በ ፡ ፪ኛ ፊደል፡ በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ ። በፊደልነት ስሙ ቤት፡ በአኃዝነት በ፪ ይባላል ።
በ፡ (መ፣ ፈ): የመና እና የፈ ተለዋዋጭ። “ዝናም”:- “ዝናብ”፡ “ኰረፍታ”:- “ኰረብታ”።
በ (ሶበ): በቁም ቀሪነቱን ሳይለቅ ከአንቀጽ በኋላ ጊዜን እያስከተለ አንቀጽ ያስቀራል። ምሳሌ: “ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ ለመ”። ማስታወሻ: "በ" ከተናባቢ ሣልስ ቅጽል ሲወጣ "መኪናን" እይ።
በ (በዘ) (ዐቢይ አገባብ): ምሳሌ: “አዳም በበደለ መድኃኔዓለም ክሶ ቀራንዮ ቆማል ከለሜዳ ለብሶ”።
በ (ቸልታ): በቦታ እየገባ በትርፍ አማርኛ ሆኖ ቆሞ ያሰኛል። ምሳሌ: “አሞራ በሰማይ ሲያይሽ ዋለ”።
በ (ደቂቅ አገባብ): ማድረጊያ፡ ፍችው በቁም ቀሪ። ምሳሌ: “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ፡ በሰባተኛው ቀን ግን ዐረፈ”።
በሐላት: ጥርኝ (የዝባድ አውሬ)።
በሐባብ፡ እሲት፡ ትባላለች።
በለ (ትግርኛ): አለ፣ ባለ (ዐድዋ)። ሰዋሰው: “ባለ”፣ “ብለኸ”፣ “በልን”፣ “ይበልን” እይ፡ "የለ" የሚለውንም ተመልከት። "አለ"፣ "በለ"፣ "ባለ"፣ "የለ" እነዚህ አራቱ አንድ ዘር ናቸው።
በለለ (በሊል፣ በለ): በነነ፣ በረረ፡ ጠፋ፣ ተበላሸ፡ መና ቀረ። ማስታወሻ: "በለበለን" እይ፡ የዚህ ድግም ነው።
በለል: የሰለለ (የጠፋ)፡ ጥፉ፣ ብላሽ። ምሳሌ: “አራያ በለል” እንዲሉ።
በለሰ (መሰለ): በለስ መሰለ፡ በለዘ፡ ነጭና ጥቍር ሆነ።
በለሰሰ: ቅንድብን ወደ ታች አለ፡ ገለጠጠ (በለጠጠ)፡ ነጠለ (የውርዴነት)።
በለሰስ/በልሳሳ: የተገለጠጠ (የተበለጠጠ)።
በለሱ: ወንዴ በለስ።
በለሳ: የአገር ስም፡ “በለሳም አገር”።
በለሴ/በለሳዊ/በለስማ: ዘክዛካ፣ ሸክሻካ (ሻካራ) ልብስ፡ መካከሉ ተሸልሎ የሚለበስ (ዘፍጥረት ፫፥፯)። ማስታወሻ: አንዳንድ መምህራን “በለሳ” በሚባል አገር ስለተሰራ "በለሴ" ተባለ ይላሉ።
በለስ (ሶች): በቁሙ የተክል እንጨት ስም፡ ከወይን ጋራ የሚተከል፡ የሾላ ወገን (ወተታም)። እንጨቱም (ፍሬውም) "በለስ" ይባላል።
በለስ (ዕድል): ዕድል (ዕድለኛ)። ማስታወሻ: “ጐበዝ ስለ በለስ” እንዲል ችግረኛ።
በለስ (ዕፀ አእምሮ): የገነት ዛፍ፡ አዳምና ሔዋን ፍሬውን በልተው ቅጠሉን የለበሱት፡ ክፉና መልካም የሚያስታውቅ።
በለስ (ግዳይ): ሔዋን የበለስን ደም እንዳፈሰሰች የሰውን ደም ማፍሰስ (ገዳይ)። ምሳሌ: “በበለሱ ድኻ በንጉሡ። ”
በለስ ዐምባ: የበለስ ዐምባ፡ በለስ ያለበት (የሚበቅልበት) መንደር፡ በላይ ወግዳ ቈላ ያለ።
በለስ አገኘ: ገደለ፡ ቀናው። ማስታወሻ: ይህ ባህል የወሎ ነው።
በለሷ/በለሲቱ: ሴቴ በለስ (ዘፍጥረት ፫፥፯)።
በለሸ (ተደራጊ): ተበላሸ፡ በከከ፣ በከተ፡ በሰበሰ፣ ነቀዘ፡ ቀለጠ፣ ተናዶ ፈረሰ፡ አደፈ፡ ተሰበረ፣ ተቀደደ (ጠፋ) (ዘፍጥረት ፮፥፲፩)።
በለቀጠ: ለየ፣ ከፈተ (የሴትን ኀፍረት)። ተመልከት: "በረገደን"።
በለቀጥ/በልቃጣ: የተከፈተ፡ ክፍት።
በለበለ (በልበለ): በነፋስ ኃይል ወዘወዘ፣ አውለበለበ፡ አስረጀ። አባባል: “የምን ባል ነው፡ ይበለብለውና” እንዲሉ ሴቶች።
በለተ (በልቶ፣ በለተ): ለየ፣ ነጠለ፡ ሥጋን በየብልቱ አወጣ።
በለተ (አደኸየ): አደኸየ፡ ድኻ (ብቸኛ) አደረገ፡ ብቻ አስቀረ።
በለተተ: አፈጀ፡ "በለተ"።
በለተተ: ፈጽሞ አረጀ (አፈጀ)፡ አሮጌ ሆነ፡ ከጕልምስና (ከልምላሜ) ተለየ (ቀዘቀዘ)፡ አፍ ቂጡ ሸበተ። ማስታወሻ: የሚነገረው ለሴት አካል ነው።
በለው (ስም): የሰው ስም።
በለው (አገር): አገርና ነገድ (የበለው አገር፣ የበለው ዘር) በትግሬ በረሓ የሚገኝ።
በለው (የኩሽ ልጅ): ከ፳፰ቱ የኵሽ ልጆች አንዱ "በለው" ይባላል። ምሳሌ: “በለው ከለው” እንዲሉ።
በለው ላት (በሎ ላ): ንገረው፣ ላት፡ ምታው፣ ላት። “ና በለው”: "ናን" ተመልከት፡ "ሞተ ብለህ"፣ "ሞትን" እይ።
በለው: ንገረው፡ ምታው፡ "ባለ"። በለው: የሰው ስም፡ "ባለ"።
በለዘ (በለሰ): ዘጐነ፣ ጠቈረ (የዐይን፣ የጥርስ፣ የገላ)። ተመልከት: "በረዘን"።
በለያ: በጐጃም ውስጥ ያለ አገር (ባልያ)፡ እንደ ምሽግ ያለ ዐምባ (ተራራ)።
በለዲ (ጨርቅ): ሕብሩ (ቀለሙ) ፍጹም ቀይ ያይደለ፡ ከፈይ (ቀይ ዓይነት) ግላስ የሚሆን ግምጃ። በዐረብኛ: “ያገር” (ሀገራዊ) ማለት ነው።
በለድ (ዐረ): የተወለዱበት አገር።
በለገ: በበጋ ዘነመ፡ በጋው ዝናም ሆነ። ማስታወሻ: በትግሪኛ ግን “አቀጠለ፣ አቈጠቈጠ” ማለት ነው፡ ለቆንና የገቦን ያሳያል።
በለጠ (ስም): የወንድ መጠሪያ ስም።
በለጠ (ትግርኛ በለጸ): አደገ፣ ከፍ አለ፡ ላቀ፣ ረዘመ፡ ተረፈ፣ በዛ (ፈደፈደ)። ሌላ ትርጉም: ብልኅ ሆነ፡ ገነነ፣ ከበረ። ተረት: “ባልንጀራዬ ሲበልጠኝ ቍንጣን ይፍለጠኝ። ” ተመልከት: "ፈራ"፣ "ፈረጠጠ" ብለህ "ፈሪን" እና "አንፈራጠጠን"።
በለጠገ (ብዕለ፣ ጸገወ): ጌተየ፡ ጌታ (ሀብታም) ሆነ፡ ብዙ ገንዘብ አገኘ፡ ከበረ (ዘመነ)።
በለጠጠ (ፈሊጥ፣ ፈለጠ): ዐይንን (ከንፈርን) ፈጽሞ ገለጠ (ቀለበሰ)።
በለጠጥ/በልጣጣ/ብልጥጥ: የተበለጠጠ፣ የተገለጠ፡ መገለጢጥ።
በለጤ/በለጠች: የሴት ስም።
በለጥ አለ: ላቅ አለ።
በለጥ: መብለጥ።
በለጨ (በረጸ፣ በረቀ፣ ፈለጸ፣ ፈለጠ): በጥቂቱ ነደደ፣ በራ፡ ፈለቀ፣ አንጸባረቀ፡ ተገለጠ።
በለጭ (በረጽ): ነጭ፡ አልማዝ፡ ቦረቦጭ። ማስታወሻ: ፈረንጆች "ሚካ" የሚሉት የምድር መስታወት።
በለጭማ (በረጸዊ): በግንባሩ ንጣት (ነጭነት) ያለው ከብት። ግጥም: “የኔ አቶ እከሌ የሰጠኝ ሙክት፡ በለጭማ ነው ባለምልክት። ”
በሉ: ንገሩ፡ ምቱ።
በሉጥ: የዛፍ ስም፡ ጥንካሬው ከእንጨት ሁሉ የሚበልጥ፡ የአብርሃም ዛፍ።
በሊ: ቡሊ ቡሊ ሲሏት ሰውን ቀባ ወዳለበት የምትመራ ዕጭ በሊታ ወፍ። “የቡሌ ቡሌማ” ማለት ነው።
በሊታ (በላዒት): የበላች፣ የምትበላ፣ የምታኝክ። ተረት: “ጠፍር በሊታ ብት ሄድ፣ ልጓም በሊታ መጣች። ”
በሊት: (ዝኒ ከማሁ)፡ "ድልሽ በሊት" እንዲሉ።
በላ (መገበ): ነከሰ፣ ቦጨቀ፣ ጋጠ፣ ገመጠ፣ ጐረሰ፡ አላመጠ፣ ዋጠ፣ ሰለቀጠ፣ ተሴሰየ፣ ተመገበ፡ ቈረጠመ፣ ዐኘከ፡ አቃጠለ፡ ወሰደ፣ አሰጠመ። ምሳሌ: “እሳት በላው”፣ “ውሃ በላው” እንዲሉ። ማስታወሻ: "መሳን" እይ። ተረት: “የበላ በለጠኝ፡ የሮጠ አመለጠኝ። ” ከነዕርሙ በላ: መርዶ ባለመስማቱ ሳያለቅስ ቀረ። ዐማ: ነቀፈ። ተዛማጅ አባባሎች: ቡዳ በላው: አሳበደው፣ ዐመመው። ጕቦ በላ: ተቀበለ። ፊቴን በላኝ: አሳከከኝ። ፊት በላሁ: በብሩህ ገጽ ተቀበሉኝ። አይበሉብሽ: የውስጥ እጅ ዠርባ። አይበላሽ: የማይበላው። አባባል: “ውሻ አይበላሽ ጥል” እንዲሉ።
በላ (ሾለ): ሰላ፣ ሾለ፡ ስል፣ ሹል፣ ስለታም ሆነ፡ ፈጠነ፣ ተባ። ማስታወሻ: "ቢላዋን"፣ "ቢላን" እይ።
በላ ልበልኻ (በልአ እበልከአ): የተጋችና የውርድ ነዢ ቃል። ትርጉም: ተናገራት፣ ልናገርህ፡ መልስ፣ ልመልስልህ።
በላለተ: ነጣጠለ፣ ከፋፈለ።
በላላ: (ዝኒ ከማሁ)፡ በናና።
በላላ: ጐራረሰ።
በላሽ: የወፍና የዝንጀሮ ማስፈራሪያ (መት)።
በላተኛ (ኞች): የበላት ወገን፡ ብዙ የሚበላ፡ ሆዳም፣ አጥፊ፣ ዘራፊ፣ በፃ፣ ፈጅ። ሰዋሰው: “በላተኛ” ቢል ሁለት አንቀጽ ይሆናል።
በላት (በላዕት): የሚበሉ (በዮች)።
በላት: በላተኛ
በላቸው (ስም): የሰው ስም።
በላቸው (በሎሙ): ንገራቸው፡ ምታቸው።
በላች (ቾች) (በላቲ): የበለተ፣ የሚበልት፡ በጋማች (ሥጋ ቤት) ዐራጅ (ባለወግ)።
በላይ ነኸ: ነሽ፡ የወንድና የሴት ስም።
በላይ ነኽ ቶራ: ያዳባይ ዥረት ሐርበኛ። (ግጥም)
"በላይ ነኸ ቶራ እሱ ባል ነበር ሰው እንደ በሬ ይታረድ ነበር"።
በላይ: በሰማይ።
"እንጃ"
ብለኸ
"እንጂልኝ"ን አስተውል።
በላይ: የሰው ስም።
በላጭ: የሚበልጥ፡ ላቂ።
በሌ (ትእዛዝ): (ዝኒ ከማሁ)፡ "ውረድ በሌ"፣ "ታች በሌ" እንዲሉ። ማስታወሻ: "ደበለን" እይ።
በሌ: የሰው ወገን (ዶሮ በሌ፣ ሰው በሌ እንዲሉ።)
በል (በለ): የአለና የባለ የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ፡ ተናገር፣ እዘዝ (ማቴዎስ ፰፥፰)። አገላለጽ: ሲያጐላምሱት "በል እኮ"፣ "በልማ" ይላል፡ ዠምር፣ አድርግ፣ ሥራ፣ ምታ ማለት ነው።
በልበላ: ነፋስ የሚወዘውዘው የደስታ ድንኳን (መደረቢያ)። አባባል: “የበልበላ ምድር” እንዲሉ። ማስታወሻ: በጋልኛ ግን "ዘንጋዳ" ማለት ነው፡ ላንፋውን ያሳያል።
በልክ: በመጠን፣ በስፍር።
በልዩ: በውቅ።
በልዩ: የወንድና የሴት ስም።
በልግ (ጎች) (ተወን): የበጋ ዝናም፡ የበጋ ቡቃያና መከር። ምሳሌ: “የበልግ ገብስ” እንዲሉ።
በልጣጭ: የበለጠጠ፣ የሚበለጥጥ፡ ዝንጀሮ፣ ሐኪም።
በሎታ (ቀስታም): በአንድ ወይም በአራት ወገን ስለት ያለው የንት የብረት ዱላ፡ በመቱበት ጊዜ ራስ ቅል የሚበልት (ቈዳን ከሥጋ፣ ዐጥንትን ከአጥንት የሚለይ) (ኢዮብ ፵፩፥፳፩)። ማስታወሻ: ዐጪሩ "ቈመጥ" ይባላል፡ "ጐመድን" ተመልከት።
በሎታ (ዱላ): ባለማንጠልጠያ፣ ራሳም፣ ከንተሮ (ሰንበር) ያለው።
በመለኮቱ: በአምላክነቱ፣ በባሕርዩ።
በመላ ሄደ: ሳይጠይቅ መሪ፣ መንገድ ሳይዝ በዳበሳ፣ እንዲያው ተራመደ (ለምሳሌ ዕውሩ መንገደኛው)።
በመላ ተናገረ: ሳያውቅ ሳይረዳ አወራ።
በመረሬ: የሚዘራ የስንዴ ስም።
በመደዳው: ዐጨደ፣ ቈረጠ፣ አሳጠረ፣ ሸራረፈ።
በማሕፀን: የተሣለ፣ የተረገዘ፣ መላወስ፣ መንቀሳቀስ የዠመረ ፅንስ። "ሲበዛ ስሎች ይላል።"
በማሪያም እጅ ተይዛለች: ሴቲቱ ነፍሴ ጡር ኾናለች።
በምሳ ከበር: ምሳ ትቶ እራት ብቻ እየበላ የከበረ ሀብታም የኾነ።
በሞተ ከዳ: በሞተና በከዳ ፈንታ ተተኪ፣ ምትክ (ወታደር)።
በሰ)፡ ጠበሳ) ፣ አጭበሰበሰ ፣ አላስነድድ፡ ኣላሳይ አለ፡ አጨሰ፡ በትክክል መንደድን ማየትን ከለከለ፡ አጭፈነፈነ። ጨነበሰንን እይ፡ የዚህ ዘር ነው።
በሰለ (መግል): መግል ያዘ (ላላ)፡ ዕባጩ። ምሳሌ: “ጕንፋኑ በሰለ” (መውረድን፣ መንቍርቍርን ተወ) ንፍጡ።
በሰለ (በሲል፣ በሰለ): ከከ፣ ተንደረከከ (ሸተ፣ ጐመራ፣ ደረቀ)፡ ጠነከረ።
በሰለ: ጐመራ፣ ደረሰ። "(ተረት)፡ ብቻ የበሉት ይሸታል ከሰው የበሉት ይሸታል (ይገማል፡ እሸት ይኾናል)።"
በሰላ (ትግሪኛ): ማሳ (ቅብቅብ)፡ የለሰለሰ ዕርሻ።
በሰላ: ለባለዳ የሚከፈል ገንዘብ፡ መከፈሉ የታወቀ (ርግጥ) የሆነ። ምሳሌ: “የበሰላ ዋስ” እንዲሉ።
በሰሎ: መብል (መጠጥ)።
በሰሰ (ዐረብኛ: በጸ): ሰለለ (ሰበቀ፣ አሳበቀ)፡ አዋሸከ።
በሰቈለ: ጐሰቈለ።
በሰቈለን እይ፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
በሰበሰ (በስበሰ፣ አንበስበሰ): ራሰ፣ ረጠበ (ሾቀ፣ ሻገተ)፡ ተበላሸ (በሸቀጠ)፡ ጠቈረ (ተለወጠ) (ዳንኤል ፬፥፲፭፣ ፳፫፣ ፳፭፣ ኢዩኤል ፪፥፳)። ተመልከት: “ቦከቦከን” እና “ቦነቸን”።
በሰበስ/በስባሳ/ብስብስ/ብስባሽ: የበሰበሰ፣ የሻገተ (የተለወጠ፣ የቦከቦከ፣ የጠቈረ) እንጨት፣ ሣር፣ ገለባ፣ ሥጋ፣ ቆዳ፡ በሽቃጣ (ሻጋታ) (ኢዮብ ፳፭፥፮)።
በሰና (ትግሪኛ: በስነወ): ባሰ፣ ማሰነ (ተለወጠ)፡ ጎማ (ከረፋ)።
በሰከ: በተከ (ቈረጠ፣ በጠሰ) በቀላል።
በሰውነቱ)፡ ሰው በመኾኑ ሥጋ፣ በመልበሱ ነፍስን በመንሣቱ።
በሳ (ትግሪኛ: በስዐ): ሰረሰረ፣ ፈለፈለ (ሸነቈረ፣ ቀደደ፣ ነደለ) (ዘጸአት ፳፩፥፮)።
በሳሳ: ሸነቋቈረ (ቀዳደደ፣ ነዳደለ)። ምሳሌ: “እንደ መስቀሉ ይበሳሳኝ” እንዲል ማለኛ።
በሳስ (ሶች): ሰባቂ (አሳባቂ)፡ ነገረ ሰሪ (ቀጣፊ)።
በሳስነት: ሰባቂነት (አዋሻኪነት)።
በሳይ/በሳል: የሚበስል፡ ጥሬ እህል (ተክል)።
በስልት፡ በስልቱ)፡ በክፍል በክፍሉ፣ በወገን በወገኑ፣ ባይነት ባይነቱ (ስም)።
በስመ አብ: የጸሎት መዠመሪያ።
በስቋላ (ሎች): ጐስቋላ።
በስባሽ: የሚበሰብስ፡ ሰው (ፈራሽ፣ ተለዋጭ)።
በስተ: በኩል (እስቲ)።
በስተቀረ: በስተቀር፡ ዝኒ ከማሁ።
በስቲያ: ወዲያ (እስቲ)።
በስከ: በኩል (እስቲ)።
በሶ (ትግሪኛ: በሰወ; አበሰበሰ: በሶን): በቁሙ ከገብስ ቆሎ የተፈጨ ዱቄት፡ በውሃ የራሰ (የተበሰበሰ)።
በሶብላ (በሶ ብላ): ለወጥ የሚሆን ተክል፡ ፍሬው እበሶ ውስጥ የሚገባ፡ ቃናው ቅቤ ቅቤ የሚል ቅመም ነው። አባባል: ጎንደሮች “ዘቃቅቤ (ዜጋ ቅቤ)” ይሉታል። ትርጉም: “ሹሮን፣ ወጥን፣ ቅቤን በሱ ብላ” ማለት ነው።
በረሰ (የውሃ): ተሰረዘ፣ በረደ (ቀዘቀዘ)፡ ፍል ውሃው።
በረሰ: ተሻረ፣ ጠፋ (ከንቱ፣ ብላሽ ሆነ)፡ የንቍጣጣሽ (መንቀያ) ለት ስላልተቀበረ ረከሰ፡ የጥንቆላ (የዓይነ ጥላ፣ የክታብ፣ የመድኃኒት፣ የሥራ ሥር)።
በረረ (በሪር፣ በረ): ቱር አለ (ከነፈ)፡ ተጣደፈ፡ በአየርና በምድር ሮጠ (ፈረጠጠ፣ ጋለበ፣ ሸሸ፣ ሸመጠጠ) (ዘኍልቍ ፲፮፥፴፬፣ ፩ኛ ሳሙኤል ፲፱፥፲)። ሌላ ትርጉም: ወደ ሰማይ ሄደ (ወጣ)። አባባል: “አሞራውም በረረ፣ ቅሉም ተሰበረ” እንዲሉ።
በረረ (አለፈ): ዐለፈ፣ ዘለቀ (ገባ)። ማስታወሻ: ስለ ጊዜ ወይም ሟች ሰው ሲነገር “ይበር፣ ይበራል” ቢል እንጂ “ይበርር፣ ይበርራል” አይልም፡ ቢልም ስህተት ነው።
በረራ: ሩጫ፣ ፍርጠጣ (ግልቢያ)።
በረር: የበረረ። አባባል: “ነጥቆ በረር” እንዲሉ።
በረሮ (ዎች): በቁሙ ጥቍር፣ ጥንዝዛ መሳይ፡ በክንፍና በእግር የሚሮጥ፡ ቆዳና ዐይነ ምድር (አተላ) የሚበላና የሚገምጥ፡ በቈላ የሚኖር (የሚቀመጥ)።
በረቀ (በሪቅ፣ በረቀ): ብልጭ አለ፣ ፈለቀ (በራ) (ኢዮብ ፴፱፥፳፫)። ሌላ ትርጉም: ተመዘዘ፣ ተወረወረ። ሌላ ትርጉም: ነጣ፣ ብርቅ (ድንቅ) ሆነ። ተመልከት: “ጸበረቀ”።
በረቀሰ (በረቀ): ነደለ፣ በሳ፣ ጣሰ (አፈረሰ፣ ጣለ)፡ የአጥር፣ የቅጥር፣ የዦር፣ የድልድል።
በረቀቀ (ትግሪኛ/ሐበሻ: በርቀቀ): አረጀ፡ ፈሱን ለቀቀ (መቋጠር አቃተው ከርጅና የተነሣ)።
በረቃቀሰ: በብዙ ወገን አፈራረሰ (በታተነ)።
በረቈጠ: በረከተ፣ በዛ፡ ተጨመረ (ታከለ፣ ረዘመ፣ ታደሰ)፡ የነገር።
በረቅ ገበያ: ግሃ፡ በረቅ ያለበት (ዐፈሩ በረቅ የሆነ) ገበያ።
በረቅ: በቁሙ ነጭ ዐፈር (ድንጋይ፣ ብሓ፣ ብክካ)፡ ቤት መለቅለቂያ (የምድር ኖራ፣ ጠመኔ) (ኤርምያስ ፳፪፥፲፬)። ተመልከት: “ገረን”።
በረቋ: ነጣ፣ ገረጣ፡ በሰለ (ደረሰ)። ምሳሌ: “የበረቋ የበረቋውን”፡ “የነጣ የነጣውን”፡ ትልቅ ትልቁን (ዕድ)።
በረበረ (በርብሮ፣ በርበረ): በዘበዘ፣ ዘረፈ፡ ጎለበጠ (የላዩን በውስጥ፣ የውስጡን በላይ አደረገ)። “መረመረን” ይመልከቱ።
በረበረ: ፈረፈረ፣ ነደለ፣ አፈረሰ። "ሰረሰረን ተመልከት፣ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።"
በረታ (ትግሪኛ: በርትዐ): ዐየለ፣ ጠና (ጠነከረ)፡ ጐበዘ (ጐለበተ)። ማስታወሻ: ዛሬ ግን ትግሮች “በርትዐን” “በርትዔ” ይሉታል።
በረታ: ሮጠ፣ ፈጠነ፣ ቀለጠፈ (ኢዮብ ፩፡ ፯። ፪ - ፪)።
በረት (ቶች): በጥብቅ የተሠራ የከብት ማደሪያ። የሚሠራውም በካብ፣ በግርግር፣ በማገርና በሽምጥ አጥር ነው (ሕዝቅኤል ፳፭፥፬-፭)።
በረነነ (ባሕረረ): ባነነ፣ ቃዠ (ደነገጠ)።
በረንዳ: በቤት በራፍ ያለ መለሳ፡ በዙሪያው የተበጀ ሰበሰብ፡ ደረጃና ንጣፍ ድንጋይ ያለበት ስፍራ። “በረንዳ” የፈረንጅ ቋንቋ ነው።
በረኛ (ኞች): (አንቀጻዊ) በር ጠባቂ (ኬለኛ) (ዮሐንስ ፲፥፫)። ወንድና ሴትን ለመለየት:
በረኛነት: በር ዘጊነት፣ ከፋችነት (ጠባቂነት)።
በረኛዋ: ያች በረኛ፣ የርሷ በረኛ።
በረኛው: ያ በረኛ፣ የርሱ በረኛ።
በረኛዪቱ: ዝኒ ከማሁ (ዮሐንስ ፲፰፥፲፮)።
በረከ/በረከከ (በሪክ፣ በረከ): ሸብረክ አለ፡ ጕልበቱን ዐጥፎ በጕልበት ቆመ (ለመውለድ፣ ለመስገድ)፡ ተጣጥፎ ተኛ (ተኰደኰደ)። ግጥም: “አዳል ግመሊቱን ይላታል ብረኪ፡ መንደሮቹ ጥቂት፣ ሰዎቹ አነካኪ። ”
በረከተ (ሆድ): ዐበጠ፣ ተነፋ (የሆድ)።
በረከተ (ቆየ): ሰነበተ፣ ቈየ። አባባል: “እብድ የያዘው መልክ አይበረክትም” እንዲሉ።
በረከተ (ባርኮ፣ ባረከ፣ በረከት): በቁሙ በዛ፣ ተጨመረ፡ ተረፈ፣ ተትረፈረፈ (ፈዶፈደ)፡ የምግብ፣ የሀብት፣ የገንዘብ።
በረከተ ሥጋ: ሀብተ ሥጋ።
በረከተ ቢስ: አሲዳም።
በረከተ ነፍስ: ሀብተ ነፍስ።
በረከታም: ባለበረከት (ረድኤታም)።
በረከት: ምርቃት፣ ጸጋ፣ ሀብት፣ ዕድል፣ ድልብ፣ ዐላባ፣ ረድኤት (ብዛት) (ዘዳግም ፳፫፥፭)።
በረከት: በቁሙ “በረከተ”።
በረካ: የወሎ ምርቃት። ምሳሌ: “በረካ ሁኑ” እንዲል ወልይ።
በረኰተ: ሊጥን ቀበረ (ደፈነ)፡ ረመጠ (ርሚጦ ጋገረ፣ አበሰለ)።
በረኸት: የአገር ስም፡ ከቡልጋ በታች ከአዳል በላይ ያለ አገር። ማብራሪያ: ግእዝ “በረከት” “በረከች፣ ተንበረከከች” ይላልና፣ በ“፮ቶ” በሚባለው ከተማ የግመሊቱን መንበርከክ ያስረዳል።
በረኻ: ምድረ በዳ፣ በረሓ።
በረዘ (በሪዝ፣ በረዘ): ጠጅ ጣለ (በጠበጠ፣ ዘለለ)፡ ጠላን ወይም ውሃን ከማር ቀላቀለ (ደባለቀ)። ተመልከት: “በረሰንና”፣ “በረዶን”። ሌላ ትርጉም: ቀዝቃዛ ውሃን በፍል ውሃ ላይ ጨመረ።
በረየ: በረገገ፣ በሬኛ፣ ወገሸ፣ ደነበረ፡ ፈራ፣ ደነገጠ፡ በረረ (ሸሸ)። ተረት: “እባብ ያየ ልጥ ቢያይ በረየ። ”
በረደ (ሞረደ): ሞረደ፣ ፈገፈገ፡ ዘረዘረ። ምሳሌ: “በረዶ” እንዲሉ።
በረደ (በሪድ፣ በረደ): በቁሙ ቀዘቀዘ፡ ሙቀት አልባ ሆነ። ቍጣው፣ ጠቡ፣ ውሃ ጥሙ፣ አየሩ። ማስታወሻ: በረደ፣ በረዘ እና በረሰ በምስጢር አንድ ናቸው።
በረደ (ደከመ): ደከመ (ደነዘዘ)። ምሳሌ: “ስለቱ በረደ”።
በረደደ (መታ): ቀጠቀጠ፣ መታ። ማስታወሻ: በረደደ ዐጕልና ገቢር መሆኑን ያስተውሉ።
በረደደ (በርዶዶ): ረጋ፣ ጸና (ጠነከረ)፡ ከበደ፣ በረታ።
በረደድ (ስም): የሰው ስም።
በረደድ/በርዳዳ: የበረደደ፣ የጸና (የበረታ፣ የከበደ)፡ ጽኑ፣ ጠንካራ (ብርቱ)።
በረድ: ነጭ፣ የብርሌና የብርጭቆ ዓይነት ድንጋይ። “እብንን” ይመልከቱ።
በረዶ (በረድ): የዝናብ ድንጋይ፡ የውሃ ጠጠር፡ የእህልና የአትክልት ጸር። የፈረንጅ ሠራሽ በረዶ: እየተሰበረ የሚሸጥ (የሚታደል)። ማስታወሻ: “በረድ” ግእዝ ነው።
በረዷም (ዘበረድ): በረዶ ያለበት ደጋ ተራራ፡ የወልን (ቧሒትን) የመሰለ።
በረጀ: ብልጭ አለ። "በረዠ"።
በረገደ: ከፈተ፣ ከፈለ፣ ተረረ፡ ሁለት አደረገ (ፈለጠ)።
በረገድ/በርጋዳ: የተከፈተ (ክፍት)፡ የተፈለጠ (ፍልጥ)።
በረገገ (ሰበረ): ፈነከተ፣ ሰበረ (ወለለ)። ምሳሌ: “ራሱን በረገገው” እንዲሉ።
በረገገ (ተገታ): ተገታ፣ ደነገጠ፣ ፈራ (ደነበረ)፡ በረየ፣ አፈገፈገ፡ ዦሮውን ቀፈረ (ዐይኑን ተኰረ)።
በረገግ/በርጋጋ: የደነበረ (ደንባራ)።
በሪ (በራሂ): የሚበራ።
በሪድ/በራድ: የበረደ (የቀዘቀዘ)፡ ቀዝቃዛ ውሃ።
በራ (ዎች) (በርሖ፣ በርሐ፣ በራሕ): መላጣ (ራሰ ገላጣ)፡ ጠጕሩ የሸሸ (ከቦታው የታጣ)፡ ቡሓ። ግጥም: “እንካ ብላ አለችኝ ደረቁን እንጀራ፡ እሷ በነካካው በራ ሰው ልትበላ። ”
በራ/ባራ (በሪህ፣ በርሀ): ቦግ (ተግ) አለ፡ ታየ፣ ተገለጠ፡ ወገገ፣ ፈካ (ነጣ)፣ ሸበረቀ። ምሳሌ: “ዕውርን ምን ትፈልጋለህ ቢሉት፡ ዐይኔ እንዲበራ አለ” (ማርቆስ ፲፥፶፩)።
በራሪ (ዎች): የሚበር፣ የሚከንፍ (የሚያልፍ)፡ አንበጣ፣ ወፍ፣ አሞራ (ጠያር፣ ጥያራ) (ምሳሌ ፳፮፥፪፣ ዘካርያስ ፭፥፪)።
በራቂ: የበረቀ፣ የሚበርቅ፡ ብልጭ ያለ (የሚበራ)።
በራቂት: የአገር ስም፡ በትግራይ ውስጥ የምትገኝ አገር። “የምትበርቅ፣ ባለበረቅ” ማለት ነው።
በራነት (ብርሐት): መላጣ መሆን፡ ቡሕነት (ዘሌዋውያን ፲፫፥፵፪)።
በራኪ: የሚበርክ።
በራዥ (ዦች): የበረዘ፣ የሚበርዝ (የሚበጠብጥ)፡ በጥባጭ፣ ጠጅ ጣይ (መሸተኛ፣ ዐጣሪ)።
በራይ: ረገጣ (አኼዶ)።
በራጅ: የሚበርድ፡ ቀዝቃዛ ብረት (ቍርበት)።
በራፍ: የአጥር፣ የቅጥር ወይም የቤት መግቢያ፡ "አፈ በር" ማለት ነው።
በሬ (ብዒር፣ በዐረ፣ ብዕር): ስሙን አይምጣ፣ ተላይ አይቸግረው፣ ተጅ አይጡ የሚሉት የቀንድ ከብት፡ ተጠምዶ የሚያርስ እንስሳ። በምሳሌያዊ አነጋገር ደግሞ ሞኝ ወይም አላዋቂ ሰው ማለት ነው። አባባል: “በሬ ሆይ ሣሩን አየኸና ገደሉን ሳታይ። ” ማስታወሻ: በሬ የሚለው ቃል የመጣው ከበረየ ነው። ለተጨማሪ ማብራሪያ “አባት” የሚለውን ይመልከቱ።
በሬ ወለደ: ፍጹም ውሸት።
በሬሳ (ኦሮምኛ): ወንዝ፡ የወንዝ ስም። ትርጓሜውም “ሸልሙ” ማለት ነው። ምሳሌ: “በሬሳ ወንዝ” እንዲሉ። ማስታወሻ: በወግዳና በተጕለት ቈላ ግን “ሱላይ” ይባላል፡ ይኸውም የደብረ ብርሃን ዠማ ነው።
በሬው: ያ በሬ ወይም የእርሱ በሬ።
በር (ሮች): ደጃፍ፣ ክፍት (ኅዋ)፡ መውጫና መግቢያ (ማለፊያ፣ መዝለቂያ)፡ ብስ፣ ነዳላ (ኬላ፣ ዐራዳ)።
በር (በረረ): "በረረ" የሚለውን ግስ ይመልከቱ።
በር (በረበረ): "በረበረ" የሚለውን ግስ ይመልከቱ።
በር (ደጃፍ): ደጃፍ (በር)።
በር መታ: “ክፈቱልኝ” አለ።
በር ከፋች ነ፡ (እምነ): የግእዝ አገባብን ይመልከቱ።
በር ከፋች: በቁሙ ቍልፍ ያዥ።
በር ዘጊ (ዐጻዌ ኆኅት): በርን የሚዘጋና የሚቆልፍ።
በር: ይህ ቃል የተለያዩ ትርጉሞች አሉት።
በርሚል (ሎች): ከብረት ወይም ከእንጨት የተሠራ ባለ ሁለት መቀነትና አንድ ፍንጭ ያለው የድብኝት ዓይነት ትልቅ መያዣ (ሻታ)። የብረት በርሚል ከውጭ ጋዝ፣ ቤንዚንና ስፒሪቶ ለመጫን ሲያገለግል፣ የእንጨት በርሚል ደግሞ ዘይትና ወይን ጠጅ ለማምጣት ይጠቅማል። ይህ ቃል ከዐረብኛ የመጣ ነው።
በርሞሌ: ቀረሻሽንቦ ከሚመስል ቅጠል የሚሠራ የሽቱ ስም።
በርቀቅ አለ: ላጥ (ቀደድ) አለ፡ ተፈሳ።
በርቃሳ/ብርቅስ: የተበረቀሰ፣ የተጣሰ (የፈረሰ)።
በርቆ: ብልጭ ብሎ። ተረት: “ባልነቃ ሰንጥቆ፣ ባልደመነ በርቆ”፡ “ገና በርቆ፣ ገና ዘንሞ”።
በርበራ: የሱማሌ አገር፡ አቅኒውና ዘሩ የበርበር ቍራጭ ስለሆነ “በርበራ” ተባለ። ትርጓሜውም “በዘበዛት፣ ዘረፋት” ማለት ነው።
በርበሬ (ቅመም): በቁሙ ቀዮ፡ ከበርበር የመጣ ተክል፡ ሲበሉት የሚያቃጥል (የሚለበልብ፣ የሚተኩስ)፡ ከሽንኵርትና ከጨው ጋራ የሚደለኽ (የሚዘጋጅ)። አባባል: “በጨው ደንደስ፣ በርበሬ ተወደስ” እንዲሉ። ተመልከት: “ሚጥሚጣንና” “ቃሪያን”። የውሻ በርበሬ: ፍሬው የማይበላ የዱር በርበሬ።
በርበሬ (በርበሪ፣ በርበራዊ): መልኩ የበርበርን ጠጕር የሚመስል ቍንዶ በርበሬ። “ቍንዶን” ይመልከቱ።
በርበር (ሮች): ያልተማረ፣ ያልሰለጠነ ሕዝብ፡ ጭንጩ፣ አረመኔ፣ ሽፍታ (ወያኔ)፣ ዘራፊ። ቦታ: ከግብጽ ቀጥሎ የሚገኝ የነገድና የአገር ስም፡ የአፍሪካ ክፍል (ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ቱኒስ፣ ትሪፖሊ) ናቸው። በግእዝ: ሐቃል ይባላሉ (ቈላስይስ ፫፥፲፫)።
በርባሪ: የበረበረ፣ የሚበረብር (የሚገለብጥ)፡ ባለመንሽ፣ ወራሪ (ዘራፊ)።
በርባሮስ: ታላቅ፣ ሰፊ ጕድጓድ፡ የጥልቅ ጥልቅ ታች (መጨረሻ፣ መቀመቅ)።
በርባን: በወንጌል የተነገረ የሰው ስም፡ ሽፍታ፣ ወንበዴ፣ ቀማኛ (የወንበዴዎች አለቃ)።
በርተሎሜዎስ: የሰው ስም፡ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ።
በርታ በል: “ጠንከር በል”፡ አበረታት (አጠናን፣ አጠነካከር)፡ መበርታት።
በርታ አለ: በረታ። ሌላ ትርጉም: “ጠንክር” አለ።
በርታ: ጥና፣ ጠንክር (ጨክን፣ ዐይል) (ሐጌ ፪፥፬)።
በርኖሴ (በርኖሳዊ): ተምች (ጥቍር ትል)፡ በርኖስ የሚመስል። ሌላ ትርጉም: “የኔ በርኖስ”።
በርኖስ (ሠቅ): ከበግ ጠጕር የተሠራ ማቅ (ዝተት)።
በርከት አለ: በረከተ (በዛ)።
በርከት አደረገ: አበረከተ።
በርከት: መበርከት።
በርከክ አለ: ተንበረከከ፡ ቀስትን ወይም ጥይትን ለመንደፍ (ለመተኰስ)።
በርከክ: መንበርከክ።
በርካ (ዐረብኛ: ቢርካ): ድልድል (ዦር)፡ የውሃ መቆሚያ (መጠራቀሚያ)።
በርካታ: የበረከተ፣ የበዛ (ብዙ)።
በርካች: የሚበረክት፣ የሚበዛ።
በርደደን እያ: በርደዶ ለሸሎ ቅጽል መኾኑን አስተውል።
በርደዶ: ብርቱ፣ ኃይለኛ፡ ራስ የሚመታ ጠላ። “ሸሎን” ይመልከቱ።
በርገግ አለ: በረገገ።
በርጋጅ: የበረገደ፣ የሚበረግድ፣ የሚሰነጥቅ።
በርጋጊ: የበረገገ፣ የሚበረግግ (ደንባሪ)።
በርጩማ (ኦሮምኛ): ሶስት እግር ያለው ክብ መቀመጫ፡ ደቅ መሳይ፡ ወይም በምስማር የተበጀ ሞላላ የሳንቃ ቍራጭ።
በሮ: ከንፎ፣ ሮጦ፣ ተጣድፎ (ኢሳይያስ ፮፥፯)። ማስታወሻ: “በርሮ” አለመባሉን ልብ ይሏል።
በሮች (አባዕር): ሁለትና ከሁለት በላይ ያሉ በሬዎች (ዘጸአት ፳፬፥፭)።
በሸረከ: በጠረቀ፣ ቀደደ (ሸረከተ)።
በሸረክ/በሽራካ: የተበሸረከ፡ ቀዳዳ (ሸርካታ)።
በሸቀ: ዐዘነ፣ ተከዘ (ተበሳጨ፣ ተናደደ)። ምሳሌ: “ልቡ በሽቋል” እንዲሉ። ማስታወሻ: በትግሪኛ ግን “ተላጠ” ማለት ነው።
በሸቀጠ: ፈጽሞ ራሰ (ረሰረሰ)፡ በሰበሰ (በከተ፣ ተበላሸ)።
በሸቀጥ/በሽቃጣ (ጦች)/ብሽቅጥ: የበሸቀጠ (የራሰ፣ የረሰረሰ)፡ በክት (ነውረኛ)።
በሸበሸ: ተጠመቀ (መላ፣ ተረፈ)፡ ወፈረ (ለሰለሰ)።
በሸከከ (አንበሸከከ): አንቀባረረ (አንበጠረረ)።
በሺ: የበሳ፣ የሚበላ (የሚነድል)፡ ሸንቋሪ።
በሻቃ/ብሽቅ: የበሸቀ፣ ያዘነ (የተከዘ፣ የተናደደ)።
በሻኸ ውረድ: ዝኒ ከማሁ።
በሻኸ: የሰው ስም፣ በፈለገኸ፣ በፈቀደኸ።
በሽ: ቅልሽልሽ (መቅለሽለሽ)። ምሳሌ: “ቅልብሽ ዞበሽ አለው”፡ “አቅለሸለሸው”፡ “ልውጣ፣ ልመለስ” አለው። ማስታወሻ: “በሽታን” ይመልከቱ፡ የዚህ ዘር ነው። “ታ” ምዕላድ ሆኖ ስለተጨመረበት በዚህ አልተጻፈም።
በሽ: ቅልብሽ (በሸበሸ)።
በሽሎ: የበጌምድር ወንዝ ስም፡ በወሎና በየጁ መካከል ያለ ዠማ።
በሽበሽ: የመላ፣ የተረፈ፡ ምሉ (ትርፍ)።
በሽቢያ፡ ጋለበ)፡ ሥር የሌለው ነገር ተናገረ።
በሽተኛ (ኞች): ዕመምተኛ (ጤና የሌለው፣ ዱያታም)።
በሽተኛነት: ዕመምተኛነት (ጤና ቢስነት)።
በሽታ (ስም): “በሽ” ማለት።
በሽታ (በሸበሸ): በቁሙ ዕመም (ራስ ምታትና ፍልጠት፣ ሆድ ቍርጠት፣ ቍርጥማት፣ ውጋት፣ ተስቦ፣ ወባ፣ ትኵሳት፣ ምች)፡ የመሰለው ሁሉ። የኅዳር በሽታ: በ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ኅዳር ፭ ቀን ላሙስ አጥቢያ ከሌሊቱ ደረቅ የመዓት ካፊያ አካፋ፡ ከዚህ የተነሳ ዓፍለኛ ወንድና ሴት፣ ልጅ፣ እግር ሁሉ አለቀ። ነገር ግን ወግዳ፣ ሕርያቆስ አገር አልገባም።
በሽታ፡ ሰከረ)፡ ሳይጠጣ መጠጥ ስለ ሸተተው።
በሽታ ወጣለት: ለቀቀው (ዳነ)።
በቀለ (በቊል፣ በቈለ፣ በቅሎ፣ በቀለ): በቁሙ ጐነቈለ፡ ከአፈር ከመሬት ተዛመደ (ተዋሐደ)፡ ጸደቀ፡ ሥርን ወደ ታች (ቅጠልን ወደ ላይ) ሰደደ፡ ሠረጸ (ተገኘ)። ሌላ ትርጉም: በልብ ዐደረ (ተያዘ) (ቂሙ፣ ጠቡ፣ ጥላው)።
በቀለኛ: ደመኛ፣ ቂመኛ፡ ደም መላሽ።
በቀላል: ወቀጠ (የቈሎ፣ ያሻሮ)።
በቀል (ሎች): የበቀለ (የወጣ)፡ እወጣጡ እንደ ዘንባባ ያማረ (የሰመረ) ወጣት። ምሳሌ: “አንድ በቀል፣ ዐብሮ በቀል” እንዲሉ።
በቀል (ቅጣት): በቁሙ ቅጣት፡ የክፉ ብድራት (ዕዳ፣ ፍዳ፣ ቂም፣ ደም፣ ዐሎ) (ሮሜ ፲፪፥፲፱)።
በቀል (ተክል): ዐረቦች ሥሩን (ጥሬውን) የሚበሉት ተክል።
በቀልት (ግእዝ): ዘንባባ።
በቀረ: ምኞትና ጸጸት። "ጥፋተኛ ሰው እቤታችን ዐድሮ ከሚያስቀጣን ምነው ሳይመጣ በቀረ። " "ንኡስ ኣገባብ ሲኾን። "
በቀር: በቁሙ "ቀረ"።
በቀር: ከጻድቃን በቀር ኃጥኣን መንግሥተ ሰማይ አይገቡም። "ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ከዮሐንስ በቀር ሌላ አልተገኘም። "
በቀቀ/ባቀቀ (በቂቅ፣ በቀ፣ ዕብ ባቃቅ፣ አስራቆተ፣ ባዶ አደረገ): ተከፈተ፣ ተለቀቀ፡ ክፍት ሆነ (ዋሻ መሰለ)፡ የአፍ (የጕድጓድ)። ማስታወሻ: ኦሮምኛ “ንቃቃትን በቀቃ” የሚለው ከዚህ ጋራ ይሰማማል። ተመልከት: "በቀበቀን"፡ የዚህ ዘር ነው።
በቀበቀ (በቂቅ፣ በቀ፣ በቅበቀ): ሠነጠቀ፣ ተረተረ፡ ዕዳሪ አወጣ፡ አጥልቆ ዐረሰ (በረበረ)።
በቀበቅ/በቅባቃ: የሚንሰቀሰቅ፡ ፈሳም፣ ላጤ።
በቀተ: ነዘነዘ፣ ነተረከ፣ ጨቀጨቀ (ዘበዘበ)።
በቀንድ አስተኛ: (ማንቍርትን፣ ወንገትን ወደ ላይ፣ ማዥራትን ወደ ታች አደረገ)፡ ዘለሰ (ለማረድ)።
በቀዳዳ: ኼደ፣ ወጣ፣ ወለቀ፣ አመለጠ።
በቁሙ፡ "ዐይን፡ እግር"፡ ተብሎ፡ በግእዝ፡ የተነገረውና፡ ሌላውም፡
ይህን፡ የመሰለው፡ ኹሉ፡ በአማርኛም፡ እንዲሁ፡ ስለ፡ ኾነ፡ ትርጓሜው፡ በቁሙ፡ ይባላል። ዳግመኛም፡ በግእዝ፡ "ገደለ፡ ነገረ፡ ሰበረ"፡ ብሎ፡ በአማርኛ፡ ፪ኛውን፡ ፊደል፡ ከማጥበቅ፡
በቀር፡ ልዩነት፡ ስለሌለው፡ በቁሙ፡ ያሠኛል።
በቁሙ፡ ሳይቀመጥ፡ ሳያርፍ። ምሳሌ: "እከሌ፡ ከኼደበት፡ በቁሙ፡ ተመለሰ። "
በቁሙ፡ በሕይወቱ፡ ሳይታመም፡ ሳይሞት፡ ከነነፍሱ። ምሳሌ: "ወንጀለኛውን፡ በቁሙ፡ ቀበሩት። "
በቁም፡ ቀሪ፡ በ፡ ለ፡ በግእዝ፡ በፈጣሪ፡ ለፈጣሪ፡ የተባለው፡
በአማርኛ፡ ስለማይለወጥ፡ በቁም፡ ቀሪ፡ ተባለ።
በቁም፡ እንዳለ፡ ሳይለወጥ።
በቁምኸ፡ "ቁመሽ፡ ሳለኸ፡ እንደ፡ ቆምኸ፡ ሳትቀመጥ፡
ታዘዝ"፡ ማለት፡ ነው። ምሳሌ: "በቁምኸ፡ ማርያም፡ ቈሎ፡ ታቈርጥምኸ"፡ እንዲሉ።
በቂ (በቋዒ): የበቃ፣ ልክ የሆነ፡ የሚበቃ (የማያንስ)፡ የሚጠቅም (ጠቃሚ)።
በቂ (ገዳይ): የገደለ (ገዳይ)፡ የሞተች። ማስታወሻ: የስም ምትክና ቅጽል ሁሉ ነው።
በቂታ (በቋዒት): የበቃች፣ ልክ የሆነች፡ ያደገች (የደረሰች)፡ የቈነዠች።
በቃ (በቊዕ፣ በቍዐ): ልክ ሆነ፡ ተገባ፡ ሰለቸ፣ ተጠገበ፡ ተወረሰ፣ ተፈጸመ፣ ደረሰ።
በቃ (ብስለት): በሀብት (በዕውቀት) ሠለጠነ፡ በቅድስና ከበረ፡ ፍጹም ሆነ፡ ጣዕም ቀመሰ (ጸጋ አገኘ)።
በቃ በለው: ማረው፡ ወይም ግደለው (ከሥቃይ አሳርፈው)።
በቃቀለ: የበቀለ ድርብ።
በቃቃ: መላልሶ በቃ (ኢሳያስ ፵፥፳፱)።
በቃች (ቾች): የበቀተ፣ የሚበቅት (የሚነተርክ)፡ ነትራኪ።
በቃይ (በቋሊ): የሚበቅል (የሚወጣ)፡ ጸዳቂ።
በቈልት (ቶች): በውሃ ርሶ (ዝናብ መቶት) የበቀለ (ያጐነቈለ) ባቄላ፣ ስንዴ።
በቈሎ (ዎች): ባር ማሽላ (ከባሕር የመጣ ማሽላ)፡ ስለ ሽቱ ጣዕም “ማር ማሽላ” ይሉታል።
በቅ/ብቁ (በቋዒ፣ ብቁዕ): በቂ። ምሳሌ: “ላገር በቅ” ያንድ ብቁ እንዲሉ።
በቅል (ሱማሌ፣ ሐረርጌ፣ ጕራጌ): የቁጥር ስም፡ መቶ። ማስታወሻ: ሸማኔዎችና ዝሓ አዝጊዎች (ድር አድሪዎች) ዝሓውን (ድሩን) “አንድ በቅል፣ ሁለት በቅል” እንዲሉ።
በቅሎ (ዎች) (በቅል፣ አብቅልት): በቁሙ አጋሰስ፡ ከአህያና ከፈረስ የሚደቀል (አባቱ አህያ፣ እናቱ ፈረስ)።
በቅሎ ገሪ: በቅሎን የሚገራ፣ የሚያሠለጥን።
በቅሎኛ (በቅላዊ): ባለበቅሎ፡ በቅሎ ያለው (በበቅሎ የተቀመጠ) ሰው።
በቅሎውን አገደ: ከለከለ፣ ሃይ አለ።
በቅጥ: በሥርዓት፡ ቀጣ።
በቋል (ሊ): ጨረባ (ጥሬ ፈጅ)፡ ጐዦ ለመሥራት ቡቃያ ቈራጭ።
በበሬ፡ በጐሽ፡ በግመል፡ ዠርባ፡ ላይ፡ ያለ፡ የስጋ፡ ዲብ፡ ክብ፡ እንክብል፡ (ጥብ)ጕብል: (ዘዳግም ፲፰፡ ፫)።
በበተ: አገባ፣ ከተተ (በውስጥ አደረገ)።
በባላገር ላይ)፡ የሚደረግ የወታደር ምሪት ወይም ሥሪት።
በባላገር ግን ለአንድ ተባትና ለእንስትም ይነገራል። "ቍንጫጪትን" እይ።
በቤተ ክርስቲያን)፡ ስለ ሞቱ ሰዎች ለካህናት የሚዘጋጅ ባቡቴ።
በብዙዎች ወንዶችና ሴቶች ቅጽል መድረሻ ሲኾን:
በተሓ (ትግሪኛ: በቲሓ): ብርዝ (ለጋ ጠጅ)፡ ጌሾ ያልበዛበት (ያልበሰለ) (፪ኛ ነገሥት ፲፱፥፴፪፣ ኢዩኤል ፩፥፭)።
በተለምዶ ደግሞ: "ዝናም መጣ"፡ "ጦር መጣ"፡ "እንግዳ መጣ"፡ "አሳር መጣ"፡ "መዓት መጣ"፡ "ሽንት መጣ"፡ "አይነ ምድር መጣ"፡ "ሰው መጣ"፡ "ነገር መጣ" በሚሉ አባባሎች ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል።
በተለየ: በብቻ፣ በክፍል።
"በተለየ ንዳ፡ በጠራ ቅዳ" እንዲሉ።
በተል: የስሜን ዓምባ ተራራ።
በተስፋ)፡ ባለኝታ፣ በተስፋ እየኖረ ደጅ የሚጠና። (ባል ብለህ ባለን ተመልከት)።
በተራ፡ በተራ)፡ በቅደም ተከተል፣ በረድፍ በረድፍ።
በተበተ (በትበተ): ቦጠቦጠ (ፈለፈለ)፡ ውስጥ ውስጡን በላ (አቃጠለ፣ በገበገ)።
በተተ: አለቀ (አረጀ)፡ የልብስ።
በተነ: ወረወረ (ዘሪ፣ አዘራ)፡ “መንሽ” አለ፡ ዘረዘረ (ዘረረ)፡ ፈታ (ለየ)፡ ፈነጠቀ (ነሰነሰ)። ምሳሌ: የዘር (የእኽዶ)፣ የገንዘብ (የአፈር)፣ የሸንጎ (የደም)፣ የሣር (ሩት ፫፥፪፣ መዝሙር ፻፲፪፥፱፣ ሉቃስ ፲፭፥፲)። ሌላ ትርጉም: “ሻ” አደረገ፡ ምግብ።
በተከ (በቲክ፣ በተከ): በሰከ (በጠቀ፣ በጠሰ፣ ቈረጠ)፡ አባላ መታ።
በተዋረድ፡ በዝቅታ፡ በላይና በታች።
በተዘዋዋሪ ደግሞ: አሳቀ ወይም አንከተከተ (ሳቅ) ማለት ነው።
በተጨማሪም: ታላቅ ጥምጥም ጠመጠመ ወይም ደመረ የሚለውንም ያመለክታል።
በተጨማሪም: አንድን ልጃገረድ በጠለፋት ሰው ሚስትነት እንድትኖር አስደረገ የሚለውን ትርጉም ይይዛል።
በተጨማሪም: ወደቀ፣ በላይ ሆነ፣ ወይም ተጫነ ለመያዝ ማለት ነው። ለምሳሌ፣ "እከሌ በደን ውስጥ ሲኼድ ድንገት ነብር ተከመረበት"።
በታተነ: ፈታታ (ለያየ)፡ ለየብቻ አደረገ (ፈነጣጠቀ፣ ነሳነሰ)።
በታተከ: በብዙ ወገን ቈረጠ።
በታኝ (ኞች): የበተነ (የሚበትን)፡ የሚዘራ (ወርዋሪ፣ ዘሪ፣ አዝሪ) (ምሳሌ ፲፰፥፱)።
በት (ቦቱ): በኃላፊና በትንቢት፣ በዘንድና በትእዛዝ አንቀጽ መጨረሻ እየገባ ይነገራል። ምሳሌ: “መጣበት”፣ “ይመጣበት”፣ “ይመጣበት ዘንድ”፣ “ይምጣበት”። ይኸውም የክፉ ነው። ተመልከት: “ለትን”። መጽሐፍ ግን “በት” ከማለት ይልቅ “ለት” ይላል፡ ስህተት ነው (፩ኛ ሳሙኤል ፲፪፥፫)።
በትረ ሙሴ: የማርያም ዘንግ (ችርንችር)፡ ባለማእዘን እንጨት። ወላድ በምጥ ጊዜ የምትይዘው።
በትረ ቃቃን: ዱቅንዱቅ (መንደልት)፡ የካክራ ብረት በትር፡ ድጅኖ። በግእዝ: “ምንኃል” ይባላል። ተመልከት: “ቃቃንን”።
በትረ ወርቅ: ከወርቅ የተሠራ ዘንግ።
በትረ ያሬድ: የተድባበ ማርያም አለቃ (ሊቀ ጳጳስ)፡ “መዠመሪያ አባት” ማለት ነው።
በትረኛ: ተማች (ዱለኛ)።
በትር (ምት): የጐራዴ ምት።
በትር (በቲር፣ በተረ፣ በትር): ዘንግ (ሽመል፣ ምርኵዝ፣ ዱላ፣ ጐመድ፣ ከንተሮ፣ መንደርቶ፣ ለበቅ፣ ንገር)። ተረት: “የፈሪ በትር ዐሥር” እንዲሉ። ታሪክ: “በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመን ይህ ተረት ተፈጽሟል። አንድ ሠዓሊ ሚስቱን ከወንድ በያዛት ጊዜ በቤቱ ውስጥ አንድ ሸክም ፍልጥ ነበርና አንዱን እየመዘዘና እያማረጠ ጥሎ ከወረሰ በኋላ የሚስቱን ውሽማ ‘ምሬኻለሁና ኺድ’ አለው እየተባለ ይወራ ነበር። ”
በትባች: የበተበተ (የሚበተብት)፡ የሚበላ (ውሻ፣ ዥብ፣ እሳት፣ ቂጥኝ)።
በትን: ዝኒ ከማሁ። “ዐጭዶ በተን” እንዲሉ።
በትኩሱ)፡ ሳይበርድ፣ ሳይቈይ።
በትግሬ በረሓ: ያለ ባለመከራ የሻንቅላ ዘር። "ጥቍር ጠቋራ።"
በትግሬ ክፍል: ያለ አውራጃ።
በቶ (መዥርጥ): ኮሶን ገድሎ መዥርጦ ከሆድ የሚያወጣ መድኃኒት (ወይም ቅጠል)።
በቾ (ኦሮምኛ: በቾ): የነገድና የአገር ስም። ሌላ ትርጉም: የኮከብ ስም። ተመልከት: “ወቦን”።
በነቂስ: በአንድ አይቀርም። "እስራኤል ከግብጽ በነቂስ ወጡ"።
በነበሩ: የሰው ስም፡ ሳይወለድ አባቱ የሞተ ልጅ "በነበሩ" ይባላል።
በነነ/ቦነነ (ባህነነ): ተነነ፣ በለለ፣ ባከነ (ጠፋ፣ ተበላሸ፣ ከንቱ ሆነ)፡ ጨሰ፣ ተበተነ፡ ነፋስ ወሰደው።
በነነ: ጨሰ፣ ተበተነ።
በነገውም: በማግስቱም።
በነገውም: በማግስቱም።
በነፍስ ደረሰ): ነፍስ ከሥጋ ሳትለይ ሰውየው ሳይሞት ከተፍ አለ (መጣ)።
በኒን: የሰው ስም።
በና ከ ሲሰማሙት)፡ "በታች" "ከታች" ይላል።
በናና: የበነነ፣ የባከነ (ከንቱ)።
በናኝ: የሚበን፡ ጉም፣ ጪስ፣ ዶቄት።
በንቅልፍ ልብ): የእውን ተቃራኒ፡ ሰው ተኝቶ ሳለ ሳይነቃ።
በኖ: ሰይጣን እንደ ጪስ በኖ (እንደ ጉም ተኖ) ጠፋ።
በዐ በሚነሳ ገቢር ግስ ሲገባ ደግሞ የማድረግ፣ የማደራረግ እና የሳቢ ዘር ልማድ መነሻ ይሆናል። ምሳሌ: ዐወቀ:- አስታወቀ:- አስተዋወቀ:- አስተዋወቅ። ማስታወሻ: አዕማድን ቁጥር 9 ተመልከት።
በአምላክነቱ: አምላክ በመሆኑ፣ በመለኮቱ።
በዓል፡ ሻሪ)፡ በዓልን የሚደፍር፣ በበዓል ቀን የሚሠራ።
በእስያ ክፍል: ያለ አገር (መዝሙር ፸፪፡ ፲)።
በዕብራይስጥ ዳዊድ ይባላል፡ ትርጓሜው ወዳጅ ማለት ነው።
በከለ: ቀባ፣ አሳደፈ፣ አበላሸ፣ ኰለፈ፣ አጠፋ (የልብስ፣ የስም)።
በከልካይ: የወንድና የሴት ስም፡ ጌትነትን፡ እመቤትነትን፡ ባለከልካይ መኾንን ያሳያል።
በከረ (በኲር፣ በኰረ): መውለድ ዠመረ፣ መዠመሪያ ወለደ፣ አፈራ፡ አላቀ፣ ከፍ አደረገ፣ አበለጠ (አባት ወይም የናት ሆድ)።
በከራ (መጫወቻ): ሁለት የእንዝርት ራስ መሳይ እንጨቶችን መካከሉን በገመድ አስረው ሳብ ረገብ እያደረጉ የሚጫወቱበት መጫወቻ (የጋሻ ተምሳሌት)።
በከራ (ጋሻ): ታላቅ ጋሻ (አላባሽ፣ አግሬ) (፩ኛ ሳሙኤል ፲፯፥፵፭)።
በከበከ (በከከ): ደገደገ፡ ፈላ፣ ዘለለ። ማስታወሻ: "በቀበቀን" እይ።
በከተ (በቲክ፣ በተከ፣ ተበትከ): ራሰ፣ በሸቀጠ፣ በሰበሰ፡ ጠነባ፣ ገማ፣ ሸተተ፡ ተበላሸ፣ ከረፋ።
በከንቱ: በብላሽ ወይም ያለዋጋ።
በከንካና/ብክንክን: የተብከነከነ፡ ቅብዝብዝ።
በከከ (በኪክ፣ በከ): ጠፋ፣ ፈረሰ፡ ብላሽ ሆነ።
በኩል: ዘንድ (አከለ)።
በኩል: ዘንድ፣ ስፍራ (መዝሙር ፻፯፥፯)። "ባንተ በኩል በርታ"፡ "በኔ በኩል አታስብ"። ዳግመኛም: ሁለተኛ "በ" ጨምሮ "በበኩሉ"፣ "በበኩልህ" እያለ በዘጠኝ መደብ ይዘረዘራል።
በኵረ ሎሚ: ከሎሚ የሚበልጥ ፍሬው ጣፍጭ ብርቱካን።
በኵራት (ሴት ልጅ): በፊት የተወለዱ ሴቶች ልጆች።
በኵራት (ፍሬ): ታላላቆች ፍሬዎች (መዠመሪያ የበሰሉ)። ምሳሌ: “ዓሥራት በኵራት” እንዲሉ።
በኵር (ሮች): በቁሙ መዠመሪያ፣ አንደኛ ልጅ፡ ታላቅ፣ አለቃ፣ አንጋፋ፣ ግንባር ቀደም፣ ፊተኛ። የቋንቋ ልዩነት: "በክር" የአማርኛ ሲሆን "በኵር" የግእዝ ነው። ሥነ-መለኮት: “ጌታችንም እንደ ሰውነቱ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለመላእክትና ለጻድቃን በኵር ይባላል። ክርስቶስ በኵራችን አይዶለም ማለት ይቅርብን” ማለት ነው (የሰማዩ ርስት - አለቃ ዕንቈ ባሕርይ)።
በኵር: በወዲህኛው በአኃዝም: አንደኛው፣ ኹለተኛው ይላል። በሴትም: ያችኛዋ፣ አንደኛዋ እያለ ይነገራል።
በኵርነት (ብኵርና): በኵር መሆን፣ በፊት መወለድ፡ ልቅና፣ ቅድምና (ዕብራውያን ፲፪፥፲፮)።
በካር (ሮች)/በኳሪት: መውለድ ዠማሪ፡ አንድ ጊዜ መዠመሪያ ወላድ።
በካከለ: ቀባባ፣ ኰላለፈ፣ አጠፋፋ።
በካከነ: ፈጽሞ ባዘነ፣ ተበተነ።
በካይ (ዮች): የበከለ፣ የሚበክል (የሚያሳድፍ)፡ ስም አጥፊ።
በካፋ: የሰው ስም። ምሳሌ: “ዐጢ በካፋ” እንዲሉ። ትርጓሜ: ትርጓሜው “እጀ ሰፊ” ማለት ይመስላል። "ካፍን" እይ።
በክ: በቁሙ "ብላሽ" (ከንቱ) (በግእዝ)። ማስታወሻ: "ቢያክን" ተመልከት፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
በክ: ብላሽ (በከከ)።
በክር/በኸር: የቀደመ፣ ቀዳሚ። ምሳሌ: “የበክር ልጅ” እንዲሉ (መዝሙረ ዳዊት ፻፭፥፴፯፣ ሉቃስ ፪፥፯)።
በክት/በከቻ/ብክት (ብትክ): የበከተ፣ የበሰበሰ፡ ታንቆ ታፍኖ የሞተ (አባላ፣ የተመታ)፡ ጥንብ፣ ውዳቂ።
በኸረ ሎሚ (ባሕረ ሎሚ): (ዝኒ ከማሁ)፡ ፖርቹጋሎች ከባሕር ያመጡት (የባሕር ሎሚ)።
በኹለት ወባን: ስለት ያለው ቀን ሰይፍ።
በወሎ ክፍል: ያለ አገር።
በወደቀ ግንድ መጥረቢያ ይበዛበታል፡ እንዲሉ።
በወገቡ አሰረ: (ዐጠቀ)።
በወገብ መካከል በሆድ ውስጥ ግራና ቀኝ ያለ ክብ፡ እንክብል ሥጋ፡ የደም ማጥሪያ፡ የዘር ፈቃድ መነሻ። "አምላክ ኵላሊት ያጤሰውን ልብ ያሠላለሰውን ያውቃል"።
በወገን በወገኑ: በአይነት በአይነቱ፣ በጐሣ በጐሣው።
በውሃ ይለቅልሽ): ዐዲስ ልብስ የለበሰውን ሰው እንዲህ ይሉታል (ውሃ ዕጥበትን ያሳያል)።
በውል: በደንብ፣ በሚገባ፣ በጣም።
በውርርድ ላይ ውርርድ፡ በነብር ላይ ስማርድ እንዲሉ።
በውኑ (ቦኑ): በውነቱ። ንኡስ አገባብ ነው (ኢዮብ ፵፥፳፭)።
በውኑ: ሳይተኛ፣ ሳያንቀላፋ፡ እያየ፣ እየሰማ።
በውኑ: በውነቱ፡ እውን።
በዘልማድ: በልማድ ሲደረግ የሚኖር።
በዘርፍነት ሲነገር: ሚጣቅ ዐማኔል፡ የሚጣቅ ዐማኔል። በግእዝ መሠረቱ መጠቀ ነው።
በዘርፍነት ሲነገር: ሚጣቅ ዐማኔል፡ የሚጣቅ ዐማኔል። በግእዝ መሠረቱ መጠቀ ነው።
በዘበዘ (በዚዝ፣ በዘ፣ በዝበዘ): በቁሙ፡ ዘረፈ፣ ቀማ፣ በረበረ፡ ዘራ፣ በተነ፣ አባከነ (ኢዮብ ፳፥፲፱፡ ናሆም ፪፥፱)። ማስታወሻ: "ወሰደን" እይ።
በዘበዘ (አጠበረበረ): አጥበረበረ፡ ትክክል ማየት ከለከለ (አንጸባረቀ)።
በዚህ: በቁሙ፣ "ዚህ"።
በዚያ፣ በዚያው፣ በዚያውም ላይ፣ በዚያም ሁለቱም
"ም"
ዋዌ ነው፡ በቂና ቅጽል።
በዚያ: በቁሙ፣ "ዚያ"።
በዚያኛው፣ በዚያ ጊዜ ቅጽል ነው።
"በዚያን ጊዜ" ማለት ስህተት ነው።
በዛ (በዚኅ፣ በዝኀ): ፈደፈደ፣ ተረፈ፣ ከልክ ዐለፈ፣ ረባ፣ በረከተ፡ ዐየለ፣ በረታ፡ ወለደ፣ ከበደ። ተረት: “ነገር ቢበዛ ባህያ አይጫንም”። ተረት: “ማር ሲበዛ ይመራል”።
በዛ፣ ተረፈ፣ ረዘመ፣ በለጠ።
በዛ አለ: በርከት አለ።
በዛ: ከልክ ወለፈ፣ ከመጠን በለጠ።
በዛብሽ: የሴት ስም።
በዛብኸ (በዝኀ፣ ብከ): የሰው ስም፡ “ያባትህ ዘር ባንተ በዛ” ማለት ነው።
በዛኹ ቀንሱልኝ አለ: የሚይዘውን ዐጣ።
በዜማ መምራት/መዝፈን: አነሣ: ከመሪ ቀጥሎ በቀኝ በግራ አንገርጋሪን፣ አዜመ።
በዝባዥ: የበዘበዘ፣ የሚበዘብዝ፣ የሚዘርፍ፡ ዘራፊ፣ ቀማኛ።
በዝባዥነት: ዘራፊነት፣ ቀማኛነት።
በዝባዦች: ዘራፎች፣ ቀማኞች (፪ኛ ነገሥት ፲፯፥፳፡ ኢሳይያስ ፳፬፥፲፮)።
በዝብዝ (ትእዛዝ): ዝረፍ፣ ቀማ (ኢሳይያስ ፰፥፩፣ ፫)። ስም: ያፄ ዮሐንስ ፈረስ። ምሳሌ: “ካሳ በዝብዝ፡ አባ በዝብዝ ካሳ” እንዲሉ።
በዞ (ቦታ): በተጕለት ወረዳ በሞጃ አጠገብ ያለ አገር።
በዞ ሜዳ: የበዞ ሜዳ።
በዠድ (ዶች): ከብልት በላይ ከንብርት በታች ያለ ገላ።
በዠገደ (ዠገደ): ዥዋዥ ነገር ሳተ።
በዢ (በዛኂ): የሚበዛ፣ በርካች።
በዥር (በጅር): "ጀና" እና "ዠ" ተወራራሽ ስለሆኑ "በጅር" ከማለት ፈንታ "በዥሮንድ" ሊባል ይችላል።
በየ (በበ): በእየ (ደቂቅ አገባብ)። ምሳሌ: “በየቤቱ፣ በየወገኑ፣ በያኳያው፣ በየሥራው፣ በየፊናው፣ በያገሩ፣ በየወንዙ” እያለ በብትን ሲነገር በቁም ቀሪነቱን ያሳያል። ማስታወሻ: "እየን" ተመልከት።
በየነ (በይኖ፣ በየነ): ዐወቀ፣ ተቸ፣ ፈረደ፣ ለየ። በየነ (ስም): የወንድና የሴት ስም። በየነበት: ፈረደበት። በየነለት: ፈረደለት።
በየደ: ደለዘ፣ በሰ፡ መረገ፣ ደፈነ፣ ቀባ።
በዪ (በሊ): ንገሪ፡ ምቺ።
በያኝ (ኞች) (በያኒ): የበየነ፣ የሚበይን (የሚፈርድ)፡ ፈራጅ፣ ዳኛ፣ ሹም።
በያጅ (ጆች): የሚበይድ፣ የሚደፍን፡ መራጊ።
በይ (በላዒ): የበላ፣ የሚበላ፣ የሚያቃጥል። ሲበዛ "በዮች" ይላል (ዮሐንስ ፮፥፲፫)። ጥላ በላ/በል: (ዝኒ ከማሁ)፡ "ግብረ በላ"፣ "ግንደ በል" እንዲሉ። ውሃ በላ: ባለጌ። ሣረ በል: እንስሳ። ሥጋ በል: አውሬ፣ አሞራ። ፍሬ በል: ወፍ።
በደለ (ዐረብኛ፡ ለወጠ፣ ቀየረ): በቁሙ፡ ዐመፀ፣ ገፋ። በደግ ፈንታ ክፉ መለሰ (አደረገ፣ ሠራ) (፩ኛ ቆሮንቶስ ፮፥፰)። ምሳሌ: “እንጨት ሆኖ የማይጨስ፡ ሰው ሆኖ የማይበድል የለም”። ማስታወሻ: "አበሰን" እይ።
በደለኛ (ተቀባይ): የተበደለ፣ በደል የተቀበለ (ኢዮብ ፳፬፥፮)።
በደለኛ (ኞች): የበደለ፣ በዳይ፡ ዐመፀኛ፣ ግፈኛ፣ ክፋተኛ (ዘዳግም ፳፭፥፩፡ ምሳሌ ፳፩፥፲፰፡ ኢሳይያስ ፲፬፥፬፡ ፪ኛ ጢሞቴዎስ ፫፥፬)። ምሳሌ: “በደለኛ እኔ፣ ዐሳረኛ እኔ፡ አምላኬን ትቼ ሰው ማመኔ” እንዳለ ጠቦ።
በደላ/ብደላ: የግፍ ሥራ።
በደል: ዐመፅ፣ ግፍ፣ ክፉ ሥራ (፪ኛ ዜና መዋዕል ፱፥፯፡ ሕዝቅኤል ፰፥፲፯)።
በደረ (በዲር፣ በደረ): ሮጠ፣ ፈጠነ፣ ቀደመ (ግእዝ)።
በደረገ (በደገ፣ በረገደ): አፈጠነ፣ ተነሥቶ መሄድን።
በደበደ (በድበደ): ታመመ፣ ለመመ።
በደበድ/በድባዳ: የተንበደበደ፣ የሚንበደበድ፡ የሚፈራ፡ ፈሪ፣ ቡከን።
በደነ (በዲን፣ በደነ): በቁሙ፡ ፈዘዘ፣ ደነዘ፡ ሬሳ ሆነ።
በደነፍስ (በድነ ነፍስ): ሰውነተ በድን፡ ድንጉጥ።
በደን: በጐድጓዳ ስፍራ ተቀመጠ፣ ተደበቀ፣ ደፈጠ፣ አደባ ለመውጋት ለመግደል (ዘጸአት ፳፩፡ ፲፫። ፳ኛ ሳሙኤል፡ ፳፫፡ ፳፫)።
በደኖ (ቦታ): በሐረርጌ ውስጥ ያለ አገር።
በደኖ (ዛፍ): ዓሣን አስክሮ የሚገድል (በድን የሚያደርግ) እሾኻም የበረሓ እንጨት።
በደዊ (በዳዊ): ዘላን፣ የበረሓ ሰው፣ በረኸኛ።
በደዊዎች (በዳውያን): በምድረ በዳ የሚኖሩ ዘላኖች (በረኸኞች)።
በደው (በዲው፣ በድወ፣ በድው): ዱር፣ በረሓ፣ ምድረ በዳ።
በደው (ነገድ): የነገድ ስም፡ በሐባብ ያለ ነገድ።
በደገ: ሠነጠቀ፣ ለየ፣ ከፈለ። ማስታወሻ: "ገደበን" እይ።
በዳ (ላዳ) (በድው): በቁሙ፡ ባዶ፣ ደረቅ፣ በረሓ፣ ሜዳ፣ ውድማ፣ ባድማ። ምሳሌ: “ምድረ በዳ”፣ “ዐቅለ በዳ” እንዲሉ። ማስታወሻ: "በዳ" የግእዝ እና የአማርኛ ሲሆን፣ "በድው" የግእዝ ብቻ ነው።
በዳ (ቀማ): ቀማ፣ ወሰደ። ምሳሌ: “ጕራጌ ቀማ ሲል በዳ” እንዲል።
በዳ (በዲው፣ በድወ፣ አብደወ. ዕብራይስጥ፡ ባዳእ. ትግርኛ፡ ሐባ፣ በድዐ): በቁሙ፡ ወጣ፣ በላይ ሆነ፡ ሰረረ፣ ጠቃ፣ መታ፣ ገሰሰ፣ አጠፋ (የድንግልና ፈታ)። መስረር: የአራዊት፣ የእንስሳትና የአዕዋፍ ነው። መጥቃት: የወይፈን ብቻ ነው። መምታት: የድንግልናና ያለሌ ነው። መግሰስና ማጥፋት: የጕልማሳ ነው። ማስታወሻ: መምህራን ግን "ዐወቀ" ይላሉ።
በዳይ (ዮች): የሚበድል፣ የሚያምፅ፣ የሚገፋ፡ ለዋጭ፣ ገልባጭ (ኢዮብ ፳፪፥፲፱፡ ፪ኛ ቆሮንቶስ ፯፥፲፪)። ምሳሌ: “ድኻ በዳይ” እንዲሉ።
በድሉ (በዕድሉ): የሰው ስም።
በድል ነጐድ: የወንጭፍ ስም፡ የጠፍር ወንጭፍ። ትርጉሙ: "ወፈ በድል፣ አብርር በት" ማለት ነው። ማስታወሻ: "ነጐድን" እይ።
በድል ናኝ: በ፲፭፻ ዓ.ም የነበረ የሐበሻ ንጉሥ። "ድልን ለወገንኸ ናኝ" ማለት ነው።
በድል: ዐምፅ፣ ግፋ።
በድረግ አለ: ሳይታሰብ በድንገት ፈጥኖ ተነሣ፡ አፈፍ አለ፡ ሮጠ።
በድረግ: ፈጠን።
በድን (ኖች): ሬሳ፡ የማይሰማ፣ የማይለማ፣ ነፍስ የተለየችው ሥጋ (፪ኛ ነገሥት ፲፱፥፴፭)።
በድን ሆነ: በደነ፣ ፈዘዘ፣ ደነጋ።
በድንነት: ሬሳነት፣ ፈዛዛነት፡ አለመስማት፣ አለመልማት።
በዶስ፡ በኀይል።
በዶስ፡ ዛር፡ ክፉ፡ መንፈስ፡ ወንደ - ገሪ፡ ገላን፡ ልምሾ፡ የሚያደርግ።
በጀ (በገየ): ሰመረ፣ አማረ፣ ተዋበ፡ መልካም ሆነ፡ ተገባ፣ ተሻለ፣ ረባ፣ ጠቀመ። ምሳሌ: “በጅ ተሠርቶ ተዘጋጅቶ”። ተረት: “ሲገደገድ ያልበጀው፡ ሲዋቀር እሳት ፈጀው” እንዲሉ። ተረት: “ለኔ እናት ምን በጄት?” (ተሻላት፣ ረባት?) ማስታወሻ: "አረጀን" እና "ፈጀን" እይ።
በጃለ (በእዴየ ብህለ): ዕሺ አለ፣ ታዘዘ።
በጄ (በእዴየ): ዕሺ፣ በጎ። ምሳሌ: “በጄ እሠራለሁ” (ይሁን) ማለት።
በጅ አይልም: አይሰማም፣ ዕሺ አይልም፣ አይታዘዝም።
በጅር (በድራ): ብድር። “የብሱን ዙሮ፣ ባሕሩን ተሻግሮ፣ ወጥቶ ወርዶ፣ ጕልበቱን ለመንግሥት ላበደረና ላገለገለ ሰው የሚሰጥ ገንዘብ”።
በጅሮንድ (በጅር ወንድ): ጅር ጭፍራው (ሠራዊቱ)፡ ወንድ ሻለቃው (ሥራ መሪው)። ማስታወሻ: "በዥርን" እይ።
በጅሮንድ (ዶች) (በድራ ወንድ): የወርቅና የብር አፍሳሾችና የአንጥረኞች አዛዥ፡ የገንዘብ ሹም (ግምጃ ቤት)። ማስታወሻ: "በጅር፣ በግር" ከማለት ከ"በገረ" የቅርብ ትእዛዝ ቢወጣ ግን፡ “በጅሮንድ” "ወንደ በግር" ተብሎ ሊተረጐም ይችላልና፣ ገንዘቡን ያሳያል።
በገ ሰማይ: ዕሪያ ቋንጣውን ውርዴ የሚበላው።
በገ ፈጅ: ታላቅ ድስት (ሰታቴ)፡ የአንድ በግ ሥጋ የሚቀቅል።
በገረ (ሞከረ): ሞከረ፣ ፈተነ፡ ነደፈ፣ መጠነ፣ ለካ፡ ምልክት አደረገ።
በገረ (በጊር፣ በገረ): ዐጉልና ገቢር፡ አደገ፣ ጐለመሰ፡ ብጕር አወጣ።
በገረ (ደፈረ): ደፈረ። ምሳሌ: “ማን በግሮ” እንዲሉ።
በገበገ (ገበገበ): ፈጀ፣ ተኰሰ፣ አቃጠለ፡ ገረፈ፣ አቈሰለ፣ አሳመመ።
በገበጣ ጠጠር መጨመር:
በገነ (ዕብራይስጥ፡ ናጌን): ቃኘ፣ ነዘረ፣ መታ፣ ደረደረ።
በገነ (ገምኖ፣ ገመነ): ደረቀ፣ ከረረ፡ ዐበጠ፣ ቈረበለ፡ ከሰለ፣ ዐረረ።
በገነ: ነደደ፣ ገመነ፣ ፈላ፣ በሰለ፣ ተቈጣ።
በገና (ዎች): ከገበቴ፣ ከሁለት ቋሚና ከአንድ አግዳሚ እንጨት የተዘጋጀ መዘመሪያ፡ መንፈሳዊ ምስጋና ማመስገኛ (መዝሙር)፡ ባለ አሥር አውታር የሚቃኝ፣ የሚነዘር፣ የሚደረደር። ምሳሌ: “ዳዊት በገናውን፣ ዕዝራ መሰንቆውን” እንዲሉ። ትርጉም: "በገና" የዥማቱን መድረቅና መክረር ያሳያል። ማስታወሻ: "ገናን" እይ።
በገና መታ: ነዘረ፣ ደረደረ፡ ዘመረ። ምሳሌ: “ከቶ አይቀርም ሞቱ ምንም ቢታክቱ” አለ።
በገና መቺ: በገና የሚመታ፣ የሚደረድር (ጠቦ ወይም ሌላ)።
በገና ምት): ድርደራ።
በገዛ፡ በራስ፣ በሰውነት፣ በባለቤትነት። "ሰው በገዛ ገንዘቡ የወደደውን ያደርጋል"። (ተረት)፡ "በዛ ዐረግ እባብ ይዛ ታስፈራራ፡ በገዛ ዳቦዬ ልብ ልቡን ዐጣኹት"።
በገዛ እጁ፡ ወዶ ፈቅዶ (ዘፀ፳፭፡ ፪)። "ይሁዳ በገዛ እጁ ሞተ"።
በገድ (ትግርኛ): ኀፍረተ ብእሲት። ማስታወሻ: “በረገደ” ማለት ከዚህ የወጣ ነው።
በጉ (በግዑ): ያ በግ፡ የርሱ በግ። ማስታወሻ: ሁለተኛውን "አለ" እይ።
በጕራጌ አጠገብ: ያለ አገር።
በጊቱ/በጊቷ (በግዕታ): ያች በግ በማለት ተባቱና እንስቱ ተለይተው ይታወቃሉ።
በጋ (በግዖ፣ በግዐ): ሐጋይ፣ ድርቅ፡ የድርቅ ወራት። ከአራቱ ክፍለ ዘመን አንዱ (ሦስት ወር ወይም ፳፩ ቀን ተሩብ)፡ ከታኅሣሥ ፳፮ እስከ መጋቢት ፳፮። ባላገር: ከመስከረም ጀምሮ እስከ ሰኔ (ከመስከረም ፳፯ እስከ ሰኔ ፳፮) በጋ ይባላል። ምሳሌ: “ለሞኝ ሰኔ በጋው፡ መስከረም ክረምቱ”። ማስታወሻ: "ባጀ"፣ "በጋ" ከማለት የወጣ ነው።
በጋማች (ሐማቴ በግዕ): በግ ዐማች፡ በግ የሚያርድ፣ የሚያወራርድ፣ የሚጠብስ፡ ሥጋ ቤት፣ ሥጋ ሸያጭ። ማስታወሻ: "ዐመተን" እይ።
በጋሪ: የበገረ፣ የሚበግር (የሚሞክር፣ የሚፈትን)፡ ሞካሪ፣ ፈታኝ።
በጋራ ቤት: በመካከል።
በጋር (ሮች): ጸርከል፣ ዙሪያ፣ ክብ፡ መንደፊያ፣ መበገሪያ መሣሪያ።
በጋኝ: የሚበግን፡ ደራቂ።
በጌ: የኔ በግ።
በጌምድር (ለም መሬት): በጎ ማለፊያ፣ ለም ምድር። ደንቢያንና ፎገራን ያሳያል።
በጌምድር (ምድረ በግዕየ): በግ ያለበት (የሚረባበት)፡ “የኔ በግ ምድር”። (በግዓዊ) “የበግ”፣ “በጋም” ማለት ነው።
በግ (በግዕ): በቁሙ፡ የቤት እንስሳ፡ ከላይ የፊት ጥርስ የሌለው፡ የሚያመሰኳ ከብት፡ የጻድቅ ምሳሌ (ዮሐንስ ፩፥፳፱)። ተረት: “ሞኝ ካመረረ፡ በግ ከበረረ”። ማስታወሻ: ተባቱም እንስቱም "በግ" ይባላል። ነገር ግን፡ -
በግር (በጅር): ሞክር፣ ፈትን። ማስታወሻ: "በደረንን" ተመልከት።
በግሮ: ሞክሮ፣ ፈትኖ፣ ደፍሮ።
በግባጊ: የበገበገ፣ የሚበገብግ፡ አቃጣይ፣ ገራፊ፡ አቍሳይ (ቂጥኝ)።
በግእዝ ምሥሃል ይባላል: (ዘጸአት ፳፭፡ ፲፰፡ ፳፩)።
በግእዝ ሰዓታተ ሌሊት ይባላል።
በግእዝ ቍናምት ይባላል።
በግእዝ አንቆቅሖ ይባላል።
በግእዝ ኰሰኰስ ይባላል።
በግእዝ ዝብል ይባላል።
በግእዝ ግን ስርቆት ማለት ነው።
በግእዝ ግን የተቈረጠች ማለት ነው (የግእዝ ትርጉም)።
በግእዝ ጸቈን ይባላል። ሙሽራውና ሙሽራዋም ከነሚዜዎቹ በማደሪያቸው ስም ጕላ ይባላሉ። "የጕላ ቤት" እንዲሉ።
በጎ (በግዓዊ): ደህና፣ ደግ፣ ማለፊያ፣ መልካም (ሥራ፣ ሰው፣ ነገር) (መዝሙር ፬፥፮)። ምሳሌ: “ዕሺ በጎ”፣ “ዐይነ በጎ” እንዲሉ።
በጎ ሆነ (ጥዕየ፣ ሐይወ): ዳነ፣ ተፈወሰ፣ ጤና አገኘ።
በጎ ነው: ደህና ነው፡ ተሽሎታል።
በጎ አድራጊ: ደግ ሠሪ (ነህምያ ፱፥፲፯)።
በጎ አድራጎት: የጽድቅ ሥራ ማድረግ (መሥራት)፡ ምግባረ ሠናይ።
በጎች (አባግዕ፣ ዓት): የቤት እንስሶች (ከብቶች)፡ የጻድቃን ምሳሌዎች (ዘጸአት ፱፥፫፡ ማቴዎስ ፭፥፵፭)።
በጎነት: በጎ መሆን (መዳን)፡ ደግነት፣ ቸርነት (ዘዳግም ፳፰፥፲፩፡ ኤርምያስ ፲፰፥፲)።
በጐዣም "ምሽት" ትባላለች።
በጓ: ያች በግ፡ የርሷ በግ።
በጠለ (በጺል፣ በጸለ፣ ተበጽለ): ተበጨቀ፣ ተነጨ፣ ተቈረጠ፣ ተላጠ፡ ተቀደደ።
በጠለለ (በጠለ፣ ባጠለ): በለለ፣ ጠፋ (የነገር)።
በጠሰ: በተከ፣ መተረ፣ ቈረጠ፣ በሰከ፣ ጐመደ፣ ቦደሰ (የገመድ፣ የጠፍር፣ የፈትል፣ የቅጠል፣ የአንገት፣ የአንጀት፣ የስልክ)። ማስታወሻ: "ቀነጠሰን" እይ።
በጠረ (ትግርኛ: ሀባ በጥረ/ዕብራይስጥ: ባጻር): ቆመ። ሌላ ትርጉም: ቀሠመ፣ አሳነሰ፣ አጐደለ።
በጠረረ (በጠረ፣ ጠረረ): ኰራ፣ ታበየ።
በጠረር/በጥራራ: የኰራ፣ የታበየ።
በጠረቀ (በጠረ፣ ጠረቀ): ነደለ፣ በሳ፣ ሸነቈረ (እንጨትን፣ ልብስን)።
በጠረቀንና (ፈተለከ)ን እይ።
በጠቀ: በጨቀ።
በጠበጠ (ትግርኛ: በጥበጠ): ጦር ሰበቀ። ማስታወሻ: "ወጠወጠን" ተመልከት።
በጠበጠ (ዐረብኛና ትግርኛ: በጽበጸ): ጠመቀ፣ በረዘ፣ መታ፣ ሰበቀ፣ ወዘወዘ፡ ዐሸ፣ ዐመሰ፣ አደፈረሰ፣ አተራመሰ፣ አወከ (የጠላ፣ የጠጅ፣ የተልባ፣ የኮሶ፣ የሆድ፣ የባሕር፣ የሕዝብ)። ተረት: “ዓሣ ያለበት ባሕር፣ ዕውር ያለበት ደብር ሳይበጠበጥ አያድር”። ግጥም: “ይህስ ጠጅ ቤታችሁ በጣም ይገርማል፡ በሚጠጣበት ቀን ይበጠብጣል”።
በጠጠ (ትግርኛ: በጠ): ለጥ አለ፡ በጠጥ ጣለ።
በጠጣም: በጠጥ ያለው፣ ባለበጠጥ፡ በጠጠ ብዙ (በግ፣ ፍየልን የመሰለ እንስሳ)።
በጠጥ (ጦች): በቁሙ፡ እንዳተር የተድበለበለ (የበግ፣ የፍየል፣ የሠሥ፣ የድኵላ፣ የብሖር) ኵስ።
በጢሕ: የዱባ ዓይነት ተክል (ብርጭቅ) (ዘኍልቍ ፲፩፥፭)።
በጣ (በጢሕ፣ በጥሐ): ፈቀ፣ ቈራ፣ ተፈተፈ፣ ሠነተረ፣ ጋረጠ (ለጌጥ ወይም ለመድኃኒት)።
በጣ፡ ፈቃ፡ ቈራ፡ ሠነተረ፡ ላይ ላዬን፡ በቅርብ በቅርብ፡ ቈረጠ፡ በፍጥነት።
በጣ: ቀደደ። "ሠነተረ፡ የካህናት፡ ሸነተረ፡ የሕዝብ፡ አነጋገር ነው።"
በጣም ቀቀለ: አበሰለ፣ አነፈረ (ሰረሰርን፣ ሌላውንም ዐጥንት)።
በጣም፡ ንኡስ አገባብ፡ አለልክ፡ በጅጉ፡ በብዙ፡ በጸና (መዝ፷፬፡ ፮። ማር፯፡ ፱)። "እከሌ በጣም ታል። "
"ካልሠሩ በጣም ገንዘብ አይመጣም። " ቀጣ ብለኸ ቅጥን ተመልከት።
በጣም ደረቀ: ከዚህ የተነሣ ቀለለ፣ ጮኸ። ("ከሸለለን" የሚለው ቃል ጋር ይዛመዳል)።
በጣሳ/ብጥስ: የተበጠሰ፣ የተበተከ፣ የተበሰከ።
በጣሽ: የበጠሰ፣ የሚበጥስ (የሚቈርጥ)፡ ቈራጭ።
በጣጠሰ: መታተረ፣ ቈራረጠ፣ በሳሰከ (ዳንኤል ፮፥፳፬)።
በጣጣ (ዐረብኛ): ድንች።
በጥ አለ: በጠጠ፡ ዟ አለ።
በጥልጣል አጠገብ: አሳሑርታ ውስጥ የሚገኝ ነገድ።
በጥራቂ: የሚበጠርቅ፣ የሚነድል (የሚበሳ)፡ በሺ፣ ሸንቋሪ።
በጥርስ፡ ሸኘ)፡ በሣቅ፣ በፈገግታ፣ ሳያበላ፣ ሳያጠጣ።
በጥባጣ: የደፈረሰ፣ የታወከ፡ ብስጩ።
በጥባጭ (ጮች): የበጠበጠ፣ የሚበጠብጥ (የሚያደፈርስ፣ የሚያውክ)፡ ሰባቂ፣ አዋኪ። ምሳሌ: “በጥባጭ ሳለ ማን ጥሩ ይጠጣል” እንዲሉ።
በጥባጭነት: ዐማሽነት፣ አዋኪነት።
በጥብጥ (ሰው): ዝኒ ከማሁ (እንደዚሁ) ለበጥባጭ። ምሳሌ: “ደብረ በጥብጥ” እንዲሉ።
በጦም ቀን ምሳ እራት ሲኾን፡ አስታረበ ምሳ አበላ ተብሎ ይተረጐማል (በጾም ቀን ምግብ ማብላት)።
በጨቀ (በቲክ፣ በተከ): በጠሰ፣ ቈረጠ፣ መተረ፣ በሰከ (የጨርቅ፣ የቅጠል)።
በጨበ (ጨበረቀ)፡ አበጠ፡ ጭብጦ፡ አባጀ።
በጨበጨ (ዕብራይስጥ: ባጻጽ፣ ባጽቤጽ): ድምፅ ሰጠ፡ ፈለቀ፣ መነጨ፡ ፈሰሰ፣ ወረደ (የቅዝን)።
በጨበጭ/በጭባ: የሚንበጨበጭ፣ የሚፈልቅ፣ የሚመነጭ።
በጨጨ: ወራ፣ ወረቀ፡ ብጫ (የልጅ ቅዝን)፡ አስኳል፣ ዐደይ መሰለ።
በጪ (ዎች) (በጣሒ): የበጣ፣ የሚበጣ፡ ተፍታፊ፣ ሠንታሪ።
በጫቂ: የበጨቀ፣ የሚበጭቅ (የሚበጥስ)፡ በጣሽ፣ ቈራጭ።
በጫጨቀ: በጣጠሰ፣ ቈራረጠ።
በጭቃ ለከለ፡ ረገጠ።
በጽርእ ፓኖስ፡ ባረብኛም ፋኑስ ይባላል።
በፍርድ ሂደት ደግሞ: በችሎት ተቀመጠ፣ ከሳሽ ተከሳሽን አነጋገረ፣ አተ፣ አነጣጠረ፣ አከራከረ፣ ወይም አበጣጠረ ማለት ነው።
በፍታ: ረዥም ሸማ (ልስልስ)፡ ወይም ሻሽ፡ ዐዲስ (ነጭ፣ ጸዐዳ) (ዘጸአት ፳፮፥፴፩፣ ሉቃስ ፳፩፥፲፪)።
በፍጥነት ሸጠ: ለወጠ።
ቡሓ ራስ: ራሰ መላጣ፣ ራሰ በራ፡ ወይም እብቅና በረቅ የሚመስል ዕከክ በራሱ ላይ ያለበት ራስ (ቡሓ ሰው)።
ቡሓ በግ: ራስ ነጭ በግ።
ቡሓ: ነጭ ዕከክ፡ ለምጽ፣ መላጣ። ምሳሌ: “በቡሓ ላይ ቈረቈር” እንዲሉ።
ቡሔ (ቡሓዊ): የበዓል ስም፡ ደብረ ታቦር። ትርጉም: የቍርባን ምሳሌ የሆነ "ኅብስት" እና የጌታችንን ግርፋት የሚያሳስብ "ጅራፍ" የሚዘጋጅበት (በዓል) ነው። ምሳሌያዊ ትርጉም: ቡሔ ማለት በደብረ ታቦር "ቧ" ብሎ የተገለጠውን የጌታችንን የፊቱን ብርሃን (ጸዳል) እና የልብሱንም እንደ በረዶ ነጭ (ጸዓዳ) መሆን ያስረዳል። ሌላ ትርጉም: ደግሞም እረኞች “አክሥቴ ቤት አለኝ ለከት” ይላሉና፡ "ቡሔ" (ብሑእየ) “ቡሖዬ” ተብሎ ቢተረጎም የታቦር ለት ተቦክቶ የሚጋገረውን ኅብስት ያሳያል። ተጨማሪ ትርጉም: የየቡሔ ቢል የነጐድጓድ ምሳሌ የሆነ ጅራፍን ይገልጻል።
ቡሄ: የበዓል ስም።
ቡሕ (በዊሕ፣ ቦሐ): ብርሃን፡ የታየ፣ የተገለጠ፣ የጐላ፣ የበራ፡ ጸዓዳ (የምድር ኖራ፣ በረቅ፣ ነጭ ኆጻ)። ማስታወሻ: "በለጭን" እይ።
ቡሕ (ነቢሕ): ቡፍ (መጮኸ)፡ የውሻ።
ቡሕ አለ (ነብሐ): ቡፍ አለ፡ ጮኸ።
ቡሕነት (ብርሃን): ዝኒ ከማሁ (እንደዚሁ)፡ መላጣነት። ማስታወሻ: "በራን" እይ።
ቡሕነት (ዕከክ): ቡሓ መሆን (ዘሌዋውያን ፲፫፥፵፪)።
ቡሖ (ብሒእ፣ ብሕአ፣ ብሑእ): የቦካ፡ የበሰለ፣ የሖመጠጠ (መፃፃ) ሊጥ። ማስታወሻ: ለቀለምና ለጭቃም ይሆናል። "ቦካን" ተመልከት።
ቡሖቃ: የቡሖ ዕቃ፡ የርሾና የሊጥ መቀመጫ (እንስራ፣ ማድጋ፣ ገበርሾ፣ ገንዳ)።
ቡላ (ቀለም): ቅላት ያለው አመድማ አህያ። ማስታወሻ: አንቀጹ "ቦለለ" ነው። ወርቅ ቡላ: ብጫ የሚመስል ፈረስ ማለት ነው (ራእይ ፮፥፰)።
ቡላ (ትግርኛ): አንቡላ፣ የጠጅ አተላ።
ቡላ (የሰው ስም): አቢብ፡ ቡላ “ጳውሎስ” ማለት ነው። "አባን" እይ።
ቡላ (ዶቄት): የንሰት ዶቄት (ነጩ፣ ጥሩው)። ማስታወሻ: ጋሎች "ቡልቡላ" የሚሉት ከዚህ ጋራ አንድ ነው።
ቡላድ: እሳት የሚወጣው የቦረቦጭ ድንጋይ (ኢዮብ ፳፰፥፱፣ ሕዝቅኤል ፫፥፱)። ማስታወሻ: ቡላድ በዐረብኛ "ፉላዝ" ይባላል። ተረት: “ከምድር አደላድሎ ከአህያ፡ ከቡላድ አደላድሎ ከቋያ። ” ተመልከት: "ዲና ሞን"።
ቡሌ (ቀለም): ጠጕሩ ፈገግ ያለ፣ ዐይጥማ በሬ። "ኩባያን" እይ።
ቡሌ: ትኵስ ወተት የሚመስል ኀይለኛ የጎንደር ጠላ።
ቡሌማ: (ዝኒ ከማሁ)፡ የቡሌ ዓይነት።
ቡል ቡል አለ: ቡልቅ ቡልቅ አለ። ተመልከት: "(ቦለቦለን)"፡ የዚህ ድግም ነው።
ቡል አለ: በኃይል ጨሰ፡ ቡን አለ።
ቡልማ: የቡላ ወገን (ትል)።
ቡልቅ (ፍልቅ): የፈለቀ፣ የወጣ። ማስታወሻ: ፈረንጆች "ቦልካን" የሚሉት እሳተ ገሞራ ከዚህ ጋራ ይሰማማል።
ቡልቅ አለ (ቦለቀ): ፍልቅ አለ፡ ዘለለ፣ ናረ፣ ተወረወረ (የውሃ፣ የጪስ፣ የእሳት)።
ቡልኮ: የጋሎች ጋቢ፡ ድር ቀጪን (ማገ፣ ወፍራም) የሚደምቅ (የሚሞቅ)፡ ቁመተ ረዥም፣ በውድ የሚሸጥ።
ቡልጋ: የአገር ስም፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተወለዱበት (እጢሳ)።
ቡልጌ: የቡልጋ ሰው።
ቡልጎች: የቡልጋ ተወላጆች።
ቡሎ (ላሎ): የልብስ መንከሪያ (ማሳመሪያ) ሰማያዊ ቀለም ነው። ምስጢሩ: "ንጣትን አይለቅም" (አይለውጥም)። አገላለጽ: በእርሱ የተነከረ ልብስ ይነጣልና። ፈረንጆች "ነጭን ላ"፣ "ሰማያዊን ብለ" ይሉታል።
ቡሎ (ግንባር ነጭ): ግንባረ ነጭ ፈረስ።
ቡሴ: የዛፍ ስም፡ እንጨቱ ቀጥ ያለ፡ በስተላይ ለጣራ ማገር የሚሆን። ዛፍነቱ ቅጠሉን የሐር ትሎች የሚበሉትን “ቱት” ይመስላል።
ቡረቃ: ዝላይ (ፍንጣ)።
ቡሩኬ: “የኔ ቡሩክ”፡ የቁልምጫ ንግግር ነው።
ቡሩክ ሆነ: ተባረከ፣ ተመረቀ (ተቀደሰ)፡ ምሩቅ ሆነ።
ቡሩክ: የተባረከ፣ የተመሰገነ (የተመረቀ፣ የተቀደሰ)፡ ክቡር (ምስጉን፣ ምሩቅ፣ ቅዱስ)።
ቡራ ከረዩ አለ: አመረረ፣ ተቈጣ፣ ወይም ጠብ አነሳ።
ቡራ: የከረዩ ጎሳ በሬ፡ ዶባ (አውሬ)። አባባል: “ቡራ ከረዩ” እንዲሉ። ማስታወሻ: “ቦራ” የሚለው የጉራጌ ቃል ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው።
ቡራቅ: ክንፍ ያለው የመብረቅ ፈረስ፡ እስላሞች መሐመድ በርሱ ተቀምጦ ወደ ገነት ወጣ ይላሉ።
ቡራቡሬ: የቡሬ ቡራ፡ ነጠብጣብ (ሰመግ)።
ቡራኬ (ወግ): የመክፈልት ወግ፡ ታላቅ ዕድል ለቄስ (ለአቃቢ፣ ለባለቤት) የሚሰጥ፡ ተባርኮ የተቈረሰ ዳቦ።
ቡራኬ: ምርቃት፣ ምስጋና፡ መባረክ፣ መቀደስ፡ በተገብሮነትም ይፈታል (ግእዝ)።
ቡሬ: ዝንጕርጕር (ነጭና ጥቍር) በሬ፡ ብርሃናዊ ማለት ነው። “ቦሩን” ይመልከቱ።
ቡሬማ: የቡሬ ዓይነትና ወገን።
ቡሬነት: ዝንጕርጕርነት።
ቡርሳ (ቀበሌ): በሲዳሞ ውስጥ ያለ ቀበሌ።
ቡርሳ (ጭፍራ): የጭፍራ ስም፡ የድሮ ዘመን የጦር ሰራዊት።
ቡርሽ: ከጠጕር የተበጀ ቀለም መቀቢያና ልብስ መጥረጊያ (ዕቃ ማጠቢያ)። ማስታወሻ: “ሙሬ ቡርሽ” እንግሊዝኛ ነው።
ቡርቅ: የተቦረቀ፣ የተዘለለ (የታለፈ)፡ ውርብ። ተመልከት: “ቦቀረ” ብለህ “ቡቅርን”።
ቡርቅቅ አለ: ተንቦረቀቀ (አለልክ ሰፋ)።
ቡርቅቅ: የተንቦረቀቀ።
ቡርቡጭ (ጥቋ): መቋጠር።
ቡርቡጭ አለ: በጥቂቱ መላ (የሆድ)።
ቡርቲ (ኦሮምኛ: ቡርዲ): በላይኛው ከንፈር መካከል ያለ ያሞጠሞጠ ትርፍ ሥጋ። አባባል: “አርቲ ቡርቲ” እንዲሉ።
ቡርፉጭ አለ: በፈር ላይ ተኛ (ወይፈኑ)፡ እንደተቀመጠ አንቀላፋ (ሰውየው)።
ቡርፉጭ: ረብ ማለት (መተኛት)። ማስታወሻ: ቡርቡጭ እና ቡርፉጭ ከረፈጠ እና ረፈቀ የወጡ ናቸው።
ቡሽ: በቁሙ የጠርሙስ (ቃሩራ) መክደኛ (መግጠሚያ፣ ማፈኛ)፡ ለስላሳ እንጨት።
ቡሽት: ጠንካራ የዝናም ልብስ፡ የድሮ ዘመን።
ቡቃ (ኦሮ): ግንባረ ነጭ በሬ ወይም ላም። ግጥም: “ጨረቃ ጭንብር ቦቃ፡ ዐጤ ቤት ገባች ዐውቃ” እንዲሉ ልጆች።
ቡቃያ (ዮች) (በቍል): ከመሬት የወጣ የቅንጣት ልምላሜ፡ የአትክልት ፍል (ችግኝ፣ ግልግል)፡ ሣሩም (ቅጠሉም፣ እህሉም)። ሌላ ትርጉም: ዐራስ ልጅ (ጨቅላ)። ብቋያ: ዝኒ ከማሁ ለቡቃያ (ዘፍጥረት ፩፥፲፩፣፲፪)።
ቡቃያ: በቁሙ "ቡአ"።
ቡቅራት: ልጭታት።
ቡቅር (ሮች): የተቦቀረ፣ አሻራ።
ቡታ ሰደደ: እሪ አለ፡ የደረሰበትን ግፍና በደል አስታወቀ (መሳፍንት ፲፱፥፳፱)።
ቡታ: ታላቅ ጩኸት (እሪታ)፡ “የሰው ያለህ፣ ደርሱልኝ” ማለት። በጋልኛ: “ነጣቂ” ማለት ነው።
ቡትርፍ አለ: በጭቅ አለ።
ቡትርፍ አደረገ: ቡጭቅ አደረገ።
ቡትርፍ: የተቦተረፈ (የተበላሸ)፡ ቡጭቅ።
ቡቺ (ች): የውሻ መጥሪያ፡ ነቲ።
ቡቺ: ኵቲ (ቡችላ)።
ቡች ቡች: ዝኒ ከማሁ፡ ኵቲ ኵቲ።
ቡችላ (ሎች): የውሻ፣ የዥብ፣ የተኩላ፣ የቀበሮ፣ የነብር፣ የግስላ፣ የአንበሳ ግልገል (ማቴዎስ ፲፭፥፳፯)።
ቡና: በቁሙ የታወቀ የተክል እንጨት ስም፡ ፍሬው ተቈልቶና ተወቅጦ ፈልቶ የሚጠጣ። ማስታወሻ: አንዳንድ ሰዎች "ቡኖ" በሚባል አገር ስለተገኘ "ቡና" ተባለ ይላሉ። ፈረንጆች ግን "በከፋ" ስላገኙት "ካፌ" (ከፋዊ) ይሉታል።
ቡን/ብን: መብነን።
ቡን አለ/ብን አለ: ቦነነ፡ በነነ።
ቡንኝ (በሬ): የበሬ ኵልልት (ደደቆ)፡ ከሣርና ከውሃ የሚመጣ።
ቡንኝ (ጤፍ): ጥቍር ጤፍ (ዛላው ብን የሚል)።
ቡኖ: የአገር ስም፡ የሚገኝበትም በኦሮ ቤት ኢሉባቦር ነው።
ቡኣ (በዊእ፣ ቦአ): አንጀት። የአንጀት መውረድ፣ መዛወር፣ መጠምዘዝ፣ አለስፍራው መግባት። ምሳሌ: “ፈረሰኛው ቡኣ ወረደው” እንዲሉ። ፍች: ንፍጥና አክታ የሚመስል የአንጀት ውስጥ በሽታ። ማስታወሻ: ኦሮሞ "ወረደ" ሲል "ቡኤ" ይላልና፡ "ቡኣ" ከኦሮምኛ ጋር ይሰማማል።
ቡከን: ባካና፣ ፈሪ፣ ቅዘናም። አባባል: “ቡከን ዘረጥራጤ” እንዲሉ።
ቡከንፈሪ: ባከነ።
ቡከኖች: ፈሪዎች።
ቡኪ (በቀል): ተበቃይ፣ ደም መላሽ። ምሳሌ: “የቡኪ ደም” እንዲሉ (፬ኛ ነገሥት ፪፥፲፭፥፮፡ ፪ኛ ነገሥት ፳፬፥፰፥፱)። ማስታወሻ: "ቡኪ" ("ብኵ") የተባለ ዳዊት ነው።
ቡኪ/ቡኬት: የቦካ፣ የተቦካ (ቡሖ)።
ቡክቡካ (ብኍብኍ): የበሰበሰ የጭስ እንጨት፡ የወይባና የሸፈሬ (የዋንዛ፣ የንግ ሥር) ቡጥ። ሴቶች ቀምመው የሚያጨሱት (የሚታጠኑት) ሽታ ያለው ማንኛውም ፍልጥ።
ቡኾ: የቦካ (ቡሖ)።
ቡዪት: ከቻች ዝቅ የምትል (መስቴ ወይም ጥዋ)።
ቡያ (ዮች): ከርግብና ከዋኔ የምታንስ፣ ከወፍ የምትልቅ (የዋኔ ወገን)።
ቡያማ: የቡያ ዓይነት ማለት ነው፡ የመጠኗን ትንሽነት ያሳያል።
ቡደን: የመሬት ዳርና ዳር ትልም (ፈር) ማቀባበያ።
ቡዳ (ዛር): ዛር፣ ጋኔን፣ ምትሃት፡ እጀ ሰብ፣ ዐይነ ወርቅ፣ ዐይነ ወግ፡ ሰውን የሚይዝ፣ የሚያሳብድ፣ የሚያስለፈልፍ፡ አተላ የሚያስጠጣ፡ እንደ ዥብ የሚያስጐነብስ፣ ዐንካሳ የሚያደርግ፣ "አው" የሚያሰኝ። ምክንያት: ሰውየው ስለሚከሳና ስለሚመነምን “ቡዳ በላው” ይባላል። ማስታወሻ: የአማርኛ ገበታ ዋርያን ተመልከት። ግጥም: “እሱ ያመጣውን እሱ እስኪመልሰው፡ ሥጋ ጠጅ አይወድም ቡዳ የበላው ሰው”። ማስታወሻ: ዐፄ ዮሐንስ "በግድ ቍረብ" ያሉት ቃልቻ።
ቡዳ (ጠይብ): ጠይብ (ጠቢብ)፡ ቀጥቃጭ፣ ባለጅ፣ ሥራ ዐዋቂ፣ ሠራተኛ፣ ጃን፣ ሸላሚ፣ አንጥረኛ፡ በጥቂት ብልህነት የሰውን ድካም የሚበላ፣ ብልህተኛ፣ ፋቂ፣ ሸማኔ። ምሳሌ: “ከሰው ቡዳ ከብት ጐዳ”። ምሳሌ: “ከባለቤት ያወቀ ቡዳ ነው”። ማስታወሻ: ይህ ስም የሀገራችን ሰዎች የቡዳሃን ሃይማኖት አለመቀበላቸውን ያሳያል። "ወረኃን" እና "ወንጀልን" ተመልከት። ማስታወሻ: ደግሞም ከህንድ በመጡት "ፈላሾች" ገዳም በመንዝ "ይልማ" እና በተጕለት "ይጣ ምግል" ዋሻ የቡዳሃ ምስል መኖሩን አቶ በእደ ማርያም ደስታ ይመሰክራሉ። የጠይብም ቡዳ መባል ምክንያቱ ይህ ነው።
ቡዳ/ቡዳሃ: የህንዶችን፣ የሺኖችንና የጃፓኖችን ሃይማኖትና ምግባር ያደሰ የህንድ ንጉሥ ልጅ፡ እውነተኛ መናኝ፣ ግሑሥ ባሕታዊ። ማስታወሻ: ህንዶች "ቡዳሃ" ይሉታል። ትርጉሙም "ፈላስፋ፣ ብልህ፣ ዐዋቂ፣ ብርሃናዊ" ማለት ነው። ማስታወሻ: ብላቴን ጌታ ኅሩይ የጻፉትን የጃፓን ታሪክ ተመልከት።
ቡዳ ዐጣኝ: ቡዳ የበላውን ሰው እያጠነ የሚያስጮህ፣ የሚያስለቅቅ፣ ባለመድኃኒት።
ቡዳነት/ቡድነት: ጠይብነት፣ ምትሃትነት፡ ቡዳ መሆን።
ቡድስ አለ: ግምስ (ጕምድ፣ ብጥስ) አለ። ማስታወሻ: "ቦዳ" ማለት ከዚህ የወጣ ነው።
ቡድስ: የተቦደሰ፣ የተገመሰ፣ የተጐመደ፡ ጕምድ፣ ግምስ፣ ደበል፣ ወደሮ፣ እርሻ።
ቡድን (ላድ) (ኛ): የገና ጨዋታ ጓድ፡ ጓደኛ፣ አቻ፣ ወደር፣ እኩያ፣ ጣምራ፣ ቅንጁ። ምሳሌ: “የቡድን አባት” እንዲሉ። የቡድን ስሞች: ነብር፣ ግስላ፣ ጐሽ፣ አንበሳ፣ አውራሪሥ ይባላል። ቡድኖች: የጨዋታ ጓዶች።
ቡድን (ጥድ): የተቦደነ ልብስ።
ቡዶች: ጠይቦች፣ ባለጆች፣ ቀጥቃጮች፣ አንጥረኞች፣ ቍንጣሮች።
ቡግሪት: እንደ መንቀል ያለች ታናሽ ጠዋ፡ የሐረግ ቢጋር (ንድፍ) ያላት፡ የተጠማ ሰው በውስጧ ያለውን መጠጥ አንድ ጊዜ ጠጥቶ ለመጨረስ (ለመጨለጥ) የሚበግራት።
ቡጢ (ዎች): የቡጥ ዓይነት፡ ጡጫ፣ ኵርኵም (ቡጢ)። ትርጉም: ቡጢ ያሰኘው በአራቱ ጣቶች መካከል እንደ ጕጥ ሆኖ የሚታየው አውራ ጣት ነው (ኤርምያስ ፲፭፥፳፩፡ ፩ኛ ቆሮንቶስ ፬፥፲፩)።
ቡጢ/ጡጫ: ቦጠቦጠ።
ቡጣም: ቡጥ ያለው፣ ባለቡጥ፡ ወፍራም እንወጥ (ዳቦ)።
ቡጥ (ምግብ): ከድስት እየተቧጠጠ የሚወጣ ቅመምና ቅባት የገባበት የሽንብራ ወጥ።
ቡጥ (ጦች): ውስጥ ልብ (የዳቦ፣ የንጨት)።
ቡጥ: መቧጠጥ፣ መጠጥ።
ቡጥ: በቁሙ፣ "ቦጠቦጠ"።
ቡጥልቅ አለ: ተቦጠለቀ፡ ተከፈለ፡ በኀይል ወይም በድንገት ወጣ።
ቡጥልቅ: የተከፈለ፣ የወጣ።
ቡጥቦጣ: ጕርጐራ፣ ጕጥጕጣ።
ቡጨቃ: ዐጨዳ፣ ቈረጣ፣ ሐሜት።
ቡጭር: የተቧጨረ፣ የተጫረ፡ ሙጭር።
ቡጭርቅታ: ውሃ በተመታ ጊዜ የሚሰጠው ድምፅ።
ቡጭቃት: ዐንገትጌ (የአንገት ማግቢያ)።
ቡጭቅ አለ: ተቦጨቀ።
ቡጭቅ አደረገ: ቦጨቀ።
ቡጭቅ: የተቦጨቀ፡ ዕጭድ፣ ቍርጥ፡ ባዘቶ፣ ሣር፣ ገላ።
ቡጭቡጭ አለ: ተበጠበጠ፣ ታወከ፡ ዐዘነ፣ ፈራ (የሆድ)።
ቡፌ: የንስራ ሽንቍር (የወተት መተንፈሻ)።
ቡፍ አለ (ትንፋሽ): አፍ አለ፡ ተነፈሰ።
ቡፍ አለ (ድምፅ): ድምፁን አሳንሶ ጮኸ (ውሻው)።
ቡፍ: በአፍንጫ መተንፈስ፡ ትንፋሽ ማውጣት (የአህያ፣ የበቅሎ፣ የፈረስ)።
ቡፍና/እንቡሽቡሽ: ያልፈላ ጕሽ፡ ወይም መናኛ (ሆድ የሚያገሣ፣ የሚያስገሣ)።
ቢ (እመ) (ዐቢይ አገባብ): ምሳሌ: “ላሳር የጣፈው ቢነግድ አይተርፈው”። አጠቃቀም: በሩቆች ወንዶችና ሴቶች ላይ በትንቢት አንቀጽ ሲገባ “ቢተኙ ነገር ያገኙ፡ ቢነሡ ነገር ይረሱ” ይላል። ማስታወሻ: ከአሉታ ጋር ሲነገር "ራብዕ" ይሆናል።
ቢላ: የሣር ጭጐጐት (ቢላዋ)።
ቢላ: የሣር ጭጐጐት፡ ቋ በልብስ ላይ የሚሰካ።
ቢላሖ (ባልሐ): እንደ ወርካና እንደ ሾላ ያለ ነጭ ዛፍ (ዐጽቃም)፡ ጥላው ከፀሓይ የሚያድን።
ቢላሆ: (ዛፍ)፡ (ቢላሖ)።
ቢላቢሎ (ብልባሌ): ሥሥ ልብስ፡ ወይም ቅዳጅ (የቢሎ ቢሎ)።
ቢላዋ (በልኀ፣ በሊኅ፣ ብልኅ): በቁሙ ካራ፣ ማረጃ፣ ማወራረጃ (መጥቢያ፣ መሰለቻ)። ተመልከት: "አባን"።
ቢላዋዎች: ካሮች፣ ማረጃዎች።
ቢል: ቢናገር፣ ቢመታ።
ቢልልኝ: የሰው ስም። "ቢፈቅድልኝ" ማለት ነው።
ቢልቢል አለ: ነደደ፣ ተቃጠለ (በጥቂቱ)።
ቢሎ: (ዝኒ ከማሁ)፡ "ቢሎ" አንድነትን፣ "ቢላቢሎ" ብዛትን ያስተረጉማል።
ቢሰኛ: ክፉ ዐሳቢ። አባባል: “ቢሰኛኸን ያርቅ” እንዲሉ።
ቢስ (ሶች)/ብኡስ: የቸር ተቃራኒ፡ ደረቅ (ዓይነ መጥፎ)፡ ክፉ (ንፉግ፣ ጩቅ)። ተመልከት: “ገድን”፣ “ልብን”፣ “ዐቅምን”። አባባል: “ቢስ አይይኸ” እንዲሉ። ተረት: “ቸርን ቢያጠብቁት ቢስ ይሆናል”።
ቢስ ገላ: ድል ቍምጥና ያለበት የተበላሸ ገላ (አካል)።
ቢስ: ንፉግ (ባሰ)።
ቢስነት: ንፉግነት (ክፋት)።
ቢራ: የፈረንጅ መጠጥ፡ ጠላ።
ቢሹ፡ ቢሹም: ቢፈልጉ፣ ቢፈልጉም። "ቢሹም አይገኝ እንዲሉ።"
ቢሻን (ኦሮ፡ ውሃ): ቢፈልገን። "ቢሻን እንጠጣለን ባይሻን እንተዋለን ጠላ ስለ ቀጠነ።"
ቢሻኸ: ቢፈልግሽ፣ ቢፈቅድኸ።
ቢሻው፡ ንኡስ አገባብ፡ በጎ፡ ደግ፡ ማለፊያ።
ቢሻው: ቢፈልገው፣ ቢፈቅደው። "(ተረት)፣ ሊጠጣ ቢሻው ይዋኛል ሊቀማ ቢሻው ይዳኛል።"
ቢተዋ (፪ኛ ሳሙኤል ፩፥፲): እንደ ዋንጫ ያለ የክንድ እንባር፡ በሁለት ወገን ማጠፊያ ያለው፡ በሽቦ የሚጋጠም። የዐሥራ ሁለት ገዳይ ሽልማት። በትግሪኛ: “ቢታ” ይባላል።
ቢትወደድ (ብሑት): የሠለጠነ (ሥሉጥ)፡ ባለመብት (ባለሙሉ ሥልጣን)። ትርጉም: “ቢት” ንጉሥ፣ “ወደድ” ወዳጅ። “የንጉሥ ወዳጅ”፣ “ንጉሥ የሚወደው”፡ “ንጉሥን የሚወድ” ዋና ባለሥልጣን ማለት ነው (ዘፍጥረት ፴፱፥፳)። ሲበዛ “ቢትወደዶች” ይላል።
ቢትወደድ: ባለሙሉ ሥልጣን (ጣንባተ)።
ቢቸግርሽ: ሳታውቂ ቢሳንሽ፣ ቢጨንቅሽ፣ ባትችዪ (ገረዘን እይ)።
ቢከፍቱ ተልባ: ርባና ቢስ ትዳር (ውስጠ ባዶ)።
ቢወጣ/ብትወጣ: የወንድና የሴት ስም፡ "ቢያድግ፣ ብታድግ" ማለት ነው።
ቢዘን: የተራራ ስም፡ በሐማሴን ግዛት ያለ ታላቅ ደብር (ገዳም)። ማስታወሻ: "ደበረን" ተመልከት።
ቢዘኖች: የቢዘን መነኰሴዎች።
ቢያ (ጓ፣ እስመ): ንኡስ አገባብ። “ኾነ ቢያ”፣ “ይኾናል ቢያ” እያለ የአንቀጽ ትራስ በመሆን ይነገራል። ማስታወሻ: "እኮንን" ተመልከት፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። "ጋሜን" እይ።
ቢያርዱ አይሞት: የተንቀሳቃሽ ስም፡ እንጭራር፡ ሞተ ብለው ሲተዉት እንደ ገና ይንቀሳቀሳል (እንጭራር)።
ቢያኩሽ: በቁሙ "ዐከከ"።
ቢያኩሽ: የሥንብጥ እኩሌታ።
ቢያክ (በኪክ፣ በከ፣ በክ): በክት፣ ሙቶ ያደረ፡ ከንቱ፣ ብላሽ፣ ዋዛ፣ ፈዛዛ። ማስታወሻ: ንኡስ አገባብ ነው።
ቢያክ ቢያክ አለ: እንደ በክት (እንደ አክታ) አየ (አደረገ)፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባ ውሻ፣ ዐር የነካው እንጨት አስመሰለ፡ አረከሰ፣ አጸየፈ፣ አጥላላ፡ ወዲያ ወዲያ አለ፡ አላገጠ፣ አፌዘ። ማስታወሻ: ቢያክ በግእዝ "በቢክ" ይባላል።
ቢያጥቡ አይጠራ: ሽንፍላ (ዐተበ)።
ቢያጥቡ አይጠራ: ሽንፍላ፡ መጨቅጨቂት፡ ቂመኛ ሰው።
ቢዳላ: ቢመች፣ ቢመቻች። "እዬዬ ቢዳላ ነው" እንዲሉ። (ግጥም): "ጌታው ደጃች ውቤ ኹል ጊዜ ጌትነት፡ ዛሬ እንኳ ለድኻው እንባ አተረፉለት"።
ቢዶ (ዎች): ፈረንጆች እንደ ቀርበታ በግመልና በአገሰስ (በአህያ) ጀርባ የሚጭኑት የውሃ ዕቃ (ከብረት የተበጀ)። ማስታወሻ: "ቢዶና" እና "ቤዶ" የ"ባዶስ" ዘር ናቸው።
ቢጆ/ብጁ: የተበጀ፡ ጕርሻ (አንድ አፍ እንጀራ)፡ እንክብክብ።
ቢጋር (ሮች): በገመድ፣ በከሰል፣ በበረቅ የተበገረ (የተሣለ፣ የተመለከተ) ምልክት፣ ንድፍ፣ መጠን፣ መሠረት። ማስታወሻ: ፈረንጆች "ፕላን" ይሉታል።
ቢጣ (ቢጻ): ባልንጀራዋ፣ ጓደኛዋ።
ቢጣ (አካል): ጐን ጡንቻ። ማስታወሻ: "ዕንብርን" እይ።
ቢጤ (ቢጽየ): ባልንጀራዬ፣ ባልንጀሬ፣ ጓደኛዬ፣ ጓዴ።
ቢጤዎች ቼ (አብያጽ፣ የ): እኩዮች ቼ፡ የኔ አቻዎች።
ቢጥ/ቢጤ (በዪጽ፣ ቤጸ፣ ቢጽ): ባልንጀራ፣ ጓደኛ፣ ባልደረባ፣ እኩያ፣ አምሳያ፣ ወደር፣ አቻ። ምሳሌ: “ቢጤ ከቢጤው” እንዲሉ።
ባ (እመ ኢ): ምሳሌ: “በላይህ ቶራ ባልነበር ሰው እንደ በሬ ይታረድ ነበር”። ማስታወሻ: ሣልሱ በትንቢት፣ ራብዑ በኃላፊ እንደገባ አስተውል።
ባ (ድምፅ): የበግ ጩኸትና ጥሪ። ምሳሌ: “በጉ 'ባ' ይላል”፡ “ምን ይላል? 'ባ' ይላል”። አጠቃቀም: "በ" በቅርብ ወንድና “እኔ” በሚል በትንቢት ሲገባ "ሳድስ" ይሆናል።
ባ፲፱፻፲፰ ዓ.ም አስመራ በግእዝ ቋንቋ የታተመው ፪ኛው መቃብያንም በምዕራፍ ፪ በቍጥር ፬ና ፭ ከተረፈ ኤርምያስ ጠቅሶ፡ ነቢዩ ኤርምያስ ድንኳኑንና ታቦቱን ከዕጣኑ መሠዊያ ጋራ እስራኤል የሚወርሱትን ርስት ለማየት ሙሴ ወደ ቆመበት ተራራ ወስዶ በዋሻ ቀበራቸው ይላል (ኤርምያስ ፫፡ ፲፮)።
ባ፲፱፻፳፰ ዓመተ ምሕረት: ወደ ኢትዮጵያ የዘመተው የጣሊያን ሰራዊት ስድስት መቶ ሺ ሲኾን (፩) የኢትዮጵያ ግን ሦስት መቶ ሺ ነበረ።
ባህል (ልማድ): ልማድ፣ ደንብ።
ባህል (ብሂል፣ ብህለ): ነገር፣ ቃል፣ ድምፅ፡ የነገር ስልት (አነጋገር፣ አባባል)።
ባሕረ ሐሳብ (ኍልቈ ዘመን): የቀን፣ የሳምንት፣ የወር፣ የአመት፡ የፀሓይ፣ የጨረቃ ቍጥር ያለበት፡ የበዓላትና የአጽዋማት ማውጫ የሚነገርበት ቍጥር ያለው ዘመን፡ ወይም የዘመን ቍጥር (ዓመተ ዓለም)። ሐሳበ ባሕር: ከባሕር የመጣ ቍጥር።
ባሕረ ሎሚ: የባሕር ሎሚ (ብርቱካን)፡ በኵረ ሎሚ።
ባሕረ ሸሽ: ባሕር የሸሸው (የሸሸበት፣ የራቀው፣ የለቀቀው፣ ትቶት የሄደ) መሬት (እርሻ)።
ባሕረ ዐረብ (ዐረበ ባሕር): የባሕር ዐረብ፡ ቀይ ነት (ተንቤን፣ አንቀልባ)። ማስታወሻ: ዐረብ ማለት ቅላቱንም እንጂ ከዐረብ አገር መምጣቱን ብቻ አያሳይም።
ባሕረ እሳት: የእሳት ባሕር፡ ፍል ውሃ።
ባሕረ ወጥ (ወፃኤ፣ ውፁአ ባሕር): ከባሕር የወጣ (የመጣ) ሰይፍ፣ ጐራዴ።
ባሕረ ጃን (ንጉሥ): ባሕረ ንጉሥ፡ የንጉሥ ባሕር።
ባሕረ ጃን (ጃነ ባሕር): ወርቅና ብር መሳይ በለጭ፡ የማዕድን ወረቀት (ቀሠብ)፡ ቀይ፣ ነጭ፣ አረንጓዴ፡ ሥሥ፣ ረቂቅ ታኒካ። ማስታወሻ: በርሱ የተሸለመና የተጌጠ የበቅሎ ዕቃ። ሌላ ትርጉም: ደግሞም "ባሕረ ጃን" “ባሕረ ነጋሽ” (የባሕር ንጉሥ) ከማለት ጋራ ይስማማል። ትርጉም ከቋንቋ: በፈረንጅ “ዦን” (ቢጫ)፡ በአማርኛ “ጃኖ” (ቀይ) ማለት ነውና፡ በቢጫና በቀይ የተጠለፈ አረንጓዴና ሰማያዊ ከፈይንም ያመለክታል።
ባሕረ ጃን (ጃኖ): የባሕር ጃኖ። ይህም በቀዩ መደበኛነት ነው።
ባሕረኛ (ኞች): የባሕር መንገድ ዐዋቂ (ሕዝቅኤል ፳፯፥፳፱)። ማስታወሻ: "ቋትልን" እይ።
ባሕሪ/ባሕራዊ: የባሕር።
ባሕር (መድኃኒት): ኮሶ፡ የኮሶ ብጥብጥ። እንቆቅልሽ: “ትንሽ ባሕር ዐጤን ታስፈር?”
ባሕር (ብሒር፣ ብሕረ): የውሃ ቦታ፣ መቆሚያ፣ መከማቻ፡ ሰፊ፣ ጥልቅ፣ ውሃው የማያልቅ፣ የማይደርቅ፡ ስፋቱ ከየብስ የሚበልጥ (፫ እጅ የሚልቅ)፡ የረጋ፣ የተኛ፣ የተንጣለለ ውቅያኖስ። ለሐይቅ፣ ለኩሬ፣ ለፈሳሽም ሁሉ ይነገራል። ማስታወሻ: ሲበዛ "ባሕሮች" ያሠኛል (ዘፍጥረት ፩፥፲)።
ባሕር (አቅጣጫ): ታናሽ የምድር ማዕዘን፡ በሰሜንና በምዕራብ መካከል ያለ (የሰሜን ምዕራብ) የሊባ አፋዛዥ (ትይዩና አንጻር)።
ባሕር (ዳር): የአገር (የምድር) ዳር። ምሳሌ: “ከባሕር እባሕር” እንዲሉ።
ባሕር መዝገብ: የወጪና የገቢ (የአናና ዘወጣ) የሂሳብ መግቢያና መውጫ የሚጻፍበት ትልቅና ሰፊ መዝገብ። ምሳሌያዊ ትርጉም: በባሕር ውስጥ ብዙ ተንቀሳቃሽ፣ ትልቅና ትንሽ (ቀን ከርሱ ሌት ከየብስ የሚውልና የሚያድር) እንስሳ እንደሚኖር፡ በመዝገብም ገቢና ወጪነት ያለው አሞሌ፣ ሎሴ፣ ጠገራ፣ ብር፣ አላድ፣ ሩብ፣ ተሙን፣ መሐለቅ፣ ቤሳ ተጽፎ ይገኝበታልና፡ "ባሕር" የሚል የስም ቅጽል ተሰጠው።
ባሕር መዝገብ: የገቢና የወጪ መዝገብ እንዲሉ።
ባሕር ሰገድ: የሰው ስም፡ “ባሕር የሰገደለት” ማለት ነው።
ባሕር ነጋሽ (ነጋሤ ባሕር): በባሕር ዳር የነገሠ (የተቀመጠ)፡ እንደ ምጽዋ ያለውን ወደብ ጠባቂ (የሐማሴን ገዥ)፡ ወይም የባሕር ንጉሥ (አርማሕ)። ማስታወሻ: ባሕር ነጋሽን የመሰሉ "ባሕረ አስግድ"፣ "ባሕረ ኤክላ" የተባሉ ሌሎች ነገሥታትም አሉ።
ባሕር ወላድ (ዘፍጥረት ፩፥፳፣ ፳፩): የብዙ ልጅ እናት፡ “ባመት ጥጃ፡ ሱሪ ቢጥሉባት የምትወልድ”።
ባሕር ዛፍ: ፍሬው ከባሕር የመጣ እንጨት።
ባሕርይ (መለኮት): ያልተፈጠረ፣ የማይመረመር፣ የማይታወቅ (ኅቡእ፣ ረቂቅ)፡ ቅድስት ሥላሴን አንድ የሚያደርግ (በሥር፣ በጕንድ፣ በነቅዕ የተመሰለ) የፈጣሪ ባሕርይ (አምላክነት)።
ባሕርይ (እንቁ): የባሕር ዕንቍ (ግእዝ)።
ባሕርይ (ጠባይ): ዝኒ ከማሁ (እንደዚሁ)፡ ጠባይ፣ ዐመል። የፍጥረት ሁሉ ሥር መሠረት (መሬት፣ ውሃ፣ ነፋስ፣ እሳት)። ማስታወሻ: “ዐመል” በአረብኛ “ሥራ” ሲሆን በአማርኛ እንደ “ጠባይ” ይታሰባል።
ባሕታዊ (ባሕተወ): ባተሌ፣ ባታይ፣ ብቸኛ፡ ከሰው ተለይቶ በበአት (ዋሻ) ተከቶ (ተዘግቶ) ለብቻው በዱር፣ በገደል፣ በተራራ የሚኖር (ነቢይ፣ መናኝ፣ መነኰሴ፣ ናዝራዊ፣ መንፈሳዊ፣ ፈላስፋ፣ የእግዜር ሰው)።
ባሕታዊ ንጉሤ: በ፲፰፻ ዓ.ም በሃይማኖት ምክንያት ከደብረ ሊባኖስ ተይዘው ጅማ አባ ጅፋር ዘንድ ታስረው የሞቱ እውነተኛ ኦርቶዶክስ፡ ትውልዳቸው ላስታ።
ባሕታዊነት (ብሕታዌ): ብቻ መሆን፡ ብቻ ብቸቻ፣ ብቻነት።
ባሕታዊዎች (ባሕታውያን): ብቸኞች፣ መናኞች፣ ጻድቃን፣ ቅዱሳን።
ባለ (መታ): መታ፣ በበትር ጠዘለ፣ ደበደበ። ግጥም: “ካንተ ተኝታ ሌላ ካማራት፡ በል ተነሣና በዱላ በላት። ”
ባለ (በአለ): በተናገረ፣ በፈቀደ። ምሳሌ: “ወንድ ባለ በለት፡ ሴት ባለች በዓመት” እንዲሉ። ሞትን እይ: "ባለን ሞተ" ብለህ "ሞትን" እይ። ካሰን: "ተካሰን" አስተውል።
ባለ (በዘሃለወ): (ቅጽል) “እከሌና እከሌ እንዲህ ባለ (በአለ) ነገር ተጣሉ። ”
ባለ (ብሂል፣ ብህለ): አለ፣ ነገረ፣ ተናገረ፣ ቃል አሰማ። ምሳሌ: "ምን ባለ?" (ጕራጌ) "ምን አለ?" (ሲል)። ማስታወሻ: "ብህለ" በአማርኛ "ባለ" መባሉ "ሀ" በንዑስ ራብዕ አድርጎ ስለተጐደለ ነው። ዳግመኛም "በባለ" ፈንታ "በለ" ይላል።
ባለሃይማኖት: ሃይማኖተኛ፡ ሃይማኖት አክባሪ።
ባለሕግ (ጎች) (በዓለ ሕግ): ባለተክሊል፡ በሕግ፣ በሥርዐት፣ በቍርባን የሚኖር እውነተኛ ክርስቲያን፡ ባላንድት ሚስት።
ባለላም (ባዕለ ላሕም): ላም ያለችው፡ ላም ዐላቢ፡ አቢላም፡ የላም እረኛ።
ባለላም: አቡ፣ አብ።
ባለል (ሎች): ውድ ወዳጅ፡ ታማኝ፡ ከንጉሥና ከመኳንንት ጋራ የሚውል (ዘፍጥረት ፴፱፥፩)። ተረት: “የባለጌ ባለል ቂጥ ገልቦ ያያል። ”
ባለል ተክሌ: የባለሎች አለቃ (በዐድዋ ጦርነት የሞቱ)።
ባለልነት: ወዳጅነት፣ ታማኝነት።
ባለመለዮ: ሠራዊት፣ ጭፍራ።
ባለመርከብ: መርከበኛ፡ የመርከብ አዛዥ።
ባለመብት: ባለፈቃድ፡ ሥልጣን (ሹመት) ያለው፡ አዛዥ።
ባለመደረቢያ: ሁለት ጣራ ያለው ድንኳን።
ባለመዳኒት (በዓለ መድኀኒት): ሐኪም፡ መዳኒተኛ፡ መዳኒት ዐዋቂ (ቀማሚ፣ ሸያጭ) (ማቴዎስ ፱፥፲፪)። ማስታወሻ: "ዐቀበ" ብለህ "ዐቃቢን" እይ።
ባለሙሉ ሥልጣን: ቢትወደድ፣ እንደራሴ።
ባለማኅተም: ማኅተም ያለው ሰው (የማኅተም ባለቤት)።
ባለማደሪያ: በመትከያና መንቀያ የመንግሥት መሬት የሚኖር ወታደር።
ባለምልክት: በለጭማ ከብት፡ ድጓ።
ባለምድር: የርስት (የመሬት) ጌታ።
ባለሞረድ: መውዜር ጠመንዣ ሞረድ ያለው።
ባለሰሞን: ሰሞነኛ፡ ከሰኞ እስከ እሑድ የሚቀድስ ቄስ (ዲያቆን)።
ባለሰገጥ: ጥልፉ ሰገጥ የሚመስል ካባ።
ባለሳምንት: በሚመጣው ወር ማኅበር የሚደግስ (ጥዋ ወሳጅ)።
ባለሥልጣን: ቄስ፣ ሹም፡ ሥልጣን ያለው።
ባለስም: ስሙ የተጠራ፡ ዝናው የተሰማ፡ ወይም መንግሥት የሹመት ስም የሰጠው።
ባለሦስት: በ፫ኛ ወር ማኅበር የሚደግስ።
ባለርስት: ርስት ያለው፡ የርስት ጌታ (ርስተኛ)።
ባለቀ (በሊቅ፣ በለቀ): (ዐጕልና ገቢር) ለዘር በቃ፡ አደገ፣ ጐለመሰ፡ በሕልም ወይም በውኑ ዘር አፈሰሰ (ሴት ዳሰሰ)። ተረት: “የታጠበ እጅ ያልባለቀ ልጅ። ” ማስታወሻ: ገናና “ባለቀ” ተወራራሾች ስለሆኑ ባለገናና ባለቀ በምስጢር ይገጥማሉ።
ባለቀላድ: የገመድ (የመሬት) ጌታ።
ባለቀሚስ (ሶች): ቀሚሳም፡ ቀሚስ የተሸለመ (የለበሰ) ካህን፣ ወታደር።
ባለቀትር: ባለጊዜ፡ ደሙ የፈላ።
ባለቅኔ: ቅኔ ዐዋቂ፡ ቅኔ የሚቀኝ።
ባለበግ (በዓለ በግዕ): የበግ ጌታ፡ በግ ያለው፡ በግም የበግ እረኛ።
ባለባል: ገለሞታ ያይደለች ባል ያላት ሴት።
ባለቤቱ: የቤቱ ጌታ፡ እርሱ፡ ወይም ሚስቱ።
ባለቤቲቱ: (ዝኒ ከማሁ)፡ እሷ።
ባለቤት (ኅብስት): ከ፫ቱ ኅብስተ ቍርባን ፪ኛው መካከለኛው (የክርስቶስ አካል ምሳሌ)፡ ቄስ ሲባርከው ሥጋ አምላክ የሚሆን፡ የቤተ ክርስቲያን ራስ (አለቃ)።
ባለቤት (ቶች) (ባዕለ ቤት): ቤት ንብረት ያለው፡ የቤት ጌታ። ተረት: “አለ ባለቤቱ አይነድም እሳቱ። ” ሌላ ትርጉም: ባል። ባለቤት (ሴት): ሚስት፡ ባልተቤት። ማስታወሻ: ሴትን ከወንድ ለመለየት “ባለቤቷ”፣ “ባለቤቲቱ” ይላል (፩ኛ ነገሥት ፲፯፥፲፯)።
ባለቤት (ዋና): የነገር ዋና፡ የዘርፍ፣ የቅጽል ጌታ፡ አንቀጽ ተቀባይ። ምሳሌ: “ክርስቶስ ተወለደ፣ ሞተ፣ ተነሣ፣ ዐረገ። ዳግመኛም ይመጣል። ”
ባለቤት አከል: ባለቤትን የሚያህል፡ እንደ ባለቤት የሚያዝ፡ ቤት አዛዥ፣ የቤት ዋና፣ አሳዳሪ፣ መጋቢ፣ አስተንታኝ፣ ቤት አባት።
ባለቤትህ: አንተ፡ ሚስትህ።
ባለቤትዎ: እርስዎ፡ ሚስትዎ።
ባለቤቷ: ያች እርሷ፡ ወይም ባሏ።
ባለተ (ጐጃም): ታሠሠ፣ ተወለወለ።
ባለተስፋ: “አገኛለሁ” ባይ፡ ባላኝታ።
ባለተራ: ተከታይ፡ ባለረድፍ፡ ሥራው (ጊዜው) የእርሱ የሆነ።
ባለነገር (በዓለ ነገር): በርስቱና በገንዘቡ የሚማገት (የሚከራከር)፡ ነገረተኛ፡ ወይም ነገረኛ (ነገር ወዳድ)፡ ነገራም።
ባለነጋሪት: ነጋሪት ያለው ራስ፣ ደጃዝማች።
ባለነጭ (ጮች): የነጭ ልብስ፣ የነጭ ጤፍ እንጀራ፣ የሥብ ሥጋ ባለቤት (አረጋ መንገስ ገጽ ፮)።
ባለንብረት: ትዳር ያለው (ያላት)።
ባለአእምሮ: ዕውቀት ያለው፡ የዕውቀት ጌታ፡ ከእንስሳ የተለየ ሰው።
ባለዕውቀት: ዕውቀት ያለው። ማስታወሻ: "ባለማወቅ"፣ "፪ኛውን አለ" እይ።
ባለዕዳ (ባዕለ ዕዳ): አበዳሪ፡ ወይም ተበዳሪ፡ ዕዳ አስከፋይ (ከፋይ)። ተረት: “ከክፉ ባለዳ ጎመን ዘር ተቀበል። ” ሰዋሰው: ወንድና ሴትን ለመለየት:
ባለእጅ (ጆች) (በዓለ እድ): ሠራተኛ፣ ቀጥቃጭ፣ ጠይብ፣ አንጥረኛ፡ እጃም፣ እጀኛ፡ እጀታ ያለው ዕቃ (መሳሪያ)።
ባለእግዚአብሔር/ባለወልድ: (የባለጌ ግጥም)።
ባለከል: ልብሱ በከል የተነከረ፡ ከል ለባሽ (ዐዘነተኛ)።
ባለኩል (ሎች): የባሏን ትዳር እኩሌታ የምትካፈል ሚስት።
ባለኩልነት: በትዳር እኩያነት (ትክክልነት) የሚስት ከባል (ጋር)።
ባለኹለት: በሁለተኛ ወር የሚደግስ ማኅበረተኛ።
ባለወልድ (በዓለ ወልድ): ወር በገባ በ፳፱ ቀን የሚከብር፡ ጌታችን በድንግል ማርያም ማኅፀን ተፀንሶ መወለዱንና ሙቶ መነሣቱን የሚያሳስብ በዓል።
ባለወስፌ: ወስፊያም፡ ወስፌ ያለው ሰው (ዣርት)።
ባለወንበር (በዓለ መንበር): ሊቅ፣ መምህር፡ በወንበር ተቀምጦ የሚያስተምር።
ባለወገን: ዘመዳም፡ ባለብዙ ዘመድ፡ ወገን ያለው፡ የወገን ጌታ (እረኛ)። ማስታወሻ: "ወገንን" ተመልከት።
ባለወግ (በዓለ ወግዕ): ወገኛ፣ ወግ ዐዋቂ፡ ባለአበል። ማስታወሻ: "ወግን" እይ።
ባለወግ (ገዳይ): ሰቃይ፣ ቈራጭ፣ ገዳይ።
ባለውሃ (በዓለ ማይ): ውሃም፡ ውሃ ያለው፡ ውሃ ተሸካሚ (የውሃ ጌታ)። ሌላ ትርጉም: እንዳይግል በጐኑ ውሃ የሚቀመጥበት መትረየስ።
ባለውለን: ደንቈሮ፣ ዝግ፡ የማይሰማ፣ የማይለማ።
ባለውል: ውለኛ፡ ውል አክባሪ፡ ቁም ነገረኛም።
ባለውቃቢ: ዛራም፣ ቆሊያም።
ባለዘርፍ (በዓለ ዘርፍ): ዘርፋም፡ ዘርፍ ያለው ልብስ (ምንጣፍ)።
ባለዘውድ: ዘውድ ያለው፡ ንጉሥ፣ ጳጳስ፡ በራሱ ላይ ዘውድ የደፋ (የተቀዳጀ)።
ባለዚህ: የዚህ ጌታ፡ የዚህ ባለቤት። ማስታወሻ: የጥያቄ ቃል ነው።
ባለዛፍ: ዛፋም፡ ዛፍ ያለበት ዱር፡ የዛፍ ሥዕል ያለው ልብስ።
ባለዝና (በዓለ ዜና): ስመ ጥር።
ባለያ (በዓለ ሙዓል): ብልህ፣ ዐዋቂ፡ ባለብዙ ዕውቀት፡ በዕውቀቱ ሲሠራ የሚውል። ማስታወሻ: ፈረንጆች "ፕሮዱክተር" ይሉታል።
ባለይሉኝታ: የይሉኝ አይል ተቃራኒ፡ ትዝብትን (ነቀፋን) የሚፈራ።
ባለደም: ነፍሰ ገዳይ፡ ተበቃይ።
ባለዳዋ: ያች ባለዳ፡ የእርሷ ባለዳ። ባለዕዳነት: ባለዕዳ መሆን።
ባለዳው: ያ ባለዳ፡ የእርሱ ባለዳ።
ባለድባብ: ድባብ ያለው (ድባብ ያዥ)።
ባለገ (ዕብ ባላግ): በረታ፣ ቻለ፣ ጠና።
ባለገ (ጠፋ): ባለቀ፡ ከሕግ ወጣ፣ ሥርዐት አልባ ኖረ፡ ሥልጣኔ ዐጣ፡ ባላገር ሆነ።
ባለገዳም: የገዳም ጌታ፡ የገዳም ሹም፡ የገዳም አባት (አበ ምኔት፣ መምህር፣ አበ ማኅበር)።
ባለገድል (በዓለ ገድል): ገድላም፣ ገድለኛ፡ ገድል ያለው (ጻድቅ፣ ሰማዕት)።
ባለጊዜ (በዓለ ጊዜ): ዘመናይ ሹም፡ ንጉሥ (እንደ ወደደ የሚያደርግ)። ግጥም: “ያደረገውን አድርጎ አበጀሁ ቢላችሁ፡ ይህን ባለጊዜ ምን ትሉታላችሁ። ” ማስታወሻ: "አለ" በ"መነሻ" ሆኖት ከ"ባል" ጋራ መተባበሩን አስተውል።
ባለጋራ በዛበት: ብዙ ሰው ጠላው (ከሰሰው)።
ባለጋራ: ዛር (በሰው የሚያድር) (ሰውን የሚያስገዝፍ) (ቀይ ዶሮ፣ ቡሓ፣ በግ ሌላም ይህን የመሰለ የአምልኮ ባዕድ ግብር የሚያስገብር)፡ የኀጢአተኛን ነፍስ ከግዜር የሚጋራ ማለት ይኾናል፡ "ባለን" ተመልከት።
ባለጋራ: ደመኛ፣ ጠላት፣ ምቀኛ፣ ከሳሽ፣ አሳጭ። ትርጉም: በሐሰትና በተንኰል የሌላውን ጥቅም የሚጋራ (የሚካፈል)። ማስታወሻ: "ገራ (ገርዐ)" ብለህ "ጋራን" እይ።
ባለጋራ: ጠላት፣ ደመኛ፣ ከሳሽ፣ አሳጭ (በሐሰት በተንኰል የሰውን ጥቅም የሚወስድ)።
ባለጋራነት: ደመኛነት፣ ጠላትነት፡ ባለጋራ መሆን።
ባለጋሮች: ደመኞች፣ ጠላቶች (ኢሳያስ ፶፱፥፲፰)።
ባለጌ (በዓለ ጌ/በዓለ ምድር): (ባለምድር)፡ የምድር ጌታ።
ባለጌ ሆነ: ባለገ፣ በባላገር ኖረ።
ባለጌ: (ባለምድር - ባለገ)።
ባለጌ: አግድሞ አደግ፣ ስድ፣ መረን፣ ያልተቀጣ፣ ያልተገሠጸ፣ ነውረኛ (ነውር ጌጡ)፡ አያት ያሳደገው ልጅ። አባባል: “ባለጌን ካሳደገው የገደለው ይጸድቃል። ” አባባል: “ባለጌ የጠገበ ለት ይርበው አይመስለውም። ”
ባለግርማ: መፈረት (መፈራት)፣ አስፈሪነት ያለው፡ ተፈሪ፣ አስፈሪ፣ ግርማም።
ባለጠጋ (በዓለ ጸጋ): ሀብታም፣ ከበርቴ፡ ዕድለኛ፣ የበዛ፡ የከበረ፣ የበለጠገ (የዘመነ፣ የጌተየ)፡ ብዙ ሀብት ያለው ዕድለኛ። ተመልከት: "ባልን"።
ባለጠጋ: ሀብታም (በለጠገ)።
ባለጠግነት: ጌትነት፣ ሀብታምነት፡ ማግኘት (፩ኛ ዜና መዋዕል ፳፱፥፲፪፣ ምሳሌ ፲፱፥፬፣ ፩ኛ ጢሞቴዎስ ፮፥፲፯)።
ባለጠጎች: ሀብታሞች፣ ጌቶች።
ባለጣት፡ ማንካ፡ "ጣቶቹ እሾኸ የሚመስሉ ጥብስ ወይም ቅቅል ሥጋ፣ መውጊያ ወደ አፍ ማስጠጊያ፣ የምግብ መሣሪያ (፩ኛ ሳሙኤል፡ ፪ - ፲፫ - ፲፬)። ሲበዛ ሹካዎች፣ ሹኮች ያሠኛል (፪ኛ ዜና፡ ፬፡ ፲፮)።"
ባለጤና (በዓለ ጥዒና): ጤናማ፡ ደኅነኛ፡ “ቃር አያውቅሽ”።
ባለጥላ (በዓለ ጽላል): ጥላ ያለው፡ ጥላ ያዥ። ሌላ ትርጉም: ትከሻም፡ የከበደ፣ የከበረ ሰው።
ባለጥንግ: የጥንግ ጌታ፡ የጥንግ ዓይነት ድርብ። ምሳሌ: “ባለጥንግ ድርብ” እንዲሉ።
ባለጨረቃ: በላዩ ጨረቃ የተሣለበት ሰይፍ፡ ወይም ዕቃ።
ባለፈርጥ: ፈርጣም፡ ፈርጥ ያለው ልብስ፡ በፈርጥ ያጌጠ ሰው።
ባለፈቃድ: “ውሰድ” የተባለ፡ ፈቃድ የተቀበለ።
ባለፋንታ: ፋንታ የደረሰው፡ ባለተራ (ባለወረፋ)።
ባሊሖ (በሊኅ): የበላ፣ የሰላ፣ የሾለ (ስል፣ ትብ፣ ሐኔ፣ ማረጃ)። ተመልከት: "ቢላዋን"።
ባላ (ሎች) (ባልሐ፣ ባልሕ): በቁሙ ቤትን ከመውደቅ የሚያድን (የሚደግፍ) ራስ መንታ እንጨት።
ባላ ባልቾ: የባሎች ባላ፡ እንደ ዋላና እንደ ርኤም ቀንድ በባላ ላይ ባላ ያለው ዛፍ፡ ወይም ሜንጦ። ማስታወሻ: ዋላ የተባለ ሀየል ነው።
ባላ: የሰው ጭንና ጭን፡ ወይም ሁለት እግር።
ባላህያ (በዓለ አድግ): አህያ ያለው፡ የአህያ ጌታ (ጠባቂ)።
ባላልቦ: አልቧም፡ አልቦ ያላት ሴት፡ ወይም ባል የሌላት። ማስታወሻ: "አልቦን" እይ።
ባላልጋ: ዐልጋ (ዙፋን) ያለው፡ የአልጋ ጌታ፡ ባላባት (ንጉሥ)።
ባላምባራስ (በዓለ ርእሰ ዐምባ): የአምባ ራስ ጌታ፡ አምባ ራስን የሚያዝ፡ ከመንግሥት በአምባ ራስ ላይ የተሾመ። ማስታወሻ: "ዐምባ ራስን" እይ። ዛሬ ግን "ባላምባራስ" የሚባል ፪ ወይም ፫ ሻምበል አዛዥ ነው።
ባላረግ (በዓለ ሐረግ): የሐረግ ጌታ (ባለቤት)፡ የሐረግ ንድፍ (ሥዕል) ያለበት መጽሐፍ።
ባላረግ (ዘመድ): ዘመዳም፣ ወገናም ሰው።
ባላራት: ሠራተኛ፣ የወር ማኅበር ደጋሽ።
ባላባት (ቶች): ትልቅ አባት ያለው፡ አባተ፡ ትልቅ አባታም።
ባላት (በዓላት): ቅዱስ ዮሐንስ፣ መስቀል፣ ገና፣ ጥምቀት፣ ስቅለት፣ ፋሲካ፣ ዕርገት፣ ጰራቅሊጦስ፣ ፍልሰታ የመሰሉ የዕረፍት ቀኖች።
ባላና ደንቆሮ (እንጨት): ባላ ያለውና የሌለው የድር ማድሪያ ሁለት እንጨት።
ባላና ደንቆሮ (የድር ጫፍ): የድር ጫፍና ጫፍ፡ ባላ መቋጠሪያው፡ ደንቆሮ መቍረጫው። ማስታወሻ: አንዳንድ ሰዎች የብልሃት ሥራ ስላለበት (ድር ስለሚሠባጠርበት) ባላን በደንቆሮ አንጻር "ብልህ" ይሉታል።
ባላን(ም)ጣ (ጦች): አምጣ ባይ፡ ርስት ተካፋይ፣ ተወላጅ፣ ዘመድ።
ባላገር (ሮች) (በዓለ ሀገር): ባለጌ፣ ባገር ቤት የሚኖር ሰው (ዘሌዋውያን ፲፯፥፲፭)። ሌላ ትርጉም: አገሬ፣ የአገር ተወላጅ።
ባላገር (አገር): አገር ቤት። ምሳሌ: “እባላገር ከርሜ መጣሁ። ”
ባላገር ግን: ትሩፋቶች ይላል።
ባላገሮች ነቢ የሚሉት: በቃልቻ ያደረውን ዛር ነው።
ባላጊ/ባለጌ (ዎች): የባለገ፣ የሚባልግ፡ ባላገር (ከርሻና ከቍፋሮ በቀር ሌላ የማያውቅ አገር ሰው)፡ ሥልጣኔና ዕውቀት የሌለው "ባለጌ" ይባላል።
ባላጐዛ: በጐዛ የሚቀመጥ መምህር፡ ዐጐዛ የሚለብስ (ሐርበኛ፣ ባለሎፊሳ)።
ባላጥንት (ባለዐጥንት): የጨዋ ልጅ። ማስታወሻ: "ዐጥንትን" እይ።
ባሌ (በዓልየ፣ ምትየ): በቁሙ የኔ ባል፡ የኔ ባለቤት (ባለቤቴ)። ግጥም: “እጓዳ ፈትዬ እጓዳ አደረግሁት፡ አትንገር ሸማኔ ባሌን አሞኘሁት። ”
ባሌ (ቦታ): ከሐሩሲ ቀጥሎ ያለ አገር። ማስታወሻ: በግእዝ መጻሕፍት "ባሊ" ይባላል።
ባል (ቁልፍ): የልብስ ቍልፍ።
ባል (በዓል): በቁሙ የደስታና የዕረፍት ቀን፡ በዓመት፣ በወር፣ በሳምንት የሚከበር። የባለጌ ግጥም: “አንጫወትም ወይ ሰኞ ተገናኝተን፡ ባልማ ሲመጣ ወዴት ተመችቶን። ” አባባል: “ሰነፍ ባል ያበዛል” እንዲሉ። የማርያም ባል: ወር በባተ በ፳፩ኛው ቀን የሚከበር። ማስታወሻ: “ባል” እየተናበበ ሲነገር እንደሚስማማው የዐጸፋና የቅጽል አፈታት ይፈታል።
ባል (ብዕለ፣ ባዕል፣ በዓል): (መትሀ፣ ምት) ሚስት ያለው ወንድ ተባት፡ የሴት ገዥ፣ አዛዥ፣ ጌታ፣ ባለቤት (ሮሜ ፯፥፪-፬)። ምሳሌ: “ባልና ሚስት” እንዲሉ። ማስታወሻ: "አባን" እይ፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው። ተረት: “አገባሻለሁ ያለሽ ላያገባሽ ከባልሽ ሆድ አትባባሽ። ” ተረት: “የአህያ ባል ከዥብ አያስጥል። ”
ባልተቤት (በዓልተ ቤት): ሴት እመቤት፡ ሚስት። ማስታወሻ: በልማድ ግን "ባለቤት" ትባላለች።
ባልታ (ብሂሎት): ማለት። "አለ" የሚለውንም እይ።
ባልታ: ማለት፡ "ባለ"።
ባልቴት (ቶች) (ባል ተየት): ያረጠች ሴት፡ ደራቁቻ (አሮጊት) የበቃች፡ ባል ብቻዋን የምትኖር (፬ኛ ነገሥት ፲፯፥፱፣፲፣ ግብረ ሐዋርያት ፮፥፳)።
ባልቴት: ያረጠች፡ "በለተ"።
ባልትና ቢስ: ያ የሌላት ሴት።
ባልትና: ዕውቀት ያ፡ የባልቴት ዘዴ።
ባልትና: ያ፡ "በለተ"።
ባልቻ (ኦሮ): ምትክ ማለት ነው።
ባልና ሚስት: በቁሙ ወንድና ሴት። አባባል: “ባልና ሚስት ሎሚ ከሁለት” እንዲሉ።
ባልንጀራ (በዓለ እንጀራ): የንጀራ ባለቤት (የንጀራ ጌታ)።
ባልንጀራ (ጓደኛ): እኩያ፣ ባልደረባ፡ አቻ፣ ዐብሮ አደግ፣ ጓደኛ፣ እንጀራ አቋራሽ (ዘፍጥረት ፲፩፥፫፣ ኢሳያስ ፵፬፥፲፩)።
ባልንጀር: (ዝኒ ከማሁ)፡ የጥሪ ቃል ነው።
ባልንጀርነት: እኩያነት፣ ባልደረብነት (፪ኛ ቆሮንቶስ ፮፥፲፭)።
ባልንጀሮች: ባልደረቦች፣ ጓደኞች (ሮሜ ፰፥፲፯)።
ባልኛ: ባለባላ።
ባልደረባ (ባልደረብ): ጓድ ያለው (ባለጓድ)። ትርጉም: የዕድሜ፣ የሥራ ጓደኛ፡ አብሮ የሚኖር፣ የሚሠራ፡ ባልንጀራ፣ እኩያ፣ አምሳያ፣ ሚስት። ማስታወሻ: አለቃም ለጭፍራው "ባልደረባ" ይባላል። "ደረበን" ተመልከት።
ባልደረብነት: እኩያነት፣ ጓደኝነት፣ ባልንጀርነት።
ባልደረቦች: ጓደኞች፣ እኩዮች።
ባልደራስ (ሶች): የደራስ ጌታ፣ የደራስ ባለቤት፡ የፈረስ ሹምና ገሪ (፩ኛ ነገሥት ፱፥፳፪)። ማስታወሻ: "ደራስን" እይ።
ባልደራስነት - ባለኹለት
ባልደራስነት: የፈረስ ሹመት፣ ገሪነት፣ ጠባቂነት።
ባልዲ (ማሕየብ): መጥለቂያ፣ የውሃ መቅጃ፣ መሳቢያ (መጐተቻ)፡ ሰዎች ማንጠልጠያው ገመድ አስረው ከጕድጓድ ውሃ የሚያወጡበት። ማስታወሻ: ባልዲ ሥራውም ስሙም የፈረንጅ ነው። ተመልከት: "ደለይን"።
ባልጩት (ቶች) (ብልጩት፣ ብልጭት፣ ብልቲት፣ እዝኅ): የቦረቦጭ (ሱፋጭ፣ ሻፎ) ሥጋ የሚቈርጥ (የሚበልት) ስለታም ድንጋይ (ዘዳግም ፰፥፲፭፣ ኢሳያስ ፶፥፯)።
ባልጪ (ኦሮ): ቦጨቦጭ፣ ቦረቦጭ።
ባሎች (አምታት): ባለሚስቶች፡ ሚስቶች ያሏቸው ወንዶች።
ባማርኛ ደንብ: ሲበዛ ሰራዊቶች ያሠኛል፣ በግእዝ ግን ሰርዌ ያንድ ሰራዊት የብዙ ነው።
ባማርኛው፡ ጀን፡ ባረብኛው፡ ረን፡ አጥብቅ።
ባምባ ዛፍ: "ባባ"።
ባሰ (መብለጥ): በለጠ፣ ከበረ። ምሳሌ: “አንተ ትብስ” እንዲሉ።
ባሰ (ብኢስ፣ ብእሰ): ጠና፣ ከፋ (በረታ፣ አገረሸ)፡ መጥፎ ሆነ። ተረት: “እግር ይብሳል ያበሰብሳል”። ሌላ ትርጉም: ተቀየመ፣ ተበሳጨ (ዐዘነ፣ ተከዘ)። ሌላ ትርጉም: ቸገረ (ገደደ)። ምሳሌ: “ምን ባሰው” እንዲሉ።
ባሰኸና: በሹሮ ፈንታ የጤፍ ዱቄት አሳርረው የሚሠሩት ዓልጫ ዶየ። ትርጓሜው: “ይህን ብታገኝ (ባሰኸና)”፡ “ከፋህና፣ መጥፎ ሆነብህና” ማለት ነው።
ባሰኸና: ዶዮ (ባሰ)።
ባስልዮስ: የሰው ስም፡ ትርጓሜውም በጽርዕ “ንጉሥ” ማለት ነው ይላሉ።
ባረቀ: በድንገት ሳይታሰብ ፈነዳ (ተተኰሰ)፡ መብረቅኛ ጮኸ (የሽጉጥ፣ የነፍጥ)። ተመልከት: “ዘባረቀን”።
ባረብኛ ዙራ፡ በጋልኛ ጆሮ ትባላለች።
ባረከ (ባርኮ፣ ባረከ): አመሰገነ፣ ምስጋና አቀረበ (መረቀ) (ማቴዎስ ፭፥፵፬)። ሌሎች ትርጉሞች: አማተበ፣ ቀደሰ፡ አበዛ፡ ጀመረ፣ ፈቀደ፡ ገመሰ፣ ቈረሰ (ዳቦን፣ እንጀራን)፡ ገዘገዘ፣ ከረከረ (ዐረደ) ፍሪዳን።
ባሩድ ቤት (ሠራዊት): ዐጤ ምኒልክ በየሻለቃው የሠሩት የቁጥር ጦር፡ ታማኝ ሰራዊት (የባሩድ ቤት ዘበኛ)።
ባሩድ ቤት (የጦር መሳሪያ): የጦር መሣሪያ በያይነቱ የሚቀመጥበት ቤት።
ባሩድ: ድኝና የእኅያ ከሰል፣ ጨው የሚባል ድንጋይ ባንድነት ተወቅጦ የተደራጀ፡ በጠመንዣና በሽጉጥ (በመትረየስ፣ በመድፍ) ቀለህ ውስጥ፣ በከምሱርና በዐረር መካከል የሚደረግ ዕይር።
ባሪያ (ሕመም): አዙሪት፡ የደም ስር በሽታ (በሰውና በበግ የሚጠና)።
ባሪያ (አሽከር): ታማኝ አሽከር፡ ባለል፡ ወታደር ሲፎክር “እኔ ባሪያህ” እንዲል።
ባሪያ/ባርያ (ባርዮ፣ ባረየ): ገብር፡ ከወገኑ ተለይቶ ከአገሩ ወጥቶ የተገዛ (ግዝ)፡ የተማረከ (ምርኮ)፡ እንደ በሬ በግድ የሚሰራ፡ በጌታው ዐሳብ ዐዳሪ፡ ነጻነት የሌለው፡ ባለመከራ (ሻግያ)፡ ባርነት ሲጸናበት ኰብሎ የሚጠፋ። አባባል: “ውላጅ ፍናጅ ቅናጅ፣ አሰለጥ አመለጥ፣ ማን ቤቴ፣ ደረባ ቤቴ፣ ዱር ቤቴ” የሚባል። ማስታወሻ: ሲበዛ “ባሮች” ይላል። አባባል: “ተበዳሪ የአበዳሪ ባሪያ ነው” (ምሳሌ ፳፪፥፯)። ማስታወሻ: ባሪያ ለወንድም ለሴትም ይነገራል። “ደበቀን” ይመልከቱ።
ባሪያ ሰደድ: ጥኑ (ጠንካራ) ገብስ። ታሪክ: በወፍጮው ምክንያት ባሮች ስለጠፉና ስለኰበለሉ “ባሪያ ሰደድ” ተባለ ይላሉ።
ባሪያ ቀይሕ: ከባሪያ ጸሊም አጠገብ ያለ አገርና ቀይ (ጠይም) ሕዝብ (ገባር)።
ባሪያ ድንጋይ: ጥቍር ድንጋይ፡ አለት፡ ጠንካራ፡ ግንብ ሲገነባ ከበሓ በታች እንጂ በላይ የማይሆን ከባድ ድንጋይ።
ባሪያ ጋብር (ትግሪኛ): ያቦ ባሪያ ጋብር፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ።
ባሪያ ጣለው: ጋኔን ደበለለው፣ አንከባለለው፣ ከመሬት መታው (ደበተው)። ማብራሪያ: ጠንቋዮች “ዐይነ ጥላ ሲጥሉ ባርያ ወሌጌዎን” ይላሉና፣ “ባሪያ ጣለው” ማለት በዚህ ምክንያት ነው። ምሳሌያዊ አነጋገር: ባላገሮች “ልክስክስ፣ የጕድፍ ጋኔን፣ ዛር ውላጅ (የጋኔን ተወራጅ)” ይሉታል። ትርጉም: ባሪያ መባሉም ጥቍረቱን (የምጣድ ቂጥ መምሰሉን) መደብ አድርጎ ለጌታው (ለሌጌዎን) የክፋትና የጥመት ታዛዥ መሆኑን፣ የጨለማ ጭፍራነቱን ያሳያል።
ባሪያ ጸሊም: የነገድና የአገር ስም፡ “ጥቍር፣ ጠቋራ፣ ሻንቅላ፣ ከሰልማ” ማለት ነው። የሚገኘውም በከረን ጠረፍ ነው።
ባሪያ ፈንጋይ: ባሪያን ጨርቅ አልብሶ ኳስ አጕርሶ የሚሸጥ፡ የደከመውን ለማስፈራራት አጋድሞ ፈንግሎ የሚያርድ፡ ባሪያ ነጋዴ (ወርጅ)።
ባሪያዋ: ያች ባሪያ ወይም የእርሷ ባሪያ።
ባሪያው: ያ ባሪያ ወይም የእርሱ ባሪያ።
ባሪያዪቱ: ዝኒ ከማሁ (ገላትያ ፬፥፳፫)።
ባራቂ: የሚባርቅ (ሳይተኩሱት የሚተኮስ)።
ባራኪ: የባረከ፣ የሚባርክ (የሚመርቅ፣ የሚቀድስ)፡ መራቂ (ቀዳሽ)። ሌላ ትርጉም: ጀማሪ (ቈራሽ) ቄስ። “ማእድ ባራኪ” እንዲሉ።
ባሬታ (ቶች): ከመዳብ፣ ከቅል፣ ወይም ከሸክላ የተሠራ የሽንት መሸኛ (መክፈያ፣ ቶፋ) ወይም ሌላ።
ባር/ባሕር: የተንጣለለ ውሃ፡ ውቅያኖስ። ባር አማርኛ ሲሆን ባሕር ደግሞ ግእዝ ነው።
ባር ሆድ: የሆድ ውስጥ።
ባር ማሽላ: የባሕር ማሽላ፡ በቆሎ ወይም ማር ማሽላ።
ባር ሜጣ: ከባሕር የመጣ የፀሐይ ቆብ።
ባር ቍልፍ: ከባሕር የመጣ ቍልፍ።
ባር ቅል (ሎች): የባሕር ቅል፡ ዱባ። ተመልከት: “ዐይንን”
ባር ባር አለው (አባሕረሮ): ፍርሀት ፍርሀት አለው፡ አባነነው (አበረገገው)፡ ወይም “ዘለህ ወደ ባሕር ግባ” አለው። አባባል: “ሆዴን ባር ባር አለው” እንዲል።
ባርሜጣ: የፀሐይ ቆብ። (ለተጨማሪ ማብራሪያ “ባር” የሚለውን ቃል ይመልከቱ)።
ባርሰነት (ቶች): የባሕር ሽነት (የአደስ እንጨት)። በግእዝ: ምርስኔ ይባላል።
ባርቅ: የሰው ስም፡ ከእስራኤል መሳፍንት አንዱ (መሳፍንት ፬፥፮-፳፪፣ ፭፥፩፣ ፲፪፣ ፲፭)።
ባርኮ ሥሉስ ቅዱስ: “ሥላሴ ባርከው፣ ቀድሰው፣ አብዛው”፡ “ዐይጥን ከማገር፣ ሰላቢን ከአገር አጥፋ። ” ማስታወሻ: ለምርትና ለቡሆ ይነገራል።
ባሮክ: የሰው ስም፡ በምስጢር ከቡሩክ ጋር አንድ ነው።
ባሻ (ሆድ): ሆዱ ያዘነ፣ የተከዘ፡ ነገር የማይችል፡ በጥቂት ምክንያት የሚቀየም፡ ቍጡ (ብስጩ፣ ኵርፍተኛ፣ አልቃሽ)። ምሳሌ: “እከሌ ሆደ ባሻ ነው” እንዲሉ።
ባሻ (በዘአፍተወ): ባስፈለገ ገንዘብ።
ባሻ (ፓሻ): የቱርክ ጦር አዛዥ፣ ዋና ዳኛ (አለቃ)፡ እንደ ራስ ያለ። ምሳሌ: “ቱርክ ባሻ ታምሬ” እንዲሉ። ማስታወሻ: በአገራችን ግን ወታደር ለበላዩ የሚሰጠው የክብረት ስም ነው። ባላም ባራስነትን ከመንግሥት ወይም ከሻለቃ እስኪያገኝ ድረስ በዚህ ስም ይጠራል። ተመልከት: “ሻ ሻየ” ብለህ “ባሻን”፡ “ቱርክን” ተመልከት።
ባሽ (በኣሲ): የባሰ፣ የከፋ (ክፉ፣ መጥፎ)።
ባሽ ባዙቅ: ቀድሞ የቱርክ የነበረ፣ ኋላም ለጣሊያን ያደረ ወታደር። “የፓሻ ባዙቅ” ማለት ነው። ተመልከት: “ባዙቅን”።
ባቄላ (ሎች): የታወቀ የአበባ እህል፡ በ፪ ቀን የሚያጐመጕም፣ በ፫ ቀን የሚያጐነቍል፡ አደፍ ድበላ። ምሳሌ: “ባቄላ የራብ ዱላ” እንዲሉ። ተመልከት: "በቀለ"።
ባቄሎ: ባቄላም አገር።
ባበለ (ልመና): ሆነ፣ ተደረገ (ልመናው፣ ቍልምው)።
ባበለ (ግእዝ): ተደባለቀ፣ ተቀየጠ፣ ተቀላቀለ።
ባቡ: የሰው ስም። “ጠላቶች ፈሩ፣ ገነገኑ” ማለት ነው።
ባቡሬ: ከጀርባው ወይም ከሆዱ ነጭ የሆነ ዓሣ።
ባቡር (ሮች): በውሃ ጭስ የሚሄድ መኪና። ፈረንጆች "ባፐር" ይሉታል።
ባቡቴ: ክብ እንክብል ኅብስት፡ ሴቶች በዔሊ አምሳል የሚጋግሩት። ምሳሌ: “አርባ ባቡቴ” እንዲሉ። ማስታወሻ: "አበቡቴን" ተመልከት።
ባቡት (ዶሮ): ራሷንና እግሯን ከድንጋይ ውስጥ የምትበብት (የምታገባ፣ የምትከት)። ድንጋይ ልብሷ፣ ፊቷ እባብ የሚመስል (እባብማ እባቡት)።
ባቢ: የሚባባ፣ ሠጊ፣ ገንጋኝ።
ባቢሌ: የአገር ስም፡ በሐረርጌ አውራጃ ያለ አገር።
ባቢሎን: የከተማ ስም። “ድብልቅልቅ፣ ዝብርቅርቅ፣ ቅይጥ፣ ውጥንቅጥ” ማለት ነው። ማስታወሻ: መጀመሪያውን "ባበለ" ተመልከት።
ባባ (በሕብሐ): ፈራ፣ ሠጋ፣ ባነነ፣ በረገገ፣ ገነገነ። ግጥም: “እንቢ አለኝ እንጂ ሆዴ እየባባ፡ ውልድሽ አንኮበር ኑሮሽ ሐር ዐምባ”።
ባባ (ዛፍ): ፍሬው የሚበላ የወርካና የሾላ ዓይነት ዛፍ። ባሕታውያን ፈልፍለው በውስጡ የሚቆሙበት፡ ቅርንጫፉ እንደ ዘንባባ የሚዘረጋ። ማስታወሻ: የመጀመሪያውና የኋለኛው "ባባ" የሚለዩት በመጥበቅና በመላላት ነው።
ባባ አለ (ቤበየ): ጮኸ፣ ጐተጐተ (እንስትን በግሩ)። ምሳሌ: “ወጠጤው ባባ ይላል”።
ባቤሎ: ነጭ አደንጓሬ፡ ዐረቦች "ፈሱሊያ" የሚሉት። ማስታወሻ: "ደንጐሎን" እይ።
ባብ (ዐረብኛ): በር፣ መግቢያ።
ባብ እልመንደብ: በኦቦክና በዓደን መካከል ያለ የጭንቅ፣ የመከራ በር። "መነደበን" እይ።
ባቦ (ሐረርና ዐረብ፡ ባባ): ወንድ አያት። የማክበር፣ የትሕትና እና የመታዘዝ ቃል ነው። ፍችው: "አባት ሆይ"፣ "አቤቶ"፣ "ጌቶ" እንደ ማለት ነው። አጠቃቀም: ከ "ዕሺታ" እና "ይኹን" በኋላ ይነገራል። ምሳሌ: “ዕሽባቦ፡ ዕሽባቦ አለ፡ ይኹን ባቦ”።
ባቦ (ጥቦ) (በአቦ): የግዝትና የማማጠን ቃል። ምሳሌ: “ባቦ በማርያም” እንዲሉ።
ባቦ: ዕሺ፣ በጎ፣ በጄ፣ ደግ።
ባተ (ብሒት፣ ብሕተ): ገባ፡ ተሾመ (ሠለጠነ)፡ ተጀመረ (ተቈጠረ)፡ የወር (ያመት)።
ባተ መልካም: ባቱ ያማረ (ሞንዳላ)። ምሳሌ: “ባትህን አሳየኝ”፡ “ቶሎ ቶሎ ኺድ”።
ባተለ (ዕብራይስጥ: ብቱላ - ልጃገረድ): ሚስት አልባ ሆነ፡ ብቻውን ሠራ (ለፋ፣ ደከመ)።
ባተሌ (ዎች): ሚስት የሌለችው ወንድ፡ ባል የሌላት ሴት። ሌላ ትርጉም: የባታይ ወገን (ብቸኛ)።
ባተሌ ሆነ: ባተለ (ባታይ ሆነ)።
ባተሌነት: ብቻነት (ብቻ መልፋት)።
ባተሎ/ዘባተሎ (ብጡል ዘበጠለ): ዕላቂ (ውዳቂ) የባተሌ ልብስ።
ባቲ (ኦሮምኛ): የጨረቃ ስም፡ ለጋ ጨረቃ። በየወሩ የምትብት ማለት ነው። ሌላ ትርጉም: በዐውሳ ውስጥ ያለ አገር። ሌላ ትርጉም: አመልካች ወፍ፡ ቡሊ (ቀርቃሬ)።
ባታ (በአታ ለማርያም): ታቦት፡ የታቦትና የጽላት ስም። ወር በገባ በ፫ የሚከበር በዓል።
ባታ (በዊእ፣ ቦአ፣ በአት): እመቤታችን ቤተ መቅደስ የገባችበት የታኅሣሥ ሦስተኛ ቀን። ምሳሌ: “ታኅሣሥ ባታ” እንዲሉ።
ባታላጋኝ): ባታቈራቍሰኝ።
ባታም (በዓታዊ): ባተ ወፍራም (ባተ ደንዳና) ሰው።
ባታይ: የባተለ፣ የሚባትል፡ ባሕታዊ (ብቻውን የሚኖር)፡ ፈት።
ባት (ቶች)/በዓት/ባሕት: በቋንዣና በቅልጥም መካከል፣ በስተኋላ ያለ አካል፡ በእግር ላይ የባተ (ኢሳይያስ ፵፥፯፣ ፲፱)።
ባነነ (ባህነነ፣ ባሕረረ): ደነገጠ፣ ጮኸ (በንቅልፍ ልብ)።
ባኒያን (ኖች) (ሰው): በህንድ አገር ከነበሩት ነጋዴዎች ወገን የሆነ የአንድ ሰው ስም። ማስታወሻ: በግእዝ "ባንያ" ይባላል። ተመልከት: "ማኒን"።
ባኒያን (ዛፍ): በወደቀበት የሚጸድቅና በቶሎ ደን የሚሆን የበለስ ዓይነት ዛፍ።
ባና (ልብስ): ነጭ ወይም ዝጕርጕር (ዝተት) የመንዞች ሥራ፡ ጥቍሩ በርኖስ እንጂ "ባና" አይባልም።
ባና (በግ): በቅላትና በንጣት መካከል ያለ የበግ ጠጕር። ማስታወሻ: "ባና" ከ"ፓና" ጋራ ይሰማማል። በትግርኛም "ባና" ውጋገን ማለት ነው። ተመልከት: "ፋናን"።
ባናኝ (ኞች): የባነነ፣ የሚባንን፡ ድንጉጥ፣ ጯኺ (ብቡ)።
ባንቺ (በአንቺ): ባንቺ።
ባንቺ ይለኩ: የሴት ስም፡ “ሌሎቹ ሴቶች ባንቺ ይመጠኑ” ማለት ነው።
ባንቼ: ከፊለ ስም።
ባንክ (ኮች) (ማእድ): የገንዘብ መቍጠሪያና መደርደሪያ ሞላላ ገበታ (ጠረጴዛ)።
ባንክ (ድርጅት): በወለድ የሚያበድርና ሐዋላ የሚያደርግ፡ የገንዘብ ትርፍ ሥራ የሚሠራ የንግድ ቤት።
ባንክ ኖት: "ኖት" ምልክት (ማስታወሻ) ማለት ነው። በሕግ ተፈቅዶ ለመገበያያ ባንክ የሚያወጣው የገንዘብ ወረቀት፡ ይኸውም በእንግሊዝ ቋንቋ መጠሪያ ስሙ ነው።
ባንዱራ: ማላጋ፣ የባሕር ጐመን፡ እንደ ትማትም የአቡን ወጥ የሚባል።
ባንዲራ: በቁሙ ዐላማ፡ የመንግሥት ምልክት። ማስታወሻ: "ባንዲራ" የጣሊያን ቋንቋ ነው፡ ከዐድዋ ጦርነት ወዲህ ተለምዷል። ተመልከት: "ፊርማን"።
ባንጃ: በወገን አንጃ።
ባንጃው (ባንጃህ): የሰው ስም፡ በፊናው፣ በፊናህ ማለት ነው።
ባንጓ: ገጋ የማር ቀለሕ።
ባዕድ/ባዳ/ባድ: "ባዕድ" የግእዝ ነው።
ባዕድ ቀለም: “አ፣ እን፣ ወ፣ ዋ፣ ው፣ መ፣ ማ፣ ም፣ ተ፣ ት (ታ)፣ ስ፣ ሽ”፡ እነዚህም ለቃል መነሻ እየሆኑ ይነገራሉ።
ባከነ: ባዘነ፣ ዛበረ፣ ተገላመጠ፣ ቃበዘ፡ ተዘራ፣ ተበተነ፣ ጐደለ (ያሳብ፣ የገንዘብ፣ የአይን፣ የምስጢር)።
ባካኝ/ባካና: የባከነ፣ የባዘነ (የተበተነ)፡ ቀበዞ፣ ባዛኝ።
ባኮ: በከፋ ውስጥ ያለ አገር ነው። በከፋ ቋንቋ "ዶሮ" ማለት ነው ይላሉ።
ባዘቀ (ተደባለቀ): ተደባለቀ (ባዜቃ)።
ባዘቀ: ተቀላቀለ፣ ተደባለቀ፡ ተዘባረቀ፣ ተማሰለ፡ እንደ መብረቅና እንደ ባዜቃ አለስፍራው (አላኳያው) ገባ።
ባዘተ (በዝቶ፣ በዘተ): ተፈለቀቀ፣ ተቦጨቀ፣ እጅ ሥራ ገባ፡ ተፍታታ፣ ለሰለሰ፣ ደቀቀ፣ ለተተ (የጥጥ፣ የሰውነት)። ምሳሌ: “ዛሬ በመንገድ ውዬ ሰውነቴ ባዝቷል” (ተገብሮ)።
ባዘተ (ገቢር): ቦጨቀ፣ አደቀቀ።
ባዘተ ደነቀ ብለሽ ባዘቶን፡ ድንቂቱን እይ።
ባዘቶ (ስም): በ፲፰፻፷ ዓ.ም የነበረች ፈንጣጣ።
ባዘቶ (ንቅሳት): የተነቀሰ፣ የለሰለሰ ፋቶ።
ባዘቶ ገላ: አካለ ለስላሳ ሴት።
ባዘነ: ዞረ፣ ተንከራተተ፣ ዛበረ። ምሳሌ: “የባዘነ ጥይት” እንዲሉ።
ባዘዘ/ቧዘዘ (በዚዝ፣ በዘ): ባዘነ፣ ዞረ፡ ባከነ፣ ተንቀዋለለ፡ ፈዘዘ፣ ነኮለለ። ማስታወሻ: "ባዘዘ" እና "አዘዘ" በአማርኛ ይተባበራሉ። ግጥም: “አሽከር የለውም ወይ ጭቃና ምስለኔ፡ ለስመኝ እንግዳ ባዘዝኹለት እኔ”።
ባዙቅ (ቆች): ዝኒ ከማሁ (እንደዚሁ)፡ አለወገኑ፣ አላለቃው ለጠላት ያደረ ከሓዲ ጭፍራ። ማስታወሻ: "ባሰ" ብለህ "ባሽን" እይ።
ባዙቅነት: ድብልቅነት፣ ከሓዲነት።
ባዛ: ጭንጫ ያለበት (የበዛበት) መሬት፡ ግርግራ።
ባዛቂ: የባዘቀ፣ የሚባዝቅ፣ የተደባለቀ።
ባዛች (በዛቲ): የባዘተ፣ የሚባዝት፣ የሚቦጭቅ፡ እጅ ሥራ የሚያገባ።
ባዛኝ (ኞች): የባዘነ፣ የሚባዝን፡ የዞረ፣ የተንከራተተ፡ ዘዋሪ፣ ከርታታ፣ ዛባሪ፡ ዕረፍተ ቢስ ሰው፡ ከመንጋ የተለየ ከብት።
ባዜቃ (ዐረብኛ: ዘይበቅ): በቁሙ፡ ወርቅን ከብርና ከሌሎች ማዕድናት ጋራ የሚያዛምድ ዝቡቅቡቅ ፈሳሽ ማዕድን።
ባዜቃ (ዕብራይስጥ: ባዛቅ): መብረቅ፣ ነጸብራቅ፣ ብልጭልጭታ።
ባዜቃ (ፍሬ): ድርን የሚያጸና፣ የሚያበረታ፣ ከውሃ ጋራ የፈላ ርሾ (ወይም ቀረራ) የንዶድ ፍሬ።
ባዜቃ ነከረ: ድርን ከፍል ርሾ አገባ (አጸና፣ አበረታ)።
ባዜን (አገር): በትግሬ በረሓ ያለ አገር። ማስታወሻ: "ቢዘን" እና "ባዜን" አንድ ዘር ናቸው።
ባዜን: ጌታችን በተወለደ ጊዜ የነበረ የሐበሻ ንጉሥ ስም።
ባዝራ (ሮች) (ዐረብኛ: በዘረ): ተከለ።
ባዝራ ተድንጕላ ወለደ: አስቀድሞ ሴት ልጅ ቀጥሎ ወንድ ልጅ ማለት ነው።
ባዝራ ተድንጕላ: እንስት ከትባት ጋራ፡ ወይም ሴት ከወንድ ጋራ። ማስታወሻ: ይህ ቃል የወንድና የሴትን መንታ ሆኖ መወለድ ያሳያል። ማስታወሻ: "ባዝራና ድንጕላ" ለግመልም ይነገራል።
ባዝራንና ድንጕላን ተመልከት። (ያቦ ፈረስ): ቀጣኒት። (የሰይጣን ፈረስ): ኹለት እግር ያላት መንኰራኵር።
ባይ (በሃሊ): ያለ፣ የሚል፣ የሚናገር፡ ተናጋሪ። ምሳሌ: “አልሁ ባይ”፣ “ይቅር ባይ” እንዲሉ። እበላ ባይ: ለጥቅም ብሎ ባለጸጋን የሚያመሰግን (የሚኰፍስ)። አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል: (አባባል)። ማስታወሻ: "ወደደ ብለኸ" የሚለውንም ተመልከት።
ባይ (ብአይ): እኔ ብመለከት፣ ባስተውል፣ ባገኝ።
ባይ ሣሣኹ (እመ እሬኢ ሠሣዕኩ): የሰው ስም። "ልጅ ባይ ሠሠትኩ" ማለት ነው።
ባይሉል (ሉል ባይ): የሰው ስም (አባ ባይሉል)፡ የሽንት መውጫ ያህል ብልት ያላቸው ሁለት ወንዶች ልጆች የወለደ።
ባይሣሣኹ: (የሰው ስም)።
ባይሤ: (የፊደል ስም)።
ባይሤ: የ"ባይ ሣሣኹ" ከፊል።
ባይተዋር (ሮች) (በሃሊ እምዋዕር): ጊዜና ዘመን ሲለወጥ “አገኛለሁ” የሚል፡ ስደተኛ፣ መጻተኛ። ማስታወሻ: "ዋርን" እይ፡ "አየን" ተመልከት።
ባይተዋር: መጻተኛ።
ባይተዋርነት: ስደተኛነት፣ መጻተኛነት፣ እንግድነት፣ ባዳነት፣ ተንከራታችነት።
ባይከዳኝ: የሰው ስም፡ እግዜር ሰጥቶ ባይነሣኝ ማለት ነው።
ባዮች: ያሉ፣ የሚሉ፡ ተናጋሮች (ሉቃስ ፰፥፳)።
ባደ (በዐደ): ተለየ፣ ተነበለ፣ ተወገደ፣ ራቀ፣ ተገለለ።
ባደግ (ቢያድግልኝ): የሰው ስም።
ባድ/ባዳ (ባዕድ): ባጋም፣ በቀጋ የማይወለድ፡ ሌላ፣ ልዩ፡ እንግዳ፣ መጤ፣ የውጭ አገር ሰው፡ ከብት። ምሳሌ: “በባዳ ቢቈጡ፡ በጨለማ ቢያፈጡ”። ምሳሌ: “ተለይ ባዳ” እንዲል እረኛ። ምሳሌ: “ላገሩ እንግዳ፡ ለሰው ባዳ”። ማስታወሻ: "ባድማን" ተመልከት፡ የዚህ ዘር ነው።
ባድማ (ብዑዳዊ፣ በዳዊ): ባዶማ፡ የባዶ፣ የወና፣ የጠፍ ወገን፡ ወናም፣ ጠፋም፡ ከቤት፣ ከንብረት፣ ከሰውና ከመኖሪያነት የተለየ ስፍራ። ማስታወሻ: "ባድን" እይ፡ ዘሩ እርሱ ነው። በግእዝ "መዝበር" ይባላል (መዝሙር ፻፪፥፮)።
ባድማ ሆነ (ኮነ በድወ): ባዶ (ጠፍ) ሆነ፡ ጠፋ፣ ተፈታ፣ ፈረሰ፣ ተደመሰሰ።
ባዶ (ብዑድ፣ በድው): ወና፡ የተፈታ፣ የፈረሰ፣ የጠፋ፣ የተደመሰሰ (አስቀድሞ ቤት ንብረት የነበረበት ቦታ)፡ ባድማ፡ አንዳች አልባ። ምሳሌ: “ሆድ ባዶ ይጠላል” እንዲሉ።
ባዶ (ዕቃ): ውሃ የሌለበት ማድጋ (ኤርምያስ ፲፬፥፫)።
ባዶ ሆነ (ብዑደ፣ በድወ ኮነ): ጠፋ፣ ተደመሰሰ፣ ፈረሰ፡ ተለየ፣ ተራቆተ (ቦታው፣ ዕቃው)።
ባዶ አደረገ (ገብረ በድወ): አጠፋ፣ ደመሰሰ፣ አፈረሰ፡ ለየ፣ አራቆተ።
ባዶ እጅ: በትር ያልያዘ ሰው።
ባዶ ወገሜት: ቅቤ የወጣለት ወተት። ግጥም: “ድልህና ቅቤ ሞልቶ በቤትህ፡ ምን ቸገረህና በባዶ በላህ”። ማስታወሻ: "ባዶ" በጋልኛ "አሬራ" ይባላል።
ባዶች (ባዕዳን): ዝምድና የሌላቸው እንግዶች።
ባጀ (ሐገየ): ደረቀ፡ በጋ ሆነ።
ባጀ (ተቀመጠ): በጋውን በአንድ ስፍራ ወይም በአንድ አገር ተቀመጠ፣ ቆየ (ኢሳይያስ ፲፰፥፯)። ማስታወሻ: "በጋ ባጀ" ተብሎ አንቀጽ ሆኗል። ደግሞም ትግሬ "በሀገ" ብሎ "ተመኘ" ይላልና፣ "ባጀ" የ"በሀገ" ዘር ሊሆን ይችላል።
ባጀባ: የሴት ስም።
ባጂ: የባጀ፣ የሚባጅ።
ባጕም (ትግርኛ፡ ዝምተኛ): የዝንጀሮ ጩኸት፡ ልጆች እንደ ዝንጀሮ እያኰበኰቡ የሚጫወቱት ጨዋታ። ምሳሌ: “ባጕም ባጕም አለ”። ግጥም: “የገደል ዝንጀሮ ይላል ባጕም ባጕም፡ አይዘነጉም ለባዳና ለጉም”።
ባጕስ: የሚወግስ፣ የሚጨብጥ፣ የሚቈርጥ (ጆሮ ቈራጭ)። ምሳሌ: ልጆች “የባጕስ፡ ጭብጦ አጐርሥ” እንዲሉ። ማስታወሻ: "ማጉስን" እይ፡ "መቀሰን" ተመልከት።
ባጐሰ (መቈሰ): ወገሰ፡ ያዘ፣ ጨበጠ፡ ጠመዘዘ፣ ጐተተ፣ ቈረጠ (የጆሮ)።
ባጠለ (በጢል፣ በጠለ): ጠፋ፣ ተፈታ፣ ፈረሰ፣ ተሻረ፣ ብላሽ ቀረ (የጠባይ፣ የግብር)።
ባጠጠ (ዕብራይስጥ: ባዐጥ): ወደ ላይ ዘለለ፡ መር፣ እንጣጥ አለ፡ ተቀማጠለ (የልጅ)።
ባጣጭ: የባጠጠ፣ የሚባጥጥ፡ ዘላይ።
ባጥ (ባጥይ): ከመሬት ከፍ ብሎ በግንብና በግድግዳ ላይ ያለ ጣራ (ምሳሌ ፲፱፥፲፫)። ማስታወሻ: "ቀባጠረን" እይ።
ባጥ አለ: ባጠጠ፡ እንጣጥ አለ፡ ፈነጨ።
ባጥ: ጣራ (ባጠጠ)።
ባጥይ: ጣራ (ባጠጠ)።
ባጨ (ቤጸ፣ ተበይጸ): ተለየ፣ ተከፈለ፡ ተበተነ።
ባፈና: የሴት ስም፡ ባጀባ ማለት ነው (ከእርሱ ጋር የሆነች)።
ባፍንጫዬ ይውጣ: ጭራሽ አልፈልገውም።
ቤል (ሽጉጥ): የፈረንሳይ ሽጉጥ፡ ፮ ተጐራሽ።
ቤል (ጣዖት): የጣዖት ስም፡ የባቢሎን ጣዖት።
ቤሰ (ነፈገ): ነፈገ (ባሰ፣ ቢስ)።
ቤሰ: ቢስ ሆነ (ነፈገ፣ ሠሠተ)።
ቤሳ (ዐረብኛ): በብር የሚሸረፍ (የሚመነዘር) የመዳብና የነሐስ ታናሽ ገንዘብ። ማስታወሻ: “ቤስቴን” ቢል “ሁለት ቤሳ” ማለት ነው። አንድ ቤሳ ሁለት ሳንቲም ተኩል ይሆናል። የወጣውም በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመን ነው።
ቤሳኝ: የሴሰነ፣ የሚሴስን፣ የሚያመነዝር፣ ሸርሙጣ።
ቤተ ልሔም (ቤተ ኅብስት): የሰው ስም። “የዳቦ (የእንጀራ) ቤት” ማለት ነው (፩ኛ ዜና መዋዕል ፪፥፶፩፣ ፶፬)። ሌላ ትርጉም: በይሁዳ ዕጣ በኤፍራታ ውስጥ ያለች ቀበሌ፡ ጌታችን የተወለደባት (ሚክያስ ፭፥፪፣ ማቴዎስ ፪፥፭)። ሌላ ትርጉም: ከካህን በቀር ምእመን (ጨዋ) የማይገባባት፡ ቍርባን የሚሠራባት የምስጢር ቤት። “ቤት” እመቤታችን፣ “ልሔም” ጌታችን። ሌላ ትርጉም: በበጌምድር ውስጥ በዙራምባ አቅራቢያ ያለ ቀበሌ፡ ቁም ዜማ የሚመሰከርበት።
ቤተ ልሔሞች: የቤተ ልሔም ተወላጆች፡ የምስጢር ቤቶች።
ቤተ መምህራን: የአስተማሪዎች ቤት። ፈረንጆች “አካዴሚያ” ይሉታል።
ቤተ መቅደስ: ቤተ እግዚአብሔር (መቅደሰ ኦሪት፣ መቅደሰ ወንጌል፣ ቤተ ክርስቲያን)፡ ከእስራኤልና ከክርስቲያን በቀር ሌላ የማይገባበት።
ቤተ መንግሥት: ነገሥታትና መኳንንት የሚገቡበት፡ ሥራ የሚሠሩበት የመንግሥት ቤት፡ የንጉሥ ግቢ።
ቤተ ማርያም: እመቤታችን የነበረችበት የቅዱስ ዮሐንስ ቤት (ዮሐንስ ፲፱፥፳፯)።
ቤተ ሠሪ ኋላ ይመጣል: ያለቀውን ሕንጻ ይነቅፋል።
ቤተ ሠሪ: ቤት የሚሠራ። ተረት: “ዘማች ለባልንጀራው ‘እኔ የገደልኩት ደም አልወጣውም’ ቢለው፡ ‘ቤተ ሠሪውን ገድለኸው ይሆናል’ አለው” ይላሉ።
ቤተ ሰብ (ሰብአ ቤት): የቤት ሰው፡ ለባለቤት የሚታዘዝና የሚያገለግል፡ ታዛዥ (አገልጋይ)፡ ተቀላቢ (ግብረ በላ)፡ ቤተኛ (የቤት ውልድ)። ምሳሌ: “ሐዋርያት፣ አርድእት፣ ምእመናን፣ ፻፳ው ቤተ ሰብ” እንዲሉ።
ቤተ ሰቦች: የቤት ሰዎች።
ቤተ ሳልገኝ: የሥጋ ብልት፡ አራት ጐድንና የወርች ሥጋ።
ቤተ ቀሊል: የቀሊል ወገን ወይም ነገድ።
ቤተ ቈማጣ: የቈማጣ ትውልድ። ተረት: “ከቤተ ቀሊል ቤተ ቈማጣ ይሻላል”።
ቤተ በረከት: ጥቂቱ ብዙ የሚሆንበት (፩ኛ ነገሥት ፲፯፥፲፱-፳፯፣ ፲፭፣ ፲፮)።
ቤተ ተውኔት: የጨዋታ (የሣቅ፣ የሥላቅ) ቤት። ፈረንጆች “ቴአትሮን” ይሉታል።
ቤተ ንጉሥ: “ሞላልኛ ሰቀልኛ” ያይዶለ ክብ ቤት (አዳራሽ) (ዳንኤል ፮፥፲)። በዚህ ዓይነት የተሰፋ ድንኳን፡ “የንጉሥ ቤት” ማለት ነው።
ቤተ ንጽሕ: መታጠቢያ ቤት።
ቤተ አይሁድ: የአይሁድ ትውልድ።
ቤተ እስራኤል: የእስራኤል ነገድና ዘር።
ቤተ እግዚአብሔር: የእግዚአብሔር ቤት፡ ቤተ መቅደስ።
ቤተ ክህነት (ወገን): የካህናት ወገን።
ቤተ ክህነት: ዲያቆን፣ ቄስ፣ መነኩሴ፣ ደብተራ፣ ጳጳስ፡ የክህነት ሥራ የሚሠሩበት (የሚያገለግሉበት) ቤተ መቅደስ (ቤተ ክርስቲያን)።
ቤተ ክርስቲያን (ቤተ ክርስቲያን): በቁሙ የክርስቶስ ወገኖች ለጸሎትና ለምስጋና፣ ለስግደት፣ ለቍርባን የሚሰበሰቡባት፡ ታቦትና መስቀል፣ ሥዕል ያለባት የክርስቲያን ቤት፡ ባለ ፫ ክፍል፡ እነዚሁም ቅኔ ማሕሌት፣ ቅድስት እና መቅደስ ናቸው። ምእመናኑም “ቤተ ክርስቲያን” ይባላሉ።
ቤተ ክርስቲያን (አብያተ ክርስቲያናት): ሁለትና ከሁለት በላይ ያሉ ብዙዎች።
ቤተ፡ ክርስቲያን፡ መሳሚያ)፡ የክት ልብስ።
ቤተ ክርስቲያን ሳሚ: ቤተ ክርስቲያን የሚስም (የሚሳለም)፡ ጠበለተኛ፡ “እጠድቅ ባይ”።
ቤተ ወጣ (ወፃኤ ቤት): ከአንድ ቤት የወጣ ብዙ ሰው፡ ወንዱም ሴቱም፣ ልጁም ዐዋቂውም።
ቤተ ዘመድ: የባልና የሚስት ወገን፡ ወይም አበ (ልጅ) ቤት።
ቤተ ዝሙት: የምንዝር (የሽርሙጥና) ቤት።
ቤተ ደራስያን: የደራሲዎች ቤት፡ ቤተ መምህራን።
ቤተ ደንብ: መሥሪያ ቤት፡ ደንብ እየተጻፈ የሚቀመጥበት።
ቤተ ጥበብ: የዕውቀት (የብልኃት፣ የፍልስፍና) ቤት።
ቤተ ጸሎት: የጸሎት ቤት (ምኩራብ፣ መስጊድ)።
ቤተ ፈት: አግንቶ ያጣ (ከብሮ የተዋረደ)። ምሳሌ: “አዳምን የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም” እንዲሉ መተርጒማን።
ቤተኛ (ኞች)/አብያታዊ: የቤት፡ ቤታም (በቤት የሚኖር) ዘመድ (አሽከር፣ ሎሌ)፡ የቤት ሰው።
ቤቱ በቃ: አልጠበበም።
ቤቱ: ያ ቤት፡ የእርሱ ቤት።
ቤቱን ሰው አያውቀውም: አንድ ቀንም ሰውን አልጋበዘም (አላበላም፣ አላጠጣም)።
ቤቱን አሸነፈ: ራሱን ቻለ (ችግርን አራቀ)።
ቤቴ ቤቴ አለ: ለትዳር (ለንብረት) ዐሰበ (ተጋ፣ ተትኰረኰረ)።
ቤቴል (ቤተ ኤል): ቤተ አምላክ (የአምላክ ቤት) (ዘፍጥረት ፳፰፥፲፱፣ ፴፭፥፲፭፣ ፲፯)።
ቤት (ሥጋ): ሥጋ (የነፍስ ማደሪያ) (ዘፍጥረት ፪፥፯፣ ዮሐንስ ፪፥፳፩)።
ቤት (በዪት፣ ቤተ፣ ቤት): በቁሙ ማደሪያ (መኖሪያ)፡ በድንጋይና በጡብ፣ በጠርብ፣ በጨፈቃ፣ በኖራ፣ በጭቃ፣ በስሚንቶ፣ በጭድ፣ በሰንበሌጥ፣ በቈርቆሮ፣ በሳንቃ የተሠራ ግንብና ግድግዳ (ጣራ)። ውስጠ ክፍት ቦታ: ዕቃ (ዋሻ፣ ፍርኩታ፣ ጐሬ፣ ጕድጓድ)፡ ለሰው ጥቅም የሚሆን ነገር ሁሉ ተሠርቶ የሚገኝበትና የሚቀመጥበት። ዘርፍ እየቀደመው ሲነገር: እንግዳ ቤት፣ እንጀራ ቤት፣ አስር ቤት፣ ባሩድ ቤት፣ ግምጃ ቤት፣ ወህኒ ቤት፣ ወጥ ቤት፣ ወፍጮ ቤት፣ ጠጅ ቤት፣ ጠላ ቤት፣ ላይ ቤት፣ ማድ ቤት፣ ምድር ቤት፣ ማለፊያ ቤት፣ መቃብር ቤት፣ መሸታ ቤት፣ ነጭ ቤት፣ ሥጋ ቤት፣ ሥራ ቤት፣ ዕቃ ቤት፣ ራስጌ ቤት፣ ሰማይ ቤት፣ ተማሪ ቤት፣ ታች ቤት። ዘርፍ ሆኖ ሲነገር: “እመቤት” ይላል። የሁሉንም ትርጉም በየስፍራው ይመልከቱ።
ቤት (ንብረት): ንብረት (ትዳር፣ ኑሮ)። አልቃሽ: “ትልቁም ትንሹም እምዬ ይልሻል፡ አንቺውስ ምንኛ ቤት አጥፊ ኑረሻል?”
ቤት (ወገን): ወገን (ነገድ)፡ የአገር ክፍል ነው። ምሳሌ: “ሰባት ቤት አገው”፣ “ሰባት ቤት ወሎ”፣ “ኦሮሞ ቤት አራት ቤት ጭፍራ” እንዲሉ። ተመልከት: “ጐዦን” እና “ቦታን”።
ቤት (ዘመድ): ዘመድ (ትውልድ)። ምሳሌ: “፩ ቤት፣ ፪ ቤት፣ ፫ ቤት፣ ፬ ቤት” እንዲሉ።
ቤት (የአኃዝ): የተራ ረድፍ፡ “የ፩፣ የ፲፣ የ፻፣ የሺ ቤት” እንዲሉ።
ቤት (የዜማ): የዜማ ዓይነት ወይም ስልት።
ቤት (የግስ): የግስ አለቃ።
ቤት (ግጥም): የዘፈን፣ የቅኔ፣ የመልክ፣ የሰላምታ፣ የነግሥ፣ የዐርኬ ግጥም ወይም ስንኝ። ሌላ ትርጉም: ፲፪ የገበታ ጕድጓድ። ሌላ ትርጉም (የፊደል ስም): በ (አለፈን ይመልከቱ)። ግጥም: “አሌፍ ብሂል ብዬ እታው ድረስ ሳውቀው፡ ቤት እመኻል ገብቶ ልቤን አስጨነቀው” (መዝሙር ፻፲፱፥፩፣ ፱)።
ቤት ለቤት: ከ… የቀረው ነው፡ ከቤት ወደ ቤት።
ቤት ለንቦሳ: አዲስ ቤት ከተሠራ በኋላ እንዲህ ይባላል። ተመልከት: “እንቦሳን”።
ቤት ለንግዳ: እንግዳን “ግባ” ለማለት የሚነገር።
ቤት መለስ: ባልትና (ያ) ዘዴ፡ የቤት አስተዳደር። ምሳሌ: “እከሊት ቤት መለስ አታውቅም” እንዲሉ።
ቤት መምቻ: የመወድስና የሌላውም ቅኔ መዠመሪያ ቤት (ስንኝ)።
ቤት መታ: የማንኛውንም ቅኔ ስንኝ ዠመረ።
ቤት ማያ: የግብዣ ስም። ሙሽሪት ከሙሽራው ጋራ የአባትና የእናቷን ቤት የምታይበት፣ ከዘመድ የምትቀላቀልበት የሰርግ ሳምንት ድግስ። ተመልከት: “መለሰ” ብለህ “መልስን”።
ቤት ሠራ): ዐነጠ፣ ገነባ፣ ማገረ፣ ከደነ።
ቤት አሳየ: ምላሽ ጠራ።
ቤት አቃጣይ: ሽፍታ (ወንበዴ)።
ቤት አባት (አበ ቤት): አዛዥ (መጋቢ)፡ ወንድ ወይም ሴት።
ቤት አባቶች: አዛዦች (መጋቢዎች)።
ቤት አንሣ: የጭፍራ ስም፡ የድሮ ዘመን።
ቤት አዛዥ: የቤት አዛዥ (አሳዳሪ)።
ቤት አይጸድ: የቀድሞ ጭፍራ ስም።
ቤት አፈረሰ: በቁሙ ናደ። ሌላ ትርጉም: ስንኝን (ግጥምን) ለወጠ።
ቤት ዓይጥ: የቀድሞ ጭፍራ ስም።
ቤት ከቤቱ ገባ: የሚስት ወገን ለባል ወገን ተዳረ።
ቤት ዠመረ: ቈረቈረ፣ መሠረተ።
ቤት የመለሰው: በቤት ውስጥ ያለ ማንኛውም ዕቃ።
ቤት የእግዚአብሔር ነው: እንግዳ ሊያድርበት ይገባል።
ቤት ያፈራው: መብል (መጠጥ)።
ቤት ጠባቂ: የቤት ዘበኛ።
ቤቶች (አብያት): ሁለትና ከሁለት በላይ ያሉ ብዙ ቤቶች። ሌላ ትርጉም: ሰዎች። ምሳሌ: “ቤቶች ብቅ በሉ” እንዲሉ። ማስታወሻ: “የዚህ ቤቶች” ቢል ግን “የዚህ ቤት ሰዎች” ማለት ነው። “ማንን” ይመልከቱ።
ቤቷ: ያች ቤት፡ የእርሷ ቤት።
ቤንዚን (ል): ከድንጋይ ከሰል ከሚገኝ ቅጥራን የሚወጣ እንፋሎት፡ ወይም የሚበን ዘይት፡ ፈጥኖ ነዳጅ በመሆኑ ለልዩ ልዩ (ይልቁንም በርቀት ለተሠሩ) ሞተሮች ማስኬጃ (ማገዶ) ይሆናል።
ቤዛ (ስም): ከምንዝ ባላባቶች አንዱ የሆነ የሰው ስም። ምሳሌ: “የቤዛ ዘር” እንዲሉ።
ቤዛ (ቤዝዎ፣ ቤዘወ): በቁሙ፡ ዋጋ፣ ካሳ፣ ለውጥ፣ ምትክ፡ ዋቢ፣ ዐላፊ፣ ዋስ፣ መድን፣ ተያዥ። የእጅ ቤዛ: የቈዳ እጅጌ (በአጨዳ ጊዜ እጅ የሚያጠልቀው)። የጣይ ቤዛ: ጥላ። የጣት ቤዛ: በስፌት ጊዜ መካከለኛ ጣት የሚገባበት የብረት ቆብ። ማስታወሻ: ፈረንጆች "ደይ" ይሉታል።
ቤዛነት: ቤዛ መሆን፡ ለውጥነት፣ ምትክነት።
ቤዠ (ቤዘወ): አዳነ፣ ታደገ፡ ገንዘቡን ወይም ራሱን ለውጥ ሰጥቶ ከጭንቅ (ከባርነት) አወጣ፡ ከባለዳ እጅ ገዛ፣ ዋጀ።
ቤዶ (ባዶስ): እንደ ጕርዝኝ ያለ አራት ፈጅ ቍና፡ የዋድሎች መስፈሪያ።
ቤጣ: የፊደል ስም፡ “በ” ቤት።
ብ: “አንተ ብትኖር ወንድሜ ባልሞተም ነበር”። “ብኖር ዓመት፡ ብበላ ጋት”። በቅርቦች ወንዶችና ሴቶችም እንደዚሁ ይገባል።
ብ: ነገድ፣ ወገን፡ ሕብራቸው (ቀለማቸው) "ብ" የሆነ (ሺንና ጃፓን)።
ብሓ: ነጭ ድንጋይ። ምሳሌ: “ብሓ ድንጋይ” እንዲሉ። ማስታወሻ: "ብክካን" ተመልከት።
ብሄሞት : የየብስ ዓሣ ነባሪ፡ የምድር አራዊትና እንስሳት ንጉሥ፡ ከባሕር ተፈጥሮ በየብስ የሚኖር፡ ምድርን በስተ የብስ የከበበ የሌዋታን ጣምራ (አቻ፣ ወደር) (ሔኖክ ፷፥፰)።
ብሄሞት (ብሂም፣ ብህመ): ጕማሬ፡ የባሕር እንስሳ፣ የወንዝ አውሬ፡ ሌሊት ከውሃ እየወጣ ሣር የሚበላ (ኢዮብ ፵፥፲፭)። ማስታወሻ: "ጅንን" እይ።
ብሔረ ሕያዋን: ሔኖክና ኤልያስ (እነሱን የመሰሉ ሰዎች) የሚቀመጡበት ዓለም።
ብሔረ ብፁዓን: የበቁ ሰዎች (ቅዱሳን፣ ባሕታውያን) የሚኖሩበት ስፍራ፡ ጌታችን በ፲፪ ዓመቱ ገብቶ ያስተማረበት። ማስታወሻ: "ትቤትን" ተመልከት።
ብሔረ ኦሪት: አምስቱ ክፍል ኦሪት።
ብሔር: አገር፡ ዓለም (ግእዝ)።
ብሆር (ብሖር): የዱር ፍየል።
ብሖር/ቡኸር (ሮች): ሲጮኽ "ቡሕ" የሚል፡ የዋላ፣ የድኵላ ዐይነት፡ የበረሓ የዱር ፍየል (ኢዮብ ፴፱፥፩)። ማስታወሻ: ተባቱም እንስቱም "ብሖር" ይባላል።
ብሉል (ሎቲ): ሎቲ፡ የሎቲ ዓይነት።
ብሉል (ርግብ): የርግብ ዓይነት፡ የምትበር ዋኖስ። ማስታወሻ: ጕራጌ ግን ርግብን "ቡላል" ይላል።
ብሉይ (በልየ): አሮጌ፣ ያረጀ፣ ያፈጀ፡ ኦሪት፣ ነቢያት።
ብሉይ ተሐዲስ: ኦሪት ከወንጌል ጋራ።
ብሉይ ኪዳን: ኦሪት፡ ነቢያት።
ብላ (ብላዕ): ጕረስ፣ ተመገብ። አባባል: “ሳትወልድ ብላ” እንዲሉ።
ብላ (ተናግራ): ባለ።
ብላ ተባላ (ብላዕ ተባላዕ): አንዱን አንዱ የሚቀማበትና የሚገድልበት ክፉ ጊዜ።
ብላሽ/ብልሹ: የተበላሸ፡ በክት (ሙቶ ያደረ)፡ ከንቱ (የማይረባ) ነገር።
ብላሽነት: ብላሽ መሆን።
ብላታ፡ አሽኔ፡ ኪዳነ፡ ማርያም።
ብላታ: ብልኅ፣ ሥልጡን (ስብቅል) ሰው፡ የነገር ብልት ዐዋቂ። ብላታ (ማዕርግ): የማዕርግ ስም።
ብላቴና ልጅ: "በለተ"።
ብላቴና: ልጅ፣ ጕብል፣ ወጣት፣ ሦታ፣ አሽከር፡ ክፉና መልካምን የለየ። ብላቴና (ሴት): ሴት ልጅ፡ ልጃገረድ።
ብላቴናው: አሽከሩ፣ ልጁ፣ ወጣቱ፣ ለጋው (ዘፍጥረት ፳፩፥፲፪፣፲፬፣፲፭)። ማስታወሻ: የሴቷን "ብላቴናዋ" ይሏል።
ብላቴናዪቱ: አሽከሪቱ፣ ወጣቷ፣ ለጋዪቱ (ልጃገረዲቱ) (ዘፍጥረት ፳፬፥፲፮፣፶፭፣፶፯)።
ብላቴን ጌታ (ኖች): የብላቴኖች (የጥቃቅኖች) ሹም፡ አዛዥ፣ መጋቢ፣ አሠልጣኝ (ምክር ዐዋቂ)። ተመልከት: "አውፋሪን"፣ "ወፈረ"፣ "ዋዛን"።
ብላቴንነት: ልጅነት፣ ወጣትነት፣ አሽከርነት (ዘሌዋውያን ፳፪፥፲፫፣ ፪ኛ ጢሞቴዎስ ፪፥፳፪)።
ብላቴኖች: ልጆች፣ የውስጥ አሽከሮች (ጥቃቅኖች) (ዘፍጥረት ፳፪፥፩፣፲፱)። ተመልከት: "ጪጪን"። ማስታወሻ: ለታላላቆችም ይነገራል (፪ኛ ሳሙኤል ፪፥፲፯)።
ብላት: ዕውቀት፡ "ብልኅ"።
ብላቶ (ብላዕ): የአውሬ ትራፊ ሥጋ፡ ዕኝክ (ግትን)፡ የገዳ ምጣጭ።
ብላጊ (ጸደይ): የበለገ፡ የበልግ ጊዜና ወር።
ብላጥ: ልባጥ። ተመልከት: "ለበጠን"።
ብሌን (ኖች): በሐማሴን ክፍል፣ በከረን አጠገብ ያለ የአገርና የነገድ ስም።
ብሌን (ዕፀ ኵሕል): የዐይን ማሚቶ (ጥቍሪቱ፣ ብረቲቱ) (መዝሙር ፲፯፥፰፣ ዘካርያስ ፪፥፰)።
ብል (ትል): የሸማ፣ የልብስ፣ የቆዳ ትል። አባባል: “ብል በላው” (በሳው፣ በጠረቀው)።
ብል (ጮች): ከወሸከራና ከወዳላት የሚበልጥ፡ በጀርባው ሲንጋለል በስተሆዱ ብልጭ የሚል ዓሣ።
ብል: “እመ እብል” (ብናገር)። ምሳሌ: “ፈጣሪ ካላለ እኔ ብል አይሆንም። ” ማስታወሻ: "ባለን" እይ።
ብልኅ (ኆች): በቁሙ ዐዋቂ፣ ጠቢብ፣ ጥበበኛ፣ አስተዋይ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋ። ማስታወሻ: በግእዝ ግን "ስለት"፣ "ሹለት" ማለት ነው።
ብልኅተኛ (ኞች): ብልኅ፣ የእጅ ጥበብ (የናላ ዕውቀትና ማስተዋል) ያለው ሰው፡ ባለአእምሮ፣ ፈላስፋ፣ ሐኪም፣ ወጌሻ፡ ሞፈር (ቀንበር፣ ጕርዳ) በሺ፡ ዕርፍ ዐራቂ፡ ድግር ጠራቢ፡ ወይፈን ወጠጤ (ወቃጭ)፡ መዝጊያና መስኮት ገጣሚ፡ ጣራ አዋቃሪ (ከዳኝ)፡ ሱሪ፣ በርኖስ (ልብስ፣ ድንኳን፣ ጥላ) ሰፊ፡ የዘርን ጊዜ ዐዋቂ፡ ወለምታና ውልቃት (ስብራት) ጠጋኝ፡ ገራዥ (እንጥል ቈራጭ)፡ ዐይን እብራ (ዳንኤል ፩፥፬፣ ማቴዎስ ፳፭፥፪፣፰፣፱)።
ብልኅተኛ ሆነ (በልኅ፣ ጠበ): ፈለሰፈ፡ ብልኅትን (ጥበብን) ፈጠረ (አገኘ፣ አወጣ)። ምሳሌ: “ባየር ሰፈፈ (መጠቀ)፡ በውቅያኖስ ውስጥ ኼደ (ጠለቀ)። ”
ብልኅት (ምክንያት): ምክንያት፣ ሰበብ። ምሳሌ: “እከሌ ገንዘቤን አለብልኅት ወሰደብኝ። ”
ብልኅት ዐለቀበት: መውጫ ቀዳዳ ዐጣ፡ ተያዘ፣ ተጨበጠ፡ ከጠላቱ በታች ሆነ (እንደ ሶምሶን፣ እንደ ናፖሊዮን)።
ብልኅት: ብላት፡ ፈሊጥ፣ ዕውቀት፣ ጥበብ፣ ዘዴ፣ ማስተዋል። ማስታወሻ: በግእዝ ግን "መስላት"፣ "መሾል"፣ "መፍጠን" ይባላል። ተረት: “የእጅ ብልኅት ባርነት፡ የአፍ ብልኅት ጌትነት። ” ተመልከት: "ሠባን"።
ብልኅነት: ጥበበኛነት፣ ዐዋቂነት፣ ሐኪምነት፣ ወጌሻነት።
ብልስ: (ዝኒ ከማሁ)፡ የተበለሰሰ፡ የውርዴ ዐይን።
ብልስስ አለ: ተበለሰሰ፡ ተበላሸ።
ብልሽት አለ: ጥፍት (ብክት) አለ።
ብልሽት: ጥፋት፡ መሰናክል።
ብልቃጥ (ጦች): በቁሙ ታናሽ ጠርሙስ (የሚከፈት፣ የሚዘጋ)፡ የዘይት፣ የሽቱ (የመድኃኒት፣ የመርዝ) መቀመጫ (መኖሪያ) (፩ኛ ሳሙኤል ፲፥፩)። ማስታወሻ: "ብልቃጥ" ዐረብኛ ነው።
ብልቅጥ: (ዝኒ ከማሁ)፡ የተበለቀጠ።
ብልብላ (ኦሮ): በሕፃን (በጥጃ፣ በበቅሎ፣ በፈረስ) አንገት የምትንጠለጠል ታናሽ ቃጭል (ዘካርያስ ፲፬፥፳)።
ብልቱግ: በትግራይ ወረዳ በብሌን የሚበቅል የማሽላ ዓይነት እህል፡ ዐረቦች "ድሑን" ይሉታል።
ብልቲት ባልጩት: "በለተ"።
ብልቲት: ጎላ የሚበጣ፣ ራስ የሚላጭ ብልጩት።
ብልት (ኀፍረት): የወንድና የሴት ኀፍረት (ዘጸአት ፳፥፳፮)።
ብልት (መብላት): (ብልዐት)፡ መብላት። አገላለጽ: “ብልት አደረገ” (ፈጥኖ በላ)።
ብልት (ሰዋሰው): በቁሙ "በለተ"።
ብልት (ቶች) (ብሉት): የተበለተ፡ የአካል (የሥጋ) ክፍል፡ የተለየ (ልዩ፣ ብቸኛ) (ዘሌዋውያን ፩፥፲፯፣ ሮሜ ፲፪፥፬፣ ፭)።
ብልት (ዐቅድ): ዐቅድ፣ ስልት፣ አዝማሚያ። ምሳሌ: “የነገር ብልት” እንዲሉ።
ብልት አወጣ: ሥጋን አወራረደ (ቈረጠ፣ ለየ፣ ከፈለ)፡ ፲፪ አደረገ።
ብልት አውጪ: ብልት የሚያወጣ፡ ዐራጅ (አወራራጅ)።
ብልዝ (ዞች): የበለዘ፣ የዘጐነ (ዝጕን)። ምሳሌ: “ብልዝ ዐይን”፣ “ብልዝ ጥርስ” እንዲሉ።
ብልዝ አለ: በለዘ፡ አቦልሴ ሆነ፡ በረሰ (በለሰ)።
ብልግ አለ: ፈጽሞ ባለገ፡ ባለጌ (ነውረኛ) ሆነ።
ብልግ: ልዕልና፣ ከፍታ፣ ክብር፣ ላቅያ (መጽሐፈ መክብብ ፯፥፲፪፣ ሕዝቅኤል ፲፭፥፪)።
ብልግ: የባለገ።
ብልግና: ሕገ ወጥ ሥራ፡ ሳይዳሩ ሳይኳሉ ማግባት (መዝሙር ፵፱፥፳)።
ብልጠት: ፈሊጥ፣ ዕውቀት፣ ብልኅት፣ ዘዴ፡ ምስጢሩ "ብልጫን አይለቅም"።
ብልጣብልጥ: የብልጥ ብልጥ፡ ብልጥነቱ የበዛ። ምሳሌ: “የጦጣ ብልጣብልጥ” እንዲሉ።
ብልጥ (ጦች): ብልኅ፣ ዐዋቂ፡ በዕውቀት ከሌላው የበለጠ።
ብልጥ ሰው: "በማንኛውም ሥራና ነገር የሚገባ።"
ብልጥ አለ: ረዘም አለ።
ብልጥ: ራሱን አይጥልም፣ ሰውነቱን አያዋርድም፣ ገንዘብ አያጣም፣ አይቸገርም።
ብልጥነት: ብልኅነት፣ ዐዋቂነት።
ብልጥግና: በቁሙ ክብር፣ ድልብ፡ ብዙ ገንዘብ፡ ዕድለኛ።
ብልጭ (ብሩጽ): የበራ፣ ቍልጭ ያለ። ተመልከት: "ብልጭ"፣ "ወፍን"።
ብልጭ አለ: ተግ ቦግ አለ፡ ፈገገ፡ በራ።
ብልጭ አደረገ: አነደደ፣ አበራ፡ አበለጨ።
ብልጭ ድርግም አለ: ከቅጽበት በራና ጠፋ። ተመልከት: "ያማርኛ ገበታ ዋሪያ" (ገጽ ፴፬)።
ብልጭልጭ አለ: አካቶ፣ ፈጽሞ ፍልቅ ፍልቅ አለ፡ ተብለጨለጨ (፩ኛ ዜና መዋዕል ፳፱፥፪)።
ብልጭልጭ አቦ: ከደብረ ሊባኖስ በስተደቡብ ያለ አገር፡ የአቦ አጥቢያ። “የብልጭልጭ አቦ” ማለት ነው።
ብልጭልጭ: የተብለጨለጨ፣ የሚብለጨለጭ፡ ዐይን የሚያፈዝ (የሚበዘብዝ) የፀሐይ፣ የመብረቅ፣ የእሳት፣ የኤሌክትሪክ (የውሃ፣ የመስታወት) ብርሃን (ናሆም ፪፥፬)።
ብልጭልጭታ (ነጠብጣብ): በጋለ ምጣድና ድስት ቂጥ ላይ የሚታይ የነበልባል ነጠብጣብ። ማስታወሻ: በግእዝ "ቀለምጺጽ" ይባላል።
ብልጭልጭታ: የብልጭታ ድጋሚ፡ ብልጭልጭ ማለት፡ ብርቅርቅታ። ማስታወሻ: ብዛቱን ያሳያል (ዳንኤል ፪፥፴፩)።
ብልጭታ: ቦግታ፣ ብርሃን፣ ነጸብራቅ።
ብሎ: ተናግሮ።
ብሎት (ብልዐት): ፍስክ፡ የጦም ቀን ያይደለ (እሑድ፣ ሰኞ፣ ማግሰኞ፣ ዐሙስ፣ ቅዳሜ)፡ ከብት የሚታረድበት (ሥጋ የሚበላበት) ጊዜ።
ብም አለ: ድም አለ፡ ድምፅ ሰጠ (ጮኸ)፡ ሰማዩ (ገደሉ፣ ናዳው፣ ከበሮው)። ማስታወሻ: "ብም" ከ"ባማ" ከግእዝ የወጣ ነው።
ብም: የመብረቅና የናዳ (የመርግ፣ የከበሮ) ድምፅ።
ብሰሳ: ስለላ (ሰብቅ)፡ ነገር መሥራት (ቅጥፈት)።
ብሳና (ኖች)/ምሳና: በቁሙ የታወቀ የወይና ደጋ እንጨት። ማስታወሻ: “ምሳና” ማለት ነቀዛምነቱን ያሳያል። “ማሰነን” እና “ሸንኰርን” ይመልከቱ። ሌላ ትርጉም: “በስተኸ ቀንበር አድርገው” ብሎ ይተረጒማል።
ብሳይ: ፍግ (ዐዛባ)፡ በበረት ወይም በጕድጓድ ውስጥ ቈይቶ የበሰለ (የተብላላ)፡ ዕርሻ የሚያሳምር። መድረቁንና “ጠቦት” መሆኑን ያሳያል።
ብስ (ሶች): የተበሳ፡ ፍልፍል (ሽንቍር፣ ቀዳዳ፣ ነዳላ፣ ንድል)።
ብስ (ዐረብኛ: ቢስ): የዓንበሳ ወገን (ድመት)። ባማርኛ: “ክፍ፣ ኺድ፣ ወግድ፣ በቃ” ማለት ነው። ዐረቦችም “በቃ” ሲሉ “በስ” ይላሉ። ማስታወሻ: አንበሳ፣ እንቦሳ፣ አንባሻ በግእዝ የበሰበሰ ዘሮች ናቸው።
ብስ: ክፉ (በሰበሰ)።
ብስል ሰው: ዋና፣ ጠንካራ ሰው፡ ዐዋቂ (ቁም ነገራም)።
ብስል ተቀሊል: ጥሩ ታደፍ፡ ጤፍና ስንዴ፣ ገብስ ከባቄላና ከአተር፣ ከሽንብራ፣ ከምስር፣ ካገዳ ጋር።
ብስል አለ: ተቀቀለ (ተከነ፣ ነፈረ)።
ብስል: የበሰለ፡ እንጀራ፣ ቈሎ (ንፍሮ፣ ገንፎ፣ ሥጋ)፡ የተቀቀለ (ቅቅል)። ሌላ ትርጉም: የጠነከረ፣ የጠና (ጥሩ፣ ማለፊያ)፡ የጐመራ ሰብል።
ብሥራተ ገብርኤል: ቅዱስ ገብርኤል ለመቤታችን መጋቢት ፳፱ ቀን የነገራት ምሥራች፡ ይኸውም ታኅሣሥ ፳፪ ቀን ይከብራል (ሉቃስ ፩፥፳፮-፴፰)።
ብሥራት: ምሥራች፡ ደስ የሚያሠኝ ወሬ።
ብስቍል: የበሰቈለ፡ ጕስቍል።
ብስቍልና: ጕስቍልና።
ብስበሳ: ርጥበት (ርሰት)።
ብስት አደረገ: በፍጥነት በሳ።
ብስትስት አለ: ተበሳሳ።
ብስትስት: የተበሳሳ (ሽንቍርቍር)።
ብስና: ክፉ ሽታ (ግማት፣ ክርፋት)፡ ከአፍ የወጣ፡ የፈስ ዓይነት (የኮሶ፣ የኰረፌ ግሣት)።
ብስናም: ባለብስና (ግም)።
ብስናታም: ግማታም (ክርፋታም)።
ብስናት: ዝኒ ከማሁ ለብስና።
ብስኪያም: የብስክ፡ ብጣሻም (ድርና ማግ፣ ገመድ፣ ጠፍር)፡ የመሰለው ሁሉ።
ብስክ (ብቱክ): የተበሰከ (የተሰተከ)፡ ብትክ (ብጥስ)።
ብስክ አለ: ቍርጥ (ብጥስ) አለ።
ብስክስክ/ብስክሳኪ: የተብሰከሰከ (የተቀማጠለ፣ የተንበሸበሸ)፡ ብትክትክ (ብጥስጥስ)።
ብስጥ: በቀድሞ ዘመን ከፋርስ የሚመጣ ምንጣፍ። በዐረብኛ “ብሳጥ” ይባላል።
ብስጩ (ዎች): የተበሳጨ፣ የተቈጣ፡ ቍጡ (ጠበኛ)።
ብስጭት አለ: ተበሳጨ።
ብስጭት: ቍጣ (ንዴት፣ ጩኸት፣ ግሣጽ)።
ብስጭትጭት አለ: ተበሰጫጨ።
ብሶል: በየብስና በባሕር፣ በአየር ለሚሄዱ ሰዎች ሰሜንን የሚያመለክት መሣሪያ፡ ፲፰ ሠላጤ ያለው መርሐ ሰሜን። ማስታወሻ: ከክርስቶስ በፊት ፲፻ ዓመት በሺን አገር ነበረ ይባላል።
ብሶት: የባሰ (የጠና) መከራ (ሥቃይ፣ ችግር፣ ጭንቅ)።
ብረ ሰብስብ: ዕንብርት ያላት ብር። የጭራ ብር: ለስላቅ ከብት ግብር ለመንግሥት የሚከፈል አንድ ብር። ሴቴ ብር: የሴት ሥዕል ያለባት ብር።
ብረ ሸሽ: ዐጥንቱ የቀጠነ፡ ሰውነቱ የመነመነ (ኰሳሳ) ሰው። “ብር” የተባለው አገዳው (ቅልጥሙ) ነው።
ብረተ ፈጅ: ብረትን የሚበላ፣ የሚፈጅ (የሚጨርስ)፣ የሚያሰላ ሻካራ ድንጋይ፡ ገርጋራ መሳል።
ብረታብረት: ከጕጣ ከዕላቆ ብረት የተሠራ፡ የብረት ብረት፡ ብዙ ዓይነት ብረት (ዶማ፣ ማረሻ፣ ወገል፣ ቢላዋ፣ መጥረቢያ፣ ማጭድ) የመሰለው ሁሉ።
ብረት (ዎች)/ኀጺን: በቁሙ እንጨት የሚቆርጥ፣ ድንጋይ የሚሰብርና የሚፈልጥ፡ ጠይቦች ከጥቍር ዐፈር አንጥረው የሚያወጡት ጠንካራ ካክራ (ማዕድን)። ምሳሌ: “ዐረብ ብረት”፣ “እግር ብረት” እንዲሉ። ንጥር ብረት: ድጅኖ፣ በትረ ቃቃን።
ብረት (የዐይን): በነጭ የተከበበ የዐይን መካከል ያለው ጥቍሩ፡ እንደ መስተዋትና ውሃ እንደ ጥሩ ብረት ረቂቅ፣ መልክ የሚያሳይ። አባባል: “ባይኔ በብረቱ አየሁት” እንዲሉ።
ብረት ለበስ: ስማርድ፡ በፈረንጅ የተሠራ የጦር መሣሪያ።
ብረት ምጣድ: ከብረት ሰሌዳ ወይም ሉሕ የተበጀ የብረት ምጣድ (ዘሌዋውያን ፪፥፭)።
ብረት ሠራ (ነሐበ): ብረት ቀጠቀጠ (አበጀ)።
ብረት ሠራ): ቀጠቀጠ፣ ጨፈለቀ፣ ቀበቀበ።
ብረት ቈሎ: የማይፈነከት፣ የማይነካ፣ የማይበገር (የማይደፈር) ጐበዝ።
ብረት አዝባጭ: ባለጅ ጠይብ።
ብረዛ: ብጥበጣ፣ ዝለላ (ቅልቀላ)።
ብሩ/ብሪቱ: የወንድና የሴት ስም ሊሆን ይችላል።
ብሪንጥ: የአረቄና የወይን ጠጅ አተላ (ዝቃጭ)።
ብሪካ: ጌታ የሌለው ከብት ወይም ገንዘብ፡ “ላምጪው የሚመረቅ”።
ብራ ሆነ (ጽሕወ): ዝናሙ ሳይጥል ቀረ።
ብራ: ዝናብ የሌለበት ቀንና ሌሊት።
ብራማ (ብራህማ): ከሦስቱ ዋና የሂንዱ አማልክት (ትሪሙርቲ) አንዱ ነው። በሥዕል ከታች አንድ ገጽ፣ ከላይ ደግሞ ሦስት ገጽ ሆኖ ይታያል። ባኒያኖች (የሂንዱ ነጋዴዎች) ብራህማን እንደ ፈጣሪና ሥጋን መጀመሪያ እንደለበሰ፡ ሴዋን (ሺቫ) እንደ ገዳይ፡ ዊሺኑን (ቪሽኑ) ደግሞ እንደ ጠባቂ ይላሉ።
ብራሪ: ዝኒ ከማሁ (ፍንጣሪ)።
ብራቅ: የእሳት ሰይፍ፡ የእሳት ፍላጻ፡ በዝናብ ጊዜ ከደመና አፎት የሚመዘዝ (የሚወረወር)። ምሳሌ: “ብራቅ ጣለ”፣ “ብራቅ መታው” እንዲሉ።
ብራብሪት: ታናሽቱ (እንስት)።
ብራብሮ (ዎች): በበጋ ይሞትና በክረምት ታድሶ የሚበርና የሚከንፍ፡ ተንቀሳቃሽ ባለብዙ ቀለምና ሕብር። በአበባ ወቅት (ከመስከረም ፳፭ እስከ ኅዳር ፭) የሚበዛ።
ብራብሮ: በቁሙ "በረረ"።
ብራና (ኖች)/ብርሃና: ከበግ፣ ከፍየል፣ ከጊደር፣ ወይም ከፈረስ ቆዳ ደደቡና ጠጕሩ ተፍቆ የተዘጋጀ የመጻፊያ ቆዳ ነው። “ብራና” ማለት በነጭ ኅጻጽ ታጥቦ የጠራና የበራ ማለት ሲሆን፣ አንቀጹ በግእዝ “በርሀ” ነው።
ብራኳ: የትከሻ ዐጥንት (ከወደ ኋላ ያለ)።
ብር (ሮች) (በሪር፣ በረ፣ ብሩር): በቁሙ ለመገበያያ ከአንዱ ወደ አንዱ የሚተላለፍ፡ የተመረጠ (የተለየ)፡ ልዩ፣ ልቅም፣ ጥሩ፣ ነጭ ማዕደን (ክቡር ገንዘብ)፡ የወርቅ ምክትል። (ዘፍጥረት ፳፫፥፲፮)። ለወንድና ለሴት: “ብሩ” (ያ ብር፣ የርሱ ብር)፡ “ብሯ” (የእርሷ ብር)። ብሪቱ: ያች ብር።
ብር (በሪር): መብረር። ተመልከት: “ፊትን”። ብር አለ: በረረ (ሮጠ)፡ “መጣ” ብለህ “መጭን” ተመልከት።
ብር (ብሩህ): የበራ፣ የጠራ (የነጣ)፡ ነጭ፡ የታየ (ግልጽ)፡ ብልኅ። ምሳሌ: “እከሌ ልበ ብር ነው” እንዲሉ። ተመልከት: "ዐይንን"።
ብር (ብርዕ): በቁሙ ከሸንበቆ፣ ከጐሽ መቃ፣ ከቀስተኒቻ (ሰሪቴ)፣ ወይም ከብረት የተቀረጸ የጽሕፈት መሣሪያ። ምሳሌ: “ብርና ቀለም” እንዲሉ። ሌላ ትርጉም: ውስጠ ክፍት አገዳ (ገለባ)። “የገብስ ብር፣ የስንዴ ብር” እንዲሉ። ተረት: “ድንቢጥ እንዳቅ በብር ትታገማለች። ” ማስታወሻ: ከግእዝ የራቁ ሰዎች ግን “ብዕር” ይሉታል።
ብር ቂንጥ አለ: ሮጠ (ተቀመጠ)።
ብር ቂንጥ: ቱር ቂብ።
ብር ብር አለ: ርግብ ርግብ አለ (የዓይን፣ የልብ)።
ብር ብር አደረገ: አሁንም አሁንም (ቶሎ ቶሎ) አበረረ (ዕረፍት ነሳ)።
ብር ነቀል (ሎች): ከተማሪ ቤት ተምሮ የወጣ፡ የመምሩን ብር ያነሳ ዐዲስ ደቀ መዝሙር። ማብራሪያ: “ብር” ትምህርቱንና ጽሕፈቱን ሲያመለክት፣ “ነቀል” ደግሞ ዕውቀቱን ያመለክታል።
ብር ዐለንጋ (የብር ዐለንጋ): የዛር ስም። ቀይ ዶሮ ዱልዱም የሚገብሩለት ዛር። “ብር” እጀታው ሲሆን “ዐለንጋ” ደግሞ ጕማሬው ነው።
ብር አንባር (የብር አንባር): ክብርና ድንግልና።
ብር ዋንጫ (የብር ዋንጫ): በፈረስ ግልቢያ ለቀደመና በኳስ ጨዋታ ለበለጠ የሚሰጥ ሽልማት።
ብርሃነ ልብ: የልቡና ጥራት።
ብርሃነ ልደት: ጌታችን የተወለደ ለት የታየ ብርሃን።
ብርሃነ መስቀል: መስቀል ከጕድጓድ በወጣበት ቀን የተገለጠ ብርሃን።
ብርሃነ ብርሃናት: የብርሃኖች ብርሃን (ጌታ፣ ፈጣሪ)።
ብርሃነ ትንሣኤ: ጌታችን ሙቶ በተነሳ ጊዜ የበራ ብርሃን።
ብርሃናት: ብርሃኖች።
ብርሃን (ኖች): በቁሙ ጸዳል፣ ውጋገን፡ እሳት (ፍም፣ ነበልባል)፡ ቀን፡ ዐይን፡ ዕውቀት (ልቡና)። ተመልከት: "ደበረን"፣ "ደጅን"፣ "ከሠተን"።
ብርሃን ሆነ: ተፈጠረ፣ ተገኘ (ዘፍጥረት ፩፥፫)።
ብርሃን ሰገድ: የ፪ኛ ኢያሱ ስመ መንግሥት።
ብርሌ (ዎች)/ቢረሌ: በቁሙ ነጭ፣ ጥሩ የባሕር ዕቃ፡ በመንቀል አምሳል የተሰራ፡ የቦረቦቼ ዓይነት፡ ልሙጥ (ሹርቤ፣ ስጕዳ፣ አረንጓዴ)። ተረት: “ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃ። ” “ጠጅ በብርሌ፣ ዜማ በሃሌ። ” “ቀይ እንደ በርበሬ፣ ጥሩ እንደ ብርሌ። ” ተመልከት: “ሞን”።
ብርቄ: “የኔ ብርቅ”፡ የወንድና የሴት መጠሪያ ስም።
ብርቅ ነህ/ነሽ: ወልዶ የማያውቅ ሰው በወለደ ጊዜ ለልጁ የሚሰጠው ስም።
ብርቅ: ዘወትር የማይታይና የማይገኝ ዐዲስ (እንግዳ) ነገር፡ ድንቅ ሥራ (ጕድ፣ ታምራት)። አባባል: “ብርቅና ድንቅ አላንድ ቀን አይደምቅ። ” ተመልከት: “ቈመጠ” ብለህ “ቈማጣን”።
ብርቅስ አለ: ተበረቀሰ (ፈረሰ)።
ብርቅስ አደረገ: በረቀሰ (ጣሰ)።
ብርቅስቅስ: የፈራረስ (ፍርስርስ)።
ብርቅርቅ: የተብረቀረቀ።
ብርቅርቅታ: ብልጭልጭታ።
ብርቅዮሽ: የብርቅ ዓይነትና ወገን።
ብርበራ: ብዝበዛ፣ ዘረፋ፣ ወረራ። በግእዝም “በርበር” ይባላል።
ብርባሮ: ግልበጣ (መገልበጥ)።
ብርብራ (ዎች)/በርባር: የዛፍ ስም፡ ፍሬው ዓሣ የሚያሰክር (የሚበረብር)፡ ባሕር የሚያሸብር።
ብርብር (ብርቡር): የተበረበረ፡ “ውሃ የበረበረው ወንዝ” ማለት ነው።
ብርብር (አገር): በገሙ ውስጥ ያለ አገር፡ የማርያም አጥቢያ። “ብርብር ማርያም” እንዲሉ።
ብርተቃቃን: ድጅኖ በትረ ቃቃን።
ብርቱ (ዎች)/ብርቱዕ: የበረታ፣ የጠነከረ፡ ኃይለኛ (ጠንካራ፣ ጕልበታም፣ ጐበዝ) (ኢሳይያስ ፲፥፳፩፣ ሕዝቅኤል ፴፱፥፳)። ተረት: “ላንድ ብርቱ ሁለት መዳኒቱ። ”
ብርቱነት: ኃይለኛነት (ጠንካራነት)።
ብርቱካን (ዐረብኛ): “በኵረ ሎሚ” (የሎሚ ዓይነት)።
ብርቱዋ/ብርቱዪቱ: ጠንካራዋ (ጠንካራዪቱ) (፩ኛ ነገሥት ፰፥፵፪)።
ብርታት: ጥናት፣ ጥንካሬ (ኃይል፣ ጕብዝና፣ ጕልበት) (ዘዳግም ፫፥፲፰፣ ምሳሌ ፰፥፲፬)።
ብርት (ሳሕን): ከመዳብና ከነሐስ የተበጀ ባለ ወንፊት ሳሕን (ደቅ)፡ የእድፍ መፍሰሻ (ማረፊያ)። “ሰንና ብርት” እንዲሉ። ተመልከት: “ዳታንን”።
ብርት (ቶች): ቀይ ብረት፡ መዳብ፡ ማዕርጉ ከብረት ሁለተኛ የሆነ። ማስታወሻ: ብርት የግእዝ ሲሆን መዳብ ያማርኛ ነው። “ንሓስ”ም በግእዝ “ብርት” ይባላል።
ብርንዶ (በረደ): ያልተጠበሰና ያልተቀቀለ ጥሬ ሥጋ፡ ስብ ያይዶለ ቀይ ሙዳ። ትርጓሜውም “በሪድ” ማለት ነው። ሲበዛ “ብርንዶች” ይላል።
ብርንጎ: በቀጪኑ የተሠራ ቍንጮ።
ብርከታ: ብዛት፣ ፍድፈዳ።
ብርኵማ (ሞች): የሽባ መንፈቅያ፡ ዐጪር ቍራጭ እንጨት፣ እጅ ማግቢያ ያለው ሁለት ዓይነት፡ የእጅ መጫሚያ (ብርካዊ፣ ዘብርክ) ማለት ነው።
ብርኩማ (በገና): እንደ “በ” ፊደል የተቀረጸ የበገና አውታር ደጋፊ፡ ከጠፍር ቍርጥራጭ ጋር በስተታች አውታሩን (ዥማቱን) ወትሮ ገትሮ የሚይዝ።
ብርኵማ (ተክል): የበርበሬ ዛላ ሥር (ቂጥ)፡ የቅንጣሽ ጫፍ።
ብርኩማ (ትራስ): ባለሽሩሶች የሚንተራሱት ትራስ፡ ከጥቍር እንጨት (ዞጲ) ወይም ከሰንደል የተበጀ። በግእዝ: መሥዕርት ይባላል። ተመልከት: “ብርኰትን”።
ብርኵታ (ቶች): በፍም የሚበስል ርሚጦ ቂጣ፡ ሲበሉት የሚያጠግብ (የሚበረክት፣ የሚመክት)፡ የጭብጦ ዓይነት። አዘገጃጀት: ትግሮች በጋለ ድንጋይ ሊጡን አድበልብለው ያበስሉታል። ሺዎች ግን ጕድጓድ ምሰው ሊጡን በቅጠል ጠቅለው ከጕድጓድ ውስጥ አስገብተው በላይ እሳት ያነዱበታል፡ ወይም በፍም ውስጥ ይረምጡታል። በግእዝ: ዳፍንት ይባላል።
ብርክ: የጕልበት መታጠፊያ፡ የጕልበት ማነስ (ፍርሀት፣ ድካም)። አባባል: “ብርክ ያዘው፣ ብርክ ብርክ አለው” እንዲሉ።
ብርክርክ አለ: ተብረከረከ (ዐቅም አነሰው)።
ብርክርክ: የተብረከረከ፡ እንቅጥቅጥ።
ብርኰት (ብርኵት): ቆዳ የለበሰ የእንጨት ትራስ። ማስታወሻ: ብርኵማ፣ ብርኳኔ እና ብርኰት ከብርክ ይወጣሉ።
ብርኳኔ: ዝኒ ከማሁ፡ የእንጨት ትራስ።
ብርዳም: ውርጫም፣ ቅዝቃዜያም። ምሳሌ: “እንደ ጣርማ በርና እንደ መገዘዝ ያለ ስፍራ። ”
ብርድ ልብስ (የብርድ ልብስ): በብርድ ጊዜና ሌሊት የሚለበስ ወፍራም ልብስ (ከጥጥ፣ ከጠጕር፣ ወይም ፈረንጅ የሰራው)።
ብርድ ብርድ አለው: በረደው (ቀዘቀዘው)።
ብርድ: ውርጭ፣ ዐመዳይ፣ ቍር፣ ቅዝቃዜ (ቈፈን)፡ ከጥቅምት ፲፫ እስከ ጥር ፲፫ የሚሰለጥን።
ብርገጋ: ድንጋጤ፣ ፍራት።
ብርጕድ: እንደ ዕጣን ያለ ጥቍር ሙጫ፡ ሴቶች የሚታጠኑት (የሚሞቁት)፡ ነጋዴዎች ከባሕር የሚያመጡት። ማስታወሻ: “ወንዴ ብርጕድ፣ ሴቴ ብርጕድ” እንዲሉ።
ብርጋና: የወፍ ስም፡ ከፀሐይ ጸዳል እንቍ የምትወልድ የባሕር ወፍ፡ የመቤታችን ምሳሌ። በግእዝ አዋልድ ብትገኝም በአሁኑ ዘመን አትታወቅም።
ብርግድ አለ: ክፍት አለ፡ ተበረገደ።
ብርግድ: ዝኒ ከማሁ፡ የተበረገደ (ኀፍረተ ብእሲት)።
ብርግግ: የተበረገገ (የተወለለ) ውልል።
ብርጭቅ (በጢሕ): የዱባ አይነት ተክል፡ ውስጡ ቀይ፣ ክብ እንክብል፣ ማር የሚል።
ብርጭቆ (ዎች): ከክርስቶስ ልደት በፊት ፫ ሺ ዓመት ግብጾች አሸዋ አንጥረው በዋንጫና በጥዋ አምሳያ ሰርተው ያወጡት የብርሌና የመስተዋት ዓይነት ዕቃ። ብርጭቃ (ራእይ ፬፥፮)። ዐረብኛ “ኩባያ” ይለዋል።
ብሮት: በሕፃን ገላ ላይ ያለ ጥቍር ነጠብጣብ፡ “ማርያም የሳመችው ነው” ይባላል።
ብሮች (አብራዕ): መጻፊያዎች (የብዕር ብዜት)።
ብሽርክ: ዝኒ ከማሁ (ሽርክት)። ብሽርክ አለ: ተበሸረከ፡ “ቅድድ” አለ፡ “ሽርክት” አለ።
ብሽርክርክ: የተቀዳደደ፡ ሽርክትክት (ብጭቅጭቅ)።
ብሽሽት: ከንፍፊት፡ ያ በስተላይ ያለ፡ ልም ገላ (ጕያ)።
ብሽቅ አለ: በሸቀ።
ብሽቅጥ አለ: ብክት አለ።
ብሽቅጥቅጥ (የተበላሸ): የተበላሸ (የረከሰ)።
ብሽቅጥቅጥ አለ: በሸቀጠ (ተበሻቀጠ)።
ብቀታ: ንትረካ፣ ንዝነዛ።
ብቃት (ብቍዐት): ንጽሐ ሥጋን፣ ንጽሐ ነፍስን (ንጽሐ ልቡናን) አግኝቶ መልአክን (ነፍስን፣ ዕመቀ ዕመቃትን፣ ሰማየ ሰማያትን) ሥላሴን ማየት፡ ፍጹምነት (ቅድስና)።
ብቅ (በቊል): መብቀል።
ብቅ አለ: ወጣ፡ ተገለጠ (ታየ)፡ ከፍ አለ።
ብቅ አደረገ: ከውስጥ አወጣ (አሳየ)።
ብቅ ጥልቅ አለ: ወጣ ገባ አለ (ተመለሰ)፡ ራሱን አሳየ (ደበቀ) ሲዋኝ።
ብቅ ጥልቅ: አንዳንድ ምታሪ ሥጋ ከሹሮ ወጥ ጋራ።
ብቅል (ሎች) (ብቁል): በውሃ ርሶ በቅጠል የተሸፈነ፡ በመሬት ተቀብሮ የበቀለ፡ የጫጩት አፍ መሳይ ገብስ ወይም ስንዴ፡ የጥሬው ግግር (ጕንቍል)፡ የጠላ ርሾ (ጥንስስ)። ተረት: “ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል” እንዲሉ።
ብቅል ሰቃይ: ረዥም ሰው፡ ኦሮምኛ “ሞፈር”።
ብቅል ረገጠ: የገብስን ጕንቍል በቅጠል ሸፈነ፡ ከመሬት ቀበረ፡ በጫማው ጨቈነ፡ ድንጋይ ሆነ።
ብቅቡቅ (ትግርኛ): እብቅ፣ ገለባ (፪ኛ ነገሥት ፲፫፥፯)።
ብቅታ (መብቀል): ብቅ ማለት።
ብቅታ: ከፍታ፣ መገለጫ፣ መታያ፡ ደፈር (ኰረብታ፣ ተራራ፣ ገመገም)፡ የተረተር ግፍ።
ብቅታ: ደፈር፡ "በቀለ"።
ብቅት (የተበቀተ): በቀተ።
ብቅት አለ: ድክም አለ፡ ተረፈቀ፡ በቤት ዋለ (በድካምና በርጅና ምክንያት)።
ብቅት: ዐቅም ማጣት።
ብቡ: የሠጋ፣ የፈራ፣ የበረገገ (ፈሪ፣ ሥጉ)።
ብብት/ብብቻ: ሕፅን ውስጥ (ከጣቶች አንዱ ቢቈስል መካከሉ የሚያብጥ) (ዘጸአት ፬፥፮-፯፡ ሰቆቃው ኤርምያስ ፪፥፲፪)። ተረት: “የቈጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች”።
ብብቶች: ሁለትና ከሁለት በላይ ያሉ ብብቶች።
ብተት: መባት (መግባት፣ መሾም)፡ አገባብ (አሠለጣጠን)። የሌሊትና የቀን ቍጥር።
ብተት: መባት (ባተ)።
ብተና: ውርወራ (ዝርዘራ፣ ፍንጠቃ)።
ብትበታ: ቡጥቦጣ (ብግበጋ፣ ፍልፈላ)።
ብትቱ: ዕላቂ (ውዳቂ)፡ ዘባተሎ ጨርቅ። ተመልከት: “በተበተን”፡ የዚህ ዘር ነው።
ብትታ: ብቻ መሆን (መለየት፣ ልዩነት)።
ብትን ሰዋስው: ቦታ፣ ጊዜ፣ አካል (ባሕርይ)፡ ስም (ግብር፣ ነገር)።
ብትን አለ: ተበተነ።
ብትን አደረገ: በተነ።
ብትን ድልህ: ስልቅ የድልህ ዶቄት፡ የላመ በርበሬ።
ብትን ድልኸ: "ድልኸና ቅቤ" እንዲሉ።
ብትን: የተበተነ (የደቀቀ)፡ ደቃቅ (ደቄት)።
ብትንትኑ ወጣ: ፈረሰ (ተናደ፣ ተመሳቀለ)።
ብትንትን አለ: ተበተነ።
ብትንትን አደረገ: በተነ።
ብትንትን: የተበታተነ (የተለያየ)፡ በብዙ ስፍራ የተዘራ። ግጥም: “እንትኑን ብትንትን አደረገው ብትንትን”።
ብትክ (ብቱክ): የተበተከ (የተበጠሰ)፡ ቋንዣው (የደም ሥሩ፣ መትኑ) የታቈረጠ፡ አባላ የተመታ፡ ጥንብ (ውዳቂ)፡ ታንቆ የሞተ ከብት (ማንኛውም እንስሳ)።
ብትክትክ (እንጀራ): ዓይነ በጎና ሰፍነግ መሳይ ጤፍ እንጀራ።
ብትክትክ አለ: ብስክስክ አለ (ተበጣጠሰ፣ ተበላሸ)።
ብትክትክ: የተበታተከ፡ ብጥስጥስ (ቍርጥርጥ፣ ብስክስክ)።
ብቸና: የአገር ስም። በጐዣም ውስጥ ያለ አገር።
ብቸኛ: ባተሌ (ባታይ)፡ ባሕታዊ (መናኝ)።
ብቻ (ባሕቱ): ዓቢይ አገባብ፡ በቁሙ “እንጂ፣ ግን”። ምሳሌ: “አላቻ ጋብቻ”፡ “ቈይ ብቻ፣ ቈይ ብቻ” (፪ኛ ዜና መዋዕል ፬፥፮)። ምሳሌ: “አርባ ሆነህ ና፡ ዓጪርና በራ ሰው አታምጣብኝ፣ ብቻ”።
ብቻ (ባሕቲት): ቅጽልና በቂ። ምሳሌ (ቅጽል): “እሱ ብቻ!” “አንተ ብቻ!” “ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ብቻ፣ ሰው ብቻ አይዶለም፡ በተዋሕዶ (ባንድነት) አምላክና ሰው ነው እንጂ”። ምሳሌ (በቂ): “ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታል”። ማስታወሻ: ንኡስ አገባብም ይሆናል (መዝሙር ፩፥፪)። ማስታወሻ: “ብቻህ”፣ “ብቻቸው”፣ “ብቻችሁ”፣ “ብቻዋ”፣ “ብቻሽ”፣ “ብቻዬ”፣ “ብቻችን” እያለ እስከ ፰ ይዘረዝራል። በደቂቅ መነሻነት ሲነገር: ለየብቻ (ለእየብቻ): ለየአንዳንዱ፡ የራስ (ለየቅል)። ምሳሌ: “ዳንኤል ረበናትን ለየብቻቸው ጠየቃቸው”።
ብቻ ለብቻ: አንድ ለአንድ። ምሳሌ: “ዳዊትና ጎልያድ፣ እስክንድርና ፉዝ ብቻ ለብቻ ተገናኙ”።
ብቻነት/ብቸኛ(ኝ)ነት: ዝኒ ከማሁ፡ ባተሌነት (ባሕታዊነት፣ መናኝነት) (መዝሙር ፳፪፥፳)።
ብኑን (ብህኑን): በኩን፣ በናና (ብኩን)፡ በረከተ ቢስ ገንዘብ፡ ያልተመረቀ ልጅ።
ብናኝ (ባህናን): የሥራይ ዶቄት (ቅመም፣ ትቢያ፣ ዐቧራ፣ ዐመድ)።
ብንታ: ብን ማለት። ተመልከት: "ነዘዘን"።
ብንን አለ: ባነነ፣ ከንቅልፍ ነቃ (ተነሳ)።
ብንን: መባነን።
ብንንታ: ብንን ማለት (ንቃት)።
ብንያም: የሰው ስም፡ የነገደ እስራኤል መቈረጫ (መጨረሻ) ልጅ።
ብከላ: ለፋ (የማሳደፍ ሥራ)።
ብኬ: የቀበሌ ስም፡ በሐረርጌ በረሓ ያለ የባቡር ጣቢያ።
ብክላት: ብከላ፣ መበከል።
ብክል አለ: ተበከለ።
ብክል አደረገ: በከለ።
ብክል: የተበከለ፣ ያደፈ (የጠፋ)፡ ጥፉ፣ አዳፋ፣ አስቀያሚ።
ብክት አለ: ፈጽሞ ራሰ፣ በከተ፣ ረሰረሰ።
ብክነት: ባካና መሆን፡ ጕድለት።
ብክንክን አለ: ተብከነከነ።
ብክካ (ብሓ): እንደ ገል የሚሰበር፣ እንደ ጓል የሚፈርስ (ነጭና ቀይ) ድንጋይ።
ብኻ: በቁሙ "ብሓ"።
ብው (በዊሕ): “ቧ” ማለት፡ መንደድ፣ መቃጠል።
ብው አለ (ቦሐ): ነደደ፣ ተቃጠለ (ቋያው፣ ጥሻው፣ ችቦው፣ ፋናው)።
ብዙ (ብዝኁ): ትእዛዝ አንቀጽ። ምሳሌ: “ብዙ ተባዙ፡ ምድርን ምሏት” (ዘፍጥረት ፩፥፳፰)።
ብዙ (ዎች) (ብዙኅ): የበዛ፣ የተረፈ፣ የተትረፈረፈ፡ እጅግ፣ ዐያሌ።
ብዙ መጠጥ ጠጣ።
ብዙ ነህ/ብዙ ነሽ: የወንድና የሴት መጠሪያ ስም።
ብዙ አንድነት: ማኅበረ በኵር።
ብዙኃን ማርያም: ኦርዮስን ለማውገዝ ፫፻፲፰ ሊቃውንት በተሰበሰቡበት መስከረም ፳፩ ቀን በዓሏ የሚከበር (የብዙዎች ማርያም) ማለት ነው።
ብዙኃን ይመውኡ: (የግእዝ ተረት) ብዙዎች ያሸንፋሉ።
ብዙኃን: ብዙዎች (ግእዝ)።
ብዙነት: ብዙ መሆን።
ብዙውን (መብዝኅቶ): እጅጉን፣ ዐያሌውን፡ ብዙ ጊዜ።
ብዝር (ፍሬ): በቁሙ፡ ፈረስን፣ በቅሎን የምታፈራ (የምቶልድ) ኦሮ፣ ቀላማ የምትላት እንስት ፈረስ።
ብዝቅ (ስም): ባዜቃ የገባ፣ የተነከረ፡ ዝቡቅ።
ብዝቅ አለ: ባዘቀ፣ ተዘባረቀ።
ብዝቅ: መባዘቅ።
ብዝበዛ: ዘረፋ፣ ቅሚያ፣ ብርበራ፣ ብተና (፪ኛ ሳሙኤል ፰፥፲፪፡ ሕዝቅኤል ፴፰፥፲፪፡ ሚክያስ ፪፥፬፡ ዘካርያስ ፲፬፥፩)።
ብዝብዝ አደረገ: በዘበዘ።
ብዝብዝ: የተበዘበዘ፣ የተዘረፈ፣ የተቀማ፣ የተበረበረ፡ ብርብር፣ ብትን።
ብዝት (ብዙት): የተባዘተ፣ የተነቀሰ፣ የተፍታታ (ጥጥ፣ የበግ ጠጕር)።
ብዝት አለ: ድቅቅ፣ ልትት አለ።
ብዥ/ብዛት (ብዝኅ፣ ብዝኀት): መብዛት፣ ብዙነት፡ ላቂያ፣ ብል (ማቴዎስ ፮፥፯)።
ብዥብዥ አለ (ቤዘ): ጥቂት ጥቂት ታየ።
ብየና (ብያኔ): ዕውቀት፣ ፍርድ፣ ፈሊጥ፣ ሥርዐት።
ብየኛ (ኞች): ካሳ የተቀበለ፣ የወሰደ፣ የበላ።
ብየዳ: ድለዛ፣ መረጋ፣ ደፈና።
ብያ (ኦሮምኛ: ብዬ): አገር፣ ዐፈር። ምሳሌ: “አባ ብያ” እንዲሉ።
ብይ (ካሳ): ካሳ፣ አፈላማ።
ብይ (ድንጋይ): የድንጋይ (የብርጭቆ) ጠጠር ልጆች እየወረወሩና እያጋጩ የሚጫወቱበት።
ብይ: ጠጠር (በላ)።
ብይን (ብዩን): የተበየነ፣ የተፈረደ (ቅጽል)። ብይን (ፍርድ): ፍርድ፣ ፍት (ጥሬ) (ኢዮብ ፴፮፥፲፯)። ምሳሌ: “ብይን ቀጠነ” እንዲሉ።
ብይዳት: ብየዳ (የመበየድ ሥራ)።
ብይድ: የተበየደ፣ የተደለዘ፡ ድልዝ፣ በስ፣ ግብዝ።
ብደራ (ልቃሔ): የብድር ስጦታ።
ብድል: የተበደለ፣ የተገፋ።
ብድራም: የብድር ጐሬ፡ ዕዳ ብቻ።
ብድራት: ለሠሪው የሚመለስ የፍዳ (የበቀል) ሥራ፡ ዕዳ፣ ቂም፣ ደም (ኢሳይያስ ፴፬፥፰፣ ፴፭፥፬፡ ዐብድዩ ፩፥፲፭፡ ሉቃስ ፲፬፥፲፪፡ ቈላስይስ ፫፥፳፭)።
ብድር (ሮች): ከአበዳሪ እጅ ለተበዳሪ ያለፈ የአራጣ (የልቆ፣ የወለድ) ገንዘብ። ምሳሌ: “በምድር አይቀር ብድር” እንዲሉ።
ብድር መለሰ: ዕዳን ወይም ደምን ከፈለ።
ብድግ (ጥድ): የተበደገ፣ የተሠነጠቀ፣ የተከፈለ፡ ሥንጥቅ።
ብድግ (ጥግ): መነሣት፣ መቆም።
ብድግ አለ (ተበደገ): አፈፍ አለ፣ ተነሣ፣ ቆመ።
ብድግ አደረገ (በደገ): አነሣ፣ አቆመ።
ብድግ ያኸል: ትልቅ። ማስታወሻ: "አንዳች አንድስን" እይ።
ብጀታ: መበጀት፡ ውበት።
ብገራ: ሙከራ፣ ፍተና፣ ምጠና፡ የመበገር ሥራ።
ብገናም: ጨብጣም፣ ዕብጠታም፣ ግምላም፣ ጠባሳም።
ብገን (ትእዛዝ): የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ። “ድረቅ”፣ “ክረር”።
ብገን (ትግ. ሐባ፡ ጨብጥ): የቈረሰጪ ቍርብጭ፡ ጅግል፣ ግምል።
ብጕራም: በፊቱ ላይ ብጕር ያለበት (የበዛበት)።
ብጕር/ብግር: በጕልማሳና በአፍለኛ ፊት ላይ የሚወጣ የአፍላ ምልክት፡ የደም አበባ (ፊትን የሚበግር) (ዘሌዋውያን ፲፬፥፲፯)።
ብጕንጅ (ጆች): በብጕርና በዕባጭ መካከል ያለ የበገነ (የከረረ) ትኵሳታም ዕብጠት። ማስታወሻ: "ብጕንጅ" ሁለት ዓይነት ነው፡ ትልቅና ትንሽ። ትንሹ “ያይጥ ብጕንጅ” ይባላል።
ብግር (ጥግ): የተበገረ፣ የተሞከረ፣ የተነደፈ፣ የተመጠነ (ምጥን)፡ የተደፈረ።
ብግበጋ: ገረፋ፣ ትኰሳ።
ብግብግ: የተበገበገ፡ ግርፍ።
ብግነት: ድርቀት፣ ቍርብጭታ።
ብግን አለ: ፈጽሞ ገመነ (ዐረረ)።
ብግን: የበገነ፣ የደረቀ፣ የከረረ፣ የገመነ፣ ያረረ።
ብጠሳ: ቈረጣ፣ የመበጠስ ሥራ።
ብጠራ: ልየታ፣ ምየዳ።
ብጡል (ዐረብኛ: በጥለ): ጐበዝ፣ ጀግና፣ ሐርበኛ፣ ኀይለኛ፣ ብርቱ። ታሪክ: ይኸውም ሊታወቅ የይተጌ ጣይቱ አባት ደጃች ብጡል በአንድ ጦር ሁለት ሰው ደርበው ወግተው ገድለዋል ይባላል። ሌላ ትርጉም: ደግሞም "ብጡል" ቅምጥል፣ ድልድል፣ ሥራ ፈት ተብሎ ይተረጐማል።
ብጡል (ጠፋ): የበጠለ፣ የባጠለ (የጠፋ)፡ ጥፉ፣ መጥፎ፣ ብልሹ፣ ከንቱ፡ ፲፭፻ ዘመነ አበው የሚያጐድል (ኦሪተ አይሁድ)።
ብጣሪ: ንፋስ (ዐሠር፣ ገለባ)፡ እንችፍ።
ብጣሻም: የብጣሽ ዓይነት (ወገን)፡ ብጣሽ ያለው፣ ባለብጣሽ።
ብጣሽ: ታናሽ ቍራጭ።
ብጤ: ብጫ የመሰለ (የብጫ ዓይነት)፡ ፊላ (ፊላዊ)። ማስታወሻ: "በጨን" ተመልከት፡ ከዚህ የወጣ ነው።
ብጤት: ዐመል፣ ሥረት፣ ምርጫ፣ ሐሳብ። ምሳሌ: “ሰው እንደ ብጤቱ ይኖራል”።
ብጥ (ብጡሕ): የተሰጣ፣ የተቈራ፣ የተጋረጠ፡ ትፍትፍ፣ ሥንትር።
ብጥሌ: የብጥል፡ ታናሽ ዕንጐቻ (ኦሮ)።
ብጥል: ዕላቂ፣ ብማቂ፣ ብጣሽ።
ብጥልጣይ (በጸላዊ): የብጥልጥል ወገን (ዓይነት)።
ብጥልጥል (ብጻል): ብትንትን፣ ብጭቅጭቅ፣ ስንጥቅጥቅ።
ብጥልጥል አለ: ተብጠለጠለ፡ ብትንትን አለ።
ብጥስ አለ: ተበጠሰ፡ ጕምድ፣ ቍርጥ አለ።
ብጥስ አደረገ: በጠሰ።
ብጥስጣሽ: ቍርጥራጭ።
ብጥስጥስ አለ: ቍርጥርጥ፣ ብስክስክ አለ።
ብጥስጥስ አደረገ: በጣጠሰ (፩ኛ ሳሙኤል ፲፩፥፯)።
ብጥስጥስ: በብዙ ወገን የተበጠሰ፣ የተቈራረጠ።
ብጥረቃ: ሽንቈራ፡ የመብሳት ሥራ።
ብጥራት: የማበጠር፣ የማንፈስ (የማጐተን) ሥራ።
ብጥር አለ: ተበጠረ።
ብጥር አደረገ: አበጠረ።
ብጥር: የተበጠረ፣ የተነፈሰ፣ የጠራ፡ ጥሩ።
ብጥርቅ አለ: ተበጠረቀ፡ ንድል፣ ብስት አለ።
ብጥርቅ: የተበጠረቀ፡ ብስ፣ ሽንቍር።
ብጥበጣ: ጠመቃ፣ ብረዛ፡ ሁከት።
ብጥብጥ (ሁከት): ንዝንዝ፣ ጭቅጭቅ፣ ሁከት፣ ሽብር፣ ጦርነት፣ ግርግር።
ብጥብጥ (ንጽ): የተበጠበጠ፣ የታሸ። ምሳሌ: “የማር ብጥብጥ፣ የተልባ ድርጥ” እንዲሉ።
ብጥብጥ አደረገ: አካቶ ፈጽሞ በጠበጠ፡ አገርን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን አጠፋ።
ብጥታት (ብጥሐት)/ብጥነት: ፍቅታት፣ ቍርታት፣ ትፍትፋት።
ብጥንቅር: የማይፈለግ ነገር።
ብጨቃ: ብጠሳ።
ብጫ (ጮች) (ብጻ): በቁሙ፡ ከጥቍር (ከአረንጓዴ) የተለየ (ዐይን፣ አበባ፣ ሱፋላ)፡ በወይባና በነጭ መካከል ያለ ቀለም (መልክ)። ማስታወሻ: "ዐደይን" ተመልከት።
ብጫ ጥለት: ብጫ የሆነ የብጫ ጥለት።
ብጫ: ቅጽል ወይም ዘርፍ ሲሆን።
ብጫቂ/ብጭቅ (ብቱክ): የተበጨቀ፣ የተቈረጠ፡ ብጣሽ።
ብጭርቅርቅ አለ: ሳያምር ቀረ (ጨበረቀ)።
ብጭቅ አለ: ተበጨቀ።
ብጭቅጫቂ: ዝኒ ከማሁ (እንደዚሁ)፡ የተበታተከ፣ የተበሳሰከ።
ብጭቅጭቅ አለ: ብጥስጥስ፣ ብትንትን አለ።
ብጭቅጭቅ: ብጥስጥስ፣ ቍርጥርጥ።
ብጭጭ አለ: ዝኒ ከማሁ (እንደዚሁ)።
ብፁዕ (በፂዕ፣ በፅዐ): ክቡር፣ ምስጉን፣ ምሩቅ (ቡሩክ)፣ ጻድቅ፣ ቸር፣ የእግዜር ሰው። በክቡርና በቅዱስ መካከል ላለ ይነገራል።
ብጹዕ/ክቡር: "ብፁዕ" የግእዝ ነው።
ቦለ: ቦረቦጭ፣ ሰበረ፡ ስለት አወጣ።
ቦለለ: ሰፋ (ሰፊ ሆነ) (የሱሪ)። ተመልከት: "ወለለን"። ቦለለ (ጪስ): ተትጐለጐለ፣ ቦነነ (የጪስ)። ተመልከት: "ቡላን"፡ የዚህ ዘር ነው።
ቦለቀ: ፈለቀ፣ ወጣ። ተመልከት: "ቦጠለቀን"።
ቦለቦለ (ፈልፈለ): አንቦለቦለ፡ አወረደ፣ አፈሰሰ፣ አንዶለዶለ።
ቦለቲከኛ: ዘዴኛ፣ ባለፈሊጥ፡ ዐዋቂ፣ በነገር ተራቃቂ።
ቦለቲክ (ፖለቲክ): የነገር ዘዴ፡ ውስጠ ተንኰል (ፈሊጥ)። ማስታወሻ: "ቦለቲክ" በግእዝ "ጕሕሉት"፣ "ኂጣን"፣ "ሚን" ይባላል፡ "ላዩ ዳባ ውስጡ ደባ" (ድለላ፣ ሽንገላ) ማለት ነው።
ቦለደ (ለየ): ለየ፣ ከፈለ፣ አራቀ፡ አስገለለ።
ቦለደ (መታ): መታ፣ አጋጨ፣ አፋለ፡ በብረት ከባልጩት እሳት አወጣ። ተመልከት: "በለጨ" ብለህ "አበለጩን"።
ቦለዳዊ: የቦለድ።
ቦለዴ: ከጅር የተለየ፣ ከገመር የሸፈተ ዝንጀሮ።
ቦለድ (መሳሪያ): የመጥረቢያና የምሣር መካከለኛ፡ መፍለጫ፣ መሠንጠቂያ (ማጤ)።
ቦለድ (ሰው): ከሰው የተለየ ሽፍታ (ወያኔ)።
ቦላላ: ሰፊ (ሱሪ)፡ ተነፋነፍ።
ቦላሌ: ስፋት (ሰፊነት) ያለው፡ የቦላላ ዓይነት።
ቦልካን: ከምድር ፈንድቶ የሚወጣ እሳተ ገሞራ። ማስታወሻ: "ቦልካን" የፈረንጅ ቋንቋ ነው። ተመልከት: "ቦለቀን"።
ቦምባ: የብረት አሸንዳ፡ ውሃ የሚወርድበት (ውስጠ ክፍት ብረት)። ማስታወሻ: በአገራችን አሸንዳ የሚሆኑ ቈልቋልና ቀርከሃ ናቸው።
ቦምባይ: የህንድ አገርና ከተማ።
ቦምብ: ፈረንጆች በመብረቅ ምሳሌ የሠሩት፡ ቈልቍል ወይም አግድም ሲወረውሩት ፈንድቶ ቤት የሚያፈርስ (የሚያቃጥል)፡ ሰው የሚገድል፡ ሲጮህ “ብም” የሚል፡ ክብ (ሞላላ) የአይሮፕላን መርግ። ማስታወሻ: በእንቍላል አምሳል የተሠራ ሾጠጥ ያለ ባለከምሱር፡ ውስጡ ባሩድ የተመላ የብረት ማሰሮ ነው።
ቦስጣ/ፖስታ: ደብዳቤ።
ቦረቀ (ቦቀረ): ጮቤ መታ፣ ዘለለ (ፈነወ)። ተመልከት: “ወረቀን”።
ቦረቀ (ዐወደ): አልፎ አልፎ ዐወደ (ሠራ)፡ ወረበ። ማስታወሻ: ቦረቀ እና ቦቀረ በፊደል መዛወር በቀር በምስጢር ልዩነት የላቸውም። ቦረቀ የሳር ሲሆን፣ ቦቀረ የጠጕር ነው።
ቦረቀቀ (አንቦረቀቀ): አሰፋ፣ አንቧለለ (ሱሪን፣ የቀሚስን ቡጭቅ)።
ቦረቀቅ/ቦርቃቃ: የሰፋ፣ ሰፊ፡ ቦላሌ (ሱሪ)።
ቦረቦረ (በረበረ): ጐረጐረ፣ ፈለፈለ፡ ባዶ አደረገ፡ አገራ። ተመልከት: "ሞረሞረንና"፣ "ቦጠቦጠን"፣ "ሸረሸረን"።
ቦረቦር: ቀይ ዐፈር፡ ፈርካሳ (ውስጡ የሚቦረቦር)።
ቦረቦጭ (ጮች): በያይነቱ ቀለም ያለው ድንጋይ (ብርጭቆ መሳይ)።
ቦረቸ: ተንፍቀቀ (በንፉቅቅ ሄደ)።
ቦረና: በሲዳሞ ክፍል ውስጥ ያለ የቦረን ነገድና አገር።
ቦረን (ኦሮምኛ): የኦሮሞ ሁለተኛ ነገድ፡ በሬንቱማን የመሰለ።
ቦረንትቻ: በግንቦት መባቻ የሚጀምር የቦረን ጎሳ የአምልኮ ሥርዓት ነው። የአምልኮው ሥርዓትም በበረት ውስጥ በግ ማረድ፣ ጌሾ ያልገባበት ጕሽ መጠጣት፣ የተለያዩ ቆሎዎችን መብላት፣ እንዲሁም ከስጋው ብልት ሁሉ ቀንጥቦ ፈርስና ርሚጦ ጨምሮ የበረቱ ፉካ ላይ ማኖርን ያካትታል። ተመልከት: “ነበየ” እና የነቢን ቂጣ።
ቦሩ (ቡሬ): የበሬ ስምና መጠሪያ።
ቦራ (ኦሮ): ብጫነት ያለው ፈረስ።
ቦራ (ጕራጌና ወላሞ): በሬ።
ቦራሌ: ብርሌን የሚመስል ነጭ ቦረቦ (አንድ ዓይነት ነጭ ዕቃ)።
ቦራቂ (ዐጫጅ): ዐጫጅ (ወራቢ)።
ቦራቂ (ዎች): የቦረቀ፣ የሚቦርቅ (የሚዘል)፡ ዘላይ።
ቦሬ: ዝኒ ከማሁ፡ ነገረ ግልጥ (ፎለፎል)።
ቦሬሳ: የአፄ ዮሐንስ የስም ቅጽል፡ ወይም ፉከራ (ድንፋታ)፡ “ወሪሳ”። ምሳሌ: “ቦሬሳው ካሳ ይዋጋል ከቱርክ እንኳን ካንካሳ። ”
ቦርማ: የቦራ ዓይነት በሬ፡ ፊቱ ነጭ፡ ቦራን የሚመስል።
ቦርሳ: የገንዘብና የወረቀት መያዣ፡ የዕቃ መክተቻ (ኰረጆ፣ ማፉዳ)። ማስታወሻ: “ቦርሳ” ጣሊያንኛ ነው።
ቦርቅ: የሚዘል ውሃ (ቦቅ)።
ቦርቦር አለ: በገርነት (በየዋህነት) ተናገረ፡ ከተንኰል ባዶ ሆነ።
ቦርቦርቲ (ጌራ): የብረት ቆብ፡ የራስ ቍር።
ቦርቧራ: ገር፣ የዋህ፡ ተንኰል የሌለበት ሰው።
ቦርደዴ: በሐረርጌ አውራጃ ከዐዋሽ ቀጥሎ የሚገኝ ቀበሌ (በረሓ፣ ምድረ በዳ)።
ቦሸሽ: የሸሸ፣ የጠፋ (የታጣ) ኮከብ። ምሳሌ: “አስታር ቦሸሽ” እንዲሉ።
ቦቀረ (ዕብ ባቃር): መረመረ (ፈተነ)፡ ቈንጮ (ያለ)፡ አሻራን በጥቂቱ ላለ፡ ሳዱላ አወጣ።
ቦቀቦቅ/ቦቅቧቃ: የተንቦቀቦቀ፣ የሚንቦቀቦቅ፡ የፈሰሰ (የወረደ)፡ ፈሪ (ጡርቂ)።
ቦቂት: የዱሮ ነፍጥ ባለ፪ ናስ ማሰር፡ ቦቂት ያሰኛት ናሱ ነው።
ቦቂት: ጠመንዣ፡ "ቦቃ"።
ቦቃሪ: የቦቀረ፣ የሚቦቅር (የሚላጭ)።
ቦቅ: ኃይለኛ ዝናም፡ ቤት የሚነድል (የሚያፈርስ) ፈሰስ።
ቦቅ: ፈሰስ፡ "ቦቀቦቀ"።
ቦቅማ: የቦቃ ዓይነት፡ የቦቃ ወገን።
ቦተረፈ (ተረፈ): ነከሰ፡ አብዝቶ ቦጨቀ (ቂጥን፣ እንትንን)፡ ባጥኖ (ቦቆ) ወሰደ።
ቦታ (ዎች) (ዐጸድ፣ መካን): ስፍራ (ሰፈር)፡ ማደሪያ (መኖሪያ)፡ ቤት (ዐጥር፣ ቅጥር) ያለውና የሌለው (ወጀድ፣ በዓት)። ማስታወሻ: “ቤት” እና “ቦታ” አንድ ዘር ናቸው።
ቦነቸ: ቦከቦከ፣ በሰበሰ።
ቦነነ: በቁሙ "በነነ"።
ቦና (ኦሮ): በጋ፣ ድርቅ። ምሳሌ: “የቦና ጥጃ” እንዲሉ።
ቦከቦከ (በኍበኈ): ወፈረ፣ ደነደነ፣ ሠባ፡ ቦነቸ፣ በሰበሰ፣ ሸተተ።
ቦካ (ላካ): ከበሬና ከበግ ሆድ የሚገኝ እንክብል (ወርቅና ብጫ የሚመስል)። ማስታወሻ: ሐረርጌዎች "ላዙና" ይሉታል። አጠቃቀም: ጋሎች በራፊ ቋጥረው በጠጅ ውስጥ ሲያደርጉት ጠጅን በፍጥነት ያፈላል (ያደርሳል)። ሕንዶች ግን "ሱካር" ለሚባል በሽታ ከሻይ ጋራ ይጠጡታል።
ቦካ (ብሒእ፣ ብሕአ): በቁሙ ደረቀ፡ መጻጻ ሆነ፣ ሖመጠጠ፣ ኮመጠጠ።
ቦኸየ (ቦሐ፣ በርሐ): በራ፣ ተገለጠ፡ በራ ሆነ፣ ተመለጠ፣ ነጣ።
ቦዘ (ዕብራይስጥ፡ ባዝ): ተናቀ፣ ተሰደበ፣ ተዋረደ፡ ደከመ፣ ፈዘዘ፣ ዘነጋ (የዓይን፣ የልብ)።
ቦዘነ (ባዘነ): ታከተ፣ ደከመ፣ ተኛ፣ ተጋደመ፣ ሰነፈ፣ ዐረፈ፡ ተዘለነ፣ ተዘለለ፣ ዞላ ዋለ። ቦዘነ (ሥራ): ቀረ፣ ታጐለ፣ ቆመ (ሥራው)።
ቦዘና ሹሮ: ክትፎ ያለበት ሹሮ ወጥ።
ቦዘኔ: የቦዘን፣ ቦዘናዊ፣ ቦዘን ወዳድ። ምሳሌ: “ምን ያመጣል ሠኔ፡ ምን ይሠራል ቦዘኔ” እንዲሉ።
ቦዘን: ሀኬት፣ ስንፍና፣ ዞላ።
ቦዘንተኛ (ኞች): ሀኬተኛ፣ ሰነፍ፣ ሥራ ፈት።
ቦዘንተኛነት: ሀኬተኛነት፣ ዞላነት።
ቦዛኝ (ኞች): የሚቦዝን፣ የሚሰንፍ።
ቦዝ (ዕብራይስጥ፡ ቡዝ): ፈዛዛ፣ ዝንጉ፡ የተናቀ፣ የተዋረደ።
ቦዝ (ድምፅ): ሁለት የበገና ዥማት፡ በድምፅ ከሊቃውንትና ከአማሪት የሚያንስ።
ቦዝ አንቀጽ: ገቢር ከመሳብ በቀር አንቀጽ የማያስቀርና የማያስር (ደካማ አንቀጽ)። ምሳሌ: “ዐስቦ፣ ዐውቆ፣ ገድሎ” የመሰለው ሁሉ። “ኖሮ ኖሮ ከሞት፡ ዞሮ ዞሮ ከቤት” እንዲሉ። ማስታወሻ: ገቢር መሳቡም አንቀጹ ገቢር ሲሆን ነው። ማስታወሻ: "አቦዘ" (አዘነጋ፣ አፈዘዘ)። "ቦዘነን" ተመልከት፡ የዚህ ዘር ነው።
ቦዠቦዠ/አንቦዠቦዠ: ከመጠጥ የተነሣ ሰውነትን አሞቀ፣ አስደሰተ፡ ድካምን አራቀ፡ አብረዠረዠ።
ቦየ: ተማሰ፣ ተቈፈረ፣ ተገመሰ።
ቦይ (ዮች): የክረምትና የበጋ ውሃ መሄጃ (መውረጃ)፡ በእርሻና በሜዳ መካከል የተማሰ (የተገመሰ) መስኖ። ምሳሌ: “ቦይ ለውሃ፡ ጐመን ለድኻ” እንዲሉ። ሌላ ቋንቋ: በእንግሊዝኛ ቋንቋ ግን "ልጅ" (boy) ማለት ነው።
ቦደሰ (በጠሰ): ገመሰ፣ ጐመደ (የመሬት፣ የወፍራም ገመድ፣ የአካል)።
ቦደነ (ልብስ): ልብስን ከቀኝ ብብት በታች አደረገ፡ ቀኝ እጁን አወጣ።
ቦደነ (ወሰነ): በመቅን ወረሰ፣ ተለመ (የድንበርንና የወሰንን አጠገብ)።
ቦደነ: ጠመረ፣ ገጠመ፡ ዐንገት ያዘ።
ቦዳ: ጭንጫ ግርግራ የሌለበት ወፍራም መሬት፡ ቀልዝ።
ቦዳሳ: ገማሳ፣ በጣሳ።
ቦዳሽ: የቦደሰ፣ የሚቦድስ፡ ጐማጅ።
ቦዳኝ: የቦደነ፣ የሚቦድን፡ ገጣሚ፣ ጠላሚ።
ቦድስ: ጥቍር፣ ውዥግራ።
ቦገቦገ/አንቦገቦገ: አንበለበለ፣ አነደደ፣ አበራ፣ አዘለለ (ነደደ፣ ዘለለ)።
ቦጋለ (ቦግ አለ): ፈጥኖ በኃይል በራ፡ ሷፋ አለ፡ በረቀ።
ቦጋለ/ቦጋለች: የወንድና የሴት ስም፡ "ዐይናሞች" መሆናቸውን ያሳያል።
ቦግ ቦግ አለ: ተግ ተግ አለ፡ ተንቦገቦገ።
ቦግ ቧ አለ: ቶሎ በራ።
ቦግ: መብራት፣ መዝለል።
ቦግታ: ብልጭታ፡ ነጸብራቅ፡ የመብረቅ ብርሃን።
ቦጠለቀ (ቦለቀ): ከፈለ፣ ሠነጠቀ፡ በኀይል አወጣ (የነገር፣ ያክታ)።
ቦጠቦጠ: በተበተ፣ ቦረቦረ፣ ጐረጐረ፣ ጐጠጐጠ፡ ውስጥ ውስጡን (ልብ ልቡን) በላ፣ ተመገበ።
ቦጥቧጭ: የሚቦጠቡጥ፣ የሚቦረቡር፡ ጐርጓሪ።
ቦጨረቀ (ጨረቀ): ረገጠ፣ መታ (ውሃን)።
ቦጨረቅ/ቦጭራቃ: የሚረግጥ፣ የሚመታ።
ቦጨቀ (በላ): በላ፣ ነከሰ፣ ቀደደ (የሰውን ሥጋ ወሰደ)።
ቦጨቀ (በጨቀ): ባዘተ፣ ዐደ፡ ቈረጠ (ደም እስኪወጣ)፡ ዐከከ (የዳመጠ፣ የሣር፣ የገላ፣ የአንገትጌ)።
ቦጨቀ (ተማ): አማ፣ ስም አጠፋ።
ቦጨቦጨ: ተበጠበጠ፣ ታወከ፡ ፍልቅ ፍልቅ አለ፡ ፈሰሰ።
ቦጨቦጭ: ደቃቅ አሸዋና ቦረቦጭ (የብርሌ ዓይነት) ድንጋይ በዶሮ መቋደሻ ውስጥ የሚገኝ።
ቦጫቂ (በጫቂ): የቦጨቀ፣ የሚቦጭቅ፡ የሚያጭድ፣ የሚባዝት።
ቦጭረቅ ቦጭረቅ አለ: ተንቦጫረቀ።
ቦጭቦጭ አለ: ዋለለ፣ ጮኸ (የንስር ውሃ)።
ቦፌ: ዝናብ የመታው (ያበሰበሰው) እንጨት፡ ውፍረትና ቅለት ያለው ልብስ።
ቦፍ: መውደቅ።
ቧ (ቦግ): መብራት፣ ጁግ (ቦግ) ማለት።
ቧ አለ (ቦሐ): በራ፣ ጁግ (ቦግ) አለ።
ቧ: የ... ወራሽ።
ቧሒት (ቡሓዊት፣ እንተ ቡሕ): የተራራ ስም፡ በስሜን ወረዳ የሚገኝ ረዥም የቅዱስ ያሬድ ተራራ። ታሪክ: “ዘወትር በላዩ ከሚታየው በረዶና ጉም የተነሣ ሻሽ ጠምጣሚ ደብተራ ስለመሰለ ቧሒት ተባለ” ይላሉ። ሌላ ስም: ፈረንጆች ግን "ራስ ዳሸን" (ራስ ዘዐሸን) ይሉታል፡ "ደ" የፈረንሳይኛ ዘርፍ አያያዥ ነውና፡ “የበረዶ ዐሸን ራስ” ማለት ነው። ማስታወሻ: ደግሞም በአረብኛ "ደ" እና "ዘ" ይወራረሳሉ (ዳል፣ ዛል)።
ቧሒት: ተራራ (ቡሕ፣ ቡሓ፣ ቧሕ)።
ቧሔ (ሙዚቃ): ከመንደርደሪያ ቀጥሎ ያለ የመወድስ ሐረግ (ቤት መምቻ ያይዶለ)።
ቧሔ (እንስሳ): በራሱ ላይ ነጭ ያለበት የኖኅ ቍራ፡ የአሞራ ሁሉ ማእድ ባራኪ። ማስታወሻ: "የቧሕ ቡሕማ" "የቡሕ" ማለት ነው። "ቧሔ" ቅጥልና በቂ መሆኑን አስተውል።
ቧሔ: ነጭ ዐረግ፡ የአረግ ሬሳ፡ ዕጸ ሳቤቅ። ምሳሌ: “ቧሔ ዐረግ” እንዲሉ።
ቧሕ/ቡሕ: ሦስተኛውን "ቡሕ" ተመልከት።
ቧለተ: ተፌዘ፣ ተተረበ፣ ተዘበተ፣ ተቀለደ።
ቧለው: የሰው ስም፡ "ቧ"።
ቧለው: የሰው ስም። “ቧ አለው፣ ቧ ያለው” (ዐይናማ) ማለት ነው። “ደጃች ቧለው” እንዲሉ። "ቡሕን" ተመልከት።
ቧልተኛ (ኞች): ዋዘኛ፣ ተረበኛ፣ ቀልደኛ። ተረት: “ስምህ ማነው?” “ላገር አይመች። ” “ማን አወጣልህ?” “ጎረባብቶች። ” “እናትህ ማነች?” “ሳልወለድ ሞተች። ”
ቧልተኛነት: ዋዘኛነት፣ ቀልደኛነት።
ቧልት: ፌዝ፣ ከቁም ነገር የተለየ፡ ዘበት (ተረብ፣ ዋዛ ፈዛዛ፣ ቀልድ)።
ቧምቧ: (ዝኒ ከማሁ)። ዘሩ (ቧቧ) "አንቧቧ" ስለሆነ "ቧንቧ" ተብሎም ሊጻፍ ይችላል።
ቧምቧ: በቁሙ "ቦምባ"።
ቧሪ (ዎች): የቧጨረ፣ የሚቧጭር (የሚጭር)፡ ጫሪ፣ ጫሪ።
ቧሸሸ (ሸሸ): ሸሸ፣ ጠፋ (ታጣ)፡ ዕልም አለ።
ቧቀሰ (ዕብ ባቃሽ): ደከመ፣ ሰለተ፣ ጠወለገ።
ቧቧ (አንቧቧ) (ነብሐ፣ አንባሕብሐ): አንፋፋ፣ አንሿሿ፡ አወረደ፣ አፈሰሰ (የአሸንዳ፣ የወንዝ፣ የንባ)። ማስታወሻ: "እንቧን" ተመልከት፡ የዚህ ዘር ነው።
ቧንግዝ: ፋደት (ጐጃም)።
ቧገተ (ወገተ): በቁሙ፡ ዞረ፣ ተንከራተተ፡ ለመነ፣ ቀለተ።
ቧገታ: ቀለታ፣ ልመና።
ቧጋች (ቾች): የቧገተ፣ የሚቧግት (የሚዞር፣ የሚቀልት)፡ ቀላች፣ ለማኝ።
ቧጠጠ፡ መላልሶ ወጋ፡ ረገጠ፡ በሰው፣ በከብት ላይ ጨፈረ (ውሻው፣ በሬው)።
ቧጠጠ: ጠጠ፣ ጨረ፡ ጠረገ (ገላን፣ ጭቃን፣ ዐዛባን፣ ጕረሮን)።
ቧጣጭ: የቧጠጠ፣ የሚቧጥጥ (የሚጥጥ)፡ ጠራጊ፣ ማሪ (ነብር፣ ወጌሻ)።
ቧጨረ: ጨረ፣ ማረ፡ ሰነዘረ፣ ዐከከ።
No comments:
Post a Comment