Tuesday, June 10, 2025

                                 

: ፲፮ኛ ፊደል በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ። በፊደልነት ስሙ "ዐይን"፡ አኃዝ ሲኾን ፬፸ ይባላል።

: የሐኀ ወራሽ፡ ወራሽነቱንም ወደ ፊት ይመለከቷል። "ኣን" እይ።

ዐለለ (ዐልሎ ዐለለ፡ ሤረየ): የስፌት ሣርን፡ ፈትልን በያይነቱ ቀለም ነከረ፡ አገባ። (በደም ዐለለ): በደም ውስጥ ዘፈቀ፡ ለወሰ (ልብስን፡ ገላን)

ዐለላ (ዎች): ቀለም የገባ ስንደዶ፡ አክርማ።

ዐለላ ሙዳይ: ዐለላ ዘርፍ፡ ሙዳይ ባለቤት ነው፡ በዐለላ የተሰፋ ሙዳይ።

ዐለመ (ሐለመ): ዕልም አየ።

ዐለመ (ዐልሞ ዐለመ): አመለከተ፡ ምልክት ሰጠ። (ሦስተኛውን ዐለበ ተመልከት)

ዐለመ: አጠፋ፡ አወደመ።

ዐለቀ: ተጨረሰ፡ ተፈጸመ፡ ተደመደመ፡ ተቈረጠ፡ ሞተ፡ ሽቅ አለ፡ ተጠነገደ። "ውሃ ቢደርቅ ዓሣ ያልቅ" እንዲሉ።

ዐለበ (ሐለበ): ከላም፡ ከበግ፡ ከፍየል፡ ከጐሽ፡ ከግመል የእንስቶቹን ጡት በጣቱ እየሳበ ወተትን አንሯሯ፡ በጮጮ፡ በቀራፎ፡ በወጭት፡ በሳሕን ውስጥ አፈሰሰ፡ ጨመረ።

ዐለበ (ሆድ): እጅግ አስቀመጠ፡ አስቀዘነ። "ጠገተን" ተመልከት።

ዐለበ (ትግ): ለበሰ፡ ታጠቀ።

ዐለበ (ዐለመ፣ አመረ): ምልክት አደረገ፡ ጥይት አጐረሠ፡ አነጣጠረ፡ አዘገበ፡ ደከረ።

ዐለበ (አንጀት): የምግብንና የውሃን ቅሬታ አወጣ።

ዐለበ: ላምና ጥጃን አገናኘ።

ዐለተ ማሪያም (ዐራተ ማርያም): የማርያም ዐልጋ። በሰላሌ ወረዳ ያለ አገር፡ ጥንታዊ የማርያም ሰበካ አጥቢያ።

ዐለት (ዐራት): ዐልጋ (መንበር)

ዐለት: የወንዝ ደንጊያ።

ዐለንጋ: ጕማሬ፡ አኰርባጅ፡ መግረፊያ፡ መሸንቈ (ምሳ፲፡ ፲፫) በአንቆቅልሽም ዐልቅት ዐለንጋ ይባላል። "ትንሽ ዐለንጋ ወንዝ ለወንዝ ትላጋ" (ምሳሌያዊ አባባል) (የምድር ዐለንጋ): ቱልት።

ዐለያ ነሽ: የሴት ስም፡ ዐሳቢ ነሽ። ዳግመኛም በዐሊ አንጻር ዐለያን ልዕልት ብሎ መተርጐም ይቻላል።

ዐለጠ (ሐለጸ፡ ዐረ ኸለጸ፡ ቀላቀለ): ዐልጫ ኾነ፡ ጣም ዐጣ (ወጡ)

ዐለፈ (ኀለፈ): ኼደ፡ ተራመደ፡ ተሻገረ፡ ዘለለ (፩ሳሙ፡ ፱፡ ፳፯) "ለፋ" ብለኸ "አለፋን" እይ። (ሰዓቱ ዐለፈ): ስድስት የነበረው ሰባት ሆነ።

ዐለፈ: ለሰጠው፡ ላደረገው "አለሁ" አለ፡ ተያዘ።

ዐለፈ: ሞተ፡ ጠፋ፡ ነፍሱ ወደ ሰማይ፡ ሥጋው ወደ መቃብር ወጣ፡ ወረደ። "እከሌ በጁ ነፍስ ስላለፈበት አገሩን ለቀቀ"

ዐለፈ: ተረፈ፡ መጣ። "ያን ለት ገንዘብ ስንካፈል ያንተ ወደኔ ዐልፋልና፡ እመልስልሃለሁ"

ዐለፈ: ተሻረ፡ ቀረ፡ ተተወ። (ጕልበት ዐለፈበት): የሥራ ዋጋ ጨርሶ አልተቀበለም፡ ቀርቶበታል።

ዐለፈ: ተነሣ፡ ተወሰደ (ዳን፬፡ ፴፩)

ዐለፈ: ደፈረ፡ ትርፍ ነገር ተናገረ። "ዐለፍከኝ" እንዲል ተማጋች።

ዐለፈ: ገፋ። "ወሰንን ዐለፈ" እንዲሉ።

ዐለፈ: ጥሩ ሆነ፡ አማረ።

ዐለፈለት: አገኘ፡ ተረፈው፡ ችግር ለቀቀው፡ እንጀራ ጠገበ።

ዐለፈበት: ዐጣ፡ ነጣ፡ ደኸየ፡ ተቸገረ።

ዐለፋ: በበጌምድር ክፍል ያለ አገር።

ዐለፋ: ፍድፋጅ (የደረቀ ቅጠል ወይም ፍሬ)

ዐለፌታ: ትርፍ ነገር።

ዐለፍ: ዝኒ ከማሁ ለዐላፊ፡ የዘለለ። "ይህ ተክል ስለ በዛ አንድ ዐለፍ ንቀለው"

ዐለፍከኝ: ዘለልከኝ፡ ተውከኝ፡ ደፈርከኝ፡ ሰደብከኝ፡ "አንቱ" ብለኸ "አንተ" አልከኝ።

ዐሊ (ዐረ): ልዑል፡ ከፍ ያለ።

ዐሊብ (ሐሊብ): ማለብ (አርእስት)

ዐሊብ (ሐሊብ): ትኵስ ወተት፡ የበሰለ ደም፡ ነጭ የሥጋ ፈሳሽ፡ የሕፃን፡ የግልገል፡ የጥጃ፡ የውርንጭላ፡ የቡችላ ምግብ (ጥሬ ዘር)

ዐሊብ (ሐይብ): ዐይብ (ተረት): "ላም አለኝ በሰማይ፡ ወተትም አልጠጣ፡ ዐሊቡንም አላይ። " (የነገረኛ ቃል): የና ይዋረሳሉና ዐይብ ዐሊብ ተባለ። "ዐየበን" ተመልከት።

ዐላሚ (ዎች): ያለመ፡ የሚያልም፡ ባለ ዕልም።

ዐላማ (ዎች): መጠሪያ፡ ብራኳ፡ ጊጤ (በጥይት የሚመቱት)፡ በሹል ዕንጨት።

ዐላማ: የዓለም መንግሥታት ሁሉ የነጻነትና የሃይማኖት ምልክት፡ ባንዲራ፡ በያይነቱ ቀለም ያለውና የሌለው፡ የሐር ልብስ ክፍል፡ የቀስተ ደመና ምሳሌ (ዘፀ፲፯፡ ፲፭፡ ዘኍ፪፡ ፫፡ ኤር፶፩፡ ፲፪) ይኸውም በሰንደቅ ላይ የሚሰቀል፡ የሚንጠለጠል ነው። "ሰንደቅ ዐላማ" እንዲሉ።

ዐላማ: ድምር፡ ርጥብ የደመራ ዕንጨት፡ ነበልባል ባለው ችቦ የሚወጋ።

ዐላቂ: የሚያልቅ፡ የሚጨረስ፡ ጥናት፡ ጥንካሬ የሌለው።

ዐላቢ (ዐላሚ): ያለበ፣ የሚያልብ፡ አነጣጣሪ

ዐላቢ (ዎች) (ሐላቢ): ያለበ፡ የሚያልብ። "ላም ዐላቢ" እንዲሉ።

ዐላባ: ነጭ ማዕድን፡ ማንኛውም ምድር የምትሰጠው ውጤት።

ዐላባ: እህል በያይነቱ። "ዐላባ ገለባ" እንዲሉ።

ዐላባ: ከጕራጌ ነገድ አንዱ።

ዐላባ: የምድር ፍሬ፡ ወተት የሚመስል ጠመቅ።

ዐላይ (ዮች): ያለለ፡ የሚያልል፡ ቀለም አግቢ።

ዐላፊ አግዳሚ: ዐላፊ ጠፊ እንዲሉ።

ዐላፊ: ዋቢ፡ ዘበኛ።

ዐላፊ: ያለፈ፡ የሚያልፍ፡ በቀጥታ ኻያጅ።

ዐላፊነት: ዐላፊ መኾን፡ ዋቢነት፡ ተያዥነት።

ዐላፎች: ዐላፊዎች፡ ኻያጆች (ኢሳ፶፩፡ ፳፫)

ዐሌ አለ: አስተባበለ፡ "የለም""አይደለም" አለ። "ሸፈጠን" "ካደን" እይ።

ዐሌ: ዝኒ ከማሁ ለዐሎ (ከዐሎ ጋር ተመሳሳይ)

ዐልቅታም: ዐልቅት ያለበት፡ የበዛበት ምንጭ ዦር።

ዐልቅት: ከረጢትነት ያለው የውሃ ውስጥ ተንቀሳቃሽ እንስሳ (ኢሳ፲፬፡ ፳፫) በበሬ ጕረሮ ተለጥፎ ደም እየጠጣ ያድጋል። (ተረት): "ዐልቅትና ድኻ ውሃ ለውሃ" (ሁለቱም በቀላሉ የሚረሱ ወይም የሚናቁ ናቸው ለማለት)

ዐልባ (ትግ ዐለባ): ልብስ፡ ዝምዝማትና ጥልፍ ያለው ጌጠኛ የሴቶች ሱሪ። "ልብን" እይ።

ዐልቦ መጋት: ርባና ቢስ ሥራ

ዐልቦ: ከወርቅና ከብር በዶቃ አምሳል የተሠራ የሴቶች እግር ጌጥ (ኢሳ፫፡ ፲፰) (ዐልቦ ማለት የወርቁንና የብሩን መቅለጥና መፍሰስ ያሳያል) (የበቅሎ ዐልቦ): ወርቅ ቅብ፡ የብር ዶቃ በበቅሎ ዐንገት የሚጠለቅ። "አልባን" "አልቦን" አስተውል።

ዐልቦ: ጡትን ስቦ ጐትቶ ወተትን ውጥቶ

ዐልቴት: የዛፍ ሙጫ።

ዐልጋ (ዐለገ): አራት እግር፣ ኹለት ዘንግ፣ ኹለት ደንብ ያለው፡ መካከሉ በጠፍር የተታታ መኝታ። (ረዥሙ ዙፋን፡ ዐጪሩ ድንክ ይባላል፡ ሲበዛ ዐልጋዎች ያሰኛል) (ጐበዝ ዐልጋ): መካከለኛ። (የብረት ዐልጋ): ከብረት ብቻ የተሠራ፡ በሽቦ የተታታ። (የወርቅ ዐልጋ): ከወርቅ የተበጀ፡ የተዘጋጀ።

ዐልጋ ነቀነቀ: ከዳሸፈተ

ዐልጋ ወራሽ: የአባቱን ዙፋን የሚወርስ የንጉሥ ልጅ።

ዐልጋ: የአንድ ንጉሥ ግዛት፡ መንበረ መንግሥት። "ባልጋ በመንግሥት" እንዲሉ።

ዐልጋ: የጣራ መሥሪያ ረዥምና ሰፊ ቈጥ።

ዐልጫ መረቅ: የመረቅ ዐልጫ፡ ወይንም ያልጫ መረቅ። (በቅቤና በጨው፣ በቃሪያ በርበሬ፣ በነጭ ሽንኵርት የተቀቀለ የሥብ መረቅ፡ ጤፍ እንጀራ እየፈተፈቱ ይበሉበታል)

ዐልጫ: በርበሬ ያልገባበት የሹሮ፡ የሥጋ ወጥ።

ዐልጫነት: ዐልጫ መኾን።

ዐልፎ ዐልፎ መጣ: አንዳንድ ጊዜ እያሰለሰ።

ዐልፎ: ቀርቶ፡ ተትቶ።

ዐልፎ: ተራምዶ፡ ዘሎ። "ዐልፎ ካያጅ" እንዲሉ።

ዐሎ (ዐለወ): ሐሰት፡ ክሕደት። "ዐሎ ብሎ የተረታ፡ መኻል አገዳውን የተመታ" እንዲሉ። "አልን" ተመልከት።

ዐሎ አለ: ካደ፡ አላመነም፡ አልተቀበለም።

ዐሎ: ብድራት፡ በቀል (አፀፋ)

ዐሎኛ: ከዳተኛ፡ ሸፍጠኛ፡ ተቃራኒ።

ዐሎውን ከፈለ: ብድሩን መለሰ፡ አጥቂውን አጠቃ።

ዐመለ ልስልስ: ደግ ሰው፡ ደንሴ አይቆረቍሬ፡ አያስቀይሜ።

ዐመለ ቢስ: ዐመለ ክፉ (መጥፎ ጠባይ ያለው)

ዐመለ ናጫ: ጨቅጫቃ ሰው።

ዐመለ ወርቅ: የሴት ስም።

ዐመለ ጌታ: በውርደት ቦታ የማይገኝ ሰው።

ዐመለ: ለመለመ፡ ወየበ፡ ደነበሸ (ከቅዝቃዜ የተነሣ)

ዐመለኛ (ኞች): ልማደኛ፡ ሠሠኛ፡ መጥፎ ዐመል ያለው ሰው።

ዐመል አወጣ: ጠባዩን፡ አካኼዱን ለወጠ፡ ከፋ፡ ክፉ ሆነ።

ዐመል እሳት: ጠንቋዮች ቁጡነትና ተናዳጅነት ያለውን ሰው "ኮከቡ ዐመል እሳት ነው" ይሉታል።

ዐመል የለሽ: ቈጭባራ (ትልቅ ነገር በትንሽ ነገር የምትለውጥ) "ዐመል የለሽ የሰው አትበዪ፡ ሀብት የለሽ የራስሽን አትበዪ" እንዲሉ።

ዐመል: ልማድ፡ ሐራራ፡ ሡሥ (ጥሩም ይሁን መጥፎ ልማድ)፡ በሥራ የሚገለጥ ክፉና ደግ ጠባይ። (ተረት): "ዐመልኽን በጕያሽ፡ ሥንቅሽን በሃያሽ" (መልካም ባህሪህን እንደ ንብረት ያዝ፡ ስንቅህን እንደ ገንዘብህን ጠብቅ) "ዐመል ያወጣል ከመኻል፡ ዐመል ያገባል እመኻል" (መልካም ወይም መጥፎ ባህሪ በህብረተሰብ ውስጥ ከፍ ወይም ዝቅ ያደርጋል) "ሞት ላይቀር ፍራት፡ ዐመል ላይቀር ቅጣት" (ሞት እንደማይቀር እንደምትፈራ ሁሉ መጥፎ ዐመል ቅጣት እንደሚያስከትል እወቅ) "መለመለ" ብለሽ "አመለመለን" እይ።

ዐመል: አኳዃን፡ ኹኔታ። "ጐባጣን እንዴት ይቀብሩ ቢሉ፡ እንዳመሉ" (ምሳሌ፡ ነገሮችን እንደሁኔታው ማስተናገድ)

ዐመል: የኮከብ ስም፡ የበግ አውራ የሚመስል የመጋቢት ኮከብ (አሪየስ)

ዐመል: የግስን አካኼድ የሚለውጡ "" እና """" እና "" ዐመል ይባላሉ (ሰዋሰዋዊ ቅጥያዎች)

ዐመልሳ: በመርሐ ቤቴ ክፍል ያለ አገር፡ ነት የሚሠራበት።

ዐመመ: ራስን አዞረ፡ ሆድን ቈረጠ፡ ጐንን ወጋ፡ እጅና እግርን ቈረጠመ፡ ነዘረ፡ በሸተ፡ ጤና ነሣ።

ዐመመ: በዛ፡ በረከተ (ግእዝ)

ዐመም (ሐሚም): ማመም።

ዐመም አደረገ: በቀላል ዐመመ።

ዐመሰ: በቀላል አሞቀ፡ አንቃቃ፡ የላዩን ወደ ውስጥ፡ የውስጡን ወደ ላይ ገለበጠ፡ አዛወረ፡ የስጥ።

ዐመሰ: አምስት አደረገ (በአምስት ከፈለ)

ዐመሰ: አወከ፡ አተራመሰ (ሕዝብን)

ዐመቀ: አበቀ፡ ወደ ውስጥ ተጫነ፡ ጨቈነ፡ ረጠጠ (ዶቄትን፡ ዐመድን፡ እብቅን) "ደረነቀን" እይ፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው።

ዐመቀ: ጥልቅ አደረገ።

ዐመቀመቅ (ዕመቀ ዕመቅ): የጥልቅ ጥልቅ ውቅያኖስ፡ አንጦርጦስ (ጥልቁ የባሕር ውስጥ)

ዐመቅ (ዕመቅ): ጥልቅ ጕድጓድ።

ዐመቅ ወረደ: ሲኦል ገባ፡ ከነነፍሱ ወይም ሙቶ (መዝ፻፮፡ ፲፯)

ዐመተ (ሐመሰ): አመሰ (ክትፎን)

ዐመተ (ትግርኛ ሐመተ): ቈረጠ፡ መተረ፡ ከተፈ።

ዐመተ: በላ፡ አነደደ፡ አቃጠለ፡ አከሰለ፡ ዐመድ አደረገ። "ዐመደን" እይ።

ዐመተ: ዐማት አደረገ (ልጁን አጋባ)

ዐመቸ: ዐማች አደረገ።

ዐመደ በል: ዐመድ የሚቅም፡ የሚበላ አህያ።

ዐመደ ፈጭ: ዐመድ የሚፈጭ ሕፃን።

ዐመደ: ዐመተ (አጨደ)፡ ቈረጠ፡ ደፈጠጠ።

ዐመደ: እሳት አጠፋ፡ ዐመድ አደረገ፡ አደቀቀ።

ዐመደ: ደገፈ፡ ተሸከመ።

ዐመዳም (ሞች): ባለዐመድ፡ ወዘ ቢስ (ምንም የሌለው)፡ ነጮ (ቆዳው ነጣ ያለ)፡ ድኻ፡ ንጣታም፡ ደረቅ።

ዐመዳይ: ዐመድ መስሎ በብርድ ጊዜ የሚዘንም፡ በውሃና በመሬት ላይ እንደ መስተዋት የሚጋገር ብትን ውርጭ፡ እህል አጥፊ፡ ነጭ ዐመድማ። "ዋግን" እይ።

ዐመዴ: የንብ ስምና መልክ።

ዐመድ መስኩ: በዐመድ ላይ የሚቀመጥ፡ የሚተኛ።

ዐመድ ማዶ (ዐመድ ማዱ): በዐመድ ላይ የሚበቅል ቅጠል፡ ዐመድ ወዳድ፡ ማዱ ዐመድ የኾነ።

ዐመድ ዐፋሽ: ከወዳጁ ወረታ የማያገኝ። "እጅን" እይ።

ዐመድ ያጠለቀው ጕልቻ የላቀው: ፍጹም ድኻ፡ ምስኪን፡ ይልሰው፡ ይቀምሰው የሌለው።

ዐመድ: ብዛት። "ግንድን" ተመልከት።

ዐመድ: እሳት የበላው፡ ያቃጠለው፡ ነጭ የእንጨት፡ የድንጋይ፡ የመሬት ዱቄት፡ ኖራ፡ ዐቧራ (በረቅ ጕብጕባ) "ዘመድ ከዘመዱ፡ አህያ ከአመዱ" (ምሳሌ) (ተረት): "ያህያ ሥጋ ዐልጋ ሲሉት ዐመድ" (የማይረባ ነገር)

ዐመድማ (ሐመዳዊ): ዐመድ የሚመስል (አህያ፡ ፈረስ)

ዐመዶ: ነጭ ገብስ።

ዐመዶ: ነጮ (ቆዳው የነጣ)፡ አበቅማ።

ዐመጃ (ዐምጃ፡ ዐመጃይ (ሐመዳዊ)): ሰበከቱ ዐመድ የሚመስል ቅጠል፡ በወይና ደጋ የሚበቅል።

ዐመጃ ከዐመገ ቢወጣ የእንጨቱን ብዛት፡ ጥቅጥቅነት ያሳያል።

ዐመገ: ሰበሰበ፡ አከማቸ፡ መሰገ። (ገናና "" ተወራራሽ ስለ ኾኑ፡ በ"ዐመቀ" ፈንታ ባላገር "ዐመገ" ይላል)

ዐመጠ: ከዳ፡ ሸፈተ፡ ግብር ነሣ፡ ከለከለ፡ በደለ፡ ገፋ።

ዐመጠኛ (ዐመፀኛ): ከዳተኛ፡ ሽፍታ፡ ገፋኛ፡ በእጁ የገደለ፡ በቃሉ የበደለ (ዕዝ፬፡ ፲፱)

ዐመጠኛነት (ዐመፀኝነት): ዐመጠኛ መኾን (፩ሳሙ፡ ፲፭፡ ፳፫)

ዐመጥ (ዐመፅ): ክዳት፡ በደል (ኃጢአት)

ዐመፀ: ዐመጠ (ከዳ፣ ዓመፅ አደረገ)

ዐመፀኛ (ኞች): ዐመጠኛ።

ዐመፀኛው (ዋ፡ ይቱ፡ ቷ): ወንድና ሴትን ለመለየት ይነገራል (ኤር፫፡ ፲፩)

ዐመፅ (ዐመፃ): ዐመጥ።

ዐሙስ የቀን ቅዱስ: ፳፰ መጋቢት፡ ቅዱስ ቍርባን ለሐዋርያት የተሰጠበት።

ዐሙስ: ፭ኛ ቀን ከእሑድ (ሐሙስ)

ዐሙድ ላይ ተንከባላይ: አህያ። "" ባይን ተመልከት።

ዐሚ (ሐማዪ): ያማ፡ የሚያማ።

ዐሚተኛ (ኞች): ዐሚታ ወዳድ፡ አፉ የማያርፍ፡ ስም አጥፊ (ምሳ፩፡ ፲፱)

ዐሚታ ጠባቂ: ሲያውቅ አበድ አጫዋች፡ እንዲህ አሉ ባይ።

ዐሚታ: ዝኒ ከማሁ (ከዐሜት ጋር ተመሳሳይ)

ዐማ: ነቀፈ፡ ስም አከፋ። "ሰውን ሰው ዐማው፡ የራሱን ሳይሰማው" (ምሳሌ) "አፍ ሲያርፍ ወዳጁን ያማል" (ምሳሌ)

ዐማመመ: ቀረጣጠፈ፡ ቈራረጠ (ሰውነትን፡ ሆድን)

ዐማሚ (አሕማሚ): ያመመ፡ የሚያምም (በሽታ አምጭ)

ዐማምቻ: የጋብቻ ጋብቻ፡ እቱን ድሮ የእቱን ባል እት እንደ ማግባት ያለ ነው (የዘመድ ትዳር)

ዐማራ (ዐም ሐራ): "ዐም" ማለት ሕዝብ፡ "ሐራ" ማለት ነጻ። በተገናኝ "ነጻ ሕዝብ""ገዢነት እንጂ ተገዢነት የማይስማማው" ማለት ነው። "አማረን" አስተውል (ቃሉ ከማማር ጋርም ሊያያዝ ይችላል)

ዐማራ ሣይንት: የሣይንት ዐማራ። ሣይንት ባለቤት (ስፍራ)፡ ዐማራ ዘርፍ ኾኖ ቢተረጐም ግን "የአማራ አገር ሣይንት" ማለት ነው። ይኸውም ዐማርኛ የሚናገሩ ሰዎች መዠመሪያ በሣይንት እንደ ነበሩ ያስረዳል (የታሪክ እና የቋንቋ ምንጭ ማጣቀሻ) "ሣይንትን" ተመልከት።

ዐማራ: ዐማርኛ

ዐማራነት: ዐማራ መኾን፡ ተገዝሮ፡ ተጠምቆ፡ ማተብ አስሮ።

ዐማሬ: የስንዴ ስም፡ ውሃ የሚመስል ስንዴ (የስንዴ ዓይነት)

ዐማሬ: የአማራ ተወላጅ፡ የአማራ ዘር። የሣይንትም አባት "ዐማሬ" ይባል ነበር ይላሉ።

ዐማርኛ: ተዛዋሪ፡ ምስጢራዊ ነገር፡ መልካምና ክፉ ባንድ ጊዜ የሚያናግር ኅብር ቃል (የቃላት አሻሚነት)

ዐማርኛ: የአማራ ቋንቋ፡ ከግእዝ የሚወለድ፡ ከሱርስትና ከዕብራይስጥ፡ ከዐረብ የሚዛመድ ሴማዊ ልሳን።

ዐማሮ: የአገር ስም፡ በሲዳሞ ያለ አገር፡ የአማራ ዘር የነበረበት፡ ሌላም አፈታት ይኖረዋል።

ዐማሮች: ሺዎች፡ ላስቶች፡ በጌምድሮች፡ ጐዣሞች፡ ወሎዎች (የአማራ ሕዝብ ንዑስ ቡድኖች)

ዐማሽ (ሾች): ያመሰ፡ የሚያምስ፡ አዋኪ (አስረማሽ)

ዐማቂ: ያመቀ፡ የሚያምቅ፡ ረጣጭ።

ዐማቂት: የደም ምች። "ያመቀች የምታምቅ" ተብሎም ይፈታል።

ዐማት (ሐማት): የባል እናት። (ተረት): "ዐማትና ምራት ሳይስማሙ መሬት" (የዐማትና ምራት አለመግባባት)

ዐማት: የሚስት አባትና እናት። "ወንድ ዐማት""ሴት ዐማት" እንዲሉ። (ተረት): "ከሞተች ሚስቴ ምን አለኝ ካማቴ" (ምንም ጥቅም የሌለው ግንኙነት) "ለቅልብ ልብ ዐማት ሲሶ በትር አላት" (የዐማት ስልጣንና ተጽዕኖ) በግእዝ ግን ወንዱ ሐም፡ ሴቷ ሐማት ይባላሉ።

ዐማች (ሐማቲ): ያመተ፡ የሚያምት። (በጋማች): በግ ዐማች፡ የበግን (የፍየልን፡ የበሬን) ሥጋ እየቈረጠ የሚሸጥ።

ዐማች ሆነ (ሐመወ): ልጃገረድን አገባ።        

ዐማች: የልጅና የእት፡ ያክስት፡ የዘመድ ባል (ዮሐ፲፰፡ ፲፫) (ተረት): "ዐማች አስታርቆ ቀንበር አርቆ" (ዐማች የሚያስታርቅና ሸክምን የሚያቀል)

ዐማኑኤል: ስመ ተዋሕዶ፡ "ዐማኑ ከኛ ኤል" (አምላክ)"አምላክ ከኛ ጋራ" ማለት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው መኾኑን፡ የድንግል ማርያምን ሥጋ መልበሱን ያሳያል።

ዐማኔል: ዝኒ ከማሁ (ከዐማኑኤል ጋር ተመሳሳይ)፡ የሕዝብ አነጋገር ነው። "ሚጣቅ ዐማኔል" እንዲሉ።

ዐማጅ: ያመደ፡ የሚያምድ፡ ቈራጭ፡ ደፍጣጭ።

ዐማጊ: ያመጎ፡ የሚያምግ፡ መሳጊ።

ዐማጋ: ምሳግ፡ የሜዳ በረት፡ ቀዬ፡ የበር ውጭ።

ዐማጭ (ዐማፂ): ያመጠ፡ የሚያምጥ። "መጣን" እይ።

ዐሜት: ማማት፡ ነቀፋ።

ዐሜዳ: በ፭፻ .. የነበረ የሐበሻ ንጉሥ። ትርጓሜው "ብዙ ነህ" ማለት ነው። "ሐመደን" አስተውል።

ዐምሌ: የወር ስም፡ ፲፩ኛ ወር ከመስከረም። "ቅጠላም""ባለቅጠል" ማለት ነው። "ዐምሌና ናሴ" እንዲል ባላገር (ወራት አዝመራ የሚበዛባቸው ወይም በተለይ ለአንድ ነገር የሚስማሙ ሲሆኑ የሚነገር)

ዐምሞ: በዝቶ። "ቄሱ ዐምሞ ጠምጥሞ መጣ" (ቄሱ ብዙ ሰው አስከትሎ መጣ)

ዐምሳ አንድ (፶፩): ዐምሳና አንድ።

ዐምሳ እግር: የትል ስም፡ በክረምት የሚታይ ተንቀሳቃሽ፡ በስተፊት ሲነኩት ጥቅልል ይላል።

ዐምሳ: ጊዜ ፲፡ ወይም ጊዜ ፭፡ ፶። ተራ ቍጥር ሲሆን ዐምሳኛዐምሳኛው ይላል።

ዐምስተኚት: ዐምስተኛዪቱ ክፍል (ክፍልፋይ)

ዐምስተኛ (፭ኛ): የአምስት ወገን።

ዐምስተኛዋ: ያች ዐምስተኛ፡ የርሷ ዐምስተኛ።

ዐምስተኛው: ዐምስተኛ፡ የርሱ ዐምስተኛ።

ዐምስተኛዪቱ: ያች ዐምስተኛ።

ዐምስት አደረገ: አለ፡ በአምስት ከፈለ።

ዐምስት: የመደበኛ ቍጥር ስም፡ ፭፡ በአራትና በስድስት መካከል ያለ አኃዝ። የማዕርግና የተራ ቍጥር ሲሆን:

ዐምስትነት: አምስት መኾን።

ዐምስትያ: አምስት መቶ ድር (የጨርቅ መለኪያ)

ዐምስትዮ: ዐምስትዮሽ፡ ከአምስት አንድ የሆነ ሽርብና ድርብ ንብብር ነገር (የተደራረበ ወይም የተጣመረ ነገር በአምስት እጥፍ)

ዐምስቶ: የአምስት ሰው ጉባኤ፡ ወይም አንድነት።

ዐምሾ: ከአምስት አንድ (የአንድ ነገር አምስተኛ ክፍል)

ዐምቆ: ዐብቆ፡ ረጥጦ።

አምበላይ: ባለ ጥርር (ዐምበላይ)

ዐምበላይ: ዐውሎ ነፋስ፡ ባሕርን የሚደርጥ፡ ጣራን የሚገለብጥ።

ዐምበላይ: የዐምበል ወገን፡ ባለጥሩር።

ዐምበላይና ዐምባላይ ልዩዎች መሆናቸውን ልብ አድርግ።

ዐምበል (ለባሴ ሐንበል): ዐምበል ለባሽ፡ የፈረሰኛ ባልደራስ፡ ገሥጋሽ፡ ወራሪ፡ ጦር መሪ፡ የሰራዊት አዛዥ፡ ሻለቃ። "የሃምሳ፡ የሶስት ዐምበል፡ ሻምበል" እንዲሉ። "ዐጼ ቴዎድሮስ የሺሑን ጭፍራ አጋፋሪ ዐምበል (ሐምበል) አሉት" (ታሪ ቴዎድሮስ)

ዐምበል (ዐረ ሐንበል፡ ግእዝ ሕንባል): የፈረስ መጣብር፡ ከብርና ከወርቅ የተሠራ፡ ወይም ከነሐስ የተበጀ፡ ወርቅ ቅብ፡ ጕብጕብነት፡ ቀለበትነት ያለው የኮርቻ ጌጥ።

ዐምበል (ድርዐ እንግድዓ): ጥሩር፡ የደረት ልብስ፡ ውስጠ ነት፡ የብረት ጥብቆ፡ ሳንቃ መጋጠሚያ ያለው ሐርበኛ፡ ጦረኛ የሚያጠልቀው።

ዐምበል: ታፋንና እንቢያን ከፍላጻ የሚከልል፡ ከብረት የተዘጋጀ የፈረስ ቤዛ። "ጥሩርን" እይ።

ዐምበል: ከኒሻን በላይ ያለ ክብ የሐር ጥብጣብ ሰንደቅ ዐላማ። "እከሌ ባልአምበል፡ ኒሻን ዐምበል የሌለው ኒሻን ተሸለመ" እንዲሉ።

ዐምበሎች: መጣብሮች፡ ጥሩሮች፡ የጦር አለቆች፡ ባለጥሩሮች (ራእ፲፱፡ ፲፰) "ሐምበልና ዐንበል ከዐምበል ጋራ አንድ ነው - ይኸ ውም የሐንና የዐን የመንና የነን መወራረስ ያሳያል ")

ዐምበር: ሽቱ። "ዐንበር"

ዐምባ (ዐም ባ፡ ሕዝብ ): የተራራ ስም፡ ዕርድ፡ ምሽግ ያለበት ተራራ። ትርጓሜው "ሕዝብ አላት""አለባት" ማለት ነው (፩ሳሙ፡ ፳፫፡ ፲፬) (ተረት): "ቀን ቢደርስ፡ ዐምባ ይፈርስ" (ኢያ፮፡ ፳)

ዐምባ ራስ (የዐምባ ራስ): የዐምባ ሹም፡ ዋና፡ ግንባር ቀደም። (ተረት): "ከጐንደር ንጉሥ ያገር ዐምባ ራስ"

ዐምባ ራስ: የተራራ ራስ፡ ጫፍ።

ዐምባ ራስ: ጣብ የሚባል ጨዋታ።

ዐምባ ራስን የሚይዝ ባልአምባራስ ይባላል። "ባልን" ተመልከት።

ዐምባ ገነን: ንጉሥ ያልሾመው፡ ባላባትነት የሌለው፡ በተራራ፡ በመንደር የገነነ ሰው።

ዐምባ ጓሮ (የዐምባ ጓሮ): የዐምባ ኋላ፡ የመንደር ጠብ፡ ጥል (ጠብ የተባለው ጓሮ መኾኑን አስተውል) (ተረት): "አላሽከር በቅሎ፡ አለወንድማማች ዐምባ ጓሮ" (በቅርብ ያለ አለመግባባት ማለት ነው)

ዐምባ ጓሮኛ (ኞች): ጠበኛ፡ ጠብ ወዳድ፡ ጥል ያለሽ (ዳቦ የሚል)

ዐምባ: ለጦርነት የተደለደለ መሬት (ሕዝ፳፩፡ ፳፪)

ዐምባ: በማንኛውም ስፍራ የተሠራ መንደር፡ ጎረቤት።

ዐምባ: በተራራ ላይ ያለ መንደር። በግእዝ "ሀገር" ይባላል።

ዐምባላ ሐባብኛ ነው (መዝ፹፫፡ ፫)

ዐምባላ: "ሕዝብ አላት"፡ ብዙ ኹኖ የሚኼድ ነጭ የዥረት አሞራ፡ ወይም ወፍ።

ዐምባላይ: ነጭ ጸዐዳ ፈረስ፡ ሻሾ። "ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ፡ ባላምባላይ ፈረስ" (ታቦት ዘፋኝ) መጽሐፍ ግን "አን()በላይ" ይላል (ዘካ፩፡ ፰፡ ፮፡ ፫፡ ራእ፲፱፡ ፲፩፡ ፲፬)

ዐምባላይነት: ዐምባላይ መኾን፡ ንጣት፡ ነጭነት። በልማድም "አምባ""አንባ""አምበል""አምባላ""አምባላይ" እየተባለ ይጻፋል።

ዐምባላዮች: ነጫጭ አሞሮች፡ ወፎች፡ ነጐዴዎች፡ ፈረሶች።

ዐምባላጌ: የዐምባላ ምድር፡ አገር። "ዐምባ ዐላጊ" ቢል ግን ትርጓሜው ሌላ ነው።

ዐምባሰል: በወሎ ግዛት ውስጥ ያለ አገር። "የማር ዐምባ""መንደር ተራራ" ማለት ነው።

ዐምባት: ዝኒ ከማሁ (ከዐምባ ጋር ተመሳሳይ)፡ በመራቤቴ ክፍል ያለ ደጋ።

ዐምቦ ዋሻ (የዐምቦ ዋሻ): በውስጡ ዐምቦ ያለበት ዋሻ። (እሱም በላይ ወግዳ በጐሽ ውሃ ቈላ ይገኛል)

ዐምቦ ውሃ: ብዙ ሕዝብና ከብት የሚሰበሰብበት ባለማዕድን ምንጭ። "አንቦ" ተብሎ ሊጻፍ ይችላልና "ነባን" እይ።

ዐምቦ: በደብረ ሊባኖስ ገዳም ያለ ባለጪስ ዦር፡ ለስ ያለ ጠጅና ጠላ የሚያፈላና የሚያሳምር።

ዐምቦ: ጨው ጨው የሚል ዐፈር፡ ወይም ጭቃ እየተሰፈረ የሚሸጥ። ትርጓሜው "ሕዝብ አለበት" ማለት ነው።

ዐምቦች: ተራሮች፡ መንደሮች (፩ሳሙ፡ ፳፬፡ ፩)

ዐምቻ (ታሕማ): ጋብቻ፡ የጋብቻ ዝምድና፡ ዐማችነት።

ዐምዛ: ወፍራም የጤፍ እንጀራ፡ ዳቤ። "ዐበዘን" ተመልከት።

ዐምደ እሳት: የእሳት ምሰሶ።

ዐምደ ወርቅ ዐምደ ጽዮን: ፲፬፻ ዓመተ ምሕረት የነበረ የሐበሻ ንጉሥ።

ዐምደ ወርቅ: በወርቅ የተለበጠ ደገፋ፡ በቅኔ ማሕሌትና በቅድስት መካከል የቆመ።

ዐምደ ደመና: የደመና ምሰሶ።

ዐምድ (ዶች): ምሰሶ፡ ደገፋ (ኤር፳፯፡ ፲፱)

ዐምድ: በዐምድ የተከፈለና ያልተከፈለ (ጥፈት) " ዐምድ"" ዐምድ"" ዐምድ" እንዲሉ።

ዐምድ: በጥፈትና በጥፈት መካከል፡ ከአርእስት እስከ ኅዳግ ያለ የገጽ መክፈያ ባዶ ብራና። "ሐውልትን" አስተውል።

ዐሞቱ ዳውላ አከለ: ሰነፈ፡ ታከተ (በጣም ደከመ)

ዐሞታም (ሐሞታዊ): ቍጡ፡ ደፋር፡ ጐበዝ፡ መራር (በዐሞት የተሞላ ባህሪ ያለው)

ዐሞት: መራራ፡ ሖምጣጣ፡ የደም ቅራሪ፡ በሆድ ውስጥ ከኩላሊት ጋራ የሚገኝ፡ ሲበዛ ሰውነትን ቢጫ ያስመስላል። የከብቱን በድልሽ (ሐሞት) እየበጠበጡ ሥጋ ይበሉበታል።

ዐሞድ: "እንዳሞድን" ተመልከት።

ዐሞጭ: የቅጠል ስም፡ በሥሩ የሚያፈራ ዕፅ፡ ፍሬው ቢበሉት የሚያቃጥል። "ዝንጀሮ ዐሞጩን ጐመጩን ሲበላ ይውላል" (ምሳሌ).

ዐሰለ (ትግ): በላይ ኾነ፡ ተቀመጠ፡ ሰፈረ፡ የንብ (ንብ መፈወስ)

ዐሰላ: በግንብና በካብ ቅጥር ላይ የተቀመጠ የድንጋይ ቀጸላ ክዳን (የድንጋይ ክዳን)

ዐሰል: ማር (ዐረብኛ)

ዐሰል: የጨው ባሕር፡ አሰል (የጨው ባሕር)

ዐሠሠ: ዞረ፡ ሻ፡ ፈለገ፡ አዘጋጀ (ዋሻን፡ ጐሬን፡ ቀፎን፡ ቤትን) (መፈለግ ወይም ማዘጋጀት)

ዐሠሠ: ጠረገ፡ ወለወለ፡ አበሰ፡ ዐደፈ (ምጣድን) (ማጽዳት)

ዐሠሣ፡ ዕሠሣ (ኀሠሣ): ጠረጋ፡ ውልወላ (የጽዳት ተግባር)

ዐሠሣ: ሁሉን የሚጠርግ ጐርፍ። "ሱቃያውን ዐሠሣ ወሰደው" (ጎርፍ ሁሉን እንደጠራረገ)

ዐሠሥ: አበስ (የጽዳት ተግባር)

ዐሠሥ: ያውድማ ጥራጊ። "አህያ ዐሠሡን ወሰሱንም ይቅማል" (ምሳሌያዊ አነጋገር፡ አህያ እንኳ የውድማ ቅሪትን ይበላል)

ዐሠር: ውሃ፡ የጠላ ቅናሽ (ቀላል ወይም ዝቅተኛ ጥራት ያለው ጠላ) "ያሠር ውሃ"፡ ወይም "ዐሠር ያለበት ውሃ" ማለት ነው።

ዐሠር: የገለባ ስም፡ የገብስ ዐሻሮ ገለባ (የገለባ ዓይነት)

ዐሠርቱ ቃላት: ከግዜር ለሙሴ የተሰጡ ዐሥር ቃሎች (ሕግና ትእዛዝ) (ዐሥርቱ ትዕዛዛት)

ዐሠርቱ: ዐሥር፡ ዐሥሩ (ዐሥሩን ነገሮች ወይም ሰዎች ለማመልከት)

ዐሰቀ: ጠለፈ፡ አስጌጠ፡ አዥጐረጐረ ልብስን (ግእዝ) (ልብስ ማጌጥ)

ዐሰበ (ሐሰበ): ነገርን በልቡ አጤነ፡ አሳደረ፡ አወጣ አወረደ፡ ያለፈውን አስታወሰ፡ አስተነተነ (ግብ ሐዋ፲፱፡ ፳፩) (ማሰብ ወይም ማጤን)

ዐሰበ: ሒሳብ አደረገ፡ አሰላ (መቁጠር ወይም ማሰላሰል)

ዐሰበ: ለካ፣ አሰላ፣ ገመተ፣ ገመገመ፣ ነፋ። "በቅሎ፡ ሲጭኑት፡ ቅናት፡ እንዳያጠብቀው፡ ሆዱን፡ ይሸልጋል፡ (ይነፋል)"

ዐሰብ (ዐረ፣ ዐጸብ): በአዳል አገር ጫፍ ያለ ወደብ፡ እንቅልቅል፡ በረሓ፡ ጭንቅ ማለት ነው፡ በግእዝ ዐጸባ ይባላል (የወደብ ስም)

ዐሰቦት: በሐረርጌ ግዛት በቈላ በበረሓ ያለ ረዥም ተራራ (የተራራ ስም) ትርጓሜው ጭንቅንና ዋጋን ያሳያል (ትርጉም) የግእዝ መጽሐፍ ወገግ ይለዋል (የግእዝ ትርጉም)

ዐሰተኛ (ኞች): ሐሰተኛ (ምሳ፲፪፡ ፲፱-፳፪፡ ዮሐ፰፡ ፶፭፡ ፪ጴጥ፡ ፪፡ ፩) (ውሸታም)

ዐሰተኛነት: ሐሰተኛነት (ውሸታምነት)

ዐሰት ጽድቁ: ዐሰት እውነቱ (ውሸት እውነቱን ሲሸፍን) "ሐሰትን" ተመልከት።

ዐሰት: ሐሰት (ውሸት)

ዐሣማ: ሆዳም ሰው (ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዐሣማ: መልከ መጥፎ የቤት እንስሳ፡ በልቶ የማይጠግብ፡ እድፍ ጕድፍ የሚበላ፡ የሚጠጣ፡ በጭቃ ላይ የሚንከባለል፡ አፉ ዐይጠ መጐጥ የሚመስል (አሳማ)

ዐሣሞች: ሆዳሞች እንስሶች፡ ሰዎች፡ በላተኞች (ብዙ ቁጥር)

ዐሳረኛ (ኞች): ዐሳር ያገኘው፡ የተዋረደ፡ መከረኛ፡ ጐስቋላ (መከራ የገጠመው ሰው) (የበገና ግጥም): "ዐሳረኛው እኔ፡ መከረኛው እኔ፡ አምላኬን ትቼ ሰው ማመኔ" (መከራን የሚገልጽ ግጥም)

ዐሳር (ኀስረ፣ ኀሳር): ውርደት፡ ጕስቍልና፡ መከራ፡ ጭንቅ (ሉቃ፩፡ ፳፭) (ውርደት ወይም መከራ) (ተረት): "ላሳር የጣፈው፡ ቢነግድ አይተርፈው" (መከራ የገጠመው ሰው አይተርፍም የሚል ምሳሌ)

ዐሣር: ውርደት፡ ዐሳር።

ዐሣሽ (ሾች): ያሠሠ፡ የሚያሥሥ፡ ፈላጊ፡ አዘጋጂ፡ ንብ ሹም፡ ጠራጊ፡ ወልዋይ (የሚፈልግ ወይም የሚያዘጋጅ)

ዐሣሽነት: ዐሣሽ መኾን።

ዐሳበ ቢስ: ዐሳበ መጥፎ (መጥፎ ሀሳብ ያለው)

ዐሳቢ (ዎች): ያሰበ፡ የሚያስብ፡ አስታዋሽ (የሚያስብ ወይም የሚያስታውስ ሰው) (ተረት): "ሩቅ ዐሳቢ፡ እቅርብ ዐዳሪ" (ስለ ሩቅ ማሰብ እንጂ ስለ ቅርብ አለማሰብን የሚገልጽ ምሳሌ)

ዐሳብ (ሐሳብ): ኅሊና፡ የነገር ጽንስ (ሀሳብ ወይም አስተሳሰብ)

ዐሳብ የለሽ: ግድ የለሽ፡ ምን ቸገረኝ ባይ (ግድ የሌለው ሰው)

ዐሳብ ገባው: አንድ ነገር በመስማት እንቅልፍ ዐጣ፡ ሌት ተቀን እሱኑ አውጠነጠነ (በሀሳብ መወጠር)

አሳተ።

ዐሥረ ፈጅ: እንቅብ፡ ላዳን ዐሥር ቍና እህል የሚይዝ፡ የሚጨርስ (ዐሥር ቍና እህል የሚይዝ ትልቅ ዕቃ)

ዐሥረኚት: ዐሥረኛዪቱ ክፍል (አንድን ነገር በዐሥር ከፍሎ አንዱን ክፍል ለመግለጽ)

ዐሥረኛዋ: ዐሥረኛዪቱ፡ ያች ዐሥረኛ (ዐሥረኛ የሆነችውን ሴት ወይም ነገር ለመጠቆም)

ዐሥረዬ: ዐሥር ጊዜ (የቁጥር ብዜት) "ዬን" እይ።

ዐሥሪያ: ካሥር አንድ የኾነ (አሥረኛ ክፍል)

ዐሥራ (ዐረ፡ ዐሸራ): ዐሥራ አንድ (፲፩)፡ ዐሥራ ኹለት (፲፪)፡ ዐሥራ አራት (፲፬)፡ ዐሥራ ዐምስት (፲፭) ያሠኛል። ትርጓሜውም "ዐሥርና አንድ"... "ዐሥርና ዐምስት" ነው።

ዐሥር፡ መቶ። "ሺን፡ ተመልከት።"

ዐሥር አደረገ (ዐሠረ): እስካሥር ቈጠረ፡ ባሥር ከፈለ (አንድን ነገር አሥር ማድረግ ወይም መከፋፈል)

ዐሥር: የቍጥር ስም፡ ፲፡ ከዘጠኝ ቀጥሎ ያለ አኃዝ። ተራ ቍጥር ሲኾን ዐሥረኛ (፲ኛ)ዐሥረኛው (፲ኛው) ይላል።

ዐሥርነት: ዐሥር መኾን (የዐሥር ቁጥር ባህሪ)

ዐሥርዮሽ: ዝኒ ከማሁ (እንደ ዐሥሪያ)

ዐሥሮ: ዐሥሪዮ፡ ዐሥርነት ያለው ነገር፡ ውስጠ ብዙ (ዐሥር እጥፍ የሆነ ወይም ብዙ የያዘ)

ዐስበ ተፈሪ: የከተማ ስም፡ በሐረርጌ ግዛት በጨርጨር አውራጃ ያለ ከተማ (የከተማ ስም)

ዐስበ ዲያቆን: ቁርባን፡ የዲያቆን ፈንታ፡ ድርሻ (የዲያቆን ድርሻ)

ዐስቢት: የእባብ ስም፡ አንድ ዓይነት የበረሓ እባብ (የእባብ ስም)

ዐስቤ (ዐስብየ): የሰው ስም፡ ምንዳዬ ማለት ነው (የሰው ስም)

ዐስብ (ዐስቦ ዐሰበ): የሥራ ዋጋ፡ ምንዳ (የሥራ ዋጋ)

ዐስቦ: የደብረ ሊባኖስ ስም፡ ደብረ ሊባኖስ ከመባል አስቀድሞ ዐስቦ ይባል ነበር፡ በግእዝ ዋጋውን ተብሎ ይተረጐማል (የደብረ ሊባኖስ ቀደምት ስም) "ደበረን" እይ።

ዐረመ: ቈረጠ፡ ከፈለ መሬትን (መሬት መከፋፈል)

ዐረመ: ተወ፡ ከለከለ፡ ለየ፡ ቀደሰ (፬ነገ፡ ፳፡ ፵፪፡ ፩ጢሞ፡ ፬፡ ፫) (መከልከል ወይም መለየት)

ዐረመ: ኰተኰተ፡ ነቀለ (እርሻ ማረም) (ተረት): "አያርም ዐራሽ፡ አያጥብ ለባሽ" (ምሳሌያዊ አነጋገር) (ግጥም): "ጤፉን ዳዋ በላው ቀለባችንን፡ አንቺ ሰው ዐርሚ እንጣላለን፡ ተወ። ያላህን ነገር ምኑን ዐውቀሽው፡ ወይ እኔ እበላው አንቺ ዐርመሽው" (ግጥም)

ዐረመ: ግድፈትን መላ፡ ትርፍን አስገለለ (ስህተትን ማረም)

ዐረመኔ: ያልተጠመቀ (ያልተጠመቀ ሰው)

ዐረማም: ዐረም፡ የበዛበት፡ ባላረም መሬት (ሳር የበዛበት መሬት)

ዐረማሞ: "" ቃለ አኅስሮን ያሳያል፡ ዝናም ሳያጠግብ የተዘራ የስንዴና የገብስ ያገዳ ፍሬ፡ በሽታ፡ ጥቀርሻ መሳይ (የሰብል በሽታ)

ዐረም (ሞች): ከብቋያ ውስጥ የሚነቀል፡ በያይነቱ ቅጠልና ሣር (የሳር ዓይነት)

ዐረም ተነበት: ተደበቀ፡ ታባ፡ ተሰወረ ነውሩ፡ ነገሩ (የተደበቀ ነገር)

ዐረሰ (ኀረሰ): መገበ፡ ቀለበ የወለደች ሴትን (ወላድ ሴት መመገብ)

ዐረሰ: ተለመ፡ ጨፈለቀ፡ ተረተረ፡ ገመሰ፡ ሰበተ፡ ገለገለ፡ ከረበተ፡ ደገመ፡ ቀበቀበ፡ ዐየመ፡ አለሰለሰ (መሬት ማረስ) "ሸመተን" እይ።

ዐረሰ: ዐራሽ።

ዐረሳ: ገመሳ፡ ግልጋሎ (የማረስ ተግባር)

ዐረስ: ዝኒ ከማሁ። "ጐሽ ዐረስ" እንዲሉ (እንደ ዐራሽ)

ዐረረ (ሐረረ፣ ሐለለ): ነደደ፡ ተቃጠለ፡ ገመነ፡ ጠቈረ፡ ከሰለ (መቃጠል) (ተረት): "ያረረበት ያማሳል" (የተጎዳ ሰው ቅሬታ ያሰማል) "ሆድ ሲያር ጥርስ ይሥቃል" (ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዐረረ: ነጠፈ፡ ደረቀ፡ ተኰማተረ፡ ዐጪር ኾነ (መድረቅ ወይም መኮማተር)

ዐረረ: ዐለቀ፡ ተበጣጠሰ። "እከሌ ልብስ ዐሮበታል" እንዲሉ (ልብስ ማለቅ ወይም መበጣጠስ)

ዐረረ: ጠቈረ፣ ከሰል መሰለ።

ዐረሩ: የወንድ ባሪያ ስም (የወንድ ባሪያ ስም)

ዐረሩ: ጥቍር አህያ (ጥቁር አህያ)

ዐረር የግእዝ፡ ርሳስ የአማርኛ ነው (የቃላት አመጣጥ)

ዐረር: የርሳስ ስም፡ በቀለሕ ጫፍ ያለ ርሳስ፡ ከጠመንዣ በተተኰሰ ጊዜ ሰውን፡ እንስሳን፡ አውሬን፡ ወፍን፡ አሞራን፡ ማንኛውንም ተንቀሳቃሽ ፍጥረት አሳርሮ የሚገድል (ዘኍ፴፩፡ ፳፪) (የጥይት ዓይነት)

ዐረር: ድርቅ፡ ደረቅ፡ ቦና (ድርቀት) "ውሃ ጠፍቶ ባረር ይለቀሳል" እንዲሉ (ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዐረቀ (ዐሪቅ፣ ዐረቀ): አቀና፡ አረታ፡ ቀጥ አደረገ፡ የዕርፍ፡ የሞፈር፡ የድር (ማቅናት ወይም ማስተካከል) "ቅዱስ ዲሜጥሮስ ዕርፍ ዐርቆ ተክል አጽድቆ ይኖር ነበር" (ምሳሌ)

ዐረቀ: በክርን መታ፡ ደሰቀ (በክርን መምታት)

ዐረቀ: አጐበጠ፡ ቀለሰ፡ ለመጠ ቀጥታውን (ማጐበጥ ወይም ማጠፍ)

ዐረቀ: ጭነትን መለሰ፡ አስተካከለ (ጭነት ማስተካከል)

ዐረቂ (ላህባዊ): የላብ ዓይነት፡ ይኸውም በአረብኛ ነው (የላብ ዓይነት ቃል)

ዐረቄ (ዐረ፣ ዐረቅ፡ ላብ): የእህልና የቅመም፡ የማር ላበት፡ የሚያሰክር ብዙ ዓይነት መጠጥ፡ ሲበዛ ልብ የሚነሣ፡ ቀልበ ቢስ የሚያደርግ ፈሳሽ (የአልኮል መጠጥ)

ዐረቄ መርፌ: ዐጪር ቀጪን መርፌ (አጭርና ቀጭን መርፌ) ዐረቄ መባሏ ላብ የወጣበት እንዳይታወቅ፡ ርሷም የገባችበትና የወጣችበት ልብስም ቢኾን ገላ ስለማይታወቅ ነው (የቃል አመጣጥ ማብራሪያ) ዳግመኛ ግእዝ (ዐራቂ) አስታራቂ በሚለው ዘይቤ ቢፈቱት በመጠን ለሚጠጣው ዐረቄው ምግብን፡ መርፌው የተቀደደ ሆድን ማዋሐዱን፡ ማሰማማቱን፡ ማገናኘቱን ያሳያል (የቃል ትርጉም ትንተና)

ዐረቄ ወገብ: ወገበ ቀጪን ሴት (ቀጠን ያለ ወገብ ያላት ሴት)

ዐረበ: መለጠ፡ ፋቀ፡ አቀላ (መላጨት፡ ማቀላቀል)

ዐረበ: ጠለቀ፡ ገባ፡ ጥንቅር አለ (መጥለቅ)

ዐረቢ (ዐረባዊ): ያረብ አገር ሰው፡ ያረብ ተወላጅ (ኢሳ፲፫፡ ፳) (የአረብ ሀገር ሰው)

ዐረቢ: ቀይ እንዶድ (የእንዶድ ዓይነት)

ዐረቢ: ዐረብኛ፡ ያረብ ፊደል (የአረብ ፊደል)

ዐረቢት (ዐረባዊት): ያረብ ሴት (የአረብ ሴት) "ዐረቢትን ዐረቧት"፡ ብልጧን በለጧት፡ ሌባን ሌባ ሰረቀው እንደ ማለት (ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዐረብ (ቦች): የነገድ ስም፡ በበረሓና በጀንበር መጥለቂያ ያለ የሴምና የካም ዘር፡ በእስያና በአፍሪቃ የሚገኝ ቀይ ሕዝብ፡ እስላም (የአረብ ህዝብ)

ዐረብ ብረት: ካክራ፡ ጠንካራ፡ ያረብ ብረት (ጠንካራ ብረት)

ዐረብ: ቀይ ቈርበት፡ ተንቤን ነት፡ ቅላት፡ ቀይነት ያለው የበግና የፍየል ቈዳ (ዘፀ፳፭፡ ፭) "ባሕር ዐረብ" እንዲሉ።

ዐረብ: ዐረብኛ

ዐረብኛ: ያረብ ቋንቋ፡ ወይም ልሳን፡ የሱርስትና የዕብራይስጥ፡ የግእዝ ወንድም (የአረብ ቋንቋ)

ዐረብያ: ጋሪ፡ ሠረገላ (ጋሪ)

ዐረቦ: መላጣ ከብት (በሬ)፡ ጠጕሩ በኖ ያለቀ (ፀጉሩ የረገፈ በሬ)

ዐረቦን (ዐርበ): መያዣ፡ ፈለማ፡ ቃብዱ (የቅድሚያ ክፍያ ወይም መያዣ)

ዐረንቋ: ማጥ (ጭቃማ ቦታ)

ዐረንዛ: ብዙ ድንጋይ (ድንጋያማ ቦታ)

ዐረዘ: አነሰ፡ ጐደለ፡ ዐጸጸ፡ ዐለቀ፡ ሣሣ (መቀነስ ወይም መጥፋት)

ዐረደ: መሬትን ማሰ፡ ጐደበ፡ አጐደጐደ (መሬትን መቆፈር)

ዐረደ: ሰረቀ፡ ሞጨለፈ (መስረቅ)

ዐረደ: ቈረጠ።

ዐረደ: አታለለ፡ አሞኘ። "እከሌ እከሌን በማዥራቱ ዐረደው" እንዲሉ (ማታለል)

ዐረደ: ከለለ፡ ጋረደ፡ መከታ አበጀ፡ መሸገ (መከላከል)

ዐረደ: የከብትን፡ የሰውን፡ የዶሮን ዐንገት ጎዘጎዘ፡ ከረከረ፡ ቈረጠ፡ ቀረደደ (፪ነገ፡ ፲፡ ፯፡ ሉቃ፲፭፡ ፳፯) (ማረድ)

ዐረዳ (ሕርደት): ክርከራ፡ ቈረጣ፡ ራስን ቸብቸቦን (የማረድ ተግባር)

ዐረድ (ዶች): ዋና ሌባ፡ አታላይ (የባለጌ ሰው)

ዐረገ: እፈጣሪ ፊት ደረሰ፡ ቀረበ መሥዋዕቱ፡ ጸሎቱ (መቅረብ)

ዐረገ: ወደ ሰማይ ኼደ፡ ወጣ፡ ከፍ ከፍ አለ (መውጣት)

ዐረጉን መዘዘ: ዘሩን ቈጠረ፡ "እከሌ ቢወልድ እከሌን" አለቃይ።

ዐረግ (ጎች): በዱር፡ በገደል፡ በዛፍ ላይ እየተሳበ የሚያድግ፡ ያጥር፡ የግድ ግዳ፡ ማሰሪያ፡ መማገሪያ፡ ዐዞ፡ ቋንዶ፡ ጠሮ፡ ሞይደር፡ ላንቍሶ፡ የመሰለው ሁሉ (ተሳቢ ተክል) (ተረት): "አንድ ዐረግ ቢስቡ ዱር ይሰበስቡ" (አንድ ነገር ለመስራት ብዙ ዝግጅት እንደሚያስፈልግ)

ዐረግ ሬሳ: ያረግ ሬሳ፡ ቧሔ ዐረግ፡ ዕፀ ሳቤቅ (የተክል ዓይነት)

ዐረግ: ዘር፡ ወገን፡ ነገድ። "መዘዘን" እይ (ትውልድ ወይም ዘር)

ዐረጠ: ባራጣ አበደረ፡ ለቃ አተረፈ (አራጣ ማበደር)

ዐረጠ: ደረቀ፡ ነጠፈ፡ የደም። ከዚህ የተነሣ መውለድን አቆመ፡ አቈረጠ፡ የማሕፀን (መውለድ ማቆም)

ዐረጠች: ደማ ቆመ፡ መውለድን ተወች፡ ወይም መውለድ ተዋት።

ዐረፈ ጣቴ: የፈትል ስም፡ ውሃ የሚመስል የባሕር ድር፡ ቀጪን ሞናና (የፈትል ዓይነት)

ዐረፈ: ቈረጠ ሸማን፡ ዕንጨትን (መቁረጥ)

ዐረፈ: ብለኸ ምዕራፍን ተመልከት።

ዐረፈ: ዐለፈ፡ ሞተ (ማለፍ ወይም መሞት)

ዐረፈ: ከሥራ፡ ከመንገድ፡ ከነገር ተለየ፡ ዝም አለ፡ ተቀመጠ፡ እፎይ አለ (ዘፀ፪፡ ፲፭፡ ፪ሳሙ፡ ፲፮፡ ፲፬) (ማረፍ) (ተረት): "አፍ ሲያርፍ ወዳጁን ያማል" (ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዐረፈ: ከጭነት፡ ከሸክም ዳነ (ከጭነት ማረፍ) "አህያ በወለደች ታርፋለች" (አህያ ስትወልድ እንደምታርፍ)

ዐረፋ (ዐረ፣ ዐረፈ፡ ዐወቀ): የበዓል ስም፡ ያዳምና የሔዋን መተዋወቅ (የበዓል ስም) ዳግመኛም እስላሞች ኦሪትን በማስተባበል በይሥሐቅ ፈንታ አብርሃም ይስማኤልን ሲሠዋ አላህ በጀነት በግ ተቤዠው እያሉ በየቤታቸው በግ በማረድ የሚያከብሩት በዓል ነው (የሙስሊሞች በዓል)

ዐረፋ (ዎች) (ሐረፈ፣ ሐረፋ): የንዶድ፡ የሳሙና፡ የሥጋ፡ የስብቅ ነጭ ውጤት፡ በውሃ ላይ ሰፎ የሚታይ (በውሃ ላይ የሚታይ አረፋ)

ዐረፋ: ምራቅ፡ ቈበር (ምራቅ) "እከሌ በድንገት ታመመና ዐረፋ ደፈቀ" (በድንገት ታሞ አረፋ አፉ ላይ መውጣት)

ዐረፋት (ሐረፋት): ዐረፋዎች። ሐረፋት በግእዝ ብዛትን እንጂ፡ አንድነትን አያሳይም (የብዙ ቁጥር አረፋ)

ዐረፋት: ዝኒ ከማሁ (ማር፱፲፳) (እንደ አረፋ)

ዐረፋት: የቀለጠ ብር (ምሳ፳፮፡ ፳፫) (የቀለጠ ብር)

ዐረፋት: የውሃ ዐረፋ፡ ወዲያው ብትን ብሎ የሚጠፋ (ሆሴ፲፡ ፯) (የሚጠፋ የውሃ አረፋ)

ዐረፍኩኸ የወር ጨው: ሰው በሞተ ጊዜ እንዲህ አለ ይላሉ። "ጨውን" እይ (ሟች ሲሞት የሚባል)

ዐሩር (ሐሩር): የፀሐይ ሙቀት፡ ከሙቀት የተነሣ በገላ ላይ ሽፍ የሚል ዕከክ (የፀሐይ ሙቀት ወይም የቆዳ ሽፍታ)

ዐሩር: ጥቍር ቀለም የሚኾን የስንዴ ከሰል፡ ሐሩርም ይባላል (ከሰል)

ዐሩን በላ: ተደበደበ፡ መከራውን አየ።

ዐሪ: ያራ፡ የሚያራ (የሚጸዳዳ)

ዐሪላ: ቂጧን የማትጠርግ ሰነፍ ሴት። "" አላት ማለት ነው።

ዐሪታ: ማታ ኵቲ። የቀረ የተረሳ ቋንቋ ነው።

ዐሪታ: አለጊዜ ያራች፡ የምታራ ሴት (አለጊዜ የምትጸዳዳ ሴት)

ዐሪዛዞ: ብርሌ፡ አሪዛዞ (የብርሌ አይነት)

ዐራ (ሐረረ፡ ሐራ)

ዐራ: ዕዳሪ ወጣ፡ ወገቡን ሞከረ፡ ኰሳ፡ ዘበለላ (መጸዳዳት) "አፍኣን" እይ። (ተረት): "አይነጋ መስሏት አቋት ዐራች" (በችኮላ የተሰራ ስራ)

ዐራ: ጨዋ፡ የጨዋ ልጅ፡ ባላባት፡ ከመታዘዝ ነጻ የኾነ።

ዐራሙቻ: ተነቅሎ የወደቀው ዐራሙቻ ይባላል (የተነቀለ ሳር)

ዐራሚ (ዎች): ያረመ፡ የሚያርም እኸልን፡ መጻፍን፡ ነቃይ፡ ኰትኳች (የሚያርም ሰው)

ዐራሚነት: ዐራሚ መኾን (አራሚነት)

ዐራም: ዐረ ብዙ፡ ሁል ጊዜ የሚያራ፡ የሚዘፈዝፍ (በጣም የሚጸዳዳ)

ዐራስ (ኀራስ): እመጫት፡ የጨቅላ እናት፡ ብረት ተንተርሳ የምትተኛ፡ ለሽንትም ወደ ውጭ ስትወጣ ቢላዋ ጨብጣ የምትኼድ (የወለደች እናት) "የማሪያም ዐራስ" እንዲሉ (የማርያም ዐራስ) ሲበዛ "ዐራሶች" ይላል፡ ለእንስሳትም ይነገራል (መዝ፸፰፡ ፸፩) (የብዙ ቁጥር) "ጥሬን" እይ።

ዐራስ ነብር: ቍጡ፡ ኀይለኛ ሰው (ቍጡ ሰው)

ዐራስ ነብር: ግልገሎች የምታጠባ (አራስ ነብር)

ዐራስ ውሻ: ቡችሎች ያሏት፡ መንገደኛን የምትነክስ (አራስ ውሻ)

ዐራስ: ርጥብ ጨቅላ ልጅ፡ የናቱን ጡት የሚጠባ፡ የሚመጠምጥ፡ ቅቤ የሚውጥ፡ ለሴትም ይነገራል (አራስ ሕፃን)

ዐራራ: ያረረ፡ የከሰለ (የተቃጠለ ወይም የከሰለ) (ተረት): "የስንዴ ዐራራ የቄንዦ መራራ" እንዲሉ (ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዐራሽ (ኀራሲ): ያረሰ፡ የሚያርስ፡ መጋቢ፡ ቀላቢ (የሚመግብ)

ዐራሽ (ሐራሲ): ያረሰ፡ የሚያርስ፡ ገበሬ (የሚያርስ ሰው)

ዐራሽ: ያራው፡ የኰሳው። "ወፍ ዐራሽ" እንዲሉ።

ዐራሾች (ሐራስያን፣ ሐረስት): ገበሬዎች (ኢሳ፷፩፡ ፭) (ገበሬዎች)

ዐራቂ: ያረቀ፡ የሚያርቅ፡ አቅኒ (የሚያርቅ ወይም የሚያስተካክል)

ዐራቢ: ያረበ፡ የሚያርብ፡ መላጭ፡ ፋቂ፡ አቅሊ (የሚላጭ)

ዐራቦ: የበሬ መዥገር የሚመልጥ፡ ራሱ እቈዳ ውስጥ የሚገባ (የበሬ መዥገር አይነት)

ዐራዳ: ቍርጥ ነገር። "ዐራዳውን ንገረኝ" እንዲል ባላገር (በቀጥታ)

ዐራዳ: በላይ ወግዳና በታች ወግዳ መካከል ያለ ስፍራ፡ ግራ ቀኙ ታርዶ ተቈፍሮ እንደ በር ያለ ጠባብ መንገድ ኹኗል (የቦታ ስም)

ዐራዳ: የታረደ፡ የተራራ ዐንገት በር (የተቆረጠ የተራራ አንገት)

ዐራዳ: የአዲስ አበባ ከተማ መካከለኛ ቦታ፡ ለገበያነት የተወሰነ፡ የተከለለ፡ ምሥራቁና ምዕራቡ በወንዝ የታረደ (የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ) ከጣሊያን ወዲህ ግን አዲስ አበቦች "ፒያሳ" ይሉታል፡ የስሕተት ስሕተት ነው። በዘርፍነት ሲነገር "ዐራዳ ጊዮርጊስ""ያራዳ ጊዮርጊስ" ይላል (የአካባቢው ስም አጠቃቀም)

ዐራድ: ትርጓሜው እንደ መዠመሪያው ዐራዳ፡ ጐራዳ ብሎ ጐራድ እንደ ማለት ያለ (እንደ ዐራዳ ያለ ትርጉም)

ዐራድማ: በመንዝ ውስጥ ያለ አገር፡ ዐራዳማ ማለት ነው (የቦታ ስም) (ተረት): "ምንም በሙቱ ዐራድማ ሸምቱ" (ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዐራጅ (ጆች): ያረደ፡ የሚያርድ፡ ዐንገት ቈራጭ (የሚያርድ ሰው)

ዐራጅ: መጎዛ፡ ፋደት፡ የቀፎ ሌባ (የሌባ ዓይነት)

ዐራጊ: ያረገ፡ የሚያርግ (የሚያርግ)

ዐራጣ (ትግ ሐረጻ): ወለድ፡ ትርፍ፡ የወለድ ገንዘብ (ዘሌ፳፭፡ ፴፯፡ መዝ፲፭፡ ፭) (ወለድ)

ዐራጭ (ጮች): ያረጠ፡ የሚያርጥ፡ ባራጣ አበዳሪ (አራጣ የሚያበድር)

ዐራፊ (ዎች): ያረፈ፡ የሚያርፍ፡ ተቀማቴ፡ ሰሞነኛ፡ ገባር (የሚያርፍ ሰው)

ዐራፊ: የቈረጠ፡ የሚቈርጥ (የሚቆርጥ)

ዐራፊነት: ዐራፊ መኾን፡ ተቀማጭነት (የማረፍ ሁኔታ)

ዐር: ኵስ፡ ዐይነ ምድር፡ ዕዳሪ፡ ሠገራ፡ የምግብ አተላ፡ ዝቃጭ (ፍሳሽ) "የብረት ዐር""የቅቤ ዐር" እንዲሉ። "ጪዋን""ዐይንን" ተመልከት።

ዐርቆ: አቅንቶ፡ ቀጥ አድርጎ (ቀጥ አድርጎ) (ተረት): "ዐማች አስታርቆ፡ ቀንበር ዐርቆ" (ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዐርበ ወጥ: ካርብ የወጣ፡ ዐዲስ ልብስ፡ ያልተሰፋ (ያልተሰፋ ልብስ)

ዐርበኛ (ኞች): ጦረኛ፡ የጦር ገበሬ፡ ጨካኝ፡ ደፋር፡ ቈራጥ፡ ጐበዝ፡ ኀይለኛ፡ በግእዝ (ያርብሕ፡ ያርብሓዊ) ይባላል (ጀግና ወይም የጦረኛ ሰው) "ሐርብን" እይ።

ዐርበኛነት ()ነት: ዐርበኛ መኾን፡ ጦረኛነት (ጀግንነት)

ዐርቤ (ሐርቤ): ገብረ ማርያም የሚባል የላስታ ንጉሥ ስም በአማርኛ የሚጠራበት፡ የጦር ሰው ማለት ነው (የንጉስ ስም)

አርቤ: የአርበኛ ወገን (ዐርቤ)

ዐርብ ሮብ: ካስመራ በታች ያለ ገደል (የቦታ ስም)

ዐርብ ሮብ: የጦም ቀኖች (የጾም ቀናት)

ዐርብ: ወርድ፡ ጐን፡ ስፋት (የሸማ) "ይህ ልብስ ዐርቡ ጠባብ ነው"

ዐርብ: የሸማኔ ዕቃ፡ ምስጢሩ የድር መግቢያነትን ያሳያል (የሸማኔ መሳሪያ)

ዐርብ: የቀን ስም፡ ፮ኛ ቀን። ትርጓሜው የሰንበት መግቢያ ማለት ነው። "ውሃን" እይ (ዐርብ)

ዐርብ: ጦር፡ ጦርነት (ጦር)

ዐርብና ቀስት: ዐርብ የተባለ ጊጤ፡ ቀስት በቁሙ፡ ወጊና ተወጊ ማለት ነው። ዳግመኛም ዐርብ (ከሐርብ) ቢወጣ "ጦርና ቀስት" ይባላል (የጦር መሳሪያዎች)

ዐርቶ ገባ (ቦች): ነፍስ ያላወቀ፡ ቂጡን ያልጠረገ ልጅ (እድሜው ያልደረሰ ልጅ)

ዐርቶ: ኰስቶ። "አባትን" ተመልከት።

ዐርነት: ሐርነት፡ ነጻነት (ሮሜ፮፡ ፳፡ ፳፪) (ነጻነት)

ዐርነት: ነጻነት (ዐራ፡ ሐራ) (ነጻነት)

ዐርኩ: በሐማሴን ጣሊያን የሚጠራበት ስም፡ ወዳጁ ማለት ነው። (ግጥም): "ሴቶች ተሰብሰቡ ፍል ውሃ ድረስ፡ ዐርኩ መኼዱ ነው እንድንላቀስ" (፲፱፻፴፩ .) (ግጥም)

ዐርኩ: የብረት አጣብቂኝ፡ ዕንጨትን፡ ብረትን፡ ጥራዝን አጣብቆ የሚይዝ፡ ባለመዘውር የቀጥቃጮችና ያናጢዎች የጻፎች መሣሪያ (ብረት ማያያዣ መሳሪያ)

ዐርኬ: ዐምስት ስንኝ ያለው የስንክሳር መርገፍ ግጥም፡ በእያንዳንዱ መልአክ፡ ነቢይ፡ ሐዋርያ፡ ጻድቅና ሰማዕት ታሪክ መጨረሻ የሚነበብ፡ ዐርከ ሥሉስ የሚባል ሊቅ ስለ ደረሰው "ዐርኬ" ተባለ ይላሉ (የግጥም ዓይነት) ዳግመኛም ዐርኬ (ዐርክየ) ወዳጄ ማለት ነውና፡ የወዳጅ ምስጋና መኾኑን ያስረዳል (የቃል ትርጉም)

ዐርኬና: የምሥጥ ንጉሥና ንግሥት መኖሪያ ቤት፡ በዙሪያው ብዙ ክፍልና በር ያለው (የምስጥ ንጉስና ንግስት መኖሪያ)

ዐርኬና: የንብ አውራ ዕልፍኝ (የንብ ንጉስ ማረፊያ)

ዐርኬና: የጣዝማ መቀመጫ (የጣዝማ ማረፊያ)

ዐርክ: ወዳጅ፡ ባልንጀራ፡ ግጥሚያ (ወዳጅ)

ዐርኳታ (ዐር፡ ኳች): ጥዳት የሌላት ሴት፡ ዐሣማ ዓይነት፡ ጥርክርክ (የሴት አሳማ ዓይነት)

ዐርዝ: ዛፍ አርዝ (የዛፍ አይነት)

ዐሮ: የመንቀፍና የማዋረድ ቃል፡ "ሰውየውን ዐር ሆይ" ማለት ነው።

ዐሮ: ጠቍሮ፡ ከስሎ (ጠቁሮ) (ተረት): "ዐሮም መሮም ማበሬን፡ ከፈልኩ" (ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዐሸ (ሐሰየ): ዳበሰ፡ ዳሰሰ፡ ለወሰ፡ አለፋ፡ አፍተለተለ፡ ዳመጠ፡ አዞረ፡ ጠመዘዘ፡ ደረጠ ውልቃትን፡ ሊጥን፡ ቈዳን፡ ገላን፡ ብልትን፡ ሆድን፡ የዘነበለ ጋንን፡ ኑግን፡ ተልባን፡ ነዶን፡ ቈሎን፡ ልስንን፡ እሸትን (ሉቃ፮፡ ፩) (ማሻሸት ወይም መዳበስ) "መከረን" አስተውል (የቃላት ትንተና) "ሳያሽ የበላ ዝንጀሮ ሲስል ያድራል" (ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዐሸለ: ለካ፡ አሸለ (ለካ)

ዐሸመ (ሐሠመ): ሲያዩት የማያምር ወፍራም ሽሩባ ሠራ፡ ጐነጐነ፡ ደበለ (ሽሩባ መሥራት)

ዐሸቦ: ከመሬት የሚታፈስ ደቃቅ አንኳር ጨው (የጨው ዓይነት) ፍችው (ዐስብ) ዋጋ፡ ዋጋነት ያለው ማለት ነው (የቃሉ ፍቺ)

ዐሸት (ሐስይ): ማሸት (ማሸት)

ዐሸት አደረገ: ዘወር፡ ጠምዘዝ አደረገ (አዞረ ወይም ጠመዘዘ)

ዐሸን (ሐሴን): ተባት ምሥጥ፡ ባለ፬ ክንፍ (አራት ክንፍ ያለው ምስጥ) ክረምት ሲገባ በብዛት ከመሬት ወጥቶ በአየር ውር ውር በማለቱ "ክረምት አግቢ" ይሉታል (የምስጥ እንቅስቃሴ)

ዐሸን ክታብ: ብዛቱ እንዳሸን የሆነ፡ ታናናሽ፣ ጥቃቅን ክታብ፡ ከአንገት ዠምሮ በጐን፣ በብብት፣ በታች የሚንጠለጠል ጌጥ፡ ውስጡ የቅል ስባሪ። ክታብ በግእዝ "መጽሐፍ" "ደብዳቤ" ማለት ነው።

ዐሸን ክታብ: የክታብ ዐሸን፡ ከተበ (የክታብ ዓይነት)

ዐሸን: (ምስጥ)

ዐሸን: ደቃቅ ረቂቅ በረዶ (ትንሽ በረዶ) "ቧሒትን ዳሸንን" ተመልከት።

ዐሸን: ጥቃቅን አንበጣ፡ ኵብኵባ፡ ምድር የሚያለብስ (አነስተኛ አንበጣ)

ዐሸንጌ ( ዐሸን): የምሥጥ፡ ያንበጣ ዐሸን የሚፈላባት ምድር፡ የራያ ቈላ (የምስጥ መገኛ ቦታ) "ዐሸንጌው በረሓ ገዳይ መንኖ እንዳለ ዝኾን ዐዳኝ" (ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዐሸድ ዐሸድ አለ: ሸፈፍ ሸፈፍ አለ (የመደበስ ድርጊት)

ዐሹራ (ዐረ): ዓሥራት፡ ካሥር አንድ (አንድ አስረኛ)

ዐሺ (ዎች) (ሐሳዪ): ያሸ፡ የሚያሽ፡ ወጌሻ (የሚያሽ ሰው)

ዐሺታ (ሐሳዪት): ያሸች፡ የምታሽ ሴት (የምትያሽ ሴት)

ዐሻ: ዕሠይ። ዐሻ ገዳዎ ረ፡ ዐሻ ገዳዎ እንዳለ ዘፋኝ (በዘፈን ውስጥ የሚገኝ አገላለጽ)

ዐሻል: አራት እግሩ ነጭ ከብት፡ አሻል (አራት እግሩ ነጭ የሆነ ከብት)

ዐሻል: ጪው፡ አሻል (ጪው)

ዐሻሚ: ያሸመ፡ የሚያሽም፡ ጐንጓኝ (ሽሩባ የሚሠራ)

ዐሻራ ዐሻሮ (ሐሠር): ከነገለባው የተቈላ የገብስ ቈሎ፡ ወይም ዶቄት (የገብስ ዱቄት)

ዐሻሸ: ደባበሰ (መዳበስ) (ግጥም): "ዐሻሺኝና ጠቍሚኝና፡ ልስጥሽ አንድ ቍና" (ግጥም)

ዐሻሻ: ዐሾ፡ ሸፋፋ (የሚያሽ)

ዐሻዳ: እግርና እግሩን የሚያፋትግ፡ ዐሾ (እግሩን የሚያፋትግ) "ዐሸን" ተመልከት።

ዐሽቶ ቀዳ: ጋንን ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ጥቂት ጥቂት እያዞረ ጠላ ቀዳ (ጠርሙስ ወይም ጋን እያዞሩ መጠጥ ማፍሰስ)

ዐሽቶ: አዙሮ፡ ጠምዞ (አዙሮ)

ዐሾ (ዎች): እግሩን ከእግሩ ጋራ እያጣመረ፡ እያሸ፡ እያፈጋፈገ የሚኼድ ሰው (እግሩን እያሻሸ የሚሄድ ሰው) "ዐሾ ገመዳ" እንዲሉ (ምሳሌያዊ አነጋገር) "ዐሻዳን" ተመልከት።

ዐቀረ: አስታቀረ (አስተሐቀረ)፡ ናቀ፡ ነቀፈ፡ አቃለለ፡ አዋረደ (ንቀት ማሳየት)

ዐቀቅ መቀቅ: ሙቀጫ (የቅኔ ቤት አማርኛ ነው)

ዐቀቅ ዘነዘናው: መቀቅ ሙቀው (የሙቀጫ ክፍሎች)

ዐቀበ: ቤተ ክሲያን ጠበቀ፡ መገበሪያ፡ ፈጬ፡ ልብምን፡ መላ ሠየመ (መጠበቅ፡ መሸፈን)

ዐቀበ: አስጠጋ (ካብን፡ ግንብን)፡ ዐፈር አስታቀፈ፡ ግድግዳን በሣር፡ በቅጠል ሸፈነ፡ ከለለ (መደገፍ፡ መከለል)

ዐቀበት: ሽቅበት፡ ዳገት፡ የቍልቍለት ተቃራኒ (፪ዜና ፳፡ ፲፮፡ ሉቃ፫፡ ፬) "ሸቀበን" አስተውል (ቁልቁለት)

ዐቀብ: ሽቅብ፡ ወደ ላይ (ወደ ላይ መውጣት)

ዐቀብተ ሀገር: አገር ጠባቆች፡ ዘበኞች (የብዙ ቁጥር)

ዐቀደ: ለካ፡ ወሰነ፡ ልክና ውሳኔ አደረገ (መለካት ወይም መወሰን)

ዐቀደ: ቀሰተ፡ አጐበጠ (ማጎብደድ)

ዐቀድ: ቅስት (ቅስት)

ዐቀድ: ብርሃን የሌለው ኮከብ (መዝ፻፵፰፡ ፫) ትርጓሜ (የጨለመ ኮከብ)

ዐቀፈ: በክንድ፡ በደረት፡ በጭን፡ በክንፍ ያዘ፡ ተሸከመ፡ ዐቈረ፡ ደገፈ (ማቀፍ፡ መደገፍ)

ዐቀፈ: ተቀበለ፡ ወደደ (ልጅን) "ወይ ንቀፈው፡ ወይ ዕቀፈው" እንዲሉ (መቀበል ወይም መጥላት)

ዐቀፈ: ከበበ፡ በዙሪያ ተቀመጠ።

ዐቀፋ: ዕቅፊያ፡ ማቀፍ።

ዐቃ: ዕቃ። የቅዳሴ መምህራን ጻሕሉን፡ ጥዋውን "ዐቃ" ይሉታል። (የቤተ ክርስቲያን ዕቃ)

ዐቃቂር: የመድኀኒት ቅመማቅመም።

ዐቃቅማ: የኵርንችት ሁለተኛ ስም (የአንድ ተክል ስም)

ዐቃቢ (ዎች): ያቀበ፡ የሚያቅብ፡ ጠባቂ፡ ፈይ (የሚጠብቅ ሰው)

ዐቃቢት (ቶች): ያቀበች፡ የምታቅብ፡ ፈጪታ (የምትጠብቅ ሴት)

ዐቃቢነት: ዐቃቢ መኾን።

ዐቃባ (ናህብ): በዠማ ግራና ቀኝ የቆመ፡ ዕለት፡ ደገፍ፡ ቃሊም (ደጋፊ ወይም ጠባቂ)

ዐቃቤ ሀገር: አገር ጠባቂ፡ ዘበኛ። ከጣሊያን ወዲህ ግን ፖሊስ ይባላል።

ዐቃቤ ሕግ: የሕግ ጠበቃ፡ ስለ ሕግ የሚከራከር (ጠበቃ)

ዐቃቤ ሰዓት ከብቴ: የጐንደር ሊቅ፡ በግእዝ ቋንቋ ምእላድ የጸፉ፡ በቅኔ ዕውቀት እጅግ የተራቀቁ፡ አራቱን ጉባኤ የሚያውቁ (ታዋቂ ምሁር)

ዐቃቤ ሰዓት: የሰዓት መኪና ጠባቂ፡ መይ፡ አስተካካይ (ሰዓት የሚጠብቅ ወይም የሚያስተካክል)

ዐቃቤ ሰዓት: የሰዓት፡ የጊዜ ልክ ጠባቂ፡ ሹም፡ አንዱን በቃኸ ውጣ፡ ሌላውን ግባ የሚል (የሰዓት ተቆጣጣሪ)

ዐቃቤ ሥራይ: ባለመድኀኒት። ፈረንጆች ፋርማሲ ይሉታል።

ዐቃቤ ርእስ: ራስ ጠባቂ፡ በገላ ውስጥ የተቀበረ መድኀኒት፡ የማያስነካ፡ የማያስመታ ድጋም (መድኃኒት ወይም ጥበቃ)

ዐቃጅ: ያቀደ፡ የሚያቅድ (የሚያቅድ ሰው)

ዐቃፊ (ፎች): ያቀፈ፡ የሚያቅፍ፡ ልጅ ያዥ (የሚያቅፍ)

ዐቃፊ: ከባቢ። "ገበታ ዐቃፊ" እንዲሉ። "ሳንባን" እይ (የሚከብ)

ዐቃፋ: ጕድጓዳ፡ ሸክላ፡ ስፌት (የዕቃ ዓይነት)

ዐቄትዠር: ገንቢና ዐናጢ (የግንባታ ባለሙያ)

ዐቈረ: ቋጠረ (ውሃን፡ ደምን) "ጌሾ የወቀጥኹበት እጄ ውሃ ዐቈረ" (ውሃን ወይም ደምን ማቆር)

ዐቈረ: ዐቀፈ።

ዐቅ: ልክ፡ መጠን፡ ስፍር (መለኪያ)

ዐቅለ በዳ (ሐቅለ በድው): ጠል፡ ልምላሜ የሌለበት፡ በረሓ፡ ምድረ በዳ (ደረቅ በረሃ)

ዐቅለ ቢስ: ዕውቀተ መጥፎ ሰው፡ ቀልበ ቢስ (ዕውቀት የሌለው)

ዐቅል (ዐረ): አእምሮ፡ ዕውቀት (አእምሮ)

ዐቅል: ዱር (ዱር)

ዐቅመ ሔዋን: ዐሥራ ዐምስት ዓመት የመላው የልጃገረድ ሰውነት፡ ገላ። "አከለ" ብለኸ "አካልን" እይ (ለጋሽ ዕድሜ)

ዐቅመ ቢስ: አንከሲስ፡ ደካማ (ደካማ)

ዐቅመ አዳም አደረሰ: ለዘር በቃ፡ ጐለመሰ፡ ባለቀ (ማግባት የሚችል ዕድሜ)

ዐቅመ አዳም: ሠላሳ ዓመት የኾነው ምሉ፡ የጕልማሳ ሰውነት፡ አካል (የአዋቂነት ዕድሜ)

ዐቅሙን አያውቅ: ክፉ ስድብ፡ የጕልበቱን ልክ የማያውቅ ሰው፡ አለአኩያው የሚጣላ፡ የሚሳደብ (በአቅሙ ልክ ያልሄደ)

ዐቅም ዐጣ: ሰለተ፡ ደከመ፡ አበቃ (አቅም ማጣት)

ዐቅም: የሰው፡ የንስሳ፡ የአውሬ፡ የመኪና ኀይል፡ ብርታት፡ ልክ፡ መጠን። "ቃረመንን""ድምቢጥን" ተመልከት (አቅም፡ ጥንካሬ)

ዐቅራብ ውሃ: ጠንቋይ ላንዳንዱ ሰው "ኮከብኸ ዐቅራብ ውሃ ነው" ይለዋል፡ የውሃ ጊንጥ ማለት ነው (ጠንቋዮች የሚጠቀሙበት ቃል)

ዐቅራብ: የኮከብ ስም፡ ጊንጥ የሚመስል የጥቅምት ኮከብ (የኮከብ ስም)

ዐቅራብ: ጊንጥ (ግእዝ) (ጊንጥ)

ዐቅደ ቢስ: ዐቅደ መጥፎ (ዕቅድ የሌለው ወይም መጥፎ ዕቅድ ያለው)

ዐቅድ ዐዋቂ: ምክርን ከሥራ አጣጥሞ የሚያውቅ፡ በዠመረበት የሚጨርስ (ብልህ እና ዕቅድን የሚያውቅ)

ዐቅድ: ዘዴ፡ ብልኀት፡ ስልት፡ ኹናቴ፡ ክፍል፡ ወገን። "እከሌ የነገር፡ የጦር ዐቅድ ያውቃል" እንዲሉ። (ዕቅድ ወይም ስልት)

ዐቋሪ: ያቈረ፡ የሚያቍር፡ ቋጣሪ፡ ዐቃፊ (የሚያቆር ሰው)

ዐቋራ: የታቈረ፡ ቋጣራ (የታቆረ ነገር)

ዐበለ (ሐብለ. ዐበለ): ቀለጠ፡ ዋሸ፡ ቀጠፈ፡ ሸፈጠ፡ ሸመጠጠ።

ዐበለ (ትግ ሐበለ): ዐይን ላይ ጣለ።

ዐበለ (ዐቢል ዐበለ): ቀለጠ፡ ወረደ፡ ፈሰሰ፡ ተናዶ ጐረፈ።

ዐበለ: ከዳ፡ አሸቀሸቀ፡ ሸሸ፡ ተንሸራተተ (መሬቱ፣ ግንቡ)

ዐበላ (ትግ ሐበላ): የአይን ሞራ። በግእዝ "ሥዓዕ" ይባላል።

ዐበላ: ፈሳሽ። "የደም ዐበላ" እንዲሉ።

ዐበሌ (ዐብሎ ዐበለ): አፋ ሰይፍ። (ግጥም): "ልጅ እንተሌ የተሳለ ዐበሌ። "

ዐበረ (ኀብረ): አንድ ኾነ፡ ባሳብ፣ በሥራ ገጠመ። "ዐደመን" ተመልከት።

ዐበረ (ዐቢር ዐበረ): ደረቀ፡ ቦና ኾነ።

ዐበረ: ዐለፈ፡ ተሻገረ።

ዐበር: ዐባሪ። "ግብር ዐበር" እንዲሉ። (ስም፡ ዐበር): ሞክሼ።

ዐበቀ: ጨመረ (አበቀ)

ዐበዘ (ኀበዘ): አሰፋ፡ ጋገረ።

ዐበዛ (ኀባዚ፡ ት): የጋገረ፡ የጋገረች፡ የምትጋግር (ጋጋሪ)

ዐበዛ: ንብ። "የማር ዐበዛ" እንዲሉ።

ዐበዛ: የሙዝ እንቡጥ (በዛፉ ላይ ተንጨርጎ የሚታይ) "የሙዝ ዐበዛ" እንዲሉ።

ዐበዛ: የማድ ቤት አዛዥ ሹም። "የንጀራ፣ የጠጅ፣ የጠላ ዐበዛ" እንዲሉ።

ዐበዛ: የንጀራ ክምር፡ መቶ እንጀራ።

ዐበዛ: የጋጋሮች አለቃ (ዘፍ፵፡ ፩-)

ዐበዞች (ኀባዝያን፡ ት): የሚጋግሩ (ጋጋሮች)

ዐበየ (ዐብየ): በለጠ፡ ከፍ አለ።

ዐበጠ (ሐብጠ): ተነፋ፡ ቅል፣ እከለ መሰለ፡ ተነረተ፡ ተቀበተተ።

ዐበጠ (ዐቢጥ፡ ዐበጠ): ሳበ፡ ጐተተ፡ አለፈቃድ ከመንገድ መለሰ፡ አወከ፡ አስቸገረ፡ በጠበጠ፡ ሰላምን፣ ጸጥታን፣ ዕረፍትን ነሣ። በትግሪኛ ግን "ዱብ አለ" "ተከመረ" "በላይ ኾነ" "አፈፍ አደረገ" ይባላል፡ ይኸውም ያንበሳ፣ የነብር፣ የድመት አያያዝ ነው።

ዐበጥ: ዐበጠ። (ተረት): "ባለጠጋ ሊሰጥ የድኻ ሙርጥ ዐበጥ። "

ዐቢይ: ትልቅ፡ ታላቅ።

ዐባ (ኀብአ): ሸሸገ፡ ሰወረ፡ ደበቀ። (ተረት): "ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል። "

ዐባሎ: ዛፍ (አባሎ)

ዐባሪ (ዎች): ያበረ፡ የሚያብር። "ዐባሪ ተነባባሪ" እንዲሉ።

ዐባሪም: ተርታ፡ መናኛ (እኸል ከጥሩው ጋራ የሚቀየጥ)"" ብዛትን ያሳያል። "አደፍን" አስተውል፡ አደፈ።

ዐባሪነት: ዐባሪ መኾን።

ዐባር: ድርቅ፡ ዝናም የታጣበት ዘመን። ይህ ቋንቋ የግእዝ ሲኾን በሐረርጌ አውራጃ ይነገራል።

ዐባያ: እንቢተኛ ወይፈን (አባያ)

ዐባይ (ዮች) (ሐባሊ): ያበለ፡ የሚያብል፡ ዋሾ፡ ቀጣፊ፡ "በሬ ወለደ" ብሎ የሚያወራ። "ዐባይና ሥንቅ እያደር ይቀላል" እንዲሉ።

ዐባይ ሌባሻይ: ያልሰረቀውን የሚይዝ።

ዐባይ ሚዛን: አጕዳይ፡ ቀምጣይ። "የሚዛን ዐባይ ለእሳት፡ የዳኛ ዐባይ ለሰንሰለት" እንዲሉ።

ዐባይ ምስክር: ያላየውን "አየኹ" ያልሰማውን "ሰማኹ" የሚል።

ዐባይ ቀላጤ: ንጉሥ ዳኞች ያላሉትን፣ ያላዘዙትን "ብለዋል" ባይ። "ቃልን" እይ።

ዐባይ ጠንቋይ: የማይኾነውን ይኾናል እያለ የሚናገር ሐሰተኛ ደብተራ። "ዐባይ ጠንቋይ ቤት ያስፈታል" እንዲሉ።

ዐባይ: ቀጣፊ (ዐበለ)

ዐባይ: ትልቋ፡ ታላቂቱ።

ዐባይ: ዠማ (አባይ)

ዐባጣ ጐባጣ: ወጣ ገባ ስፍራ። በግእዝ "መብእስ ወጐዳጕጽ" ይባላል።

ዐባጣ: ያበጠ፡ ታናሽ ጕብታ።

ዐባጭ (ሐባጢ): የሚያብጥ።

ዐባጭ (ጮች) (ዐባጢ): ያበጠ፡ የሚያብጥ፡ አዋኪ፡ አስቸጋሪ።

ዐብሎ መስካሪ: ዐባይ ምስክር።

ዐብሎ አይደክም: ፍጹም ዐባይ፡ ዋሾ፡ ቀጣፊ፡ መልቲ፡ ቈርጦ ቀጥል።

ዐብሎ: ዋሽቶ፡ ቀጥፎ።

ዐብረንታንት: የገዳም ስም፡ በዋልድባ ውስጥ የሚገኝ የበረሓ ገዳም። "ዐብረን ታንተ ጋራ እንኺድ" ማለት ነው።

ዐብሬ: ዐበሩ፡ የሰው ስም።

ዐብሮ መብላት: አለመሠሠት፡ መሳተፍ።

ዐብሮ መኖር: አለመለያየት፡ አለመፋታት። ከዚህም በቀር "ዐብሮ መሥራት" "ዐብሮ መሞት" እያለ ይነገራል፡ ንኡስ አገባብ ነው።

ዐብሮ በቀል: ጋማ።

ዐብሮ አደግ: የዕድሜ ባልንጀራ፡ እኩያ፡ ባልደረባ። (ተረት): "ካብሮ አደግሽ አትሰደድ። "

ዐብሮ ኻያጅ: የመንገድ ጓድ።

ዐብሮ: አንድነት፡ አንድጋ ኹኖ።

ዐብዛ: እንጀራ። "በና " ተወራራሽ ስለ ኾኑ ዐብዛ በማለት ፈንታ "ዐምዛ ምጣድ" እንዲሉ።

ዐብዬ: የጋሼ ታላቅ (አብዬ)

ዐብደላ: በቡልጋናና በወግዳ ክፍል ያለ ቀበሌ።

ዐብደላ: ያምላክ ባሪያ፡ በዝርዝር "ዐብድ አላህ" ይባላል።

ዐብደላካኒ: ጥሩ የሐር ቀሚስ፡ መንግሥት ለጦር አለቆችና ለሌሎችም ሹማምት፣ ለካህናት የሚሸልመው ባለቀለም ልብስ፡ ሰንጠረዥ ወይም ሰንበር ያለው። ኣንዳንድ ሽማግሎች "ዐብደልኻን" የሚባል የህንድ ነጋዴ ከባሕር ስላመጣው "ዐብደላካኒ" ተባለ ይላሉ።

ዐብደል: የዛር ስም፡ ያረብ አገር ዛር።

ዐብድ (ዐረ): ባሪያ፡ የተገዛ፡ የተማረከ፡ አገልጋይ።

ዐብድ መለክ (ዕብ፡ ዔቤድ፡ ሜሌኸ): ገብረ ንጉሥ፡ የንጉሥ ባሪያ (ኤር፴፰፡ ፯-፰፡ ፲፡ ፲፩፡ ፲፪) የግእዝ መላሽ ግን አለ

ዐብድ ናጎ: የናጎ ባሪያ፡ ሚሳኤል (ከሠለስቱ ደቂቅ ፫ኛው)

ዐብድ እልመሲሕ: የመሲሕ ባሪያ፡ ጎብረ ክርስቶስ።

ዐብጤ: የሰው ስም፡ "ጠላትን ዐብጥ አስቸግር" ማለት ነው።

ዐቧራ: ያፈር፣ የደንጊያ፣ የንጨት፣ የሣር፣ የቅጠል ዱቄት፡ ብናኝ።

ዐቧሬ: ዐቧራ ያለበት፣ የበዛበት ስፍራ (ባዲስ አበባ ውስጥ ያለ)"ያቧራ ዐቧራዊ" ማለት ነው። "ዐቧሬ ገበያ" እንዲሉ።

ዐቧር: የዛፍ ስም፡ የሾላ ዐይነት ዕንጨት፡ ደሙ ሰባራ ዕቃ የሚያጣብቅ።

ዐተመ (ኀተመ): ዘጋ፡ ደፈነ፡ በማኅተም ረገጠ፡ ተጫነ፡ እንዳይከፈት ምልክት አደረገ (ዳን፮፡ ፲፯፡ ማቴ፳፯፡ ፷፮) (ማኅተም ማድረግ ወይም መዝጋት)

ዐተመ: በመኪና ጻፈ (በማሽን መጻፍ)

ዐተረ: ቈረበጨ፡ ተቋጠረ፡ ዐተር መሰለ፡ ኣከለ (መጠምዘዝ ወይም ማጠር) በትግሪኛ ግን ዐተረ፣ ያዘ፡ ጨበጠ ተብሎ ይተረጐማል (በትግርኛ ያለው ትርጉም)

ዐተሬ (ዐተራዊ): የቂጥኝ ስም፡ ዐተር የሚያካክል ቂጥኝ (የቂጥኝ ዓይነት)

ዐተሬ (ዐተርየ): የኔ ዐተር (የኔ አተር)

ዐተር (ሮች): ክብ እንክብል፡ ያበባ እህል፡ አገዳው እንደ ሐረግ ያለ (ኢሳ፳፰፡ ፳፯) (የአተር ፍሬ)

ዐተበ (ዐቲብ፣ ዐተበ): ዕትብት ቈረጠ፡ ማተብ አሰረ (ምህርትን መቁረጥ ወይም ማተብ ማሰር)

ዐተተ (ሐተተ): መረመረ፡ ተቸ (መረመረ)

ዐተተ: ወገደ አተተ።

ዐታሚ (ዎች): ያተመ፡ የሚያትም፡ ማኅተም ያዥ፡ የማተሚያ ቤት ሠራተኛ (የሚያትም ሰው)

ዐታሞ: አማሪት፡ ተመመ።

ዐታቢ (ዎች): ያተበ፡ የሚያትብ፡ ዕትብት ቈራጭ (ምህርትን የሚቆርጥ ወይም ማተብ የሚያስር)

ዐታች (ሐታቲ): ያተተ፡ የሚያትት፡ መርማሪ፡ ተቺ (የሚመረምር ወይም የሚተች)

ዐቸር: ዐሥረኛ፡ የቀባርዋ ምት (አስረኛ ምት)

ዐነቀ: ሥጋ በጕረሮ ውስጥ ተወትፎ አላናግር፡ አላስተነፍስ አለ (በምግብ መታነቅ)

ዐነቀ: አጣበቀ፡ ማደግ ከለከለ (ማቴ ፲፫፡ ፯፡ ማር፬፡ ፯) (ማገድ፡ ማነቅ)

ዐነቀ: ጕረሮን ያዘ፡ አሰረ፡ ፈተረ (ማነቅ)

ዐነቀፈ: የእግርን ጣት ገጯ፡ መታ፡ አሰናከለ። "ወንቃፍን" ተመልከት፡ የዚህ ዘር ነው፡ "ወለከፈን""ደነቀፈን" እይ (ማሰናከል)

ዐነከሰ: ዐፈረ፡ ተሰቀጠጠ፡ የእግርን (እግርን) ከዚህ የተነሣ ሰውየው በአንድ እግሩ ረገጠ፡ አነከለ (ዕብ፲፪፡ ፲፪) (ማንከስ)

ዐነገተ: በአንገት፡ በደረት፡ በዠርባ ተሸከመ፡ አንጠለጠለ (ጠመንዣን፡ መጻፍን፡ እንስራን)

ዐነጐተ: ዕንጐቻ ጋገረ (ለሕፃን፡ ለረኛ)

ዐነጠ: ቀረጠ ኮለል አበጀ፣ ሰነደቀ።

ዐነጠ: ቤት ሠራ፡ መዝጊያን፡ መስኮትን ገጠመ።

ዐነጠ: ጠረበ፡ ሸለተ፡ ላፃ፡ ፈለፈለ፡ በሳ፡ ቀረጻ፡ መገዘ (ዕንጨትን) (የእንጨት ስራ መስራት)

ዐነጠሰ: ፊቱን አከፋ፡ አፉን ከፈተ፡ በአፍና በአፍንጫ ከበርበሬ፡ ከክፉ ሽታ፡ ከካፊያ፡ ከጕንፋን የተነሣ በኃይል ተነፈሰ፡ ትንፋሹ ሲወጣ ተሰማ በአፍንጫው ንፍጥ፡ በአይኑ እንባ እስኪታይ ድረስ (፪ነገ ፬፡ ፴፭) (ማስነጠስ) "ባላገሮች ሕፃን ከናቱ ማሕፀን በወጣ ጊዜ የሚያነጥሰው መልአክ ዐፈር አምጥቶ ሲያሸተው ነው ይላሉ። " (የህዝብ እምነት) "ውሻም ሲያነጥስ እንግዳ ይመጣል ይባላል። " (የህዝብ እምነት)

ዐነጠጠ: ፋቀ፡ አለዘበ፡ ሰነጠ፡ አሰነበረ (ቀንድን)፡ ዋንጫ አበጀ (አንድን ነገር ማለስለስና ቅርጽ መስጠት)

ዐናቂ: ያነቀ፡ የሚያንቅ፡ ጠላት፡ ወጥመድ (የሚያንቅ ነገር ወይም ሰው)

ዐናቋ: የምድር ዕጥፋት፡ ወይም ቅንፋት፡ ያንድ በኩል ክበብ፡ ፈሳሽን ዐንቆ የሚይዝ (የምድር ቅርጽ)

ዐናት (ትግርኛ ሐናት): ለግዳ ቅምሖ፡ የጕረሮ ውስጥ መንታ ዕብጠት፡ የሚቧጠጥ (በጉሮሮ ውስጥ የሚከሰት እብጠት)

ዐናት: መኻል ራስ፡ ቍንጮ (የራስ ቅል የላይኛው ክፍል)

ዐናት: ቅቤ ሻ፣ ለመተኰሻ።

ዐናት: እንጥል (የአንድ ነገር ጫፍ ወይም ጕብት)

ዐናነጠ: ጠራረበ፡ ላላገ (በደንብ ጠረበ)

ዐናጢ (ዎች) (ሐናጺ): ያነጠ፡ የሚያንጥ፡ ጠራቢ፡ ላጊ፡ ቤተ ሠሪ፡ ገበዝ ዐምባ (የግንባታ ባለሙያ)

ዐናጢነት: ዐናጢ መኾን፡ ጠራቢነት።

ዐንቃ: ዕንጨት፡ አንቃ (እንጨት መሰል ነገር)

ዐንቃፊ: ያነቀፈ፡ የሚያነቅፍ፡ አሰናካይ (የሚያሰናክል ሰው ወይም ነገር)

ዐንቋሊት: ዐይብ፡ አንቋሊት (የአንድ ነገር መታወቂያ)

ዐንበል: ሻለቃ ዐምበል (የወታደራዊ ማዕረግ)

ዐንበሪ (ዐንበር) (ግእዝ): ታላቅ ዓሣ፡ መርከብ የሚገለብጥ፡ ታናሹን ዓሣ የሚውጥ፡ የሚሰለቅጥ፡ ዓሣ ነባሪ።

ዐንበሬ ጭቃ: ዐንበራዊ ጭቃ፡ ወይም የዐንበር ጭቃ፡ ቅባትነት ያለው የባሕር ሽቱ።

ዐንበር (ግእዝ): የሽቱ ስም፡ ጥንታዊ ሽቱ።

ዐንከስ (ሐንክሶ): ማንከስ።

ዐንከስ አለ: ዐሸድ አለ።

ዐንካሲት: ያነከሰች፡ የምታነክስ ሴት እንስት።

ዐንካሳ (ሶች) (ሐንካስ): ያነከሰ፡ የሚያነክስ፡ ትክክል የማይረግጥ፡ አንካላ (ኢሳ ፴፫፡ ፳፫) (የሚያነክስ ወይም አካል ጉዳተኛ)

ዐንካሳ ነገር: እውነት ብቻ ያይዶለ (እውነት የጎደለው ነገር)

ዐንካሳ: ቃል (አካላዊ ያልሆነ አንካሳነት)

ዐንካሳዋ: ዐንካሳዪቱ፡ ያች ዐንካሳ (ሚክ፬፡ ፮፡ ፯)

ዐንካሴ (ሐንካሳዊ): ወፈር ባለና ቅጥነቱ መጠነኛ በሆነ በትር፡ ጫፍ በአንድ በኩል የተዋደደ ሹል ብረት፡ የአንካሳ ምርኵዝ፡ ቢወጉበት የሚያስነክስ፡ ምዥራጥ፡ ሽብዳ፡ የመሰለው ሁሉ (፩ሳሙ ፲፫፡ ፳፩) (የማንከሻ መሳሪያ)

ዐንካስ: ዐንካሳ።

ዐንካስነት: ዐንካሳ መኾን።

ዐንገተ መቃ: ዐንገቱ/ መቃ የሚመስል (የሚያምር) ወንድ፡ ሴት።

ዐንገተ ሰባራ: ሸቍራራ፡ ዐይን ዐፋር ሰው (እፍረት ወይም ፍርሃት የተሰማው)

ዐንገተ ረዥሜ: ሰው (ረጅም አንገት ያለው ሰው)

ዐንገተ ረዥሜ: ዐንገታም፡ ዐንገተ ረዥም፡ የሜዳ ፍየል ዐይነት የበረሓ እንስሳ።

ዐንገተ ደንዳና (ኖች): የሚመጣበትን የማያውቅ (ዘፀ፴፪፡ ፱) (የማይታዘዝ፣ ግትር)

ዐንገቱን አዋቃ: አንገሸገሸ፡ አነቃነቀ፡ ከትከሻው ጋራ አማታ።

ዐንገቱን ደፋ: አቀረቀረ (ኢሳ፰፡ ፲፬) (አፍሮ ወይም ሀዘንተኛ ሆኖ)

ዐንገት: ሰመግ (ለእንስሳት አንገት የሚሰጥ ስም)

ዐንገት: በቁሙ፡ ከዕልቅት በላይ፡ ካገጭ በታች ያለ ገላ፡ ራስ ተሸካሚ፡ ከወደ ኋላ ማዥራት ይባላል። "ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ሐዋርያት ዐንገት ላንገት ተያይዘው አለቀሱ" (ከፍተኛ ሀዘን ለመግለጽ)

ዐንገት: ዐራዳ በር፡ በተራራ መካከል ያለ ጠባብ መተላለፊያ።

ዐንገትጌ: የአንገት ስፍራ፡ ዐንገትን የሚሸፍን የእጅጌ፡ ጠባብና የቀሚስ፡ የጥብቆ ክሣድ፡ በስተላይ ያለ ጫፍ (ዘፀ፳፰፡ ፴፪)

አንገቸገቸ: ዘከዘከ (ገቸገቸ)

ዐንገች: አገረ ወገብ፡ ከቈላ በላይ ያለ (የአገር አካባቢ)

ዐንጋች (ቾች): ያነገተ፡ የሚያነግት፡ ሰናድር ያዥ (አንገት ላይ የሚሸከም)

ዐንጋችነት: ዐንጋች መኾን።

ዐንጓች: ያነጐተ፡ የሚያነጕት። "ዐዛኝ ቅቤ ዐንጓች" እንዲሉ።

ዐንጣሽ: ያነጠሰ፡ የሚያነጥስ (የሚያስነጥስ ነገር ወይም ሰው)

ዐንጣጭ (ጮች) (ጎንጻጺ): ያነጠጠ፡ የሚያነጥጥ፡ ፋቂ፡ ዋንጫ፡ እንዝርት ሠራተኛ።

ዐኘከ: ቈረጠመ፡ በላ፡ ገተገተ፡ አላመጠ፡ አላመ፡ አመነዠኸ፡ አመሰኳ (ማኘክ) "ዐኝከኸ ዐኝከኸ ወደ ወገንኸ ዋጥ" እንዲሉ (አንድን ነገር በደንብ መረዳት ወይም መመርመር)

ዐኛኘከ: ቈረጣጠመ፡ በላላ (በደንብ ማኘክ)

ዐኛኪ: ያኘከ፡ የሚያኝክ፡ አላማጭ (የሚያኝክ ሰው ወይም እንስሳ)

ዐኝ መንከስ: ዐኘከ (ማኘክ)

ዐኝ አለ: በጥርስ ያዘ፡ ነከሰ፡ በላ።

ዐኝ አለ: ነከሰ፡ ዐኘከ።

ዐኝ: መንከስ፡ መብላት።

አኞ (አንጆ): ዐኘከ።

ዐኞ: ሲያኝኩት የማይደቅ ሥጋ፡ ማንጆ (ለማኘክ አስቸጋሪ የሆነ ሥጋ)

ዐኞ: ችኮ ሰው (የማይታዘዝ ወይም ግትር ሰው)

ዐከለ (ዕብ ዐካር): ዐዘነ፣ አለቀሰ፡ ተቸገረ።

ዐከመ (ሐከመ): ያበጠውን አፈረጠ፡ የጐረበውን ላጠ፡ ሀገመ፡ ተኰሰ፡ በጣ፡ ቀደደ፡ ጠገነ፡ መድኃኒት ሰጠ፡ አጠጣ፡ አዋጠ፡ በመርፌ ወጋ፡ አስታመመ፡ ፈወሰ፡ አዳነ።

ዐከረ: የአበባ እህል ዘራ (አከረ)

ዐከበ: ሰበሰበ (አከበ)

ዐከተ: ሰብስቦ አሰረ (አከተ)

ዐከከ (ሐከከ): በጥፍር፡ በንጨት፡ በመሬት ገላውን ፎከተፈገፈገ (የደግ) "ጠቈመን" "ነዘገን" ተመልከት።

ዐከከ: በቀላል ላገ፡ ፋቀ (ዕንጨትን)

ዐከከ: አደፈ

ዐከከ: ወረ፡ ቧጠጠ፡ ሰነዘረ (ሰውን፡ እንስሳን፡ አንበሳ፡ ነብር) (የክፉ)

ዐኪም (ሞች) (ሐኪም): በሽታንና መድኃኒትን ሁሉ የሚያውቅ፡ ፈዋሽ፡ አዳኝ፡ ወጌሻ። "የአንጐል፣ የዐይን፣ የዦሮ፣ የጥርስ፣ የሆድ ዐኪም (ሐኪም)" እንዲሉ። (ዐኪም የሕዝብ፡ ሐኪም የካህናት አነጋገር ነው)

ዐካሚ (ዎች): ያከመ፣ የሚያክም፡ ዐጋሚ።

ዐካከከ: መላልሶ ዐከከ (እንደገና ደጋገመ ማከክ)

ዐካኪ (ሐካኪ): ያከከ፡ የሚያክ፡ ቧጫሪ፡ ቧጣጭ፡ ሰንዛሪ፡ ጥፍራም አውሬ።

ዐካኪ አካኪ ተብሎ ቢጻፍ ግን: አዋኪ፡ አሸባሪ፡ በጦር ሜዳ ተከራካሪ፡ የጐበዝ ጐበዝ ማለት ነው (፩ሳሙ፡ ፲፯፡ ፵፮-፶፩)

ዐካኪ ዘራፍ: የፉከራ ቃል፡ ዐካኪን የሚዘርፍ፡ የሚቀማ፡ ካንበሳ፡ ከድብ በግን የሚያስጥል (፩ሳሙ፡ ፲፯፡ ፴፬-፴፯)

ዐካካ: ኹለንተናው ዕከክ

ዐወረ (አዖረ): ኹለት ዐይን ዐጠፋ፡ ዕውር አደረገ፡ ከለለ፡ ጋረደ፡ አጨለመ፡ ሰወረ።

ዐወቀ (ዖቀ): ተማረ፡ አጠና፡ ለመደ፡ ተረዳ፡ ለየ፡ ልብ አደረገ፡ አስተዋለ፡ ሠለጠነ (መሳ፲፯፡ ፲፫፡ ፲፰፡ ፫፡ ዮሐ፬፡ ፶፫) (ተረት): "ለራሱ አያውቅ፡ ነዳይ ቅቤ ለመነ ላዋይ። ሴት ታውቅ፡ በወንድ ያልቅ። "

ዐወደ (ዖደ): ዞረ፡ ክብ ኾነ።

ዐወደ: ቈራረጠ፡ መላልሶ ዐጨደ።

ዐወደ: ዑድኛ ሸተተ (አልባብ አልባብ አለ)፡ አጋሙ፡ ርጐፍቱ፡ የሎሚ እሸቱ። "ደን ኹሉ በጥቅምት ያውዳል" [ይባላል]

ዐወደ: ዒድ (ዐረ)፡ የበዓል ስም፡ የእስላም ዓመት በዓል።

ዐወጀ (ዖደ): እየዞረ ዐዋጅ ነገረ፡ ለፈፈ።

ዐወጠ (ሐወጸ): ጐበኘ።

ዐዋሪ: ያወረ፡ የሚያውር።

ዐዋሽ (ሐዋሽ): የወንዝ ስም፡ የሺዋንና የሐረርጌን ግዛት እየለየ ወደ አዳል በረሓ የሚወርድ፡ ካዲስ አበባ በስተደቡብ ያለ ታላቅ ዠማ፡ ከሜ ተራራ የሚነሣ። "በክረምት መልቶ መፍሰሱን፡ መትረፉን፡ መትረፍረፉን፡ በዐውሳ በረሓ ብዙ ሜዳ መያዙን፡ መንጣለሉን፡ በበጋ ግን መሥረጉን፡ ማነሱን፡ መጕደሉን፡ ባሕረ ሸሽ መኾኑን ያሳያል" [ይባላል] እሱም ባጤ ዘርዐ ያዕቆብ ታሪክ "ሐዋሽ" ይባላል፡ ምስጢሩ "በሖሰ ዘይቤ" መነቃነቅንና መንቀሳቀስን ያስረዳል።

ዐዋሽ (ሾች): ታላቅ ጋን፡ ገች፡ ፭ ቍና እኸል የሚጠምቅ። "ዐዋሽ ወንዝ ወደ ርሱ ከሚገቡት ወንዞች እንዲልቅ፡ ዐዋሽ ጋንም ከጋኖች መብለጡን፡ ጠጁ ወይም ጠላው በብዙ እንስራና ማድጋ መቀዳቱን ያሳያል" [ይባላል]

ዐዋቂ (ቆች): ያወቀ፡ የሚያውቅ (መዝ፻፯፡ ፵፫፡ ኤር፱፡ ፲፪)

ዐዋቂ: ጠንቋይ፡ ሐኪም፡ ወጌሻ፡ ፈላስፋ። "የምድር ዐዋቂ" እንዲሉ። (የሚዛን ዐዋቂ): ሚዛን፡ መመዘኛ፡ ማስተካከያ ብረት፡ ርሳስ፡ ደንጊያ (ዘሌ፲፱፡ ፴፮፡ ኢሳ፵፡ ፲፭፡ ራእ፲፮፡ ፳፩) በግእዝ "መክሊት" ይባላል።

ዐዋቂ: ጨዋ፡ ሽማግሌ፡ ያምሳ ዓመት ሰው፡ በግእዝ "ልሂቅ" ይባላል።

ዐዋቂት: ነፍስ።

ዐዋዜ: የዐዋዝ፡ ፍሬው ከወጣ ቀይ ዛላ በርበሬ የተዘጋጀ ብትን ወይም ብጥብጥ ድልኽ (የሥጋ መብሊያ)፡ ሲያዩት ደስ የሚያሠኝ። ይኸውም ከተቀቀለ ነጭ ሽንኵርት ጋራ ይላማል፡ ነጭ አዝሙድ፡ ኰረሪማ፡ ዝንጅብል፡ የበሶብላ ፍሬ ይገባበታል።

ዐዋዝ (ሓወዘ ሐዋዝ): ያማረ፡ የጣፈጠ።

ዐዋዲ: የወንዝ ስም፡ ከይፋት ፈልቆ ወደ ግራ ይዞርና ዐዋሽ የሚገባ (ዠማ)፡ በግእዝ "የዞረ፡ የሚዞር፡ ዘዋሪ" ማለት ነው።

ዐዋጅ (ዐዋዲ): ያወጀ፡ የሚያውጅ፡ የሚለፍ፡ ለፋፊ።

ዐዋጅ (ዐዋድ): ከመንግሥት ለሕዝብ የሚነገር ደንብ፡ ውሳኔ፡ ትእዛዝ። "ዐዋጅ ዐዋጅ የደበሎ ቅዳጅ፡ ያዋጁን በዦሮ" እንዲሉ።

ዐዋጅ መንገሪያ: ከፍተኛ ስፍራ።

ዐዋጅ ነጋሪ (ነጋሬ ዐዋድ): ዐዋጅን የሚነግር፡ ስማ ስማ ባይ (ዮሐ፩፡ ፳፫)

ዐዋጅ: "የወደቀን አንሣ፡ የሞተን ቅበር። "

ዐዋጅ: ዘዋሪ። "ዐይን ዐዋጅ ኾነበት" እንዲሉ።

ዐውላ: የማር ርሾ።

ዐውሎ ነፋስ (መንፈሰ ዐውሎ): ጥቅል ነፋስ፡ ጠሮ ኵርፊት፡ ኀይለኛ፡ ቤት የሚያፈርስ፡ መርከብ የሚገለብጥ፡ ዐፈርን፣ ባሕርን ወደ ላይ የሚያነሣ፡ የሚያቆም (መዝ፲፩፡ ፮፡ ፪ነገ፡ ፪፡ ፩፡ ሕዝ፩፡ ፬)

ዐውሳ (ዐረ ዐውጻህ): የበረሓ ስም፡ ያዳል አገር ምድረ በዳ።

ዐውቂያ (ዐውቅ): የሚያውቁት ሰው።

ዐውቅልሽ: ጥንቈላ።

ዐውቆ አበድ: ሳያብድ ኾኖ ብሎ ያበደ። (ሲያውቅ አበድ): ዝኒ ከማሁ [ያው ማለት ነው]

ዐውቆ ፈረንጅ: ሳይማር እንደ ፈረንጅ የሚለብስ።

ዐውቆ: ወዶ ፈቅዶ።

ዐውዛ (ሐውዝ): አፍልተው የሚጠጡት የት ውሃ፡ የጨብጥ መድኀኒት።

ዐውዜን: የአገር ስም (ሐውዜን)

ዐውዜን: የእህል ጐተራ (ሐውዜን)

ዐውደ ነገሥት: የጥንቈላ መጣፍ፡ ፲፮ ክብ ሰንጠረዥ ያለው። ዐረቦች "ጠላዋት አልሙሉክ" ይሉታል።

ዐውዳመት (ዐውደ ዓመት): ያመት ዐውድማ፡ መስከረም ሲብት በአመት የሚከብር በዓል፡ ቅዱስ ዮሐንስ የዘመን መለወጫ። ያመትን መዞርና፡ የሕዝብን ስብሰባ ያሳያል። "ዳግመኛም አጿማትና በዓላት ተሰብስበው በመስከረም ቀን ይነገራሉና ዐውዳመት ተባለ" ይላሉ። "ገናና፣ ጥምቀት፣ ፋሲካ፣ ዕርገት፣ ጰራቅሊጦስ፣ መስቀል፣ ሌላውም ታላላት በዓል ኹሉ ዐውዳመት ይባላል። "

ዐውድ: አደባባይ፡ ሸንጎ፡ የሕዝብ መሰብሰቢያ። "ጥጋብ ሲበዛ ዐውድ ይጥላል" [ይባላል]

ዐውድ: ዙሪያ፡ ክበብ።

ዐውድ: የቍጥር ስም፡ ክብነት ያለው ቍጥር፡ ባለሰንጠረዥ። "ዐውደ ጨረቃ፡ ዐውደ ፀሓይ" እንዲሉ።

ዐውድ: ጻሕል፡ ሳሕን፡ ዝርግ ሰታታ፡ ወጭት፡ ክብ የቍርባን መቀመጫ።

ዐውድማ: ዙሪያማ፡ ባለዙሪያ፡ እኸል የሚወቃበት፡ ምርት የሚታፈሥበት፡ ኵልኵል ያለው ወለል (ይኸውም አስቀድሞ ውሃ እየተርከፈከፈ በጭድ በገለባ ይረገጣል፡ ቀጥሎም በበት ይለቀለቃል) (ማቴ፫፡ ፲፪) "ሲበዛ ዐውድሞች ይላል" (ዮኤ፪፡ ፳፬) (የወይን ዐውድማ): የወይን ፍሬ መርገማ። (ጥማ) ውድማ: ዝኒ ከማሁ [ያው ማለት ነው]

ዐዘለ (ሐዘለ): በዠርባ ላይ ተሸከመ፡ እንቡቡ አለ፡ ያዘ፡ ለጠፈ፡ ደረበ።

ዐዘል: ዝኒ ከማሁ [ያው ማለት ነው]፡ ያዘለ፡ ያዘለች። "ለቆ ዐዘል፡ አውራ ዐዘል" እንዲሉ።

ዐዘሎ: የተራራ ስም፡ ባዳል በረሓ ውስጥ ያለ ረዥም ደብር፡ የመናኞች ኖሪያ።

ዐዘመ: በሰው ክፉ መድኀኒት አደረገ፡ ኣፈዘዘ፡ እደነዝዘ፡ እደነዘዘ።

ዐዘቅት: በደብረ ሊባኖስ ገዳም በገደልና በወንዝ ውስጥ ያለ ዋሻ፡ የግሑሣን መኖሪያ፡ በግንብ የተዘጋ።

ዐዘቅት: የውሃ ወይም የኩስ ጉድጓድ።

ዐዘበ (ሐዘበ): ጠለፈ፡ አያያዘ፡ አወራረሰ፡ አገናዘበ፡ ቈለፈ፡ መሚያን ሠራ።

ዐዘበ (ዐዝቦ ዐዘበ): ጣለ፡ ወረወረ፡ አሽቀነጠረ።

ዐዘበ: ጐነጐነ፡ ቋድ አበጀ (ዕዛብ)

ዐዘቦ: አገር (አዘቦ)

ዐዘቦት: ሥራ የማይሠራበት ሰሞን። በግእዝ "በዓለ ተሐውሶ ክብረ ቅዱሳን" ይባላል፡ "ዛሬ የሥራ ጊዜ ነውና ይህን ነገር ባዘቦቱ ቀን እንነጋገረዋለን" [እንዲሉ። ]

ዐዘነ (ሐዘነ): ተከዘ፡ አለቀሰ፡ ተጸጸተ፡ ራራ፡ ተቈረቈረ፡ ተከፋ፡ ተቀየመ (ዘፍ፮፡ ፮፡ ፪ሳሙ፡ ፲፱፡ ፪፡ ዮሐ፲፩፡ ፴፫)

ዐዘነ፡ ነደደ፡ ተከነ፡ ገመነ፡ የልብ።

ዐዘነ: ተቈረቈረ ከደስታ ከፈገግታ ራቀ

ዐዘነተኛ (ኞች): ዐዘን ያለው፡ ዐዘን ያጠቃው፡ የጐዳው፡ አልቃሽ፡ አባትና እናት፡ ሚስት፡ ልጅ፡ ወንድም፡ እት፡ ዘመድ፡ ወዳጅ የሞቱበት፡ ንብረቱ የጠፋበት፡ ታላቅ አደጋ ያገኘው፡ የደረሰበት ሰው።

ዐዘና: ርኅራኄ፡ ጸጸት።

ዐዘኔታ: ቸርነት፡ ደግነት፡ ርኅራኄ፡ ምሕረት።

ዐዘን (ሐዘን): ለቅሶ፡ ትካዜ (ዮሐ፲፮፡ ፮፡ ፪ቆሮ፡ ፪-) (አልቃሽ): "የሞተው ወንድምሽ፡ የገደለው ባልሽ። ዐዘንሽ ቅጥ ዐጣ፡

ዐዘን ተቀመጠ: ወይም ቀን አለቀሰ፡ ለቅሶኛ ተቀበለ።

ዐዘን ተፍሥሓ: መወለድና መሞት፡ ማጣትና ማግኘት፡ ሰርግና ለቅሶ፡ "ይህን የመሰለ ኹሉ ባንድ ቀን ቢደረግ ዐዘን ተፍሥሓ ይባላል" (መዝ፴፡ ፭)

ዐዘንተኛ: ዝኒ ከማሁ [ያው ማለት ነው]

ዐዘንተኞች: ዐዘነተኞች (ዮሐ፲፮፡ ፳፪)

ዐዘዘ (ዐዝዞ ዐዘዘ): በለጠ፡ ተረፈ፡ ጠና።

ዐዘዞ: አገር (አዘዞ)

ዐዚማም: ዐዚም ደጋሚ፡ ባለዐዚም።

ዐዚም: አፍዝ፡ አደንግዝ።

ዐዛሚ: ያዘመ፡ የሚያዝም፡ አፍዛዥ።

ዐዛቢ (ዎች): ያዘበ፡ የሚያዝብ፡ ጐንጓኝ፡ አያያዥ።

ዐዛባ: ከመሬት ካፈር ጋራ የላቈጠ እበትና ፋንድያ በጠጥ፡ ከበረት ከጋጣ ውስጥ አውጥተው የሚጥሉት።

ዐዛት: አፈ ሰፊ፡ ቀጪን ቁመተ ሾጣጣ ዓሣ።

ዐዛኝ (ኞች): ያዘነ፡ የሚያዝን፡ ርኅሩኅ። "ዐዛኝ ማሪያም" እንዲሉ። (ተረት): "ዐዛኝ ቅቤ ዐንጓች። "

ዐዛኝቱ: ርኅሩኂቱ፡ ርግብ ሆዷ ወላላዋ ማሪያም። (የባለጌ ግጥም): "የተማሪ ወዳጅ ይቅር ምናባቱ፡ ጐራዴ ሲመዘዝ ይላል ባዛኝቱ። " (የገለሞታ መልስ): "እንኳን ባዛኝቱ ይበል በሥላሴ፡ እኔ እወደዋለኹ እስቲወጣ ነፍሴ። "

ዐዛውንት (ትግ. ዐዘወ፡ ደግ ኾነ): ደግ፡ ደገኛ፡ ጥኑ፡ ጠንካራ፡ ታላቅ፡ ጪዋ፡ ሽማግሌ፡ ማለፊያ ሰው፡ መታፈርና መከበር ያለው። በግእዝ "ልሂቅ" ይባላል። ትግሮችም "ዕዝው" ይሉታል።

ዐዛውንቶች: ደገኞች፡ ታላላቆች፡ ጩዋዎች፡ ጐምቱዎች። "ዐዛውንት የዕዝው ብዥ ሲኾን ባማርኛ ስላንድ ይነገራል" [ይባላል] "ይኸውም በግእዝ አነጋገር ኅጻውንት ዐቃርብት ባለው ይታወቃል" [ይባላል] "ዳግመኛም አውሬ፡ አውሬዎች በማለት ፈንታ አራዊት፡ አራዊቶች እንደ ማለት ያለ ነው" [ይባላል] "ዐዞን" ተመልከት።

ዐዛዜ: ባለትልቅ ፍሬ፡ ስንዴ፡ ጥናት፡ ጥንካሬ ያለው፡ ዐመድማ።

ዐዛዩን ነካሽ: ክፉ ሰው፡ ወረታ ቢስ፡ ወዳጁን ጐጂ።

ዐዛይ (ዮች) (ሐዛሊ): ያዘለ፡ የሚያዝል አባት፡ የምታዝል እናት፡ እንስት ጦጣ፡ ዝንጀሮ፡ ተሸካሚ። " ባይ ዳውላን ዐዛይ እንዳለ ተማሪ" [ይባላል]

ዐዞ (ትግ): ሖምጣጣ፡ መጣጣ፡ ነጭ ሽንኵርትና ሰናፍጭ የገባበት ርጎ፡ ለሰርግ የሚኾን። (ግጥም): "እኅቶችኸ የሉ፡ ወይ እናትኸ የሉ፡ ማን ሠራልኸና ዐዞ በላኸ ኣሉ። "

ዐዞ (ዐዘዘ): የባሕር አውሬ፡ ሆደ መጋዝ፡ ጋድሚያ፡ እንቅልፋም (ዘሌ፲፩፡ ፴) "ያገኘውን ሰውና እንስሳ በዥራቱ እየጠለፈ ወደ ባሕር ይዞ ይገባል" [ይባላል] እንስቲቱ በአሸዋ ውስጥ ዕንቍላል ትወልዳለች፡ ከዚያም ገላግልት ይወጣሉ። "ሲበዛ ዐዞዎች ያሠኛል" [ይባላል] "አዘዘና ዐዞ ባማርኛ ይተባበራሉ" [ይባላል] (ግጥም): "ልጄን ኣትጥሉብኝ ቢያዛችኹ ተሹሞ፡ አዐዞ አያውቅምና ከዚህ አስቀድሞ። ግባተ መሬቱን አትድገሙ እናንተ፡ ታዞ ኺዷል እንጂ፡ ልጄ መቼ ሞተ። ላንድ ቀን ትእዛዝ ሰው ይመረራል፡ የኔ ወንድም ታዞ አባይ ላይ ይኖራል (ኣባቱና እናቱ እቱ) "

ዐዞ ዐረግ: ጥኑ፡ ጠንካራ ዐረግ። "አበባው እድልኸ ይገባል፡ ቅጠሉንም በክንድ ላይ ያሰሩት እንደ ኾነ ኣቃጥሎ ያቈስላል" [ይባላል] "ዐዞ ከያዘች እንደማትለቅ ያዞ ዐረግም ማሰሪያነት ጥብቅ መኾኑን ያሳያል" [ይባላል] "ዐዛትን" ተመልከት።

ዐዞ ከል: የስንዴ፡ የወይን፡ የበለስ ቅጥራን። "ዐዞ እንዳለፈው ትግሪኛ፡ ከል ዐረብኛ ነው" [ይባላል]

ዐየ (ዐየነ): ተመለከተ፣ አስተዋለ፣ ተኰረ፣ ዓይኑን ጣለ።

ዐየለ (ኀየለ): በረታ፡ በዛ።

ዐየለ: የወንድ ስም።

ዐየለች: የሴት ስም።

ዐየል አለ: በዛ፡ በርታ አለ።

ዐየል: በርታ። "ሚስቱ ዐየለች ዐየል ብላበታለች" እንዳለ ካታ ወልደ ሚካኤል (በተረት ወይም በውዝዋዜ የተጠቀሰ)

ዐየመ (ዔመ፡ መሰገ): ዐረሰ፡ ቀበቀበ፡ አለሰለሰ።

ዐየረ (ዐይሮ ዐየረ): ቀላቀለ፡ ደባለቀ፡ አዋዋደ።

ዐየር: ሰማይ፡ ነፋስ (አየር)

ዐየበ (ሔበ): አረጋ፣ ዓይብ አበጀ፣ አዘጋጀ፡ ጠለቀ፣ ቀዳ።

ዐያሌ: ዝኒ ከማሁ፡ ለዐያል (ተመሳሳይ ማለት ነው፡ ለዐያል የሚሆን)

ዐያሌው: የሰው ስም።

ዐያል: ብዙ፡ እጅግ። "ለደመራ ዐያል ሰው መጣ። "

ዐያሚ: ያየመ፡ የሚያይም፡ ዐራሽ፡ አለስላሽ።

ዐያሪ: ያየረ፡ የሚያይር፡ ቀላቃይ፡ አዋዋጅ።

ዐይበት (ቶች): የወይፈን ስልቻ፡ ጭልጊ፡ አቍማዳ፡ ቀርበታ፡ የውሃ መቅጃ (ዘፍ፵፪፡ ፳፭፣ ፳፯፣ ፳፰)

ዐይብ (ሐይብ): አጓትና ቅቤ የወጣለት የወተት አተላ፡ ከእንጀራ ጋር የሚበላ። (ተረት): "ከይሉኝ አይል ዐይብ አትብላ፡ አይመረው አይተኵሰው፡ ውጦ ውጦ ይጨርሰው" "ዐይቡ ዳኛ፡ ቅቤው መልከኛ" "ዐለበ" ብለኸ "ዐሊብን" ተመልከት።

ዐይቦ ንጣቱ: ዓይብ የሚመስል ነጭ በሬ፡ የጌታችን ምሳሌ። "ቀንድን" አስተውል።

ዐይቦ: ነጭ ስንዴ፡ ጣይ፡ ሶራና ቡን እግርም ይባላል።

ዐይነ ሌባ: አመንዝራ፡ በዐይን የሚሰርቅ፣ የምትሰርቅ። "የማነሽ ቀዘባ፡ አንቺ ዐይነ ሌባ" እንዳለ ዘፋኝ።

ዐይነ ልም: ዐይነ ደካማ፡ ቅንድበ ቢስ።

ዐይነ ልብ: የልብ ዐይን።

ዐይነ መዓት: የቁጣ ዐይን

ዐይነ ማዝ: ማዝ የሚባል የዐይን በሽታ የሚበላ የሚያሳክክ

ዐይነ ምሕረት: የምሕረት፡ የይቅርታ ዐይን

ዐይነ ምድር: ኵስ ዐር (ኢሳ፴፮፡ ፲፪)

ዐይነ ምድር: የምድር ዐይን የተባለ ፊንጥጣውና ጕድጓዱ ነው።

ዐይነ ሞራ: የዐይን ሞራ፡ ዐበላ። "ዐረረ" ብለኸ "ዕርርትን" ተመልከት።

ዐይነ ሥቡን አለው: ዐይኑን መታው፡ አነጐደው።

ዐይነ ሥብ: የዐይን ጕድጓድ። (ሥብ የተባለ ነጩ ነው)

ዐይነ ስውር: ዐይኑ ባለማየት የተሰወረ የተከለለ

ዐይነ ሥጋ: ግዙፍ የሥጋ ዐይን

ዐይነ ርግብ: ትንሽና ትልቅ ኹለት የድጕስ መሣሪያ።

ዐይነ ርግብ: ከሽቦ የተበጀ፡ የተዘጋጀ ጥልፍልፍ ውስብስብ

ዐይነ ርግብ: የሐር ክር ትት፡ የወይዛዝር ፊት ጌጥ። (ርግብ አይተው መራራታቸውን፡ ያይናቸውን ማማር ያሳያል)

ዐይነ ርግብ: የደርብ ሰበስብ ጌጥ፡ በተበሳሳ ሳንቃ የተሠራ (፬ነገ፡ ፯፡ ፬፡ ፪ነገ፡ ፩፡ ፪)

ዐይነ ሸውራራ: ዐይነ ጠማማ፡ ወይንም ወልጋዳ።

ዐይነ በጎ: ከጨጓራ ጋራ የሚገኝ የብጥብጥ ምግብ፡ ሥጋዊ ከረጢት ሰፍነግና ባለማያ ሴት የጋገረችው ነጭ ጤፍ እንጀራ መሳይ።

ዐይነ ባር: እንደ መስተዋት ያለ ብራና፡ የባሕር ዐይነት ጽፈትን በዠርባው የሚያሳይ። ፈረንጆች "ትራንስፓራን" ይሉታል።

ዐይነ ባና: ዐይኑ ባና የመሰለ ፈረስ ለምጦ።

ዐይነ ብሩት (ብርህተ ዐይን): አነባበሮ፡ ባለብዙ ዐይን።

ዐይነ ብር: ድመት።

ዐይነ ተኵላ: ክብ ሞላላ የማር መቁረግ ሸክላ፡ ጪስ መያዣ፡ ባለብዙ ዐይን (ብስ) (ተኵላ የተባለ ቀፎ የሚደፋ ዐራጅ ነው)

ዐይነ ተኵላው ጠፋ: የነገሩ መላው ኹኔታው ቅጡ ታጣ፡ ቸገረ።

ዐይነ ነፍስ: ረቂቅ የነፍስ ዐይን

ዐይነ ወርቅ: ሰውን ወደ እንስሳነትና ዕቃነት የሚለውጥ ምትሃተኛ ጠንቋይ

ዐይነ ወርቅ: ዐይንን ብጫ ወርቅ የሚያስመስል የሐሞት በሽታ

ዐይነ ወግ: በዐይን ወግቶ የሚያሳምም ቡዳ።

ዐይነ ውሃ (ያይን ውሃ): ውሃ የሚመስል ያይን ብረት።

ዐይነ ውሃ: "ዘሎ ባይኔ"፡ የውሃ ዐይን ክብ እንክብል (እብጠት)

ዐይነ ውሃ: የቅኔ ስም ነው።

ዐይነ ደረቅ: ዕፍረተ ቢስ። "የሌባ ዐይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ" እንዲሉ።

ዐይነ ደረቅ: ያየውን የሚያደርቅ ሰው።

ዐይነ ደካማ: ዐይኑ የደከመ።

ዐይነ ገመድ (ገመደ ዐይን): የዐይን ገመድ ልክ፡ ማየት።

ዐይነ ገብ: የሚያምር መልክ።

ዐይነ ጥላ: "ጸሎት በእንተ ዐይነ ጥላ" ብሎ የሚጀምር የአስማት ክታብ

ዐይነ ጥላ: ጥላ ከፀሓይ ሙቀት እንዲከልል፣ የሰው ልቡና ትጋትን ዕውቀትን እንዳያገኝ የሚያደርግ የስንፍና መንፈስ

ዐይነ ጨምጫማ: ዐይኑ ሁልጊዜ የሚያለቅስ

ዐይነተኛ: ባለመልክ፡ ዋና ሰው፡ ግንባር፡ ቀደም፡ መደበኛ፡ ስሙና ግብሩ የታወቀ፡ ቀዋሚ ነገር

ዐይነተኛነት: ዋናነት፡ መደበኛነት፡ ዐይነተኛ መኾን።

ዐይነተኞች: ዋኖች ሰዎች፡ በዓሎች (፪ዜና፡ ፰፡ ፲፡ ሕዝ፵፬፡ ፳፬)

ዐይነታ: ጭገሬታ መሰል ዐይነት።

ዐይነት (ሕብር): ልዩ ልዩ መልክ ያለው ፍጥረት፡ ሥራው፡ ኹኔታው እየራሱ የኾነ ወገን፡ ነገድ፡ ጠባይ። "ምን ዐይነት"፡ ዐይነቱ የማይታወቅ" እንዲሉ። (የንጨት፡ የደንጊያ፡ የሣር፡ ያውሬ፡ የወፍ፡ የንስሳ፡ የከብት፡ የሰው ዐይነቱ ብዙ ነው) (ምግብ፡ መጠጥ፡ ልብስ፡ ዕቃ፡ በያይነቱ): በየመልኩ፡ በየቀለሙ ማለት ነው።

ዐይነት: አምሳያ፡ ምሳሌ። "መልክንና" "ሕብርን" ተመልከት።

ዐይነት: ዐይንነት፡ ዐይን መኾን፡ ምሰል

ዐይነት: ዕከክ፡ ቍስል፡ ስፋቱ ዐይን የሚያካክል።

ዐይነቶች: መልኮች፡ ቀለሞች፡ ቍስሎች።

ዐይኑ ላይ ጣለበት: ጉም አስመሰለው

ዐይኑ ቍራኛ: የዐይን ዘበኛ፡ ወይም እስረኛ

ዐይኑ ባከነ: ተቅበዘበዘ

ዐይኑ ብር አለ: ከሳጐደጐደ

ዐይኑ ተመረገ: አልገለጥ አለ።

ዐይኑ፡ ተሰወረ) ታወረ፣ ኣላይ አለ፣ ተሰወረ፣ ረቀቀ።

ዐይኑ ተንከራተተ: በብዙ ወገን አየ፡ የሚፈልገውን ለማግኘት።

ዐይኑ ተጐለጐለ: ወጣፈጠጠ

ዐይኑ ታወከ: አላይ አለ፡ ማየት ተሳነው።

ዐይኑ : ዐይን የሚጻፍ በዐ ስለኾነ የዐ ስም ዐይኑ ተባለ።

ዐይኑ ደገደገ: ወየበ፡ ብጫ መሰለ፡ ፈዘዘ

ዐይኑ ደፈረሰ: ነጩና ጥቁሩ አልተለየም

ዐይኑ ጠገበ: ከማእዱ ብዛት የተነሣ ሳይበላ በማየት ጠገበ

ዐይኑ ጠፋ: ታወረ፡ አላይ አለ።

ዐይኑ ጠፋ: ጫፉ ታጣ፡ የፈትሉ፡ የሐሩ፡ የሽቦው፡ የክሩ።

ዐይኑ ፈሰሰ: ጠፋወደመ

አይኑት: ትንሽ ማሰሮ (ዐይኑት)

ዐይኑት: ከጭንቍላ የምታንስ ማሰሮ

ዐይኑን ሰካ: ባለማቋረጥ አስተዋለ

ዐይኑን ባይኑ አየ: አስመስሎ ወለደ

ዐይኑን ተከለ: ትክ ብሎ አየ፡ ተኰረ (ግብ ሐዋ፮፡ ፲፭)

ዐይኑን አራመደ: ከቅርብ ወደ ሩቅ ተመለከተ

ዐይኑን አነሣ: አቀና

ዐይኑን አያሳየኝ አለ: ፈጽሞ ጠላ፡ መረዘ።

ዐይኑን ገለጠ: ዐወቀዐዋቂ ኾነ

ዐይኑን ገደለ: አጨለገጨነቆረ

ዐይኑን ጣለ: አስተያየቱን በአንድ ነገር ላይ አደረገ

ዐይና: ዐይን። "አንድ ዐይና""አራት ዐይና" እንዲሉ። (በግእዝ ግን ዐይኗ ማለት ነው)

ዐይናማ ደንጊያ: እንደ ንብ እንጀራ ብስ ጠቃጠቆ ያለው።

ዐይናማ: ዐይነ ትልልቅ። (ዋ፣ ዪቱ በመጨረሻ ሲጨመሩበት ዐይናማው፣ ዐይናማዋ፣ ዐይናማዪቱ እያለ ወንድና ሴትን ይለያል)

ዐይናማዬ: የኔ ዐይናማ። የዘፈን አዝማች ነው።

ዐይናር: የዐይን ዐር፡ የዐይን እድፍ።

አይናገር፣ አይጋገር: ድዳ፣ ዱድማ።

ዐይኔን ዕጠቡኝ አለ: ፈጽሞ እንቢ አለ

ዐይን (ኖች): የማየት ህዋስ፡ በንስሳና በአውሬ፡ በወፍ፡ በሰው ፊት ግራና ቀኝ የተተከለ ኹለት ሥጋዊ መብራት፡ ብርሃን፡ ዙሪያው ነጭ፡ መካከሉ ጥቍር፡ በማየት ከኹሉ ይፈጥናል። "ካይን የፈጠነ፡ ከውሃ የቀጠነ" እንዲሉ። "ርሱ ሲጠፋ አካል ኹሉ በጨለማ ይኖራል" (ማቴ፯፡ ፳፪፣ ፳፫)

ዐይን ላይን ተሳበረ: ዐይን ከዐይን ጋራ በመተያየት ተሸናነፈ

ዐይን ላይን: ፊት ለፊት

ዐይን ባይን: እየታየ፡ በግልጥ። "አንዳንዱ ሌባ ዐይን ባይን ይሰርቃል"

ዐይን ዐምባ: የቀበሌ ስም፡ በእንሳሮ ውስጥ ያለ መንደር።

ዐይን አበባ: ብጫ ጥለት።

ዐይን አብራ: የዐይን ሐኪም።

ዐይን አወጣ: አበጀ፡ አሳመረ።

ዐይን አወጣ: አፈሰሰ፡ አጠፋ፡ አፈጠጠ፡ ዕፍረት ዐጣ።

ዐይን ዐዋጅ: ዘዋሪ ዐይን። "ዐይን ዐዋጅ ኾነበት" እንዲሉ።

ዐይን አውጣ: ባለጌ፡ ዐይንን የሚያወጣ፡ ዕፍረት የለሽ (፩ሳሙ፡ ፲፩፡ ፪)

ዐይን ዐፋር: ዐንገተ ሰባራ፡ ሰውን የሚያፍር፡ የሚፈራ፡ ቀና ብሎ የማያይ። ዐይን ዐፋር ለሴትም ይነገራል። "ዐይን ዐፋር ልጃገረድ ከወንድ ታረግዛለች" እንዲሉ።

ዐይን ጣለ: አስተያየቱን በአንድ ነገር ላይ አደረገ

ዐይን: በቍና ይሰፍራል፡ የክፉ መጨረሻ ነው፡ ክፋትን "ይህ ቀረኝ" እያለ ይሠራል (የዐይን ክፋትን ያመለክታል)

ዐይን: በተንቀሳቃሽ መኪና ግንባር ያለ የኤሌትሪክ ብርሃን።

ዐይን: ብስ ቀዳዳ። "የንጀራ ዐይን""የመርፌ ዐይን" እንዲሉ።

ዐይን: የልቃቂት ፈትል ጫፍ። ዐይን ዘርፍ ይዞ ከአንቀጽ አስቀድሞ እየገባ በዘርፍነትና በባለቤትነት፡ በቅጽልነትና በበቂነት፡ በተሳቢነት ይነገራል።

ዐይን: የንጨት ጕጥ፡ የቅጥይ መብቀያ።

ዐይን: የፊደል ስም፡ ዐ።

ዐይንና ዐፈር: ተጣይ፡ የማይሰማማ ባለጋራ

ዐይንን እይ።

ዐይንኸ ላፈር አለ: ዐይንሽ ውስጥ ዐፈር ይግባ፡ ሞተኸ ተቀበር አለ፡ ረገመ

ዐይጠ መጐጥ (ጦች): አፉ ጕጠት የሚመስል አፈ ሹል ዐይጥ፡ ድመቶች የሚፈሩት። (መጐጠ ዐይጥ): የዐይጥ መጐጥ። "መጐጥን" እይ።

ዐይጠ በላ: ዐይጥ የሚበላ ድመት፡ ሰው።

ዐይጡ: ዐይጥ (ተባቱን ለመለየት)

ዐይጡት: "የኔን ጥርስ ላንቺ፡ ያንቺን ጥርስ ለኔ" እንዲል የ፯ ዓመት ልጅ።

ዐይጣም: ዐይጥ የረባበት፡ የበዛበት ስፍራ።

ዐይጥ (ጦች): የአውሬ ስም፡ የዱርና የቤት አውሬ። ከማነሱ በቀር ዐሣማንና ዝኆንን ይመስላል። (ተረት): "ያይጥ ሞት የድመት ሰርግ ነው" "ዐይጥ ወልዳ ወልዳ ዥራት ሲቀር" "ሢጥ ያይጥ ምስክሯ ድምቢጥ"

ዐይጥ በላ አበላ: በገበጣ ጨዋታ ተሸነፈ፡ አሸነፈ።

ዐይጥ በበላ ዳዋ ተመታ: አንዱ ባጠፋ ሌላው ተጎዳ።

ዐይጥ አፍ: በቁሙ፡ የዐይጥ አፍ። ድመት ዐይጠ በላ። "ይህ ድመት በዐይጥ አፉ ወጭቱን ለከፈው። "

ዐይጥ: የሰው ጡንቻ ሲመቱት እንዳይጥ ቁጥር ብሎ የሚታይ።

ዐይጥማ: ዐይጥ የሚመስል ከብት፡ አውሬ፡ ወፍ፡ አሞራ።

ዐይጥና ድመት: ተጠቂና አጥቂ።

ዐይጦ: ዐይጥ ሆይ፡ ቃለ አኅስሮ ወይም አጋኖ ነው።

ዐይጧ: ዐይጡት፡ ያች ዐይጥ (እንስቷን ለመለየት)

ዐደለ (ዐዲል፡ ዐደለ): ለኹሉ በመደዳ፡ በነፍስ ወከፍ ሰጠ፡ አሳለፈ፡ አስተናበረ።

ዐደሌ (ዐደላዊ): ዐደልማ፡ የዐደል ዐይነት ወንዴ ጥጥ (ጧፍና መናኛ ልብስ የሚኾን)

ዐደል (ዐድል): ጥኑ፡ ጠንካራ፡ ሻካራ፡ እንደ ማስ ሰበከት ያለ።

ዐደመ (ዐድሞ፡ ዐደመ): ጠራ፡ ቀጠረ፡ "በዚህ ቀን " አለ (ለሰርግ)

ዐደመ: አሤረ፡ ሰውን ሰበሰበ (በድብቅ፡ በስውር)፡ ዶለተ፡ መከረ፡ ነገር ቋጠረ፡ ዐድማ አደረገ (ክፉ ለመሥራት)

ዐደመ: የሰው ስም።

ዐደሰ (ሐደሰ): ጠገነ፡ ባሮጌ ፈንታ አዲስ ተካ፡ ለወጠ፡ መለሰ (፪ዜና፡ ፲፭፡ ፰)

ዐደስ: ባርሰነት (አደስ)

ዐደረ (ኀደረ): ባንድ ቤት ወይም ስፍራ ሌሊቱን አሳለፈ፡ አነጋ። (ዘብ ዐደረ): ጠበቀ። (ለግዜር ዐደረ): የጽድቅ ሥራ ሠራ። (ለጌታ ዐደረ): ተጠጋ፡ አሽከር፡ ሎሌ ኾነ። (ጦም ዐደረ): እራት አልበላም፡ ምንም አልቀመሰምም። (ሳይታረስ ዐደረ): ቀረ፡ ቈየ። (ተረት): "እውሻ ሆድ ቅቤ አያድርም፡ የሰው በልቶ አያድሩም ተኝቶ። "

ዐደረ: ሕዝብን ሰበሰበ (ቁም ነገር ለመሥራት)፡ ዐድሮ ቈይቶ የሚገኝ ሥራት ሠራ፡ ደነባ፡ እጸና፡ የማይፈርስ፡ የማይለወጥ አደረገ፡ ዐገገ።

ዐደረ: በጥንቃቄ ተጠበቀ።

ዐደራ በላ: የማይታመን፡ ከዳተኛ፡ ሸፍጠኛ፡ እምነተ ቢስ።

ዐደራ በሰማይ፡ ዐደራ በምድር: () ስለ ሕፃን ልጁ የሚያደርገው ኑዛዜ። ምድር ሰው፡ ሰማይ እግዜር።

ዐደራ አለ: ባደራ አኖረ፡ አስቀመጠ፡ አስጠበቀ። "የሙት ቀናተኛ ሚስቴን ዐደራ" ይላል። (ተረት): "ዐደራ ቢሏቸው ይብሳሉ እሳቸው። "

ዐደራ ከታች: የታመነ፡ ጨዋ ሰው።

ዐደራ ጥብቅ ሰማይ ሩቅ: ዐደራ የጠበቀ ነው፡ ሰማይ የራቀ ነው።

ዐደራ: የተጠበቀ ጥብቅ፡ "አኑርልኝ፡ ጠብቅልኝ፡ አሳድግልኝ" ብሎ ለሰው የሰጡት ዕቃ፣ ከብት፣ ገንዘብ፣ ማንኛውም ነገር ኹሉ (ግብ ሐዋ፲፬፡ ፳፮) "ያደራ ገንዘብ፡ ያደራ ልጅ" እንዲሉ።

ዐደር: ዐዳሪ። "ዕርስ ዐደር" እንዲሉ።

ዐደር: ያደረ፡ ያለ፡ የቈየ። "በጅ ዐደር ወርቅ ርካሽ ነው" [ይባላል]

ዐደነ (ትግ. ሐደነ): በረሓ ገባ፡ ሻ፡ ፈለገ፡ ሸመቀ፡ አደባ፡ ያዘ፡ ሳበ፡ አቀረበ፡ ወጋ፡ ገደለ (ዘፍ፳፯፡ ፴፩)

ዐደን: ታድኖ የመጣ ሥጋ (ዘፍ፳፯፡ ፳፭)

ዐደን: የማድባት፡ የመግደል ሥራ። (ተረት): "የንጉሥ ልጅ ዐዘን ቢነግሩት ዐደን። "

ዐደየ: መለሰ፡ ከፈለ።

ዐደየ: ሰጪ 'መሰለ፡ ነጣ፡ ነጭ ኾነ። "ኦሮ ነጭን ዐዲ፡ ፀሓይን ዐዱ" የሚለው ከዚህ የወጣ ነው።

ዐደይ አበባ: በመስከረም የሚፈነዳ የምድር ጌጧ፡ ሽልማቷ። "ዐደይ ላሰባ" ቅጽል ወይም ዘርፍ ነው። "ሉልን" አስተውል።

ዐደዳ (ዐዲድ፡ ዐደደ): ንዝንዝ፡ ጭቅጭቅ።

ዐደገ (ኀደገ): ተወ፡ ለቀቀ።

ዐደገ (ትግ፡ ገዛ): መለሰ፡ አቀና፡ ቀጥ አደረገ (ጐባጣ ዕንጨትን በመቍረጥ)

ዐደገ: ቁመት ጨመረ (አደገ)

ዐደፈ (ኀደፈ): ጠረገ፡ ዐሠሠ፡ ወለወለ። "አበሰን" እይ።

ዐደፈ: እድፋም ኾነ፡ አደፈ።

ዐዲስ (ሶች): አሮጌ ያይደለ፡ በቅርብ የተሠራ ሥራ፡ አኹን ዛሬ የመጣ እንግዳ ሰው።

ዐዲስ ልብስ: ዐርበ ወጥ ያልተለበሰ።

ዐዲስ ነገር: ዘመን አመጣሽ።

ዐዲስ አበባ (ዐዲሳበባ): ያገር፣ የከተማ ስም፡ ዐጤ ምኒልክ በሺዋ የቈረቈሩት ራስ ከተማ፡ መናገሻ፡ መዲና።

ዐዲስ አበቦች: ያዲስ አበባ ሰዎች። "ወረትን" እይ።

ዐዲስ አደረገ: ዐደሰ።

ዐዲስ ዓለም (ሐዲስ ዓለም): መንግሥተ ሰማይ፡ ጻድቃን ታድሰው ረቀው የሚወርሱት።

ዐዲስ ዓለም: ካዲስ አበባ በስተምዕራብ ያለ ከተማ።

ዐዲስ ኪዳን: ከማቴዎስ እስከ ራእየ ዮሐንስ (፪ቆሮ፡ ፫፡ ፯፡ ዕብ፲፪፡ ፳፬) "ሐዲስን" ተመልከት።

ዐዲስ ወሬ: ተሰምቶ የማይታወቅ።

ዐዲስ ፈሊጥ አመጣበፈሊጥ ተናገረ እንዲሉ።

ዐዲስነት: ዐዲስ መኾን።

ዐዲስጌ: በተጕለት ውስጥ የሚገኝ አገር፡ ከዜጋ ወደም በስተግራ ያለ ቀበሌ። ( ሐዲስ): ሐዲስ የሚባል ሰው ምድር።

ዐዲስጌዎች: ያዲስጌ ተወላጆች።

ዐዲት: ለሴት፡ ለእንስት ይነገራል።

ዐዳ: ዐፍንጫ ደፍጣጣ ዝንጀሮ፡ ሰው።

ዐዳ: የሚታጨድ እኸል፡ መከር።

ዐዳል: የነገድ ስም (አዳል)

ዐዳሚ: ያደመ፡ የሚያድም፡ ጠሪ፡ ቀጣሪ፡ እሢያሪ።

ዐዳሩ ሞቀ: ራሱን ቻለ፡ ከበረ።

ዐዳሩን መጣ: ለማደር መጣ።

ዐዳሩን ኼደ: ሊያድር ኼደ።

ዐዳሪ (ኀዳሪ): ያደረ፡ የሚያድር። (ዱር ዐዳሪ): ሽፍታ፡ ወንበዴ፡ ዘላን። (ጦም ዐዳሪ): ምስኪን።

ዐዳሪ: ሎሌ፡ ታዛዥ። "የጌታ ዐዳሪ" እንዲሉ።

ዐዳሪዎች: የሚያድሩ፡ ዘበኞች፡ ጠባቆች።

ዐዳር ቀና: ሰላ፡ ማለፊያ ኾነ።

ዐዳር: ማደር። "ላንድ ቀን ዐዳር" እንዲሉ።

ዐዳር: ትዳር (ምሳ፴፡ ፰፡ ሉቃ፳፩፡ ፴፬) "የጠፋ ዐዳር ከለማ አንድ ነው" እንዲሉ። (የጌታ ዐዳር): አሽከርነት፡ ሎሌነት።

ዐዳሽ (ሾች) (ሐዳሲ): ያደሰ፡ የሚያደስ፡ ጠጋኝ።

ዐዳኝ (ኞች): ያደነ፡ የሚያድን፡ የሚፈልግ፡ የሚያደባ፡ የሚሸምቅ፡ አድቢ፡ ሸማቂ። "ዐዳኝ ውሻ ጭገር ባፋ በትር ትርፋ" እንዲሉ።

ዐዳኝነት: ዐዳኝ መኾን፡ ፈላጊነት፡ ሸማቂነት፡ ገዳይነት።

ዐዳኝገለሌ (ሐቃላዊ)፡ የገለል ወገን፡ በረኸኛ፣ ዐርበኛ።

ዐዳይ (ዮች): ያደለ፡ የሚያድል፡ አሳላፊ፡ አስተናባሪ።

ዐዳይነት: ዐዳይ መኾን፡ አሳላፊነት።

ዐዳደሰ: ጠጋገነ።

ዐዳጊ: ያደገ፡ የሚያድግ፡ መላሽ። (ጥደ) ማደግ: መመለስ፡ ማቅናት።

ዐዳፊ (ኀዳፊ): ያደፈ፡ የሚያድፍ፡ ጠራጊ፡ ዐሣሽ።

ዐዴ: የዐድ ዐይነት፡ ወይም ወገን።

ዐድ: ዝኒ ከማሁ (ከዐዳ ጋር ተመሳሳይ)፡ አንኮ (የዝንጀሮ ዓይነት)

ዐድመኛ (ኞች): ዐድማ ወዳድ፡ ባለዐድማ፡ ያድማ አለቃ፡ ሤረኛ።

ዐድመኛነት: ዐድመኛ መኾን።

ዐድማ መታ: ዐደመ፡ ሤራ ቈረጠ፡ አደረገ።

ዐድማ: ተንኰልና ክፋት ያለበት ምክር፡ ሤራ፡ ዱለት።

ዐድር ብዬ: ተለማማጭ።

ዐድሮ ኻያጅ: እንግዳ፡ መንገደኛ።

ዐድሮ: ሌሊቱን አሳልፎ።

ዐድዋ: በትግሬ ክፍል ያለ አገር፡ በ፲፰፻፹፰ .. የካቲት ፳፫ ቀን እሑድ ዐጤ ምኒልክ ከጣሊያን ጋራ ተዋግተው ድል ያደረጉበት።

ዐዶ (ዐደወ ዕድው): በበረሓ የሚቀመጥ ዐዳኝ፡ ያውሬ ጠላት፡ ባለጋራ።

ዐዶ (ዐፅ): ባዶ፡ ባድማ፡ በረሓ፡ ደን። በትግሪኛም አገር "ዐድ" ይባላል።

ዐዶ (ኦሮ): የቃልቻ አስተርጓሚ።

ዐዶ ነዳይ (ነዳየ ዐፅ): የምድረ በዳ ድኻ፡ ጠጕሩ የተንጨረፈፈ፡ ቤት ንብረት የሌለው። "ዐጥን" ተመልከት።

ዐዶ ከቢር (ሮች): ዐፍለኛ ወንድና ሴት እየያዘ የሚያስገዝፍና የሚያስጨፍር ዛር፡ የብልግና፣ የዝሙት አሠሪ ክፉ መንፈስ። ሲፎክርም "የትግሬ ልጅ እባብ ዐለንጋው አሸዋ ልብሱ ዳዊት ደጋሚ" ይላል። "ከበረን" እይ።

ዐዶ ወሸባ: ያዳኝ ዘፈን፡ አዝማች። "ዐዶ ወሸባ ዐዶ ወሸባዬ፡ ዐዳኝ ወሸባ ጓሮዬ" እንዲሉ።

ዐዶ: ከዝኆን ኰቴ የተበጀ እንደ መጋዝ ያለ ያዳኝ አንባር።        

ዐጀለ (ዐገለ): ሸፈነ፡ አለበሰ፡ ጠቀለለ፡ ስለሰለሰ (ደረቅ ቈዳን በቅጠል፡ ገላን ባብሽ)

ዐጀሚ (ዐጀማዊ): የዐጀም፣ የፋርስ ሰው (ኢሳ፳፰፡ ፲፩)

ዐጀም ኰንታ: ዐጀም እንዳለፈው፡ ኰንታ ኩርድ፡ ወይም በኢትዮጵያ በዳር አገር ኮንታ የሚባል ዘር የዐጀም ዘርፍ የኾነ ይመስላል። ጊዮርጊስ ወልደ ሐሚድም ኰንታን ኩርድ ይለዋል።

ዐጀም: የነገድ ስም፡ በፋርስ ውስጥ የሚገኝ አረመኔ፣ ቀማኛ ሕዝብ። ይህ በአረብኛ ነው። (ቈላ፫፡ ፲፩) በግእዝም "ዐዠም ሀገሪት ሐቃል" ይባላል።

ዐጀረ (ዘኀረ፡ ትግ. ዐዘረ፡ ተመካ): አሰፋ፡ ዘረጋ፡ አሳበጠ፡ ነፋ፡ አኰራ፡ አስታበየ፡ አስመካ።

ዐጀበ (ዐረ፡ ሐጀበ፡ ሸፈነ): ከበበ፡ ተከተለ (ጌታውን፡ እመቤቱን)

ዐጀበ (ዐጺብ፡ ዐጸበ): ገረመ፡ ደነቀ።

ዐጀበ: ሰበሰበ፡ አከማቸ፡ መሰገ፡ አንድ ላይ አደረገ፡ ዐጨቀ።

ዐጀባ: ከበባ፡ ክተላ፡ መጋረጃ። (ግጥም): "እንዳላይሽ እንዳላይሽ፡ ዐጀባ ኹኗል ጥላሽ። "

ዐጀብ: ብዙ ጭፍራ፡ ሰራዊት። "የሻለቃው ዐጀብ ይሰበር ይመስላል። "

ዐጀብ: ዕጹብ፡ ድንቅ፡ ግሩም (የወለዱ ማጀብ) "ዐጀብ ጃሎ" እንዲል ሐርበኛ።

ዐጀብ: የመክበብ፡ የመከተል ኹኔታ። "ዛሬ ዐጀብ አለብኝ" እንዲል ወታደር።

ዐጃ (ዐዘዘ): የእህል ስም፡ ከነገለባው ተዘርቶ ከነገለባው የሚመርት አኸል፡ የስንዴ፣ የዐዛዜ ዐይነት (ኢሳ፳፰፡ ፳፭) (ተረት): "ዐጃ ወቅጦ ቢዘሩ፡ ተመልሶ ከዘሩ። "

ዐጃቢ (ቦች): ያጀበ፡ የሚያጅብ፡ ከባቢ፡ ተከታይ፡ ሰብሳቢ፡ አካቢ።

ዐጃይ: ያጀለ፡ የሚያጅል፡ አልባሽ፡ አለሻሽ።

ዐጅሪት: ወንዲት አንበሲት፡ እንደ ያይልና እንደ ዮዲት ያለች ሴት (መሳ፬፡ ፳፩፡ ዮዲ፲፫፡ ፰-፱፲)

ዐጅራች (መዝኅራት): ገለሞቶች። (ግጥም): "ያውና እዚያ ማዶ፡ ያውና እዚያ ላይ፡ የናጅራች አገር የነሰው ገዳይ። " ለወንዶችም ይነገራል።

ዐጅሬ (መዝኅራዊ): እሱ፡ የዐጅር ወገን፡ አኵሪ፡ አትንኩኝ ባይ። (ሽለላ): "ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልተባለ ዐጅሬ፡ እሜዳ ስደዱት፡ ሣር ይብላ እንደ በሬ። "

ዐጅር (አዝኃሪ): ያጀረ፡ የሚያጅር፡ የሚያኰራ፡ የሚያስታብይ፡ አስመኪ።

ዐጅሮች (መዝኅራን): የሚያኰሩ፡ የሚያስመኩ፡ አኩሪዎች፡ አስመኪዎች፡ ወንዶች ጐበዞች።

ዐገለ (ዐግሎ፡ ዐገለ): ጫረ፡ ኰተኰተ፡ ዐፈር አስታቀፈ (ተክልን)

ዐገለ: መለሰ፡ ዐደሰ (ቂጥኝን)

ዐገመ (ሐገመ): ሳበ፡ ጠባ፡ መጠጠ፡ መጠመጠ፡ መጥፎ ደምን አወጣ።

ዐገመና ገመጠ: በአማርኛ ይገጥማሉ። (ተረት): "እከሊት ስለ ሞተች ሰዎች ይገምጧት ወጡ። "

ዐገም (ሐጊም): ማገም።

ዐገም ጠቀም: ደግ ወይም ክፉ የማይባል ሥራ፡ እነገር ኹሉ መግባት፡ እዚያም እዚያም ማለት። ዐገም ጠቀም ቀዶ መስፋትን ያሳያል።

ዐገሠ (ዐግሦ፡ ዐገሠ): አስታገሠ (አስተዐገሠ)፡ አስቻለ፡ ትግሥት ሰጠ፡ ዝም አሠኘ፡ አጸና።

ዐገሸ: አቋተ፡ ደቀነ።

ዐገተ (ዐጊት፡ ዐገተ): የዋስን ገንዘብና ዕቃ ወሰደ፡ ሰብልን፣ ክልክልን፣ ኣትክልትን የበላ ከብትን ከቦ ያዘ፡ ወደ በረቱ አገባ።

ዐገዘ (ሐገዝ): ረዳ፡ ሥራን፣ ድካምን ተካፈለ (ዕዝ፰ - ፴፮)

ዐገዜታ: ዝኒ ከማሁ፡ ርዳታ።

ዐገገ (ሐገገ): ደነባ፡ ወሰነ፡ ደነገገ፡ ሕግ ሥርዐት ሠራ። "ሐገገን" እይ።

ዐጕለቲ: ያጕል ወገን።

ዐጕሊጥ (ዐጕለቲ): ቧልተኛ፡ ዋዘኛ።

ዐጕሊጥ: ዐጒል ሊጥ ማለት ይመስላል።

ዐጕል ጊዜ: ለሥራ የማይመች ሰዓት።

ዐጕል: መጥፎ (የጠባይ፣ የግብር)፡ እካብ አይገባ ድንጋይ።

ዐጋሚ (ዎች): ያገመ፡ የሚያግም። "ዦሮን" ተመልከት።

ዐጋም: እሾኻም ዕንጪት፡ አጋም።

ዐጋች (ቾች): ያገተ፡ የሚያግት፡ ያዥ፡ ዋስ። "ዐጋች" እንዲሉ [ይባላል]

ዐጋዥ (ዦች): ያገዘ፡ የሚያግዝ (ረዳት) (ፊልሞ፡ ፩፡ ፊልጵ፬፡ ፫) (ተረት): "ባሪያ ዐጋዥ ብታገኝ መጇን ደበቀች። "

ዐጋዥ ግንድ: ከፊት ግንድ ቀጥሎ የተተከለ፡ ድርን በማፈጋፈግና ወጥሮ በመያዝ የፊት ግንድን ስለሚያግዝ ዐጋዥ ግንድ ተባለ።

ዐጋዥ: ጥርስ የሌለው ማጭድ፡ ጐዣሜ።

ዐጋይ (ሐጋይ): በጋ። "ጤፍ ዐጋይ" እንዲሉ።

ዐጋይ (ዮች): ያገለ፡ የሚያግል፡ ኰትኳች። "አትክልት ዐጋይ" እንዲሉ።

ዐጋይነት: ኰትኳችነት።

ዐጋጊ (ሐጋጊ): ያገገ፡ የሚያግግ፡ ደንጋጊ (ያዕ፬፡ ፲፪)

ዐጎት: የአባት፣ የእናት ወንድም (አጎት)

ዐጐዛ: ጌጠኛ ደበሎ፡ የረኛ፣ የጦረኛ ልብስ፡ በለምድ ዐይነት የተዘጋጀ ሸማ፡ ማገዣ (ዘሌ፲፫፡ ፵፰-፵፱) (የባሕር'ዐጐዛ): ነጭ ሐር የሚመስል ረዥምና ለስላሳ ጠጕር ያለው የታናሽ እስያ ፍየል ሎፊሳ። "ሱፋላን" እይ።

ዐጓት: የወተት ውሃ።

ዐጓጕሊት: ወንድ አይሏት ሴት የማትረባ።

ዐጓጕል (ሎች): ያጕል ዐጕል፡ ፍጹም ዐጕል፡ ዐጕልነቱ በብዙ ወገን የሚታይ፡ ኹለት ልብ (፬ነገ፡ ፲፰፡ ፳፩)

ዐጠረ (ሐጸረ): ዕንወት ተከለ፡ ገረገረ፡ ማገረ፡ ሸመጠጠ፡ ጀጐለ፡ ቀጠረ፡ የጠርብ፡ የሳንቃ ዐጥር አበጀ፡ ገነባ፡ ካበ፡ ከበበ፡ ዙሪያውን ዘጋ። (አርቆ ዐጠረ): በዳር፡ በወደብ፡ በወሰን፡ በድንበር ምሽግ አደረገ፡ ጠላትን ተከላከለ።

ዐጠረ (ኀጽረ): ዐጪር ኾነ (ቁመቱ፡ ዕድሜው)፡ አነሰ። (እጅ ዐጠረው): ገንዘብ ዐለቀበት።

ዐጠረ (ዐረ): ሸተተ፣ አማረ፣ ተዋበ።

ዐጠረ (ዐጽሮ ዐጸረ): ጠመቀ፣ ጨመቀ፣ ዘለለ፣ መሸተ።

ዐጠረ: መሸተኛን፣ ዐጣሪን አስገበረ፡ ከልክ አሳልፎ ቀረጠ።

ዐጠረ: ቀጠረ ጀጐለ ጋረደ ከለለ ዐቀበ "ጠገነን፡ እይ።"

ዐጠረ: አመነዘረ፣ ነውር ሠራ።

ዐጠረ: ዕጥርን፣ ጥለትን፣ ማተብን፣ የጪስ ዕንወትን፣ ዕጣንን ሸጠ ለወጠ ሸቀጠ "በማታለል ቸረቸረን" እይ።

ዐጠራ: ያጥር ሥራ፡ ከበባ።

ዐጠቀ) (ዐጢቅ ዐጠቀ): ታጠቀ፡ በወገቡ ላይ ሰይፍን፡ ዝናርን፡ ሽጕጥን፡ ሱሪን፡ ቀሚስን፡ ቀበቶን አሰረ፡ ሸብ አደረገ፡ መቀነትን ጠመጠመ፡ ሸማን አደገደገ (ዘፀ፲፪፡ ፲፩፡ ፩ሳሙ፡ ፲፯፡ ፴፱፡ ኢሳ፴፪፡ ፲፩) (ባጪር ታጠቀ): ለሥራ፡ ለጦርነት ተዘጋጀ። "ያረገዘች ታስታውቅ፡ ከደረቷ ትታጠቅ" እንዲሉ፡ "ቦዶነን" "ሸነቀረን" አስተውል። (ስላልተለመደ ነው እንጂ፡ ዐጠቀን "አሰረ" "ቀነተ"፡ ታጠቀን "ታሰረ" "ተቀነተ" ቢል በቀና ነበር።) "ከተለ" ብለኸ "ተከተለን""ዐቀፈ" ብለኸ "ታቀፈን" ተመልከት።

ዐጠበ (ኀፀበ): ረገጠ፡ አንጨፈጨፈ፡ ዐሸ፡ አጐረፈ፡ ለቀለቀ፡ አጠራ፡ አነጣ፡ አጸዳ፡ እድፍን አስለቀቀ። (እጄን ዐጠበኝ): ክፉኛ ቈረጠኝ። (ተረት): "እጅ ሲያጥቡት ያድፋል፡ ልጅ ሲመክሩት ይጠፋል። " "ዐወቅሽ ዐወቅሽ ቢሏት መጣፍ ዐጠበች"

ዐጠበ: ሰረቀ፡ አሞለጨ።

ዐጠባ (ኀፀባ): የማጠብ ሥራ፡ ረገጣ፡ ልቅለቃ። "ልብስ ዐጠባ" እንዲሉ።

ዐጠብ: ሌባ፡ ሰራቂ።

ዐጠነ (ሐፀነ): አሳደገ (ልጅን) (ዐጠነን "አሳደገ" ማለት አልተለመደም)

ዐጠነ (ዐጢን ዐጠነ): ጥናን ከፍምና ከዕጣን ጋራ ወዘወዘ። የዕጣንን፡ የወገርትን፡ የቡክቡካን፡ የርጐፍትን፡ የሎሚ እሸትን፡ የጪስ ዕንጨትን፡ የመድኅኒትን፡ የጥድን፡ የንብ ኣስልን ሽታ (መዐዛ) አጨሰ፡ ሰጠ፡ አቀበለ (ለታቦት፡ ለጣዖት፡ ለልብስ፡

ዐጠደ መልካም: ደጎች ቤተሰቦች ያሉት ሹም። "ዳግመኛም አሽከሮች፡ ቤተሰቦች፡ ካህናት፡ መኰንን፡ ሹም፡ ታቦት ነው" "ዐጠደ ክፉ፡ ታቦተ ደግ" እንዲሉ።

ዐጠደ ማሪያም (ዐጸደ ማርያም): ሴት የምትጠራበት የክርስትና ስም፡ የማሪያም ቦታ ማለት ነው።

ዐጠደ ክፉ: ምግባር ያነሳቸው አሽከሮች ያሉት መኰንን።

ዐጠድ (ዐጸደ ዐጸድ፡ ቦታ): የቤተ ክርስቲያን ዛፍ፡ ከገረገራ ግቢ ያለ። "ዐጠድ የሌለው ደብር፡ ጢም የሌለው መምር" እንዲሉ።

ዐጠድ: ገረገራ። "ገረገረን" "ዐጸድን" ተመልከት።

ዐጠዶች: ዛፎች፡ ጥዶች፡ ወይሮች፡ ግራሮች፡ ሌሎችም።

ዐጠጠ (ሐጸ): ጐደለ፡ አነሰ።

ዐጠጥ: ያጠጠ፡ ጐደሎ፡ ባለጌ።

ዐጠፈ (ዐጢፍ ዐጠፈ): ጠቀለለ፡ ሸበለለ (ግእዝ)

ዐጠፈ (ዐጺፍ ዐጸፈ): ጥንድ አደረገ፡ ደረበ፡ ለበሰ፡ መለሰ፡ ቀለበሰ፡ ጫፍና ፍን ገጠመ፡ ኰረመተ።

ዐጠፈ (ጠቀለለ/ጥንድ አደረገ)

ዐጠፈ: በመጽሐፍ ማለ ተማሪው።

ዐጠፈ: ኰረተመ ዐጥፎ አሰረ (ያህያን፣ የበግን፣ የፍየልን ፊተኛ እግር) "ሰከለን፡ ተመልከት።"

ዐጠፋ: (የስም ምትክ) ዐጸፈ፡ ዐጸፋ።

ዐጠፋ: ዕጥፈት፡ የማጠፍ ሥራ።

ዐጠፌታ: ባንድ ፈንታ ኹለት ኹኖ የሚከፈል ዕዳ፡ መቀጮ።

ዐጡን ባር (ዕጣነ ባሕር): የእንዡባን ዐይነት ቅጠል፡ ማለፊያ ሽታ ያለው፡ በሶ ብላ መሳይ።

ዐጣ (ኀጥአ): (ኀጢአት ሠራ)፡ ከዚህ የተነሣ ምድራዊ ሀብትን ሰማያዊ ጸጋን ሳያገኝ ቀረ። "ማጠ" ብለኸ "ምጥን" እይ። (ተረት): "ይበላው ካጣ ይበላበት ያጣ። " (ባጣ ቆዪኝ): ካንቺ የተሻለች ሴት ባላገኝ ሌላ እንዳታገቢ፡ ጠብቂኝ። (ተጅ አይጡ): የበሬ ስም፡ ገንዘብ ከጃቸው አይለቅባቸው።

ዐጣ ነጣ: ፈጽሞ ደኸየ፡ የንጀራ ገመዱ ተበጠሰ፡ ንጣት ያዘው።        

ዐጣ: ገደፈ፡ ረሳ።

ዐጣሪ (ኀጻሪ): የሚያጥር ልብስ።

ዐጣሪ (ሐጻሪ): ያጠረ፡ የሚያጥር፡ ዐጥር ሠሪ። (ተረት): "እሾኽ ዐጣሪውን፡ ነገር ሠሪውን (ይወጋል፡ ይጐዳል)"

ዐጣሪ (መጸብሓዊ): ሽቱ ሸያጭን፣ መሸተኛን፣ ሌላውንም አስገባሪ ቀረጥ ተቀባይ (ማቴ፲፡ ፫፡ ፲፰፡ ፲፯)

ዐጣሪ ሰፈር: አዲስ አበባ በቅዱስ ሩፋኤል አጥቢያ ያለ ቀበሌ።

ዐጣሮች (መጸብሓን): መሻቾች፣ ቀራጮች (ማቴ፳፩፡ ፴፩)

ዐጣቢ (ዎች): ያጠበ፡ የሚያጥብ፡ እጽጂ።

ዐጣኝ (ኞች): ያጠነ፡ የሚያጥን ቄስ፡ ወይም ሌላ ሰው። "ዘውድ ዐጣኝ፡ ቡዳ ዐጣኝ" እንዲሉ።

ዐጣኝነት: ዐጣኝ መኾን፡ ጸሎተ ዕጣን መድገም።

ዐጣጠበ: አነጣጣ፡ አጸዳዳ።

ዐጣጠፈ: ኹለት፡ ሦስት ጊዜ ዐጠፈ።

ዐጣጥ (ጦች): የዕንጨት ስም፡ እሾኽ፡ ትንንሽ ዕንጨት (ሉቃ፮፡ ፵፬)

ዐጣፊ: ያጠፈ፡ የሚያጥፍ።

ዐጣፋ: ኀሣ፡ የማእዘን ደንጊያ፡ ቀናፋ።

ዐጤ (ሐፄ ሐፄጌ): ዐጪ፡ ምድርን ለመግዛት ያጨ፡ የመንግሥት ዕጮኛ፡ የምድር ጌታ፡ ዐፄ፡ ንጉሠ ነገሥት። "ዐጤ ካሌብ""ዐጤ ፋሲል""ዐጤ ቴዎድሮስ""ዐጤ ምኒልክ""ዐጤ ኀይለ ሥላሴ" እንዲሉ።

ዐጤ መስቀል (መስቀለ ሐፄ): ያጤ መስቀል፡ ዐጤ ዳዊት ከኢየሩሳሌም ያስመጡት ግማደ መስቀል (የመስቀሉ ግማሽ)

ዐጤ መስቀል: የበዓል ስም፡ በመስከረም ቀን የሚውል በዓል ነው። "ግሼንን" እይ።

ዐጤ ሥራ: ያጤ ሥራ፡ የንጉሥ ሑዳድ የሚታረስበት፡ ዋና የሥራ ቀን፡ በዓል አልባ።

ዐጤ: ንጉሠ ነገሥት።

ዐጥ (ዐፅ): በረሓ፡ ጠፍ። "ትግሮችም አገርን 'ዐድ' ይሉታል፡ ይኸውም ፀና ተወራራሾች ስለ ኾኑ ነው። "

ዐጥ ረገጥ: ሰው የረገጠው ስፍራ። "አቶ እከሌ ካቶ እከሌ ዐጥ ረገጥ አይደርስም። "

ዐጥመ ርስት (ርስተ ዐፅም): (ዘፍ፶፡ ፲፫) ያባት፡ ያያት፡ የቅድም አያት ዐጥም የተቀበረበት ርስት።

ዐጥሚት: ያጃ ሙቅ (ጠምዐ)

ዐጥም (ዐፅም): ዐጥንት፡ አስከሬን።

ዐጥረ ገጥ: ያጥር ፊት ማለት ነው። "ረገጠን" እይ።

ዐጥራም: ዐጥር ያለበት፡ ባላጥር ቤት፡ ቦታ፡ ተክል።

ዐጥር (ሮች) (ሐጹር): በቤትና ባትክልት ዙሪያ ያለ የንጨት፡ የካብ፡ የግንብ፡ የግርግር፡ የድድቅ ቅጥር፡ የቅጠል ጀጐል።

ዐጥር ቅጥር: ዐጥር የውስጥ፡ ቅጥር የውጭ መካበቢያ (ኢሳ፭፡ ፭) "ዐጥር ጣሽ፡ ቅጥር አፍራሽ" እንዲሉ።

ዐጥር አፋፍ: ዐልፎ ዐልፎ በደንጊያ ዐጥር የተከበበ መዋጊያ አፋፍ፡ በላይኛው ወግዳ ያለ ውሎ ማዋያ።

ዐጥር ግቢ: ከቅጥር በስተውስጥ ያለ ስፍራ።

ዐጥር: ዐጠረ አዋሰበ (ክትክታን፣ አጋምን ከግርግር ጋራ)

ዐጥር: የሾኽ ዘለሳ፡ ወዘፍ።

ዐጥቅ የለሽ: የሴት ስም፡ ወሰን የለሽ ማለት ነው።

ዐጥቅ: የመቃ፡ የሽመል፡ የቀርክሓ፡ ያገዳ፡ የሸንኰራገዳ፡ የቅልጥም፡ የጣት አንጓ፡ ወሰን፡ ትጥቅ መሳይ።

ዐጥቆች: ያንጓ ሰንበሮች መሥመር የሚመስሉ (ዐጥቆች)

ዐጥበኸ ዕዘን: አንድ ጊዜ ሲታጠብ የሚለቅ ጥለት።

ዐጥንተ ጥሩ: የጨዋ፡ የባላባት ዘር።

ዐጥንታም: ዐጥንተ ሰፊ ሰው።

ዐጥንቴ እሾኽ ኹኖ ይውጋኸ አለ: ፈጽሞ ረገመ።

ዐጥንት (ቶች) (ዐፅም፡ አዕፅምት): የንስሳ፡ የአውሬ፡ የወፍ፡ የሰው ውስጣዊ ገላ፡ በቈዳ የተሸፈነ፡ በሥርና በዥማት የተያያዘ፡ እንደ ዕንጨት ጥንካሬ ያለው።

ዐጥንት ለባለዐጥንት: የሚጋጥ፡ ዐጥንት፡ የሚመጠጥ ቅልጥም ለባለቤት፡ ለጨዋ ልጅ ይገባል።

ዐጥፍ (ዐጽፍ): ከበሬ፡ ካጋዘን፡ ከድኵላ ማስ የተበጀ የመነኵሴና የመነኵሲት ተደራቢ ልብስ፡ ዳባ፡ ወይባ የገባና ያልገባ።

ዐጥፎ: ዘቅዝቆ ታጠቀ (ልብስን ለሐዘን) "ኣሸነፈጠች፡ ተብሎ፡ በሴት፡ አንቀጽ፡ ይነገራል፡ ለወንድ፡ ግን፡ በርኖሱን፡ ገልብጦ፡ ለበሰ፡ ይባላል። ዘሩ፡ ሸፈጠ፡ ነው ነ፡ በስሯጽነት፡ ገብቶበታል።"

ዐጨቀ (ዐጸቀ): ወጠቀ፡ ሰብስቦ አገባ፡ ጨመረ፡ ከተተ፡ ዐጀበ (እንደ ቅጠል)

ዐጨደ (ዐጸደ): ብዙውን ባንድነት ጠረገ፡ ቈረጠ፡ ቦጨቀ፡ አመሸከ (ሣር፡ ስንዴ፡ ገብስ፡ ያጃ፡ ጤፍ)

ዐጨዳ: የማጨድ ሥራ፡ ቈረጣ (ዘሌ፲፱፡ ፱፡ ኢሳ፲፯፡ ፲፩)

ዐጨዳዬ ረገፈ አለ: ቸኰለ፡ ተጣደፈ።

ዐጪ (ኀጣኢ): ያጣ፡ የሚያጣ፡ ያላገኘ፡ የማያገኝ።

ዐጪ (ሐፀየ): ሚስት ፈለገ፡ የወንድ አባት የሴትን አባት "ልጅሽን ለልጄ ስጠኝ" አለ፡ ሽማግሌ ላከ፡ እጪዋ ቤት ገባ። ከዚህ በኋላ ልጁ ለልጃገረዲቱ ማተብና ቀለበት ሰጥቶ ቃል አሰረ። (ተረት): "ልጃገረድ ዐሥር ያጭሽ፡ አንድ ያገባሽ። ያጨሽ ላያገባሽ ከባልሽ ሆድ አትባባሽ። "

ዐጪ (ሐፃዪ): ያጭ፡ የሚያጭ፡ ሚስት ፈላጊ።

ዐጪ() (ሮች) (ኅጺር): ያጠረ፡ ድንክ፡ ድንክዬ፡ ኵርምባጥ፡ ዝራጭ፡ ድውይ፡ ድኑር፡ ከርከሮ፡ ታናሽ፡ ቁመተ ዶሮ።

ዐጪሬ: ዘንጋዳ።

ዐጪሬ: ያጪር ወገን፡ የዶሮ ዳሌ። "ጐሰረ" ብለኸ "ጐሳራን" "ጕስርን" እይ።

ዐጪር ቀጪን: ዐጪርነት ከቀጪነት ያለው ሰው።

ዐጪር ቍርጭኝ: ታናሽ መጣፍ፡ ወይም ታሪክ።

ዐጪር ቃል: ዝብዝብ የሌለበት ነገር።

ዐጪርነት: ዐጪር መኾን፡ ድንክነት።

ዐጪታ (ሓፃዪት): ያጨች፡ የምታጭ፡ ልታገባው የፈለገችውን ወንድ በልቧ የምታኖር ልጃገረድ፡ ወይም ሴት።

ዐጫቂ (ዐጻቂ): ያጨቀ፡ የሚያጭቅ፡ ከታች ዐጃቢ።

ዐጫጅ (ዐጻዲ): ያጨደ፡ የሚያጭድ፡ ቈራጭ (ኢሳ፲፯፡ ፭)

ዐጫጆች (ዐጸድ): የሚያጭዱ (ማቴ፲፫፡ ፴፡ ፴፱፡ ያዕ፭፡ ፬)

ዐጫጭር (ሮች): ውስጠ ብዙ ዐጪር።

ዐጭዶ ገብ: የማንንም እኸል ዐጭዶ የሚገባ፡ ማን ዘራሽ።

ዐጭዶ: ቈርጦ፡ ጠርጎ።

ዐጸባ: ከራ፡ ችግር፡ ጭንቀት፡ ዕጦት፡ ድኽነት (ችግር ወይም ጭንቀት)

ዐጸደ ምኵሳሕ: ጓሮ ቤት (የኋላ ክፍል)

ዐጸደ ሥጋ: የሥጋ መኖሪያ፡ ምድር፡ ይህ ዓለም (ምድራዊ ቦታ)

ዐጸደ ነፍስ: የነፍስ ስፍራ፡ ገነት፡ መንግሥተ ሰማያት (መንፈሳዊ ቦታ)

ዐጸዳም: ዐጸድ ያለው፡ ባለዐጸድ፡ ደብር፡ መቅደስ (ዐጸድ ያለበት ቦታ)

ዐጸድ (ዶች): የቤተ ክሲያን ዛፍ፡ አድባር (፪ዜና ፴፩፡ ፩) "ዐጠድን" እይ (የቤተ ክርስቲያን ዛፍ)

ዐጸድ: ስፍራ፡ ቦታ፡ ሰፈር (ቦታ)

ዐጸጸ: ጐደለ፡ አነሰ። "ዐጠጠን" ተመልከት። (መቀነስ፡ መጉደል)

ዐጸፈ: ለበስ፡ ዐጠፈ፡ መለሰ። "ዐጠፈን" እይ።

ዐጸፋ: አስቀድሞ በተነገረ ስም ፈንታ የሚነገር የስም ምትክ። ይኸውም ርሱ አንተ እነሱ እነዚያ እናንተ ርሷ ያች እኔ እኛ የሚል ቃል ነው። (ተተኪ ስም)

ዐጺር: በግእዝ የወይን ጥማቂ (ጭማቂ) ነው። ' ይጠብቃል።

ዐፄ መስቀል በዓል: ዐጯ (የመስቀል በዓል ሌላ ስም)

ዐፄ ፈንታ: የዐፄ ፈንታ፡ ነጭ ማር፡ ማለፊያ ዶቄት (ምርጥ ነገር)

ዐጼ: ንጉሠ ነገሥት፡ ዐፄ (ንጉሥ)

ዐፄ: የንጉሠ ነገሥት ስም ቅጽል (ንጉሥ) "ዐጨ" ብለኸ "ዐጤን" አስተውል።

ዐፅም: ዐጥንት። "ዐጥምን" እይ (አጥንት)

ዐጽቅ: የዛፍ፡ የሐረግ ቅጥይ ክንፍ፡ ከነፉ (የዛፍ ቅርንጫፍ ወይም ቅጠል)

ዐጽፍ: በቁሙ፡ ዐጥፍ (አጣጥፎ መያዝ ወይም መመለስ)

ዐፈለ: አደገ፡ ጐለመሰ፡ ጐበዘ፡ በረታ (ሰውነት ማደግ ወይም መብረታት)

ዐፈሌ: ያፈለ፡ ያፈለች (ያደገ ወይም የጎለመሰ)

ዐፈረ: ፈራ ሠጋ

ዐፈሩን ገለባ ያድርግለትና: የችን ስም ለማንሣት አስቀድሞ እንዲህ ይባላል (አንድን ሰው ከማንሳት በፊት የሚባል አባባል)

ዐፈር (ዕፍረት): የሽቱ ስም፡ ሽቱ።

ዐፈር መለሰ: ቀበረ፡ ደፈነ (መቅበር)

ዐፈር መልስ: ለሚጠጣው ታላቅ ጐዳት የሚሰጥ፡ እስከ መቃብር የሚያደርስ መጥፎ መጠጥ፡ ካቲካላ (የአልኮል ዓይነት)

ዐፈር ቀመሰ: ተቀበረ።

ዐፈር ቃም: በውስጡ ዐፈር ያለበት ካብ፡ ዐፈር የቃመ ማለት ነው (አፈር የያዘ)

ዐፈር ብዛት: ብዙ (ብዛትን ለመግለጽ)

ዐፈር አልባሽ: ባል፡ ወይም ሚስት (አንድ ላይ መኖር)

ዐፈር ኰቸር: በቈሎ የሚመስል ደረቅ የንጨት ቅርጣፊ፡ ሴቶች እንደ አደስ ደቍሰው ከቅቤ ጋራ የሚቀቡት (ለፀጉር የሚያገለግል)

ዐፈር ኾነ: ወደ መሬት ተመለሰ።

ዐፈር የሚመስል ሰው: (የአፈርን ቀለም ወይም ባህሪ ያለው ሰው)

ዐፈር ይፈጫል: ሕፃን ነው (ገና ሕፃን መሆኑን ለመግለጽ)

ዐፈር ገደል: ዐፈርን ገደል የሚሰድ፡ ጭንጫ፡ ግርግራ፡ ሸርታቴ ስፍራ (አፈር የበዛበት ቦታ)

ዐፈር ገፊ: ዐራሽ፡ ገበሬ (ጐንደር) (ገበሬ)

ዐፈር ጠራው: በባዕድ አገር ሞተ (ከሀገር ውጭ መሞት)

ዐፈር ፋሮ: የፋሮ ዐፈር፡ ዐፈር፡ ፋሪ (የአፈር ዓይነት)

ዐፈር: መሬት፡ ትቢያ (አፈር)

ዐፈርማ: ዐፈር መሳይ፡ ባለዐፈር (አፈር የሚመስል)

ዐፈርሳታ: አውጫጭኝ አፈርሳታ።

ዐፈርቻ: ዐፈር አስተኔ (አፈር መሰል ነገር)

ዐፈርነት: ዐፈር መኾን።

ዐፈሮ: ብዙ ሰራዊት፡ ብዛቱ እንዳፈር የኾነ፡ ባለነጋሪት፡ ጭፍራ (ብዙ ሰራዊት)

ዐፈነ: ሸፈነ፡ ደፈነ፡ ጠቀጠቀ፡ ኣለመ (ዋሻን በጪስ) (በጭስ መሸፈን)

ዐፈነ: ዘገነ፡ ያዘ (እህልን) (እህልን ማከማቸት)

ዐፈነ: ዘጋ፡ ወተፈ የባሪያን አፍ በኳስ፡ ጩኸትን፡ ትንፋሽን ከለከለ (ማፈን፡ ማስቆም)

ዐፈነ: ፈረስን፡ በቅሎን በቤት አዋለ፡ ቀለበ (እንስሳን ማሰር ወይም ማላመድ)

ዐፈና: ሽፈና፡ ወሊስ፡ የማያቋርጥ ዝናብና ጉም (አንድን ነገር መሸፈን ወይም የማያቋርጥ ዝናብ)

ዐፋኝ (ኞች) (ሐፋኒ): ያፈነ፡ የሚያፍን፡ ዘጋኝ፡ ሸፋኝ (የሚያፍን ሰው ወይም ነገር)

ዐፍለኛ (ኞች): ዐፈሌ፡ የ፴ ዓመት ጐበዝ፡ ያ፲፭ ዓመት ቈንዦ፡ ዐፍል ያለው፡ ያላት፡ ባለዐፍል (ጎልማሳ ወይም ውብ)

ዐፍለኛ: ቂጣነትና ሑምጣጤ የሌለው እንጀራ፡ ዳቤ፡ ዳቦ (ቂጣ ያልሆነ ለስላሳ ዳቦ)

ዐፍለኛነት: ዐፍለኛ መኾን።

ዐፍላ፡ ዐፍል: ሙሉ ሰውነት፡ ጕብዝና፡ አካለ መጠን፡ ጕልምስና (የጎለመሰ ዕድሜ)

ዐፍላ እንቅልፍ: ከባድ፡ ብርቱ (ኢዮ፴፫፡ ፲፭) (ጥልቅ እንቅልፍ)

ዐፍላ ጦር: ብርታት ያለው፡ ያልበረደ፡ ጋብ ያላለ (የማይፈራ ጀግና)

ዐፍሌታ: ጥዋ፡ አፍሌታ (የተወሰነ የእድገት ወቅት)

ዐፍሮ ቀረ: ሰውን ማየት ፈርቶ አልመጣም አለ።

ዐፍሮ አይገባ: ያሞራ ስም፡ እንደ ጥንበ በላ ያለ ታናሽ አሞራ፡ ሰው ሲያይ በሩቁ የማይሸሽ፡ የማይፈራ፡ ደረቅ ዐጥንት፡ ውዳቂ ለቃቃሚ፡ ሦስት ዐይነት መልክ (የአሞራ ዓይነት)

ዐፍሮ: ፈርቶ፡ ግንባሩ ታጥፎ (ፈርቶ ያቀረቀረ)

ዐፍሻት: ጥዋ፡ ዐፈሠ (የአንድ ነገር መውጣት ወይም መበተን)

ዑመር እብነ እልኸጣብ: ጻድቅ ሰው፡ የእስላም ንጉሥ፡ ለክርስቲያኖች ነጻነት የሰጠ፡ የጦር አለቆች ድኻን እንዳያጠቁ የከለከለ፡ ሰሌን እየሠራ ፍሬ ጻማውን የተመገበ (የእስልምና ታሪክ ውስጥ ታላቅ ሰው)

ዑመር ወልደ ዐፅ: በ፰፻ .. ግብጽን የያዘ፡ በቅብጥ ቋንቋ የተጻፉ (ዐምሳ ሺሕ) የጥበብ መጻሕፍት ያቃጠለ (ታሪካዊ ሰው)

ዑመር: ሸኅ ዑመር፡ የወረ ሸኆች አባት፡ በየጁ የነበረ (ታሪካዊ ሰው)

ዑመር: የሰው ስም፡ "ዕድሜያም" ማለት ነው ይላሉ።

ዑቃቤ: ውቃቢ፡ ጥበቃ። "ውቃቢን" ተመልከት።

ዑደት: ዙረት።

ዑደት: የታቦት፣ የካህናት፣ የሕዝብ ጊዜ ዙረት።

ዑድ (ዐረ): ዋግራ፡ የሬት ዕንጨት ሽቱ፡ በግእዝ "ዐልው" ይባላል።

ዑድ ሰንደል: ዑድና ሰንደል ለየ ብቻው ሲኾን ባንድነት መነገሩ ዐማሮች ሰንደልን በዑድ ስም ስለ ጠሩት ነው። ይኸውም የጪስ ዕንጨታቸው ኹኔታ መመሳሰሉን ያሳያል። "ነድንና ሰንደልን" እይ።

ዑድ: ዙር (ግእዝ)

ዑድ: የሽቱ ስም።

ዑድ: የሽቱ ስም፡ እንደ ሰንደል የተበጀ ሽቱ፡ ኹለቱም የጪስ ዕንጨቶች ናቸው።

ዓለመ መላእክት: ሰማይ፡ ኤረር፡ ራማ፡ ኢዮር።

ዓለመ ሰብእ: ምድር፡ የሰው መኖሪያ።

ዓለመ ሥጋ: ይህ ዓለም።

ዓለመ ነፍስ: መንግሥተ ሰማይ።

ዓለመኛ: ዝኒ ከማሁ (ከዓለማዊ ጋር ተመሳሳይ)፡ የዓለም ሰው፡ ዓለም ወዳድ፡ ባለቅልጣን (ገንዘብ ወዳድ)

ዓለሙ: ዓለሜ፡ የሰው ስም፡ የርሱ፡ የኔ ዓለም ማለት ነው።

ዓለሚት: የሴት ስም።

ዓለማዊ: መናኝ፣ እውነተኛ መነኵሴ ያልሆነ፡ ጥቁር ራስ፡ በዓለም ያለ፡ ዓለም ፈላጊ።

ዓለም (ሞች): በቁሙ፡ ሰማይና ምድር፡ የአድራጊና የፈጣሪ መኖር ምልክት።

ዓለም (በቀጥታ ትርጉም): ዝንት ዘላለም ዓለም ዘላለም ማለት ነው። (ሁለተኛውን ዓለም እይ)

ዓለም ሰገድ: የአጼ ፋሲል ስመ መንግሥት፡ ዓለም የሰገደለት ማለት ነው።

ዓለም ዐላፊ: መልክ ረጋፊ።

ዓለም አታላይ: እንዲሉ።

ዓለም አየ: ተደሰተ፡ ደላው፡ ተመቸው።

ዓለም ዘላለም: መንግሥተ ሰማይ። "ዘላለምን" እይ።

ዓለም ዘዋሪ: ዓለም ዋሾ።

ዓለም ጥበብ: የዓለም ተንኰል። "ዓለም ጥበብ ጨለማ ተገን" እንዲሉ።

ዓለም: ሰው ሁሉ፡ አዳሜ። "በዚህ ነገር ዓለም ሁሉ ተስማምቶበታል። "

ዓለም: እዱኛ፡ ተድላ፡ ደስታ፡ ሹመት፡ ሀብት፡ ንብረት፡ ጌትነት፡ ቅልጣን።

ዓለምን፡ አሸነፈ) እውነትን ወደደ፣ ዐመፅን ጠላ።

ዓመተ ምሕረት: የምሕረት፡ የይቅርታ ዘመን፡ ክርስቶስ ከተወለደ ዠምሮ የሚቈጠር፡ ሰው ከፈጣሪ የታረቀበት፡ ድኅነት ያገኘበት ጊዜ ማለት ነው።

ዓመተ ሰማዕታት: ሰማዕታት ዐንገታቸውን ለስለት፡ ዐይናቸውን ለፍላት የሰጡበት ዘመን።

ዓመተ ሥጋዌ: ጌታችን ሥጋ የለበሰበት፡ ሰው የኾነበት ዘመን።

ዓመተ ዓለም: ዓለም ከተፈጠረ እስኪያልፍ ድረስ ያለው ዘመን።

ዓመተ ኵነኔ: የቅጣት፡ የመከራ ዘመን፡ ከአዳም እስከ ክርስቶስ ያለው።

ዓመተ ፍዳ: ዓመተ ኵነኔ።

ዓመት ባል: በዓመት የሚከበር በዓል፡ ዐውዳመት።

ዓመት ተመንፈቅ: ዐሥራ ስምንት ወር።

ዓመት ዐውዳመት: መስከረም ቀን ቅዱስ ዮሐንስ (የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት) ዐውዳመት የዓመት ቅጽል ነው። "ዐወደን" እይ።

ዓመት ዓመት ድገመኝ: "እዛሬ ዓመት አድርሰኝ፡ የሚመጣውን ዓመት እሸት አብላኝ" ማለት ነው። አንደኛው "ዓመት" አዲሱን የሚመጣውን፡ ኹለተኛው "ዓመት" የዘንድሮውን፡ የተዠመረውን ያሳያል።

ዓመት ዕለት ነው: ቶሎ ይደርሳል፡ ብዙው ጊዜ ሺሕ ዓመት እንዳንድ ቀን ይታሰባል (ዘኍ፲፬፡ ፴፬፡ መዝ፺፡ ፬፡ ሕዝ፬፡ ፭ - )

ዓመት: ፲፪ ወር፡ ፫፻፷፭ () ቀን፡ ፶፪ ጊዜ ከአ፩ () ቀን፡ ወይም ፵፭ ሳምንት ከአ፭ () ቀን ነው። ፶፪ ሳምንት ማለት ግን ስሕተት ነው (የጊዜ መለኪያ)

ዓመት: ዘመን፡ ጊዜ።

ዓምና: ያለፈ ዓመት። "ዓምናና ዘንድሮ" እንዲሉ። "ኻች ዓምና": ከዓምና አስቀድሞ የነበረ ዓመት። "ኻችን" እይ።

ዓሣ ለቃሚ: ዝኒ ከማሁ፡ የወንዝ አመቴ፡ ወይም ሌላ (የዓሣ ዓይነት)

ዓሣ ነባሪ (የምታጠባ): (ወተት የምታጠባ ዓሣ ነባሪ)

ዓሣ ነባሪ መባሉ: በቀድሞ ዘመን ዓሣ ነባሪ ሲሞት ዐጥንቱ አዝራር ይበጅ እንደ ነበረ ያስረዳል (የስያሜው አመጣጥ)

ዓሣ ነባሪ: ታላቅ ዓሣ፡ የዓሦች ንጉሥ፡ መርከብ የሚገለብጥ። ነባሪ ነዋሪ ማለት ነው (የሚኖር) በግእዝ ዐንበር ይባላል።

ዓሣ ነባሪ: አዝራር፡ ከሰደፍ ዐጥንት፡ ከባሕር ዛጐል የተሠራ የእጅጌ፡ የጥብቆ፡ የቀሚስ ቍልፍ (አዝራር ከዓሣ ነባሪ አጥንት መሠራቱን የሚያሳይ)

ዓሣ ነባሪዎች (ዐናብርት): ታላላቆች ዓሦች።

ዓሣ ነባሪዎች: አዝራሮች (ብዙ ቁጥር)

ዓሣ አሥጋሪ: ዝኒ ከማሁ (እንደ ዓሣ አጥማጅ)

ዓሣ አውጭ: ዓሣን ከባሕር የሚያወጣ አሞራ (ዘሌ፲፩፡ ፲፫)

ዓሣ አጥማጅ (ጆች): ዓሣን በወጥመድ የሚይዝ (ኢሳ፲፱፡ ፰)

ዓሣ ወጋሪ: ዓሣን ይይዝና እድንጊያ ላይ እየመታ የሚገድል (ዓሣን በጦር የሚያድን)

ዓሣ ዋጭ: ዓሣ የሚውጥ (ዘዳ፲፬፡ ፲፫) በግእዝ አልያጦን ይባላል።

ዓሣ: የውሃ ውስጥ ተንቀሳቃሽ፡ ትልቅና ትንሽ፡ ምግብ የሚኾን (ወሸኸሬ፡ ወዶላት፡ ብል፡ ግልገል፡ ግንቡል፡ ዠመት፡ ሦርዞ፡ ጐርዞ፡ ቋሮ) (የተለያዩ የዓሣ ዓይነቶች)

ዓሥራታይ (ዓሥራት አይ): ዓሥራት የሚያይ፡ ዓሥራት አሰፋሪ፡ ጭቃ ሹም (ዐሥራት የሚሰበስብ ወይም የሚቆጣጠር)

ዓሥራት በኵራት: ዓሥራት እንዳለፈው፡ በኵራት የከብት፡ የተክል፡ የእሸት፡ የልጅ መዠመሪያዎች፡ መልካካም ነገሮች፡ ምርጦች ናቸው (የመጀመሪያ እና ምርጥ የሆኑትን ከአንድ አሥረኛ ጋር መስጠት)

ዓሥራት አወጣ: ከፈለ፡ ሰጠ ካሥር አንድን።

ዓሥራት: ካሥር አንድ፡ ለቤተ ክህነትና ለቤተ መንግሥት የሚሰጥ እህል፡ ገንዘብ፡ ከብት፡ ቀረጥ፡ ግብር (ከአንድ አሥረኛ የሚሰጥ ግብር)

ዓሥርት: የወላድ ሴት ዐሥረኛ ቀን ፀሓይ የምትሞቅበት (አንዲት ሴት ከወለደች በኋላ ዐሥረኛ ቀን የምትደገምበት የዕለት ስያሜ)

ዓደን: የጠረፍ ስም፡ የየመን ወደብ። ከ፲፱፻፴፫ .. ወዲህ ግን ዐዲስ አበቦች እንደ እንግሊዝኛ "ኤደን" ይሉታል፡ ስሕተት ነው።

ዓዲ: ዳግመኛ (ግእዝ)

ዔሊ (ሔለይ): የአውሬ ስም፡ ድንጋይ ልብሱ፡ ፬፻ ዓመት የሚኖር አውሬ (ዘሌ፲፩፡ ፴) አንድ ነገር ባየ ጊዜ ራሱን፣ የፊት እግሩንና የኋላ እግሩን በልብሱ ውስጥ ይደብቃል። "ለዔሊ ድንጋይ ያለበሰ አምላክ" እንዲሉ። ሲበዛ "ዔሊዎች" ይላል።

ዔሊ: የሰው ስም፡ ከሳሙኤል በፊት የነበረ ሊቀ ካህናት።

ዔሊዋ: ያች ዔሊ፡ የርሷ ዔሊ (እንስቷን ለመለየት)

ዔሊው: ዔሊ፡ የርሱ ዔሊ (ተባቱን ለመለየት)

ዔላም: በደብረ ሊባኖስ ውስጥ ያለ ስፍራ፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሁለተኛ የተቀበሩበት፡ ምንጫም፡ ጠበላም ማለት ነው።

ዔሮባ (ኤሮፓ): የፈረንጆች አገር፡ ምዕራብ ማለት ነው፡ ሌላም አፈታትና ትርጓሜ ይኖረዋል (አውሮፓ)

ዔሮፓ፡ ዔሮባ: ዐረበ።

ዔቦር: የሰው ስም፡ የሳላሕ ልጅ፡ የሴም ፭ኛ ትውልድ።

ዔድን (ዔዶም): ምቹ ስፍራ (ገነተ ተድላ) የግእዝ መጽሓፍ "ኤዶም" ይለዋል፡ አዳምና ሔዋን ከስሕተት በፊት የነበሩበት ምድረ ገነት ነው (ዘፍ፪፡ ፰-፲፡ ፫፡ ፳፬)

ዕሕ አለ: ተነፈሰ፡ እፎይ አለ።

ዕሕ አለ: አማጠ፡ ወደ ውጭ ገፋ።

ዕሕ አለ: ጠየቀ፡ እህ።

ዕሕ: የወላድ ድምፅ።

ዕሕታ: ምጥ፡ ማማጥ፡ የተቅማጥ በሽታ።

ዕሕታ: ጥያቄ፡ እህ።

ዕለተ ምጽአት: ጌታችን በክብር ወደዚህ ዓለም መጥቶ "ጻድቃንን ወደኔ ኑ፡ ኃጥአንን ከኔ ዘንድ ኺዱ" የሚልበት ቀን።

ዕለተ ሞት: የሞት ቀን፡ ነፍስ ከሥጋ የምትለይበት።

ዕለተ ቀኑ: ዕለት የግእዝ፡ ቀን የአማርኛ (ቅጽል "" የጌታ፣ የመልአክ፣ የጻድቅ፣ የሰማዕት ዝርዝር ነው) "መጋቢት ፳፯ የመድኀኔ ዓለም ዕለተ ቀኑ ነው (በዓሉ ይከበራል)"

ዕለተ ቀን: ከጧት እስከ ማታ።

ዕለተ ደይን: የፍርድ፡ የምጽአት ቀን።

ዕለተ ጠብ: ድንገተኛ የጊዜ ጠብ፡ ቍርሾ የሌለው።

ዕለት: ቀን። በግእዝ ግን ዕለት የሚባለው ሌሊቱን ጨምሮ ፳፬ ሰዓት ነው። "ዓመትን" ተመልከት።

ዕላቂ: ውራጅ ወርቅ፡ ቁረንጮ፡ ደላጎ።

ዕላቆ: የማረሻ፡ የዶማ ብረታ ብረት ቅሬታ።

ዕላፊ: ሰው ወደ ሥራውና ወደ ጕዳዩ በተወሰነው ሰዓት ሳይገባ ያሳለፈው ጊዜ። "የሰዓት ዕላፊ" እንዲሉ።

ዕላፊ: ዐለፌታ። "ያፍ ዕላፊ" እንዲሉ።

ዕላፊ: ግማሽ ብራና፡ ኅላፍ፡ አጋማሹ ወደ ሌላ የሚያልፍ።

ዕልል (ዕሉል): የታለለ፡ በደም የተነከረ (ራእ፲፱፡ ፲፫)

ዕልም (ሕልም): ራእይ በንቅልፍ ልብ የሚታይ፡ ማግኘትና ማጣት፡ ደስታና ሐዘን፡ ማንኛውም እውነተኛ ነገርና ሐሞታዊ ቅዠት ሁሉ።

ዕልም አለ: ጥፍት፡ ውድም አለ፡ (የመብራት፡ የዐይን፡ የሰው፡ የመንፈስ)

ዕልም ያድርገው: አምላክ ይህን ነገር በሥራ አይግለጠው፡ አይፈጽመው።

ዕልም ድርግም አለ: ፈጽሞ ጠፋ፡ ደለመ።

ዕልም: የጠፋ፡ ዕቡ። "ዕልም ዕልም" እንዲሉ።

ዕልቂት: ሸቀቀ

ዕልቂያ (ዕልቀት፣ ዕልቂት): የብዙ ሰው ሞት። (የከብት ዕልቂት): በ፲፰፻፹፪ .. በኢትዮጵያ የሆነ፡ የተደረገ። (ይኸውም ጣሊያኖች በሽታ ያለበትን ጐሽ ከህንድ አገር አምጥተው በትግሬ በረሓ ስለ ለቀቁት ነው የሚል ጽሑፍ በጣሊያንኛ ይገኛል)

ዕልቅ አለ: ጭርስ፡ ፍጽም አለ።

ዕልቅ: ዕልቂያ፡ ማለቅ።

ዕልቅ: ያለቀ፡ የተወረሰ።

ዕልቅት (ሐለቀ ሕልቅ): የደረት ሣፍ፡ የጕረሮ ሥር።

ዕልቆ መሳፍርት: የመስፈሪያዎች ቁጥር፡ ወይም የቁጥር መስፈሪያዎች።

ዕልቆ: ቍጥር፡ ልክ።

ዕልበት (ሕልበት): ጨው፣ ነጭ ሽንኵርት፣ ቅመም፣ የሱፍ ውሃ፣ ሰናፍጭ የገባበት ነጭ የባቄላ ወጥ፡ በጦም የሚበላ።

ዕልባት (ቶች): የፈትል፡ የሐር ክር፡ በመጻፍ ውስጥ ያለ።

ዕልባት አደረገ: ዐለበ፡ አመለከተ።

ዕልብ (ሕሉብ): የታለበ ጡት፣ ወተት።

ዕልብ (ዕሉም): የታለበ ምልክት፡ የተደረገበት።

ዕልክ: በቁሙ አለከ

ዕልዋ (ኀለወ): ሌሊት በፈረቃ ከብትን መጠበቅ፡ ወይም ጥበቃ፡ ዘብ (ሉቃ፪፡ ፰)

ዕልፈት: ሞት፡ ከዚህ ዓለም ተሰናብቶ መኼድ (ምሳ፲፡ ፳፭)

ዕልፊት: ድፍረት፡ ዐለፌታ፡ ነቀፋ።

ዕልፍ አለ: ፈቀቅ አለ።

ዕልፍ አደረገ: ፈቀቅ አደረገ።

ዕልፍ: ከልክ፡ ከስፍር፡ ከመጠን፡ ከቁጥር ያለፈ፡ ዕላፊ። "ዕልፍ ትርፍ" እንዲሉ።

ዕልፍ: ፈቀቅ፡ ስፍራ መልቀቅ።

ዕልፍታ: ዕልፍ ማለት፡ ፈቀቅታ።

ዕልፍኝ ታዳራሽ: ዕልፍኝነት ከአዳራሽነት ያለው ቤት፡ የታላላቆች ሰዎች ግብር መብሊያ።

ዕልፍኝ አዳራሽ: ሰውን ወደ ዕልፍኝ የሚያቃርብ (የሚያደርስ) ቤት።

ዕልፍኝ አዳራሽ: የንጉሥ ድንኳን።

ዕልፍኝ: በሐር የተቈነጠጠ፡ በግምጃ የተለበጠ ጌጠኛ ራስጌ ቤት፡ ባዳራሽ ዐልፎ የሚገባበት (፪ዜና፡ ፳፪፡ ፲፩)

ዕመም (ሕማም): በሽታ፡ ምታት፡ መጋኛ፡ ቍርጥማት፡ ቍርጠት፡ ፍልጠት፡ ውጋት፡ ወባ፡ ተስቦ፡ ተቅማጥ፡ እውከት፡ የመሰለው ሁሉ (የህመም ዓይነቶች)

ዕመምተኛ (ኞች): ዕመም ያለበት፡ ያደረበት፡ በሽተኛ፡ ዱያታም (በህመም የተጎዳ)

ዕመምተኛነት: ዕመምተኛ መኾን፡ በሽተኛነት።

ዕመት (ሕመት): የዕጣን ዐመድ፡ ከሰል (የቃጠሎ ቅሪት)

ዕመት: የቅዱሳን መሬት፡ ደማቸው የፈሰሰበት፡ ዐፅማቸው የረገፈበት። ምስጢሩ እምነትን ያሳያል።

ዕምስ (ኅሙስ): አምስት የሆነ፡ የተከፋፈለ።

ዕምስ (ሕሙስ): የታመሰ፡ የሞቀ፡ የተንቃቃ፡ ሙቀት የተቀበለ፡ ቅይጥ ዱቄት፡ ውቅጥ በርበሬ (የተደባለቀ)

ዕምስ (ኅምስ): የሴት ኀፍረት፡ ፭ኛ ሕዋስ።

ዕምስ አንቀጥቅጥ ዕምስ ፈሪ: ዝኒ ከማሁ፡ ኅምስ ዘይፈርሆ (እንደ ዕምስ የሚፈራ)

ዕምስ አንቀጥቅጥ: ሽታ ያለው ቅጠል፡ ጕዝጓዝ የሚሆን፡ ከዐመጃይ ጋራ የሚበቅል።

ዕምቅ (ዕሙቅ): የታመቀ፡ የተረጠጠ፡ ጥርጥጥ።

ዕምት (ትግርኛ ሕምቶ፡ ዱለት): የታመተ፡ የተከተፈ ክትፎ፡ የታመሰ ዕምስ።

ዕምድ መታው: ዐመዳይ አጠፋው፡ አበላሸው።

ዕምድ: የታመደ፡ የተቈረጠ (ቅጽል)

ዕምግ (ሕሙግ): የታመገ፡ ስብስብ፡ ክምችት።

ዕሰባ: በልብ የሚሠራ ያሳብ ኹኔታ (የሀሳብ ሁኔታ)

ዕሠዬ: የሰው ስም፡ የኔ ዕሠይ ማለት ነው።

ዕሠዬው: "" ያው ከማለት የመጣ ነው።

ዕሠይ ዕሠይ: ደግ ደግ፡ ማለፊያ ማለፊያ፡ መልካም መልካም፡ ይበጅ፡ ያድርግ። የእልልታ ምስጢር አለበት (ሕዝ፳፮፡ ፪) (የደስታ መግለጫ)

ዕሰይ: የደስታ ቃል፡ ዕሠይ።

ዕሠይታ: ዕሠይ ማለት፡ መደሰት።

ዕሣሽ: የምጣድ ጥራጊ።

ዕሴይ: የሰው ስም፡ እሴይ።

ዕሥሥ: የታሠሠ፡ የተጠረገ፡ ውልውል (የተጸዳዳ)

ዕሥሥት (ቶች) (ኅሥሥት): የተንቀሳቃሽ ስም፡ ያየውን መልክ የሚመስል፡ ተለዋዋጭ አውሬ (ዘሌ፲፩፡ ፴) (ቅርጽ የሚቀያይር እንስሳ)

ዕሥሥት: ማንቊርት ዐንቆ ለመግደል የምትፈለግ ማለት ነው

ዕሥሥት: ወረተኛ፡ ገልባጣ ሰው፡ ዛሬ ካንዱ ነገ ከሌላው የሚወዳጅ (ተለዋዋጭ ሰው)

ዕሥር: የታሠረ፡ ዐሥር የኾነ (የታሠረ ወይም ዐሥር ሆኖ የተገኘ)

ዕስቅ (ዕሱቅ): የታሰቀ፡ የተጠለፈ፡ የተጌጠ፡ ዝንጕርጕር ልብስ (የተጌጠ ልብስ)

ዕስባት: ሒሳብ፡ ስሌት (ሂሳብ ወይም ስሌት)

ዕስብ (ሕሱብ): የታሰበ (የታሰበ)

ዕስብታ: ትውስታ (ትውስታ)

ዕስክ፡ ዕሽክ፡ ዕችክ: (የድምጽ አገላለጽ)

ዕሦ (ሐሠየ፡ ዐሠየ)

ዕሶ፡ ዕሠይ: ዕሦ።

ዕሦ: የዕሠይን ፍች እይ። ተደጋግሞ ሲነገር "ዕሦ ዕሦ" ይላል።

ዕረፍ: ተቀመጥ፡ ዝም በል (የማረፊያ ትዕዛዝ) (ጥር) ዐርፎ ዐርፎ: ቈርጦ ቈርጦ (መቁረጥን የሚያመለክት)

ዕሩር (ሮች): ላይ ላዩ በእሳት ያረረ፡ የከሰለ የንጨት ጥንግ (በእሳት የከሰለ እንጨት)

ዕሩቅ ብእሲ: የጳውሎስ ሳሚሳጢና የንስጥሮስ፡ ባህል፡ የክርስቶስን ኣምላክነት ክዶ (ዕሩቅ ብእሲ) ሰው ብቻ ነው ማለት (ክርስቶስ ሰው ብቻ ነው ብሎ የሚያምን) "ኀድረትን" እይ።

ዕሩቅ: የተራቈተ፡ የታረዘ፡ ብቻ (ግእዝ) (ራቁቱን የሆነ)

ዕሪ: ጩኸት፡ አረረ (ጩኸት)

ዕሪም (ሞች): ታናሽ የመሬት ክፍል፡ ሰፊና ታላቅ ከኾነ ርስት ተከፍሎ ላገለገለ አሽከር፡ ለሎሌ፡ ለወዳጅ፡ ለካህን የተሰጠ ማሳ፡ ዕን ጐርዶ ሪም ቢል ዕዛብን ዛብ እንደ ማለት ያለው ነው (አነስተኛ የመሬት ክፍል)

ዕሪያ ሲባል እንደ አሳማ በሰው መብት የማይኖር ነጻነት ያለው ማለት ነው። "ከርከሮን" እይ (ነጻ አውሬ)

ዕሪያ ጥርስ: ጥርሰ ገጣጣ ሰው፡ የሪያ ጥርስ ተብሎም ይተረጐማል (የአሳማ ጥርስ የሚመስል ጥርስ ያለው ሰው)

ዕሪያ: በዱር የሚኖር የዓሣማ ዓይነት አውሬ፡ ጥርሱ ተከንፈሩ ውጭ ወጥቶ የሚታይ እንስሳ (የዱር አሳማ)

ዕራሪ (ሕራር): የነጠፈ፡ የደረቀ፡ የሸሸ (የደረቀ)

ዕራሪ: ንጥፈት፡ ድርቀት። "የጡት ዕራሪ" እንዲሉ (ድርቀት)

ዕራሪ: ከራራ፡ ድውይ (የታመመ)

ዕራሽ: የርሻ ይዘታ (የእርሻ ይዞታ)

ዕራቍት (ዕሩቅ): የተራቈተ (ዮሐ፳፩፡ ፯) ያለፈው ጥሬ፡ ይህ ቅጽል መኾኑን አስተውል (ራቁቱን የሆነ)

ዕራፊ (ዎች): የሸማ ቍራጭ፡ ዐዲስ፡ ወይም አሮጌ፡ ያለቀ፡ የተቀደደ ልብስ፡ መጣፊያ (የተቆራረጠ ጨርቅ)

ዕር: ፍየል መከልከያ፡ እር (ፍየል መከልከያ)

ዕርመ በላ: እዘመዱ ለቅሶ ያልደረሰ፡ ያላለቀሰ (ለቅሶ ያልደረሰ)

ዕርሙን አወጣ: ለሞተ ዘመዱ አለቀሰ (ለሞተ ዘመድ ማልቀስ)

ዕርማት: የማረም፡ የመታረም ሥራ (የማረም ተግባር)

ዕርም (ሕሩም): የታረመ፡ የተነቀለ (የታረመ)

ዕርም (ሕርም): ሊቀምሱት፡ ሊበሉት፡ ሊነኩት የማይገባ፡ ክልክል ነገር (ኢያ፯፡ ፲፩፡ ፲፪፡ ፲፫) (የተከለከለ) "ዕርም የሰው ሥጋ" እንዲሉ (የሰው ስጋ ክልክል እንደሆነ) (ተረት): "ዳገት ዕርሙ፡ ሜዳ ወንድሙ" (ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዕርም ተባለ: ታረመ፡ ዕርም ኾነ (የተከለከለ ሆነ)

ዕርም ታኽል: በጣም ያነሰች፡ እምር ታኸል፡ አመረ (በጣም ትንሽ)

ዕርም ነው: አይቀመስም፡ አይበላም፡ ክልክል ነው (የተከለከለ ነው)

ዕርም አለ: ዐረመ፡ እንደ ሰው ሥጋ ቈጠረ (እንደ ሰው ስጋ ክልክል አደረገ)

ዕርም: ለወገን፡ ለዘመድ አለማልቀስ። "በላ" ብለኸ "አበላን" እይ (ለዘመድ ያለቅሶ አለመድረስ)

ዕርምኸን አውጣ: አልቅስ፡ እንባኸን አፍስስ (እንባ ማፍሰስ)

ዕርስ (ሕሩስ): የታረሰ፡ የተሰበተ (የታረሰ)

ዕርስ ዐደር ኾነ: ጦም ዐደረ (ራብ ላይ መዋል)

ዕርስ ዐደር: ታርሶ ሳይዘራ የቀረ መሬት (የታረሰ ግን ያልተዘራ መሬት)

ዕርር (ሐሪር): ማረር (መቃጠል)

ዕርር ምርር አለ: ፈጽሞ ኦለቀሰ፡ በሐዘን ተጨበጠ (በጣም ማልቀስ)

ዕርር አለ: ክስል፡ ግምን አለ (ከሰለ)

ዕርር ኵምትር አለ: እጅግ ዐረረ፡ ተኰማተረ (በጣም መኮማተር)

ዕርርታም: ዕርርት ያለበት፡ ባለዕርርት (ዕርርት ያለበት)

ዕርርት (ሕርርት): ያረረች (የተቃጠለች)

ዕርርት: ሞራ፡ በበሬ፡ በሰው ዐይን ላይ የሚወጣ ትርፍ ሥጋ፡ ዐራራ መሳይ (ዓይን ላይ የሚወጣ ሥጋ) የባላገር ሐኪምም በሬውን ጥሎ ዕርርቱን በመርፌ ወግቶ በክር ይስብና ከቆረጠ በኋላ ዐይኑ ውስጥ የወይናግፍት ዶቄት ይጨምርበታል (የሕክምና ዘዴ) የበሬን ጭራ የሚቈርጥ ቍስል (የቁስል ዓይነት)

ዕርሻ (ሕርስ): ማሳ፡ ቅብቅብ (ኤር፴፪፡ ፵፫) (እርሻ)

ዕርሻ ዠመረ: ተለመ።

ዕርሻዎች፡ ዕርሾች: ማሳዎች፡ ቅብቅቦች (ኤር፴፪፡ ፵፬) (እርሻዎች)

ዕርቀ ሰላም: የሰላም ዕርቅ፡ ወይም የዕርቅ ሰላም (ሰላማዊ ዕርቅ)

ዕርቃነ ሥጋ: የሥጋ ዕራቍት። የሰቅለት ለት የጌታችን ዕርቃነ ሥጋ እንዳይታይ ፀሓይ ጨለመ፡ ጨረቃ ደም ኾነ (የሥጋ ራቁት)

ዕርቃን የግእዝ፡ ዕራቍት የአማርኛ ነው (ዘፍ፪፡ ፳፭፡ ፱፡ ፳፩) (የቃላት አመጣጥ)

ዕርቃን: ዕራቍት፡ አካላዊ ግንድ፡ መለመላ፡ ልብስ የሌለው፡ ባዶ ገላ (ራቁት አካል)

ዕርቅ: (ምሳ፲፭፡ ፬) ስምም፡ ፍቅር (ስምምነት ወይም ፍቅር) (ተረት): "ዕርቅ አይፈርስ፡ ዐይን አይፈስ" (ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዕርቅ: የታረቀ፡ ቀጥ ያለ (ርቱዕ) (የታረቀ)

ዕርቅና: ዕራቍትነት፡ ዕራቍት መኾን፡ ልብስ አልባነት (ሚክ፩፡ ፲፩፡ ዘፍ፱፡ ፳፪፡ ፳፫) (ራቁትነት)

ዕርበት: ጥልቀት (ግእዝ) "የንጉሥ ሞት የጀንበር ዕርበት" እንዲሉ። (ጥልቀት)

ዕርቡን: ዝኒ ከማሁ። ዐረቦን ግእዝ፡ ዕርቡን ዐረብኛ ነው።

ዕርከን (ኖች): የመሬት ደረጃ፡ ከፍና ዝቅ ብሎ የሚታይ፡ ከድንጋይ፡ ከሳንቃ፡ ከስሚንቶ የተበጀ፡ የደርብ፡ የመንበር መውጫና መውረጃ (፬ነገ፡ ፲፡ ፲፱፡ ፳) (ደረጃ)

ዕርዝ (ዕሩዝ፡ የለበሰ): የታረዘ፡ የተራቈተ (ራቁቱን የሆነ)

ዕርዝተኛ (ኞች): ዝኒ ከማሁ፡ ልብሱ ያለቀበት፡ ገላው የሚታይ (ልብስ የሌለው ሰው)

ዕርዝና: ዕርዛት፡ ዕርዝተኛ መኾን፡ ዕራቍትነት (እርቃንነት)

ዕርድ (ሕሩድ): የታረደ፡ ማንቍርቱ የተቈረጠ (የታረደ)

ዕርድ: ሥጋ። "የርድ ከብት" እንዲሉ (ሥጋ)

ዕርድ: ጕድባ፡ ምሽግ፡ ፈፋ፡ ጕድጓድ (ጉድጓድ ወይም ምሽግ)

ዕርጃ: ዝኒ ከማሁ (እንደ ዐረዳ)

ዕርገተ ቃል: የቃል፡ የጌታ ወደ ላይ ማረግ። የክርስትና ስም።

ዕርገት: ወደ ሰማይ መውጣት (ወደ ላይ መውጣት)

ዕርገት: የበዓል ስም፡ ጌታችን እንደ ሰውነቱ ያረገበት፡ በግንቦት ቀን ኀሙስ የሚከብር ታላቅ በዓል (የበዓል ስም)

ዕርግ በራሕ: ሕፃናት በነቢዩ ኤልሳዕ ያላገጡት ለግጥ። በራሕ በግእዝ በራ፡ መላጣ ማለት ነው (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክን የሚያመለክት)

ዕርግ: ውጣ።

ዕርጓ: ቀጪን፡ ሽመል፡ ረጋ (ረግቶ የተቀመጠ)

ዕርጥ (የደም ዕርጥ): በብዛት የሚወርደውን የሴት ደም የምታቆም ታናሽ ዶቃ፡ አስማት የተደገመባት ቀይ ድባ ሳንባ መሳይ (ደም ማቆሚያ)

ዕርጥ: የክርስቶስ ኀይል (ማር፭፡ ፳፬) (የክርስቶስ ኃይል)

ዕርጭ: ዝም፡ ረ (ዝም ማለት)

ዕርፈ መስቀል: በመጨበጫው ጫፍ መስቀል ያለበት ማንካ፡ የሥጋ ወደሙ መስጫ፡ ማቀበያ፡ ከንዋየ ቅድሳት አንዱ (የቤተ ክርስቲያን ዕቃ)

ዕርፈ መስቀል: የምሳሌ አነጋገር፡ ዕርፍ ሠም፡ መስቀል ወርቅ (ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዕርፊተ ቢስ: የማያርፍ፡ እፎይ የማይል (እረፍት የሌለው)

ዕርፊት (ዕረፍት): ማረፍ፡ ሞት፡ ዝምታ፡ ጸጥታ (ዕረፍት፣ ሞት፣ ወይም ጸጥታ)

ዕርፊት የለሽ: ዝኒ ከማሁ፡ የሚዋትት (እረፍት የሌለው፣ የማይታክት)

ዕርፍ (ፎች): ለርሻ ሥራ የተቈረጠ፡ ከሞፈርና ከማረሻ የተዋደደ፡ የበሬ ዕቃ፡ ከኹለት ድግር ጋራ ወገል የጐረሠው የእርሻ መሣሪያ (ሢራ፴፰፡ ፳፭፡ ሉቃ፱፡ ፷፪) (የእርሻ መሣሪያ)

ዕርፍ መጣያ: የነሐሴ ፲፯ኛ ቀን ፍልሰታ፡ ዕርፍ ከርሻ ተለይቶ የሚቀመጥበት ማለት ነው (ዕርፍ የሚቀመጥበት ቦታ)

ዕሸማ: ጕንጐና (ሽሩባ)

ዕሺ (ዐሠየ): የእንቢ ተቃራኒ፡ በጄ እሠራለሁ፡ አደርጋለሁ (የእሺታ ወይም የመስማማት ቃል) "ዕሺ ይበልጣል ከሺ" እንዲሉ (የእሺታን ጥቅም የሚያሳይ አባባል)

ዕሺ በጎ አለ: ደግ ማለፊያ ይሁን አለ (ምኞት ወይም በጎ ፈቃድ)

ዕሺ ባይ: ታዛዥ፡ ፈቃደኛ፡ ትሑት፡ ገር (ኦሆ በሃሊ) (ታዛዥ ሰው)

ዕሺ አለ: ታዘዘ፡ ትእዛዝ ተቀበለ (ዳን፮ * ) (መታዘዝ)

ዕሺ አሠኘ: አንድ ነገርን፡ ዕርቅን አስፈቀደ፡ አስቀበለ (እንዲስማሙ ወይም እንዲፈቅዱ አደረገ)

ዕሺታ: ዕሺ ማለት፡ መታዘዝ (የመታዘዝ ድርጊት)

ዕሺና ዕሽ በአማርኛ ይተባበራሉ (የቃላት ግንኙነት) (ግጥም): "አውራ ዶሮ ጭሮ ስጥሽን ሲያፈሰው፡ እንዴት ዕሽ ማለት ይቸግራል ለሰው" (የመታዘዝን አስፈላጊነት የሚገልጽ ግጥም)

ዕሻ: ዕሽ፡ አይዶለም። ዕሻ ዝም በሉ እንዲል ጐንደሬ (በጎንደር አካባቢ ጥቅም ላይ የሚውል አገላለጽ)

ዕሽ (ሐሰ): ክልከላ (እገዳ ወይም ክልከላ) (ተረት): "ዕሽ አትበሉኝ፡ የሹም ዶሮ ነኝ" (እገዳን የሚገልጽ ምሳሌያዊ አነጋገር)

ዕሽ አለ: በመቅደስ ውስጥ በቅዳሴ ጊዜ ጠቀሰ፡ ጠራ፡ አዘዘ፡ " በል" እለ (የሃይማኖታዊ ሥርዓት አካል)

ዕሽ አለ: ከለከለ፡ የዝንብ፡ የዶሮ፡ የወፍ፡ የባለክንፍ (መከልከል፣ በተለይም በበረራ ላይ ያሉትን)

ዕሽማት: የዕሽም ሥራ፡ ጕንጕናት (የሽሩባ ሥራ)

ዕሽም: ከ፫ና ካ፬ የማይበልጥ (ጥብ) ድብል ሽሩባ (አነስተኛ ሽሩባ)

ዕሽሽ (ዐሠሠ): ትግ ዕሻሽ)፡ የታሠሠ፡ የተጠረገ፡ ዕሣሽ፡ ዕሥሥ፡ ብናኝ፡ ዐቧራ (የተጠረገ ወይም አቧራ)

ዕሽሽ ኵምሽሽ አለ: ሰውነቱ ዐለቀ፡ ተጨበጠ፡ ዕፍር አለ (አንድ ሰው በጣም ሲደክም ወይም ሲዝል የሚያሳይ አገላለጽ)

ዕሽሽ: ድቄት፡ ጤና ማጣት፡ ውሽሽን አስተውል (ድካም ወይም ጤና ማጣት)

ዕሽባቦ (ዕሺ ባቦ): በጄ ማለት፡ መታዘዝ (መታዘዝ)

ዕሽባቦ አለ: ፈቃድ ፈጻሚ ኾነ፡ አንተ እንዳልክ አለ (ፈቃደኛ መሆን) "ዕሺንና ባቦን" እይ።

ዕሽባቦ ዕሽባቦ አለ: አሽበለበለ (አሽበለበለ)

ዕሽታት: የማሸት፡ የመታሸት ሥራ (የማሸት ተግባር)

ዕሽት (ሕስየት): ማሸት፡ መታሸት፡ የገላ፡ የልስን (ማሸት)

ዕሽት አደረገ: አጥብቆ ዐሸ (አጥብቆ አሸ)

ዕሽት: ሙቅ ውሃ እየተጨመረበት የታሸ ደቃቅ ኑግ፡ ዳግመኛም በንስራ ውስጥ አድርገው ሲያዞሩት በፀሐይ ሙቀት ቅባት ይወጣዋል (የዘይት ዓይነት)

ዕቁብ: የተጠበቀ፡ ጥብቅ፡ የመዋጮ ገንዘብ፡ በአንድ ሰው እጅ ተጠብቆ፡ በዕጣ ለዕቁብተኛው የሚታደል፡ መጨረሻ ከሚወስደው በቀር ሌላው ሁሉ ይመልሳል (የኢትዮጵያ ባህላዊ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ስርዓት)

ዕቁብተኛ (ኞች): ባለዕቁብ፡ የዕቁብ ማኅበረተኛ (የዕቁብ አባል)

ዕቃ መጣ) በሸክም፣ በጭነት ተጋዘ። ካህናት ግን መፃ ይላሉ።

ዕቃ መጥረቢያ: ዕንጨት ማለዘቢያ፡ ማሾያ፡ መሸለቻ፡ ስለት ያላት ታናሽ መጥረቢያ፡ ሞፈር፡ ቀንበርን፡ ድግርን፡ ቈሬን፡ ገበቴን፡ መዝጊያን፡ መቃንና፡ ጕበንን፡ ዋልታን፡ ጠርብን፡ ማእዘንን፡ ሣጥንን፡ ያልጋ፡ ሸንኰርን፡ ደንብን፡ ዘንግን፡ ኮርቻን፡ በርጩማን፡ ወንበርን፡ መንበርን፡ የመሰለውን ሁሉ ያንጡባታል (የአናጺ መሳሪያ)

ዕቃ ቤት: ማንኛውም ዕቃ የሚቀመጥበት ቤት፡ ቤተ መዛግብት (ዕቃ ማስቀመጫ)

ዕቃ ቤት: ዕቃ ጠባቂ፡ የዕቃ ቤት ሹም (ዕቃ የሚጠብቅ ሰው)

ዕቃ ቤትነት: የዕቃ ቤት ሹመት፡ ሹምነት። (ተረት): "ሰባት ወልዶ ዕቃ ቤትነት" (ብዙ ነገሮችን ለማስተዳደር የሚከፈል ዋጋ)

ዕቃ ቤቶች: የዕቃ መቀመጫዎች፡ መኖሪያዎች (ሕዝ፵፪፡ ፲፡ ፲፪) (ብዙ ዕቃዎች የሚቀመጡባቸው ቦታዎች)

ዕቃ ቤቶች: የዕቃ ዘበኞች (ዕቃ የሚጠብቁ ሰዎች)

ዕቃ ወዘተ ከቦታው ወጥቶ ተበታተነ፡ ተጨፈለቀ: ምሳሌ: "ዕዳሪው ተተረተረ።"

ዕቃ ግምጃ ቤት: ዕቃና ግምጃ የሚቀመጥበት ቤት (ዕቃና ንብረት የሚቀመጥበት)

ዕቃ ግሴት: ሰባራ፡ ሥንጥር፡ ቅራቅንቦ፡ ቋንቍሬ፡ ኵተት (የተሰባበሩና ያረጁ ዕቃዎች)

ዕቃ ጦር: የጦር መሣሪያ (፪ቆሮ ፮፡ ፯)

ዕቃ: በር የመለሰው፡ ማጀት የጐረሠው፡ በቈጥ የተሰቀለ፡ በማጎር የተንጠለጠለ፡ የንጨት፡ የብረት፡ የማዕድን፡ የሸክላ፡ የስፌት፡ የቈዳ፡ ማንኛውም መሣሪያ ሁሉ (የተለያዩ መሣሪያዎችና ዕቃዎች)

ዕቅ አለ: ሕቅ አለ።

ዕቅ: ሕቅ (የማለት ድምጽ)

ዕቅባት: ሽፍናት። "ተንበረክን" እይ (መሸፈን)

ዕቅብ: የተመላ፡ የተሠየመ።

ዕቅብና: ዝኒ ከማሁ፡ ጥበቃ (መጠበቅ)

ዕቅታ: ሕቅታ። "ሕቅን" እይ።

ዕቅዳት: የዐቅድ አኳዃን (የዕቅድ አፈጻጸም)

ዕቅድ: የታቀደ፡ በአሳብ የተለካ፡ የተመጠነ፡ ምጥን (ዕቅድ)

ዕቅፍ (ሕቁፍ): የታቀፈ፡ በዕቅፍ የተያዘ።

ዕቅፍ (ትግርኛ ሐባ፡ ሕቅፍ): ሕፅን ብብት (ብብት)

ዕቅፍ አደረገ: በፍጥነት ዐቀፈ። "፬ኛውን " እይ።

ዕቅፍ ዶሮ: በ፪ ክንፎቿ ውስጥ ጫጩቶች የታቀፈች እመጫት ዶሮ (ጫጩቶቿን የምታቅፍ ዶሮ)

ዕቅፍ: ማቀፊያ፡ ፪ እጅ፡ ወይም ክንድና ጡንቻ። "ዕንጨት በቅፍሽ ይዘኸ " (በእጅ መያዝ)

ዕቅፍ: ያቀፈ፡ የያዘ (የሚያቅፍ ወይም የሚይዝ ሰው)

ዕቅፍቅፍ አለ: ተቃቀፈ።

ዕቅፍቅፍ: የተቃቀፈ፡ ድግፍግፍ (አይነቱ)

ዕቅፍታ: የማቀፍ ሥራ።

ዕቋ (ሕቋ): የሱረት ማስቀመጫ ታናሽ ቅል፡ ከሕቍ የተበጀ ባለመግጠሚያ፡ ብልቃጥ (ሱረት ማስቀመጫ)

ዕቋ: የርቦ አራተኛ መስፈሪያ፡ የሰንደል፡ የዞጲ፡ የብረት፡ የቈርቈሮ፡ የታኒካ ታናሽ ሙዳይ። በአረብኛ ሖቀት ትባላለች። (መለኪያ)

ዕቋሪ: የረጋ ውሃ (ሕዝ፵፯፡ ፲፩) (የረጋ ውሃ)

እበት: የበሬና የላም ሽንት። ለውድማ፣ ለቤት፣ ለጎታ፣ ለድብኝት መለቅለቂያ ይሆናል። ከአመድ ጋራ እየደባለቁም ወታቦና አክንባሎ ይሰራሉ። ጎሽ፣ አውራሪስ፣ ወደቢ፣ ቶራ፣ ድፋርሳ እና እነዚህን የመሰሉ የዱር እንስሶች ሁሉ እበት ይጥላሉ (ሕዝቅኤል ፬፥፲፭) "የጠገራ ላም ባደረችበት በረት እበት አይገኝም"

ዕበጥ (ሕበጥ): ብጕር፡ ብጕንጅ፡ ዕጢ፡ የመሰለው ኹሉ (ዘዳ፳፰፡ ፳፯፡ ፩ሳሙ፡ ፭፡ ፮፡ ፮፡ ፬) ሲበዛ "ዕበጦች" ይላል (፩ሳሙ፡ ፮፡ ፲፯)

ዕቡ (ኅቡእ): የታባ፡ ሽሽግ፡ ስውር፡ ድብቅ። (ተረት): "እግዜር የሔዋንን ልጆች ሊያይ በመጣ ጊዜ እኩሌቶቹን ደብቃ እኩሌቶቹን ብታሳየው፡ 'ልጆችሽ እነዚህ ብቻ ናቸውን' አላት። እሷም 'አዎን' አለችው። 'እንግዲያውስ ያባሻቸው ዕቡ ይኹኑብሽ' አለ" ይላሉ። "ዕቡ" የተባሉም የብሔረ ብፁዓን ሰዎች ናቸው።

ዕቡ ኾነ (ኅቡአ ኮነ): ሽሽግ፡ ረቂቅ፡ የማይታይ ኾነ፡ ጠፋ፡ ታጣ።

ዕቡይ (ዮች): የታበየ፡ ትቢተኛ፡ ክፉ፡ ጭቦኛ (ዘኍ፲፮፡ ፳፮፡ ፪ጢሞ፡ ፫፡ ፪)

ዕቡይ ካሳ: የታወቁ የቅኔ መምር (ቅኔያቸው የሚያከራ)

ዕባጫም: ዕባጭ የወጣበት፡ ያለበት ሰው፡ ባለዕባጭ።

ዕባጭ (ጮች): ዝኒ ከማሁ፡ ያበጠ፡ የተነፋ፡ ያሞለሞለ (ዱባ የመሰለ)፡ በጕያ፣ ባንገት፣ ከገላ ባንዱ ክፍል ከምች የተነሣ የሚወጣ፡ በተኵስ በመድኀኒት ፈንድቶ የሚፈርጥ ክፉ በሽታ። "ዕበጥ" የካህናት፡ "ዕባጭ" የሕዝብ ነው።

ዕብለታም (ሞች): ዐባይ፡ ዕብለት ወዳድ፡ ባለዕብለት።

ዕብለት: ውሸት፡ ቅጥፈት፡ ፈጽሞ ከውነት የራቀ።

ዕብስተ መና: ኅብስተ መና። ባላገር "ኅብስት" በማለት ፈንታ "ዕብስት" ይላል። "ኅብስትን" ተመልከት።

ዕብስት: ዕብዝት፡ ኅብስት።

ዕብረት: ኅብረት።

ዕብራዊ: የዔቦር ዘርና ወገን።

ዕብራውያን: የዔቦር ነገዶች፡ የዔቦር ተወላጆች (ሕዝበ እስራኤል)

ዕብራይስጥ: የዔቦር ቋንቋ፡ ሱርስትን፣ ግእዝን፣ ዐረብኛን የመሰለ። ኦሪት፣ ነቢያት የተጻፉበት። ቀድሞ የእስራኤል ወግን፡ ዛሬ ካህናተ ኦሪት (ረበናት) ይነጋገሩበታል።

ዕብዝ (ኀቡዝ): የታበዘ (ግግር)

ዕብዝት (ኅብዝት): የታበዘች (ታናሽ ዳቦ) "ዕብስት፣ ኅብስትን" ተመልከት።

ዕብጠት (ቶች): ዕበጥ፡ ዕባጭ።

ዕተማ: የማተም ሥራ፡ ረገጣ (የማተም ተግባር)

ዕትማት (ኅትመት): የማኅተም ጽፈት፡ ድርጊት (የማተም ድርጊት)

ዕትም (ኅቱም): የታተመ፡ የእጅ ጽፈት ያይዶለ (የታተመ)

ዕትራት (ቶች): የዕብጠት ቅንጣት፡ ቍርብጭታ (እብጠት)

ዕትባት: የዕትብት ቈረጣ ኹናቴ (ምህርት የመቁረጥ ሁኔታ)

ዕትብ (ዕቱብ): የታተበ፣ ዕትብቱ የተቈረጠ (ምህርቱ የተቆረጠ)

ዕትብት: ፍጥረት ሁሉ በናቱ ማሕፀን ሳለ በንብርቱ ጫፍ እንዳረቄ አሸንዳ ተተክሎ ከናቱ ሆድ ምግብ የሚቀበልበት ሥጋዊ መትረብ (የእምብርት ገመድ)

ዕችክ (ሐሰከ): ዕስክ፡ ዕሽክ፡ የዝናብ፡ የውሃ ጠብታ፡ ካፊያ በገላ ላይ ባረፈ ጊዜ የሚባል ዘዬ (የውሃ ጠብታ ድምጽ ወይም ስሜት) "ዕችክ ዕችካ የነጐፌ ወርካ" እንዲሉ ልጆች (የልጆች ጨዋታ ወይም ዘፈን) ትርጓሜውም በረደኝ፡ ቀዘቀዘኝ ማለትን ያሳያል (ትርጉም)

ዕንቍ: ሉል፡ በባሕር ውስጥ ሰደፍ የምትወልደው፡ ዳግመኛም በግእዝ ባሕርይ ይባላል። "ብርጋናን" እይ (ውድ ድንጋይ፡ ሉል)

ዕንቍ: አልማዝ፡ ፈርጥ፡ ክቡር ድንጊያ የሚባል፡ ብዙ ስምና መልክ አለው (ሌሎች ውድ ድንጋዮች)

ዕንቍላል ቤት: ደርብ፡ ሰገነት፡ መስጊድ፡ ዕንቍላል የሚመስል ዐናት ያለው (የተጠጋጋ ቅርጽ ያለው ሕንፃ)

እንቍላል: በቁሙ (ዕንቍላል)

ዕንቍላል: ከወፍ፡ ከዶሮ፡ ካሞራ፡ ከእባብ፡ ከዐዞ ሳይቀር የሚወለድ ጥጥር፡ ክብ፡ እንክብል ነገር። በውስጡ ያለው ውሃ እየረጋ ጫጩት (ግልገል) ይሆናል (እንቁላል) (ተረት): "ከሰነበተ ዕንቍላል በእግሩ ይኼዳል" (ምሳሌያዊ አነጋገር፡ የቆየ ነገር ይፋ ይሆናል) "ካፍ የወጣ ቃል፡ ከእጅ የወደቀ ዕንቍላል" (የተነገረ ቃል እንደተሰበረ እንቁላል አይመለስም)

ዕንቍላል: የጕንዳን፡ የምሥጥ፡ የዘመሚት፡ የሸረሪት፡ የቍጭ፡ የንብ፡ የተርብ ዕጭ፡ ዕንቍላል፡ የጡንቻ፡ የባት፡ ፈርስ፡ አስኳል (ዕጢ) (የተለያዩ ፍጥረታት እንቁላሎች ወይም የሰውነት እብጠት)

ዕንቍጣጣሽ: እንግጫ፡ ነቈጠ (የአንድ ጨዋታ ወይም ተግባር ስም)

ዕንቂያ (ዕንቂት) (ኅንቀት): በእጅ፡ በሸምቀቆ ማነቅ፡ መታነቅ፡ ድንገተኛ ሞት፡ ታንቆ ሲል ብሎ (የማነቅ ተግባር ወይም ውጤት)

ዕንቈ ብርሃን: የብርሃን ዕንቍ (ብሩህ ዕንቍ)

ዕንቅ (ሕኑቅ): የታነቀ፡ ዕፍን።

ዕንቅ አደረገ: ዐነቀ።

ዕንቅርታም (ሞች): ዕንቅርት የወጣበት፡ ያለበት፡ ባለዕንቅርት ሰው፡ ወፍ (በዕንቅርት የተጠቃ)

ዕንቅርት: በሰው ዐንገት ላይ ያለ ዕብጠት፡ በውሃ ምክንያት የሚመጣ፡ ድምፅን የሚዘጋ፡ ትንፋሽን የሚከለክል (በፍራንክ በሽታ ምክንያት የሚመጣ የአንገት እብጠት)

ዕንቅርት: በቈላ ይይዛል፡ ደጋ ሲወጣ ይጠፋል፡ ይሽሻል (የበሽታው ባህሪ)

ዕንቅፋታም: ዕንቅፋት የሚያጠቃው፡ ሁል ጊዜ የሚመታው ሰው፡ ዕንቅፋት ያለበት ስፍራ (መሰናክል የበዛበት)

ዕንቅፋት (ቶች) (ዕቅፍት): በመንገድ ላይ ያለ ደንጊያ፡ ወይም ሌላ ነገር፡ ጕልጥምት፡ የእግር መሰናክል (ማሰናከያ ነገር)

እንቅፋት: መሰናክል (ዐነቀፈ)

ዕንቅፋትነት: ዕንቅፋት መኾን፡ መሰናክልነት።

ዕንቆቅልሽ: የምሳሌ ጥያቄ፡ እንቆቅልሽ።

ዕንቆቆ: ዛፍ፡ እንቆቆ (የዛፍ ዓይነት ወይም ስም)

ዕንባቦ (ሕንባብ): በ፲፰፻፸፬ .. ዐጤ ምኒልክና ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት የተዋጉበት አገር፡ በወለጋ ክፍል፡ በጉድሩ ያለ።

ዕንብሩን ሳተ: ጠገበ፡ ከልክ ዐለፈ፡ ይይዘውን ዐጣ።

ዕንብር (ሕንብርት): ልክ፡ መጠን፡ ውሳኔ።

ዕንብር ቢጣ: ብብት ጐን። ጡንቻንም ያስተረጕማል፡ የጐን ጓዳ ማለት ነው። "በንብር ቢጣው ያዘ" እንዲሉ።

ዕንብርቱን የተተኰሰ: የሰማውን የማይደብቅ ሰው (ምስጢር ጠባቂ ያልሆነ)

ዕንብርት (ቶች): በሆድ መካከል ያለ ገላ፡ የንዝርት ራስ መሳይ። ልጅ በናቱ ማሕፀን ሳለ ዕንብርቱ በዕትብት ከናቱ ሆድ ስለ ተያያዘ ምግብን ሁሉ በዚያው ያገኛል።

ዕንብርት የለሽ: ሆዳም፡ በልቶ በቶሎ የማይጠግብ፡ የጋማ ከብት።

ዕንኩ: ተቀበሉ፡ ውሰዱ (የብዙ ቁጥር ትዕዛዝ)

ዕንካ ስላንቲያሽ በምንንቲያኸ፣ በወንፊት ምን አለኸ፣ በወንፊት ከልጆቹ ኹሉ አንተ ነኸ ምድር ፊት እንዲል እረኛ (ዕንካ ስላንቲያ): ጭቅጭቅ፣ ንዝንዝ፣ እሽኰለሌ።

ዕንካ ስላንቲያኸ: የባለጌ ጥያቄና የስድብ ጨዋታ፡ እሽኮለሌ። "ዕንካ ስላንቲያኸ""በምን እንቲያኸ" እንዲል እረኛ። "ስላንቲያን" እይ።

ዕንካ በንካ: ሰጥቶ መቀበል፡ ማድፋፋት፡ አለማበርከት (ትንሽ ነገር በመስጠትና በመቀበል መደፋፋት)

ዕንካ አለ (ሐነከ): እጅ በጅ ሰጠ፡ አቀበለ (አሳልፎ ሰጠ)

እንካ: ተቀበል (ዕንካ)

ዕንካ: ትእዛዝ፡ አንቀጽ፡ "ያዝ""ተቀበል""ውሰድ" (የአንድን ነገር መውሰድ ወይም መቀበል የሚያመለክት)

ዕንካችኹ (ሕንክሙ): እናንተ ተቀበሉ፡ ውሰዱ (ለብዙ ሰዎች ትዕዛዝ)

ዕንክ (ሕንክ): ተሰቅጠጥ፡ ተመለስ፡ ወደ ኋላ በል (እንዳትነካ ወይም እንዳትቀርብ ለማለት) "በሬን ተው፡ ዕንክ" እንዲል ገበሬ።

ዕንክስ ዕንክስ አለ: እንክል እንክል አለ፡ ዥብኛ ኼደ (በአንካሳ መንገድ መሄድ)

ዕንክስ: ዝኒ ከማሁ ለዐንከስ (እንደ ዐንከስ)

ዕንኳ: ንኡስ አገባብ (ሰዋሰዋዊ ቃል)

ዕንኾ: ዝኒ ከማሁ (እንደ ዕንኩ)

ዕንዝዝ: በክንፍ ሲኼድ ዕዝ ጥዝ የሚል፡ ሦስት ዐይነት ጥንዝዛ ማር የሚሠራ (ንብ ወይም ዝንብ ዓይነት)

ዕንዝዝ: አበት፡ አድበልባይ፡ ትልቅና ትንሽ፡ ኹለተኛ ስሙ ሥሥት ነው።

ዕንጐቻ: ታናሽ እንጀራ፡ ስንዝር የምታክል፡ ወይም የምታንስ (ኤር፯፡ ፲፰)

ዕንጐችት (ዕንጐት): የአረግ ስም፡ ቅጠሉ ከማነሱ በቀር እንደ ዕንጐቻ ክብነት ያለው።

ዕንጣ: ሕንጻ፡ ያናጢ ሥራ፡ ቅርጽ፡ ፍልፍል፡ በሳንቃ የተሠራ ቤት። "ዕንጣ" የሚል ባላገር ነው፡ በቤተ ክህነትና በከተማ ግን "ሕንጻ" ይባላል።

ዕንጥስ ቢሉ ቅንጥስ: በጥቂት ነገር የሚጠፋ ትዳር፡ ሥር አልባ (ያልጸና ግንኙነት)

ዕንጥስ አለ: ዐነጠሰ።

ዕንጥስታ (ዕጠስ): ማንጠስ፡ የጕንፋን፡ የሳል ዋዜማ (ኢዮ፵፩፡ ፲) (የማስነጠስ ድምፅ ወይም ምልክት)

ዕንጦ: ቀሠብ፡ ውስጠ ክፍት ነገር፡ እንደ ቀረሻሽንቦና እንደ ውዥሞ ያለ (ቧንቧ መሰል ነገር)

ዕንጦ: ኹለተኛ ጕረሮ፡ የምንዣኸ መውጫ፡ ምንዣኹም ዕንጦ ይባላል።

ዕንጨት: እርጥብና ደረቅ ዛፍ፡ ተቈርጦ ተፈልጦ ለቤት መሥሪያና ማገዶ የሚሆን፡ ትንሹም ትልቁም (እንጨት) (ተረት): "ከልጅ አትወት፡ ያወጣኻል በእንጨት" (ልጅን እንዳታላግጥ፡ ሊጎዳህ ይችላል) "በሰው ቍስል ዕንጨት ስደድበት" (አንድ ሰው ሲጎዳበት ሁኔታውን የበለጠ አክፋበት ማለት ነው)

ዕንፉጭ: ነፋስና ብርድ የመታው ቀላል ፍሬ እህል፡ መንሽ በተባለ ጊዜ ከገለባ ጋራ የሚኼድ (ለነፋስ የተጋለጠ ቀላል ፍሬ)

ዕኚ: ወንፈል ዐኘከ።

ዕኛኪ: ታኝኮ የተጣለ፡ ብላቶ፡ ምጣጭ (የታኘከና የተተፋ ነገር)

ዕኝ አለ: ድዱን ገለጠ፡ አሰጣ፡ ጥርሱን አሳየ (ሰውየው፡ ዝንጀሮው) (ጥርሱን ማሳየት)

ዕኝ: ወንፈል፡ የጕልበት ብድር። "ዕኝ ተባብሮ መብላትን፡ የመንጋጋን ምስጢር ያሳያል" (የምሳሌያዊ አነጋገር ፍቺ)

ዕኝኝ ብላ: ከነሐሴ ፳፰ ቀን እስከ ባለማቋረጥ የሚዘንብ ዝናብ፡ ወሊስ (የአንድ የዝናብ ወቅት ስያሜ)

ዕኝኝ አለ: ጨቀጨቀ፡ ነዘነዘ፡ ነገር አበዛ (በማስቸገር ወይም በድምፅ ማበሳጨት)

ዕኝኝ: ጭቅጭቅ፡ ንዝንዝ (ድምፅ ወይም ግጭት)

ዕኝክ (ሕኑክ): የታኘከ፡ የተበላ፡ የተመሰኳ፡ የተመነዠኸ፡ ምንዥኸ (የታኘከ ነገር)

ዕኝክ አደረገ: ዐኘከ።

ዕከማ: የማከም፡ የማስታመም ሥራ፡ ማዳን።

ዕከካም: ዕከክ ያለበት፣ ባለዕከክ፡ ዕከክ የያዘው፣ የወረሰው።

ዕከክ: ፎከት፣ ደረመን፣ ፈረሳቤት፣ የጥፍር ንኪት (ዘዳ፳፰፡ ፳፯)

ዕክል: ዐዘን፣ ለቅሶ፣ ችግር። "እከሌን ዕክል ገባው (አገኘው)" እንዲሉ።

ዕክም አለ: ጸጥ አለ፡ ጨመተ፡ ረጋ (ከመታከም የተነሣ)

ዕክም: የታከመ፡ መድኃኒት የተደረገለት።

ዕክምና (ሕክምና): ሐኪምነት፡ ሐኪም መኾን።

ዕወቅ (ዑቅ): የቅርብ ወንድ፡ ትእዛዝ አንቀጽ፡ ተጠንቀቅ፡ ተጠበቅ።

ዕወቅልኝ: ባታውቅብኝ (ከሳሽና ተከሳሽ ለምስክር የሚያቀርቡት ጥያቄ)

ዕወጃ: ለፈፋ።

ዕውረ ልብ: አንዳች ዕውቀት የሌለው፡ ለጣዖት የሚሰግድ አረመኔ፡ ደንቈሮ፡ ኣላዋቂ፡ ልበ ዕውር።

ዕውሪት (ዕውርት): የታወረች።

ዕውር (ሮች) (ዕዉር): የታወረ፡ ዐይን የሌለው፡ በሰው ትከሻ እየተመራ የሚኼድ። (ተረት): "ዕውር ሲወበራ ከመሪው ይጣላ። ዕውር ያለበት ደብር፡ ዓሣ ያለበት ባሕር ሳይበጠበጥ አያድር። "

ዕውር መሪ: ዕውርን በትከሻው የሚመራ።

ዕውር መሪ: ዕውርን የሚመራ።

ዕውር ዕከክ: እዥና መግል የሌለው።

ዕውር የዘራው: አንድ ላይ ችፍግ ብሎ የበቀለ ብቋያ።

ዕውር: የጐለደፈ፡ ጐልዳፋ፡ ብርሃናዊ፡ ጥፍሩን ያጣ።

ዕውርነት: ዕውር መኾን (ዘካ፲፪፡ ፬)

ዕውሮች (ዕዉራን) (ዕዉራት): ዐይኖቻቸው የታወሩ፡ የተሰወሩ ወንዶችና ሴቶች።

ዕውቀት (ቶች): ዘዴ፡ ፈሊጥ፡ ብልኀት፡ ፍልስፍና፡ ማወቅ፡ ማስተዋል። "ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ፡ ዕውቀትም ይበዛል" (ዳን፲፪፡ ፬) "ዕውቀትና ፍጥረት አንድ ቀን ነው" [ይባላል] "ካይን ማየት የልብ ዕውቀት" እንዲሉ። (በውቀት ባለውቀት): እያወቀ፡ ሳያውቅ።

ዕውቀትና ፍጥረት አንድ ቀን ነው እንዲሉ።

ዕውቂያ: ልምድ፡ ማወቅ (መሳ፲፰፡ ፳፰)

ዕውቅ (ዕዉቅ): የታወቀ፡ የተለመደ። (በውቅ የተሠራ): ለዘመድ፣ ለወዳጅ ጥሩና ንጹሕ ኹኖ የተበጀ ዕቃ።

ዕዛብ (ሕዛብ): የጠፍር ቋድ፡ የልጓም መያዣ፡ መግቻ፡ አራት ማእዘን። "ሲበዛ ዕዛቦች ይላል" [ይባላል]

ዕዝ (ሕንዝዝ): የጥንዝዛ ድምፅ።

ዕዝ አለ: ጥዝ አለ፡ ጮኸ (ንቡ)፡ ጥንዝዛው፡ ተርቡ፡ ዝንቡ።

ዕዝል (ሕዙል): የታዘለ፡ በዠርባ ላይ ያለ ልጅ፡ ወይም በሽተኛ።

ዕዝል (ሕዝል): የዜማ ስም፡ የሐዘን ዜማ፡ በመቤታችን ዠርባ የታዘለ የጌታችን ምሳሌ። "ይኸውም ከአይሁድ የሚያሳዝን መከራ መቀበሉንና መሰቀሉን ያሳያል" [ይባላል] "ወርድ ንባብም የዕዝል ተከታይ ስለ ኾነ ዜማ ሐዘን ይባላል" [ይባላል]

ዕዝል: በጽፈት ዐናት የተደረበ ፊደል ጭረት። "የውጣ ዕዝል ቅጽል የላትም" [ይባላል]

ዕዝናት: ለሰው ዐዝኖ ተቈርቍሮ የሚመክሩት ምክር፡ ተግሣጽ።

ዕዝን: የታዘነ ዐዘን።

ዕየማ: ዐረሳ፡ ቅብቀባ።

ዕየራ: ቅልቀላ፡ ድብለቃ።

ዕይም: የታየመ፡ የለሰለሰ፡ ቅብቅብ።

ዕይራት: ቅልቅልነት፡ ድብልቅነት።

ዕይር: የታየረ ቀለም፡ ጠገራ፡ ባሩድ፡ አቦልሴ፡ ውጥንቅጥ (ሔኖ፲፬፡ ፫) ትርጓሜ።

ዕደላ: ማደል።

ዕደሳ (ሕዳሴ): ጥገና፡ የማደስ ሥራ።

ዕደና: ፍለጋ፡ ሽመቃ።

ዕዳ (ዎች): በቅጣትና በብድር፣ በካሳ ምክንያት ለመንግሥት፣ ላበዳሪ፣ ለተበደለ የሚከፈል ገንዘብ። "ዕዳና ደም፡ ዱብ ዕዳ" እንዲሉ። (ተረት): "ያባት ዕዳ ለልጅ፡ ያፍንጫ ዕዳ ለእጅ። "

ዕዳ ሰርጉ: ተበድሮ የሚደሰት።

ዕዳ በዕዳ ኾነ: በዕዳ ላይ ዕዳ መጣ፡ ተጨመረ።

ዕዳ በደል: የበደል ዕዳ፡ ካሳ።

ዕዳ ተሜዳ: ያልታሰበ ዕዳ።

ዕዳ ኾነበት: መጣበት፡ ተደረገበት።

ዕዳ: በቁሙ ዐደየ።

ዕዳሪ አወጣ: ጠጋ፣ ፈለቀ።

ዕዳሪ አወጣ: ጨፈለቀ።

ዕዳሪ ወጣ: ወገቡን ሞከረ፡ ኰሳ። (ጥር) ዐደር (ኅዲር): ማደር። "ዋለን" እይ።

ዕዳሪ: ውጭ ሜዳ፡ አፍኣ።

ዕዳሪ: ያልታረሰ መሬት፡ ቀርጣ፡ ጥጋት።

ዕድለ ቢስ: ዕድለ መጥፎ።

ዕድለኛ: ዝኒ ከማሁ፡ ባለዕድል።

ዕድላም: የታደለ።

ዕድላት: የማደል፡ የመታደል ሥራ።

ዕድል የለሽ: ያልታደለ።

ዕድል ፈንታ: የድርሻ ዕድል። "ዕድል ፈንታ ጥዋ ተርታ" እንዲሉ።

ዕድል: ስጦታ፡ ዕጣ፡ ክፍል፡ መክፈልት።

ዕድመኛ (ኞች): ዕድም ያለው፡ ባለ ዕድም፡ እሴት ሙሽራ አባት ቤት የሚመጣ።

ዕድሜ: ሰው ተወልዶ እስኪሞት ድረስ ያለው ዘመን፡ ዓመት፡ ለአራዊትና ለአን ስላት፣ ለአዕዋፍ፣ ለዕፀዋት ሳይቀር ይነገራል። የዕድሜ ትርጓሜ በግእዝ "ቀጠሮ" ይባላል። "ዕድሜ ለንስሓ ዘመን ለፍሥሓ" "ዕድሜና ጨርቅ እንደ ምንም ያልቅ" እንዲሉ።

ዕድሜያም (ሞች): ባለብዙ ዕድሜ፡ ብዙ ዘመን የኖረ (ማቱሳላ፣ ወይም ሌላ፡ ሔኖክና ኤልያስ፣ ዕዝራ ሱቱኤል)

ዕድም (ቅጽል): የታደመ፡ የተቀጠረ (የተቃጠረ)

ዕድም (ጥሬ ስም): ጥሪ።

ዕድሞ: ያፈር ቤት (እድሞ)

ዕድሞች: የተቃጠሩ (ምሳ፱፡ ፲፡ ፲፰)

ዕድር ገባ: ከዕድር ስለ ቀረ መቀጮ ከፈለ።

ዕድር: ስብሰባ፡ ጽኑ ደንብ። (ተረት): "ያገር ዕድር ለንጉሥ ያስቸግር። "

ዕድርተኛ (ኞች): ዕድር ያለው፡ ባለዕድር።

ዕድን: የታደነ፡ የተያዘ፡ የተወጋ፡ የተገደለ እንስሳ፡ ወይም ሥጋ።

ዕድያት (ትግ): የጥለት ስም፡ ብጫን መደብ አድርጎ ማንኛውንም ጥለት ያሳያል።

ዕድጋት (ኅድገት): በጥለትና በቍቲት መካከል የተጣለ ማግ።

ዕድጋት: ቈረጣ፡ ምለሳ።

ዕድግ: የታደገ፡ የተመለሰ፡ ምልስ፡ የተገዛ (ግዝ)

ዕጀላ: ሽፈና፡ ጥቅለላ።

ዕጅላት: ሽፍናት፡ ጥቅልላት።

ዕጅል: የታጀለ፡ የተሸፈነ፡ ስልቻ፡ ቅሪላ፡ ቈርበት፡ ደበሎ (እጅ፣ እግር)

ዕጅር (ዝኁር): የታጀረ፡ ዕቡይ፡ ኵሩ፡ ተከባሪ፡ ተጓዳጅ፡ ኵራተኛ፡ ትቢተኛ፡ ትምክሕተኛ።

ዕጅብ: የታጀበ፡ የተከበበ፡ የታከበ፡ ክምቹ፡ ዕጭቅ።

ዕጅብኝ: ረፋድ ከብት የሚመሰግበት።

ዕገውጡ (ውፁአ ሕግ): ሕገ ወጥ፡ መረን።

ዕገዛ: ዕግዣ፡ የማገዝ፡ የመርዳት ሥራ።

ዕጉም: (ጐዣም) የሙጥኝ።

ዕጉሥ: ታጋሽ (ግእዝ)

ዕግ: ሕግ፡ ደንብ፡ ውሳኔ።

ዕግል: የቂጥኝ ምላሽ።

ዕግል: ያትክልት እንቦቀቅላ፡ የተጫረ፡ የተኰተኰተ።

ዕግም: የታለመ ደም፡ የወጣው።

ዕግት (ዕጉት): የታገተ፡ የተከበበ፡ የተያዘ፡ የተወሰደ።

ዕጐቻ (ዘዳ፳፬፡ ፯፡ ፲፡ ፲፩፡ ኢዮ፳፬፡ ፫፡ ዓሞ፪፡ ፰)

ዕጎቻ: የዋስ ዕቃ፡ ገንዘብ፡ ከብት።

ዕጠ መሰውር (ዕፅ መሰውር): አስማተኛን፡ ከአጋንንት ጋራ አንድነት ያደረገውን ሰው ከመታየት የሚሰውር ዕጥ። "ባላገሮችም ጋኔን አንዳንድ ጊዜ በምትሀት ገዝፎ ሲታይ 'ዕጡን የጣለ ሰይጣን' ይሉታል፡ ዕጥ የተባለም ርቀት ነው። "

ዕጠ ፋርስ (ዕፀ ፋርስ): ከፋርስ አገር የመጣ ዕንጨት። "ተማሮች ቅጠሉን አፍልተው ከጤፍ እንጀራ ጋራ ፈትፍተው በቀመሱት ጊዜ አእምሯቸውን ለውጦ ማደሪያቸውን ያናግራል፡ ማብረሻውም የኑግ ልጥልጥ ወይም በሶ ነው። "

ዕጠ ፋርስ: የፍሬው ልብስ እሾኽ ያለበት፡ ተክልነት የሌለው የዱር ዕንጨት፡ "ቅጠሉን በጎች ቢበሉት ራሳቸውን ያዞራል፡ ሰውም ቢቀምሰው ያሳብዳል" "ባላገሮችም ዐጤ ፋሪስ ይሉታል። " "ይህ ኹለት ዐይነት ዕንጨት ባገዳ፡ በቅጠል፡ በፍሬ ልዩ ሲኾን ልብን በመንሣት ስለ ተባበረ ባንድ ስም ተጠራ። በካህናት ዘንድ ግን ፪ኛው ካ፩ኛው ተለይቶ 'አስተናግር' ይባላል፡ 'ነገረን' እይ። "

ዕጡ ዱብ አለ: ደነገጠ፡ ክው አለ፡ ውቃቢ ራቀው።

ዕጡብ (ዐጸበ ዕጹብ): ድንቅ፡ ግሩም፡ ልዩ።

ዕጡብ ድንቅ ቢል: የድንቅ ድንቅ ማለትን ያሳያል።

ዕጢ (ኀጠጠ ኅጢ): በገላ ውስጥ ያለ ዕትራት፡ ቋር፡ የሥጋ ቅንጣት፡ ጓጓላ።

ዕጣ (ዐፀወ ዕፃ): ዐጪርና ቀጪን ዕንጨት፡ ከመካከለኛ ጣት የሚበልጥ፡ በክፍያ ጊዜ በእያንዳንዱ ሰው ዕድልና ድርሻ ላይ የሚወድቅ። "ሲበዛ ዕጣዎች ይላል" በእስራኤልም መንግሥት ክፉ የሠራ ሰው ዕጣ ይወድቅበት ነበር (ኢያ፯፡ ፲፰፡ ፩ሳሙ፡ ፲፬፡ ፵፪፡ ዮና፩፡ ፯) "ዕጣ በድግጣ" እንዲሉ።

ዕጣ ሑዳድ: ላንድ ገባር በዕጣ የተሰጠ የሑዳድ ድርሻ።

ዕጣ ሰበረ: ዕጣ አዘጋጀ፡ ምልክት አደረገበት።

ዕጣ ተጣጣለ: ዕጣ ዕጣ "ለዚህ ጌታ ይውጣ" ተባባለ (ዐብድ፩፡ ፲፩፡ ማቴ፳፯፡ ፴፭)

ዕጣ ወጣ: ድርሻው ለባለዕድሉ ተሰጠ።

ዕጣ ወጣለት: አንድ ነገር አገኘ፡ ተሾመ፡ ተሸለመ።

ዕጣ ወጣበት: ለቅጣት፡ ለሞት ተገባ።

ዕጣ ጣለ: በማንኛውም ዕቃና በቅርግን ሥጋ ላይ አስቀመጠ።

ዕጣ: ዕጣ ያረፈበት፡ የወደቀበት ፈንታ።

ዕጣቢ: የልብስ፡ የዕቃ እድፍ። "ተስዐቱ ቅዱሳን ከደብረ ሲና የመጡ የኹለት መነኮሳት እግር ዕጣቢ ጠጡ፡ መነኮሳቱም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ናቸው" ይባላል።

ዕጣነ ሞገር: የቅኔ ስም፡ በቅዳሴ መጨረሻ የሚቀኙት ፱ኛ ቅኔ፡ ኹለት ዐይነት ዜማ (ግእዝና ዕዝል) ያለው። "ወገረ" ብለኸ "ሞገርን" ተመልከት።

ዕጣን (ሕፃን): በቁሙ፡ ዐራስ፡ ጨቅላ፡ ርጥብ፡ ለጋ፡ ትንሽ ልጅ፡ ማሞ፡ ማሚት። (በግእዝ ሕፃንና ዕጣን ልዩዎች ሲኾኑ ባማርኛ ይገጥማሉ።) "ዝባድ ለመነገድ ከመውረድ መተማ ዕጣኑ ይሻላል፡ ለለት እራትማ (በክፉ ቀን ልጇን የበላች ሴት) " "ምን ያሉ ቄስ ናቸው የማይጠብቁ ዕቃ፡ እቤተ ክርስቲያን ጓሮ ዕጣኒቱ ወድቃ። " (ዳግመኛም ባላገሮች፡ ሕፃን ሕፃናት በማለት ፈንታ ጣናት ጣናቶች ይላሉ።)

ዕጣን (ኖች): ሽታው የሚጣፍጥ የዛፍ ሙጫ፡ "ዕንጨቱ በውጋዴና በመርሐ ቤቴ በረሓ ይገኛል"

ዕጥ (ዕፅ): ዕንጨት፡ ዛፍ፡ ትልቁም ትንሹም፡ ርጥቡም ደረቁም።

ዕጥ የኾነ ስምጥ: ድንገት የጠፋ ነገር የደረሰበት ባይታወቅ፡ "ዕጥ የኾነ ስምጥ" ይባላል። "ዕጥ ቅለትን (ቅጠልነትን)፡ ስምጥ ክብደትን (ደንጊያነትን) ያሳያል፡ 'ነፋስ ይውሰደው፡ ውሃ ይብላው' አልታወቀም ማለት ነው"

ዕጥ: የክታብ ውስጥ ታናሽ ዕንጨት።

ዕጥር (ኅጥር): የሽቱ ስም፣ ማንኛውም ሽቱ። በአረብኛ "ዐጥር" ይባላል። "ኅጥርን" ተመልከት።

ዕጥር (ሕጸር): የታጠረ፡ የተከበበ።

ዕጥር ምጥን አለ: ረዥምም ሆነ አጭር ሳይሆን መካከለኛ ወይም ድልድል ሆነ ማለት ነው።

ዕጥር አለ: ዐጠረ።

ዕጥር: ማጠር።

ዕጥበት: ዐጠባ፡ መታጠብ።

ዕጥቤ: ዐጠብ።

ዕጥብ (ኅፁብ): የታጠበ፡ ጥሩ፡ ጸዐዳ።

ዕጥብ ያለ: ዋና ሌባ። "ልብስ ሲታጠብ ከእድፍ እንዲለይ፡ ከጨዋነትና ሠርቶ ከመብላት የራቀ" ማለት ነው።

ዕጥብጣቢ: የብዙ ሸማና ዕቃ፡ የዕጣቢ።

ዕጥጥ ሙጥጥ አለ: ጕድል፡ ጥርግ አለ።

ዕጥጥ: ዝኒ ከማሁ [ያው ማለት ነው]

ዕጥፋት (ቶች): የማጠፍ፡ የመታጠፍ አኳዃን፡ ቅልብሳት፡ ቅንፋት፡ የልብስ፡ የቈዳ ስብራት።

ዕጥፍ (ዕጹፍ): የታጠፈ፡ ጥንድ፡ ነጠላ ያይዶለ ልብስ፡ ወይም ሌላ ነገር። (ካህናት ግን "ዕጽፍ" ይላሉ)

ዕጥፍ አለ: ታጠፈ።

ዕጥፍ አደረገ: ዐጠፈ።

ዕጥፍ ዘርጋ አለ: እየታጠፈ ተዘረጋ (ጣቱ፡ የጐመኑ ትል)

ዕጥፍ ድርብ (ምክዕቢት): ኹለት ዕጥፍ፡ አራት እጅ።

ዕጥፍጥፍ አለ: ተጣጠፈ።

ዕጥፍጥፍ: የተጣጠፈ።

ዕጦተኛ: ችግረኛ።

ዕጦት (ኅጥአት): ማጣት፡ ችግር፡ ድኸነት።

ዕጨ: የዕጨጌ ከፊል (ለምሳሌ) "ዕጨ ዮሐንስ""ዕጨ ዕንባቆም" እንዲሉ።

ዕጨጌ (ዎች) (ሕፁየ ): የምድር ዕጮኛ፡ ሊቀ ካህናት (ጳጳሳት)፡ መንፈሳዊ ሹም፡ ባለሥልጣን፡ የመንግሥት የደብረ ሊባኖስ ኣበ ምኔት (የገዳም ኣባት)፡ በነብሪድ ፈንታ የገባ። "ይህ ስም የተዠመረው ባጤ ይኩኖ አምላክ ዘመን ነው፡ በግእዝ 'ሐፄጌ' ይባላል። አላዋቂዎች ግን 'ጮጌ' ከማለት ከወላምኛ የመጣ ነው ይላሉ። " "ጌን" "ንቡረ እድን" ተመልከት።

ዕጨጌ: አቡን፡ ጳጳስ። (ግጥም): "መኳንንቱ ሠለጠኑ፡ የወጌን አገር ለመኑ። እኔ የምፈራው ይህነን፡ ካቡን በላይ መኾን። "

ዕጨጌ: የምድር ዕጮኛ፡ ዐጪ።

ዕጨጌነት (ግነት): ዕጨጌ መኾን፡ መንፈሳዊና ሥጋዊ ሹመት ደርቦ መያዝ።

ዕጨጌነት ከሚስት: "ዐጤ ይኩኖ አምላክን ያነገሡ ፪ኛው ተክለ ሃይማኖት ባለሕግ ነበሩና ሚስታቸው ከሞተች በኋላ በደብረ ሊባኖስ መንኵሰው ዕጨጌ ስለ ኾኑ፡ 'አቦ ብላት ዕጩጌነት ከሚስት' ይሏቸዋል ( ) "

ዕጩ (ሕፁይ): የታጩ፡ ለቁም ነገር የታሰበ፡ "ሲበዛ ዕጩዎች ያሠኛል"

ዕጩ (ዕፄሁ): ዕጭ፡ የርሱ ዕጭ።

ዕጩ: ትሉ፡ ዕጭ።

ዕጭ (ጮች) (ዐፀየ፡ ተላ፡ ዕፄ፡ ትል): የንብና የተርብ፡ የጥንዝዛ ዕንቍላል ቅርጽ አበጅቶ እስኪንቀሳቀስና ክንፍ እስኪያወጣ ድረስ ዕጭ ይባላል፡ ትል ማለት ነው።

ዕጭ አዋለ: ሠራ፡ አበጀ፡ አተላ።

ዕጭ ጐመጭ: የጐመጭ ዕጭ፡ ወይም ዕጭ ያለበት ጐመጭ። "ጐመጭን" ተመልከት።

ዕጭቅ: የታጨቀ፡ የተከተተ፡ ዕጅብ (ቅጠል፡ ወይም ሌላ)

ዕጭዳት: የማጨድ፡ የመታጨድ ኹኔታ፡ የማጭድ ቅሬታ።

ዕጭድ (ዕጹድ): የታጨደ፡ የተቈረጠ፡ ቍርጥ። "ጭድን" አስተውል።

ዕጭድ አደረገ: ቍርጥ ቡጭቅ አደረገ።

ዕጮኛ (ኞች): ሴት ያጨ ጕልማሳ፡ ለባል የታጨች ልጃገረድ (ማቴ፩፡ ፲፮፡ ፲፬)

ዕፀ ሕይወት: በገነት የሚገኝ። የሕይወት ዛፍ፡ የሥጋ ወደሙ ምሳሌ። "ሲሎንዲን" እይ (የሕይወት ዛፍ)

ዕፀ ልቡና: ዕውቀትን፡ ማስተዋልን የሚገልጥ (የዕውቀት መገኛ)

ዕፀ መስቀል: የመስቀል ዕንጨት (መስቀል የተሰራበት እንጨት)

ዕፀ መድኀኒት: ዝኒ ከማሁ ለዕፀ ሕይወት (እንደ ዕፀ ሕይወት)

ዕፀ ሞት: መርዝነት ያለው ዛፍ፡ ሰውን የሚገድል (መርዛማ ዛፍ)

ዕፀ ሳቤቅ: ቧሔ ዐረግ (የዕፅዋት ዓይነት)

ዕፀ በለስ: የበለስ ዕንጨት።

ዕፀ ተከዚ: አሓያ፡ ወይም ሌላ (የዕፅዋት ዓይነት)

ዕፀ አእምሮ: በለሶን (የጥበብ ዛፍ)

ዕፀ ጥበብ: የገነት በለስ።

ዕፀ ፋርስ: ቅጠል፡ ዕጥ (የፋርስ ቅጠል)

ዕጹብ: ቃለ አንክሮ (የአድናቆት ቃል)

ዕጹብ: ድንቅ፡ ጭንቅ፡ ጥብ (ድንቅ የሆነ ነገር)

ዕፅ ከንቱ: ጧት ይበቅልና ማታ የሚደርቅ (መዝ፮፡ ፮) (የማይጸና ነገር)

ዕፅ: ዕንጨት፡ ዛፍ፡ ርጥቡም ደረቁም (ዛፍ፡ ዕፅዋት)

ዕጽፍ: የታጠፈ፡ ጥንድ፡ ዕጥፍ (የታጠፈ ነገር፡ እጥፍ ድርብ)

ዕፍረተ ሥጋ (ኀፍረተ ሥጋ): የወንድና የሴት ብልት፡ ሲያዩት የሚያሳፍር (፩ቆሮ ፲፪፡ ፳፫) (የብልት ክፍሎች)

ዕፍረተ ቅል: የፍርሀት፡ የማፈር ቅል፡ የምሳሌ አነጋገር። ቅል ሠም፡ ዕፍረት ወርቅ ነው (ምሳሌያዊ አነጋገር) "እከሌ ዕፍረተ ቅሉን ሰብሯል" (ይሉኝ አይል ኾኗል) እንዲሉ። ዳግመኛም "ቅል ራስ""ዕፍረት ይሉኝታ" ይኾናል (እፍረት ወይም ይሉኝታ)

ዕፍረተ ቢስ: ሰውን የማያፍር፡ የዶሮ ዐይን የበላ (የማያፍር ወይም እፍረት የሌለው)

ዕፍረቱን ጣለ: ገለጠ፡ ተጋለጠ (እፍረቱን አጣ)

ዕፍረት (ኀፍረት): ማፈር፡ ውርደት፡ ፍራት፡ ገመና፡ ነውር (መዝ፻፴፪፡ ፲፰) (ውርደት ወይም ነውር)

ዕፍረት የለሽ: ግንባረ ደረቅ (እፍረት የሌለው)

ዕፍረት: አባለ ዘር፡ ሕልጽ (ዘሌ፲፰፡ ፮፡ ፲፱) (የብልት ክፍል)

ዕፍረት: ግእዝኛ ነው።

ዕፍኝ (ኞች) (ሕፍን): ኹለት ውስጥ እጅ ጐን ለጐን ባንድነት ሲገጥም ዕፍኝ ይባላል (በሁለት እጅ የሚዘገን ነገር) "በዱር ያለ ሰው በዕፍኙ ውሃ ይጠጣል" (የእጅ ውሃ) "ለዶሮ እህል በዕፍኙ ይሰጣል" (በእፍኝ መለካት) "ጥርኝን" ተመልከት።

ዕፍኝ: ጥርኝ፡ ፩ ድብልዝኝ (የመለኪያ ክፍል)

ዕፍኝ: በዕፍኝ የተያዘ፡ የተለካ። "አንድ ዕፍኝ እህል" እንዲሉ።

: ስመ አምላክ፡ ደኃራዊ፡ ኋለኛ፡ መጨረሻ። "አልፋን" ተመልከት፡ አለፈ።


No comments:

Post a Comment

ሽፋን

  ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ