ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ሸ ፡ የሠሰ ወራሽ ዲቃላ ባማርኛ ። (ማስረጃ) ፡ ነገሠ - ነጋሽ፡ ዐሠሠ - ዐሣሽ፡ ቀደሰ - ቀዳሽ፡ ወረሰ - ወራሽ ። በዕብራይስጥና በሱርስት በዐረብ ቋንቋ ግን "ሸ" መደበኛ ፊደል እንጂ ተወራጅ አይዶለም ። በግእዝም ከሠ ላማ በፊት ከዋናነት በቀር ምክትልነት አልነበረውም ይባላል፡ ይኸውም ሠውት "ሠ" ነው ።
ሸ) አሸ (ዠ) ፡ በውስጥና በውጭ እሳት አነደደ፣ ተኰሰ፣ አገነፈለ (ባዲስ ሸክላ መዠመሪያ ቀቀለ፡ ምጣድን ብዙ ጊዜ ዐሠሠ፣ ወለወለ ከዚያ በኋላ ጋገረ) ።
ሸሐኝ፣ ሻሕኝ (ዕብ ሺሒን) ፡ በአፍንጫና በፊት ላይ የሚወጣ ደረቅ ቍስል እሾኻም” ። ጭንቍን" ተመልከት ።
ሸሐኝ ነቀርሳ ኪንታሮት የመሰለው ኹሉ (ስም) ።
ሸኅ (ኆች) ፡ የአስላም ቄስ (የቍርኣን ካህን ሰባኪ) ።
ሸኅ፡ አንበሶ፡ የዛር፡ ስም፡ "ያረብ፡ አገር፡ ዛር። "
ሸለለ፡ ሸለተ፡ ሸለፈ፡ ሸነገለ።
ሸለለ፡ ሸረረ።
ሸለለ፡ ሸደሸደ፡ ወሰወሰ፡ ቶረበ፡ አያያዘ፡ አጋጠመ፡ ሰፋ፡ (ዘፍጥረት ፫፡ ፯)።
ሸለለ፡ ጠፍ፣ ባድማ፡ ባዶ፡ አደረገ።
ሸለሊት፡ ሸረሪት። "ወደ፡ ፊት፡ እንሽላሊትን፡ እይ። "
ሸለሊት፡ ያውሬ፡ ሽንት፡ የበሰበሰ፡ ጭቃ። "የእግሬን፡ ጣት፡ ሸለሊት፡ ቈረጠችኝ፡ እንዲል፡ ባላገር። "
ሸለል ፣ ዕዳሪ፡ ኵስ፡ ጓሮ፡ ቤት፡ ዐይነ፡ ምድር፡ ሠሣራ። "የብዔልንም፡ ቤት፡ አፈረሱ፡ ሸለልም፡ (ጕድፍ፡ መጣያም)፡ አደረጉት፡ (፪ኛ ነገሥት፡ ፲፡ ፳፯)። "
ሸለል፡ አለ፡ ሸረር፡ አለ፡ በፍጥነት ተሳበ፡ ተጐተተ።
ሸለመ፡ ሽልማት፡ ሰጠ፡ እለበሰ፡ አንቈጠቈጠ፡ "ያ፡ ለሠራ፡ ሰው፡ ብድሩን፡ ለመክፈል፡ ሸለመ፡ በቀላል፡ ዐመመና፡
ተወ፡ ወጣ፡ ለቀቀ፡ በሽታ፡ ከብትን፡ ፈንጣጣ፡ ሰውን። "
ሸለመ፡ አስጌጠ።
ሸለመ፡ ጠቃጠቆ፡ አደረገ፡ ፊትን።
ሸለም ፣ የዘንባባ፡ የኮባ፡ የንሰት፡ የሙዝ፡ ሙሽራ፡ ውልብልቢት።
ሸለሸል፡ (ሎች)፡ የዱር፡ ኵበት። "ከሸለል፡ ጋራ፡ አንድ፡ ነው። "
ሸለቀቀ፡ (ለቀቀ)፣ቀደደ፡ ላጠ፡ ገፈፈ፡ ከውስጥ፡ አወጣ፡ ቍርዝን።
ሸለቀቀ፡ አጠበበ፡ አቀጠነ።
ሸለተ፡ ዘበተ፡ አታለለ፡ አሳተ።
ሸለተ፡ ጠረበ፡ ላገ፡ አሾለ፡ ዕንጨትን።
ሸለግ፡ ስሌት፡ ሒሳብ፡ "በገንዘብ፡ ፈንታ ለንጉሥ፡ የተሰጠ፡ ልጅ። "
ሸለፈ፡፡ አታለለ፡ ሸነገለ፡ ካንገት፡ በላይ፡ ተናገረ፡ አላገጠ፡ (ኢሳያስ ፴፯፡ ፬)። "እከሌ፡ እንዲህ፡ ያለኸ፡ ሲሸልፍኸ፡ ነው። "
ሸለፈታም፡ ልንበጣም፡ ሽፍን።
ሸለፈት፣ (ቍልፈት፡ ከተማ፡ ነፍስት)፣ ልንቡጥ፡ ወሸላ።
ሸለፈፈ፡ ገለፈፈ፡ ላጠ፡ ዐማ።
ሸለፈፍ፣ ሸልፋፋ፡ የተሸለፈፈ።
ሸላ፣ ተንኰለኛ፡ ሰው፡ መኼጃ፡
የማይታወቅ፣ እባብ። "
ሸላ፡ ትንሹ፡ መጠማጥ፡ ትልቁ። "
ሸላለመ፡ መላልሶ፡ አስጌጠ፡ አለባበሰ።
ሸላለተ፡ ቈራረጠ፡ ጠራረበ፡ ዐናነጠ።
ሸላሚ፡ (ዎች)፡ የሸለመ፡ የሚሸልም፡ አስጊያ፡ አንጥረኛ። "ጃን፡ ሸላሚ፡ እንዲሉ። "
ሸላች፡ (ቾች)፡ የሸለተ፡ የሚሸልት፡ ቈራጭ፡ (፩ኛ ሳሙኤል፡ ፳፭፡ ፲፩። ኢሳያስ ፶፫፡ ፯። የሐዋርያት ሥራ ፰፡ ፴፪)።
ሸላች፡ አሿይ፡ አታላይ፡ አሳች።
ሸላይ፡ (ዮች)፡ የሸለለ፡ የሚሸልል፡ አቅራሪ፡ ጌትዬ፡ ወይም፡ ሌላ።
ሸላይ፡ ሸድሻጅ፡ ወስዋሽ።
ሸላጊ፡ የሸለገ፡ የሚሸልግ፡ ገማች፡ ገምጋሚ፡
ሸላፊ፡ የሸለፈ፡ የሚሸልፍ፡ አታላይ፡ ሸንጋይ።
ሸሌ ፣ ሸላዊ፡ የሸላ፡ ወገን።
ሸሌ መጠማጥ፡ ሸሌ፡ ሰልቶ፡
ሾልኮ፣ የሚኼድ፡ መጠማጥ፡ ጠቢ፡ መጥማጭ፡
ማለት፡ ነው። "ይኸውም፡ ሊታወቅ፡ በባላገር፡
የፍየልን፡ እግር፡ በዥራቱ፡ እየጋዳ፡ ጡቷን፡ ይጠባል፡ ይባላል ፣ እሱም፡ ሽንጣም፡ ዥራተ፡ ረዥም፡ እግሮቹ፡ ዐጫጭሮች፡ ናቸው።
ሸሌ፣ መጠማጥ፡ ብርቱ፡ የጠላ፡
መጥ።
ሸልቃቂ፣የሸለቀቀ፡ የሚሸልቅቅ፡ ቀዳጅ፡ ገፋፊ፡ አውጪ።
ሸልቋቋ፡ ሸልቋቍቻ፣ጠባብ፡ ሱሪ፡ ሠላጤ፡ ቀልቀሎ፡ "ባንድ፣ እግር፡ የወጣ፡ ስልቻ። "
ሸመሸመ፡ ብዙ፡ ቃመ።
ሸመቀ፡ አሸማጠጠ፡ አስተጣጠረ፡ አሳሳበ፡ ሽምጥን።
ሸመቀቅ ፣ ሸምቃቃ፡ (ቆች)፡ ጨመደድ፡ ምዳዳ፡ "ትክክል፡ የማይረግጥ። "
ሸመቃ፡ ሽመቃ፡ ደፈጣ፡ ደባ፡ (ኤርምያስ ፶፩፡ ፲፪)።
ሸመተረ፣(ሸመተ፡ መተረ)
ሸመታ፡ ልወጣ፡ ግዥ።
ሸመነ፡ (ሰመነ)
ሸመደ ፣ ሸመጠጠ።
ሸመድማዳ ፣ ሽምድምድ፣ የተሽመደመደ ፣ እግረ፡ ወልጋዳ።
ሸመገለ፡ ሾመ ፣ (መ)፡ አክበረ፡ እሠለጠነ ማዕርግ፡ ሰ፡ አገር፡ አስገዛ፡ "ሰውን፡ መ፡ ሾመ፡ መባለ፡ ወና፡ የ፡ ተወራራሽ፡ ስለ፡ ኾኑ፡ ነው። "
ሸመጠ)፡ አሸመጠ፣ አኰረፈ፣ ኣዶበረ። "ሰመጠን፡ አስተውል።"
ሸመጠረ፡ (ሸመተረ)፡ አለልክ፡ ሓመጠጠ፡ ዦሮ፡ ወጋ።
ሸመጠጠ፡ (መጠጠ)፡ ጠጣ፡ ጨለጠ፡ ዥው፡ አደረገ፡ ለጋ፡ ለገሸ፡ ፊረሰ፡ በፍጥነት።
ሸመጠጠ፡ መዠመሪያ፡ ሽሩባ፡ ሠራ።
ሸመጠጠ፡ ሮጠ፡ ጋለበ፡ (ዦሮውን፡ ሸመጠጠ)፡ ወደ፡ ኋላ፡ አለ፡
መለሰ።
ሸመጠጠ፡ ቀኙን፡ ወይም፡ ግራ፡ እጁን፡ ተመረኰዘ፡ ገላውን፡ እሰየፈ፡ ኳስ፡ እንዳይመው።
ሸመጠጠ፡ ተራ፡ መናኛ፡ ፈትል፡ ፈተለ።
ሸመጠጠ፡ ዠመገገ፡ እሸትን፡ ፍሬን።
ሸመጠጠ፡ ድርቄን፡ በባሕር፡ ዐረብ፡ አስጌጠ፡ ሸለመ፡ ደጐሰ።
ሸመጠጠ፡ ፀበል፡ ዋሸ ፣ ቀጠፈ።
ሸመጥ፡ ጥቍርና፡ ቀን፡ ስንዴ።
ሸማ፡ "በየፈርጁ፡ ይለበሳል፡ ሰው፡ በየጠባዩ፡ ይወደዳል። "
ሸማ፡ መሥሪያ፡ የሸማኔ፡ ጕድጓድ።
ሸማ፡ ዐጣቢ፣ ሸማ፡ የሚያጥብ፡ የሚያጐርፍ፡
የሚለቀልቅ።
ሸማ፡ የተሰፋና፡ ያልተሰፋ፡ ልብስ፡ ዐርበ።
ሸማ፡ ፈጅ፡ በልብስ፡ ስፌት፡ ውስጥ፡ ያለ፡ የፈትል፡ ድቃቂ፡ ዐቧራ።
ሸማመተ ፣ ገዛዛ፡ ለዋወጠ።
ሸማማ፡ የሸመመ፡ ዐንካሳ።
ሸማሜ፣ ሪሰ፡ ትልቅ፡ ስንዴ። "ሸማሜ፡ ያሠኘው፡ በራሱ፡ ክብደት፡ ወዳንድ፡ ወገን፡ መዝመው፡ ነው። "
ሸማሜ፡ የሸማማ፡ ዐይነት።
ሸማቂ፡ (ቆች)፡ የሚሸምቅ፡ ደፋጭ፡ አድቢ፡ (ኢዮብ ፩፡ ፭)።
ሸማች፡ (ቾች)፡ የሸመተ፡ የሚሸምት፡ እኸል፡ ገዢ፡ ሸያጭ።
ሸማኔ፡ (ሸማኒ)፡ የሸመነ፡ የሚሸምን፡ ሸማ፡ የሚሠራ።
ሸማጥር: በንግሥት በይተጊ ዙሪያ የሚያዝ የሸማ ዐጥር። "በመካከሉ ዐልፎ ዐልፎ ዘንግ አለበት።"
ሸማጥር: የቤተ መቅደስ መጋረጃ (ዘኍልቍ ፫፡ ፳፮)።
ሸምሸም (ትግ፡ ሐባ): አሸዋ። "ሽምሽም ጤፍ የሚመስል።"
ሸምሸር: ሸጢን የማይነቅዝ ዕዕ (የበረሓ ግራር ሀሎ - ዘፀ፡ ፳፳፭፡ ፲፣ ፲፫) ። አርዝ ልምጭ ዝግባ በለጥ ወይም ጥቍር ዕንጨት ዞጲ (ሕቍ) ዋንዛ ኮሶ ሰንደል ጐቢል ታቦት የሚኾን ።
ሸምሻሚ: የሸመሸመ፣ የሸመሽም፣ አጕራሽ፣ ከርታፊ፣ ሸርካች።
ሸምቀቆ (ዎች): የበሬ፣ ያውሬ፣ የወፍ መያዣ፣ ማነቂያ፣ ወጥመድ። "ከቀላድ፣ ከፍር፣ ከጭራ የተበጀ። በግእዝ፡ ፀንፈርት፡ ይባላል። ሸምቀቆ፡ ማጡኔ።"
ሸምቃቂ: የሸመቀቀ፣ የሚሸመቅቅ።
ሸምታሪ: የሸመተረ፣ የሚሸመትር፣ ሸንቋጭ፣ ገራፊ።
ሸምን:
"ከደብረ ሊባኖስ፣ በስተቀኝ ቀበሌ ያለ ታናሽ ወንዝ። ትርጓሜው ሸማ ሥራ ማለት ነው። ገድለ ተክለ ሃይማኖት ፈለገ ሸምን ይለዋል።"
ሸምጣራ: ሖምጣጣ።
ሸምጣጭ: የሸመጠጠ፣ የሚሸመጥጥ፣ ሯጭ።
ሸሞረ (ሰመረ፡ ፀመረ): ጠቀሰ (ጓጐጠ ወአነ አተ) ።
ሸሞረ: አጣምሮ ሰደበ። "፱ኛውን ሰመረ።"
ሸሞነ)፡ ኣሽሞነሞነ፣ በሸማ ሸፈነ፣ ኣከናነበ፣ አነሰነሰ፣ እንዳሻንጕሊት አደረ።
ሸረሞጠ: ጠቀሰ (ጓጐጠ ወአነ አተ)።
ሸረሞጠች: ሴሰነች። "አንተ ውጣ፣ እንተ ግባ ኣለች።"
ሸረረ (ሰረረ): ወጣ፣ ታዘለ።
ሸረረ: ተነኰለ፣ ተንኰል ሠራ፣ አደረገ።
ሸረሪት (ቶች): የተንቀሳቃሽ ስም (በፈትላ መሰላልነት ከላይ ወደ ታች የምትወርድ ከታች ወደ ላይ የምትወጣ ተሐሸረሪት) ።
ሸረሪት: ምስር ዐኝኮ ሲተፉበት የሚድን ቍስል ስም። "ሸለለ ብለኸ ሸለሊትን እይ።"
ሸረሪቶች: የዘር፣ የነገድ ስም። "ከሸሪሪት ትውልድ አለን የሚሉ ሰዎች። እነዚህም ሸረሪት አይገድሉም። ሸረሪት በሚባለው ቍስል ላይ ምስር ይተፋሉ። ዋና ስማቸው እነሴ ነው።"
ሸረር (ጐዣም): ፈር።
ሸረር አለ: እባብኛ፣ ሸረሪትኛ ኼደ፣ ሀወር አለ።
ሸረር: የቀበሌ ስም። በቡልጋና በደብረ ሊባኖስ ቈላ በስተደቡብ ያለ የሥላሴ ኣጥቢያ ባለሸንተረር።
ሸረሸ)፡ ተሸራሸ፣ ተደላደለ፣ ተመቻቸ፣ ተንዘራፈጠ።
ሸረሸረ (ትግ፡ ሸርሸረ፡ መገዘ): በረበረ ፈረፈረ ነደለ አፈረሰ” ። ሰረሰረን" ተመልከት (ከዚህ ጋራ አንድ ነው) ።
ሸረሸር: ፈረፈር፣ ፈፋ፣ ጕድባ።
ሸረበ (ዐረ): ሰቸ (ረበን" እይ) ።
ሸረበ: ፫ቱን፣ ፬ቱን ገመድ ባንድነት ወደ አንድ አደረገ (ደበለ ጠሞረ ደረበ - ሹርባና ሽራብ ሠራ ታታ) ።
ሸረተተ) አንሸራተተ፡ አዳለጠ እንሻተተ (እግርን ነቀለ ጣለ በቅምጥ ወይም በዠርባ ቍልቍል ወሰደ ኣወረደ - እኻልን ከቍና ላይ በቶሎ ገለበጠ) ።
ሸረተት፣ ሸርታታ፡
ተዳፋት (ዐፈርገደል) ።
ሸረኛ (ኞች): ክፋተኛ፣ ተንኰለኛ፣ መሠሪ፣ ሰበበኛ።
ሸረከ (ሠረከ): ወደደ ዐበረ ገጠመ (አንድ ኾነ በሥራ በንግድ) ።
ሸረከተ: ቀደደ ዘረከተ ።
ሸረከተ: ሳያደቅ ፈጨ ።
ሸረከት: ሸርካታ፣ ሽርክት፣ ረከተ፣ ቅድ፣ ዝርክት።
ሸረክራካ: ሽርክርክ፣ የተሽረከረከ፣ ፍርክርክ።
ሸረደመ፡ የጋማ ከብቱ ብዙ ጥሬ ባፉ ሙሉ ይዞ ቈረጠመ ዐኘኸ ።
ሸረደደ፡ ዋሸ ቀጠፈ ሰደበ ዐማ ነቀፈ አፌዘ አላገጠ አሾፈ (ምፀት ተናገረ) ።
ሸረገደ፡ ጠፋ ጐደለ ተበደለ ።
ሸረጠ (ዐረ) ፡
ገደበ ገደብ እደረገ ።
ሸረጠ)፡ ሠረጠ)፡ አሸረጠ፣ አገለደመ፣ በወገብ ላይ ኣሰረ።
ሸረፈ (ሰረፈ፡ በሳ): ስበረ ቈረሰዕቃን ዳቦን ከፍ ።
ሸረፈ (ዐረ፡ ጸረፈ): መነዘረ፣ ዘረዘረ፣ አበዛ (ብርን ላላድ፣ لتሙን፣ ለሩብ፣ ለመሐለቅ፣ ለቤሳ፣ ለመቶ ሳንቲም ለወጠ)።
ሸረፈ: መነዘረ።
ሸረፈ: ነቀለ (ከብት ጥርስን ከሥር)።
ሸረፋ: ሰበራ፣ ቈረሳ፣ ምንዘራ፣ ምንዛሪ።
ሸረፍ: የሰበረ፣ የነቀለ። "አንድ ሸረፍ ኹለት ሸረፍ እንዲሉ።"
ሸሪት: ኝጥል ጌጥ ።
ሸሪክ (ኮች): ወዳጅ፣ ባልንጀራ፣ ጓደኛ።
ሸሪክ መኾን: ወዳጅነት፣ ግጥሚያ፣ አንድነት።
ሸራ: ውሃ የሚቋጥር ወፍራም ልብስ (ርኰት ድንኳን የሚኾን የመርከብ ሸማ) ።
ሸራረበ: ገማመደ።
ሸራረፈ: መነዛዘረ።
ሸራረፈ: ሰባበረ፣ ቈራረሰ።
ሸራረፈ: ነቃቀለ።
ሸራቢ: የሸረበ፣ የሚሸርብ፣ ጠሪ።
ሸራፊ (ፎች): የሸረፈ፣ የሚሸርፍ፣ ሰባሪ፣ ቈራሽ፣ መንዛሪ። "ካህናት ግን አንቀጹን ሰረፈ፣ ቅጽሉንም ሰራፊ ይላሉ።"
ሸር (ዐረ): ተንኰል፣ ክፋት።
ሸር: ተንኰል ሸረረ።
ሸርሙጣ (ጦች): የሸረሞጠ፣ የሚሸረሙጥ፣ አመንዝራ፣ ጋለሞታ፣ ቅሬ፣ ሴሰኛ፣ ቅንዝርኛ።
ሸርሙጣነት: ሸርሙጣ መኾን፣ አመንዝራነት።
ሸርማ: መንታ ጥንድ ።
ሸርሜ: የቍልም አጠራር፣ ዘማዊ።
ሸርሞ ለሸርሞ: ጐን ለጐን (፪ኛ ነገሥት፡ ፬ ' ፳፭)።
ሸርሞ: ጐን አጠገብ ።
ሸርሻሪ (ሰርሳሪ): የሸረሸረ፣ የሚሸርሽር፣ በርባሪ፣ ፈርፋሪ፣ አፍራሽ፣ ነዳሊ (ውሃ)።
ሸርቋጣ: ሽርቍጥ፣ ስብስብ፣ ቀልጣፋ።
ሸርካች (ቾች): የሸረከተ፣ የሚሸረክት፣ ቀዳጅ፣ ፈይ።
ሸርዳሚ: የሸረደመ፣ የሚሸረድም፣ ቈርጣሚ፣ ዐኛኪ።
ሸርዳጅ (ጆች): የሸረደደ፣ የሚሸረድድ፣ ዋሾ፣ ቀጣፊ፣ ነቃፊ፣ እሿፊ።
ሸርጣን (ኖች): ጐርምጥ (ብዙ እጅና እግር ያለው የባሕር ተንቀሳቃሽ አቡ - መቀስ) ።
ሸርጣን: መልኩ ጐርምጥ የሚመስል የሠኔ ኮከብ። "ሸርጣን፡ ነገረ ሰይጣን እንዲል ጠንቋይ።"
ሸሸ (ሠሥዐ): አፈገፈገ ወደ ኋላ ኣለ (ዠርባውን አሳየ ሮጠ ጋለበ ፈረጠጠ ኰበለለ) ።
ሸሸ)፡ በዠድ። "ጕያን፡ ተመልከት።"
ሸሸ: ተጠጋ፣ ተማጠነ (ከጠብ፣ ከጦርነት) (፬ኛ ነገሥት፡ ፲፪፡ ፲፰። ኢሳይያስ ፴፡ ፲፯)። "(ተረት)፡ ከዥብ ጐሬ ሲሸሹ እዥብ ጐሬ።"
ሸሸገ: ፈነ ዐባ ሰወረ ደበቀ ቀበረ (ዘፀ፡
፪፡ ፲፪፡ ፪ዜና፡ ፳፪፡ ፲፩፣ ፲፪፡ ምሳ፡ ፩፡ ፲፩፡ ኢሳ፡ ፵፱፡ ፪) ። (ተረት - ሆድና ግንባር አይሸሸግም) ።
ሸሺ: የሸሸ፣ የሚሸሽ፣ ሯጭ፣ ፈርጣጭ፣ ኰብላይ፣ ፈሪ፣ ቡኩን።
ሸሻጊ: የሸሸገ፣ የሚሸሽግ፣ ሰዋሪ፣ ደባቂ።
ሸሽ: ዝኒ ከማሁ። "ባሕረ ሸሽ፣ ብረ ሸሽ፣ ሬሳ ሸሽ እንዲሉ።"
ሸሽቦ: ያፍንጫ ቀለበት” ። ጒይዲ ግን 'ሸሽቦና ሻሽል አንድ ናቸው' ይላል" ።
ሸሽታ: የሸሸች፣ የምትሸሽ።
ሸቀሸቀ: ሠቀሠቀ ጓጐጠ (መላልሶ ወጋ - "ሸከሸከን" አስተውል)።
ሸቀቀ (ሠቀቀ): ገደለ ጨረሰ ጠነገደ ።
ሸቀበ (ዐረ): ለከፈ፣ አታለለ፣ ሰለበ።
ሸቀበ: ለከፈ አታለለ ሰለበ።
ሸቀነ: ዐከከ አደፈ።
ሸቀናም፡ ሸቀን ያለበት (ባለሸቀን) ።
ሸቀን፡ የራስ እድፍ ደረቅ ወዝ (ፈረፈረ" ብለኸ "ፎረፎርን" እይ) ።
ሸቀጠ (ዐረ) ፡
ሸጠ ለወጠ (ከነጋዴ እየገዛ አተረፈ) ።
ሸቀጣም፡
ባለብዙ ሸቀጥ ።
ሸቀጣሸቀጥ፡
የሸቀጥ ሸቀጥ (ብዙ ዐይነት ሸቀጥ) ።
ሸቀጥ (ጦች) ፡
የንግድ ዕቃ (በየረድፉ በመደብር የተደረደረ) ።
ሸቀጥ፡
መብልና መጠጥ ምግብ በያይነቱ ።
ሸቃቢ፡
የሸቀበ፣ የሚሸቅብ (የሚያታልል) ።
ሸቃባ፡
አታላይ ግደ ቢስ ሰላቢ ።
ሸቃጭ፡
የሸቀጠ፣ የሚሸቅጥ (ሸያጭ ለዋጭ ዐጣሪ) ።
ሸቃጭነት፡
ሸቃጭ መኾን (ሸያጭነት) ።
ሸቃጮች፡
ለዋጮች አትራፊዎች (ኢዮ፡
ጫ፡ ፴፡ ፪ዜና፡ ፱፡ ፲፬) ።
ሸቈረረ (ሰቈራር) ፡
ዐፈረ ፈራ ሠጋ ።
ሸቈረር፣ ሸቍራራ (ስቍሩር) ፡
ጥይፍተኛ ዐፋር ዐንገተ ሰባራ ።
ሸቅማጥ፡ ሽንት ማጥ (የሽንት ምጥ) ።
ሸቅሻቂ፡
የሸቀሸቀ፣ የሚሸቀሽቅ (ጓጓጭ) ።
ሸበለቀ፡
ሽብልቅ አበጀ፣ እሾለ፣ አገባ፣ ቀረቀረ (በሽብልቅ ወጋ) ።
ሸበላ (ሰብል) ፡
ወጣት ልጅ (ሽንጥመልካም ሽንቅጥ ፎጠና ጠምጣማ) ።
ሸበላ፡
የሰሌን የኮባ የንሰት ሙሽራ ።
ሸበላዊ፣ ሸበልማ፣ ሸበላም” ። ዋቢ ሸበሌ" እንዲሉ”
። ዋቢ ንብ ሸበሌ ነብር"
(በተገናኝ ንብና ነብር ያለበት ወንዝ ማለት ነው) ።
ሸበሌ፡ ዝኒ ከማሁ ።
ሸበል፡
በጐዣም ክፍል ያለ አገር ።
ሸበል፡ ነብር (ሱማሌ) ።
ሸበሎች፡
ሽንቅጦች ፎጠኖች ።
ሸበረ) (ሰበረ) ፡
አሸበረ፣ አስደነገጠ፣ ኣወከ፣ ኣስፈራ (በጠበጠ ጸጥታን ሰላምን ኣጠፋ አስጠፋ) ።
ሸበረቀ (ጸብረቀ፣
ሣርኅ) ፡ ጠራ፣ በራ፣ ጸደለ፣ አማረ፣ ተዋበ (የፊት) ።
ሥሩ "በረቀ" ነው፡ "ሸ" በባዕድነት ወይም በ"ጸ" ለውጥነት ተጨምሮበታል ።
ሸበረከ (በረከ) ፡
ተንበረከከ ።
ሸበሸበ (ሠብሠበ) ፡
ሸነሸነ፣ እጠጋጋ፣ ኣቀራረበ (ልብስን በስፌት)” ። ሰበሰበን" ተመልከት ።
ሸበሽብ፡
ደብተራ ።
ሸበበ፡ የጋማ ከብትን አገጭ ጠለፈ፡
ወይም ላይኛውን ስርንና ታችኛውን መንገጭሊ ፥ ባንድነት አሰረ፡
መሳቢያን ኣበተ ።
ሥሩ በግእዝ ሠበብ፣
ሠበ ነው ።
ሸበተ (ሤብ) ፡
ነጣ ጥጥ መሰለ፡
አረጀ፡ ሸመገለ” ። አፍ ቂጡ ሸበተ" እንዲሉ
። እንስሳትና አራዊትም ይሸብታሉ
።
ሸበተ፡ ሻገተ ጉም መሰለ (ሸነበትእየሩ) ።
ሸበቶ፡
የሸበተ ጠጕሩ የነጣ ሽማግሌ ።
ሸበየ (ሠቢብ፣
ሠበ) ፡ ደረቀ፣ ሰለለ፣ ቀጠነ፣ ዐጪር ኾነ (ተንጠለጠለ) ።
ሸበየ፡ ሽቦ (ዎች) ፡
የብረት የብር የወርቅ የንሓስ የመዳብ ክር (ቀጪንና ወፍራም - ሕዝ፡
ጫ፡ ፲፮፣ ፳፮) ።
ሸበደደ፡
ጐነበሰ፣ ጐበደደ (በሸበድ ታጠፈ) ።
ሸበደድ፣ ሸብዳዳ፡
ጐበደድ፣ ጐብዳዳ (ጐንባሳ) ።
ሸበዲያም፡
ከበዠዱ ሸበዱ በልጦ የሚታይ ሰው ።
ሸበድ፡
ከበዠድ ግራና ቀኝ ያለ የጭንና የሆድ መጋጠሚያ ቈዳ ተላ ።
ሸባ (ሰሐበ) ፡
መሸቢያ አበጀ ለጠፈ በመሸቢያ አሰረ” ። ሸበበን" እይ ።
ሸባቢ፡
የሸበበ፣ የሚሸብብ (አፍ ኣሳሪ) ።
ሸባታ፡ ሻጋታ (እንጀራ ዳቦ ሥጋ) ።
ሸባች፡
የሚሸብት፣ የሚሻግት ።
ሸብ፡
መሸበብ፡ ሸበበ ።
ሸብ ሸብ አደረገ፡
መላልሶ ጠለፈ ።
ሸብ ተደረገ፡
በቀላል ታሰረ ።
ሸብ አደረገ፡
ሳያጠብቅ አሰረ ።
ሸብ፡
ከደንጊያ የሚገኝ ማዕድን (ለተቀደደ ቈርቈሮና ታኒካ ከርሳስ ራ ተመማሪ መጣብቅ) ።
ለታመመ ዐይንም በኵልነት መድኀኒት ይኾናል ።
ሸብላቂ፡
የሸበለቀ፣ የሚሸበልቅ (ወጊ) ።
ሸብላይ (ዮች) ፡
የሸበለለ፣ የሚሸበልል (ጠቅላይ) ።
ሸብረክ አለ፡
አሸድ አለ (እልኩ ረገበ ቍጣው በረያ) ።
ሸብራካ፡ አሻዳ ።
ሸብሻቢ (ዎች) ፡
የሸበሸበ፣ የሚሸበ
ሸተረ (ሰተረ) ፡
ሸለመ አስጌጠ ።
ሸተተ፡ ግማ ከረፋ ጠነባ ቈነሰ (ተነፈገ ቀረና ቍስሉ ሽንቱ ውዳቂው ጥንቡ - ጠረኑ የክፉ - ዘፀ፡
፯፡ ፳፩) ።
ሸተተ፡ ጥሩ ሽታ ሰጠ (ላፍንጫ ጣፈጠ - አበባው ሽቶው ጠጁ ወጡ -
"የበጎ ሸተን" እይ) ።
ሸተቴ (ትግ፡
ሸተት) ፡ ሸርታቴ ተዳፋት (የሸተት ሸተትማ" ማለት ነው) ።
ሸተት፡ መሽተት ።
ሸተት አለ፡
ሸተተ ።
ሸታች፡
የሸተተ፣ የሚሸት ።
ሸነ፣ ሸና (ሤነ) ፡
አጨረቀ ረጨ ፈነጠቀ አንፎከፎከ ለቀቀ አፈሰሰ አንዣረረ (ፊር አደረገ -
"ሸነና ሺ ነዋ" በአማርኛ ይገጥማሉ -
"፭፻ና ፭፻ ስንት ነው ሺነዋ) ።
ሸነሸነ (ሰነሰነ) ፡
ሸበሸበ ሠነጠቀ (በቀጫኑ) ።
ሸነቀለ፡ ጠቈረ ከሰል መሰለ ።
ሸነቀረ (ሰነቀረ) ፡
ሰበሰበ ዐጠፈ ቀነፈ ሸጐጠ (የሱሪን የቀሚስን ጝፍ ውሃና ጭቃ እድፍ እንዳይነካው) ።
ሸነቀጠ፡
ተኰሰተረ ተሰበሰበ ቀለጠፈ ።
ሸነቈረ (ሰቈረ) ፡
በሳ ነደለ ቀደደ ።
ሸነቈጠ፡ ሾጥ አደረገ ገረፈ (ሸመተሪ" መ) ።
ሸነቋቈረ፡
በሳሳ ነዳደለ ።
ሸነተረ (ሠነተረ) ፡
በጣ ቀደደ” ። ሠነተረ የካህናት ሸነተረ የሕዝብ አነጋገር ነው" ።
ሸነከ፡
ተነኰለ እጠፋ ።
ሸነከፈ (ሸከፈ) ፡
ዐጠፈ ኰረተመ
ሸነገለ (ሰነገለ) ፡
ጥቂት ምግብ መገበ (አባበለ አረሳሳ ደለለ አታለለ አሞኘ -
"የማ ይሰጠውን እሰጣለኹ" አለ - ሮሜ፡
፫፡ ፲፫ - "ሸግላን" እይ - የዚህ ዘር ነው) ።
ሸነገለኝ፡
የሰው ስም (ደለለኝ" ማለት ነው) ።
ሸነጓ (ሰንጐጐ) ፡
ሰውን ሰበሰበኣከበ (አበጀ አዘጋጀ ሸንጎን) ።
ሸነጠ (ሰነጠ፣
ነሸጠ) ፡ በለተ ነለየ (ሽንጥ አወጣ) ።
ሸነፈ) (ሰነፈ) አሸነፈ (ዘፍ፡
፯፡ ፲፱፣ ፳፬፡ ራእ፡ ፭፡ ፭) ፡
አሰነፈ (አቃተ አባተ ሠለጠነ ዐየለ በረታ ድል ነሣ ድል አደረገ ረታ መታ ሻረ አዋረደ አታከተ አደከመ -
"ትዳሩን አሸነፈ"
- ራሱን ቻለ -
"ዓለምን አሸነፈ"
- እውነትን ወደደ ዐመፅን ጠላ) ።
ሸነፈጠ) አሸነፈጠ፡
ዐጥፎ ዘቅዝቆ ታጠቀ (ልብስን ለሐዘን -
"ኣሸነፈጠች" ተብሎ በሴት አንቀጽ ይነገራል፡
ለወንድ ግን በርኖሱን ገልብጦ ለበሰ ይባላል - ዘሩ ሸፈጠ ነው "ነ" በስሯጽነት ገብቶበታል) ።
ሸናሽ (ሾች) ፡
የነገድ ስም (በዳሞት ባባይ ዳርና ዳር በሌላም ስፍራ የሚገኝ ሕዝብ) ።
ሸናጣ፡ ዥላላ ሾጣጣ መሬት ሠላጤ ኦራፊ መጣፊያ ።
ሸናጭ፡
የሸነጠ፣ የሚሻንጥ (ነጣይ) ።
ሸንሻኝ (ኞች) ፡
የሸነሸነ፣ የሚሸነሽን (ሸብሻቢ ሠንጣቂ) ።
ሸንቍጤ፣ ሸንቍጥ፡
የሰው ስም (ጠላታችንን ግረፍ" ማለት ነው) ።
ሸንቃሪ፡
የሸነቀረ፣ የሚሸነቅር (ሰብሳቢ ዐጣፊ ቀናፊ) ።
ሸንቃጣ፣ ሽንቅጥ (ጦች) ፡
ኰስታራ ኵስትር ቀልጣፋ (አለባበሱ ሰውነቱ ዘርፋፋ ዘርፋጣ ያይዶለ ጠምጣማ ሸበላ ሾጤ) ።
ሸንቋሪ፡
የሸነቈረ፣ የሚሸነቍር (በሺቀዳጅ) ።
ሸንቋራ፣ ሽንቍር፡
የተሸነቈረ (ብስቀዳዳ ነዳላ) ።
ሸንቋጭ (ጮች) ፡
የሸነቈጠ፣ የሚሸነቍጥ (ገራፊ) ።
ሸንበቆ (ሥን፡
በቍዖ) ፡ መቃ” ። ሸንበቆ ትግሪኛ መቃ ዐማርኛ ነው" ።
ሸንተረር (ሮች) ፡ ሰው
የሚወጣበትና የሚወርድበት ጠባብ መንገድ (ግራ ቀኙ ገደል ወይም ተዳፋት ዘቅዛቃ - የተራራና የኰረብታ ሲኾን "ተረተር"
ይባላል - የሸንተረር ምሳሌው በስተውጭ ያለ ያራት ማእዘን ግንብ መመለሻና ማጠፊያ ነው) ።
ሸንካፊ፡
የሸነክፈ፣ የሚሸነክፍ (ዐጣፊአሳሪ) ።
ሸንካፋ፣ ሽንክፍ፡
የተሸነከፈ (ታጥፎ የታሰረ ኵርትም) ።
ሸንኰራ፡
በቡልጋና በምንጃር አጠገብ ያለ አገር (ሸንኰር የሚበቅልበት) ።
ሸንኰራገዳ (ሸንኰር አገዳ) ፡
ሸንኰርነት (ሱካርነት ያለው የሱካር አገዳ - ጥንቅሽም ሸንኰራገዳ ሊባል ይገባል -
"ግጥም) ።
ሸንኰሬ፡ የኔ ሸንኰር (የታላቅ እት የታላቅ የእትዬ ተከታይ ያበባ ተቀዳሚ) ።
ሸንኰር፣ ሸንኰራ
(ሶከር) ፡ የተክል ስም
(ዐጥቁ ሽመልን ቀርክሓን መቃን ጐሽ መቃን የሚመስል ጣፋጭ ተክል - ፈረንጆች በመኪና እየፈጩ ሱካር ያደርጉታል) ።
ሸንኰር፡ ያልጋ እግር (በሸንኰር አምሳል የታነጸ የተቀረጸ) ።
ሸንኰር፡ ጌጠኛ መስቴ (ዐልፎ ዐልፎ መሸቢያ ያላት -
"ሻንኵራን" እይ) ።
ሸንኰፍ (ሰንኰፍ) ፡
ልንበጥ ቈለፈት ወሸላ ሽፍን ።
ሸንጋይ (ዮች) ፡
የሸነገለ፣ የሚሸነግል (ደላይ አታላይ - መዝ፡
፭፡ ፮፡ ምሳ፡ ፲፬፡ ፳፭፡ ሚል፡ ፩፡ ፲፬) ።
ሸንጎ (ች) ፡
አደባባይ ዐውድ የሕዝብ መሰብሰቢያ ዳኛ የሚያስችልበት ወግ ሥርዐት የሚሠራበት ዐዋጅ የሚነገርበት ።
በግእዝ "ዐውድ፣
ጽጕ" ይባላል (ዮሐ፡
፲፰፡ ፳፰፣ ፴፫) ። (ገበሬ ሸንጎ) ፡ ገበሬ ተሰብስቦ ዕድር የሚያድርበት ስፍራውል ።
ሸንጎ፡ ሕዝብ ጉባይ (ማር፡
፲፭፡ ፩) ።
ሸንጎበት፡
በታችኛ ከንፈር መካከልና ባዦጭ ላይ የበቀለ ሪዝ (ዘሌ፡
፲፫፡ ፳፱-፴)” ። የውበት ሸንጎ ማለት ነው፡
ጕራጌም ጢምን ሸንጎበት ይለዋል" ።
ሸንጎኛ፡ ሸንጎ ወዳድ (በሸንጎ የሚውል) ።
ሸንጥሮ፡ ሸለቆ (፪ሳሙ፡
፲፭፡ ፳፫፡ ፲፯፡ ፳፡ ፩ነገ፡ ፪፡ ፴፯)” ። ሸነተረ" ብለኸ "ሽንትርን" እይ ።
ሸንጥሮች፡
ሸለቆዎች (መዝ፡ ፻፬፡ ፲) ።
ሸኘ (ሰነየ፣ ትግ፡ አሰነየ) ፡ እንግዳን ጋበዘ (ከቤት ወደ ውጭ ወሰደ
እመንገድ አደረሰ ጐዳናን መራ አሳየ - አሰናበተ ሰውን ዛርን - "የሸኘ ትርጓሜ ፪ኛነትን ያሳያል" -
"በጥርስ ሸኘ" - በሣቅ በፈገግታ ሳያበላ ሳያጠጣ) ።
ሸኘ፡ ሸነገለ
ሸኚ (ዎች) (ትግ፡
መሰነይታ) ፡ የሸኘ፣ የሚሸኝ (ከመንገደኛ ተለይቶ የሚመለስ -
"ሸኚ እቤት አያገባም" እንዲሉ - ድረስ) ።
ሸኚታ፡
የሸኘች፣ የምትሸኝ ።
ሸከመ፣ ሰከመ) አሸከመ፡
ከምድር አንሥቶ በሰው ራስና ትከሻ ላይ አደረገ (ነአሳዘለ አሲያዘ አስነገተ - ፩ነገ፡
፲፡ ፪፡ ሉቃ፡ ፳፩፡ ፵፯) ።
ሸከማ፡
የሸክም ሥራ ።
ሸከረ (ሠክረ) ፡
አነሰ ተቀጠረ ተከተለ” ። ወሸከሬን" እይ (የዚህ ዘር ነው) ።
ሸከሸከ (ሠቀሠቀ) ፡
በቀላል ወቀጠ (የቈሎ ያሻሮ) ።
ሸከሸከ፡
ሸደሸደ ወጋጋ (በሳሳ አላላዘረዘረ ዘከዘከ አራራቀ - የልብስ የስፌት) ።
ሸከኛ፡ ክፋተኛ ተንኰለኛ ።
ሸከከ፣ ሠጠጠ) ሸከክ አደረገ፡
ሠጠጥ አደረገ ።
ሸከክ አለ፡
ሠጠጥ አለ ሐሩ ።
ሸከፈ፡ አካፋ ተፈተፈ አጠቀነ ።
ሸካሸከ፡
ወቃቀጠ ።
ሸክ አደረገ፡
ተንኰል ሠራ ።
ሸክ፡ ክፋት ።
ሸከሸከ ።
ሸክ፡ ክፋት ተንኰል ።
ሸክለኛ (ኞች) ፡
ሸክላ ሠሪ ባለሸክላ (ይብ ረጋ"
- ኢሳ፡ ፵፩፡ ፳፭) ።
ሸክላ (ሎች) ፡
የሸክላ ዕቃ (ከሸክላ የተሠራ) ።
ሸክላ፡ ቀይ ዐፈር (መዝ፡
፪፡ ፬) ።
ሸክላ በቅሎ፡
ቀይ በቅሎ ።
ሸክላ ቧጣጭ፡
የጠይብ ሚስት ።
ሸክም (ሞች) ፡ ዕንጨት ውሃ ዐፈር ደንጊያ ዕቃ መሣሪያ
እኸል ሣር (በሰው ላይ ኹኖ ታስሮ ወይም ሳይታሰር በኹለት እጅ የተያዘ) ።
ሸክም ኾነ፡
አስቸገረ ።
ሸክሻኪ፡
የሸከሸከ፣ የሚሸከሽክ (ወቃጭሸድሻጅ ዘርዛሪ ዘክዛኪ) ።
ሸክሻካ፣ ሽክሽክ፡
የተሸከሸከ (ውቅጥ ዘርዛራ ዝርዝር በለሴ) ።
ሸኰተ፡ መታ ጸፋ ውስጥ እጅን በውስጥ እጅ ።
ሸኰተ፡ መናኛ ጠላ ጠመቀ ።
ሸኰቴ፡ ከብቅልና ከእንኵሮ ካንድ ዕፍኝ የጌሾ
ቅጠል ዱቄት በቀር ጌሾ በብዛት የማይገባበት ጠላ (ትሕርምተኛ መነኵሴ የሚጠጣው) ።
ሸኽ፡
የቍርኣን ካህን፡ ሸኅ ።
ሸወረረ (ሾረ) ፡
ዞረ ጠመመ ወልጋዳ ኾነ ።
ሸወረር፣ ሸውራራ (ሮች) ፡
ዘዋራ ጠማማ ዐይን ።
ሸወርኒ፡ ያይን ቍራኛ (ዐይን እያየ ያላየ መምሰል) ።
አንቀጹ "ሾረ" ነው ።
ሸወተ፡ ሽኩቻ አደረገ ።
ሸወታ፡ ቍትቻ ሽኵቻ ።
ሸወከ፡ ሰበቀ አዋሸከ” ። ወሸከን" እይ ።
ሸወደ፡ አሳተ ።
ሸዋዳ፡ አሳች ።
ሸውረር አለ፡
ሸወረረ ።
ሸውሸዌ፡ የዛፍ ስም (ነፋስ ሲነካው ሽው ሽው የሚል ዕንወት) ።
ሸውሻዋ፡ ቀላል ወሬኛ ሰው (አባ ንፋው) ።
ሸውከኛ (ኞች) ፡
ሰብቀኛ አዋሻኪ ።
ሸውከኛነት፡
ሸውከኛ መኾን (አሳባቂነት) ።
ሸውክ (ሦክ) ፡
ሰብቅ ሰውን እንደ እሾኸ የሚጐዳ ።
ሸውዳራ፡ ከሰው የማይገጥም ።
ሸየተ (ሸወተ) ፡
ዕጣ ጣለ ።
ሸየጠ፣ ሼጠ (ሤጠ) ፡
አቀና፣ ለወጠ (ለገዢ ሰጠ) ።
ሸያጭ (ሠያጢ) ፡
የሼጠ፣ የሚሼጥ (ለዋጭ ዐጣሪ ባለመደብር) ።
ሸያጭነት፡
ሸያጭ መኾን” ። ሽጦሽ ልወጣ" ።
ሸያጮች፡
ለዋጮች ዐጣሮች ።
መጽሐፍ ግን "ሻጮች" ይላል ስሕተት ነው (ዘካ፡
፲፩፡ ፭)” ። ሻጠን" ተመልከት ።
ሸዬ፣ ሾዬ (ኮሞል) ፡ የዛፍ ስም (ዐጥንታም ፍሬው ከታች ሰፋ
ከላይ ሾጠጥ የሚል ምግብነት ያለው)” ። እሼን" እይ (ከዚህ ጋራ አንድ ነው) ።
ሸደሆ፡
የቀበሌ ስም (በላስታ ክፍል ያለ ገጠር) ።
ሸደሸድ፣ ሸድሻዳ፣ ሽድሽድ፡
የተሸደሸደ (ውስውስ ሽክሽክ ሽል) ።
ሸድሻጅ፡
የሸደሸደ፣ የሚሽደሽድ (ወስዋሽ ሸክሻኪ) ።
ሸገሸገ) (ሸሸገ) ፡
አሸገሸገ (አፈገ ፈገ - ለመራቅ ለመቅረብ)” ። ሰገሰገንና ሸቀሸቀን" ተመልከት ።
ሸገነ (ሰገነ) ፡
አማረ፣ ተዋበ፣ ቈነዠ ።
ሸገነ፡ ሽግ፣
ሽጕችቦ፡ ሸገገ ።
ሸገና፣ ሸገን፡
የሰው ስም (መልከመልካም) ።
ሸገገ (ጸጐጐ) ፡
ሞቀ ለብ አለ ።
ሸገገን ተመልከት (ለቤ፣
ለሴ ጢብኛ መላብ መሞቅ መውዛት መፍሰስ አላሰ) (አልሀበ) ።
ሸጕራ፡ ሻግያ (የሚሼጥ ባሪያ ዐመለ ሻካራ) ።
ሸጊቱ፡ ውቢቱ ቈንዦዪቱ” ። ሸጋ ሸጌ ሸጊቱ" በኦሮምኛም ይነገራል
።
ሸጋ (ጎች) ፡
የሸገነ ያማረ የተዋበ (ውብ ቈንዦ) ።
ሸጋ፡ ውብ ።
ሸጋኝ፡
የሚሸግን (የሚያምር) ።
ሸጋዝ፡ የዛፍ ስም ።
ሸጌ፣ ሸጋዊ፡
የሸጋ ወገን ዐይነት (የኔ ሸጋ) ።
ሸግ አለ፡
ሞቅ አለ ተንገረገበ ።
ሸግ አለ፡
ተንገረገበ (ሸገገ) ።
ሸግ አደረገ፡
አሞቀ አንገረገበ ።
ሸግላ፡ ድለላ (ላይሰጥ እሰጣለኹ ላያደርግ አደርጋለኹ" የማለት ቃል)” ። ወላወለ ብለኸ ወላን" ተመልከት ።
ሸግታ፡ ሸግ ማለት ።
ሸጐረ (ሠጊር፣
ሠገረ) ፡ ወረወረ፣ ቀረቀረ (ዘጋ ደነቀረ) ።
ሸጐበ (ሰገበ) ፡
ፈራ ዥራቱን ዐጠፈ ቀለሰ እጕያው አገባ (ሸጐ ውሻው) ።
ሸጐጠ (ሰገጠ) ፡
አገባ ወተፈ (በቅርብ ደበቀ ሸሸገ) ።
ሸጓሪ፡
የሸጐረ፣ የሚሸጕር (ቀርቃሪ) ።
ሸጓቢ፡
የሸጐበ፣ የሚሸጕብ (ፈሪ) ።
ሸጓባ፣ ሽጕብ፡
የተሸጐበ የታጠፈ ቅልስ ።
ሸጓጐጠ፡
ወታተፈ ደባበቀ ።
ሸጓጭ፡
የሸጐጠ፣ የሚሸጕጥ (ወታፊ) ።
ሸጠ፡ -ለወጠ (ሸየጠ) ።
ሸጠጠ፡ መጠጠ ።
ሸጠጥ፡ መጠጥ ።
ሸጠጥ አደረገ፡
ሠጠጥ አደረገ (በፍጥነት ቀደደ ሸረከተ -
"ሸከከኝ" አስተውል) ።
ሸጢን፡
የማይነቅዝ ዕንጨት (የሸምሸር ዐይነት ሣጥን የሚኾን) ።
ሸጥ አለ፡
ተለወጠ (ሸየጠ) ።
ሸጥ፡
ፈረፈር ፈፋ (ጐዣም) ።
ሸፈሬ፡ የቈላ ዛፍ (ሞፈር ቀንበር የሚኾን ዕንጨት -
"ቡክቡካን" አስተውል) ።
ሸፈሸፈ (ሸፈፈ) ፡
በመደዳው ዐጨደ (ቈረጠ አሳጠረ ሸራረፈ) ።
ሸፈተ (ሸፈጠ) ፡
ከሕዝብ ተለየ ከዳ ዐመጠ ወነበደ (እዱር እበረሓ ገባ - ለሕግ ለመንግሥት አልታዘዝ አለ - ፬ነገ፡
፲፪፡ ፲፱) ። ሸፋች (ሸፋጭ) ፡
የሚሸፍት፣ የሚከዳዐማቦ ።
ሸፈነ (ጸፈነ፣
ሰፈነ) ፡ አለበሰ ጋረደ (እንዳይታይ አደረገ ከለለ ጨፈነ ከደነ) ።
ሸፈጠ (ሰፈጠ) ፡
ካደ ከዳ ዐበለ አሞኘ አቄለ ኣታለለ ሸነገለ ።
ሸፈጣ፣ ሽፈጣ፣ ሸፍጥ (ስፍጠት) ፡
አሉታ ክዳት (የኾነውን የተደረገውን አልኾነም የለም አይዶለም ማለት) ።
ሸፈጥ (ሰፊጥ) ፡
ነሸጥ ።
ሸፈጥ አደረገ፡
ነሸጠ ።
ሸፈፈ (ሰፈፈ) ፡
ሰፋ ሽፋፍ አበጀ (ሸለመ አስጌጠ) ።
ሸፈፈ፡
ሰበሰበ አከበ አገባ ከተተ ።
ሸፈፈ፡ እወጣ እበቀለ ።
ሸፈፈ፡ ወደ ጐን ረገጠ (ሸነደለን" እይ) ።
ሸፈፍ ሸፈፍ አለ፡
ዐሸድ ዐሸድተንሻፈፈ (ሸፋፋ ኾነ ወነከሰ ነፋስ እንደ ነካው አንበጣ ባንድ ወገን ረገጠ ኼደ) ።
ሸፈፍ፡ ባንድ እግር መርገጥ ።
ሸፈፍ አለ፡
ዐሸድ ዐንከስ አለ ።
ሸፋሽፍት (ቶች) ፡
የቅንድብ ጠጕር ምርቅ የሚመስል ያይን ጨፈቃ የማያድግ ።
ዳግመኛም ሸፋሽፍት በመብቀያው ስም ቅንድብ ይባላል” ። ቅንድብን" ተመልከት (ምሳ፡
፴፡ ፲፫፡ ኤር፡ ፱፡ ፲፰) ።
ሸፋኝ (ኞች) ፡
የሸፈነ፣ የሚሸፍን (አልባሽ ከላይ ፊፋኝ ከዳኝ) ።
ሸፋጭ (ጮች) (ሰፋጢ) ፡
የሸፈጠ፣ የሚሸፍጥ (ሀባይ ታላይ ሸንጋይ መልቲ - ጐንደሮች ጠበቃን ሸፋጭ ይሉታል - ግብ፡
ሐዋ፡ ፳፬፡ ፩፣ ፲፱) ።
ሸፋጭነት፡
ሸፋጭ መኾን (ዐባይነት አታላይነት) ።
ሸፋፈነ፡
አለባበሰ ከዳደነ ።
ሸፋፋ፡ ዐሻዳ እግረ ወልጋዳ (ባካኼድ ባረማመድ) ።
ሸፍሻፊ፡
የሸፈሸፈ፣ የሚሸፈሽፍ (ሀጅ ቈራጭ) ።
ሸፍሻፋ፡
የተሸፈሸፈ ።
ሸፍት (ሸፈሸፈ) ፡
የበሬ ሽንት መሸኛ (የቀዳዳው ዙሪያ) ።
ሸፍጠኛ (ኞች) ፡
ባለሸፍጥ እሉተኛከዳተኛ (ፀባይ ቀጣፊ) ።
ሸፍጠኛነት፡
ሸፍጠኛ መኾን ።
ሸፎ፡
ዐሻዳ፡ ሸፈፈ ።
ሸፎ፡ ዝኒ ከማሁ (ዐሾ) ።
ሸፎ ገመዳ፡
እግሩን እያጋመደ የሚኼድ ሰው ።
ሹለት፡ የጫፍ ቅጥነት (እንደ ጦር እንደ ወስፌ መኾን) ።
ሹላፍ (ሹል አፍ) ፡
አፈ ሹል ነገረኛ ሰው (አሳባቂ) ።
ሹል (ስሑል) ፡
የሾለ የቀጠነ ሾጣጣ ።
ሹል፡
የሾለ፡ ሾለ ።
ሹልኪት፡
የሾለከች ።
ሹልክ አለ፡
ሾለከ ። (ተረት) ፡ "ዋስ ጠርቼ ሹልክ ብዬ መጣኹ" ።
ሹልክልኪት፡
ዐጨር ባሕረ ሐሳብ ከ፳ው ፩ እያለ የሚቈጥር ።
ሹልክልኪት፡
የተሹለከለከች ።
ሹልክልክ፡
የተሹለከለከ፣ የሚሹለከለክ (እባብ ሸላ ዋልጋ ማንኛውም አውሬ ነፍሰ ገዳይ ሰው) ።
ሹልክታ፡ ሹልክ ማለት ።
ሹልዳ (ዶች) ፡ ታናሽ በሚባለው የሥጋ ብልት ውስጥ
የሚገኝ ቀይ ሥጋ ። በግእዝ "ጸክ" ይባላል እሱንም የእስራኤልና የአማራ ዘር አይበላውም ። ዳግመኛም ስለ
መንቀጥቀጡ "ሥጋ ፈሪ" ይሉታል ።
ሹመት (ሢመት) ፡
ክብር ማዕርግ መብት የበላይነት ።
መንፈሳውያን ግን ሹመትን ሺሕ ሞት ይሉታል ።
ሹመት፡ የሴት ደም አለመውረድ ።
ሹመት ያዳብር፡ ይጨምር ያሳድግ (ለተሾመ ይነገራል) ።
ሹመን፡
ስምንተኛ የቀባርዋ ምት ።
ሹማምት፡ ሹሞች (፪ዜና፡
፱፡ ፲፬፡ ዕዝ፡ ፯፡ ፳፭፡ ኢሳ፡ ፷፡ ፲፯)” ። ሹማምቶች" ቢል የብዙ ብዙ ነው ።
ሹም (ሥዩም) ፡
የተሾመ ማዕርግ ያገኘ አገረ ገዥ አዛዥ ባለሥልጣን ባለመብት ።
ሹም ሽር (ሥዩም ስዑር) ፡
የተሻረ ሹም ።
ዳግመኛም
ሹም ሽር፡
ሹም የተሾመው ሽር የተሻረው ማለት ነው (ሹመትን ሽረትን ያሳያል) ።
ሹም ተንቤን (ሥዩመ ተንቤን) ፡
የተንቤን ሹም (የተንቤን ገዥ ባላባት) ።
ሹምነት፡ ሹም መኾን ።
ሹሞች (ሥዩማን) ፡
የተሾሙ የተሸለሙ አለቆች አዛዦች መኳንንት ።
ሹራብ (ቦች) ፡
ከጥጥ ከጠጕር ገመድ የተታታ ጥብቆ (ቀሚስ መደረቢያ) ።
ሹራብ፡ እጅን እግርን ማግቢያ መክተቻ (የእጅ ሹራብ የእግር ሹራብ" እንዲሉ) ።
ሹር፡ ዝኒ ከማሁ (በክርስቲያን ዘንድ ያለፈ የቀረ የአይሁድ ሰንበት -
"ቅዳሜ ሹር" እንዲሉ) ።
ሹር፡
የተሻረ፡ ሻረ ።
ሹርባ፡ ሠራ ጣሰ ከፈለ ወሸመ ቈነነ ጐነጐነ ቈነጣጠረ ቈነደለ ።
ሹርባ፣ ሽሩባ፡
የሴት ራስ ጠጕር የተጐነጐነ ።
ሹርቤ፡
ባለመሥመር (ብርሌ የሹርባ ዐይነት) ።
ሹሽ (ዐረ፡ ሱስ፡ ትል፡ ወላሞ፡ ሾሻ፡ እባብ) ፡ ከሕፃናት ሆድ የሚወጣ ነጭ
ትል (ፈጽሞ ያነሰ የቀጠነ - ዐረብ "ሱስ" የሚለው ባማርኛ "መስክ" ይባላል) ።
ሹካ (ሦክ) ፡ ባለጣት ማንካ (ጣቶቹ እሾኸ የሚመስሉ
ጥብስ ወይም ቅቅል ሥጋ መውጊያ ወደ አፍ ማስጠጊያ የምግብ መሣሪያ - ፩ሳሙ፡ ፪፡ ፲፫-፲፬) ። ሲበዛ "ሹካዎች፣
ሹኮች" ያሠኛል (፪ዜና፡ ፬፡ ፲፮) ።
ሹካና ማንካ፡
ኹለቱ ባንድነት ።
ሹክ ሹክ አለ (አልኈሰሰ) ፡
አሾከሾከ ።
ሹክ አለ (ሸከመ) ፡
ሹክ አለ (ሾከ) ።
ሹክ አለ፡
ዦሮን ተጠግቶ ተናገረ ።
ሹክሹክታ፡
ብዙ ሸክታ ማሾክሾክ (፪ሳሙ፡
፲፪፡ ፲፱) ።
ሹክታ (ለኈሳስ) ፡
ከተናጋሪውና ከሰሚው በቀር ሌላ ሰው የማያውቀው ጕዳይ ።
ሹክክ፡
መሾከክ ።
ሹክክ አለ፡
ሾከከ (ቅልል አለ ተንሿከከ ሾካካ ኾነ ጥላ ቀለለው) ።
ሹጣም (ሞች) ፡
ሹጥ ያለበት የበዛበት (ባለሹጥ)” ። ኮሶን" እይ ።
ሹጥ (ሰሐጠ፣
ሶጠ) ፡ የሆድ ውስጥ ትል (ትርጓሜው "የተሻጠ የተጨመረ ጭምር" ማለት ነው) ።
ሲበዛ "ሸጦች" ይላል ።
ሺ (ሺሕ) ፡
የቍጥር ስም (፲፪፥ ዐሥር ጊዜ መቶ፡
ወይም መቶ ጊዜ ዐሥር) ።
ሺ በንባብ ውስጥ እንጂ ከአኃዝ ጋራ እየተዛነቀ በገጽና በምዕራፍ አይጻፍም ።
ሺ መልስ፡
ታናሽ ዋንጫ መጠጥ ማዳረሻ ።
ሺ መልስ፡
የሰው ስም (የጐበዝ ጐበዝ) ።
ሺ በሺ፡
የሰው ስም (የሺ መሣ የሺ ለውጥ ማለት ነው) ።
ሺ እግር፡
ክረምት አፈራሽ ትል ባለብዙ እግር ።
ከፊት ሲነኩት ሳይዞር ወደ ኋላ ይኼዳል ።
ሺ ገዳይ፡
ሺ የገደለ ሐርበኛ እንደ ሳኦል ያለ ።
ሺ ጊዜ ሺ፡
መቶ እልፍ (አንድ ሚሊዮን) ።
ሺ ፈራ፡
የሰው ስም ።
ሺ ፈራው፡ ዝኒ ከማሁ ። ሺ የስም ዘርፍ እየኾነ
ሲነገር "የሺ የሺእመቤት የሻረግ" ይላል” ። ሻውልን ሻለቃን ሻምበልን ሻቃን" በየስፍራው አስተውል ።
ሺ ፈጅ፡
የመስቀል ስም (በታች ወግዳ ማጢ በሚባል አገር በጊዮርጊስ ቤተ ክሲያን የሚገኝ መማማያ መስቀል) ።
እሱንም ቄሶቹ ከሰማይ ወርዶ የነካውን ሺ ማይምን ስለ ገደለ "ሺ ፈጅ" ተባለ ይላሉ ።
ሺሓምጥ፡ የሰው ስም (አንተ አንድ ስትኾን - ሺሕ ዐምጥ"
- ሸሑን ሰው ክዳ በድል ማለት ነው) ።
ሺሕ (ሖች) ፡
ዐሥር መቶ” ። ሺን" ተመልከት ።
ሺራራ፡ የቈዳ ግልድም (ትግ) ።
ሺሾ፡ የቈላ ጕንዳን ሲኼድ የሚንሻሻ (ሽንጣም ችስችሳ) ።
ሺን (ኖች) ፡ የነገድና ያገር ስም (ሴማዊ ነገድ የምሥራቅ
መዠመሪያ - ዘፍ፡ ፲፡ ፪ - የህንድና የመስኮብ ጎረቤት - በግእዝ "ሲን" ይባላል - "ተረት - ሺን
ዐሸን" - "ስኒን ሻይን" እይ) ።
ሺዋ (ሺሕ ሽኋ) ፡ የሴት ስም (የግሼ ባላባት ያገባት
የወሎ ባላባት ሴት ልጅ) ። ብዙ ልጆች ስለ ወለደች አባቷ "ልጄ ሺኋ አላት" በዚህ ምክንያት የልጆቿ አገር
"ሺዋ" ተባለ ይላሉ (ኪ፡ ወ፡ ክ) ።
ሺዋ ረገድ፡
ዝኒ ከማሁ ።
ሺዋ ረጋ፡
የወንድና የሴት ስም ።
ሺዋ ርካብሽ፡
የሴት ስም ።
ሺዋ ርካብኸ፡
የወንድ ስም ።
ሺዋ ታጠቅ፡
የሰው ስም ።
ሺዋ፡
ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ግዛቶች አንዱ ።
ሺዋ የሚባለው ከግሼ ከመንዝ ዠምሮ ዋየት በመለስ እስከ ዐዋሽ ነው ይባላል ።
ሺዋ ጊሚራ፡
በከፋ አጠገብ ቀድሞ የሺዋ ሰው የሰፈረበት አገር ።
ሺዋ ጽዮን (የሺዋ ጽዮን)፡ በጐዣም ክፍል ያለ ገጠር የማሪያም አጥቢያ ።
ሺዋን ላንቺ፡
የሴት ስም ።
ሺዋን ከተርሽ፡
የሴት ስም ።
ሺዋን ዳኝ፡
የወንድ ስም ።
ሺዋን ግዛው፡
የወንድ ስም ።
ሺዋን ግዢው፡
የሴት ስም ።
ሺዌ (ሺዬ) ፡
የሺዋ ሰው (የሺዋ ተወላጅ) ።
ሲበዛ "ሺዎች" ያሠኛል ።
ሺዬ፡ የሺዋ ሰው፡
ሺዋ ።
ሻ (ስሒው፣
ተሥዕዮ) ፡ መበተን፣ መጕደል ።
ሻ (ዐረ ሻአ) ፡
ኀላፊ አንቀጽ (ፈለገ ፈቀደ - ፩ነገ፡
፲፱፡ ፲) ።
ሻ ብትን፡
መለያየት፣ መጥፋት ።
ሻ ብትን፡ የሕፃናት ጨዋታ (እጆቻቸውን በማቈናጠጥ
አነባብረው የቍንጢጥ የቀንጢጥ ይሉና እጃቸውን ሲለዩ "ሻ ብትን" ይላሉ) ።
ሻ አለ (ተሥዕየ - ዐረ ሸዐ) ፡
ተበተነ፣ ጐደለ (ምግብ ከሆድ ውስጥ) ።
ሻ አለው (ስሕወ ልቡ) ፡
ልቡ ከዳው ።
ሻ አደረገ (ሠዐየ) ፡
በተነ” ። ፀረቄ ምግብን ሻ ያደርጋል" ።
ሻ፡
የቅርብ ወንድ ትእዛዝ አንቀጽ (ፈልግ"
- ተረት) ፡ "ምናልባት ቢሰበር ዐናት ቅቤ ሻ ለመተኰሻ" ።
ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች "ሻ ሹ ሺ" በማለት ፈንታ "እሻ እሹ እሺ" እያሉ ይጽፋሉ፡
ስሕተት ነው ።
ሻሖ፡
በጥልጣል አጠገብ አሳሑርታ ውስጥ የሚገኝ ነገድ ።
ሻለ (ሣህለ፣
ሥዕረ) ፡ ሻረ ዳነ በጥቂቱ ።
ሻለ (ተሥህለ) ፡
በሽታው ቀለለ ቍስል ጠገገ ዳነ ።
ሻለቃ (ቆች) ፡
የሺ አለቃ ጦር ጠቅላይ አገረ ገዢ (ከባላምባራስ እስከ ራስ ያለ የሺ ጭፍራ አዛዥ ምክትሉ ሻምበል ነው) ።
ከሺ በላይም ሰራዊት በኖረው ሻለቃ ይባላል (ዘፍ፡
፬፡ ዘፀ፡ ፲፰፡ ፳፩)” ። የሻላን" ተመልከት ።
ሻል (ሥሂል) ፡
ጥቂት ጤና ድኅነት መሻል ።
ሻል፡ ራስ መሸፈኛ ቀጸላ ሻሽ ።
ሻል ብሎታል፡
ድኗል (ከሞት አፋርሷል) ።
ሻል አለው፡
ጤና አገኘ ።
ሻመደ፡
ተቈረጠመ ታኘከ ተበላ ።
ሻሚት፡ ገፈራ ።
ሻማ (ሠምዕ) ፡
የማር ሰፈፍ (ማር ጠጅ ሲጣል ሲነጠር ይንሳፈፋል) ።
በግእዝ "ምዕ" በአረብኛ "ሸመዕ" በአማርኛ "ሠም ሻማ" ይባላል ።
ይኸውም ግግሩ ልጥልጡ እየቀለጠ ጧፍ ፋና የሚኾን ነው ።
ሻማ ግን በፍንታ ይነገራል
።
ሻማ (ትግ - ነጠቀ ቀማ ጥል አልባ) ።
ሻማ፡ ዝኒ ከማሁ ነጠቃ” ። ግዳይ ሻማ ነው"
(ሻማ" እንዲል ዝኆን ገዳይ) ።
ሻሜ፡ ታናሽ ገንዘብ (ቤሳ ክንሓስ የተሠራ) ።
በግእዝ "ጸሪቅ" ይባላል ።
ሻሜ፡ ነጭ ሞላላ የዛጐል ዶቃ (የጮሌ ማፈኛ የሻም ሻማዊ ማለት ይመስላል -
"ሻምን" አስተውል) ።
ሻሜት፡
አጥሚት ።
ሻሜት፡
የበሶና የማር ጭብጦ፡ (ጥማ) ሻማ ።
ሻሜት፡
የበሾና የማር ጭብጦ (እየተሻሙ የሚበሉት) ።
ሻም፡ ያገር ስም (ሶርያ - ግብ፡
ሐዋ፡ ፲፭፡ ፳፫) ።
ሻምበል (የሺ ዐምበል) ፡
የሺ አጋፋሪ በላይ (የሻለቃ ምክትል የሺ ነፍጠኛ አዛዥ -
"ሻለቃን" እይ) ።
ሻምበልነት፡
የሻምበል ሹመት (ሻምበል መኾን) ።
ሻምበሎች፡
የሸ ጭፍራ አለቆች ።
ሻሞች፡ የሻም ሰዎች (የሻም ተወላጆች ዐረቦች የደማስቆ ሕዝቦች) ።
ሻረ (ሰዐረ) ፡
አዋረደ ወሰደ (ሹመትን ገፈፈ ክብርን - ፪ዜና፡
፴፯፡ ፫) ።
ሻረ (ሥዕረ) ፡
ሻለ ዳነ ተፈወሰ (እሸለተ ሰውነቱ ተመለሰ) ።
ሻረ፡
አሳለፈ አስቀረ ማንኛውንም ነገር (ኢሳ፡
፳፭፡ ፰፡ ማቴ፡ ፭፡ ፲፱) ።
ሻረ፡ አጠፋ ደመሰሰ (አደረቀ ባሕርን) ።
ሻረ፡
አፈረሰ ካብን ።
ሻረ፡ ፈታ አሸነፈ (ድል ነሣ ጦርን) ።
ሻሪ (ሠዓሪ) ፡
የሚሽር፣ የሚድን ።
ሻሪ (ዎች) (ሰዓሪ) ፡
የሻረ፣ የሚሽር (በዓል ሻሪ) ፡
በዓልን የሚደፍር (በበዓል ቀን የሚሠራ) ።
ሻሸረ፡ ዕርቁ ፈረሰ ።
ሻሸረ፡ ፍራ ኣልባ ኾነ እኸሉ ።
ሻሸጎ፡
የቀድሞ ዘመን ነፍጥ ።
ሻሻቴ (ወሎ) ፡
ታናሽ መስፈሪያ ።
ሻሻቴ (ዎች) ፡
ብዙ ፊት ።
ሻሻቴ፡ ጩት (ሻሻ) ሿሿቴ ፈሳሽ (ሿሿ) ሸተ (ሠወየ) ፡
በሰለ ጐመራ ደረሰ ። (ተረት - ብቻ የበሉት ይሸታል ከሰው የበሉት ይሸታል"
- ይገማል እሸት ይኾናል) ።
ሻሽ (ሠሥዐ) ፡
ነጭ በፍታ ሥሥ ራስ ማሰሪያ መሸፈኛ (ዘፀ፡
፳፭፡ ፬) ። (ተረት - የፊት ወዳጅኸኝ በምን ቀበርከው - በሻሽ የኋለኛው እንዳይሸሽ) ።
ሻሽል፡ የዦሮ ቀለበት ።
ሻሽዬ፡ ሻሽ አበባ (የንቍጣጣሽለት ልጃገረዶች የሚዘፍኑት ዘፈን አዝማች) ።
ሻሾ፡ የበሬ ስም (ነጭ በራ ወይም ዐምባላይ ፈረስ) ።
ሻቃ (ሺ) ፡
ሻለቃ (የሥጋ ቤት ሹም) ።
ሻበ (ሰሐበ፣
ሠቢብ፣ ሠበ) ፡ ሽቦ ሠራ፣
መዘመዘ፣ አቀጠነ፣ ጠመዘዘ፣ ጠመጠመ ።
ሻተረ) አሻተረ፡
አጫረ አሾተለኣቈተመ (ተረን" ተመልከት) ።
ሻተተ) አንሻተተ፡
አንሸራተተ እግርን ሚዛንን ።
ሻታ (ስሕተት) ፡
ተቅማጥ አጣዳፊ ቅዘን” ። የሽታ ምስጢር አለበት" ።
ሻታ፡
ዋግንቦ (ባፉ ውስጥ ብዙ ሹል ዕንጨት ያለበት ዓሣ መያዣ) ።
ሻታ፡ ያሣ ቀፎ፡
ሻታ፡ ያሣ ቀፎ ውስጤ ብስ ግንድ ።
ሻንቅላ (ሎች) ፡ የነገድ ስም (ባፍሪታ ውስጥ የሚኖር
የካም የኵሽ ዘር ጥቍር ሕዝብ ገላው በፀሓይ ሙቀት ብዛት የጠቈረ - ባሜሪካም ላገር ማቅኒያ ካፍሪቃየኼዱ ሻንቅሎች አሉ) ።
ሻንቆ፡
የንጉሥ ሚካኤል ፈረስ ስምአባን እይ ።
ሻንቆ፡ ጌጥ አልባ ልሙጥ ጋሻ ።
ሻንቆ፡
ጥቍረትና ውፍረት ያለው ንብ ።
ሻንቆ፡ ጥቍር ንብ ።
ሻንበል፡
የሻለቃ ምክትልምበል ።
ሻንኵራ፡
ባላንድ ዦሮ ዳብሬ ማድጋ ።
ሻንጣ (ዐረ፡
ሻምጣ) ፡ ከቈዳ የተበጀ ኰረጀ ማፉዳ (ከሐረግ ከካርቶን ከቈርቈሮ የተሠራ ቀላል የመንገድ ጥን) ።
ሻኛ (ስናም) ፡
በበሬ በጐሽ በግመል ዠርባ ላይ ያለ የሥጋ ዲብ ክብ እንክብል (ጥብ - ጕብል - ዘዳ፡
፲፰፡ ፫) ።
ሻኛማ፡ ዝኒ ከማሁ ።
ሻኛም (ዘስናም) ፡
ሻኛው ትልቅ የኾነ ኣውራ ኰርማ በሬ ።
ሻኝ፡
የሸነ፣ የሚሽን ።
ሻከረ፡
ተቅረፈረፈ (ከመለዘብ ራቀ ልስላሴ ዐጣ ሞዠቀ -
"ሆዱ ሻከረ"
- ነገር ገባው) ።
ሻኵራ፣ ሻኹራ፡
የጥና የጕልላት የመሶብ የመረሻት አጫዋች (ከንሓስ ከመዳብ የተበጀ የተዘጋጀ) ።
እጅና ነፋስ ሲነካው ይንሿሿል ድምፅ ይሰጣል
።
ሻኵራ፡ የልጅ ቍንጮና የበግ ላት ጠጕር (በቅቤና በጥጥ ፍሬ ባዛባ የተድበለበለ) ።
ሻካራ፣ ሸካራ፡ የሻከረ፣ የሚሻክር (እርጃኖ ዝኆን ገላ
የበሬ ምላስ ሞረድ እንቧይ ሰበከት ክፉ ነገር)” ። ሻካራ የሕዝብ ሸካራ የካህናት" ነው ።ሻክላ በላው፡
ቀረፈው አበላሸው ።
ሻክላ፡
የንስራና የጋን በሽታ (ከቡሖ ከጠላ የሚመጣ የውስጥ ቅርፍርፍነት - ፍርክ ርክነት) ።
ሻኰረ፡ ክብ እንክብል ኾነ ።
ሻኽ፣ ሻሽ፡
ፈለግ'ኸ፣ ፈለግሽ ።
ሻው፣ ሻኽ፣ ሻሽ፡
ፈለገው፣ ፈለገኸ፣ ፈለገሽ ። ዐቢይ አገባብ ቀድሞት በስምነት ሲነገር "እንደሻው እንደሻኸ እንደሻሽ" ይላል” ። እንደን" እይ ።
ሻውል (ሺ አውል) ፡ የሰው ስም (የሺ ሰው አዛዥ የሺ ጌታ የሺእመቤት
አንጻር ሺውን ሰው በፈቃድኸ ኣውል ማለት ነው)” ። ሻውል ሲሞት ሺ ይሙት" እንዲሉ ።
ሻይ (ቻይ) ፡
የቅጠል ስም (ዓለም ኹሉ ከሱካር ጋራ እያፈላ የሚጠጣው የሺን አገር ተክል - ሺናዊ ቻይናዊ ማለት ነው) ።
ሻይ፡ የሚሻ (ሻ ሻየ) ።
ሻይ፡ የሻ፣
የሚሻ፣ የሻየ፣ የሚሻይ (ፈላጊ -
"ሌባላይ" እንዲሉ) ።
ሻድሬ፡
የሻድር ዐይነት ዋጋው ርካሽ የኾነ መናኛ ።
ሻድር፡
የእስላም ልብስ ።
ሻገረ) ተሻገረ፡
በወንዝ በዥረት በዠማ በባሕር በጐድጓዳ ስፍራ ላይ ዐለፈ (ወዲያ ማዶ ኼደ - ዘፍ፡
፴፪፡ ፳፪፡ ዮሐ፡ ፭፡ ፳፬) ። ሥሩ "ሠገረ" ነው ። (ተረት) ፡ "ይኽን ውሃ ማ ይሻገረዋል ቢሉ፡
ተዝካር ያየ ተማሪ" ።
ሻገተ፡
ታመመ፣ በሰበሰ፣ ተለወጠ፣ ተበላሸ (ጥጥ ለበሰ - ኢያ፡
፱፡ ፲፪) ።
ሻጕራ፡
ቅርቃር ።
ሻጋታ፡
የሻገተ የተበላሸ እንጀራ ዳቦ መጠጥ ።
ሻጋች፡
የሚሻግት ።
ሻግሌ፡ የግምጃ ስም ጥንታዊ ግምጃ ።
ሻግያ፡
በትግሬ በረሓ ያለ ባለመከራ የሻንቅላ ዘር (ጥቍር ጠቋራ) ።
ሻጠ (ሰሐጠ) ፡
ተከለ፣ ሰካ፣ ሳገ፣ አቆመ ።
ሻጣ፡ ትንሽ ሥንጥር ጕድፍ (የገብስ ገለባ በሊጥ በንጀራ ውስጥ የሚገኝ - ያልተነፋ ዶቄት) ።
ሻጣም፡ ሻጣ ያለበት (ባለሻሳካ) ።
ሻጥ (ስሒጥ) ፡
መሻጥ ።
ሻጥ አደረገ፡
ስክት አደረገ ።
ሻጥር (ዐረ) ፡
ብልጥ ሰው በማንኛውም ሥራና ነገር የሚገባ ።
ሻጭ (ጮች) (ሰሓጢ) ፡
የሻጠ፣ የሚሽጥ (ተካይ ሰኪ) ።
የግስን ጠባይ ያልመረመሩ ሰዎች ግን "በሸያጭ" ፈንታ "ሻጭ" እያሉ ይጽፋሉ፡
ስሕተት ነው ።
ሻፈረ) አሻፈረ፡
እንቢ አለ (ጭራሽ ፈጽሞ) ።
ሻፈሪ) ፡ ከሰፈረ ይወጣል (ሻገረን" እይ) ።
ሻፈደ (ትግ፡
ሠይዐ) ፡ ሠየ ጐመዠ (ሴትን እንስትንሻ - ፈለገ) ።
ሻፈደች፡ ሠየች ጐመዦች (ወንድ ተባት ፈለገች - ደራች እንደ ሰፌድ ኾነች) ።
ሻፋጅ፣ ሻፋዳ፣ ሽፍድ፡
የሻፈደ፣ የሚሻፍድ (ፈታዊ) ።
ሻፎ፡
ስለታም ዱላ ።
ሻፎ፡
ስለትና ሹለት ያለው የባሕር ቋጥኝ (በየብስም ይገኛል) ።
ሻፎ፡ ሹል ቋጥኝ፡
ሸፈሸፈ ።
ሼጠ፡ ለገዢ ሰጠ (ሸየጠ) ።
ሼጥ፡ ለወጥ ።
ሼጥ አለ፡
ጊዜው ተለወጠ (ሸመታ ተወደደ ትንሽ ረኃብ ኾነ) ።
ሼጦ፡ ለውጦ ።
ሼጦ ለጕዳይ፡
ባሪያ ።
ሽ (ኪ) ፡ የአንቀጽና የስም ዝርዝር ወይም ምእላድ
ለቅርብ ሴት” ። በላሽ ጠጣሽ ኼድሽ መጣሽ ነሽ እጅሽ እግርሽ ። እሱ አንቺን ዐወቀሽ" ።
ሽ፡ የቅጽል ባዕድ መነሻ ከደጊመ ቃል ተደራጊ አንቀጽ የሚወጣ ። ከረከረ - ተሽከረከረ -
ሽክርክር ። ቈጠቈጠ - ተሽቈጠቈጠ - ሽቍጥቍጥ ። ቀረቀረ - ተሽቀረቀረ - ሽቅርቅር ።
ሽ፡
የነገር ትራስ (ግንዶሽ ውጦሽ ስርቆሽ ርሚጦሽ) ።
ሽህር —ሽሕር (ሮች) ፡
መሲና (የላም ድልብ) ።
ሽሕኛ፡ ከሺ አንድ የሺ ቤት አኃዝ ፲፻ (1000) ።
ሽለ በላ፡
ስል የሚበላ አረመኔ ።
ሽለላ፡
ሽድሽዳ ውስወሳ ።
ሽለላ፡
ቅርርት” ። አለ ነገር አለ ነገር ቍልቍለቱን ወርደን ወንዙን ስንሻገር" ማለት ።
ሽለላ) ፡ ነፋኝ ቀበተተኝ እታራጄ ድረስ (አምላኬ አትግደ ለኝ የልቤን ሳላደርስ) ።
ሽለላ) ፡ ከወታደርም፡
አለ፡ ተልካሻ፡ ጠመንዣ፡ ይዞ፡ ድንጋይ፡ የሚሻ
ሽለማ፡
የማስጌጥ ሥራ ።
ሽለታ (ቅርፀት) ፡
ጠጕር ቈረጣ ።
ሽለጋ፡ ግመታ ግምገማ ።
ሽላች፡ ሹል ሾጣጣ ሥራ ።
ሽላን (ትግ) ፡
እንስላል ። በግእዝ "ሲላን" ይባላል ።
ሽላን፡
ሸለቀቀ ።
ሽል (ሰይል) ፡
በማሕፀን የተሣለ የተረገዘ (መላወስመንቀሳቀስ የዠመረ ፅንስ) ።
ሲበዛ "ስሎች" ይላል ።
ሽል አለ፡
ስለለ ቀጠነ (ሽል መሰለ) ።
ሽል ያለ ራሱ፡
ትንሽ ገላው አካሉ ወፍራም የኾነ ሰው ።
ሽልል፡
የተሸለለ (ሽድሽድ ውስውስ) ።
ሽልማት (ትርሲት) ፡
ጌጥ ካባ ቀሚስ ድርብ ኒሻን ጌጠኛ የጦር መመሪያ የውቀት የትልቅ ሥራ ዋጋ ።
ሽልሜ፡
የሽልም ወገን (ወታደር የጦር ስው ጥሩርና ቍር ለባሽ) ።
ልጅንም ለማቈላመጥ ይነገራል (የኔ ቈንዦ" እንደ ማለት) ።
ሽልም፡
ሓረግና ጠልሰም (በያይነቱ ሥዕል የሰው ምሳሌ ያለበት አንኮላ) ።
ሽልም፡
የተሸለመ፣ የተመሰለ (ሽልማት ያገኘ የተቀበለ የለበስ የተጌጠ የተንቈጠቈጠ ለተሸላሚ የተሰጠ - ኢሳ፡
፲፫፡ ፲፱) ።
ሽልምልሜ (ሽመልመሌ) ፡
የሽልምልም ዐይነት ወገን ።
ሽልምልሜ፡
የድፎ ግርፍ ።
ሽልምልም፡
የተዥጐረጐረ ዥጕርጕር (ዙሪያ ገባው የተሸለመ) ።
ሽልሸላ፣ ሽልሻሎ፡
ጐመሳ ብቅበቃ ነቀላ ።
ሽልቃቂ፣ ሽልቅቅ፡
የተሸለቀቀ (እንደ ዥራት እንደ ኮባ ሙሽራ እንደ ወይል ዕንጨት ተሸልቅቆ የወጣ) ።
ሽልቅቅ አለ፡
ተሸለቀቀ ።
ሽልባት፣ ሽልብታ፡
ጭፈና እንጕልቻ ።
ሽልብ አደረገ፡
ጭፍን ክድን አደረገ ።
ሽልብ፡
የሸለበ የተከደነ (ጭፍን) ።
ሽልት (ቅሩዕ) ፡
የተሸለተ፣ የተጠረበ (የተላፃ ቍርጥ ጥርብ ጠጕር ዕንጨት) ።
ሽልጋት፡
ግምጋሚ (የዋጋ ለውጥ) ።
ሽልግ፡
የተሸለገ የተገመተ (ግምት ልክ) ።
ሽልጦ (ዎች) ፡
አለቅጠል ባምዛ ምጣድ የተጋገረ ጢብኛ ።
ዘሩ በግእዝ "ሰለጠ" ይመስላል ።
ሽልፋ፡ ሥሥ ቀላል ቈዳ ።
ሽልፋፊ፡
ግልፋፊ ።
ሽልፍ፡
የተሸለፈ (ሽንግል) ።
ሽመለኛ፡ ተማች ደብዳቢ ።
ሽመላ (ዎች) ፡
ሽመላዊ እግረ ረዥም የባሕር ዳር አሞራ ትለ በላ ።
በግእዝ "ሄሮድያኖስ" ይባላል ።
ሽመላ፡ እግሩ እንደ ሽመል የኾኑ ቍርዬ
(በዓለም እየዞረ በመከር ጊዜ የማንንም አዝመራ የሚበላ - ኤር፡ ፰፡ ፯) ። (ተረት) ፡ "ካህንና ሽመላ ያልዘራውን
ይበላ" ።
ሽመል (ሎች) ፡
እንደ መቃ ዐጥቅ አንጓ ያለው ዕንጨት (ውስጥ ድፍን ዘንግ ሶማያ በትር የሚኾን - ኢሳ፡
፳፰፡ ፳፯፡ ኤር፡ ፰፡ ፲፯) ።
ሽመልመሌ (ዎች) ፡ የበትር ስምንጣ ትና ጥቍረት ያለው
በትር (እረኞች የደመራ ለት የሚይዙት ርስ በርሱ የሚያሳብሩት ርጥብ ዱላ)” ። የሽመልመሌ ትርጓሜ ሽልምልሚ" ማለት
ነው ።
ሽሙር፣ አሽሙር (ሮች) ፡ ጠቃሽ (ቀጻቢ) ችንካር (የብረት እሾኸ
አርቃሾ መውግያ መንጐ ማትጊያ ማነቃቂያ - በግእዝ "ቅትር፣ ቅትራት" ይባላል) ።
ሽሙንሙኒ፡
የሽሙንሙን ዐይነት (የኔ ሽሙንሙን) ።
ሽሙንሙን፡
የተሽሞነሞነ (ኵንስንስ) ።
ሽሙጥ፡
ምፀት፡ ማጠጠ ።
ሽሙጥ፡
የንቀት፡ ስድብ፡ ምፀት፡ ቀልድ፡ ለግጥ፡ (ሕዝ፡
፭፡ ፲፩)
ሽሚያ፡
ሰላማዊ ንጥቂያ ቅሚያ ።
ሽማት፡ ስመ አያት፭ኛ፡
የቅማት ኣባት፣ እናት ።
ሽማች፡ ልዋጭ ዋጋ (የእኸል ሽማች" እንዲሉ) ።
ሽማግሌ (ሎች) ፡
የሸመገለ ያረጀ አሮጌ ወግ ታሪክ ዐዋቂ (ጨዋ ገላጋይ አስታራቂ - ራእ፡
፬፡ ፩፣ ፲፡ ፭፡ ፭፣ ፰፣ ፲፩፣ ፲፬) ።
ሽማግሌነት፡
ሽማግሌ መኾን ገላጋይነት ።
ሽማግሌው፡
ያ ሽማግሌ (የርሱ ሽማግሌ - ፪ዮሐ፡
፩፡ ፫ዮሐ፡ - ፩) ።
ሽሜ፡ ዘመን አመጣሽ የንቀት አጠራር (ከጣሊያን ወዲህ) ።
ሽምልምል አለ፡
ሽብልል አለ ።
ሽምሸማ፡ ክተፋ ።
ሽምሽማት፡
ክርትፋት ።
ሽምሽም፡
የተሸመሸመ (የጤፍ ገርም ክርትፍ) ።
ሽምቀቃ፡
ጭምደዳ ሽብሸባ ።
ሽምቅ፡
የሸመቀ (የደፈጠ) ።
ሽምቅቃት፡
ጥበት ሽብሽባት ።
ሽምቅቅ አለ፡
ጭምድድ አለ ።
ሽምቅቅ: የተሸመቀቃ የከረጢት አፍ፣ ቋንዣ፣ ጭንደያ።
ሽምት: የተሸመተ፣ የተገዛ እኸል።
ሽምትር አደረገ: ሸመተረ።
ሽምትር: የተሸመተረ፣ ሽንቍጥ፣ ግርፍ።
ሽምገላ: ሽምግልና፣ እርጅና (ዘፍጥረት ፲፩፡ ፲፭። ፩ኛ ነገሥት ፲፬፡ ፬። ፳ኛ ዜና መዋዕል፡ ፳፱፡ ፳፰)።
ሽምግል አለ: እርጅት አለ።
ሽምግል: እርጅት።
ሽምጠጣ: ዥም”። "የለመደች ጦጣ ኹል ጊዜ ሽምጠጣ።"
ሽምጠጣ: ጋለባ፣ ግልቢያ።
ሽምጣጦ: ፅሽም፣ የማያምር ሽሩባ፣ የፋፊ ፈትል።
ሽምጣጭ፡ በስያፍ ያጐበሰሰው።
ሽምጥ: ሽምጥጥ፣ የተሸመጠጠ ጥር፣ ግልቢያ፣ ሰገባ።
ሽምጥ: ኦሮቢ፣ ዝምጋገ።
ሽምጥር አለ: ሑምጥጥ አለ።
ሽምጥር: የሸመጠረ፣ የሖመጠ።
ሽምጥጥ አደረገ: ጭልጥ አደረገ። "እውነትን ትቶ ሐሰት ብቻ ተናገረ።"
ሽምጥጥ: ጭልጥ፣ ጭርስ። "ኮሶ ሲጠጣ ስቅጥጥ፣ ወተት ሲጠጣ ሽምጥጥ እንዲሉ።"
ሽረባ: የመሸረብ ሥራ።
ሽረት (ሥዕረት): የሕመም ተቃራኒ፣ ድኅነት፣ ጤና፣ ጤንነት። "በሽተኛው ቍርባን ይቀበልና ሽረቱንና ሞቱን ይለይለት።"
ሽረት (ስዕረት): የሹመት ተቃራኒ (ላጥሻ)፣ መሻር፣ መሻር (ዕብራውያን ፯፡ ፲፰)።
ሽራፊ: ስባሪ፣ ቍራሽ (ያሞሌ፣ የዳቦ)።
ሽሬ: በትግሬ ክፍል ያለ አገር ።
ሽር (ስዑር): የተሻረ፣ ከሹመት የተወገደ። "ሹም ሽር እንዲሉ።"
ሽር አለ: ሠለጠነ።
ሽር አደረገ: ሸነ፣ ለቀቀ።
ሽርሙጥ አለ: ጕድል አለ።
ሽርሙጥ: የጐደለ።
ሽርሙጥሙጥ አለ: ተሸረሞጠ (ቅሉ፣ ዱባው)።
ሽርሙጥሙጥ: የተሸሪሞጠ (ሥርድጕድ ጐደሎና ሙሉ)።
ሽርሙጥና: ዝኒ ከማሁ።
ሽርሽር አለ: ተንሸረሸረ።
ሽርሽር: ዙረት፣ መንሸርሸር፣ ኣየር መለወጥ።
ሽርሽር: የተሸረሸረ ንድል።
ሽርቍጥ አለ: ቅልጥፍ አለ።
ሽርብ: የተሸረበ፣ ድብል፣ ጥር፣ ድርብ።
ሽርቦሽ: ሽርባት፣ የሽርብ ሥራ።
ሽርንክት፡ ያልደቀቀ ዶቄት ።
ሽርንክት: ያልደቀቀ ዶቄት ሸረከተ።
ሽርከታ: ቀደዳ።
ሽርክርክ አለ: ተሽረከረከ።
ሽርክት አለ: ቅድድ አለ።
ሽርክትክት አለ: ተሸረካከተ።
ሽርክትክት: የተሸረካከተ፣ ዝርክትክት።
ሽርክና: ሸሪክ መኾን (ወዳጅነት ግጥሚያ አንድነት)።
ሽርደዳ: ቅጥፈት፣ ሐሜት፣ ነቀፋ፣ ለበጣ፣ ከውነት የራቀ ነገር፣ ለግጥ፣ ፌዝ።
ሽርጣም: ባለሽርጥ፣ የባላገር ሴት ግልድማም፣ ዐረብ፣ እስላም።
ሽርጥ (ጦች): የተሸረጠ፣ ከደረት በታች የታሰረ ግልድም።
ሽርፍ አለ: ተሸረፈ።
ሽርፍ: የተሸረፈ፣ የተሰበረ።
ሽርፍራፊ: ስብርባሪ፣ ምንዛሪ፣ ቤሳ፣ ሳንቲም።
ሽርፍርፍ አለ: ተሸራረፈ።
ሽርፍርፍ: ስብርብር፣ ቍርስርስ።
ሽሮ (ስዒሮ): ደፍሮ። "በዓል ሽሮ የከበረ ጦም ገድፎ የወፈረ የለም።"
ሽሮ፡ ሹሮ (ሥዒሮ): ከተቈላ ባቄላና ዐተር ጓያ የተዘጋጀ ዶቄት፣ የጦም ወጥ የሚኾን። "(ግጥም)፡ ዐል መረቁን ወጡን ሸለቸን፣ ምኒልክ ተነሥቶ ሽሮ ባበላን። ዐተር አልዘራኹም አልሰጥዎ ክክ፣ ይህን ኹሉ ሽሮ በሰጠዎ አምላክ (ስለ ገጤ ቴዎ)።"
ሽሮሽ: በታችኛው ወግዳ ውስጥ ያለ ቀበሌ (ሸመትሽን ወስዶብሽ" ወይም "ያንቺ ሽሮ" ማለት ነው)።
ሽሸ)፡ ማረጃ ካራ።
ሽሸጋ: ደፈና፣ ስወራ፣ ድበቃ።
ሽሹ: በዠድ (ጕያን" ተመልከት)።
ሽሽተኛ: ሸሸ፣ ኦሮቢ።
ሽሽት: መሸሽ፣ ሩጫ፣ ግልቢያ፣ ፍርጠጣ፣ ኵብለላ።
ሽሽጉ ጌ: የሰው ስም። ዲቃላ ወይም በጓዳ ያደገ።
ሽሽጋት: ስውርነት፣ ድብቅነት።
ሽሽግ (ጎች): የተሸሸገ፣ የተደበቀ፣ ስውር፣ ድብቅ (ኢሳይያስ ፵፰፡ ፲፯)።
ሽሽግነት: ሽሽግ መኾን።
ሽሽጓ: የሴት ስም።
ሽቍጥቍጥ፡ የተሽቈጠቈጠ፡ የተለማመጠ።
ሽቍጥቍጥ: የተለማመጠ፣ ቈጠቈጠ።
ሽቅ አለ: ዐለቀ፡
ሸቀቀ።
ሽቅ አለ: ሞተ፣ ዐለቀ፣ ተጨረሰ፣ ተጠነገደ።
ሽቅ አለ: ዐለቀ፣ ሸቀቀ።
ሽቅርቅር (ሮች): የተሽቀረቀረ፡
ጌጠኛ። "(ግጥም) እሱ ጥቍር ጐራዴው ሽቅርቅር፡
ይምጣ ወይ ይቅር።
"
ሽቅሽቅ አለ: ተንሸቀሸቀ።
ሽቅብ ሽቅብ አለ: አወከ (ሆድን)።
ሽቅብ: ዐቀብ፣ ዐቀበት፣ ወደ ላይ። "ዐቀብ ግእዝ፣ ዐቀበትና ሽቅብ ዐማርኛ ነው።"
ሽቅታ: ዕልቂት፡
ሸቀቀ።
ሽቅታ: ሽቅ ማለት፣ ዕልቂት።
ሽበባ: ሽቢያ፣ ጠለፋ፣ አሰራ።
ሽበታም (ሞች): ሽበት ያለው፣ ባለሽበት፣ ሸበቶ።
ሽበት (ቶች) (ሢበት): ነጭ የሰው ጠጕር፣ በዘርና በዕድሜ የሚወጣ። "በእንጨትና በድንጋይ ላይም ይታያል።"
ሽባ (ዎች): እጁ የማይጨብጥ፣ እግሩ የማይረግጥ ሰው፣ ጥምልምል።
ሽባ ኾነ: ተጥመለመለ።
ሽባ: እጅ እግሩ ሰላላ፣ ሸበየ።
ሽባይ (ሳብዓይ): ሰባተኛ የቀባርዋ ምትክ።
ሽባጥ (ሠበጠ፡ ሥባጥ፡ ዳረጎት): ስሯጽ ሽብልቅ ጣልቃ ሠላጤ ። አለሥራውም የገባ ሰው ሽባጥ ይባላል” ። ወሽመጥን" እይ።
ሽብለላ: ጥቅለላ።
ሽብልላት: ጥቅልላት።
ሽብልል አለ: ጥቅልል አለ።
ሽብልል: የተሸበለለ፣ ጥቅል (ብራና፣ ወረቀት፣ ቍርበት፣ ሸማ፣ የሙዝ፣ የኮባ ቅጠል)፣ ኣምልማሎ።
ሽብልቅ (ቆች): ሹል ዕንጨት ወይም ብረት (ስም)።
ሽብልቅ አበጀ: እሾለ፣ አገባ፣ ቀረቀረ፣ በሽብልቅ ወጋ።
ሽብልቅ፡ የተሸበለቀ፣ ቅርቅር፣ ውግ (ቅጽል)።
ሽብልብል: ልምን ሸበለለ፣ በቁመት ጠቀለለ።
ሽብልብል: የተሽበለበለ፡ ልምም።
ሽብረቃ (ሡራኄ): ወዝ፣ ውበት፣ ጸዳል፣ የመልክ ጥራት፣ ጥሩነት፣ ወለልታ፣ ላሕይ።
ሽብረኛ (ኞች): ሽብር ፈጣሪ፣ አሸባሪ፣ ተሸባሪ (ዘኍልቍ ፳፬፡ ፲፯)።
ሽብሩ: ሽብሬ። "በሽብር ጊዜ የተወለደ ሰው ስም።"
ሽብር: ሁከት ግርግር ታፍጅት ብጥብጥ።
ሽብርቅ አለ: ሸበረቀ።
ሽብርቅ: የሸበረቀ፣ ወዛም።
ሽብሸባ: ሽንሸና።
ሽብሽባት: የወገብጌ፣ የቀሚስ፣ የእጅጌ ሽንሽናት።
ሽብሽብ: የተሸበሸበ፣ የተጨማደደ።
ሽብሽቦ: ሽንሽን።
ሽብባት: ያፍ፣ ያገጭ እስራት፣ ሽቢያ። (ጥሸ)
ሽብብ: የተሸበበ፣ አፉ የታሰረ።
ሽብት አለ: ሸበተ።
ሽብት: መሸበት።
ሽብዳ: ጫፉ አራት ማእዘን የኾነ ዐር ዐንካሴ። "ረዥሙ ምዥራጥ ይባላል።"
ሽቦ ፡ (ዎች)፣ የብረት ፡ የብር ፡ የወርቅ ፡ የንሓስ ፡ የመዳብ ፡ ክር ፣ ቀጪንና ፤ ወፍራም ፡ (ሕዝ፵፩ ፡ ፲፮ ፡ ፳፯) ። (ሎጋው ፡ ሽቦ) ፤ በጦር ፡ ጕረሮ
፡ ላይ ፡ ያለ ፡ ሽቦ ፤ ሎጋ ፡ የተባለ ፤ ጦሩ ፡ ነው ።
ሽቦ ሠራ: መዘመዘ፣ አቀጠነ፣ ጠመዘዘ፣ ጠመጠመ።
ሽቱ፡ ሽቶ: በቁሙ ሸተተ።
ሽቱ: ሽቶ። "ዕጣንን፣ ሎሚን፣ ርጐፍትን፣ ባርሰነትን፣ ሽነትን ከመሰሉ ዕፀዋት ተቀምሞ የነጠረ ጣፋጭ ፈሳሽ፣ ያፍንጫ ምግብ (፪ኛ ቆሮንቶስ፡ ፪፡ ፲፭)። እንዝባን፣ ሪሓን፣ ጠጅ ሣር።"
ሽታ: "ሕፃን ሲወለድ በፊቱ ላይ ዐልፎ ዐልፎ የሚታይ ጥቍር-ነጠብጣብ፣ ማሪያም የሳመችው።"
ሽታ: ጣዕም፣ መዐዛ፣ ማለፊያና መጥፎ (፪ኛ ቆሮንቶስ፡ ፪፡ ፲፯)።
ሽትር: የተሸተረ፣ ጌጠኛ።
ሽቶ፡ ፈልጎ፣ ፈቅዶ።
ሽነት (ቶች): የዛፍ ስም (ሽታውመዐዛው የሚጣፍጥ ዕንጨት - ጕይዲ ግን መዠመሪያ ሽነትን "ሽሾ" ብሎ ተርጕሞታል)።
ሽንሸና: ሽብሸባ፣ ሥንጠቃ።
ሽንሽና: አልቃሽ ልጅ ላንቍሶ።
ሽንሽናት: የሽንሸና ሥራ፣ ሽብሽቦ።
ሽንሽን (ኖች): የተሸነሸነ፣ የተሸበሸበ፣ ሽብሽብ፣ ፍልጥ።
ሽንቀራ: ስብሰባ፣ ዐጠፋ፣ ቅነፋ።
ሽንቍራት: ነዳላነት፣ ቀዳዳነት።
ሽንቍር አለ: ብስት አለ፣ ተሸነቈረ።
ሽንቍርቍር: የተሸነቋቈረ፣ ብስትስት።
ሽንቍጥ: የተሸነቈጠ፣ ግርፍ።
ሽንቈራ: ቀደዳ፣ ነደላ።
ሽንቈጣ: ገረፋ፣ ግርፊያ።
ሽንቅራት: ዕጥፋት፣ ቅንፋት።
ሽንቅር: የተሸነቀረ፣ ስብስብ፣ ቅንፍ።
ሽንብሩት (ሽንብራዊት): ቅጠሏ ሽንብራ የሚመስል ዐረግ።
ሽንብሩት: መልከ ሽንብራ ንብ።
ሽንብራ (ሽን፡ ብራ): የእኸል ስም (ክረምት ውጭ በመስከረም የሚዘራ ያበባ እኸል - "ዱባን ዓሣን" አስተውል - ዎች)።
ሽንብራ፡ ሽንብሮች: ፪ና ከ፪ በላይ ያሉ ፍሬዎች።
ሽንብራ ዓሣ: የሽንብራ ወጥ ዓሣ አስመስለው ሴቶች የሠሩት (ምግብን ከሌላ ነገር ጋር ማመሳሰል)።
ሽንታም (ሞች): ሽንተ ብዙ። "አኹንም አኹንም የሚሸን።"
ሽንታም: ፈሪ፣ ጡርቂ።
ሽንት ማጥ: የሽንት ምጥ።
ሽንት ቤት: በውስጡ የሽንትና ያይነ ምድር ጕድጓድ ያለበት ቤት።
ሽንት ዘር: ልጅ። "ሣይንትን ተመልከት።"
ሽንት: ዘር ልጅ” ። ሣይንትን" ተመልከት።
ሽንት: በቁሙ ሸነ።
ሽንት: አፍን መንገድ አድርጎ ወደ ሆድ የገባ የመጠጥ ቅሬታ። "ሽታው ጕንፋንና ሳል የሚያመጣ ግማታም የሆድ ውስጥ ፈሳሽ።"
ሽንትር: የተሸነተረ፣ የተበጣ ብጥ። "ሸንጥሮን እይ፡ በምስጢር ከዚህ ጋራ አንድ ነው።"
ሽንትርትር: የተሸነታተረ።
ሽንቶ: ሽንክ፣ ችንች።
ሽንቶ: ችንች፣ ሸነ።
ሽንከፋ: ዐጠፋ፣ ኣሰራ።
ሽንኵርት (ሶመት፡ በጸል): የተክል ስም (ነጭና ቀይ ተክል ለወጥ ቅመም የሚኾን -
"ነጭ ሽንኵርት ቀይ ሽንኵርት" እንዲሉ - ሲበዛ "ሽንኩርቶች" ይላል - "የዥብ ሽንኵርት"
- የዱር ቅጠል)።
ሽንኵርት፡ ሽንኵርት: የቀበሌ ስም። "ከደብረ ሊባኖስ በስተግራ አፋፍ ላይ ያለ የራስ ዳርጌ ከተማ፣ ከቈላ እየመጣ ብዙ ሽንኩርት የሚሼጥበት ገበያ ያለው።"
ሽንክ: ችንች፣ ነጭ አባ ጨጓሬ ሽንቶ ክመክር በኋላ። "የቅሞን፣ የኰሽምን፣ የጦሚትን፣ የትለምን፣ የእንቡስን ቅጠል በልቶ የሚጨርስ አጥፊ።"
ሽንክፍ: ሽንክፋት፣ ዕጥፋት፣ እስራት።
ሽንጣም: ሽንጠ ረዥም ሰው ወይም ከብት፣ ሞላላ ድንጋይ።
ሽንጣሞች: ረዣዥሞች (ሰዎች፣ ከብቶች፣ ደንጎች)።
ሽንጥ፡ ራስ: የሽንጥ ጫፍ።
ሽንጥ: የታወቀ የሥጋ ብልት። "ከፍሪዳ ዠርባ ላይ ተከፍሎ የሚወጣ ጥንትና ክዳ ያለበት ክፍል።"
ሽንጥ: የዠርባ ወንዝ፣ ከማዥራት እስከ መቀመጫ ግራና ቀኝ ያለ ዝላ። "በግእዝ ስመጥ ይባላል።"
ሽንጦች: ኹለትና ከኹለት በላይ ያሉ ሥጋዎች።
ሽንፍ: የተሸነፈ፣ ድል የኾነ፣ የተረታ፣ የተመታ።
ሽንፍላ (ሎች): የሆድ ዕቃ ስም (ምግብ የሚከማችበት ብዙ ክፍል ያለው ውስጠ ንብብር ሥጋዊ ከረጢት - የጨጓራ ዘርፍ ቢያጥቡ አይጠራ)።
ሽንፍጥ: የተሸነፈጠ፣ የታጠፈ፣ ዝቅዝቅ።
ሽኵምኵም: የተሽኰረመመ፡
ተሽኰርማሚ፡ ተጫዋች። "ዥግሪቴ ዥግሪቴዐመለ ደኅኒቴ፡
ነይ ሽምኵምከኔ እንዳለእረኛ።
"
ሽኩቻ: የእጅ፣ የጣት ውድድር። "ይኸውም መቀስ ወስፌን፣ ሰይፍ መቀስን፣ መዶሻ ሰይፍን፣ ታቦት ኹሉን ይረታል። አገናን አስተውል።"
ሽክ አለ: አጌጠ፣ ተሸተረ።
ሽክ: ማጌጥ፣ መሸተር።
ሽክረት: ሻካራነት።
ሽክርክሪት (ቶች): ከቀጪን ዕንጨት ጋር የተዋደደች የንዝርት ራስ ወይም ገል፡ የልጆች መጫወቻ፡ ሴቴ ሬት የዝንጀሮ ቂጣ፡ ክብ የመንኰራኵር ብረት ክሊሊ።
ሽክርክር አለ: ተሽከረከረ።
ሽክርክር: የተሽከረከረ።
ሽክርክር: የተሽከረከረ፣ ከረከረ።
ሽክሸካ: ወቀጣ፣ ሽድሽዳ፣ ዝርዘራ፣ ዝክዘካ።
ሽክሽካት: ሽድሽዳት፣ መናኛ ስፌት።
ሽክት: የዛፍ ስም (በዠማ ዳር የሚበቅል
ዕንጨት ቅጠሉ የሽንብራ ቅጠል ይመስላል ዐዲሳበቦችም የፈረንጅ ግራር ይሉታል) ።
ሽክና (ሰከነ): ጥልቂት፣ እንኮላ። "ሲበዛ ሽክኖች ይላል።"
ሽክፍ: የተሸከፈ፣ ትፍትፍ፣ ጥቃቅን ጥርስ ካፊያ።
ሽኮኮ (ዎች): (መስቈቅው) ፡ ያውሬ ስም (በጐሬ በየቋጥኙ ሥር
የሚኖር የጥንቸል ዐይነት አውሬ ማታ በጨለማ ሲጸልይ የሚያለቅስ ይመስላል) ። ከጩኸቱም በኋላ ይነፋነፋል ስለዚህ
"የሽኮኮ ጸሎት" ይባላል።
ሽኾሮ: ድብልብል ጌጥ፣ ከወርቅና ከብር የተሠራ።
ሽው ሽው አለ: መላልሶ ነፈሰ። "ሣሩ ድምጥ ሰጠ ከነፋስ የተነሣ።"
ሽው ሽው: ንፍስ ንፍስ፣ ብር ብር። "አካል ሽው ሽው ትዳሬ ብለሽው እንዳለ ዘፋኝ።"
ሽው አለ: ነፈሰ፣ በረረ፣ ዐለፈ (ነፋሱ፣ አሞራው)፣ በጥቂቱ ተሰማ (ወሬው)።
ሽው: መንፈስ መብረር” ። ሸውሻዋን" እይ (ከዚህ ጋራ አንድ ዘር ነው)።
ሽውታ: ምች፣ ምታት፣ ግርፋት። "ከነፋስ፣ ከፀሓይ የሚመጣ።"
ሽውታ: ሽው ማለት።
ሽየታ: መሸየት።
ሽያጭ (ሤጥ): ዋጋ ለውጥ። "በሸቀጥና በንግድ ዕቃ ፈንታ ሽያጭ ይላል (ራእይ ፲፰፡ ፲፩)።"
ሽድሸዳ: ውስወሳ፣ ሽክሸካ፣ ሽለላ።
ሽድሽዳት: ሽክሽካት፣ መናኛ ስፌት።
ሽድይ: ስድስተኛ የቀባርዋ ምት።
ሽጕር: የተሸጐረ፣ ቅርቅር።
ሽጕብ አደረገ: ሸጐበ።
ሽጕዱ: ምንድር ነው (ጕዳዩ ምንድር ነው)።
ሽጕድ (ሰገደደ): አንቂድ ጕዳይ ስውር ነገር።
ሽጕጥ (ጦች): የመሣሪያ ስም፣ ፮ ጥይት የሚጐርሥ፣ ዝናርና ቤት ያለው። "በወገብ የሚያዝ፣ የሚንጠለጠል ዕቃ ጦር ሽጕጥ።"
ሽጕጥ ሽጕጥ አለ: ድብቅ ድብቅ አለ። (ጥሸ)
ሽጕጥ አለ: ውትፍ አለ።
ሽጕጥ ጠጣ: የሽጕጥን ጥይት ባፉ አገባ። "በገዛ እጁ ለመሞት።"
ሽጕጥ: የተሸጐጠ፣ የገባ፣ የተደበቀ።
ሽግ ሽጕ (ጽገ): ችቦ፣ ዳቦት፣ ቴሃ።
ሽግ ሽጕችቦ: ሸገገ።
ሽግል: ጨብጥ።
ሽግት አለ: ሻገተ።
ሽግት: መሻገት።
ሽጐራ: ውርወራ፣ ቅርቀራ።
ሽጐጣ: ውተፋ፣ ድበቃ።
ሽጦሽ: ልወጣ።
ሽፈና: ክለላ፣ ጭፈና፣ ከደና።
ሽፋ፡ ሽፋፍ: ሸፈፈ።
ሽፋ: ሽፍ፣ የተሸፈሸፈ፣ የታጨደ።
ሽኮኮ (ዎች): (መስቈቅው) ፡ ያውሬ ስም (በጐሬ በየቋጥኙ ሥር
የሚኖር የጥንቸል ዐይነት አውሬ ማታ በጨለማ ሲጸልይ የሚያለቅስ ይመስላል) ። ከጩኸቱም በኋላ ይነፋነፋል ስለዚህ
"የሽኮኮ ጸሎት" ይባላል።
ሽፋን: ልባስ፣ ከለላ፣ ቀጸላ፣ ሻሽ፣ ዕራፊ፣ ክዳን።
ሽፋው: ዝኒ ከማሁ፣ የው ዝርዝርነት ኣባትን ያያል።
ሽፋፍ (ፎች): የጦር፣ የቢላዋ፣ የፍላጻ ቤት ማግቢያ፣ መክተቻ፣ ማኅደር። "ጐረንጐሬን ተመልከት።"
ሽፍ አለ: ወጣ፣ ሸፈፈ።
ሽፍ አለ: ፈላ፣ ገነፈለ፣ ወጣ፣ በተለተገለበጠ፣ በላይ ኾነ።
ሽፍ: መውጣት፣ መብቀል።
ሽፍሻፊ፡ መናኛ ሳንቃ ወይም ጠርብ፣ ገማጣ፣ ሽርፍራፊ።
ሽፍሽፋ: ዐጨዳ፣ ቈረጣ።
ሽፍታ (ቶች): የሸፈተ ዐመጠኛ፣ ዳንዴ፣ ወንበዴ፣ ቀማኛ፣ ጋዱ።
ሽፍታ፡ ሐሩር፣ ሸፈፈ።
ሽፍታ(ት)ነት: ሽፍታ መኾን፣ ዐመጠኛነት፣ ከዳተኛነት (ዕዝራ ፬፡ ፲፱)።
ሽፍታ: ሥራው የሚያምር፣ ቀጪን ሽሩባ።
ሽፍታ: ሽፍ ማለት፣ ሐሩር (የቡቃያ፣ የዕከክ ፍል)፣ ረቂቅ በረዶ።
ሽፍታ: በሚናጥ ወተት ላይ ሽፍ ብሎ ሰፎ የሚታይ የቅቤ ውጥን።
ሽፍናት: ሽፋን፣ መሸፈኛ።
ሽፍን አለ: ተሸፈነ።
ሽፍን አደረገ: ሸፈነ።
ሽፍን: የተሸፈነ፣ ጭፍን፣ ባር፣ ማሽላ፣ ወሸላ፣ ቈላፍ (ሮሜ ፪፡ ፳፭፡ ፳፮)።
ሽፍን: የተሸፈነች እመቤት፣ ወይዘሮ።
ሽፍንነት: ወሸላነት (ሮሜ ፪፡ ፳፮)።
ሽፍንፍን አለ: ተሸፋፈነ።
ሽፍንፍን: የተሸፋፈነ፣ ክንብንብ።
ሽፍድ አለ: ሻፈደ።
ሽፍጃ: ሽፍደት፣ ድራት፣ ፍትወት።
ሽፍጥ (ስፉጥ): የተሸፈጠ፣ ድልል፣ ሽንግል።
ሽፍጥ አደረገ: ሸፈጠ።
ሾ: የይፋት በርበሬ።
ሾለ (ተስሕለ) ፡
ክፉ ቀጠነ (ሾጠጠ - ኢሳ፡
፵፱፡ ፪) ።
ሾለቀ፡ ሾለ ሾጠጠ (ከስምንት ተከፈለ የዳቤ)” ። ሾለከን" እይ ።
ሾለቅ (ቆች) ፡
አፈ ሹል አሞራ (እሱ ሲጮኸ ዝናም ይመጣል ይባላል) ።
ሶለግና ሾለቅ በምስጢር አንድ ናቸው ።
ሾለቅ፡ ሕፅን ሠላጤ ሾጣጣ ዳቤ (ከስምንት አንድ የኵርማን እኩሌታ) ።
ሾለከ (ሰለከ) ፡
በቀዳዳ ኼደ ወጣ ወለቀ አመለጠ ።
ሾላ (ዎች) ፡
የዛፍ ስም (ፍሬው የሚበላ ዕንጨት የበለስና የወርካ ወፃን) ።
በግእዝ "ሰግላ" ይባላል ።
ሾላ ሜዳ: ሾላ የበቀለበት ሜዳ። "በይፋት ክፍል ያለ ቀበሌ። አላንኮበር ሾላ ሜዳ አይገኝም እንዳሉ መምር ዕዝራ።"
ሾላ ሸሎ: በርደዶ፣ ልብ ራስ የሚመታ፣ የሚቀጠቅጥ። "ስካሩ የጸና የበረታ መጠጥ ማለት ነው።"
ሾላ በድፍን: ያልተገለጠ ነገር።
ሾላካ: የሾለከ፣ የሚሾልክ።
ሾላካ: የዱር ኣውሬ፣ የድመት ወገን፣ የቆቅና የዶሮ ጠላት፣ መልከጥ ቍር፣ ዐፈርማ። "ትግሬ ሐባብም ቀጠነ ሲል ሸልሐ ይላልና ሸላ ከዚህ ሲወጣ ይችላል።"
ሾላጌ: ሾላ ያለባት፣ የበዛባት ምድር።
ሾሌ (ሾላዊ): ኣፉ ከንፈሩ የበሰለ ሾላ የሚመስል ፈረስ። "አፈ ሾሌ እንዲሉ።"
ሾመ መላ: ጢም አደረገ (ጠላን፣ ሆድን፣ ባሕርን)።
ሾመ እከ: ሰበሰበ፣ አንድነት አደረግ፣ ሸለመ፣ ኣክሊል አስመሰለ (ምርትን)።
ሾመ፡ ዝም: አሠኘ።
ሾመ: መላ ጢም አደረገ (ጠላንሆድን ባሕርን)።
ሾመ: አበጀ፣ አዘጋጀ (እንዝርትን ጠገነ)።
ሾመየ: ሹም ኾነ።
ሾረ: ዞረ ሠሠረ ተሽከረከረ።
ሾርባ (ዐረ): የስንዴ ሙቅ እንትክትክ።
ሾርቤት: የማያሰክር የሴቶች መጠጥ፣ ብጥብጥ ሱካር።
ሾቀ: ተቀቀለ ራስ ረሰረሰ (የባቄላ ያተር የሽንብራ ቈሎ በፈላ ውሃ)።
ሾቅ፡ ራስ።
ሾቅ አለ: ራስ አለ።
ሾተላ: ያገር ስም።
ሾተሌ፡ ዥብሪ: "ልጆችን በጥላው የሚያከሳ፣ የሚያቀጥን፣ የሚያመነምን የሰማይ ሾተላይ፣ የሾተል ባለሾተል፣ ሾተላም፣ ሾተልማ፣ በሴቶች ማሕፀን እያደረ ወንዶችን የሚገድል፣ ሕፃናትን ሲወለዱ የሚያጨናጕል። በግእዝ አስማንድዮስ ይባላል (ጦቢት ፫፡ ፰)።"
ሾተሌ፡ ጠሮ: የባሕር ጋኔን። "መርከብን እየገለበጠ ሰውን የሚያሰጥም።"
ሾተሌ: ሲላ፣ ነጣቂ አሞራ። "ጥፍረ ሾተል አሞሮች ኹሉ የያዙትን የሚቀማ።"
ሾተል (ሰውተል): በኹለት ወገንስለት ያለው ቀን ሰይፍ።
ሾተል ሾተል (ትግ፡ ሐባ): አፋ ፊቢ።
ሾቴ: ጥቃቅን በረዶ በምድር ላይ ሽፍ ብሎ የሚታይ።
ሾከከ (ሦክ): ሾለ ቀጠነ (እንደ እሾኸ እንደ ሹካ ኾነ ቀለለ)።
ሾካካ: የሾከከ (ጥላ ቢስ)።
ሾካካ: የሾከከ፣ ጥላ ቢስ።
ሾኬ: የሾካካ ዐይነት ወገን፣ ሰብቀኛ ዦሮ ዐጋሚ።
ሾክሾከ (ሾከከ): አሾከሾከ፡ በዦሮ ነገረ።
ሾክሿካ: አሾክሿኪ።
ሾዬ (ኮሞል): የዛፍ ስም። "ዐጥንታም ፍሬው ከታች ሰፋ ከላይ ሾጠጥ የሚል ምግብነት ያለው።"
ሾዬ: ሸዬ።
ሾጠጠ (ሶጠ): ከፍ ቀጠነ፣ ሾለቀ።
ሾጠጥ: ቀጠን።
ሾጣጣ (ጦች): የሾጠጠ። "እንደ ዐለን በስተላይ የቀጠነ።"
ሾጤ: የሾጥ ዐይነት። "ወገበ ቀን ሴት አንዠቷ በመርፌ የማይገኝ። (ተረት)፡ ቢቸግረነ ሾጤ ኾነ።"
ሾጤነት: ሾ መኾን፣ ቅጥነት።
ሾጥ (ሰሐጠ፡ ሶጠ): ሸነቈጠ (በጨንገር መታ ገረፈ)።
ሾጥ (ሰዊጥ): መሸንቈጥ፣
መግረፍ።
ሾጥ (ሰውጥ): ዐለንጋ፣ ልምጭ።
ሾጥ አደረገ (ሶጠ): ሸነቈጠ፣ በጨንገር መታ፣ ገረፈ።
ሾጥ አደረገ: ገረፈ፣ ሸመተረ።
ሾፈ)፡ ዐረ፡ ሻፍ፡ አየ።
ሿ አለ፡ ፈሰሰ (ሿሿ): ፈሰሰ።
ሿ አለ: ዧ አለ፣ ተንሿሿ።
ሿሚ (ሞች): የሾመ፣ የሚሾም፣ እክባሪ። "ሿሚ ሸላሚ እንዲሉ።"
ሿሚነት: ሿሚ መኾን፣ አክባሪነት።
ሿሿ)፡ ሳዕስዐ)፡ አንሿሿ (አንሳዕስዐ)፣ አፈላ፣ አገነፈለ፣ አፈሰሰ፣ አወረደ፣ ድምዕ ኣሰማ።
ሿሿ)፡ ሾተል፣ የተንቀሳቃሽ የዶሮ።
ሿሿመ: ብዙ ሰው ሾመ።
ሿሿቴ (ሰርብ): የገደል ላይ ውሃ ፋፋቴ፣ የጽና፣ የጸናጽል ሻኩራ፣ የመረሻት፣ የጕልላት አጫዋች፣ መርገፍ።
ሿሿቴዎች (አስራብ): ፋፋቴዎች።
No comments:
Post a Comment