Friday, June 6, 2025

 

ዘ፡ ፯ኛ ፊደል በግእዝ አልፍ ቤት በአበገደ በአኃዝነት ዘ፯ ("በፊደልነት ዛይ ይባላል")
ዘ፡ በቂ
ዘ፡ የደ ወራሽ ("ደፈቀ ዘፈቀ")
ዘኅነን ዝኅንን፡ (ፐፒራ) ምንጭ ርር፡ የሚባል፡ ሐረግ፡ የሥሩ፡ ዱቄት
ዘህነን፡ የቀለም ዱቄት ዘኅ ነን
ዘኅነን/ዝኅንን (ፐፒራ) ምንጭ ርር የሚባል ሐረግ ("የሥሩ ዱቄት")
ዘለለ (ዘሊል ዘለ ቀነጸ አንፈርዐጸ) ናረ/ነጠረ/ጓነ/መር አለ ("ፈረ") ( ሳሙ. ፮፡ ፲፯)
ዘለለ (ዘልሐ ዐጸረ) ውሃ ጨመረ/ መላ ("ጠመቀ በጠበጠ አቦካ")
ዘለለ፡ ተወ/ዐለፈ/ተራመደ
ዘለለ፡ አሳረፈ/ዘረጋ/ዘረረ
ዘለለ፡ አደገ/ከፍ አለ/ላቀ/በለጠ ("ዘለግ አለ")
ዘለለ፡ ዘላለም
ዘለላ (ዎች) ፍሬዎች ያሉባት አንዲት ዐረግ (ዘፍ. ፵፡ ፲፡ ዘኍ. ፲፫፡ ፳፫, ፳፬)
ዘለላ፡ አንድ ጊዜ የወረደ እንባ ("ተለላ")
ዘለሌ፡ ዘለለው ("የሰው ስም በለጤ በለጠው ማለት ነው")
ዘለል (ሎች) የዘለለች
ዘለል፡ መር/ላቅ/በለጥ ("አለል ዘለልእንዲሉ)
ዘለል አለ፡ አመንዝራ ኾነ/ባለገ/ከልክ ዐለፈ
ዘለል አለ፡ ከፍ አለ/ላቀ
ዘለልታ፡ ዝኒ ከማሁ
ዘለመ (ዐረ ከዳ ካደ ሸፈጠ) ወለመ ("ጠመመ ጠማማ ኾነ")
ዘለመ ዘለቀ
ዘለም አለ፡ ወለም ጠመም አለ
ዘለሰ (ዘለፈ) ቈረጠ/ቈጠቈጠ/መለመለ/አወደቀ/ቀለሰ/አስተኛ/አጋደመ ("ለሸለሸ የደን")
ዘለሠ፡ አስተኛ ("ዘለሰ")
ዘለሰ፡ አቀረቀረ/አዘነበለ ዐንገቱን
ዘለሰ፡ ዘሙደ
ዘለሰኛ፡ የመሰንቆ ምት ("ባለኹለት ግጥም ረገብ አድርጎ የሚዜም")
ዘለሳ፡ ቈረጣ/ቍጥቈጣ/ምልመላ
ዘለሳ፡ የወዘፍ ዐጥር
ዘለሳ፡ ዳስ ("የዳስ ዐይነት ማስ፵ የመ ሰለ ሰቀላ")
ዘለስ፡ ተደራርቦ የወደቀ ቅርንጫፍ/ ጽቅ/ቅጠል
ዘለስላሳ፡ የሚዝለሰለስ ("ዘለፍላፋ ቀለ ስላሳ")
ዘለቀ (ዘለገ) መጣ/ገባ/ጠለቀ (" ልቅ ኾነ")
ዘለቀ፡ ቈየ/ሰነበተ
ዘለቀ፡ በሳ/ነደለ/ዐለፈ/ኼደ/ራቀ
ዘለቀ፡ ብቅ አለ ("ታየ") ( ነገ. ፮፡ ፳፮)
ዘለቀ፡ አነበበ/ወጣ/ፈጸመ/ጨረሰ
ዘለቀ፡ የሰው ስም
ዘለቃ ወጋ፡ በስተዠርባ ወጣ ("የጦሩ ውልብልሲት")
ዘለቃ፡ የወንድና የሴት ስም ("አቶ ዘለቃ እመት ዘለቃ")
ዘለቃ ጦር፡ ጨርሶ ወግቶ ከነሶማያው ሾልኮ የሚኼድ
ዘለቃ/ዘለቄታ፡ ፍጻሜ/መጨረሻ
ዘለቅ፡ መዝለቅ
ዘለቅ አለ፡ ገባ አለ/አራሰ
ዘለበት (ቶች) የፈረስ/የበቅሎ ዕቃ ("የቀበቶ የሠቅ የዝናር ማጋጠሚያ ብረት")
ዘለባበደ፡ ነገር ለዋወጠ ("ዕሥሥትኛ ኾነ ንግግሩ ቃሉ")
ዘለባብዳ፡ ዕሥሥት
ዘለብ (ዘነብ) ዥራት
ዘለነ፡ አጐዳን/አዛወረ ("የማደሪያ የመንጋ ፪ኛውን ዘለለ እይ")
ዘለንጋ (ጎች) በያይነቱ ዕቃ ማስ ቀመጫ ቈጥ ("እንደ መንበር ኹኖ የተሠራ በጭቃ ተመርጎ በበት የተለቀለቀ ፪ና ረድፍ ያለው")
ዘለዘለ (ዘረዘረ) ሠነጠቀ/ሸነሸነ/አቀጠነ ("አረዘመ የሥጋ")
ዘለዘለ፡ በጣም ነከሰ/ዘነተረ
ዘለዘል/ዘልዛላ/ዘልዘልቱ፡ የተንዘለዘለ ("ሐግ ያልተባለ መረን ስድ አግድሞ ኣደግ ዘዋሪ ወሮ በላ እንዛዝላ")
ዘለገ (ዘለቀ) ረዘመ/አደገ/ከፍ አለ
ዘለግ አለ፡ መለል አለ
ዘለግ ያለ፡ የረዘመ ( ሳሙ. ፱፡ )
ዘለግተኛ፡ ከፍተኛ ቁመታም
ዘለግታ፡ መለልታ/ከፍታ ( ሳሙ. ፲፮፡ )
ዘለግታ፡ ዘለግ ማለት ("መርዘም")
ዘለጐሰ (ዘልገሰ ቈሰለ) ጥፈትን ዘለለ/ገደፈ/ኣበላሸ ("አላገባብ ጻፈ ሸት")
ዘለጐሰ፡ ዘለለ
ዘለፈ (ዘሊፍ ዘለፈ) ገሠጸ/ወቀሠ/ መከረ/ነቀፈ/ሰደበ (ዘፍ. ፳፩፡ ፳፭፡ ሳሙ. ፫፡ ፰፡ ሚል. ፫፡ ፲፩)
ዘለፈ፡ ዘለሰ/አዘነበለ
ዘለፋ፡ ግሠጻ/ነቀፋ/ስድብ/ምክር
ዘለፍ አለ፡ ዘንበል አለ/ተጐነበሰ
ዘለፍ አደረገ፡ ዐንገቱን ደፋ/አዘነበለ
ዘለፍላፋ፡ የሚዝለፈለፍ ("ደካማ ልል")
ዘለፍላፌ፡ የዘለፍላፋ ወገን/ዐይነት
ዘሊል፡ ሰነፍ ("የሰንበት እበት ሊል ዘሊልእንዲሉ)
ዘሊሞ፡ የዛፍ ስም ("ጠማማ ዕንጨት")
ዘሊቅ፡ ዝኒ ከማሁ
ዘሊቅ፡ የሰው ስም
ዘሊቦ (ዝሉፍ) ወራዳ/ልፍስፍስ
ዘላለለ፡ ጨፋፈረ ("መር መር አለ")
ዘላለማዊ፡ የዘላለም ("እግዜር")
ዘላለም (ዘለዓለም) ፍጸሜ መጨ ረሻ የሌለው ጊዜ/ዓመት/ዘመን ("ፍጻሜ ላለውም ይነገራል። እከሌ በደንጊያ ብቻ የዘላለም ቤት ሠራ በግእዝ ግን (ዘለዓለም) የዘላለም ማለት ነው")
ዘላለምነት፡ ዘላለም መኾን/መኖር
ዘላለፈ፡ ገሣሠጸ/ነቃቀፈ/ተቈጣጣ
ዘላላ፡ ዝኒ ከማሁ
ዘላሌ፡ የዘላላ ወገን
ዘላሳ፡ ወደ ታች የተመለሰ ("ቀላሳ ንድ")
ዘላሽ (ሾች) የዘለሰ/የሚዘልስ (" ራጭ ቈጥቋጭ")
ዘላቂ፡ የዘለቀ/የሚዘልቅ ("ጠላቂ ገቢ ጦር ቅባት")
ዘላበደ (ለበደ) ወላበደ/ወላወለ/ቃል ለወጠ/ቀላመደ
ዘላባጅ (ጆች) ወላባጅ/ወላዋይ
ዘላን (ኖች) በዱር በበረሓ ከብት እያረባና እየጐዳኘ የሚኖር ሕዝብ
ዘላንነት፡ ዘላን መኾን
ዘላይ (ዮች) የዘለለ/የሚዘል/የሚጨፍር/የሚያልፍ ("ዐላፊ ጨፋሪ")
ዘላይ፡ ዘለላን የሚዘልል/የሚጠምቅ ("ጠማቂ በጥባጭ ጠላን ጠጅን")
ዘላጋ፡ ረዥም/መለሎ
ዘላፊ (ፎች) የዘለፈ/የሚዘልፍ/የሚ ገሥጽ ("ነቃፊ") (ኢዮ. ፵፡ )
ዘላፊ፡ ዘላሽ
ዘል መንዘል አለ፡ ወዳንድ ፊት ደፋ
ዘልስ፡ የፈረስ ስም ("አባ ዘልስእንዲሉ)
ዘልባዳ፡ ኹለት ምላስ/ቀልማዳ
ዘልዘል አለ፡ ተንዘለዘለ
ዘልዛላነት፡ ዘልዛላ መኾን ("መረንነት")
ዘልዛይ (ዮች) የዘለዘለ/የሚዘለዝል ("አጥብቆ ነካሽ")
ዘልዳ የልዳ፡ ሰው፡
ዘልጓሳ/ዝልጕስ፡ የተዘለጐሰ ("ብላሽ መጽሐፍ አላዋቂ የጻፈው")
ዘልጓሽ፡ የዘለጐሰ/የሚዘለጕስ ("ገዳፍ")
ዘሎ ባይኔ፡ ዐይነ ውሃ ("የውሃ ዐይን ወይም እንክብል ፈረንጆች ቡልዶ ይሉታል")
ዘሎ ባይኔ፡ ውሃና መስተዋት መሳይ ትልቅ ዶቃ ("መካከሉ ተረተርማ የኾነ አምሮስለሚታይ ዘሎ ባይኔ ተባለ")
ዘሎ፡ ትቶ/ዐልፎ/ንሮ/ነጥሮ
ዘሎ ገባ፡ ጌታውን ትቶ እሌላ ሰው ቤት የገባ ዘው ያለ ውሻ
ዘመላክ (ዘመልአክ) የክርስትና፡
ዘመመ (ዘሚም ዘመ) ዘነበለ/ጋደለ ("በዘንግ በመቋሚያ ምድርን በመድቃትና በመውጋት አዜመ")
ዘመመ፡ ከለከለ/ዝም አሠኘ
ዘመመ፡ ዝማም ሠራ/አገባ
ዘመመ፡ ደረደረ/ከመረ ("ጐቸ ሞላላ አድርጎ")
ዘመመን፡ ሞላላና ዥልጥ ጕቾ ድር
ዘመሚት (ቶች) ቀይ የደጋ ሥጥ ("ደም የሚመስል እሱ የበላው ዕንጨት ስለሚዘም ዘመሚት ተባለ")
ዘመም (ዘሚም) መዝመም
ዘመም አለ፡ ዘንበል አለ
ዘመስ፡ ዝኒ ከማሁ (ራእ. ፲፬፡ ) ("ትር ጓሜ")
ዘመረ (ዘምሮ ዘመረ) ዝማሬ ቃኘ/ በገና መታ/ደረደረ ("ዳዊት አዜመ ምስጋና አቀረበ")
ዘመር፡ የሐሳዊ መሲሕ ስም ("ዐጪር ምልክት ጓሜ")
ዘመተ (ትግ ዘመተ ዘረፈ ቀማ) ወደ ጦርነት/ወደ ውጊያ ኼደ ("ለመግደል ለመውረር ለመዝረፍ ለመቀማት")
ዘመቻ፡ የውጊያጕዞ ("ወይም ግሥገሣ")
ዘመቻ፡ ጠብ/ጥል/ግድያ/ውጊት/ዘረፋ/ቅሚያ
ዘመቻ ፈሪ፡ ዘመቻን የፈራ/የሚፈራ
ዘመነ ሐዲስ፡ የወንጌል ዘመን
ዘመነ ሰማዕታት፡ የነዲዮቅልጥያኖስ ጊዜ ("ሰማዕታት መከራ እየተቀበሉ የሞቱበት")
ዘመነ ሥጋዌ፡ ጌታችን ሥጋ የለበ ሰበት/ሰው የኾነበት ጊዜ ("ከዚያም ወዲህ ያለው ዓመት")
ዘመነ ብሉይ፡ የኦሪት ዘመን
ዘመነ እንኰዬ፡ እንደ ልብ የሚበሉበት/የሚጠጡበት የጥጋብ ጊዜ
ዘመነ ግልምቢጥ፡ የግልብጮ ዘመን ("እውነት የጠፋበት ሐሰት የሠለጠነበት ጊዜ")
ዘመናይ (ዮች) (ዘመናዊ) ዘበናይ ("ባለጊዜ")
ዘመን (ኖች) ረዥም ጊዜ/ብዙ ዓመት
ዘመን አመጣሽ፡ ዘመን ያመጣው/የወለደው ዘፈን/ልብስ ("ወይም ሌላ ነገር")
ዘመንፈስ የክርስትና ስም።
ዘመወ) እመነዘረ/ሴሰነ/ቀነዘረ
ዘመወ) ዘመዘመ
ዘመዘመ (ዐረ ዘምዘመ) አገደ
ዘመዘመ (ዘመመ) ሰፋ/ጠቀመ/ ቀመቀመ/ጠለፈ/አስጌጠ ("የበርኖስ የቀሚስ ዐንገትጌን ያዝራር መግቢያን")
ዘመዘመ፡ ዘመመ
ዘመደ (ዘሚድ ዘመደ) ወለደ/ ዘመድ አደረገ/ወገነ/ቀላቀለ ("ደምን ከደም")
ዘመዳም (ሞች) ባለዘመድ ("ዘመደ")
ዘመዴ፡ የኔ ዘመድ
ዘመድ (ዶች) ተወላጅ/ዘር ("የአባትና የናት ወገን ቅርብና ሩቅ ቤት ቤት ቤት ቤት ቤት ከዚህም በላይ ያለ ቤተ ዘመድ")
ዘመድ ኹን፡ የሰው ስም
ዘመድ ዘር፡ ቃሉ ከአባት ዘር ያልተለየ ("በሥሩ ባዕድ በጫፉ ምእላድ ያልጨ መረ ስም ወይም ጥሬ ይህም ዘለቀ ብሎ ዘለቃ ዘመተ ብሎ ዘመቻ ማለቱን ያሳያል")
ዘመድ ገዛ፡ ወዳጅ አበጀ/ወገን አበዛ
ዘመድነት፡ ዘመድ መኾን
ዘሚካኤል የክርስትና፡ ስም፡ ገብረሚካኤል፡ ወልዶ፡ ሚካኤል፡ ማለት፡ ነው ።ባላገር፡ ግን፡ ዘሚኻዬል፡ ይላል (ተረት) ቢቸግር፡ ነው፡ እንጂ፡ ዘሚኻዬል፡ ስም፡ ነው። እየተወለደ፡ ዘሚኻዬል
ዘማ፡ አመንዝራ ሴት፡ (ዘመወ)
ዘማ፡ ጋለሞታ/አመንዝራ ሴት/ሸርሙጣ ኻያጅ
ዘማሚ፡ የሚዘም/የሚያዜም ("ካህን ደብተራ ዘንባይ")
ዘማሚ፡ የሚዘምም ("ደርዳሪ ከማሪ")
ዘማሪ (ዎች) የዘመረ/የሚዘምር ("በገና መቺ ደርዳሪ")
ዘማሪያም (ዘማርያም) የክርስትና ስም።
ዘማት፡ ቅጠሉ ሽነት የሚመስል ሥረ ብዙ ዛፍ ("በገደል ላይ የሚዘምት ዐጽቃም ደም የሚወጣው")
ዘማች (ቾች) የዘመተ/የሚዘምት ("የጦር ሰራዊት ወታደር ጭፍራ")
ዘማች አሞራ፡ ተወግቶ የወደቀውን ሰው ዐይን ለመጥቃትና ሥጋውን ለመብላት ከዘማች ጋራ የሚኼድ አሞራ ("በግእዝ አውስት ይባላል")
ዘማች አንቀጽ፡ በኀላፊ/በትንቢት/በዘንድ/በትእዛዝ ("ባ፭ አዕማድ ባድራጊ ባስደራጊ በተደራጊ በተደራራጊ ባደራራጊ የሚ ረባ ግስ ዐወቀን ገደለን ቀደሰን የመሰለ")
ዘማኑም፡ የጥንብ በላ ዐይነት አሞራ
ዘማዊ፡ የሚሴስን/ሴሰኛ/ቅንዝረኛ ("አመንዝራ ወንድ የዘማ ወገን")
ዘምቶ ተወረስ፡ ዘምቶ የተወረሰ ("ባጕል የቀረ ጥፋተኛ")
ዘምቶ፡ እጦር ኺዶ
ዘምዘም፡ የእስላሞች ጠበል ("እግዜር ለአጋርና ለልጂ ለይስማኤል ያፈለቀው") (ዘፍ. ፳፩፡ ፲፱)
ዘምዛሚ (ሞች) የዘመዘመ/የሚዘመዝም ("ጠቃሚ ቀምቃሚ ጠላፊ")
ዘሞተ (ዘመወ) ከሰው ሴት ኼደ ("ያችንም ያችንም ለከፈ")
ዘሞተ፡ አመነዘረ፡ (ዘመወ)
ዘሴ፡ የክርስትና ፊለ ስም ("ዘሥላሴ ማለት ነው")
ዘረ መልካም፡ ዘረ ደግ/ዘረ ማለፊያ
ዘረ መትር፡ ያሣ ወጥመድ ("ባለወንፊት መረብ ያሣን ዘር የሚመትር")
ዘረ መጥፎ፡ ዘረ ቢስ
ዘረ ቈርጥም፡ የዘሩበትን የማያበቅል መሬት
ዘረ ቢስ፡ ዘሩ ወገኑ ንፉግ የኾነ ("ዘረ መጥፎ")
ዘረ ክፉ፡ ዘሩ ክፉ የኾነ
ዘረ ደግ፡ ዘሩ ቸር የኾነ ("ዘረ መልካም")
ዘረ ጥሩ፡ የጨዋ ልጅ ነውር እንከን የሌለበት
ዘረመትር/ያሣ ወጥመድ ዘራ (ዘርዐ)
ዘረመጠ፡ በኀይል ሰረረ ("የእንስሳ")
ዘረምቦ (ዘረንቦ) ከሻሻቴ የሚበ ልጥ ከሲውሲዋ የሚያንስ ዶሮ
ዘረረ፡ አደረሰ
ዘረረ፡ ዘለለ/ዘረጋ/አሰጣ/ሰተረ/ለፀሓይ ሰጠ ("አስተኛ አጋደመ ኹለተኛውን ዘለለ እይ")
ዘረር፡ የጐመን ስም ("ሰናፍጭ የሚመስል ነጭ የዱር ጐመን በማሳ ውስጥ የሚ በቅል የወፍ ዘረር እንዲሉ ዘረር ማለት ፍሬው ረግፎ በመሬት መሰጣቱንና የወፍ መኖ መኾኑን ያሳያል")
ዘረበ (ዘሪብ ዘረበ) መታ/ቀጠቀጠ (ግእዝ)
ዘረበበ (ረበበ) ውሃን ከተቀቀለ ነገር ውስጥ አፈሰሰ ("አጠነፈፈ አንጠፈጠፈ")
ዘረበብ/ዘረበቦ/ዘርባባ፡ የተንዘረበበ ("እንዝርብ በግእዝም (ዘረበበ ዘረበቦ) የዘረጋ የዘረጋው ማለት ነው")
ዘረብረብ አለ፡ ጠብ ጠብ/ዘረክ ረክ አለ
ዘረብረብ፡ የቧልት ንግግር
ዘረብራባ/ዝርብርብ፡ የተዝረበረበ ("እንጥብጥብ ልጋግ")
ዘረት፡ የቀበሌ ስም ("ካዳባይ በስተቀኝ ያለ ገጠር")
ዘረነቀ (ዘረቀ) አለስፍራው/አለጕ ዳዩ ኣገባ/ጨመረ/ዶለ/ነከረ
ዘረነቀ፡ ነገር አበላሸ/ዘባረቀ
ዘረከ/ዘሪክ ዘረከ) አዝረከረከ ("በያለበት ዐልፎ ዐልፎ ጣለ ገደፈ አዝረፈረፈ")
ዘረከቦ (ዘከረቦ) ቅርጫት ሆድ ("ዘርጣጣ በግእዝ ግን ያገኘው ተብሎ በቅጽልነት ይፈታል")
ዘረከተ፡ ቀደደ/ቦጨቀ/ሸረከተ/ዘረ ገፈ
ዘረከተ፡ ነፋ ("ሆድን")
ዘረኰተ (ረኰተ) ዘለጐሰ/አበላሸ ("ቃል ዘለለ ጣለ")
ዘረኰተ፡ ዘረፈ
ዘረዘረ (ዘርዘረ ሰብለ) ምርቅ አበጀ ("በተነ ለየ ድብድቡን ፍሬ ዠመረ ለመውለድ ለመሸት")
ዘረዘረ፡ ሞረደ/ፈገፈገ/ሳለ ("ለማጭድ ለመጋዝ ጥርስ አወጣ")
ዘረዘረ፡ ሸከሸከ/ዘከዘከ/አሣሣ/አራራቀ ("የሸማ የወንፊት የጥርስ")
ዘረዘረ፡ ብርን መነዘረ/ሸረፈ
ዘረዘረ፡ ነገርን አንድ ባንድ አስረዳ
ዘረዘረ፡ ዘረጠ
ዘረዘረ፡ የፊደልን ቅርጽ አሣጥን ውስጥ አገባ መለሰ
ዘረገገ (ትግ ዘረገ) በጠበጠ/ አደፈረሰ
ዘረገገ፡ ዘረዘረ
ዘረገግ/ዘርጋጋ፡ የተንዘረገገ/የሚንዘረገግ ("ጕትት እንዝርግ")
ዘረገፈ (ትግ ዘርፈ፡ ጠጕርን አበጠረ) ጐመንን/ሥጋን/ንፍሮን ከማሰሮ ("አንዠትን ፈርስን ከሆድ ከጨጓራ እኸልን ከስልቻ ጨርሶ አወጣ አፈሰሰ") ( ሳሙ. ፳፡ )
ዘረገፈ፡ ክፉኛ ነከሰ/ቦጨቀ/ዘበተረ/ ቦተረፈ/ዘረከተ ("ውሻ ባትን አስኳልን")
ዘረጋ (ትግ ዘርግሐ) ሰተረ/አሰጣ/ዘረረ/አጠፈጠፈ/አሣሣ (መዝ. ፻፴፮፡ )
ዘረጋጋ፡ አነጣጠፈ
ዘረጠ፡ ተሳደበ
ዘረጠ፡ ዐጠረ ("ዐጪር ኾነ ዘረጠ ተፈሳ")
ዘረጠጠ፡ ሳበ/ጐተተ ("እግርን")
ዘረጠጠ፡ ናደ/አፈረሰ ("ክምርን")
ዘረጠጠ፡ አዋረደ ("ሰውን")
ዘረጠጠ፡ ዘረከተ
ዘረጠጥ/ዘርጣጣ፡ የተንዘረጠጠ ("እን ዝርጥ ዘረከቦ")
ዘረጠፈ፡ ፀረፈ ("ፈጽሞ ሰደበ")
ዘረጥ አደረገ/አለ፡ አህይኛ ፈላ ("ተፈሳ")
ዘረጥራጣ፡ የተዝረጠረጠ ("ፈሪ")
ዘረጥራጤ፡ የዘረጥራጣ ወገን ዐይነት
ዘረፈ (ትግ ሐባ ዘርፈ፡ ማረከ) ወረረ/በዘበዘ/ቀማ/ነጠቀ/ገፈፈ/ወሰደ ("በጦርነት")
ዘረፈ፡ ቅኔ ሳይቈጥር አመጣ/ተቀኘ/ ተናገረ
ዘረፈጠ፡ ተረፈቀ
ዘረፈጥ/ዘርፋጣ፡ ርፍቅ ከተቀመጠበት የማይነሣ ("ሆደ ትልቅ")
ዘረፈፈ) አንዘረፈፈ ("ዘርፍ አወጣ አረዘመ ጐተተ አንቀረፈፈ በተገብሮነትም ይፈታል")
ዘረፈፍ/ዘርፋፋ፡ የተንዘረፈፈ ("የታቦት ልብስ ረዥም ጕትት ቀርፋፋ ሰው")
ዘረፉ፡ የሰው ስም (" አባትንና እና ትን ያያል")
ዘረፋ (ትግ ሐባ ምርኮ) ወረራ/ ቅሚያ
ዘረፋ፡ የወንድና የሴት መጠሪያ ስም
ዘረፋ፡ ድንገተኛ ቅኔ
ዘረፍራፋ/ዝርፍራፊ/ዝርፍርፍ፡ የተዝረፈረፈ ("ዝርክርክ")
ዘሪ (ዎች) የዘራ/የሚዘራ ("በታኝ ገበሬ") (ኢሳ. ፶፭፡ ፲፡ ማቴ. ፲፫፡ )
ዘራ (ዘርዐ) በተነ/ነሰነሰ/እንጠ ባጠበ (ማቴ. ፲፫፡ ፳፬)
ዘራ፡ ሸነ ("የሩካቤ")
ዘራ፡ አገባ/አሳደረ
ዘራ/ዘረወ/ዘረየ) አዘራ ("በ፪ እጅ እየነቀነቀ አፈሰሰ ለነፋስ ሰጠ ፍሬን ከገለባ ለየ") (ኢዮ. ፴፡ ፳፪)
ዘራረፈ፡ መላልሶ ዘረፈ
ዘራንዘር፡ የዘር ዘር (" ብዛትን ያሳያል")
ዘራፊ (ፎች) የዘረፈ/የሚዘርፍ ("ወራሪ ቀማኛ") (ናሖ. ፪፡ )
ዘራፊነት፡ ዘራፊ መኾን ("ቀማኛነት")
ዘራፍ፡ ለወሬ መካች ("ከፉከራ የሚ በልጥ ፉከራ")
ዘራፍ፡ ዘርፎ በብዙ የሚሰጥ ("ቸር ለጋስ")
ዘራፍ፡ ዝኒ ከማሁ ለዘራፊ ("ጐበዝ ሐመር ዘራፍ ዐካኪዘራፍእንዲል ሐርበኛ)
ዘራፍ፡ የፉከራ ቃል።
ዘር (ሮች) (ዘርዕ) የእኸል/የተክል ፍሬ ("ቅንጣት ተዘርቶ የሚበቅል በቅሎ የሚረግፍ")
ዘር፡ ልጅ/ትውልድ/ወገን/ነገድ
ዘር ቈጠራ፡ እከሌ ቢወልድ እከሌን ማለት ("(ከታች ወደ ላይ) አባት አያት ቅድማያት (እሚታ) ቅማት ቅማያት ሽማት ምዝላት እንጅላት")
ዘር በዘር (ዕንብርተ ቀዳዳ) እንደ ልጅ ያየውንና የሰማውን የሚናገር
ዘር አሰዳቢ፡ እንደ አስቆሮታዊ ያለ ዘሩን የሚያሰድብ ነውረኛ
ዘር አዳም (ዘርዐ አዳም) ክርስ ቲያን ለኾነ ላዳም ዘር (ልጅ) ኹሉ የሚደደረግ ዐጪር የባይተዋርና የድኻ ፍታት ገንዘብ የማይከፈልበት
ዘር፡ ካባት ዘር የወጣ ጥሬ ዘር ("ስም")
ዘር፡ የቋንቋ ሥር/መሠረት/አርእስት ("ማወቅ መግደል ይህን የመሰለ")
ዘር ይመስክር፡ የልዑል ራስ መኰንን አባት ክቡር ደጃዝማች ወልደ ሚካ ኤል የተናገሩት ነው
ዘር ይውጣልኸ፡ የበቃ የነቃ ልጅ ውለድ ("ተባረክ")
ዘርቶ፡ በትኖ/አንጠባጥቦ
ዘርና ነባር፡ አባት ዘርና ጥሬ ዘር ከነባር ጋራ
ዘርናቂ፡ የዘረነቀ/የሚዘረንቅ ("ነካሪ ዘባ ራቂ")
ዘርካታ/ዘርጋፋ፡ ሆደ ትልቅ/ቦር ጫም
ዘርካች፡ የዘረከተ/የሚዘረክት ("ዘርጋፊ")
ዘርኳታ፡ ዘልጓሳ መጽሐፍ
ዘርኳች፡ የዘረኰተ/የሚዘረኵት ("ዘል ጓሽ ገዳፍ")
ዘርዘር አለ፡ ራቅ ራቅ አለ
ዘርዛሪ፡ የዘረዘረ/የሚዘረዝር ("በታኝ ሸክሻኪ ሞራጅ ሸማኔ ባለጅ")
ዘርዛሪዎች፡ የዘረዘሩ/የሚዘረዝሩ ("ባለጆች ጠይቦች ሠራተኞች")
ዘርዛራ፡ የተዘረዘረ ("ሸክሻካ ወንፊት በለሴ ማጭድ ጥርስ")
ዘርያ፡ ዐይነት፡ ዘራ
ዘርያ፡ ዐይነት/ነገድ/ዘመድ/ተወላጅ/ወገን
ዘርጊ፡ የዘረጋ/የሚዘረጋ ("አስጪ ዘራሪ ዘርጊ ዘርጊባቸው የሴት ስም")
ዘርጋ፡ መዘርጋት
ዘርጋ አለ፡ ተዘረጋ ("ዕጥፍ ዘርጋ አለእንዲሉ)
ዘርጋ አደረገ፡ ዘረጋ
ዘርጋው፡ ዘርጋባቸው ("የወንድ ስም")
ዘርጋፊ (ፎች) የዘረገፈ/የሚዘረ ግፍ ("አውጪ")
ዘርጋፋ፡ ቦርጫም ("ሆደ ትልቅ ዘር ካታ")
ዘርጠጥ አለ፡ ተንዘረጠጠ
ዘርጣ፡ ተሳዳቢ/አፈኛ ("ሰውአዋራጅ")
ዘርጣጭ (ጮች) የዘረጠጠ/የሚዘ ረጥጥ ("ናጂ አፍራሽ ሳቢ ጐታች")
ዘርጭ፡ ታናሽ/አነስተኛ
ዘርጭ እንቧይ፡ ከበር እንቧይ በጣም ያነሰ
ዘርፈሽዋል፡ የሴት ስም ("ሀብቱን ውበቱን ማለት ነው")
ዘርፉ/ዘርፋ፡ የወንድና የሴት መጠሪያ ስም (" አባትን እናትን ያያል የርሱ የርሷ ዘርፍ ማለት ነው")
ዘርፍ (ዘፈር) ቍቲት/መርገፍ/ አጫዋች/እንጥልጥል (ዘኍ. ፲፭፡ ፴፰, ፴፱፡ መዝ. ፻፴፫፡ ፪፡ ኢሳ. ፮፡ )
ዘርፍ አያያዥ፡ ዘርፍን ከባለቤት የሚያያይዝ ፊደል ("ይኸውም ነው የሰማይ አምላክ የአዳም ልጅ እንዲሉ በግእዝ ልማድ ግን ዘሰማይ አምላክ ዘአዳም ወልድ ቢል ደፊ ይባላል")
ዘርፍ አያያዥ፡ የሳድስ ወራሽ ግእዝ ፊደል ("እም ባል እመቤት ባለቤት ዘርፍና ባለቤት ተቀዳሚናተከታይ ፲ወይም ተናባቢ ቃል")
ዘርፍ፡ እንደ ግእዝ አካኼድ ተከትሎ ("እንዳማርኛ ልማድ ቀድሞ ተከትሎ የሚነ ገር ቃል ግእዝ አምላከ ሰማይ ሲል ሰማይ ዘርፍ ይባላል ባማርኛም እጀ ሰብ ቢል ሰብ ዘርፍ ነው ቤተ ሰብ ሲል ቤት ዘርፍ ሰብ ባለቤት ይኾናል")
ዘርፍ፡ ዘረረ
ዘርፎች (አዝፋር) ቍቲቶች/መርገ ፎች/አጫዋቾች/እንጥልጥሎች ("ያንቀልባ የቈርበት የደበሎ ጫፎች")
ዘቀቀ (ዕብ ዛቃቅ) አጠራ/ጥሩ አደረገ
ዘቀዘቀ (ዘቀ) (ኢዮ. ፳፪፡ ፳፱) ቈለቈለ/አፈሰሰ/ደፋ ("አርእስትን ወደ ታች ኅዳግን ወዶ ላይ አደረገ ቍልቍል ሰቀለ ' ተማሪው መጣፉን ዘቀዘቀው")
ዘቀጠ (ዘገጠ) ሰጠመ/ሠረገ/አተለ ("በታች በሥር ኾነ")
ዘቀጠ፡ ዘራ
ዘቃ፡ በሶብላ ("ዜጋ ማለት ነው")
ዘቃቅቤ (ዜጋ ቅቤ) የበሶብላ ቅጠል ("እወጥ ቢጨምሩት ቅቤ ቅቤ ይላልና በዚህ ምክንያት ዘቃቅቤ ተባለ")
ዘቅዛቂ፡ የዘቀዘቀ/የሚዘቀዝቅ ("አቈል ቋይ")
ዘቅዛቃ፡ ቍልቍለት/ተዳፋት
ዘበለለ (ዘቢል ዘበለ) አብዝቶ ዐራ ("ዘፈዘፈ ኰሳ")
ዘበለለ፡ ዘባረቀ
ዘበሬታ፡ ቀልድ/ቧልት/ፍሬ ቢስ ነገር
ዘበተ (ሰለተ) ቀለደ/አላገጠ/ተሣ ለቀ
ዘበተ፡ ቈለለ/ከመረ/አነባበረ
ዘበተ፡ ዘጋ
ዘበተ፡ ዛተ/ፎከረ/አስፈራራ
ዘበተረ፡ ዘነተረ
ዘበታ፡ መዘበት
ዘበት (ስላት) ዋዛ/ቀልድ/ለግጥ/ ሥላቅ
ዘበነ (ዘመነ) ዘበናይ ኾነ ("ዘበን ሰጠው አገኘ ከበረ")
ዘበነ በልግ፡ የበልግ ዘመን
ዘበነ ግልምቢጥ፡ የተገላቢጦ ዘመን
ዘበነነ) ተዘባነነ፡ ዘበናይኛ ተናገረ ("ተጓደደ ኰራ")
ዘበናይ (ዮች) የዘመን ("ባለጊዜ መን የወለደው ንጉሥ የወደደው በግእዝ ዘመናዊ ይባላል")
ዘበናይነት፡ ባለጊዜነት/ጌትነት
ዘበን (ኖች) ዘመን/ጊዜ/ዓመት
ዘበኛ (ኞች) (ዘባናዊ) ባለዘብ ("ዘብ ዐዳሪ ዘብ ጠባቂ ወር ተረኛ ቤትን ዕቃን ከተማን አገርን የሚጠብቅ") (ነሐ. ፬፡ )
ዘበኛ ጠባቂ፡ ዘብ
ዘበኛነት፡ ዘበኛ መኾን ("ጠባቂነት")
ዘበኝነት፡ ዝኒ ከማሁ
ዘበዘበ (ዘብዘበ) ነዘነዘ/ነተረከ/ቀቀ ("ነገር አበዛ ጐተተ")
ዘበደ፡ ጠረገ/አጠራቀመ
ዘበጠ (ዘቢጥ ዘበጠ መታ) ደራ/ ተለመጠ ("ለጥ አለ ወዳቃ ኾነ የጣራ የዠርባ የስፍራ") (መክ. ፲፡ ፲፰)
ዘበጠረ፡ ሠበጠረ ("ዘና ሠሰ ይወራረ ሳሉ")
ዘበጠጠ (ዘፈጠጠ) ወደ ኋላ አለ ("ቀረ ዘቀጠ")
ዘበጠጥ/ዘብጣጣ፡ የዘበጠጠ ("የቀረ")
ዘቢ፡ የሚዘባ/የሚለመጥ ("ተለማጭ")
ዘቢብ፡ የወይን ፍሬ ዘይብ
ዘቢጥ፡ በበጌምድር ክፍል ያለ አገር
ዘባ (ዘብሐ ትግ. ዘብዐ) ደራ/ ተለመጠ ("በቀጥታና በጕብጠት መካከል ኾነ የበትር የጣራ የሌላውም ዕንጨት")
ዘባረቀ (ባረቀ) ክፉና በጎ ተና ገረ
ዘባረቀ፡ አማሰለ/ቀላቀለ/ደባለቀ
ዘባራቂ (ዎች) የዘባረቀ/የሚዘባ ርቅ ("ደባላቂ")
ዘባተሎ (ዘበጠለ) ዛተሎ ("የተቀዳ ደድ የተበታተነ የባታይ ጨርቅ")
ዘባች፡ የዘበተ/የሚዘብት ("ቀላጅ አላ ጋጭ ፎካሪ አስፈራሪ")
ዘባጣ/ዘብጥ፡ የዘበጠ ("በዳገትና በዳገት ሥር ያለ ቀጥታ ሰታታ ቦታ ረባዳ የምድር ዋዲያት")
ዘባጭ፡ የሚዘብጥ/የሚደራ ("ተለማጭ")
ዘብ (ዘቢን ዘበነ) ጥበቃ ("የመጠ በቅ ሥራ በተራ በፈረቃ የሚደረግ") (ግብ. ሐዋ. ፲፪፡ )
ዘብ ዐደረ፡ ሌሌት ጠበቀ
ዘብ ይደሩ፡ የወንድና የሴት ስም
ዘብላይ፡ የዘበለለ/የሚዘበልል የሚ ያራ
ዘብራ፡ ኀይለኛ የበረሓ አህያ ("ሯጭ ፈርጣጭ በዐውሳና በውጋዴ ይገኛል ሱማልኛ ወይልድአስ ይባላል")
ዘብር፡ በመንዝ ክፍል ያለ አገር
ዘብታሪ፡ የዘበተረ/የሚዘበትር ("ዘን ታሪ")
ዘብዛቢ፡ የዘበዘበ/የሚዘበዝብ ("ነዝናዥ ነትራኪ ጨቅጫቂ")
ዘብዛባ፡ ነዝናዛ/ነትራካ/ጨቅጫቃ
ዘብጥያ (ዘብጣዊ) የሌባ/የቀጣፊ/የወስላታ ማሰሪያ ቤት ("በዝቅተኛና በጐድጓዳ ስፍራ የተሠራ የሲኦል ምሳሌ እከሌ ስለ ሰረቀ ዘብጥያ ገባ")
ዘቦ (ዘቦ ዘቦቱ) ያለው
ዘቦጠ) አዝቦጠቦጠ (ቦጠቦጠ አስቦጠቦጠ) ደባለቀ/ቀላቀለ/በጠ በጠ/አወፈረ
ዘተር፡ ዱባ፡ ዘጠር
ዘተበ፡ አፉን መላ ብዙ በላ
ዘተዘተ፡ ነከሰ/ነካከሰ/በጣጠሰ/ገተገተ ("ዐኝ ዐኝ አለ እንደ ዝተት አደረገ")
ዘትብ፡ ያፍ ምላት/ምሉነት " ተዘተበ ተመሳ ምሉ ኾነ
ዘች፡ መሮጥ
ዘነመ፡ በቁሙ ("ዘነበ ዝናም ዝናብ")
ዘነቀ፡ ቀየጠ/ቀላቀለ/ደባለቀ
ዘነቈለ፡ ደነቈለ/ጠነቈለ/ኣነቈረ
ዘነበ (ዘንመ) ከላይ ከሰማይ ከደ መና ተንጠባጠበ ("በዝቶ ወረደ መጣ ዱብ ዱብ ጠብ ጠብ አለ የዝናብ የበረዶ የእሳት")
ዘነበ፡ ዘነብ ("የወንድ ስም")
ዘነበለ፡ ጋደለ/ዘለፍ አለ/ጐነበሰ/ዘመመ/ተቈለቈለ/ተዘቀዘቀ ("ዕቃው ሰዉ ፀሓዩ") (መዝ. ፵፡ ፩፡ ሉቃ. ፳፬፡ ፳፱)
ዘነበች፡ የሴት ስም
ዘነተረ (ሠነተረ) ነከሰ/ ዘበተረ/ ቦጨቀ/ቦተረፈ/በላ
ዘነነ (ትግ ዘነነ) ቍስልን አሰረ/ ጠቀለለ ("ራሱን መለስ ቀለስ አደረገ")
ዘነነ፡ ራሳም ኾነ ("ከራሱ ከበደ")
ዘነከተ፡ ደግ/የዋህ ኾነ ("ገራ በነገር በጠባይ")
ዘነኰረ/ዘነከረ (ነኰረ ነከረ) ነገር አበላሸ
ዘነዘና (ሺዋ) የሙቀጫ ልጅ ("መው ቀ፵ ሐሚናሚና ዘነዘና የብር ዘነዘናእንዲሉ ልጆች ሲበዛ ዘነዘኖች ይላል)
ዘነዘና (ጐንደር) ከዘነዘና የተበጀ ውዥሞ
ዘነዘና (ጐዣም) የንጨት ስም ("ታናሽ ዛፍ ውስጠ ክፍት ንጣት ቀጥታነት ያለው ቀፎ የሚኾን")
ዘነደበ፡ አረዘመ ("በሩቅ መታ")
ዘነደበ፡ ወለደ
ዘነጀረ፡ አሰረ/ቀፈደደ
ዘነጋ (ዘንግዐ) ረሳ ("የሚያውቀውን አጠፋ ዐጣ ጥንቃቄና ንቃት አልባ ኾነ") (ኢሳ. ፳፰፡ )
ዘነጐለ (ዛጐለ) ብላሽ ኾነ ("የነገር")
ዘነጐረ (ዘጐረ) ነብር መሰለ
ዘነጠ፡ አውደለደለ/ቀበጠ ("ዘመን አመጣሽ ቋንቋ ነው")
ዘነጠለ (ነጠለ) በሾኸ ነደለ/ በሳ/ ቀደደ ("ፈነቀለ እግርን")
ዘነጠለ፡ ነፋ/አወፈረ
ዘነጠለ፡ ንባብ አበላሸ ("የማይነሣውን ቃል አነሣ")
ዘነጠለ፡ ክምርን ናደ/አፈረሰ
ዘነጠፈ (ነጠፈ) ዠመገገ/ሸመጠጠ/ ቈረጠ/ገነጠለ/አረገፈ/አወረደ
ዘነጠፈ፡ አረዘመ/ሽንጣም አደረገ
ዘነጠፈ፡ ዘነፈ
ዘነጣጠለ፡ በሳሳ ቀዳደደ
ዘነፈ (ትግ ሰደበ) በዛተረፈ ረዘመ/በለጠ
ዘነፈለ፡ ዘነበለ ("ጋደም አለ")
ዘነፈለ፡ ዘፈዘፈ
ዘና (ዘነየ) ቀበጠ/ደራ ("በፍትወት")
ዘና (ዝኅነ) ዐረፈ/ረጋ/ጸጥ አለ ("ዐሳብ ተወ")
ዘናቂ፡ የዘነቀ/የሚዘንቅ ("ቀያጭ ቀላ ቃይ")
ዘናነበ፡ ወራረደ/መላልሶ ዘነበ
ዘናና፡ ክብ እንክብል ("መካከለ ብስ ደንጊያ በንጨት ላይ የሚሰካ")
ዘናና፡ ያትሮንስ መልሕቅ
ዘናፊ፡ የሚዘንፍ
ዘንቅ፡ ቅየጣ/ቅልቀላ/ድብለቃ
ዘንበል አለ፡ ጋደል አለ
ዘንበል፡ ጋደል/ዘለፍ
ዘንቢል (ሎች) (ዐረ) ከቃጫ/ከሰሌን የተበጀ አኩፋዳ ዕቃ መያዣ
ዘንቢል፡ ዘንጎባ፡
ዘንባላ፡ የዘነበለ/የዘመመ
ዘንባባ (ዎች) የተምር ዐይነት ዛፍ ("ወንዴ ተምር ፍሬው የማይበላ ሰሌንን ተመልከት")
ዘንባባ፡ በወግዳ ውስጥ ያለ ቀበሌ
ዘንባይ፡ የሚዘነብል ("ጋዳይ")
ዘንተራ፡ በደንቢያ ውስጥ ያለ ቀበሌ
ዘንታሪ (ሮች) የዘነተረ/የሚዘነትር ("ነካሽ ዘብታሪ ውሻ ዥብ ጨቅ")
ዘንቶ (ወሎ) ከቅል የተበጀ መስ ፈሪያ ("፬ቱ ዘንቶ ቍና ነው")
ዘንቶ፡ ተደላድሎ/ተሸራሽቶ/ተመቻችቶ ("ዘንቶ ተቀመጠእንዲሉ)
ዘንቶመስፈሪያ፡ ዘና
ዘንች (ቾች) የታላቅ ጐታ/የሪቅ/የጐተራ ጋድም መረጋገጫ ዕንጨት ("በስተው ስጥ በመካከል ያለ")
ዘንካታ (ቲት) ገር/የዋህ ("አነጋገሩ የሚገርም የሚያሥቅ እንደ ንጉሥ ኀይለመለ ኮት እናት እንደ እመት በዛብሽ ያለ ዘንካቶች ገሮች የዋሆች ቂም አል ቦች")
ዘንኳራ/ዝንኵር፡ ብላሽ ነገር ("ሰው ዬውም ዘንኳራ ይባላል")
ዘንዘሪጡ፡ የዲያቆን ተወራጅ ገፈፎ
ዘንዳባ፡ ዝንድብ ("የተዘነደበ ቁመተ ረዥም")
ዘንድ አንቀጽ፡ በትንቢትና በትእዛዝ መካከል ያለ ("ይበላ ዘንድ ይጠጣ ዘንድ እን ዲበላ ሊበላ እያለ የሚነገር") (ማቴ. ፭፡ ፵፭፡ ፮፡ ፩፡ ፰፡ )
ዘንድ፡ ዘንዳ (" ጐን አጠገብ ቀበሌ ስፍራ ቦታ እሱ ዘንድ አንተ ዘንድ ሲጨመርበት ዓመት ዘመን ይኾናል")
ዘንድሮ፡ ንኡስ አገባብ ("የዱሮ ተቃራኒ የዛሬ ያኹን ዓመት ዘመን ያላለቀ ያልተፈጸመ ገና የተዠመረ የተያዘ ጊዜ ዘን ድን እይ")
ዘንድብ፡ የዘነደበ/የሚዘነድብ ("አርዛሚ ለቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽም ይኾናል")
ዘንዶ
ዘንዶ (ዎች) የምድር አውሬ እግር የሌለው መርዘኛ የእባብ ወገን ("አስቀድሞ በዛፍ ላይ (ዘንድ) ይጠመጠምና አራዊትንና እንስሳትን በዥራቱ እየጠለፈ ልሶ የሚውጥ የሚሰለቅጥ ጐረጐረ ዘወረ ዞረ ብለኽ ጐር ጓሪን ዙሪያን ተመልከት")
ዘንዶ፡ በገመድ የተጠቀለለ ጭራሮ ("የጣራ ክባስ የክዳን ትራስ የጋን የገበር ምጣድ ማቶት ዐይነት በቤት ውስጥ ዙሪያውን ወጋግራ የሚሸከመውና በስተሰበሰብ ክፍክፋት ተሸካሚ")
ዘንዶ ጕር፡ በተጕለት ዐናት ከዛንጅራ በታች ያለ ቀበሌ ("ዘንዶ ያለበት የዘንዶ ጕር ማለት ነው")
ዘንገሊል (ዘንገ ልል) ሞኝ ("ላላ በያዘው በትር የሚመታ")
ዘንገሊል፡ ሞኝ፡ ዘንግ
ዘንገኛ (ኞች) ባለዘንግ/ዘንጋም ("ጠበቃ ተማጋች ዘንግ ይዞ የሚገት የሴት ዘንገኛ የናት ምቀኛእንዲሉ)
ዘንጊ፡ የሚዘነጋ ("ረሺ")
ዘንጋ (ዘንግዖ) መዘንጋት
ዘንጋ አለ፡ ዘነጋ
ዘንጋዳ (ዶች) (ዘንገ አገዳ) አንጓ ላንፋ ያለው ያገዳ እኸል ("በቈላ የሚበቅል የጥቍሬታ ዐይነት እንጭብሌ ጐምዤ ጐረንጆ ድኵዬ ዘገብሬል ዠተሬ ኰልኝ ዐጪሬ የመሰለው ኹሉ")
ዘንግ (ጎች) ቀጠን ያለ በትር/ምር ኵዝ ("ረዥምና ዐጪር") (ዘፀ. ፮፡ ፴፰)
ዘንግ፡ እስኪት ("የወንድ ኀፍረት")
ዘንግ፡ የሸማኔ ልክ (" ዘንግ ክንድ ሸማ")
ዘንግ፡ የእግር ብረት ቅርቃር
ዘንጎባ፡ የቅጥራን ስም ("ቅጥራን")
ዘንጠፍ አለ፡ ዱብ ጠብ እለ ("ወረደ")
ዘንጣላ፡ ዝንጥል ("የተዘነጠለ ቦር ንድል ፍንቅል ቅድ")
ዘንጣይ (ዮች) የዘነጠለ/የሚዘነጥል ("ፈንቃይ")
ዘንጣፊ፡ የዘነጠፈ/የሚዘነጥፍ ("ዠም ጋጊ")
ዘንጣፋ (ፎች) ረዥም/ዠርጋዳ ("አቋቋመ መልካም")
ዘንፋላ (ሎች) የተዘናፈለ ("መከዳ የጨነቀው ጌታ")
ዘንፋላዬ፡ የኔ ዘንፋላ
ዘአምላኪየ፡ የቅኔ ስም ("፪ኛ ቅኔ")
ዘኢያገድፍ፡ የተማሩትን የማያስረሳ አስማት/መድኀኒት (አፍልሖ)
ዘእስራኤል ፪ኛው ካሌብ ልጅ እስራኤልን ይመስላል፡ እጅግ በጣም ያምራል (መዝ ፵፭ )
ዘከረ (ዘኪር ዘከረ ዘክሮ ዘከረ) የእግዜርን/የማሪያምን/የመላእክትን ስም ጠራ ("በስማቸው ጸለየ የለት ውዳሴ ማሪያምና ከመዝሙር ከነቢያት ደገመ አቡነ ዘበሰማያት በሰላመ ገብርኤል አለ ጠዲቅ ባረከ ገመሰ ቈረሰ ፈተተ ተነተነ")
ዘከረ፡ ዐሰበ/አስታወሰ/አወሣ
ዘከዘከ (ዘሕዝሐ) ዘቀዘቀ/ዘረገፈ ("ኣወጣ አፈሰሰ")
ዘከዘከ ዘረዘረ/ሸከሸከ/ቀደደ
ዘከዘከ፡ ነቀነቀ/ሰነገጩ
ዘከዘከ፡ አጥብቆ ነከሰ ("ውሻ ሰውን")
ዘከዘከ፡ የሰማውን ኹሉ ኣወራ
ዘከዘክ/ዘክዛካ/ዘርዛራ/ሸክሻካ፡ ለሴ ' ወንፊት ("ሲኼድ ዘክዘክ የሚል በቅሎ")
ዘካ (ዐረ) ዓሥራት ("ያሥራት እኸል")
ዘካሪ (ዎች) የዘከረ/የሚዘክር ("ባራኪ ቈራሽ ካህን ቄስ ደብተራ")
ዘካሪ፡ ዐሳቢ/ተቈርቋሪ
ዘኬ ለቃሚ፡ ዘኬ የሚለቅም/የሚሰ በስብ ተማሪ
ዘኬ/ዘካዊ፡ ሖምጣጣ የተዝካር እንጀራ ("ካ፲ አውጥቶ የሚዘጋጅ")
ዘክዘክ አለ፡ አህይኛ/አጋሰስኛ ኼደ
ዘክዛኪ፡ የዘከዘከ/የሚዘከዝክ ("ዘርጋፊ አፍሳሽ ነቅናቂ ዘርዛሪ ሸክሻኪ")
ዘኸተት (ቶች) ቂል/ግተት/ሞኝ ("ዘርፋፋ ጕትት")
ዘኸነነ (ዘኅነነ) ከዘኅነን፡ አገባ፡ ከረ፡ አቀለመ፡ ዐለለ፡ አቀላ፡ ነጭ፡ ጭራን፡ ልብ ስን
ዘኸነነ (ዘኅነነ) ከዘኅነን አገባ ከረ/አቀለመ/ዐለለ/አቀላ ("ነጭ ጭራን ልብ ስን")
ዘወልዴ (ዘወልድ) ገብረ ወልድ ተክለ ወልድ ማለት ነው
ዘወረ (ዘውሮ ዘወረ) መዘውር ሠራ ("አዞረ ጠመዘዘ አሽከረከረ በዙሪያ ኣስ ኬደ")
ዘወረደ፡ የሑዳዴ መዠመሪያ ሳምንት ("ጾመ ሕርቃል")
ዘወር (ዘውሮ) መለስ/ጠምዘዝ
ዘወር በል፡ ወኺድ
ዘወር አለ፡ ስፍራ ለቀቀ/ተገለለ/ተወገደ ("ዞረ ተመለሰ")
ዘወር አለበት፡ በሽታ ጐበኘው ("ሰውየውን")
ዘወር አለበት፡ ጠላው ማለገ
ዘወር አደረገ፡ መለሰ/አገለለ/ወገደ
ዘወርታ፡ ዘወር ማለት ("ምለሳ")
ዘወርዋራ፡ ዝውርውር ("የተዘዋወረ የተጣመመ ጠማማ ዙሪያ ክብ መንገድ ቀጥታ ያይዶለ") (ምሳ. ፰፡ )
ዘወቀ፡ ዘነቀ/ዘባረቀ ነገርን
ዘወትር (ወተረ) ንኡስ አገባብ (" ቁሙ ወትሮ በግእዝ ግን ወትር ወትሮ ዘወትር የወትሮ የዘወትር ማለት ነው")
ዘወትር (ወተረ) ንኡስ፡ አገባብ፡ ቁሙ፡ ወትሮ በግእዝ፡ ግን፡ ወትር፡ ወትሮ፡ ዘወትር፡ የወትሮ፡ የዘወትር፡ ማለት፡ ነው ተረን፡ ተመልከት
ዘወትር፡ ዛኅርት
ዘወደ (ዐረ. ሥንቅ ሰጠ) ከበበ/ክብ አደረገ ("ዘውድ ሠራ አበጀ")
ዘወገ (ዘውጎ) ወገነ ("ጥንድ አደረገ")
ዘወፅእና ዘገብአ (ዘወፅአ ወዘገ ብአ) ዘወፅኣ የወጣ ("ዘገብኣ የገባ የተመለሰ ገንዘብ ወጪና ገቢ")
ዘዋሪ (ዎች) የሚዞር ("ዟሪ ተሽከ ርካሪ በዙረት ኻያጅ ዕረፍት የለሽ እተነ ሣበት ተመልሶ የሚመጣ ጨረቃ ኮከብ ቍርዬ አንበጣ መንኰራኵር ሠረገላ አዝማሪ") (ምሳ. ፳፡ ፲፱)
ዘዋሪ (ዎች) የዘወረ/የሚዘውር/ ሚያዞር ("መዘውር ሠሪ መኪና ነጂ ወይም መሪ አሽከርካሪ")
ዘዋራ፡ ዝኒ ከማሁ ("የዞረ ጠምዛዛ ንጨት መንገድ")
ዘዌ፡ የዛፍ ስም ("የመርዝ መድኀኒት የሚ ኾን ዕንጨት እባብ ጧት በምሥራቅ ምሽት ሲኾን በምዕራብ ኹኖ ፍሬውን የሚበላው እንዲህም ማድረጉ ጥላው እንዳያርፍበት ነው ርግብም እባቡ እንዳይነድፋት ጧት በስተምዕራብ በሠርክ በስተምሥራቅ ኹና ፍሬውን ትመገባለች")
ዘው (ዘዊዕ ዘዊሕ) ድንገት መግባት
ዘው አለ፡ (ትግ. ዘውሐ "አፈ ሰሰ") ግብት/ጥልቅ አለ
ዘው ዘው አለ፡ ገባ ገባ አለ ("መላልሶ ገባ")
ዘውዲቱ፡ የዳግማዊ ምኒልክ ልጅ
ዘውዴ/ዘውዲቱ፡ ዘውድ ነኸ/ነሽ ("የወንድና የሴት መጠሪያ ስም")
ዘውድ (ዶች) የክብር ጕልላት/ክብ ነት ያለው አክሊል ("ከወርቅ የተሠራ ውስጠ ክፍት ጌጥ ዕንቍና (አልማዝ) ፈርጥ ያለ በት ንጉሥ በነገሡ ጊዜ በራሱ ላይ የሚ ደፋው የሚቀዳጀው መጨረሻ ማዕርግ ማሸነፍ ምልክት ቤት ተከድኖ ሲያልቅ ጕልላት እንደሚጫንበት ይህም እንደዚያ ነው")
ዘውድ ዐጣኝ፡ ዘውድን የሚያጥን ቄስ ዐጤ
ዘውድ ደፋ፡ በራሱ ላይ አደረገ ("ተቀዳጀ")
ዘውድ ጫነ፡ ነገሠ
ዘውግ፡ ወን ነገድ ("ጥንድ ጣምራ ይህ የግእዝ ነው ዞግን እይ")
ዘየመ) አዜመ (ዘዪም ዜመ) ዜማ ደረሰ/ተማረ ("ጮኸ ሃሌ አለ ማሕሌት ቆመ ዘመረ ቀደሰ ቃኘ ተቀኘ")
ዘየረ (ዐረ) ጐበኘ/ደረሰ/ሰላም አለ ("አንጐራጐረ ዘፈነ ምስጋና አቀረበ በተቀደሰ ቦታ")
ዘየነ (ዘይኖ ዘየነ) ሸለመ/አስጌጠ
ዘየን ዘየን አለ፡ አጊጦ ተሽኰንትሮ ዞረ ("ተመላለሰ")
ዘየደ (ተደራጊ) ዘዴኛ ኾነ ("ዐወቀ ተጠበበ")
ዘየደ (ኣድራጊ) ጨመረ/አበዛ/አተ ረፈ
ዘያሪ፡ የዘየረ/የሚዘይር ("ጐብኚ ደራሽ ዘፋኝ አመስጋኝ")
ዘያኝ (ኞች) የዘየነ/የሚዘይን ("ሸላሚ አስጊያጭ")
ዘዬ (ዘይቤ) የነገር፡ ልማድ፡ ፈሊጥ፡ ባህል፡ አንዳንድ፡ ሰዎች፡ በጨዋታ፡ መኻል፡ ጣልቃ፡ እያገቡ፡ መላልሰው፡ የሚናገሩት
ዘዬ (ዘይቤ) የነገር ልማድ/ፈሊጥ/ ባህል ("አንዳንድ ሰዎች በጨዋታ መኻል ጣልቃ እያገቡ መላልሰው የሚናገሩት")
ዘይ ዘይ፡ ዘየን፡ ዘየን፡ ዘየነ
ዘይ ዘይ አለ፡ ዝኒ ከማሁ
ዘይ ዘይ፡ ዘየን ዘየን ዘየነ
ዘይቤ፡ ነጠላ ትርጓሜ ("የሰዋስው ትም ርት ትርፍ ነገር ሳይጨመርበት ቃል በቃል የሚነገር ዘይቤ የሚል ማለት ነው")
ዘይቱም፡ ፍሬው የሚበላ ተክል ("በሐረ ርጌ አውራጃ የሚበቅል")
ዘይታ፡ በመራቤቴ ክፍል ያለ አገር ("ዘይቷ ' የርሷ ዘይት ማለት ነው")
ዘይት (ቶች) የወይራ ዐይነት ዛፍ ("እንስት ወይራ ፍሬው የሚበላ ዘይት የግ እዝ ወይራ ያማርኛ ነው ደብረ ዘይትእንዲሉ)
ዘይት፡ ከምድር የሚወጣ ነፍት/ጋዝ/ቤንዚን ("በግእዝ ነፍጥ ይባላል")
ዘይት፡ ከሱፍ/ከኑግ/ከሰሊጥ/ከተልባ/ከጕሎ የሚገኝ ቅባት ኹሉ
ዘይት፡ ከሴቴ ወይራ ፍሬ ነጥሮ የወጣ ("ሰዎች የሚበሉትና የሚቀቡት ፈሳሽ")
ዘይት፡ ዘከረ
ዘይቶን፡ የዘይት ተክል (ግእዝ)
ዘይኑን፡ የጽርእ ንጉሥ ስም ("የቅድስት ኢላርያ አባት ጉባኤ ኬልቄዶንን የሻረ")
ዘይእዜ፡ የቅኔ ስም ("፮ኛ ቅኔ")
ዘዴ፡ ዕውቀት ዘየደ
ዘዴ፡ ዕውቀት/ፈሊጥ/ብልኀት/ጥበብ ("እያደር እየቀደም እየተጨመረ እየሰፋ የሚ ኼድ ኑሮ በዘዴእንዲሉ)
ዘዴኛ (ኞች) ባለዘዴ/ዕውቀተኛ/ ጥበበኛ
ዘዴኛነት፡ ዘዴኛ መኾን ("ብልኅነት")
ዘገሌ፡ ከቃፍር የሚበልጥ በግ
ዘገመ፡ ዝግ አለ ("በቀስታ በዝግታ ኼደ ተጓዘ የበሽተኛ የደካማ")
ዘገም አለ፡ ዘገመ
ዘገም አደረገ፡ አዘገመ
ዘገምተኛ፡ ዝግተኛ ("አዝግሞ ኻያጅ")
ዘገምታ፡ የቀስታ/የዝግታ መኼድ አካኼድ
ዘገረ (ረጊዝ ረገዘ) ወጋ/ዘረከተ
ዘገር (ሮች) ጥንታዊ የንጉሥ ጦር
ዘገር ነጠቀ፡ ጦር አነሣ
ዘገበ (ዘጊብ ዘገበ) ሰበሰበ/እከማቸ/ አጠራቀመ ("ብዙውን ባንድነት አደረገ አደ ለበ")
ዘገበ፡ ረጨ/አርከፈከፈ/ተቀባ
ዘገባ፡ ስብሰባ ("ትልቅ መስፈሪያ")
ዘገብሬል፡ ዘንጋዳ ገበረ
ዘገብሬል፡ የክርስትና ስም ("የገብሬል ማለት ነው")
ዘገብሬል፡ የዘንጋዳ ስም (ቀይ ዘንጋዳ)
ዘገነ (ትግ) ዠገነ/በረታ/ገነነ
ዘገነ (ዘጊን ዘገነ) ጠረን በጥርኝ ያዘ/ጨበጠ
ዘገነነ፡ ሰቀጠጠ/ጨፈገገ ("ጭፍግግ አደረገ ጨመደደ አስፈራ ሰውነትን")
ዘገዘገ (ዘገገ) ረዘመ/ረዥም ኾነ ("የዜማ የስብከት")
ዘገየ፡ ቈየ ("ባንድ ስፍራ ባንድ ሥራ ዋለ ዐደረ ሰነበተ") (ዘፍ. ፲፱፡ ፲፮)
ዘገጀ (ዘግደየ) ዝግጁ ኾነ
ዘገገ፡ ኣወደቀ/ዘረጋ/ዘረረ ("ከፍጥነት አራቀ")
ዘጊ፡ ስም ("ደንቡ የቤተ መንግሥት በር መዝጋት የኾነ ሰራዊት")
ዘጋ (ዘጊሕ) መዝጋት
ዘጋ (ዘግሐ) ( ነገ. ፬፡ ፴፫) ከደነ ("ማለ") ደፈነ/ዐፈነ/አወለነ ("ኣፉን ዘጋ ዝም አለ አረመመ")
ዘጋ፡ ራሱን ከሰው ለየ ("በዋሻ (በኣት) ከተተ")
ዘጋ አደረገ፡ ከደን/ገጠም/መለስ አደረገ
ዘጋበት፡ አንዱ ሌላው ጥቅም እንዳያ ገኝ መከረበት
ዘጋቢ፡ የዘገበ/የሚዘግብ ("ሰብሳቢ አጠ ራቃሚ")
ዘጋኝ (ኞች) የዘገነ/የሚዘግን ("ቃሚ")
ዘጋጋ፡ መላልሶ ዘጋ ("ገጣጠመ ከዳደነ")
ዘጌ (ዘገየ) በጣና ባሕር አጠገብ ያለ አገር ("የጐዣም ግዛት ዘጌ ዘገየ ማለት ይመስላል")
ዘጌዎች፡ የዘጌ ሰዎች/የዘጌ ተወላጆች
ዘግ አለ፡ ዘፍ/ዘለፍ አለ
ዘግ፡ ዘፍ ዘገገ
ዘግ፡ ዘፍ ዝርግት
ዘግዛጊ፡ የዘገዘገ/የሚዘገዝግ ("ረዛሚ")
ዘግዛጋ፡ የረዘመ ("ረዥም")
ዘግዪ፡ የሚዘገይ/የሚቈይ
ዘጐረ፡ ነብርማ ኾነ
ዘጐነ ዘወገ
ዘጐነ፡ ዛጐለ ("ደም ሠረበ ዐዘለ ለዘ ጠቈረ")
ዘጠረ (ዘተረ) ውሃና ጨው ሞጀረ ("ኣበዛ መላ ነፋ ወጠረ ሆድን")
ዘጠር (ዘተር) ዱባ ("የባሕር ቅል")
ዘጠር (ዘተር) ዱባ፡ የባሕር፡ ቅል (ጥጠ) መዘጠር፡ መንፋት፡ መወጠር ተዘጠረ ምሉ፡ ኾነ፡ ተነፋ፡ ተወጠረ፡ በጠ
ዘጠነ (ተስዐ) ዘጠኝ አደረገ ("ከዘ ጠኝ ከፈለ")
ዘጠነ (ተስዐ) ዘጠኝ፡ አደረገ፡ ከዘ ጠኝ፡ ከፈለ
ዘጠነኚት፡ ዘጠነኛዪቱ ክፍል
ዘጠነኚት ዘጠነኛዪቱ፡ ክፍል ዘጠኞ ዘጠኒዮ፡ ዘጠኝነት፡ ያለው፡ ስጠ፡ ብዙ
ዘጠነኛ (፱ኛ) የዘጠኝ፡ ወገን፡ ቍጥር፡ ማዕርግ
ዘጠነኛ (፱ኛ) የዘጠኝ ወገን/ቍጥር ማዕርግ
ዘጠና () በ፹ና በ፻ መካከል ያለ ያ፲ ቤት ቍጥር (" ዘጠኝ ዐሥር ወይም ዐሥር ጊዜ ዘጠኝ")
ዘጠና () በ፹ና፡ በ፻፡ መካከል፡ ያለ፡ ያ፲፡ ቤት፡ ቍጥር ዘጠኝ፡ ዐሥር፡ ወይም፡ ዐሥር፡ ጊዜ፡ ዘጠኝ ቀጠነ፡ ብለኸ፡ ቀጠናን፡ እይ
ዘጠና ዘጠኝ፡ ፻፡ ሊመላ፡ ፩፡ የጐደ ለው፡ ("ማቴ. ፲፰፡ ፲፪, ፲፫")
ዘጠና ዘጠኝ፡ ሊመላ የጐደ ለው (ማቴ. ፲፰፡ ፲፪, ፲፫)
ዘጠናኛ (፺ኛ) የዘጠና፡ ወገን፡ ቍጥር፡ ማዕርግ
ዘጠናኛ (፺ኛ) የዘጠና ወገን/ቍጥር ማዕርግ
ዘጠንያ፡ ከዘጠኝ አንድ
ዘጠንያ ከዘጠኝ፡ አንድ ዝጠና መዘጠን
ዘጠኝ () የቍጥር ስም ("በ፰ና ባ፲ መካከል ያለ ተራ ቍጥር ያ፩ ቤት")
ዘጠኝ () የቍጥር፡ ስም፡ በ፰ና፡ ባ፲፡ መካከል፡ ያለ፡ ተራ፡ ቍጥር ያ፩፡ ቤት፡
ዘጠኝ ጐራሽ፡ አመንዝራ፡ ሸርሙጣ፡
ዘጠኝ ጐራሽ፡ አመንዝራ/ሸርሙጣ ሴት
ዘጠኝ ጐራሽ፡ ዘጠኝ ጥይት የሚጐ ርሥ ጠመንዣ
ዘጠኝ ጐራሽ፡ ዘጠኝ፡ ጥይት፡ የሚጐ ርሥ፡ ጠመንዣ
ዘጠኝነት፡ ዘጠኝ መኾን
ዘጠኝነት ዘጠኝ፡ መኾን
ዘጠኞ/ዘጠኒዮ፡ ዘጠኝነት ያለው ስጠ ብዙ
ዘጠዘጠ) አዘጠዘጠ፡ ሮጠ/አነጠ ነጠ
ዘጠዘጥ/ዘጥዛጣ/አዘጥዛጭ፡ የበልግ አህያ ("ውዲላ")
ዘጣኝ የዘጠነ፡ የሚዘጥን
ዘጣኝ፡ የዘጠነ/የሚዘጥን
ዘጥ እንዘጥ በቂጥ፡ መውደቅ እንዘጥ አለ፡ ወደቀ፡ ቂጡን፡ መሬት፡ መታው
ዘጥ እንዘጥ፡ በቂጥ መውደቅ
ዘጥ ዘጭ፡መውደቅ
ዘጥ/ዘጭ፡ መውደቅ
ዘጥር ምላት፡ ብዛት፡
ዘጥር፡ ምላት ብዛት
ዘጥዘጥ አለ፡ አዘጠዘጠ
ዘጥዘጥ አለ፡ አዘጠዘጠ
ዘጭ እንዘጭ አለ፡ ዝኒ ከማሁ
ዘጭ እንዘጭ፡ አለ፡ ዝኒ፡ ከማሁ ዛጠጠ ፈሳ፡ ፈሱን፡ ለቀቀ ዛጤ ፈሳም ላጤ መዛጠጥ መፍሳት
ዘፈቀ፡ ዘቀዘቀ
ዘፈቀ፡ ደፈቀ ("እውሃ ውስጥ አገባ ነከረ አጠለቀ አሰጠመ")
ዘፈነ (ዘፊን ዘፈነ) ቀነቀነ/ ወረዶ ("ግጥም ገጠመ አዜመ አንጐራጐረ ዘለለ ተረገረገ")
ዘፈነ፡ ተንቀጠቀጠ/ተንዘፈዘፈ ("ይህ በሽተኛ እጁ ይዘፍናል።")
ዘፈን (ኖች) በቁሙ ቅንቀና/ ግጥም/እንጕርጕሮ
ዘፈን አወረደ፡ የዘፈንን ዜማ መራ
ዘፈዘፈ (ዘፍዘፈ) ነከረ/አራሰ (" ውሃ ውስጥ አስቀመጠ ተወ ደፈደፈ ዘፈዘፈ ዐራ ወዘፈ በደ")
ዘፈዘፈ፡ ወፈረ ("ሆደ ትልቅ ኾነ በደ")
ዘፈጠጠ) አንዘፈጠጠ/ እንዘረ ጠጠ/አንገፈጠጠ ("አስረገዘ አንቀበደደ ተንዘፈጠጠ ተንዘረጠጠ ተንገፈጠጠ አረገዘ ሆዱ ተነፋ")
ዘፈጠጠ) ዘፈፈ
ዘፈጠጥ/ዘፍጣጣ፡ የተንዘፈጠጠ ("ዘረጠጥ ዘርጣጣ ቦርጫም ቀፈታም")
ዘፈፈ (ሰፈፈ) ጣለ/አወደቀ/አጋ ደመ
ዘፈፍ አለ፡ ተንዛፈፈ
ዘፋቂ፡ የዘፈቀ/የሚዘፍቅ ("ደፋቂ ኣጥላቂ")
ዘፋኝ (ኞች) የዘፈነ/የሚዘፍን ("አውራጅ አንጐራጓሪ ዘፈን ወዳድ") (መዝ. ፹፯፡ )
ዘፋኝ ዳዊት፡ ባ፲፯፻፲ . . የነበረ የኢትዮጵያ ንጉሥ
ዘፋዘፎ (ዎች) ረዥምዥም ጣራ አሞራ ዛፍ " ውዥም
ዘፋፈነ፡ መላልሶ ዘፈነ
ዘፋፋ፡ የተንዛፈፈ ("ረዥም የዛፍ ዐጽቅ ክንፍ")
ዘፍ፡ መውደቅ፡ ዘፈፈ
ዘፍ፡ መውደቅ/መተኛት/መጋደም
ዘፍ አለ፡ ወደቀ/ተጋደመ/ተኛ
ዘፍዛፊ፡ የዘፈዘፈ/የሚዘፈዝፍ ("ወዛፊ ደፍዳፊ")
ዘፍዛፋ፡ ዝኒ ከማሁ ("ከባድ ሰፊ ወፍ ራም")
ዙሓ (ሖች) ጠገራ ("የጠገራ ብረት የላ ጡት ዙሓ")
ዙሓ (ሖች) ጠገራ፡ የጠገራ፡ ብረት ዙሓ ሰፊ፡ ትልቅ የላ፡ ጡት፡ ዙሓ፡
ዙሃ፡ ጠገራ ዙሓ
ዙሐል፡ ከፀሓይ ብርሃን ከሚነሡ ፯ቱ ኮከቦች ፭ኛው ኮከብ
ዙረት፡ ምለሳ/መዞር/ዑደት (መዝ. ፲፱፡ ፮፡ ተሰ. ፫፡ ፲፩)
ዙሪያ (ዘውር) ክበብ/ዳር (ኢዮ. ፵፩፡ )
ዙሪያ ንግግር፡ አግቦ
ዙሪያ ገባ ገብ፡ ባጥር ግቢ ስጥ ያለ ስፍራ
ዙሪያ ገባው፡ መላው/ኹለንተናው
ዙሪያ ጥምጥም፡ ዐጪርና ቅርብ ይዶለ ("ረዥም መንገድ በግእዝ ፍኖት መጐ ንድይ ይባላል") (ፊልክ. ፲፬)
ዙሪያክበብ፡ ዞረ
ዙሪያው ዘንዶ፡ የረኃብ ስም ("በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ጊዜ የኾነ ክፉ ቀን ሪያው ዘንዶ ብሄሞትንና ሌዋታንን ያሳስ ባል") (ኢዮ. ፵፩፡ - )
ዙራምባ (ዙር ዐምባ) ያገር ስም ("በጋይንት አውራጃ ያለ የመዋሥእትና የዝ ማሬ መምህራን የሚገኙበት ክብ ተራራ")
ዙራምቤ፡ እንግዳ ("የዙራምባ ተወላጅ ወይም መምር በደብረ ሊባኖስ የነበሩ ኦር ቶዶክሳዊ ሊቅ መናኝ መነኵሴ")
ዙር (ዒል) ትእዛዝ/አንቀጽ ("በዙ ሪያ ኺድ ተመለስ መለስ በል")
ዙር፡ የስፌት ደረጃ/ዕርከን
ዙር፡ የተዞረ ("የዞረ ስፌት ሽሩባ ጤፍ እንጀራ")
ዙር ጋሜ፡ መካከሉ ተላጭቶ በራስ ዙሪያ ያለ ጠጕር
ዙሮሽ፡ መዞር/ጥምጥም ጠጕር
ዙፋሪ፡ ልግም በገላ ("ባንድነት የተሰፋ ኩታ")
ዙፋን (ኖች) (ሰፈነ) ቁመተ ረዥም/ጐነ ሰፊ/ታላቅ የንጉሥ ዐልጋ ("ወይም መንበረ ዳዊት")
ዙፋን ቤት፡ ዙፋን ያለበት ("የዙፋን ቤት")
ዙፋን ቤቶች፡ የዙፋን ቤት ሠራተኞች ("አንጣፎች ጋራጆች የውስጥ አሽከሮች")
ዚህ ( ዝየ ዕብ. ዜህ) ይህ/ይኸ
ዚቀኛ (ኞች) ባለዚቅ/ዚቅ አው ራጅ ("ነገር ትች ዐዋቂ እከሌ ዚቀኛ ነውእንዲሉ)
ዚቅ (ዪቅ ዜቀ) ተመሳሳይ ቃል በማሕሌት ጊዜ ከንግሥ ከመልክ ከማሕሌተ ጽጌ ከሰቈቃወ ድንግል እየተነጻጸረ የሚመ ረገድ የዜማ ጥቅስ
ዚቅ አወረደ፡ አዜመ ደብተራው
ዚቅ፡ የነገር ውሻል/ሽብልቅ/ማስ ረጃ
ዚያ (ዚኣ) ቅጽልነትን አካ ልነትን ያሳያል ("ትርጓሜው ርሱ እሱ")
ዚያ (ዚኣ) ዚ፡ ቅጽልነትን፡ ያ፡ አካ ልነትን፡ ያሳያል፡ ትርጓሜው፡ ርሱ፡ እሱ ፰፡ ደቂቅ፡ አገባቦች፡ ሲጫኑት፡ ለሚታይና፡ ለማይ ታይ፡ የሩቅ፡ ነገር፡ ለቦታ፡ ለጊዜ፡ ለአካል፡ ዐጸ ፋና፡ በቂ፡ ቅጽል፡ ይኾናል (ማስረጃ)
ዛኅርታም (ዝኅራዊ) ሆዳም፡ በላ ተኛ፡ ልከ፡ ቢስ፡ በልቶ፡ አይጠግብ፡ ሆደ፡ ሣጥን ያሣማ፡ የዥብ፡ ወገን አሲድን፡ ተመልከት
ዛኅርታም (ዝኅራዊ) ሆዳም/በላ ተኛ ("ልከ ቢስ በልቶ አይጠግብ ሆደ ሣጥን ያሣማ የዥብ ወገን")
ዛኅርት (ዘኀረ ዝኅር) ሰፊ ሆድ ("የምግብ ጕድጓድ የመብልና የመጠጥ መቃ ብር")
ዛኅርት (ዘኀረ፡ ዝኅር) ሰፊ'ሆድ' የምግብ፡ ጕድጓድ ' የመብልና፡ የመጠጥ፡ መቃ ብር
ዛለ (ዝሕለ) ላላ/ደከመ/ዝልፍልፍ አለ ("እንደ ታረደ እንደ ሞተ ኾነ ራሱን ደፋ አቀረቀረ መያዝ መጨበጥ መቆም ተሳነው ኣቃተው")
ዛላ (ዎች) አንድ የብር እኽል ("ያጃ የስንዴ የገብስ ራስ የስንዴው ዛላ ፍኝ ይመላእንዲሉ) (ኢሳ. ፲፯፡ ፭፡ ማር. ፬፡ )
ዛላ፡ የሰውነት አቋም
ዛላ፡ የብር እኸል ራስ፡
ዛላ፡ ደረቅ ቃሪያ ከነፍሬው
ዛል (ዘሓል) የጭን የኋላ እግር ሥጋ
ዛመ (ዐረ ዘሐመ ገፋ) ሞቀ/ ኰሰ/ተንቀጠቀጠ/ዞረ
ዛራም (ሞች) ዛር ያለበት/የፈለቀ በት ("ባለዛር ቆሊያም")
ዛሬ (ዘረየ) ንኡስ አገባብ ("በትላንትናና በነገ መካከል ያለ ሌሊትና ቀን በዘርፍነት ሲነገር")
ዛሬ (ዛርየ) የኔ ዛር ማለት ነው
ዛሬ ሌሊት፡ የዛሬ ሌሊት
ዛሬ ቀን፡ የዛሬ ቀን
ዛር (ዕብ ባዕድ ልዩ) ክፉ መንፈስ ከግዚር ከመላእክት የተለየ ውቃቢ ትግሬት በሰው ላይ እያደረ ሰውን የሚያስ ጓራ የሚያስገዝፍ
ዛር አንጋሽ፡ ዛርን በሰው ላይ የሚያነግሥ/የሚያረጋግጥ ቃልቻ
ዛር፡ እብድ ወንድ ወይም ሴት
ዛር ወጣበት፡ ፈለቀበት/ተቀመጠበት
ዛር ፈረስ (የዛር ፈረስ) ዛር የሰፈረበት/የተቀመጠበት ሰው ("የሰፈረባት የተቀመጠባት ሴት")
ዛሮ፡ በተጕለት መጨረሻ አዳባይ በላይ ያለ አገር ("ዛር ሆይ ማለት ነው")
ዛቀ (ዘሐቀ) ጠረገ/ጋፈ/አወጣ ("ኣብዝቶ ወሰደ ቅቤን ማርን ጭቃን ዐዛባን ዱቄትን እኸልን")
ዛቀ፡ ጫረ ፍምን ("ሰበሰበ ጋይን")
ዛቍኔ፡ ዝቅተኛ ዳኛ/ተወራጅ
ዛቂ፡ የዛቀ/የሚዝቅ ("ጠራጊ ዐዛባ ዛቂ ቦይ ዛቂእንዲሉ)
ዛቂታ፡ የዛቀች/የምትዝቅ ሴት
ዛቈነ፡ ለፋ/ደከመ ("እንደ ጦመኛ ያቆን")
ዛቈነ፡ ዳቈነ ("ድቍና ተቀበለ ዘና ተወራራሽ መኾናቸውን አትዘንጋ")
ዛቅ (ዝሒቅ) መዛቅ
ዛቅ አደረገ፡ አብዝቶ ዛቀ
ዛቋኝ (ኞች) የዛቈነ/የሚዛቍን (" ቋኝ")
ዛበረ (ዘቢር ዘበረ) ዋለለ/ቃዠ/ አቃሰተ ("ኢዮሄ ወለሌ o አለ ተጨነቀ ይይዘ ውን ይናገረውን ይኾነውን ዐጣ ከበሽታ የተነሣ አሠኘ")
ዛቢያ (ትግ) ሶማያ ( ነገ. ፲፯፡ )
ዛቢያ (ዎች) (ዘበየ) የዶማና የመ ጥረቢያ እጀታ ("ቀላሳ ወይም ቈላፋ ዕንጨት ወዶ ገባ")
ዛቢያ ገንጥል፡ ጕልበታም ሰው ቈፍር ዛቢያ የሚገነጥል
ዛባሪ፡ የዛበረ/የሚዛብር ("አቃሳች")
ዛብ (ቦች) ዝኒ ከማሁ
ዛብ፡ የልጓም ቋድ፡ ዐዘበ ዕዛብ
ዛብሽ ወርቅ የምራት ስም
ዛተ (ዝህተ) አስፈራራ/ዘበተ/ ከረ/ዳነተ
ዛተሎ፡ ዕላቂ ጨርቅ፡ ዘባተሎ
ዛቲ፡ ታናሽ ዕንጐቻ ("ባልቴቶች የሚሰጡት የቤተ ክሲያን መባ በግእዝ ግን (ዛቲ) ይህች ማለት ነው ስንክሳር (ወበዛቲ ዕለት) ካለው መጥቷል")
ዛቻ (ዛህት) ዘበት/ፉከራ/ጕራ/ ማስፈራርቾ
ዛች፡ የዛተ/የሚዝት ("ፎካሪ")
ዛኒጋባ (ዘንትጋባእ ባቲ) ሰቀላ/ጓሮ ቤት ("አንድ ጣራ") ( ነገ. ፬፡ , ፲፩፡ ሕዝ. ፵፡ ፵፮)
ዛኒጋባ፡ ዘነጀረ
ዛንቂል፡ የሚዘነቍል ("ደንቈሮ ቂል")
ዛንታ፡ ወግ/ታሪክ
ዛንጅራ፡ የቀበሌ ስም ("በደብረ ብርሃን አጠገብ ያለ ገጠር የእስረኛ ስፍራ ማለት ይመስላል")
ዛንጅር (ዐረ ዘንጊር) ያንገትና የእጅ ማሰሪያ ሰንሰለት ("ሠዓሊዎች በዲያብሎስ ዐንገት ላይ ያደርጉታል")
ዛንጅር፡ መንቈር ("የሽፍታ ቀንበር") ( ዜና. ፴፫፡ ፲፩)
ዛንጅሮ (ጃን ጅሮ) ጃን ንጉሥ/ጅሮ ጅር ሰራዊት ("ማለት ይመስላል")
ዛንጅሮ፡ ዘነጠለ
ዛንጅሮ፡ የእናሪያ ከተማ ስም ("በጅማ አውራጃ ያለ ጥንታዊ ከተማ ዛንጅሮ የዘንዶ ምስጢር አለበት")
ዛዘለ ረዘመ፡ ተጐተተ፡ ተግዠለዠለ እንዛዝላ (ሎች) ደንደሎ፡ ያባያ፡ ቅጫ፡ ረዥም፡ ግንድ፡ ወይም፡ እንዶድ
ዛዘለ፡ ረዘመ/ተጐተተ/ተግዠለዠለ
ዛዘነ (ሰሰነ) ጮኸ ("ሚያው ሚያው አለ ዞረ")
ዛዘነ (ሰሰነ) ጮኸ፡ ሚያው፡ ሚያው፡ አለ፡ ዞረ ዛዘለና፡ ዛዘነ፡ አንድ፡ ዘር፡ ናቸው ዛዛኝ (ኞች) የዛዘነ፡ የሚዛዝን፡ ምት
ዛዛ) አንዛዛ (ዛሕዝሐ ሳሕስሐ) አበዛ/አሰፋ/አረዘመ ("የቤት")
ዛዛ) ዛሕዝሐ፡ ሳሕስሐ) አንዛዛ አበዛ፡ አሰፋ፡ አረዘመ፡ የቤት
ዛዛቴ፡ የተንዛዛ ሰው ("ረዥምና ሰፊ ቤት")
ዛዛቴ የተንዛዛ፡ ሰው፡ ረዥምና፡ ሰፊ፡ ቤት
ዛዛኝ (ኞች) የዛዘነ/የሚዛዝን ድመት
ዛይ፡ የፊደል ስም ("")
ዛይን፡ የፊደል ስም (" ዛይ ጌጥ ልማት ማለት ነው")
ዛይዳ፡ ጭማሪ/ትርፍ/ፍድፋጅ
ዛገ (ትግ. ዘዐገ "ወረዛ አዠ ጠበ ራሰ") አደፈ/መረተ ("ዐፈር መሬት መሰለ ተበላሸ ጠቈረ") (ያዕ. ፭፡ )
ዛጉፍ፡ ከቀርክሓ ከሸንበቆ ከውስጠ ፍት ዕንወት የተበጀ ዋሽንት ( ሳሙ. ፲፰፡ ፮፡ ዳን. ፫፡ )
ዛጊ፡ የዛግ/የሚዝግ/የሚያድፍ ("ጥቍር ብረት")
ዛጔ፡ ሰሎሞን ከንግሥተ አዜብ ገረድ የወለደው የላስታ ነገሥታት መዠመሪያ አባት
ዛጐለ፡ ዛጐል መሰለ ("ዘጐነ")
ዛጐል (ሎች) ደረቅ/ጠንካራ የባ ሕር ተሳቦ ልብስ ("ትልቅና ትንሽ ሕብሩ ጭና አረንጓዴ የኾነ")
ዛጐል ልብሱ፡ የየብስ ተሳቦ ንድ አውጣ ("ዛጐል ለባሽ የበጋ የክ ረምት ተንቀሳቃሽ")
ዛጐል በርበሬ፡ መናኛ የበርበሬ ዛላ
ዛጐል ዐይን፡ ዐይኑ ዛጐል የሚ መስል ሰው
ዛጐል ጣለ፡ ዛጐልን እመሬት ላይ በተነ ("ጠነቈለ")
ዛጐል ጣይ (ዮች) ማርተኛ/ጠንቋይ ("ዛጐል እየጣለ እንዲህይኾናል ንዲህ ይደረጋል የሚል መለኛ") ( ነገ. ፲፯፡ ፲፯)
ዛጐልማ፡ የዛጐል ዐይነት ("የዛጐል መልክ ያለው ዶሮ")
ዛጐምቢል፡ የዛፍ ስም ("ቀንበርና ደጋን የሚኾን ቀላል ዕንወት")
ዛጠጠ፡ ፈሳ ("ፈሱን ለቀቀ")
ዛጤ፡ ፈሳም ("ላጤ")
ዛፉ፡ ወንዴ ዛፍ
ዛፉ፡ ዛፍ ("የርሱ ዛፍ")
ዛፋ፡ ያች ዛፍ ("የርሷ ዛፍ")
ዛፋ/ዛፊቱ፡ ሴቴ ዛፍ (ዘፍ. ፫፡ )
ዛፋም፡ ዛፍ ያለበት/የመላበት ("ባለዛፍ ዱር")
ዛፍ፡ ሰቁሙ ("በዱር የሚበቅል ርጥብ ዕንጨት ዐጽቃም ቅጠላም ክንፋም ትንሹም ትልቁም ዐጪሩም ረዥሙም ባንድ ነት ዛፍ ይባላል")
ዛፍ፡ በቁሙ፡ ዘፈፈ
ዛፎች፡ ፪ና ከ፪ በላይ ያሉ ብዙዎች (ኢሳ. ፷፩፡ )
ዜመኛ (ኞች) ዜማ ዐዋቂ/ባለዜማ
ዜማ (ሞች) መንፈሳዊ ዘፈን ("ባለ ምልክት ጠጅ በብርሌ ዜማ በሃሌእንዲሉ)
ዜማ ሐዘን፡ ወርድ ንባብ
ዜማ ሰበረ፡ የቅኔን ንባብ ከውሳኔው አሳለፈ ("አላገባብ ተቀኘ ማን")
ዜማ፡ በቁሙ (ዘየመ)
ዜር (ዘየረ) የቀበሌ ስም ("በላይኛው ወግዳ በጋሾጥ በላይ ያለ አፋፍ")
ዜሮ (ዎች) የህንድ ቍጥር ማብዣ አኃዝ ("ካ፩ እስከ ያሉትን ቍጥሮች - ፲፻ የሚያደርግ ከዚህም በላይ የሚ ያበዛ ሌላ አኃዝ ካልቀደመው ግን የዜሮ (0) ትርጓሜ ባዶ ማለት ነው")
ዜገ (ዘዪግ ዜገ) ደኸየ/ማዕ ርጉን ዐጣ/ተዋረደ/ተገዛ/ዜጋ ኾነ/ገበረ
ዜጋ፡ ገባር/ተገዥ ("የሌላ ሰው ቅኝ እግር ዜጋ ነውእንዲሉ)
ዜጋመል ማሪያም፡ በዜጋመል ያለ የማሪያም ታቦት
ዜጋመል፡ ከዜጋወደም በላይ በስተ ግራ ያለ ቀበሌ ("የማሪያም አጥቢያ ባላገሮች ግን ደብረ ሊባኖስን ዜጋመል ይሉታል")
ዜጋመል፡ የቀበሌ ስም ዜገ
ዜጋመሎች፡ የዜጋመል ሰዎች ተወላ ጆች ("ቤተ ተክለ ሃይማኖቶች ተዋሕዶዎች (ጸጋ ልጆች)")
ዜጋወደም፡ ዠማ ዜገ
ዜጋወደም፡ የወንዝ ስም ("በደብረ ሊባኖስ በታች ያለ ዠማ ትርጕሙ ጋና ደም (ዘመድ) ማለት ነው")
ዜግነት፡ ተዠዥነት/ጎባርነት ("ዜጋ ኾን")
ዜጎች፡ ገባሮች/ታዛዦች ( ነገ. )
ዝ፡ የዜማ ምልክት ("የፍዝ ከፊል ዘዘ ብለኸ ፍዝን አይ")
ዝሓ (ዛሕዝሐ) ጠንካራ፡ ፈትል፡ ድር፡ ቀጪን ወይም፡ ወፍራም። መጽሐፍ፣ ግን፡ በዝሓ፡ ፈንታ፡ ዝሃብ፡ ይላል፡ ስሕተት፡ ነው፡ ("ዘሌ. ፲፫፡ ፵፰, ፶፱") ዝሓ፡ በግእዝ፡ ስፍሕ፡ ይባ ላል
ዝሓ (ዛሕዝሐ) ጠንካራ ፈትል/ድር ("ቀጪን ወይም ወፍራም መጽሐፍ ግን በዝሓ ፈንታ ዝሃብ ይላል ስሕተት ነው") (ዘሌ. ፲፫፡ ፵፰, ፶፱)
ዝሓ በዝሓ መጥረቢያ፡ የንጨት ዛቢያ የሌለው ("ከብረት ብቻ የተበጀ")
ዝሓ በዝሓ፡ መጥረቢያ፡ የንጨት፡ ዛቢያ፡ የሌለው፡ ከብረት፡ ብቻ፡ የተበጀ ዙሐል ከፀሓይ፡ ብርሃን፡ ከሚነሡ ፯ቱ፡ ኮከቦች፡ ፭ኛው፡ ኮከብ
ዝሓ በዝሓ፡ ድር በድር ("ርስ በርሱ የተሠራ ሸማ")
ዝሓ አዝጊ፡ ድር፡ አድሪ ለሩቅ፡ ንድ፡ በቂ፡ ለቅርብ፡ ሴት፡ ትእዛዝ፡ ነው ዝሓ በዝሓ፡ ድር፡ በድር፡ ርስ፡ በርሱ፡ የተሠራ፡ ሸማ
ዝሓ አዝጊ፡ ድር አድሪ ("ለሩቅ ወንድ በቂ ለቅርብ ሴት ትእዛዝ ነው")
ዝሓ፡ የሸረሪት ፈትል ("ወተር") (ኢሳ. ፶፱ - )
ዝሓ የሸረሪት፡ ፈትል፡ ወተር፡ ("ኢሳ. ፶፱ - ")
ዝሃ፡ ድር ዝሓ
ዝሁራ፡ ከፀሓይ ብርሃን ከሚነሡ ፯ቱ ኮከቦች ፪ኛው ኮከብ
ዝኆኔ የዝኆን፡ ዝኆናዊ፡ ቅርፍርፍ፡
ዝኆኔ፡ የዝኆን/ዝኆናዊ ("ቅርፍርፍ ጥኝ")
ዝኆን (ኖች) (ዝኅነ ዝኁን) ታላቅ አውሬ ("በየብስ ካሉት አራዊት ኹሉ የሚ በልጥ ረዣዥሞች ቀንድ የሚመስሉ ጥር ሶቹ በውድ ተሼጠው በያይነቱ የጌጥ መሣ ሪያ ይኾናሉ")
ዝኆን (ኖች) ዝኅነ፡ ዝኁን) ታላቅ፡ #
ዝኆን እግር፡ ኰብሽ የያዘው ቀጫ እግር
ዝኆን እግር፡ ኰብሽ፡ የያዘው፡ ቀጫ፡ እግር
ዝለላ፡ ብጥበጣ/ጠመቃ
ዝለቅ፡ ወደ ቤት ግባ
ዝለት፡ ድካም/ዝልፍልፍነት
ዝሊያ፡ ዝላይ/ጭፈራ ("ጮቤ ለምዶ መርታ እንደርዶ í ጨዋታ")
ዝል፡ የተዘለለ፡ ዘለለ
ዝል፡ የተዘለለ/የታለፈ/የተተወ
ዝልል፡ ዝርር/ዝርግ
ዝልል፡ የተዘለለ/የተጠመቀ/የተበጠበጠ ("ብጥብጥ የዳቦ ሊጥ በገበር ምጣድ ውስጥ የተመረገ ባለትንሽ ቅሬታ (ሊጥ) እሷን አይተው እሳት ያነዱበታል ዝልል መባሉ ኩፍ ስላላለ ነው")
ዝልስ አለ፡ ትኝት አለ ("ተዘለሰ")
ዝልስ፡ የተዘለሰ/የተኛ/የተጋደመ (" ልስ")
ዝልስልስ አለ፡ ዝልፍልፍ/ቅልስልስ አለ
ዝልስልስ፡ የተዝለሰለሰ
ዝልቀት፡ ጥልቀት
ዝልቅ (ቆች) የተዘለቀ/የተጨረሰ (" ጹም")
ዝልቅ ነገር፡ እውነተኛ ርግጥ/ሐቅ
ዝልቅ ዋሻ፡ ጥልቅ ሩቅ
ዝልቅልቅ፡ የተበሳሳ የብረት ወንፊት የሚመስል መስኮት ("ሠቅሠቅ")
ዝልቅነት፡ ዝልቅ መኾን
ዝልቦ፡ ሳይቀረደድ የተቀቀለ ጐመን
ዝልንግድ፡ ረዥም ቀውላላ ("ሰነፍ የማይረባ ሰው")
ዝልዘላ፡ ሥንጠቃ/ሽንሸና/ነከሳ
ዝልዝላት፡ ሥንጥቃት/ሽንሽናት/ንክሳት ("የዝልዝል ኹናቴ")
ዝልይት፡ ጋድሚያ፡ ዘለለ
ዝልይት፡ ጋድሚያ/ርጥጥ ሴት (" ቢስ የጋገረችው የማይበላ")
ዝልጊት (ቶች) ወንጠፍት ("የጠላ የጠጅ ማጥለያ ማጥሪያ")
ዝልጊት፡ ወንጠፍት፡ ዘለገ
ዝልፊያ፡ ዝኒ ከማሁ
ዝልፍልፍ አለ፡ ተዝለፈለፈ
ዝልፍልፍ፡ የተዝለፈለፈ ("ጥምልምል ራሱን የማይችል (ላላ) ዞላ")
ዝልፍልፍታ፡ ስልምልምታ
ዝልፍልፍነት፡ ጥምልምልነት
ዝመራ፡ መዘመር
ዝሙተኛ (ኞች) ዘማዊ/ዝሙት ወዳድ ወንድ ("ወይም ሴት")
ዝሙት፡ ሴሰን (ዘመወ)
ዝሙት፡ ሴሰን/ቅንዝር/ሽርሙጥና/ምንዝር (ዮሐ. ፰፡ ፵፩)
ዝማ (መርዘም) ራስ ምታት ("የራስ በሽታ")
ዝማ፡ ምንሾ/ተቅማጥ ("ሆድ ዝማእንዲሉ)
ዝማሜ፡ መቋሚያን በመወዝወዝ የሚባል ዜማ
ዝማም (ሞች) የከብት/የጥጃ አፍ መዝጊያ ("ታናሽ የገመድ ቅርጫት የማያስበላ የማያስጠባ")
ዝማም፡ በተጫነ አጋሰስ ወይም ህያ አፍ የተወተፈ ጐባጣ ዕንጨት ("ዋይክማ ልጓጥ")
ዝማም ወርቅ፡ የተቀጠቀጠ ጥሩ ወርቅ (ዘፀ. ፴፯፡ ፲፯)
ዝማም ወርቅ፡ የወርቅ ዝማም ("በሴቶች አፍንጫና ዦሮ መካከል የተንጠለጠለ ቀለበት")
ዝማም፡ የበሬ/የላም/የግመል ስናግ
ዝማሞ፡ በመንዝ ውስጥ ያለ አገር ("ዝማም ሆይ ማለት ነው")
ዝማሬ መዋሥእት፡ የዝማሬና የመዋሥእት መጻፍ ("ወይም ትምርት ቅዱስ ያሬድ የደረሰው")
ዝማሬ፡ የቍርባን ምስጋና ("ከድርገት በኋላ በግእዝ በዕዝል በአራራይ የሚዘመር የሚዘመም ባላ፭ ክፍል ክፍሎቹም ኀብስት ጽዋዕ መንፈስ የደብተራ አኰቴት የዲያቆን ምስጢር የቄስ ናቸው ይላሉ")
ዝም (ጸመ ጽም) ጭጭ ("ቃል አለመስጠት አለመናገር ምንም አለማለት ዝም አይነቅዝምእንዲሉ)
ዝም፡ መጨረሻ ቍጥር
ዝም በል፡ አትናገር ("አፍኸን ያዝ")
ዝም ባይ፡ ዝም ያለ ("የሚል የማይ ናገር")
ዝም ብሎ (ጽመ ክመ) ንኡስ አገባብ ("ሳይናገር እንዲሁ እንዲያው አለምክንያት") ( ቆሮ. ፯፡ ፲፱፡ ፲፭፡ ፲፬)
ዝም አለ፡ አረመመ ("ከመናገር ተከ ለከለ")
ዝም፡ አለመናገር፡ ዘመመ
ዝም አሠኘ፡ አስረመመ
ዝም ዕክም አለ፡ ጸጥተኛ ኾነ
ዝም ዝም አለ፡ አንዱም አንዱም ኹሉም ድምቡጭ ("ጭጭ አለ አፉን ገጠሙ")
ዝም፡ የሸማ ጥበብ ("በኩታና በቀሚስ ላይ የሚጣል የሚጠበብ")
ዝምም፡ የተዘመመ/የተጐተተ ("አፉ ከዝማም የገባ ከብት ድር")
ዝምተኛ (ኞች) ዝምታ ወዳድ ("ባለዝምታ አርማሚ ባሕታዊ")
ዝምተኛነት፡ አርማሚነት ("ዝምተኛ መኾን")
ዝምታ፡ ዝም ማለት/ማታ (ኢዮ. ፬፡ ፲፮፡ መዝ. ፻፳፪፡ ፪፡ መክ. ፫፡ ፯፡ ራእ. ፰፡ )
ዝምታ፡ ጫታ፡ ዘመመ
ዝምዘማ፡ ጠቀማ/ቅምቀማ/ጠለፋ
ዝምዝማት (ቶች) ጥቅማት/ቅም ቅማት
ዝምዝም፡ የተዘመዘመ/የተቀመቀመ ("ቅምቅም በርኖስ ቀሚስ ዝናር")
ዝምድ፡ የቅኔ አገባብ ስም
ዝምድና፡ ዘመድነት
ዝሞት (ቶች) ያለቃና የምንዝር ወላጅ ርስት ተካፋይ ("የወንድማማችና የትማማች ልጅ ባላንጣንና ምንዝርን ተመልከት")
ዝሪት (ዝርዕት) የተዘራች ("ዘር ብቋያ ሰብል")
ዝራር/አዝራር (ሮች) ዝርግ ታታ ("የልብስ ቍልፍ ሞላላውና ክቡም በዚሁ ስም ይጠራ")
ዝራንጭ (ዝራጭ) ቍንጮ ("የቍ ንጮ ዐይነት")
ዝራጭ (ጮች) ዐጪር ሰው/ድንክ
ዝር (ዝሩዕ) የተዘራ ("ብትን ንስ ንስ እኸል")
ዝር መድረስ፡ ዘረረ
ዝር አለ፡ ደረሰ ("ትርው አለ")
ዝርር፡ የተዘረረ ("ዝልል ዝርግ ስትር ስጥ ጋድሚያ")
ዝርኵት፡ የተዘረኰተ ("ዝልጕስ ግዱፍ")
ዝርክራኪ/ዝርክርክ፡ የተዝረከረከ ("ግዱፍ")
ዝርክርካም፡ ባለዝርክርክ/ግድፈታም ("ስሕተት ያለበት የመላበት መጣፍ ዝርክርክ አለ ዝርፍርፍ አለ")
ዝርክርክ፡ ልብሱን የማይሰበስብ ሞኝ ("ከረፈፍ ሽማግሌ")
ዝርክት፡ የተዘረከተ ("ቀዳዳ ቡጭቅ ዝርክት አለ ቅድድ ቡጭቅ አለ")
ዝርክትክት፡ የተዘረካከተ ("ቡጭቅጭቅ ሽርክትክት")
ዝርዘራ፡ ብተና/ሽክሸካ ("የመዘርዘር የመሞረድ ሥራ")
ዝርዝረ ቀጭ፡ ዝርዝርን የሚቀጭ ሕፃን ("ታናሽ ልጅ")
ዝርዝር (ሮች) (ዝርዙር) ምርቁ የተበተነ ("ጨርቋ ሰብል ዛላ")
ዝርዝር (ሮች) በያንቀጹና በየጥሬው ጫፍ እየተጨመረ ሩቅና ቅርብን አንድና ብዙን ወንድና ሴትን የሚለይ ፊደል ("፪ኛ ስሙ ምእላድ ይባላል እነዚሁም ግእዝ ካዕብ ችኹ ናቸው ተናባቢ ቅጽልነትና ባለቤትን ይገልጣሉ በጥሬ ሩቁ ወንድ ካዕብና የሩቋ ሴት ራብዕ እኔ የሚለው ኃምስ ናቸው ካዕብና ኃምስም ዘመድ ዝርዝር የቀሩት ኹሉም ባዕድ ዝርዝር ይባላሉ ፪ኛው ዝይጠብቃል")
ዝርዝር ምስክር፡ አውራምስክር ያይደለ
ዝርዝር ርባታ፡ እነዚህ ከዚህ በላይ ያሉትና ሌሎችም () ቸው እየተጨመሩበት በስሳ መደብ የሚረባ ቃል
ዝርዝር፡ በብዙ ገጽ ተጽፎ ያልተደመረ ብር ("ወይም ሌላ ዕቃ")
ዝርዝር፡ ተራ ያለው ነገር
ዝርዝር፡ ኰኰኔ ("ባውራ ዶሮ ግንባር ላይ ያለ ነጠላና ሥሥ የኾነ ረዥም የቄዳ ቍንጮ ጫፉ ክፍል ክፍል ያለው ዐጪሩ ዱልዱም ይባላል")
ዝርዝር፡ የተመነዘረ ("ብትን ገንዘብ መሐለቅ ተሙን ቤሳ")
ዝርጊት፡ ምርጊት ("ሰፊ የእግር ፵ማ ዝርግት መዘርጋት")
ዝርግ፡ ሥራ ፈት ሴት
ዝርግ፡ የተዘረጋ ("ስትር ስጥ ዝርር ጠፍጣፋ ሥሥ ውጥር ንጥፍ")
ዝርግት አለ፡ ስትር አለ (ኢዮ. ፴፮፡ ፳፱)
ዝርግፍ አለ፡ ውጥት ፍስስ አለ
ዝርግፍ ወርቅ፡ ከወርቅ የተበጀ ዶቃ ("ወይም እንጥልጥል ጌጥ ዝርግፍ መባሉ አለክር አለማተብ ሲኾን ነው") ( ጴጥ. ፫፡ )
ዝርግፍ፡ የተዘረገፈ/የወጣ
ዝርጠጣ፡ የመናድ/የመጐተት ሥራ
ዝርጥርጥ፡ ዝርክርክ ("የቀረ ዝርጥርጥ አለ ተዝረጠረጠ")
ዝርጥጥ፡ የተዘረጠጠ/የተናደ ("ክምር ዝርጥጥ አደረገ ዘረጠጠ")
ዝርፊያ፡ ዝኒ ከማሁ ለዘረፋ ("ብዝበዛ")
ዝቀት (ዝሕቀት) ዝኒ ከማሁ
ዝቃጭ፡ የዘቀጠ ("አተላ አንቡላ")
ዝቄ፡ ዝኒ ከማሁ ("ከፊለ ስም ነው")
ዝቅ አለ፡ ከላይ ለቀቀ/ወረድ ' አለ/ወደ ታች ኾነ/አነሰ
ዝቅ አሠኘ፡ ወደ ግርጌ አስወረደ
ዝቅ አርጋቸው፡ የሰው ስም
ዝቅ አደረገ፡ ራስጌን አስለቀቀ/አወረደ (ዳን. ፬፡ ፴፯)
ዝቅ፡ ወረድ/መውረድ
ዝቅ ዝቅ አደረገ፡ ሌላውን ወይም ራሱን አዋረደ (ሉቃ. ፲፰፡ ፲፲፬)
ዝቅ፡ የማስ ጋን ርኰት
ዝቅተኛ (ኞች) ታናሽ ነገር/አነ ስተኛ/ምክትል/ተወራጅ
ዝቅታ፡ ተዋረድ፡ ዘቀዘቀ
ዝቅታ፡ ተዋረድ/ገበታ
ዝቅታ፡ ታች/የከፍታ ግርጌ (መሳ. ፲፰፡ ፳፰፡ ሕዝ. ፮፡ ፫፡ ሮሜ. ፰፡ ፴፱)
ዝቅታ፡ ዝቅ ማለት
ዝቅወረድ ዘቀዘቀ
ዝቅዘቃ/ዝቅዝቆሽ/ዝቅዝቂት፡ የመዘቅዘቅ/የማቈልቈል ሥራ/ድርጊት
ዝቅዝቅ (ቆች) የተዘቀዘቀ ("ቍልቍል ዝቅዝቅ ሰባት ፈርጅ ጋቢ ተዘቅ ዝቆ የተሰፋ")
ዝቅዝቅ አለ፡ ተዘቀዘቀ ("ፍስስ እለ")
ዝቅጥቃጭ፡ የዝቃጭ ዝቃጭ
ዝቆሽ፡ ጠረጋ/ስብሰባ ("የቦይ ሥራ")
ዝቋላ ( ቈላ) የተራራ ስም ("በሺዋ ግዛት ያለ ያቦ ገዳም እሳቸው ያቀኑት የጸለዩበት ዝቋላ ማለት በስተምሥራቁ ያለውን ቈላ ያመለክታል")
ዝቋሎች፡ የዝቋላ መነኵሴዎች ("ሕዝቦች እንግዳ ተቀባዮች")
ዝቡቅቡቅ (ሰበቀ) ወፍራም/ለስ ላሳ/ለምለም ማለፊያ እንጀራ
ዝቡቅቡቅ አለ፡ ወፈረ/ለሰለሰ ("ወዛም ኾነ")
ዝቡጥቡጥ አለ፡ ተዝቦጠቦጠ
ዝቡጥቡጥ፡ የተዝቦጠቦጠ ("ብጥብጥ ቡሖ ጠሳ ጠጅ ቅቤ ማር ኑግ ተልባ ሰሊጥ")
ዝባዝንኪያም (ሞች) ኰተታም ባለጣጣ
ዝባዝንኬ፡ ዞብል
ዝባዝንኬ፡ የማይረባ ኰተት ("ምና ምን ምናምንቴ እንቶ ፈንቶ ጣጣ")
ዝባድ፡ ጥርኝ ("ከምትባል አውሬ የሚ ገኝ የሽቱ ቅባት")
ዝብ፡ የዘባ ("ድር ለማጣ ልምጥ ጥታ የሌለው")
ዝብለላ፡ ዝፍዘፋ/መዘብለል
ዝብልል አደረገ፡ ዘበለለ
ዝብልል፡ የተዘበለለ ("የታራ ዐር ኵስ በግእዝ ዝብል ይባላል")
ዝብርቅ (ድብርቅ) የተዘባረቀ/የተ ሳሳተ ("ቅልቅል ድብልቅ")
ዝብርቅርቅ አለ፡ ድብልቅልቅ አለ ("ተዘበራረቀ")
ዝብርቅርቅ፡ የተዘበራረቀ ድብልቅልቅ
ዝብብት፡ ዛቻ/ፉከራ/ፉክክር
ዝብት፡ የፍግ ክምር
ዝብትር፡ የተዘበተረ ("ዝንትር")
ዝብዘባ፡ ንዝነዛ/ንትረካ/ጭቅጨቃ
ዝብዝብ፡ ንዝንዝ/ንትርክ/ጭቅጭቅ/ውዝግብ ("እስከ የሌለው ነገር")
ዝብዝብ፡ የተዘበዘበ/የተነተረከ
ዝብድይ (ፍያል) እግራም ጣባ ("ወይም ወጭት የዝባድ የለስታ ቅቤ መቀበያ ማስቀመጫ") (ኢሳ. ፷፭፡ )
ዝብጥር፡ ሥብጥር
ዝብጥርጥር አለ፡ ሥብጥርጥር አለ
ዝተታም፡ ዝተት ለባሽ/አሸራጭ ("ባለዝተት")
ዝተት (ቶች) ያልተሰፋ ነጠላ ማቅ
ዝትዝት፡ የተዘተዘተ ("ብጥስጥስ ግትግት አዘታዘት አገታገት መዘትዘት")
ዝኒ ከማሁ፡ ይህም እንደዚያው ነው
ዝኒ፡ ዘነበለ
ዝኒ፡ ይህ/ ይህ
ዝና (ዜነወ ዜና) ወሬ/ነገር/ ብዱ
ዝና ወዳድ፡ ታሪክ/ዠብዱ ወዳድ ("እንዲህ ሠራ እንዲህ አደረገ ልባል ስሜ ይጠራ ባይ ሐርበኛ ጐበዝ ጦረኛ ሆያ ሆዬ ጕዴ ዝና ወዳዴ" እንዲሉ ልጀች)
ዝናመ መዓት፡ የቍጣ ዝናም
ዝናመ ምሕረት፡ የምሕረት ዝናም
ዝናሙ አቆመ) አቈረጠ
ዝናማ (ዜናዊ) ባለዝና/ስመ ጥር
ዝናር (ሮች) በቁሙ የወታደር መታ ጠቂያ ("የጥይት የቀለሕ ጐሬ")
ዝናሽ፡ ዝናሽ ብዙ ("የሴት ስም")
ዝናበ ከልክል፡ ጉዴላ የከንባታ ሰው ("እኸል ሳይቀምስ ወደ ሰማይ አፍ እያለ በዘንግ ደመናን ግራና ቀኝ ይመራል ዝናብ እንዳይዘንብ ያደርጋል")
ዝናቡ፡ ዝናብ ("የርሱ ዝናብ")
ዝናባም፡ ባለዝናብ ("ዝናበ ብዙ አገር ተራራ ደን")
ዝናብ (ቦች) (ዝናም ማት) ከባሕር የወጣ የሰማይ ውሃ
ዝናት (ዝኅነት) ዕረፍት/ጸጥታ
ዝናት (ዝንየት) ድራት/ፍት ወት ("የዝሙት ሥራ")
ዝናኸ፡ ዝናኸ ብዙ ("የሰው ስም ያንተ ዝና ዝናኸ ብዙ ነው")
ዝናው ተሰማ፡ ያው ታላቅ ሥራው በሰው ኹሉ ዦሮ ፈሰሰ/ተደመጠ (ማቴ. ፬፡ ፳፬)
ዝናው፡ የሰው ስም ("የርሱ ዝና ለት ነው")
ዝናድ፡ ኣስቴ
ዝናፊ፡ ትርፍ/ዕላፊ ("የቃል። ዝንፋት ዝኒ ከማሁ ትርፎቻ ብል ርዝማኔ")
ዝንቅ አለ፡ ቅልቅል ' አለ
ዝንቅ፡ የተዘነቀ ("ቅይጥ ውጥንቅጥ ድብልቅ ዝብርቅ")
ዝንበ ከልክል፡ ዝንብ የማያስገባ ማት መሶብ
ዝንበላ (ጽናኔ) መዘንበል ( ጴጥ. ፪፡ ፲፪)
ዝንባሌ፡ ዝኒ ከማሁ
ዝንባም (ሞች) ባለዝንብ ("ዝንብ የወረረው ፈዛዛ ፊቱን የማያጥብ የማያጸዳ ዝንባምነት ዝንባም መኾን ፈዛዛነት")
ዝንብ (ቦች) በቁሙ የታወቀ ተን ቀሳቃሽ በክንፍ የሚበር የሚንዣበብ ("በዐ ረብ ዝቡብ ይባላል")
ዝንብል (ድኑን ጽኑን) የዘነበለ/ የተዘነበለ
ዝንቦ፡ የበር ላይ ጣራ
ዝንቦ፡ የገና ስድብ ("ቃለ አኅስሮ ዕሽ እነዝንቦእንዲል የገና ተሳዳቢ)
ዝንተ ዓለም፡ ድንተ ዓለም
ዝንት፡ ድንት
ዝንትር፡ የተዘነተረ ("ንክስ ዝብትር ቡጭቅ ቡትርፍ")
ዝንኵርኵር አለ፡ ብልሽትሽት አለ
ዝንኵርኵር፡ የተዘነኳኰረ
ዝንኵት፡ የዘነከተ ("ዘንካታ")
ዝንኪላ መሰለ፡ ቀላ/ደም ለበሰ ("ያይን")
ዝንኪላ፡ የጕመሮና የቀንጠፋ ዐይነት ዕንጨት ("ፍሬው ቀይ")
ዝንድ፡ የበር ብረት የመዝጊያ መሸጐሪያ ("ረዥም ሸንገል ጫፍና ጫፉ እንደ ወገል ሜንጦነትና ቀለበትነት ያለው")
ዝንጀር (ሪት) ዝኒ ከማሁ
ዝንጀር ጐሹ፡ በጥይት የሞተ ገመር
ዝንጀሮ (ዎች) ፊቱ ሰው የሚመስል አውሬ ("ጥቍርና ነጭ አፍንጫ ዐዳ በገደል ላይ ዐዳሪ ተባቱም እንስቱም ዝንጀሮ ይባላል") ( ዜና. ፱፡ ፳፩)
ዝንጅብል (ሎች) የተክል ስም ("ሥሩ ለወጥ ቅመም የሚኾን እንደ በርበራ የሚያቃጥል ተክል ዝንጅብልና ኰረሪማእንዲሉ)
ዝንጉ፡ የዘነጋ/የረሳ (ምሳ. ፲፫፡ ፲፯፡ ኢሳ. ፫፡ ፲፩)
ዝንጕር፡ ሽልም
ዝንጕርጕሪት ቱ፡ ሽልምልሚት (ዘፍ. ፴፯፡ ፳፫, ፴፪)
ዝንጕርጕር (ሮች) ዥጕርጕር/ሽል ምልም
ዝንጕርጕርነት፡ ነጭነትና ጥቍርነት
ዝንጉነት፡ ዝንጉ መኾን (ኢሳ. ፱፡ ፲፰)
ዝንጋታ፡ ርሳታ/ዕጦት
ዝንግ፡ የተዘነጋ/የተረሳ
ዝንግልግል አለ፡ ከከ
ዝንግልግል፡ የከከ ሙክክ ያለ
ዝንግሪር፡ ትልቅ የጠላ ጋን ("ሳሌ")
ዝንግት፡ ርስት
ዝንጎች፡ ዝንጉዎች ("የዘነጉ የረሱ") (ኢዮ. ፴፬፡ ፲፰፡ ኢሳ. ፲፬፡ )
ዝንጠላ፡ ፍንቀላ/ነደላ
ዝንጠፋ፡ ዥምፂጋ/ሽምጠጣ/ቈረጣ
ዝንጣፊ፡ የተዘነጠፈ ("የተምር የበለስ የወይን የሌላውም ተክል ዘለላ ቍራጭ ግንጣይ") (ዮሐ. ፲፪፡ ፲፫)
ዝንጣፎች፡ ቍራጮች/ግንጣዮች (ራእ. ፯፡ )
ዝንጥል አለ፡ ብስት ቅድድ አለ
ዝንጥል ጉፍታ፡ የተበሳ የተቀደደ
ዝንጥልጥል አለ፡ ሽርክትክት አለ
ዝንጥልጥል አደረገ፡ ብስትስት አደ ረገ
ዝንጥልጥል፡ የተዘነጣጠለ/የተበሳሳ ሽርክትክት
ዝንጥፍ፡ ዝኒ ከማሁ ለዝንጣፊ (" ምግግ")
ዝንፍ አለ፡ ረዘም አለ ("ከልክ ከመጠን ዐለፈ ትርፍ ነገር ተናገረ")
ዝንፍ፡ የዘነፈ ("የበለጠ")
ዝክር (ሮች) ያምላክ/የማሪያም/የመልአክ/የጻድቅ/የሰማዕት በዓል ("በሚውልበት ቀን የሚደረግ ድግስ የስም መጠሪያ")
ዝክዘካ፡ ንቅነቃ/ዝርገፋ
ዝክዝክ (ዝሕዙሕ) የተዘከዘከ ("ዝር ግፍ ዝርዝር ሽክሽክ")
ዝክዝክ አደረገ፡ ዘከዘከ
ዝውር፡ የተዘወረ
ዝውተራ፡ የማዘውተር ሥራ
ዝውተራ የማዘውተር፡ ሥራ፡ አዘወተረ (አውተረ) ዘወትር፡ ዕለት፡ ዕለት፡ በየጊዜው፡ በየቀኑ፡ መላልሶ፡ ሠራ፡ ጋገመ፡ ዐሳቡን፡ ባንድ፡ ነገር፡ ላይ፡ አደረገ
ዝውትር፡ የተዘወተረ
ዝየራ፡ ጕብኘታ/ዘፈን/ምስጋና
ዝየና፡ ሽለማ
ዝየዳ፡ ጭመራ
ዝዪ ( ዮች) የባሕር አሞራ ዋነ ተኛ ("በጋልኛ ዳክዬ ይባላል ወደ ውስጥ የምትጠልቀው ይብራ ናት")
ዝይን፡ የተዘየነ ("ያጌጠ ሽልም")
ዝዶም፡ የቈላ ዛፍ
ዝገት፡ እድፈት/ጥቍረት (ምሳ. ፳፭፡ ፬፡ ሕዝ. ፳፬፡ - ፲፩, ፲፪፡ ያዕ. - )
ዝጕን፡ የዘጐነ ("ጥቍር ገላ ብልዝ ጥርስ ዐይን")
ዝጉዳ፡ ብርሌ ባለአረንጓዴ ቀለም (" ይም ሌላ ዐይነት")
ዝጉዳ፡ ዘገነ
ዝጋግ (ትግ) በዝግታ ዐንገትን ሚያበላሽ ምሽሮ/ነቀርሳ
ዝግ (ዝጉሕ) የተዘጋ ("ድፍን ደን ቈሮ ውለናም")
ዝግ፡ ቀስ ("አለመፍጠን")
ዝግ፡ ቀስ ዘገገ
ዝግ አለ፡ ቀስ አለ
ዝግ፡ ከሰው ተለይቶ በበኣት ተከቶ የሚኖር ባሕታዊ/መናኝ/መነኵሴ
ዝግ፡ የተዘጋ ("ዘጋ")
ዝግራ (ሥግሪያ) ወንከር ወንከር ("ድንኵል ድንኵል ማለት ዥግርኛ መኼድ መሥገር ታቱ ዝግራእንዲሉ)
ዝግባ (ዘግባ) የንጨት ስም ("ብዙ ቅጠልና ዐጽቅ ያለው ዛፍ")
ዝግብ (ዝጉብ) የተዘገበ ("ስብስብ ክምቹ ጥርቅም ድልብ")
ዝግብ፡ ያገር ስም ("በተጒለት ያለ ወረዳ")
ዝግተኛ (ኞች) ባለዝግታ ("ዝግ ባይ")
ዝግታ፡ ቀስታ
ዝግታ፡ ቀስታ ዘገገ
ዝግት (ዝግሐት) መዝጋት
ዝግት አለ፡ ግጥም/ክድን አለ
ዝግትግት አደረገ፡ ግጥምጥም/ ድንድን አደረገ
ዝግን (ትግ. ዝግኒ) ክትፎ ከቅቤና ከድልኸ ጋራ የታመሰ የስጋ ወጥ ("በእጅ በጭልፋ በንጀራ ተዘግኖ የሚበላ")
ዝግን፡ በጨው የተቀቀለ መተሮ እየተዘገነ የሚታደል
ዝግን አደረገ፡ ዘገነ ("ቃም አደረገ")
ዝግንትላም፡ ዝግንትል ለባሽ ("ባለዝ ግንትል ወይም ተሸካሚ እብድ ሰው")
ዝግንትል (ዝግን ትል) የተቀዳ ደደ/የተበጫጨቀ ጨርቅ/ስልቻ/ደላጎ ("ባለ ብዙ ተባይ")
ዝግንን አለው፡ አስፈራው ("አኹን ኹን ኣለው")
ዝግንንታ (ሰዖዛዝ) ስቅጥጥታ
ዝግኝ (ኞች) የተዘገነ ("ጥርኝ") (ዘኍ. ፳፭፡ ፳፮)
ዝግዘጋ፡ ርዝማኔ/ረዥምነት
ዝግዝግታ፡ ዝክዘካ
ዝግየታ/ዝግይት፡ ቈይታ
ዝግዩ፡ የዘገየ/የቈየ
ዝግይት አለ፡ ዘገየ
ዝግጁ (ዎች) የተዘጋጀ ("ድርጁ ስንዱ")
ዝግጅት፡ ድርጅት/መሰናዶ
ዝግጅቶች፡ ድርጅቶች
ዝግጣ ዕንጨት፡ ድግጣ
ዝጠና፡ መዘጠን
ዝጥር፡ የተዘጠረ ("ንፍ ውጥር")
ዝጥር የተዘጠረ፡ ንፍ፡ ውጥር (ጥዘ) መዘጠር፡ መነፋት፡ መወጠር
ዝጥን፡ የተዘጠነ ("ዘጠኝ የኾነ")
ዝፍቅ፡ የተዘፈቀ/የተነከረ ("ነከርት ሞኝ ዝፍቅ ቂልእንዲሉ)
ዝፍት፡ ሰነፍ ሴት ("ዝቃጭ አተላ ማለት ነው")
ዝፍት፡ የንጨት/የሙጫ/ቅጥራን ጣብቅ የሚኾን (ኢሳ. ፴፡ , )
ዝፍዘፋ፡ ነከራ/ድፍደፋ
ዝፍዝፍ፡ የተዘፈዘፈ ("ንክር ድፍድፍ ርጥጥ ውዝፍ")
(ኮፈፈ) ኩፍ አለ ("ተነሣ ብድግ አለ የሊጥ ኩፍ አለ ኣኰረፈ ለብቻው ተቀመጠ ")
ዞላ (ዝሑል) ልል/ደካማ/ዐቅመ ቢስ ሴታውል
ዞላ፡ ቦዘን ("ሥራ መፍታት ዞላ ዋለ ቦዘነ ሥራ ፈታ")
ዞላ፡ ቦዘን፡ ዘለለ
ዞልዞል አለ፡ ዝኒ ከማሁ
ዞማ፡ በመራቤቴ ክፍል ያለ ቀበሌ
ዞማ፡ ዝርግ ማለፊየኾነ ረዥም የራስ ጠጕር ("ቶሎ ቶሎ የሚያድግ የሚገሠግሥ")
ዞረ (ዘዊር ዞረ) ተንቀዋለለ/ተን ከዋረረ/ዐወደ ("በዙሪያ ኼደ ከበበ ታጠፈ ተጠመጠመ ተጠመዘዘ ተመለሰ መንገድ ለቀቀ")
ዞረ፡ ሰከረ/ኣበደ/ተናወጠ ራሱ
ዞረ፡ ዐወደ፡ ዘወረ
ዞረሬ፡ የቀድሞ የምንጃር ስም
ዞረሽ ዕቀፊኝ፡ የፈትል ስም ("ከባ ሕር የመጣ ድር ኰምታሬ")
ዞሪቴ፡ ዝኒ ከማሁ ("ሶራዊት")
ዞሪት (ሶሪት) ዠርባዋ ጥቍር ደረተ ነጭ ክንፈ ቀይ የምታምር ወፍ ("ባረብኛ ዙራ በጋልኛ ጆሮ ትባላለች")
ዞሪት፡ ዘች ዘች አለ ("ሩጭ ሩጭ አለ የበሬ")
ዞሮ፡ ተመልሶ/ተጠምዞ
ዞብል፡ በየጁ አውራጃ ያለ ተራራ
ዞግ (ዘውግ) ወገን/ነገድ ("ዘወገን")
ዞግ፡ ሰበብ/ምክንያት ("የወገን ሳቢያ የዞግ ዞግእንዲሉ)
ዞጠ ሶጠ) አዞጠ፡ ገረፈ/መታ/ ደበደበ/መደወተ
ዞጠ) ሶጠ) አዞጠ ገረፈ፡ መታ፡ ደበደበ፡ መደወተ
ዞጲ (ዘኢትዮጵያ) አፍሪቃዊ ("በኢትዮጵያ የሚበቅል ጥቍር ዕንጨት ዋጋው ክቡርና ውድ የኾነ") (ኢሳ. ፵፩፡ ፲፱)
ዞፍ፡ የማሕፀን ልፋጭ፡ ወዘፈ
አለ፡ (ትግ. ዘውሐ "አሰፋ ሰፊ አደረገ") ተሰጣ/ተዘረጋ
ዟ፡ ዘግ/ዘፍ ("መሰጣት መዘርጋት")
ዟሪ (ዎች) የዞረ/የሚዞር/የሚንቀ ዋለል ("ዘዋሪ ከውታታ ቀውላላ አገር ላገር ኻያጅ አግዳማይ")
ዟይ (ዝዋይ) ያገርና የባሕር ስም ("ባሩሲ ወረዳ ያለ ባሕር በውስጡ ካለው ደሴት ጋራ ባንድነት ዟይ ይባላል ብሎ የተሰጣ የተዘረጋ ካ፭ ደሴት የገጠመ ውሃ ማለት ነው")
ዠደድ፡ የበዛ/ብዙ

No comments:

Post a Comment

ሽፋን

  ሀ   ለ   ሐ   መ   ሠ   ረ   ሰ   ሸ   ቀ   በ   ተ   ቸ   ኀ   ነ   ኘ   አ   ከ   ኸ   ወ   ዐ   ዘ   ዠ   የ   ደ   ጀ   ገ   ጠ   ጨ   ጰ   ጸ   ፀ   ፈ   ፐ