ቸ (ከተ): የተደቀለ የአማርኛ ፊደል (ቸከለንና ቸኩለን ተመልከት)።
ቸ (የነና፣ የከ፣ የጸና፣ የቀ፣ የጄ ተወራራሽ): "ኄር"፣ "ቸር"፣ "ክህለ"፣ "ቻለ"፣ "ጸፈቀ"፣ "ቸፈገ"፣ "ቃመ"፣ "ቻመ"፣ "ጀነነ"፣ "ቸነነ" የመሰለው ኹሉ (ማለት ነው)።
ቸ (የፊ): ወራሽ።
ቸለለ (ጸለለ): ተወ፣ ለገመ (ተለለን ተመልከት)።
ቸለሰ: ከነበለ፣ ደፋ፣ ገለበጠ፣ ጨርሶ አፈሰሰ (ብዙ ውኃን፣ ደምን)። በቀንድ አስተኛ (ማንቍርትን፣ ወንገትን ወደ ላይ፣ ማዥራትን ወደ ታች አደረገ)፡ ዘለሰ (ለማረድ)።
ቸላሳ/ችልስ: የተቸለሰ፣ የፈሰሰ (ክንብል፣ ዝልስ)።
ቸላሽ (ቸላሾች): የቸለሰ፣ የሚቸልስ፣ አፍሳሽ።
ቸል/ቸለል: መተው፣ መጥመም፣ መለገም፣ ዝም ማለት (ዘዳ ፴፩፡ ፯-፰)።
ቸል አለ/ቸለል አለ: ጠመመ፣ ለገመ፣ ዝም አለ።
ቸልተኛ (ቸልተኞች): ቸል የሚል። (መዝ ፲፭፡ ፬፡ ምሳ ፩፡ ፴፪፡ ፲፫፡ ፲፭)።
ቸልታ: ቸል ማለት፣ ጥመት፣ ልግም፣ ዝምታ (ኤር ፵፰፡ ፲)።
ቸልቻ (ንኡስ አግባብ): ና። ምሳሌ: "ብሉና ጠመቱና ዕረፉ።" (ቦዝ አንቀጽ) "ሰው ዐርሶ ወይም ነግዶ ያድራል" (እንዲሉ።)
ቸመቸመ (ከተመተመ): ደመደመ፣ ቸረቸመ፣ አጠረሰ፣ አስተካከለ። አብዝቶ ሠራ፡ ዘራ፡ ቤትን፡ እኽልን አቆመ፡ ጦርን።
ቸምቻሚ: የቸመቸመ፣ የሚቸመችም፣ አብ።
ቸምቻማ/ቸርቻማ: ደምዳማ።
ቸሰረ: ረፈቀ፣ ደነሰረ።
ቸሰቸስ/ቸስቻሳ: የተንቸሰቸሰ፣ የሚንቸሰቸስ (እርጥበት ያለው እንጨት)።
ቸሳሪ: የቸሰረ፣ የሚቸስር (ደንሳሪ)።
ቸሳራ/ችስር: የተቸሰረ (ደንሳራ፣ ድንስር)።
ቸስቸስ አለ: አጐበጐበ።
ቸረ/ቼረ (ከሰኀየረ/ኄረወ): ሰጠ፣ ናኘ፣ ለገሰ።
ቸረቸመ: ሰበረ፣ ሸረፈ፣ በጠፈ፣ አጠረሰ፣ ስለት አሳጣ።
ቸረቸረ (ከሰተረተረ): ፈታ፣ በተነ፣ ተነተነ፣ ዘረዘረ (በጥቂት በጥቂቱ)፣ ሺ (ዕቃን ከመደብር ገዝቶ በዳ ተቀምጦ)።
ቸረቸፈ: ቸረቸመ።
ቸረፈፍ/ቸርፋፋ: የተንቸረፈፈ፣ የሚንቸረፈፍ (እራፊ፣ እንችርፍ)።
ቸሩ: ደጉ፣ ለጋሱ፣ ዶልዷሊ፣ ሳይለምኑት ዝናምን ለዘር፣ ጠልን ለመከር የሚሰጥ መጋቢ ዓለማት። ምሳሌ: "ስለ ቸሩ እግዚኦ" እንዲል ተማሪ።
ቸሪቱ/ቸሪት: ደጊቱ/ደጊት።
ቸሬ (የሰው ስም): "የኔ ቸር" ማለት ነው። ቸሬ የሚባል ሰው ከ፲፱፻፳፰ ዓ.ም በፊት በአዲስ አበባ ይሠራው የነበረ የጥይት ክልስ ነው።
ቸር ቸር አለ: መር አለ (እባቡ፣ ነብሩ)።
ቸር አገር ሄደ: ሞተ፣ ነፍሱ ወደ ሰማይ ዐረገች።
ቸር አገር: የቸር አገር፣ ገነት፣ መንግሥተ ሰማይ፣ ደግ አገር።
ቸር/ቼር (ኄር): ደግ፣ ጻድቅ ሰው፣ ለጋስ፣ እባ መስጠት፣ እጀ ሰፊ፣ ለነፃ የማይል፣ ለድኻ ቆርሶ የሚያጐርስ፣ ቀዶ የሚያለብስ። (ዮሐ ፯፡ ፲፪፡ ፲፡ ፲፩)። በጎ፣ ደህና። ምሳሌ: "ቸር ያውልኽ"፡ "ቸር ያሳድርኽ"፡ "ቸር ያሰማኽ" እንዲሉ።
ቸርቻሚ: የቸረቸመ፣ የሚቸረችም (ሽሪፊ፣ አጥራሽ)።
ቸርቻማ: ሰባራ፣ ሸራፋ።
ቸርቻሪ (ቸርቻሪዎች): የቸረቸረ፣ የሚቸረችር (በታኝ፣ ተንታኝ፣ ዘርዛሪ)፣ ከመደብር ውጭ ሽያጭ።
ቸርቻሪነት: ቸርቻሪ መኾን።
ቸርነት (ኂርውና): ቸር መኾን፣ ለጋስነት። (፩ሳሙ ፳፡ ፲፭፡ ሉቃ ፭፡ ፪ቆሮ ፮፡ ፮)። (የሰው ስም)።
ቸሮች (ኄራን): ሰዎች፣ ለጋሶች፣ ደጃች ሰዎች፣ ጻድቃን።
ቸበቸበ (ጨበጨበ): ጣለ፣ መታ፣ ደበደበ። ምሳሌ: ወጣ እኽልን በለበት። እሳትን በአፈር ወይም በቅጠል አጠፋ። በርካሽ ሸጠ። ዐረደ፣ ቈረጠ።
ቸባቸበ: ወቃቃ፣ ደባደበ።
ቸብ ቸብ አደረገ: እጁን ጸፋ፣ መላልሶ አጨበጨበ።
ቸብ አደረገ: ጭብጨባ ዠመረ። ምሳሌ: "ቸብ አድርግ" እንዲል ዘፋኝ። በፍጥነት ሸጠ፣ ለወጠ።
ቸብቸቦ: ራስ፣ ካንገት በላይ ያለ የሰውነት ክፍል (ቁንጮንና ቆንዳላንም ያስተረጕማል)። ምሳሌ: "ዳዊት የጎልያድን ቸብቸቦ በቈረጠ ጊዜ የፍልስጥኤም ሰዎች ድል ኾነው ሸሹ።" (የወረብና የቅኔ) ጭብጨባ፣ ከጭብጨባ ጋራ የሚባል ወረብ።
ቸብቻቢ: የቸበቸበ፣ የሚቸበችብ (ወቂ)።
ቸቸረ: ገፈረ፣ ቃመ።
ቸቻሪ: የቸቸረ፣ የሚቸችር (ገፋሪ፣ ቃሚ)።
ቸነነ: ጀነነ፣ አኰራ፣ ቈነነ፣ አጓደደ። ወነገ፣ ወሰጠ።
ቸነኔ/ቸናና/ችንን: የተቸነነ (ጅንን፣ ቍንን)። የተወነገ (ውንግ)።
ቸነከረ (ከነከረ፡ ተከለ): ሰመረ፣ በችንካር ከእንጨት ጋራ ወጋ፣ መታ፣ አያያዘ፣ አጣበቀ፣ አናኘ፣ አነከረ።
ቸነፈር (ከሰነፈረ): የበሽታ ስም፣ ዕልቂት፣ መቅሰፍት፣ ከጦርነት በኋላ የሚመጣ፣ ሰውን እያናፈረ ቶሎ የሚገድል ሕመም። (በግእዝ ብድብድ ይባላል)። ምሳሌ: "ሀባ ቸነፈር" እንዲሉ። (ዕን ፫፡ ፭፡ ማቴ ፳፱፡ ፯)።
ቸናኝ: የቸነነ፣ የሚቸንን (ጀናኝ፣ ቈናኝ)።
ቸንማ: ከርሳስ የተበጀ፣ የገበጣ ጠጠር።
ቸንቧ ቸንቧ አለ: በጭርቅ በጭርቅ አለ።
ቸንቻም (ቸንቻሞች): ድዳም፣ ቸንቹ። የዓፈር ከንፈር።
ቸንች: ድድ፣ የድድ መስመር።
ቸንካሪ: የቸነከረ፣ የሚቸነክር።
ቸከ (ከስሕከ): ኣደፈ፣ ለመመ፣ ደገደገ።
ቸከለ (የግእዝ): ቸከለና ቸኰለ የአማርኛ ናቸው። ቀበቀበ፣ ከሰመ፣ እመሬት ኣገባ፣ ሻጠ፣ ወተፈ፣ ሸጐጠ፣ አቆመ (፩ኛ ቆሮንቶስ፡ ፫፡ ፮)።
ቸከቸከ: ውኃ ነቀሰ፣ ጠቀጠቀ።
ቸካይ: የቸከለ፣ የሚቸል (ቀብቃቢ)።
ቸክ አደረገ: ጠቅ አደረገ።
ቸክ አደረገ: ጠቅ አደረገ።
ቸክ: ውግት።
ቸኰለ: ጠደፈ፣ ፈጠነ (በሥራ፣ በነገር)። (ተረት): "የቸኰለች አፍሳ ለቀመች።"
ቸኰል (የሰው ስም): "ቶሎ ተወለደ" ማለት ነው።
ቸኳይ (ቸኳዮች): የሚቸኵል፣ ጠዳፊ።
ቸው (የሩቆች ወንዶችና ሴቶች ዝርዝር): ምሳሌ: "እሱ እነሱን ዐወቃቸው፡ ወደዳቸው።" (ጥሬ ሲገባ) "ቤታቸው፡ ሥራቸው።"
ቸገረ: ጠፋ፣ ታጣ፣ ጨነቀ፣ ተሳነ። (ተረት): "የቸገረው እርጉዝ ያገባል፡ የባሰበት እመጫት።" (ተገረን አስተውል)።
ቸጋሪ: የቸገረ፣ የሚቸግር (ልብስ፣ ጕርሥ)።
ቸግሮ: ገዶ፣ ጨንቆ፣ ተስኖ።
ቸፈረ (ከሰሰፈረ): ቃመ፣ በአፍ መላስ።
ቸፈቸፈ (ከሰተፈተፈ): ጨቀጨቀ፣ ጨፈጨፈ፣ ሸፈሸፈ። አዠ፣ አካፋ (አደረገ)።
ቸፈቸፍ: ጨፈጨፍ።
ቸፈነነ (ከሰቸነነ): ጀነነ፣ አኰራ።
ቸፈገ (ከሰጸፈቀ): ፈተ፣ ጠቀጠቀ፣ አቀራረበ፣ አበዛ፣ ጅብ አደረገ።
ቸፋሪ: የቸፈረ፣ የሚቸፍር (ቃሚ)።
ቸፋፈር: እቃቃም፣ መቸፈር።
ቸፍቻፊ (ተፍታፊ): የቸፈቸፈ፣ የሚቸፈችፍ (ጨቅጫቂ፣ ፍረ)።
ቸፍቻፋ: ጨቅጫቃ፣ ነገረኛ።
ቹ (ቁ): (የሩቅ ወንድ ዝርዝር) በብዙዎች ስም መጨረሻ የሚነዝር።
ቺን (የአገር/የነገድ ስም): ሺን። (ዝርዝር) "እኛ" የሚሉ ወንዶችና ሴቶች፡ የአንቀጽና የጥሬ ዝርዝር። ምሳሌ: "እሷ እኛን ዐወቀችን፡ ዐይናችን፡ ዦሯችን።"
ቺኮሮ: የተክል ስም፣ የባሕር አገር ተክል ነው።
ቻ (ቅጥያ): በስም መጨረሻ ላይ እየገባ ምእላድ የሚሆን። ትርጓሜውም ዓይነትንና ሁኔታን ያሳያል። ምሳሌ: ዳር፡ - ዳርቻ፣ ዐፈር፡ - ዐፈርቻ፣ ፀረም፡ - ዐራሙቻ፣ ሥር፡ - ሥርቻ፣ ጥል፡ - ጥላቻ።
ቻለ (ክህለ): ተሸከመ፣ ወሰነ፣ ያዘ፣ አጻመረ፣ ጨረሰ፣ ማሰ።
ቻል (ከሃል): (በሴት ልጅ ላይ) "አትተው"፡ "ሚስት አድርግ"። (ለለፈና ለደፈረ ልጃገረድ ይነገራል)። ዐሥረ ፈጅ ጋን።
ቻመ: ቃመ (ቸፈረን እይ)።
ቻቻታ: ጩኸት (ቻቻ)። የጉባኤ ጩኸት።
ቻቻቼ: ከላይ ካለው ጋር ተመሳሳይ፣ ጩኸት (ቻቻ)።
ቻች (ከሰተሐተ): ታናሽ ጥዋ፣ የመንተል ዓይነት። (መስቴን፣ ቡይትንና በግራትን ተመልከት)።
ቻይ (ከሃሊ): የቻለ፣ የሚችል፣ ተሸካሚ፣ ወሳኝ፣ ታጋሽ፣ ልበ ሰፊ፣ ነገር ዐላፊ፣ ቻይ ተክልሻይ።
ቻይ: የሚችል (ቻለን እይ)።
ቼ (ኧዬ): (ዝርዝር) "እኔ" ለሚሉ ወንድና ሴት ባለቤትነትን የሚያሳይ። ምሳሌ: ላሞች፡ - ላሞቼ (የኔ ላሞች)፣ ፈረሶች፡ - ፈረሶቼ (የኔ ፈረሶች)። (ቃለ ምልልስ) ፈረስን ለመከልከል፣ ለመንዳትና ለመጋለብ የሚነገር ቃል። ምሳሌ: "ቼ ፈረሴ ቍና ገብሴ" እንዲሉ ልጆች።
ቼ በለው (ዜማ): የክራር መቺ ዘፈን አዝማች።
ቼ ቼ ቼ (የፈረስ ምስጋና): ሰንጋ ምት በማሲንቆ። "ና ቼ ቼ ቼ ቼ ና ቼ ቼ ቼ ቼ" (ከፈረሰኞች የምናውቃቸው በሻኽ አቦዬ፣ ኀይሌ አንዳርጋቸው)። (ቼቼን እይ)።
ቼቼ አለ: አዘለ፣ በዠርባ ተሸከመ (ቼን ተመልከት)።
ቼቼ: ማዘል፣ እንቡቡ በታች መኾን።
ቼክ: ልዩ ወረቀት፣ ከባንክ ገንዘብ ማዘዣ።
ች (ቅጥያ): ስምን ለማብዛት የሚውል፣ "ዎች" ማለት ነው። (ቅጥያ) ለሩቅ ሴት የዘማችና የነባር ግስ ዝርዝር።
ችሃ (የአገር/የነገድ ስም): ከሰባት ቤት ጕራጌ አንዱ ችሃ ይባላል።
ችለሳ: ክንበላ፣ ግልበጣ።
ችለሳ: ክንበላ፣ ግልበጣ።
ችላ ባይ: ችላ የሚል፣ ቸልተኛ፣ ሀኪተኛ።
ችላ አለ: ቸል አለ፣ ተከየ።
ችላ አይቶ: እንዳላዩ፣ ሰምቶ እንዳላሰሙ መኾን። ምሳሌ: "መግዛት ቢያምርኽ ችላ፡ ጥጋብ ቢያምርሽ ጠላ" እንዲሉ።
ችላ: ቸል፣ ተወት፣ ሀኬት።
ችልስ ችልስ አለ: ፍስስ ፍስስ አለ።
ችልስ አለ: ግልብጥ አለ፣ ተቸለሰ።
ችልስ አደረገ: ድፍት አደረገ፣ ቸለስ አለ።
ችሎተኛ (ችሎተኞች): በችሎት የሚቀመጥ፣ ነገረተኛ።
ችሎታ: የሥራ ዕውቀት።
ችሎት (ክሂሎሁ): ታግምት። (ክሂሎት) ዳኝነት፣ ሙግት፣ ክርክር። (የዳኝነት ሥራ ብዙ ትዕግሥትና ዕውቀት ስለሚፈልግ ችሎት መቻል ተባለ)። ሥልጣን፣ መብት። (ለዜና ፳፱፡ ፲፩፡ ዮሐ ፲፡ ፲፰)። ሸንጎ፣ አደባባይ፣ ዐውድ።
ችሎት ተመለሰ: ዳኛ ተነሣ፣ ጉባኤው ተበተነ።
ችሎቶች: ሥልጣኖች፣ መብቶች።
ችምችም ለፎ: ብዙ ሰራዊት (ለፎን ተመልከት)። ዘንጋዳ አበቃቀሉ፣ ብዛት ያለው።
ችምችም አለ: በዝቶ ታየ።
ችምችም ያለ: ጭፍቅ፣ ችፍግ ያለ።
ችምችም: የተቸመቸመ፣ ችርችም፣ ስለት መንደር፣ ብዙ ጦር።
ችምችሞ: ብዙ ዓይነት ምግብ።
ችሰራ: ድንሰራ።
ችስ አለ: ፍም ወይም ትኩስ ቈሎ ውሃ በገባበት ጊዜ የጪስ የላበት ድምፅ አሰማ።
ችስር አለ: ድንስር አለ፣ ተቸሰረ።
ችስችሳ: የቈላ ወይም የበረሓ ጕንዳን ምሥል (ሺሾ)።
ችርቸራ: መቸርቸር።
ችርቻሪ/ችርቻሮ: ዝርዘራ፣ ብተና፣ ትንተና፣ የብትን፣ የትንትን ዕቃ አሻሻጥ።
ችርችም አለ: ጥርስ አለ።
ችርችም: የተቸረቸመ፣ ስብር፣ ሽርፍ።
ችርንችር: አራት ማእዘን ያለው እንፊት፣ በትረ ሙሴ።
ችሮታ (ኂሩት): "አገኘዋለሁ፡ ይመለስልኛል" የማይባል ስጦታ፣ ቸርነት።
ችብቸባ: ውቂያ፣ ጭብጨባ።
ችቦ: የጭራሮ መብራት፣ ዳቦት፣ ቲሃ።
ችቸራ: የመቸቸር ኹኔታ።
ችችር: የተቸቸረ፣ የተገፈረ፣ በጕንጭ ውስጥ ያለ ጥፊ።
ችንች: ሽንቶ፣ ስንክ ነጭ። (አባ ጨዓረ) ከመከር በኋላ የእንቡስንና የትለምን ዛፍ ቅጠል ከታች እስከ ላይ በልቶ የሚስ።
ችንከራ: የመቸንከር ሥራ።
ችንካር (ችንካሮች): አራት ማዕዘን ያለው የዱሮ ምስማር። (ልብ) ውጋት። በቁመትም በውፍረትም ከዛሬው ይበልጣል። (በግእዝ ቀኖት ይባላል)። (ኢሳ ፳፪፡ ፳፭)። (ማዕድን) ከድንጋይ የሚገኝ፡ መጣብቅ (ነው)። የተሠራውን ወይም የተሰበረውን የነሓስና የመዳብ፣ የብርና የወርቅ ዕቃ ጥቂት ክብረ ሰማይ ተጨምሮበት ማያያዣ፡ ማገናኛ። ሳንቃን ከሳንቃ የሚያገናኝ ውስጣዊ የእንጨት ቅርቃር (ሰፊና ቀን)። (ዘፀ ፳፮፡ ፲፯)።
ችንክር: የተቸነከረ፣ የተወጋ፣ የተጣበቀ። ቍንወት ብረት (የጌታችን እጅና እግር)።
ችኩል (ችኩሎች): የቸኰለ፣ ጥዱፍ (መክ ፯፡ ፱፡ ፪ጢሞ ፫፡ ፬)። ምሳሌ: "የዥብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል" እንዲሉ።
ችኩልነት: ጥዱፍነት።
ችካል: የእንጨት፣ የብረት ቅብቃብ (መሳ ፭፡ ፳፮)።
ችካሎች: ቅብቃቦች (ዘኍ ፬፡ ፴፪)።
ችካም: በጥርሱ ላይ ችክ ያለበት፣ የበዛበት።
ችክ (ችኽ): የጥርስ እድፍ፣ ልማም፣ ስሓ፣ ሳካ።
ችክ ምንችክ አለ: ሞዘዘ (መነቸከን እይ)።
ችክ አለ: ሙዝዝ አለ።
ችክ: የብስ ስም።
ችክል: የተቸከለ፣ የተቀበቀበ፣ ቅብቅብ።
ችክታ: ያፍላ፣ የውበት ተቃራኒ፣ አለማማር፣ የፊት መብረድ፣ ችክ ማለት።
ችኮ: ሞዛዛ፣ ዝኝ፣ መንቻካ።
ችኰላ: ጥድፊያ፣ ፍጥነት (ዘዳ ፲፮፡ ፫፡ ገላ ፮፡ ፩)።
ችኹ: (የቅርቦች ወንዶችና ሴቶች የአንቀጽና የስም ዝርዝር) ምሳሌ: "እሱ እናንተን ዐወቃችኹ፡ እጃችኹ፡ እግራችኹ።"
ችጉር: የተቸገረ፣ ችጋረኛ፣ ራብተኛ፣ ዕርዝተኛ። (ጥቸ) መቸገር: መጨነቅ፡ ማጣት፡ መራብ፡ መጠማት፡ መታረዝ።
ችጋረኛ (ችጋረኞች): ራብተኛ፣ ቀጠና የያዘው ሰው፣ ይልሰው ይቀምሰው የሌለው (መዝ ፱፡ ፲፰፣ ፲፡ ፰፣ ፬፣ ፱፡ ፱፣ ፲፪፣ ፻፪፡ ፲፯፡ ኢሳ ፴፪፡ ፯)።
ችጋር: ራብ፣ ጠኔ (ምሳ ፯፡ ፲፩)።
ችግ (ቃለ ምልልስ): በግን ለመከልከል የሚነገር ቃል ነው። "ዘሩ ሸገገ ነው።"
ችግ አለ: ከለከለ፣ መለሰ (በግን)።
ችግረኛ (ችግረኞች): የተቸገረ፣ ችግር የገባው፣ የጸናበት፣ ድኻ።
ችግሬ: የችግር፣ መናኛ ሥራ፣ ልብስ፣ ጣራ ሥሥ (የፈረንጅ ምላጭ)።
ችግር አለው: ጨነቀው፣ ጠበበው፣ የሚያደርገውን ዐጣ።
ችግር: ዕጦት፣ የመፍቀድ ጥፋት (አማረን እይ)።
ችግኝ (ከተገነ): የሣር፣ የቅጠል፣ የዛፍ፣ የተክል ፍል (ከላይ በዳስ፣ ከታች በጀጐል የሚተገን)። (ቍኝንና ጭጕኝን ተመልከት)።
ችፌ (ችፋዊ): የቍስል ስም፣ ኹል ጊዜ የሚያዥ፣ የወፈፍ ዓይነት ቍስል፣ አልፎ አልፎ ሽፍ የሚል። (ዘዳ ፳፰፡ ፳፯፡ ዘሌ ፲፬፡ ፶፬)። መድኀኒቱም የተወቀጠ ኮሶ በማር ለውሶ መቀባትና ቅጠል ለጥፎ በራቅ ማሰር ነው።
ችፌ: ቍስል ነው። ቸፈቸፈ (ማለት ነው)።
ችፍ ችፍ አለ: ጭፍጭፍ፣ ክፍክፍ አለ (በረቂቅ ዘ)።
ችፍ አለ: እዥ አለ፣ እሳየ ሸፈ።
ችፍ: ሐሩር፣ ረቂቅ፣ ዕከክ።
ችፍርግ (ከሰቸፈገ): ቁመተ ወርቅ፣ ጸጽቀ፣ ብዙ ዕንጨት፣ ችፍግ፣ ሥሯጽ ነው።
ችፍችፋም: ጭቅጭቃም፣ ንዝንዛም።
ችፍችፍ: ጭቅጭቅ፣ ንዝንዝ።
ችፍግ (ጽፉቅ): የተቸፈገ፣ ጭፍቅ፣ ጥቅጥቅ (ዱር) (መዝ ፲፡ ፱፡ ኤር ፬፡ ፯፡ ሕዝ ፲፱፡ ፸፮)።
ችፍግ አለ (ከሰተጸፍቀ): ጥቅጥቅ አለ፣ ደን፣ ምሣ ኾነ።
ችፍግነት: ጥቅጥቅነት (ኢሳ ፲፡ ፴፬፡ ሕዝ ፴፩፡ ፫)።
ቿ (ችዋ): (የሩቅ ሴት ዝርዝር) ምሳሌ: "ቤቶች፡ - ቤቶቿ (የርሷ ቤቶች)፣ ላሞች፡ - ላሞቿ (የርሷ ላሞች)።"
No comments:
Post a Comment