Friday, June 6, 2025

                                 

: የጠ ዲቃላ (የጸፀ ወራሽ ወይም ተለዋዋጭ። (ማስረጃ) ጠመቀ ጨመቀ ጸቈነ ጨቈነ ፀረረ ጠረረ ወረረ ፀርሰ ጨረሰ አንዳንድ ጊዜም የቀ ወራሽ ኹኖ ይገኛል ቂርቆስ ጨርቆስ ቃቂል ቃጭል እንቃቅላ እንጭላ)

፡ የቸ ተወራራሽ ("ችግኝ ጭጕኝ

፡ የጀ ተለዋጭ (ጀጐለ ጐለ

ጨሃ፡ ዳባ ሳም፡ ትክክል ስፍር፡ ዕልፍ ትርፍ የሌለው፡ በትግሪኛ "ደፍደፍ" ይባላል።

ጨለቀ(ትግ፡ ጨለቀ፡ ዐነጐተ እንደ ዕንጐቻ ያለ የተልባን ልጥልጥ ዐዥ፡ በጠበጠ፡ ከማር ጋራ በውሃ መታ። በግእዝ ሥሩ ጠለቀ ነው። ደረጠን አስተውል።

ጨለቅለቃ፡ የተኛ ውሃ፡ የሚያንጸበርቅ ኩሬ፡ ጭቃማ።

ጨለውታ(ትግ)፡ ምች፡ ግርፋት፡ ገረፍታ፡ ወረርሽኝ በሽታ። ሥሩ በግእዝ እለወ ነው።

ጨለደ(ትግ፡ ጫለደ)፡ በጉች ወጣ፡ አቀጠለ፡ ኣፈጠፈጠ፡ ለጠፈ፡ ብዙ ወለደ፡ ያገዳ እኸል።

ጨለገ(ትግ፡ ጸለገ)፡ ሰቀለ፡ ሰቀጠጠ፡ ከለከለ፡ ወተትን፡ የላም ወሽ።

ጨለጠ(ጸለጠ፡ ሰለጠ)፡ ጨርሶ ጠጣ፡ አነቀረ (ዐብድ፩፡ ፲፮) (ተረት) "ጨልጠሽ ጋግሪ ካለ ፈጣሪ። "

ጨለፈ(ጠለፈ)፡ ጠለቀ፡ ቀዳ፡ አወጣ ወጥን።

ጨለፈ፡ ነጠቀ፡ ቀማ።

ጨላቂ፡ የጨለቀ፡ የሚወልቅ፡ ዐሺ፡ በጥባጭ።

ጨላቃ፡ ጨምጫማ፡ ድፍርስ ዐይን።

ጨላጭ(ጮች)፡ የጨለጠ፡ የሚጨልጥ፡ አንቃሪ።

ጨላፊ፡ የጨለፈ፡ የሚጨልፍ፡ ወጠ፡ ቀጂ።

ጨሌ የሣር ችግኝ፣ጨለጨለ።

ጨሌ የጌጥ ስም፣ ወለወለ።

ጨመለቀ)ተጨማለቀ፡ ተደፋጩ፡ ጭቃ ተቀባ፡ ተበከለ፡ ተኵለፈለፈ። ጨለቀን እይ፡ ሥሩ ርሱ ነው።

ጨመለቅጨምላቃ፡ የተጨማለቀ፡ ነገረ በክ፡ ችኮ።

ጨመረ(ፀመረ)፡ አገባ፡ ዶለ፡ ከተተ፡ አሰናዳ።

ጨመረ፡ ኣከለ፡ ደበለ፡ አንድ አደረገ።

ጨመቀ፡ ካይኑ እንባን አፈሰሰ።

ጨመተ(ትግ)፡ ደከረ፡ አዘገበ፡ አነጣጠረ፡ በርጋታ።

ጨመተ(ጸመወ)፡ አረመመ፡ ዝምተኛ ኾነ፡ ዝም፡ ዕክም አለ (ኢዮ፫፡ ፳፮)

ጨማመረ(ፀማመረ) ኣገባባ፡ አስነዳዳ።

ጨማመረ፡ አካከለ፡ በላይ፡ በላዬ።

ጨማሪ(ዎች)፡ የጨመረ፡ የሚጨምር፡ ከታች፡ አሰናጂ።

ጨማቂ (ቆች)፡ የጨመቀ፡ የሚጨምቅ፡ ጠምዛዥ፡ አጥሪ።

ጨምታራ፡ ኰምታራ፡ ጨምዳዳ።

ጨሰ (ጠይስ፡ ጤሰ): ተትጐለጐለ፡ ቡልቅ ቡልቅ እለ፡ በነነ፡ ተነነ፡ ታጠነ።

ጨረ (መጸረ): ጫረ፣ ቧጨረ፣ በቀላል ዐረሰ።

ጨረመመ (ጸረመ): ዘነበለ፡ እንቅልፍ የገረዘዘው ሰው መሰለ፡ ጠማማ ኾነ ቤቱ በክብደት ብዛት።

ጨረመም: ጨርማማ (ጸራሞ)፡ የተረመመ፡ ሊወድቅ የቀረበ። "ጸረመ፡ ጸራሞ፡ ጥንታዊ ዐማርኛ ነው። "

ጨረመተ: ጨመተረ፡ ጨመደደ።

ጨረመደ (ጨረመተ): ብዙ እንጀራ በላ። "ጨረገደን እይ"

ጨረሰ (ጠርሰ፡ ፀርሰ): ፈጀ፡ ገደለ፡ ፈጸመ፡ ከወነ፡ ደመደመ፡ አበቃ፡ አከተመ፡ በጥርስ ወይም በሌላ መሣሪያ።

ጨረረ (ጠረረ። ፀረረ): ነዛፈ፡ ነጠቀ፡ ላከ፡ ሰደደ ብርሃንን፡ ዘረጋ ጮራን።

ጨረረ፡ መታ፡ ከለከለ፡ ዕሽ አለ፡ አበረረ ዝንብን፡ ትንኝን።

ጨረረ፡ ነሰነሰ፡ ወዘወዘ ጭራን።

ጨረረ፡ ወጋ፡ አሳመመ ራስን፡ ዐይንን።

ጨረረ: መታ፡ ከለከለ፡ ዕሽ አለ፡ አበረረ ዝንብን፡ ትንኝን።

ጨረረ: ነሰነሰ፡ ወዘወዘ ጭራን።

ጨረረ: ወጋ፡ አሳመመ ራስን፡ ዐይንን።

ጨረር: ሰባት ያራባ ክፍል፡ አራባን እይ።

ጨረር: ክብ፡ የፀሓይ ሰሌዳ፡ ጧትና ማታ የሚታይ። "ጨረሯ ወጋችኝ እንዲል ባላገር"

ጨረቀ (ሠረቀ): ወጣ፡ ነጣ።

ጨረቀ (ጠሪቅ፡ ጠረቀ፡ ቀዘነ): ተከፈለ፡ ጠብ ጠብ አለ።

ጨረቀ (ጸረቀ): ዐለቀ፡ ሣሣ።

ጨረቂት (ጨረቃዊት): የማሽላ ስም፡ ነጭ ማሽላ። "፪ኛ ስማ ወገሬ ይባላል"

ጨረቃ (ሠርቅ): የሰማይ መብራት ስም፡ የፀሓይ ታናሽ ወንድም፡ ከፀሓይ የምትነሣው ብርሃኗ ከመላ በኋላ እያለቀ የሚኼድ፡ ጠፍ የሚኾን። "ጠፍ ጨረቃ፡ ለጋ ጨረቃ፡ ሙሉ ጨረቃ እንዲሉ"

ጨረቃ ምድር ያዘች: ማታ ሳትወጣ ጧት ወጣች፡ ታየች።

ጨረቃ ተወለደች: ብቅ አለች፡ በቀለች፡ ተገለጠች።

ጨረቃ፡ የሰማይ መብራት ስም፡ የፀሓይ ታናሽ ወንድም፡ ከፀሓይ የምትነሣው ብርሃኗ ከመላ በኋላ እያለቀ የሚኼድ፡ ጠፍ የሚኾን። "ጠፍ ጨረቃ፡ ለጋ ጨረቃ፡ ሙሉ ጨረቃ እንዲሉ"

ጨረቃ ዳቦ ጣይልኝ: የልጆች ጨዋታ።

ጨረቃ: ጨዋታ።

ጨረቋ (ትግ፡ ጨልቅዐ): ፍሬ ዝመረ፡ ጨርቋ ኾነ።

ጨረባ (ቦች): የወፍ ስም፡ ብዙ ኹኖ የሚታይ ወፍ፡ በቋል ጥሬ ፈጅ። "የጨረባ ተዝካር እንዲሉ"

ጨረተስለለ፡ ቀጠነ።

ጨረተተጨመረ፡ ታከለ፡ በዛ፡ ፈደፈደ፡ የዋጋ።

ጨረተ: ስለለ፡ ቀጠነ።

ጨረተ: ተበተነ፡ ባዘተ፡ አሸዋ፡ ጭራ መሰለ፡ ነጣ፡ ጭረት፡ ጭርት ኾነ።

ጨረተ: ተጨመረ፡ ታከለ፡ በዛ፡ ፈደፈደ፡ የዋጋ።

ጨረቻ (ኦሮ): ያሸዋ ስም፡ አሸዋ።

ጨረች: የሰው ስም። (ተረት): "ጭቅጭቅ ነው፡ አቶ ጨረች ገዝተኹ ልበሱ"

ጨረነቀ (ደረነቀ): አሳነሰ፡ ዐጨር አደረገ፡ ጨቈነ። "ይህ ሸክም ዐንገቴን ጨረነቀው"

ጨረንፌ: ከአስታ ጋራ የሚበቅል ዕንጨት።

ጨረገደ (ጠረገ፡ ረገደ): ባንድነት ዐጨደ፡ ቈረጠ ሣርን፡ ቅጠልን።

ጨረገደ: መታ፡ ደበደበ። "እከሌ እከሌን በዱላ ወረገደው"

ጨረገደ: የተጠቀለለ እንጀራን ባፉ ቈረሰ፡ ገመጠ፡ በላ።

ጨረገገ) (ዠረገገ): አንጨረገገ፡ ብዙ ፍሬ አፈራ፡ አንዠረገገ፡ አንጠለጠለ። "በተደራጊነትም ይፈታል"

ጨረጨረ) (ጨረረ): አንጨረጨረ፡ ያለሸክላ በፍም ላይ በጣም ቈላ፡ ጠበሰ። "በተገብሮነትም ይፈታል። "

ጨረጪሰ (ጨረሰ፡ ጠረሰ): አፈጀ፡ ጨርሶ አረጀ፡ ጥርሱ ረገፈ። "ጠረጠሰን እይ፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው"

ጨረፈ (ፀረፈ፡ ሰደበ): በቀላል መታ፡ ቈረጠ። "የፀረፈ ምስጢር ስድቡ እንዳይጐዳበትሩ አለመጕዳቱን ያሳያል"

ጨረፈፈ) (ጨፈረረ፡ ጨበረረ): አንጨረፈፈ፡ አንጨፈረረ፡ አሳደገ፡ አረዘመ፡ አቆሙ፡ አደረቀ፡ ጭራንፎ አስመሰለ ጠጕርን። "በተደራጊነትም ይፈታል" "(ጨረፈፈ) ለጠጕር ብቻ፡ (ጨፈረረ) ለጭራሮም ይነገራል። "

ጨረፈፍ: ጨርፋፋ።

ጨረፈፍ: ጨርፋፋ፡ ጨፈረር፡ ጨፍራራ፡ እንጭርፍ።

ጨረፍታ: ትክክል ያልኾነ የጐን ምት፡ ወይም የማየት እኩሌታ።

ጨራ: መጨር፣ ጭረት።

ጨራረሰ: ፈጻጸመ።

ጨራሽ (ሾች): የጨረሰ፡ የሚጨርስ፡ ፈጻሚ፡ ነገር ወራሽ እንዲሉ።

ጨራቃ: ሽንታም፡ ፈሪ።

ጨርማዳ: የተጨራመደ፡ ወጭማዳ። "ጨረመተን ተመልከት፡ ጸና ተ፡ ተወራራሾች ስለ ኾኑ ወረመተ በማለት ፈንታ ወረመደ ይላል"

ጨርሶ: ፈጽሞ፡ ደምድሞ።

ጨርቀ ለባሽ: ቍርጩ፡ መናጢ፡ ድኻ፡ ጨርቅ የሚለብስ (ማቴ፭፡ ፳፪)

ርቁ: ጨርቅ፡ የርሱ ወርቅ። የልብስ፡ የሸማ ዕላቂ (ሕዝ፲፫፡ ፳፡ ፳፩) የጨርቅ ጨርቅብዙ ዐይነት ጨርቅ፡ የዕላቂ ዕላቂ። "በዘመናችን ግን ከባሕር የመጣውን ዐዲስ ልብስና ሐር ኹሉ ወርቅ ይሉታል፡ ስሕተት ነው። የባሕር ጨርቅ እንዲሉ"

ጨርቃም: ባለወርቅ፡ ቅርንጥሳም፡ ዘባተሏም።

ጨርቃጨርቅ: የጨርቅ ጨርቅ፡ ብዙ ዐይነት ጨርቅ፡ የዕላቂ ዕላቂ። "በዘመናችን ግን ከባሕር የመጣውን ዐዲስ ልብስና ሐር ኹሉ ወርቅ ይሉታል፡ ስሕተት ነው። የባሕር ጨርቅ እንዲሉ"

ጨርቅ ኾነ: ለፋ፡ ለተተ፡ ለሰለሰ፡ የቈርበት የሰው ገላ።

ጨርቆሲ: ዝኒ ከማሁ፡ የኔ ጨርቆስ፡ ወይም ጨርቆሳዊ። "የወልደ ቂርቆስ ከፊል ነው። "

ጨርቆስ (ቂርቆስ): የሰው ስም፡ በግእዝ ቂርቆስ የተባለው በሕዝብ አነጋገር ጨርቆስ ይባላል።

ጨርቋ፡ (ትግ ጨልቅዐ)ፍሬ ዝመረ፡ ጨርቋ ኾነ።

ጨርቋ (ዕውቅ)እንጭጭ፡ ለጋ ፍሬ። "ጨርቅና ጨርቋ በአማርኛ ይተባበራሉ። " (ግጥም): "እንዲያ ስናከብራት እመቤት ብለን በጨርቋ ቀበሯት ምን ትዋብ ወሌን"

ጨርቋ በርበሬ: ቃሪያ ያልበሰለ።

ጨርቋ: የርሷ ጨርቅ። "ጨረቋ ብለኸ ጨርቋን አስተውል"

ጨርቋዎች: ለጋዎች፡ ቃሪያዎች።

ጨርናቂ: የጨረነቀ፡ የሚወረንት፡ ከባድ ነገር።

ጨርናቃ: የተጨረነቀ፡ ዐንገተ ዐር ሰው።

ጨርጨር: በሐረርጌ ክፍል ያለ ሞቃት አገር።

ጨርጨቤ: ጠንቋይ፡ በሰው ቁመት ልክ የሚጽፈው ክታብ፡ አስማት።

ጨቀለ: ወለደ።

ጨቀየ (ሰቀየ፡ ጸቀወ): ረካ፡ ራሰ፡ ጭቃ ኾነ።

ጨቀጨቀ: ርጥብ ጌሾ ወቀጠ።

ጨቀጨቀ: ነዘነዘ፡ አተከረ፡ ነተረከ።

ጨቀጨቀ: ጠቀጠቀ፡ ደፈነ።

ጨቀጨቀ: ጨቆ አደረገ፡ አጨቀየ።

ጨቀጨቅ: ጭቃማ ስፍራ፡ የሃና የጭቃ አንድነት፡ ድብልቅነት፡ ጨቆጨቅ።

ጨቈነ (ጸቈነ): ተጫነ፡ ዐመቀ፡ ረጠጠ፡ በታች አደረገ፡ ቀንበር ጫነ፡ አገዛዝ አጸና፡ አስጨነቀ፡ አስቸገረ (ዓሞ፪፡ ፲፫)

ጨቈነ: ጨፈቀ፡ ለሰቀ።

ጨቈን (ጸቈን): ዐጪር፡ የፍል፡ የችግኝ ዳስ፡ ጀጐል። "የወቈን ምስጢር ሽምጥን ያያል"

ጨቈን: ከባድ ሸክም።

ጨቅላ (ሎች): ዐራስ፡ ለጋ ልጅ፡ ሰውነቱ ያልጠና፡ ያልጠነከረ፡ ራሱን ያልቻለ፡ ርጥብ ሕፃን (ዘፍ፴፫፡ ፲፫)

ጨቅጫቂ (ዎች): የጨቀጨቀ፡ የሚጨቀጭቅ፡ ደፋኝ፡ ነዝናዥ።

ጨቅጫቃ (ቆች): ነዝናዛ፡ ነትራካ።

ጨቆ (ጸቀወ): ጭቃ ለምጨቅ። "ይቀየን ተመልከት"

ጨቆ: ጨቀጨቅ።

ጨቋቈነ: ጫን ጫን አደረገ፡ ጨፋፈቀ፡ አጠጋጋ።

ጨቋኝ (ኞች): የጨቈነ፡ የሚጨቍን፡ ተጫኝ፡ ምቀኛ።

ጨቋኝነት: ጨቋኝ መኾን፡ ተኝነት።

ጨበረ(ፀመረ)፡ ከጥቍረት ወደ ንጣት ተለወጠ፡ ነጭ ኾነ፡ ሌላ መልክ አመጣ።

ጨበረረ(ጨፈረረ፡ ጨረፈፈ)፡ ቆመ፡ የዣርት ወስፌ መሰለ፡ የሽፍታ ደረቀ የናዝራዊ፡ የሐዘነተኛ፡ ያረመኔ ጠጕር።

ጨበረቀ) ጸብረቀ) ጭብርቅርቅ ብጭርቅርቅ አለ (አንፆረረ) ተንሸዋረረ፣ ሳይደምቅ ሳያምር ቀረ (ዘፈኑ፣ ማሕሌቱ፣ አስተያየቱ)

ጨበራይ(ትግ)፡ ዝኒ ከማሁ፡ ለእስንሳ ኹሉ ይነገራል።

ጨበሬ፡ በራዊ፡ ቀይ ዐፈር ቅላት ከብጫነት ያለው፡ ድልኸማ፡ ወርቅማ፡ ዐይን አበባ መሬት። ጠመነንን ተመልከት።

ጨበር (ሮች)፡ ጸበል)፡ ነጭ በቅሉ፡ አስቀድሞ ዋርዳ የነበረ። ግራጫን እይ።

ጨበርማ(ጸበላዊ)፡ የጨበር ዐይነት፡ ወገን፡ ነጭነት የተነፋበት፡ ዐመድማ። (በቅሎ፡ እንዲሉ።

ጨበጨበ(ትግ፡ ጨብጨበ)፡ አፈጠፈጠ፡ አቈጠቈጠ፡ ለመለመ፡ ቅጠል አወጣ፡ አጀፈጀፈ (ኢዮ፲፬፡ ፯፡ ፱። ማሕ፪፡ ፲፫። ኢሳ፳፯፡ ፮)

ጨባ፡ የዛፍ ስም፤ ከሰል የሚኾን ዕንጨት።

ጨብራሬ፡ የጨብራራ ዐይነት፡ ደረቅ ጠጕሩ እንደ እሾኸ የሚዋጋ፡ የሚለበልብ። "አባ ጠብራሬ" እንዲሉ፡ "አባ ጨጓሬ" ሲሉ።

ጨቦ፡ በጕራጌ አጠገብ ያለ አገር።

ጨነቀ(ጸዐቀ)፡ ጠበበ፡ ቸገረ፡ አወከ (ኢሳ፷፫፡ ፱) (ተረት) "የጨነቀው እርጉዝ ያገባል፡ የባሰበት እመት። " ጠነቀን ተመከት።

ጨነቀረ: ደፈጠ።

ጨነቈረ (ጠነቀረ): ዐይኑን ገደለ፡ አደከመ፡ አስተያየቱን ቈጠበ፡ አሳነሰ። . ዐይኑን ጨፍኖ በአ፩ ዐይኑ አየ።

ጨነበስጨንባሳ፡ የተጨናበሰ፡ የሚጨናበስ፡ ጤና ቢስ ዐይን።

ጨነበረ(ጨበረ) ሮጠ፡ ፈጠነ፡ ጠለቀ፡ ዐረበ።

ጨነበረ፡ ሳተ፡ ስሕተተኛ ኾነ።

ጨነገዘ፡ ቈረጠ፡ ቀደደ።

ጨነገፈ(ጸንገፈ። ትግ፡ ጨንገፈ)፡ መለመለ፡ ጣለ፡ አረገፈ፡ አወረደ፡ አወጣ፡ አጠናወተ (ገቢር)

ጨነገፈ፡ ወረደ፡ ወጣ፡ ተጠናወተ፡ ተጣለ (ተገብሮ) (ዘፀ፳፩፡ ፳፪)

ጨነጋገዘ፡ ቈራረጠ፡ ቀዳደደ (፪ነገ፡ ፲፭፡ ፲፮። ሕዝ፲፫ - ፲፩)

ጨነጐለ(ጨጐለ)፡ እጐለ፡ ሰነከለ፡ በዥምር አስቀረ። (ጠነወተ)ጨነገፈን እይ።

ጨነፈረ)ጨፈረ፡ ጠፈረ። ፈር)

ጨነፈረ)ንና: " ኰፈን፡ ቈረፈን፡ ተመልከት"

ጨንገሬ፡ የጨንገር፡ ንገራዊ፡ የኔ ጨንገር።

ጨንገር፡ ልምጭ፡ አርጩሜ፡ አሽንቋጦ (፪ሳሙ፡ ፯፡ ፲፬። ምሳ፲፫፡ ፳፬)

ጨንገር፡ ሰርገኛ ጤፍ፡ አገዳው እንደ መሥመር ቀጥ ብሎ የሚወጣ።

ጨንገር፡ ባለመሥመር የሐር ልብስ፡ የሮንዜና የመጠብር ሥራ ዐይነት፡ ሰንበር መሳይ።

ጨንገር፡ የዛር ስም።

ጨንገሮች፡ ልምጮች፡ አርጩሜዎች።

ጨንጋፊ፡ የጨነገፈ፡ የሚጨነግፍ፡ መልማይ።

ጨንጋፋጭንጋፊ የጨነገፈ፡ የወረደ፡ የወጣ፡ ውርጃ።

ጨኖ(ዎች)፡ ያውሬ ስም፡ ገጥታው ኹናቴው የጭላዳ፡ ጠጕሩ የጕሬዛ። በታላቅ ተራራና በቋጥኝ ላይ ይኖራል፡ ሥራሥርና የዛፍ ፍሬ ተንቀሳቃሽ ይበላል። ፈረንጆች ዤላዳ ይሉታል።

ጨኖ፡ ያገር ስም፡ በይፋት አውራጃ ያለ ገጠር። "ጨኖ ገበያ" እንዲሉ።

ጨከነ(ጸቈነ)፡ በረታ፡ ቻለ፡ ታገሠ።

ጨከነ፡ ከፋ፡ ልቡ ጠና፡ ከርኅራኄ ራቀ፡ ደፈረ፡ ጠነከረ (ነሐ፬፡ ፯)

ጨከነ: ጠነከረ፣ ወንድ ወጣው።

ጨከን፡ መጨከን።

ጨከን አለ፡ ጨከነ።

ጨከክ አለ፡ ቀዘዝ አለ፡ ጨሃ ኾነ።

ጨካኝ(ጥቡዕ፡ ድሩክ)፡ የጨከነ፡ የሚጨክን፡ ለበጎ፡ ለክፉ፡ ቻይ፡ ታጋሽ፡ ደፋር፡ ቈራጥ፡ ጥኑ፡ ጠንካራ፡ ልበ ብርቱ፡ ክፉ፡ እናት፡ አይምሬ፡ ምሕረት የለሽ (፪ሳሙ፡ ፳፫፡ ፳። ፪ዜና፡ ፲፯፡ ፲፯) "ጨካኝና ጪስ መውጫ አያጣም። "

ጨካኝነት፡ ጨካኝ መኾን።

ጨካኞች፡ ደፋሮች፡ ብርቱዎች (፪ሳሙ፡ ፳፫፡ ፲፮- ፲፯። ፪ዜና፡ ፲፯፡ ፲፫፡ ፲፬። ኤር፵፰፡ ፲፬)

ጨወተ(ጸወተ)፡ ተነገረ፡ ኾነ፡ ተደረገ፡ ጨዋታው።

ጨወታጨዎታ፡ ዝኒ ዓዲ ከማሁ (ዘዳ፳፰፡ ፴፯። ፩ጢሞ፡ ፩፡ ፬)

ጨወት ጨወታ፡ የመምህራን ንግግር ነው።

ጨወትጨዎት፡ ዝኒ ከማሁ፡ ክፉና በጎ።

ጨወየ) አጨወየ፣ ጨው አደረገ፣ በጨው ዐጀለ።

ጨዋ ማይምን፣ ጪው።

ጨዋ(ሐራ)፡ የንጉሥ አሽከር፡ ዘማች፡ ወታደር፡ የጦር ሰው፡ ምሪተኛ፡ ስላገልግሎቱ በባላገር ላይ እየተሠራ በቀን ብዛት መልከኛ ባላባት የኾነ፡ ይኸውም ዐማራ (ዐም ሐራ) ነው። "የጨዋ ልጅ" እንዲሉ። "የጨዋ ልጅ ተዋርዶ፥ ዕንጨት ሰበራ ቈላ ወርዶ፡ ሲያነደው ያድራል ሌሊቱን ቀን የሰበረውን" (አዝማሪ) ዳግመኛም ጨዋ ግእዝ ጼዋ ካለው ቢወጣ የምርኮኛን ባላባትነት፡ ክብርና ማዕርግ ያሳያል (ዳን፩፡ ፫፡ ፬ ፮። ፫፡ ፲፪)

ጨዋ(ልሂቅ)፡ ዐዋቂ፡ ዐዛውንት፡ ሽማግሌ፡ አስታራቂ፡ ገላጋይ። "ጨዋ ዐር ያበላል" እንዲሉ። "ጨዋ በልጅነቱ ሲሠራው የነበረውን ልጆች ሲሠሩት ቢያይ ይነቅፋል። " ጨው ምግብን ኹሉ እንደሚያሰማማ ጨዋም መክሮ ዘክሮ "አንተም ተው አንተም ተው" ብሎ የተጣላን ያስታርቃል፡ በጠብ የተለያየውን በፍቅር አንድ ያደርጋልና፡ ጨው እንደ ማለት ጨዋ ተባለ። ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን "እናንተ የምድር ጨው ናችኹ" እንዳለ (ማቴ፭፡ ፲፫)

ጨዋ(ዎች)፡ ፊደል ያልቈጠረ፡ ትምርት ያልተማረ፡ ማይምን።

ጨዋታ ነገር፡ ሩጫ፡ ልፊያ፡ ዘፈን፡ ዋዛ ፈዛዛ፡ ሣቅ፡ ሥላቅ፡ ኳስ መወርወር፡ ጥንግ መምታት። "በገና ጨዋታ አይቈጡም ጌታ" እንዲሉ።

ጨዋነት፡ ጨዋ መኾን፡ ሽምግልና።

ጨው(ዎች)፡ ጼው)፡ ምግብን ኹሉ የሚያጣፍጥ፡ ደንጊያ ማዕድንነትና ገንዘብነት ያለው፡ በውሃ የሚቀልጥ፡ የሚጝ፡ ጋንፉር፡ ልመደው፡ አሞሌ፡ ዐሸቦ፡ አሻል።

ጨው(ጸገወ)፡ ለምለም ስንደዶ።

ጨው በሌ፡ የወንዝ ስም፡ በሚቅ አቅራቢያ ያለ ወንዝ። "የነጋዴ ጨው ስለ ወሰደ በዚህ ስም ተጠራ" ይላሉ።

ጨው ባሩድ፡ የሚቃጠል የባሩድ፡ የቦረቦጭ ደንጊያ። ባሩድን ተመልከት።

ጨው ጪው አለ፡ ጣፈጠ፡ ያሰጠ።

ጨውቴ(ዎች)፡ የጨውት፡ የዝንጀሮ ልጅ፡ ጨዋታ ዐዋቂ ሰው።

ጨውቴነት፡ ጨውቴ መኾን።

ጨውት(ጸውት)፡ ጩኸት፡ ጫጫታ።

ጨውናና፡ ፊተ መጣጣ፡ ዐሸቦ የነፉበት የሚመስል ሰው።

ጨዳጅ፡ የወደደ፡ የሚወድድ፡ ከፋይ፡ ከባቢ።

ጨድዴ፡ የወድድ ወገን፡ ጣሴ በኛ የጦር ገበሬ፡ በጠላት ጦር ሰራዊት መካከል የወንድ በር የተሰጠው (፩ሳ፡ ፳፫፡ ፲፮)

ጨገት(ጠጋ፡ ተጠጋ)፡ ጫት፡ ጭጐት ሠራ፡ ኣበጀ።

ጨገገ(ጠገገ። ጸጐጐ)፡ ቅፍፍ አለ፡ ጭጋግ ኾነ።

ጨገገ፡ ተጠጋ፡ ተጣበቀ።

ጨጐለ(ጸቈነ)፡ ጀጐለ፡ ቀየደ፡ ከበበ፡ ጋረደ፡ በሐር፡ በአበባ ሸፈነ፡ ኣስጌጠ፡ ሸለመ፡ አሳመረ፡ አንቈጠቈጠ። ወነጐለን እይ።

ጨጐል፡ መክበብ፡ መጋረድ፡ መሸፈን፡ ማስጌጥ።

ጨጐረ(ጸጐረ)፡ ጠጕራም ኾነ፡ ዐረም በቀለ፡ ጠገበ፡ ጨጓራ መሰለ።

ጨጐፈ፡ ጨጐረ፡ ጠጕሩ በዛ፡ በኹለተናው ላይ።

ጨጐፌ፡ ጐፋም፡ ፊቱ ጨጐፍ የለበሰ።

ጨጐፍ፡ ብዛት ያለው ጠጕር።

ጨጓራ፡ በሆድ ውስጥ ያለ የምግብ ከረጢት (ቋት)፡ ሥጋዊ ጠጕር ያለው (ዘፀ ፲፪፡ ፬) የሚያመሰኳ እንስሳ ግን ጨጓራው ነው። ፩ኛው የሽርክት፡ ፪ኛው የልዝብ። ፈረንጆች ጨጓራን "እስቶማክ" ይሉታል። ዶለተን እይ።

ጨጓሬ(ጸጕራዊ፡ ዘጸጕር)፡ ዝኒ ከማሁ፡ የጨጓራ ዐይነት፡ ወገን፡ ኹለንተናው ጠጕር የኾነ፡ ጠጕር የለበሰ ትል። "አባ ጨጓሬ" እንዲሉ። ጨብራሬን ተመልከት።

ጨጓር(ጸጓር)፡ ጠጕራም፡ ጭገራም፡ ባለጠጕር፡ ጠጕሩ የበዛ፡ የረዘመ።

ጨጓይ የጨኈለ፡ የሚጨጕል፡ አስጊያጭ።

ጨጓፋ፡ የጨጐፈ፡ ባለብዙ ጠጕር፡ ከብት፡ ሰው።

ጨጨ፡ የጠንቋይ ጽፈት። ራፎንን ተመልከት።

ጨጨሆ፡ በበጌምድር ክፍል ያለ አገር። "ጨጨሆ በር" እንዲሉ። በትግሪኛ "ነጭ" ማለት ነው።

ጨፈለቀ (ጨፈቀ): ረገጠ፡ ዳጠ፡ ደፈጠጠ፡ አጨማለቀ።

ጨፈለቀ: ዐዲስ ብረት ሠራ፡ ቀጠቀጠ። "ጨፈለቀ ከጨፈቀና ከፈለቀ የተዴቀለነው"

ጨፈለቀ: ዕዳሪ አወጣ፡ ዐረሰ፡ ተረተረ፡ ሠነጠቀ። "ጠጋን እይ"

ጨፈላለቀ: አበለሻሸ፡ እንዳለወገን አረገ (፪ዜና፡ ፴፬፡ ፯)

ጨፈረ (ጸፈረ): ዘለለ፡ አረገደ፡ መርመር አለ፡ ባንገት ወረደ። "ደነከረን እይ"

ጨፈረ: ቀረበ፡ ተጠጋ።

ጨፈረረ) (ጨረፈፈ): አንጨፈረረ፡ አንረፈፈ። "ወበረረን እይ"

ጨፈረር: ጨፍራራ፡ የተንጨፈረረ።

ጨፈቀ: አከበበ፡ አድበለበለ። "ጨበጠን እይ"

ጨፈቀ: አጠጋጋ፡ ጠቀጠቀ፡ አበዛ፡ ቸፈገ፡ ጨፈገ።

ጨፈቃ (ቆች): ተጨፍቆ የደረቀ ባለጭራሮ ዕንጨት፡ ያጥር፡ የግድግዳ መሥሪያ።

ጨፈቃ (ትግ): ጭቃ።

ጨፈቃ: ቅንድብ ጭፋር።

ጨፈነ (ጸፈነ): ዐይኑን ከደነ፡ ዐፈነ፡ ደፈነ፡ ወለሰ፡ ሸፈነ፡ ደመና ምድርን።

ጨፈንታ: የቀድሞ ወታደር ስም፡ ቡርሳን ቤት አንሣን የመሰለ ጭፍራ። "(ጸፈናዊ በዓለ ጸፈን) ማለት ይመስላል"

ጨፈገ: ወፈቀ፡ ቸፈገ።

ጨፈገገ: ግንባሩን ቋጠረ፡ አጠቈረ፡ ሳይጠዳው ቀረ። "ገገን እይ"

ጨፈጨፈ (ጠፈጠፈ): መታ፡ ቈረጠ፡ ቈራረጠ፡ ተፈተፈ፡ ጫፍን፡ አውሬን፡ ከብትን ሳይወድቅ በቁሙ።

ጨፈጨፈ: ሰደበ፡ ፀረፈ፡ ወረፈ።

ጨፈጨፈ: ነገርን ዐለፈ፡ ሻረ። ዳኛው "ጨፈጨፈ"

ጨፈጨፍ (ጠፈጠፍ): የክረምት ጭቃና ውሃ የሰውን እግር የሚቈርጥ፡ የሚያቈስል

ጨፋ/ጨፌ (ኦሮ): የመስክ ስም፡ መስክ፡ ለምጮቅ ወቆ (ማሕ፮፡ ፲፩)

ጨፋሪ (ዎች): የጨፈረ፡ የሚጨፍር፡ ዘላይ፡ አርጋጅ።

ጨፋቂ (ቆች): የጨፈቀ፡ የሚወፍቅ፡ ለሳቂ።

ጨፋኝ (ኞች): የጨፈነ፡ የሚጨፍን፡ ሸፋኝ።

ጨፋፈረ: ዘላለለ።

ጨፋፈነ: ከዳደነ፡ ሸፋፈነ።

ጨፌ: ጠጕራም ጋቢ፡ ቡልኮ፡ ንጉሥ ወይም ሀብታም የሚለብሰው። "ጩፋዊ ማለትን ያሳያል፡ ጠጕሩ የሚታጨድ ይመስላልና"

ጨፍላቂ (ቆች): የጨፈለቀ፡ የሚጨፈልቅ፡ ዳጭ፡ ዐራሽ፡ ቀጥቃጭ።

ጨፍጫፊ: የጨፈጨፈ፡ የሚጨፈጭፍ፡ ቈራጭ፡ ተፍታፊ።

፡ የጀ፡ ተለዋጭ። "ጀጐለ፡ ጐለ"

ጩርቅርቅ አለ (አንፆረረ): ፈራ፡ ሽንቱን ለቀቀ፡ በሽንት ተበከለ።

ጩርቲ: ድምጠ ሰላላ፡ ዕድሜው የበዛ፡ ጠጕሩ የነጣ፡ አፍ ቂጡ የሸበተ ሽማግሌ፡ ዥዡ። "ነጮሬን ናጩርትን አስተውል"

ጩርጩር አለ: ጥቂት ጥቂት ወረደ፡ ጭልጭል አለ።

ጩርጩር አለ: ጥቂት ጥቂት ወረደ፡ ጭልጭል አለ።

ጩቅ (ቆች): (ጠዋዒ)፡ ንፉግ፡ ሥሥታም፡ ቢስ፡ "እጁን ቢሉት ጤብ የማይለው"

ጩቅ: ንፉግ ጮቀ።

ጩኮ፡ በግራና በቀኝ ክንፍ ያለው የአረመኔ ጦር።

ጩኸ፡ እሪ በል። (ተረት)"ባላደራ ጩኸ በተራራ። " "ለራስ ምታት ጩኸበት፡ ለሆድ ቍርጠት ብላበት። "

ጩኸታም፡ ጩኸት ወዳድ፡ ባለጩኸት።

ጩኸት፡፡ "ለቍራ መብል ላሞራ" እንዲሉ።

ጩኸት(ቶች)፡ እሪታ፡ ቍቍታ፡ ፍጅት፡ አቤቱታ። "ጩኸቴን ቀሙኝ" እንዲሉ።

ጩኸት ትርፌ፡ ቍቁ ቢሉ ሰው የማይደርስበት ጐድጓዳ፡ የቀማኛ ስፍራ፡ እሪ በከንቱ።

ጩኸት፡ ያውሬ፡ የንስሳ፡ የወፍ ድምጥ።

ጩኻ፡ ጮኻ፡ (ተረት)"ጩኻ የማታውቅ ወፍ ዕርን ብትጮኸ ዕለቁ ዕለቁ። "

ጩፋ (ኦሮ): የብርና የወርቅ አንባር። ንጉሥ ሁለት ጠላት ለገደለ የሚሸልመው። "ማልደያን ተመልከት"

ጩፋ: ግጥም ያለ የሽሩባ ሥራ። "ጩፋ በጋልኛ ሁሉ ዝጉ ማለት ነው"

(መዊጽ፡ ሞጸ፡ ካሰ። ትግርኛ፡ መወጸ): ፋቀ፣ ፈገፈገ፣ ጠረገ፣ አጸዳ (ጥርሰን) እንደ ግእዙ በካዕ ዘይቤ ቢፈቱት ሰውየው ጥርሱን ስላሳደፈ ጽዳትን፣ ጥራትን በማጫ ካሰ ማለትን ያሳያል።

(መዊጽ፡ ሞጸ፣ ካሰ፡ ትግርኛ፡ መወጸ): ፋቀ፣ ፈገፈገ፣ ጠረገ፣ አጸዳ ጥርስን። እንደ ግእዙ በካዕ ዘይቤ ቢፈቱት ሰውየው ጥርሱን ስላሳደፈ ጽዳትን፣ ጥራትን በማጫ ካሰ ማለትን ያሳያል።

(ከግእዝ መዊጽ፡ ሞጸ፣ ካሰ፡ በትግርኛ መወጸ): ይህ ቃል ጥርን መፋቅ፣ መፈግፈግ፣ መጥረግ ወይም ማጽዳትን ያመለክታል። በግእዝ በካዕ ዘይቤ ሲተረጎም፣ አንድ ሰው ጥርሱን ስላሳደፈ በንጽሕና ወይም በጥራት (በማጫ) እንደካሰ ያሳያል።

: የሚጩህ ወይም የሚጭር።

: የጩ፣ የሚጭ።

ጪሰኛ (ኞች): ጪስ የሚያጨስ፡ ባለጪስ፡ በሰው መሬት ላይ ቤት ሠርቶ የሚኖር። "ጪስ፡ ለጊዜው ታይቶ በኋላ እንዲታጣ፡ ጪሰኛም መሬትን ለቆ ይኼዳልና፡ በዚህ ስም ተጠራ። " (ተረት): "ያተር ክምር የጯሰኛ ክብር"

ጪሰኛ()ነት: ጪሰኛ መኾን።

ጪሳም: ጪስ የበዛበት ቤት፡ ዋሻ።

ጪስ (ጢስ): የጉም ዐይነት፡ ብናኝ፡ የእሳት እንፋሎት፡ የማገዶ ውት። የወገርት፡ የቡክቡካ፡ የዕጣን፡ የልባንጃ፡ የጽጌ ረዳ፡ የማንኛውም የጪስ ዕንጨት መዐዛ፡ መልካም ሽታ። (ተረት): "እንባ ሲሻኝ ዐይኔን ጪስ ወጋኝ" "ሥራ ጠፍቶ ጪስ ይሞቃል። "

ጪስ አባይ: የጥቍር አባይ ፍፍቴ፡ ብናኝ።

ጪስ ጪስ አለ: ለበላተኛ፡ አፍ የጪስ ጣዕም ሰጠ ምግቡ።

ጪስ: እንደ ገባው ንብ ኾነ።

ጪራ: የሣር ስም፡ ፍሬው ጤፍ የሚመስል ሣር፡ ከጤፍ ጋራ የሚበቅል።

ጪራ: የሣር ስም፡ ፍሬው ጤፍ የሚመስል ሣር፡ ከጤፍ ጋራ የሚበቅል።

ጪራፊ: የጨረፈ፡ የሚጨርፍ።

ጪበረርጨብራራ፡ የተንጨበረረ፡ የተቃጠለ፡ ጨፈረር፡ ጨፍራራ፡ ቁም ጠጕር።

ጪዎች፡ አሞሌዎች፡ ጋንፉሮች።

ጪዎች፡ ጨዋዎች፡ ማይምኖች።

ጪጨ የሰው ስም፡ የጪጪ ወገን ማለት ነው።

ጪጪ ታናሽ ልጅ፣ ጫጪ።

ጪጪ(ዎች) በቤተ መንግሥት የሚያድግ ሕፃን፡ የጨዋ ልጅ፡ በሺዋ ባንኮበር ማዕርጉ ፫ኛ ክፍል የኾነ።

አለ፡ ከሳ፡ ቀለለ፣ የፊት።

አለ፡ ዝም፡ ርጭ አለ።

ጫማ(ሞች)፡ ሰኰና፡ ከቍርጭምጭሚት በታች ያለ የእግር ዠርባና ውስጥ፡ መርገማ፡ መኼጃ (ጻማ) ድካም ጣመን የሚሰማው (ዘዳ፳፰፡ ፷፭) (የደም ጫማ)፡ ጋሬጣ የወጋው፡ ዕንቅፋት የመታው ደሙን ያፈሰሰው ጫማ፡ ርምጃ፡ የጫማ ስፍር ወይም ልክ።

ጫማ(ጻመወ)፡ ለፋ፡ ደከመ፡ ወመነ፡ ካከመ።

ጫማ፡ መጫሚያ፡ የእግር ቤዛ (ማሕ፯፡ ፪። ኢሳ፭፡ ፳፯። ዓሞ፪፡ ፮)

ጫማ ሳመ፡ ጭም አደረገ።

ጫማ፡ ጫማና ጫሜ አበጀ፡ ሠራ። ያለፈው አንቀጽ የሚመጣው ስም መኾኑን አስተውል።

ጫማ ፣ፊ፡ ነጠላ ጫማ፡ ኩፍ ጫማ፡ የወርቅ ጫማ፡ የንጨት እንዲሉ። ጫማን መጫሚያ ማለት ኀዳሪ፡ በማኅደር ነው። ሰዎች በማለት ፈንታ ቤቶች እንዲሉ። ነገር ግን ገላንና ዕቃን ባንድ ስም መጥራት አይገባም

ጫሜ(ማዊ)፡ የማ ዐይነት፡ የጐራዴ ጫፍ ጌጥ፡ ሎሚታ ያለውና የሌለው፡ ከብርና ከወርቅ የተሠራ ሽልማት። ከሰገባው ጋራ እንደ ጫማ ይዋደዳል።

ጫረ (ትግ ጸሐረ): መሬትን ረ፡ በጥቂቱ (ላመል) ቈፈረ፡ ኳተ፡ ፋረ፡ ወይም ጐደፈረ፡ መነጨረ፡ በተነ በሬው ሰው።

ጫረ: መናኛ ጽፈት ጸፈ፡ ከተበ።

ጫረ: ክብሪትን በሣጥኑ ላይ መክብሪት፡ ማረ እንዲሉ።

ጫረ: ፍምን ከምድጃ ዛቀ፡ ወሰ። "እሳት ጫረ እንዲሉ"

ጫረታ: የዋጋ ብልጫ፡ ፍክክር።

ጫሪ (ዎች) (ጸሓሪ): የጫረ፡ የሚጭር፡ ፋሪ፡ ቈፋሪ፡ ጫሪ፡ ጐድፋሪ፡ ጻፊ። "ጫር፡ ብለኸ ፍምን አስተውል"

ጫሪ: የጨረ ወይም የሚጭር፡ ጫሪ፣ ቧሪ።

ጫሪ: የጨረ፣ የሚጭር፡ ጫሪ፣ ቧሪ።

ጫራ: ያገር ስም።

ጫሬ: ጯኺ፡ ነወሬ።

ጫሬ: ጯኺ፡ ነወሬ።

ጫር አደረገ: ጫረ።

ጫር ጫር አደረገ: ቈፈር ቈፈር፡ ፋር ፋር፡ ጻፍ ጻፍ አደረገ።

ጫቀታ: በወለቃ አጠገብ ያለ አገር።

ጫቅ: ሙጫ።

ጫቅ: እንደ ጭቃ እየኾነ ከንጨት የሚወጣ፡ የሙጫ ዐይነት።

ጫቅማ: ጕሎ፡ የጕሎ ዐይነት ዛፍ።

ጫተረ (ትግ፡ ጻሕተረ): መሬትን ቈፈረ፡ ጐደፈረ፡ ለውጊያ አጫረ። "ጫረን እይ፡ ሥሩ እሱ ነው"

ጫታ(ጽማዌ)፡ ዝምታ፡ ርጋታ፡ ጸጥታ።

ጫታ: ዝምታ (ጫጫ)

ጫታሪ: ጫታራ፡ የተረ፡ የሚጫትር፡ የለፋ፡ የደከመ።

ጫት (ቶች): የተክል ስም፡ ለጋውን ቀንበጡን እስላሞች የሚያኝኩት ዕንጨት። "ግትና ቡና እንዲሉ" "ባረብኛ ቃት ይባላል"

ጫት (ወፅአ፡ ፃት): ርጥብ ዐራስ ልጅ። "እመጫት እንዲሉ"

ጫት፡ በታችኛው ወግዳ ከጫጫ በስተቀኝ ያለ አገር፡ የገብሬል አጥቢያ።

ጫት አሞራ: ሳቢሳ፡ በበሬ ዠርባ ላይ ቁሞ ዠማ የሚሻገር።

ጫት: ጭሪ፡ ገጣባ፡ ለመብላት በክብዠርባ የምትታዘል ወፍ (ጐዣም)

ጫነ(ጸዐነ)፡ ኮርቻን፡ ጭነትን፡ በበቅሎ፡ በፈረስ፡ ባህያ፡ በግመል፡ በበሬ፡ በዝኆን ዠርባ አደረገ፡ አሰረ፡ መጫኛን ላገ፡ የተጫነውም ዐረቀ። (ተረት)"ጫን ያለው ኮርቻውን ለምን ያለው ስልቻውን አያጣውም። " ቀነበረ ብለኸ ቀንበርን እይ።

ጫነ፡ ማንኛውንም ሸክም ለሰው አሸከመ፡ አሳዘለ፡ በጨፈቃ፡ በመቃብር፡ በሚታረቅ ዕንጨት ላይ ደንጊያን፡ ግንድን አከበደ፡ ባንድ ነገር ላይ እጁን (መዳፉን) አኖረ።

ጫነ፡ ቅኔ ቈጥሮ መንገር፡ መቀኘት ለማይችል ተማሪ የራሱን ቅኔ ነገረ፡ አስጠና።

ጫነ በል፡ ከርሣም፡ ሆዳም።

ጫነ፡ ዘውድ ደፋ፡ ተቀዳጀ፡ ነገሠ፡ (አቀዳጀ፡ አነገሠ)

ጫና፡ ጭቈና፡ የመጨቈን ሥራ። "የእከሌ እዝ የማና ነው"

ጫን(ተጽዕኖ)፡ መጫን።

ጫን አለ፡ ዐየል፡ ከበድ አለ።

ጫን፡ የመጠን፡ የስፍር ስም፡ ፫ ዳውላ እኸል፡ በቍና ፰፡ በማድጋ በእንቅብ ፮፡ በጕርዝኝ ፲፪ ይኾናል (፩ነገ፡ ፬፡ ፳፪። ኢሳ፭፡ ፲። ሆሴ፫ = )

ጫን፡ የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ፡ "አንተ አሽከር ፈረሱን ፵ን። "

ጫን ያለው፡ የወንድ መጠሪያ።

ጫንቃ: በትከሻና በትከሻ መካከል ያለው ገላ፡ ደንደስ፡ ማዥራት፡ የጀርባ ጫፍ (ኢሳ፱፡ ፮። ፴፡ ፮። ዘካ፯፡ ፲፩)

ጫኝ(ኞች)፡ የጫነ፡ የሚጭን፡ ለጓሚ፡ ጐረደማን።

ጫኝ፡ በጕዞ፡ በዘመቻ ጊዜ የንጉሥ ዕቃ የሚጭን ሰራዊት ስም፡ ደንቡ ጭነት የኾነ ጭፍራ።

ጫዌ፡ የቈላ ቍስል፡ እግርን ጨው የሚያስመስል፡ ጐርምጥ።

ጫገት(ቶች)፡ ዐጪር የጦጣ ወጥመድ፡ በላዩ ደንጊያ ያለበት ጣራና ግድግዳ። ጦጣው ይገባና በገመድ ታስሮ በመካከሉ የተንጠለጠለውን ያጎዳ ራስ በሳበው ጊዜ መዝጊያው ወዲያው በቶሎ ይዘጋል፡ እሱንም ሰዎች በጦር እየወጉ ይገድሉታል።

ጫጕላ(ዎች)፡ የሙሽራ ቤት፡ በሐር የተንቈጠቈጠ፡ በአበባ ያጌጠ። (ግጥም)"እቴ ሸንኰሬ፡ ጫጕላሽ አብቧል ዛሬ። "

ጫጨ(ፃእፅአ)፡ አነሰ፡ ኰሰሰ፡ ከሳ፡ ቀጠነ፡ መነመነ፡ ኰሰመነ፡ ሰለለ።

ጫጩት(ጻጹት)፡ የዶሮ፡ የወፍ፡ ያሞራ ልጅ፡ ታናሽ ፍጥረት። በግእዝ ግን ትንኝም ጻጹት ይባላል። ሲበዛ ጫጩቶች ይላል (ዘሌ፲፪ ' ፰። ኢዮ፴፱፡ ፴)

ጩት፡ የዶሮ ልጅ፣ ፊ።

ጫጩቶች፡ ብዙ ልጅ፡ እንዳሸዋ በሜዳ፡ ፍስስ ያለ።

ጫጫ፡ የዠማ ስም፡ በወግዳ መካከል የሚወርድ ታላቅ ዥረት።

ጫጫረ: ቈፋፈረ፡ ሞጫጨረ፡ ጻጻፈ።

ጫጫታ ጩኸት ()

ጫጫታ፡ ቻቻታ፡ ጩኸት፡ ፍጅት፡ የወፍና የልጅ።

ጫጫቴ ወፍ ልጅ።

ጫጫቴ፡ ጫታ የሚያደርግ፡ ተኰልኰሎ፡ ብዛት ያለው።

ጫፉ ደረቅ: ለዛ ሙጥጤ።

ጫፍ: መጨረሻ።

ጫፍ: ራስ፡ መጨረሻ፡ ውልብልቢት፡ ቀንበጥ፡ ዐናት (ዘፍ፰፡ ፲፩። ኢሳ፵፬፡ ፲፱) "የተራራ፡ የዛፍ፡ የነገር ጫፍ እንዲሉ" "ቅርንጫፍን ተመልከት"

ጫፍና ጫፍን ገጠመ: ልብስን፡ ክርን፡ ገመድን፡ ጠፍርን፡ ሽቦን አንድ ጊዜ ዐጠፈ።

ጫፎች: ራሶች፡ ዐናቶች (ዘፀ፳፭፡ ፴፭። ሕዝ፴፩፡ ፭፡ ፮። ሮሜ፲፩፡ ፲፮፡ ፲፯፡ ፲፰፡ ፳፩)

ጭለጣ፡ የመጨለጥ ሥራ።

ጭለፋ፡ የመጥለቅ፡ የመቅዳት ሥራ።

ጭሉዳ፡ ቍግ።

ጭሉፋት(ቶች)፡ እንደ ጭልፊት ድንገት የሚነጥቅ፡ ጭልፊትዊ፡ ቀማኛ፡ ነጣቂ።

ጭላሃ፡ ዕንጐቻ።

ጭላት፡ ነጣቂ አሞራ፡ የዶሮ፡ የወፍ ጠላት፡ ጭልፊት፡ ሲላ፡ ገዲ (ኢዮ፴፱፡ ፳፮)

ጭላንጭል(ለጨለ)፡ ጥቃቅን የጣራና የግድግዳ ቀዳዳ፡ የጫሌ ብስ የሚያካክል የጨረር ፍንጣቂ ሰልቶ የሚገባበት። ሲበዛ ጭላንጭሎች ይላል።

ጭላንጭል፡ ክፉ ቀን ሲወጣ የነበረ ጊዜ፡ የረኃብ ጨለማ እየፈገገ የጥጋብ ውጋጋን ሲታይ፡ (አሲድ ተቀነሰ፡ በረከት ተዠመረ)

ጭላዳ(ዶች)፡ የዝንጀሮ ልጅ ብዛት፡ ብዙነት ያለው፡ በገደል፡ በሆድ ተለጥፎ የሚያድር፡ የሚያድግ።

ጭላጭ፡ የውሃ፡ የመጠጥ ቅሬታ፡ ንቃሪ።

ጭላፊጭልፍ፡ የተጨለፈ፡ የተቀዳ፡ ወጥ፡ መረቅ።

ጭል አለ(ጨረረ)፡ ጭር፡ ርጭ፡ ጸጥ አለ፡ እንቅልፍ ወሰደው።

ጭልቃ፡ የተወለቀ፡ የተበጠበጠ፡ ብጥብጥ ተልባ።

ጭልጊ(ጅልጊ)፡ ጭልጋዊ፡ የጭልጋ፡ የወይፈን ስልቻ ዐይበት፡ አቍማዳ፡ የጨው መክተቻ።

ጭልጊ፡ የሰው ስም።

ጭልጋ፡ በጐንደር ክፍል ያለ ነበር።

ጭልጎች፡ ዐይበቶች፡ የጭልጋ።

ጭልጥ አለ፡ ተወለጠ።

ጭልጥ አለ፡ ፈጽሞ ኼደ፡ ጐደ፡ ጠፋ፡ ታጣ፡ ካይን ተሰወረ።

ጭልጥ አደረገ፡ ሽምጥጥ እረገ፡ ጨለጠ።

ጭልጥ፡ ዕልቅ፡ ፍጽም። "ፉት ሲሉ ጭልጥ" እንዲሉ።

ጭልጥ፡ የተጨለጠ፡ የተጨረሰ፡ ያለቀ።

ጭልፊት(ቶች)፡ ዶሮን፡ ሥጋን፡ ዓሣን የምትነጥቅ አሞራ፡ ባምሌና በናሴ የማትታይ። ጭላትን ተመልከት።

ጭልፋ(ፎች)፡ ከንጨት፡ ከብረት፡ ከብር፡ ከቅል የተበጀ ዕቃ፡ ከድስት ወጥ መቅጃና ማውጫ፡ ትልቁም፡ ትንሹም (ዘኍ፯፡ ፲፫፡ ፲፱)

ጭመራ፡ የመጨመር ሥራ፡ እከላ።

ጭመታ(ጽማዌ)፡ የመጨመት ሥራ፡ ርጋታ፡ ዝምታ።

ጭማሪ(ተውሳክ)፡ ትርፍ ነገር፡ ቀድሞ ያልነበረ፡ ኋላ የታከለ።

ጭማቂ፡ የተጨመቀ፡ ጥማቂ። "የዚህ ለም እሳት ለወዲያኛው ዓለም እሳት የነ-ጊዜ ጭማቂው ነው" ይባላል (አፈ፡ ጨዋ)

ጭምላቂጭምልቅጭምላቆ፡ ዝኒ ከማሁ፡ ኵልፍልፍ።

ጭምልቅልቅ የተጨመላለቀ፡ ኹለንተናው ጭቃ።

ጭምልቅልቅ አለ፡ ኵልፍልፍ አለ፡ ተጨመላለቀ።

ጭምር(ፅሙር)፡ የተጨመረ፡ የገባ።

ጭምር፡ ንኡስ አገባብ፡ አንድነት አድርጎ። "እከሌን ዐይኑን ጭምር ራሱን ያመዋል። " ጋራን ተመልከት።

ጭምርማሪ የተጨማመረ።

ጭምቅ፡ ዝኒ ከማሁ፡ (ቅጽል) (ጥቅ)

ጭምቅ፡ የቅጠል ስም፡ መርዝነት ያለው ዕፅ፡ ሰዎች በውዳቂ ሥጋ ላይ ብናኙን ነሰነሱ፡ አንበሳን፡ ነብርን፡ ዥብን፡ በውሃ፡ እድበጠበጡ ዝንጀሮን የሚገድሉበት ክፉ መድኀኒት፡ (ስም)

ጭምቆ፡ ተጨምቆ በወንፊት የተጣራ ጕሽ።

ጭምት(ቶች)፡ ጽምው)፡ የመተ፡ የረጋ፡ ደኅና ሰው፡ ድምጡ የማይሰማ፡ ዝምተኛ (ዘፍ፳፭፡ ፳٧) (ተረት)"ጭምት ሲሞት ልቡን፡ ንጉሥ ሲሞት ግንቡን። "

ጭምትር፡ የተጨመተረ፡ ጭምድድ።

ጭምትርትር አለ፡ ኩምትርትር አለ፡ ተጨመታተረ።

ጭምትርትር፡ የተጨመታተረ፡ ኵምትርትር።

ጭምትነት ጭምት መኾን።

ጭረሳ: ፍጸማ፡ የመፈጸም ሥራ።

ጭረት (ጽሕረት): መጫር፡ የመማር ሥራ።

ጭረት: ሙጭር፡ ጫረ።

ጭረት: ሙጭር፡ ጫር ተደርጎ የተጻፈ፡ የዜማ የተመለስ ምልክት።

ጭረት: የሣርና የንጨት ቀጪን ሥር፡ የጭራ ዐይነት።

ጭረት: የቃጫ ባዘቶ፣ ጨረተ።

ጭረት: የና፡ የሳማ፡ የቃጫ፡ የንሰት፡ የጕናጕና፡ የክሥዳ ባዘቶ።

ጭረት: የንጨት ሥር ረተ።

ጭሪ/ጭሬ: አፈ ቀይ አረጭ፡ የከብትን ገላ የምትጭር ቍስልና መዥገር በል ወፍ።

ጭሪ: መንጫሪ፡ በታኝ።

ጭሪዎች: አረጮች።

ጭራ (ዎች): የዥራት፡ የጋማ ጫፍ፡ ቍግ። "ቈነነን ተመልከት"

ጭራ (ዎች): የዥራት፡ የጋማ ጫፍ፡ ቍግ። "ቈነነን ተመልከት" (ይህ ቃል "ጨረር" ጋር ተደጋግሞ ሊሆን ይችላል)

ጭራ (ጽሒራ): ቈፍራ። (ተረት): "ዶሮ ጭራ መታረጃዋን አወጣች" "ዶሮ ጭራ የምታወጣው ምስጢር" (የዝንጀሮ ግጥም): "ልጄ ጭራም አትበላ፡ እናይ ኋላ"

ጭራ: ባንድነት የታሰረ የናስ ሽቦ። "ናስን አስተውል"

ጭራ: የዥራት ፍ፣ ጨረረ።

ጭራሮ (ዎች): ደረቅ ዕንጨት፡ ተጪን፡ ሳይቈረጥ ፀሓይ አቃጥሎ ያደረቀ።

ጭራሮ ደብር: የቀበሌ ስም፡ በታች ወግዳና በተጕለት ያለ የጭራሮ ደብር (ቤተ ክሲያን)፡ ወይም ተራራ ማለት ነው።

ጭራሮ: ቅንድብ ጭፋር። "ዞሮ ዞሮ መዝጊያው ጭራሮ" (እንቆቅልኸ)

ጭራሽ የማያፈራ የዛፍ ስም: ኮማን ይመልከቱ።

ጭራሽ: ንኡስ አገባብ፡ ፈጽሞ።

ጭራሽ: ፍጻሜ፡ መጨረሻ። "ጭራሹን አሳየ"

ጭራቅ (ሢራክ)ዐዋቂ፡ ብልኅ፡ ዕራት ዐይና። "እከሌ ጭራቅ ነው እንዲሉ" "ፈረንጆች ዲፕሎማቲክ (ዕጥፍ ዐይን) ይሉታል" "ሲበዛ ጭራቆች ያሠኛል" "አራት ዐይና ማለትም ፍጹም ዕውቀትን እንጂ ዐይንን አያሳይም" "አራትን ተመልከት" የሰው ዥብ ሰው በሌ፡ ሰውን እያረደ የሚበላ ባላራት ዐይን። "በማዥራቱ ያለውን ዐይን በጨርቅ ይሸፍነዋል፡ የሰው ሥጋ የሚቀቅልበት የብረት ጋን አለው ይባላል። ምንም የሰው ሥጋ መብላቱ ርግጥ ቢኾን አራት ዐይን አለው ማለት ተረት ነው። ኛምኛምን እይ"

ጭራቅ (ሢራክ): ዐዋቂ፡ ብልኅ፡ ዕራት ዐይና። "እከሌ ጭራቅ ነው እንዲሉ" "ፈረንጆች ዲፕሎማቲክ (ዕጥፍ ዐይን) ይሉታል" "ሲበዛ ጭራቆች ያሠኛል" "አራት ዐይና ማለትም ፍጹም ዕውቀትን እንጂ ዐይንን አያሳይም" "አራትን ተመልከት"

ጭራቅ: የሰው ዥብ ሰው በሌ፡ ሰውን እያረደ የሚበላ ባላራት ዐይን። "በማዥራቱ ያለውን ዐይን በጨርቅ ይሸፍነዋል፡ የሰው ሥጋ የሚቀቅልበት የብረት ጋን አለው ይባላል። ምንም የሰው ሥጋ መብላቱ ርግጥ ቢኾን አራት ዐይን አለው ማለት ተረት ነው። ኛምኛምን እይ"

ጭራንፎ (ዎች): የጭራሮ ጫፍ (ሚል፬፡ ፩። ሆሴ፲፬፥፮)

ጭራው አይያዝም: ሲፈልጉት አይገኝም ሰውየው።

ጭራው ጮሌ: ብልጥ ሰው።

ጭራውን ለበሰ: ጭራውን አቅንቶ ሮጠ፡ ፈረጠጠ፡ ጋለበ።

ጭራውን ለበሰ: ጭራውን አቅንቶ ሮጠ፡ ፈረጠጠ፡ ጋለበ። የጨረር ብርሃን በመስኮት የሚገባ፡ ጦር ምርቅና፡ ጭራ ቅንድብ መስሎ የሚታይ። "ጀንበሯ ጮራ ሰደደች እንዲሉ" ማቃጠል፡ ማንጨብረር፡ ማሳረር፡ መግረፍ፡ ማጮኸ።

ጭራፍ: ቡቃያ (ጐንደር)

ጭሬ (ዎች): የጦር ስም፡ ከአበታና ካፎቄ የሚያንስ ቅጠለ ጠባብ ጦር (፩ሳሙ፡ ፲፯፡ ፵፭)

ጭሬ: "እኔ" ለሚል ቦዝ አንቀጽ መንጭሬ፡ በትኜ። (ተረት): "ባልበላ ጭሬ አላፍስም ወይ" አለች ዶሮ።

ጭር አለ (ጸርሐ): ጮኸ፡ ድምጥ ሰጠ፡ አሰማ አውራ ዶሮ።

ጭር አለ:፡ ርጭ አለ፡ ድምጥ ሰጠ፡ ወረረ።

ጭር አለ: ርጭ፡ ጸጥ አለ፡ ድምጥ ታጣ። "ፊትን ተመልከት"

ጭር አለች: ምድር ያዘች፡ ተቀመጠች፡ ዝም አለች።

ጭር አለች: ጮኸች፡ ጫጩቶቿን አስጠነቀቀች ዶሮዋ።

ጭር: ርጭ፡ ጸጥ።

ጭርምትምት አለ: ጭምትርትር አለ፡ ተጨረማመተ።

ጭርምትምት: የተጨረማመተ፡ ጭምትርትር።

ጭርስ አለ: ፍጽም፡ ዕልቅ አለ።

ጭርስ: የተወረሰ፡ ያለቀ።

ጭርር አለ: ዕርር አለ፡ እንደ እንጭራር ጮኸ።

ጭርቂያም: ጭርቅ የሚያደርግ።

ጭርቂያም: ጭርቅ የሚያደርግ።

ጭርቅ አለ: ጨረቀ።

ጭርቅ አደረገ: በጥቂቱ ሸነ፡ ቀዘነ፡ ሽንቱን ቈረጠ።

ጭርቅ: ጥቂት ሽንት።

ጭርታ: ጭር ማለት፡ ዝምታ፡ ጸጥታ፡ ጫታ።

ጭርታ: ጭር ማለት፡ ዝምታ፡ ጸጥታ፡ ጫታ። አሳረረ፡ አንጨበረረ፡ አገመነ፡ አኰማተረ፡ ገረፈ፡ አጮኸ።

ጭርታም: ጭርት ያለበት ሰው፡ ባለጭርት።

ጭርት: ደቃቅ አሸዋ የሚመስል ነጭና ደረቅ ዕከክ።

ጭርንቍሳም: ጨርቃም፡ ቍረንጮም።

ጭርንቍስ: ወርቅ ቍረንጮ ባንድነት የተሰፋ። "ቅርንጥስን እይ"

ጭርንቅ: ዝኒ ከማሁ።

ጭርግድ: የተጨረገደ፡ ዕጭድ።

ጭርጭስ አለ: ጨረጪሰ፡ እርጅት አለ።

ጭርጭስ: የጨረጨሰ፡ ያረጀ፡ ያፈጀ፡ ሽማግሌ።

ጭርፋት (ጥጪ): የመጨረፍ ኹናቴ።

ጭርፍ: የተጨረፈ።

ጭሮሽ: ተጭሮ የወጣ የሠረገላ፡ ውሃ።

ጭቍን (ጽቁን): የተጨቈነ፡ ሌላ የተጫነው ሽምጥ።

ጭቍንቍን (ጽቍንቍን): የተጭቈነቈነ፡ ቅርብርብ።

ጭቍኝ (ኞች): (ችግኝ)፡ ታላቅ ሽታ ያለው ቅጠል፡ ባረንዛ መካከል ተጨቍኖ የሚበቅል፡ በመዐዛው ክፉ ሽታን የሚወቍን፡ ቅጠሉ ባፍንጫ ተወትፎ የሚወቈን።

ጭቃ ሱሪ: በክረምት የሚጠለቅ የጭቃ ሱሪ።

ጭቃ ረጋጭ: ጭቃን የሚረግጥ፡ የሚያቦካ።

ጭቃ ሹም (ሞች): የጭቃ ሹም፡ ባለምድርን የሚያዝ። "ሾመን እይ"

ጭቃ ኾነ: ላቈጠ።

ጭቃ: በቁሙ፡ ጨቀየ።

ጭቃ: ወልቅ፡ አረንቋ፡ ማጥ፡ ረግረግ።

ጭቃ: ዝናም ከጣለ የታረሰ የርሻ ይዘታ። "ጭቃዬን አለቅም እንዲል ባላገር"

ጭቃ: የሰው አካል፡ ሥጋ። "እከሌ ከወደ ጭቃው በዛ ብሏል" (ዘፍ፪፡ ፯)

ጭቃ: የራሰ፡ የረሰረሰ ዐፈር፡ የመሬት ሊጥ ያልቦካና የቦካ። (ተረት): "ማር ሲበዛ ጭቃ ነው" "አፍን ዐንበርን ተመልከት"

ጭቃ: ገባር፡ በጭቃው፡ በመሬቱ፡ በርሻው የሚገብር። " ጭቃ፡ ፪ ጭቃ እንዲሉ"

ጭቃማ: ሥጋማ፡ አካለ ወፍራም ሰው።

ጭቃማ: ጭቃም፡ ባለጭቃ ስፍራ፡ ጭቃ ያለበት፡ የበዛበት።

ጭቈና: ጫና፡ የመጨቈን ሥራ።

ጭቅቅታም: ጭቅቅት ያለበት፡ የበዛበት፡ ታጥቦ የማያውቅ ሰው።

ጭቅቅት (ጸንቀቀ፡ ጽንቅቅት): የመጨቅጨቂት ዐይነት፡ ጥቍር እድፍ ቢያጥቡ አይጠራ።

ጭቅና (ኖች): የሥጋ ስም፡ ካ፲፪ቱ የበሬ ብልት ፩ዱ። ቀጪን፡ ሠጥርና ኵላሊት ሥብ ያለበት፡ ለመረቅ የሚፈለግ የሰብራዳ ክፍል።

ጭቅይት አለ: ጨቀየ።

ጭቅይት: መጪቅየት።

ጭቅጨቃ: ደፈና፡ ንዝነዛ፡ ንትረካ።

ጭቅጭቀኛ (ኞች): ጨቅጫቃ፡ ጭቅጭቅ ወዳድ፡ ነገር ቢያልቅበት የማይፈቅድ።

ጭቅጭቃም: ባለጭቅጭቅ፡ ንዝንዛም።

ጭቅጭቅ (ቆች): ንዝንዝ፡ ንትርክ፡ ውዝግብ። "፪ኛውን አጥብቅ"

ጭቅጭቅ አለ: ፍንጥቅ ፍንጥቅ አለ ውሃው፡ ጭቃው፡ ተነዛ፡ ተበተነ። "፪ቱንም አጥብቅ"

ጭቅጭቅ: የተወቀጠ የጌሾ ቅጠል።

ጭቅጭቅ: የተጨቀጨቀ፡ በመጨቅጨቂት የተደፈነ እንጀራ።

ጭብርር አለ፡ ተንጨበረረ።

ጭብርር፡ የጨበረረ፡ የተንጨበረረ።

ጭብርብር፡ የተጭበረበረ።

ጭብጨባ አልባብ፡ አለማለም፡ መጨብጨብ፡ ማጨብጨብ።

ጭብጨባ፡ የመጨብጨብ፡ የማጨብጨብ ሥራ፡ ኹናቴ፡ የዘፈን፡ የለቅሶ ማድመቂያ።

ጭብጨባ ጀመረ: ምሳሌ: "ቸብ አድርግ" እንዲል ዘፋኝ።

ጭብጭቦ፡ የጨበጨበ፡ ደፍጀፎ (ኢዮ 10: 2)

ጭብጭቦች፡ ጀፍጀፎች፡ ቅርንጫፎች (ኢዮ፲፭፡ ፴)

ጭታ፡ ሽም) ዝባን፣ ግንደበልን የሚያዝ የባላገር ሹም። ጭቃ የተባለው የኀባር መሬት ነው።

ጭነ ጥብቅ፡ ብርቱ ፈረሰኛ።

ጭነት(ጽዕነት)፡ የከብት ሸክም፡ ሲራራ፡ ቀርቃባ ወይም ሞላላ፡ ሣር፡ ዕንት፡ ደንጊያ፡ ዐፈር፡ ውሃ፡ እኸል፡ ልብስ፡ ዕታ - ማንኛውም ለሰው ጥቅም የሚኾን ነገር ኹሉ።

ጭን ጕንዳን ጨጨረ(ፀፀረ)፡ በጣም ጠጠረ፡ ጠና፡ ጠነከረ፡ "አልቈረጠም፡ አልታኘኸም" እለ የቈሎ።

ጭን(ኖች)፡ ከጕልበት በላይ ከታፋ በታች ያለ አንደኛ የእግር ክፍል፡ ሕፃን በላዩ የሚጫንበት፡ የሚቀመጥበት (ዘፀ፲፪። ዮሐ፲፱፡ ፴፩፡ ፴፪፡ ፴፫) በትግሪኛ ግን "ጭን አጥግቢኝ" ማለት ነው፡ ውፍረቷን፡ ሥጋ ማነቷን ያስረዳል። ዘርፍ ኹኖ ሲነገር፡ "የጭን በቅሎ""የጭን ፈረስ" ይላል፡ ይኸውም መቀመጫነትን ያሳያል።

ጭን ገረድ(የጭን ገረድ)፡ ጌታዋን በጭኖቿ ውስጥ የምታቅፍ፡ ወይም ርሱ ጭኑን የሚጭንባት የመንገድ፡ የዘመቻ ጊዜ ገረድ፡ ማዕርጓ ከሚስት ከቁባት የሚያንስ። ገረድን እይ።

ጭንቀት፡ ጭንቅ፡ ጥበት፡ ችግር፡ ጣር፡ ጋር፡ ሥቃይ፡ መከራ።

ጭንቍላ: ታናሽ ማሰሮ ዐይነቱን የምትበልጥ፡ የራስ ልጅ ጭንቅላት የምታክል (ምናልባት "የራስ ልጅ ጭንቅላት የምታክል" ሊሆን ይችላል) "ልጆች ሲምሉ፡ 'ከሰማይ የወረደ ጭንቍላ ያርገኝ' እንዲሉ"

ጭንቍር/ጭንኰር: ሸሐኝ፡ ዐይንን የሚጨነቍር፡ አፍንጫን የሚያበላሽ ቍስል፡ "ቍጭርን እይ" በግእዝ፡ "ጥንቁር" ይባላል።

ጭንቍር: የተጨነቈረ።

ጭንቅ(ጻዕቅ)፡ የጠበበ፡ ጥብ፡ የቸገረ፡ ችግር። "ጭንቅ አለመቃብር የለም። "

ጭንቅ በጥሬነቱ ጭንቀት ጋራ አንድ መኾኑን አስተውል (ኢሳ ፴፡ ፮፡ ፳። ኤር፮፡ ፳፬)

ጭንቅ አለው፡ ጥብብ፡ ችግር አለ፡ የሚያደርገውን ዐጣ።

ጭንቅላታም: ዘናና፡ ገመሞ ራስ።

ጭንቅላት (ጭንቅ አላት): የራስ ስም፡ የተንቀሳቃሽ ሁሉ ራስ። "ቅልን እይ"

ጭንቅላቶች: ፪ና ከ፪ በላይ ያሉ ራስ ቅሎች።

ጭንቅሎ: ዝኒ ከማሁ፡ የቍልምጫ ስም፡ ራሳም፡ ራሰ ትልቅ።

ጭንቡል(ጸቢል)፡ ጥፍት፡ ዕልም።

ጭንቡል አለ(ኮነ፡ ከመ፡ ጸበል)፡ ኼደ፡ ነጐደ፡ ካይን ተሰወረ፡ በቶሎ ዐለፈ።

ጭንቡሬ፡ ሯጭ፡ ፈጣን።

ጭንብል(ፅንብል) ፣የራስ ማሰሪያ ወይም ጌጥ።

ጭንብስብስ አለ፡ ተወነባበሰ።

ጭንብስብስ፡ የተጨነባበሰ።

ጭንብሬ፡ የሜዳ ስም፡ በታችኛው ወግዳ ያለ ሰፊ ሜዳ፡ መሮጫ፡ መጋለቢያ።

ጭንብር ቦቃ(ጭምር፡ ቦቃ)፡ በስተምዕራብ ብርሃን የተሣለባት፡ የተጨመረባት፡ በስተምሥራቅ ግን ጨለማ ያለባት ጨረቃ "ጨረቃ ጭንብር ቦታ ዐጤ ቤት ገባች ዐውቃ" እንዲሉ ልጆች። ቦቃ ጋልኛ ነው፡ ንጣትን፡ ነጭነትን ያሳያል። "ግንባረ ቦቃ" እንዲሉ።

ጭንብር፡ የሮጠ፡ የፈጠነ፡ የጠለቀ።

ጭንና ጭን፡ ኹለት ጭኖች፡ ግራና ቀኝ ያሉ (ማሕ፭፡ ፲፭)

ጭንኵሮራሰ፡ ብትን፡ ዘንጋዳ፡ እንጭብሌ። ዘሩ ጠነከረ ነው።

ጭንኰር፡ የቍስል ስም፡ ሸሐኝ (ዘፀ፱' ' ፲። ፪ጢሞ፡ ፪፡ ፲፯) ጭንቍርን እይ።

ጭንገር፡ ክፍል ክፍል ያለው የሰንጠረዥ መሥመር። ፊንገር፡ ሰንጠረዥ እንዲሉ።

ጭንገፋ፡ ምልመላ፡ ውርጃ፡ የማርገፍ፡ የማጠናወት ሥራ (፪ነገ፡ ፪፡ ፳፩)

ጭንጋፍ(ፎች)፡ ዝኒ ከማሁ፡ አለቀኑ የተወለደ፡ አካለ ጐደሎ፡ ሞኝ (ዘኍ፲፪፡ ፲፪። መክ፮፡ ፫)

ጭንግ፡ ባጤ ምኒልክ አዳራሽ ፊት ለፊት ያለ ወልወል አደባባይ፡ ሸንጎ።

ጭንግፍ(ጽንጉፍ)፡ የተመለመለ፡ ምልማይ፡ ርጋፊ።

ጭንጩ(ዎች)፡ ከባዕድ ያልተደባለቀ፡ ያልተዋለደ፡ ያልተዳቀለ፡ ያልተለወጠ ነገድ፡ ወገን፡ ሌላ ቋንቋ የማያውቅ የሰው ዘር። "ጭንጩ ዐማራ፡ ጭንጩ ኦሮ" እንዲሉ።

ጭንጫ(ጮች)፡ ኰኵሕ)፡ ከደንጊያነት በቀር ዐፈር፡ አሸዋ የሌለበት ስፍራ፡ የማይታረስ፡ የማይዘራ፡ አለት ገጠር (ምሳ፳፡ ፲፯። ሰቈ፫፡ ፲፭) ሸከረን ተመልከት።

ጭንጫማጭንጫም፡ ጭንጫ፡ ያለው፡ ባለጭንጫ መሬት።

ጭንጭራ(ትግ)፡ መቋደሻ በውስጡ ጥቃቅን ጭንጫ የሚገኝበት።

ጭኖ፡ የዕንጨት ስም፡ እሾኹ ቀንጠፋ የሚመስል ዛፍ።

ጭከና(ጥብዐት፡ ትብዐት)፡ ብርታት፡ ትግሥት፡ የመጨከን፡ የመታገሥ ሥራ።

ጭካኔ፡ ዝኒ ከማሁ፡ ክፋት፡ ድርቅና።

ጭኮ(ኦሮ)፡ የመብል ስም፡ በጨው፡ በበርበሬ፡ በቅመምና በንጥር ቅቤ የተዘጋጀ በሶ፡ ጣም ያለው ምግብ።

ጭው(ጸውዖ፡ ጸዊት)፡ መጮኸ።

ጭው አለ፡ ከሳ፡ ደረቀ፡ ቀለለ፡ የፊት፡ የደም ግባት።

ጭው አለ፡ ጨዋም ምድረ በዳ ኾነ። "ጭው ያለ በረሓ" እንዲሉ (መዝ፻፯፡ ፴፬)

ጭው አለ፡ ጮኸ፡ ጩኸት አሰማ፡ የዦሮ፡ የት፡ የወፍ።

ጭው ጭው አለ፡ መላልሶ ጮኸ።

ጭውውት፡ ንግግር።

ጭዳ(ኦሮ)፡ የሰርግ ስም፡ ሰርግ።

ጭዳ(ጭዳን)፡ የከብት ቍላ፡ አረማውያን (የቀድሞ ሰዎች) የበጉን ቍላ ፍሬውን አውጥተው በውስጡ ገለባ ይጨምሩና ሰፍተው ከፈረስ ዐንገት ያጠልቁታል፡ ስሙንም "መጤቻ" ይሉታል።

ጭዳ አለ፡ በቤት ውስጥ በአድባር ሥር ለጣዖት ለሰይጣን መሥዋዕት ሠዋ፡ የበግና የፍየል ወጠጤ፡ ወይፈን ኰርማ (የቍላ) ከብት ዐረደ። ግንባሩንና የፈረሱን ግንባር በደም ቀባ፡ ወይም ደሙን በጋሻው ቀዳ፡ አምልኮ ባዕድ አደረገ። ወደ ሰርግ ቤት ደም ረግጦ ገባ፡ ኣማረተ።

ጭድ(ዐጪደ፡ ዕጭድ)፡ የጤፍ ገለባ፡ ፈጥኖ የሚነድ፡ የበሬ መኖና ጭቃ መርገጫ (ኢሳ፲፩፡ ፯) "እከሌና እከሌ እሳትና ጭድ ናቸው" እንዲሉ።

ጭድድ፡ የተወደደ፡ ተቈርጦ የቀረ፡ ምልስ፡ ዙሪያውን የተከበበ፡ የታጨደ፡ የተሠራ።

ጭገራም፡ ጭገረ ብዙ፡ ባለጭገር።

ጭገሬታ፡ መልክ፡ መሰል፡ ምልክት፡ ሕብር ዐይነት፡ ፍለጋ፡ ጭገር ያረፈበት፡ የወደቀበት። "ጭገሬታው ጠፋ" እንዲሉ።

ጭገር፡ ጠጕር።

ጭገር፡ ጭጕኝ።

ጭገታ፡ ዝኒ ከማሁ ለጫገት።

ጭጕኝ(ተገነ)፡ የኀፍረት ጠጕር፡ የጕያ ችግኝ።

ጭጋግ(ጽጋግ፡ ቆባር)፡ ጉም የሚመስል ዐቧራ፡ በአየር፡ በምድር የሚታይ።

ጭጋግ ፊት፡ ፊቱን የማይጠዳው፡ ፊተ ጨፍጋጋ ሰው።

ጭጐት(ቶች)፡ የግንብ ሣጥን፡ የዕቃ ማስቀመጫ፡ ማኖሪያ፡ ዳግመኛም ጐለት ይባላል።

ጭጐጐት(ቶች)፡ ቅጥነቱም መጠኑም እንደ መርፌ የኾነ ጥቍር እሾኸ። በጫፉ ከልብስ ከበርኖስ የሚጣበቅ ሻካራ ጠጕር አለው፡ የንጨቱ ኹናቴ የኑግ አገዳ ይመስላል። ቢላንና ፍቅሩ ጥኑን እይ።

ጭጐጐት ፊት፡ ፊተ መጥፎ፡ አይጠዳሽ።

ጭጨት የከብት በረት ፍግ፡ መሬት የሚያሠባ።

ጭጫት፡ ብዙ ልጅ፡ ጫጨ።

ጭጫን (ፃፄ) ጕንዳን፡ ዘመሚት፡ ቍጭ።

ጭጭ በታናሽ ቃል መጮኸ። "ወፍ ጭጭ ሰማይ ብልጭ ቢል ይህ ነገር አይደረግም"

ጭጭ ምጭጭ(ጭጭ፡ ምንም፡ ጭጭ) ባሕታዊ ቅጠል ሲበላ ዕሥሥ ሢጥ ብትልበት የተሲያት እኸል፣ "ጭ፡ ምጭጭ፡ የለም" አለ ይላሉ።

ጭጭ በል፡ ዝም በል።

ጭጭ አለ(ጸመወ)፡ ዝም፡ ዕክም፡ ጸጥ አለ፡ አፉን ያዘ።

ጭጭ አለ፡ ድምዕ ሰጠ፡ አሰማ፡ ጮኸ፡ እንደ ጫጩት።

ጭጭ አይበሉ፡ የሰው ስም፡ በላቶች የወፍ ያኸል፡ አይጩኹ፡ አይናገሩ ማለት ነው።

ጭፈራ: ጭፋሮ፡ ዝላይ፡ ረገዳ። "ጮቤን አስተውል"

ጭፈቃ: ጥቅጠቃ፡ ልሰቃ።

ጭፈና: ከደና፡ ዐፈና፡ ደፈና፡ ሽፈና።

ጭፋር (ሮች): የቅንድብ ጠጕር፡ በሸፋሽፍት ፍና ጫፍ ተቀራርቦና ተደራርቦ የሚታይ።

ጭፋር: የዘንባባና የተምር ቅጠል፡ ሰሌን።

ጭፍልቅ (ቆች): የተጨፈለቀ፡ የተሠራ፡ የታረሰ።

ጭፍልቅ አለ: ተጨፈለቀ።

ጭፍልቅ አደረገ: ጨፈለቀ።

ጭፍልቅ: ዐዲስ ዕርሻ፡ ዐዲስ የብረት ዕቃ።

ጭፍራ (ሮች): ወታደር፡ የቍጥር ጦር እየጨፈረ ወደ ጠላት የሚቀርብ ስራዊት (ኢሳ፵፭፡ ፲፪። ሉቃ፫፡ ፲፬)

ጭፍርር አለ: ተንጨፈረረ።

ጭፍርር: ዝኒ ከማሁ።

ጭፍቅ (ጽፉቅ): የተጨፈቀ፡ በከባድ ነገር የተረገጠ፡ ልስቅ፡ ችፍግ፡ የተጠቀጠቀ (ኢዮ፴፰፡ ፵) "ጭፍቅ ያለ ዱር እንዲሉ"

ጭፍቅ: በ፪ በቅል የተሠራ ፲፪ ክንድ መቀነት፡ በጣም ተመቶ የተጠቀጠቀ ሱሪ የሚኾን ልብስ።

ጭፍቅ: ጥቅጥቅ ያለ ፭ያ፡ ዐርብ፡ በርሱ የተሠራ ልብስ። "ጭፍቅ ኩታ፡ ጭፍቅ ቀሚስ እንዲሉ" "ጥርሱ ቀጪንና የተቀራረበ ከኾነ ፬ያውም ጭፍቅ ይባላል። የእከሌ ዐርብ ጭፍቅ ነው እንዲሉ"

ጭፍቆ: ባለቅመም ዳቦ ቈሎ፡ እንደ ጭብጦ የተድበለበለ፡ ኳስ መሳይ የኑግ ልጥልጥ። "ሻሜትን ተመልከት"

ጭፍና: ዐይነ ጨፋና።

ጭፍና: የቀን ጨለማ፡ የጉም ዐፈና፡ ወሊስ።

ጭፍን አለ: ድፍን አለ፡ ተጨፈነ።

ጭፍን አደረገ: ክድን፡ ሽፍን አደረገ።

ጭፍንፍን: የተጭፈነፈነ፡ ክድን፡ ግልጥ።

ጭፍግ አለ: ችፍግ አለ።

ጭፍግ: ጭፍቅ፡ ችፍግ።

ጭፍጝፊ: የነገር ትርፍራፊ።

ጭፍጨፋ: ቈረጣ፡ ትፍተፋ።

ጭፍጭፍ አለ: ችፍ ችፍ አለ፡ ተቅለጠለጠ፡ የወዝ የማውጌ እንጀራ።

ጭፍጭፍ አደረገ: አንጨፈጨፈ።

ጭፍጭፍ: ማዠት። (፪ቱም፡ ፍ፡ ይጠብ ቃል)

ጭፍጭፍ: የተጨፈጨፈ፡ የጫፍ ቅንጥብጣቢ፡ ቍርጥራጭ።

ጮለ(ጦለ)፡ ብልኅ ኾነ፡ ሠለጠነ፡ ቀለጠፈ፡ ፈጠነ፡ ልጁ፡ ፈረሱ።

ጮለ፡ በጥፊ ተመታ።

ጮሌ(ዎች)፡ የጮለ፡ ብልጥ፡ ብልኅ፡ ቀልጣፋ፡ ፈጣን፡ ሯጭ፡ ሸምጣጭ። "ጮሌ ፈረስ" እንዲሉ። "ጮሌ ሲያረጅ መጋዣ ይኾናል። " አፍን እይ።

ጮሌነት ጮሌ መኾን፡ ብልኅነት፡ ፈጣንነት።

ጮሌንካ፡ የለምድ፡ የካባ መጋጠሚያ ሳንቃ።

ጮረረ (ፆረረ። ትግ፡ ፀረረ): ወረደ፡ ፈሰሰ፡ ተንቈረቈረ።

ጮረቃ: ሽንትና ዐዛባ፡ ጨረቀ።

ጮረቃ: የከብት ሽንትና የዝናም ውሃ ካዛባ ጋራ።

ጮራ (ጾር): የጨረር ብርሃን በመስኮት የሚገባ፡ ጦር ምርቅና፡ ጭራ ቅንድብ መስሎ የሚታይ። "ጀንበሯ ጮራ ሰደደች እንዲሉ"

ጮራ: የጨረር ብርሃን፡ ጨረረ።

ጮሬ (ኦሮ): መጠማጥ።

ጮሬ: ካዋሽ ወንዝ በስተግራ ያለ አገር።

ጮቀ (ጦዐ፡ ዐወገ): ነፈገ፡ ሠሠተ።

ጮቄ: የጮቅ፡ ባለጮቅ፡ ደጋ፡ ጮቅማ ስፍራ። "ኦሮም ቄን አጥብቆ ጭቃን ጮቄ ይላል" "ጨቆን ተመልከት"

ጮቄ: ደጋ ጨቀየ።

ጮቅ: የእግር ጣት ቍስል፡ ጨቀየ።

ጮቅ: የእግር ጣት ውስጥ ቍስል፡ በጭቃ ምክንያት መካከሉ ይቈስላል፡ (ይከረከራል)

ጮቅ: የክረምት ጭቃ፡ ጨቀጨቅ።

ጮነበሰ)ጠነበዘ ትግ፡ በሰ)

ጮክ፡ መጮኸ።

ጮክ አለ፡ በጣም ጮኸ፡ ድምጡን አበረታ።

ጮኸ ተንጓጓ፡ ተመመ፡ ተንጫጫ።

ጮኸ(ጸውዐ። ዕብ፡ ጻዋሕ)፡ እሪ ቍቍ አለ፡ ድምጥ አሰማ፡ "የሰው ያለኸ፡ ድረሱልኝ" አለ፡ አገረረ፡ ቡታ ሰደደ። (ተረት)"ቆቅና ባለጌ በራሱ ይጮኻል። " "ወፍ እንዳገሯ ትጮኻለች። "

ጮኸ፡ ለዳኛ፡ ለንጉሥ አቤት አለ።

ጮኸ፡ አናፋ።

ጮኸ፡ አዉ ዉዉ አለ። (ተረት)"ውሻ እበላበት ይጮኻል። " "ዥብ ከኼደ ውሻ ጮኸ። "

ጮኸ፡ አገሣ (ራእ፲፡ ፫)

ጮኸ ኵኵሉ አለ።

ጮኸ፡ ዜማ ተማረ።

ጮኸበት ተቈጣው።

ጮጮ፡ የስፌት ዕቃ፡ የወተት ማለቢያ፡ ቄጆ፡ አኮሌ።

ጮጮ፡ የወይባ ዐይነት ዕንጨት፡ ከሰል የሚኾን።

አለ፡ ዝም አለ፡ () ጯ፡ አለ፣ ከሳ፣ ጭው።

አለ፡ ዝኒ ከማሁ።

፡ የቸ፡ ተወራራሽ። "ችግኝ፡ ጭጕኝ"

ጯኺ(ዎች)፡ የጮኸ፡ የሚጮኸ፡ የተበደለ፡ አቤት ባይ (ኢሳ፮፡ ፬። ኤር፵፰፡ ፵፭)

ጯጯኸ፡ መላልሶ ጮኸ።

No comments:

Post a Comment

ሽፋን

  ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ