Friday, June 6, 2025

                                
ጀ፡ የደ ዲቃላ መጨረሻው ኾነ ግስ ሳድሱ በሣልስ ቅጽል ጫፍ ብዑ በመስም መድረሻ ይገኛል
ጀለ፡ ቄለ/ሰነፈ/ደነቈረ/ተሞኘ ("እንደ ልጅ ኾነ ዘሩ በግእዝ ዐገለ ነው")
ጀለተ (ዠለተ) አደገ/ረዘመ/ሰፋ/ተንሰራፋ/በዛ ("ናቸ ያትክልት")
ጀላ፡ እስኪት ነዊኅ
ጀሌ፡ ወረጋ ባዶ እጅ የጦር መግ ሪያ ያሊያዘ ዘማች
ጀሌ፡ የግስ ስም አለቃና ጭፍራ የሌ ለው ግስ (" ")
ጀልባ (ዎች) (ዐረ. ጀለበ ሳበ ጐተተ) ከታች ሳንቃ ከላይ ተራዳና መድ ያለው ባለሸራ ጥንታዊ መርከብ ("ታንኳ ፍልኳ በባሕር ላይ በነፋስ ኀይል እየተነዳ የሚኼድ ተሳቢ ተጐታች")
ጀመለ (ዐረ) ደመረ ("ብዙውን አን ድነት አደረገ የቍጥር የዕቃ")
ጀመረ ወጠነ ዠመረ
ጀመሬ (ደመረ) የቋድ ስም ("ዛብ ሥራ")
ጀማ ዥረት ዠማ
ጀማ ጃን
ጀምበር፡ ፀሓይ ጀንበር
ጀምጀም፡ በኦሮ ቤት በሲዳሞ ክፍል ያለ አገር
ጀረጀፈ (ገረገፈ) ፈጽሞ አረጀ/አፈጀ/ሸመገለ ("ሰውነቱ ከበደ") (ተመልከት፡ ገረጀፈን ተመ ልከት ከዚህ ጋራ አንድ ነው)
ጀር፡ በተጕለት ጫፍ ያለ አገር
ጀር፡ በደብረ ሊባኖስ ሰሜን ያለ አገር ("የቅድስት ሥላሴ መቅደስ የታነጸበት ጀር ገዳምእንዲሉ)
ጀርመኑ፡ ጀርመን
ጀርመን፡ የነገድ ስም ("ባውሮጳ ያለ ሕዝብ ከመስኮብ አገር ከወጣ ጎት ከሚ ባል ዘር የወረደ ጥበባዊ ጥበበኛ ነገድ እነ ዲልማንና አንስታይስ የተፈጠሩበት ሲበዛ ጀር መኖች ይላል")
ጀርመኖቹ፡ እነዚያ ጀርመኖች
ጀርመኗ/ጀርመኒቱ፡ ያች ጀርመን
ጀርጃፋ፡ የጀረጀፈ ("ገርጃፋ ሽማግሌ")
ጀሮች፡ የጀር መነኮሳት ("በጀር የሚ ኖሩ ሰዎች")
ጀበል (ዐረ) የተራራ ' ስም ("በየመን ያለ ተራራ ጀበል ሐበሽ እንዲል የመናዊ")
ጀበራ/ጅብራ (ሮች) የዛፍ ስም ("ታናሽ ዛፍ ቅጠለ ሰፋፊ ቀጥ ብሎ የሚ ቆም እንደ ጅብራ ተገተረእንዲሉ)
ጀበርቲ፡ የነገድ ስም ("ሸማ እየሠራ በትግሬ ውስጥ የሚኖር ሕዝብ")
ጀበና (ገመነ) የቡና ማፍሊያ ከብረት የተሠራ ዐንገታም ማሰሮ ("ከሸክላ የተ በጀ ጡታም ኵስኵስት ሲበዛ ጀበኖች ይላል")
ጀባ (ዎች) (ዘብድው) ባለጠጕር ዳባ
ጀብ፡ በይፋት ወረዳ ያለ አገር
ጀብ ውሃ፡ የጀብ ውሃ ("የጀብ ንዝ")
ጀብ/ጀይብ (ዐረ) በቀሚስ በእጀ ጠባብ ውስጥ የተሰፋ ኪስ
ጀብጀባ (ጃጃ)
ጀብጀባ ዛፍ፡ ጀጀባ
ጀቦነ (ገበነ) አለበሰ/ደረበ/ዐጀለ/ሸፈነ
ጀተሬ አገዳ፡ ዠተሬ
ጀነት (ዐረ) የገነት ስም ("ገነት")
ጀነቶ፡ ነጭና ቀይ ጠቃጠቆ ድብል ብል ዶቃ
ጀነነ (ዐረ. አሳበደ) አኰራ/አስ ታበየ/ዝም አሠኘ
ጀነነ = (ጃን በርህ) የብርሃን ጋን
ጀነጀነ (ትግ. ጀንጀነ ለገሰ ሰጠ) አብዝቶ አገባ/ጨመረ/መላ ጠቀጠቀ/ረገ ረገ/ጐዘጐዘ
ጀኒ፡ ቅማንት ያለበት አገር
ጀና/ዠ፡ ተወራራ ሾች ስለ ኾኑ ያጤ ዘርዐ ያዕቆብ ታሪክ ዣን ይላል
ጀናነነ፡ አኰራራ
ጀናኝ፡ የጀነነ/የሚጀንን ("የሚያኰራ አኵሪ")
ጀንበር (ጃን በርህ) የፀሓይ ስም ("ፀሓይ ትርጓሜው ትልቅ ብርሃን") (ዘፍ. ፩፡ ፲፯)
ጀንብ (ዐረ. አጠገብ) ከቀርቃባ ጭነት አንደኛው ("ባንድ ወገን ያለው ብዙ ጊዜም ጀንብ ለጨው ይነገራል")
ጀንዲ (ዎች) ተንቤን ነት ከጀዲ ሌጦ የተለፋ
ጀንዲ፡ የቈዳ ለምድ
ጀንገደር፡ የሣር ስም ("በጐዣም የሚ በቅል አበባ ያለው ግራምጣ ለቤት ክዳን ይኾናል") (ተመልከት፡ ኋደሬን እይ)
ጀንፎ የበትር ቀለበት፡ ዠንፎ
ጀዐል (ዐረ. ጀዐለ ሠራ) በረከት ጥጋብ የሥራ ፍሬ እንዳንራብ ጀዐል ("እንዳንሠራ በዓልእንዲሉ)
ጀውጃዋ/ዥዡ፡ ገውጋዋ
ጀዲድ (ዐረ) ዐዲስ
ጀጀረ (ገገረ) ምግብ ከለከለ ("አላ ስበላም አለ አወከ ቈሸበ ጀጀበ")
ጀጀበ ጀለተ
ጀጀበ፡ ጀጀረ/ቈሸበ
ጀጀባ፡ በወንዝ ዳር እንደ ወንዝ አድምቅ የሚበቅል ዛፍ ("ፍሬው የሚበላ በይፋትና በሐረርጌ አውራጃ በሌላውም አገር ኸሉ ይገኛል ቅዱስ መጽሐፍ ግን ጀብጀባ ይለዋል") (ኢዮ. ፵፡ ፳፪)
ጀገጀገ ረዘመ፡ ዠገዠገ
ጀገጀገ፡ ድምጥ ሰጠ/አሰማ
ጀገጀግ ዥማት፡ ዠገዠግ
ጀግና/ሐርበኛ ዠግና፡
ጀጐለ (ጨጐለ) ካበ/ገረገረ/ዐጠረ/ማገረ/ሸመጠጠ
ጀጐላም፡ ጀጐል ያለው ("ባለጀጐል ዐጥራም")
ጀጐል፡ ካብ/ግርግር/ዐጥር/ቅጥር/ጨቈን ("ሽምጥ የቤት ያትክልት ተገን ከለላ ጀጐል የውሻ ስም")
ጀጓይ፡ የጀጐለ/የሚጀጕል ("ማጋሪ ሸምጣጭ")
ጀፈል (ዐረ) የቡና እንቡጥ (ተመልከት፡ ገፈ ልን እይ)
ጀፈጀፈ (ገፈገፈ) በዝቶ በቀለ = ጐነቈለ/ለመለመ/አቈጠቈጠ (ነሐ. ፰፡ ፲፭) (ተመልከት፡ ደፈደፈን እይ)
ጀፍጀፎ፡ ቡቃያ ሣር ችግኝ
ጀፍጃፋ፡ የጀፈጀፈ ("በዛፍ ላይ የሚ ታይ ብዙ ቅጠል ተገድራ")
አለ ነደደ ("(ፋፋ)")
ጁኅ (ዐረ) በያይነቱ ቀለም የገባ ግምጃ
ጁህ ቀለም የገባ ልብስ፡ ጁኅ
ጁሆ፡ ቃብዱ መያዣ
ጁር (ትግ. ወገረ ሰረረ) አውራ በሬ እንዲጠቃና እንዲሰር ከእረኛ የሚነገር ቃል
ጁባ፡ የኦሮ ቤት ዠማ ("ዳዋና ገናሌ ዶሎ በሚባል ከተማ ከተጋጠሙ በኋላ ጁባ ይባላሉ")
ጂና፡ የቈዳ ጐመድ ቀለበት መሳይ
ጃሌ/ጃልዬ፡ የሰው ስም ("ልጄ የኔ ልጅ ማለት ነው") (ተመልከት፡ ገበታን እይ)
ጃል (ዕጓል) የስም ምትክ ("ልጅ ማለት ነው እባክኸ ጃልእንዲሉ)
ጃል፡ የቀበሌ ስም ("በደብብ ውስጥ ያለ ወረዳ")
ጃሎ ( ዕጓል) የሽለላ ዘፈን ("የጦር ልጅ ሐርበኛ ሆይ ማለት ነው")
ጃሎ መገን፡ ሽለላ ቅርርት
ጃሎዬ፡ የኔ ጃል/ጃሎ ሆዬ
ጃስ፡ ለውሻ የሚነገር ትዛዝ ("ያዝ ንከስ ማለት ነው ጃስ ኵቲእንዲል ባላ ገር) (ተመልከት፡ ያዘን እይ)
ጃራ፡ በሺዋ ክፍል በይፋት ውስጥ ያለ አገር
ጃርት ያውሬ ስም፡ ዣርት
ጃቡሳ (ሶች) ኀይለኛ ወንበዴ (" ማኛ ኦሮ ዘንዶ ሲል ጀዌ ቀማኛ ሲል ጀዌሳ የሚለው ከዚህ ጋራ አንድ ነው")
ጃን (ትግ) ትልቅ ዝንብ
ጃን (ትግ. ሐባ ጋን) ትልቅ
ጃን ሐፀና፡ የቀድሞ ዘመን ዳኛ የፍርድ ባለሥልጣን ማዕርግ ("ንጉሥ አሳደጋት ማለት ነው")
ጃን ሆይ (ጋን ሆይ ዝኆን ሆይ) ትልቅ ገናና ንጉሥ ሆይ
ጃን መራቂ፡ መንግሥትዎን ያስፋ ጠላትዎን ያጥፋ ብሎ ንጉሥን የሚመርቅ
ጃን ማሰሬ (ማሰሬ ጃን) የቀድሞ ዘመን ፈራጅ የማዕርግ ስም ("ጣለው ግረፈው የሚል ዳኛ (ማሰሬ ጃን) የንጉሥ ጅራፍ")
ጃን ማሰሬ፡ በጐንደር ያደባባይ ኢየ ሱስ ሹም ("ንጉሥ እንዳቡነ ፊልጶስ ዐለንጋ ሰጥቶ የሾመው ማለት ነው") (ተመልከት፡ ራቀ ብለኸ ራቅ ማሰሬን እይ ከዚህ ጋራ አንድ ነው)
ጃን ማሰሬዎች፡ ዳኞች/ፈራጆች
ጃን ሜዳ (ሜዳ ጃን) የንጉሥ ሜዳ ("ንጉሡ የጦር ሰራዊት ሰልፍ የሚያይ")
ጃን ሜዳ፡ ትልቅና ሰፊ ሜዳ
ጃን ሥዩም (ሥዩመ ጃን) የንጉሥ ስም ("ባ፲፩፻ በላስታ የነገሠ የኢትዮጵያ ንጉሥ ትልቅ ሹም ወይም አባቱ ንጉሥ ዐልጋውን ያወረሰውና የሾመው ተብሎ ይተረጐማል")
ጃን ሸላሚ፡ የንጉሥ አንጥረኛ የዕ ንቍና ያልማዝ የወርቅና የብር ሽልማት ራተኛ ("ንጉሥን በብዙ ዐይነት ጌጥ የሚሸል ምና የሚያንቈጠቍጥ ዘውድ የሚያቀዳጅ")
ጃን ተከል፡ የቤተ መንግሥት ዝቅ ተኛ መኰንን በጐንደር
ጃን ተከል፡ የጐንደር ንጉሥ ባደባ ባይ ዐልፎ ዐልፎ የተከለው (የሠራው) ዥም የግንብ ዐምድ የበለው ንጉሥ የሚን በረከክበት ("የሩቁን ማያ መመልከቻ በግእዝ ማኅፈድ ይባላል")
ጃን፡ ትልቅ ሹም ባለሥልጣን ዳኛ አገረ ገዥ
ጃን አሞራ፡ ያገር ስም ("በጐንደር በኩል ያለ አገር ትልቅ አሞራ ማለት ነው ጃን አሞራ የማዕርግ ስም")
ጃን አስግድ፡ በ፲፫፻ ዓመተ ምሕ ረት የነበረ የሐበሻ ንጉሥ ("ትርጓሜው ንጉ ሥን አሰግድ ማለት ነው")
ጃን ደረባ (ደረባ ጃን) የንጉሥ ባለል ' ታማኝ ("ስልብ ሴት ጠባቂ") (ኤር. ፴፰፡ ፯፡ ኢሳ. ፶፮፡ )
ጃን ደረባ፡ ስለ ጽድቅ በፈቃዱ ከሴት የራቀ (ማቴ. ፲፱፡ ፲፪)
ጃን ደረባ፡ በተፈጥሮ ትእምርተ ተባ ዕት ያነሰው የጐደለው ("ብልቱ የሽንብራ አፍንጫ የሚያኸል ሰው")
ጃን ደረባ አደረገ (ኀጸወ) ሰለበ ("ኣባለ ዘርን ቈረጠ ጐመደ")
ጃን ገበር (ገበሬ ጃን) የንጉሥ ገበሬ ሑዳድ ዐራሽ
ጃን ገበር፡ ከሠራተኛ ኹሉ የሚበ ልጥ ትልቅ ገበሬ
ጃን ጥላ (ጥላ ጃን) የንጉሥ ጥላ ከግምጃ ከሐር የተበጀ ("በክብር ከድባብና ከቀጤማ ጥላ ስለሚበልጥ ጃን ጥላ (ታላቅ ጥላ) ተባለ")
ጃን ጥላ፡ በያይነቱ ቀለም የገባ ተራ ጥላ ("በዝናምና በፀሓይ ጊዜ የሚያዝ")
ጃን ጥራር (ጃን ጽላል) ጽላለ ጃን ("የንጉሥ ጥላ")
ጃን ጥራር (ፅራረ ጃን) የማዕርግ ስም ("የንጉሥ ጥሩር ሹም ያምባሰል ባላባት በዚህ ስም ይጠራል ጃን ጥራር አስፋውእንዲሉ)
ጃን ጥራር፡ ትልቅ ጥራር ("ጥላነት ያለው")
ጃን ጽራግ (ጽራገ ጃን) የንጉሥ ዐንገት ጌጥ ("ወይም የጽራግ ሹም") (ተመልከት፡ ጽራግን እይ)
ጃንደረባ፡ በዥሮንድ የገንዘብ ሹም (ግብ. ሐዋ. ፰፡ ፳፯) (ተመልከት፡ ደረብን እይ)
ጃንጁላቴ፡ ቍንጯም ወፍ እንድርማ ሚት (ትር መቅ ወን)
ጃኖ (ዎች) በሰፊ ቀይ ጥለት የተሠራ ዝቅዝቅ ልብስ (ተመልከት፡ ድርብን ባሕርን)
ጃኖ፡ የቀይ ጥለት ስም
ጃዊ፡ የጭፍራ ስም ("በጐንደር መንግ ሥት የነበረ የከተማ ዘበኛ ይኸውም ከግቤ ጥቶ በአባይ ዳር የተቀመጠ የኦሮ ነገድ ነው ጃዊ የደጃች ውቤ የፈረስ ስም አባ ጃዊ እንዲሉ")
ጃዌ (ጁኃዊ) ቀይ ሱቲ ለመሶብ ለሌላውም ዕቃና መሣሪያ ልብስ የሚኾን
ጃጃታ፡ ጋጋታ
ጃግሬ፡ ጋሻና ሰይፍ ያዥ፡ ግሬ
ጅኁር (ትግ. ሐባ) ትምክሕተኛ ጕረኛ ማለት ነው ("በግእዝ ዝኁር ይባላል ጅኁር የቀበሌ ስም የጅሩ አፋፍ")
ጅሁር የቀበሌ ስም፡ ጅኁር
ጅላዋት፡ ዝኒ ከማሁ ለጅል ("ቂል አስተኔ ኀዋትን እይ ርግጠኛው ቃል (ኀዋተ ጅል) የጅል ወንድሞች (ወንድም) ነው ቈለ ብለኸ ቂልን ተመልከት")
ጅላጅል፡ የጅል ጅል
ጅል፡ ቂል/ሰነፍ/ደንቈሮ/ሞኝ/አላ ዋቂ/መጥፎ (መክ. ፪፡ )
ጅልነት፡ ጅል መኾን ("ሞኝነት") (መክ. ፩፡ ፲፯)
ጅልጊ፡ የቈርበት ስልቻ ልጊ
ጅሎች፡ ቂሎች/ሞኞች (ምሳ. ፰፡ )
ጅማ፡ በኦሮ ቤት ያለ አገር
ጅም (ዐረ. ጀመመ በዛ) ብዙ ጠጠር በገበጣ ጕድጓድ አንዳንድ ላይ የታ ከበ የተሰበሰበ ("ስብስብ እክብ ጅሙ የታ ፈሠ ገበጣእንዲሉ)
ጅም ታለኝ፡ በጅሜ እጫወታለኹ
ጅም ታለኸ፡ በጅምኸ ተጫወት
ጅምላ፡ ድምር ("መላው ጠቅላላው በጅምላ ገዛእንዲሉ)
ጅሥ (ጊሢ) ላምን ለመከልከል የሚነገር ቃል ("ገሥግሽ ኺጂ ማለት ነው") (ተመልከት፡ ውስን)
ጅስ ኺጂ
ጅሪ፡ የጅር ' ወገን
ጅራፍ (ፎች) (ገረፈ ግራፍ) ከጠ ፍር ከልጥ ከቃጫ ከጭረት ከሣር የተበጀና የተገመደ ("ገበሬ በሬን የሚገርፍበት ንጉሥ ጥፋተኛን የሚቀጣበት እረኛ ለቡሔ የሚያ ጮኸው ግንዶሽ ሶለግ ቍግ እጀታ ዕንጨት ያለው")
ጅር (ገረገረ) የዝንጀሮ መንጋ ባንድ ገመር የሚመራ ("ሙሊውም ደቦ ሉም")
ጅርጅር አለ፡ ግርግር አለ ("ተነ ሣሣ")
ጅቡቲ (እጀ ቡቲ) በህንድ ውቅያኖስ ዳር በምሥራቅ በኩል ያለ የኢትዮጵያ ጠረፍ የባሕር ወደብ የመርከብ መቆሚያ ("ባፄ ምኒልክ ጊዜ ፈረንሳዮች እስከ ደወሌ ቅኚ አድርገው ይዘውታል እጀ ቡቲ ለት የእፍኝት ዐይን (ኦሮ)")
ጅቡቲዎች፡ የጅቡቲ ተወላጆች (" ይም ነዋሪዎች ሰዎች")
ጅቡን፡ የተጀቦነ ("ዕጅል ሽፍን")
ጅባር፡ ደብር/ተራራ
ጅብ፡ በቁሙ፡ ዥብ
ጅብ አለ (ተጋብአ ገብአ) ተሰ በሰበ/ተጠራቀመ/ታጀበ/ተከማቸ/ታከበ/አን ድነት ኾነ
ጅብሪ አሞራ ዥብሪ
ጅብታ፡ ጅብ ማለት ("ርጋታ ጸጥታ")
ጅብታ ጸጥታ፡ ጅብ አለ
ጅብና (ግብነት) ያይብ ልጥልጥ ("ወይም ዶቄት ፈረንጆች ፍሮማዥ ይሉታል")
ጅኒያም፡ ጋኔናም ("ጋኔን ያደረበት እብድ በዐረብ መጅኑን ይባላል")
ጅን
ጅን (ዐረ) ጋኔን/ሰይጣን/ዛር
ጅን ዋሻ (የጅን ዋሻ) ከጫ ወንዝ በስተቀኝ ያለ ቀበሌ ("የታች ወግዳ ክፍል ያማኔል አጥቢያ ጅን ዋሻ ዐማኔልእንዲሉ)
ጅን፡ የባሕር በሬ ("የጅን ከብት ዲኖ ከባሕር እየወጣ ሌሊት ሣር የሚበላ ላም የሚሰር የዶባና ያጋዘን ዐይነት ጅን መባሉ ቀን ባለመታየቱ ነው")
ጅን፡ ጋኔን
ጅንን (ኖች) የተጀነነ ("ኵሩ ኵራ ተኛ")
ጅንጅን አለ፡ ግጥም አለ
ጅንጅን፡ የተጀነጀነ ("ምሉ ጥቅጥቅ እንግዳ የጎበጣ ጠጠር")
ጅንግላ (ገንዶራ) የእግር ማሰሪያ ግንድ ("ያባያ ቀንበር ግንዲላ")
ጅኖች፡ አጋንንት/ዛሮች (ኢሳ. ፲፫፡ ፳፩)
ጅጀት፡ በዠማና በወንዝ ውስጥ ያለ ኰረት ("ትልቁም ትንሹም እንደ ጕዝጓዝ ኹኖ ውሃ በላዩ የሚተኛበትና የሚያልፍበት የወጣበት አንቀጽ ዣዣ ስለ ኾነ ዥዠት ሊባልም ይችላል")
ጅጅጋ፡ ያገር ስም ("በሐረርጌና በው ጋዴ መካከል ያለ አገር ኦሮና ሱማሌ ግን ጅግጅጋ ይሉታል የሚናድ ፈራሽ ማለት ነው የመሬቱን ልልነት ያሳያል ይኸውም ኦሮ ጅጌ ፈረሰ ጅግጅጌ ፈራረሰ ከሚለው ቃል የወጣ ነው")
ጅጕል፡ የተጀጐለ/የተሸመጠጠ
ጅጊ፡ ራስ ስሞሽ í ብዙ ሰው የሚሠራው ግብርና ዕርሻ ቍፋሮ ዐጨዳ ያዝ
ጅግል (ደገለለ) ጨብጥ ቍላን የሚ ደገልል ' የሚያሳብጥ
ጅግራ በቁሙ፡ ዥግራ
ጅግጅጋ፡ ያገር ስም ጅጅጋ
ጅግጅግታ፡ የክንፍ የላንፋ የቅጠል የፋፋቴ ድምጥ (ሕዝ. ፩፡ ፳፬)
ጅፋር (ኦሮ) ጌጥ ማለት ነው
ጆቴ፡ የወለጋ ባላባት
ጆንያ (ዮች) የጭረት የቃጫ ከረ ጢት ("እንደ ጭልጊ የተሰፋ ትልቁም ትን ሹም")
ጆፌ፡ ላባውና ጠጕሩ የበዛ አሞራ ጥንበ በላ
ጆፌ፡ ብዙ ላባ፡ ጀፈጀፈ
ጆፍጆፌ፡ ብዛትና ርዝማኔ ያለው ቈንዳላ ጠጕር

No comments:

Post a Comment

ሽፋን

  ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ