ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ
ሐ፡ ፰ኛ ፊደል ("በግእዝ አልፍ ቤት በጥንታዊው ተራ በአበገደ በአኃዝነት ሐ፰ በፊደልነት ሐውት ይባላል ጻፎች ግን ሐ መር ሐ ይሉታል") ።
ሐለቀ)፡ ከፈለ/ለየ (ግእዝ) ።
ሐለየ)፡ ዘፈነ/አመሰገነ (ግእዝ) ።
ሐለይተ ብርት፡ የመዳብ/የብረት ዘፋኞች ("በሰው ምሳሌ የተሠሩ") (ዜና እስ.) ።
ሐመ/ሐመመ)፡ ታመመ (ግእዝ) ።
ሐመር (ዐረ)፡ ቀይነት ያለው ዳማ ፈረስ ።
ሐመር ዘራፍ፡ የፉከራ ቃል ("ሐመ ርን ዘራፊ ቀሚ ማለት ነው") ።
ሐመር ፈረስ፡ ቀይ ፈረስ (ዘካ. ፩፡ ፰) ።
ሐመር፡ መርከብ/ጀልባ/ታንኳ/ፍልኳ (ግእዝ) ።
ሐመር፡ በባኮ ውስጥ ያለ አገር ("ሐመር ባኮ እንዲሉ") ።
ሐመር፡ ኹለተኛ የሐውት ሐ ስም ("ሐመር ሐ እንዲሉ ጻፎች") ።
ሐመር፡ የመቃድሾ ፪ኛ ስም ።
ሐመር፡ የብርብራ ዐይነት ዛፍ ("የፍ ሬው መታቈሪያ ጌጥ መኰሊያ የሚኾን ፍሬው ሲበሉት የሚጣፍጥ የሚሖመጥጥ ጋሎች ሮቃ ይሉታል ፈረንጆችም ቀላል መጠጥ ያደርጉታል") ።
ሐመር፡ የታቦት መቀመጫ መንበር ("ከርሠ ሐመር እንዲሉ") ።
ሐመነ)፡ ለፈለፈ/ቀባጠረ ("የሰጠውን መረቀ የነሣውን ሰደበ አጐጠጠ እኔም መጣኹ እንዳባቴ ስልቻዬን በብብቴ ዐልን ጋዬን በጣቴ አለ") ።
ሐመደ (ሐመድ)፡ ከ፮ቱ ነገደ ዮቅጣን ፭ኛው ነገድ ።
ሐሙስ፡ ፬፡ ፭ኛ ቀን፡ ኀሙስ ።
ሐሚታ (ሐመየ)፡ ዐሚታ ("ማማት የሰው ስም ማንሣት ማጥፋት") ።
ሐሚና (ትግ. ሐሜን)፡ ለፍላፊ/ቀባ ጣሪ/ተሳዳቢ ።
ሐሚናሚና፡ የቡሔ ዘፈን ("ልጆች ዳቦ ለሰጣቸው የሚያቀርቡት ምስጋና ሐሚ") ።
ሐሚናም ነት፡ ሐሚና ያለው ("ባለሐሚና") ።
ሐማል (ሐመለ)፡ ተሸካሚ/ኩሊ (ዐረብ) ።
ሐማሴኔ/ሐማሴናዊ፡ የሐማሴን ሰው ።
ሐማሴን (ሐመሰ)፡ በምጥዋና በመ ረብ መካከል ያለ አገር ።
ሐማሴኖች፡ የሐማሴን ሰዎች ("የሐማሴን ተወላጆች ትግሮች (ሐማስያን) የምጥዋ ዋነተኞች የባሕር ነጋሽ ታዛዦች") ።
ሐሜ (ሐቅ)፡ ለጋማ ከብት የሚነገር ቃል ("ኺድ ሩጥ ጋልብ ማለት ነው") ።
ሐሜት፡ ዝኒ ከማሁ ("ነቀፋ") ።
ሐም፡ ነጭሎ ነጭ ዛፍ (ኢዮ. ፳፪) ።
ሐምሌ (ሐምል)፡ የወር ስም ("፲፩ኛ ወር ከመስከረም (ሐምላዊ) ባለቅጠል ቅጠ ላም ቅጠል ያለው የልምላሜ ወር ማለት ነው") ።
ሐምሳ፡ ፭፲፡ ኀምሳ ።
ሐምበለይ (ትግ. ሐባ)፡ ነጭ ፈረስ ዐመድማ ።
ሐምበላይ፡ ዐውሎ ነፋስ ("ባሕርን የሚደርጥ ጣራ የሚገለብጥ") ።
ሐምበል፡ ሻለቃ፡ ዐምበል ።
ሐሞቱ ፈሰሰ፡ ደከመ/ዛለ ።
ሐሞታም (ሐሞታዊ)፡ ባለሐሞት ("ጐበዝ መራር") ።
ሐሞት (ሐመወ)፡ ከሙቀት/ከትኵሳት የተነሣ የሚበዛ መራራ ፈሳሽ ("ከጕበት ጋራ የሚገኝ ምግብ አሖምጣጭ የሆድ ውስጥ ባለከረጢት ዐረቄ ቅጠልያ ከድልኸ ጋራ ተበጥብጦ የሥጋ መብሊያ ይኾናል ይኸውም የበሬ የበየል የበግ ነው በሕዝብ አነጋገር ዐሞት ይባላል") ።
ሐሰተኛ፡ ዋሾ/ውሸታም ("ሐሰት ወዳድ ሐሰት ተናጋሪ ዐብሎ መስካሪ በቃሉ የማ ይረጋ አታላይ መልቲ ሐሰተኛ ምስክር እንዲሉ") ።
ሐሰተኛነት፡ ሐሰተኛ መኾን ("ዋሾነት ቀጣፊነት መልቲነት") ።
ሐሰተኞች፡ ዋሾዎች/ዐባዮች (ማቴ. ፯፡
ሐሰቱ፡ የሰው ስም ።
ሐሰት፡ ውሸት/ዕብለት/ቅጥፈት ("የው ንት ተፃራሪ") ።
ሐሰን/ሑሴን፡ የፋጡማ መሐመድ ወንዶች ልጆች ("የሚያማምሩ መልከ መልካሞች ማለት ነው አባታቸው ዐሊ ናቸው") ።
ሐሰወ)፡ ዋሸ/ዐበለ (ግእዝ) ።
ሐሲዳ፡ ያሞራ ስም (ዘሌ. ፲፩፡ ፲፱) ።
ሐሳብ፡ ኅሊና፡ ዐሰበ ።
ሐሳዊ መሲሕ፡ ከውነት የራቀ ሐሰተኛ መምር ("ሐሰተኛ ክርስቲያን ውሸቱ አንድና ኹለት የማይባል") (፩ ዮሐ. ፪፡ ፲፰፡ ፪ ዮሐ. ፩፡ ፯) ።
ሐሳዊ፡ ዋሾ/ዐባይ/ቀጣፊ ።
ሐሳዌ መሲሕ፡ ክርስቶስን የሚያስተባብል/የማያምን ("ክርስቶስ እኔ ነኝ የሚል") ።
ሐረራዊ፡ የሐረር ሰው ("ከትግሬ የኼደ") ።
ሐረር (ሐረረ)፡ የከተማ ስም ("በሺዋ ምሥራቅ ያለ ታናሽ ከተማ በግንብ ቅጥር የተከበበ የታጠረ ቈላ ሞቃት ማለት ነው") ።
ሐረርኛ፡ የሐረር ቋንቋ ("ከግእዝ ካማርኛ ከትግሬ ከትግሪኛ ከአርጎባ ከጕራጌ የሚገጥም") ።
ሐረርጌ (ጌ፡ ሐረር)፡ ምድረ ቈላ በረሓ ("ካዋሽ ማዶ ያለ አገር ጠቅላይ ግዛት") ።
ሐረርጌዎች፡ የሐረርጌ ተወላጆች ።
ሐረግ ጣለ፡ ሐረግ ሣለ/መሰለ ("በሐረግ ሸለመ አስጌጠ") ።
ሐረግ፡ በመጽሐፍ አርእስትና በልብስ በዕቃ በጌጥ በጥልፍ ኹሉ በድጕስ በማዕድን ላይ የተጣለ የተቀረጸ የሐረግ ሥዕል ።
ሐረግ፡ ተራ የቅኔ ንባብ ("በቤትና በቤት መካከል ያለ") ።
ሐረግ፡ ዐረግ ።
ሐረጸ፡ በግእዝ ("ፈጩ" ማለት ስለ ኾነ - እኸል በተፈጨ ጊዜ እንዲፈደፍድና እንዲያተርፍ - ዐራጣም እንደዚያ ነው ") ።
ሐሩር፡ ሙቀት/ወበቅ/ትኵሳት/ላበት ።
ሐሩር፡ የሙቀት አገር ("ዕከክ በሰው ገላ ላይ ሽፍ የሚል የሚገነፍል") ።
ሐሩር፡ የስንዴ ዐራራ ጥቍር ቀለም የሚኾን ።
ሐራ (ሐሪር/ሐረረ)፡ ነጻ/ጨዋ ("ጭፍራ ወታደር") ።
ሐራ ሰማይ፡ መላእክት ።
ሐራ ሰማይ፡ ዐላዊ ንጉሥ ("እቀዝቃዛ ባሕር ውስጥ የጣላቸው አርባ ሰማዕታት") (ስንክ. መጋ. ፲፫) ።
ሐራ ሰማይ፡ ፀሓይ/ጨረቃ/ኮከብ ።
ሐራ ዘመን፡ የዘመን ጭፍራ ("ዓመቱን አንዳንድ ወር ተካፍለው የሚመግቡ ፲፪ ከዋክብት") ።
ሐራራ (ትግ. ሐረረ፡ ሠየ ጐመዠ)፡ የቡና ሡሥ ("ሥየታ ጕምዠታ ( የትን ባኾ ልማድ ዐመል የቡናውንና የትንባኾውን ዐራራነት ያሳያል") ።
ሐራጅ፡ ሙሼጥ፡ ኀራጅ ።
ሐር፡ (ሐሰወ) ።
ሐር (ሐሪር)፡ ቱት የሚባል ቅጠል እየበላ የሐር ትል የሚያደራው ሻካራ ነጭ ፈትል ("የሸረሪት ድር የሚመስል በያይነቱ ቀለም ሲገባ ግን ቀይ አረንጓዴ ብ፵ ሰማያዊ ኀምራይ ወይን ጠጅ ውጥኔ ይባላል") (ራእ. ፲፰፡ ፲፪-፲፮) ።
ሐር ማተብ)፡ ከሐር የተ ገመደ ማተብ ።
ሐር ዐምባ፡ (የሐር ዐምባ) በይ ፋት ውስጥ ያለ አገር ("የሐር ተራራ ወይም መንደር ማለት ነው") ።
ሐርበኛ (ኞች)፡ ጦረኛ ።
ሐርነት አገኘ፡ ተለቀቀ/ተተወ ("ነጻ ወጣ") ።
ሐርነት ወጣ፡ ከጌታው/ከመቤቱ ቤት ተሰናበተ/ኼደ ።
ሐርነት፡ ነጻነት/ነጻ መኾን ።
ሐቀኛ (ኞች)፡ ደግ/እውነተኛ/ትክ ክለኛ ሰው ።
ሐቀኛነት፡ ሐቀኛ መኾን ("እውነተኛ ነት") ።
ሐቅ (ሐቂቅ/ሐቀ)፡ ዐቅ/እውነት/ርግጥ/ትክክል ።
ሐበላ (ትግ ሐበለ፡ ዐይን ላይ ጣለ)፡ ያይን ጉም ዕርርት ።
ሐበሻ (ዐረ. ሐበሽ)፡ የነገድ ስም ("ፊት ከባቢሎን ኋላም ከየመን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ከሳባ ከአቢስ የተደረቡ ሕዝብ ጀበል ሐበሽ እንዲል የመኒ") ።
ሐበሻ፡ በየመን የነበረ ክርስቲያን ("ያጤ ካሌብ ሥሪት የሐበሻ ቤተ ክሲያን ሲል ከኒሰት እልሐበሽ እንዲል የመኒ") ።
ሐበሻ፡ ያገር ስም ("ጽርኣውያን አገራችንን በኵሽ ኢትዮጵያ በአሲስ አቢሲኒያ እንዲሏት ዐረቦችም በሐበሽ ሐበሽ ብለዋታል የሐበሽም ትርጓሜ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ሕዝብ ማኅበረ ሕዝብ ጉባኤ ሕዝብ ማለት ነው ይላሉ ነገር ግን አቢስ ፊተኛ ሐበሽ ኋላኛ መኾኑን አንዘነጋም") ።
ሐበሾች (ሐበሻት)፡ የሐበሽ ነገዶች ("የሐበሻ ተወላጆች የዮቅጣን ዘሮች ሌሎችም በሐበሻ ያሉ ልዩ ልዩ ወገኖች ኢትዮጵያው ያን ሐበሻት ማለትም የ፮ቱ ነገደ ዮቅጣን ጠቅላይ ስም ነው እንጂ ዐረቦች እንደሚ ሉት ቅልቅል ማለት አይዶለም ጊዮርጊስ ወልደ ሐሚድም ልዩ ልዩ የጦርመሣሪያ በመ ሥራታቸው ብዙ አገር ለመያዝቻሉ ይላል") ።
ሐባብ፡ የነገድና ያገር ስም ("የትግሬ ቈላ በረሓ የሓባብ ትርጓሜ ፍቁር ወዳጅ ማለት ነው") ።
ሐባቦች፡ የሐባብ ተወላጆች ሕዝቦች ነገዶች ።
ሐብሐብ፡ በጢሕ ዱባ መሐሌ ።
ሐብል፡ ገመድ ("የሰዓት ያንገት ሰንሰለት (ግእዝ)") ።
ሐተተኛ (ኞች)፡ ሐተታ ወዳድ ("መርማሪ ተመራማሪ ከዚህ የቀረው የሐ ግስና ነባር በዐ ስለ ተለወጠ የዐን ግስ በተራው ተመልከት") ።
ሐተታ (ሐተተ)፡ ምርምር/ምርመራ ።
ሐተታ ወልደ ሕይወት፡ በ፲፮፻ ዓ. ም በግእዝ ቋንቋ የተጻፈ የፍልስፍና መጽሐፍ ።
ሐተታ ዘርዐ ያዕቆብ፡ ዝኒ ከማሁ ("የፊተኛው ደቀ መዝሙር የኋለኛው መምር ያገራቸውን ክብር የማይፈልጉ አንዳንድ ሐሰተኞች ሰዎች ግን እነዚህን ፈላስፎች የውጭ አገር ሊቃውንት ናቸው ይላሉ") ።
ሐች፡ ያለፈ፡ ኻች ።
ሐና ማሪያም፡ የማሪያም ሐና ("የማሪያም እናት እመቤታችን እናት አደግ ስለ ኾነች እናቷ በሷ ስም ትጠራለች") ።
ሐና፡ የወንድና የሴት መጠሪያ ስም ("ትርጓሜው ምሕረተ እግዚአብሔር ማለት ነው") ።
ሐናና ቀያፋ፡ ጌታችንን የሰቀሉ የካህናት አለቆች ።
ሐኔ (ዕብ. ሐኒት፡ ጦር)፡ ጐባጣና ሰፊ ጐራዴ ("ማረጃ ማወራረጃ ባንድ በኩል ስለት ያለው") ።
ሐኔ፡ ካሽጣጭ በታች ያለ ቀጥተኛ የሰገባ ግፍ ።
ሐኔ፡ የሐና ("ሐናዊ ሐናዬ የኔ ሐና ማለት ነው ወልደ ሐና በማለት ፈንታ ወልደ ሐኔ እንዲል ባላገር") ።
ሐንበል፡ ሻለቃ፡ ዐምበል ።
ሐኪም (ሐከመ)፡ መድኀኒተኛ/ባለመድኀኒት/ወሸባ/አግቢ/ፈዋሽ/ወጌሻ ("ፈረ ንጆች ዶክተር ይሉታል") ።
ሐኪምነት፡ ሐኪም መኾን ("ወጌሻነት") ።
ሐኪሞች፡ ፪ና ከ፪ በላይ ያሉ ብ ዙዎች ።
ሐዊ፡ የመጽሐፍ ስም ።
ሐዊ፡ የሰው ስም ("እሳታዊ ማለት ነው") ።
ሓዊ፡ የጻፈው መጽሐፍ ።
ሐዋላ (ዐረ)፡ የመንገድ ኪራይ ከ ፍሎ ገንዘብን ካንዱ አገር ወደ ሌላው ማዛወር ።
ሐዋርያ (ሖረ)፡ መንገደኛ/መልክተኛ/ኻያጅ/ ሰባኪ ("ሐዋርያ ጴጥሮስ ሐዋርያ ጳው ሎስ እንዲሉ") ።
ሐዋርያ መስቀል)፡ ዲያቆን በመጾር ላይ የሚይዘው ታላቅ መስቀል ።
ሐዋርያት፡ ብዙዎች መንገደኞች ("መንገድ ዐላፎች የወንጌል መልክተኞች ሰባኮች የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት አስቀድሞ ዓሣ አሥጋሪ ልብደ ሠሪ በቅሎ ገሪ የነበሩ አር ድእት ፲፪ቱ ሐዋርያት እንዲሉ") ።
ሐዋርያነት፡ ሐዋርያ መኾን መንገደኛ ነት ።
ሐዋት፡ ወንድሞች፡ ኀዋት ።
ሐውልት (ሐወለ)፡ የዐምድ ስም ("የቀድሞ ሰዎች አሸዋና ኖራ አዋሕደው ደንጊያ ጠርበው አለዝበው በላዩ ጽፈት ጽፈው ያቆሙት መታሰቢያ ሲበዛ ሐውልቶች ይላል") ።
ሐውልት፡ የመጽሐፍ ገጽ አካፋይ ።
ሐውት፡ የፊደል ስም ሐ ("ሕይወት ማለት ነው") ።
ሐውዜን፡ የእኸል ጐተራ ጕርጅ ።
ሐውዜን፡ ያገር ስም ("በትግሬ ውስጥ ያለ አገር") ።
ሐዘን፡ (ሐዘነ)፡ ዐዘን ።
ሐዛብ (ቦች)፡ አረመኔ ("ፊት ኦሪትን ያልተቀበለ ኋላም በወንጌል አምኖ ያልተጠመቀ ለንጨት ለደንጊያ ለውሃ ለእሳት ለፀ ሓይ ለጨረቃ ለኮከብ ላውሬ ለወፍ ለልዩ ልዩ ፍጥረት የሚሰግድ ኀጢአትን ኹሉ የሚሠራ ጨካኝ እከሌ ሐዛብ ነው እንዲሉ") ።
ሐዝሐዝ አለ፡ ውሽኛ ጮኸ ።
ሐዝሐዝ፡ ማጥ ረግረግ (ግእዝ) ።
ሐይ (ትግ. ሐባ ሕያይት)፡ እን ስሳ ።
ሐይ (ዕብ. ሐያ)፡ የቤት/የዱር አ ውሬ ።
ሐይ በል፡ ጠብቅ/ከልክል ።
ሐይ አለ፡ አገደ/ከለከለ ("ከብትን በሬን ተው ዕንክ ላምን ጅሥ ጥጃን ወገ ዝን ውስ ፈረስን ቼ በቅሎን መጭ አህያን ወሽ ቲውሽ ፍየልን እር በግን ችግ ግልገልን ክስ ውሻን ና ኺድ ድመትን ክፍ ብስ ዶሮን ዕሽ አለ") ።
ሐይቅ (ቆች)፡ የባሕር ዳር ወሰን ድንበር ።
ሐይቅ፡ በሾጣጣነት ወደ ባሕር የገባ የምድር ሠላጤ ("ልሳነ ምድር") ።
ሐይቅ፡ በወሎ አውራጃ ያለ ደሴት ("በባሕር የታጠረ የተከበበ") ።
ሐይወ)፡ ዳነ/በጤና ኖረ (ግእዝ) ።
ሐደደ (ዐረ. ሐደ)፡ ቀጠቀጠ ብረ ትን ።
ሓደደ፡ ሑዳድ ዐረሰ/ዘራ/ሀረሙ/ ዐጨደ/ወቃ ።
ሐዲስ (ሐደሰ)፡ በቁሙ ዐዲስ ("አሮጌ ያይዶለ ልብስ ወይም ሌላ ነገር") ።
ሐዲስ፡ የብሉይ ፍሬ ("ከማቴዎስ ወን ጌል እስከ ራእየ ዮሐንስ ያለው የሐዋርያት መጽሐፍ ሌላውም በዘመነ ወንጌል ከአር ድእት ከሊቃውንት የተጻፈው ኹሉ") ።
ሐዲድ (ዐረ)፡ ብረት ("የብረት ወገን የባቡር ሐዲድ እንዲሉ") ።
ሐዳድ፡ ቀጥቃጭ ።
ሐገገ)፡ ሐዲስ ።
ሐገገ)፡ ዐገገ (ግእዝ) ።
ሐግ (ሐግጎ)፡ ማገግ/መገሠጽ ።
ሐግ አለ፡ ገሠጸ/ተቈጣ/መከረ/ዘ ለፈ ("ሕግን ነገረ በሕግ ቀጣ") ።
ሐጭ አለ፡ ሮጠ/ጋለበ/በረረ ።
ሐጭ አለ፡ ኺድ አለ ("ከለከለ") ።
ሐፀነ)፡ አሳደገ (ግእዝ) ።
ሑዳደኛ፡ ሑዳድ ዐራሽ ።
ሑዳዳቸው፡ የርሳቸው/የነርሱ ሑዳድ ።
ሑዳዴ/ሑዳዳዊ፡ የሑዳድ ("ዐቢይ ጾም ከጾመ ፈቃድ የሚበልጥ ሰማያዊ ገበሬ ክርስ ቶስ የሖደደው ዛሬም እስራኤል ዘነፍስ (ክርስቲያኖች) በያመቱ የሚሖድዱት መንፈሳዊ ዕርሻ") ።
ሑዳድ (ዶች)፡ ትግ ሕዳድ ("ለም ምድር") የንጉሥ/የሻለቃ (ያገረ ገዢ) የመ ልከኛ የኾነ ሰፊ መሬት ማለፊያ ዕርሻ ገባር የሚያርሰው ("ዕጣ ሑዳድ እንዲሉ") ።
ሒሳብ (ሐሰበ፡ ሐሳብ)፡ ስሌት/ስፍር/ቍጥር/ልክ/መጠን ።
ሒና፡ እንደ እንሶስላ ሴቶች እግራቸውንና እጃቸውን የሚያሞቁት ("ፊታቸው ሳይ ቀር የሚቀቡት") ።
ሔት፡ ጥያቄ፡ የት ።
ሔት፡ የፊደል ስም ሐ ።
ሔዋን (ሐይወ)፡ መዠመሪያ ሴት ("የአዳም ሚስት ትርጓሜው ሕይወት ማለት ነው") ።
ሕልመ ሌሊት፡ ሌሊት በሕልም ሴት መዳሰስ ።
ሕልመ ዮሴፍ፡ ለጠጅ አሳላፊና ለንጀራ አዛዥ ለፈርዖንም ዮሴፍ የተረጐመላ ቸው ሕልም (ዘፍ. ፵፡ ፲፫, ፲፰, ፲፱፡ ፵፩፡ ፲፭, ፪) ።
ሕልመ ዮሴፍ፡ የአስማት መጻፍ ("አንዳንድ ሰዎች የሚደግሙት") ።
ሕልመልመሌክ፡ የሰጋ ኮከብ ።
ሕልማም (ሞች)፡ ሕልም የሚያይ ("ባለሕልም") (ይሁ. ፰) ።
ሕልም (ሐለመ)፡ ሌሊት ተኝቶ በዐይነ ልብ የሚታይ ነገር ("እውነተኛና ሐሰተኛ እውነተኛው ራእይ ሐሰተኛው ምት ሀት ቅዠት ከንቱ ይባላል") ።
ሕመት፡ ሐራ ።
ሕመት፡ የዕጣን ዐመድ ዐ መተ ።
ሕማማተ መስቀል፡ ፲፬ የመስቀል መከራዎች ("ጌታችን በዕለተ ዐርብ የስቅለት ለት የተቀበላቸው እነዚሁም መያዝ የኋሊት መታሰር በጥፊ መመታት መገረፍ መራቈት ኣክሊለ ሥክ ኵርዐተ ርእስ መስቀል መሸከም ድካም መውደቅ ከሐሞት ጋራ መፃፃ መጠጣት ስቅለት ውሃ ጥም መሞት ናቸው") ።
ሕማማት፡ ዕመሞች/ደዌዎች/መከራዎች/ ሥቃዮች ።
ሕማማት፡ ከሆሳዕና ዠምሮ እስከ ትንሣኤ ያለው ስምንት ቀን ።
ሕማም፡ ዕመም/ደዌ/በሽታ/መከራ/ሥቃይ ።
ሕምያር (ሮች)፡ ነገደ ዮቅጣን ሐበሻ ("ቀያይ የቀይ ዳማ ሕዝብ ጡብና ሸክላ የሚመሳስል") ።
ሕር ሕር አለ፡ ተንደቀደቀ/ተንበቀበቀ ("የጕረሮ") ።
ሕርመት/ትሕርምት (ሐረመ)፡ ምግብ መለየት ("ቀን እኽል ሳይቀምሱ ውሎ ማታ አንድ ጊዜ ጥሬ መብላት ውሃ መጠጣት") ።
ሕቅ አለ፡ ሞተ/ዐረፈ ።
ሕቅ/ሕቅታ፡ ዕቅ/ዕቅታ/ስርቅታ ("መጨረሻ ትንፋሽ የነፍስ መውጣት ግጥም ማለት") ።
ሕቋ፡ ዕቋን እይ ።
ሕብረ መልክእ፡ የመልክ ቀለም በ ያይነቱ ።
ሕብረ ሰማይ፡ ሰማይ የሚመስል የቍስል መድኀኒት ("የሚያቃጥል የሚያንገበግብ ከደንጊያ የሚገኝ የኩል የኒል ዐይነት ዳግመኛም በሕዝብ አነጋገር ክብረ ሰማይ ይባላል") ።
ሕብር (ሐበረ)፡ የቀለም ዐይነት ።
ሕንዝዝ፡ ጥንዝዛ ።
ሕንጻ (ሐነጸ)፡ የቤት ሥራ ("ጣራና ግድግዳው ባንድነት ከንጨት የተሠራ") ።
ሕክምና፡ ዝኒ ከማሁ ("ገላን የማገም የመተኰስ የመብጣት የመቅደድ የማከም የመጠገን የመድኀኒት መስጠት መቀባት ማጠ ጣት ሥራ ዘዴ") ።
ሕዋሳት፡ አካሎች (መልኮች) ፪ና ከ፪ በላይ ያሉ ።
ሕዋስ (ሖሰ)፡ ፭ የአካል (የመልክ) ስም ("ዐይን ዦሮ አፍንጫ አፍ እጅ በነፍስ በሥጋ የማየት የመስማት የማሽተት የመቅመስ የመዳሰስ መሣሪያ እግርና አባ ለ ዘር ቢጨመሩ ፯ ይኾናሉ") ።
ሕዛዛ፡ ቡሓ የራስ ዕከክ ።
ሕዝበ ናኝ፡ በ፲፭፻ ዓ. ም የነበረ የኢትዮጵያ ንጉሥ ።
ሕዝበ አስግድ፡ በ፲፫፻ ዓ. ም የነበረ የኢትዮጵያ ንጉሥ ።
ሕዝበ ክርስቲያን፡ የክርስቲያን ወገን ("በክርስቶስ ያመነ") ።
ሕዝባዊ (ውያን)፡ የሕዝብ ወገን ("ማይምን ጨዋ") ።
ሕዝብ (ሐዘበ)፡ ካንድ ወይም ከልዩ ልዩ ነገድ ተሰብስቦ ባንድ ስፍራ የተከማቸ ብዙ ሰው ("በጉባኤ በሸንጎ ባደባባይ በገበያ በማርገጃ ያለ የተቀመጠ") ።
ሕዝብ ኣሕዛብ፡ ሕዝብ እስራኤል ("አሕዛብ እንዳለፈው") (መዝ. ፻፲፯፡ ፩፡ ሮሜ. ፲፭፡ ፲፩) ።
ሕዝቦች፡ ብዙዎች ሰዎች/ነገዶች/ወገኖች ("አንድነት ያሉ ሰራዊቶች ጭፍሮች ሕዝበ እግዚአብሔር የግዜር ወገን እስራኤል") ።
ሕያው እግዚአብሔር፡ የነቢያት ማላ ("ዝናም እንዳይዘንም ሰማይን የሚዘጋ ተራ ራን የሚያፈልስ ባሕርን የሚያደርቅ") (፬ ነገ. ፲፯፡ ፳) ።
ሕያው፡ የማይታመም/የማይሞት ("ለባሕ ርዩ ጥፋት ኅልፈት የሌለበት እግዜር መልአክ ነፍስ ደኅነኛ ኗሪ ማለት ነው") ።
ሕያውነት፡ ደኅነኛነት/ነዋሪነት ።
ሕይወተ ሥጋ፡ የሥጋ መኖር/አኗኗር ("ሥጋ የተባለ ሰውነት ነው ልብስ ጕርሥ") ።
ሕይወተ ነፍስ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ("ሥጋ ወደሙ ምግባር ሃይማኖት") ።
ሕይወት፡ ደኅንነት/ጤና/ጤንነት ("መዳን መኖር") (ዘፍ. ፵፪፡ ፲፭, ፲፯) ።
ሕገ ልቡና፡ አዳም ሲፈጠር ከግዜር የተሰጠው ።
ሕገ መንግሥት፡ መንግሥት ያወጣው ባዋጅ ያጸደቀው የመንግሥት አቋም የበላይ ሕግ ።
ሕገ ርትዕ፡ ኦሪት ።
ሕገ ወጥ (ዕገ ውጡ)፡ ውፁአ ሕግ ("ከሕግ የወጣ ባለጌ ማን ዘራሽ ውሳኔ አፍራሽ") ።
ሕገ ጠብቅ፡ ኣስማት መድኀኒት ("የሕግ ሚስትን ሌላ ወንድ እንዳይደርስባት የሚጠብቅ") ።
ሕግ (ጎች)፡ የግዜር/የሰው ደንብ/ውሳኔ ("አታድርግ የሚል ሥርዐት ፲ቱ ቃላተ ኦሪት ፮ቱ ቃላተ ወንጌል ዐዋጅ ያጤ ሥር ተጽፎ ታትሞ የሚወጣ የሚታወጅ የሚነገር ማስታወቂያ") ።
ሕግ መምሪያ፡ ሕዝብ የመረጣቸው አማካሮች ("ላገር የሚጠቅም ሕግ የሚመሩበት ምክር ቤት የሕግ ረቂቅ የሚመነጭበት") ።
ሕግ መወሰኛ፡ ንጉሥ የሾማቸው አማካሮች ("የመንግሥት ሕግ የሚያመነጩበትና የሚመክሩበት ምክር ቤት") ።
ሕግ ተላላፊ፡ ሕግ አፍራሽ ኀጢአተኛ (ምሳ. ፳፮፡ ፳) ።
ሕግ አፈረሰ፡ ከሰው ሴት ኼደ ("፲ቱ ቃላትን ሻረ") ።
ሕግ አፍራሽ፡ ሕግን የጣሰ/ያፈረሰ ("ዐመፀኛ ወንጀለኛ ሌባ ቀማኛ ነፍሰ ገዳይ ቤት ኣቃጣይ አመንዝራ ሐሰተኛ ጒቦኛ አድላዊ የመሰለው ኹሉ") ።
ሕግ፡ ክብርና ድንግልና ።
ሕጸጽ (ሐጸ)፡ ጕድለት/ጐደሎነት/እ ንከን ።
ሕጹጽ፡ ጐደሎ ።
ሕፃነ አእምሮ፡ ዕውቀቱ በጣም ያነዕ ።
ሕፃናት፡ ዐራሶች/ጨቅሎች/እንቦቀቅሎች ።
ሕፃን ሞአ፡ አባ ጣርማ ("ሕፃን አሸነፈ ማለት ነው") ።
ሕፃን፡ ያይን አምሮት የልብ ምኞት የኾነ ዐራስ ጨቅላ ለጋ ቀንበጥ ("ጡት የሚጠባ ልጅ ለማይጠባም ይነገራል ትርጓሜው የሚያድግ ማለት ነው እሱም ወንዱን አባባ ሴቱን እማማ ይላል") ።
ሕፃንነት፡ ሕፃን መኾን ("ልጅነት") (መክ. ፲፪፡ ፩) ።
ሕጽር፡ ሽቱ ኅጽር ።
ሕፅነ አብርሃም፡ ያብርሃም አጠገብ ("የጽድቅ ስፍራ") (ግእዝ) ።
ሕፅን፡ ፪ና ፫ ራስና እግር ባላቸው ፊደሎች በየቅርጻቸው መካከል ያለው ክፍቱ ባዶው ("ትርጓሜው አጠገብ ማለት ነው ውስጥንም ያስተረጕማል") ።
ሕፅን፡ ብብት አጠገብ ።
ሕፅን፡ የጥብቆ/የእጀ ጠባብ ሠላጤ/ወሽመጥ ።
ሖመጠጠ፡ ሐሚታ ።
ሖመጠጠ (ዕብ. ሐሜጽ)፡ ቦካ/ኮመጠጠ/ሸመጠረ ።
ሖምጠጥ አለ፡ ሖመጠጠ ("ሸምጠር አለ") ።
ሖምጣጢ፡ ያውሬ፡ ስም፡ እንደ፡ ተኵላ፡ ያለ፡ ጠባየ፡ ክፉ፣ አውሬ፡ ቍጡ፡ በግእዝ፡ መፄፂት፡ ይባላል።
ሖምጣጣ፡ የሖመጠጠ ("ኮምጣጣ መጣጣ መራራ ሰንፋጣ አውጥ ዐሞጭ") ።
ሖምጣጤ፡ የሖምጣጣ ዐይነት ወገን የካረመ ወይን ጠጅ ።
ሖረጠ (ሐረጸ)፡ ወጥ አፍን ፈጀ/ኣቃጠለ ("ምራቅን ኰሰተረ ድልኽ ስለ በዛ") ።
ሖቅ፡ ለፈረስ የሚነገር ቃል ("በሐቅ ጋልብ ማለት ነው") ።
ሖናና፡ ሞኝ/ቂል ።
ሖደደ፡ አርባ ቀን ጦመ ("ውሎ አንድ ጊዜ በ፱ ሰዓት መብል በላ ውሃ ጠጣ ክፉ ከመስማት ከማየት ከመናገር ተከለከለ") ።
ሖዳጅ (ጆች)፡ የሖደደ/የሚሖድድ ("ገባር ጦመኛ") ።
ሖጭ አደረገ፡ ብር አቀረበ/ሰጠ ።
ሖጭ፡ መቅረብ/መሰጠት/መቃጨል ።
ሖጻ፡ አሸዋ፡ ኆጻ ።
ሖፃ፡ አሸዋ፡ ኆጻ ።

No comments:
Post a Comment