የ : ፲ኛ ፊደል፡ በአበገደ በጥንታዊው ተራ ቍጥር፡ በፊደልነት ስሙ የማን፡ በአኃዝነት የ፲ ይባላል።
የ (አ): ለሩቅ ሴት፡ ለሩቆች፡ ለቅርቦች፡ ወንዶችና ሴቶች፡ የአንቀጽና የዝርዝር አያያዥ፡ ፍቺው ርሱ።
"ይኸውም ዐወቀ ያት ያቸው ያችኹ በማለት ፈንታ፡ ራሱን ጐርዶ፡ ዐወቃት፡ ዐወቃቸው፡ ዐወቃችኹ እያለ፡ በርባታ ጊዜ የአንቀጹን መድረሻ ራብዕ ማድረጉን ያሳያል"። "ያ ስምን፡ ኣ አካልን ይተረጕማል"። "ስምንም ከዝርዝር ሲያያይዝ፡ እጃችን፡ እግራችን፡ ቀበሌ፡ ቀበሌያችን፡ ዕድሜ፡ ዕድሜያችን ይላል"። "አንድ ዐይነት ቅጽልንና ስምን ሲያናብብ፡ ገራገር፡ ወንዛወንዝ ያሠኛል"።
የ (ኢ): አሉታ።
"(ጥለ) አለ፡ የለ"። "፪ኛውን የለ፡ ተመልከት"።
የ (ዘ): በኀላፊ አንቀጽ መነሻ፡ ዅሉ እየገባ ባለቤት ሳይኖር በቂ ይኾናል። "የበላ በለጠኝ፡ የሮጠ አመለጠኝ"። "ያረገዘች ታስታውቅ፡ ከደረቷ ትታጠቅ"። "የፈሩት ይደርሳል፡ የጠሉት ይወርሳል"። "አባት ያበጀው ለልጅ ይበጀው"። "ዘመን የወለደው ንጉሥ የወደደው"። "፬ኛውን ይ፡ ተመልከት"።
የ (ዘ): ባለቤት ሲኖር ቅጽል ይኾናል።
"ያልሰማ ዦሮ ከጎረቤት ያጣላል"። "የሞተ ልጅ ዐንገቱ ረዥም ነው"። "ዘመን የሰጠው ቅል ደንጊያ ይሰብራል። " "ለና የ፡ ሲቀድሙት ተውጦ ይቀራል። " (ግጥም):
"ቅዱስ ሚካኤል ለወደደው ከሳት ያወጣል ከነደደው። ለየወደደው ከየነደደው ማለት ነው"።
የ (ዘ): የዘርፍ ደፊ፡ ወይም አያያዥ።
"የሰማይ አምላክ፡ የአቤል መሥዋዕት፡ የሙሴ ጽላት፡ የሰሎሞን መቅደስ"። "የልጅ ጥፉ በስም ይደግፉ ቢል፡ ጥፉ የኾነን ልጅ ያሠኛል። " "ቅጽልን፡ ከነተሳቢው ሲደፋ፡ ያህያ ውሃ ጠጪ ይላል"። "፭ኛውን ያ፡ እይ"።
የ (ዚኣ): ባለገንዘብነትን የሚገልጥ ጠቃሽ፡ ይኸውም አያያዥ ካለው ይገባል።
"ይህ ቤት የሱ፡ የሷ፡ የኔ፡ የኛ፡ የነኛ፡ የናንተ፡ ያንተ፡ ያንቺ ነው"።
የሐር ጐፍላ፡ በመጐናጸፊያ (በድባብ) (በመሶበ ወርቅ) ላይ የሚንጠለጠል የሐር ዘርፍ ጌጥ፡ ከፀምር ከጥጥ የተበጀ ኳስ (ዘዳ፳፪:፲፪)።
የሐናን ለወለተ ሐና: ያንዱን ለሌላው።
የኃጢአት ዋጋ፡ ኩነኔ፣ ቅጣት፣ ሥቃይ፣ መከራ።
የሑዳድ ፈሪ: ዕጣ ሑዳዱን ሳይሖድድ የቀረ የሚከፍለው ዕዳ።
የህንድ፡ ዶሮ፡ ባፍንጫውና፡ ባንገቱ፡ ላይ፡ እንጥልጥል፡
ያለው፡ አሞራ
' ሥጋው፡ ጣፋጭ፡ (የተሙን፡ ተቤሳ፡ ዶሮ)፡ ቅሌታም፡ ሰው።
የሕግ ጋብቻ ሥርዐት: ከለለ።
የሆድ ዕቃ ስም፡ "ምግብ የሚከማችበት ብዙ ክፍል ያለው ውስጠ ንብብር ሥጋዊ ከረጢት የጨጓራ ዘርፍ ቢያጥቡ አይጠራ:" (የሰውነት አካል)።
የሆድ ውስጥ ትል ትርጓሜው፡ "የተሻጠ የተጨመረ ጭምር ማለት ነው። ሲበዛ ሸጦች ይላል:" (የህክምና ቃል)።
የኋሊት፡ ወደ ኋላ አካሄድ፡ አረማመድ። ልጁ ፊቱን ሳይመልስ የኋሊት ይኼዳል።
የኋላ እሸት፡ የኋላ ወርቅ፡ የወንድና የሴት ስም፡ ዘግይቶ/ዘግይታ የተገኘ/የተገኘች ማለት ነው።
የኋላ የኋላ፡ ቆይቶ ቆይቶ በሐሰት ከፍ ከፍ ያለ የኋላ የኋላ መውደቁ አይቀርም።
የለ (ላለ): ባለ (ሐማሴን)።
የለ፡ የለም (ኢሀለወ፡ ወኢሀለወ): እሱ የለ።
የለ፡ የል (ኢሀለወ): "ኣለ" ያለውን "የለ" በማለት የሚነገር አፍራሽ አሉታ አንቀጽ። "ሌለን" ተመልከት። "በ፰ ሰራዊት በዋዌና አለዋዌ ሲነገር፣ ዋዌውም ም፡ ነው"።
የለሰለሰ የጣፈጠ: መብል፡ ገንፎን፣ ዐልጫ፣ መረቅን የመሰለ።
የለሽ፡ የለሽም (ኢሀሎኪ፡ ወኢሀሎኪ): አንቺ የለሽ።
የለሽ፡ የሌለው: "ዋስ የለሽ" እንዲሉ።
የለት ጕርሥ: ያመት ልብስ፡ ዐንገት ልብስ፡ ሹራብ እንዲሉ።
የለች፡ የለችም (ኢሀለወት፡ ወኢሀለወት): እሷ የለች።
የለን፡ የለንም (ኢሀለወነ፡ ወኢሀለወነ): "ዕውቀት የለን" ይላል። "ግእዝ መጪ መሩ ያማርኛውን ሞክሼ ለመለየት ነው"። የሊ (ዔሊ): ድንጋይ ልብሱ። "አዐና" እና "የ" ተወራራሽ ስለ ኾኑ ባላገር በ"ዔሊ" ፈንታ "የሊ" ይላል፡ በእተጌ ፈንታ "ይተጌ" እንዲል። "ዔሊን" እይ።
የለን፡ የለንም (ኢሀሎነ፡ ወኢሀሎነ): እኛ የለን ይላል። ሲዘረዝርም፡
የለኝ፡ የለኝም (ኢሀለወኒ፡ ወኢሀለወኒ): "ገንዘብ የለኝ"።
የለኸ፡ የለኸም (ኢሀለወከ፡ ወኢሀለወከ): "ገንዘብ የለሽ"።
የለኸ፡ የለኸም (ኢሀሎከ፡ ወኢሀሎከ): አንተ የለኸ።
የለኹ፡ የለኹም (ኢሀሎኩ፡ ወኢሀሎኩ): እኔ የለኹ።
የለው፡ የለውም (ኢሀለዎ፡ ወኢሀለዎ): "ዕውቀት የለው"።
የሉ፡ የሉም (ኢሀለዉ፡
ወኢሀለዉ):
እነዚያ የሉ።
የላመ የጣመ: የመኳንንት ምግብ።
የላም ልጅ: ከላም የወጣ፣ የተገኘ ጥጃ፡ ወተት።
የላም ጡት)፡ ሥሩ አራት ዘርፍ ያለው፤ እረኞች በክረምት መሬቱን እየቆፈሩ የሚበሉት ታናሽ የምድር ቅጠል። "አባትን"፣ "እናትን"፣ "ልጅን" ተመልከት።
የላት፡ የላትም (ኢሀለዋ፡ ወኢሀለዋ): "አላንድ የላት"፡ "እንቅልፍ የላት"። "ነቀሰንና" (ቀለፋ) ብለኸ "እንቅልፍን" ተመልከት።
የላቸው፡ የላቸውም (ኢሀለዎሙን፡ ወኢሀለዎሙን): "ትጋት የላቸው"።
የላችኹ፡ የላችኹም (ኢሀለወክሙን፡ ወኢሀለወክሙን): "ዕውቀት የላችኹ"።
የላችኹ፡ የላችኹም (ኢሀሎክሙ፡ ወኢሀሎክሙ): እናንተ የላችኹ።
የሌለ: "ያልነበረ"፡ "ሌለ"።
የሌለ: ያልተገኘ፣ ያልተቀመጠ፣ ያልቈየ፣ ያልኖረ፣ ያልነበረ። (ዘዳ. ፳፱፡ ፲፭)
የሌለበት: ያልነበረበት፣ ያልተገኘበት። (ዮሐ. ፰፡ ፯)
የሌለው: ያልተቀበለ፣ ያሊያዘ።
የሌት ወፍ፡ ቀን ተደብቃ ትውልና ሌሊት እየበረረች ምግቧን የምትፈልግ፡ እንደ ዐይጥ ጥርስና ጡት ጆሮ፡ እንደ ወፍ ክንፍና እግር ያላት ልዩ ወፍ፡ ላባ የለሽ፡ የወላዋይ ሰው ምሳሌ።
የልመና፡ ቃል፡ "ስላቦ፡ ስለግዜር፡ ስለ ጊዮርጊስ፡ ስለ ማሪያም፡ ስለ ነፍስ፡ እንዲል፡ ለማኝ።" "ብለኸ፡ ማለትንና፡ አማላጅነትን፡ ያሳያል።"
የልብ ልብ በቃው): በሰው ታመነ፡ የጭካኔ ጭካኔ ተሰጠው፡ አልፈራም፡ እንዳሻው ተናገረ፡ የያዘውን ይዞ።
የልብ ዐውቃ): ሥልጡን አሽከር። "ቈነጨ" ብለሽ "ቍንጨን" እይ።
የልብ ጩኸት: ሰረሰረ።
የልካ (ኦሮ፡ ኢልካን): የዝኆን ጥርስ፡ አንባር።
የልጅ ዐዋቂ): ጭምት፡ የረጋ፡ ቁም ነገርን የሚከተል።
የልፍኝ፡ አሽከር)፡ አንጣፊ፣ ጋራጅ፣ አስታጣቢ፣ አልባሽ፣ መጫሚያ አቀባይ፣ ዠርባ ጠቋሚ፣ ተረኛ፣ የውስጥ አሽከር።
የሎሄ: ኤሎሄ። "የሎሄ የሎሄ" አለ፡ የጭንቅ ጩኸት ጮኸ፡ "ኢዮሂ"፡ "ኢዮሄ" አለ። "ኤሎሄና"፡ "ኢዮሄ"፡ "የሎሄ" ፫ቱ ኹሉ አንድ ዘር ናቸው።
የሎሚ፡ እሸት)፡ ቅጠሉ የምስር ቅጠል የሚመስል ታናሽ ዕንጨት፣ ሽታው የሚጣፍጥ፣ በመስከረምና በጥቅምት የሚያውድ።
የሎስ (ሶች): ያሞራ ስም፡ ንስር ግልገል፡ አንሣ፡ መቀነትማ። "የሎስ ያንሣኸ" እንዲሉ። መልኩ በስተዠርባው ጥቍር አረንጓዴ፣ በስተፊቱ ከላድማ ነው፡ ባፉና በክንፉ በእግሮቹ ላይ ንጣት አለው። ከክንፍ እስከ ክንፉ ፭ ክንድ ይኾናል።
የመሰንቆ ጭራን በዕጣን ፈገፈገ።
የመስቀል መሬት: የካህን ርስት።
የመስቀል ምልክት): ማመልከቻና መካከለኛ ጣት።
የመስቀል ወፍ፡ በመስከረም ወር በመስቀል ሰሞን የምትታይ ጥቍር ድምቢጥ።
የመሸተኛ፡ ግጥም)፡ "እጅግ ያስደንቃል፡ የኛማ፡ ነገር፡ ሠርቶ፡ ለሸርሙጣ፡ ጠጥቶ፡ መስከር።"
የመንግሥታት ማኅበር: የመንግሥታት መልክተኞች ጉባኤ፣ አደባባይ፣ ዐውድ።
የመንግሥት፡ የሃይማኖት)፡ ወኪል፣ እንደራሴ።
የመዝጊያ፡ ቍላ፡ የመርዋ፡ ቍላ፡ "ማሞ፡ ቍላው፡ ታሞ"፡ እንዲሉ።
የመዝጊያ እግር: ወንዳወንዴ የመዝጊያ ቁላ። "ውስጥን" እይ፡ "ዐምሳን"ና "ሺን" ተመልከት።
የመዠመሪያው መሰነና ማሰነ አንድ ዘር ናቸው።
የመጠጥ ዐረፋ: ኰረፌ (የመጠጥ አረፋ)።
የመጣ ቢመጣ: አስቀድሞ የተደረገ መከራ ወደፊትም ቢደረግ።
የመጣፍ ገበሬ፡ መጣፍ ዐዋቂ ሊቅ።
የመጥረቢያ ልጅ: ጥልቆ።
የመጥፎ ሴት ግጥም): "ዐጪሬን ሞንዳሴን ሲኼድ እያየኹት፡ የልጆቼን አባት ጕስርን ጠላኹት።"
የሙሾው አዝማች: "ሰው ሰው። "
የሙቀጫ ልጅ: ዘነዘና።
የሙት ልጅ: አባት እናቱ በሕፃንነቱ የሞቱበት፡ በግእዝ ዕጓለ ማውታ ይባላል።
የሙጥኝ አለ: ተማጠነ፡ የሰውን ልብስ ያዘ፡ ተቈራኘ።
የሙጥኝ: ተማጣኝ፡ የሚጠጋው ሰው።
የሚ (ዘይ): በትምቢት መነሻ እየገባ ለሩቅ ወንድ፡ ለሩቆች ወንዶችና ሴቶች ቅጽልና በቂ ይኾናል። "የሚሞት ሽማግሌ አይርገምኸ"። "የሚያድግ ልጅ አይጥላኸ"። "የሚማሩ ልጆች"። "የሚመጣ ይምጣ"። "አመነ፡ አሳየ፡ ዐወቀ" ብሎ የትንቢቱን ቅጽል፡ "የሚያምን"፡ "የሚያሳይ"፡ "የሚያውቅ" በማለት ፈንታ፡ "የሚአምን"፡ "የሚአሳይ"፡ "የሚዐውቅ" ማለት የስሕተት ስሕተት ነው።
የሚስቱ ሙሾ: "አወይ ዝንጀር ጐሹ፡ ውድማ ፈላሹ፡ የኔን ነገር ወትሮ እያሉብኝ ችላ፡ በጡንቻኹ አደገ የክንፉ ቡችላ። "
የሚሻ፡ ሻ፡ ሻየ: (የመፈለግ ግስ)።
የሚታይ: ሰማይ፣ ፀሓይ፣ ጨረቃ፣ ኮከብ፣ ደመና፣ ዝናም፣ ምድር፣ ውሃ፣ እሳት፣ እንስሳ፣ አውሬ፣ ወፍ፣ ሰው። (በዓይን የሚታዩ ነገሮች)።
የሚዛን ቈዳ: በገመድ የተንጠለጠለው ቋቱ።
የሚደፋ፡ በመደፍ፡ ብል።
የማ (ዘኢይ): የትንቢት አሉታ በቂ ቅጽል መነሻ። "የማይሠራ አይብላ"። "የማይማር"፡ "የማይማሩ"። "አይን" ተመልከት።
የማ): የትንቢት አሉታ፡ በቂና ቅጽል መነሻ።
"ያይወድ፡
ያይለያይ፡ ያይጠላ" (ማር፡ ይሥ፡ ገጽ፡ ፬)። ምእላድ እየኾነ በቃል መጨረሻ ይገባል። "ጠደፈ፡ ጥድፊያ፡ ጻፈ፡ መጻፊያ፡ ጠረገ፡ መጥረጊያ፡ እንግድ፡
እንግዲያ፡ እንከ፡ እንኪያ፡ ቀረበ፡ አቀረበ፡ አቅራቢያ፡ ዘመመ፡ አዘመመ፡ አዝማሚያ"።
የማምሻ: ከመሸ በኋላ የሚነድ የማታ ማገዶ።
የማሪያም ምሳ: መዠመሪያው የአራስ ገንፎ።
የማሪያም ግርዝ: ወሸላ ኹኖ ያልተወለደ ሕፃን።
የማር - እሸት)፡ ቀጠላ፣ ዐዲስ ማር።
የማር ልጅ: ማር የተቀባ አውራ ጣት ጠብቶ "ልጅ" የተባለ።
የማር ሰፈፍ: "ማር ጠጅ ሲጣል ሲነጠር ይንሳፈፋል። በግእዝ: 'ምዕ'፣ ባረብኛ: 'ሸመዕ'፣ ባማርኛ: 'ሠም'፣ ሻማ ይባላል። ይኸውም ግግሩ፣ ልጥልጡ እየቀለጠ ጧፍ፣ ፋና የሚሆን ነው። ሻማ ግን በፍ ፈንታ ይነገራል።"
የማር በሶ: ሻሜት (ጣፋጭ ምግብ)። ግጥም: “ድኻ ሲናገር ሬት ኮሶ፡ ሀብታም ሲናገር የማር በሶ። ” ተመልከት: “ሻሜትን”።
የማርያም ዘንግ: ችርንችር፡ በትረ ሙሴ።
የማን: የፊደል ስም "የ"፡ ቀኝ ማለት ነው።
የማዕርግ ስም: በግእዝ "ቀኛዝማች" ማለት ነው።
የማይምን መልስ: "የተማሪ ወዳጅ ቢቀር ምን አባቱ፡ ጐራዴ ሲመዘዝ ይላል ባዛኝቱ። "
የማይታይ: እግዜር፣ መልአክ፣ ነፍስ፣ ነፋስ፣ ሐሳብ፣ ድምፅ የመሰለው ኹሉ። (በዓይን የማይታዩ ነገሮች)
የም (ዘ): ለቅርቦቹ ለ፫ቱ ሰራዊትና "እኔ"፡ "እኛ" ለሚሉ በትንቢት መነሻ እየገባ ቅጽልና በቂ ይኾናል። የምትማር (አንተ፡ እሷ)፡ የምትማሩ፡ የምትማሪ፡ የምማር፡ የምንማር። ተመልሰሽ "የሚን" እይ።
የምሳሌ ታሪክ: በ፰ኛው ሺ ሰው ሁሉ ያልቅና ምድር ባዶ ስትሆን፡ "ምነው ይኸ ዛፍ ሰው በሆነ" የሚባልበት ጊዜ ይመጣል ይላሉ።
የምሥራች: ሙሽራው ሙሽራይቱን ባወቀ ጊዜና ልጅ ዳዊት በደገመ (በጨረሰ) ሰዓት የሚቀበለው ስጦታ ወይም ሽልማት።
የምሥራች: የደስታ ወሬ፡ ምሥራች።
የምሥጥ ቤት: ኵይሳ።
የምሩ: ውሃ ሥንቁ፡ የደስታ ተክለ ወልድ አያት፣ የአባት አባት።
የምሩ: የሰው ስም፡ አባትና እናት ወልደው ከሞተባቸው በኋላ የወለዱትን ልጅ "የምሩ" ይሉታል፡ "አምላክ ይኸን ልጅ የሰጠን የውነቱ ይኾን" ማለት ነው ሲዘረዝርም "የምሩ፣ የምርኸ፣ የምራቸው፣ የምራችኹ፣ የምሯ፣ የምርሽ፣ የምሬ፣ የምራችን ነው" ይላል።
የምሩ: የውነቱ፡ መረረ።
የምር: የውነት፡ መረረ።
የምር: የውነት፣ የርግጥ። "እከሌ ይህ ነገር የምርኸ ነውን። "
የምሽት ረዴ: በሥራ፣ በነገር እንዲመሽ የሚያደርግ።
የምሽት አለ: ፈጽሞ መሸ።
የምቡት የምቡት: የልጆች ፈሊጥ።
"የምቡት የምቡት፡ ይኸን ያልመታ ይሞት"።
የምድር አጫዋች)፡ ድንክ ሰው።
የምድር ዕንብርት: ኢየሩሳሌም (የአለም ማዕከል እንደሆነች የሚታመንባት)።
የምድር ዳቦ): ቅጠሉ ኮባ የሚመስል ታናሽ የምድር ፍሬ። ከማነሱ በቀር ዳቦ የሚመስል፤ እሱንም እረኞች ይበሉታል።
የምድር ጉድ፡ ድንክ፣ ዐጪር ሰው፣ በሽንብራ ጥላ የሚውል።
የሞተ ሞተ: የተለየ ተለየ፡ አይመለስም።
የሞተ እንጀራ: ጥሬነት የሌለው፡ ተዘርቶ የማይበቅል፣ ተፈጭቶ፣ ተቦክቶ፣ ተጋግሮ በመሶብ ያለ፣ እገበታ የቀረበ እንጀራ።
የሞት ሞት: ሞትን የሚሽር ሕይወት ክርስቶስ።
የሞት ሞት: የሥጋ ወደ መቃብር መውረድ፡ የነፍስ እገሃነም መግባት።
"እስረኛው ከወህኒ ቤት የሞት ሞቱን አመለጠ" ቢል፡ "ብሞትም ልሙት" ብሎ ማለት ነው።
የሞት ጥላ)፡ ውድቅት፡ ድቅድቅ ጨለማ፡ በጨለማ ላይ የተጨመረ የዛፍ፡ የገደል ጥላ፡ ምሳሌ በኀጢአት ላይ የሃይማኖት ክሕደት (ኢዮ፫፡ ፭። ኢሳ፱፡ ፪)።
የሞጋሳ ልጅ: በፍቅር፣ በወዳጅነት ብዛት ካባቱ ቤት ወጥቶ በዘመድ ወይም በባዕድ ዘንድ ማደጎ የኾነ።
የሠለስት: የሦስትኛ ሰዓት ጸሎት አቍጣሮ።
የሠላጢን መሬት: የወታደር ይዘታ። "ጠፋንና ለማን" ብለኸ "አሸን" እይ።
የሰማ ገማ፡ ክፉ ነገርን ሰምቶ የተቀበለ፡ ተነቀፈ፣ ተቀጣ። (ተረት)፡ "ተማክሮ የፈሱት ፈስ አይገማም"።
የሠሥቴ ከስቴ: የሠሠተ ከሳ፡ የሠሢታ ከሲታ። ጕይዲ ግን ዐጪርና ቀጪን ቅጠል አረንጓዴ መልክ ይለዋል።
የሠርክ (ዘሠርክ): የምሽት ጸሎት፡ ዜማ፡ አቍጣሮ።
የሰዓት መርፌ: ሰዓትን፣ ደቂቃን፣ ካልኢትን፣ ቅጽበትን የሚቆጥሩ ፫ መርፎች።
የሰው ምሰሶ): እህል።
የሰው ስም: "ምሥራቃዊ ስማዕት" (ስንክሳር፡ ጥር ፲፪)። በጽርእ: ቴዎዶሮስ 'የእግዜር ስጦታ' ማለት ነው ይላሉ።"
የሰው ስም: ትርጉሙም የነጠረ፣ ንጥር፣ ጥሩ፣ ወይም መጨረሻ፣ መደምደሚያ ማለት ይመስላል። (ለምሳሌ: ኮላስ)
የሰው ስም: የሺ ሰው አዛዥ፣ የሺ ጌታ፣ የሺ እመቤት። አንጻር: "ሺውን ሰው በፈቃድኸ ኣውል ማለት ነው።"
የሰው ስም: የአብርሃም አባት።
የሰው በታች: ሞኝ፣ ወራዳ።
የሰው ዥብ): ተፈጥሮው ሰው ሲሆን እንደ ዥብ ሰው የሚበላ።
የሰውነት ክፍል ቀጥ አለ: ቀና አለ።
የሰይጣን መልክተኛ: ጋኔን ወይም ክፉ ሰው። (፪ቆሮ. ፲፪፡ ፯)
የሰዳጅ፡ የላከ፣ የተመረጠ (የሥጋ ብልት)። "የሰዳጅ፡ ለወዳጅ፡ እንዲሉ።"
የሳታት፡ ሰላምታ)፡ ስንኙ ሦስት እየኾነ የተደረሰ ግእዛዊ ግጥም፤ "ሰላም ለከ ኪ ክሙ" እያለ የሚነሣ።
የሴት ምራቋ ደንዳና ነው: ስታበስል ከዚያም ከዚያም ትቀምሳለች። "ቈበርን" እይ።
የሴት ስም: "የግሼ ባላባት ያገባት የወሎ ባላባት ሴት ልጅ። ብዙ ልጆች ስለ ወለደች አባቷ ልጄ ሺኋ አላት። በዚህ ምክንያት የልጆቿ አገር ሺዋ ተባለ ይላሉ። (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ)።"
የሴት ስም: ቦለለ።
የሴት ስም: ያብርሃም ሚስት።
የሥላሴ ሦስትነታቸው: በአካልና በአካላዊ ግብር በስም ነው።
የስሚስሚ: የመስማት መስማት፣ የወሬ ወሬ። (ብዙ የመስማት ወይም የወሬ መብዛት)
የሥጋ መልሚያ: ያጥንት መለምለሚያ ምግብ።
የረር: ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ያለ ተራራ፡ በሐረርጌም የሚገኝ ቀበሌ።
"ኤረርን"
እይ።
የሩቅ፡ ሴት)፡ እሷ።
የሩፋኤል ጠበል)፡ ጳጕሜ ፫ ቀን የዘነበ ዝናብ። ሰው ሁሉ ይታጠብበታል፤ ሴቶችም እቡሖ ዕቃ ይጨምሩታል።
የራስ ድጋፍ: ራሰራስ።
የራስጌ፡ ሰይፍ)፡ ዐልጋ ላይ በከዳ ውስጥ የሚቀመጥ። በግእዝ መተርእስት ይባላል።
የርሱ: የሱ፡ የዚያ፡ ርስ፡ እስ።
የርብርብ፡ የርዳ፡ ተራዳ፡ ጠብ፣ የጕንዳን፡ አያያዝ።
የርቦራ: የዝኆን ጥርስ፡ አንባር፡ ጠላቱን ለገደለ የሚሰጥ።
የርጎ ዝንብ: ጥልቅ ብዬ ወንድ ወይም ሴት።
የሸሎ ምስጢር: በደም ሥር መስላትን ያሳያል።
የሸማኔ ዕቃ: ሸማ መሥሪያ ዐርብ (የሸማኔ መሣሪያ)።
የሸበለለ: የሚሸበልል፣ ጠቅላይ።
የሸንበቆ ምርኵዝ: መቃ (የያዥውን እጅ ተሠንጥሮ እንዲወጋ)፡ አምኖ የተጠጋውን የሚጐዳ እንጂ የማይጠቅም (ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰደ ምሳሌ)።
የሺ አለቃ: ጦር ጠቅላይ፣ አገረ ገዢ። "ከባላምባራስ እስከ ራስ ያለ የሺ ጭፍራ አዛዥ ምክትሉ ሻምበል ነው። ከሺ በላይም ሰራዊት ቢኖረው፣ ሻለቃ ይባላል (ዘፍጥረት ፬። ዘጸአት ፲፰፡ ፳፩)። የሻላን ተመልከት።"
የሺ: የሴት ስም፡ የሺመቤት ከፊል።
"ሺን"
ተመልከት።
የሻላ ሀብተ ማርያም: የጠራ ገሊላ ባላባት።
የሻላ ጥሬ ወርቅ: ዝኒ ከማሁ፡ ፩ኛው ልጅ፡ ፪ኛው አባት።
የሻላ: የቀድሞ ማዕርግ ስም፡ የሻለቃ ከፊል፡ ባለግምጃ ሱሪ።
የሼጠ: የሚሼጥ፣ ለዋጭ፣ ዐጣሪ፣ ባለመደብር።
የሽንብራ ኩፍታ (ትግርኛ): (የምግብ አይነት)።
የሽኮኮ ጐመን)፡ የዱር ቅጠል፣ የሽኮኮ መኖ፣ የተስቦ መዳኒት።
የሾለ: ሾለ።
የሾከከ፡ ጥላ ቢስ።
የሾጠጠ: "እንደ ዐለን በስተላይ የቀጠነ።"
የቀለም አባት: አስተማሪ።
የቀረ: የተተወ፣ ያለፈ፣ የተረሳ ነገር።
የቀረ: ያልመጣ።
የቀበሌ ስም: በላስታ ክፍል ያለ፣ ገጠር።
የቀበጠ ቤት: ያጌጠ (የተሸለመ)፡ ያማረ (ዕልፍኝ)።
የቀባጭ፡ ሰው፡ አያገባው፡ ገብቶ፡ ስለ፡ ሠራና፡
ስለ፡ ተናገረ፡ የሚከፍለው፡ ዕዳ፡ መቀጮ።
የቀትር: በቀትር የሚጸለይ ጸሎት፣ አቍጣሮ። "የቀትር እባብ፣ የቀትር ጋኔን" እንዲሉ።
የቀድሞ ዘመን ነፍጥ: (የጦር መሳሪያ አይነት)።
የቀጨማ፡ የጠፋ፡ ከብት፡ ይዞ፡ ለተጎን፡ ወይም፡
ላሳደረ፡ የከብት፡ ጌታ፡ የሚሰጠው፡ ገንዘብ፡ (አንድ፡
ብር)። ዳግመኛም፡ የዥብ፡ አፍ፡ ይባላል።
የቍላ፡ ያልተወቀጠ፡ ያልተቀጠቀጠ በሬ።
የቍራ መላክተኛ: ከተላከበት ያልተመለሰ፣ የኖኅ ቍራ፡ ወይም ሰው።
የቍራ ምሳ: ውስጡ ደም የሚመስል የወይናደጋ ዐረግ ፍሬ ወይም እርሱ ራሱ ዐረጉ።
የቍር: በቡልጋ ውስጥ ያለ ቀበሌ።
የቍርኣን፡ ካህን)፡ ሸኅ።
የቍጥር ስም ፲፪: ዐሥር ጊዜ መቶ ወይም መቶ ጊዜ ዐሥር። (አንድ ሺህ)
የቈላ ዛፍ: ሞፈር፣ ቀንበር የሚሆን ዕንጨት። "ቡክቡካን አስተውል።"
የቈሎ ተማሪ: ቈሎ እየበላ የተማረ።
የቈዳ ግልድም (ትግ): (የቆዳ መሸፈኛ)።
የቈጣሪ፡ ድርን፡ ቈጥሮ፡ ለቋጠረ፡ የሚሰጥ፡ አነባበሮ። "ድረሽ፡ የቈጣሪ፡ ይዘሽ"፡ እንዲል፡ ሸማኔ።
የቅ: የጭ፡ ወዲያ፡ ቀና፡ ጨ። ተወራራሾች ስለ ኾኑ "የጭ" በማለት ፈንታ "የት" ይላል። "ቂርቆስ"፡ "ጨርቆስ"።
የቅሬ ልጅ: ካጣሪ፣ ከመሸተኛ የተወለደ ማንዘራሽ።
የቅርብ፡ ሴት)፡ አንቺ።
የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ ስም ሲኾን መጨረሻው ሳድስ ፊደል በኃምስነት ይነገራል። (የሰዋስው ህግ)
የቅብጢ፡ ቅብጢ፡ የቀበጥ፡ ቀበጥ።
የቅንቦ ወተት): የተፈተነ፣ የመጋኛ መድኀኒት።
የቅጠል፡ ከፍታት፡ በፊት፡ አለቀኑ፡ የተበላ፡ ተዝካር። የቅጠል፡ ማለት፡ ጕዝጓዙን፡ ያሳያል።
የቅጽል ባዕድ መነሻ ከደጊመ ቃል ተደራጊ አንቀጽ የሚወጣ: "ከረከረ፡ ተሽከረከረ፡ ሽክርክር። ቈጠቈጠ፡ ተሽቈጠቈጠ፡ ሽቍጥቍጥ። ቀረቀረ፡ ተሽቀረቀረ፡ ሽቅርቅር።" (የሰዋስው ህግ)
የበረት (መሥዋዕት): በበረት የሚደረግ መሥዋዕት፡ የኦሮሞ አምልኮ። ተመልከት: “ቦረንትቻን”።
የበረት ልጅ: ዐጥር ግቢ የተወለደ ዲቃላ፡ ወላጁ ያልታወቀ።
የበሬ ሽንት መሸኛ: የቀዳዳው ዙሪያ።
የበሬ፡ ሽንት)፡ ውልግድግድ (የሸማ ጥበብ)፣ የምሽግ መሰናክል።
የበሬ፡ የበቅሎ፡ የፈረስ፡ የቤት፡ የንግድ፡
የማይ ዕቃ እንዲሉ። ሲበዛ ዕቆች ይላል (ዘፀ፴፭፡ ፲፮)። "ቡሖን ሆድን ለመጠ፡ ላመ ብለሽ ልሙጥን፡ ልምን እይ" (ሌሎች ቃላት ለማየት የሚያመላክት)።
የበቃ: ቅዱስ የሆነ፡ እረፍት (ግዝፈት) የማይከለክለው፡ ኃላፊያትንና መጻኢያትን የሚያውቅ። ምሳሌ: “እሴይ የበቃ፣ የነቃ ልጅ ወለደ። ”
የበታች በታች: መጨረሻ ታች ስፍራ፣ ጭፍራ።
የበትና፡ ሰላምታ)፡ በበገና የሚዘመር ያማርኛ ግጥም።
የበዓል ተቃራኒ: ውሃ ዋና፣ ሰንጠረዥ፣ በገና፣ ፈረስ ግልቢያ፣ ብረት ቅጥቀጣ፣ ጽፈት፣ ድጕሰት፣ ንግድ የመሰለው ኹሉ። ሲበዛ ሥራዎች ይላል። (የቤት ሥራ): ሕንጻ፡ ግንብ። (የወዲያ ሥራ): የውጭ አገር፡ የፈረንጅ። (የሰይጣን ሥራ): ክፋት፡ ጥመት፡ የመሰለው ኹሉ።
"እጀ ሥራ፣ ሸማ ሥራ፣ ክፉ ሥራ፣ ደግ ሥራ" እንዲሉ። (ኹለተኛ ሥራ): መሞት፡ መፍረስ፡ መበስበስ (የተፈጥሮ ተቃራኒ)።
የበኵር ልጅ: መዠመሪያ የተወለደ፡ በኵር የኾነ ልጅ፡ በኵር የወለደው።
የበግ ላት: የቅጠል ስም፡ ዠርባው ነጭ የኾነ፡ ገላላ ቅጠል።
የቡና አለገ፡ አንድ ዐይኑን ገድሎ ባንድ ዐይኑ እየ፡ አወለገ፡ አነጣጠረ።
የቡድን አባት: የገና ጨዋታ አለቃ።
የቢስ የቸር: የክፉ የበጎ። ምሳሌ: “ዛሬ ሌሊት የቢስ የቸር ሲለኝ (ሲያሳየኝ) ዐደረ”።
የባሕር ሠላጤ: ልሳነ ባሕር (የዓደን፣ የፋርስ)።
የባሕር፡ ቍልቋል)፡ ከበርበር የመጣ እሾኻም ተክል፤ ፍሬው የሚበላ።
የባሕር ዐረፋ: ይደርቅና የዛገ ብረት መወልወያና መድመፅ የሚኾን ሻካራ ድንጋይ (ደረቅ የባህር አረፋ)።
የባሕር ዘንዶ: (ኢሳ 27:20)።
የባሕርይ ልጅ: ካባት ዘር፣ ከናት ደም ተከፍሎ የተወለደ፡ ያጥንት ፍላጭ፣ የሥጋ ቍራጭ።
የባል መልስ): "ለልጆቼ ብዬ ብከሳ ብነጣ፡ ጕስር የሚሉ ስም ከየት አባትሽ መጣ።"
የባል፡ ዶሮ፡ ባለምድር፡ ለመልከኛ፡ ባውዳመት፡ የሚሰጠው፡
ዶሮ።
የቤት አውሬ: ውሻ፣ ድመት፣ ዐይጥ። "አርዌን" ተመልከት።
የብስ (የብሰ): ደረቅ ምድር፡ ባሕር የሌለባት።
የብረት፡ ልጥ) ፡ ሥሥ፡ ብረት፡
የሳንቃና፡ የንጨት፡ ማእዘን፡ ማ ያያዣ፡ የጣቃ፡ መቀፈጃ ።
የብረት፣ የብር፣ የወርቅ፣ የንሓስ፣ የመዳብ ክር: ቀጪንና ወፍራም (ሕዝቅኤል ፵፩፡ ፲፮፡ ፳፮)። (የቁሳቁስ አይነት)
የብረት ጋን፡ ከብረት የተበጀ። "ደምን" ተመልከት።
የብርድ የዝናም ልብስ): በብርድና በዝናም ጊዜ የሚለበስ።
የተ ያዲስ ግንብ ልብስ: በረከ።
የተለመጠጠ: የተቃጠለ፣ የተገረፈ፡ የሰፋ ስፋት ያለው መሬት።
የተላከ: የደብዳቤ አርእስት።
"የተላከ ከአቶ እከሌ"
እንዲሉ።
የተመች: የተረታ ሰው፡ ለፍርድ ስለ መመቸቱ የሚከፍለው ትርፍ እዳ። ይህ ቋንቋ በሐረርጌ ይነገራል።
የተመኝ: የወንድና የሴት መጠሪያ ስም፡ "አባት የተመኘውን ልጅ አገኘ" ማለት ነው።
የተማሪ ግጥም: "ተማሪ ጠጅ ነው፡ አዘንብለሽ ጠጪው። ማይም ምን አተላ ነው፡ ምን ጊዜም አታጪው። "
የተሰረሰረ: የተበሳ፣ ብስ፣ ነዳላ፣ ሰባራ (ሸክላ፣ ብረት፣ ግንብ፣ ቅል)።
የተረሳ ግስ: በ፪ ከባቢ ታጥሮ የሚጻፍ ትርጓሜ ኣልባ ግስ፡ (ከተለ፣ መካ፣ ዐገሠ፣ ዐወሰ፣ ዐጠቀ፣ ቀበለ፣ ቀመጠ፣ ሳነ፣ ሻገረ፣ ሸከመ)፡ ይህን የመሰለ ኹሉ።
የተራራ፣ የገደል፣ የግንብ መጋጠሚያ: የዠርባ ወንዝ መሳይ ጠባብ፣ የዳገት መንገድ (ነህምያ ፫፡ ፳፬፡ ፳፭)።
የተሸሪሞጠ: ሥርድጕድ፣ ጐደሎና ሙሉ።
የተሻ ወርቅ: የሰው ስም።
የተሻ: የተፈለገ።
የተቀበለ፡ የተቀበለች፡ ቅብል፡ የኾነ፡ የኾነች፡ (ሮሜ ፲፪፡ ፪ ፣ ፲፭፡ ፲፮)።
የተቃረ: የጐመዠ፣ የሠየ።
የተተረጐመ: የተፈታ፣ የተገለበጠ፣ የተıለ፣ ግልጥ ንግግር።
የተታታ: ጥፍር፣ ውስብስብ፣ ጥልፍልፍ፣ ቍልፍልፍ (የስንደዶ፣ የክር፣ የገመድ ጠፍር)።
የተትረፈረፈ: ተርፎ የፈሰሰ።
የተንቀሳቃሽ ስም: "በፈትላ መሰላልነት ከላይ ወደ ታች የምትወርድ፣ ከታች ወደ ላይ የምትወጣ ተሐዋሲት። ዳግመኛም በዱር ዕንጨት ላይ ከቀኝ ወደ ግራ ከግራ ወደ ቀኝ ሌሊት ስታደራ ታድራለች። የግእዝ ስማ፡ ሣሬት ነው።" (የእንስሳ ዝርያ)
የተንቃቃ: የሞቀ፣ የደረቀ (ቅይጥ እንጀራ)፡ የተጕላላ ሰው።
የተካነ: የጣመ፣ የጣፈጠ ወይም የመኳንንት ወጥ።
የተካነ: ዲያቆን ወይም ካህን (ቄስ) የሆነ፡ የሠለጠነ።
የተክል ስም: "ነጭና ቀይ ተክል ለወጥ ቅመም የሚኾን። ነጭ ሽንኵርት፡ ቀይ ሽንኵርት እንዲሉ። ሲበዛ ሽንኩርቶች ይላል።"
የተክል ስም: ጣዕም ከመዐዛ ያለው ተክል።
የተዋበ/የተዋበች: ያማረ/ያማረች።
የተዝካር ቀኖች እንደ ፴ (30)፣ ፵ (40)፣ ፹ (80)፣ መንፈቅ (ግማሽ ዓመት)፣ ሙት ዓመት (አንድ ዓመት)፣ እና ፯ (7) ዓመት ተብለው ይጠራሉ። (ገነደሰን የሚለውን ተመልከት)።
የተደቀለ የአማርኛ ፊደል: (ለምሳሌ ቸከለንና ቸኩለን ተመልከት)።
የተዳረ፡ የተሰረገ፡ ሚስት፡ ያገባ፡ ጕልማሳ።
የተገባ: የበጀ (የተመቸ፣ የቀና)፡ ምቾት (ቅን) ነገር።
የተጣራ፡ ሰውን የጠራ።
የተጣራ፡ የማር፡ የወይን ጠጅ።
የተጣራ፡ ጠጅ፣ ጠራ (ጸርየ)።
የተጣበበ: ጐለጐለ።
የታቦት እግር: ቄስ ታቦት ተሸካሚ። "ከሺህ ምስክር የታቦት እግር" እንደሚባለው።
የታቦት ዘፈን: "ያምናን ቀን ዐማኹት፡ ላፌ ለጠብ የለው፡ የዘንድሮው መጣ፡ እጅ እግር የሌለው። "
የታችኛውና የላይኛው ሶርያ: የአሶር የአራም ቋንቋ። "ሶርያን እይ።"
የታደለ (ች፡ ሉ): ዕድላም፡ ባለዕድል።
የቴፈ ሥር: በግእዝ፡ ተፈየ ነው።
የት (አይቴ): ንኡስ አገባብ፡ የጥያቄ ቃል፡ የቦታ በቂ። ከአንቀጽ በፊት እየገባ ይነገራል።
"የት አለኸ"፡ "የት ባጀኸ"፡ "የት ዋልኸ"፡ "የት ከረምኸ"፡ "የት ኼድኸ"፡ "የት ዐደርኸ"፡ "የት ሰነበትኸ"። መምህራንም በ"የት"
ፈንታ
"ሔት"
ይላሉ። ደቂቅ አገባቦች እንደ
"ከ"፡ "ወደ" "እስከ"
መነሻ ሲኾኑት፡ "እንዴት"፡ "ከየት"፡ "ወዴት"፡ "እስከ የት" ይላል። በዝርዝርነት የስም ምትክ ሲኾን፡ "የቱ የትኛው ነው"፡ "የትኞች ቹ የኛዎች ቹ ናቸው"፡ "የትኛዋ ይቱ ናት" ይላል። "የየት ነኸ" ቢል፡ የየት አገር ሰው ያሠኛል፡ ቅጽልነትንም ያሳያል። (ተረት):
"አገርኸ የት ነው፡ ማሪያም ውሃ፡ እንግዲያውማ ዘመዴ ነኻ"።
የት እየለሌ: በጣም የተለያየና የተራራቀ ስፍራ፡ ግሼና፣ ቡልጋ፣ ሐር ዐምባና ቈቦ እንደ ማለት ያለ።
የት እየለሌ: እጅግ መራራቅን ያስረዳል።
"(ለሌ)ን" ተመልከት።
የት ውዬ የት ዐድር ብዬ: የወፍ ጩኸትና ስም።
"እዛፍ ላይ ብሠራ አሞራው መከራ፡ እካብ ላይ ብሠራ እባቡ መከራ፡ እምድር ላይ ብሠራ እረኛው መከራ፡ የት ውዬ የት ዐድር ብዬ ትላለች" ይላሉ።
የትም የት: የትም የት ሲኼዱ ከግ (መዝ፻፴፱፡ ፯-፲፡ ዮና፩፡ ፲፮፡ ፪፡ ፩) ዜር አያመልጡ።
የትም:
"ም"
ዋዌ ነው።
"ፈጨን"
እይ።
የትንባኾ ዱቄት: ካመድ ጋራ፣ ሥንቀን፣ ጕርፎ።
የነበረ: የነበረ፡ "ገብሬል ተወገረ። "
የነቢ: በበረት ፉካ ውስጥ የሚቀመጥ የቦረንትቻ መሥዋዕት፣ የበግና የፍየል ሥጋ ብልት ቅንጣቢ፡ የጕሽ አተላ፡ ቈሎ በያይነቱ ርሚጦ።
የነቢ: የነቢይ ፈንታ፣ ድርሻ።
የነካ ነካ: የዞግ ዞግ፣ የሳቢያ ሳቢያ፡ አንዱን የነካ ነገር ሌላውን ነካ፡ በጓዱ ሰበብ ባልንጀራው ተያዘ ማለት ነው። "ዳፈ ብለኸ ዳፋን"፣ "፪ኛውን ተረፈ" አስተውል።
የነጂ: ተጠብሶ እረኛ፣ ከብት ጠባቂ የሚበላው (የፍየል፣ የበግ ወጠጤ፣ ቍላ)።
የነጂ: የረኛ አበል፡ ነዳ።
የነገር ሠረገላ: ስውርና ድብቅ።
የነገር አባት: ጠበቃ፣ ነገረ ፈጅ።
የነገድ ስም: "በዳሞት ባባይ ዳርና ዳር በሌላም ስፍራ የሚገኝ ሕዝብ።"
የነገድ ስም: በታናሽ እስያና ባውሮጳ በግሪክ አገር የሚኖር ሕዝብ።
የነገድ ስም: በወለጋ ክፍል ያለ ሻንቅላ። "ገና ጀ ተወራራሽ ስለ ኾኑ ሸሖጀሌ ተብሎም ይጠራል።"
የነገድና ያገር ስም: "ሴማዊ ነገድ የምሥራቅ መዠመሪያ (ዘፍጥረት ፲፩፡ ፪) የህንድና የመስኮብ ጎረቤት። በግእዝ: ሲን ይባላል። (ተረት) ሺን ዐሸን። ስኒን ሻይን እይ።"
የነጋሪት አገር: ባለነጋሪት የሚገዛው።
"ፈራ"
ብለህ
"አፈራን"
እይ።
የነጠነጠ ሥር: በግእዝ ነጢጥ ነጠ ነው።
የነፍስ ልጅ/የንስሓ ልጅ: ኀጢአቱን በቄስ ፊት የሚያምን ክርስቲያን።
የነፍስ ዋጋ፡ ጉማ፣ ወጆ፣ የቀንድ ከብት (ሰማኒያ ብር)።
የኔ (የእኔ): መዠመሪያውን "የ" ባ፭ኛ ተራ ተመልከት።
የኔ ቢጤ: የኔ ባልንጀራ፣ የኔ ዓይነት፡ ድኻ፣ ለማኝ።
የኔታ: የኔ (የእኔ) ጌታ፡ ጌታዬ፡ አስተማሪዬ፡ መምሬ።
የንስራና የጋን በሽታ: "ከቡሖ ከጠላ የሚመጣ የውስጥ ቅርፍርፍነት - ፍርክርክነት።"
የንጨት፡ ሽበት)፡ ሽብቶ ሳለ ግብሩ መጥፎ የኾነ ሰው። ወረረ ብለኸ አወረረን እይ።
የንጨት ቤት: ከሳንቃ የተሠራ ሕንጻ።
የአሕዛብ ነገሥታት ዐይን በፍላት ያፈሳሉ።
የአህያ ዦሮ: ቀጠጥና፣ ደባክድ።
የአልጋ ዘንግ: በቀኝና በግራ ከራስጌ እስከ ግርጌ ያለ አራት ማእዘን እንጨት።
የአማርኛ፡ ቅኔ፡ መወድስ)። "አወይ፡ አወይ፡ ወይ፡ እኔ፡ ወይ፡ እኔ፡ የበደልኩሽ፡
በደል፡ ጌታዬ፡ ከሰማይ፡ ኮከብ፡ ይበዛ። ከባሕር፡
አሸዋም፡ ቢቈጠር፡ አያንስምና፡ እምብዛ ወይ፡
እኔ፡ ሞኙ፡ ሆይ፡ ደንቈሮ፡ ፈዛዛ። ሕያው፡
አምላከ፡ ሎዛ፡ ስላዳም፡ ብለኸ፡ በሸንጎ፡ ከለሜዳ፡ ለብሰሽ፡ ደምኸ፡ የተነዛ ዓለም፡ ቈንዦ፡ እያለችኝ፡ ሕፃን፡ እንጂ፡ ነኸ፡ ወሬዛ፡ ዛሬ፡ ተጫውተን፡
ነገ፡ እንጽደቅ፡ መሰንቆ፡ ሽንገላ፡ በጣቷ፡ ይዛ ያንን፡
ሽንገላ፡ ሳደምጥ፡ ዕድሜዬ፡ ዐለቀ፡ በዋዛ፡ የመኼዴን፡ ነገር፡ ቍርጡን፡ ሳውቀው፡ ዳቦ፡ ንስሓ፡ ሥንቄን፡ ሳልገዛ። "
የአማርኛ፡ ቅኔ)፡ ኅብርነት፡ ያለው፡ ያማርኛ፡ ስንኝ፡ ወይም፡
ግጥም።
"ኹለተኛውን፡
ቈጠረ፡ እይ።
"
የአስላም ቄስ: የቍርኣን ካህን፣ ሰባኪ።
የአስተሰረየና የሰረየ ትርጓሜ: ባማርኛ እንጂ በግእዝ አንድነት የለውም።
የአትሮንስ መልሕቅ። (ዘነዘና ማለት የዚህ ዘር ነው።)
የአንባር ምስጢር፡ ከጥንት የነበረ መሆኑን ያሳያል።
የአይን ምሳ: አበባ፣ ሥዕል፣ የሚያምር ፍጥረትና ሥራ ሁሉ።
የአዳም ዘር ሲኾን: ትንሣኤን ያስከትላል።
የአገር ስም: "ኰላ"።
የዓሣ ዐይነቱና ስሙ: በያገሩ ብዙ ነው። (ተረት): "ዓሣን መብላት በብልኀት" (ዓሣን መብላት ጥንቃቄን እንደሚጠይቅ)።
የእህል ዐረቄ: የቁርጠት መድኃኒት ነው (የእህል ዐረቄ የሕክምና ጥቅም)።
የእርሱ ነገር በቃኝ: ሰለቸኝ።
የዕቡይ ሞረድ: ትቢተኛን ከልክ የሚያገባ፣ ዕቡይ ገሪ።
የእንጀራ አባት: የእናት ባል፡ እንጀራ እየበላ ያሳደገ።
የእንጨት ምንቸት): "ራሱ አይድን፡ ሌላ አያድን።"
የእኸል' ስም: "ክረምት ውጭ በመስከረም የሚዘራ ያበባ እኸል። ዱባን ዓሣን አስተውል።"
የዕዳ ደብዳቤ): "አለብኝ፣ ተበድሪያለኹ፣ ወስጃለኹ" ተብሎ የተጻፈበት መጽሐፈ ዕዳ።
የዕዳ ጐሬ: ተከፍሎ የማያልቅ ዕዳ ያለበት ሰው።
የእጅ ጥራጊ)፡ በፍርፋሪ እጅን ጠርጎ ለሙክት የሚሰጡት ምግብ።
የከሰ (ትግ፡ ወከሰ)፡ ጠየቀ፡ ጥያቄ አቀረበ።
የከሰል ምርት: የከሰል ብዛት፣ ብዙነት። "ሸለመን"፣ "ሰነፈን" እይ።
የከረረ ጠጅ): የደረቀ ወይም የኖረ (ከራሚ)።
የከብት በሽታ: በሬና ላምን የሚያስለቅስና የሚያስቀዝን። ተመልከት: “ዐለቀን”። አንዳንድ ሰዎች “ታን” ያጠብቁና “በሽታ” ከ “ሸተተ” የወጣ ነው ይላሉ።
የከብትን ወይም የዶሮን ቍላ ቀደደ፣ ሠነተረ፣ ሰነጋ፣ ጐነደለ፣ ወይም አወጣ ማለት ነው።
የከነፈ: ያበደ።
የከንቱ ከንቱ: የብላሽ ብላሽ፡ የመጥፎ መጥፎ።
የኩል (የእኩል): የጋራ። "የኩል ዐራሽ"፣ "የኩል ቤት" እንዲሉ። የመንዝራ ግጥም: “ሚስትም አላገባ፡ ላሳብም አልቸኩል፡ አንዱ ያገባትን እይዛለሁ የኩል”።
የኩል ቤት: የበላይና የበታች አዛዥና ታዛዥ የሌለበት።
የኵፍኝ ስም: በሽታው ከፈንጣጣ የሚያንስ ስለ ኾነ እንከሊስ ተባለ።
የካ (ኦሮ፡ ኤካ፡ እውነት ነው)፡ በአዲስ አበባ ውስጥ በስተምሥራቅ በኩል ያለ ቀበሌ። "የካ ሚካኤል" እንዲሉ።
የካሽ (ሾች)፡ የየከሰ፡
የሚየክስ፡ ጠያቂ።
የካቲት (ከተተ): የወር ስም፡ ፯ኛ ወር ከመስከረም። የመከር መክተቻ ማለት ነው፡ "ከተተን" እይ።
የክት: ዝኒ ከማሁ (ልክ እንደ ክት)፡ በጋን፣ በሣጥን ተከቶ የሚቀመጥ፡ ለበዓል ብቻ የሚለበስ። "የክት ልብስ" እንዲሉ።
የኰርምት (የኰርማች) ሴት: ባጠገቡ ተኝታ እያለች ሳይፈልጋት (ሳይነካት) ጕልበቱን ኰርምቶ ያደረውን ወንድ ባለጌዎች 'የኰርምት ክፈል' ይሉታል።
የኹሉንም ፍች በየ ስፍራው ተመልከት።
የኾነው ይኹን: ከዚህ በፊት የተደረገው፣ የመጣው መከራ ይደረግ፡ ይምጣ። ጠላት ገፍቶ ባጠቃ ጊዜ እንዲህ ይባላል።
የወለፌንድ: የጠማማ ዐመል ሥራ፣ ከሰው የማይስማማ።
የወላሴ: የእግረ ምልስ ማለትን ያሳያል። "ወለሰን" ተመልከት።
የወል፡ የተራራ ስም።
"ወለለ"።
የወል: በወሎ ክፍል ያለ ተራራ።
የወል: የሕዝብ፣ የማኅበር፣ ያንድነት፣ የጋራ ርስት፣ ገንዘብ፡ ወይም ሌላ ነገር። "ዳኛ የወል ምሰሶ የመካከል" እንዲሉ።
የወሰን ደንጊያ: ወንዝ፣ ተራራ (ለምሳሌ "ወሰን ክልል")።
የወረብና የቅኔ) ጭብጨባ፡ ከጭብጨባ ጋራ የሚባል ወረብ።
የወረንጦ ቤት: የተሸበለለ ሲር፡ ወረንጦ መክተቻ።
የወሬ አባት: ወሬ ነጋሪ።
የወር ስም: ታኅሣሥ።
የወር፡ ቀለብ፡ ደመ ወዝ።
የወር ጨው)፡ ለቤት መፍቀድ በወር የሚወጣ ገንዘብ። ዐረፈ ብለሽ ዐረፍኩኸን እይ።
የወርቅ ሰሌዳ (ዘጸአት ፳፰፡ ፴፮፡ ፴፰): (የጌጣጌጥ አይነት)።
የወርቅ ሣጥን: ከወርቅ የተሠራ፡ በወርቅ የተለበጠ፡ የወርቅ ማስቀመጫ ማለት ነው።
የወተት መና ቀዳዳ: ውታፍ፣ በነቀሉት ጊዜ በነፋስ ኃይል ወተት ወይም ቅቤ የሚተፋ።
የወታደር ድንኳን ዐሯ: ትንሿ። ጕይዲ ግን ባለመደረቢያ የንጉሥ ድንኳን ጌጠኛ ይለዋል።
የወንድ በር: በጠላት ሰራዊት መካከል የጐበዝ መተላለፊያ መንገድ (፪ኛ ነገሥት ፳፫፥፲፯)።
የወንድም ልጅ: ባይወልዱትም ልጅ። (ዘዳ፳፭፡ ፭)
የወገን ወገን: የዘመድ ዘመድ።
የወግ ዕቃ: ፈረስ፡ በቅሎ፡ ከነሥራቱ፡ የጦር ልብስ፡ የጦር መሣሪያ፡ ሻለቃ በሞተ ጊዜ ወደ ቤተ መንግሥት የሚመለስ (ባህላዊ ወይም ወታደራዊ ዕቃ)።
የወፍ ቤት: በቀን ብዛት ከሣር የተበጀ።
የወፍ ቤት: ወፎች የሚኖሩበት መዋቅራዊ መጠለያ።
የወፍጮ ልጅ: መጅ።
የዋህ (የውሀ)፡ ገር፡ ቅን፡ ሞኝ፡
እንስላ፡ ደንሴ። "ሠረየን"፡ "ርግብን"፡ "ረባ" ብለሽ "ርባታን" ተመልከት።
የዋህ ኾነ (ተየውሀ)፡ ለዘበ፡ ገራ፡ ወደ ወሰዱት ኼደ።
የዋህነት፡ ገርነት፡ ሞኝነት።
የዋሆች: ገሮች፡ ሞኞች፡ እከይ አልቦች።
የዋግ ምስጢር፡ መውጋትና ዋጋ ማሳጣት ነው።
የውሃ ዕቃ: ገንቦ፡ ዳብሬ፡ እንስራ፡ ቅል፡ መንቀል፡ ርኰት፡
ቀርበታ
(ውሃ መያዣ)።
የውሃ፡ ዶሮ፡ በባሕር፡ ውስጥ፡ የምትቀመጥ፡ የሰይጣን፡
ዶሮ።
የውርርድ፡ በብር የሚከፈል የዳኝነት ገንዘብ።
የውሻ ልጅ: ቡችላ።
የውሻ ቍስል): ቶሎ የሚሽር።
የውሻ በለስ: ፍሬው የማይበላ የዱር በለስ።
የውሻ ና): የማይለበልብ ናጫ መሳይ ቅጠል (መናኛ)።
የውሻ ዝንብ: ተርብ፡ ተቈናጣጭ፡ ደም መጣጭ ዝንብ፡ ትንኝ አፈ ሹል፡ ከመስከረም እስከ ኅዳር ይሠለጥናል።
የውሽንብር፡ የኀዋት፡ የቍትቻ ዕዳ፡ መብልና መጠጥ።
የውብ፡ ዳር፡ የሴት፡ ስም።
የውዝፍ: ስለ ውዝፍ የሚከፈል ዕዳና መቀጮ።
የውጥር: እጅና አግሩ በገመድ ታስሮ የሚሳብ፣ የሚጨነቅ። "እከሌ የውጥር ተይዟል" እንዲሉ።
የዘለላ: ምስጢር አለበት (ዘኍ 13:24)።
የዘመቻ ፈሪ: ዘመቻ ፈርቶ የቀረ የሚከፍለው ገንዘብ።
የዘንጋዳ ስም: ቀይ ማሽላ የሚመስል ዘንጋዳ።
የዘወትር የኹለዬ፣ የሠርክ፣ የዕለት፣ የጊዜ፣ የቀን ሥራ፣ ምግብ፣ ልብስ፣ ጸሎት፣ ጀንበር በሠረቀ ቍጥር የሚደረግ ማንኛውም ነገር ነው።
የዘገር: በዘገር የቀና፣ የተያዘ የንጉሥ፣ የመንግሥት ርስት፣ ጕልት፣ የቤተ ክህነት፣ ያይዶለ።
የዚህም ምስጢር: ተረግዞ መወለድ፣ ተወልዶ መሞት ነው።
የዚያ፣ የነዚያ: የእርሱ፣ የእነርሱ ጠቃሽና በቂ።
የዚያየሱ፡ ዚያ።
የዛር ወጥ ቤት: እብድ።
የዛር ውላጅ: ሥጋ የለበሰ ጋኔን፡ ከዛር የወለደው የጕድፍ ተልከስካሽ ጋኔናዊ ባሪያ። "ጋኔን በተጐተተ ጊዜ መንገድ ጠራጊ ኹኖ ይመጣል" ይላሉ። ነገር ግን ጋኔን ወይም ዛር በምትሀት ገዝፎ ሥጋ ለብሶ ወንድና ሴት መስሎ ቢታይ እንጂ፡ እንደ ሰው ይዋለዳል፣ ይሞታል ማለት የተረት ተረት ነው።
የዛር ውላጅ: ሥጋ የለበሰ ጋኔን፡ ከዛር የወለደው የጕድፍ ተልከስካሽ ጋኔናዊ ባሪያ። "ጋኔን በተጐተተ ጊዜ መንገድ ጠራጊ ኹኖ ይመጣል" ይላሉ። ነገር ግን ጋኔን ወይም ዛር በምትሀት ገዝፎ ሥጋ ለብሶ ወንድና ሴት መስሎ ቢታይ እንጂ፡ እንደ ሰው ይዋለዳል፣ ይሞታል ማለት የተረት ተረት ነው።
የዛፍ ስም: "ሽታው መዐዛው የሚጣፍጥ ዕንጨት። ጉይዲ ግን መዠመሪያ ሽነትን ሽሾ ብሎ ተርጉሞታል።" "በዠማ ዳር የሚበቅል ዕንጨት። ቅጠሉ የሽንብራ ቅጠል ይመስላል። ዐዲሳበቦችም የፈረንጅ ግራር ይሉታል።" "ፍሬው የሚበላ ዕንጨት። የበለስና የወርካ ወፃን። በግእዝ ሰግላ ይባላል።" የጦሚት ዐይነት ዕንጨት።
የዜማ መጻሕፍት: 7 ናቸው: ድጓ፣ ጾመ ድጓ ከነጓዙ፣ ክሥተት፣ አርያም፣ ምዕራፍ፣ መዋሥእት፣ ዝማሬ፣ ቅዳሴ ከነጓዙ፣ ሳታት መዓል ሳታት ናቸው።
የዝሙት ዋዜማ: ድሪያ።
የዝም ብሎ: የንዲያው፡ የንዲሁ፡ ከንቱ፡ ብላሽ።
የዝን (የዕዝን): ላዘነተኛ የሚሰጥ ፱ እንጀራ፡ ንፍሮ (ሕዝ፳፬፡ ፲፯፡ ሆሴ፱፡ ፩)።
የዥብ ' ሽንኵርት)፡ የዱር ቅጠል።
የዥብ ምርኵዝ: የታናሽ ዛፍ ስም፡ በወይናደጋ ቈላ የሚበቅል ተራ ዕንጨት።
የዦሮ ቀለበት: ለጆሮ የሚደረግ ጌጥ።
የዦሮ ብሌን: መስሚያ።
የየ (ዘዘ)፡ የደጊመ ቃል በቂ። በነገር መነሻ እየገባ የስሙን መጨረሻ ፊደል ካዕብ አድርጎ ይነገራል። "የያገሩ"፡ "የያንዳንዱ"፡ "የየሰዉ" ብሎ ደንብን፡ ጠባይን፡ ጕዳይን፡ ማንኛውንም ነገር ያሳያል።
የየሩሳሌም ንግሥት): ባላገሮች በተረታቸው ብዙ ፍሪዳ ታሳርድና አሞራ ሁሉ ሊበላ ሲሰበሰብ ፊቷን በገለጠች ጊዜ አሞራው ይጠነገዳል (ያልቃል) ይላሉ።
የየካሽ (ጠየቀ): ጠያቂ; ተጠያቂ; ወይም ራሱን ጠይቆ እሱው መልስ የሚሰጥ; ሌላ መልስ ሰጪ የሌለው። "መምህራን ግን የተየካሽ ተየካሽ ይሉታል" (ትርጓሜ፡ ትምህርተ፡ ኅቡኣት)።
የዪ (ኦሮ)፡ የተኩላ ስም፡ ተኵላ።
የያተኛ: የቀን ሠራተኛ ደመ ወዝ፣ ቀለብ፡ እኸልና ገንዘብ፣ የጕልበት ዋጋ። ነዳ ብለህ ምንዳን እይ።
የደስ፡ ደስ፡ የጪስ፡ ዕንጨት። ይህ፡ ሴት፡ የደስ፡ ደስ፡ ይሸታል።
የደስ፡ ደስ፡ ገባር፡ ለተሾመ፡ የሚሰጠው፡ ገንዘብ፡ መተያያ።
የደስታ መሬት: የድንኳን ተካይ ምድር።
የደበሎን ጠጕር በቀጋ ጠረገ: አበጠረ፣ ጕድፉንና ክስካሹን አወጣ፣ ገላን ወረ።
የደንጊያ ልብስ): በደንጊያ ላይ የሚበቅል ረቂቅ አረንጓዴ መሳይ ሣር፡ ኋላም ሽበት ይኾናል።
የደንጊያ ንጉሥ: አልማዝ፣ ዕንቍ፣ ፈርጥ፣ አለት፣ የነጠረ ብረት (በትረ ቃቃን፣ ድጅኖ)።
የዱር ክብር: አዝመራ፡ ዛፍ፡ እንስሳ፡ ማዕድን (ኢሳ፲፡ ፲፰)።
የዲያ: የዚያ፡ የጭ።
"ዲያ የዲያብሎስ ከፊል ነው"።
የዳኛ እግር: ምስክር ካለበት ቦታ ሄዶ ለሚያመሳክር ዳኛ የሚከፈል ገንዘብ።
የድመት፡ ጠጕር)፡ ከሣር ጋራ የሚገኝ ታናሽ ቅጠል። ጐሽን፣ ዞማን እይ።
የድስት ጥራጊ)፡ ከድስት ውስጥ በንጀራ የተጠረገ ወጥ።
የድንኳን ምሰሶ: ረዳ።
የድኻ አባት: ድኻ ሰብሳቢ።
የዶማና የማረሻ ዕላቂ ብረት: ("ጕጭማን" የሚለውን ይመልከቱ)።
የዶሮ ማር: የገረንገሬ ሙጫ።
የጁ (የእጁ): ያገር ስም፡ የቀድሞ ስሙ ገነቴ ነው። "አለቃ ታየ የጻፉትን የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ተመልከት"።
የጃልዬ ገበታ፡ በላይ በላዩ እንጀራ እየተጣለ ከጧት እስከ ማታ የሚበላበት።
የጅ ውሃ: ሜዳ መውጫ፣ ከቶፋ ካይቻል የሚጨመር።
የጅራፍ ዕንጨት: እጀታ (የጅራፍ መያዣ)።
የጅን ከብት: የባሕር በሬ።
የገበጣ ጕድጓድ፡ ፲፪ የጅም መቀመጫ።
የገብስ ስሞች አንበዲያት፣ እንዳሪያ፣ ባሪያ፣ ሰደድ፣ ግንቦቴ፣ ገንዴት፣ ደሞዬ፣ ጠበል፣ ጠመዥ፣ ጦም፣ አረዥን፣ ልጅ አልቅሶ ጋ፣ ማውጊ፣ ማርያም፣ ዘር ስንዴ፣ ማና፣ ሰነፍ፣ ቈሎ ይባላል።
የገቦ (ዘገቦ): የጐን፡ በጐን የሚወጣ፡ የሚያፈጠፍጥ፡ የሚያቈጠቍጥ፡ የማሽላ ቅጥይ፡ የበቈሎ ፍሬ። "መጽሐፍ ግን ገቦ ይላል (ዘሌ፳፭፡ ፭)"። "ገቦ በግእዝ ጐን ማለት ነው"።
የገቦ: ሳይዘሩት የሚበቅል እኸል፡ ወፍ ዐራሽ (ዘሌ፳፭፡ ፲፩)። "የገቦ ማለት በመከር ጊዜ ረግፎ እመሬት የገባ መኾኑን ያስረዳል"። "ገባን - እይ፡ አንቀጹ፡ ርሱ ነው"።
የገነፈለ ዋዌ: በግእዝ ንባብ ውስጥ አለስፍራው የተነገረ ወ።
የገንዘብ ስም: ቁም ከብት የሚገዛበት፡ የሚለወጥበት ማንኛውም ገንዘብ፡ ወርቅ፡ ብር፡ ሌባ እንዳይሰርቀው በሣጥን፡ በጓዳ ተሰውሮ የሚቀመጥ (ማቴ፮፡ ፳፬፡ ሉቃ፡ ፲፮፡ ፲፫)። (ተረት)፡ "ከብቴ አትውጪ ከቤቴ፡ ታጣሊኛለሽ ከጎረቤቴ"። ሞኝ፡ አላዋቂ ሰው።
የገዛ፡ እጁን፡ ሳመ)፡ ለዳኛ፣ ላገረ ገዢ ክበሬታ ሰጠ (በፍርድ ጊዜ)።
የገዛ፣ የራስ፣ የሰውነት፡ ምስጢሩ ለገዙት ነገር ባለቤት መሆንንና የሥጋን ለነፍስ፣ የነፍስን ለሥጋ መገዛት ያሳያል።
የገደል ሲኾን: ሸንተረር ይባላል።
የጕልበት ዋጋ፡ ቀለብ፣ ደመ ወዝ፣ ምንዳ።
የጕሎ ዘንግ: የማይረባ ሰው።
የጉም፡ ሽንት)፡ ረቂቅ ካፊያ፣ ከም የሚጎኝ።
የጕድፍ፡ ፈንጣጣን የሚመስል ቀላል የልጆች በሽታ፣ ወይም አካል አጕዳፊ እከክ።
የጊዜና፡ ኀላፊ፡ ትንቢቱ ይሰልል፣ ይሰልላል ይላል።
የጋማ ከብቱ ብዙ ጥሬ ባፉ ሙሉ ይዞ ቈረጠመ: ዐኘኸ።
የጋማ ከብትን አገጭ ጠለፈ: ወይም "ላይኛውን ስርንና ታችኛውን መንገጭሊ ባንድነት አሰረ፣ መሳቢያን፣ ኣበተ። ሥሩ በግእዝ ሠበብ ሠበ ነው።"
የጋራ (የጋርዮሽ): ያንድነት፣ የማኅበር፣ የሽርክና ገንዘብ ወይም ሌላ ነገር።
የጋሻ ዕንብርት: ጕብሩ፡ መካከሉ (የጋሻ መሃል)።
የጋዣ ማር: ንብ ጋዣውን ቀሥማ የጋገረችው ማር። በጥቅምት ወር በጋዣና በቋ ሣር፣ በአገዳ ላይ የሚገኝ ማር።
የጌሾ ዐጥንት): ሳይወቀጥ ለጠጅ፡ ተወቅጦ ለጠላ ድፍድፍ የሚኾን የጌሾ ዕንጨት። "ዐጥምን" "አስከሬንን" ተመልከት።
የግስ ጣልቃ።
"ሠጠጠ፡
ተንሢያጠጠ፡ አንሢያጠጠ"።
የግራ ካራ: ዐመሉ መጥፎ ሰው።
የግብር ይ ወጣ፡ አላገባብ መሥራት፡ አዩኝ አላዩኝ ማለት።
የግእዝ፡ ቅኔ፡ መወድስ)። "ኦ፡ ባዕል፡ እግዚአብሔር፡ ምሉአ፡ ሀኬት፡
ገብርከ፡ እጸንሐከ፡ ጸኒሐ፡ ከመ፡ ተሀበኒ፡ ሊተ፡ ወርቀ፡ መለኮት፡ ፈሪሀ። ወአኀሥሥ፡ እምኔከ፡ ኢትምትር፡ አስካለ፡ ዕድሜየ፡ ለጎሚድ፡ ዘበጽሐ'እንበለ፡ ንስሓ፡ ማእረረ፡ ሎጥ ' እንዘ፡ በላዕሌሁ፡ ታሌዕል፡ ማዕጸደ፡ ሞት፡
በሊኀ። ዕዉርሂ፡ ልበ፡ ዚኣየ፡ ውስተ፡ ፍና አሚን፡ ከልሐ፡ ወልደ፡ ቤተ፡ ዳዊት፡ ኪዳነ፡
ወልድ፡ ዐይነ፡ አሚኖቱ - እስከ፡ አብርሀ። ወመራሕያን፡
ተምዑ፡ ወገሠጽዎ፡ ብዙኀ፡ ከመ፡ ያርምም፡ ተሞጠሖ፡ ዘጽልመት፡ መዋጥሐ፡ እንበይነ፡ ሃይማኖት፡ ብርሃን፡ እስመ ኣዕበየ፡ ጸሪሐ። ደስታ፡፡ ተክለ፡ ወልድ። "
የግእዝ ጳጳስነት: ያማርኛ ነው።
የግፍ ግፍ፡ የበደል በደል (ዦሮን እይ)።
የጐሽ ልጅ: ጥጃ።
የጐሽ መቈናቍን: ውድ የማይገኝ።
የጐዣም፡ የጐዣም ስንዴ።
የጐድን በር: ለግብር ወደ ቤተ መንግሥት አዳራሽ ሥጋ የሚገባበት።
የጠመንዣ ዘንግ: መደቅደቂያ።
የጠረኘ፡ ያፈለ፡ የጐለመሰ።
የጠበቃ ትች: ውርድ ይባላል።
የጠገተ ሥር ርሱ ነው፡ ምስጢሩም የጥጃንና ያላቢን ወደ ላም ጡት መጠጋት ያስረዳል።
የጠፍ፡ ባለቤት የሌለው ገንዘብ፡ ለሹም ወይም ላምጪው የሚገባ።
የጡት ልጅ: ያልወለደውን ሰው ጡት ጠብቶ ወራሽ፣ ቈራሽ የኾነ።
የጡት አባት: ጡቱን (አውራ ጣቱን) አጥብቶ ልጅ ያደረገ። "የክርስትና፣ የንስሓ፣ የነፍስ፣ የቆብ አባት" እንደሚባለው።
የጣላ ጣላ፣ ካንዱ ወዳንዱ የተላለፈ ሰው፡ ወሬ።
የጣመ፡ (ጥዑም)፡ የጣፈጠ፡ ጣፋጭ ምግብ። "የላመ የጣመ" እንዲሉ።
የጣት ውሃ: እጅ መታጠቢያ (በዳታን፣ በሰን፣ በኩስኩስት የሚቀርብ)።
የጣዎስ ሥዕል በላዬ ያለበት: (ግጥም)፡ ሶራ ሶራ ልበስ የጊዮርጊስ ፈረስ።
የጣዝማ ማር: ጣዝማ በመሬት ውስጥ የምታዘጋጀው ማር። የማር ጣዕም በተምር፣ በበለስ ፍሬ፣ በሸንኰራ ገዳ፣ በሙዝ፣ በሱካር ድንች፣ በጥንቅሽ፣ በሬት አበባ በዝቶ ይገኛል። "ሸተንን" እይ።
የጣይ፡ ሸንት)፡ በበጋ ሰዓት ቀን የሚወርድ የደጋ ርጥበት።
የጥላ)፡ በቍስል አጠገብ የሚታሰር ዛጐል፡ ሴቴ ሬት።
የጥርስ እድፍ: ልማም፣ ስሓ፣ ሳካ።
የጦር ልብስ): ራስ ቍር፡ ጥሩር፡ ጐፈር፡ ጉሜ።
የጦር መሣሪያ: የበዳ ጸብት፡ ሰይፍ፡ ጋሻ፡ ጠመንዣ፡ ወንጭፍ፡ መድፍ፡ መትረየስ፡
ሽጕጥ፡ የመሰለው ኹሉ። ፈረንጆች
"ኣርማ"
ይሉታል።
"ጦርን"
ተመልከት።
የጦር፡ ሹም)፡ የዐሥር፣ የሃምሳ፣ የሶስት አለቃ፣ ሻምበል፣ ባላምባራስ፣ ግራዝማች፣ ቀኛዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ደጃዝማች፣ ራስ። ሻለቃን እይ። ፈረንጆች ሹምን ጉበርነር ይሉታል።
የጦር አበጋዝ (ግእዝ): የጦር መሪ።
የጦር ገበሬ፡ ሐርበኛ፣ ጐበዝ።
የጦፈ፡ ጧፍ የኾነ፡ የነደደ፡ ያበደ፡ ሙር።
የጨረባ ተዝካር: ለጊዜው ተንጫጭቶ በቶሎ መበተንን ያመለክታል።
የጪስ ዕንጨት: ወገርት፡ ቡክቡካ፡ ምጥን፡ ብርጕድ (ጭስ የሚያመርት እንጨት)።
የጭ (የዕጭ): ኣክሽ፡ የዲያ ወዲያ፡ አስቀያሚ፡ ጸያፍ ነገር። "በማር ውስጥ ያለ ዕጭ እንዲያሠቅቅ፡ ይህም እንደዚያ ነው። "
የጭ፡ ወዲያ፡ ዕጭ።
የጭን በቅሎ: መቀመጫ (ሠጋር)። ተመልከት: "ግራጫን"፣ "ዋርዳን"፣ "ጨበርን"፣ "ሸክላን"፣ "ሳሙናን"። ተረት: “በቅሎ አባትህ ማነው ቢሉት፡ እናቴ ፈረስ ነች አለ። ”
የጭን ገረድ: ጌታዋ ያወቃት (የደረሰባት) ይዟት የሚዘምት።
የጭንጫ፵፡ አሽከር)፡ ለውጭ ሥራ የሚታዘዝ (ያደባባይ አሽከር)።
የጸሎት ስም: "ከመንፈቀ ሌሊት እስከ ነግህ በዜማ የሚጸለይ ያባ ጊዮርጊስ ድርሰት የሌሊት ጸሎት።"
የፈረስ፡ ስም)፡ አባ ዲና።
የፈረስ ዘንግ: ፍሬው ጕተና የሚመስል እንጨት፡ ራስ ክምር።
የፈረንጅ፡ አሽከር)፡ ነጭ ለባሽ፣ ሳሕን አመላላሽ።
የፈታይ ምንዳ: ክር ፈትሎ የሚገኝ ደመወዝ፣ ዋጋ።
የፈታይ ግብሩ: ግብሩ ወይም ቀረጥ ፈትል ሆኖ የሚከፈልበት መሬት ወይም ርስት።
የፈናጅራ: የመጥፎ ሰው ጠባይ፡ ከሌላው አንድነት፡ ስምምነት የሌለው።
የፈናፍንት: የጕዳጕድ ሥራ።
የፊት ግንድ፡ ዐጋዥ ግንድ።
የፊደል ትርጓሜ: የነገር የቃል ምልክት ሥዕል ማጕሊያ መግለጫ ማለት ነው። "መዝገበ ፊደል" እይ።
የፊጥኝ አሰረ: ኹለት እጆችን ወደ ኋላ ገጥሞ ቀፈደደ (ግብ ሐዋ፳፪፡ ፳፭)።
የፊጥኝ: የኋሊት፡ ፈጠነ።
የፋሲካ ምስጢር: ከግብጽ ወደ ፍልስጥኤም፡ ከሲኦል ወደ ገነት መሻገር ነው።
የፍንጥር: ላሻሻጭ የተገዛ መጠጥ።
የፍየል ልጅ: ግልገል።
የፍየል ዐይን ወደ ቅጠል፡ የነብር ዐይን ወደ ፍየል። ተባቱንና እንስቱን ለመለየት።
ዩ: የዜማ ምልክት።
"ሥረይን አስተውል"።
ዪ (ኢ): የሣልስ ፊደል መሠረት።
"አዪ፣ ኢ፡ በዪ፣ ቢ"። "መዝገበ ፊደል አስተውል"።
ዪቱ (ዪት፡ ዊት): የእንስት፡ የሴት መለዮ።
"ውን"፡ "ዋን" እይ። አንደኛዪቱ፡ ኹለተኛዪቱ፡ ጨረቃዪቱ፡ አህያዪቱ፡ ጥጃዪቱ፡
ፍሬዪቱ፡ ዶሮዪቱ። በራብዕ፡ በኃምስ፡ በሳብዕ በማይጨርስ ስም ግን
"ዪ"
ትጐረዳለች።
"ላሚቱ"፡ "በጊቱ" እንዲሉ። "ዪ" ፊደልን ኹሉ ሣልስ ማድረጓን አስተውል።
ያ (መዋያ): ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ዘዴ፣ ብልኀት። "ባለማያ ሰው"፡ "ባለያ ሴት" እንዲሉ። (ግጥም) "ያገሩን ርቀት እናንት መች ዐውቃችኹ፡ ያ ማደሪያ ነው፡ እኔ ልንገራችኹ። "
ያ (ዊ): ወገን ቅጽል።
"ቅጠል፡ ቅጠልያ፡
አባት፡ አባትያ፡ እናት፡ እናትያ፡ ሦስትያ፡ አራትያ፡ ዐምስትያ፡ ማን አስተውል"። "ያገርን ባለቤት ሲገልጽ፡ ኢትዮጵ፡ ኢትዮጵያ፡ አርመን፡ አርማንያ፡
እስክንድር፡ እስክንድርያ፡ ሮም፡ ሮምያ ይላል"።
ያ (ውእቱ): የሩቅ ወንድ በቂና ዐጸፋ።
"ያ ይምጣ፡ ያ ይቅር"። "ያ ሌላ፡ ይኸ ሌላ"።
"ያ ይሙት፡ ያ ይዳን"። "ከደቂቅ አገባብም ጋራ በስቲያ፡ ወዲያ፡ እንዲያ እያለ ይነገራል፡ በገቢርም ጊዜ ያን ይላል"።
ያ (ውእቱ): የሩቅ ወንድ ደቂቅ ቅጽል ይኾናል፡ ትርጓሜው እሱ፡ ርሱ።
"ያ ሰው"። "ያ ሲበዛ እኒያ፡ እሊያ ይላል፡ በስፍራው ተመልከት፡ ያችን እይ"።
ያ ፲ ኛ: መቅኒያ፡ መቅኛ።
ያ ሌላ: ይኸ ሌላ፡ ያ ቍቅታ፡ ይኸ ሢጥጥታ፡ ምን ገጥሞት።
ያ ቢስ: ዕውቀተ ቢስ፣ ሥራ የለሽ፡ አውታታ፣ ከርታታ።
ያ ተማደሪያ: ሌት ተቀን የሚሠራ ሥራ።
ያ ዕውቀት: (ከዋለ ግስ የመጣ)።
ያ ዕውቀት: (ከዋለ ግስ የመጣ)።
ያ: መዋያ፣ መገኛ። "አንባር ያ"፡ "ንፍፊት ያ" እንዲሉ።
ያ: የቀን ሥራ፡ ቁም ነገር። (ኢሳ፲፱፡ ፲)
ያ: ያተኛ ።
ያ: ያኛው ።
ያለ (ብህለ):
"የተናገረ፡ አለ"።
ያለ (አለ፡ እንበለ): አለ በገባበት እየገባ ሲነገር፡ "ያላገባብ"፡ "ያለደንብ"፡ "ያለወድ"፡ "በግድ"፡ "ያለልክ"፡ "ያለመጠን"፡ "ያላቅም"፡ "ያለፈቃድ" ማለቱን ያሳያል። ከዚህ የቀረውን በአለ ተራ ተመልከት። "ዚህና"፡ "ዚያ" ዘርፍ ሲኾኑት፡ "ያለዚህ"፡ "ያለዚያ" ይላል። ፍችውም በአለ ተጽሯል።
ያለ (ዘሀለወ): ቅጽልና በቂ። በቂ: “ያን ጊዜ በቤት ያለ እደጅ አይውጣ”። “ፈረስ በቅሎ ጭኖ ከሚከተለው፡ እቤቱ ያለውን ይወደዋል ሰው”። ቅጽል: “እንዲህ ያለ ዘመን፣ ዘመነ ግልምቢጥ፡ ውሻ ወደ ሰርዶ፣ አህያ ወደ ሊጥ። ”
ያለ (ዘብህለ): በቂና ቅጽል። በቂ: “ካስ ያለ ታግሦ፡ እጸድቅ ያለ መንኵሶ”። ቅጽል: “እገድል ያለ መጋኛ፡ እበላ ያለ ዳኛ”።
ያለ የሌለ (ዘሀለወ፣ ዘኢሀለወ): የታወቀና ያልታወቀ፡ ጥሩና መናኛ። “ዛሬ ሌሊት ሌባ እከሌ ቤት ገብቶ፣ ያለ የሌለውን ሰረቀው። ” "ሌለን" እይ። በሌላ ትርጉም: ያለ ማለት ለጊዜው የነበረ፡ የሌለ ማለት በፊት ያልኖረ ማለት ነው (ራእይ ፲፯፥፰ እና ፲፩)።
ያለ፡ ያለ (ሀለወ):
"የሌለ የነበረ፡ ያልነበረ"።
ያለ፡ ያለ (ሀለወ):
"የነበረ አለ"።
ያለህ (ዘሀለወከ): ገንዘብ የያዝህ፣ የቋጠርህ። ተረት: “ያለህ ምዘዝ፡ የሌለህ ፍዘዝ”።
ያለህ (ጩኸት): የጩኸትና የምጥንታ ቃል። "የሰው ያለህ"፣ "የንጉሥ ያለህ" እንዲሉ። የሰው እርዳታ፣ የንጉሥ ዳኝነት "ያለህ ድረስልኝ" ማለት ነው።
ያለኽ:
"የያዝኸ አለ" (ሀለወ)።
ያለው: የሰው ስም። ያዘዘው፣ የተናገረው፣ የፈቀደው፣ የወደደው። ታቦት ዘፋኝ: “ያለው ሊሆን ያለው ሊሆን፡ ዐሳብ አደቀቀው ጐኔን”።
ያለጊዜው፡ ያለቀኑ፣ ያለሰዓቱ።
ያላለ (የአልአለ): ያልተናገረ። ቅጽልና በቂ ነው።
ያላለቀለት): ዐፍላውን ያልጨረስ፡ ጸያፉን ያልከተተ፡ ምራቁን ያልዋጠ ሰው።
ያላለቀላት): ያላረጠች፡ ባልቴትነት የሌላት ሴት።
ያላለያ:
"ያልተናገረ"፡ "አል"።
ያል (የአል): በቂና ቅጽል። በቂ: "ያልተነካ ግልግል ያውቃል"። ቅጽል: "ያልጎደለ ዘማች"፣ "ያልወለደ አማች"። "ሰማን" ተመልከት።
ያል: በቂና ቅጽል፡ "አል"።
ያልወለዶ አጋድሞ ዐረደ: (ምሳሌያዊ አነጋገር)።
ያልደቀቀ ዶቄት: ሸረከተ።
ያመሳካሪ: ለዳኛ እግር የሚከፈል ገንዘብ።
ያመራማሪ: ላመራመረ የሚሰጥ ገንዘብ።
ያመንኳሽ: ካህናት የሚበሉት የቆብ፣ አርባ፣ ተዝካር ድግስ።
ያመድ ወይፈን: በአመድ የሚጫወት ልጅ።
ያማች ዳሩ: መጨረሻ፡ ክፉ ዐማች።
ያም (ውእቱኒ):
"ም"
ዋዌ ነው።
"ያም ኾነ ያም ኾነ ሞት አይቀርም"። "ያን" አስተውል።
ያም ያም: አንዱም አንዱም።
ያሣ ቀፎ: ዓሣ የሚቀመጥበት ቅርጫት።
ያሳድግህ: ሽማግሌ ለልጅ የሚሰጠው ምርቃት።
ያስታራቂ: ግብዣ፡ መብል፡ መጠጥ (የማስታረቂያ ግብዣ)።
ያስችልህ: ትግሥት ይስጥህ።
ያረጠች ባልቴት እንዲሉ (የወሊድ እድሜ ያለፈባት ሴት)።
ያራስ ቤት: በመቃኑ ላይ ሴቴ ሬትና ሰሪቴ ያለበት።
ያሬድ: የሰው ስም፡ ትርጓሜው መውረድ ማለት ነው። ከዕለት እስካመት በግእዝ ቋንቋ ድጓ የደረሰ የኢትዮጵያ ሊቅ ቅዱስ ካህን።
ያርብ ውሃ: ዐርብ የተቀዳ። (ዮሐ፳፡ ፴፬)
ያሸነደረ: የሚያሸነድር።
ያሻል: ያስፈልጋል።
ያቍራቢ: ለቍራቢ (ለቀዳሾች) የሚሰጥ ምሳ፡ ወይም ገንዘብ።
ያቃባሪ፡ የዝን፡ ንፍሮ።
ያቃይ፡ የቃጭል፡ መቺ፡ የሰሞነኛ፡ ምድር።
ያበባ፡ መስቀል)፡ ካበባ የተበጀ፣ የተጐነጐነ (እንቍጣጣሽ)።
ያቡን እግር: ነጭ ስንዴ (ጣይ ሶራ)።
ያቤሎ: በሲዳሞ ክፍል ያለ አገር።
ያተኛ (ኞች): ለሰው ሲያርስ፣ ሲቈፍር፣ ሲያርም፣ ሲያጭድ፣ ሲሸከም፣ ሲሠራ የሚውል። (ማር፩፡ ፳) በግእዝ ገባኢ ይባላል።
ያቻት: ያች ናት፡ አለች።
ያቻትና: ያች እሷ፡ "ት" ናት፡ "ና" (ናሁ) እንሆ። በተገናኝ፡ እንሆ እሷ ናት፡ በሩቅ አለች ያሠኛል።
ያች (ይእቲ): የሩቅ ሴት ዐጸፋና ቅጽል ወይም በቂ፡ እሷ ማለት ነው፡ "ዋን" እይ። "ያች ትምጣ"፡ "ያች ትቅር" (ዐጸፋ)። "ያች ሴት"፡ "ያች ልጅ" (ቅጽል)። "ው" ሲጨመርበት መኖርን ያሳያል።
ያችኛዋ:
"ኛዋ"
ዝርዝር ምእላድ ነው፡ ፪ኛውን
"ኛ"
እይ።
ያችው: ያቻት።
"ው"
ቦታን ያስረዳል።
ያችውና:
"ው"
እንዳለፈው፡ "ና" ናት፡ አለች። ማዶ ለማዶ በሩቅ ለምትታይ ሴት ወይም ሌላ ነገር ማመልከቻ ቃል ነው።
ያን (ያ፡ ውእተ): ለሩቅ የነገር ስም የሚነገር፡ ገቢር ቅጽልና ዐጸፋ ወይም በቂ።
"ያን ጊዜ"፡ "ያን ለት"፡ "ያን ነገር" (ቅጽል)። "ያን ጥለኸ"፡ "ያን ያኸላል"፡ "ያን ውደድ"፡ "ያን ጥላ" (በቂ)።
ያንበሳ መደብ: አንበሳ ተዘግቶ የሚኖርበት ስፍራ በብረት የታጠረና የተዘጋ።
ያንበሳ መደብ: የንጉሥ ዐዘቅተ ኵስሕ ጓሮ ቤት።
ያንበሳ: ል ጋማ ይዞ። "የልመና እኽል" እንዲሉ።
ያንካሴ የወላሴ: የልጆች ጨዋታ፡ ልጆች አንዳንድ እግራቸውን ዐጥፈው "ያንካሴ የወላሴ" እያሉ በአንድ እግራቸው ያኵበኵባሉ (የልጆች ጨዋታ ዓይነት)።
ያንካሴ: የአንካሳ ወገን፡ ወይም ዐይነት።
ያኛው:
"ኛው"
ዝርዝር ምእላድ ነው፡ ፪ኛውን
"ኛ"
እይ።
ያከራይ ተከራይ: ቤት ያከራየ ሰው ለመንግሥት የሚከፍለው ግብር።
ያክፋይ: ለአክፋይ የሚሰጥ አንጀራና ወጥ፣ ዳቦና ጠላ፣ ሙክት ፍሪዳ።
ያኰላሽ ወይም የሚያኰላሽ: ሰንጊ።
ያኸል (ዘየአክል): የሚያክል፡ ቅጽልና ትንቢት። ከጥያቄ ጋራ ሲነገር "ምን ያህል?"፣ "ምን ያህል?" ያሰኛል።
ያኽል፡ የሚያኸል፡ አከለ።
ያዋዋይ: ለዳኛ ስለ ማዋዋል የሚከፈል ገንዘብ፡ የፍንጥር።
ያዋይ በላ: ለአዋይ የተቀመጠውን የሚበላ፡ ችጋራም፣ ራብ የማይችል፡ ስግብግብ፣ ቅልብልብ።
ያዋይ: በሌማት ውስጥ የሚውል ቍራሽ እንጀራ፡ "አዋይ ትመገበዋለች" ይባላል።
ያው (ያ)፡ እሱ ነው፡ አለ።
"ው"
ከ"ነው" መጥቶ ከ"ያ" ተደርቧል። ሲዘረዝር፥ ያውልኸ፡ ያውልሽ፡ ያውላችኹ፡ ያውልኹ፡ ሲደጋገም ያው ያው ይላል።
"ያውልኹ እማገሩ፡ ክፉ አትናገሩ"።
ያው: መነሻና መድረሻ ነው።
ያውልኸ፡ ዕንካ፡ ውሰደው። (ግጥም):
"ጣዩ የልኸ የልኸ፡ ዝናቡ የልኸ የልኸ፡ ትዘራውም እንደኹ ቅብቅቡ ያውልኸ"።
ያውና፡ ያ፡ እሱ፡ ው፡ ነው፡ ና፡ እንሆ። በተገናኝ፡ እንሆ እሱ ነው፡ (በሩቅ)፡ አለ፡ ና፡ ከናሁ፡ መጥቷል (የባለጌ ግጥም)። "ያውና እዚያ ማዶ ዛፍ ይወዛወዛል፡ ያንቺ ልብ እንዴት ነው፡ የኔስ ይናውዛል"። "ያውና እዚያ ማዶ ፍሪዳ ተጥሏል፡ ቢላዋው ደንዞ ልብ አልቈርጥ ብሏል"። "ፈሪዳ የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። "
ያዘ (አኀዘ)፡ አፈፍ ለቀም አደረገ፡ ከእጅ አገባ፡ ጨበጠ፡ ተሸከመ፡ ቻለ፡ አገመረ፡ ወሰነ። (አፍንጫውን ያዘ): ዐፈነ፡ ደፈነ። (በወጥመድ ያዘ): ዐነቀ። (በልብስ ያዘ): ታቀፈ። (ባፍ ያዘ): ጐረሠ። (ልጓም ያዘ): ገታ። (መግል ያዘ): ዐቈረ፡ ቋጠረ። (ሥጋ ያዘ): ወፈረ። (ሥራ ያዘ): ረባ፡ ጠቀመ፡ አገለገለ። (ሥር ያዘ): እሥር ገባ፡ ተመለሰ። (ዐይን ያዘ): ጨለመ፡ ማየት ከለከለ። (ቀለም ያዘ): አጠና፡ ዐወቀ፡ ልብ አደረገ። (ቂም ያዘ): በልቡ አሳደረ። (ስፍራ ያዘ): ቆመ፡ ተደገፈ።
"ያዘ በነገር ኹሉ እየገባ እንዳመጣጡ መፈታቱን አስተውል"። (ተረት):
"ከበሮ በሰው እጅ ያምር፡ ሲይዙት ያደናግር"። "አፍን" እይ።
ያዘብጣጭ: የቀሪ ዕዳ።
ያዘው: (ይህ ቃል ትርጉም አልተሰጠውም፣ ምናልባት የሌላ ቃል አካል ሊሆን ይችላል)
ያዝ (አኀዝ)፡ አንሣ፡ ጨብጥ፡
አንግብ (መዝ፴፭፡ ፪)። ቶሎ በል፡ ንከስ። ባላገር፡ ግ፡ ጃስ፡ ኵቲ፡ ይላል።
ያዝ (እኂዝ)፡ መያዝ። ያዝ አደረገ: በፍጥነት ያዘ። ያዝ ለቀቅ: መያዝ፡ መልቀቅ።
ያዢ (ዥ፡ ዦች)፡ የያዘ፡ የሚይዝ፡
ተሸካሚ፡ ጨባጭ፡ ገቺ፡ ጐበዝ። "ያዢ ሲይዘው ብረት ያራል"። "ጠመንዣ ያዥ፡ ሰናድር ያዥ" እንዲሉ።
ያዢ: ስም።
ያየር: በአየር የሚኖር ጋኔን፣ ሰይጣን።
ያየኸ ይራድ: የሰው ስም። "ራደን" ተመልከት።
ያይን ቍራኛ: ዐይን እያየ ያላየ መምሰል። "አንቀጹ ሾረ ነው።"
ያይን፡ ቆብ)፡ ቅንድብ፣ ሸፋሽፍት።
ያይጥ ዓሣ: ውንጅር (የዓሣ ዓይነት)።
ያይጥ ወንበር: ልጆች ከርጥብ የስንዴ ብር የሚያበጁት።
ያደግድጉ: የወንድና የሴት ስም።
ያዳይ ጠጪ፡ የግመል ፈንጪ እንዲሉ።
ያገሩን ሰርዶ: ባገሩ ገበሬ።
ያገር አባት: ሽማግሌ፣ መካር። ዛሬ አንዱ ቤት፣ ሌላው ቤት እያደረ የሚጦር።
ያግሉ፡ የሰው ስም፡ "ጠላቶች ይወግዱ፣ ራሳቸውን ያርቁ" ማለት ነው።
ያጣኝ: ተዝካር በተበላ በ፫ኛ ቀን የሚደረግ የካህናት ግብዣ።
ያጥንት ልጅ: በ፱ ወር ከ፭ ቀን ያልተወለደ።
ያፈላላጊ: ጥቅም፡ ረብ።
ያፈር ገንፎ፡ መልከ ጥፉ ሰው። "ቀጸለ"፣ "ተቀጸለ" ብለኸ "ተቀጽላን" እይ።
ያፋቺ የተማቺ: ሚስቱን የፈታ ባል፡ ባሏን የፈታች ሚስት (ኺጂ ልኺድ ያለች)፡ (ሰው የመታ) ለዳኛ የሚከፍለው፡ የምትከፍለው ገንዘብ። ዱሮ አንድ አሞሌ ነበር፡ ከ፲፱፻፴፬ ዓ.ም ወዲህ ግን ዐምስት ብር ነው።
ያፍ፡ ሳቻ)፡ ነቀፋ፣ ስድብ።
ያፍንጫ ቀለበት: "ጒይዲ ግን ሸሽቦና ሻሽል አንድ ናቸው ይላል።"
ያፍንጫ ተረተር: የአፍንጫ ድልድይ።
ያፍጣጭ: ሰዎች ሲበሉ ላፈጠጠ የሚሰጥ ምግብ (ለአፍጣጭ የሚሰጥ ምግብ)።
ዬ (ኢ): የማድነቅ ቃል።
"ዬ ወንድሜ አንተ ታግሠኸኝ ነው እንጂ፡ እኔስ የበደልኩኸ በደል ብዙ ነበር"።
ዬ (ኤ): የኃምስ ፊደል ኹሉ መሠረት።
"አዬ ኤ፡ በዬ ሴ"። "መዝገበ ፊደል እይ"። ዕሠይ፡ ወሰው እኮ። "አበባዬ፡ መስከረም ጠባዬ"።
ዬ (ወዮ): የሐዘንና የጸጸት ቃል።
"ዬ ቤቴን በጊዜው ሳልከድን ዝናም ቢጥል እንዴት እኾናለኹ"። (ግጥም):
"ማሽላዬ ወማይ በላሽ ወዬ"። "ዬዬንና እዬዬን ተመልከት"።
ዬ (ዊ): ባገር ስም መጨረሻ እየገባ ለተወላጅ በቂ ይኾናል። "የጁ፡ የጁዬ፡ ወሎ፡ ወሎዬ"። ወገን ቅጽል:
"ድንክ፡ ድንክዬ"።
ዬ (የ): በራብዕና በኃምስ በሳብዕ ፊደል በሚጨርስ ስም እኔ ለሚል ዝርዝር። "ሥራ፡ ሥራዬ፡ ዕጣ፡ ዕጣዬ፡ ጌታ፡ ጌታዬ፡ ፍሬ፡ ፍሬዬ፡
ከበሮ፡ ከበሮዬ፡ ማሲንቆ፡ ማሲንቆዬ"።
ዬ ጊዜ:
"አንደዬ፡ ዐሥረዬ"። "አንድና ዐሥር ለዬ ቅጽሎች ናቸው"።
ዬዬ፡ ወዮ ወዮ። "ዬን" ተመልከት፣ ይህ የሱ ደጊመ ቃል ነውና።
ይ (ሆይ): ንኡስ አገባብ፡
የአንክሮና የአጋኖ፡ የአክብሮ ቃል።
"ሰውዮ፡ ሴትዮ"።
ይ (ዊ): ወገን ቅጽል።
"ድንግል፡
ድንግላይ፡ ኀምር፡ ኀምራይ፡ ሾተል፡ ሾተላይ"። በትንቢት መነሻ እየገባ በቂ ይኾናል። "ድኻ ይበላው እንጂ ይከፍለው አያጣም"። "ይኸውም በየሚ፡ ፈንታ የተነገረ ነው"።
ይ ለ፡ የሚጨርስ ግስ፡ የሣልስ ቅጽል መድረሻ:
"ከፈለ፡ ከፋይ፡
ከለለ፡ ከላይ፡ ፈነገለ፡ ፈንጋይ፡ ሰቀለ፡ ሰቃይ"። "ይኸውም የና ለ፡ ተወራራሽ መኾናቸውን ያስረዳል"።
ይ የቦ (ኦሮ): የጦር ስም፡ ታናሽ ጦር፡ ጭሬ።
ይ: ለሩቅ ወንድ፡ ለሩቆች ወንዶችና ሴቶች፡ የትንቢት፡ የዘንድ፡ የትእዛዝ አንቀጽ መነሻ።
"ገደለ፡ ይገድል፡
ይገድል ዘንድ፡ ይግደል"። "አንቀጹ በአዐ ሲነሣ ከትእዛዝ በቀር ያ ይኾናል። አመነ፡ ያምን፡ ያምን ዘንድ"።
"ዐረፈ፡ ያርፍ፡
ያርፍ ዘንድ"። "ባስደራጊም አስቀደሰ፡ ያስቀድስ፡ ያስቀድስ ዘንድ፡ ያስቀድስ ይላል"።
ይሁዲ (ዐረ)፡ ይሁዳዊ፡ የይሁዳ ወገን ወይም ነገድ፡ ነገደ እስራኤል፡ ፈላሻ ግዙር።
ይሁዲነት (ይሁድና)፡ ይሁዲ መኾን፡ ፈላሻነት (ግብ፡ ሐዋ፮፡ ፭)።
ይሁዲዎች፡ አይሁድ፡
አይሁዶች። "አይሁድ" የይሁዳ ነገዶች፡ እስራኤሎች።
"አሥራቱ ነገድ በያዕቆብ እስራኤል እንደ ተባሉ በይሁዳም አይሁድ ተብለዋል" (አስቴ፫፡ ፮፡ ዮሐ፩፡ ፲፱)።
ይሁዳ (የሀደ)፡ የሰው ስም፡ ከአሥራቱ ነገደ እስራኤል አንዱ። ትርጓሜው ኦኒ (አማኝ) ማለት ነው።
ይሕ፡ "ይበሉ ሕዝብ"
(ቅዳሴ)።
ይህ (ዝ): የቅርብ ዐጸፋና ጭብጥ ቅጽል።
"ባይን የሚታይ፡ በእጅ ሊጨበጥ የሚቻል፡ ፊት ለፊት ያለ ነገር፡ ይህ ይባላል። " "ይህ ሲበዛ እኒህ፡ እሊህ ያሠኛል"። "ይኸን እይ፡ ከዚህ ጋራ አንድ ነው"። "ይህ ሰው ቅጽል፡ ይህ ነው ዐጸፋ"። "ከደቂቅ ጋራ ሲናበብ፡ እንዲህ፡ ወዲህ ይላል"። የገቢር ቅጽል። "ይህን ብትሰጥ፥ ምን ትውጥ። " "ይህን ያልመታ የማሪያም ጠላት"
ልጆች እንዲህ ካሉ በኋላ ዛፍን በድንጋይ ይወግራሉ፡ (ይደበድባሉ)።
ይህ ዕሽ ማለት ቀዳሾቹ እጆቻቸውን መዘርጋታቸውንና የመላእክትን መኖር ያሳያል (የድርጊቱ ትርጉም)።
ይህ: ይህኛው ።
ይህታ (ይህችታ)፡ "ታን" ተመልከት።
ይህች (ይህ)፡ ለቅርብ ሴት ዐጸፋና ቅጽል። "ይህች ሴት፡ ይህች ናት"።
ይህነን፡ ዝኒ ከማሁ፡ ይኸንን ተመልከት።
ይለፍ: ኬላውን ይውጣ፡ አይከልከል (የመውጫ ፈቃድ)።
ይሉኝ (ይብሉኒ): የአሁን ትንቢት አንቀጽ። ምሳሌ: “ደግ ብሠራ የጠሉኝ፣ ክፉ ባደርግ ምን ይሉኝ?” “ገቢህን ስታውቅ ይሉኝ አትበል። ” ይሉኝ አይል: ሐሜት የማይፈራ። ምሳሌ: “ከይሉኝ አይል ዐይብ አትብላ፡ አይመረው አይተኩሰው፡ ውጦ ውጦ ይጨርሰው። ” አገባብ: "እንዲሉኝ"፣ "ሊሉኝ"፣ "ይሉኝ ዘንድ" እያለ በሦስተኛ አንቀጽ ይገባል።
ይሉኝ: በቁሙ፡ አለ (ብህለ)።
ይሉኝተኛ: ባለ ይሉኝታ።
ይሉኝታ ቢስ: ግድ የለሽ፡ "ይሉኝ አይል"።
ይሉኝታ: ረቂቅ የነገር ስም (ምሳሌ ፫፥፬)፡ “እንዲህ ይሉኛል” ማለት። ትዝብትን፣ ሐሜትን፣ ነቀፌታን መፍራት። ምሳሌ: “ይሉኝታ የራስ ዐሊን ቤት የፈታ። ” “ይሉኝታና መጠቀም በአንድነት አይገኝም። ” መነሻ: "ይሉኝ" የነገር ስም መሆኑ "ታ" በምእላድነት ስለተጨመረበት ነው።
ይሉኝታ: በቁሙ አለ (ብህለ)።
ይላል (ይል አል): ይብል ሀለወ። ይናገራል፣ ይመታል።
ይላማ (ዐላማ): ምልክት፡ ወርውረው የሚወጉት፡ ተኵሰው የሚመቱት ነገር።
"ጊጤን"
እይ።
ይል: ይናገር፡ የጊዜ ትንቢት ነው።
ይልልቅ: ይበልጥ፣ እጅግ። (ማሕ. ፩፡ ፬)።
ይልልቅስ: ስ አፍራሽ ነው፡ የሚበልጥስ፣ የሚሻልስ።
ይልማ (ጥማ): በመንዝ ውስጥ ያለ ቀበሌ፡ የጠይቦች ጎዳም የሚገኝበት።
ይልማ: የሰው ስም፡ "ይርባ፣ ይብዛ"
ማለት ነው።
ይልማና: በጐዣም ክፍል ያለ አገር።
ይልቁንም: ን ተሳቢ፣ ም ዋዌ ነው። ይበልጡንም፣ እጅጉንም።
ይልቅ: ይበልጥ፡ ላቀ።
ይሎ: የጣራ ማዋቀሪያ ረዥም አጣና፡ ተለብልቦ የተላጠ ተራዳ።
ይመናሹ: የሴት ስም፡ "ወንዶች ባንቺ ላይ ይዋጉ" ማለት ነው።
ይመናሹ: ይዋጉ፡ መንሽ።
ይመኙሻል: የሴት ስም።
ይማማ (ዐረ፡ ዒማማ): የይማሞቶ ጥምጥም።
"አመመን"
እይ።
ይማም (አመመ፡ ቀደመ፡ ሀረ፡ ዐመመ፡ ጠመጠመ): የእስልምና ስም፡ ግንባር ቀደም ካህን ማለት ነው። ባላባትነትንም ያሳያል።
ይማሞች: ግንባር ቀደሞች፡ ዋኖች፡ የወሎ ባላባቶች።
ይማና: ሰው ሳያይ ሳይሰማ በእምነት የሚሰጥ የአደራ ገንዘብ።
ይማና: ያደራ ገንዘብ፡ አመነ።
ይሞት በቃ: ተገባ።
ይሣቅ (ይሥሐቅ): (ዘፍ፳፩፲፫፡ ፮) የሰው ስም፡ ያብርሃም ልጅ የያዕቆብ አባት። እናቱ ሳራ ካረጀች በኋላ ስለ ወለደችው ሰው ኹሉ ይገረም ይሣቅ በማለቷ በዚህ ስም ተሰየመ ይባላል።
ይስሙላ: ተሰምቶ የማይፈጸም ነገር። "ፍችውም ይስሙላት ማለት ነው።"
ይስማ ሰራዪት: በሠራ አካላት ላይ ግልብጥ ብሎ የሚታይ ቂጥኝ።
ይስገዱ: የወንድና የሴት ስም።
ይርጋ ፣ ልስን፡ ማስተካከያ፡ ዕንጨት፡ የተላገ።
ይርጋ፡ የሰው፡ ስም።
ይርጋ፡ የንጉሥ፡ ዐዋጅ። "መሬት፡ በያዘው፡ ሰው፡ እጅ፡ ይኑር፡ አይወሰድ፡
ማለት፡ ነው።
"
ይቅር (ጥተ): ይተው፡ ቀረ።
ይቅር ባይ: ማሪ፣ ሰላማዊ።
ይቅር ተባለ: ታረቀ (ሰውየው)፡ ተተወ (ጥሉ)።
ይቅር ተባባለ: ተጐናበሰ፣ ተራረቀ፣ ተሳሳመ፣ ተሰማማ።
ይቅር አለ: ጠላቱን ማረ፡ ቍርሾውን ተወ፡ ከልቡ ፋቀ፣ አጠፋ።
ይቅር አሠኘ: አስታረቀ።
ይቅር: ትእዛዝ አንቀጽ። "ይቅር ለግዜር፡ ይቅር ላንተ፡ ቂሙ አይያዝ፣ አይታሰብ ማለት ነው። " "በአንተ ፍቅር በስመ አብ ይቅር እንዳለ ሰይጣን። "
ይቅርታ ጠየቀ: "በድያለኹ ልካስ፣ ቀምቻለኹ ልመልስ" አለ።
ይቅርታ: ይቅር ማለት፡ ምሕረት፣ ዕርቅ (መዝሙር ፻፴፡ ፬)። "ከማስቀመጥ ስጦታ፡ ከቂም ይቅርታ" እንዲሉ።
ይቆን: የጋኔን ስም፡ ደቂቀ ሴትን ያሳተ ሰይጣን (ሔኖ፲፱፡ ፲፯)።
ይበል: ደስ የሚያሰኝ፣ ማለፊያ ቅኔ በተሰማ ጊዜ ከሰሚው የሚነገር ቃል፡ “እሱ ዘወትር ይቀኝ” ማለት ነው። ማስታወሻ: "መልክ ብለኸ" የሚለውን ተመልከት።
ይበጃል: ይሻላል፣ ይሆናል። ምሳሌ: “ይበጃል ያሉት አይበጅ”።
ይበጅ/ያድርግ: ያደርግ ዘንድ ይገባል።
ይባዝ: በይፋት ክፍል ያለ ቀበሌ። (ግጥም):
"የሣህለ ሥላሴ ጠላቱ ከበዛ ይጣ ይኺድ እንጂ፡ ይባዝን አይግዛ"።
ይብላኝ (ይብልዐኒ): የሐዘንና የትካዜ፣ የጸጸት ቃል፡ ንኡስ አገባብ። አባባል: “ይብላኝ ለሞተ” እንዲሉ።
ይብላኝለት: በማቹ ፈንታ “እኔን መሬት ይብላኝ” ማለት ነው።
ይብስ: ቅጥራን፡ የቅጥራን ዐይነት።
ይብረኹ: የወንድና የሴት ስም፡ “ይስገዱ” ማለት ነው። ምሳሌ: “አቶ ይብረኹ፣ እመቤት ይብረኹ” እንዲሉ።
ይብራ: የውሃ ዶሮ፡ እውሃ ውስጥ ጠልቃ የምትወጣ፡ እግረ ቀይ፡ መልከ ብዙ (ዘሌ፲፩፡ ፲፰)። "ዝዪን ተመልከት"። "ትእዛዝ አ?ቀጽ ሲኾን፡ በራ፡
ይበራል፡ ይብራ ይላል"።
ይብጀው: ይሻለው። ምሳሌ: “እሳት ለፈጀው ምን ይብጀው”።
ይብጅህ: አይዞህ፣ አትፍራ።
ይተጌ (እኅተ ሐፄጌ): እተጌ፡ ንጉሥ
"እቴ"
የምትላት ሚስቱ፡ ጣምራው፡ የንጉሥ ባልተ ቤት።
"ይተጌ ጣይቱ"፡ "ይተጌ መነን"፡ "ይተጌ ሰብለ ወንጌል" እንዲሉ። "ሲበዛ ይተጌዎች ይላል"።
ይታክቱ: የወንድና የሴት ስም።
ይታገሡ: የወንድና የሴት ስም።
ይቶት (እኅት): ሴት ስትመነኵስ የምትጠራበት ስም፡ የፍቅር፡ የሃይማኖት፡ የማኅበር እት ማለት ነው፡ ዳግመኛም እመ፡ እማሆይ ትባላለች። በግእዝ ቋንቋም መነኵሲቷ (እኅት) እት፡ መነኵሴው (እኅው) ወንድም ይባላሉ። በብዙም ለመናገር (አኀው አኃት) ወንድሞች፡ እቶች ያሠኛል።
ይቶት አለስም: ብቻውን ሲነገር እንዳለፈው በቂ፡ ከ: ፲፩ኛ ፊደል በግእዝ እልፍ ቤት በአበገደ፡ ይኸውም በተራ ቍጥር ነው። በፊደልነት ስሙ ካፍ፡ በአኃዝነት ከ፳ (ካያ፡ ኻያ) ይባላል። የ"ገ" ወራሽ ወይም ተለዋጭ፡ "ገረደፈ"፡ "ከረተፈ"። "ቸን" እይ። የ"ኈ" ወራሽ ከግእዝ ወዳማርኛ።
"በኍበኈ"፡ "ቦከቦከ"። የ"ቀ"
ወራሽ።
"ቀላድ"፡ "ከላድ"። ዐቢይ አገባብ።
"ከበላ ብላ"፡ "ከሰው አትጣላ"። ይህ ጋራን ይዞ ሲነገር ነው። ኋላን ይዞ ሲፈታ፡ "ውሃ ከፈሰሰ አልታፈሠ"። "ዥብ ካኰተኰተ ሰው ከተከተተ"። "ከመነኰሰች ባሰች"፡ "ከቈረበች አፈረሰች"።
ይቻላል: ይሆናል፣ ይደረጋል።
ይች ቺ:
"ይህችን"
ተመልከት።
ይችው: በቅርቡ አለች።
ይችውና: እንሆ እዚሁ አለች።
ይነሡ: የሰው ስም፡ "ብድግ ይበሉ"
ማለት ነው።
ይኑር: ይቀመጥ፣ ይቈይ፣ ይዘግይ፡ ዕድሜው ይብዛ።
"ይኑር ዘለዓለም እከሌ አብርሃም"
እንዲሉ ካህናት።
ይናዱ: የወንድና የሴት መጠሪያ ስም፡ "ጠላቶች ይሽሹ"
ማለት ነው።
ይንበርበሩ: የሰው ስም።
"በረ"።
ይንበርበሩ: የሰው ስም፡ “ጠላቶች ይበርበሩ፣ ይወረሩ፣ ይዘረፉ” ማለት ነው። ማስታወሻ: አንበረበረ እና ተንበረበረ ከዚህ ቀደም አልተለመደም፡ ዳግመኛም እንበለበለ እና ተንበለበለ ከማለት ይልቅ የተነገረ ሊሆን ይችላል።
ይከራያል: ለሚከራይ ይሰጣል (ቤቱ፣ ዕቃው፣ ከብቱ፣ መሬቱ)። በፈረንሳይኛ 'አሉዌ' ይባላል።
ይካ፡ "ይበል ካህን"
(ቅዳሴ)።
ይኸ (ይህ)፡ የይህን አፈታት ተመልከት፡ ለማናበብና ሌላ ፊደል ለመጨመር ይህ፥ ይኸ ተብሏል።
ይኸን (ዘንተ)፡ የገቢር ቅጽል።
"ይኸን ጊዜ"፡ "ይኸን ነገር ተው"። "ይህን" እይ።
ይኸንን፡ ዝኒ ከማሁ፡ "ይህነን"
አስተውል።
ይኸው፡ "ው" የ"ነው" ከፊል ነው፡ "ይኸ"፡ "ነው" አለ ያሠኛል። ሲዘረዝርም፡ ይኸውልዎ፡ ይኸው አለልዎ።
ይኸውለት፡ ይኸው አለለት። ይኸውልሽ፡ ይኸው አለልኸ። ይኸውልሽ፡ ይኸው አለልሽ። ይኸውላቸው፡ ይኸው አለላቸው። ይኸውላችኹ፡ ይኸው አለላችኹ። ይኸውላት፡ ይኸው አለላት ይላል።
ይኸውና፡ እንሆ ይኸ አለ፡ "እንሆ" የተባለው "ና" ከግእዛዊ ቃል "ከናሁ" የተከፈለ ነው።
ይኹን: ዕሺ፡ በጄ፡ ይደረግ።
ይዋይብኸ: የርግማን ቃል፡ ዋይ ይባልብኸ፣ ይለቀስብኸ።
ይዋጣለት: ኀይሉ ይታወቅለት፣ ይለይለት፣ ይባባል፣ ይሸናነፍ።
ይውጣብኸ: ባንተ ዠብዱ ይሠራ፡ ስመ ጥር ኹን፡ ዝናኸ ይሰማ።
ይዘታ (ዎች)፡ የተያዘ፡ በጅ፡
ዐደር፡ ነገር።
ይዘት (ቶች) (እኅዘት)፡ መያዝ። የዜማ ምልክት፡ አንዲት ነጥብ ()፡ የንባብ ማጥበቂያም ትኾናለች።
"መዝገበ ፊደል"
እይ።
ይዘጋ ካላችኹ መርሀባ: ይዘጋ አዳራሹ ባጋም ዕልፍኙ በቀጋ (የወሎ አልቃሽ)።
ይደነቃል፡ የሰው፡ ስም። ይድነቃቸው፡ ዝኒ፡ ከማሁ፡ ይግረማቸው፡ ማለት፡ ነው።
ይዲ: ይበል ዲያቆን (ቅዳሴ)።
ይድረስ፡ (ይብጻሕ)፡ የደብዳቤ'የመ ልክት፡ አርእስት። ይቅረብ፡ ማለት፡ ነው።
ይድረስታ፡ ይድረስ ማለት፡ አድራሻ።
ይድኖ: ከዠማ በስተግራ ያለ አገር ስም።
ይገም: የወረዳ ስም፡ በመንዝ ክፍል ያለ ቀበሌ። "ይሳብ፡ ይምጠጥ"
ማለት ነው።
ይገባል (ብዉሕ፣ መፍትው፣ ርቱዕ፣ ይደሉ): “ሰውን ከመመን እግዚአብሔርን ማመን ይገባል (ይሻላል)”።
ይገባል (ይትገባእ ኀሎ): መግባት ይቻላል።
ይገዙ፡ የሰው ስም፡ "ሰዎች ላንተ ይገዙ" ማለት ነው።
ይጋርዱ: የሴት ስም።
ይግለጡ፡ የሰው ስም፡ "ጠላቶች መንገድ ይልቀቁ" ማለት ነው።
ይግባኝ አለ: የተፈረደበትን ፍርድ ሳይቀበል ቀረ፡ “ለበላይ አስማለሁ” አለ (አማጠነ)።
ይግባኝ: ወደ በላይ ዳኛ “ይግባልኝ” (ይሰማልኝ)።
ይግባኝታ: ይግባኝ ማለት (ምጥንታ፣ አቤቱታ)።
ይግባኞች: አቤቱታዎች።
ይጠቅመኛል፡ ያጠግበኛል፡ ይበቃኛል።
ይጣ፡ ቀበሌ፡ ዐጣ።
ይጣ: በይፋት ክፍል ያለ ቀበሌ። "ይባዝን" ተመልከት።
ይጣ: የሩቅ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ፡ አያግኝ።
ይፋ (ኦሮ፡ ኢፋ፡ ብርሃን): ግልጥ፡ ስውር ያይዶለ ነገር።
"እከሌ በይፋ ተናገረ"
እንዲሉ።
ይፋታዊ: የይፋት ማለት ነው።
ይፋት: በሺዋ አውራጃ ያለ እፃር። በግእዝ "ዊፋት" ይባላል፡ በአረብኛም
"ወፋት"
ሞት ማለት ነው ይላሉ።
ይፋቶ: የገብስ ስም።
ይፋቶች: የይፋት ሰዎች፡ የይፋት ተወላጆች።
ይፋግ: በበጌምድር ከቃሮዳ በታች ያለ አገር።
ይፋግ: በበጌምድር ክፍል ያለ አገር (የቦታ ስም)።
ይፍቱኝ፡ እግዜር ይፍታ: የተናዛዥና ያናዛዥ ቃል።
ይፍጀው: ያቃጥለው፡ ይጨርሰው፡ ይቻለው (እንዲያቃጥል ወይም እንዲጨርስ)። "ሆድ ይፍጀው" እንዲሉ (አንድን ነገር በውስጥ መያዝን የሚያመለክት አባባል)።
ዮሐንስ (ጽርእ)፡ የሰው ስም፡ በዕብራይስጥ ዮሐናን ይባላል። ትርጓሜውም እግዜር ምሕረቱን ሰጠ ማለት ነው፡ ዳግመኛም ደስታ ተብሎ ይተረጐማል (ሉቃ፩፡ ፲፫፡ ፲፬)። ሌሎችም በዚህ ስም የሚጠሩ ብዙ ናቸው። "ዮሐንስ አፈ ወርቅ"፡ "ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ"፡ "ዮሐንስ መደብር"፡ "ዮሐንስ መጥምቅ" እንዲሉ።
ዮር: ከፊለ ስም፡ ዮርዳኖስ።
ዮር: የዮርዳኖስ ከፊል።
"በዮር በታቦር"
እንዲሉ መተርጕማን።
ዮርዳኖስ: የወንዝ ስም፡ ከላይ ፫፡ ከታች ፩ የኾነ ዠማ፡ ጌታችን የተጠመቀበት። ትርጓሜው የዳን ወንዝ ማለት ነው ይላሉ።
ዮሽ: የነገር ትራስ።
"ብርቅዮሽ"፡ "ሦስትዮሽ"።
ዮቅጣን: የሰው ስም፡ የዔቦር ልጅ። ዘሩ ቀጠነ ነው (ዘፍ፲፡ ፳፭-፳፱)።
ዮናኤል: የመልአክ ስም፡ ርግበ አምላክ ማለት ነው (ገድ ኪሮ)።
No comments:
Post a Comment