ ጠጕርን አበጠረ (ጥጥን አጠራ ሰውነቱን አሳመረ) ።
ነቀሳ/ንቅሻ፡ የመንቀስ/የማጥራት የ ማበጠር ሥራ።
ነቀስ፡ ዝኒ ከማሁ ("ለነቃሽ") ።
ነቀረ)፡ አነቀረ፡ ጠጠ/አጝጠጠ ' ጨለጠ (ጨርሶ ቀዳ - "መነቀረን" እይ - የዚህ መስም ግስ ነው) ።

ነቀርሳ፡ የቍስል ስም (የሰውን ገላ የሚነድል ደምን የሚያነቅር በሽታ - ኹለተኛ ስሙ ምሽሮ ነው) ።
ነቀሸ፡ ተሰበረ/ተቀለጠመ ።
ነቀበ፡ በሳ/ነደለ (ስፌት ሰፋ) ።
ነቀተ ' ነከተ)፡ አነቀተ፡ ከረተፈ ፈ ቀቀለ (እንቀትን) ።
ነቀተ ' ነከተ)፡ አነቀተ፡ ከረተፈ ፈ ቀቀለ (እንቀትን) ።
ነቀነቀ (ትግ. ቀንቀነ)፡ ቀሰቀሰ/ወዘ ወዘ/ናጠ/አናወጠ/አንገሸገሸ (ሰውን ዐልጋን ሀንገትን ራስን - ኢሳ. ፲፫፥፲፫ - "በግእዝ መሠረቱ ነክነክ ነው" - "ነከነከን" እይ) ።
ነቀነቀ፡ ሰበቀ ጦርን።
ነቀነቀ፡ ሰበቀ ጦርን።
ነቀነቅነቅናቃ፡ የተነቀነቀ/የተወዘወዘ ወዝዋዛ ።
ነቀዘ (ነቅዘ)፡ ጠነጠነ (ዐመድ ኾነ - "ብሳና ይነቅዛልን ቢሉ ለንጩት ኹሉ መንቀዝን ያስተማረ ማነው" - "(ተረት)" - ዝም አይ ነቅዝም) ።
ነቀዛም፡ ነቀዝ ያለበት (ባለነቀዝ " ንቅዝ (ንቁዝ)" - የነቀዘ ጥንጣኁ የበ) ።
ነቀዝ (ዞች) (ቍንቍኔ)፡ ከንጨት ባሕርይ የሚፈጠር ትል (ወይራን ጥድን ኮሶን ዋንዛን ዝግባን አርዝን ሀሎን የማይመስ ለውን ዕንጨት ኹሉ ውስጥ ውስጡን በልቶ ዐመድ ያደርጋል ዳግመኛም ጥንጣን ይባላል) ።
ነቀዝ (ፃፄ)፡ ከእኸል ውስጥ የሚፈጠር ባለክንፍ ተንቀሳቃሽ (ከቅማል ከፍ ይላል ጥሬ እኸልን ያበላሻል - ማቴ. ፮፥፳) ላው።
ነቀዝ፡ ሆዳም በላተኛ ሰው።
ነቀደ (ደነቀ)፡ ትግ. አንቀደ (ዐሰበ ' ተጋ)፡ ዘየደ ድንቅ አደረገ፡ ተናገረ፡ ተረከ።
ነቀፈ (ነቂፍ/ነቀፈ/ቀረፈ)፡ የሰ ውን ስምና ግብር አጥላላ/ሰደበ (ዋጋና ክብር ኣሳጣ ናቀ አቀለለ አጸየፈ አነወረ ተቈጣ ገሠጸ ወቀሠ ዘለፈ - ፫ኛውን ዐቀፈ እይ) ።
ነቀፋ/ነቀፌታ/ንቅፊያ/መንቀፍ፡ ስድብ/ንቀት/ቍጣ/ወቀሣ።
ነቍጣ፡ በበግ በፍየል ገላ ላይ ያለ ጥቃቅን ነጠብጣብ (ንጣት ነጭነት - ዘፍ. ፴፥፴፭) ።
ነቍጣ፡ ዝኒ ከማሁ (ዐረብም አንዱን ጠብታ ኑቅጣ ይለዋል) ።
ነቍጥ (ጦች)፡ የነጥብ ስም (የቃል የንባብ መለያ ኹለት ጠብታ () አራቱም ጦብታ (.) ነቍጥ ይባላል) ።
ነቂ (ነቃሂ)፡ የሚነቃ/የሚተጋ።
ነቂስ፡ ኹሉ ምሉ ጠቅላላ።
ነቃ (ነቂህ)፡ መንቃት። ነቃ አለ፡ ጠንቀቅ አለ።
ነቃ (ነቅሀ)፡ ተቀሰቀሰ (ከእንቅልፍ ተነሣ ብንን አለ - ፩ነገ. ፫፥፲፭) ።
ነቃ (ነቅዐ. ዕብ. ናቃቅ)፡ በጥቂቱ ተሠነጠቀ/ተተረተረ (የተረከዝ የንጨት የግንብ - "(ግጥም)" - ብርሌ ከነቃ ኣይኾንም ዕቃ) ።
ነቃ በል፡ ጠንቀቅ በል/ትጋ።
ነቃ፡ ተጋ/ተጠነቀቀ።
ነቃ ነቃ አለ፡ ሰውነቱን ጠበቀ በልብስ ጽዳት።
ነቃ፡ ወጣ/መነጨ/ፈለቀ/ተገኘ።
ነቃላ/ንቅል/ንቁል፡ የተነቀለ/የተ መዘዘ/የተመነገለ።
ነቃሽ (ሾች)፡ የነቀሰ/የሚነቅስ ("ጠ ጕር ነቃሽ ጥርስ ነቃሽ" እንዲሉ) ።
ነቃሽ፡ መስካሪ/ምስክር (እውነትን ከሐሰት ነቅሶ (ለይቶ አጥርቶ) የሚናገር) ።
ነቃሽነት፡ ነቃሽ መኾን (ምስክርነት) ።
ነቃሾች፡ ምስክሮች ።
ነቃቀለ፡ መዛዘዘ/መነጋገለ።
ነቃቃ፡ ተሠነጣጠቀ።
ነቃዥ፡ የነቀዘ/የሚነቅዝ (ዕንጨት እ ኸል ሣር) ።
ነቃይ ተካይ፡ ሰውን ከምድርና ከሥራ ላይ የሚተክልና የሚነቅል ሹም ዳኛ ባለሥልጣን ።
ነቃይ(ዮች)፡ የነቀለ/የሚነቅል ("ዐተር ሽንብራ ተልባ ምስር ጓያ ድንኳን ነቃይ" እንዲሉ) ።
ነቃፊ(ዎች)፡ የነቀፈ/የሚነቅፍ ሰዳቢ።
ነቃፊ(ዎች)፡ የነቀፈ/የሚነቅፍ ሰዳቢ።
ነቈረ (ነቍር/ነቈረ)፡ ጠቅ አደረገ ' ነከስ ወጋ በሳ ቀደደ።
ነቈጠ (ነቍጠ)፡ ነጠበ (ጠብ አለ) ።
ነቅ (ነቅዕ)፡ ዝኒ ከማሁ (እንከን - ቄስ ነቅ የሌለበትን ኅብስት መርጦ ወደ መንበር ያቀርባል) ።
ነቅ፡ ምንጭ/መነሻ።
ነቅናቂ(ዎች)፡ የነቀነቀ/የሚነቀንቅ (ወዝዋዥ ") ።
ነቅናቂ(ዎች)፡ የነቀነቀ/የሚነቀንቅ (ወዝዋዥ ") ።
ነቅዐ ኀልዮ፡ የማሰብ መገኛ ልብ።
ነቋሪ፡ የነቈረ/የሚነቍር።
ነቋራ (ነቋር)፡ አንድ ነገር ያነቈረው ' ኣንድ ዐይና።
ነበልባል፡ ለፍላፊ ተናጋሪ አፈኛ ሰው ።
ነበልባል፡ የእሳት ላንቃ፡ በለ በለ።
ነበልባል፡ የእሳት ላንቃ፡ ነዲዱ ነቡ ብርሃኑ ወላፈኑ ።
ነበልባሎች፡ ወላፈኖች ለፍላፊዎች ።
ነበረ (ነቢር/ነበረ)፡ አለ/ኖረ/ቈየ/ተቀመጠ (ዮሐ. ፩፥፩, ፪ - "እግዜር ከዓለም አስቀድሞ ነበረ" - "አለኝ እንጂ ነበረኝ አይጠቅምም") ።
ነበረ፡ በ፱ ፥ ሰራዊት ሲዘረዘር ይላል።
ነበረረ (ነበረ)፡ አንዱ ረ ተቀጽላ ነው (ፈጽሞ አረጀ ከሳ ደረቀ ሰውነቱ ሰለለ ድምጡ ብዙ ዘመን ከመኖር የተነሣ - ዠበረረን እይ) ።
ነበረር፡ ነብራራ (የነበረረ/የሚነበርር ዠብራራ) ።
ነበረሽ፡ አለሽ/ኖረሽ።
ነበረን፡ አለን/ኖረን።
ነበረኝ፡ አለኝ/ኖረኝ።
ነበረኸ፡ ኣለኸ/ኖረኸ።
ነበረው፡ አለው/ኖረው።
ነበረዎ፡ አለዎ/ኖረዎ።
ነበራርት (ቶች)፡ የነብር ዲቃላ (ነብር የሚመስል ጥቍረትና ንጣት ቅላት አለው) ።
ነበራት፡ አላት/ኖራት።
ነበራቸው፡ አላቸው/ኖራቸው።
ነበራችኹ፡ ለናንተ ዕውቀት ነበራችኹ።
ነበር፡ በትንቢትና በቦዝ መጨረሻ እየገባ የቈየ የዘገየ ኀላፊ ይኾናል ("ዐውቅነበር"፡ "ዐውቄ ነበር" - መዠመሪያውን "አለ" እይ) ።
ነበር፡ ነበረ ("ከ የ ለ ሲሰማሙት ከነበር ከነበር ይሻላል - የነበረ የነበረ ገብሬል ተወገረ - ለነበር ለወግ ለታሪክ ለዝና - ለነበር ነው ይላል") ።
ነበርነ ባይ፡ ወገኛ።
ነበርና፡ አለና/ኾነና/ተደረገና።
ነበበ (ነቢብ/ነበ)፡ ተናገረ/አለ ("ያቶ እከሌ ቤቱ ነቧል") ።
ነበበ፡ ተሠነጠቀ/ተተረተረ (ራስ ቅሉ እንስራው - ኤር. ፵፮፥፳፪) ጋሪ።
ነበበ፡ ነደደ እሳቱ።
ነበበ፡ ከበረ/ገነነ።
ነበበ፡ ጮኸ/ተሰማ ከበሮው።
ነበነበ (ነበበ/ዐረ. ነብነበ)፡ ንብኛ ጮኸ (ባለማቋረጥ ተናገረ/ነዘነዘ - ነበነብ/ነብናባ፡ ነዘነዝ/ነዝናዛ/ለፍላፊ) ።
ነበዘ (ነቢዝ/ነበዘ)፡ ቀማ/ገፈፈ (ነበዘ፡ ልብ አሳጣ/ለወጠ - ነፈዘን ተመልከት) ።
ነበዘ፡ መረዘ ("ቀለሙ ልብሱን ነበዘው") ።
ነበዘ፡ ሰለበ/ቈረጠ።
ነበዘ፡ አከሳ/አገረጣ።
ነበዘው፡ ቀለመው/መረዘው።
ነበዘው፡ ቀማው/ገፈፈው።
ነበየ/ነባ)፡ አስነበየ፡ መጪውን አስነገረ/አስወራ።
ነበጀለ (ነበበ ጀለ)፡ ንባበ ጅል ነገረ በክ ኾነ (ነኈረጠ ቂልኛ ተናገረ - ጀለን እይ) ።
ነበጀል፡ ነኈረጥ።
ነቢ (ዐረ)፡ ነቢይ ("ካላህ አልኾንኩ ከነቢ" እንዳለ እስላም።
ነቢብ፡ መናገር (ግእዝ - "በነቢብ በገቢር" እንዲል ቄስ) ።
ነቢየ ሐሰት፡ ያላየውን አየኹ ያልስማውን ሰማኹ የሚል የሐሰት ነቢይ (፩ነገ. ፲፫፥፲፩, ፲፰, ፳፮, ፳፱) ።
ነቢየ ጽድቅ፡ የውነት ነቢይ።
ነቢያት፡ ቀድሞ ከሔኖክ በኋላም ከሙሴ ዠምሮ እስከ ጌታችን የነበሩ ትንቢተኞች (ትንቢት ተናጋሮች ደጋጎች ሰዎች ኀላፍያትንና መጻእያትን የሚያውቁ - በሕዝብ ኣነጋገር "ነቢያቶች" ይባላሉ) ።
ነቢያት፡ በዳዊት መዝሙር መጨረሻ ተጽፎ የሚገኝ ፲፭ የነቢያት ጸሎት።
ነቢይ፡ በቁሙ ያለፈውንና የሚመጣውን ዐውቆ የሚናገር ሰው ብቃት ያለው ("ነባይ" ዐማርኛ "ነቢይ" ግእዝ ነው - ነቢይን በሴት ለመናገር "ነቢዪቱ" ይላል - ሉቃ. ፪፥፴፮) ።
ነባ (ነብዐ)፡ መነጨ/ወረደ/ፈሰሰ እንባው።
ነባሪ (ዎች)፡ የነበረ/ያለ/የኖረ/የቈየ (የዳኛ አቀማማጭ ምስክር) ።
ነባሪ የዓሣ ቅጽል፡ ዓሣ።
ነባሪነት፡ ነባሪ መኾን (ኗሪነት/ተቀማጭነት) ።
ነባር (ሮች)፡ ነባሪ/ኗሪ (ሴትና ወንድ ያስተባብራል።)
ነባር አንቀጽ፡ በ፱ መደብ በኀላፊ ብቻ በራሱ ዝርዝር እየጨመረ የሚረባ ትንቢትና ዘንድ ትእዛዝ አንቀጽ የሌለው (ተቀማጭ የማይንቀሳቀስ ማለት ነው - "ነውን" እይ) ።
ነባር፡ ከአንቀጽ የማይወጣ ስም (ውሃን/ኣሞራን የመሰለ) ።
ነባቢ፡ የነበበ/የሚነብ/የሚናገር (ተናጋሪ) ።
ነባቢት፡ የተናገረች/የምትናገር ነፍስ።
ነባዛ፡ ከሲታ/መጣጣ ("ፊተ ነባዛ" እንዲሉ) ።
ነባዛ፡ የተነበዘ/የተቀማ (ልውጥ ልበ ቢስ - በግእዝ "እንቡዝ" ይባላል) ።
ነባይ፡ ደግ ጻድቅ የግርዜር ሰው
ነቤላ፡ በበረሓ የሚበቅል የምድር ፍሬ (ግመሎች ምግብነቱን የሚወዱት) ።
ነብ፡ የእሳት ላንቃ ("ጂ ጂ" የሚል ነድ) ።
ነብሩ፡ ያ ነብር (የርሱ ነብር) ።
ነብሩቴ፡ ሽልምልም ባቡቴ።
ነብሪድ፡ ዝኒ ከማሁ (ትግሮች ንቡረ እድን ነብሪድ ይሉታል) ።
ነብራም፡ ነብር ያለበት ዱር ባለነብር።
ነብር (ነምር)፡ ያውሬ ስም የታወቀ ዥጕርጕር አውሬ ቍጡ የፍየል ጠላት (ተባቱም እንስቱም - ተረት፡ "እንቅልፍ ታበዢ ከነብር ትፋዘዢ" - ሲበዛ "ነብሮች" ያሠኛል - ማሕ. ፬፥፰ - ነብር ሲርበው የሞተ መስሎ በዠርባው ይተኛና እጆቹን ወደ ላይ ያንጨፈርራል ጆፌ አሞራም በቀረበው ጊዜ ይዞ ይበላዋል) ።
ነብር ሳይዝ አይሞትም፡ አንድ ሰው ሳያጠፋ አይገደልም።
ነብር አጥማጅ፡ ነብርን በወጥመድ የሚይዝ (ስማርድን አስተውል) ።
ነብር ወለደች፡ በፀሓይ ዝናብ ሲጥል እረኞች "ነብር ወለደች" ይላሉ።
ነብሮ፡ ቃለ አክብሮ ("ነብር ሆይ" ማለት ነው - "አያ ነብሮ" እንዲሉ ልጆች በተረት) ።
ነብሮ፡ የሥጋ ስም (ንጣትና ብርንዶነት ያለው የጡንቻ ሥጋ) ።
ነብሮች ነብርማ (ነምራዊ)፡ ነብር የሚመስል (ፍየል ጠራጠርማ) ።
ነብሯ/ነብሩት፡ ያች ነብር።
ነብጃላ፡ ነኍራጣ።
ነተሰ፡ ነከሰ።
ነተሳ፡ ንክሻ።
ነተረረ፡ ቈረጠ።
ነተረከረከ፡ ተንከባለለ (እንደ ድንጋይ) ።
ነተረፈ፡ ተረፈ።
ነተረፈረፈ፡ በዛ/ተረፈረፈ።
ነተፈ፡ በጠበጠ/ነፋ።
ነታች፡ ነካሽ።
ነታፊ፡ ነፋፊ።
ነች/ናት (ነያ)፡ እሷነች/ናት እ ለች።
ነችሽ፡ ፡ የእንስት አህያ መጥሪያ ("ነ ነዪ ችሽ ቲውሽ የማለት ለውጥ ነው" - "ነችሽ ነችሽ አለ ኵርኵር አለ") ።
ነነ፡ ቀጠነ/አነሰ/አማረ።
ነነ፡ ነን (እኛ የሚሉ ወንዶችና ሴቶች ነባር አንቀጽ - "ነውን" ተመልከት) ።
ነነዌ፡ የ፫ ቀን ጦም (የነነዌ ሰዎች የጦሙት - ባላገር ግን ነይነይ ይላል) ።
ነነዌ፡ ያገር/የከተማ ስም (በእስያ ክፍል ያለች ጥንታዊት የአሶር ከተማ ዮናስ የሰበከባት) ።
ነነጭ፡ ነጭናጫ (የተነጫነጨ/የሚነጫነጭ ጨቅጫቃ ብስጩ) ።
ነን/ነነ (ነየነ)፡ እኛ ነን/ነነ አለን ነ።
ነኛ (አነኬ)፡ ቃለ አጋኖ ("አባት ልጆቹን ከናንተ ዛሬ የሚላከኝ ማነው ብሎ ሲጠይቅ ፈቃደኛው እኔ ነኛ ይላል") ።
ነኝ (ነየ)፡ እኔ ነኝ ኾንኹ አለኹ (ዮሐ. ፲፫፥፴፫) ።
ነኝ፡ እኔ የሚል/የምትል የወንድና የሴት ነባር አንቀጽ ("ነውን" እይ) ።
ነአኵተከ፡ ፪ኛ የዘወትር ጸሎት አባ ጊዮርጊስ የደረሱት።
ነአኵተከ፡ ፪ኛ፡ የዘወትር፡ ጸሎት፡ አባጊዮርጊስ፡ የደረሱት ።
ነከለ) ነቀለ፡ አነከለ (እግሩን ነቀለ አነሣ ዐነከሰ) ።
ነከሰ (ነሲክ/ነሰከ)፡ ዐኝ አለ/ዘነ ተረ/ዘበተረ/በላ/ቦጨቀ/ቦተረፈ/ዘከዘከ/ዘረ ከተ/ዘለዘለ/ዘተዘተ ("ዘረገፈን" ተመልከት - "(ጥርሱን ነከሰ)" - ጨከነ ዕመምን ቻለ ታገሠ - "(ከን ፈሩን ነከሰ)" - ዛተ አስፈራራ - "ገመጠን" እይ) ።
ነከሰ፡ ነደፈ/ጠቅ አደረገ ("እባብ ነከሰው ጊንጥ ነከሰው" እንዲሉ) ።
ነከሰ፡ ፈጽሞ ጠላ/መረዘ።
ነከሳ፡ መንከስ።
ነከረ (ነኪር/ነከረ)፡ ለየ/አስገለለ ("ምከረው ምከረው ባይሰማ ንከረው (ከሕዝብ ከማኅበር)" - ለየው - ተረት)
ነከረ (ጠምዐ)፡ ዘፈ/አራሰ/ዐለለ።
ነከረ፡ አጠመቀ/ዘፈቀ/አጠለቀ/ዘፈ
ነከረ፡ ጠለቀ/አጠቀሰ (ዮሐ. ፲፫፥፳፮) ።
ነከራ፡ ዝፍዘፋ።
ነከርት፡ ሞኝ/ቂል (ዘርፋፋ እቂልነት ባሕር ነክሮ ያወጣው ከብልኅ የተለየ) ።
ነከርት፡ ጥቍሬታ።
ነከርቶች፡ ሞኞች/ቂሎች (ጠባየ ልዩ ዎች) ።
ነከተ፡ ተሰበረ/ደቀቀ (አነሰ) ።
ነከነከ (ነክነከ)፡ አብዝቶ በላ ("በግእዝ ግን ወዘወዘ ማለት ነው ይኸውም የመ ንጋጋን መነቃነቅ ያሳያል።")
ነከነከ፡ ነዘነዘ መታ ("ሌሊት ዝናሙ ሲነከንከው ዐደረ") ።
ነከፈ (ትግ)፡ ለኰስ/አቃጠለ።
ነከፈ፡ ቈለ/ጀለ ("ነቀፈን" ተመልከት) ።
ነኪ፡ የነካ/የሚነካ።
ነካ (ነከየ)፡ ዳበሰ/ዳሰሰ/ደረሰ/ ጐነጠ (ድል አለ አቈሰለ ገጠበ በደለ - "አብ ሲነካ ወልድ ይነካ" - "እከሌን ጠላቶቹ ዐር የነካው ዕንጨት አደረጉት" - "ጐሸመጠን ጣቈሰን" ተመልከት) ።
ነካ (ነክይ)፡ መንካት።
ነካ ነካ አደረገ፡ ዳበስ ዳበስ አደረገ።
ነካ አደረገ፡ ዳበስ አደረገ ነካ።
ነካሪ፡ የነከረ/የሚነክር።
ነካሽ (ሾች)፡ የነከሰ/የሚነክስ (ዘንታሪ - "ዐዛዬን ነካሽ" እንዲሉ - "(ጠፍር ነካሽ)" - የፈረስ/የበቅሎ ዕቃ ሰፊ - የሥራ ፈቶች ዐ ማርኛ ነው) ።
ነካታ፡ የነከተ (ሰባራ) ።
ነካች፡ የሚነክት í ደቃቂ።
ነካከሰ፡ ዘነታተረ/ቦጫጨቀ።
ነካከተ፡ ተሰባበረ።
ነካካ፡ ደባበሰ መላልሶ ነካ።
ነክ፡ ዝኒ ከማሁ ("ጎላ ነክ ሰንበት ነክ" እንዲሉ) ።
ነክናኪ፡ የነከነከ/የሚነከንክ (ነዝናዥ) ።
ነኰረ) ነቈረ፡ አነኰረ (ወጋ'ዐረሰ አማሰለ ገለበጠ የውስጡን በላይ የላዩን በውስጥ አደረገ) ።
ነኰተ፡ እንደ እንኵቶ ኾነ ("ነከተነኳታ" - የነኰተ ነካታ) ።
ነኸ፡ አንተ ለሚባል የቅርብ ወንድ ነባር አንቀጽ ("ነውን" እይ) ።
ነኽ (ነየከ)፡ አንተ ነኸ አለኸ።
ነኾለለ (ኮለለ)፡ ደነቈረ (አእምሮውና ንግግሩ ተበላሸ ራሱ ዞረ) ።
ነኾለል/ነኹላላ፡ የነኾለለ (ደንቈሮ ሞኝ ቂል ነጕላ እንቆ) ።
ነወረ (ነዊር/ኖረ)፡ ኾነ/ተደረገተገኘ ነውሩ።
ነወረ፡ ኖረ።
ነወር፡ ሰው በመጣ ጊዜ ተቀማጭ ተነሥቶ የሚናገረው የከበሬታ ቃል (ትርጓ ሜው ኑሮ ተቀመጥ ማለት ነው) ።
ነወር አለ፡ ብድግ አለ (መቀመጫውን ለቀቀ) ።
ነወርታ፡ ነወር ማለት (ሰውን ማክበር) ።
ነወነ፡ ጨቀጨቀ ("ነጩን" እይ) ።
ነወዘ/ናወዘ (ናወተ)፡ ዞረ/ባከነ/ዋተተ/ተንከራተተ።
ነወጠ (ትግ. ነወጸ)፡ ነቀነቀነ/ናጠ/አወከ (ጸጥታ አሳጣ አገርን ሕዝብን ልብን ናላን) ።
ነዋ፡ ነው (ከስም ምትክና ከደቂቅ አገባብ ጋራ በቃለ አጋኖ ሲነገር "እሱ ነዋ" "እንዲህ ነዋ" "እንዴት ነዋ" ያሠኛል - ፪ሳሙ. ፬፥፲፩ - በግእዝ ግን "እንሆ" ማለት ነው - "ሸነን" ተመልከት)
ነዋ፡ የነው ቃለአጋኖ —ነው።
ነዋሪ (ዎች)፡ ኗሪ
ነዋሪነት፡ ነዋሪ መኾን (አለመጥፋት አለመታጣት) ።
ነዋዛ/ናዋዥ፡ የናወዘ/የሚናውዝ (ዟሪ ባካና) ።
ነዌ፡ የሰው ስም (ጌታችን በወንጌል የተናገረው ባለጠጋ - "ንዋያም ገንዘባም" ማለት ነው - ኪ.ወ.ክ) ።
ነዌ፡ የኢያሱ አባት (ኢያ. ፩፥፩) ።
ነው (ነዋ/ነዮ/ናሁ)፡ ባንድ የሩቅ ወንድ ስም የሚነገር ነባር አንቀጽ (በጥያቄና በስም ሲያስር "ከሰማይ የወረደ ወደ ሰማይ የወጣ ዳግመኛ የሚመጣ ማነው" ብሎ ለሚጠይቅ "ክርስቶስ ነው" ተብሎ ይመለሳል - "ያይጥ ሞት የድመት ሰርግ ነው" - "ሰውን ማመን ቀብሮ ነው" - "እኮንና ና ስበው" ሲያስቀ ሩት "ነው እኮን ነውና" ያሠኛል - "ነው" ሳይጻፍና ሳይነገር በማሰሪያነት ተመርምሮ ይገለ ጣል - "የፈሪ በትር ዐሥር" እንዲሉ) ።
ነው፡ አለ ("እሱ እቤት ነው" - ከጥያቄ ጋራ ሲነገር "ነውን" ይላል - በ፰ ሰራዊት ተዘርዝሮ ማሰሪያ ሲኾን) ።
ነውረ ሥጋ፡ ኮሶ/ወስፋት/አደፍ።
ነውረኛ (ኞች)፡ ጕደኛ/ነውር አድራጊ ባለነውር - ፪ጴጥ. ፪፥፲፫) ።
ነውረኛነት፡ ነውረኛ መኾን (ነውር ጌጡ ልክስክስ ይሉኝ አይልም - ነውር ነው እን እንኳን ሊሠሩት ሊሰሙት አይገባም) ።
ነውር፡ በሰው በእንስሳ ገላ ላይ ያለ ዕብጠት ጕድለት (ላይን የሚያስቀይም ክፉ ግብር ኀጢአት ስካርን ምንዝርን የመሰለ - ነውራም፡ ነውር ያለበት -
ነውጠኛ (ኞች)፡ ነውጥ አድራጊ (ባለነውጥ አዋኪ) ።
ነውጠኛነት፡ ነውጠኛ መኾን።
ነውጡ፡ የሰው ስም (የርሱ ነውጥ) ።
ነውጤ፡ ዝኒ ከማሁ (የኔ ነውጥ ማለት ነው) ።
ነውጥ፡ ሁከት (የመናወጥ ኹኔታ) ።
ነዉ (ነጻዪ)፡ የነጩ/የሚነጭ (ነቃይ ቦጫቂ) ።
ነዎ/ነኹ፡ ርስዎ ነዎ/ነኹ አሉ ("ረ እንዴት ነኹ አቡዬ" እንዳለ ታቦት ዘፋኝ - ግጥም፡ "እንዴት ነኸ እንዴት ነሽ አንባባልም ወይ ሰው ካባቱ ገዳይ ይታረቅ የለም ወይ") ።
ነዘለ (ዐረ)፡ ወረደ/ተቈለቈለ ("መነዘለን" እይ የዚህ ባዕድ ግስ ነው) ።
ነዘረ (ነዚር/ነዘረ)፡ ወረወረ (በትር አሳረፈ በሰው ላይ) ።
ነዘረ፡ በመርዝ ወጋ/ጠቅ አደረገ/ነደፈ/ጠዘጠዘ/ነዘነዘ (ቀየ የቍስል - "ነዘረ የፍላጻ ምስጢር አለበት" - "መነዘረን" እይ የዚህ መስም ግስ ነው) ።
ነዘራ፡ ውርወራ/ነደፋ/ጥዝጠዛ።
ነዘር/ነዝር፡ ተናዳፊ ከይሲ (እስራኤልን በበረሓ እየነደፈ የገደላቸው - "ነዝር እባብ" እንዲሉ) ።
ነዘነዘ (ነዘዘ)፡ ጨቀጨቀ/ነተረከ/አተከረ (ዘፀ. ፳፪፥፳፭፡ ምሳ. ፮፥፫፡ ኤር. ፯፥፲፯፡ ሉቃ. ፲፰፥፭) ።
ነዘነዘ፡ ጠዘጠዘ/ቈረጠመ (ጤና ነሣ) ።
ነዘነዝ/ነዝናዛ፡ ዝኒ ከማሁ (ጨቅ ጫቃ - ምሳ. ፲፬፥፳፱) ።
ነዘዘ (ሐዘዘ)፡ ብን/ትን አለ (ወጣ ፈሰሰ) ።
ነዘገ፡ ዐከከ/ፎከተ።
ነዘፈ (ምጥዋ. ነዝፈ)፡ ለበስ ("ወነዘፈን" - አስተውል) ።
ነዘፈ (ዐረ. ነፀፈ)፡ አጠራ/አጸዳ/እ ነጣ (ንድፍ አስመሰለ) ።
ነዚፋ፡ ጥሩ የጸዳ ነጭ ነጠላ (ጸዐዳ ልብስ - ይህ ስም በሐረርጌ ይነገራል።)
ነዛ (ነዝሀ)፡ ረጩ/ፈነጠቀ (ውሃን/ደምን በተነ ጥሬ እኸልን በምጣድ ላይ - "መነዠኸን" አስተውል የዚህ ዘር ነው) ።
ነዛ፡ አሠራጨ (መርዝን) ።
ነዛ፡ አዘመተ/አደረሰ (ወሬን) ።
ነዛ፡ ዘረጋ (መረብን) ።
ነዛሪ፡ የነዘረ/የሚነዝር (ጠንቀኛ) ።
ነዝናዥ፡ የነዘነዘ/የሚነዘንዝ (ጨቅቂ) ።
ነዢ፡ የነዛ/የሚነዛ (በታኝ) ።
ነየለ፡ በኒል ነከረ ዐለለ ("ኒል" - ሰማያዊ ቀለም) ።
ነዪ (ንዒ)፡ የቅርብ ሴት የመምጣት ትእዛዝ አንቀጽ።
ነያ (ንዒአ)፡ ቃለ መልእክት።
ነይ፡ ዝኒ ከማሁ።
ነይማ (ንዒ እም)፡ እናት ነይ (ዳግመኛም ማ ቃለ አጋኖ ይኾናል።)
ነይነይ፡ ነነዌ።
ነይኮ (ንዒኬ)፡ ቃለ አጋኖ።
ነይጡን፡ ከፀሓይ ብርሃን ከሚነሡ ኮከቦች ፯ኛው ኮከብ።
ነደለ (ነዲል/ነደለ)፡ ፈለፈለ/ሸረሸረ/በሳ/ሸነቈረ/ቀደደ/አፈረሰ (ድልድልን/ዦርን/ቤትን/ምርጊትን/ሸክላን/ስልቻን/ከረጢትን ምድርን - ኢዮ. ፳፬፥፲፯፡ ዓሞ. ፱፥፪፡ ማቴ. ፯፥፲፱ - "ዘነጠለን" አስተውል) ።
ነደላ፡ ሽንቈራ/ቀደዳ (የመብሳት የመሸንቈር ሥራ) ።
ነደረ (ትግ. አንደረ)፡ ዘለለ/ፈነጩ ("እንድር" ከዚህ የወጣ ነው) ።
ነደቀ፡ ገነባ/ናሰ (ግእዝ፡
ነደየ (ነድየ)፡ ዐጣ/ደኸየ።
ነደደ (ነዲድ/ነደ)፡ ቧ አለ/ተቃጠለ/እሳት ኾነ/ተንቦገቦገ ("ኀላፊ ትንቢቱም ይነዳል ቢል እንጂ ይነድዳል አይልም"
ነደደ፡ ዐዘነ/ተበሳጩ - ተረት፡ "እጅ ሲነድ ልብ ይንደድ" - "እንደ ነደደች ተነሥታ የሰው ለቅሶ አጠፋች") ።
ነደድ፡ በወሎ ክፍል ያለ አገር ወይም ሜዳ።
ነደድ፡ ነዳጅ ("ጨሰን" ተመልከት) ።
ነደድ ገደደ፡ ደገኛ ቈለኛ ወንድሙን ስለ ኑሮው ቢጠይቀው "ነደድ ገደድ" አለው ይላሉ (ይኸውም ንግግር ሙቀትንና ችግርን ባንድነት ያሳያል - "ወይናን" አስተውል) ።
ነደፈ (ነዲፍ/ነደፈ)፡ በተነ/ጠቅ አደረገ/ጠዘጠዘ/ወጋ/ነከሰ (በደጋን/በጥርስ በመርዝ በፍላጻ ጥጥን ሰውን - ፪ሳሙ. ፲፥፳፬፡ መክ. ፲፥፲፩፡ ራእ. ፭) ።
ነደፈ፡ ለካ/በረ (ኢሳ. ፵፬፥፲፫) ።
ነደፈ፡ በነገር ነካ።
ነደፋ፡ ንድፊያ (ብተና ጥዝጠዛ ውጊያ) ።
ነዲድ፡ ነበልባል ("በግእዝ ግን መንደድ ማለት ነው") ።
ነዳ (ነድአ)፡ ቀረበ/ወሰደ/ተከተለ (፩ሳሙ. ፮፥፲፡ ሰቈ. ፫፥፪ - ተረት፡ "ሥብ ሊያርዱ ጕፋያ ይነዱ" - "የሰጡን ይሰጧል የገዙን ይነዷል") ።
ነዳ፡ በብዙ አስቀመጠ/አስቀዘነ ("ይኸ ቀጯቸው አያስቀምጥም ሲሉ ይኸው ይነዳዋል ሰራዊቱን ኹሉ" - አለቃ በዛብኸ) ።
ነዳሊ፡ የነደለ/የሚነድል (ሸንቋሪ) ።
ነዳላ፡ የተነደለ/የተበሳ (ብስ ቀዳዳ - ሕዝ. ፯፥፯፡ ዓሞ. ፬፥፫) ።
ነዳቂ፡ ገንቢ -
ነዳይ፡ ድኻ (የለት ጕርሥ ያመት ልብስ ያለው ከምስኪን ይሻላል - ተረት፡ "ለራሱ አያውቅ ነዳይ ቅቤ ለመነ ላዋይ" - ነዳያን፡ ድኾች የሰው እጅ አይተው የሚያድሩ) ።
ነዳደለ፡ በሳሳ ሸነቋቈረ/አፈራረሰ።
ነዳጅ (ነዳዲ)፡ የሚነድ/የሚቃጠል ዕንጨት/ቅባኑግ/ጋዝ/ነፍት/ስበርቶ/ቤንዚን።
ነዳፊ (ፎች)፡ የነደፈ/የሚነድፍ (ወጊ ንብ ተርብ) ።
ነድ (ዐረ)፡ ዑድ የሚጨስ ሽቱ።
ነድ፡ ቀይ ቀለም ጥቂት ጠቈር የሚል።
ነድ፡ ነበልባል፡ነደደ።
ነድ፡ እሳት የሚመስል ቀይ ዶቃ (ትልቅ ድባ) ።
ነድ፡ ዝኒ ከማሁ (የእሳት ላንቃ ነብ) ።
ነዶ (ዕብ. ዐናድ፡ አሰረ. ትግ. ሐባ. ንድእ፡ ነዶ)፡ ታጭዶ ከነብሩ የታሰረ የስንዴ/የገብስ/የጠመዥ/ያጃ ዛላ።
ነዶ፡ የሩቅ ወንድ ቦዝ አንቀጽ (ተቃጥሎ ለሰውነትም ይነገራል - "ዋይ ነዶ" እንዲሉ) ።
ነጂ (ነዳኢ)፡ የነዳ/የሚነዳ (የሚቀርብ/የሚከተል እረኛ - ባቡር/መርከብ/ኦቶሞቢል/ካሚዎን/አይሮፕላን/ጋሪ ነጂ ቢል መሪጠባቂ ማለት ነው) ።
ነጂዎች፡ ነጆች (የነዱ/የሚነዱ እረኞች/ጠባቆች - ኢሳ. ፫፥፲፪) ።
ነገ (ነግ)፡ ንኡስ አገባብ (ማግስት ኹለተኛ ቀን ከዛሬ ቀጥሎ ያለው - ዘፀ. ፲፯፥፲፱ - "ለነገ አትበሉ ነገ ለራሷ ታስባለችና" - "እንብላ እንጠጣ ነገ እንሞታለንና" - ኢሳ. ፳፪፥፲፫) ።
ነገለ (ነጊል/ነገለ)፡ ከሥር ተነቀለ/ፈለሰ (የግንድ) ።
ነገለ፡ ሠሠተ/ነፈገ/ጮቀ (ቸርነት ከልቡ ራቀ) በላ።
ነገሌ፡ ሥሥታም/ቀብቃባ (ብዙ የሚበላ) ።
ነገል፡ ሥሥት/ንፍገት።
ነገሠ (ነጊሥ/ነግሠ)፡ ተቀባ/ዘውድ ደፋ/ጫነ/ተቀዳጀ (ሉል ጨበጠ ንጉሥ ኾነ በዙፋን ተቀመጠ ሠለጠነ ገዛ ነዳ ከበረ ገነነ በዛ - ፩ነገ. ፲፭፥፩, ፪) ።
ነገሠ፡ ወጣ/ዞረ/ዑደት አደረገ (ታቦቱ) ።
ነገሥት፡ ነገሥታት (ንጉሦች - በግእዝ "ነገሥት" ብዙ "ነገሥታት" የብዙ ብዙ ናቸው) ።
ነገሥት፡ የመጻፍ ስም (የእስራኤልን ነገሥታት ታሪክ የሚናገር መጻፍ) ።
ነገረ (ነጊር/ነገረ)፡ አለ/አወራ/በዦሮ አፈሰሰ (አስተማረ/አስጠና/ተረከ/ሰበከ/አስታወቀ/አሰማ/መሰከረ) ።
ነገረ ማርያም፡ የመቤታችን የሕይወት ታሪክ (ቅዱስ ቴዎፍሎስ የጻፈው) ።
ነገረ ሠሪ፡ በሰው ላይ ነገር የሚሠራ ክፉ ማሽንክ ተንኰለኛ አሳባቂ አዋሻኪ።
ነገረ ሰይጣን፡ ሲ በለው ሲሲ በለው (ለከፋው ክፋው ደስ ላለው ደስ በለው - ማታ በሸማ ማጠቢያ ሰይጣን እንደዚህ ይዘፍናል ይላሉ ባላገሮች) ።
ነገረ ሥራ፡ የአካል ኹኔታ (ጡት አዘራር) ።
ነገረ ደብተራ፡ ተዛዋሪ (ሰዋስውኛ - ነገር ወዳድ ጨቅጫቃ ነዝናዛ) ።
ነገረ ግልባጭ፡ የልጆች ቋንቋ ("ቤት ውሃ" በማለት ፈንታ "ትቤ ሃው" እየተባለ የኋሊት የሚነገር) ።
ነገረ ፈጅ፡ ነገር ጨራሽ (ጠበቃ ተጋች የነገር አባት) "
ነገረለት፡ መሰከረለት።
ነገረልኝ፡ መሰከረልኝ።
ነገረበት፡ መሰከረበት።
ነገረተኛ (ኞች)፡ ባለነገር (በርስቱ በገንዘቡ ሙግት ክርክር ያለበት ሰው - "ተኛን" ተመልከት) ።
ነገረኛ (ኞች)፡ ነገር ወዳድ (ጨቅጫቃ - "ነገረኛ ናቸው አርቃችኹ ቅበሯቸው" - "ከነገረኛ ሰው ሥንቅ አይደባልቁም") ።
ነገረው፡ ሰደበው ("ነገረው ሰምቶ ዝም አለው" እንዲሉ ልጆች) ።
ነገሪቱ፡ ያች ነገር (ማር. ፬፥፲) ።
ነገር (ሮች)፡ ወሬ/ቃል/ዝና/ሙግት/ክርክር ("ከነገሩ ጦም ዕደሩ" - "ነገር ፈጣሪውን እሾኸ ዐጣሪውን" - "ነገር ከሥሩ ውሃ ከጥሩ" - "ነገር አለብኝ ከማለት ሥራ አለብኝ ማለት ይሻላል") ።
ነገር ሠራ፡ አሳበቀ/አዋሸከ/አሳጣ።
ነገር ቋጣሪ፡ ነገር የሚቋጥር (ነገር ዠማሪ አሢያሪ ዐድመኛ) ።
ነገር ዐላፊ፡ ትግሥተኛ።
ነገር አወጣ አወረደ፡ አሰላሰለ።
ነገር አዞረ፡ ለወጠ (ሌላ ስሜት ሰጠ ምስጋናውን ስድብ አደረገ) ።
ነገር ዓለሙን ትቶታል፡ ቢሰጡት አልተቀበለም ቢሰድቡት አልመለሰም።
ነገር ዓለም፡ የዓለም ነገር ወይም ኹናቴ።
ነገር ዘሪ፡ ነገርን የሚዘራ/የሚበትን (ግብ. ሐዋ. ፲፯፥፲፰) ።
ነገር፡ የማንኛውም ስምና ግብር በቂ ("እከሌ ከኼድክበት ስትመለስ ባዶ እጅኸን አትምጣ አንድ ነገር ይዘኸ ና እንጂ") ።
ነገር ግን (ባሕቱ)፡ ንኡስ አገባብ የነገር አፍራሽ ("ጌታችን በሰውነቱ ታመመ ነገር ግን በመለኮቱ አልታመመም" - "በሽተኛው ውሃ ይጠጣል ነገር ግን እንጀራ አይበላም" - ይህ የግን አዳማቂ ነው) ሰው።
ነገር ፈላጊ፡ ሳይነኩት የሚነካ ሳይጣሉት የሚጣላ።
ነገርን ነገር ያነሣዋል፡ ያሳስበዋል ያስታውሰዋል ("ነሣ" ብለኸ "አነሣን" ተመልከት) ።
ነገበ፡ ተያዘ (ሸክም ኾነ) ።
ነገብ (ትግ. ሐባ)፡ ዕድል/ፈንታ።
ነገታ፡ ማግስት (ታ ምእላድ ነው - "በነገታው" በተከታዩ ቀን) ።
ነገነገ (ነቀነቀ)፡ ተሰማ ድምጡ።
ነገደ (ነጊድ/ነገደ)፡ ሩቅ አገር ኼደ/ወጣ/ወረደ (ገዛ/ሼጠ/ለወጠ/ሸቀጠ/ዐጠረ ለማትረፍ - ተረት፡ "የነገደ አበደ ያረሰ ነገሠ" - "ላሳር የጣፈው ቢነግድ አይተርፈው") ።
ነገደ መላእክት፡ ፺፱ የመላእክት ነገድ።
ነገደ እስራኤል፡ ፲፪ የእስራኤል ነገድ።
ነገደ፡ እባዕድ ግዛት ደረሰ (እንግዳ ኾነ) ።
ነገደ፡ ወገነ (ወገን አደረገ - ሣልስ ቅጽሉን "ነጋጅ" በማለት ፈንታ "ነጋዴ" ይላል ከግእዝ የወሰደው ነው - "ሸመነ" ብለኸ "ሸማኔን" እይ) ።
ነገድ (ዶች)፡ ወገን/ዘር/ጐሣ።
ነጕላ (ሎች)፡ ቂል/ሞኝ (ግጥም፡ "አንቺን መሳይ ልጅ እንዲህ ስታምሪ ከዚህ ከነጕላ እንዴት ትኖሪ" - ፫ኛውን "ተኛ" እይ) ። አነጐለ፡ አፈረጠ/አወጣ (እረኛው አንጐልን) ።
ነጋ (ነግሀ)፡ ጠባ/በራ/ጧት ኾነ (ሌሊቱ ዐለፈ መዓልቱ መጣ) ።
ነጋ ሌሊቱ፡ ሠጋ ሌማቱ (ችጋረኛ/ራብተኛ ሰው - ሠጋን ተመልከት) ።
ነጋ፡ የሰው ስም (ሲነጋ የተወለደ ልጅ "ነጋ" ይባላል) ።
ነጋ ጠባ፡ ጠባ ይቀድማል ("ዐረበ" ብለኸ ዐረብን እይ) ።
ነጋሢ፡ ነጋሽ ("ነጋሢ" የግእዝ "ነጋሽ" ያማርኛ ነው) ።
ነጋሢ፡ የሰው ስም (ባ፲፯፻ ዓ.ም. የነበረ የሺዋ ባላባት) ።
ነጋሪ (ዎች)፡ የነገረ/የሚነግር (አውሪ/አስተማሪ - ፪ጢሞ. ፩፥፲፩ - "ንባብ ነጋሪ ዜማ ነጋሪ ዐዋጅ ነጋሪ ቅኔ ነጋሪ" እንዲሉ) ።
ነጋሪተኛ (ኞች)፡ ነጋሪት መቒ ባለነጋሪት።
ነጋሪት (ቶች)፡ በቁሙ ጐነ ሰፊ ቁመተ ዐጪር እንዳፍ የከበሮ ዐይነት መሣሪያ (ባዋጅ/በግብር/በዘመቻ/በንግሥ ቀን የሚጐሸም/የሚመታ - ትርጓሜው በግእዝ "የነገረች የምትነግር" ማለት ነው - ንጉሥ በሰፊ ነጋሪታቸው በቈላፋ ዕንጨታቸው ዐዋጅ ነገሩ - ነጋሪትና እት ባማርኛ ይተባበራሉ።
ነጋሪት መታ፡ ጐሸመ (ድም ድም) ።
ነጋሪት፡ የሠም/የሞራ ልጥልጥ አደረገ።
ነጋሪነት፡ ነጋሪ መኾን።
ነጋሽ (ሾች)፡ የነገሠ/የሚነግሥ (የንጉሥ ልጅ - ባሕርን እይ) ።
ነጋሽ፡ የሰው ስም።
ነጋሽነት፡ ነጋሽ መኾን።
ነጋይ፡ የሚነግል (ተነቃይ) ።
ነጋዴ (ነጋዲ)፡ የነገደ/የሚነግድ (ማንኛውንም ተፈላጊ ነገር ሸያጭ/ለዋጭ/ዐጣሪ/ሸቃጭ/አትራፊ/አምጪና ወሳጅ) ።
ነጋዴ፡ ነጋዴን (ግእዝ) ።
ነጋዴነት፡ ነጋዴ መኾን (አትራፊነት) ።
ነጋዴዎች (ነጋድያን)፡ ዐጣሪዎች/ሸቃጮች (መደብር ያላቸውና የሌላቸው ነጋዶች - ዝኒ ከማሁ - ተረት፡ "የቄስ ነጋዴ ይኾናል ወንበዴ" - ወረትን ተመልከት) ።
ነጋድ፡ ዝኒ ከማሁ ለነጋዴ።
ነጋድራስ (ርእሰ ነጋድያን)፡ የነጋዴ አለቃ (ከመንግሥት የተሾመ - መንግሥት ባልሾመው ነጋድራስ የሚታዘዝ አንድ ክፍል የነጋዴ ማኅበርም በጐንደር ነጋድራስ ይባላል - ታሪ. ቴዎ) ።
ነግ (ነግህ)፡ ጧት/ማለዳ።
ነግ ሠልስት፡ ኹለተኛ ሦስተኛ ቀን ("እከሌ ነግ ሠልስት እያለ ቶሎ ሳይመጣ ቀረ" - በከ መነሻነት በመካከል ኹኖ ሲነገር "ከነግ በስቲያ/ከነግ ወዲያ/ከነፃ ነገ" ይላል - ፩ኛው ነገ ማግስት ፪ኛው ነገ ሠልስት) ።
ነግ ነግ አለ፡ ተነቃነቀ (አነገነገ) ።
ነግሥ፡ የመጻፍ ስም (እንደ መልክ ዐምስት ቤት እየኾነ በስንኝ የተደረሰ በየወሩ ማሕሌት ሲቆም ይልቁንም ታቦት በሚነግሥበት በዓልና ዐውዳመት የሚባል ድርሰት ዐጤ ዘርዐ ያዕቆብ የደረሱት) ።
ነጐለ (ትግ. ለጐነ)፡ ፈረጠ ወጣ።
ነጐለ፡ ቄለ ተሞኘ።
ነጐለለ፡ ደነቈረ (ደንቈሮ ኾነ - አንጐሉ ተናወጠ/ተነፋለለ) ።
ነጐለል፡ ነጕላላ (የነጐለለ/የሚነጐልል ደንቈሮ ነፈለል ነፍላላ) ።
ነጐሊያም፡ ዝኒ ከማሁ (ንፍጣም) ።
ነጐሌ፡ የነጐል ዐይነት ወገን።
ነጐል፡ ንፍጥ።
ነጐረ፡ ፈላ/ቀለጠ/ፈሰሰ (ከእድፍና ከጕድፍ ተለየ - ቅቤው ያለቅመም) ።
ነጐደ፡ ተመታ።
ነጐደ፡ ዕልም አለ (ኼደ/ዐለፈ በረረ) ።
ነጐደ፡ ጮኸ/ተመመ/አስገመገመ።
ነጐዳ፡ ጩኸት/ተመማ (የመብረቅ ጓታ ነጐድጓድ) ።
ነጐዴ፡ ብዛት ያለው ጀሌ/መደዴ ("ነጐዴ ነጐዴ ርዳው ነጐዴ" እንዳለ ዘፋኝ) ።
ነጐዴ፡ ዝኒ ከማሁ (የነጐድ/ነጐዳዊ ዐይነቱ ወገኑ) ።
ነጐድ፡ ባንድነት ግር ብሎ የሚበር/የሚነጕድ ብዙ ወፍ ("መቄ በድል ነጐድን" እይ በደለ) ።
ነጐድጓድ፡ በቁሙ፡ ጐደጐደ።
ነጐድጓድ፡ የመብረቅ ግጭት (ጓታ ግሩምና ታላቅ ድምጥ የሚያስፈራ/የሚያንቀጠቅጥ)።
ነጐድጓዶች፡ ግጭቶች/ጓታዎች (ራእ. ፲፡ ፫-፬) ።
ነጐጠ (ጐነጠ)፡ ተነካ/ተወጋ።
ነጓ (ነጕዐ)፡ ጮኸ ("ጓ/ዷ/ኳ" ኣለ)፡ ተሰበረ፡ ፈሰሰ (አንጓው/ቅልጥሙ/ቅባቱ) ።
ነጓጅ፡ የነጐደ/የሚነጕድ (በእግር/በክንፍ ኻያጅ በራሪ) ።
ነጠለ (ነጸለ - ዕብ. ናጣል)፡ ለጠጠ/ለየ/ነጠላ አደረገ/ዘረጋ ደረገ።
ነጠላ፡ ባላንድ ቍንጮ (ተባት ዶሮ) ።
ነጠላ፡ ትከሻ የሌለው ሰው (ጥላ ቢስ ከውካዋ ቀላል) ።
ነጠላ፡ አጋማሽ ' ቍና።
ነጠላ፡ ዕጥፍ ያይዶለ (ኹለት ፈርጅ ሸማ የኩታ እኩሌታ - ዘፀ. ፳፰፥፬፡ ፩ዜና. ፲፭፥፳፯ - "ጠላት ይገፋል ዲቃላ ቀን ያሳ ልፋል ነጠላ" - ተረት)
ነጠላ፡ ግስ (ከፈለ ዐወቀ እያለ በሩቅ ወንድ የሚነገር አንቀጽ) ።
ነጠረ (ነጢር/ነጠረ)፡ ምድርን መታ/ናረ/ዘለለ/ጓነ (ወደ ላይ ተወረወረ - "መነጠረን" እይ የዚህ መስም ግስ ነው) ።
ነጠረ (ነጸረ)፡ በሩቅ አየ/ተመለከተ።
ነጠረ፡ ፈላ/ቀለጠ/ፈሰሰ/ተለየ (ጠ ለለ ጠራ ጥሩ ኾነ ጣፈጠ ተፈተነ ተመረመረ) ።
ነጠረቀ፡ በኀይል መታ ("ነተረከን" እይ አካኼዱ ከዚህ ጋራ አንድ ነው) ።
ነጠር፡ ጥራት/ጥሩነት (እውነት ምርምር - "እከሌ ባፈሣ ተይዞ ነበር ነገር ግን በነጠር ወጣ ተለቀቀ") ።
ነጠቀ፡ ቀማ/ወሰደ/ሳበ/አፈጠነ (ገንዘብን ሥጋን ቅኔን ድፎን ዠርባን እግርን - ዮሐ. ፯፥፲፭ - "መነጠቀን" እይ) ።
ነጠቀ፡ ቈነጠለ (ጥቂት ተማረ) ።
ነጠቀ፡ አዳነ/አወጣ (መዝ. ፻፴፮፥፳፬) ።
ነጠቃ፡ መንጠቅ።
ነጠቅ ነጠቅ አደረገ፡ እግሩን ፈጠን ፈጠን አደረገ።
ነጠቅ፡ ዝኒ ከማሁ ለነጣቂ ("ጥራዝ ነጠቅ" እንዲሉ) ።
ነጠበ (ነጥበ)፡ ወደቀ/ጠብ አለ/ፈሰሰ ("በነጠበ በጐደለ" እንዲል ቀዳሽ ቄስ - ተገብሮ) ።
ነጠበ፡ ደፈረ/ዘለፈ/ወረፈ/ሰደበ/ነቀፈ/አዋረደ (አሰረ - ገቢር) ።
ነጠባ፡ መንጠብ።
ነጠብጣብ (ቦች)፡ ጠፈጠፍ (ብዙ ጠብታ የቀለም የመልክ ፍንጥቅጣቂ - ዘፍ. ፴፥፴፭፡ ዘዳ. ፴፪፥፪) ።
ነጠነጠ (ትግ. ነጽነጸ)፡ ነቀነቀ/አርገፈገፈ (ደበደበ - "ጠነጠነን" ተመልከት = መነጥነጥ መደብደብ) ።
ነጠዘ ።
ነጠዘ (ዕብ. ናጣሽ)፡ ጣለ (ተጣለ እንዘጥ አለ የምሉ እንስራ) ።
ነጠፈ (ነጢፍ/ነጠፈ)፡ ጠለለ/ጠራ ("ወንጠፍት" - የወይን/የጠጅ/የጠላ/የቅቤ/የዘይት/የቅባኑግ ማጥለያ ማጥሪያ ዝርዝር በለሲ ወንፊት ሽቦ ዝተት) ።
ነጠፈ (ነፅፈ)፡ ደረቀ/አቈረጠ/እ ቆመ ጡቱ።
ነጠፈች፡ ወተቷን አቈረጠች/አቆ መች ላጝ።
ነጡር፡ ዘበኛ/ጠባቂ/ተመልካች።
ነጣ (ነጺሕ)፡ መንጣት።
ነጣ (ነጽሐ)፡ ነጭ ኾነ/ጠራ/ጸዳ (ከጥቍረት ከእድፍ ራቀ - "ነጻን" ተመልከት - "ነጣ የሕዝብ ነጻ የካህናት ነው") ።
ነጣ (ንጹሕ)፡ ነጻ (ባርነት ግብር የቀረለት) ።
ነጣ ነጣ፡ መነጣጣት ("ከእግር ነጣ ነጣ ከእጅ ነጣ ነጣ እንዲህ አይዶለሞይ ቍምጥና ሲመጣ" - ላሊበላ) ።
ነጣ አለ፡ ፈገግ አለ (ጥቂት ነጣ ገረጣ) ።
ነጣ፡ ዐከከ ("ዐጣን ፈገገን ገረጣን" እይ) ።
ነጣ አወጣ፡ ገባርነትን አስቀረ (፩ሳሙ. ፲፯፥፳፭) ።
ነጣ ወጣ፡ በራሱ ዐሳብ ዐደረ።
ነጣሪ፡ የሚነጥር/የሚንር (ቀላ) ።
ነጣቂ (ዎች)፡ የነጠቀ/የሚነጥቅ (ቀ ማኛ ተኵላ ጭልፊት ባለዋገምት - መዝ. ፳፪፥፲፫፡ ኢሳ. ፳፬፥፲፯፡ ማቴ. ፯፥፲፭፡ ፩ቆሮ. ፮፥፲፡ ኢዮ. ፲፪፥፮) ።
ነጣቂነት፡ ነጣቂ መኾን (ቀማኛነት) ።
ነጣቢ፡ የነጠበ/የሚነጥብ/የሚወድቅ (ደፋር አዋራጅ) "
ነጣነት፡ ነጻነት "
ነጣይ፡ የነጠለ/የሚነጥል።
ነጣጠለ፡ ለያየ/ዘረጋጋ።
ነጣጠቀ፡ ቀማማ።
ነጣጣ፡ መላልሶ ነጣ።
ነጣፊ፡ የሚነጥፍ/የምትነጥፍ።
ነጣፋ፡ ዝርግ/ሰታታ (ድንጋይ) ።
ነጥር (ሮች) (ልጥር)፡ የሚዛን ልክ ክፍልፋይ ብረት (፲፪ ወቄት ፩ ነጥር ይባላል ይኸውም ፫፻፴፮ ከ፱ ሳንቲ ግራም ነው - ፈረንጆችም ሊትር ይሉታል) ።
ነጥር፡ ቈራጭ።
ነጥሮን፡ ባንዳንድ ስፍራ ከጨው ውስጥ የሚገኝ የልብስ ማጠቢያ ማዕድን (ከጥ ንት ዠምሮ የታወቀ - ኤር. ፪፥፳፪) ።
ነጥቆ፡ ቀምቶ ("ነጥቆ በረር" እንዲሉ) ።
ነጥቆ በረረ ("ከትላፋ ከላፋ ነጥቆ በረር ከተለፈኝ ድንገት ነጠቀኝ ወሰደብኝ ከተመ ") (ከቲም/ከተመ) ።
ነጥቆ፡ አንሥቶ ("ጋሻ ነጥቆ ዘገር ነቅንቆ") ።
ነጥብ (፡ ።)፡ የቀለም ጠብታ (የቃል መ ለያ - "ተማሪው አለስሕተት ከነጥብ እነጥብ ያነ
ነጥቦች፡ ኹለትና አራት (ከነዚህም በላይ ያሉ ጠብታዎች - ገበታ) ።
ነጨ ዝንጀሮ፡ ዐመድማ ' እንዳሞድ ለው።
ነጨ፡ የነጭ ዐይነት
ነጨሬ፡ ጯኺ/አልቃሽ።
ነጨቀ፡ ወጣ ወረደ (ላይና ታች አለ ሸክሙ - "ነጨቀ አልተለመደም") ።
ነጨቀ፡ የመነጨቀ ከፊል ነው።
ነጩ (ነጸየ)፡ አብዝቶ ነቀለ (ጠጕርን ሣርን - "እንስሳ ሣር ነጭቶ ውሃ ተጐንጭቶ ያድራል።")
ነጩ (ዘሌ. ፲፱፥፳፰)፡ ወሸ/ፈተገ/ሞዠቀ/ላጠ/መለጠ/ቦጨቀ/አቈሰለ ("ብነጨው ፊቴን ብደግመው ደረቴን" - ተረት፡ "መቼም የሞተ ሰው ያዝንለት አያጣ አሞራ እንኳን ወርዶ ፊቱን ነጭቶ ወጣ" - ግጥም)
ነጩ፡ ነቃቀለ/ላላጠ/መላለጠ።
ነጩ፡ የሰውን ገንዘብ ነጠቀ ወሰደ።
ነጩ፡ ያ ነጭ (የርሱ ነጭ - "ከጨርቅ ነጩ ከበራ ልጩ ይሻላል የቀረው ነው") ።
ነጫነጭ፡ የነጭ ነጭ።
ነጫጭባ (ነጣ ነጪ)፡ ፊቱ/ፊቷ ነጫጭ ዕከክ ፎከት ንጭታት ያለበት ሰው/ያለባት ሴት ("እየብቻው ለማውጣት") ።
ነጫጭባ (ነጫጭ ባ)፡ ነጭ እን ዳለፈው (ባ አለባት) ።
ነጭ (ጮች) (ጸዐድዒድ)፡ ብዙ ነጭ ("ነጫጭ በጎች ነጭ ፍየሎች ነጭ ርግቦች" እንዲሉ) ።
ነጭ ሐር፡ ቀለም ያልገባ።
ነጭ ለባሽ፡ ነጭ የለበሰ ቀዳሽ ("ነጭ ለባሽ ጸጥታ ጠባቂ") ።
ነጭ ልብስ፡ ያላደፈ (ራእ. ፫፥፬, ፭) ።
ነጭ፡ ማኛ ¡ ማለፊያ ጤፍ እንጀራ።
ነጭ ስንዴ፡ ጣይ ሶራ ያቡን እግር (ከዚህም በቀር ነጭ ገብስ ነጭ ዶሮ ነጭ ዥብ ነጭ ኰርማ ነጭ ሽንኵርት ነጭ ተልባ እያለ በቅጽልነት ይነገራል) ።
ነጭ ቀለም፡ የንጨት ደም ወይም ሰው ሠራሽ።
ነጭ በግ፡ ጠጕሩ ወተት የሚመስል።
ነጭ ቤት፡ የነጭ ጤፍ እንጀራ ቤት ("ነጭ ቤት ነጭ ጋጋሪ ዐበዛ") ።
ነጭ ቤት፡ ጥሩ የጸዳ ቤት (የመኳንንትና የነጭ ልጆች የሚማሩበትና የሚያድሩበት) ።
ነጭ፡ ብዛት ብዙነት ("የጥምቀት ለት የሰው ነጭ ታየ") ።
ነጭ፡ ንጣት የያዘው ሰው ዐመዳም ("ወዛም ገማ ቢሉ የነጭ ወሬ ነው" - ተረት)
ነጭ አሞራ፡ ራዛ ሳቢሳ።
ነጭ ኣባይ (ጊዮን)፡ ውሃው ነጭ የኾነ ዠማ ("አባይን" ተመልከት) ።
ነጭ እሾኸ)፡ መርዘኛ ሴት አፍ ።
ነጭ ዕከክ፡ ፎከት።
ነጭ፡ የነጣ (ሥነ ፍጥረት) ።
ነጭ ደንጊያ፡ እብነ በረድ (ብክካ) ።
ነጭ ጠላ፡ ጦጢ።
ነጭ ጤፍ፡ ማኛ።
ነጭ ፈረስ፡ ዐምባላይ (ራእ. ፮፥፪) ።
ነጭ፡ ፈረንጅ (የያፌት ልጅ - "እኔ መዩ ነጭ ባይ የምሸሽ ነኝ ወይ?" - ዐጢ ቴዎ) ።
ነጭ፡ ፈገግታ ("ዝናሙ በነጩ ይዞታል።")
ነጭ ፍየል፡ ጥቍረት አልባ።
ነጭሎ፡ የቅጠል ስም፡ነጣ።
ነጭሎ፡ የንጨት ስም (ወዙ አረንጓዴ ሰበከቱ ነጭ የኾነ ቅጠል በወይናደጋ የሚበ ቅል - "ነጭ" በቁሙ "ሎ አለው" ማለት ነው) ።
ነጭታ፡ የነጮች የምትነጭ።
ነጮ፡ ነጭ ሆይ (ቃለ አኅስሮ ነው) ።
ነጮ ድኻ፡ ላጤ መላጤ ምንም የሌ
ነጮች፡ ፈረንጆች (የምዕራብ ሰዎች) ። ነጭ፡ ከስም አስቀድሞ እየገባ ቅጽልና ዘርፍ በቂ ይኾናል) ።
ነጯ፡ ካጥንት ላይ ሥጋን ዘነተረ በላ ("ሲመትሩለት ይነጭ" - ተረት)
ነጸረ (ነጽሮ/ነጸረ)፡ አየ/ተመለከተ/አስተዋለ ("ነጠረን" እይ) ።
ነጸብራቅ፡ ብልጭታ ።
ነጸብራቅ፡ ብልጭታ ("(ጸበረቀ)" –
ነጸብራቅማ፡ ሌሊት የሚያበራ ወፍ ትል ።
ነጸፈ፡ አነጠፈ/ዘረጋ - ግእዝ) ።
ነጻ (ነጽሐ)፡ ጠራ/ጠዳ (ንጹሕ ኾነ ከእድፍ ከባርነት ራቀ ከለምጽ ዳነ ተፈወሰ - ፪ነገ. ፭፥፲ - "ነጣን" ተመልከት) ።
ነጻ አወጣ፡ ከቤቴ ኺድ በወደድኸበት ኑር አለ።
ነጻ አደረገ፡ ባሪያን ለቀቀ።
ነጻ ወጣ፡ ሐርነት አገኘ (ከባርነት ተለቀቀ) ።
ነጻነት፡ ነጻ መኾን (መለቀቅ - "ነጻነት አገኘ" - ባርነት ቀረለት) ።
ነጻዎች፡ የተለቀቁ ባሮች።
ነፈለ፡ ተለገደ (ነፍናፋ ኾነ) ።
ነፈለለ (ፈለለ)፡ ተሞኘ - ቄለ (ነኾለለ ጀለ ደነቈረ) ።
ነፈለል/ነፍላላ፡ ቂል/ሞኝ (የማይረባ ደንቈሮ) ።
ነፈሊያም፡ ዝኒ ከማሁ።
ነፈላም፡ የነፈል ወገን (ነፈል ከርሱ ጋራ ያለ ባለነፈል ነኊራጣ ነፍናፋ ነቅ) ።
ነፈል፡ ያፍንጫ ውስጥ ትርፍ ሥጋ ለገድ።
ነፈሰ (ነፍሰ)፡ ረቀቀ (ረቂቅ ኾነ) ።
ነፈሰ፡ ሽው ሽው እብድ እብድ አለ (ማቴ. ፯፥፳፭) ።
ነፈሰ፡ ቀለለ (ሹመቱ ክብሩ ከነፋስ ጋራ ኼደ ወሬው) ።
ነፈሰበት፡ ጠላ በጋን ውስጥ እንጀራ በምጣድ ላይ ነፋስ ነካው (ጣዕሙ መልኩ ተለወጠ ጠፋ) ።
ነፈረ (ትግ)፡ ወደ ሰማይ በረረ ወጣ (የባለክንፍ) ።
ነፈረ (ነፊር/ነፈረ)፡ እጅግ ሞቀ ' ፈላ (ተፍለቀለቀ ተቀቀለ) ።
ነፈረቀ (ፈረቀ)፡ በብዙ ወገን መገለ/አዠ/ሞቀሞቀ።
ነፈረቀ፡ በጣም አለቀሰ/ተንሠቀሠቀ/አነባ/ተስረቀረቀ።
ነፈረቅ/ነፍራቃ፡ የነፈረቀ/የሚነፈርቅ (አልቃሽ) ቀስ።
ነፈራረቀ፡ መጋገለ።
ነፈቀ (ነፊቅ/ነፈቀ)፡ ለየ/ከፈለ (እኩሌታ አደረገ) ።
ነፈነፈ (ነፍነፈ አካፋ)፡ ኣብዝቶ በላ/ጋጠ/ነጨ (ርጥብ ሣርን ሥጋን - "የፈረሴ ጕማጅ እቅብቅብ ገብቶ ሲነፈንፍ አገኘኹት" እንዳለ ቍንጨ - ትግሬ ግን ነፍነፈ ብሎ ጣለ አወደቀ ይላል) ላት።
ነፈነፍ፡ ነፍናፋ (ነኈረጥ ነኍራጣ ጕንፋናም ሰርነ ሰባራ) ።
ነፈዘ (ነበዘ)፡ ልብ ዐጣ/ቀለለ።
ነፈዝ፡ ልበ ቢስ/ቀላል።
ነፈገ (ነፈቀ)፡ ለይቶ ተወ (ቤሰ ሠሠተ ጮቀ ቀቀተ) ።
ነፈጠ (ነፍጸ)፡ ወጣ (ወጥቶ ኼደ ሸሸ - "ነፈጠ" ግእዛዊ ቃል ነው) ።
ነፈፈ፡ ናፈረ
ነፈፈ፡ ጀለ/ተሞኘ።
ነፊ (ነፋዪ)፡ የነፋ/የሚነፋ (አንዘር ዛሪ) ።
ነፊ (ዎች) (ነፋኂ)፡ የነፋ/የሚ ነፋ ("እንቢልታ ነፊ" እንዲሉ በጥ) ።
ነፊታ፡ የነፋች/የምትነፋ ሴት።
ነፊዎች (ነፋይያን/ት)፡ ዱቄትን የሚነፉ ወንዶችና ሴቶች።
ነፋ (ነፈየ)፡ አንዘረዘረ (ዱቄትን ጥሬ ጤፍን ካሠር ከገለባ ከእብቅ ለየ አወረደ - ኢሳ. ፴፥፳፰) ።
ነፋ (ነፍኀ)፡ ቀበተተ/አሳበጠ/ አንገፈጠጠ/አንጠረዘዘ/ቀበጠጠ/እንዘረጠጠ (ስልቻን ሆድን - "የነፋሽ የቀበተተሽ" እንዲል ጕልማሳ) ።
ነፋ፡ አካፋ።
ነፋ፡ እፍ አለ (በትንፋሽ አስጮኸ ዋሽንትን መለከትን - ራእ. ፰፥፯, ፲፥፲፪ - "(አፍንጫውን ነፋ)" - ተነፋነፈ) ።
ነፋ፡ ወሬ ነዛ።
ነፋሲት (ነፋሳዊት)፡ ነፋስ ያለባት ቀበሌ (ካስመራ በታች የምትገኝ) ።
ነፋስ (ሶች)፡ የምድር መሠረት (የሰ ማይ ዐምድ ካራቱ ባሕርያት ሦስተኛው ባሕ ርይ ድምፁ የሚሰማ አካሉ የማይታይ የማ ይዳሰስ የፍጥረት ኹሉ ሕይወት አንቀሳቃሽ መዝጊያን የሚዘጋና የሚከፍት ዕቃን የሚያነሣና የሚጥል ባሕርን የሚወስድና የሚመ ልስ - ሔኖክ ፬ የምሕረት ፰ የመዓት ነፋሶች አሉ ይላል - "(ጥቅል ነፋስ)" - ዐውሎ ነፋስ ኵርፊት) ።
ነፋስ መውጫ፡ በጋይንት ክፍል ያለ አገር !
ነፋስ ስልክ፡ ራዲዮ ስልክ።
ነፋስ ስልክ)፡ ራዲዮ (ማርኮኒ የሚባል ጣሊያን በእንግሊዝ አገር ያወጣው) ።
ነፋስ፡ እብድ ዕርፊተ ቢስ ልጅ ("ነፋስ ገባው" - ፍቅር አንድነት ስምምነት ዐጣ ተለያየ ሕዝቡ) ።
ነፋሪ፡ የሚነፍር (በትግሪኛ ግን በ ራሪ ወፍ ማለት ነው) ።
ነፋሻ (ነፋሳዊ)፡ ነፋሳም ስፍራ ቦታ (ደጋ ተራራ አፋፍ) ።
ነፋሽ፡ የነፈሰ/የሚነፍስ።
ነፋጊ፡ የሚነፍግ (ሠሣች) ።
ነፋፈሰ፡ መላልሶ ነፈሰ።
ነፋፋ፡ መላልሶ ፈጽሞ ነፋ/አሳበጠ (ኹለንተናን ቅል አስመሰለ) ።
ነፋፋ ሞኝ፡ ነፈፈ።
ነፋፋ፡ ሞኝ/ቂል/ጅል/ከርፋፋ።
ነፍሰ ቢስ፡ ለሰውነቱ የማይሣሣ ' ጐበዝ።
ነፍሰ እግዚሐር፡ ፈጣሪ ነፍስን በሥጋው ያሳደረበት ቀጪን ኰሳሳ ልጅ።
ነፍሰ ገዳይ፡ ነፍስን (ሰውን) የገደለ።
ነፍሰ ግዳይ፡ ነፍስ መግደል።
ነፍሰ ጡር (ጸዋሪተ ነፍስ)፡ እርጉዝ ሴት (በማሕፀኗ ነፍስ የተሸከመች - "ጦረን" ተመልከት) ።
ነፍሰ ጡርነት፡ እርግዝና/እርጉዝነት።
ነፍሰ ጡሮች (ጸዋርያተ ነፍስ)፡ እርጉዞች ሴቶች " ቀጠነ።
ነፍሰ ጥኑ፡ ቢያርዱ ኣይሞት ውሻ (ቶሎ የማይሞት) ።
ነፍሱን መረመረ፡ ለድኻ ምጿት ሰጠ።
ነፍሳት (ተሐዋስያን)፡ ከቍጭ ያነሱ ረቂቆች ፍጥረቶች ተንቀሳቃሾች ("በባላገር ግን ላንድ ተባትና ለእንስትም ይነገ ራል። ቍንጫጪትን" እይ) ።
ነፍሳት (ነፍሶች)፡ (ግእዝ) ።
ነፍሳውጪ (ነፍስ አውጪ)፡ ነፍስን ከሥጋ የሚያወጣ/የሚለይ (ፈጣሪ/መ ላከ ሞት) ።
ነፍስ (ሶች)፡ በቁሙ ረቂቅ ፍጥረት (የመልአክ ዐይነት ከፈጣሪ ላዳም ልጅ ኹሉ የምትሰጥ - ሰው ሲፀነስ ዠምራ በሥ ጋው ታድራለች ተውሕዳው ትኖራለች በሞት ትለያለች - ምሳ. ፲፩፥፴፡ ዮሐ. ፲፱፥፴፡ ፩ጴጥ. ፫፥፲፱ - "በጣረ ሞት ጊዜ ውጪ ነፍስ ግቢ ነፍስ" እንዲሉ - "ደማ" ብለኸ "ደምን" እይ - ነፍስ ሰው) ።
ነፍስ አሳለፈ፡ ሰውን ገደለ ("ሥጋን ወደ መቃብር ነፍስን ወደ ሰማይ አ ስኬደ (ኣገባ አወጣ)") ።
ነፍስ አባት፡ የነፍስ አባት ቄስ (የንስሓ አባት) ።
ነፍስ ዐወቀች፡ ባለአእምሮ ኾነ/ች ("(በነፍስ ደረሰ)" - ነፍስ ከሥጋ ሳትለይ ሰውየው ሳይሞት ከተፍ አለ/መጣ) ።
ነፍስ አዋለ፡ እንጭጭ ኾነ።
ነፍስ አድን፡ እንጀራ ("እንቆቅልሽን" አስተውል) ።
ነፍስ ኾነ፡ ተወደደ/ተጨበጠ።
ነፍስ ዘራ፡ ተነፈሰ/ተንቀሳቀሰ።
ነፍስ ያለው፡ ያልሞተ/ያልከሳ/ያል ቀጠነ።
ነፍት፡ የምድር ዘይት (በግእዝ ነፍጥ ይባላል ይኸውም ጋዝ ነው) ።
ነፍናፊ፡ የነፈነፈ/የሚነፈንፍ (የበላ) ።
ነፍጠኛ (ኞች)፡ ባለነፍጥ ወታደር (ነፍጥ ያለው የንጉሥ የሻለቃ አሽከር) ።
ነፍጠኛ(ኝ)ነት፡ ነፍጠኛ መኾን (ወ ታደርነት) ።
ነፍጥ (ጦች)፡ በያይነቱ ጠመንዣ (ከውስጡ ዐረር በወጣ ጊዜ ጠላትን የሚያሸሽ የጦር መሣሪያ - "ካሽከር ገበየኹ ከነፍጥ ጐበዛየኹ" እንዲሉ - ዳግመኛም በግእዝ ነፍጥ ነፍት ጋዝ ይባላል - የነፍጡም የጋዙም ምስጢር - መቃጠልና ማቃጠል ነው) ።
ኑ (ንዑ/ንዓ)፡ የቅርቦች ወንዶችና ሴቶች ትእዛዝ አንቀጽ ("ኑ ልጆቼ ስሙኝ ልንገራችኹ" - "ኑና እንተያይ") ።
ኑ፡ አዳማቂ ምእላድ ("አኹን አኹኑኑ"፡ "እሱ እሱኑ"፡ "ወዲያው ወዲያውኑ" - በን ፈንታ እየገባ ገቢር ሲኾን፡ "ቅድሙን ቅድሙኑ"፡ "ዱሮውን ዱሮውኑ" ይላል) ።
ኑስ (ንኡስ)፡ ግማሽ ገንዘብ (አላድ እኩሌታ - "ባረብኛም ታናሽ ማለት ነው") ።
ኑር፡ ቁም/ቈይ/ክረም።
ኑርልኝ፡ የሰው ስም ("ቁምልኝ ቈይልኝ" ማለት ነው) ።
ኑሮ —መኖር ኖረ።
ኑሮ፡ መኖር/ትዳር/ንብረት ("ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል" - ተረት፡ "ኑሮ በዘዴ" - ሉቃ. ፲፮፥፮, ፰) ።
ኑሮ ኑሮ፡ ቦዝ አንቀጽ (ቈይቶ ቈይቶ - "ውሎ ውሎ ከቤት ኑሮ ኑሮ ከሞት" እንዲሉ) ።
ኑበለጣጠግ፡ አከባበር፡ መበልጠግ ።
ኑና (ወንዑ)፡ ኑ በቁሙ (ና ቸልታ - "ኑና እንተያይ" - መጥታችኹ ማለት ነው - ኢሳ. ፩፥፲፰ - "ኑን" ተመልከት) ገነፈለ።
ኑዛዜ፡ መናዘዝ (ምስጢረ ንስሓ መቀ በል - ባላገር ግን "ንዛዜ" ይለዋል) ።
ኑዛዜው፡ ፈሰሰ/ተነበበ/ተነገረ/ተገለጠ።
ኑግ (ንሒጕ)፡ የቅመም ስም (ሲወቅጡት ዘይት የሚወጣው ጥቍር ቅመም - አገዳው መጭ ይመስላል - "ቀባ" ብለሽ "ቅብን" እይ) ።
ኑፋቄ፡ ጥርጥር ("(ግእዝ)" –
ኒ (ዊ)፡ የነገር ትራስ ("ጥንበኒ ግመኒ ሸወርኒ" - "ጥንባታም/ግማም" ተብሎ ሊተረጐም ይቻላል) ።
ኒል፡ የቀለም ስም ("ነየለ") ።
ኒሻን (ዐረ)፡ የዕንቍ/የወርቅ/የብር/ የንሓስ ሽልማት (ተሸላሚ በደረቱ ላይ የሚያንጠለጥለው ጌጥ - የኒሻን ዐይነቱ ብዙ ነው - ፈረንጆች ሜዳይ ይሉታል) ።
ኒሻን፡ THYTEደስታ ተክለወጽ በኢትዮዽያ
ኒሻኖች፡ ሽልማቶች።
ኒቆዲሞስ፡ የሰው ስም (ጌታችንን ከዮሴፍ ጋራ በማለፊያ ሽቱ በጥሩ በፍታገንዞ የቀበረ የአይሁድ አለቃ) ።
ኒኒ፡ የሴት ልጅ ስም።
ኒካ፡ የስላም ጋብቻ ደንብ ሥርዐት።
ኒኬል፡ የማዕድን ስም (በብር ፈንታ ገንዘብ የቤት ዕቃ የሚኾን ነጭ ማዕድን ፈረንጅ አመጣሽ) ።
ና (ምእላድ)፡ ፍችው "አነት" ("ደረቀ ድርቅና"፡ "አረገዘ እርግዝና"፡ "ሰነፈ ስንፍና"፡ "ሞሸረ ሙሽርና"፡ "ላቀ ልቅና" - በግእዝ መሠረቱ "ና" ነው) ።
ና (ነዐ)፡ የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ (ምጣ፲ ድረስ የኺድ ተቃራኒ ነው - ዮሐ. ፳፩፥፵፫ - "ና" ያሉት እንግዳ አራቱ ፍሪዳ - "ና ብላኝ የት ኼደች" - "ና ውጣ/ና ውረድ/ና ኺድ/ና ኵቲ" እንዲሉ) ።
ና በለው፡ ጥራው ("መጥተኸ ምታው" - ባለን ተመልከት) ።
ና፡ በትእዛዝ አንቀጽ እየገባ አንቀጹን ያስቀራል። "ይሥራና ይብላ" - "ይሙትና ይረፍ"።
ና፡ ቸልታ ("ውረድ እንውረድ ተባባሉና አስደበደቡት አፋፍ ቆሙና" - ፪ሳሙ. ፲፩፥፲፮, ፲፯ - የቅንጦተኛ ግጥም፡ "፩ ጣባ አሹቁን ግትም ያደርግና ፩ አንኮላ ውሃ ጥጥት ያደርግና ያንን ደላጎውን ይቀጣጥልና ያችን ዐመዳሙን ዕቅፍ ያደርግና ተመስገን ይለዋል ኑሮ ተገኘና") ።
ና ና (ነዐ ነዐ)፡ ምጣ ምጣ/ድረስ ድረስ ("ሆያ ሆዬ ና ና በሰፊው ጐዳና" እንዲሉ ልጆች) ።
ና፡ ንቀት (የንቀት ቃ - "ሐዋርያት ተርበው ነበር ወይ ሐዋርያት ይቅሩና ክርስቶስ እንኳ ተርቧል" - በግእዝ መሠረቱ "ሰ" ነው) ።
ና፡ ዐቢይ አገባብ (የነገር አስረጅ - "ዓለም በውሃ ጠፋ ኀጢአት ሠርቷልና" - "ፈጣሪ ሞተ ሥጋ ለብሷልና" - "ወደ ሰማይም ዐረገ ሙቶ ተነሥቷልና" - በግእዝ መሠረቶቹ "እስመ/አምጣነ/አኮኑ" ናቸው) ።
ና፡ አዳማቂ ወይም አጐላማሽ ("ሠልስት ሠልስትና"፡ "ቀበጥ ቀበጢና"፡ "ትላንት ትላንትና"፡ "ወዝ ወዘና" - ምእላድም ሊባል ይቻላል) ።
ናላ (ኖለወ)፡ አንጐል (የራስ ቅል) ።
ናላው ዞረ፡ ተበላሸ (አእምሮ ዐጣ) ።
ናሚና፡ ዘነዘና ("የብር ዘነዘና ጌታዬን ያማሰው ነጭ ዕከክ ይውረሰው እንዲሉ") ።
ናሰ (ነሐሰ)፡ ናስ ሠራ ' ገነባ ' እድሞ ' አበጀ ።
ናሴ (ነሐሴ)፡ የወር ስም (፲፪ኛ ወር - ዘይቤው የኔ ናስ ግንቤ ማለት ነው - የፈረሰውን ኹለቱን ቤተ መቅደስ ያሳስባል) ።
ናስ (ናሕስ)፡ ግንብ/እድሞ (ያፈር ቤት ጣራ በላዩ ሣር የሚበቅልበት - ፩ሳሙ. ፲፰፥፲፩፡ ሕዝ. ፲፫፥፲፪፡ ዳን. ፭፥፭፡ ዕን. ፪፥፲፩) ። ናሶች፡ ብረቶች ' ግንቦች ።
ናስ (ንሓስ)፡ ብ፵ የሚመስል ብረት ከመሬት የሚገኝ (፩ሳሙ. ፲፯፥፭, ፮፡ ዳን. ፭፥፬, ፳፫) ።
ናስ ማሰር፡ ማሰሪያው/መሸቢያው ናስ የኾነ ትልቅና ትንሽ ጠመንዣ ("ናስ ማሰር ውዥግራ" እንዲሉ) ።
ናስ፡ ከናስ የተበጀ ታናሽ ገንዘብ (እንደ ቤሳ ያለ - ማር. ፮፥፰፡ ሉቃ. ፲፪፥፮) ።
ናስ፡ ያገር ስም (በተጕለት አውራጃ ያለ ገጠር - "ናስ ማሪያም" እንዲሉ) ።
ናስ ጭራ፡ እንደ ጭራ ያለ የናስ ሽቦ (የዛገ ጌጥ ማጠቢያ መወልወያ - "ኰላን" ተመልከት) ።
ናረ (ነሀረ)፡ ነጠረ/ጓነ/ተወረወረ (ወደ ላይ ዘለለ - የውሃ የእሳት የኳስ የደንጊያ) ። ናሪ (ነሃሪ)፡ የናረ/የሚንር (ጓኝ ዘ ላይ) አየር።
ናረት፡ ሆድ (ሆደ ትልቅ) ።
ናረት(ቶች)፡ ጭልፂ/ዳውላ።
ናር ናር አለ፡ መላልሶ ናረ (ኀይለ ቃል ተናገረ) ።
ናርኤል፡ የክረምት ኮከብ ("ያምላክ እሳት ወይም ብርሃን" ማለት ነው)
ናርዱ፡ የሽቱ ስም (ግእዝ) ።
ናርዶስ፡ የናርዱ ቅጠል ' ወይም ሽቱ።
ናርጅ (ናርዳዊ)፡ ጌጠኛ የንጨት ' ጮጮ በሽቱ የጣፈጠ ቅቤ ማስቀመጫ።
ናሸረ፡ ደሙ ።
ናሽ (ነሓሲ)፡ የናሰ/የሚንስ (ናስ ሠራ ' ገንቢ) ።
ናቀ (ትግ. ነዐቀ)፡ አኰሰሰ/እቀለለ/አዋረደ/ጠላ (ክብርን መወደድን አሳጣ - ዘኍ. ፲፭፥፴፩፡ ኢሳ. ፳፫፥፱ - "(ተረት)" - ዐወቅኹሽ ናቅኹሽ - ሰውን ሰው ናቀው የራሱን ሳያውቀው) ።
ናቀ፡ መነነ/ተወ/ጣለ (ዓለምን) ።
ናቁስ፡ ድምፁ የሚያምር ጸናጽል።
ናቁስ፡ ድምፁ የሚያምር ጸናጽል።
ናቂ (ዎች)፡ የናቀ/የሚንቅ (አኰሳሽ - "ሰው ናቂ" - ትቢተኛ ኵራተኛ) ።
ናቂያ፡ የመናቅ ኹናቴ (ጥላቻ ' ናቅ መናቅ) ።
ናቄ፡ የሰው ስም።
ናቅ አደረገ፡ ናቀ።
ናበ (ነሀበ)፡ ቀጠቀጠ/ሠራ (ብረትን ናበ)፡ ጋገረ/አሰፋ (ማርን) ።
ናበለ (መበለ)፡ ወደ ላይ ተወረወረ/ዘለለ/ጨፈረ/ከፍ አለ ("ፈረሱ ይናብላል ውሃው ይናብላል" እንዲሉ - "ናፈለን" ተመልከት) ።
ናበተ፡ ቀለጠፈ/ፈጠነ (ተገብሮ) ።
ናበተ፡ ቀማ/ነጠቀ/መነተፈ (ገቢር) ።
ናቡቴ (ዎች)፡ የናበተ/የሚናብት (ነጣቂ - "እከሌ ናቡቴ ነው" እንዲሉ) ።
ናቡቴ፡ የሰው ስም (ኤልዛቤል ርስቱን ለመውሰድ በግፍ ያስገደለችው ሰው) ።
ናቡቴ፡ ፈጣን/ቀልጣፋ (ግጥም፡ "የኛማ ልጆች ናቡቴዎቹ ይናደፋሉ እንደ ንቦቹ") ።
ናቢ (ነሃቢ)፡ የናበ/የሚንብ (ቀጥቃጭ/ጠይብ ጃን ሸላሚ) ።
ናባል፡ የሰው ስም (ከዳዊት ቍጣ የተነሣ በድንጋጤ የሞተ - ናባል ደንቈሮ አላዋቂ ማለት ነው - ፩ሳሙ. ፳፭፥፳፭) ።
ናብሊስ፡ ቃጭል መርዋ (ዳግመኛም ያገር ስም ይኾናል - ግእዝ) ።
ናቸው (ነዮሙ/ነዮን)፡ እነሱ ናቸው አሉ ቸው።
ናችሽ ናችሽ አለ፡ ና ና አለ ' ጠራ ።
ናችሽ፡ የተባት አህያ መጥሪያ (ለበቅ ሎና ለፈረስም ይነገራል።)
ናችኹ (ነየክሙ/ነየክን)፡ እናንተ ናችኹ አላችኹ ይላል ("እንደ" ብለኸ "እንዴት"ን እይ) ።
ናኑ፡ ጋሜ/ገርዳሳ።
ናና (ናሕንሐ)፡ በዛ ፈላ ገነፈለ።
ናና፡ ፩ኛው ና አንቀጽ (፪ኛው ና ቸልታ - "መጥተኸ ማለት ነው ናና እይ" - ዮሐ. ፳፩፥፴፬ - "ናን" አስተውል) ።
ናና፡ ሠየ/ጐመዠ።
ናኘ፡ አብዝቶ ሰጠ/ኣቀበለ/ዐደለ/ነዛ/በተነ/ዘራ/ኣዘዘ ("ባላዋቂ ቤት እንግዳ ናኘበት" - ተረት)
ናኝ/ኚ፡ የኖኘ/የሚናኝ (ሰጪ በታኝ) ።
ናዕናዕ፡ የተክል ስም (ሲያሸቱትና ሲመገቡት ጣዕም ያለው ቅጠል - በግእዝ አ ዛብ ይባላል) ።
ናኦድ፡ ዓ.ም. በ፲፭፻ የነገሠ መልከ ማሪያምን የደረሰ የኢትዮጵያ ንጉሥ ስም (ንኡድ)፡ ክቡር ማለት ነው።
ናኵራ፡ በቀይ ባሕር (ኤርትራ) ውስጥ በአዳል መሬት አንጻር የሚገኝ ደሴት (በዚህም ስፍራ በጣሊያን እጅ ብዙዎች ሐበሾች እየታሰሩ ዐልቀዋል) ።
ናኸ) ናእክ፡ ቃታ ጩኸት።
ናኸ) ንእከ፡ አናኸ (ተጨነቀ እቃ ሰተ ጮኸ ወለሌ አለ) ።
ናወተ (ኖተወ)፡ ተንከራተተ (በባሕር በየብስ ላይ - "ኖት" ማለት ከዚህ ሊወጣ ይችላል - "ነወዘን" እይ) ።
ናወነ ።
ናዋች (ኖትያ)፡ የናወተ/የሚናውት (ተንከራታች ቋትለኛ) ።
ናዘረ፡ ዛዘነ (ሚያው ሚያው አለ ዞረ እንስት ፈለገ የሚነድፈውን እንደሚሻ ነገር ናዜራ ኾነ) ።
ናዘረች፡ ዛዘነች (ተባት ፈለገች) ።
ናዘዘ (ናዝዞ/ናዘዘ)፡ በተሳተ/በተገደፈ ሲያውቁ በድፍረት ሳያውቁ በስሕተት ከልጅነት እስከ ዕውቀት በተሠራ ኀጢአት ሰይጣን ባሸመቀው መንፈስ ቅዱስ ባወቀው እግ ዜር ይፍታ አለ (ተስፋ ሰጠ አጸናና አረጋጋ) ።
ናዛዥ (ዦች)፡ የናዘዘ/የሚናዝዝ (ቄስ የነፍስ አባት) ።
ናዜራ (ሮች)፡ ሸረሪት የሚመስል ጥቍር ተንቀሳቃሽ (ሰውን በነደፈ ጊዜ የሚሣቅይና የሚጠዘጥዝ የሚነዝር ኹለተኛ ስሙ ዳሞትራ ነው) ።
ናዝራዊ (ውያን)፡ የክርስቶስ ወገን ክርስቲያን።
ናዝራዊ፡ የናዝር ወገን (ጠጕራም ባሕታዊ መናኝ እንደ ሶምሶን ያለ ራሱን የማ ይላጭ ሥጋ የማይበላ ጠጅ የማይጠጣ) ። ናዝራዊ (ናዝሬታዊ)፡ የናዝሬት ሰው (በናዝሬት ተወልዶ ያደገ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ - ማቴ. ፪፥፳፫) ።
ናዝሬት፡ ያገር ስም (በኢየሩሳሌም እውራጃ ያለች ቀበሌ የተናቀች የተዋረደች ማ ለት ነው - ኪ.ወ.ክ) ።
ናዝር (ዕብ. ናዚር)፡ የብፅዐት የስለት ልጅ ማለት ነው (ኪ.ወ.ክ) ።
ናዞ፡ የገብስ ስም (አንድ ዐይነት ገብስ) ።
ናዡድ (ናዝወርድ)፡ ናስ ጽጌረዳ የሚመስል ቀለም።
ናይ፡ ተረተረ/ፈታ (ልቃቂትን) ።
ናይት፡ ዝኒከማሁ።
ናደ (ነዐደ)፡ ጐተተ/ዘረጠጠ/ሻረ/ኣፈረሰ/አወረደ/አንከባለለ/አወደቀ/አሸሸ (ክምርን/ግንብን/ገደልን ጦርን - "ነዐደ" ጥንታዊ ዐማርኛ ነው ይኸውም ሊታወቅ በክብረ ነገሥት ብቻ "ድል ነዓድ" ተብሎ ቅጽሉ ይገኛል) ።
ናደለ፡ ተጠገበ/ተዘለለ/ተጨፈረ።
ናደው/ናዴ፡ የሰው ስም።
ናዳ (ዶች)፡ ከገደል/ከተራራ ተንዶ የተንከባለለ/የወረደ ደንጊያ (ትንሹም ትልቁም) ።
ናጅ (ነዓዲ/ነዓድ)፡ የናደ/የሚንድ (አፍራሽ) ።
ናጌብ፡ ከአድማስ ወዲያ ያለ የዓለም ዳር መጨረሻ (ሰማይን በዙሪያ እንደ ግድግዳ ተሸክማል ይባላል - አለቃ ኪዳነ ወልድ ግን የምድረ እስራኤል ዳርቻ ውቅያኖስ ብለውታል) ።
ናግራን፡ ያገር ስም (በየመን የነበረች ከተማ ፴፮ ሺሕ ሰማዕታት የተገደሉባት - ሀገርን እይ) ።
ናጠ (ትግ. ሐባ. ነሐፀ - ዕብ. ናጥ)፡ ታወከተ/ነቃነቀ (ገፋ ወዘወዘ ነቀነቀ ወተ ትን) ።
ናጠረ) ነጠረ (ናደለ)፡ አናጠረ (ዘለለ መር መር አለ ጨፈረ የፈረስ - "ወይ እኔ አቶ ፈረስ በሰፈሩት ቍና መሰፈር አይቀር ጋሪ በወገቤ ያናጥር ዠ መር" - ግጥም)
ናጠጠ (ነጢጥ/ነጠ)፡ ዘለለ/ፈነጩ (አነጠነጠ - "ናደለን" አስተውል) ነጥ።
ናጩርት፡ ጩኸት። ናጩርቲያም፡ ጩኸታም።
ናጫ (ጮች)፡ የንጨት ስም (ቅጠሉ እንደ ሳማ የሚለበልብ ዕንጨት ልጡ ተልጦ ይጨርትና ገመድ ይኾናል - ጠጕሩ ዐይን ውስጥ በገባ ጊዜ እሾኸ በወጋት ቅማል ያወጡታል - "ዐመልን" ተመልከት - "(የውሻ ና)" የማይለበልብ ናጫ መሳይ ቅጠል መናኛ) ።
ናጫ፡ ዕንጨት፡ነጩ።
ናጫጌ፡ በተጕለት ውስጥ ያለ አገር (ናጫ የበዛባት የና፵ ምድር ማለት ነው) ።
ናጯ፡ የናጠ/የሚንጥ (ገፊ ወዝዋዥ) ።
ናፈለ፡ ወደቀ (ተጨነቀ) ።
ናፈረ (ትግ. ሐባ)፡ ዘለለ ("ናፈለንና ናበለን" እይ) ።
ናፈቀ (ናፍቆ/ናፈቀ)፡ ሻ/ፈለገ (ተመኘ ልጅ አባት እናቱን አባት ልጁን ወዳጅ ወዳጁን - ምሳ. ፯፥፲፭፡ ፪ቆሮ. ፯፥፯፡ ፩ተሰ. ፫፥፮) ።
ናፈቀ፡ ተጠራጠረ።
ናፈቀች፡ እናት ልጇን ፈለገች (ተመ ኘት) ።
ናፈቅ፡ ዝኒ ከማሁ ("አባቱን አያውቅ አያቱን ናፈቅ" እንዲሉ) ።
ናፋሊ፡ የሚናፍል (የሚወድቅ የሚጫ ንፉል) ።
ናፋቂ፡ የናፈቀ/የሚናፍቅ (የሚሻ የሚፈልግ ፈላጊ ተጠራጣሪ) ።
ናፍቆት፡ ንፍቂያ (የዘመድ የወዳጅ ፍለጋ ፍላጎት - ፪ቆሮ. ፯፥፲፩) ።
ንሓስ፡ በቁሙ ናስ።
ንሡ፡ ተቀበሉ/ውሰዱ (ዘዳ. ፴፩፥፳፮) ።
ንሣ ንሣ፡ የደጊመ ቃል ንኡስ አገባብ (እንዴት እንዴት እንደ ማለት ያለ - "ይነሡ" - የሰው ስም ብድግ ይበሉ ማለት ነው) ።
ንስሓ አባት፡ ንስሓን የሚነግሩት (የንስሓ አባት ዳግመኛም ነፍስ አባት ይባላል) ።
ንስሓ ገባ (ነስሐ)፡ በክፉሥራው ዐዘነ/ተጸጸተ (በደሉን ገለጠ ኀጢአቱን ተናፃረ ' አመነ ") ።
ንስሓ፡ ጸጸት/ሐዘን (በተሠራ ኀጢአት ምክንያት የሚደረግ) ።
ንስር (ሮች)፡ ካየር ተወርዋሪ ታላቅ ' አሞራ (የፍየል ግልገልና ሠሥ አንሥቶ የሚወስድ የሚበላ ዐይነ ጥሩ ባየር መጥቆ ወደ ታች በተመ ለከተ ጊዜ የሰናፍጭ ቅንጣት የምታኸል ሥጋ አትሰወረውም ይላሉ - ንስር ፫ ዐይነት ነው - ግልገል አንሣ የሎስ ጐሢ - በግእዝ ግን የወል ስም ነው) ።
ንስነሳ፡ ብተና/ጕዝጐዛ/ውዝወዛ።
ንስናሽ፡ የንስንስ ቅሬታ።
ንስንስ፡ ፡ የተነሰነሰ/የተጐዘጐዘ (ጕዝጕዝ ሣር አበባ የተበተነ ዐመድ ትቢያ ጥንጣን ዱቄት ጤፍ) ።
ንስንስ አለ፡ ተነሰነሰ።
ንስንስ አደረገ፡ ነሰነሰ ") ።
ንረታ፡ ድብደባ/ጥዘላ።
ንረት፡ ንጥሪያ/ጕኖሽ/ዝላይ።
ንርት፡ የተመታ/የተጠዘለ።
ንርት፡ የተነረተ/የተነፋ (ንፍ) ።
ንሮሽ፡ ዝኒ ከማሁ ።
ንሺ፡ ተቀበዪ ("(ጥሺ) ንሺ እቴ" - ጭማሪ) ንኡስ አገባብ የነገር።
ንሽ፡ ርጥበት ("ነሣ") ።
ንሽ ኾነ፡ ረጠበ/ራሰ ዕርሻው ("(ላሣ) ንሣ" - ተቀበል ውሰድ - "(ጥሣ) ንሣ" - የነቀፌታ ቃል። ንሣ ይህ ሰው ምን ይላል - በባላገር ግን እሣ ይባላል - "ንሣማ" - ማ ቃለ አጋኖ ነው) ።
ንሽ፡ የመሬት ርጥበት የሚደርቅ/የሚነሣ (ወይም ማሳ ከዝናብ የነሣው የተቀበለው ማለትን ያሳያል) ።
ንቀት፡ ሌላውን መናቅ (ለራስ መናቅ - አስ. ፩፥፲፰፡ ኢዮ. ፲፪፥ ፳፩) ።
ንቁፍ፡ የተነቀፈ/የተሰደበ (ስዱብ ነው ረኛ) ።
ንቃ፡ የትከሻ ስም ("ትከሻ ግንቃ ጠላ እንዲሉ") ።
ንቃሪ፡ የተነቀረ (ጭላጭ ሙጣጭ ጥን ፋፊ) ።
ንቃሻም፡ ንቃሽ ያለበት/የበዛበት (ጕ ድፋም ጥጥ ጐፈሬ) ።
ንቃሽ (ሕጸጽ)፡ ቈሻሻ/ጕድፍ ("የጥጥ ንቃሽ" እንዲሉ) ።
ንቃሽ፡ ጕዳይ/ጐደል/ቅናሽ "
ንቃቃት (ንቅዐት)፡ የመሬት የእለት ሥንጥቃት።
ንቃቃት፡ የመሬት ሥንጥቃት ("ነቃ (ነቅዐ)") ።
ንቃቃት፡ የመሬት ሥንጥቃት ("ነቃ (ነቅዐ)") ።
ንቃቃቶች (ንቅዐታት)፡ ኹለትና ከ ኹለት በላይ ያሉ ብዙዎች።
ንቃት (ንቅሀት)፡ ብንንታ/እንቅስቃሴ (ትጋት ጥንቃቄ መንቃት) ።
ንቃይ፡ ዝኒ ከማሁ ("ለንቅል" - ችግኝ/ምስማር ' ቈርቈሮ - "ያንድ ጊዜ ንቃይ የኹለት ጊዜ ንቃይ" እንዲሉ) ለቅ።
ንቅ (ንቁዕ)፡ የነቃ/የተሠነጠቀ (ሥን ጥቅ ትርትር - "ንቅ ያለበት ዕንጨት ታቦት አይኾንም") ።
ንቅ/ንቁ (ንቁህ)፡ የነቃ/የተጠነ ቀቀ ("ነቅቶ ተግቶ የተቀመጠ ትጉህ ጠንቃቃ") ።
ንቅለኛ (ኞች)፡ ዝኒ ከማሁ።
ንቅላት፡ ውልቃት።
ንቅል፡ ርስቱን ያጣ ሰው።
ንቅል አለ፡ ውልቅ አለ (ተነቀለ) ።
ንቅል አደረገ፡ ምንግል አደረገ።
ንቅልቅል አለ፡ ውልቅልቅ አለ።
ንቅልቅል፡ የተነቃቀለ (ምንግልግል) ።
ንቅሳት፡ ውቅራት/ጥቍራት።
ንቅስ አደረገ፡ ንቅል አደረገ (ነቀሰ) ።
ንቅስ፡ የተነቀሰ (ጥርስ ገላ የጌጥ የቤት ዕቃ የጦር መሣሪያ ሥዕል) ።
ንቅነቃ፡ ቅስቀሳ/ውዝወዛ።
ንቅናቄ (ንክናኬ)፡ ውዝዋዜ ' ቅስቃሴ።
ንቅንቅ (ንክኑክ)፡ ዝኒ ከማሁ (ውዝ ውዝ) ።
ንቅዝ አለ፡ ነቀዘ።
ንቅፍቅፍ፡ የተነቃቀፈ።
ንቆች፡ ማዥራቶች/ትከሾች (ዘፀ. ፳፰፡ ፲፪) ።
ንቡረ እድ፡ በራሱ ላይ እጅ የተጫነበት ያኵስም ጳጳስ ሊቀ ጳጳሳት (በዘመን ብዛት ግን ይህ መንፈሳዊ ሹመት ለመኳንንት ተሰጥቷል - ዕጨጌን ተመልከት) ።
ንቡሬ፡ ሯጭ ፈጣን ።
ንቡር፡ የተቀመጠ/የተጫነ (ግእዝ) ።
ንባብ ቤት፡ የንባብ ቤት ንባብ መ።
ንባብ ትምርት፡ የንባብ ትምርት (በግእዝ "ትምህርተ ምንባብ" ይባላል) ።
ንባብ ዐዋቂ፡ ንባብ የሚያውቅ (በበንግ የሚያነብ) ።
ንባብ፡ ከወርድ ንባብ በኋላ ተማሪ እየጮኸና እያሰማ በፍጥነት የሚናገረው ከነቍጥ እስከ ነቍጥ ያለ የሚነሣና የሚወድቅ የሚጠብቅና የሚላላ የግእዝ ቃል (በግእዝም ነገር ማለት ነው) ማሪያ።
ንባቦ (ሕንባብ)፡ ባ፲፰፻፸፬ ዓ ም
ንብ (ቦች/ንህብ)፡ በቁሙ ባለክንፍ ተንቀሳቃሽ ተባትና እንስት አበባን ኹሉ እየቀሠመች የምትጋግር የማር ዐበዛ ትጉ (ትግህት) ሠራተኛ (ቀፎዋን የነካባትን እሾኽ በሚመስል ፍላጻዋ/ጦር መሣሪያዋ መርዟ ትነድፋለች - ዐርኬና በሚባል ዕልፍኝ የሚውሉ ባጀብ የሚኼዱ አውራ ንጉሥና ንግሥት ውሃ ቀጂ ድንጕል አሏት አውራው ከንግሥቲቱ ጋራ ተራክቦ ካደረገ በኋላ ንቦቹ ይገድሉታል ይባላል ከንግሥትም ንግሥት በተወለደች ጊዜ የናቷን ሰራዊት ከፍላ ከቀፎ) ።
ንብ አስል)፡ ነጭ ሽቶ መሳይ የገደል ቅጠል (ዐዲስ ቀፎ ማጠኛ) ። "ንብ አስኰብላይ" ማለት ነው።
ንብላ (ፅንብል)፡ የራስ ማሰሪያ ወይም ጌጥ ።
ንብረታለም (ንብረተ ዓለም)፡ የዓለም ንብረት።
ንብረት፡ መቀመጥ/አቀማመጥ።
ንብረት፡ ኑሮ/ትዳር/ገንዘብ (ጐዦና ጕልቻ) ።
ንብብር፡ የተነባበረ/የተደራረበ (ድርብርብ በጐታ ውስጥ ያለ እኸል) ።
ንብዝ፡ ልብ ማጣት (አደጋ መከራ ወዳለበት መገሥገሥ/መፍጠን - በግእዝ "እንባዜ" ይባላል - "እከሌ ንብዝ ይዞታል" እንዲሉ - "ንብዝ አደረገ"፡ ቅምት ኣደረገ/ወሰደ - "ንብዝ አለ"፡ ተነበዘ የማይለቅ ኾነ እድፉ) ።
ንብዣ፡ ቅሚያ/ገፈፋ/ሰለባ።
ንብጌ፡ (ነበየ/ነባ) ።
ንብጌ፡ አገር ናበ።
ንትርካም፡ ባለንትርክ (ጭቅጭቃም) ።
ንትርክ፡ ንዝንዝ/ጭቅጭቅ/አተካራ።
ንትርክ፡ የተነተረከ ንዝንዝ ብቅት ("(ጥነ)መነትረክ መበቀት ") ቀተ ።
ንትፋ፡ ንፋት።
ንን፡ አንደኛው ን ዝርዝር (ኹለተኛው ን ገቢር ነው - "እጃችንን ታጠብን ምሳችንን በላን") ።
ንኡሰ ክርስቲያን፡ እምነትና ጥምቀት ያልተፈጸመለት ሰው።
ንኡስ (ንእሰ)፡ ያነሰ/ታናሽ።
ንኡስ ርባታ)፡ አርእስት ቅጽል ሳቢ ዘር ።
ንኡስ አንቀጽ፡ አርእስት ሳቢ ዘር ሣልስ ቅጽል ሳድስ ቅጽል ቦዝ (እነዚህ ኹሉ ማሰሪያነት የሌላቸው ናቸው) ።
ንኡስ አገባብ፡ በትጋት ተግቶ።
ንኡስ፡ የዳዊት መዝሙር መጨረሻ (ትርፍ) ።
ንኪት፡ የተስቦ ጠንቅ ጕዳት።
ንክ (ንኩይ)፡ የተነካ (ገጣባ ፈረስ በቅሎ አያ ግመል።)
ንክ፡ ወፈፍተኛ ሰው።
ንክሳት (ንስከት)፡ ንክሻ (በጥርስ የቈሰለ ገላ ውግታት) ።
ንክስ (ንሱክ)፡ የተነከሰ (ዐኝ የተባለ) ።
ንክር፡ የተነከረ/የተደፈቀ/የራሰ።
ንክሻ (ንስከት)፡ ዝኒ ከማሁ ("እከሌ ጠላቱን ባይን ጥቅሻ በከንፈር ንክሻ አስገደለው") ።
ንክት፡ ዝኒ ከማሁ።
ንክች (ንክየት)፡ መንካት ("ንክች አደረገ" - ጥቂት ላመል ነካ) ።
ንክንክ፡ የተነከነከ/የተበላ።
ንክኪ፡ ባጥንት በኮርቻ በልብስ በመ ኝታ የሚጋባ ቍስል ቂጥኝ።
ንክኪት፡ ዝኒ ከማሁ።
ንዋየ ሐቅል፡ የጦር መሣሪያ የበዳ ጸብት ("በሮማይስጥ አርማ ይባላል") ።
ንዋየ ማሕሌት፡ የዘፈን መሣሪያ (በገና/ማሲንቆ/ጸናጽል/ከበሮ የመሰለው ኹሉ) ።
ንዋየ ቅድሳት፡ የተቀደሱ የክርስቶስ ሥጋና ደም መያዣ ማክበሪያ የቤተ ክሲያን ጻሕል ዐውድ ጽዋዕ ጽና ዕርፈ መስቀል መሶበ ወርቅ አልባሳት።
ንዋየ ቅድሳት)፡ የቅዱስ ቍርባን መቀመጫ ።
ንዋይ (ነወየ)፡ የገንዘብ ስም (ዕንቍ/ፈርጥ/ወርቅ/ብር/ማዕድን/ልብስ ማንኛውም ዕቃ) ።
ንውጥውጥ፡ የተነዋወጠ/የተነቃነቀ ("ንውጥውጥ አለ" - ተነዋወጠ -
ንውጥውጥታ፡ ንቅናቄ - ካህናት ግን "ንውጽውጽታ" ይላሉ) ።
ንውጽውጽታ፡ ንውጥውጥታ ("ነወጠን" እይ) ።
ንዛት (ንዝሀት)፡ የመንዛት ልክና መጠን ("ቈሎውን ቈልቼ አንድ ንዛት ቀርቶኛል") ።
ንዛዣም፡ ትንታም ዞ
ንዛዥ፡ ብንታ ትንታ "
ንዝ (ንዙህ)፡ የተነዛ (በሠማይ ምጣድ ላይ ያለ እኸል) ።
ንዝህላል (ሎች) (ዛህለለ)፡ ዝንጉ/እልል ዘለል ባይ (ሞኝ/ቂል/ሰካር/ተላላ/ከረፈፍ ሥራ ፈት አውታታ - በግእዝ ግን ንዝህ ሉል/እንዝህሉል ይባላል) ።
ንዝህላልነት፡ ንዝህላል መኾን (ዝንጋታ) ።
ንዝነዛ/ንዝናዜ፡ የመነዝነዝ ሥራ (ጭቅጭቃ) ።
ንዝንዛም፡ ንትርካም/ጭቅጭቃም።
ንዝንዝ፡ ኹለተኛው ን ይጠብቃል (ጭቅጭቅ ንትርክ ውዝግብ - ስም) ።
ንዝንዝ፡ የተነዘነዘ (ቅጽል - መነዝነዝ መዠመሪያው ነ ይጠብቃል መጨቅጨቅ) ።
ንዣም (ሞች)፡ ንዥ ያለበት (ባለንዥ) ።
ንዥ (ዢ)፡ የበሽታ ስም (ከንፈርን የሚበላና የሚያቃጥል ቍስል ዕከክ መሳይ - ይኸውም በፍየልና በአንዳንድ ሰው ከንፈር ላይ ተነዝቶ ይታያል - በፈረንጅኛ "አፍት" ይባላል) ።
ንዳዳም፡ ንዳድ ያለበት አገር ወባም።
ንዳድ፡ ትኵሳት ያላት ወባ/ተቅማጥ (ዘዳ. ፳፰፥፳፪፡ ሉቃ. ፬፥፴፰) ።
ንዴተኛ (ኞች)፡ ንዴት ያለበት ተናዳጅ (ቍጡ ብስጩ) ።
ንዴት (ንደት)፡ ቅጥለት/ቃጠሎ/መናደድ/ብስጭት (ኢሳ. ፲፫፥፲፫ - በግእዝ ግን ድኽነት ማለት ነው አንቀጹ "ነድየ" ነውና) ።
ንዴት (ንድየት)፡ ድኽነት ("ንዴት ቅጥለት" - ነደደ) ።
ንዴት፡ ቅጥለት/ድኽነት፡ነደደ/ነደየ።
ንድ (ንዱእ)፡ የተነዳ/የተወሰደ።
ንድ (ንዱድ)፡ የነደደ ("ዋይ ንድድ" እንዲሉ) (ጥድ) ።
ንድላት፡ የውግታት ቀዳዳ።
ንድል (ንዱል)፡ ዝኒ ከማሁ (ሽንቍር) ።
ንድል አደረገ፡ ብስት አደረገ።
ንድሎሽ፡ ዝኒ ከማሁ።
ንድቂያ፡ የመንደቅ (ግንብ) ኣሠራር።
ንድድ አለ፡ ቅጥል አለ።
ንድፋት፡ የፍላጻ የመርዝ ውግታት ("በግእዝ ንድፈት ይባላል") ።
ንድፍ (ንዱፍ)፡ በቁሙ በደጋን ዥማት የተነደፈ የተበተነ ጥጥ ("ንድፍ" ቅጽልና ስም ነው) ።
ንድፍ፡ ድን አትጫን (እከሰል ውሃ በተነከረ ቀጪን ገመድ የተመታ የተመለከተ የሳንቃ የማእዘን ቢጋር - ፩ነገ. ፯፥፴፯ - ፈረንጆች "ፕላን" ይሉታል) ።
ንድፍታም፡ ንድፍት ያለበት ባለንድ ፍት አገር) ።
ንድፍት (ጥድ)፡ የሚቈስል ዕብጠት (የበቅሎና የፈረስ የግመል በሽታ በቈላ ምድር ይይዛቸ ውና ይበጣጥሳቸዋል - "ንድፍት" በግእዝ "የተነደፈች (የተወጋች)" ማለት ነው ድ አይጠብቅም -
ንገር፡ ክፍል ክፍል ያለው የሰንጠ ረዥ መሥመር ።
ንጉሠ ሰላም፡ የፍቅር የደኅንነት ንጉሥ መድኀኔ ዓለም።
ንጉሠ ነገሥት፡ የንጉሦች ንጉሥ (በበታቹ ሌሎች ንጉሦች ያነገሠ እንደ ትግሬው ዐጤ ዮሐንስ ያለ፡ ወይም በንጉሠ ነገሥት ዐልጋ የተቀመጠ ዳግማዊ ምኒልክን ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴን የመሰለ ዐጤ ጃን ሆይ የሚባል።)
ንጉሠ ጽድቅ፡ የውነት ንጉሥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ።
ንጉሡ ምድር፡ ሞት የሚሽረው የምድር ንጉሥ።
ንጉሡ ሠ፡ የሠውት ሠ ስም።
ንጉሡ ሰማይ፡ የዓለም ጌታ እግዜር (ሞት የማይሽረው የሰማይ ንጉሥ) ።
ንጉሣዊ፡ የንጉሥ ወገን መልከኛ።
ንጉሤ፡ የሰው ስም ("የኔ ንጉሥ" ማለት ነው) ።
ንጉሥ (ሦች)፡ በቁሙ የነገሠ (ያገር አውራ የሕዝብ እረኛ መሪና አሳዳሪ ለወዳጁ ሹመት ሽልማት ለጠላቱ እሳት ስለት የሚሰጥ ከገበሬና ከነጋዴ ከሌላውም ሠራተኛ ካ፲ ፩ የሚቀበል - ከሞተ ንጉሥ የቆመ ዐምባ ራስ - ንጉሥ በመንግሥቱ ጕልማሳ በሚስቱ - ተረት፡ "መካር የሌለው ንጉሥ አላንድ ዓመት አይነግሥ" - ዐማንን አስተውል - የደንጊያ ንጉሥ፡ አልማዝ ዕንቍ ፈርጥ ፥አለት የነጠረ ብረት በትረ ቃቃን ድጅኖ) ።
ንጉሥ ሚካኤል፡ የወሎ ባላልጋ።
ንጉሥ ተቈጣ፡ ክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት አለ (ዘመቻ አዘዘ) ።
ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት፡ የጐ ዣም ባላልጋ።
ንጉሥ፡ ዐሥር የዳዊት መዝሙር።
ንጉሥ፡ ከሰንጠረዥ መጫወቻ አንዱ።
ንጉሥ፡ የንብ አውራ የንግሥት ባል።
ንጉሥነት፡ ንጉሥ መኾን።
ንጉሥና ንግሥት፡ የነገሠና የነገሠች (ጃን ሆይና ይተጌ) ።
ንጉሥኛ፡ የንጉሥ አነጋገር።
ንጕር ቅቤ)፡ ኣለቅመም የቀለጠ ።
ንጕር፡ የነጐረ/የፈላ/የቀለጠ ("ንጕር ቅቤ" እንዲሉ) ።
ንጋቱ/ንጋቷ፡ በንጋት የተወለዱ ልጆች በዚህ ስም ይስየማሉ።
ንጋት፡ ጠባ (ጸብሐ) ።
ንጋት፡ ጥቢ/ጥባት/አጥቢያ (ጧት ከ፩ ሰዓት እስከ ፫ ሰዓት ያለ ጊዜ - ዘፀ. ፲፬፥፳፬፡ መዝ. ፻፴፥፮፡ ኢሳ. ፰፥፳፡ ዓሞ. ፬፥፲፫) =
ንግል አለ፡ ንቅል ፍልስ አለ።
ንግል፡ የነገለ (ንቅል/ፍልስ) ።
ንግሥ፡ መንገሥ (አነጋገሥ) ፫ ንጉሥና ንግሥት መኾን ቅባት (የታቦት ዑደት) ዙረት።
ንግሥተ ሣባ፡ ንግሥተ አዜብ ("ንግሥተ ሳባ የሳባ ንግሥት ማክዳ") ።
ንግሥተ ነገሥታት፡ የነገሥታት ንግሥት (እንደ ግርማዊት ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ ያለች) ።
ንግሥተ ንግሥታት፡ የንግሥታት ንግሥት (የንጉሠ ነገሥት ባልተቤት ባሏ ንጉሠ ነገሥት ሲባል እሷ ንግሥተ ንግሥታት ትባላለች) ቶች።
ንግሥተ አዜብ፡ የአዜብ ንግሥት (የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ኢየሩሳሌም የኼደች) ።
ንግሥታት፡ ለብቻቸው የነገሡ ሴቶች።
ንግሥታት፡ የንጉሦች ሚስቶች ይተጌዎች (ማሕ. ፮፥፰፡ ኢሳ. ፵፱፥፳፫ - ባላገር ግን መንግሥትን ንግሥታት ይለዋል) ።
ንግሥት ማክዳ፡ በሐበሻ በትግሬ ሳባ መዠመሪያ የነገሠች ነገሠ።
ንግሥት ቤተ ክርስቲያን፡ ፍሪዳ ሥጋ ወደሙ አሞራ ሰይጣን ወይም ማደሪያው ኀጢአተኛ ሰው ነው - ፩ቆሮ. ፲፩፥፳፯, ፳፱) ።
ንግሥት፡ ዐልጋው ያባቷ ኹኖ ባሏ ሳይነግሥ ብቻዋን የነገሠች እንደ ማክዳ ያለች፡ ወይም ዐልጋው የባሏ ኹኖ ከባሏ ጋራ የነገሠች ይተጌ (የየሩሳሌም ንግሥት፡ ባላገሮች በተረታቸው ብዙ ፍሪዳ ታሳርድና አሞራ ኹሉ ሊበላ ሲሰበሰብ ፊቷን በገለጠች ጊዜ አሞራው ይጠነገዳል (ያልቃል) ይላሉ -
ንግሥት፡ እንስት ንብ ዕንቍላል የምትወልድ።
ንግሥት፡ ከሰንጠረዥ መጫወቻ አንዷ ንግሥት ትባላለች።
ንግረኛ (ኞች)፡ ንግር ያለው (ባለንግር ወሬኛ) ።
ንግር፡ አስቀድሞ የተነገረ ትንቢት ነገረ።
ንግርተኛ (ኞች)፡ ባለንግርት/ንግርታም) ።
ንግርት፡ የተነገረች/የተተነባች።
ንግዴ፡ የሰው ስም (በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ጊዜ የነበረ ወንበዴ) ።
ንግድ የመሰለው ኹሉ። ሲበዛ ሥራዎች ይላል ። "(የቤት ሥራ)" ሕንጻ ግንብ ። "(የወዲያ ሥራ)" የውጭ አገር የፈረንጅ ። "(የሰይጣን ሥራ)" ክፋት ጥመት የመሰለው ኹሉ። "እጀ ሥራ ሸማ ሥራ ክፉ ሥራ ደግ ሥራ" እንዲሉ ። "(ኹለተኛ ሥራ)" መሞት መፍረስ መበስበስ የተፈጥሮ ተቃራኒ ።
ንግድ፡ የነጋዴ ሥራ።
ንግግር፡ ጭውውት።
ንግግሮች፡ ጭውውቶች።
ንጠላ፡ ልየታ።
ንጢ ።
ንጣታም፡ ንጣት የያዘው (ባለንጣት ችግረኛ) ።
ንጣት፡ ነጭ ዕከክ/ፎከት።
ንጣት፡ ነጭነት/ጽዳት።
ንጣይ/ንጥል (ንጻይ/ንጹል)፡ የተነጠለ (ልጣጭ ልዩ ሐር ድር) ።
ንጣጭ፡ የዋንጫ ፍቄት፡ ዐነ ጠጠ።
ንጣፊ፡ ወተት የሌለው ጡት ("ዕራሪን" አስተውል) ።
ንጣፊ፡ የመሬት የቦታ ምትክ ለውጥ።
ንጣፍ፡ በቤት ውስጥ የተነጠፈ (ሉሕልባጥ ሳንቃ) ።
ንጥ፡ የተነጠጠ የተፋቀ የተሰነጠï ስንጥ። ንጣጭ የዋንጫ የሳንቃ የብረት ፍቄት። አነጣጠጥ፡ አፋፋቅ፡ ማንጠጥ ። ባስደራ ጊውና በተደራጊው በሳድስ ቅጽሉ በሳቢ ዘሩ ዐ ' መታጣቱን አስተውል ።
ንጥላት፡ የመነጠል ኹናቴ "
ንጥልጥል፡ የተነጣጠለ ("ንጥልጥል አለ" - ልይትይት አለ - ተነጣጠለ) ።
ንጥሪያ፡ ጕኖሽ/ንሮሽ/ዝላይ።
ንጥር (ንጡር)፡ የፈላ/የነጠረ (ቅቤ ማር ሜሮን ቅባ ኑግ ዘይት ወርቅ ብር መድኀኒት) ።
ንጥር ቅቤ)፡ ከቅመም ጋራ የቀለጠ የፈላ ። (ተረት)፡ "ድኻ በልሙ ቅቤ ባይጠጣ ንጣት ይገድለው ነበር" ።
ንጥሻ፡ ማንጠስ፡ዐነጠሰ።
ንጥሻ፡ ዝኒ ከማሁ ።
ንጥቂያ፡ ቅሚያ (ኢዮ. ፳፬፥፪፡ ሕዝ. ፲፰፥፯, ፲፮፡ ዓሞ. ፫፥፲፡ ናሆ. ፪፥፲፪, ፫፥፩) ።
ንጥበት፡ ነጠባ/ጠብታ።
ንጥቢያ፡ ድፍረት/ዘለፋ/ነቀፋ/ስድብ።
ንጥየተ (ጥጥ) ተነጠጠ/ዐነጠጠ።
ንጥጥር፡ ክርክር ሙግት።
ንጥፍ (ንጹፍ)፡ የተጸፈጸፈ (ደንጊያ ደረጃ ጸፍጸፍ እብነ በረድ) ።
ንጥፍ (ንፁፍ)፡ የነጠፈ/የደረቀ/ ያቈረጠ ወሽ።
ንጩ (ንጹይ)፡ የተነጨ í ንቅል።
ንጭታት፡ በጕንጭ ላይ ያለ የሐዘን ቍስል (ጠጕሩ የተነጨ ቈዳው የተላጠ) ።
ንጭት (ንጽየት)፡ መንጨት/መነ
ንጭት አደረገ፡ ንቅል አደረገ።
ንጸራ (ንጻሬ)፡ እይታ/ምልከታ (ማየት መመልከት) ጥር።
ንጹሕ፡ የነጻ/የጠዳ (ከማመንዘር የራቀ ሰው ነጭ ጸዐዳ ልብስ) ።
ንጹሕ ደም፡ የጻድቅ/የእውነተኛ ሰው ደም (በግፍ የፈሰሰ - ኤር. ፯፥፮፡ ማቴ. ፳፫፥፴፭) ።
ንጽሐ ልቡና፡ የልቡና ንጽሕና (የፍጹም ማዕርግ) ።
ንጽሐ ሥጋ፡ የሥጋ ንጽሕና (የወጣኒ ማዕርግ) ።
ንጽሐ ነፍስ፡ የነፍስ ንጽሕና (የማእከላዊ ማዕርግ) ።
ንጽሐ ጠባይዕ፡ የባሕርይ ንጽሕና።
ንጽሕ/ንጽሕና።
ንጽሕና፡ ንጹሕ መኾን (ጥራት ጥዳት - ፪ቆሮ. ፮፥፮) ።
ንፉል፡ የናፈለ (ውዱቅ) ።
ንፉግ (ጎች)፡ የነፈገ (ቢስ ጩቅ ሥሡ ሥሥታም ቅቅታም - ምሳ. ፩፥፲፱፡ ኢሳ. ፴፪፥፭) ።
ንፉግነት፡ ንፉግ መኾን (ቢስነት) ።
ንፋሻም፡ ንፋሽ የበዛበት እኸል ባ ለንፋሽ።
ንፋሽ፡ የተነፈሰ (ከፍሬ የተለየ ዐሠር) ።
ንፋት (ንፍኀት)፡ ዝኒ ከማሁ (ከ ረቦ መምሰል ማስመሰል) ።
ንፋው፡ አንዘርዝረው ("ንፋው ወሬኛ" - "አባን" እይ) ።
ንፌት፡ ዐፈር ሰበር ዐሠር።
ንፍ (ንፉኅ)፡ የተነፋ/ያበጠ/የተቀ
ንፍር፡ የነፈረ (በጣም የሞቀ የፈላ ሊነኩት የማይቻል ቢቀርቡትም የሚልጥ የሚመልጥ የሚለመጥጥ - "ንፍር ውሃ" እንዲሉ) ።
ንፍርቅ፡ ዝኒ ከማሁ ("ንፍርቅ አለ" - ነፈረቀ) ።
ንፍርቅርቅ አለ፡ ሥንጥቅጥቅ አለ።
ንፍርቅርቅ፡ የተሠነጣጠቀ ቍስል።
ንፍሮ፡ እስኪክክ ድረስ የተቀቀለ እኸል) ።
ንፍቅ፡ የዲያቆን/የቄስ ምክትል ተወራጅ ("ንፍቅ ያዲቆን ንፍቅ ቄስ" እንዲሉ) ።
ንፍጊያ/ንፍገት፡ ሥሥት/ቅቅት (ም ሳ. ፳፰፥፲፮፡ ኢሳ. ፶፮፥፲፩፡ ኤር. ፰፥፲፡ ፪ቆሮ. ፱፥፭ ' ፮) ።
ንፍጣም (ሞች)፡ ባለብዙ ንፍጥ (ካፍንጫው ንፍጥ የማይለይ ሞኝ - ትግሬ ምጥዋም ንፍጥን ነፍጥ ንፍጣምን ነፋጥ ይለዋል።)
ንፍጥ፡ በቁሙ ከአፍንጫ ውስጥ የሚወጣ ተረፈ አንጐል። ("አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል።" - ተረት)
ንፍፊታም፡ ንፍፊት የያዘው/ያለበት (ባለንፍፊት) ።
ንፍፊት (ቶች)፡ የጕያ/የብብት ዕ ብጠት (እጅና እግር በቈሰሉ ጊዜ የሚመጣ - "ፍርንትትን" እይ) ።
ንፍፊት ሞያ፡ ንፍፊት የሚያብጥበት የሚታይበት የብልት ግራና ቀኝ።
ንፍፊት፡ የጕያ ዕብጠት፡ነፋ (ነፍኀ) ።
ንፎ (ትግ. ንፎኅ)፡ እንደጕልላት ያለ ክብር የተሠራ ጌጥ።
ንፎ፡ ያፍን ቀለበት፡ነፋ (ነፍኀ) ።
ንፎ፡ ያፍንጫ ቀለበት (ትንፋሽ የሚያርፍበት ጕትቻ) ።
ኖኅ (ኖኀ)፡ የሰው ስም (በጥፋት ውሃ ባስረሽ ምቺው ጊዜና ከዚያም በኋላ የነበረ ሰው ከሰብኣ ትካት ይልቅ ዕድሜው ስለ ረ ዘመ ኖኅ ተባለ ይላሉ) ።
ኖኅ፡ ብዙ ዝናም።
ኖህ፡ የሰው ስም፡ኖኅ።
ኖኅት/ኖኂት፡ በተጻፈ ፊደል ራስጌና ግርጌ አግድም በመካከል ያለ ጽፈት አልባ ።
ኖረ፡ በራ።
ኖረ፡ ተቀመጠ (እለ ነበረ ቈየ ዘገየ ከረመ) ።
ኖረ —ተቀመጠ ቈየ —ነወረ።
ኖራ፡ በቁሙ በእሳት የተቃጠለ ደንጊያ ዱቄት (ዐመድ) ነጭ ጠመኔ በረቅ መሳይ (ካሸዋ ጋራ ግንብ መገንቢያ ቤት መለሰኛ መለቅለቂያ ድልድይ መሥሪያ ይኾናል - የኖራ ምስጢር ነጭነትና ብሩህነት ብዙ ጊዜ መኖር ነው - "ሠሪ ፍጥረቱን አታለለ በኖራ ሠራኹ እያለ መች እንጠፋ ነበር እውነት ኖራ ቢኾን" - ማኀተመ ወርቅ እሸቴ) ።
ኖራ፡ የደንጊያ ዐመድ —ነወረ።
ኖሬ፡ የሰው ስም (የሕዝቅኤል አባት - "ፋና" ማለት ነው) ።
ኖሬ ፋና —ነወረ።
ኖሮ፡ ዝኒ ከማሁ (ለኑሮ ንኡስ ኣገባብ የነገር ጭማሪ - "እከሌ ዋና ያውቅ ኖሮ ዠማውን አሻገረን" - ፲፰ ክፍል ቍጥር ፭ ተመልከት) ።
ኖቀኖቀ ' ነገነገ)፡ አኖቀኖቀ፡ ድምፅ ሰጠ (የርግብ ያውራ) ።

ኖባ፡ ነበበ።
ኖባ፡ የሰው ስም (በቈላይቱ ኢትዮጵያ ከግብጽ ወዲህ የሚኖር የኵሽ ልጅ የትግሬ ሳባ ታናሽ ወንድም - ዐቢይ ልዑል ማለት ነው) ።
ኖባ፡ ያገር/የነገድ ስም (ኹለተኛም በአረብኛ ሱዳን ይባላል - ሱዳንን እይ - ኖባእምነትንና ጥምቀትን የተቀበለ በሐዋርያት ዘመን ነው - ግብ. ሐዋ. ፰፥፳፯—፴፱ - በ፲፬፻ ዓ.ም. በዐጤ ሰይፈ አርዓድ ጊዜ ጊዮርጊስ የሚባል ክርስቲያናዊ ንጉሥ በኖባ እንደ ነበረ ስንክሳር ይመሰክራል።
ኖብ፡ የሰው ስም (የታወቀ ጻድቅ) ።
ኖብያ፡ የኖባ አገር (ታችኛውና ላይኛው ሱዳን - በግእዝ ኖባ ይባላል) ።
ኖን፡ የፊደል ስም (ነ - ነሐስ እባብ ማለት ነው) ።
ኖኖ፡ ያገር ስም (ዳር አገር) ።
ኗሪ (ዎች)፡ የኖረ/የሚኖር (ያለ/የነበረ ከማለቅ ከመጥፋት ከመለወጥ የራቀ) ።
ኝ (ኒ)፡ እኔ ለሚል የአንቀጽ ዝር ዝር (በሩቅ ወንድ በኀላፊ የሚነገር - "እሱ እኔን ወደደኝ አመነኝ አመሰገነኝ") ።
ኝ፡ በነ የሚጨርስ ግስ የሣልስ (ሳድስ) ቅጽል መድረሻ ("አመነ አማኝ ዘገነ - ዘጋኝ ኰነነ ኰናኝ መነነ መናኝ ") ።
ኝ፡ ወገን ቅጽል ("ግራ ግራኝ አውራ አውረኝ ሙዝ ሙዝኝ") ።

No comments:
Post a Comment